Advertisement

More Related Content

Advertisement

Homiletic.pptx

 1. ሲ.ኤም ሲ. ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን 3/24/2023 Petros Geset
 2. መግቢያ የስብከትና የማስተማር አገልግሎትን ለቤተክርቲያን የሰጠው ጌታ ኢየሱስ ከመሆኑም ባሻገር ስብከት ለቤተክርቲያን መመስረትና ለምዕመናን መንፈሳዊ ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ስለሆነም በመጽሀፍ ቅዱስ የተፃፈውን እውነት ወይንም እግዚአብሔር የገለጠልንን ቃል እንዴት አድርገን ማዘጋጀትና ለሕዝቡ ማስተላለፍ እንዳለብን ስልቱን ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ በሌላ አባባል (God give revelation and man provides presentation) እንደማለት ነው፡፡ በመሆኑም ስለ ስብከት አቀራረብ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ትምህርት ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ 3/24/2023 Petros Geset ‹‹እንዲህም አላቸው ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ›› ማር 16፡15
 3. 3/24/2023 Petros Geset ሰው መንገድ መልዕክቱ (ሰባኪ) (ዝግጅት) (ስብከት) ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው የመንፈስ ቅዱስ መገኘት፣ ሃይል፣ ተፅእኖ ማሳደር እና ሙላት
 4. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው ትምህርት አንድ ዓላማ፡- • የስብከትን ትርጓሜ፣ ጥቅም፣ ምክንያት፣ ስነመለኮታዊ እውነት እና መፅሃፍ ቅዱሳዊ መሠረቱን ለተማሪው ማሳወቅ ጠባቡ ትርጉም • ስብከት ማለት ወደ ሰዎች ሁሉ መድረስ ያለበት መለኮታዊና ሰማያዊ ድምፅ ነው፣ የዳነ ሰው ላዳነው ጌታ መሳሪያ በመሆን የሚያስተላልፈው የእግዚአብሄር መልዕክት ነው እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ መልካም ዜና ነው፡፡
 5. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው ሠፊው ትርጓሜ ስብከት ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ፀጋ ወይም ስጦታ ብቻ ሳይሆን ጥበብና ሳይንስም ጭምር ነው፡፡ • ስብከት ስጦታ ነው ስንል በውስጡ የሚፈጠር መነሳሳት፣ መለኮታዊ ጥሪ፣ ያሰቡትን የማድረግ ችሎታ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው ለማለት ነው፡፡ • ስብከት ሳይንስ ነው ስንል ደግሞ ሰባኪውን ውጤታማ ሊያደርጉት የሚችሉ ተጨባጭ መርሆዎችን በመማርና በማጥናት ሊያድግ የሚችልበትን እውቀት ማግኘት ነው፡፡ • ስብከት ጥበብ ነው ስንል ደግሞ የስብከቱን መርህ ወደ ተግባር መቀየርና ውበት ያለው እንዲሁም ትርጉም የሚሰጥ ሆኖ በሰባኪው አማካኝነት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
 6. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው 1.2. የስብከት ዘዴ • ሆሚሌቲክስ የሚዳስሳቸው ክፍሎች በተለይም ዝግጅትንና መልዕክት አቀራረብን ነው፡፡ በጥናት የተመሠረተ ሂደትንና መንፈሳዊ ገጽታን ባካተተ መልኩ የሚታይ ሆኖ የሰውንና የመለኮትን ነገሮች አጣምሮ በስብከቱ፣ በሰባኪው እንዲሁም በአድማጮች መካከል መግባባትን የሚፈጥር ጥበብ ነው፡፡
 7. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው 1.2.2.ስለሆሚሌቲክስ የተሳሳቱ አመለካከቶች • ሰባኪው የስብከቱን ይዘት በተመለከተ አስፈላጊ ዝግጅት ካደረገ የስብከት ዘዴው ወዲያውኑ በቅጽበት ሊመጣለት ይችላል ይላሉ፡፡ • ሁለተኛው የተሳሳተ አመለካከት ደግሞ ሆሚሌቲክስ ዝግጅትና ጥናት ላይ ያተኮረ ሰው ሰራሽ ዘዴ በመሆኑ የመንፈሳዊን የስብከት ዝግጅት ገጽታ የሚያደበዝዝ ነው ማለት • ሰብአዊ የሆነ ችሎታና መለኮታዊ ብቃት በተናጠል የሚታይ እንጂ በአንድነት ተጣምረው የሚታዩ የሰባኪ ውጤቶች አይደሉም የሚል ነው፡፡
 8. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው 1.3. ለምን መስበክ አስፈለገ? • ትዕዛዝ ስለሆነ (ማር 16፡15) • ታላቅ ደስታ ለሰዎች ማብሰር ስለሆነ (ኢሳ 52፡7) • ሰዎችን ለማዳን ፍቱን መድሃኒት ስለሆነ (1ቆሮ 1፡21) • አማኞችን ለእግዚአብሔር መንግስት ለማዘጋጀት (2ጴጥ 3፡8- 9) • ለቤተክርስቲያን መመስረትና እድገት አስፈላጊ ስለሆነ (ማቴ 16፡18 የሐዋ 17፡6 1ቆሮ 2፡1-5 የሐዋ 19፡26) • የስብከት አገልግሎት ከጌታ አገልግሎት አንዱ ስለነበርና ፈለጉን መከተል ስለሚገባ (ሉቃ 4፡18)
 9. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው የእግዚአብሔር መለኮታዊ ባህሪ • ስብከታችን ስለእግዚአብሔር ያለንን መረዳት በሚገባ ይገልጠዋል፡፡ አምላካችን ራሱን ከገለጠባቸው ዋናውና ትልቁ መንገድ በመፅሐፍ ቅዱሳችን ነው፡፡ ዕብ 1፡1-3 መፅሀፍ ቅዱስ ቤተክርስቲያን 1.5. የስብከት ስነ-መለኮታዊ ባህሪ
 10. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው 1.6. የስብከት ጠቀሜታ ሀ. የእግዚአብሔርን ባህርይ ለመግለጥ ይጠቅማል • ባህሪውን በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል ገልጧል፡- • ባህሪው በልጁ በኩል ገልጧል፡- • ባህሪው በመልእክተኞቹ በኩል ተገልጧል፡- ለ. ለመንፈሳዊ ዕድገት ይጠቅማል፡፡ • ቅዱሳን ሰዎችን ሁሉ ለአገልግሎት ማዘጋጀት ከወንጌል ስርጭት አንጻር • አማኞችን በእምነትና በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ማሳደግ • መምራት፡፡ • ቅዱሳንን ከሃሰት ትምህርት መጠበቅ
 11. 3/24/2023 Petros Geset ሐ. መለኮታዊ ጥሪን ለማከናወን ይጠቅማል መ. ለወንጌል ስርጭት ይጠቅማል ሠ. የሰውን ችግር ለመፍታት ይጠቅማል ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው
 12. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው 2. ስብከት በታሪክ ውስጥ እና በስብከት ውስጥ የሰዎች ድርሻ 2.1. ስብከት በታሪክ ውስጥ • መጥምቁ ዮሐንስ፣ ኢየሱስ እና ሐዋርያት ይህን አድርገዋል የሐዋ ሥራ በሐዋርያት ዘመን ስለተከሰተው የስብከት አስደናቂ ውጤት ይነግረናል፡፡ እድገቱም የተመዘገበው በመንፈሳዊና በቁጥር ነው፡፡ (የሐዋ 2፡41-47፣ 4፡4፣ 6-7፣ 8-4)፡፡
 13. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው 2.1.2. ስብከት በቤተክርስቲያን አባቶች ዘመን • በስብከት ከፍተኛ ለውጥ የመጣውና የተመዘገበው በ4ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ነው፡፡ “ዮሐንስ አፈወርቅ” (ስሙ ለነበረው የንግግር ችሎታ የተሰጠው መጠሪያ ነበር፣) እንዲሁም ቅዱስ አውግስጢኖስ ሌሎች አምብሮስ፣ ታላቁ ባሲል፣ ጎርጎሪዮስ እንዲሁም ሂላሪን የመሳሰሉት ታሪክ የማይረሳቸው የለውጥ ሰዎች ነበሩ፡፡ 2.1.3. ስብከት በጨለማው ዘመን • ከዚህ በኋላ መካከለኛው የጨለማ ዘመን (ከ430 - 1095 ዓ.ም) በመባል የሚታወቀው ወቅት ነው፡፡ ስብከት የሞተበት
 14. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው 2.1.4. የተሃድሶ ዘመን • የተሐድሶ ዘመን (ከ1361-1572 ዓ.ም.) ቤተክርስቲያን በመንፈሳዊ አቋም እድገት ያሳየችበት ጊዜ ነው፡፡ ጆን ዊክሊፍ፣ ጆን ሀስ፣ ካልቪን፣ ኖክስ፣ ዘዊንግሊ እና ፊልጵ የመሳሰሉት 2.1.5. ስብከት በዘመነኛው ዓለም • በማንሰራራት ዘመን (ከ1611-1900 ዓ.ም) ቤተክርስቲያን የእድገትና የውድቀት ሁለት ገጽታዎች ነበሯት፡፡ የጆንዌስሊ፣ የቻርልስ ዌልሲ እንዲሁም የጆርጅ ዋይት ፊልድ የወንጌላዊነት ጸጋን የተሞላ ስብከት ነበር
 15. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው 2.1.6. ስብከት ከድህረ ዘመናዊነት በኋላ • በዘመናዊ አለም ከ1900 እስከ ዛሬ ደግሞ ጠንካራ የሆነ የስብከት እድገትና ውድቀት የተስተናገደበት እና እየተስተናገደ ያለበት ጊዜ ነው፡፡ • ያለው መንፈሳዊነትና የቁጥር እድገት ከስብከት ውጤት ጋር ተያይዞ የሚታሰብ ነው፡፡ • በሌላኛው ገፅታ ደግሞ የመንግስት ወንጌል ስብከት ከአስተምህሮ ጥራት አንፃር ሊሆን ከሚገባው ወደታች ወርዶ ይገኛል፡፡ ቢሊግርሃም
 16. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው 2.2. በስብከት ውስጥ የሰውና የእግዚአብሔር ድርሻ • የስብከትን መርህ የተከተለ ጥናትና ዝግጅት በማድረግ እንዲቀርብ • የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም ስልት የተከተለ እንዲሆን • የሰውን ልጅ ተፈጥሮ በመረዳት የስነልቦና መርህ በመከተል የተሻለ መነሳሳት እንዲፈጥር • ግብ ያለውና ውጤቱም የሚታይ ስብከት አቀራረብ እንዲኖረው የሚያበቃ በቂ ዝግጅት እንዲያደርግ • ለእያንዳንዱ የስብከት ተግባር ታማኝና የተሟላ የፀሎት ጊዜ የሚኖረው እንዲሆን • በፀሎትና በኑሮ ባለው እንቅስቃሴ በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ውስጥ እንዲኖር • የመጽሐፍ ቅዱስን ክፍል በሚችለው መጠን በቃሉ እንዲያጠና
 17. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ አንድ የስብከት አጠቃላይ ገፅታው 2.2.1. የሰባኪ የብቃት መስፈርቶች •የኃጢአት ይቅርታ በማግኘት የዳነ መሆን ይገባዋል •የቅድስናን ኑሮ የሚናፍቅ መሆን አለበት •የኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነት በግሉ የሚያምን መሆን ይኖርበታል(ሮሜ 14፡1-9፣ 1ቆር 4፡1-2 •ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታን የተቀበለ መሆን ይኖርበታል (ሉቃ 24፡47-49 የሐዋ •ቃሉን ለመስበክ ከፍተኛ ፍላጐት ያለው •ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስንና የሚያገለግላቸውን ሰዎች የሚወድ ሊሆን ይገባል •የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ያስፈልጋል
 18. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች
 19. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች ትምህርት ሦስት ዓላማ፡- • ስለ ስብከት ዓይነቶችን ግንዛቤ በማስጨበጥ ተማሪዎች እንዲለማመድ መርዳት 3. የስብከት ዓይነቶች በስነ-ስብከት ውስጥ በዋናነት ልናወሳቸው ከሚገቡ ነገሮች አንዱና መሰረታዊው እውነት የስብከት አይነቶች ናቸው፡፡ይህም የስብከት ዓይነቶችን ጠንካራና ደካማ ጎን የበለጠ ለመለየት እንድንችል ይረዳናል፡፡
 20. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 3.1. ርዕሰ-ጉዳያዊ ስብከቶች (Topical Sermon) ትርጉም ይህ የስብከት ዘዴ ዋና ጭብጡና የስብከቱ ክፍልች ከአንድ ሁነኛ ምንባብ ሳይሆን ከርዕሱ የሚመነጭበት ዘዴ ነው፡፡ • ርዕሰ ጉዳያዊ ስብከት ከአንድ ነባራዊ ጭብጥ ሊጀምር ወይም ሊነሳ ይችላል • የመነሻ ጭብጡ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሊደገፍ ይገባል
 21. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 3.1.1. እንዴት እንምረጥ • በእግዚአብሔር ምሪት በፀሎትና ያነበብነውን ቃል በማሰላሰል • ከተለያዩ ቦታዎች በሚነሱ ጥየቄዎችና ከወቅታዊ ጉዳዮች • አንድ የመፅሀፍ ቅዱስ ቁጥር እንደመነሻ አድርገን በመነሳት የሃሳብ ፍሰቱን በመጠበቅ ልንመርጥ እንችላለን፡፡
 22. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 3.1.3.ጥቅሙ • ብዙ ስር-መሰረት(ዳራ) እና መጽሀፍ ቅዱሳዊ ምርምር አለመጠየቁ • በአንድ ምንባብ የለመታሰርና የመፅሀፍ ቅድስ ክፍሎችን እያሰሰ ጭብጡን ለማዳበር ሰፊ ነፃነት መስጠቱ • ከሌሎች ስብከት ዘዴዎች ይልቅ እያደገ የመሄድ ዝንባሌ መኖሩ 3.1.4. ጉዳቱ • ሰባኪያን ተወዳጅ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ማድረጉ • መፅሀፍ ቅዱሳዊ ላልሆኑ ስብከቶች ለመንሸራተት በር መክፈቱ • ርዕሱ የሚመነጨው በአብዛኛው ከመጽሀፍ ቅዱስ ሳይሆን
 23. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 3.1.5.የርዕሳዊ ስብከት ቅርፅ አሰጣጥ ማውጫና ማዕከላዊ ሃሳብ(የክፍሉ ርዕስ) የሚወሰነው ከአወቃቀሩ ሲሆን ትኩረት ከመሳቡ የተነሳ ‹‹እንዴት›› የሚል ጥያቄ መፍጠሩ አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ ወደሚፈለገው ነጥብ ለመንደርደር ይረዳል፡፡ መሠረታዊ የሆነ ሃሳብ የማግኛ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማውጫ(አስተዋፅዎ) ማዘጋጀት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ እምነትን………….
 24. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 3.2. አውዳዊ ስብከት ዘዴ (Textual Sermon) 3.2.1. ትርጉም አውዳዊ ስብከት ዘዴ ዋናው የሃሳብ መነሻ ሆኖ የሚያገለግለው መፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ የተፃፈው ጥቅስ ሲሆን የመጨረሻ ትልቅ በውስጡ የሚይዘው ቁጥር 3 ይሆናል ፡፡ ርዕሱም ሆነ ዋና ክፍሉ ከመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ሌሎች ንዑስ ክፍሎችን ከሌላ የሚዛመዱ ክፍሎች ሊያወጣ ይችላል፡፡ ነገር ግን ንዑስ ክፍፍሎቹ ዋናውን ክፍል በሚገባ የሚደግፉ ሊሆኑ ይገባል፡፡
 25. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች • እምነት ምንድን ነው፡- የእምነት ስነ-ተፈጥሮ(ትርጉም መዳሰስ) • እምነት የሚመጣው ከየት ነው፡- (የእምነት መገኛ (ምንጭ) ምን እንደሆነ ማሳያ) • እምነት መለማመድ የሚቻለው መቼ ነው፡- (የእምነት ጊዜ የሚገለፅበት) • እምነት የሚነሳው በምንድን ነው፡- (የእምነት ምክንያትን መጥቀስ) • እምነትን እንዴት መለማመድ ይቻላል (እምነትን የመለማመድ ዘዴ የምናሳበት) • እምነትን ለምን መለማመድ ያስፈልጋል፡- (የእምነት ዓላማ የሚንፀባረቅበት) • እምነትን በመለማመድ ምን ውጤት ይገኛል፡- ( የእምነት
 26. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 3.2.2. አውዳዊ ስብከት ቅርፅ • የምንባብን ክፍል ከፍተኛ ጥንቃቄ መምረጡ ፡፡ • ዋና ክፍሎችን ከዚሁ የምንባብ ክፍል ማውጣት ፡፡ • በአብዛኛው ጊዜ የምንፈልገውን ሐሣብ ፈልጐ ለማግኘት የሚከተሉትን መጠይቆች መጠቀም ይገባል፡፡ ምን? መቼ? ለምን? ማን? • በአንድ አውድ ምንባብ ውስጥ ሦስት እና አራት የሚሆኑ የተለያዩ አስተዋጽዎችን ለማዘጋጀት አለመሞከር፡፡
 27. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 3.2.3. እንዴት እናዘጋጅ • የክፍሉ ዋና ዋና ቅርፆች የሚያሳዩት ዋናውን ሃሳብ እንዲሆኑ ማድረግ • ዋና ዋና ክፍፍሎቹ እውነትን ማስያዝ • አንድ ርዕስ በተቀመጠለት ቅርጽ ውስጥ ማሳደር/ማስቀመጥ • ዋና ዋና ክፍሎቹ በሃሳብም ይሁን በቅደም ተከተል ቀጣይነት ያለውን እድገት የሚያሳዩ ማድረግ • በክፍሉ ውስጥ ያሉትን ቃላት በመጠቀም መከፋፈል • በማወዳደርና በማነፃፀር መዝ 1፡1-2 ምሳ 14፡11
 28. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 3.2.4. አውዳዊ ስብከት ለማዘጋጀት የጥቅስ አመራረጥ • ከሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንፃር ማየት ይገባል፡፡ • ዘወትር መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብን ልማድ ማድረግ • የመንፈስ ቅዱስ ምሪትን መጠየቅ • በምንባብና ጥናት ጊዜ ማስታወሻ መያዝ፣ • መንፈሣዊ መፃህፍትን የማንበብ ልማድ ማዳበር፣ • የምንመርጠው ጥቅስ ወይም የምንባብ ክፍል ግልጽ መሆኑን ማረጋገጥ፣ • አወዛጋቢ ወይም አሻሚ የሆኑ ለአተረጓጐም የሚያስቸግሩ ምንባቦችን አለመምረጥ፣ • የተቆራረጠ ሀሣብ ወይም ጅምር ሐረግ አለመጠቀም • የያዝነውን ወይም የመረጥነውን ክፍል በትክክልና በጥንቃቄ መተርጐም መቻል • በአተረጓጐም ጊዜ ሁሉን ነገር መንፈሣዊ ትርጉም ከመስጠት መቆጠብ ይኖርብናል፡፡
 29. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 3.2.5. ጠቃሚ ጎን • ከጊዜያዊ ነገሮች ይልቅ መፅሃፍ ቅዱስ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዲቻል ማድረጉ • በተሻለ መንገድ ሃሳቡን ማሳደግና ለሰሚ ማቅረብ ማስቻሉ • በቀላሉ ለማዘጋጀት የሚያስችል መሆኑ አንድ ሃሳብ ላይ ብቻ ማተኮሩ • ስብከቱን በቀላሉ ለመረዳትና ለማስታወስ መቻሉ 3.2.6. ደካማ ጎን • በቂ የሆነ የዝግጅት ጊዜ አለመጠየቁ • ጠባብና ጥልቅ የሆነ ነገር የሚገኝበት ያለመሆኑ • አንዳንድ ክፍሎችን ያላሉትን እንዲሉ የሚገፋፋ መሆኑ • ክፍሉን ከምንባቡ ውጪ እዲተረጎሙ በር መክፈቱ
 30. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች ምሳሌ 1 • ጥቅስ፡- ዮሃ 3፡16 • ርዕስ፡- ‹‹ደህንነት›› ዋና ዋና ክፍሎች • የደህንንት ምንጩ ማን ነው ? • ደህንነት የሚያስፈልገው ለማን ነው ? • ደህንነት ለምን አስፈለገ ? • የደህንነት ዋጋው ምንድን ነው ? • ደህንነት የሚገኘው በምን መልኩ ነው ? • የደህንነት ውጤት ምንድን ነው ?
 31. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አጠቃላይ ገፅታው 4.1. ትንታኔያዊ ስብከት (Expository Sermon) 4.1.1 ትርጉም ይህ የስብከት ዓይነት በመጽሃፍ ቅዱስ አንድ ክፍል ላይ የተመሰረተ ሲሆን ጭብጡ፣ የስብከቱ ክፍሎችና ድጋፍ ሰጪ ሃሳቦች ከራሱ ከምንባቡ የሚመነጩበት ነው፡፡ የዚህ ስብከት ሌላው ዓይነተኛ ባህሪው ከመጽሀፍ ቅዱስ የተወሰደ መሆኑና በተቃራኒው በሌሎች ጠቃሚ ሃሳቦች ላይ ያልተደገፈ አንድ ዓላማና ጭብጥ ያለው መሆኑ ነው፡፡ • በትንሹ 4 ቁጥሮችን ያካትታል • መፅሀፍ ቅዱሳዊ ለሆነ የንባብ ድጋፍ ቅድሚያ ይሰጣል • ጭብጡ ክፍፍሉ ማለትም አብይና ንዑስ ከራሱ ከክፍሉ ይሆናል • ነጠላ ቃል ሳይሆን ፀሃፊው በክፍሉ ምን ማለት እንደፈለገ ትኩረት ያደረጋል
 32. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.1.2. እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል • የተመረጠውን ክፍል በተገቢው መንገድ ደጋግሞ ማንበብ • ጸሃፊው በመንፈስ ቅድስ አማካኝነት ለአድማጮች የሚናገረው ምን እንደሆነ መረዳት • ቃሎችን እንደ አገባባቸው መፍታትና መከፋፈል • ለእኛስ የሚለው ምንድን ነው ብሎ መጠየቅና ማግኘት • ማድረግ ያለብንን (ተዛምዶ) ምንድን እንደሆነ ለይቶ ማውጣት
 33. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.1.3. ጠቃሚ ጎን • የእግዚአብሔርንና የፈቃዱን መጽሃፍ ቅዱሳዊ መገለጥ ያስተላልፋል • ወደቃሉ ስንቀርብ የመሳት እድላችን ይጠባል • ጥንቃቄ የሚጠይቁና አወዘጋቢ ጉዳዮችን በቅደም ተከተላዊ ትምህርተ ዓውድ በቀላሉ ሊስተናገዱ ይችላሉ • ሰዎች በቀላሉ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እንዲገናኙ ያደርጋል • ከአውዳዊና ከርዕሰ ጉዳዮች በበለጠ የመጽሀፍ ቅዱስ ሃሳብ የያዘ ነው 4.1.4. ደካማ ጎን • በስብከትም ይሁን ከመጽሀፍ ቅዱስ አተረጓጎም አንፃር ሰፊ የዝግጅት ጊዜ መጠየቁ • ለመጀመሪያ አድማጮች ያለውን ትርጉም መሳት • ወደተለያዩ መጽሀፍ ቅዱስ ማብራሪያዎችና ንባቦች ላይ በማተኮር መደናገር • ረዥም በመሆኑ ለመሰብሰብ መቸገር • በአንድ ጊዜ ሰብስቦ ለማስተማር አዳጋች መሆን
 34. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች ምሳሌ 1 ጥቅም፡- ኤፌ 6፡10-18 ርዕስ፡- “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ” ዋና ዋና ሃሳቦች 1. የክርስቲያን ሞራል (ኤፌ 6፡10-13) በጌታ ፀጋ ከፍ ያለ መሆን አለበት (-10) በጌታ ፀጋ ጽኑ መሆን አለበት (11-13) 2. የክርስቲያን የጦር እቃ (6፡18) ራሱን የሚጠብቅበት መከላከያ (6፡14-17) የሚያጠቃበት (-17) 3. የክርስቲያን የፀሎት ህይወት (ቁ-18) በመንፈስ መፀለይ በንቃት መፀለይ ለሌሎች በመማለድ መፀለይ
 35. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.2. ትረካዊ የስብከት ዘዴ 4.2.1. ትርጉም ትረካዊ ሰብከት ከትረካዊ ምንባብ ወደ ሚመጣው ዓብይ ሃሳብ በሚመራ መልኩ መፅሃፍ ቅዱሳዊ ታሪክን የሚያቀርብ የስብከት ዘዴ ነው፤ ይህ የስብከት ዘዴ አድማጮችን በቀላሉ ለመማረክ ወደ ሚፈለገው አቅጣጫ ለማምጣት በእጅጉ የሚረዳ መንገድ ነው፡፡
 36. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.2.2. እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል • ባለ ታሪኩን ማንነት በሚገባ መገንዘብ • የባለታሪኩን የበስተኋላ ታሪክ መነሻውን፣ ጊዜውንና ቦታውን ማወቅ • ባለታሪኩ የነበረበት ዘመን ሁኔታ መረዳት • በኖረበት ዘመን የገጠመው ሁኔታ የእርሱና /የእግዚአብሔር ምላሽ ምን እንደነበር ማጥናት • የታሪኩ አካላት በሆኑት በገፀ-ባህሪያቱ፣ በሴራው፣ በጡዘቱና በመደምደሚያው አማካኝነት ማዳበር
 37. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.2.3 ጠቃሚ ጎን • የሚያብራራና አስደሳች የሰዎችን ሃሳብ በቀላሉ ለመያዝ የሚያስችል መሆኑ 4.2.4 ደካማ ጎን • የስብከቱ ዋና ሃሳብ ግልፅ ያለመሆን • የሚበልጠውን ጊዜ ትረካው መውሰድና ሃሳብ ዳብሮ እንዳይወጣ በቂ ጊዜ አለመስጠቱ
 38. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች ምሳሌ 1 ጥቅስ ዮሃ 11 ርዕስ፡- ትንሳኤ የኢየሱስ ማልቀስ ያምናሉ •የማርያምና ማርታ ጭንቀት •የደቀመዛሙርት ፍርሃት •የክርስቶስ መዘግየት •የአልአዛር መሞት
 39. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.3. ምሳሌያዊ የስብከት ዘዴ 4.3.1. ትርጉም • በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰውን ምሳሌ ወይም ምልክት ባህሪና ድርጊት ማዕከል ያደረገ የስብከት ዘዴ ነው • ጥሩ የሆኑ አድማጮችን መፍጠር ይችላል • በቀላሉ ሊደመጥ የሚችል ነው • ይህ ስብከት በቦታ፣ በሰው፣ በእንስሳ፣ በውሃ፣ በባህሪና በዛፍ የተመሰሉትን ሊሆን ይችላል
 40. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.3.2. እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል • ግልፅና ቀላል የሆኑ ምልክቶችን መጠቀም • የትርጉም ባለቤት ጌታ ስለሆነ የግል አመለካከትን ከመሰረታዊ እውነቶች ጋር ያለማያያዝ • ማንኛውንም የስነ-ስብከት ዘዴ መጠቀም ይችላል ምሳሌ 1 • በግልጽ የታረደው በግ የክርስቶስ ምሳሌ ነው (ዮሀ 1፡29) • ወይን በክርስቶስ መመሰል (ኢሳ 5 እና ዮሀ 15፡1-2) • የሙሴ ህግ በክርስቶስ ሊመጣ ላለው መልካም ነገር ምሳሌ (ዕብ 10፡1)
 41. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.4. ጥቅስ ላይ የተመሰረተ ስብከት(Texual Topical Sermon) ምንባባዊ ርዕሳዊ ስብከት ማለት የስብከቱ ማዕከላዊ ነጥቦች ወይም ሐሣብ አሊያም ርዕስ የሚወጣው ከዚያው ከተወሰነው የምንባብ ክፍል ሆኖ ዋና ዋና ሐሣቦቹ ማዕከላዊ ሐሣቡን ወይም ርዕሱን ለማጉላት (ለመደገፍ) ሲባል በምንባብ ክፍሉ ብዙ ሳይደገፉ እየተስማሙና እያደጉ የሚሄዱበት ነው፡፡ ክፍሉንና አንዳንድ ሊያጐለብቱ የሚችሉ ማጣፊያዎችም ከሌሎች የምንባብ ክፍሎችና ውጫዊ ምንጮች ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡
 42. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.4.1. የስብከቱ ባህሪያት • ሁሉን ዓይነት የስብከት ዓይነቶች ይዘት ጠቅልሎ የያዘ ነው፡፡ • ማዕከላዊ ሐሳቡ ከምንባብ ክፍሉ የወጣ ነው፡፡ ይህን በምናይበት ጊዜ የአውደ ምንባባዊ ስብከትን ይዘት ዓይነት እንዳለው ልብ እንላለን፡፡ በእርግጥ አውዳዊ ስብከት ከአውድ ውጭ አይሄድም • ዋና እና ንዑሳዊ ክፍሎቹ እንዲሁም ሌሎች ተግባራዊ ይዘቶች ርዕሱ ወይንም ዋና ሐሳቡን ለማሳደግ የሚረዱ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ የርዕሳዊ ስብከት ዓይነት ባህርይ እንዳለው ያሳያል፡፡
 43. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.4.3. ስብከትን በጥቅስ ሃሣብ (Text) ላይ መመስረት ያለው ጥቅም • የሰባኪው ሐሣብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዲሆን ይረዳል፡፡ • የአድማጮችን የመስማት ፍላጐት ይጨምራል፡፡ • አድማጮች በቀላሉ የተሰበኩትን እንዲያስታውሱት ይረዳቸዋል፡፡ ክፍል ባነበቡ ጊዜ ስብከቱን እንዲያስታውሱ ይረዳል፡፡ • የስብከት ሀሣብ የተመሠረተበት ክፍል ለማየት ሲባል እግረ መንገድ ሙሉውን የምንባብ ክፍል እንዲያነቡ ለማነሳሳት ይረዳል፡፡ • ሰባኪው ያዝ ለቀቅ እያደረገ ዋናውን ጭብጥ ትቶ በተበታተነ ሃሣብ ውስጥ እንዳይገባ ይረዳል። • ሰባኪው ያለ ፍርሀት በነፃነትና በመተማመን እንዲሰብክ
 44. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.5. ቁጥር በቁጥር ትንተና (Running Commentary Sermon) ቁጥር በቁጥር ትንተና ስብከት ሲገለጽ በጣም ቀላል፣ ለቀቅ ያለ ሆኖ ረዘም ያለና ከምንባብ ክፍል ውስጥ የሚወጣ • መንደርደሪያ፤ • እንድነት • ቅደም ተከተል የጠበቀ ነው፡፡ • ከአንድ የምንባብ ክፍል ቁጥር በቁጥር እያደገ ከሚሄድ ተከታታይ መንፈሣዊ እውነታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው፡፡
 45. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.5.1. የቁጥር በቁጥር ትንተና ስብከት • የስብከት ሁሉም ክፍሎች ሊኖሩት ይገባል፡፡ • የምንባብ ክፍሉ ማዕከላዊ የሐሣብ ፍሰት ኖሮት ቢያንስ ማዕከላዊ አንድነትና ቅደም ተከተል ሊኖረው ይገባል፡፡ • የሆነ የምንባብ ክፍሉ ስብከቱ መሠረቱን እንዳይለቅ የሚያደርገው ነው፡፡ • የቁጥር በቁጥር ትንተና እንደመሆኑ መጠን ቅደም ተከተሉን ማስተካከል አያስፈልገውም፡፡ • ተከታታይነት፣ ወጥነትና ተዛማጅ እውነታ ያለው ሆኖ የስብከት ዘዴውን ዋና ክፍል ማዕከላዊነት ሊጠብቅ ያስፈልጋል፡፡
 46. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.6. የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ስብከት (Bible Reading Sermon) ይህ የስብከት ዓይነት ማዕከላዊ ሃሣቡን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከሆኑ ቃላት በመጀመር በመላው የመጽሐፍ ቅዱስ የምንባብ ክፍሎች የሚገኙ ተመሣሣይነት ያላቸውና የመነሻ ሐሳቡን የሚደግፉትን ዓረፍተ ነገሮች፣ ቃላት ወይም ሐረግ በመምረጥ እያስደገ ይሄዳል፡፡ ለምሣሌ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ እምነት እያለ የሚፈልገውን ይመርጣል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ስብከት መግቢያ ሲታይ ርዕሳዊ ስብከትን ይመስላል፡፡
 47. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.6.1. የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ስብከት አስተዋጽኦና አዘገጃጀት፡- • በተደጋጋሚ የታዩ ቁልፍ ቃላትን ወይም እንደ ርዕስ የጐሉትን መምረጥ • የተወሰኑ የምንባብ ክፍሎችን በመምረጥ ጐን በጐን ማጥናትና • ከእያንዳንዱ ደጋፊ የምንባብ ክፍል ሁሉ ሳይቀር የአተረጓጐምን ስልት በመከተል መስራት፡፡ • የተመረጡትን ተጓዳኝ የምንባብ ክፍሎች የዋና ክፍሉን ሐሣብ ሊደግፉ በሚችሉበት መልክ ማቀናጀትና አስተዋጽኦውን ማሣደግ፡፡ • በሥሩም ንዑሳን ክፍሎቹን በየዋና ክፍሉ ሥር ማስቀመጥ፡፡ • በአስተዋጽዎ ውስጥ ያሉን ሐሣቦች ማቀናጀት፡፡ • አስተዋጽዎውን ለማዳበር እንዲረዳ መደምደሚያውን ማጠናክር ያስፈልጋል፡፡
 48. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.7.የተግባራዊ ጥናት ሂደት 4.7.1. ጥናትን ማቀድ፡- አንዱ መንገድ፥ ከብሉይ ኪዳንና ከአዲስ ኪዳን እያፈራረቁ አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ በተወስነ ጊዜ ማጥናት ነው። እያንዳንዱ መጽሐፍ ለየብቻ የተጻፈ እንደመሆኑ፥ እያንዳንዱ መጽሐፍ የተለየ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። አንድ መጽሐፍ ከመረጡ በኋላ አጭር የጥናት ከፍሎችን ይወስኑ። ከ20 እስከ 30 ቁጥሮች ቢሆን መልካም ነው።
 49. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች የቀጠለ……… መጽሐፍ ቅዱስ በአንቀጽ የተከፋፈለ መሆኑም ለጥናት ይረዳል። ከወንጌላት ረጃጅም ክፍሎችን፥ ከመልእክቶች ደግሞ አጫጭር ክፍሎችን ለመውሰድ ይችላሉ። ሙሉ ምዕራፎችን መምረጥ የተሻለ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በጣም ረጃጅም ምዕራፎች ያጋጥማሉ። የምዕራፉ አከፋፈልም የአሳቡን ሂደት የተከተለ አይሆንም። ቢሆንም የጥናት ክፍሎችን በመምረጥ ረገድ ግትር የሆነ ውሳኔ የለም።
 50. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.7.2. ለጥናት መፀለይ፡- እግዚአብሔር በቅዱስ መንፈሱ አማካይነት እንዲያስተምርን መጠየቅ። እርሱ ካላስተማረን ጥናታችን ሁሉ ፍሬ አልባ መሆኑን በመረዳት ጥናታችንን ከማቀድና ከእያንዳንዱ ቀን ሥራችን በፊት መጸለይ ያስፈልጋል። 4.7.3. ማንበብ የአንድን መጽሐፍ፥ የትኛውንም ክፍል ጥናት ከመጀመሩ በፊት መላውን መጽሐፍ ቢያንስ አንዴ ወይም ሁለቴ ማንበቡ። ሦስት ወይም አራት ክፍሎችን ካጠናን በኋላ መላውን መጽሐፍ እንደገና ማንበብ። በጥናት ጊዜ ሁሉ የተመረጠውን ክፍል ደጋግሞ ማንበብ፡፡ ከንባቡ ጋር ሳንለማመድ መልእክቱን
 51. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.7.4. ማስተዋል፡- መረዳትዎ የሚመሠረተው በማስተዋልዎ ላይ ይሆናል" የተባለውን ካልተረዳን ትርጓሜውን ልናውቅ አንችልም። ምንድን ነው ልናስተውል የሚገባን ሀ. የምንባቡ ሥነ-ጽሑፋዊ ቅርጽ መለየት” የአጻጻፍ ስልቱ ትረካ፥ ሥነ-ግጥም፥ ማስተማሪያ፥ ትንቢት...ወዘተ. ነውን? ለ. የተደጋገሙ ቃላትና ሐረጎችን ማየት።
 52. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች ሐ. አጣማሪ ወይም አያያዥ ቃላት። የእነዚህ ቃላት ምሳሌዎች፦ “እና”፣ “ግን”፣ “ለ”፣ “ስለ”፣ “ስለዚህ፣ “ሲሆን”፣ “በኋላ” መ. ጊዜ አመልካች ቃላት” እነዚህ የሚገኙት በተለይ በትረካ ውስጥ ነው። እነርሱም “በኋላ”፣ “ከዚያ” “ወዲያውኑ”፣ በፊት”፣ “በምሽት”፣ “ከአንድ ሰዓት በኋላ” ሠ. የስፍራ ወይም ቦታ ቃላት። የእነዚህ ምሳሌዎች፦ “ይሁዳ” ቁ. 5፣ “ናዝሬት” ቁ. 9፣ “የገሊላ ባሕር” (ቁ. 16) የሚሉት ናቸው።
 53. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች ረ. ማነጻጸርና ማወዳደር። “መልእክተኛዬ” የሚለው ቃል “ጌታ” ከሚለው ጋር (ቁ. 2-3)፤ “በሰይጣን ተፈተነ” የሚለው “መላእክቱም አገለገሉት” ከሚለው ጋር (ቁ. 13) ተነጻጽረዋል። “የእግዚአብሔር ልጅ” የሚለው “የምወድህ ልጄ” ከሚለው ጋር (ቁ. 1፥11) ሊወዳደር የሚችል ሲሆን፥ የዮሐንስ ስብከት ደግሞ ከኢየሱስ ስብከት ጋር (ቁ. 7 እና 14) ይነጻጸራል። ሰ. የማይታወቁ ቃላት። “ሥርየት” (ቁ. 4) እና “ጠፍር” (ቁ. 7) የሚሉትን ቃላት በክፍሉ እናያለን።
 54. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች ሸ. የእያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር ፍሬ አሳብ” በረጅምና በተያያዙ ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ ባለቤቱን፣ ዋናውን ግሥና ተሳቢውን (ካለ) ማስተዋል ይገባል። በ. ዘይቤያዊ አባባሎች፡- ዘይቤያዊ አባባልን አስመልክቶ በማርቆስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሱት ምሳሌዎች፥ “ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ” ቁ. 7፣ እና “ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ” ቁ. 17 የሚሉት ናቸው።
 55. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች በ. ሥርዓት ያለው ቅደም ተከተል፡- በአንድ ምንባብ ውስጥ ያሉ ሁለት ጉዳዮች ብዙ ጊዜ፥ አንዱ ለሌላው ምክንያት የመሆን፤ ወይም አንዱ ለሌላው ምክንያት የመስጠት ቅደም ተከተልና ዝምድና አላቸው። ተ. እንግዳ፣ ያልተለመደ ወይም ያልተጠበቀ ማንኛውም ነገር፡- ለምሳሌ፥ የመጥምቁ ዮሐንስ ልብስና ምግብ የተለመዱ አይደሉም (ቁ. 6)። ቸ. ተዛማጅ ሕልው አካላ፡- እነዚህ፥ ሰዎች፥ ነገሮች፥ ባሕርያት ...ወዘተ፥ ለምሳሌ እንደ
 56. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች ኀ. ሰዋስዋዊ ፍሬ ነገሮች፡- ግልጥ ባልሆኑ ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ በተለይ ስሞችን (መጠሪያዎችን) ግሦችን፣ ቅጽሎችንና ሌሎችንም የንግግር ከፍሎች ማስተዋል አ. ስድስቱን ጥያቄዎች መጠየቅ ነው፦ ምን? መቼ? የት? ማን? እንዴት? ለምን? የሚሉትን" የመጀመሪያዎቹ አራት ጥያቄዎች መልሶች ከምንባቡ በቀላሉ የሚገኙ እውነታዎች ናቸው እውነታዎቹ የመጨረሻዎቹን ሁለት ጥያቄዎችም መመለስ አለባቸው" የመጨረሻው ግን በምንባቡ የተባለውን ለማለት ያስቻለውን ምክንያት ወደ መገመት፥ ወይም ምክንያቱ ባይሰጥም ወደ
 57. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሁለት የስብከት አይነቶች 4.7.5. በማስታወሻ ማስፈር። የምናጠናቸውን ነገሮች መጻፍ፡፡ በአእምሮ ብቻ ያሉ አሳቦች የተዘበራረቁ ይሆኑ ይሆናል፤ በጽሑፍ ካሰፈርናቸው ግን ግልጥ እንዲሆኑ ያደርጓቸዋል። ለትክክለኛነትም ይረዳናል። ነገሮችን መጀመሪያ እንዳገኘን አለማገጣጠም፤ የምንመለከተውን ሁሉን ግን መጻፍ። 4.7.6. ማሰላሰል እና መተንተን። አንድን ክፍል ብዙ ጊዜ ካነበብንና፥ ከጻፍን በኋላ ያስተዋልናቸውን ነገሮች ልናሰላስላቸው እንችላለን" በዚህ ጊዜ እውነተኛውን ትርጉም ለማወቅ የምንችለውን ሁሉ መጣር አለብን።
 58. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት
 59. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት ትምህርት አምስት ዓላማ፡- • የስብከት አወቃቀር እና ክፍሎቹ ምን እንደሚመስሉ ግንዛቤ ማስጨበጥ 5. የስብከት አወቃቀር እና ክፍሎች የስብከት ለዋጭነት እንደተጠበቀ እንዲቀጥል ለማድረግ ከዋናው ማዕከላዊ ሐሣብ የወጣና አሻሚ ሐሳቦች ያልሰፈሩበት ሊሆን ይገባል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እያደገና እስከመጨረሻው የሚቀጥል የሐሣብ ፍሰትና የተለያዩ ገጽታን የሚያንፀባርቁ የስብከቱ ዋና ክፍሎች ሊኖሩት ይገባል፡፡
 60. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.1. የስብከት አስተዋጽኦ አጠቃላይ ቅርፅ (ፎርማት) አንድን የስብከት ዓይነት እና የመጽሐፍ ቅዱስ የመነሻ የምንባብ ክፍል ከመረጥን በኋላ ቅደም ተከተል ያለው የአወቃቀር ሥርዓቱን መከተል ይገባል፡፡ አወቃቀሩ የሚያካትታቸውም ክፍሎች መግቢያ፣ መንደርደሪያ፣ መጠይቅ ናቸው፡፡
 61. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.1. ርዕስ • የስብከታችንን ዋና ሃሳብ በተገቢው መልኩ የምናስተዋውቀበት (የምናስተምርበት) ዘዴ ነው፡፡ርዕስ ሊሆን የሚገባው፡- • ከስብከታችን ጋር በተገቢው መንገድ የሚዛመድ • ሃሳብን የሚያሳምር • ከርዕሰ-ጉዳይ ሰፋ ያለ ሊሆን ይገባል
 62. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.1.1. ርዕስ የማዘጋጃ መንገድ • ከመልዕክቱ ሃሳብ ጋር አግባብ ያለው ግንኙነት ሊኖረው ይገባል ምሳሌ፡- “የመታዘዝ ዋጋው” ዘፍ 22፡1-18 • የሚስብ መሆን አለበት • ከጊዜና ከሁኔታው ጋር የተዛመደ • ሌላ ትርጉም የማያስፈልገው • በአንድ ሃረግ የተቀመጠ • ግልፅ ሊሆን ይገባል፡፡
 63. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.2. መግቢያ መግቢያ መልዕክትን በሚገባ መንገድ ለማስተላለፍ እንዲቻልና የሰዎችን አእምሮ ለማዘጋጀት ለመልእክቱ የሚያዘጋጅ መንደርደሪያ ነው፡፡ 5.2.2.1 አዘገጃጀት • የሚዘጋጀው ሰባኪው ስብከቱን ጽፎ ከጨረሰ በኋላ • ግልፅ ሊሆን ይገባል • የሚስብ • ወደ መልዕክቱ ወይም ዋናው ሃሳብ ሊመራ ይገባል
 64. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.3. የስብከቱ መዋቅር/አስተዋፅዎ 5.2.3.1. ዋና ሃሳብ (body) በዚህ ክፍል በዋናነት ከተመረጠው አርዕስትና ጥቅስ ውስጥ ለጉባኤው ሊተላለፍ /እንዲጨበጥ የታሰበው ሃሳብ የሚቀመጥበት ክፍል ነው፡፡ ምሳሌ…………
 65. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት ምሳሌ 1 ጥቅም፡- ኤፌ 6፡10-18 ርዕስ፡- “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ” ዋና ዋና ሃሳቦች 1. የክርስቲያን ሞራል (ኤፌ 6፡10-13) በጌታ ፀጋ ከፍ ያለ መሆን አለበት (-10) በጌታ ፀጋ ጽኑ መሆን አለበት (11-13) 2. የክርስቲያን የጦር እቃ (6፡18) ራሱን የሚጠብቅበት መከላከያ (6፡14-17) የሚያጠቃበት (-17) 3. የክርስቲያን የፀሎት ህይወት (ቁ-18) በመንፈስ መፀለይ በንቃት መፀለይ ለሌሎች በመማለድ መፀለይ
 66. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.3.2. አዘገጃጀት • አገናኝ ቃሎችን ለይቶ ማውጣት • በጊዜ በቦታና በመልክዓ-ምድር አቀማመጥ ማስተካከል • በግልፅ በፅሁፍ ለሰሚ በሚመች መልኩ ማስቀመጥ • ዋና የሆነው ሀሳብ በበቂ መንገድ መግለፅ • በተቻለ መጠን ጥቂት ማድረግ • በዓይነት ለማስቀመጥ መሞከር (የማያሰለች) • ወጥነት ያለው እንዲሆነ ማድረግ (ምሳ በጥያቄ …ወዘተ)
 67. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.4. ንዑስ ሃሳብ የንዑስ ክፍል የመነሻ ሃሳብ ምንጊዜም ቢሆን ሊሆን የሚገባው ከዋናው ሃሳብ የሚገኝ (የሚወጣ) መሆን ይኖርበታል 5.2.4.1.አዘገጃጀት • ለዋናው ክፍል የተጠቀምንበትን መንገድ መጠቀም • ከዋናው ሃሰብ የሚመጣ ሊሆን ይገባል • ተመሳሳይ የሆነ ቅርፅ ሊኖረው ይገባል • የተመጠነ መሆን አለበት
 68. 3/24/2023 Petros Geset አያያዥ ዋና ሃሳብ ንዑስ ሃሳብ ማብራሪያ ንዑስ ሃሳብ ማብራሪያ ዋና ሃሳብ ንዑስ ሃሳብ ማብራሪያ ንዑስ ሃሳብ ማብራሪያ ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.4. ንዑስ ሃሳብ የቀጠለ…….
 69. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.5 አሸጋጋሪ /አያያዥ ቃላቶች/ በዚህ ክፍል መግቢያውንና ዋና ርዕሱን ጥቅሱንና ዋናውን ሃሳብ የምናያይዝበት ቃል ነው፡፡ ምሳሌ • የዲያቢሎስን ሽንገላ ለመቃወም ክርስቲያን ምን መሆን አለበት 1. በሞራል የበቃ መሆን አለበት 2. የጦር እቃውን መጠቀም አለበት 3. የፀሎት ሕይት ሊኖረው ይገባል
 70. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.6. ማብራሪያ (ውይይት) ዋና ክፍልና ንዑስ ክፍሎች የስብከቱ አካሄድ የአስተሳሰብን መስመር ለማሳየት የቆመ አጽመ-አካል ናቸው። ውይይት ወይም ማብራሪያ በየክፍሎች የሚነሳው ሐሣብ ሳይቀለበስ የሐሳብ ፍሰቱን እንዲቀጥል የሚረዳ ዘዴ ነው፡፡ አንድ ማብራሪያ የተለያዩ መስፈርቶች እንዲኖሩት ያስፈልጋል፡- • የሐሳብ አንድነት ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ የሚሰጠው ማብራሪያ ከያዝነው ዋና ክፍልና 'ንዑስ ክፍሎች ሐሳብ የምናጐላበት ነው፡፡ • ማመጣጠን ያስፈልጋል። ብዙ ማብራሪያ በሚያስፈልገው
 71. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት • እያንዳንዷ ዓረፍተ ነገር የውይይቱን ቅደም ተከተልና እድገት እያሳየ መሄድ መቻል አለበት፡፡ • የማብራሪያ ክፍሉ የተቆራረጠና በሀረግ ስለሚፃፍ ትርጉም የሌለው ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ስውርና የማይታወቅ ሆኖ ያስቸግራል ስለዚህ በጥሩ ዓረፍተ ነገር ግልጽ ሆኖ ሊፃፍ ያስፈልጋል፡፡ • የእያንዳንዱ ክፍል ማብራሪያ ያልተድበሰበሰና ጥርት ያለ ሊሆን ይገባል፡፡ • ማብራሪያው ጠቀሜታ ያለውና የሰሚዎችን ልብ የሚማርክ ሊሆን ያስፈልጋል፡፡ • ማብራሪያው ድግግሞሽ የበዛበት እንዳይሆን የግድ ጥንቃቄ
 72. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.6.1. ለማብራሪያ እንደ ምንጭ የሚጠቅሙ ነገሮችን ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ ከተጓዳኝ ጽሁፎች፤ ከህይወት ልምምድ፣ በየቀኑ ከሚታየው በዙሪያችን ካለ እንቅስቃሴ፤ ከግምታዊ ምናብ እና ከሌሎችም ሁኔታዎች ማግኘት ይችላል። ሰባኪው ማብራሪያ ሲሰጥ ሰሚዎቹ በምን ዓይነት የመረዳት ደረጃ ላይ ያሉ መሆናቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ መወገድ ያለባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ • ታማኝነት የጐደለው ማብራሪያ፣ ዕብራይስጥና ግሪክ ምንም ለማያውቁ አድማጮች መጥቀስ፣ • ሰዎች አቅም የማይመጥን ቃላትን መጠቀም • በጣም አስቸጋሪና ከባድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን የአስተምህሮ ማብራሪያ መስጠት፣ • በጣም የሰፋና የተንዘረጠጠ አተረጓጐምን መከተል የመሳሰሉት
 73. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.7. የስብከት ምሣሌ (መግለጫ) የስብከት ምሣሌ ማለት በተለያዩ ምሣሌዎች አንዱን ሐሣብ ግልጽ ማድረግ መቻል ነው። በምሣሌዎች አማካኝነት ብርሀን በስብከት ላይ መፈንጠቅ ተብሎም ይታወቃል፡፡ ሰባኪው ስብከቱን ሲያብራራ ይቆይና ጠቅለል ባለ መልኩ ስብከቱን ግልጽ በሆነ መልኩ ሰዎች እንዲረዱት የሚያግዝ ምሣሌ ነው፡፡
 74. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.7.2.1 የስብከት መግለጫ (ምሣሌ) ጠቀሜታዎች • ግምትን ሰፋ ለማድረግ ይረዳሉ፡፡ • በተነቃቃ ስሜት አድማጮች መልስ እንዲሰጡ ያደርጋል • መጽሐፉ የተፃፈበትን እና እኛ የምንገኝበትን የዘመን ርቀት ለመሙላት ይረዳል፡፡ • በየትኛውም ዘመንና ባህል ወይንም አሠራር ተፈትነው እውነት የሆነ ነገሮችን ለማስተላለፍ ይረዳሉ። • ያልታወቀን ነገር የታወቀ እንዲሆን አድርጐ ለማስተማር ይረዳል፡፡ • ለስብከቱ አማራጭ አቅጣጫ ይሰጣል፡ • አንዳንድ ጽንሰ ሐሳቦችን ለመድገም ይረዳል፡፡
 75. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.7.2. የስብከት ምሣሌዎችን ከየት ማግኘት ይቻላል? • ከመጽሐፍ ቅዱስ ግለስቦች የህይወት ታሪክ እና ሌሎች የተከናወኑ ታሪካዊ ድርጊቶችን በማሰላሰል ልናገኝ እንችላለን፡፡ • በሰባኪውም ሆነ በሌሎች ሰዎች የህይወት ልምድ ውስጥ የታዩ ብዙ ምሣሌዎች ይኖራሉ፡፡ • የአነጋገር ዘይቤዎች፣ ተረቶች፣ ሥነ ፍጥረት እና ሌሎችም • ወቅታዊ ክስተቶች፣ ጥቅሶች፣ ስነ ጽሁፍ፤ የሚታዩ ነገሮች እና ለሎችም ጉዳዮች የምሣሌ ምንጮች ናቸው፡፡
 76. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.7.3.ምሣሌ ማሟላት ያለበት ነገሮች፡- • በቀጥታ እንደሚያገለግል ተደርጐ ቢቀርብ የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ • በጣም ቀልብ የሚስብ ቢሆን ይመረጣል፡፡ • ለህይወት አዲስ ምዕራፍ ከፋች ወይም አዲስ እይታ የሚፈጥር ቢሆን ጥሩ ነው፡ • ለግምት የሚያመች መሆን አለበት፡፡ • ከሁኔታው፣ ከአድማጩ እና ከትምህርቱ ጋር በትክክል አብሮ የሚሄድ ቢሆን አድማጮች በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉ እና ተጨባጭ
 77. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.8. ከህይወት ጋር ማዛመድ ማዛመድ ማለት አድማጮች የሰሙትን ስብከት ወይም የቃሉን እውነት በመቀበል በህይወታቸው ወደ ተግባር እርምጃ የሚሸጋገሩበት ወሳኝ ጊዜ ነው፡፡ የማዛመድ ዘዴ ማሟላት የሚገባቸው ነገሮች ፡- • ወቅታዊ ማድረግ፡- ስብከቱን ሊሰሙ ቁጭ ያሉ ሰዎች በተለያዩ መንፈሣዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የተለያየ የአካባቢ አመጣጥ ያላቸው በመሆኑ ተዛምዶውም ይህን ግምት ውስጥ ያስገባና ወቅታዊ መሆን ይኖርበታል፡፡ • ተጨባጭ እንዲሆን ያስፈልጋል፡- የሚዛመደው ከሰው
 78. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.8. ከህይወት ጋር ማዛመድ ……….የቀጠለ የማዛመድ ዘዴ ማሟላት የሚገባቸው ነገሮች ፡- • ለእግዚአብሔርና ለሌሎች ሰዎች ምን ዓይነት አስተሳሰብ አለን በሚለው ዙሪያ የሚያጠነጥን እንዲሁም የእግዚአብሔርን ሐሣብ በማወቅና በማድረግ ዙሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ • በህይወታችን ውስጥ ያለ ሊወገድ ወይም ሊያድግ የሚገባ ባህርይ ካለ አጠቃላይ ልማዳችንና ባህሪያችንን መፈተሽ፡፡ • ህዝቡ ከሰውና ከእግዚአብሔር ጋር ምን ዓይነት ሰላም ያለው ህዝብ ነው? • በህይወታችን ዋጋ የምንሰጣቸው እና ቅድሚያ የሚሰጠው ነገርስ ምንድን ነው? • የመነሻ ሐሳቦቻችንን መፈተሽ ይኖርብናል፡፡
 79. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ ሦስት የስብከት አወቃቀር እና አደረጃጀት 5.2.9. መደምደሚያ መደምደሚያ ሰባኪው አላማው ግብ እንዲሚታ ለማድረግ የሚጠቀምበት የመጨረሻው የስብከቱ ሁሉ ጣራ ነው፡፡ 5.2.9.1.የመደምደሚያ ሃሳብ አቀማመጥ • በስብከቱ ውስጥ የተነሱትን ሃሳቦች በግልፅ መንገድ በድጋሚ ማስቀመጥ • ምሳሌ መስጠት • ተዛምዶ መስራት • ለተግባራዊ ምላሽ ማንቀሳቀስ (ማነቃቃት)
 80. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ - አራት ስብከትን ማደራጀትና ማቅረብ
 81. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ - አራት ስብከትን ማደራጀትና ማቅረብ ትምህርት ስድስት ዓላማ • የስብከት አደረጃጀት መንገድን ማሳየት 6. የስብከት አደረጃጀት 6.1. የስብከት አደረጃጀት ሂደት • መግቢያ መጀመሪያ ማስቀመጥ መደምደሚያን በመጨረሻ መስራት • የመግቢያና ዋና ዋና ክፍሎችን ሃሳብ በሚገባ ማስቀመጥ • በአእምሮአችን የሚመጡልንን ሃሳቦች ፅፎ መያዝና በተገቢው ቦታና ጊዜ መጠቀም
 82. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ - አራት ስብከትን ማደራጀትና ማቅረብ 6.2. የስብከት አወቃቀር ደረጃዎች • ርዕሰ ጉዳዩን መምረጥ • ከእግዚአብሔር ወይም ከነባራዊ ሁኔታ መነሳት • ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር የሚዛመድ የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል መምረጥ • አያያዥ ቃሎችን መመስረት • ስብከቱን ማዋቀር • እየሞሉ መሄድ • በጸሎት ማሰላሰል • የተለያዩ መጽሃፎችን የግል መረጃዎቻችን መጠቀም • በድጋሚ ማረጋገጥ
 83. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ - አራት ስብከትን ማደራጀትና ማቅረብ 6.3. የስብከት ፕሮግራም አዘገጃጀት • አስተምህሮተ ክርስትና እና ተግባርን ያተኮረ፡- ይህ ሃሳብ የሚገልፀው መለኮታዊ እውነትን መንፈሳዊ ጤናማነትና ጠንካራ አማኝን የተመለከተ ይሆናል፡፡ • ተግባራዊ፡- ተግባራዊ ስብከት የግል ጉዳይን፣ ህብረተሰብን፣ ሃገራዊና አለምአቀፋዊ ጉዮችን፣ ሰብአዊ ቀውሶችን፣ ስነ-ምግባራዊ፣ ሞራልና ክርስቲያናዊ እሴቶችን ያካተተ • ሃይማኖታዊ ዋጋ ያለው፡- ከሚያምኑበትና ከሚያስተምሩት አንፃር በአገልግሎት ክፍሎች ወንጌል ስርጭትና ተልዕኮ፣ ወጣት፣ ልጆች፣ ትምህርት፣ ሴቶች የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ • ልዩ በዓላትን ተኮር የሆነ፡- (ሉቃ 4፡16-26) (የሐዋ 2፡14-41) (የሐዋ 7፡1 ) ልዩ በሆነ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ
 84. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ - አራት ስብከትን ማደራጀትና ማቅረብ 6.4. የስብከት አቀራረብ ዝግጅት 6.4.1. የስነ አእምሮ ዝግጅት ይህ ዝግጅት ሰዎችን ለማሳመን ምን ማድረግ እንዳለብንና ወደ ሚፈለገው አቅጣጫ የማምጣት አቅምን በሰባኪው ውስጥ የሚጨምር ነው፡፡ 6.4.1.1. እንዴት እንዘጋጅ • እራስን ከክርቶስ ጌትነት በታች ማምጣት • ድካምን ማወቅና በእግዚአብሄርን ቃል ብርሃን ውስጥን ማጠንከር • በሙሉ ስሜትና ሃሳብ በእግዚአብሔር መታመን
 85. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ - አራት ስብከትን ማደራጀትና ማቅረብ 6.4.1.2. የቃላት አጠቃቀም ዝግጅት በዚህ ክፍል ውስጥ ሰባኪው የሚያቀርብበት መንገድ፣ ዘይቤና በቃልም ይሁን በምልክት የመግባባት መንገድ የሚከታተልበት መንገድ ነው፡፡ • የአነባበብ ዘዴው፡- ርዕሱን ሙሉ አንብቦ መጨረሱ፣ ትክክለኛነት፣ የተሳሳተ ጥቅስ ያለመስጠት • በደረጃ በቅርፅ የተዋቀረ፣ ርዝመትን የሚቆጣጠር እና መተማመን ያለው • የሌላውን ሰው ሃሳብ በአግባቡ ማለት አለማለትን • ነፃ ስብከት፡- ሌሎች ስለጉዳዩ ያሉትን ችላ ማለት፣ ቅርፅ፣ ፍሬ
 86. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ - አራት ስብከትን ማደራጀትና ማቅረብ 6.4.1.3. የስብከት ዘይቤዎች ዘይቤ አንድን ስብከት በቋንቋ፣ በሃሳብና በማንነት ለማቅረብ የምንጠቀምበት ስርዓት ባህል ነው፡፡ ሀ. ውጤታማ ባህሪያት • የቃላት አጠቃቀም፡- ሰዎች ሊረዱት የሚችሉትን፣ በአእምሮ የሚቀረጽ፣ መፅሀፍ ቅዱሳዊ፣ ስሜትን የሚያነቃቁና ተገቢ የሆነ ቃሎችን መጠቀም ያካትታል፡፡
 87. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ - አራት ስብከትን ማደራጀትና ማቅረብ ለ. መወገድ ያለባቸው • አፍራሽ የሆኑ ቃሎችን አለመጠቀም፣ • ለቦታው አስፈላጊ ያልሆኑ ቃላትን አለመጠቀም • በተወሰነ ቡድኖች የሚነገሩ ቃሎችን ጥቅም ላይ አለማዋል • ድግግሞሽን ማስወገድ • መልስ የሆነ ጥያቄ አለማቅረብ
 88. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ - አራት ስብከትን ማደራጀትና ማቅረብ 6.4.1.4. በቃል የማቅረቢያ ዘዴ ዝግጅት ሀ. የድምጽ ባህሪ • የስፋት መጠን • ሃይልና ጥንካሬ • ከፍታና ዝቅታ • ፍጥነት • ሜሎዲ (መታዘዝ፣ ጥራት፣ ግልፅነት፣ ለስላሳነት)
 89. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ - አራት ስብከትን ማደራጀትና ማቅረብ ለ. አካላዊ እንቅስቃሴ ዝግጅት • አይን እይታ፡- መልካም ግንኙነት ለመፍጠር፣ እንዴት እየተከታተሉ እንዳለ ለመረዳት፣ ስሜትን የያዘ ለመመስረት እና ጉባዔውን ለመቆጣጠር፡፡ • የሠውነት እንቅስቃሴ፡- ይህ አቀራረብ በሁለት ሲከፈል እነሱም የፊት ገፅታና የሰውነት እንቅስቃሴ ይባላሉ፡፡ • እይታዊ የማስተማሪያ ዘዴ መጠቀም፡- ፍላሽ ካርድ፣ ቻርትና ስዕሎችን • መልካም ስብዕና፡- የእግዚአብሔርን መገኘት የሚጋብዝ፣ ፀጋ የሞላውና በመለኮት ብቃት የሚታመን ሊሆን ይገባል፡፡
 90. 3/24/2023 Petros Geset ምዕራፍ - አራት ስብከትን ማደራጀትና ማቅረብ ሐ. መንፈሳዊ ዝግጅት በስብከት አገልግሎት ውስጥ በዋነኛነት ሊተኮርበትና ዋጋ ሊሰጠው ከሚገባ አንዱ ጉዳይ የመንፈስ ቅዱስ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ያለእርሱ ምንም ልንሆንና ልናደርግ ስለማንችል ነው፡፡ በስብከታችን ውስጥ መሰረታዊ ከሆኑ ነገሮች መካከል • የእግዚአብሐር ቃል (መልዕክቱ) • የእግዚአብሔር ሰው (መልዕክተኛው) • መንፈስ ቅዱስ (ምንጩ) ዋነኞቹ ናቸው፡፡
 91. 3/24/2023 Petros Geset
Advertisement