SlideShare a Scribd company logo
1 of 58
መመሪያ ቁጥር 30/2013
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና
ለመቆጣጣር የወጣ መመሪያ
መግቢያ
• የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በአለም አቀፍ ደረጃ ፣
በአህጉራችን ፣ እንዲሁም በሃገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ
ጉዳት እያደረሰ ያለ እና ትልቅ ስጋት የደቀነ ወረርሽኝ
ነው።
• በአሁኑ ወቅት ይህን ወረርሽኝ መግታት እና መከላከል
ትልቅ ሃገራዊ የትኩረት አጀንዳ ነው። ከበሽታው
አስከፊነት አንጻር በርካታ ሀገራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
በማወጅ ሰዎች ከቤት እንይወጡ/ እንቅስቃሴዎችን
በመገደብ እንዲሁም ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን
እንዲወስዱ ሲያስገድዱ ቆይተዋል፡፡
•
• በሀገራችንም የወረርሺኙን መከሰት ተከትሎ መንግስት
ይህንን አደገኛ ወረርሽኝን ለመከላከል ዘርፈ ብዙ
እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን
 ይህ ወረርሺኝ በቀላሉ የሚተላለፍ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ
አድማሱን በማስፋት የዜጎችን ህይወት እንዲሁም የሀገርን
ህልውና አደጋ ጭምር አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ
 ወረርሽኙን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት
ለመቀነስ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለማሳለጥ እና ውጤታማ
ለማድረግ
 ከተለመደው አሠራር እና ሕገ-መንግሥታዊ ማዕቀፍ ወጥቶ በልዩ
ሁኔታ መንቀሳቀስ የሚጠይቅ ሆኖ በመገኘቱ የኢፌዴሪ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመደንገግ
ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ በማጸደቅ ለ5 ወራት
ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
 የዚህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሻውም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-
መንግሥት ሲሆን ህገ መንግስቱም ለሃገር እና ለህዝብ አደጋ
የሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ
የሚተዳደርበትን ሥርዓት በአንቀጽ 93 ላይ አስቀምጧል።
 በአንቀጽ 93 (1) (ሀ) መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
እንዲታወጅ መነሻ ከሚሆኑ ሁኔታዎች አንዱ “የሕዝብን
ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት” የሚል ነው።
የኮቪድ-19 የሕዝብን ጤንነት በከፍተኛ ደረጃ አደጋ ላይ
የሚጥል በሽታ እንደሆነ ዕሙን ነው።
 አዋጁ መንግሥት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል አስፈላጊ
የሆኑ እርምጃዎችን በሚወስድበት ጊዜ የተሻለ ነጻነት እና
አቅም እንዲኖረው፣ የመንግስት ሥልጣን ላይ ያሉ ገደቦች
ወይም የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች በተለየ ሁኔታ ለጊዜው
ተፈጻሚነታቸው ቀርቶ/ ታግዶ በሙሉ ኃይል፣ በተቀላጠፈ እና
በተቀናጀ መልኩ ለወረርሽኙ ምላሽ መስጠት የሚያስችል
መሆኑ ታምኖበት እንደታወጀ መረዳት ይቻላል፡፡
 አዋጁ ጠቅለል ያሉ ድንጋጌዎችንና አዋጁን ተከትለው
የሚወጡ ደንብና መመሪያዎች ላይ የሚጣሉ ክልከላዎችና
ግዴታዎች በሚተላለፉ አካላት ላይ የወንጀል ቅጣቶችን
ያስቀመጠ ነው፡፡
 በተጨማሪም ይህንንም አዋጅ ለማስፈጸም ይረዳ ዘንድ
ደንብ ቁጥር 466/2012 በሚኒስትሮች ም/ቤት ጸድቆ
ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ይህ ደንብ ወረርሽኙን ለመከላከል
በግለሰቦች፣ የግልም ሆነ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት
ሰጪ ተቋማት፣ ወዘተ የተጣሉ ክልከላዎችና ግዴታዎችን
ያስቀመጠ ሲሆን
 የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና
የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚሰራውን ስራ
በበላይነት የሚመራና የሚያስተባብርና በም/ጠቅላይ ዐቃቤ
ህግ የሚመራ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በሚል ተቋቁሞ ደንቡን
ለማስፈጸም የሚረዱ መመሪያዎችን ለማውጣት በተሰጠው
ስልጣን መሰረት የተለያዩ መመሪያዎችን አውጥቶ ተግባራዊ
ተደርገዋል፡፡
በእነዚህ መመሪያዎች ተጨማሪ ክልከላዎችና
ግዴታዎች ተደንግገው ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡
በአጠቃላይ በደንቡና በመመሪያዎቹ ላይ ከበሽታው
ባህሪ አንጻር በግለሰቦች፣ በመንግስትና በግል ተቋማት፣
ህዝብ በብዛት የሚሰበሰብባቸው በሀይማኖች
ቦታዎች፣ በመዝናኛዎች፣ ገበያዎች፣ ሰርግ፣ ቀብር
ወዘተ፣ የሚተገበሩ ክልከላዎችና ግዴታዎችን
በመደንገግ ሲተገበር ቆይቷል፡፡
መንግስትም ህብረተሰቡ እነዚህን ክልከላዎችና
ግዴታዎች በተለያየ መንገድ ግንዛቤ ከመፍጠር ጎን
ለጎን የተጣሉ ግዴታዎችንና ክልከላዎችን የተላለፉ
ግለሰቦችና ተቋማት ተጠያቂ የማድረግ ስራ ሲሰራ
ቆይቷል፡፡
 አነዚህ የአስቸኳይ ጊዜ ህግጋት በህዝብ ተወካዩች ም/ቤት
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ (ለ5 ወራት) ሲተገበሩ ቆይተው
ከህብረሰብ ጤና ኢኒስቲትዩትና ጤና ሚ/ር በቀረበው ሪፖርት
መነሻ ወረርሺኙን በተለመደው አሰራር /በመደበኛ የህግ
ማስከበር ስርዓት በጥንቃቄ መከላከልና መቆጣጠር
እንደሚቻል ታምኖበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነስቷል፡፡
 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ በኋላ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን
ለመከላከልና የሚያስከትለው ጉዳት ለመቀነስ ስለሚወሰዱ
ክልከላዎች እና ግዴታዎች በህግ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ
በመገኘቱ በመላው ሀገሪቱ ተፈጻሚ የሚሆን "የኮቪድ-19
ወረርሺኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያሰችል
መመሪያ ቁጥር 30/2013" በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና
ኢንስቲትዩት ጸድቆ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ተመዝግቦ
ከ25/01/2013 ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ መመሪያው ክልከላዎችንና ግዴታዎችን
ያካተተ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ፡-
• የተከለከሉ ተግባራት እና የተጣሉ ግዴታዎች (በዋናነት በግለሰቦች፣ በግልና
በመንግስት ተቋማት ላይ)
• በቤት ውስጥ ማቆያ እናክብካቤ ወቅት መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ
• የቀብር ስነ ስርአት፣ የአስክሬን ማጓጓዝ እና የሀዘን ስነ ስርአት
• በስብሰባ ወቅት መወሰድ ስላለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች
• በሀይማኖታዊ ስነስርዓት፣ በየቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶች፣ እና
የአደባባይ በዓላት አከባበር ወቅት ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ
እርምጃዎች
• የመዝናኛ፣ የመስተንግዶ አገልግሎቶች እና ስፖርታዊ ውድድሮች ሊከተሉት
የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
• በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚገኙባቸው
ተቋማት ላይ የተጣሉ ክልከላዎች እና መደረግ ያለባቸው የጥንቃቄ
እርምጃዎች
• የህግ ተጠያቂነት
የተከለከሉ ተግባራት እና የተጣሉ
ግዴታዎች
የተከለከሉ ተግባራት (አንቀጽ 4)
ማንኛውም ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ቫይረሱ እንዳለበት
እያወቀ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት፣ ወይም ቫይረሱ ወደ
ሌሎች ሰዎች ሊተላለፍ በሚችልበት ሁኔታ ከሌሎች
ሰዎች ጋር መገናኘት የተከለከለ ነው፣
 ማንኛውም ሰው ለሰላምታና ሌላ ለማንኛውም አላማ
በእጅ መጨባበጥ፣ሆነ ብሎ የእርስ በእርስ አካላዊ ንክኪ
ማድረግ የተከለከለ ነው፣
የተከለከሉ …
 ዕድሜያቸው ከስድስት አመት በታች የሆነ ህጻናት ወይም በማስረጃ
የተረጋገጠ የመተንፈሻ አካላት ችግር ያለባቸው ሰዎች በስተቀር ማንኛውም
ሰው ከመኖርያ ቤት ውጪ በማንኛውም ቦታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ
ሳያደርግ መገኘት የተከለከለ ነዉ፣
 በማንኛውም መንግስታዊ እና የግል ተቋም ሰራተኞች ከሁለት የአዋቂ
እርምጃ በታች ተጠጋግተው እና የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ
አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ወይም
 ተገልጋዮች በሚቀመጡበት ጊዜም ይሁን በማንኛዉም አኳኋን አገልግሎቱ
ሲያገኙ ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ተጠጋግተው እና የአፍ እና
አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ወይም በአንድ
ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግ የተከለከለ ነው፣
የተከለከሉ …
ማንኛውም የንግድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አፍና
አፍንጫውን ላልሸፈነ ሰው አገልግሎት መስጠት
የተከለከለ ነው፣
በክፍት ገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣
ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች
ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከሁለት የአዋቂ
እርምጃ በታች ርቀት መቆምም ሆነ መቀመጥ
የተከለከለ ነው፣
የተከለከሉ …
 ማንኛውም የግልም ሆነ የመንግስት ትምህርት ቤት፣ ኮሌጅ ወይም
ዩኒቨርሲቲ የፊትለፊት ትምህርት መስጠት መጀመር እንደሚቻል
ሳይወሰን እንዲሁም አጠቃላይ የመማር ማስተማር ስራውን
በተመለከተ በመመሪያ የሚወጡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ሳያከብር
ትምህርት መስጠት የተከለከለ ነው፣
 ማንኛውም የህጻናት ማቆያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት
እንደሚቻል ሳይወሰን እንዲሁም አገልግሎት የሚሰጥበት ሁኔታ
በተመለከተ በመመሪያ የሚወጡ ሊወሰዱ የሚገባቸው የጥንቃቄ
እርምጃዎችን ሳያከብር አገልግሎት መስጠት አይችልም።
የተጣሉ ግዴታዎች (አንቀጽ 5)
 ማንኛውም ኮቪድ 19 በሽታ አለብኝ ብሎ እራሱን
የሚጠረጥር ሰው ለሚመለከተው አካል ሪፖርት በማድረግ
የመመርመርና ቫይረሱ ወደ ሌሎች እንዳይተላፍ አስፈላጊውን
ጥንቃቄ የማድረግ ሀላፊነት አለበት፣
 በሽታው አለበት ተብሎ የሚጠረጠር ሰው ሰለመኖሩ
የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ለጤና ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ
ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣በአቅራቢያው ለሚገኙ የጤና
ተቋም ወይም ባለሞያ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣
የተጣሉ ግዴታዎች…
ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጥ የመንግስታዊም እና
የግል ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ
ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ
የንፅህና መጠበቂያ ቁሳሶችን የማቅረብ፣ ተገልጋዮች
ሁለት የአዋቂ እርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ
ምልክት የማድረግ እና ተገልጋዮች የአፍ እና አፍንጫ
መሸፈኛ ማድረጋቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፣
የተጣሉ ግዴታዎች…
ማንኛውም የመንግስታዊ እና የግል ተቋማት
ለሰራተኞች ስለበሽታው አስፈላጊውን መረጃ
የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣
በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ
ቦታዎች በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ
ነገሮችን የማዘጋጀት ፣ የበሽታውን ስርጭት
ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን
የማቅረብ፣ እና የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ
ማድረጋቸውን ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን
መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፤
የተጣሉ ግዴታዎች…
ማንኛውም የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው
ሀገር አቀፍም ሆነ የከተማ ውስጥ ትራንስፖርትን
በተመለከተ በህግ ከሚወሰነው የመጫን አቅም ልክ
ሰዎችን የመጫን፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረጉ
ሰዎችን አገልግሎት አለመስጠት፣ በቂ የአየር
ዝውርውር እንዲኖር የማድረግ ሌሎች መወሰድ
የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በመተግበር
አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፣
የተጣሉ ግዴታዎች…
ማንኛውም በሆቴል፣ በአስጎብኚነት እና በሌሎችም የቱሪዝም መስክ
የተሰማሩ ተቋማት በሰራተኞቻቸው እና ተገልጋዮቻቸው መካከል
ሁለት የአዋቂ እርምጃ ወይም የሁለት ሜትር ርቀት እንዲኖር የማድረግ፣
የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን የመቆጣጠር፣ በሽታውን
ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን የማዘጋጀት ፣ ለሰራተኞቻቸው
የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን
የማቅረብ፣ እንዲሁም የቱሪዝም አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ዘርፉ
በመመሪያ የሚያስቀምጣቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች ተግባራዊ
የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
የተጣሉ ግዴታዎች…
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አሰሪዎች በግንባታ
ሳይቶች ላይ
ማንኛውም በኢንዱስትሪ እና ምርት መስክ
የተሰማሩ መንግስታዊ እና የግል ተቋማት
ለሰራተኞቻቸው
በቤት ውስጥ ማቆያ እና ክብካቤ ወቅት መደረግ
ስላለበት ጥንቃቄ (አንቀጽ 6)
 “የቤት ውስጥ መቆያ” ማለት መኖሪያ ቤት ሆኖ በቂ የአየር
ዝውውር እንዲኖር በሚያስችል መልኩ መስኮት ወይም አየር
ማስገቢያ ያለው እና ለኮቪድ 19 በሽታ የተጋለጡ፣ የተጠረጠሩ
ወይንም ተመርምረው በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች
የሚቆዩበት ስፍራ ነው፡፡ (አንቀጽ 2 /6/)
 ማንኛውም ቀላል ወይም ምንም አይነት የኮቪድ-19 ምልክት
የሌለበት ታማሚ በቤት ውስጥ የኮቪድ 19 ህክምና አገልግሎት
እንዲያገኝ ይደረጋል።
በቤት ውስጥ ማቆያ እና ክብካቤ ላይ የሚገኝ የኮቪድ 19
ታማሚ ወይም በኮቪድ-19 በሽታ ተይዟል ተብሎ የተጠረጠረ
ግዴታዎች
 በቤተሰብ ወይም በራሱ ተለይቶ በተዘጋጀ በቂ የአየር ዝውውር ያለው
(በርና መስኮት ) ባለው ክፍል ውስጥ መቆየት፣
 ራስን ቢያንስ ለ 14 ተከታታይ ቀናት በመለየት መቆየት፣ በነዚህ ወቅቶች
ከቤት አለመውጣት፣ አፍ እና አፍንጫን በተገቢው መንገድ መሸፈን፣
 ክትትል ከሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎች ጋር ለሚኖር ግንኙነት መስመር
ክፍት ማድርግ፣ ለዚህም መስማማቱን በተዘርጋውና በቀጣይ በሚዘረጉት
የአሰራር መንገዶች ማረጋገጥ፣
በቤት ውስጥ ማቆያ … ታማሚ ወይም የተጠረጠረ
ግዴታዎች …
የኮቪድ-19 በሽታ ምልክቶቹ ከተባባሱ ወዲያውኑ
ለሚመለከተው ተቋም በስልክ ሪፖርት ማድረግ
• የተጠቀሙበትን ሶፍት፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ
ማስክ፣ የእጅ ጓንትና መሰል ቁሳቁሶችን ክዳን ባለው
ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ወይም በፕላስቲክ ከረጢት
ቋጥሮ በጥንቃቄ ማስወገድ፣
• ማንኛውም ንክኪ በሚኖርበት ወቅት በውሃና
ሳሙና መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር የእጅን
ንጽህና መጠበቅ፣
በቤት ውስጥ ማቆያ … ታማሚ ወይም
የተጠረጠረ ግዴታዎች …
• ሰዎች በጋራ ከሚጠቀሙባቸው እንደሳሎን፣
መታጠቢያ እና ምግብ ማብሰያ ያሉ ቦታዎች
በተቻለ መጠን ከመጋራት መቆጠብ ወይም
መቀነስ፣
• የተለያዩ የመጠቀሚያ እቃዎችን፣ በሮችን እና
የመሳሰሉትን ነገሮች ከመንካት መቆጠብ፣ እነዚህን
እቃዎች ነክቶ ከሆነም ጥቅም ላይ ከመዋላቸው
በፊት በአግባቡ እንዲጸዱ የማድረግ፣
የኳራንቲን እና የድንበር ላይ ጤና ቁጥጥርን
በተመለከተ (አንቀጽ 8-12)
 በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ አለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች
በኩል የኮሮና ቫይረስ የRT PCR ምርመራ ውጤት ይዞ
የሚመጣ መንገደኛን በተመለከተ (አንቀጽ 8)
 በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች በኩል የኮሮና
ቫይረስ የRT PCR ምርመራ ውጤት ሳይዝ የሚመጣ
ከስደት ተመላሽ (አንቀጽ 9)
 በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የሚያልፍ
የትራንዚት መንገደኛን በተመለከተ (አንቀጽ 10)
 በየብስ ድንበር የሚገቡ ሰዎችን በተመለከተ (አንቀጽ 11)
 ከውጭ አገር የሚጓጓዝ አስክሬን (አንቀጽ 12)
የቀጠለ…
የቀብር ስነ ስርዓት፣ የአስክሬን ማጓጓዝ እና የሀዘን
ስነ ስርዓት (አንቀጽ 13-16)
በአስክሬን ማስተካከልና ግነዛ ወቅት ሊደረጉ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች፡-
(አንቀጽ 13)
 የሟች ቤተሰብ ወይም ለሟች ኃላፊነት ያለበት ሰው አስክሬን ከጤና ተቋም ወይንም ከውጭ
ሀገር በሚረከብበት ጊዜ የአስክሬን መለየት ሂደት ላይ ከአስክሬኑም ሆነ ከሳጥኑ ጋር
ማንኛውም አይነት ንክኪ ያለማድረግ ኃላፊነት አለበት፣
 ከጤና ተቋም ውጭ ሞት ተከስቶ የሟችን አስክሬን የሚገንዙ ሰዎች ሂደቱን ካጠናቀቁ በኋላ
የተጠቀሙበትን የእጅ ጓንት፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እና ሰውነታቸውን የሸፈኑበትን
ፕላስቲክ ወይም ጋዎን በአግባቡ የማስወገድ እና እጆቻቸውን በውሃ እና በሳሙና
የመታጠብ ግዴታ አለባቸው፣
 በለቅሶ ቦታ የተገኘ ማንኛውም ሰው ተገቢውን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ፣
እንዲሁም ሌሎች ሊወሰዱ የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች የመተግበር ግዴታ አለበት።
በአስክሬን መጓጓዝ ወቅት እና በቀብር አፈፃጸም
ወቅት የሚኖሩ ግዴታዎች (አንቀጽ 14)
 ከጤና ተቋም ውጭ ሞት ተከስቶ የሟች አስክሬን ከተገነዘ በኃላ የሟች
ቤተሰብ በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲቀበር ማድረግ ኃላፊነት አለበት
 በጤና ተቋማት ላይ ሞት ከተከሰተ በኋላ ወይንም አስክሬን ከውጭ ሀገር
የሚገባ ከሆነ የሟች ቤተሰቦች አስክሬን ከተቀበሉ በኋላ ወደ ቤት ሳይወስዱ
በቀጥታ ወደ ቀብር ቦታ የመውሰድ ግዴታ አለባቸው፣
 የቀብር ስነስርዓት አፈጻጸም በአጠቃላይ ከ50 ሰው ሳይበልጥ፣ የአፍና
አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግና ሁለት የአዋቂ እርምጃ በመራራቅ መከናወን
አለበት፣
 ማንኛውም ለቅሶ ሊደርስ የመጣ ሰው ወደ ለቅሶ ቤት ከመግባቱ በፊትና
ከለቅሶ ቤት ሲወጣ እጁን በውሃና ሳሙና የመታጠብ ወይም በሳኒታይዘር
የማፅዳት ግዴታ አለበት፣
በቀብር አፈፃጸም ወቅት የሚኖሩ ግዴታዎች. ..
• አስከሬኑን ወደ ማጓጓዣው የሚጭን ወይም
ተሸክሞ ወደ ቀብር የሚወስድ ማናቸውም ሰው
አፍና አፍንጫውን የመሸፈን እንዲሁም የእጅ ጓንት
የማድረግ ግዴታ አለበት፣
• ማንኛውም በቀብሩ ላይ የተገኘ ሰው፣ እጁን በውሃና
በአስክሬን ማጓጓዝ ወይም በግብአተ መሬት ወቅት
የተሳተፈ ሰው፣ሳሙና የመታጠብ ወይም
በሳኒታይዘር የማፅዳት እና ሌሎች የጥንቃቄ
እርምጃዎችን የመተግበር ግዴታ አለበት።
ከቀብር ስነ-ስርአት በኋላ የሚኖሩ ግዴታዎች
(አንቀጸ 15)
• ከቀብር በኋላ ለቅሶ መቀመጥ በድንኳን፣ በቤት
ውስጥ ወይም ለዚሁ በተዘጋጀ ቦታ ላይ ሲደረግ
ሀዘንተኛው እና የቤተሰቡ አባላት እና ለቅሶ
የሚደርሰው ሰው ከ50 ሰው ሳይበልጥ እና ሁለት
የአዋቂ እርምጃ ርቀትን በመጠበቅና ባለመነካካት፣
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ሌሎች
በአገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው ማንዋል ላይ
የተቀመጡትን ጥንቃቄ ተፈጻሚ በማድረግ መሆን
አለበት፣
ከቀብር ስነ-ስርአት በኋላ የሚኖሩ ግዴታዎች . ..
• በለቅሶ እና በቀብር ስርአት በኋላ ከሌሎች ሰዎች ጋር በመነካካት ወይም ሊያነካካ በሚችል
መልኩ መመገብ፣ ወይም በሌሎች ሰዎች በተነካኩና ባልታጠቡ እቃዎች መመገብ የተከለከለ
ነው፣
• ማንኛውም ለቅሶ ሊደርስ የመጣ ሰው ወደ ለቅሶ ቤት ከመግባቱ በፊትና ከለቅሶ ቤት ሲወጣ
እጁን በውሃና ሳሙና የመታጠብ ወይም በሳኒታይዘር የማፅዳት ግዴታ አለበት
• ሌሎች የሚከናወኑ የሀዘን ስርአቶች እንደ ሰባት፣ አርባ ፣ሙት አመትና ሰደቃ
የመሳሰሉትን ለማክበር የሚኖሩ ማህበራዊ ስብስብን በተመለከተ በዚህ መመሪያ
አንቀጽ 22 መሰረት ይፈጸማል። (ከቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር
የተከለከለ ነው፣)
ሞት ሲከሰት የሚመለከታቸው አካላት
ግዴታዎች(አንቀጽ 16)
 እድሮች ወይም ሌሎች የሚመለከታቸው ማህበራዊ
አደረጃጀቶች በአስክሬን አገናነዝ፣በጉዞ ወቅት እና በቀብር
ስነስርዓቱ ላይ እንዲሁም በሀዘን ቤት በሚኖር የቆይታ ጊዜ
በዚህ መመሪያ ውስጥ የተጠቀሱትን የኮቪድ መከላከል
የጥንቃቄ መስፈርቶች መሟላታቸውን የማረጋገጥ ግዴታ
አለባቸው፣
 በሥርዓተ ቀብር ላይ የሚገኙት የሀይማኖት ተቋማት
ኃላፊዎች ወይም የሀይማኖት አባቶች አፍና አፍንጫቸውን
የመሸፈን፣ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት የመጠበቅ፣ በስርዓቱ
ላይ ከ50 ሰው በላይ አለመገኘቱን የማረጋገጥ፣ በለቅሶ ስርአቱ
ላይ ለሚገኘው ማህበረሰብ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር የተያያዘ
ትምህርት የመስጠት ግዴታ አለባቸው፣
ሞት ሲከሰት የሚመለከታቸው አካላት ግዴታዎች …
• በፌዴራልና ክልሎች በየደረጃው የሚገኙ የጤና፣
የፖሊስ እና ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስት
ተቋማት፣ የዞን፣ የከተማ፣ የወረዳ እና የቀበሌ
አስተዳደሮች በዚህ ክፍል ስር የተቀመጡትን
ግዴታዎች (የቀብር ስነ ስርዓት፣ የአስክሬን
ማጓጓዝ እና የሀዘን ስነ ስርዓት የተመለከቱትን)
መሟላታቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት እና በአገር
አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው ማንዋል መሰረት
የተጣሉባቸውን ዝርዝር ግዴታዎች የመተግበር
ግዴታዎች አለባቸው።
በስብሰባ ወቅት መወሰድ ስላለባቸው የጥንቃቄ
እርምጃዎች (አንቀጽ 17-20)
የተሰብሳቢዎች ብዛትን በተመለከተ (አንቀጽ 17)
 ስብሰባው በተሳታፊዎች መሀል ሁለት የአዋቂ እርምጃ ያህል (2 ሜትር)
ለመጠበቅ በሚያስችል አዳራሽ ያለ ተጨማሪ ፈቃድ እስከ 50 ሰው ሆኖ
መሰብሰብ ይቻላል
 ከላይ የተቀመጠው እንዳለ ሆኖ ከ50 ሰው በላይ መሰብሰብ ግዴታ ሆኖ
ከተገኘ ስብሰባው ሊደረግበት የታሰበበት አዳራሽን ጠቅላላ ስፋት ከግምት
ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን
በማይበልጥ ሰው ልዩ ፈቃድ ከሰላም ሚኒስቴር እና በተዋረድ ባሉ የክልል፣
ዞን እና ወረዳ የሰላም እና ፀጥታ መዋቅሮች አስቀድሞ በማኘት ሊከናወን
ይችላል።
ስብሰባውን የጠራው አካል መውሰድ ስለሚገባው
የጥንቃቄ እርምጃዎች (አንቀጽ 18)
 የግድ ካልሆነ በስተቀር በአካል የሚደረጉ ስብሰባዎችን
ከማመቻቸት ይልቅ በተቻለ መጠን በኦንላይን አማራጮች
ስብሰባዎች እንዲካሄዱ ማድረግ፣
 ስብሰባውን በሚጠራበት ጊዜ ስብሰባው በተሳታፊዎች መሀል
ሁለት የአዋቂ እርምጃ ያህል (2 ሜትር) ለመጠበቅ በሚያስችል
አዳራሽ ከ50 ሰው ሳይበልጥ መካሄድ መቻሉን የማረጋገጥ፣ የእጅ
መታጠቢያ ወይም ከአልኮል የተዘጋጀ የእጅ ማጽጃ (ሳኒታይዘር)
በበቂ መዘጋጀቱን የማረጋገጥ እና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን
የመተግበር ግዴታ አለባቸው፣
 ለስብሰባ የሚጠሯቸውን ተሳታፊዎች ስለኮሮና ቫይረስ በሽታ
መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዶች እንዲሁም በስብሰባ ወቅት
ሊከተሏቸው ስለሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች በቂ መረጃ
የመስጠት ግዴታ አለባቸው።
ስብሰባውን የሚያስተናግደው መስተንግዶ ሰጪ አካል
መውሰድ ስለሚገባው የጥንቃቄ እርምጃዎች (አንቀጽ 19)
 የስብሰባ አዳራሾች በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖራቸው
የማድረግ፣ የእጅ ንጽህናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ በቂ
ግብዓቶችን የማዘጋጀት፣ በተቻለ መጠን የተሰብሳቢዎች
መግቢያና መውጫ የተለያየ እንዲሆን የማድረግ፣
ተሰብሳቢዎች የሚጠቀሙባቸው እና በተደጋጋሚ የሚነኩ
ቁሳቁሶችን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ጸረ ተህዋሲያን ውህድ
የማፅዳት፣ እና ሌሎች በተዘጋጀው የጥንቃቄ እርምጃዎችን
የመተግበር ግዴታ አለባቸው፣
 የእያንዳንዱን ተሳታፊ ስም፣ ስልክ እና አድራሻን መዝግቦ
እስከ 14 ቀን ድረስ በፋይል የማቆየት እና በ14 ቀን ውስጥ
በበሽታው የተያዘ ወይንም የተጠረጠረ ሰው ከሌለ መረጃውን
የተሳታፊዎችን የግል መረጃ ሚስጥራዊነት በጠበቀ መልኩ
የማስወገድ፣
ስብሰባውን የሚያስተናግደው …
• ስብሰባው በተሳታፊዎች መካከል ሁለት የአዋቂ እርምጃ
ያህል (2 ሜትር) ተጠብቆ ከ50 ሰው ሳይበልጥ ስብሰባ
የማካሄድ፣ እያንዳንዱ ተሰብሳቢ የአፍና አፍንጫ
መሸፈኛ ካላደረገ ስብሰባ ወደሚደረግበት ቦታ
እንዳይገባ የመከልከል፣ እንዲሁም ከመግባቱ በፊት
የሙቀት ልኬት የማድረግ ግዴታ አለበት፣
• በስብሰባው ወቅት የኮቪድ-19 የጥንቃቄ እርምጃዎችን
አወሳሰድ በተመለከተ የሚከታተል፣ የሚቆጣጠርና
አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ አንድ ሰው በቋሚነት
የመመደብ፣
ስብሰባውን የሚያስተናግደው …
• የኮቪድ ምልክት የታየበት ግለሰብ ቢኖር ለጤና
ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና
ኢንስቲትዩት፣ በአቅራቢያው ለሚገኙ የጤና ተቋም
ወይም ባለሞያ የማሳወቅ ግዴታ እና በጊዜያዊነት
ለማቆያ አገልግሎት የሚውል ለይቶ ማቆያ ክፍል
ማዘጋጀት፣
• ተሰብሳቢዎች በእረፍት ሰአት ወይም በምሳ ሰአት
አካላዊ ርቀታቸዉን እንዲጠብቁ የሚያስችል
ምልክት የማስቀመጥ
የስብሰባ ታዳሚ መውሰድ ስለሚገባው የጥንቃቄ
እርምጃዎች (አንቀጽ 20)
 የኮቪድ-19 ምልክቶች ካሳየ ማለትም የሳል፣ የሙቀት መጨመር
ለመተንፈስ መቸገር ወይም ለኮቪድ 19 አጋላጭ ሁኔታ ውስጥ
ከነበረ በበሽታው አለመያዙ እስካልተረጋገጠ ድረስ በስብሰባው
አለመሳተፍ፣
 ስብሰባው እስከሚጠናቀቅ ድረስ እንደምግብ ለመመገብ አይነት
አስገዳጅ ተግባራት ውጭ በማንኛውም ጊዜ የአፍ እና አፍንጫ
መሸፈኛ ጭንብል በአግባቡ የማድረግ፣ በስብሰባ ወቅት ጥያቄ
በሚጠየቅበት እና ሃሳብ በሚሰጥበት ወቅት የአፍና አፍንጫ
መሸፈኛ ጭንብሉን አለማውለቅ ወይም ወደአገጭ ዝቅ
ያለማድረግ ግዴታ አለበት፣
 ከማንኛውም ሰው ቢያንስ በሁለት ሜትር አካላዊ ርቀትን ጠብቆ
መሳተፍ፣ እጅን ቶሎ ቶሎ መታጠብ ወይንም በሳኒታይዘር
ማፅዳት፣ የተጠቀሙበትን ሶፍት እና ሌሎች የተጸዳዱበትን ቁሶች
በአግባቡ ክዳን ባለዉ ቆሻሻ ማስወገጃ ማስወገድ፣
ስብሰባውን የጠራው አካል መውሰድ ስለሚገባው
የጥንቃቄ እርምጃዎች (አንቀጽ 18)
የስብሰባ አዳራሾች በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖራቸው
የማድረግ፣ የእጅ ንጽህናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ በቂ
ግብዓቶችን ማዘጋጀት
አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረገ ተሳታፊ ስብሰባ
ወደሚደረግበት ቦታ እንዳይገባ መከልከል፣ እንዲሁም
ከመግባቱ በፊት የሙቀት ልኬት ማድረግ
በሀይማኖታዊ ስነስርዓት፣ በየቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶች፣
እና የአደባባይ በዓላት አከባበር ወቅት ሊወሰዱ ስለሚገባቸው
የጥንቃቄ እርምጃዎች
የሃይማኖት ስነስርዓቶችን አተገባበርን በተመለከተ
(አንቀጽ 21)
• ማንኛውም ሀይማኖታዊ ስርዓት የሚፈጽሙ ሰዎች
ሀይማኖታዊ ስርዓቱን በሚፈጽሙበት ወቅት ከሁለት
የአዋቂ እርምጃዎች በታች ተጠጋግቶ ስርዓቱን መፈጸም
የተከለከለ ነው፣
• የሀይማኖቱ ስርዓት የሚከናወንበት ህንፃ ውስጥ ህንፃው
የሚሸፍነውን ጠቅላላ ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት
ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን
የማይበልጥ ሰው በመያዝ ስርዓቱን ማካሄድ
ይኖርባቸዋል፣
የሃይማኖት ስነስርዓቶችን …
• የእምነቱ ተከታዮች የእምነት ስርዓቱን በሚፈጽሙበት ወቅት
ሲቆሙም ሆነ ሲቀመጡ የሁለት ሜትር ርቀት የመጠበቅ
ግዴታ አለባቸው፣
• ማንኛውም ሰው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ሳይደረግ
ወደእምነት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ መግባት የተከለከለ
ነው፣
• ማንኛውም የእምነት ተቋም ስለ በሽታው አስፈላጊውን መረጃ
የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ እንዲሁም
የለሀይማኖቱ መሪዎች እና በእምነት ተቋሙ ውስጥ
ለሚያገለግሉት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ
የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፣ የጥንቃቄ
እርምጃዎች በእምነቱ ተከታዮት መፈጸማቸውን የመቆጣጠር
ግዴታ አለበት።
የቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶችን በተመለከተ
(አንቀጽ 22)
ለልደት፣ ምረቃ፣ማህበር፣ሀዘንን መሰረት የሚያደርጉ
ዝግጅቶች (ከቀብር እና ከቀብር መልስ ያሉ ስነ ስርዓቶች
ውጭ) እና መሰል በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ማህበራዊ
በዓላት ከቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጭ ተጠራርቶ
ማክበር የተከለከለ ነው፣)
ከላይ የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ ማንኛውም ሰው ከ50
በላይ የማይበልጡ ሰዎች በመሆን እና ሁለት የአዋቂ
እርምጃ (ሁለት ሜትር) ተራርቆ፣ የአፍና አፍንጫ
መሸፈኛ በማድረግ እና ተገቢውን የኮቪድ 19 መከላከያ
የንጽህና እርምጃዎች በመተግበር የሰርግ ስነስርዓት
ማካሄድ ይችላል፣
የአደባባይ በዓላት አከባበርን በተመለከተ
(አንቀጽ 23)
• ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም የአደባባይ በዓላት ማለት ህዝብን በብዛት የሚያሳትፉ በክፍት ስፍራዎች
የሚደረጉ ስብስቦች ናቸው።
• ህዝብን በብዛት የሚያሳትፉ የአደባባይ ላይ በዓላት የወረርሽኑ ስርጭት መረጋጋት እስኪጀምር
ድረስ በታቸለ አቅም ባይደረጉ ይመከራል፣
• በዓላትን የሚታደምም ሆነ አከባበሩን የሚያስተባበር ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የማድረግ
እና በአከባበርም ወቅት ሁለት ሜትር ርቀትን ጠብቆ የመቆምና መቀመጥ ግዴታ አለበት፣
• በዓላትን የሚያስተባብር አካል በዓላት የሚከበሩባቸው አደባባዮች የሚሸፍኑትን ጠቅላላ ቦታ
ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን
የማይበልጥ ሰው በመያዝ ስርዓቱን ማካሄድ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፣
• የበዓላቱ አስተባባሪዎች ወደ በዓላቱ የሚከበሩበት አደባባዮች የሚወስዱ መንገዶችን እና
መግቢያ ቦታዎች ላይ የበዓላቱ ታዳሚዎች ተገቢውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ
መሟላታቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፣
የአደባባይ በዓላት ….
 የበዓላቱ አስተባባሪዎች አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም
የማድረስ ግዴታ አለባቸው፣
 በአላቱ በሚከበሩበት ወቅት መጨናነቅ እንዳኖር የመግቢያ እና የመውጫ መንገዶችን
መለየትን ጨምሮ ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን የመውሰድ ግዴታ አለባቸው፣
 የበዓላቱ አዘጋጆች እና አስተባባሪዎች በበዓሉ አከባበር ወቅት ሊደረጉ
የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች አስቀድሞ የመለየት፣ ለተሳታፊዎች
የማሳወቅ፣ እና አፈጻጸሙን የመከታተል ግዴታ አለባቸው፣
 ማንኛውም ታዳሚ የበዓላቱ አዘጋጆች እና አስተባባሪዎች የሚያውጧቸውን
የጥንቃቄ እርምጃዎች የመተግበር ግዴታ አለባቸው፣
የአደባባይ በዓላት ….
በበዓላት አከባበር ወቅት ማናቸውም ለንክኪ የሚዳርጉ
እንቅስቃሴዎች እና የአከባበር ስርዓቶች የተከለከሉ
ናቸው፣
የጥንቃቄ እርምጃዎች የማይተገበሩ ከሆነ አስፈላጊውን
እርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት አግባብ ባላቸው
የመንግስት አካላት የሚፈጸም ይሆናል፣
አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ካፌዎች፣ ባርና ሬስቶራንቶች፣መጠጥ
ቤቶች፣ ቡና ቤቶች፣የጭፈራ ቤቶች፣ እና የመዝናኛ እና መጫዎቻ
አገልግሎት የሚሰጡ ስፍራዎች (አንቀጽ 24)
• በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ ማስተናገድ የተከለከለ ሲሆን
በእያንዳንዱ ጠረጴዛ መካከል የሁለት ሜትር ርቀት ሊጠበቅ
ይገባል፣
• አገልግሎትን የሚሰጡ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ
ግዴታ አለባቸው፣
• የሚስተናገዱ ሰዎች ከሚመገቡበት እና ከሚጠጡበት ወቅት ውጭ
የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው፣
• ተቋማቱ በመግቢያና መውጫ በሮች እና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች
ላይ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን
ማዘጋጀት፣ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር የማድረግ፣ እንዲሁም
ለሰራተኞቻቸው የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ
የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፤
• የጭፈራ ቤቶች አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት
አገልግሎት የሚሰጡበት ስፍራ ስፋት ከግምት
ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው
ብዛት አንድ አራተኛውን የሚበልጥ ሰው ሳይዙ፣
በተገልጋዮች መሀል ሁለት የአዋቂ እርምጃ (ሁለት
ሜትር) በሁሉም ጊዜ በማስጠበቅ፣ ማንኛውም
ለንክኪ የሚዳርጉ እንቅስቃሴዎችን በመከልከል፣ እና
ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ሙሉ በሙሉ
በመተግበር ሊሆን ይገባል፣
ሲኒማ ቤቶች፣ ቲያትር ቤቶች እና የስዕል ጋላሪ
(አንቀጽ 25)
 ለሰራተኞቻቸው የበሽታውን ስርጭት ለመግታት
የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ ግዴታ
አለባቸው፣
አገልግሎቱ የሚሰጥበት አዳራሽ ወይም ስፍራ ስፋት
ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው
ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን የማይበልጥ ሰው
በመያዝ እና ሁለት የአዋቂ እርምጃ (ሁለት ሜትር)
በማራራቅ አገልግሎቱን መስጠት ይኖርባቸዋል፣
ማንኛውም ሰው በእነዚህ ተቋማት ለመስተናገድ
ተቋማቶቹ የሚያውጧቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች
የመተግበር ግዴታ አለበት፣
ስፖርታዊ ውድድሮች (አንቀጽ 26)
የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እይታየ
በሌላ መመሪያ እስኪወሰን ድረስ የእግር ኳስ፣ መረብ
ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ቴኒስ፣ አትሌቲክስ እና
ሌሎች የስፖርት ውድድሮች በውድድሩ ላይ በቀጥታ
የሚሳተፉ እና ለነዚሁ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ከሆኑት
ውጭ ታዳሚዎች በሌሉበት መከናወን አለባቸው፣
በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን
የሚገኙባቸው ተቋማት ላይ የተጣሉ ክልከላዎች እና መደረግ
ያለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች (አንቀጽ 27)
• የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እየታየ በሌላ
መመሪያ እስኪወሰን ድረስ የአረጋዊያን መጦሪያዎች
ስፍራዎች እና የማገገሚያ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን
በአካል መጠየቅ የተከለከለ ነው
• በማረሚያ ቤቶች ላይ የሚደረግ የታራሚን በአካል
የመጎብኘት ሂደት በታራሚው እና በጠያቂው መሀል ሁለት
የአዋቂ እርምጃ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ፣ ታራሚውም ሆነ
ጠያቂው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ በማስደረግ፣ ጠያቂው
ወደማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ከመግባቱም በፊት እና ሲወጣ
እጁን በውሃ እና ሳሙና እንዲታጠብ ወይንም በሳኒታይዘር
እንዲያጸዳ በማድረግ፣
የመተባበር ግዴታ (አንቀጽ 28)
• ማንኛውም ሰው እና ተቋም ለዚህ መመሪያ ተፈፃሚነት የመተባበር ግዴታ አለበት።
የህግ ተጠያቂነት (አንቀጽ 30)
• በመመሪያው የተደነገጉ ክልከላዎችን እና ግዴታዎችን የተላለፈ ማንኛውም ሰው
አግባብነት ባለው የወንጀል ህግ መሰረት ተጠያቂ እንደሚሆን የተደነገገ ሲሆን
• አግባብነት ያላቸው የወንጀል ህጎች ድንጋጌዎችን ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ፡-
 የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር
ቁጥር 661/2002 ይህ አዋጅ ስለተላላፊ በሽታዎች አንቀጽ 26 እና 27
እንደሚያስቀምጠው፡-
የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና
ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር ቁጥር 661/2002 …
 ማንኛውም ወደ ሀገር የሚገባ ወይም ከሀገር የሚወጣ መንገደኛ
ሀገሪቱ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የጤና አጠባበቅ መስፈርቶች
መሠረት….በተላላፊ በሽታ ሲጠረጠር ለምርመራ የመተባበር ግዴታ
እንዳለበት፣
 ....ወረርሽኝ ካለበት ቦታ የመጣ ሰው ወደ ሀገር አንዳይገባ ሊታገድ
እንደሚችል፣
 አግባብ ያለው የጤና ባለሙያ በወረርሽኝ ተላላፊ በሽታ የተያዘን
ወይም የተጠረጠረን ማንኛውም ሰው ለተወሰነ ጊዜ ተገልሎ
እንዲቆይ ማድረግ እንዳለበት፣
 በወረርሽኝ ተላላፊ በሽታ የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው
ለምርመራ፣ለሕክምና…ፈቃደኛ መሆን እንዳለበት ተደንግጎዋል።
 በአዋጁ መሰረት እነዚህን ድንጋጌዎች መጣስ እስከ ስድስት ወር
በሚደርስ እስራት ሊያስቀጣ ይችላል።
የኢፌድሪ የወንጀል ሕግ
 በወንጀል ህጉ አንቀጽ 514 ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ተላላፊ
በሽታን ማስተላለፍ በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል አድርጎ ደንግጓል።
ይህን አንቀጽ በመጣስ የሚፈጽም ወንጀል እስከ አስር አመት
የሚደርስ የእስራት ቅጣት ሊያስከትል እንደሚችል ሲሆን
በተለይም ተላላፊው በሽታ በወረርሽኝ ወይም በኢፒደሚክ መልክ
የተከሰተ ሲሆን እንደነገሩ ክብደት ቅጣቱ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት
ወይም ሞት ሊያስቀጣ እንደሚችል የወንጀል ሕጉ ያሳያል።
 በወንጀል ህጉ 522 መሰረት ማንም ሰው ተላላፊ በሽታ
ለመከላከል፣ ለመግታት፣ ወይም ለማቆም በህግ የተደነገጉትን
የጥንቃቄ እርምጃዎች አስቦ የጣሰ እንደሆነ እስከ ሁለት ዓመት
በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ይቀጣል በቸልተኝነት
ከሆነ እስከ 6 ወር በሚደርስ ቀላል እስራት ሊቀጣ ይችላል፡፡
• የወንጀል ሕጉ በአንቀጽ 830 የህዝብ ጤና እና ጤናማነትን
ለመቆጣጠር በሚል ርዕስ ባሉት ደንጋጌዎች እንደተገለጸው
በሽታዎችን በተለይም ተላላፊ በሽታዎችንና ወረርሽኝ
ስለመከላከል፣ መኖራቸውን ስለማሳወቅ፣ ለመከላከል የሚረዱ
ህክምናዎችን ስለማድረግ ወይም ስለመቆጣጠር የወጣን
መመሪያ መጣስ በመቀጮ ወይም በማረፊያ ቤት እስራት
ሊያስቀጣ የሚችል ወንጀል ነው
• በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 485 መሰረት ለህዝብ ጤና አስጊ የሆን አደጋ
እንደሚደርስ በማስፈራራት ሆን ብሎ ህዝብን ያሸበረ ከሶስት
አመት በማይበልጥ ቅላል እሰራት ወይም እንደነገሩ ክብደት ከሶስት
አመት በማይብለጥ ጽኑ እስራት ሊቀጣ እንደሚችል ተደንግጎዋል።
ማጠቃለያ
ወረርሺኙ በተለያዩ የግለሰብና የቡድን መብቶች ላይ
ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል፡- እነዚህም፡-
• በጤንነትና በህይወት መኖር መብት፣
• ከቦታ ቦታ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት፣
• ሰርቶ የመኖር (የመስራት መብት)
• የሀይማኖትና እምነት ነጻነት መብት
• የመማር መብት፣
• የመሰብሰብ መብት
• በሴቶችና ህጻናት መብት ( የሀይል ጥቃት)
• የኮቪድ 19 ወረርሺኝን ለመከላከል የወጡ ህግጋትን
የማስፈጸም ስራው የመጨረሻው ግብ የሰዎችን
በጤንነትና በህይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት
ማክበርና ማስከበር ነው፡፡
• በዚህ ረገድ በመመሪያው የተጣሉ ግዴታዎችንና
ክልከላዎችን በሚጥሱ አካላት ላይ አግባብ ባለው
ወንጀል ህግ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ ስለሚደነግግና
ህጉንም በማስፈጸም ረገድ የፍትህ አካላት ድርሻ
ከፍተኛ ነው፡፡
• ፖሊስ ፡-ወንጀልን በመከላከል ፣በምርመራ፣ የህዝብ ትራንስፖርት
ቁጥጥር
• ዐቃቤ ህግ ፡-ክስ መመስረት፣ ችሎት ክትትል፣ ህጉን እስከ ወረዳ
ባለው መዋቅር ግንዛቤ የመፍጠር፣ ማረሚያና ማረፊያ ጉብኝት ---
• የጤናው ዘርፍ የሚመሩ ተቋማት፡- ወረርሺኙን ለመከላከል
ከሚያደርጓቸው የቅርብ ክትትሎች፣ የማስገንዘብ እንዲሁም
ከሚወስዷቸው አስተዳደራዊ እርምጃዎች (በቀጥታ
የሚቆጣጠሯቸውን ተቋማት) ባሻገር የወንጀል ድርጊት ውስጥ
የገቡትን ለፍትህ አካላት ጥቆማ በመስጠት የበኩላቸውን ድርሻ
ሊወጡ ይገባል፡፡
• እነዚህና ሌሎች ስልጣንና ተግባራትን በመወጣት ወረርሺኙ
በመከላከል ረገድ ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል
እናመሰግናለን!
!

More Related Content

Featured

How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
ThinkNow
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Kurio // The Social Media Age(ncy)
 

Featured (20)

2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot
 
Everything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTEverything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPT
 
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsProduct Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
 
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
 
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfAI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
 
Skeleton Culture Code
Skeleton Culture CodeSkeleton Culture Code
Skeleton Culture Code
 
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
 
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
 
How to have difficult conversations
How to have difficult conversations How to have difficult conversations
How to have difficult conversations
 
Introduction to Data Science
Introduction to Data ScienceIntroduction to Data Science
Introduction to Data Science
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best Practices
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project management
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
 

New directive to prevention of COVID-19.pptx

  • 1. መመሪያ ቁጥር 30/2013 የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የወጣ መመሪያ
  • 2. መግቢያ • የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በአለም አቀፍ ደረጃ ፣ በአህጉራችን ፣ እንዲሁም በሃገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለ እና ትልቅ ስጋት የደቀነ ወረርሽኝ ነው። • በአሁኑ ወቅት ይህን ወረርሽኝ መግታት እና መከላከል ትልቅ ሃገራዊ የትኩረት አጀንዳ ነው። ከበሽታው አስከፊነት አንጻር በርካታ ሀገራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ሰዎች ከቤት እንይወጡ/ እንቅስቃሴዎችን በመገደብ እንዲሁም ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ሲያስገድዱ ቆይተዋል፡፡ •
  • 3. • በሀገራችንም የወረርሺኙን መከሰት ተከትሎ መንግስት ይህንን አደገኛ ወረርሽኝን ለመከላከል ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን  ይህ ወረርሺኝ በቀላሉ የሚተላለፍ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አድማሱን በማስፋት የዜጎችን ህይወት እንዲሁም የሀገርን ህልውና አደጋ ጭምር አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ  ወረርሽኙን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለማሳለጥ እና ውጤታማ ለማድረግ  ከተለመደው አሠራር እና ሕገ-መንግሥታዊ ማዕቀፍ ወጥቶ በልዩ ሁኔታ መንቀሳቀስ የሚጠይቅ ሆኖ በመገኘቱ የኢፌዴሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመደንገግ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ በማጸደቅ ለ5 ወራት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
  • 4.  የዚህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሻውም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ- መንግሥት ሲሆን ህገ መንግስቱም ለሃገር እና ለህዝብ አደጋ የሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የሚተዳደርበትን ሥርዓት በአንቀጽ 93 ላይ አስቀምጧል።  በአንቀጽ 93 (1) (ሀ) መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ መነሻ ከሚሆኑ ሁኔታዎች አንዱ “የሕዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት” የሚል ነው። የኮቪድ-19 የሕዝብን ጤንነት በከፍተኛ ደረጃ አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ እንደሆነ ዕሙን ነው።  አዋጁ መንግሥት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን በሚወስድበት ጊዜ የተሻለ ነጻነት እና አቅም እንዲኖረው፣ የመንግስት ሥልጣን ላይ ያሉ ገደቦች ወይም የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች በተለየ ሁኔታ ለጊዜው ተፈጻሚነታቸው ቀርቶ/ ታግዶ በሙሉ ኃይል፣ በተቀላጠፈ እና በተቀናጀ መልኩ ለወረርሽኙ ምላሽ መስጠት የሚያስችል መሆኑ ታምኖበት እንደታወጀ መረዳት ይቻላል፡፡
  • 5.  አዋጁ ጠቅለል ያሉ ድንጋጌዎችንና አዋጁን ተከትለው የሚወጡ ደንብና መመሪያዎች ላይ የሚጣሉ ክልከላዎችና ግዴታዎች በሚተላለፉ አካላት ላይ የወንጀል ቅጣቶችን ያስቀመጠ ነው፡፡  በተጨማሪም ይህንንም አዋጅ ለማስፈጸም ይረዳ ዘንድ ደንብ ቁጥር 466/2012 በሚኒስትሮች ም/ቤት ጸድቆ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ይህ ደንብ ወረርሽኙን ለመከላከል በግለሰቦች፣ የግልም ሆነ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ወዘተ የተጣሉ ክልከላዎችና ግዴታዎችን ያስቀመጠ ሲሆን  የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚሰራውን ስራ በበላይነት የሚመራና የሚያስተባብርና በም/ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሚመራ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በሚል ተቋቁሞ ደንቡን ለማስፈጸም የሚረዱ መመሪያዎችን ለማውጣት በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተለያዩ መመሪያዎችን አውጥቶ ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡
  • 6. በእነዚህ መመሪያዎች ተጨማሪ ክልከላዎችና ግዴታዎች ተደንግገው ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ በአጠቃላይ በደንቡና በመመሪያዎቹ ላይ ከበሽታው ባህሪ አንጻር በግለሰቦች፣ በመንግስትና በግል ተቋማት፣ ህዝብ በብዛት የሚሰበሰብባቸው በሀይማኖች ቦታዎች፣ በመዝናኛዎች፣ ገበያዎች፣ ሰርግ፣ ቀብር ወዘተ፣ የሚተገበሩ ክልከላዎችና ግዴታዎችን በመደንገግ ሲተገበር ቆይቷል፡፡ መንግስትም ህብረተሰቡ እነዚህን ክልከላዎችና ግዴታዎች በተለያየ መንገድ ግንዛቤ ከመፍጠር ጎን ለጎን የተጣሉ ግዴታዎችንና ክልከላዎችን የተላለፉ ግለሰቦችና ተቋማት ተጠያቂ የማድረግ ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
  • 7.  አነዚህ የአስቸኳይ ጊዜ ህግጋት በህዝብ ተወካዩች ም/ቤት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ (ለ5 ወራት) ሲተገበሩ ቆይተው ከህብረሰብ ጤና ኢኒስቲትዩትና ጤና ሚ/ር በቀረበው ሪፖርት መነሻ ወረርሺኙን በተለመደው አሰራር /በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርዓት በጥንቃቄ መከላከልና መቆጣጠር እንደሚቻል ታምኖበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነስቷል፡፡  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ በኋላ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና የሚያስከትለው ጉዳት ለመቀነስ ስለሚወሰዱ ክልከላዎች እና ግዴታዎች በህግ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በመላው ሀገሪቱ ተፈጻሚ የሚሆን "የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያሰችል መመሪያ ቁጥር 30/2013" በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጸድቆ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ተመዝግቦ ከ25/01/2013 ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
  • 8. በአጠቃላይ መመሪያው ክልከላዎችንና ግዴታዎችን ያካተተ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ፡- • የተከለከሉ ተግባራት እና የተጣሉ ግዴታዎች (በዋናነት በግለሰቦች፣ በግልና በመንግስት ተቋማት ላይ) • በቤት ውስጥ ማቆያ እናክብካቤ ወቅት መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ • የቀብር ስነ ስርአት፣ የአስክሬን ማጓጓዝ እና የሀዘን ስነ ስርአት • በስብሰባ ወቅት መወሰድ ስላለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች • በሀይማኖታዊ ስነስርዓት፣ በየቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶች፣ እና የአደባባይ በዓላት አከባበር ወቅት ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች • የመዝናኛ፣ የመስተንግዶ አገልግሎቶች እና ስፖርታዊ ውድድሮች ሊከተሉት የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች • በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚገኙባቸው ተቋማት ላይ የተጣሉ ክልከላዎች እና መደረግ ያለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች • የህግ ተጠያቂነት
  • 9. የተከለከሉ ተግባራት እና የተጣሉ ግዴታዎች
  • 10. የተከለከሉ ተግባራት (አንቀጽ 4) ማንኛውም ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ቫይረሱ እንዳለበት እያወቀ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት፣ ወይም ቫይረሱ ወደ ሌሎች ሰዎች ሊተላለፍ በሚችልበት ሁኔታ ከሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘት የተከለከለ ነው፣  ማንኛውም ሰው ለሰላምታና ሌላ ለማንኛውም አላማ በእጅ መጨባበጥ፣ሆነ ብሎ የእርስ በእርስ አካላዊ ንክኪ ማድረግ የተከለከለ ነው፣
  • 11. የተከለከሉ …  ዕድሜያቸው ከስድስት አመት በታች የሆነ ህጻናት ወይም በማስረጃ የተረጋገጠ የመተንፈሻ አካላት ችግር ያለባቸው ሰዎች በስተቀር ማንኛውም ሰው ከመኖርያ ቤት ውጪ በማንኛውም ቦታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርግ መገኘት የተከለከለ ነዉ፣  በማንኛውም መንግስታዊ እና የግል ተቋም ሰራተኞች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ተጠጋግተው እና የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ወይም  ተገልጋዮች በሚቀመጡበት ጊዜም ይሁን በማንኛዉም አኳኋን አገልግሎቱ ሲያገኙ ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ተጠጋግተው እና የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ወይም በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግ የተከለከለ ነው፣
  • 12. የተከለከሉ … ማንኛውም የንግድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አፍና አፍንጫውን ላልሸፈነ ሰው አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፣ በክፍት ገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ርቀት መቆምም ሆነ መቀመጥ የተከለከለ ነው፣
  • 13. የተከለከሉ …  ማንኛውም የግልም ሆነ የመንግስት ትምህርት ቤት፣ ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ የፊትለፊት ትምህርት መስጠት መጀመር እንደሚቻል ሳይወሰን እንዲሁም አጠቃላይ የመማር ማስተማር ስራውን በተመለከተ በመመሪያ የሚወጡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ሳያከብር ትምህርት መስጠት የተከለከለ ነው፣  ማንኛውም የህጻናት ማቆያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ሳይወሰን እንዲሁም አገልግሎት የሚሰጥበት ሁኔታ በተመለከተ በመመሪያ የሚወጡ ሊወሰዱ የሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎችን ሳያከብር አገልግሎት መስጠት አይችልም።
  • 14. የተጣሉ ግዴታዎች (አንቀጽ 5)  ማንኛውም ኮቪድ 19 በሽታ አለብኝ ብሎ እራሱን የሚጠረጥር ሰው ለሚመለከተው አካል ሪፖርት በማድረግ የመመርመርና ቫይረሱ ወደ ሌሎች እንዳይተላፍ አስፈላጊውን ጥንቃቄ የማድረግ ሀላፊነት አለበት፣  በሽታው አለበት ተብሎ የሚጠረጠር ሰው ሰለመኖሩ የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ለጤና ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣በአቅራቢያው ለሚገኙ የጤና ተቋም ወይም ባለሞያ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣
  • 15. የተጣሉ ግዴታዎች… ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጥ የመንግስታዊም እና የግል ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳሶችን የማቅረብ፣ ተገልጋዮች ሁለት የአዋቂ እርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ ምልክት የማድረግ እና ተገልጋዮች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፣
  • 16. የተጣሉ ግዴታዎች… ማንኛውም የመንግስታዊ እና የግል ተቋማት ለሰራተኞች ስለበሽታው አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን የማዘጋጀት ፣ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ እና የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፤
  • 17. የተጣሉ ግዴታዎች… ማንኛውም የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው ሀገር አቀፍም ሆነ የከተማ ውስጥ ትራንስፖርትን በተመለከተ በህግ ከሚወሰነው የመጫን አቅም ልክ ሰዎችን የመጫን፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረጉ ሰዎችን አገልግሎት አለመስጠት፣ በቂ የአየር ዝውርውር እንዲኖር የማድረግ ሌሎች መወሰድ የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በመተግበር አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፣
  • 18. የተጣሉ ግዴታዎች… ማንኛውም በሆቴል፣ በአስጎብኚነት እና በሌሎችም የቱሪዝም መስክ የተሰማሩ ተቋማት በሰራተኞቻቸው እና ተገልጋዮቻቸው መካከል ሁለት የአዋቂ እርምጃ ወይም የሁለት ሜትር ርቀት እንዲኖር የማድረግ፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን የመቆጣጠር፣ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን የማዘጋጀት ፣ ለሰራተኞቻቸው የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ እንዲሁም የቱሪዝም አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ዘርፉ በመመሪያ የሚያስቀምጣቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
  • 19. የተጣሉ ግዴታዎች… የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አሰሪዎች በግንባታ ሳይቶች ላይ ማንኛውም በኢንዱስትሪ እና ምርት መስክ የተሰማሩ መንግስታዊ እና የግል ተቋማት ለሰራተኞቻቸው
  • 20. በቤት ውስጥ ማቆያ እና ክብካቤ ወቅት መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ (አንቀጽ 6)  “የቤት ውስጥ መቆያ” ማለት መኖሪያ ቤት ሆኖ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር በሚያስችል መልኩ መስኮት ወይም አየር ማስገቢያ ያለው እና ለኮቪድ 19 በሽታ የተጋለጡ፣ የተጠረጠሩ ወይንም ተመርምረው በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች የሚቆዩበት ስፍራ ነው፡፡ (አንቀጽ 2 /6/)  ማንኛውም ቀላል ወይም ምንም አይነት የኮቪድ-19 ምልክት የሌለበት ታማሚ በቤት ውስጥ የኮቪድ 19 ህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል።
  • 21. በቤት ውስጥ ማቆያ እና ክብካቤ ላይ የሚገኝ የኮቪድ 19 ታማሚ ወይም በኮቪድ-19 በሽታ ተይዟል ተብሎ የተጠረጠረ ግዴታዎች  በቤተሰብ ወይም በራሱ ተለይቶ በተዘጋጀ በቂ የአየር ዝውውር ያለው (በርና መስኮት ) ባለው ክፍል ውስጥ መቆየት፣  ራስን ቢያንስ ለ 14 ተከታታይ ቀናት በመለየት መቆየት፣ በነዚህ ወቅቶች ከቤት አለመውጣት፣ አፍ እና አፍንጫን በተገቢው መንገድ መሸፈን፣  ክትትል ከሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎች ጋር ለሚኖር ግንኙነት መስመር ክፍት ማድርግ፣ ለዚህም መስማማቱን በተዘርጋውና በቀጣይ በሚዘረጉት የአሰራር መንገዶች ማረጋገጥ፣
  • 22. በቤት ውስጥ ማቆያ … ታማሚ ወይም የተጠረጠረ ግዴታዎች … የኮቪድ-19 በሽታ ምልክቶቹ ከተባባሱ ወዲያውኑ ለሚመለከተው ተቋም በስልክ ሪፖርት ማድረግ • የተጠቀሙበትን ሶፍት፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ፣ የእጅ ጓንትና መሰል ቁሳቁሶችን ክዳን ባለው ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ወይም በፕላስቲክ ከረጢት ቋጥሮ በጥንቃቄ ማስወገድ፣ • ማንኛውም ንክኪ በሚኖርበት ወቅት በውሃና ሳሙና መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር የእጅን ንጽህና መጠበቅ፣
  • 23. በቤት ውስጥ ማቆያ … ታማሚ ወይም የተጠረጠረ ግዴታዎች … • ሰዎች በጋራ ከሚጠቀሙባቸው እንደሳሎን፣ መታጠቢያ እና ምግብ ማብሰያ ያሉ ቦታዎች በተቻለ መጠን ከመጋራት መቆጠብ ወይም መቀነስ፣ • የተለያዩ የመጠቀሚያ እቃዎችን፣ በሮችን እና የመሳሰሉትን ነገሮች ከመንካት መቆጠብ፣ እነዚህን እቃዎች ነክቶ ከሆነም ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት በአግባቡ እንዲጸዱ የማድረግ፣
  • 24. የኳራንቲን እና የድንበር ላይ ጤና ቁጥጥርን በተመለከተ (አንቀጽ 8-12)  በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ አለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች በኩል የኮሮና ቫይረስ የRT PCR ምርመራ ውጤት ይዞ የሚመጣ መንገደኛን በተመለከተ (አንቀጽ 8)  በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች በኩል የኮሮና ቫይረስ የRT PCR ምርመራ ውጤት ሳይዝ የሚመጣ ከስደት ተመላሽ (አንቀጽ 9)  በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የሚያልፍ የትራንዚት መንገደኛን በተመለከተ (አንቀጽ 10)  በየብስ ድንበር የሚገቡ ሰዎችን በተመለከተ (አንቀጽ 11)  ከውጭ አገር የሚጓጓዝ አስክሬን (አንቀጽ 12)
  • 26. የቀብር ስነ ስርዓት፣ የአስክሬን ማጓጓዝ እና የሀዘን ስነ ስርዓት (አንቀጽ 13-16) በአስክሬን ማስተካከልና ግነዛ ወቅት ሊደረጉ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች፡- (አንቀጽ 13)  የሟች ቤተሰብ ወይም ለሟች ኃላፊነት ያለበት ሰው አስክሬን ከጤና ተቋም ወይንም ከውጭ ሀገር በሚረከብበት ጊዜ የአስክሬን መለየት ሂደት ላይ ከአስክሬኑም ሆነ ከሳጥኑ ጋር ማንኛውም አይነት ንክኪ ያለማድረግ ኃላፊነት አለበት፣  ከጤና ተቋም ውጭ ሞት ተከስቶ የሟችን አስክሬን የሚገንዙ ሰዎች ሂደቱን ካጠናቀቁ በኋላ የተጠቀሙበትን የእጅ ጓንት፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እና ሰውነታቸውን የሸፈኑበትን ፕላስቲክ ወይም ጋዎን በአግባቡ የማስወገድ እና እጆቻቸውን በውሃ እና በሳሙና የመታጠብ ግዴታ አለባቸው፣  በለቅሶ ቦታ የተገኘ ማንኛውም ሰው ተገቢውን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ፣ እንዲሁም ሌሎች ሊወሰዱ የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች የመተግበር ግዴታ አለበት።
  • 27. በአስክሬን መጓጓዝ ወቅት እና በቀብር አፈፃጸም ወቅት የሚኖሩ ግዴታዎች (አንቀጽ 14)  ከጤና ተቋም ውጭ ሞት ተከስቶ የሟች አስክሬን ከተገነዘ በኃላ የሟች ቤተሰብ በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲቀበር ማድረግ ኃላፊነት አለበት  በጤና ተቋማት ላይ ሞት ከተከሰተ በኋላ ወይንም አስክሬን ከውጭ ሀገር የሚገባ ከሆነ የሟች ቤተሰቦች አስክሬን ከተቀበሉ በኋላ ወደ ቤት ሳይወስዱ በቀጥታ ወደ ቀብር ቦታ የመውሰድ ግዴታ አለባቸው፣  የቀብር ስነስርዓት አፈጻጸም በአጠቃላይ ከ50 ሰው ሳይበልጥ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግና ሁለት የአዋቂ እርምጃ በመራራቅ መከናወን አለበት፣  ማንኛውም ለቅሶ ሊደርስ የመጣ ሰው ወደ ለቅሶ ቤት ከመግባቱ በፊትና ከለቅሶ ቤት ሲወጣ እጁን በውሃና ሳሙና የመታጠብ ወይም በሳኒታይዘር የማፅዳት ግዴታ አለበት፣
  • 28. በቀብር አፈፃጸም ወቅት የሚኖሩ ግዴታዎች. .. • አስከሬኑን ወደ ማጓጓዣው የሚጭን ወይም ተሸክሞ ወደ ቀብር የሚወስድ ማናቸውም ሰው አፍና አፍንጫውን የመሸፈን እንዲሁም የእጅ ጓንት የማድረግ ግዴታ አለበት፣ • ማንኛውም በቀብሩ ላይ የተገኘ ሰው፣ እጁን በውሃና በአስክሬን ማጓጓዝ ወይም በግብአተ መሬት ወቅት የተሳተፈ ሰው፣ሳሙና የመታጠብ ወይም በሳኒታይዘር የማፅዳት እና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን የመተግበር ግዴታ አለበት።
  • 29. ከቀብር ስነ-ስርአት በኋላ የሚኖሩ ግዴታዎች (አንቀጸ 15) • ከቀብር በኋላ ለቅሶ መቀመጥ በድንኳን፣ በቤት ውስጥ ወይም ለዚሁ በተዘጋጀ ቦታ ላይ ሲደረግ ሀዘንተኛው እና የቤተሰቡ አባላት እና ለቅሶ የሚደርሰው ሰው ከ50 ሰው ሳይበልጥ እና ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀትን በመጠበቅና ባለመነካካት፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ሌሎች በአገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው ማንዋል ላይ የተቀመጡትን ጥንቃቄ ተፈጻሚ በማድረግ መሆን አለበት፣
  • 30. ከቀብር ስነ-ስርአት በኋላ የሚኖሩ ግዴታዎች . .. • በለቅሶ እና በቀብር ስርአት በኋላ ከሌሎች ሰዎች ጋር በመነካካት ወይም ሊያነካካ በሚችል መልኩ መመገብ፣ ወይም በሌሎች ሰዎች በተነካኩና ባልታጠቡ እቃዎች መመገብ የተከለከለ ነው፣ • ማንኛውም ለቅሶ ሊደርስ የመጣ ሰው ወደ ለቅሶ ቤት ከመግባቱ በፊትና ከለቅሶ ቤት ሲወጣ እጁን በውሃና ሳሙና የመታጠብ ወይም በሳኒታይዘር የማፅዳት ግዴታ አለበት • ሌሎች የሚከናወኑ የሀዘን ስርአቶች እንደ ሰባት፣ አርባ ፣ሙት አመትና ሰደቃ የመሳሰሉትን ለማክበር የሚኖሩ ማህበራዊ ስብስብን በተመለከተ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 22 መሰረት ይፈጸማል። (ከቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር የተከለከለ ነው፣)
  • 31. ሞት ሲከሰት የሚመለከታቸው አካላት ግዴታዎች(አንቀጽ 16)  እድሮች ወይም ሌሎች የሚመለከታቸው ማህበራዊ አደረጃጀቶች በአስክሬን አገናነዝ፣በጉዞ ወቅት እና በቀብር ስነስርዓቱ ላይ እንዲሁም በሀዘን ቤት በሚኖር የቆይታ ጊዜ በዚህ መመሪያ ውስጥ የተጠቀሱትን የኮቪድ መከላከል የጥንቃቄ መስፈርቶች መሟላታቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፣  በሥርዓተ ቀብር ላይ የሚገኙት የሀይማኖት ተቋማት ኃላፊዎች ወይም የሀይማኖት አባቶች አፍና አፍንጫቸውን የመሸፈን፣ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት የመጠበቅ፣ በስርዓቱ ላይ ከ50 ሰው በላይ አለመገኘቱን የማረጋገጥ፣ በለቅሶ ስርአቱ ላይ ለሚገኘው ማህበረሰብ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር የተያያዘ ትምህርት የመስጠት ግዴታ አለባቸው፣
  • 32. ሞት ሲከሰት የሚመለከታቸው አካላት ግዴታዎች … • በፌዴራልና ክልሎች በየደረጃው የሚገኙ የጤና፣ የፖሊስ እና ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት፣ የዞን፣ የከተማ፣ የወረዳ እና የቀበሌ አስተዳደሮች በዚህ ክፍል ስር የተቀመጡትን ግዴታዎች (የቀብር ስነ ስርዓት፣ የአስክሬን ማጓጓዝ እና የሀዘን ስነ ስርዓት የተመለከቱትን) መሟላታቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት እና በአገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው ማንዋል መሰረት የተጣሉባቸውን ዝርዝር ግዴታዎች የመተግበር ግዴታዎች አለባቸው።
  • 33. በስብሰባ ወቅት መወሰድ ስላለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች (አንቀጽ 17-20) የተሰብሳቢዎች ብዛትን በተመለከተ (አንቀጽ 17)  ስብሰባው በተሳታፊዎች መሀል ሁለት የአዋቂ እርምጃ ያህል (2 ሜትር) ለመጠበቅ በሚያስችል አዳራሽ ያለ ተጨማሪ ፈቃድ እስከ 50 ሰው ሆኖ መሰብሰብ ይቻላል  ከላይ የተቀመጠው እንዳለ ሆኖ ከ50 ሰው በላይ መሰብሰብ ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ስብሰባው ሊደረግበት የታሰበበት አዳራሽን ጠቅላላ ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን በማይበልጥ ሰው ልዩ ፈቃድ ከሰላም ሚኒስቴር እና በተዋረድ ባሉ የክልል፣ ዞን እና ወረዳ የሰላም እና ፀጥታ መዋቅሮች አስቀድሞ በማኘት ሊከናወን ይችላል።
  • 34. ስብሰባውን የጠራው አካል መውሰድ ስለሚገባው የጥንቃቄ እርምጃዎች (አንቀጽ 18)  የግድ ካልሆነ በስተቀር በአካል የሚደረጉ ስብሰባዎችን ከማመቻቸት ይልቅ በተቻለ መጠን በኦንላይን አማራጮች ስብሰባዎች እንዲካሄዱ ማድረግ፣  ስብሰባውን በሚጠራበት ጊዜ ስብሰባው በተሳታፊዎች መሀል ሁለት የአዋቂ እርምጃ ያህል (2 ሜትር) ለመጠበቅ በሚያስችል አዳራሽ ከ50 ሰው ሳይበልጥ መካሄድ መቻሉን የማረጋገጥ፣ የእጅ መታጠቢያ ወይም ከአልኮል የተዘጋጀ የእጅ ማጽጃ (ሳኒታይዘር) በበቂ መዘጋጀቱን የማረጋገጥ እና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን የመተግበር ግዴታ አለባቸው፣  ለስብሰባ የሚጠሯቸውን ተሳታፊዎች ስለኮሮና ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዶች እንዲሁም በስብሰባ ወቅት ሊከተሏቸው ስለሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች በቂ መረጃ የመስጠት ግዴታ አለባቸው።
  • 35. ስብሰባውን የሚያስተናግደው መስተንግዶ ሰጪ አካል መውሰድ ስለሚገባው የጥንቃቄ እርምጃዎች (አንቀጽ 19)  የስብሰባ አዳራሾች በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖራቸው የማድረግ፣ የእጅ ንጽህናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ በቂ ግብዓቶችን የማዘጋጀት፣ በተቻለ መጠን የተሰብሳቢዎች መግቢያና መውጫ የተለያየ እንዲሆን የማድረግ፣ ተሰብሳቢዎች የሚጠቀሙባቸው እና በተደጋጋሚ የሚነኩ ቁሳቁሶችን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ጸረ ተህዋሲያን ውህድ የማፅዳት፣ እና ሌሎች በተዘጋጀው የጥንቃቄ እርምጃዎችን የመተግበር ግዴታ አለባቸው፣  የእያንዳንዱን ተሳታፊ ስም፣ ስልክ እና አድራሻን መዝግቦ እስከ 14 ቀን ድረስ በፋይል የማቆየት እና በ14 ቀን ውስጥ በበሽታው የተያዘ ወይንም የተጠረጠረ ሰው ከሌለ መረጃውን የተሳታፊዎችን የግል መረጃ ሚስጥራዊነት በጠበቀ መልኩ የማስወገድ፣
  • 36. ስብሰባውን የሚያስተናግደው … • ስብሰባው በተሳታፊዎች መካከል ሁለት የአዋቂ እርምጃ ያህል (2 ሜትር) ተጠብቆ ከ50 ሰው ሳይበልጥ ስብሰባ የማካሄድ፣ እያንዳንዱ ተሰብሳቢ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ካላደረገ ስብሰባ ወደሚደረግበት ቦታ እንዳይገባ የመከልከል፣ እንዲሁም ከመግባቱ በፊት የሙቀት ልኬት የማድረግ ግዴታ አለበት፣ • በስብሰባው ወቅት የኮቪድ-19 የጥንቃቄ እርምጃዎችን አወሳሰድ በተመለከተ የሚከታተል፣ የሚቆጣጠርና አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ አንድ ሰው በቋሚነት የመመደብ፣
  • 37. ስብሰባውን የሚያስተናግደው … • የኮቪድ ምልክት የታየበት ግለሰብ ቢኖር ለጤና ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በአቅራቢያው ለሚገኙ የጤና ተቋም ወይም ባለሞያ የማሳወቅ ግዴታ እና በጊዜያዊነት ለማቆያ አገልግሎት የሚውል ለይቶ ማቆያ ክፍል ማዘጋጀት፣ • ተሰብሳቢዎች በእረፍት ሰአት ወይም በምሳ ሰአት አካላዊ ርቀታቸዉን እንዲጠብቁ የሚያስችል ምልክት የማስቀመጥ
  • 38. የስብሰባ ታዳሚ መውሰድ ስለሚገባው የጥንቃቄ እርምጃዎች (አንቀጽ 20)  የኮቪድ-19 ምልክቶች ካሳየ ማለትም የሳል፣ የሙቀት መጨመር ለመተንፈስ መቸገር ወይም ለኮቪድ 19 አጋላጭ ሁኔታ ውስጥ ከነበረ በበሽታው አለመያዙ እስካልተረጋገጠ ድረስ በስብሰባው አለመሳተፍ፣  ስብሰባው እስከሚጠናቀቅ ድረስ እንደምግብ ለመመገብ አይነት አስገዳጅ ተግባራት ውጭ በማንኛውም ጊዜ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በአግባቡ የማድረግ፣ በስብሰባ ወቅት ጥያቄ በሚጠየቅበት እና ሃሳብ በሚሰጥበት ወቅት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሉን አለማውለቅ ወይም ወደአገጭ ዝቅ ያለማድረግ ግዴታ አለበት፣  ከማንኛውም ሰው ቢያንስ በሁለት ሜትር አካላዊ ርቀትን ጠብቆ መሳተፍ፣ እጅን ቶሎ ቶሎ መታጠብ ወይንም በሳኒታይዘር ማፅዳት፣ የተጠቀሙበትን ሶፍት እና ሌሎች የተጸዳዱበትን ቁሶች በአግባቡ ክዳን ባለዉ ቆሻሻ ማስወገጃ ማስወገድ፣
  • 39. ስብሰባውን የጠራው አካል መውሰድ ስለሚገባው የጥንቃቄ እርምጃዎች (አንቀጽ 18) የስብሰባ አዳራሾች በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖራቸው የማድረግ፣ የእጅ ንጽህናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ በቂ ግብዓቶችን ማዘጋጀት አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረገ ተሳታፊ ስብሰባ ወደሚደረግበት ቦታ እንዳይገባ መከልከል፣ እንዲሁም ከመግባቱ በፊት የሙቀት ልኬት ማድረግ
  • 40. በሀይማኖታዊ ስነስርዓት፣ በየቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶች፣ እና የአደባባይ በዓላት አከባበር ወቅት ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች የሃይማኖት ስነስርዓቶችን አተገባበርን በተመለከተ (አንቀጽ 21) • ማንኛውም ሀይማኖታዊ ስርዓት የሚፈጽሙ ሰዎች ሀይማኖታዊ ስርዓቱን በሚፈጽሙበት ወቅት ከሁለት የአዋቂ እርምጃዎች በታች ተጠጋግቶ ስርዓቱን መፈጸም የተከለከለ ነው፣ • የሀይማኖቱ ስርዓት የሚከናወንበት ህንፃ ውስጥ ህንፃው የሚሸፍነውን ጠቅላላ ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን የማይበልጥ ሰው በመያዝ ስርዓቱን ማካሄድ ይኖርባቸዋል፣
  • 41. የሃይማኖት ስነስርዓቶችን … • የእምነቱ ተከታዮች የእምነት ስርዓቱን በሚፈጽሙበት ወቅት ሲቆሙም ሆነ ሲቀመጡ የሁለት ሜትር ርቀት የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው፣ • ማንኛውም ሰው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ሳይደረግ ወደእምነት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው፣ • ማንኛውም የእምነት ተቋም ስለ በሽታው አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ እንዲሁም የለሀይማኖቱ መሪዎች እና በእምነት ተቋሙ ውስጥ ለሚያገለግሉት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፣ የጥንቃቄ እርምጃዎች በእምነቱ ተከታዮት መፈጸማቸውን የመቆጣጠር ግዴታ አለበት።
  • 42. የቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶችን በተመለከተ (አንቀጽ 22) ለልደት፣ ምረቃ፣ማህበር፣ሀዘንን መሰረት የሚያደርጉ ዝግጅቶች (ከቀብር እና ከቀብር መልስ ያሉ ስነ ስርዓቶች ውጭ) እና መሰል በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ማህበራዊ በዓላት ከቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር የተከለከለ ነው፣) ከላይ የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ ማንኛውም ሰው ከ50 በላይ የማይበልጡ ሰዎች በመሆን እና ሁለት የአዋቂ እርምጃ (ሁለት ሜትር) ተራርቆ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ተገቢውን የኮቪድ 19 መከላከያ የንጽህና እርምጃዎች በመተግበር የሰርግ ስነስርዓት ማካሄድ ይችላል፣
  • 43. የአደባባይ በዓላት አከባበርን በተመለከተ (አንቀጽ 23) • ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም የአደባባይ በዓላት ማለት ህዝብን በብዛት የሚያሳትፉ በክፍት ስፍራዎች የሚደረጉ ስብስቦች ናቸው። • ህዝብን በብዛት የሚያሳትፉ የአደባባይ ላይ በዓላት የወረርሽኑ ስርጭት መረጋጋት እስኪጀምር ድረስ በታቸለ አቅም ባይደረጉ ይመከራል፣ • በዓላትን የሚታደምም ሆነ አከባበሩን የሚያስተባበር ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የማድረግ እና በአከባበርም ወቅት ሁለት ሜትር ርቀትን ጠብቆ የመቆምና መቀመጥ ግዴታ አለበት፣ • በዓላትን የሚያስተባብር አካል በዓላት የሚከበሩባቸው አደባባዮች የሚሸፍኑትን ጠቅላላ ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን የማይበልጥ ሰው በመያዝ ስርዓቱን ማካሄድ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፣ • የበዓላቱ አስተባባሪዎች ወደ በዓላቱ የሚከበሩበት አደባባዮች የሚወስዱ መንገዶችን እና መግቢያ ቦታዎች ላይ የበዓላቱ ታዳሚዎች ተገቢውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ መሟላታቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፣
  • 44. የአደባባይ በዓላት ….  የበዓላቱ አስተባባሪዎች አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ ግዴታ አለባቸው፣  በአላቱ በሚከበሩበት ወቅት መጨናነቅ እንዳኖር የመግቢያ እና የመውጫ መንገዶችን መለየትን ጨምሮ ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን የመውሰድ ግዴታ አለባቸው፣  የበዓላቱ አዘጋጆች እና አስተባባሪዎች በበዓሉ አከባበር ወቅት ሊደረጉ የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች አስቀድሞ የመለየት፣ ለተሳታፊዎች የማሳወቅ፣ እና አፈጻጸሙን የመከታተል ግዴታ አለባቸው፣  ማንኛውም ታዳሚ የበዓላቱ አዘጋጆች እና አስተባባሪዎች የሚያውጧቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች የመተግበር ግዴታ አለባቸው፣
  • 45. የአደባባይ በዓላት …. በበዓላት አከባበር ወቅት ማናቸውም ለንክኪ የሚዳርጉ እንቅስቃሴዎች እና የአከባበር ስርዓቶች የተከለከሉ ናቸው፣ የጥንቃቄ እርምጃዎች የማይተገበሩ ከሆነ አስፈላጊውን እርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት አግባብ ባላቸው የመንግስት አካላት የሚፈጸም ይሆናል፣
  • 46. አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ካፌዎች፣ ባርና ሬስቶራንቶች፣መጠጥ ቤቶች፣ ቡና ቤቶች፣የጭፈራ ቤቶች፣ እና የመዝናኛ እና መጫዎቻ አገልግሎት የሚሰጡ ስፍራዎች (አንቀጽ 24) • በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ ማስተናገድ የተከለከለ ሲሆን በእያንዳንዱ ጠረጴዛ መካከል የሁለት ሜትር ርቀት ሊጠበቅ ይገባል፣ • አገልግሎትን የሚሰጡ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው፣ • የሚስተናገዱ ሰዎች ከሚመገቡበት እና ከሚጠጡበት ወቅት ውጭ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው፣ • ተቋማቱ በመግቢያና መውጫ በሮች እና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች ላይ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን ማዘጋጀት፣ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር የማድረግ፣ እንዲሁም ለሰራተኞቻቸው የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፤
  • 47. • የጭፈራ ቤቶች አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት አገልግሎት የሚሰጡበት ስፍራ ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን የሚበልጥ ሰው ሳይዙ፣ በተገልጋዮች መሀል ሁለት የአዋቂ እርምጃ (ሁለት ሜትር) በሁሉም ጊዜ በማስጠበቅ፣ ማንኛውም ለንክኪ የሚዳርጉ እንቅስቃሴዎችን በመከልከል፣ እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ሙሉ በሙሉ በመተግበር ሊሆን ይገባል፣
  • 48. ሲኒማ ቤቶች፣ ቲያትር ቤቶች እና የስዕል ጋላሪ (አንቀጽ 25)  ለሰራተኞቻቸው የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት አዳራሽ ወይም ስፍራ ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን የማይበልጥ ሰው በመያዝ እና ሁለት የአዋቂ እርምጃ (ሁለት ሜትር) በማራራቅ አገልግሎቱን መስጠት ይኖርባቸዋል፣ ማንኛውም ሰው በእነዚህ ተቋማት ለመስተናገድ ተቋማቶቹ የሚያውጧቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች የመተግበር ግዴታ አለበት፣
  • 49. ስፖርታዊ ውድድሮች (አንቀጽ 26) የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እይታየ በሌላ መመሪያ እስኪወሰን ድረስ የእግር ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ቴኒስ፣ አትሌቲክስ እና ሌሎች የስፖርት ውድድሮች በውድድሩ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉ እና ለነዚሁ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ከሆኑት ውጭ ታዳሚዎች በሌሉበት መከናወን አለባቸው፣
  • 50. በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚገኙባቸው ተቋማት ላይ የተጣሉ ክልከላዎች እና መደረግ ያለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች (አንቀጽ 27) • የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እየታየ በሌላ መመሪያ እስኪወሰን ድረስ የአረጋዊያን መጦሪያዎች ስፍራዎች እና የማገገሚያ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በአካል መጠየቅ የተከለከለ ነው • በማረሚያ ቤቶች ላይ የሚደረግ የታራሚን በአካል የመጎብኘት ሂደት በታራሚው እና በጠያቂው መሀል ሁለት የአዋቂ እርምጃ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ፣ ታራሚውም ሆነ ጠያቂው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ በማስደረግ፣ ጠያቂው ወደማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ከመግባቱም በፊት እና ሲወጣ እጁን በውሃ እና ሳሙና እንዲታጠብ ወይንም በሳኒታይዘር እንዲያጸዳ በማድረግ፣
  • 51. የመተባበር ግዴታ (አንቀጽ 28) • ማንኛውም ሰው እና ተቋም ለዚህ መመሪያ ተፈፃሚነት የመተባበር ግዴታ አለበት። የህግ ተጠያቂነት (አንቀጽ 30) • በመመሪያው የተደነገጉ ክልከላዎችን እና ግዴታዎችን የተላለፈ ማንኛውም ሰው አግባብነት ባለው የወንጀል ህግ መሰረት ተጠያቂ እንደሚሆን የተደነገገ ሲሆን • አግባብነት ያላቸው የወንጀል ህጎች ድንጋጌዎችን ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ፡-  የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር ቁጥር 661/2002 ይህ አዋጅ ስለተላላፊ በሽታዎች አንቀጽ 26 እና 27 እንደሚያስቀምጠው፡-
  • 52. የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር ቁጥር 661/2002 …  ማንኛውም ወደ ሀገር የሚገባ ወይም ከሀገር የሚወጣ መንገደኛ ሀገሪቱ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የጤና አጠባበቅ መስፈርቶች መሠረት….በተላላፊ በሽታ ሲጠረጠር ለምርመራ የመተባበር ግዴታ እንዳለበት፣  ....ወረርሽኝ ካለበት ቦታ የመጣ ሰው ወደ ሀገር አንዳይገባ ሊታገድ እንደሚችል፣  አግባብ ያለው የጤና ባለሙያ በወረርሽኝ ተላላፊ በሽታ የተያዘን ወይም የተጠረጠረን ማንኛውም ሰው ለተወሰነ ጊዜ ተገልሎ እንዲቆይ ማድረግ እንዳለበት፣  በወረርሽኝ ተላላፊ በሽታ የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ለምርመራ፣ለሕክምና…ፈቃደኛ መሆን እንዳለበት ተደንግጎዋል።  በአዋጁ መሰረት እነዚህን ድንጋጌዎች መጣስ እስከ ስድስት ወር በሚደርስ እስራት ሊያስቀጣ ይችላል።
  • 53. የኢፌድሪ የወንጀል ሕግ  በወንጀል ህጉ አንቀጽ 514 ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ተላላፊ በሽታን ማስተላለፍ በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል አድርጎ ደንግጓል። ይህን አንቀጽ በመጣስ የሚፈጽም ወንጀል እስከ አስር አመት የሚደርስ የእስራት ቅጣት ሊያስከትል እንደሚችል ሲሆን በተለይም ተላላፊው በሽታ በወረርሽኝ ወይም በኢፒደሚክ መልክ የተከሰተ ሲሆን እንደነገሩ ክብደት ቅጣቱ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም ሞት ሊያስቀጣ እንደሚችል የወንጀል ሕጉ ያሳያል።  በወንጀል ህጉ 522 መሰረት ማንም ሰው ተላላፊ በሽታ ለመከላከል፣ ለመግታት፣ ወይም ለማቆም በህግ የተደነገጉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች አስቦ የጣሰ እንደሆነ እስከ ሁለት ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ይቀጣል በቸልተኝነት ከሆነ እስከ 6 ወር በሚደርስ ቀላል እስራት ሊቀጣ ይችላል፡፡
  • 54. • የወንጀል ሕጉ በአንቀጽ 830 የህዝብ ጤና እና ጤናማነትን ለመቆጣጠር በሚል ርዕስ ባሉት ደንጋጌዎች እንደተገለጸው በሽታዎችን በተለይም ተላላፊ በሽታዎችንና ወረርሽኝ ስለመከላከል፣ መኖራቸውን ስለማሳወቅ፣ ለመከላከል የሚረዱ ህክምናዎችን ስለማድረግ ወይም ስለመቆጣጠር የወጣን መመሪያ መጣስ በመቀጮ ወይም በማረፊያ ቤት እስራት ሊያስቀጣ የሚችል ወንጀል ነው • በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 485 መሰረት ለህዝብ ጤና አስጊ የሆን አደጋ እንደሚደርስ በማስፈራራት ሆን ብሎ ህዝብን ያሸበረ ከሶስት አመት በማይበልጥ ቅላል እሰራት ወይም እንደነገሩ ክብደት ከሶስት አመት በማይብለጥ ጽኑ እስራት ሊቀጣ እንደሚችል ተደንግጎዋል።
  • 55. ማጠቃለያ ወረርሺኙ በተለያዩ የግለሰብና የቡድን መብቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል፡- እነዚህም፡- • በጤንነትና በህይወት መኖር መብት፣ • ከቦታ ቦታ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት፣ • ሰርቶ የመኖር (የመስራት መብት) • የሀይማኖትና እምነት ነጻነት መብት • የመማር መብት፣ • የመሰብሰብ መብት • በሴቶችና ህጻናት መብት ( የሀይል ጥቃት)
  • 56. • የኮቪድ 19 ወረርሺኝን ለመከላከል የወጡ ህግጋትን የማስፈጸም ስራው የመጨረሻው ግብ የሰዎችን በጤንነትና በህይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበርና ማስከበር ነው፡፡ • በዚህ ረገድ በመመሪያው የተጣሉ ግዴታዎችንና ክልከላዎችን በሚጥሱ አካላት ላይ አግባብ ባለው ወንጀል ህግ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ ስለሚደነግግና ህጉንም በማስፈጸም ረገድ የፍትህ አካላት ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡
  • 57. • ፖሊስ ፡-ወንጀልን በመከላከል ፣በምርመራ፣ የህዝብ ትራንስፖርት ቁጥጥር • ዐቃቤ ህግ ፡-ክስ መመስረት፣ ችሎት ክትትል፣ ህጉን እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር ግንዛቤ የመፍጠር፣ ማረሚያና ማረፊያ ጉብኝት --- • የጤናው ዘርፍ የሚመሩ ተቋማት፡- ወረርሺኙን ለመከላከል ከሚያደርጓቸው የቅርብ ክትትሎች፣ የማስገንዘብ እንዲሁም ከሚወስዷቸው አስተዳደራዊ እርምጃዎች (በቀጥታ የሚቆጣጠሯቸውን ተቋማት) ባሻገር የወንጀል ድርጊት ውስጥ የገቡትን ለፍትህ አካላት ጥቆማ በመስጠት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል፡፡ • እነዚህና ሌሎች ስልጣንና ተግባራትን በመወጣት ወረርሺኙ በመከላከል ረገድ ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል