SlideShare a Scribd company logo
የስኳር ኢንዱስትሪ
በኢትዮጵያ
Ethiopiansugar.com
facebook.com/etsugar
ታህሳስ 2009 ዓ.ም
የስኳር ኮርፖሬሽን ተልዕኮ፣ ራዕይ
እና እሴቶች
ተልዕኮ
በአገሪቱ ያለውን እምቅ ሃብት ለማልማት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰው ሀይል
አቅም በማፍራት ስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች በማምረትና የስኳር ተረፈ ምርትን ጥቅም ላይ
በማዋል የሀገር ውስጥ ፍላጎት ከማርካትና የህዝቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ
የጎላ የኤክስፖርት ድርሻ በመያዝ የሀገሪቱን ልማት መደገፍ፡፡
ራዕይ
ቀጣይነት ባለው እድገት በ2016ዓ.ም በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች ሀገራት
ተርታ መሰለፍ፣
እሴቶች
•	 የማያቋርጥ ለውጥና ቀጣይ ተወዳዳሪነት
•	 መልካም ስነ ምግባር
•	 ምርታማነት የህልውናችን መሠረት ነው!
•	 ህዝባዊነት መለያችን ነው!
•	 መማር አናቋርጥም!
•	 ፈጠራንና የላቀ ሥራን እናበረታታለን!
•	 በቡድን መንፈስ መስራት መለያችን ነው!
•	 አካባቢ ጥበቃ ለልማታችን መሠረት ነው!
•	 የሰው ሃብት ልማት ለስኬታማነታችን ወሳኝ ነው!
2 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
በማቋቋሚያ አዋጅ ደንብ ቁጥር
192/2003 መሰረት የስኳር ኮርፖሬሽን ዓላማ
•	 የሸንኮራ አገዳና ስኳር የሚያስገኙ ሌሎች ሰብሎች ማልማት፣
•	 ስኳር፣ የስኳር ውጤቶችን፣ የስኳር ተረፈ ምርቶችን እና የስኳር ተረፈ ምርት ውጤቶችን
በፋብሪካ ማዘጋጀትና ማምረት፣
•	 ምርቶቹንና ተረፈ ምርቶቹን ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
•	 አዳዲስና የማስፋፊያ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት፣ የዲዛይን ዝግጅት፣
የቴክኖሎጂ መረጣና ድርድር፣ የተከላና ኮሚሽኒንግ ስራዎች እንዲካሄዱ ማድረግ፣
•	 ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በሸንኮራ አገዳና በስኳር አመራረት ቴክኖሎጂ
ጥናትና ምርምር ማካሄድና ጠቃሚ ውጤቶችን በስራ ላይ ማዋል፣
•	 አቅሙ ካላቸው የሀገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች
የሚያስፈልጉ የማምረቻ መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች ዲዛይንና ፋብሪኬሽን ሥራዎች
በሀገር ውስጥ እንዲከናወኑ ማድረግ፣
•	 በሕግ መሰረት ለስራው የሚያስፈልገው መሬት ባለይዞታ መሆንና ማልማት፣
•	 የአገዳ ምርታቸውን ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የሚያቀርቡ አገዳ አብቃዮችን
ማበረታታትና መደገፍ፣
•	 ለስኳር ኢንዱስትሪ የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ሃይል በሚፈለገው አይነት፣ መጠንና
ጥራት ለማፍራት እንዲቻል ከሚመለከታቸው የትምህርት ተቋማት ጋር መተባበር፣
•	 የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የሚያወጣውን መመሪያና የፖሊሲ አቅጣጫ
መሰረት በማድረግ ቦንድ መሸጥና በዋስትና ማስያዝ እና ከአገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ
ምንጮች ጋር የብድር ውል መደራደርና መፈራረም፣
•	 ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን መስራት ናቸው፡፡
3ስኳር ኮርፖሬሽን
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የስኳር ፍላጎት
የደረሰበት ደረጃ ሲታይ የዛሬ 62 ዓመት
ገደማ በላንድሮቨር መኪና በየገበያው
በመዘዋወር ስኳርን ለማስተዋወቅ ብርቱ
ጥረት ተደርጎ እንደነበር ማመን ይከብዳል፡፡
በወቅቱ ሻይ በ”ቅመሱልኝ” በነጻ በመጋበዝ
ሕዝቡን ከምርቱ ጋር ለማላመድ የተደረገው
እንቅስቃሴ ከብዙ ጥረት በኋላ ውጤት
ማስገኘት ችሏል፡፡
በዚህ ሁኔታ የተጀመረው የስኳር ትውውቅ
ዛሬ ላይ ታሪኩን በመቀየር ሀገሪቱ
እያስመዘገበች ካለችው ተከታታይ የኢኮኖሚ
እድገት ጋር በተያያዘ በጣም ተፈላጊ ምርት
ሆኗል፡፡ 	
በሀገራችን ዘመናዊ የስኳር ኢንዱስትሪ
የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግሥት ኤች
ቪ ኤ (HVA) ከተባለ የሆላንድ ኩባንያ
ጋር የአክስዮን ስምምነት ከፈረመበት
ከ1943ዓ.ም አንስቶ ነው፡፡ ኩባንያው 5
ሺ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ማልሚያ መሬት
ተረክቦ ሥራውን የጀመረው ከአዲስ አበባ 110
ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በወንጂ
ከተማ ሲሆን፣ በቅድሚያ የወንጂ ስኳር
ፋብሪካን ገንብቶ መጋቢት 11 ቀን 1946ዓ.ም
ስራ አስጀምሯል፡፡ ፋብሪካው በወቅቱ በቀን
1 ሺ 400 ኩንታል ስኳር እያመረተ ምዕዙን
ስኳር እና ባለ 10 ሳንቲም እሽግ ስኳር ለገበያ
ያቀርብ ነበር፡፡
በወቅቱ የወንጂ አካባቢ በዓለማችን ከፍተኛ
ምርት ከሚያስመዘግቡና ለስኳር ምቹ ከሆኑ
አካባቢዎች አንዱ ስለነበር ከወንጂ ስኳር
ፋብሪካ ምስረታ ጋር ተያይዞ የወንጂ ከረሜላ
ፋብሪካ ሰኔ 1953ዓ.ም ተቋቁሞ ደስታ
ከረሜላ ለገበያ ማቅረብ ጀመረ፡፡
የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሥራ ከጀመረ ከዘጠኝ
ዓመት በኋላ በ1955ዓ.ም እዛው ወንጂ ላይ
የተቋቋመው የሸዋ ስኳር ፋብሪካ በቀን 1 ሺ
700 ኩንታል ስኳር ያመርት ነበር፡፡
ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በሚል የጋራ
መጠሪያ በአንድ አስተዳደራዊ መዋቅር
ስር ይተዳደሩ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ
ፋብሪካዎች አንድ ላይ በዓመት 750 ሺ
ኩንታል ስኳር ገደማ ያመርቱ እንደነበር
መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የወንጂ እና
ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ከግማሽ ምዕተ ዓመት
የስኳር ኢንዱስት
መግቢያ
4 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
በላይ ካገለገሉ በኋላ በእርጅና ምክንያት
እንደ ቅደም ተከተላቸው በ2004ዓ.ም
እና በ2005ዓ.ም መጨረሻ የተዘጉ ሲሆን፣
በምትካቸው አዲስ ዘመናዊ ፋብሪካ
ተገንብቶ ከ2006ዓ.ም ጀምሮ ስኳር
እያመረተ ይገኛል።
በኢትዮጵያ የስኳር አዋጭነትን የተረዳው
የሆላንዱ ኩባንያ በተመሳሳይ የመተሐራ
ስኳር ፋብሪካን ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ
ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መርቲ ከተማ
ሰኔ 26 ቀን 1957ዓ.ም በአክሲዮን መልክ
በመመስረት በ1962ዓ.ም ፋብሪካውን ሥራ
አስጀመረ፡፡
ይሁንና እነዚህ ፋብሪካዎች በ1967ዓ.ም
በሀገሪቱ በተደረገው የመንግሥት ለውጥ
ምክንያት ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ይዞታ
ስር ወደቁ፡፡ ይህን ተከትሎ በኢንዱስትሪ
ሚኒስቴር ሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር
58/1970 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ስኳር
ኮርፖሬሽን ወንጂ ሸዋ እና መተሐራ ስኳር
ፋብሪካዎችን ጨምሮ አዲስ ከተማና አስመራ
ከረሜላ ፋብሪካዎችን እንዲያስተዳድር
ተደረገ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከስኳር ልማት ጋር
በተያያዘ በፊንጫአ ሸለቆ በ1967ዓ.ም
በተካሄደ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት አካባቢው
ለስኳር ምርት አዋጭ ሆኖ ተገኘ፡፡ ይህን
ተከትሎም ለአገሪቱ ሦስተኛ የሆነውን
የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ለመገንባት ጠለቅ
ያለ ጥናት እንዲካሄድ ተወስኖ ቡከርስ
አግሪካልቸራል ኢንተርናሽናል ሊሚትድ
በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ አማካይነት
ከ1970ዓ.ም ጀምሮ ዝርዝር ጥናት ተካሄደ፡፡
በፋይናንስ እጥረት ሳቢያ ተጓቶ የነበረው
የፋብሪካው ግንባታ በ1981ዓ.ም፤ የሸንኮራ
አገዳ ተከላ ስራው ደግሞ በ1984ዓ.ም
ተጀመረ፡፡ ከስምንት ዓመት በኋላ
የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ በ1991ዓ.ም
ወደ መደበኛ የማምረት ሥራ ተሸጋገረ፡፡
ከቀደምቶቹ ስኳር ፋብሪካዎች በተሻለ
ዘመናዊ የሆነውን የፊንጫአ ስኳር ልማት
ፕሮጀክት የፋብሪካና ኤታኖል ግንባታ
ያከናወኑት ኤፍ.ሲ.ሼፈርና አሶሽየትስ የተባለ
የአሜሪካ ኩባንያና በእርሱ ስር የፋብሪካውን
ተከላ ያካሄደው ድዌቶ ኢንተርናሽናል የተባለ
የደች ኩባንያ ሲሆኑ፣ በግንባታው በርካታ
ትሪ በኢትዮጵያ
5ስኳር ኮርፖሬሽን
የስኳር ኢንዱስትሪ...
የሀገር በቀል ድርጅቶች ተሳትፈዋል፡፡
ልማቱ በዚህ መልክ እየተካሄደ ባለበት ወቅት አራት
ፋብሪካዎችን ያስተዳድር የነበረው የኢትዮጵያ ስኳር
ኮርፖሬሽን ከ14 ዓመታት ቆይታ በኋላ በ1984ዓ.ም
በሕግ ፈረሰ፡፡ በምትኩም በደንብ ቁጥር 88/85
መተሐራ ስኳር ፋብሪካ፤ በደንብ ቁጥር 88/85 ወንጂ
ሸዋ ስኳር ፋብሪካና በደንብ ቁጥር 199/86 ፊንጫኣ
ስኳር ፋብሪካ እራሳቸውን የቻሉ የመንግሥት ልማት
ድርጅቶች ሆነው እንዲቋቋሙ ተደረገ፡፡
ኋላም ለስኳር ፋብሪካዎቹ የጋራ አገልግሎት እንዲሰጥ
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ድጋፍ ሰጪ ማዕከል
አክስዮን ማህበር በሶስቱ ስኳር ፋብሪካዎች፣ በልማት
ባንክ እና በመድን ድርጅት በአክስዮን መልክ ህዳር
1990ዓ.ም ተቋቋመ፡፡ ከዓመታት በኋላም በማዕከሉ
ምትክ የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር
504/98 ተመስርቶ የስኳር ፋብሪካዎቹን በመቆጣጠር፣
በፕሮጀክት ልማት፣ በምርምር፣ በስልጠናና በግብይት
ረገድ ድጋፍ ሲሰጥ ቆየ፡፡
በዚህ ጊዜ ውስጥ የኢፌዲሪ መንግሥት የስኳር ልማቱን
ለማስፋፋት በማቀድ በአፋር ክልል የተገነባውን
አራተኛውን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በደንብ ቁጥር
122/98 አቋቋመ፡፡ ፋብሪካው በ50 ሺህ ሄክታር መሬት
ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀም
ሲሆን፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ በዓመት 3 ሚሊዮን
ኩንታል ስኳር እና 30 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል የማምረት
አቅም ያለው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ በዚህ መሰረት
የፋብሪካው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ስኳር
ማምረት ጀምሯል፡፡
6 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ልማት እንቅስቃሴው በዚህ መልክ ከቀጠለ በኋላ ከጥቅምት 19 ቀን 2003ዓ.ም ጀምሮ
የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኤጀንሲ እንዲፈርስ ተደርጎ በምትኩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
ቁጥር 192/2003 የስኳር ኮርፖሬሽን ተቋቋመ፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ በስራ አመራር
ቦርድ የሚተዳደር ሆኖ፣ የኢፌዲሪ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው
አዋጅ ቁጥር 916/2008 መሰረት ተጠሪነቱ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር
እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን
የስኳር ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ ስትራተጂያዊ
ማዕቀፍ
የሀገራችን ኢንዱስትሪ በኢኮኖሚው ውስጥ
የመሪነቱን ሚና እንዲጫወት የላቀ አስተዋጽኦ
ካላቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች መካከል
የስኳር ልማት አንዱ ነው። ኢትዮጵያ ይህን
ኤክስፖርት መር የሆነ የማኑፋክቸሪንግ
ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስፋፋትና
ምርታማነቱን ለማሳደግ የሚያስችል ከፍተኛ
የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሃብት አላት፡፡
በተለይም ሀገሪቱ ለሸንኮራ አገዳ ልማት
ተስማሚ አየር ንብረት፣ በመስኖ ሊለማ
የሚችል ሰፊ የእርሻ መሬት (ከ500ሺ
ሄክታር በላይ) እንዲሁም በቂ ውሃ ያላት
በመሆኑ ዘርፉ የበለጠ ትኩረት እንዲሰጠው
ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባሻገር መንግስት የሀገሪቱ
ህዝቦች ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ
በሚከተለው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት
በወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ እና ፊንጫአ ስኳር
ፋብሪካዎች ብቻ ለረጅም ዓመታት ያህል
ተወስኖ የቆየውን የስኳር ኢንዱስትሪ
በተለይም ከ2003ዓ.ም ወዲህ በደቡብ
ብ/ብ/ሕ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በአማራ እና
በትግራይ ክልሎች እያስፋፋ ይገኛል፡፡
በዚህ መሰረት በአማራና በቤኒሻንጉል
ጉሙዝ ክልሎች በጣና በለስ ስኳር ልማት
ፕሮጀክት በ50ሺ ሄክታር መሬት የሚለማን
የሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት የሚጠቀሙ
እያንዳንዳቸውበቀን12ሺቶንአገዳመፍጨት
የሚችሉ ሁለት የስኳር ፋብሪካዎች በግንባታ
ላይ ይገኛሉ፡፡
በተጨማሪም በደቡብ ብሔር፣
ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ፣
ቤንች ማጂ እና ካፋ ዞኖች በኦሞ ኩራዝ
ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ100 ሺህ ሄክታር
መሬት የሚለማን ሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት
የሚጠቀሙ እያንዳንዳቸው በቀን 12 ሺህ ቶን
አገዳ መፍጨት የሚችሉ ሦስት ፋብሪካዎችን
እንዲሁምበቀን24ሺህቶንአገዳየመፍጨት
አቅም ያለውን አንድ ፋብሪካ በጠቅላላው
አራት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት
7ስኳር ኮርፖሬሽን
የስኳርኢንዱስትሪ-የቀጠለ
ታቅዶ የፋብሪካዎቹ ግንባታ እየተካሄደ
ይገኛል፡፡ በተለይም የኩራዝ አንድ ስኳር
ፋብሪካ ምርት ለመጀመር በዝግጅት ላይ
ይገኛል፡፡
በተመሳሳይ በትግራይ ክልል
በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት
በ50ሺህ ሄክታር መሬት የሚለማን
የሸንኮራ አገዳ ተጠቅሞ በቀን 24ሺህ
ቶን አገዳ መፍጨት የሚችል የስኳር
ፋብሪካ እየተገነባ ነው፡፡
ምንም እንኳ ኢንዱስትሪው ከግማሽ
ምዕተ አመት በላይ እድሜ ያስቆጠረ
ቢሆንም፣
•	 ኢንዱስትሪው በሚፈልገው ፍጥነት
አለማደግ፣
•	 ሀገሪቱ በተከታታይ እያስመዘገበች
ካለችው ፈጣን የኢኮኖሚያዊ
እድገት ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡ
የስኳር ፍላጐት በከፍተኛ ደረጃ
እያደገ መምጣት፣
•	 ነባር የስኳር ፋብሪካዎች
የሚያመርቱት የስኳር መጠን
እያደገ የመጣውን የሀገር ውስጥ
ፍላጎት ማርካት አለመቻል፣
•	 የሕዝብ ቁጥር ማደግ እና
•	 ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ
ኢንዱስትሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ
ከመስፋፋት ጋር ተያይዞ የስኳር
ፍላጎትና አቅርቦት ሊጣጣም
አልቻለም፡፡
ሀገራዊ የስኳር አቅርቦት
አሁን ያለው ሀገራዊ የስኳር አቅርቦት መጠን
በዓመት ከ6 እስከ 6.5 ሚሊዮን ኩንታል
ያህል ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ባለፉት ዓመታት
ከ3.25 እስከ 4 ሚሊዮን ኩንታል የሚደርስ
ስኳር በሀገር ውስጥ የተመረተ ሲሆን፣
በፍላጎትና በአቅርቦት መካከል ያለው ከ2
እስከ 2.5 ሚሊዮን ኩንታል ልዩነት በከፍተኛ
የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን የአንድ ሰው አመታዊ
የስኳር ፍጆታ ከ10 ኪሎ ግራም በላይ
እንደሚደርስ ቢገመትም፣ እየቀረበ ያለው
መጠን ግን 7 ኪሎ ግራም ያህል ነው፡፡
ከዚህ አንጻር መንግሥት የስኳር ፍላጎትና
አቅርቦትን ለማጣጣም በየአመቱ ከፍተኛ
ድጎማ እያደረገ በውጭ ምንዛሪ ስኳር
ከውጪ ሀገር እያስገባ በተመጣጣኝ ዋጋ
ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡
ይሁንና ክፍተቱን ለመሙላት ስኳር ከውጭ
መግዛት ዘላቂ መፍትሔ ባለመሆኑና
በዚህ ሁኔታም መቀጠል ስለማይቻል
ከመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን
ዕቅድ ዘመን አንስቶ በሀገራችን ከፍተኛ
ትኩረት ከተሰጣቸው የማኑፋክቸሪንግ
የኢንዱስትሪ ዘርፎች አንዱ የስኳር
8 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
በስኳር ልማት ዘርፍ በመጀመሪያው
የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን
የተከናወኑ አበይት ተግባራት፡-
•	 በማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የወንጂ ሸዋና የፊንጫአ ነባር ስኳር ፋብሪካዎችን
በማዘመን የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ ተችሏል፡፡
•	 ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠንን በ2002ዓ.ም መጨረሻ ከነበረበት 2 ሚሊዮን 903 ሺ
740 ኩንታል በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ (2007ዓ.ም) ወደ 4 ሚሊዮን ኩንታል ለማሳደግ
ተችሏል፡፡
•	 የከሰምና የአርጆ ዲዴሳ አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችን ግንባታ በማጠናቀቅ ሥራ ማስጀመር
ተችሏል፡፡
•	 በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን
የሙከራ ምርት ማስጀመር ተችሏል፡፡
•	 የአገዳ ልማትን በተመለከተም በዕቅድ ዘመኑ ተጨማሪ 65 ሺ 363 ሄክታር መሬት
በአገዳ ለምቷል፡፡ ይህም በእቅዱ መነሻ ከነበረው 30ሺ 397 ሄክታር ጋር ሲነጻጸር የ215
በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡
•	 የኤታኖል የምርት መጠንም በ2002ዓ.ም ከነበረበት 7 ሚሊዮን 117 ሺህ ሊትር በእቅድ
ዘመኑ መጨረሻ ወደ 19 ሚሊዮን 804 ሺህ ሊትር ከፍ ብሏል፡፡ ከዚህ ውስጥ 18 ሚሊዮን
480 ሺህ ሊትር ከቤንዝል ጋር ተቀላቅሎ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡
•	 የአገዳ ምርታማነትን ያሳደጉ በርካታ የምርምር ሥራዎችም ተከናውነዋል፡፡
ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ ሊሆን ችሏል፡፡
በዚህ መሰረት መንግሥት፡-
•	 የስኳር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም፣
•	 በዘርፉ ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር
የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል፣
•	 በተለይም በልማቱ አካባቢዎች የሚኖሩ
ሕዝቦች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እና
•	 ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ የውጪ
ምንዛሪ ለማስገኘት ግዙፉ የተንዳሆ
ስኳር ፋብሪካን ከመገንባት አንስቶ
“የስኳር አብዮት” በሚያስብል ሁኔታ
በተለያዩ የሀገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች
መጠነ ሰፊ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች
በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
9ስኳር ኮርፖሬሽን
•	 የጊዜያዊ ግድብ (ኮፈር ዳም) እና
የውሃ መቀልበሻ (ዊር)፣ የሰፋፊ መስኖ
መሰረተ ልማት አውታሮች፣ የውስጥ
ለውስጥ መንገዶች፣ የቤቶች እና የግዙፍ
አዳዲስ ፋብሪካዎች ግንባታ እንዲሁም
የመሬት ዝግጅት ሥራዎች በስፋት
ተካሂደዋል፡፡
•	 31 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል
ወደ ብሔራዊ የሃይል ቋት ማስገባት
ተጀምሯል፡፡
•	 ልማቱን ተከትሎም አነስተኛ ከተሞችና
በርካታ መንደሮች ተመስርተዋል፡፡
•	 በአጠቃላይ በዕቅድ ዘመኑ ባጋጠሙ
የተለያዩ ተግዳሮቶች በዘርፉ
የታቀደውን ያህል ውጤት ማግኘት
ባይቻልም እንኳ፣ በተከናወኑ መጠነ
ሰፊ ሥራዎች ሀገሪቱ ወደፊት በስኳር
ምርት በዓለም ገበያ ከፍተኛ ድርሻ
እንዲኖራት የሚያስችሉ መደላድሎችን
ለመፍጠር ተችሏል፡፡
የማህበረሰብ ተጠቃሚነት
•	 ልማቱን ተከትሎ በርካታ የማኅበራዊ
አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ትምህርት
ቤት፣ ጤና ተቋማት፣ ወፍጮ ወዘተ)
እና የመሰረተ ልማት አውታሮች
(ንጹህ መጠጥ ውሃ፣ መንገድ ወዘተ)
ተገንብተው የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች
ተጠቃሚ በመሆን የኑሮ ደረጃቸው
መሻሻል ጀምሯል፡፡
•	 ለአካባቢው ተወላጆች ልጆች ቅድሚያ
በመስጠትና በትራክተር ኦፕሬተርነት፣
በግምበኛነት፣ በአናጺነት፣ በጥበቃና
በመሳሰሉት ሙያዎች በማሰልጠን
በየፕሮጀክቶቹ ተመድበው እንዲሰሩ
ተደርጓል፡፡
•	 የአካባቢው ወጣቶች በጥቃቅንና
አነስተኛ ማኅበራት ተደራጅተው
በልማቱ ሥራ ውስጥ እንዲሳተፉና ገቢ
እንዲገኙ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
•	 በመስኖ የለማ መሬት ለአካባቢው
ነዋሪዎች አመቻችቶ በማስረከብ
በተለይም በስኳር ልማት ፕሮጀክቶች
አካባቢ የሚገኘው ማህበረሰብ እንደ
በቆሎ የመሳሰሉ ሰብሎችን አምርቶ
እንዲጠቀም ተደርጓል፡፡ በቀጣይም
ማህበረሰቡ በዘላቂነት ሸንኮራ አገዳ
አልምቶ ለፋብሪካ እንዲያቀርብ
ለማስቻል ለወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ
አገዳ አብቅለው ከሚያቀርቡ አርሶ
10 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
አደሮች (አውት ግሮወርስ) ልምድ እንዲያገኝ የሚያስችል እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
•	 በአጠቃላይ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አመታት በዘርፉ ከ350
ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች ቋሚ፣ ጊዜያዊና የኮንትራት የሥራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡
11ስኳር ኮርፖሬሽን
የስኳር ኢንዱስትሪ ቅኝት በንጽጽር
12 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
አሮጌውና አዲሱ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች
13ስኳር ኮርፖሬሽን
በስኳር ልማት ዘርፍ በሁለተኛው
የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን
የታቀዱ አበይት ተግባራት
•	 የህብረተሰቡን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት በዘላቂነት ማሳደግ፣
•	 ልማቱ በሚፈጥረው የስራ ዕድል በቋሚነት፣ በጊዜያዊነት፣ በኮንትራትና በማህበራት
ከ637 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል መፍጠር፣
•	 በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ግንባታቸው ተጀምሮ በተለያዩ
የአፈጻጸም ደረጃዎች የሚገኙ ሰባት አዳዲስ ፋብሪካዎችን ማለትም የኦሞ ኩራዝ 1፣ 2፣ 3
እና 5፤ የጣና በለስ 1 እና 2 እንዲሁም የወልቃይት ስኳር ፋብሪካዎችን ግንባታ አጠናቆ
ሥራ ማስጀመር፣
•	 ዓመታዊ የስኳር መጠንን በዕቅድ ዓመቱ መጨረሻ ወደ 2.8 ሚሊዮን ቶን በማሳደግ
የሀገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማርካት ባሻገር ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ ከፍተኛ
የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት፣
•	 ዓመታዊ የኢታኖል ምርት መጠንን በዕቅድ ዓመቱ መጨረሻ 28 ሚሊዮን 105 ሺ ሊትር
ማድረስ፣
•	 ከፍተኛ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ማስገባት፣
•	 የመስኖ መሰረተ ልማትና የቤቶች ግንባታን በስፋትና በጥራት ማካሄድ፣
•	 የሸንኮራ አገዳ ልማትን ከማስፋፋት አኳያም፣ በ2007 በጀት ዓመት መጨረሻ በአገዳ
ከተሸፈነው 95 ሺህ 760 ሄክታር መሬት በተጨማሪ በዕቅድ ዘመኑ 211 ሺህ 564 ሄ/ር
በመትከል በ2012ዓ.ም መጨረሻ 307 ሺህ 324 ሄክታር ላይ ማድረስ፣
•	 በተጓዳኝ ምርቶችም በሰብልና ፍራፍሬ እንዲሁም በእንስሳት ሃብት ልማት ሰፊ ስራዎችን
ማከናወን ናቸው፡፡
14 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
I. ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ
ስኳር ፋብሪካዎች
በሀገራችን የስኳር ፋብሪካ ታሪክ ፋና ወጊ
የሆነው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ በ1946ዓ.ም
ግንባታው ተጠናቆ ማምረት የጀመረ ሲሆን፣
የሸዋ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ እዛው ወንጂ ላይ
በ1955ዓ.ም ተመርቆ ስራ የጀመረ ሌላኛው
ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ ሁለቱም ስኳር
ፋብሪካዎች ኤች ቪ ኤ በተባለ የሆላንድ
ኩባንያ የተገነቡና በኩባንያውና በመንግሥት
የጋራ ባለቤትነት በሽርክና የተቋቋሙ ነበሩ፡፡
በአንድ አስተዳደር ስር እየተዳደሩ ስኳር
ያመርቱ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ ፋብሪካዎች
በእርጅና ምክንያት ስራቸውን እስካቆሙበት
ጊዜ ማለትም ወንጂ እስከ 2004ዓ.ም
እንዲሁም ሸዋ እስከ 2005ዓ.ም መጨረሻ
ድረስ የነበራቸው አማካኝ አመታዊ ስኳር
የማምረት አቅም 75ሺህ ቶን ወይም 750
ሺህ ኩንታል ነበር፡፡
ነባሩን የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በአዲስና
ዘመናዊ ፋብሪካ ለመተካት የማስፋፊያ
ፕሮጀክት በፋብሪካ እና በእርሻ ዘርፍ
ተከናውኖ የፋብሪካ ማስፋፊያ ስራው
በ2005ዓ.ም መጨረሻ ላይ ተጠናቀቀ፡፡
በ2006ዓ.ም መጀመሪያ ላይም ፋብሪካው
ሥራ ጀመረ፡፡
አዲሱ ስኳር ፋብሪካ የተገነባው ነባሮቹ
በሚገኙበት የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ
ዞን ዶዶታ ወረዳ ቢሾላ ቀበሌ ገበሬ ማህበር
ነው፡፡
ከአዲስአበባበ110ኪ.ሜርቀትላይየሚገኘው
ይህ ፋብሪካ አሁን ባለበት ደረጃ በቀን
6ሺህ 250 ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት
ከ174ሺህ ቶን በላይ ስኳር የማምረት አቅም
አለው፡፡ ወደፊት የማምረት አቅሙን በሂደት
በማሳደግ በቀን ወደ 12ሺህ 500 ቶን አገዳ
እየፈጨ ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠኑን
እስከ 222ሺህ 700 ቶን እንደሚያሳድግ
15ስኳር ኮርፖሬሽን
ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡
ከዚህ ዘመናዊ የስኳር ፋብሪካ ተረፈ
ምርት በዓመት እስከ 12 ሚሊዮን
800ሺህ ሊትር የሚደርስ ኤታኖል
ለማምረት የሚያስችል የኤታኖል ፋብሪካ
ለመገንባት ታቅዷል፡፡ የኤሌክትሪክ
ኃይል በማመንጨት ረገድም 31 ሜጋ
ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 11
ሜጋ ዋቱን ለራሱ ተጠቅሞ፣ ቀሪውን 20
ሜጋ ዋት ለብሔራዊ የኃይል ቋት እያስገባ
ይገኛል፡፡
የፋብሪካው የአገዳ እርሻ ማስፋፊያ
ፕሮጀክት ዋቄ ጢዮ፣ ሰሜን ዶዶታ
እና ወለንጪቲ ተብለው በሚታወቁ
አካባቢዎች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የእርሻ
ማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ
ሲጠናቀቅ አዲሱ ፋብሪካ በአጠቃላይ
16ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት
ይኖረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከለማው 12ሺህ 800
ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት ውስጥ
7ሺህ ሄክታሩ በፋብሪካው አካባቢ
በሚገኙ በ32 የሸንኮራ አገዳ አብቃይና
አቅራቢ ማኀበራት በታቀፉ 9ሺህ
100 አርሶ አደር አባላት የለማ ነው፡፡
በዚህም አባላቱ በሚያገኙት ከፍተኛ ገቢ
ከልማቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ለአብነት
በአንዳንድ ማህበራት በአማካይ በየ18
ወራት በሚደረግ የትርፍ ክፍፍል አባላት
እንደየስራቸው መጠን በነፍስ ወከፍ
ከ50ሺህ እስከ 240ሺህ ብር ድረስ ገቢ
ያገኙበትን አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡
ፋብሪካው ለአርሶ አደሮቹ በመስኖ የለማ
መሬት በማዘጋጀት፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት
በማመቻቸት፣ ሙያዊና ቴክኒካዊ
ድጋፍ በመስጠት አርሶ አደሮቹ ሸንኮራ
አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በመሸጥ
ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን
ፈጥሯል፡፡
ወንጂሸዋስኳርፋብሪካ
16 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
II. መተሐራ ስኳር ፋብሪካ
17ስኳር ኮርፖሬሽን
ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በመቀጠል
በሆላንዱ ኤች ቪ ኤ ተገንብቶ በ1962ዓ.ም
ወደ ስራ የገባው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
ከአዲስ አበባ በ200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ
ይገኛል፡፡ ፋብሪካው ከ10ሺህ ሄክታር በላይ
በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ መሬት ያለው ሲሆን፣
ዓመታዊ አማካይ ስኳር የማምረት አቅሙ
በዓመት 136ሺህ 692 ቶን ይደርሳል፡፡
ፋብሪካው ባካሄደው የማስፋፊያ ፕሮጀክት
የኤታኖል ፋብሪካ ገንብቶ ከ2003ዓ.ም
አጋማሽ ጀምሮ ኤታኖል በማምረት ላይ
ይገኛል፡፡ ኤታኖል የማምረት ዓመታዊ
አቅሙም በአመት እስከ 12.5 ሚሊዮን
ሊትር ይሆናል፡፡ በተጨማሪ “ባጋስ” ተብሎ
ከሚጠራው የሸንኮራ አገዳ ገለባ 9 ሜጋ ዋት
የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት የራሱን
የኃይል ፍላጎት እያሟላ የሚገኝ እድሜ ጠገብ
ፋብሪካ ነው፡፡
ስለ መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሲነገር
የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍናን ማንሳት
የግድ ይላል፡፡ ፋብሪካው ካይዘንን
በሚገባ በመተግበርና ውጤት በማስመዝገብ
ቀዳሚ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ በሀገር አቀፍ
ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የካይዘን
ውድድር በተቋም፣ በልማት ቡድንና
በግለሰብ አንደኛ በመሆን የዋንጫና
የሜዳሊያ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡
በዚህ ብቻ አላበቃም በተመሳሳይ መስከረም
8 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን
ሆቴል በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የካይዘን
ውድድርላይካይዘንንበማስቀጠልበተቋምና
በልማት ቡድን ደረጃ በድጋሚ የአንደኝነት
የክብር ሜዳሊያዎችንና ዋንጫዎችን
ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም
ደሳለኝ እጅ ተቀብሏል፡፡
III. ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ
18 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ
በምዕራብ አቅጣጫ 350 ኪ.ሜ ርቀት ላይ
በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን
በአባይ ጮመን ወረዳ በፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ
ልዩ ስሙ አገምሳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ
ይገኛል፡፡
የፊንጫአ ሸለቆ ለስኳር ኢንዱስትሪ ተስማሚ
ሆኖ በመገኘቱ ቡከርስ አግሪካልቸራል
ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተባለ የእንግሊዝ
ኩባንያ ከ1970ዓ.ም ጀምሮ የቦታው
አዋጭነት፣ የመሬቱ አቀማመጥና የአፈር
ይዘት ሁኔታ ላይ ዝርዝር ጥናት ተካሂዶ
አዋጭነቱ ተረጋገጠ፡፡
የአፍሪካ ልማት ባንክና የአፍሪካ ልማት
ፈንድ፣ የስዊዲን፣ የአውስትራሊያና የስፔን
መንግስታት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ባንኮች
የፋይናንስ ምንጮች መሆናቸው ተረጋግጦ
የፕሮጀክቱ ሥራ ጥር 1981ዓ.ም ተጀመረ፡፡
ከፊንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ እና ምስራቅ
የሚገኘውን ቦታ ጨምሮ የፊንጫአ ስኳር
ፋብሪካ ጠቅላላ ይዞታ (ኮማንድ ኤሪያ)
67ሺህ 98 ሄክታር ነው፡፡ የፊንጫአ ሸለቆ
ውስጥ በማለፍ ለሃይድሮ ኤሌክትሪክ
ማመንጫነት ከዋለ በኋላ ሸለቆውን ከሁለት
ከፍሎ ወደ ሰሜን በመጓዝ ከአባይ ወንዝ ጋር
በሚቀላቀለው የፊንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ
ክፍል (ዌስት ባንክ) ያለውን 6ሺህ 476.72
ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ በማልማት
እና የፋብሪካ
ተከላ በማከናወን
ነበር የፊንጫአ
ስኳር ፋብሪካ
የተገነባው፡፡
የአካባቢው ከፍታ
ከባህር ወለል
በላይ ከ1ሺህ 350
እስከ 1ሺህ 600
ሜትር ይደርሳል፡፡
በሸለቆው ውስጥ
ያለው ከፍተኛው የሙቀት መጠን 31 ዲግሪ
ሴንቲግሬድ ሲሆን፣ ዝቅተኛው 15 ዲግሪ
ሴንቲግሬድ ይሆናል፡፡ ዓመታዊ የዝናብ
መጠኑም በአማካይ 1ሺህ 300 ሚሊ ሊትር
ይጠጋል፡፡ ይህም የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ
አካባቢን “ለምለም በረሃ” በሚል ልዩ ስም
እንዲታወቅ አድርጎታል፡፡
ፋብሪካው ኢታኖልን በማምረት ከቤንዚል
ጋር ተደባልቆ ለተሸከርካሪዎች በነዳጅነት
እንዲውል ከሚሰጠው አገልግሎት
በተጨማሪ ለሌሎች ኢንዱስትሪዎችም
በግብዓትነት በማገልገል ለሀገራችን ኢኮኖሚ
ጉልህ ድርሻ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡ የነባሩ
ፋብሪካ ግንባታ ተጠናቆ የሙከራ ምርት
የጀመረው የካቲት 1990ዓ.ም ቢሆንም
መደበኛ የማምረት ስራውን የጀመረው ግን
በ1991ዓ.ም ነበር፡፡
የፋብሪካው አጠቃላይ የማስፋፊያ ፕሮጀክት
19ስኳር ኮርፖሬሽን
የፊንጫአስኳርፋብሪካአጠቃላይየማስፋፊያ
ፕሮጀክት የተጀመረው በ1998ዓ.ም ነው፡፡
በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በአገዳ ልማት
በኩል በዌስት ባንክ 8ሺህ 300 ሄክታር
በአገዳ የተሸፈነ መሬት እና የኢስት ባንክ
እና ነሼ አካባቢዎችን በማከል ወደ 21ሺህ
ሄክታር መሬት ለማሳደግ የታቀደ ሲሆን፣
ከዚህ ውስጥ 7ሺህ ሄክታር በኢስት ባንክ
እንዲሁም 4ሺህ 670 ሄክታር በነሼ አካባቢ
ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የፋብሪካውን አገዳ
የመፍጨት አቅም በማሳደግ አመታዊ የስኳር
ምርቱን ወደ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል
እንዲሁም ኤታኖል የማምረት አቅሙን ወደ
20 ሚሊዮን ሊትር ከፍ ለማድረግ ታቅዶ
የማስፋፊያ ሥራው ተካሄደ፡፡
የፋብሪካው ማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራ
ተጠናቆ ከ2006ዓ.ም ጀምሮ ወደ ማምረት
ሂደት ውስጥ የገባ ሲሆን፣ በእርሻ ማስፋፊያ
ስራም ከ19ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በአገዳ
ለመሸፈን ተችሏል፡፡
በዚህ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በቀን 6ሺህ
600 ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት
1ሚሊዮን 600ሺህ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ
ነጭ ስኳር የማምረት አቅም ያለው አንድ
ተጨማሪ የስኳር ፋብሪካ ተገንብቷል፡፡
ይህ ደግሞ ነባሩ ፋብሪካ ካለው አቅም ጋር
ተዳምሮ አጠቃላይ በሁለቱም ፋብሪካዎች
የሚመረተውን አመታዊ የስኳር መጠን 2
ሚሊዮን 700ሺህ ኩንታል ያደርሰዋል፡፡
ለመኖሪያ መንደሮችና ለፋብሪካው
አገልግሎት የሚውል የኃይል አቅርቦትን
በተመለከተም ፋብሪካው በመሰረታዊነት
የራሱን የኃይል ምንጭ ቀደም ሲልም
በመጀመሪያው ምዕራፍ ከተተከለ ሁለት ባለ
3.5 ሜጋ ዋት የእንፋሎት ተርባይን ያሟላ
ነበር፡፡ በማስፋፊያ የተገነባው ሁለት ባለ 12
ሜጋ ዋት የእንፋሎት ተርባይን ሲጨመርም
በድምሩ 31 ሜጋ ዋት ማመንጨት ይችላል፡፡
ከዚህ ውስጥ ለፋብሪካው እና ለመስኖ
ፓምፖች እንዲሁም ለሠራተኛ መኖሪያ
መንደሮች እና ለልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫ
ተቋማት 21 ሜጋ ዋት የሚያስፈልግ ሲሆን፣
ቀሪውን 10 ሜጋ ዋት ደግሞ ወደ ብሔራዊ
የኃይል ቋት ማስገባት ተጀምሯል፡፡
IV. ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ
20 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
በአዋሽ ተፋሰስ ዝቅተኛው አካባቢ በአፋር
ክልል በ50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ
የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት
የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ
ከአዲስ አበባ በ670 ኪሎ ሜትር ርቀት
ላይ ይገኛል፡፡
በግዙፍነቱ እና በተሻለ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ
ተጠቃሚነቱ ጭምር ከሌሎቹ ነባር ስኳር
ፋብሪካዎች የሚለየው ይህ ፋብሪካ
ከሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ በስተምስራቅ
ወደ ጅቡቲ የሚወስደውን መንገድ
ተከትሎ ከጅቡቲ ወደብ በ300 ኪ.ሜ
ርቅት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ምቹ ሁኔታም
ወደፊት የፋብሪካውን ምርት ወደ ውጭ
ለመላክ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
በ1998ዓ.ም የፕሮጀክት ሥራው የተጀመረው
የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ይዞታ በሚሌ፣
በዱብቲ፣ በአሳኢታ እና በአፋምቦ ወረዳዎች
ውስጥ ይገኛል፡፡ ግንባታው OIA (Overseas
Infrastructure Alliance) በተባለ የህንድ
ኩባንያ የሚካሄደው ግዙፉ የተንዳሆ ስኳር
ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፍ ጥቅምት
2007ዓ.ም የሙከራ ምርት ጀምሮ በአሁኑ
ወቅት በመደበኛ የምርት ሂደት ውስጥ
ይገኛል፡፡
ፋብሪካው ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ
ሲደርስ በቀን 13ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት
በዓመት 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የማምረት
አቅም ይኖረዋል፡፡
በተጨማሪም ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ
ማምረት ሲጀምር ከሚያመነጨው 60 ሜጋ
ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 38 ሜጋ ዋቱን
21ስኳር ኮርፖሬሽን
ለብሔራዊ የኃይል ቋት በማስገባት እንዲሁም
31 ሚሊዮን ሊትር ያህል ኤታኖል በማምረት
ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን
ያረጋግጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ለፋብሪካው በግብዓትነት ከሚያስፈልገው
በ50ሺህ ሄክታር መሬት ከሚለማ የሸንኮራ
አገዳ ውስጥ 25ሺህ ሄክታሩ የሚለማው
በፋብሪካው ሲሆን፣ ቀሪው 25ሺህ ሄክታር
መሬት ደግሞ በአካባቢው በሚገኙ አገዳ
አብቃይና አቅራቢ አርብቶ አደሮች የሚለማ
ነው፡፡ የአገዳ ልማቱ በመከናወን ላይ
የሚገኘው በአዋሽ ወንዝ ላይ በተገነባው
የተንዳሆ ግድብ አማካኝነት ሲሆን፣ ከ1.86
ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ በላይ የመያዝ
አቅም ያለው ይህ ግድብ 60ሺህ ሄክታር
መሬት እንደሚያለማ ይጠበቃል፡፡
ፋብሪካው በመስኖ የሚለማ መሬት
ለአካባቢው አርብቶ አደሮች በማመቻቸቱም
አርብቶ አደሩ ወደ ከፊል አርሶ አደርነት
መሸጋገር የቻለበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ
ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል፡፡
የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ
•	 በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከ22 ሺህ 835
ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ሆኗል፤
•	 ከ42 ኪ/ሜ በላይ የዋና ቦይና ተያያዥ
ስትራክቸሮች ግንባታ ተከናውኗል፤
የአገዳ ልማት
•	 በመጀመሪያው ዙር 20 ሺህ 866
ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤
የቤቶች ግንባታ
•	 175 የመኖሪያ ቤቶች እና ለተለያዩ
አገልግሎቶች የሚውሉ 429 ሕንጻዎች
(ብሎኮች) ተገንብተዋል፤
22 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
V.የከሰም ስኳር ፋብሪካ
ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ፣ ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ 50 ኪ.ሜ ያህል የሚርቀው ይህ
ፋብሪካ፣ በአፋር ክልል በዞን ሦስት አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች ውስጥ ይገኛል፡፡
ፕሮጀክቱ 500 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ባለው የከሰም ግድብ አማካኝነት
በ20ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ በማልማት ላይ ይገኛል፡፡ የአገዳ ልማቱም
የሚከናወነው በከሰም እና ቦልሀሞን በተሰኙ አካባቢዎች ነው፡፡
የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ሆኖ
የተጀመረ ቢሆንም ስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመ ወዲህ ቦታው ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
ካለው ርቀት አንፃር ተመዝኖና ተጠንቶ እራሱን ችሎ እንደ አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲንቀሳቀስ
ተደርጓል፡፡
ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ፣ በ2007ዓ.ም መጨረሻ ላይ
የሙከራ ምርት ጀምሯል፡፡ አሁን ስኳር እያመረተ ሲሆን፣ በሂደት በቀን 6ሺህ ቶን አገዳ
የመፍጨት አቅም ላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ ፋብሪካው በቀጣይም 10ሺህ ቶን ሸንኮራ
አገዳ በቀን ወደሚፈጭበት ደረጃ እያደገ የሚሄድ ሲሆን፣ የኤታኖል ፋብሪካና የኮጀነሬሽን
ፋሲሊቲም ይኖረዋል፡፡
23ስኳር ኮርፖሬሽን
ፋብሪካው በመጀመሪያ ምዕራፍ 1 ሚሊዮን 530ሺህ ኩንታል ስኳር እና 12 ሚሊዮን 500ሺህ
ሊትር ኢታኖል በዓመት የማምረት አቅም የሚኖረው ሲሆን፣ ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ
ሲደርስ ደግሞ በዓመት 2 ሚሊዮን 600ሺህ ኩንታል ስኳር እና 30 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል
ማምረት ይችላል፡፡ ከዚህ ባሻገር 26 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 15 ሜጋ
ዋቱን ለብሔራዊ የኃይል ቋት እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡
የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ
•	 2ሺህ 946 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤
•	 የ20.5 ኪ.ሜ የዋና ቦይ ግንባታ ተጠናቋል፤
የአገዳ ልማት
•	 በፋብሪካው አማካኝነት 2ሺህ 413 ሄክታር መሬት እንዲሁም በአሚባራ እርሻ ልማት (አውት
ግሮወር) 6ሺህ ሄክታር መሬት በአጠቃላይ 8 ሺህ 443 ሄክታር በአገዳ ተሸፍኗል፤
የቤቶች ግንባታ
•	 517 የመኖሪያ ቤቶች እና 20 አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤
24 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት
በምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል
በምስራቅ ወለጋ እና በኢሉ አባቦራ ዞኖች
በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ ከአዲስ አበባ - ጅማ -
በደሌ - ነቀምቴ መስመር በ540 ኪ.ሜ ርቀት
ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ በኢሉአባቦራ፣
በምስራቅ ወለጋና በጅማ ዞኖች ውስጥ
የሚገኙ 49 ቀበሌዎችን የሚያካትት ነው፡፡
የአካባቢው ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ
በአማካይ 1350 ሜትር ሲሆን፣ የአየር
ሁኔታው ሞቃታማ ነው፡፡ አመታዊ አማካይ
የዝናብ መጠኑ ደግሞ 1400 ሚሊ ሊትር
ይደርሳል፡፡ የዝናብ ስርጭቱም ከግንቦት
እስከ ጥቅምት ይዘልቃል፡፡ በአብዛኛው
ጥቁርና አልፎ አልፎ ቀይ ቡናማ አፈር
የሚገኝበት ይህ አካባቢ ከአየር ንብረቱ
ጋር ተዳምሮ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ምቹና
ተስማሚ እንዲሆን አስችሎታል፡፡
AL-Habasha Sugar Mills PLC ከተባለ
የፓኪስታን ኩባንያ በ2005ዓ.ም ወደ ስኳር
ኮርፖሬሽን ይዞታነት የተሸጋገረው ይህ
ፋብሪካ በሂደት በ20 ሺህ ሄክታር መሬት
የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት
በመጠቀም በቀን 8 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት
አቅም ላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡
ፕሮጀክቱ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን
በተዘዋወረበት ወቅት የፋብሪካው የግንባታ
ስራ ከ90 በመቶ በላይ ተጠናቆ የነበረ
ሲሆን፣ ከ2005 በጀት ዓመት ጀምሮ የስራ
VI. አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ
25ስኳር ኮርፖሬሽን
አመራር አባላት ተመድቦለትና በየደረጃው የሰው ኃይል ተሟልቶለት ተልዕኮውን ለማሳካት
እየሰራ ይገኛል፡፡
ፋብሪካው በግብአትነት የሚጠቀምበትን ሸንኮራ አገዳ ለማልማት ውሃ ከዲዴሳ ወንዝ
የሚያገኝ ሲሆን፣ ከስኳር ምርቱ በተጨማሪ ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም የኤሌክትሪክ
ኃይል በማመንጨት ራሱን ከመቻል አልፎ ቀሪውን ለብሔራዊ የኃይል ቋት እንደሚያበረክት
ይጠበቃል፡፡ ከፍተኛ የኤታኖል ምርት የማምረት አቅምም አለው፡፡
ፋብሪካው ግንቦት 6 ቀን 2007ዓ.ም በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ
ተመርቆ ስኳር ማምረት ጀምሯል፡፡
የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ
•	 1ሺ 660 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል
የአገዳ ልማት
•	 3ሺህ 448 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤
የቤቶች ግንባታ
•	 64 የመኖሪያ ቤቶች እና ሁለት አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤
26 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የፕሮጀክቱ ዋና ካምፕ ከአዲስ አበባ በደቡብ
አቅጣጫ 900 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
የስኳር ልማቱ በደቡብ ብሔር፣ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን የሰላማጎ
እና የኛንጋቶም ወረዳዎች፣ በቤንች ማጂ
ዞን የሱርማ እና የሜኢኒትሻሻ ወረዳዎች
እንዲሁም በካፋ ዞን የዴቻ ወረዳ የተመረጡ
አካባቢዎች እየተካሄደ ነው፡፡ በፕሮጀክቱ
በ100ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ
የሸንኮራ አገዳ የሚጠቀሙ አራት ስኳር
ፋብሪካዎች እየተገነቡ ነው፡፡
ከእነዚህ ውስጥ ሶስቱ እያንዳንዳቸው
በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት
278ሺህ ቶን ስኳር እንዲሁም እያንዳንዳቸው
በዓመት 26ሺህ 162 ሜትር ኩብ ኤታኖል
ያመርታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አንዱ
ፋብሪካ ደግሞ በቀን 24ሺህ ቶን አገዳ
በመፍጨት በዓመት 556ሺህ ቶን ስኳር
እንዲሁም በዓመት 52ሺህ 324 ሜትር ኩብ
ኤታኖል ያመርታል፡፡
ለሸንኮራ አገዳ ልማቱ የሚያስፈልገው
I ኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት
በተለያየ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚገኙ
የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብረካ
27ስኳር ኮርፖሬሽን
የመስኖ ውሃ ኦሞ ወንዝ ላይ በሚገነባና 381 ሜትር ስፋት እና 22.4 ሜትር ከፍታ በሚኖረው
የውኃ መቀልበሻ ዊር አማካይነት የሚገኝ ነው፡፡
በፕሮጀክቱ የሚገነቡት አራቱ ስኳር ፋብሪካዎች ሙሉ የማምረት አቅማቸው ላይ ሲደርሱ
በአጠቃላይ በዓመት እስከ 13 ሚሊዮን 390ሺህ ኩንታል ስኳር እና 130 ሚሊዮን 810ሺህ
ሊትር ኤታኖል ማምረት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም 415 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል
በማመንጨት 275 ሜጋ ዋቱን ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ያስገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በፕሮጀክቱ እየተገነቡ ያሉት አራቱም ስኳር ፋብሪካዎች በሁለተኛው የእድገትና
ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ወደ ምርት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብረካ
28 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
ኦሞ ኩራዝ-1 ስኳር ፋብሪካ
•	 በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ
ኮርፖሬሽን (METEC) እየተገነባ
የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ-1 ስኳር ፋብሪካ
በ2009ዓ.ም ወደ ምርት ይገባል ተብሎ
ይጠበቃል፤
•	 ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት
ሲጀምር በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ
የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፤
የመስኖ መሠረተ ልማት
•	 ለኩራዝ 1 እና ኩራዝ 2 ፋብሪካዎች
በ100 ኪሎ ሜትሮች የሚቆጠሩ
የሁለተኛ፣ ሶስተኛና አራተኛ ቦዮችና
ተያያዥ ግንባታዎች ተጠናቀው ከ16
ሺህ 141 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤
የአገዳ ልማት
•	 ለኦሞ ኩራዝ 1፣2 እና 3 ፋብሪካዎች
12 ሺህ 903 ሄክታር መሬት በአገዳ
ተሸፍኗል፤
የቤቶች ግንባታ
•	 በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 830 መኖሪያ
ቤቶችና 29 አገልግሎት መስጫ
ተቋማት (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤
ኦሞ ኩራዝ-2 ስኳር ፋብሪካ
•	 ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ
እየተገነባ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ 2
ፋብሪካ በ 2009ዓ.ም ሥራ ለመጀመር
የሚያስችለው ደረጃ ላይ ይገኛል፤
•	 ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት
ሲጀምር በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ
የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፡፡
ኦሞ ኩራዝ-3 ስኳር ፋብሪካ
•	 በተመሳሳይ ኮምፕላንት በተባለ የቻይና
ኩባንያ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ፋብሪካ
በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን
12ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም
ይኖረዋል፤
ኦሞ ኩራዝ-5 ስኳር ፋብሪካ
•	 ፋብሪካውን ለመገንባት JJIEC ከተባለ
የቻይና ኩባንያ ጋር የኮንትራት ውል
ተፈርሞ የሲቪል ስራው ተጀምሯል፤
•	 ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት
ሲጀምር በቀን 24ሺህ ቶን አገዳ
የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፤
29ስኳር ኮርፖሬሽን
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብረካ
30 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
II. ጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት
ከአዲስ አበባ 576 ኪ.ሜ ርቀት ላይ
የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት በዋናነት የሚገኘው
በአማራ ክልል ሲሆን፣ የተወሰነ የአገዳ እርሻ
ልማቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚካተት
ነው፡፡
በዚህ ፕሮጀክት እያንዳንዳቸው በቀን
12ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያላቸው
ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች እየተገነቡ ሲሆን፣
በ50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማን
የሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት ይጠቀማሉ፡፡
ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚውለው የመስኖ
ውሃ የሚገኘው በበለስ ወንዝ ላይ በተገነባ
የውሃ መቀልበሻ ዊር አማካይነት ነው፡፡
ፋብሪካዎቹ ሙሉ የማምረት አቅማቸው ላይ
ሲደርሱ እያንዳንዳቸው በዓመት 2 ሚሊዮን
420ሺህ ኩንታል ስኳር እና 20 ሚሊዮን
827ሺህ ሊትር ኤታኖል የማምረት አቅም
ይኖራቸዋል፡፡ በፕሮጀክቱ በመገንባት ላይ
የሚገኙት ሁለቱ ፋብሪካዎች በሁለተኛው
የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን
ግንባታቸው ተጠናቆ ስራ ይጀምራሉ ተብሎ
ይጠበቃል፡፡
ጣና በለስ-1 ስኳር ፋብሪካ
•	 በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ
ኮርፖሬሽን (METEC) እየተገነባ
የሚገኘው የጣና በለስ-1 ስኳር ፋብሪካ
ግንባታው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ
ማምረት ሲጀምር በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ
የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፤
የመስኖ መሠረተ ልማት
•	 በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 30 ኪ/ሜ
ርዝመት ያለውና 60 ሜ/ኩ ውሃ
በሰከንድ ማስተላለፍ የሚችል የወንዝ
መቀልበሻ፣ መቆጣጠሪያ፣ የደለል
ማስወገጃ እና የዋና ቦይ ግንባታ
ተጠናቋል፤
•	 12 ሺህ 807 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ
ተደርጓል፤
31ስኳር ኮርፖሬሽን
የአገዳ ልማት
•	 በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 13ሺህ 49
ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤
የቤቶች ግንባታ
•	 በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 1ሺህ 945
መኖሪያ ቤቶች እና 20 አገልግሎት
መስጫ ተቋማት (ብሎኮች)
ተገንብተዋል፤
ጣና በለስ-2 ስኳር ፋብሪካ
•	 በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና
ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC)
እየተገነባ የሚገኘው የጣና በለስ ቁጥር
2 ስኳር ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ
በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን
12 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም
ይኖረዋል፤
ጣና በለስ-1 ስኳር ፋብሪካ
32 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
III. ወልቃይት ስኳር
ልማት ፕሮጀክት
ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ በ1ሺ 300 ኪ.ሜ
ርቀት ላይ በትግራይ ክልል በምዕራባዊ ዞን
ወልቃይት ወረዳ ይገኛል፡፡ በፕሮጀክቱ
በ50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ
የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት ተጠቅሞ
በቀን 24ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም
ያለው የስኳር ፋብሪካ ይገነባል፡፡ በዚህ
መሰረት CAMC ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር
የኮንትራት ውል ተገብቶ ስራው በመካሄድ
ላይ ይገኛል፡፡
በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን
ዕቅድ ዘመን ግንባታው ተጠናቆ ስራ
ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው የወልቃይት
ስኳር ፋብሪካ ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ
ሲደርስ በዓመት 4 ሚሊዮን 840ሺ ኩንታል
ስኳር እና 41 ሚሊዮን 654 ሊትር ኤታኖል
ማምረት ይችላል፡፡
ለሸንኮራአገዳልማቱየሚያስፈልገውየመስኖ
ውሃ አቅርቦት ዛሬማ ወንዝ ላይ በመገንባት
ላይ ከሚገኘው የሜይ-ዴይ ግድብ የሚገኝ
ሲሆን፣ ግድቡ ሲጠናቀቅ 840 ሜትር ስፋት
እና 135.5 ሜትር ቁመት ይኖረዋል፡፡
የመስኖ መሠረተ ልማት
•	 3 ቢሊዮን 497 ሚሊዮን ሜትር ኩብ
ውኃ የመያዝ አቅም የሚኖረው የዛሬማ
ግድብ ግንባታ በመከናወን ላይ ይገኛል፤
•	 ከግድብ ግንባታው ጎን ለጎን በጠብታ
መስኖ 7ሺህ ሄ/ር መሬት ለማልማት
NETAFIM ከተባለ የእስራኤል ኩባንያ
የመስኖ መሠረተ ልማት ሥራ ተቋራጭ
ጋር ውል ተገብቶ ሥራው ተጀምሯል፤
•	 የ10 ኪ/ሜትር የዋና ቦይ (Main canal)
ግንባታ ተጠናቋል፤
•	 የ3ሺህ ሄ/ር መስኖ መሠረተ ልማት
ግንባታ እየተከናወነ ሲሆን፣ የመስኖ
ውሃው እስከሚደርስ ድረስ የጥጥ
ልማት እየተካሄደ ነው፤
•	 261 ሄክታር መሬት ውሃ ገብ ሆኗል፤
የአገዳ ልማት
•	 	220 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤
የቤቶች ግንባታ
800 መኖሪያ ቤቶች እና 36 አገልግሎት
መስጫ ተቋማት (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤
33ስኳር ኮርፖሬሽን
ምርምርና ልማት ማዕከል
በሀገራችን በስኳር ኢንዱስትሪ
የምርምር ስራ የተጀመረው ኤች.ቪ.ኤ
በተባለ የደች ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ1951
ነበር። የምርምር ክፍሉ ዋናው
ማዕከል በአምስተርዳም ሆኖ በወቅቱ
በኢትዮጵያ የስኳር ፋብሪካዎች
እንዲስፋፉ ጠንካራ ድጋፍ ይሰጥ
ነበር፡፡
ኩባንያው በወንጂ ሸንኮራ አገዳ
መትከልና ስኳር ማምረት ሲጀምር
እ.ኤ.አ. ከ1958 አንስቶ በስኳር
ኢንዱስትሪ ስልጠና መስጠት
እንደጀመረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
የስኳር ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 192/2003 ሲቋቋምም ለምርምርና ስልጠና ተግባራት
ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሥራው በዘርፍ ደረጃ እንዲመራ ተወስኖ ከ2003ዓ.ም ጀምሮ
የሚከተሉትን አበይት ተግባራት ሲፈጽም ቆይቷል፡፡
•	 ችግር ፈቺነትን መሰረት ያደረገ ምርምር (applied research) በማካሄድ ለኮሜርሽያል
አገልግሎት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ፤
•	 ምርታማነትን በማሳደግ ምርትን መጨመርና ወጪን መቀነስ፤
•	 የአመራረት ቅልጥፍናን ለማሻሻል የተገኘውን የምርምር ውጤት በእያንዳንዱ ስኳር
ፋብሪካና ማሳ ላይ በአግባቡ እንዲውል ማስረጽ፤
•	 በአመራረት ሥርአት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃዎች
(optimization) እንዲወሰዱ የቴክኒክና የምክር አገልግሎት መስጠት፤
•	 ስራ ላይ የዋሉ የምርምር ውጤቶች ለኢንዱስትሪው ያስገኙትን ፋይዳ እና በአካባቢው
ላይ ያደረሱትን ተጽዕኖ መገምገምና አዳዲስ የምርምር አቅጣጫዎችንና ስትራቴጂዎችን
34 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
መንደፍ፤
•	 ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ፣ በሽታ
የሚቋቋሙ፣ ከፍተኛ የስኳር ይዘት
ያላቸውና ቶሎ የሚደርሱ የሸንኮራ አገዳ
ዝርያዎችንእንዲሁምየተሻሻሉየሸንኮራ
አገዳና የስኳር አመራራት ዘዴዎችና
ቴክኖሎጂዎችን ለፋብሪካዎችና
ፕሮጀክቶች ማስተዋወቅና በስራ ላይ
ማዋል፤
•	 በኦፕሬሽን ላይ የነበሩ ቴክኖሎጂዎች
ደረጃቸው (ስታንዳርድ) ሳይጓደል
ትግበራቸው የሚቀጥልበትን አሰራር
መቀየስ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን
መቀመርና ማስተግበር፤
•	 ኢንዱስትሪውን በሰለጠነና ውጤታማ
በሆነ የሰው ኃይል ለመደገፍ
ሥልጠናዎችን በማመቻቸትና
በማሰልጠን ቁልፍ ሚና መጫወት፡፡
ከአዲስ አበባ በ110 ኪ.ሜ ርቀት ወንጂ
ላይ የሚገኘው የምርምርና ልማት ማዕከል
እነዚህን ተግባራት በብቃት ለመወጣት
በ2008ዓ.ም በአዲስ መልክ ተደራጅቷል፡፡
ማዕከሉ በወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ፣
ተንዳሆ፣ አርጆ ዲዴሳ እና ከሰም ስኳር
ፋብሪካዎች እንዲሁም በጣና በለስ፣
ኦሞ ኩራዝ እና ወልቃይት ስኳር ልማት
ፕሮጀክቶች የምርምር ጣቢያዎችን አቋቁሞ
የሸንኮራ አገዳ፣ የዝርያ ልማት እና የስኳር
ቴክኖሎጂ ምርምሮችን በማካሄድ ላይ
ይገኛል፡፡
35ስኳር ኮርፖሬሽን
በመላ ሀገሪቱ የስኳር ሥርጭት የሚከናወነው የንግድ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የስኳር መጠን
(ኮታ) የሥርጭት አሠራር ሥርዓት መሰረት ሲሆን፣ የሚከናወነውም በሚከተሉት ሦስት
መንገዶች ነው፡፡
የስኳር ሥርጭት -
በአዲስ አበባ
ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስኳር የሚሰራጨው
በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በኩል ኮታ
በተመደበላቸው የሸማቾች የሕብረት ሥራ
ማኅበራት አማካኝነት ሲሆን፣ ሥርጭቱ
የሚከናወነው በማኅበራቱ ሱቆችና እነሱ
በሚያከፋፍሏቸው ቸርቻሪ ነጋዴዎች መሸጫ
መደብሮች ነው፡፡ እንዲሁም የአትክልትና
ፍራፍሬ ተጓዳኝ ምርቶች ንግድ ዘርፍ
(የቀድሞ ኢትፍሩት) ከአዲስ አበባ ንግድ
ቢሮ ከሚያገኘው ኮታ ላይ ለአገልግሎት
ሰጪ ተቋማት ያከፋፍላል፡፡
የስኳር ሥርጭት - በክልሎች
በክልሎች ስኳር ለተጠቃሚዎች
የሚሰራጨው በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ
ግብዓቶች ልማት ድርጅት (የቀድሞ ጅንአድ)
አማካኝነት ሲሆን፣ ምርቱ ወደ ተመረጡ
ማሰራጫ ከተሞች ከተጓጓዘ በኋላ በየክልሉ
ንግድ ቢሮ በኩል ለቸርቻሪ ነጋዴዎች
ይሰራጫል፡፡
የስኳር ሥርጭት - ለልዩ ልዩ
ኢንዱስትሪዎች
ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ የተለያዩ
ኢንዱስትሪዎች የንግድ ሚኒስቴርና ስኳር
ኮርፖሬሽን በጥናት የመደቡላቸውን የስኳር
መጠን (ኮታ) ያገኛሉ፡፡
በስኳር ሥርጭት የሚሳተፉ ተቋማት ስኳር
የሚያገኙት ከኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የስኳር
መጋዘኖችና ከስኳር ፋብሪካዎች ነው፡፡
የስኳር ሥርጭት
የስኳር ኮርፖሬሽን አደረጃጀት
ከመጋቢት 2008ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ
በተደረገው የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ
ቤት የአደረጃጀት ለውጥ የተቋሙን ወሳኝ
የስራ ሂደቶች መሠረት በማድረግ በዋና
ሥራ አስፈጻሚ ስር በምክትል ዋና ሥራ
አስፈጻሚዎች የሚመሩ የስትራተጂያዊ ድጋፍ፣
የኢንቨስትመንት ጥናትና ልማት፣ የኦፕሬሽንስ
እና የማርኬቲንግ የሥራ ዘርፎች ተዋቅረዋል፡፡
በእነዚህ እና በዋና ሥራ አስፈጻሚ ፅ/ቤት
ስር በሥራ አስፈጻሚዎች የሚመሩ 21 የስራ
ክፍሎች ተቋቁመዋል፡፡ እንዲሁም ለዋና ሥራ
አስፈጻሚው በቀጥታ ተጠሪ የሆኑ የዋና ሥራ
አስፈጻሚ ጽ/ቤት፣ የፋይናንስ፣ የምርምርና
ልማት ማዕከል፣ የፕላኒንግ፣ የማሽነሪና የቴክኒክ
አገልግሎት፣ የሥነ ምግባርና የመልካም
አስተዳደር እና የኦዲት የሥራ ክፍሎች በአዲስ
መልክ ተደራጅተዋል፡፡
በተጨማሪም የዋና ሥራ አስፈጻሚ የኮርፖሬት
ሪፎርምና አቅም ግንባታ እና የፕሮጀክትና
ኦፕሬሽንስ አማካሪዎች በመዋቅሩ ውስጥ
ተካተዋል፡፡
ተ.ቁ በስትራቴጂያዊ ድጋፍ ስር የተደራጁ የስራ ክፍሎች
1 ሰው ኃብት ልማትና አመራር
2 ካይዘንና ለውጥ አመራር
3 ግዥና ሎጀስቲክስ
4 ንብረትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት
5 አይ ሲ ቲ
ተ.ቁ በኢንቨስትመንት ጥናትና ልማት ስር የተደራጁ የስራ ክፍሎች
1. የህዝብ ተሳትፎና ልማት
2. የመስኖ መሰረተ ልማት ኮንትራት አስተዳደር
3. የፋብሪካ ግንባታ ኮንትራት አስተዳደር
36 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
ተ.ቁ በኦኘሬሽንስ ስር የተደራጁ የስራ ክፍሎች
1. የፋብሪካ ኦኘሬሽንስ ክትትልና ድጋፍ /ክላስተር- 1/
2. የፋብሪካ ኦኘሬሽንስ ክትትልና ድጋፍ /ክላስተር- 2/
3. የእርሻ ኦኘሬሽንስ ክትትልና ድጋፍ /ክላስተር- 1/
4. የእርሻ ኦኘሬሽንስ ክትትልና ድጋፍ /ክላስተር- 2/
5. የተጓዳኝ ምርቶች
ተ.ቁ በማርኬቲንግ ስር የተደራጁ የስራ ክፍሎች
1. የገበያ ጥናትና ኘሮሞሽን
2. የሀገር ውስጥ ግብይት
3.
የውጭ ግብይት
ተ.ቁ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ስር የተደራጁ የስራ ክፍሎች
1. የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን
2. የሕግ አገልግሎት
3. የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ
4. የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ሴክሬታሪያት
4
የመሬት ዝግጅትና አገዳ ልማት
5 የቤቶችና መሰረተ ልማት ኮንትራት አስተዳደር
37ስኳር ኮርፖሬሽን
38 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
1.የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
•	 የዋና ሥራ አስፈጻሚውን ጽ/ቤት ያደራጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣
•	 ከባለድርሻ አካላት የሚመጡ መልዕክቶችን፣ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን ተቀብሎ
በማስተናገድ ምላሽ ይሰጣል፣ ለዋና ሥራ አስፈጻሚ የሚቀርቡ ጉዳዮችን ለይቶ በማቅረብ
ያስወስናል፣
•	 ከመሠረታዊ የሠራተኛ ማህበርና ከሠራተኞች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን፣ አቤቱታዎችንና
ቅሬታዎችን ተቀብሎ ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመመካከር ውሳኔ
እንዲሰጥባቸው ያደርጋል፡፡
2.የኢንቨስትመንት ጥናትና ልማት
•	 የስኳርና የስኳር ተጓዳኝ ልማቶችን የአዋጭነት ጥናቶች እንዲጠኑ ያደርጋል፣ ሲጸድቁም
ይተገብራል፣
•	 በስኳር ልማት አካባቢዎች የሚገኘውን ማህበረሰብ የልማቱ አጋር እንዲሆን ይሰራል፣
ከልማቱም ተጠቃሚ እንዲሆን የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናል፣
•	 የፋብሪካ፣ የመስኖ፣ የቤቶችና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲሁም የመሬት ዝግጅት
ኮንትራቶችን ያስተዳድራል፣
•	 ልማቱን በሽርክና ወይም በጋራ ለማልማት አቅሙ ያላቸውን የአገር ውስጥና የውጪ
ባለሃብቶችን በማፈላለግና አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በማመቻቸት
ከስምምነት ላይ በመድረስ ወደ ሥራ ያስገባል፡፡
3.ኦፕሬሽንስ
•	 በስራ ላይ ያሉ ፋብሪካዎችን እንቅስቃሴ ለመከታተልና ለመደገፍ የሚያስችል ስትራቴጂያዊ
ዕቅድ ይነድፋል፣ የድርጊት መርሃ ግብር አውጥቶ ሥራ ላይ ያውላል፣
•	 ወደ ኦፕሬሽን የሚገቡ አዳዲስ ፋብሪካዎችን ከፍተሻና ከሙከራ ምርት (ኮሚሽኒንግ) ጀምሮ
ያላቸውን እንቅስቃሴ ይከታተላል፣
•	 የተጓዳኝ ምርቶችን በመጠቀም የሰብልና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንስሳት ሃብት ልማትን
ያስፋፋል፣
•	 ለፋብሪካዎች የሚያስፈልጉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማጥናትና በመምረጥ በስራ ላይ
ያውላል፡፡
በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሚመሩ የሥራ ዘርፎችና የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት አበይት
ተግባራትና ኃላፊነት የሚከተሉት ናቸው፡፡
39ስኳር ኮርፖሬሽን
አዘጋጅ፡- ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን
የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ፡- ጋሻው አይችሉህም
የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ፡- ካዛንቺስ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- ሞባይል - +251911 67 77 54
ቢሮ - +25111 552 74 75
ኢ-ሜይል- pr@ethiopiansugar.com
4.ማርኬቲንግ
•	 ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመግባት የሚያስችል የገበያ ጥናትና ማርኬት ቅኝት (ኢንተለጀንስ)
ያደርጋል፣
•	 የሀገር ውስጥ ገበያ የስኳር ፍላጎት መሟላቱን እና የሥርጭት ሥርዓቱ ፍትሃዊ መሆኑን
ያረጋግጣል፣
•	 በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያግዙ የብራንዲንግ፣ የፓኬጂንግና ሌሎች
የስታንዳርዳይዜሽንና የሰርቲፊኬሽን ሥራዎችን ያከናውናል፣
•	 ተቋማዊ ገጽታን የሚገነቡ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶችን፣ ባዛሮችንና የንግድ ትርኢቶችን
ያዘጋጃል፤ በውጭ ሀገራት በሚዘጋጁት ላይም እንደአስፈላጊነቱ ይሳተፋል፡፡
5.ስትራቴጂያዊ ድጋፍ
•	 በስትራቴጂያዊ ዕቅድ ላይ ተመስርቶ ሥራዎችን ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ያቀናጃል፣ ይመራል፣
•	 የካይዘንና ለውጥ አመራር ሥራዎችን በዕቅድ ላይ በተመሰረተ አቅጣጫ እንዲከናወኑ
ያደርጋል፣
•	 የግዥ፣ የሎጂስቲክስ እንዲሁም በወደብና በጉምሩክ መጋዘን ያሉ ንብረቶች ክሊራንስ
ሥራዎች በጤናማ የንግድ ውድድር አግባቦች እንዲፈጸሙ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣
•	 የመልካም አስተዳደር ችግር መንስኤዎችንና የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮችን በመለየት
ይፈታል፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ
በኢትዮጵያ
ስኳር ኮርፖሬሽን
:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283
: 20034 Code 1000 A.A info@ethiopiansugar.com
Ethiopiansugar.com
facebook.com/etsugar

More Related Content

What's hot

supply chain analysis of dg cement
supply chain analysis of dg cementsupply chain analysis of dg cement
supply chain analysis of dg cement
Zuhair Bin Jawaid
 
DG cement Operations management
DG cement Operations management DG cement Operations management
DG cement Operations management
Mubasher Fiaz
 
Udaipur cement industries limited
Udaipur cement industries limitedUdaipur cement industries limited
Udaipur cement industries limited
Home
 
How to Start Mustard Oil Mill. Profitable Business Idea
How to Start Mustard Oil Mill. Profitable Business IdeaHow to Start Mustard Oil Mill. Profitable Business Idea
How to Start Mustard Oil Mill. Profitable Business Idea
Ajjay Kumar Gupta
 
Computer Applications in Mining Engineering, AKS University
Computer Applications in Mining Engineering, AKS UniversityComputer Applications in Mining Engineering, AKS University
Computer Applications in Mining Engineering, AKS University
Prof-GoldSmith Briz
 
Dumper Cycle Study
Dumper Cycle StudyDumper Cycle Study
Dumper Cycle Study
Mousom Singha
 
HR practices in sugar industries
HR practices in sugar industries HR practices in sugar industries
HR practices in sugar industries
jennna
 
Organization study at sri renuka sugars
Organization study at sri renuka sugarsOrganization study at sri renuka sugars
Organization study at sri renuka sugars
Projects Kart
 
Lucky cement internship report
Lucky cement internship reportLucky cement internship report
Lucky cement internship report
Dawood University Of Engineering And Technology
 
Cement Industry Pakistan
Cement Industry PakistanCement Industry Pakistan
Cement Industry Pakistan
Yumna Qaiser
 
Cement Manufacturing Plant Construction
Cement Manufacturing Plant ConstructionCement Manufacturing Plant Construction
Cement Manufacturing Plant Construction
Shyam Anandjiwala
 
The productivity of lhd in underground coal mines
The productivity of   lhd in underground coal minesThe productivity of   lhd in underground coal mines
The productivity of lhd in underground coal mines
Safdar Ali
 
Sugar1
Sugar1Sugar1
Sugar1
phulcritude
 
Gujarat Ambuja Cement Limited | Operations Management
Gujarat Ambuja Cement Limited | Operations ManagementGujarat Ambuja Cement Limited | Operations Management
Gujarat Ambuja Cement Limited | Operations Management
Lokendra Singh Rathore
 
renuka sugar company
renuka sugar companyrenuka sugar company
renuka sugar company
Ankita Varma
 
Sugar industry in india
Sugar industry in indiaSugar industry in india
Sugar industry in india
Ranjan Kotian
 
Oil and gas industry
Oil and gas industryOil and gas industry
Oil and gas industry
domsr
 
Oil & gas sector presentation
Oil & gas sector presentationOil & gas sector presentation
Oil & gas sector presentation
Infraline Energy
 
Cement manufacturing process by shubham malviya
Cement manufacturing process by shubham malviyaCement manufacturing process by shubham malviya
Cement manufacturing process by shubham malviya
ShubhamMalviya25
 
Internship report bawany sugar mills ltd
Internship report bawany sugar mills ltdInternship report bawany sugar mills ltd
Internship report bawany sugar mills ltd
Zubair Memon
 

What's hot (20)

supply chain analysis of dg cement
supply chain analysis of dg cementsupply chain analysis of dg cement
supply chain analysis of dg cement
 
DG cement Operations management
DG cement Operations management DG cement Operations management
DG cement Operations management
 
Udaipur cement industries limited
Udaipur cement industries limitedUdaipur cement industries limited
Udaipur cement industries limited
 
How to Start Mustard Oil Mill. Profitable Business Idea
How to Start Mustard Oil Mill. Profitable Business IdeaHow to Start Mustard Oil Mill. Profitable Business Idea
How to Start Mustard Oil Mill. Profitable Business Idea
 
Computer Applications in Mining Engineering, AKS University
Computer Applications in Mining Engineering, AKS UniversityComputer Applications in Mining Engineering, AKS University
Computer Applications in Mining Engineering, AKS University
 
Dumper Cycle Study
Dumper Cycle StudyDumper Cycle Study
Dumper Cycle Study
 
HR practices in sugar industries
HR practices in sugar industries HR practices in sugar industries
HR practices in sugar industries
 
Organization study at sri renuka sugars
Organization study at sri renuka sugarsOrganization study at sri renuka sugars
Organization study at sri renuka sugars
 
Lucky cement internship report
Lucky cement internship reportLucky cement internship report
Lucky cement internship report
 
Cement Industry Pakistan
Cement Industry PakistanCement Industry Pakistan
Cement Industry Pakistan
 
Cement Manufacturing Plant Construction
Cement Manufacturing Plant ConstructionCement Manufacturing Plant Construction
Cement Manufacturing Plant Construction
 
The productivity of lhd in underground coal mines
The productivity of   lhd in underground coal minesThe productivity of   lhd in underground coal mines
The productivity of lhd in underground coal mines
 
Sugar1
Sugar1Sugar1
Sugar1
 
Gujarat Ambuja Cement Limited | Operations Management
Gujarat Ambuja Cement Limited | Operations ManagementGujarat Ambuja Cement Limited | Operations Management
Gujarat Ambuja Cement Limited | Operations Management
 
renuka sugar company
renuka sugar companyrenuka sugar company
renuka sugar company
 
Sugar industry in india
Sugar industry in indiaSugar industry in india
Sugar industry in india
 
Oil and gas industry
Oil and gas industryOil and gas industry
Oil and gas industry
 
Oil & gas sector presentation
Oil & gas sector presentationOil & gas sector presentation
Oil & gas sector presentation
 
Cement manufacturing process by shubham malviya
Cement manufacturing process by shubham malviyaCement manufacturing process by shubham malviya
Cement manufacturing process by shubham malviya
 
Internship report bawany sugar mills ltd
Internship report bawany sugar mills ltdInternship report bawany sugar mills ltd
Internship report bawany sugar mills ltd
 

Viewers also liked

Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006 የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
Ethiopian Sugar Corporation
 
The Omo-Kuraz Sugar Development Project
The Omo-Kuraz Sugar Development Project The Omo-Kuraz Sugar Development Project
The Omo-Kuraz Sugar Development Project
Ethiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
Ethiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ምየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar Corporation
Ethiopian Sugar Corporation
 
Comparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industryComparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industry
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
Ethiopian Sugar Corporation
 
PALLAVI GUPTA RESUMEE
PALLAVI  GUPTA RESUMEEPALLAVI  GUPTA RESUMEE
PALLAVI GUPTA RESUMEE
PALLAVI GUPTA
 
The 10 pillar OMO Model
The 10 pillar OMO Model The 10 pillar OMO Model
The 10 pillar OMO Model
IAWG Africa
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013Ethiopian sugar corporation facts – December 2013
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013
Ethiopian Sugar Corporation
 
Botany of maize
Botany of maizeBotany of maize
Botany of maize
Rione Drevale
 
Most frequently asked bank interview questions
Most frequently asked bank interview questionsMost frequently asked bank interview questions
Most frequently asked bank interview questions
Girma Adugna
 
omos
omosomos

Viewers also liked (18)

Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
 
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006 የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
 
The Omo-Kuraz Sugar Development Project
The Omo-Kuraz Sugar Development Project The Omo-Kuraz Sugar Development Project
The Omo-Kuraz Sugar Development Project
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ምየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
 
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol. 2. No.2 , By Ethiopian Sugar Corporation
 
Comparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industryComparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industry
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007
 
PALLAVI GUPTA RESUMEE
PALLAVI  GUPTA RESUMEEPALLAVI  GUPTA RESUMEE
PALLAVI GUPTA RESUMEE
 
The 10 pillar OMO Model
The 10 pillar OMO Model The 10 pillar OMO Model
The 10 pillar OMO Model
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
 
External vacancy
External vacancyExternal vacancy
External vacancy
 
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013Ethiopian sugar corporation facts – December 2013
Ethiopian sugar corporation facts – December 2013
 
Botany of maize
Botany of maizeBotany of maize
Botany of maize
 
Most frequently asked bank interview questions
Most frequently asked bank interview questionsMost frequently asked bank interview questions
Most frequently asked bank interview questions
 
omos
omosomos
omos
 

Similar to የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ምጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
Meresa Feyera
 
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
Ethiopian Sugar Corporation
 

Similar to የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ (12)

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ምጣፋጭ ዜና  መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ልዩ ዕትም መስከረም 2012 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008
 

More from Ethiopian Sugar Corporation

Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Ethiopian Sugar Corporation
 
Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI] Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI]
Ethiopian Sugar Corporation
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Ethiopian Sugar Corporation
 

More from Ethiopian Sugar Corporation (13)

Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
 
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
 
Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI] Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI]
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 መጋቢት 2008
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ

  • 2. የስኳር ኮርፖሬሽን ተልዕኮ፣ ራዕይ እና እሴቶች ተልዕኮ በአገሪቱ ያለውን እምቅ ሃብት ለማልማት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰው ሀይል አቅም በማፍራት ስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች በማምረትና የስኳር ተረፈ ምርትን ጥቅም ላይ በማዋል የሀገር ውስጥ ፍላጎት ከማርካትና የህዝቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ የጎላ የኤክስፖርት ድርሻ በመያዝ የሀገሪቱን ልማት መደገፍ፡፡ ራዕይ ቀጣይነት ባለው እድገት በ2016ዓ.ም በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች ሀገራት ተርታ መሰለፍ፣ እሴቶች • የማያቋርጥ ለውጥና ቀጣይ ተወዳዳሪነት • መልካም ስነ ምግባር • ምርታማነት የህልውናችን መሠረት ነው! • ህዝባዊነት መለያችን ነው! • መማር አናቋርጥም! • ፈጠራንና የላቀ ሥራን እናበረታታለን! • በቡድን መንፈስ መስራት መለያችን ነው! • አካባቢ ጥበቃ ለልማታችን መሠረት ነው! • የሰው ሃብት ልማት ለስኬታማነታችን ወሳኝ ነው! 2 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
  • 3. በማቋቋሚያ አዋጅ ደንብ ቁጥር 192/2003 መሰረት የስኳር ኮርፖሬሽን ዓላማ • የሸንኮራ አገዳና ስኳር የሚያስገኙ ሌሎች ሰብሎች ማልማት፣ • ስኳር፣ የስኳር ውጤቶችን፣ የስኳር ተረፈ ምርቶችን እና የስኳር ተረፈ ምርት ውጤቶችን በፋብሪካ ማዘጋጀትና ማምረት፣ • ምርቶቹንና ተረፈ ምርቶቹን ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣ • አዳዲስና የማስፋፊያ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት፣ የዲዛይን ዝግጅት፣ የቴክኖሎጂ መረጣና ድርድር፣ የተከላና ኮሚሽኒንግ ስራዎች እንዲካሄዱ ማድረግ፣ • ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በሸንኮራ አገዳና በስኳር አመራረት ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ማካሄድና ጠቃሚ ውጤቶችን በስራ ላይ ማዋል፣ • አቅሙ ካላቸው የሀገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የሚያስፈልጉ የማምረቻ መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች ዲዛይንና ፋብሪኬሽን ሥራዎች በሀገር ውስጥ እንዲከናወኑ ማድረግ፣ • በሕግ መሰረት ለስራው የሚያስፈልገው መሬት ባለይዞታ መሆንና ማልማት፣ • የአገዳ ምርታቸውን ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የሚያቀርቡ አገዳ አብቃዮችን ማበረታታትና መደገፍ፣ • ለስኳር ኢንዱስትሪ የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ሃይል በሚፈለገው አይነት፣ መጠንና ጥራት ለማፍራት እንዲቻል ከሚመለከታቸው የትምህርት ተቋማት ጋር መተባበር፣ • የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የሚያወጣውን መመሪያና የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ቦንድ መሸጥና በዋስትና ማስያዝ እና ከአገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ ምንጮች ጋር የብድር ውል መደራደርና መፈራረም፣ • ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን መስራት ናቸው፡፡ 3ስኳር ኮርፖሬሽን
  • 4. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የስኳር ፍላጎት የደረሰበት ደረጃ ሲታይ የዛሬ 62 ዓመት ገደማ በላንድሮቨር መኪና በየገበያው በመዘዋወር ስኳርን ለማስተዋወቅ ብርቱ ጥረት ተደርጎ እንደነበር ማመን ይከብዳል፡፡ በወቅቱ ሻይ በ”ቅመሱልኝ” በነጻ በመጋበዝ ሕዝቡን ከምርቱ ጋር ለማላመድ የተደረገው እንቅስቃሴ ከብዙ ጥረት በኋላ ውጤት ማስገኘት ችሏል፡፡ በዚህ ሁኔታ የተጀመረው የስኳር ትውውቅ ዛሬ ላይ ታሪኩን በመቀየር ሀገሪቱ እያስመዘገበች ካለችው ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ጋር በተያያዘ በጣም ተፈላጊ ምርት ሆኗል፡፡ በሀገራችን ዘመናዊ የስኳር ኢንዱስትሪ የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግሥት ኤች ቪ ኤ (HVA) ከተባለ የሆላንድ ኩባንያ ጋር የአክስዮን ስምምነት ከፈረመበት ከ1943ዓ.ም አንስቶ ነው፡፡ ኩባንያው 5 ሺ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ማልሚያ መሬት ተረክቦ ሥራውን የጀመረው ከአዲስ አበባ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በወንጂ ከተማ ሲሆን፣ በቅድሚያ የወንጂ ስኳር ፋብሪካን ገንብቶ መጋቢት 11 ቀን 1946ዓ.ም ስራ አስጀምሯል፡፡ ፋብሪካው በወቅቱ በቀን 1 ሺ 400 ኩንታል ስኳር እያመረተ ምዕዙን ስኳር እና ባለ 10 ሳንቲም እሽግ ስኳር ለገበያ ያቀርብ ነበር፡፡ በወቅቱ የወንጂ አካባቢ በዓለማችን ከፍተኛ ምርት ከሚያስመዘግቡና ለስኳር ምቹ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ ስለነበር ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ ምስረታ ጋር ተያይዞ የወንጂ ከረሜላ ፋብሪካ ሰኔ 1953ዓ.ም ተቋቁሞ ደስታ ከረሜላ ለገበያ ማቅረብ ጀመረ፡፡ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሥራ ከጀመረ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ በ1955ዓ.ም እዛው ወንጂ ላይ የተቋቋመው የሸዋ ስኳር ፋብሪካ በቀን 1 ሺ 700 ኩንታል ስኳር ያመርት ነበር፡፡ ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በሚል የጋራ መጠሪያ በአንድ አስተዳደራዊ መዋቅር ስር ይተዳደሩ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ ፋብሪካዎች አንድ ላይ በዓመት 750 ሺ ኩንታል ስኳር ገደማ ያመርቱ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የወንጂ እና ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ከግማሽ ምዕተ ዓመት የስኳር ኢንዱስት መግቢያ 4 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
  • 5. በላይ ካገለገሉ በኋላ በእርጅና ምክንያት እንደ ቅደም ተከተላቸው በ2004ዓ.ም እና በ2005ዓ.ም መጨረሻ የተዘጉ ሲሆን፣ በምትካቸው አዲስ ዘመናዊ ፋብሪካ ተገንብቶ ከ2006ዓ.ም ጀምሮ ስኳር እያመረተ ይገኛል። በኢትዮጵያ የስኳር አዋጭነትን የተረዳው የሆላንዱ ኩባንያ በተመሳሳይ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካን ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መርቲ ከተማ ሰኔ 26 ቀን 1957ዓ.ም በአክሲዮን መልክ በመመስረት በ1962ዓ.ም ፋብሪካውን ሥራ አስጀመረ፡፡ ይሁንና እነዚህ ፋብሪካዎች በ1967ዓ.ም በሀገሪቱ በተደረገው የመንግሥት ለውጥ ምክንያት ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ይዞታ ስር ወደቁ፡፡ ይህን ተከትሎ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 58/1970 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ወንጂ ሸዋ እና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን ጨምሮ አዲስ ከተማና አስመራ ከረሜላ ፋብሪካዎችን እንዲያስተዳድር ተደረገ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከስኳር ልማት ጋር በተያያዘ በፊንጫአ ሸለቆ በ1967ዓ.ም በተካሄደ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት አካባቢው ለስኳር ምርት አዋጭ ሆኖ ተገኘ፡፡ ይህን ተከትሎም ለአገሪቱ ሦስተኛ የሆነውን የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ለመገንባት ጠለቅ ያለ ጥናት እንዲካሄድ ተወስኖ ቡከርስ አግሪካልቸራል ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ አማካይነት ከ1970ዓ.ም ጀምሮ ዝርዝር ጥናት ተካሄደ፡፡ በፋይናንስ እጥረት ሳቢያ ተጓቶ የነበረው የፋብሪካው ግንባታ በ1981ዓ.ም፤ የሸንኮራ አገዳ ተከላ ስራው ደግሞ በ1984ዓ.ም ተጀመረ፡፡ ከስምንት ዓመት በኋላ የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ በ1991ዓ.ም ወደ መደበኛ የማምረት ሥራ ተሸጋገረ፡፡ ከቀደምቶቹ ስኳር ፋብሪካዎች በተሻለ ዘመናዊ የሆነውን የፊንጫአ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካና ኤታኖል ግንባታ ያከናወኑት ኤፍ.ሲ.ሼፈርና አሶሽየትስ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያና በእርሱ ስር የፋብሪካውን ተከላ ያካሄደው ድዌቶ ኢንተርናሽናል የተባለ የደች ኩባንያ ሲሆኑ፣ በግንባታው በርካታ ትሪ በኢትዮጵያ 5ስኳር ኮርፖሬሽን
  • 6. የስኳር ኢንዱስትሪ... የሀገር በቀል ድርጅቶች ተሳትፈዋል፡፡ ልማቱ በዚህ መልክ እየተካሄደ ባለበት ወቅት አራት ፋብሪካዎችን ያስተዳድር የነበረው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ከ14 ዓመታት ቆይታ በኋላ በ1984ዓ.ም በሕግ ፈረሰ፡፡ በምትኩም በደንብ ቁጥር 88/85 መተሐራ ስኳር ፋብሪካ፤ በደንብ ቁጥር 88/85 ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካና በደንብ ቁጥር 199/86 ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ እራሳቸውን የቻሉ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሆነው እንዲቋቋሙ ተደረገ፡፡ ኋላም ለስኳር ፋብሪካዎቹ የጋራ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ድጋፍ ሰጪ ማዕከል አክስዮን ማህበር በሶስቱ ስኳር ፋብሪካዎች፣ በልማት ባንክ እና በመድን ድርጅት በአክስዮን መልክ ህዳር 1990ዓ.ም ተቋቋመ፡፡ ከዓመታት በኋላም በማዕከሉ ምትክ የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 504/98 ተመስርቶ የስኳር ፋብሪካዎቹን በመቆጣጠር፣ በፕሮጀክት ልማት፣ በምርምር፣ በስልጠናና በግብይት ረገድ ድጋፍ ሲሰጥ ቆየ፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ የኢፌዲሪ መንግሥት የስኳር ልማቱን ለማስፋፋት በማቀድ በአፋር ክልል የተገነባውን አራተኛውን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በደንብ ቁጥር 122/98 አቋቋመ፡፡ ፋብሪካው በ50 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀም ሲሆን፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ በዓመት 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር እና 30 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል የማምረት አቅም ያለው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የፋብሪካው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ስኳር ማምረት ጀምሯል፡፡ 6 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
  • 7. የስኳር ልማት እንቅስቃሴው በዚህ መልክ ከቀጠለ በኋላ ከጥቅምት 19 ቀን 2003ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኤጀንሲ እንዲፈርስ ተደርጎ በምትኩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 192/2003 የስኳር ኮርፖሬሽን ተቋቋመ፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ በስራ አመራር ቦርድ የሚተዳደር ሆኖ፣ የኢፌዲሪ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 መሰረት ተጠሪነቱ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን የስኳር ኢንዱስትሪ ንኡስ ዘርፍ ስትራተጂያዊ ማዕቀፍ የሀገራችን ኢንዱስትሪ በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነቱን ሚና እንዲጫወት የላቀ አስተዋጽኦ ካላቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች መካከል የስኳር ልማት አንዱ ነው። ኢትዮጵያ ይህን ኤክስፖርት መር የሆነ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስፋፋትና ምርታማነቱን ለማሳደግ የሚያስችል ከፍተኛ የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሃብት አላት፡፡ በተለይም ሀገሪቱ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ተስማሚ አየር ንብረት፣ በመስኖ ሊለማ የሚችል ሰፊ የእርሻ መሬት (ከ500ሺ ሄክታር በላይ) እንዲሁም በቂ ውሃ ያላት በመሆኑ ዘርፉ የበለጠ ትኩረት እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባሻገር መንግስት የሀገሪቱ ህዝቦች ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚከተለው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት በወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ እና ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች ብቻ ለረጅም ዓመታት ያህል ተወስኖ የቆየውን የስኳር ኢንዱስትሪ በተለይም ከ2003ዓ.ም ወዲህ በደቡብ ብ/ብ/ሕ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች እያስፋፋ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት በአማራና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ50ሺ ሄክታር መሬት የሚለማን የሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት የሚጠቀሙ እያንዳንዳቸውበቀን12ሺቶንአገዳመፍጨት የሚችሉ ሁለት የስኳር ፋብሪካዎች በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ፣ ቤንች ማጂ እና ካፋ ዞኖች በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ100 ሺህ ሄክታር መሬት የሚለማን ሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት የሚጠቀሙ እያንዳንዳቸው በቀን 12 ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችሉ ሦስት ፋብሪካዎችን እንዲሁምበቀን24ሺህቶንአገዳየመፍጨት አቅም ያለውን አንድ ፋብሪካ በጠቅላላው አራት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት 7ስኳር ኮርፖሬሽን
  • 8. የስኳርኢንዱስትሪ-የቀጠለ ታቅዶ የፋብሪካዎቹ ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በተለይም የኩራዝ አንድ ስኳር ፋብሪካ ምርት ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ በትግራይ ክልል በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ50ሺህ ሄክታር መሬት የሚለማን የሸንኮራ አገዳ ተጠቅሞ በቀን 24ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችል የስኳር ፋብሪካ እየተገነባ ነው፡፡ ምንም እንኳ ኢንዱስትሪው ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ እድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም፣ • ኢንዱስትሪው በሚፈልገው ፍጥነት አለማደግ፣ • ሀገሪቱ በተከታታይ እያስመዘገበች ካለችው ፈጣን የኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡ የስኳር ፍላጐት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣት፣ • ነባር የስኳር ፋብሪካዎች የሚያመርቱት የስኳር መጠን እያደገ የመጣውን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ማርካት አለመቻል፣ • የሕዝብ ቁጥር ማደግ እና • ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ከመስፋፋት ጋር ተያይዞ የስኳር ፍላጎትና አቅርቦት ሊጣጣም አልቻለም፡፡ ሀገራዊ የስኳር አቅርቦት አሁን ያለው ሀገራዊ የስኳር አቅርቦት መጠን በዓመት ከ6 እስከ 6.5 ሚሊዮን ኩንታል ያህል ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ባለፉት ዓመታት ከ3.25 እስከ 4 ሚሊዮን ኩንታል የሚደርስ ስኳር በሀገር ውስጥ የተመረተ ሲሆን፣ በፍላጎትና በአቅርቦት መካከል ያለው ከ2 እስከ 2.5 ሚሊዮን ኩንታል ልዩነት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን የአንድ ሰው አመታዊ የስኳር ፍጆታ ከ10 ኪሎ ግራም በላይ እንደሚደርስ ቢገመትም፣ እየቀረበ ያለው መጠን ግን 7 ኪሎ ግራም ያህል ነው፡፡ ከዚህ አንጻር መንግሥት የስኳር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም በየአመቱ ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ በውጭ ምንዛሪ ስኳር ከውጪ ሀገር እያስገባ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ይሁንና ክፍተቱን ለመሙላት ስኳር ከውጭ መግዛት ዘላቂ መፍትሔ ባለመሆኑና በዚህ ሁኔታም መቀጠል ስለማይቻል ከመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን አንስቶ በሀገራችን ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው የማኑፋክቸሪንግ የኢንዱስትሪ ዘርፎች አንዱ የስኳር 8 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
  • 9. በስኳር ልማት ዘርፍ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የተከናወኑ አበይት ተግባራት፡- • በማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የወንጂ ሸዋና የፊንጫአ ነባር ስኳር ፋብሪካዎችን በማዘመን የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ ተችሏል፡፡ • ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠንን በ2002ዓ.ም መጨረሻ ከነበረበት 2 ሚሊዮን 903 ሺ 740 ኩንታል በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ (2007ዓ.ም) ወደ 4 ሚሊዮን ኩንታል ለማሳደግ ተችሏል፡፡ • የከሰምና የአርጆ ዲዴሳ አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችን ግንባታ በማጠናቀቅ ሥራ ማስጀመር ተችሏል፡፡ • በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን የሙከራ ምርት ማስጀመር ተችሏል፡፡ • የአገዳ ልማትን በተመለከተም በዕቅድ ዘመኑ ተጨማሪ 65 ሺ 363 ሄክታር መሬት በአገዳ ለምቷል፡፡ ይህም በእቅዱ መነሻ ከነበረው 30ሺ 397 ሄክታር ጋር ሲነጻጸር የ215 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ • የኤታኖል የምርት መጠንም በ2002ዓ.ም ከነበረበት 7 ሚሊዮን 117 ሺህ ሊትር በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ ወደ 19 ሚሊዮን 804 ሺህ ሊትር ከፍ ብሏል፡፡ ከዚህ ውስጥ 18 ሚሊዮን 480 ሺህ ሊትር ከቤንዝል ጋር ተቀላቅሎ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ • የአገዳ ምርታማነትን ያሳደጉ በርካታ የምርምር ሥራዎችም ተከናውነዋል፡፡ ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ ሊሆን ችሏል፡፡ በዚህ መሰረት መንግሥት፡- • የስኳር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም፣ • በዘርፉ ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል፣ • በተለይም በልማቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ሕዝቦች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እና • ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ የውጪ ምንዛሪ ለማስገኘት ግዙፉ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን ከመገንባት አንስቶ “የስኳር አብዮት” በሚያስብል ሁኔታ በተለያዩ የሀገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች መጠነ ሰፊ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ 9ስኳር ኮርፖሬሽን
  • 10. • የጊዜያዊ ግድብ (ኮፈር ዳም) እና የውሃ መቀልበሻ (ዊር)፣ የሰፋፊ መስኖ መሰረተ ልማት አውታሮች፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ የቤቶች እና የግዙፍ አዳዲስ ፋብሪካዎች ግንባታ እንዲሁም የመሬት ዝግጅት ሥራዎች በስፋት ተካሂደዋል፡፡ • 31 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ወደ ብሔራዊ የሃይል ቋት ማስገባት ተጀምሯል፡፡ • ልማቱን ተከትሎም አነስተኛ ከተሞችና በርካታ መንደሮች ተመስርተዋል፡፡ • በአጠቃላይ በዕቅድ ዘመኑ ባጋጠሙ የተለያዩ ተግዳሮቶች በዘርፉ የታቀደውን ያህል ውጤት ማግኘት ባይቻልም እንኳ፣ በተከናወኑ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ሀገሪቱ ወደፊት በስኳር ምርት በዓለም ገበያ ከፍተኛ ድርሻ እንዲኖራት የሚያስችሉ መደላድሎችን ለመፍጠር ተችሏል፡፡ የማህበረሰብ ተጠቃሚነት • ልማቱን ተከትሎ በርካታ የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ትምህርት ቤት፣ ጤና ተቋማት፣ ወፍጮ ወዘተ) እና የመሰረተ ልማት አውታሮች (ንጹህ መጠጥ ውሃ፣ መንገድ ወዘተ) ተገንብተው የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተጠቃሚ በመሆን የኑሮ ደረጃቸው መሻሻል ጀምሯል፡፡ • ለአካባቢው ተወላጆች ልጆች ቅድሚያ በመስጠትና በትራክተር ኦፕሬተርነት፣ በግምበኛነት፣ በአናጺነት፣ በጥበቃና በመሳሰሉት ሙያዎች በማሰልጠን በየፕሮጀክቶቹ ተመድበው እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡ • የአካባቢው ወጣቶች በጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት ተደራጅተው በልማቱ ሥራ ውስጥ እንዲሳተፉና ገቢ እንዲገኙ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ • በመስኖ የለማ መሬት ለአካባቢው ነዋሪዎች አመቻችቶ በማስረከብ በተለይም በስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አካባቢ የሚገኘው ማህበረሰብ እንደ በቆሎ የመሳሰሉ ሰብሎችን አምርቶ እንዲጠቀም ተደርጓል፡፡ በቀጣይም ማህበረሰቡ በዘላቂነት ሸንኮራ አገዳ አልምቶ ለፋብሪካ እንዲያቀርብ ለማስቻል ለወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አገዳ አብቅለው ከሚያቀርቡ አርሶ 10 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
  • 11. አደሮች (አውት ግሮወርስ) ልምድ እንዲያገኝ የሚያስችል እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ • በአጠቃላይ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አመታት በዘርፉ ከ350 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች ቋሚ፣ ጊዜያዊና የኮንትራት የሥራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡ 11ስኳር ኮርፖሬሽን
  • 12. የስኳር ኢንዱስትሪ ቅኝት በንጽጽር 12 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
  • 13. አሮጌውና አዲሱ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች 13ስኳር ኮርፖሬሽን
  • 14. በስኳር ልማት ዘርፍ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን የታቀዱ አበይት ተግባራት • የህብረተሰቡን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት በዘላቂነት ማሳደግ፣ • ልማቱ በሚፈጥረው የስራ ዕድል በቋሚነት፣ በጊዜያዊነት፣ በኮንትራትና በማህበራት ከ637 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል መፍጠር፣ • በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ግንባታቸው ተጀምሮ በተለያዩ የአፈጻጸም ደረጃዎች የሚገኙ ሰባት አዳዲስ ፋብሪካዎችን ማለትም የኦሞ ኩራዝ 1፣ 2፣ 3 እና 5፤ የጣና በለስ 1 እና 2 እንዲሁም የወልቃይት ስኳር ፋብሪካዎችን ግንባታ አጠናቆ ሥራ ማስጀመር፣ • ዓመታዊ የስኳር መጠንን በዕቅድ ዓመቱ መጨረሻ ወደ 2.8 ሚሊዮን ቶን በማሳደግ የሀገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማርካት ባሻገር ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት፣ • ዓመታዊ የኢታኖል ምርት መጠንን በዕቅድ ዓመቱ መጨረሻ 28 ሚሊዮን 105 ሺ ሊትር ማድረስ፣ • ከፍተኛ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ማስገባት፣ • የመስኖ መሰረተ ልማትና የቤቶች ግንባታን በስፋትና በጥራት ማካሄድ፣ • የሸንኮራ አገዳ ልማትን ከማስፋፋት አኳያም፣ በ2007 በጀት ዓመት መጨረሻ በአገዳ ከተሸፈነው 95 ሺህ 760 ሄክታር መሬት በተጨማሪ በዕቅድ ዘመኑ 211 ሺህ 564 ሄ/ር በመትከል በ2012ዓ.ም መጨረሻ 307 ሺህ 324 ሄክታር ላይ ማድረስ፣ • በተጓዳኝ ምርቶችም በሰብልና ፍራፍሬ እንዲሁም በእንስሳት ሃብት ልማት ሰፊ ስራዎችን ማከናወን ናቸው፡፡ 14 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
  • 15. I. ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ስኳር ፋብሪካዎች በሀገራችን የስኳር ፋብሪካ ታሪክ ፋና ወጊ የሆነው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ በ1946ዓ.ም ግንባታው ተጠናቆ ማምረት የጀመረ ሲሆን፣ የሸዋ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ እዛው ወንጂ ላይ በ1955ዓ.ም ተመርቆ ስራ የጀመረ ሌላኛው ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ ሁለቱም ስኳር ፋብሪካዎች ኤች ቪ ኤ በተባለ የሆላንድ ኩባንያ የተገነቡና በኩባንያውና በመንግሥት የጋራ ባለቤትነት በሽርክና የተቋቋሙ ነበሩ፡፡ በአንድ አስተዳደር ስር እየተዳደሩ ስኳር ያመርቱ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ ፋብሪካዎች በእርጅና ምክንያት ስራቸውን እስካቆሙበት ጊዜ ማለትም ወንጂ እስከ 2004ዓ.ም እንዲሁም ሸዋ እስከ 2005ዓ.ም መጨረሻ ድረስ የነበራቸው አማካኝ አመታዊ ስኳር የማምረት አቅም 75ሺህ ቶን ወይም 750 ሺህ ኩንታል ነበር፡፡ ነባሩን የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በአዲስና ዘመናዊ ፋብሪካ ለመተካት የማስፋፊያ ፕሮጀክት በፋብሪካ እና በእርሻ ዘርፍ ተከናውኖ የፋብሪካ ማስፋፊያ ስራው በ2005ዓ.ም መጨረሻ ላይ ተጠናቀቀ፡፡ በ2006ዓ.ም መጀመሪያ ላይም ፋብሪካው ሥራ ጀመረ፡፡ አዲሱ ስኳር ፋብሪካ የተገነባው ነባሮቹ በሚገኙበት የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ ቢሾላ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው፡፡ ከአዲስአበባበ110ኪ.ሜርቀትላይየሚገኘው ይህ ፋብሪካ አሁን ባለበት ደረጃ በቀን 6ሺህ 250 ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት ከ174ሺህ ቶን በላይ ስኳር የማምረት አቅም አለው፡፡ ወደፊት የማምረት አቅሙን በሂደት በማሳደግ በቀን ወደ 12ሺህ 500 ቶን አገዳ እየፈጨ ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠኑን እስከ 222ሺህ 700 ቶን እንደሚያሳድግ 15ስኳር ኮርፖሬሽን
  • 16. ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡ ከዚህ ዘመናዊ የስኳር ፋብሪካ ተረፈ ምርት በዓመት እስከ 12 ሚሊዮን 800ሺህ ሊትር የሚደርስ ኤታኖል ለማምረት የሚያስችል የኤታኖል ፋብሪካ ለመገንባት ታቅዷል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ረገድም 31 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 11 ሜጋ ዋቱን ለራሱ ተጠቅሞ፣ ቀሪውን 20 ሜጋ ዋት ለብሔራዊ የኃይል ቋት እያስገባ ይገኛል፡፡ የፋብሪካው የአገዳ እርሻ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዋቄ ጢዮ፣ ሰሜን ዶዶታ እና ወለንጪቲ ተብለው በሚታወቁ አካባቢዎች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የእርሻ ማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ አዲሱ ፋብሪካ በአጠቃላይ 16ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት ይኖረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከለማው 12ሺህ 800 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት ውስጥ 7ሺህ ሄክታሩ በፋብሪካው አካባቢ በሚገኙ በ32 የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኀበራት በታቀፉ 9ሺህ 100 አርሶ አደር አባላት የለማ ነው፡፡ በዚህም አባላቱ በሚያገኙት ከፍተኛ ገቢ ከልማቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ለአብነት በአንዳንድ ማህበራት በአማካይ በየ18 ወራት በሚደረግ የትርፍ ክፍፍል አባላት እንደየስራቸው መጠን በነፍስ ወከፍ ከ50ሺህ እስከ 240ሺህ ብር ድረስ ገቢ ያገኙበትን አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፋብሪካው ለአርሶ አደሮቹ በመስኖ የለማ መሬት በማዘጋጀት፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት በማመቻቸት፣ ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት አርሶ አደሮቹ ሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በመሸጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል፡፡ ወንጂሸዋስኳርፋብሪካ 16 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
  • 17. II. መተሐራ ስኳር ፋብሪካ 17ስኳር ኮርፖሬሽን ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በመቀጠል በሆላንዱ ኤች ቪ ኤ ተገንብቶ በ1962ዓ.ም ወደ ስራ የገባው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ፋብሪካው ከ10ሺህ ሄክታር በላይ በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ መሬት ያለው ሲሆን፣ ዓመታዊ አማካይ ስኳር የማምረት አቅሙ በዓመት 136ሺህ 692 ቶን ይደርሳል፡፡ ፋብሪካው ባካሄደው የማስፋፊያ ፕሮጀክት የኤታኖል ፋብሪካ ገንብቶ ከ2003ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ኤታኖል በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ ኤታኖል የማምረት ዓመታዊ አቅሙም በአመት እስከ 12.5 ሚሊዮን ሊትር ይሆናል፡፡ በተጨማሪ “ባጋስ” ተብሎ ከሚጠራው የሸንኮራ አገዳ ገለባ 9 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት የራሱን የኃይል ፍላጎት እያሟላ የሚገኝ እድሜ ጠገብ ፋብሪካ ነው፡፡ ስለ መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሲነገር የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍናን ማንሳት የግድ ይላል፡፡ ፋብሪካው ካይዘንን በሚገባ በመተግበርና ውጤት በማስመዝገብ ቀዳሚ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የካይዘን ውድድር በተቋም፣ በልማት ቡድንና በግለሰብ አንደኛ በመሆን የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ በዚህ ብቻ አላበቃም በተመሳሳይ መስከረም 8 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የካይዘን ውድድርላይካይዘንንበማስቀጠልበተቋምና በልማት ቡድን ደረጃ በድጋሚ የአንደኝነት የክብር ሜዳሊያዎችንና ዋንጫዎችን ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እጅ ተቀብሏል፡፡
  • 18. III. ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ 18 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በምዕራብ አቅጣጫ 350 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአባይ ጮመን ወረዳ በፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ ልዩ ስሙ አገምሳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ይገኛል፡፡ የፊንጫአ ሸለቆ ለስኳር ኢንዱስትሪ ተስማሚ ሆኖ በመገኘቱ ቡከርስ አግሪካልቸራል ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ከ1970ዓ.ም ጀምሮ የቦታው አዋጭነት፣ የመሬቱ አቀማመጥና የአፈር ይዘት ሁኔታ ላይ ዝርዝር ጥናት ተካሂዶ አዋጭነቱ ተረጋገጠ፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክና የአፍሪካ ልማት ፈንድ፣ የስዊዲን፣ የአውስትራሊያና የስፔን መንግስታት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ባንኮች የፋይናንስ ምንጮች መሆናቸው ተረጋግጦ የፕሮጀክቱ ሥራ ጥር 1981ዓ.ም ተጀመረ፡፡ ከፊንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ እና ምስራቅ የሚገኘውን ቦታ ጨምሮ የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ጠቅላላ ይዞታ (ኮማንድ ኤሪያ) 67ሺህ 98 ሄክታር ነው፡፡ የፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ በማለፍ ለሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫነት ከዋለ በኋላ ሸለቆውን ከሁለት ከፍሎ ወደ ሰሜን በመጓዝ ከአባይ ወንዝ ጋር በሚቀላቀለው የፊንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ ክፍል (ዌስት ባንክ) ያለውን 6ሺህ 476.72 ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ በማልማት እና የፋብሪካ ተከላ በማከናወን ነበር የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ የተገነባው፡፡ የአካባቢው ከፍታ ከባህር ወለል በላይ ከ1ሺህ 350 እስከ 1ሺህ 600 ሜትር ይደርሳል፡፡ በሸለቆው ውስጥ ያለው ከፍተኛው የሙቀት መጠን 31 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሲሆን፣ ዝቅተኛው 15 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይሆናል፡፡ ዓመታዊ የዝናብ መጠኑም በአማካይ 1ሺህ 300 ሚሊ ሊትር ይጠጋል፡፡ ይህም የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ አካባቢን “ለምለም በረሃ” በሚል ልዩ ስም እንዲታወቅ አድርጎታል፡፡ ፋብሪካው ኢታኖልን በማምረት ከቤንዚል ጋር ተደባልቆ ለተሸከርካሪዎች በነዳጅነት እንዲውል ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ለሌሎች ኢንዱስትሪዎችም በግብዓትነት በማገልገል ለሀገራችን ኢኮኖሚ ጉልህ ድርሻ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡ የነባሩ ፋብሪካ ግንባታ ተጠናቆ የሙከራ ምርት የጀመረው የካቲት 1990ዓ.ም ቢሆንም መደበኛ የማምረት ስራውን የጀመረው ግን በ1991ዓ.ም ነበር፡፡
  • 19. የፋብሪካው አጠቃላይ የማስፋፊያ ፕሮጀክት 19ስኳር ኮርፖሬሽን የፊንጫአስኳርፋብሪካአጠቃላይየማስፋፊያ ፕሮጀክት የተጀመረው በ1998ዓ.ም ነው፡፡ በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በአገዳ ልማት በኩል በዌስት ባንክ 8ሺህ 300 ሄክታር በአገዳ የተሸፈነ መሬት እና የኢስት ባንክ እና ነሼ አካባቢዎችን በማከል ወደ 21ሺህ ሄክታር መሬት ለማሳደግ የታቀደ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 7ሺህ ሄክታር በኢስት ባንክ እንዲሁም 4ሺህ 670 ሄክታር በነሼ አካባቢ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የፋብሪካውን አገዳ የመፍጨት አቅም በማሳደግ አመታዊ የስኳር ምርቱን ወደ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል እንዲሁም ኤታኖል የማምረት አቅሙን ወደ 20 ሚሊዮን ሊትር ከፍ ለማድረግ ታቅዶ የማስፋፊያ ሥራው ተካሄደ፡፡ የፋብሪካው ማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራ ተጠናቆ ከ2006ዓ.ም ጀምሮ ወደ ማምረት ሂደት ውስጥ የገባ ሲሆን፣ በእርሻ ማስፋፊያ ስራም ከ19ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በአገዳ ለመሸፈን ተችሏል፡፡ በዚህ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በቀን 6ሺህ 600 ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 1ሚሊዮን 600ሺህ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ነጭ ስኳር የማምረት አቅም ያለው አንድ ተጨማሪ የስኳር ፋብሪካ ተገንብቷል፡፡ ይህ ደግሞ ነባሩ ፋብሪካ ካለው አቅም ጋር ተዳምሮ አጠቃላይ በሁለቱም ፋብሪካዎች የሚመረተውን አመታዊ የስኳር መጠን 2 ሚሊዮን 700ሺህ ኩንታል ያደርሰዋል፡፡ ለመኖሪያ መንደሮችና ለፋብሪካው አገልግሎት የሚውል የኃይል አቅርቦትን በተመለከተም ፋብሪካው በመሰረታዊነት የራሱን የኃይል ምንጭ ቀደም ሲልም በመጀመሪያው ምዕራፍ ከተተከለ ሁለት ባለ 3.5 ሜጋ ዋት የእንፋሎት ተርባይን ያሟላ ነበር፡፡ በማስፋፊያ የተገነባው ሁለት ባለ 12 ሜጋ ዋት የእንፋሎት ተርባይን ሲጨመርም በድምሩ 31 ሜጋ ዋት ማመንጨት ይችላል፡፡ ከዚህ ውስጥ ለፋብሪካው እና ለመስኖ ፓምፖች እንዲሁም ለሠራተኛ መኖሪያ መንደሮች እና ለልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት 21 ሜጋ ዋት የሚያስፈልግ ሲሆን፣ ቀሪውን 10 ሜጋ ዋት ደግሞ ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ማስገባት ተጀምሯል፡፡
  • 20. IV. ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ 20 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ በአዋሽ ተፋሰስ ዝቅተኛው አካባቢ በአፋር ክልል በ50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ670 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በግዙፍነቱ እና በተሻለ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነቱ ጭምር ከሌሎቹ ነባር ስኳር ፋብሪካዎች የሚለየው ይህ ፋብሪካ ከሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ በስተምስራቅ ወደ ጅቡቲ የሚወስደውን መንገድ ተከትሎ ከጅቡቲ ወደብ በ300 ኪ.ሜ ርቅት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ምቹ ሁኔታም ወደፊት የፋብሪካውን ምርት ወደ ውጭ ለመላክ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በ1998ዓ.ም የፕሮጀክት ሥራው የተጀመረው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ይዞታ በሚሌ፣ በዱብቲ፣ በአሳኢታ እና በአፋምቦ ወረዳዎች ውስጥ ይገኛል፡፡ ግንባታው OIA (Overseas Infrastructure Alliance) በተባለ የህንድ ኩባንያ የሚካሄደው ግዙፉ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፍ ጥቅምት 2007ዓ.ም የሙከራ ምርት ጀምሮ በአሁኑ ወቅት በመደበኛ የምርት ሂደት ውስጥ ይገኛል፡፡ ፋብሪካው ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በቀን 13ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ከሚያመነጨው 60 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 38 ሜጋ ዋቱን
  • 21. 21ስኳር ኮርፖሬሽን ለብሔራዊ የኃይል ቋት በማስገባት እንዲሁም 31 ሚሊዮን ሊትር ያህል ኤታኖል በማምረት ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ያረጋግጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለፋብሪካው በግብዓትነት ከሚያስፈልገው በ50ሺህ ሄክታር መሬት ከሚለማ የሸንኮራ አገዳ ውስጥ 25ሺህ ሄክታሩ የሚለማው በፋብሪካው ሲሆን፣ ቀሪው 25ሺህ ሄክታር መሬት ደግሞ በአካባቢው በሚገኙ አገዳ አብቃይና አቅራቢ አርብቶ አደሮች የሚለማ ነው፡፡ የአገዳ ልማቱ በመከናወን ላይ የሚገኘው በአዋሽ ወንዝ ላይ በተገነባው የተንዳሆ ግድብ አማካኝነት ሲሆን፣ ከ1.86 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ በላይ የመያዝ አቅም ያለው ይህ ግድብ 60ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚያለማ ይጠበቃል፡፡ ፋብሪካው በመስኖ የሚለማ መሬት ለአካባቢው አርብቶ አደሮች በማመቻቸቱም አርብቶ አደሩ ወደ ከፊል አርሶ አደርነት መሸጋገር የቻለበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል፡፡ የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ • በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከ22 ሺህ 835 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ሆኗል፤ • ከ42 ኪ/ሜ በላይ የዋና ቦይና ተያያዥ ስትራክቸሮች ግንባታ ተከናውኗል፤ የአገዳ ልማት • በመጀመሪያው ዙር 20 ሺህ 866 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤ የቤቶች ግንባታ • 175 የመኖሪያ ቤቶች እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ 429 ሕንጻዎች (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤
  • 22. 22 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ V.የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ፣ ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ 50 ኪ.ሜ ያህል የሚርቀው ይህ ፋብሪካ፣ በአፋር ክልል በዞን ሦስት አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች ውስጥ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ 500 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ባለው የከሰም ግድብ አማካኝነት በ20ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ በማልማት ላይ ይገኛል፡፡ የአገዳ ልማቱም የሚከናወነው በከሰም እና ቦልሀሞን በተሰኙ አካባቢዎች ነው፡፡ የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ሆኖ የተጀመረ ቢሆንም ስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመ ወዲህ ቦታው ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ካለው ርቀት አንፃር ተመዝኖና ተጠንቶ እራሱን ችሎ እንደ አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲንቀሳቀስ ተደርጓል፡፡ ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ፣ በ2007ዓ.ም መጨረሻ ላይ የሙከራ ምርት ጀምሯል፡፡ አሁን ስኳር እያመረተ ሲሆን፣ በሂደት በቀን 6ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ ፋብሪካው በቀጣይም 10ሺህ ቶን ሸንኮራ አገዳ በቀን ወደሚፈጭበት ደረጃ እያደገ የሚሄድ ሲሆን፣ የኤታኖል ፋብሪካና የኮጀነሬሽን ፋሲሊቲም ይኖረዋል፡፡
  • 23. 23ስኳር ኮርፖሬሽን ፋብሪካው በመጀመሪያ ምዕራፍ 1 ሚሊዮን 530ሺህ ኩንታል ስኳር እና 12 ሚሊዮን 500ሺህ ሊትር ኢታኖል በዓመት የማምረት አቅም የሚኖረው ሲሆን፣ ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ ደግሞ በዓመት 2 ሚሊዮን 600ሺህ ኩንታል ስኳር እና 30 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል ማምረት ይችላል፡፡ ከዚህ ባሻገር 26 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 15 ሜጋ ዋቱን ለብሔራዊ የኃይል ቋት እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡ የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ • 2ሺህ 946 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤ • የ20.5 ኪ.ሜ የዋና ቦይ ግንባታ ተጠናቋል፤ የአገዳ ልማት • በፋብሪካው አማካኝነት 2ሺህ 413 ሄክታር መሬት እንዲሁም በአሚባራ እርሻ ልማት (አውት ግሮወር) 6ሺህ ሄክታር መሬት በአጠቃላይ 8 ሺህ 443 ሄክታር በአገዳ ተሸፍኗል፤ የቤቶች ግንባታ • 517 የመኖሪያ ቤቶች እና 20 አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤
  • 24. 24 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ እና በኢሉ አባቦራ ዞኖች በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ ከአዲስ አበባ - ጅማ - በደሌ - ነቀምቴ መስመር በ540 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ በኢሉአባቦራ፣ በምስራቅ ወለጋና በጅማ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ 49 ቀበሌዎችን የሚያካትት ነው፡፡ የአካባቢው ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ በአማካይ 1350 ሜትር ሲሆን፣ የአየር ሁኔታው ሞቃታማ ነው፡፡ አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኑ ደግሞ 1400 ሚሊ ሊትር ይደርሳል፡፡ የዝናብ ስርጭቱም ከግንቦት እስከ ጥቅምት ይዘልቃል፡፡ በአብዛኛው ጥቁርና አልፎ አልፎ ቀይ ቡናማ አፈር የሚገኝበት ይህ አካባቢ ከአየር ንብረቱ ጋር ተዳምሮ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ምቹና ተስማሚ እንዲሆን አስችሎታል፡፡ AL-Habasha Sugar Mills PLC ከተባለ የፓኪስታን ኩባንያ በ2005ዓ.ም ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን ይዞታነት የተሸጋገረው ይህ ፋብሪካ በሂደት በ20 ሺህ ሄክታር መሬት የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት በመጠቀም በቀን 8 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ ፕሮጀክቱ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን በተዘዋወረበት ወቅት የፋብሪካው የግንባታ ስራ ከ90 በመቶ በላይ ተጠናቆ የነበረ ሲሆን፣ ከ2005 በጀት ዓመት ጀምሮ የስራ VI. አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ
  • 25. 25ስኳር ኮርፖሬሽን አመራር አባላት ተመድቦለትና በየደረጃው የሰው ኃይል ተሟልቶለት ተልዕኮውን ለማሳካት እየሰራ ይገኛል፡፡ ፋብሪካው በግብአትነት የሚጠቀምበትን ሸንኮራ አገዳ ለማልማት ውሃ ከዲዴሳ ወንዝ የሚያገኝ ሲሆን፣ ከስኳር ምርቱ በተጨማሪ ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ራሱን ከመቻል አልፎ ቀሪውን ለብሔራዊ የኃይል ቋት እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡ ከፍተኛ የኤታኖል ምርት የማምረት አቅምም አለው፡፡ ፋብሪካው ግንቦት 6 ቀን 2007ዓ.ም በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተመርቆ ስኳር ማምረት ጀምሯል፡፡ የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ • 1ሺ 660 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል የአገዳ ልማት • 3ሺህ 448 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤ የቤቶች ግንባታ • 64 የመኖሪያ ቤቶች እና ሁለት አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤
  • 26. 26 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ ዋና ካምፕ ከአዲስ አበባ በደቡብ አቅጣጫ 900 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የስኳር ልማቱ በደቡብ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን የሰላማጎ እና የኛንጋቶም ወረዳዎች፣ በቤንች ማጂ ዞን የሱርማ እና የሜኢኒትሻሻ ወረዳዎች እንዲሁም በካፋ ዞን የዴቻ ወረዳ የተመረጡ አካባቢዎች እየተካሄደ ነው፡፡ በፕሮጀክቱ በ100ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ የሚጠቀሙ አራት ስኳር ፋብሪካዎች እየተገነቡ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሶስቱ እያንዳንዳቸው በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 278ሺህ ቶን ስኳር እንዲሁም እያንዳንዳቸው በዓመት 26ሺህ 162 ሜትር ኩብ ኤታኖል ያመርታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አንዱ ፋብሪካ ደግሞ በቀን 24ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 556ሺህ ቶን ስኳር እንዲሁም በዓመት 52ሺህ 324 ሜትር ኩብ ኤታኖል ያመርታል፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ልማቱ የሚያስፈልገው I ኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በተለያየ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚገኙ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብረካ
  • 27. 27ስኳር ኮርፖሬሽን የመስኖ ውሃ ኦሞ ወንዝ ላይ በሚገነባና 381 ሜትር ስፋት እና 22.4 ሜትር ከፍታ በሚኖረው የውኃ መቀልበሻ ዊር አማካይነት የሚገኝ ነው፡፡ በፕሮጀክቱ የሚገነቡት አራቱ ስኳር ፋብሪካዎች ሙሉ የማምረት አቅማቸው ላይ ሲደርሱ በአጠቃላይ በዓመት እስከ 13 ሚሊዮን 390ሺህ ኩንታል ስኳር እና 130 ሚሊዮን 810ሺህ ሊትር ኤታኖል ማምረት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም 415 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 275 ሜጋ ዋቱን ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ያስገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በፕሮጀክቱ እየተገነቡ ያሉት አራቱም ስኳር ፋብሪካዎች በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ወደ ምርት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብረካ
  • 28. 28 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ኦሞ ኩራዝ-1 ስኳር ፋብሪካ • በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) እየተገነባ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ-1 ስኳር ፋብሪካ በ2009ዓ.ም ወደ ምርት ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፤ • ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፤ የመስኖ መሠረተ ልማት • ለኩራዝ 1 እና ኩራዝ 2 ፋብሪካዎች በ100 ኪሎ ሜትሮች የሚቆጠሩ የሁለተኛ፣ ሶስተኛና አራተኛ ቦዮችና ተያያዥ ግንባታዎች ተጠናቀው ከ16 ሺህ 141 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤ የአገዳ ልማት • ለኦሞ ኩራዝ 1፣2 እና 3 ፋብሪካዎች 12 ሺህ 903 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤ የቤቶች ግንባታ • በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 830 መኖሪያ ቤቶችና 29 አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤ ኦሞ ኩራዝ-2 ስኳር ፋብሪካ • ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ እየተገነባ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ 2 ፋብሪካ በ 2009ዓ.ም ሥራ ለመጀመር የሚያስችለው ደረጃ ላይ ይገኛል፤ • ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፡፡ ኦሞ ኩራዝ-3 ስኳር ፋብሪካ • በተመሳሳይ ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፤ ኦሞ ኩራዝ-5 ስኳር ፋብሪካ • ፋብሪካውን ለመገንባት JJIEC ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር የኮንትራት ውል ተፈርሞ የሲቪል ስራው ተጀምሯል፤ • ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 24ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፤
  • 29. 29ስኳር ኮርፖሬሽን ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብረካ
  • 30. 30 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ II. ጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ 576 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት በዋናነት የሚገኘው በአማራ ክልል ሲሆን፣ የተወሰነ የአገዳ እርሻ ልማቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚካተት ነው፡፡ በዚህ ፕሮጀክት እያንዳንዳቸው በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያላቸው ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች እየተገነቡ ሲሆን፣ በ50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማን የሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት ይጠቀማሉ፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚውለው የመስኖ ውሃ የሚገኘው በበለስ ወንዝ ላይ በተገነባ የውሃ መቀልበሻ ዊር አማካይነት ነው፡፡ ፋብሪካዎቹ ሙሉ የማምረት አቅማቸው ላይ ሲደርሱ እያንዳንዳቸው በዓመት 2 ሚሊዮን 420ሺህ ኩንታል ስኳር እና 20 ሚሊዮን 827ሺህ ሊትር ኤታኖል የማምረት አቅም ይኖራቸዋል፡፡ በፕሮጀክቱ በመገንባት ላይ የሚገኙት ሁለቱ ፋብሪካዎች በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ግንባታቸው ተጠናቆ ስራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጣና በለስ-1 ስኳር ፋብሪካ • በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) እየተገነባ የሚገኘው የጣና በለስ-1 ስኳር ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፤ የመስኖ መሠረተ ልማት • በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 30 ኪ/ሜ ርዝመት ያለውና 60 ሜ/ኩ ውሃ በሰከንድ ማስተላለፍ የሚችል የወንዝ መቀልበሻ፣ መቆጣጠሪያ፣ የደለል ማስወገጃ እና የዋና ቦይ ግንባታ ተጠናቋል፤ • 12 ሺህ 807 ሄ/ር መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤
  • 31. 31ስኳር ኮርፖሬሽን የአገዳ ልማት • በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 13ሺህ 49 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤ የቤቶች ግንባታ • በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 1ሺህ 945 መኖሪያ ቤቶች እና 20 አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤ ጣና በለስ-2 ስኳር ፋብሪካ • በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) እየተገነባ የሚገኘው የጣና በለስ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 12 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፤ ጣና በለስ-1 ስኳር ፋብሪካ
  • 32. 32 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ III. ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ በ1ሺ 300 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በትግራይ ክልል በምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ይገኛል፡፡ በፕሮጀክቱ በ50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት ተጠቅሞ በቀን 24ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው የስኳር ፋብሪካ ይገነባል፡፡ በዚህ መሰረት CAMC ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር የኮንትራት ውል ተገብቶ ስራው በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ግንባታው ተጠናቆ ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በዓመት 4 ሚሊዮን 840ሺ ኩንታል ስኳር እና 41 ሚሊዮን 654 ሊትር ኤታኖል ማምረት ይችላል፡፡ ለሸንኮራአገዳልማቱየሚያስፈልገውየመስኖ ውሃ አቅርቦት ዛሬማ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ ከሚገኘው የሜይ-ዴይ ግድብ የሚገኝ ሲሆን፣ ግድቡ ሲጠናቀቅ 840 ሜትር ስፋት እና 135.5 ሜትር ቁመት ይኖረዋል፡፡ የመስኖ መሠረተ ልማት • 3 ቢሊዮን 497 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም የሚኖረው የዛሬማ ግድብ ግንባታ በመከናወን ላይ ይገኛል፤ • ከግድብ ግንባታው ጎን ለጎን በጠብታ መስኖ 7ሺህ ሄ/ር መሬት ለማልማት NETAFIM ከተባለ የእስራኤል ኩባንያ የመስኖ መሠረተ ልማት ሥራ ተቋራጭ ጋር ውል ተገብቶ ሥራው ተጀምሯል፤ • የ10 ኪ/ሜትር የዋና ቦይ (Main canal) ግንባታ ተጠናቋል፤ • የ3ሺህ ሄ/ር መስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ እየተከናወነ ሲሆን፣ የመስኖ ውሃው እስከሚደርስ ድረስ የጥጥ ልማት እየተካሄደ ነው፤ • 261 ሄክታር መሬት ውሃ ገብ ሆኗል፤ የአገዳ ልማት • 220 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤ የቤቶች ግንባታ 800 መኖሪያ ቤቶች እና 36 አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤
  • 33. 33ስኳር ኮርፖሬሽን ምርምርና ልማት ማዕከል በሀገራችን በስኳር ኢንዱስትሪ የምርምር ስራ የተጀመረው ኤች.ቪ.ኤ በተባለ የደች ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ1951 ነበር። የምርምር ክፍሉ ዋናው ማዕከል በአምስተርዳም ሆኖ በወቅቱ በኢትዮጵያ የስኳር ፋብሪካዎች እንዲስፋፉ ጠንካራ ድጋፍ ይሰጥ ነበር፡፡ ኩባንያው በወንጂ ሸንኮራ አገዳ መትከልና ስኳር ማምረት ሲጀምር እ.ኤ.አ. ከ1958 አንስቶ በስኳር ኢንዱስትሪ ስልጠና መስጠት እንደጀመረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 192/2003 ሲቋቋምም ለምርምርና ስልጠና ተግባራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሥራው በዘርፍ ደረጃ እንዲመራ ተወስኖ ከ2003ዓ.ም ጀምሮ የሚከተሉትን አበይት ተግባራት ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ • ችግር ፈቺነትን መሰረት ያደረገ ምርምር (applied research) በማካሄድ ለኮሜርሽያል አገልግሎት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ፤ • ምርታማነትን በማሳደግ ምርትን መጨመርና ወጪን መቀነስ፤ • የአመራረት ቅልጥፍናን ለማሻሻል የተገኘውን የምርምር ውጤት በእያንዳንዱ ስኳር ፋብሪካና ማሳ ላይ በአግባቡ እንዲውል ማስረጽ፤ • በአመራረት ሥርአት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃዎች (optimization) እንዲወሰዱ የቴክኒክና የምክር አገልግሎት መስጠት፤ • ስራ ላይ የዋሉ የምርምር ውጤቶች ለኢንዱስትሪው ያስገኙትን ፋይዳ እና በአካባቢው ላይ ያደረሱትን ተጽዕኖ መገምገምና አዳዲስ የምርምር አቅጣጫዎችንና ስትራቴጂዎችን
  • 34. 34 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ መንደፍ፤ • ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ፣ በሽታ የሚቋቋሙ፣ ከፍተኛ የስኳር ይዘት ያላቸውና ቶሎ የሚደርሱ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችንእንዲሁምየተሻሻሉየሸንኮራ አገዳና የስኳር አመራራት ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎችን ለፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ማስተዋወቅና በስራ ላይ ማዋል፤ • በኦፕሬሽን ላይ የነበሩ ቴክኖሎጂዎች ደረጃቸው (ስታንዳርድ) ሳይጓደል ትግበራቸው የሚቀጥልበትን አሰራር መቀየስ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስተግበር፤ • ኢንዱስትሪውን በሰለጠነና ውጤታማ በሆነ የሰው ኃይል ለመደገፍ ሥልጠናዎችን በማመቻቸትና በማሰልጠን ቁልፍ ሚና መጫወት፡፡ ከአዲስ አበባ በ110 ኪ.ሜ ርቀት ወንጂ ላይ የሚገኘው የምርምርና ልማት ማዕከል እነዚህን ተግባራት በብቃት ለመወጣት በ2008ዓ.ም በአዲስ መልክ ተደራጅቷል፡፡ ማዕከሉ በወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ፣ ተንዳሆ፣ አርጆ ዲዴሳ እና ከሰም ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም በጣና በለስ፣ ኦሞ ኩራዝ እና ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የምርምር ጣቢያዎችን አቋቁሞ የሸንኮራ አገዳ፣ የዝርያ ልማት እና የስኳር ቴክኖሎጂ ምርምሮችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
  • 35. 35ስኳር ኮርፖሬሽን በመላ ሀገሪቱ የስኳር ሥርጭት የሚከናወነው የንግድ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የስኳር መጠን (ኮታ) የሥርጭት አሠራር ሥርዓት መሰረት ሲሆን፣ የሚከናወነውም በሚከተሉት ሦስት መንገዶች ነው፡፡ የስኳር ሥርጭት - በአዲስ አበባ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስኳር የሚሰራጨው በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በኩል ኮታ በተመደበላቸው የሸማቾች የሕብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ሲሆን፣ ሥርጭቱ የሚከናወነው በማኅበራቱ ሱቆችና እነሱ በሚያከፋፍሏቸው ቸርቻሪ ነጋዴዎች መሸጫ መደብሮች ነው፡፡ እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ተጓዳኝ ምርቶች ንግድ ዘርፍ (የቀድሞ ኢትፍሩት) ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከሚያገኘው ኮታ ላይ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያከፋፍላል፡፡ የስኳር ሥርጭት - በክልሎች በክልሎች ስኳር ለተጠቃሚዎች የሚሰራጨው በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (የቀድሞ ጅንአድ) አማካኝነት ሲሆን፣ ምርቱ ወደ ተመረጡ ማሰራጫ ከተሞች ከተጓጓዘ በኋላ በየክልሉ ንግድ ቢሮ በኩል ለቸርቻሪ ነጋዴዎች ይሰራጫል፡፡ የስኳር ሥርጭት - ለልዩ ልዩ ኢንዱስትሪዎች ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የንግድ ሚኒስቴርና ስኳር ኮርፖሬሽን በጥናት የመደቡላቸውን የስኳር መጠን (ኮታ) ያገኛሉ፡፡ በስኳር ሥርጭት የሚሳተፉ ተቋማት ስኳር የሚያገኙት ከኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የስኳር መጋዘኖችና ከስኳር ፋብሪካዎች ነው፡፡ የስኳር ሥርጭት
  • 36. የስኳር ኮርፖሬሽን አደረጃጀት ከመጋቢት 2008ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት የአደረጃጀት ለውጥ የተቋሙን ወሳኝ የስራ ሂደቶች መሠረት በማድረግ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ስር በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች የሚመሩ የስትራተጂያዊ ድጋፍ፣ የኢንቨስትመንት ጥናትና ልማት፣ የኦፕሬሽንስ እና የማርኬቲንግ የሥራ ዘርፎች ተዋቅረዋል፡፡ በእነዚህ እና በዋና ሥራ አስፈጻሚ ፅ/ቤት ስር በሥራ አስፈጻሚዎች የሚመሩ 21 የስራ ክፍሎች ተቋቁመዋል፡፡ እንዲሁም ለዋና ሥራ አስፈጻሚው በቀጥታ ተጠሪ የሆኑ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት፣ የፋይናንስ፣ የምርምርና ልማት ማዕከል፣ የፕላኒንግ፣ የማሽነሪና የቴክኒክ አገልግሎት፣ የሥነ ምግባርና የመልካም አስተዳደር እና የኦዲት የሥራ ክፍሎች በአዲስ መልክ ተደራጅተዋል፡፡ በተጨማሪም የዋና ሥራ አስፈጻሚ የኮርፖሬት ሪፎርምና አቅም ግንባታ እና የፕሮጀክትና ኦፕሬሽንስ አማካሪዎች በመዋቅሩ ውስጥ ተካተዋል፡፡ ተ.ቁ በስትራቴጂያዊ ድጋፍ ስር የተደራጁ የስራ ክፍሎች 1 ሰው ኃብት ልማትና አመራር 2 ካይዘንና ለውጥ አመራር 3 ግዥና ሎጀስቲክስ 4 ንብረትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት 5 አይ ሲ ቲ ተ.ቁ በኢንቨስትመንት ጥናትና ልማት ስር የተደራጁ የስራ ክፍሎች 1. የህዝብ ተሳትፎና ልማት 2. የመስኖ መሰረተ ልማት ኮንትራት አስተዳደር 3. የፋብሪካ ግንባታ ኮንትራት አስተዳደር 36 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
  • 37. ተ.ቁ በኦኘሬሽንስ ስር የተደራጁ የስራ ክፍሎች 1. የፋብሪካ ኦኘሬሽንስ ክትትልና ድጋፍ /ክላስተር- 1/ 2. የፋብሪካ ኦኘሬሽንስ ክትትልና ድጋፍ /ክላስተር- 2/ 3. የእርሻ ኦኘሬሽንስ ክትትልና ድጋፍ /ክላስተር- 1/ 4. የእርሻ ኦኘሬሽንስ ክትትልና ድጋፍ /ክላስተር- 2/ 5. የተጓዳኝ ምርቶች ተ.ቁ በማርኬቲንግ ስር የተደራጁ የስራ ክፍሎች 1. የገበያ ጥናትና ኘሮሞሽን 2. የሀገር ውስጥ ግብይት 3. የውጭ ግብይት ተ.ቁ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ስር የተደራጁ የስራ ክፍሎች 1. የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን 2. የሕግ አገልግሎት 3. የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ 4. የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ሴክሬታሪያት 4 የመሬት ዝግጅትና አገዳ ልማት 5 የቤቶችና መሰረተ ልማት ኮንትራት አስተዳደር 37ስኳር ኮርፖሬሽን
  • 38. 38 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ 1.የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት • የዋና ሥራ አስፈጻሚውን ጽ/ቤት ያደራጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ • ከባለድርሻ አካላት የሚመጡ መልዕክቶችን፣ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን ተቀብሎ በማስተናገድ ምላሽ ይሰጣል፣ ለዋና ሥራ አስፈጻሚ የሚቀርቡ ጉዳዮችን ለይቶ በማቅረብ ያስወስናል፣ • ከመሠረታዊ የሠራተኛ ማህበርና ከሠራተኞች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን፣ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመመካከር ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ያደርጋል፡፡ 2.የኢንቨስትመንት ጥናትና ልማት • የስኳርና የስኳር ተጓዳኝ ልማቶችን የአዋጭነት ጥናቶች እንዲጠኑ ያደርጋል፣ ሲጸድቁም ይተገብራል፣ • በስኳር ልማት አካባቢዎች የሚገኘውን ማህበረሰብ የልማቱ አጋር እንዲሆን ይሰራል፣ ከልማቱም ተጠቃሚ እንዲሆን የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናል፣ • የፋብሪካ፣ የመስኖ፣ የቤቶችና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲሁም የመሬት ዝግጅት ኮንትራቶችን ያስተዳድራል፣ • ልማቱን በሽርክና ወይም በጋራ ለማልማት አቅሙ ያላቸውን የአገር ውስጥና የውጪ ባለሃብቶችን በማፈላለግና አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ከስምምነት ላይ በመድረስ ወደ ሥራ ያስገባል፡፡ 3.ኦፕሬሽንስ • በስራ ላይ ያሉ ፋብሪካዎችን እንቅስቃሴ ለመከታተልና ለመደገፍ የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ይነድፋል፣ የድርጊት መርሃ ግብር አውጥቶ ሥራ ላይ ያውላል፣ • ወደ ኦፕሬሽን የሚገቡ አዳዲስ ፋብሪካዎችን ከፍተሻና ከሙከራ ምርት (ኮሚሽኒንግ) ጀምሮ ያላቸውን እንቅስቃሴ ይከታተላል፣ • የተጓዳኝ ምርቶችን በመጠቀም የሰብልና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንስሳት ሃብት ልማትን ያስፋፋል፣ • ለፋብሪካዎች የሚያስፈልጉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማጥናትና በመምረጥ በስራ ላይ ያውላል፡፡ በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሚመሩ የሥራ ዘርፎችና የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት አበይት ተግባራትና ኃላፊነት የሚከተሉት ናቸው፡፡
  • 39. 39ስኳር ኮርፖሬሽን አዘጋጅ፡- ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ፡- ጋሻው አይችሉህም የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ፡- ካዛንቺስ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ገባ ብሎ ስልክ ቁጥር፡- ሞባይል - +251911 67 77 54 ቢሮ - +25111 552 74 75 ኢ-ሜይል- pr@ethiopiansugar.com 4.ማርኬቲንግ • ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመግባት የሚያስችል የገበያ ጥናትና ማርኬት ቅኝት (ኢንተለጀንስ) ያደርጋል፣ • የሀገር ውስጥ ገበያ የስኳር ፍላጎት መሟላቱን እና የሥርጭት ሥርዓቱ ፍትሃዊ መሆኑን ያረጋግጣል፣ • በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያግዙ የብራንዲንግ፣ የፓኬጂንግና ሌሎች የስታንዳርዳይዜሽንና የሰርቲፊኬሽን ሥራዎችን ያከናውናል፣ • ተቋማዊ ገጽታን የሚገነቡ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶችን፣ ባዛሮችንና የንግድ ትርኢቶችን ያዘጋጃል፤ በውጭ ሀገራት በሚዘጋጁት ላይም እንደአስፈላጊነቱ ይሳተፋል፡፡ 5.ስትራቴጂያዊ ድጋፍ • በስትራቴጂያዊ ዕቅድ ላይ ተመስርቶ ሥራዎችን ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ያቀናጃል፣ ይመራል፣ • የካይዘንና ለውጥ አመራር ሥራዎችን በዕቅድ ላይ በተመሰረተ አቅጣጫ እንዲከናወኑ ያደርጋል፣ • የግዥ፣ የሎጂስቲክስ እንዲሁም በወደብና በጉምሩክ መጋዘን ያሉ ንብረቶች ክሊራንስ ሥራዎች በጤናማ የንግድ ውድድር አግባቦች እንዲፈጸሙ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ • የመልካም አስተዳደር ችግር መንስኤዎችንና የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮችን በመለየት ይፈታል፡፡
  • 40. የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A info@ethiopiansugar.com Ethiopiansugar.com facebook.com/etsugar