SlideShare a Scribd company logo
1 of 28
Download to read offline
የፌዴራል የስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን
የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ተቋማት ልምዶች፣ በሀገራችን የፀረ ሙስና
ትግል ያለበት ደረጃ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ሊወሰዱ የሚገባቸው
የመፍትሔ እርምጃዎች
ለህግ አውጭው አካል የቀረበ
ጥናታዊ ፅሁፍ አቅራቢ ፡ ሐረጎት አብረሃ
የስነ ምግባር አውታሮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር
መጋቢት 2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ
2
ማውጫ
ርዕስ ገፅ
1. መግቢያ-----------------------------------------------------------------------------------------------3
2. የሙስና ታሪካዊ አመጣጥ በኢትዮጵያ-----------------------------------------------------------4
3. የሙስና ትርጉም------------------------------------------------------------------------------------5
4. በፀረ ሙስና ትግል ውጤታማ የሆኑ ሀገሮች ልምድ-----------------------------------------7
4.1 የእስያ ሀገሮች ልምድ---------------------------------------------------------------------10
4.2 የአውሮፓ ልምድ----------------------------------------------------------------------------11
4.3 የአፍሪካ ልምድ------------------------------------------------------------------------------12
4.4 ሊወሰድ የሚገባው መልካም ልምድ------------------------------------------------------13
5. የሀገራችን የፀረ ሙስና ትግል የደረሰበት ደረጃ----------------------------------------------17
5.1 የኢፌድሪ የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አመሰራረት---------------------------17
5.2 የኮሚሽኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም -------------------------------------------------18
5.2.1 የግንዛቤ ፈጠራ ስራ አፈፃፀም----------------------------------------------------------18
5.2.2 የሙስና መከላከል ስራ አፈፃፀም-------------------------------------------------------19
5.2.3 የሃብት ማሳወቅ እና ምዝገባ ስራ አፈፃፀም -----------------------------------------20
5.2.4 የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ማደራጀት እና መደገፍ ስራ አፈፃፀም--------21
5.2.5 የህዝብ ተሳትፎ ተሳትፎ ስራ አፈፃፀም ተግባራት -------------------------------22
5.2.6 ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው የቅንጅት እና ትብብር ስራ አፈፃፀም-------------23
5.2.7 የኮሚሸኑ የሰው ሀብት በተመለከተ----------------------------------------------------23
5.2.8 የክስ እና ምርመራ ስራ አፈፃፀም-----------------------------------------------------24
6. ማጠቃላያ--------------------------------------------------------------------------------------------25
7. የፀረ ሙስና ትግሉ ለማጠናከር ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎች--------------------------26
3
የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ተቋማት ልምዶች፣ በሀገራችን የፀረ ሙስና ትግል ያለበት ደረጃ፣
ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ሊወሰዱ የሚገባቸው የመፍትሔ እርምጃዎች
1. መግቢያ
ሙስና የነፃ ገቢያ ውድድርን በማዳከም የሀገሮችን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ፣ አለመረጋጋትን
የሚያስከትል እና ዲሞክራሲን በከፍተኛ ደረጃ በማናጋት ለቀውስ የሚዳርግ አደገኛ ወንጀል መሆኑ
መግባባት ላይ ከተደረሰበት ቆየት ብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የፀረ ሙስና
ስምምነቶች እና ትብብሮችን በማድረግ ይህን ዓለም አቀፍ የሆነ ችግር ለመግታት ጥረት ሲደረግ
ይታያል፡፡
ሀገራት በዚህም ሳይወሰኑ የራሳቸው የሙስና መከላከያ እና መዋጊያ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው
ከማደረጋቸውም በላይ ተቋም አቋቁመው ችግሩን ለመግታት ጥረት በማደረግ ላይ ናቸው፡፡ ይሁን
እንጅ ከወንጀሉ ልዩ ባህሪ በመነጨ ማለትም ሙስና ከአለው አደገኛነት፣ውስብስብነት እና
ተለዋዋጭነት አንፃር አብዛኞቹ ያደረጉትን ትግል ያህል ከሙስና መፅዳት እንዳልቻሉ በዘርፉ
የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡በተቃራኒዉ ደግሞ በቁጥር ዉስን ቢሆኑም ተጋላጭነታቸውን እና
ጉዳቱን በከፍተኛ ርብርብ በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ የሰላማቸው እና የልማታቸው ጠንቅ ወደ
ማይሆንብት ደረጃ ያደረሱ ሀገሮች አሉ፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያም የሙስናን ጎጅነት፣ ለልማት እና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ያለውን
አደገኛነት በመረዳት የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ከማድረጓም በላይ ትግሉን የሚያስተባብር እና
የሚያቀናጅ ተቋም እንደሚያስፈልጋት መግባብት ላይ ተደርሷል:: በዚህ መሰረት በ1993 ዓ.ም
በአዋጅ ቁጥር235/1993፣ በአዋጅ ቁጥር 433/1997 እንደገና በማሻሻያ በአዋጅ ቁጥር 883/2007
ዓ.ም እንደገና በማሻሻል የፌዴራል የስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አቋቁማ ለአለፉት 19
ዓመታት ሙስናን ለመግታት ጥረት ስታደረግ ቆይታለች፡፡ ከማቋቋሚያ አዋጆች በተጨማሪ
የሙስናን ወንጀል በሚመለከት እጅግ ጥብቅ የሆኑ እንደ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ
አዋጅ 881/2007፣ የፀረ-ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/97 እና
882/2007፣ የጠቋሚዎች እና የምስክሮች ጥበቃ እና ከለላ ህግ የመሳሰሉ ለሙስና መከላከል እና
ትግል የሚያገለግሉ ህጎች ወጥተዋል፡፡
4
በእነዚህ አመታት የተገኙ አበረታች ውጤቶች ቢኖሩም አሁንም የሰላማችን እና የልማታችን ጠንቅ
መሆኑ አልቀረም፡፡ በመሆኑም ሙስና የልማታችን እና የሰላማችን ጠንቅ ወደ ማይሆንበት ደረጃ
ላይ ማድረስ አልተቻለም፡፡ ሀገራችን የተረጋጋ ሰላም እና ልማት እንዳይኖራት ከፍተኛ ማንቆ ሆኖ
እየቀጠለ ይገኛል፡፡ በፀረ ሙስና ትግል ላይ የተሳካ ትግል ያደረጉ ሀገሮች በቀጣይነት የተረጋጋ
ፖለቲካዊ ሰርዓት፣ ቀጣይነት ያለው እና ህዝብን አሳታፊ ያደረገ ልማት መገንባት የቻሉት በፀረ
ሙስና ትግሉ ህዝቡ ባለቤት እንዲሆን የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣታቸው፣ መንግስት ከህዝብ
በአደራ የተሰጠውን ሥልጣን ለግል መገልገያ እንዳይሆን ለመታገል የሚያስችል ሰርዓት
በመፍጠራቸው፣ መንግስት የፀረ ሙስና ትግሉ ላይ ተገቢ እገዛ እና ድጋፍ ከመስጠቱ በተጨማሪ
ሙስናን የመፈፀሙ የመንግስት መርምረው ወደ ህግ እንዲቀርቡ በማድረግ ከፍተኛ ቁርጠኝነት
ያሳዩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ይህን የፀረ ሙስና ትግል የሚመራ እና የሚያስተባብር ነፃና እና
ጠንካራ የፀረ ሙስና ተቋም አደረጃጀት በመፍጠራቸው የመጣ ውጤት መሆኑን ብዙ ጥናቶች
ያሳያሉ፡፡
በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል አንዱ ሙስናን በብቃት እና በተቀናጀ መልኩ
ለመዋጋት የሚያስችል ሰርዓት ማጠናከር የሚገባት ሲሆን በሙስና ላይ የምናደርገው ትግል
ውጤታማ እንዲሆን ሌሎች በዚህ ረገድ የተሳካ ትግል ያደረጉ ሐገሮችን ልምድ በመውሰድ
ሐገራችን በፀረ ሙስና ትግሉ ያሉትን ክፍተቶች እና እያጋጠሙ ያሉትን ችግሮች በጥልቀት
መመርመር፣ የመፍትሄ ሃሳብ ማመንጨት እና በሙስና ላይ የምናደረገው ትግል ለውጥ
እንዲያመጣ የፖሊሲ እና የህግ አውጭው አካላት በጉዳዩ ላይ ተገቢ ግንዛቤ እንዲይዙ እና ያሉትን
ክፍተቶች እንዲፈቱ የበኩላቸውን አሰተዋፀኦ እንድያደርጉ መነሻ ሀሳብ ማቅረብ የሚገባ መሆኑ
ታምኖበታል፡፡
በመሆኑም የህግ አውጭው አካል ለውይይት መነሻ እንዲሆን በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት
በማድረግ የጋራ መግባባት ይፈጠራል የሚል እምነት ያለው ሲሆን ትግሉን አንድ ርምጃ ወደፊት
ሊያራምድ የሚችል ውሳኔ እንዲሚወሰን ይጠበቃል፡፡
2. የሙስና ታሪካዊ አመጣጥ በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የሙስናን ታሪካዊ አመጣጥ እና እድገት ስንመለከት ጉቦ እና በዝምድና መስራት እንደ
መጥፎ ድርጊት ተደርጎ የሚወሰድ አልነበርም፡፡በዘመናዊቷ ኢትዮጵያም በተገነባው መንግስታዊ
5
መዋቅር ውስጥ ጉቦ እና እጅ መንሻ ነውርነቱ ጎልቶ የሚታይ አልነበርም፡፡ በዚህ ምክንያት “ሲሾም
ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” የሚል ብሂል በስፋት ጥቅም ላይ ይዉል እንደነበረ ይታወሳል፡፡
ሀገራችን በ1948 ባወጣችው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ እና በሌሎች ህጎቿ ውስጥ ጉቦ እና በዝምድና
መስራት ወንጀል መሆኑ የተደነገገ ቢሆንም ችግሩ የግለሰብ እንጅ የስርዓት እና የህብረተሰብ ችግር
ተደርጎ ይወሰድ ስላልነበር ከመገታት ይልቅ ስር እየሰደደ እንደሄደ መረዳት ይቻላል፡፡
ከ1984 ዓ.ም ወዲህ የነፃ ገቢያ ስርዓት በሀገራችን ተግባራዊ መሆንን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለዉን
የገቢያ ክፍተት ለመሙላትና ፍታሃዊነትን ለማረጋገጥ ሲባል በተመረጠ መንገድ መንግስት ጣልቃ
የሚገባበት የኢኮኖሚ አቅጣጫ ተግባራዊ በመሆኑ ከዚህ በመነጨ ሊከሰት ለሚችል ሙስና
መጋለጣችን እንደማይቀር ታምኖበት የጠነከረ የህግ ማዕቀፍና ተቋም እንዲኖረን ተደርጎ የነበረ
ሲሆን በዚህም እጅግ በርካታ የማይናቁ ስራዎች ተስርተዋል፡፡ ሆኖም ግን በሚፈለገው ልክ ውጤት
ባለማምጣታችን እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተደምረው አሁንም ሙስና የልማታችን አልፎ
ተርፎሞ የተረጋጋ ሰላም እና ፖለቲካዊ ስርዓት እንዳይፈጠር ጠንቅ ሆኖ ይገኛል ፡፡
3. የሙስና ትርጉም
በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊያግባባ የሚችል አንድ ወጥ የሆነ ትርጉም እስካሁን ድረስ ለቃሉ መስጠት
አልተቻለም፡፡ ለቃሉ አንድ ወጥ ትርጉም ከመስጠት ይልቅ ሀገሮች በህጎቻቸው ውስጥ የሙስና
ወንጀሎች የሚባሉትን በመዘርዘር መግባባት ላይ ለመደረስ ጥረት ሲያደርጉ ይታያል፡፡ ፅሁፉም
በሙስና ላይ አንድ ወጥ ትርጉም በመሰጠት ጊዜን ማጥፋት ይገባል ብሎ አያምንም፡፡ በመሆኑም
ለጊዜው መግባባት ላይ የተደረሰበትን የሙስና ትርጉም ማስቀመጥ ለጋራ መግባባት እና ለግንዛቤ
ስለሚረዳ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
3.1 በተለያዩ መዝገበ-ቃላቶች ለሙስና የተሰጡ ትርጉም
 “…ቅንነትን እና መርህን የጣሰ ተግባር፣ ህጋዊ ሃላፊነትን ወይንም የሌሎችን መብት በጣሰ
መልኩ ጥቅም የማቅረብ ድርጊት”፣ (Source: Black’s law Dictionary, 8th
Edition,
p.371)
 “መበስበስ፣ የሞራል (የስነ ምግባር) ዝቅጠት፣ የሙሰኝነት ተግባራት ስብስብ ነዉ”፡፡
(Decomposition, Moral Detrioration, Set of corrupt practice) (ኮንሳይንስ ኦክስፎርድ
መዝገበ ቃላት)
6
 “በተለይ ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች የአታላይነትና የህገ ወጥ ባህሪ ነዉ”፡፡ (Dishonest or
Illegal behaviour especially of people of authority) (ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት)
 “ተገቢ ባልሆነና ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ስህተት ለመፈጸም ወይንም ለማጥፋት መነሳሳት
ነዉ” ፡፡ (Inducement to wrong by improper or unlawful means) (ማሪየም ዌብስተር
መዝገበ ቃላት)
 “በስልጣን ወይም በሰራ ድርሻ አላግባብ የመገልገል፣ የመጠቀም ወይም የመጥቀም ድርጊት
ነው” ሲል የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት እና ምርምር ማዕከል በ2001
በአሳተመው የአማረኛ መዝገበ ቃላት ላይ ትርጉም ሰጥቶታል ፡፡
3.2 የፍልስፍና፣ የሃይማኖትና የሞራላዊ አስተምህሮት ለሙስና የሰጡት ትርጉም
 ህሊናዊ ወይንም ሞራላዊ ብልሽት ወይንም
 ከእዉነታ፣ ከመልካምና ጥሩ ከሆነ ነገር ማፈንገጥ ነዉ ይሉታል፡፡
3.3 አለማቀፍ ተቋማት ለሙስና የሰጡት ትርጉም
 “የመንግስት (የህዝብ) ስልጣንን ለግል ጥቅም ሲባል አላግባብ መገልገል ወይንም መያዝ”
(World Bank)፣
 “በአደራ የተሰጠ ስልጣንን ለግል ጥቅም ሲባል አላግባብ መገልግል” (Transparency
International)፣
 “ስልጣንን ለግል ጥቅም ሲባል አላግባብ መገልግል” (EU, 2003) ነው ብሎታል፡፡
3.4 የሙስና ወንጀሎች ህግ ለሙስና የሰጡት ትርጉም
 የተባበሩት መንግሰታት የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን፣ የአፍሪካ ህብረት የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን፣
በአውሮፓ ህብረት የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን እና የኢትዮጵያ የሙስና ወንጀሎች ህግ የፀረ-
ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/97 እና 882/2007፣ የሙስና
ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ 881/2007፣ በአጠቃላይ ብንመረምር ለሙስና ትርጉም
ከመሰጠት ተቆጥበዋል፣
 ትርጉም ከመስጠት ይልቅ የሙስና ወንጀሎች የሚባሉትን መዘርዘር ላይ ትኩረት
አድርገዋል፣
 የዚህ ዋነኛ ምክንያት ወጥ የሆነ ትርጉም ለመሰጠት አስቸጋሪ እና አወዛጋቢ በመሆኑ ነው፡፡
7
ለማጠቃለል ያህል ከዚህ በላይ ለሙስና የተሰጠት ትርጉሞች አንድ ወጥ ባይሆኑም በአብዛኛው
ከስልጣን እና ስልጣንን አለግባብ መገልገል ጋር የተያያዘ መሆኑ የሚያግባባ ቢሆንም ሙስና
ከስልጣን መያዝ ውጭም የሚከሰትባቸው መስኮች እንዳሉ መገንዘብ ይገባል፡፡
4. በሙስና ትግል ውጤታማ የሆኑ ሀገሮች ልምድ
በአለም ላይ ያሉ ሐገሮች ሙስናን ለመታገል የተለያዩ ሞዴሎችን ተከትለው ተቋሞቻቸውን
ያደራጃሉ፡፡ ከእነዚህም ሞዴሎች ውስጥ ጎላ ብለው የሚታወቁት ሶስት ናቸው፡፡ እነሱም፡-
1. የሙስና መከላከል ብቻ ሞዴል የሚከተሉ /Corruption Prevention Model/
ይህ አይነት ሞዴል የሚጠቀሙ አገሮች በአብዛኛው ጠንካራ የህግ ማስከበር ሰርዓት ቀደም ብለው
የፈጠሩ፤ ሙስናን የሚጠየፍ ጠንካራ የሆነ የህ/ሰብ ባህል ያላቸው፣ የእርስ በርስ ቁጥጥር ሰርዓት
በመፍጠር የተዋጣለቸው አገሮች የሚከተሉት ሞዴል ነው፡፡ ይህን አይነት ሞዴል መሰረት
አድርገው የፀረ ሙስና ተቋም አደረጃጀት የፈጠሩ አግሮች በአብዛኛው መንግስት ሊከተለው የሚገባ
የፀረ ሙሰና ፖሊሲ ለማማከር (Advisory role )፣ የመንግስት ባለሰልጣናት ሀብት ለህዝብ ግልፅ
ለማድረግና ለመቆጣጠር፣ የፀረ ሙስና ሰርቨይ ለማካሄድ፣ የመንግስት አጭር እና ረዥም የፀረ
ሙስና እቅድ (Anti corruption strategy ) ለማዘጋጀት ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚደራጁ
የፀረ ሙስና አካላት ናቸው፡፡ የሙስና ወንጀሎች ለመመርምር እና ለመክሰስ የሚያስችል ሰልጣን
አልተሰጣቸውም፡፡ ይህን ሰልጣን የተሰጣቸው በየአገራቱ ውስጥ የሚገኙ የፖሊስ እና የዓቃቤ ህግ
ተቋማት ናቸው፡፡ ይህን አይነት ሞዴል የሚከተሉ አገሮች በአብዛኛው የፀረ ሙስና ኮሚሽን
/ኤጅንሲ/ Anti Corruption Commission/Agency የሚል ስም ከመጠቀም ይልቅ Ethics
committee, Corruption prevention committee, Central Committe for prevention,
National integrity office etc የሚል አይነት ስም የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ ፈረንሳይ(Central
Service for Prevention of corruption)፣ አሜሪካ(Office of Government for Ethics)፣
ብራዚል(Office of Control General)፣ አልጀሪያ(National Agency for the Prevention
Combating of Corruption)፣ ሰርቪያ(Anti Corruption Agency)፣ ሱሉቪኒያ( Commission for
Prevention of Corruption)፣ ሜቄዶንያ (State Commission for Prevention of
Corruption)፣ ይህን አይነት ሞዴል ከሚከተሉ አገሮች ውስጥ በምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
2. የሙስና መከላከል እና የህግ ማስከበር ስራን አጣምረው የሚጠቀሙ ሀገሮች ሞዴል /Multi
Purpose Anti Corruption Model or The Universal Model/
ይህን አይነት ሞዴል በዋናነት ሦስት የፀረ ሙስና መታግያ ስልት ይዘው የሚሄዱ ናቸው፡፡ አንድ
አንድ ጊዜ የሶስት ጦር ውጊያ ስልት ይባላል፡፡ ሙስና በብቃት ለመዋጋት አንድኛ ህዝብ በሙስና
ላይ እንዲዘምት ማስተማር እና ማስተባበር፣ ሁለተኛ የሙስና መከላከል ዘዴዎች (የህግ እና
የአሰራር ማሻሻያዎች) ተግባራዊ በማድረግ ሲሆን ሶስተኛ በሙስና ላይ የተሳተፉ አካላት ተጠያቂ
8
ማድረግ (በመርመር) ነው፡፡ ይህን ሞዴል የሚከተሉ አግሮች እነዚህ ሰልጣን ለአንድ ተቋም
በመሰጠት ውጤታማ እና የተቀናጀ የፀረ ሙስና ትግሉ እንዲኖር ያግዛል የሚል እምነት አላቸው፡፡
በእንዲህ አይነት አደረጃጃት የተከማቸ ሰልጣን እንዳይፈጠር እና የcheck and balance ሰርዓት
እንዲኖር በተወሰነ መልኩ የክስ ስራ ከፀረ ሙስና አደረጃጀቱ ነፃነት ተሰጥቶች እንዲሰራ /እንዲደራጅ
የሚደረግበት አግባብ አለ፡፡ እዚህ ላይ ሊሰመር የሚገባው ጉዳይ ግን ይህን አይነት ሞዴል
የሚከተሉ አገሮች ቢያንስ የምርመራ ሰራ በስራቸው እንዲደራጅ የሚያደርጉበት ሁኔታ አለ፡፡
ይህን አይነት የፀረ ሙስና ሞዴል የሚከተሉት አገሮች በዋናነት የሚታወቁት ለረዥም ጊዜ
በሙስና ተዘፍቀው የነበሩ/ ያሉ፣ የመንግስት ተቋማት ህግ አሰከባሪ አካላት (Law enforcement
institutions) ጭምር በሙስና የሚጠረጠሩበት እና ሙስና ሰለባ የሆኑበት፣ በተነፃፃሪ በኢኮኖሚ
እድገት ወደ ኋላ የቀሩ፣ የዳበረ የዴሞክራሲ የሌላቸው እና ዝቅተኛ የመንግስት የCheck and
Balance ሰርዓት የነበራቸው/ያላቸው አገሮች ናቸው ፡፡
ይህን አይነት የፀረ ሙስና አደረጃጃት በዋናነት ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ከቅኝ ግዛት ነፃ መውጣት
በኋላ በአፍሪካ፣ በኤስያ፣ በላቲን አሜሪካ እንዲሁም በአውሮፓ በተወሰኑ አገሮች ተቀባይነት ያገኘ
እና እንደ ምሳሌ የሚወሰድ የፀረ ሙስና አደረጃጀት ሞዴል ነው፡፡ ይህን አደረጃጃት የሚከተሉ
አገሮች በዋናነት የሚታወቁት ከአስፈፃሚው አካል ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ ተቋም እንዲደረጁ
የማድረግ፣ አሰፈላጊ ሰልጣን፣ ሀብት/ በጀት እና ጠንካራ የህግ ማእቀፍ እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፡፡
ነፃ እና ጠንካራ የሆነ የፀረ ሙስና አደረጃጀት እንዲኖር ማድረግ መንግስታት ሙስና ለመታገል
ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳያ ተደርጎ በህዝቡ የሚወሰድበት ሁኔታ አለ፡፡ ሀገራችንም ለሙስና በጣም
ተጋላጭ በመሆንዋ ለ14 ዓመታት ያህል ይህን ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ጭምር ልምድ
በመውሰድ ሰፊ ጥናት ስታደርግ ቆይታ በ1993 ዓ.ም ይህን ሞዴል ተግባራዊ ለማድረግ ችላ ነበር፡
፡ ሆኖም ግን ከ2008 ጀምሮ አጥጋቢ ባልሆነ ምክንያት እና በተወሰደ የተሳሳተ ግንዛቤ የነበረውን
የፀረ ሙስና አደረጃጃት የተልዕኮ ለውጥ እንዲኖረው ተደርጓል፡፡
በአሁን ሰዓት ከክስ በመለስ ያለውን ሁለገብ ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ሆንግ ኮንግና
ቻይና(Independent Commission Against Corruption)፣ ሲንጋፖር(Corrupt Practice
Investigation Office)፣ ሉቲኒያ(Special Investigation Service)፣ ላቲቪያ(Corruption
Prevention and Combating Office)፣ ፖላንድ(Central Anti Corruption Bearo)፣
ኢንዶኒዥያ(Corruption Eradication Commission)፣ ኡጋንዳ( Anti Corruption Commission፣
9
ቦትስዋና (Directorate on Corruption and Economic Crime)፣ አውስትራሊያ፣ ደቡብ ኮሪያ፣
ታይላንድ፣ አርጀንቲና እና ኢካዶርን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡
በተለይም በአፍሪካ ቦትስዋናን የፈጠረችው የፀረ ሙስና ተቋም ለሌሎች አርአያ የሚሆን ተቋም
ሲሆን በአፍሪካ ሙስና በመታገል የተሻለች አገር ሆና ተቀምጣለች ፡፡
3. ህግን የማስከበር ስራን ብቻ ሞዴል የሚከተሉ/ Law Enforcement Model/
ይህን አይነት ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ሙስናን ለመታገል የሚያስችላቸው በዋናነት በምርመራ
እና ክስ ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ ይህን ስራ ለመስራት በተለመደው የህግ ማስበር ስርዓት ማለትም
በፖለስ እና ዓቃቤ ህግ ተቋማት እንዲሰሩ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ አንዳንድ አገራት
ልዩ ዲፓርትመንት (special department) በማቋቋም የሚታገሉበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህን አይነት
ሞዴል ውጤታማነቱ እንደየ አገር ሁኔታ ይለያል፡፡ ለምሳሌ በታዳጊ አገሮች ያሉት የፖሊስ እና
የአቃቤ ህግ ተቋማት ነፃ እና ጠንካራ ከአሰፈፃሚ አካል ጣልቃ ገብነት የፀዱ ባለመሆናቸው
ውጤታማ አይደሉም፡፡ እንዲያውም እንዲህ አይነት አደረጃጀት “ፖሊስ እንደያማህ ብላ በለው፣
እንዳይበላ ግፋው” እንደሚባለው አይነት አባባል መንግስት ሙስና መታገል አይፈልግም የሚለውን
ሀሜት ለማስወገድ የሚደራጁ እንጂ መንግስት ከልቡ ሙሰናን ለመዋጋት ፍላጎት ስላለው አይደለም
የሚያቋቁመው ተብሎ በስፋት የሚተችበት ሁኔታ አለ፡፡ በአደጉ አገሮች በገነቡት ጠንካራ
የዲሞክራሲ ባህል፣ የግልፅነት ሰርዓት እንዲሁም በሂደት ባገኙት ልምድ ታግዘው ሙስናን ጨምሮ
በተወሰነ ወንጀል ላይ ትኩረት ሰጠው የሚሰሩበት እና ውጤታማ የሆኑበት ሁኔታ አለ፡፡ ለምሳሌ
እንግሊዝን ለአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡
ሆኖም ግን ይህን ሞዴል የሚከተሉ አገሮች የሙስና መከላከል ስራ ከህግ ማስከበር ስራው(ምርመራ
እና ክስ) ጋር አጣምረው ሰለማይሰሩ በተለይም ታዳጊ በሆኑ አገሮች የተቀናጀ የፀረ ሙስና ትግል
በማድረግ በኩል ችግር ያለባቸው እና ህዝብ ሞብላይዜይሽን ስራ አነሳ ትኩረት የሚሰጡበት ሁኔታ
ስለአለ ውጤታማ አይደሉም ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካን ማንሳት ይቻላል፡፡ እንደ አማራጭ ሞዴል
በተመሳሳይ መልኩ ይህ አማራጭ ውጤታማ የሚሆነው ጠንካራ የህግ ማስከበር ስርዓት በሂደት
የገነቡ፣ የነቃ ህብረተሰብ የገነቡ እና ያደጉ አገሮች ላይ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል እንጂ እንደኛ
አገር በጣም ሰፊ የህግ ማስከበር ስርዓት ክፍትት ያለበት፣ የነቃ እና የተደራጀ ህብረተሰብ በተሟላ
ሁኔታ ባልተፈጠረበት ሁኔታ የሙስና መካለከል ስራውን በአንድ ላይ አጣምሮ ለመሄድ የሚያስችል
ስርዓት ባለመሆኑ ይህ ሞዴል በአፍሪካ ተመራጭነቱ በጣም ያነሰ ነው፡፡ ይህን ተግባራዊ ያደረጉ
10
አገሮችም ብዙም ለውጥ አላመጡም፡፡ ስፔን( Special Prosecutor’s Office Against Corruption
and Organized Crime)፣ ሩማንያ(National Anti Corruption Directorate)፣ ክሮሽያ(Office for
Suppression of Corruption and Organized Crime)፣ ኖርዌዬ(The Norwegian National
Authority for Investigation and Prosecution of Economic and Environmental Crime)፣
እንግሊዝ(Metro Politian Police Anti Corruption Command)፣ ኬንያ(Anti Corruption
Commission)፣ ደቡብ አፍሪካ(The Special Investigation Unit of South Africa)፣ ቤልጄም
(Central Office for the Reparation of Corruption) ይህን ሞዴል በመከተል በምሳሌ የሚነሱ
አገሮች ናቸው::
በአለም አቀፍ ደረጃ ከላይ የተነሱ ሞዴሎች በብዛት ተግባራዊ የተደረጉ ቢሆንም ከእነዚህ ለየት ያለ
ሞዴል የሚከተሉ ሀገሮች መኖራቸው አልቀረም፡፡ ለምሳሌ ደቡብ ኮሪያ እና ጋና የፀረ ሙስና
ኮሚሽንና ሠብአዊ መብትን በአንድ ላይ አቀላቅለው አደራጅተዋል፡፡ የፀረ ሙስና፣ የህዝብ እንባ
ጠባቂ እና ዋና ኦዲተርን በአንድ ላይ አቀላቅለው የሚያደራጁ አገሮችም አሉ፡፡ ሩዋንዳ በዚህ እንደ
ምሳሌ የምትጠቀስ አገር ናት፡፡ ለዚህ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ ውስን የሆነውን የህዝብ ሃብት
በአግባቡ ለመጠቀም ነው ይላሉ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ሙስና የመከላከል ሞዴል እና የህግ
ማስከበር ሰርዓት ሁለቱም ተግባራዊ በሚያደርጉበት ጊዜ Multi agency model የሚከተሉ አገሮች
ናቸው ይባላል፡፡ በአንድ አገር ከሁለት በላይ የፀረ ሙስና ተቋማት ማደራጀት በተለይም በታዳጊ
አገሮች የሀብት ብክነት የሚያስከትል፣ ለስልጣን ፉክክር የሚጋብዝ፣ መንግስት ወጥ የሆነ
የአመራር ስርዓት ለመስጠት የሚቸገርበት፣ በተቋማቱ መሀል ቅንጅታዊ አሰራር ክፍተት
እንዲፈጠር እድል የሚፈጠር እና ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ አንድ ጠንካራ የፀረ ሙስና
ተቋም እንዳይኖር ያደርጋል በሚል በብዛት የሚተችበት ሁኔታም አለ ፡፡ እንዲያውም ባላደጉ አገሮች
ይህን ሞዴል መከተል እንደ passive model ወይም በአሁን ሰዓት ተቀባይነቱ እምብዛም ያልሆነ
ሞዴል ተብሎ የሚወሰድበት ሁኔታ አለ፡፡
ሙስና ካለው ባህሪ ነፃ እና ጠንካራ ተቋም ማደራጀት ተገቢ መሆኑን ብዙ ምሁራን ቢስማሙበትም
ሀገሮች የሚከተሉት ሞዴል የተለያየ በመሆኑ በዛው ልክ ሙስና በመከላከል ውጤታማነታቸውም
ይለያያል፡፡ በአብዛኛው ውጤታማነታቸው ደረጃ የሚታወቀው ገለልተኛ ነው ተብሎ በሚገመተው
ሐገሮች የሚግባቡበት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት
በየአመቱ በተለያዩ መለኪያዎች መዝኖ እና አወዳድሮ የሚያወጣውን የሙስና ቅኝት
11
ጥናት/Corruption Perception Index (CPI)/ በመውሰድ ነው:: ሀገሮች በዚህ ጥናት መሰረት
ያላቸውን ደረጃ ደግሞ በሚቀጥለው የየሀገሮችን ልምድ ከአየን በኋላ የምንመለከተው ይሆናል፡፡
ከዚህ ቀጥሎ የምናየው ከላይ ከገልፀነው ሰፋ ባለ መልኩ የየሀገሮቹ ልምድ በአሁኑ ወቅት የተሻለ
የሙስና መከላከል ስራ ሰርተው ሙስናን መግታት ችለዋል የምንላቸውን ብቻ ይሆናል፡፡ በዚህ
ረገድ የማይታበለው ሀቅ ግን የሀገሮች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚዊ እና ማህበራዊ መስተጋብራቸው እና
አወቃቀራቸው እጅግ የተለያየ በመሆኑ ሀገሮች ለሙስና ያላቸው ተጋልጭነት አንድ እና ያው ነው
የሚባል አለመሆኑን ነው፡፡ ይሁን እንጅ ሙስናን ለመግታት ከሚከተሉት ሞዴል አንፃር እና ከእኛ
ጋር ተቀራራቢነት ያላቸውን ተመሳሳይ ሀገሮች ከየክፍላተ ሀገሮቹ ለይቶ በማየት ለእኛ ሀገር
የሚሆነውን ልምድ በመወስድ ማስተካከያዎችን ለማድረግ ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡
4.1 የእሲያ ሀገሮች ልምድ
የእሲያ ሀገሮች ፈጣን እድገት በማስመዝገብ ላይ ያሉ ሀገሮች ከመሆናቸውም በላይ በፀረ ሙስና
ትግል ውጤታማነት ረገድ የሚወሰዱ መልካም ተሞክሮዎች አሏቸው፡፡ በዚህ አፈጻጸማቸው
ምክንያት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በየአመቱ በሚያወጣው ሪፖርት ከቻይና በስተቀር
አብዛኛዎቹ ሀገሮች እስከ 15ኛ ደረጃ ውስጥ የሚደረሰውን የሚይዙ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሀገሮች ውስጥ
ሲንጋፖርን እና ሆንግ ኮንግን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በ2017 ከ183 ሀገሮች ሲንጋፖር 84%
በማምጣት 5ኛ ደረጃ፣ የያዘች ሲሆን በ2018 ከ180 ሀገሮች ደግሞ 85% በማምጣት 3ኛ ደረጃ
እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 85% በማምጣት 4ኛ ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡ ሆንግ ኮንግ ደግሞ
በ2017 ከ183 ሀገሮች 77 % በማምጣት 13ኛ ደረጃ፣ የያዘች ሲሆን በ2018 ደግሞ ከ180 ሀገሮች
76% በማምጣት 14ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 76% በማምጣት 16ኛ ደረጃ ላይ
የምትገኝ ሀገር ነች፡፡
እነዚህ ሀገሮች የፀረ ሙስና ትግሉን የሚመራ ተቋም ያላቸው ሲሆን ዋነኛ ትኩረታቸው መልካም
ስነ-ምግባር በመገንባት እና የሰዎችን አስተሳሰብ በመቀየር የሚሰሩ ሲሆኑ ሁለገብ የፀረ ሙስና
ሞዴል የሚባለውን የሚከተሉ ናቸው፡፡ ለዚህ ስራ ከፍተኛ ሃብት እና ምርጥ የተባሉ ኃላፊዎች እና
ባለሙያዎች መድበው ሁሉንም አማራጮች ተጠቅመው ለውጤት ይሰራሉ፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን
ደግሞ የምርመራ ስራቸውን በፀረ ሙስና ተቋማቸው ስር አድርገው የሙስና ወንጀል የፈፀሙ
ሰዎችን መርምረው ያለ ምንም ምህረት ለህግ አቅረበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ያስደርጋሉ፡፡
አንዳንዶች ሀገሮች ለመቀጣጫ እንዲሆን እስከ ሞት ፍርድ ድረስ አስፈርደው በስቅላት ሳይቀር
12
ይቀጣሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ሙስናን ሙሉ በሙሉ ያላጠፉ ቢሆንም የሰላምና የእድገታቸው
እንቅፋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ማድረስ ችለዋል፡፡ ሙስናን መቆጣጠር እና መከላከል
በመቻላቸው ተከታታይነት ያለውን ኢኮኖሚያ እድገት ማምጣት ችሏል፡፡
4.2 የአውሮፓ ልምድ
አውሮፓ የበለፀገ የገቢያ እና ዳበረ የዴሞክራሲ ሥርዓት ያላቸው ሀገራትን የያዘ አህጉር ሲሆን
ሀገራቱም ሙስና ለስርዓታቸው አደጋ ወደ ማይሆንበት ደረጃ የደረሰ ነው ቢባልም ችግሩ እነሱም
ጋር ቢሆን የለም ማለት አይቻልም፡፡ ዜጋው መብቱን ከሞላ ጎደል የሚያውቅ በመሆኑ የሙስና
ሰለባ የመሆን እድሉ ዝቅተኛ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ሙስና ዓለም አቀፍ ወንጀል ከመሆኑም በላይ
ደንበር ተሻጋሪ ወንጀል መሆኑን ተገንዘበው ሌላ ለየት ያለ የምርመራ እና የክስ አደረጃጀት
ሳያስፈልጋቸው በመደበኛው የፍትህ ስርዓታቸው አማካኝነት ለመከላከል ጥረት ያደርጋሉ፡፡ በዚህም
እጅግ ውጤታማ መሆን እና እድገታቸውን ማስቀጠል ቸለዋል፡፡ ትራንሰፓረንሲ ኢንተርናሽናል
በየዓመቱ በሚያወጣው ሪፖርት ከሞላ ጎደል እነ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ሰፔን ወዘተ የመሳሰሉት
ሀገሮች ከ10ኛ ደረጃ በታች የሚወጡ እና ሙስና በከፍተኛ ደረጃ የቀነሱ ለኑሮ በጣም የሚመቹ
ሐገራት በመባል ይታወቃሉ፡፡
ከእነዚህ ሀገሮች ውስጥ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ እና ኖርዌይን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ዴንማርክ
በ2017 ከ183 ሀገሮች 88% በማምጣት 1ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን 2018 ከ180 ሀገሮች ደግሞ 88%
በማምጣት 1ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 87% በማምጣት 1ኛ ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡
ፊንላንድ በ2017 ከ183 ሀገሮች 85% በማምጣት 3ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን በ2018 ከ180 ሀገሮች
ደግሞ 86% በማምጣት 3ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 53% በማምጣት 51ኛ ደረጃ
ይዛ ትገኛለች፡፡ ኖርዌዬ በ2017 ከ183 ሀገሮች 85% በማምጣት 3ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን በ2018
ከ180 ሀገሮች ደግሞ 84% በማምጣት 7ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 84%
በማምጣት 7ኛ ደረጃ ይዘው ይገኛሉ፡፡
ይሁን እንጅ አውሮፓ እጅግ የበለፀገ እና የህብረሰተሰቡ የንቃተ ህሌና ደረጃ እጅግ በተለየ እና
በተሻለ ሁኔታ የሚታይ ነው፡፡ በመሆኑም ከአውሮፓ የሚወሰድ ልምድ የለም በሂደትም የእነሱን
13
መንገድ መከተል አያስፈልገንም ባይባል እንኳን አሁን ከአለንበት ሁኔታ ጋር ስናነፃፅረው ሶሻል
አወቃቀራቸው ከታዳጊ ሀገሮች በእጅጉ የተለየ በመሆኑ ተግባራዊ ለማድረግ አስቸጋሪ ነው፡፡
4.3 የአፍሪካ ልምድ
በአፍሪካ ውስጥ ሙስናን ከመታገል አንፃር አብዛኛዎቹ ሀገሮች ዘግይተው የጀመሩ ከመሆናቸውም
በላይ ከእኛ ልምድ ሲወስዱ የነበሩ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት በእድገታቸው ወደ ኋላ የቀሩ
ከመሆናቸውም በላይ የሚበዙት ሀገሮች በሙስና በከፋ መልኩ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ
የተወሰኑ ሀገሮችም ቢሆኑ በእድገት ላይ ያሉን ሙስናን ትርጉም በአለው ደረጃ በመቀነሳቸው
የሚደነቁ እና ልምድ የሚወሰድባቸው ሐገሮች አሉ፡፡ ከእነዚህ ሀገሮች ውስጥ ቦትስዋናን እና
ሩዋንዳን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በሚያወጣው ደረጃ
የተጠቀሱት ሀገራት ከ2017 ጅምሮ በአለው ጊዜ ከ50ኛ ደረጃ በታች ያለውን ደረጃ የሚይዙ ናቸው፡
፡ከእነዚህ ሀገሮች ውስጥ ቦትስዋና እና ሩዋንዳን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በ2017 ከ183 ሀገሮች
ቦትስዋና 61% በማምጣት 34ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን በ2018 ከ180 ሀገሮች ደግሞ 61% በማምጣት
34ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 61% በማምጣት 34ኛ ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡ ሩዋንዳ
ደግሞ በ2017 ከ183 ሀገሮች 55% በማምጣት 48ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን 2018 ከ180 ሀገሮች
ደግሞ 66% በማምጣት 48ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 53% በማምጣት 51ኛ ደረጃ
ይዘው ይገኛሉ፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ እነዚህ ሀገሮች ቀደም ብለው ከእኛ የፀረ ሙስና ትግል ልምድ ሲወስዱ የነበሩ
ዘግይተውም ቢሆን የልማታዊ መንግስትን መንገድ የተከተሉ እና በጥሩ ሁኔታ እያደጉ ያሉ ሀገሮች
ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ አሁን በአለው ሁኔታ ግን ከእኛ በእጥፍ በልጠው ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ
ኢትዮጵያ በ2017 ከ183 ሀገሮች 35% በማምጣት 107ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን በ2018 ከ180
ሀገሮች ደግሞ 34% በማምጣት 108ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 37% በማምጣት
96ኛ ደረጃን ያዛ ነው የምትገኘው፡፡ ይህ ደረጃ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቶባቸዋል ከሚባሉ
ሀገሮች ተርታ ሊያሰልፋት ወደ ሚችል ደረጃ እያመራች ከመሆኑም በላይ ከአማካኙ ደረጃ በታች
በመሆኗ የሙስና ትግላችን አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከዚህ ችግር ወጥተን
የሙስና ትግላችን መልክ ከአልያሳዝነው የእድገታችን ፀረ ከመሆኑ አልፎ የሰላማችን ጠንቅ መሆኑ
አይቀርም፡፡
14
ለማጠቃለል ያህል በፀረ ሙስና ትግል ላይ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የእሲያ እና የአፍሪካ
ሀገሮችን ልምድ ስንመረምር ለውጤታማነት ያበቃቸው ነገር ሙስናን ለመከላከል ያስቀመጡትን
ስርዓት በጥብቅ ተግባራዊ ማደረጋቸው፣ መንግስት ቁርጠኛ ሆኖ ዜጋው ሙስናን የማይሽከምና
የሙስና ትግሉ ባለቤት እንዲሆን ማድረግ በመቻላቸው እና ከዚህ ጎን ለጎን ሙስና የፈፀሙ ሰዎች
ሲያጋጥሟቸው መመርመር እና መክሰስ የሚችል ነፃና ጠንካራ የህግ ማስከበር ስራን በሚሰራው
የፀረ ሙስና ተቋም /ኮሚሽን/ ውስጥ በማደራጀት በቁርጠኝነት በመስራታቸው ነው፡፡ በዚህ ምክንያት
ሙስናን በመታገል ረገድ ጥሩ ልምድ/Best practice/ እና ትምህርት የሚወሰድባቸው ሀገሮች
ሁነዋል፡፡
4.4 ሊወሰድ የሚገባው መልካም ልምድ
ከዚህ በላይ የተመለከትናቸው ሀገሮች ልምድ የሚያሳየው ነገር ቢኖር ውጤታማ የሙስና
መከላከል ስራ ሊሰሩ የቻሉት ከእኛ የተለየ ጥብቅ የሙስና ህግና ተቋም ስለአላቸው አይደለም፡፡
ይለቁንስ ህዝባቸው እና መንግስታቸው ሙስና ጎጅ መሆኑን ከልብ ተቀብለው በአንድ በኩል ሙስና
ለመፈፀም የሚያስችል እድል እንዳይኖር በራቸውን አጥብቀው የቆለፉ መሆናቸው በልላ በኩል
ደግሞ ሙስና በመከላከል ብቻ ሊገታ እንደማይችል ተገንዘበው ጥብቅ የሆነ የምርመራ እና የክስ
ስርዓት አደረጅተው ለህግ የማቅረብ ስራ በአንድ ማእቀፍ በመስራታቸው ነው፡፡ በዚህ ረገድ ጥሩ
ልምድ ያላቸውን የእሲያ እና የአፍሪካ ሀገሮችን ልምድ ብንመለከት የምንወስዳቸው 3 መልካም
ልምዶችን ነው፡፡
1. የተጠናከረ የሙስና መከላከል ስራ መስራታቸው ቀዳሚው ሆኖ እናገኘዋለን
ከዚህ አንፃር ዜጋቸው መልካም ስነምግባር ያለው እንዲሆን ሁሉንም አማራጮቻቸውን ተጠቅመው
ሌት ተቀን ይሰራሉ፡፡ ለዚህም የትምህርት ተቋማትን፣ ሚዲያን፣ የሀይማኖት ተቋማትን፣ መደበኛ
ያልሆኑ የማስተማሪያ ዜዴዎችን እና ቴክኖሎጅዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ይህን በማድረጋቸው ህዝባቸው
ስርቶ መበልፀግን ብቻ አማራጭ እና ባህል እንዲያደረግ ከማድረጋቸውም በላይ የሙስና ትግሉ
ባለቤትና ዋናው ተዋናይ ሰራዊታቸው እንዲሆን ለማደረግ እና ለማሰለፍ ችለዋል፡፡ በእነዚህ
ሀገሮች ሙስና እየተፈፀመ አይቶ የሚያልፍ እና የሚታገስ ህዝብ የለም፡፡ የመንግስት አገልግሎት
የሚሰጠው በጎቦ እና በዘመድ ሳይሆን በህግ የሚሰጥ እና መብታቸው መሆኑን ተገንዘበዋል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ የሰው እና የገንዘብ ግንኙነት በቴክኖሎጅ ላይ የተመሰረት እንዲሆን በማደረግ
እያንዳንዷ የገቢ ምንጭ ቁጥጥር የሚደረገባት እንዲሆን ስለአደረጉ የተሰረቀ ሃብት ቢኖር እንኳን
15
ወዲያው የሚታወቅ እና እርምጃ የሚወሰድበት እንዲሆን በማድረጋቸው ነው፡፡ ይህን በማድረግ
ሃብት ማሳወቅ፣ማስመዝገብ እና ማጣራት ሳያስፈልጋቸው ከገቢ በላይ የተገኘ እና ምንጩ
ያልታወቀን ሃብት በቀላሉ ማወቅ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ሙስና የመፈፀምን እድል ሙሉ በሙሉ
ባይዘጉትም አደገኛነቱን መቀነስ እና ለእድገታቸው፣ ለሰላማቸው እና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት
ግንባታቸው እንቅፋት እንዳይሆን ማደረግ ችለዋል፡፡
2. የተጠናከረ የህግ ማስከበር ስራ የሚሰሩ መሆናቸው
ከአውሮፓ ውጭ ያሉት ሀገሮች ሙስናን ትርጉም ባለው ደረጃ መቀነስ የቻሉት መልካም
ስነምግባር ከመገንባት እና ሙስናን ከመከላከል ጎን ለጎን ሙስና የሚፈፅሙ እና በሙስና ለመክበር
የሚፈልጉ ሀይሎች ሲያጋጥሟቸው ነፃ የሆነ የምርመራ እና ክስ ስርዓት በአንድ ማእቀፍ
አደራጅተው ለህግ ማቅረብ በመቻላቸው ነው፡፡ ነፃ የሆነ የፀረ ሙስና ተቋም እና እሱ የሚመሩት
ምርመራ እና ክስ የሚያከናውን አደረጃጀት የፈጠሩበት ምክንያት ምርመራ የፖሊስ፣ ክስ ደግሞ
የአቃቢ ህግ ተፈጥሮዊ ስራ መሆኑን ዘንግተውት ሳይሆን ሙስና የሚፈፀምበት ስልት፣ ባህሪው፣
ውስብስብነቱ እና ፍጥነቱ በመደበኛው የምርመራ እና የክስ ስርዓት ለመቆጣጠር እንደማይችሉ
በመገንዘባቸው ነው፡፡ የፀረ ሙስና ተቋም አደረጃጀቱ ነፃ እና ከአስፈፃሚው አካል ተፅእኖ የተላቀቀ
ተጠሪነቱ ለህግ አውጭው እንዲሆን በማድረግ ደፍሮ በነፃነት የሚሰራ ስለሆነ ነው ጤታማ
የሆነው፡፡ ጠንካራ ግን ቁጥጥር የሚደረግበት የምርመራ አካል ስላላቸው ሙስናን በአግባቡ
መርምሮ ለህግ የማቅረብ ብቃት እንዳላቸው ተሞክሮውን መውሰድ ጠቃሚ ነው፡፡
በዚህ ረገድ ያደጉት ሀገሮች በተለይ መላው አውሮፓ ምርመራ እና ክስን በመደበኛው ስርዓት
ውስጥ አድርገው መምራታቸው እነሱ ከደረሱበት የእድገት ደረጃ እና ከአላቸው የቴክኖሎጅ አቅም
አንፃር ሲታይ ተገቢ ነው ሊባል ይችላል፡፡ የቱንም ያህል ውስብስብ የሙስና ወንጀል ቢፈፀም
መርምሮ ለህግ ለማቅረብ የሚችል በረጅም ጊዜ የተገነባ መደበኛ የምርመራ እና የክስ ስርዓት
ስላላቸው ሌላ አካል ማደረጃት አይገባቸውም፡፡ የስነምግባር ግንባታ እና የግንዛቤ ፈጠራ ላይ ብቻ
ሊስራ የሚችል ተቋም ከአላቸው በቂ ሊሆን ይችላል፡፡
ከዚህ አንፃር ለእኛ ሊወሰድ የሚገባው ተስማሚው ልምድ የአፍሪካ እና የእሲያ የምርመራ እና
የክስ አያያዝ ሥርዓት ነው፡፡ የአፍሪካ እና የእሲያ ሙስናን የመታገል ልምድ ምንም ችግር
16
የሌለበት ነው ሊባል አይችልም፡፡ በእነሱም ሀገር ሙስና የጠፋበት እና ለስርዓታቸው አደጋ ሊሆን
ወደ ማይችልበት ደረጃ አልደረሰም፡፡ ነገር ግን ትርጉም በአለው ደረጃ ቀንሰውታል፣ በሂደትም
ሊገቱት ይችላሉ ተብሎ ሊገመት ይችላል፡፡
በእኛም ሀገር ይኸው ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ ምርመራ እና ክስ በኮሚሽኑ ስር እንዲሆን ተደርጎ
ነበር፡፡ ነገር ግን የተበታተነውን ምርመራ እና ክስ ወደ አንድ ለማሰባሰብ በሚል አሳማኝ ባልሆነ
ምክንያት ወደ ሌሎች አካሎች እንዲሄድ ተደርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት ኮሚሽኑ የሙስና መከላከሉን
ከባዱን ተልዕኮ ያለ ምርመራ ይዞ ለአለፉት ጥቂት አመታት የቀጠለ ቢሆንም ሙስናን ለመከላከል
በሚያደረገው ጥረት ትግሉን ጀምሮ በራሱ መጨረስና ዳር ማድረስ ባለመቻሉ ሰሚ አጥቶ “ጥርስ
የሌለው አንበሳ” ሆኗል፡፡ ቀደም ሲል ክስ እና ምርመራ በኮሚሽኑ ስር በነበሩበት ጊዜ ሊያድጉ
የሚገባቸው መልካም ጅምሮች እና ውጤቶች ቢኖሩትም በሚከተሉት ጉልህ ችግሮች የተሳካ ስራ
ሰርቶ ውጤታማ ሆኗል ማለት አይቻልም፡፡ለዚህ ደግሞ በርካታ መሰረታዊ የሆኑ ሃገራዊ ቁልፍ
ምክንያቶች ያሉ ቢሆንም በተመረጡ ከባድ የሙስና ወንጀሎች ላይ ብቻ ባለማትኮሩ ሀሉንም
የሙስና ወንጀል ለመመርመር የሚያስችል የተደራሽነትም ሆነ የአቅም ችግር እና የአቅጣጫ
መሳት ችግር እንደነበረበት የሚካድ አይደለም፡፡ ይህን አጥንቶ በማስተካከል የኮሚሽኑን አቅም
በማሳደግ ውጤታማ ማድረግ ሲቻል የማንዴት ለውጥ በማድረግ ህዝቡን እና መንግስትን ይጎዳ
እንደሆነ እንጅ የሚያመጣው ጥቅም የለም፡፡
ምርመራ እና ክስ ወደ ፖሊስ እና አቃቢ ከመሄዱ ከአንድ አመት በፊት በ2007 ዓ.ም የኮሚሽኑን
የመርመር እና የመክሰስ ስልጣን የሚያጠናክሩ እጅግ ከባድ የሆኑ ስልጣኖች በአዋጅ ቁጥር 881፣
882 እና 883/2007 ዓ.ም በተባሉ የሙስና ህጎች ተሰጥተውት ነበር፡፡ የፀረ-ሙስና ልዩ የሥነ-
ሥርዓትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 882/2007 ለፍርድ ቤቶች ብቻ የሚሰጥ በሙስና የተዘረፈ
እና ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብን ለመቆጣጠር እንዲቻል የእግድ ትእዛዝ ሁሉ እንዲሰጥ ስልጣን
ተሰጥቶት ነበር፡፡በተመሳሳይ መልኩ በመንግስት ተቋማት ብቻ ተወስኖ የቆየዉ የኮሚሽኑ የስልጣን
ወሰን በአዋጅ ቁጥር 882/2007 መሰረት ወደግል ዘርፍ ማለትም ማህበራትን እንዲያካትት ተደርጎ
ተሸሽሏል፡፡ይሁን እንጅ እነዚ ማሻሻያዎች በተደረጉ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በ2008 ዓ.ም
በአልተጠና እና ጥድፊያ በሚታይበት መልኩ የተበታተነውን የምርመራ እና የክስ ሥራ
ለመሰብሰብ በሚል ሰበብ የምርመራ እና የክስ ስራ ወደ ሌሎች አካላት እንዲዛወር ተደርጓል፡፡
እንዲያውም ሞራል ለመንካት በሚመሰል መንገድ የነበረበት ህንፃ ተነጥቆ ለፌዴራል ቤቶች
17
ኮርፖሬሽን እንዲሰጥ እና ኃላፊነት በጎደለው መንገድ ያን ያክል የተደከመበት ሃብት እና ሰነድ
እንዲሁም የተገነባ የሰው ሀይል እንዲበታተን ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት በአለፉት ሶስት
ዓመታት የሙስና መከላከል ስራችን ከፍተኛ ችግር ገጥሞት ይገኛል፡፡ በመሆኑም የሙስና
መከላከል ስራው እንዲደክም እና ውጤታማ እንዳይሆን ተደርጓል፡፡
እስካሁን በአደረግናቸው እንቅስቃሴዎች የሙስና ትግሉ የተዳከመ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች
የሚታዩ ቢሆንም ይህንኑ በጥናት ለማስደገፍ በገለልተኛ አካል ማስጠናት ተገቢ በመሆኑ 3ኛው
ሀገር አቀፍ የሙስና ቅኝት ጥናት እየተካሄደ ሲሆን ውጤቱ ተጠቃሉ ሲቀርብ በሙስና መከላከል
ረገድ የደረስንበት ደረጃ የሚታወቅ ይሆናል፡፡
ጥናቱ ተጠቃልሎ ሲቀርብ ሙሉውን ስዕል መያዝ የሚቻል ቢሆንም በሀገራችን የተቀናጅ እና
የተሟላ ስልጣን ኖሮት፣ አሁን ያለው የፀረ ሙስና ትግል ያሉትን የቅንጅት ችግር ለመፍታት፣
የሚነሱ በፓሊስ እና ዓቃቤ ህግ ተቋማት የሚነሱ የገለልተኝነት እና የነፃነት ጥያቄዎች ከግምት
ውስጥ በማስገባት ምርመራን ጨምሮ ሁሉንም የሙስና መከላከል ስራ የሚሰራ ጠንካራ የፀረ
ሙስና ተቋም በመፍጠር የጀመርነውን ለውጥ ጉዞ ዳር ማድረስ ይገባል፡፡
3. ሙስናን ለመታገል ቁርጠኛ የሆነ መንግስት መፍጠር ይገባል
በሙስና ትግል ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት የቻሉት ሀገሮች የሚያሳየን ሌላው ልምድ
ቢኖር ሙስናን ለመታግል መንግስት ከልቡ ቁርጠኛ መሆን ያለበት መሆኑን ነው፡፡ ሙስና ከስልጣን
ጋር ብቻ የተያያዘ ነው ማለት ባይቻልም በበጀት እና በካዝና ላይ የማዘዝ ስልጣን ያለው
አስፈፃሚው አካል ስለሆነ እሱን ከሙስና ማፅዳት እና ህብረተሰቡን በሙስና ትግል ላይ ሚና
እንዲጫወት ማደረግ ይጠበቅበታል፡፡ ይህን ሳናድርግ የቱንም ያህል ጠንካራ እና ግዙፍ የፀረ ሙስና
ተቋም ብናደራጅ ውጤታማ መሆን እንደማይቻል ከሌሎች ሀገሮች ብቻ ሳይሆን ከእራሳችን
ልምድም መማር እንችላለን፡፡
በማንኛውም እንቅስቃሴ ውስጥ የህዝብ ተሳትፎ እና ወሳኝነት ምንም ተቃውሞ የማይቀርብበት ሃቅ
ቢሆንም የመሪዎች ሚና በቀላሉ የሚታይ ስላልሆነ ሙስናን በመታገል እና እራስን በማፅዳት
አርዕያ መሆን አለባቸው፡፡ “ስርአታችን ትልልቅ ሃላፊነትና ስልጣን በተሰጣቸዉ እና ይታመናሉ
ተብለዉ በሚጠበቁ ሰዎች (አመራሮች) ላይ የሚወሰን ነዉ ብሎ ነበር’’ Paul O’Neill, Secretary
of the Treasury, July 9, 2002፣ አባባሉ የራሱ ችግር ያለበት ቢሆንም ከከፍተኛ የመንግስት
18
የስራ ኃፊዎች የሚጠበቀውን ከፍተኛ የስነምግባር ደረጃ መያዝ ያለበቸው መሆኑን ያመላክታል፡፡
ለዚህ ደግሞ የጥቅም ግጭትን ማስተዳደር እና የከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን የስነምግባር
ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል፡፡
5. የሀገራችን የፀረ ሙስና ትግል የደረሰበት ደረጃ
5.1 የኢፌዴሪ የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አመሰራረት
የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በ1993 ዓ.ም ለመቋቋም መነሻ የሆነው በመንግስት
ከ1983 ጀምሮ የወሰዳቸው የተለያዩ የማሻሻያ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ ከተወሰዱት የማሻሻያ
ፕሮግራሞቹ አንዱ የስነ ምግባር ማሻሻያ ንኡስ ፕሮግራም ሲሆን በዚህ ንኡስ ፕሮግራም ተይዘው
ከነበሩ ፕሮጀክቶች አንዱ በሀገር ደረጃ የሰነ ምግባር ግንባታ ሙስናን በማእከል ደረጃ የሚያስተባብር
እና የሚመራ ተቋም ማደራጀት ነው፡፡ ቢዘህ መሰረት ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተጣጥሞ
የሚሄድ የፀረ ሙስና ትግሉን የሚመራ እና የሚያስተባብር ተቋም ለመፍጠር ለ14 ዓመታት ያህል
ሰፊ ጥናት ከተደረገ እና ከተለያዩ የአውሮፓ እና የኤስያ አገራት ልምድ ከተወሰደ በኋላ በ1993
ተቋቁሟል፡፡ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ መልካም ሰነ ምግባር የተላበሰ እና ሙስና የሚጠየፍ ህ/ሰብ
እንዲፈጠር፣ ሙስናና ብልሹ አሰራር ለልማታችን እና እድገታችን እንቅፋት እንዳይሆን ለማድረግ
ሰፊ ጥረት አድርገዋል፡፡ ከዚህ አልፎ ሙስና ላይ የተሳተፉ አከላት ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ
በኩል የማይናቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ በአጠቃላይ ሙስና የሚለውን በህ/ሰብ ዘንድ አጀንዳ እንዲሆን
በየዓመቱ በሺ የሚቆጠሩ ጥቆማዎች በመቀበል እና በማጣራት መንግስት እና ህዝብ የጣለበትን
ኃላፊነት ለመወጣት ጥረት አድርጓል፡፡ ኮሚሽኑ ከእነ ድክመቱም ቢሆንም እስከ 2007 በነበሩት
ጊዜያት ባከናወናቸው የፀረ ሙስና ተግባራት፣ በሰራቸው የምርመራ እና ክስ ስራዎች ለሌሎች
የአፍሪካ አገሮች ልምድ በማካፈል ጭምር ጥሩ ስም መገንባት ችሎ የነበረ ተቋም ነው፡፡
ሆኖም ግን ከ2008 ጀምሮ የተሰጡትን የምርመራ እና የክሰ ስራዎች ተነሰተው ለፖሊስ እና ዓቃቤ
ህግ አጥጋቢ ባላሆነ ምክንያት በመሰጠቱ በስራው ላይ የተለያየ ተፅእኖ መፍጠሩ አልቀረም፡፡
ኮሚሽኑ ገንብቶት የነበረው ስም እና በህዝቡ የነበረውን ተቀባይነት ባለፉት ዓመታት በተለይም
19
ከ2008 ጀምሮ ደረጃው እየቀነሰ መጥቷል፡፡ ለዚህ ተቀባይነት ማነስ የኮሚሽኑ የራሱ ድክመት
እንደተጠበቀ ሆኖ የምርመራ እና ዓቃቤ ህግ ስራዎች ከኮሚሸኑ ሰልጣን መውጣቱ ግን በእጅጉ
የህዝብ ተሳትፎ እንዲቀንስ፣ ኮሚሽኑ አሁን እየሰራቸው ባሉ ማንዴቶች አፈፃፀም/ተግባራዊነት/ ላይ
አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል ፡፡ ይባስ ብሎ በአሁን ሰዓት ኮሚሽኑ “ጥርሰ የሌለው አንበሳ እንዲባል”
አስችሎታል፡፡ ህግ አውጨው እና አስፈፃሚው አካል መረዳት የሚገባቸው ጉዳይ የኮሚሽኑ አፈፃፀም
ዝቅ እንዲል የተለያዩ ሀገራዊ እና ተቋማዊ ምክንያቶች ቢኖርም ኮሚሸኑ የተማላ ሰልጣን
(ማንዴት) እንዳይኖረው መደረጉ በኮሚሽኑ ዋና ዋና አፈፃፀሞች ላይ መድከም መታየቱ የአንበሳው
ድርሻ ይወስዳል፡፡ ግልፅ የሆነ ግንዛቤ እና አረዳድ እንዲኖረን በኮሚሽኑ የምርመራ እና ዓቃቤ ህግ
እያለ እና ከሄደ በኋላ በኮሚሽኑ ዋና ዋና ስራዎች ላይ የነበረው አፈፃፀም መመለከት የፈጠረውን
ተፅእኖ በቀላሉ ለመረዳት ያስቻላል ፡፡
5.2 የኮሚሽኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም
5.2.1 የግንዛቤ ፈጠራ ስራ አፈፃፀም
ኮሚሽኑ በአዋጅ ከተሰጡት ተግባራት አንዱ በሙስና ዙሪያ የህ/ሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና በፀረ ሙስና
ትግሉ የሚኖራውን ሚና እና ተሳትፎ ማሳደግ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በህትመት ሚድያ፣
በኤሌክትሮኒኪስ ሚድያ፣ በፊት ለፊት ትምህርት እና በተለያዩ የህ/ሰብ አካላት አማካኝነት የተለያዩ
የሰነ ምግባርና የፀረ ሙስና ትምህርት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከ2008 ጀምሮ የኮሚሸኑ የህግ
ማስከበር ስራ ከመሰዱ ጋር ተያይዞ በሰነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዙሪያ የሚሰጡ የስነ ምግባርና ፀረ
ሙስና ትምህርቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በጥራትም ይሁን በብዛት እየቀነሰ መጥቷል ማለት ይቻላል፡፡
የምርመራ እና ክስ ኬዞች ከትምህርትና ሰልጠና ጋር ተቀናጅተው የማይሄዱ በመሆኑ በትምህርቱ
ሳቢነት እና ተቀባይነት ተፅእኖ የፈጠረ ሲሆን ሰልጣኞች በተደጋጋሚ የሚያሰኑት ጉዳይ ሆኗል፡፡
ከዚህ አልፎ በሚሰጡ ትምህርቶች ላይ የምርመራ እና ክስ ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ እየተነሳ በሰልጠና
ሰጪዎች ላይ ቀላል የማይባል ጫና እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ኮሚሽኑ ድጋፍ አደርጎላቸው ወደ ታች
ወርደው አባሎቻቸው እንደያሰለጥኑ ተደራጅተው የነበሩ የስነ ምግባር አውታሮች የሚሰጡት
ትምህርት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቀባይቱ በእጅጉ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ አሰልጣኞች ላይ የፈጠረው ጫና
በራሱ በሙያ ረዥም ልምድ የነበራቸው ባለሙያዎች ኮሚሽኑ እንዲለቁ እድል ፈጥሯል፡፡
ለንፅፅር እንዲመች ሲሰጡ የነበሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ምን ያህል ተሳታፊ እየቀነሰ
እንደመጣ ከሰንጠረዡ በቀላሉ መረዳት ይቻላል::
20
ሰንጠረዥ 1.የተከናወኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች
ተ
.
ቁ
የትምህርት መሰጫ
ዘዴ
ምርመራና ዓቃቤ ህግ እያለ ምርመራ እና ዓቃቤ ሀግ ከሄደ በኋላ
2004 2005 2006 2007 2008 2009 2010 2011
1 በፊት ለፊት የተሰጠ
ትምህርት/ሰዎች ብዛት/
18,690 40,108 44,360 51,990 14,100 3134 7291 27,596
2 በብሮሸር የተሰጠ
ትምህርት/የታተመ
ብሮሸር /
20,000 20,427 60,000 116,000 20,000 75,000 10,000 201384
3 በሬድዮና ተለቬዥን
የተላለፉ ትምህርታዊ
ማስታወቅያ /ስፖቶች/
17 20 35 22 29 17 12 30
4 በሰነ ምግባር አውታሮች
የተሰጡ ትምህርቶች
6,842 286 19,790,82
8
10,975,
529
9,512 ,020 3,933 38,462 16,249 ---
5.2.2 የሙስና መከላከል ተግባራት ስራ አፈፃፀም
ኮሚሸኑ በአዋጅ ከተሰጡት ተልእኮዎች ሌላው በመንግስት መሰሪያ ቤቶች እና የልማት ድርጅቶች
የአሰራር ስርዓት ጥናት ማካሄድ እና አሰቸካይ የሙስና መካላከል ስራዎች ማከናወን ሲሆን የተሰጡ
ምክረ ሃሳቦች እና የተጠኑ ጥናቶች ተግባራዊ መሆናቸውን መከታተል ነው፡፡ ይሁን እንጅ ከ2008
ጀምሮ የምርመራ እና አቃቤ ህግ ስራ ከኮሚሽኑ በመውጣት በጥናቱ ሂደቱ፣ አተገባበሩ እና
ውጤታማነቱ ላይ ተፅእኖ ያረፈበት ሰራ ሆኗል፡፡ በተለይም የተጠኑ ጥናቶች ተቋማት ተግባራዊ
እንዲያደርጉ፣ የተሰጣቸውን ምክረ ሃሳብ ተብለው ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ምክር ሲሰጣቸው
ለመፈፀም ፍቃደኛ ያለመሆን፣ ኮሚሽኑ ይህን የሚያስገድድበት አቅም ሰለሌለው ከፍተኛ ወጪ
ወጥቶባው የተጠኑ ጥናቶች በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንዳይሆኑ እና ሸልፍ ላይ እንዲቀመጡ
እድል እየፈጠረ ይገኛል፡፡ የተሰጡ የሙስና መከላከል ምክረ ሃሳቦች ተግባራዊ በማድረግ በኩልም
የተቋማት ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ የአሰቸካይ የሙስና መከላከል ስራዎች
ተፈፃሚነት በተመሳሳይ ሁኔታ አተገባበሩ ላይ የተቋማት ፍቃደኝነት የሚጎድልበት ሁኔታ አለ፡፡
በዚህ መሰረት ከ2004 እስከ 2011 ዓ.ም ደረስ ለመፈፀም የታቀዱ የአሰራር ስርዓት ጥናቶች 579
ሲሆኑ 421 ወይ የእቅዱ 72.7% የተከናወኑ ሲሆኑ በተለይም የአደረጃጀት ለዉጡን ተከትሎ
እነዚህን ጥናቶች ተጠኝ ተቋማት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ሁኔታ
21
ባለመኖሩ ተፈፃሚነታቸው የሚጠበቀውን ያህል ሆኖ ሙስናን በሚፈለገዉ ደረጃ ለመከላለከል
አልቻሉም፡፡
ለምሳሌ ያክል በአስቸኳይ መከላከል ሥራ ኮሚሽኑ በ2007 በጀት አመት ብቻ ከ645,015,929.00
በላይ የህዝብ ሃብት ለማዳን የቻለ ሲሆን ከዚያ ወዲህ ባሉት ተከታታይ አመታት የተሰራዉ ድምር
ዉጤት ከዚህ አህዝ ጋር የሚመጣጠን አይደለም፡፡
ሰንጠረዥ 2. የተከናወኑ የሙስና መካላከል ስራዎች
ተ
.ቁ
የተከናወኑ የሙስና
መካላከል ስራዎች
የምርመራና ዓቃቤ ህግ ስራ
በኮሚሸኑ እያለ
ምርመራና ዓቃቤ ሀግ ስራ ከሄደ በኋላ
2004 2005 2006 2007 2008 2009 2010 2011
1 የታቀዱ የአሰራር ሰርዓቶች
ጥናቶች
64 87 87 88 30 65 74 81
2 ተግባራዊ የተደረጉ
የአሰራር ሰርዓት
ጥናቶች
37 69 78 83 32 33 31 61
3 የቀረቡ አሰቸካይ የሙስና
መከላከል ስራዎች
11 20 --- -- 28 19 29 26
5.2.3 የሃብት ማሳወቅ እና ምዝገባ ስራ አፈፃፀም
በተመሳሳይ ሁኔታ የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ስራ ከባለፉት ዓመታት ከነበረው የማሳወቅ እና
የማስመዝገብ እንቅስቃሴ ብዙ የተለየ ለውጥ ባይኖርም በተሿሚዎች አከባቢ የነበረው የሀብት
ምዝገባ ግን በራሱ ከፍተኛ ችግር የታየበት ነው፡፡
የምርመራ እና የክስ ስራ ከኮሚሽኑ ከተነሳ ጀምሮ የተመራጮች እና የመንግስት ሰራተኞች ምዝገባ
እየጨመረ ቢሄድም የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የሀብት ምዝገባ ቁጥር ግን እዚህ ግባ
የሚባል አይደለም ፡፡ በተለይም በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ያሉ አመራሮች ሀብት ለማስመዝገብ ሆነ
በአዋጁ መሰረት ጊዜው ጠብቆ ለማሳደስ ያለው ፍላጎት፣ ትብብር እና አርአያነት በጣም አነስተኛ
ነው፡፡ የሀብት ምዝገባ ስርዓት በከፍተኛ ሃላፊዎች ደረጃ መዳከም ኮሚሽኑ ከነበረው ማንዴት እና
22
ተፅእኖ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ግልፅ ነው፡፡ ምክንያቱም ኮሚሸኑ ማንዴቱ ከመወሰዱ በፊት
የነበረው የሀብት ምዝገባ በእጅጉ ተፈፃሚነት የነበረው ነው ማለት ይቻላል፡፡ በተለይም ሀብት
ለማስመዝገብ ወይም ለማሳደስ ፍቃደኛ ያልሆኑ አመራሮች ኮሚሽኑ ይህን ማስፈፀም የሚችል
አቅም የለውም ከሚል የመነጨ አሰተሳስብ ሊሆን እንሚችል ይገመታል፡፡ በሰንጠረዡ ላይ የቀረበው
መረጃ የሀብት ምዝግባ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ የሚያሳይ ቢሆንም የከፍተኛ አመራሮች
የማስመዘገብ እና የማሳደስ ዳታ ግን ችግር እንዳለ ከግምት ውስጥ መውሰድ ይገባል ፡፡
ሰንጠረዥ 3 ፡ የተከናወኑ የሀብት ምዝገባ ስራዎች
ተ
.ቁ
የተከናወኑ የሀብት
ምዝገባ ስራዎች
ምርመራና ዓቃቤ ህግ በኮሚሸኑ እያለ ምርመራ እና ዓቃቤ ሀግ ከሄደ ቡሃላ
2004 2005 2006 2007 2008 2009 2010 2011
1 ሀብታቸው ያስመዘገቡ
ሰራተኞች /
ተሸዋሚዎች ፤
ተመራጮች
10208 9968 17285 14423 34191 14150 13922 21363
5.2.4 የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ማደራጀት እና መደገፍ ስራ አፈፃፀም
ኮሚሽኑ ሌላ በአዋጁ ከተሰጡት ኃላፊነቶች ውስጥ አንዱ በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የልማት
ድርጅቶች የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ማደራጅት፤ ማብቃት እና ድጋፍ መሰጠት ነው፡፡
እኒዘህ ክፍሎች በየተቋሙ በስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዙሪያ የበላይ ኃላፊ የሚያማክሩ ሲሆኑ
የምርመራ እና ዓቃቤ ህግ ስራ በነበረበት ግዝያት ስነ ምግባር መኮነኖች ከኮሚሽኑ የነበራቸው
ትብብር እና ቅንጅት የተጠናከረ እና ጥሩ የነበረ የመከላከል፣ የጥቆማ እና ክስ አገልግሎት በአንድ
ተቋም የሚያገኙ የነበሩ በመሆኑ ጠንካራ ግኑኝነት ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከ2008
ጀምሮ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ከሦስት ተቋማት እንዲገናኙ እድል በመፍጠሩ የቅንጅት
እና የመነባብ ችግር ተከስቷል፡፡ የሚሰጣቸው ድጋፍ እና እገዛ ከተለያየ ተቋማት መሆኑ ለአላስፈላጊ
ምልልስ እና እንግልት ዳርጓቸዋል፡፡
23
ቀደም ሲል የተቋማት የበላይ ኃላፊዎች ይሰጥዋቸው የነበረውን ድጋፍ እና ተቀባይነት ቀንሷል፡፡
ከዚህ አልፍ ብሎ አደረጃጃታቸው እንዲታጠፍ፣ እንዲባረሩ ወይም ከነበሩበት ደረጀ ዝቅ እንዲሉ
እድል ፈጥሯል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ 169 የሚሆኑ የስነ ምግባር መኮነኖች (አዲስ የተደራጁ)
ጨምሮ በራሳቸው ፍቃድ የለቀቁ፣ ወደ ሌላ ስራ የቀየሩ ወይም በጫና ምክንያት የሰራ ለውጥ
ያደረጉ ናቸው፡፡ በቅርብ ጊዜ ተግባራዊ የተደረገውን ጂኤጂ አሰራር ምክንያት አለአግባብ ከስራ
መደቦቹ የተፈናቀሉ የስነ ምግባር መኮነኖች ቁጥርም ቢዘህ ውሰጥ የሚታይ ነው፡፡ ኮሚሸኑ ችግሩ
ለመቅረፍ እና ይህን ተገቢ ያልሆነ ድርጊት የፈፀሙ ተቋማት ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል
አቅም የሌለው በመሆኑ ይህን ችግር ጎልቶ እንዲወጣ እድል ፈጥሯል ፡፡
ሰንጠረዥ 2. የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ድጋፍ እና እገዛ ስራዎች
ተ
.
ቁ
የተከናወኑ የሙስና
መካላከል ስራዎች
የምርመራና ዓቃቤ ህግ ስራ
በኮሚሸኑ እያለ
ምርመራ እና ዓቃቤ ሀግ ስራ ከሄደ
በኋላ
2004 2005 2006 2007 2008 2009 2010 2011
1 ነባር በመልቀቃቸው
የተተኩ እና በአዲስ
መልክ የተደራጁ የስነ
ምግባር መከታተያ
ከፍሎች
20 34 38 20 38 36 87 169
5.2.5 የህዝብ ተሳትፎ ስራ አፈፃፀም
በፀረ ሙስና ትግሉ የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ ከሚባሉ ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ ያለ ህዝብ ተሳትፎ እና
ድጋፍ ውጤታማ የፀረ ሙስና ትግል ከቶ የሚታሰብ አይደለም፡፡ በተለይም ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት
ጊዜ ጀምሮ የነበረውን የህዝብ ተሳትፎ እና ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ህዝቡ ኮሚሽኑ የእኔ ነው የሚል
ስሜት ፈጥሮ በተለያየ አደረጃጀት ስር ታቅፎ ሲንቀሳቀስ የነበረበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡ ነገር ግን
ባለፉት ዓመታት የህዝብ ተሳትፎ እና ድጋፍ በእጅጉ የቀነሰበት የኮሚሽኑ ሰልጣን እና ኃላፊነት
መነሳት አግባብ አይደለም የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ በህዝብ ክንፍ መድረክ አቅርቧል፡፡ ከቅሬታ
ማንሳት አልፎ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የተለያዩ የፀረ ሙስና ጥምረቶች ከፀረ ሙስና ትግሉ
ወጥተዋል፡፡
ከ2001 ጀምሮ እስከ 2007 በሙያ፣ በፆታ እና በብዙሃን ማህበራት ተደራጅተው የነበሩትን 16 የፀረ
ሙስና አደረጃጀቶች (ወደ 920 ማህበራት እና አደረጃጀቶች) ቀንሰው በአሁኑ ሰዓት ወደ 6 የፀረ
24
ሙስና አደረጃጆት (ከ70 ማህበራት ያልበለጡ) ወርዷል፡፡ ይህ የሚያሰየው ህዝቡ ለኮሚሽኑ
ሲሰጠው የነበረውን ድጋፍ እና እገዛ በእጅጉ መቀነሱ ያሳያል፡፡ ኮሚሽኑ “ጥርስ የሌለው አንበሳ ነው
ስለሚባል” ከዚህ ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት ትርፉ ድካም ነው የሚል አሰተሳሰብ ጭምር በስፋት
እየተንፀባረቀ መጥቷል፡፡
5.2.6 ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው የቅንጅት እና ትብብር ስራ አፈፃፀም
ከ2008 ጀምሮ በሀገራችን የፀረ ሙስና ትግሉ ስራ በኃላፊነት እንድያሰተባብሩ የተሰጣቸው አካላት
ሦስት ናቸው ፡፡ እነዚህም የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
እንዲሁም የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ናቸው፡፡ በእነዚህ አካላት መካከል ጠንካራ እና
ተከታታይነት ያለው መረጃ የመለዋወጥ፣ የመደጋገፍ፣ በፀረ ሙስና ትግሉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን
በመለየት ተቀናጅቶ እና ተናቦ በመሄድ እና አንደ አንድ ጠንካራ የፀረ ሙስና እንቅስቃሴ እንዲፈጠር
በማድረግ በኩል ከፍተቶች ታይቷል፡፡ በእነዚህ ተቋማት አለመቀናጀት በተገልጋዮች በተለይ
በጠቋሚዎች እና ሰነ ምግባር መከተታያ ክፍሎች ሚቀርቡ የአገልገሎት አሰጣጥ ቅሬታዎች እና
አቤቱታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የመጡበት ሁኔታ እንዳለ ይስተዋላል፡፡
በ2008 እና በ2009 አካበቢ የተወሰነ የጋራ መድረክ በመፍጠር የቅንጅት ስራዎች ለመገምግም እና
አቅጣጫ ለመስጠት ጥረት የተደረገ ቢሆንም በቅንጅት የመገምገም ስራዎች ከሞላ ጎደል ተቋርጧል
ማለት ይቻላል፡፡ በአለፈው ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ተቋማቱ በጋራ ሊሰርዋቸው የሚገቡ ጉዳዮች
በመለየት የጋራ መግባባት ስምምነት ሰነድ ተፈራርመው ወደ ስራ ለመግባት ጥረት ያደረጉ ቢሆንም
የተፈለገው ለውጥ መጥቷል ተብሎ አይወሰድም፡፡ ከዚህ ውጪ በዚህ ዓመት እንደ ትልቅ እሴት
የሚወሰደው ፓርላማ እና ኮሚሽኑ የነበራቸውን ግኑኝነት ለማጠናከር እና የተቋሙ ችግሮች
ለመረዳት እና ለመፍታት የነበረውን ተነሳሽነት በእጅጉ የሚደነቅ ነው፡፡ ከሌሎች መሰል ባለድርሻ
አካላት ያለው ግኑኝነትም በቀጣይ ተጠናክሮ መሄድ ካልቻለ በፀረ ሙስና ትግሉ የሚፈጠረው ጫና
ቀላል አይደለም፡፡
5.2.7 የኮሚሸኑ የሰው ሀብት በተመለከተ
ኮሚሸኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን የሰው ሀይል ከጊዜ ወደ ጊዜ በቁጥር እየጨመረ የሄደ
ቢሆንም የሰው ሀይሉ ጥራት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የሄደበት ሁኔታ አለ፡፡ አዳዲስ ሰራተኞች
በመቅጠር እና በማሰልጠን ነባር እና የተሻለ እውቀት የነበውን ባለሙያ ለመተካት ጥረት የተደረገ
ቢሆንም ቀደም ሲል ተሰጥቶት የነበረውን የተሻለ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም privilege ባለመቀጠሉ
25
የነበረው የሰው ሀይል ማቆየት አልቻለም፡፡ በተለይም የነበውን ማንዴት መነሳቱ በሰራተኛ ዘንድ
አግባብ አይደለም የሚል አመለካከት ያለ በመሆኑ በተቋሙ የሚቆይበት ጊዜ በጣም አጭር እየሆነ
የሄደበት ሁኔታ አለ፡፡ በየወሩ ከኮሚሽኑ የሚለቅ ሰራተኛ ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ዛሬ ቀጥሮ ነገ
የሚሸኝ ተቋም ሆኗል ብለን ብንናገር ማጋነን አይሆንም፡፡
የፀረ ሙስና ተቋማት በህዝብ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ከተፈለገ ከመንግስት
የተሻለ ትኩረት የሚሹ፣ ተገቢውን ጥቅማጥቅም እንዲሁም ምቹ የሰራ ሁኔታ ተመቻችቶላቸው
ሊሰሩ እንደሚገባ ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ኮንቬንሸን ይመክራል፡፡ የተቋሙ ሰራተኞች በመንግስት
የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ህግ አውጪው ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ
የሚደግፍበት ሁኔታ መፍጠር አለበት፡፡
5.2.8 ምርመራና ክስ ወደ ፊዴራል ፖሊስና አቃቤ ህግ ከመሄዱ በፊት የነበረው ሁኔታ
የምርመራ እና ክስ ስራ ኮሚሽኑ ከተቋቋመ በኋላ ከ2003 ዓም ድረስ ተጠንክሮ ሲሰራ የነበረ
ቢሆንም በአሃዝ ደግፎ ለማሳየት እንዲቻል በመጀመሪያው ዘመን የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን
የእቅድ ዘመን እና ምርመራ እና ክስ ወደ ሌሎች ተቋማት ከመሄዱ በፊት ያለውን ብቻ ለማሳያ
ማቅረብ በቂ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
በዚህ መሰረት ከ2003 እሰከ 2007 በነበረው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽ ዘመን የቀረበ ጥቆማ
16,082 ሲሆን ከዚህ ውስጥ በራሳችን አቅም 2,148 በውክልና 921 ምርመራ የተደረገ ሲሆን
በ5,079 ላይ ደግሞ ቃቢ ህግ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በፍርድ ቤት ከቀረቡት 981 መዛግብት ውስጥ 853
ለኮሚሽኑ የተወሰነ ሲሆን በመዝገብ የመርታት ምጣኔ 86.95%፡፡ ለፍርድ ቤት ከቀረቡት 2,278
ተከሳሾች ውስጥ 1,798 ጥፋተኛ ተብለዋል በዚህም የመርታት ምጣኔ 78.92% ነበር፡፡
በስትራቴጅክ ዘመኑ በሙስና ተመዝበረው ከነበሩት ውስጥ የተመለሱትን ደግሞ 7 መኖሪያ ቤት፣
12 ህንፃዎች፣ 22 ተሸከርካሪዎች፣ 9 የንግድ ቤቶች፣ 538,683.3 ካሬ ሜትር የከተማ መሬት
ሲሆኑ ብር 125,918,715 በጥሬ ገንዘብ እና 81,422.76 ግራም ወርቅ ወደ መንግስት ካዝና
እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ ይህ የሚሳየው ነገር ቢኖር የኮሚሽኑ የመመርመር የማስቀጣት እና
የተመዘበርን የህዝብ ሃብት የማሥመለስ ልምድ እያደበረ የመጣ እና ተገቢውን የአመራር ድጋፍ
ቢያገኝ ከፍተኛ ውጤት ሊያሥመዘገብ የሚችል እንደነበር የሚያሳይ ነው፡፡
26
ይሁን እንጅ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የአለውን አፈፃጸም በዚህ ፁሁፍ ውስጥ ለማጠቃለል ጥረት
አድረገን የተጠቃለለ መረጃ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከጠቅላይ አቃቢ ህግ ማግኘት ባለመቻላችን
ዳታውን ለማከተት እና ለማነፀፃር አልቻልንም፡፡
6. ማጠቃለያ
ኮሚሽኑ በአዋጅ ሲቋቋም ምርመራ የፖሊስ ክስ ደግሞ የአቃቢ ህግ ስራ መሆኑ እየታወቀ ሀገራችን
ከአለባት የሙስና ተጋላጭነት አንፃር ታይቶ ምርመራ እና ክስ በኮሚሽኑ ውስጥ እንዲሆን ተደርጎ
ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ምርመራ እና ክስ ወደ ፖሊስ እና አቃቢ ከመሄዱ ከአንድ አመት በፊት
በ2007 ዓ.ም የኮሚሽኑን የመርመር እና የመክሰስ ስልጣን የሚያጠናክሩ እጅግ ከባድ የሆኑ
ስልጣኖች በአዋጅ ቁጥር 881፣ 882 እና 883/2007 ዓ.ም በተባሉ የሙስና ህጎች ተሰጥተውት
ነበር፡፡ ይሁን እንጅ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በ2008 ዓ.ም አጥጋቢ በአልሆነ ምክንያት
የተበታተነውን የምርመራ እና የክስ ሥራ ለመሰብሰብ እና ወደ ባለቤቶች ለመመለስ ነው በሚል
ሰበብ የምርመራ እና የክስ ስራ ወደ ሌሎች አካሎች እንዲዛወር ተደርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት
በአለፉት ሶስት ዓመታት የሙስና መከላከል ስራችን ከፍተኛ ችግር ገጥሞት ይገኛል፡፡ በመሆኑም
እንደ ሌሎቹ ሁለገብ የሙስና መከላከል ስራ እንደሚሰሩ ሀገሮች የምርመራ እና የክስ ስራው ከበቂ
በጀት እና ፋሲሊቲ ጋር ወደ ነበረበት ሊመለስ ከአልቻለ በሙስና ላይ ትርጉም ያለው ውጤት
ማምጣት አይቻልም፡፡
በአብዘኛዎቹ አገራት ስኬታማ የፀረ ሙስና ትግል ያካሄዱ ጨምሮ ያሳለፍዋቸው
ልምዶች/ተመክሮዎች እንደሚያሳዩት በእነዚህ ተቋማት የሚካሄድ መሰል ውጣ ውረዶች እና
የማደነቀፍ እንቅስቃሴዎች የተለመዱ መሆናቸው ነው ፡፡ የሄም ከተቻለ የፀረ ሙስና ትግሉ ሙሉ
ለሙሉ ለማጥፋት ከላሆነም ደግም ከማህበረ ሰቡ በመነጠል ተአማኒነቱን ለማሳጣት ዓላማ ያላቸው
መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምን ጊዜም ቁርጠኛ እና የጉዳዮች አቀራረብ በውል
ተረድቶ ምለሽ መሰጠት የሚችል የአመራር ቁርጠኝነት በተሟላበት ሁኔታ ከእነዚህ መሰናክሎች
ወጥተው ለውጤት እንዲበቁ አሰተወፀኦ ጉልህ የነበረ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻለል ፡፡
ተቋማት ለሙስና መከላከል እንቅስቃሴ የሚሰጡት ትኩረት በእጅጉ እያሽቆለቆለ መጥቷል፡፡
በተቋማት ዉስጥ የተቀናጀ የሙስና መከላከል ሥራ ለማከናወን ከ2008 በጀት አመት ጀምሮ
እንቅስቃሴ የተጀመረ ቢሆንም ቢኖርም ተቋማት ያላቸው ፍላጎት ዝቅተኛ በመሆኑ እና የህግ
አስገዳጅነት ባለመኖሩ ትርጉም ያለዉ ሥራ እየተከናወነ አይደለም፡፡ ሙስናን ለመከላከል ኮሚሽኑ
27
ከሚያካሂዳቸዉ ዋና ዋና ተግባራት አንዱ በጥናት ላይ ተመስርቶ የተቋማትን አሰራር ለሙስና እና
ለብልሹ አሰራር እንዳይጋለጥ ለማስቻል የአሰራር ስርአታቸው ተፍትሾ የማሻሻያ ሃሳቦች እና ምክር
ሃሳብ የሚቀርብ ቢሆንም ተቀብሎ ለመፈፀም ፈቃደኛ የማይሆኑ ተቋማት ከእለት እለት
ተበራክተዋል፡፡
ኮሚሽኑ በስነምግባር እና በሙስና ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የግንዛቤ ፈጠራ እና መጠነ
ሰፊ የስልጠና ስራዎችን መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ይሁን እንጅ አቅም እና ልምድ ያላቸው
ባለሙያዎች በስራው ላይ ለመቆየት የሚያችስችል አሰራር እና አደረጃጀት ያልተፈጠረለት በመሆኑ
ስልጠናው የአመለካከት ለዉጥ ለማምጣት በሚያሥችል መንገድ እየሄደ አይደለም፡፡ ከዚህም በላይ
የበጀት እና የማሰልጠኛ ቦታዎች እጥረትም አለበት፡፡
በተለያዩ ተቋማት በተለይም የበላይ አመራሩ የሃብት ምዝገባ ሥራን በአግባቡ ትኩረት ሰጥቶ
ያለማከናወን ሁኔታ ስለሚታይ ከገቢ በላይ የሚገኝ እና ምንጩ ያልተወቀን ሃብት መቆጣጠር
አልተቻለም፡፡ ከዚህ በላይ የተመዘገበው ሃብት እና ሰነድ በቢሮ እጥረት ምክንያት ለችግር ተጋል
ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተመዘገበውን ሃብት ለህዝብ ይፋ የሚደረግበት ሶፍት ወይር ልማት
ተጠናቆ ወደ ስራ ባለመግባቱ የሃብት ምዝገባ ሰራ አመኔታን እያጣ መጥቷል፡፡
ሙስናን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ለመከላከል እና መልካም ስነምግባር ያለው ትውልድ ለመፈጠር
እንዲቻል ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በየተቋሙ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎችን በአግባቡ ለማደራጀት
ጥረት ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጅ አደራጅቶ በአግባቡ ከመጠቀም ይልቅ ባልተገባ መንገድ የማፍረስና
የማሸማቀቅ ሥራዎች በሰፊዉ እየተስተዋሉ ነዉ፡፡ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የስነምግባር መከታተያ ክፍሎችን አደረጃጀት በማጠናከር ወደ ስራ ከማስገባት አንፃር ያለው ሁኔታ
በአግባቡ መቀረፍ ይኖርበታል፡፡
በፀረ ሙስና ትግሉ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸዉ የሚታመንባቸው የህዝብ አደረጃጀቶችን የሚወክሉ
ማህበራትና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ጋር ጥምረት የፈጠረ እና ትግሉን ወደ ህዝብ ለማድረስ
የሚያስችሉ ጥምረቶች እና ስራ አስፈፃሚዎች የነበሩት ሲሆን በአዩት የትኩረት ማነስ ምክንያት
ከጥምረቱ ሲወጡ እና ተስፋ ሲቆርጡ ታይተዋል፡፡ በመሆኑም አደረጃጀቶችን የትግሉ ባለቤት
ሊያደርጉ የሚችሉ አደረጃጀቶችን ማጠናከር እና ወደ ህዝብ መድረስ ይገባል፡፡
28
7. የፀረ ሙስና ትግሉ ለማጠናከር ሊወሰዱ የሚገባቸዉ እርምጃዎች
የሙስና ችግር በሃገራችን ሊፈጥር የሚችለዉን የከፋ ጉዳት ለመከላከል ዉጤታማ የሆነ ሥርአት
እና አደረጃጀት ፈጠሮ ለተግባራዊነቱ ተገቢዉን ርብርብ ማድረግ የሚጠይቅ እና ጊዜ የማይሰጠው
ጉዳይ ሆኗል፡፡
በመሆኑም ከዚህ ቀጥለው የቀረቡ እርምጃዎች በህግ አውጭው አካል መወሰድ እና ትግሉን ወደ
ከፍታ ማሽገር አለብን ብለን እናምናለን፡፡
1. ኮሚሽኑ በጥናት ላይ ተመስርቶ በአዋጅ ሲቋቋም በአዋጅ ቁጥር 235/1993፣ በአዋጅ ቁጥር
433/1997 እንደገና በማሻሻያ በአዋጅ ቁጥር 883/2007 ተሰጥተውት የነበሩት የምርመራ
እና የክስ ስራዎች እንዲመለሱለት ቢደረግ፣
2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተመለከተው አማራጭ የመፍትሄ ሃሳብ ተግባራዊ የማይደረግበት
ነባራዊ እና አሰማኝ ምክንያት ካለ የሙስና መከላለከል እና የምርመራ ስራዎች አንድ ላይ
ተጣምረው ተግባራዊ የሚደረግበት የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ቢደረግ፣
3. ተቋሙ በህግ የተሰጠው ኃላፊነት በሙሉ ዓቅሙ ውጤታማ ሆኖ እንዲሰራ እና ሌሎች
ፈፃሚ የመንግስት ተቋማትን በፀረ ሙስና ትግሉ የተጣሉባቸውን ሓላፊነትና ተግባር
በአግባቡ እንዲፈፅሙ የሚያስችል እና በማይፈፀሙ ተቋማት ላይ ተጠያቂነት የሚያስከትል
አሰገዳጅ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ቢደረግ፣
4. ኮሚሽኑ ተቋማዊ ነፃነት ኖሮት በህግ የተሰጡትን ተግባር እና ኃላፊነቶች በአግባቡ
ለመወጣት የሚያስችለው የሰው ኃይል፣ የፋሲሊቲ እና በቂ የበጀት ድጋፍ የሚያገኝበት
ሁኔታ ቢፈጠር በሀገሪቱ በፀረ ሙስና ትግል ላይ የሚደረገውን ትግል ወደላቀ ደረጃ
እንደሚያሸጋግረው ይታመናል ፡፡

More Related Content

What's hot

Т.Энхжаргал - НИЙТИЙН ЗОРЧИГЧДЫН АВТО ТЭЭВРИЙН ТУЛГАМДСАН АСУУДАЛ, ТҮҮНИЙГ ШИ...
Т.Энхжаргал - НИЙТИЙН ЗОРЧИГЧДЫН АВТО ТЭЭВРИЙН ТУЛГАМДСАН АСУУДАЛ, ТҮҮНИЙГ ШИ...Т.Энхжаргал - НИЙТИЙН ЗОРЧИГЧДЫН АВТО ТЭЭВРИЙН ТУЛГАМДСАН АСУУДАЛ, ТҮҮНИЙГ ШИ...
Т.Энхжаргал - НИЙТИЙН ЗОРЧИГЧДЫН АВТО ТЭЭВРИЙН ТУЛГАМДСАН АСУУДАЛ, ТҮҮНИЙГ ШИ...batnasanb
 
Г.Уранчимэг - Цахим менежмент
Г.Уранчимэг - Цахим менежментГ.Уранчимэг - Цахим менежмент
Г.Уранчимэг - Цахим менежментbatnasanb
 
хүүхдийн хүмүүжил
хүүхдийн хүмүүжилхүүхдийн хүмүүжил
хүүхдийн хүмүүжилTsedo Batsukh
 
Төгсөгчдийн хөдөлмөр эрхлэлтийн судалгаа
 Төгсөгчдийн хөдөлмөр эрхлэлтийн судалгаа Төгсөгчдийн хөдөлмөр эрхлэлтийн судалгаа
Төгсөгчдийн хөдөлмөр эрхлэлтийн судалгааHodolmor
 
Feed back may_report_contents (1)
Feed back may_report_contents (1)Feed back may_report_contents (1)
Feed back may_report_contents (1)berhanu taye
 
Education and Training for All ACTION RESEARCH ET -.pdf
Education and Training for All  ACTION RESEARCH ET -.pdfEducation and Training for All  ACTION RESEARCH ET -.pdf
Education and Training for All ACTION RESEARCH ET -.pdfberhanu taye
 
хөдөлмөрийн гэрээний загвар
хөдөлмөрийн гэрээний загвархөдөлмөрийн гэрээний загвар
хөдөлмөрийн гэрээний загварZaya G
 
Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptx
Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptxLife Skill Training PPT Final Aug 19.pptx
Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptxMasreshaA
 
Community-based organization__leadership_and_capacity_building_to_woreda_ass...
 Community-based organization__leadership_and_capacity_building_to_woreda_ass... Community-based organization__leadership_and_capacity_building_to_woreda_ass...
Community-based organization__leadership_and_capacity_building_to_woreda_ass...berhanu taye
 
сургалтын чиглэлээр хий сэн ажлын тайлан 2014.09.
сургалтын чиглэлээр хий сэн ажлын тайлан 2014.09.сургалтын чиглэлээр хий сэн ажлын тайлан 2014.09.
сургалтын чиглэлээр хий сэн ажлын тайлан 2014.09.Мөнхжаргал Пүрэвдорж
 
багш ажлын байранд хөгжихөд хамтын үйл ажиллагааны үр
багш ажлын байранд хөгжихөд хамтын үйл ажиллагааны үрбагш ажлын байранд хөгжихөд хамтын үйл ажиллагааны үр
багш ажлын байранд хөгжихөд хамтын үйл ажиллагааны үрza tosontsengel L.Tsendiin neremjit 11 Jil
 
материал сонголт
материал сонголтматериал сонголт
материал сонголтschool14
 
Hudulmuriin geree
Hudulmuriin gereeHudulmuriin geree
Hudulmuriin gereeMzul Zula
 
УРЬДЧИЛАН ШИЙДВЭРЛЭХ АЖИЛЛАГАА ХИЙГДЭХ МАРГААНЫ ТӨРЛҮҮД
УРЬДЧИЛАН ШИЙДВЭРЛЭХ АЖИЛЛАГАА ХИЙГДЭХ МАРГААНЫ ТӨРЛҮҮДУРЬДЧИЛАН ШИЙДВЭРЛЭХ АЖИЛЛАГАА ХИЙГДЭХ МАРГААНЫ ТӨРЛҮҮД
УРЬДЧИЛАН ШИЙДВЭРЛЭХ АЖИЛЛАГАА ХИЙГДЭХ МАРГААНЫ ТӨРЛҮҮДUmguullin Mongol Umguulugch
 
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]berhanu taye
 

What's hot (20)

Т.Энхжаргал - НИЙТИЙН ЗОРЧИГЧДЫН АВТО ТЭЭВРИЙН ТУЛГАМДСАН АСУУДАЛ, ТҮҮНИЙГ ШИ...
Т.Энхжаргал - НИЙТИЙН ЗОРЧИГЧДЫН АВТО ТЭЭВРИЙН ТУЛГАМДСАН АСУУДАЛ, ТҮҮНИЙГ ШИ...Т.Энхжаргал - НИЙТИЙН ЗОРЧИГЧДЫН АВТО ТЭЭВРИЙН ТУЛГАМДСАН АСУУДАЛ, ТҮҮНИЙГ ШИ...
Т.Энхжаргал - НИЙТИЙН ЗОРЧИГЧДЫН АВТО ТЭЭВРИЙН ТУЛГАМДСАН АСУУДАЛ, ТҮҮНИЙГ ШИ...
 
Г.Уранчимэг - Цахим менежмент
Г.Уранчимэг - Цахим менежментГ.Уранчимэг - Цахим менежмент
Г.Уранчимэг - Цахим менежмент
 
хүүхдийн хүмүүжил
хүүхдийн хүмүүжилхүүхдийн хүмүүжил
хүүхдийн хүмүүжил
 
Төгсөгчдийн хөдөлмөр эрхлэлтийн судалгаа
 Төгсөгчдийн хөдөлмөр эрхлэлтийн судалгаа Төгсөгчдийн хөдөлмөр эрхлэлтийн судалгаа
Төгсөгчдийн хөдөлмөр эрхлэлтийн судалгаа
 
Feed back may_report_contents (1)
Feed back may_report_contents (1)Feed back may_report_contents (1)
Feed back may_report_contents (1)
 
Education and Training for All ACTION RESEARCH ET -.pdf
Education and Training for All  ACTION RESEARCH ET -.pdfEducation and Training for All  ACTION RESEARCH ET -.pdf
Education and Training for All ACTION RESEARCH ET -.pdf
 
хөдөлмөрийн гэрээний загвар
хөдөлмөрийн гэрээний загвархөдөлмөрийн гэрээний загвар
хөдөлмөрийн гэрээний загвар
 
Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptx
Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptxLife Skill Training PPT Final Aug 19.pptx
Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptx
 
Hudulmuriin geree
Hudulmuriin gereeHudulmuriin geree
Hudulmuriin geree
 
Community-based organization__leadership_and_capacity_building_to_woreda_ass...
 Community-based organization__leadership_and_capacity_building_to_woreda_ass... Community-based organization__leadership_and_capacity_building_to_woreda_ass...
Community-based organization__leadership_and_capacity_building_to_woreda_ass...
 
Lecture 1
Lecture 1Lecture 1
Lecture 1
 
сургалтын чиглэлээр хий сэн ажлын тайлан 2014.09.
сургалтын чиглэлээр хий сэн ажлын тайлан 2014.09.сургалтын чиглэлээр хий сэн ажлын тайлан 2014.09.
сургалтын чиглэлээр хий сэн ажлын тайлан 2014.09.
 
багш ажлын байранд хөгжихөд хамтын үйл ажиллагааны үр
багш ажлын байранд хөгжихөд хамтын үйл ажиллагааны үрбагш ажлын байранд хөгжихөд хамтын үйл ажиллагааны үр
багш ажлын байранд хөгжихөд хамтын үйл ажиллагааны үр
 
Melanoma tumor
Melanoma tumorMelanoma tumor
Melanoma tumor
 
материал сонголт
материал сонголтматериал сонголт
материал сонголт
 
Hudulmuriin geree
Hudulmuriin gereeHudulmuriin geree
Hudulmuriin geree
 
УРЬДЧИЛАН ШИЙДВЭРЛЭХ АЖИЛЛАГАА ХИЙГДЭХ МАРГААНЫ ТӨРЛҮҮД
УРЬДЧИЛАН ШИЙДВЭРЛЭХ АЖИЛЛАГАА ХИЙГДЭХ МАРГААНЫ ТӨРЛҮҮДУРЬДЧИЛАН ШИЙДВЭРЛЭХ АЖИЛЛАГАА ХИЙГДЭХ МАРГААНЫ ТӨРЛҮҮД
УРЬДЧИЛАН ШИЙДВЭРЛЭХ АЖИЛЛАГАА ХИЙГДЭХ МАРГААНЫ ТӨРЛҮҮД
 
Trainig2 (4)
Trainig2 (4)Trainig2 (4)
Trainig2 (4)
 
Hicheel12
Hicheel12Hicheel12
Hicheel12
 
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
 

More from HeryBezabih

Anti corruption institutions challenges in Ethiopia (haregot Abreha ).docx
Anti corruption institutions challenges in Ethiopia  (haregot Abreha ).docxAnti corruption institutions challenges in Ethiopia  (haregot Abreha ).docx
Anti corruption institutions challenges in Ethiopia (haregot Abreha ).docxHeryBezabih
 
corruption in Ethiopia projects(haregot abreha ).pdf
corruption in Ethiopia projects(haregot abreha ).pdfcorruption in Ethiopia projects(haregot abreha ).pdf
corruption in Ethiopia projects(haregot abreha ).pdfHeryBezabih
 
Haregot abreha feacc- us deligation ppt
Haregot abreha   feacc- us deligation pptHaregot abreha   feacc- us deligation ppt
Haregot abreha feacc- us deligation pptHeryBezabih
 
Haregot abreha ethiopian civil socities working on anti corruption-world banl
Haregot abreha   ethiopian civil socities working on anti corruption-world banlHaregot abreha   ethiopian civil socities working on anti corruption-world banl
Haregot abreha ethiopian civil socities working on anti corruption-world banlHeryBezabih
 
Haregot abreha anti corruption day celebration report
Haregot  abreha  anti corruption day celebration reportHaregot  abreha  anti corruption day celebration report
Haregot abreha anti corruption day celebration reportHeryBezabih
 
Haregot abreha uncac presentation
Haregot  abreha   uncac presentationHaregot  abreha   uncac presentation
Haregot abreha uncac presentationHeryBezabih
 
Haregot abreha anti corruption report -world bank
Haregot  abreha anti corruption  report -world bankHaregot  abreha anti corruption  report -world bank
Haregot abreha anti corruption report -world bankHeryBezabih
 
Haregot aberha undp progress report -anti corruption commission
Haregot  aberha  undp progress report -anti corruption commissionHaregot  aberha  undp progress report -anti corruption commission
Haregot aberha undp progress report -anti corruption commissionHeryBezabih
 

More from HeryBezabih (8)

Anti corruption institutions challenges in Ethiopia (haregot Abreha ).docx
Anti corruption institutions challenges in Ethiopia  (haregot Abreha ).docxAnti corruption institutions challenges in Ethiopia  (haregot Abreha ).docx
Anti corruption institutions challenges in Ethiopia (haregot Abreha ).docx
 
corruption in Ethiopia projects(haregot abreha ).pdf
corruption in Ethiopia projects(haregot abreha ).pdfcorruption in Ethiopia projects(haregot abreha ).pdf
corruption in Ethiopia projects(haregot abreha ).pdf
 
Haregot abreha feacc- us deligation ppt
Haregot abreha   feacc- us deligation pptHaregot abreha   feacc- us deligation ppt
Haregot abreha feacc- us deligation ppt
 
Haregot abreha ethiopian civil socities working on anti corruption-world banl
Haregot abreha   ethiopian civil socities working on anti corruption-world banlHaregot abreha   ethiopian civil socities working on anti corruption-world banl
Haregot abreha ethiopian civil socities working on anti corruption-world banl
 
Haregot abreha anti corruption day celebration report
Haregot  abreha  anti corruption day celebration reportHaregot  abreha  anti corruption day celebration report
Haregot abreha anti corruption day celebration report
 
Haregot abreha uncac presentation
Haregot  abreha   uncac presentationHaregot  abreha   uncac presentation
Haregot abreha uncac presentation
 
Haregot abreha anti corruption report -world bank
Haregot  abreha anti corruption  report -world bankHaregot  abreha anti corruption  report -world bank
Haregot abreha anti corruption report -world bank
 
Haregot aberha undp progress report -anti corruption commission
Haregot  aberha  undp progress report -anti corruption commissionHaregot  aberha  undp progress report -anti corruption commission
Haregot aberha undp progress report -anti corruption commission
 

Anti corruption institutions challenges in Ethiopia (haregot Abreha ).pdf

  • 1. የፌዴራል የስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ተቋማት ልምዶች፣ በሀገራችን የፀረ ሙስና ትግል ያለበት ደረጃ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ሊወሰዱ የሚገባቸው የመፍትሔ እርምጃዎች ለህግ አውጭው አካል የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅራቢ ፡ ሐረጎት አብረሃ የስነ ምግባር አውታሮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር መጋቢት 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ
  • 2. 2 ማውጫ ርዕስ ገፅ 1. መግቢያ-----------------------------------------------------------------------------------------------3 2. የሙስና ታሪካዊ አመጣጥ በኢትዮጵያ-----------------------------------------------------------4 3. የሙስና ትርጉም------------------------------------------------------------------------------------5 4. በፀረ ሙስና ትግል ውጤታማ የሆኑ ሀገሮች ልምድ-----------------------------------------7 4.1 የእስያ ሀገሮች ልምድ---------------------------------------------------------------------10 4.2 የአውሮፓ ልምድ----------------------------------------------------------------------------11 4.3 የአፍሪካ ልምድ------------------------------------------------------------------------------12 4.4 ሊወሰድ የሚገባው መልካም ልምድ------------------------------------------------------13 5. የሀገራችን የፀረ ሙስና ትግል የደረሰበት ደረጃ----------------------------------------------17 5.1 የኢፌድሪ የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አመሰራረት---------------------------17 5.2 የኮሚሽኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም -------------------------------------------------18 5.2.1 የግንዛቤ ፈጠራ ስራ አፈፃፀም----------------------------------------------------------18 5.2.2 የሙስና መከላከል ስራ አፈፃፀም-------------------------------------------------------19 5.2.3 የሃብት ማሳወቅ እና ምዝገባ ስራ አፈፃፀም -----------------------------------------20 5.2.4 የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ማደራጀት እና መደገፍ ስራ አፈፃፀም--------21 5.2.5 የህዝብ ተሳትፎ ተሳትፎ ስራ አፈፃፀም ተግባራት -------------------------------22 5.2.6 ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው የቅንጅት እና ትብብር ስራ አፈፃፀም-------------23 5.2.7 የኮሚሸኑ የሰው ሀብት በተመለከተ----------------------------------------------------23 5.2.8 የክስ እና ምርመራ ስራ አፈፃፀም-----------------------------------------------------24 6. ማጠቃላያ--------------------------------------------------------------------------------------------25 7. የፀረ ሙስና ትግሉ ለማጠናከር ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎች--------------------------26
  • 3. 3 የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ተቋማት ልምዶች፣ በሀገራችን የፀረ ሙስና ትግል ያለበት ደረጃ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ሊወሰዱ የሚገባቸው የመፍትሔ እርምጃዎች 1. መግቢያ ሙስና የነፃ ገቢያ ውድድርን በማዳከም የሀገሮችን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ፣ አለመረጋጋትን የሚያስከትል እና ዲሞክራሲን በከፍተኛ ደረጃ በማናጋት ለቀውስ የሚዳርግ አደገኛ ወንጀል መሆኑ መግባባት ላይ ከተደረሰበት ቆየት ብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የፀረ ሙስና ስምምነቶች እና ትብብሮችን በማድረግ ይህን ዓለም አቀፍ የሆነ ችግር ለመግታት ጥረት ሲደረግ ይታያል፡፡ ሀገራት በዚህም ሳይወሰኑ የራሳቸው የሙስና መከላከያ እና መዋጊያ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው ከማደረጋቸውም በላይ ተቋም አቋቁመው ችግሩን ለመግታት ጥረት በማደረግ ላይ ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ ከወንጀሉ ልዩ ባህሪ በመነጨ ማለትም ሙስና ከአለው አደገኛነት፣ውስብስብነት እና ተለዋዋጭነት አንፃር አብዛኞቹ ያደረጉትን ትግል ያህል ከሙስና መፅዳት እንዳልቻሉ በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡በተቃራኒዉ ደግሞ በቁጥር ዉስን ቢሆኑም ተጋላጭነታቸውን እና ጉዳቱን በከፍተኛ ርብርብ በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ የሰላማቸው እና የልማታቸው ጠንቅ ወደ ማይሆንብት ደረጃ ያደረሱ ሀገሮች አሉ፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም የሙስናን ጎጅነት፣ ለልማት እና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ያለውን አደገኛነት በመረዳት የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ከማድረጓም በላይ ትግሉን የሚያስተባብር እና የሚያቀናጅ ተቋም እንደሚያስፈልጋት መግባብት ላይ ተደርሷል:: በዚህ መሰረት በ1993 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር235/1993፣ በአዋጅ ቁጥር 433/1997 እንደገና በማሻሻያ በአዋጅ ቁጥር 883/2007 ዓ.ም እንደገና በማሻሻል የፌዴራል የስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አቋቁማ ለአለፉት 19 ዓመታት ሙስናን ለመግታት ጥረት ስታደረግ ቆይታለች፡፡ ከማቋቋሚያ አዋጆች በተጨማሪ የሙስናን ወንጀል በሚመለከት እጅግ ጥብቅ የሆኑ እንደ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ 881/2007፣ የፀረ-ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/97 እና 882/2007፣ የጠቋሚዎች እና የምስክሮች ጥበቃ እና ከለላ ህግ የመሳሰሉ ለሙስና መከላከል እና ትግል የሚያገለግሉ ህጎች ወጥተዋል፡፡
  • 4. 4 በእነዚህ አመታት የተገኙ አበረታች ውጤቶች ቢኖሩም አሁንም የሰላማችን እና የልማታችን ጠንቅ መሆኑ አልቀረም፡፡ በመሆኑም ሙስና የልማታችን እና የሰላማችን ጠንቅ ወደ ማይሆንበት ደረጃ ላይ ማድረስ አልተቻለም፡፡ ሀገራችን የተረጋጋ ሰላም እና ልማት እንዳይኖራት ከፍተኛ ማንቆ ሆኖ እየቀጠለ ይገኛል፡፡ በፀረ ሙስና ትግል ላይ የተሳካ ትግል ያደረጉ ሀገሮች በቀጣይነት የተረጋጋ ፖለቲካዊ ሰርዓት፣ ቀጣይነት ያለው እና ህዝብን አሳታፊ ያደረገ ልማት መገንባት የቻሉት በፀረ ሙስና ትግሉ ህዝቡ ባለቤት እንዲሆን የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣታቸው፣ መንግስት ከህዝብ በአደራ የተሰጠውን ሥልጣን ለግል መገልገያ እንዳይሆን ለመታገል የሚያስችል ሰርዓት በመፍጠራቸው፣ መንግስት የፀረ ሙስና ትግሉ ላይ ተገቢ እገዛ እና ድጋፍ ከመስጠቱ በተጨማሪ ሙስናን የመፈፀሙ የመንግስት መርምረው ወደ ህግ እንዲቀርቡ በማድረግ ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያሳዩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ይህን የፀረ ሙስና ትግል የሚመራ እና የሚያስተባብር ነፃና እና ጠንካራ የፀረ ሙስና ተቋም አደረጃጀት በመፍጠራቸው የመጣ ውጤት መሆኑን ብዙ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል አንዱ ሙስናን በብቃት እና በተቀናጀ መልኩ ለመዋጋት የሚያስችል ሰርዓት ማጠናከር የሚገባት ሲሆን በሙስና ላይ የምናደርገው ትግል ውጤታማ እንዲሆን ሌሎች በዚህ ረገድ የተሳካ ትግል ያደረጉ ሐገሮችን ልምድ በመውሰድ ሐገራችን በፀረ ሙስና ትግሉ ያሉትን ክፍተቶች እና እያጋጠሙ ያሉትን ችግሮች በጥልቀት መመርመር፣ የመፍትሄ ሃሳብ ማመንጨት እና በሙስና ላይ የምናደረገው ትግል ለውጥ እንዲያመጣ የፖሊሲ እና የህግ አውጭው አካላት በጉዳዩ ላይ ተገቢ ግንዛቤ እንዲይዙ እና ያሉትን ክፍተቶች እንዲፈቱ የበኩላቸውን አሰተዋፀኦ እንድያደርጉ መነሻ ሀሳብ ማቅረብ የሚገባ መሆኑ ታምኖበታል፡፡ በመሆኑም የህግ አውጭው አካል ለውይይት መነሻ እንዲሆን በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ይፈጠራል የሚል እምነት ያለው ሲሆን ትግሉን አንድ ርምጃ ወደፊት ሊያራምድ የሚችል ውሳኔ እንዲሚወሰን ይጠበቃል፡፡ 2. የሙስና ታሪካዊ አመጣጥ በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የሙስናን ታሪካዊ አመጣጥ እና እድገት ስንመለከት ጉቦ እና በዝምድና መስራት እንደ መጥፎ ድርጊት ተደርጎ የሚወሰድ አልነበርም፡፡በዘመናዊቷ ኢትዮጵያም በተገነባው መንግስታዊ
  • 5. 5 መዋቅር ውስጥ ጉቦ እና እጅ መንሻ ነውርነቱ ጎልቶ የሚታይ አልነበርም፡፡ በዚህ ምክንያት “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” የሚል ብሂል በስፋት ጥቅም ላይ ይዉል እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ሀገራችን በ1948 ባወጣችው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ እና በሌሎች ህጎቿ ውስጥ ጉቦ እና በዝምድና መስራት ወንጀል መሆኑ የተደነገገ ቢሆንም ችግሩ የግለሰብ እንጅ የስርዓት እና የህብረተሰብ ችግር ተደርጎ ይወሰድ ስላልነበር ከመገታት ይልቅ ስር እየሰደደ እንደሄደ መረዳት ይቻላል፡፡ ከ1984 ዓ.ም ወዲህ የነፃ ገቢያ ስርዓት በሀገራችን ተግባራዊ መሆንን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለዉን የገቢያ ክፍተት ለመሙላትና ፍታሃዊነትን ለማረጋገጥ ሲባል በተመረጠ መንገድ መንግስት ጣልቃ የሚገባበት የኢኮኖሚ አቅጣጫ ተግባራዊ በመሆኑ ከዚህ በመነጨ ሊከሰት ለሚችል ሙስና መጋለጣችን እንደማይቀር ታምኖበት የጠነከረ የህግ ማዕቀፍና ተቋም እንዲኖረን ተደርጎ የነበረ ሲሆን በዚህም እጅግ በርካታ የማይናቁ ስራዎች ተስርተዋል፡፡ ሆኖም ግን በሚፈለገው ልክ ውጤት ባለማምጣታችን እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተደምረው አሁንም ሙስና የልማታችን አልፎ ተርፎሞ የተረጋጋ ሰላም እና ፖለቲካዊ ስርዓት እንዳይፈጠር ጠንቅ ሆኖ ይገኛል ፡፡ 3. የሙስና ትርጉም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊያግባባ የሚችል አንድ ወጥ የሆነ ትርጉም እስካሁን ድረስ ለቃሉ መስጠት አልተቻለም፡፡ ለቃሉ አንድ ወጥ ትርጉም ከመስጠት ይልቅ ሀገሮች በህጎቻቸው ውስጥ የሙስና ወንጀሎች የሚባሉትን በመዘርዘር መግባባት ላይ ለመደረስ ጥረት ሲያደርጉ ይታያል፡፡ ፅሁፉም በሙስና ላይ አንድ ወጥ ትርጉም በመሰጠት ጊዜን ማጥፋት ይገባል ብሎ አያምንም፡፡ በመሆኑም ለጊዜው መግባባት ላይ የተደረሰበትን የሙስና ትርጉም ማስቀመጥ ለጋራ መግባባት እና ለግንዛቤ ስለሚረዳ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ 3.1 በተለያዩ መዝገበ-ቃላቶች ለሙስና የተሰጡ ትርጉም  “…ቅንነትን እና መርህን የጣሰ ተግባር፣ ህጋዊ ሃላፊነትን ወይንም የሌሎችን መብት በጣሰ መልኩ ጥቅም የማቅረብ ድርጊት”፣ (Source: Black’s law Dictionary, 8th Edition, p.371)  “መበስበስ፣ የሞራል (የስነ ምግባር) ዝቅጠት፣ የሙሰኝነት ተግባራት ስብስብ ነዉ”፡፡ (Decomposition, Moral Detrioration, Set of corrupt practice) (ኮንሳይንስ ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት)
  • 6. 6  “በተለይ ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች የአታላይነትና የህገ ወጥ ባህሪ ነዉ”፡፡ (Dishonest or Illegal behaviour especially of people of authority) (ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት)  “ተገቢ ባልሆነና ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ስህተት ለመፈጸም ወይንም ለማጥፋት መነሳሳት ነዉ” ፡፡ (Inducement to wrong by improper or unlawful means) (ማሪየም ዌብስተር መዝገበ ቃላት)  “በስልጣን ወይም በሰራ ድርሻ አላግባብ የመገልገል፣ የመጠቀም ወይም የመጥቀም ድርጊት ነው” ሲል የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት እና ምርምር ማዕከል በ2001 በአሳተመው የአማረኛ መዝገበ ቃላት ላይ ትርጉም ሰጥቶታል ፡፡ 3.2 የፍልስፍና፣ የሃይማኖትና የሞራላዊ አስተምህሮት ለሙስና የሰጡት ትርጉም  ህሊናዊ ወይንም ሞራላዊ ብልሽት ወይንም  ከእዉነታ፣ ከመልካምና ጥሩ ከሆነ ነገር ማፈንገጥ ነዉ ይሉታል፡፡ 3.3 አለማቀፍ ተቋማት ለሙስና የሰጡት ትርጉም  “የመንግስት (የህዝብ) ስልጣንን ለግል ጥቅም ሲባል አላግባብ መገልገል ወይንም መያዝ” (World Bank)፣  “በአደራ የተሰጠ ስልጣንን ለግል ጥቅም ሲባል አላግባብ መገልግል” (Transparency International)፣  “ስልጣንን ለግል ጥቅም ሲባል አላግባብ መገልግል” (EU, 2003) ነው ብሎታል፡፡ 3.4 የሙስና ወንጀሎች ህግ ለሙስና የሰጡት ትርጉም  የተባበሩት መንግሰታት የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን፣ የአፍሪካ ህብረት የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን፣ በአውሮፓ ህብረት የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን እና የኢትዮጵያ የሙስና ወንጀሎች ህግ የፀረ- ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/97 እና 882/2007፣ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ 881/2007፣ በአጠቃላይ ብንመረምር ለሙስና ትርጉም ከመሰጠት ተቆጥበዋል፣  ትርጉም ከመስጠት ይልቅ የሙስና ወንጀሎች የሚባሉትን መዘርዘር ላይ ትኩረት አድርገዋል፣  የዚህ ዋነኛ ምክንያት ወጥ የሆነ ትርጉም ለመሰጠት አስቸጋሪ እና አወዛጋቢ በመሆኑ ነው፡፡
  • 7. 7 ለማጠቃለል ያህል ከዚህ በላይ ለሙስና የተሰጠት ትርጉሞች አንድ ወጥ ባይሆኑም በአብዛኛው ከስልጣን እና ስልጣንን አለግባብ መገልገል ጋር የተያያዘ መሆኑ የሚያግባባ ቢሆንም ሙስና ከስልጣን መያዝ ውጭም የሚከሰትባቸው መስኮች እንዳሉ መገንዘብ ይገባል፡፡ 4. በሙስና ትግል ውጤታማ የሆኑ ሀገሮች ልምድ በአለም ላይ ያሉ ሐገሮች ሙስናን ለመታገል የተለያዩ ሞዴሎችን ተከትለው ተቋሞቻቸውን ያደራጃሉ፡፡ ከእነዚህም ሞዴሎች ውስጥ ጎላ ብለው የሚታወቁት ሶስት ናቸው፡፡ እነሱም፡- 1. የሙስና መከላከል ብቻ ሞዴል የሚከተሉ /Corruption Prevention Model/ ይህ አይነት ሞዴል የሚጠቀሙ አገሮች በአብዛኛው ጠንካራ የህግ ማስከበር ሰርዓት ቀደም ብለው የፈጠሩ፤ ሙስናን የሚጠየፍ ጠንካራ የሆነ የህ/ሰብ ባህል ያላቸው፣ የእርስ በርስ ቁጥጥር ሰርዓት በመፍጠር የተዋጣለቸው አገሮች የሚከተሉት ሞዴል ነው፡፡ ይህን አይነት ሞዴል መሰረት አድርገው የፀረ ሙስና ተቋም አደረጃጀት የፈጠሩ አግሮች በአብዛኛው መንግስት ሊከተለው የሚገባ የፀረ ሙሰና ፖሊሲ ለማማከር (Advisory role )፣ የመንግስት ባለሰልጣናት ሀብት ለህዝብ ግልፅ ለማድረግና ለመቆጣጠር፣ የፀረ ሙስና ሰርቨይ ለማካሄድ፣ የመንግስት አጭር እና ረዥም የፀረ ሙስና እቅድ (Anti corruption strategy ) ለማዘጋጀት ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚደራጁ የፀረ ሙስና አካላት ናቸው፡፡ የሙስና ወንጀሎች ለመመርምር እና ለመክሰስ የሚያስችል ሰልጣን አልተሰጣቸውም፡፡ ይህን ሰልጣን የተሰጣቸው በየአገራቱ ውስጥ የሚገኙ የፖሊስ እና የዓቃቤ ህግ ተቋማት ናቸው፡፡ ይህን አይነት ሞዴል የሚከተሉ አገሮች በአብዛኛው የፀረ ሙስና ኮሚሽን /ኤጅንሲ/ Anti Corruption Commission/Agency የሚል ስም ከመጠቀም ይልቅ Ethics committee, Corruption prevention committee, Central Committe for prevention, National integrity office etc የሚል አይነት ስም የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ ፈረንሳይ(Central Service for Prevention of corruption)፣ አሜሪካ(Office of Government for Ethics)፣ ብራዚል(Office of Control General)፣ አልጀሪያ(National Agency for the Prevention Combating of Corruption)፣ ሰርቪያ(Anti Corruption Agency)፣ ሱሉቪኒያ( Commission for Prevention of Corruption)፣ ሜቄዶንያ (State Commission for Prevention of Corruption)፣ ይህን አይነት ሞዴል ከሚከተሉ አገሮች ውስጥ በምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ 2. የሙስና መከላከል እና የህግ ማስከበር ስራን አጣምረው የሚጠቀሙ ሀገሮች ሞዴል /Multi Purpose Anti Corruption Model or The Universal Model/ ይህን አይነት ሞዴል በዋናነት ሦስት የፀረ ሙስና መታግያ ስልት ይዘው የሚሄዱ ናቸው፡፡ አንድ አንድ ጊዜ የሶስት ጦር ውጊያ ስልት ይባላል፡፡ ሙስና በብቃት ለመዋጋት አንድኛ ህዝብ በሙስና ላይ እንዲዘምት ማስተማር እና ማስተባበር፣ ሁለተኛ የሙስና መከላከል ዘዴዎች (የህግ እና የአሰራር ማሻሻያዎች) ተግባራዊ በማድረግ ሲሆን ሶስተኛ በሙስና ላይ የተሳተፉ አካላት ተጠያቂ
  • 8. 8 ማድረግ (በመርመር) ነው፡፡ ይህን ሞዴል የሚከተሉ አግሮች እነዚህ ሰልጣን ለአንድ ተቋም በመሰጠት ውጤታማ እና የተቀናጀ የፀረ ሙስና ትግሉ እንዲኖር ያግዛል የሚል እምነት አላቸው፡፡ በእንዲህ አይነት አደረጃጃት የተከማቸ ሰልጣን እንዳይፈጠር እና የcheck and balance ሰርዓት እንዲኖር በተወሰነ መልኩ የክስ ስራ ከፀረ ሙስና አደረጃጀቱ ነፃነት ተሰጥቶች እንዲሰራ /እንዲደራጅ የሚደረግበት አግባብ አለ፡፡ እዚህ ላይ ሊሰመር የሚገባው ጉዳይ ግን ይህን አይነት ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ቢያንስ የምርመራ ሰራ በስራቸው እንዲደራጅ የሚያደርጉበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህን አይነት የፀረ ሙስና ሞዴል የሚከተሉት አገሮች በዋናነት የሚታወቁት ለረዥም ጊዜ በሙስና ተዘፍቀው የነበሩ/ ያሉ፣ የመንግስት ተቋማት ህግ አሰከባሪ አካላት (Law enforcement institutions) ጭምር በሙስና የሚጠረጠሩበት እና ሙስና ሰለባ የሆኑበት፣ በተነፃፃሪ በኢኮኖሚ እድገት ወደ ኋላ የቀሩ፣ የዳበረ የዴሞክራሲ የሌላቸው እና ዝቅተኛ የመንግስት የCheck and Balance ሰርዓት የነበራቸው/ያላቸው አገሮች ናቸው ፡፡ ይህን አይነት የፀረ ሙስና አደረጃጃት በዋናነት ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ከቅኝ ግዛት ነፃ መውጣት በኋላ በአፍሪካ፣ በኤስያ፣ በላቲን አሜሪካ እንዲሁም በአውሮፓ በተወሰኑ አገሮች ተቀባይነት ያገኘ እና እንደ ምሳሌ የሚወሰድ የፀረ ሙስና አደረጃጀት ሞዴል ነው፡፡ ይህን አደረጃጃት የሚከተሉ አገሮች በዋናነት የሚታወቁት ከአስፈፃሚው አካል ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ ተቋም እንዲደረጁ የማድረግ፣ አሰፈላጊ ሰልጣን፣ ሀብት/ በጀት እና ጠንካራ የህግ ማእቀፍ እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፡፡ ነፃ እና ጠንካራ የሆነ የፀረ ሙስና አደረጃጀት እንዲኖር ማድረግ መንግስታት ሙስና ለመታገል ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳያ ተደርጎ በህዝቡ የሚወሰድበት ሁኔታ አለ፡፡ ሀገራችንም ለሙስና በጣም ተጋላጭ በመሆንዋ ለ14 ዓመታት ያህል ይህን ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ጭምር ልምድ በመውሰድ ሰፊ ጥናት ስታደርግ ቆይታ በ1993 ዓ.ም ይህን ሞዴል ተግባራዊ ለማድረግ ችላ ነበር፡ ፡ ሆኖም ግን ከ2008 ጀምሮ አጥጋቢ ባልሆነ ምክንያት እና በተወሰደ የተሳሳተ ግንዛቤ የነበረውን የፀረ ሙስና አደረጃጃት የተልዕኮ ለውጥ እንዲኖረው ተደርጓል፡፡ በአሁን ሰዓት ከክስ በመለስ ያለውን ሁለገብ ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ሆንግ ኮንግና ቻይና(Independent Commission Against Corruption)፣ ሲንጋፖር(Corrupt Practice Investigation Office)፣ ሉቲኒያ(Special Investigation Service)፣ ላቲቪያ(Corruption Prevention and Combating Office)፣ ፖላንድ(Central Anti Corruption Bearo)፣ ኢንዶኒዥያ(Corruption Eradication Commission)፣ ኡጋንዳ( Anti Corruption Commission፣
  • 9. 9 ቦትስዋና (Directorate on Corruption and Economic Crime)፣ አውስትራሊያ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይላንድ፣ አርጀንቲና እና ኢካዶርን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ በተለይም በአፍሪካ ቦትስዋናን የፈጠረችው የፀረ ሙስና ተቋም ለሌሎች አርአያ የሚሆን ተቋም ሲሆን በአፍሪካ ሙስና በመታገል የተሻለች አገር ሆና ተቀምጣለች ፡፡ 3. ህግን የማስከበር ስራን ብቻ ሞዴል የሚከተሉ/ Law Enforcement Model/ ይህን አይነት ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ሙስናን ለመታገል የሚያስችላቸው በዋናነት በምርመራ እና ክስ ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ ይህን ስራ ለመስራት በተለመደው የህግ ማስበር ስርዓት ማለትም በፖለስ እና ዓቃቤ ህግ ተቋማት እንዲሰሩ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ አንዳንድ አገራት ልዩ ዲፓርትመንት (special department) በማቋቋም የሚታገሉበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህን አይነት ሞዴል ውጤታማነቱ እንደየ አገር ሁኔታ ይለያል፡፡ ለምሳሌ በታዳጊ አገሮች ያሉት የፖሊስ እና የአቃቤ ህግ ተቋማት ነፃ እና ጠንካራ ከአሰፈፃሚ አካል ጣልቃ ገብነት የፀዱ ባለመሆናቸው ውጤታማ አይደሉም፡፡ እንዲያውም እንዲህ አይነት አደረጃጀት “ፖሊስ እንደያማህ ብላ በለው፣ እንዳይበላ ግፋው” እንደሚባለው አይነት አባባል መንግስት ሙስና መታገል አይፈልግም የሚለውን ሀሜት ለማስወገድ የሚደራጁ እንጂ መንግስት ከልቡ ሙሰናን ለመዋጋት ፍላጎት ስላለው አይደለም የሚያቋቁመው ተብሎ በስፋት የሚተችበት ሁኔታ አለ፡፡ በአደጉ አገሮች በገነቡት ጠንካራ የዲሞክራሲ ባህል፣ የግልፅነት ሰርዓት እንዲሁም በሂደት ባገኙት ልምድ ታግዘው ሙስናን ጨምሮ በተወሰነ ወንጀል ላይ ትኩረት ሰጠው የሚሰሩበት እና ውጤታማ የሆኑበት ሁኔታ አለ፡፡ ለምሳሌ እንግሊዝን ለአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን ይህን ሞዴል የሚከተሉ አገሮች የሙስና መከላከል ስራ ከህግ ማስከበር ስራው(ምርመራ እና ክስ) ጋር አጣምረው ሰለማይሰሩ በተለይም ታዳጊ በሆኑ አገሮች የተቀናጀ የፀረ ሙስና ትግል በማድረግ በኩል ችግር ያለባቸው እና ህዝብ ሞብላይዜይሽን ስራ አነሳ ትኩረት የሚሰጡበት ሁኔታ ስለአለ ውጤታማ አይደሉም ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካን ማንሳት ይቻላል፡፡ እንደ አማራጭ ሞዴል በተመሳሳይ መልኩ ይህ አማራጭ ውጤታማ የሚሆነው ጠንካራ የህግ ማስከበር ስርዓት በሂደት የገነቡ፣ የነቃ ህብረተሰብ የገነቡ እና ያደጉ አገሮች ላይ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል እንጂ እንደኛ አገር በጣም ሰፊ የህግ ማስከበር ስርዓት ክፍትት ያለበት፣ የነቃ እና የተደራጀ ህብረተሰብ በተሟላ ሁኔታ ባልተፈጠረበት ሁኔታ የሙስና መካለከል ስራውን በአንድ ላይ አጣምሮ ለመሄድ የሚያስችል ስርዓት ባለመሆኑ ይህ ሞዴል በአፍሪካ ተመራጭነቱ በጣም ያነሰ ነው፡፡ ይህን ተግባራዊ ያደረጉ
  • 10. 10 አገሮችም ብዙም ለውጥ አላመጡም፡፡ ስፔን( Special Prosecutor’s Office Against Corruption and Organized Crime)፣ ሩማንያ(National Anti Corruption Directorate)፣ ክሮሽያ(Office for Suppression of Corruption and Organized Crime)፣ ኖርዌዬ(The Norwegian National Authority for Investigation and Prosecution of Economic and Environmental Crime)፣ እንግሊዝ(Metro Politian Police Anti Corruption Command)፣ ኬንያ(Anti Corruption Commission)፣ ደቡብ አፍሪካ(The Special Investigation Unit of South Africa)፣ ቤልጄም (Central Office for the Reparation of Corruption) ይህን ሞዴል በመከተል በምሳሌ የሚነሱ አገሮች ናቸው:: በአለም አቀፍ ደረጃ ከላይ የተነሱ ሞዴሎች በብዛት ተግባራዊ የተደረጉ ቢሆንም ከእነዚህ ለየት ያለ ሞዴል የሚከተሉ ሀገሮች መኖራቸው አልቀረም፡፡ ለምሳሌ ደቡብ ኮሪያ እና ጋና የፀረ ሙስና ኮሚሽንና ሠብአዊ መብትን በአንድ ላይ አቀላቅለው አደራጅተዋል፡፡ የፀረ ሙስና፣ የህዝብ እንባ ጠባቂ እና ዋና ኦዲተርን በአንድ ላይ አቀላቅለው የሚያደራጁ አገሮችም አሉ፡፡ ሩዋንዳ በዚህ እንደ ምሳሌ የምትጠቀስ አገር ናት፡፡ ለዚህ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ ውስን የሆነውን የህዝብ ሃብት በአግባቡ ለመጠቀም ነው ይላሉ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ሙስና የመከላከል ሞዴል እና የህግ ማስከበር ሰርዓት ሁለቱም ተግባራዊ በሚያደርጉበት ጊዜ Multi agency model የሚከተሉ አገሮች ናቸው ይባላል፡፡ በአንድ አገር ከሁለት በላይ የፀረ ሙስና ተቋማት ማደራጀት በተለይም በታዳጊ አገሮች የሀብት ብክነት የሚያስከትል፣ ለስልጣን ፉክክር የሚጋብዝ፣ መንግስት ወጥ የሆነ የአመራር ስርዓት ለመስጠት የሚቸገርበት፣ በተቋማቱ መሀል ቅንጅታዊ አሰራር ክፍተት እንዲፈጠር እድል የሚፈጠር እና ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ አንድ ጠንካራ የፀረ ሙስና ተቋም እንዳይኖር ያደርጋል በሚል በብዛት የሚተችበት ሁኔታም አለ ፡፡ እንዲያውም ባላደጉ አገሮች ይህን ሞዴል መከተል እንደ passive model ወይም በአሁን ሰዓት ተቀባይነቱ እምብዛም ያልሆነ ሞዴል ተብሎ የሚወሰድበት ሁኔታ አለ፡፡ ሙስና ካለው ባህሪ ነፃ እና ጠንካራ ተቋም ማደራጀት ተገቢ መሆኑን ብዙ ምሁራን ቢስማሙበትም ሀገሮች የሚከተሉት ሞዴል የተለያየ በመሆኑ በዛው ልክ ሙስና በመከላከል ውጤታማነታቸውም ይለያያል፡፡ በአብዛኛው ውጤታማነታቸው ደረጃ የሚታወቀው ገለልተኛ ነው ተብሎ በሚገመተው ሐገሮች የሚግባቡበት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በየአመቱ በተለያዩ መለኪያዎች መዝኖ እና አወዳድሮ የሚያወጣውን የሙስና ቅኝት
  • 11. 11 ጥናት/Corruption Perception Index (CPI)/ በመውሰድ ነው:: ሀገሮች በዚህ ጥናት መሰረት ያላቸውን ደረጃ ደግሞ በሚቀጥለው የየሀገሮችን ልምድ ከአየን በኋላ የምንመለከተው ይሆናል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የምናየው ከላይ ከገልፀነው ሰፋ ባለ መልኩ የየሀገሮቹ ልምድ በአሁኑ ወቅት የተሻለ የሙስና መከላከል ስራ ሰርተው ሙስናን መግታት ችለዋል የምንላቸውን ብቻ ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድ የማይታበለው ሀቅ ግን የሀገሮች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚዊ እና ማህበራዊ መስተጋብራቸው እና አወቃቀራቸው እጅግ የተለያየ በመሆኑ ሀገሮች ለሙስና ያላቸው ተጋልጭነት አንድ እና ያው ነው የሚባል አለመሆኑን ነው፡፡ ይሁን እንጅ ሙስናን ለመግታት ከሚከተሉት ሞዴል አንፃር እና ከእኛ ጋር ተቀራራቢነት ያላቸውን ተመሳሳይ ሀገሮች ከየክፍላተ ሀገሮቹ ለይቶ በማየት ለእኛ ሀገር የሚሆነውን ልምድ በመወስድ ማስተካከያዎችን ለማድረግ ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ 4.1 የእሲያ ሀገሮች ልምድ የእሲያ ሀገሮች ፈጣን እድገት በማስመዝገብ ላይ ያሉ ሀገሮች ከመሆናቸውም በላይ በፀረ ሙስና ትግል ውጤታማነት ረገድ የሚወሰዱ መልካም ተሞክሮዎች አሏቸው፡፡ በዚህ አፈጻጸማቸው ምክንያት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በየአመቱ በሚያወጣው ሪፖርት ከቻይና በስተቀር አብዛኛዎቹ ሀገሮች እስከ 15ኛ ደረጃ ውስጥ የሚደረሰውን የሚይዙ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሀገሮች ውስጥ ሲንጋፖርን እና ሆንግ ኮንግን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በ2017 ከ183 ሀገሮች ሲንጋፖር 84% በማምጣት 5ኛ ደረጃ፣ የያዘች ሲሆን በ2018 ከ180 ሀገሮች ደግሞ 85% በማምጣት 3ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 85% በማምጣት 4ኛ ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡ ሆንግ ኮንግ ደግሞ በ2017 ከ183 ሀገሮች 77 % በማምጣት 13ኛ ደረጃ፣ የያዘች ሲሆን በ2018 ደግሞ ከ180 ሀገሮች 76% በማምጣት 14ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 76% በማምጣት 16ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገር ነች፡፡ እነዚህ ሀገሮች የፀረ ሙስና ትግሉን የሚመራ ተቋም ያላቸው ሲሆን ዋነኛ ትኩረታቸው መልካም ስነ-ምግባር በመገንባት እና የሰዎችን አስተሳሰብ በመቀየር የሚሰሩ ሲሆኑ ሁለገብ የፀረ ሙስና ሞዴል የሚባለውን የሚከተሉ ናቸው፡፡ ለዚህ ስራ ከፍተኛ ሃብት እና ምርጥ የተባሉ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች መድበው ሁሉንም አማራጮች ተጠቅመው ለውጤት ይሰራሉ፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ የምርመራ ስራቸውን በፀረ ሙስና ተቋማቸው ስር አድርገው የሙስና ወንጀል የፈፀሙ ሰዎችን መርምረው ያለ ምንም ምህረት ለህግ አቅረበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ያስደርጋሉ፡፡ አንዳንዶች ሀገሮች ለመቀጣጫ እንዲሆን እስከ ሞት ፍርድ ድረስ አስፈርደው በስቅላት ሳይቀር
  • 12. 12 ይቀጣሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ሙስናን ሙሉ በሙሉ ያላጠፉ ቢሆንም የሰላምና የእድገታቸው እንቅፋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ማድረስ ችለዋል፡፡ ሙስናን መቆጣጠር እና መከላከል በመቻላቸው ተከታታይነት ያለውን ኢኮኖሚያ እድገት ማምጣት ችሏል፡፡ 4.2 የአውሮፓ ልምድ አውሮፓ የበለፀገ የገቢያ እና ዳበረ የዴሞክራሲ ሥርዓት ያላቸው ሀገራትን የያዘ አህጉር ሲሆን ሀገራቱም ሙስና ለስርዓታቸው አደጋ ወደ ማይሆንበት ደረጃ የደረሰ ነው ቢባልም ችግሩ እነሱም ጋር ቢሆን የለም ማለት አይቻልም፡፡ ዜጋው መብቱን ከሞላ ጎደል የሚያውቅ በመሆኑ የሙስና ሰለባ የመሆን እድሉ ዝቅተኛ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ሙስና ዓለም አቀፍ ወንጀል ከመሆኑም በላይ ደንበር ተሻጋሪ ወንጀል መሆኑን ተገንዘበው ሌላ ለየት ያለ የምርመራ እና የክስ አደረጃጀት ሳያስፈልጋቸው በመደበኛው የፍትህ ስርዓታቸው አማካኝነት ለመከላከል ጥረት ያደርጋሉ፡፡ በዚህም እጅግ ውጤታማ መሆን እና እድገታቸውን ማስቀጠል ቸለዋል፡፡ ትራንሰፓረንሲ ኢንተርናሽናል በየዓመቱ በሚያወጣው ሪፖርት ከሞላ ጎደል እነ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ሰፔን ወዘተ የመሳሰሉት ሀገሮች ከ10ኛ ደረጃ በታች የሚወጡ እና ሙስና በከፍተኛ ደረጃ የቀነሱ ለኑሮ በጣም የሚመቹ ሐገራት በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከእነዚህ ሀገሮች ውስጥ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ እና ኖርዌይን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ዴንማርክ በ2017 ከ183 ሀገሮች 88% በማምጣት 1ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን 2018 ከ180 ሀገሮች ደግሞ 88% በማምጣት 1ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 87% በማምጣት 1ኛ ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡ ፊንላንድ በ2017 ከ183 ሀገሮች 85% በማምጣት 3ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን በ2018 ከ180 ሀገሮች ደግሞ 86% በማምጣት 3ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 53% በማምጣት 51ኛ ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡ ኖርዌዬ በ2017 ከ183 ሀገሮች 85% በማምጣት 3ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን በ2018 ከ180 ሀገሮች ደግሞ 84% በማምጣት 7ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 84% በማምጣት 7ኛ ደረጃ ይዘው ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጅ አውሮፓ እጅግ የበለፀገ እና የህብረሰተሰቡ የንቃተ ህሌና ደረጃ እጅግ በተለየ እና በተሻለ ሁኔታ የሚታይ ነው፡፡ በመሆኑም ከአውሮፓ የሚወሰድ ልምድ የለም በሂደትም የእነሱን
  • 13. 13 መንገድ መከተል አያስፈልገንም ባይባል እንኳን አሁን ከአለንበት ሁኔታ ጋር ስናነፃፅረው ሶሻል አወቃቀራቸው ከታዳጊ ሀገሮች በእጅጉ የተለየ በመሆኑ ተግባራዊ ለማድረግ አስቸጋሪ ነው፡፡ 4.3 የአፍሪካ ልምድ በአፍሪካ ውስጥ ሙስናን ከመታገል አንፃር አብዛኛዎቹ ሀገሮች ዘግይተው የጀመሩ ከመሆናቸውም በላይ ከእኛ ልምድ ሲወስዱ የነበሩ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት በእድገታቸው ወደ ኋላ የቀሩ ከመሆናቸውም በላይ የሚበዙት ሀገሮች በሙስና በከፋ መልኩ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ የተወሰኑ ሀገሮችም ቢሆኑ በእድገት ላይ ያሉን ሙስናን ትርጉም በአለው ደረጃ በመቀነሳቸው የሚደነቁ እና ልምድ የሚወሰድባቸው ሐገሮች አሉ፡፡ ከእነዚህ ሀገሮች ውስጥ ቦትስዋናን እና ሩዋንዳን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በሚያወጣው ደረጃ የተጠቀሱት ሀገራት ከ2017 ጅምሮ በአለው ጊዜ ከ50ኛ ደረጃ በታች ያለውን ደረጃ የሚይዙ ናቸው፡ ፡ከእነዚህ ሀገሮች ውስጥ ቦትስዋና እና ሩዋንዳን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በ2017 ከ183 ሀገሮች ቦትስዋና 61% በማምጣት 34ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን በ2018 ከ180 ሀገሮች ደግሞ 61% በማምጣት 34ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 61% በማምጣት 34ኛ ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡ ሩዋንዳ ደግሞ በ2017 ከ183 ሀገሮች 55% በማምጣት 48ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን 2018 ከ180 ሀገሮች ደግሞ 66% በማምጣት 48ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 53% በማምጣት 51ኛ ደረጃ ይዘው ይገኛሉ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ እነዚህ ሀገሮች ቀደም ብለው ከእኛ የፀረ ሙስና ትግል ልምድ ሲወስዱ የነበሩ ዘግይተውም ቢሆን የልማታዊ መንግስትን መንገድ የተከተሉ እና በጥሩ ሁኔታ እያደጉ ያሉ ሀገሮች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ አሁን በአለው ሁኔታ ግን ከእኛ በእጥፍ በልጠው ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ኢትዮጵያ በ2017 ከ183 ሀገሮች 35% በማምጣት 107ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን በ2018 ከ180 ሀገሮች ደግሞ 34% በማምጣት 108ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2019 ከ180 ሀገሮች 37% በማምጣት 96ኛ ደረጃን ያዛ ነው የምትገኘው፡፡ ይህ ደረጃ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቶባቸዋል ከሚባሉ ሀገሮች ተርታ ሊያሰልፋት ወደ ሚችል ደረጃ እያመራች ከመሆኑም በላይ ከአማካኙ ደረጃ በታች በመሆኗ የሙስና ትግላችን አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከዚህ ችግር ወጥተን የሙስና ትግላችን መልክ ከአልያሳዝነው የእድገታችን ፀረ ከመሆኑ አልፎ የሰላማችን ጠንቅ መሆኑ አይቀርም፡፡
  • 14. 14 ለማጠቃለል ያህል በፀረ ሙስና ትግል ላይ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የእሲያ እና የአፍሪካ ሀገሮችን ልምድ ስንመረምር ለውጤታማነት ያበቃቸው ነገር ሙስናን ለመከላከል ያስቀመጡትን ስርዓት በጥብቅ ተግባራዊ ማደረጋቸው፣ መንግስት ቁርጠኛ ሆኖ ዜጋው ሙስናን የማይሽከምና የሙስና ትግሉ ባለቤት እንዲሆን ማድረግ በመቻላቸው እና ከዚህ ጎን ለጎን ሙስና የፈፀሙ ሰዎች ሲያጋጥሟቸው መመርመር እና መክሰስ የሚችል ነፃና ጠንካራ የህግ ማስከበር ስራን በሚሰራው የፀረ ሙስና ተቋም /ኮሚሽን/ ውስጥ በማደራጀት በቁርጠኝነት በመስራታቸው ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ሙስናን በመታገል ረገድ ጥሩ ልምድ/Best practice/ እና ትምህርት የሚወሰድባቸው ሀገሮች ሁነዋል፡፡ 4.4 ሊወሰድ የሚገባው መልካም ልምድ ከዚህ በላይ የተመለከትናቸው ሀገሮች ልምድ የሚያሳየው ነገር ቢኖር ውጤታማ የሙስና መከላከል ስራ ሊሰሩ የቻሉት ከእኛ የተለየ ጥብቅ የሙስና ህግና ተቋም ስለአላቸው አይደለም፡፡ ይለቁንስ ህዝባቸው እና መንግስታቸው ሙስና ጎጅ መሆኑን ከልብ ተቀብለው በአንድ በኩል ሙስና ለመፈፀም የሚያስችል እድል እንዳይኖር በራቸውን አጥብቀው የቆለፉ መሆናቸው በልላ በኩል ደግሞ ሙስና በመከላከል ብቻ ሊገታ እንደማይችል ተገንዘበው ጥብቅ የሆነ የምርመራ እና የክስ ስርዓት አደረጅተው ለህግ የማቅረብ ስራ በአንድ ማእቀፍ በመስራታቸው ነው፡፡ በዚህ ረገድ ጥሩ ልምድ ያላቸውን የእሲያ እና የአፍሪካ ሀገሮችን ልምድ ብንመለከት የምንወስዳቸው 3 መልካም ልምዶችን ነው፡፡ 1. የተጠናከረ የሙስና መከላከል ስራ መስራታቸው ቀዳሚው ሆኖ እናገኘዋለን ከዚህ አንፃር ዜጋቸው መልካም ስነምግባር ያለው እንዲሆን ሁሉንም አማራጮቻቸውን ተጠቅመው ሌት ተቀን ይሰራሉ፡፡ ለዚህም የትምህርት ተቋማትን፣ ሚዲያን፣ የሀይማኖት ተቋማትን፣ መደበኛ ያልሆኑ የማስተማሪያ ዜዴዎችን እና ቴክኖሎጅዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ይህን በማድረጋቸው ህዝባቸው ስርቶ መበልፀግን ብቻ አማራጭ እና ባህል እንዲያደረግ ከማድረጋቸውም በላይ የሙስና ትግሉ ባለቤትና ዋናው ተዋናይ ሰራዊታቸው እንዲሆን ለማደረግ እና ለማሰለፍ ችለዋል፡፡ በእነዚህ ሀገሮች ሙስና እየተፈፀመ አይቶ የሚያልፍ እና የሚታገስ ህዝብ የለም፡፡ የመንግስት አገልግሎት የሚሰጠው በጎቦ እና በዘመድ ሳይሆን በህግ የሚሰጥ እና መብታቸው መሆኑን ተገንዘበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሰው እና የገንዘብ ግንኙነት በቴክኖሎጅ ላይ የተመሰረት እንዲሆን በማደረግ እያንዳንዷ የገቢ ምንጭ ቁጥጥር የሚደረገባት እንዲሆን ስለአደረጉ የተሰረቀ ሃብት ቢኖር እንኳን
  • 15. 15 ወዲያው የሚታወቅ እና እርምጃ የሚወሰድበት እንዲሆን በማድረጋቸው ነው፡፡ ይህን በማድረግ ሃብት ማሳወቅ፣ማስመዝገብ እና ማጣራት ሳያስፈልጋቸው ከገቢ በላይ የተገኘ እና ምንጩ ያልታወቀን ሃብት በቀላሉ ማወቅ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ሙስና የመፈፀምን እድል ሙሉ በሙሉ ባይዘጉትም አደገኛነቱን መቀነስ እና ለእድገታቸው፣ ለሰላማቸው እና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታቸው እንቅፋት እንዳይሆን ማደረግ ችለዋል፡፡ 2. የተጠናከረ የህግ ማስከበር ስራ የሚሰሩ መሆናቸው ከአውሮፓ ውጭ ያሉት ሀገሮች ሙስናን ትርጉም ባለው ደረጃ መቀነስ የቻሉት መልካም ስነምግባር ከመገንባት እና ሙስናን ከመከላከል ጎን ለጎን ሙስና የሚፈፅሙ እና በሙስና ለመክበር የሚፈልጉ ሀይሎች ሲያጋጥሟቸው ነፃ የሆነ የምርመራ እና ክስ ስርዓት በአንድ ማእቀፍ አደራጅተው ለህግ ማቅረብ በመቻላቸው ነው፡፡ ነፃ የሆነ የፀረ ሙስና ተቋም እና እሱ የሚመሩት ምርመራ እና ክስ የሚያከናውን አደረጃጀት የፈጠሩበት ምክንያት ምርመራ የፖሊስ፣ ክስ ደግሞ የአቃቢ ህግ ተፈጥሮዊ ስራ መሆኑን ዘንግተውት ሳይሆን ሙስና የሚፈፀምበት ስልት፣ ባህሪው፣ ውስብስብነቱ እና ፍጥነቱ በመደበኛው የምርመራ እና የክስ ስርዓት ለመቆጣጠር እንደማይችሉ በመገንዘባቸው ነው፡፡ የፀረ ሙስና ተቋም አደረጃጀቱ ነፃ እና ከአስፈፃሚው አካል ተፅእኖ የተላቀቀ ተጠሪነቱ ለህግ አውጭው እንዲሆን በማድረግ ደፍሮ በነፃነት የሚሰራ ስለሆነ ነው ጤታማ የሆነው፡፡ ጠንካራ ግን ቁጥጥር የሚደረግበት የምርመራ አካል ስላላቸው ሙስናን በአግባቡ መርምሮ ለህግ የማቅረብ ብቃት እንዳላቸው ተሞክሮውን መውሰድ ጠቃሚ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ያደጉት ሀገሮች በተለይ መላው አውሮፓ ምርመራ እና ክስን በመደበኛው ስርዓት ውስጥ አድርገው መምራታቸው እነሱ ከደረሱበት የእድገት ደረጃ እና ከአላቸው የቴክኖሎጅ አቅም አንፃር ሲታይ ተገቢ ነው ሊባል ይችላል፡፡ የቱንም ያህል ውስብስብ የሙስና ወንጀል ቢፈፀም መርምሮ ለህግ ለማቅረብ የሚችል በረጅም ጊዜ የተገነባ መደበኛ የምርመራ እና የክስ ስርዓት ስላላቸው ሌላ አካል ማደረጃት አይገባቸውም፡፡ የስነምግባር ግንባታ እና የግንዛቤ ፈጠራ ላይ ብቻ ሊስራ የሚችል ተቋም ከአላቸው በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ አንፃር ለእኛ ሊወሰድ የሚገባው ተስማሚው ልምድ የአፍሪካ እና የእሲያ የምርመራ እና የክስ አያያዝ ሥርዓት ነው፡፡ የአፍሪካ እና የእሲያ ሙስናን የመታገል ልምድ ምንም ችግር
  • 16. 16 የሌለበት ነው ሊባል አይችልም፡፡ በእነሱም ሀገር ሙስና የጠፋበት እና ለስርዓታቸው አደጋ ሊሆን ወደ ማይችልበት ደረጃ አልደረሰም፡፡ ነገር ግን ትርጉም በአለው ደረጃ ቀንሰውታል፣ በሂደትም ሊገቱት ይችላሉ ተብሎ ሊገመት ይችላል፡፡ በእኛም ሀገር ይኸው ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ ምርመራ እና ክስ በኮሚሽኑ ስር እንዲሆን ተደርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን የተበታተነውን ምርመራ እና ክስ ወደ አንድ ለማሰባሰብ በሚል አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ወደ ሌሎች አካሎች እንዲሄድ ተደርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት ኮሚሽኑ የሙስና መከላከሉን ከባዱን ተልዕኮ ያለ ምርመራ ይዞ ለአለፉት ጥቂት አመታት የቀጠለ ቢሆንም ሙስናን ለመከላከል በሚያደረገው ጥረት ትግሉን ጀምሮ በራሱ መጨረስና ዳር ማድረስ ባለመቻሉ ሰሚ አጥቶ “ጥርስ የሌለው አንበሳ” ሆኗል፡፡ ቀደም ሲል ክስ እና ምርመራ በኮሚሽኑ ስር በነበሩበት ጊዜ ሊያድጉ የሚገባቸው መልካም ጅምሮች እና ውጤቶች ቢኖሩትም በሚከተሉት ጉልህ ችግሮች የተሳካ ስራ ሰርቶ ውጤታማ ሆኗል ማለት አይቻልም፡፡ለዚህ ደግሞ በርካታ መሰረታዊ የሆኑ ሃገራዊ ቁልፍ ምክንያቶች ያሉ ቢሆንም በተመረጡ ከባድ የሙስና ወንጀሎች ላይ ብቻ ባለማትኮሩ ሀሉንም የሙስና ወንጀል ለመመርመር የሚያስችል የተደራሽነትም ሆነ የአቅም ችግር እና የአቅጣጫ መሳት ችግር እንደነበረበት የሚካድ አይደለም፡፡ ይህን አጥንቶ በማስተካከል የኮሚሽኑን አቅም በማሳደግ ውጤታማ ማድረግ ሲቻል የማንዴት ለውጥ በማድረግ ህዝቡን እና መንግስትን ይጎዳ እንደሆነ እንጅ የሚያመጣው ጥቅም የለም፡፡ ምርመራ እና ክስ ወደ ፖሊስ እና አቃቢ ከመሄዱ ከአንድ አመት በፊት በ2007 ዓ.ም የኮሚሽኑን የመርመር እና የመክሰስ ስልጣን የሚያጠናክሩ እጅግ ከባድ የሆኑ ስልጣኖች በአዋጅ ቁጥር 881፣ 882 እና 883/2007 ዓ.ም በተባሉ የሙስና ህጎች ተሰጥተውት ነበር፡፡ የፀረ-ሙስና ልዩ የሥነ- ሥርዓትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 882/2007 ለፍርድ ቤቶች ብቻ የሚሰጥ በሙስና የተዘረፈ እና ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብን ለመቆጣጠር እንዲቻል የእግድ ትእዛዝ ሁሉ እንዲሰጥ ስልጣን ተሰጥቶት ነበር፡፡በተመሳሳይ መልኩ በመንግስት ተቋማት ብቻ ተወስኖ የቆየዉ የኮሚሽኑ የስልጣን ወሰን በአዋጅ ቁጥር 882/2007 መሰረት ወደግል ዘርፍ ማለትም ማህበራትን እንዲያካትት ተደርጎ ተሸሽሏል፡፡ይሁን እንጅ እነዚ ማሻሻያዎች በተደረጉ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በ2008 ዓ.ም በአልተጠና እና ጥድፊያ በሚታይበት መልኩ የተበታተነውን የምርመራ እና የክስ ሥራ ለመሰብሰብ በሚል ሰበብ የምርመራ እና የክስ ስራ ወደ ሌሎች አካላት እንዲዛወር ተደርጓል፡፡ እንዲያውም ሞራል ለመንካት በሚመሰል መንገድ የነበረበት ህንፃ ተነጥቆ ለፌዴራል ቤቶች
  • 17. 17 ኮርፖሬሽን እንዲሰጥ እና ኃላፊነት በጎደለው መንገድ ያን ያክል የተደከመበት ሃብት እና ሰነድ እንዲሁም የተገነባ የሰው ሀይል እንዲበታተን ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት በአለፉት ሶስት ዓመታት የሙስና መከላከል ስራችን ከፍተኛ ችግር ገጥሞት ይገኛል፡፡ በመሆኑም የሙስና መከላከል ስራው እንዲደክም እና ውጤታማ እንዳይሆን ተደርጓል፡፡ እስካሁን በአደረግናቸው እንቅስቃሴዎች የሙስና ትግሉ የተዳከመ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች የሚታዩ ቢሆንም ይህንኑ በጥናት ለማስደገፍ በገለልተኛ አካል ማስጠናት ተገቢ በመሆኑ 3ኛው ሀገር አቀፍ የሙስና ቅኝት ጥናት እየተካሄደ ሲሆን ውጤቱ ተጠቃሉ ሲቀርብ በሙስና መከላከል ረገድ የደረስንበት ደረጃ የሚታወቅ ይሆናል፡፡ ጥናቱ ተጠቃልሎ ሲቀርብ ሙሉውን ስዕል መያዝ የሚቻል ቢሆንም በሀገራችን የተቀናጅ እና የተሟላ ስልጣን ኖሮት፣ አሁን ያለው የፀረ ሙስና ትግል ያሉትን የቅንጅት ችግር ለመፍታት፣ የሚነሱ በፓሊስ እና ዓቃቤ ህግ ተቋማት የሚነሱ የገለልተኝነት እና የነፃነት ጥያቄዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ምርመራን ጨምሮ ሁሉንም የሙስና መከላከል ስራ የሚሰራ ጠንካራ የፀረ ሙስና ተቋም በመፍጠር የጀመርነውን ለውጥ ጉዞ ዳር ማድረስ ይገባል፡፡ 3. ሙስናን ለመታገል ቁርጠኛ የሆነ መንግስት መፍጠር ይገባል በሙስና ትግል ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት የቻሉት ሀገሮች የሚያሳየን ሌላው ልምድ ቢኖር ሙስናን ለመታግል መንግስት ከልቡ ቁርጠኛ መሆን ያለበት መሆኑን ነው፡፡ ሙስና ከስልጣን ጋር ብቻ የተያያዘ ነው ማለት ባይቻልም በበጀት እና በካዝና ላይ የማዘዝ ስልጣን ያለው አስፈፃሚው አካል ስለሆነ እሱን ከሙስና ማፅዳት እና ህብረተሰቡን በሙስና ትግል ላይ ሚና እንዲጫወት ማደረግ ይጠበቅበታል፡፡ ይህን ሳናድርግ የቱንም ያህል ጠንካራ እና ግዙፍ የፀረ ሙስና ተቋም ብናደራጅ ውጤታማ መሆን እንደማይቻል ከሌሎች ሀገሮች ብቻ ሳይሆን ከእራሳችን ልምድም መማር እንችላለን፡፡ በማንኛውም እንቅስቃሴ ውስጥ የህዝብ ተሳትፎ እና ወሳኝነት ምንም ተቃውሞ የማይቀርብበት ሃቅ ቢሆንም የመሪዎች ሚና በቀላሉ የሚታይ ስላልሆነ ሙስናን በመታገል እና እራስን በማፅዳት አርዕያ መሆን አለባቸው፡፡ “ስርአታችን ትልልቅ ሃላፊነትና ስልጣን በተሰጣቸዉ እና ይታመናሉ ተብለዉ በሚጠበቁ ሰዎች (አመራሮች) ላይ የሚወሰን ነዉ ብሎ ነበር’’ Paul O’Neill, Secretary of the Treasury, July 9, 2002፣ አባባሉ የራሱ ችግር ያለበት ቢሆንም ከከፍተኛ የመንግስት
  • 18. 18 የስራ ኃፊዎች የሚጠበቀውን ከፍተኛ የስነምግባር ደረጃ መያዝ ያለበቸው መሆኑን ያመላክታል፡፡ ለዚህ ደግሞ የጥቅም ግጭትን ማስተዳደር እና የከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን የስነምግባር ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል፡፡ 5. የሀገራችን የፀረ ሙስና ትግል የደረሰበት ደረጃ 5.1 የኢፌዴሪ የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አመሰራረት የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በ1993 ዓ.ም ለመቋቋም መነሻ የሆነው በመንግስት ከ1983 ጀምሮ የወሰዳቸው የተለያዩ የማሻሻያ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ ከተወሰዱት የማሻሻያ ፕሮግራሞቹ አንዱ የስነ ምግባር ማሻሻያ ንኡስ ፕሮግራም ሲሆን በዚህ ንኡስ ፕሮግራም ተይዘው ከነበሩ ፕሮጀክቶች አንዱ በሀገር ደረጃ የሰነ ምግባር ግንባታ ሙስናን በማእከል ደረጃ የሚያስተባብር እና የሚመራ ተቋም ማደራጀት ነው፡፡ ቢዘህ መሰረት ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተጣጥሞ የሚሄድ የፀረ ሙስና ትግሉን የሚመራ እና የሚያስተባብር ተቋም ለመፍጠር ለ14 ዓመታት ያህል ሰፊ ጥናት ከተደረገ እና ከተለያዩ የአውሮፓ እና የኤስያ አገራት ልምድ ከተወሰደ በኋላ በ1993 ተቋቁሟል፡፡ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ መልካም ሰነ ምግባር የተላበሰ እና ሙስና የሚጠየፍ ህ/ሰብ እንዲፈጠር፣ ሙስናና ብልሹ አሰራር ለልማታችን እና እድገታችን እንቅፋት እንዳይሆን ለማድረግ ሰፊ ጥረት አድርገዋል፡፡ ከዚህ አልፎ ሙስና ላይ የተሳተፉ አከላት ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ በኩል የማይናቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ በአጠቃላይ ሙስና የሚለውን በህ/ሰብ ዘንድ አጀንዳ እንዲሆን በየዓመቱ በሺ የሚቆጠሩ ጥቆማዎች በመቀበል እና በማጣራት መንግስት እና ህዝብ የጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ጥረት አድርጓል፡፡ ኮሚሽኑ ከእነ ድክመቱም ቢሆንም እስከ 2007 በነበሩት ጊዜያት ባከናወናቸው የፀረ ሙስና ተግባራት፣ በሰራቸው የምርመራ እና ክስ ስራዎች ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች ልምድ በማካፈል ጭምር ጥሩ ስም መገንባት ችሎ የነበረ ተቋም ነው፡፡ ሆኖም ግን ከ2008 ጀምሮ የተሰጡትን የምርመራ እና የክሰ ስራዎች ተነሰተው ለፖሊስ እና ዓቃቤ ህግ አጥጋቢ ባላሆነ ምክንያት በመሰጠቱ በስራው ላይ የተለያየ ተፅእኖ መፍጠሩ አልቀረም፡፡ ኮሚሽኑ ገንብቶት የነበረው ስም እና በህዝቡ የነበረውን ተቀባይነት ባለፉት ዓመታት በተለይም
  • 19. 19 ከ2008 ጀምሮ ደረጃው እየቀነሰ መጥቷል፡፡ ለዚህ ተቀባይነት ማነስ የኮሚሽኑ የራሱ ድክመት እንደተጠበቀ ሆኖ የምርመራ እና ዓቃቤ ህግ ስራዎች ከኮሚሸኑ ሰልጣን መውጣቱ ግን በእጅጉ የህዝብ ተሳትፎ እንዲቀንስ፣ ኮሚሽኑ አሁን እየሰራቸው ባሉ ማንዴቶች አፈፃፀም/ተግባራዊነት/ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል ፡፡ ይባስ ብሎ በአሁን ሰዓት ኮሚሽኑ “ጥርሰ የሌለው አንበሳ እንዲባል” አስችሎታል፡፡ ህግ አውጨው እና አስፈፃሚው አካል መረዳት የሚገባቸው ጉዳይ የኮሚሽኑ አፈፃፀም ዝቅ እንዲል የተለያዩ ሀገራዊ እና ተቋማዊ ምክንያቶች ቢኖርም ኮሚሸኑ የተማላ ሰልጣን (ማንዴት) እንዳይኖረው መደረጉ በኮሚሽኑ ዋና ዋና አፈፃፀሞች ላይ መድከም መታየቱ የአንበሳው ድርሻ ይወስዳል፡፡ ግልፅ የሆነ ግንዛቤ እና አረዳድ እንዲኖረን በኮሚሽኑ የምርመራ እና ዓቃቤ ህግ እያለ እና ከሄደ በኋላ በኮሚሽኑ ዋና ዋና ስራዎች ላይ የነበረው አፈፃፀም መመለከት የፈጠረውን ተፅእኖ በቀላሉ ለመረዳት ያስቻላል ፡፡ 5.2 የኮሚሽኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም 5.2.1 የግንዛቤ ፈጠራ ስራ አፈፃፀም ኮሚሽኑ በአዋጅ ከተሰጡት ተግባራት አንዱ በሙስና ዙሪያ የህ/ሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና በፀረ ሙስና ትግሉ የሚኖራውን ሚና እና ተሳትፎ ማሳደግ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በህትመት ሚድያ፣ በኤሌክትሮኒኪስ ሚድያ፣ በፊት ለፊት ትምህርት እና በተለያዩ የህ/ሰብ አካላት አማካኝነት የተለያዩ የሰነ ምግባርና የፀረ ሙስና ትምህርት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከ2008 ጀምሮ የኮሚሸኑ የህግ ማስከበር ስራ ከመሰዱ ጋር ተያይዞ በሰነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዙሪያ የሚሰጡ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ትምህርቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በጥራትም ይሁን በብዛት እየቀነሰ መጥቷል ማለት ይቻላል፡፡ የምርመራ እና ክስ ኬዞች ከትምህርትና ሰልጠና ጋር ተቀናጅተው የማይሄዱ በመሆኑ በትምህርቱ ሳቢነት እና ተቀባይነት ተፅእኖ የፈጠረ ሲሆን ሰልጣኞች በተደጋጋሚ የሚያሰኑት ጉዳይ ሆኗል፡፡ ከዚህ አልፎ በሚሰጡ ትምህርቶች ላይ የምርመራ እና ክስ ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ እየተነሳ በሰልጠና ሰጪዎች ላይ ቀላል የማይባል ጫና እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ኮሚሽኑ ድጋፍ አደርጎላቸው ወደ ታች ወርደው አባሎቻቸው እንደያሰለጥኑ ተደራጅተው የነበሩ የስነ ምግባር አውታሮች የሚሰጡት ትምህርት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቀባይቱ በእጅጉ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ አሰልጣኞች ላይ የፈጠረው ጫና በራሱ በሙያ ረዥም ልምድ የነበራቸው ባለሙያዎች ኮሚሽኑ እንዲለቁ እድል ፈጥሯል፡፡ ለንፅፅር እንዲመች ሲሰጡ የነበሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ምን ያህል ተሳታፊ እየቀነሰ እንደመጣ ከሰንጠረዡ በቀላሉ መረዳት ይቻላል::
  • 20. 20 ሰንጠረዥ 1.የተከናወኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተ . ቁ የትምህርት መሰጫ ዘዴ ምርመራና ዓቃቤ ህግ እያለ ምርመራ እና ዓቃቤ ሀግ ከሄደ በኋላ 2004 2005 2006 2007 2008 2009 2010 2011 1 በፊት ለፊት የተሰጠ ትምህርት/ሰዎች ብዛት/ 18,690 40,108 44,360 51,990 14,100 3134 7291 27,596 2 በብሮሸር የተሰጠ ትምህርት/የታተመ ብሮሸር / 20,000 20,427 60,000 116,000 20,000 75,000 10,000 201384 3 በሬድዮና ተለቬዥን የተላለፉ ትምህርታዊ ማስታወቅያ /ስፖቶች/ 17 20 35 22 29 17 12 30 4 በሰነ ምግባር አውታሮች የተሰጡ ትምህርቶች 6,842 286 19,790,82 8 10,975, 529 9,512 ,020 3,933 38,462 16,249 --- 5.2.2 የሙስና መከላከል ተግባራት ስራ አፈፃፀም ኮሚሸኑ በአዋጅ ከተሰጡት ተልእኮዎች ሌላው በመንግስት መሰሪያ ቤቶች እና የልማት ድርጅቶች የአሰራር ስርዓት ጥናት ማካሄድ እና አሰቸካይ የሙስና መካላከል ስራዎች ማከናወን ሲሆን የተሰጡ ምክረ ሃሳቦች እና የተጠኑ ጥናቶች ተግባራዊ መሆናቸውን መከታተል ነው፡፡ ይሁን እንጅ ከ2008 ጀምሮ የምርመራ እና አቃቤ ህግ ስራ ከኮሚሽኑ በመውጣት በጥናቱ ሂደቱ፣ አተገባበሩ እና ውጤታማነቱ ላይ ተፅእኖ ያረፈበት ሰራ ሆኗል፡፡ በተለይም የተጠኑ ጥናቶች ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉ፣ የተሰጣቸውን ምክረ ሃሳብ ተብለው ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ምክር ሲሰጣቸው ለመፈፀም ፍቃደኛ ያለመሆን፣ ኮሚሽኑ ይህን የሚያስገድድበት አቅም ሰለሌለው ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባው የተጠኑ ጥናቶች በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንዳይሆኑ እና ሸልፍ ላይ እንዲቀመጡ እድል እየፈጠረ ይገኛል፡፡ የተሰጡ የሙስና መከላከል ምክረ ሃሳቦች ተግባራዊ በማድረግ በኩልም የተቋማት ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ የአሰቸካይ የሙስና መከላከል ስራዎች ተፈፃሚነት በተመሳሳይ ሁኔታ አተገባበሩ ላይ የተቋማት ፍቃደኝነት የሚጎድልበት ሁኔታ አለ፡፡ በዚህ መሰረት ከ2004 እስከ 2011 ዓ.ም ደረስ ለመፈፀም የታቀዱ የአሰራር ስርዓት ጥናቶች 579 ሲሆኑ 421 ወይ የእቅዱ 72.7% የተከናወኑ ሲሆኑ በተለይም የአደረጃጀት ለዉጡን ተከትሎ እነዚህን ጥናቶች ተጠኝ ተቋማት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ሁኔታ
  • 21. 21 ባለመኖሩ ተፈፃሚነታቸው የሚጠበቀውን ያህል ሆኖ ሙስናን በሚፈለገዉ ደረጃ ለመከላለከል አልቻሉም፡፡ ለምሳሌ ያክል በአስቸኳይ መከላከል ሥራ ኮሚሽኑ በ2007 በጀት አመት ብቻ ከ645,015,929.00 በላይ የህዝብ ሃብት ለማዳን የቻለ ሲሆን ከዚያ ወዲህ ባሉት ተከታታይ አመታት የተሰራዉ ድምር ዉጤት ከዚህ አህዝ ጋር የሚመጣጠን አይደለም፡፡ ሰንጠረዥ 2. የተከናወኑ የሙስና መካላከል ስራዎች ተ .ቁ የተከናወኑ የሙስና መካላከል ስራዎች የምርመራና ዓቃቤ ህግ ስራ በኮሚሸኑ እያለ ምርመራና ዓቃቤ ሀግ ስራ ከሄደ በኋላ 2004 2005 2006 2007 2008 2009 2010 2011 1 የታቀዱ የአሰራር ሰርዓቶች ጥናቶች 64 87 87 88 30 65 74 81 2 ተግባራዊ የተደረጉ የአሰራር ሰርዓት ጥናቶች 37 69 78 83 32 33 31 61 3 የቀረቡ አሰቸካይ የሙስና መከላከል ስራዎች 11 20 --- -- 28 19 29 26 5.2.3 የሃብት ማሳወቅ እና ምዝገባ ስራ አፈፃፀም በተመሳሳይ ሁኔታ የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ስራ ከባለፉት ዓመታት ከነበረው የማሳወቅ እና የማስመዝገብ እንቅስቃሴ ብዙ የተለየ ለውጥ ባይኖርም በተሿሚዎች አከባቢ የነበረው የሀብት ምዝገባ ግን በራሱ ከፍተኛ ችግር የታየበት ነው፡፡ የምርመራ እና የክስ ስራ ከኮሚሽኑ ከተነሳ ጀምሮ የተመራጮች እና የመንግስት ሰራተኞች ምዝገባ እየጨመረ ቢሄድም የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የሀብት ምዝገባ ቁጥር ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ፡፡ በተለይም በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ያሉ አመራሮች ሀብት ለማስመዝገብ ሆነ በአዋጁ መሰረት ጊዜው ጠብቆ ለማሳደስ ያለው ፍላጎት፣ ትብብር እና አርአያነት በጣም አነስተኛ ነው፡፡ የሀብት ምዝገባ ስርዓት በከፍተኛ ሃላፊዎች ደረጃ መዳከም ኮሚሽኑ ከነበረው ማንዴት እና
  • 22. 22 ተፅእኖ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ግልፅ ነው፡፡ ምክንያቱም ኮሚሸኑ ማንዴቱ ከመወሰዱ በፊት የነበረው የሀብት ምዝገባ በእጅጉ ተፈፃሚነት የነበረው ነው ማለት ይቻላል፡፡ በተለይም ሀብት ለማስመዝገብ ወይም ለማሳደስ ፍቃደኛ ያልሆኑ አመራሮች ኮሚሽኑ ይህን ማስፈፀም የሚችል አቅም የለውም ከሚል የመነጨ አሰተሳስብ ሊሆን እንሚችል ይገመታል፡፡ በሰንጠረዡ ላይ የቀረበው መረጃ የሀብት ምዝግባ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ የሚያሳይ ቢሆንም የከፍተኛ አመራሮች የማስመዘገብ እና የማሳደስ ዳታ ግን ችግር እንዳለ ከግምት ውስጥ መውሰድ ይገባል ፡፡ ሰንጠረዥ 3 ፡ የተከናወኑ የሀብት ምዝገባ ስራዎች ተ .ቁ የተከናወኑ የሀብት ምዝገባ ስራዎች ምርመራና ዓቃቤ ህግ በኮሚሸኑ እያለ ምርመራ እና ዓቃቤ ሀግ ከሄደ ቡሃላ 2004 2005 2006 2007 2008 2009 2010 2011 1 ሀብታቸው ያስመዘገቡ ሰራተኞች / ተሸዋሚዎች ፤ ተመራጮች 10208 9968 17285 14423 34191 14150 13922 21363 5.2.4 የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ማደራጀት እና መደገፍ ስራ አፈፃፀም ኮሚሽኑ ሌላ በአዋጁ ከተሰጡት ኃላፊነቶች ውስጥ አንዱ በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የልማት ድርጅቶች የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ማደራጅት፤ ማብቃት እና ድጋፍ መሰጠት ነው፡፡ እኒዘህ ክፍሎች በየተቋሙ በስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዙሪያ የበላይ ኃላፊ የሚያማክሩ ሲሆኑ የምርመራ እና ዓቃቤ ህግ ስራ በነበረበት ግዝያት ስነ ምግባር መኮነኖች ከኮሚሽኑ የነበራቸው ትብብር እና ቅንጅት የተጠናከረ እና ጥሩ የነበረ የመከላከል፣ የጥቆማ እና ክስ አገልግሎት በአንድ ተቋም የሚያገኙ የነበሩ በመሆኑ ጠንካራ ግኑኝነት ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከ2008 ጀምሮ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ከሦስት ተቋማት እንዲገናኙ እድል በመፍጠሩ የቅንጅት እና የመነባብ ችግር ተከስቷል፡፡ የሚሰጣቸው ድጋፍ እና እገዛ ከተለያየ ተቋማት መሆኑ ለአላስፈላጊ ምልልስ እና እንግልት ዳርጓቸዋል፡፡
  • 23. 23 ቀደም ሲል የተቋማት የበላይ ኃላፊዎች ይሰጥዋቸው የነበረውን ድጋፍ እና ተቀባይነት ቀንሷል፡፡ ከዚህ አልፍ ብሎ አደረጃጃታቸው እንዲታጠፍ፣ እንዲባረሩ ወይም ከነበሩበት ደረጀ ዝቅ እንዲሉ እድል ፈጥሯል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ 169 የሚሆኑ የስነ ምግባር መኮነኖች (አዲስ የተደራጁ) ጨምሮ በራሳቸው ፍቃድ የለቀቁ፣ ወደ ሌላ ስራ የቀየሩ ወይም በጫና ምክንያት የሰራ ለውጥ ያደረጉ ናቸው፡፡ በቅርብ ጊዜ ተግባራዊ የተደረገውን ጂኤጂ አሰራር ምክንያት አለአግባብ ከስራ መደቦቹ የተፈናቀሉ የስነ ምግባር መኮነኖች ቁጥርም ቢዘህ ውሰጥ የሚታይ ነው፡፡ ኮሚሸኑ ችግሩ ለመቅረፍ እና ይህን ተገቢ ያልሆነ ድርጊት የፈፀሙ ተቋማት ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል አቅም የሌለው በመሆኑ ይህን ችግር ጎልቶ እንዲወጣ እድል ፈጥሯል ፡፡ ሰንጠረዥ 2. የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ድጋፍ እና እገዛ ስራዎች ተ . ቁ የተከናወኑ የሙስና መካላከል ስራዎች የምርመራና ዓቃቤ ህግ ስራ በኮሚሸኑ እያለ ምርመራ እና ዓቃቤ ሀግ ስራ ከሄደ በኋላ 2004 2005 2006 2007 2008 2009 2010 2011 1 ነባር በመልቀቃቸው የተተኩ እና በአዲስ መልክ የተደራጁ የስነ ምግባር መከታተያ ከፍሎች 20 34 38 20 38 36 87 169 5.2.5 የህዝብ ተሳትፎ ስራ አፈፃፀም በፀረ ሙስና ትግሉ የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ ከሚባሉ ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ ያለ ህዝብ ተሳትፎ እና ድጋፍ ውጤታማ የፀረ ሙስና ትግል ከቶ የሚታሰብ አይደለም፡፡ በተለይም ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን የህዝብ ተሳትፎ እና ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ህዝቡ ኮሚሽኑ የእኔ ነው የሚል ስሜት ፈጥሮ በተለያየ አደረጃጀት ስር ታቅፎ ሲንቀሳቀስ የነበረበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡ ነገር ግን ባለፉት ዓመታት የህዝብ ተሳትፎ እና ድጋፍ በእጅጉ የቀነሰበት የኮሚሽኑ ሰልጣን እና ኃላፊነት መነሳት አግባብ አይደለም የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ በህዝብ ክንፍ መድረክ አቅርቧል፡፡ ከቅሬታ ማንሳት አልፎ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የተለያዩ የፀረ ሙስና ጥምረቶች ከፀረ ሙስና ትግሉ ወጥተዋል፡፡ ከ2001 ጀምሮ እስከ 2007 በሙያ፣ በፆታ እና በብዙሃን ማህበራት ተደራጅተው የነበሩትን 16 የፀረ ሙስና አደረጃጀቶች (ወደ 920 ማህበራት እና አደረጃጀቶች) ቀንሰው በአሁኑ ሰዓት ወደ 6 የፀረ
  • 24. 24 ሙስና አደረጃጆት (ከ70 ማህበራት ያልበለጡ) ወርዷል፡፡ ይህ የሚያሰየው ህዝቡ ለኮሚሽኑ ሲሰጠው የነበረውን ድጋፍ እና እገዛ በእጅጉ መቀነሱ ያሳያል፡፡ ኮሚሽኑ “ጥርስ የሌለው አንበሳ ነው ስለሚባል” ከዚህ ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት ትርፉ ድካም ነው የሚል አሰተሳሰብ ጭምር በስፋት እየተንፀባረቀ መጥቷል፡፡ 5.2.6 ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው የቅንጅት እና ትብብር ስራ አፈፃፀም ከ2008 ጀምሮ በሀገራችን የፀረ ሙስና ትግሉ ስራ በኃላፊነት እንድያሰተባብሩ የተሰጣቸው አካላት ሦስት ናቸው ፡፡ እነዚህም የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ናቸው፡፡ በእነዚህ አካላት መካከል ጠንካራ እና ተከታታይነት ያለው መረጃ የመለዋወጥ፣ የመደጋገፍ፣ በፀረ ሙስና ትግሉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት ተቀናጅቶ እና ተናቦ በመሄድ እና አንደ አንድ ጠንካራ የፀረ ሙስና እንቅስቃሴ እንዲፈጠር በማድረግ በኩል ከፍተቶች ታይቷል፡፡ በእነዚህ ተቋማት አለመቀናጀት በተገልጋዮች በተለይ በጠቋሚዎች እና ሰነ ምግባር መከተታያ ክፍሎች ሚቀርቡ የአገልገሎት አሰጣጥ ቅሬታዎች እና አቤቱታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የመጡበት ሁኔታ እንዳለ ይስተዋላል፡፡ በ2008 እና በ2009 አካበቢ የተወሰነ የጋራ መድረክ በመፍጠር የቅንጅት ስራዎች ለመገምግም እና አቅጣጫ ለመስጠት ጥረት የተደረገ ቢሆንም በቅንጅት የመገምገም ስራዎች ከሞላ ጎደል ተቋርጧል ማለት ይቻላል፡፡ በአለፈው ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ተቋማቱ በጋራ ሊሰርዋቸው የሚገቡ ጉዳዮች በመለየት የጋራ መግባባት ስምምነት ሰነድ ተፈራርመው ወደ ስራ ለመግባት ጥረት ያደረጉ ቢሆንም የተፈለገው ለውጥ መጥቷል ተብሎ አይወሰድም፡፡ ከዚህ ውጪ በዚህ ዓመት እንደ ትልቅ እሴት የሚወሰደው ፓርላማ እና ኮሚሽኑ የነበራቸውን ግኑኝነት ለማጠናከር እና የተቋሙ ችግሮች ለመረዳት እና ለመፍታት የነበረውን ተነሳሽነት በእጅጉ የሚደነቅ ነው፡፡ ከሌሎች መሰል ባለድርሻ አካላት ያለው ግኑኝነትም በቀጣይ ተጠናክሮ መሄድ ካልቻለ በፀረ ሙስና ትግሉ የሚፈጠረው ጫና ቀላል አይደለም፡፡ 5.2.7 የኮሚሸኑ የሰው ሀብት በተመለከተ ኮሚሸኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን የሰው ሀይል ከጊዜ ወደ ጊዜ በቁጥር እየጨመረ የሄደ ቢሆንም የሰው ሀይሉ ጥራት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የሄደበት ሁኔታ አለ፡፡ አዳዲስ ሰራተኞች በመቅጠር እና በማሰልጠን ነባር እና የተሻለ እውቀት የነበውን ባለሙያ ለመተካት ጥረት የተደረገ ቢሆንም ቀደም ሲል ተሰጥቶት የነበረውን የተሻለ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም privilege ባለመቀጠሉ
  • 25. 25 የነበረው የሰው ሀይል ማቆየት አልቻለም፡፡ በተለይም የነበውን ማንዴት መነሳቱ በሰራተኛ ዘንድ አግባብ አይደለም የሚል አመለካከት ያለ በመሆኑ በተቋሙ የሚቆይበት ጊዜ በጣም አጭር እየሆነ የሄደበት ሁኔታ አለ፡፡ በየወሩ ከኮሚሽኑ የሚለቅ ሰራተኛ ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ዛሬ ቀጥሮ ነገ የሚሸኝ ተቋም ሆኗል ብለን ብንናገር ማጋነን አይሆንም፡፡ የፀረ ሙስና ተቋማት በህዝብ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ከተፈለገ ከመንግስት የተሻለ ትኩረት የሚሹ፣ ተገቢውን ጥቅማጥቅም እንዲሁም ምቹ የሰራ ሁኔታ ተመቻችቶላቸው ሊሰሩ እንደሚገባ ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ኮንቬንሸን ይመክራል፡፡ የተቋሙ ሰራተኞች በመንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ህግ አውጪው ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ የሚደግፍበት ሁኔታ መፍጠር አለበት፡፡ 5.2.8 ምርመራና ክስ ወደ ፊዴራል ፖሊስና አቃቤ ህግ ከመሄዱ በፊት የነበረው ሁኔታ የምርመራ እና ክስ ስራ ኮሚሽኑ ከተቋቋመ በኋላ ከ2003 ዓም ድረስ ተጠንክሮ ሲሰራ የነበረ ቢሆንም በአሃዝ ደግፎ ለማሳየት እንዲቻል በመጀመሪያው ዘመን የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን የእቅድ ዘመን እና ምርመራ እና ክስ ወደ ሌሎች ተቋማት ከመሄዱ በፊት ያለውን ብቻ ለማሳያ ማቅረብ በቂ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በዚህ መሰረት ከ2003 እሰከ 2007 በነበረው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽ ዘመን የቀረበ ጥቆማ 16,082 ሲሆን ከዚህ ውስጥ በራሳችን አቅም 2,148 በውክልና 921 ምርመራ የተደረገ ሲሆን በ5,079 ላይ ደግሞ ቃቢ ህግ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በፍርድ ቤት ከቀረቡት 981 መዛግብት ውስጥ 853 ለኮሚሽኑ የተወሰነ ሲሆን በመዝገብ የመርታት ምጣኔ 86.95%፡፡ ለፍርድ ቤት ከቀረቡት 2,278 ተከሳሾች ውስጥ 1,798 ጥፋተኛ ተብለዋል በዚህም የመርታት ምጣኔ 78.92% ነበር፡፡ በስትራቴጅክ ዘመኑ በሙስና ተመዝበረው ከነበሩት ውስጥ የተመለሱትን ደግሞ 7 መኖሪያ ቤት፣ 12 ህንፃዎች፣ 22 ተሸከርካሪዎች፣ 9 የንግድ ቤቶች፣ 538,683.3 ካሬ ሜትር የከተማ መሬት ሲሆኑ ብር 125,918,715 በጥሬ ገንዘብ እና 81,422.76 ግራም ወርቅ ወደ መንግስት ካዝና እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ ይህ የሚሳየው ነገር ቢኖር የኮሚሽኑ የመመርመር የማስቀጣት እና የተመዘበርን የህዝብ ሃብት የማሥመለስ ልምድ እያደበረ የመጣ እና ተገቢውን የአመራር ድጋፍ ቢያገኝ ከፍተኛ ውጤት ሊያሥመዘገብ የሚችል እንደነበር የሚያሳይ ነው፡፡
  • 26. 26 ይሁን እንጅ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የአለውን አፈፃጸም በዚህ ፁሁፍ ውስጥ ለማጠቃለል ጥረት አድረገን የተጠቃለለ መረጃ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከጠቅላይ አቃቢ ህግ ማግኘት ባለመቻላችን ዳታውን ለማከተት እና ለማነፀፃር አልቻልንም፡፡ 6. ማጠቃለያ ኮሚሽኑ በአዋጅ ሲቋቋም ምርመራ የፖሊስ ክስ ደግሞ የአቃቢ ህግ ስራ መሆኑ እየታወቀ ሀገራችን ከአለባት የሙስና ተጋላጭነት አንፃር ታይቶ ምርመራ እና ክስ በኮሚሽኑ ውስጥ እንዲሆን ተደርጎ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ምርመራ እና ክስ ወደ ፖሊስ እና አቃቢ ከመሄዱ ከአንድ አመት በፊት በ2007 ዓ.ም የኮሚሽኑን የመርመር እና የመክሰስ ስልጣን የሚያጠናክሩ እጅግ ከባድ የሆኑ ስልጣኖች በአዋጅ ቁጥር 881፣ 882 እና 883/2007 ዓ.ም በተባሉ የሙስና ህጎች ተሰጥተውት ነበር፡፡ ይሁን እንጅ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በ2008 ዓ.ም አጥጋቢ በአልሆነ ምክንያት የተበታተነውን የምርመራ እና የክስ ሥራ ለመሰብሰብ እና ወደ ባለቤቶች ለመመለስ ነው በሚል ሰበብ የምርመራ እና የክስ ስራ ወደ ሌሎች አካሎች እንዲዛወር ተደርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት በአለፉት ሶስት ዓመታት የሙስና መከላከል ስራችን ከፍተኛ ችግር ገጥሞት ይገኛል፡፡ በመሆኑም እንደ ሌሎቹ ሁለገብ የሙስና መከላከል ስራ እንደሚሰሩ ሀገሮች የምርመራ እና የክስ ስራው ከበቂ በጀት እና ፋሲሊቲ ጋር ወደ ነበረበት ሊመለስ ከአልቻለ በሙስና ላይ ትርጉም ያለው ውጤት ማምጣት አይቻልም፡፡ በአብዘኛዎቹ አገራት ስኬታማ የፀረ ሙስና ትግል ያካሄዱ ጨምሮ ያሳለፍዋቸው ልምዶች/ተመክሮዎች እንደሚያሳዩት በእነዚህ ተቋማት የሚካሄድ መሰል ውጣ ውረዶች እና የማደነቀፍ እንቅስቃሴዎች የተለመዱ መሆናቸው ነው ፡፡ የሄም ከተቻለ የፀረ ሙስና ትግሉ ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ከላሆነም ደግም ከማህበረ ሰቡ በመነጠል ተአማኒነቱን ለማሳጣት ዓላማ ያላቸው መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምን ጊዜም ቁርጠኛ እና የጉዳዮች አቀራረብ በውል ተረድቶ ምለሽ መሰጠት የሚችል የአመራር ቁርጠኝነት በተሟላበት ሁኔታ ከእነዚህ መሰናክሎች ወጥተው ለውጤት እንዲበቁ አሰተወፀኦ ጉልህ የነበረ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻለል ፡፡ ተቋማት ለሙስና መከላከል እንቅስቃሴ የሚሰጡት ትኩረት በእጅጉ እያሽቆለቆለ መጥቷል፡፡ በተቋማት ዉስጥ የተቀናጀ የሙስና መከላከል ሥራ ለማከናወን ከ2008 በጀት አመት ጀምሮ እንቅስቃሴ የተጀመረ ቢሆንም ቢኖርም ተቋማት ያላቸው ፍላጎት ዝቅተኛ በመሆኑ እና የህግ አስገዳጅነት ባለመኖሩ ትርጉም ያለዉ ሥራ እየተከናወነ አይደለም፡፡ ሙስናን ለመከላከል ኮሚሽኑ
  • 27. 27 ከሚያካሂዳቸዉ ዋና ዋና ተግባራት አንዱ በጥናት ላይ ተመስርቶ የተቋማትን አሰራር ለሙስና እና ለብልሹ አሰራር እንዳይጋለጥ ለማስቻል የአሰራር ስርአታቸው ተፍትሾ የማሻሻያ ሃሳቦች እና ምክር ሃሳብ የሚቀርብ ቢሆንም ተቀብሎ ለመፈፀም ፈቃደኛ የማይሆኑ ተቋማት ከእለት እለት ተበራክተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በስነምግባር እና በሙስና ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የግንዛቤ ፈጠራ እና መጠነ ሰፊ የስልጠና ስራዎችን መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ይሁን እንጅ አቅም እና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በስራው ላይ ለመቆየት የሚያችስችል አሰራር እና አደረጃጀት ያልተፈጠረለት በመሆኑ ስልጠናው የአመለካከት ለዉጥ ለማምጣት በሚያሥችል መንገድ እየሄደ አይደለም፡፡ ከዚህም በላይ የበጀት እና የማሰልጠኛ ቦታዎች እጥረትም አለበት፡፡ በተለያዩ ተቋማት በተለይም የበላይ አመራሩ የሃብት ምዝገባ ሥራን በአግባቡ ትኩረት ሰጥቶ ያለማከናወን ሁኔታ ስለሚታይ ከገቢ በላይ የሚገኝ እና ምንጩ ያልተወቀን ሃብት መቆጣጠር አልተቻለም፡፡ ከዚህ በላይ የተመዘገበው ሃብት እና ሰነድ በቢሮ እጥረት ምክንያት ለችግር ተጋል ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተመዘገበውን ሃብት ለህዝብ ይፋ የሚደረግበት ሶፍት ወይር ልማት ተጠናቆ ወደ ስራ ባለመግባቱ የሃብት ምዝገባ ሰራ አመኔታን እያጣ መጥቷል፡፡ ሙስናን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ለመከላከል እና መልካም ስነምግባር ያለው ትውልድ ለመፈጠር እንዲቻል ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በየተቋሙ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎችን በአግባቡ ለማደራጀት ጥረት ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጅ አደራጅቶ በአግባቡ ከመጠቀም ይልቅ ባልተገባ መንገድ የማፍረስና የማሸማቀቅ ሥራዎች በሰፊዉ እየተስተዋሉ ነዉ፡፡ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስነምግባር መከታተያ ክፍሎችን አደረጃጀት በማጠናከር ወደ ስራ ከማስገባት አንፃር ያለው ሁኔታ በአግባቡ መቀረፍ ይኖርበታል፡፡ በፀረ ሙስና ትግሉ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸዉ የሚታመንባቸው የህዝብ አደረጃጀቶችን የሚወክሉ ማህበራትና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ጋር ጥምረት የፈጠረ እና ትግሉን ወደ ህዝብ ለማድረስ የሚያስችሉ ጥምረቶች እና ስራ አስፈፃሚዎች የነበሩት ሲሆን በአዩት የትኩረት ማነስ ምክንያት ከጥምረቱ ሲወጡ እና ተስፋ ሲቆርጡ ታይተዋል፡፡ በመሆኑም አደረጃጀቶችን የትግሉ ባለቤት ሊያደርጉ የሚችሉ አደረጃጀቶችን ማጠናከር እና ወደ ህዝብ መድረስ ይገባል፡፡
  • 28. 28 7. የፀረ ሙስና ትግሉ ለማጠናከር ሊወሰዱ የሚገባቸዉ እርምጃዎች የሙስና ችግር በሃገራችን ሊፈጥር የሚችለዉን የከፋ ጉዳት ለመከላከል ዉጤታማ የሆነ ሥርአት እና አደረጃጀት ፈጠሮ ለተግባራዊነቱ ተገቢዉን ርብርብ ማድረግ የሚጠይቅ እና ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ሆኗል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ቀጥለው የቀረቡ እርምጃዎች በህግ አውጭው አካል መወሰድ እና ትግሉን ወደ ከፍታ ማሽገር አለብን ብለን እናምናለን፡፡ 1. ኮሚሽኑ በጥናት ላይ ተመስርቶ በአዋጅ ሲቋቋም በአዋጅ ቁጥር 235/1993፣ በአዋጅ ቁጥር 433/1997 እንደገና በማሻሻያ በአዋጅ ቁጥር 883/2007 ተሰጥተውት የነበሩት የምርመራ እና የክስ ስራዎች እንዲመለሱለት ቢደረግ፣ 2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተመለከተው አማራጭ የመፍትሄ ሃሳብ ተግባራዊ የማይደረግበት ነባራዊ እና አሰማኝ ምክንያት ካለ የሙስና መከላለከል እና የምርመራ ስራዎች አንድ ላይ ተጣምረው ተግባራዊ የሚደረግበት የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ቢደረግ፣ 3. ተቋሙ በህግ የተሰጠው ኃላፊነት በሙሉ ዓቅሙ ውጤታማ ሆኖ እንዲሰራ እና ሌሎች ፈፃሚ የመንግስት ተቋማትን በፀረ ሙስና ትግሉ የተጣሉባቸውን ሓላፊነትና ተግባር በአግባቡ እንዲፈፅሙ የሚያስችል እና በማይፈፀሙ ተቋማት ላይ ተጠያቂነት የሚያስከትል አሰገዳጅ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ቢደረግ፣ 4. ኮሚሽኑ ተቋማዊ ነፃነት ኖሮት በህግ የተሰጡትን ተግባር እና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችለው የሰው ኃይል፣ የፋሲሊቲ እና በቂ የበጀት ድጋፍ የሚያገኝበት ሁኔታ ቢፈጠር በሀገሪቱ በፀረ ሙስና ትግል ላይ የሚደረገውን ትግል ወደላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይታመናል ፡፡