SlideShare a Scribd company logo
1 of 52
Download to read offline
1 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የተዘጋጀ መማሪያ
የማህበረሰብ ውይይት አመቻች መማሪያ
አዘጋጅ፡ ቱሩፋት ቱኩራ ገመቹ
የኖርወይ እርዳታ ሰጪ ቤተ ክርስቲያን ድርጅት የሥርዓተ ጾታ እና
ልማት ፕሮግራም አማካሪ
ጥር‚ 2022
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
2 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
አርዕስት ገጽ
መግቢያ..............................................................................................................................................3
ክፍል አንድ...........................................................................................................................................5
የማህበረሰብ ውይይት መሰረታዊ ፍሬ ሀሳቦች.................................................................................................5
ክፍል ሁለት.....................................................................................................................................22
ክፍል አንድ፡ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን አሁናዊ እውቀት፤አመለካከት እና ልምድን መረዳት ...............24
ክፍል ሁለት፡ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ን በተመለከተ የእውቀትና የግንዛቤ ክፍተትን መሙላት ..................29
ክፍል ሶስት፡ የማህበሰብ ደረጃ ሀብትን በማቀናጀት የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መከላከል ( Mobilizing local
resources).........................................................................................................................................................39
ክፍል አራት፡ የጋራ እቅድ ( Joint planning) ..........................................................................................................40
4.1 ማህበራዊ ውሳኔ (Community decision).........................................................................................................40
ክፍል አምስት ፡ የዕቅድ ትግበራ ምዕራፍ ( Implementation phase)...................................................................... 46
ክፍል ስድስት፡ አፈጻጸም መገምገም እና አጠቃላይ ሂደትን መሰነድ (Performance review and documentation)_ 47
የማህብረሰብ ውይይት አባላት በራሳቸው ላይ ያመጡት ለውጥ መሙያ ፎርማት.....................................................51
ዋብ መጽሐፍት...................................................................................................................................52
3 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
መግቢያ
ኢትዮጵያ የህጻናት እና የሴቶችን መብት ለማስከበር ዓለም እና አህጉር አቀፍ ስምምነቶችን ያጻደቀች አገር
ነች፡፡ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የቤተሰብ ህግን በማሻሻል የጋብቻ ዕድሜ ለወንድና ለሴት 18 ዓመትና
ከዚያ በላይ እንድሆን ደንግጎል፡፡ በተመሳሳይ የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንደ ሴት ግርዛት ወንጀል መሆኑን
የተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ይደነግጋል፡፡ ቢሆንም ያለ ዕድሜ ጋብቻና የሴት ግርዛት ስርጭት ኢትዮጵያ
ውስጥ ቀጥለዋል፡፡
በ 2016 የኢትዮጵያ የስነ-ህዝብ እና የጤና ዳሰሳ መረጃ መሰረት ያለ ዕድሜ ጋብቻ ስርጭት 40% ስሆን
የሴት ግርዛት 74% ነው፡፡ ኢኮኖሚያዊ፤አካላዊ፤ ወስባዊ እና ስነ ልቦናዊ በሰፋት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩ
የጥቃት አይነት መሆናቸውን መረጃው ያስረዳል፡፡ በመሆኑም የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ሥርዓተ
ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ውስጥ የሚመደቡ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ጎልተው የሚታዩ
ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው። እነዚህ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ኢትዮጵያ ውስጥ የሥርጭት መጠናቸው
ከቦታ ቦታ ይለያያል። ለዚህም የማህበረሰቡ ጎጂ ልማዶች፤ አሉታዊ ወጎች፤ የተዛቡ እሴቶች፤ሀይማኖታዊ
አስተምሮቶችን በአግባቡ አለመረዳት፤ የአኗኗር ዜይቤና የመሳሰሉት በዋነኝነት የሚጠቀሱ ምክንቶች ናቸው።
በተጨማሪም የባለ ድርሻ አካላት በቅንጅት አለመሥራት፤ የህግ አፈጻጸም ክፍተት፤ የአካባቢውን ማህበረሰብ
አሳታፊ ያላደረጉ የመፍትሔ አቅጣጫዎችና የመሳሰሉት ለችግሩ ቀጣይነት ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። የሴት
ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ በሴቶች ላይ መጠነ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ፤ማህበራዊ፤ስነ ልቦናዊ እና አካላዊ
ቀውሶች ያስከትላሉ።
ስለሆነም የማህበረሰብ ውይይት ማህበረሰቡ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የሚደረሱ ሥርዓተ ጾታን መሠረት
ያደረጉ ጥቃቶችን እንደ ያለ ዕድሜ ጋብቻና የሴት ግርዛት በመገንዘብ በአካባቢው የሚገኙ ሀብቶችን
በመለየት መፍትሔ ለመፈለግና ለመከላከል ይረዳል። ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በተለይ
ያለ ዕድሜ ጋብቻና የሴት ግርዛት ወጥ በሆነ መንገድ መፍታት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ መፍትሔው
ሀሳቦችም ችግሮቹ ከሚከሰቱበት ማህበረሰብ ካልመጣ በስተቀር ዘላቂ አይሆንም። መፍትሔው በሌላ
አካል የሚመጣ ከሆነ የአካባቢው ማህበረሰብ ለመፍትሔው ባለቤት የመሆን ፍላጎት በጣም አናሳ ይሆናል።
በመሆኑም ማህበረሰብ አቀፍ መፍትሔ እና ማህበረሰቡን የችግሩን የመፍትሔ አካል ለማድረግ የማህበረሰብ
ውይይት ዋነኛ ስልት ነው። የማህበረሰብ ውይይት በማህበረብ ውስጥ ያሉ አካባቢ በቀል ሀብትና
እውቀቶችን ለመለየትና ለመጠቀም ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
4 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
በመሆኑም የማህበረሰብ ውይይት አመቻች የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፊዎች በንቃት ውይይቱ ላይ
እንዲሳተፉ ውይይቱን በክህሎት መምራት ይኖርበታል። የውይይት ተሳታፊዎች ለችግሮቹ የሚሰሩ
የመፍትሔ ተግባራት ማስቀመጥ፤መተግበር፤ የቀሰሙትን እውቀት በሚያገኙት ማህበራዊ ትስስሮች ሁሉ
ለማህበረሰቡ ማካፈል መቻል አለባቸው። ይህን ለማድረግ ትምህርት ቤቶች፤ የመገበያያ ቦታዎች፤የጤና
ተቋማት፤ የቤተ እምነት ተቋማት፤የእድር ስብስባዎች ዋነኛ የቁልፍ መልእክቶች ማሰራጫ ቦታዎች ናቸው።
በመሆኑም ፖሊስ፤ ፍርድ ቤት፤ እድሮች፤የጤና ባለሙያዎች፤የሀይማኖት አባቶች፤የግብርና ባለሙያች፤የጤና
ኤክስቴሽን ባለሙያዎች፤ የሀገር ሽማግሌዎች፤የሴቶች አደረጃጄት ቁልፍ የማህበረሰብ ውይይት ውሳኔዎች
ማስፈጸሚያ ባለድርሻ አካላት ናቸው፡፡
ይህ መማሪያ መጽሐፍ በሁለት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ክፍል አጠቃላይ የማህበረሰብ
ውይይት ዋና ፍሬ ሐሳቦችን፤ ለውይይቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፤የማህብረሰብ ውይይት አባላት ምርጫ፤
ከአመቻች የሚጠበቁ ዝግጅቶችና የመሳሰሉት ፍሬ ሐሳቦችን፤ የያዘ ሲሆን የማህበረሰብ ውይይት አመቻች
ሁልጊዜ ማንበብና ማወቅ አለበት። አመቻቹ ለማህበረሰብ ውይይት ሲዘጋጅ ይህን ክፍል ማንበብና
መረዳት ይኖርበታል፡፡
የማህበረሰብ ውይይት አባላት 20 እስከ 25 ሰው ይሆናል፡፡ የውይይቱ አባላት በቀበሌው ከሚገኙ ት/ቤቶች፤
የሀይማኖት ተቋማት፤ የሀገር ሽማግሌዎች፡የእድር መሪዎች፤ ዕድሜው 12 ዓመትና ከዛ በላይ የሆነ ወጣት፤
የፍትህ ቢሮ፤ ጤና ተቋማት ይመሰረታል፡፡ ውይይቱ ከ 4 እስክ 5 ሰው በቡድን በመክፈል ይካሄዳል፡፡
የማህበረሰብ ውይይት ለስድስት ወራት የሚካሄድ ሲሆን በወር ሁለት ጊዜ ለሁለት ሰዓት ይደረጋል፡፡
በአጠቃላይ ለአስራ ሁለት ሳምንት ይካሄዳል፡፡ከስድስት ወር በኋላ የማህበረሰብ ውይይት አባላት
፟
ይመረቃሉ፡፡ለመመረቅ ቢያንስ እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ቢያንስ ሰባት ሳምንትና ከዛ በላይ ውይይቱ
ላይ መሳተፍ አለባቸው፡፡ ውይይቱ ቦታና ቀን በአባላት ይወሰናል፡፡አመቻቹ እንደየ አካባቢዊ ተጨባጭ
ሁኔታ ውይይቱን ማስከድ አለበት፡፡
የማህበረሰብ ውይይት ቡድን ሲመሠረት በጥንቃቄና በተሰጠው መምሪያ መሠረት መሆን ይኖርበታል።
ሁለተኛው ክፍል የማህበረሰብ ውይይት ክፍሎች ሲሆኑ አመቻቹ በእያንዳዱ ደረጃ የተመለከቱ ርዕሶች
በሚገባ መረዳትና ውይይቱን መምራት ይጠበቅበታል። ተሳታፊዎች የቀሰሙትን እውቀት በተግባር ማዋል
እንዲሁም ሌሎች የማህበረሰብ አባላትን ማስተማር አለባቸው። በውይይቱ ወቅት ተጨማሪ ማብራሪያ
በሚያስፈልጉ ርዕሶች ላይ እንደ አስፈላጊነቱ የሀይማኖት አባቶች ፤የህግ እና የጤና ባለሙያዎችን በመጋበዝ
ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ማድረግ ይችላል፡፡ በተጨማሪ በዚህ መማሪያ የሚገኙት ቅጾች በሙሉ
በተሰጠው መምሪያ መሰረት በተግባር ላይ መዋል አለባቸው፡፡
5 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
ራዕይ (Vision)
የማህበረሰብ ውይይት አባላት የውይይታቸው መዳረሻ ሊኖራቸው ይገባል። የማህበረስብ ውይይት ያለ
ራዕይ መዳረሻ የለሌው ይሆናል። በመሆኑም የስድስት ወራት ራዕይ መኖር አለበት።
ራዕይ፡ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በተለይም የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልምዶችን
የሚጠየፍ ግለሰብ፤ቤተሰብ፤ማህበረሰብ እና ተቋማት ተፈጥሮ ማየት።
ተልዕኮ ( Mission)
የማህበረሰብ ውይይት አባላት ወደ ራዕይ የሚወስዳቸው መንገድ ያስፈልጋቸዋል። ያለ ተልኮ ራዕይ ላይ
መድረስ አይቻልም። ስለሆነም የማህበረሰብ ውይይት አባላት የተመሠረቱበት ተልኮ ሊኖራቸው ይገባል።
ተልኮ፡ በማህረሰባችን በሚገኘው ሀብት በመጠቀም ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም
የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻንየሚከላከል ግለሰብ፤ቤተሰብ፤ማህበረሰብና ተቋማት መፍጠር።
ግብ (Goal)
የማህበረሰብ ውይይት አባላት የሚለካ ግብ ሊኖራቸው ይገባል። የማህበረሰብ ውይይት አባላት መጨረሻ
ላይ የውይይታቸው ስኬት ባስቀመጡት ግብ አንጸር መለካት አለባቸው።
ግብ አንድ፡ በማህበረሰባችን ውስጥ ስለ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ስለመከላከል ማህበራዊ
መድረኮችን በመጠቀም ግንዛቤን ማሳደግ ።
ግብ ሁለት፡ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ለመከላከል የተቋማት አቅም ማሳደግ።
ግብ ሶስት፡ የማህበረሰባችንን ለሥርዓተ ጾታ መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም የሴት ግርዛት እና ያለ
ዕድሜ ጋብቻ የሚያጋልጡ ባህሪዎችን እንዲሁም አስተሳሰቦችን መቀየር
የሚለኩ ዋና ዋና ዓላማዎች ( Short term objectives)
የማህበረሰብ ውይይት አባላት ወደ ግብ መድረሳቸውን የሚያሳይ የአጭር ጊዜ ዓላማ ማስቀመጥ አለባቸው።
ዓላማዎችን ለመጻፍ የፕሮጀክት አስተባባሪው የመነሻ የዳሰሳ መረጃ መሰብሰብ አለበት። ለምሳሌ፡
አንድ
6 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
❖ በ2015/2016 በቀበሌው የሚገኙት ሁሉም ባህላዊ መዋቅሮች ለምሳሌ እንደ እድር ያሉ ሥርዓተ
ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ግንዛቤ
በ70% ወይም ማሳደግ።
❖ በ2015/2016 በቀበሌው የሚገኙት የሁሉም ቤተ እምነት መሪዎች ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ
ጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ የሚሰሩ 60%
ወይም ማሳደግ።
❖ በ2015/2016 በቀበሌው የሚገኙት የሁሉም ት/ቤቶች ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን
በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ የሚሰሩ 100% ወይም
ማሳደግ።
❖ በ2015/2016 የቀበሌውን ሕዝብ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት
ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ያለውን እውቀት በ85% ማሳደግ፡፡
ዝርዝር ዓላማዎች ( Specific objectives)
ዝርዝር ዓላማዎች ዋና ዓላማን ለመድረስ የሚተገበሩ ዝርዝር ተግባራት ናቸው። በመሆኑም የዋና ዓላማው
ዝርዝር ተግባራት፤
❖ የማህበረሰብ አባላት ማለትም ወጣቶች፤ ባህላዊ መሪዎች፤ወላጆች፤የማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች
በሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ውይይት የሚያደርጉበትን መድረክ ለመፍጠር፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መፍትሔ
መፈለግና መተግበር፤
❖ በሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ምክንያት የሚመጣውን መጠነ ሰፍ ጉዳቶችን መለየት፤
❖ ማህበረሰቡ ለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የሚጫወተውን ሚና ማሳደግ፤
❖ የግለሰብ፤የቤተሰብ፤የማህበረሰብ እና በማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት አቅም በማጎልበትና
በማጠናከር የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን( ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት)
መከላከል፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን የሚያበረታቱ ልምዶች፤ እሴቶች እና ወጎችን መገንዘብ፤
❖ ትምህርት ቤቶች፤የጤና ተቋማት፤ የቤተ እምነት ተቋማት፤የእድሮቸ ፤የአካባቢዊ የብዙሀን
መገናኛዎች ዘውትር ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ቁልፍ መልእክቶች እንድያሰራጩ
ማድረግ።
7 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የአባላት ሚና ( Roles of community conversation members)
የማህበረሰብ ውይይት አባላት የሚከተሉትን ተግባራት በማከናወን ለማህበረሰባቸው የበኩላቸውን
መወጣት አለባቸው።
❖ በማህበረሰብ ውይይት ወቅት ያገኙትን እውቀት ለመጡበት ቀበሌ ወይም መ/ቤት ለማስተማር
ማቀድ፤
❖ በውይይቱ ወቅት በመጡበት አካባቢያ ያለው ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉጥቃቶችን
በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ያለውን እውነተኛ ሐሳብ ማንሳት፤
❖ የተለያዩ መድረኮችን በመጠቀም ማለትም ለጎረቤትና ለቤተሰብ ቡና ሲጠጣ፤በስግደት ሰዓት
መልስ፤በፀሎት ሰዓት መልስ፤ በገበያ ቀናት፤ በእድር ስብስባ፤በት/ቤቶች፤ያገኙትን እውቀት
ማስተማር፤
❖ በማህበረሰብ ውስጥ የሚነሱ ሰለ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት
ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ያሉ ልምዶችና የተሳሳቱ እምነቶችን ለውይይት ማቅረብ፤
አስፈላጊነት ( Essence of community conversation)
የማህበረሰብ ውይይት ማለት ማህበረሰብና ማህበረሰብ አቀፍ የባለ ድርሻ አካላት አቅማቸውን
በማጎልበት በጋራ የራሳቸውን ችግሮች የሚለዩበትና የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያስቀምጡበት ሂደት ነው።
ሁሉንም አሳታፊ እንዲሁም ተግባቦት በሆነ መንገድ ፤ በግለሰቦችና በቡድኖች መካከል ሀሳብ
በመለዋወጥ የሚሰራ መፍትሔ በስምምነት ለማስቀመጥ ይረዳል። ሁሉም ተሳታፍዎች ስለማህበረሰቡ
ችግሮች በጥልቀት የራሳቸውን ሀሳብና ፍላጎት በመግለጽ የጋራ ግብ ያስቀምጣሉ።
የማህበረሰብ ውይይት ማህበረሰቡ በአካባቢያቸው ጎልተው የሚታዩ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ
የሚደርሱ ሥርዓተ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ማለትም የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን
ለመከላከል ግልጽ ውይይት፤ በመከባበር ላይ የተመሰረተ እና መፍትሔ ተኮር መድረክ ሆኖ ያገለግላል፡
፡ውይይት የማህበረሰብን የአንድነት መንፈስ ያጠናክራል፤ ማህበረሰቡ ለጋራ ችግራቸው በአንድነት
እንድሰሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
8 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የሚጠበቁ ውጤቶች (Expected outcomes)
ከማህበረሰብ ውይይት የሚጠበቁ ውጤቶች መኖር አለባቸው።የማሀበረሰብ ውይይት ውጤት ተኮር
መሆን አለበት። ውጤቶች የለሌው ውይይት እውቀት፤አመለካከት እና ልምድን የመለወጥ እድል
የለውም፡፡
❖ በግለሰብ ደረጃ የተለዩ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሱ ሥርዓተ ጾታን መሰረት ያደረጉ
ጥቃቶችን መቀነስ፤
❖ ማህበረሰቡ በአንድነት የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን (ሥርዓተ ጾታን መሰረት
ያደረገ ጥቃት) ለመከላከል እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የሚሰራ ውሳኔ ማሳለፍ
❖ በጥልቀት አሁናዊ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ
ዕድሜ ጋብቻ ላይ ልምዶችን የተገነዘበ ማህበረሰብ መፍጠር
❖ በግለሰብ፤ በቤተሰብ እና በማህበረሰብ ደረጃ የተለዩ በአካባቢው የሚገኙትን ዕድሎችና ለባህርይ
ለውጥ እንቅፋት የሆኑትን መለየት
❖ በአንድነት የሚሰሩ ማህበረሰብ አቀፍ ተቋማት ማለትም ትምህርት ቤቶች፤ ጤና፤ቀበሌ
አስተዳደር፤ፍትህ፤ባህላዊ አስተዳደር፤የጎሳ መሪዎች እና እድሮች ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት
እንዲከላከሉ ማስቻል፤
❖ ማህበረሰቡ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ
ዕድሜ ጋብቻን ለማስወገድ የሚረዱ የታወቁ የአካባቢ ሀብቶችን መለየትና ማሰባሰብ፤
❖ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሱ ሥርዓተ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃትን የተገነዘበና
የሚከላከል ማህበረሰብ መፍጠር፤
❖ (ሥርዓተ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እና ልጃገረዶችን ) አስፈላጊውን
እገዛ የሚያደርግ ማህበረሰብ መፍጠር ፤
❖ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን
ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት መሆኑን የተረዳ ማህበረሰብ መፍጠር፡፡
መሰረታዊ መርሆች ( Fundamental principles)
ውጤታማ የማህበረሰብ ውይይት ለማካሄድ መሠረታዊ መርሆችን መከተል ተገቢ ነው።
የማህበረሰብ ውይይትን ውጤታማ ለማድረግ መሪህ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት።
9 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
❖ ሁሉም አቀፍነት፡ በቀበሌው የሚገኙ ሁሉም ጎሳዎች፤ብሔረሰቦች፤ ሀይማኖቶች፤ ተቋማትን
ማካተት ግደታ ነው። ይህም የተለያዩ ሀሳቦችን ለማስተናገድና ልተገበር የሚችል መፍትሔን
ያስገኛል።
❖ የጋራ ባለቤትነት፡ ሁሉም የውይይቱ ተሳታፍዎች በቁርጠኝነት፤በቅንነት፤በታማኝነት፤ትርጉም
ባለው መንገድ መሳተፍ አለባቸው።
❖ መማር፡ ሁሉም የውይይቱ ተሳታፍዎች በግልጸኝነት የችግሩን መጠንና ስፋት በመረዳት ለመማር
ዝግጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
❖ ሰብአዊነት፡ ተሳታፍዎች የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጉዳት የደረሰበት ሰው ምትክ
ራሳቸውን በማስቀመጥ ርህራኄን መግለጽ።
❖ ምስጢራዊነት፡ በውይይቱ ወቅት እርስ በእርስ በመተማመን፤ ተሳታፍዎች ያለ መፍራት ሀሳባቸውን
በነጻነት መግለጽ አለባቸው።
❖ ዘላቂነት ያለው ረጅም ጊዜ አመለካከት፡ ጊዜያዊ መፍትሔ ከማስቀመጥ ይልቅ ጎጂ የሆኑ ወጎች
እና ልምዶች በዘላቂነት ወደ ጠቃሚና ሴቶች እና ልጃገረዶችን ከጥቃት የሚጠብቁ መሆን ማስቻል
።
❖ መልካም እምነት፡ ተሳታፍዎች ድብቅ ፍላጎቶችንና አጀንዳዎችን በመተው በቅንነት እውቀታቸውን
ማካፈል።
አመቻች ክህሎት ( Facilitator’s skills)
የማህበረሰብ ውይይት አመቻች ለውይይት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ተሳታፍዎች ሀሳባቸውን፤
እውቀታቸውን፤ የሚያሳሰባውን ጉዳይ በነጻነት ያለ ፍርሀት እንድገልጹ ማድረግ አለበት። እስከ ውይይት
መጨረሻ ድረስ ተሳታፍዎች አካላዊና ስሜታዊ ምቹነት እንድኖራቸው አመቻች ማረጋገጥ አለበት።
በመሆኑም የውይይት አመቻች ሲመረጥ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ከአመቻች የሚጠበቁ ብቃቶች (Competence)
❖ የውይይት ሀሳቦችን በአጭሩ ለተሳታፍዎች መግለጽ፤
❖ ለተሳታፍዎች የውይይቱ ፍሬ ሀሳብ ማስረዳት፤
❖ ሁሉም ተሳታፍዎችን እኩል ማሳተፍ፤
❖ የሀሳብ ልዩነቶችን መቀበልና የሚያሰማሙ ነጥቦችን መለየት፤
10 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የአመቻች ማስታወሻ
ግጭት ማለት በሁለት ቡድኖች መካከል የሚከሰት አለመግባባት ነው።
❖ ግጭት የሚፈጠረው በሀብት እጥረት፣ በሀሳብ አለመግባባት፣
የመልካም አስተዳደር እጦትና በመሳሰሉት ይከሰታል።
❖ ግጭት ለመከላከል፦ አሳታፊ መሆን፣ ከአድሎ ነፃ መሆን፤
አካታችነት፤ግልጽነት ውሳኝ ነው።
❖ በውይይት ወቅት ግጭት ሲፈጠር በአግባቡ መፍታት፤
❖ ተሳታፍዎችን ለአዳድስ ሀሳቦች ማበረታትና ግብረ መልስ መስጠት፤
❖ በውይይት ወቅት ተገቢውን የሰውነት እንቅስቃሴን ማሳየት።
❖ የሚያፍሩን የማይሳተፉ አባላትን እንዲሳተፉ ማበረታታት
ተሳታፍዎችን ለመምረጥ መደረግ ያለባቸው ነጥቦች(Preconditions)
❖ ውይይት ልደረግበት የታሰበት ቦታ/ ቀበሌ የሚገኙ ሁሉም የባለ ድርሻ አካላትን መለየትና
በማስታወሻ ላይ መጻፍ፤
❖ የውይይቱ የባለ ድርሻ አካላት የሚባሉ መምህራን፤ የሁሉም ቤቴ እምነቶች የሀይማኖት አባቶች፤
የጎሳ መሪዎች፤የሀገር ሽማግሌዎች፤ታዋቂ ሰዎች፤ የህክምና ባለሙያዎች፤ወጣቶች፤ የቀበሌ
አስተዳዳሪ፤ ዳኞች፤ ፖሊሶች፤ የእድር አባላት፤የተለያዩ ማህበራት አባላት መለየት፤
❖ በአካባቢው/ በቀበሌው የሚገኙትን ሁሉም ተቋማት መለየትና በማስታወሻ ላይ መጻፍ። ተቋማት
የሚባሉት ትምህርት ቤቶች፤ የጤና ኬላዎች፤የጤና ጣቢያዎች፤ሆስፒታሎች፤ቤቴ እምነቶች፤እድር፤
የቀበሌ አስተዳደር መ/ቤቶች፤ ፖሊስ ጣቢያ፤ የፍትህ እና ባህላዊ ተቋማት።
የአባላት ምርጫ መመዘኛዎች (Criteria of members selection)
❖ የመሳተፍ ፍላጎት፡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት `በፍላጎትና በነጻነት መሳተፍ አለባቸው።
❖ ብዙሀነትን መጠበቅ፡ የውይይት ተሳታፍዎች ሚዛኑን በጠበቀ መልክ ስለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ
ጋብቻ መረጃ እና እውቀት ያለው የህብረተሰብ ክፍል እና መረጃና እውቀት የለሌው የህብረተሰብ
ክፍል እኩል መወከል አለባቸው።
11 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
❖ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አካታችነት፡ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት እስከ ውይይቱ መጨረሻ ሂደት
ድረስ መሳተፍ አለባቸው። ይህም የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ስለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ
ያላቸውን የተለያዩ ሀሳቦችን ለመረዳት አስተዋጽኦ ያደርጋል።
❖ በውይይቱ የመሳተፍ ተገቢነት፡ ማን ውይይቱ ላይ ብሳተፍ ለባህርይ ለውጥ አስተዋጽኦ ያደርጋል
የሚለውን በደንብ ማየት ተገቢ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ግጭትን ለማስወገድ ከፍተኛ ሚና
ይጫወታል።
❖ አሳታፍ ውሳኔ ሰጪነት፡ የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፍዎች ሁሉም የቀበሌ ባለድርሻ አካላት እና
ተቋማት በተገኙበት ይመረጣሉ።
❖ ሁሉም አቀፍነት፡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እና ተቋማት መወከል አለባቸው።
❖ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ መሆን፡ በማህበራዊ ደረጃ፤ በሀብት ልዩነት እና በፖለቲካ ምክንያት
የተከለሉና አናሳ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማካተት።
❖ ማብቃት፡ የተመረጡ የማህበረሰብ አባላት፤በነጻነት የሚሰማቸውን ሀሳብን መግለጽ የሚችሉ፤ ለሎች
ድምጽ ልሆኑ የሚችሉ፤ የለውጥ አካል እንድሆኑ ማብቃት።
❖ ሁሉም ጾታዎች ማካተት፡ አንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ወንዶችና ሴቶች አንድ ላይ
እንድወያያዩ ማድረግ፤ የአካባቢው ባህል የማይፈቅድ ከሆነ ወንዶችና ሴቶች ብቻ ለብቻ እንድወያዩ
ማድረግ ግደታ ነው። ቁጥራቸው 20 እስከ 25 አባላት ሲሆን ልጃገርዶች፤ እናቶች እና አዋቅዎች
የውይይቱ አካል መሆን አለባቸው።
❖ የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፍ ስነ ምግባር፡ የውይይት ተሳታፊ አባላት ስነ ምግባርና ተቀባይነት
በትክክል መላው የቀበሌ ህዝብ በተገኘበት አባላቶቹ ላይ አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ ተገቢ
ነው። ምክንቱም የውይይቱ ፍሬ ሀሳቦች ተሳታፍው ለማህበረሰቡ ማካፈል መቻል አለበት። ብልሹ
ስነ ምግባር ካለው ሀሳቡ ተሰሚነት አያገኝም።
❖ በጎ ፍቃደኝነት፡ የውይይቱ አባላት በበጎ ፍቃደኝነት ማህበረሰቡን ለማገልገል ፍቃደኝነታቸን
ማረጋገጥ አለባቸው። ለዚህም በምርጫው ላይ ተገቢውን ትኩረት መስጠት ወሳኝ ነው።
12 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የማህበረሰብ ውይይት አመቻች ሁልጊዜ ማንበብና ማወቅ አለበት። አመቻቹ ለማህበረሰብ
ውይይት ስዘጋጅ ቀጥሎ ያለውን በሰንጠረዥ ያለውን ሀሳብ ማንበብና መረዳት ተገቢ
ነው።
13 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የአመቻች የትኩረት ቦታዎቸ ( Attention areas for facilitator)
የትኩረት ድርጊቶች አብይ ተግባራት
የትኩረት ነጥቦች
1. ውይይት ከመጀመሩ በፍት ተሳታፍዎች ስለ መምጣታቸው ማመስገንና ሁሉም ሰው ሐሳብ እኩል መሆኑን መግለጽ፤
2. አንድ ሰው ሲናገር ሌሎች ማዳመጥ እንዳለባቸውና ተራ ጠብቀው እንዲናገሩ ማድረግ፤
3. ማንኛውም ሰው በነጻነት ስለ ርዕሱ የሚሰማውን ሐሳብ እንድናገር ማበረታት፤
4. ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ቦታ ላይ መቀመጡን ማረጋገጥ፤
5. ሁሉም ሰው የመፍትሔ ሐሳብ ጭምር ማቅረብ እንዳለበት ማበረታት፤
6. የመፍትሔ ሐሳብ ከአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መቅረብ እንዳለበት ማሳወቅ፤
7. ሁሉም አባላት የባለፈውን የውይይት ርዕስ ለሌሎች ለማስተማር ያወጡትን እቅድ አፈጻጸም እንድያቀርቡ ማድረግ፤
8. ውይይት ከመጀመሩ በፊት የውይይት ተሳታፍዎችን ከ10 እስከ 15 ማከፋፈልና የሚወያዩበትን የውይይት ሐሳብ መስጠት፤
9. የተወያዩትን ሐሳብ እንድያቀርቡ ማድረግና ሁሉም ቡድኖች እንድወያዩበት ማድረግ፤
10. የርዕሱን ዓላማዎች ሁሉም ሰው መረዳት በሚችለው ቋንቋ ማስረዳትና ግልጽ መሆኑን ማረጋገጥ፤
11. የዕለቱን የውይይት ጥያቄዎች ማስረዳት፤
12. ስምምነት የተደረሰባቸውን የውይይት ነጥቦችን መመዝገብ፤
13. የማህበረሰብ ውይይት አባላት ተግባራት ለአባላት ማስረዳት፤
14. ተሳታፍዎች በንቃት እንድሳተፉ ማነሳሳት፤
15. ተሳታፍዎች በአካባቢያቸው ያለውን አሁናዊ ሁኔታን መሰረት አድርገው ችግር ፈች ውይይት እንድያደርጉ ማድረግ፤
16. በውይይቱ ላይ የተገኙትን አባላት መመዝገብ፤
17. የዕለቱ ውይይት ካለቀ በኋላ ሁሉም አባላት በቃሌ ጉባዬ መዝገብ ላይ መፈራማቸውን ማረጋገጥ፤
18. የውይይቱ ርዕሱ ላይ ብቻ ትኩረት መደረጉን ማረጋገጥ፤
14 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
19. በአካበቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ የሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በጭውውት፤ በድራማ እና በግጥም እንድገልጹ
ማድረግ፤
20. በውይይቱ ላይ የተገኙ የኃይማኖት አባቶች ተራ በተራ እንድጸልዩ ማድረግ፤
21. ተሳታፍዎችን ማክበርና ሁሉም ሰው ሀሳብ እንድሰጥ ማሳተፍ፤
22. የውይይቱ ተሳታፍዎች በአግባቡ ውይይቱን እንድከታተሉና ጥያቄ እንድጠይቁ ማድረግ፤
23. መሻሻል ያለባቸውን ነጥቦች መለየትና እንድሻሻሉ ማድረግ፤
24. ተሳታፊዎች የጋራ ደንቦችንና መመሪያዎችን እንዲያከብሩ ማስታወስ፤
25. ሀሳብን በግልጽ እና ከዋናው ጉዳይ ሳይወጣ መግለጽ፤
26. ሁሉም ሰው የዕለቱን የውይይት ርዕስ መረዳቱን ማረጋገጥ፤
27. የሰዎችን ሐሳብ እና የአካባቢውን ባሕል ማክበር።
28. ለተሳታፍዎች የአካባቢያቸውን እውነታ ከማስረዳት መቆጠብ።
የውይይት ቦታና ጊዜ
እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ሁሉም ተሳታፍዎች የሚመቻቸውን የውይይት ቀን፤ሰዓት እና ቦታ በተሳታፍዎች ስምምነት መወሰን
አለበት። የውይይት ቦታ ሁሉም ተሳታፍዎች ነጻነት ይሰማናል ብሎ የሚሰማሙበት ቦታ መሆን አለበት። ቦታው ከሚረብሽ ድምጽ ነጻ
መሆኑንና ለወንዶችና ሴቶች ቅርብ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
የውይይት ቦታ የሚከተለው ልሆን ይችላል፡
❖ ትምህርት ቤት ገቢ/ መማሪያ ክፍል
❖ ገበያ ቦታ
❖ ዛፍ ጥላ ስር
❖ የቀበቤው መ/ቤት
15 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
❖ ቤቴ እምነቶች
❖ የስብስባ አደራሽ እና የመሰሰሉት
የጊዜ ሰሌዳ
❖ ሁሉም የውይይት ክፍሎች በወር ሁለት ጊዜ የሚካሄዱ ስሆን፤ ለስድስት ተከታታይ ወራት ይካሄዳሉ።
❖ ሁሉም የውይይት ክፍሎች ለሁለት ሰዓት መካሄድ አለባቸው።
❖ የውይይቱን ሂደት አመቻቹ ሁልጊዜ በየዕለቱ መለካት ወይም መገምገም እና መከተታተል አለበት።
ቅደመ ዝግጅት ❖ አመቻቹ የአመቻች መማሪያ በሚገባ ማንበብና መረዳት አለበት።
ሪፖርት ❖ አመቻቹ በየወሩ ማህበረሰብ ውይይት ሪፖርት መላክ አለበት።
የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ❖ የአመቻች መማሪያ፤ የቃሌ ጉባዬ መዝገብ፤ እስክብርቶ፤ማስታወሻ ደብተር።
ፍሬ ሐሳብና ግብረ
መልስ
❖ የዕለቱን ዋና ዋና ፍሬ ሀሳቦችን በመግለጽና ስምምነት የተደረሰባቸውን ሐሳቦች ብቻ በቃሌ ጉባዬ መዝገብ መመዝገብ፤ ከተሳታፍዎች
ለሚነሳኑ ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ መስጠት።
❖ ጥያቄው ሙያው ትንተና/ተጨማረ ማብራሪያ የሚያስፈልግ ከሆነ በማስታወሻ በመያዝ በቀጣይ ውይይት የሚመለከተውን ባለሙያ
መጋበዝና ገለጻ እንድያደርግ ማድረግ።
❖ በተጨማሪ የዕለቱ ውይይት ላይ አጠቃላይ ግብረ መልስ መስጠት።
❖ የዕለቱን ውይይት ጠንካራና መሻሻል ያለባቸውን ነጥቦች መለየትና ለቀጣይ እንድሻሻል የጋራ ስምምነት ማድረግ።
ማጠቃልያ ❖ ለተሳታፍዎች ምስጋና በማቅረብ የዕለቱን ውይይት ማጠቃለልና ለቀጣይ መዘጋጀት።
❖ የተዘጋጁ ሥዕላዊ መግለጫዎች ካሉ ማሳየት በጣም አስፈላጊ ነው።
16 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የማህበረሰብ ውይይት ቡድን ማቋቋም (Establishment of community conversation team)
የማህበረሰብ ውይይት አባላት የሚመሰረቱት በቀበሌው ወይም ውይይት የሚደርግበት አካባቢ
ከተለዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ነው። የማህበረሰብ ውይይት
አባላት መላው የቀበሌው ህዝብ በተገኘበት ምርጫ ይደረጋል። ምርጫው ከተደረገ በኋላ በተመራጮች
ላይ አስተያየት ይሰጥበታል። ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ በቀበሌው የተመረጡ ሰዎች የማህበረሰብ
ውይይት አባላት እንድሆኑ በግልጸኝነት፤ እና በብቅንነት ከሁሉም ተቋማትና የባለ ድርሻ አካላት
የተወከሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በመላው የቀበሌ ህዝብ መጽደቅ አለበት።
የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፍዎች ይሆናሉ። በማህበረሰብ ውይይት አመቻች የተመረጡ አባላት
ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተወጣጡ መሆናቸውን ያረጋግጣል። ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች
መወከላቸውን ካረጋገጠ በኋላ የውይይት አመቻች በሚከተሉትን ተግባራትን ያከናውናል፤
❖ ውጤታማና ፍሬያማ የማህበረሰብ ውይይት ለማካሄድ የውይይቱ አባላት ከ20 እስከ
25 መሆን አለባቸው። በውይይት ወቅት አባላቱ 4 እስከ 5 ሰው በድን ይሆናል፡፡
❖ የማህበረሰብ ውይይት አባላት ስብጥር ወንዶች 40% ስሆኑ ሴቶች 60% መሆን
አለባቸው።
❖ ወንዶች ከሁሉም ማለትም ወጣቶች እና ሽማግሌዎች ከሁሉም ተቋማት የተወጣጡ መሆን
አለባቸው። ሴቶችም በተመሳሳይ ወጣቶች እና አዋቂ ከሁሉም ተቋማት የተወጣጡ መሆን
አለባቸው። ዕድሜው 12 ዓመትና ከዛ በላይ የሆኑ ወጣቶች መሳትፍ አለባቸው፡፡
❖ የተመረጡ አባላትን ራሳቸውን እንድያስተዋውቁ ማድረግ፤
❖ የተመረጡ አባላትን መመዝገብ፤ የወንድና የሴት ስብጥር 40% ለወንድ እና 60% ለሴት
መሆኑን ማረጋገጥ፤
❖ አመቻቹ ራሱን ከህዝቡ ጋር ያስተዋውቃል፤ የስራ ድርሻውን በአጭሩ ይገልጻል፤
❖ ከተመረጡ አባላት የሚጠበቅባቸውን ተግራት ያብራራል፤አስተያየታቸውን ይቀበላል፤
❖ የማህበረሰብ ውይይት ራዕይ፤ ዓላማዎች፤ግብ፤ የሚጠበቁ ውጤቶች ለአባላቱ ና ለህዝቡ
ያስረዳል፤
❖ የጋራ መተዳደሪያ ደንብ በተመረጡ አባላት ጋር ያወጣል፤
❖ በስምምነት ላይ የተደረሱ ደንቦችን ይመዘግባል፤
❖ ቀጣይ የውይይት ቀን፤ቦታ እና ሰዓትን ያስወስናል።
17 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
❖ እንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ማስተላለፍ፤
❖ አባላቶቹ ከ30 እስከ 40 መሆናቸውን ማረጋገጥ
❖ የተሳታፍዎች ግንኙነት መፍጠር፤
❖ የተሳታፍዎች ትውውቅ
ስም
የመጡበት ቀበሌ/ሰፈር
ሀይማኖት
ስራ/ መተዳደሪያ
የትምህርት ደረጃ
ኃላፍነት
እንድታወቅልኝ የሚፈልገው ባህርይ
ከውይይቱ የሚጠበቀው ውጤት
የሚወዱት ነገር
የማህበረሰብ ውይይት አባላት መመዝገቢያ ቅጽ ( ቅጽ አንድ)
ሁሉም የማህበረሰብ አባላት በቀበሌው ህዝብ ከጸደቁ በኋላ መመዝገብ አለባቸው፡፡
ተ/ቁ የአባላት ስም ዝርዝር ጾታ ዕድሜ ሀይማኖት አድራሻ መተዳደሪያ ስልክ ቁ ምርመራ
1 ገመቹ አበበ ወ 35 ኦርቶዶክስ 01 ቀበሌ የቤ/ያን አገልግሎች 01916854572
ማሳሰቢያ፡ የማህበረሰብ ውይይት አባላት በምሳሌው መሰረት ይመዘገባሉ፡፡
የአመቻች ስም ፊሪማ ቀን
የቀበሌው አስተዳደሪ ስም ፊሪማ ቀን
የቀበሌው ማህተም
የአመቻች ማስታወሻ
18 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
❖ የቡድን ውይይት ከማድረግ በፊት የውይይት ተሳታፍዎችን ከ10 እስከ 12 ማከፋፈል፤
❖ ተሳታፍዎች የውይይቱን ጥያቄዎች ከአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ እንድያስረዱ
ማድረግ፤
❖ ቡድኑ የተወያየበትን ሀሳብ ተራ በተራ እንድያቀርቡ ማድረግ፤
❖ የዕለቱን የውይይት ጥያቄዎችን ማስረዳት፤
❖ የጥያቄዎችን መልስ በቃሌ ጉባዬ መዝገብ መመዝገብ፤
❖ ስምምነት የተደረሰባቸው ነጥቦችን መመዝገብ፤
❖ በውይይቱ ወቅት የሚከናወኑ ተግባራት ለተሳታፍዎች ማስረዳት፤
❖ ተሳታፍዎችን በንቃት እንድሳታተፉ ማበረታት፤
❖ ሁሉም ተሳታፍዎች ማሳተፍ፤
❖ በውይይቱ ላይ የተገኙትን አባላት መመዝገብ፤
❖ ዋና ዋና የውይይቱን ነጥቦች መድገም፤
❖ የውይይቱን ዓላማ ለተሳፍዎች በደንብ ማስረዳት፤
❖ የዕለቱ ውይይት ካለቀ በኋላ ሁሉም አባላት በቃሌ ጉባዬ መዝገብ ላይ መፈረም አለባቸው፤
❖ አንድን የውይይት ክፍለ ጊዜ ከመጀመሩ በፍት የባለፈውን የውይይት ነጥቦችን መድገም ፤
❖ ተሳታፍዎች ከባለፈው ውይይት የሚያስታውሱትን ዋና ዋና ነጥቦች እንድገለጹ ማድረግ።
የመወያያ ሐሳቦች
❖ የስብሰባው ቀን መቼ ይሁን፤ በስንት ሰዓት ይጀመራል?
❖ የት ቦታ ይካሄዳል?
❖ በውይይት ጊዜ ልንከተላቸው የሚገቡ ደንቦች ምንድናቸው?
❖ በሚያረፍዱና በሚቀሩ አባላት ምን ይደረጋሉ?
የአመቻች ማስታወሻ
19 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
ቀን
ማሳሰቢያ፡ እነዚህ አጠቃላይ የማህበረሰብ ውይይት መማሪያና ለሎች የአመቻች ማስታወሻችን
የማህበረሰብ ውይይት አመቻች በሁሉም የውይይት ርዕስ መጠቀም አለበት። በመሆኑም አመቻቹ
ሁልጊዜ ማንበብና ማስታወስ ይጠበቅበታል።
20 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የማህበረሰብ ውይይት ወርሀዊ ሪፖርት ማድረግያ ቅጽ ( ቅጽ ሶስት)
1. መግቢያ
የውይይት ርዕስ
የውይይት ዝርዝር ዓላማዎች
የውይይት ተሳታፍዎች ወ ሴ
ቀን የስብስባ ቦታ
2. የውይይት ሂደት
የማህበረሰብ ውይይት አባላት ተሳትፎ ምን ይመስል ነበረ?
ሁሉም አባላት እንድሳተፉ ምን ዓይነት ዜደ ጥቅም ላይ ዋለ
3. ዋና ዋና ነጥቦችና የድርጊቶች
በውይይቱ ውቅት የተነሱ ዋና ዋና ሐሳቦች
በውይይት ርዕሱ ላይ የተወሰዱ ድርጊቶች
4. አስተያየትና ተሞክሮዎች
የውይይቱ ሰዓትና ቦታ ለሁሉም ሰው ምቹ ነበረ?
በውይይቱ ወቅት የተኛው አካሄድ ይሰራል?
በውይይቱ ወቅት የተኛው አካሄድ አይሰራም?
ምን መሻሻል አለበት?
የአመቻች ፊሪማ
የቀበሌ ልቀመንበር ፊሪማ
የቀበሌ ማህተም
21 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
1. መልካም አስተዳደር
2. ማስፈጸሚያ ስልት
3. ሀብት
4. አሳታፍነት
5. የግጭት አፈታት
6. የውይይት ተሳታፍዎች ፍላጎት
7. የአመቻች ቁርጠኝነት
8. የተቋማት ቁርጠኝነት
9. የአካባቢው ወግ፤እሴት፤ ባህል፤መሠረተ ልማት
የማህበረሰብ ውይይት ውጤታማነትን የሚወስኑ ምክንያቶች
22 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
በዚህ ክፍል ውስጥ ስድስት የማህበረሰብ ክፍሎች ያሉ ስሆን፤ እያንዳንዱ ክፍል ንዑስ ክፍል ይኖረዋል፡፡
ለስድስት ወራት የሚካሄድ ስሆን በወር ጊዜ ሁለት ስዓት ይካሄል፡፡በአጠቃላይ 12 ሳምንትን ይፈጃል፡፡ ከ12
ሰምንት በኋላ የማህበረሰብ ውይይት አባላት ይመረቃሉ፡፡
ክፍል ሁለት
የማህበረሰብ ውይይት ክፍሎች
23 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የማህበረሰብ ውይይት የመማሪያ ደረጃዎች
የክፍል ደረጃ የመማሪያ ርዕስ ዋና ዓላማ ዘዴዎች
ክፍል አንድ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ አሁናዊ
እውቀት፤አመለካከት እና ልምድን መረዳት
አሁናዊ ሁኔታን መረዳትና መተንተን ሁሉም አቀፍ ውይይት፤የነበረውን
ልምድ ማካፈል፤በድራማና ጭውውት
ሁኔውን ማስረዳት
ክፍል ሁለት የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጥቃትን
በተመለከተ የእውቀትና የግንዛቤ ክፍተትን መሙላት
እውቀትና ግንዛቤን ማሳደግ ንቁ ውይይት፤እውቀትን ለማካፈል
መለማመድ
ክፍል ሶስት የማህበሰብ ደረጃ ሀብትን በማቀናጀት ሴት ግርዛት
እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መከላከል
አካባቢ በቀል እውቀትና ልምድን በመጠቀም
ችግሮችን መፍታት
የቡድን ውይይትና የውይይቱን ሀሳብ
ማቅረብ፤የግል ምልከታን ማንጸባረቅ
ክፍል አራት የጋራ እቅድ የተገኘውን ልምድ በመቀመር ችግር ፈች
አካባቢ በቀል እቅድ ማዘጋጀት
ከሁሉም የተውጣጣው የእቅድ
የሚያቅድ ጥምር ኃይል ማቋቋ
ክፍል አምስት የእቅድ ትግበራ ምዕራፍ ለውጥን ማመቻቸት ወይም አፈጻጸምን
መታተል
የተደራጀ ክትትል፤ለውጥን መመዝገብ
ክፍል ስድስት የአፈጻጸም ገምገማና አጠቃላይ ሂደትን መሰነድ የተገኘውን ልምድ እና ምርጥ ተሞክሮችን
መያዝ ወይም አዳድስ የመማሪያ ሀሳቦችን
መለየት፤ እንደገና ማቀድ ወይም ማሻሻል
አስተያየት መሰብሰብ፤ግብረ መልስ
መቀበል፤ለውጥ አመላካች ታርኮችን
መመዝገብ
የማህበረሰብ ውይይት አባላት እቅድ ቅጽ ( ቅጽ አራት)
እንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አባል ውይይት የሚደረግበትን እያንዳዱ ርዕስ የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም ማስተማር አለበት። ያስተማረውን
ሪፖርት ማቅረብ መቻል አለበት። ውይይት ከመጀመሩ በፍት ሪፖርት መቅረብ አለበት። ርፖርቱ ስቀርብ አመቻቹ የተከናወኑ ተግባራትን መመዝገብ
አለበት። የቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት በማካሄድ ተሳታፍዎች ልምዳቸውን በማካፈል እርስበርሳቸው የሚመሩበት መድረግ መፍጠር አስፈላጊ ነው።
የአባሉ ስም ቀን ቀበሌ
ተቁ ተግባራት ቁልፍ መልእክት ያገኘው የሰው ብዛት በግምት ቁልፍ መልእክት የተላለፈበት ቦታ ቁልፍ መልእክቱን ለማስተላልፍ ጥቅም
ላይ የዋለው ዜደ
ወንድ ሴት
1 የልጅነት ጋብቻ 42 50 እድር ስብስባ በገዳቡላት መንደር በቃል
2
24 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
ዝርዝር ዓላማዎች
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መሠረት መለየት እና መረዳት፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች ማወቅ፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻንመሠረት ላደረጉ ጥቃቶች የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን
መለየት፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ለመከላከል ያሉ እድሎች፤
ማነቆችንና ስጋቶችን መረዳት፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ ምን እንደተሠራ ማወቅ፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል ምን መደረግ
እንዳለበት መገንዘብ፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መሠረት ያደረጉ የጥቃት ዓይነቶችን መዘርዘር፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን የአካባቢዊ አሁናዊ ሁኔታን መረዳት።
የውይይት መግቢያ ፍሬ ሀሳቦች
❖ የውይይቱን ዓላማ በደንብ መግለጽ፤
❖ ተሳታፍዎች በንቃት እንድሳተፉ ማድረግ፤
❖ ተሳታፍዎችን 4 እስክ 5 መክፈል፤
❖ ለአባላት የተማሩትን ሌሎች ማስተማር እንዳለባቸው ማብራራት፤
❖ የቡድኑ አባላት የተወያዩበትን ሐሳቦች እንድያቀርቡ ማድረግ፤
❖ የተወያዩበት ርዕስ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ስምምነት መድረስና ማጠቃልያ መስጠት፤
❖ ዋና ዋና ነጥቦችን በቃለ ጉባኤ መዝገብ መመዝገብ።
የውይይት ይዘት
1. እስከ አሁን ድረስ በእናንተ አካባቢ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ምን ተሰራ? በማን?
2. ሥርዓ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል ምን ዓይነት እድሎች አሉ?
3. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻለመከላከል ምን ዓይነት ማነቆዎች አሉ?
ክፍል አንድ፡ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን አሁናዊ እውቀት፤አመለካከት እና ልምድን
መረዳት
25 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
1.1 ባህል የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ( Culture, child
marriage and female genital mutilation)
4. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻለመከላከል ምን ዓይነት ክፍተቶች አሉ?
5. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ ምን ዓይነት ጉዳቶች ያስከትላሉ?
6. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ ለምን ይደረጋል?
በአካባቢያው የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ የተሰራ ዳሰሳ ቅጽ ( ቅጽ አምስት)
ተ/ቁ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ
ጋብቻ ለመከላከል ያለው ዕድል
ማነቆ እስከአሁን የተሰራው ሥራ ካለ የማነቆው መፍትሔ
1
2
3
ክልል ወረዳ ቀበሌ
የቦታው ስም
የአመቻቾች ስም ቀን ፊርማ
የውይይት መግቢያ ፍሬ ሀሳቦች
❖ በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ
ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤
❖ የባለፈው ሳምንት ዋና ዋና ነጥቦችን መጠየቅ፤
❖ ተሳታፍዎች በንቃት እንድሳተፉ ማድረግ፤
❖ ተሳታፍዎችን 4 እስክ 5 መክፈል፤ የአካባቢያቸው የሴቶችና ልጃገረዶችን ጉዳት የሚያደርሱ
ድርጊቶች እንድለዩ ማድረግ፤
❖ ባህል የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለማስቆም ወይም ለማስቀጠል ያለው አስተዋጽኦ
እንድገልጹ ማድረግ፤
❖ የቡድኑ አባላት የተወያዩበትን ነጥቦች እንድያቀርቡ ማድረግ፤
❖ የተወያዩበት ርዕስ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ስምምነት መድረስና ማጠቃልያ መስጠት፤
❖ ዋና ዋና ነጥቦችን በቃሌ ጉባኤ መመዝገብ።
26 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የውይይት ይዘት
1. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንድቀጥል የሚያደርጉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የትኞቹ ናቸው?
2. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል ምን መደረግ አለበት?
3. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል የወንዶች ሚና ምን መሆን አለበት?
በአካባቢው ያለው ባህላዊ ልማዶች መሰብሰቢያ ቅጽ ( ቅጽ ስድስት)
በአካባቢው ያለው የባህል ዓይነት መካከል ለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ አስተዋጽኦ
የሚያደርጉትን መለየት አስፈላጊ ነው፡፡
ተ/ቁ የባህል ዓይነት ሴቶችና ልጃገረዶች ላይ
የሚያደርሰው ጉዳት
መቀጠል ያለበት መለወጥ ያለበት መቆም ያለበት
1
2
የአመቻች ማስታወሻ
❖ ጾታ፡- ማለት በተፈጥሮ ወንድ ወይም ሴት ሆኖ መፈጠር ነው፡፡
❖ ሥርዓተ ጾታ፡ ማለት በህብረተሰቡ ተቀባይነት ያገኘ ሴቶች እንደ ሴትነታቸው ወንዶችም
እንደ ወንድነታቸው በተለያዩ ሁኔታዎች እና ጊዜያት ማሳየት የሚገባቸው በቃላትና
በድርጊት ባህሪያት የሚገልፅ ነው፡፡
❖ ባህል፡ ኢንሳይክሎፒዲያ ባህል አጠቃላይ የሰው ልጅ አኗኗርን የሚወስን መስተጋብር
ነው። ባህል የማህበረሰብን አባላት ስብዕናን በመቅረጽና በመፍጠር ባህሪያቸውን በእጅጉ
ይቆጣጠራራል። እያንዳንዱ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ የባህላዊ ልማዶች አሉት።እሱ ቋንቋን
ሂደቶችን ፣ የኑሮ መንገዶችን ፣ ወጎችን ፣ ልምዶችን ፣ እሴቶችን ፣ መሣሪያዎችን እና
እውቀቶችን ያጠቃልላል ፡፡
❖ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ፡ የሰውን አካላዊና ስነልቦናዊ ደህንነትን እንዲሁም የሰብአዊ
መብቶችን እና የስነተዋልዶ ጤናን የሚፈታተኑ ልማታዊ ዕድገትንም የሚጐዱ ናቸው።
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ በሴቶች እና ልጀገረዶች ላይ ከፍተኛ ማህበራዊ፤
ኢኮኖሚያዊ፤የስነ ልቦና፤ አካላዊ እና የጤና ችግሮችን የሚያስከትሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች
ናቸው።
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ዋነኛ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት
መሆኑን ተሳታፍዎች መረዳት አለባቸው።
27 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
ዝርዝር ዓላማዎች
❖ ተሳታፍዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንድረዱ ማድረግ፤
❖ ተሳታፍዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ያላቸውን ሀሳብ እንድገልጹ ማድረግ፤
❖ ተሳታፍዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ የሚሰጡ ምክንያቶችን እንድያስረዱ
ማድረግ።
የውይይት መግቢያ ፍሬ ሀሳቦች
በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ
ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤
❖ የቡድን ውይይት ከማድረግ በፊት የውይይት ተሳታፍዎችን ከ 4 እስከ 5 ማከፋፈል፤
❖ የዕለቱን የውይይት ጥያቄዎች ማስረዳት፤
❖ የጥያቄዎችን መልስ በቃሌ ጉባዬ መዝገብ መመዝገብ፤
❖ ስምምነት የተደረሰባቸው ነጥቦችን መመዝገብ፤
❖ ተሳታፍዎችን በንቃት እንድሳታተፉ ማበረታት፤
❖ ሁሉም ተሳታፍዎችን ማሳተፍ፤
❖ በውይይቱ ላይ የተገኙትን አባላት መመዝገብ፤
❖ ዋና ዋና የውይይቱን ነጥቦች መድገም፤
❖ የውይይቱን ዓላማ ለተሳፍዎች በደንብ ማስረዳት፤
❖ ከባለፈው ውይይት ዋና ዋና ነጥቦች ተሳታፍዎች እንድገልጹ ማድረግ፤
❖ የዕለቱ ውይይት ካለቀ በኋላ ሁሉም አባላት በቃለ ጉባዬ መዝገብ ላይ መፈረም
አለባቸው።
የሴት ግርዛት የውይይት ይዘት
1. የሴት ግርዛት የሚያስከትለው ችግር ምንድ ነው?
2. ማህበረሰቡ የሴት ግርዛት ለምን ያደርጋል?
3. የሴት ግርዛት ለመፈጸም ማህበረሰቡ ምን ምክንያት ይሰጣል?
4. የሴት ግርዛትን ለማስቆም ከእኛ ምን ይጠበቃል?
1.2 የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ
28 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
ያለዕድሜ ጋብቻ የውይይት ይዘት
1. ያለ ዕድሜ ጋብቻ የሚያስከትለው ችግር ምንድ ነው?
2. ማህበረሰቡ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለምን ይፈጽማል?
3. ያለ ዕድሜ ጋብቻ ማህበረሰቡ ምን ምክንያት ይሰጣል?
4. ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለማስቆም ከእኛ ምን ይጠበቃል?
29 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
2.1 የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጉዳቶች
ዝርዝር ዓላማዎች
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ምክንያት የሚመጡ ጉዳቶች እንድገልጹ ማድረግ፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ የተደነገጉ የኢትዮጵያ ህጎችን እንድያውቁ ማድረግ፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ከሀይማኖት አንጻር እንድረዱ፤
❖ ማህበራዊ ስነ ምህዳርን እንድገነዘቡ ማድረግ፤
❖ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን የሚያበረታቱ ማህበረሰብ አቀፍ ልማዶች እንድረዱ
ማድረግ።
የውይይት መግቢያ
በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ
ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤
የሴት ግርዛት የውይይት ይዘት ዝናሽ ታርክ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
ዝናሽ የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ ትምህርቷን አቋርጣ ለጋብቻ ዝግጅት በእናቷ ግፍት ተገረዘች፡፡ እሷ
በተወለድችበት አካባቢ ልጃገረዶች ለጋብቻ ይገረዛሉ፡፡ ማህበረሰቡ የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት
ለጋብቻ ዝግጁ ስሆኑ ልጃገረዶች እንድገረዙ ያደረጋሉ፡፡ ከሚሰጡ ምክንያቶች መካከል ንጽና ለመጠበቅ፤
ለግብረ ስጋ ግኑኝነት ምቹ ለማድረግ፤ለባሏ ታማኝ እንድትሆን እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ዝናሽ ምጥ ላይ
ረጅም ሰዓት ስለቆየች የመጀመሪያ ልጆዋን የወለደችው በቀዶ ጥገና ነው፡፡ ከወልድ በኃላ በደም ማነስ
ታማለች፡፡ ህጻኑም ጡት አልጠባም በማለቱ ህይወቱ አልፋል፡፡ዝናሽ ሁለተኛ ልጆዋን አሁንም በቀዶ ጥገና
ወለደች፡፡
1. በዝናሽ ላይ ምን ጉዳት ደረሰ?
2. በዝናሽ ላይ የደረሰውን ዓይነት ጉዳት እንዴት መከላከል ይቻላል?
3. በአካባቢያችሁ የሴት ግርዛት የሚካሄድበት ዕድሜ ስንት ነው?
4. አልማዝ የተገረዘችው ለምንድን ነው?
5. አልማዝ የተወለደችበት ማህበረሰብ ሴት ግርዛት የሚካሄድበት ምክንያት ምንድነው?
ክፍል ሁለት፡ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ን በተመለከተ የእውቀትና የግንዛቤ ክፍተትን
መሙላት
30 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
6. የሴት ግርዛት ልማድን ለማቆም የወንዶች ድርሻ ምን መሆን አለበት?
7. በአካባቢያችሁ በግርዛት ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ሰው አለ?
8. በዝናሽ ልጅ ላይ ምን ጉዳት ደረሰ?
ያለ ዕድሜ ጋብቻ የውይይት ይዘት በአልማዝ ታርክ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
አልማዝ የተወለደችው ገጠር ውስጥ ነው፡፡ አንደኛ ክፍል እየተማረች እያለች ወላጆች ለአንድ ባለሀብት
በአስራ ስድስት ዓመቷ ዳሯት፡፡ ትምህርቷን በጋብቻ ምክንያት አቋርጣለች፡፡ በተወለድችበት አካባቢ በእሷ
ዕድሜ ማግባት የተለመደ ነው፡፡ ምክንያቱም ሳያገቡ የሚቆዩ ሴቶች ማህበረሰቡ ፈሳሽ ያለቀባት፤ቤተሰብ
አሰዳቢ፤ ፈላጊ ያጣች ስለሚባሉ ልጃገረዶች ይህን በመፍራት ቶሎ ያገባሉ፡፡ አልማዝ የመጀመሪያ ልጇን
ቤት ስትወልድ ታፍኖ ሞቶባቷል፡፡ እሷም ከፍተኛ ደም ስለፈሰሰባት ደም ተሰቷት ከሞት ለትንሽ ተረፈች፡
፡ አራት ልጆቾን በአካባቢው በሚገኘው ጤና የወለደች ቢሆንም ክትባት አልተከተቡም በዚህ ምክንያት
ሁልጊዜ ይታመማሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ለምግብ እጥረት ተዳርገዋል፡፡ ባሏ ሁልጊዜ ይደበደባታል፤
ይሰድባታል፤ቀለብ አይሰጣትም፡፡ ከዚህ የተነሳ ተፋታለች፡፡
1. ለአልማዝ ጋብቻ ምክንያት የሆነው ምንድን ናቸው?
2. አልማዝ ስንት ዓመት አገባች ?
3. የአልማዝ ልጆች ምን ጉዳት ደረሰባቸው?
4. አልማዝ በጋብቻው ተሰማምታለች?
5. ያለ ዕድሜ ጋብቻ የሚፈጸመው በስንት ዓመት ነው?
6. አልማዝ የተወለድችበት አካባቢ ሰዎች ለማያገቡ ሴቶች ምን ይላሉዝ?
7. አልማዝ ዓይነት ታርክ ለማቆም የወንዶች ድርሻ ምን መሆን አለበት?
8. በአካባቢያችሁ የአልማዝ ዓይነት ታርክ ያለው ሰው አለ?
ገራዧ ተብላ የምትታወቀው ይህች ሴት ሞምባሳ ኬንያ ውስጥ ሴቶችን ለመግረዝ የምትጠቀምበትን ምላጭ ይዛ ነው።
የሴት ግርዛት ሆን ተብሎ የሴት ልጅን የመራቢያ ክፍል አካል መቁረጥ ማለት ነው።
31 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የዓለም ጤና ድርጅት ብዙ ጊዜ የሴት ልጅ ግርዛት ሲፈጸም የብልት ከንፈሮችን እና ቂንጥርን መቁረጥን ያካትታል ይላል።
የግርዛት አይነቶች
አራት አይነት የግርዛት አይነቶች አሉ።
1. ክሊቶሪዲክቶሚይ (Clitoridectomy)፡ ይህ ማለት በቂንጥር እና በአከባቢው የሚገኝ ስስ ቆዳ ሙሉ በሙሉ
ወይም በከፊል ማስወገድ ማለት ነው።
2. ኤክሲሺን (Excision)፡ ይህ ማለት ቂንጥርን እና የብልትን የውስጠኛውን ከንፈር ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል
ማስወገድ ማለት ነው።
3. ኢንፊቢዩሊሽን (Infibulation)፡ ይህ ማለት ቂንጥርን እና የብልት ክንፈሮችን ቆርጦ በመጣል ብልትን በመስፋት
የግብረ ስጋ ግንኙነት ምቹ እንዳይሆን ማድረግ ማለት ነው። ይህ ተግባር የሚያስከትለው ህመም ከፍተኛ
ከመሆኑም በላይ ለኢንፌክሽን ተጋላጭነትን ከፍ ያደርጋል። በተጨማሪም ሽንት እና የወር አበባ ፍሳሽ በቀላሉ
እንዳይወጣ ያደርጋል።
4. ሌላኛው የግርዛት አይነት የሴት ልጅ የመራቢያ አካላትን መውጋት፣ መብሳት፣ መቧጠጥ እና ማቃጠል
የመሳሰሉትን ያካትታል።
ምንጭ፡ የዓለም የጤና ድርጅት( 2021)። የሴት ልጅ ግርዛት
የአመቻች ማስታወሻ
32 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የሴት
ግርዛት
በሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ምክንያት የሚመጡ ጉዳቶችን ለማስረዳት የችግር ዛፍ መጠቀም በጣም
አስፈላጊ ነው።የችግር ዛፍ ሶስት ክፍሎች አሉት። እነሱም ስር፤ግንድ እና ቅርጫፍ ናቸው።
1. ስር፡ የሚወክለው መሰረታዊ የሴት ግርዛት ወይም ያለ ዕድሜ ጋብቻ ምክንያቶች፤
2. ግንድ፡ የሴት ግርዛት ወይም ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልማድን ይወክላል፤
3. ቅርጫፍ፡ የሴት ግርዛት ወይም ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጉዳቶችና መዘዞች።
ቅርንጫፍ
1/ የጤና ችግር
2/ ስነ ልቦናዊ ጉዳቶች
3/ ማህበራዊ ጉዳት
4. ሰብዓዊ መብት
ግንድ ስር
❖ አሉታዊ ወግ
❖ የሀይማኖት ትዕዛዝ
❖ ውበት ለመጨመር
❖ ንጽህና ለመጠበቅ፤
33 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
በልጅነት)
34 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የአመቻች ማስታወሻ
የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንዲቀር የኃይማኖት አባቶች ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ አመቻች በደንብ
ማስረዳት አለበት። በውይይቱ ላይ በቀበሌው ከሚገኙት ቤቴ እምነቶች ቁልፍ ሰዎችን በመጋበዝ የቤቴ
እምነታቸውን አስተምሮ እንድገልጹ ማድረግ አስፈላጊ ነው። የኃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸውን የሚጎዱ
ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል ጉልህ ሚና መጫወት አለባቸው። ስለዚህ እነሱን የማህበረሰብ ውይይት
ላይ ማስተፍ ወሳኝ ነው። በተጨማሪ የጤና ባለሙያዎችና የጤና ኤክስቴሽን ሠረተኞችን በመጋበዝ በጤና
ጉዳቶችን እንዲያስረዱ መጋበዝ ይችላል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ የአገርቱ ህጎች የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንደምከለክሉ ለማስረዳት የህግ
ባለሙያን በመጋበዝ ውይይቱ ላይ ተጨማሪ ገለጻ እንድያደርግ ማድረግ ተገቢ ነው።
የውይይት መግቢያ
በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ
ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤
የውይይት ይዘት
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ በቤተ እምነቶች እንዴት ይታያል?
❖ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በተለይም የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል
የኃይማኖት አባቶች ኃላፍነት ምን መሆን አለበት ?
❖ ብሔራዊ ህጎች ሰለ ያለ ዕድሜ ጋብቻንና ግርዛት ምን ይላሉ?
❖ በቤተ እምነቶች እስከአሁን ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በተለይም የሴት ግርዛት እና
ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል ያላቸው ልምድ ምንድን ነው?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ህጎች ( National laws)
የኢትዮጵያ ሕጎች በሕጉ የተመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮች
የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 7 ፡ ወንዱም ሆነ ሴቷ 18 ዓመት ሳይሞላቸው ማግባት አይችሉም።
2.2 ኃይ ማ ኖ ት እና ህግ ( Religion and Law)
35 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
2.3 አሉታዊ ወጎች (Negative social norms)
የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 565፡ ማንም ሰው በየትኛውም ዕድሜ ክልል የምትገኘውን ሴት
መግረዝን ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል፤
አንቀጽ 648፡ ለአካለ መጠን ያልደረች ልጅ ማግባት ወንጀል መሆኑን
ይደነግጋል፤
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 14፡ ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገረሰስ
በሕይወት የመኖር፤የአካል
፟ ደህንነት መብት አለው።
አንቀጽ 16፡ ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ
መብት አለው።
ዝርዝር ዓላማዎች
❖ ተሳታፍዎች ስለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜጋብቻ በሚመለከት አሉታዊ ወጎችን ለማረም
የድርሻቸውን እንድወጡ ማድረግ፤
❖ ስለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ያሉ አሉታዊ ወጎች እንድለዮና እንድታረሙ
ማድረግ፤
❖ ስለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ የተሳሳቱ አሉታዊ ወጎች ለመቀየር ትምህርት ቤቶች፤
የሀይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግሎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን መረዳት፤
የውይይት መግቢያ
በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ
ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤
ውይይት ይዘት
1. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለማስቆም አስቸጋር የሚያደርጉ ምክያቶች በእናተ አካባቢ ምን
ምን ናቸው?
2. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ የሚያበረታቱ አሉታዊ ወጎችን ለማረም ምን መድረግ አለበት?
3. አሉታዊ ወጎችን ለማረም የእናንተ ድርሻ ምን መሆን አለበት?
36 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
4. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ አሉታዊ ወጎችን ለማስቀረት ግለሰብ፤ ማህበረሰብ፤ ትምህርት
ቤቶች፤ የሀይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግሎች ድርሻ ምን መሆን አለበት?
የአመቻች ማስታወሻ
የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ አሉታዊ ወጎች እንደየ አካባቢው ይለያያል። በመሆኑም
የውይይቱ ተሳታፍዎች በአካባቢያቸው ያለውን ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ተመሰርተው እንድወያዩ
ማድረግ ያስፈልጋል።
ያለ ዕድሜ ጋብቻን በተመለከተ የአካባቢያቸውን አሉታዊ ወጎችና ምክንያቶች ከሚከተሉት ሊመረጡ
ይችላሉ፤
❖ ድህነት፤
❖ ባህል እና ልማድ፤
❖ ደካማ የሕጎች አተገባበር፤
❖ የግንዛቤ እጥረት፤
❖ የልጃቸው የወደፊት ሁኔታ አለመተማመን፤
❖ የትምህርት እጥረት፤
❖ በሴት ልጆች ላይ የደህንነት ስጋት እና የግብረ-ሥጋ ግንኙነትን መቆጣጠር፤
❖ የልጅነት ጋብቻን የሚቃወሙ ሕጎች ግንዛቤ ማነስ፤
❖ የጥሎሽ ስርዓት፤
❖ የህብረተሰቡ ጫና፤
❖ ልጃገረዶችን እንደ የቤት ውስጥ ረዳት አድርገው መቁጠር፤
❖ በጦርነት እና በግጭት ጊዜ አለመረጋጋት፤
❖ ለሴት ልጆች የትምህርት እጦት እና የስራ እድሎች።
ስለሴት ግርዛት የአካባቢያቸውን አሉታዊ ወጎችና ምክንያቶች ከሚከተሉት ልመርጡ ይችላሉ፤
❖ እቃ ሰብራለች፤
❖ ያልተገረዘች ሴት ትሰደባለች፤
❖ ያልተገረዘች ሴት ክብር የላትም፤
❖ አትረጋጋም ሁል ጊዜ ወስብ ትፈልጋለች፤
❖ ወንድን ታሸንፋለች በወስብ ወቅት፤
37 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
2.4 ማህበራዊ ስነ ምህዳር ሞደል (Socio-ecological model)
ዝርዝር ዓላማዎች
❖ በግለሰብ፤በቤተሰብ፤በማህበረሰብ እና ተቋም ያለው አመለካከት፤እውቀት፤ልማድ ጾታን መሰረት
ያደረገ ጥቃት ለመከላከል ወይም ምክንያት የመሆን ሚና መገንዘብ፤
❖ በእያዳንዱ ደረጃ ያለውን የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንደቀጥል የሚያደርጉ ምክያቶች
እንድለዩ ማድረግ፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የሚረዱ ምቹ ሁኔታዎችን እንድለዩ ማድረግ፤
ተሳታፍዎች የራሳቸውን ሚና በግለሰብ፤በቤተሰብ፤በማህበረሰብ እና ተቋም ደረጃ እንድገልጹ
ማድረግ፤
❖ የወንድ ብልት ይመስላል፤
❖ ልጅ ሲወለድ ቂንጥር አፍንጫ ስነካ ይሞታል፤
❖ ንጽና ለመጠበቅ
❖ ውበት ለመጨመር
❖ በውስብ ወቅት ለባል ምቹ ለማድረግ
❖ የሀይማኖት ትዕዛዝ
❖ የጋብቻ ቅድመ ሁኔታ፤
❖ ወንዶች ያልተገረዘችን ሴት አያገቡም፤
❖ ያልተገረዘች ሴት በወልድ ወቅት ትቸገራለች፤
❖ ያልተገረዘች ሴት በቀላሉ በሽታ ትያዛለች፤
❖ ከዘር ዘር ሲተላለፍ የመጣን ባህልና ወግ ለማክበር፤
❖ የማንነት መገለጫ ነው፤
❖ እናቶቻችን ተገርዘው ምን ሆኑ?
❖ የማህብረሰብ አስተሳሳብ
❖ ኃይማኖት፣
❖ ከንጽህና ጋር የተያያዘ የተሳሳተ ዕምነት፣
❖ ድንግልናን ለማቆየት በማሰብ፣
❖ ሴት ልጅ ትዳር እንድታገኝ በማሰብ
❖ የወንድ ልጅ የወሲብ እርካታን ለመጨመር።
38 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የአመቻች ማስታወሻ
1. ግለሰብ ፡ እውቀት፥ አመለካከት፥ አስተሳሰብ እና ልማድ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ላይ
ከፍተኛ ሚና አላቸው።
2. ቤተሰብ፡ አመለካከት፥ አስተሳሰብ እና ልምድ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ይወስናሉ።
3. ማህበረሰብ፡ አሉታዊ ወጎች፤ ልማዳዊ ድርጊቶች ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት የመከላከል
ወይም የማስቀጠል አቅም አላቸው።
4. ተቋማማት፡ ባህላዊ አደረጃጀቶች፤ ጤና ተቋማት፤ትምህርት ቤቶችና ሀይማኖት ተቋማት የመሳሰሉት
ሥርዓተ ጾታ መሠረት ያደረገ ጥቃት እንድቀጥሉ ወይም እንድቀሩ የማድረግ ተጽኖአቸው ከፍተኛ
ነው።
5. አገር፡ ህጎች፥ ፖሊሲዎች፥ የመንግስት አሰራሮች አለመኖር ወይም በትክክል አለመተግበር።
አገር
ተቋም
ማህበረሰብ
ቤተሰብ
ግለሰብ
ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት (የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ) ማህበራዊ ስነ ምህዳር
39 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የአመቻች ማስታወሻ
በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ሰባት የሀብት ዓይነቶች አሉ። እነዚህ የሀብት ዓይነቶች አንድ ማህበረሰብ የራሱን የተለያዩ
ችግሮች ለመፍታት ይረዳሉ። የማህበረሰብ ሀብቶች የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከልና ዘላቂ
መፍትሔ ለማምጣት ይረዳሉ።
1. የሰው ሀብት፡ የእያንዳንዱ ሰው እውቀት፤አመለካከት፤ ልምድ እና ችሎታን ያጠቃልላል።
2. ማህበራዊ ሀብት፡ ማህበራዊ ትስስር፤ አዋታዊና አሉታዊ ወግ፤ ልማድ፤ እድር፤የሀይማኖት ተቋማት፤
ትምህርት ቤቶች፤ የጤና ተቋማት፤ የቀበሌ አስተዳደር ቢሮዎች።
3. የፖሊቲካ ሀብት፡ በቀበሌ ውስጥ ያለው ሀብት ምን ላይ መዋል እንዳለበት ልወስን ይችላል።
4. የገንዘብ ሀብት፡ ቀበሌው ውስጥ ያለው በገንዘብ ልገመት የሚችል የሀብት መጠን።
ዝርዝር ዓላማዎች
❖ አከባቢ በቀል የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የሚረዱ እውቀቶችን መለየት፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል በማህበረሰብ ደረጃ የሚገኘውን ሀብት
እንዲለዩ ማድረግ፤
❖ በማህበረሰብ ደረጃ ያለውን ሀብት የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል እንደሚረዳ
እንድገነዘቡ ማድረግ፤
❖ በውይይት የተለዩ የማህበረሰብ ሀብቶችንና እውቀቶችን የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን
ለመከላከል ወደ ትግበራ መለውጥ፤
❖ በቡድን 4 እስከ 5 ሰው ሆነው እንድወያዩና የትኞቹ ሀብቶች የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ
ጋብቻን ለመከላከል እንደሚረዱ እንድያስረዱ ማድረግ፤
የውይይት መግቢያ
በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንዲቀርብ
ማድረግና አስተያየት እንዲሰጥበት ማድረግ፤
የውይይት ይዘት
1. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የሚረዳ ምን ሀብት አለ?
2. እናንተ አካባቢ ያለውን የሀብት ዓይነት ምንድን ናቸው?
3. የማህበረሰቡን ሀብት እንደት የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መከላከል ያችላል ?
ክፍል ሶስት፡ የማህበሰብ ደረጃ ሀብትን በማቀናጀት የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን
መከላከል ( Mobilizing local resources)
40 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
ክፍል አራት፡ የጋራ እቅድ ( Joint planning)
ዝርዝር ዓላማዎች
❖ የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋበቻን ለማስቀረት በማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙትን ሀብቶች
በመጠቀም ውሳኔ ማሳለፍ፤
❖ የአካባቢውን ሀብት መሰረት በማድረግ የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል እቅድ
ማዘጋጀት፤
❖ የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ የማህበረሰቡ ችግሮች መሆናቸውን መቀበል እና መፍትሄ
መፈለግ ላይ ትኩረት ማድረግ፡፡
4.1 ማህበራዊ ውሳኔ (Community decision)
ዝርዝር ዓላማዎች
❖ የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋበቻንለማስቀረት በማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙትን ሀብቶች
በመጠቀም ውሳኔ ማሳለፍ፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልምድ መሰረታዊ የሆኑ ምክያቶችን ለይቶ ውሳኔ
እንድተላለፍ ማድረግ፤
❖ የተወሰነው ውሳኔ እንደት ተግባራዊ እንደምሆን የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥ፤
❖ ውሳኔዎችን ለማስፈጸም የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፍዎች ሚና ምን መሆን እንዳለበት ስምምነት
ላይ መድረስ፤
❖ የወጣውን ውሳኔ ለማስፈጸም ስልት መቀየስ፤
❖ የጸደቀውን ውሳኔ መላውን የቀበሌ ህዝብ ስብስባ በመጥራት ማሳወቅ፤
የውይይት መግቢያ
በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ
ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤
5. ባህላዊ ሀብት፡ሽምግልና፤ ባህላዊ አስተዳደር፤ ባህላዊ እርቅ፤ ባህላዊ የግጭት አፈታት፤ ታላቅን ማክበር፤
ባህላዊ ማዕቀብ።
6. ቁሳዊ ሀብት፡ በሰው የተሰሩ ሀብቶችን ይመለከታል። ባህላዊ መሰብሰቢያ ቦታዎች፤የቤት ቅርሶች፤ ልብሶች፤
የስልክ መስመሮች፤መንገድ፤ የመንግስት መ/ቤቶች፤ የጤና ተቋማት፤መንገድ፤መብራት፤ ፋብርካ።
7. የተፈጥሮ ሀብት፡ ደን፤ውሀ፤አየር፤ እንስሳት፤የተለያዩ የእጽዋት።
41 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የውይይት ይዘት
1. ምን ዓይነት ማህበረሰብ አቀፍ ውሳኔዎችን እናስተላልፍ?
2. በማህበረሰብ ደረጃ ልተገበር የሚችል ውሳኔ የትኛው ነው?
3. የተወሰነውን ውሳኔ ለመተግበር የትኛው ሀብት እንጠቀም?
4. የተወሰነው ውሳኔ ለመተግበር ምን ዓይነት ስልት እንጠቀም?
5. ውሳኔውን ለማስፈጸም ከሀይማኖት አባቶችና ከባህል አባቶች ምን ይጠበቃል?
የአመቻች ማስታወሻ
የማህበሰብ ውይይት የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ የማህበረሰቡ ችግሮች መሆናቸውን መለየትና
በማህበረሰቡ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ቁርጠኝነትን ማበረታታት አለበት። ማህበራዊ ውሳኔዎች ይህንን ውጤት
ለማምጣት አስተዋጽኦ ያድርጋሉ።
በማህበሰብ ውይይት የሚተላለፉ ማህበራዊ ውሳኔዎች ማህበራዊ ማዕቀብ እና ለህግ አሳልፎ መስጠትን ሊያካትቱ
ይችላሉ። የውሳኔው አይነት እንደችግሩ መጠንና ስፋት ሊለያይ ይችላል።
የሚውሰኑት ውሳኔዎች ከታች የተዘረዘሩትን እና ሊሎችንም ሊሆኑ ይችላሉ፣
❖ ከቤቱ/ቷ እሳት አንጭርም፣
❖ ከእድርና ከሌሎች ማህበራዊ ጉዳች መገለል፣
❖ ለህግ አሳልፈን እንሰጣለን፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልምድ በቀበሌያችን አይደረግም በማለት የአቋም መግለጫ
ማውጣት፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልምድ ምክንያት ችግር የደረሰባቸውን ሴቶችን መርዳት፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልምድ ምክንያት ችግር የደረሰባቸውን ሴቶችና ልጃገርዶችን የት
የህግና የጤና አገልግሎት እንደሚያገኙ መርዳት ወዘተ።
❖ የገንዘብ ወይም ተጣጥኝ ቅጣት (ሀያ ፍየሎች፤ ሶስት ግመል፤ አምስት በጎች የመሳሰሉት።፤
❖ በባህል ሽማግሌዎች ድርጊቱን መወገዝ፤
ቁልፍ የማህበረሰብ ውይይት ውሳኔዎች ማስፈጸሚያ ባለድርሻ አካላት
❖ የኃይማኖት አባቶች፡ በሀይማኖት በዓላት ወቅት በተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ ለተከታያቸው የሴት ግርዛት
እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች ያስተላልፋሉ። የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸውን ከጎጂ ልማዳዊ
ድርጊቶች ይጠብቃሉ፡፡ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ተከታዮቻቸው ላይ መጠነ ሰፊ የጤና፤
የኢኮኖሚ፤የሥነ ልቦና እና ማህበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትሉ አውቀው የመንፈሳዊ አባትነታቸውን ሚና
እንድጫቱ ማስገንዘብ ወሳኝ ነው። በተለይ የሴት ግርዛት እና ዕድሜ ጋበቻ ተከታዮቻቸው ላይ መጠነ ሰፊ
የጤና፤ የኢኮኖሚ፤የሥነ ልቦና እና ማህበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትሉ አውቀው የመንፈሳዊ አባትነታቸውን
ሚና እንድጫቱ ማስገንዘብ ወሳኝ ነው።
42 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
3.2 የዕቅድ ዝግጅት (Planning phase)
❖ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች፡ በቀበሌው የስብስባ ቀን ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች
ያስተላልፋሉ፡፡
❖ ዕድር፡ በእድር ስብስባ ላይሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶችን ያስተላልፋሉ፡፡
❖ የሀገር ሽማግሌዎች፡ በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶችን
ያስተላልፋሉ፤
❖ የልማት ሰራዊት፡ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶችን ያስተላልፋሉ፤
❖ የግብርና ባለሙያዎች፡ በግብርና ስራዎች ወቅት ስለ ሴት ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻግርዛት እና
ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች ያስተላልፋሉ።
❖ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፡ በክትባት ቀን ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች
ያስተላልፋሉ፡፡
❖ ትምህርት ርዕሰ መምህራን፡ በሰንደቅ ዓላማ ሥነ ሥርዓት ወቅት ለተማሪዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ
ጋብቻ ቁልፍ ቁልፍ መልእክቶች ያስተላልፋሉ፡፡
❖ የጤና ባለሙያዎች፡ የጤና ትምህርት ርዕስ አንዱ ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች
ያስተላልፋሉ፡፡
❖ ፍርድ ቤቶች፡ ለፍትህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች
ያስተላልፋሉ፡፡
❖ ፖሊስ፡ ለህግ ታራምዎችና ለፖሊስ አገልግሎት ፈላጊዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ
መልእክቶች ያስተምራሉ።
የቁልፍ መልእክት ምሳሌ፡
❖ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ሴት ልጆችን ከትምህርት እና ራሳቸውን ከመቻል ያስቀራቸዋል!
❖ የሴት ግርዛት ሴቶችን በወሊድ ጊዜ የጤና እክል ይፈጥራል!
❖ ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የበኩሌን እወጣለሁ!
❖ ህብረተሰቡን በማስተማር ያለ ዕድሜ ጋብቻና ግርዛትን እንከላከል!
ዝርዝር ዓላማዎች
❖ እቅዱን የሚያዘጋጅ ጥምር ቡድን ከሁሉም የማህበረሰብ ውይይት አባላት ማዋቀር፤
❖ ጥምር ኃይሉ እቅዱን እንድያዘጋጅ ማድረግ፤
43 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የአመቻች ማስታወሻ
ተግባራት እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መታቀድ አለባቸው፡፡
ለምሳሌ፡
1. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን የጤና ጉዳቶችን በትምህርት ለተማሪዎች ማስተላለፍ::
2. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የወላጅ ሚና ላይ በገበያ ቀናት መልእክት
ማስተላለፍ::
3. በቤተ እምነቶች የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል ቁልፍ መልእክቶችን
ማስተላለፍ፡፡
የመሳሰሉት
❖ የታቀደውን እቅድ የማስፈጸሚያ ስልት
፟ እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አባላቶች በደንብ
ተወያይተው መለየ አለባቸው፡፡
❖ በአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት የሚሰራ እቅድ እንዲጋጅ ማድረግ፤
❖ ስለ እቅዱ ክትትልና መለካት መወያየት፤
❖ የወጣውን እቅድ ለቀበሌው ማሳወቅ፤
❖ ለእቅዱ ውጤታማነት የማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ ሀብቶች ሚና ላይ መወያየት፤
❖ የተዘጋጀውን እቅድ መላው የቀበሌ ሕዝብ እንዲሰበሰብ ማድረግና እንድጸደቅ ማድረግ፤
❖ የተዘጋጀውን እቅድ መላው የቀበሌ ሕዝብ እንድሰበሰብ ማድረግና እንድጸደቅ ማድረግ፤
የውይይት መግቢያ
በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ
ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤
የእቅድ ቅድመ ዝግጅት ትንተና
1. እቅዱን ለማስፈጸም የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፊዎች ጠንካራ
ጎኖች
2. እቅዱን ለማስፈጸም
ያሉ ምቹ አጋጣሚዎች
3. እቅዱን ለማስፈጸም በማህበረሰብ ውይይት ተሳታፊዎች መሻሻል
ያለባቸው ነጥቦች
4. እቅዱን ለማስፈጸም
ያሉ ስጋቶች
44 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
ለምሳሌ፡
1. የእድር ስብስባ ላይ ሰዎች እንድወያዩ ሀሳብ ማቅረብ፤
2. በጸሎት ቤቶች ለውይይት ማቅረብ፤
3. በሀይማኖታዊ በዓላት ወቅት መልእክቶቸን፤
4. በቀበሌው ስብስባ ላይ ለውይይት ማቅረብ፤
የመሳሰሉት
45 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የሴት ግርዛት እና ዕድሜ ጋበቻን ለማስቀረት የማህበረሰብ እቅድ ቅጽ( ቅጽ ሰባት)
ግብ፡ በ 2015/2016 ማህበረሰባችን ውስጥ ስለ የሴት ግርዛት እና ዕድሜ ጋበቻ ግንዛቤ 70% ማሳደግ።
የሴት ግርዛት እና ዕድሜ ጋበቻ ዝርዝር ተግባራት ፈጻሚ ባለድርሻ ቦታ ሀብት ልያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች
ለምሳሌ፡ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክት
ማስተላለፍ
የእድር ሊቀመንበር የእድር ቤት የእድር
ሊቀመንበር
ሰው መስማት ላይፈልግ
ይችላል
ማሳሰቢያ፡
1. ዝርዝር ተግባራት በአካባቢው ተጨባጭ የሚሰሩ መታቀድ አለባቸው፡፡
2. በምሳሌው መሰረት መታቀድ አለበት፡፡
ቀበሌ ቀን የአመቻች ስም ፊሪማ
የቀበሌው ማህተም
የተከናወኑ ተግባራት ወርሃዊ ሪፖርት ማድረግያ ቅጽ ( ቅጽ ስምንት)
ተ/ቁ የታቀደው ተግባር ክንውን/የተሰራው ያልተሰራው ቀጣይ ተግባራት
1
2
ቀን የአመቻቹ ስም የቀበሌው ማህተም
46 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
ክፍል አምስት ፡ የዕቅድ ትግበራ ምዕራፍ ( Implementation phase)
ዝርዝር ዓላማዎች
❖ የወጣውን እቅድ ለመተግበር ትምህርት ቤቶች፤ጤና ተቋማት፤ስብሰባ እና ሕዝብ የተሰበሰበት
ቦታዎች፤ የሀይማኖት ተቋማት፤ የገበያ ቀናትንና እድሮችን በመጠቀም የሴት ግርዛት እና ዕድሜ
ጋበቻን ጉዳቶችና መከላከያ ቁልፍ መልእክቶችን ማስተላለፍ፤
❖ የወጣውን እቅድ በመተግበር እንደ አስፈላጊነቱ በአካባቢው/ቀበሌው አስተዳደር ጋር በመሆን
መከለስ፤
❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለማሰቀረት የሚረዱ ቁልፍ መልእክቶች በአካባቢው ቋንቋ
ማስተላለፍ፤
❖ በእቅዱ ትግበራ ላይ መወያየትና የማህበረሰብ ውይይት አባላት የስራ ድርሻ እንድከፋፈሉ ማድረግ፤
❖ የእቅድ ማስፈጸሚያ ሰልትን ላይ በደንብ መወያየትና እንደ አካባቢው ተጨባጭ የሚሰራ ስልትን
መምረጥ፤
❖ ለባለድርሻ አካላት የሚሰሩትን ሥራ በፍላጎት እንዲመርጡ መስማማት፤
❖ የባለድርሻ አካላት ያላቸውን አስተያየት እንድሰጡ እድል መስጠት።
የውይይት መግቢያ
በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ
ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤
የትግበራ ውጤት መከታተያ ( Performance monitoring template) ቅጽ (ቅጽ ዘጠኝ)
የትግበራ ውጤት ጠቋሚ የመረጃ ምንጭ ፈጻሚ የመረጃ መሰብሰቢያ መንገድ መረጃ ሰብሳቢ
በያለ ዕድሜ ጋብቻ
የተላለፈ ቁልፍ መልእክት
ቁልፍ መልክት የሰሙ
ተማሪዎች በቁጥር
የሰልፍ ላይ ፎቶ ር/መምህር ቃለ መጠይቅ፤ወርሀዊ
ሪፖርት
የቀበሌው አመቻች
ማሳሰቢያ፡
1. ይህ የትግበራ ውጤት መከታተያ በምሳሌው መሰረት ይሞላል።
2. ስልት ማለት፡የወጣውን የጋራ እቅድ ማስፈጸሚያ መንገድ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ በጥምቀት ቀን ቁልፍ መልእክት
በሴት ግርዛት ላይ ለምዕሚናን ማስተላለፍ እና የመሳሰሉት፡፡
3. የማህበረሰብ ውይይት አባላት የአፈጻጸም መለኪያ ጠቋሚ በስምምነት መሰየም አለባቸው፡፡
47 | P a g e
የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ
የውይይት ይዘት
ክፍል ስድስት፡ አፈጻጸም መገምገም እና አጠቃላይ ሂደትን መሰነድ (Performance
review and documentation)
ዝርዝር ዓላማዎች
❖ አጠቃላይ የማህበረሰብ ውይይት ጠንካና መሻሻል ያለባቸውን ነጥቦች መለየት፤
❖ የቀበሌ ሕዝብ ጋር በመሆን በአለፉት ስድስት ወራት በማህበረሰብ ውይይት ወቅት የተገኙ
ውጤቶችና ለውጦችን መገምገም፤
❖ የማህበሰብ ውይይት አባላት በውይይቱ ምክንያት በአለፉት ስድስት ወራት ውስጥ
የመጡ ለውጦች መለካትና መገምገም፤
❖ በውይይት ውቅት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮችና ለውጦችን መለየትና መሰድ፤
❖ ያጋጠሙ ችግሮች መለየትና እንደት እንደተፈቱ ለቀጣይ ትምህርት መውሰድ፤
❖ በውይይቱ ውቅት የሚሰሩና የማይሰሩ አካሄዶችን መለየትና ለቀጣይ ትምህርት መውሰድ፤
❖ የማህበረሰብ ውይይት መረጃዎች ማጠናከር።
የውይይት መግቢያ
የታቀደው አጠቃላይ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ ማድረግና የመጡ ለውጦችን
መገምገም
❖ የማህበረሰብ ውይይቱ ላይ ምን መሻሻል አለበት?
❖ የማህበረሰብ ውይይትቱ ምን ጠንካራ ጎን አለው?
❖ በዚህ ውይይት ላይ በመሳተፋችሁ ምን ተሰማችሁ?
❖ ማህበረሰብ ውስጥ በውይይቱ ምክንያት ምን ለውጥ መጣ?
❖ በማህበረሰብ ውይይቱ ላይ ምን ማነቆች ነበሩ?
❖ በማህበረሰብ ውይይት ወቅት ምን ምቹ አጋጣሚዎች ነበሩ?
የማህበረሰብ ውይይት አመቻች መምሪያ.pdf
የማህበረሰብ ውይይት አመቻች መምሪያ.pdf
የማህበረሰብ ውይይት አመቻች መምሪያ.pdf
የማህበረሰብ ውይይት አመቻች መምሪያ.pdf
የማህበረሰብ ውይይት አመቻች መምሪያ.pdf

More Related Content

Featured

2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by HubspotMarius Sescu
 
Everything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTEverything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTExpeed Software
 
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsProduct Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsPixeldarts
 
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthThinkNow
 
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfAI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfmarketingartwork
 
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024Neil Kimberley
 
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)contently
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024Albert Qian
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsKurio // The Social Media Age(ncy)
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Search Engine Journal
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summarySpeakerHub
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Tessa Mero
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentLily Ray
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best PracticesVit Horky
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementMindGenius
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...RachelPearson36
 

Featured (20)

2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot
 
Everything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTEverything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPT
 
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsProduct Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
 
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
 
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfAI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
 
Skeleton Culture Code
Skeleton Culture CodeSkeleton Culture Code
Skeleton Culture Code
 
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
 
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
 
How to have difficult conversations
How to have difficult conversations How to have difficult conversations
How to have difficult conversations
 
Introduction to Data Science
Introduction to Data ScienceIntroduction to Data Science
Introduction to Data Science
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best Practices
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project management
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
 

የማህበረሰብ ውይይት አመቻች መምሪያ.pdf

  • 1. 1 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የተዘጋጀ መማሪያ የማህበረሰብ ውይይት አመቻች መማሪያ አዘጋጅ፡ ቱሩፋት ቱኩራ ገመቹ የኖርወይ እርዳታ ሰጪ ቤተ ክርስቲያን ድርጅት የሥርዓተ ጾታ እና ልማት ፕሮግራም አማካሪ ጥር‚ 2022 አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
  • 2. 2 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ አርዕስት ገጽ መግቢያ..............................................................................................................................................3 ክፍል አንድ...........................................................................................................................................5 የማህበረሰብ ውይይት መሰረታዊ ፍሬ ሀሳቦች.................................................................................................5 ክፍል ሁለት.....................................................................................................................................22 ክፍል አንድ፡ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን አሁናዊ እውቀት፤አመለካከት እና ልምድን መረዳት ...............24 ክፍል ሁለት፡ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ን በተመለከተ የእውቀትና የግንዛቤ ክፍተትን መሙላት ..................29 ክፍል ሶስት፡ የማህበሰብ ደረጃ ሀብትን በማቀናጀት የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መከላከል ( Mobilizing local resources).........................................................................................................................................................39 ክፍል አራት፡ የጋራ እቅድ ( Joint planning) ..........................................................................................................40 4.1 ማህበራዊ ውሳኔ (Community decision).........................................................................................................40 ክፍል አምስት ፡ የዕቅድ ትግበራ ምዕራፍ ( Implementation phase)...................................................................... 46 ክፍል ስድስት፡ አፈጻጸም መገምገም እና አጠቃላይ ሂደትን መሰነድ (Performance review and documentation)_ 47 የማህብረሰብ ውይይት አባላት በራሳቸው ላይ ያመጡት ለውጥ መሙያ ፎርማት.....................................................51 ዋብ መጽሐፍት...................................................................................................................................52
  • 3. 3 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ መግቢያ ኢትዮጵያ የህጻናት እና የሴቶችን መብት ለማስከበር ዓለም እና አህጉር አቀፍ ስምምነቶችን ያጻደቀች አገር ነች፡፡ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የቤተሰብ ህግን በማሻሻል የጋብቻ ዕድሜ ለወንድና ለሴት 18 ዓመትና ከዚያ በላይ እንድሆን ደንግጎል፡፡ በተመሳሳይ የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንደ ሴት ግርዛት ወንጀል መሆኑን የተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ይደነግጋል፡፡ ቢሆንም ያለ ዕድሜ ጋብቻና የሴት ግርዛት ስርጭት ኢትዮጵያ ውስጥ ቀጥለዋል፡፡ በ 2016 የኢትዮጵያ የስነ-ህዝብ እና የጤና ዳሰሳ መረጃ መሰረት ያለ ዕድሜ ጋብቻ ስርጭት 40% ስሆን የሴት ግርዛት 74% ነው፡፡ ኢኮኖሚያዊ፤አካላዊ፤ ወስባዊ እና ስነ ልቦናዊ በሰፋት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩ የጥቃት አይነት መሆናቸውን መረጃው ያስረዳል፡፡ በመሆኑም የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ውስጥ የሚመደቡ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ጎልተው የሚታዩ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው። እነዚህ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ኢትዮጵያ ውስጥ የሥርጭት መጠናቸው ከቦታ ቦታ ይለያያል። ለዚህም የማህበረሰቡ ጎጂ ልማዶች፤ አሉታዊ ወጎች፤ የተዛቡ እሴቶች፤ሀይማኖታዊ አስተምሮቶችን በአግባቡ አለመረዳት፤ የአኗኗር ዜይቤና የመሳሰሉት በዋነኝነት የሚጠቀሱ ምክንቶች ናቸው። በተጨማሪም የባለ ድርሻ አካላት በቅንጅት አለመሥራት፤ የህግ አፈጻጸም ክፍተት፤ የአካባቢውን ማህበረሰብ አሳታፊ ያላደረጉ የመፍትሔ አቅጣጫዎችና የመሳሰሉት ለችግሩ ቀጣይነት ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ በሴቶች ላይ መጠነ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ፤ማህበራዊ፤ስነ ልቦናዊ እና አካላዊ ቀውሶች ያስከትላሉ። ስለሆነም የማህበረሰብ ውይይት ማህበረሰቡ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የሚደረሱ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን እንደ ያለ ዕድሜ ጋብቻና የሴት ግርዛት በመገንዘብ በአካባቢው የሚገኙ ሀብቶችን በመለየት መፍትሔ ለመፈለግና ለመከላከል ይረዳል። ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በተለይ ያለ ዕድሜ ጋብቻና የሴት ግርዛት ወጥ በሆነ መንገድ መፍታት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ መፍትሔው ሀሳቦችም ችግሮቹ ከሚከሰቱበት ማህበረሰብ ካልመጣ በስተቀር ዘላቂ አይሆንም። መፍትሔው በሌላ አካል የሚመጣ ከሆነ የአካባቢው ማህበረሰብ ለመፍትሔው ባለቤት የመሆን ፍላጎት በጣም አናሳ ይሆናል። በመሆኑም ማህበረሰብ አቀፍ መፍትሔ እና ማህበረሰቡን የችግሩን የመፍትሔ አካል ለማድረግ የማህበረሰብ ውይይት ዋነኛ ስልት ነው። የማህበረሰብ ውይይት በማህበረብ ውስጥ ያሉ አካባቢ በቀል ሀብትና እውቀቶችን ለመለየትና ለመጠቀም ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
  • 4. 4 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ በመሆኑም የማህበረሰብ ውይይት አመቻች የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፊዎች በንቃት ውይይቱ ላይ እንዲሳተፉ ውይይቱን በክህሎት መምራት ይኖርበታል። የውይይት ተሳታፊዎች ለችግሮቹ የሚሰሩ የመፍትሔ ተግባራት ማስቀመጥ፤መተግበር፤ የቀሰሙትን እውቀት በሚያገኙት ማህበራዊ ትስስሮች ሁሉ ለማህበረሰቡ ማካፈል መቻል አለባቸው። ይህን ለማድረግ ትምህርት ቤቶች፤ የመገበያያ ቦታዎች፤የጤና ተቋማት፤ የቤተ እምነት ተቋማት፤የእድር ስብስባዎች ዋነኛ የቁልፍ መልእክቶች ማሰራጫ ቦታዎች ናቸው። በመሆኑም ፖሊስ፤ ፍርድ ቤት፤ እድሮች፤የጤና ባለሙያዎች፤የሀይማኖት አባቶች፤የግብርና ባለሙያች፤የጤና ኤክስቴሽን ባለሙያዎች፤ የሀገር ሽማግሌዎች፤የሴቶች አደረጃጄት ቁልፍ የማህበረሰብ ውይይት ውሳኔዎች ማስፈጸሚያ ባለድርሻ አካላት ናቸው፡፡ ይህ መማሪያ መጽሐፍ በሁለት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ክፍል አጠቃላይ የማህበረሰብ ውይይት ዋና ፍሬ ሐሳቦችን፤ ለውይይቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፤የማህብረሰብ ውይይት አባላት ምርጫ፤ ከአመቻች የሚጠበቁ ዝግጅቶችና የመሳሰሉት ፍሬ ሐሳቦችን፤ የያዘ ሲሆን የማህበረሰብ ውይይት አመቻች ሁልጊዜ ማንበብና ማወቅ አለበት። አመቻቹ ለማህበረሰብ ውይይት ሲዘጋጅ ይህን ክፍል ማንበብና መረዳት ይኖርበታል፡፡ የማህበረሰብ ውይይት አባላት 20 እስከ 25 ሰው ይሆናል፡፡ የውይይቱ አባላት በቀበሌው ከሚገኙ ት/ቤቶች፤ የሀይማኖት ተቋማት፤ የሀገር ሽማግሌዎች፡የእድር መሪዎች፤ ዕድሜው 12 ዓመትና ከዛ በላይ የሆነ ወጣት፤ የፍትህ ቢሮ፤ ጤና ተቋማት ይመሰረታል፡፡ ውይይቱ ከ 4 እስክ 5 ሰው በቡድን በመክፈል ይካሄዳል፡፡ የማህበረሰብ ውይይት ለስድስት ወራት የሚካሄድ ሲሆን በወር ሁለት ጊዜ ለሁለት ሰዓት ይደረጋል፡፡ በአጠቃላይ ለአስራ ሁለት ሳምንት ይካሄዳል፡፡ከስድስት ወር በኋላ የማህበረሰብ ውይይት አባላት ፟ ይመረቃሉ፡፡ለመመረቅ ቢያንስ እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ቢያንስ ሰባት ሳምንትና ከዛ በላይ ውይይቱ ላይ መሳተፍ አለባቸው፡፡ ውይይቱ ቦታና ቀን በአባላት ይወሰናል፡፡አመቻቹ እንደየ አካባቢዊ ተጨባጭ ሁኔታ ውይይቱን ማስከድ አለበት፡፡ የማህበረሰብ ውይይት ቡድን ሲመሠረት በጥንቃቄና በተሰጠው መምሪያ መሠረት መሆን ይኖርበታል። ሁለተኛው ክፍል የማህበረሰብ ውይይት ክፍሎች ሲሆኑ አመቻቹ በእያንዳዱ ደረጃ የተመለከቱ ርዕሶች በሚገባ መረዳትና ውይይቱን መምራት ይጠበቅበታል። ተሳታፊዎች የቀሰሙትን እውቀት በተግባር ማዋል እንዲሁም ሌሎች የማህበረሰብ አባላትን ማስተማር አለባቸው። በውይይቱ ወቅት ተጨማሪ ማብራሪያ በሚያስፈልጉ ርዕሶች ላይ እንደ አስፈላጊነቱ የሀይማኖት አባቶች ፤የህግ እና የጤና ባለሙያዎችን በመጋበዝ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ማድረግ ይችላል፡፡ በተጨማሪ በዚህ መማሪያ የሚገኙት ቅጾች በሙሉ በተሰጠው መምሪያ መሰረት በተግባር ላይ መዋል አለባቸው፡፡
  • 5. 5 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ራዕይ (Vision) የማህበረሰብ ውይይት አባላት የውይይታቸው መዳረሻ ሊኖራቸው ይገባል። የማህበረስብ ውይይት ያለ ራዕይ መዳረሻ የለሌው ይሆናል። በመሆኑም የስድስት ወራት ራዕይ መኖር አለበት። ራዕይ፡ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በተለይም የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልምዶችን የሚጠየፍ ግለሰብ፤ቤተሰብ፤ማህበረሰብ እና ተቋማት ተፈጥሮ ማየት። ተልዕኮ ( Mission) የማህበረሰብ ውይይት አባላት ወደ ራዕይ የሚወስዳቸው መንገድ ያስፈልጋቸዋል። ያለ ተልኮ ራዕይ ላይ መድረስ አይቻልም። ስለሆነም የማህበረሰብ ውይይት አባላት የተመሠረቱበት ተልኮ ሊኖራቸው ይገባል። ተልኮ፡ በማህረሰባችን በሚገኘው ሀብት በመጠቀም ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻንየሚከላከል ግለሰብ፤ቤተሰብ፤ማህበረሰብና ተቋማት መፍጠር። ግብ (Goal) የማህበረሰብ ውይይት አባላት የሚለካ ግብ ሊኖራቸው ይገባል። የማህበረሰብ ውይይት አባላት መጨረሻ ላይ የውይይታቸው ስኬት ባስቀመጡት ግብ አንጸር መለካት አለባቸው። ግብ አንድ፡ በማህበረሰባችን ውስጥ ስለ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ስለመከላከል ማህበራዊ መድረኮችን በመጠቀም ግንዛቤን ማሳደግ ። ግብ ሁለት፡ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ለመከላከል የተቋማት አቅም ማሳደግ። ግብ ሶስት፡ የማህበረሰባችንን ለሥርዓተ ጾታ መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ የሚያጋልጡ ባህሪዎችን እንዲሁም አስተሳሰቦችን መቀየር የሚለኩ ዋና ዋና ዓላማዎች ( Short term objectives) የማህበረሰብ ውይይት አባላት ወደ ግብ መድረሳቸውን የሚያሳይ የአጭር ጊዜ ዓላማ ማስቀመጥ አለባቸው። ዓላማዎችን ለመጻፍ የፕሮጀክት አስተባባሪው የመነሻ የዳሰሳ መረጃ መሰብሰብ አለበት። ለምሳሌ፡ አንድ
  • 6. 6 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ❖ በ2015/2016 በቀበሌው የሚገኙት ሁሉም ባህላዊ መዋቅሮች ለምሳሌ እንደ እድር ያሉ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ግንዛቤ በ70% ወይም ማሳደግ። ❖ በ2015/2016 በቀበሌው የሚገኙት የሁሉም ቤተ እምነት መሪዎች ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ የሚሰሩ 60% ወይም ማሳደግ። ❖ በ2015/2016 በቀበሌው የሚገኙት የሁሉም ት/ቤቶች ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ የሚሰሩ 100% ወይም ማሳደግ። ❖ በ2015/2016 የቀበሌውን ሕዝብ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ያለውን እውቀት በ85% ማሳደግ፡፡ ዝርዝር ዓላማዎች ( Specific objectives) ዝርዝር ዓላማዎች ዋና ዓላማን ለመድረስ የሚተገበሩ ዝርዝር ተግባራት ናቸው። በመሆኑም የዋና ዓላማው ዝርዝር ተግባራት፤ ❖ የማህበረሰብ አባላት ማለትም ወጣቶች፤ ባህላዊ መሪዎች፤ወላጆች፤የማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች በሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ውይይት የሚያደርጉበትን መድረክ ለመፍጠር፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መፍትሔ መፈለግና መተግበር፤ ❖ በሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ምክንያት የሚመጣውን መጠነ ሰፍ ጉዳቶችን መለየት፤ ❖ ማህበረሰቡ ለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የሚጫወተውን ሚና ማሳደግ፤ ❖ የግለሰብ፤የቤተሰብ፤የማህበረሰብ እና በማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት አቅም በማጎልበትና በማጠናከር የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን( ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት) መከላከል፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን የሚያበረታቱ ልምዶች፤ እሴቶች እና ወጎችን መገንዘብ፤ ❖ ትምህርት ቤቶች፤የጤና ተቋማት፤ የቤተ እምነት ተቋማት፤የእድሮቸ ፤የአካባቢዊ የብዙሀን መገናኛዎች ዘውትር ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ቁልፍ መልእክቶች እንድያሰራጩ ማድረግ።
  • 7. 7 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የአባላት ሚና ( Roles of community conversation members) የማህበረሰብ ውይይት አባላት የሚከተሉትን ተግባራት በማከናወን ለማህበረሰባቸው የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው። ❖ በማህበረሰብ ውይይት ወቅት ያገኙትን እውቀት ለመጡበት ቀበሌ ወይም መ/ቤት ለማስተማር ማቀድ፤ ❖ በውይይቱ ወቅት በመጡበት አካባቢያ ያለው ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ያለውን እውነተኛ ሐሳብ ማንሳት፤ ❖ የተለያዩ መድረኮችን በመጠቀም ማለትም ለጎረቤትና ለቤተሰብ ቡና ሲጠጣ፤በስግደት ሰዓት መልስ፤በፀሎት ሰዓት መልስ፤ በገበያ ቀናት፤ በእድር ስብስባ፤በት/ቤቶች፤ያገኙትን እውቀት ማስተማር፤ ❖ በማህበረሰብ ውስጥ የሚነሱ ሰለ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ያሉ ልምዶችና የተሳሳቱ እምነቶችን ለውይይት ማቅረብ፤ አስፈላጊነት ( Essence of community conversation) የማህበረሰብ ውይይት ማለት ማህበረሰብና ማህበረሰብ አቀፍ የባለ ድርሻ አካላት አቅማቸውን በማጎልበት በጋራ የራሳቸውን ችግሮች የሚለዩበትና የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያስቀምጡበት ሂደት ነው። ሁሉንም አሳታፊ እንዲሁም ተግባቦት በሆነ መንገድ ፤ በግለሰቦችና በቡድኖች መካከል ሀሳብ በመለዋወጥ የሚሰራ መፍትሔ በስምምነት ለማስቀመጥ ይረዳል። ሁሉም ተሳታፍዎች ስለማህበረሰቡ ችግሮች በጥልቀት የራሳቸውን ሀሳብና ፍላጎት በመግለጽ የጋራ ግብ ያስቀምጣሉ። የማህበረሰብ ውይይት ማህበረሰቡ በአካባቢያቸው ጎልተው የሚታዩ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሱ ሥርዓተ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ማለትም የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል ግልጽ ውይይት፤ በመከባበር ላይ የተመሰረተ እና መፍትሔ ተኮር መድረክ ሆኖ ያገለግላል፡ ፡ውይይት የማህበረሰብን የአንድነት መንፈስ ያጠናክራል፤ ማህበረሰቡ ለጋራ ችግራቸው በአንድነት እንድሰሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
  • 8. 8 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የሚጠበቁ ውጤቶች (Expected outcomes) ከማህበረሰብ ውይይት የሚጠበቁ ውጤቶች መኖር አለባቸው።የማሀበረሰብ ውይይት ውጤት ተኮር መሆን አለበት። ውጤቶች የለሌው ውይይት እውቀት፤አመለካከት እና ልምድን የመለወጥ እድል የለውም፡፡ ❖ በግለሰብ ደረጃ የተለዩ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሱ ሥርዓተ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መቀነስ፤ ❖ ማህበረሰቡ በአንድነት የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን (ሥርዓተ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት) ለመከላከል እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የሚሰራ ውሳኔ ማሳለፍ ❖ በጥልቀት አሁናዊ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ልምዶችን የተገነዘበ ማህበረሰብ መፍጠር ❖ በግለሰብ፤ በቤተሰብ እና በማህበረሰብ ደረጃ የተለዩ በአካባቢው የሚገኙትን ዕድሎችና ለባህርይ ለውጥ እንቅፋት የሆኑትን መለየት ❖ በአንድነት የሚሰሩ ማህበረሰብ አቀፍ ተቋማት ማለትም ትምህርት ቤቶች፤ ጤና፤ቀበሌ አስተዳደር፤ፍትህ፤ባህላዊ አስተዳደር፤የጎሳ መሪዎች እና እድሮች ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲከላከሉ ማስቻል፤ ❖ ማህበረሰቡ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለማስወገድ የሚረዱ የታወቁ የአካባቢ ሀብቶችን መለየትና ማሰባሰብ፤ ❖ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሱ ሥርዓተ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃትን የተገነዘበና የሚከላከል ማህበረሰብ መፍጠር፤ ❖ (ሥርዓተ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እና ልጃገረዶችን ) አስፈላጊውን እገዛ የሚያደርግ ማህበረሰብ መፍጠር ፤ ❖ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በተለይም እንደ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት መሆኑን የተረዳ ማህበረሰብ መፍጠር፡፡ መሰረታዊ መርሆች ( Fundamental principles) ውጤታማ የማህበረሰብ ውይይት ለማካሄድ መሠረታዊ መርሆችን መከተል ተገቢ ነው። የማህበረሰብ ውይይትን ውጤታማ ለማድረግ መሪህ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት።
  • 9. 9 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ❖ ሁሉም አቀፍነት፡ በቀበሌው የሚገኙ ሁሉም ጎሳዎች፤ብሔረሰቦች፤ ሀይማኖቶች፤ ተቋማትን ማካተት ግደታ ነው። ይህም የተለያዩ ሀሳቦችን ለማስተናገድና ልተገበር የሚችል መፍትሔን ያስገኛል። ❖ የጋራ ባለቤትነት፡ ሁሉም የውይይቱ ተሳታፍዎች በቁርጠኝነት፤በቅንነት፤በታማኝነት፤ትርጉም ባለው መንገድ መሳተፍ አለባቸው። ❖ መማር፡ ሁሉም የውይይቱ ተሳታፍዎች በግልጸኝነት የችግሩን መጠንና ስፋት በመረዳት ለመማር ዝግጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ❖ ሰብአዊነት፡ ተሳታፍዎች የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጉዳት የደረሰበት ሰው ምትክ ራሳቸውን በማስቀመጥ ርህራኄን መግለጽ። ❖ ምስጢራዊነት፡ በውይይቱ ወቅት እርስ በእርስ በመተማመን፤ ተሳታፍዎች ያለ መፍራት ሀሳባቸውን በነጻነት መግለጽ አለባቸው። ❖ ዘላቂነት ያለው ረጅም ጊዜ አመለካከት፡ ጊዜያዊ መፍትሔ ከማስቀመጥ ይልቅ ጎጂ የሆኑ ወጎች እና ልምዶች በዘላቂነት ወደ ጠቃሚና ሴቶች እና ልጃገረዶችን ከጥቃት የሚጠብቁ መሆን ማስቻል ። ❖ መልካም እምነት፡ ተሳታፍዎች ድብቅ ፍላጎቶችንና አጀንዳዎችን በመተው በቅንነት እውቀታቸውን ማካፈል። አመቻች ክህሎት ( Facilitator’s skills) የማህበረሰብ ውይይት አመቻች ለውይይት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ተሳታፍዎች ሀሳባቸውን፤ እውቀታቸውን፤ የሚያሳሰባውን ጉዳይ በነጻነት ያለ ፍርሀት እንድገልጹ ማድረግ አለበት። እስከ ውይይት መጨረሻ ድረስ ተሳታፍዎች አካላዊና ስሜታዊ ምቹነት እንድኖራቸው አመቻች ማረጋገጥ አለበት። በመሆኑም የውይይት አመቻች ሲመረጥ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ከአመቻች የሚጠበቁ ብቃቶች (Competence) ❖ የውይይት ሀሳቦችን በአጭሩ ለተሳታፍዎች መግለጽ፤ ❖ ለተሳታፍዎች የውይይቱ ፍሬ ሀሳብ ማስረዳት፤ ❖ ሁሉም ተሳታፍዎችን እኩል ማሳተፍ፤ ❖ የሀሳብ ልዩነቶችን መቀበልና የሚያሰማሙ ነጥቦችን መለየት፤
  • 10. 10 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የአመቻች ማስታወሻ ግጭት ማለት በሁለት ቡድኖች መካከል የሚከሰት አለመግባባት ነው። ❖ ግጭት የሚፈጠረው በሀብት እጥረት፣ በሀሳብ አለመግባባት፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና በመሳሰሉት ይከሰታል። ❖ ግጭት ለመከላከል፦ አሳታፊ መሆን፣ ከአድሎ ነፃ መሆን፤ አካታችነት፤ግልጽነት ውሳኝ ነው። ❖ በውይይት ወቅት ግጭት ሲፈጠር በአግባቡ መፍታት፤ ❖ ተሳታፍዎችን ለአዳድስ ሀሳቦች ማበረታትና ግብረ መልስ መስጠት፤ ❖ በውይይት ወቅት ተገቢውን የሰውነት እንቅስቃሴን ማሳየት። ❖ የሚያፍሩን የማይሳተፉ አባላትን እንዲሳተፉ ማበረታታት ተሳታፍዎችን ለመምረጥ መደረግ ያለባቸው ነጥቦች(Preconditions) ❖ ውይይት ልደረግበት የታሰበት ቦታ/ ቀበሌ የሚገኙ ሁሉም የባለ ድርሻ አካላትን መለየትና በማስታወሻ ላይ መጻፍ፤ ❖ የውይይቱ የባለ ድርሻ አካላት የሚባሉ መምህራን፤ የሁሉም ቤቴ እምነቶች የሀይማኖት አባቶች፤ የጎሳ መሪዎች፤የሀገር ሽማግሌዎች፤ታዋቂ ሰዎች፤ የህክምና ባለሙያዎች፤ወጣቶች፤ የቀበሌ አስተዳዳሪ፤ ዳኞች፤ ፖሊሶች፤ የእድር አባላት፤የተለያዩ ማህበራት አባላት መለየት፤ ❖ በአካባቢው/ በቀበሌው የሚገኙትን ሁሉም ተቋማት መለየትና በማስታወሻ ላይ መጻፍ። ተቋማት የሚባሉት ትምህርት ቤቶች፤ የጤና ኬላዎች፤የጤና ጣቢያዎች፤ሆስፒታሎች፤ቤቴ እምነቶች፤እድር፤ የቀበሌ አስተዳደር መ/ቤቶች፤ ፖሊስ ጣቢያ፤ የፍትህ እና ባህላዊ ተቋማት። የአባላት ምርጫ መመዘኛዎች (Criteria of members selection) ❖ የመሳተፍ ፍላጎት፡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት `በፍላጎትና በነጻነት መሳተፍ አለባቸው። ❖ ብዙሀነትን መጠበቅ፡ የውይይት ተሳታፍዎች ሚዛኑን በጠበቀ መልክ ስለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ መረጃ እና እውቀት ያለው የህብረተሰብ ክፍል እና መረጃና እውቀት የለሌው የህብረተሰብ ክፍል እኩል መወከል አለባቸው።
  • 11. 11 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ❖ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አካታችነት፡ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት እስከ ውይይቱ መጨረሻ ሂደት ድረስ መሳተፍ አለባቸው። ይህም የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ስለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ያላቸውን የተለያዩ ሀሳቦችን ለመረዳት አስተዋጽኦ ያደርጋል። ❖ በውይይቱ የመሳተፍ ተገቢነት፡ ማን ውይይቱ ላይ ብሳተፍ ለባህርይ ለውጥ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚለውን በደንብ ማየት ተገቢ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ግጭትን ለማስወገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ❖ አሳታፍ ውሳኔ ሰጪነት፡ የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፍዎች ሁሉም የቀበሌ ባለድርሻ አካላት እና ተቋማት በተገኙበት ይመረጣሉ። ❖ ሁሉም አቀፍነት፡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እና ተቋማት መወከል አለባቸው። ❖ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ መሆን፡ በማህበራዊ ደረጃ፤ በሀብት ልዩነት እና በፖለቲካ ምክንያት የተከለሉና አናሳ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማካተት። ❖ ማብቃት፡ የተመረጡ የማህበረሰብ አባላት፤በነጻነት የሚሰማቸውን ሀሳብን መግለጽ የሚችሉ፤ ለሎች ድምጽ ልሆኑ የሚችሉ፤ የለውጥ አካል እንድሆኑ ማብቃት። ❖ ሁሉም ጾታዎች ማካተት፡ አንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ወንዶችና ሴቶች አንድ ላይ እንድወያያዩ ማድረግ፤ የአካባቢው ባህል የማይፈቅድ ከሆነ ወንዶችና ሴቶች ብቻ ለብቻ እንድወያዩ ማድረግ ግደታ ነው። ቁጥራቸው 20 እስከ 25 አባላት ሲሆን ልጃገርዶች፤ እናቶች እና አዋቅዎች የውይይቱ አካል መሆን አለባቸው። ❖ የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፍ ስነ ምግባር፡ የውይይት ተሳታፊ አባላት ስነ ምግባርና ተቀባይነት በትክክል መላው የቀበሌ ህዝብ በተገኘበት አባላቶቹ ላይ አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ ተገቢ ነው። ምክንቱም የውይይቱ ፍሬ ሀሳቦች ተሳታፍው ለማህበረሰቡ ማካፈል መቻል አለበት። ብልሹ ስነ ምግባር ካለው ሀሳቡ ተሰሚነት አያገኝም። ❖ በጎ ፍቃደኝነት፡ የውይይቱ አባላት በበጎ ፍቃደኝነት ማህበረሰቡን ለማገልገል ፍቃደኝነታቸን ማረጋገጥ አለባቸው። ለዚህም በምርጫው ላይ ተገቢውን ትኩረት መስጠት ወሳኝ ነው።
  • 12. 12 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የማህበረሰብ ውይይት አመቻች ሁልጊዜ ማንበብና ማወቅ አለበት። አመቻቹ ለማህበረሰብ ውይይት ስዘጋጅ ቀጥሎ ያለውን በሰንጠረዥ ያለውን ሀሳብ ማንበብና መረዳት ተገቢ ነው።
  • 13. 13 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የአመቻች የትኩረት ቦታዎቸ ( Attention areas for facilitator) የትኩረት ድርጊቶች አብይ ተግባራት የትኩረት ነጥቦች 1. ውይይት ከመጀመሩ በፍት ተሳታፍዎች ስለ መምጣታቸው ማመስገንና ሁሉም ሰው ሐሳብ እኩል መሆኑን መግለጽ፤ 2. አንድ ሰው ሲናገር ሌሎች ማዳመጥ እንዳለባቸውና ተራ ጠብቀው እንዲናገሩ ማድረግ፤ 3. ማንኛውም ሰው በነጻነት ስለ ርዕሱ የሚሰማውን ሐሳብ እንድናገር ማበረታት፤ 4. ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ቦታ ላይ መቀመጡን ማረጋገጥ፤ 5. ሁሉም ሰው የመፍትሔ ሐሳብ ጭምር ማቅረብ እንዳለበት ማበረታት፤ 6. የመፍትሔ ሐሳብ ከአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መቅረብ እንዳለበት ማሳወቅ፤ 7. ሁሉም አባላት የባለፈውን የውይይት ርዕስ ለሌሎች ለማስተማር ያወጡትን እቅድ አፈጻጸም እንድያቀርቡ ማድረግ፤ 8. ውይይት ከመጀመሩ በፊት የውይይት ተሳታፍዎችን ከ10 እስከ 15 ማከፋፈልና የሚወያዩበትን የውይይት ሐሳብ መስጠት፤ 9. የተወያዩትን ሐሳብ እንድያቀርቡ ማድረግና ሁሉም ቡድኖች እንድወያዩበት ማድረግ፤ 10. የርዕሱን ዓላማዎች ሁሉም ሰው መረዳት በሚችለው ቋንቋ ማስረዳትና ግልጽ መሆኑን ማረጋገጥ፤ 11. የዕለቱን የውይይት ጥያቄዎች ማስረዳት፤ 12. ስምምነት የተደረሰባቸውን የውይይት ነጥቦችን መመዝገብ፤ 13. የማህበረሰብ ውይይት አባላት ተግባራት ለአባላት ማስረዳት፤ 14. ተሳታፍዎች በንቃት እንድሳተፉ ማነሳሳት፤ 15. ተሳታፍዎች በአካባቢያቸው ያለውን አሁናዊ ሁኔታን መሰረት አድርገው ችግር ፈች ውይይት እንድያደርጉ ማድረግ፤ 16. በውይይቱ ላይ የተገኙትን አባላት መመዝገብ፤ 17. የዕለቱ ውይይት ካለቀ በኋላ ሁሉም አባላት በቃሌ ጉባዬ መዝገብ ላይ መፈራማቸውን ማረጋገጥ፤ 18. የውይይቱ ርዕሱ ላይ ብቻ ትኩረት መደረጉን ማረጋገጥ፤
  • 14. 14 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ 19. በአካበቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ የሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በጭውውት፤ በድራማ እና በግጥም እንድገልጹ ማድረግ፤ 20. በውይይቱ ላይ የተገኙ የኃይማኖት አባቶች ተራ በተራ እንድጸልዩ ማድረግ፤ 21. ተሳታፍዎችን ማክበርና ሁሉም ሰው ሀሳብ እንድሰጥ ማሳተፍ፤ 22. የውይይቱ ተሳታፍዎች በአግባቡ ውይይቱን እንድከታተሉና ጥያቄ እንድጠይቁ ማድረግ፤ 23. መሻሻል ያለባቸውን ነጥቦች መለየትና እንድሻሻሉ ማድረግ፤ 24. ተሳታፊዎች የጋራ ደንቦችንና መመሪያዎችን እንዲያከብሩ ማስታወስ፤ 25. ሀሳብን በግልጽ እና ከዋናው ጉዳይ ሳይወጣ መግለጽ፤ 26. ሁሉም ሰው የዕለቱን የውይይት ርዕስ መረዳቱን ማረጋገጥ፤ 27. የሰዎችን ሐሳብ እና የአካባቢውን ባሕል ማክበር። 28. ለተሳታፍዎች የአካባቢያቸውን እውነታ ከማስረዳት መቆጠብ። የውይይት ቦታና ጊዜ እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ሁሉም ተሳታፍዎች የሚመቻቸውን የውይይት ቀን፤ሰዓት እና ቦታ በተሳታፍዎች ስምምነት መወሰን አለበት። የውይይት ቦታ ሁሉም ተሳታፍዎች ነጻነት ይሰማናል ብሎ የሚሰማሙበት ቦታ መሆን አለበት። ቦታው ከሚረብሽ ድምጽ ነጻ መሆኑንና ለወንዶችና ሴቶች ቅርብ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። የውይይት ቦታ የሚከተለው ልሆን ይችላል፡ ❖ ትምህርት ቤት ገቢ/ መማሪያ ክፍል ❖ ገበያ ቦታ ❖ ዛፍ ጥላ ስር ❖ የቀበቤው መ/ቤት
  • 15. 15 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ❖ ቤቴ እምነቶች ❖ የስብስባ አደራሽ እና የመሰሰሉት የጊዜ ሰሌዳ ❖ ሁሉም የውይይት ክፍሎች በወር ሁለት ጊዜ የሚካሄዱ ስሆን፤ ለስድስት ተከታታይ ወራት ይካሄዳሉ። ❖ ሁሉም የውይይት ክፍሎች ለሁለት ሰዓት መካሄድ አለባቸው። ❖ የውይይቱን ሂደት አመቻቹ ሁልጊዜ በየዕለቱ መለካት ወይም መገምገም እና መከተታተል አለበት። ቅደመ ዝግጅት ❖ አመቻቹ የአመቻች መማሪያ በሚገባ ማንበብና መረዳት አለበት። ሪፖርት ❖ አመቻቹ በየወሩ ማህበረሰብ ውይይት ሪፖርት መላክ አለበት። የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ❖ የአመቻች መማሪያ፤ የቃሌ ጉባዬ መዝገብ፤ እስክብርቶ፤ማስታወሻ ደብተር። ፍሬ ሐሳብና ግብረ መልስ ❖ የዕለቱን ዋና ዋና ፍሬ ሀሳቦችን በመግለጽና ስምምነት የተደረሰባቸውን ሐሳቦች ብቻ በቃሌ ጉባዬ መዝገብ መመዝገብ፤ ከተሳታፍዎች ለሚነሳኑ ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ መስጠት። ❖ ጥያቄው ሙያው ትንተና/ተጨማረ ማብራሪያ የሚያስፈልግ ከሆነ በማስታወሻ በመያዝ በቀጣይ ውይይት የሚመለከተውን ባለሙያ መጋበዝና ገለጻ እንድያደርግ ማድረግ። ❖ በተጨማሪ የዕለቱ ውይይት ላይ አጠቃላይ ግብረ መልስ መስጠት። ❖ የዕለቱን ውይይት ጠንካራና መሻሻል ያለባቸውን ነጥቦች መለየትና ለቀጣይ እንድሻሻል የጋራ ስምምነት ማድረግ። ማጠቃልያ ❖ ለተሳታፍዎች ምስጋና በማቅረብ የዕለቱን ውይይት ማጠቃለልና ለቀጣይ መዘጋጀት። ❖ የተዘጋጁ ሥዕላዊ መግለጫዎች ካሉ ማሳየት በጣም አስፈላጊ ነው።
  • 16. 16 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የማህበረሰብ ውይይት ቡድን ማቋቋም (Establishment of community conversation team) የማህበረሰብ ውይይት አባላት የሚመሰረቱት በቀበሌው ወይም ውይይት የሚደርግበት አካባቢ ከተለዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ነው። የማህበረሰብ ውይይት አባላት መላው የቀበሌው ህዝብ በተገኘበት ምርጫ ይደረጋል። ምርጫው ከተደረገ በኋላ በተመራጮች ላይ አስተያየት ይሰጥበታል። ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ በቀበሌው የተመረጡ ሰዎች የማህበረሰብ ውይይት አባላት እንድሆኑ በግልጸኝነት፤ እና በብቅንነት ከሁሉም ተቋማትና የባለ ድርሻ አካላት የተወከሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በመላው የቀበሌ ህዝብ መጽደቅ አለበት። የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፍዎች ይሆናሉ። በማህበረሰብ ውይይት አመቻች የተመረጡ አባላት ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተወጣጡ መሆናቸውን ያረጋግጣል። ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች መወከላቸውን ካረጋገጠ በኋላ የውይይት አመቻች በሚከተሉትን ተግባራትን ያከናውናል፤ ❖ ውጤታማና ፍሬያማ የማህበረሰብ ውይይት ለማካሄድ የውይይቱ አባላት ከ20 እስከ 25 መሆን አለባቸው። በውይይት ወቅት አባላቱ 4 እስከ 5 ሰው በድን ይሆናል፡፡ ❖ የማህበረሰብ ውይይት አባላት ስብጥር ወንዶች 40% ስሆኑ ሴቶች 60% መሆን አለባቸው። ❖ ወንዶች ከሁሉም ማለትም ወጣቶች እና ሽማግሌዎች ከሁሉም ተቋማት የተወጣጡ መሆን አለባቸው። ሴቶችም በተመሳሳይ ወጣቶች እና አዋቂ ከሁሉም ተቋማት የተወጣጡ መሆን አለባቸው። ዕድሜው 12 ዓመትና ከዛ በላይ የሆኑ ወጣቶች መሳትፍ አለባቸው፡፡ ❖ የተመረጡ አባላትን ራሳቸውን እንድያስተዋውቁ ማድረግ፤ ❖ የተመረጡ አባላትን መመዝገብ፤ የወንድና የሴት ስብጥር 40% ለወንድ እና 60% ለሴት መሆኑን ማረጋገጥ፤ ❖ አመቻቹ ራሱን ከህዝቡ ጋር ያስተዋውቃል፤ የስራ ድርሻውን በአጭሩ ይገልጻል፤ ❖ ከተመረጡ አባላት የሚጠበቅባቸውን ተግራት ያብራራል፤አስተያየታቸውን ይቀበላል፤ ❖ የማህበረሰብ ውይይት ራዕይ፤ ዓላማዎች፤ግብ፤ የሚጠበቁ ውጤቶች ለአባላቱ ና ለህዝቡ ያስረዳል፤ ❖ የጋራ መተዳደሪያ ደንብ በተመረጡ አባላት ጋር ያወጣል፤ ❖ በስምምነት ላይ የተደረሱ ደንቦችን ይመዘግባል፤ ❖ ቀጣይ የውይይት ቀን፤ቦታ እና ሰዓትን ያስወስናል።
  • 17. 17 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ❖ እንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ማስተላለፍ፤ ❖ አባላቶቹ ከ30 እስከ 40 መሆናቸውን ማረጋገጥ ❖ የተሳታፍዎች ግንኙነት መፍጠር፤ ❖ የተሳታፍዎች ትውውቅ ስም የመጡበት ቀበሌ/ሰፈር ሀይማኖት ስራ/ መተዳደሪያ የትምህርት ደረጃ ኃላፍነት እንድታወቅልኝ የሚፈልገው ባህርይ ከውይይቱ የሚጠበቀው ውጤት የሚወዱት ነገር የማህበረሰብ ውይይት አባላት መመዝገቢያ ቅጽ ( ቅጽ አንድ) ሁሉም የማህበረሰብ አባላት በቀበሌው ህዝብ ከጸደቁ በኋላ መመዝገብ አለባቸው፡፡ ተ/ቁ የአባላት ስም ዝርዝር ጾታ ዕድሜ ሀይማኖት አድራሻ መተዳደሪያ ስልክ ቁ ምርመራ 1 ገመቹ አበበ ወ 35 ኦርቶዶክስ 01 ቀበሌ የቤ/ያን አገልግሎች 01916854572 ማሳሰቢያ፡ የማህበረሰብ ውይይት አባላት በምሳሌው መሰረት ይመዘገባሉ፡፡ የአመቻች ስም ፊሪማ ቀን የቀበሌው አስተዳደሪ ስም ፊሪማ ቀን የቀበሌው ማህተም የአመቻች ማስታወሻ
  • 18. 18 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ❖ የቡድን ውይይት ከማድረግ በፊት የውይይት ተሳታፍዎችን ከ10 እስከ 12 ማከፋፈል፤ ❖ ተሳታፍዎች የውይይቱን ጥያቄዎች ከአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ እንድያስረዱ ማድረግ፤ ❖ ቡድኑ የተወያየበትን ሀሳብ ተራ በተራ እንድያቀርቡ ማድረግ፤ ❖ የዕለቱን የውይይት ጥያቄዎችን ማስረዳት፤ ❖ የጥያቄዎችን መልስ በቃሌ ጉባዬ መዝገብ መመዝገብ፤ ❖ ስምምነት የተደረሰባቸው ነጥቦችን መመዝገብ፤ ❖ በውይይቱ ወቅት የሚከናወኑ ተግባራት ለተሳታፍዎች ማስረዳት፤ ❖ ተሳታፍዎችን በንቃት እንድሳታተፉ ማበረታት፤ ❖ ሁሉም ተሳታፍዎች ማሳተፍ፤ ❖ በውይይቱ ላይ የተገኙትን አባላት መመዝገብ፤ ❖ ዋና ዋና የውይይቱን ነጥቦች መድገም፤ ❖ የውይይቱን ዓላማ ለተሳፍዎች በደንብ ማስረዳት፤ ❖ የዕለቱ ውይይት ካለቀ በኋላ ሁሉም አባላት በቃሌ ጉባዬ መዝገብ ላይ መፈረም አለባቸው፤ ❖ አንድን የውይይት ክፍለ ጊዜ ከመጀመሩ በፍት የባለፈውን የውይይት ነጥቦችን መድገም ፤ ❖ ተሳታፍዎች ከባለፈው ውይይት የሚያስታውሱትን ዋና ዋና ነጥቦች እንድገለጹ ማድረግ። የመወያያ ሐሳቦች ❖ የስብሰባው ቀን መቼ ይሁን፤ በስንት ሰዓት ይጀመራል? ❖ የት ቦታ ይካሄዳል? ❖ በውይይት ጊዜ ልንከተላቸው የሚገቡ ደንቦች ምንድናቸው? ❖ በሚያረፍዱና በሚቀሩ አባላት ምን ይደረጋሉ? የአመቻች ማስታወሻ
  • 19. 19 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ቀን ማሳሰቢያ፡ እነዚህ አጠቃላይ የማህበረሰብ ውይይት መማሪያና ለሎች የአመቻች ማስታወሻችን የማህበረሰብ ውይይት አመቻች በሁሉም የውይይት ርዕስ መጠቀም አለበት። በመሆኑም አመቻቹ ሁልጊዜ ማንበብና ማስታወስ ይጠበቅበታል።
  • 20. 20 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የማህበረሰብ ውይይት ወርሀዊ ሪፖርት ማድረግያ ቅጽ ( ቅጽ ሶስት) 1. መግቢያ የውይይት ርዕስ የውይይት ዝርዝር ዓላማዎች የውይይት ተሳታፍዎች ወ ሴ ቀን የስብስባ ቦታ 2. የውይይት ሂደት የማህበረሰብ ውይይት አባላት ተሳትፎ ምን ይመስል ነበረ? ሁሉም አባላት እንድሳተፉ ምን ዓይነት ዜደ ጥቅም ላይ ዋለ 3. ዋና ዋና ነጥቦችና የድርጊቶች በውይይቱ ውቅት የተነሱ ዋና ዋና ሐሳቦች በውይይት ርዕሱ ላይ የተወሰዱ ድርጊቶች 4. አስተያየትና ተሞክሮዎች የውይይቱ ሰዓትና ቦታ ለሁሉም ሰው ምቹ ነበረ? በውይይቱ ወቅት የተኛው አካሄድ ይሰራል? በውይይቱ ወቅት የተኛው አካሄድ አይሰራም? ምን መሻሻል አለበት? የአመቻች ፊሪማ የቀበሌ ልቀመንበር ፊሪማ የቀበሌ ማህተም
  • 21. 21 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ 1. መልካም አስተዳደር 2. ማስፈጸሚያ ስልት 3. ሀብት 4. አሳታፍነት 5. የግጭት አፈታት 6. የውይይት ተሳታፍዎች ፍላጎት 7. የአመቻች ቁርጠኝነት 8. የተቋማት ቁርጠኝነት 9. የአካባቢው ወግ፤እሴት፤ ባህል፤መሠረተ ልማት የማህበረሰብ ውይይት ውጤታማነትን የሚወስኑ ምክንያቶች
  • 22. 22 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ በዚህ ክፍል ውስጥ ስድስት የማህበረሰብ ክፍሎች ያሉ ስሆን፤ እያንዳንዱ ክፍል ንዑስ ክፍል ይኖረዋል፡፡ ለስድስት ወራት የሚካሄድ ስሆን በወር ጊዜ ሁለት ስዓት ይካሄል፡፡በአጠቃላይ 12 ሳምንትን ይፈጃል፡፡ ከ12 ሰምንት በኋላ የማህበረሰብ ውይይት አባላት ይመረቃሉ፡፡ ክፍል ሁለት የማህበረሰብ ውይይት ክፍሎች
  • 23. 23 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የማህበረሰብ ውይይት የመማሪያ ደረጃዎች የክፍል ደረጃ የመማሪያ ርዕስ ዋና ዓላማ ዘዴዎች ክፍል አንድ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ አሁናዊ እውቀት፤አመለካከት እና ልምድን መረዳት አሁናዊ ሁኔታን መረዳትና መተንተን ሁሉም አቀፍ ውይይት፤የነበረውን ልምድ ማካፈል፤በድራማና ጭውውት ሁኔውን ማስረዳት ክፍል ሁለት የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጥቃትን በተመለከተ የእውቀትና የግንዛቤ ክፍተትን መሙላት እውቀትና ግንዛቤን ማሳደግ ንቁ ውይይት፤እውቀትን ለማካፈል መለማመድ ክፍል ሶስት የማህበሰብ ደረጃ ሀብትን በማቀናጀት ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መከላከል አካባቢ በቀል እውቀትና ልምድን በመጠቀም ችግሮችን መፍታት የቡድን ውይይትና የውይይቱን ሀሳብ ማቅረብ፤የግል ምልከታን ማንጸባረቅ ክፍል አራት የጋራ እቅድ የተገኘውን ልምድ በመቀመር ችግር ፈች አካባቢ በቀል እቅድ ማዘጋጀት ከሁሉም የተውጣጣው የእቅድ የሚያቅድ ጥምር ኃይል ማቋቋ ክፍል አምስት የእቅድ ትግበራ ምዕራፍ ለውጥን ማመቻቸት ወይም አፈጻጸምን መታተል የተደራጀ ክትትል፤ለውጥን መመዝገብ ክፍል ስድስት የአፈጻጸም ገምገማና አጠቃላይ ሂደትን መሰነድ የተገኘውን ልምድ እና ምርጥ ተሞክሮችን መያዝ ወይም አዳድስ የመማሪያ ሀሳቦችን መለየት፤ እንደገና ማቀድ ወይም ማሻሻል አስተያየት መሰብሰብ፤ግብረ መልስ መቀበል፤ለውጥ አመላካች ታርኮችን መመዝገብ የማህበረሰብ ውይይት አባላት እቅድ ቅጽ ( ቅጽ አራት) እንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አባል ውይይት የሚደረግበትን እያንዳዱ ርዕስ የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም ማስተማር አለበት። ያስተማረውን ሪፖርት ማቅረብ መቻል አለበት። ውይይት ከመጀመሩ በፍት ሪፖርት መቅረብ አለበት። ርፖርቱ ስቀርብ አመቻቹ የተከናወኑ ተግባራትን መመዝገብ አለበት። የቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት በማካሄድ ተሳታፍዎች ልምዳቸውን በማካፈል እርስበርሳቸው የሚመሩበት መድረግ መፍጠር አስፈላጊ ነው። የአባሉ ስም ቀን ቀበሌ ተቁ ተግባራት ቁልፍ መልእክት ያገኘው የሰው ብዛት በግምት ቁልፍ መልእክት የተላለፈበት ቦታ ቁልፍ መልእክቱን ለማስተላልፍ ጥቅም ላይ የዋለው ዜደ ወንድ ሴት 1 የልጅነት ጋብቻ 42 50 እድር ስብስባ በገዳቡላት መንደር በቃል 2
  • 24. 24 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ዝርዝር ዓላማዎች ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መሠረት መለየት እና መረዳት፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች ማወቅ፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻንመሠረት ላደረጉ ጥቃቶች የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን መለየት፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ለመከላከል ያሉ እድሎች፤ ማነቆችንና ስጋቶችን መረዳት፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ ምን እንደተሠራ ማወቅ፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል ምን መደረግ እንዳለበት መገንዘብ፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መሠረት ያደረጉ የጥቃት ዓይነቶችን መዘርዘር፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን የአካባቢዊ አሁናዊ ሁኔታን መረዳት። የውይይት መግቢያ ፍሬ ሀሳቦች ❖ የውይይቱን ዓላማ በደንብ መግለጽ፤ ❖ ተሳታፍዎች በንቃት እንድሳተፉ ማድረግ፤ ❖ ተሳታፍዎችን 4 እስክ 5 መክፈል፤ ❖ ለአባላት የተማሩትን ሌሎች ማስተማር እንዳለባቸው ማብራራት፤ ❖ የቡድኑ አባላት የተወያዩበትን ሐሳቦች እንድያቀርቡ ማድረግ፤ ❖ የተወያዩበት ርዕስ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ስምምነት መድረስና ማጠቃልያ መስጠት፤ ❖ ዋና ዋና ነጥቦችን በቃለ ጉባኤ መዝገብ መመዝገብ። የውይይት ይዘት 1. እስከ አሁን ድረስ በእናንተ አካባቢ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ምን ተሰራ? በማን? 2. ሥርዓ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል ምን ዓይነት እድሎች አሉ? 3. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻለመከላከል ምን ዓይነት ማነቆዎች አሉ? ክፍል አንድ፡ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን አሁናዊ እውቀት፤አመለካከት እና ልምድን መረዳት
  • 25. 25 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ 1.1 ባህል የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ( Culture, child marriage and female genital mutilation) 4. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻለመከላከል ምን ዓይነት ክፍተቶች አሉ? 5. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ ምን ዓይነት ጉዳቶች ያስከትላሉ? 6. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ ለምን ይደረጋል? በአካባቢያው የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ የተሰራ ዳሰሳ ቅጽ ( ቅጽ አምስት) ተ/ቁ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል ያለው ዕድል ማነቆ እስከአሁን የተሰራው ሥራ ካለ የማነቆው መፍትሔ 1 2 3 ክልል ወረዳ ቀበሌ የቦታው ስም የአመቻቾች ስም ቀን ፊርማ የውይይት መግቢያ ፍሬ ሀሳቦች ❖ በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤ ❖ የባለፈው ሳምንት ዋና ዋና ነጥቦችን መጠየቅ፤ ❖ ተሳታፍዎች በንቃት እንድሳተፉ ማድረግ፤ ❖ ተሳታፍዎችን 4 እስክ 5 መክፈል፤ የአካባቢያቸው የሴቶችና ልጃገረዶችን ጉዳት የሚያደርሱ ድርጊቶች እንድለዩ ማድረግ፤ ❖ ባህል የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለማስቆም ወይም ለማስቀጠል ያለው አስተዋጽኦ እንድገልጹ ማድረግ፤ ❖ የቡድኑ አባላት የተወያዩበትን ነጥቦች እንድያቀርቡ ማድረግ፤ ❖ የተወያዩበት ርዕስ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ስምምነት መድረስና ማጠቃልያ መስጠት፤ ❖ ዋና ዋና ነጥቦችን በቃሌ ጉባኤ መመዝገብ።
  • 26. 26 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የውይይት ይዘት 1. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንድቀጥል የሚያደርጉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የትኞቹ ናቸው? 2. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል ምን መደረግ አለበት? 3. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል የወንዶች ሚና ምን መሆን አለበት? በአካባቢው ያለው ባህላዊ ልማዶች መሰብሰቢያ ቅጽ ( ቅጽ ስድስት) በአካባቢው ያለው የባህል ዓይነት መካከል ለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ አስተዋጽኦ የሚያደርጉትን መለየት አስፈላጊ ነው፡፡ ተ/ቁ የባህል ዓይነት ሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት መቀጠል ያለበት መለወጥ ያለበት መቆም ያለበት 1 2 የአመቻች ማስታወሻ ❖ ጾታ፡- ማለት በተፈጥሮ ወንድ ወይም ሴት ሆኖ መፈጠር ነው፡፡ ❖ ሥርዓተ ጾታ፡ ማለት በህብረተሰቡ ተቀባይነት ያገኘ ሴቶች እንደ ሴትነታቸው ወንዶችም እንደ ወንድነታቸው በተለያዩ ሁኔታዎች እና ጊዜያት ማሳየት የሚገባቸው በቃላትና በድርጊት ባህሪያት የሚገልፅ ነው፡፡ ❖ ባህል፡ ኢንሳይክሎፒዲያ ባህል አጠቃላይ የሰው ልጅ አኗኗርን የሚወስን መስተጋብር ነው። ባህል የማህበረሰብን አባላት ስብዕናን በመቅረጽና በመፍጠር ባህሪያቸውን በእጅጉ ይቆጣጠራራል። እያንዳንዱ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ የባህላዊ ልማዶች አሉት።እሱ ቋንቋን ሂደቶችን ፣ የኑሮ መንገዶችን ፣ ወጎችን ፣ ልምዶችን ፣ እሴቶችን ፣ መሣሪያዎችን እና እውቀቶችን ያጠቃልላል ፡፡ ❖ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ፡ የሰውን አካላዊና ስነልቦናዊ ደህንነትን እንዲሁም የሰብአዊ መብቶችን እና የስነተዋልዶ ጤናን የሚፈታተኑ ልማታዊ ዕድገትንም የሚጐዱ ናቸው። ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ በሴቶች እና ልጀገረዶች ላይ ከፍተኛ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤የስነ ልቦና፤ አካላዊ እና የጤና ችግሮችን የሚያስከትሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው። ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ዋነኛ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት መሆኑን ተሳታፍዎች መረዳት አለባቸው።
  • 27. 27 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ዝርዝር ዓላማዎች ❖ ተሳታፍዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንድረዱ ማድረግ፤ ❖ ተሳታፍዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ያላቸውን ሀሳብ እንድገልጹ ማድረግ፤ ❖ ተሳታፍዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ የሚሰጡ ምክንያቶችን እንድያስረዱ ማድረግ። የውይይት መግቢያ ፍሬ ሀሳቦች በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤ ❖ የቡድን ውይይት ከማድረግ በፊት የውይይት ተሳታፍዎችን ከ 4 እስከ 5 ማከፋፈል፤ ❖ የዕለቱን የውይይት ጥያቄዎች ማስረዳት፤ ❖ የጥያቄዎችን መልስ በቃሌ ጉባዬ መዝገብ መመዝገብ፤ ❖ ስምምነት የተደረሰባቸው ነጥቦችን መመዝገብ፤ ❖ ተሳታፍዎችን በንቃት እንድሳታተፉ ማበረታት፤ ❖ ሁሉም ተሳታፍዎችን ማሳተፍ፤ ❖ በውይይቱ ላይ የተገኙትን አባላት መመዝገብ፤ ❖ ዋና ዋና የውይይቱን ነጥቦች መድገም፤ ❖ የውይይቱን ዓላማ ለተሳፍዎች በደንብ ማስረዳት፤ ❖ ከባለፈው ውይይት ዋና ዋና ነጥቦች ተሳታፍዎች እንድገልጹ ማድረግ፤ ❖ የዕለቱ ውይይት ካለቀ በኋላ ሁሉም አባላት በቃለ ጉባዬ መዝገብ ላይ መፈረም አለባቸው። የሴት ግርዛት የውይይት ይዘት 1. የሴት ግርዛት የሚያስከትለው ችግር ምንድ ነው? 2. ማህበረሰቡ የሴት ግርዛት ለምን ያደርጋል? 3. የሴት ግርዛት ለመፈጸም ማህበረሰቡ ምን ምክንያት ይሰጣል? 4. የሴት ግርዛትን ለማስቆም ከእኛ ምን ይጠበቃል? 1.2 የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ
  • 28. 28 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ያለዕድሜ ጋብቻ የውይይት ይዘት 1. ያለ ዕድሜ ጋብቻ የሚያስከትለው ችግር ምንድ ነው? 2. ማህበረሰቡ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለምን ይፈጽማል? 3. ያለ ዕድሜ ጋብቻ ማህበረሰቡ ምን ምክንያት ይሰጣል? 4. ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለማስቆም ከእኛ ምን ይጠበቃል?
  • 29. 29 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ 2.1 የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጉዳቶች ዝርዝር ዓላማዎች ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ምክንያት የሚመጡ ጉዳቶች እንድገልጹ ማድረግ፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ የተደነገጉ የኢትዮጵያ ህጎችን እንድያውቁ ማድረግ፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ከሀይማኖት አንጻር እንድረዱ፤ ❖ ማህበራዊ ስነ ምህዳርን እንድገነዘቡ ማድረግ፤ ❖ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን የሚያበረታቱ ማህበረሰብ አቀፍ ልማዶች እንድረዱ ማድረግ። የውይይት መግቢያ በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤ የሴት ግርዛት የውይይት ይዘት ዝናሽ ታርክ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ዝናሽ የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ ትምህርቷን አቋርጣ ለጋብቻ ዝግጅት በእናቷ ግፍት ተገረዘች፡፡ እሷ በተወለድችበት አካባቢ ልጃገረዶች ለጋብቻ ይገረዛሉ፡፡ ማህበረሰቡ የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት ለጋብቻ ዝግጁ ስሆኑ ልጃገረዶች እንድገረዙ ያደረጋሉ፡፡ ከሚሰጡ ምክንያቶች መካከል ንጽና ለመጠበቅ፤ ለግብረ ስጋ ግኑኝነት ምቹ ለማድረግ፤ለባሏ ታማኝ እንድትሆን እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ዝናሽ ምጥ ላይ ረጅም ሰዓት ስለቆየች የመጀመሪያ ልጆዋን የወለደችው በቀዶ ጥገና ነው፡፡ ከወልድ በኃላ በደም ማነስ ታማለች፡፡ ህጻኑም ጡት አልጠባም በማለቱ ህይወቱ አልፋል፡፡ዝናሽ ሁለተኛ ልጆዋን አሁንም በቀዶ ጥገና ወለደች፡፡ 1. በዝናሽ ላይ ምን ጉዳት ደረሰ? 2. በዝናሽ ላይ የደረሰውን ዓይነት ጉዳት እንዴት መከላከል ይቻላል? 3. በአካባቢያችሁ የሴት ግርዛት የሚካሄድበት ዕድሜ ስንት ነው? 4. አልማዝ የተገረዘችው ለምንድን ነው? 5. አልማዝ የተወለደችበት ማህበረሰብ ሴት ግርዛት የሚካሄድበት ምክንያት ምንድነው? ክፍል ሁለት፡ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ን በተመለከተ የእውቀትና የግንዛቤ ክፍተትን መሙላት
  • 30. 30 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ 6. የሴት ግርዛት ልማድን ለማቆም የወንዶች ድርሻ ምን መሆን አለበት? 7. በአካባቢያችሁ በግርዛት ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ሰው አለ? 8. በዝናሽ ልጅ ላይ ምን ጉዳት ደረሰ? ያለ ዕድሜ ጋብቻ የውይይት ይዘት በአልማዝ ታርክ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ አልማዝ የተወለደችው ገጠር ውስጥ ነው፡፡ አንደኛ ክፍል እየተማረች እያለች ወላጆች ለአንድ ባለሀብት በአስራ ስድስት ዓመቷ ዳሯት፡፡ ትምህርቷን በጋብቻ ምክንያት አቋርጣለች፡፡ በተወለድችበት አካባቢ በእሷ ዕድሜ ማግባት የተለመደ ነው፡፡ ምክንያቱም ሳያገቡ የሚቆዩ ሴቶች ማህበረሰቡ ፈሳሽ ያለቀባት፤ቤተሰብ አሰዳቢ፤ ፈላጊ ያጣች ስለሚባሉ ልጃገረዶች ይህን በመፍራት ቶሎ ያገባሉ፡፡ አልማዝ የመጀመሪያ ልጇን ቤት ስትወልድ ታፍኖ ሞቶባቷል፡፡ እሷም ከፍተኛ ደም ስለፈሰሰባት ደም ተሰቷት ከሞት ለትንሽ ተረፈች፡ ፡ አራት ልጆቾን በአካባቢው በሚገኘው ጤና የወለደች ቢሆንም ክትባት አልተከተቡም በዚህ ምክንያት ሁልጊዜ ይታመማሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ለምግብ እጥረት ተዳርገዋል፡፡ ባሏ ሁልጊዜ ይደበደባታል፤ ይሰድባታል፤ቀለብ አይሰጣትም፡፡ ከዚህ የተነሳ ተፋታለች፡፡ 1. ለአልማዝ ጋብቻ ምክንያት የሆነው ምንድን ናቸው? 2. አልማዝ ስንት ዓመት አገባች ? 3. የአልማዝ ልጆች ምን ጉዳት ደረሰባቸው? 4. አልማዝ በጋብቻው ተሰማምታለች? 5. ያለ ዕድሜ ጋብቻ የሚፈጸመው በስንት ዓመት ነው? 6. አልማዝ የተወለድችበት አካባቢ ሰዎች ለማያገቡ ሴቶች ምን ይላሉዝ? 7. አልማዝ ዓይነት ታርክ ለማቆም የወንዶች ድርሻ ምን መሆን አለበት? 8. በአካባቢያችሁ የአልማዝ ዓይነት ታርክ ያለው ሰው አለ? ገራዧ ተብላ የምትታወቀው ይህች ሴት ሞምባሳ ኬንያ ውስጥ ሴቶችን ለመግረዝ የምትጠቀምበትን ምላጭ ይዛ ነው። የሴት ግርዛት ሆን ተብሎ የሴት ልጅን የመራቢያ ክፍል አካል መቁረጥ ማለት ነው።
  • 31. 31 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የዓለም ጤና ድርጅት ብዙ ጊዜ የሴት ልጅ ግርዛት ሲፈጸም የብልት ከንፈሮችን እና ቂንጥርን መቁረጥን ያካትታል ይላል። የግርዛት አይነቶች አራት አይነት የግርዛት አይነቶች አሉ። 1. ክሊቶሪዲክቶሚይ (Clitoridectomy)፡ ይህ ማለት በቂንጥር እና በአከባቢው የሚገኝ ስስ ቆዳ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ማስወገድ ማለት ነው። 2. ኤክሲሺን (Excision)፡ ይህ ማለት ቂንጥርን እና የብልትን የውስጠኛውን ከንፈር ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ማስወገድ ማለት ነው። 3. ኢንፊቢዩሊሽን (Infibulation)፡ ይህ ማለት ቂንጥርን እና የብልት ክንፈሮችን ቆርጦ በመጣል ብልትን በመስፋት የግብረ ስጋ ግንኙነት ምቹ እንዳይሆን ማድረግ ማለት ነው። ይህ ተግባር የሚያስከትለው ህመም ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ለኢንፌክሽን ተጋላጭነትን ከፍ ያደርጋል። በተጨማሪም ሽንት እና የወር አበባ ፍሳሽ በቀላሉ እንዳይወጣ ያደርጋል። 4. ሌላኛው የግርዛት አይነት የሴት ልጅ የመራቢያ አካላትን መውጋት፣ መብሳት፣ መቧጠጥ እና ማቃጠል የመሳሰሉትን ያካትታል። ምንጭ፡ የዓለም የጤና ድርጅት( 2021)። የሴት ልጅ ግርዛት የአመቻች ማስታወሻ
  • 32. 32 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የሴት ግርዛት በሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ምክንያት የሚመጡ ጉዳቶችን ለማስረዳት የችግር ዛፍ መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው።የችግር ዛፍ ሶስት ክፍሎች አሉት። እነሱም ስር፤ግንድ እና ቅርጫፍ ናቸው። 1. ስር፡ የሚወክለው መሰረታዊ የሴት ግርዛት ወይም ያለ ዕድሜ ጋብቻ ምክንያቶች፤ 2. ግንድ፡ የሴት ግርዛት ወይም ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልማድን ይወክላል፤ 3. ቅርጫፍ፡ የሴት ግርዛት ወይም ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጉዳቶችና መዘዞች። ቅርንጫፍ 1/ የጤና ችግር 2/ ስነ ልቦናዊ ጉዳቶች 3/ ማህበራዊ ጉዳት 4. ሰብዓዊ መብት ግንድ ስር ❖ አሉታዊ ወግ ❖ የሀይማኖት ትዕዛዝ ❖ ውበት ለመጨመር ❖ ንጽህና ለመጠበቅ፤
  • 33. 33 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ በልጅነት)
  • 34. 34 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የአመቻች ማስታወሻ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንዲቀር የኃይማኖት አባቶች ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ አመቻች በደንብ ማስረዳት አለበት። በውይይቱ ላይ በቀበሌው ከሚገኙት ቤቴ እምነቶች ቁልፍ ሰዎችን በመጋበዝ የቤቴ እምነታቸውን አስተምሮ እንድገልጹ ማድረግ አስፈላጊ ነው። የኃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸውን የሚጎዱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል ጉልህ ሚና መጫወት አለባቸው። ስለዚህ እነሱን የማህበረሰብ ውይይት ላይ ማስተፍ ወሳኝ ነው። በተጨማሪ የጤና ባለሙያዎችና የጤና ኤክስቴሽን ሠረተኞችን በመጋበዝ በጤና ጉዳቶችን እንዲያስረዱ መጋበዝ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የአገርቱ ህጎች የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንደምከለክሉ ለማስረዳት የህግ ባለሙያን በመጋበዝ ውይይቱ ላይ ተጨማሪ ገለጻ እንድያደርግ ማድረግ ተገቢ ነው። የውይይት መግቢያ በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤ የውይይት ይዘት ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ በቤተ እምነቶች እንዴት ይታያል? ❖ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በተለይም የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል የኃይማኖት አባቶች ኃላፍነት ምን መሆን አለበት ? ❖ ብሔራዊ ህጎች ሰለ ያለ ዕድሜ ጋብቻንና ግርዛት ምን ይላሉ? ❖ በቤተ እምነቶች እስከአሁን ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በተለይም የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል ያላቸው ልምድ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ህጎች ( National laws) የኢትዮጵያ ሕጎች በሕጉ የተመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮች የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 7 ፡ ወንዱም ሆነ ሴቷ 18 ዓመት ሳይሞላቸው ማግባት አይችሉም። 2.2 ኃይ ማ ኖ ት እና ህግ ( Religion and Law)
  • 35. 35 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ 2.3 አሉታዊ ወጎች (Negative social norms) የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 565፡ ማንም ሰው በየትኛውም ዕድሜ ክልል የምትገኘውን ሴት መግረዝን ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል፤ አንቀጽ 648፡ ለአካለ መጠን ያልደረች ልጅ ማግባት ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል፤ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 14፡ ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገረሰስ በሕይወት የመኖር፤የአካል ፟ ደህንነት መብት አለው። አንቀጽ 16፡ ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው። ዝርዝር ዓላማዎች ❖ ተሳታፍዎች ስለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜጋብቻ በሚመለከት አሉታዊ ወጎችን ለማረም የድርሻቸውን እንድወጡ ማድረግ፤ ❖ ስለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ያሉ አሉታዊ ወጎች እንድለዮና እንድታረሙ ማድረግ፤ ❖ ስለሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ የተሳሳቱ አሉታዊ ወጎች ለመቀየር ትምህርት ቤቶች፤ የሀይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግሎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን መረዳት፤ የውይይት መግቢያ በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤ ውይይት ይዘት 1. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለማስቆም አስቸጋር የሚያደርጉ ምክያቶች በእናተ አካባቢ ምን ምን ናቸው? 2. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ የሚያበረታቱ አሉታዊ ወጎችን ለማረም ምን መድረግ አለበት? 3. አሉታዊ ወጎችን ለማረም የእናንተ ድርሻ ምን መሆን አለበት?
  • 36. 36 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ 4. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ አሉታዊ ወጎችን ለማስቀረት ግለሰብ፤ ማህበረሰብ፤ ትምህርት ቤቶች፤ የሀይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግሎች ድርሻ ምን መሆን አለበት? የአመቻች ማስታወሻ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ አሉታዊ ወጎች እንደየ አካባቢው ይለያያል። በመሆኑም የውይይቱ ተሳታፍዎች በአካባቢያቸው ያለውን ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ተመሰርተው እንድወያዩ ማድረግ ያስፈልጋል። ያለ ዕድሜ ጋብቻን በተመለከተ የአካባቢያቸውን አሉታዊ ወጎችና ምክንያቶች ከሚከተሉት ሊመረጡ ይችላሉ፤ ❖ ድህነት፤ ❖ ባህል እና ልማድ፤ ❖ ደካማ የሕጎች አተገባበር፤ ❖ የግንዛቤ እጥረት፤ ❖ የልጃቸው የወደፊት ሁኔታ አለመተማመን፤ ❖ የትምህርት እጥረት፤ ❖ በሴት ልጆች ላይ የደህንነት ስጋት እና የግብረ-ሥጋ ግንኙነትን መቆጣጠር፤ ❖ የልጅነት ጋብቻን የሚቃወሙ ሕጎች ግንዛቤ ማነስ፤ ❖ የጥሎሽ ስርዓት፤ ❖ የህብረተሰቡ ጫና፤ ❖ ልጃገረዶችን እንደ የቤት ውስጥ ረዳት አድርገው መቁጠር፤ ❖ በጦርነት እና በግጭት ጊዜ አለመረጋጋት፤ ❖ ለሴት ልጆች የትምህርት እጦት እና የስራ እድሎች። ስለሴት ግርዛት የአካባቢያቸውን አሉታዊ ወጎችና ምክንያቶች ከሚከተሉት ልመርጡ ይችላሉ፤ ❖ እቃ ሰብራለች፤ ❖ ያልተገረዘች ሴት ትሰደባለች፤ ❖ ያልተገረዘች ሴት ክብር የላትም፤ ❖ አትረጋጋም ሁል ጊዜ ወስብ ትፈልጋለች፤ ❖ ወንድን ታሸንፋለች በወስብ ወቅት፤
  • 37. 37 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ 2.4 ማህበራዊ ስነ ምህዳር ሞደል (Socio-ecological model) ዝርዝር ዓላማዎች ❖ በግለሰብ፤በቤተሰብ፤በማህበረሰብ እና ተቋም ያለው አመለካከት፤እውቀት፤ልማድ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ለመከላከል ወይም ምክንያት የመሆን ሚና መገንዘብ፤ ❖ በእያዳንዱ ደረጃ ያለውን የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንደቀጥል የሚያደርጉ ምክያቶች እንድለዩ ማድረግ፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የሚረዱ ምቹ ሁኔታዎችን እንድለዩ ማድረግ፤ ተሳታፍዎች የራሳቸውን ሚና በግለሰብ፤በቤተሰብ፤በማህበረሰብ እና ተቋም ደረጃ እንድገልጹ ማድረግ፤ ❖ የወንድ ብልት ይመስላል፤ ❖ ልጅ ሲወለድ ቂንጥር አፍንጫ ስነካ ይሞታል፤ ❖ ንጽና ለመጠበቅ ❖ ውበት ለመጨመር ❖ በውስብ ወቅት ለባል ምቹ ለማድረግ ❖ የሀይማኖት ትዕዛዝ ❖ የጋብቻ ቅድመ ሁኔታ፤ ❖ ወንዶች ያልተገረዘችን ሴት አያገቡም፤ ❖ ያልተገረዘች ሴት በወልድ ወቅት ትቸገራለች፤ ❖ ያልተገረዘች ሴት በቀላሉ በሽታ ትያዛለች፤ ❖ ከዘር ዘር ሲተላለፍ የመጣን ባህልና ወግ ለማክበር፤ ❖ የማንነት መገለጫ ነው፤ ❖ እናቶቻችን ተገርዘው ምን ሆኑ? ❖ የማህብረሰብ አስተሳሳብ ❖ ኃይማኖት፣ ❖ ከንጽህና ጋር የተያያዘ የተሳሳተ ዕምነት፣ ❖ ድንግልናን ለማቆየት በማሰብ፣ ❖ ሴት ልጅ ትዳር እንድታገኝ በማሰብ ❖ የወንድ ልጅ የወሲብ እርካታን ለመጨመር።
  • 38. 38 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የአመቻች ማስታወሻ 1. ግለሰብ ፡ እውቀት፥ አመለካከት፥ አስተሳሰብ እና ልማድ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ላይ ከፍተኛ ሚና አላቸው። 2. ቤተሰብ፡ አመለካከት፥ አስተሳሰብ እና ልምድ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ይወስናሉ። 3. ማህበረሰብ፡ አሉታዊ ወጎች፤ ልማዳዊ ድርጊቶች ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት የመከላከል ወይም የማስቀጠል አቅም አላቸው። 4. ተቋማማት፡ ባህላዊ አደረጃጀቶች፤ ጤና ተቋማት፤ትምህርት ቤቶችና ሀይማኖት ተቋማት የመሳሰሉት ሥርዓተ ጾታ መሠረት ያደረገ ጥቃት እንድቀጥሉ ወይም እንድቀሩ የማድረግ ተጽኖአቸው ከፍተኛ ነው። 5. አገር፡ ህጎች፥ ፖሊሲዎች፥ የመንግስት አሰራሮች አለመኖር ወይም በትክክል አለመተግበር። አገር ተቋም ማህበረሰብ ቤተሰብ ግለሰብ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት (የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ) ማህበራዊ ስነ ምህዳር
  • 39. 39 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የአመቻች ማስታወሻ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ሰባት የሀብት ዓይነቶች አሉ። እነዚህ የሀብት ዓይነቶች አንድ ማህበረሰብ የራሱን የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት ይረዳሉ። የማህበረሰብ ሀብቶች የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከልና ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ይረዳሉ። 1. የሰው ሀብት፡ የእያንዳንዱ ሰው እውቀት፤አመለካከት፤ ልምድ እና ችሎታን ያጠቃልላል። 2. ማህበራዊ ሀብት፡ ማህበራዊ ትስስር፤ አዋታዊና አሉታዊ ወግ፤ ልማድ፤ እድር፤የሀይማኖት ተቋማት፤ ትምህርት ቤቶች፤ የጤና ተቋማት፤ የቀበሌ አስተዳደር ቢሮዎች። 3. የፖሊቲካ ሀብት፡ በቀበሌ ውስጥ ያለው ሀብት ምን ላይ መዋል እንዳለበት ልወስን ይችላል። 4. የገንዘብ ሀብት፡ ቀበሌው ውስጥ ያለው በገንዘብ ልገመት የሚችል የሀብት መጠን። ዝርዝር ዓላማዎች ❖ አከባቢ በቀል የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የሚረዱ እውቀቶችን መለየት፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል በማህበረሰብ ደረጃ የሚገኘውን ሀብት እንዲለዩ ማድረግ፤ ❖ በማህበረሰብ ደረጃ ያለውን ሀብት የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል እንደሚረዳ እንድገነዘቡ ማድረግ፤ ❖ በውይይት የተለዩ የማህበረሰብ ሀብቶችንና እውቀቶችን የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል ወደ ትግበራ መለውጥ፤ ❖ በቡድን 4 እስከ 5 ሰው ሆነው እንድወያዩና የትኞቹ ሀብቶች የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል እንደሚረዱ እንድያስረዱ ማድረግ፤ የውይይት መግቢያ በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንዲቀርብ ማድረግና አስተያየት እንዲሰጥበት ማድረግ፤ የውይይት ይዘት 1. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የሚረዳ ምን ሀብት አለ? 2. እናንተ አካባቢ ያለውን የሀብት ዓይነት ምንድን ናቸው? 3. የማህበረሰቡን ሀብት እንደት የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መከላከል ያችላል ? ክፍል ሶስት፡ የማህበሰብ ደረጃ ሀብትን በማቀናጀት የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መከላከል ( Mobilizing local resources)
  • 40. 40 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ክፍል አራት፡ የጋራ እቅድ ( Joint planning) ዝርዝር ዓላማዎች ❖ የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋበቻን ለማስቀረት በማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙትን ሀብቶች በመጠቀም ውሳኔ ማሳለፍ፤ ❖ የአካባቢውን ሀብት መሰረት በማድረግ የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመከላከል እቅድ ማዘጋጀት፤ ❖ የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ የማህበረሰቡ ችግሮች መሆናቸውን መቀበል እና መፍትሄ መፈለግ ላይ ትኩረት ማድረግ፡፡ 4.1 ማህበራዊ ውሳኔ (Community decision) ዝርዝር ዓላማዎች ❖ የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋበቻንለማስቀረት በማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙትን ሀብቶች በመጠቀም ውሳኔ ማሳለፍ፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልምድ መሰረታዊ የሆኑ ምክያቶችን ለይቶ ውሳኔ እንድተላለፍ ማድረግ፤ ❖ የተወሰነው ውሳኔ እንደት ተግባራዊ እንደምሆን የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥ፤ ❖ ውሳኔዎችን ለማስፈጸም የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፍዎች ሚና ምን መሆን እንዳለበት ስምምነት ላይ መድረስ፤ ❖ የወጣውን ውሳኔ ለማስፈጸም ስልት መቀየስ፤ ❖ የጸደቀውን ውሳኔ መላውን የቀበሌ ህዝብ ስብስባ በመጥራት ማሳወቅ፤ የውይይት መግቢያ በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤ 5. ባህላዊ ሀብት፡ሽምግልና፤ ባህላዊ አስተዳደር፤ ባህላዊ እርቅ፤ ባህላዊ የግጭት አፈታት፤ ታላቅን ማክበር፤ ባህላዊ ማዕቀብ። 6. ቁሳዊ ሀብት፡ በሰው የተሰሩ ሀብቶችን ይመለከታል። ባህላዊ መሰብሰቢያ ቦታዎች፤የቤት ቅርሶች፤ ልብሶች፤ የስልክ መስመሮች፤መንገድ፤ የመንግስት መ/ቤቶች፤ የጤና ተቋማት፤መንገድ፤መብራት፤ ፋብርካ። 7. የተፈጥሮ ሀብት፡ ደን፤ውሀ፤አየር፤ እንስሳት፤የተለያዩ የእጽዋት።
  • 41. 41 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የውይይት ይዘት 1. ምን ዓይነት ማህበረሰብ አቀፍ ውሳኔዎችን እናስተላልፍ? 2. በማህበረሰብ ደረጃ ልተገበር የሚችል ውሳኔ የትኛው ነው? 3. የተወሰነውን ውሳኔ ለመተግበር የትኛው ሀብት እንጠቀም? 4. የተወሰነው ውሳኔ ለመተግበር ምን ዓይነት ስልት እንጠቀም? 5. ውሳኔውን ለማስፈጸም ከሀይማኖት አባቶችና ከባህል አባቶች ምን ይጠበቃል? የአመቻች ማስታወሻ የማህበሰብ ውይይት የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ የማህበረሰቡ ችግሮች መሆናቸውን መለየትና በማህበረሰቡ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ቁርጠኝነትን ማበረታታት አለበት። ማህበራዊ ውሳኔዎች ይህንን ውጤት ለማምጣት አስተዋጽኦ ያድርጋሉ። በማህበሰብ ውይይት የሚተላለፉ ማህበራዊ ውሳኔዎች ማህበራዊ ማዕቀብ እና ለህግ አሳልፎ መስጠትን ሊያካትቱ ይችላሉ። የውሳኔው አይነት እንደችግሩ መጠንና ስፋት ሊለያይ ይችላል። የሚውሰኑት ውሳኔዎች ከታች የተዘረዘሩትን እና ሊሎችንም ሊሆኑ ይችላሉ፣ ❖ ከቤቱ/ቷ እሳት አንጭርም፣ ❖ ከእድርና ከሌሎች ማህበራዊ ጉዳች መገለል፣ ❖ ለህግ አሳልፈን እንሰጣለን፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልምድ በቀበሌያችን አይደረግም በማለት የአቋም መግለጫ ማውጣት፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልምድ ምክንያት ችግር የደረሰባቸውን ሴቶችን መርዳት፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ልምድ ምክንያት ችግር የደረሰባቸውን ሴቶችና ልጃገርዶችን የት የህግና የጤና አገልግሎት እንደሚያገኙ መርዳት ወዘተ። ❖ የገንዘብ ወይም ተጣጥኝ ቅጣት (ሀያ ፍየሎች፤ ሶስት ግመል፤ አምስት በጎች የመሳሰሉት።፤ ❖ በባህል ሽማግሌዎች ድርጊቱን መወገዝ፤ ቁልፍ የማህበረሰብ ውይይት ውሳኔዎች ማስፈጸሚያ ባለድርሻ አካላት ❖ የኃይማኖት አባቶች፡ በሀይማኖት በዓላት ወቅት በተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ ለተከታያቸው የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች ያስተላልፋሉ። የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸውን ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ይጠብቃሉ፡፡ ሥርዓተ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ተከታዮቻቸው ላይ መጠነ ሰፊ የጤና፤ የኢኮኖሚ፤የሥነ ልቦና እና ማህበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትሉ አውቀው የመንፈሳዊ አባትነታቸውን ሚና እንድጫቱ ማስገንዘብ ወሳኝ ነው። በተለይ የሴት ግርዛት እና ዕድሜ ጋበቻ ተከታዮቻቸው ላይ መጠነ ሰፊ የጤና፤ የኢኮኖሚ፤የሥነ ልቦና እና ማህበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትሉ አውቀው የመንፈሳዊ አባትነታቸውን ሚና እንድጫቱ ማስገንዘብ ወሳኝ ነው።
  • 42. 42 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ 3.2 የዕቅድ ዝግጅት (Planning phase) ❖ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች፡ በቀበሌው የስብስባ ቀን ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች ያስተላልፋሉ፡፡ ❖ ዕድር፡ በእድር ስብስባ ላይሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶችን ያስተላልፋሉ፡፡ ❖ የሀገር ሽማግሌዎች፡ በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶችን ያስተላልፋሉ፤ ❖ የልማት ሰራዊት፡ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶችን ያስተላልፋሉ፤ ❖ የግብርና ባለሙያዎች፡ በግብርና ስራዎች ወቅት ስለ ሴት ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች ያስተላልፋሉ። ❖ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፡ በክትባት ቀን ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች ያስተላልፋሉ፡፡ ❖ ትምህርት ርዕሰ መምህራን፡ በሰንደቅ ዓላማ ሥነ ሥርዓት ወቅት ለተማሪዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ ቁልፍ መልእክቶች ያስተላልፋሉ፡፡ ❖ የጤና ባለሙያዎች፡ የጤና ትምህርት ርዕስ አንዱ ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች ያስተላልፋሉ፡፡ ❖ ፍርድ ቤቶች፡ ለፍትህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች ያስተላልፋሉ፡፡ ❖ ፖሊስ፡ ለህግ ታራምዎችና ለፖሊስ አገልግሎት ፈላጊዎች ስለ ሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክቶች ያስተምራሉ። የቁልፍ መልእክት ምሳሌ፡ ❖ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ሴት ልጆችን ከትምህርት እና ራሳቸውን ከመቻል ያስቀራቸዋል! ❖ የሴት ግርዛት ሴቶችን በወሊድ ጊዜ የጤና እክል ይፈጥራል! ❖ ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የበኩሌን እወጣለሁ! ❖ ህብረተሰቡን በማስተማር ያለ ዕድሜ ጋብቻና ግርዛትን እንከላከል! ዝርዝር ዓላማዎች ❖ እቅዱን የሚያዘጋጅ ጥምር ቡድን ከሁሉም የማህበረሰብ ውይይት አባላት ማዋቀር፤ ❖ ጥምር ኃይሉ እቅዱን እንድያዘጋጅ ማድረግ፤
  • 43. 43 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የአመቻች ማስታወሻ ተግባራት እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መታቀድ አለባቸው፡፡ ለምሳሌ፡ 1. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን የጤና ጉዳቶችን በትምህርት ለተማሪዎች ማስተላለፍ:: 2. የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል የወላጅ ሚና ላይ በገበያ ቀናት መልእክት ማስተላለፍ:: 3. በቤተ እምነቶች የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል ቁልፍ መልእክቶችን ማስተላለፍ፡፡ የመሳሰሉት ❖ የታቀደውን እቅድ የማስፈጸሚያ ስልት ፟ እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አባላቶች በደንብ ተወያይተው መለየ አለባቸው፡፡ ❖ በአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት የሚሰራ እቅድ እንዲጋጅ ማድረግ፤ ❖ ስለ እቅዱ ክትትልና መለካት መወያየት፤ ❖ የወጣውን እቅድ ለቀበሌው ማሳወቅ፤ ❖ ለእቅዱ ውጤታማነት የማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ ሀብቶች ሚና ላይ መወያየት፤ ❖ የተዘጋጀውን እቅድ መላው የቀበሌ ሕዝብ እንዲሰበሰብ ማድረግና እንድጸደቅ ማድረግ፤ ❖ የተዘጋጀውን እቅድ መላው የቀበሌ ሕዝብ እንድሰበሰብ ማድረግና እንድጸደቅ ማድረግ፤ የውይይት መግቢያ በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤ የእቅድ ቅድመ ዝግጅት ትንተና 1. እቅዱን ለማስፈጸም የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፊዎች ጠንካራ ጎኖች 2. እቅዱን ለማስፈጸም ያሉ ምቹ አጋጣሚዎች 3. እቅዱን ለማስፈጸም በማህበረሰብ ውይይት ተሳታፊዎች መሻሻል ያለባቸው ነጥቦች 4. እቅዱን ለማስፈጸም ያሉ ስጋቶች
  • 44. 44 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ለምሳሌ፡ 1. የእድር ስብስባ ላይ ሰዎች እንድወያዩ ሀሳብ ማቅረብ፤ 2. በጸሎት ቤቶች ለውይይት ማቅረብ፤ 3. በሀይማኖታዊ በዓላት ወቅት መልእክቶቸን፤ 4. በቀበሌው ስብስባ ላይ ለውይይት ማቅረብ፤ የመሳሰሉት
  • 45. 45 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የሴት ግርዛት እና ዕድሜ ጋበቻን ለማስቀረት የማህበረሰብ እቅድ ቅጽ( ቅጽ ሰባት) ግብ፡ በ 2015/2016 ማህበረሰባችን ውስጥ ስለ የሴት ግርዛት እና ዕድሜ ጋበቻ ግንዛቤ 70% ማሳደግ። የሴት ግርዛት እና ዕድሜ ጋበቻ ዝርዝር ተግባራት ፈጻሚ ባለድርሻ ቦታ ሀብት ልያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች ለምሳሌ፡ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ቁልፍ መልእክት ማስተላለፍ የእድር ሊቀመንበር የእድር ቤት የእድር ሊቀመንበር ሰው መስማት ላይፈልግ ይችላል ማሳሰቢያ፡ 1. ዝርዝር ተግባራት በአካባቢው ተጨባጭ የሚሰሩ መታቀድ አለባቸው፡፡ 2. በምሳሌው መሰረት መታቀድ አለበት፡፡ ቀበሌ ቀን የአመቻች ስም ፊሪማ የቀበሌው ማህተም የተከናወኑ ተግባራት ወርሃዊ ሪፖርት ማድረግያ ቅጽ ( ቅጽ ስምንት) ተ/ቁ የታቀደው ተግባር ክንውን/የተሰራው ያልተሰራው ቀጣይ ተግባራት 1 2 ቀን የአመቻቹ ስም የቀበሌው ማህተም
  • 46. 46 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ ክፍል አምስት ፡ የዕቅድ ትግበራ ምዕራፍ ( Implementation phase) ዝርዝር ዓላማዎች ❖ የወጣውን እቅድ ለመተግበር ትምህርት ቤቶች፤ጤና ተቋማት፤ስብሰባ እና ሕዝብ የተሰበሰበት ቦታዎች፤ የሀይማኖት ተቋማት፤ የገበያ ቀናትንና እድሮችን በመጠቀም የሴት ግርዛት እና ዕድሜ ጋበቻን ጉዳቶችና መከላከያ ቁልፍ መልእክቶችን ማስተላለፍ፤ ❖ የወጣውን እቅድ በመተግበር እንደ አስፈላጊነቱ በአካባቢው/ቀበሌው አስተዳደር ጋር በመሆን መከለስ፤ ❖ የሴት ግርዛት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለማሰቀረት የሚረዱ ቁልፍ መልእክቶች በአካባቢው ቋንቋ ማስተላለፍ፤ ❖ በእቅዱ ትግበራ ላይ መወያየትና የማህበረሰብ ውይይት አባላት የስራ ድርሻ እንድከፋፈሉ ማድረግ፤ ❖ የእቅድ ማስፈጸሚያ ሰልትን ላይ በደንብ መወያየትና እንደ አካባቢው ተጨባጭ የሚሰራ ስልትን መምረጥ፤ ❖ ለባለድርሻ አካላት የሚሰሩትን ሥራ በፍላጎት እንዲመርጡ መስማማት፤ ❖ የባለድርሻ አካላት ያላቸውን አስተያየት እንድሰጡ እድል መስጠት። የውይይት መግቢያ በባለፈው የውይይት ርዕስ ላይ የታቀደውን የእንዳንዱ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ ማድረግና አስተያየት እንድሰጥበት ማድረግ፤ የትግበራ ውጤት መከታተያ ( Performance monitoring template) ቅጽ (ቅጽ ዘጠኝ) የትግበራ ውጤት ጠቋሚ የመረጃ ምንጭ ፈጻሚ የመረጃ መሰብሰቢያ መንገድ መረጃ ሰብሳቢ በያለ ዕድሜ ጋብቻ የተላለፈ ቁልፍ መልእክት ቁልፍ መልክት የሰሙ ተማሪዎች በቁጥር የሰልፍ ላይ ፎቶ ር/መምህር ቃለ መጠይቅ፤ወርሀዊ ሪፖርት የቀበሌው አመቻች ማሳሰቢያ፡ 1. ይህ የትግበራ ውጤት መከታተያ በምሳሌው መሰረት ይሞላል። 2. ስልት ማለት፡የወጣውን የጋራ እቅድ ማስፈጸሚያ መንገድ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ በጥምቀት ቀን ቁልፍ መልእክት በሴት ግርዛት ላይ ለምዕሚናን ማስተላለፍ እና የመሳሰሉት፡፡ 3. የማህበረሰብ ውይይት አባላት የአፈጻጸም መለኪያ ጠቋሚ በስምምነት መሰየም አለባቸው፡፡
  • 47. 47 | P a g e የማህበረሰብ ውይይት የአመቻች መምሪያ የውይይት ይዘት ክፍል ስድስት፡ አፈጻጸም መገምገም እና አጠቃላይ ሂደትን መሰነድ (Performance review and documentation) ዝርዝር ዓላማዎች ❖ አጠቃላይ የማህበረሰብ ውይይት ጠንካና መሻሻል ያለባቸውን ነጥቦች መለየት፤ ❖ የቀበሌ ሕዝብ ጋር በመሆን በአለፉት ስድስት ወራት በማህበረሰብ ውይይት ወቅት የተገኙ ውጤቶችና ለውጦችን መገምገም፤ ❖ የማህበሰብ ውይይት አባላት በውይይቱ ምክንያት በአለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የመጡ ለውጦች መለካትና መገምገም፤ ❖ በውይይት ውቅት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮችና ለውጦችን መለየትና መሰድ፤ ❖ ያጋጠሙ ችግሮች መለየትና እንደት እንደተፈቱ ለቀጣይ ትምህርት መውሰድ፤ ❖ በውይይቱ ውቅት የሚሰሩና የማይሰሩ አካሄዶችን መለየትና ለቀጣይ ትምህርት መውሰድ፤ ❖ የማህበረሰብ ውይይት መረጃዎች ማጠናከር። የውይይት መግቢያ የታቀደው አጠቃላይ የማህበረሰብ ውይይት አፈጻጸም እንድቀርብ ማድረግና የመጡ ለውጦችን መገምገም ❖ የማህበረሰብ ውይይቱ ላይ ምን መሻሻል አለበት? ❖ የማህበረሰብ ውይይትቱ ምን ጠንካራ ጎን አለው? ❖ በዚህ ውይይት ላይ በመሳተፋችሁ ምን ተሰማችሁ? ❖ ማህበረሰብ ውስጥ በውይይቱ ምክንያት ምን ለውጥ መጣ? ❖ በማህበረሰብ ውይይቱ ላይ ምን ማነቆች ነበሩ? ❖ በማህበረሰብ ውይይት ወቅት ምን ምቹ አጋጣሚዎች ነበሩ?