ዳይሬክቶሬቱ የዳታ ቤዝ አድሚንስትሬተር ቡድን፣ የዌብ ሳይትና ማህበራዊ ሚዲያ አስተዳደር ቡድን፣ የሚዲያ ልማትና ቤተ‐መዛግብትና ቤተ‐መጽሀፍት ሥራ ክፍሎችን ያቀፈ ነው፡፡
ዘርፉ ወቅታዊ፣ ተአማኒና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ በተደራጀና በዘመነ መልኩ ለህብረተሰቡ ለማድረስ የሚሠራ ሲሆን ዳታ ቤዝና ዌብ ሳይት የማልማት ስራም የተጠናቀቀ በመሆኑ በ2017 የተዳራሽነት አድማስ በማስፋት በ2016 በጀት ዓመት የተከናወኑ ጠንካራ አፈጻጸሞችን በማጠናከርና የታዩ ክፍተቶችን በማረም፣ ዘርፉ የሚያከናውናቸውን ስራዎች የ2017 ዓ.ም 2ተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ እንደሚከተለው አዘጋጅቷል፡፡
የዕቅዱ ዓላማ
የመንግስት የመረጃ ማእከልና ዲጂታል ሚዲያ አስተዳደር አላማ የዜጎችንና የመንግስትን መረጃ የማግኘት ጥያቄ እና የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት ክፍተት፣ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ጥያቄዎችን እንዲሁም የመረጃ ስርአት ክፍተትን መነሻ በማድረግ መረጃዎችን በተለያየ ጊዜ በመሰብሰብ፣ በማከማቸት፣ በማደራጀት፣ የተለያዩ ዲጂታል ሲስተሞችን በማልማት፣ መረጃዎችን በሲስተሞቹ በመልቀቅ፣ ለህትመትና ለማስታወቂያ ስራ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በመስጠት እና በሙያዊ ክትትልና ድጋፍ አሰራሩን በማጠናከር የተደራጁ መረጃዎችን፣ የተገነቡ ዲጂታል ሲስተሞችንና የተለቀቁ መረጃዎችን እንዲሁም የተሰጡ የብቃት ማረጋገጫ ደብዳቤዎችን እንደ ውጤት በማቅረብ የዘመነ የመረጃ አስተዳደርን መፍጠርና የህብረተሰቡንና የመንግስትን ፍላጎት ማርካት ነው።
የዕቅዱ አስፈላጊነት
ከመረጃ ውስንነትና ከአዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂ፤ የፖሊቲካና ሌሎች ማህበራዊ ለውጦች ጋር ተያይዘው በሚፈጠሩ ድንገተኛ ነገሮች የተነሳ በውሳኔ አሰጣጥና በተገልጋዩ ፍላጎት መካከል ሊፈጠሩ የሚችሉ ክፍተቶች እንዳይፈጠሩ ስለሚያደርግና የዘርፉን ብቃት አስተማማኝ መሰረት እንዲኖረው ስለሚያስችል፤
ዘርፉ ከመንግስት የሚመደብለትን ውስን ገንዘብና ሀብት በቁጠባ እንዲጠቀምና ቁልፍ ለሆኑ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም እንዲችልና ከብክነት የጸዳ መሰረታዊ የአሰራር ስርአትና ባህል እንዲኖረው ስለሚያስችል፤
ተቋማት ዘመናዊ የአመራር ስርአትን እንዲከተሉና በተገልጋዮቻቸው ዘንድ የሚኖራቸው አመኔታ እንዲጨምር ስለሚያስችል ነው፡፡
አስቻይ ሁኔታዎችና ቁልፍ ችግሮች
ዋና ዋና አስቻይ ሁኔታዎች
ሀገራዊ የዲጂታል ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የማሰፋፋት እንቅስቃሴዎች፣
የኅብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችል አዲስ ክልላዊ አደረጃጀት መፈጠሩ፣
ልዩ የመረጃ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ጭምር የመንግስት ኢንፎርሜሽን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው፣
ዲጂታል ተኮር አገልግሎት እያደገ መምጣቱ፣
የሰለጠነና ልምድ ያለው የሰው ኃይል እየተሟላ መሆኑ፣
ዲጂታል ስትራቴጂ ተኮር አመራር እየተፈጠረ መሆኑ፣
አሳታፊ የሆነ አሰራር መኖሩ፣
የሴክተሩ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ መኖሩ፣
የመገናኛ ብዙሀንና የመረጃ ነጻነት አዋጅ መኖሩ፣
እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ለገጽታ ግንባታ አስተዋጽኦ መኖሩ፣
ለዲጂታል ቱሪዝም ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱ፣
የዲጂታል መሠረተ-ልማት አገልግሎት እየተስፋፋ መሆኑ፣
ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለክልሉ ገጽታ ግንባታ ትልቅ ድርሻ መኖሩ፣
ለዲጂታል ልማት ተነሳሽ የሆነ ህዝብ መኖሩ፣
ፈጣንና ዘመናዊ የዲጂታል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ያለው ምቹ ሁኔታና ፍላጎት እያደገ መምጣቱ፣
የዲጂታል መገናኛ ብዙሀን አውታሮች በመስፋፋት ላይ መሆናቸው፣
ዳይሬክቶሬቱ የዳታ ቤዝ አድሚንስትሬተር ቡድን፣ የዌብ ሳይትና ማህበራዊ ሚዲያ አስተዳደር ቡድን፣ የሚዲያ ልማትና ቤተ‐መዛግብትና ቤተ‐መጽሀፍት ሥራ ክፍሎችን ያቀፈ ነው፡፡
ዘርፉ ወቅታዊ፣ ተአማኒና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ በተደራጀና በዘመነ መልኩ ለህብረተሰቡ ለማድረስ የሚሠራ ሲሆን ዳታ ቤዝና ዌብ ሳይት የማልማት ስራም የተጠናቀቀ በመሆኑ በ2017 የተዳራሽነት አድማስ በማስፋት በ2016 በጀት ዓመት የተከናወኑ ጠንካራ አፈጻጸሞችን በማጠናከርና የታዩ ክፍተቶችን በማረም፣ ዘርፉ የሚያከናውናቸውን ስራዎች የ2017 ዓ.ም 2ተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ እንደሚከተለው አዘጋጅቷል፡፡
የዕቅዱ ዓላማ
የመንግስት የመረጃ ማእከልና ዲጂታል ሚዲያ አስተዳደር አላማ የዜጎችንና የመንግስትን መረጃ የማግኘት ጥያቄ እና የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት ክፍተት፣ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ጥያቄዎችን እንዲሁም የመረጃ ስርአት ክፍተትን መነሻ በማድረግ መረጃዎችን በተለያየ ጊዜ በመሰብሰብ፣ በማከማቸት፣ በማደራጀት፣ የተለያዩ ዲጂታል ሲስተሞችን በማልማት፣ መረጃዎችን በሲስተሞቹ በመልቀቅ፣ ለህትመትና ለማስታወቂያ ስራ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በመስጠት እና በሙያዊ ክትትልና ድጋፍ አሰራሩን በማጠናከር የተደራጁ መረጃዎችን፣ የተገነቡ ዲጂታል ሲስተሞችንና የተለቀቁ መረጃዎችን እንዲሁም የተሰጡ የብቃት ማረጋገጫ ደብዳቤዎችን እንደ ውጤት በማቅረብ የዘመነ የመረጃ አስተዳደርን መፍጠርና የህብረተሰቡንና የመንግስትን ፍላጎት ማርካት ነው።
የዕቅዱ አስፈላጊነት
ከመረጃ ውስንነትና ከአዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂ፤ የፖሊቲካና ሌሎች ማህበራዊ ለውጦች ጋር ተያይዘው በሚፈጠሩ ድንገተኛ ነገሮች የተነሳ በውሳኔ አሰጣጥና በተገልጋዩ ፍላጎት መካከል ሊፈጠሩ የሚችሉ ክፍተቶች እንዳይፈጠሩ ስለሚያደርግና የዘርፉን ብቃት አስተማማኝ መሰረት እንዲኖረው ስለሚያስችል፤
ዘርፉ ከመንግስት የሚመደብለት