SlideShare a Scribd company logo
1 of 7
Download to read offline
ዜና መፅሔት
ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር
አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ!
ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
www.ethiopiansugar.com || facebook.com/etsugar
ጣፋጭ
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ከኮርፖሬሽኑ አመራሮች ጋር ተወያዩ
• የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካንና ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል
»» ወደ ገጽ 2 ዞሯል
»»ወደገጽ3ዞሯል
በውስጥ
ገጾች
በቻይና የጃንግዚ ግዛት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተመራ የልዑካን ቡድን ከስኳር ኮርፖሬሽን አመራሮች...>>6
የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በስኳር ምርት ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመግባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለፀ >>3
የኮርፖሬት ሊደርሺፕ ሥልጠና ተሰጠ >>5
በስኳር ኢንዱስትሪው በቀጣይ ሊተገበሩ
ስለሚገባቸው ሥራዎች እና የአሠራር ሥርዓት
ላይ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር
ከስኳር ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር ህዳር
23/2009 ዓ.ም ተወያዩ፡፡
በዚሁ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ተወካይና የስትራተጂያዊ ድጋፍ ም/ዋና ሥራ
አስፈጻሚ አቶ በዛብህ ገብረየስ የኢትዮጵያ
ስኳር ኢንዱስትሪ ልማት ንዑስ ዘርፍ አጠቃላይ
ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፉን ስኳር ድርጅት ጉባኤን ለማስተናገድ ተመረጠች
* እ.ኤ.አ በ2017 የድርጅቱን ምክር ቤት የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በምክትል
ሊቀመንበርነት ይመራሉ
ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፍ የስኳር ድርጅት አባል አገሮች ጉባኤን እ.ኤ.አ በ2018
እንድታስተናግድ ተመረጠች፡፡ ተቀማጭነቱ ለንደን የሆነውን የዓለም ስኳር
ድርጅት ምክር ቤትን እ.ኤ.አ በ2017 የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ
በምክትል ሊቀመንበርነት እንዲመሩ በአባል አገራት ተመርጠዋል፡፡
ከህዳር 20 እስከ 23/2009 ዓ.ም በለንደን የተካሄደው ዓለም አቀፍ የስኳር
ድርጅት ጉባኤ የታወቁ ስኳር አምራች አገሮች፣ ባለሀብቶች፣ የዘርፉን
ተመራማሪዎችና ሌሎችንም ያሳተፈ እንደነበር ታውቋል፡፡
የስኳር ኢንደስትሪው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ
አስቀድሞ ምንም አይነት መሰረተ ልማት ባልነበረባቸው አካባቢዎች
እየተካሄዱ ያሉት የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ተስፋ ሰጪ
መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ታህሳስ 9/2009ዓ.ም በኦሞ
ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት እየተገነቡ የሚገኙ ስኳር ፋብሪካዎችን
ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከስኳር »» ወደ ገጽ 2ዞሯል
ገጽታን የሚያሳይ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
ይህንን ተከትሎ በተደረገው ውይይት ላይ
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር
ዶ/ር ግርማ አመንቴ እንደተናገሩት፣ ከስኳር
ልማት ዘርፍ የሚጠበቀውን ከፍተኛ ውጤት
ለማስመዝገብ ተቋሙን በግልጽ የአሠራር
ሥርዓት መምራትና የሥራዎችን ቅደም
ተከተል በማውጣት መፈጸም ይገባል፡፡
ዶ/ር ግርማ አመንቴ
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር
ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም2 3e t h i o p i a n s u g a r. c o m
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ... »» ከገጽ 1 የዞረ
ስኳር ኮርፖሬሽንን የመሰለ ትልቅ የልማት ተቋም ሥራን በትክክል
መመዘን የሚያስችል የውጤት ምዘና ሥርዓት ላይ ትኩረት ማድረግ
ይገባዋል ያሉት ሚኒስትሩ፣ ሰዎች በሥራቸው ውጤት ብቻ እየተመዘኑ
ሥራ ላይ መቆየትና ማደግ እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡
አክለውም ሰዎች በሥራቸው ውጤት ብቻ የሚኖሩበት ተቋም
መፍጠር ካልተቻለ የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብም ሆነ ብቃት
ያላቸውን ባለሙያዎች ይዞ መቀጠል አይቻልም ብለዋል፡፡
ለዘርፉ ቀጣይ እድገት ካለፉት ስህተቶች እና ስኬቶች ትምህርት
መውሰድ ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ፣ በተለይም ኮርፖሬሽኑ ያሉበትን
ተግዳሮቶች ለይቶና የሚፈቱበትን ስትራተጂ ቀርጾ በፍጥነት ወደ
ውጤታማ ሥራ መግባት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑን የፋይናንስ አሠራር ለማሻሻል የተጀመረው የኮርፖሬት
ፋይናንስ ማሻሻያ ፕሮጀክት ትክክለኛና ተገቢ መሆኑን ያወሱት
ሚኒስትሩ፣ ሥራው በፍጥነት መጠናቀቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ሥራዎችን ወይም
ፕሮጀክቶችን መለየትና የተለየ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ
የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በስኳር ምርት ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመግባት
ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለፀ
የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የሀገር ውስጥ የስኳር
ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር ሀገሪቷ በስኳር
ምርት ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመግባት
ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ
እንደሚያበረክት የመንግሥት የልማት
ድርጅቶች ሚኒስትር ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ከሚኒስቴር
መ/ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎች ጋር
በመሆን ፋብሪካውን በጎበኙበት ወቅት
በሰጡት ማብራሪያ፣ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ
የሀገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማርካት
ባለፈ ከማምረት አቅሙ ከፍተኛነትና
ለጅቡቲ ወደብ ካለው ቅርበት አኳያ ምርቱን
ወደ ውጪ ለመላክ ከፍተኛ ስትራተጂያዊ
ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ፋብሪካው በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና
በሰው ሃይል ረገድም በወጣት ባለሙያዎችና
ጠንካራ አመራሮች የተደራጀ መሆኑን
ዶ/ር ግርማ ገልጸው፣ የተመለከቱት የሥራ
እንቅስቃሴ ሁሉ አበረታችና ተስፋ ሰጪ
መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፉን... »» ከገጽ 1 የዞረ
በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያን በመወከል
የተሳተፉትና ምክር ቤቱን በምክትል
ሊቀመንበርነት እንዲመሩ የተመረጡት የስኳር
ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ
አብቴ እንደገለጹት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2018
ጉባኤውን እንድታስተናግድ መመረጧ እንደ
አገርና እንደ ስኳር ኮርፖሬሽን ታላቅ ስኬት
በመሆኑ ደስ ብሎናል ብለዋል፡፡
አቶ እንዳወቅ ኢትዮጵያ የጉባኤው አስተናጋጅ
አገር መሆኗን ተከትሎ እ.ኤ.አ ከሐምሌ
2017 እስከ ሰኔ 2018 የዓለም ስኳር ድርጅት
ምክር ቤትን ለአንድ አመት በሊቀመንበርነት
እንደሚመሩም ታውቋል፡፡
ጉባኤው አምራቾችን፣ ባለሀብቶችን፣
ሻጮችንና በዘርፉ ምርምር የሚያደርጉ
አካላትን በአንድነት የሚያገናኝ በመሆኑ
ለአገር ገጽታ ግንባታና ለኮንፈረንስ ቱሪዝም
ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አቶ እንዳወቅ
ተናግረዋል፡፡
አገሪቱ በስኳር ምርት ያለችበትን ደረጃ
ለማስተዋወቅ፣ የውጭ የገበያ እድል
ለማግኘት እንዲሁም በዘርፉ ኢንቨስትመንት
ለመሳተፍ የሚፈልጉ የአገር ውስጥና የውጪ
ባለሀብቶችን ለመሳብ ጉባኤው መልካም
አጋጣሚ እንደሚፈጥርም ነው ዋና ስራ
አስፈጻሚው ያስረዱት፡፡
የዓለም የስኳር ድርጅት በዓለም ስኳር ገበያ
ላይ ወሳኝ ሚና እንዳለው የተናገሩት ዋና ሥራ
አስፈጻሚው፣ ጉባኤው ለኢትዮጵያ የስኳር
የውጭ ገበያ ዕድል መፍጠሪያ መድረክ ሆኖ
ሊያገለግል እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡
የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን በማሟላት
ጉባኤው በሚስተናገድበት አመት ስኳር
ወደ ውጭ ለመላክ ርብርብ በመደረግ ላይ
እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡
በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ የስኳር ምርት
አቅሟን በማሳደግ የዓለም ገበያን ለመቀላቀል
ከወዲሁ በማድረግ ላይ የምትገኘው ዝግጅት፣
አገሪቱ ለዓለም ገበያ ያላት ቅርበት እና
በምርት አዘገጃጀት ላይ ያላት ምቹነት በስፋት
ተገልጿል፡፡ በዚሁ ወቅት ባለሀብቶች በግልም
ሆነ በቡድን በዘርፉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ
ጥሪ ቀርቧል፡፡
ጉባኤው የስኳር ምርት ተግዳሮቶችን፣ ለስኳር
አምራቾች የሚያስፈልጉ የቴክኒክ ድጋፎችና
የቴክኖሎጂ ግብአቶችን፣ የገበያ ዕድሎችና
ትስስሮች መጠናከር ስለሚችሉበት ሁኔታም
በሰፊው ተወያይቷል፡፡
የስኳር ምርት እንደ ቡናና ነዳጅ ተፈላጊነቱ
እየጨመረ በመምጣቱ የገበያ ትስስር ገጽታው
ምን መምሰል እንዳለበት እንዲሁም ዘርፉ
የኤታኖል ምርትን በማስፋፋት በአየር ንብረት
ለውጥ ቅነሳ ላይ ሊጫወት ስለሚገባው ሚናም
ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ዓለም አቀፉ የስኳር ድርጅት ክርክሮችን
በማድረግ፣ ልዩ ጥናቶች በማካሄድ እንዲሁም
ሴሚናሮችን፣ ኮንፈረሶችንና ወርክሾፖችን
በማዘጋጀት የስኳር ገበያ የተሻለ እንዲሆን
የሚሰራና 87 አባል አገሮች ያሉት
በይነመንግስታዊ ድርጅት ነው፡፡
አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ዶ/ር ግርማ፣ ኮርፖሬሽኑ በራሱ አቅም
መወጣት ያልቻላቸውን ተግባራት ሚኒስቴር መ/ቤቱ አሠራር
በመዘርጋት ኮርፖሬሽኑን ለመደገፍና በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን
አስታውቀዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት በሚኒስትሩ ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች
የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ የተንዳሆ ስኳር
ፋብሪካን እንዲሁም የኦሞ ኩራዝ እና የጣና በለስ ስኳር ልማት
ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡
ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡
እየለማ ያለው በአንድ ቀን የሚታረስ መሬት አይደለም ያሉት ጠቅላይ
ሚኒስትሩ ፋብሪካዎቹ እዚህ ደረጃ ደርሰው ማየታቸው በራሱ ትልቅ
ኩራት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያን የመሰሉ ሀገራት የተለጠጠ ዕቅድ ካላቀዱ ከድህነት
ለመውጣት አዳጋች እንደሚሆንባቸው ተናግረው፣ በዚህ
ረገድ በዘርፉ ያጋጠመ የማስፈጸም አቅም ችግር እንደነበር
አስታውሰዋል፡፡ አክለውም ኮርፖሬሽኑ እየወደቀ እየተነሳ አሁን
የደረሰበት አቅም አስተማማኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅት ለአዳዲሶቹ ስኳር ፋብሪካዎች የሸንኮራ አገዳ
ቆራጮችእጥረት መኖሩንየተረዱትአቶኃይለማርያምለሜካናይዜሽን
የሚረዱ ማሽኖች እንዲገዙ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
የስኳር ልማቱ ባለፉት ዓመታት የነበረበትን ሁኔታ አሁን ከሚታየው
አፈጻጸም ጋር በማነጻጸር የተሰማቸውን ሲናገሩም “በዘርፉ ላይ አምና
ከነበረኝ ዘንድሮ ያለኝ ተስፋ ጨምሯል፡፡ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1፣ 2 እና 3
ስኳር ፋብሪካዎች በቅርቡ ወደ ማምረት ይሸጋገራሉ፡፡ ከሰምበግማሽ
አቅም ማምረት ጀምሯል፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሙሉ አቅሙ
ይደርሳል፡፡ ተስፋ አስቆራጭ የነበረው ተንዳሆም አሁን በሙሉ
አቅሙ ለመስራት ዝግጁ ሆኗል፡፡ በለስ አንድም በቅርቡ ይደርሳል
ብዬ አምናለሁ፡፡ የበለስ ሁለትን መለስተኛ ችግር ለመቅረፍ እየሰራን
ነው፡፡ ወልቃይትም ጥሩ እየሄደ ነው” በማለት ያላቸውን ተስፋ
አብራርተዋል፡፡
በጉብኝቱ የተሳተፉት የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች
የስኳር ኢንደስትሪው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ...
ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ በበኩላቸው
ፕሮጀክቱን ባለፈውም ዓመት መጎብኘታቸውን አስታውሰው በተለይ
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ፋብሪካ ግንባታ ተስፋ ሰጪ በሆነ መልኩ
እየተፋጠነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት ለኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር ማድረጉን
እንደሚቀጥል የገለጹት ርእሰ መስተዳድሩ፣ ኮርፖሬሽኑ በተለይ የክልሉን
ወጣቶች እና አርብቶ አደሮች የኑሮ ሁኔታ ከመቀየር አንጻር ትርጉም
ያለው ሥራ መስራቱን አድንቀዋል፡፡
በሌላ በኩል ርእሰ መስተዳድሩ ኮርፖሬሽኑ በምርምር ዘርፍ እያደረገ
ያለውን ጥረት በመስክ በመመልከት የተከናወኑ የምርምር ሥራዎችን
አድንቀዋል፡፡ በቆላማ አካባቢ የማይበቅሉ ሰብሎች ተሞክረው
ውጤታማ መሆናቸውም የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡
»» ከገጽ 1 የዞረ
አቶ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና
ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር
ሚኒስትሩ አክለውም “በስኳር ልማት ዘርፍ
የተለጠጠ እቅድ ይዘን እና ፈጥነን ወደ ሥራ
ለመግባት ከነበረን ጉጉት አኳያ በሂደት ብዙ
እንቅፋቶች ያጋጠሙንና ለከፍተኛ ወጪ
የተዳረግንበት ሁኔታ ቢኖርም እስካሁን
የመጣንበት ርቀት ለወደፊቱ የልማት
ጥረታችን እጅግ ጠቃሚ ትምህርት ሰጥቶን
ያለፈ መሆኑን ማጤን ይገባል፡፡” ብለዋል፡፡
በቀጣይ በዘርፉ የሚቀሩ ሥራዎችን
በማጠናቀቅ ወደ ስኬት ለመጓዝ ጠንክሮ
መስራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ሚኒስትሩ፣
በዚህ ረገድ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች
ሚኒስቴር ከልማት ጥረቱ ጎን በመሆን
ተፈላጊው ውጤት እንዲመጣ አስፈላጊውን
ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡
የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፍ
ግንባታ ተጠናቆ ጥቅምት 2007ዓ.ም የሙከራ
ምርት የጀመረ ቢሆንም፣ ባጋጠመው
የቴክኒክ ችግር እና ለቦይለር የሚውል የንጹህ
ውሃ እጥረት ምክንያት ለረጅም ጊዜያት
ቆሞ ነበር፡፡ ይሁንና በአሁኑ ወቅት ችግሮቹ
ተፈተው ስኳር በማምረት ላይ ይገኛል፡፡
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ፋብሪካውን በጎበኙበት ወቅት
ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም4 5e t h i o p i a n s u g a r. c o m
የስኳር ፋብሪካዎች የ2008 ዓ.ም የክረምት
ጥገና በግብአት አቅርቦትና በሰው ኃይል ልዩ
ዝግጅት ተደርጎበት መከናወኑን የኦፕሬሽንስ
ዘርፍ አስታወቀ፡፡ ጥገናው የተከናወነላቸው
ስኳር ፋብሪካዎች ወደ መደበኛ የምርት ሂደት
ገብተዋል፡፡
በስኳር ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽንስ ምክትል ዋና
ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ እንደገለጹት፤
በ2009 በጀት ዓመት በዝግጅት ምዕራፍ
የተካሄደው የክረምት ጥገና በመደበኛ ምርት
ውስጥ በሚገኙ አራት ነባርና ወደ ኦፕሬሽን
በመግባት ላይ ባሉ የተንዳሆና የአርጆ
ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካዎች የተከናወነ ሲሆን፣
የክረምት ጥገናው በግብአት አቅርቦትና በሰው
ኃይል ረገድ ልዩ ዝግጅት ተደርጎበት ወደ ሥራ
በመገባቱ ጥገናው በስኬት ተጠናቋል፡፡
ለክረምት ጥገናውና ለ2009 የምርት ዘመን
የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከሀገር ውስጥና
ከውጪ የማቅረብ፣ የሰው ኃይል የማሟላት
እንዲሁም በፋብሪካዎችና በኮርፖሬሽኑ
ዋና መስሪያ ቤት ደረጃ ሁሉንም ባለድርሻ
አካላትን ባሳተፈና መሠረታዊ ለውጥ
በሚያመጣ መልኩ ዝግጅት መደረጉን
የገለጹት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣
ይህም የክረምት ጥገናው በስኬት መጠናቀቅ
ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል ብለዋል፡፡
የጥገናው ዝግጅት የኮርፖሬሽኑን የገንዘብ
አቅም፣ በመጋዘኖች ያለውን መለዋወጫ
እንዲሁም የውጪ ምንዛሪ ግኝትን ታሳቢ
ያደረገ በመሆኑ ጥገናው ከዚህ በፊት
ከተደረጉ ተመሳሳይ የክረምት ጥገናዎች
ልዩ እንደሚያደርገው የጠቆሙት አቶ ወዮ፣
ይህም የ2009 የምርት ሂደት ሳይስተጓጎል
እንዲቀጥል ያስችላል የሚል እምነት
እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በ2008 ዓ.ም የምርት ሥራውን ያደናቀፉና
በውጪ ባለሙያዎች የተለዩ እንዲሁም
በ2009 የምርት ሂደት ተፅዕኖ ሊፈጥሩ
ይችላሉ የተባሉ ችግሮች ተለይተውና ቅደም
ተከተል ወጥቶላቸው መለዋወጫ ከውጪ
ገብቶ እንዲጠገኑ መደረጉንም ምክትል ዋና
ሥራ አስፈጻሚው አክለው ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት የ2008
ዓ.ም የክረምት ጥገና አፈጻጸም ሲገመገም
ከሌሎች ተመሳሳይ የክረምት ጥገናዎች
የተሻለ፣ በቂ ጊዜ ተሰጥቶትና አስፈላጊው
ግብአት ቀርቦለት ጥራቱን ጠብቆ የተከናወነ
ነው ብለዋል፡፡
የክረምት ጥገናው የተሳካ እንዲሆን
የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ፣
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴርና
ሌሎች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ
ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ አስተዋጽኦ
ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡
የክረምት ጥገናውን መጠናቀቅ ተከትሎ
የወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ፣ ከሰም፣
ተንዳሆና አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካዎች
ወደ መደበኛ የምርት ስራ ውስጥ
መግባታቸውን አቶ ወዮ አስታውቀዋል፡፡
በታህሳስ ወር ወደ ስራ ከገባው አርጆ ዲዴሳ
ስኳር ፋብሪካ በስተቀር የተቀሩት አምስት
ፋብሪካዎች ከህዳር 2009 ዓ.ም ጀምሮ ወደ
ምርት ሂደት መግባታቸውን ያመለከቱት አቶ
ወዮ፣ አጀማመራቸውም ካለፉት አመታት ጋር
ሲነጻጸር የተሻለ ነው ብለዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የክረምት ጥገና ከተደረገላቸው
ስድስት ፋብሪካዎች በተጨማሪ የኦሞ
ኩራዝ ቁጥር 1 እና 2 አዳዲስ ፋብሪካዎችን
ሥራ በማስጀመር በ2009 በጀት አመት 7
ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ ስኳር በማምረት
የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማሟላት አቅዶ
እየሰራ ነው፡፡
የፋብሪካዎች የክረምት ጥገና በልዩ ዝግጅት መከናወኑ ተገለጸ
• ፋብሪካዎቹ ወደ መደበኛ የምርት ሂደት ገብተዋል
ስኳር ኮርፖሬሽን የ2009ዓ.ም ዕቅድን
ለማሳካት እንዲረዳው በየደረጃው ለሚገኙ
ከፍተኛና መካከለኛ አመራር አካላት በሦስት
ዙር ስልጠና ተሰጠ፡፡
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሽን አካዳሚ
በተሰጠው ሥልጠና የኮርፖሬሽኑን ዋና
ሥራ አስፈጻሚ ጨምሮ ከዋና መስሪያ
ቤት፣ ከስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች
የተውጣጡ ከፍተኛ እና መካከለኛ የሥራ
መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ሥልጠናው የሀገሪቱ ስኳር ኢንዱስትሪ
የተጋረጡበትን ችግሮች ከመፍታትና
ውጤታማ ስኳር ኢንዱስትሪ ከመገንባት
አንጻር ይስተዋሉ የነበሩ የዕውቀትና
የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት እንደሚረዳ
ታምኖበታል፡፡
ስልጠናውን የተከታተሉ የኮርፖሬሽኑ የሥራ
መሪዎች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተገኙ
ተሞክሮዎችንና ልምዶችን ከኮርፖሬሽኑ
ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ተቀምሮና
የማስፈጸሚያ ፓኬጅ ተቀርጾለት ተግባራዊ
መደረግ እንደሚገባው ስምምነት ላይ
ደርሰዋል፡፡
ይህንን በተግባር የተደገፈ የንድፈ ሃሳብ
ሥልጠና የሠጡት የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ዋናሥራ አስፈጻሚአቶ ተወልደገብረማርያም
እና ሌሎች ከፍተኛ የአየር መንገዱ የሥራ
ሓላፊዎች ናቸው፡፡
በዚሁ ወቅት የስልጠናው ተሳታፊዎች የአየር
መንገዱን የጥገና ክፍልና ሌሎች የሥራ
ክፍሎችን ጎብኝተዋል፡፡
ሥልጠናው Facility and resource utiliza-
tion, coping with Changing situations,
leading corporations successfully,
Corporate finance, performance man-
agement, and leadership በሚሉ ርዕሰ
ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
ሥልጠናውን ያስተባበረው የኮርፖሬሽኑ
የሰው ሃብት አመራርና ልማት የሥራ ክፍል
ነው ፡፡
የኮርፖሬት ሊደርሺፕ ሥልጠና ተሰጠ
ለኮርፖሬሽኑ የፋይናንስና የኦዲት ባለሙያዎችና
ሓላፊዎች በዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት
ሥርዓት ላይ ሥልጠና ተሰጠ
የኦፕሬሽንስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ስልጠና ሲሰጡ
ለስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት፣ ለፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የፋይናንስ
እና የኦዲት ባለሙያዎችና ሓላፊዎች በዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት
ሥርዓት (IFRS) ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የተሰጠውን ሥልጠና
ያዘጋጁት የኮርፖሬሽኑ የሰው ሃብት ልማት እና የፋይናንስ የሥራ ክፍሎች
ከኮሌጁ የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ዲፓርትመንት ጋር በመሆን ነው፡፡
የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ይትባረክ ተክሌ ሥልጠናውን አስመልክተው በሰጡት
ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ወደሚጠይቅ ኢንዱስትሪ
እየገባች በመሆኑ ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት ያለው የፋይናንስ ሪፖርት
ያስፈልጋል ማለታቸውን ዩኒቨርሲቲው በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡
በሦስት ዙሮች በተሰጠው ሥልጠና 200 የፋይናንስና የኦዲት ባለሙያዎች
ተካፍለዋል ፡፡
ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ሥርዓት (IFRS) ለመጀመሪያ
ጊዜ ሥራ ላይ የዋለው በአውሮፓ ሕብረት ሲሆን፣ ዓላማውም
የንግድ ጉዳዮችና ሒሳቦቻቸውን በአህጉሪቱ በቀላሉ ተደራሽ
ለማድረግ ነው፡፡ ሥርዓቱ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለመግባባት
ምቹ ሆኖ በመገኘቱ በአጭር ጊዜ በመላው ዓለም ተቀባይነቱ
ሊሰፋ ችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሪፖርት ሥርዓቱ በ120 ሀገራት
በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም6 7e t h i o p i a n s u g a r. c o m
»» ወደ ገጽ 8 ዞሯል
በቻይና የጃንግዚ ግዛት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተመራ የልዑካን
ቡድን ከስኳር ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር ተወያየ
በቻይና የጃንግዚ ግዛት ምክትል ርዕሰ
መስተዳድር የተመራ የልዑካን ቡድን ከስኳር
ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር በተለያዩ የትብብር
መስኮች ላይ ተወያየ፡፡
በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ
በተካሄደው ውይይቱ የግዛቲቱ ምክትል
ርዕሰ መስተዳድር ሚስተር ሊዩ ቻንግሊን
የቻይና መንግሥት በኢትዮጵያ በተለይም
በስኳር ኢንዱስትሪው መስክ የሚያደርገውን
ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል
ገልጸዋል፡፡ በኢንቨስትመንትና በፋይናንስ
ረገድ የተጀመረው ትብብር በቀጣይነት
እየጎለበተ እንደሚሄድም ነው የተናገሩት፡፡
የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ
አቶ እንዳወቅ አብቴ በበኩላቸው በስኳር
ኢንዱስትሪው ከተሰማሩት የቻይና
ኩባንያዎች ጋር ጠንካራና መልካም ግንኙነት
እንዳላቸው አስታውሰው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ
ከሚገኙ 13 ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች
ውስጥ አምስቱ በቻይና መንግሥት በተገኘ
ብድርና በቻይናውያን ኮንትራክተሮች
እየተገነቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተለይም በቀን 24 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት
አቅም ያለው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር
ፋብሪካ ከጃንግዚ ግዛት በተገኘ ገንዘብና
የግዛቱ ኩባንያ በሆነው JJIEC በመገንባት ላይ
መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከጃንግዚ ግዛት ጋር በስኳር ልማት
ዘርፍ የተጀመረው ትብብር ተጠናክሮ
እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት የገለጹት ዋና
ሥራ አስፈጻሚው፣ በቀጣይ የአቅም ግንባታ
ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡
አክለውም በዘርፉ በቀጥታ የውጪ
ኢንቨስትመንት/FDI እና በሽርክና/Joint ven-
ture ለመስራት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን
ጠቁመው፣ የቻይና ኩባንያዎች ወደ ሀገር
ቤት መጥተው በስፋት እንዲሰማሩ ጥሪ
አቅርበዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ 38 ባለሙያዎችን ለሥልጠና ወደ ቻይና ላከ
ስኳር ኮርፖሬሽን ከቻይናው ኮምፕላንት
ኩባንያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ሥልጠና
ላይ ለመሳተፍ 38 ባለሙያዎች ህዳር
23/2009ዓ.ም ወደ ቻይና ሄደዋል፡፡
ሠልጣኞቹ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር
ፋብሪካ ሥራ ሲጀምር በሚሰለጥኑበት
መስክ የሚሰማሩ ሲሆን፣ በሁለት ወራት
የቻይና ቆይታቸው ለሁለት ሳምንት የንድፈ
ሃሳብ፣ በቀሪው ጊዜ ደግሞ በቻይና የስኳር
ፋብሪካዎች ተገኝተው በተግባር የተደገፈ
ሥልጠና እንደሚከታተሉ ታውቋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽንስ ም/ዋና ሥራ
አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ሠልጣኞችን ሲሸኙ
ባደረጉት ንግግር፣ ኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎቹ
ከሥልጠና መልስ ውጤት የሚያመጡ
ሥራዎችን ያከናውናሉ ብሎ እንደሚያምን
አመልክተዋል፡፡
የሰው ሃብት አመራርና ልማት ሥራ አስፈፃሚ
ወይዘሮ አዛለች ለማ በበኩላቸው ሠልጣኞቹን
“ከሥልጠናው ብቻ ሳይሆን ከምትሄዱበት
ቦታም የሥራ ባህልን ተማሩ” ብለዋል፡፡
ሥልጠናው የሚያተኩረው በኤክስትራክሽን፣
በፕሮሰስ፣ በፓወር ፕላንት፣ በDCS እና PLC
እንዲሁም በወተር ትሪትመንት ዙሪያ መሆኑ
ተገልጿል፡፡
በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት
እየተገነቡ ከሚገኙ አራት ስኳር ፋብሪካዎች
ውስጥ አንዱ የሆነው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር
ሁለት ፋብሪካ ግንባታ በቻይናው ኮምፕላንት
እየተካሄደ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት ሥራ
ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታን ለማፋጠን
በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ
የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታን
ከማፋጠን ጋር በተያያዘና በሌሎች ተዛማጅ
ጉዳዮች ዙሪያ JJIEC ከሚባል የቻይና
ኮንትራክተር እና Sino Sure ከተባለ የቻይና
የኢንሹራንስ ኩባንያ ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
በስኳር ኮርፖሬሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ
በተደረገው በዚህ ውይይት ኮርፖሬሽኑን
በመወከልአቶአብርሃም
የስኳር ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት፣
የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የሥራ
ሓላፊዎችና ሠራተኞች “ሕገ መንግሥታችን
ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችንና ለህዳሴያችን!”
በሚል መሪ ቃል 11ኛውን የኢትዮጵያ
ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን
በተለያዩ ዝግጅቶች አከበሩ፡፡
በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህዳር 20 ቀን
2009ዓ.ም በተከበረው በዚህ በዓል ላይ
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ
አቶ በዛብህ ገብረየስ በዓሉን አስመልክተው
ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች
መተማመንንና መቻቻልን እንደ ቁልፍ የሀገር
ግንባታ ዕሴቶች በመውሰድ አንድነትና
ብዝሃነትን አጣጥመው አንድ የጋራ ሀገራዊ
ማኅበረሰብ ለመገንባት ያስቻለ የፌዴራል
ሥርዓት መመስረታቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ሀገሪቷ ከደርግ ውድቀት በኋላ
በመሰረተችው ሕብረ-ብሔራዊ የፌዴራል
ሥርዓት ባለፉት 25 ዓመታት በሁሉም
መስኮች በርካታ ስኬቶችን ለማስመዝገብ
ችላለች ብለዋል፡፡
የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የተጀመረውን
የህዳሴጉዞበማጠናከርረገድባለፉትአመታት
በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እንዲወጠኑ
መሰረት ጥሏል ያሉት አቶ በዛብህ፣ ከፍተኛ
ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተካሄዱ ካሉ ሜጋ
ፕሮጀክቶች አንዱ የስኳር ልማት ዘርፍ
መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን
ዕቅድ ዘመን ባጋጠሙ የተለያዩ ተግዳሮቶች
በዘርፉ የታቀደውን ያህል ውጤት ማግኘት
አልተቻለም ያሉት አቶ በዛብህ፣ ይሁንና
በዕቅዱ ዓመታት በስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ
ዘርፍ በተከናወኑ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ሀገሪቱ
በ2016ዓ.ም በዓለም ከሚገኙ ከፍተኛ
የስኳር አምራች አገሮች ተርታ መሰለፍ
የምትችልበትን እድል እውን ለማድረግ
የሚያስችሉ መደላድሎችን ለመፍጠር
መቻሉን ገልጸዋል፡፡
አክለውም “በሁለተኛው የእድገትና
ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በስኳር ልማት
ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት ሕገ
መንግስቱ ለሀገራችን ህዳሴ መሰረት መሆኑን
እናረጋግጣለን” ብለዋል፡፡
በዕለቱ “ሕብረ ብሔራዊ የጋራ ሀገር ግንባታ”
በሚል ርዕስ በአቶ መንግሥተአብ ገ/ኪዳን
የኮርፖሬት ሪፎርምና አቅም ግንባታ አማካሪ
ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሁፍ ቀርቦ
በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመጨረሻም በዓሉን አስመልክቶ በኢፌዲሪ
ሕገ መንግሥት፣ በፌደራሊዝም ሥርዓትና
በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የቀረበ የጥያቄና
መልስ ውድድር አሸናፊዎች ከእለቱ የክብር
እንግዳ እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በዓሉ በስኳር ፋብሪካዎችና
ፕሮጀክቶች በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ
ሁኔታ ተከብሯል፡፡
የስኳር ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት፣ የፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች
ሠራተኞች የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አከበሩ
                                     
አቶ መንግሥተአብ ገ/ኪዳን የኮርፖሬት ሪፎርምና አቅም ግንባታ አማካሪ የውይይት መነሻ ጽሁፍ ባቀረቡበት ወቅት
ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም8 9e t h i o p i a n s u g a r. c o m
የጸረ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ቀን በኮርፖሬሽን ደረጃ ተከበረ
                                     
29ኛው አለም አቀፍ የጸረ ኤች አይ ቪ/ኤድስ
ቀን በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት፣
በስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች በተለያዩ
ዝግጅቶች ተከበረ፡፡
በዓሉ በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ህዳር
22 ቀን 2009ዓ.ም በተከበረበት ወቅት የዋና
ሥራ አስፈጻሚው ተወካይ አቶ በዛብህ
ገብረየስ እንደተናገሩት፣ ኤች አይ ቪ/
ኤድስን ለመግታት ወደ ራሳችን በመመልከት
መድሎና እና መገለልን አስወግደን ለቀጣይ
ዕድገት እንትጋ ብለዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የጸረ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ግብረ
ኃይል ሰብሳቢ አቶ ዘመድኩን ተክሌ በአሉን
አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት
ወረርሽኙ ሰፋፊ የመንግሥት የልማት
ፕሮጀክቶች በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች
እና በገጠራማ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተስፋፋ
መምጣቱ የሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት የጀርባ
አጥንት የሆነው የግብርናው እና የስኳር ልማት
ክፍለ ኢኮኖሚ ምርታማነት እንዲቀንስ እና
በምግብ እህል ራስን የመቻል ሀገራዊ ጥረት
ለአደጋ እንዲጋለጥ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
ኤች አይ ቪ/ኤድስ የልማት ችግር ያልሆነባት
ኢትዮጵያን ማየትን ራዕያችን እናድርግ
ብለዋል አቶ ዘመድኩን በማጠቃለያቸው፡፡
በዓሉን የተመለከተ የመወያያ ጽሑፍ
በኮርፖሬሽኑ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ሴክሬታሪያት
ከፍተኛ ባለሙያ ሲስተር ትዕግስት ዓለሙ
ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመጨረሻም በኮርፖሬሽኑ ኤች አይ ቪ/
ኤድስ መከላከያና መቆጣጥሪያ ሴክሬታሪያት
ሲስተር ካሰች ሺበሺ አስተባባሪነት
የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ገንዘብ በማዋጣት
ድጋፍ እያደረጉላቸው የሚገኙ በኤች አይ
ቪ/ኤድስ ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናት
ከኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ጋር ተዋውቀዋል፡፡
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የሙዚቃ ቡድን
የተለያዩ ጣዕመ ዜማዎችን በማቅረብ ለበዓሉ
ድምቀት ሰጥቷል፡፡
የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረአ
የስኳር ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች
ዘጠነኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ
ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነታችን
መገለጫ፣ በብዝሃነታችን ላይ ለተመሰረተው
አንድነታችን ዓርማ ነው” በሚል መሪ ቃል
ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም አከበሩ፡፡
በአሉ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶችም
ተከብሯል፡፡
በዋና መ/ቤት በተከበረው በዓል ላይ
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ
እንዳወቅ አብቴ ባስተላለፉት መልዕክት፣
ሰንደቅ ዓላማ ከብሔራዊ ኩራት ምልክትነት
ባሻገር የአንድን ሀገር ሕዝብና መንግሥት
ራዕይና ስኬት ጥልቀት ባለው ሁኔታ አጠቃሎ
የያዘ ዓርማ ነው ብለዋል፡፡
ሰንደቅ ዓላማ የመንግሥትና ሕዝብ
ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ሥልጣንና ነፃነት፣
እድገትና ማኅበረሰባዊ ትስስር መገለጫ ነው
ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ከዚህ አንጻር
የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች ሕገ
መንግሥታዊና ሕዝባዊ መሰረት ያለውን
የሀገሪቷን ሰንደቅ ዓላማ በመጠበቅ፣
በማክበርና በማስከበር ልዕልናን የማረጋገጥ
ሓላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
በመልዕታቸው ማጠቃለያም የተስፋ ዓርማ
በሆነው ሰንደቅ አላማ ነጸብራቅ ውስጥ
የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሠራተኛ የስኳር
ልማት ዘርፍ ግቦችን አሻግረው በመመልከት
ለስኬቱ በላቀ ቁርጠኝነት እንዲረባረቡ ጥሪ
አቅርበዋል፡፡
በዓሉን በማስመልከት “የኢትዮጵያ ሰንደቅ
ዓላማና ዴሞክራሲያዊ አንድነት በኢፌዲሪ
ሕገ መንግሥት” በሚል ርዕስ በአቶ ፋሲል
ገ/ማርያም የሕግ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ
ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሁፍ ቀርቦ
ውይይት ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም የቃለ መሃላና የኢትዮጵያን
ሰንደቅ አላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት
ተካሂዷል፡፡
በተያያዘ ዜና ዘጠነኛው ብሔራዊ የሰንደቅ
ዓላማቀንበስኳርፋብሪካዎችናፕሮጀክቶችም
በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን ከሆራይዘን አዲስ ጎማ አክስዮን ማኅበር ጋር
የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
ስኳር ኮርፖሬሽን በስኳር ፋብሪካዎች
እና ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች
የሚያስፈልጉ ፍሎቴሽን ጎማዎችን
ሆራይዘን አዲስ ጎማ አ.ማ አምርቶ
እንዲያቀርብለት የመግባቢያ ሰነድ
ተፈራረመ፡፡
በሸራተን አዲስ በተካሄደ የመግባቢያ
ሰነድ ፊርማ ሥነ ስርዓት ላይ
የሚድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያ
በሆነው ሆራይዘን ፕላንቴሽን አክስዮን
ማኅበር ስር የተቋቋመው ሆራይዘን
አዲስ ጎማ አ.ማ ስኳር ኮርፖሬሽን
በየዓመቱ የሚፈልጋቸውን 20 ሺህ
ፍሎቴሽን ጎማዎችን ለማምረት ተስማምቷል፡፡
ኮርፖሬሽኑን በመወከል የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት የኦፕሬሽንስ
ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወዮ ሮባ፣ ለስኳር ኢንደስትሪው
ከባድ ማሽኖች እና ተሽከርካሪዎች የተለያዩ አይነት ጎማዎች በከፍተኛ
የውጪ ምንዛሪ እንደሚገዙ በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
የተደረሰው ስምምነትን አስመልክቶ ሲናገሩም፣ “ሀገር በቀል ኩባንያው
የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታን ለማፋጠን...
ደምሴ የኢንቨስትመንት ጥናትና ልማት ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኦሞ
ኩራዝ ቁጥር 5 ፋብሪካን እና አጠቃላይ የስኳር ኢንዱስትሪው
ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ በኮርፖሬሽኑ በኩል በመከናወን ላይ
የሚገኙ ሥራዎችን አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም ከቻይና የልዑካን
ቡድን ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት የፋብሪካውን ግንባታ ለመጀመር የሚያስፈልጉ የዝግጅት
ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን እና የፋብሪካው ግንባታም
በ2011ዓ.ም ተጠናቆ ሥራ እንደሚጀምር በኮንትራክተሩ ተገልጿል፡፡
የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት
ሲጀምር በቀን 24ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፡፡
በምንፈልገው መጠን፣ ብዛት እና ጥራት ማምረቱ ለኮርፖሬሽኑ እፎይታ
እንዲሁም የውጪ ምንዛሬን ለማዳን
የሚያስችል ነው፡፡ ከአሁን በኋላ
ውጪ ማየት አቁመን ጎማ ከበራችን
ላይ እናገኛለን፡፡ ” ብለዋል፡፡
ሆራይዘን ፕላንቴሽን አክስዮን
ማኅበርን በመወከል የመግባቢያ
ሰነዱን የፈረሙት የተቋሙ ዋና ሥራ
አስኪያጅ አቶ አካለወልድ አድማስ
በበኩላቸው፣ “በሀገር ምርት የማመን
ትልቅ ነገር በስኳር ኮርፖሬሽን
አይተናል፡፡ ፍሎቴሽን ጎማውን
የማምረት በቂ ቴክኖሎጂ እና የመዋዕለ
ነዋይ ዝግጅት አለን፡፡ የስኳር ልማት ዘርፍ ከሀገሪቱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች
አንዱ መሆኑንም እንረዳን፡፡” ብለዋል፡፡
ሆራይዘን አዲስ ጎማ አ.ማ በዓለም በጎማ ኢንደስትሪ በትልቅነቱ ሦስተኛ
ደረጃ ላይ ከሚገኘው ኮንቲነንታል ጀርመን ጋር አብሮ የሚሰራ በመሆኑ
ለስኳር ኮርፖሬሽን የሚያመርታቸውን ጎማዎች በጥራት እና በብዛት
ለማቅረብ እንደሚያስችለው በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡
»» ከገጽ 7 የዞረ
በኮርፖሬሽኑ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጥሪያ ሴክሬታሪያት ሲስተር ካሰች ሺበሺ በዓሉን አስመልክተው ማብራሪያ ሲሰጡ
ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት
ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም10 11e t h i o p i a n s u g a r. c o m
የመሠረታዊ ሠራተኛ ማኅበር የመጀመሪያ የምክር ቤት
ስብሰባ ተካሄደ
የስኳር ኮርፖሬሽን የመሠረታዊ ሠራተኛ ማኅበር ምክር ቤት
የመጀመሪያ ስብሰባውን ኅዳር 1/2009 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ
ቤት አካሄደ፡፡
የምክር ቤቱ 50 አባላት የተገኙበትን ስብሰባ በንግግር የከፈቱት
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ እንዳስታወቁት፣
በሠራተኛውና በማኅበሩ እንዲሁም በአመራሩ መካከል ጤናማ
የሥራ ግንኙነት በመፍጠር በስኳር ልማት ዘርፍ የተጀመረውን ወገብ
የሚያጎብጥ ዕቅድ ለስኬት እናበቃለን ብለዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት ለማኅበሩ አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር
እንደሚያደርግ እና በቅርበትም እንደሚሰራ አክለው ገልጸዋል፡፡
የሠራተኛ ማኅበሩ ሊቀመንበር አቶ ተመስገን ወልደ መስቀል
በበኩላቸው ማኅበሩ ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር ተቀራርቦ በመስራት እና
ችግሮችም ሲያጋጥሙ በጋራ በመፍታት በስኳር ልማት ዘርፍ ተቀመጡ
ግቦችን ለማሳካት እንደሚረባረቡ ተናግረዋል፡፡
የምክር ቤቱ አስተባባሪ እና የሠራተኛ ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ
ኮሚቴ አባል አቶ ተሾመ ያሚ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ እና ዋና ሥራ
አስፈጻሚው ለነባር ፋብሪካዎች ሠራተኞች ባለፉት ዓመታት ተቋርጦ
የነበረው የማትጊያ ክፍያ እንዲፈጸም በማድረጋቸው አመስግነዋል፡፡
ይህም በነባር ፋብሪካዎችም ሆነ ወደ ምርት በሚገቡ አዳዲስ ስኳር
ፋብሪካዎች የሚሰሩ ሠራተኞችን በማነቃቃት የኮርፖሬሽኑን ዕቅድ
ለማሳካት እንደሚያስችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በስብሰባቸው ማጠቃለያ ባወጡት የአቋም
መግለጫ በስራቸው የታቀፉ አባላትን አስተባብረው በነባርና ወደ
ምርት በሚገቡ አዳዲስ ፋብሪካዎች ውጤታማ ሥራ በማከናወን
የኮርፖሬሽኑ ግቦች እንዲሳኩ ጠንክረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡
፡ በተጨማሪም የስኳር ኢንዱስትሪው ሰላምን ጠብቆ ለማቆየት
አስታውቀዋል፡፡
ህዳር 2008 ዓ.ም በአዲስ መልክ የተቋቋመው የስኳር ኮርፖሬሽን
መሠረታዊ የሠራተኛ ማኅበር ኮርፖሬሽኑ ካሉት ቋሚ እና ጊዜያዊ
ሠራተኞች ሁለት ሦስተኛውን ያቀፈ ነው፡፡
በፕሮጀክቱ ቅጥር ግቢ የአንደኛ ክፍል መደበኛ ትምህርት መስጠት ተጀመረ
በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በመለስ ጠቅላይ ሰፈር የአንደኛ
ክፍል መደበኛ ትምህርት መስጠት ተጀመረ፡፡
በተያዘው የትምህርት ዘመን በፕሮጀክቱ ቅጥር ግቢ የፕሮጀክቱ
ሠራተኞች ልጆች የሆኑ 38 ሕፃናት የአንደኛ ክፍል መደበኛ ትምህርት
በመማር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ከፕሮጀክቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል በደረሰን መረጃ የፕሮጀክቱ
ማህበረሰብ ለረጅም ጊዜ ሲያነሳው የነበረውን የመደበኛ ትምህርት
ይከፈትልን ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የፕሮጀክቱ የህዝብ አደረጃጀት
ዘርፍ ከጃዊ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
ባደረገው ውይይት ይሁንታ አግኝቷል፡፡ በዚህ መሰረት ተጠሪነቱ
ለአሊኩራንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሆነ የ1ኛ ክፍል ሳተላይት
ት/ቤት ተከፍቷል፡፡
የተማሪዎቹ ወላጆች በበኩላቸው ልጆቻቸው በቅርበት የትምህርት
ዕድል በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ቀጣዮቹን
ክፍሎች ደረጃ በደረጃ ለመክፈት እንዲሁም መምህራን እና ቁሳቁስ
ለማሟላት ቃል መግባቱን ማወቅ ተችሏል፡፡
በአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ የኤችአይቪ/ኤድስ ምርመራ ተካሄደ
በአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ከጥቅምት 16 እስከ ህዳር 30/2009ዓ.ም
ድረስ በተደረገ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ምርመራ 504 የፋብሪካው ሠራተኞች
መመርመራቸውን የፋብሪካው ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡
ፋብሪካውና የጅማ አርጆ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በጋራ ባዘጋጁት በዚህ
የምርመራ አገልግሎት ከ400 በላይ ሠራተኞች በፈቃደኝነት ተመርምረው
ራሳቸውን አውቀዋል፡፡
በርካታ ሰው በአንድ ጊዜ በብዛት ሊመረመር የቻለበትን ምክንያት የህዝብ
ግንኙነት ክፍሉ ሲገልጽ፣ ሠራተኛው በአቻ ለአቻ ትምህርት በማግኘቱ እና
በዚህም የባሕርይ ለውጥ በመምጣቱ ነው ብሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋብሪካው ሠራተኞች ህዳር 22 ቀን 2009ዓ.ም የዓለም
በፕሮጀክቱ ከ13ዐ በላይ የአገዳ ዝርያዎችን ለማላመድ እየተሞከረ ነው
በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከ130
በላይ አዳዲስ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችን
ለማላመድ እየተሞከረ መሆኑን ፕሮጀክቱ
አስታወቀ፡፡
የፕሮጀክቱ የምርምር ቡድን መሪ አቶ ኪዳኔ
ተ/ሚካኤል በስኳር ምርት ላይ የምርታማነትና
የጥራት ችግር እንዳያጋጥም ቅድሚያ ትኩረት
በመስጠት ልዩ ልዩ ባህሪያት ያላቸውን የአገዳ
ዝርያዎች በማሰባጠር ማላመድ ማስፈለጉን
ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሠረት ከተለያዩ የምርምር ማዕከላት
የመጡ ከ13ዐ በላይ ዝርያዎች በፕሮጀክቱ
ተተክለው እንዲላመዱ እየተደረገ ነው
ብለዋል፡፡
በፕሮጀክቱ ከዚህ ቀደም የነበሩ የዝርያ
ዓይነቶች ጥቂት እንደነበሩ ያስታወሱት
ቡድን መሪው፣ በሙከራ ላይ ለሚገኙ የአገዳ
ዝርያዎች ልዩ ክትትል እየተደረገ መሆኑን
አብራርተዋል፡፡
በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት እየተገነቡ
ለሚገኙት ሁለት ፋብሪካዎች እስካሁን 13 ሺህ
ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ ተሸፍኗል፡፡
የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄደ
የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም
ለሁለተኛ ጊዜ በስኳር ኮርፖሬሽን ተካሄደ፡፡
በወንጂ ሸዋና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም በኦሞ ኩራዝና
ወልቃይት ፕሮጀክቶች የተካሄደው ይህ ፕሮግራም በአካባቢ ልማት፣
በኪነ ጥበባት፣ በትምህርትና በሰብዓዊ አገልግሎት ነው፡፡
በዚህም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሰማራት በማኅበረሰቡ ዘንድ
ከፍተኛ መነቃቃትን መፍጠር እንዲሁም ሠራተኞችና የአካባቢው
ማኅበረሰብ ስለ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰፊ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ
ተችሏል፡፡
ዘንድሮ በልዩ ልዩ የአካልና የአዕምሮ ብቃት ማጎልበቻ ስፖርቶች የጎላ
እንቅስቃሴ ከመካሄዱም በላይ በተለይ የሴቶችና የወንዶች የእግር
ኳስ ውድድሮች በዙር ሲደረጉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የስፖርት
አፍቃሪዎችና ፕሮፌሽናል አሠልጣኞች መታደማቸው በሙያው
ለመቀጠል ዝንባሌ ላላቸው ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር
ተጠቁሟል፡፡
ፕሮግራሙ ከውስጥ ደንበኞች በተለይም ከካይዘን፣ ከጤና፣ ከስነ
ምግባር፣ ከህዝብ አደረጃጀት፣ ከህዝብ ግንኙነት እና ከአካባቢ ጥበቃ
ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ በመሆኑ ለቀጣይ ሥራዎች
የተጠናከረ ትስስር መፍጠር እንዳስቻለም ታውቋል፡፡
የተፈጠረውን የተነሳሽነት መንፈስ በበጋው ወራት አጠናክሮ
ለማስቀጠል መታቀዱና በሁሉም ንዑሳን ፕሮግራሞች ወንዶችና
ሴቶች በእኩልነት መሳተፋቸውም ተመልክቷል፡፡
ባለፈው ዓመት በኮርፖሬሽኑ በተካሄደ የክረምት ወራት የወጣቶች
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም 4,679 ወንዶችና 1,331 ሴቶች
በድምሩ 6 ሺህ 10 ወጣቶችን በቀጥታ በተለያዩ ፕሮግራሞች
እንዲሳተፉ በማድረግ የወጣቶችን ማኅበራዊ ተሳትፎ ማጎልበት
መቻሉን የኮርፖሬት ሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ገልጿል፡፡ በጎ ፈቃደኛ
ወጣቶቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ182,401 ብር በላይ የሚገመት
ውጤታማ ተግባራትን ማከናወናቸውም ታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኮርፖሬት ሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ በወንጂ
ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለተቋቋመ ቤተ መፃህፍት
ከግለሰብ ለጋሾች ያሰባሰባቸውን ዋጋቸው 20 ሺህ ብር የሚገመት
መፃህፍት በስጦታ አበርክቷል፡፡
ኤድስ ቀንን “አሁንም ትኩረት ለኤች.አይ.ቪ መከላከል” በሚል
መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበራቸውን የህዝብ ግንኙነት
ክፍሉ ዘግቧል፡፡
ቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም12 e t h i o p i a n s u g a r. c o m
እናስተዋውቃችሁ
ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ፣ ከመተሐራ ስኳር
ፋብሪካ ደግሞ 50 ኪ.ሜ ያህል የሚርቀው
ይህ ፋብሪካ፣ በአፋር ክልል በዞን ሦስት
አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች ውስጥ
ይገኛል፡፡
ፕሮጀክቱ 500 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
ውሃ የመያዝ አቅም ባለው የከሰም ግድብ
አማካኝነት የሚለማ 20ሺህ ሄክታር የሸንኮራ
አገዳ መሬት ይኖረዋል፡፡ የአገዳ ልማቱም
የሚከናወነው በከሰም እና ቦልሀሞን በተሰኙ
አካባቢዎች ነው፡፡
የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የመተሐራ
ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል
ሆኖ የተጀመረ ቢሆንም ስኳር ኮርፖሬሽን
ከተቋቋመ ወዲህ ቦታው ከመተሐራ ስኳር
ፋብሪካ ካለው ርቀት አንፃር ተመዝኖና
ተጠንቶ እራሱን ችሎ እንደ አንድ የስኳር
ፋብሪካ እንዲንቀሳቀስ ተደርጓል፡፡
ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው
ይህ ፋብሪካ፣ በ2007ዓ.ም መጨረሻ ላይ
የሙከራ ምርት ጀምሯል፡፡ አሁን ስኳር
እያመረተ ሲሆን፣ በሂደት በቀን 6ሺህ ቶን
አገዳ የመፍጨት አቅም ላይ እንደሚደርስ
ይጠበቃል፡፡ ፋብሪካው በቀጣይ 10ሺህ ቶን
ሸንኮራ አገዳ በቀን ወደሚፈጭበት ደረጃ
እያደገ የሚሄድ ሲሆን፣ የኤታኖል ፋብሪካና
የኮጀነሬሽን ፋሲሊቲም ይኖረዋል፡፡
ፋብሪካው በመጀመሪያ ምዕራፍ በዓመት
1 ሚሊዮን 530ሺህ ኩንታል ስኳር እና 12
ሚሊዮን 500ሺህ ሊትር ኢታኖል የማምረት
አቅም የሚኖረው ሲሆን፣ ሙሉ የማምረት
አቅሙ ላይ ሲደርስ ደግሞ በዓመት 2 ሚሊዮን
600ሺህ ኩንታል ስኳር እና 30 ሚሊዮን
ሊትር ኤታኖል ማምረት ይችላል፡፡ ከዚህ
ባሻገር 26 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል
በማመንጨት 15 ሜጋ ዋቱን ለብሔራዊ
የኃይል ቋት እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡
የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ
•	 3ሺህ 161 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤
•	 	የ20.5 ኪ.ሜ የዋና ቦይ ግንባታ
ተጠናቋል፤
የአገዳ ልማት
•	 በፋብሪካው አማካኝነት 2ሺህ 432
ሄክታር መሬት እንዲሁም በአሚባራ
እርሻ ልማት (አውት ግሮወር) 6ሺህ
ሄክታር መሬት በአጠቃላይ 8 ሺህ 432
ሄክታር በአገዳ ተሸፍኗል፤
የቤቶች ግንባታ
•	 517 የመኖሪያ ቤቶች እና 20
አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮች)
ተገንብተዋል፤
ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ሲጎበኙ
የከሰም ስኳር ፋብሪካ

More Related Content

What's hot

ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ምጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ምMeresa Feyera
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007Ethiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation
 

What's hot (8)

ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ምጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
 
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
 

Viewers also liked

Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013Ethiopian sugar corporation facts – December 2013
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013Ethiopian Sugar Corporation
 

Viewers also liked (8)

Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
 
Ethiopian Sugar Industry Profile - Jan 2015
Ethiopian Sugar Industry Profile - Jan 2015Ethiopian Sugar Industry Profile - Jan 2015
Ethiopian Sugar Industry Profile - Jan 2015
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
 
Comparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industryComparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industry
 
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar Corporation
 
External vacancy
External vacancyExternal vacancy
External vacancy
 
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013Ethiopian sugar corporation facts – December 2013
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013
 

More from Ethiopian Sugar Corporation

Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Ethiopian Sugar Corporation
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 

More from Ethiopian Sugar Corporation (14)

Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
 
Ethiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry ProfileEthiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry Profile
 
Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI] Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI]
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
 
Ethiopian sugar industry profile
Ethiopian sugar industry profileEthiopian sugar industry profile
Ethiopian sugar industry profile
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
 
Ethiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry ProfileEthiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry Profile
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 

ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም

  • 1. ዜና መፅሔት ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ! ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም www.ethiopiansugar.com || facebook.com/etsugar ጣፋጭ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ከኮርፖሬሽኑ አመራሮች ጋር ተወያዩ • የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካንና ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል »» ወደ ገጽ 2 ዞሯል »»ወደገጽ3ዞሯል በውስጥ ገጾች በቻይና የጃንግዚ ግዛት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተመራ የልዑካን ቡድን ከስኳር ኮርፖሬሽን አመራሮች...>>6 የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በስኳር ምርት ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመግባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለፀ >>3 የኮርፖሬት ሊደርሺፕ ሥልጠና ተሰጠ >>5 በስኳር ኢንዱስትሪው በቀጣይ ሊተገበሩ ስለሚገባቸው ሥራዎች እና የአሠራር ሥርዓት ላይ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ከስኳር ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር ህዳር 23/2009 ዓ.ም ተወያዩ፡፡ በዚሁ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይና የስትራተጂያዊ ድጋፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በዛብህ ገብረየስ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ልማት ንዑስ ዘርፍ አጠቃላይ ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፉን ስኳር ድርጅት ጉባኤን ለማስተናገድ ተመረጠች * እ.ኤ.አ በ2017 የድርጅቱን ምክር ቤት የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በምክትል ሊቀመንበርነት ይመራሉ ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፍ የስኳር ድርጅት አባል አገሮች ጉባኤን እ.ኤ.አ በ2018 እንድታስተናግድ ተመረጠች፡፡ ተቀማጭነቱ ለንደን የሆነውን የዓለም ስኳር ድርጅት ምክር ቤትን እ.ኤ.አ በ2017 የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በምክትል ሊቀመንበርነት እንዲመሩ በአባል አገራት ተመርጠዋል፡፡ ከህዳር 20 እስከ 23/2009 ዓ.ም በለንደን የተካሄደው ዓለም አቀፍ የስኳር ድርጅት ጉባኤ የታወቁ ስኳር አምራች አገሮች፣ ባለሀብቶች፣ የዘርፉን ተመራማሪዎችና ሌሎችንም ያሳተፈ እንደነበር ታውቋል፡፡ የስኳር ኢንደስትሪው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ አስቀድሞ ምንም አይነት መሰረተ ልማት ባልነበረባቸው አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉት የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ተስፋ ሰጪ መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ታህሳስ 9/2009ዓ.ም በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት እየተገነቡ የሚገኙ ስኳር ፋብሪካዎችን ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከስኳር »» ወደ ገጽ 2ዞሯል ገጽታን የሚያሳይ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ በተደረገው ውይይት ላይ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ እንደተናገሩት፣ ከስኳር ልማት ዘርፍ የሚጠበቀውን ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ተቋሙን በግልጽ የአሠራር ሥርዓት መምራትና የሥራዎችን ቅደም ተከተል በማውጣት መፈጸም ይገባል፡፡ ዶ/ር ግርማ አመንቴ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር
  • 2. ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም2 3e t h i o p i a n s u g a r. c o m የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ... »» ከገጽ 1 የዞረ ስኳር ኮርፖሬሽንን የመሰለ ትልቅ የልማት ተቋም ሥራን በትክክል መመዘን የሚያስችል የውጤት ምዘና ሥርዓት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባዋል ያሉት ሚኒስትሩ፣ ሰዎች በሥራቸው ውጤት ብቻ እየተመዘኑ ሥራ ላይ መቆየትና ማደግ እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡ አክለውም ሰዎች በሥራቸው ውጤት ብቻ የሚኖሩበት ተቋም መፍጠር ካልተቻለ የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብም ሆነ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች ይዞ መቀጠል አይቻልም ብለዋል፡፡ ለዘርፉ ቀጣይ እድገት ካለፉት ስህተቶች እና ስኬቶች ትምህርት መውሰድ ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ፣ በተለይም ኮርፖሬሽኑ ያሉበትን ተግዳሮቶች ለይቶና የሚፈቱበትን ስትራተጂ ቀርጾ በፍጥነት ወደ ውጤታማ ሥራ መግባት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑን የፋይናንስ አሠራር ለማሻሻል የተጀመረው የኮርፖሬት ፋይናንስ ማሻሻያ ፕሮጀክት ትክክለኛና ተገቢ መሆኑን ያወሱት ሚኒስትሩ፣ ሥራው በፍጥነት መጠናቀቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ሥራዎችን ወይም ፕሮጀክቶችን መለየትና የተለየ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በስኳር ምርት ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመግባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለፀ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የሀገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር ሀገሪቷ በስኳር ምርት ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመግባት ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ገለጹ፡፡ ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎች ጋር በመሆን ፋብሪካውን በጎበኙበት ወቅት በሰጡት ማብራሪያ፣ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የሀገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማርካት ባለፈ ከማምረት አቅሙ ከፍተኛነትና ለጅቡቲ ወደብ ካለው ቅርበት አኳያ ምርቱን ወደ ውጪ ለመላክ ከፍተኛ ስትራተጂያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ፋብሪካው በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በሰው ሃይል ረገድም በወጣት ባለሙያዎችና ጠንካራ አመራሮች የተደራጀ መሆኑን ዶ/ር ግርማ ገልጸው፣ የተመለከቱት የሥራ እንቅስቃሴ ሁሉ አበረታችና ተስፋ ሰጪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፉን... »» ከገጽ 1 የዞረ በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፉትና ምክር ቤቱን በምክትል ሊቀመንበርነት እንዲመሩ የተመረጡት የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ እንደገለጹት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2018 ጉባኤውን እንድታስተናግድ መመረጧ እንደ አገርና እንደ ስኳር ኮርፖሬሽን ታላቅ ስኬት በመሆኑ ደስ ብሎናል ብለዋል፡፡ አቶ እንዳወቅ ኢትዮጵያ የጉባኤው አስተናጋጅ አገር መሆኗን ተከትሎ እ.ኤ.አ ከሐምሌ 2017 እስከ ሰኔ 2018 የዓለም ስኳር ድርጅት ምክር ቤትን ለአንድ አመት በሊቀመንበርነት እንደሚመሩም ታውቋል፡፡ ጉባኤው አምራቾችን፣ ባለሀብቶችን፣ ሻጮችንና በዘርፉ ምርምር የሚያደርጉ አካላትን በአንድነት የሚያገናኝ በመሆኑ ለአገር ገጽታ ግንባታና ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አቶ እንዳወቅ ተናግረዋል፡፡ አገሪቱ በስኳር ምርት ያለችበትን ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የውጭ የገበያ እድል ለማግኘት እንዲሁም በዘርፉ ኢንቨስትመንት ለመሳተፍ የሚፈልጉ የአገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶችን ለመሳብ ጉባኤው መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥርም ነው ዋና ስራ አስፈጻሚው ያስረዱት፡፡ የዓለም የስኳር ድርጅት በዓለም ስኳር ገበያ ላይ ወሳኝ ሚና እንዳለው የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ጉባኤው ለኢትዮጵያ የስኳር የውጭ ገበያ ዕድል መፍጠሪያ መድረክ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡ የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን በማሟላት ጉባኤው በሚስተናገድበት አመት ስኳር ወደ ውጭ ለመላክ ርብርብ በመደረግ ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡ በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ የስኳር ምርት አቅሟን በማሳደግ የዓለም ገበያን ለመቀላቀል ከወዲሁ በማድረግ ላይ የምትገኘው ዝግጅት፣ አገሪቱ ለዓለም ገበያ ያላት ቅርበት እና በምርት አዘገጃጀት ላይ ያላት ምቹነት በስፋት ተገልጿል፡፡ በዚሁ ወቅት ባለሀብቶች በግልም ሆነ በቡድን በዘርፉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡ ጉባኤው የስኳር ምርት ተግዳሮቶችን፣ ለስኳር አምራቾች የሚያስፈልጉ የቴክኒክ ድጋፎችና የቴክኖሎጂ ግብአቶችን፣ የገበያ ዕድሎችና ትስስሮች መጠናከር ስለሚችሉበት ሁኔታም በሰፊው ተወያይቷል፡፡ የስኳር ምርት እንደ ቡናና ነዳጅ ተፈላጊነቱ እየጨመረ በመምጣቱ የገበያ ትስስር ገጽታው ምን መምሰል እንዳለበት እንዲሁም ዘርፉ የኤታኖል ምርትን በማስፋፋት በአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ላይ ሊጫወት ስለሚገባው ሚናም ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ዓለም አቀፉ የስኳር ድርጅት ክርክሮችን በማድረግ፣ ልዩ ጥናቶች በማካሄድ እንዲሁም ሴሚናሮችን፣ ኮንፈረሶችንና ወርክሾፖችን በማዘጋጀት የስኳር ገበያ የተሻለ እንዲሆን የሚሰራና 87 አባል አገሮች ያሉት በይነመንግስታዊ ድርጅት ነው፡፡ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ዶ/ር ግርማ፣ ኮርፖሬሽኑ በራሱ አቅም መወጣት ያልቻላቸውን ተግባራት ሚኒስቴር መ/ቤቱ አሠራር በመዘርጋት ኮርፖሬሽኑን ለመደገፍና በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት በሚኒስትሩ ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን እንዲሁም የኦሞ ኩራዝ እና የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡ ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡ እየለማ ያለው በአንድ ቀን የሚታረስ መሬት አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፋብሪካዎቹ እዚህ ደረጃ ደርሰው ማየታቸው በራሱ ትልቅ ኩራት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያን የመሰሉ ሀገራት የተለጠጠ ዕቅድ ካላቀዱ ከድህነት ለመውጣት አዳጋች እንደሚሆንባቸው ተናግረው፣ በዚህ ረገድ በዘርፉ ያጋጠመ የማስፈጸም አቅም ችግር እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ አክለውም ኮርፖሬሽኑ እየወደቀ እየተነሳ አሁን የደረሰበት አቅም አስተማማኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በጉብኝታቸው ወቅት ለአዳዲሶቹ ስኳር ፋብሪካዎች የሸንኮራ አገዳ ቆራጮችእጥረት መኖሩንየተረዱትአቶኃይለማርያምለሜካናይዜሽን የሚረዱ ማሽኖች እንዲገዙ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ የስኳር ልማቱ ባለፉት ዓመታት የነበረበትን ሁኔታ አሁን ከሚታየው አፈጻጸም ጋር በማነጻጸር የተሰማቸውን ሲናገሩም “በዘርፉ ላይ አምና ከነበረኝ ዘንድሮ ያለኝ ተስፋ ጨምሯል፡፡ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1፣ 2 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች በቅርቡ ወደ ማምረት ይሸጋገራሉ፡፡ ከሰምበግማሽ አቅም ማምረት ጀምሯል፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሙሉ አቅሙ ይደርሳል፡፡ ተስፋ አስቆራጭ የነበረው ተንዳሆም አሁን በሙሉ አቅሙ ለመስራት ዝግጁ ሆኗል፡፡ በለስ አንድም በቅርቡ ይደርሳል ብዬ አምናለሁ፡፡ የበለስ ሁለትን መለስተኛ ችግር ለመቅረፍ እየሰራን ነው፡፡ ወልቃይትም ጥሩ እየሄደ ነው” በማለት ያላቸውን ተስፋ አብራርተዋል፡፡ በጉብኝቱ የተሳተፉት የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የስኳር ኢንደስትሪው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ... ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ በበኩላቸው ፕሮጀክቱን ባለፈውም ዓመት መጎብኘታቸውን አስታውሰው በተለይ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ፋብሪካ ግንባታ ተስፋ ሰጪ በሆነ መልኩ እየተፋጠነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የክልሉ መንግሥት ለኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር ማድረጉን እንደሚቀጥል የገለጹት ርእሰ መስተዳድሩ፣ ኮርፖሬሽኑ በተለይ የክልሉን ወጣቶች እና አርብቶ አደሮች የኑሮ ሁኔታ ከመቀየር አንጻር ትርጉም ያለው ሥራ መስራቱን አድንቀዋል፡፡ በሌላ በኩል ርእሰ መስተዳድሩ ኮርፖሬሽኑ በምርምር ዘርፍ እያደረገ ያለውን ጥረት በመስክ በመመልከት የተከናወኑ የምርምር ሥራዎችን አድንቀዋል፡፡ በቆላማ አካባቢ የማይበቅሉ ሰብሎች ተሞክረው ውጤታማ መሆናቸውም የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡ »» ከገጽ 1 የዞረ አቶ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሚኒስትሩ አክለውም “በስኳር ልማት ዘርፍ የተለጠጠ እቅድ ይዘን እና ፈጥነን ወደ ሥራ ለመግባት ከነበረን ጉጉት አኳያ በሂደት ብዙ እንቅፋቶች ያጋጠሙንና ለከፍተኛ ወጪ የተዳረግንበት ሁኔታ ቢኖርም እስካሁን የመጣንበት ርቀት ለወደፊቱ የልማት ጥረታችን እጅግ ጠቃሚ ትምህርት ሰጥቶን ያለፈ መሆኑን ማጤን ይገባል፡፡” ብለዋል፡፡ በቀጣይ በዘርፉ የሚቀሩ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ስኬት ለመጓዝ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ሚኒስትሩ፣ በዚህ ረገድ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ከልማት ጥረቱ ጎን በመሆን ተፈላጊው ውጤት እንዲመጣ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ጥቅምት 2007ዓ.ም የሙከራ ምርት የጀመረ ቢሆንም፣ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር እና ለቦይለር የሚውል የንጹህ ውሃ እጥረት ምክንያት ለረጅም ጊዜያት ቆሞ ነበር፡፡ ይሁንና በአሁኑ ወቅት ችግሮቹ ተፈተው ስኳር በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ፋብሪካውን በጎበኙበት ወቅት
  • 3. ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም4 5e t h i o p i a n s u g a r. c o m የስኳር ፋብሪካዎች የ2008 ዓ.ም የክረምት ጥገና በግብአት አቅርቦትና በሰው ኃይል ልዩ ዝግጅት ተደርጎበት መከናወኑን የኦፕሬሽንስ ዘርፍ አስታወቀ፡፡ ጥገናው የተከናወነላቸው ስኳር ፋብሪካዎች ወደ መደበኛ የምርት ሂደት ገብተዋል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽንስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ እንደገለጹት፤ በ2009 በጀት ዓመት በዝግጅት ምዕራፍ የተካሄደው የክረምት ጥገና በመደበኛ ምርት ውስጥ በሚገኙ አራት ነባርና ወደ ኦፕሬሽን በመግባት ላይ ባሉ የተንዳሆና የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካዎች የተከናወነ ሲሆን፣ የክረምት ጥገናው በግብአት አቅርቦትና በሰው ኃይል ረገድ ልዩ ዝግጅት ተደርጎበት ወደ ሥራ በመገባቱ ጥገናው በስኬት ተጠናቋል፡፡ ለክረምት ጥገናውና ለ2009 የምርት ዘመን የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከሀገር ውስጥና ከውጪ የማቅረብ፣ የሰው ኃይል የማሟላት እንዲሁም በፋብሪካዎችና በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ደረጃ ሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈና መሠረታዊ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ዝግጅት መደረጉን የገለጹት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ይህም የክረምት ጥገናው በስኬት መጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል ብለዋል፡፡ የጥገናው ዝግጅት የኮርፖሬሽኑን የገንዘብ አቅም፣ በመጋዘኖች ያለውን መለዋወጫ እንዲሁም የውጪ ምንዛሪ ግኝትን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ ጥገናው ከዚህ በፊት ከተደረጉ ተመሳሳይ የክረምት ጥገናዎች ልዩ እንደሚያደርገው የጠቆሙት አቶ ወዮ፣ ይህም የ2009 የምርት ሂደት ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል ያስችላል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ በ2008 ዓ.ም የምርት ሥራውን ያደናቀፉና በውጪ ባለሙያዎች የተለዩ እንዲሁም በ2009 የምርት ሂደት ተፅዕኖ ሊፈጥሩ ይችላሉ የተባሉ ችግሮች ተለይተውና ቅደም ተከተል ወጥቶላቸው መለዋወጫ ከውጪ ገብቶ እንዲጠገኑ መደረጉንም ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለው ገልጸዋል፡፡ በአጠቃላይ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት የ2008 ዓ.ም የክረምት ጥገና አፈጻጸም ሲገመገም ከሌሎች ተመሳሳይ የክረምት ጥገናዎች የተሻለ፣ በቂ ጊዜ ተሰጥቶትና አስፈላጊው ግብአት ቀርቦለት ጥራቱን ጠብቆ የተከናወነ ነው ብለዋል፡፡ የክረምት ጥገናው የተሳካ እንዲሆን የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴርና ሌሎች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡ የክረምት ጥገናውን መጠናቀቅ ተከትሎ የወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ፣ ከሰም፣ ተንዳሆና አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካዎች ወደ መደበኛ የምርት ስራ ውስጥ መግባታቸውን አቶ ወዮ አስታውቀዋል፡፡ በታህሳስ ወር ወደ ስራ ከገባው አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በስተቀር የተቀሩት አምስት ፋብሪካዎች ከህዳር 2009 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ምርት ሂደት መግባታቸውን ያመለከቱት አቶ ወዮ፣ አጀማመራቸውም ካለፉት አመታት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ነው ብለዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የክረምት ጥገና ከተደረገላቸው ስድስት ፋብሪካዎች በተጨማሪ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 2 አዳዲስ ፋብሪካዎችን ሥራ በማስጀመር በ2009 በጀት አመት 7 ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ ስኳር በማምረት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማሟላት አቅዶ እየሰራ ነው፡፡ የፋብሪካዎች የክረምት ጥገና በልዩ ዝግጅት መከናወኑ ተገለጸ • ፋብሪካዎቹ ወደ መደበኛ የምርት ሂደት ገብተዋል ስኳር ኮርፖሬሽን የ2009ዓ.ም ዕቅድን ለማሳካት እንዲረዳው በየደረጃው ለሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራር አካላት በሦስት ዙር ስልጠና ተሰጠ፡፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሽን አካዳሚ በተሰጠው ሥልጠና የኮርፖሬሽኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጨምሮ ከዋና መስሪያ ቤት፣ ከስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች የተውጣጡ ከፍተኛ እና መካከለኛ የሥራ መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ሥልጠናው የሀገሪቱ ስኳር ኢንዱስትሪ የተጋረጡበትን ችግሮች ከመፍታትና ውጤታማ ስኳር ኢንዱስትሪ ከመገንባት አንጻር ይስተዋሉ የነበሩ የዕውቀትና የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት እንደሚረዳ ታምኖበታል፡፡ ስልጠናውን የተከታተሉ የኮርፖሬሽኑ የሥራ መሪዎች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተገኙ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን ከኮርፖሬሽኑ ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ተቀምሮና የማስፈጸሚያ ፓኬጅ ተቀርጾለት ተግባራዊ መደረግ እንደሚገባው ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ይህንን በተግባር የተደገፈ የንድፈ ሃሳብ ሥልጠና የሠጡት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናሥራ አስፈጻሚአቶ ተወልደገብረማርያም እና ሌሎች ከፍተኛ የአየር መንገዱ የሥራ ሓላፊዎች ናቸው፡፡ በዚሁ ወቅት የስልጠናው ተሳታፊዎች የአየር መንገዱን የጥገና ክፍልና ሌሎች የሥራ ክፍሎችን ጎብኝተዋል፡፡ ሥልጠናው Facility and resource utiliza- tion, coping with Changing situations, leading corporations successfully, Corporate finance, performance man- agement, and leadership በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ሥልጠናውን ያስተባበረው የኮርፖሬሽኑ የሰው ሃብት አመራርና ልማት የሥራ ክፍል ነው ፡፡ የኮርፖሬት ሊደርሺፕ ሥልጠና ተሰጠ ለኮርፖሬሽኑ የፋይናንስና የኦዲት ባለሙያዎችና ሓላፊዎች በዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ሥርዓት ላይ ሥልጠና ተሰጠ የኦፕሬሽንስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ስልጠና ሲሰጡ ለስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት፣ ለፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የፋይናንስ እና የኦዲት ባለሙያዎችና ሓላፊዎች በዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ሥርዓት (IFRS) ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የተሰጠውን ሥልጠና ያዘጋጁት የኮርፖሬሽኑ የሰው ሃብት ልማት እና የፋይናንስ የሥራ ክፍሎች ከኮሌጁ የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ዲፓርትመንት ጋር በመሆን ነው፡፡ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ይትባረክ ተክሌ ሥልጠናውን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ወደሚጠይቅ ኢንዱስትሪ እየገባች በመሆኑ ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት ያለው የፋይናንስ ሪፖርት ያስፈልጋል ማለታቸውን ዩኒቨርሲቲው በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡ በሦስት ዙሮች በተሰጠው ሥልጠና 200 የፋይናንስና የኦዲት ባለሙያዎች ተካፍለዋል ፡፡ ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ሥርዓት (IFRS) ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ ላይ የዋለው በአውሮፓ ሕብረት ሲሆን፣ ዓላማውም የንግድ ጉዳዮችና ሒሳቦቻቸውን በአህጉሪቱ በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ ነው፡፡ ሥርዓቱ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለመግባባት ምቹ ሆኖ በመገኘቱ በአጭር ጊዜ በመላው ዓለም ተቀባይነቱ ሊሰፋ ችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሪፖርት ሥርዓቱ በ120 ሀገራት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
  • 4. ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም6 7e t h i o p i a n s u g a r. c o m »» ወደ ገጽ 8 ዞሯል በቻይና የጃንግዚ ግዛት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተመራ የልዑካን ቡድን ከስኳር ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር ተወያየ በቻይና የጃንግዚ ግዛት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተመራ የልዑካን ቡድን ከስኳር ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር በተለያዩ የትብብር መስኮች ላይ ተወያየ፡፡ በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ውይይቱ የግዛቲቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሚስተር ሊዩ ቻንግሊን የቻይና መንግሥት በኢትዮጵያ በተለይም በስኳር ኢንዱስትሪው መስክ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ በኢንቨስትመንትና በፋይናንስ ረገድ የተጀመረው ትብብር በቀጣይነት እየጎለበተ እንደሚሄድም ነው የተናገሩት፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ በበኩላቸው በስኳር ኢንዱስትሪው ከተሰማሩት የቻይና ኩባንያዎች ጋር ጠንካራና መልካም ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ 13 ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ውስጥ አምስቱ በቻይና መንግሥት በተገኘ ብድርና በቻይናውያን ኮንትራክተሮች እየተገነቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተለይም በቀን 24 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ ከጃንግዚ ግዛት በተገኘ ገንዘብና የግዛቱ ኩባንያ በሆነው JJIEC በመገንባት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከጃንግዚ ግዛት ጋር በስኳር ልማት ዘርፍ የተጀመረው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በቀጣይ የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡ አክለውም በዘርፉ በቀጥታ የውጪ ኢንቨስትመንት/FDI እና በሽርክና/Joint ven- ture ለመስራት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቁመው፣ የቻይና ኩባንያዎች ወደ ሀገር ቤት መጥተው በስፋት እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ 38 ባለሙያዎችን ለሥልጠና ወደ ቻይና ላከ ስኳር ኮርፖሬሽን ከቻይናው ኮምፕላንት ኩባንያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ሥልጠና ላይ ለመሳተፍ 38 ባለሙያዎች ህዳር 23/2009ዓ.ም ወደ ቻይና ሄደዋል፡፡ ሠልጣኞቹ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ ሥራ ሲጀምር በሚሰለጥኑበት መስክ የሚሰማሩ ሲሆን፣ በሁለት ወራት የቻይና ቆይታቸው ለሁለት ሳምንት የንድፈ ሃሳብ፣ በቀሪው ጊዜ ደግሞ በቻይና የስኳር ፋብሪካዎች ተገኝተው በተግባር የተደገፈ ሥልጠና እንደሚከታተሉ ታውቋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽንስ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ሠልጣኞችን ሲሸኙ ባደረጉት ንግግር፣ ኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎቹ ከሥልጠና መልስ ውጤት የሚያመጡ ሥራዎችን ያከናውናሉ ብሎ እንደሚያምን አመልክተዋል፡፡ የሰው ሃብት አመራርና ልማት ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አዛለች ለማ በበኩላቸው ሠልጣኞቹን “ከሥልጠናው ብቻ ሳይሆን ከምትሄዱበት ቦታም የሥራ ባህልን ተማሩ” ብለዋል፡፡ ሥልጠናው የሚያተኩረው በኤክስትራክሽን፣ በፕሮሰስ፣ በፓወር ፕላንት፣ በDCS እና PLC እንዲሁም በወተር ትሪትመንት ዙሪያ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት እየተገነቡ ከሚገኙ አራት ስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ፋብሪካ ግንባታ በቻይናው ኮምፕላንት እየተካሄደ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት ሥራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታን ለማፋጠን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታን ከማፋጠን ጋር በተያያዘና በሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ JJIEC ከሚባል የቻይና ኮንትራክተር እና Sino Sure ከተባለ የቻይና የኢንሹራንስ ኩባንያ ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተደረገው በዚህ ውይይት ኮርፖሬሽኑን በመወከልአቶአብርሃም የስኳር ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት፣ የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች “ሕገ መንግሥታችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችንና ለህዳሴያችን!” በሚል መሪ ቃል 11ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች አከበሩ፡፡ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህዳር 20 ቀን 2009ዓ.ም በተከበረው በዚህ በዓል ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ በዛብህ ገብረየስ በዓሉን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች መተማመንንና መቻቻልን እንደ ቁልፍ የሀገር ግንባታ ዕሴቶች በመውሰድ አንድነትና ብዝሃነትን አጣጥመው አንድ የጋራ ሀገራዊ ማኅበረሰብ ለመገንባት ያስቻለ የፌዴራል ሥርዓት መመስረታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ሀገሪቷ ከደርግ ውድቀት በኋላ በመሰረተችው ሕብረ-ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት ባለፉት 25 ዓመታት በሁሉም መስኮች በርካታ ስኬቶችን ለማስመዝገብ ችላለች ብለዋል፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የተጀመረውን የህዳሴጉዞበማጠናከርረገድባለፉትአመታት በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እንዲወጠኑ መሰረት ጥሏል ያሉት አቶ በዛብህ፣ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተካሄዱ ካሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች አንዱ የስኳር ልማት ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ባጋጠሙ የተለያዩ ተግዳሮቶች በዘርፉ የታቀደውን ያህል ውጤት ማግኘት አልተቻለም ያሉት አቶ በዛብህ፣ ይሁንና በዕቅዱ ዓመታት በስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ በተከናወኑ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ሀገሪቱ በ2016ዓ.ም በዓለም ከሚገኙ ከፍተኛ የስኳር አምራች አገሮች ተርታ መሰለፍ የምትችልበትን እድል እውን ለማድረግ የሚያስችሉ መደላድሎችን ለመፍጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡ አክለውም “በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በስኳር ልማት ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት ሕገ መንግስቱ ለሀገራችን ህዳሴ መሰረት መሆኑን እናረጋግጣለን” ብለዋል፡፡ በዕለቱ “ሕብረ ብሔራዊ የጋራ ሀገር ግንባታ” በሚል ርዕስ በአቶ መንግሥተአብ ገ/ኪዳን የኮርፖሬት ሪፎርምና አቅም ግንባታ አማካሪ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሁፍ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በመጨረሻም በዓሉን አስመልክቶ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት፣ በፌደራሊዝም ሥርዓትና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የቀረበ የጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊዎች ከእለቱ የክብር እንግዳ እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡ በተመሳሳይ በዓሉ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት፣ የፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ሠራተኞች የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አከበሩ                                       አቶ መንግሥተአብ ገ/ኪዳን የኮርፖሬት ሪፎርምና አቅም ግንባታ አማካሪ የውይይት መነሻ ጽሁፍ ባቀረቡበት ወቅት
  • 5. ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም8 9e t h i o p i a n s u g a r. c o m የጸረ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ቀን በኮርፖሬሽን ደረጃ ተከበረ                                       29ኛው አለም አቀፍ የጸረ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ቀን በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት፣ በስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡ በዓሉ በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ህዳር 22 ቀን 2009ዓ.ም በተከበረበት ወቅት የዋና ሥራ አስፈጻሚው ተወካይ አቶ በዛብህ ገብረየስ እንደተናገሩት፣ ኤች አይ ቪ/ ኤድስን ለመግታት ወደ ራሳችን በመመልከት መድሎና እና መገለልን አስወግደን ለቀጣይ ዕድገት እንትጋ ብለዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ የጸረ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ ዘመድኩን ተክሌ በአሉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ወረርሽኙ ሰፋፊ የመንግሥት የልማት ፕሮጀክቶች በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች እና በገጠራማ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተስፋፋ መምጣቱ የሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት የጀርባ አጥንት የሆነው የግብርናው እና የስኳር ልማት ክፍለ ኢኮኖሚ ምርታማነት እንዲቀንስ እና በምግብ እህል ራስን የመቻል ሀገራዊ ጥረት ለአደጋ እንዲጋለጥ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ ኤች አይ ቪ/ኤድስ የልማት ችግር ያልሆነባት ኢትዮጵያን ማየትን ራዕያችን እናድርግ ብለዋል አቶ ዘመድኩን በማጠቃለያቸው፡፡ በዓሉን የተመለከተ የመወያያ ጽሑፍ በኮርፖሬሽኑ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ሴክሬታሪያት ከፍተኛ ባለሙያ ሲስተር ትዕግስት ዓለሙ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በመጨረሻም በኮርፖሬሽኑ ኤች አይ ቪ/ ኤድስ መከላከያና መቆጣጥሪያ ሴክሬታሪያት ሲስተር ካሰች ሺበሺ አስተባባሪነት የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ገንዘብ በማዋጣት ድጋፍ እያደረጉላቸው የሚገኙ በኤች አይ ቪ/ኤድስ ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናት ከኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ጋር ተዋውቀዋል፡፡ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የሙዚቃ ቡድን የተለያዩ ጣዕመ ዜማዎችን በማቅረብ ለበዓሉ ድምቀት ሰጥቷል፡፡ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረአ የስኳር ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ዘጠነኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነታችን መገለጫ፣ በብዝሃነታችን ላይ ለተመሰረተው አንድነታችን ዓርማ ነው” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም አከበሩ፡፡ በአሉ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶችም ተከብሯል፡፡ በዋና መ/ቤት በተከበረው በዓል ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሰንደቅ ዓላማ ከብሔራዊ ኩራት ምልክትነት ባሻገር የአንድን ሀገር ሕዝብና መንግሥት ራዕይና ስኬት ጥልቀት ባለው ሁኔታ አጠቃሎ የያዘ ዓርማ ነው ብለዋል፡፡ ሰንደቅ ዓላማ የመንግሥትና ሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ሥልጣንና ነፃነት፣ እድገትና ማኅበረሰባዊ ትስስር መገለጫ ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ከዚህ አንጻር የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች ሕገ መንግሥታዊና ሕዝባዊ መሰረት ያለውን የሀገሪቷን ሰንደቅ ዓላማ በመጠበቅ፣ በማክበርና በማስከበር ልዕልናን የማረጋገጥ ሓላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ በመልዕታቸው ማጠቃለያም የተስፋ ዓርማ በሆነው ሰንደቅ አላማ ነጸብራቅ ውስጥ የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሠራተኛ የስኳር ልማት ዘርፍ ግቦችን አሻግረው በመመልከት ለስኬቱ በላቀ ቁርጠኝነት እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በዓሉን በማስመልከት “የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና ዴሞክራሲያዊ አንድነት በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት” በሚል ርዕስ በአቶ ፋሲል ገ/ማርያም የሕግ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም የቃለ መሃላና የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ በተያያዘ ዜና ዘጠነኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማቀንበስኳርፋብሪካዎችናፕሮጀክቶችም በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን ከሆራይዘን አዲስ ጎማ አክስዮን ማኅበር ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ ስኳር ኮርፖሬሽን በስኳር ፋብሪካዎች እና ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የሚያስፈልጉ ፍሎቴሽን ጎማዎችን ሆራይዘን አዲስ ጎማ አ.ማ አምርቶ እንዲያቀርብለት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡ በሸራተን አዲስ በተካሄደ የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ሥነ ስርዓት ላይ የሚድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያ በሆነው ሆራይዘን ፕላንቴሽን አክስዮን ማኅበር ስር የተቋቋመው ሆራይዘን አዲስ ጎማ አ.ማ ስኳር ኮርፖሬሽን በየዓመቱ የሚፈልጋቸውን 20 ሺህ ፍሎቴሽን ጎማዎችን ለማምረት ተስማምቷል፡፡ ኮርፖሬሽኑን በመወከል የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት የኦፕሬሽንስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወዮ ሮባ፣ ለስኳር ኢንደስትሪው ከባድ ማሽኖች እና ተሽከርካሪዎች የተለያዩ አይነት ጎማዎች በከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ እንደሚገዙ በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡ የተደረሰው ስምምነትን አስመልክቶ ሲናገሩም፣ “ሀገር በቀል ኩባንያው የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታን ለማፋጠን... ደምሴ የኢንቨስትመንት ጥናትና ልማት ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ፋብሪካን እና አጠቃላይ የስኳር ኢንዱስትሪው ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ በኮርፖሬሽኑ በኩል በመከናወን ላይ የሚገኙ ሥራዎችን አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም ከቻይና የልዑካን ቡድን ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በዚሁ ወቅት የፋብሪካውን ግንባታ ለመጀመር የሚያስፈልጉ የዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን እና የፋብሪካው ግንባታም በ2011ዓ.ም ተጠናቆ ሥራ እንደሚጀምር በኮንትራክተሩ ተገልጿል፡፡ የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 24ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፡፡ በምንፈልገው መጠን፣ ብዛት እና ጥራት ማምረቱ ለኮርፖሬሽኑ እፎይታ እንዲሁም የውጪ ምንዛሬን ለማዳን የሚያስችል ነው፡፡ ከአሁን በኋላ ውጪ ማየት አቁመን ጎማ ከበራችን ላይ እናገኛለን፡፡ ” ብለዋል፡፡ ሆራይዘን ፕላንቴሽን አክስዮን ማኅበርን በመወከል የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት የተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አካለወልድ አድማስ በበኩላቸው፣ “በሀገር ምርት የማመን ትልቅ ነገር በስኳር ኮርፖሬሽን አይተናል፡፡ ፍሎቴሽን ጎማውን የማምረት በቂ ቴክኖሎጂ እና የመዋዕለ ነዋይ ዝግጅት አለን፡፡ የስኳር ልማት ዘርፍ ከሀገሪቱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑንም እንረዳን፡፡” ብለዋል፡፡ ሆራይዘን አዲስ ጎማ አ.ማ በዓለም በጎማ ኢንደስትሪ በትልቅነቱ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ኮንቲነንታል ጀርመን ጋር አብሮ የሚሰራ በመሆኑ ለስኳር ኮርፖሬሽን የሚያመርታቸውን ጎማዎች በጥራት እና በብዛት ለማቅረብ እንደሚያስችለው በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡ »» ከገጽ 7 የዞረ በኮርፖሬሽኑ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጥሪያ ሴክሬታሪያት ሲስተር ካሰች ሺበሺ በዓሉን አስመልክተው ማብራሪያ ሲሰጡ ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት
  • 6. ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም10 11e t h i o p i a n s u g a r. c o m የመሠረታዊ ሠራተኛ ማኅበር የመጀመሪያ የምክር ቤት ስብሰባ ተካሄደ የስኳር ኮርፖሬሽን የመሠረታዊ ሠራተኛ ማኅበር ምክር ቤት የመጀመሪያ ስብሰባውን ኅዳር 1/2009 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት አካሄደ፡፡ የምክር ቤቱ 50 አባላት የተገኙበትን ስብሰባ በንግግር የከፈቱት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ እንዳስታወቁት፣ በሠራተኛውና በማኅበሩ እንዲሁም በአመራሩ መካከል ጤናማ የሥራ ግንኙነት በመፍጠር በስኳር ልማት ዘርፍ የተጀመረውን ወገብ የሚያጎብጥ ዕቅድ ለስኬት እናበቃለን ብለዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት ለማኅበሩ አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንደሚያደርግ እና በቅርበትም እንደሚሰራ አክለው ገልጸዋል፡፡ የሠራተኛ ማኅበሩ ሊቀመንበር አቶ ተመስገን ወልደ መስቀል በበኩላቸው ማኅበሩ ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር ተቀራርቦ በመስራት እና ችግሮችም ሲያጋጥሙ በጋራ በመፍታት በስኳር ልማት ዘርፍ ተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት እንደሚረባረቡ ተናግረዋል፡፡ የምክር ቤቱ አስተባባሪ እና የሠራተኛ ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ተሾመ ያሚ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ እና ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለነባር ፋብሪካዎች ሠራተኞች ባለፉት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የማትጊያ ክፍያ እንዲፈጸም በማድረጋቸው አመስግነዋል፡፡ ይህም በነባር ፋብሪካዎችም ሆነ ወደ ምርት በሚገቡ አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች የሚሰሩ ሠራተኞችን በማነቃቃት የኮርፖሬሽኑን ዕቅድ ለማሳካት እንደሚያስችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት በስብሰባቸው ማጠቃለያ ባወጡት የአቋም መግለጫ በስራቸው የታቀፉ አባላትን አስተባብረው በነባርና ወደ ምርት በሚገቡ አዳዲስ ፋብሪካዎች ውጤታማ ሥራ በማከናወን የኮርፖሬሽኑ ግቦች እንዲሳኩ ጠንክረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡ ፡ በተጨማሪም የስኳር ኢንዱስትሪው ሰላምን ጠብቆ ለማቆየት አስታውቀዋል፡፡ ህዳር 2008 ዓ.ም በአዲስ መልክ የተቋቋመው የስኳር ኮርፖሬሽን መሠረታዊ የሠራተኛ ማኅበር ኮርፖሬሽኑ ካሉት ቋሚ እና ጊዜያዊ ሠራተኞች ሁለት ሦስተኛውን ያቀፈ ነው፡፡ በፕሮጀክቱ ቅጥር ግቢ የአንደኛ ክፍል መደበኛ ትምህርት መስጠት ተጀመረ በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በመለስ ጠቅላይ ሰፈር የአንደኛ ክፍል መደበኛ ትምህርት መስጠት ተጀመረ፡፡ በተያዘው የትምህርት ዘመን በፕሮጀክቱ ቅጥር ግቢ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ልጆች የሆኑ 38 ሕፃናት የአንደኛ ክፍል መደበኛ ትምህርት በመማር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ ከፕሮጀክቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል በደረሰን መረጃ የፕሮጀክቱ ማህበረሰብ ለረጅም ጊዜ ሲያነሳው የነበረውን የመደበኛ ትምህርት ይከፈትልን ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የፕሮጀክቱ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከጃዊ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ባደረገው ውይይት ይሁንታ አግኝቷል፡፡ በዚህ መሰረት ተጠሪነቱ ለአሊኩራንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሆነ የ1ኛ ክፍል ሳተላይት ት/ቤት ተከፍቷል፡፡ የተማሪዎቹ ወላጆች በበኩላቸው ልጆቻቸው በቅርበት የትምህርት ዕድል በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ቀጣዮቹን ክፍሎች ደረጃ በደረጃ ለመክፈት እንዲሁም መምህራን እና ቁሳቁስ ለማሟላት ቃል መግባቱን ማወቅ ተችሏል፡፡ በአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ የኤችአይቪ/ኤድስ ምርመራ ተካሄደ በአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ከጥቅምት 16 እስከ ህዳር 30/2009ዓ.ም ድረስ በተደረገ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ምርመራ 504 የፋብሪካው ሠራተኞች መመርመራቸውን የፋብሪካው ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡ ፋብሪካውና የጅማ አርጆ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በጋራ ባዘጋጁት በዚህ የምርመራ አገልግሎት ከ400 በላይ ሠራተኞች በፈቃደኝነት ተመርምረው ራሳቸውን አውቀዋል፡፡ በርካታ ሰው በአንድ ጊዜ በብዛት ሊመረመር የቻለበትን ምክንያት የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ሲገልጽ፣ ሠራተኛው በአቻ ለአቻ ትምህርት በማግኘቱ እና በዚህም የባሕርይ ለውጥ በመምጣቱ ነው ብሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋብሪካው ሠራተኞች ህዳር 22 ቀን 2009ዓ.ም የዓለም በፕሮጀክቱ ከ13ዐ በላይ የአገዳ ዝርያዎችን ለማላመድ እየተሞከረ ነው በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከ130 በላይ አዳዲስ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችን ለማላመድ እየተሞከረ መሆኑን ፕሮጀክቱ አስታወቀ፡፡ የፕሮጀክቱ የምርምር ቡድን መሪ አቶ ኪዳኔ ተ/ሚካኤል በስኳር ምርት ላይ የምርታማነትና የጥራት ችግር እንዳያጋጥም ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ልዩ ልዩ ባህሪያት ያላቸውን የአገዳ ዝርያዎች በማሰባጠር ማላመድ ማስፈለጉን ተናግረዋል፡፡ በዚህ መሠረት ከተለያዩ የምርምር ማዕከላት የመጡ ከ13ዐ በላይ ዝርያዎች በፕሮጀክቱ ተተክለው እንዲላመዱ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ በፕሮጀክቱ ከዚህ ቀደም የነበሩ የዝርያ ዓይነቶች ጥቂት እንደነበሩ ያስታወሱት ቡድን መሪው፣ በሙከራ ላይ ለሚገኙ የአገዳ ዝርያዎች ልዩ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት እየተገነቡ ለሚገኙት ሁለት ፋብሪካዎች እስካሁን 13 ሺህ ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ ተሸፍኗል፡፡ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄደ የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ለሁለተኛ ጊዜ በስኳር ኮርፖሬሽን ተካሄደ፡፡ በወንጂ ሸዋና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም በኦሞ ኩራዝና ወልቃይት ፕሮጀክቶች የተካሄደው ይህ ፕሮግራም በአካባቢ ልማት፣ በኪነ ጥበባት፣ በትምህርትና በሰብዓዊ አገልግሎት ነው፡፡ በዚህም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሰማራት በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትን መፍጠር እንዲሁም ሠራተኞችና የአካባቢው ማኅበረሰብ ስለ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰፊ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል፡፡ ዘንድሮ በልዩ ልዩ የአካልና የአዕምሮ ብቃት ማጎልበቻ ስፖርቶች የጎላ እንቅስቃሴ ከመካሄዱም በላይ በተለይ የሴቶችና የወንዶች የእግር ኳስ ውድድሮች በዙር ሲደረጉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የስፖርት አፍቃሪዎችና ፕሮፌሽናል አሠልጣኞች መታደማቸው በሙያው ለመቀጠል ዝንባሌ ላላቸው ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተጠቁሟል፡፡ ፕሮግራሙ ከውስጥ ደንበኞች በተለይም ከካይዘን፣ ከጤና፣ ከስነ ምግባር፣ ከህዝብ አደረጃጀት፣ ከህዝብ ግንኙነት እና ከአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ በመሆኑ ለቀጣይ ሥራዎች የተጠናከረ ትስስር መፍጠር እንዳስቻለም ታውቋል፡፡ የተፈጠረውን የተነሳሽነት መንፈስ በበጋው ወራት አጠናክሮ ለማስቀጠል መታቀዱና በሁሉም ንዑሳን ፕሮግራሞች ወንዶችና ሴቶች በእኩልነት መሳተፋቸውም ተመልክቷል፡፡ ባለፈው ዓመት በኮርፖሬሽኑ በተካሄደ የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም 4,679 ወንዶችና 1,331 ሴቶች በድምሩ 6 ሺህ 10 ወጣቶችን በቀጥታ በተለያዩ ፕሮግራሞች እንዲሳተፉ በማድረግ የወጣቶችን ማኅበራዊ ተሳትፎ ማጎልበት መቻሉን የኮርፖሬት ሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ገልጿል፡፡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ182,401 ብር በላይ የሚገመት ውጤታማ ተግባራትን ማከናወናቸውም ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የኮርፖሬት ሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለተቋቋመ ቤተ መፃህፍት ከግለሰብ ለጋሾች ያሰባሰባቸውን ዋጋቸው 20 ሺህ ብር የሚገመት መፃህፍት በስጦታ አበርክቷል፡፡ ኤድስ ቀንን “አሁንም ትኩረት ለኤች.አይ.ቪ መከላከል” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበራቸውን የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ዘግቧል፡፡
  • 7. ቅፅ 5 . ቁጥር 2 | ታህሳስ 2009 ዓ.ም12 e t h i o p i a n s u g a r. c o m እናስተዋውቃችሁ ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ፣ ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ 50 ኪ.ሜ ያህል የሚርቀው ይህ ፋብሪካ፣ በአፋር ክልል በዞን ሦስት አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች ውስጥ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ 500 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ባለው የከሰም ግድብ አማካኝነት የሚለማ 20ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት ይኖረዋል፡፡ የአገዳ ልማቱም የሚከናወነው በከሰም እና ቦልሀሞን በተሰኙ አካባቢዎች ነው፡፡ የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ሆኖ የተጀመረ ቢሆንም ስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመ ወዲህ ቦታው ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ካለው ርቀት አንፃር ተመዝኖና ተጠንቶ እራሱን ችሎ እንደ አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲንቀሳቀስ ተደርጓል፡፡ ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ፣ በ2007ዓ.ም መጨረሻ ላይ የሙከራ ምርት ጀምሯል፡፡ አሁን ስኳር እያመረተ ሲሆን፣ በሂደት በቀን 6ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ ፋብሪካው በቀጣይ 10ሺህ ቶን ሸንኮራ አገዳ በቀን ወደሚፈጭበት ደረጃ እያደገ የሚሄድ ሲሆን፣ የኤታኖል ፋብሪካና የኮጀነሬሽን ፋሲሊቲም ይኖረዋል፡፡ ፋብሪካው በመጀመሪያ ምዕራፍ በዓመት 1 ሚሊዮን 530ሺህ ኩንታል ስኳር እና 12 ሚሊዮን 500ሺህ ሊትር ኢታኖል የማምረት አቅም የሚኖረው ሲሆን፣ ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ ደግሞ በዓመት 2 ሚሊዮን 600ሺህ ኩንታል ስኳር እና 30 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል ማምረት ይችላል፡፡ ከዚህ ባሻገር 26 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 15 ሜጋ ዋቱን ለብሔራዊ የኃይል ቋት እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡ የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ • 3ሺህ 161 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤ • የ20.5 ኪ.ሜ የዋና ቦይ ግንባታ ተጠናቋል፤ የአገዳ ልማት • በፋብሪካው አማካኝነት 2ሺህ 432 ሄክታር መሬት እንዲሁም በአሚባራ እርሻ ልማት (አውት ግሮወር) 6ሺህ ሄክታር መሬት በአጠቃላይ 8 ሺህ 432 ሄክታር በአገዳ ተሸፍኗል፤ የቤቶች ግንባታ • 517 የመኖሪያ ቤቶች እና 20 አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤ ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ሲጎበኙ የከሰም ስኳር ፋብሪካ