SlideShare a Scribd company logo
front inside
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
1
ተምሳሌት
በትምህርት እና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር
በየ 15 ቀኑ የሚታተም መጽሔት ነው፡፡
ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
በውስጥ ገጾች
የልብ ነገር
ልቤን ቆረጠኝ፣ አመመኝ በርካታ ጊዜ ብለን
ይሆናል፡፡ ልብና ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው
ችግሮች ከእድሜ መግፋት ጋር በተያያዘ ብቻ
እንደሚበጣ የሚገምቱ አሉ፡፡
ንቃ ያለው!
ንቃ ያለው ባʼርባ ቀኑ አትንቃ ያለው ባʼርባ ዓመቱም
አይነቃም አለኝ አንዱ ባልንጀራዬ፡፡ መንቃት
እንዳʼግባብነቱ ሰፊ ትርጓሜ የያዘ ሁለት ቃል ነው፡፡
ነቃ፤ ነቄ፤ ንቃተ-ህሊና እያልን ቃላቱን እያራከምን
(እያባዛን) አቻ ትርጉም ብንፈልግለት
የማህበራዊ ድረ-ገጾች
አገራችን በዓለም ላይ ከሚገኙ ዝቅተኛ
የኢንተርኔት(የበይነ መረብ) ተጠቃሚ ከሆኑ አገራት
አንዷ ናት፡፡ ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበይነ
መረብ ፍጥነትና ተደራሽነት ከምንግዜውም
በተሻለ ሁኔታ እያደገ ይገኛል፡፡
6 10 16
7 13 20
8 14 21
ኤስ ኦ ኤስ
የኤሰ ኦ ኤስ ዓለም አቀፍ የህጻናት መንደሮች ዓለም አቀፍ
ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን የዛሬ 60 ዓመት በ1949
ዓ.ም (እ.አ.አ) በፕሮፌሰር ኸርማን ሜየር
በተባሉ ግለሰብ በኦስትሪያ ተመሰረተ፡፡
የአኗኗራችን ነገር
እኒህ ሰው የ 59 ዓመት ጎልማሳ ናቸው፡፡ ከታዋቂው የሲ
ኤን ኤን የቢዝነስ ዘጋቢ ሪቻርድ ኩዊስት ጋር ፊት ለፊት
ቁጭ በለው ይነጋገራሉ፡፡ ሰውዬው ብላክ ቤሪ ዘመናዊ
ስልኮች አምራች ኩባንያ ቺፍ ኤክስክውተቭ
(ዋና ኃላፊ) ናቸው፡፡
ሰሌዳው ተበይዷል
ታክሲ ውስጥ ነኝ፡፡ ከሹፌሩ ኋላ፡፡ ማለዳ 1ሰአት
አካባቢ፡፡ ሁሉ ወደየጉዳዩ ለመሄድ ከቤቱ የሚወጣበት
ሰአት በመሆኑ ከመነሻው በመግባቴ ጥሩ ቦታ
አገኘሁ እንጂ በየጎማውና በየሞተሩ ላይ
ተቀምጦመሄድ ልማዴ ነበር፡
እስቲ ላ’ንድ ቀን
እንደው አንዳንዴ. ምን አንዳንዴ በ’ለት ተዕለት
ኑሮአችን የሚደረጉ ድርጊቶች ፍትሐዊ አልሆን
ብሎን ተበሳጭተን. እርር ድብን ብለን.
አልቅሰን ባ’ቅመ-ቢስ ስሜት ውስጥ ሆነን
የሥነ ምግባር ጉዳይ
ከ2 ዓመታት በፊት በአንድ ጋዜጣ ላይ አንድ
አስገራሚም፣ አስደንጋጭም፣ አሳዛኝም ዘገባ ማንበቤን
አስታውሳለሁ። በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ
የግል ት/ቤቶች ውስጥ በአንዱ
የዩኒቨርሲቲ ህይወት
በሰውልጅህይወት ውስጥ ድርጊት፣ ሁኔታና ቦታ
ከጊዜጋር በሚኖራቸው መስተጋብር አማካይነት
ከሚፈጥሩት ወቅታዊ እውነት ባሻገር
ትዝታቸውንም በአእምሮ ውስጥ አኑረው
ያልፋሉ፡፡
2
ተምሳሌት
በትምህርት እና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ
የሚያተኩር በየ 15 ቀኑ የሚታተም መጽሔት
ነው ፡፡ ተምሳሌት መጽሔት በኢትዮጽያ
ብሮድካስት ባለሥልጣን ምዝገባ ቁጥር
279/2006 እና በንግድ ምዝገባ ቁጥር kik/
AA/2/0003278/2007 ሐምሌ 15 ቀን 2006
ዓ.ም ተመሰረተ፡፡
ዋና አዘጋጅ
ንጉስ ይልማ
አድራሻ --- ክ/ከተማ ወረዳ---- የቤት ቁጥር
E-mail eyobneguss@gmail.com
ማኔጂንግ ዳይሬክተር
ከድር አህመድ
Kidunet.ahmed7@gmail.com
ኤዲቶሪያል ቡድን
ደሳለኝ መኩሪያ
desu.meku@gmail.com
አዲስ ፀጋዬ
rasaddis16@gmail.com
በለጠ ጌታቸው
mesiblete@gmail.com
አለማየሁ ስሜነህ
sevastefol@yahoo.com
አምደኞች
ጽጌሬዳ ........
መላኩ ..........
ክቡር ..........
ታምራት መቻል
ሄኖክ ሰይፉ
የኮምፒዩተር ጽሁፍ
አዜብ አለማየሁ
azuzihabesha1@gmail.com
ገበያ ስርጭት እና ክትትል
ዮርዳኖስ
የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ
ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት
ቁጥር 3277 ዘርሽታ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር
212 ስልክ ቁጥር 251 911225298 ፖ.ሳ.ቁ
54154 ኢ-ሜይል temsaletmagazine@
gmail.com
አሳታሚ
ኤኬቢዲ የፕሬስ የማስታወቂያና የማማከር
አገልግሎት
የተምሳሌት አቋም
ሰው ልጅ በመደበኛም ይሁን ኢ-መደበኛ በሆነ ሁኔታ አካባቢውን እየለወጠ ዛሬ በምንገኝበት ደረጃ
ላይ የደረስነው በትምህርት ነው፡፡ ጥፋትም ሆነ ልማት የሚከናወነው በትምህርት ነው፡፡ መልካሙን
ነገር ብቻ አጎልብቶ ጥፋትን ማስወገድ የሚያስችል ትምህርት መስክ አልተፈጠረም፤ ወደፊትም
አይፈጠርም፡፡ የመድሃኒትን ጥቅም መቶ በመቶ ከመድሃኒቱ የጎንዮሽ ጉዳት ማስወገድ የሚቻልበት
ቴክኖሎጂ ላይ አልደረስንም፡፡ የጨለማና ብርሃን፤ መኖርና መሞት፤ ሀብትና ድህነት፤ የጽድቅና ኩነኔ
ሂደቶች የዚህ ተምሳሌት ናቸው፡፡ ዓለም የምትባለው የፍጥረት መኖሪያ ከተመሰረተች ጀምሮ የነበረ
አሁንም ያለ ወደፊትም የሚኖር አውድ (ኡደት) ነው፡፡ ይህ ተፈጥሮ ሚዛኗን የምትጠብቅበት ስልት
ነው፡፡
ዛሬ በደረስንበት የቴክኖሎጂ እድገት ዘመን ዘምኖ እና ደርጅቶ አለመገኘት ከነባራዊው ዓለም ጋር
ያለመራመድ የኋላ ቀርነት ብቻ ሳይሆን ያላዋቂነት መገለጫ ነው፡፡ የሀገራችን ስረዓት ትምህርት
እድሜው የሚጀምረው ከአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ይሁን እንጂ በትምህርት ሚ/ር ስርዓት
ተበጅቶለት ትምህርትን ለጥቂት የህብረተሰቡ ክፍል መስጠት የተጀመረው በአጤ ኃ/ሥላሴ የአገዛዝ
ዘመን ነው፡፡ የአንድን ማህበረሰብ በትምህርት ተለውጧል ለማለት ዘመን ተሸጋሪ የሆነ ወጥነት ያለው
የትምህርት ስርዓት ሊኖር እንደሚገባ በመስኩ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡ አንድን ማህበረሰብ
ሚዛን ላይ የምናወጣው በተማረው የሙያ መስክ ለህበረተሰቡ እና ለሃገሩ ያለው አበርክቶ ነው፡፡
ቁጥራቸው የበዛ የትምህርት ተቋሞች መገንባትና ቁጥራቸው የበዛ የሰው ኃይል ማፍራት እጅግ የተቀደሰ
ተግባር ቢሆንም፤ ከመጀመሪያ ድግሪ እስከ ሦስተኛ ድግሪ መማር እጅግ የሚያስከብር የምሁርነት
መገለጫ ቢሆንም፤ ማህበረሰቡን በአንድ እርምጃ ወደፊት ካላራመደ፤ ከነበረው ነባራዊ የአሰራር
ሂደት ጋት እንኳ ፈቀቅ ካላለ፤ ከተደጋጋሚ ሃገሪቷ በነጮቹ መዝገበ ቃላት ውስጥ ያላትን የረሃብተኛ
ስም የትርጉም ፍቺ ካላስለወጠ፤ ዛሬም እንደጥንቱ በበሬማረሳችን እርግጥ ከሆነ፤ በየዓመቱ በብዙ
ሺህ የሚቆጠሩ ተመራቂዎችን ማፍራት ፋይዳው ምኑ ላይ ሊሆን ነው ሲል ተምሳሌት ያጠይቃል፡፡
ትምህርት የለውጥ መሳሪያ እንጂ በራሱ ለውጥ አይደለም፤ መማር ማወቅ መረዳት እንጂ በራሱ ለውጥ
አይደለም፡፡ ማወቅ የለውጥ የመጀመሪያ እርምጃ እንጂ በራሱ ግብ አይደለም፡፡
ይህ የለውጥ ግብ ከሚለካባቸው ዘርፈ ብዙ መንገዶች ውስጥ አንዱ በመማር ማስተማር ሂደት የሚነሱ
የምርምር ስራዎችን ከሸልፍ ማድመቂያነት ይልቅ ለህትመት የሚበቁበትና ችግር ፈቺ የሚሆኑበት፤
በማህበራዊው ህይወት የአኗኗር ዘዬ በባህል፤ በኢኮኖሚ፤ በፖለቲካ በኪነ-ጥበብ፤ እንዲሁም በመዝናኛ
ያሉትን የቀን ተቀን ውሎ በህትመት እና በብሮድካስት ሚዲያ ሽፋን ተሰጥቶት ሲሰራበት ነው፡፡
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኤፍ ኤም
ሚዲያ ስርጭት ቢኖራቸውም በማህበረሰቡ ዘንድ ከነመኖራቸውም የሚያውቅ ጥቂት የህብረተሰብ
ክፍል ነው፡፡ በህትመት ሚዲያ ቢሆን የባሰ እንጂ የተሻለ ነገር አይታይም፡፡
ተምሳሌት መጽሔት ከዚህ በላይ ያነሳናቸውን በትምህርት እና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ ተዛማጅ
የሆኑ ጉዳዬችን በማንሳት የተለያዩ ዓምዶችን በማዘጋጀት፤ በየመስኩ ያሉ ባለሙያዎችን በማሳተፍ
ውይይቶችን፤ ክርክሮችን በማድረግና መማርያ መድረክ በመፍጠር ለማህበረሰብ እና ለሀገር ፋይዳ
ያለው ለውጥ እንዲያመጡ የበኩሏን ድርሻ ትወጣለች፡፡
ሰ
የለውጥ መሳሪያ
ሊሆን ይገባል
ትምህርት
3
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከቴክኖጂ ጋር የተያያዙ ስራዎችን እየሰራ ለማህበረሰቡ እያቀረበ መሆኑን
አስታወቀ፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢንኩቤሽን ማዕከል የሚል የምርምር ስራዎችን ማጎልበቻ ተቋም
መሰረተ፡፡
በአዲስ አበባከ 167 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 65
ትምህርት ቤቶች በስኩልኔት የመረጃ መረብ ተገናኙ
አዲስ አበባ ት/ቢሮ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን በድረ-ገጽ ሊያስተሳስር መሆኑ
ተገለፀ ፡፡ አስተዳደሩትምህርት ቢሮ የትምህርት የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ
የሥራ ሂደት መሪ አቶ የኔጌጥ በለጠ እንደተናገሩት፥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘው ይህ
የመረጃ መረብ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያስችላል። በቀጣይ ሁለት ወር ውስጥም
ሙሉ በሙሉ ሥራ የሚጀምር ይሆናል። በአሁኑ ወቅትም 65 ያህል ሁለተኛ ደረጃ እና
መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂው እርስ በእርስ እንዲገናኙ ተደርጓል።
ቴክኖሎጂው በፕላዝማዎች ኢንተርኔትን መጠቀም የሚቻልበትን ዕድል በመፍጠር
ተማሪዎች በመምህራኖቻቸው አጋዥነት ትምህርት ነክ ጉዳዮችን በመማሪያ ክፍላቸው
ሆነው እንዲማሩና የዕውቀት አድማሳቸውን እንዲያሰፉ ለማድረግ ይረዳል። የመረጃ መረቡ
በመብራት መጥፋት ምክንያት በፕላዝማ የሚሰጥ ትምህርት ቢቋረጥ እንኳን ተማሪዎች
መከታተል ያልቻሉትን የትምህርት ክፍል የሚከታተሉበትንም ዕድል የሚፈጥር ነው።
Uniliver የተባለ ድርጅት በኢትዮጽያ ውስጥ የሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን በማወዳደር
ሽልማት አበረከተ
ጅ
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???ወሬ ነጋሪ
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
ተምሳሌት
የኛ
	 በዝግጅት ክፍሉ
ለእናትነት ወግ ያልበቃች እናት የጎስቋላዊቱን
ምድር ጨልማ ለብሳ ትቃትታለች፡፡ ገና
ዘመነ ቡረቃዋን ሳትጨርስ በሰቅጣጭ
አካላዊ ህመምና በማህበራዊ ሴፍ
መሰየፍን በመሳሰሉ ሁለትዮሽ ስቃዮች በመፈተን ላይ
ያለች ቀንበጥ ያለማቋረጥ እሪታዋን ብታቀልጠው
አይፈረድባትም፡፡ ለምን ቢባል በጨቅላይቱ የጨቅላ
እናት ላይ የዘመተው ደዌ ፌስቱላ ነዋና ኡኡታን
ያለማሰለስ ኡኡ ቢያስብል የተገባ ነው፡፡ ዳሩ የዘመናት
የፍዳ ምች ሁለመናዋን እያማታት ያለው አዛውንቷ
ኢትዮጵያ የእንቦቀቅላይቱን እዬዬ መስማት የሚቻላት
አይነት አልነበረችም፡፡ እናም በፌስቱላ እስር የታሰረች
ይህቺ አሳዛኝ እናት ባንድ ፊት ህመሟን በተስፋ ቢስነት
እያስታመመች በሌላ ወገን ማህበራዊ ጥቂታን ከአቅሟ
በላይ እያስተናገደች ባለችባት አገሯ ሰማይ ላይ
“ካትሪን” የተባለች ጸሀይ ሳትታሰብ ብቅ አለች፡፡
በምድረ አውስትራሊያ እንደ አደይ ፈክታ ስትምነሸነሽ
የነበረችው ካትሪን ከአብሲኒያ ደሳሳ ጎጆዎች ስር
ካቆረው የስቃይ ኩሬ ውስጥ ሰጥማ ትቀራለች ብሎ
ያሰበ ያለ አይመስልም፡፡ ይሁንና ይታደሉታል እንጂ
አይታገሉትም እንዲሉ በምጥ ስቃይ እጅግ በርካታ
እናቶች ለሞትና ለከፋ አካላዊ ጉዳት ሲጋለጡባት
የቆየችው ኢትዮጵያ ካትሪንን መሳይ የተስፋ ጸዳል
በአንዲት ወርቃማ አጋጣሚ ከእጇ አስገባች፡፡
በ1959 ዓ.ም. አገሪቱ የህክምና ባለሙያዎችን
ለመቅጠር መፈለጓን በማስታወቂያ ትገልጻለች፡
፡ በወቅቱ ባለትዳርና የአንድ ወንድ ልጅ እናት
የነበሩት ዶ/ር ካትሪን ሀምሊን ጥሪውን በይሁንታ
ይቀበሉና ገና ቦርቆ ያልጠገበውን የስድስት አመቱን
ይህ አምድ በቀዳሚነት የሚዘክረው በስራቸው ስኬታማነት
በዓለማችን ላይ በጎ ተጽእኖን ማሳደር የቻሉ ግለሰቦችን
እንዲሁም ተቋማትን ይሆናል፡፡
ልጃቸውንና እንደርሳቸው ሁሉ በህክምና ሙያ ላይ
የተሰማሩትን ባለቤታቸውን ይዘው ወደ አዲስ አበባ
ይመጣሉ፡፡ የጽንስና የማህጸን ሀኪም የሆኑት ተወዳጇ
ካትሪን ወደዚህ የመጡት ለሶስት አመታት ለመቆየት
የሚያስችል የኮንትራት ውል ተፈራርመው ነበር፡፡
ዳሩ እንቅብ ሙሉ ፍዳ ያሳቀፋቸው የኮንትራት ዘመን
ሲያበቃ ጠብቀው “ኢትዮጵያ ሆይ ሶስት የመከራ
አመታትን አብሬሽ ገፋሁ፤አታካቹን እሩጫ በምድርሽ
ላይ እሮጬ ጨርሻለሁና ወደ አገሬ ላቅና” አላሉም፡
፡ ይልቁንም ዶ/ር ካትሪን ኢትዮጵያዊያን እናቶች
እየገፉት ያለውን የመከራ ዳገት እሰከ መጨረሻይቱ
እስትንፋሳቸው ድረስ አብረው ሊገፉ የቃል ኪዳን
ማህተብ በልባቸው አኖሩ፡፡
ዶ/ር ሀምሊን አገራቸው ሳሉ በፌስቱላ ህመም
የምትንገላታ እናት ገጥማቸው አታውቅም፡፡
የህክምና ባለሙያዎች በተደጋጋሚ እንደሚገለጹት
በወሊድ ወቅት በሽንት ፊኛ እና በማህጸን መካከል
የሚከሰተው በተፈጥሮ ያልነበረ ቀዳዳ ፌስቱላ ይባላል፡
፡ በዶ/ር ካትሪን ሀምሊን ሆስፒታል የህክምና ባለሙያ
ከሆኑት ከወ/ሮ ፌቨን ገለጻ መረዳት እንደሚቻለው
በተለይ አንዲት ሴት ለፌስቱላ ችግር የመጋለጥ
እድሏ የሚያይለው አካሏ የምጥን ጫና ለመቋቋም
በሚያስችል መልኩ ያልጎለበተ እንደሆነ ነው፡፡
በእንዲህ አይነቱ አሳዛኝ አጋጣሚ ሽሉ በሚያደርሰው
ከአቅም በላይ የሆነ ውጥረት ከላይ በተገለጸው አኳኋን
ሴቲቱ የፌስቱላ ሰለባ ትሆናለች፡፡ በሌላም በኩል
ምንም እንኳን አንዲት እናት የሚጠበቀውን ያህል
አካላዊ ጥንካሬ ያላት ብትሆንም ሽሉ በትክክለኛው
አቅጣጫ የማይመጣ ከሆነ ለተመሳሳይ ችግር ልትዳረግ
ከኢትዮጵያ ስወጣ
እድሜ እቀንሳለሁ
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
ተምሳሌት
የኛ
የሚያስችል የህክምን ማእከል ባልከፈቱ ነበር፡፡ ለነገሩ ለዚች አገር ያላቸውን ጥልቅ
ፍቅር “ከኢትዮጵያ ወጥቼ ስመለስ እድሜ እቀንሳለሁ” በማለት ውብ አድርገው
ገልጸውታል፡፡ ልክ እንደ ምእራቡ አለም በፍጹም ግለሰባዊነት ተውጦ ለማህበራዊው
መስተጋብር ጀርባውን ያልሰጠውን ኢትዮጵያዊ ማንነት እርሳቸው አብዝተው
ይወዱታል፡፡ ሰው ስለራሱ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ
ስለሌላውም እየተጨነቀ እንዲኖር በሚያስችል መልኩ የተቃኘውን ኢትዮጵያዊ
አኗኗር ዶ/ር ካትሪን ከልብ ያደንቁታል፡፡
ከሶስት አመት በፊት የኑሮ አጋራቸውን ያጡት ዶ/ር ካትሪን የዘጠና አመት የእድሜ
ባለጸጋ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የፍቅር አጸዷ ካትሪን እያሽቆለቀለች ያለችውን የእድሜ
ጀንበር መሬት መሬት እያዩ የሚያሳልፏት አይነት እናት አይደሉም፡፡ ዛሬም ድረስ
በሚያስደንቅ ወኔ ለህክምና ማእከሉ ፍሬያማነት ይተጋሉ፡፡ የዘመናት ደመኛቸውን
ፌስቱላን ቀዬው ድረስ ዘልቆ መዋጋት የሚሻል መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት አዋላጅ
ነርሶች የሚሰለጥኑበትን መንገድ አመቻችተዋል፡፡ ሰልጥነው የወጡትም በድፍን
ኢትዮጵያ ተሰማርተው የሙያ አበርክቷቸውን እያበረከቱ ነው፡፡
“ዶ/ር ካትሪን ሀምሊን” ከመባል ይልቅ “እማማ ካትሪን ሀምሊን” ተብለው መጠራትን
የሚመርጡትንየእኚህንእናትሰናይነትእንዲህበአጭሩአውግቶመጨረስስለሚያዳግት
እረጅም እድሜንና ጤናን እየተመኘንላቸው ሀሳባችንን በዚሁ እንቋጫለን፡፡
ትችላለች፡፡ የዚህ ህመም ተጠቂ የሆነች እናት ሽንቷን ለመቆጣጠር ስለማትችል
እጅግ የከፋ ስነ-ልቦናዊ ስብራትና ማህበራዊ መገለል ይደርስባታል፡፡
በአንድ ወቅት የደረሰው ገጠመኝ እንዲህ ነበር አንድ የፌስቱላ ሄስፒታል ነርስ በራሱ
ጉዳይ ወደ መንፈሳዊ ቦታ ይጓዛል፤ በሄደበት ቦታ የገጠመው ግን አንዲት እናት
ከ40 ዓመታት በላይ በፌስቱላ ህመም ተሰቃይተው ራሳቸውን ወደ ህክምና ማዕከል
ሳይወስዱ የፈጣሪ እርግማን እንደደሆነ በማመን ገዳም ገብተው ቀሪ ህይወታቸውን
ይመሩነበር፡፡ታዲያእዚያበራሱጉዳይመንፈሳዊቦታላይየተገኘውነርስእርሳቸውን
አሳምኖ ለማሳከም ከ ሁለት ወራት በላይ ነበር የፈጀበት ፤ ምክንያቱም ይህ የፈጣሪ
እርግማ ን ነው ብለው ላመኑት ሴት እንዴት ተደርጎ በ ሁለት ቀን የሚፈወስ እጅግ
ቀላል ደዌ መሆኑን ይንገራቸው ፡፡ የሆነውና የተደረገው ግን ይሄ ነበር እናም ለ40
ዓመታት በፌስቱላ ህመም ሲሰቃዩ የነበሩት እናት እናታችን በሚሏቸው ዶ/ር ካትሪን
ሃምሊን የሰለጠነ ነርስ ፈወሳቸው ፡፡
#ሰው ስለራሱ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ሚዛኑን
በጠበቀ መልኩ ስለሌላውም እየተጨነቀ እንዲኖር
በሚያስችል መልኩ የተቃኘውን ኢትዮጵያዊ አኗኗር
ዶ/ር ካትሪን ከልብ ያደንቁታል”
ወደ እማማ ካትሪን ገድል ስንመለስ የዘመንን እንቅልፍ እንዳይሆን እንዳይሆን
የምታንቀላፋው ኢትዮጵያን እንዲህ በቶሎ መቀስቀስ የሚቻል እንዳልሆነ አበክረው
የተረዱ የሚመስሉት ዶ/ር ካትሪን ገና በጠዋቱ አጥብቀው የታጠቁትን መቀነት
ሳይፈቱ እነሆ ወደ አመሻሹ ዘልቀዋል፡፡ አሁን ጦር ሀይሎች በመባል በሚታወቀው
በቀድሞ ልእልት ጸሀይ ሆስፒታል ስራ የጀመሩት ዶ/ር ካትሪን በተለያዩ አገሮች
በመዘዋወር እንግዳ ስለሆነባቸው ፌሰቱላ ትምህርት በመቅሰም ለታላቁ ዘመቻ
እራሳቸውን ብቁ አደረጉ፡፡ መቼም ለሀምሳ-አምስት (55) አመታት የሚፋለሙትን
ጠላት እንዲህ በዋዛ ፈዛዛ ይጋፈጡት ዘንድ ይቸግራልና የሞራሉንም ሆነ የእውቀቱን
ስንቅ አሰማምሮ መሰነቁ በእጅጉ ያስፈልግ ነበር፡፡ ዶ/ር ካትሪን ያደረጉትም ይህንኑ
ነው፡፡ እንዲህም በማድረጋቸው የመገለል ከርሰ-መቃብርን ፈንቅለው በሺዎች
የሚቆጠሩ እናቶችን ለዳግም ትንሳኤ አብቅተዋል፡፡
አንዳንድ ጊዜ መውደድ በራሱ ትልቅ እዳ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ዶ/ር ካትሪን አገረ-
ኢትዮጵያን ከሚገመተው በላይ መውደዳቸው የእድሜያቸውን አብላጫ ችግሯን
እሹሩሩ ሲሉ እንዲቆዩ አስችሏቸዋል፡፡ እንዲያ ባይሆን ኖሮ የደጅ ጠኚ እሮሮ
ምሱ የሆነውን አበሻዊ ቢሮክራሲ ታግሰው በተሟላ አኳኋን ፌስቱላን ለማከም
6
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
ፈዋሽተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
ፈዋሽ
ልቤን ቆረጠኝ፣ አመመኝ በርካታ ጊዜ ብለን ይሆናል፡፡ ልብና ከልብ
ጋር ተያያዥነት ያላቸው ችግሮች ከእድሜ መግፋት ጋር በተያያዘ
ብቻ እንደሚበጣ የሚገምቱ አሉ፡፡ የህክምን ባለሙያዎች ይህ
ስህተት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የሰው ልጅ ከተወለደበት ቀን አንስቶ
እስከሚሞትበት ጊዜ ድረስ ሊያጠቃው የሚችል በሽታ ነው፡፡
ይሁን እንጂ በተቻለ መጠን ለህመሙ እንዳንጋለጥ ጥንቃቄ ማድረግ
አንድ በሉ….
 በመደበኛነት ደምን መለካት (ከ120/80 ከፍ ካለ ሁኔታው አሳሳቢ ነው፡፡)
 በሰውነት ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን መቆጣጠር (ከ40 እስከ 100
የኮሌስትሮል መጠን መደበኛ (normal) ሲሆን ከዚህ ከበለተም ካነሰም
አደጋው ያመዝናል፡፡)
 የስኳር ህመም ምርመራ ማድረግ
 በቀን ቢያንስ ለ20 ደቂቃ እንቅስቃሴ ማድረግ
 ከ24 ሰዐት ውስጥ 7ቱን በእንቅልፍ ማሳለፍ
 በቀን 6 ብርጭቆ ውሀ መጠጣት
 አመጋገብ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ (የቅባት፣ የኮሌስትሮል፣ የካሎሪና
ካርቦሀይድሬት መጠናቸው ዝቅተኛ የሆነ ምግቦችን መመገብ)
 ፈጣን ምግቦችን (fast food) አዘውትሮ አለመመገብ
 ሲጋራ አለማጨስ
እነዚህ መከላከያዎች ለሁሉም እድሜና ጾታ የሚሆኑ ናቸው፡፡ በተለይ ግን
እድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል፡፡
በጾታ ብናየው ደግሞ ሴቶች ወገባችሁ ከ35-40 ኢንች…..ወንዶች ደግሞ ከ40-45
ኢንች እንዳይበልጥ ተብላችኃል፡፡
እስቲ ልብ ህመም በቅድሚያ የሚያሳያቸውን ምልክቶች እንመልከት
ሁለት አትሉም….
ነገር…
ሴቶች ላይ የሚታዩ ምልክቶች
 ደረት አካባቢ ህመም መሰማት ወይም በተያያዘ በክንድ፣በአንገትና መንጋጋ
አካባቢዎች የሚሰማ ህመም
 ማስመለስን ያልተለመደ የአካል መዳከም
 እንቅስቃሴ ሲደረግ ወይም ተንጋለው ሲተኙ የሚፈጠር የትንፋሽ
ማጠር(መቆራረጥ)
 የድብርት ስሜት መሰማት
 የእንቅልፍ ማጣትና ምቾት አለመሰማት
ወንዶች ላይ የሚታዩ
 በደረት አካባቢ ምቾት ማጣት
 የትንፋሽ ማጠር
 የደም ግፊት መቀነስ በዚህ ምክንያት የሚፈጠር የራስ ምታት ህመም
 ቀዝቃዛ ላብ ማላብና የድብርት ስሜት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የ ል ብ
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
7
	 ከድር አህመድ
ንቃ ያለው ባʼርባ ቀኑ አትንቃ ያለው ባʼርባ ዓመቱም አይነቃም አለኝ
አንዱ ባልንጀራዬ ፡፡ መንቃት እንዳʼግባብነቱ ሰፊ ትርጓሜ የያዘ ሁለት
ቃል ነው ፡፡ ነቃ፤ ነቄ፤ ንቃተ-ህሊና እያልን ቃላቱን እያራከምን (እያባዛን)
አቻ ትርጉም ብንፈልግለት አንድም ነቃ.. ተሰነጠቀ፤ ተተረተረ የሚለውን
አንድም ነቃ.. እንቅልፉን ጨረሰ፤ ባነነ፤ ንቁ፤ ትጉህ፤ ቀልጣፋ ሆነ ጠረጠረ እያልን
ጮሌ ድረስ የሚጓዘውን የኢትዮጽያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር አማርኛ መዝገበ
ቃላት እናገኛለን ፡፡
የነቃ የሚለው ቃል የተማረ የሚለውን ትርጓሜ ይሰጠናል ብዬ አላምንም ወይም
ለማመን ብዙ የጥናት ማገዶ ይፈጃል፡፡ የእኛ ህብረተሰብ ግን እውነት ነቄ ነው? በምን
አትሉኝም የተግባራዊ እና የነባራዊ ነፀብራቅ ውጤት በሆነው የሰው ልጅ አይምሮ
አስተሳሰብ ውጤት ፡፡
ህዝባችን ለአቅመ-ፖለቲካ ንቃተ ህሊና አልደረሰም ደርሷል የሚለውን በጥናት
ያልበሰለ ምልከታ ትተን እስቲ ማህበራዊ ንቃተ ህሊናችን ገና ጨቅላ፤ እንቦቃቅላ
መሆኑን ለማጠየቅ እማኝ መጥራት ሳያስፈልገን በዕለት ተዕለት ህይወታቸን
የምንታዘበውን አንድ ሁለት እያልን እንመያየጥ ፡፡
ቆሻሻ መጣል ነውር ነው፤ አጥር ጥግ የሚሸና ውሻ ነው እያልን በደማቅ ጽሁፎች
ያደመቅን ቀድመን የነቃን የህብረተሰቡ ክፍሎች ዘግይተው ባልነቁ ከሊቅ አስከ
ደቂቅ በሆኑ “ጥቂት” ሰወች ከአንደበታችን ከሚወጡ ቆሻሻ ቃላቶች ጀምሮ በመንገድ
ላይ፤ በጎረቤቶቻችን አጥር ስር፤ በአደባባይ ላይ በመኪናችን ጎማ ላይ በአደባባይ
ላይ ሽንታቸውን የሚያንፎለፉሉ “ጥቂት” ሰወች መመልከት አዲስ ነገር አይደለም፡፡
በትራንስፖርት ላይ ወይም በመንገድ የበሉትን ፍራፍሬ አልያም የጫት ገራባ መሃል
መንገድ ላይ እንደዘበት ጥሎ መሄድ “ለጥቂት” ሰወች እንደምን ነውር ይሆናል፡፡
አጋጣሚውንአግኝተንወንድሜ/እህቴለምንእንዲህታደርጋለህብለንብንጠይቃቸው
ከጣሉት ቆሻሻ ባልተናነሰ የስድብ ወይም የቡጢ ናዳ ከመሰንዘር የማይመለሱ “ጥቂት”
አጉራ ዘለል ሰወችስ ምን እንላቸዋለን፡፡ ታዲያ መቼ ነው ʼምነቃው?
የህዝብ መገልገያ አውቶቡስ ወይም ታክሲ አልያም ሃይገር ውስጥ ገብተን ከቴፑ
የሚወጣውን አደንቋሪ ሙዚቃ አይሉት የጨረባ ዘፈን እንዲቀነስ አልያም
እንዲዘጋ ጠይቀን የሚሰነዘርብንን ክበረ-ነክ ስድብ ትተን መስኮቶች ይከፈቱ ብለን
በመጠየቃችን የሚነሳው አቧራ የቱ ድረስ እንደሚሄድ የምናውቅ “ጥቂት” ሰወች
እናውቀዋለን ፡፡ የታክሲ ረዳት ተፋቀሩ ብሎ እንደ ምንትስ ሲያጭቀን የተቃወምን
“ጥቂት” ሰወች አይደለም ከረዳቱ ከራሳችን ከተሳፋሪው የሚደርስብን አሳፋሪ ድርጊት
ምን ያህል እንዳሳቀቀን የምናውቅ “ጥቂት” ሰወች እናውቀዋለን ፡፡ በተቀመደበለት
ትራንስፖርት ታሪፍ ለመጓዝ ስንሞክር “በጥቂት” ሾፌሮችና ረዳቶች የሚደርስብንን
ጫና ለመቋቋም በምናደርገው እስጥ አገባ “ጥቂት” ተሳፋሪዎች የሚያሳዩን ያልተገባ
ባህሪይ እውንየመንቃታችን ዋዜማ ነው ወይስ መባቻ ላይ ነው ያለነው ያሰኛል፡፡
በእኔ እድሜ ልጅ ሲያጠፋ ወላጅ ባይኖር ቀድሞ የሚቀጣ የሚገስጽ ጎረቤት አልያም
የሰፈር ሰው ነበር ፡፡ ማህበራዊ መስተጋብሩ ከቤት አልፎ፤ ጎረቤት፤ ሰፈር ፤ አካባቢ..
እያለ ሰፊ ማህበረሰብን ያካልል ነበር ፡፡ ዛሬ የቀደመ ማህበራዊ እሴቶቻችንን
ለመተግበር የምንሞክር የዋሃን የለንም እንጂ ብንኖር ምን ላይ እንደበቀለ ግራ
ከሚገባን ወጣት ጋር መላተማችን ሳይታለም የተፈታ ነው ፡፡
ድሮ ማለት በሚከብድ ሁኔታ እንደ ባህል የምንኮራበት አንተ ቅደም አንቺ ቅደሚ
የሚል መገለጫ ነበረን ፡፡ ዛሬ ይሄ ባህል መኪና በሚያሽከረክሩ ሰወች ዘንድ ጎጂ
ባህል ከሆነ ውሎ አድሯል ፡፡ ለእግረኛ ቅድሚያ በመከልከል የደረሰ አድጋ የምትለዋን
የተለመደች የትራፊክ ፖሊስ ሪፖርት ትተን፤ በአደባባይ የተገናኙ መኪኖች ለየትኛው
ቅድሚያ ሰጥቶ ማለፍ እንደሚገባ የመንጃ ፈቃዱን አሰጣጥ የማለፊያ መመዘኛ አንዱ
መለከያ ሆኖ ሳለ፤ አንድ ምግባር የጎደለው ዋልጌ መሃል አደባባይ ላይ በመቆም
ከየአቅጣጫው የሚመጣውን የትራፊክ ፍሰት በመዝጋት አፀያፊ ስድብ ሲሳሰደብ
መመልከት እውነት ከመንጃ ፍቃዱ ጋር አብሮ የሚሰጥ የምግባር ብልሹነት
ሰርተፊኬት ይኖር ይሆን ፤ ይሆን ያሰኛል ፡፡
ከዚሁ በተጓዳኝ በትራፊክ መጨናነቅ የተነሳ ረጅም ረድፍ ሰርተው ከቆሙት
መካከል አፈንግጦ በመውጣት ከተቃራኒ አቅጣጫ የሚመጣውን መኪና መንገድ
ዘግቶ አላፊ አግዳሚውን አላሳልፍ የሚል የመኪና አሽከርካሪ ከየትኛው ሃገር ወይም
ማህበረሰብ የወስድነው ባህል፤ ትውፊት እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል፡፡ ጊዜያችን
ለኔ.. ለኔ.. የሚባልበት ማጭበርበር፤ ማምታታት፤ ጉቦኝነት፤ ሸፍጥ፤ ክህደት
“ቢዝነስ” የሚል ካባ ደርቦ የሚሞካሽበት፤ የሚሽሞነሞንበት ዘመን ላይ መሆናችን
ከጅብ ቆዳ የተሰራ መሰንቆ ቅኝቱ “እንብላው እንብላው” ነው የሚሉትን ተረት
ያስታውሰናል፡፡ ታዲያ መቼ ነው ምነቃው? ኢትዮጽያዊ ባህሎቻችንና ትውፊቶቻችን
ከአውሮፓና ከአሜሪካ በመጡ አደንዛዥ ፕሮግራሞች መጠመዳችን፤ የኛነታችን
መለያ የሆኑትን የአባቶቻችን ተጋድሎ ማራከስና ማንቋሸሽ የወጣቶቻችን መለያ
ከሆኑ ሁለት አስርተታትን አስቆጠረዋል፡፡ ወላጆች ለልጆቻችን ምናወጣው ስም
የማንን ባህል እና እምነት እንደሚያንጸባርቅ ከቶ ሊገባን አይችልም፡፡ ክፉ መንገድ
እመልካም ግብ አያደርስም፤ ክፉ ስራ እንደተኮሱት ጥይት አላማውን ይገድላል
የሚል አባባል የት ነበር ያነበብኩት፡፡ ይህንን ማህበራዊ ቀውስ “ጥቂቶች” የነቁ
ቢረዱትም የት ወስደው ከማን ጋር ተመካክረው ቅጥ እንደሚያስዙት ግራ
ገብቷቸው መቆዘም ብቻ ሆኗል እጣ ፈንታቸው፡፡ በኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች
የሚለቀቀው ፕሮግራም ይህንን ማህበራዊ ውጥንቅጥ እና ቀውስ ከማስተካከል ይልቅ
በእሳት ላይ ቤንዚን የሚያርከፈክፉ ሃይ ባይየሌላቸው ሚዲያዎች መኖራቸውን
ልብ ይሏል፡፡ “ጥቂቶችን” እንደሆነ ልብ ይባልልኝ ግን፤ ግን መቼ ነው ʼምነቃው
ብለን ማጠየቃችን አልቀረም ፡፡ጥሪታችንን አሟጠን በእውቀት ሰጪነቱ፤ በገንዘብ
ተቀባይነቱ አንቱ የተባለ ት/ቤት እውቀት እንዲገበዩ የላክናቸው ልጆቻችን ነገ የሀገር
ተረካቢ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ መሆኑን ያሰብን “ጥቂት” ወላጆች ልጆቻችን
ስልጣኔ ምልክት ተደረጎ በሚወሰደው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ልክፍት በያዛቸው “ጥቂት”
ት/ቤቶች አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር የተከለከለ ነው በማለት ህግና
ስርዓት ሲያወጡ ስንመለከት እውነት ያለነው እምዬ ኢትዮጽያ ውስጥ ነው ወይስ
.. ብለን መደናገራችን አይቀርም፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ በትምህርት ቤት ያለውየተማሪና
የአስተማሪ የመከባበር ስነ-ምግባር ከተናደ እንዲሁ አስርታትን አስቆጥሯል፡፡ እነዚህ
ተቋማት በእውቀት አንጸውና ኮትኩተው የሚያፈሩት ትውልድ ሀገር በሁለት እግሩ
እንዲቆም የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወሰድ ይታወቅ ነበር፡፡ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት
አያችሁ የጄኔሬሽን ዝቅጠት አለብን ያሉ ሰው አስታውሳለሁ፡፡ በዛሬውና በርሳቸው
ጊዜ የነበረው የጄኔሬሽን ዝቅጠት ሚዛን የትኛው ውሃ ያነሳ ይሆን፡፡ ከዝቅጠትስ
በታች ቋንቋ ይኖር ይሆን? ታዲያ መቼ ነው ʼምነቃው?
የእነዚህ እና የሌሎች ማህበራዊ ህፀፆቻችን ድምር ውጤት ነው የፖለቲካ ንቃተ-
ህሊናችንን የሚያጎለብተው፡፡ ጥቃቅን ሚመስሉን ነገር ግን በጥቅሉ ሲታዩ ማህበራዊ
እሴቶቻችንን የሚጎዱ ድርጊቶች ናቸው ነቅተዋል አልነቁም የሚያሰኙን፡፡ ሰድበው
ለተሳዳቢ የሚሰጡን፡፡ ያʼርባ ቀኑን ጉዞ አርባ ዓመት የሚያስጉዙን፡፡ ትንሽ ፍሳሽ
መርከብ ታስመጣለች እንዲል ቤንጃሚን ፍራንክሊን፡፡
እነሆ ዛሬም 3ሺህ ዘመን ትርክት ላይ ሆነን አልነቃችሁም ገና እያንጎላጃችሁ ነው
እየተባልን ነው፡፡ ጎበዝ አያሳፍርም? ስንቴ ይሆን የምናፍረው? በስንቱስ ይሆን
የምናፍረው? ለብዙ ኪ.ሜትሮች መነሻው አንድ እርምጃ ነው የሚሉት ቻይናዎች
ሃገራችን ገብተው እየሰሩ ነው ከʼነሱ ጋር አንድ ብንል እኮ ነገ..
ንቃ ያለው!
የኔ ሃሳብ
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
8
	 በዓለማየሁ ስሜነህ
አገራችን በዓለም ላይ ከሚገኙ ዝቅተኛ የኢንተርኔት(የበይነ መረብ)
ተጠቃሚ ከሆኑ አገራት አንዷ ናት፡፡ ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
የበይነ መረብ ፍጥነትና ተደራሽነት ከምንግዜውም በተሻለ ሁኔታ እያደገ
ይገኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ከሁሉም በተሻለ መጠን የበይነ መረብ
አንዱ አካል የሆነው የማህበራዊ ድረ-ገጽና የመወያያ መድረኮች (chat forum) ግን
በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ የማህበራዊ ድረ-ገጾች ጠቅላላ ጠቀሜታ እጅግ
ብዙ እና ዘርዝረን የማንጨርሰው ነው፡፡ ነገር ግን በአንዳዶች ዘንድ ለወጣቶች ለግል
ወሬ እና ለመዝናኛ አገልግሎት ብቻ የዋለ መድረክ ሆኖ በብዙዎች ይቆጠራል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚደረጉ ጥናቶች እንዲሁም እንቅስቃሴዎች እንደሚያሳዩት
ማህበራዊ ድረ-ገጾች ጠቀሜታቸው ሰፊ እና ለታላላቅ ተግባሮች መሳሪያ እንዲሆኑ
ነው፡፡ በሰለጠነው ዓለምም የፕሬሱን ሚና እስከ መጫወት እንደደረሱ በግልፅ
የምናየው ነው፡፡ ተጠቃሚዎቹን በተመለከተም እንድ በፈረንጆቹ በታህሳስ
2014ዓ.ም. የተደረገ ጥናት እንደሚገልፀው በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ
እንደሆኑ ነው፡፡
በዝርዝሩም እንደተገለፀው፡፡
በዓለም ላይ ከሚገኙ የበይነ መረብ ተገልጋዮች ውስጥ 72% ማህበራዊ ድረ-ገጾችን
እንደሚጠቀሙና በሰንጠረዡ እንደተቀመጠው በሁሉም እድሜ ክልል ውስጥ
የሚገኙ ሰዎች በተገለጸው ፐርሰንት መጠን የተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾችን ለተለያየ
ዓላማ እንደሚገለገሉበት አያይዞ ገልጸል ፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት ፌስ ቡክ(face
book) ብቻ የሚጠቀሙ ሰዎች 1.15 ቢሊዮን እንደሚሆንም ታውቋል፡፡
በአገራችንም ያለው ገፅታ በቁጥር ለማስቀመጥ ጥናት ቢያስፈልግም የበይነ መረብ
ተደራሽንት ከምንግዜውም በተሻለ ፍጥነትና ጥራት እያደገ መምጣቱን ጨምሮ
በዙሪያችን የምንመለከተው የቀን ተቀን ገጠመኞቻችን የሚነግረን ግን ማህበራዊ
ድረ-ገጾችን መጉብኘት በብዙች ዘንድ እየተለመደ የመጣና የህይወታችን አንዱ ገፅታ
እንደሆነ ነው፡፡
እንግዲህ ከበዛው የማህበራዊ ድረ-ገጾች ጥቅምና አገልግሎት ውስጥ እዚህ ላይ
ትኩረት የተደረገበት ጉዳይ ትምህርታዊ ፋይዳ ሲሆን በዚህ ረገድም ማህበራዊ ድረ-
ገጾች በሰለጠነው ዓለም ለትምህርት ትልቅ መንገድና መድረክ በመሆን በተለይም
ለተማሪዎችና ለትምህርት ቤቶች ብዙ ጥቅምን ሲሰጡ ታያሉ፡፡
በአሁኑ ወቅትም በአገራችን በተለይም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ በማህበራዊ ድረ-
ገጽ ላይ ስሙ የማይገኛ ተማሪ ቢኖር የበይነ መረብ ባልደረሰበት እና በተወሰነው
አከባቢ ብቻ እንደሚሆን ይታመናል ፡፡ እንደውም በአዲስ አበባ አከባቢ የሚገኙ
ትምህርት ቤቶች ጋር ያለው መረጃ እንደሚጠቁመው የተወሰኑየ5 እና የ6ኛ ክፍል
ተማሪዎችም ጭምር መህበራዊ ድረ-ገጾችን እንደሚጠቀሙ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ከዚህ የቴክኖሎጂ ውጤት ተማሪዎችም ሆኑ ትምህርት ቤቶች ምን
ጥቅም ያገኛሉ የሚል ጥያቄ እዚህ ጋር ይነሳል፡፡ ማህበራዊ ድረ-ገጾች ለመማርና ሀሳብን
ዕድሜ ክልል	 ተጠቃሚዎች%
18 – 29	 89%
30 – 45	 72%
50 – 60	 48%
65 >	 	 43%
የማህበራዊ ድረ-ገጾች
ማህበራዊ ተቃርኖ
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
9
ለመለዋወጥ ብዙ እድሎችን እፈጠረ ይገኛል፡፡ ተማሪዎች ማህበራዊ ድረ-ገጾችን
በመጉብኘት የሚያገኙትን ጥቅም በቀላሉ ማየት ይቻላል፡፡ ተያይዞም በመጀመሪያ
ደረጃ የሚጠቀሰው ፋይዳ ተማሪዎች በአካል ሳይገናኙ ወይም ሳይተያዩ ድረ-ገጾች ላይ
በመገኘት በየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኝ ሰው ጋር መወያየትና መረጃን በተለያየ
መልክ መለዋወጥ ያስችላል ፡፡ እንግዲህ በነዚህ ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ግለሰቦች
ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ድርጅቶችን ጨምሮ
ስለሚገኙ አንድ የተፈለገን መረጃ ከሚመለከተው አካል የድርጅቱን ወይም ግለሰቡን
ገጽ በማገናኝት ወጃጅ ለመሆን (Like) በማድረግ ጓደኝነትን እንዲሁም ግንኙነትን
ለመፍጠር ገለሰቡ ወይም ድርጅቱ የሚያስተላልፈውን መረጃና መልዕክት በቀላሉ
ማግኘት ይቻላል፡፡
እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ማህበራዊ ድረ-ገጾችን በመጠቀም በቀላሉ ከተማሪዎች
እንዲሁም ከወላጆች ጋር የቀረበ ግንኙነት ማድረግ ይቻላሉ፡፡ በዚህም ወላጆች
በሚመቻቸው ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ እንዲመዘገቡ ወይም Account
እንዲኖራቸው ይደረጋል፡፡ በዚህም ትምህርት ቤቱ የሚፈለገውን መልዕክት
ማስተላለፍ ከወላጆችም ጥያቄ ወይም አስተያየትን በቀላሉ ማግኘትይችላል፡፡
ይህም ደብዳቤ ከመፃፃፍ ለወላጅም በአካል ትምህርት ቤቱ ድረስ ከመሄድ በፍጥነቱ
በቀላልነቱ እንዲሁም በርካሽነቱ የተሻለ ያደርገዋል፡፡
በርግጥ አንድ ነገር ሊነሳ ይችላል ይህም ይዘታቸውንና ደረጃቸውን ያልጠበቁ
መረጃዎች ከየትኛው ወገን ሊመጣ ስለመቻሉና የመረጃው ደህንነት ጉዳይ ነው፡
፡ ነገር ግን ለነዚህ እንደ መፍትሄ ሊወሰድ የሚችለው አሉታዊ ተፅዕኖውን ብቻ
በማሰብ ፋይዳውን ሙሉ ለሙሉ ከማጣት ይልቅ በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ብዙ የዘርፉ
ባለሙያዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ የአጠቃቀም ፖሊሲና ዕውቀትን ከባለሙያ ጋር
በማቀናጀት በቀላሉ የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ መሆን ይቻላል፡፡
ሌላው ሊጠቀስ የሚችለው ልምድ ደግሞ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ተማሪዎች
ፎቶ በመቀያየር ይሁን ሀሳብ በመለዋወጥ የበይነ መረብ (internet) የመጠቀም
ልምዳቸውን ማዳበራቸው ነው፡፡ ይህ ልምድ ደግሞ ለየትኛውም ስራ ወይም ቢዝነስ
በጣም አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን እግረ መንገዳቸውን ወደፊት ለሚኖራቸው የስራ
ዘመን ራሳቸውን ብቁ እያደረጉ ይመጣሉ፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ተግባር የማህበራዊ ድረ-ገጾች ተፅዕኖ አዲስ
ክስተት የፈጠረው አዲስ የሽያጭ (Marketing) ዘርፍ ነው፡፡ ይህም (social media
marketing) የማህበራዊ ድረ-ገጽ ሽያጭ በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህም መፍጠርና
ማደግ በብዙ አገራት የሚገኙ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን የማህበራዊ ድረ-ገጽ
ማርኬቲንግ ስትራቴጂ መንደፍ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡
በአገራችን ብዙ ድርጅቶች ይህንን በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም የተማሪዎች
ይህ ልምድ ወደ ስራው ዓለም ሲገቡ ጥሩ የማህበራዊ ድረ-ገጽ ማርኬቲንግ ባለሙያ
ሊሆኑ እንደሚችሉ ከወዲሁ ማሰብ ያስፈልጋል ፡፡ ወይም በቀላሉ በዚህ ዘርፍ ላይ
መሰማራት ይችላሉ ለማለት ይስችላል፡፡
በተለያዩ አገራት የሚገኙ መምህራንም በሚያስተምሩት ትምህርት ዓይነት ስም
ማህበራዊ ድረ-ገጽ በመክፈት የቤት ስራን አንኳን በተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾች
አማካኝነት በመስጠትና ለመወያየት ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ ይህም ተማሪዎች
ከትምህርት ሰዓት በተጨማሪ ትምህርታዊ ጉዳዮችን ከመምህራኖቻቸው ጋር
ለመለዋወጥም ሌላኛው መንገድ ነው፡፡
የፅሁፍ ክህሎትንም ማዳበር ከዚህ የሚገኝ ሌላው ተጨማሪ አብሮ ሊጠቀስ የሚችል
ጥቅም ነው፡፡ ሌላው በአደጉት አገራት የምንመለከተው ት/ቤቶች የትምህርት
ቤቱን ስምና የሚሰጠውን አገልግሎት እንዲሁም የት/ቤቱን አላማ፣ ተልዕኮና ጉዞ
በማስተዋወቅ እንዲሁም ማህበራዊ ድረ-ገጽን ከዋናው የት/ቤቱ ድረ-ገጽ ጋር
በማገናኘት ማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ የሚገኙትን ግንኙነቶች ወደ ዋናው የት/ቤቱ
ድረ-ገጽ በመምራት በዛ ላይ የሚገኙትን መልዕክቶችና አገልግሎቶች ብዙዎች
እንዲገነዘቡት ለማድረግ ይጠቀሙበታል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ይኸው ከላይ የጠቀስነው ጥናት እንደሚጠቁመን ወደ 75%
የሚጠጉት ዋና ድረ-ገጽ ጉብኝት የተደረጉት በማህበራዊ ድረ-ገጽች በኩል
እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ስለሆነም ማህበራዊ ድረ-ገጾች ለሌሎች ገጾች መጎብኝት
ትልቅ ሚና እንዳላቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ት/ቤቶች ማህበራዊ
ድረ-ገጽ እንዲኖራቸው በማድረግና በሚገባ በማንቀሳቀስ የተለያዩ መልካም
ስራዎችን ማበረታታትና ስለ እያንዳዱም አገልግሎታቸው ጥራትና አስተያየትን
ከሚመለከታቸው ወገኖች ለማግኘት ያስችላል፡፡ ስለዚህ ይህንን ከማህበራዊ ድረ-
ገጾች የሚገኘውን ጥቅም በማሰብ ተማሪዎች በአግባቡ እንዲገለገሉበት የማድረግ
እና እንዲሁም የፅሁፍ እና የበይነ መረብ መረጃዎችን የመጠቀም ፍላጎታቸውና
አቅማቸውን የማሳደግ የሁሉም ሀላፊነት ሊሆን ይገባዋል፡፡
እዚህ ጋር ሊነሳ የሚችለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተለያዩ ጉዳዮች
ሃሳብ እንዲቀያየሩ ለፈጠረው ተማሪኔት WWW.temarinet.com ለተባለው ድረ-
ገጽ ምስጋና ሊቸረው ይገባል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን በዜና አውታር እንደተገለጸው ተማሪዎች የኤሌክትሮኒክ
መፅሐፎችን እንዲሁም መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ የሚረዳውን የመንግስት
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ቤተ መፃሐፍት እና ቤተ ሙከራዎችን በኔትወርክ
የማስተሳሰር እና የማገናኘት እንቅስቃሴም ሊደነቅ የሚገባው ተግባር ነው፡፡
እንግዲህ ዘመኑ የኢንተርኔት እንደመሆኑና ወጣቱም ሚዲያ እየተገለገለ ስለሚገኝም
በሚገለገልበት ሚዲያ ተጠቅሞ ወጣቱን ማግኘትና ወደሚፈለገው የእድገት ደረጃና
አቅጣጫ መምራትና ማስተማር ተመራጭ መንገድ እንደሆነ የዘርፉ ጥናት ባለሙያዎ
የሚጋሩት ሃሳብ ነው፡፡ ነገር ግን በአንዳዶች እንደሚደረገው ማህበራዊ ድረ-ገጾችን
እንዳይጠቀሙ መከላከሉና መዝጋቱ ወጣቱን ከዚህ ፍላጎት ለማራቅ የሚረዳ መንገድ
አድርጎ መውሰዱ የሚያዋጣ አይመስልም፡፡ ለዚህም አንዱ ምክንያት ከዚህ በኋላ
ይህንን የቴክኖሎጂ አገልግሎት በአገራችን እንኳን እጃችን ላይ ባለው የስልክ ቀፎ
አማካኝነት በየትኛውም ስፍራ ያውም አሁን በቅርቡ ስራ ላይ በሚውለው ዓለም
በደረሰበት ከፍተኛ ፍትነት 4G lte ቴክኖሎጂ ኔትወርክ ማግኘት ስለሚቻል፡፡
ነገር ግን የተወሰኑ የማህበራዊ ድረ-ገጾች ሊያሳድሩ የሚችሉ አሉታዊ ተፅዕኖ ስጋት
በመጋራት በአግባቡ የመጠቀም ባህሪ ማዳበር እና ቅድሚያ ሚሰጠውን የህይወት
ተግባራት ጊዜና ትኩረትን ከሚፈለገው በላይ በማይሰርቅ መልኩ መከናወን
እንዳለበት ፀሐፊያን ያምናሉ፡፡
በመጨረሻም የዚህ ቴክኖሎጂ ማለትም የማህበራዊ ድረ-ገጾችን አጠቃቀም
በምንፈልገው ይዘትና መጠን የማሳደግ ጉዳይ ጊዜና ትግስትን የሚፈልግ በመሆኑ
በጊዜ ሂደትሁሉንም ልምድና ዕውቀትን እያገኘን ያደጉት አገራት በሚጠቀሙት
ደረጃየማንገለገልበት ምንም ምክንያት አይኖርም፡፡ ነገር ግን ለዚህ ቴክኖሎጂና
ለሂደቱ ሁሉም ወገን ቀና አመለካከት እንዲኖረው ያስፈልጋል
ቴክኖ-እመርታ
10
	 በዝግጅት ክፍሉ
የኤሰ ኦ ኤስ ዓለም አቀፍ የህጻናት መንደሮች
ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን የዛሬ
60 ዓመት በ1949 ዓ.ም (እ.አ.አ) በፕሮፌሰር
ኸርማን ሜየር በተባሉ ግለሰብ በኦስትሪያ
ተመሰረተ፡፡ ወቅቱም 2ኛ የዓለም ጦርነት ማብቂያ
እንደመሆኑ በጊዜው በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ህይወት
በመጥፋቱ ምክንያት የብዙ ቤተሰቦች እና ዘመዳሞች
አድራሻ በመጥፋቱ ግለሰቡ በዚህ አስከፊ ወቅት
የተጎዱትን በመደገፍ እና የተጠፋፉትን በማገናኘት
የራሳቸውን አስተዋጽዎ ለማድረግ ታስቦ የተቋቋመ
ተቋም ነበር፡፡ ይህንን መሰረት አድርጎ የተቋቋመው
ኤስ ኦ ኤስ የስራ አድማሱን በማስፋት በአሁኑ ወቅት
ሃገራችንን ጨምሮ በ134 አገሮች ላይ እየሰራ ይገኛል ፡
፡ በቅርቡ ፋይናንሻል ታይምስ /Finnancial Times/
በተባለ ታዋቂ የፕሬስ ድርጅት በተደረገ ጥናት ድርጅቱ
በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ከሚንቀሳቀሱ በጎ አድራጊ
ድርጅቶች በአቅም እና በበጎ አድራጎት 33ኛ ደረጃ ላይ
ይገኛል፡፡
ኤስ ኦ ኤስ በኢትዮጽያ የዛሬ 40 ዓመት በ1974 ዓ.ም
(እ.አ.አ) በሃገራችን ተከስቶ በነበረው ድርቅ በተለይም
በትግራይ ክልል የነበረውን ችግር ለመፍታት በክልሉ
ተቋቋመ፡፡ በወቅቱ የተከሰተውን ጊዜያዊ ችግር
ለመታደግ ይመስረት እንጂ የስራ አድማሱን በማስፋት
ላለፉት 40 ዓመታት የተለያዩ በጎ ስራዎችን በተለያዩ
የሃገራችን ክፍሎች ሰርቷል እየሰራም ይገኛል ፡፡
ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጽያ በሦስት ዋና
ዋና ተግባሮች መሰማራቱን የገለጹልን አቶ ወርቅነህ
ንጉሴ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጁ ዲን እነዚህም ትምህርት፤
ጤና እና የህጻናት እንክብካቤ ናቸው፡፡ አያይዘውም
ድርጅቱ ይህን አገልግሎት የሚሰጠው በሰባት የሃገሪቱ
ክልሎች ሲሆን እነርሱም አዲስ አበባ፤ ሐዋሳ፤ መቀሌ፤
ሐረር፤ ባህርዳር፤ ጎዴ እና ጅማ ናቸው ፡፡
ድርጅቱ በዋነኛነት የተነሳለት ዓላማ ቤተሰብ
የሌላቸውን ቤት እና ቤተሰብ (መንደር) እንዲኖራቸው
ማድረግ ሲሆን በሃገራችንም ቤተሰባቸውን በተለያዩ
አለም ዓቀፍ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ
አቶ ወርቅነህ ንጉሴ የኤሰ ኦ ኤስ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲን
በዚህ አጭር ጽሁፍ ኤሰ ኦ ኤስ በአትዮጵያ ያሳለፈውን 40 ዓመት መዳሰስ እጅግ በጣም ከባድ ነው፡፡ ይሁንና
ከአቶ ወርቅነህ ንጉሴ የኤስ ኦ ኤስ የቴክኒክና ሙያ ት/ቤት ዲን ከተምሳሌት ጋር ያደረጉትን አጭር ቆይታ
ለአንባቢ በሚመች መልኩ ቀንጨብ አድረገን አቅርበነዋል፡፡ ወደፊት የኮሌጁን አጠቃላይ የትምህርት አሰጣጥ
እንዲሁም ተደራሽነት በስፋት የምንመለስበት መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለአንባቢዎቻችን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ኤስ ኦ ኤስ
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???ገጽ ለገጽ
11
ነው፡፡ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርት ጋር በተያያዘ
የተቋሙን አሰራር ያስረዱን አቶ ወርቅነህ ኮሌጁ 10ኛ
እና 12ኛ ክፍልን አጠናቅቀው በአካዳሚክ ትምህርት
መስክ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግባት
ያልቻሉትን ወጣቶች ፍላጎታቸው ወደ ቴክኒክና
ሙያ የሆኑ ተማሪዎችን የሚቀበል ሲሆን በመንግስት
መመዘኛ የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ቅበላ ያደርጋል፡፡
የሚቀበላቸው ተማሪዎችም በሦስት ምድብ የተከፈሉ
መሆናቸውን የሚገልጹት አቶ ወርቅነህ እነዚህም
ኤስ ኦ ኤስ በተለያዩ ፕሮጄክቶች እያሳደጋቸው ካሉ
ቦታዎች የሚመጡ ወጣቶች፤ በህብረተሰቡ ውስጥ
ለኑሮ አማራጭ በማጣት የተጎዱ የህብረተሰቡ ክፍሎች
የሚመጡ ወጣቶች /disadvantage affermative
action community segment/ እና የትምህረት
ወጪ ክፍያን በግላቸው ከፍለው ለመማር ወደ ተቋሙ
የሚመጡ ተማሪዎች ናቸው፡፡ በኮሌጁ የሚሰጡ
የትምህረት አልግሎት ለሁሉም ተጠቃሚ እኩል
መሆኑና በኤስ ኦ ኤስ የተለያዩ ፕሮጄክቶች ታቅፈው
ከህጻንነት እድሜያቸው ጀምሮ በእንክብካቤ አድገው
ወደ ኮሌጁ የሚቀላቀሉ ወጣቶች በኮሌጁ የጤና
አገልግሎት፤ መጠለያን፤ ማደሪያን እንዲሁም የምግብ
ወጪ በኮሌጁ በተለየ ሁኔታ ድጋፍ ይደረግላቸዋል ፡፡
የተቋሙ ቴክኒክና ሙያ ት/ቤት የሚያስተምርባቸው
ሂደቶች ከ1ኛ-5ኛ የደረጃ እርከን ያላቸው ሲሆን
በእያንዳንዱ እርከን ተማሪዎች መማር ያለባቸውን
መሰረታዊ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እንደሚቀስሙ
ዲኑገልጸውልናል፡፡ በተቋሙ የሚሰጠው የቴክኒክና
ሙያ ትምህርት በሃገሪቱ አሉ ከተባሉ ተቋማት ጋር
ሲነጻጸር በመምህራን ብቃት፤ በማስተማሪያ ቁሳቁስ
አደረጃጀት፤ እንዲሁም በማስተማሪያ ቦታ ስፋትና
ጥራት ብቃት ያለው መሆኑን አስመርቆ የሚያወጣቸው
ወጣቶችም ለሃገሪቱ የተማረ የሰው ኃይል በማቅረብ
ረገድ ክፍተኛ አስተዋጽዎ እያደረገ መሆኑን
ገልጸውልናል ፡፡
የኮሌጁን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት የጨረሱትን
ወጣቶች የስራ ፈጠራን አስተዳደር ትምህርትን
እንዲሁም የተለያዩ የማነቃቂያ /motivational/
ንግግር የሚያደርጉ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በከፍተኛ
ክፍያ በማስመጣት እና በመጋበዝ ተጨማሪ ስልጠና
ይሰጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተወሰኑ ወጣቶችን
በማደራጀት ከመንግስት እና ከገንዘብ ተቋማት ጋር
ቅንጅት በመፍጠር የተለያዩ ፕሮጄክቶችን በመንደፍ
ወጣቶች ራሳቸውን እንዲችሉ ከዚያም አልፎ ስራ አጥ
ወገኖቻቸውን በመቅጠር ድጋፍ እንዲያደርጉ ከፍተኛ
ማበረታቻ ይደረግላቸዋል ፡፡
ኤስ ኦ ኤስ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ከሌሎች በሃገሪቱ
ከሚገኙ ተመሳሳይ ተቋማት የሚለይባቸው የራሱ ባህሪ
እንዳለው የሚገልጹት ዲኑ በኮሌጁ ተምረው የተመረቁ
ወጣቶች ተመልሶ የቤተሰብ ጥገኛ እንዳይሆኑ ስራ
እስከማስያዝ እና ከኮሌጁ ከወጡ በኋላም በማህበረሰቡ
ውስጥ ያላቸውን አበርክቶ እስከመከታተል የሚያደርስ
ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸውልናል፡፡
ምክንያቶች ያጡ በሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናትን እንደ
ወላጅ በመንከባከብ ለቁም ነገር ማብቃት ነው፡፡ እነዚህ
ህጻናት ለቁም ነገር የሚበቁበትን ሂደት ያብራሩት አቶ
ወርቅነህ ቤትና ቤተሰብ የሌላቸውን እንዲሁም ቤት
እና ቤተሰብ ኖሯቸው በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙትን
በማሰባሰብ እርዳታ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት
ነው፡፡ ቤትና ቤተሰብ የሌላቸውን ወገኖች ድርጅቱ
በገነባው የህጻናት ማሰደጊያ በመሰብሰብ 10 ህጻናት
በአንድ ቤተሰብ ውስጥ በማደራጀት እንደ እናት
ተንከባካቢ የሆኑ ሞግዚቶችን በመመደብ እንዲያድጉ
የሚደረግበት አሰራር ሲሆን፤ በአንድ መንደር ውስጥ
ከ16 - 19 የሚደርሱ ፕሮጄክቶች የተካተቱበት ነው፡
፡ በሌላ ወገን የሚገኙት ተረጂዎች ማለትም ቤተሰብ
ኖሯቸው ነገር ግን በተለያዩ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ
ችግሮች ቤተሰቦቻቸውን ለማጣት የተቃረቡ ህጻናትን
ተንከባካቢ ወገን ባለበት የቤተሰብ ማጠናከሪያ
ፕሮግራም በማዘጋጀት እርዳታ እያከናወነ ይገኛል፡፡
ዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው እና ከፍተኛ ትኩረት
ተሰጥቶት በመሰራት ላይ የሚገኘው ተግባር ትምህርት
ነው፡፡ ትምህርት በሁሉም መንደሮች ላይ ከህጻናት
ማቆያ አንስቶ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የሚደርስ የቀለም
ትምህርት በመስጠት ህጻናቱን ይንከባከባል ፡፡ ድርጅቱ
በሁለት የሃገሪቱ ቦታዎች የኮሌጅ ትምህርት እየሰጠ
እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ወርቅነህ እነዚህም የቴክኒክና
ሙያ ስልጠና በአዲስ
አበባ እንዲሁም ነርሲንግ ሙያ ትምህርት በመቀሌ
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???ገጽ ለገጽ
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
12
	 በአዜብ ዓለማየሁ
ባህሌን………..ባህሌን…………ያልኩባቸው ቀናቶችና ጊዜያቶች እጅግ እየበረከቱ
ከመጡ ውለው አድረዋል እራሴን ዘውር ብዬ እንድመለከት ያደረጉኝ ጊዜያቶችም
በረከቱ ያ’ገሬ ልጆች… እስቲ ለሰከንድ ምን ላይ እንዳለን እራሳችንን እንመልከት
ውበታችንን፣ ማንነታችንን፣ ባህላችንን፣ ራሳችንን ከረሳነው እና በሌሎች ማንነት
ከተሸፈንን ሰንብተን…. የምወዳቸው የአገሬን ልጆች እንድታዘብ ያደረገኝ እና ይህንን
ፅሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ ሰሞኑን በአገራችን ተካሂዶ በነበረው አንድ የሽልማት ስነ-
ስርዓት ነው “ሰው ለሰው” ድራማ ፡፡ ድራማው በኢብኮ ለ3 ዓመት ተኩል ሲተላለፍ
የነበረ ድራማ ነበር፤ እኔ በዚህ ጽሁፌ ስለድራማው ይዘት ልጠቅስ አልፈልግም ነገር
ግን ተሸላሚዎቹ ለብሰዋቸው የነበሩት አልባሳት ላይ ያለኝን አስተያየት ለመሰንዘር
እንጂ በቀን ተቀን ኑሮችን ውስጥ የባህል ልብሳችንን እንልበስ ወይም በየዝግጅቱ
የባህል ልብስ ግድ ይለበስ የሚል አቋም የለኝም ነገር ግን በእንደዚህ ዓይነት ትላልቅ
ዝግጅቶች ላይ በተለይ ታዋቂ ሰዎቻችን(አርቲስቶቻችን) የኛ ኢትዮጵያውያን
መገለጫ አገርኛ የሆኑ አልበሳቶችን ለማስተዋወቅ ከእንደኔ አይነቱ ተራ ሰው የተሻሉ
አምባሳደሮች ይመስሉኛል፡፡
በዚህ የሽልማት ዝግጅት ላይ ከሁለት ወይም ከሦስት የማይበልጡ አርቲስቶች
የባህል አልባሳቶቻቸውን የለበሱ ቢሆንም አብዛኛኞቹ ግን እጅግ አጫጭር
ቀሚሶችንና ለዝግጅቱ ሊመጥኑ የማይችሉ አልባሳትን ነበር ምርጫ ያደረጉት ሌላው
ቢቀር እድሜን እንኳን ያላገናዘበ አለባበስ የለበሱ አርቲስቶችን ተመልክቼ ነበር፡፡
እንደ’ነዚህ ዓይነት ዝግጅቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ የመታየት እድላቸው እጅጉን የጎላ
ነው፡፡ ስለዚህም እንዳ’ባቶቻችን እንደ አያት ቅም-አያቶቻችን ብሂል “ባ’ንድ ድንጋይ
ሁለት ወፍ” እንዲሉ ለብሰነው ብንታይ ድምቀትና ውበት ፣ ግርማ ሞገስና ጌጥ
የሚሰጠን ኩራቻችን ከዚየም አልፎ መደምቂያችን የሚሆን አገርኛ አልባሳታችን
በሆነ ነበር ፡፡ እናም ታዋቂ ሰዎቻችን እኔ እናተን ልመክር ባልዳዳም እንደው እንደ
እስተያየት እንድታስቡበት ለማለት ያህል ነው፡፡
ሌላው አገርኛ ያልሆኑ አሁን አሁን እንደውም ፍፁም ኢትዮጵያዊ እየመሰሉ ያሉ እና
ድንበር ዘለል የሆኑ ክብረ በዓላቶች እየበዙና እየሰፉ ከመጡ አመታትን አስቆጥረዋል፡
፡ ምን እየሆነ እንደመጣ ለመገመት ቢከብደኝም ሁላችንም ራሳችንን ለማጠየቅ
ባህል፣ ወግ፣ ቅርስ፣ ማንነት የሚባሉት ኢትዮጵያን፤ ኢትዮጵያ ህዝቦቿንም ሉዓላዊ
ያስባሉት ትውፊቶች በአሁኑ ሰዓት ፈፅሞ እየተረሱና እየጠፉ ለመሆኑ ምስክር
መጥራት አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡
ሌላው ቢቀር እኔ አገሬን እወዳታለሁ፣ እኔ ሐበሻ ነኝ፣ ኢትዮጵያዊነቴ ኩራቴ ነው ብሎ
መናገር እንደ ኋላ ቀር እና አላዋቂነት እየተቆጠረ ያለበት ጊዜ ላይ ቆመን እንገኛለን ፡፡
ቫላንታይንስ ደይ፣ ክሬዚ ደይ፣ አፕሬል ዘ ፉል ደይ፣ ክሬስማስ ደይ……..ወዘተ
እየተባሉ ሙሉ በሙሉ ከእኛ ባህልና ወግ የወጡ ማንነታችንን ፍፁም በሚያጎድፉ
አጓጉል በዓላት ውስጥ ተዘፍቀን እንገኛለን፡፡ አንድ ነገር ላውራ…. የገና በዓልን
እናስታውስ በእያንዳዳችን ስልክ ላይ ከቴሌም ሆነ የቅርብ ጓደኞቻችን የሚደርሰን
አጭር የፁሁፍ መልክትን እናስተውለው… ከጥቂቶች በስተቀር (Merry x-mass,
happy x-mass) የሚሉ መልዕክቶች ናቸው በእውነቱ ግን እኛን መልካም የገና
በዓል የሚለው ነው ሊገልጸው የሚችለው? ወይስ x-mass የሚለው የፈረንጅ አፍ
መልሱን ሁሉም በልቦናው ይያዘው
ማንነታችንን ሊገልጽን የማይችል የገና ዛፍና ባዶ ካርቶኖችን በስጦታ ወረቀት
አሸብርቀን ቤታችንን አድምቀን በዓል ለማክበር እንታትራለን ፤ ስለ እውነት ነው
የምለው እኔ ትርጓሜው እንኳ አይገባኝም፡፡ የገና ጨዋታን በዓለም አቀፍ ደርጃ
ማስተዋወቅ ስንችል እኛ ግን ስለ ገና ጨዋታ ማውራት የማንችንል ትውልዶች
ሆነናል ፡፡
ለእኔ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ 365 ቀን የፍቅር ቀን ነው ብዬ አስባለሁ ፍቅር ከሁሉ
ይበልጣልና ታድያ ለዚህ ከሁሉ ይበልጣል ለተባለው ፍቅር በአመት አንድ ቀን
ሰጥቶ ማክበር አያሳፍርም፡፡ በው’ኑ ለኛ ቫላንታይን ይመጥነን ነበር ? በርግጥ ቄስ
ቫላንታይንን አከብራቸዋለሁ መልካም ቄስም ነበሩ፣ መልካም ስራ ሰርተው ያለፉ…
እኚ ቄስ ለጥቂት ጥንዶች ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ አባት ናቸው…. አያችሁ እኚ
ፈረንጆች ብልጦች ናቸው በስማቸው ቀን ሰይመው ዓለም እንዲዘክራቸው አደረጉ፡፡
እስቲ አንድ ኢትዮጵያዊ ካህንን ላስታውሳችሁ አቡነ ጴጥሮስ ይባላሉ ……አቡነ
ጴጥሮስም ልክ እንደ ቄስ ቫላንታይን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሃይማኖታዊ አገልጋይ
ነበሩ እኚህ አባት በሚገርም ሁኔታ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለምድሬቷ ጭምር በግፍ
የተገደሉ ጠንካራ አባት (ሰማዕት) ነበሩ ፡፡ እስቲ ስንቶቻችን አቡነ ጴጥሮስ ለፋሺሽት
ኢጣሊያ ህዝቦቿ ብቻ ሳሆኑ ምድሬቷም ጭምር እንዳትገዛ ገዝተው ለጥቂቶች
ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያዊ ሲሉ እራሳቸውን አሳልፈው በግፍ ከ ሰላሳ ጥይት
በላይ ተርከፍክፎባቸው እንደሞቱልን የምናውቅ ስንቶቻችን እንሆን? መሰዋትነትን
የተቀበሉበትን ቀን የምናውቅና አስበን የምንውልስ ኢትዮጵያዊያን ስንቶች ነን ልብ
ያለው ልብ ይል ዘንድ ሐምሌ 22/1928 ዓ.ም መሆኑን ጠቅሼ ማለፍን መረጥኩ፡፡
እንግዲህ እነዚህ ሁለት አባቶች በተለያዩ ቦታዎች የተፈጠሩ ለተለያየ ዓላማ
የሞቱ ሰዎች ነበሩ ፡፡ ግን ግን ለኛ ኢትዮጵያውያን ኩራታችን ሊሆን የሚገባው
ማን እንደነበር መናገር አይጠበቅብኝም ፡፡ አስተዋዮች ብንሆን ኖሮ ግን አቡነ
ጴጥሮስን ከእኛ አልፈን እንደ ብልጦቹ ጣልያኖች በአለም አቀፍ ደረጃ ቀን አሰይመን
ልናከብራቸው እና ልናዘክራቸው በተገባ ነበር፡፡ በእጅ የያዙት ወርቅ ሆነና ነገሩ
በሰው ጌጥ እኛ ለመድመቅ እንታትራለን ፡፡
ባ’ገራችን ከእኛ አልፈው ሌሎች እንዲያከብሯቸውና እንዲዘክሯቸው ልናደርጋቸው
የሚገቡ ብዙ ቀኖች እንዳሉን ልብ ልንል ይገባል፡፡አበቃሁ…………ኢትዮጵያ ለዘላለም
ትኑር፡፡
እኔ’ምለው
የኔ ሃሳብ
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
13
	 በዝግጅት ክፍሉ 	
እኒህ ሰው የ 59 ዓመት ጎልማሳ ናቸው፡፡ ከታዋቂው የሲ ኤን ኤን የቢዝነስ ዘጋቢ
ሪቻርድ ኩዊስት ጋር ፊት ለፊት ቁጭ በለው ይነጋገራሉ፡፡ ሰውዬው ብላክ ቤሪ
ዘመናዊ ስልኮች አምራች ኩባንያ ቺፍ ኤክስክውተቭ (ዋና ኃላፊ) ናቸው፡፡ ጆንቼን
ይባላሉ ዋልት ደዝኒ የመሳሰሉ ትላልቅ ኩባንያዎችን ያስተዳድሩም ናቸው፡፡ ጄን
በዓመት ውስጥ እጅግ ጥቂት ቀናት ብቻ በእረፍት ያሳልፋሉ፡፡ እሳቸው ከ3 አና ከ4
ቀን አይበልጥም ባይ ናቸው፡፡
ሰውዬው በዓመት ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንዳላቸው ይነገራል፡፡ እናም
ጊዜያቸውን በሙሉ በድርጅቱ ስራ ላይ ያሳልፋሉ፡፡
ሪቻርድ ኪዊስት ጠየቀ ፡- ከስራ ውጪ ጊዜ ምትሰጠው ጉዳይ ምንድነው?
ጆን ቼን መለሱ ፡- ከስራ ውጪ ለሁለት ነገሮች ጊዜ እሰጣለሁ ከ 24 ሰዓቱ 2 ወይም
3 የሚሆኑትን ሰዓታት የመጀመሪያው ለቤተሰቦቼ የምሰጠው ጊዜ ሲሆን ሌላው
ለንባብ የምሰጠው ጊዜ ነው፡፡ እነዚህ ጊዜያት ከስራም ከቴክኖሎጂ ውጤቶችም ነፃ
የሆኑ ናቸው፡፡ ቴሌቭዥን፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ አይ ፓድ ከመሳሰሉ
በህይወቴ በየእለቱ ከሚያጋጥሙኝ ነገሮች የምርቅበት ነፃ ጊዜ ናቸው አሉ ሚስተር
ቼን ፈገግ ብለው፡፡
እኔም ከቴክኖሎጂ ጥገኝነት (Technological dependency) ነፃ የምሆንበት ጊዜ
በመሆን እጅጉን የምወደው ሰዓት ነው አሉ ቼን፡፡
የጆን ቼንን ሃሳብ ያነሳሁት እሩቅ ሳትሄዱ እዚህ ያለን የኢትዮጵያውያን ህይወትም
በቴክኖሎጂ የተከበበ ሆኗል፤ ነው፡፡ ተፈጥሯዊ ስጦታዎቻችንን ለመጠቀም ፈፅሞ
እየሰነፍን ነው፡፡ ማለዳ ከእንቅልፋችን ተነስተን ማታ ወደ መኝታችን እስክንመለስ
ድረስ ምን ያህል ህይወታችን ከአዳዲስ እና ነባር የፈጠራ (የቴክኖሎጂ) ውጤቶች
ጋር እንደተሳሰርን ለአፍታ አስበነው እናውቃለን፡፡ ባለሱቁ በእጁ የሂሳብ ማሽን
(ካልኩሌተር ካያልዙ) ሂሳብ ድሮ ቀረች…… የሂሳብ ደብተርምእንዲሁ፤ የስልክ ቁጥር
መመዝገቢያ ደብተር ያላቸው ቁጥራቸው ጥቂት የሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡ ማስታወሻ
ደብተርም ዛሬ የለም ተንቀሳቃሽ ስልካችን ብዙ ነገርን ፈታ ፤ ብዙ ነገሮችን አቃለለ፡፡
ግን፤ ግን ለ 10+5 ሁሉ ቴክኖሎጂ የምንጠቀም ነገር አልመሰላችሁም፡፡
የስነ ልቦና ባለሙያዎች ጥገኝነት (dependency) ሚባለው ሊሆን እንደሚችል እና
በምክንያቶች የተሞላ ነው፡፡ በውስጡ ብዙ የጥገኝነት አይነቶች ይይዛል፡፡ የግብ
ጥገኝነት (Goal dependency) ፣ የተግባር ጥገኝነት (Task dependency) እና የግዴታ
ጥገኝነት (Hard dependency) ን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ ይጥገኝነት ሁኔታዎች
መልካም ነገሮችን በመፈለግ ስለሙያው (ሰለስራው) ለማወቅ በመፈለግ የሚደረግ እና
አንዳዴ ደግሞ ሰዎች አማራጭ በማጣት የሚፈፅሟቸው ጥገኝነቶች ናቸው፡፡
በዛ የሚሉት ግን ለራስ አብልጦ ከማሰብ፣ ከፍርሃት፣ በራስ ካለመተማመንና
ስኬታማነትን በአቋራጭ ከመፈለግ ስሜቶች የሚነሱ ናቸው፡፡ እነዚህ ጋር
በተደጋጋሚ የአለቃ እና የሰራተኛ ፣ የመምህር እና ተማሪ እስከ ወሲብ ትንኮሳ የደረሱ
ታሬኮችን ማስታወስ እንችላለን፡፡ ምንም እንኳ ብዙ የስነ ልቦና ባለሙያዎች የምጣኔ
ሀብት (ኢኮኖሚ) ጥገኝነት በአለማችን ላይ ላቅ ያለውን ስፍራ ይይዛሉ ቢሉም፤ ይህ
ጥገኝነት አገራትም ጭምር በሌሎች አገራት እግር ስር እንዲንበረከኩ የሚያደርግ
ነው፡፡
ከማህበራዊ ጥገኝነት በተለየ አቅጣጫ የሚቀመጠው ደግሞ Related dependency
(ተያያዥ ጥገኝነት) ነው ፡፡ ይህ አይነት ጥገኝነት ከሰዎች የእለት ተእለት ግንኙነት
የሚፈጠር አይደለም፡፡ ይልቁንም ሰዎች ከሌሎች ነገሮች በሚፈጠር የጠበቀ
ግንኙነት የሚፈጠር ነው፡፡ እዚህ ጋር ቀደም ሲል የተነሳውን የቴክኖሎጂ ጥገኝነት
ማንሳት ይቻላል፡፡ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችም ይሁኑ ቁሳቁሶች የሰው ልጆችን
እንቅስቃሴ ለማቅለል ልፋቱን ለመቀነስ በራሱ በሰው ልጅ የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ነገር
ግን እነዚህ የቴክኖሎጂ ምርቶች ከዚህ ፍላጎት ብዙ እርቀው የሰውን ልጅ መልሰው
በቁጥጥራቸው ስር አውለውታል፡፡ የሰው ልጅ ራሱ በፈጠራቸው ቁሳቁሶች ቅኝ
ግዛት ተይዟል፡፡
አንድ ጊዜ አንድ ትልቅ ቤተሰብ ውስጥ ስለተፈጠረ ሁኔታ ወዳጄ ያጫወተኝን እዚህ
ጋር ማንሳቱ ተገቢ ሆኖ አገኘሁት፡፡ ትልቅ ቤተሰብ የሚለውን ቃል የተጠቀምኩት
Joint family የሚለውን የእንግሊዝኛ መጠሪያ ለመውሰድ ነው፡፡ ይህ ማለት ቤተሰቡ
እናት፣ አባትና ልጆች ብቻ ሳይሆኑ አያቶችና ሌሎችም ቤተዘመዶች መኖራቸውን
ለመግለፅ ይሆናል፡፡ ሰፊ ቤተሰብ አይነት ነገር ፡፡
እናም ቤተሰቡ ከውጭ አገር የሚኖሩ ልጆች የላኳቸው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች
አሉ እናም አያቶች ቴሌቭዥን ላይ፣ አባትና እና እናት ላፕቶፖቻቸው ላይ፣ ልጆች
አይፓዶቻቸው ላይ እንዳፈጠጡ ቀኑ ይመሻል፡፡ እናም ወዳጄ እንዲህ አለኝ
ቤተሰቡን ስትገልጸው ይህ በቤተሰብ መካከል ሀሳብ መለዋወጥ መነጋገር መደማመጥ
የሚባሉ ነገሮች ጠፍተዋል ፡፡ አብረው እየኖሩ አብረው አይኖሩም፡፡ እኔም በእሳት
ዳር ሰብሰብ ብለው መረጃን የሚለዋወጡ፣ የአገሩን ታሪክና ቅርስ የሚያወራ ወገኔ
በአይምሮዬ ብቅ አለ፡፡ ወይ ነዶ….ወይ ንዶ…..
ገና፣ ፈረስ ጉግስ፣ ገበጣና ሌሎችም ጫወታዎቻችን በሞባይልና ኮምፒውተር ጌሞች
ተለውጠዋል፡፡ ንባብም እርግፍ አድርገን ትተነዋል የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ማህበራዊ
ቁርኝታችንንበጣጥሶታል ዛሬ በየመዝናኛ ስፍራው ጨዋታና ሳቁ የለም ሁሉም
ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ አፍጥጧልና፡፡ ይህ ውሸት ነው ያላችሁ ጠዋት ከቤታችሁ
ስትወጡ ተንቀሳቃሽስልካችሁን መኖሪያ ቤታችሁ የረሳችሁ እና ቀኑን ሙሉ
ሲያቅበጠብጣችሁ ሲያባትታችሁ የዋላችሁ ምስክር ትሆናላችሁ፡፡
ስነ-ልቦና
የአኗኗራችን ነገር
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
14
	 ከጽጌሬዳ	
ታክሲ ውስጥ ነኝ፡፡ ከሹፌሩ ኋላ፡፡ማለዳ 1ሰአት አካባቢ፡፡ሁሉ ወደየጉዳዩ ለመሄድ
ከቤቱ የሚወጣበት ሰአት በመሆኑ ከመነሻው በመግባቴ ጥሩ ቦታ አገኘሁ እንጂ
በየጎማውና በየሞተሩ ላይ ተቀምጦመሄድ ልማዴ ነበር፡
መቼ እንደጀመረኝ እንጃ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለድምፆች ትኩረት እሰጣለሁ፡፡
በሙዚቃ መሃል በሰዎች ንግግር መሃል ለብዙዎች ያልተሰሙ ቢሰሙም ችላ ተብለው
የሚታለፉድምፆችጎልተውይሰሙኛል፡፡እዚህምየመኪናውሞተርይጮሃል፡፡አልፎ
አልፎ ከታክሲዋ ሆድ በሚወጣው ጡሩምባ ታጅቦ ችፍፍፍ የሚል የሃምሌ ዝናም
ከጣሪያው ይሰማል፡፡(በበጋው ወቅት ወደ ሰማይ የተነነውን አቧራ ያየ ተጠራቅሞ
ዘንድሮ በክረምት ከአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ጭቃ እነደሚዘንብ ቢተነብይም ትንቢቱ
አልሰራ ኖሮ ይኸው ቀደሞ የምናውቀው ዝናም ራሱ ከሰማይ ይወርዳል)፡፡
ጋቢና ከሹፌሩ አጠገብ የተቀመጠው ሰው ትከሻውን እያርገፈገፈ ያለማቋረጥ ይስላል-
ብርዱ ነው መሰል፡፡እዛው ጋቢና ከሱ በስተቀኝ ያለው ብላቴና ኪሱን እየዳበሰ
”ከዚህ ሜክሲኮ ስንት ነው?” ብሎ ጠየቀ አንገቱን ወደ ሹፌሩ አስግጎ፡፡
“እሱን ጠይቀው” አለ ሹፌሩ በአውራ ጣቱ ወደ ረዳቱ እየጠቆመ፡፡ሆ! አሁን እውነት
ሳያውቀው ቀርቶ ነው?ሆን ብሎ ነው እንጂ ሲሸፍጥ፡፡አንዳንድ የታክሲ ሹፌሮች
ታሪፍ ሲጠየቁ ደረጃቸውን ወደ ረዳትነት ዝቅ ያደረጉባቸው ይመስል እንደሁ እንጃ
ቅር ይላቸዋል፡፡ ለመመለስም ያቅማማሉ፡፡ልክ አንዳንድ ሴት ዶክተሮች ነጯን
ጋወን በመልበሳቸው ምክንያት “ሲስተር”“ነርስ” ሲባሉ ቅር እንደሚላቸው አይነት
ይመስለኛል ስሜቱ…የረዳትን ለረዳት የምን ማምታታት ነው?
እንዲያውምለስራፈጣሪዎችየሚሆንአንድሃሳብአለኝ፡፡የታክሲረዳቶችማሰልጠኛ
ቢኖርስ? አዎ ስለ ደንበኛ እና ገንዘብ አያያዝ፤ስለ አጠራር አይነቶች፤የሰፈር ስሞችን
በቀላሉ የማወቅ ዘዴ፤ስለ መልስ አሰጣጣጥ እና ሂሳብ ስሌት፤የረዳቶች የልምድ
ልውውጥ…እንደ ሞያ የተወሰነ ስልጠና ቢኖረው ደግ ይመስለኛል ..
ወደ ታክሲው ልመልሳችሁ በግጥም እና በዜማ ታጅባ“አታስፈራራኝ” እያለች
በማስፈራራት ትፎክራለች -አንዷ፡፡ ከኋላዬ ደግሞ ሌላዋ በጆሮ ግንዷ በለጠፈችው
ሞባይል ጥፋተኛ አለመሆኗን ለማስረዳት የመሃላ መኣት በመደረደር ይቅርታ
ትጠይቃለች፡፡-ምን ለበ ደንዳናው ቢገጥማት ነው እንዲህ እምባ እስኪቀራት
የምትማፀነው? ይኸው እዚህ ታክሲውስጥ ከገባሁ ጀምሮ ልመና ላይ ናት፡፡በአካል
ብታገኘውማ በ4 እግሯ ተጉዛ ከመሬት በተጎዘጎዘች፡፡በስልክ እንዲህ የሆነች…
አታደርገውም አይባልም መቼም፡፡
ከእሷ አጠገብ ያለው ተሳፋሪ ደግሞ በአዲሱ ታሪፍ መነሾ ከረዳቱ ጋር ይነታረካል፡
፡መብቴ እኮ ነው እያለ፡፡አይ መብት እቴ!‹መብትህ ታክሲ ውስጥ ስትገባ ብቻ
ትዝ አይበልህ› የሚል ጥቅስ እዚህኛው ባይሆንም ሌላ ታክሲ ውስጥ ማንበቤ ትዝ
ይለኛል፡፡ እስማማለሁ፡፡ አስቡት እስቲ ሱፉን ግጥም ያደረገ ጎልማሳ ላፕቶፑን
ተሸክሞ ወይም የቦርሳዋን እና የጫማዋን ቀለም አመሳስላ የወጣች ዘንካታ የገቡበት
ታክሲ ረዳት ሂሳብ ቢሳሳት መሳሳቱን በጥሩ ቋንቋ አስረድቶ መግባባት ሲቻል ገናለገና
‹ሊያጭበረብረኝ ነው› በሚል እሳቤስድድቡ እልፍ ሲልም ግብግቡን ይጀምሩታል፡
፡ስነምግባር የላቸውም፤ አረጋውያንን አያከብሩም ከሚለው ባሻገር በአላስፈላጊ
ሱሳቸው እና በንፅህና ጉድለታቸው ይወቀሳሉ የታክሲ ረዳቶች፡፡
ግን ያ ባለላፕቶፑ ሰውዬ ዩኒቨርሲቲ ግብቶ አካውንቲንጉን ሲማር ይህ የታክሲ ረዳት
የት ነበር? ምናልባት የትምህርት ቤት ደጅ ከረገጠ አመታት ተቆጠሩበት ወይም
በጭራሽ ትምህርትቤት ሄዶም አያውቅ ይሆናል ፤ ምናልባትም ያልጅ ነገን በተሻለ
‹‹ሰሌዳው
ተበይዷል››
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
15
ለመጠበቅ ገንዘብ ሲቆጥብ ቁርሱን አልበላ ይሆናል፤ምናልባት ደግሞ ታማሚ እናት
እና የሱን እጅ ጠብቀው የሚያድሩ ታናናሾች ይኖሩት ይሆናል፤ምናልባትም ያቺ
ዘንካታ ክብደቷን ለመቀነስ ያልበላቸውን እራት ትርፍራፊ እንኳን አጥቶት ፆሙን
ያደረ ይሆናል፤
ምናልባትም ያ ልጅ…ታዲያ እኛ ማን ነን? ያልዘራነውን፤ ያላረምነውን ልናጭድ
ማጭዳችንን ስለን የምንወጣ?
እንዲያውምለስራፈጣሪዎችየሚሆንአንድሃሳብአለኝ፡፡የታክሲረዳቶችማሰልጠኛ
ቢኖርስ? አዎ ስለ ደንበኛ እና ገንዘብ አያያዝ፤ስለ አጠራር አይነቶች፤የሰፈር ስሞችን
በቀላሉ የማወቅ ዘዴ፤ስለ መልስ አሰጣጣጥ እና ሂሳብ ስሌት፤የረዳቶች የልምድ
ልውውጥ…እንደ ሞያ የተወሰነ ስልጠና ቢኖረው ደግ ይመስለኛል፡፡መቼም አንድ
ሰው ስራዬ ብሎ ከቤት ከወጣ እና ገቢ አግኝቶ ከተዳደረበት ወንጀል እስካልሆነ
ድረስ ሙያው ነውና የሚያዳብርበት መንገድ ቢያገኝ አይጠላም፡፡
እኛ ምሁራን እኛ ስልጡናን ነን ባዮች ካፌ ገብተን ከተጠቀምነው በተጨማሪ
ለአስተናጋጆች 5 እና 10 ብር ቲፕ ስንሰጥ ቅር አይለንም፡፡ የታክሲ ረዳት ለተሳሳተው
5 እና 10 ሳንቲም ግን ግብ ግብ እንገጥማለን፡፡ለመሆኑ ቲፕ ብንሰጠውስ ምን አለበት?
ከማለዳ ጀምሮ እሰከ ምሽት ስንቱን አይነት ሰው ሲያስተናግዱ፤ በዛ በማይመች
አቋቋም ቆመው እንደሚውሉ፤ ጉሮሯቸው እስኪደርቅ ሲጠሩን እንደሚውሉ
አስባችሁታል የ12 ሰው ሂሳብ አስቦ(12 አልኩ እንዴ ?በስህተት ነው፡፡
አሁን አሁን እንኳ የአንድ ሚኒባስ አማካኝ የጭነት ልክ 15 ሰው ሳይሆን አይቀርም
ብታምኑም ባታምኑም ለ 12 ሰው በተሰራው ሚኒ ባስ 22 ሆነን ሄደን እናውቃልን ፡፡
ሹፌሩ እና ረዳቱ ሳይቆጠሩ፡፡ጋቢና 3 ሰው ባትሪ ላይ 2 ለሁለት ሰው የተሰሩት ሶስቱ
ላይ ሶስት ሶስት ከኋላ 4 ጎማ ላይ 3 ቆጠራችሁ?22፡፡)እናም በአንድ ጉዞ የዚህን ሁሉ
ሰው ሂሳብ አስልቶ መልስ መልሶ አንዳንዱ ደግሞ የራሱን ብቻ አይከፍል የ2 ወይም
የ3 ሰው ይላል የተለያየ ቦታ ሲደርሱም “ወራጅ አለ” ብሎ… እስቲ ራሳችሁን ለ1
ቀን በዛ ቦታ አስቡት::ከባድ አይሆንም? ረዳትነታቸው ለሹፌሩ ብቻ ሳይሆን ለኛም
ጭምር አይደለም?ብዙ ጊዜ ግን አላስፈላጊ ሱሳቸው እና ለሰው ክብር ማጣታቸው
ብቻ ጎልቶ፤ ጨዋና አገልጋዮቹ ተረስተው ሁሉን በአንድ ቁና ሰፍሮ በአንድ ሚዛን
መመዘን ይቀናናል፡፡
ከተሳፋሪስ ስንት አይነት ምግባረ ብልሹ አለ? ሳይከፍል “ከፍያለሁ” ብሎ ድርቅ
የሚል ከተሳካለትም አረሳስቶ የሚወርድ አደባባይ ላይ “ወራጅ አለ” የሚል ለምኖ
ተለማምጦ ትርፍ ከተጫነ በኋላ ትራፊክ ሲመጣ የክሱን ወረቀት ለመፃፊያ ብእር
የሚያቀብል፡፡
እኔ በበኩሌ ለ5 እና 10 ሳንቲም ብሎ መጨቃጨቅ እና መመናጨቅ መብት ከሆነ
ይቅርብኝ በገንዘብ የማየገኘውን ንፁህ ስሜት ማደፍረስ በቁጣ መሞላት መሰደብና
መሰዳደብ መብት ከሆነ ለዘላለሙም ይቅርብኝ ያውም በጠዋት ቀኔን ለምን
ላበላሸው?
ወደ ታክሲያችን ስንመለስ…
ከወደ ኋላ የአንዱ ሞባይል ስልክ ጮኸ -ኖኪያ ቶን፡፡“እንዴት ነበር እሱ
ድምፅ?”አላችሁ?ረሳችሁት አይደል?ሀገር ምድሩ በስማርት ፎን ሲጥለቀለቅ ያዳስተር
የመሰለው ሞባይል ተረሳ?እጃችንን እንዳላፍታታንበት፤ ሲቆለፍ ለመክፈት “እንዴት
ነበር?” እንዳላልንበት ኖኪያ ቶን ተረሳች ማለት ነው?እኔ ግን አልረሳኋትም፡፡ይሄው
እሷ ድምፅ ጮኸች ይሄ ሰውዬ ግን ከየት አግኝቷት ይሆን?
አደባባዩን እንደተሻገርን 3ኛው ወንበር ላይ “ወራጅ አለ” ማለቷ ያልተሰማላት ተሳፋሪ
እጇ ላይ በተመለሰላት ሳንቲም በቅርብ ያገኘችውን የታክሲ አካል ትቀጠቅጣለች፡፡
ሰቅጣጭ ድምፅ፡፡“በዚህ በዝናብ እግሬ ልታስመልሰኝ ነው?” ብላ እየተንጫነጨች
ወረደች
መጨረሻው ወንበር ላይ ደግሞ “አበሩ ከፍያለሁ እንዳትከፍይ” የሚል የጎልማሳ ሴት
ድምፅ አጠገቤ ላለችው ልጅ እግር አሻግሮ ያስጠነቅቃል፡፡
ይህእንግዲህበአንዱየስሜትህዋስ(ጆሮ)ብቻተጠቅሜያገኘሁትነው፡፡አንዳቸውም
እንኳ ድምፃቸው ጉዳዩ በማይመለከተው ሰው ጆሮ መግባቱን አላስተዋሉም፡፡
ቢያስተውሉም ግድ የላቸውም፡፡
ፀጥታ ሆይ ወዴት ነሽ?ሁካታ ከቦን ተጨነቅንልሽ!!!ከውጪ የትራፊክ ፖሊስ ፊሽካ
ድምፅ ተሰማ፡፡ሹፌራችን ግራና ቀኙን አይቶ ለሱ መሆኑን ሲረዳ ዳሩን ይዞ አቆመን፡
፡ “ወይኔ ትርፍ ይዘሃል እንዴ?” ዞሮ ረዳቱ ላይ አፈጠጠ “ያዝበት ጫንበት የሰው
ትርፍ የለውም” ሲል ቆይቶ ጉዳዩ የሚያስጠይቀው መሆኑን ሲያወቅ እጁንመታጠቡ
እኮ ነው እንደ ጲላጦስ “አላውቅም:: ከደሙ ንፁህ ነኝ::”ሊል፡፡
ለትራፊክ ፖሊሱ ክብር ሲል በሩን ከፍቶ ወርዶ አናገረው መንጃ ፍቃድ ሳይጠይቀው
አልቀረም ከኪሱ ወረቀት አውጥቶ አሳየው፡፡እጁን እያወናጨፈ ለማስረዳት ሲሞክር
በፊት መስታወቱ አሻግሬ አየዋለሁ፡፡የመከላከያ ሃሳቡ ተቀባይነትን አላገኘ ኖሮ አጅሬ
ትራፊክ መፍቻውን ይዞ ወደ ሰሌዳው አጎነበሰ፡፡
ቆይቶ ቆይቶ የግንባሩ ደም ስሮች ተገታትረው ቀና ቢልም ያሰበውን ባለማሳካቱ
እየተበሳጨ ነበር፡፡የፊቱን ሰሌዳ ትቶ ወደ ኋለኛው ያደረገው ጉዞም የአንድ ታክሲ
ቁመት ያህል ሁለት እና ሶስት ርምጃ ሳይሆን ትልቅ ግዳይ እንደጣለ የአራዊት ንጉስ
አንበሳ በድል አድራጊነት መንፈስ ጎምለል ጎምለል እያለ ነበር ምን ዋጋ አለው
የአቅሙን ያህል ቢለፋም የኋላውንም ሰሌዳ መፍታት አልቻለም፡፡ ከሹፌሩ ጋ ቆሞ
መደራደር ሲጀምር እስካሁን ድምፃቸውን ያልሰማሁት አዛውንት “ምነው ልጄ ቶሎ
የምትጥፈውን ጣፍና አሰናብተኒ የማንሄድም እንደሁ ቁርጡን አውቀን እንውረድ፡፡
”አሉ፡፡ ጋሽ ፖሊሱም መለሰ “አባባ እርሶ ምንምአያውቁም መንጃ ፍቃድም አልያዘ
ሰሌዳውም ተበይዷል የክስ ወረቀት በብቻ ያሳየኛል::”አላቸው::
“መንጃ ፍቃዱስ እሺ ሊረሳ ሊጠፋ በቅጣት ሊያዝም ይችላል…ሰሌዳ ግን እንዴት
ይበየዳል?ይቻላል?” ብዬ ጠየቅኩ ራሴን አዎ ይቻላል ቢቻልማ ነው የተበየደው፡፡
ልክ መሆን አለመሆኑን ግን እንጃ፡፡
ሰሌዳ የማንነት መለያ አይደለምን? ቀድሞ ነገር የሚወልቅ እና የሚጠልቅ ሆኖ ለምን
ይሰራል? የእያንዳንዳቸን የተበየደ ሰሌዳ ምን ይሆን? የማይለዋወጥ ማንነታችን፤
በክረምትቢሆን በበጋ፤ በማግኘት ቢሆን በማጣት፤ በክብር ቢሆን በውርደት፤
ስናጠፋ የማይወልቅ፤ ስናዝን የማይርቅ፤ ስንደሰት የማይለቅ፤ የጊዜ ርዝመት
የማያደበዝዘው፤ ማንነታችን ምን ይሆን የተበየደው ሰሌዳችን? ለቀኑ የሚሆን
የማሰላሰያ ሃሳቤን ያዝኩ:: ትራፊኩም ተስፋ ቆርጦ መሰለኝ መንገዳችንን እንድንቀጥል
ፈቀደልን:: እኔም የማሰላሰያ ሃሳቤን ለእናንተ እንዲህ አካፈልኩ::
እንዲያውም ለስራ ፈጣሪዎች
የሚሆን አንድ ሃሳብ አለኝ፡፡ የታክሲ
ረዳቶች ማሰልጠኛ ቢኖርስ? አዎ
ስለ ደንበኛ እና ገንዘብ አያያዝ፤ስለ
አጠራር አይነቶች፤የሰፈር ስሞችን
በቀላሉ የማወቅ ዘዴ፤ስለ መልስ
አሰጣጣጥ እና ሂሳብ ስሌት፤የረዳቶች
የልምድ ልውውጥ…እንደ ሞያ
የተወሰነ ስልጠና ቢኖረው ደግ
ይመስለኛል፡፡መቼም አንድ ሰው
ስራዬ ብሎ ከቤት ከወጣ እና
ገቢ አግኝቶ ከተዳደረበት ወንጀል
እስካልሆነ ድረስ ሙያው ነውና
የሚያዳብርበት መንገድ ቢያገኝ
አይጠላም፡፡
ተምሳሌት 	 	 	 	 	 	 	 	 	 	 ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???
16
	 በዝግጅት ክፍሉ
እንደው አንዳንዴ.. ምን አንዳንዴ በ’ለት ተዕለት ኑሮአችን የሚደረጉ
ድርጊቶች ፍትሐዊ አልሆን ብሎን ተበሳጭተን.. እርር ድብን ብለን..
አልቅሰን ባ’ቅመ-ቢስ ስሜት ውስጥ ሆነን ወደ ሰማይ አንጋጠን
አናውቅም? ወደ ላይ ካንጋጠጥንበት ቦታ አንጀት የሚያርስ ነገር
ወዲያው ባለማግኘታችን እንዲሁ ንዴታችን ሰማይ ጥግ ደርሶ አያውቅም ? ታዲያ
ይህቺ ምድር ፍትሐዊ አይደለችም ብላችሁ ደምድማችኋል ፡፡ ከዚህ በተቃራኒ
አንዳንድ ሰወች የሚያደርጉት ሰምሮላቸው .. የተናገሩት ተደምጦላቸው የገደሉት
ያስገደሉት #ተቀብሮላቸው; ወደ ሰማይ ቢያንጋጥጡም ያው እንደ ምድራዊ ህይወት
ሁሉ ተሳክቶላቸው ሁሉ በ’ጃቸው ሁሉ በደጃቸው ሆኖ ሲታይ በ’ነርሱ ዘንድ ምድር
ፍትሐዊ ፍርድም አምላካዊ መሆኑ አምነው ደምድመዋል ፡፡
ግን፤ ግን ሕግ፤ ፍትህ ምንድን ነው? .. ሁሉም ሰው ሊያስማማ የሚችል ትርጓሜ
ወይም ፍቺ አልተገኘም፡፡ በየዘመኑ የተነሱ የሕግ ፍልስፍና ት/ቤቶች / School of
thoughts / የራሳቸው ትረጓሜ እየሰጡ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ወጥነት ያለው
ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል ትርጉም አልተገኘም፡፡
ሕግ መካኒካል ባህሪይ አለው ብለው የሚያምኑ ሰወች ለዚህ እምነታቸው
የሚያቀርቡት ማስረጃ ባ’ዋጅ ወይም በሕግ ድንጋጌ መግቢያ ላይ እንዲህ ማለት
ሌላ ትርጉም እስካልተሰጠው ድረሰ እንዲህ ማለት ነው ተብሎ የተሰጠውን ትረጓሜ
ከሕግ መሰረታዊ ፍቺ ጋር አጣምረው ሲተረጉሙት ይስተዋላል ፡፡ በሕግ ቋንቋ አንድ
ሲደመር አንድ አንድም ሁለት ፤ አንድም አስራ አንድ የሚሆንበት አጋጣሚ ብዙ
ነው ፡፡ ይህ አረዳድ ከህግ ጋር ተዛምዶ ለሌላቸው የማህበረሰቡ ክፍሎች ከአመክንዮ
(ሎጂክ) ውጪ ነው፡፡ ይሁንና በዚህ ርዕስ በሌላ ጽሁፍ የምንገናኝ መሆኑን
በማስታወስ ወደ ዛሬው ጽሁፌ ተሸጋገርኩ፡፡
የፍጥረታት ሁሉ መኖሪያ የሆነችው ምድር ምንም እንኳ ፍትሐዊ አይደለችም ብለን
ብናማርራት እና ብንወቅሳት እስቲ አንድ ጥያቄ አንስተን መልሳችን ለራሳችን ትዝብት
እንተዉ ፡፡ የሰው ልጅ በሕግና በስርዓት ለመመራት ባይመርጥ ኖሮ ሕይወቱ ምን
ሊመስል
እንደሚችል አስበነው እናውቅ ይሆን ? የሰው ልጅ በሕግና በስርዓት ባይተዳደር
ኖሮ ዕጣ ፈንታው ምን ሊሆን እንደሚችል አስቦት ያውቅ ይሆን ? እስቲ ለአንድ ቀን
መንግስት ሀገሩን የሚያስተዳድርበትን ሕግጋትና መመሪያዎች ሁሉ ለአንድ ቀን ብቻ
ተግባራዊ እንዳይሆኑ አፈጻጸማቻን ሁሉ አግጃለሁ የሚል አዋጅ ቢደነግግ ምን አይነት
ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል በዓይነ-ህሊናችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ ? እስኪ ሕግና
ስርዓት የሌለበትን የዚህን ቀን ውሎ በዓይነ-ህሊናችን ለመቃኘት እንሞክር ፡፡
እስቲ
ላ’ንድ
ቀን
በዚህ ቀን ሰው ሁሉ በሽብር፤ በፍርሃት፤ ባለመተማመን፤ በዕልቂት፤ በአጠቃላይ
በስርዓት አልበኝነት ቀኑን ሁሉ አይነተኛ ባህሪው አድርጎት ይውላል ፡፡ ከመኖሪያ
ቤቱ እንጀምር .. በአንድ ቤተሰብ ከሚኖሩ አባወራ ወይም እማወራ አንደኛው
በሰላሙ ጊዜ ያስቀየመውን ቂም በመበቀል ይጀምራል ፡፡ አንተ’ኮ…. አንቺ’ኮ በዛን
ወቅት ያደረከኝ፤ ያደረግሽኝ… የበደልከኝ ፤ የበደልሽኝ እየተባባሉ አንድ ሁለት
በመባባል ጀምረው ፍጻሜያቸው የት ሊሆን እንደሚችል መገመቱ ይከብዳል ፡፡
ወደ ጎረቤት እንቀጥል .. የሰው ልጅ በ’ለት ተዕለት ሕይወቱ ከአጉራባቹ ጋር በሰላም
መኖርእንዳለሁሉበጸብእናባለመግባባትኖሯል፡፡ታዲያየዚያችቀንየሰላሙሳይሆን
አለመግባባቱ.. የፍቅሩ ሳይሆን የጥላቻው ትውስ ይለውና ወሰኔን ገፍተሃል፤ አጥሬን
አፍርስሃል፤ ሚሽቴን/ባሌን አማግጠሃል፤ ንበረቴን ወርሰሃል፤ ባለጠግነትህን መከታ
አድርገህ በድልህኛል … እየተባባለ ቂሙን ለመወጣት ይበጀኛል የሚለውን አቅሙ
የፈቀደውን ከማድረግ ወደኋላ አይልም፡፡ ምክንያቱም ሕግጋት እና መመሪያዎች
ለአንድ ቀን ተግባራዊ እንዳይሆኑ ተደርገዋልና ነው ፡፡
ወደ አካባቢ እንቀጥል.. የሰው ልጅ ማህበራዊ እንስሳ በመሆኑ ከቤቱ እና ከጎረቤቱ
አልፎ ከአካባቢው ጋር በመልካምም በእኩይም ይገናኛል፡፡ እንዳው ያቺ አንድ ቀን
ሕግና መመሪያ የተሻረበት ቀን የሰው ልጅ በአካባቢው የሚያደርገውን ብናስብ እጅግ
የከፋ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የቀድሞውን ዘመን ትተን እንደዛሬው የከፋ እንደማይሆን
እያሰብን 1983 ዓ.ም መንግስት የተቀየረበትን ጊዜ ማስታወስ እንችላለን፡፡
ዝርፊያውን፤ ስርዓት አልበኝነቱን ብቻ ማንሳቱ በቂ ይመስለኛል፡፡ በ1993 ዓ.ም
በተነሳው ረብሻ የነበረውን ዝርፊያ እና ሽብር እንዲሁ ማንሳት እንችላለን፡፡
በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ዛሬ በሚዲያ የምናየው የፖለቲካ አለመረጋጋት የሰው
ልጅ ምን ያህል ጨካኝ፤ ስርዓት አልበኛ ከአውሬ የባሰ አደገኛ መሆኑን የምንረዳበት
ነው፡፡ ዋይታው ፤ ዘረፋው፤ አስገድዶ መድፈር፤ ሽብር ፤ ግድያ የ’ለት ተዕለት የህይወት
አውድ ነው፡፡
በነዚያ የእንስሳት ዓለም እንደምናየው ነጻ የሆነ ሕይወት የማይኖርበት ደካማው አውሬ
የህይወት ዋስትና የሰላም መድን አጥቶ እበረገገ እና እየተጠቃ የሚኖርበት ጉልበተኛው
በተራው አርጅቶና ደክሞ በተራው የ’ጁን እስኪያገኝ ድረስ የጫካው ንጉስ ሆኖ
እየተንጎማለለ አቅመ-ቢስ አራዊትን እያጠቃ ህይወቱ የሚቀጥልበት፡፡ የአራዊት
ህይወት ሁል ጊዜ የማጥቃትና የመከላከል የፍልሚያ አውድማ ነው፡፡ ታዲያ ይህንን
የአኗኗር ስርዓት ሊቃውንቱ የዱር ሕግ /The law of Jungle/ በማለት ይጠሩታል፡፡ የኛ
የሰው ልጆች መኖሪያ ለአንድ ቀን ህግና መመሪያ ቢሻር የዱርእንስሳት የአኗኗር ዘዬን
አያስንቅም ትላላችሁ ፡፡
ስለ ሕግ ሲነሳ
ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3
ተምሳሌት_3

More Related Content

What's hot

Musclular system introduction
Musclular system introductionMusclular system introduction
Musclular system introduction
Nikhil Vaishnav
 
General Anatomy of Joints
General Anatomy of JointsGeneral Anatomy of Joints
General Anatomy of Joints
MuhammadAteeq31
 
Terima kasih guruku
Terima kasih gurukuTerima kasih guruku
Terima kasih guruku
Amir Gombang Adiratna Pekaca
 
Joints
JointsJoints
Joints
SUSHIL BHATT
 
תחזוקת המוח (Hebrew)
תחזוקת המוח (Hebrew)תחזוקת המוח (Hebrew)
תחזוקת המוח (Hebrew)shvax
 
Muscular system
Muscular systemMuscular system
Bab Perawatan Jenazah: Mengkafani jenazah 3
Bab Perawatan Jenazah: Mengkafani jenazah 3Bab Perawatan Jenazah: Mengkafani jenazah 3
Bab Perawatan Jenazah: Mengkafani jenazah 3
Annis Farrida
 
Skeletal and Muscular System
Skeletal and Muscular System Skeletal and Muscular System
Skeletal and Muscular System
Jenny Dixon
 

What's hot (8)

Musclular system introduction
Musclular system introductionMusclular system introduction
Musclular system introduction
 
General Anatomy of Joints
General Anatomy of JointsGeneral Anatomy of Joints
General Anatomy of Joints
 
Terima kasih guruku
Terima kasih gurukuTerima kasih guruku
Terima kasih guruku
 
Joints
JointsJoints
Joints
 
תחזוקת המוח (Hebrew)
תחזוקת המוח (Hebrew)תחזוקת המוח (Hebrew)
תחזוקת המוח (Hebrew)
 
Muscular system
Muscular systemMuscular system
Muscular system
 
Bab Perawatan Jenazah: Mengkafani jenazah 3
Bab Perawatan Jenazah: Mengkafani jenazah 3Bab Perawatan Jenazah: Mengkafani jenazah 3
Bab Perawatan Jenazah: Mengkafani jenazah 3
 
Skeletal and Muscular System
Skeletal and Muscular System Skeletal and Muscular System
Skeletal and Muscular System
 

Similar to ተምሳሌት_3

Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 PagesTemsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 PagesAddis Tsegaye
 
Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi) founder, Professo...
Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professo...Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professo...
Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi) founder, Professo...
Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Yeehadegchinqet 131015131752-phpapp01
Yeehadegchinqet 131015131752-phpapp01Yeehadegchinqet 131015131752-phpapp01
Yeehadegchinqet 131015131752-phpapp01haramaya university
 
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Amharic - The Epistle of Ignatius to the Philadelphians.pdf
Amharic - The Epistle of Ignatius to the Philadelphians.pdfAmharic - The Epistle of Ignatius to the Philadelphians.pdf
Amharic - The Epistle of Ignatius to the Philadelphians.pdf
Filipino Tracts and Literature Society Inc.
 
Semayawi1 131015152400-phpapp01
Semayawi1 131015152400-phpapp01Semayawi1 131015152400-phpapp01
Semayawi1 131015152400-phpapp01
haramaya university
 

Similar to ተምሳሌት_3 (7)

Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 PagesTemsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
 
Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi) founder, Professo...
Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professo...Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professo...
Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi) founder, Professo...
 
Yeehadegchinqet 131015131752-phpapp01
Yeehadegchinqet 131015131752-phpapp01Yeehadegchinqet 131015131752-phpapp01
Yeehadegchinqet 131015131752-phpapp01
 
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
 
Amharic - The Epistle of Ignatius to the Philadelphians.pdf
Amharic - The Epistle of Ignatius to the Philadelphians.pdfAmharic - The Epistle of Ignatius to the Philadelphians.pdf
Amharic - The Epistle of Ignatius to the Philadelphians.pdf
 
Geez 1
Geez 1Geez 1
Geez 1
 
Semayawi1 131015152400-phpapp01
Semayawi1 131015152400-phpapp01Semayawi1 131015152400-phpapp01
Semayawi1 131015152400-phpapp01
 

ተምሳሌት_3

  • 1.
  • 3. ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? 1 ተምሳሌት በትምህርት እና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር በየ 15 ቀኑ የሚታተም መጽሔት ነው፡፡ ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? በውስጥ ገጾች የልብ ነገር ልቤን ቆረጠኝ፣ አመመኝ በርካታ ጊዜ ብለን ይሆናል፡፡ ልብና ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ችግሮች ከእድሜ መግፋት ጋር በተያያዘ ብቻ እንደሚበጣ የሚገምቱ አሉ፡፡ ንቃ ያለው! ንቃ ያለው ባʼርባ ቀኑ አትንቃ ያለው ባʼርባ ዓመቱም አይነቃም አለኝ አንዱ ባልንጀራዬ፡፡ መንቃት እንዳʼግባብነቱ ሰፊ ትርጓሜ የያዘ ሁለት ቃል ነው፡፡ ነቃ፤ ነቄ፤ ንቃተ-ህሊና እያልን ቃላቱን እያራከምን (እያባዛን) አቻ ትርጉም ብንፈልግለት የማህበራዊ ድረ-ገጾች አገራችን በዓለም ላይ ከሚገኙ ዝቅተኛ የኢንተርኔት(የበይነ መረብ) ተጠቃሚ ከሆኑ አገራት አንዷ ናት፡፡ ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበይነ መረብ ፍጥነትና ተደራሽነት ከምንግዜውም በተሻለ ሁኔታ እያደገ ይገኛል፡፡ 6 10 16 7 13 20 8 14 21 ኤስ ኦ ኤስ የኤሰ ኦ ኤስ ዓለም አቀፍ የህጻናት መንደሮች ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን የዛሬ 60 ዓመት በ1949 ዓ.ም (እ.አ.አ) በፕሮፌሰር ኸርማን ሜየር በተባሉ ግለሰብ በኦስትሪያ ተመሰረተ፡፡ የአኗኗራችን ነገር እኒህ ሰው የ 59 ዓመት ጎልማሳ ናቸው፡፡ ከታዋቂው የሲ ኤን ኤን የቢዝነስ ዘጋቢ ሪቻርድ ኩዊስት ጋር ፊት ለፊት ቁጭ በለው ይነጋገራሉ፡፡ ሰውዬው ብላክ ቤሪ ዘመናዊ ስልኮች አምራች ኩባንያ ቺፍ ኤክስክውተቭ (ዋና ኃላፊ) ናቸው፡፡ ሰሌዳው ተበይዷል ታክሲ ውስጥ ነኝ፡፡ ከሹፌሩ ኋላ፡፡ ማለዳ 1ሰአት አካባቢ፡፡ ሁሉ ወደየጉዳዩ ለመሄድ ከቤቱ የሚወጣበት ሰአት በመሆኑ ከመነሻው በመግባቴ ጥሩ ቦታ አገኘሁ እንጂ በየጎማውና በየሞተሩ ላይ ተቀምጦመሄድ ልማዴ ነበር፡ እስቲ ላ’ንድ ቀን እንደው አንዳንዴ. ምን አንዳንዴ በ’ለት ተዕለት ኑሮአችን የሚደረጉ ድርጊቶች ፍትሐዊ አልሆን ብሎን ተበሳጭተን. እርር ድብን ብለን. አልቅሰን ባ’ቅመ-ቢስ ስሜት ውስጥ ሆነን የሥነ ምግባር ጉዳይ ከ2 ዓመታት በፊት በአንድ ጋዜጣ ላይ አንድ አስገራሚም፣ አስደንጋጭም፣ አሳዛኝም ዘገባ ማንበቤን አስታውሳለሁ። በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ የግል ት/ቤቶች ውስጥ በአንዱ የዩኒቨርሲቲ ህይወት በሰውልጅህይወት ውስጥ ድርጊት፣ ሁኔታና ቦታ ከጊዜጋር በሚኖራቸው መስተጋብር አማካይነት ከሚፈጥሩት ወቅታዊ እውነት ባሻገር ትዝታቸውንም በአእምሮ ውስጥ አኑረው ያልፋሉ፡፡
  • 4. 2 ተምሳሌት በትምህርት እና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር በየ 15 ቀኑ የሚታተም መጽሔት ነው ፡፡ ተምሳሌት መጽሔት በኢትዮጽያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ምዝገባ ቁጥር 279/2006 እና በንግድ ምዝገባ ቁጥር kik/ AA/2/0003278/2007 ሐምሌ 15 ቀን 2006 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡ ዋና አዘጋጅ ንጉስ ይልማ አድራሻ --- ክ/ከተማ ወረዳ---- የቤት ቁጥር E-mail eyobneguss@gmail.com ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከድር አህመድ Kidunet.ahmed7@gmail.com ኤዲቶሪያል ቡድን ደሳለኝ መኩሪያ desu.meku@gmail.com አዲስ ፀጋዬ rasaddis16@gmail.com በለጠ ጌታቸው mesiblete@gmail.com አለማየሁ ስሜነህ sevastefol@yahoo.com አምደኞች ጽጌሬዳ ........ መላኩ .......... ክቡር .......... ታምራት መቻል ሄኖክ ሰይፉ የኮምፒዩተር ጽሁፍ አዜብ አለማየሁ azuzihabesha1@gmail.com ገበያ ስርጭት እና ክትትል ዮርዳኖስ የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 3277 ዘርሽታ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 212 ስልክ ቁጥር 251 911225298 ፖ.ሳ.ቁ 54154 ኢ-ሜይል temsaletmagazine@ gmail.com አሳታሚ ኤኬቢዲ የፕሬስ የማስታወቂያና የማማከር አገልግሎት የተምሳሌት አቋም ሰው ልጅ በመደበኛም ይሁን ኢ-መደበኛ በሆነ ሁኔታ አካባቢውን እየለወጠ ዛሬ በምንገኝበት ደረጃ ላይ የደረስነው በትምህርት ነው፡፡ ጥፋትም ሆነ ልማት የሚከናወነው በትምህርት ነው፡፡ መልካሙን ነገር ብቻ አጎልብቶ ጥፋትን ማስወገድ የሚያስችል ትምህርት መስክ አልተፈጠረም፤ ወደፊትም አይፈጠርም፡፡ የመድሃኒትን ጥቅም መቶ በመቶ ከመድሃኒቱ የጎንዮሽ ጉዳት ማስወገድ የሚቻልበት ቴክኖሎጂ ላይ አልደረስንም፡፡ የጨለማና ብርሃን፤ መኖርና መሞት፤ ሀብትና ድህነት፤ የጽድቅና ኩነኔ ሂደቶች የዚህ ተምሳሌት ናቸው፡፡ ዓለም የምትባለው የፍጥረት መኖሪያ ከተመሰረተች ጀምሮ የነበረ አሁንም ያለ ወደፊትም የሚኖር አውድ (ኡደት) ነው፡፡ ይህ ተፈጥሮ ሚዛኗን የምትጠብቅበት ስልት ነው፡፡ ዛሬ በደረስንበት የቴክኖሎጂ እድገት ዘመን ዘምኖ እና ደርጅቶ አለመገኘት ከነባራዊው ዓለም ጋር ያለመራመድ የኋላ ቀርነት ብቻ ሳይሆን ያላዋቂነት መገለጫ ነው፡፡ የሀገራችን ስረዓት ትምህርት እድሜው የሚጀምረው ከአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ይሁን እንጂ በትምህርት ሚ/ር ስርዓት ተበጅቶለት ትምህርትን ለጥቂት የህብረተሰቡ ክፍል መስጠት የተጀመረው በአጤ ኃ/ሥላሴ የአገዛዝ ዘመን ነው፡፡ የአንድን ማህበረሰብ በትምህርት ተለውጧል ለማለት ዘመን ተሸጋሪ የሆነ ወጥነት ያለው የትምህርት ስርዓት ሊኖር እንደሚገባ በመስኩ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡ አንድን ማህበረሰብ ሚዛን ላይ የምናወጣው በተማረው የሙያ መስክ ለህበረተሰቡ እና ለሃገሩ ያለው አበርክቶ ነው፡፡ ቁጥራቸው የበዛ የትምህርት ተቋሞች መገንባትና ቁጥራቸው የበዛ የሰው ኃይል ማፍራት እጅግ የተቀደሰ ተግባር ቢሆንም፤ ከመጀመሪያ ድግሪ እስከ ሦስተኛ ድግሪ መማር እጅግ የሚያስከብር የምሁርነት መገለጫ ቢሆንም፤ ማህበረሰቡን በአንድ እርምጃ ወደፊት ካላራመደ፤ ከነበረው ነባራዊ የአሰራር ሂደት ጋት እንኳ ፈቀቅ ካላለ፤ ከተደጋጋሚ ሃገሪቷ በነጮቹ መዝገበ ቃላት ውስጥ ያላትን የረሃብተኛ ስም የትርጉም ፍቺ ካላስለወጠ፤ ዛሬም እንደጥንቱ በበሬማረሳችን እርግጥ ከሆነ፤ በየዓመቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተመራቂዎችን ማፍራት ፋይዳው ምኑ ላይ ሊሆን ነው ሲል ተምሳሌት ያጠይቃል፡፡ ትምህርት የለውጥ መሳሪያ እንጂ በራሱ ለውጥ አይደለም፤ መማር ማወቅ መረዳት እንጂ በራሱ ለውጥ አይደለም፡፡ ማወቅ የለውጥ የመጀመሪያ እርምጃ እንጂ በራሱ ግብ አይደለም፡፡ ይህ የለውጥ ግብ ከሚለካባቸው ዘርፈ ብዙ መንገዶች ውስጥ አንዱ በመማር ማስተማር ሂደት የሚነሱ የምርምር ስራዎችን ከሸልፍ ማድመቂያነት ይልቅ ለህትመት የሚበቁበትና ችግር ፈቺ የሚሆኑበት፤ በማህበራዊው ህይወት የአኗኗር ዘዬ በባህል፤ በኢኮኖሚ፤ በፖለቲካ በኪነ-ጥበብ፤ እንዲሁም በመዝናኛ ያሉትን የቀን ተቀን ውሎ በህትመት እና በብሮድካስት ሚዲያ ሽፋን ተሰጥቶት ሲሰራበት ነው፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኤፍ ኤም ሚዲያ ስርጭት ቢኖራቸውም በማህበረሰቡ ዘንድ ከነመኖራቸውም የሚያውቅ ጥቂት የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ በህትመት ሚዲያ ቢሆን የባሰ እንጂ የተሻለ ነገር አይታይም፡፡ ተምሳሌት መጽሔት ከዚህ በላይ ያነሳናቸውን በትምህርት እና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ ተዛማጅ የሆኑ ጉዳዬችን በማንሳት የተለያዩ ዓምዶችን በማዘጋጀት፤ በየመስኩ ያሉ ባለሙያዎችን በማሳተፍ ውይይቶችን፤ ክርክሮችን በማድረግና መማርያ መድረክ በመፍጠር ለማህበረሰብ እና ለሀገር ፋይዳ ያለው ለውጥ እንዲያመጡ የበኩሏን ድርሻ ትወጣለች፡፡ ሰ የለውጥ መሳሪያ ሊሆን ይገባል ትምህርት
  • 5. 3 ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከቴክኖጂ ጋር የተያያዙ ስራዎችን እየሰራ ለማህበረሰቡ እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢንኩቤሽን ማዕከል የሚል የምርምር ስራዎችን ማጎልበቻ ተቋም መሰረተ፡፡ በአዲስ አበባከ 167 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 65 ትምህርት ቤቶች በስኩልኔት የመረጃ መረብ ተገናኙ አዲስ አበባ ት/ቢሮ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን በድረ-ገጽ ሊያስተሳስር መሆኑ ተገለፀ ፡፡ አስተዳደሩትምህርት ቢሮ የትምህርት የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የሥራ ሂደት መሪ አቶ የኔጌጥ በለጠ እንደተናገሩት፥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘው ይህ የመረጃ መረብ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያስችላል። በቀጣይ ሁለት ወር ውስጥም ሙሉ በሙሉ ሥራ የሚጀምር ይሆናል። በአሁኑ ወቅትም 65 ያህል ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂው እርስ በእርስ እንዲገናኙ ተደርጓል። ቴክኖሎጂው በፕላዝማዎች ኢንተርኔትን መጠቀም የሚቻልበትን ዕድል በመፍጠር ተማሪዎች በመምህራኖቻቸው አጋዥነት ትምህርት ነክ ጉዳዮችን በመማሪያ ክፍላቸው ሆነው እንዲማሩና የዕውቀት አድማሳቸውን እንዲያሰፉ ለማድረግ ይረዳል። የመረጃ መረቡ በመብራት መጥፋት ምክንያት በፕላዝማ የሚሰጥ ትምህርት ቢቋረጥ እንኳን ተማሪዎች መከታተል ያልቻሉትን የትምህርት ክፍል የሚከታተሉበትንም ዕድል የሚፈጥር ነው። Uniliver የተባለ ድርጅት በኢትዮጽያ ውስጥ የሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን በማወዳደር ሽልማት አበረከተ ጅ ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???ወሬ ነጋሪ
  • 6. ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? ተምሳሌት የኛ በዝግጅት ክፍሉ ለእናትነት ወግ ያልበቃች እናት የጎስቋላዊቱን ምድር ጨልማ ለብሳ ትቃትታለች፡፡ ገና ዘመነ ቡረቃዋን ሳትጨርስ በሰቅጣጭ አካላዊ ህመምና በማህበራዊ ሴፍ መሰየፍን በመሳሰሉ ሁለትዮሽ ስቃዮች በመፈተን ላይ ያለች ቀንበጥ ያለማቋረጥ እሪታዋን ብታቀልጠው አይፈረድባትም፡፡ ለምን ቢባል በጨቅላይቱ የጨቅላ እናት ላይ የዘመተው ደዌ ፌስቱላ ነዋና ኡኡታን ያለማሰለስ ኡኡ ቢያስብል የተገባ ነው፡፡ ዳሩ የዘመናት የፍዳ ምች ሁለመናዋን እያማታት ያለው አዛውንቷ ኢትዮጵያ የእንቦቀቅላይቱን እዬዬ መስማት የሚቻላት አይነት አልነበረችም፡፡ እናም በፌስቱላ እስር የታሰረች ይህቺ አሳዛኝ እናት ባንድ ፊት ህመሟን በተስፋ ቢስነት እያስታመመች በሌላ ወገን ማህበራዊ ጥቂታን ከአቅሟ በላይ እያስተናገደች ባለችባት አገሯ ሰማይ ላይ “ካትሪን” የተባለች ጸሀይ ሳትታሰብ ብቅ አለች፡፡ በምድረ አውስትራሊያ እንደ አደይ ፈክታ ስትምነሸነሽ የነበረችው ካትሪን ከአብሲኒያ ደሳሳ ጎጆዎች ስር ካቆረው የስቃይ ኩሬ ውስጥ ሰጥማ ትቀራለች ብሎ ያሰበ ያለ አይመስልም፡፡ ይሁንና ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም እንዲሉ በምጥ ስቃይ እጅግ በርካታ እናቶች ለሞትና ለከፋ አካላዊ ጉዳት ሲጋለጡባት የቆየችው ኢትዮጵያ ካትሪንን መሳይ የተስፋ ጸዳል በአንዲት ወርቃማ አጋጣሚ ከእጇ አስገባች፡፡ በ1959 ዓ.ም. አገሪቱ የህክምና ባለሙያዎችን ለመቅጠር መፈለጓን በማስታወቂያ ትገልጻለች፡ ፡ በወቅቱ ባለትዳርና የአንድ ወንድ ልጅ እናት የነበሩት ዶ/ር ካትሪን ሀምሊን ጥሪውን በይሁንታ ይቀበሉና ገና ቦርቆ ያልጠገበውን የስድስት አመቱን ይህ አምድ በቀዳሚነት የሚዘክረው በስራቸው ስኬታማነት በዓለማችን ላይ በጎ ተጽእኖን ማሳደር የቻሉ ግለሰቦችን እንዲሁም ተቋማትን ይሆናል፡፡ ልጃቸውንና እንደርሳቸው ሁሉ በህክምና ሙያ ላይ የተሰማሩትን ባለቤታቸውን ይዘው ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ፡፡ የጽንስና የማህጸን ሀኪም የሆኑት ተወዳጇ ካትሪን ወደዚህ የመጡት ለሶስት አመታት ለመቆየት የሚያስችል የኮንትራት ውል ተፈራርመው ነበር፡፡ ዳሩ እንቅብ ሙሉ ፍዳ ያሳቀፋቸው የኮንትራት ዘመን ሲያበቃ ጠብቀው “ኢትዮጵያ ሆይ ሶስት የመከራ አመታትን አብሬሽ ገፋሁ፤አታካቹን እሩጫ በምድርሽ ላይ እሮጬ ጨርሻለሁና ወደ አገሬ ላቅና” አላሉም፡ ፡ ይልቁንም ዶ/ር ካትሪን ኢትዮጵያዊያን እናቶች እየገፉት ያለውን የመከራ ዳገት እሰከ መጨረሻይቱ እስትንፋሳቸው ድረስ አብረው ሊገፉ የቃል ኪዳን ማህተብ በልባቸው አኖሩ፡፡ ዶ/ር ሀምሊን አገራቸው ሳሉ በፌስቱላ ህመም የምትንገላታ እናት ገጥማቸው አታውቅም፡፡ የህክምና ባለሙያዎች በተደጋጋሚ እንደሚገለጹት በወሊድ ወቅት በሽንት ፊኛ እና በማህጸን መካከል የሚከሰተው በተፈጥሮ ያልነበረ ቀዳዳ ፌስቱላ ይባላል፡ ፡ በዶ/ር ካትሪን ሀምሊን ሆስፒታል የህክምና ባለሙያ ከሆኑት ከወ/ሮ ፌቨን ገለጻ መረዳት እንደሚቻለው በተለይ አንዲት ሴት ለፌስቱላ ችግር የመጋለጥ እድሏ የሚያይለው አካሏ የምጥን ጫና ለመቋቋም በሚያስችል መልኩ ያልጎለበተ እንደሆነ ነው፡፡ በእንዲህ አይነቱ አሳዛኝ አጋጣሚ ሽሉ በሚያደርሰው ከአቅም በላይ የሆነ ውጥረት ከላይ በተገለጸው አኳኋን ሴቲቱ የፌስቱላ ሰለባ ትሆናለች፡፡ በሌላም በኩል ምንም እንኳን አንዲት እናት የሚጠበቀውን ያህል አካላዊ ጥንካሬ ያላት ብትሆንም ሽሉ በትክክለኛው አቅጣጫ የማይመጣ ከሆነ ለተመሳሳይ ችግር ልትዳረግ ከኢትዮጵያ ስወጣ እድሜ እቀንሳለሁ
  • 7. ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? ተምሳሌት የኛ የሚያስችል የህክምን ማእከል ባልከፈቱ ነበር፡፡ ለነገሩ ለዚች አገር ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር “ከኢትዮጵያ ወጥቼ ስመለስ እድሜ እቀንሳለሁ” በማለት ውብ አድርገው ገልጸውታል፡፡ ልክ እንደ ምእራቡ አለም በፍጹም ግለሰባዊነት ተውጦ ለማህበራዊው መስተጋብር ጀርባውን ያልሰጠውን ኢትዮጵያዊ ማንነት እርሳቸው አብዝተው ይወዱታል፡፡ ሰው ስለራሱ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ ስለሌላውም እየተጨነቀ እንዲኖር በሚያስችል መልኩ የተቃኘውን ኢትዮጵያዊ አኗኗር ዶ/ር ካትሪን ከልብ ያደንቁታል፡፡ ከሶስት አመት በፊት የኑሮ አጋራቸውን ያጡት ዶ/ር ካትሪን የዘጠና አመት የእድሜ ባለጸጋ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የፍቅር አጸዷ ካትሪን እያሽቆለቀለች ያለችውን የእድሜ ጀንበር መሬት መሬት እያዩ የሚያሳልፏት አይነት እናት አይደሉም፡፡ ዛሬም ድረስ በሚያስደንቅ ወኔ ለህክምና ማእከሉ ፍሬያማነት ይተጋሉ፡፡ የዘመናት ደመኛቸውን ፌስቱላን ቀዬው ድረስ ዘልቆ መዋጋት የሚሻል መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት አዋላጅ ነርሶች የሚሰለጥኑበትን መንገድ አመቻችተዋል፡፡ ሰልጥነው የወጡትም በድፍን ኢትዮጵያ ተሰማርተው የሙያ አበርክቷቸውን እያበረከቱ ነው፡፡ “ዶ/ር ካትሪን ሀምሊን” ከመባል ይልቅ “እማማ ካትሪን ሀምሊን” ተብለው መጠራትን የሚመርጡትንየእኚህንእናትሰናይነትእንዲህበአጭሩአውግቶመጨረስስለሚያዳግት እረጅም እድሜንና ጤናን እየተመኘንላቸው ሀሳባችንን በዚሁ እንቋጫለን፡፡ ትችላለች፡፡ የዚህ ህመም ተጠቂ የሆነች እናት ሽንቷን ለመቆጣጠር ስለማትችል እጅግ የከፋ ስነ-ልቦናዊ ስብራትና ማህበራዊ መገለል ይደርስባታል፡፡ በአንድ ወቅት የደረሰው ገጠመኝ እንዲህ ነበር አንድ የፌስቱላ ሄስፒታል ነርስ በራሱ ጉዳይ ወደ መንፈሳዊ ቦታ ይጓዛል፤ በሄደበት ቦታ የገጠመው ግን አንዲት እናት ከ40 ዓመታት በላይ በፌስቱላ ህመም ተሰቃይተው ራሳቸውን ወደ ህክምና ማዕከል ሳይወስዱ የፈጣሪ እርግማን እንደደሆነ በማመን ገዳም ገብተው ቀሪ ህይወታቸውን ይመሩነበር፡፡ታዲያእዚያበራሱጉዳይመንፈሳዊቦታላይየተገኘውነርስእርሳቸውን አሳምኖ ለማሳከም ከ ሁለት ወራት በላይ ነበር የፈጀበት ፤ ምክንያቱም ይህ የፈጣሪ እርግማ ን ነው ብለው ላመኑት ሴት እንዴት ተደርጎ በ ሁለት ቀን የሚፈወስ እጅግ ቀላል ደዌ መሆኑን ይንገራቸው ፡፡ የሆነውና የተደረገው ግን ይሄ ነበር እናም ለ40 ዓመታት በፌስቱላ ህመም ሲሰቃዩ የነበሩት እናት እናታችን በሚሏቸው ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን የሰለጠነ ነርስ ፈወሳቸው ፡፡ #ሰው ስለራሱ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ ስለሌላውም እየተጨነቀ እንዲኖር በሚያስችል መልኩ የተቃኘውን ኢትዮጵያዊ አኗኗር ዶ/ር ካትሪን ከልብ ያደንቁታል” ወደ እማማ ካትሪን ገድል ስንመለስ የዘመንን እንቅልፍ እንዳይሆን እንዳይሆን የምታንቀላፋው ኢትዮጵያን እንዲህ በቶሎ መቀስቀስ የሚቻል እንዳልሆነ አበክረው የተረዱ የሚመስሉት ዶ/ር ካትሪን ገና በጠዋቱ አጥብቀው የታጠቁትን መቀነት ሳይፈቱ እነሆ ወደ አመሻሹ ዘልቀዋል፡፡ አሁን ጦር ሀይሎች በመባል በሚታወቀው በቀድሞ ልእልት ጸሀይ ሆስፒታል ስራ የጀመሩት ዶ/ር ካትሪን በተለያዩ አገሮች በመዘዋወር እንግዳ ስለሆነባቸው ፌሰቱላ ትምህርት በመቅሰም ለታላቁ ዘመቻ እራሳቸውን ብቁ አደረጉ፡፡ መቼም ለሀምሳ-አምስት (55) አመታት የሚፋለሙትን ጠላት እንዲህ በዋዛ ፈዛዛ ይጋፈጡት ዘንድ ይቸግራልና የሞራሉንም ሆነ የእውቀቱን ስንቅ አሰማምሮ መሰነቁ በእጅጉ ያስፈልግ ነበር፡፡ ዶ/ር ካትሪን ያደረጉትም ይህንኑ ነው፡፡ እንዲህም በማድረጋቸው የመገለል ከርሰ-መቃብርን ፈንቅለው በሺዎች የሚቆጠሩ እናቶችን ለዳግም ትንሳኤ አብቅተዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ መውደድ በራሱ ትልቅ እዳ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ዶ/ር ካትሪን አገረ- ኢትዮጵያን ከሚገመተው በላይ መውደዳቸው የእድሜያቸውን አብላጫ ችግሯን እሹሩሩ ሲሉ እንዲቆዩ አስችሏቸዋል፡፡ እንዲያ ባይሆን ኖሮ የደጅ ጠኚ እሮሮ ምሱ የሆነውን አበሻዊ ቢሮክራሲ ታግሰው በተሟላ አኳኋን ፌስቱላን ለማከም
  • 8. 6 ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? ፈዋሽተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? ፈዋሽ ልቤን ቆረጠኝ፣ አመመኝ በርካታ ጊዜ ብለን ይሆናል፡፡ ልብና ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ችግሮች ከእድሜ መግፋት ጋር በተያያዘ ብቻ እንደሚበጣ የሚገምቱ አሉ፡፡ የህክምን ባለሙያዎች ይህ ስህተት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የሰው ልጅ ከተወለደበት ቀን አንስቶ እስከሚሞትበት ጊዜ ድረስ ሊያጠቃው የሚችል በሽታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተቻለ መጠን ለህመሙ እንዳንጋለጥ ጥንቃቄ ማድረግ አንድ በሉ….  በመደበኛነት ደምን መለካት (ከ120/80 ከፍ ካለ ሁኔታው አሳሳቢ ነው፡፡)  በሰውነት ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን መቆጣጠር (ከ40 እስከ 100 የኮሌስትሮል መጠን መደበኛ (normal) ሲሆን ከዚህ ከበለተም ካነሰም አደጋው ያመዝናል፡፡)  የስኳር ህመም ምርመራ ማድረግ  በቀን ቢያንስ ለ20 ደቂቃ እንቅስቃሴ ማድረግ  ከ24 ሰዐት ውስጥ 7ቱን በእንቅልፍ ማሳለፍ  በቀን 6 ብርጭቆ ውሀ መጠጣት  አመጋገብ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ (የቅባት፣ የኮሌስትሮል፣ የካሎሪና ካርቦሀይድሬት መጠናቸው ዝቅተኛ የሆነ ምግቦችን መመገብ)  ፈጣን ምግቦችን (fast food) አዘውትሮ አለመመገብ  ሲጋራ አለማጨስ እነዚህ መከላከያዎች ለሁሉም እድሜና ጾታ የሚሆኑ ናቸው፡፡ በተለይ ግን እድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በጾታ ብናየው ደግሞ ሴቶች ወገባችሁ ከ35-40 ኢንች…..ወንዶች ደግሞ ከ40-45 ኢንች እንዳይበልጥ ተብላችኃል፡፡ እስቲ ልብ ህመም በቅድሚያ የሚያሳያቸውን ምልክቶች እንመልከት ሁለት አትሉም…. ነገር… ሴቶች ላይ የሚታዩ ምልክቶች  ደረት አካባቢ ህመም መሰማት ወይም በተያያዘ በክንድ፣በአንገትና መንጋጋ አካባቢዎች የሚሰማ ህመም  ማስመለስን ያልተለመደ የአካል መዳከም  እንቅስቃሴ ሲደረግ ወይም ተንጋለው ሲተኙ የሚፈጠር የትንፋሽ ማጠር(መቆራረጥ)  የድብርት ስሜት መሰማት  የእንቅልፍ ማጣትና ምቾት አለመሰማት ወንዶች ላይ የሚታዩ  በደረት አካባቢ ምቾት ማጣት  የትንፋሽ ማጠር  የደም ግፊት መቀነስ በዚህ ምክንያት የሚፈጠር የራስ ምታት ህመም  ቀዝቃዛ ላብ ማላብና የድብርት ስሜት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የ ል ብ
  • 9. ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? 7 ከድር አህመድ ንቃ ያለው ባʼርባ ቀኑ አትንቃ ያለው ባʼርባ ዓመቱም አይነቃም አለኝ አንዱ ባልንጀራዬ ፡፡ መንቃት እንዳʼግባብነቱ ሰፊ ትርጓሜ የያዘ ሁለት ቃል ነው ፡፡ ነቃ፤ ነቄ፤ ንቃተ-ህሊና እያልን ቃላቱን እያራከምን (እያባዛን) አቻ ትርጉም ብንፈልግለት አንድም ነቃ.. ተሰነጠቀ፤ ተተረተረ የሚለውን አንድም ነቃ.. እንቅልፉን ጨረሰ፤ ባነነ፤ ንቁ፤ ትጉህ፤ ቀልጣፋ ሆነ ጠረጠረ እያልን ጮሌ ድረስ የሚጓዘውን የኢትዮጽያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር አማርኛ መዝገበ ቃላት እናገኛለን ፡፡ የነቃ የሚለው ቃል የተማረ የሚለውን ትርጓሜ ይሰጠናል ብዬ አላምንም ወይም ለማመን ብዙ የጥናት ማገዶ ይፈጃል፡፡ የእኛ ህብረተሰብ ግን እውነት ነቄ ነው? በምን አትሉኝም የተግባራዊ እና የነባራዊ ነፀብራቅ ውጤት በሆነው የሰው ልጅ አይምሮ አስተሳሰብ ውጤት ፡፡ ህዝባችን ለአቅመ-ፖለቲካ ንቃተ ህሊና አልደረሰም ደርሷል የሚለውን በጥናት ያልበሰለ ምልከታ ትተን እስቲ ማህበራዊ ንቃተ ህሊናችን ገና ጨቅላ፤ እንቦቃቅላ መሆኑን ለማጠየቅ እማኝ መጥራት ሳያስፈልገን በዕለት ተዕለት ህይወታቸን የምንታዘበውን አንድ ሁለት እያልን እንመያየጥ ፡፡ ቆሻሻ መጣል ነውር ነው፤ አጥር ጥግ የሚሸና ውሻ ነው እያልን በደማቅ ጽሁፎች ያደመቅን ቀድመን የነቃን የህብረተሰቡ ክፍሎች ዘግይተው ባልነቁ ከሊቅ አስከ ደቂቅ በሆኑ “ጥቂት” ሰወች ከአንደበታችን ከሚወጡ ቆሻሻ ቃላቶች ጀምሮ በመንገድ ላይ፤ በጎረቤቶቻችን አጥር ስር፤ በአደባባይ ላይ በመኪናችን ጎማ ላይ በአደባባይ ላይ ሽንታቸውን የሚያንፎለፉሉ “ጥቂት” ሰወች መመልከት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ በትራንስፖርት ላይ ወይም በመንገድ የበሉትን ፍራፍሬ አልያም የጫት ገራባ መሃል መንገድ ላይ እንደዘበት ጥሎ መሄድ “ለጥቂት” ሰወች እንደምን ነውር ይሆናል፡፡ አጋጣሚውንአግኝተንወንድሜ/እህቴለምንእንዲህታደርጋለህብለንብንጠይቃቸው ከጣሉት ቆሻሻ ባልተናነሰ የስድብ ወይም የቡጢ ናዳ ከመሰንዘር የማይመለሱ “ጥቂት” አጉራ ዘለል ሰወችስ ምን እንላቸዋለን፡፡ ታዲያ መቼ ነው ʼምነቃው? የህዝብ መገልገያ አውቶቡስ ወይም ታክሲ አልያም ሃይገር ውስጥ ገብተን ከቴፑ የሚወጣውን አደንቋሪ ሙዚቃ አይሉት የጨረባ ዘፈን እንዲቀነስ አልያም እንዲዘጋ ጠይቀን የሚሰነዘርብንን ክበረ-ነክ ስድብ ትተን መስኮቶች ይከፈቱ ብለን በመጠየቃችን የሚነሳው አቧራ የቱ ድረስ እንደሚሄድ የምናውቅ “ጥቂት” ሰወች እናውቀዋለን ፡፡ የታክሲ ረዳት ተፋቀሩ ብሎ እንደ ምንትስ ሲያጭቀን የተቃወምን “ጥቂት” ሰወች አይደለም ከረዳቱ ከራሳችን ከተሳፋሪው የሚደርስብን አሳፋሪ ድርጊት ምን ያህል እንዳሳቀቀን የምናውቅ “ጥቂት” ሰወች እናውቀዋለን ፡፡ በተቀመደበለት ትራንስፖርት ታሪፍ ለመጓዝ ስንሞክር “በጥቂት” ሾፌሮችና ረዳቶች የሚደርስብንን ጫና ለመቋቋም በምናደርገው እስጥ አገባ “ጥቂት” ተሳፋሪዎች የሚያሳዩን ያልተገባ ባህሪይ እውንየመንቃታችን ዋዜማ ነው ወይስ መባቻ ላይ ነው ያለነው ያሰኛል፡፡ በእኔ እድሜ ልጅ ሲያጠፋ ወላጅ ባይኖር ቀድሞ የሚቀጣ የሚገስጽ ጎረቤት አልያም የሰፈር ሰው ነበር ፡፡ ማህበራዊ መስተጋብሩ ከቤት አልፎ፤ ጎረቤት፤ ሰፈር ፤ አካባቢ.. እያለ ሰፊ ማህበረሰብን ያካልል ነበር ፡፡ ዛሬ የቀደመ ማህበራዊ እሴቶቻችንን ለመተግበር የምንሞክር የዋሃን የለንም እንጂ ብንኖር ምን ላይ እንደበቀለ ግራ ከሚገባን ወጣት ጋር መላተማችን ሳይታለም የተፈታ ነው ፡፡ ድሮ ማለት በሚከብድ ሁኔታ እንደ ባህል የምንኮራበት አንተ ቅደም አንቺ ቅደሚ የሚል መገለጫ ነበረን ፡፡ ዛሬ ይሄ ባህል መኪና በሚያሽከረክሩ ሰወች ዘንድ ጎጂ ባህል ከሆነ ውሎ አድሯል ፡፡ ለእግረኛ ቅድሚያ በመከልከል የደረሰ አድጋ የምትለዋን የተለመደች የትራፊክ ፖሊስ ሪፖርት ትተን፤ በአደባባይ የተገናኙ መኪኖች ለየትኛው ቅድሚያ ሰጥቶ ማለፍ እንደሚገባ የመንጃ ፈቃዱን አሰጣጥ የማለፊያ መመዘኛ አንዱ መለከያ ሆኖ ሳለ፤ አንድ ምግባር የጎደለው ዋልጌ መሃል አደባባይ ላይ በመቆም ከየአቅጣጫው የሚመጣውን የትራፊክ ፍሰት በመዝጋት አፀያፊ ስድብ ሲሳሰደብ መመልከት እውነት ከመንጃ ፍቃዱ ጋር አብሮ የሚሰጥ የምግባር ብልሹነት ሰርተፊኬት ይኖር ይሆን ፤ ይሆን ያሰኛል ፡፡ ከዚሁ በተጓዳኝ በትራፊክ መጨናነቅ የተነሳ ረጅም ረድፍ ሰርተው ከቆሙት መካከል አፈንግጦ በመውጣት ከተቃራኒ አቅጣጫ የሚመጣውን መኪና መንገድ ዘግቶ አላፊ አግዳሚውን አላሳልፍ የሚል የመኪና አሽከርካሪ ከየትኛው ሃገር ወይም ማህበረሰብ የወስድነው ባህል፤ ትውፊት እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል፡፡ ጊዜያችን ለኔ.. ለኔ.. የሚባልበት ማጭበርበር፤ ማምታታት፤ ጉቦኝነት፤ ሸፍጥ፤ ክህደት “ቢዝነስ” የሚል ካባ ደርቦ የሚሞካሽበት፤ የሚሽሞነሞንበት ዘመን ላይ መሆናችን ከጅብ ቆዳ የተሰራ መሰንቆ ቅኝቱ “እንብላው እንብላው” ነው የሚሉትን ተረት ያስታውሰናል፡፡ ታዲያ መቼ ነው ምነቃው? ኢትዮጽያዊ ባህሎቻችንና ትውፊቶቻችን ከአውሮፓና ከአሜሪካ በመጡ አደንዛዥ ፕሮግራሞች መጠመዳችን፤ የኛነታችን መለያ የሆኑትን የአባቶቻችን ተጋድሎ ማራከስና ማንቋሸሽ የወጣቶቻችን መለያ ከሆኑ ሁለት አስርተታትን አስቆጠረዋል፡፡ ወላጆች ለልጆቻችን ምናወጣው ስም የማንን ባህል እና እምነት እንደሚያንጸባርቅ ከቶ ሊገባን አይችልም፡፡ ክፉ መንገድ እመልካም ግብ አያደርስም፤ ክፉ ስራ እንደተኮሱት ጥይት አላማውን ይገድላል የሚል አባባል የት ነበር ያነበብኩት፡፡ ይህንን ማህበራዊ ቀውስ “ጥቂቶች” የነቁ ቢረዱትም የት ወስደው ከማን ጋር ተመካክረው ቅጥ እንደሚያስዙት ግራ ገብቷቸው መቆዘም ብቻ ሆኗል እጣ ፈንታቸው፡፡ በኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የሚለቀቀው ፕሮግራም ይህንን ማህበራዊ ውጥንቅጥ እና ቀውስ ከማስተካከል ይልቅ በእሳት ላይ ቤንዚን የሚያርከፈክፉ ሃይ ባይየሌላቸው ሚዲያዎች መኖራቸውን ልብ ይሏል፡፡ “ጥቂቶችን” እንደሆነ ልብ ይባልልኝ ግን፤ ግን መቼ ነው ʼምነቃው ብለን ማጠየቃችን አልቀረም ፡፡ጥሪታችንን አሟጠን በእውቀት ሰጪነቱ፤ በገንዘብ ተቀባይነቱ አንቱ የተባለ ት/ቤት እውቀት እንዲገበዩ የላክናቸው ልጆቻችን ነገ የሀገር ተረካቢ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ መሆኑን ያሰብን “ጥቂት” ወላጆች ልጆቻችን ስልጣኔ ምልክት ተደረጎ በሚወሰደው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ልክፍት በያዛቸው “ጥቂት” ት/ቤቶች አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር የተከለከለ ነው በማለት ህግና ስርዓት ሲያወጡ ስንመለከት እውነት ያለነው እምዬ ኢትዮጽያ ውስጥ ነው ወይስ .. ብለን መደናገራችን አይቀርም፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ በትምህርት ቤት ያለውየተማሪና የአስተማሪ የመከባበር ስነ-ምግባር ከተናደ እንዲሁ አስርታትን አስቆጥሯል፡፡ እነዚህ ተቋማት በእውቀት አንጸውና ኮትኩተው የሚያፈሩት ትውልድ ሀገር በሁለት እግሩ እንዲቆም የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወሰድ ይታወቅ ነበር፡፡ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት አያችሁ የጄኔሬሽን ዝቅጠት አለብን ያሉ ሰው አስታውሳለሁ፡፡ በዛሬውና በርሳቸው ጊዜ የነበረው የጄኔሬሽን ዝቅጠት ሚዛን የትኛው ውሃ ያነሳ ይሆን፡፡ ከዝቅጠትስ በታች ቋንቋ ይኖር ይሆን? ታዲያ መቼ ነው ʼምነቃው? የእነዚህ እና የሌሎች ማህበራዊ ህፀፆቻችን ድምር ውጤት ነው የፖለቲካ ንቃተ- ህሊናችንን የሚያጎለብተው፡፡ ጥቃቅን ሚመስሉን ነገር ግን በጥቅሉ ሲታዩ ማህበራዊ እሴቶቻችንን የሚጎዱ ድርጊቶች ናቸው ነቅተዋል አልነቁም የሚያሰኙን፡፡ ሰድበው ለተሳዳቢ የሚሰጡን፡፡ ያʼርባ ቀኑን ጉዞ አርባ ዓመት የሚያስጉዙን፡፡ ትንሽ ፍሳሽ መርከብ ታስመጣለች እንዲል ቤንጃሚን ፍራንክሊን፡፡ እነሆ ዛሬም 3ሺህ ዘመን ትርክት ላይ ሆነን አልነቃችሁም ገና እያንጎላጃችሁ ነው እየተባልን ነው፡፡ ጎበዝ አያሳፍርም? ስንቴ ይሆን የምናፍረው? በስንቱስ ይሆን የምናፍረው? ለብዙ ኪ.ሜትሮች መነሻው አንድ እርምጃ ነው የሚሉት ቻይናዎች ሃገራችን ገብተው እየሰሩ ነው ከʼነሱ ጋር አንድ ብንል እኮ ነገ.. ንቃ ያለው! የኔ ሃሳብ
  • 10. ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? 8 በዓለማየሁ ስሜነህ አገራችን በዓለም ላይ ከሚገኙ ዝቅተኛ የኢንተርኔት(የበይነ መረብ) ተጠቃሚ ከሆኑ አገራት አንዷ ናት፡፡ ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበይነ መረብ ፍጥነትና ተደራሽነት ከምንግዜውም በተሻለ ሁኔታ እያደገ ይገኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ከሁሉም በተሻለ መጠን የበይነ መረብ አንዱ አካል የሆነው የማህበራዊ ድረ-ገጽና የመወያያ መድረኮች (chat forum) ግን በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ የማህበራዊ ድረ-ገጾች ጠቅላላ ጠቀሜታ እጅግ ብዙ እና ዘርዝረን የማንጨርሰው ነው፡፡ ነገር ግን በአንዳዶች ዘንድ ለወጣቶች ለግል ወሬ እና ለመዝናኛ አገልግሎት ብቻ የዋለ መድረክ ሆኖ በብዙዎች ይቆጠራል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚደረጉ ጥናቶች እንዲሁም እንቅስቃሴዎች እንደሚያሳዩት ማህበራዊ ድረ-ገጾች ጠቀሜታቸው ሰፊ እና ለታላላቅ ተግባሮች መሳሪያ እንዲሆኑ ነው፡፡ በሰለጠነው ዓለምም የፕሬሱን ሚና እስከ መጫወት እንደደረሱ በግልፅ የምናየው ነው፡፡ ተጠቃሚዎቹን በተመለከተም እንድ በፈረንጆቹ በታህሳስ 2014ዓ.ም. የተደረገ ጥናት እንደሚገልፀው በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እንደሆኑ ነው፡፡ በዝርዝሩም እንደተገለፀው፡፡ በዓለም ላይ ከሚገኙ የበይነ መረብ ተገልጋዮች ውስጥ 72% ማህበራዊ ድረ-ገጾችን እንደሚጠቀሙና በሰንጠረዡ እንደተቀመጠው በሁሉም እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በተገለጸው ፐርሰንት መጠን የተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾችን ለተለያየ ዓላማ እንደሚገለገሉበት አያይዞ ገልጸል ፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት ፌስ ቡክ(face book) ብቻ የሚጠቀሙ ሰዎች 1.15 ቢሊዮን እንደሚሆንም ታውቋል፡፡ በአገራችንም ያለው ገፅታ በቁጥር ለማስቀመጥ ጥናት ቢያስፈልግም የበይነ መረብ ተደራሽንት ከምንግዜውም በተሻለ ፍጥነትና ጥራት እያደገ መምጣቱን ጨምሮ በዙሪያችን የምንመለከተው የቀን ተቀን ገጠመኞቻችን የሚነግረን ግን ማህበራዊ ድረ-ገጾችን መጉብኘት በብዙች ዘንድ እየተለመደ የመጣና የህይወታችን አንዱ ገፅታ እንደሆነ ነው፡፡ እንግዲህ ከበዛው የማህበራዊ ድረ-ገጾች ጥቅምና አገልግሎት ውስጥ እዚህ ላይ ትኩረት የተደረገበት ጉዳይ ትምህርታዊ ፋይዳ ሲሆን በዚህ ረገድም ማህበራዊ ድረ- ገጾች በሰለጠነው ዓለም ለትምህርት ትልቅ መንገድና መድረክ በመሆን በተለይም ለተማሪዎችና ለትምህርት ቤቶች ብዙ ጥቅምን ሲሰጡ ታያሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትም በአገራችን በተለይም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ በማህበራዊ ድረ- ገጽ ላይ ስሙ የማይገኛ ተማሪ ቢኖር የበይነ መረብ ባልደረሰበት እና በተወሰነው አከባቢ ብቻ እንደሚሆን ይታመናል ፡፡ እንደውም በአዲስ አበባ አከባቢ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጋር ያለው መረጃ እንደሚጠቁመው የተወሰኑየ5 እና የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችም ጭምር መህበራዊ ድረ-ገጾችን እንደሚጠቀሙ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ከዚህ የቴክኖሎጂ ውጤት ተማሪዎችም ሆኑ ትምህርት ቤቶች ምን ጥቅም ያገኛሉ የሚል ጥያቄ እዚህ ጋር ይነሳል፡፡ ማህበራዊ ድረ-ገጾች ለመማርና ሀሳብን ዕድሜ ክልል ተጠቃሚዎች% 18 – 29 89% 30 – 45 72% 50 – 60 48% 65 > 43% የማህበራዊ ድረ-ገጾች ማህበራዊ ተቃርኖ
  • 11. ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? 9 ለመለዋወጥ ብዙ እድሎችን እፈጠረ ይገኛል፡፡ ተማሪዎች ማህበራዊ ድረ-ገጾችን በመጉብኘት የሚያገኙትን ጥቅም በቀላሉ ማየት ይቻላል፡፡ ተያይዞም በመጀመሪያ ደረጃ የሚጠቀሰው ፋይዳ ተማሪዎች በአካል ሳይገናኙ ወይም ሳይተያዩ ድረ-ገጾች ላይ በመገኘት በየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኝ ሰው ጋር መወያየትና መረጃን በተለያየ መልክ መለዋወጥ ያስችላል ፡፡ እንግዲህ በነዚህ ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ድርጅቶችን ጨምሮ ስለሚገኙ አንድ የተፈለገን መረጃ ከሚመለከተው አካል የድርጅቱን ወይም ግለሰቡን ገጽ በማገናኝት ወጃጅ ለመሆን (Like) በማድረግ ጓደኝነትን እንዲሁም ግንኙነትን ለመፍጠር ገለሰቡ ወይም ድርጅቱ የሚያስተላልፈውን መረጃና መልዕክት በቀላሉ ማግኘት ይቻላል፡፡ እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ማህበራዊ ድረ-ገጾችን በመጠቀም በቀላሉ ከተማሪዎች እንዲሁም ከወላጆች ጋር የቀረበ ግንኙነት ማድረግ ይቻላሉ፡፡ በዚህም ወላጆች በሚመቻቸው ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ እንዲመዘገቡ ወይም Account እንዲኖራቸው ይደረጋል፡፡ በዚህም ትምህርት ቤቱ የሚፈለገውን መልዕክት ማስተላለፍ ከወላጆችም ጥያቄ ወይም አስተያየትን በቀላሉ ማግኘትይችላል፡፡ ይህም ደብዳቤ ከመፃፃፍ ለወላጅም በአካል ትምህርት ቤቱ ድረስ ከመሄድ በፍጥነቱ በቀላልነቱ እንዲሁም በርካሽነቱ የተሻለ ያደርገዋል፡፡ በርግጥ አንድ ነገር ሊነሳ ይችላል ይህም ይዘታቸውንና ደረጃቸውን ያልጠበቁ መረጃዎች ከየትኛው ወገን ሊመጣ ስለመቻሉና የመረጃው ደህንነት ጉዳይ ነው፡ ፡ ነገር ግን ለነዚህ እንደ መፍትሄ ሊወሰድ የሚችለው አሉታዊ ተፅዕኖውን ብቻ በማሰብ ፋይዳውን ሙሉ ለሙሉ ከማጣት ይልቅ በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ብዙ የዘርፉ ባለሙያዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ የአጠቃቀም ፖሊሲና ዕውቀትን ከባለሙያ ጋር በማቀናጀት በቀላሉ የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ መሆን ይቻላል፡፡ ሌላው ሊጠቀስ የሚችለው ልምድ ደግሞ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ተማሪዎች ፎቶ በመቀያየር ይሁን ሀሳብ በመለዋወጥ የበይነ መረብ (internet) የመጠቀም ልምዳቸውን ማዳበራቸው ነው፡፡ ይህ ልምድ ደግሞ ለየትኛውም ስራ ወይም ቢዝነስ በጣም አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን እግረ መንገዳቸውን ወደፊት ለሚኖራቸው የስራ ዘመን ራሳቸውን ብቁ እያደረጉ ይመጣሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ተግባር የማህበራዊ ድረ-ገጾች ተፅዕኖ አዲስ ክስተት የፈጠረው አዲስ የሽያጭ (Marketing) ዘርፍ ነው፡፡ ይህም (social media marketing) የማህበራዊ ድረ-ገጽ ሽያጭ በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህም መፍጠርና ማደግ በብዙ አገራት የሚገኙ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን የማህበራዊ ድረ-ገጽ ማርኬቲንግ ስትራቴጂ መንደፍ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ በአገራችን ብዙ ድርጅቶች ይህንን በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም የተማሪዎች ይህ ልምድ ወደ ስራው ዓለም ሲገቡ ጥሩ የማህበራዊ ድረ-ገጽ ማርኬቲንግ ባለሙያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ከወዲሁ ማሰብ ያስፈልጋል ፡፡ ወይም በቀላሉ በዚህ ዘርፍ ላይ መሰማራት ይችላሉ ለማለት ይስችላል፡፡ በተለያዩ አገራት የሚገኙ መምህራንም በሚያስተምሩት ትምህርት ዓይነት ስም ማህበራዊ ድረ-ገጽ በመክፈት የቤት ስራን አንኳን በተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾች አማካኝነት በመስጠትና ለመወያየት ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ ይህም ተማሪዎች ከትምህርት ሰዓት በተጨማሪ ትምህርታዊ ጉዳዮችን ከመምህራኖቻቸው ጋር ለመለዋወጥም ሌላኛው መንገድ ነው፡፡ የፅሁፍ ክህሎትንም ማዳበር ከዚህ የሚገኝ ሌላው ተጨማሪ አብሮ ሊጠቀስ የሚችል ጥቅም ነው፡፡ ሌላው በአደጉት አገራት የምንመለከተው ት/ቤቶች የትምህርት ቤቱን ስምና የሚሰጠውን አገልግሎት እንዲሁም የት/ቤቱን አላማ፣ ተልዕኮና ጉዞ በማስተዋወቅ እንዲሁም ማህበራዊ ድረ-ገጽን ከዋናው የት/ቤቱ ድረ-ገጽ ጋር በማገናኘት ማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ የሚገኙትን ግንኙነቶች ወደ ዋናው የት/ቤቱ ድረ-ገጽ በመምራት በዛ ላይ የሚገኙትን መልዕክቶችና አገልግሎቶች ብዙዎች እንዲገነዘቡት ለማድረግ ይጠቀሙበታል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ይኸው ከላይ የጠቀስነው ጥናት እንደሚጠቁመን ወደ 75% የሚጠጉት ዋና ድረ-ገጽ ጉብኝት የተደረጉት በማህበራዊ ድረ-ገጽች በኩል እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ስለሆነም ማህበራዊ ድረ-ገጾች ለሌሎች ገጾች መጎብኝት ትልቅ ሚና እንዳላቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ት/ቤቶች ማህበራዊ ድረ-ገጽ እንዲኖራቸው በማድረግና በሚገባ በማንቀሳቀስ የተለያዩ መልካም ስራዎችን ማበረታታትና ስለ እያንዳዱም አገልግሎታቸው ጥራትና አስተያየትን ከሚመለከታቸው ወገኖች ለማግኘት ያስችላል፡፡ ስለዚህ ይህንን ከማህበራዊ ድረ- ገጾች የሚገኘውን ጥቅም በማሰብ ተማሪዎች በአግባቡ እንዲገለገሉበት የማድረግ እና እንዲሁም የፅሁፍ እና የበይነ መረብ መረጃዎችን የመጠቀም ፍላጎታቸውና አቅማቸውን የማሳደግ የሁሉም ሀላፊነት ሊሆን ይገባዋል፡፡ እዚህ ጋር ሊነሳ የሚችለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተለያዩ ጉዳዮች ሃሳብ እንዲቀያየሩ ለፈጠረው ተማሪኔት WWW.temarinet.com ለተባለው ድረ- ገጽ ምስጋና ሊቸረው ይገባል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን በዜና አውታር እንደተገለጸው ተማሪዎች የኤሌክትሮኒክ መፅሐፎችን እንዲሁም መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ የሚረዳውን የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ቤተ መፃሐፍት እና ቤተ ሙከራዎችን በኔትወርክ የማስተሳሰር እና የማገናኘት እንቅስቃሴም ሊደነቅ የሚገባው ተግባር ነው፡፡ እንግዲህ ዘመኑ የኢንተርኔት እንደመሆኑና ወጣቱም ሚዲያ እየተገለገለ ስለሚገኝም በሚገለገልበት ሚዲያ ተጠቅሞ ወጣቱን ማግኘትና ወደሚፈለገው የእድገት ደረጃና አቅጣጫ መምራትና ማስተማር ተመራጭ መንገድ እንደሆነ የዘርፉ ጥናት ባለሙያዎ የሚጋሩት ሃሳብ ነው፡፡ ነገር ግን በአንዳዶች እንደሚደረገው ማህበራዊ ድረ-ገጾችን እንዳይጠቀሙ መከላከሉና መዝጋቱ ወጣቱን ከዚህ ፍላጎት ለማራቅ የሚረዳ መንገድ አድርጎ መውሰዱ የሚያዋጣ አይመስልም፡፡ ለዚህም አንዱ ምክንያት ከዚህ በኋላ ይህንን የቴክኖሎጂ አገልግሎት በአገራችን እንኳን እጃችን ላይ ባለው የስልክ ቀፎ አማካኝነት በየትኛውም ስፍራ ያውም አሁን በቅርቡ ስራ ላይ በሚውለው ዓለም በደረሰበት ከፍተኛ ፍትነት 4G lte ቴክኖሎጂ ኔትወርክ ማግኘት ስለሚቻል፡፡ ነገር ግን የተወሰኑ የማህበራዊ ድረ-ገጾች ሊያሳድሩ የሚችሉ አሉታዊ ተፅዕኖ ስጋት በመጋራት በአግባቡ የመጠቀም ባህሪ ማዳበር እና ቅድሚያ ሚሰጠውን የህይወት ተግባራት ጊዜና ትኩረትን ከሚፈለገው በላይ በማይሰርቅ መልኩ መከናወን እንዳለበት ፀሐፊያን ያምናሉ፡፡ በመጨረሻም የዚህ ቴክኖሎጂ ማለትም የማህበራዊ ድረ-ገጾችን አጠቃቀም በምንፈልገው ይዘትና መጠን የማሳደግ ጉዳይ ጊዜና ትግስትን የሚፈልግ በመሆኑ በጊዜ ሂደትሁሉንም ልምድና ዕውቀትን እያገኘን ያደጉት አገራት በሚጠቀሙት ደረጃየማንገለገልበት ምንም ምክንያት አይኖርም፡፡ ነገር ግን ለዚህ ቴክኖሎጂና ለሂደቱ ሁሉም ወገን ቀና አመለካከት እንዲኖረው ያስፈልጋል ቴክኖ-እመርታ
  • 12. 10 በዝግጅት ክፍሉ የኤሰ ኦ ኤስ ዓለም አቀፍ የህጻናት መንደሮች ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን የዛሬ 60 ዓመት በ1949 ዓ.ም (እ.አ.አ) በፕሮፌሰር ኸርማን ሜየር በተባሉ ግለሰብ በኦስትሪያ ተመሰረተ፡፡ ወቅቱም 2ኛ የዓለም ጦርነት ማብቂያ እንደመሆኑ በጊዜው በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ህይወት በመጥፋቱ ምክንያት የብዙ ቤተሰቦች እና ዘመዳሞች አድራሻ በመጥፋቱ ግለሰቡ በዚህ አስከፊ ወቅት የተጎዱትን በመደገፍ እና የተጠፋፉትን በማገናኘት የራሳቸውን አስተዋጽዎ ለማድረግ ታስቦ የተቋቋመ ተቋም ነበር፡፡ ይህንን መሰረት አድርጎ የተቋቋመው ኤስ ኦ ኤስ የስራ አድማሱን በማስፋት በአሁኑ ወቅት ሃገራችንን ጨምሮ በ134 አገሮች ላይ እየሰራ ይገኛል ፡ ፡ በቅርቡ ፋይናንሻል ታይምስ /Finnancial Times/ በተባለ ታዋቂ የፕሬስ ድርጅት በተደረገ ጥናት ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ከሚንቀሳቀሱ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በአቅም እና በበጎ አድራጎት 33ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ኤስ ኦ ኤስ በኢትዮጽያ የዛሬ 40 ዓመት በ1974 ዓ.ም (እ.አ.አ) በሃገራችን ተከስቶ በነበረው ድርቅ በተለይም በትግራይ ክልል የነበረውን ችግር ለመፍታት በክልሉ ተቋቋመ፡፡ በወቅቱ የተከሰተውን ጊዜያዊ ችግር ለመታደግ ይመስረት እንጂ የስራ አድማሱን በማስፋት ላለፉት 40 ዓመታት የተለያዩ በጎ ስራዎችን በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ሰርቷል እየሰራም ይገኛል ፡፡ ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጽያ በሦስት ዋና ዋና ተግባሮች መሰማራቱን የገለጹልን አቶ ወርቅነህ ንጉሴ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጁ ዲን እነዚህም ትምህርት፤ ጤና እና የህጻናት እንክብካቤ ናቸው፡፡ አያይዘውም ድርጅቱ ይህን አገልግሎት የሚሰጠው በሰባት የሃገሪቱ ክልሎች ሲሆን እነርሱም አዲስ አበባ፤ ሐዋሳ፤ መቀሌ፤ ሐረር፤ ባህርዳር፤ ጎዴ እና ጅማ ናቸው ፡፡ ድርጅቱ በዋነኛነት የተነሳለት ዓላማ ቤተሰብ የሌላቸውን ቤት እና ቤተሰብ (መንደር) እንዲኖራቸው ማድረግ ሲሆን በሃገራችንም ቤተሰባቸውን በተለያዩ አለም ዓቀፍ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ አቶ ወርቅነህ ንጉሴ የኤሰ ኦ ኤስ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲን በዚህ አጭር ጽሁፍ ኤሰ ኦ ኤስ በአትዮጵያ ያሳለፈውን 40 ዓመት መዳሰስ እጅግ በጣም ከባድ ነው፡፡ ይሁንና ከአቶ ወርቅነህ ንጉሴ የኤስ ኦ ኤስ የቴክኒክና ሙያ ት/ቤት ዲን ከተምሳሌት ጋር ያደረጉትን አጭር ቆይታ ለአንባቢ በሚመች መልኩ ቀንጨብ አድረገን አቅርበነዋል፡፡ ወደፊት የኮሌጁን አጠቃላይ የትምህርት አሰጣጥ እንዲሁም ተደራሽነት በስፋት የምንመለስበት መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለአንባቢዎቻችን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ኤስ ኦ ኤስ ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???ገጽ ለገጽ
  • 13. 11 ነው፡፡ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርት ጋር በተያያዘ የተቋሙን አሰራር ያስረዱን አቶ ወርቅነህ ኮሌጁ 10ኛ እና 12ኛ ክፍልን አጠናቅቀው በአካዳሚክ ትምህርት መስክ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግባት ያልቻሉትን ወጣቶች ፍላጎታቸው ወደ ቴክኒክና ሙያ የሆኑ ተማሪዎችን የሚቀበል ሲሆን በመንግስት መመዘኛ የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ቅበላ ያደርጋል፡፡ የሚቀበላቸው ተማሪዎችም በሦስት ምድብ የተከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጹት አቶ ወርቅነህ እነዚህም ኤስ ኦ ኤስ በተለያዩ ፕሮጄክቶች እያሳደጋቸው ካሉ ቦታዎች የሚመጡ ወጣቶች፤ በህብረተሰቡ ውስጥ ለኑሮ አማራጭ በማጣት የተጎዱ የህብረተሰቡ ክፍሎች የሚመጡ ወጣቶች /disadvantage affermative action community segment/ እና የትምህረት ወጪ ክፍያን በግላቸው ከፍለው ለመማር ወደ ተቋሙ የሚመጡ ተማሪዎች ናቸው፡፡ በኮሌጁ የሚሰጡ የትምህረት አልግሎት ለሁሉም ተጠቃሚ እኩል መሆኑና በኤስ ኦ ኤስ የተለያዩ ፕሮጄክቶች ታቅፈው ከህጻንነት እድሜያቸው ጀምሮ በእንክብካቤ አድገው ወደ ኮሌጁ የሚቀላቀሉ ወጣቶች በኮሌጁ የጤና አገልግሎት፤ መጠለያን፤ ማደሪያን እንዲሁም የምግብ ወጪ በኮሌጁ በተለየ ሁኔታ ድጋፍ ይደረግላቸዋል ፡፡ የተቋሙ ቴክኒክና ሙያ ት/ቤት የሚያስተምርባቸው ሂደቶች ከ1ኛ-5ኛ የደረጃ እርከን ያላቸው ሲሆን በእያንዳንዱ እርከን ተማሪዎች መማር ያለባቸውን መሰረታዊ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እንደሚቀስሙ ዲኑገልጸውልናል፡፡ በተቋሙ የሚሰጠው የቴክኒክና ሙያ ትምህርት በሃገሪቱ አሉ ከተባሉ ተቋማት ጋር ሲነጻጸር በመምህራን ብቃት፤ በማስተማሪያ ቁሳቁስ አደረጃጀት፤ እንዲሁም በማስተማሪያ ቦታ ስፋትና ጥራት ብቃት ያለው መሆኑን አስመርቆ የሚያወጣቸው ወጣቶችም ለሃገሪቱ የተማረ የሰው ኃይል በማቅረብ ረገድ ክፍተኛ አስተዋጽዎ እያደረገ መሆኑን ገልጸውልናል ፡፡ የኮሌጁን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት የጨረሱትን ወጣቶች የስራ ፈጠራን አስተዳደር ትምህርትን እንዲሁም የተለያዩ የማነቃቂያ /motivational/ ንግግር የሚያደርጉ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በከፍተኛ ክፍያ በማስመጣት እና በመጋበዝ ተጨማሪ ስልጠና ይሰጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተወሰኑ ወጣቶችን በማደራጀት ከመንግስት እና ከገንዘብ ተቋማት ጋር ቅንጅት በመፍጠር የተለያዩ ፕሮጄክቶችን በመንደፍ ወጣቶች ራሳቸውን እንዲችሉ ከዚያም አልፎ ስራ አጥ ወገኖቻቸውን በመቅጠር ድጋፍ እንዲያደርጉ ከፍተኛ ማበረታቻ ይደረግላቸዋል ፡፡ ኤስ ኦ ኤስ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ከሌሎች በሃገሪቱ ከሚገኙ ተመሳሳይ ተቋማት የሚለይባቸው የራሱ ባህሪ እንዳለው የሚገልጹት ዲኑ በኮሌጁ ተምረው የተመረቁ ወጣቶች ተመልሶ የቤተሰብ ጥገኛ እንዳይሆኑ ስራ እስከማስያዝ እና ከኮሌጁ ከወጡ በኋላም በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን አበርክቶ እስከመከታተል የሚያደርስ ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸውልናል፡፡ ምክንያቶች ያጡ በሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናትን እንደ ወላጅ በመንከባከብ ለቁም ነገር ማብቃት ነው፡፡ እነዚህ ህጻናት ለቁም ነገር የሚበቁበትን ሂደት ያብራሩት አቶ ወርቅነህ ቤትና ቤተሰብ የሌላቸውን እንዲሁም ቤት እና ቤተሰብ ኖሯቸው በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙትን በማሰባሰብ እርዳታ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው፡፡ ቤትና ቤተሰብ የሌላቸውን ወገኖች ድርጅቱ በገነባው የህጻናት ማሰደጊያ በመሰብሰብ 10 ህጻናት በአንድ ቤተሰብ ውስጥ በማደራጀት እንደ እናት ተንከባካቢ የሆኑ ሞግዚቶችን በመመደብ እንዲያድጉ የሚደረግበት አሰራር ሲሆን፤ በአንድ መንደር ውስጥ ከ16 - 19 የሚደርሱ ፕሮጄክቶች የተካተቱበት ነው፡ ፡ በሌላ ወገን የሚገኙት ተረጂዎች ማለትም ቤተሰብ ኖሯቸው ነገር ግን በተለያዩ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግሮች ቤተሰቦቻቸውን ለማጣት የተቃረቡ ህጻናትን ተንከባካቢ ወገን ባለበት የቤተሰብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም በማዘጋጀት እርዳታ እያከናወነ ይገኛል፡፡ ዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው እና ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በመሰራት ላይ የሚገኘው ተግባር ትምህርት ነው፡፡ ትምህርት በሁሉም መንደሮች ላይ ከህጻናት ማቆያ አንስቶ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የሚደርስ የቀለም ትምህርት በመስጠት ህጻናቱን ይንከባከባል ፡፡ ድርጅቱ በሁለት የሃገሪቱ ቦታዎች የኮሌጅ ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ወርቅነህ እነዚህም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና በአዲስ አበባ እንዲሁም ነርሲንግ ሙያ ትምህርት በመቀሌ ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ???ገጽ ለገጽ
  • 14. ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? 12 በአዜብ ዓለማየሁ ባህሌን………..ባህሌን…………ያልኩባቸው ቀናቶችና ጊዜያቶች እጅግ እየበረከቱ ከመጡ ውለው አድረዋል እራሴን ዘውር ብዬ እንድመለከት ያደረጉኝ ጊዜያቶችም በረከቱ ያ’ገሬ ልጆች… እስቲ ለሰከንድ ምን ላይ እንዳለን እራሳችንን እንመልከት ውበታችንን፣ ማንነታችንን፣ ባህላችንን፣ ራሳችንን ከረሳነው እና በሌሎች ማንነት ከተሸፈንን ሰንብተን…. የምወዳቸው የአገሬን ልጆች እንድታዘብ ያደረገኝ እና ይህንን ፅሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ ሰሞኑን በአገራችን ተካሂዶ በነበረው አንድ የሽልማት ስነ- ስርዓት ነው “ሰው ለሰው” ድራማ ፡፡ ድራማው በኢብኮ ለ3 ዓመት ተኩል ሲተላለፍ የነበረ ድራማ ነበር፤ እኔ በዚህ ጽሁፌ ስለድራማው ይዘት ልጠቅስ አልፈልግም ነገር ግን ተሸላሚዎቹ ለብሰዋቸው የነበሩት አልባሳት ላይ ያለኝን አስተያየት ለመሰንዘር እንጂ በቀን ተቀን ኑሮችን ውስጥ የባህል ልብሳችንን እንልበስ ወይም በየዝግጅቱ የባህል ልብስ ግድ ይለበስ የሚል አቋም የለኝም ነገር ግን በእንደዚህ ዓይነት ትላልቅ ዝግጅቶች ላይ በተለይ ታዋቂ ሰዎቻችን(አርቲስቶቻችን) የኛ ኢትዮጵያውያን መገለጫ አገርኛ የሆኑ አልበሳቶችን ለማስተዋወቅ ከእንደኔ አይነቱ ተራ ሰው የተሻሉ አምባሳደሮች ይመስሉኛል፡፡ በዚህ የሽልማት ዝግጅት ላይ ከሁለት ወይም ከሦስት የማይበልጡ አርቲስቶች የባህል አልባሳቶቻቸውን የለበሱ ቢሆንም አብዛኛኞቹ ግን እጅግ አጫጭር ቀሚሶችንና ለዝግጅቱ ሊመጥኑ የማይችሉ አልባሳትን ነበር ምርጫ ያደረጉት ሌላው ቢቀር እድሜን እንኳን ያላገናዘበ አለባበስ የለበሱ አርቲስቶችን ተመልክቼ ነበር፡፡ እንደ’ነዚህ ዓይነት ዝግጅቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ የመታየት እድላቸው እጅጉን የጎላ ነው፡፡ ስለዚህም እንዳ’ባቶቻችን እንደ አያት ቅም-አያቶቻችን ብሂል “ባ’ንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ” እንዲሉ ለብሰነው ብንታይ ድምቀትና ውበት ፣ ግርማ ሞገስና ጌጥ የሚሰጠን ኩራቻችን ከዚየም አልፎ መደምቂያችን የሚሆን አገርኛ አልባሳታችን በሆነ ነበር ፡፡ እናም ታዋቂ ሰዎቻችን እኔ እናተን ልመክር ባልዳዳም እንደው እንደ እስተያየት እንድታስቡበት ለማለት ያህል ነው፡፡ ሌላው አገርኛ ያልሆኑ አሁን አሁን እንደውም ፍፁም ኢትዮጵያዊ እየመሰሉ ያሉ እና ድንበር ዘለል የሆኑ ክብረ በዓላቶች እየበዙና እየሰፉ ከመጡ አመታትን አስቆጥረዋል፡ ፡ ምን እየሆነ እንደመጣ ለመገመት ቢከብደኝም ሁላችንም ራሳችንን ለማጠየቅ ባህል፣ ወግ፣ ቅርስ፣ ማንነት የሚባሉት ኢትዮጵያን፤ ኢትዮጵያ ህዝቦቿንም ሉዓላዊ ያስባሉት ትውፊቶች በአሁኑ ሰዓት ፈፅሞ እየተረሱና እየጠፉ ለመሆኑ ምስክር መጥራት አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ ሌላው ቢቀር እኔ አገሬን እወዳታለሁ፣ እኔ ሐበሻ ነኝ፣ ኢትዮጵያዊነቴ ኩራቴ ነው ብሎ መናገር እንደ ኋላ ቀር እና አላዋቂነት እየተቆጠረ ያለበት ጊዜ ላይ ቆመን እንገኛለን ፡፡ ቫላንታይንስ ደይ፣ ክሬዚ ደይ፣ አፕሬል ዘ ፉል ደይ፣ ክሬስማስ ደይ……..ወዘተ እየተባሉ ሙሉ በሙሉ ከእኛ ባህልና ወግ የወጡ ማንነታችንን ፍፁም በሚያጎድፉ አጓጉል በዓላት ውስጥ ተዘፍቀን እንገኛለን፡፡ አንድ ነገር ላውራ…. የገና በዓልን እናስታውስ በእያንዳዳችን ስልክ ላይ ከቴሌም ሆነ የቅርብ ጓደኞቻችን የሚደርሰን አጭር የፁሁፍ መልክትን እናስተውለው… ከጥቂቶች በስተቀር (Merry x-mass, happy x-mass) የሚሉ መልዕክቶች ናቸው በእውነቱ ግን እኛን መልካም የገና በዓል የሚለው ነው ሊገልጸው የሚችለው? ወይስ x-mass የሚለው የፈረንጅ አፍ መልሱን ሁሉም በልቦናው ይያዘው ማንነታችንን ሊገልጽን የማይችል የገና ዛፍና ባዶ ካርቶኖችን በስጦታ ወረቀት አሸብርቀን ቤታችንን አድምቀን በዓል ለማክበር እንታትራለን ፤ ስለ እውነት ነው የምለው እኔ ትርጓሜው እንኳ አይገባኝም፡፡ የገና ጨዋታን በዓለም አቀፍ ደርጃ ማስተዋወቅ ስንችል እኛ ግን ስለ ገና ጨዋታ ማውራት የማንችንል ትውልዶች ሆነናል ፡፡ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ 365 ቀን የፍቅር ቀን ነው ብዬ አስባለሁ ፍቅር ከሁሉ ይበልጣልና ታድያ ለዚህ ከሁሉ ይበልጣል ለተባለው ፍቅር በአመት አንድ ቀን ሰጥቶ ማክበር አያሳፍርም፡፡ በው’ኑ ለኛ ቫላንታይን ይመጥነን ነበር ? በርግጥ ቄስ ቫላንታይንን አከብራቸዋለሁ መልካም ቄስም ነበሩ፣ መልካም ስራ ሰርተው ያለፉ… እኚ ቄስ ለጥቂት ጥንዶች ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ አባት ናቸው…. አያችሁ እኚ ፈረንጆች ብልጦች ናቸው በስማቸው ቀን ሰይመው ዓለም እንዲዘክራቸው አደረጉ፡፡ እስቲ አንድ ኢትዮጵያዊ ካህንን ላስታውሳችሁ አቡነ ጴጥሮስ ይባላሉ ……አቡነ ጴጥሮስም ልክ እንደ ቄስ ቫላንታይን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሃይማኖታዊ አገልጋይ ነበሩ እኚህ አባት በሚገርም ሁኔታ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለምድሬቷ ጭምር በግፍ የተገደሉ ጠንካራ አባት (ሰማዕት) ነበሩ ፡፡ እስቲ ስንቶቻችን አቡነ ጴጥሮስ ለፋሺሽት ኢጣሊያ ህዝቦቿ ብቻ ሳሆኑ ምድሬቷም ጭምር እንዳትገዛ ገዝተው ለጥቂቶች ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያዊ ሲሉ እራሳቸውን አሳልፈው በግፍ ከ ሰላሳ ጥይት በላይ ተርከፍክፎባቸው እንደሞቱልን የምናውቅ ስንቶቻችን እንሆን? መሰዋትነትን የተቀበሉበትን ቀን የምናውቅና አስበን የምንውልስ ኢትዮጵያዊያን ስንቶች ነን ልብ ያለው ልብ ይል ዘንድ ሐምሌ 22/1928 ዓ.ም መሆኑን ጠቅሼ ማለፍን መረጥኩ፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁለት አባቶች በተለያዩ ቦታዎች የተፈጠሩ ለተለያየ ዓላማ የሞቱ ሰዎች ነበሩ ፡፡ ግን ግን ለኛ ኢትዮጵያውያን ኩራታችን ሊሆን የሚገባው ማን እንደነበር መናገር አይጠበቅብኝም ፡፡ አስተዋዮች ብንሆን ኖሮ ግን አቡነ ጴጥሮስን ከእኛ አልፈን እንደ ብልጦቹ ጣልያኖች በአለም አቀፍ ደረጃ ቀን አሰይመን ልናከብራቸው እና ልናዘክራቸው በተገባ ነበር፡፡ በእጅ የያዙት ወርቅ ሆነና ነገሩ በሰው ጌጥ እኛ ለመድመቅ እንታትራለን ፡፡ ባ’ገራችን ከእኛ አልፈው ሌሎች እንዲያከብሯቸውና እንዲዘክሯቸው ልናደርጋቸው የሚገቡ ብዙ ቀኖች እንዳሉን ልብ ልንል ይገባል፡፡አበቃሁ…………ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡ እኔ’ምለው የኔ ሃሳብ
  • 15. ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? 13 በዝግጅት ክፍሉ እኒህ ሰው የ 59 ዓመት ጎልማሳ ናቸው፡፡ ከታዋቂው የሲ ኤን ኤን የቢዝነስ ዘጋቢ ሪቻርድ ኩዊስት ጋር ፊት ለፊት ቁጭ በለው ይነጋገራሉ፡፡ ሰውዬው ብላክ ቤሪ ዘመናዊ ስልኮች አምራች ኩባንያ ቺፍ ኤክስክውተቭ (ዋና ኃላፊ) ናቸው፡፡ ጆንቼን ይባላሉ ዋልት ደዝኒ የመሳሰሉ ትላልቅ ኩባንያዎችን ያስተዳድሩም ናቸው፡፡ ጄን በዓመት ውስጥ እጅግ ጥቂት ቀናት ብቻ በእረፍት ያሳልፋሉ፡፡ እሳቸው ከ3 አና ከ4 ቀን አይበልጥም ባይ ናቸው፡፡ ሰውዬው በዓመት ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንዳላቸው ይነገራል፡፡ እናም ጊዜያቸውን በሙሉ በድርጅቱ ስራ ላይ ያሳልፋሉ፡፡ ሪቻርድ ኪዊስት ጠየቀ ፡- ከስራ ውጪ ጊዜ ምትሰጠው ጉዳይ ምንድነው? ጆን ቼን መለሱ ፡- ከስራ ውጪ ለሁለት ነገሮች ጊዜ እሰጣለሁ ከ 24 ሰዓቱ 2 ወይም 3 የሚሆኑትን ሰዓታት የመጀመሪያው ለቤተሰቦቼ የምሰጠው ጊዜ ሲሆን ሌላው ለንባብ የምሰጠው ጊዜ ነው፡፡ እነዚህ ጊዜያት ከስራም ከቴክኖሎጂ ውጤቶችም ነፃ የሆኑ ናቸው፡፡ ቴሌቭዥን፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ አይ ፓድ ከመሳሰሉ በህይወቴ በየእለቱ ከሚያጋጥሙኝ ነገሮች የምርቅበት ነፃ ጊዜ ናቸው አሉ ሚስተር ቼን ፈገግ ብለው፡፡ እኔም ከቴክኖሎጂ ጥገኝነት (Technological dependency) ነፃ የምሆንበት ጊዜ በመሆን እጅጉን የምወደው ሰዓት ነው አሉ ቼን፡፡ የጆን ቼንን ሃሳብ ያነሳሁት እሩቅ ሳትሄዱ እዚህ ያለን የኢትዮጵያውያን ህይወትም በቴክኖሎጂ የተከበበ ሆኗል፤ ነው፡፡ ተፈጥሯዊ ስጦታዎቻችንን ለመጠቀም ፈፅሞ እየሰነፍን ነው፡፡ ማለዳ ከእንቅልፋችን ተነስተን ማታ ወደ መኝታችን እስክንመለስ ድረስ ምን ያህል ህይወታችን ከአዳዲስ እና ነባር የፈጠራ (የቴክኖሎጂ) ውጤቶች ጋር እንደተሳሰርን ለአፍታ አስበነው እናውቃለን፡፡ ባለሱቁ በእጁ የሂሳብ ማሽን (ካልኩሌተር ካያልዙ) ሂሳብ ድሮ ቀረች…… የሂሳብ ደብተርምእንዲሁ፤ የስልክ ቁጥር መመዝገቢያ ደብተር ያላቸው ቁጥራቸው ጥቂት የሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡ ማስታወሻ ደብተርም ዛሬ የለም ተንቀሳቃሽ ስልካችን ብዙ ነገርን ፈታ ፤ ብዙ ነገሮችን አቃለለ፡፡ ግን፤ ግን ለ 10+5 ሁሉ ቴክኖሎጂ የምንጠቀም ነገር አልመሰላችሁም፡፡ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ጥገኝነት (dependency) ሚባለው ሊሆን እንደሚችል እና በምክንያቶች የተሞላ ነው፡፡ በውስጡ ብዙ የጥገኝነት አይነቶች ይይዛል፡፡ የግብ ጥገኝነት (Goal dependency) ፣ የተግባር ጥገኝነት (Task dependency) እና የግዴታ ጥገኝነት (Hard dependency) ን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ ይጥገኝነት ሁኔታዎች መልካም ነገሮችን በመፈለግ ስለሙያው (ሰለስራው) ለማወቅ በመፈለግ የሚደረግ እና አንዳዴ ደግሞ ሰዎች አማራጭ በማጣት የሚፈፅሟቸው ጥገኝነቶች ናቸው፡፡ በዛ የሚሉት ግን ለራስ አብልጦ ከማሰብ፣ ከፍርሃት፣ በራስ ካለመተማመንና ስኬታማነትን በአቋራጭ ከመፈለግ ስሜቶች የሚነሱ ናቸው፡፡ እነዚህ ጋር በተደጋጋሚ የአለቃ እና የሰራተኛ ፣ የመምህር እና ተማሪ እስከ ወሲብ ትንኮሳ የደረሱ ታሬኮችን ማስታወስ እንችላለን፡፡ ምንም እንኳ ብዙ የስነ ልቦና ባለሙያዎች የምጣኔ ሀብት (ኢኮኖሚ) ጥገኝነት በአለማችን ላይ ላቅ ያለውን ስፍራ ይይዛሉ ቢሉም፤ ይህ ጥገኝነት አገራትም ጭምር በሌሎች አገራት እግር ስር እንዲንበረከኩ የሚያደርግ ነው፡፡ ከማህበራዊ ጥገኝነት በተለየ አቅጣጫ የሚቀመጠው ደግሞ Related dependency (ተያያዥ ጥገኝነት) ነው ፡፡ ይህ አይነት ጥገኝነት ከሰዎች የእለት ተእለት ግንኙነት የሚፈጠር አይደለም፡፡ ይልቁንም ሰዎች ከሌሎች ነገሮች በሚፈጠር የጠበቀ ግንኙነት የሚፈጠር ነው፡፡ እዚህ ጋር ቀደም ሲል የተነሳውን የቴክኖሎጂ ጥገኝነት ማንሳት ይቻላል፡፡ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችም ይሁኑ ቁሳቁሶች የሰው ልጆችን እንቅስቃሴ ለማቅለል ልፋቱን ለመቀነስ በራሱ በሰው ልጅ የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ የቴክኖሎጂ ምርቶች ከዚህ ፍላጎት ብዙ እርቀው የሰውን ልጅ መልሰው በቁጥጥራቸው ስር አውለውታል፡፡ የሰው ልጅ ራሱ በፈጠራቸው ቁሳቁሶች ቅኝ ግዛት ተይዟል፡፡ አንድ ጊዜ አንድ ትልቅ ቤተሰብ ውስጥ ስለተፈጠረ ሁኔታ ወዳጄ ያጫወተኝን እዚህ ጋር ማንሳቱ ተገቢ ሆኖ አገኘሁት፡፡ ትልቅ ቤተሰብ የሚለውን ቃል የተጠቀምኩት Joint family የሚለውን የእንግሊዝኛ መጠሪያ ለመውሰድ ነው፡፡ ይህ ማለት ቤተሰቡ እናት፣ አባትና ልጆች ብቻ ሳይሆኑ አያቶችና ሌሎችም ቤተዘመዶች መኖራቸውን ለመግለፅ ይሆናል፡፡ ሰፊ ቤተሰብ አይነት ነገር ፡፡ እናም ቤተሰቡ ከውጭ አገር የሚኖሩ ልጆች የላኳቸው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች አሉ እናም አያቶች ቴሌቭዥን ላይ፣ አባትና እና እናት ላፕቶፖቻቸው ላይ፣ ልጆች አይፓዶቻቸው ላይ እንዳፈጠጡ ቀኑ ይመሻል፡፡ እናም ወዳጄ እንዲህ አለኝ ቤተሰቡን ስትገልጸው ይህ በቤተሰብ መካከል ሀሳብ መለዋወጥ መነጋገር መደማመጥ የሚባሉ ነገሮች ጠፍተዋል ፡፡ አብረው እየኖሩ አብረው አይኖሩም፡፡ እኔም በእሳት ዳር ሰብሰብ ብለው መረጃን የሚለዋወጡ፣ የአገሩን ታሪክና ቅርስ የሚያወራ ወገኔ በአይምሮዬ ብቅ አለ፡፡ ወይ ነዶ….ወይ ንዶ….. ገና፣ ፈረስ ጉግስ፣ ገበጣና ሌሎችም ጫወታዎቻችን በሞባይልና ኮምፒውተር ጌሞች ተለውጠዋል፡፡ ንባብም እርግፍ አድርገን ትተነዋል የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ማህበራዊ ቁርኝታችንንበጣጥሶታል ዛሬ በየመዝናኛ ስፍራው ጨዋታና ሳቁ የለም ሁሉም ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ አፍጥጧልና፡፡ ይህ ውሸት ነው ያላችሁ ጠዋት ከቤታችሁ ስትወጡ ተንቀሳቃሽስልካችሁን መኖሪያ ቤታችሁ የረሳችሁ እና ቀኑን ሙሉ ሲያቅበጠብጣችሁ ሲያባትታችሁ የዋላችሁ ምስክር ትሆናላችሁ፡፡ ስነ-ልቦና የአኗኗራችን ነገር
  • 16. ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? 14 ከጽጌሬዳ ታክሲ ውስጥ ነኝ፡፡ ከሹፌሩ ኋላ፡፡ማለዳ 1ሰአት አካባቢ፡፡ሁሉ ወደየጉዳዩ ለመሄድ ከቤቱ የሚወጣበት ሰአት በመሆኑ ከመነሻው በመግባቴ ጥሩ ቦታ አገኘሁ እንጂ በየጎማውና በየሞተሩ ላይ ተቀምጦመሄድ ልማዴ ነበር፡ መቼ እንደጀመረኝ እንጃ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለድምፆች ትኩረት እሰጣለሁ፡፡ በሙዚቃ መሃል በሰዎች ንግግር መሃል ለብዙዎች ያልተሰሙ ቢሰሙም ችላ ተብለው የሚታለፉድምፆችጎልተውይሰሙኛል፡፡እዚህምየመኪናውሞተርይጮሃል፡፡አልፎ አልፎ ከታክሲዋ ሆድ በሚወጣው ጡሩምባ ታጅቦ ችፍፍፍ የሚል የሃምሌ ዝናም ከጣሪያው ይሰማል፡፡(በበጋው ወቅት ወደ ሰማይ የተነነውን አቧራ ያየ ተጠራቅሞ ዘንድሮ በክረምት ከአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ጭቃ እነደሚዘንብ ቢተነብይም ትንቢቱ አልሰራ ኖሮ ይኸው ቀደሞ የምናውቀው ዝናም ራሱ ከሰማይ ይወርዳል)፡፡ ጋቢና ከሹፌሩ አጠገብ የተቀመጠው ሰው ትከሻውን እያርገፈገፈ ያለማቋረጥ ይስላል- ብርዱ ነው መሰል፡፡እዛው ጋቢና ከሱ በስተቀኝ ያለው ብላቴና ኪሱን እየዳበሰ ”ከዚህ ሜክሲኮ ስንት ነው?” ብሎ ጠየቀ አንገቱን ወደ ሹፌሩ አስግጎ፡፡ “እሱን ጠይቀው” አለ ሹፌሩ በአውራ ጣቱ ወደ ረዳቱ እየጠቆመ፡፡ሆ! አሁን እውነት ሳያውቀው ቀርቶ ነው?ሆን ብሎ ነው እንጂ ሲሸፍጥ፡፡አንዳንድ የታክሲ ሹፌሮች ታሪፍ ሲጠየቁ ደረጃቸውን ወደ ረዳትነት ዝቅ ያደረጉባቸው ይመስል እንደሁ እንጃ ቅር ይላቸዋል፡፡ ለመመለስም ያቅማማሉ፡፡ልክ አንዳንድ ሴት ዶክተሮች ነጯን ጋወን በመልበሳቸው ምክንያት “ሲስተር”“ነርስ” ሲባሉ ቅር እንደሚላቸው አይነት ይመስለኛል ስሜቱ…የረዳትን ለረዳት የምን ማምታታት ነው? እንዲያውምለስራፈጣሪዎችየሚሆንአንድሃሳብአለኝ፡፡የታክሲረዳቶችማሰልጠኛ ቢኖርስ? አዎ ስለ ደንበኛ እና ገንዘብ አያያዝ፤ስለ አጠራር አይነቶች፤የሰፈር ስሞችን በቀላሉ የማወቅ ዘዴ፤ስለ መልስ አሰጣጣጥ እና ሂሳብ ስሌት፤የረዳቶች የልምድ ልውውጥ…እንደ ሞያ የተወሰነ ስልጠና ቢኖረው ደግ ይመስለኛል .. ወደ ታክሲው ልመልሳችሁ በግጥም እና በዜማ ታጅባ“አታስፈራራኝ” እያለች በማስፈራራት ትፎክራለች -አንዷ፡፡ ከኋላዬ ደግሞ ሌላዋ በጆሮ ግንዷ በለጠፈችው ሞባይል ጥፋተኛ አለመሆኗን ለማስረዳት የመሃላ መኣት በመደረደር ይቅርታ ትጠይቃለች፡፡-ምን ለበ ደንዳናው ቢገጥማት ነው እንዲህ እምባ እስኪቀራት የምትማፀነው? ይኸው እዚህ ታክሲውስጥ ከገባሁ ጀምሮ ልመና ላይ ናት፡፡በአካል ብታገኘውማ በ4 እግሯ ተጉዛ ከመሬት በተጎዘጎዘች፡፡በስልክ እንዲህ የሆነች… አታደርገውም አይባልም መቼም፡፡ ከእሷ አጠገብ ያለው ተሳፋሪ ደግሞ በአዲሱ ታሪፍ መነሾ ከረዳቱ ጋር ይነታረካል፡ ፡መብቴ እኮ ነው እያለ፡፡አይ መብት እቴ!‹መብትህ ታክሲ ውስጥ ስትገባ ብቻ ትዝ አይበልህ› የሚል ጥቅስ እዚህኛው ባይሆንም ሌላ ታክሲ ውስጥ ማንበቤ ትዝ ይለኛል፡፡ እስማማለሁ፡፡ አስቡት እስቲ ሱፉን ግጥም ያደረገ ጎልማሳ ላፕቶፑን ተሸክሞ ወይም የቦርሳዋን እና የጫማዋን ቀለም አመሳስላ የወጣች ዘንካታ የገቡበት ታክሲ ረዳት ሂሳብ ቢሳሳት መሳሳቱን በጥሩ ቋንቋ አስረድቶ መግባባት ሲቻል ገናለገና ‹ሊያጭበረብረኝ ነው› በሚል እሳቤስድድቡ እልፍ ሲልም ግብግቡን ይጀምሩታል፡ ፡ስነምግባር የላቸውም፤ አረጋውያንን አያከብሩም ከሚለው ባሻገር በአላስፈላጊ ሱሳቸው እና በንፅህና ጉድለታቸው ይወቀሳሉ የታክሲ ረዳቶች፡፡ ግን ያ ባለላፕቶፑ ሰውዬ ዩኒቨርሲቲ ግብቶ አካውንቲንጉን ሲማር ይህ የታክሲ ረዳት የት ነበር? ምናልባት የትምህርት ቤት ደጅ ከረገጠ አመታት ተቆጠሩበት ወይም በጭራሽ ትምህርትቤት ሄዶም አያውቅ ይሆናል ፤ ምናልባትም ያልጅ ነገን በተሻለ ‹‹ሰሌዳው ተበይዷል››
  • 17. ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? 15 ለመጠበቅ ገንዘብ ሲቆጥብ ቁርሱን አልበላ ይሆናል፤ምናልባት ደግሞ ታማሚ እናት እና የሱን እጅ ጠብቀው የሚያድሩ ታናናሾች ይኖሩት ይሆናል፤ምናልባትም ያቺ ዘንካታ ክብደቷን ለመቀነስ ያልበላቸውን እራት ትርፍራፊ እንኳን አጥቶት ፆሙን ያደረ ይሆናል፤ ምናልባትም ያ ልጅ…ታዲያ እኛ ማን ነን? ያልዘራነውን፤ ያላረምነውን ልናጭድ ማጭዳችንን ስለን የምንወጣ? እንዲያውምለስራፈጣሪዎችየሚሆንአንድሃሳብአለኝ፡፡የታክሲረዳቶችማሰልጠኛ ቢኖርስ? አዎ ስለ ደንበኛ እና ገንዘብ አያያዝ፤ስለ አጠራር አይነቶች፤የሰፈር ስሞችን በቀላሉ የማወቅ ዘዴ፤ስለ መልስ አሰጣጣጥ እና ሂሳብ ስሌት፤የረዳቶች የልምድ ልውውጥ…እንደ ሞያ የተወሰነ ስልጠና ቢኖረው ደግ ይመስለኛል፡፡መቼም አንድ ሰው ስራዬ ብሎ ከቤት ከወጣ እና ገቢ አግኝቶ ከተዳደረበት ወንጀል እስካልሆነ ድረስ ሙያው ነውና የሚያዳብርበት መንገድ ቢያገኝ አይጠላም፡፡ እኛ ምሁራን እኛ ስልጡናን ነን ባዮች ካፌ ገብተን ከተጠቀምነው በተጨማሪ ለአስተናጋጆች 5 እና 10 ብር ቲፕ ስንሰጥ ቅር አይለንም፡፡ የታክሲ ረዳት ለተሳሳተው 5 እና 10 ሳንቲም ግን ግብ ግብ እንገጥማለን፡፡ለመሆኑ ቲፕ ብንሰጠውስ ምን አለበት? ከማለዳ ጀምሮ እሰከ ምሽት ስንቱን አይነት ሰው ሲያስተናግዱ፤ በዛ በማይመች አቋቋም ቆመው እንደሚውሉ፤ ጉሮሯቸው እስኪደርቅ ሲጠሩን እንደሚውሉ አስባችሁታል የ12 ሰው ሂሳብ አስቦ(12 አልኩ እንዴ ?በስህተት ነው፡፡ አሁን አሁን እንኳ የአንድ ሚኒባስ አማካኝ የጭነት ልክ 15 ሰው ሳይሆን አይቀርም ብታምኑም ባታምኑም ለ 12 ሰው በተሰራው ሚኒ ባስ 22 ሆነን ሄደን እናውቃልን ፡፡ ሹፌሩ እና ረዳቱ ሳይቆጠሩ፡፡ጋቢና 3 ሰው ባትሪ ላይ 2 ለሁለት ሰው የተሰሩት ሶስቱ ላይ ሶስት ሶስት ከኋላ 4 ጎማ ላይ 3 ቆጠራችሁ?22፡፡)እናም በአንድ ጉዞ የዚህን ሁሉ ሰው ሂሳብ አስልቶ መልስ መልሶ አንዳንዱ ደግሞ የራሱን ብቻ አይከፍል የ2 ወይም የ3 ሰው ይላል የተለያየ ቦታ ሲደርሱም “ወራጅ አለ” ብሎ… እስቲ ራሳችሁን ለ1 ቀን በዛ ቦታ አስቡት::ከባድ አይሆንም? ረዳትነታቸው ለሹፌሩ ብቻ ሳይሆን ለኛም ጭምር አይደለም?ብዙ ጊዜ ግን አላስፈላጊ ሱሳቸው እና ለሰው ክብር ማጣታቸው ብቻ ጎልቶ፤ ጨዋና አገልጋዮቹ ተረስተው ሁሉን በአንድ ቁና ሰፍሮ በአንድ ሚዛን መመዘን ይቀናናል፡፡ ከተሳፋሪስ ስንት አይነት ምግባረ ብልሹ አለ? ሳይከፍል “ከፍያለሁ” ብሎ ድርቅ የሚል ከተሳካለትም አረሳስቶ የሚወርድ አደባባይ ላይ “ወራጅ አለ” የሚል ለምኖ ተለማምጦ ትርፍ ከተጫነ በኋላ ትራፊክ ሲመጣ የክሱን ወረቀት ለመፃፊያ ብእር የሚያቀብል፡፡ እኔ በበኩሌ ለ5 እና 10 ሳንቲም ብሎ መጨቃጨቅ እና መመናጨቅ መብት ከሆነ ይቅርብኝ በገንዘብ የማየገኘውን ንፁህ ስሜት ማደፍረስ በቁጣ መሞላት መሰደብና መሰዳደብ መብት ከሆነ ለዘላለሙም ይቅርብኝ ያውም በጠዋት ቀኔን ለምን ላበላሸው? ወደ ታክሲያችን ስንመለስ… ከወደ ኋላ የአንዱ ሞባይል ስልክ ጮኸ -ኖኪያ ቶን፡፡“እንዴት ነበር እሱ ድምፅ?”አላችሁ?ረሳችሁት አይደል?ሀገር ምድሩ በስማርት ፎን ሲጥለቀለቅ ያዳስተር የመሰለው ሞባይል ተረሳ?እጃችንን እንዳላፍታታንበት፤ ሲቆለፍ ለመክፈት “እንዴት ነበር?” እንዳላልንበት ኖኪያ ቶን ተረሳች ማለት ነው?እኔ ግን አልረሳኋትም፡፡ይሄው እሷ ድምፅ ጮኸች ይሄ ሰውዬ ግን ከየት አግኝቷት ይሆን? አደባባዩን እንደተሻገርን 3ኛው ወንበር ላይ “ወራጅ አለ” ማለቷ ያልተሰማላት ተሳፋሪ እጇ ላይ በተመለሰላት ሳንቲም በቅርብ ያገኘችውን የታክሲ አካል ትቀጠቅጣለች፡፡ ሰቅጣጭ ድምፅ፡፡“በዚህ በዝናብ እግሬ ልታስመልሰኝ ነው?” ብላ እየተንጫነጨች ወረደች መጨረሻው ወንበር ላይ ደግሞ “አበሩ ከፍያለሁ እንዳትከፍይ” የሚል የጎልማሳ ሴት ድምፅ አጠገቤ ላለችው ልጅ እግር አሻግሮ ያስጠነቅቃል፡፡ ይህእንግዲህበአንዱየስሜትህዋስ(ጆሮ)ብቻተጠቅሜያገኘሁትነው፡፡አንዳቸውም እንኳ ድምፃቸው ጉዳዩ በማይመለከተው ሰው ጆሮ መግባቱን አላስተዋሉም፡፡ ቢያስተውሉም ግድ የላቸውም፡፡ ፀጥታ ሆይ ወዴት ነሽ?ሁካታ ከቦን ተጨነቅንልሽ!!!ከውጪ የትራፊክ ፖሊስ ፊሽካ ድምፅ ተሰማ፡፡ሹፌራችን ግራና ቀኙን አይቶ ለሱ መሆኑን ሲረዳ ዳሩን ይዞ አቆመን፡ ፡ “ወይኔ ትርፍ ይዘሃል እንዴ?” ዞሮ ረዳቱ ላይ አፈጠጠ “ያዝበት ጫንበት የሰው ትርፍ የለውም” ሲል ቆይቶ ጉዳዩ የሚያስጠይቀው መሆኑን ሲያወቅ እጁንመታጠቡ እኮ ነው እንደ ጲላጦስ “አላውቅም:: ከደሙ ንፁህ ነኝ::”ሊል፡፡ ለትራፊክ ፖሊሱ ክብር ሲል በሩን ከፍቶ ወርዶ አናገረው መንጃ ፍቃድ ሳይጠይቀው አልቀረም ከኪሱ ወረቀት አውጥቶ አሳየው፡፡እጁን እያወናጨፈ ለማስረዳት ሲሞክር በፊት መስታወቱ አሻግሬ አየዋለሁ፡፡የመከላከያ ሃሳቡ ተቀባይነትን አላገኘ ኖሮ አጅሬ ትራፊክ መፍቻውን ይዞ ወደ ሰሌዳው አጎነበሰ፡፡ ቆይቶ ቆይቶ የግንባሩ ደም ስሮች ተገታትረው ቀና ቢልም ያሰበውን ባለማሳካቱ እየተበሳጨ ነበር፡፡የፊቱን ሰሌዳ ትቶ ወደ ኋለኛው ያደረገው ጉዞም የአንድ ታክሲ ቁመት ያህል ሁለት እና ሶስት ርምጃ ሳይሆን ትልቅ ግዳይ እንደጣለ የአራዊት ንጉስ አንበሳ በድል አድራጊነት መንፈስ ጎምለል ጎምለል እያለ ነበር ምን ዋጋ አለው የአቅሙን ያህል ቢለፋም የኋላውንም ሰሌዳ መፍታት አልቻለም፡፡ ከሹፌሩ ጋ ቆሞ መደራደር ሲጀምር እስካሁን ድምፃቸውን ያልሰማሁት አዛውንት “ምነው ልጄ ቶሎ የምትጥፈውን ጣፍና አሰናብተኒ የማንሄድም እንደሁ ቁርጡን አውቀን እንውረድ፡፡ ”አሉ፡፡ ጋሽ ፖሊሱም መለሰ “አባባ እርሶ ምንምአያውቁም መንጃ ፍቃድም አልያዘ ሰሌዳውም ተበይዷል የክስ ወረቀት በብቻ ያሳየኛል::”አላቸው:: “መንጃ ፍቃዱስ እሺ ሊረሳ ሊጠፋ በቅጣት ሊያዝም ይችላል…ሰሌዳ ግን እንዴት ይበየዳል?ይቻላል?” ብዬ ጠየቅኩ ራሴን አዎ ይቻላል ቢቻልማ ነው የተበየደው፡፡ ልክ መሆን አለመሆኑን ግን እንጃ፡፡ ሰሌዳ የማንነት መለያ አይደለምን? ቀድሞ ነገር የሚወልቅ እና የሚጠልቅ ሆኖ ለምን ይሰራል? የእያንዳንዳቸን የተበየደ ሰሌዳ ምን ይሆን? የማይለዋወጥ ማንነታችን፤ በክረምትቢሆን በበጋ፤ በማግኘት ቢሆን በማጣት፤ በክብር ቢሆን በውርደት፤ ስናጠፋ የማይወልቅ፤ ስናዝን የማይርቅ፤ ስንደሰት የማይለቅ፤ የጊዜ ርዝመት የማያደበዝዘው፤ ማንነታችን ምን ይሆን የተበየደው ሰሌዳችን? ለቀኑ የሚሆን የማሰላሰያ ሃሳቤን ያዝኩ:: ትራፊኩም ተስፋ ቆርጦ መሰለኝ መንገዳችንን እንድንቀጥል ፈቀደልን:: እኔም የማሰላሰያ ሃሳቤን ለእናንተ እንዲህ አካፈልኩ:: እንዲያውም ለስራ ፈጣሪዎች የሚሆን አንድ ሃሳብ አለኝ፡፡ የታክሲ ረዳቶች ማሰልጠኛ ቢኖርስ? አዎ ስለ ደንበኛ እና ገንዘብ አያያዝ፤ስለ አጠራር አይነቶች፤የሰፈር ስሞችን በቀላሉ የማወቅ ዘዴ፤ስለ መልስ አሰጣጣጥ እና ሂሳብ ስሌት፤የረዳቶች የልምድ ልውውጥ…እንደ ሞያ የተወሰነ ስልጠና ቢኖረው ደግ ይመስለኛል፡፡መቼም አንድ ሰው ስራዬ ብሎ ከቤት ከወጣ እና ገቢ አግኝቶ ከተዳደረበት ወንጀል እስካልሆነ ድረስ ሙያው ነውና የሚያዳብርበት መንገድ ቢያገኝ አይጠላም፡፡
  • 18. ተምሳሌት ቅፅ 1 ቁጥር 1 ግንቦት ??? 16 በዝግጅት ክፍሉ እንደው አንዳንዴ.. ምን አንዳንዴ በ’ለት ተዕለት ኑሮአችን የሚደረጉ ድርጊቶች ፍትሐዊ አልሆን ብሎን ተበሳጭተን.. እርር ድብን ብለን.. አልቅሰን ባ’ቅመ-ቢስ ስሜት ውስጥ ሆነን ወደ ሰማይ አንጋጠን አናውቅም? ወደ ላይ ካንጋጠጥንበት ቦታ አንጀት የሚያርስ ነገር ወዲያው ባለማግኘታችን እንዲሁ ንዴታችን ሰማይ ጥግ ደርሶ አያውቅም ? ታዲያ ይህቺ ምድር ፍትሐዊ አይደለችም ብላችሁ ደምድማችኋል ፡፡ ከዚህ በተቃራኒ አንዳንድ ሰወች የሚያደርጉት ሰምሮላቸው .. የተናገሩት ተደምጦላቸው የገደሉት ያስገደሉት #ተቀብሮላቸው; ወደ ሰማይ ቢያንጋጥጡም ያው እንደ ምድራዊ ህይወት ሁሉ ተሳክቶላቸው ሁሉ በ’ጃቸው ሁሉ በደጃቸው ሆኖ ሲታይ በ’ነርሱ ዘንድ ምድር ፍትሐዊ ፍርድም አምላካዊ መሆኑ አምነው ደምድመዋል ፡፡ ግን፤ ግን ሕግ፤ ፍትህ ምንድን ነው? .. ሁሉም ሰው ሊያስማማ የሚችል ትርጓሜ ወይም ፍቺ አልተገኘም፡፡ በየዘመኑ የተነሱ የሕግ ፍልስፍና ት/ቤቶች / School of thoughts / የራሳቸው ትረጓሜ እየሰጡ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ወጥነት ያለው ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል ትርጉም አልተገኘም፡፡ ሕግ መካኒካል ባህሪይ አለው ብለው የሚያምኑ ሰወች ለዚህ እምነታቸው የሚያቀርቡት ማስረጃ ባ’ዋጅ ወይም በሕግ ድንጋጌ መግቢያ ላይ እንዲህ ማለት ሌላ ትርጉም እስካልተሰጠው ድረሰ እንዲህ ማለት ነው ተብሎ የተሰጠውን ትረጓሜ ከሕግ መሰረታዊ ፍቺ ጋር አጣምረው ሲተረጉሙት ይስተዋላል ፡፡ በሕግ ቋንቋ አንድ ሲደመር አንድ አንድም ሁለት ፤ አንድም አስራ አንድ የሚሆንበት አጋጣሚ ብዙ ነው ፡፡ ይህ አረዳድ ከህግ ጋር ተዛምዶ ለሌላቸው የማህበረሰቡ ክፍሎች ከአመክንዮ (ሎጂክ) ውጪ ነው፡፡ ይሁንና በዚህ ርዕስ በሌላ ጽሁፍ የምንገናኝ መሆኑን በማስታወስ ወደ ዛሬው ጽሁፌ ተሸጋገርኩ፡፡ የፍጥረታት ሁሉ መኖሪያ የሆነችው ምድር ምንም እንኳ ፍትሐዊ አይደለችም ብለን ብናማርራት እና ብንወቅሳት እስቲ አንድ ጥያቄ አንስተን መልሳችን ለራሳችን ትዝብት እንተዉ ፡፡ የሰው ልጅ በሕግና በስርዓት ለመመራት ባይመርጥ ኖሮ ሕይወቱ ምን ሊመስል እንደሚችል አስበነው እናውቅ ይሆን ? የሰው ልጅ በሕግና በስርዓት ባይተዳደር ኖሮ ዕጣ ፈንታው ምን ሊሆን እንደሚችል አስቦት ያውቅ ይሆን ? እስቲ ለአንድ ቀን መንግስት ሀገሩን የሚያስተዳድርበትን ሕግጋትና መመሪያዎች ሁሉ ለአንድ ቀን ብቻ ተግባራዊ እንዳይሆኑ አፈጻጸማቻን ሁሉ አግጃለሁ የሚል አዋጅ ቢደነግግ ምን አይነት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል በዓይነ-ህሊናችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ ? እስኪ ሕግና ስርዓት የሌለበትን የዚህን ቀን ውሎ በዓይነ-ህሊናችን ለመቃኘት እንሞክር ፡፡ እስቲ ላ’ንድ ቀን በዚህ ቀን ሰው ሁሉ በሽብር፤ በፍርሃት፤ ባለመተማመን፤ በዕልቂት፤ በአጠቃላይ በስርዓት አልበኝነት ቀኑን ሁሉ አይነተኛ ባህሪው አድርጎት ይውላል ፡፡ ከመኖሪያ ቤቱ እንጀምር .. በአንድ ቤተሰብ ከሚኖሩ አባወራ ወይም እማወራ አንደኛው በሰላሙ ጊዜ ያስቀየመውን ቂም በመበቀል ይጀምራል ፡፡ አንተ’ኮ…. አንቺ’ኮ በዛን ወቅት ያደረከኝ፤ ያደረግሽኝ… የበደልከኝ ፤ የበደልሽኝ እየተባባሉ አንድ ሁለት በመባባል ጀምረው ፍጻሜያቸው የት ሊሆን እንደሚችል መገመቱ ይከብዳል ፡፡ ወደ ጎረቤት እንቀጥል .. የሰው ልጅ በ’ለት ተዕለት ሕይወቱ ከአጉራባቹ ጋር በሰላም መኖርእንዳለሁሉበጸብእናባለመግባባትኖሯል፡፡ታዲያየዚያችቀንየሰላሙሳይሆን አለመግባባቱ.. የፍቅሩ ሳይሆን የጥላቻው ትውስ ይለውና ወሰኔን ገፍተሃል፤ አጥሬን አፍርስሃል፤ ሚሽቴን/ባሌን አማግጠሃል፤ ንበረቴን ወርሰሃል፤ ባለጠግነትህን መከታ አድርገህ በድልህኛል … እየተባባለ ቂሙን ለመወጣት ይበጀኛል የሚለውን አቅሙ የፈቀደውን ከማድረግ ወደኋላ አይልም፡፡ ምክንያቱም ሕግጋት እና መመሪያዎች ለአንድ ቀን ተግባራዊ እንዳይሆኑ ተደርገዋልና ነው ፡፡ ወደ አካባቢ እንቀጥል.. የሰው ልጅ ማህበራዊ እንስሳ በመሆኑ ከቤቱ እና ከጎረቤቱ አልፎ ከአካባቢው ጋር በመልካምም በእኩይም ይገናኛል፡፡ እንዳው ያቺ አንድ ቀን ሕግና መመሪያ የተሻረበት ቀን የሰው ልጅ በአካባቢው የሚያደርገውን ብናስብ እጅግ የከፋ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የቀድሞውን ዘመን ትተን እንደዛሬው የከፋ እንደማይሆን እያሰብን 1983 ዓ.ም መንግስት የተቀየረበትን ጊዜ ማስታወስ እንችላለን፡፡ ዝርፊያውን፤ ስርዓት አልበኝነቱን ብቻ ማንሳቱ በቂ ይመስለኛል፡፡ በ1993 ዓ.ም በተነሳው ረብሻ የነበረውን ዝርፊያ እና ሽብር እንዲሁ ማንሳት እንችላለን፡፡ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ዛሬ በሚዲያ የምናየው የፖለቲካ አለመረጋጋት የሰው ልጅ ምን ያህል ጨካኝ፤ ስርዓት አልበኛ ከአውሬ የባሰ አደገኛ መሆኑን የምንረዳበት ነው፡፡ ዋይታው ፤ ዘረፋው፤ አስገድዶ መድፈር፤ ሽብር ፤ ግድያ የ’ለት ተዕለት የህይወት አውድ ነው፡፡ በነዚያ የእንስሳት ዓለም እንደምናየው ነጻ የሆነ ሕይወት የማይኖርበት ደካማው አውሬ የህይወት ዋስትና የሰላም መድን አጥቶ እበረገገ እና እየተጠቃ የሚኖርበት ጉልበተኛው በተራው አርጅቶና ደክሞ በተራው የ’ጁን እስኪያገኝ ድረስ የጫካው ንጉስ ሆኖ እየተንጎማለለ አቅመ-ቢስ አራዊትን እያጠቃ ህይወቱ የሚቀጥልበት፡፡ የአራዊት ህይወት ሁል ጊዜ የማጥቃትና የመከላከል የፍልሚያ አውድማ ነው፡፡ ታዲያ ይህንን የአኗኗር ስርዓት ሊቃውንቱ የዱር ሕግ /The law of Jungle/ በማለት ይጠሩታል፡፡ የኛ የሰው ልጆች መኖሪያ ለአንድ ቀን ህግና መመሪያ ቢሻር የዱርእንስሳት የአኗኗር ዘዬን አያስንቅም ትላላችሁ ፡፡ ስለ ሕግ ሲነሳ