Presentation HIV.pptx
- 1. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ
አመራር ኮሚሽን
ኤችአይቪን ለመግታት አለም አቀፋዊ ትብብር የጋራ ኃላፊነት (global
shared responsibility ) በሚል መሪቃል የሚከበረዉን የፀረ ኤድስ ቀን
በማስመልከት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ
አቅራቢ ፡-ብርሀነመስቀል መኮንን
22/03/2013 ዓ.ም
8/29/2023 1
- 2. መግቢያ
ኤችአይቪ በአለም አቀፍ ደረጃ
ኤችአይቪ መከሰቱ ከታወቀበት እ.ኤ.አ ከ 1981 ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ32.7
ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡
38 ሚሊዮን ሰዎች በአሁን ሰዓት ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸዉ እንዳለ ይገመታል፡፡
በየአመቱ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች አዲስ በኤችአይቪ ይያዛሉ
690,000 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት እንደሚዳረጉ መረጃዎች ያሳያሉ (UNAIDS SHEET
2019)
8/29/2023 2
- 3. የቀጠለ……
ኤች አይቪ ኤድስ በሀገራችን
የሀገራችን የኤችአይቪ የስርጭት ምጣኔ 0.93 % ሲሆን በዚህም ስሌት 669,236 የሚሆኑ
ወገኖች ኤችአይቪ በደማቸዉ እንደሚገኝ ሀገራዊ የኤችአይቪ ስርጭት ግምት (HIV
ESTIMATES AND PROJECTION SPECTRUM, 2019) ያሳያል ፡፡
ከነዚህም ዉስጥ 61.8 % ያሉት ሴቶች ናቸዉ፡፡
የስርጭቱ ምጣኔ ከክልል ክልል፤ ከአንድ ቦታ ሌላ ቦታ ፤ በማህበረሰብ ክፍሎች እንዲሁም
በከተማ እና በገጠር የሚለያይና ክስተቱም እየቀነሰ እንዳልሆነ መረጃዎች ያሳያሉ
8/29/2023 3
- 4. የቀጠለ……
እ.ኤ.አ በ2019 በሀገራችን 14,843 ሰዎች አዲስ በኤችአይቪ ተይዘዋል
67 % የሚሆነዉ እድሜያቸዉ ከ30 ዓመት
ከእነዚህ ዉስጥ 20 % አዲስ ከተያዙት ዉስጥ ዕድሚያቸዉ ከ20-24 ዓመት ነዉ
19 % ድግሞ ከ0-4 ዓመት የሚገኙ ህፃናት ናቸዉ፡፡
በአሁኑ ወቅት የኮቪደ 19 ወረርሽኝ የአለምን ትኩረት በእጅጉ የወሰደበት ግዜ ላይ እንገኛለን፡፡
UNAIDS ወቅታዊ መግለጫ እንደሚያሳየዉ ጥምር የሆነ የኤች አይቪ እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝን
ሊገታ የሚችል ሁለንተናዊ ምላሾችን መስጠት ሲቻል ብቻ ለዉጥ ማምጣት እንደሚቻል ይገልጣል፡፡
8/29/2023 4
- 5. የ2ዐ13 ዓ/ም የሚከበረው የዓለም ኤድስ ቀን የመሪ ቃሉ ፅንስ ሀሳብ
ኤች አይቪን ለመግተት ዓለም አቀፋዊ ትብብር የጋራ ኃላፊነት
በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ኤች አይቪ በደማቸው ለሚገኝባቸውና በቫይረሱ ጉዳት ለደረሰባቸው
ወገኖች ድጋፋቸውን ለማሳየት እንዲሁም በኤድስ ህይወታቸውን ያጡትን ወገኖች
ለማስታወስ በየዓመቱ ህዳር 22 ቀን የዓለም ኤድስ ቀንን አሰበው ይውላሉ፡፡
እ.ኤ.አ. በ2ዐ2ዐ የዓለም ትኩረት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በጤና በህይወትና በኑሮ እያስከተለው
ባለው ተጽዕኖ ላይ አርፏል፡፡
8/29/2023 5
- 6. የቀጠለ…….
ይህንን ከግምት በማስገባት በዚህ ዓመት የዓለም ኤድስ ቀን Global ኤች አይቪን
ለመግታት ዓለም አቀፋዊ ትብብር የጋራ ኃላፊነት በሚል መሪ ቃል ታስቦ ይውላል፡፡
የአመራሩና የማህበረሰቡ ተሳትፎ ለኤች አይቪ/ኤድስ ዘርፈ-ብዙ ምላሽ ስኬት የማይተካ
ሚና እንደነበረው ሁሉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመግታቱ ረገድም ቁልፍ ሚና ይኖረዋል
የማህበረሰቡ ንቁ ተሳትፎና ለጋራ ዓላማ በትብብር በኤች አይቪ/ኤድስ ጉዳት ለደረሰባቸው
ወገኖች መረጃ አገልግሎት ማህበራዊ ጥበቃ እንዲሁም ተስፋ በመስጠቱ ረገድ ከፍተኛ
አስተዋፅኦ እንዳበረከተ ብዙ ተሞክሮዎችን አይተናል፡፡
8/29/2023 6
- 7. ይሁን እንጂ ለጋራ ዓላማ መተባበር የማህበረሰቡ ኃላፊነት ብቻ ሊሆን አይገባም፡፡
መንግስታዊ ተቋማት ለጋሽ ድርጅቶች የሐይማኖት መሪዎች ሲቪክ ማህበራትና እያንዳንዱ
ግለሰብ የተሻለ ኤች አይቪ ስርጭት በመግታት ጤናማና ለመኖር ምቹ የሆነች ሀገር
በመገንባት ሂደቱ የማይተካ አሻራቸውን ማሳረፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
8/29/2023 7
- 8. በሀገራችን ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የፀረ- ኤች አይቪ ህክምና እንዳይቋረጥ
የተደረገውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሉ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆነ ተቋማት መካከል
ከፍተኛ ትብብር ያስተዋልን ሲሆን የጤና ባለሙያዎችም ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል፡፡
8/29/2023 8
- 9. • እኤአ በ2ዐ3ዐ ኤድስ የማህበረሰቡ የጤና ችግር የማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ በተያዘው
ዕቅድ የመጨረሻዎቹ አስር ዓመታት ላይ እንደ መገኘታችን መጠን ከግቡ ለመድረስ ከዚህ
በፊት ውጤታ ያስመዘገብንበትን የአመራር ቁርጠኝነት መልሰን ማረጋገጥ ተተኪ የሌለው
መፍትሄ ነው፡፡
8/29/2023 9
- 10. በሃገራችን በኤች አይቪ በኩል የተመዘገበ ዉጤቶች
በየአመቱ አዲስ ኤች አይቪ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር እኤአ በ2ዐ1ዐ ከነበረበት በ46 በመቶ እና
በኤድስ ምክንያት የሚከሰትን ሞት በ52 በመቶ በላይ እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡
የኤች አይቪ ስርጭት ምጣኔ በ199ዐ ዎቹ መጨረሻ ከነበረበት 3 በመቶ በ2ዐ17 ወደ 1
በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል
ኤች አይቪ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ምጣኔ በ6 ሳምንታት ውስጥ እና የጡት ማጥባት
ጊዜን ጨምሮ/እኤአ በ2ዐ1ዐ ከነበረበት 16% እና 3ዐ.2% እ.ኤ.አ በ2ዐ19 ወደ 8.9 እና
16.9% በተከታታይ በመውረድ ሁለቱም በ44 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል
8/29/2023 10
- 11. የቀጠለ……
በ2ዐ19 የኤች አይቪ በደማቸው ይገኛል ተብሎ ከሚመቱ ወገኖቹ መካከል 79 በመቶ
የሚሆኑት መርምረው ራሳቸውን እንዲያውቁና ከእነዚህ መካከል 9ዐ በመቶ ያህሉን ደግሞ
የፀረ-የኤች አይቪ መድሀኒት ላይ እንዲቀመጡና መድኃኒት ከሚወስዱት ውስጥ 91 በመቶ
ያህሉን የቫይረስ ልኬት መጠን በሚፈልገው መጠን እንዲወርድ ማድረግ ተችሏል፡፡
8/29/2023 11
- 12. ያጋጠሙ ተግዳሮቶች
የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠልና በ2ዐ3ዐ ኤድስ የማህበረሰቡ የጤና ችግር
ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ የተያዘውን ሀገራዊ ራዕይ ዕውን ለማድረግ መፍትሄ
የሚያስፈልጋቸውን ተግባሮቶች አሉ፡፡ ተግዳሮቶቹ እርስ በርስ የተሳሰሩ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ
ከዚህ በታች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
8/29/2023 12
- 13. የቀጠለ……..
ከዚህ ቀደም ብሎ ለተመዘገበው የዘርፈ-ብዙ ምላሹ ስኬት ከፍተኛ ሚና የነበረው የአመራሩ
ቁርጠኝነት ዛሬ ላይ መታየት አለመቻል ዋነኛው ተግዳሮት ሲሆን ማሳያዎቹም የአመራር
አደረጃጀቶች /የኤድስ ምክር ቤት የሥራ አመራር ቦርድ በሚፈለገው መልኩ አለመቋቋምና
አለመጠናከር/ ተቋማት የኤች አይቪ ሜይንስትሪሚንግ ኘሮግራሞችን በባለቤትነት አለመተግበር
ከችግሩ አስቸኳይነትና አሳሳቢነት አንፃር ጉዳዮ የሚፈልገውን የሰው የገንዘብ ኃይል በወቅቱ
የማግኘት ተግዳሮት በዘርፍ-ብዙ ምላሹ ላይ እያጋጠሙ ካሉት ተግዳሮቶች ውስጥ የሚጠቀሱ
ናቸው፡፡
8/29/2023 13
- 14. የቀጠለ……..
አዲስ የኤች አይቪ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር በሚፈለገው መጠን መቀነስ ያልተቻለ ሲሆን
በአገር አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ ከነበረበት በ2ዐ2ዐ በ75 ከመቶ ለመቀነስ የተቀመጠው ግብ
ቢኖርም እስከ እ.ኤ.አ 2ዐ19 መጨረሻ ድረስ ማሳካት የተቻለው 46 ከመቶ ብቻ ነው፡፡
8/29/2023 14
- 15. የቀጠለ……..
ከፀረ-የኤች አይቪ ሕክምናን አስመልክቶ በአዋቂዎች ላይ ከአስመዘገብነው የስኬት ጉዞ ጋር
ሲነፃፀር የህፃናትና የአፍላ ወጣቶች ሕክምና በእጅጉ ወደኃላ ቀርቷል፡፡ ከ0-4ዓመት ባሉ
ህፃናት 26%ሲሆን ከ5-10 ዓመት ባሉት ላይ 46% እና ከ1ዐ-14 ዓመት ባሉት ላይ
58%ነው፡፡
ከ15 በታች በሚገኙ ህፃናት የቫይረሱን መጠን በሚፈለገው መጠን የማውረድ አፈፃፀም
78.9%ብቻ ነው፡፡
8/29/2023 15
- 16. የትኩረት አቅጣጫዎች
1. የጤና ፕሮግራሙን ሙሉ ወጪን መሸፈን
2. የጤና ስርዓትን ማጠናከር
3. የኤችአይቪ ኤድስ አገልግሎት ተደራሽነትን ማረጋገጥ
4. ሰብዓዊ መብትን መጠበቅ
5. የኤችአይቪ ፕሮግራሞች የሴቶችና የልጃገረዶች መብትና የፆታ እኩልነትን ያማከለ
እንዲሆን ማድረግ፡፡
8/29/2023 16