More Related Content
Similar to ስነ ዜጋ ማስታወሻ ለ7 ክፍል.pdf
Similar to ስነ ዜጋ ማስታወሻ ለ7 ክፍል.pdf (9)
More from marakiwmame (20)
ስነ ዜጋ ማስታወሻ ለ7 ክፍል.pdf
- 1. 0 | P a g e
እንኳን ሇ2013 ዓ᎐ም በሰሊም አዯረሳችው!
እንኳን ሇ2013 የትምህርት ዘመን በሰሊም አዯረሳችው።
ዓመቱ
የሰሊም
የፍሬያማ
የብሌጽግና
የፍቅር
የዯስታ
ይሁንሊችው።
ከመ/ር በሃይለ ወ᎐
- 2. 1 | P a g e
ስኩሌ ኦፍ ሪዯምሽን 2013 የት/ ዘመን የስነዜጋ ት/ት ሇ7ተኛ
ክፍሌ የተዘጋጀ ማስታወሻ ከምዕራፍ 1
ምዕራፍ አንዴ
ዳሞክራሲያዊ ስርዓት
ዳሞክራሲያዊ ስርዓት የህዝብ ዴምጽ የሚከበርበት፣በዳሞክራሲያዊ ምርጫ በመሳተፍ
ተወካዮቹን ወይም መሪዎችን የሚመርጥበት ስርዓት ነው።
የዳሞክራሲ ስርዓት መርሆች
የዳሞክራሲ ስርዓት መርሆች የሚባለት:−
1) ነጻ የፖሇቲካ ስሌጣን ውዴዴር
2) የህግ የበሊይነት
3) ግሌጽነት እና ተጠያቂነት
4) የብዙሃን ዴምጽ የበሊይነት እና የአነስተኛው ቁጥር ዴምጽ መከበር
1᎐ነጻ የፖሇቲካ ስሌጣን ውዴዴር
የዳሞክራሲያዊ ስርዓት አንደ መርህ ነጻ የፖሇቲካ ሥሌጣን ውዴዴር መኖር ነው።
ነጻ የፖሇቲካ ውዴዴር ሲባሌ በመጀመርያ ዯረጃ የሚያመሇክተው የመንግስት ስሌጣን
ሇመያዝ ቢያንስ ሁሇት እና ከዛ በሊይ የፖሇቲካ ፓርቲዎች ወይም ግሇሰቦች ሇምርጫው
መወዲዯር ይችሊለ።
2᎐የህግ የበሊይነት
የዳሞክራሲያዊ ሥርዓት ላሊው መሰረታዊ መርህ የህግ የበሊይነት ነው።
የህግ የበሊይነት መርህ የዳሞክራሲያዊ ስርዓት የሚቆምበት ምሰሶ ነው።
በዳሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ማንኛውም ሰው የመንግስት ባሇስሌጣናትን ጨምሮ
ሇህግ ተገዢ ይሆናለ።
የስራ አስፈጻሚው አካሌ ሥሌጣንን ያሇአግባብ አይጠቀምም።
3᎐ግሌጽነት እና ተጠያቂነት
የዳሞክራሲያዊ ሥርዓት ሶስተኛው መሰረታዊ መርህ በህዝብ የሚመረጡትም ሆኖ
በመንግስት የሚሾሙት ባሇስሌጣናትም በሚሰሩት ስራ ግሌጸነትና ተጠያቂነት ያሇባቸው
መሆኑ ነው።
መንግስት የህዝብ ስራ በሚሰራበት ጊዜ አሰራሩ ሇህዝብ ግሌጽ ማዴረግ
ከዚህም በሊይ የመንግስት ሃሊፊው ሆነ ተመራጩ ሃሊፊነቱን ካሌተወጣ ተጠያቂ የሚሆን
መሆኑን ህዝበም በመረጠው ተወካይ ሊይ እምነት ባጣ ጊዜ ተወካዮቹን ሇማንሳት የሚችሌ
መሆኑን ያመሇክታሌ።
ሰኞ መስከረም 11/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ አንዴ/ lesson one
ስነዜጋ እና ስነምግባር ት/ት
ሇ 7ተኛ
ክፍሌ
ረቡዕ መስከረም 13/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ ሁሇት/ lesson two
አርብ መስከረም 15/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ ሶስት / lesson three
- 3. 2 | P a g e
4᎐የብዙሃን ዴምጽ የበሊይነት እና የአነስተኛው ቁጥር ዴምጽ መከበር
የዳሞክራሲያዊ ስርዓት ላሊው መስረታዊ መርህ የብዙሃን ዴምጽ የበሊይነት ነው።
የዳሞክራሲ ስርዓት መገሇጫ ከሆኑት ተግባራት ውስጥ :−
o ግሌጽ ውይይት፥
o የሃሳብ ሌውውጥ
o ክርክር ማካሄዴ እና
o ሇችግሮቹ ወይም ሇሌዩነቶቹ በሰሊማዊ መንገዴ እሌባት መስጠት ይጠቅሳሌ።
ሙለ በሙለ ከመግባባት እና በስምምነት መፍታት ሲያቅት በዴምጽ ብሌጫ በመፍታት
ውሳኔ ሊይ መዴረስ የግዴ የሆናሌ።
ሰብዓዊና ዳሞክራሲያዊ መብቶች
ሰብዓዊ መብቶች:−ማሇት ሰዎች ሰው በመሆናቸው የሚጎና ጸፈበት በማንም አካሌ የማይጣሱ
የተፈጥሮ መብቶች ናቸው።
ከነዚህም መካከሌ የሚከተለት ዋናዋንና ናቸው።
የመሰሇውን እምነት(ሃይማኖት) የመያዝ(የማመን)ነጻነት
ሰብዓዊ ክብሩን ያሇማውረዴ
በህግ መሰረት ካሌሆነ በስተቀር ያሇመታሰር እና የግሌ መኖሪያ ቤቱ ያሇመፈተሽ ነጻነት
በማንኛውም ስፍራ በሰብዓዊ ነቱ እውቅና የማግኘት
በህይወት የመኖር
በአካለ ሊይ ጉዲት እንዲይዯርስ ፣የጭካኔ ዴርጊት እንዲይፈጸምበት የመጠበቅ ።
በኢ᎐ፌ᎐ዳ᎐ሪ ህገ መንግስት የሰብዓዊ መብቶች በተሇያዪ አንቀጾች ተዯንግገዋሌ። ሇምሳላ:−
የማይዯፈርና የማይገሰስ በህይወት የመኖር መብት(አንቀጽ 15)
የአካሌ ዯህንነትና ነጻነትመብት(አንቀጽ 14)
የክብር እና የመሌካም ስም መብት(አንቀጽ 24)
የሃይማኖት፣ የእምነት እና የአመሇካከት ነጻነት(አንቀጽ27)
ከህግ ውጭ ያሇመያዝ (አንቀጽ 17)በተጨማሪም በተባበሩት መንግስታት ዴርጅት
የረቀቁና የጸዯቁ ሰበዓዊ መብቶችን አባሌ ሃገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ ተቀብሇው
አጽዴቀውታሌ።
የግሇሰብ እና የቡዴን ሰበዓዊ መብቶች
የግሇሰብ ሰበዓዊ መብቶች
በህይወት የመኖር መብት
በአካሌ ሊይ ጉዲት እንዲይዯርስ የመጠበቅ መብት
ከህግ ውጭ ያሇመያዝ፣ያሇመከሰስ እና ያሇመታሰር መብት
1᎐በህይወት የመኖር መብት
ሰው ላልችን መብቶች ና ነጻነቶችን ከመጠየቁ በፊት አስቀዴሞ እርሱ ራሱ
በህይወት መኖር ይገባዋሌ። በሕይወት የመኖር መብት ዋናና መሰረታዊ መብት
ነው።
2᎐በአካሌ ሊይ ጉዲት እንዲይዯርስ የመጠበቅ መብት
ሰኞ መስከረም 18/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ አራት / lesson four
ረቡዕ መስከረም 20/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ አምስት / lesson five
- 4. 3 | P a g e
ይህ መብት በህይወት ከመኖር መብት የሚመነጭ መብት ነው። በህይወት የመኖር
መብት ተከብሮ የአካሌ ዯህንነት መብት ካሌተጠበቀ ትርጉም የሇውም። በአካለ
ሊይ ኢሰበዓዊ ዴርጊቶች እየተፈጸሙበት መኖር የሚፈሌግ ሰው የሇም።
ስሇዚህ የአካሌ ስቃይና ጉዲት የላሇበት ህይወት ሇሰው ሌጆች በህይወት እንዯመኖር
ሁለ አስፈሊጊ ነው።
3᎐ከህግ ውጭ ያሇመያዝ፣ ያሇመከሰስና ያሇመታሰር መብት
ይህ መብት ማንኛውም ሰውበህግ ከተዯነገገው ስርዓት ውጭ ክስ ሳይቀርብበት ወይም
ሳይፈረዴበት መያዝም ሆነ መታሰር እንዯላሇበት የሚያሳይ ነው። በዚህ መሰረት
ማንም ሰው ያሇበቂ ማስረጃ እና በጽሁፍ ከተዯገፈ የፍርዴ ቤት ትዕዛዝ ውጭ
ሉያዝ አይገባም።
የቡዴን ሰብዓዊ መብቶች
የእኩሌነት መብት
የሃይማኖት፣የእምነትና ያመሇካከት ነጻነት
1᎐የእኩሌነት መብት
በእኩሌ ዓይን መታየት ነው።
የተሇያዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በአንዴ ሊይ በሚኖርበት አገር የእኩሌነት
መብት መረጋገጥ የቡዴን ሰበዓዊ መብቶችን እንዱከበሩ ያገሇግሊሌ። ይህም ሇሰሊም፣
ሇእዴገትና ሇዳሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መፍጥን አስተዋጽኦ ያበረክታሌ።
2᎐የሃይማኖት ፣የእምነትና የአመሇካከት ነጻነት
የሃይማኖት፣የእምነት እና የአመሇካከት ነጻነት ማሇት የፈሇጉትን ሃይማኖት ወይም
እምነት የመቀበሌ እና የመከተሌ ነጻነት ማሇት ነው።
የሃይማኖት እና የእምነት ነጻነትየህዝብን ዯህንነት፣ሰሊምን፣የላልች ሰዎችን መሰረታዊ
መብቶች ሇማስከበር በሚወጡ ህጎች ገዯብ ሉጣሌበት ይችሊሌ።
የግሇሰብ እና የቡዴን ዳሞክራሲያዊ መብቶች
የዳሞክራሲ መብቶች:−ማሇት የዜጎችን ማህበራዊ ፣ፖሇቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች
ናቸው።
ከዜጎች ዳሞክራሲያዊ መብቶች መካከሌ የሚከተለትን በምሳላነት መመሌከት
ይቻሊሌ:−
ዜጎች የመሰሊቸውን አመሇካከት የመያዝ
የመዯራጀት፣የመሰብሰብ እና ሰሊማዊ ሠሌፍ የማዴረግ
ያሇፍቃዴ ዜግነቱን ያሇመግፈፍ እና በፍቃደ ዜግነቱን የመቀየር
የግሌ ሀብት የማፍራት እና ባሇቤት የመሆን
የመዘዋወር ነጻነት፣እና የመሳሰለት መብቶች ዳሞክራሲያዊ መብቶች በመባሌ
ይታወቃለ።
የኢፌዳሪ ሕገመንግስትም የዜጎችን ዳሞክራሲያዊ መብቶች በተሇያዩ አንቀጾች በዝርዝር
አስቀምጧሌ።
ሀ᎐ፖሇቲካዊ መብቶች
የአመሇካከት እና ሃሳብን በነጻነት የመግሇጽ መብት(አንቀጽ 29)
አርብ መስከረም 22/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ ስዴስት / lesson six
ሰኞ መስከረም 25/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ ስባት / lesson seven
- 5. 4 | P a g e
የዜግነት መብቶች(አንቀጽ 33)
የመምረጥና የመመረጥ መብት(አንቀጽ 38)
የመሰብሰብ፣ሰሊማዊ ሰሌፍ የማዴረግ፣ ነጻነትና አቤቱታ የማቀረብ መብት(አንቀጽ 30
)ወዘተ᎐᎐᎐
ሇ᎐ማህበራዊ መብቶች
የጋብቻ ፣የግሌና የቤተሰብ መብቶች(አንቀጽ 34)
የአካባቢ ዯህንነት መብት(አንቀጽ 44)ወዘት᎐᎐᎐
ሐ᎐ኢኮኖሚያዊ መብቶች
የንብረት መብት(አንቀጽ 40)
የሌማት መብት(አንቀጽ 43)
የሰራተኞች መብት(አንቀጽ 42)
የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብቶች
አመሇካከትንና ሃሳብን በነጻ የመያዝና የመግሇጽ መብት
የመዘዋወር ነጻነት
1᎐አመሇካከትንና ሃሳብን በነጻ የመያዝና የመግሇጽ መብት
ይህ መብት የራስን ሃሳብና አመሇካከት የመግሇጽ ብቻ ሳይሆን እኛ የምንፈሌገውን
ማንኛውም መረጃ የመጠየቅ እና የማግኘት መብትንም የሚያጠቃሌሌ ነው።
አመሇካከትንና ሃሳብንበነጻ የመግሇጽ መብት የሃገርን ዯህንነት የሰውን ክብርና
መሌካም ስም ሇመጠበቅ ሲባሌ ህጋዊ ገዯብ ሉጣሌበት ይችሊሌ።
2᎐የመዘዋወር ነጻነት
ይህ መብትበሀገር ውስጥ የመዘዋወር፣ወዯ ውጭ ሃገር የመሄዴና የመመሇስ ፣በፈሇጉበትና
በመረጡበት ስፍራ የመኖርን መብት የሚያካትት ነው።
በአንዴ ስፍራ ወይም አካባቢ እንዱኖር የተገዯበ ሰው የመዘዋወር ነጻነት የሇውም። በእንዯዚህ
ዓይነት ሁኔታ የሚኖር ሰው በአብዛኛው እስረኛ ወይም ከእስረኛ የማይሻሌ ነው ሇማሇት
ይቻሊሌ።
የቡድን ዴሞክራሲያዊ መብቶች
የብሔሮች ፣የብሔረሰቦች እና የህዝቦች ራስን በራስ የማስተዲዯር መብት
የመዯራጀት፣የመሰብሰብ፣ሰሊማዊ ሰሌፍ የማዴረግ እና አቤቱታ የማቅረብ መብት
የሕዝብ ለዓሊዊነት
1᎐የብሔሮች ፣የብሔረሰቦች እና የህዝቦች ራስን በራስ የማስተዲዯር መብት
ይህ መብት ብሄሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ራሳቸውን የማስተዲዯር፣ባህሌና ቋንቋቸውን
የማሳዯግ እና ከፈሇጉም የራሳቸውን ነጻ አስተዲዯር የመመስረት መብት አሊቸው። ከዚህ
በተጨማሪ ሇህዝቡ የተረጋገጠሇት ላሊው መብት በዳሞክራሲያዊ መብት ተጠቅሞ
የመረጣቸው የመንግስት ባሇስሌጣናት የመቆጣጠርና በእርሱ ሊይ እምነት ሲያጣ
የመሻርና ላሊውን የመተካት መብትአሇው።
ረቡዕ መስከረም 27/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ ስምንት / lesson Eight
አርብ መስከረም 29/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ ዘጠኝ / lesson nine
ሰኞ ጥቅምት 2/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ አስር / lesson ten
- 6. 5 | P a g e
2᎐የመዯራጀት፣የመሰብሰብ፣ሰሊማዊ ሰሌፍ የማዴረግ እና አቤቱታ የማቅረብ መብት
እነዚህ መብቶች መሰረታዊና ከፍተኛ ቦታ የሚሰጣቸው ናቸው።
ሰዎች ሇህይወታቸው የሚያስፈሌጋቸውን ሇማሟሊት በተሇያዩ አቅጣጫዎች ተሰባስበውና
ተዯራጅተው የጋራችግሮቻቸውንና በህብረት መፍታት ይኖርባቸዋሌ።
የመዯራጀት፣ የመሰባሰብ ፣ሰሊማዊ ሰሌፍ የማዴረግ መብት የዜጎች ዯህንነት ክብርና
መሌካም ስም ሇመጠበቅ ፣የጦርነይ ቅስቀሳዎችን እንዱሁም ሰብዓዊ ክብርን ይሚነኩ
የአዯባባይ መግሇጫዎችን ሇመከሊከሌ ሲባሌህጋዊ ገዯብሉጣሌባቸው ይችሊሌ።
3᎐የሕዝብ ለዓሊዊነት
የህዝብ ለዓሊዊነት ማሇት የአንዴ ሃገር ህዝቦች የስሌጣን ምንጭና ባሇቤት ናቸው ማሇት
ነው።
የህዝብ ለዓሊውነት አሇ ሇማሇት የምንችሇው ህዝቡ የራሱን ዕዴሌበራሱ መወሰን ሲችሌ፣
የሚያስተዲዴሩትን ተወካዮችን መምረጥ ሲችሌ፣በፈሇገ ጊዜ ዯግሞ ከስሌጣን ማውረዴ
ሲችሌ ነው።
ልዩነቶችን ማቻቻል
ሌዩነት:−በተፈጥሮና በህብረተሰቡ ውስጥ ያሇ ክስተት።
የሰው ሌጅ በዘር፣በብሔር፣በጎሳ፣በሃይማኖት፣በባህሌ፣በቋንቋ፣በአመሇካከት፣በጾታ፣በጸባይ
በመሌክ በቁመና ወዘተ ይሇያያሌ።
መቻቻሌ:−ማሇት የሰዎችን መኖርንና የፈሇጉትን የመሆን መብት ማወቅና ማክበር ማሇት
ነው።
ሌዩነቶችን ማቻቻሌ አብሮ ሇመኖር ከፍተኛ ጠቀሜታ አሇው።
ሌዩነቶችን ማቻቻሌ በየትኛውም ቦታ እና በማንኛውም ጊዜ የሰው ሌጅ በሌዩነቶች
ውስጥ አንዴነትን ፈጥሮ በሰሊምና በፍቅር አብሮ ሇመኖር እንዱቻሌ ያዯርጋሌ።
የሃሳብ ሌዩነቶችን አቻችል አብሮ መኖር ማሇት ተሳስበው ተፋጭቶ በማሸነፍ
ሌዩነቶችን ማስወገዴ፣በሰሊማዊ መንገዴ በመወያየትና በመከራከር፣ሌዩነቶችን
ማስወገዴ ካሌተቻሇ ዯግሞ ሌዩነቶችን እንዲለ ተቀብል በሰሊም አብሮ መኖር
መቻሌማሇት ነው።
ሌዩነቶችን ማቻቻሌ አብሮ ሇመኖር ያሇው ጠቀሜታ
ሌዩነቶችን ማቻቻሌ አብሮ ሇመኖር ያሇው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።
ምክንያቱም ሌዩነቶችን ማቻቻሌ ሰሊምን፣ፍቅርን እና መተሳሰብን ሇማስፈን
ወሳኝ ስሇሆነ ነው።
ሌዩነቶችን ማቻቻሌ ሕብረተሰቡ በሌዩነት ውስጥ አንዴነት ፈጥሮ በሰሊምና
በፍቅር አብሮ መኖር እንዱቻሌ ያዯርጋሌ።
የመንግስት ተግባራት
መንግስት:−በህዝብ መካከሌ ህግ እንዱከበር፣ ሃገር እንዱጠበቅ እና ስነስርዓት እንዱኖር
የሚያዯርግ አንዴ ተቋም ነው።
ረቡዕ ጥቅምት 4/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ አስራ አንዴ / lesson eleven
አርብ ጥቅምት 6/2013 ዓ᎐ም ክፍሌ አስራ ሁለት / lesson twelve
- 7. 6 | P a g e
መንግስት ከህዝብ የወጣና ህዝብን የሚያስተዲዴር አካሌነው።
መስተዲዯር:−የአንዴ አካባቢ ህዝብ የሚወክሌ ወይም የሚያስተዲዴር ነው።
የኢትዮጵያ የፌዳራሌ መንግስት ተግባራት
የኢትዮጵያ ፌዳራሊዊ መንግስት የሚያከናውናቸው በርካታ ተግባራት አለት። ዋና ዋናዎቹ
የሚከተለት ናቸው:−
ሀ᎐ሕገ መንግስቱን ይጠብቃሌ ይከሊከሊሌ፣
ሇ᎐የሀገሪቱ አጠቃሊይ የኢኮኖሚ፣የማህበራዊና የሌማት ፖሉሲ፣ ስትራቴጂና ዕቅዴ ያወጣሌ፣
ያስፈጽማሌ፣
ሐ᎐የሀገርንና የህዝብ የመከሊከያና የዯህንነት እንዱሁም የፌዳራሌ መንግስት የፖሉስ ሃይሌ
ያዯራጃሌ፣ይመራሌ፣
መ᎐ብሔራዊ ባንክን ያስተዲዴራሌ፣ገንዘብ ያትማሌ፣ይበዯራሌ፣የውጭ ምንዛሪና ገንዘብ ሌውውጥን
ይቆጣጠራ።
ሠ᎐የውጭ ግንኙነት ፖሉሲን ይወስናሌ፣ፖሉሲዎችንም ያስፈጽማሌ፣ዓሇምአቀፍ ስምምነቶችን
ይዋዋሊሌ፣ያጸዴቃሌ፣
ረ᎐የአየር፣ የባቡር፣የባህር መጓጓዣ፣የፖስታና የቴላኮሙኒኬሽን አገሌግልቶች እንዯዚሁም ሁሇት
ወይም ከሁሇት በሊይ ክሌልችን የሚያገናኙ አውራ መንገድችን ያስፋፋሌ፣ያስተዲዴራሌ፣
ይቆጣጠራሌ፣
ሰ᎐ወዯ ሀገር የመግብያና የመውጫ ጉዲዮችን ስሇስዯተኞችና ስሇፖሇቲካ ጥገኝነት ይወስናሌ፣
ይመራሌ።
አዘጋጅ:መ/ር በኃይለ ወ᎐