SlideShare a Scribd company logo
1 of 38
Download to read offline
በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የግማሽ አመት መፅሔት
ቅጽ 1 ቁጥር 15/2011
አንቀልባአንቀልባአንቀልባ
LIDILIDILIDI
Engineering TomorrowEngineering TomorrowEngineering Tomorrow
2
1.ዓላማ
የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች ቴክኖሎጂዎች
ልማትና ሽግግርን በማፋጠን ኢንዱስትሪዎች
ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ፈጣን ልማት ኢንዲያስመዘግቡ
ማብቃት
2.ራዕይ
ኢንስቲትዩቱን ውጤታማ ተቋም በማድረግ በ2017
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ በዓለም አቀፍ ያለውን
የገበያ ድርሻ በ10 እጥፍ አድጎ ማየት
3.ተልዕኮ
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪን ዘላቂና ፈጣን በሆነ
መልኩ እንዲስፋፋ በማድረግ በኢንቨስትመንት፣
በምርትና በግብይት ለልማታዊ ባለሀብቱ ቀልጣፋ
የቴክኖሎጂ፣ የማማከር አገልግሎትና ድጋፍ
በመስጠት አገሪቷ ከቆዳ ሀብቷ ከፍተኛ ተጠቃሚ
እንድትሆን ማድረግ
የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት
3
አንቀልባአንቀልባአንቀልባ AnkelbaAnkelbaAnkelba
ማዉጫ
የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት..................................4
የአዘጋጁ መልዕክት...............................................5
ዜና አንቀልባ........................................................6
የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እና ለዘርፉ
ማሻሻል የኢንስቲትዩቱ ሚና................................17
በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ ሩቅ ለመሄድ
ከፈለክ አብረን እንሂድ ” …………………….…….18
ለሥጋ ብቻ ሳይሆን… .......................................21
ዓለም አቀፍ እውቅናን ለማስቀጠል.....................22
መዝናኛ.............................................................25
ጤና...................................................................26
ፎቶ ማህደር ......................................................28
ዋና አዘጋጅ / Editor In
chief/
አቶ ብርሃኑ ሥርጃቦ / Mr.
Birhanu Serjabo/
አዘጋጆች /Editors/
ገነት ደምሴ /Genet Demis-
se/
ወንድወሰን አሊሙሳ /
Wondweson Ali Mussa
ሠላማዊት ራያ /Selamawit
Raya
ብሩክ ዋጋዬ /Bruk
Wagaye
የካሜራ ባለሙያና ሌይ
አዉት ዲዛይን/
Photographer, and lay-
out Designer /
ብሩክ ዋጋዬ /Bruk
Wagaye/
4
የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት
የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ መሪነቱ አቅጣጫ
እውን እንዲሆን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ጉልህ
አሰተዋፅኦ እንዲያደርግ፣የኢንደስትሪውን የማምረት አቅም
በማሳደግ፣ የምርት ጥራት ደረጃን በማሻሻል እና ለአካባቢ
ተስማሚ የሆነ የምርት ሂደትን በማጎልበት፣ አስተማማኝ
የሆነ ሃገራዊ ኢንዱስትሪ በመገንባት ረገድ የሃገሪቱን
የውጭ ምንዛሬ አቅም ለማሳደግ በሚደረገው ጥረትም
የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩታችን ሚና ከፍተኛ
እንደሆነ ይታመናል፡፡
ሀገራችን ከኢንዱስትሪው ማግኘት የሚገባት ኢኮኖሚያዊና
ማኀበራዊ ጠቀሜታ ከፍ እንዲል ነባር ፋብሪካዎች በሙሉ
አቅማቸው ጥራት ያለው ምርት የማምረትና ያመረቱትንም ምርት በሙሉ የመሸጥ አቅም ለመገንባት፣
አዳዲስ የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች በብዛት ወደዘርፉ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ እስከአሁን ከነበረው በተሻለ
መንገድ ክትትል ለማድረግና ድጋፍ ለመስጠት በዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል፡፡
በዘርፉ የተሰማሩ ፋብሪካዎች ያሉባቸው ችግሮች ተቀርፈውላቸው ትኩረታቸውን የምርት ስብጥር
በማብዛት፣ አዳዲስ የኤክስፖርት መዳሪሻዎችን በማስፋት፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢ በማሳደግ እና ለዜጎች
ተጨማሪ የሥራ ዕድል በመፍጠር ላይ እንዲያደርጉ የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንትና ሠራተኞች
ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት፣ በትጋትና በቁርጠኝነት
በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡
ለበርካታ ዓመታት በማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አካባቢ ስለቆየሁ በቆዳ ኢንዱስትሪው ንዑስ ዘርፍ
ለሚታዩ ችግሮችና ችግሮችን ለመፍታት ኢንስቲትዩቱ በተሻለ ቁመና ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠንቅቄ
ስለማውቅ በተቻለ መጠን ችግሮችን በፍጥነት በማስወገድ ዘርፉን ወደ ተወዳዳሪነት ማምጣት
እንደሚቻል አምናለሁ፡፡ ለዚህም በኢንስቲትዩቱ አሳሳቢ እየሆነ ያለው የባለሙያዎች ፍልሰት እንዲቀንስና
ሠራተኞች በኢንስቲትዩቱ ተረጋግተው እንዲቆዩ ምቹ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ
እየተሠራ ይገኛል፡፡
በመጨረሻም ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከዘርፉ ማህበራት፣ ከፋብሪካ ባለቤቶችና ባለሙያዎች፣
ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የዘርፉን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማስወገድ በሁሉም አቅጣጫ
የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በማጠናከር በቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በከፍተኛ
ትኩረት እየተሠራ መሆኑን እየገለጽሁ፣ ዕቅዳችን እንዲሳካ የዘርፉ ማኀበራትና ባለሀብቶች እና
የሚመለከታችሁ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆናችሁ አካላት ከኢንስቲትዩቱ ጎን ሆናችሁ እንድታግዙን
እጠይቃለሁ፡፡
አመሰግናለሁ፡፡
4
5
የአዘጋጁ መልዕክት
የሀገራችን እንስሳት ቆዳና ሌጦ በተፈጥሮ የተለየ ባህሪ
ያለው ቢሆንም በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት
ጥራቱ በጣም የወረደ በመሆኑ ሀገራችን ያላትን የእንስሳት
ሀብት ያህል ከቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተጠቃሚ
አይደለችም፡፡ እነዚህ ችግሮች እንስሳት በቁም እያሉ፣ በእርድ
ስነ ስርዓት ወቅት እና ከእርድ በኋላ የሚከሰቱ ሲሆኑ
በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው
ከሰሩ ሊቀንሱ የሚችሉ ናቸው፡፡
የኢፌዲሪ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የሰለጠነ
የሰው ሀብት በማፍራት፣ በምርምርና ስርፀት፣ በምርት
ልማትና ማማከር፣ በጥራት ፍተሻና የቴክኒክ ድጋፍ የቆዳና
የቆዳ ውጤቶች ፋብሪካዎች ምርቶቻቸውን በጥራትና
በብዛት አምርተው ለዓለም ገበያ በማቀረብ ሀገራችን
ከዘርፉ የምታገኘው ጠቀሜታ ከፍ እንዲል ለዘርፉ ሁሉን
አቀፍ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ የዘርፉን የሰለጠነ የሰው ሀብት ፍላጐት ለማሟላት በሀገር ውስጥ
ከስድስት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ እና ከ42 የቴክኒክና
ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ጋር በመተባበር ከደረጃ 1 እስከ 4 በርካታ ባለሙያዎችን በማፍራት
ላይ ይገኛል፡፡ በርካታ ችግር ፈች ምርምሮች፣ የምርት ልማት ሥራዎች፣ የጥራት ፍተሻ አገልግሎቶችና
በሥራ ላይ ስልጠናዎችም እየተሰጡ ነው፡፡
የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትም በኢንስቲትዩቱ የተከናወኑና የሚከናወኑ ተግባራትን እና የተገኙ
ውጤቶች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ለሕብረተሰቡ ለማድረስ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በ2011
የመጀመሪያ ግማሽ በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትንም በዚህ አንቀልባ መጽሔታችን አካትተን
አቅርበናል፡፡ ለምናደርገው መሻሻል የደንበኞቻችን አስተያየት የአንበሳውን ድርሻ ስለሚወስድ
ለአስተያየታችሁ የተለመደ ትብብራችሁን እየጠየቅን መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
አመሰግናለሁ፡፡
5
6
ኢኒስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አገኘ
የምስክር ወረቀቱ ለሁለተኛ ጊዜ የተሠጠው መሆኑም ታውቋል፡፡
በገነት ደምሴ
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ለሁለተኛ ጊዜ ዓለም አቀፋዊ እውቅናና ከፍተኛ የጥራት ስራ
አመራር ደረጃ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አገኘ፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተዘጋጀ የሚሰጠውን የአይ.ኤስ.ኦ 9001፡2015 ከፍተኛየጥራት ደረጃ ማረጋገጫ የምስክር
ወረቀት ያገኘዉ በየጀርመን የተስማሚነት ምዘና ተቋም ከሆነው የዲ. ኪው.ኤስ /DQS/ ጥራት ሥራ አስኪያጅ
አቶ አለማየሁ በለጠ ናቸዉ፡፡ የምስክር ወረቀቱ የኢትዮጵያን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት የሠው ኃይል
ስምሪት፣ የሃብት አጠቃቀም፣ የደንበኛ እርካታን፣ የስጋት ጊዜ አመራርንና የላብራቶሪ አገልግሎትን በሚመለከት
ዓለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟላ መሆኑን የሚያበስር እንደሆነ ታውቋል፡፡
አይ. ኤስ. ኦ. በዓለም ዙርያ የሚገኙ
20,000 ተቋማትን በአባልነት ያቀፈ ዓለም
አቀፍ ተቋም ሲሆን፣ በተለያዩ ሃገራት
የሚገኙ ተቋሟትን አገልግሎት አሰጣጥ
በሚመለከት ፍተሻና የተስማሚነት ምዘና
የሚያደርግና እውቅና የሚሰጥ ተቋም
ነው፡፡
የምስክር ወረቀቱ የተሰጠዉ በአዲስ
ዓመት በአንድነት ለዕድገት በትጋት
ለመስራት የተቋሙ ሠራተኞች ቃል
ለመግባት በቢሾፍቱ ከተማ በፒራሚድ
ሆቴል ውስጥ በተዘጋጀው ሥነ ሥርዓት
ላይ በታደሙበት ወቅት አንደነበረ ማወቅ
ተችሏል፡፡
6
7
የቻይና የቆዳ ኢንዱስትሪ ምርምር ኢንስቲትዩት ልዑካን
ቡድን ጉብኝት…
በወንድወሰን አሊ
የቻይና የቆዳ ኢንዱስትሪ ምርምር ኢንስቲትዩት ልዑካን ቡድን አባላት ነሀሴ 8 ቀን 2010 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩቱ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ የጉብኝታቸው ዓላማም
ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር የትብብር ግንኙነት ለመመስረት እንደሆነ ታውቋል፡፡
የልዑካኑ ቡድን በኢንስቲትዩቱ ማኔጀመንት አቀባበል ከተደረገለት በኋላ ኢንስቲትዩቱ አሁን ያለበት
ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለጻ ተደርጎለታል፣ በአፍሪካ ደረጃም በዘርፉ ስልጠና በመስጠት እውቅና
በማግኘት፣ የጥራት ፍተሻ ማረጋገጫ ያገኘና ቆዳ በማልፋት ሂደት፣ በማስተዋወቅና በሌሎችም
ተያያዥ ሥራዎች ስኬቶች ማግኝቱን ተናግረዋል፡፡
በቀረበው ገለጻ መሰረት የተለያዩ ጥያቄዎች ከልዑካን ቡድኑ የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ቻይና
እና ኢትዮጵያ በቆዳው ዘርፍ ስላላቸው ጠንካራ ግንኙነት፣ በዘርፉ እየተተገበረ ስላለው ፖሊሲ፣ በቆዳ
ፋብሪካዎች ስርጭት ኢንስቲትዩቱ
ለቆዳ ፋብሪካዎች ስለሚሰጠው
ድጋፍ፣ ስለአካባቢ ጥበቃ፣
ኢንቨስትመንት እና ሌሎች
ጉዳዮችን የተመለከቱ እንደነበሩና
በቂ መልስም እንደተሰጣቸው
ለመረዳት ተችሏል፡፡
7
8
በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት የመቶ
ቀናት እቅድ ላይ የኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንት አባላት፣
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማኀበር አመራሮችና
ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ህዳር 25 ቀን 2011
ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ መሰብሰብያ አዳራሽ ውይይት
ተካሂዷል፡፡
ዕቅዱ በኢንስቱትዩቱ
የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና
ግምገማ ዳይሬክቶሬት
ዳይክተር በሆኑት አቶ
ተስፋዬ ብርሃኑ ቀርቧል፡፡
ዳ ይ ሬ ክ ተ ሩ የ ነ ባ ር
ኢንዱስትሪዎች የማምረት
አቅም እና የእሴት ጭማሪ
አፈፃፀም ዝቅተኛ መሆን፤
የቆዳ ፋብሪካዎች አካባቢን
የመበከል ችግር፤ ደካማ
የ ኢ ን ቨ ስ ት መ ን ት
ፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና
ዝቅተኛ የኢንቨስትመንት አቅም፤ ሀገራዊ ኢንቨስትመንትን
ለማስፋፈት የሚያስችል የተቀናጀ እንቅስቃሴ ያለመኖሩ፤
ዝቅተኛ የወጪ ንግድ አፈፃፀም፤ በቂና ውጤታማ ያልሆነ
ተቋማዊ ድጋፍ፤ የድጋፍና ክትትል ውጤታማነት ችግር፤
የ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ
አፈጻጸም ግምገማ፤ በመንግስት የተሰጠ አቅጣጫ፤ ደካማ
ቅንጅታዊ አሰራር የዕቅዱ መነሻ ሁኔታዎች እንደሆኑ
አቅርበዋል፡፡
የዕቅዱ ዓላማም የቆዳና ቆዳ ውጤቶች እንዱስትሪን
የማምረት አቅም፣ የምርታማነትና የምርት ጥራት ደረጃ
እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃና የእሴት ጭማሪ አቅም
በየደረጃው በማጎልበት ቀጣይነት ላለው አስተማማኝ
ሀገራዊ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ግብ ስኬት ምቹ ሁኔታን
በመፍጠር የንዑስ ዘርፉን የውጭ ምንዛሪ ግኝት እና
የሥራ ዕድል ፈጠራ
አቅም ማሳደግ እንደሆነ
ዳይሬክተሩ አክለው
አስረድተዋል፡፡
የ ደ ጋ ፊ ተ ቋ ሙ ን
ሁለንተናዊ የድጋፍ አቅም
ማ ሳ ደ ግ ፤ ጥ ራ ቱ
የተጠበቀ የምርት
ግብዓት በሚፈለገው ልክ
እንዲቀርብ ማድረግ
የ ኢ ን ዱ ስ ት ሪ ው ን
የሰለጠነ የሰው ኃይል
ፍላጎ ት በአ ግባቡ
ማሟላት፤ የቴክኖሎጂ ብቃትና የአሰራር ስርዓት ዓቅምን
ማሳደግ፤ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የምርት መዳረሻ
ገበያዎች እንዲስፋፉ ማድረግ፤ የውጭ ምንዛሬ፣ የኃይል
አቅርቦት እንዲሁም ሌሎች ማነቆዎች እንዲፈቱ ማድረግ
ቅንጅታዊ አሰራርን ማሻሻል ፣ ተጨማሪ የኢንቨስትመንት
አቅሞችን ወደ ሥራ ማስገባት እና የክትትል፣ ድጋፍና
ግምገማ አሰራርን ማጠናከር የአፈፃፀም አቅጣጫዎች
እንደሆኑም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በመቶ ቀናት እቅድ ላይ ከዘርፉ ማህበር
አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ
8
9
በገነት ደምሴ
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንደስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት በ2011
ትምህርት ዘመን ተመዝግበው ለመሰልጠን የተመረጡ
ከሰላሳ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በቆይታቸው ማከናወን
የሚገባቸውን ተግባራት አሳወቋል፡፡
በኢኒስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
አማካኝነት ለተማሪዎች በተዘጋጀው የቅበላ ፕሮግራም ላይ
በ2011 ዓ.ም የትምህርትና የስልጠና ዘመን አዲስ ገቢ
ተማሪዎች በኢኒስቲትዩቱ ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ
የሚወስዷቸውን የስልጠና ዓይነቶችና የሚቸግራቸውን
ለሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ መፍትሄ
የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቸ መሆኑን የኢኒስቲትዩቱ
ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ሁሴን ተናግረዋል፡፡
በዚህ ዓመት ኢኒስቲትዩቱ በቴክኒክና ሙያ ከደረጃ አንድ
እስከ ደረጃ 4 በቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በተከታታይ
ለሚያሰለጥናቸው ተማሪዎች በሞዴል ፋብሪካዎች
አማካኝነት የተግባር ትምህርት እንደሚወስዱም ምክትል
ዋና ዳይሬክተሩ ከመግለጻቸውም በተጨማሪ
እንደደረጃቸውና እንደትምህርት አቀባበላቸው የቆይታ
ግዜያቸውም እንደሚወሰን አቶ ዮናስ ተፈራ የኢኒስቲትዩቱ
የቴክኖሎጂ ሽግግርና ስልጠና የቡድን መሪ ለተማሪዎቹ
ማብራርያ በመስጠት ተማሪዎች በቆይታቸው ሥለተቋሙ
ማወቅ የሚገባቸውን ጉዳይ አስረድተዋል፡፡
በኢኒስቲትዩቱ የመሰብሰብያ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደው
በዚህ ፕሮግራም ላይ አሰልጣኝ መምህራን ከተማሪዎች ጋር
እንዲተዋወቁ ሲደረግ፣ የመማርያ ክፍሎችን፣ ሞዴል
የጫማ ፋብሪካ፤ሞዴል የቆዳ እቃዎችና አልባሳት ፋብሪካ፣
የቤተመጻህፍትና ሌሎች አገልግሎቶችን
የሚያገኙባቸውን ቦታዎች ተማሪዎች ጎብኝተዋል፡፡
ኢነስቲትዩቱ ለትምህርት የተመዘገቡ ተማሪዎችን የእንኳን ደህና
መጣችሁ ቅበላ አደረገ
የኢትዮጵየ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር አመራሮች ዘርፉ
አደጋ ላይ የወደቀ በመሆኑ የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችን
ችግሮች ለመፍታት ኢንስቲትዩቱ ምን ዓይነት ድጋፍ
እንደሚያደርግ፣ የቆዳ ዘርፉን አስመልክቶ መንግስት
የነደፈው ፖሊሲ የአገር ውስጥ አምራቾችን ክፉኛ ስለጎዳው
እንዲሻሻል፣ የፋይናንስ ድጋፍና የብድር አገልግሎት
አሠሰጣጥ ችግር ያለበት ስለሆነ እነዚህ ችግሮች ተፈትተው
ዘርፉ ከመውደቅ ሊታደግ ይገባል በማለት አስተያየት
አቅርበዋል፡፡ ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የኢኒስቲትዩቱ
ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ ፈለቀና ሌሎች የማኔጅመንት
አባላት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በተለይ የዘርፉ ችግር የፖሊሲ
ሳይሆን የፋብሪካዎች የሥራ አመራር ችግር በመሆኑ ችግሩን
ለመፍታት ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው፣ ፋብሪካዎች
የሚያቀርቡት ችግር በቁጥር የተደገፈ ወይም ገላጭ ሳይሆን
በደፈናው የሚቀርብ በመሆኑ መፍትሔ ለመስጠት አስቸጋሪ
እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡ የፖሊሲ ማሻሻያ
ለማድረግም ሆነ ሌሎች ድጋፎችን ለማድረግ የሚያስችል
በእውቀትና በጥናት ላይ የተመሠረተ ትክክለኛ መረጃ
መቅረብ ያለበት መሆኑንም ኃላፊዎቹ አስረድተዋል፡፡ ችግሩን
ለመፍታትም የማህበሩ መሪዎችና ኢንስቲትዩቱ በጋራ
የሚያከናውኑት መሆኑን በመተማመን በቀጣይ ተጨማሪ
ውይይት ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በሌላ በኩል ከኢንዱስትሪው የሚወጡ ደረቅ ቆሻሻ
አወጋገድን በሚመለከት ከአዲስ አበባ መስተዳድርና
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር መልሶ በማልማት
ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግም
የኢንስቲትዩቱ ሃላፊዎች አስረድተዋል፡፡ በመጨረሻም
የማኀበሩ አመራሮች ዕቅዱ ሁሉንም አካትቶ የያዘና ጥሩ
ዕቅድ መሆኑን በመግለጽ ለዕቅዱ ስኬታማነት የበኩላቸውን
የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ገልፀዋል፡፡
9
10
የቀድሞዉ የኢንስቲትዩቱ ዋና
ዳይሬክተር በይፋ ተሸኙ
በሽኝት መርሀ ግብሩ ላይ አዲሱ የኢንስቲትዩቱ ዋና
ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ ፈለቀም አቀባበል
ተደርጎላቸዋል፡፡
በብሩክ ዋጋዬ
አቶ ወንዱ ለገሰ ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ በተቋሙ በባለሙያ ደረጃ
ተቀጥረዉ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆኑ ኢንስቲትዩቱ ከቀድሞ
መጠሪያዉ የቆዳና ቆዳ ዉጤቶች ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተለያዬ
ተግባርና ሀላፊነቶችን አካትቶ ወደ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት
ኢንስቲትዩት ከተቀየረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 2011ዓ.ም ለስምንት
ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ዉስጥ በተዘጋጀ ፕሮግራም አዲሱ ዋና
ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ ፈለቀና የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች
እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት አሸኛኘት
ሲደረግላቸው ለአዲሱ ዋና ዳይሬክተር ደግሞ የእንኳን ደህና መጡ
አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ለተቋሙ
ያላቸዉን ክብር የገለፁ ሲሆን ለትምህርት ወደ ህንድ ሀገር ለመሄድ
ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት የገጠማቸዉን አዝናኝ ገጠመኝና
ትዝታ አውስተዋል፡፡
በትምህርትና ስልጠና፣በቁርኝት መርሀግብርና የተቋሙን አቅም
በመገንባት፣ የቆዳዉ ዘርፍ ከፍተኛ የዉጭ ንግድ ገቢ
እንዲያስመዘግብ፣ በምርምርና ፍተሻ ዙሪያ ከፍተኛ ተግባራት
እንዳከናወኑና ምርምሮቹም በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ጭምር
እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸዉን የስራ
ባልደረቦቻቸዉና የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
ከሀላፊነታቸው ለመልቀቅ የወሰኑበትን ምክንያት ሲገልጹም
ሥራው በአዲስ ሃይል መተካት እንደሚኖርበት ስለአመንኩና
ላሳካችዉ ያልቻልኩዋቸዉ ነገሮችን መስራት ወደምችልበትና
በባለሙያ ደረጃ ከፍተኛ ለዉጥ ለማስመዝገብ በመፈለጌ ነዉ
ብለዋል፡፡
ቀጣይ ለዘርፉ ምን አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ? ብለን
ላቀረብንላቸዉ ጥያቄም ለዘርፉ አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ የሚችሉ
መፅሀፍትን የዘርፉ ባለሙያዎች በቀላሉ ሊረዱት እንዲችሉ
በአማርኛ ቋንቋ ለማዘጋጀት እንዳቀዱ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም
አዲስ ከመጡት ዋና ዳይሬክተር ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ
መሆናቸውንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
11
በኢጣልያ የውጭ ጉዳይ ምክትል
ሚኒስትር ክብርት ሚስስ ኢማኑዌላ
ዲለር የሚመራ 17 ከፍተኛ
ባለስልጣናትን የያዘ የልዑካን ቡድን
ቅዳሜ ህዳር 29 ቀን 2011 ዓ.ም
ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ጀምሮ
በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት
ኢኒስቲትዩት ጉብኝት አድርጓል፡፡ ልኡካን
ቡድኑ የኢፌዲሪ ንግድና ኢንዱስትሪ
ሚኒስቴር የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ
ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ
ዮሐንስ ድንቃየሁ እና የኢፌዲሪ የቆዳ
ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ዋና
ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ ፈለቀ አቀባበል
አድርገዉላቸዋል፡፡
በጣልያን ምክትል የውጭ ጉዳይ
ሚኒስትር ክብርት ሚስስ ኢማኒዊላ
ዲለር የሚመራው የልዑካን በድን
በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ አቀባበል
እንደተደረገለቸው የኢንስቲትዩቱን
ሞዴል ቆዳ ፋብሪካና የቆዳ ምርምር
ማዕከል፣ ሞዴል የቆዳ አልባሳትና
ዕቃዎች ፋብሪካ፣ ሞዴል የጫማ
ፋብሪካና የጫማ ምርምርና ምርት
ልማት ማዕከል እና የምርምርና ፍተሻ
ላቦራቶሪን ተዘዋውረዉ ከጎበኘ በኋላ
ስለኢፌዲሪ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት
ኢንስቲትዩትና የሀገራችን ቆዳ
ኢንዱስትሪ ታሪካዊ አመጣጥ እና
ዘርፉን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ
ለማድረግ በመንግስት ስለተሰጠው ልዩ
ትኩረት የኢንስቲትዩቱ የዕቅድ ዝግጅት
ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብርሃኑ
በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ዳይሬክተሩ
የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪ አሁን
ያለበት ደረጃ እንዲደርስ የጣልያን
መንግስት የልማት ትብብር ኤጀንሲ
ከፍተኛ ድጋፍ እንዳደረገ ገልጸዋል፡፡
የሀገሪቱ የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ
በዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆንም
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት
ኢኒስቲትዩት በአገሪቱ ከሚገኙ ከፍተኛ
የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር
150 ተማሪዎችን በመጀመሪያ፣
በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ ደረጃ
እያስለጠነ ሲሆን ከ42 በላይ ከሆኑ
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሰልጠና
ኮሌጆች ጋር በመተባበር ለበርካታ
ተማሪዎች ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4
ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝም አቶ
ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ
ቦጋለ ፈለቀ በበኩላቸው የኢጣሊያን
መንግስት ለሀገራችን የቆዳ ኢንዱስትሪ
ዘርፍ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ
አመስግነው ወደፊትም ድጋፉን
አጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው
መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የንግድና
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
ክቡር አቶ ዮሐንስ ድንቃየሁ
በበኩላቸው የኢትዮጵያና የጣሊያን
ረጅም ዓመታት ያስቆጠረው ታሪካዊ
ግንኙነት በሁሉም ረገድ የሁለቱም
አገራት ጥቅም በሚያሳድግ መልኩ
ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትኩረት ተሰጥቶ
እንደሚሠራ አስረድተዋል፡፡ ክብርት
የጣልያን ውጭ ጉዳይ ምክትል
ሚኒስትሯ በበኩላቸው ለተደረገላቸው
ደማቅ አቀባበል አመስግነው
በኢንስቲትዩቱ ባዩት የተሠሩ
የምርምርና የምርት ልማት ሥራዎች
መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ በጣሊያንና
በኢትዮጵያ የቆየው የረጅም ጊዜ
ታሪካዊ ግንኙነት ከሌሎች አገሮች
በ ተ ለ የ ሁ ኔ ታ ተ ጠ ና ክ ሮ
እንደሚቀጥልም በመግለጽ የጣልያን
መንግሥት የኢትዮጵያን የቆዳ
ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሻለ ደረጃ ላይ
እንዲደርስ በተሻለ ሁኔታ ድጋፉን
አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር እና
ሌሎች የጣሊያን መንግስት የኢኮኖሚ
ትብብር ኤጀንሲና የዩኒዶ
ባለሥልጣናትም የቆዳ ኢንዱስትሪ
ዘርፍ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ
እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
በጣልያን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር የሚመራ ቡድን
የኢትዮጵያን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩትን ጎበኘ
11
12
ለካይዘን አማካሪዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ
ስልጠናዉን የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ለኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎችና ከቆዳ
ኢንዱስትሪ ለተወጣጡ ባለሙያዎች ሰጥቷል፡፡
በብሩክ ዋጋዬ
የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር የካይዘን
አፈፃፀም ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተመስገን
የሀገራችን ኢንዱስትሪ ሁኔታ በጥራትና
ምርታማነት ላይ ያላደገ በመሆኑ ይህን ለማሳደግ
አንዱ ትልቁ መሳሪያ ካይዘን በመሆኑ ስልጠናዉ
እጂግ አስፈላጊ መሆኑን ይናገራሉ፡፡
በ2010 ዓ.ም አራት ለሚሆኑ የቆዳ ዘርፍ
ፋብሪካዎች የካይዘን ስልጠናዉ መሰጠቱንና
የተመዘገበዉ ዉጤትም ጥሩ በመሆኑ
በዘንድሮዉ 2011 ዓ.ም ደግሞ ዘጠኝ ለሚሆኑ
በቆዳዉ ዘርፍ ለተሰማሩ ፋብሪካዎች ይህንን
ስልጠና መስጠት ማስፈለጉን የቆዳ ኢንዱስትሪ
ልማት ኢንስቲትዩት የለዉጥና መልካም
አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አንዳለ
ዘለቀ ተናግረዋል፡፡
የስልጠናዉ ዓላማ ካይዘንን ሊያሰለጥኑ የሚችሉ
አማካሪዎችን በቆዳዉ ዘርፍ ላይ ማፋራት
የሚለወን የያዘ ሲሆን ስልጠናዉም የካይዘን
ምንነት፣ ዘዴዎች እና ፍልስፈናዉ ምን ይላል
የሚለዉን እንዲሁም የአሰለጣጠን ዘዴን ያካተተ
መሆኑን የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት በቆዳ
ኢንዱስትሪዎች የካይዘን ሽግግር እና ልማት
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መስፍን
ወንድሙ ተናግረዋል፡፡
የዚህ ስልጠና መዳረሻዉ ለቆዳ ፋብሪካዎች፣
ለጫማ ፋብሪካዎች፣ ለቆዳ አልባሳትና እቃ
ፋብሪካዎች ለተከታታይ ስድስት ወራት
በፋብሪካዎች ዉስጥ ቀጣይነት ያለዉ ስልጠና
እንደሚሰጥ አስታወቀዉ አማካሪዎች ራሳቸዉን
የሚያበቁበት እንዲሁም ኢንዱስትሪዎች ከዚህ
የማማከር አገልግሎት ተጠቅመው የስራ
አካባቢያቸዉን የሚያደራጁበት በይበልጥ ጥራት
እና ምርታማነትን እንዲጨምሩ የሚያስችል
ስልጠና መሆኑ ታውቋል፡፡
ስልጠናዉ ለአምስት የሥራ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን
በሁለቱ የእረፍት ቀናት ደግሞ መመዘኛ
እንደሚሰጥ፣ እንዲሁም እጩ አማካሪዎች
መመዘኛዉን ከ75 ፐርሰንት በላይ ሲያስመዘግቡ
ብቻ አማካሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ስልጠናዉን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር
በበላይነት የሚከታተለዉ ሲሆን በካይዘን
ኢንስቲትዩት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
12
13
በወንድዎሰን አሊ
በቆዳና ጫማ ዘርፍ በህንድ አገር የ2ኛ ዲግሪ
ትምህርታቸውን አጠናቀው ለተመለሱ 13
ተማሪዎች ኢንስቲትዩቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ
አቀባበል አደረገ፡፡
ፕሮግራሙን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት
የኢንስቲትዩቱ የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር አቶ
ወንዱ ለገሰ የትምህርት እድሉን አግኝታችሁ
ከነችግሩ በማለፍ ለዚህ በመብቃታችሁ እንኳን
ደስ አላችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፤
በተጨማሪም ተማሪዎቹ ትምህርታችውን
በሚከታተሉበት ወቅት ባሳዩት ብቃትና መልካም
ስነ-ምግባር በኢንስቲዩቱ ስም ምስጋናቸውን
አቅርበዋል፡፡ውጭ ተምረው ያመጡትን
የትምሀርት ክህሎትና ልምድ ወደ አገራቸው
በማባዛትና በመቀመር በሴክተሩ የሚታዩ
ችግሮችን በመፍታት ሀላፊነታቸውን በብቃት
እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡
በበጀት ዓመቱም ተማሪዎቹ የሲቪል ሰርቪሱን
መመሪያ በተከተለ፣ አገልግሎታችውና የትምህርት
ደረጃቸው በሚፈቅደው መሠረት ወደስራቸው
የተመደቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ተማሪዎቹ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ የሰው
ሀብቱን የአቅም ክፍተት ለመሙላት የውጭ አገር
ስልጠና ለሰራተኞቹ መስጠቱን በማድነቅ
የማኔጅመንቱ ጥረት የሚደነቅ መሆኑንም
ገልጸዋል፡፡
የምርምር ዘርፉ ከሌሎች የስራ ዘርፎች ጋር
ተጣምረው እንዴት መሰራት እንዳሚችሉም
ልምድ ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ህንድ አገር ተምረው ለተመለሱ ተማሪዎች የአንኳን ደህና
መጣችሁ አቀባበል ተደረገ
13
14
በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ሠራተኞች ነሃሴ 30 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገ የጉልበትና
የገንዘብ ድጋፍ ጥገናው ተጀምሮ የነበረው የአረጋውያኑ ቤት ግንባታ ተጠናቆ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር
በተገኙበት መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም ተመርቋል፡፡
ጥገናው ከመከናወኑ በፊት ከጥገና በኋላ
በቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 5 ነዋሪ የሆኑት አቶ ከበደ ሞላና ወ/ሮ ሽታዬ ጥላሁን ተጠልለውበት የነበረ
ቤት ከመውደቁ በፊት አዛውንቶቹን ለመደገፍ ከኢንስቲትዩቱ በተገኘ የቁሳቁስ ድጋፍና ከሠራተኛው
በተዋጣ ገንዘብ ተጠግኖ በመስቀል ማግስት ከቀኑ 5፡30 እስከ 6፡30 በተካሄደ ፕሮግራም መላው
የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች በተገኙበት ተመርቋል፡፡
በምረቃው ሥነስርዓት ላይም ዋና
ዳይሬክተሩ አቶ ወንዱ ለገሰ ባደረጉት
ንግግር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/
ር አብይ አህመድ በጀመሩት በፍቅር
የመደመርና በይቅርታ የመሻገር መርህ
መሰረት ሁላችንም ተሳትፈን ውጤት
አሳይተናል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን በጎ ተግባር
በማስቀጠል ሌሎችንም አረጋውያን
መደገፍ ብቻም ሳይሆን አብረናቸው
እንደምንሆን ብናሳያቸው ለበርካቶች
ተስፋ እንሆናለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አረጋውያኑም በዕለቱ ለተደረገላቸው በጎ ሥራ የተቋሙን ሠራተኞች በማመስገን በአዲስ ዓመት ከጎናቸው
ሆነው በዓሉን በጋራ ተሰብሰበው እንደዚህ ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲያከብሩ ስላደረጉ የተሰማቸውን
ደስታ በመግለጽ ይህን በጎ ሥራ በቅን ልቦና በመነሳሳት የመሩትን የተቋሙን ሠራተኞች፣ የኮሚቴ
አባላትና ሃላፊዎች አመስግነዋል፡፡
በተቋሙ ሠራተኞች የጉልበትና የገንዘብ ድጋፍ ተጀምሮ
የነበረው የአረጋውያኑ ቤት ተመረቀ
14
15
የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር የስምምነት ሰነድ
ተፈረመ
ታህሣሥ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት
ኢኒስቲትዩትና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት
የመሀል ኢትዮጵያ የጫማና የቆዳ ዕቃዎች ልማት ትምህርት፣ ስልጠናና
ምርምር ተቋማት እና ኢንዱስትሪ ትስስር ንዑስ ቀጠናዊ ፎረም
መግባቢያ የስምምነት ሰነድ ፊርማ ሥነሥርዓት ተካሂዷል፡፡
በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ በተካሄደው
የትስስር ፎረም ምስረታ ስነስረዓት ከኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት
ኢንስቲትዩት፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ
አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ እና
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች
ልማት ኮርፖሬሽን እና ከ16 የጫማ ፋብሪካዎች አመራሮች ተገኝተው
የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም የመግባቢያ ሰነድ
ተፈራርመዋል፡፡
በትምህርትና ሥልጠና፣ በምርምር ሥራዎችና የኢንዱስትሪ ተግባር
ልመምድን በሚመለከት በተካሄደው የፊርማ ሥነስርዓት ላይ
የመግቢያ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ድባቦ የሱፍ የአዲስ አበባ ሳይንስና
ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዘዳንት በመግባባት ላይ
የተመሠረተ የጋራ የትምህርትና የኢንዱስትሪ ትስስር ቀጠናዊ ፎረም
መመስረት በቆዳው ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በምርምር ለመፍታት፣
ተማሪዎች ብቃት ኖሯቸው በተግባር ልምምድ ራሳቸውን አጎልብተው
ኢንደስትሪውን እንዲያሳድጉ፣ በኢንደስትሪው ባለቤቶችና በምርምር
ተቋማት መካከል የሚመሰረተው ትስስር አስፈላጊነቱ ታምኖበት
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንደስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት መድረኩን
በማመቻቸት ሃላፊነቱን ተወጥቷል ብለዋል፡፡
የኢንዱስትሪውን ችግር ከመፍታት አንጻር በትስስሩ የሚከናወኑ የጋራ
የምርምር ስራዎችን፣ የኢንዱስትሪውን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ምክረ
ሃሳቦችን፣ የተማሪዎችን የተግባር ልምምድን የዩኒቨርሲቲ መምህራን
በኢንደስትሪ ውስጥ የተግባር ልምምድ ማድረግን፣ የጋራ የምክክር
መድረክ አዘጋጅቶ ችግሮችን የመፍታት ስራዎችን፣ የኢንዱስትሪዉ
ባለሙያ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ሄዶ የተግባር ስልጠና ከመስጠት ጋር
በተያያዘ፣ እንዲሁም ለኢንዱስትሪው ሰራተኞች የአጭር ጊዜና የረጅም
ጊዜ ስልጠና ማዘጋጀትና መተግበርን የሚሸፍን መሆኑን በቆዳ
ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስርና
የቴክኖሎጂ ሽግግር ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ለዓለም ዳኛቸው
አስረድተዋል፡፡
በየዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር የሥራ
ክፍሎች በአደረጃጀት፣ በበጀት፣ በሰው ኃይል፣ በሎጂስቲክ የተሟሉ
አለመሆን፤ በትስስሩ የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች እና የማማከር
ሥራዎች ተገቢውን ትኩረት አለማግኘታቸውና ለምርምር፣ ለማማከር
እና ለአቅም ግንባታ ሥልጠና የሚከፈለው የማበረታቻ ክፍያ በጥናት
መሠረት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑ፤ ከማበረታቻ ጋር በተያያዘ
ዩኒቨርስቲዎች የግል ኢንዱስትሪዎች ላይ ምርምር ማድረግ ላይ ፍላጎት
ማጣት)፤ ኢንዱስትሪዎች የተማሪን ቅበላ እንደወጪ ብቻ እንዲያዩት
ማድረጉ፤ በኢንዱስትሪውና በዩኒቨርስቲ መካከል ጠንካራ በተግባር
የተደገፈ መተማመን እንዲፈጠር አስቀድሞ እና ተከታታይነት ያለው
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች አለመሰራመስራት፤ ሲሚናሮችን
በየወቅቱ በማዘጋጀት በዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር የተጀመሩ
ምርምርና ጥናቶችን የመከታተል፣ የመገምገም እና የተሸሉ
ተሞክሮችን የማስፋፋት ስራዎችን በጋራ ለመስራት ምቹ ሁኔታዎች
አለመኖር፤ በዘርፉ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስርን፤ የምርምር እና
ስርጸት ስራዎችን በተመለከተ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚስተሳሰር
አሰራር አለመኖር በኢንዱስትሪ ዩኒቨርስቲ ትስስር ትግበራ ሂደት
የሚታዩ ክፍተቶች መሆናቸውን አቶ ለዓለም ዳኛቸው አስረድተዋል፡፡
ከፊርማ ሥነሥርዓቱ በኋላም በዶክተር በለጠ ሥራህብዙ የሚመራ
አምስት አባላት ያሉት የትስስር ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴውም
ማንኛውንም በኢንዱስትሪውና በትምህርት ተቋማቱ መካከል
የሚኖረውን ተግባራዊ ሂደት በመመርያው መሠረት ለመምራት
እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት
ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ሁሴን በቀጣይ በተግባራዊ
ሂደት ውስጥ ለሚከሰቱ ችግሮች ኢኒስቲትዩቱ የማማከርና መፍትሄ
በመስጠት ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር በቅርበት
እንደሚሰራም አስረድተዋል፡፡
15
16
በገነት ደምሴ
የቆዳ ኢንደስትሪ ዘርፍን የተወዳዳሪነት አቅም ለማጎልበትና
እድገቱን በዘላቂነት ለማስቀጠል በኢትዮጵያ የቆዳ ልማት
ኢንደስትሪ ኢኒስቲትዩትና በህንድ ማዕከላዊ የቆዳ
ምርምርና የጫማ ዲዛይን ልማት ኢኒስቲትዩቶች መካከል
በተደረገ የፕሮጀክት ስምምነት መሰረት እስከአሁን
የተከናወኑ ተግባራትና መሰናክሎቻቸው እንደሁም
መሰናክሎቹን ለማስወገድ የተወሰዱ አርምጃዎች
ተገምግመዋል፡፡
ነሃሴ 7ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ጀምሮ
በኢኒስቲትዩቱ መለስተኛ አዳራሽ ውስጥ በህንዳውያኑ ዶ/
ር ሳራቫናንና ዶ/ር ማዳን በቀረበ ገለጻ በሁለቱ ሀገራት
ስምምነት በተነደፈ ፕሮጀክት አማካኝነት የተከናወኑ
ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ የቆዳ ልማት ኢኒስቲትዩትና የህንዱ ማዕከላዊ
የቆዳ ምርምር ኢኒስቲትዩትና የጫማ ዲዛይን ልማት
ኢኒስቲትዩት በጋራ መስራት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ
በርካታ የአቅም ግንባታ፣ የሰው ኃይል ልማት፣ የመዋቅር
ማሻሻያና የአካባቢ ጥበቃ ፕሮጀክት ስራዎች
እንደተከናወኑ ይታወሳል፡፡
የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዓለማ የሃገሪቱን የቆዳ ኢንደስትሪ
ልማትና እድገት በዘላቂነት ማስቀጠል የሚያስችል የአቅም
ግንባታና የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራትም ባሻገር
ሌሎች ሃገራት በዚህ ዘርፍ የደረሱበት ደረጃ ለማድረስ
የሚያስችል ፕሮጀክት ነው፡፡ በዚህ መሠረት በሃገር ውሰጥ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢኒስቲትዩት በዲግሪ ፕሮግራም ትምህርት እየተሰጠ
ሲሆን በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ ደረጃ በህንድ አገር
በሚገኙ አጋር ተቋማት ሲሰጥ መቆየቱም ታውቋል፡፡
የኢኒስቲቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ ለገሰ በመግቢያ
ንግግራቸው እንደገለጹት በሁለት ዙር በቁርኝት መርሃ
ግብሩ የተከናወኑ ተግባራት በሁለቱ ሃገራት እስካሁን
በጋራ የተወሰዱ እርምጃዎች በመልካም የሚታዩ መሆኑን
በመግለጽ ፕሮጀክቱን ለማስቀጠል የሚቻለው መሻሻል
የሚገባቸውን ተግባራት ማሻሻል ስንችል ብቻ ነው ሲሉ
ተናግረዋል፡፡
የኢኒስቲቲዩቱ ልዩ ልዩ የስራ ሃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላትና
ሠራተኞች በግምገማው የተገኙ ሲሆን፣በፕሮጀክቱ ሂደት
የታዩ መልካም ተግባራትን በማጠናከር ችግሮቹን
በመለየት ለዘለቄታው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ
መስራት ይገባናል ሲሉ ተሳታፊዎች አስተያየት
ሰጥተዋል፡፡
ቴክኖሎጂን ማዘመን አቅምን መገንባት የቁርኝት
ቀጣይ ሥራ
16
17
የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እና ለዘርፉ ማሻሻል የኢንስቲትዩቱ
ሚና
በብርሃኑ ሥርጀቦ
ኢትዮጵያ በበርካታ የተፈጥሮ በረከቶች
የተቸረች አገር ነች፡፡ ከየትም አገር በተሻለ
ያላት የአየር፣ የአፈር፣ የወንዞች፣
የእንስሳት፣ የአእዋፋት፣ ወዘተ የተፈጥሮ
ሀብቶቿ እና ጥንታዊ ቅርሶቿ በዓለም
እንድትታወቅ አድርጓታል፡፡ ከእነዚህ
የተፈጥሮ ሀብቶቿ ውስጥ የእንስሳት
ሀብት አንዱ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ሲገለጽ
እንደቆየው ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት ሀብት
ከአፍሪካ ግንባር ቀደም ስትሆን በዓለምም
ከአሥሮቹ ግንባር ቀደም አገሮች አንዷ ነች፡፡
በአገራችን ከጥንት ጀምሮ ሰዎች ሀገሪቷ
ያላትን የተፈጥሮ ሀብቶች በመጠቀም
የተለያዩ ለሰው ልጆች ኑሮ የሚያገለግሉ
ቁሳቁሶች እየሠሩ ሲገለገሉባቸው እንደቆዩ
ይነገራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በተለይ ሰዎች
የእንስሳትን ቆዳና ሌጦን በባህላዊ ዘዴ
እያለፉና እያለሰለሱ ለአልባሳት፣ ለመጫሚያ፣
ለምንጣፍ፣ ለእህል ማሰገቢያ፣ ለጠፍር እና
ሌሎች የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች
መስሪያነት ሲጠቀሙ ቆይተዋል፡፡
እንደማንኛውም አለም ከጥንታዊ የጋርዮሽ
ስርአት ጀምሮ የነበረውና እያደገ የመጣው
ባህላዊው የቆዳ ማልፋትና ማለስለስ ሥራ
በሀገራችን ከ1920ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ
በዘመናዊ መልክ ቆዳ የማልፋትና የማለስለስ
እስከጫማ ማምረት ተጀመረ፡፡ በቆዳና ሌጦ
እሴት ሲጨመር የሚመረተው ምርት ዓይነት
ስለሚጨምር ጠቀሜታውም እየጨመረ
ይሄዳል፡፡ በተለይ ለዜጎች የሚፈጠረው የሥራ
ዕድል በጣም ይጨምራል፡፡
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ኢትዮጵያ
በእንስሳት ሀብት ግንባር ቀደም ከሆኑ አገሮች
አንዷ ብትሆንም ከቆዳ ሀብቷ የምታገኘው
ጠቀሜታ ካላት የእንስሳት ሀብቷ ጋር
የሚመጣጠን አይደለም፡፡ ለዘርፉ ፋብሪካዎች
የሚቀርበው ጥሬ ቆዳና ሌጦ የጥራት ጉድለት
ያለበት ከመሆኑም በላይ የጥራት ጉድለቱን
በቴክኖሎጂ ለማሻሻል የሚያስችል እውቀት
ገና በበቂ ሁኔታ አልዳበረም፡፡ ባለው የጥራት
ደረጃ ልክ የምርት ስብጥር በማብዛት የተለያዩ
የገበያ መዳረሻዎችን ያለማስፋት
ውስንነቶችም በዘርፉ ፋብሪካዎች ዘንድ
ይታይል፡፡ በእነዚህና በሌሎች መሰል ችግሮች
ምክንያት ከዘርፉ መገኘት ያለበት የውጭ
ምንዛሪ ገቢ አልተገኘም፡፡ ለዜጎችም
የሚጠበቀውን ያህል የሥራ ዕድል
አልተፈጠረም፡፡
የሀገራችን የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለበት
ችግር ተወግዶ የዘርፉ ምርቶች በዓለም አቀፍ
ደረጃ ተወዳዳሪ በመሆን ለሀገሪቷ የኢኮኖሚ
ዕድገት የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍ እንዲል
የማድረግ ኃላፊነት የተሰጠው የቆዳ
ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከተቋቋመበት
ጊዜ ጀምሮ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት
የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት ጀምሮ
በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ዘርፉን
ተወዳዳሪ ለማድረግ የሳይንስና ቴክኖሎጂ
እውቀትን የሚጠይቅ በመሆኑ ኢንስቲትዩቱ
በሀገር ውስጥ ከሚገኙ ስድስት
ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከ42 ቴክኒክና ሙያ
ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች እና በውጭ አገር
ከሚገኙ ሁለት የምርምር ተቋማት ጋር
በመተባበር በዘርፉ ሙያዎች ከደረጃ አንድ
እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ባለሙያዎችን በማፍራት
ላይ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ የተለያዩ ችግር
ፈች ምርምሮችና ምርት ልማት ሥራዎችን
በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ለዘርፉ ፋብሪካዎች
የምርቶች ደረጃ፣ የምርት ጥራት ፍተሻ፣
የምክርና የቴክኒክ አገልግሎት ድጋፎች
እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡
ለዜጎች በርካታ የሥራ ዕድል ለመፍጠር
በዕቅድ ተይዞ ከኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር
በመነጋገር ፋብሪካዎቻቸውን በማስፋፋት
ተጨማሪ የሥራ እድል እንዲፈጥሩ
ከሚደረገው በተጨማሪ ከተለያዩ የልማት
አጋሮች ጋር በመሆኑ ለሥራ አጥ ዜጎች ስልጠና
በመስጠት በሰለጠኑበት ሙያ በፋብሪካዎች
የመቀጠር እድል እንዲያገኙ ወይም
የራሳቸውን ሥራ ፈጥረው እንዲሠሩ
እየተደረገ ይገኛል፡፡ እስከአሁንም በርካታ ዜጎች
ሰልጥነው ሥራ ፈጣሪ በመሆን ከራሳቸው
አልፈው ለሌሎች ሥራ አጦች የሥራ እድል
ፈጥረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ከአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና
ኤጀንሲ እና ፒፕል ኢን ኒድ ከተባለው ግብረ-
ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከአራት ክፍለ
ከተሞች ለተውጣጡ 478 ወጣቶች በጄነራል
ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ፣
በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ እና በምስራቅ
ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአጭር ጊዜ ስልጠና
እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ስልጠናውን ከሁሉም ክፍለ ከተሞች
ለተውጣጡ ወጣቶች የሚቀጥል መሆኑን
የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት
የቴክኖሎጂ ሽግግርና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክተር አቶ ደነቦ መኩሪያ ገልፀዋል፡፡ በዚህ
ዙር ወጣቶቹ እየተሰጣቸው የሚገኘው
ስልጠና በቆዳ አልባሳት፣ በጫማ እና በቆዳ
እቃዎች የስራ ዘርፎች በቆረጣና በስፌት
ሙያዎች ላይ እንደሆነ ዳይሬክተሩ አክለው
ገልፀዋል፡፡ ስልጠናውን እየወሰዱ የሚገኙት
ወጣቶች ስልጠናውን እንደጨረሱ በሁሉም
የቆዳና የጫማ ፋብሪካዎች ተቀጥረው
የሚሰሩ በመሆኑ ለወጣቶቹ የስራ እድል
ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው
ከመሆኑም በላይ ለኢንዱስትሪዎቹ የሰለጠነ
የሰው ሀይል እንዲያገኙ
ያስችላቸዋል፡፡ 17
18
“በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ ሩቅ ለመሄድ ከፈለክ አብረን እንሂድ ”
በገነት ደምሴ
በቆዳው ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በምርምር ለመፍታት፣ ተማሪዎች ብቃት ኖሯቸው በተግባር ልምምድ ራሳቸውን
አጎልብተው ኢንደስትሪውን እንዲያሳድጉ፣ በኢንደስትሪው ባለቤቶችም የምርት ጥራታቸውን እንዲያሻሽሉና በቴክኖሎጂ
የተደገፈና በጥናት ላይ የተመሠረተ ችግሮችን የመፍታት ሂደት እንዲኖርና በእድገቱም የጋራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ለማድረግ፣ በሁለቱ መካከል የሚመሰረተው ትስስር አስፈላጊነቱ ታምኖበት የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንደስትሪ ኢኒስቲትዩት
መድረኩን በማመቻቸት ሃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡
የኢንዱስትሪውን ችግሮች በምርት ጥራት ላይ፣በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የዘርፉን ጠሬ ሃብት በዘላቂነት ለማቆየትና
የመሳሰሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ምክረ-ሃሳቦችን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን የተግባር ልምምድን
(internship)፣ በትስስሩ የሚከናወኑ የጋራ የምርምር ስራዎች፣የኢንዱስትሪዉ ባለሙያ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ሄዶ የተግባር
ሥልጠና ከመስጠት ጋር በተያያዘ፣ እንዲሁም ለኢንዱስትሪው ሠራተኞች የአጫጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ስልጠና
ማዘጋጀትና መተግበርን የሚሸፍኑ ይሆናሉ ተብሎ ይታመናል፡፡
የትስስሩ ማጠንጠኛ በማምረቻና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ያደጉ ሀገራት ቴክኖሎጂዎችን የማፈላለግ፣ የመምረጥ፣
የማላመድ እና የመጠቀም በሂደትም የማሻሻል ሀገራዊ አቅም መገንባት ላይ ያተኮረ መሆኑን በመረዳት፤ ቅንጅታዊ
አሠራሩ በጋራ መግባባት፣ በተደጋጋፊነት እና የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሠረተ መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ጉዳይ
ነው፡፡
ትስስሩ ሀብትን በጋራ በማቀናጀት የጋራ ስምምነት በተደረሰበትና አስቀድሞ በተለዩ ፍላጎቶች ላይ ተመስርቶ በተዘጋጀ
ዕቅድ ተግባራዊ እንደሚደረግ በመረዳት፤ ለኢንዱስትሪው ትርፋማነቱን እና ተወዳዳሪነቱን በማሳደግ፣ለትምህርትና
ሥልጠና እና ለምርምር ተቋማት ደግሞ ብቃትና ጥራት ያለው የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት እንዲሁም
የተመራማሪዎችን አቅም በማጎልበት ረገድ ለሁሉም ተዋናዮች የሚያበረክተውን ጠቀሜታ በጥልቀት በመገንዘብ፤ ነው፡፡
ምንም እንኳን ትስስሩ እውቀትን ለመለዋወጥ፣ የትምህርት ደረጃውን ለማሳደግና ልምድን ለማዳበር የሚያደርገው
አስተዋጽኦ ከፍተኛ ቢሆንም ትስስሩ ውስጥ የሚያጋጥሙ ክፍተቶችና ችግሮችም አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በተግባር የታዩና
በጥናት የተደረሰባቸው የሚከተሉት ናቸው፡፡
 በየዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር የሥራ ክፍሎች በአደረጃጀት፣ በበጀት፣ በሰው ኃይል፣
በሎጂስቲክ የተሟሉ አለመሆን፤
 በትስስሩ የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች እና የማማከር ሥራዎች ተገቢውን ትኩረት አለማግኘታቸውና ለምርምር፣
ለማማከር እና ለአቅም ግንባታ ሥልጠና የሚከፈለው የማበረታቻ ክፍያ በጥናታዊ መሠረት ላይ የተገነባ አለሞሆኑ፤
 ከማበረታቻ ጋር በተያያዘ ዩኒቨርስቲዎች የግል ኢንዱስትሪዎች ላይ ምርምር ማድረግ ላይ ፍላጎት ማጣት፤
 ኢንዱስትሪዎች የተማሪን ቅበላ እንደወጪ ብቻ እንዲያዩት ማድረጉ
 በኢንዱስትሪውና በዩኒቨርስቲ መካከል ጠንካራ በተግባር የተደገፈ መተማመን እንዲፈጠር አስቀድሞ እና
ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች አለመሰራት፤
 ሲሚናሮችን በየወቅቱ በማዘጋጀት በዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር የተጀመሩ ምርምርና ጥናቶችን የመከታተል፣
የመገምገም እና የተሻሉ ተሞክሮዎችን የማስፋፋት ስራዎችን በጋራ ለመስራት ምቹ ሁኔታዎች አለመኖር፤
 በዘርፉ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስርን፤ የምርምር እና ስርጸት ስራዎችን በተመለከተ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት
የሚያስተሳሰር አሰራር አለመኖር፤ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
18
19
የጋራ ስምምነት ሰነድ ዓላማዎች፡-
በስምምነት ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የሚካሔደው የትምህርት መርሐ-ግብር እና በዘርፉ
ኢንዱስትሪዎች ለመምህራንና ተማሪዎች የሚሰጠው የተግባር ሥልጠና ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲተገበር ለማስቻል፤
ኢንዱስትሪዎች የቆዳ ዉጤቶች ችግርን መነሻ አድርገው ከሚሰሩ የጋራ ምርምሮች ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ዝርዝር
ጉዳዮች አግባብነት ያለው ሥርዓት በማበጀት ውጤታማነቱን ለማሳደግ፤ የስምምነት ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና
ተቋማት መምህራንን /አሠልጣኞችን/ አቅም በመጠቀም በዘርፉ ለተሰማሩ የኢንዱስትሪ ዉጤቶች የሚሰጠውን
የማማከር አገልግሎት ሥርዓት ለማጎልበት፤ በትስስሩ ውስጥ የስምምነት ፈራሚዎቹን የጋራና የተናጠል ኃላፊነት እና
ተግባር በግልጽ በማመላከት ሚናቸውን የሚወጡበትን አግባብ ለማሳደግ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት እስከአሁን ድረስ ዬኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስርን በብሄራዊ ደረጃ
በማከናወን በወሎና አካባቢው የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን፣ በባህርዳርና በአካባቢው አንዲሁም ከኢኒስቲትዩቱ ጋር
መምህራን ቅርበት እንዲኖራቸው በማድረግ ረገድ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና በአካባቢው የሚገኙ
የቆዳ አልባሳትና ጫማ አምራች ኢንደስትሪዎችን አስተሳስሯል፡፡
ወደፊትም የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢኒስቲትዩትንና የአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩትን ከአካባቢው የቆዳ
ኢንዱስትሪዎች ጋር ለማስተሳሰር ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል፡፡
አንድ የጋራ ወጥ የሆነ አግባብ የሚፈጠርበት ወርክሾፕ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለማካሄድና የጋራ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት
እቅድ የተያዘ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡
በዚህ የትስስር ሂደት ውስጥ 16 የቆዳ ውጤት አምራች ፋብሪካዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፤ በተጨማሪም ሦስቱ ዩኒቨርሲቲዎች
የባህርዳር ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ወሎና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው፡፡
ከዩኒቨርሲቲዎች ሌላ በአዲስ አበባከተማ መስተዳድር ሥር የሚገኙ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ፣የተስፋ ቴክኒክና ሙያ
ኮሌጅ፣የልደታ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ፣አዲስ ከተማ ኢንደስትሪያል ኮሌጅና የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና
ቢሮ እንዲሁም የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኮርፖሬሽን የትስስሩ ፈራሚ አካላት ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩትና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት 16 የጫማ
ፋብሪካዎች፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮና የመስተዳድሩ የአነስተኛና መካከለኛ
ኢንተርፕራይዞች ልማት ኮርፖሬሽን መካከል የጋራ መግባቢያ የስምምነት ሰነድ ፊርማ ሥነሥርዓት ተካሂዷል፡፡
በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ ባለድርሻ አካላት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣና ተፈራርሞ ከመለያየት በዘለለ
ኢንዱስትሪዎችም ሠልጣኞች ሲመረቁ የስራ እድሉን የመስጠት፣ አሰልጣኞችም ብቃት ያላቸውን ዜጎች ማፍራትና
ኢንዱስትሪው ያለበትን ችግር የሚፈታ ጥናትና ምርምር ማካሄድ ተገቢ መሆኑን አውስተዋል፤ ለትስስሩም መተግበርያ
ይበጅ ዘንድ የድርጊት መርሃ ግብር በጋራ በማውጣት መንቀሳቀስ እንደሚገባ መተማመን ላይ መደረሱም ታውቋል፡፡
በትስስሩ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትም የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች፣ የጋራ ምርምር ሥራዎች፣ የማማከር
አገልግሎት፣የ (Internship and Externship) ሥራዎች ናቸው፡፡
19
20
 የስምምነት ፈራሚዎቹ በትምህርትና እና ተግባራዊ ሥልጠና ማዕቀፍ የሚሰሩ ጉዳዮችን በጋራ ይለያሉ፤
 ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት በትትስሩ ሥር ለሚገኙ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ሥልጠና ሰጪውና
ሥልጠና ተቀባዩ በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት የመጀመሪያ፣ የሁለተኛ ዲግሪ እና የአጫጭር ጊዜ ሥልጠና
እንዲሁም የትምህርት ዕድል በስምምነት ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት አሠራር እና በትምህርት
ሚኒስቴር የቅበላ መስፈርት መሠረት ይሰጣል፤
 የቆዳና ቆዳ ዉጤቶች ዘርፍ የስምምነት ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ሰልጣኞች የዘርፉ ኢንዱስትሪዎች
በየዓመቱ ተግባራዊ ስልጠና እንዲያገኙ ይደረጋል፤
 በተግባራዊ ሥልጠና ተሳታፊ ለሚሆኑ የዘርፉ የስምምነት ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ሰልጣኞች
የምግብ፣ የመጓጓዣ እና የኪስ ገንዘብ ወጪዎች እንደየአግባቡ በራሳቸው በት/ት ተቋማቱ የሚሸፈኑ ይሆናሉ፤
 ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የትምህርትና ሥልጠና መርሐ-ግብሮችን በመከለስ፣ በማሻሻል እና አዲስ
በመክፈት ሂደት ውስጥ የስምምነት ፈራሚ የዘርፉ ኢንዱስትሪዎችን እንደየአግባቡ ተሳታፊ ይደረጋሉ፤
 በተግባራዊ ሥልጠና ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉትን የመገልገያ መሳሪያዎች ጥፋትና ብልሽት ለመከላከል ሥራው
በአማካሪውና በአሠልጣኙ እገዛ የሚከናወን ይሆናል
የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ተግባርና ኃላፊነት፤
 በኢንስቲትዩቱ አደረጃጀት ቅንጅታዊ አሠራር በመፍጠር የኢንዱስትሪ ትስስር አንኳር ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ
አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
 የልማት ፕሮግራሞችንና በየዘርፋቸው ያለውን ኢንዱስትሪ የትስስሩ አካል እንዲሆኑ የመሪነት ሚና ይጫወታል፤
 ለብሔራዊና ቀጠናዊ የትስስር ፎረሙ ምስረታ እና ውጤታማ የተግበር እንቅስቃሴ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል፤
 በመደበኛና በአጫጭር ጊዜ ፕሮግራሞች የአሠልጣኞች ሥልጠና ይሰጣል፤ በሚያስፈልግበት ጊዜ የኢንስቲትዩቱን
ሞዴል ፋብሪካ /ወርክ-ሾፕ/ ለዘርፉ ትምህርትና ሥልጠና አገልግሎት እንዲውል ያደርጋል፤
 በትስስሩ ለሚከናወኑ የምርምር ሥራዎች ተመራማሪዎች የምርምር ፋሲሊቲዎችን የሚጠቀሙበትን ሁኔታ
ያመቻቻል፤ ተመራማሪ ባለሙያዎችን በመመደብም ድጋፍ ያደርጋል፤
የስምምነት ፈራሚዎቹ የጋራ ተግባርና ኃላፊነት፡-
 ትስስሩን በተጨባጭ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል የጋራ ዕቅድ በየበጀት ዓመቱ ማዘጋጀት፤
 የዕቅዱን አፈፃፀም በየወሩ ለሥራው በተመደቡ ባለሙያዎች ደረጃ በየሶስት ወሩ ደግሞ በበላይ አመራር ደረጃ
መገምገም፤
 የጋራ መግባቢያ የስምምነት ሰነዱን አተገባበር መከታተል፤ ለትስስሩ እንደ ተግዳሮት የሚነሱ ጉዳዮች ላይ በመምከር
የመፍትሔ አቅጣጫ መስጠት፤
 የተፈጠረውን ትስስር ተግባራዊ የሚያደርጉ አካላትን እና የጋራ አደረጃጀቶችን መሰየም (ምሳሌ፡- የትስስሩን
ሰብሳቢና ጸሐፊ፣ የጋራ ምርምር ቡድን፣ የምርምር ገምጋሚና አጽዳቂ ቴክኒካል ኮሚቴ ወዘተ)፤
 ከትስስሩ ጋር የተያያዙ የውይይት መድረኮችን እና ወርክሾፖችን በጋራ ማዘጋጀት፤
 ከብሔራዊም ሆነ ቀጠናዊ የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ የትስስር ፎረሞች በየጊዜው የሚሰጡ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ
ማድረግ፤
ስለ ትስስሩ እና በዚህ ማዕቀፍ በየደረጃው የሚገኙ ውጤቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ፤
ይህ የጋራ መግባቢያ የስምምነት ሰነድ ሁሉም የስምምነቱ ፈራሚዎች ተስማምተው ፊርማቸውን በዚህ ሰነድ ላይ
ካሰፈሩበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
20
21
በሰላማዊት ራያ
ኢትዮጵያ በቀንድ ከብቶች የታደለች ሀገር ስትሆን
የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪም ዘጠና ዓመታትን
አስቆጥሮአል፡፡ በ57,829,953 ከብቶች በአፍሪካ
አንደኛ በዓለም ስምንተኛ ፣ በ28,892,380 በጎች
በአፍሪካ ሶስተኛ በዓለም አስረኛ እና በ29,704,958
ፍየሎች በአፍሪካ ሶስተኛ በዓለም አስረኛ ደረጃ ላይ
ትገኛለች፡፡ ወደ ቆዳ ማልፊያ ከሚቀርቡት ቆዳ እና
ሌጦ 1.4 ሚሊየን የከብት ፣6.7 ሚሊየን
የፍየል፣13.2 ሚሊየን የበግ ነው፡፡ዘርፉ ካለው
ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር የቆዳ
ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ የቆዳና
ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ልማትና ሽግግርን
በማፋጠን ኢንዱስትሪዎቹ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና
ፈጣን ልማት እንዲያስመዘግቡ ማብቃትን ዓላማ
አድርጐ የተቋቋመ የምርምር ኢንስቲትዩት ነው፡፡
ኢንስቲትዩቱ የቆዳ ኢንዱስትሪን ዓለም አቀፍ
ተወዳዳሪ ለማድረግ የዘርፉ ኢንቨስትመንት
እንዲስፋፋ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ልማት
ዘርፍን የሚያግዙና ተወዳዳሪ የሚያደርጉ
የቴክኖሎጂ፣ የቴክኒክ፣ የግብይት፣ የሥራ አመራርና
ሌሎች እንደ አስፈላጊነቱ የሚያግዙ ተግባር ተኮር
ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት፣ የምርምርና ስርጸት፣
የምክርና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት የቆዳ ምርትና
ምርታማነትን ለማሳደግ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በመንግስት ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ማምረቻ
ኢንደስትሪ ዘርፍ አንዱ ነው፡፡በተለይም የኢትዮጵያ
በኣላት አከባበር ከእርድ ጋር ያላቸው ቁርኝት ጥብቅ
ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው
ለስጋው እንጂ ለቆዳው አይደለም በ2011 በጀት
ዓመት ከ133 ሚሊዮን ካሬ ጫማ ቆዳና ሌጦ
ማልፋትና በማለስለስ ያለቀለት ቆዳን ማምረት
የሚችሉ ከ32 በላይ የቆዳ ፋብሪካዎች ቢኖሩም
ለፋብሪካዎቹ የሚቀርቡት ቆዳና ሌጦዎች ቁጥር
በጣም አነስተኛ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ የጥራት
ችግር አለባቸው፡፡ በዚህም የተነሳ አገራችን ማግኘት
የሚገባትን ጥቀም በማግኘት ላይ አይደለችም፡፡
ይህም በተለይ በእርድ ወቅትና ከእርድ በኋላ
በሚፈጠር ሰው ሰራሽ ችግር የተነሳ እንደሆነ ጥናቶች
ይጠቁማሉ፡፡ ከዚህም በመነሳት በዕርድ ጊዜና ከእርድ
በኋላ ቆዳው በሚሰበሰብበት ወቅት በሰብሳቢዎች
መወሰድ የሚገባውን ጥንቃቄ ተግባራዊ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡ ቆዳ በቢላ ሳይበሳ፣ሳይቀደድ እና
ሳይተፈተፍ ያለምንም ሰው ሰራሽ እንከን መግፈፍ
በዕርድ ወቅት አንገት ከተቆረጠ ወይም ከተባረከ
በኋላ እንስሳውን መሬት ላይ አለመጎተት፤ዘመናዊ
ቄራዎች በሌሉባቸው አካባቢዎች በእንስሳት ዕርድ በቂ
ልምድና ሙያ ባላቸው ሰዎች እርድ ማካሄድ፤ከቆዳው
መወገድ ያለባቸውን እንደ ኮቴ፣ጆሮ እና የመሳሰሉትን
ማስወገድ፣ ሥጋን እና አጥንትን በቆዳው ላይ
አለመከትከት፣ በተቻለ ፍጥነት ጨው ቀብቶ
በአቅራቢያ ለሚገኙ ቆዳ ሰብሳቢዎች በሽያጭ
ማቅረብ፤ጨው ማግኘት ካልተቻለ ቆዳ እንዳይበሰብስ
ዘረጋግቶ አየር እንዲያገኝ በማድረግ ለቆዳ ሰብሳቢዎች
በሽያጭ ማቅረብ፣ ጨው ያልተቀባን ቆዳ የቆዳውን
40% ክብደት በሚመዝን ንፁህ ጨው በአግባቡ
ሁሉንም የቆዳ ክፍል መቀባት፤ጨው የተቀባውን ቆዳ
መደርደሪያ በርብራብ መልክ ከመሬት ከፍ ያለ ሆኖ
እንዲዘጋጅ በማድረግ ከቆዳው የሚወጣውን ደምና
ፈሳሽ የሚንጠፈጠፍበት ክፍተት ማዘጋጀት፤ጨው
የተቀባውን ቆዳ የውስጠኛው /የስጋውን ክፍል
በማገናኘት ቀዝቃዛና ነፋሻማ መጋዘን ውስጥ
ማስቀመጥ፣ ጨው የተቀባውን ቆዳ በመደርደሪያው
ላይ በደንቡ መሰረት ሲቀመጥ የድርድሩ ከፍታ
ከአንድ ሜትር እንዳይበልጥ መጠንቀቅ፣ ህብረተሰቡ
ለቆዳ የሚያደርገው ጥንቃቄ ከእንስሳት እርባታ እስከ
አለቀለት ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ግብይት ድረስ ባሉት
የግብይት ሰንሰለቶች፣ ቆዳ እንዳይባክን ሁሉም
የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንደሚጠበቅ የዘርፉ
ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ
ኢኒስቲትዩት ያሳስባል፡፡
********************************
ለሥጋ ብቻ ሳይሆን…
21
22
በገነት ደምሴ
የቆዳ ኢንደስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍን
ተወዳዳሪነት ለማሳደግና የውጭ ገበያውን ለመሳብ
ከተቋቋመበት 1991 ዓ.ም ጀምሮ በውስጡ በሚገኙ ልዩ ልዩ
የስራ ዘርፎች አማካኝነት ሥራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በኢንስቲትዩቱ ካሉት ዳይሬክቶሮቶች መካከል ለዛሬ
የኢኒስቲትዩቱን የምርምርና ፍተሻ ላብራቶሪ እንመለከታለን፡፡
በኢኒስቲትዩቱ ውስጥ ስለሚገኘው የላብራቶሪው አገልግሎትና
ተግዳሮቶቹ መረጃውን የሰጡን በዘርፉ የቡድን መሪና
የፊዚካልና መካኒካል ፍተሻ ኤክስፐርት ወ/ሮ አስቴር መካሻንና
የኬሚካልና ኢኒስትሩመንታል ላብራቶሪ ፍተሻ ኤክስፐርት
የቡድን መሪ የሆኑትን ወ/ሮ ሜሮን መንግስቱን አነጋግረን
የሰጡንን መልስ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንደስትሪ ኢኒስቲትዩት በስሩ ከሚገኙ14
ዳይሪክቶሬቶች መካከል አንዱ ሲሆን የላብራቶሪ ምርምርና
ፍተሻ ዳይሬክቶሬት የሚል ስያሜ የተሰጠው ነው፡፡ በዚህ
ዳይሬክቶሬት ሥር ደግሞ 4 የላብራቶሪ አገልግሎት የሚሰጡ
የስራ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የላብራቶሪ ክፍሎች
የመጀመርያው የአካላዊ (ፊዚካል) ፍተሻና ምርምር ላብራቶሪ፣
ሁለተኛው የኬሚካል ላብራቶሪ፣ ሦስተኛው የውጋጅ ውሃ /
West water/ ላብራቶሪና የመጨረሻው ከባቢያዊ ጤናን
ለማስጠበቅ የሚረዳው /Environmental Laboratory/
የሚባሉ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል ለዛሬ የፊዚካል፣ ኬሚካል
ፍተሻ ላብራቶሪ ክፍል ተግባራትን እንቃኛለን፡፡
በዚህ ክፍል አልባሳትን፣ ቆዳንና የጫማ ዓይነቶችን ኬሚካል
ሳይጠቀሙ ልዩ ልዩ ማሽኖችንና መሳርያዎችን ብቻ
በመጠቀምና በማንቀሳቀስ አካላዊ (ፊዚካል) የጥንካሬና
የጥራት ፍተሻ የሚካሄደበት ክፍል ነው፡፡ አንድ ቆዳ
ተለፍቶ፣ተቀልሞና ተቆርጦ ተሰፍቶና ልብስ፣ ጫማ፣ ወይም
ጓንት ሆኖ ከተሰራ በኋላ ጥቅም ላይ ከመዋሉ አስቀድሞ
ከሚፈለገው የጥራት ደረጃ ላይ መሆኑን ለማረጋገጥ ናሙናዎች
ተወስደው ምርመራ የሚደረግበት አገልግሎት ክፍል ነው፡፡
በዚህ ክፍል የላብራቶሪ ፍተሻ የሚደረገው አንድ ምርት
ያለቀለት ወይም ደግሞ ገና በመሰራት ሂደት ላይ እያለ ሊሆን
ይችላል፡፡ በላብራቶሪው ፍተሻ የሚደረግላቸው በቆዳ
ኢንደስትሪው ዘርፍ የተሰማሩትን ባለሃብቶች ምርት ብቻ
ሳይሆን ከሌሎች የጥናትና ምርምር ተቋማት፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና
ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን የሚላኩ ቁሳቁሶች ጭምር
ናቸው፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ተቋማትና ኢነዱስትሪዎች ፍተሻ
እንዲደረግላቸው ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዚ ተመጣጣኝ የሆነ
ክፍያ በማስከፈል እንደጥያቄያቸው ቅደም ተከተልና ትዕዛዝ
የላብራቶሪ ፍተሻው ይከናወናል፡፡
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ምርምር ለማድረግ
በሚፈልጉበት ጊዜ ሁሉ ምርምሩን ማካሄድ ይችላሉ፡፡ ነገርግን
ሁሉም ተቋማት በቅድምያ የሚፈልጉትን የምርመራ ወይም
ፍተሻ ዓይነትና ምርት በመጥቀስ በደብዳቤ ወይም በፋክስ
ኢኒስቲቲዩቱን መጠየቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በርካታ የፍተሻ ዓይነቶች አሉ፤ ከነዚህ የፍተሻ ዓይነቶች አንዱን
እንደምሳሌ ብንወስድ /ISO/ International standard or-
ganization (ዓለም አቀፍ አውቅና ሰጪ ተቋም)
የሚያስቀምጠው በአንድ ኢንደስትሪ ውስጥ የምርቱ የኬሚካል
መጠን፣ የጥንካሬና የተስማሚነት ደረጃ ወሰን በምርመራ
ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡
ተቋማት ፍተሻና ምርምር ከመጀመራቸውና ከውጤት በኋላም
የማማከር አገልግሎት ይሰጣቸዋል፡፡ ለምሳሌ አንድ የቆዳ
ፋብሪካ ምርቱን ከማስፈተሹ በፊት የምርቱን የትኛውን ክፍል
አካልና ኬሚካላዊ ይዘት አንደሚያስፈትሽ የማማከር ሥራ
ይሰራል ፡፡ ከፍተሻውም በኋላ በውጤቱ ላይ ምን መቀነስ ምን
መጨመር አንዳለባቸውና ሥራቸውን በምን መልኩ በጥራት
ማስቀጠል እንደሚችሉም ድጋፍ እንደሚሰጥ የላብራቶሪው
የቡድን መሪና የፊዚካልና ሜካኒካል ፍተሻ ኤክስፐርት የሆኑት
ወ/ሮ አስቴር መካሻ አስረድተዋል፡፡
በፍተሻው ወቅት በሚያመጡት ናሙና ላይ ችግር ካለ
በላብራቶሪው ንባብ ውጤት መሰረት ተቋሙ ወይም
ኢንደስትሪው ምርቱን እንዲያሻሽል ሪፖርት ይሰጣል፡፡ እንዴት
አድርጎ የምርቱን ወይም የምርምር ውጤቱን ማሻሻል
እንዳለበትም ይገልጻል፡፡ ከዚህም ሌላ እንደሶስተኛ ወገን የጥራት
ደረጃ እውቅና ሰርተፊኬት እንሰጣለን ብለዋል ወ/ሮ አስቴር፡፡
በኬሚካል ላብራቶሪ መረጃ የሰጡን ደግሞ ወ/ሮ ሜሮን
መንግስቱ ሲሆኑ እርሳቸው እንደገለጹት አንድ ያለቀለት ቆዳ
ወይም ምርት በተወሰነ ፓራ ሜትር እርቀት ውስጥ በውስጡ
የሚገኙ እንደክሮምየም፣ ፎርማል አልዲሃይድና ሌሎችም
ውህድ መጠን በተቋሙ ይፈተሻል፡፡ ይህን ፍተሻ ለማከናወንም
በዓለም አቀፍ ተቋማት የወጣውን ደረጃና የፍተሻ ዘዴ መሰረት
በማድረግ ነው፡፡
በዚህ የፍተሻ ዘዴ ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎች ውህዶች መጠን
በምንፈትሽበት ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው
መጠን በላይና በታች ሲሆን በላብራቶሪው ሪፖርት ማሳወቅያ
ቅጽ አማካኝነት ለአምራቾች ወይም ለመርምር ተቋማት
በማሳወቅ ወይም በሚሰጣቸው ውጤት መሰረት ማሻሻል
የሚችሉ ከሆነ ያሻሽላሉ መወገድ የሚገባውንም
ያስወግዳሉ፡፡
ዓለም አቀፍ እውቅናን ለማስቀጠል
22
23
ለምሳሌ በቆዳ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቆዳውን ለማልፋት
የሚጠቅም /Basic Chromium sulfate/ አለ ይህ ውህድ
በውስጡ የሚገኘው የክሮሞ ኦክሳይድ /Chromo Oxide/
መጠን በምርት ሂደት ውስጥ ይለካል፡፡ ቆዳው ውስጥ
የሚቀረው የክሮምየም መጠን ምን ያህል መሆን እንዳለበት
የተቀመጠ ዓለም ዓቀፍ ደረጃ አለ፡፡ በዚህ ዓለም አቀፍ ደረጃ
መሰረት ማንኛውም ለምርት የተዘጋጀ ቆዳ ከተቀመጠው
መስፈርት መጠን በላይ የክሮምየም መጠን ካለው በሪፖርት
የሚገለጽ ሲሆን ጥያቄዎቹ ወደ ኢንደስትሪያቸው ተመልሰውም
በማስተካከል መጠኑ እንዲቀንስ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
በቆዳ ኢንደስትሪ ውስጥ አንድ ልብስ፣ ጫማ፣ ወይም ቦርሳ
ለማምርት ዋናኛ ግበዓት የሆነውን ቆዳን ለማልፋት፣
ለማቅለምና ለማድረቅ የሚጨመሩ የኬሚካል ዓይነቶች አሉ፡፡
እነዚህ ኬሚካሎች በሰው ልጅ ጤና ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ
በተወሰነ ደረጃ መጠናቸው መቀነስ አለበት ለጤና ተስማሚ
በሆነ ፐርሰንት ላይ ሲደርሱ መፈተሽና ተለክተው ማረጋገጫ
ማግኘት አለባቸው፡፡ ይህ ፍተሻ ከተሰራ በኋላ ውጤቱን
ለጠያቂው በመስጠት እንዲያስተካክሉ ይደረጋል፡፡
ኢንደስትሪዎች የሚጠቀሙባቸው ኬሚካሎች ሁሉ ከቆዳው
ናሙና በመውሰድ ይለካሉ ማለት ነው፡፡
አልባሳት ለሰው ልጅ ተስማሚ በሆነ የሙቀት መጠን ውስጥ
በምን ያህል ፐርሰንት ኬሚካል መኖር እንዳለበት
የተቀመጠውን ዓለም አቀፍ ደረጃ ያልጠበቀ ምርት መመረት
የለበትም፡፡ ስለዚህም ምርቶች ከመመረታቸው በፊትና በምርት
ሂደት ውስጥ ፍተሻ ይደረግላቸዋል፡፡ ለምሳሌ በአንድ ቆዳ ላይ
በራሱ በተፈጥሮው የሚገኝ ስብ አለው፤ በማምረት ሂደት
ለማልፊያነት፣ ለማቅለምና ለማድረቅ ከሚጨመሩ ኬሚካሎች
ጋር ሲደመር የሚያስከትለው ችግር አለ፡፡ የዚህ የስብ መጠን
በዓለም አቀፍ ደረጃ በተቀመጠ መስፈርት መጠን (ደረጃ)
በቆዳው ውስጥ መኖር አለበት፡፡ የቆዳው ስብ መጠን
መብዛትም ማነስም የለበትም ተስማሚ የሚሆነው መጠኑ
በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሰላው ፐርሰንት ላይ ሲደርስ ትክክል
መሆኑ ይረጋገጣል፡፡ ይህን ማረጋገጫ ደግሞ ደንበኞች
እንዲፈተሸላቸው ሲጠይቁ ፍተሻውን በማካሄድ ውጤቱ
ይሰጣል፡፡
በይበልጥ ደግሞ ምርቶቻቸውን ወደውጭ የሚልኩ የንግድ
ድርጅቶች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የምርት ውጤት
ከሌላቸውና የኛን የምስክር ወረቀት ካላገኙ ተቀባይነት
ስለማይኖራቸው ምርቶቻቸውን አስፈትሸው የማረጋገጫ
ሰርተፊኬት መያዝ ግድ ይላቸዋል ብለዋል ወ/ሮ ሜሮን
መንግስቱ፡፡
ፋብሪካዎች በምርት ሂደት ውስጥ የሚያስወግዱት ቆሻሻ ፍሳሽ
አለ፡፡ ይህ ውጋጅ ቆሻሻ ውሃ ወደውጭ ሲለቀቅ በሰው፣
በእንሰሳት፣ በዕጽዋትና በአካባቢ ላይ የሚያስከትለው ብክለት
ሊኖር ይችላል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ውጋጅ ቆሻሻ ደግሞ ችግር
ከማስከተሉ በፊት በላብራቶሪ ውስጥ ይፈተሻል፡፡ በዚህ /west
water laboratory/ አማካኝነት አካባቢያችን ከብክለት የጸዳ
ለማድረግ እንጠቀምበታለን፡፡
ፋብሪካዎችም ከምርት ፍሳሽ ውጋጅ የውሃ ናሙና ለሶስት ግዚ
ይዘው በመምጣት ያስፈትሻሉ፤ የመጀመርያው ምርቱን
ለማምረት በዝግጅትና በማልፋት ሂደት፣ሁለተኛ በማምረት
ሂደትና የመጨረሻው የማምረት ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ
በማስፈተሸ ውጤቱ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ተለክቶ
ይሰጣቸዋል፡፡ ውጤቱን መሰረት በማድረግ ማስተካከል
ይገባቸዋል ማለት ነው፡፡
ፍተሻው በዓለም አቀፉ የአካባቢ እንክብካቤ ተቋም ባወጣው
ደረጃና መስፈርት መሰረት የሚሰራ ነው፤ በዚህ ፍተሻ ወደ 16
የሚሆኑ የኬሚካል ዓይነቶች ይፈተሻሉ፡፡ አንድ ፋብሪካ
ከመመስረቱ በፊትም ሆነ በኋላ ድጋፎች ይሰጣሉ፡፡ ለምሳሌ
አንድ የቆዳ ፋብሪካ ላብራቶሪ እንዲኖረው ይደረጋል፤ ይህን
ላብራቶሪ በማቋቋም ድጋፍ ይሰጣቸዋል፡፡ ስለፋብሪካው
አጠቃላይ አወቃቀርና አመራረት ሂደት ድጋፍ የሚሰጡ የተለያዩ
ዳሬክቶሬቶችም አሉ፡፡
በላብራቶሪያችን ውስጥ ዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠላቸውም
ያልተቀመጠላቸውም የላብራቶሪ ፍተሻዎች ይከናወናሉ፡፡
ሆኖም ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመገናኘት
የተካሄደው የንጽጽር ፍተሻና ምርምር /Proficiency Test/
ዋጋ እንዲኖረው ወይም በሌሎች ተመሳሳይ ዓለም አቀፍ
ተቋማትም እንዲረጋገጥና ተመሳሳይ ውጤት እንዲገኝ
የሚደረግበት ሂደትም አለ፡፡
በላብራቶሪ ውጋጅ አወጋገድ ላይ ጥሩ ተሞክሮ ያላቸው
ፋብሪካዎች ውጤታቸው ለሌሎች ፋብሪካዎች ማስተማርያ
ይሆናል፡፡ በላብራቶሪ ውስጥ የሚካሄዱ ፍተሻዎች ሁሉ
እንደየዓይነታቸው፣ እንደሚወስዱት የግብዓት መጠንና ወጪ
ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ ለተቋሙ ይከፍላሉ፡፡
ለምሳሌ አንድን ቆዳ ወይም ምርት ለማቅለም ከሚጠቀሙበት
ኬሚካል አንዱ የአሮማቲክ አማይን መጠንን ለመፈተሽ በአንድ
ትንሽ ናሙና አስከ1,500 ይካፍላሉ፡፡ ይሁን እንጂ
እንደየፍተሻው ዓይነትና መጠን ክፍያው ይለያያል፡፡
እያንዳንዱ ተቋም የፍተሻ ውጤት ማረጋገጫ የሚሰጠው አንድ
ጊዜ ላመጣው ናሙና ብቻ እንጂ ውጤቱ ዘላቂ ማረጋገጫ
የሚሰጥበት ሁኔታ የለም፡፡ ለቀረበው ናሙና የሚሰጥ ውጤት
በመሆኑ ላልተፈተሸ ናሙና የኣንድ ጊዜ ፍተሻ ለሌላ ግዜ ምርት
ማረጋገጫ አይሆንም (አይሰራም)፡፡
ላብራቶሪያችን ደረጃቸውን በጠበቁ የኬሚካል ዓይነቶች፣
በፍተሻ መሳርያዎችና በእውቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት
የሚሰጥ በመሆኑ ዓለም አቀፍ እውቅና ያለውና ከፍተኛ ደረጃ
የተሰጠው ስለሆነ ይህን አስጠብቆ ለማቆየት ጥረት
በየጊዜው እየተደረገ አስተማማኝ ውጤት እየተገኘ
ነው፡፡ 23
24
ይህንንም ሁኔታ በየጊዜው ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ
የላብራቶሪ ባለሙያዎች መኖር ወሳኝ ነው፡፡ አንድ ባለሙያ
የሚሰራውን የፍተሻ ውጤት ከሌሎች ዓለም አቀፍ እውቅና ካገኙ
107 የውጭ ተቋማት ጋር በማነጻጸር /proficiency test/
ውጤቱን ስራውን መልሶ የሚያይበት የስራ ግንኙነትም አለ፡፡
አዳዲስ የምርምር ውጤቶችንም ለማሳወቅና ደረጃ እንዲሰጠው
ማድረግ የሚቻልበት አጋጣሚም ክፍት ነው፡፡ በዚህ ረገድ አንድ
ባለሙያ የሚጠቅምባቸው የላብራቶሪ መመርያዎች፣ ኬሚካሎች፣
መሳርያዎችና እውቀቱን ተጠቅሞ የሚያገኘውን ውጤት በትክክል
ከሌሎች ዓለም አቀፍ ላብራቶሪዎች ጋር አነጻጽሮ ውጤት
ሲያስቀምጥ ሂደቱን የሚከታተልና ትክክለኛነቱን የሚያረጋግጥ
ሌላ ባለሙያ በላብራቶሪው ውስጥ አለ፡፡ በቆዳ ኢንደስትሪ ዘርፍ
ብቻ ሳይሆን በሌሎች ምርቶችም ላይ የተሰማሩ ኢንደስትሪዎች፣
የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች የላብራቶሪውን አገልግሎት
የሚያገኙበት መንገድም ክፍት ነው፡፡
በአጠቃላይ ላብራቶሪው የናሙና ፍተሻ፣ የምርምር፣ እውቅና
የመስጠት፣ የድጋፍ፣ ዓለም አቀፍ ንጽጽርና የለውጥ ስራዎችን
እንሰራለን፡፡ ዓለም አቀፍ እውቅናችንን ዘላቂ ለማድረግ የላብራቶሪ
እቃዎችን፣ ሠራተኞችን መሳርያዎችንና ሌሎች ግበዓቶችን
በተገቢው መንገድ ጠብቆ ማቆየትና በየጊዜው ከሌሎች
ላብራቶሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የውስጥና የውጭ ኦዲት
ስራዎች አንዲከናወኑ እናደርጋለን፡፡
የተቋሙን የላብራቶሪ አገልግሎት የሚገዳደሩ ችግሮች
ፈጣን የደንበኛ አገልግሎትን በሚመለከት፡- ከአንድ ተቋም
ወይም ፋብሪካ ሊፈተሽ የመጣ የምርት ናሙና ፍተሻ
እስኪጠናቀቅና ውጤት እስኪደርሰው ድረስ ሌሎች ወረፋ ሊጠብቁ
ስለሚችሉና ጊዜም ስለሚወስድ ይህን ችግር ለመፍታት ተጨማሪ
የላብራቶሪ መፈተሻ መሳርያዎችና ኪሚካሎች ግዢ ጠይቀናል ይህ
ሲሟላ ችግሩ ይቀንሳል ውጤት የመስጠቱ ሥራም ይፋጠናል፡፡
ደረጃውን የጠበቀ ጥራት ያለው ኬሚካል አለማግኘት /
የኬሚካል ብራንድ/፡- በፋይናንስ፣ ግዢና ንብረት አስተዳደር
አሰራር መሰረት የኬሚካል ግዢ የሚከናወነው ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረቡ
ተቋማት መሆኑ እሙን ነው፡፡ በዝቅተኛ ዋጋ የሚገዙ ኬሚካሎች
ደግሞ የጥራት ደረጃቸው የወረደ የሚሆንበት አጋጣሚ ከፍተኛ
ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ በውጤታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ
የሚያሳድርና እውቅናንም የሚፈታተን ነው፡፡
በጨረታ የሚገዙ ኬሚካሎችን ጥራት ለማወቅ አስቸጋሪ ስለሆነና
በውጤት ላይ፣ በመሳሪያዎቻችንንና በእውቅናችን ላይ
የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የጨረታ ግዢ
እንዲቀርና በልዩ ፍቃድ የኬሚካል ግዢ የሚከናወንበት መንገድ
ከመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ተፈቅዶልናል፡፡
የመብራት መቆራረጥ፡- አሁን ያሉት ጄነረተሮች ተጠግነው ስራ
ላይ ቢውሉም ለላብራቶሪ አገልግሎት አስተማማኝ የማይሆኑበት
አጋጣሚ አለ፡፡ መብራት ሲጠፋ ጀኔረተሩ ስራ እስኪጀምር
በሚወስደው አስር ሰከንድ ውስጥ እንኳን በሰው ላይ ጉዳት፣
በመሳርያና በናሙናዎች ላይ ብልሽት ያጋጥማል፤ ይህ ደግሞ
ጊዜን፣ የሰው ኋይልን ያሳጣናል ከፍተኛ የግብዓት ወጪንም
ያስከትላል፤ ችግሩን ለማቃለል በርካታ UPS /Uninterrupted
power supply/ ቢገዙም በብልሽት ምክንያት የማይሰሩ
በመሆናቸውና በስራ ላይ ያሉትም በቂ ባለመሆናቸው ችግሩ
እንደቀጠለ ነው፡፡
የውሃ ጥራት ደረጃ፡- የቧንቧ ውሃ ፍሰት መቆራረጥ የላብራቶሪ
ስራ እንዲዘገይ ከማድረጉም በላይ በፍተሻ ሂደት ላይ ከፍተኛ
የጥራት ጉድለት ችግር ሆነው ከሚታዩ ጉዳዮች እንደዋንኛ ችግር
የሚወሰድ ነው፡፡ በክፍሉ በአብዛኛዎቹ የፍተሻ መስመሮች
የሚገኘው የጉርጓድ ውሃ በመሆኑ የጥራት ችግር አለው፤ የተጣራ
ንጹህ የቧንቧ ውሃ በጥቂት ቦታ ብቻ የሚገኝ በመሆኑ ለፍተሻ
ጥራት አንዱ ተግዳሮት ሆኖብናል፡፡
የማሽን ጥገና፡- በላብራቶሪው ውስጥ በርካታ ስራዎችን
ለመስራት የሚያስችሉ ማሽኖች ቢኖሩም ከኢኒስቲቲዩቱ ላብራቶሪ
ባለሙያዎች እውቀትና አቅም በላይ የሆኑና በሃገር አቀፍ ደረጃም
ሊሰሩ ሊጠገኑ የማይችሉ ማሽኖች ቦታ ይዘው መቀመጣቸው
ሌላው ችግር ነው፡፡ ይህን ችግር ለማቃለል ተብሎ ባለሙያዎች
ከውጭ እንዲመጡ ከዚህም ወደውጭ ሄደው እንዲሰለጥኑ
ቢደረግም በቂ ግን አልነበረም፡፡
/Calibration Machines/፡- አንድ ማሽን በስራ ላይ እያለ
በትክክል እየሰራ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ በሃገራችን
ስራዉን የሚያከናውነው ደግሞ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ተቋም /
NMIE/ (National Metrology Institute of Ethiopia) ነው፡፡
የሜትሮሎጂ ድርጅት አቅም ከኛ ላብራቶሪ ማሽኖች አንጻር ሲታይ
አቅሙ ውስን በመሆኑ ሁሉንም የኛን ማሽኖች የፍተሻ ውጤት
ማረጋገጥ የሚችል አይደለም:: የማረጋገጡ ስራ በተወሰነ ጊዜ
ውስጥ ካልተከናወነ ደረጃችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ አስጠብቀን
መሄድ አንችልም:: ይሄ ደግሞ እኛም ሆንን አምራቾች የምርት
ውጤታቸው ከደረጃ በታች እንዲሆን ስለሚያደርግ ለውጭ ገበያ
የምናቀርበውን ምርት ጥራት ይቀንሳል፤ ወይም ደግሞ ምርቱ
ውድቅ ይሆናል:: ይህ ደግሞ ፋብሪካውን ለኪሳራ የውጭ ምንዛሬ
ገቢን ይቀንሳል፡፡ ኪሳራው አገራዊ ነው፡፡ ዓለም አቀፍ እውቅናችንን
ለማስቀጠልም ካላብሬሽን አንዱ መስፈርት ነው፡፡
የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍልሰት፡- በአንድ ላብራቶሪ ውስጥ
የሚሰራ ባለሙያን ለማብቃት ከፍተኛ ወጪና ጊዜ የሚጠይቅ
ነው፡፡ ባለሙያዎች ለብቃታቸው የእውቅና የምስክር ወረቀት
ከዓለም አቀፍ አውቅና ሰጪ ተቋማት ካገኙ በኋላ ስለሚለቁ
እነርሱን ለመተካት የሚያስፈልገው የስልጠና ወጪ፣ ግዜና አቅም
ከፍተኛ በመሆኑ በዚህ ምክንያት የሚኖረው ችግር ከፍተኛ ነው፡፡
የላብራቶሪ ክፍሉ አደረጃጀት፡- የምንሰራበትና የማረፍያ ክፍል
ባለመለየቱ ምክንያት እዚሁ እናርፋለን፣ እንመገባለን፣ ማሽኖች
ሲንቀሳቀሱ፣ የኬሚካል ፍተሻ ሲከናወን የሚወጣው ጭስ፣ ፍሳሽ፣
የኬሚካል ትነት፣ ድምጽ ለሰራተኞች የጤና ችግር የሚያስከትል
መሆኑ እሙን ነው፡፡ በርካታ ኬሚካሎች የመተንፈሻ አካላትን
የሚጎዱ ናቸው፡፡ የኬሚካል ክፍሉና የውጤት መመዝገቢያው
የተጠጋጉና አየር ማስገቢያ ባለመኖሩ ለብክለት
ተጋልጠናል፤ ሲሉ ወ/ሮ ሜሮን መንግስቱ ሃሳባቸውን
አጠናቀዋል፡፡ 24
25
አውደ መዝናኛ
25
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen

More Related Content

Similar to #LIDI Ankelba 2011 magazen

ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ምጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
Tvet strategy training berhanu tadesse taye for students, leaders and commu...
Tvet strategy training berhanu tadesse taye for students,   leaders and commu...Tvet strategy training berhanu tadesse taye for students,   leaders and commu...
Tvet strategy training berhanu tadesse taye for students, leaders and commu...berhanu taye
 
Technical vocational education_(tvet)_institutional_establishment_and_other_p...
Technical vocational education_(tvet)_institutional_establishment_and_other_p...Technical vocational education_(tvet)_institutional_establishment_and_other_p...
Technical vocational education_(tvet)_institutional_establishment_and_other_p...berhanu taye
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007Ethiopian Sugar Corporation
 
City government of_addis_ababa_gullelle_sub-5
City government of_addis_ababa_gullelle_sub-5City government of_addis_ababa_gullelle_sub-5
City government of_addis_ababa_gullelle_sub-5berhanu taye
 
Tvet strategy presentation
Tvet strategy presentationTvet strategy presentation
Tvet strategy presentationberhanu taye
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008Ethiopian Sugar Corporation
 
National fishery and Aquatic Life Research Center 2011 Annual report
National fishery and Aquatic Life Research Center 2011 Annual reportNational fishery and Aquatic Life Research Center 2011 Annual report
National fishery and Aquatic Life Research Center 2011 Annual reportEyob Bezabeh
 
Training for students
Training for studentsTraining for students
Training for studentsberhanu taye
 
የማምረት አቅም አጠቃቀም አመላካቾች እና የአለካክ ስልቶች ማኑዋ EDITED by me.pptx
የማምረት አቅም አጠቃቀም አመላካቾች እና የአለካክ ስልቶች ማኑዋ EDITED by me.pptxየማምረት አቅም አጠቃቀም አመላካቾች እና የአለካክ ስልቶች ማኑዋ EDITED by me.pptx
የማምረት አቅም አጠቃቀም አመላካቾች እና የአለካክ ስልቶች ማኑዋ EDITED by me.pptxAssocaKazama
 
Berhanu.tadesse
Berhanu.tadesseBerhanu.tadesse
Berhanu.tadesseberhanu taye
 
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007Ethiopian Sugar Corporation
 
Trainig2 (4)
Trainig2 (4)Trainig2 (4)
Trainig2 (4)berhanu taye
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006Ethiopian Sugar Corporation
 

Similar to #LIDI Ankelba 2011 magazen (20)

ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ምጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
 
Tvet strategy training berhanu tadesse taye for students, leaders and commu...
Tvet strategy training berhanu tadesse taye for students,   leaders and commu...Tvet strategy training berhanu tadesse taye for students,   leaders and commu...
Tvet strategy training berhanu tadesse taye for students, leaders and commu...
 
Technical vocational education_(tvet)_institutional_establishment_and_other_p...
Technical vocational education_(tvet)_institutional_establishment_and_other_p...Technical vocational education_(tvet)_institutional_establishment_and_other_p...
Technical vocational education_(tvet)_institutional_establishment_and_other_p...
 
Ethiopian leather sector 2018 2019 focus
Ethiopian leather sector 2018 2019 focusEthiopian leather sector 2018 2019 focus
Ethiopian leather sector 2018 2019 focus
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
 
City government of_addis_ababa_gullelle_sub-5
City government of_addis_ababa_gullelle_sub-5City government of_addis_ababa_gullelle_sub-5
City government of_addis_ababa_gullelle_sub-5
 
Tvet strategy presentation
Tvet strategy presentationTvet strategy presentation
Tvet strategy presentation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
 
National fishery and Aquatic Life Research Center 2011 Annual report
National fishery and Aquatic Life Research Center 2011 Annual reportNational fishery and Aquatic Life Research Center 2011 Annual report
National fishery and Aquatic Life Research Center 2011 Annual report
 
Training for students
Training for studentsTraining for students
Training for students
 
የማምረት አቅም አጠቃቀም አመላካቾች እና የአለካክ ስልቶች ማኑዋ EDITED by me.pptx
የማምረት አቅም አጠቃቀም አመላካቾች እና የአለካክ ስልቶች ማኑዋ EDITED by me.pptxየማምረት አቅም አጠቃቀም አመላካቾች እና የአለካክ ስልቶች ማኑዋ EDITED by me.pptx
የማምረት አቅም አጠቃቀም አመላካቾች እና የአለካክ ስልቶች ማኑዋ EDITED by me.pptx
 
Berhanu.tadesse
Berhanu.tadesseBerhanu.tadesse
Berhanu.tadesse
 
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
 
Trainig2 (4)
Trainig2 (4)Trainig2 (4)
Trainig2 (4)
 
letter
letterletter
letter
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
 

#LIDI Ankelba 2011 magazen

  • 1. በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የግማሽ አመት መፅሔት ቅጽ 1 ቁጥር 15/2011 አንቀልባአንቀልባአንቀልባ LIDILIDILIDI Engineering TomorrowEngineering TomorrowEngineering Tomorrow
  • 2. 2 1.ዓላማ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች ቴክኖሎጂዎች ልማትና ሽግግርን በማፋጠን ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ፈጣን ልማት ኢንዲያስመዘግቡ ማብቃት 2.ራዕይ ኢንስቲትዩቱን ውጤታማ ተቋም በማድረግ በ2017 የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ በዓለም አቀፍ ያለውን የገበያ ድርሻ በ10 እጥፍ አድጎ ማየት 3.ተልዕኮ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪን ዘላቂና ፈጣን በሆነ መልኩ እንዲስፋፋ በማድረግ በኢንቨስትመንት፣ በምርትና በግብይት ለልማታዊ ባለሀብቱ ቀልጣፋ የቴክኖሎጂ፣ የማማከር አገልግሎትና ድጋፍ በመስጠት አገሪቷ ከቆዳ ሀብቷ ከፍተኛ ተጠቃሚ እንድትሆን ማድረግ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት
  • 3. 3 አንቀልባአንቀልባአንቀልባ AnkelbaAnkelbaAnkelba ማዉጫ የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት..................................4 የአዘጋጁ መልዕክት...............................................5 ዜና አንቀልባ........................................................6 የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እና ለዘርፉ ማሻሻል የኢንስቲትዩቱ ሚና................................17 በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ ሩቅ ለመሄድ ከፈለክ አብረን እንሂድ ” …………………….…….18 ለሥጋ ብቻ ሳይሆን… .......................................21 ዓለም አቀፍ እውቅናን ለማስቀጠል.....................22 መዝናኛ.............................................................25 ጤና...................................................................26 ፎቶ ማህደር ......................................................28 ዋና አዘጋጅ / Editor In chief/ አቶ ብርሃኑ ሥርጃቦ / Mr. Birhanu Serjabo/ አዘጋጆች /Editors/ ገነት ደምሴ /Genet Demis- se/ ወንድወሰን አሊሙሳ / Wondweson Ali Mussa ሠላማዊት ራያ /Selamawit Raya ብሩክ ዋጋዬ /Bruk Wagaye የካሜራ ባለሙያና ሌይ አዉት ዲዛይን/ Photographer, and lay- out Designer / ብሩክ ዋጋዬ /Bruk Wagaye/
  • 4. 4 የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ መሪነቱ አቅጣጫ እውን እንዲሆን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ጉልህ አሰተዋፅኦ እንዲያደርግ፣የኢንደስትሪውን የማምረት አቅም በማሳደግ፣ የምርት ጥራት ደረጃን በማሻሻል እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ የምርት ሂደትን በማጎልበት፣ አስተማማኝ የሆነ ሃገራዊ ኢንዱስትሪ በመገንባት ረገድ የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም ለማሳደግ በሚደረገው ጥረትም የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩታችን ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ሀገራችን ከኢንዱስትሪው ማግኘት የሚገባት ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ጠቀሜታ ከፍ እንዲል ነባር ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ጥራት ያለው ምርት የማምረትና ያመረቱትንም ምርት በሙሉ የመሸጥ አቅም ለመገንባት፣ አዳዲስ የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች በብዛት ወደዘርፉ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ እስከአሁን ከነበረው በተሻለ መንገድ ክትትል ለማድረግና ድጋፍ ለመስጠት በዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል፡፡ በዘርፉ የተሰማሩ ፋብሪካዎች ያሉባቸው ችግሮች ተቀርፈውላቸው ትኩረታቸውን የምርት ስብጥር በማብዛት፣ አዳዲስ የኤክስፖርት መዳሪሻዎችን በማስፋት፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢ በማሳደግ እና ለዜጎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል በመፍጠር ላይ እንዲያደርጉ የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንትና ሠራተኞች ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት፣ በትጋትና በቁርጠኝነት በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለበርካታ ዓመታት በማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አካባቢ ስለቆየሁ በቆዳ ኢንዱስትሪው ንዑስ ዘርፍ ለሚታዩ ችግሮችና ችግሮችን ለመፍታት ኢንስቲትዩቱ በተሻለ ቁመና ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠንቅቄ ስለማውቅ በተቻለ መጠን ችግሮችን በፍጥነት በማስወገድ ዘርፉን ወደ ተወዳዳሪነት ማምጣት እንደሚቻል አምናለሁ፡፡ ለዚህም በኢንስቲትዩቱ አሳሳቢ እየሆነ ያለው የባለሙያዎች ፍልሰት እንዲቀንስና ሠራተኞች በኢንስቲትዩቱ ተረጋግተው እንዲቆዩ ምቹ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ይገኛል፡፡ በመጨረሻም ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከዘርፉ ማህበራት፣ ከፋብሪካ ባለቤቶችና ባለሙያዎች፣ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የዘርፉን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማስወገድ በሁሉም አቅጣጫ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በማጠናከር በቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በከፍተኛ ትኩረት እየተሠራ መሆኑን እየገለጽሁ፣ ዕቅዳችን እንዲሳካ የዘርፉ ማኀበራትና ባለሀብቶች እና የሚመለከታችሁ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆናችሁ አካላት ከኢንስቲትዩቱ ጎን ሆናችሁ እንድታግዙን እጠይቃለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ 4
  • 5. 5 የአዘጋጁ መልዕክት የሀገራችን እንስሳት ቆዳና ሌጦ በተፈጥሮ የተለየ ባህሪ ያለው ቢሆንም በተፈጥሮና ሰው ሰልሽ ችግሮች ምክንያት ጥራቱ በጣም የወረደ በመሆኑ ሀገራችን ያላትን የእንስሳት ሀብት ያህል ከቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተጠቃሚ አይደለችም፡፡ እነዚህ ችግሮች እንስሳት በቁም እያሉ፣ በእርድ ስነ ስርዓት ወቅት እና ከእርድ በኋላ የሚከሰቱ ሲሆኑ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው ከሰሩ ሊቀንሱ የሚችሉ ናቸው፡፡ የኢፌዲሪ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የሰለጠነ የሰው ሀብት በማፍራት፣ በምርምርና ስርፀት፣ በምርት ልማትና ማማከር፣ በጥራት ፍተሻና የቴክኒክ ድጋፍ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፋብሪካዎች ምርቶቻቸውን በጥራትና በብዛት አምርተው ለዓለም ገበያ በማቀረብ ሀገራችን ከዘርፉ የምታገኘው ጠቀሜታ ከፍ እንዲል ለዘርፉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ የዘርፉን የሰለጠነ የሰው ሀብት ፍላጐት ለማሟላት በሀገር ውስጥ ከስድስት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ እና ከ42 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ጋር በመተባበር ከደረጃ 1 እስከ 4 በርካታ ባለሙያዎችን በማፍራት ላይ ይገኛል፡፡ በርካታ ችግር ፈች ምርምሮች፣ የምርት ልማት ሥራዎች፣ የጥራት ፍተሻ አገልግሎቶችና በሥራ ላይ ስልጠናዎችም እየተሰጡ ነው፡፡ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትም በኢንስቲትዩቱ የተከናወኑና የሚከናወኑ ተግባራትን እና የተገኙ ውጤቶች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ለሕብረተሰቡ ለማድረስ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በ2011 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትንም በዚህ አንቀልባ መጽሔታችን አካትተን አቅርበናል፡፡ ለምናደርገው መሻሻል የደንበኞቻችን አስተያየት የአንበሳውን ድርሻ ስለሚወስድ ለአስተያየታችሁ የተለመደ ትብብራችሁን እየጠየቅን መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ 5
  • 6. 6 ኢኒስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አገኘ የምስክር ወረቀቱ ለሁለተኛ ጊዜ የተሠጠው መሆኑም ታውቋል፡፡ በገነት ደምሴ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ለሁለተኛ ጊዜ ዓለም አቀፋዊ እውቅናና ከፍተኛ የጥራት ሾል አመራር ደረጃ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አገኘ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተዘጋጀ የሚሰጠውን የአይ.ኤስ.ኦ 9001፡2015 ከፍተኛየጥራት ደረጃ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያገኘዉ በየጀርመን የተስማሚነት ምዘና ተቋም ከሆነው የዲ. ኪው.ኤስ /DQS/ ጥራት ሼል አስኪያጅ አቶ አለማየሁ በለጠ ናቸዉ፡፡ የምስክር ወረቀቱ የኢትዮጵያን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት የሠው ኃይል ስምሪት፣ የሃብት አጠቃቀም፣ የደንበኛ እርካታን፣ የስጋት ጊዜ አመራርንና የላብራቶሪ አገልግሎትን በሚመለከት ዓለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟላ መሆኑን የሚያበስር እንደሆነ ታውቋል፡፡ አይ. ኤስ. ኦ. በዓለም ዙርያ የሚገኙ 20,000 ተቋማትን በአባልነት ያቀፈ ዓለም አቀፍ ተቋም ሲሆን፣ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ ተቋሟትን አገልግሎት አሰጣጥ በሚመለከት ፍተሻና የተስማሚነት ምዘና የሚያደርግና እውቅና የሚሰጥ ተቋም ነው፡፡ የምስክር ወረቀቱ የተሰጠዉ በአዲስ ዓመት በአንድነት ለዕድገት በትጋት ለመስራት የተቋሙ ሠራተኞች ቃል ለመግባት በቢሾፍቱ ከተማ በፒራሚድ ሆቴል ውስጥ በተዘጋጀው ሥነ ሥርዓት ላይ በታደሙበት ወቅት አንደነበረ ማወቅ ተችሏል፡፡ 6
  • 7. 7 የቻይና የቆዳ ኢንዱስትሪ ምርምር ኢንስቲትዩት ልዑካን ቡድን ጉብኝት… በወንድወሰን አሊ የቻይና የቆዳ ኢንዱስትሪ ምርምር ኢንስቲትዩት ልዑካን ቡድን አባላት ነሀሴ 8 ቀን 2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩቱ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ የጉብኝታቸው ዓላማም ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር የትብብር ግንኙነት ለመመስረት እንደሆነ ታውቋል፡፡ የልዑካኑ ቡድን በኢንስቲትዩቱ ማኔጀመንት አቀባበል ከተደረገለት በኋላ ኢንስቲትዩቱ አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለጻ ተደርጎለታል፣ በአፍሪካ ደረጃም በዘርፉ ስልጠና በመስጠት እውቅና በማግኘት፣ የጥራት ፍተሻ ማረጋገጫ ያገኘና ቆዳ በማልፋት ሂደት፣ በማስተዋወቅና በሌሎችም ተያያዥ ሥራዎች ስኬቶች ማግኝቱን ተናግረዋል፡፡ በቀረበው ገለጻ መሰረት የተለያዩ ጥያቄዎች ከልዑካን ቡድኑ የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ቻይና እና ኢትዮጵያ በቆዳው ዘርፍ ስላላቸው ጠንካራ ግንኙነት፣ በዘርፉ እየተተገበረ ስላለው ፖሊሲ፣ በቆዳ ፋብሪካዎች ስርጭት ኢንስቲትዩቱ ለቆዳ ፋብሪካዎች ስለሚሰጠው ድጋፍ፣ ስለአካባቢ ጥበቃ፣ ኢንቨስትመንት እና ሌሎች ጉዳዮችን የተመለከቱ እንደነበሩና በቂ መልስም እንደተሰጣቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡ 7
  • 8. 8 በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት የመቶ ቀናት እቅድ ላይ የኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንት አባላት፣ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማኀበር አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ህዳር 25 ቀን 2011 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ መሰብሰብያ አዳራሽ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ዕቅዱ በኢንስቱትዩቱ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይክተር በሆኑት አቶ ተስፋዬ ብርሃኑ ቀርቧል፡፡ ዳ ይ ሏ ክ ተ ሊ የ ነ ባ ር ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም እና የእሴት ጭማሪ አፈፃፀም ዝቅተኛ መሆን፤ የቆዳ ፋብሪካዎች አካባቢን የመበከል ችግር፤ ደካማ የ ኢ ን ቨ ሾ ት መ ን ት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና ዝቅተኛ የኢንቨስትመንት አቅም፤ ሀገራዊ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፈት የሚያስችል የተቀናጀ እንቅስቃሴ ያለመኖሩ፤ ዝቅተኛ የወጪ ንግድ አፈፃፀም፤ በቂና ውጤታማ ያልሆነ ተቋማዊ ድጋፍ፤ የድጋፍና ክትትል ውጤታማነት ችግር፤ የ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ፤ በመንግስት የተሰጠ አቅጣጫ፤ ደካማ ቅንጅታዊ አሰራር የዕቅዱ መነሻ ሁኔታዎች እንደሆኑ አቅርበዋል፡፡ የዕቅዱ ዓላማም የቆዳና ቆዳ ውጤቶች እንዱስትሪን የማምረት አቅም፣ የምርታማነትና የምርት ጥራት ደረጃ እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃና የእሴት ጭማሪ አቅም በየደረጃው በማጎልበት ቀጣይነት ላለው አስተማማኝ ሀገራዊ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ግብ ስኬት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የንዑስ ዘርፉን የውጭ ምንዛሪ ግኝት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅም ማሳደግ እንደሆነ ዳይሬክተሩ አክለው አስረድተዋል፡፡ የ ደ ጋ ፊ ተ ቋ ሙ ን ሁለንተናዊ የድጋፍ አቅም ማ ሳ ደ ግ ፤ ጥ ል ቱ የተጠበቀ የምርት ግብዓት በሚፈለገው ልክ እንዲቀርብ ማድረግ የ ኢ ን ዱ ሾ ት ሪ ው ን የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎ ት በአ ግባቡ ማሟላት፤ የቴክኖሎጂ ብቃትና የአሰራር ስርዓት ዓቅምን ማሳደግ፤ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የምርት መዳረሻ ገበያዎች እንዲስፋፉ ማድረግ፤ የውጭ ምንዛሬ፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም ሌሎች ማነቆዎች እንዲፈቱ ማድረግ ቅንጅታዊ አሰራርን ማሻሻል ፣ ተጨማሪ የኢንቨስትመንት አቅሞችን ወደ ሼል ማስገባት እና የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ አሰራርን ማጠናከር የአፈፃፀም አቅጣጫዎች እንደሆኑም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በመቶ ቀናት እቅድ ላይ ከዘርፉ ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ 8
  • 9. 9 በገነት ደምሴ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንደስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት በ2011 ትምህርት ዘመን ተመዝግበው ለመሰልጠን የተመረጡ ከሰላሳ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በቆይታቸው ማከናወን የሚገባቸውን ተግባራት አሳወቋል፡፡ በኢኒስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ስልጠና ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ለተማሪዎች በተዘጋጀው የቅበላ ፕሮግራም ላይ በ2011 ዓ.ም የትምህርትና የስልጠና ዘመን አዲስ ገቢ ተማሪዎች በኢኒስቲትዩቱ ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ የሚወስዷቸውን የስልጠና ዓይነቶችና የሚቸግራቸውን ለሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ መፍትሄ የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቸ መሆኑን የኢኒስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ሁሴን ተናግረዋል፡፡ በዚህ ዓመት ኢኒስቲትዩቱ በቴክኒክና ሙያ ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ 4 በቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በተከታታይ ለሚያሰለጥናቸው ተማሪዎች በሞዴል ፋብሪካዎች አማካኝነት የተግባር ትምህርት እንደሚወስዱም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ከመግለጻቸውም በተጨማሪ እንደደረጃቸውና እንደትምህርት አቀባበላቸው የቆይታ ግዜያቸውም እንደሚወሰን አቶ ዮናስ ተፈራ የኢኒስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ስልጠና የቡድን መሪ ለተማሪዎቹ ማብራርያ በመስጠት ተማሪዎች በቆይታቸው ሥለተቋሙ ማወቅ የሚገባቸውን ጉዳይ አስረድተዋል፡፡ በኢኒስቲትዩቱ የመሰብሰብያ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይ አሰልጣኝ መምህራን ከተማሪዎች ጋር እንዲተዋወቁ ሲደረግ፣ የመማርያ ክፍሎችን፣ ሞዴል የጫማ ፋብሪካ፤ሞዴል የቆዳ እቃዎችና አልባሳት ፋብሪካ፣ የቤተመጻህፍትና ሌሎች አገልግሎቶችን የሚያገኙባቸውን ቦታዎች ተማሪዎች ጎብኝተዋል፡፡ ኢነስቲትዩቱ ለትምህርት የተመዘገቡ ተማሪዎችን የእንኳን ደህና መጣችሁ ቅበላ አደረገ የኢትዮጵየ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር አመራሮች ዘርፉ አደጋ ላይ የወደቀ በመሆኑ የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችን ችግሮች ለመፍታት ኢንስቲትዩቱ ምን ዓይነት ድጋፍ እንደሚያደርግ፣ የቆዳ ዘርፉን አስመልክቶ መንግስት የነደፈው ፖሊሲ የአገር ውስጥ አምራቾችን ክፉኛ ስለጎዳው እንዲሻሻል፣ የፋይናንስ ድጋፍና የብድር አገልግሎት አሠሰጣጥ ችግር ያለበት ስለሆነ እነዚህ ችግሮች ተፈትተው ዘርፉ ከመውደቅ ሊታደግ ይገባል በማለት አስተያየት አቅርበዋል፡፡ ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ ፈለቀና ሌሎች የማኔጅመንት አባላት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በተለይ የዘርፉ ችግር የፖሊሲ ሳይሆን የፋብሪካዎች የሥራ አመራር ችግር በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው፣ ፋብሪካዎች የሚያቀርቡት ችግር በቁጥር የተደገፈ ወይም ገላጭ ሳይሆን በደፈናው የሚቀርብ በመሆኑ መፍትሔ ለመስጠት አስቸጋሪ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡ የፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግም ሆነ ሌሎች ድጋፎችን ለማድረግ የሚያስችል በእውቀትና በጥናት ላይ የተመሠረተ ትክክለኛ መረጃ መቅረብ ያለበት መሆኑንም ኃላፊዎቹ አስረድተዋል፡፡ ችግሩን ለመፍታትም የማህበሩ መሪዎችና ኢንስቲትዩቱ በጋራ የሚያከናውኑት መሆኑን በመተማመን በቀጣይ ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በሌላ በኩል ከኢንዱስትሪው የሚወጡ ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድን በሚመለከት ከአዲስ አበባ መስተዳድርና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር መልሶ በማልማት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግም የኢንስቲትዩቱ ሃላፊዎች አስረድተዋል፡፡ በመጨረሻም የማኀበሩ አመራሮች ዕቅዱ ሁሉንም አካትቶ የያዘና ጥሩ ዕቅድ መሆኑን በመግለጽ ለዕቅዱ ስኬታማነት የበኩላቸውን የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ገልፀዋል፡፡ 9
  • 10. 10 የቀድሞዉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በይፋ ተሸኙ በሽኝት መርሀ ግብሩ ላይ አዲሱ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ ፈለቀም አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ በብሩክ ዋጋዬ አቶ ወንዱ ለገሰ ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ በተቋሙ በባለሙያ ደረጃ ተቀጥረዉ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆኑ ኢንስቲትዩቱ ከቀድሞ መጠሪያዉ የቆዳና ቆዳ ዉጤቶች ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተለያዬ ተግባርና ሀላፊነቶችን አካትቶ ወደ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከተቀየረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 2011ዓ.ም ለስምንት ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ዉስጥ በተዘጋጀ ፕሮግራም አዲሱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ ፈለቀና የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት አሸኛኘት ሲደረግላቸው ለአዲሱ ዋና ዳይሬክተር ደግሞ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ለተቋሙ ያላቸዉን ክብር የገለፁ ሲሆን ለትምህርት ወደ ህንድ ሀገር ለመሄድ ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት የገጠማቸዉን አዝናኝ ገጠመኝና ትዝታ አውስተዋል፡፡ በትምህርትና ስልጠና፣በቁርኝት መርሀግብርና የተቋሙን አቅም በመገንባት፣ የቆዳዉ ዘርፍ ከፍተኛ የዉጭ ንግድ ገቢ እንዲያስመዘግብ፣ በምርምርና ፍተሻ ዙሪያ ከፍተኛ ተግባራት እንዳከናወኑና ምርምሮቹም በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ጭምር እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸዉን የስራ ባልደረቦቻቸዉና የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡ ከሀላፊነታቸው ለመልቀቅ የወሰኑበትን ምክንያት ሲገልጹም ሥራው በአዲስ ሃይል መተካት እንደሚኖርበት ስለአመንኩና ላሳካችዉ ያልቻልኩዋቸዉ ነገሮችን መስራት ወደምችልበትና በባለሙያ ደረጃ ከፍተኛ ለዉጥ ለማስመዝገብ በመፈለጌ ነዉ ብለዋል፡፡ ቀጣይ ለዘርፉ ምን አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ? ብለን ላቀረብንላቸዉ ጥያቄም ለዘርፉ አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ የሚችሉ መፅሀፍትን የዘርፉ ባለሙያዎች በቀላሉ ሊረዱት እንዲችሉ በአማርኛ ቋንቋ ለማዘጋጀት እንዳቀዱ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም አዲስ ከመጡት ዋና ዳይሬክተር ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
  • 11. 11 በኢጣልያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ክብርት ሚስስ ኢማኑዌላ ዲለር የሚመራ 17 ከፍተኛ ባለስልጣናትን የያዘ የልዑካን ቡድን ቅዳሜ ህዳር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ጉብኝት አድርጓል፡፡ ልኡካን ቡድኑ የኢፌዲሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዮሐንስ ድንቃየሁ እና የኢፌዲሪ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ ፈለቀ አቀባበል አድርገዉላቸዋል፡፡ በጣልያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ሚስስ ኢማኒዊላ ዲለር የሚመራው የልዑካን በድን በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ አቀባበል እንደተደረገለቸው የኢንስቲትዩቱን ሞዴል ቆዳ ፋብሪካና የቆዳ ምርምር ማዕከል፣ ሞዴል የቆዳ አልባሳትና ዕቃዎች ፋብሪካ፣ ሞዴል የጫማ ፋብሪካና የጫማ ምርምርና ምርት ልማት ማዕከል እና የምርምርና ፍተሻ ላቦራቶሪን ተዘዋውረዉ ከጎበኘ በኋላ ስለኢፌዲሪ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትና የሀገራችን ቆዳ ኢንዱስትሪ ታሪካዊ አመጣጥ እና ዘርፉን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ በመንግስት ስለተሰጠው ልዩ ትኩረት የኢንስቲትዩቱ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብርሃኑ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ የጣልያን መንግስት የልማት ትብብር ኤጀንሲ ከፍተኛ ድጋፍ እንዳደረገ ገልጸዋል፡፡ የሀገሪቱ የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆንም የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት በአገሪቱ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር 150 ተማሪዎችን በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ ደረጃ እያስለጠነ ሲሆን ከ42 በላይ ከሆኑ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሰልጠና ኮሌጆች ጋር በመተባበር ለበርካታ ተማሪዎች ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4 ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝም አቶ ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ ፈለቀ በበኩላቸው የኢጣሊያን መንግስት ለሀገራችን የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አመስግነው ወደፊትም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዮሐንስ ድንቃየሁ በበኩላቸው የኢትዮጵያና የጣሊያን ረጅም ዓመታት ያስቆጠረው ታሪካዊ ግንኙነት በሁሉም ረገድ የሁለቱም አገራት ጥቅም በሚያሳድግ መልኩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ አስረድተዋል፡፡ ክብርት የጣልያን ውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትሯ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነው በኢንስቲትዩቱ ባዩት የተሠሩ የምርምርና የምርት ልማት ሥራዎች መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ በጣሊያንና በኢትዮጵያ የቆየው የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ከሌሎች አገሮች በ ተ ለ የ ሁ ኔ ታ ተ ጠ ና ክ ሎ እንደሚቀጥልም በመግለጽ የጣልያን መንግሥት የኢትዮጵያን የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ በተሻለ ሁኔታ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር እና ሌሎች የጣሊያን መንግስት የኢኮኖሚ ትብብር ኤጀንሲና የዩኒዶ ባለሥልጣናትም የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ በጣልያን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር የሚመራ ቡድን የኢትዮጵያን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩትን ጎበኘ 11
  • 12. 12 ለካይዘን አማካሪዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ ስልጠናዉን የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ለኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎችና ከቆዳ ኢንዱስትሪ ለተወጣጡ ባለሙያዎች ሰጥቷል፡፡ በብሩክ ዋጋዬ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር የካይዘን አፈፃፀም ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተመስገን የሀገራችን ኢንዱስትሪ ሁኔታ በጥራትና ምርታማነት ላይ ያላደገ በመሆኑ ይህን ለማሳደግ አንዱ ትልቁ መሳሪያ ካይዘን በመሆኑ ስልጠናዉ እጂግ አስፈላጊ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በ2010 ዓ.ም አራት ለሚሆኑ የቆዳ ዘርፍ ፋብሪካዎች የካይዘን ስልጠናዉ መሰጠቱንና የተመዘገበዉ ዉጤትም ጥሩ በመሆኑ በዘንድሮዉ 2011 ዓ.ም ደግሞ ዘጠኝ ለሚሆኑ በቆዳዉ ዘርፍ ለተሰማሩ ፋብሪካዎች ይህንን ስልጠና መስጠት ማስፈለጉን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የለዉጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አንዳለ ዘለቀ ተናግረዋል፡፡ የስልጠናዉ ዓላማ ካይዘንን ሊያሰለጥኑ የሚችሉ አማካሪዎችን በቆዳዉ ዘርፍ ላይ ማፋራት የሚለወን የያዘ ሲሆን ስልጠናዉም የካይዘን ምንነት፣ ዘዴዎች እና ፍልስፈናዉ ምን ይላል የሚለዉን እንዲሁም የአሰለጣጠን ዘዴን ያካተተ መሆኑን የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት በቆዳ ኢንዱስትሪዎች የካይዘን ሽግግር እና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መስፍን ወንድሙ ተናግረዋል፡፡ የዚህ ስልጠና መዳረሻዉ ለቆዳ ፋብሪካዎች፣ ለጫማ ፋብሪካዎች፣ ለቆዳ አልባሳትና እቃ ፋብሪካዎች ለተከታታይ ስድስት ወራት በፋብሪካዎች ዉስጥ ቀጣይነት ያለዉ ስልጠና እንደሚሰጥ አስታወቀዉ አማካሪዎች ራሳቸዉን የሚያበቁበት እንዲሁም ኢንዱስትሪዎች ከዚህ የማማከር አገልግሎት ተጠቅመው የስራ አካባቢያቸዉን የሚያደራጁበት በይበልጥ ጥራት እና ምርታማነትን እንዲጨምሩ የሚያስችል ስልጠና መሆኑ ታውቋል፡፡ ስልጠናዉ ለአምስት የሥራ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በሁለቱ የእረፍት ቀናት ደግሞ መመዘኛ እንደሚሰጥ፣ እንዲሁም እጩ አማካሪዎች መመዘኛዉን ከ75 ፐርሰንት በላይ ሲያስመዘግቡ ብቻ አማካሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ስልጠናዉን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር በበላይነት የሚከታተለዉ ሲሆን በካይዘን ኢንስቲትዩት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ 12
  • 13. 13 በወንድዎሰን አሊ በቆዳና ጫማ ዘርፍ በህንድ አገር የ2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን አጠናቀው ለተመለሱ 13 ተማሪዎች ኢንስቲትዩቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አደረገ፡፡ ፕሮግራሙን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ ለገሰ የትምህርት እድሉን አግኝታችሁ ከነችግሩ በማለፍ ለዚህ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፤ በተጨማሪም ተማሪዎቹ ትምህርታችውን በሚከታተሉበት ወቅት ባሳዩት ብቃትና መልካም ስነ-ምግባር በኢንስቲዩቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ውጭ ተምረው ያመጡትን የትምሀርት ክህሎትና ልምድ ወደ አገራቸው በማባዛትና በመቀመር በሴክተሩ የሚታዩ ችግሮችን በመፍታት ሀላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡ በበጀት ዓመቱም ተማሪዎቹ የሲቪል ሰርቪሱን መመሪያ በተከተለ፣ አገልግሎታችውና የትምህርት ደረጃቸው በሚፈቅደው መሠረት ወደስራቸው የተመደቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ተማሪዎቹ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ የሰው ሀብቱን የአቅም ክፍተት ለመሙላት የውጭ አገር ስልጠና ለሰራተኞቹ መስጠቱን በማድነቅ የማኔጅመንቱ ጥረት የሚደነቅ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የምርምር ዘርፉ ከሌሎች የስራ ዘርፎች ጋር ተጣምረው እንዴት መሰራት እንዳሚችሉም ልምድ ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ህንድ አገር ተምረው ለተመለሱ ተማሪዎች የአንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደረገ 13
  • 14. 14 በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ሠራተኞች ነሃሴ 30 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገ የጉልበትና የገንዘብ ድጋፍ ጥገናው ተጀምሮ የነበረው የአረጋውያኑ ቤት ግንባታ ተጠናቆ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር በተገኙበት መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም ተመርቋል፡፡ ጥገናው ከመከናወኑ በፊት ከጥገና በኋላ በቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 5 ነዋሪ የሆኑት አቶ ከበደ ሞላና ወ/ሎ ሽታዬ ጥላሁን ተጠልለውበት የነበረ ቤት ከመውደቁ በፊት አዛውንቶቹን ለመደገፍ ከኢንስቲትዩቱ በተገኘ የቁሳቁስ ድጋፍና ከሠራተኛው በተዋጣ ገንዘብ ተጠግኖ በመስቀል ማግስት ከቀኑ 5፡30 እስከ 6፡30 በተካሄደ ፕሮግራም መላው የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች በተገኙበት ተመርቋል፡፡ በምረቃው ሥነስርዓት ላይም ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ወንዱ ለገሰ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ ር አብይ አህመድ በጀመሩት በፍቅር የመደመርና በይቅርታ የመሻገር መርህ መሰረት ሁላችንም ተሳትፈን ውጤት አሳይተናል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን በጎ ተግባር በማስቀጠል ሌሎችንም አረጋውያን መደገፍ ብቻም ሳይሆን አብረናቸው እንደምንሆን ብናሳያቸው ለበርካቶች ተስፋ እንሆናለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አረጋውያኑም በዕለቱ ለተደረገላቸው በጎ ሼል የተቋሙን ሠራተኞች በማመስገን በአዲስ ዓመት ከጎናቸው ሆነው በዓሉን በጋራ ተሰብሰበው እንደዚህ ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲያከብሩ ስላደረጉ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ይህን በጎ ሼል በቅን ልቦና በመነሳሳት የመሩትን የተቋሙን ሠራተኞች፣ የኮሚቴ አባላትና ሃላፊዎች አመስግነዋል፡፡ በተቋሙ ሠራተኞች የጉልበትና የገንዘብ ድጋፍ ተጀምሮ የነበረው የአረጋውያኑ ቤት ተመረቀ 14
  • 15. 15 የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር የስምምነት ሰነድ ተፈረመ ታህሣሥ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩትና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የመሀል ኢትዮጵያ የጫማና የቆዳ ዕቃዎች ልማት ትምህርት፣ ስልጠናና ምርምር ተቋማት እና ኢንዱስትሪ ትስስር ንዑስ ቀጠናዊ ፎረም መግባቢያ የስምምነት ሰነድ ፊርማ ሥነሥርዓት ተካሂዷል፡፡ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ በተካሄደው የትስስር ፎረም ምስረታ ስነስረዓት ከኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኮርፖሬሽን እና ከ16 የጫማ ፋብሪካዎች አመራሮች ተገኝተው የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡ በትምህርትና ሥልጠና፣ በምርምር ሥራዎችና የኢንዱስትሪ ተግባር ልመምድን በሚመለከት በተካሄደው የፊርማ ሥነስርዓት ላይ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ድባቦ የሱፍ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዘዳንት በመግባባት ላይ የተመሠረተ የጋራ የትምህርትና የኢንዱስትሪ ትስስር ቀጠናዊ ፎረም መመስረት በቆዳው ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በምርምር ለመፍታት፣ ተማሪዎች ብቃት ኖሯቸው በተግባር ልምምድ ራሳቸውን አጎልብተው ኢንደስትሪውን እንዲያሳድጉ፣ በኢንደስትሪው ባለቤቶችና በምርምር ተቋማት መካከል የሚመሰረተው ትስስር አስፈላጊነቱ ታምኖበት የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንደስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት መድረኩን በማመቻቸት ሃላፊነቱን ተወጥቷል ብለዋል፡፡ የኢንዱስትሪውን ችግር ከመፍታት አንጻር በትስስሩ የሚከናወኑ የጋራ የምርምር ስራዎችን፣ የኢንዱስትሪውን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ምክረ ሃሳቦችን፣ የተማሪዎችን የተግባር ልምምድን የዩኒቨርሲቲ መምህራን በኢንደስትሪ ውስጥ የተግባር ልምምድ ማድረግን፣ የጋራ የምክክር መድረክ አዘጋጅቶ ችግሮችን የመፍታት ስራዎችን፣ የኢንዱስትሪዉ ባለሙያ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ሄዶ የተግባር ስልጠና ከመስጠት ጋር በተያያዘ፣ እንዲሁም ለኢንዱስትሪው ሰራተኞች የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ስልጠና ማዘጋጀትና መተግበርን የሚሸፍን መሆኑን በቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ለዓለም ዳኛቸው አስረድተዋል፡፡ በየዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር የሥራ ክፍሎች በአደረጃጀት፣ በበጀት፣ በሰው ኃይል፣ በሎጂስቲክ የተሟሉ አለመሆን፤ በትስስሩ የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች እና የማማከር ሥራዎች ተገቢውን ትኩረት አለማግኘታቸውና ለምርምር፣ ለማማከር እና ለአቅም ግንባታ ሥልጠና የሚከፈለው የማበረታቻ ክፍያ በጥናት መሠረት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑ፤ ከማበረታቻ ጋር በተያያዘ ዩኒቨርስቲዎች የግል ኢንዱስትሪዎች ላይ ምርምር ማድረግ ላይ ፍላጎት ማጣት)፤ ኢንዱስትሪዎች የተማሪን ቅበላ እንደወጪ ብቻ እንዲያዩት ማድረጉ፤ በኢንዱስትሪውና በዩኒቨርስቲ መካከል ጠንካራ በተግባር የተደገፈ መተማመን እንዲፈጠር አስቀድሞ እና ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች አለመሰራመስራት፤ ሲሚናሮችን በየወቅቱ በማዘጋጀት በዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር የተጀመሩ ምርምርና ጥናቶችን የመከታተል፣ የመገምገም እና የተሸሉ ተሞክሮችን የማስፋፋት ስራዎችን በጋራ ለመስራት ምቹ ሁኔታዎች አለመኖር፤ በዘርፉ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስርን፤ የምርምር እና ስርጸት ስራዎችን በተመለከተ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚስተሳሰር አሰራር አለመኖር በኢንዱስትሪ ዩኒቨርስቲ ትስስር ትግበራ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶች መሆናቸውን አቶ ለዓለም ዳኛቸው አስረድተዋል፡፡ ከፊርማ ሥነሥርዓቱ በኋላም በዶክተር በለጠ ሥራህብዙ የሚመራ አምስት አባላት ያሉት የትስስር ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴውም ማንኛውንም በኢንዱስትሪውና በትምህርት ተቋማቱ መካከል የሚኖረውን ተግባራዊ ሂደት በመመርያው መሠረት ለመምራት እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ሁሴን በቀጣይ በተግባራዊ ሂደት ውስጥ ለሚከሰቱ ችግሮች ኢኒስቲትዩቱ የማማከርና መፍትሄ በመስጠት ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር በቅርበት እንደሚሰራም አስረድተዋል፡፡ 15
  • 16. 16 በገነት ደምሴ የቆዳ ኢንደስትሪ ዘርፍን የተወዳዳሪነት አቅም ለማጎልበትና እድገቱን በዘላቂነት ለማስቀጠል በኢትዮጵያ የቆዳ ልማት ኢንደስትሪ ኢኒስቲትዩትና በህንድ ማዕከላዊ የቆዳ ምርምርና የጫማ ዲዛይን ልማት ኢኒስቲትዩቶች መካከል በተደረገ የፕሮጀክት ስምምነት መሰረት እስከአሁን የተከናወኑ ተግባራትና መሰናክሎቻቸው እንደሁም መሰናክሎቹን ለማስወገድ የተወሰዱ አርምጃዎች ተገምግመዋል፡፡ ነሃሴ 7ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ጀምሮ በኢኒስቲትዩቱ መለስተኛ አዳራሽ ውስጥ በህንዳውያኑ ዶ/ ር ሳራቫናንና ዶ/ር ማዳን በቀረበ ገለጻ በሁለቱ ሀገራት ስምምነት በተነደፈ ፕሮጀክት አማካኝነት የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ የቆዳ ልማት ኢኒስቲትዩትና የህንዱ ማዕከላዊ የቆዳ ምርምር ኢኒስቲትዩትና የጫማ ዲዛይን ልማት ኢኒስቲትዩት በጋራ መስራት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የአቅም ግንባታ፣ የሰው ኃይል ልማት፣ የመዋቅር ማሻሻያና የአካባቢ ጥበቃ ፕሮጀክት ስራዎች እንደተከናወኑ ይታወሳል፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዓለማ የሃገሪቱን የቆዳ ኢንደስትሪ ልማትና እድገት በዘላቂነት ማስቀጠል የሚያስችል የአቅም ግንባታና የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራትም ባሻገር ሌሎች ሃገራት በዚህ ዘርፍ የደረሱበት ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል ፕሮጀክት ነው፡፡ በዚህ መሠረት በሃገር ውሰጥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት በዲግሪ ፕሮግራም ትምህርት እየተሰጠ ሲሆን በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ ደረጃ በህንድ አገር በሚገኙ አጋር ተቋማት ሲሰጥ መቆየቱም ታውቋል፡፡ የኢኒስቲቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ ለገሰ በመግቢያ ንግግራቸው እንደገለጹት በሁለት ዙር በቁርኝት መርሃ ግብሩ የተከናወኑ ተግባራት በሁለቱ ሃገራት እስካሁን በጋራ የተወሰዱ እርምጃዎች በመልካም የሚታዩ መሆኑን በመግለጽ ፕሮጀክቱን ለማስቀጠል የሚቻለው መሻሻል የሚገባቸውን ተግባራት ማሻሻል ስንችል ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የኢኒስቲቲዩቱ ልዩ ልዩ የስራ ሃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላትና ሠራተኞች በግምገማው የተገኙ ሲሆን፣በፕሮጀክቱ ሂደት የታዩ መልካም ተግባራትን በማጠናከር ችግሮቹን በመለየት ለዘለቄታው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት ይገባናል ሲሉ ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ቴክኖሎጂን ማዘመን አቅምን መገንባት የቁርኝት ቀጣይ ሼል 16
  • 17. 17 የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እና ለዘርፉ ማሻሻል የኢንስቲትዩቱ ሚና በብርሃኑ ሥርጀቦ ኢትዮጵያ በበርካታ የተፈጥሮ በረከቶች የተቸረች አገር ነች፡፡ ከየትም አገር በተሻለ ያላት የአየር፣ የአፈር፣ የወንዞች፣ የእንስሳት፣ የአእዋፋት፣ ወዘተ የተፈጥሮ ሀብቶቿ እና ጥንታዊ ቅርሶቿ በዓለም እንድትታወቅ አድርጓታል፡፡ ከእነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶቿ ውስጥ የእንስሳት ሀብት አንዱ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ሲገለጽ እንደቆየው ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት ሀብት ከአፍሪካ ግንባር ቀደም ስትሆን በዓለምም ከአሥሮቹ ግንባር ቀደም አገሮች አንዷ ነች፡፡ በአገራችን ከጥንት ጀምሮ ሰዎች ሀገሪቷ ያላትን የተፈጥሮ ሀብቶች በመጠቀም የተለያዩ ለሰው ልጆች ኑሮ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች እየሠሩ ሲገለገሉባቸው እንደቆዩ ይነገራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በተለይ ሰዎች የእንስሳትን ቆዳና ሌጦን በባህላዊ ዘዴ እያለፉና እያለሰለሱ ለአልባሳት፣ ለመጫሚያ፣ ለምንጣፍ፣ ለእህል ማሰገቢያ፣ ለጠፍር እና ሌሎች የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች መስሪያነት ሲጠቀሙ ቆይተዋል፡፡ እንደማንኛውም አለም ከጥንታዊ የጋርዮሽ ስርአት ጀምሮ የነበረውና እያደገ የመጣው ባህላዊው የቆዳ ማልፋትና ማለስለስ ሼል በሀገራችን ከ1920ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ በዘመናዊ መልክ ቆዳ የማልፋትና የማለስለስ እስከጫማ ማምረት ተጀመረ፡፡ በቆዳና ሌጦ እሴት ሲጨመር የሚመረተው ምርት ዓይነት ስለሚጨምር ጠቀሜታውም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ በተለይ ለዜጎች የሚፈጠረው የሥራ ዕድል በጣም ይጨምራል፡፡ ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ኢትዮጵያ በእንስሳት ሀብት ግንባር ቀደም ከሆኑ አገሮች አንዷ ብትሆንም ከቆዳ ሀብቷ የምታገኘው ጠቀሜታ ካላት የእንስሳት ሀብቷ ጋር የሚመጣጠን አይደለም፡፡ ለዘርፉ ፋብሪካዎች የሚቀርበው ጥሬ ቆዳና ሌጦ የጥራት ጉድለት ያለበት ከመሆኑም በላይ የጥራት ጉድለቱን በቴክኖሎጂ ለማሻሻል የሚያስችል እውቀት ገና በበቂ ሁኔታ አልዳበረም፡፡ ባለው የጥራት ደረጃ ልክ የምርት ስብጥር በማብዛት የተለያዩ የገበያ መዳረሻዎችን ያለማስፋት ውስንነቶችም በዘርፉ ፋብሪካዎች ዘንድ ይታይል፡፡ በእነዚህና በሌሎች መሰል ችግሮች ምክንያት ከዘርፉ መገኘት ያለበት የውጭ ምንዛሪ ገቢ አልተገኘም፡፡ ለዜጎችም የሚጠበቀውን ያህል የሥራ ዕድል አልተፈጠረም፡፡ የሀገራችን የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለበት ችግር ተወግዶ የዘርፉ ምርቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በመሆን ለሀገሪቷ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍ እንዲል የማድረግ ኃላፊነት የተሰጠው የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት ጀምሮ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እውቀትን የሚጠይቅ በመሆኑ ኢንስቲትዩቱ በሀገር ውስጥ ከሚገኙ ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከ42 ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች እና በውጭ አገር ከሚገኙ ሁለት የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር በዘርፉ ሙያዎች ከደረጃ አንድ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ባለሙያዎችን በማፍራት ላይ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ የተለያዩ ችግር ፈች ምርምሮችና ምርት ልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ለዘርፉ ፋብሪካዎች የምርቶች ደረጃ፣ የምርት ጥራት ፍተሻ፣ የምክርና የቴክኒክ አገልግሎት ድጋፎች እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡ ለዜጎች በርካታ የሥራ ዕድል ለመፍጠር በዕቅድ ተይዞ ከኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር በመነጋገር ፋብሪካዎቻቸውን በማስፋፋት ተጨማሪ የሥራ እድል እንዲፈጥሩ ከሚደረገው በተጨማሪ ከተለያዩ የልማት አጋሮች ጋር በመሆኑ ለሼል አጥ ዜጎች ስልጠና በመስጠት በሰለጠኑበት ሙያ በፋብሪካዎች የመቀጠር እድል እንዲያገኙ ወይም የራሳቸውን ሼል ፈጥረው እንዲሠሩ እየተደረገ ይገኛል፡፡ እስከአሁንም በርካታ ዜጎች ሰልጥነው ሼል ፈጣሪ በመሆን ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ሼል አጦች የሥራ እድል ፈጥረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ እና ፒፕል ኢን ኒድ ከተባለው ግብረ- ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከአራት ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ 478 ወጣቶች በጄነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ፣ በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ እና በምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአጭር ጊዜ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናውን ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ ወጣቶች የሚቀጥል መሆኑን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ሽግግርና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደነቦ መኩሪያ ገልፀዋል፡፡ በዚህ ዙር ወጣቶቹ እየተሰጣቸው የሚገኘው ስልጠና በቆዳ አልባሳት፣ በጫማ እና በቆዳ እቃዎች የስራ ዘርፎች በቆረጣና በስፌት ሙያዎች ላይ እንደሆነ ዳይሬክተሩ አክለው ገልፀዋል፡፡ ስልጠናውን እየወሰዱ የሚገኙት ወጣቶች ስልጠናውን እንደጨረሱ በሁሉም የቆዳና የጫማ ፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሰሩ በመሆኑ ለወጣቶቹ የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ከመሆኑም በላይ ለኢንዱስትሪዎቹ የሰለጠነ የሰው ሀይል እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡ 17
  • 18. 18 “በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ ሩቅ ለመሄድ ከፈለክ አብረን እንሂድ ” በገነት ደምሴ በቆዳው ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በምርምር ለመፍታት፣ ተማሪዎች ብቃት ኖሯቸው በተግባር ልምምድ ራሳቸውን አጎልብተው ኢንደስትሪውን እንዲያሳድጉ፣ በኢንደስትሪው ባለቤቶችም የምርት ጥራታቸውን እንዲያሻሽሉና በቴክኖሎጂ የተደገፈና በጥናት ላይ የተመሠረተ ችግሮችን የመፍታት ሂደት እንዲኖርና በእድገቱም የጋራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ፣ በሁለቱ መካከል የሚመሰረተው ትስስር አስፈላጊነቱ ታምኖበት የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንደስትሪ ኢኒስቲትዩት መድረኩን በማመቻቸት ሃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ የኢንዱስትሪውን ችግሮች በምርት ጥራት ላይ፣በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የዘርፉን ጠሬ ሃብት በዘላቂነት ለማቆየትና የመሳሰሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ምክረ-ሃሳቦችን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን የተግባር ልምምድን (internship)፣ በትስስሩ የሚከናወኑ የጋራ የምርምር ስራዎች፣የኢንዱስትሪዉ ባለሙያ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ሄዶ የተግባር ሥልጠና ከመስጠት ጋር በተያያዘ፣ እንዲሁም ለኢንዱስትሪው ሠራተኞች የአጫጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ስልጠና ማዘጋጀትና መተግበርን የሚሸፍኑ ይሆናሉ ተብሎ ይታመናል፡፡ የትስስሩ ማጠንጠኛ በማምረቻና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ያደጉ ሀገራት ቴክኖሎጂዎችን የማፈላለግ፣ የመምረጥ፣ የማላመድ እና የመጠቀም በሂደትም የማሻሻል ሀገራዊ አቅም መገንባት ላይ ያተኮረ መሆኑን በመረዳት፤ ቅንጅታዊ አሠራሩ በጋራ መግባባት፣ በተደጋጋፊነት እና የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሠረተ መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ትስስሩ ሀብትን በጋራ በማቀናጀት የጋራ ስምምነት በተደረሰበትና አስቀድሞ በተለዩ ፍላጎቶች ላይ ተመስርቶ በተዘጋጀ ዕቅድ ተግባራዊ እንደሚደረግ በመረዳት፤ ለኢንዱስትሪው ትርፋማነቱን እና ተወዳዳሪነቱን በማሳደግ፣ለትምህርትና ሥልጠና እና ለምርምር ተቋማት ደግሞ ብቃትና ጥራት ያለው የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት እንዲሁም የተመራማሪዎችን አቅም በማጎልበት ረገድ ለሁሉም ተዋናዮች የሚያበረክተውን ጠቀሜታ በጥልቀት በመገንዘብ፤ ነው፡፡ ምንም እንኳን ትስስሩ እውቀትን ለመለዋወጥ፣ የትምህርት ደረጃውን ለማሳደግና ልምድን ለማዳበር የሚያደርገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ቢሆንም ትስስሩ ውስጥ የሚያጋጥሙ ክፍተቶችና ችግሮችም አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በተግባር የታዩና በጥናት የተደረሰባቸው የሚከተሉት ናቸው፡፡  በየዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር የሥራ ክፍሎች በአደረጃጀት፣ በበጀት፣ በሰው ኃይል፣ በሎጂስቲክ የተሟሉ አለመሆን፤  በትስስሩ የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች እና የማማከር ሥራዎች ተገቢውን ትኩረት አለማግኘታቸውና ለምርምር፣ ለማማከር እና ለአቅም ግንባታ ሥልጠና የሚከፈለው የማበረታቻ ክፍያ በጥናታዊ መሠረት ላይ የተገነባ አለሞሆኑ፤  ከማበረታቻ ጋር በተያያዘ ዩኒቨርስቲዎች የግል ኢንዱስትሪዎች ላይ ምርምር ማድረግ ላይ ፍላጎት ማጣት፤  ኢንዱስትሪዎች የተማሪን ቅበላ እንደወጪ ብቻ እንዲያዩት ማድረጉ  በኢንዱስትሪውና በዩኒቨርስቲ መካከል ጠንካራ በተግባር የተደገፈ መተማመን እንዲፈጠር አስቀድሞ እና ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች አለመሰራት፤  ሲሚናሮችን በየወቅቱ በማዘጋጀት በዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር የተጀመሩ ምርምርና ጥናቶችን የመከታተል፣ የመገምገም እና የተሻሉ ተሞክሮዎችን የማስፋፋት ስራዎችን በጋራ ለመስራት ምቹ ሁኔታዎች አለመኖር፤  በዘርፉ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስርን፤ የምርምር እና ስርጸት ስራዎችን በተመለከተ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚያስተሳሰር አሰራር አለመኖር፤ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ 18
  • 19. 19 የጋራ ስምምነት ሰነድ ዓላማዎች፡- በስምምነት ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የሚካሔደው የትምህርት መርሐ-ግብር እና በዘርፉ ኢንዱስትሪዎች ለመምህራንና ተማሪዎች የሚሰጠው የተግባር ሥልጠና ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲተገበር ለማስቻል፤ ኢንዱስትሪዎች የቆዳ ዉጤቶች ችግርን መነሻ አድርገው ከሚሰሩ የጋራ ምርምሮች ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ዝርዝር ጉዳዮች አግባብነት ያለው ሥርዓት በማበጀት ውጤታማነቱን ለማሳደግ፤ የስምምነት ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት መምህራንን /አሠልጣኞችን/ አቅም በመጠቀም በዘርፉ ለተሰማሩ የኢንዱስትሪ ዉጤቶች የሚሰጠውን የማማከር አገልግሎት ሥርዓት ለማጎልበት፤ በትስስሩ ውስጥ የስምምነት ፈራሚዎቹን የጋራና የተናጠል ኃላፊነት እና ተግባር በግልጽ በማመላከት ሚናቸውን የሚወጡበትን አግባብ ለማሳደግ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት እስከአሁን ድረስ ዬኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስርን በብሄራዊ ደረጃ በማከናወን በወሎና አካባቢው የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን፣ በባህርዳርና በአካባቢው አንዲሁም ከኢኒስቲትዩቱ ጋር መምህራን ቅርበት እንዲኖራቸው በማድረግ ረገድ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና በአካባቢው የሚገኙ የቆዳ አልባሳትና ጫማ አምራች ኢንደስትሪዎችን አስተሳስሯል፡፡ ወደፊትም የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢኒስቲትዩትንና የአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩትን ከአካባቢው የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ጋር ለማስተሳሰር ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል፡፡ አንድ የጋራ ወጥ የሆነ አግባብ የሚፈጠርበት ወርክሾፕ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለማካሄድና የጋራ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እቅድ የተያዘ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡ በዚህ የትስስር ሂደት ውስጥ 16 የቆዳ ውጤት አምራች ፋብሪካዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፤ በተጨማሪም ሦስቱ ዩኒቨርሲቲዎች የባህርዳር ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ወሎና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው፡፡ ከዩኒቨርሲቲዎች ሌላ በአዲስ አበባከተማ መስተዳድር ሼር የሚገኙ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ፣የተስፋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ፣የልደታ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ፣አዲስ ከተማ ኢንደስትሪያል ኮሌጅና የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ እንዲሁም የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኮርፖሬሽን የትስስሩ ፈራሚ አካላት ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩትና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት 16 የጫማ ፋብሪካዎች፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮና የመስተዳድሩ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኮርፖሬሽን መካከል የጋራ መግባቢያ የስምምነት ሰነድ ፊርማ ሥነሥርዓት ተካሂዷል፡፡ በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ ባለድርሻ አካላት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣና ተፈራርሞ ከመለያየት በዘለለ ኢንዱስትሪዎችም ሠልጣኞች ሲመረቁ የስራ እድሉን የመስጠት፣ አሰልጣኞችም ብቃት ያላቸውን ዜጎች ማፍራትና ኢንዱስትሪው ያለበትን ችግር የሚፈታ ጥናትና ምርምር ማካሄድ ተገቢ መሆኑን አውስተዋል፤ ለትስስሩም መተግበርያ ይበጅ ዘንድ የድርጊት መርሃ ግብር በጋራ በማውጣት መንቀሳቀስ እንደሚገባ መተማመን ላይ መደረሱም ታውቋል፡፡ በትስስሩ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትም የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች፣ የጋራ ምርምር ሥራዎች፣ የማማከር አገልግሎት፣የ (Internship and Externship) ሥራዎች ናቸው፡፡ 19
  • 20. 20  የስምምነት ፈራሚዎቹ በትምህርትና እና ተግባራዊ ሥልጠና ማዕቀፍ የሚሰሩ ጉዳዮችን በጋራ ይለያሉ፤  ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት በትትስሩ ሼር ለሚገኙ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ሥልጠና ሰጪውና ሥልጠና ተቀባዩ በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት የመጀመሪያ፣ የሁለተኛ ዲግሪ እና የአጫጭር ጊዜ ሥልጠና እንዲሁም የትምህርት ዕድል በስምምነት ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት አሠራር እና በትምህርት ሚኒስቴር የቅበላ መስፈርት መሠረት ይሰጣል፤  የቆዳና ቆዳ ዉጤቶች ዘርፍ የስምምነት ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ሰልጣኞች የዘርፉ ኢንዱስትሪዎች በየዓመቱ ተግባራዊ ስልጠና እንዲያገኙ ይደረጋል፤  በተግባራዊ ሥልጠና ተሳታፊ ለሚሆኑ የዘርፉ የስምምነት ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ሰልጣኞች የምግብ፣ የመጓጓዣ እና የኪስ ገንዘብ ወጪዎች እንደየአግባቡ በራሳቸው በት/ት ተቋማቱ የሚሸፈኑ ይሆናሉ፤  ፈራሚዎች የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የትምህርትና ሥልጠና መርሐ-ግብሮችን በመከለስ፣ በማሻሻል እና አዲስ በመክፈት ሂደት ውስጥ የስምምነት ፈራሚ የዘርፉ ኢንዱስትሪዎችን እንደየአግባቡ ተሳታፊ ይደረጋሉ፤  በተግባራዊ ሥልጠና ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉትን የመገልገያ መሳሪያዎች ጥፋትና ብልሽት ለመከላከል ሥራው በአማካሪውና በአሠልጣኙ እገዛ የሚከናወን ይሆናል የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ተግባርና ኃላፊነት፤  በኢንስቲትዩቱ አደረጃጀት ቅንጅታዊ አሠራር በመፍጠር የኢንዱስትሪ ትስስር አንኳር ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤  የልማት ፕሮግራሞችንና በየዘርፋቸው ያለውን ኢንዱስትሪ የትስስሩ አካል እንዲሆኑ የመሪነት ሚና ይጫወታል፤  ለብሔራዊና ቀጠናዊ የትስስር ፎረሙ ምስረታ እና ውጤታማ የተግበር እንቅስቃሴ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል፤  በመደበኛና በአጫጭር ጊዜ ፕሮግራሞች የአሠልጣኞች ሥልጠና ይሰጣል፤ በሚያስፈልግበት ጊዜ የኢንስቲትዩቱን ሞዴል ፋብሪካ /ወርክ-ሾፕ/ ለዘርፉ ትምህርትና ሥልጠና አገልግሎት እንዲውል ያደርጋል፤  በትስስሩ ለሚከናወኑ የምርምር ሥራዎች ተመራማሪዎች የምርምር ፋሲሊቲዎችን የሚጠቀሙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤ ተመራማሪ ባለሙያዎችን በመመደብም ድጋፍ ያደርጋል፤ የስምምነት ፈራሚዎቹ የጋራ ተግባርና ኃላፊነት፡-  ትስስሩን በተጨባጭ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል የጋራ ዕቅድ በየበጀት ዓመቱ ማዘጋጀት፤  የዕቅዱን አፈፃፀም በየወሩ ለሥራው በተመደቡ ባለሙያዎች ደረጃ በየሶስት ወሩ ደግሞ በበላይ አመራር ደረጃ መገምገም፤  የጋራ መግባቢያ የስምምነት ሰነዱን አተገባበር መከታተል፤ ለትስስሩ እንደ ተግዳሮት የሚነሱ ጉዳዮች ላይ በመምከር የመፍትሔ አቅጣጫ መስጠት፤  የተፈጠረውን ትስስር ተግባራዊ የሚያደርጉ አካላትን እና የጋራ አደረጃጀቶችን መሰየም (ምሳሌ፡- የትስስሩን ሰብሳቢና ጸሐፊ፣ የጋራ ምርምር ቡድን፣ የምርምር ገምጋሚና አጽዳቂ ቴክኒካል ኮሚቴ ወዘተ)፤  ከትስስሩ ጋር የተያያዙ የውይይት መድረኮችን እና ወርክሾፖችን በጋራ ማዘጋጀት፤  ከብሔራዊም ሆነ ቀጠናዊ የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ የትስስር ፎረሞች በየጊዜው የሚሰጡ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ ማድረግ፤ ሾለ ትስስሩ እና በዚህ ማዕቀፍ በየደረጃው የሚገኙ ውጤቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ፤ ይህ የጋራ መግባቢያ የስምምነት ሰነድ ሁሉም የስምምነቱ ፈራሚዎች ተስማምተው ፊርማቸውን በዚህ ሰነድ ላይ ካሰፈሩበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ 20
  • 21. 21 በሰላማዊት ራያ ኢትዮጵያ በቀንድ ከብቶች የታደለች ሀገር ስትሆን የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪም ዘጠና ዓመታትን አስቆጥሮአል፡፡ በ57,829,953 ከብቶች በአፍሪካ አንደኛ በዓለም ስምንተኛ ፣ በ28,892,380 በጎች በአፍሪካ ሶስተኛ በዓለም አስረኛ እና በ29,704,958 ፍየሎች በአፍሪካ ሶስተኛ በዓለም አስረኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ወደ ቆዳ ማልፊያ ከሚቀርቡት ቆዳ እና ሌጦ 1.4 ሚሊየን የከብት ፣6.7 ሚሊየን የፍየል፣13.2 ሚሊየን የበግ ነው፡፡ዘርፉ ካለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ልማትና ሽግግርን በማፋጠን ኢንዱስትሪዎቹ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ፈጣን ልማት እንዲያስመዘግቡ ማብቃትን ዓላማ አድርጐ የተቋቋመ የምርምር ኢንስቲትዩት ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱ የቆዳ ኢንዱስትሪን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ የዘርፉ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍን የሚያግዙና ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የቴክኖሎጂ፣ የቴክኒክ፣ የግብይት፣ የሥራ አመራርና ሌሎች እንደ አስፈላጊነቱ የሚያግዙ ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት፣ የምርምርና ስርጸት፣ የምክርና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት የቆዳ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በመንግስት ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ማምረቻ ኢንደስትሪ ዘርፍ አንዱ ነው፡፡በተለይም የኢትዮጵያ በኣላት አከባበር ከእርድ ጋር ያላቸው ቁርኝት ጥብቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ለስጋው እንጂ ለቆዳው አይደለም በ2011 በጀት ዓመት ከ133 ሚሊዮን ካሬ ጫማ ቆዳና ሌጦ ማልፋትና በማለስለስ ያለቀለት ቆዳን ማምረት የሚችሉ ከ32 በላይ የቆዳ ፋብሪካዎች ቢኖሩም ለፋብሪካዎቹ የሚቀርቡት ቆዳና ሌጦዎች ቁጥር በጣም አነስተኛ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ የጥራት ችግር አለባቸው፡፡ በዚህም የተነሳ አገራችን ማግኘት የሚገባትን ጥቀም በማግኘት ላይ አይደለችም፡፡ ይህም በተለይ በእርድ ወቅትና ከእርድ በኋላ በሚፈጠር ሰው ሰልሽ ችግር የተነሳ እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚህም በመነሳት በዕርድ ጊዜና ከእርድ በኋላ ቆዳው በሚሰበሰብበት ወቅት በሰብሳቢዎች መወሰድ የሚገባውን ጥንቃቄ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ቆዳ በቢላ ሳይበሳ፣ሳይቀደድ እና ሳይተፈተፍ ያለምንም ሰው ሰልሽ እንከን መግፈፍ በዕርድ ወቅት አንገት ከተቆረጠ ወይም ከተባረከ በኋላ እንስሳውን መሬት ላይ አለመጎተት፤ዘመናዊ ቄራዎች በሌሉባቸው አካባቢዎች በእንስሳት ዕርድ በቂ ልምድና ሙያ ባላቸው ሰዎች እርድ ማካሄድ፤ከቆዳው መወገድ ያለባቸውን እንደ ኮቴ፣ጆሮ እና የመሳሰሉትን ማስወገድ፣ ሥጋን እና አጥንትን በቆዳው ላይ አለመከትከት፣ በተቻለ ፍጥነት ጨው ቀብቶ በአቅራቢያ ለሚገኙ ቆዳ ሰብሳቢዎች በሽያጭ ማቅረብ፤ጨው ማግኘት ካልተቻለ ቆዳ እንዳይበሰብስ ዘረጋግቶ አየር እንዲያገኝ በማድረግ ለቆዳ ሰብሳቢዎች በሽያጭ ማቅረብ፣ ጨው ያልተቀባን ቆዳ የቆዳውን 40% ክብደት በሚመዝን ንፁህ ጨው በአግባቡ ሁሉንም የቆዳ ክፍል መቀባት፤ጨው የተቀባውን ቆዳ መደርደሪያ በርብራብ መልክ ከመሬት ከፍ ያለ ሆኖ እንዲዘጋጅ በማድረግ ከቆዳው የሚወጣውን ደምና ፈሳሽ የሚንጠፈጠፍበት ክፍተት ማዘጋጀት፤ጨው የተቀባውን ቆዳ የውስጠኛው /የስጋውን ክፍል በማገናኘት ቀዝቃዛና ነፋሻማ መጋዘን ውስጥ ማስቀመጥ፣ ጨው የተቀባውን ቆዳ በመደርደሪያው ላይ በደንቡ መሰረት ሲቀመጥ የድርድሩ ከፍታ ከአንድ ሜትር እንዳይበልጥ መጠንቀቅ፣ ህብረተሰቡ ለቆዳ የሚያደርገው ጥንቃቄ ከእንስሳት እርባታ እስከ አለቀለት ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ግብይት ድረስ ባሉት የግብይት ሰንሰለቶች፣ ቆዳ እንዳይባክን ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንደሚጠበቅ የዘርፉ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ኢኒስቲትዩት ያሳስባል፡፡ ******************************** ለሥጋ ብቻ ሳይሆን… 21
  • 22. 22 በገነት ደምሴ የቆዳ ኢንደስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍን ተወዳዳሪነት ለማሳደግና የውጭ ገበያውን ለመሳብ ከተቋቋመበት 1991 ዓ.ም ጀምሮ በውስጡ በሚገኙ ልዩ ልዩ የስራ ዘርፎች አማካኝነት ሥራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በኢንስቲትዩቱ ካሉት ዳይሬክቶሮቶች መካከል ለዛሬ የኢኒስቲትዩቱን የምርምርና ፍተሻ ላብራቶሪ እንመለከታለን፡፡ በኢኒስቲትዩቱ ውስጥ ስለሚገኘው የላብራቶሪው አገልግሎትና ተግዳሮቶቹ መረጃውን የሰጡን በዘርፉ የቡድን መሪና የፊዚካልና መካኒካል ፍተሻ ኤክስፐርት ወ/ሎ አስቴር መካሻንና የኬሚካልና ኢኒስትሩመንታል ላብራቶሪ ፍተሻ ኤክስፐርት የቡድን መሪ የሆኑትን ወ/ሎ ሜሮን መንግስቱን አነጋግረን የሰጡንን መልስ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንደስትሪ ኢኒስቲትዩት በስሩ ከሚገኙ14 ዳይሪክቶሬቶች መካከል አንዱ ሲሆን የላብራቶሪ ምርምርና ፍተሻ ዳይሬክቶሬት የሚል ስያሜ የተሰጠው ነው፡፡ በዚህ ዳይሬክቶሬት ሼር ደግሞ 4 የላብራቶሪ አገልግሎት የሚሰጡ የስራ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የላብራቶሪ ክፍሎች የመጀመርያው የአካላዊ (ፊዚካል) ፍተሻና ምርምር ላብራቶሪ፣ ሁለተኛው የኬሚካል ላብራቶሪ፣ ሦስተኛው የውጋጅ ውሃ / West water/ ላብራቶሪና የመጨረሻው ከባቢያዊ ጤናን ለማስጠበቅ የሚረዳው /Environmental Laboratory/ የሚባሉ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል ለዛሬ የፊዚካል፣ ኬሚካል ፍተሻ ላብራቶሪ ክፍል ተግባራትን እንቃኛለን፡፡ በዚህ ክፍል አልባሳትን፣ ቆዳንና የጫማ ዓይነቶችን ኬሚካል ሳይጠቀሙ ልዩ ልዩ ማሽኖችንና መሳርያዎችን ብቻ በመጠቀምና በማንቀሳቀስ አካላዊ (ፊዚካል) የጥንካሬና የጥራት ፍተሻ የሚካሄደበት ክፍል ነው፡፡ አንድ ቆዳ ተለፍቶ፣ተቀልሞና ተቆርጦ ተሰፍቶና ልብስ፣ ጫማ፣ ወይም ጓንት ሆኖ ከተሰራ በኋላ ጥቅም ላይ ከመዋሉ አስቀድሞ ከሚፈለገው የጥራት ደረጃ ላይ መሆኑን ለማረጋገጥ ናሙናዎች ተወስደው ምርመራ የሚደረግበት አገልግሎት ክፍል ነው፡፡ በዚህ ክፍል የላብራቶሪ ፍተሻ የሚደረገው አንድ ምርት ያለቀለት ወይም ደግሞ ገና በመሰራት ሂደት ላይ እያለ ሊሆን ይችላል፡፡ በላብራቶሪው ፍተሻ የሚደረግላቸው በቆዳ ኢንደስትሪው ዘርፍ የተሰማሩትን ባለሃብቶች ምርት ብቻ ሳይሆን ከሌሎች የጥናትና ምርምር ተቋማት፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን የሚላኩ ቁሳቁሶች ጭምር ናቸው፡፡ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ተቋማትና ኢነዱስትሪዎች ፍተሻ እንዲደረግላቸው ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዚ ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ በማስከፈል እንደጥያቄያቸው ቅደም ተከተልና ትዕዛዝ የላብራቶሪ ፍተሻው ይከናወናል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ምርምር ለማድረግ በሚፈልጉበት ጊዜ ሁሉ ምርምሩን ማካሄድ ይችላሉ፡፡ ነገርግን ሁሉም ተቋማት በቅድምያ የሚፈልጉትን የምርመራ ወይም ፍተሻ ዓይነትና ምርት በመጥቀስ በደብዳቤ ወይም በፋክስ ኢኒስቲቲዩቱን መጠየቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በርካታ የፍተሻ ዓይነቶች አሉ፤ ከነዚህ የፍተሻ ዓይነቶች አንዱን እንደምሳሌ ብንወስድ /ISO/ International standard or- ganization (ዓለም አቀፍ አውቅና ሰጪ ተቋም) የሚያስቀምጠው በአንድ ኢንደስትሪ ውስጥ የምርቱ የኬሚካል መጠን፣ የጥንካሬና የተስማሚነት ደረጃ ወሰን በምርመራ ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ ተቋማት ፍተሻና ምርምር ከመጀመራቸውና ከውጤት በኋላም የማማከር አገልግሎት ይሰጣቸዋል፡፡ ለምሳሌ አንድ የቆዳ ፋብሪካ ምርቱን ከማስፈተሹ በፊት የምርቱን የትኛውን ክፍል አካልና ኬሚካላዊ ይዘት አንደሚያስፈትሽ የማማከር ሼል ይሰራል ፡፡ ከፍተሻውም በኋላ በውጤቱ ላይ ምን መቀነስ ምን መጨመር አንዳለባቸውና ሥራቸውን በምን መልኩ በጥራት ማስቀጠል እንደሚችሉም ድጋፍ እንደሚሰጥ የላብራቶሪው የቡድን መሪና የፊዚካልና ሜካኒካል ፍተሻ ኤክስፐርት የሆኑት ወ/ሎ አስቴር መካሻ አስረድተዋል፡፡ በፍተሻው ወቅት በሚያመጡት ናሙና ላይ ችግር ካለ በላብራቶሪው ንባብ ውጤት መሰረት ተቋሙ ወይም ኢንደስትሪው ምርቱን እንዲያሻሽል ሪፖርት ይሰጣል፡፡ እንዴት አድርጎ የምርቱን ወይም የምርምር ውጤቱን ማሻሻል እንዳለበትም ይገልጻል፡፡ ከዚህም ሌላ እንደሶስተኛ ወገን የጥራት ደረጃ እውቅና ሰርተፊኬት እንሰጣለን ብለዋል ወ/ሎ አስቴር፡፡ በኬሚካል ላብራቶሪ መረጃ የሰጡን ደግሞ ወ/ሎ ሜሮን መንግስቱ ሲሆኑ እርሳቸው እንደገለጹት አንድ ያለቀለት ቆዳ ወይም ምርት በተወሰነ ፓራ ሜትር እርቀት ውስጥ በውስጡ የሚገኙ እንደክሮምየም፣ ፎርማል አልዲሃይድና ሌሎችም ውህድ መጠን በተቋሙ ይፈተሻል፡፡ ይህን ፍተሻ ለማከናወንም በዓለም አቀፍ ተቋማት የወጣውን ደረጃና የፍተሻ ዘዴ መሰረት በማድረግ ነው፡፡ በዚህ የፍተሻ ዘዴ ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎች ውህዶች መጠን በምንፈትሽበት ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው መጠን በላይና በታች ሲሆን በላብራቶሪው ሪፖርት ማሳወቅያ ቅጽ አማካኝነት ለአምራቾች ወይም ለመርምር ተቋማት በማሳወቅ ወይም በሚሰጣቸው ውጤት መሰረት ማሻሻል የሚችሉ ከሆነ ያሻሽላሉ መወገድ የሚገባውንም ያስወግዳሉ፡፡ ዓለም አቀፍ እውቅናን ለማስቀጠል 22
  • 23. 23 ለምሳሌ በቆዳ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቆዳውን ለማልፋት የሚጠቅም /Basic Chromium sulfate/ አለ ይህ ውህድ በውስጡ የሚገኘው የክሮሞ ኦክሳይድ /Chromo Oxide/ መጠን በምርት ሂደት ውስጥ ይለካል፡፡ ቆዳው ውስጥ የሚቀረው የክሮምየም መጠን ምን ያህል መሆን እንዳለበት የተቀመጠ ዓለም ዓቀፍ ደረጃ አለ፡፡ በዚህ ዓለም አቀፍ ደረጃ መሰረት ማንኛውም ለምርት የተዘጋጀ ቆዳ ከተቀመጠው መስፈርት መጠን በላይ የክሮምየም መጠን ካለው በሪፖርት የሚገለጽ ሲሆን ጥያቄዎቹ ወደ ኢንደስትሪያቸው ተመልሰውም በማስተካከል መጠኑ እንዲቀንስ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ በቆዳ ኢንደስትሪ ውስጥ አንድ ልብስ፣ ጫማ፣ ወይም ቦርሳ ለማምርት ዋናኛ ግበዓት የሆነውን ቆዳን ለማልፋት፣ ለማቅለምና ለማድረቅ የሚጨመሩ የኬሚካል ዓይነቶች አሉ፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች በሰው ልጅ ጤና ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ በተወሰነ ደረጃ መጠናቸው መቀነስ አለበት ለጤና ተስማሚ በሆነ ፐርሰንት ላይ ሲደርሱ መፈተሽና ተለክተው ማረጋገጫ ማግኘት አለባቸው፡፡ ይህ ፍተሻ ከተሰራ በኋላ ውጤቱን ለጠያቂው በመስጠት እንዲያስተካክሉ ይደረጋል፡፡ ኢንደስትሪዎች የሚጠቀሙባቸው ኬሚካሎች ሁሉ ከቆዳው ናሙና በመውሰድ ይለካሉ ማለት ነው፡፡ አልባሳት ለሰው ልጅ ተስማሚ በሆነ የሙቀት መጠን ውስጥ በምን ያህል ፐርሰንት ኬሚካል መኖር እንዳለበት የተቀመጠውን ዓለም አቀፍ ደረጃ ያልጠበቀ ምርት መመረት የለበትም፡፡ ስለዚህም ምርቶች ከመመረታቸው በፊትና በምርት ሂደት ውስጥ ፍተሻ ይደረግላቸዋል፡፡ ለምሳሌ በአንድ ቆዳ ላይ በራሱ በተፈጥሮው የሚገኝ ስብ አለው፤ በማምረት ሂደት ለማልፊያነት፣ ለማቅለምና ለማድረቅ ከሚጨመሩ ኬሚካሎች ጋር ሲደመር የሚያስከትለው ችግር አለ፡፡ የዚህ የስብ መጠን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተቀመጠ መስፈርት መጠን (ደረጃ) በቆዳው ውስጥ መኖር አለበት፡፡ የቆዳው ስብ መጠን መብዛትም ማነስም የለበትም ተስማሚ የሚሆነው መጠኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሰላው ፐርሰንት ላይ ሲደርስ ትክክል መሆኑ ይረጋገጣል፡፡ ይህን ማረጋገጫ ደግሞ ደንበኞች እንዲፈተሸላቸው ሲጠይቁ ፍተሻውን በማካሄድ ውጤቱ ይሰጣል፡፡ በይበልጥ ደግሞ ምርቶቻቸውን ወደውጭ የሚልኩ የንግድ ድርጅቶች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የምርት ውጤት ከሌላቸውና የኛን የምስክር ወረቀት ካላገኙ ተቀባይነት ስለማይኖራቸው ምርቶቻቸውን አስፈትሸው የማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዝ ግድ ይላቸዋል ብለዋል ወ/ሎ ሜሮን መንግስቱ፡፡ ፋብሪካዎች በምርት ሂደት ውስጥ የሚያስወግዱት ቆሻሻ ፍሳሽ አለ፡፡ ይህ ውጋጅ ቆሻሻ ውሃ ወደውጭ ሲለቀቅ በሰው፣ በእንሰሳት፣ በዕጽዋትና በአካባቢ ላይ የሚያስከትለው ብክለት ሊኖር ይችላል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ውጋጅ ቆሻሻ ደግሞ ችግር ከማስከተሉ በፊት በላብራቶሪ ውስጥ ይፈተሻል፡፡ በዚህ /west water laboratory/ አማካኝነት አካባቢያችን ከብክለት የጸዳ ለማድረግ እንጠቀምበታለን፡፡ ፋብሪካዎችም ከምርት ፍሳሽ ውጋጅ የውሃ ናሙና ለሶስት ግዚ ይዘው በመምጣት ያስፈትሻሉ፤ የመጀመርያው ምርቱን ለማምረት በዝግጅትና በማልፋት ሂደት፣ሁለተኛ በማምረት ሂደትና የመጨረሻው የማምረት ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ በማስፈተሸ ውጤቱ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ተለክቶ ይሰጣቸዋል፡፡ ውጤቱን መሰረት በማድረግ ማስተካከል ይገባቸዋል ማለት ነው፡፡ ፍተሻው በዓለም አቀፉ የአካባቢ እንክብካቤ ተቋም ባወጣው ደረጃና መስፈርት መሰረት የሚሰራ ነው፤ በዚህ ፍተሻ ወደ 16 የሚሆኑ የኬሚካል ዓይነቶች ይፈተሻሉ፡፡ አንድ ፋብሪካ ከመመስረቱ በፊትም ሆነ በኋላ ድጋፎች ይሰጣሉ፡፡ ለምሳሌ አንድ የቆዳ ፋብሪካ ላብራቶሪ እንዲኖረው ይደረጋል፤ ይህን ላብራቶሪ በማቋቋም ድጋፍ ይሰጣቸዋል፡፡ ስለፋብሪካው አጠቃላይ አወቃቀርና አመራረት ሂደት ድጋፍ የሚሰጡ የተለያዩ ዳሬክቶሬቶችም አሉ፡፡ በላብራቶሪያችን ውስጥ ዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠላቸውም ያልተቀመጠላቸውም የላብራቶሪ ፍተሻዎች ይከናወናሉ፡፡ ሆኖም ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመገናኘት የተካሄደው የንጽጽር ፍተሻና ምርምር /Proficiency Test/ ዋጋ እንዲኖረው ወይም በሌሎች ተመሳሳይ ዓለም አቀፍ ተቋማትም እንዲረጋገጥና ተመሳሳይ ውጤት እንዲገኝ የሚደረግበት ሂደትም አለ፡፡ በላብራቶሪ ውጋጅ አወጋገድ ላይ ጥሩ ተሞክሮ ያላቸው ፋብሪካዎች ውጤታቸው ለሌሎች ፋብሪካዎች ማስተማርያ ይሆናል፡፡ በላብራቶሪ ውስጥ የሚካሄዱ ፍተሻዎች ሁሉ እንደየዓይነታቸው፣ እንደሚወስዱት የግብዓት መጠንና ወጪ ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ ለተቋሙ ይከፍላሉ፡፡ ለምሳሌ አንድን ቆዳ ወይም ምርት ለማቅለም ከሚጠቀሙበት ኬሚካል አንዱ የአሮማቲክ አማይን መጠንን ለመፈተሽ በአንድ ትንሽ ናሙና አስከ1,500 ይካፍላሉ፡፡ ይሁን እንጂ እንደየፍተሻው ዓይነትና መጠን ክፍያው ይለያያል፡፡ እያንዳንዱ ተቋም የፍተሻ ውጤት ማረጋገጫ የሚሰጠው አንድ ጊዜ ላመጣው ናሙና ብቻ እንጂ ውጤቱ ዘላቂ ማረጋገጫ የሚሰጥበት ሁኔታ የለም፡፡ ለቀረበው ናሙና የሚሰጥ ውጤት በመሆኑ ላልተፈተሸ ናሙና የኣንድ ጊዜ ፍተሻ ለሌላ ግዜ ምርት ማረጋገጫ አይሆንም (አይሰራም)፡፡ ላብራቶሪያችን ደረጃቸውን በጠበቁ የኬሚካል ዓይነቶች፣ በፍተሻ መሳርያዎችና በእውቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ዓለም አቀፍ እውቅና ያለውና ከፍተኛ ደረጃ የተሰጠው ስለሆነ ይህን አስጠብቆ ለማቆየት ጥረት በየጊዜው እየተደረገ አስተማማኝ ውጤት እየተገኘ ነው፡፡ 23
  • 24. 24 ይህንንም ሁኔታ በየጊዜው ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ የላብራቶሪ ባለሙያዎች መኖር ወሳኝ ነው፡፡ አንድ ባለሙያ የሚሰራውን የፍተሻ ውጤት ከሌሎች ዓለም አቀፍ እውቅና ካገኙ 107 የውጭ ተቋማት ጋር በማነጻጸር /proficiency test/ ውጤቱን ስራውን መልሶ የሚያይበት የስራ ግንኙነትም አለ፡፡ አዳዲስ የምርምር ውጤቶችንም ለማሳወቅና ደረጃ እንዲሰጠው ማድረግ የሚቻልበት አጋጣሚም ክፍት ነው፡፡ በዚህ ረገድ አንድ ባለሙያ የሚጠቅምባቸው የላብራቶሪ መመርያዎች፣ ኬሚካሎች፣ መሳርያዎችና እውቀቱን ተጠቅሞ የሚያገኘውን ውጤት በትክክል ከሌሎች ዓለም አቀፍ ላብራቶሪዎች ጋር አነጻጽሮ ውጤት ሲያስቀምጥ ሂደቱን የሚከታተልና ትክክለኛነቱን የሚያረጋግጥ ሌላ ባለሙያ በላብራቶሪው ውስጥ አለ፡፡ በቆዳ ኢንደስትሪ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ምርቶችም ላይ የተሰማሩ ኢንደስትሪዎች፣ የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች የላብራቶሪውን አገልግሎት የሚያገኙበት መንገድም ክፍት ነው፡፡ በአጠቃላይ ላብራቶሪው የናሙና ፍተሻ፣ የምርምር፣ እውቅና የመስጠት፣ የድጋፍ፣ ዓለም አቀፍ ንጽጽርና የለውጥ ስራዎችን እንሰራለን፡፡ ዓለም አቀፍ እውቅናችንን ዘላቂ ለማድረግ የላብራቶሪ እቃዎችን፣ ሠራተኞችን መሳርያዎችንና ሌሎች ግበዓቶችን በተገቢው መንገድ ጠብቆ ማቆየትና በየጊዜው ከሌሎች ላብራቶሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የውስጥና የውጭ ኦዲት ስራዎች አንዲከናወኑ እናደርጋለን፡፡ የተቋሙን የላብራቶሪ አገልግሎት የሚገዳደሩ ችግሮች ፈጣን የደንበኛ አገልግሎትን በሚመለከት፡- ከአንድ ተቋም ወይም ፋብሪካ ሊፈተሽ የመጣ የምርት ናሙና ፍተሻ እስኪጠናቀቅና ውጤት እስኪደርሰው ድረስ ሌሎች ወረፋ ሊጠብቁ ስለሚችሉና ጊዜም ስለሚወስድ ይህን ችግር ለመፍታት ተጨማሪ የላብራቶሪ መፈተሻ መሳርያዎችና ኪሚካሎች ግዢ ጠይቀናል ይህ ሲሟላ ችግሩ ይቀንሳል ውጤት የመስጠቱ ሥራም ይፋጠናል፡፡ ደረጃውን የጠበቀ ጥራት ያለው ኬሚካል አለማግኘት / የኬሚካል ብራንድ/፡- በፋይናንስ፣ ግዢና ንብረት አስተዳደር አሰራር መሰረት የኬሚካል ግዢ የሚከናወነው ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረቡ ተቋማት መሆኑ እሙን ነው፡፡ በዝቅተኛ ዋጋ የሚገዙ ኬሚካሎች ደግሞ የጥራት ደረጃቸው የወረደ የሚሆንበት አጋጣሚ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ በውጤታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድርና እውቅናንም የሚፈታተን ነው፡፡ በጨረታ የሚገዙ ኬሚካሎችን ጥራት ለማወቅ አስቸጋሪ ስለሆነና በውጤት ላይ፣ በመሳሪያዎቻችንንና በእውቅናችን ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የጨረታ ግዢ እንዲቀርና በልዩ ፍቃድ የኬሚካል ግዢ የሚከናወንበት መንገድ ከመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ተፈቅዶልናል፡፡ የመብራት መቆራረጥ፡- አሁን ያሉት ጄነረተሮች ተጠግነው ሾል ላይ ቢውሉም ለላብራቶሪ አገልግሎት አስተማማኝ የማይሆኑበት አጋጣሚ አለ፡፡ መብራት ሲጠፋ ጀኔረተሩ ሾል እስኪጀምር በሚወስደው አስር ሰከንድ ውስጥ እንኳን በሰው ላይ ጉዳት፣ በመሳርያና በናሙናዎች ላይ ብልሽት ያጋጥማል፤ ይህ ደግሞ ጊዜን፣ የሰው ኋይልን ያሳጣናል ከፍተኛ የግብዓት ወጪንም ያስከትላል፤ ችግሩን ለማቃለል በርካታ UPS /Uninterrupted power supply/ ቢገዙም በብልሽት ምክንያት የማይሰሩ በመሆናቸውና በስራ ላይ ያሉትም በቂ ባለመሆናቸው ችግሩ እንደቀጠለ ነው፡፡ የውሃ ጥራት ደረጃ፡- የቧንቧ ውሃ ፍሰት መቆራረጥ የላብራቶሪ ሾል እንዲዘገይ ከማድረጉም በላይ በፍተሻ ሂደት ላይ ከፍተኛ የጥራት ጉድለት ችግር ሆነው ከሚታዩ ጉዳዮች እንደዋንኛ ችግር የሚወሰድ ነው፡፡ በክፍሉ በአብዛኛዎቹ የፍተሻ መስመሮች የሚገኘው የጉርጓድ ውሃ በመሆኑ የጥራት ችግር አለው፤ የተጣራ ንጹህ የቧንቧ ውሃ በጥቂት ቦታ ብቻ የሚገኝ በመሆኑ ለፍተሻ ጥራት አንዱ ተግዳሮት ሆኖብናል፡፡ የማሽን ጥገና፡- በላብራቶሪው ውስጥ በርካታ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችሉ ማሽኖች ቢኖሩም ከኢኒስቲቲዩቱ ላብራቶሪ ባለሙያዎች እውቀትና አቅም በላይ የሆኑና በሃገር አቀፍ ደረጃም ሊሰሩ ሊጠገኑ የማይችሉ ማሽኖች ቦታ ይዘው መቀመጣቸው ሌላው ችግር ነው፡፡ ይህን ችግር ለማቃለል ተብሎ ባለሙያዎች ከውጭ እንዲመጡ ከዚህም ወደውጭ ሄደው እንዲሰለጥኑ ቢደረግም በቂ ግን አልነበረም፡፡ /Calibration Machines/፡- አንድ ማሽን በስራ ላይ እያለ በትክክል እየሰራ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ በሃገራችን ስራዉን የሚያከናውነው ደግሞ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ተቋም / NMIE/ (National Metrology Institute of Ethiopia) ነው፡፡ የሜትሮሎጂ ድርጅት አቅም ከኛ ላብራቶሪ ማሽኖች አንጻር ሲታይ አቅሙ ውስን በመሆኑ ሁሉንም የኛን ማሽኖች የፍተሻ ውጤት ማረጋገጥ የሚችል አይደለም:: የማረጋገጡ ሾል በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ካልተከናወነ ደረጃችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ አስጠብቀን መሄድ አንችልም:: ይሄ ደግሞ እኛም ሆንን አምራቾች የምርት ውጤታቸው ከደረጃ በታች እንዲሆን ስለሚያደርግ ለውጭ ገበያ የምናቀርበውን ምርት ጥራት ይቀንሳል፤ ወይም ደግሞ ምርቱ ውድቅ ይሆናል:: ይህ ደግሞ ፋብሪካውን ለኪሳራ የውጭ ምንዛሬ ገቢን ይቀንሳል፡፡ ኪሳራው አገራዊ ነው፡፡ ዓለም አቀፍ እውቅናችንን ለማስቀጠልም ካላብሬሽን አንዱ መስፈርት ነው፡፡ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍልሰት፡- በአንድ ላብራቶሪ ውስጥ የሚሰራ ባለሙያን ለማብቃት ከፍተኛ ወጪና ጊዜ የሚጠይቅ ነው፡፡ ባለሙያዎች ለብቃታቸው የእውቅና የምስክር ወረቀት ከዓለም አቀፍ አውቅና ሰጪ ተቋማት ካገኙ በኋላ ስለሚለቁ እነርሱን ለመተካት የሚያስፈልገው የስልጠና ወጪ፣ ግዜና አቅም ከፍተኛ በመሆኑ በዚህ ምክንያት የሚኖረው ችግር ከፍተኛ ነው፡፡ የላብራቶሪ ክፍሉ አደረጃጀት፡- የምንሰራበትና የማረፍያ ክፍል ባለመለየቱ ምክንያት እዚሁ እናርፋለን፣ እንመገባለን፣ ማሽኖች ሲንቀሳቀሱ፣ የኬሚካል ፍተሻ ሲከናወን የሚወጣው ጭስ፣ ፍሳሽ፣ የኬሚካል ትነት፣ ድምጽ ለሰራተኞች የጤና ችግር የሚያስከትል መሆኑ እሙን ነው፡፡ በርካታ ኬሚካሎች የመተንፈሻ አካላትን የሚጎዱ ናቸው፡፡ የኬሚካል ክፍሉና የውጤት መመዝገቢያው የተጠጋጉና አየር ማስገቢያ ባለመኖሩ ለብክለት ተጋልጠናል፤ ሲሉ ወ/ሎ ሜሮን መንግስቱ ሃሳባቸውን አጠናቀዋል፡፡ 24