SlideShare a Scribd company logo
1 of 59
የማስተማር ዘዴ
አዘጋጅ፡- ወ/ዊ በለጠ ሀብተጊዮርጊስ
ክፍል አንድ፡- መግቢያ
1፡1. ጥቅል
• አሁን ያለችው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የምታምነውን አውቃ ፣
ያንንም እውቀት በሚገባ አደራጅታ ማስተላለፍና ስትኖረው መገኘት ተገቢ
ነው ፡፡
• የሚያምነውን የማያውቅ ፣ ያመነውን መኖር የተሳነውና አቅርቦቱም
የተዘበራረቀበት ግለሰብም ሆነ ክርስቲያን ማህበረሰብ መርከብ ያለመሪ
እንደሚጉዋዝና ህሊናው እንደናወዘ ብኩን መሆኑ የማይቀር ነው ፡፡ ለዚህም
ጤናማ ሆኖ የመገኘት ዓይነተኛ ጉዳይ ቀዳሚ ሚና መጫወት የሚገባቸው
የቤተክርስቲያን መሪዎች ናቸው ፡፡
• የእምነትን እውቀት በጥራት መያዝ ፣ ያንን እውቀት አስጠብቆ መኖር ፣
ይህንኑ ጉልበት በተደራጀ መልኩ ጥሩ የሚባል የማስተላለፊያ ክህሎትና
በዚህ ተለዋዋጭ ዘመን የተረጋጋ የቤተክርስቲያንን የእውቀት አምባ
ለመገንባት የሚያስችል ብልሃትን ዓላማ አድርጎ መሥራት የሚጠበቅበትም
ያው ከእግዚአብሔር ዘንድ ትክክለኛ ጥሪ ያለው የቤተክርስቲያን አመራርና
የአገልግሎት ክፍል ነው ፡፡
• በሥነ ምግባር የታነጸና የራሱን በሥራ የሚተረጎም እሴት ይዞ
የሚንቀሳቀስ የመሪዎች ሠራዊት ደግሞ ይህንን ለማድረግ
አይቸገርም ፣ ቢቸገርም እንዴት እንደሚታረም ያውቃል ፡፡
ኃላፊነቱንና ተጠያቂነቱን እንዴት እንደሚወጣው ገብቶታል
ተብሎ የሚጠበቅ ነውና!!
• ትኩረት ተነፍጎአቸው የሚገኙት የተመሪና ተማሪ ፍላጎቶችም አሳሳቢ
ከሆኑ ሰንብተዋል፡፡ የእውቀቱ መገኘት ፣ የተገኘውን የእውቀት ይዘት
ማስተላለፍ ፣ በተደራጀ መልክ ተዘጋጅቶ በሚቀመጥ መልኩ ተሠርቶ
አሻራ መተው እንደተጠበቀ ሆኖ የተመሪውን ፍላጎቶች ባማከለ
መልኩ መሥራት ሌላው አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው ፡፡
• አብዛኛው የጽሁፍም ሆነ የመድረክ አቅርቦት ጸሎት፣ጥናትና
ምርምር፣ የአዋቂዎች (ምሁራን) ምክክር፣ላሉበት ጊዜና የአቅርቦቱ
ተቀባዮች እንዲሆን አውዳዊነት አይታይበትም፡፡
• በፈንታው ግልብ በሆነ የአቅርቦት ሂደት የላይ የላዩ ብቻ እየተነካካ
ሁነኛ ለውጥና የሚዳሰስ የዓይነትና የጥራት እድገት እየጠፋ፣ግንኙነት
እየተጎሳቆለ፣ክርስትናችን የቆዳ ጥልቀት ያህል ሆኖ መገኘቱ
ባልተጭበረበረ መልኩ የተገለጠ ነው፡፡
በዚህም ምዕመናን
• ስሜታቸው ብቻ የሚፈልገውን፣
• ሊወቀሱበትና ሊለወጡበት የማይችሉበት ስብከት ወይም ትምህርት
እየቀረበ
• በሐቅና በጽድቅ ፊት ልፍስፍስ ምእመናንን አትርፈንበታል፡፡
• ምእመናኑም የምቾት ጠርዛቸውን ብቻ የሚያስቡበትንና የክርስቶስ
መስቀል ሥርዓት ተካፋይ መሆናቸውን የሚያስረሳ ስብከትና
ትምህርት ይሰጣቸዋል
• በክርስትና ሕይወታቸው ጥንቁቅና ከክፋት የጸዱ እንዲሆኑ
የሚረዳቸውን እውነታ ማቅረብም ደንታ የሚሰጠን እንዳልሆነ
ይስተዋላል፡፡
• ይህን ሁሉ የኅሊና ወቀሳ አጥተንበት ብልጥግናቸውን ብቻ
እንዲያስቡና ኃላፊነታቸቸውን እንዲዘነጉ ማድረግ ላይ አውቀንም ሆነ
በስህተት ትኩረት መሰጠቱ ችግራችን ሆኖ ሰንብቶአል፡፡
• ለዚህም ጸጸት የሚባል አልፈጠረብንም፡፡
• ለዚህ ሁሉ የሚሆነን አንዱ ምላሽ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከላይ
እንዳየን የዕውቀትን አምባ መሥራት አስፈላጊ ይሆናል፡፡
• ይህን ለማድረግ የሚረዳን ደግሞ ቤተክርስቲያን “ማስተማር”
የሚለውን እውነት በዓጽንኦት ማስመር ስትችል ነው፡፡
• ይህንኑ ጉዳይ በሥራ ለመተርጎምም አገልጋዮችዋ የማስተማር
ክህሎትንና ሊኖረው የሚገባውን የፍሰት ዘዴ ሊላበሱ ይገባል፡፡
1፡2. አንዳንዶች ለማስተማር ይረዳሉ ብለው
የሚከተሉአቸው መንገዶች አሉ፡፡ ከነዚህም፡-
1፡2፡1. አራት የማስተማር ዘዴዎች
ሀ) መምሕር ተኮር፡- ይህ መምህሩ የሚሠጠው ነገር ላይ
ብቻ ያተኮረ፣ መምህሩን እንደ ባለሥልጣን ብቻ
የሚስል፣ የሚፈልገውን ጠይቆ የሚመዝንበትና
በፈለገው ጊዜ ብቻ የሚከውንበት ወዘተ. ነው፡፡
ለ) ተማሪ ተኮር፡- ይህ ዘዴ ተማሪው ጥያቄ
የሚመልስበት፣ ችግር ፈቺ ለመሆን የሚጥርበት፣
የራሱን ጥያቄ የሚቀርጽበት፣ ውይይትን ሙግት
የሚሠራበት ነው፡፡
ሐ) ይዘት ተኮር፡- በዚህ የምናገኘው ተማሪው
መሠረቱ የጠበቀና የሚጋፈጠውን ዕውቀት
ለማግኘት የተደራጀ ትምህርት ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡
ትኩረቱ አሳቦች፣ ጽነሰ-አሳቦችና መርሆዎች ላይ
ይሆናል፡፡ ተማሪው ትምህርቱን ለትምህርቱ ሲባል
ብቻ ይማረዋል
መ) ተሳትፎአዊ/በይነተገናኝ/Interactive ፡-
ተማሪው በዚህ ዘዴ ያገኘውን ክህሎት መጠቀሚያና
ማዳበሪያ ጊዜ አድርጎ የሚከውንበት፣ በራሱ
ተነሳሽነት ለማደግ እመርታ የሚያሳይበት ነው፡፡
በዚህ ጊዜም ነው መምህሩ የተማሪውን የሚጨምር
ዕውቀት እየመዘነ በተለያየ ጊዜ እንደየ አቅሙና
ግለሰቡ መረዳት እንደ ሚያስፈልገውም ግብአት
የሚሠራበት ሂደት የሚሆነው
1፡2፡2. የማስተማር ደረጃዎች
ሀ) ሠርቶ ማሳያ
 የመምህሩን ችሎታ፣ የትምህርቱን ይዘት ጠቀሜታ፣ ያ ትምህርት
አምጥቶት ያለውን ውጤት ማገናዘቢያ ነው፡፡
 የሚዳሰስ፣ በመረጃ ሊቀርብ የሚችል፣ ቀጣይነት ባለው መንገድ
የተሠራ መሆኑን ማመላከቻ፣ ማሳየት የሚቻል (ለምሳሌም
አኑዋኑዋር ወይም ልኬት ያለው ውጤት ማቅረቢያ) ነው፡፡
ለ) አፍርሶ መገንባት (Deconstruction):-
 በአንድ በኩል ማብጠልጠልና ማጣጣል ማለት ሲሆን በሌላ በኩል
ደግሞ በሌላ አዲስ መንገድ ለመቅረጽ መቻል ማለት ይሆናል
ሐ) በመረዳት አቅም ሐቅን መጨበጥ (understanding with the
power of intellect)
 ይዘቱን (የተሰጠውን እውነት) ማግኘት መቻል፣ ቁምነገሩን አግኝቶ
የራስ ማድረግ
መ) ድርጊትን መፈጸም
 ቁምነገሩን በሥራ ላይ ማዋል፣ የጠራ አፈጻጸምን ማሳየት
1፡3. ሦስት ዘይቤዎች (Styles):-
ሀ) ምራ
 ለተማሪዎችህ ቀጥተኛ ምሪት ስጥ፣ ምን እንደሚያደርጉም ንገራቸው
ለ) ተወያይ
 ጥያቄ ጠይቅ፣ ዝም ብለህም ስማ
ሐ) ወክል
 ተማሪዎችህን አስታጥቃቸው
 ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ጊዜ የትምህርት ማሰልጠኛዎችና ሌሎቸም የትምህርት
መስመሮች እውነትን ለማስረጽና በሥራ የሚተረጎምን ዕውቀት ለማስጨበጥ
የክርስቶስን የማስተማር ዘዴ የራስ በማድረግ ላይ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡
ክፍል ሁለት፡- ትርጉም ለውጥ አምጪ ግብ ማበጀት
2፡1. ትርጉም
 ስለ ትርጉም ስናስብ ደህና የሚሆነው “መምህር” የሚለውን እሳቤ
ቅድሚያ በመስጠት መጀመር ስንችል ነው፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት
“መምህር” የሚለውና የእንግሊዘኛ መጠቀሚያ የሆነው ቃል
ከአንግሎ ሳክሰን ቲካን (teacan) ከሚለው የተገኘ ነው ይላሉ፡፡ ይህም
ማለት “ማሳየት”፣ “መጠቆም” የሚል ነው፡፡
ማስታወሻ፡- “አንግሎ ሳክሰን” የሚለው ከጀርመን መጥተው ዛሬ
የታላቁዋ ብሪታኒያ ክፍል የሆነውን የወረሩ፣ ሴልቲክ የሚባሉ
በታላቁዋ ብሪታኒያ ይኖሩ የነበሩ፣ ከዴንማርክ የመጡ ወራሪዎችን
የሚመለከት ነው
 በግሪኩ አጠቃቀም “መምህር” የሚለው ቃል “ዲዳሰካሎስ”
ሲባል በሉቃስ ወንጌል አንዳንድ ጊዜ “ኤፒስቴስ” ይሰኛል፡፡
ይሀ አንዳንዴም “ጌታ” (Master) ማለት ይሆናል፡፡
ይህ ቃል አሁንም በዕብራይስጡ “ራባይ” ተብሎ መጠቀ
ሚያ ነው፡፡ ለመምህሩም የተሰጠ የአክብሮት መጠሪያም ነው
ወንጌላት ጌታ ክርስቶስን፡-
“መምህር” ብለው እንደጠሩት ወንጌላት ይመሰክራሉ ( ማር.
2፡14፣10፡1፣12፡35)፡፡
ሕዝብን ያስተምር እንደነበር፣ ይህን ማድረግ እንደ ልማድ
የያዘው እንደሆነ፣በመቅደስም እንዲሁ ያደርግ እንደነበረ
የሚታይ ነው(ሉቃስ 19፡47)
ከዚህ ተነስተን ስናይ፡-
የጌታ ክርስቶስ ተከታዮች 31 ጊዜ በዚህ ስም ጠርተውታል፡፡
 ጌታ ራሱን በዚሁ መጠሪያ አምስት ጊዜ ጠርቶአል፤
 ራቡኒ የሚለው መጠሪያ አስራ አራት ጊዜ የጌታ መጠሪያ ሆኖአል ፡፡
 ይህም “የኔ ጌታ” የሚለውን የያዘም ጭምር ነው (ዮሐ. 1፡38)
አንድ ሲ.ቢ.ኢቬይ የሚባሉ ሰው እንደተናገሩት፡-
 ጌታ ክርስቶስ “ብዙ ጊዜ ፈዋሽ፣ አንዳንድ ጊዜ ተዓምር ሠሪ፣ ሁል ጊዜ
ግን አስተማሪ ነበር” ብለዋል፡፡ እውነት ነው!
ሦስት ነገሮች የጌታ ክርስቶስን መምህርነትም አስረግጠው ይናገራሉ
ይላሉ፡፤ እነዚህም፡
 ብዙሐኑ ሕዝብ እንደ መምህር ያዩት ነበር
 ወንጌላት የርሱን የሥራ እንቅስቃሴ እንደማስተማር ክንዋኔ ይቆጥሩት
ነበር
 ተከታዮቹ ደቀመዛሙርት ተብለው ይጠሩ ነበር፤ ተከታይ ካለ
2፡2. መምህር ለውጥ አምጪ ትምህርትን ግብ ማድረግ
የሚችል ነው
 ስለ ለውጥ አምጪ ትምህርት ስናስብ ሊመጣብን የሚገባው ነገር
ተማሪዎቻችንን ለአዳዲስ መረጃዎች ራሳቸውን ሊያዛምዱ ይችላሉ
የሚለውን እሳቤ የያዘ መሆኑ ነው፡፡
 በዚህም አሮጌውን ትተው ለአዲሱ ትምህርት ራሳቸውን ሊሰጡ
ይችላሉ፡፡ስለሆነም ለውጥ ለማምጣት የምናስተምራቸው ሰዎች
የቀደመውን ልክ ያልሆነ አስተሳሰብ የሚለውጡበት የእውነት ጫና
ሊያገኙ የሚችሉበትም ሂደት ነው፡፡
በዚህም ሂደት ውስጥ እታዲያ የሚከተሉትን ጉዳዮች ታሳቢ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡ እነዚህም፡-
2፡2፡1. የግርታ /የግራ መጋባት እሳቤ ውጥረት
 ይህ ጊዜ ተማሪው በፊት በነበረውና ተማርሁት በሚለው ነገር ላይ ትክክለኛ
ላይሆን የሚችልበትን ነገር የሚያገኝበት ነው፡፡ ይህም ግርታ ሊፈጥር ይችል
ይሆናል፡፡ ደግሞም ትክክልና ለውጥ ለማምጣት የመጀመሪያ ርምጃና “የ
አሃ” ጊዜ ነው፡፡
 ለተማሪው ምቾት የማይሰጥ የማያስደስትም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ለውጥ
አምጪ ትምህርትን ለማስተማር ትክክለኛውን እሳት ለመጫር የሚረዳ ጊዜ
ነው፡፡
2፡2፡2. ራስን የመመርመሪያ ጊዜ
 ይህ ጊዜ የጥልቅ ጥሞና ጊዜ ነው፡፡ ከላይ ያየነው ልምምድ በትክክል
ከተፈጸመ በሁዋላ ተማሪዎች ስለእምነታቸውና አረዳዳቸው የራሳቸውን
አቁዋም መመርመር ይጀምራሉ፡፡
 ያለፈውን ልምምዳቸውንና የግርታ ጊዜያቸውን እንዴት እንደሚወጡት
 በዚህም የእነርሱ አመለካከት ብቻውን የመጨረሻ እውነት እንደሆነ
ማሰቡን መተው ይጀመራሉ
2፡2፡3. አመለካከቶችን አበጥሮ የማያ ጊዜ
 በዚህ ጊዜ ተማሪዎች ጠለቅ ያሉ የእሳቤዎች አካሄዶችን ወደራሳቸው
አመለካከቶች በመውሰድ በራሳቸው ላይ ጨከን ብለው የሚሠሩበት
ጊዜ ነው
 በዚህም አንዳንድ ትክክለኛነት የሌላቸውን ጉዳዮች በማግለል
ለአዳዲስ እውነቶች ራሰቸውን የሚከፍቱበት ጊዜ ይሆናል
2፡2፡4. የድርጊት ዕቅድ ማበጀት
 ከላይ ያየናቸውን ሦስት ደረጃዎች በትክክል የወሰዱ የድርጊት እቅድ
ያወጣሉ፡፡ አሁን ምን ዓይነት ትምህርት እንደሚወስዱና ላሉበት
ሁኔታ የሚረዳ እውቀት የሚጨምር ወይም ችግር የሚፈታ መንገድ
አስምረው ይሄዳሉ
 አሁን ስልት ይነድፋሉ፡፡ አዳዲስ አመለካከቶች ውስጥ ይገባሉ፡፡
የተለያዩና አዳዲስ ሰዎችን ባገኙት አዲስ አመለካከት ሳቢያ
ያነጋግራሉ፡፡ ወዘተርፈ
 ይህንንም ለዋጭ ትምህርት የራሳቸው በማድረግ ክህሎትን
ያዳብራሉ፡፡ ያገኙትን ነገር በሥራ ለመተርጎም ይደፍራሉ፡፡ ለአዳዲስ፣
መሠረታዊ ለሆኑና ትክክለኛነት ላላቸው ትምህርቶች ራሳቸውን
ይሰጣሉ፡፡ ይህም ቀላል የማይባል ጊዜና ድካም ራስንም መስጥት
የሚጠይቅ ይሆናል፡፡
2፡2፡5. አዲስ የኃላፊነት መንገድን መቀበል
 በለዋጭ የትምህርት ሂደት አዳዲስ ለውጥን መቀበል ግድ ይሆናል፡፡
 ለውጥን መረዳትም የስኬት አንዱ መንገድ ነው፡፡
 ይህም ከትምህርት በላይ ይሆናል፡፡
 ለራስ አዳዲስና የሚጨምሩ መረዳቶችን የመቀበያ ሂደት ነው፣
መንገዱ በትክክል ተጀምሮአልና
2፡2፡6. የራስን ብቃት ማዳበር
 የራስን እምነትና ውሳኔ ሰጪነት ማጎልበት
 በራስ መተማመንን ማስረጽ
 “ተማሪ እንደመምህሩ መሆኑ ይበቃዋል” የሚለውን ማበረታቻ የራስ
ማድረግ
ክፍል ሦስት፡- የማስተማር ዘዴ ፡ በክርስቶስ ኢየሱስ መንገድ
ማሰተማር፡- ትርጉም
ማስተማር ምንድን ነው? ማስተማር ይላሉ አንዳንዶች
 ተሳቶፎአዊ ሆኖ ማቀድና ያንኑ ዕቅድ በሥራ መተርጎምን የያዘ ሂደት ነው፡፡
በዚህም የተፈለገ ውጤት ለማምጣት ምሪት የሚሰጥበት ድርጊት ሆኖ ይገለጻል
 የጋራ ግብ ለመያዝ በውስጥ ሰውነት ፣ ዕውቀት፣ ክህሎትና ባሕርይ ላይ ለውጥ
ለማምጣት የሚከወን ድርጊት ነው
የማስተማር ክህሎት ይላሉ አንዳንዶች፣ መምህሩን፡-
 ተማሪዎች መማር እንዲችሉ ፣ውጤት እንዲያመጡና ያገኙትን ዕውቀት በሥራ
እንዲተረጉሙ የሚረዳ (የድርጊት ውጤት) አቅም
 የተፈለገውን ትምህርት በሚገባ አኩዋሁዋን ለመግለጥና ለማስረዳት የሚረዳ
ቅመም
 የልህቀት (Excellence) ደረጃን ከፍ በሚያደርግ መንገድ ማመዛዘንን ፣ መገምገምን
፣ ችግር ፈቺ መሆንንና ተግባቦትን በሚገባ ለማስረጽ የሚረዳ ነው
 ከላይ ያየነውን በእርግጠኝነት ሳያዛንፍ በድርጊት የሚተረጉምልን
መኖር አለበት
 ለዚህና ስለ የማስተማር ዘዴ ስንነጋገር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን
ሞዴል አለማድረግ ክፉኛ ኪሳራ ውስጥ የሚከት ይሆናል
 እርሱ ተራ መምህር እንዳልነበረ የምናይባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
እነዚህን ጉዳዮች በዚሁ የመማስተማር ዘዴው ሂደት ውስጥ
እናያቸዋለን
 አንዳንዶች ጌታ ክርስቶስ “አስተማሪው ነቢይ” ተብሎ ቢጠራ
የሚያስገርም አይሆንም ይላሉ፡፡
 ምክንያታቸውም ነቢያቱ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” ብለዋል ፡፡
ፈሪሳዊያን “ሕጉ እንዲህ ይላል” አሉ፡፡ ጌታ ክርስቶስ “እኔ ግን እንዲህ
አላችሁዋለሁ” እያለ አሰተምሮአልና፡፡
ከላይ ያየነው ነገር የሚወስደን ታዲያ ጌታ ክርስቶስን ልዩ ወደሚያደርጉት
ነገሮች ላይ ነው፡፡ ከነዚህም፡-
3፡1. በሥልጣን ማስተማር
 ክርስቶስ ኢየሱስን ልዩ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ራሱ የራሱ ባለሥልጣንና ተርጉዋሚ መሆኑ ነው፡፡
 ከጌታ ከአባቱ ጋር ካለው የጠለቀ ግንኙነት ውስጥ የሚወጣ ሀብት ይዞ የሕይወትን ሐቆችና
ልምምዶች በራሱ ሥልጣን ይተነትናቸው ነበር
በቃሉም ፡-
“አትግደል እንደሚል ሰምታችሁአል፣ --- እኔ ግን እላችሁአለሁ ---” (ማቴ. 5፡21-22)
“እኔ ስለ ራሴ--- እኔ--- እኔ ብፈርድ--- ስለራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ--- የላከኝም አብ ስለ እኔ
ይመሰክራል” (ዮሐ. 8፡14-17) ይላል፡፡
 ጌታ ክርስቶስ ስለ ራሱ ሥልጣን እርግጠኝነት ሞልቶት ነው የተናገረው፡፡ ዛሬም
በቃሉ የሚናገረን ይህንኑ ነው፡፡ እንዲህም ይላል፡-
“ሥልጣን በሰማይና በምድር ሁሉ ተሰጥቶኛል---” (ማቴ 28፡18)
ሰዎችም ሲመሰክሩለት በግራሞት ተሞልተው ነው፡-
“---ወዲያውም ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማረ፡፡ እንደ ባለሥልጣን ያስተምራቸው
ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ” (ማር. 1፡21-22)
 በምድር ላይ ያሉ ምሁራን አንዳቸው ከሌላው በማጣቀስ ይናገራሉ፣
ይጽፋሉም፡፡ ጌታ ክርስቶስ ግን የሚናገረው በራሱ ሥልጣን ነው፡፡
 በክርስቶስ ኢየሱስ የዚህ ሥልጣኑ ፍሰት ውስጥ “ማስተማር” እና “መስበክ”
የሚሉትን እሳቤዎች በተለያየ ሁኔታ ያያቸዋል፡፡ ቃሉም እንደሚል፡-
“ኢየሱስም በምኩራባቸው “እያስተማረ”፣ የመንግሥትንም ወንጌል
“እየሰበከ” በሕዝብም ያለውን ሕማም ሁሉ “እየፈወሰ” በገሊላ ሁሉ
ይዞር ነበር (ማቴ. 4፡23)፡፡
 ማርቆስና ሉቃስም ይህንኑ በተለይም የማስተማር ሥራውን ነግረዉናል
(ማር. 4፡1-2፤ ሉቃ. 4፡17-22)
ይህ የክርስቶስ ሥልጣን የማንነቱ መገለጫም ነው፡፡
 ጸጋና እውነት ተተሞላ (ዮሐ. 1፡14)፤ ንጽህናን የተላበሰ (ዮሐ. 17፡19)፤ የማወቅ
ኃይል ያለው፣በሰው ያለውን ያውቅ ነበረና (ዮሐ. 2፡25)
 ማንነቱን የሚያምርና ማራኪ ያደረጉት ባህርዩ፣ ለሌሎች ያለው ፍላጎት፣
እርግጠኝነትና ይዞት የመጣው ተልዕኮ ናቸው
 ሌሎች ያላሉትን የተናገረ ነው፡፡ ለምሳሌም፡- “እኔ መንገድን፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤
በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐ. 14፡6)፤ “ከናንተ ስለ ኃጢአት የሚከሰኝ
ማነው”
 የማስከተልና ጫና የማሳደር ኃይሉ የሚገርም ነበር፡፡ “ተከተለኝ፤ ወደ እኔ ኑ”
የሚሉት አባባሎች ትዕዛዝ አዘልና የባለሥልጣን ግብዣ አመላካች ነበሩ
 ሰዎች የጠየቃቸውንና ምክንያታዊ የማይመስሉ ነገሮችን በሥራ ያስተረጎመ ነበር፡፡
ለምሳሌ የጴጥሮስ በውሃ ላይ መሄድ
ይህን ሥልጣኑን አጠቃቀም በሚመለከትም
 በክርስቶስ ያለውን ሥልጣንና እኛ በእርሱ ውስጥ ሆነን በጽድቅ
ልንጠቀምበት የሚገባውን ሥልጣን አሳየን (ማቴ. 28፡18-20)
 ሥልጣኑ ወደሌሎችም የሚተላለፍ መሆኑን ነገረን (ማቴ. 9፡35-38)፡፡
በየትውልዱም ይህ እንደሚሆን አስተማረን (የሐወ. 13፡1-5)
 ታላቅነትም ራስን ባለመቆጠብ መስጠት እንደሆነ በመስቀሉ ሥርዓት ነገረን
(ማቴ. 16፡24-28)
 በዚህም ታላቅነት የመጨረሻውን ሥፍራ ለመውሰድ መምረጥ፣ ይህን
ለማድረግ በራስ ላይ መጨከንና በንጽህና መራመድ አስፈላጊ ነው አለን
(ማቴ. 23፡1-12፣ሉቃስ 22፡24-27)
 ይህም የሚነግረን የጌታ ክርስቶስ ትልቁ ግብ የሰው ልጆች ከአምላካቸው ጋር
ታርቀው ፍጹም የሆነ ግንኙነት ፈጥረው መኖር ነው፤ በዚህም እርሱን
እየመሰሉ መኖር፡፡
3፡2. ምሳሌዎችን መጠቀምና የነዚያው መጠቀሚያዎች ባለቤትና
ተረጉዋሚ ሆኖ ማስተማር
 ምሳሌዎች የሕጻናትንም ሆነ ያደጉ ሰዎችን ቀልብ ለመሳብ ዛሬም
ፍቱን ናቸው፡፡
 ከተወሳሰቡና ክርክር ከሚያስነሱ አቅርቦቶች ይልቅ ግልጽ የሆነ
የይዘትና የባሕርይ አቅርቦት እንዲኖርም ይረዳሉ
 ስለዚህም ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ የሚፈልገውን እውነት በሰው
ሕይወት ለማንቆርቆር ምሳሌዎችን ተመራጭ አድርጎ ይጠቀምባቸው
ነበር
 አንዳነድ እውነቶች ከዚህ ዘዴ በስተቀር እንዴት ሊቀርቡ እንደሚችሉ
ለማየት አዳጋች ነው፡፡
 የተናገራቸው ምሳሌዎች ለትውልዶች ሁሉ ደግመው ደጋግመው
ሙግትን የሚደነቅሩ፣ ሐቅን የሚነግሩ፣ቁምነገርን የሚያስጨብጡና
እውነትን የሚመብራሩ ሆነው እስከ ዛረሬ ድረስ ሰንብተዋል፡፡
ጌታ ክርስቶስ ያቀረባቸው ምሳሌዎች ሁላቸውም፡-
3፡2፡1. አመኔታን የሚያሳድሩ ነበሩ
 የተነገሩት ምሳሌዎች መሬት ያልረገጡ፣ የተጋነኑ ፣ ሰውንና ልምምዱን
ያላገናዘቡ፣ ርካሽና ተራ ወዘተ. አልነበሩም፡፡ ዳሩ ግን የግልና የማህበር
ሕይወት ላይ ጫና ለማሳደር የነበራቸው የተግባቦት ኃይል እጅግ
አስገራሚ ነበር
 ጌታም ያቀረባቸው ምሳሌዎች የቤት እመቤቶችን፣ ለማኞችና ዘራፊዎችን፣
ገበሬዎችና የቀን ሠራተኞችን፣ ባለንብረትና ተዳዳሪዎችን፣ ወዘተርፈ. ያቀፉ
ነበሩ፡፡ ይህም ማለት ማንም የሚረዳውና በሕይወት ልምምድ ውስጥ የነበረ
እውነታ ነው
 አመኔታን የሚያሳድሩና አስተማሪ ምሳሌዎች ስለነበሩ ሰሚዎቹ የነገሩ
ፍቺና ቁምነገር ላይ በማትኮር ይገረሙ ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን ሰዎች
ምሳሌዎችን ሲሰሙዋቸው የራሳቸውን ሕይወት መፈተሻ አድርገዋቸው
ለመገኘት አቅም አላቸው
 በሉቃስ 18፡9-14 ያለውን ክፍል ብንመለከት ዛሬም ቢሆን የፈሪሳዊነት
የሕይወት ድባብ ላጠላብን ለእኛ እጅግ ጠቃሚ ምክር የያዘ ነው፡፡
አምልኮ በትሕትና፣ በመገዛት፣ መነሻን ባለመርሳት ለእግዚአብሔር
አምላክ የሚሰጥ የልጅነት ምላሸ መሆኑን መርሳት ትልቅ ክስረት
ነው፡፡
3፡2፡2. ለተለየ ምክንያት የሚደረጉ ነበሩ
 ይህንን የተለየ ዓላማ ያለውን ምክንያታዊነት ያስተላለፈው በሁለት
መንገድ ነው፡፡
ሀ) ምሳሌው የያዘው የራሱ ትርጉም አንዱ ሲሆን
ለ) ምሳሌው መነሻ የሆነበት አውድ ሌላው ነበር
 ሁለቱን ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ሁለቱም የየራሳቸው ቦታ
አላቸው፡፡ ለምሳሌ የመልካሙ ሳምራዊ ምሳሌ የተነገረበት ራሱን
የቻለ የማስተማሪያ ትርጉም ቢኖረውም የተነሳበት አውድ ደግሞ
ክርስቶስ ኢየሱስ ሊያስተምረው የፈለገው ነገር ምን እንደሆነ
 የክርስቶስ ሥነ ስርዓታዊነት ራሱና በትኩረት ሊሙዋላ የሚገባው ዓላማ
ሁለቱም የማይነጣተሉ ሆነው የተሰናሰሉ ናቸው፡፡
 ከዚህ ተነስተን ልንል የምንችለው ክርስቶስ ኢየሱስ ምሳሌዎችን
ሲጠቀምባቸው እያመናፈሳቸው አልነበርም፡፡ በተቃራኒው ሰሚዎች
ተቀብለው ሊጠቀሙባቸው እንዲችሉ ተደርገው የቀረቡ ናቸው
3፡2፡3. ምሳሌዎቹ የሰውን የማሰቢያ ዓለም የሚያነቃቁ ነበሩ
 ምሳሌ ሲነገር ፈተና የሚሆነው ብዙ መዘብዘብ ወይም ሰው ሊጨብጠው
የማይችለውን ቁንጽል የሆነ እውነታ ማቅረብ ነው
 ጌታ ክርስቶስ ግን ምን ማለት እንዳለበትና በምን ያህል መጠን ማቅረብ
እንዳለበት ጠንቅቆ የሚያውቅ ጌታ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ምሳሌዎቹ
የሰውን የማሰቢያ ዓለም ጨምድደው ይዘው ለትርጉም ፍለጋ የሚያነሳሱ
ነበሩ
 ለምሳሌ የጠፋው ልጅ ታሪክ (ሉቃ. 15፡11-32) የሚገርም የአባትና የልጅ፣
የማንድማማቾች፣ የቤተሰብ ግንኙነት ያማከለ ልብ አንጠልጣይ ምሳሌ
ነው፡፡
 የጠፋው ልጅ የሄደበት መንገድ፣ ያጋጠመው ፍትጊያና ክስረት፣ የምርጫና
ውሳኔ ውጤት ውጣ ውረድ ሁሉ በሚገርም መንገድ የተተረከበት ነበር፡፡
 የሰማው ሁሉ ለሕይወቱ የሚሆነውን ነገር ጨምቆ እየቀመረ በማሰላሰል
ወደ ሕይወት ውሕደት የሚወስድበትን ሂደት ፈጥሮላቸው ነበር
3፡2፡4. መደነቅን የሚፈጥሩ ነበሩ
 ሉቃስ 10፡19-31 ያለው ክፍል ሕብረተሰቡ ከለመደው የባለጠጋና ደሃ
አመለካከት ያፈነገጠ ሲሆን እንዴት አስደንጋጭ አይሆንም
 የማቴ. 20፡1-16 የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ የተመለከተ የሦስት ሰዓተም
የአስራ አንድ ሰዓቱም የቀን ሠራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ አንድ ነው
የሚለው አሳብ እንዴት አያስገርምም
 በሉቃስ 10፡31-37 ያለውና ስለሳምራዊው ሰውዬ የነበረው መልካም
አመለካከከት እንዴት ክርክርን የሚያስነሳና በግብዝነት የሚኖሩትን፣
የሚያስተምሩትንና የሚፈርዱት ፈሪሳዊያንን እያበሳጨ አያስገርማቸውም
3፡3. ምሳሌያዊ ንግግሮች ማጉያ መረጃዎች/መነጽሮች ናቸው
3፡3፡1. ከየዕለቱ የሕይወት አኑዋኑዋር የተወሰዱ ናቸው
 የክርስቶስ ኢየሱስ ምሳሌዎች የተወሰዱት በየዕለቱ ከሚያጋጥሙ
የሕይወት ልምምዶች ሆነው ለየግለሰቡ ያደርግ የነበረው ጥሪ ዕለታዊ
አኑዋኑዋርን የሚሙዋገት ነበር
 ይህም የውስጥ ሰውነት አመለካከትን በመቀየር አጠቃላዩን ሕይወት
የሚማርክ ሙግት ነበር፡፡ ለምሳሌም ያህል፡-
 አነጴጥሮስን አሳ ለማግኘት ሌሊቱን ሲዳክሩ ቆይተው “ሰውን
አጥማጆች አደርጋችሁዋለሁ ሲላቸው ” የሚረዱት በዕለታዊ
ኑሮአቸው ውስጥ የመጣውን የልምምድ መዛመድና ሽግግር ነው
(ሉቃስ 5፡1-10)
 በምጽዋት ሙዳይ ውስጥ የመጨረሻ ሳንቲሙዋን የጣለችውን ሴት
አይቶ የተረጎመው የሰጪዋ ልምምድ የሚገርም ነበር (ሉቃስ 15፡8-
10)
 ንጉሡን “…በዚህ ሁሉ ክብሩ ሰለሞን እንደዚህ አለበሰም…” በሚል ከአበቦች
ጋራ አዛምዶ የተናገረበት መንገድ አስተማሪ ነው (ማቴ. 6፡27-29)
 በገሊላ ባሕር አጠገብ “ምን ልታዩ ወጣችሁ” ያለበትና “ንፋስ
የሚወዘውዘውን ሸምበቆ” አስመልክቶ የተናገረበት ድምጸት የሚገርም ነበር
(ማቴ. 11፡7፤ ሉቃስ 7፡24)
3፡3፡2. ለተጣራ /ግልጽ የሆነ ሁኔታ ተስማሚ ማጉያዎች
 ለይዕለቱ አኑዋኑዋራችን የሚኖረን መጨነቅ በአግባቡ እንድንይዘው ነው
በአምስት ሳንቲም ስለሚሸጡ ደንቢጦችና በኮረብታዎች ላይ ስለሚበቅሉ
አበቦች የተናገረው (ማቴ. 6፡26-30)
 በዓለት ላይ ወይም በአሸዋ ላይ ቤትን ስለማነጽ የሰጠን ትምህርት
የሚገርም የማጉያ/የመደገፊያ መሣሪያ ነበር (ማቴ. 7፡24-27)
3፡3፡3. ማጉያዎቹ የድርጊት እሳቤን የሚያነቃቁ ነበሩ
 ጌታ ክርስቶስ የፈጠረውን አጋጥሞ መያዝ፣ መምራትና በክትትል
መቆጣተር፣ ይቅር ማለትና መፍረድ፣ ማዳንና ማደስ የሁልጊዜ
ክንዋኔዎቹ ናቸው፡፡
 በዚህም እግዚአብሔርን በሁሉ ነገራችን ውስጥ
እንደናየው/እንድንገናኘው ለማድረግ የድርጊት ሰዎችም እንድንሆን
ምሳሌያችን ነው
 ሰዎችም በእምነት መረዳትና ልምምዳቸው በትኩረት ተሳታፊ
እንዲሆኑ፣ መልካምን እንዲያደርጉ፣ የመለገስ ሥራዎችን
እንዲያዘወትሩ፣ ከሚጠበቅባቸው አልፈው ለድርጊት እንዲንደረደሩ፣
በእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ላይ በቂ ጊዜ ሰጥተው ዋጋ ለመክፈል
ዝግጁ እንዲሆኑ የሚረዳ ማጉያ አድርጎ ምሳሌዎችን ይጠቀምባቸዋል
3፡3፡ 4. የክርስቶስን ፈገግታ የመጫር/የማፍታታት ኃይል
የሚያሳዩ ናቸው
 ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታችን ኅይወትን ቀለል አድርገን የምናይበትንና ፈካ
የሚያደርጉ ጥጎችን ይጠቀማል፡፡ ይህ ማለት ግን የግለሰቦችን ሰው
መሆንና መከራቸውን የረሳ አይደለም፡፡ ከተጠቀመባቸው ጥቂቶቹ፡-
 መብራትን አብርቶ ከእንቅብ በታች ማስቀመጥ (ማቴ. 5፡15)
 “ባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ
ቢያልፍ ይቀላል አላቸው፡፡ እነርሱም ያለመጠን ተገረሙና እርስ
በርሳቸው፡- እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል አሉ” የሚለው
(ማቴ.19፡23-26)
 ሰውየው በሌላው ሰው ዓይን ውስጥ ያየው ጉድፍ ነው፣ በራሱ ዓይን
ውስጥ ግን ያለውን ምሰሶ ችላ ብሎአል (ማቴ 7፡3-5፤ሉቃ. 6፡41)
3፡3፡5. ሰዎች ወደ ትክክለኛው እምነት እንዲሻገሩባቸው ይጠቀምባቸዋል
 ለክርስቶስ ምሳሌዎች የሰውን የምናብ/የአስተሳሰብ ዓለም ነክተው
ሲያበቁ የሰሙዋቸው ሰዎች በትምህርቱና በእግዚአብሔር ላይ
እምነታቸውን እንዲያሳድሩ ይረዳሉ (ምናብ ወደ እምነት ማለት ነው)
 ለአሳብ መነሳሳት፣ በትልቀት ለማየት የተደረገው ነገር የሰውን ፈቃድ
ለማግኘት ጉልበታም ነው፡፡ ይህም ደግሞ ሐቅ ያለበትመን የእምነት
ምላሽ በሰሚዎች ውስጥ መፍጠር ይችላል
 ጌታ ክርስቶስ የሕይወት እንጀራ፣ የሕይወት ውሃ ነኝ ሲል ሰዎች
በራሳቸው “ምን ማለት ነው” ለሚለው ጥያቄ ምላሸስ እመንዲፈልጉ
ዕድል የሚሰጥ ነው(ዮሐ. 6፡35)፡፡ ውሃው ሲፈላና ሲቀዳ፣ እንጀራም
ሲቆረስ የጌታ ሕይወት ለኛ ያመጣውን ለማገናዘብ ይረዳል
የሚከተሉትን ጥቅሶች ባለፈው ክፍል ያዛመደባቸውን አይቶ መጠቀም
ይቻላል
 ከዕለታዊ ኑሮ፡- ሉቃስ 5፡31፣6፡48፣7፡32፣9፡48፣11፡33-36፣20፡24
 ከተፈጥሮ፡- 6፡33-34፣9፡58፣11፡11፣13፡6-9፣15፡4
 ገጸባህርያት፡- 5፡31፣10፡30፣12፡39፣12፡58፣18፡2፣19፡12
3፡4. ጥያቄና መልስ ተጠቀመ
 ማንኛውም የመማር ማስተማር ሂደት ያለ ጥያቄና መልስ ሙሉዕ
አይሆንም፡፡ የመጀመሪያው ጠቃሚ ነገር ተመሪዎቻ ያላቸውን
እውቀትና ሊሙዋላላቸው የሚገባውን እጦት መለየት የሚያስችል
ነገር ነው
 በሌላም በኩል መጠየቅ ተማሪዎች የተቀበሉትን ቁምነገር በትክክል
አውቀውት እንደሆነ የመለያ ጉልበት ይሆናል፡፡ በተጨማሪም
የምናስተምራቸው ሰዎች ሕይወት ውስጥ የታመቀ ግን ለማፍሰስ
ዕድል ያልተሰጠው እውቀት ሊኖር ስለሚችል ያንንም እምቅ ሃብት
ለማውጣት ይረዳል
 በማስተማር መማር ሂደቱ እንደገና ተማሪዎች የሚጠይቁበት ዕድል
ያስፈልጋቸዋል፡፡ይህን ማድረግ የማይችል መምህር የተሙዋላ
 በክርስትና ልምምዳችን ውስጥ የመጠየ ቅና የመወያየት ሂደት እይታና
ትርጉምን በሥርዓት ለማስኬድና የመረዳት አድማስን ለማስፋት
ጠቀሜታው ብዙ ነው፡፡
 በዚህ ሂደት ውስጥ የመረዳት ባለጠግነት በመምህሩ ብቻ ሳይሆን
በተማሪዎቹም የሕይወት ልምምድ የሚገለጥ መሆኑን ማወቅ የትልቅ
ብልጽግና እሳቤ ነው
 በክርስቶስ ኢየሱስ የማስተማር ሂደቶች ውስጥ ጥያቄዎች ጥያቄዎች ሰፊ
ሚና ነበራቸው፡፡
 ሲጠይቅ ግን መልሶች በጥያቄዎች ውስጥ እንዲኖሩ አድርጎ ስለነበር
አብዛኛውን ጊዜ ከማንም መልስ ሳይጠብቅ የጀመረውን ይጨርስ ነበር
 ጌታ ክርስቶስ ያነሳው “የፈሪሳውያን እርሾ” ትምህርቱ ውስጥ ብቻ አስር
ጥያቄዎችን ጠይቆአል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ታጭቀው የሚገኙት በሰባት
 የጠየቃቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት መልኮች ያሉት ነው
3፡4፡1. መልስ አዘል ጠያቄዎችን ድራማዊነት ባለው መልክ
አቅርቦአል
 እነዚህን በማድረግ ሲጠይቅ ተመሳስሎን በመጠቀም ነው፡፡ ይህም
ማለት መዝሙር ነክ የሆኑ ድምጾች የሚመዘኑት በሕብር ነው፡፡
በዚህም የምናገኘው የተለያየ ነገር የሚናገሩ የሚመስሉ ግመን ደግሞ
በሰው ድምጥ ሲባሉ ተመሳሳይ ነት ያላቸው ይመስላሉ
 እነዚህን ጥያቄዎች ሲጠይቅ በእርሱ ጊዜ ለነበሩ አይሁድ ልምምድ
በሚመች መንገድ የተጠቀመባቸው ናቸው፡፡ በዚህም የአሳቦች
ተመሳስሎን በማውጣት የሚጠይቃቸው ጥያቄዎች ነበሩት ማለት
ነው፡
 ለምሳሌም፡- “የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ?
ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን…?”
 በዚህም ሁለት ጥያቄዎችን ሳይሆን የሚጠይቀው በአንድ አሳብ ጥላ
ሥር የሚያስኬዳቸው ተመሳስሎዎች ናቸው
 እንዳንድ ጊዜም አንድን እሳቤ በአንድ ጥያቄ አመላካችነት ሌላ ጥግ
ላይ ያለውን እሳቤ በዚያው የእሳቤ ትንፋሽ በሌላ ጥያቄ ያቀርባል
(ማቴ. 6፡27-28)
 በሌላም በኩል ክርስቶስ ኢየሱስ የእሳቤዎችን ጥምረት በሁለት
የተለያዩ ጥያቄዎች ያቀረበ በሚመስል መንገድ ያቀርበዋል (ማቴ.
7፡16)
3፡4፡2. ጥያቄን በጥያቄ መመለስ
 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በወንጌላት ውስጥ እንደምናገኘው መቼም
ቢሆን በሰዎች የጥያቄ ወጥመድ ውስጥ ገብቶላቸው አያውቅም ፡፡
በተለይም እርሱን ስህተተኛ ለማድረግ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች እጅ
ሰጥቶ አያውቅም (ማቴ. 22፡34-40)
 ምንም እንኩዋን ሙግትን ባይጠላም/ባያገልም እርሱ ግን ጠብ ጫሪ
ንግግሮችን ጀማሪ አልነበረም ፡፡ ይህም ለሙግቱ ሲባል ብቻ!
 ተቀናቃኞቹም እጅግ የተጨናነቀ ጥያቄ ሲጠይቁት ዝርዝር ነገር
ውሰጥ ከመግባት ይልቅ ጥያቄውን ወደራሳቸው ይመልሰው ነበር፡፡
ለምሳሌም፡- “በሰንበት መፈወስ” የሚያመጣውን በጎ ነገር በቅንነት
ባለማጤን ክርስቶስን ለመፈተን የሞከሩት ሰዎች “ከእናንተ…” ብሎ
ነው የመለሰባቸው (ማቴ. 12፡11-12)
3፡4፡3. የሙግት አቅርቦት ያለበትን ጥያቄ መጠየቅ
 ጌታ ኢየሱስ ሰዎች የራሳቸው መልስ እንዲኖራቸው እንጂ የመልሶች
ጫና እንዳይከመርባቸው ለማድረግ የሚያስችላቸው ጥያቄዎች
ነበሩት፡፡ ይህም እነርሱን ለማወናበድ ሳይሆን እውነት ነጥሮ
እንዲወጣ ለማድረግ በመፈለጉ ነው
 ከዚህም ጋር ሰዎች እንዲብራራላቸውም ይሁን ወይም ምላሽ
የሚጠብቁበት ፍላጎት ይዘው ብቅ ሲሉ ጥያቄያቸውን ወዲያው
ከመመለስ ይልቅ መረዳት ያገኙ መሆናቸውንና ሊከተሉት የወሰኑ
እንደሆነ የሚያረጋግጥበትን ጥያቄ ያቀርብ ነበር፡፡ ለዚህ መረጃ
የሚሆኑን ዓይ ሥውራኑ ናቸው ( ማቴ. 9፡27-30፣ 20፡29-34)
 ከማንኛቸውም ይልቅ የክርስቶስ ጥያቄ እንደመዘውር መጠቀሚያ
የሆነው የቄሳሪያው ልምምድ ነው (ማር. 8፡27-31፤ማቴ. 16፡13-20)፡፡
ይህ የክርስቶስን የአገልግሎት ሂደትና የእውነተኛ ደቀመዛሙርትን
ማንነት የለየ ነው፡፡
እነዚህን የጥያቄ ጥቅሶች በግል እንይ፡-
ለብዙሃን፡- ሉቃ. 6፡32-46፣7፡14-26፣9፡25፣ 12፡56-57፣ 13፡18-20
ለደቀመዛሙርት፡- ሉቃ. 8፡5፣9፡18-30፣16፡12፣12፡25፣12፡42
የሐይማኖት መሪዎች፡- ሉቃ. 6፡3፣ 6፡9፣13፡15፣14፡3-5፣ 20፡4፣20፡17
በተናጠል ያናገራቸው፡- ሉቃ.7፡42፣10፡26፣17፡17፣22፡48፣22፡52
3፡5. ለትምህርት ያለው ቦታ
 በክርስቶስ ጌታ የማስተማር ዘዴ ሂደት ሁለት አቀራረቦች አሉ፡- “ትምህርት
ራሳቸውን ለሰጡ” እና “ትምህርት ራሳቸውን ላልሰጡ፡፡” ይህም ማለት ጌታ
ክርስቶስ የሚያስተምረውን ትምህርት ለሚቀበሉት አድማጮች አውድ የሚሆን
አድርጎ የሚያቀርበው መሆንንም አመላካች ነው፡፡በዚህ ሂደትም አንዲቀበሉት
ለማድረግ ጥድፊያ የሞላበት የእውነት አቅርቦቶች አልነበሩትም
 በዮሐ. 16፡12 ላይ እንደምናገኝ “የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፣ ነገር ግን አሁን
ልትሸከሙት አትችሉም” ብሎ ነበር፡፡ ይህም የሚያሳየን ጌታ ክርስቶስ ፍጹምነት
ያለውና የሚፈልገውን ዕድገት ቶሎ የሚያመጣ ምላሽ ከአድማጮቹ አይጠብቅም
ነበር ማለት ነው፡፡
 ምናልባትም የተሙዋላ የአስተምህሮው ፍላጎትና ይዘት ከደቀመዛሙርቱ ሲያጣ
ወደሁዋላ መልሶአቸው የማዝረክረክ ልምድ አልነበረውም፡፡ ታጋሽ መምህር ነበር!!
 በዚህ ዘመን የሚታየው የማስተማር ሂደትና የመምሀራን ልምድ የሚነግረን
ትዕግሥት የጎደለውና ሁሉን ነገር ለሚያስተምሩአቸው በመዘርገፍ ሰሚዎቻቸው
ዝግጁነት ሳይኖራቸው የሚሠሩት ጉድለት ነው፡፡ ምራቅ ለዋጡ የሚሰጠውን
መለየት መልካም ነው!!
 የተራራውን ስብከት ስንመለከት ቁምነገሮቹ በማተ. 5-7 በእነድ ላይ
ቢገኙም ይላሉ አንዳንድ ሰዎች፣ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙና ጌታ በተለያየ
ጊዜ ያስተማረባቸው ናቸው፡፡ ሉቃስ ወንጌልም እነዚህን የያዘ ነው (ሉቃ.
4፡16-21፣ 6፡20-29፣9፡23-27፣ 12፡1-40)
ስለዚህም የትምህርቱን ይዘት ስናይ፡-
3፡5፡1. ለትክክለኛ ደረጃ የተሰጠ ነበር
 ከደቀመዛሙርቱ ጋር በነበረው ግንኙነት የቀረቤታ፣የጥልቀት፣ የራሱን ማንነት
በሚገልጥ መንገድ በይዘቱ ለየት ያለና ሥር የሰደደ አቅርቦት ነበረው
 የሚያስተምረውን ትምህርት ለአድማጮች እንዲመጥን አድርጎ ያቀርበው ነበር፡፡
አንዳንዶች ይህን ዓይነት አቀራረብ መነሳሳትን ለመፍጠር ድክመት አለው ይላሉ፡፡
 ጌታ ክርስቶስ ግን በተናገረ ጊዜ ሁሉ ጥያቄ የሚፈጥር መሆኑ፣ ለማወቅ ተነሳሽነት
መታየቱ፣አመኔታ በእርሱ ላይ ለማሳደር እንዲችሉና በጥንቃቄ እንዲያስቡ
የሚያደርጋቸውን ይሰጥ ነበር
 በዚህ ምክንያት ነበር የጌታ አቅርቦት ደርሶአቸው የነበሩ ደቀመዛሙርቱ “…እነሆ አሁን
በግልጥ ትናገራለህ፣ በምሳሌም ምንም አትነግርም፡፡ ሁሉን እንድታውቅ፣ ማንም ሊጠይቅህ
እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን አሉት”
(ዮሐ. 16፡19-30)
 ይህ የማስተማር ሂደቱ ማለትም የሰሚዎችን የመቀበል ደረጃ የመጠነ አቅርቦት
መሆኑ ምላሽ የሚሰጡትን ሁሉ ቀስ በቀስ ሊደርሱ ወደሚፈልገው ግብ
የሚወስዳቸው ነው፡፡ የሚሰሙትን ሁሉ ግን በአንድ ጎዳና ላይ በጅምላ
አይነዳቸውም፡፡ ለዚህ ነው “አሁን አወቅን” ያሉት
3፡5፡2. ሰዎችን ለድርጊት ያነሳሳበት ነው
 አንዳንድ የሥነ ልቡና ምሁራን እንደሚሉት ስሜትን የሚያነሳሱ ነገሮች ብቻ
ለሰሚዎች መስጠት በሰው ሥብዕና ላይ ሊኖረው የሚችለውን ችግር በጥንቃቄ
መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚሰነዘሩ አሳቦች/እሳቤዎች እጅግ የሚያሳስት መረጃ
ሰጥተው ሲገኙ የሚፈለገውን ለውጥ በሥራ ለመተርጎም አስቸጋሪ ያደርጉታልና
 ክርስቶስ ኢየሱስ ግን ከዚህ ለየት ያለ ነበር፡፡ የሰጣቸው ትምህርቶች ሁሉ እሳቤንና
ምናብን በሥራ ለመተርጎም የሚያስችሉ ነበሩ፡፡ ከትምህረቱ ጋራ በሥራ የሚተረጎም
ምግትን አጣምሮ ሰጥቶአል
 ክርስቶስ ዒየሱስ ባስተማረው ትምህርት ሶች በመገዛት ተረድተውት በውጤቱ
ሕይወታቸው ተለውጦ “ብርሃንና ጨው” እንደሆኑ በመረዳት የእግዚአብሔር
መንግሥት አባልነታቸውን የሚያሳዩበት ልምምድ ነው (ማቴ፣5፡13-14፣7፡21)
3፡5፡3. ትክክለኛ የውስጥ ተነሳሽነት/ዝንባሌ እንዲኖር አስተምሮአል
 በማቴ. 5፡38-48 ያለው ክፍል የሚደንቅ የውስጥ ሰውነት መሰጠትን የሚጠይቅ፣
በመታዘዝ ለመኖር የተለወጠ ሕይወት የሚያመለክት ነው፡፡ “ቀኝን ሲመቱ ገራን
ማዞር፣…ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣…የሚረግሙአችሁንም መርቁ፣…ለሚጠሉአችሁ
መልካም አድርጉ፣ ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” የሚለው አብዮታዊ የሚመስልና
የካድሬ ንግግር ነው የሚመስለው
 ይህ እሳቤ በእግዚአብሔር አስተዳደርና በመንግሥቱ ውስጥ ፍቅቀና ይቅርታ ትልቁን
ሥፍራ የዘው እነዳሉ ብስራት የተሰማበት ነው
 ራስን በመካድ የሚደረገው የጠለቀ ዋጋ መክፈል፣ በእግዚአብሔር መንግሥት
ትምህርት ውስጥ የተቀመጠ ግብ ነው (ማቴ. 10፡34-42)፡፡
 እግዚአብሔርም “የሰማዩ አባት” እንደሆነና ለራሱ የቤተሰብ አባላት በሁሉ ቦታ
የሚያስብ እንደሆነ መረዳት እጅግ የሞቀ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው (ማቴ.6፡7-
13)፡፡
3:5:4. ትምህርቱ የማይጠፉ ምልክቶች የሚተው ነው
 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምህርቱ ይዘት ውስጥ ሊደረስበት የማይችል
ሃይማኖታዊ ፍልስፍና ወይም ከሰሚዎች አቅም በላይ የሆነና ሊደረስበት ሊጨበጥ
የማይችል የረቀቀ ንግግር አላስተላለፈም
 በተቃራኒው ከሰሚዎች ሊጠፉ የማይችሉና ለብዙሃኑ ሰዎች ልፍስፍስ ያልሆኑ፣
ቀርበው ለሚከተሉት ለደቀመዛሙርቱ ደግሞ ከሥብዕናው የወጡ የሕይወት
መርሆዎች አስተላልፎአል
 የተራራው ስብከት ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ እግዚአብሔር በሥራ ላይ እንዳለ፣
የእግዚአብሔርም መንግሥት መገለጫ እውነት እንደሆነ ሊታወሱ የሚችሉ
መርሆዎች የተሞላ እነደሆን የምመንማርበት ነው
 በዚህ የተራራ ስብከት ውስጥ በመንፈስ ድሃ መሆን፣ ማዘን፣ ጽድቅን መራብ፣
ምህረት ማድረግ፣ ልብን ማንጻት፣መታረቅና ማስታረቅ፣ ለጽድቅ መሰደድ
እያንዳንዳቸው ከተከታይ በረከቶቻቸው ጋር ተነስተዋል፡፡ ድምር ውጤቱ ብጽዕና
ነው!!
3፡6. በሁኔታ ውስጥ ማስተማር
 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን የማስተማር ዘዴ ተጠቅሞበታል፡፡
በሁኔታዎች ውስጥ የተገኙትንም ሰዎች ለማስተማር ችሎአል፡፡ ይህን
ስንል ሦስት ነገሮችን በማሰብ ነው፡-
ሀ) በጊዜው የመጣውን ዕድል መጠቀም ትክክለኛ አተረጉዋጎም ይዞ
መግለጥና ለሁኔታው የሚሆን የአሳብ ዳኝነትን መስጠት ጥሩ ነው
ለ) በተገኘው ዕድል ውስጥ ሲጠቀም የሐቅ ሥርዓተ-ጥለት (Pattern)
ከመኪያስተምረው ትምህርት ውስጥ ይገኛል፡፡ በክርስቶስ ትምህርት
ሁሉ ውስጥ ያለ ይመስላል የምንለው በዘዴዎቹና በተሳተፈበት
ሁኔታዎች ሁሉ ውስጥ በትምህርቱና በሁኔታው መካከል
ስምምነት/ኅብር (Harmony) ነበረው
ሐ) የሁኔታዎች ዕድል ሲገኝ ብቻ ሳይሆን በምናብ ውስጥ ወይም
በታሰበ ሂደት ውስጥ ማደራጀት ይቻላል፡፡ በማንኛውም ጊዜ
ታስቦበትም ይሁን ዕድሉ ራሱን ሰጥቶ አስፈላጊው ነገር እውነትን
ለተከሰተው ሁኔታ በሚስማማ መንገድ መግለጥ ዋናው ነገር ነው
አሁን ክርስቶስ ትምህርቱን የገለጠባቸውን ሁኔታዎች እንመልከት
3፡6፡1. ተአምራትና ምልክቶች በተከሰቱ ጊዜ
 ጌታ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ከክብሩና በረከቱ ጋር የሚሰሙት ሑሉ
እንዲረዱለት ሲሠራ ነበር፡፡ ምንም እንኩዋን እርሱ ራሱ ሰው ሆኖ ቢመላለስም ደግሞም
ፍጹም አምላክ ስለሆነ ወደ እርሱ የመጡትን ችግረኞች ሁሉ ለመርዳት፣ ለመደገፍና
ለመፈወስ ይችል ነበር
 ሆኖም ሊፈውሳቸው የሚፈልጋቸውን ጥቂት ሰዎች ብቻ መርጦ አልነበረም የረዳቸው፡፡
ለማስተማር ምቹ በሆነ ጊዜ ሁሉ ትምህርቱን ሰጥቶአል፡፡ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ፈውስ
ባካሄደባቸው ጊዘያት ሁሉ አላስተማረም
 ዕድል ራሱዋን ስትሰጠው ግን ጊዜ አላጠፋም፡፡ በዚህም፡-
ሀ) ምን ማድረግ እንደሚፈልግ ያብራራ፣ የሠራውን ለምን እንደሚሠራው ይናገር ነበር
ለ) የተፈጸመውን ተአምር ለደቀመዛሙርቱ አንጸባራቂ ምልክት ሰጪ እንዲሆን አድርጎ
ያበጀው ነበር
 ከዚህ ሁሉ ውስጥ የምናወጣው ቁምነገር ታዲያ የሕይወት ሙላትና ደህንነት
መገኘት መቻሉን ነው፡፡ ይህም ማለት የተገለጠው የእግዚአብሔር ኃይል ሕየወትን
አጠቃሎ የሚለውጥ ጉልበት እንደሆነ ያስረዳበት ነውና
 የተራቡትን መመገብ ረሃብን የማስታገስ ሥራ ብቻ ሳይሆን የሚያመላክተው
የሕይወት እንጀራም እንዳለ በመሆኑ የክርስቶስ ሕይወት ወሳኝ የግለሰቡ የሕይወት
ምዕራፍ ጅማሬ እንደሆነም አስረጂ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ዕድል በተገኘ ጊዜ ሁሉ
ትምህርትንና የአሳብ ሙግትን ለአድማጮቹ ያቀርብ ነበር
3፡6፡2. ሰዎችን በግልም ሆነ በቡድን በተገናኛቸው ጊዜ
ለምሳሌ ያህል፡-
 የክርስቶስ ኢየሱስ እናት ማሪያም ከወንድሞቹ ጋር በተገናኘችው ጊዜ የሥራ
ባልደረቦቹን ብቻ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የገቡትን ሁሉ እንደቤተሰብ
አባላት የሚያቅፍበትን ሁኔታ ነበር ያበሰረው (ማር. 3፡33-34፤ ማቴ. 12፡47-48፤
ሉቃ. 8፡19-21)
 የሳምራዊቲቱን ሴት ታሪክ ውሃ ልትቀዳ የመጣችበትን ጊዜ ተጠቅሞ ነው የሠራበት
(ዮሐ. 4፡4-29)
3፡6፡3. የሰዎችን ምላሽ ለድርጊት በመጠቀም
 በአይሁድ ሕብረተሰብ ውስጥ የነበረው የሞራልና የህብረተሰብ አኑዋኑዋር
ከሃይማኖታዊ እሳቤዎች ጋር ተያይዘው እንዲገኙ ማድረግ ነበር ልምዱ የነበረው
 እየቆየ ሲሄድ የእግዚአብሔር ሕግ መንፈስ እየጠፋ ሰዋዊ የሆነው ሥርዓት እየበዛ
በመሄዱ ምክንያት ጌታ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ “እኔ ሕግን ለመሻር አልመጣሁም
ልፈጽም እንጂ” ብሎ ያንን የተጣራ/ግልጽ የሆነ የሕግ መንፈስ ወደ ከፍተኛ ደረጃ
ለመውሰድ አስተማረ
 በዚህም የቀጥታ ትርጉም የያዘ የሕግ አጠቃቀም ተወግዶ እንዲገኝ በሥራ
የተተረጎመ አኑዋኑዋርን አስገባ፡፡ በዚህም የሚያደርገውን ለምን እንዳደረገ
ለማስረዳትና ለማብራራት ከፍተኛ ዕድል ሰጥቶት ተገኝቶአል
ጥቅሶችን እንይ
 በምልክቶችና ተአምራት ጊዜ፡- ሉቃ. 5፡12-26፣6፡6-11፤14፡1-14
 ሰዎችን ሲያገኝ፡- ሉቃ. 7፡36-50፣ 9፡46-48፣10፡25-37፣14፡7-24
 ለሰዎች አስተያየት በተሰጠ ምላሽ፡- ሉቃ. 5፡26-35፣6፡6-10፣11፡37-54፣15፡7-32
 የደቀመዛሙርት ልምምድ፡- ሉቃ. 9፡28-31
3:7. የቃሉ አጠቃቀም
 የእግዚአብሔርን ቃል በመጠቀም የማስተማር ጊዜ መነጋገሪያ የሆኑ ቅራኔዎችን ሲነሱ እንደነበረ
የቆየ ጉዳይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የሚነሱትም የሥልጣን ጉዳይ፣ የይዘት ነገር፣ የባሕርይ ፍሰት፣
የዘዴው ዓይነትና በያንዳንዱ መምህር የሚሰጡ መልሶች ናቸው፡፡
3፡7፡1. ጌታ ክርስቶስ ራሱ የቃሉን ሥልጣን ተቀብሎ ሠርቶበታል፣ኖሮበታልም
 ይህም ሲባል አዲስ መረዳትን አምጥቶበት አሳይቶአል ማለታችን ነው፡፡ ይህንንም ለማድረግ ሲነሳ
በብሉይ ያለውን የእግዚአብሔርን ቃልእነደገባ እንጂ ፍጻሜ ሊሰጠው ወደዓለም ሊያጠፋ
እንዳልመጣ ነበር ያስረዳው (ማቴ. ፡17-20)
 ለመልካም አኑዋኑዋር ተምሮ ለመገኘት የሚያስፈልገውንም ሲጠየቅ በብሉይ ኪዳን ያለው
የእግዚአብሔር ሕግ አስፈላጊ መሆኑን ለማሳየት፡-
 የፈወሳቸውን ለምጻሞች እንደ ሕጉ ራሳቸውን ለካህናት ማሳየት እንዲችሉ ማድረጉ (ሉቃ.
17፡11-19)
 የዘላለም ሕይወት ለመውረስ የምን ላድርግ ጥያቄ ለጠየቀው ሰው በሰጠው ምላሽ ውስጥ (ማር.
10፡17-21)
 ሊፈትነው ለነበረ መምህርና በተመሳሳይ ድምጸት ለተጠየቁ ጥያቄዎች በሰጠው ምላሽ ውስጥ
(ሉቃ. 10፡25-28፣18፡18-21፣ማቴ. 19፡16-22፣ማቴ. 22፡34-40)
 ጌታ ክርስቶስ ይህንን የሕግ ትምህርት ወደ ጠለቀ መረዳትና መንፈሳዊነት
ለመውሰድ የሄደበት መሥመር ይታያል፡፡
 ከላይ አንስተነው በነበረው የተራራው ስብከት ላይ እንደምናገኝ ለጎረቤታችን፣
ለወንድማችን፣ ለቤተሰብም ሊኖረን የሚገባውን የውስጥ ዝንባሌ መናገሩ
ይታወሳል፡፡
 አእምሮና ልብ ውስጥ ጅማሬያቸውን የሚያደርጉት መግደል፣ፍቺ፣በቀል፣ወዘተርፈ.
የመሳሰሉት አደገኛ ጉዳዮች በብሉይ ኪዳን በጨከነ መንገድ ልክ አለመሆናቸው
ተሰምሮበታል
 ይህ ውጪያዊ ግን በውስጥ ሰውነት ተቀምሮ በሥራ የሚተረጎመው ጉዳይ
መሠረታዊ የሆነውንና ሕጉ የሚሰጠውን የውስጥ መንፈሳዊነት ግብዝ ወደሆነ
አስመሳይነት/የፈሪሳዊነት ልማድ በመለወጡ መክንያት ጌታ ክርስቶስ ወደ
መሠረቱ የሚመልስ ግን በተለየ መረዳት ወደሚኖር መንፈሳዊ አኑዋኑዋር መለሰው
3፡7፡2.የቃሉን ሥልጣን ከሰዎች የተነሳበትን ተቃውሞ ለማረቅ
አልተጠቀመበትም
 ጸሐፍትና ፈሪሳዊያን ራሳቸውን የሐይማኖቱ ቁንጮና የጥያቄዎች
ሁሉ ምላሽ እነርሱ ጋ እንዳለ አድርገው በመቁጠር የሚኖሩ፣
የሚሠሩና የሚያስተምሩ ስለነበሩ እነርሱን ተካክሎና በልጦ የተገኘው
ጌታ ክርስቶስ ብቻ ነው
 በጌታና በደቀመዛሙርቱ ላይ እነርሱ የሚሉት የሕግጋትን፣ ደንቦችንና
በዓላትን አጠባበቅ ድክመት፣ ጌታ ራሱ ስለ መሲሁ የተናገረውን
ምክንያታዊ አቅርቦትና ነቁዋም፣ ለሰንበት ያላቸው አመለካከት ላይ
ቅሬታቸው ጥልቅ ነበር
 ጌታ ክርስቶስ ግን ለእነዚህ ጉዳዮች ቃሉን በመጠቀም የሰጣቸው
ምላሾች ማንም ሊኖረው የሚችለውን አዋቂነት የተላበሰ እንደነበረና
እርሱም ይህን አካሄድ የተጠቀመው ቃሉን በትክክል ባለመተርጎም
የመጣውን የተሳሳተ ሂደት ለማረም ነው
3፡7፡3. ጌታ ይዞ የመጣውን ተልዕኮ ደቀመዛሙርቱ እንዲረዱት ያደረገው
በቃሉ ነው
 ይህም ሲባል ጌታ ሲያስተምር፣ ተአምራትና ምልክቶችን ሲያደርግ ተልዕኮውን በትክክል
በመተርጎም ሊያስረዳቸው መቻሉ ነው
 መሲሁ መከረኛ መሲህ እንደሆነ ከብሉይ ኪዳን እየወሰደ አስተምሮአል (ኢሳ.
52፡13-53፡12
3፡8. ትምህርትን በድርጊት መማር
 አሁን ባለንበት ዘመን ትምህርትን በተሳትፎና ድርጊቶችን በመከወን መማር መለመድ
አለበት የሚባልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነበረው
የማስተማር መማር ሂደት ውስጥ ይህንኑ የተጠቀመ ይመስላል፡፡ የሚከተሉትን እንይ፡-
3፡8፡1. ለመታዘዝ ፈቃደኛ መሆን
 ጌታ ክርስቶስ በመማር ማስተማር ግንኙነቱ ሂደት ውስጥ ሰዎች አመኔታቸውን በእርሱ ላይ
እንዲያሳድሩ ይሻል፡፡ ለዚህም ፈቃደኛ ሆነው እንዲገኙ ይሻል፡፡ የጌታ እናት ማርያም በቃና
ዘገሊላ ሠርግ ላይ ለአዘጋጆች ያለቻቸው አሳብ የሚጠበቅ ነው (ዮሐ. 2፡5)
 ደግሞም የክርስቶስ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መግባት፣ የጌታን ራትም ለማዘጋጀት
የተሰጠን ጥዕዛዝ አቀባበል መታዘዝና መከተልን የሚያስረግየት ነው (ማር. 11፡1-7፤ማቴ.
21፡1-7፤ ሉቃ. 19፡28-35)
 የጴጥሮስ በውሃ ላይ ለመራመድ የነበረው ታዝዞ መንገድ መጀመር ይህንኑ የሚያሳይ ነበር
 የጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ መከረኛነት አስተማሪ ነው፡፡ ክርስቶስ ራሱ መታዘዝን
የተማረው በመከራ ነው (ዕበራው. 2፡10፣ 5፡7-8)፡፡ ደቀመዛሙርቱም ከመከራቸው
ይማራሉ የሚለው እውነትም የተጠበቀ ነው (ማቴ. 5፡11-12፤ ዕብራ. 11፡35-38)
3፡8፡2. ከውድቀት መማር
 ጌታ ክርስቶስ ሐዋርያቱ ስህተት በፈጸሙ ጊዜ አርሞ ግን ደግሞ ከሄዱበት መንገድ
ሊማሩ የሚችሉበትንም መውጪያ ያሳያቸው ነበር፡፡
 ለምሳሌም እርሱ በሌለበት የፈውስ ልምዳቸውን ለመከወን ሞክረው ነበር፡፡ ጌታ
ፍላጎታቸውና የማገልገል ዝንባሌያቸው ላይ ሳይሆን አትኩሮ የነበረው በውስጥ
ሕይወታቸው ሊኖራቸው የሚገባው መንፈሳዊነት ላይ ነበር (ማር. 9፡14-29፤ሉቃ.
9፡37-42፤ማቴ. 17፡14-20)
 ልጆች ወደ ጌታ ክርስቶስ ሲመጡ የእግዚአብሔር መንግሥት እነርሱን
እንደምትጨምር ያልበራላቸው ደቀመዛሙርቱ ሲከለክሉአቸው “ተውአቸው” ነው
ያለው፡፡ በዚያ ግን አልቆመም፤ የተደላደለና ጥልቅ የሆነ መርህ ነው ያስተማረበት
(ማር. 10፡13-16)
 በጌትሴማኒ ጌታ በተያዘ ጊዜ ሰይፍ አንስተው ሊዋጉ ሲሞክሩ “ሰይፋችሁን ወደ
ሰገባው” ያለበት ልምምድ የማስተማሪያ ስህተት ነበር (ማተ. 26፡51-54)ሉቃ.
22፡49-51)
3፡8፡3. ራስን የመስጠትና የመልካም ባህርይን ልማድ ዋጋ በማወቅ
 መንፈሳዊ ሕይወትን ለማጎልበትና ስለ ሕይወት ያለውን ትክክለኛ አመለካከት
ለመያዝ አስፈላጊ የሆነው ነገር ራስን ለክርስቶስ በማስገዛትና ክርስትና
የሚጠይቀውን ትክክለኛ ባሕርይ በመለማመድ ነው
 ደቀመዛሙርቱ ሕይወታቸው እየተለወጠ እንዲጎለብት ያደረጋቸው ለክርስቶስ ጌታ
በመታዘዛቸውና በማያቁዋርጥ ልምምድ ውስጥ በመገኘታቸው ነው
 የክርስቶስ ኢየሱስም የማያቁዋርጥ ጸሎቱና ከአባቱ ጋር የነበረው ቀረቤታ
ስለማረከው ነው “ጌታ ሆይ ዮሐንስ ደቀመዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ
አስተምረን” ብሎ “ከደቀመዛሙርቱ አንዱ” የጠየቀው ፡፡ ጌታም “ስትጸልዩ እንዲህ
በሉ…” ብሎአቸዋል፡፡ የተዋጣለት ሞዴል ነበር!!

More Related Content

What's hot

(01) apresentação aula 1 a bíblia
(01) apresentação aula 1 a bíblia(01) apresentação aula 1 a bíblia
(01) apresentação aula 1 a bíblia
GlauciaSlides
 
Trabalho de administração eclesiástica
Trabalho de administração eclesiásticaTrabalho de administração eclesiástica
Trabalho de administração eclesiástica
Bruno Torres Cerqueira
 

What's hot (20)

Talk10 growing in the spirit
Talk10 growing in the spiritTalk10 growing in the spirit
Talk10 growing in the spirit
 
Coaching 101 - The Basics
Coaching 101 - The BasicsCoaching 101 - The Basics
Coaching 101 - The Basics
 
Mentoring
MentoringMentoring
Mentoring
 
Liderança cristã 01 gil juvep
Liderança cristã 01 gil juvepLiderança cristã 01 gil juvep
Liderança cristã 01 gil juvep
 
Transição e Implantação de Células nas Igrejas
Transição e Implantação de Células nas IgrejasTransição e Implantação de Células nas Igrejas
Transição e Implantação de Células nas Igrejas
 
Aula 3 - Terceiro Período - A Igreja Imperial
Aula 3 -  Terceiro Período - A Igreja ImperialAula 3 -  Terceiro Período - A Igreja Imperial
Aula 3 - Terceiro Período - A Igreja Imperial
 
Coaching introduction
Coaching introductionCoaching introduction
Coaching introduction
 
04 principio-da-formacao-de-lideres
04 principio-da-formacao-de-lideres04 principio-da-formacao-de-lideres
04 principio-da-formacao-de-lideres
 
Discipulado - Escola Bíblica de Obreiros em Bauru (SP)
Discipulado - Escola Bíblica de Obreiros em Bauru (SP)Discipulado - Escola Bíblica de Obreiros em Bauru (SP)
Discipulado - Escola Bíblica de Obreiros em Bauru (SP)
 
Carta aos gálatas
Carta aos gálatasCarta aos gálatas
Carta aos gálatas
 
O desafio de Liderança Participante
O desafio de Liderança ParticipanteO desafio de Liderança Participante
O desafio de Liderança Participante
 
A influencia do pragmatismo na teologia
A influencia do pragmatismo na teologiaA influencia do pragmatismo na teologia
A influencia do pragmatismo na teologia
 
15 DICAS DE LIDERANÇA
15 DICAS DE LIDERANÇA15 DICAS DE LIDERANÇA
15 DICAS DE LIDERANÇA
 
A importância da teologia hoje
A importância da teologia hojeA importância da teologia hoje
A importância da teologia hoje
 
Homilética Aula 1
Homilética Aula 1Homilética Aula 1
Homilética Aula 1
 
Slide dons espirituais
Slide dons espirituaisSlide dons espirituais
Slide dons espirituais
 
(01) apresentação aula 1 a bíblia
(01) apresentação aula 1 a bíblia(01) apresentação aula 1 a bíblia
(01) apresentação aula 1 a bíblia
 
Introduction to Christian Education: Section 4
Introduction to Christian Education: Section 4Introduction to Christian Education: Section 4
Introduction to Christian Education: Section 4
 
Liderança missional e igreja missional
Liderança missional e igreja missionalLiderança missional e igreja missional
Liderança missional e igreja missional
 
Trabalho de administração eclesiástica
Trabalho de administração eclesiásticaTrabalho de administração eclesiástica
Trabalho de administração eclesiástica
 

Similar to የማስተማር ዘዴ.pptx a presentation about the KMKC church

Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptx
Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptxLife Skill Training PPT Final Aug 19.pptx
Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptx
MasreshaA
 

Similar to የማስተማር ዘዴ.pptx a presentation about the KMKC church (8)

Christian educationeducation in the twenty one century
Christian educationeducation in the twenty one centuryChristian educationeducation in the twenty one century
Christian educationeducation in the twenty one century
 
christianeducationanoverviewjan312015-150131081842-conversion-gate01 (1).pptx
christianeducationanoverviewjan312015-150131081842-conversion-gate01 (1).pptxchristianeducationanoverviewjan312015-150131081842-conversion-gate01 (1).pptx
christianeducationanoverviewjan312015-150131081842-conversion-gate01 (1).pptx
 
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
 
action-research-manual-2 (1).pdf
action-research-manual-2 (1).pdfaction-research-manual-2 (1).pdf
action-research-manual-2 (1).pdf
 
EYA leadership.Kibralem Demisse W/semhatpptx
EYA leadership.Kibralem Demisse W/semhatpptxEYA leadership.Kibralem Demisse W/semhatpptx
EYA leadership.Kibralem Demisse W/semhatpptx
 
EYA leadership.Kibralem Demisse W/semhatpptx
EYA leadership.Kibralem Demisse W/semhatpptxEYA leadership.Kibralem Demisse W/semhatpptx
EYA leadership.Kibralem Demisse W/semhatpptx
 
Pastoral caring and counseling in the church
Pastoral caring and counseling in the churchPastoral caring and counseling in the church
Pastoral caring and counseling in the church
 
Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptx
Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptxLife Skill Training PPT Final Aug 19.pptx
Life Skill Training PPT Final Aug 19.pptx
 

More from PetrosGeset

More from PetrosGeset (9)

PPP - Dechasa Pastors Conference April 20 2024.ppt
PPP - Dechasa Pastors Conference April 20 2024.pptPPP - Dechasa Pastors Conference April 20 2024.ppt
PPP - Dechasa Pastors Conference April 20 2024.ppt
 
Missional Leader By Aychiluhm Final.pptx
Missional Leader By Aychiluhm  Final.pptxMissional Leader By Aychiluhm  Final.pptx
Missional Leader By Aychiluhm Final.pptx
 
English vocabulary to kindergarten students
English vocabulary to kindergarten studentsEnglish vocabulary to kindergarten students
English vocabulary to kindergarten students
 
leadership types and There character in the xhurch
leadership types and There character in the xhurchleadership types and There character in the xhurch
leadership types and There character in the xhurch
 
it is about how increasing student access
it is about how increasing student accessit is about how increasing student access
it is about how increasing student access
 
ew_target_board_with_arrows_tags_and_icons_flat_powerpoint_design [Autosaved]...
ew_target_board_with_arrows_tags_and_icons_flat_powerpoint_design [Autosaved]...ew_target_board_with_arrows_tags_and_icons_flat_powerpoint_design [Autosaved]...
ew_target_board_with_arrows_tags_and_icons_flat_powerpoint_design [Autosaved]...
 
Christology.pptx
Christology.pptxChristology.pptx
Christology.pptx
 
fundraising Presentation 1.pptx a presentation about the KMKC church
fundraising Presentation 1.pptx a presentation about the KMKC churchfundraising Presentation 1.pptx a presentation about the KMKC church
fundraising Presentation 1.pptx a presentation about the KMKC church
 
fundraising Presentation 1.pptx
fundraising Presentation 1.pptxfundraising Presentation 1.pptx
fundraising Presentation 1.pptx
 

የማስተማር ዘዴ.pptx a presentation about the KMKC church

  • 1. የማስተማር ዘዴ አዘጋጅ፡- ወ/ዊ በለጠ ሀብተጊዮርጊስ
  • 2. ክፍል አንድ፡- መግቢያ 1፡1. ጥቅል • አሁን ያለችው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የምታምነውን አውቃ ፣ ያንንም እውቀት በሚገባ አደራጅታ ማስተላለፍና ስትኖረው መገኘት ተገቢ ነው ፡፡ • የሚያምነውን የማያውቅ ፣ ያመነውን መኖር የተሳነውና አቅርቦቱም የተዘበራረቀበት ግለሰብም ሆነ ክርስቲያን ማህበረሰብ መርከብ ያለመሪ እንደሚጉዋዝና ህሊናው እንደናወዘ ብኩን መሆኑ የማይቀር ነው ፡፡ ለዚህም ጤናማ ሆኖ የመገኘት ዓይነተኛ ጉዳይ ቀዳሚ ሚና መጫወት የሚገባቸው የቤተክርስቲያን መሪዎች ናቸው ፡፡ • የእምነትን እውቀት በጥራት መያዝ ፣ ያንን እውቀት አስጠብቆ መኖር ፣ ይህንኑ ጉልበት በተደራጀ መልኩ ጥሩ የሚባል የማስተላለፊያ ክህሎትና በዚህ ተለዋዋጭ ዘመን የተረጋጋ የቤተክርስቲያንን የእውቀት አምባ ለመገንባት የሚያስችል ብልሃትን ዓላማ አድርጎ መሥራት የሚጠበቅበትም ያው ከእግዚአብሔር ዘንድ ትክክለኛ ጥሪ ያለው የቤተክርስቲያን አመራርና የአገልግሎት ክፍል ነው ፡፡
  • 3. • በሥነ ምግባር የታነጸና የራሱን በሥራ የሚተረጎም እሴት ይዞ የሚንቀሳቀስ የመሪዎች ሠራዊት ደግሞ ይህንን ለማድረግ አይቸገርም ፣ ቢቸገርም እንዴት እንደሚታረም ያውቃል ፡፡ ኃላፊነቱንና ተጠያቂነቱን እንዴት እንደሚወጣው ገብቶታል ተብሎ የሚጠበቅ ነውና!! • ትኩረት ተነፍጎአቸው የሚገኙት የተመሪና ተማሪ ፍላጎቶችም አሳሳቢ ከሆኑ ሰንብተዋል፡፡ የእውቀቱ መገኘት ፣ የተገኘውን የእውቀት ይዘት ማስተላለፍ ፣ በተደራጀ መልክ ተዘጋጅቶ በሚቀመጥ መልኩ ተሠርቶ አሻራ መተው እንደተጠበቀ ሆኖ የተመሪውን ፍላጎቶች ባማከለ መልኩ መሥራት ሌላው አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው ፡፡
  • 4. • አብዛኛው የጽሁፍም ሆነ የመድረክ አቅርቦት ጸሎት፣ጥናትና ምርምር፣ የአዋቂዎች (ምሁራን) ምክክር፣ላሉበት ጊዜና የአቅርቦቱ ተቀባዮች እንዲሆን አውዳዊነት አይታይበትም፡፡ • በፈንታው ግልብ በሆነ የአቅርቦት ሂደት የላይ የላዩ ብቻ እየተነካካ ሁነኛ ለውጥና የሚዳሰስ የዓይነትና የጥራት እድገት እየጠፋ፣ግንኙነት እየተጎሳቆለ፣ክርስትናችን የቆዳ ጥልቀት ያህል ሆኖ መገኘቱ ባልተጭበረበረ መልኩ የተገለጠ ነው፡፡ በዚህም ምዕመናን • ስሜታቸው ብቻ የሚፈልገውን፣ • ሊወቀሱበትና ሊለወጡበት የማይችሉበት ስብከት ወይም ትምህርት እየቀረበ • በሐቅና በጽድቅ ፊት ልፍስፍስ ምእመናንን አትርፈንበታል፡፡
  • 5. • ምእመናኑም የምቾት ጠርዛቸውን ብቻ የሚያስቡበትንና የክርስቶስ መስቀል ሥርዓት ተካፋይ መሆናቸውን የሚያስረሳ ስብከትና ትምህርት ይሰጣቸዋል • በክርስትና ሕይወታቸው ጥንቁቅና ከክፋት የጸዱ እንዲሆኑ የሚረዳቸውን እውነታ ማቅረብም ደንታ የሚሰጠን እንዳልሆነ ይስተዋላል፡፡ • ይህን ሁሉ የኅሊና ወቀሳ አጥተንበት ብልጥግናቸውን ብቻ እንዲያስቡና ኃላፊነታቸቸውን እንዲዘነጉ ማድረግ ላይ አውቀንም ሆነ በስህተት ትኩረት መሰጠቱ ችግራችን ሆኖ ሰንብቶአል፡፡ • ለዚህም ጸጸት የሚባል አልፈጠረብንም፡፡
  • 6. • ለዚህ ሁሉ የሚሆነን አንዱ ምላሽ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከላይ እንዳየን የዕውቀትን አምባ መሥራት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ • ይህን ለማድረግ የሚረዳን ደግሞ ቤተክርስቲያን “ማስተማር” የሚለውን እውነት በዓጽንኦት ማስመር ስትችል ነው፡፡ • ይህንኑ ጉዳይ በሥራ ለመተርጎምም አገልጋዮችዋ የማስተማር ክህሎትንና ሊኖረው የሚገባውን የፍሰት ዘዴ ሊላበሱ ይገባል፡፡
  • 7. 1፡2. አንዳንዶች ለማስተማር ይረዳሉ ብለው የሚከተሉአቸው መንገዶች አሉ፡፡ ከነዚህም፡- 1፡2፡1. አራት የማስተማር ዘዴዎች ሀ) መምሕር ተኮር፡- ይህ መምህሩ የሚሠጠው ነገር ላይ ብቻ ያተኮረ፣ መምህሩን እንደ ባለሥልጣን ብቻ የሚስል፣ የሚፈልገውን ጠይቆ የሚመዝንበትና በፈለገው ጊዜ ብቻ የሚከውንበት ወዘተ. ነው፡፡ ለ) ተማሪ ተኮር፡- ይህ ዘዴ ተማሪው ጥያቄ የሚመልስበት፣ ችግር ፈቺ ለመሆን የሚጥርበት፣ የራሱን ጥያቄ የሚቀርጽበት፣ ውይይትን ሙግት የሚሠራበት ነው፡፡
  • 8. ሐ) ይዘት ተኮር፡- በዚህ የምናገኘው ተማሪው መሠረቱ የጠበቀና የሚጋፈጠውን ዕውቀት ለማግኘት የተደራጀ ትምህርት ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡ ትኩረቱ አሳቦች፣ ጽነሰ-አሳቦችና መርሆዎች ላይ ይሆናል፡፡ ተማሪው ትምህርቱን ለትምህርቱ ሲባል ብቻ ይማረዋል መ) ተሳትፎአዊ/በይነተገናኝ/Interactive ፡- ተማሪው በዚህ ዘዴ ያገኘውን ክህሎት መጠቀሚያና ማዳበሪያ ጊዜ አድርጎ የሚከውንበት፣ በራሱ ተነሳሽነት ለማደግ እመርታ የሚያሳይበት ነው፡፡ በዚህ ጊዜም ነው መምህሩ የተማሪውን የሚጨምር ዕውቀት እየመዘነ በተለያየ ጊዜ እንደየ አቅሙና ግለሰቡ መረዳት እንደ ሚያስፈልገውም ግብአት የሚሠራበት ሂደት የሚሆነው
  • 9. 1፡2፡2. የማስተማር ደረጃዎች ሀ) ሠርቶ ማሳያ  የመምህሩን ችሎታ፣ የትምህርቱን ይዘት ጠቀሜታ፣ ያ ትምህርት አምጥቶት ያለውን ውጤት ማገናዘቢያ ነው፡፡  የሚዳሰስ፣ በመረጃ ሊቀርብ የሚችል፣ ቀጣይነት ባለው መንገድ የተሠራ መሆኑን ማመላከቻ፣ ማሳየት የሚቻል (ለምሳሌም አኑዋኑዋር ወይም ልኬት ያለው ውጤት ማቅረቢያ) ነው፡፡ ለ) አፍርሶ መገንባት (Deconstruction):-  በአንድ በኩል ማብጠልጠልና ማጣጣል ማለት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በሌላ አዲስ መንገድ ለመቅረጽ መቻል ማለት ይሆናል
  • 10. ሐ) በመረዳት አቅም ሐቅን መጨበጥ (understanding with the power of intellect)  ይዘቱን (የተሰጠውን እውነት) ማግኘት መቻል፣ ቁምነገሩን አግኝቶ የራስ ማድረግ መ) ድርጊትን መፈጸም  ቁምነገሩን በሥራ ላይ ማዋል፣ የጠራ አፈጻጸምን ማሳየት
  • 11. 1፡3. ሦስት ዘይቤዎች (Styles):- ሀ) ምራ  ለተማሪዎችህ ቀጥተኛ ምሪት ስጥ፣ ምን እንደሚያደርጉም ንገራቸው ለ) ተወያይ  ጥያቄ ጠይቅ፣ ዝም ብለህም ስማ ሐ) ወክል  ተማሪዎችህን አስታጥቃቸው  ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ጊዜ የትምህርት ማሰልጠኛዎችና ሌሎቸም የትምህርት መስመሮች እውነትን ለማስረጽና በሥራ የሚተረጎምን ዕውቀት ለማስጨበጥ የክርስቶስን የማስተማር ዘዴ የራስ በማድረግ ላይ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡
  • 12. ክፍል ሁለት፡- ትርጉም ለውጥ አምጪ ግብ ማበጀት 2፡1. ትርጉም  ስለ ትርጉም ስናስብ ደህና የሚሆነው “መምህር” የሚለውን እሳቤ ቅድሚያ በመስጠት መጀመር ስንችል ነው፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት “መምህር” የሚለውና የእንግሊዘኛ መጠቀሚያ የሆነው ቃል ከአንግሎ ሳክሰን ቲካን (teacan) ከሚለው የተገኘ ነው ይላሉ፡፡ ይህም ማለት “ማሳየት”፣ “መጠቆም” የሚል ነው፡፡ ማስታወሻ፡- “አንግሎ ሳክሰን” የሚለው ከጀርመን መጥተው ዛሬ የታላቁዋ ብሪታኒያ ክፍል የሆነውን የወረሩ፣ ሴልቲክ የሚባሉ በታላቁዋ ብሪታኒያ ይኖሩ የነበሩ፣ ከዴንማርክ የመጡ ወራሪዎችን የሚመለከት ነው
  • 13.  በግሪኩ አጠቃቀም “መምህር” የሚለው ቃል “ዲዳሰካሎስ” ሲባል በሉቃስ ወንጌል አንዳንድ ጊዜ “ኤፒስቴስ” ይሰኛል፡፡ ይሀ አንዳንዴም “ጌታ” (Master) ማለት ይሆናል፡፡ ይህ ቃል አሁንም በዕብራይስጡ “ራባይ” ተብሎ መጠቀ ሚያ ነው፡፡ ለመምህሩም የተሰጠ የአክብሮት መጠሪያም ነው ወንጌላት ጌታ ክርስቶስን፡- “መምህር” ብለው እንደጠሩት ወንጌላት ይመሰክራሉ ( ማር. 2፡14፣10፡1፣12፡35)፡፡ ሕዝብን ያስተምር እንደነበር፣ ይህን ማድረግ እንደ ልማድ የያዘው እንደሆነ፣በመቅደስም እንዲሁ ያደርግ እንደነበረ የሚታይ ነው(ሉቃስ 19፡47)
  • 14. ከዚህ ተነስተን ስናይ፡- የጌታ ክርስቶስ ተከታዮች 31 ጊዜ በዚህ ስም ጠርተውታል፡፡  ጌታ ራሱን በዚሁ መጠሪያ አምስት ጊዜ ጠርቶአል፤  ራቡኒ የሚለው መጠሪያ አስራ አራት ጊዜ የጌታ መጠሪያ ሆኖአል ፡፡  ይህም “የኔ ጌታ” የሚለውን የያዘም ጭምር ነው (ዮሐ. 1፡38) አንድ ሲ.ቢ.ኢቬይ የሚባሉ ሰው እንደተናገሩት፡-  ጌታ ክርስቶስ “ብዙ ጊዜ ፈዋሽ፣ አንዳንድ ጊዜ ተዓምር ሠሪ፣ ሁል ጊዜ ግን አስተማሪ ነበር” ብለዋል፡፡ እውነት ነው! ሦስት ነገሮች የጌታ ክርስቶስን መምህርነትም አስረግጠው ይናገራሉ ይላሉ፡፤ እነዚህም፡  ብዙሐኑ ሕዝብ እንደ መምህር ያዩት ነበር  ወንጌላት የርሱን የሥራ እንቅስቃሴ እንደማስተማር ክንዋኔ ይቆጥሩት ነበር  ተከታዮቹ ደቀመዛሙርት ተብለው ይጠሩ ነበር፤ ተከታይ ካለ
  • 15. 2፡2. መምህር ለውጥ አምጪ ትምህርትን ግብ ማድረግ የሚችል ነው  ስለ ለውጥ አምጪ ትምህርት ስናስብ ሊመጣብን የሚገባው ነገር ተማሪዎቻችንን ለአዳዲስ መረጃዎች ራሳቸውን ሊያዛምዱ ይችላሉ የሚለውን እሳቤ የያዘ መሆኑ ነው፡፡  በዚህም አሮጌውን ትተው ለአዲሱ ትምህርት ራሳቸውን ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ስለሆነም ለውጥ ለማምጣት የምናስተምራቸው ሰዎች የቀደመውን ልክ ያልሆነ አስተሳሰብ የሚለውጡበት የእውነት ጫና ሊያገኙ የሚችሉበትም ሂደት ነው፡፡ በዚህም ሂደት ውስጥ እታዲያ የሚከተሉትን ጉዳዮች ታሳቢ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህም፡-
  • 16. 2፡2፡1. የግርታ /የግራ መጋባት እሳቤ ውጥረት  ይህ ጊዜ ተማሪው በፊት በነበረውና ተማርሁት በሚለው ነገር ላይ ትክክለኛ ላይሆን የሚችልበትን ነገር የሚያገኝበት ነው፡፡ ይህም ግርታ ሊፈጥር ይችል ይሆናል፡፡ ደግሞም ትክክልና ለውጥ ለማምጣት የመጀመሪያ ርምጃና “የ አሃ” ጊዜ ነው፡፡  ለተማሪው ምቾት የማይሰጥ የማያስደስትም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ለውጥ አምጪ ትምህርትን ለማስተማር ትክክለኛውን እሳት ለመጫር የሚረዳ ጊዜ ነው፡፡ 2፡2፡2. ራስን የመመርመሪያ ጊዜ  ይህ ጊዜ የጥልቅ ጥሞና ጊዜ ነው፡፡ ከላይ ያየነው ልምምድ በትክክል ከተፈጸመ በሁዋላ ተማሪዎች ስለእምነታቸውና አረዳዳቸው የራሳቸውን አቁዋም መመርመር ይጀምራሉ፡፡  ያለፈውን ልምምዳቸውንና የግርታ ጊዜያቸውን እንዴት እንደሚወጡት
  • 17.  በዚህም የእነርሱ አመለካከት ብቻውን የመጨረሻ እውነት እንደሆነ ማሰቡን መተው ይጀመራሉ 2፡2፡3. አመለካከቶችን አበጥሮ የማያ ጊዜ  በዚህ ጊዜ ተማሪዎች ጠለቅ ያሉ የእሳቤዎች አካሄዶችን ወደራሳቸው አመለካከቶች በመውሰድ በራሳቸው ላይ ጨከን ብለው የሚሠሩበት ጊዜ ነው  በዚህም አንዳንድ ትክክለኛነት የሌላቸውን ጉዳዮች በማግለል ለአዳዲስ እውነቶች ራሰቸውን የሚከፍቱበት ጊዜ ይሆናል
  • 18. 2፡2፡4. የድርጊት ዕቅድ ማበጀት  ከላይ ያየናቸውን ሦስት ደረጃዎች በትክክል የወሰዱ የድርጊት እቅድ ያወጣሉ፡፡ አሁን ምን ዓይነት ትምህርት እንደሚወስዱና ላሉበት ሁኔታ የሚረዳ እውቀት የሚጨምር ወይም ችግር የሚፈታ መንገድ አስምረው ይሄዳሉ  አሁን ስልት ይነድፋሉ፡፡ አዳዲስ አመለካከቶች ውስጥ ይገባሉ፡፡ የተለያዩና አዳዲስ ሰዎችን ባገኙት አዲስ አመለካከት ሳቢያ ያነጋግራሉ፡፡ ወዘተርፈ  ይህንንም ለዋጭ ትምህርት የራሳቸው በማድረግ ክህሎትን ያዳብራሉ፡፡ ያገኙትን ነገር በሥራ ለመተርጎም ይደፍራሉ፡፡ ለአዳዲስ፣ መሠረታዊ ለሆኑና ትክክለኛነት ላላቸው ትምህርቶች ራሳቸውን ይሰጣሉ፡፡ ይህም ቀላል የማይባል ጊዜና ድካም ራስንም መስጥት የሚጠይቅ ይሆናል፡፡
  • 19. 2፡2፡5. አዲስ የኃላፊነት መንገድን መቀበል  በለዋጭ የትምህርት ሂደት አዳዲስ ለውጥን መቀበል ግድ ይሆናል፡፡  ለውጥን መረዳትም የስኬት አንዱ መንገድ ነው፡፡  ይህም ከትምህርት በላይ ይሆናል፡፡  ለራስ አዳዲስና የሚጨምሩ መረዳቶችን የመቀበያ ሂደት ነው፣ መንገዱ በትክክል ተጀምሮአልና
  • 20. 2፡2፡6. የራስን ብቃት ማዳበር  የራስን እምነትና ውሳኔ ሰጪነት ማጎልበት  በራስ መተማመንን ማስረጽ  “ተማሪ እንደመምህሩ መሆኑ ይበቃዋል” የሚለውን ማበረታቻ የራስ ማድረግ
  • 21. ክፍል ሦስት፡- የማስተማር ዘዴ ፡ በክርስቶስ ኢየሱስ መንገድ ማሰተማር፡- ትርጉም ማስተማር ምንድን ነው? ማስተማር ይላሉ አንዳንዶች  ተሳቶፎአዊ ሆኖ ማቀድና ያንኑ ዕቅድ በሥራ መተርጎምን የያዘ ሂደት ነው፡፡ በዚህም የተፈለገ ውጤት ለማምጣት ምሪት የሚሰጥበት ድርጊት ሆኖ ይገለጻል  የጋራ ግብ ለመያዝ በውስጥ ሰውነት ፣ ዕውቀት፣ ክህሎትና ባሕርይ ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚከወን ድርጊት ነው የማስተማር ክህሎት ይላሉ አንዳንዶች፣ መምህሩን፡-  ተማሪዎች መማር እንዲችሉ ፣ውጤት እንዲያመጡና ያገኙትን ዕውቀት በሥራ እንዲተረጉሙ የሚረዳ (የድርጊት ውጤት) አቅም  የተፈለገውን ትምህርት በሚገባ አኩዋሁዋን ለመግለጥና ለማስረዳት የሚረዳ ቅመም  የልህቀት (Excellence) ደረጃን ከፍ በሚያደርግ መንገድ ማመዛዘንን ፣ መገምገምን ፣ ችግር ፈቺ መሆንንና ተግባቦትን በሚገባ ለማስረጽ የሚረዳ ነው
  • 22.  ከላይ ያየነውን በእርግጠኝነት ሳያዛንፍ በድርጊት የሚተረጉምልን መኖር አለበት  ለዚህና ስለ የማስተማር ዘዴ ስንነጋገር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሞዴል አለማድረግ ክፉኛ ኪሳራ ውስጥ የሚከት ይሆናል  እርሱ ተራ መምህር እንዳልነበረ የምናይባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በዚሁ የመማስተማር ዘዴው ሂደት ውስጥ እናያቸዋለን  አንዳንዶች ጌታ ክርስቶስ “አስተማሪው ነቢይ” ተብሎ ቢጠራ የሚያስገርም አይሆንም ይላሉ፡፡  ምክንያታቸውም ነቢያቱ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” ብለዋል ፡፡ ፈሪሳዊያን “ሕጉ እንዲህ ይላል” አሉ፡፡ ጌታ ክርስቶስ “እኔ ግን እንዲህ አላችሁዋለሁ” እያለ አሰተምሮአልና፡፡
  • 23. ከላይ ያየነው ነገር የሚወስደን ታዲያ ጌታ ክርስቶስን ልዩ ወደሚያደርጉት ነገሮች ላይ ነው፡፡ ከነዚህም፡- 3፡1. በሥልጣን ማስተማር  ክርስቶስ ኢየሱስን ልዩ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ራሱ የራሱ ባለሥልጣንና ተርጉዋሚ መሆኑ ነው፡፡  ከጌታ ከአባቱ ጋር ካለው የጠለቀ ግንኙነት ውስጥ የሚወጣ ሀብት ይዞ የሕይወትን ሐቆችና ልምምዶች በራሱ ሥልጣን ይተነትናቸው ነበር በቃሉም ፡- “አትግደል እንደሚል ሰምታችሁአል፣ --- እኔ ግን እላችሁአለሁ ---” (ማቴ. 5፡21-22) “እኔ ስለ ራሴ--- እኔ--- እኔ ብፈርድ--- ስለራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ--- የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል” (ዮሐ. 8፡14-17) ይላል፡፡  ጌታ ክርስቶስ ስለ ራሱ ሥልጣን እርግጠኝነት ሞልቶት ነው የተናገረው፡፡ ዛሬም በቃሉ የሚናገረን ይህንኑ ነው፡፡ እንዲህም ይላል፡- “ሥልጣን በሰማይና በምድር ሁሉ ተሰጥቶኛል---” (ማቴ 28፡18)
  • 24. ሰዎችም ሲመሰክሩለት በግራሞት ተሞልተው ነው፡- “---ወዲያውም ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማረ፡፡ እንደ ባለሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ” (ማር. 1፡21-22)  በምድር ላይ ያሉ ምሁራን አንዳቸው ከሌላው በማጣቀስ ይናገራሉ፣ ይጽፋሉም፡፡ ጌታ ክርስቶስ ግን የሚናገረው በራሱ ሥልጣን ነው፡፡  በክርስቶስ ኢየሱስ የዚህ ሥልጣኑ ፍሰት ውስጥ “ማስተማር” እና “መስበክ” የሚሉትን እሳቤዎች በተለያየ ሁኔታ ያያቸዋል፡፡ ቃሉም እንደሚል፡- “ኢየሱስም በምኩራባቸው “እያስተማረ”፣ የመንግሥትንም ወንጌል “እየሰበከ” በሕዝብም ያለውን ሕማም ሁሉ “እየፈወሰ” በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር (ማቴ. 4፡23)፡፡  ማርቆስና ሉቃስም ይህንኑ በተለይም የማስተማር ሥራውን ነግረዉናል (ማር. 4፡1-2፤ ሉቃ. 4፡17-22)
  • 25. ይህ የክርስቶስ ሥልጣን የማንነቱ መገለጫም ነው፡፡  ጸጋና እውነት ተተሞላ (ዮሐ. 1፡14)፤ ንጽህናን የተላበሰ (ዮሐ. 17፡19)፤ የማወቅ ኃይል ያለው፣በሰው ያለውን ያውቅ ነበረና (ዮሐ. 2፡25)  ማንነቱን የሚያምርና ማራኪ ያደረጉት ባህርዩ፣ ለሌሎች ያለው ፍላጎት፣ እርግጠኝነትና ይዞት የመጣው ተልዕኮ ናቸው  ሌሎች ያላሉትን የተናገረ ነው፡፡ ለምሳሌም፡- “እኔ መንገድን፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤ በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐ. 14፡6)፤ “ከናንተ ስለ ኃጢአት የሚከሰኝ ማነው”  የማስከተልና ጫና የማሳደር ኃይሉ የሚገርም ነበር፡፡ “ተከተለኝ፤ ወደ እኔ ኑ” የሚሉት አባባሎች ትዕዛዝ አዘልና የባለሥልጣን ግብዣ አመላካች ነበሩ  ሰዎች የጠየቃቸውንና ምክንያታዊ የማይመስሉ ነገሮችን በሥራ ያስተረጎመ ነበር፡፡ ለምሳሌ የጴጥሮስ በውሃ ላይ መሄድ
  • 26. ይህን ሥልጣኑን አጠቃቀም በሚመለከትም  በክርስቶስ ያለውን ሥልጣንና እኛ በእርሱ ውስጥ ሆነን በጽድቅ ልንጠቀምበት የሚገባውን ሥልጣን አሳየን (ማቴ. 28፡18-20)  ሥልጣኑ ወደሌሎችም የሚተላለፍ መሆኑን ነገረን (ማቴ. 9፡35-38)፡፡ በየትውልዱም ይህ እንደሚሆን አስተማረን (የሐወ. 13፡1-5)  ታላቅነትም ራስን ባለመቆጠብ መስጠት እንደሆነ በመስቀሉ ሥርዓት ነገረን (ማቴ. 16፡24-28)  በዚህም ታላቅነት የመጨረሻውን ሥፍራ ለመውሰድ መምረጥ፣ ይህን ለማድረግ በራስ ላይ መጨከንና በንጽህና መራመድ አስፈላጊ ነው አለን (ማቴ. 23፡1-12፣ሉቃስ 22፡24-27)  ይህም የሚነግረን የጌታ ክርስቶስ ትልቁ ግብ የሰው ልጆች ከአምላካቸው ጋር ታርቀው ፍጹም የሆነ ግንኙነት ፈጥረው መኖር ነው፤ በዚህም እርሱን እየመሰሉ መኖር፡፡
  • 27. 3፡2. ምሳሌዎችን መጠቀምና የነዚያው መጠቀሚያዎች ባለቤትና ተረጉዋሚ ሆኖ ማስተማር  ምሳሌዎች የሕጻናትንም ሆነ ያደጉ ሰዎችን ቀልብ ለመሳብ ዛሬም ፍቱን ናቸው፡፡  ከተወሳሰቡና ክርክር ከሚያስነሱ አቅርቦቶች ይልቅ ግልጽ የሆነ የይዘትና የባሕርይ አቅርቦት እንዲኖርም ይረዳሉ  ስለዚህም ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ የሚፈልገውን እውነት በሰው ሕይወት ለማንቆርቆር ምሳሌዎችን ተመራጭ አድርጎ ይጠቀምባቸው ነበር  አንዳነድ እውነቶች ከዚህ ዘዴ በስተቀር እንዴት ሊቀርቡ እንደሚችሉ ለማየት አዳጋች ነው፡፡  የተናገራቸው ምሳሌዎች ለትውልዶች ሁሉ ደግመው ደጋግመው ሙግትን የሚደነቅሩ፣ ሐቅን የሚነግሩ፣ቁምነገርን የሚያስጨብጡና እውነትን የሚመብራሩ ሆነው እስከ ዛረሬ ድረስ ሰንብተዋል፡፡
  • 28. ጌታ ክርስቶስ ያቀረባቸው ምሳሌዎች ሁላቸውም፡- 3፡2፡1. አመኔታን የሚያሳድሩ ነበሩ  የተነገሩት ምሳሌዎች መሬት ያልረገጡ፣ የተጋነኑ ፣ ሰውንና ልምምዱን ያላገናዘቡ፣ ርካሽና ተራ ወዘተ. አልነበሩም፡፡ ዳሩ ግን የግልና የማህበር ሕይወት ላይ ጫና ለማሳደር የነበራቸው የተግባቦት ኃይል እጅግ አስገራሚ ነበር  ጌታም ያቀረባቸው ምሳሌዎች የቤት እመቤቶችን፣ ለማኞችና ዘራፊዎችን፣ ገበሬዎችና የቀን ሠራተኞችን፣ ባለንብረትና ተዳዳሪዎችን፣ ወዘተርፈ. ያቀፉ ነበሩ፡፡ ይህም ማለት ማንም የሚረዳውና በሕይወት ልምምድ ውስጥ የነበረ እውነታ ነው  አመኔታን የሚያሳድሩና አስተማሪ ምሳሌዎች ስለነበሩ ሰሚዎቹ የነገሩ ፍቺና ቁምነገር ላይ በማትኮር ይገረሙ ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን ሰዎች ምሳሌዎችን ሲሰሙዋቸው የራሳቸውን ሕይወት መፈተሻ አድርገዋቸው ለመገኘት አቅም አላቸው
  • 29.  በሉቃስ 18፡9-14 ያለውን ክፍል ብንመለከት ዛሬም ቢሆን የፈሪሳዊነት የሕይወት ድባብ ላጠላብን ለእኛ እጅግ ጠቃሚ ምክር የያዘ ነው፡፡ አምልኮ በትሕትና፣ በመገዛት፣ መነሻን ባለመርሳት ለእግዚአብሔር አምላክ የሚሰጥ የልጅነት ምላሸ መሆኑን መርሳት ትልቅ ክስረት ነው፡፡ 3፡2፡2. ለተለየ ምክንያት የሚደረጉ ነበሩ  ይህንን የተለየ ዓላማ ያለውን ምክንያታዊነት ያስተላለፈው በሁለት መንገድ ነው፡፡ ሀ) ምሳሌው የያዘው የራሱ ትርጉም አንዱ ሲሆን ለ) ምሳሌው መነሻ የሆነበት አውድ ሌላው ነበር  ሁለቱን ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ሁለቱም የየራሳቸው ቦታ አላቸው፡፡ ለምሳሌ የመልካሙ ሳምራዊ ምሳሌ የተነገረበት ራሱን የቻለ የማስተማሪያ ትርጉም ቢኖረውም የተነሳበት አውድ ደግሞ ክርስቶስ ኢየሱስ ሊያስተምረው የፈለገው ነገር ምን እንደሆነ
  • 30.  የክርስቶስ ሥነ ስርዓታዊነት ራሱና በትኩረት ሊሙዋላ የሚገባው ዓላማ ሁለቱም የማይነጣተሉ ሆነው የተሰናሰሉ ናቸው፡፡  ከዚህ ተነስተን ልንል የምንችለው ክርስቶስ ኢየሱስ ምሳሌዎችን ሲጠቀምባቸው እያመናፈሳቸው አልነበርም፡፡ በተቃራኒው ሰሚዎች ተቀብለው ሊጠቀሙባቸው እንዲችሉ ተደርገው የቀረቡ ናቸው 3፡2፡3. ምሳሌዎቹ የሰውን የማሰቢያ ዓለም የሚያነቃቁ ነበሩ  ምሳሌ ሲነገር ፈተና የሚሆነው ብዙ መዘብዘብ ወይም ሰው ሊጨብጠው የማይችለውን ቁንጽል የሆነ እውነታ ማቅረብ ነው  ጌታ ክርስቶስ ግን ምን ማለት እንዳለበትና በምን ያህል መጠን ማቅረብ እንዳለበት ጠንቅቆ የሚያውቅ ጌታ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ምሳሌዎቹ የሰውን የማሰቢያ ዓለም ጨምድደው ይዘው ለትርጉም ፍለጋ የሚያነሳሱ ነበሩ
  • 31.  ለምሳሌ የጠፋው ልጅ ታሪክ (ሉቃ. 15፡11-32) የሚገርም የአባትና የልጅ፣ የማንድማማቾች፣ የቤተሰብ ግንኙነት ያማከለ ልብ አንጠልጣይ ምሳሌ ነው፡፡  የጠፋው ልጅ የሄደበት መንገድ፣ ያጋጠመው ፍትጊያና ክስረት፣ የምርጫና ውሳኔ ውጤት ውጣ ውረድ ሁሉ በሚገርም መንገድ የተተረከበት ነበር፡፡  የሰማው ሁሉ ለሕይወቱ የሚሆነውን ነገር ጨምቆ እየቀመረ በማሰላሰል ወደ ሕይወት ውሕደት የሚወስድበትን ሂደት ፈጥሮላቸው ነበር 3፡2፡4. መደነቅን የሚፈጥሩ ነበሩ  ሉቃስ 10፡19-31 ያለው ክፍል ሕብረተሰቡ ከለመደው የባለጠጋና ደሃ አመለካከት ያፈነገጠ ሲሆን እንዴት አስደንጋጭ አይሆንም  የማቴ. 20፡1-16 የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ የተመለከተ የሦስት ሰዓተም የአስራ አንድ ሰዓቱም የቀን ሠራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ አንድ ነው የሚለው አሳብ እንዴት አያስገርምም  በሉቃስ 10፡31-37 ያለውና ስለሳምራዊው ሰውዬ የነበረው መልካም አመለካከከት እንዴት ክርክርን የሚያስነሳና በግብዝነት የሚኖሩትን፣ የሚያስተምሩትንና የሚፈርዱት ፈሪሳዊያንን እያበሳጨ አያስገርማቸውም
  • 32. 3፡3. ምሳሌያዊ ንግግሮች ማጉያ መረጃዎች/መነጽሮች ናቸው 3፡3፡1. ከየዕለቱ የሕይወት አኑዋኑዋር የተወሰዱ ናቸው  የክርስቶስ ኢየሱስ ምሳሌዎች የተወሰዱት በየዕለቱ ከሚያጋጥሙ የሕይወት ልምምዶች ሆነው ለየግለሰቡ ያደርግ የነበረው ጥሪ ዕለታዊ አኑዋኑዋርን የሚሙዋገት ነበር  ይህም የውስጥ ሰውነት አመለካከትን በመቀየር አጠቃላዩን ሕይወት የሚማርክ ሙግት ነበር፡፡ ለምሳሌም ያህል፡-  አነጴጥሮስን አሳ ለማግኘት ሌሊቱን ሲዳክሩ ቆይተው “ሰውን አጥማጆች አደርጋችሁዋለሁ ሲላቸው ” የሚረዱት በዕለታዊ ኑሮአቸው ውስጥ የመጣውን የልምምድ መዛመድና ሽግግር ነው (ሉቃስ 5፡1-10)  በምጽዋት ሙዳይ ውስጥ የመጨረሻ ሳንቲሙዋን የጣለችውን ሴት አይቶ የተረጎመው የሰጪዋ ልምምድ የሚገርም ነበር (ሉቃስ 15፡8- 10)
  • 33.  ንጉሡን “…በዚህ ሁሉ ክብሩ ሰለሞን እንደዚህ አለበሰም…” በሚል ከአበቦች ጋራ አዛምዶ የተናገረበት መንገድ አስተማሪ ነው (ማቴ. 6፡27-29)  በገሊላ ባሕር አጠገብ “ምን ልታዩ ወጣችሁ” ያለበትና “ንፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆ” አስመልክቶ የተናገረበት ድምጸት የሚገርም ነበር (ማቴ. 11፡7፤ ሉቃስ 7፡24) 3፡3፡2. ለተጣራ /ግልጽ የሆነ ሁኔታ ተስማሚ ማጉያዎች  ለይዕለቱ አኑዋኑዋራችን የሚኖረን መጨነቅ በአግባቡ እንድንይዘው ነው በአምስት ሳንቲም ስለሚሸጡ ደንቢጦችና በኮረብታዎች ላይ ስለሚበቅሉ አበቦች የተናገረው (ማቴ. 6፡26-30)  በዓለት ላይ ወይም በአሸዋ ላይ ቤትን ስለማነጽ የሰጠን ትምህርት የሚገርም የማጉያ/የመደገፊያ መሣሪያ ነበር (ማቴ. 7፡24-27)
  • 34. 3፡3፡3. ማጉያዎቹ የድርጊት እሳቤን የሚያነቃቁ ነበሩ  ጌታ ክርስቶስ የፈጠረውን አጋጥሞ መያዝ፣ መምራትና በክትትል መቆጣተር፣ ይቅር ማለትና መፍረድ፣ ማዳንና ማደስ የሁልጊዜ ክንዋኔዎቹ ናቸው፡፡  በዚህም እግዚአብሔርን በሁሉ ነገራችን ውስጥ እንደናየው/እንድንገናኘው ለማድረግ የድርጊት ሰዎችም እንድንሆን ምሳሌያችን ነው  ሰዎችም በእምነት መረዳትና ልምምዳቸው በትኩረት ተሳታፊ እንዲሆኑ፣ መልካምን እንዲያደርጉ፣ የመለገስ ሥራዎችን እንዲያዘወትሩ፣ ከሚጠበቅባቸው አልፈው ለድርጊት እንዲንደረደሩ፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ላይ በቂ ጊዜ ሰጥተው ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ እንዲሆኑ የሚረዳ ማጉያ አድርጎ ምሳሌዎችን ይጠቀምባቸዋል
  • 35. 3፡3፡ 4. የክርስቶስን ፈገግታ የመጫር/የማፍታታት ኃይል የሚያሳዩ ናቸው  ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታችን ኅይወትን ቀለል አድርገን የምናይበትንና ፈካ የሚያደርጉ ጥጎችን ይጠቀማል፡፡ ይህ ማለት ግን የግለሰቦችን ሰው መሆንና መከራቸውን የረሳ አይደለም፡፡ ከተጠቀመባቸው ጥቂቶቹ፡-  መብራትን አብርቶ ከእንቅብ በታች ማስቀመጥ (ማቴ. 5፡15)  “ባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል አላቸው፡፡ እነርሱም ያለመጠን ተገረሙና እርስ በርሳቸው፡- እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል አሉ” የሚለው (ማቴ.19፡23-26)  ሰውየው በሌላው ሰው ዓይን ውስጥ ያየው ጉድፍ ነው፣ በራሱ ዓይን ውስጥ ግን ያለውን ምሰሶ ችላ ብሎአል (ማቴ 7፡3-5፤ሉቃ. 6፡41)
  • 36. 3፡3፡5. ሰዎች ወደ ትክክለኛው እምነት እንዲሻገሩባቸው ይጠቀምባቸዋል  ለክርስቶስ ምሳሌዎች የሰውን የምናብ/የአስተሳሰብ ዓለም ነክተው ሲያበቁ የሰሙዋቸው ሰዎች በትምህርቱና በእግዚአብሔር ላይ እምነታቸውን እንዲያሳድሩ ይረዳሉ (ምናብ ወደ እምነት ማለት ነው)  ለአሳብ መነሳሳት፣ በትልቀት ለማየት የተደረገው ነገር የሰውን ፈቃድ ለማግኘት ጉልበታም ነው፡፡ ይህም ደግሞ ሐቅ ያለበትመን የእምነት ምላሽ በሰሚዎች ውስጥ መፍጠር ይችላል  ጌታ ክርስቶስ የሕይወት እንጀራ፣ የሕይወት ውሃ ነኝ ሲል ሰዎች በራሳቸው “ምን ማለት ነው” ለሚለው ጥያቄ ምላሸስ እመንዲፈልጉ ዕድል የሚሰጥ ነው(ዮሐ. 6፡35)፡፡ ውሃው ሲፈላና ሲቀዳ፣ እንጀራም ሲቆረስ የጌታ ሕይወት ለኛ ያመጣውን ለማገናዘብ ይረዳል
  • 37. የሚከተሉትን ጥቅሶች ባለፈው ክፍል ያዛመደባቸውን አይቶ መጠቀም ይቻላል  ከዕለታዊ ኑሮ፡- ሉቃስ 5፡31፣6፡48፣7፡32፣9፡48፣11፡33-36፣20፡24  ከተፈጥሮ፡- 6፡33-34፣9፡58፣11፡11፣13፡6-9፣15፡4  ገጸባህርያት፡- 5፡31፣10፡30፣12፡39፣12፡58፣18፡2፣19፡12
  • 38. 3፡4. ጥያቄና መልስ ተጠቀመ  ማንኛውም የመማር ማስተማር ሂደት ያለ ጥያቄና መልስ ሙሉዕ አይሆንም፡፡ የመጀመሪያው ጠቃሚ ነገር ተመሪዎቻ ያላቸውን እውቀትና ሊሙዋላላቸው የሚገባውን እጦት መለየት የሚያስችል ነገር ነው  በሌላም በኩል መጠየቅ ተማሪዎች የተቀበሉትን ቁምነገር በትክክል አውቀውት እንደሆነ የመለያ ጉልበት ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የምናስተምራቸው ሰዎች ሕይወት ውስጥ የታመቀ ግን ለማፍሰስ ዕድል ያልተሰጠው እውቀት ሊኖር ስለሚችል ያንንም እምቅ ሃብት ለማውጣት ይረዳል  በማስተማር መማር ሂደቱ እንደገና ተማሪዎች የሚጠይቁበት ዕድል ያስፈልጋቸዋል፡፡ይህን ማድረግ የማይችል መምህር የተሙዋላ
  • 39.  በክርስትና ልምምዳችን ውስጥ የመጠየ ቅና የመወያየት ሂደት እይታና ትርጉምን በሥርዓት ለማስኬድና የመረዳት አድማስን ለማስፋት ጠቀሜታው ብዙ ነው፡፡  በዚህ ሂደት ውስጥ የመረዳት ባለጠግነት በመምህሩ ብቻ ሳይሆን በተማሪዎቹም የሕይወት ልምምድ የሚገለጥ መሆኑን ማወቅ የትልቅ ብልጽግና እሳቤ ነው  በክርስቶስ ኢየሱስ የማስተማር ሂደቶች ውስጥ ጥያቄዎች ጥያቄዎች ሰፊ ሚና ነበራቸው፡፡  ሲጠይቅ ግን መልሶች በጥያቄዎች ውስጥ እንዲኖሩ አድርጎ ስለነበር አብዛኛውን ጊዜ ከማንም መልስ ሳይጠብቅ የጀመረውን ይጨርስ ነበር  ጌታ ክርስቶስ ያነሳው “የፈሪሳውያን እርሾ” ትምህርቱ ውስጥ ብቻ አስር ጥያቄዎችን ጠይቆአል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ታጭቀው የሚገኙት በሰባት
  • 40.  የጠየቃቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት መልኮች ያሉት ነው 3፡4፡1. መልስ አዘል ጠያቄዎችን ድራማዊነት ባለው መልክ አቅርቦአል  እነዚህን በማድረግ ሲጠይቅ ተመሳስሎን በመጠቀም ነው፡፡ ይህም ማለት መዝሙር ነክ የሆኑ ድምጾች የሚመዘኑት በሕብር ነው፡፡ በዚህም የምናገኘው የተለያየ ነገር የሚናገሩ የሚመስሉ ግመን ደግሞ በሰው ድምጥ ሲባሉ ተመሳሳይ ነት ያላቸው ይመስላሉ  እነዚህን ጥያቄዎች ሲጠይቅ በእርሱ ጊዜ ለነበሩ አይሁድ ልምምድ በሚመች መንገድ የተጠቀመባቸው ናቸው፡፡ በዚህም የአሳቦች ተመሳስሎን በማውጣት የሚጠይቃቸው ጥያቄዎች ነበሩት ማለት ነው፡  ለምሳሌም፡- “የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን…?”
  • 41.  በዚህም ሁለት ጥያቄዎችን ሳይሆን የሚጠይቀው በአንድ አሳብ ጥላ ሥር የሚያስኬዳቸው ተመሳስሎዎች ናቸው  እንዳንድ ጊዜም አንድን እሳቤ በአንድ ጥያቄ አመላካችነት ሌላ ጥግ ላይ ያለውን እሳቤ በዚያው የእሳቤ ትንፋሽ በሌላ ጥያቄ ያቀርባል (ማቴ. 6፡27-28)  በሌላም በኩል ክርስቶስ ኢየሱስ የእሳቤዎችን ጥምረት በሁለት የተለያዩ ጥያቄዎች ያቀረበ በሚመስል መንገድ ያቀርበዋል (ማቴ. 7፡16)
  • 42. 3፡4፡2. ጥያቄን በጥያቄ መመለስ  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በወንጌላት ውስጥ እንደምናገኘው መቼም ቢሆን በሰዎች የጥያቄ ወጥመድ ውስጥ ገብቶላቸው አያውቅም ፡፡ በተለይም እርሱን ስህተተኛ ለማድረግ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች እጅ ሰጥቶ አያውቅም (ማቴ. 22፡34-40)  ምንም እንኩዋን ሙግትን ባይጠላም/ባያገልም እርሱ ግን ጠብ ጫሪ ንግግሮችን ጀማሪ አልነበረም ፡፡ ይህም ለሙግቱ ሲባል ብቻ!  ተቀናቃኞቹም እጅግ የተጨናነቀ ጥያቄ ሲጠይቁት ዝርዝር ነገር ውሰጥ ከመግባት ይልቅ ጥያቄውን ወደራሳቸው ይመልሰው ነበር፡፡ ለምሳሌም፡- “በሰንበት መፈወስ” የሚያመጣውን በጎ ነገር በቅንነት ባለማጤን ክርስቶስን ለመፈተን የሞከሩት ሰዎች “ከእናንተ…” ብሎ ነው የመለሰባቸው (ማቴ. 12፡11-12)
  • 43. 3፡4፡3. የሙግት አቅርቦት ያለበትን ጥያቄ መጠየቅ  ጌታ ኢየሱስ ሰዎች የራሳቸው መልስ እንዲኖራቸው እንጂ የመልሶች ጫና እንዳይከመርባቸው ለማድረግ የሚያስችላቸው ጥያቄዎች ነበሩት፡፡ ይህም እነርሱን ለማወናበድ ሳይሆን እውነት ነጥሮ እንዲወጣ ለማድረግ በመፈለጉ ነው  ከዚህም ጋር ሰዎች እንዲብራራላቸውም ይሁን ወይም ምላሽ የሚጠብቁበት ፍላጎት ይዘው ብቅ ሲሉ ጥያቄያቸውን ወዲያው ከመመለስ ይልቅ መረዳት ያገኙ መሆናቸውንና ሊከተሉት የወሰኑ እንደሆነ የሚያረጋግጥበትን ጥያቄ ያቀርብ ነበር፡፡ ለዚህ መረጃ የሚሆኑን ዓይ ሥውራኑ ናቸው ( ማቴ. 9፡27-30፣ 20፡29-34)  ከማንኛቸውም ይልቅ የክርስቶስ ጥያቄ እንደመዘውር መጠቀሚያ የሆነው የቄሳሪያው ልምምድ ነው (ማር. 8፡27-31፤ማቴ. 16፡13-20)፡፡ ይህ የክርስቶስን የአገልግሎት ሂደትና የእውነተኛ ደቀመዛሙርትን ማንነት የለየ ነው፡፡ እነዚህን የጥያቄ ጥቅሶች በግል እንይ፡- ለብዙሃን፡- ሉቃ. 6፡32-46፣7፡14-26፣9፡25፣ 12፡56-57፣ 13፡18-20 ለደቀመዛሙርት፡- ሉቃ. 8፡5፣9፡18-30፣16፡12፣12፡25፣12፡42 የሐይማኖት መሪዎች፡- ሉቃ. 6፡3፣ 6፡9፣13፡15፣14፡3-5፣ 20፡4፣20፡17 በተናጠል ያናገራቸው፡- ሉቃ.7፡42፣10፡26፣17፡17፣22፡48፣22፡52
  • 44. 3፡5. ለትምህርት ያለው ቦታ  በክርስቶስ ጌታ የማስተማር ዘዴ ሂደት ሁለት አቀራረቦች አሉ፡- “ትምህርት ራሳቸውን ለሰጡ” እና “ትምህርት ራሳቸውን ላልሰጡ፡፡” ይህም ማለት ጌታ ክርስቶስ የሚያስተምረውን ትምህርት ለሚቀበሉት አድማጮች አውድ የሚሆን አድርጎ የሚያቀርበው መሆንንም አመላካች ነው፡፡በዚህ ሂደትም አንዲቀበሉት ለማድረግ ጥድፊያ የሞላበት የእውነት አቅርቦቶች አልነበሩትም  በዮሐ. 16፡12 ላይ እንደምናገኝ “የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፣ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም” ብሎ ነበር፡፡ ይህም የሚያሳየን ጌታ ክርስቶስ ፍጹምነት ያለውና የሚፈልገውን ዕድገት ቶሎ የሚያመጣ ምላሽ ከአድማጮቹ አይጠብቅም ነበር ማለት ነው፡፡  ምናልባትም የተሙዋላ የአስተምህሮው ፍላጎትና ይዘት ከደቀመዛሙርቱ ሲያጣ ወደሁዋላ መልሶአቸው የማዝረክረክ ልምድ አልነበረውም፡፡ ታጋሽ መምህር ነበር!!  በዚህ ዘመን የሚታየው የማስተማር ሂደትና የመምሀራን ልምድ የሚነግረን ትዕግሥት የጎደለውና ሁሉን ነገር ለሚያስተምሩአቸው በመዘርገፍ ሰሚዎቻቸው ዝግጁነት ሳይኖራቸው የሚሠሩት ጉድለት ነው፡፡ ምራቅ ለዋጡ የሚሰጠውን መለየት መልካም ነው!!
  • 45.  የተራራውን ስብከት ስንመለከት ቁምነገሮቹ በማተ. 5-7 በእነድ ላይ ቢገኙም ይላሉ አንዳንድ ሰዎች፣ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙና ጌታ በተለያየ ጊዜ ያስተማረባቸው ናቸው፡፡ ሉቃስ ወንጌልም እነዚህን የያዘ ነው (ሉቃ. 4፡16-21፣ 6፡20-29፣9፡23-27፣ 12፡1-40) ስለዚህም የትምህርቱን ይዘት ስናይ፡- 3፡5፡1. ለትክክለኛ ደረጃ የተሰጠ ነበር  ከደቀመዛሙርቱ ጋር በነበረው ግንኙነት የቀረቤታ፣የጥልቀት፣ የራሱን ማንነት በሚገልጥ መንገድ በይዘቱ ለየት ያለና ሥር የሰደደ አቅርቦት ነበረው  የሚያስተምረውን ትምህርት ለአድማጮች እንዲመጥን አድርጎ ያቀርበው ነበር፡፡ አንዳንዶች ይህን ዓይነት አቀራረብ መነሳሳትን ለመፍጠር ድክመት አለው ይላሉ፡፡  ጌታ ክርስቶስ ግን በተናገረ ጊዜ ሁሉ ጥያቄ የሚፈጥር መሆኑ፣ ለማወቅ ተነሳሽነት መታየቱ፣አመኔታ በእርሱ ላይ ለማሳደር እንዲችሉና በጥንቃቄ እንዲያስቡ የሚያደርጋቸውን ይሰጥ ነበር
  • 46.  በዚህ ምክንያት ነበር የጌታ አቅርቦት ደርሶአቸው የነበሩ ደቀመዛሙርቱ “…እነሆ አሁን በግልጥ ትናገራለህ፣ በምሳሌም ምንም አትነግርም፡፡ ሁሉን እንድታውቅ፣ ማንም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን አሉት” (ዮሐ. 16፡19-30)  ይህ የማስተማር ሂደቱ ማለትም የሰሚዎችን የመቀበል ደረጃ የመጠነ አቅርቦት መሆኑ ምላሽ የሚሰጡትን ሁሉ ቀስ በቀስ ሊደርሱ ወደሚፈልገው ግብ የሚወስዳቸው ነው፡፡ የሚሰሙትን ሁሉ ግን በአንድ ጎዳና ላይ በጅምላ አይነዳቸውም፡፡ ለዚህ ነው “አሁን አወቅን” ያሉት
  • 47. 3፡5፡2. ሰዎችን ለድርጊት ያነሳሳበት ነው  አንዳንድ የሥነ ልቡና ምሁራን እንደሚሉት ስሜትን የሚያነሳሱ ነገሮች ብቻ ለሰሚዎች መስጠት በሰው ሥብዕና ላይ ሊኖረው የሚችለውን ችግር በጥንቃቄ መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚሰነዘሩ አሳቦች/እሳቤዎች እጅግ የሚያሳስት መረጃ ሰጥተው ሲገኙ የሚፈለገውን ለውጥ በሥራ ለመተርጎም አስቸጋሪ ያደርጉታልና  ክርስቶስ ኢየሱስ ግን ከዚህ ለየት ያለ ነበር፡፡ የሰጣቸው ትምህርቶች ሁሉ እሳቤንና ምናብን በሥራ ለመተርጎም የሚያስችሉ ነበሩ፡፡ ከትምህረቱ ጋራ በሥራ የሚተረጎም ምግትን አጣምሮ ሰጥቶአል  ክርስቶስ ዒየሱስ ባስተማረው ትምህርት ሶች በመገዛት ተረድተውት በውጤቱ ሕይወታቸው ተለውጦ “ብርሃንና ጨው” እንደሆኑ በመረዳት የእግዚአብሔር መንግሥት አባልነታቸውን የሚያሳዩበት ልምምድ ነው (ማቴ፣5፡13-14፣7፡21)
  • 48. 3፡5፡3. ትክክለኛ የውስጥ ተነሳሽነት/ዝንባሌ እንዲኖር አስተምሮአል  በማቴ. 5፡38-48 ያለው ክፍል የሚደንቅ የውስጥ ሰውነት መሰጠትን የሚጠይቅ፣ በመታዘዝ ለመኖር የተለወጠ ሕይወት የሚያመለክት ነው፡፡ “ቀኝን ሲመቱ ገራን ማዞር፣…ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣…የሚረግሙአችሁንም መርቁ፣…ለሚጠሉአችሁ መልካም አድርጉ፣ ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” የሚለው አብዮታዊ የሚመስልና የካድሬ ንግግር ነው የሚመስለው  ይህ እሳቤ በእግዚአብሔር አስተዳደርና በመንግሥቱ ውስጥ ፍቅቀና ይቅርታ ትልቁን ሥፍራ የዘው እነዳሉ ብስራት የተሰማበት ነው  ራስን በመካድ የሚደረገው የጠለቀ ዋጋ መክፈል፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ትምህርት ውስጥ የተቀመጠ ግብ ነው (ማቴ. 10፡34-42)፡፡  እግዚአብሔርም “የሰማዩ አባት” እንደሆነና ለራሱ የቤተሰብ አባላት በሁሉ ቦታ የሚያስብ እንደሆነ መረዳት እጅግ የሞቀ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው (ማቴ.6፡7- 13)፡፡
  • 49. 3:5:4. ትምህርቱ የማይጠፉ ምልክቶች የሚተው ነው  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምህርቱ ይዘት ውስጥ ሊደረስበት የማይችል ሃይማኖታዊ ፍልስፍና ወይም ከሰሚዎች አቅም በላይ የሆነና ሊደረስበት ሊጨበጥ የማይችል የረቀቀ ንግግር አላስተላለፈም  በተቃራኒው ከሰሚዎች ሊጠፉ የማይችሉና ለብዙሃኑ ሰዎች ልፍስፍስ ያልሆኑ፣ ቀርበው ለሚከተሉት ለደቀመዛሙርቱ ደግሞ ከሥብዕናው የወጡ የሕይወት መርሆዎች አስተላልፎአል  የተራራው ስብከት ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ እግዚአብሔር በሥራ ላይ እንዳለ፣ የእግዚአብሔርም መንግሥት መገለጫ እውነት እንደሆነ ሊታወሱ የሚችሉ መርሆዎች የተሞላ እነደሆን የምመንማርበት ነው  በዚህ የተራራ ስብከት ውስጥ በመንፈስ ድሃ መሆን፣ ማዘን፣ ጽድቅን መራብ፣ ምህረት ማድረግ፣ ልብን ማንጻት፣መታረቅና ማስታረቅ፣ ለጽድቅ መሰደድ እያንዳንዳቸው ከተከታይ በረከቶቻቸው ጋር ተነስተዋል፡፡ ድምር ውጤቱ ብጽዕና ነው!!
  • 50. 3፡6. በሁኔታ ውስጥ ማስተማር  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን የማስተማር ዘዴ ተጠቅሞበታል፡፡ በሁኔታዎች ውስጥ የተገኙትንም ሰዎች ለማስተማር ችሎአል፡፡ ይህን ስንል ሦስት ነገሮችን በማሰብ ነው፡- ሀ) በጊዜው የመጣውን ዕድል መጠቀም ትክክለኛ አተረጉዋጎም ይዞ መግለጥና ለሁኔታው የሚሆን የአሳብ ዳኝነትን መስጠት ጥሩ ነው ለ) በተገኘው ዕድል ውስጥ ሲጠቀም የሐቅ ሥርዓተ-ጥለት (Pattern) ከመኪያስተምረው ትምህርት ውስጥ ይገኛል፡፡ በክርስቶስ ትምህርት ሁሉ ውስጥ ያለ ይመስላል የምንለው በዘዴዎቹና በተሳተፈበት ሁኔታዎች ሁሉ ውስጥ በትምህርቱና በሁኔታው መካከል ስምምነት/ኅብር (Harmony) ነበረው ሐ) የሁኔታዎች ዕድል ሲገኝ ብቻ ሳይሆን በምናብ ውስጥ ወይም በታሰበ ሂደት ውስጥ ማደራጀት ይቻላል፡፡ በማንኛውም ጊዜ ታስቦበትም ይሁን ዕድሉ ራሱን ሰጥቶ አስፈላጊው ነገር እውነትን ለተከሰተው ሁኔታ በሚስማማ መንገድ መግለጥ ዋናው ነገር ነው
  • 51. አሁን ክርስቶስ ትምህርቱን የገለጠባቸውን ሁኔታዎች እንመልከት 3፡6፡1. ተአምራትና ምልክቶች በተከሰቱ ጊዜ  ጌታ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ከክብሩና በረከቱ ጋር የሚሰሙት ሑሉ እንዲረዱለት ሲሠራ ነበር፡፡ ምንም እንኩዋን እርሱ ራሱ ሰው ሆኖ ቢመላለስም ደግሞም ፍጹም አምላክ ስለሆነ ወደ እርሱ የመጡትን ችግረኞች ሁሉ ለመርዳት፣ ለመደገፍና ለመፈወስ ይችል ነበር  ሆኖም ሊፈውሳቸው የሚፈልጋቸውን ጥቂት ሰዎች ብቻ መርጦ አልነበረም የረዳቸው፡፡ ለማስተማር ምቹ በሆነ ጊዜ ሁሉ ትምህርቱን ሰጥቶአል፡፡ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ፈውስ ባካሄደባቸው ጊዘያት ሁሉ አላስተማረም  ዕድል ራሱዋን ስትሰጠው ግን ጊዜ አላጠፋም፡፡ በዚህም፡- ሀ) ምን ማድረግ እንደሚፈልግ ያብራራ፣ የሠራውን ለምን እንደሚሠራው ይናገር ነበር ለ) የተፈጸመውን ተአምር ለደቀመዛሙርቱ አንጸባራቂ ምልክት ሰጪ እንዲሆን አድርጎ ያበጀው ነበር
  • 52.  ከዚህ ሁሉ ውስጥ የምናወጣው ቁምነገር ታዲያ የሕይወት ሙላትና ደህንነት መገኘት መቻሉን ነው፡፡ ይህም ማለት የተገለጠው የእግዚአብሔር ኃይል ሕየወትን አጠቃሎ የሚለውጥ ጉልበት እንደሆነ ያስረዳበት ነውና  የተራቡትን መመገብ ረሃብን የማስታገስ ሥራ ብቻ ሳይሆን የሚያመላክተው የሕይወት እንጀራም እንዳለ በመሆኑ የክርስቶስ ሕይወት ወሳኝ የግለሰቡ የሕይወት ምዕራፍ ጅማሬ እንደሆነም አስረጂ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ዕድል በተገኘ ጊዜ ሁሉ ትምህርትንና የአሳብ ሙግትን ለአድማጮቹ ያቀርብ ነበር 3፡6፡2. ሰዎችን በግልም ሆነ በቡድን በተገናኛቸው ጊዜ ለምሳሌ ያህል፡-  የክርስቶስ ኢየሱስ እናት ማሪያም ከወንድሞቹ ጋር በተገናኘችው ጊዜ የሥራ ባልደረቦቹን ብቻ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የገቡትን ሁሉ እንደቤተሰብ አባላት የሚያቅፍበትን ሁኔታ ነበር ያበሰረው (ማር. 3፡33-34፤ ማቴ. 12፡47-48፤ ሉቃ. 8፡19-21)  የሳምራዊቲቱን ሴት ታሪክ ውሃ ልትቀዳ የመጣችበትን ጊዜ ተጠቅሞ ነው የሠራበት (ዮሐ. 4፡4-29)
  • 53. 3፡6፡3. የሰዎችን ምላሽ ለድርጊት በመጠቀም  በአይሁድ ሕብረተሰብ ውስጥ የነበረው የሞራልና የህብረተሰብ አኑዋኑዋር ከሃይማኖታዊ እሳቤዎች ጋር ተያይዘው እንዲገኙ ማድረግ ነበር ልምዱ የነበረው  እየቆየ ሲሄድ የእግዚአብሔር ሕግ መንፈስ እየጠፋ ሰዋዊ የሆነው ሥርዓት እየበዛ በመሄዱ ምክንያት ጌታ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ “እኔ ሕግን ለመሻር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ” ብሎ ያንን የተጣራ/ግልጽ የሆነ የሕግ መንፈስ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለመውሰድ አስተማረ  በዚህም የቀጥታ ትርጉም የያዘ የሕግ አጠቃቀም ተወግዶ እንዲገኝ በሥራ የተተረጎመ አኑዋኑዋርን አስገባ፡፡ በዚህም የሚያደርገውን ለምን እንዳደረገ ለማስረዳትና ለማብራራት ከፍተኛ ዕድል ሰጥቶት ተገኝቶአል ጥቅሶችን እንይ  በምልክቶችና ተአምራት ጊዜ፡- ሉቃ. 5፡12-26፣6፡6-11፤14፡1-14  ሰዎችን ሲያገኝ፡- ሉቃ. 7፡36-50፣ 9፡46-48፣10፡25-37፣14፡7-24  ለሰዎች አስተያየት በተሰጠ ምላሽ፡- ሉቃ. 5፡26-35፣6፡6-10፣11፡37-54፣15፡7-32  የደቀመዛሙርት ልምምድ፡- ሉቃ. 9፡28-31
  • 54. 3:7. የቃሉ አጠቃቀም  የእግዚአብሔርን ቃል በመጠቀም የማስተማር ጊዜ መነጋገሪያ የሆኑ ቅራኔዎችን ሲነሱ እንደነበረ የቆየ ጉዳይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የሚነሱትም የሥልጣን ጉዳይ፣ የይዘት ነገር፣ የባሕርይ ፍሰት፣ የዘዴው ዓይነትና በያንዳንዱ መምህር የሚሰጡ መልሶች ናቸው፡፡ 3፡7፡1. ጌታ ክርስቶስ ራሱ የቃሉን ሥልጣን ተቀብሎ ሠርቶበታል፣ኖሮበታልም  ይህም ሲባል አዲስ መረዳትን አምጥቶበት አሳይቶአል ማለታችን ነው፡፡ ይህንንም ለማድረግ ሲነሳ በብሉይ ያለውን የእግዚአብሔርን ቃልእነደገባ እንጂ ፍጻሜ ሊሰጠው ወደዓለም ሊያጠፋ እንዳልመጣ ነበር ያስረዳው (ማቴ. ፡17-20)  ለመልካም አኑዋኑዋር ተምሮ ለመገኘት የሚያስፈልገውንም ሲጠየቅ በብሉይ ኪዳን ያለው የእግዚአብሔር ሕግ አስፈላጊ መሆኑን ለማሳየት፡-  የፈወሳቸውን ለምጻሞች እንደ ሕጉ ራሳቸውን ለካህናት ማሳየት እንዲችሉ ማድረጉ (ሉቃ. 17፡11-19)  የዘላለም ሕይወት ለመውረስ የምን ላድርግ ጥያቄ ለጠየቀው ሰው በሰጠው ምላሽ ውስጥ (ማር. 10፡17-21)  ሊፈትነው ለነበረ መምህርና በተመሳሳይ ድምጸት ለተጠየቁ ጥያቄዎች በሰጠው ምላሽ ውስጥ (ሉቃ. 10፡25-28፣18፡18-21፣ማቴ. 19፡16-22፣ማቴ. 22፡34-40)
  • 55.  ጌታ ክርስቶስ ይህንን የሕግ ትምህርት ወደ ጠለቀ መረዳትና መንፈሳዊነት ለመውሰድ የሄደበት መሥመር ይታያል፡፡  ከላይ አንስተነው በነበረው የተራራው ስብከት ላይ እንደምናገኝ ለጎረቤታችን፣ ለወንድማችን፣ ለቤተሰብም ሊኖረን የሚገባውን የውስጥ ዝንባሌ መናገሩ ይታወሳል፡፡  አእምሮና ልብ ውስጥ ጅማሬያቸውን የሚያደርጉት መግደል፣ፍቺ፣በቀል፣ወዘተርፈ. የመሳሰሉት አደገኛ ጉዳዮች በብሉይ ኪዳን በጨከነ መንገድ ልክ አለመሆናቸው ተሰምሮበታል  ይህ ውጪያዊ ግን በውስጥ ሰውነት ተቀምሮ በሥራ የሚተረጎመው ጉዳይ መሠረታዊ የሆነውንና ሕጉ የሚሰጠውን የውስጥ መንፈሳዊነት ግብዝ ወደሆነ አስመሳይነት/የፈሪሳዊነት ልማድ በመለወጡ መክንያት ጌታ ክርስቶስ ወደ መሠረቱ የሚመልስ ግን በተለየ መረዳት ወደሚኖር መንፈሳዊ አኑዋኑዋር መለሰው
  • 56. 3፡7፡2.የቃሉን ሥልጣን ከሰዎች የተነሳበትን ተቃውሞ ለማረቅ አልተጠቀመበትም  ጸሐፍትና ፈሪሳዊያን ራሳቸውን የሐይማኖቱ ቁንጮና የጥያቄዎች ሁሉ ምላሽ እነርሱ ጋ እንዳለ አድርገው በመቁጠር የሚኖሩ፣ የሚሠሩና የሚያስተምሩ ስለነበሩ እነርሱን ተካክሎና በልጦ የተገኘው ጌታ ክርስቶስ ብቻ ነው  በጌታና በደቀመዛሙርቱ ላይ እነርሱ የሚሉት የሕግጋትን፣ ደንቦችንና በዓላትን አጠባበቅ ድክመት፣ ጌታ ራሱ ስለ መሲሁ የተናገረውን ምክንያታዊ አቅርቦትና ነቁዋም፣ ለሰንበት ያላቸው አመለካከት ላይ ቅሬታቸው ጥልቅ ነበር  ጌታ ክርስቶስ ግን ለእነዚህ ጉዳዮች ቃሉን በመጠቀም የሰጣቸው ምላሾች ማንም ሊኖረው የሚችለውን አዋቂነት የተላበሰ እንደነበረና እርሱም ይህን አካሄድ የተጠቀመው ቃሉን በትክክል ባለመተርጎም የመጣውን የተሳሳተ ሂደት ለማረም ነው
  • 57. 3፡7፡3. ጌታ ይዞ የመጣውን ተልዕኮ ደቀመዛሙርቱ እንዲረዱት ያደረገው በቃሉ ነው  ይህም ሲባል ጌታ ሲያስተምር፣ ተአምራትና ምልክቶችን ሲያደርግ ተልዕኮውን በትክክል በመተርጎም ሊያስረዳቸው መቻሉ ነው  መሲሁ መከረኛ መሲህ እንደሆነ ከብሉይ ኪዳን እየወሰደ አስተምሮአል (ኢሳ. 52፡13-53፡12 3፡8. ትምህርትን በድርጊት መማር  አሁን ባለንበት ዘመን ትምህርትን በተሳትፎና ድርጊቶችን በመከወን መማር መለመድ አለበት የሚባልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነበረው የማስተማር መማር ሂደት ውስጥ ይህንኑ የተጠቀመ ይመስላል፡፡ የሚከተሉትን እንይ፡- 3፡8፡1. ለመታዘዝ ፈቃደኛ መሆን  ጌታ ክርስቶስ በመማር ማስተማር ግንኙነቱ ሂደት ውስጥ ሰዎች አመኔታቸውን በእርሱ ላይ እንዲያሳድሩ ይሻል፡፡ ለዚህም ፈቃደኛ ሆነው እንዲገኙ ይሻል፡፡ የጌታ እናት ማርያም በቃና ዘገሊላ ሠርግ ላይ ለአዘጋጆች ያለቻቸው አሳብ የሚጠበቅ ነው (ዮሐ. 2፡5)  ደግሞም የክርስቶስ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መግባት፣ የጌታን ራትም ለማዘጋጀት የተሰጠን ጥዕዛዝ አቀባበል መታዘዝና መከተልን የሚያስረግየት ነው (ማር. 11፡1-7፤ማቴ. 21፡1-7፤ ሉቃ. 19፡28-35)  የጴጥሮስ በውሃ ላይ ለመራመድ የነበረው ታዝዞ መንገድ መጀመር ይህንኑ የሚያሳይ ነበር
  • 58.  የጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ መከረኛነት አስተማሪ ነው፡፡ ክርስቶስ ራሱ መታዘዝን የተማረው በመከራ ነው (ዕበራው. 2፡10፣ 5፡7-8)፡፡ ደቀመዛሙርቱም ከመከራቸው ይማራሉ የሚለው እውነትም የተጠበቀ ነው (ማቴ. 5፡11-12፤ ዕብራ. 11፡35-38) 3፡8፡2. ከውድቀት መማር  ጌታ ክርስቶስ ሐዋርያቱ ስህተት በፈጸሙ ጊዜ አርሞ ግን ደግሞ ከሄዱበት መንገድ ሊማሩ የሚችሉበትንም መውጪያ ያሳያቸው ነበር፡፡  ለምሳሌም እርሱ በሌለበት የፈውስ ልምዳቸውን ለመከወን ሞክረው ነበር፡፡ ጌታ ፍላጎታቸውና የማገልገል ዝንባሌያቸው ላይ ሳይሆን አትኩሮ የነበረው በውስጥ ሕይወታቸው ሊኖራቸው የሚገባው መንፈሳዊነት ላይ ነበር (ማር. 9፡14-29፤ሉቃ. 9፡37-42፤ማቴ. 17፡14-20)  ልጆች ወደ ጌታ ክርስቶስ ሲመጡ የእግዚአብሔር መንግሥት እነርሱን እንደምትጨምር ያልበራላቸው ደቀመዛሙርቱ ሲከለክሉአቸው “ተውአቸው” ነው ያለው፡፡ በዚያ ግን አልቆመም፤ የተደላደለና ጥልቅ የሆነ መርህ ነው ያስተማረበት (ማር. 10፡13-16)  በጌትሴማኒ ጌታ በተያዘ ጊዜ ሰይፍ አንስተው ሊዋጉ ሲሞክሩ “ሰይፋችሁን ወደ ሰገባው” ያለበት ልምምድ የማስተማሪያ ስህተት ነበር (ማተ. 26፡51-54)ሉቃ. 22፡49-51)
  • 59. 3፡8፡3. ራስን የመስጠትና የመልካም ባህርይን ልማድ ዋጋ በማወቅ  መንፈሳዊ ሕይወትን ለማጎልበትና ስለ ሕይወት ያለውን ትክክለኛ አመለካከት ለመያዝ አስፈላጊ የሆነው ነገር ራስን ለክርስቶስ በማስገዛትና ክርስትና የሚጠይቀውን ትክክለኛ ባሕርይ በመለማመድ ነው  ደቀመዛሙርቱ ሕይወታቸው እየተለወጠ እንዲጎለብት ያደረጋቸው ለክርስቶስ ጌታ በመታዘዛቸውና በማያቁዋርጥ ልምምድ ውስጥ በመገኘታቸው ነው  የክርስቶስ ኢየሱስም የማያቁዋርጥ ጸሎቱና ከአባቱ ጋር የነበረው ቀረቤታ ስለማረከው ነው “ጌታ ሆይ ዮሐንስ ደቀመዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን” ብሎ “ከደቀመዛሙርቱ አንዱ” የጠየቀው ፡፡ ጌታም “ስትጸልዩ እንዲህ በሉ…” ብሎአቸዋል፡፡ የተዋጣለት ሞዴል ነበር!!