Successfully reported this slideshow.
We use your LinkedIn profile and activity data to personalize ads and to show you more relevant ads. You can change your ad preferences anytime.

Semayawi1 131015152400-phpapp01

741 views

Published on

YES

Published in: Education
 • Be the first to comment

 • Be the first to like this

Semayawi1 131015152400-phpapp01

 1. 1. ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 1
 2. 2. ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 2 ጋዜጣችንን ማሳተም እንድንችል ዛሬም እንጠይቃን! ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የዛሬ አንድ መቶ ዓመት ገደማ ለሀገራችን ዕድገት ብሩህ ራዕይ በነበራቸውና ሕዝብ መረጃንና ዕውቀት እንዲያገኝ መልካም ምኞት በነበራቸው አባቶቻችንና እናቶቻችን የተመሠረተ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የተቋቋመበትን አብይ ዓላማ ዕውን ለማድረግም ብርሃንና ሰላም በሀገራችን የእውቀት አድማስ እንዲሠፋና ዜጐችም መረጃ እንዲያገኙ ባበረከተው የረጅም ጊዜ አገልግሎት ባለውለታነቱና ፈር ቀዳጅነቱ በታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥለት አኩሪ ሃቅ ነው፡፡ ብርሃንና ሰላምን ለማቋቋም ምንም እንኳን የግለሰቦች ባለብሩህ ራዕይነት ባይካድም ድርጅቱ የተቋቋመውም ሆነ ሲተዳደር የኖረው ከእያንዳንዱ ዜጋ በግብር እና በታክስ መልክ በሚሰበሰብ ገንዘብ በመሆኑ ንብረትነቱም የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ሃብት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ስለሆነም ዜጐችን በተናጠልም ሆነ የሀገሪቱን ተቋማት እንደተቋም በእኩልነትና በግልፅነት ማገልገል እንዳለበት ለድርጅቱም ሆነ ለሕዝብ የተገለፀ ሃቅ ነው፡፡ እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩ መሠረታዊ እውነታዎች በመመርኮዝ ፓርቲያችን በነሐሴ 22/2004 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ በብርሃንና ሰላም የሕትመት አገልግሎት ለማግኘት ጠይቆ ነበር፡፡ ለጥያቄአችን መልስ የሚሠጥ በማጣታችን የፓርቲያችን አመራር አባላት በአካል በመገኘት የድርጅቱን የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ቢያነጋግሩም መፍትሔ የሚሰጥ ሰው አልተገኘም፡ ፡ የፓርቲያችን አመራሮች በአካል ያነጋገሯቸው የተለያዩ ክፍሎች የሥራ ኃላፊዎች ጥያቄውን አስመልክቶ በቃል የሰጧቸው መልሶች የተለያዩ፤ ነገር ግን ጋዜጣችንን ለማተም የማይችሉ መሆኑንና ጋዜጣችንን ላለማተም የሚያቀርቡልን ምክንያቶች ደግሞ እጅግ የተለያዩና የተድበሰበሱ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ድርጅቱን የጠየቀው በጽሑፍ ስለሆነ ጋዜጣችንን የማታትሙበትን ምክንያት የሚመለከተው አካል በጽሑፍ መልስ እንዲሰጠን በማለት ብንጠይቅም እንኳን ለጥያቄያችን መልስ ልናገኝ ቀርቶ በሕጋዊ አካልነትና በሰውነት እንኳ የሚቆጥረን አካል አጥተናል፡፡ ይህ ጥያቄያችን መፍትሄ እንዲያገኝም ተቋሙን በበላይነት ለሚመራው ቦርድ እንደገና በጽሁፍ አቤት ብለናል፡፡ መልስ ግን አሁንም የለም እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት የጐደለውና ተጠያቂነት የጠፋበት ተቋም ይዘን፤ በመንግሥት በኩል በየመሥሪያ ቤቱ ተለጥፈው የምናያቸውን የሥነ-ምግባር መርሆችን በሥራ ላይ ማዋል ቀርቶ ማሰብ እንኳን የማይቻል እንደሆነ ነጋሪ አያሻውም፡፡ እኛ የጠየቅነው የሕትመት አገልግሎት ጥያቄ ለቦርድ አባላት ቀርቦ ጊዜአቸውን የሚያጠፉበት ጉዳይ ሳይሆን ተራ የቀን ተቀን አገልግሎት ጥያቄ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ክስተት ተጠያቂነት በጐደለበት ቦታ ሁሉ የሀገር ሀብትና ጊዜ እየባከነ የዜጐችም መጉላላት እየበረከተ እንደሚሄድ ማሳያ ጉልህ ማስረጃ ነው፡፡ በመሆኑም ፓርቲያችን በገበያ ዋጋ የሚጠበቅበትን ከፍሎ፣ በሕግ ማሟላት የሚገባውን አሟልቶ ዛሬ ብዙ ዓይነት ሕትመቶችን ማከናወን ከሚችል ግዙፍ ድርጅት የአንድ ሣምንታዊ ጋዜጣ የሕትመት አገልግሎት ለማግኘት ለቀረበው ጥያቄ መልስ እንኳን የሚሰጠው አካል ማጣት (ምንም እንኳን የአንድን ድርጅት ድክመት ብቻ መነሻ አድርጐ መወሰን በቂ ባይሆንም) ሀገራችን በእውነት ያለችበት የአስተዳደር ችግር እና የተቋማት ምክነት የት እንደደረሰ አመላካች ነው፡ ፡ ይህ ድርጊት የሕሊናና የታሪክ ተጠያቂነት የሚያመጣ ሲሆን መልካም አስተዳደር በሰፈነበት ሀገር ደግሞ የሕግም ተጠያቂነት ያመጣ ነበር፡፡ ፓርላማ ተገኝተው የ ሶስተኛ አመት የፕሬዘደንቱን መክፈቻ ንግግር ማብራሪያ ያቀረቡት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም በአንድነት ፓርቲ ተወካይ በኩል ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ ኢህአዴግ ተጠያቂነትን እንደማይፈራና ለዚህም ስጋት እንዳይገባቸው የሚያስተማምን ነበር፡፡ ይህ ከሆነ ዘንዳን የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስተዳደር፤ የመንግስት ተቋማት የሆኑ የንግድ ድርጅቶች በአግባቡ ሥራቸውን እያከናወኑ እንደሆነ መከታተልና መቆጣጠር የሚኖርበት የበላይ አካል እንደመሆኑ፤ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅትንም በዚሁ መልክ በመቃኘትና በመጠየቅ ተጠያቂነትን በዚህ አግባብ ሊያሰፍን ይገባል፡፡ ዜጐችን በእኩል ዐይን አይቶ በፍትሐዊነት እያገለገለ ካልሆነም አስፈላጊው የእርምት እርምጃ በአስቸኳይ ሊወሰድበት ይገባል፡፡ በመንግስት ድርጅትነት ስም ብልሹ አስተዳደርን፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን እና በጥቅማ ጥቅም በአድሎ የመሥራት ሁኔታም ካለ ድርጅቱን ከላይ እስከታች መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡ በመንግስታዊ ሌባም የመንግስት ፖሉሲ፣ አሠራርና መልካም ስም እየጐደፈ እንዳይሆን ማጣራት ያሻል፡፡ አለበለዚያ እንደው በደፈናው ይህ የንግድ እንጂ የአስተዳደር ጉዳይ አይደለም! ብሎ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት የጠቅላይ ሚኒስትሩን “አዲስ” አካሄድ ወይም አመራር ያስጠረጥራል፡፡ እንደቀድሟቸው ሁሉ እኚህም ጠቅላይ ሚኒስትር መሬት ካለው ሀቅ ጋር የማይሄዱ ነገሮችን በርቱዕ አንደበት በመናገር ብቻ ችግር እንደሌለ ማስመሰል ችግሩን በምንም ዓይነት አይቀርፈውም፡፡ እንደውም ያባብሰዋል! በመሆኑም ዛሬ የዚህች ሀገር ዜጐች በምናወጣው አንጡራ ሀብት የሚተዳደረውና የሕዝብ ሀብት የሆነው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ እንዲሁም አዲሱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተዳደር እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች ለምን እንደሚፈፀሙ አጣርቶ መልስ እንዲሰጠንና ወደፊትም እንዳይደገሙ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወስድ እየጠቆምን አፅንዖት ሰማያዊ በሰማያዊ ፓርቲ በየ15 ቀኑ ዕየታተመ የሚወጣ መፅሄት ነው፡ ፡ ዋና አዘጋጅ አናኒያ ሶሪ አድራሻ፡ አዲስ ከተማ ክ/ከ ወረዳ 8 የቤት ቁጥር 377 ኢ-ሜይል፡- anania20006@yahoo.com ኮምፒውተር ጽሁፍ በሰማያዊ ፓርቲ ሌይአውት ዲዛየን በሰማያዊ ፓርቲ አከፋፋይ ፡- ነብዩ ሞገስ ህትመት ክትትል የሽዋስ አሰፋ አሳታሚው፡- ሰማያዊ ፓርቲ አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከ ወረዳ፡- 7 የቤት ቁጥር- 227 ስልክ፡- 0116514240 ፖ.ሳ.ቁ፡- 180298 ድረ-ገጽ፡ www.semayawiparty.org ኢ-ሜይል info@semayawiparty.org አታሚ፡- ስፕሪንግ ማተሚያ ቤተ ስልክ፡- 0911844887 0911410926
 3. 3. ሰማያዊ፡- በቅድሚያ ለቃለ-መጠይቁ ስለተባበሩን በጣም ነው የምናመሰግነው፡፡ በቀጥታ ወደ ጥያቄው ስገባ፡- በጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ሞት ምን እንደተሰማዎ ቢገልፁልንና ከዚያ ብንጀምር….. ኘሮፌሰር መስፍን፡- የአቶ መለስ ሞት ድንገተኛ ነው፤ ድንገተኛ በመሆኑም ያስደነግጣል፡፡ ለማናችንም ቢሆን ሞት የማይቀር መሆኑንም ብናውቅ፤ እንኳን እንደዚህ በድንገት ሲሆንና ታመውም ቆይተው በሚሞቱበት ጊዜ ማዘን አይቀርም፡፡ ምንም አይነት ሰው ይሁን! እኔ በመለስ ሞት ያደረብኝ ስሜት፤ ከዚህ በፊት በጠ/ሚኒስትርነቱ ወይም በኘሬዚዳንትነቱ አሊያም በፈላጭ ቆራጭነቱ ያደረገው ነገር አይደለም፡፡ ድንገት በመሆኑ፣ ዕድሜ ለንስሃ ሳያገኝ መቅረቱ ያሳዝናል፡፡ …… እና …. መቼም…..እእእ….. የሱ ሞት ለብዙዎቻችን እንደዚሁ እንደማንም እንደሰው የሰው ባህርይ ሆኖ የመጣ መሆኑን ብንገነዘበውም፤ ለጓደኞቹ ደግሞ እንደዚህ አልነበረም ይመስለኛል፡፡ እነሱ ይበልጥ የደነገጡ፣ የተደናበሩ፣ ሞትን ለመደበቅ የሞከሩ፣ የማይደበቀውን ለመደበቅ የሞከሩ በመሆናቸው ትንሽ የመለስን ሞት እእ….. አንድ ያጠላበት አጉል ነገር ነበረና እሱ ያሳዝናል፡፡ እሱም በራሱ በኩል ሆነ፤ ለርሱም የሚቆም ሰው-የሚመለከተው፣ ለቤተሰቡ ያ ሁኔታ እና ለመደበቅ የተደረገው ሽር-ጉድ (እስካሁንም ድረስ ብዙ ነገር ተደብቋል) ያ ደግሞ ይበልጥ ያሳዝናል- ከሞቱም ይበልጥ ያሳዝናል-አሟሟቱ! ይኸው ነው፡፡ ሰማያዊ፡- በዚህ ዙሪያ ግን በዚያን ሰሞን በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ በረከት ሰምኦን ተጠይቀው፡- “ይሄ በፓርቲያችን የተለመደ ባህል ነው፤አዲስ አይደለም፡ ፡ የአንድ ሰው መታመም ወይም መሞት ብዙ ስለማያስደንቀን በአደባባይ መግለፁንም ያን ያክል አሳሳቢ አድርገን አናየውም” ብለው ነበረ፡፡ በዚህ ረገድ ሌሎች ደግሞ፡- “የኢትዮጵያ ህዝብ የማወቅ መብት ነበረው፤ ሊደበቁ የሚገቡ ነገሮች ብሔራዊ የደህንነት ምስጢሮች ወይም የመከላከያ ምስጢሮች ተብለው ሊያዙ የሚችሉ የመኖራቸውን ያህል ስለአንድ የአገሩ ጠቅላይ-ሚኒስትር ግን ለዚያውም የህዝብ ኃላፊነት ቦታ እና ስልጣን እንደመያዛቸው፤ህዝቡ በይፋ ማወቅ ይገባው ነበረ” ብለው የሚከራከሩም አሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ የጋናውን ኘሬዚዳንት ሞትና ወዲያው ለህዝቡ በይፋ መገለፁን ብሎም በተገቢው ወቅት ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር መካሄዱን እንደአብነት ጠቅሰው ያስረዳሉ፡፡ እርስዎ በዚህ ላይ ምን አስተያየት አልዎት? ኘሮፌሰር መስፍን፡- እንግዲህ በረከት እኛ ሲል እነማን ናቸው እነሱ? እኛ የሚለው! እንደዚህ ልዩ ባህል ያለው! የተለየ የሆነው! ከኢትዮጵያ ህዝብ ባህል፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ልማድ ውጭ የቆመ ማን ነው እሱ? ማነው በረከትና ቡድኑ? ኢህአዴግን እንደሆነ ኢህአዴግ አንድ የፖለቲካ ቡድን ነው፤ግንባር ነው፤ ብዙዎች አሉበት ውስጡ-ሰዎች! አሁን እንደዚህ ‘መርዶ ባህላችን አይደለም’ ሲሉ ከዚህ በፊትም ሰምቻለሁ በሌላ አጋጣሚ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያሉት እኮ! የኢትዮጵያን ህዝብ ነው የሚያስተዳድሩት፤ ለኢትዮጵያ ህዝብም ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ካልሆነ ይሄ የተለመደው የነሱ ግዴታቸውን ቸል የማለት እና ‘እኛ ነን ሁሉንም ነገር የምንወስነው- ልማድንም ባህልንም የምንወስነው እኛ ነን፤ ከእኛ በላይ ማንም የለም! ህዝቡም ቢሆን የራሱ ባህል የለውም! የማወቅም መብት የለውም፤ ማለት ይችላል በረከት ከዚህ በፊት በሌላም ነገር እንዳለው፡ ፡ ነገር ግን ይሄ ቅድም እንዳልኩት፡- በመለስ ሞት ምክንያት ተደናብረው እንጂ በረከት ስቶት አይደለም፡፡ በመሆኑም፡- በድንብርብር ውስጥ ሆነው አንዴ ‘ታሟል!፣ አንዴ ‘ደህና ነው!፣ አንዴ አሁን ነው!፣ “እንዲህ ነው…. እንዲህ ነው….” እያሉ ቆይተው ስለነበረ፤ በእውነቱ የነሱን መደናበር እና በትክክለኛው አእምሮ ውስጥ እንዳልነበሩ የሚያሳይ ነው፡፡ ሰማያዊ፡- በአቶ መለስ ሞት ላይ መደናበሩን ምን አመጣው ይላሉ? ኘሮፌሰር መስፍን፡- ስለራሳቸው ነውኮ እነሱ የሚደናበሩት እንጂ መለስማ ሞቷል፡፡ ሰማያዊ፡- ለማለት የፈለግሁት፡- ‘የፖለቲካ ድርጅት ወይም ቡድን ነን፣ የምንመራበት መስመር አለን የሚሉ እስከሆኑ ድረስ በቀጣይነት ተተኪው ነገር…. ኘሮፌሰር መስፍን፡- አልተዘጋጁም! ድንገተኛ ነበር ይሄ ነገር፡፡ በእርግጥ እንዲህ ቢሆን እንዲህ እናደርጋለን ብለው፣ ህጉ ግልፅ ሆኖ ፣ የሚፈለግ ሰው ወዲያው የሚተካ ቢሆን፤ አንዳንድ አገር…. ቅድም እንደተናገርከው ጋና እንደዚህ ሆኗል፡፡ እ… አሜሪካ ኬኔዲ በሞተ ጊዜ ምክትል ኘሬዚዳንቱ ወደዋሽንግተን ሲመለስ አውሮኘላን ላይ ቃለ-መሐላ ፈፀመና ኘሬዚዳንት ሆነ፡፡ እንደዚህ በቀጥታ ህጉ የሚከበርበት አገር ምንም ችግር የለም፡ ፡ እዚህ ህጉ እኮ እነሱ በፈለጉት መንገድ እንዲሄድ ነው የሚፈልጉት፡፡ እና አሁንም በህጉ ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ ይግባ ከተባለ፣ አሁን ያለው ምክትል ጠ/ሚኒስትር ይግባ ከተባለ እነሱ ያንን የጠ/ሚንስትርነቱን ቦታ እንዲይዝ ይፈልጉታል ወይ? ወይስ ደግሞ ሌላ ያንን ቦታ የሚፈልግ አለ? ሌላውም ቦታውን በሚፈልጉትና ይህ ሰው እዛ ቦታ ላይ እንዲሆን በማይፈልጉት መሃከል ፉክክር ይነሳል፡፡ ያ ፉክክር ነው እንግዲህ መደናበር ውስጥ የከተታቸው፡፡ ምን እናድርግ? ምን እንሁን? እንዴት እናድርገው? እንዴት እንስማማ? በሚሉና በረድ ብለው በሰከነ አይምሮ እስኪወስኑ ድረስ መጀመሪያው ላይ በጣም ተደናበሩ፡፡ ያ መደናበር ነው ያን ሁሉ ነገር ያመጣው የሚመስለኝ እኔ፡፡ ሰማያዊ፡-ምናልባት ይሄ “ሥልጣን ባህልና እና አገዛዝ” በሚል መጽሐፍዎ ላይ ያነሱት “ሥልጣንን እስሁንም ድረስ መግራት አልቻልንም-እንደኢትዮጵያውያን!” ብለው ነበር፡፡ እና ከዚያ ጋር የሚያያዝ ነፀብራቅ ይኖረው ይሆን? ኘሮፌሰር መስፍን፡- ሁልጊዜም አለ እሱ እኮ! እሱ ባህላችን ነው-አገዛዝን ሳንገራ አለን እስካሁን ድረስ፤ ታሪካችን ነው፡፡ እና….. ውስጣችን ነው እሱ! ሰማያዊ፡- ኢህአዴግ ግን አሁን በአብዮታዊ ይህ ቃለ መጠይቅ ሰኞ በ21/1/2ዐዐ5 ዓ.ም. በኘሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መኖሪያ አፓርትመንት ውስጥ በሚገኘው የግል-ቢሮአቸው የተካሄደ ሲሆን በአቶ መለስ ሞት ዙሪያ፣ ትተዋቸው ባለፏቸው መታሰቢያዎች(legacy)፣ እንዲሁም በመፃዒ የኢህአዴግ እና የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታዎች ላይ ያነጋገራቸው የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን የሆነው የ“ሰማያዊ” ሚድያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ነው፡፡ መልካም ንባብ! ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 3
 4. 4. ዴሞክራሲያዊ መስመር ሥልጣንን በማሸጋገር በገዥነት መቀጠል እችላለሁ ብሎ በይፋ የሚናገር ድርጅት ነው፡፡ አሁን ደግሞ ያሉት ነገሮች (ከመጋረጃ ጀርባ ያሉት እንደተጠበቁ ሆነው) እስካሁን ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር የተደረገ ያስመስላል፡፡ እና ምናልባት ይሄ ኢህአዴግን ልክ ያሰኘው ይሆን? ኘሮፌሰር መስፍን፡- አልገባኝም! ሰማያዊ፡- ማለት ብዙዎች ከአቶ መለስ በኋላ የሚመጣው ስርዓት ያልተደላደለ፣ ሰላማዊ የማይሆን፣ ብዙ የሥልጣን ሽኩቻ የሚኖርበት ሲሉ ተንብየውና ተንትነው ነበር፡፡ በአንፃሩ ግን የሆነው፡- ም/ጠ/ሚ የነበሩት አቶ ኃ/ ማርያም ደሳለኝ ናቸው በቦታው የተተኩት፡ ፡ እና ይሄ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በዚች አገር አለ ሊያስብል ይችላል? ኘሮፌሰር መስፍን፡- ገና ነን እኮ! አሁን ለሁሉም የተመቸ በመሆኑ የኃ/ማርያምን ጠቅላይ ሚኒስትርነት አፀደቁ፡፡ ነገር ግን የኃ/ማርያም አሠራር በሥልጣኑ መጠቀም ሲጀምር ከማን ጋር ይሰለፋል? ከነማን ጋር አይሰለፍም? ማንን ያስቀይማል? ማንን ይደግፋል? በየትኛው መስመር ይሄዳል? ገና ነው….. ገና አልተጀመረም፤ ይሄ ሁሉ ሆኗል! ደህና ተረጋግቷል! ሰላም ነው! ምን የሚባል ነገር የለም ለኔ፡፡ ገና ነው! ጊዜ ይፈልጋል ይሄ፡፡ ሰማያዊ፡- አቶ መለስ በጠ/ሚኒስትርነት ዘመናቸው ብቁ አመራር ነበራቸው! የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ በዓለም-አቀፍ መድረክም በአገር- አቀፍም አስማሚ ሰው ናቸው! ሁሉንም ከሞላ ጐደል አቻችለው ይሄዱ ነበረ ብለው የሚያምኑ አሉ፤ የለም እሳቸው ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የሚጥሱ በስልጣናቸው ብቻ ሲያስቡ የኖሩና ለአገር ደግሞ ብዙም ግድ የሌላቸው ናቸው! የሚሉም አሉ፡፡ በዚህ መሃል አሁን በተያዘው የኘሮፖጋንዳ ስራ ላይ አቶ መለስን እንደቅዱስ የሚስሉ ክስተቶች አሉ፡፡ የሁሉ ነገር ባለራዕይ፣ ሃሳብ አመንጪና የልማት ሁሉ አርበኛ እስከማለት የደረሱ አሉ፡ ፡ በተቃራኒው ደግሞ፡- የሰብዓዊ መብትን የደፈጠጡ፣ ብዙዎችን ያሰሩ፣ የኘሬስ ነፃነትን የተጋፉ፣ እንዳሻቸው ህግን በአንድ ዕለት ያወጡ ናቸው ብለው የሚኮንኗቸው አሉ፡፡ የርስዎ አስተያየት በዚህ ላይ ምንድነው? ኘሮፌሰር መስፍን፡- ይሄ እኮ ምን….. ለኔ ጥያቄው ባዶ ነው፡፡ ባዶ የሚሆንበት ምክንያት ምንድነው.... መለስን እየካቡ የሚናገሩት ሰዎች እነማን ናቸው? ሊክቡት የሚገባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ከሱ ጋራ የተሰለፉ ሰዎች ናቸው፡፡ ከዛ ሌላ ከዛ ውጪ ሊወጡ አይችሉም፡፡ ስለዚህ እነሱ ያንን የተናገሩት ለነሱ እውነት ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ፡- የለም መለስ ስልጣንን ጨብጦ ለራሱ ብቻ ይዞ ሲጠቀምበት የነበረ ጉልበተኛ ነው፤ አምባገነን ነው የሚሉ ሰዎች የፖለቲካ ቡድኑ የስልጣን ተካፋይ እንሁን ብለው የሞከሩ ያቃታቸው ሰዎች ናቸው፡፡ የነሱም ልክ ነው፡፡ በነሱ በኩል ሆነህ ስታየው፡፡ ስለዚህ ይሄንን ልታወዳድረው አትችልም፡፡ ይሄም ከሱ በኩል ሆነህ ስታየው ልክ ነው፤ ያኛውም ከሱ በኩል ሆነህ ስታየው ልክ ነው፡፡ እንደው በኢትዮጵያዊ ዓይን ብቻ ከፖለቲካዊ የስልጣን ትግሉ ወጣ ብለህ ልመልከተው ያልከው እንደሆነ ግን፤ መለስ የአርቆ ማስተዋል ችሎታ አለው ብዬ እኔ አልገምትም፡፡ ይሄንን አርቆ ማየት አለመቻሉን እኮ አሟሟቱ ራሱ ይገልፀዋል፡፡ በደንብ አድርጐ ይገልፀዋል- ለእኔ፡፡ አሟሟቱ፣ የፓርቲው መርበድበድ፣ መረበሽ ይሄ ሁሉ ቀደም ብሎ ያልታየ ያልታሰበበት ነገር መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም መለስ…. እ…. ኖረ ለማለት እንኳን እኔ በእውነት አልችልም፡፡ በፍርሃት ኖሮ….. ከቤቱ ወጥቶ አውሮኘላን ማረፊያ እስኪደርስ ድረስ ስንት ወታደር በየመንገዱ ላይ ቆሞ በዚያ ዓይነት ፍርሃትና ጭንቀት ውስጥ የኖረ ሰው ነው፡፡ እ…. ምናልባት ለራሱ ትንሽ ነፃነት ቢሰጥና ያንን ነፃነትም ለሌሎች እንደዚሁ ቢያስተጋባ ምንአልባት ልንገራችሁ ከማለት ብቻ ወጥቶ የማዳመጥም (የማይፈልገውንም ነገር ቢሆን የማዳመጥ) ችሎታ ቢያዳብር ኖሮ በብዙ ነገር ችሎታውን ይስልለት ነበር፡፡ እ…. ለኢትዮጵያም ህዝብ…. እንደው ከልብ እ…..እንደው ከሱ ኋላ መቆም የሚችልበትን ሁኔታ መፍጠር አያቅተውም ነበር ይመስለኛል፡፡ ግን ሁሉንም እንደጠላት አድርጐ በመገመት ሊያደርግ የሚችለውን ሊያስማማው የሚችለውን ኢትዮጵያንም ሊለውጣት የሚችለውን የኢትዮጵያን ህዝብም ሊለውጥ የሚችለውን ነገር ሁሉ አደረገ- ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለማለት አልችልም እኔ፡፡ እ…..እሱ የሚፈልገውን ነገር፣ እሱ በሚፈልገው መንገድ፣ እሱ ባለው ጊዜ አድርጓል፡፡ ያ ስንት ሰው አስከፍቷል? ስንት ሰውስ ጐድቷል? ስንት ሰው አስደስቷል? ይሄ እንግዲህ ታሪክ-ፀሐፊዎች ወደፊት የሚናገሩት ነገር ነው፡፡ ሰማያዊ፡-ስለዚህ ምናልባት ዴሞክራሲያዊና አሳታፊ አለመሆናቸው ኢትዮጵያዊነታቸው ላይ የጥያቄ ምልክት ያሳርፍ ይሆን? ኘሮፌሰርመስፍን፡- እኔ ኢትዮጵያዊነቱ ላይ የጥያቄ ምልክት አላስቀምጥም፡፡ ኢትዮጵያዊነቱ ሌላ ነገር ነው፡፡ በተፈጥሮው ያገኘው ነገር ነው-ማንም ሊወስደው አይችልም፤ እሱ ራሱ እኔ አይደለሁም ካላለ በቀር እንደኢሳይያስ አፈወርቂ! ይሄ ሲወለድ ያገኘው ነው፡፡ ማንም ኢትዮጵያዊ አይደለህም ሊለው አይችልም፡፡ ማንም ሌላውን ሰው አንተ ከእኔ ያነስክ ኢትዮጵያዊ ነህ በኢትዮጵያዊነት ብሎ ማለት የሚችል የለም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሚዛን በእጁ የጨበጠ አንድም ሰው የለም፡፡ ሁላችንም እኩል ነን፡፡ ሁላችንም እንደታየን፣ እንደተሰማን፣ እንዳስተዳደጋችን፣ እንደትምህርታችን” ኢትዮጵያን ሀገራችን ኢትዮጵያውያንን ወገናችን ብለን እንሰየማለን፡ ፡ ነገር ግን አንተ ያነስክ ኢትዮጵያዊ ነህ፤ አንተ የተሻልክ ኢትዮጵያዊ ነህ ማለት የሚቻልበት መንገድ ምንም የለም፡፡ ስለዚህም፡ - መለስ ከማናችንም የማያንስ ከማናችንም የማይበልጥ ነው- በኢትዮጵያዊነቱ፡፡ ያንን እሱ ራሱ እንደፈተለው ነው የሚሸመነው፡፡ ሰማያዊ፡- ከዚህ ጋር ተያይዞ አንዳንዶች የሚያነሱት፡- ከ97 ወዲህ ምርጫውን ተከትሎ ነው ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ህዝብ የልብ ትርታ እየገመተ ከተቃዋሚ ጐራውም ቢሆን አጀንዳዎችን ኮርጆ የባንዲራ ቀን እስከማክበር፣ ብሔር-ብሔረሰቦችን በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር እስከማቀፍና ብሔራዊ አጀንዳ የሚባሉ ነጥቦችን ማንሳት ያጐላው ብለው የሚያዩ አሉ፡፡ እና በዚህ ረገድ አቶ መለስም በታሪክ ትተው ለማለፍ የፈለጉት ነገር ኢትዮጵያዊነትን የሚወክል ሲሆን ይህን ሃሳባቸውን ሳያሳኩት በአጭር ባይቀጩ ኖሮ ብዙ ህልም ነበራቸው የሚሉ ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 4 አሁን መለስ የለም! መለስ ከሞተ በኋላ እንዲህ ነው እንዲህ ነው ብዬ እሱን ለመውቀስ አልፈልግም፡፡ እኔ ከወደቀ እና ከሞተ ጋር መታገል አልወድም፡፡ ከመንግሥቱ ኃ/ማርያምም ጋር ከኃይለ ሥላሴም ጋራ! አንድ ጊዜ ከሄዱ በኋላ ከነሱ ጋር መታገል አያሻም፡፡ መታገል ኃይል ካለው፤ ሊያናግርህ ሊያነጋግርህ ከሚችል ኃይል ጋር ነው፡፡ ከሌለ ኃይል ጋራ ስለሱ ስላለፈው ነገር ማውራቱ ምንም ጥቅም የለውም፡፡
 5. 5. አሉ፡፡ ከክልላዊ ማዕቀፍ ይልቅ ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ስሜትን የሚያጐሉ እርምጃዎችን እየወሰዱ እንደነበርም በቁጭት ያነሳሉ፡ ፡ በህይወት ኖረው ቢቀጥሉ ኖሮ የብሔር ፖለቲካውንና በዚሁ ላይ የቆመውን አወቃቀር እያሻሻሉት በሂደት እየቀየሩት ይሄዱ ነበር ብለው የሚያስቡ አሉ፡፡ እዚህ ላይስ የርስዎ አስተያየት? ኘሮፌሰር መስፍን፡- ምን እላለሁ በዚህ ላይ? ምን አውቃለሁ? እነዛ የሚያውቁ ሰዎች የሚያውቁትን ነገር ሲነግሩን ምናልባት እንነጋገር ይሆናል፡፡ እኔ ምንም አላውቅም፤ ስለዚህ የሰማሁት ነገር የለም፡፡ እኔ መለስ በሚያደርጋቸው ነገሮች በሚናገራቸው ነገሮች ባለፉት 21 ዓመታት ውስጥ ብዙ ብያለሁ፣ ፅፌያለሁ፣ ተናግሬያለው፡፡ እና አሁን መለስ የለም! መለስ ከሞተ በኋላ እንዲህ ነው እንዲህ ነው ብዬ እሱን ለመውቀስ አልፈልግም፡፡ እኔ ከወደቀ እና ከሞተ ጋር መታገል አልወድም፡፡ ከመንግሥቱ ኃ/ ማርያምም ጋር ከኃይለ ሥላሴም ጋራ! አንድ ጊዜ ከሄዱ በኋላ ከነሱ ጋር መታገል አያሻም፡፡ መታገል ኃይል ካለው፤ ሊያናግርህ ሊያነጋግርህ ከሚችል ኃይል ጋር ነው፡፡ ከሌለ ኃይል ጋራ ስለሱ ስላለፈው ነገር ማውራቱ ምንም ጥቅም የለውም፡፡ ተናግሬዋለሁ ደግሞ! ያልተናገርኩት ነገር የለም፡፡ መለስ ባደረጋቸው ነገሮች ሁሉ፤ በተናገራቸው ነገሮች ሁሉ እሱ ባለበት ጊዜ ተናግሬዋለሁ፡ ፡ እና አሁን ትርፍ ነው፡፡ እንደ ስብሐት ነጋ አልሆንም! ማለት…. ማንትሴ ሞተ ማንትሴ ሞተ መለስም ሞተ! የሚባለው ነገር…. እኔ እንደዛ ዓይነት ድረስ አላወርደውም፡፡ እ…. ግን….የለም አሁን፡፡ በሌለበት ይሄን አደረገ- ይሄን አደረገ- ይሄን አደረገ ብለን መነጋገሩ ለኔ ለህሊናዬ ምንም ዋጋ የለውም፡፡ ሰማያዊ፡-ከአቶ መለስ ሞት በኋላስ የኢህአዴግና የኢትዮጵያ ዕጣ - ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? ኘሮፌሰር መስፍን፡- ይሄ….. በምን?…. እኔ….አላውቀውም በውነቱ፤ ጠንቋይ አይደለሁም! ነገሩ….. ሰዎች ሁላችንም በጐ መንፈስ ካደረብን ብዙ ነገር ካለፉት 21 ዓመታት ልንማራቸው የምንችላቸው ነገሮች አሉ፡፡ የመለስ ሞት ራሱ ያስተምረናል- ሁላችንንም! የኢህአዴግም ሌሎቹንም ያሉትን ባለሥልጣኖች ይሄ ሊያስተምራቸው ይገባል፡ ፡ የአቡነ ጳውሎስ አለመኖር ሊያስተምር ይገባል- ሌሎቹን ጳጳሳት፤ ሌሉቹን መንፈሳዊ መሪዎች! እና እንዲህ ነው፡፡ ዕድሜያችን በጉልበትም እንኳን በሃይለኞችም እንኳን ባይቀጭ፤ ኃይለኞችም ብንሆን ጉልበተኞችም ብንሆን፤ ከላይ ደሞ የሚመጣ ያንኑ ህይወት የሚቀጨው ሞት አለ-ሁልጊዜ፡፡ በተፈጥሯችን ሰው በመሆናችን ያለ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ በጐ መንፈስ በላያችን እንዲያድር ብናደርግ፣ መርዝ ለመንዛት ባንጥር! ምሳሌ፡- የአቶ ኃ/ ማርያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ተመልክቶ ስብሐት ነጋ ይሄ ሆነ ብለን ያደረግነው እና የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ወንበር ከኦርቶዶክስ እና ከአማራ እንዲወጣ ለማድረግ ያደረግነው ነው አለ፡፡ ይሄ አባባል መርዝ ነው፡፡ መርዝነቱ እንዴት ነው…. ኃ/ ማርያም ደሳለኝ ማነው ብለው ለማያውቁ ሰዎች ኃ/ማርያም ደሳለኝ አማራ አይደለም፤ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን አይደለም ብሎ ለማወጅ ነው ስብሐት ነጋ የፈለገው፡፡ እነዚህን ሁለት አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮች ለማወጅ ደግሞ አማራን እዛ ውስጥ አስገብቶ ይጨፈልቀዋል፡፡ ያንን ጥላቻውን ያመጣል፡፡ ይሄ መርዝ ነው- ሁለቱም! ኃ/ ማርያም ኦርቶዶክስ ሆነ አልሆነ፤ አማራ ሆነ አልሆነ እኔ እንደሚመስለኝ ለኔ ጉዳዬ አይደለም፡፡ በፍፁም! ከሚዛን ውስጥ የሚገባ አይደለም ሁለቱም፡፡ ሚዛን ውስጥ የሚገባው እንዴት ነው? ለምሳሌ፡- ሃይማኖቱ ሚዛን ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ በኃ/ማርያም ደሳለኝ በራሱ አንደበት ያነበብኩት እኔ እውነት ከሆነ፣ እውነት ብሎት እንደሆነ እውነት ተናግሮት እንደሆነ ‘ለእናቴ እፀልያለሁ አልዳነችም’ የሚል ነገር አንብቤያለሁ ይመስለኛል፡፡ እንግዲህ ይሄ በጣም በጣም አስደንጋጭ ነው! እንኳን ለአንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአንድ መደበኛ ፖለቲከኛም እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ እንደዚህ ዓይነት አስተያየት አደገኛ ነው፡፡ እናቱን፣ ኃ/ማርያም ብለው ስም ያወጡለትን ሰው ‘አልዳኑም…. እኔ ድኛለሁ!’ …. በዛ ሂሳብ 99.9 የኢትዮጵያ ህዝብ አልዳነም- ከኃ/ማርያም ደሳለኝ ጋራ፡፡ ያ አደገኛ ነው፡፡ ይሄ ዳነ አልዳነም አደገኛ ነው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ስም በማይጠራበት ቦታ ላይ እግዚአብሔርን የሚያምን ሰው፣ ፈሪሃ-እግዚአብሔር ያለው ሰው እዛ መቀመጡ ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 5 ወደ ገጽ 18 ዞሯል
 6. 6. አይዞህ አትደንግጥ! ልብህ አይሸበር! እንዲህም አትሸማቀቅ! ግራ-ቀኝህን በጥርጣሬና በፍራቻ መቃኘትም አያሻህ! እረ አትገለማመጥ! እንዲህ መርበድበድ ምንድነው? በቅድሚያ ጽሁፉን አንብበህ ጨርስና ከዚያ በኋላ የራስህን/የራስሽን አቋም ትወስዳለህ፡፡ ጽሁፉን በሙሉ ሳታነብ ግን ቸኩለህ አትደምድም፡፡ ከስህተት ላይ ትወድቃለህና! የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳልና! የብዙዎቻችን ችግርስ ምን ሆነና?! ይኸው በወሬ እና በስሚ- ስሚ እየተፈታን ብሎም እየተነዳን አይደለ እንዴ በዘመናችን ሁሉ የተቀለደብን?! ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው! እንዲል ተረቱ፡ ፡ ስለዚህ “አንድን መጽሐፍ በሽፋኑ ብቻ አትፍረደው!” /Never Judge a book by its cover/ እንደሚባለው የፈረንጆቹ አባባል በርዕሱ ብቻ ተመርተህ የጽሑፉን ጭብጥ እንዳገኘኸው ሆኖ አይሰማህ፡፡ ርዕሱ ቁንጽል ሀይለ-ቃል ብቻ ነው፡፡ ቁም- ነገሩን በዝርዝሩ ውስጥ ነው የምታገኘው፡ ፡ “ሰይጣኑ ያለው በዝርዝሮቹ ውስጥ ነው” /The Devil is in the details/ ይላሉ ፈረንጆች ስለአንድ ጉዳይ አብጠርጥሮ ለማወቅ፤ ነገሩን በዝርዝር እና በጥሞና መመርመር እንደሚያስፈልግ ሲያስገነዝቡ፡ ፡ አለበለዚያ የአገራችን ቀደምት ሊቃውንት አዋቂ-መሳይ አላዋቂን እንደሚሰይሙት “ጥራዝ-ነጠቅ” መሆን ይከተላል፡፡ በጥራዝ- ነጠቅነት ደግሞ መፍትሄ አይገኝም፡ ፡ እንኳንና መፍትሄ ጉዳዩን በቅጡ መረዳትም አይኖርም፡፡ በመሆኑም ርዕስ አንጠልጥሎ ጭብጥ ጥሎ፤ የሚደረግ ውይይትና ንግግር አሊያም ገረፍ-ገረፍ ንባብ የባሰ መደናበር እና ግራ መጋባትን በማስከተል የጉዳዩን ውል ያሳጣናል፡፡ በዚህም ማናችንም አንጠቀምም፡፡ ለማንኛውም ወደ ርዕሰ-ጉዳዩ በቀጥታ ልሂድና ለማለት የፈለግኩትን ልበል፡፡ አትነሳም ወይ?! ከእንቅልፍ ነው? ከሞት ነው? ከሞት ከበረታ ድንዛዜ ነው? ፎቶ ነው? ራጂ ነው? ክርስትና ነው? …. በክፉ ነው የምትነሳው? በደግ ነው የምትነሳው? በትንሳዔ-ሙታን ነው የምትነሳው? በምንድነው የምትነሳው? ለምንድነው የምትነሳው? ወዴት ነው የምትነሳው? መቼ ነው የምትነሳው? እንዴትስ ነው የምትነሳው? መቼም ኢትዮጵያውያን በባህላችን ብልፅግና የተነሳ አንድ ትልቅ ሰው ወይም አረጋዊ ከውጭ መጥቶ ወደቤት ውስጥ ሲገባ ከተቀመጥንበት ብድግ ብለን ተነስተን “ኖር! ኖር!” እንላለን፡፡ ምላሹም “በእግዜር!” አሊያም “እረ በልጆቻችን!” ይሆናል፡፡ ታዲያ አንተ ወንድሜስ ለእንዲህ ዓይነቱ የትልቅ ሰው አክብሮት የሚገባውን መነሳት ነው የምትነሳው? ማለቴ-ክብር ለሚገባው ክብርን ለመስጠት፡፡ አሊያስ ከወደቅህበት ረግረግ እና ረመጥ ውስጥ ነው የምትነሳው? ወይ ኪስህ ወይ ቀኑ ጐደሎብህ፣ ወይ ርቦህ አሊያም ታመህ፣ ወይ ደክሞህ ፣ ወይ መሄጃ አጥተህ፣ ወይ ጭንቀትህን ማራገፊያ ወይ ጊዜህን ማሳለፊያ አጥተህ፣ ወይ ድህነትን አሊያም ጭቅጭቅን ሸሽተህ፣ ወይ ሰክረህ ወይ አብደህ ከየአውራ- ጐዳናዎቹ ጥጋጥግ እስከ ጫት ቤቶች ምንጣፍ እንዲሁም ከየካቲካላ ቤቶች ደጃፍ እስከምናምንቴ ‘አልጋ-ቤት’ ተብዬዎች ፍራሽ የተረፈረፍከው ወጣት አወዳደቅህ ምንኛ አሳዛኝ እና ታላቅ ኖሯል?! ኦ ወንድሜ …. ከዚህ የበለጠ ውድቀትስ ምን አለ; በቁም ከመሞት የበለጠ ሞትስ በወዴት አለ; አደራ-አልሞትኩም ብለህ ራስህን እንዳታታልል፡፡ ሰው ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር ዓላማ የተለየ ዕለት ሞቷልና! የእግዚአብሔር ዓላማ ላንተ ደግሞ መልካምና ያማረ እንጂ የተዋረደና የረከሰ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ አንተ፣ እኔ፣ እሷ፣ ሁላችን በጥሩ ጤንነት፣ በረከት፣ ነፃነት እና ክብረት እየተዋደድን ብሎም እየተሳሰብን በፍቅር እንድንኖር እንጂ በአምባገነኖች እና በሱሶች ተረግጠን ከእግራቸው መረገጫ በታች አይወድቁ አወዳደቅ ወድቀን በግፍ እንድንገዛ አይደለም፡ ፡ ከቶም የእግዜአብሔር ዓላማ ይኸ ሆኖ አያውቅም! በአምሳሉ ለፈጠረን ውድ ልጆቹ እግዚአብሔር ይኼን አይመኝልንም፡፡ ይህ የጨለማው የዚህ ምድር ገዢ የክፉው ሀሳብ ነው፡፡ ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ሊያወጣህ ደግሞ እነሆ የብርሃናት አምላክ የሆነው እርሱ በደጅህ ቆሞ ይጠራሃል፡፡ እውነት ያናግርሃል፤ ህይወት ኑርብኝ! እያለ ይጋብዝሃል፤ መንገድ ና! ተጓዝብኝ! ይልሃል፡፡ አዎ-አምላክህ ይጠራሃል! ፈጠን ብለህ አቤት! በለው፡ ፡ የልብህን በር ወለል አርገህ ክፈትለት፡ ፡ “ተነስተህ ሂድ! እምነትህ አድኖሃል” እንዲልህ” ሽባነትህን እንዲፈውሰው ከወደቅህበት እንዲያነሣህ ፈጥነህ ታዘዝ፡፡ አንቺስ እህቴ፡- ከወደቀው ጋር አብረሽ የምትወድቂ ውዳቂ የሆንሽው ከቶ ስለምንድነው?የወደቀውንእንደማንሳትአንቺ የቆምሽውን ሲጥልሽ መንፈስሽ የማይቆጣው ህሊናሽ የማይቆጠቁጠው በምን የተነሳ ነው? ስጋሽ እህል በራበው ቁጥር ከህሊናሽ እምነትሽን ቆርሰሽ እያበላሽው እስከመቼ ከራስሽ ጋር ተጣልተሽ ትዘልቂያለሽ? አምላክሽስ ምን ይላል? ከመብልስ ነብስ እጅጉን አይበልጥምን? ከልብስስ ሰውነት አይሻልምን? ታዲያ አስቀድመሽ ጽድቁንና መንግሥቱን አለመሻትሽ ስለምንድነው? ሌላው ሁሉ እንደሚጨመርልሽ ዘንግተሽው ነው? ለልብስና ለመብል ስትይስ እስከመቼ ነፍስሽንና ሰውነትሽን አራቁተሽ የአምላክሽን ትዕዛዝ ተላልፈሽ ትኖሪያለሽ? እኒያ ደጋግ እናቶችሽ ያወረሱሽ የመንፈስ ቅርስ ይሄ ነውን; እምነትን መብላትስ የመልካም ሴት ምግባር ነውን? ለዚች አጭር ምድራዊ ህይወትስ ዘላለማዊቷን ነፍስ መቨጥ ይገባልን? ለሚያልፍ ችግር ብለሽ ንፁህ ማንነትሽን ማጉደፍስ ተገቢ ነው? የሰውነት ክብርን ወደ ሸቀጥነት ተራ አውርዶ ለገበያ ማቅረብና ነውርን መነገድስ ለህሊና እረፍት ይሰጣል? በሰው ውርደትና ስቃይ ሰይጣናዊ እርካታ ለማግኘት ሲባል የአምላክ ፍጡርን በገንዘብ የሚሸጥ የሚለወጥ ቁስ ደረጃ አሽቀንጥሮ ቁልቁለቱ ላይ መጣልስ ከሰብዓዊነት እና ከወንድማዊነት ይጠበቃል? የፈጠረን አምላክ በፈቀደልን መንገድ ላይ ትዕዛዙን አክብረን በጥንቃቄ ብንጓዝ ኖሮስ ከቶ ይቸግረን ነበር? ፈጣሪያችን የሰጠንንስ የሚከለክለን ማነው? “ለምኑ ይሰጣችሁማል! ፈልጉ ታገኙማላችሁ! መዝጊያን አንኳኩ ይከፈትላችሁማል፡፡ የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና! የሚፈልገውም ያገኛል! መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል፡ ፡ ወይስ ከእናንተ ልጁ እንጀራ ቢለምነው ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን አትነሳም ወይ?! አናንያ ሶሪ ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 6
 7. 7. ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው! ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና፡፡” ታዲያ ዛሬ እኛ፡- ሰዎች እንዲያደርጉልን የምንወደውን ነው ለሰዎች እያደረግን ያለነው? ለሰዎች ቀና ቀናውን እናስባለን? እንደግፋቸዋለን? ወይስ እንጠልፋቸዋለን? እንረማመድባቸዋለን ወይስ እናራምዳቸዋለን? በሰው ስቃይ እናዝናለን ወይስ ሀሴት እናደርጋለን? እዚህ ሁሉ የሞራል አዘቅት ውስጥ ሆነንስ የምንለምነውን መቀበል፣ የምንፈልገውን ማግኘት፣ የምናንኳኳውን ማስከፈት ከቶ ይቻለናልን? ልባችን ሳይለወጥ፣ ከአምላካችን ጋር በንስሃ ሳንታረቅ በያዝነው የመሸነጋገል እና የማታለል ብሎም እውነታውን የመካድ ጠማማ መንገድ ከቀጠልን ጉዟችን ሁሉ መጨረሻው ተያይዞ የመጥፋት ገደል ነው፡ ፡ እርስ በርስ ካልተዋደድን፣ ካልተዛዘንን፣ ካልተረዳዳን በምን ተዓምር ኑሯችን ሰላምና ፍቅር ይኖረዋል? በምን ተዓምርስ በሃጢያት ድካም ከወደቅንበት ትቢያ ላይ እንነሳለን? ‘እኔ ምን ጐደለብኝና? ምንስ አገባኝ? ከራስ በላይ ንፋስ!’ እያልክ እንደሰነፍ ከንቱ ሰው አትዘናጋ፡፡ አንተ ብቻህን የምትኖር ደሴት አይደለህም፡፡ ወንድም፣እህት፣ ጓደኛ፣ ጐረቤት፣ ሚስት፣ ልጅ፣ ወገን፣ ዘመድ- አዝማድ፣ የሙያ አጋር፣ የሥራ ባልደረባ ያለህ፣ የፍጥረት አቻህ የሆኑ የሰው ልጆች በሞላ የምትኖርበት ምድርን አብረው የሚጋሩህ ማህበራዊ-ፍጡር ነህ፡፡ ብቻህን ልትደሰት አትችልም፤ ስታዝንም ስትደሰትም ሰው ትሻለህ! “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለምና” ብሏል መፅሐፉም፡ ፡ በመሆኑም ከቤተሰብ እስከ ማህበረሰብ ድረስ በተለያዩ ውስብስብ የማህበራዊ ድርና- ማጐች (social fabric) የተሳሰርን ስንሆን፣ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአንዱ ማጣት ማዘንና መከፋት ሌሎቻችንን የሚነካን ፍጥረቶች ነን፡ ፡ አካባቢያችን ተተራምሶ ቤታችን የሰላም ሰገነት ሊሆን አይችልም፡፡ ስለሆነም፡- ከቤት እስከ ጐረቤት፣ ከሰፈር እስከሃገር፣ ከሃገር እስከ አህጉር፣ ከአህጉር እስከዓለም፣ ድረስ የማያገባን ጉዳይ የለም፡፡ ይመለከተናል! የወንድምህ ጐዳና ላይ መውደቅ የአንተ ቤተሰባዊነት እና ኢትዮጵያዊነት መዋረድ ነው! የእህትህ በየባዕድ አገራቱ ጐዳና ላይ ለገበያ መቅረብ የቤተሰብህ እና የአገርህ አንገት መደፋት ነው! የአገርህ መራብ እና መረገጥ እንዲሁም እጅግ ኋላ-መቅረት እግርህ በረገጠበት የዓለሙ ዳርቻዎች ሁሉ መታወቂያህ እና ማፈሪያህ ነው! ታዲያ አንተ ወንድሜ ራስህን እንደሰጐን አሸዋ ውስጥ ቀብረህ የእውነታውን ዓለም እያየህ እንዳላየህ ሆነህ የምትኖረው እስከመቼ ነው? እውነታው እንደሆነ አፍጥጦ አፍንጫህ ድረስ መምጣቱን አይተው! በዛች በተሸጐጥክባት ጠባብ ቢሮ ውስጥ ተወስነህ የሚከናወኑ ደባዎችን እየተመለከትህ አንደበትህን ለጉመህ፣ ህሊናህን ጠፍረህ፣ ለእንጀራህ ስትል ብቻ ዝም ማለትህ በስተመጨረሻ ላንተስ ይበጅ ይመስልሃል? የሙያ ስነ ምግባርህ የሚያዝህስ ከመቃብር የሚያስፈራ ዝምታን ነውን? እረ እልፍ በል! ያንተ ፍፃሜ ይኼ ብቻ አይደለም፡፡ ተቀጥሮ ደሞዝ ከመብላት ባለፈ በሙያህ ለማህበረሰብህ የምታበረክተው ውድ ስጦታም አለ፡፡ ወንድሜ፡- በስጋ ለመኖር ስትል በነፍስህ አትሙት! ነፍስህ ደግሞ እውነትን ማወጅ ትወዳለች! ነፃነትን ትጠማለች! ፍትህን ትናፍቃለች! ፈጠራን ታፈልቃለች! አዲስ ነገርን ትሻለች! ታዲያ አንተ ወንድሜ፡- ስለምን ነፍስህን ትጨቁናታለህ? እስከ መቼስ ነፍስህ እሆድ-ዕቃህ ውስጥ እንደወደቀች ትቀራለች? አትነሳም ወይ?!... ነፍስህ! አትነሳም ወይ?!… አንተ! ኑሮ እጅ-እጅ ያለህ እና ያንገፈገፈህ አንተ ሥራ-አጥ ወጣትስ እስከመቼ የምስኪኗን እናትህን የመሃረብ ቋጠሮ የምታስፈለቅቅ ብኩን የወጣት-ተጧሪ ትሆናለህ? ይሄ ቀንስ መቼ ነው የሚያልፈው? 4ኪሎና ጊዮርጊስ እየተመላለስክ በየሥራ-ማስታወቂያው ግድግዳ ላይ እንጀራህን ስትፈልግ የምትንከራተተው እውነት ላንተ ሥራ ጠፍቶ ነው? የተማርክበት የትምህርት ፖሊሲ የመጨረሻ ግቡ አንተን ሥራ-ፈላጊ ተንከራታች ማድረግ ነውን? ወትሮውንስ ይህ ከሆነ ዓላማው ጊዜህን ለምን በትምህርት ቤት አሳለፍክ? አፍላውን የወጣትነት ዕድሜህን በነፃነት ለሥራ እንድትጠቀምበት ያልቻልከውስ ከምን የተነሳ ነው? የዴሞክራሲ፣ የነጻነት፣ የእኩልነት፣ የብልጽግና፣ እንደልብ የመናገር፣ ሀሳብን የመግለፅ፣ ሠርቶ ጥሮ-ግሮ የማደግ ተስፋን በየዕለቱ እየመገቡህ እና እነዚህን ሁሉ እንደሚሰጡህ እየማሉና እየተገዘቱ ቃል የገቡልህ መሪዎችህ አንዳቸውን እንኳ በቅጡ ሳይለግሱህ ወሽመጥህን ቆርጠው እነርሱ በተደላደለ መንበራቸው ላይ ከተቀመጡ ይኸው 21 ዓመት ሆናቸው፡፡ አንተስ? አንተና አንቺ የ21 ዓመት ወጣት የሆናችሁት ብላቴኖችስ? በዚህ ዕድሜያችሁ ምን አላችሁ? ምን ጥሪት ቋጥራችኋል? ሥራ-አለሽ? ገቢ አለህ? ኑሮህ/ሽ ዋስትና ያለው ዘላቂ ነው? ወይንስ እንደቁማር የዕድል ኑሮ ነው? ‘ ባገኝ በልቼ ባጣ ተደስቼ’ የሚሉት ዓይነት ይሆን ህይወትህ? የአየር-ባየር ኑሮ የሚያዋጣው ታዲያ እስከመቼ ነው? አንተ እና አንቺ ተመልካች፤ ሌሎች ኗሪ የሆናችሁት እረ ስለምንድነው? አይበቃህም የግፍ አገዛዝ? አይበቃሽም የግፍ አገዛዝ? አልተንገሸገሻችሁም?የጉልቤ- አስተዳደር አላስመረራችሁም? አላሳደዳችሁም? አላሰደዳችሁም? በኢኮኖሚ-የዘር-ማጥፋት እና በኢኮኖሚ- አፓርታይድ እንደቅጠል አላረገፋችሁም? ወላጆች፡- የልጆቻችሁን የፍላጐት ዓይኖች በመሸሽ አልተሳቀቃችሁም? ልጆችስ፡ - የወላጆቻችሁን ከቀድሞው የክብር ደረጃ መዋረድ እና መጎሳቆል ላለማየት ቤቱ አላስጠላችሁም? የጐረቤቱ ማባሪያ-የሌለው ጭቅጭቅና አለመተማመን ነብሳችሁን አላሰቀቃትም? ንገሩኝ እስቲ እናንት የ21 ዓመት ወጣቶች? እስቲ ሳትፈሩ የልባችሁን አውጉኝ! የልጅነት ህልማችሁን በእውን እየኖራችሁት ነው? የልጅነት ህልማችሁንስ ማን ሰረቀው? ራዕያችሁን ማን ሰለበው? ትልቅ እንዳትመኙ በትናንሽ ‘ሥራዎች’ የጠመዳችሁ ማነው? እናንተስ ቻይና ሄዶ መማር፣ ዘመናዊ መኪና መንዳት፣ በምቹ ቤት ውስጥ መኖር፣ በውጭ ንግድ መሠማራት፣ አስመጭና ላኪ መሆን፣ በጥሩ አለም-አቀፍና አገር-አቀፍ መሥሪያ-ቤቶች ውስጥ በወፍራም ደሞዝ መቀጠር፣ ኑሮን ማደላደል፣ መልካም ምግብ መመገብ፣ ያማረ መልበስ፣ ከከተማ ወጣ ብሎ መዝናናት፣የንግድ ድርጅት ማቋቋም፣ በነፃነት መመራመር፣ ትዳር መያዝ፣ ልጆች ማፍራት፣ ጥሪት መቋጠር አይወድላችሁም? እናንተ የእንጀራ ልጆች ናችሁ? ለዚህ ሁሉ ክብርና ማዕረግስ ያልተገባችሁ የሰው-መናኛ የምርጦች- ትራፊ ናችሁ? እናንተ ለለቅሶ፣ለድጋፍ ሰልፍ፣ ለጦር-ግንባር አሊያም ለኮብልስቶን ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 7 ኢህአዴግ ሆይ፡- ለራስህ ስትል ጣፍጥ አሊያ ድንጋይ ነው ብለን ወደደጅ አውጥተን እንጥልሃለን! ወደ ገጽ 24 ዞሯል
 8. 8. የሰው ልጅ በጊዜያቶች መቀያየር ያመጣውን የዲፕሎማሲ ዘመን ከማግኘቱ በፊት ያለፈበት የእንስሳዊ ባህሪ ነበረው ይህም የሰው ልጅ የመጀመሪያው ማህበራዊ አኗኗር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ያለውን ጊዜ ያጠቃልላል የሰው ልጅ ማህበራዊ ህይወት ጀምሮበታል የሚባለው ጊዜ አደን እያደኑ መብላት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ነው አብዛኛዎቹ ሣይንቲስቶች ሰዎች ይሏቸዋል አንዳንድ ሣይንቲስቶች ግን ሰው ነበሩ ለማለት ያዳግታል ይላሉ ይህ የሰው ልጅ ፍራፍሬ ለቅሞ ከመብላት ወደ አደን የተሸጋገረበት ጊዜ ነበር አደን ለብቻ አስቸጋሪ የሚፈለገውን ውጤት ለብቻ ሆኖ ከማግኘት አንፃር አዳጋች ከመሆኑም በላይ ሊያጠቃ የመጣን አውሬ ለሁለት ለሶስት ሆኖ መከላለከል ተመራጭ ስለነበር መተጋገዝ የተጀመረው በዚህ ጊዜ ነው እንደሚታወቀው ቀደም ባለው ሂወታቸው ፍራፍሬ ለቅሞ መብላት የቡድን ህብረትን የማይጠይቅ እንዲሁም ከአውሬ ራስን ለመከላከል በአራት እግር ይጠቀሙ ስለነበር ማለትም ሁለት እጃቸውንና ሁለት እግራቸውን ሮጠው ዛፍ ላይ በመውጣት ያመልጡ ነበር ከዚህ ሁሉ ጊዜያት መቀያየር በኃላ እንግዲህ እነዚህ አዳኝ ሰዎች የተፈጠሩት ከአደን መልስም የታደነውን የአውሬ ስጋ ቀስ በቀስ እያበሠሉ መመገብ ጀመሩ ይህ ክስተት የሰው ልጅ እሣት ከፈጠረበት ጊዜ ጋር የሚያያዝ ነው፡ ፡ ይህ ቀን ቀን ምግብ ለማብሰልና ፀሀይ ስትጠልቅ ደግሞ የብርድ ቆፈን እጅና እግርን ሲቆላልፍ እራስን ከብርድና ከአውሬ ለመከላለከል የሚከቡት እሳት የመገናኘታቸውን አንድ ላይ የመተሣሠራቸውን ባህል አሠፋው ይህ ልማድ እያደገ ሄዶ ቤተሠብ እስከመመስረት ማህበረሰብ ሠፈር እያለ ሀገር የሚለው ደረጃ ላይ ደረሰ የሰው ልጅ በዚያን ጊዜ እሣት ባይኖር ኖሮ እንደ አንዳንድ ሳይንቲስቶች አገላለፅ አሁን የሰው ዘር ላይገኝ የሚችልበት እድል ሊኖር ይችል ነበር ኢትዮጵያዊ እሣት!! ታዲያ ሀገራችን በአሁን ወቅት ልክ ይህ እሣት የዛን ጊዜ ሰዎች እንደታደጋቸው እኛም እዚህ እንድንገኝ ምክንያት እንደሆነን ሀገራችንንም የሚታደርጋት አንድ ሀይል በአሁን ሰአት ያስፈልጋታል ኢትዮጵያዊ እሳት ልክ እንደቀድሞው ሰዎች በዙሪያው ከበን የምንወያይበት ከአደጋ የምናመልጥበት መሸሸጊያ ማኩረፊያ ማለት ነው ይህ ኢትዮጵያዊ እሣት ግለሠብ ሊሆን ይችላል ድርጅት ሊሆን ይችላል ነገር ግን በእውነት እና በእውቀት ላይ የተመሠረተ አላማ ያለው በጎ አሣቢ የተጣላውን አስታራቂ የተሰደደውን ሠብሣቢ ለእውነት የሚሞት ጀግና ሀገራችን ትፈልጋለች ይህን ኢትየጰጵያ እሣት ለማቀጣጠል የሚችለው ማንም ሊሆን ይችላል ነገር ግን ህዝባዊ ተቋማትና ድርጅቶች እንዲሁም ትልቅ የሚባሉት በዙሪያቸው ብዙ ህዝብን ያስከተሉ ግለሰቦች ከፍተኛውን ድርሻ ሊወስዱ ይችላሉ ይህም ከፍተኛ ሀላፊነት ጋር አብሮ የሚመጣ ነው በዙሪያቸው እሣቱን ሊሞቅ የሚመጣውን የሰው ቁጥር ማብዛት ወይም የራሳቸውን ሀሳባዊ ፖለቲካ ማስፈን ሳይሆን የቆሙለትን አላማ ማሳካትና በጎ ነገር ለሀገር ማበርከት መሆን አለበት አለበለዚያ ይህ እሣት ለነፍሳችን መዳን ለሀገራችን መታደጊያ ከመሆኑ ይልቅ አጥፊነቱ ሊያመዝን ይችላል መጠንቀቅና ትልቅ ሀላፊነትን መውሰድ ያስፈልጋል ይህ ኢትዮጵያ እሳት እስከዛሬ በሀገራችን ሊቀጣጠል ያልቻለበትን ምክንያት በሶስት ከፍን ማወቅ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ለዚህም ያለፉትን ሶስት አይነት የኢትዮጵያ አመራሮችን መመልከት እንችላለን ፡፡ 1ኛው በነበረው የአመራር ክፍተት እንዲሁም በአጋጣሚዎች ሾልከው ስልጣን ላይ የወጡ መሪዎች ሲሆኑ ያመራር ብቃታቸውም የአስተሣሠብ ደረጃቸውም ሀገር ለመምራት አይመጥንም ነበር ለዚህም ድክመቶቻችውን በአምባገነንነት በከባድ እርምጃዎች ነበር የሚሸፍኑት ስለዚህም ቀርቦ ስህተቶቻቸውን ለማረምም ለመወያየትም እጅግ አስፈሪና የማይታሰብ ነበር ለዚህም እንደ ምሳሌ ጓድ ሻለቃ መንግስቱ ሀይለማርያምን መጥቀስ ይቻላል ነገር ግን በነበራቸው የሀገር ፍቅር እና ወኔ ሀገራቸውን ሣይሸጡ ሣያስደፍሩ አቆይተዋታል፡፡ 2ተኛው የመሪዎቹ አቅም ከፍተኛ ሆኖ ሣለ የሚመሩትን ህዝብ በተሻለ የአስተሳሰብ ደረጃ ላይ ማድረስ ያልቻሉ ወይም የህዝቡ አስተሣሠብ ኃላ ቀር የነበረ በመሆኑ የመሪዎችንና የተመሪዎችን አስተሣሠብ አጣጥሞ ለመሄድ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የተፈጠሩበት የአመራር አይነት ነው ለዚህም ምሣሌ አፄ ቴውድሮስን እና አጼ ሚኒሊክን መጥቀስ ይቻላል አፄ ቴውድሮስ በጊዜው ከነበረው ከዘመነ መሳፍንት እኔ ልግዛው እርስ በርስ እልቂት እንዲያወጡና የተሻለች ኢትዮጵያን እንዲፈጥሩ ያስቻላቸው የነበራቸው ሀገራዊ ራዕይና የመምራት ብቃት ነው ይህም ሁሌም ቢሆን በኢትዮጵያ የዐንድነት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራን ያሰጣቸዋል፡፡ አፄ ሚኒሊክን ኢትዮጵያውያን ካላቸው ፍቅር አንፃር እምዬ ምኒሊክ ይሏቸዋል፡፡ በአድዋ በሰሩት ታሪካዊ ገድል ጎልተው ቢታወሱም አሁን በየኪሳችን ከተነው ለምንዞረው ስልክ ከቦታ ቦታ ለምንቀሳቀስበት መኪና ከውጭ የሚመጡ እንግዶቻችንን በተንደላቀቀ ሁኔታ የሚስተናገዱበትን ሆቴል የባቡር ትራንስፖርት በየቤታችን ለሚመጣልን የኤሌክትሪክ ብርሀን መነሻው አፄ ሚኒሊክ ናቸው፡፡ ለዚህም ስራቸው በመጀመሪያም ብዙ ተወቅሰዋል፡፡ የሰይጣን ስራ ነው በሚልም በአማካሪዎቻቸው ተመክረዋል ፡፡ ነገር ግን ይህን ምክር ተቀብለው በጨለማ አላስቀሩንም ይልቁን በነበራቸው የተሻለ የአስተሣሠብና የአመራር ብቃት ተጠቅመው ሀገራቸውን ወደ ተሻለ ቦታ አድርሰው አልፈዋል፡፡ 3ተኛው የአመራር አይነት የመምራት አቅም የማገናዘብ ችሎት ያላነሣቸው ነገር ግን የመምራት ችሎታቸውንና አቅማቸውን ለመጠቀም ያሉበት ሁኔታ ወይም ስርአት የማይፈቅድላቸው ወይም በጎ ፍቃዳቸው ሲሆን ጥሩ የሚሠሩ ወይም እንደ ሚሠሩ የሚያስመስሉ ናቸው ለዚህም ምሳሌ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊን መጥቀስ ይቻላል ምዕራባውያን ጠ/ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ከፍተኛ ያመራር አቅም እንዳላቸው ነገር ግን የተተበተቡበት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ያላቸውን ችሎታ አውጥተው እንዲጠቀሙበት አላስቻላቸውም ይላሉ ለኔ ግን ምክኒያቱ ይህ አይመስለኝም አንድን ሀገር በፈለጉት አውጥቶ በፈለጉት ማስገባት ህገ መንግስቱን እንደፈለጉት መተርጎም የትኛውንም ሰው በስልጣናቸው የፈለጉትን ማድረግ የሚችሉ ሰው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ መተብተብ ብቻ የአመራር ችሎታቸውን ሊያወጡ አልቻሉም የሚለውን ሀሳብ አልቀበለውም፡፡ ይልቁንም በጎ ነገር ለመስራት ፍቃዳቸው ሣይሆን ቀርቶ እንጂ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ እድሜህን በስልጣን ላይ ጨርሰህ ሙት የሚል አይመስለኝም ፡፡ እነዚህ ሶስቱ የአመራር አይነቶች ኢትዮጵያዊ እሳት ማቀጣጠል ባይችሉም ይህ የእሣት ጭላንጭል በሀገራችን መጀመሩን ሣናይ አልቀረንም በድሮ ባህልና ወጋቸው አባቶች ዛፍ ስር ሰብስበው እንደሚመክሩት እንደሚያስትሩት ሁሉ ከተመሰረተ አመት እሣት!! ዳዊት ሙሉጌታ ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 8 ወደ ገጽ 15 ዞሯል
 9. 9. በመዲናችን አዲስ አበባ ከሜክሲኮ-ልደታ ወደ ጦር ኃይሎች አደባባይ በሚወስደው በዋና መንገድ በእግርዎም ሆነ በተሽከርካሪ ሲጓዙ ወደ መኮንኖች ክበብ የሚያስገባውን የቀኝ እጥፋት ትንሽ አለፍ እንዳሉ፣ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ዋና በር ጋር ከመድረስዎ በፊት ወታደራዊ የማዕረግ ልብሳቸውን እንደለበሱ የሚታዩ የአንድ ሰው ፎቶግራፍ በትልቁ ተተክሎ ያገኛሉ፡፡ እኚህ ሰው ሜጀር ጄኔራል ሀየሎም አርአያ ናቸው፡፡ ጄኔራሉ በሕወሓት የትጥቅ ትግል ወቅት ከደርግ ጋር በነበራቸው ፍልሚያና መራራ ጦርነት ጠንካራ የጀግንነት ገድል እና የጦርነት አመራር ብቃት መፈፀማቸው ዛሬም ድረስ ይነገርላቸዋል፡፡ ነገም ቢሆን ታሪክ ያወሳቸዋል፡፡ ከደርግ ውድቀት ማግስት ጀምሮ እስከ 1989 ዓ.ም. ድረስ ጄኔራል ሀየሎም በኢፌዴሪ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ የጦር ኃይል ክፍሉን በበላይነት ከሚመሩት ጄኔራሎች መካከል ግንባር ቀደሙ ነበሩ፡ ፡ ሆኖም በ1989 ዓ.ም ኦሎምፒያ አካባቢ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ በአንድ ቅጥረኛ ኤርትራዊ ነፍስ ገዳይ በአሳዛኝ ሁኔታ በጥይት ተመትተው ተገድለዋል፡፡ አሟሟታቸውን አስመልክቶ በወቅቱ ብዙ የተባለበት ጉዳይ ነው… የሆነ ሆኖ ከላይ በመግቢያዬ ከገለፅኩት የሜጀር ጄኔራል ሀየሎም ፎቶግራፍ ጐን ‹‹…ጀግና ሁን!›› የሚል ፅሁፍ ሰፍሯል፡፡ ትክክል ነው፤ ጀግንነት ያስደስታል፣ ያኮራል፣ ያስመሰግናል… ሌላም ሌላም፡፡ የሀየሎም ንግግር እውነተኛ ነበር፡፡ የሰው ልጅ በምድር ላይ ሲኖር ጀግና መሆን አለበት፡፡ ጀግንነት ተፈጥሯዊ እሴት ነው - በተለይም ለእኛ ለኢትዮጵያውያን፡፡ በዚህም አፄ ዮሐንስንና አፄ ቴዎድሮስን በቀደምትነት እናነሳቸዋለን፡ ፡ በፋሽስት ጣሊያን ወረራ ወቅት አኩሪ የጀግንነት ገድልን በበላይነት በመምራት አፄ ምኒሊክንና ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱን ልናስባቸው ግድ ይላል፡፡ የዛሬ 113 ዓመት በአድዋ ጦርነት ላይ ድልን የተቀዳጁ ጀግኖች አርበኞችን፣ ቅድመ አያቶቻችንን እና በዚያን ጊዜ የነበሩትን ህዝቦቻችንን ልናከብራቸውና ልናመሰግናቸው ይገባል - ለዛሬዋ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ የአኩሪ ታሪክ መሠረት ስለሆኑም፡፡ ምን ይኼ ብቻ! ዓለም ለጥቁር አፍሪካውያን የነፃነት ተምሳሌት አድርጋን የለም እንዴ?! ‹‹ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት…›› ሕወሓት/ኢህአዴግ ደርግን ለመጣል አድርጐት በነበረው የ17 ዓመት እልህ አስጨራሽ መራራ ትግል ወቅት ደም ፈስሷል፤ አጥንት ተከስክሷል፡፡ ውድ ሕይወት ተገብሯል፡፡ መራብ መጠማት፣ በበረሃ መንከራተት፣ መታመምና ወድቆ መነሳት… የያኔው ሃቅ ነበር፡፡ አፍላ ወጣትነትን፣ ከቤተሰብ ጋር የመኖር ሕልምን፣ አጓጊው የወጣትነት ፍቅርን፣ ናፍቆትን… መስዋዕትነት አድርገዋል - ታጋይ ወንድና ሴቶች፡፡ …ሁሉም አለፈና ግንቦት 20/1983 ዓ.ም. የመንግስታቶቻችን መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባን ኢህአዴግ ተቆጣጠራት፡፡ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ‹‹የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬዲዮ ጣቢያ ተቆጣጥሮታል…›› የሚል የአንድ ታጋይ ንግግር ተደጋግሞ በኢትዮጵያ ምድር ተደመጠ፡፡ ምንም እንኳን ህወሓት በየካቲት ወር 1967 ዓ.ም. አላማ አድርጐ ወደ ደደቢት በረሃ ለትጥቅ ትግሉ የገባበትና በመካከል ሲይዛቸውና ሲለቃቸው የነበሩት አላማዎች የተደበላለቁ ቢሆኑም በአፍሪካ አስፈሪ ጦር የነበረውን ደርግን ታግሎ ማሸነፉ ግን ጀግንነት ነው፡፡ ከዚያም ስልጣን የተቆጣጠረው ኢህአዴግ በሀገሪቷ ላይ በተለያዩ ነገሮች ለውጥ እንዲመጣ በንግግር፣ በፅሁፍና በተግባር የተገበራቸው ጉዳዮች ነበሩ፡፡ ለአብነት ጥቂቱን ልጥቀስ፡- ሕገ-መንግስትን አርቅቆ ማፅደቅ፣ ሪፈረንደም፣ የሽግግር መንግስት ማቋቋም፣ ብሔራዊ ምርጫ፣ ነፃ ፕሬስን መፍጠር፣ ዴሞክራሲን መገንባት፣ ልማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲኖሩ ማድረግ፣ የብሔር ብሔረሰቦችን መብትና ቋንቋ አረጋግጦ እውቅና መስጠት፣ ከተለያዩ የውጭ አገራት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዲፕሎማሲያዊና የሁለትዮሽ ግንኙነት መጀመር ይገኙበታል፡ ፡ ለኢህአዴግ በጥቂቱም ቢሆን የተሳኩለት ነገሮች መኖራቸው አይካድም፡፡ በአንፃሩም ፖለቲካዊ ትርፍና ኪሳራቸው ታይቶ ለአንድ ሉዓላዊት አገርና ህዝቦቿ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮች በርተው የጠፉበት ሁኔታም አለ፡፡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በሰበብ አስባቡ የጠበቡ ምህዳሮች፣ የተወሰዱ ከባድ እርምጃዎች፣ አይንን በጨው በማጠብ ሽምጥጥ ተደርገው የተካዱና የተለወጡ አጀንዳዎች ሌላም ሌላም….ባሳለፍነው 21 ዓመታት ውስጥ መኖራቸውን መዘንጋት አይቻልም፡፡ በመናገር፣ ሀሳብን በነፃነት በመግለፅ፣ በመደራጀት፣ በመሰብሰብ፣ በምርጫ፣ ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን በአደባባይ በመግለፅ… ወዘተ ዙሪያ ጠርናፊ፣ አሸማቃቂና ነፃነትን የሚጥሱ ሕጐች፣ አዋጆችና ደንቦች በተለያየ አኳኋን ህዝቡ ዘንድ መድረሳቸው ትናንት በገሃድ የታየ እውነት ነው፡፡ ዛሬም አለ፡፡ ነገም ከዚህ በበለጠ ሊቀጥል ይችል ይሆናል፡፡ ዛሬ… ብዙ ነገሮችን በሀሳብ አውጥቼ አውርጄ፤ የሚነበቡ ነገሮችን አገላብጬ፣ የኅብረተሰቡን የዕለት ተዕለት ኑሮን በመመልከት፣ በማድመጥና በመጠየቅ ‹‹አሁን ያለውን ኢህአዴግ በምን ጀግና እንበለው?›› ስል እጠይቃለሁ፡፡ ሕገ-መንግስትን አክበሮ በማስከበሩ?፣ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋቱ?፣ ዴሞክራሲን በየደረጃው ከፍ አድርጐ በማስፈኑ?፣ ሰብዓዊ መብቶችን በአግባቡ በማክበርና በመጠበቁ?፣ ድህነትን ተረት በማድረጉ?፣ በቀን ሶስት ጊዜ ህዝብን በማብላቱ?፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚን በመፍጠሩ?፣ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ጤናማ ፖሊሲን በመከተሉ?. . . በየትኛው ይሆን ኢህአዴግ ጀግና መንግስት የሚባለው?! ኧረ ሌላም አለኝ፡፡ ኢትዮጵያዊ ባህልና ዕሴቶቻችንን ጠብቆ በማቆየቱ?፣ ከአጓጉል ነገር የፀዳ ትውልድን ፈጥሮ ውጤታማ በማድረጉ?፣ ሥራ አጥነትን በመቅረፉ?፣ ነፃነት የሚሰማው ትውልድን በመፍጠሩ?፣ ‹‹እንከን የለሽ›› ምርጫ በማድረጉ?፣ ሰላማዊ ትግልን በመደገፉ?፣ በምርጫ ቢሸነፍ ስልጣኑን በሰላም ለመልቀቅ ዝግጁ በመሆኑ?፣ ከመንግስት ሥራ አስፈፃሚ አካል ነፃና ገለልተኛ የፍትህ ስርዓትን በማቋቋሙ?… ወዘተ በእነዚህ ሁሉ ለኔ የኢህአዴግ ጀግንነት አይታየኝም፡፡ ይኼ ጨለምተኝነት ወይም ራሱ ኢህአዴግ ብዙ ጊዜ እንደሚናገረው ስርዓቱን የማጠልሸት እኩይ ዕሳቦት አይደለም፡፡ በስርዓቱ ትላንት ያየነው፣ ዛሬ እያየነው ያለውና ነገም ልናየው የምንችለው ነገር በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹የዴሞክራሲ ኦክስጅን›› አሌክስ ቶኪዊቪል የተባለው የፈረንሳይ የፖለቲካ ፀሃፊ አሜሪካንን ከሁለት መቶ አመት በፊት ሲጐበኝ እንደታዘበው ‹‹ያለዴሞክራሲ እውነተኛ ጋዜጦች ሊኖሩ አይችልም፣ ዴሞክራሲም ያለ ጋዜጠኞች ሊኖር አይችልም›› ሲል ተናግሯል፡፡ በተያያዘም፣ የዩናይትድ ስቴትስ ሶስተኛው ፕሬዚዳንት የነበሩት ቶማስ ጄፈርሰን በ1787 እ.ኤ.አ እንደፃፉት ‹‹የመንግስታችን መሠረት የህዝብ አስተያየት እንደመሆኑ መጠን የመጀመሪያው አላማችን ያንን መብት መጠበቅ ነው፤ መንግስት ያለ ጋዜጣ ወይም የዛሬውን ኢህአዴግ በምን ጀግና እንበለው?! በኤልያስ ገብሩ ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 9 ወደ ገጽ 16 ዞሯል
 10. 10. ሰማያዊ፡- የሰማያዊ ፓርቲ ምሰሶ የሚባሉ ዋና ዋና የሚያራምዳቸው ፖለቲካዊ አቋሞች ምንድናቸው? ኢ/ር ይልቃል፡- ፖለቲካ በየጊዜው እንደሁኔታው የሚለወጥ፣ የሚሻሻልና የሚያድግ ቢሆንም! ሰማያዊ ፓርቲ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ታሪክና ካሉብን ችግሮች በመነሳት ዋና ዋና የምንላቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡- አንደኛ፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ የተለያየ ልማድ፣ ባህል፣ ቋንቋ እና እምነት ያላቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የጋራ የወል ስነ-ልቦና አዳብረው በአንድነት የሚኖሩበት አገር ነው ብለን በአብዛኛው በወጣቶች የተቋቋመው ሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በተለያዩ ሃገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሰማያዊ ፓርቲ ድረ-ገጽ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ እጅግ አንኳርና አንገብጋቢ ነጥቦችን ይዞ ቀርቧል፡፡ የመጀመሪያውን ክፍል እነሆ ብለናል፡- እናምናለን፡፡ ይህም ስለሆነ፡- የኢትዮጵያ ፖለቲካ በመሠረቱ ማተኮርና መነሳት ያለበት ከዜግነት እና ከግለሰብ መብት ላይ መሆን አለበት ብለን እናምናለን፡፡ እነዚህም የዜግነት እና ሰብዓዊ መብቶች እስከተከበሩ ድረስ የማይከበር የመብት ዓይነት የለም! ብሎ ነው ፓርቲያችን የሚያምነው፡፡ ከዚያ ውጭ ያሉ መብቶች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ ባለሙያዎች በሙያቸው ተደራጅተው የሚጠይቁት የጋራ መብት ይኖራቸዋል! ሠራተኞች በጋራ ተሰባስበው የሚጠይቁት መብት ይኖራቸዋል፡ ፡ ወጣቶችም በዕድሜያቸው፣ ሴቶችም በጾታቸው እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባህላቸውን፣ ዕምነታቸውን ለማበልፀግ የራሳቸው መብቶች አሏቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ መብቶች ከዜግነት እና ከሰውነት መብት በላይ አይደሉም፡፡ በመሆኑም፡- የዜግነት እና የሰውነት መሠረታዊ መብቶች በተከበሩ ጊዜ ሌሎቹ የጠቀስኳቸው መብቶች ሁሉ አብረው ይከበራሉ ብለን እናምናለን፡፡ ሁለተኛውና ዋናው ነገር፡- በኢትዮጵያ ውስጥ ድህነትና ግብርና ላይ የተመሠረተ ኋላ ቀር አኗኗር በመኖሩ! በዚህም ዓይነት የኑሮ ዘይቤ ብዙው የህብረተሰብ ክፍል በገጠሮች ውስጥ የሚገኝና ህልውናውን በመሬት ላይ መሠረት ያደረገ ስለሆነ ይህ የህብረተሰብ ክፍል እንዲያድግ እና ኑሮው እንዲሻሻል ማድረግ የሚቻለው ሙሉ ነፃነቱን በማቀዳጀትና በመሬቱ ላይ ብቸኛ ወሳኝ ተዋናይ ለማድረግ መሬቱን የግል-ንብረቱ እንዲሆን በማስቻል ነው ብሎ ያምናል ፓርቲያችን፡፡ ይሄ በተለያዩ ጥናቶችም የተረጋገጠ ትክክለኛው አቋም ነው፡፡ ነፃነት የሌለው ህዝብ በምንም ዓይነት መንገድ ልማትን እንደማያመጣ! በአገራችን ያሉት ገበሬዎችም ነፃነት እስካላገኙ ድረስ ከኢትዮጵያ ውስጥ ችጋር እንደማይጠፋ የኛም አገር አንጋፋ-ምሁራን ያጠኑት ነው፡ ፡ ዓለማቀፍ ዕውቅ ምሁራንም ለምሳሌ አማርትያ ሴን (የኖቤል ተሸላሚ ኢኮኖሚስት) በጥናቱ በሚገባ እንዳብራራው ነፃነት ለልማት መሠረቱ መሆኑን ነው፡፡ ኘሮፌሰር መስፍንወ/ ማርያምም Suffering under God’s Environment በሚለውና Rural vulnerability to famine in Ethiopia በሚለው መጽሐፋቸው በአመርቂ ሁኔታ እንዳስረዱት ገበሬው ነፃ እስካልወጣ ድረስ ችጋር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚቀጥል ነው፡፡ ስለዚህ ገበሬው ነፃ ይሁን ከተባለ የሚያርሰው መሬት የራሱ መሆን አለበት፡፡ በፊት የፊውዳል ጭሰኛ እንደነበረው ዛሬ ደግሞ የመንግሥት ጭሰኛ መሆን የለበትም፡፡ በመሆኑም የፓርቲያችን አቋም በዚህ ጉዳይ ላይ በገጠርም የሚታረሰው ሆነ በከተማ የሚኖርበት መሬት የዜጐች የግል ይዞታ መሆን አለበት ነው፡፡ በዚህም አግባብ ገበሬዎችም ሆኑ የከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ነፃነት እና ያለምንም ዋስትና-የማጣት ስሜት የመሬትን የገበያ ዋጋ በተገቢው መንገድ ለመጠቀም ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ ገበሬውም ከካድሬና ከመንግሥት ጭሰኝነት ነፃ ከሆነ እምቅ አቅሙን አውጥቶ በመጠቀም መሬቱን የመጠበቅ፣ የመንከባከብ፣ የማልማት፣ በባንክ የማስያዝ እንዲሁም የማውረስ፣ የመሸጥ እና የመለወጥ መብት ይኖሩታል ማለት ነው፡ ፡ ይሄ ለቴክኖሎጂ ሽግግርም ራሱን የቻለ አስተዋፅኦ አለው ብለን እናምናለን፡፡ ስለዚህ እነዚህ የጠቀስኳቸው አቋሞች መሠረታዊ እሴቶቻችን ናቸው፡፡ በፌዴራል አወቃቀር ላይ ያለን አቋም ደግሞ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለዚህ ዓይነት የመንግሥት ቅርፅ እንግዳ ባለመሆኗ እና በተለያየ ጊዜ የዚህ አካባቢ ንጉስ የዚያ አካባቢ ንጉስ ከዚያም ንጉሠ-ነገሥት እየተባለ በሰፊው በባህላዊ ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 10
 11. 11. የአገዛዝ ዘመንም የተለማመድነው በመሆኑ! ይህንኑ ማዳበርና ዘመናዊ ይዘት እንዲኖረው ማድረግ ያሻል፡፡ ይሄም ሆኖ ግን የአስተዳደር ምቹነትን፣ መልክዓ-ምድርን የህዝቦች አሰፋፈርን፣ ባህልን፣ ቋንቋን ግምት ውስጥ አስገብቶ የሚደረግ እንጂ እንደው አሁን እንደሚባለው በጐሣ ከረጢት ውስጥ ያሉ ጎሳዎች ተስማምተው አገሪቷን ገና እንደአዲስ እየፈጠሯት እንደሆነ የሚያስመስለው አቀራረብ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ ኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ የሀገረ-መንግሥትነት ታሪክ ያለውና የረጋ ህዝብ ብሎም የጋራ ስነ-ልቦና ያለው ህብረተሰብ የሚኖርባት አገር ነች፡፡ በመሆኑም፡- እነዚህ ግምት ውስጥ ገብተው የሚዋቀር ፌዴራላዊ ቅርፅ ነው ለሀገራችን የሚበጃት ብለን እናምናለን- እንደሰማያዊ፡፡ ታሪክን በመፈልሰፍ አንድ ጐሣና አንድ ጐሣ እንደተዋጉ የሚያስመስለው አቀራረብም በፍፁም የተሳሳተና አውዳሚ ነው፡፡ መንግሥት ከመንግሥት፣ የአካባቢው አገዛዝ ከአካባቢው አገዛዝ ተጣልተው ያውቃሉ እንጂ አንድ ብሔረሰብ ከሌላው ብሔረሰብ ጋር በታሪክ ለዚያውም በታቀደ ሁኔታ ጎሣን መሠረት አድርጎ የተደረገ የፖለቲካ ትግል የለም በአገራችን ውስጥ፡፡ ይሄ ከቅርብ ጊዜ በኋላ በጥራዝ ነጠቅነት ሣር-ቅጠሉ ኮሚዩኒስት በነበረበት ከ66ቱ አብዬት ጋር ተያይዞ እንደወረደ ስለተቀበልነው የመጣ ነገር እንጂ የአገራችንን እውነተኛ ገፅታ የሚያሳይ አይደለም ብለን እናምናለን፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ መሠረት የጣልንባቸው እና አጥብቀን የያዝናቸው ዋና ዋና አቋሞቻችን፡፡ ሰማያዊ፡- አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዋነኛ ፖለቲካዊ ችግር ምንድነው ብላችሁ ነው የምትገነዘቡት? የብሔር ጭቆና ነው? የመደብ ልዩነት ነው? ወይስ አምባገነን የመንግሥት ሥርዓት? ኢ/ር፡ይልቃል፡- እንግዲህ ኢትዩጵያ እስካሁን ድረስ ከአገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ አልሄደችም፡፡ ያለው አገዛዝ ከባህላዊ አገዛዝ የጀመረ እና በ1967 ለውጥም መጣ ተብሎ ከንጉሳዊ አገዛዝ ወደጠብመንጃ አገዛዝ ተዘዋውረናል፡፡ እስካሁን ያለው መንግሥት ድረስ ምርጫ በሚመስል ሁኔታ ልባስ ተሰጥቶት ቅቡልነት ያለው ለማድረግ ቢሞከርም የምር ፖለቲካውን ካየነው ኢትዮጵያ ከጠብመንጃ አገዛዝ እስካሁንም ድረስ አልተላቀቀችም፡፡ ስለዚህ የጉልበት አገዛዝ ነው መሠረቱ፡፡ አንዳንዶቹ ፍልስፍናዊ ቅርፅ በመስጠትና በውጭ አገር ከነበሩ የፖለቲካ እምነቶች ጋራ ለማዛመድ የየራሳቸውን ተቀፅላ ይጨምሩበት ይሆናል እንጂ እስካሁንም ድረስ ኢትዮጵያውያን በጠብመንጃ አገዛዝ ስር ነን፡፡ በመሆኑም ሰማያዊ የሚያምነው የሰዎች የዜግነት እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከተከበረ እንዲሁም ስልጣን የህዝብ ከሆነ ከዚያ በኋላ የሚመጡት ነገሮች በሁለተኛ ደረጃ የሚታዩ ናቸው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የሚታዩት፡- የዜጐች ባህላቸውን የማበልፀግ ጉዳይ፣ እምነታቸውን በነፃ የማራመድ መብት፣ በሙያቸው ተሰባስበው የሙያቸውን መብት የመጠየቅ ሁኔታ እና የመሳሰሉት ሁሉ ነገሮች ሥልጣን የህዝብ ከሆነ በኋላ የሚመጡ ቁም ነገሮች ናቸው፡፡ በመሆኑም ዋናው ችግር ሥልጣን የአገሬው ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ ባለቤትነት ውስጥ ለመሆን አለመቻሉና በጠብመንጃ አገዛዝ ስር መውደቁ ነው፡፡ ሌሎች ፍልስፍናዊ ዓይነት ይዘት የተሰጣቸው ነገሮች ሁሉ ከዚህ በመለስ ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ሰማያዊ፡- በቅርቡ የተካሄደውን የኢህአዴግ የስልጣን ሽግሽግ በተመለከተ ፓርቲያችሁ ያለው አስተያየት ምን ይመስላል? ኢ/ር፡ይልቃል፡- እ….. በመጀመሪያ ደረጃ የተካሄደው የስልጣን ሽግሽግ አይደለም፡ ፡ እ…ባዶ ነበር ቦታው… በመሆኑም ያ ባዶ ቦታ መተካት ነበረበት፡፡ ስለዚህ ጠ/ ሚኒስትሩ በሌሉም ጊዜ ቢሆን የሚተኩት ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ ነበሩ፡፡ ስለዚህ ጠ/ሚኒስትሩ ለዘላለሙም ሲሄዱ ከኋላ ዘሎ ከማምጣት ምክትሉን መተካት ይሻላል በሚል በዚሁ መሠረት ተካሄደ፡፡ ስለዚህም የተከናወነው የስልጣን ሽግግርም አይደለም! ሌላ ዴሞክራሲያዊ የተለየ ነገርም አልተደረገም፡፡ በታሪካችን እንዲሁ ያለውን ነገር ምናልባትም በተሻለ ሁኔታ የዛሬ 1ዐዐ ዓመት ገደማ ኢትዮጵያ ውስጥ ተደርጓል፡፡ ንግሥት ዘውዲቱ በሞቱ ጊዜ አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ንጉሠ-ነገሥት ሆነው ተሰይመዋል፡፡ የንግሥት ዘውዲቱም የቀብር ስነ-ስርዓት በተሟላ የመንግሥት ደንብ protocol በክብር ተፈፅሟል፡፡ የአፄ ኃ/ሥላሴም ንግስና ሥርዓት ጠብቆ ቤተክርስቲያን በጊዜው ባላት ሥልጣን መሠረት በአግባቡ ተፈፅሟል፡፡ እና ይሄ ዓይነቱ የስልጣን መተካት ከሆነ በፊትም ተደርጓል፡፡ ስለዚህም ኢህአዴግ ታሪክ ሠራ ተብሎ ኢህአዴግን የተለየ ሊያደርገው የሚችል ነገር አልተፈጠረም፡፡ የስልጣን ሽግግር ሊባል የሚችለው አንደኛ፡- ከአንድ ፓርቲ ወደ ሌላ ፓርቲ ቢሄድ ወይም ደግሞ አቶ መለስ እያሉ ተወዳድረው በሌላ አካል ተበልጠው ቢሸነፉ ነው፡፡ አሊያም ደግሞ በቃኝ ብለው ለቀው ሌሎች ተወዳድረው ቢያሸንፉ ያኔ የስልጣን ሽግግር ተካሄደ ሊያስብል ይችላል፡፡ ከሞቱ በኋላ ግን በሌላ ሰው መተካት ግዴታ ነው፡ ፡ ቦታው ባዶውን መቅረት የለበትምና! በመሆኑም ፓርቲው የመረጠውን ሰው ተካ፡፡ ስለዚህ ይህ የስልጣን ሽግግርም ሆነ ሽግሽግ ሊባል አይችልም፡፡ ሰማያዊ፡- የኢህአዴግ አብዬታዊ- ዴሞክራሲያዊ መስመር የራሱ የሆነ ሥልጣን የማሸጋገሪያ ቀመር እና አካሄድ አለው! ብለው የሚያነሱ የፓርቲው ሰዎች አሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እውነተኛ የስልጣን ሽግግር ከፓርቲው መጠበቅ የዋህነት ነው! የሚሉም አልታጡም፡ ፡ በዚህ መሃል ደግሞ የፓርቲውን የመተካካት ጉዞ የሚታዘቡ ሰዎች ምናልባት ስልጣን በትጥቅ ከታገሉት ወደ ሲቪል-ኢህአዴጎች እየሄደ ከመጣ ተስፋ ይኖር ይሆናል! የሚሉ አሉ፡፡ እናንተ ደግሞ እንደተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ሊያሳትፋችሁ የሚችል የስልጣን መጋራት መንገድ ከኢህአዴግ ትጠብቃላችሁ? ኢ/ር፡ይልቃል፡- እውነቱን ለመናገር እኔ መጀመሪያም ከኢህአዴግ ዓይነት ድርጅት የምር የምጠብቀው ነገር የለም፡፡ ፓርቲው በራሱ እጅግ የጠቅላይነት (Totalitarian) አስተሳሰብ ያለው አምባገነን ነው፡፡ አንድ ጠንካራ ፓርቲ በመመስረት እና የልማታዊ መንግሥት ምስል ለራሱ በመፍጠር ከዚህ በኋላ ለ3ዐ እና 4ዐ ዓመት ለመግዛት የሚያልም ፅኑዕ የሥልጣን ሱሰኝነት የተፀናወተው ድርጅት ነው፡፡ የአገዛዝን ነገር ፍልስፍና ለማላበስ የሚጥር! ለሥልጣኑ መቀጠል ሲል እጅግ በአያሌው ጂምናስቲክ ሲሰራ የኖረ ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ደቡብ ኮሪያ እና ታይዋን ያሉ የማይዛመዱን አገሮችን በአርአያነት እየጠቀሰ እነዚህ አገራት በአንድ ወቅት ሲያራምዱት የነበረውን ፖለቲካዊ ፍልስፍና በኢትዮጵያ ላይ በመጫን ለረዥም ዓመታት ሊገዛን የሚፈልግ አስመሳይ-አምባገነን ሥርዓት ነው፡፡ እነዚህ አገራት ግን በቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ወቅት በነበረው የጐራ ልዩነት ከአሜሪካ ያገኙትን የዕርዳታ ቁሳቁስ የቴክኖሎጂ ድጋፍ፣ እና የገንዘብ እገዛ ካላቸው ልምድ ጋር በማቀናጀት በራሳቸው ሁኔታ ያደጉ ናቸው፡፡ ነባራዊ ሁኔታቸውም ከኢትዮጵያ ጋር በፍፁም አይገናኝም፡፡ እንደውም እኮ ኢህአዴግ እስከ 97 ሲል የነበረው ‘ጠንካራ ተቃዋሚ አጣን! ብናገኝ እስከግማሽ መንገድ ድረስ ሄደን እንቀበላለን!’ ምናምን የሚሉ ባዶ ቃላትን ነበር፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ግን 97 ላይ የዴሞክራሲው መንገድ እንደማያዋጣና ሥልጣንን በአጭር ጊዜ እንደሚያስለቅቅ ሲያውቁ አምባገነንነትን ፍልስፍና ለማላበስ የተፈጠረ አብዬታዊ-ዴሞክራሲ እንጂ የምር ስልጣንን ማጋራት የሚችል አሳታፊ ስርዓት አይደለም፡፡ በመሆኑም የኢህአዴግ መንግሥት አንድ ወጥ የሆነ አገዛዝ፣ ሌላውን ሁሉ የሚያንቋሽሽ የሚያቃልል፣ በመደብ ቅራኔ ውስጥ ነገሮችን ከፋፍሎ ወዳጅ እና ጠላት ብሎ የሚያይ እስካሁን ድረስ የሚታገልላቸውና የሚታገላቸው አመለካከቶች ያሉት እንጂ ፖለቲካዊ መስመሩን አስተካክሎ የሌላውንም ድምፅ ግምት ውስጥ አስገብቶ የሚሄድ ሥርዓት ነው ብዬ አላስብም፡፡ ስለዚህ በህዝብ የምር ትግል መለወጥ ይቻል እንደሆን እንጂ ኢህአዴግ በውስጡ በራሱ እያደገ በሚሄድ ዴሞክራሲ ይቀየራል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሰማያዊ፡- እንግዲህ የህዝብ የምር ትግል ሲባል ብዙ ጊዜ የሚነሳው ከ97 ወዲህ የህዝቡ ለፖለቲካ ፍላጎት የማሳየት ሁኔታ እጅግ እንደተዳከመ ነው፡፡ በዚህ ረገድም ከዚህ ወቅት በኋላ! ሰው በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ተስፋ አድርጐ ከእናንተም ጋር አብሮ ቆሞም ቢሆን ወደነፃነት እና ዴሞክራሲ የሚጓዝ ይመስላችኋል? እናንተስ አዋጪ መንገድ አለን ትላላችሁ? ኢ/ር፡ይልቃል፡- የ97ቱ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ይነገራል፡፡ ራሳችንን በተስፋ ለመመገብም ጭምር እየፈለግን እንጂ እኔ የ97ቱን ጉዳይ ብዙ ሰው በትክክል የተረዳው አይመስለኝም፡ ፡ እንዴት መጣ? የሚባለውን ነገር በትክክል ካየነው በ1993 ዓ.ም. ህወሓት ከኤርትራ ጦርነት በኋላ ከተከፋፈለ ጀምሮ! በብዛት አንድ ሰው ጐልቶ እየወጣ የነበረበት! የአፍሪካ መሪ እየተባለ የኔፓድ መሪ…. የዚህ መሪ…. በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ አቶ ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 11 ወደ ገጽ 19 ዞሯል
 12. 12. ከኘሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረ ማርያም ትርጉም ከነፃነት ለሀገሬ በድጋሚ እውነት፣ሃይልን ለተነፈጉ ላለፉት በርካታ ስለ ሥልጣን ተጠቃሚዎች ዕውነትን ስናገር ነበር፡፡ የጦማሬ ገጼ መግቢያ መስመሩ ለሰብዓዊ መብት ተሟገት፡፡ ስለሥልጣን ተጠቃሚዎች እውነትን መስክር; ነው የሚለው፡፡ ይህ ደሞ ልዩ ትርጉም ያለው፣ ጠንካራ ሞራልና ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ አላግባብ የሚጠቀሙበትን፣ ከመጠን በላይ ለሚተማመኑበት ኢሰብዓዊ ድርጊት ማስገንዘቢያ የሆነ ስንኝ ነው፡፡ ለባለሥልጣናት ነን ባዮች እውነትን መናገር፣ ተናጋሪው በዚህ ባለስልጣናት ላይ ስልጣናቸው የተዘረጋው በሃሰት ላይ መሆኑን ምስክርነቱን ያረጋግጣል፡ ፡ አልፎ አልፎም ሃቅን መናገር የስልጣን ሰለባ ለሆኑትም አስፈላጊ ነው፡፡ ስልጣን አልባዎች በምንም መልኩ ስልጣንን ሊያዛቡ የሚችሉበት ሁኔታ የለም፡፡ ስህተታቸው ግን የስልጣናቸውን እውነተኛ መብት አለማወቃቸው ነው፡፡ ሥልጣንን መከታ በማድረግ ግፍ የሚፈጽሙት ጉልበተኛ ሆነው ቢታዩም የስልጣን ተነፋጊዎች ደግሞ የሥልጣን ባለቤትነት መብት አላቸው፡፡ የሥልጣን እውነታነትና መብት ነው የሥልጣን ተነፋጊዎች በትግላቸው ሂደት ሊጠቀሙበትና ለድል የሚያበቃቸውን መንገድ ሊከተሉ የሚገባቸው፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ይህን አስመልክተው፣ ለጊዜው ትክክለኛነት ቢሸነፍም፣ ከሰይጣናዊና እኩይ ድል የበለጠ ነው; ብለዋል፡፡ በሰኔ 2ዐ1ዐ፣ እውነትን ስልጣን ለተነፈጉ መናገር; የሚል ጦማር ጽፌ ነበር፡፡ በዚያም ጦማሬ ላይ በግንቦት 2ዐ1ዐ፣ ቀን በቀን በገዢው ፓርቲ የተሰረቀውንና ድሌ 99.6 በማለት ፓርላማውን የተቆጣጠረበትን የምርጫ ውጤት በተመለከተ፣ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ የፖለቲካ መሽመድመድ የታየበትና አንዳችም ተግባር ያልተከወነበት ሂደት እንደነበር አሳስቤ ነበር፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በጥንቃቄ ትኩረት ሰጥተው ራሳቸውን ማስተካከያ መንገድ እንዲፈልጉም አሳስቤ ነበር፡፡ ዓላማዬ ዲስኩር ለማድረግ ወይም ተቃዋሚዎችን ለመኮርኮም ሳይሆን ሃሳባችንን በማጽዳት ቆሻሻውን በመጣልና ወደ ዴሞክራሲ የሚያደርሰንን ረጂሙን መንገድ ቀና ለማድረግ ለመርዳት መሆኑን በወቅቱ አስረድቻለሁ፡፡ እውነት ይጎዳል; ቢባልም እኔ አልስማማበትም፡፡ እውነት ለማገገም ይረዳል፡ ሃይል ይሰጣል፡ ታጋዮችንም ነጻ ያወጣል፡፡; የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች በገዢው ፓርቲ እይታ የ2ዐ1ዐን ምርጫ ተከትሎ እንደተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የነጻው ኘሬስ ጋዜጠኞች፣ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በገዢው ፓርቲ የሚደርስባቸውን ሰቆቃ በተመለከተ የገዢው አመራሮች አገኘን ለሚሉት ድልና የምርጫ ውጤት ስለተቃዋሚ ፓርቲዎች /ስለህዝቡ/ ያላቸው ግንዛቤና አመለካከት ያስገርመኛል፡ ፡ ያን ጊዜም አሁን እንደማስበው፡ በገዢው ባለስልጣናት እይታ ተቃዋሚዎችን መመልከት፣ ተቃዋሚዎችን በተለይም የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያለውን ሁኔታ በማገናዘብ ሊከተሉት የሚገባውን መንገድ ያመላክታል ብዬ አምናለሁ፡፡ ……መለስ ተቃዋሚዎች እራሳቸውን ለክተው እንደማያውቁ ያውቃል፡፡ በሚገባ አጥንቷቸዋል፣ አስጠንቷቸዋልና ስራቸውን እንዴት እንደሚያከናውኑ /እንደማያከናውኑ/ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ በጥንቃቄ የተበጠሩት ሕዝባዊ ዲስኩሮቹ ላይ ዘወትር የማይለወጥና መጥፎ አመለካከቱን ያሳያል፡፡ ተቃዋሚዎችን በችሎታቸውን በእውቀትም የበታቾቹ አድርጎ አስቀምጧቸዋልና በፈለገው ስዓትና ወቅት በአስተሳሰብ እንደሚበልጣቸው፣ በአመለካከት እንደሚያልፋቸው፣ በተንኮል እንደማይደርሱበት፣ በእኩይ አስተሳሰብ እንደማይስተካከሉትና ባሻው ጊዜ ድል እንደሚያደርጋቸው ያምናል፡፡ በመለስ አስተባሰብ፣ እንቅስቃሴያቸው ድውይ፣ የማያድጉና ያልበሰሉ፣ አድሮ ጥጃ፣ በመሆናቸው ሥልጣኑን የሚያሰጉት እንዳልሆኑ አረጋግጧል፡፡ በንግግሮቹ ሁሉ ተቃዋሚዎች ላይ ያለውን ንቀትና ጥላቻ ብቻ ነው የሚያንፀባርቀው፡፡ እድገታቸውን እንዳልጨረሱ ሕጻናት እለት ተእለት ክትትል የሚያስፈልጋቸውና ስርዓት እንዲኖራቸውም የዲሲኘሊን ሽንቆጣ እንደሚያስፈልጋቸው ነው የሚደሰኩረው፡፡ ልክ ሕጻናትን እንደማታለል አይነት፣ ለአንዳንዶች፣ ስኳር ያልሳቸዋል፣ በሥራ፣ በመኪና ችሮታ፣ በቤት ስጦታ፣ እና አፋቸውን ሊያፍን የሚያስችለውን ሁሉ ያደርግላቸዋል፡፡ በዚህ ሊደልላቸው የማይችላቸውን ደሞ በመከታተልና ሲገቡ ሲወጡ በመተንኮስ፣ በስለላ አባላት በማስጨነቅ በመጨረሻውም አስሮ ይፈርድባቸዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ተቃዋሚዎችን ያታልላቸዋል፣ ይቀልድባቸዋል፡፡ ሽማግሌዎችን ለእርቅ በመላክ፣ ጊዜ እየገዛ የቆመበትን መሰረት ያሳጣና፣ ድርድር በሚል ዘዴ እያታለለ የራሱን ድል ይገነባል፡፡ የተለመደ አስማታዊ የሆነውን የተንኮል ጠበል ይረጭና ያንኑ ውጤት አልባ የሆነውን ጨዋታውን ጀምሮ በመጨረሻው እንቅልፍ አስወስዷቸው በድል ደወል ሲነቁ ማርፈዱን ይገነዘባሉ፡፡ በዚህም ተቃዋሚዎች የጨበጡትን ሁሉ ለቀው ተሸናፊ ሆነው ይሰለፋሉ፡፡ በኢትዮጵያ ተቃዋሚው ሃይል ማነው? ይህ ጥያቄ ምናልባትም አወዛጋቢና እንዲያውም ቁርጥ ያለ መልስም ሊገኝለት የማይችል ይሆናል፡፡ አሁን በሃገሪቱ ውስጥ የተጠናከረና ጉልበት ኖሮት የተዋቀረም ፓርቲ አለ ማለት ያስቸግራል፡፡ በዚህም የተነሳ ተቀናጅተውና ሃይላቸውንና አቋማቸውን አስተባብረው ገዢውን ፓርቲ ሊሞግቱና ገዢውን ፓርቲ ሊቋቋሙት ብቃት ያላቸው ፓርቲዎች ውህደት አይታይም፡፡ በምሁራንም የተጠናከረና የተዘጋጀ ተቃዋሚ የለም፡፡ ከሲቪል በማህበረሰቡም፣ ከማህበራት፣የተዋቀረ ፓርቲም የለም፡፡ የህብረተሰቡን ሃይል ያካተተም እንቅስቃሴም ሆነ ተቃዋሚ ሃይል የለም፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ችግር ከ196ዐዎቹ ጀምሮ የኖረው የአፍሪካ ያረጀው ችግር ነው፡ ፡ በአፍሪካ አንድ ሰው አንድ ፓርቲ በማለት በጋና በከዋሚ ንክሩማ ዘመን የተፈጠረ ሂደት ነው፡፡ ንክሩማ ተቃዋሚዎቹን፣ አጠፋ፣ አጋዘ፣ ለፍርድ አቅርቦ ያለአግባብ አስፈረደባቸው፡ ፡ በዚህም ሂደት ውስጥ ዳኞች፣ የማህበራት መሪዎች፣ ተካተዋል፡፡ ባለፈው ግማሽ ምዕተ ዓመት ውስጥ፣ በኢትዮጵያ በጉልበት ስልጣን የወጡትን ገዢዎች የተቃወመ ሁሉ፣ በፖለቲካው መድረክ መወቀስና መወገዝ ብቻ ሳይሆን፣ ያለአግባብ በፍርድ ስም መሰቃየትና ከዚያም አልፎ ለሞት መዳረግ የታየበት ዘመን ነው፡፡ የኢትዩጵያን የተቃዋሚ ሃይላት ምንነትና ሁኔታ እንዲህ ነው ለማለት እቸገራለሁ፡ ፡ ከሜይ 2ዐ1ዐ ምርጫ በኋላ ባቀረብኩት ጦማሬ ላይ አንስቼው እንደነበረው! ያ ተስፋ የቆረጥንበት ተቃዋሚ ሃይል፣ የተከፋፈለ፣ ያ በነጋ በመሸ ቁጥር በረባ ባልረባው ጉረሮ ለጉረሮ የሚተናነቀውና ዋናውን ሊታገሉት የሚገባውን ሃይል የዘነጉት ናቸው አሁንም ተቃዋሚ ናቸው የምንላቸው? ወይስ እነዚያ በደካማው የሚንቀሳቀሱትን እንደአመቺነቱ ብቅ ጥልቅ የሚሉትን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሲቪክ ማህበረሰቡ አሰባሳቢዎች፣ጋዜጠኞች፣ እና ሌሎቹን የሚዲያ ባለሙያዎችና ምሁራኑን ናቸው? ወይስ ለመሳርያ ትግል ታጥቀውና ቆርጠው የተነሱትንና ገዢውን ፓርቲና አፋኝና ጨቋኝ ሥርዓቱን ለማጥፋት የተነሱትን ናቸው ተቃዋሚ የምንላቸው?; ሁሉም ናቸው ወይስ ሁሉም አይደሉም? በኢትዮጵያ ትክክለኛው የተቃዋሚዎች ተግባር ምንድን ነው? የፖሊስ ጭቆናዊ አስተዳደር በተንሰራፋበት ሃገር ውስጥ በተቃዋሚነት መቆም እጅጉን አስቸጋሪና አደገኛም ነው፡፡ የሜይ 2ዐዐ5ቱን ምርጫ ተከትሎ ሁሉም የተቃዋሚ ፓርቲ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ የዴሞክራሲ ጮራ ስትወጣ ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 12

×