SlideShare a Scribd company logo
1 of 123
Download to read offline
የማሽከርከር ህግ
መርዕድ በሻህ
0968573578
1.አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች
አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች በሚሰጡት ትርጉም ወይም በሚያስተላልፉት
መልዕክት/ትዕዛዝ/ ልዩነት የተነሳ በሶስት ክፍሎች ይከፈላሉ።
1.የሚያስጠነቅቁ
2.የሚቆጣጠሩ
3.መረጃ የሚሰጡ
1.የሚያስጠነቅቁ
• ቅርጻቸው - አብዛኞቹ ሶስት ማዕዘን ናቸው
• መደባቸው - ነጭ
• መልዕክቱ - በጥቁር ሆኖ በስዕል፣በምልክት፣በቁጥር...ይተላለፈል
1 በመንገዱ ላይ ጠባብ ድልድል ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ እለፍ::
2 መንገዱን የሚጠግኑ ሠራተኞች ስላሉ ፍጥነትህን በመቀነስተጠንቅቀህ እለፍ::
3 ባለ 4 አቅጣጫ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ቆመህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡
4 ፊት ለፊት ወደ ግራ የሚያስኬድ መገናኛ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡
5 ፊት ለፊትና ወደ ቀኝ የሚያስኬድ መገናመንገድ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡
6 መገናኛ መንገዱ ወደ ግራና ወደ ቀኝ የሚታጠፍ እንጂ ፊት ለፊት የማያስኬድ ስለሆነ
ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
7 የተበላሸ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡
8 የምታሽከረክርበት መንገድ ወደ ግራ ስለሚታጠፍ የቀኝ ረድፍህን ይዘህ በጥንቃቄ እለፍ፡፡
9 የምታሽከረክርበት መንገድ ወደቀኝ ስለሚታጠፍ የቀኝ ረድፍህን ጠብቀህ በጥንቃቄ እለፍ፡፡
10 መጀመሪያ ወደ ግራ ቀጥሎ ወደ ቀኝ የሚታጠፍ ጠመዝማዛ መንገድ ስለሚያጋጥምህ
ተጠንቅቀህ እለፍ::
11 መጀመሪያ ወደ ቀኝ ቀጥሎ ወደ ግራ የሚታጠፍ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ
አሽከርክር፡፡
12 ወደ ግራ እየጠበበ የሚሄድ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ እለፍ
13 ወደ ቀኝ እየጠበበ የሚሄድ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ እለፍ
14 መዝጊያ ያለው የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
15
መዝጊያ የሌለው የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለሚያጋጥምህ ቆመህ ባቡር አለመኖሩን
አረጋግጠህ በጥንቃቄ እለፍ፡፡
16 አደገኛ ቁልቁለት ስለሚያጋጥምህ ከባድ ማርሽ በማስገባት ተጠንቅቀህ እለፍ::
17 በአጭር እርቀት ውስጥ የተደጋገመ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ መኖሩን የሚያስጠነቅቅ ምልክት
ነው፡፡
ሀ. ባለሦስት ሠረዙ በ25ዐ ሜትር ለ. ባለሁለት ሠረዙ 170 ሜትር
ሐ. ባለአንድ ሠረዙ በ1ዐዐ ሜትር ርቀት ላይ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለሚያጋጥምህ
ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡
18 በመንገድ ላይ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
19 የሁለት ባቡሮች ሐዲድ መንገዱን የሚያቋርጥ ስለሆነ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
20 በመንገድ ላይ ብዙ ሰዎች የሚተላለፉበት አካባቢ ስለሆነ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
21 ተማሪዎች የሚበዙበት አካባቢ ስለሆነ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
22 በአንድ አቅጣጫ ብቻ ለማሽከርከር በተፈቀደበት አካባቢ ላይ ለጊዜው በሁለቱም አቅጣጫ
በኩል ተሽከርካሪዎች እንዲተላለፉበት ስለተፈቀደ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
23 በመንገዱ ላይ አስጊ ወይም አደገኛ ሁኔታ ስለአለ በጥንቃቄ አሽከርክር፡፡
24 ወደ ፊት የትራፊክ መብራት አለ፡፡
25 ወደ ግራ የሚታጠፍ አደገኛ ኩርባ /ምልክቱ ሲዞር ወደ ቀኝ የሚታጠፍ አደገኛ ኩርባ/፡፡
26 በመንገድ አግድም የሚነፍስ ሀይለኛ ንፋስ አለ፡፡
27 ወደ ፊት ክብ አደባባይ አለ፡፡
28 ሁለት ነጠላ መንገድ ወደ አንድ ነጠላ መንገድ ይለወጣል፡፡
29 መንገዱ በስተቀኝና በግራበኩል ይጠባል።
30 በመንገድ ላይ የሚፈናጠር ድንጋይ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
31 ወደ ፊት የትራፊክ መጨናነቅ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
32 ወደ ፊት የቤት እንሰሳት ስለአሉ /መንገዱን ስለሚያቋርጡ/ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ
እለፍ፡፡
33 የአካል ጉዳተኞች ስለአሉ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
34 ወደ ፊት የእርሻ መሣሪያዎች ስለአሉ/መንገዱን ስለሚያቋርጡ/ ፍጥነትህን በመቀነስ
ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
35 አደገኛ ጠመዝማዛ መንገድ ስለሚያጋጥም ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
36 ወደ ፊት የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ ስለአለ /የእሳት አደጋ መከላከያ ተሸከርካሪ
ስለሚያቋርጥ/ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
37 ወደ ፊት የጭነት ተሸከርካሪዎች ስለአሉ/መንገዱን ስለሚያቋርጡ/ ፍጥነትህንበመቀነስ
ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
38 ወደ ፊት የህጻናት መጫዎቻ ቦታ ስለአለ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡
39
መንገድ ለሁለት መከፈል የሚጀምርበት ስለሆነ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
40 ለሁለት ተከፍሎ የነበረው መንገድ ማብቂያ ስለሆነ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
41 ቁም የሚል ምልክት ወደ ፊት ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
42 ቅድሚያ ስጥ የሚል ምልክት ወደ ፊት ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
43 በጎን በኩል ማዕዘናዊ ቅርፅ ሰርቶ የሚገኝ መንገድ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ
እለፍ፡፡
44 Y ቅርፅ ያለው መገናኛ መንገድ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
45 በባንዲራ ትራፊክን የሚያስተናግድ ሰው ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
46 መንገድ ቀያሽ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ፣ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
47 በቀኝ በኩል የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
48 በጎን በኩል ከተገናኘ መንገድ ትይዩ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ
ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
49 T ቅርፅ ካለው መንገድ ትይዩ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ
ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
50 የአስፋልት መንገድ መጨረሻ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
51 ናዳ ያለበት መንገድ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
52 ተ ተንቀሳቃሽ /ተነሺ/ ድልድይ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
53 ወደ ወንዝ ዳርቻ የሚወስድ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
54 የመንገዱ ዳር አደገኛ ስለሆነ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
55 ዝቅ ብለው የሚበሩ አውሮፕላኖች ስላሉ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
56 ከፊት ለፊት መሷለኪያ ስላለ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
57 ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
58 ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
59
ከፊት ለፊትህ የዱር አራዊት መንገዱን የሚያቋርጡ ስላሉ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
60 የሚያንሸራትት መንገድ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
2.የሚቆጣጠሩ
የሚቆጣጠሩ አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች በሶስት ንዑሳን ክፍሎች ይከፈላል
ሀ. የሚከለክሉ
ለ. የሚያስገድዱ/ወሳኝ
ሐ. ቅድሚያ የሚሰጡ
ሀ. የሚከለክሉ
• ቅርጻቸው - ክብ
• መደባቸው - ነጭ
• መልዕክቱ - በጥቁር ሆኖ በስእል፣በምልክት፣በቁጥር...ይተላለፈል
1 ማናቸውም ዓይነት ተሽከርካሪና በእጅ የሚገፉትም ጭምር እንዳያልፉበት የተዘጋ መንገድ፡፡
2 ምልክቱ ባለበት አቅጣጫ እያሽከረከሩ ማለፍ ክልክል ነው፡፡
3 ቀስቱ በሚያመለክተው አንጻር ወደ ቀኝ መታጠፍ የተከለከለ ነው፡፡
4 ቀስቱ በሚያመለክተው አንጻር ወደግራ መታጠፍ የተከለከለ ነው፡፡
5 ከሁለት እግር በላይ ያላቸውን አነስተኛ ተሽከርካሪዎች ምልክቱ ከተተከለበት ሥፍራ ጀምሮ
«መጨረሻ» የሚል ሌላ ምልክት እስከሚታለፍበት ድረስ መቅደምየተከለከለ ነው፡፡
6 መቅደም ክልክል ነው የሚል ምልክት መጨረሻ፡፡
7 ከሁለት እግር በላይ ያላቸው የሞተር ተሽከርካሪዎች በዚህ በኩል እንዳይሄዱ ተከልክለዋል፡፡
8 ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር የተከለከለበት መንገድ፡፡
9 በሞተር ኃይል የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ዓይነት ተሽከርካሪ እንዳያልፍ የተከለከለበት መንገድ፡፡
10 ጠቅላላ ክብደቱ በኪሎ ግራም በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ የጭነት ተሽከርካሪ
ማለፍ የተከለከለ፡፡
11 ጠቅላላ ክብደቱ በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ማንኛውም ዓይነት ተሽከርካሪ ማለፍ
የተከለከለ፡፡
12 ቀስቱ እንደሚያመለክተው በስተግራ ወደ ኋላ ዞሮ መመለስ ክልክል ነው፡፡
13 ቀስቱ እንደሚያመለክተው በስተቀኝ ወደ ኋላ ዞሮ መመለስ ክልክል ነው፡፡
14 ይህ ምልክት ባለበት መንገድ ብስክሌት እያሽከረከሩ ማለፍ ክልክል ነው፡፡
15 ለማንኛውም እንሰሳና በእንሰሳት ለሚሳቡ ተሽከርካሪዎች ጭምር በዚህ በኩል ማለፍ የተከለከለ ነው
16 በሰው ኃይል የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን በዚህ በኩል ማሳለፍ ክልክል ነው፡፡
17 ይህ ምልክት በአለበት መንገድ ላይ እግረኞች እንዳይሄዱበት ይከለክላል፡፡
18 የአክስሉ ጭነት በምልክቱ ላይ ከተመለከተው ኪሎ ግራም ክብደት በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ
የተከለከለ፡፡
19 ጠቅላላ ስፋቱ በሜትር በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ የተከለከለ፡፡
20 ጠቅላላ ከፍታው በሜትር በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ የተከለከለ፡፡
21 የከተማ ክልል ምልክት በከተማ ውስጥ ለማሽከርከር የተወሰኑትን ሕጎች አክብር፡፡
22 የከተማ ክልልና የፍጥነት ወሰን መጨረሻ፡፡
23 ማንኛውንም ዓይነት የማስጠንቀቂያና የጡሩንባ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡
24 ይህ ምልክት ከተተከለበት ስፍራ ጀምሮ፦
ሀ/ መገናኛ ወይም መስቀለኛ መንገድ እስክታልፍ ድረስ ወይም
ለ/ በውስጡ «መጨረሻ» የሚል ጽሑፍ ያለበትን የዚህ ዓይነት ምልክት እስክታልፍ ድረስ
ተሽከርካሪህን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡
25 ይህ ምልክት ከተተከለበት ስፍራ ጀምሮ፦
ሀ/ የሚቀጥለውን መገናኛ ወይም መስቀለኛ መንገድ እስክታልፍ ድረስ ወይም
ለ/ «መጨረሻ» የሚል ጽሑፍ የተፃፈበት የዚህ ዓይነት ሌላ ምልክት እስክታልፍ ድረስ ተሽከርካሪን
በማዘግየት ማቆም የተከለከለ ነው፡፡ ነገር ግን አሽከርካሪው ከመኪናው ነሳይወጣ ሰዎችን ለማሳፈር
ዕቃ ለመጫንና ለማውረድ ብቻ ለጥቂት ጊዜ ይቻላል፡፡
26 ይህ ምልክት ባለበት መንገድ ላይ ከፊት ለፊት ለሚመጣ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ሳይሰጡ ማሽከርከር
ክልክል ነው፡፡
27 ቁም! የጉምሩክ መ/ቤት /ፍተሻ ቦታ/ ነው፡፡ይህ ምልክት ባለበት ቦታ ሁሉ ማንኛውም
አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን አቁሞ በጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች ሳያስፈትሽ እንዳያልፍ የሚከለክል
ነው፡፡
28 መኪና ለማቆም የሚከለክለው ምልክት ትዕዛዝ መጨረሻ መሆኑን የሚገልጽ ምልክት ነው፡፡
29 ይህ ምልክት ካለበት ጀምሮ እስከሚቀጥለው መስቀለኛ መንገድ ወይም «መጨረሻ» ከሚል ቃል
ጋር ቀጥሎ የሚገኝ የዚህ ዓይነት ምልክት እስከአለበት ድረስ ለአጭርም ሆነ ለረዥም ጊዜ ማቆም
የተከለከለ፡፡
30 በምልክቱ ላይ ከሚታየው በአነሰተኘA ርቀት ተጠግቶ ማሽከርከር ክልክል ነው፡፡
31 አደገኛ ፍንዳታ የሚያስከትል ጭነት ለጫነ ተሸከርካሪ ማለፍ የተከለከለ ነው፡፡
32 ለጭነት ተሸከርካሪ ማለፍ የተከለከለ፡፡
33 የተበላሸ ተሸከርካሪ እየጎተቱ መጓዝ የተከለከለበት መንገድ፡፡
34 ጠቅላላ ርዝመቱ በምልክቱ ላይ ከተጠቀሰው ሜትር በላይ ለሆኑ ተሸከርካሪዎች ማለፍ
የተከለከለ፡፡
35 ለጭነት ትከርካሪዎች ተሸከርካሪዎች ማለፍ የተከለከለ፡፡
36 ሞተር ሳይክ ለሚያሽከረክሩ ማለፍ የተከለከለ፡፡
37 በሰዓት ከተሰጠው ፍጥነት በላይ ማሽከርከር ክልክል ነው
38
በሰዓት የተሰጠው ፍጥነት መጨረሻ
39 ሲጋራ ማጨስ ክልክል ነው፡፡
40 በእንስሳ ለሚጎተቱ ተሸከርካሪዎች ማለፍ ክልክል ነው፡፡
ለ. የሚያስገድዱ/ወሳኝ
• ቅርጻቸው - ክብ
• መደባቸው - ሰማያዊ
• መልዕክቱ - በነጭ ሆኖ በስእል፣በምልክት፣በቁጥር፣በቀስት...ይተላለፈል
1 ብስክሌቶች ብቻ ለማሽከርከር የተፈቀደ መንገድ፡፡
2 በመንገዱ ላይ የማሽከርከሪያ አነስተኛ ፍጥነት፡፡
3 የአነስተኛ ፍጥነት መጨረሻ፡፡
4 የጭነት ተሸከርካሪዎች እንዲተላለፉበት የተፈቀደ መንገድ፡፡
5 አደገኛ ፍንዳታ የሚያስከትል ጭነትለጫነ ተሸከርካሪ የተፈቀደበትመንገድ፡፡
6 የደሴቱን ቀኝ በመያዝ አሽከርክር፡፡
7 የደሴቱን ግራ በመያዝ አሽከርክር፡፡
8 የቀስት ምልክቱ እንደሚያመለከተው በስተቀኝ በኩል ታጥፈህ ብቻ እለፍ፡፡
9 የቀስት ምልክቱ እንደሚያመለከተው በስተቀኝ በኩል ብቻ እለፍ፡፡
10 የቀስት ምልክቱ እንደሚያመለከተው በስተግራ በኩል ባለው መንገድ ላይ ብቻ
እለፍ፡፡
11 ቀስቱ በሚያመለክተው አቅጣጫ በኩል ባለው ግራ መንገድ ላይ ብቻ አሽከርክር፡፡
12 ቀስቱ በሚያመለክተው አቅጣጫ በኩል ባለው ቀኝ መንገድ ላይ ብቻ አሽከርክር፡፡
13 ይህ ምልክት ባለበት ቦታ ላይ ወደ ትራፊኩ ክብ ወይም ደሴት አስቀድሞ ለገባ
ተሽከርካሪ ቅድሚያ ስጥ፡፡
14 ምልክቱ በሚታይበት አቅጣጫ ቀስቱ እንደሚያመለክተው ከምልክቱ በስተግራና
በስተቀኝ በኩል ብቻ እለፍ፡፡
15 ይህ ምልክት ባለበት አካባቢ ለተሽከርካሪዎች ማቆሚያ የተዘጋጀ ወይም የተወሰነ
ሥፍራ አለ፡፡ መኪናህን ቀስቱ ወደሚያመለክተው በኩል በሚገኘው የማቆሚያ ክልል
ውስጥ ብቻ ማቆም ይኖርብሀል፡
ሐ. ቅድሚያ የሚሰጡ
• የተለያየ ቅርጽ አላቸው
• አንድ አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ
1 ቁም! ይህ ምልክት ባለበት ማንኛውም የሚመጣ ተሸከርካሪ መስቀለኛ መንገድ ከመግባቱ
በፊት መቆም አለበት፡፡
2 ቅድሚያ ያለው መንገድ፡፡
3 ቅድሚያ ያለው መንገድ የሚለው ምልክት ትዕዛዝ መጨረሻ፡፡
4 ከወደፊት ለሚመጣ ተሸከራካሪ ቅድሚ ስጥ፡፡
5 በመንገደኛ መንገድ ላይ ለተላላፊ ቅድሚያ በመስጠት ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
6 በተለያየ ረድፍ ውስጥ ተፈጻሚ እንዲሆን የተቀመጠ ከፍተኛ የፍጥነት
ወሰን፡፡
7 በተለያየ ረድፍ ውስጥ ተፈጻሚ እንዲሆን የተቀመጠ አነስተኛ የፍጥነት
ወሰን፡፡
8 ለአንድ ረድፍ ከተቀመጠው አነስተኛ ፍጥነት በላይ ማሽከርከር
የሚያስገድድ፡፡
3.መረጃ ሰጪ
መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች ቅርጻቸው አራት ማዕዘን ሆኖ በሁለት
ይከፈላሉ።
1. መረጃ ሰጪ
2. አቅጣጫ አመልካች
1.መረጃ ሰጪ
• አገልግሎት የምናገኝበትን ቦታ መረጃ ይሰጡናል
1 ለተበላሹ ተሽከርካሪዎች የጥገና አገልግሎት መስጫ
2 ቴሌፎን/ስልክ/
3 የነዳጅ መቅጂያ/ማደያ/
4 በእግር ጉዞ መጀመሪያ /ቦታ/
5 ሆቴል ወይም ሞቴል
6 የጎብኝዎች ማረፊያ/መንደር/
7
8 የወጣቶች መኖሪያ
9 የእግር ጉዞ አካባቢ /ክልል/የወጣቶች መኖሪያ
10 ሰረገላዎች/ ማረፊያ ድንኳኖች ያሉበት አካባቢ
11 መዝናኛ ወይም ቡና ቤት
12 ምግብ ቤት ያለበት አካባቢ
13 የማቆሚያ ቦታ
14 ድንገተኛ ህክምና መስጫ ቦታ
2.አቅጣጫ አመልካች
• የመንገዶች ዘላቂ መሆንና አለመሆንን የሚገልጽ የመንገድ ዳር ምልክት ነው
1 ፊት ለፊት የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው
2 ወደ ቀኝ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው
3 ወደ ግራ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው
4
የመንገድ አቅጣጫ አመልካች
5 የመንገድ አቅጣጫ አመልካች
1.የመንገድ ዳር ምልክቶች በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
2. የሚያስጠነቅቁ የመንገድ ዳር ምልክቶች ቅርጻቸው ክብ እና ክፈፋቸው ቀይ ነው፡፡ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
3. አንድ አሽከርካሪ ዞሮ ለመመለስ ከመሞከሩ በፊት ዞሮ መመለስ ክልክል ነው የሚል ምልክት አለ
መኖሩን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
4. የመንገድ ዳር ምልክቶች አገር አቀፍ እንጂ አለም አቀፍ አይደሉም ሀ. እውነት ለ. ውሸት
5.ቅርፃቸው 4 ማእዘን የሆነና የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን የሚያመለክቱ ምልክቶች ምን የመንገድ
ዳር ምልክቶች ናቸው?
ሀ. የሚከለክሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች ለ. ቅድሚያ የሚየሰጡ የመንገድ ዳር ምልክቶች
ሐ. የሚያስገድዱ የመንገድ ዳር ምልክቶች መ. መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች
6.በአንድ አቅጣጫ ብቻ ለማሽከርከር ከተፈቀደበት መንገድ ላይ ለጊዜው በሁለቱም አቅጣጫ በኩል
እንዲተላለፍ መፈቀዱን መልዕክት የሚያስተላልፍ፡፡
ሀ. የሚያስገድድ የመንገድ ዳር ምልክት ለ. ቅድሚያ ስጥ የሚል የመንገድ ዳር ምልክት
ሐ. የሚያስጠነቅቅ የመንገድ ዳር ምልክት መ. መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክት
7.በአብዛኛው ቅርጻቸው ክብ፣ ዙሪያ ክባቸው ቀይና መደባቸው ነጭ የሆኑ የመንገድ ዳር ምልክቶች
የሚያስጠነቅቁ ናቸው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
8.ከመንገድ ዳር ምልክቶች ውስጥ የሁለት ባቡሮች ሃዲድ መንገዱን እንደሚያቋርጥ መልዕክት
የሚያስተላልፉ፡፡
ሀ. የሚያስገድድ ለ. አቅጣጫ አመልካች ሐ. የሚያስጠነቅቅ መ. ቅድሚያ ስጥ የሚል
9.የሚያስገድዱና የሚከለክሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች መደባቸው በአጠቃላይ ተመሳሳይ ነው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
10. መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች ወሳኝ ምልክቶች በመባል ይጠራሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
11. ከመንገድ ዳር ምልክቶች ውስጥ መጀመሪያ ወደ ቀኝ ቀጥሎ ወደ ግራ የሚታጠፍ ጠመዝማዛ
መንገድ እንደሚያጋጥምህ መልዕክት የሚያስተላልፍ
ሀ. መረጃ ሰጪ ለ. አቅጣጫ አመልካች ሐ. የሚያስጠነቅቅ መ. የሚከለክል
12.ቅድሚያ ስጥ የሚሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች፡፡ ሀ. በቅርጽ የተለያዩ ናቸው
ለ. የሚቆጣጠሩ ምልክቶች ምድብ ይመደባሉ ሐ. ቅድሚያ ሰጥተን እንድናሽከረክር ያስገድዱናል
መ. ሁሉም መልስ ናቸው
13.በከተማ ክልል ውስጥ ለፍጥነትና ሌሎች ህጐች ትዕዛዝ የሚያስተላልፈው የመንገድ ዳር
ምልክት ከሚከለክሉት ውስጥ ይመደባል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
14.መንገዶችን ዘላቂ መሆንና አለመሆን የሚያስተላልፉ የመንገድ ዳር ምልክቶች …….ውስጥ
ይመደባሉ፡፡
ሀ. የሚያስጠነቅቅ ለ. አቅጣጫ አመልካች ሐ. ቅድሚያ የሚያሰጡ መ. የሚቆጣጠሩ
15.መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች፡፡ ሀ. ወሳኝ መልክቶች ናቸው
ለ. የሚከለክሉ ምልክቶች ናቸው ሐ. ቅድሚያ የሚሰጡ መልክቶች ናቸው መ. መልስ አልተሰጠም
16.የአገልግሎት ሰጪ ድርጅት ቦታንና አቅጣጫን ለማመልከት የምንጠቀምበት ምልክት……
ይመደባል፡፡
ሀ. የሚያስጠነቅቁ ምልክቶች ውስጥ ሐ. መረጃ ሰጪ ምልክቶች ውስጥ
ለ. ቅድሚያ የሚሰጡ ውስጥ መ. የሚያስገድዱ ምልክቶች ውስጥ
17.በአውቶሞቢል ምደብ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማሽከርከር የሚቻለው ተሽከርካሪ የመጫን
አቅሙ ነጂውን ጨምሮ ከ…. ሰው ያልበለጠ መሆን ካለበት ነው፡፡
ሀ. 12 ለ. 8 ሐ. 15 መ. 24
18.የመንገድ ዳር ምልክቶች በማንኛውም አካል ሊተከሉ ይችላሉ:: ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
19.መደባቸው ሰማያዊ የሚያስተላልፉት መልዕክት በነጭ ቀስት የተሠራ የመንገድ ዳር ምልክቶች፡፡
ሀ. አቅጣጫ አመልካች ለ. መረጃ ሰጪ ሐ. የሚያስገድድ መ. መልስ አልተሰጠም
20. መረጃ ሠጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች፡፡ ሀ. መንገዶች ወዴት እንደሚዘልቁ ይጠቁሙናል
ለ.መቆምና መቅደም የተከለከለበትን ሥፍራ ይጠቁማል
ሐ. የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ርቀት ይጠቁማል መ. “ሀ” እና “ሐ” መልስ ናቸው
21.አብዛኛውን ጊዜ በመገናኛ ደሴቶች ላይ አደገኛ የሆኑ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ምልክቶች ይባላሉ፡፡
ሀ. የሚያስገድዱ ለ. ወሳኝ ሐ. የሚከለክሉ መ. "ሀ" እና "ለ" መልስ ናቸው፡፡
22.በቅርፅ የተለያዩና በመልዕክት ግን ተመሣሣይ የሆኑ መንገድ ዳር ምልክቶች ምን ይባላሉ፡፡
ሀ. የሚቆጣጠሩ ለ. የሚያስገድዱ ሐ. የሚከለክሉ መ. ቅድሚያ የሚሰጡ
23. መንገዶች ዘላቂ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን የሚገልፅ የመንገድ ዳር ምልክት ይባላል፡፡
ሀ. መረጃ ሰጪ ለ. የሚቆጣጠር ሐ. አገልግሎት አመላካች መ. መልሱ የለም
24. ከአለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች ውስጥ 3 ንዑስ ዘርፍ ያለው ይባላል፡፡
ሀ. የሚያስጠነቅቁ ለ. የሚቆጣጠሩ ሐ. መረጃ የሚሰጡ መ. መልሱ አልተሰጠም
25.ከፊት ለፊት ያለውን የመንገድ ሁኔታ አስቀድሞ የሚገልጽ የመንገድ ዳር ምልክት ይባላል፡፡
ሀ. መረጃ ሰጪ ለ. የሚያስጠነቀቅ ሐ. የማቆጣጠር መ. ሁሉም
26.በአሽከርካሪ የተፈጸመ ቀላል ጥፋት ለ1 አመት በሪከርድነት ይያዛል፡፡ ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
27. በአሽከርካሪ የተፈጸመ ከባድ ጥፋት ለ 5 አመት በሪከርድነት ይያዛል፡፡ ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
28.የሀገራችን አዲሱ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ በስንት ዋና ዋና ዓይነቶች ይመደባሉ፡፡
ሀ/ በ 5 ለ/ በ 6 ሐ/ በ 12 መ/ በ 7
29.አለም አቀፍ ይዘት የሌለው የትራንስፖርት ህግ የሆነዉ የቱ ነዉ
ሀ/ የመንገድ ዳር ምልክቶች ሐ/ የፍጥነት ወሰን ገደብ
ለ/ የመንገድ መሀል መስመሮች መ/ የትራፊክ መብራት
30. የሚቆጣጠሩ የመንገድ ዳር ምልክቶች ንዑስ ክፍል የሆነው የቱ ነዉ
ሀ/ የሚያሰጠነቅቁ ለ/ የሚከለክሉ ሐ/ አቅጣጫ የሚጠቁሙ መ/ መረጃ ሰጪ
31.በመሰቀለኛና በመገናኛ ቦታዎች ላይ የምናገኛቸው መደባቸው ሰማያዊ የሆነ ምልክቶች
የሚያሰተላልፋት መልዕክት በነጭ ቀለም በተሰራ ቀሰት ሰዕል ወይም ፀሑፍ የሆኑ የመንገድ ዳር
ምልክቶች ምን ይባላሉ?
ሀ. የሚከላከሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች ለ. ቅድሚያ የሚያሰጡ የመንገድ ዳር ምልክቶች
ሐ. የሚያሰገድዱ የመንገድ ዳር ምልክቶች መ. መረጃ ሰጭ የመንገድ ዳር ምልክቶች
32. ቅርፃቸው ክብ የሆነ ዙሪያቸውን በቀይ ቀለም የተቀቡ ሆነው መድባቸው ነጭ
የሚያሰተላልፉት መልዕክት ደግሞ በጥቁር ቀለም በተሰራ ሰዕል ወይም ቀሰት ወይም ፀሑፍ የሆነ
የመንገድ ዳር ምልክቶች ምን ይባሉ?
ሀ. የሚከላከሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች ለ. ቅድሚያ የሚሠጡ የመንገድ ዳር ምልክቶች
ሐ. የሚያሰገድድ የመንገድ ዳር ምልክቶች መ. መረጃ ሰጭ የመንገድ ዳር ምልክቶች
33. ሰለሚያሰጠነቅቁ የመንገድ ዳር ምልክቶች ሰህተት የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ቅርፃቸው ሶሰት መአዘን ነው ለ. መደባቸው ነጭ ነው
ሐ. የሚያሰተላልፉት መልዕክት በጥቁር ቀለም በምስል፣ በቀሰት፣ በቁጥር ወይም በምልክት በመቅረፅ
ነው
መ. አንዳንድ ጊዜ ቅርፃቸዋ ክብ እና አራት መአዘን ሆነው እናገኛቸዋለን
34.የአንድ የመንገድ ዳር ምልክት ወደ ጅማ የሚሄድ መሆኑን ካመለከተን ይህ የመንገድ ዳር
ምልክት በየትኛው ምድብ ውስጥ ይመደባል
ሀ/ ቅድሚያ በሚያሰጡ ለ/ በሚያስጠነቅቁ ሐ/ በመረጃ ሰጪ መ/ የሚያስገድዱ
35. ማናቸውም ዓይነት ተሽከርካሪና በእጅ የሚገፉትም ጭምር እንዳያልፉበት የተዘጋ መንገድ
መኖሩን የሚያመለክት የመንገድ ዳር ምልክት የቱ ነዉ
ሀ/ የሚያስገድድ ለ/ ቅድሚያ የሚያሰጥ ሐ/ የሚከላከል መ/ የሚያስጠነቅቅ
2.አለም አቀፍ የመንገድ ላይ መስመሮች
መንገዶች ላይ የሚሰመሩ መስመሮች አገልግሎታቸው
• የት ቦታ መቅደም እንደምንችል ይጠቁማሉ
• መታጠፊያና ማዞሪያ ቦታ ይጠቁማል
• የትራፊክ መብራት አከባቢ የምንቆምበትን ስፍራ ያመለክታል
• የመንገድን መሀልና ጠርዝ ያመለክታል
• የእግረኛና ማቋረጫን ያመለክታል
• አንድን መንገድ ሁለት አቅጣጫ ይከፈላል
• የመንገድ ዳር ምልክቶችን ተክተው ይሰራሉ
አለም አቀፍ የመንገድ ላይ መስመሮች በሁለት ይከፈላሉ
ሀ. በመንገድ አግድም የሚሰመሩ መስመሮች
ለ. በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ መስመሮች
ሀ. በመንገድ አግድም የሚሰመሩ መስመሮች
• የእግረኛ ማስተላለፊያ መስመር ነው
2. በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ መስመሮች
1.የተቆራረጠ መስመር
• የተቆራረጠ መስመር ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድን ሲከፍል
• ግልጽና የትራፊክ መጨናነቅ የሌለበት ቦታ ይሰመራል
• የተቆራረጠ መስመርን አቋርጦ መቅደም፣ወደ ግራ ዞሮ መመለስና ወደ ግራ
መታጠፍ ይቻላል
2.ያልተቆራረጠ/ድፍን መስመር
• ያልተቆራረጠ መስመር ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድን ሲከፍል
• ግልጽ ያልሆነ ቦታናየትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ቦታ ይሰመራል
• ድፍን መስመርን መስመርን አቋርጦ መቅደም፣ወደ ግራ ዞሮ መመለስና ወደ
ግራ መታጠፍ አይቻልም
3.የተቆራረጠና ያልተቆራረጠ መስመር
• በተቆራረጠ መስመር በኩል ያለው አሽከርካሪ ሁለቱን መስመሮች አልፎ መቅደም፣ወደ
ግራ ዞሮ መመለስና ወደ ግራ መታጠፍ ይችላሉ።
• ባልተቆራረጠው መስመር በኩል ያለው አሽከርካሪ መስመሮቹን አልፎ መቅደም፣ወደ ግራ
ዞሮ መመለስና ወደ ግራ መታጠፍ አይቻልም።
•
ባለአንድ አቅጣጫ መንገድ በተቆራረጠ ነጭ መስመር
በረድፍ ሲከፈል
ማንኛውም አሽከርካሪ በራሱ ረድፍ ውስጥ በማሽከርከር ፍጥነት ለመጨመር፣ለመቀነስ ወይም
ለመታጠፍ በሚፈልግበት ወቅት የተቆራረጠውን መስመር አልፎ ማሽከርከር ይችላል። መንገዱ
ባለ አንድ አቅጣጫ በመሆኑ ዞሮ መመለስ ክልክል ነው።
አንድ መንገድ ከመስመር በተሰራ የትራፊክ ደሴት ለሁለት ሲከፈል
ማንኛውም አሽከርካሪ የትራፊክ ደሴትን ረግጦ መቅደም፣ወደ ግራ ዞሮ መመለስና ወደ ግራ
መታጠፍ አይፈቀድለትም።ዞሮ መመለስና መታጠፍ የፈለገ አሽከርካሪ እንደ መንገዱና እንደ
ትራፊኩ ሁኔታ በጥንቃቄ በደሴቱ ማረጫ ለመታጠፍና ለመዞር በተዘጋጀ ስፍራ ላይ ወደ ቀኝ
አስፍቶ ዞሮ መመለስና መታጠፍ ይቻላል።በተጨማሪም ቀድሞ በተገለጸው ሁኔታ ደሴቱን
ሳይረግጥ በራሱ ነጠላ መንገድ የግራ ረድፍን ይዞ መቅደም ይቻላል።
በመንገድ ላይ የሚቀቡ ቅቦች
በመንገድ ላይ የሚቀቡ ቅቦች በሶስት ይከፈላሉ።እነሱም፡-
1.የመቆሚያ ስፍራ ቅብ፡- አሽከርካሪዎች በምልክቱ ውስጥ ለማቆሚያ በተዘጋጀው ስፍራ ላይ ብቻ
መቆም አለባቸው።
2.የማስተላለፊያ ምልክት ቅብ፡-የቀለም ነጠብጣብ ባላቸው ክልሎች ውስጥ ማሽከርከር ክልክል ነው
3.ቅድሚያ ስጥ የሚል ምልክት ቅብ፡- ምልክቱ/ቅቡ/ቅድሚያ ለተላላፊ በመስጠት በጥንቃቄ
ማሽከርከር እንዳለብህ መልእክት ያስተላልፋል።
1. የመንገድ ላይ መስመሮች ጠቀሜታ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. አንድ አቅጣጫ መንገድን በረድፍ መከፈል ለ. አንድን መንገድ በሁለት ነጠላ መንገድ መክፈል
ሐ. ለእግረኛ መተላለፊያ መንገድ ማመልከት መ. ሁሉም መልስ ነው
2. የመንገድ ላይ መሥመሮች ጠቀሜታ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የት ቦታ ላይ አቅጣጫ ቀይረን ተሽከርካሪን መቅደም እንደምንችል ማመልከቱ
ለ. መታጠፊያና ዞሮ መመለሻ መንገዶችን ማመላከት
ሐ. የመንገድ መሀልና ጠርዝን ማመልከት መ. ሁሉም መልስ ነው
3. የተቆራረጠ የመንገድ መሀል መስመር በተሠመረበት መንገድ ላይ አሽከርካሪዎች መስመሩን
አቋርጠው አቅጣጫ መቀየርም ሆነ ዞሮ መመለስ አይችሉም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
4.የማያቋርጥ የቀለም መሥመር በተሠመረበት መንገድ ላይ ማንኛውም አሽከርካሪ ወደ ቀኝ መጠምዘዝ
ይፈቀድላቸዋል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሃሰት
5. በትራፊክ ደሴት ዙሪያ የሚያሽከረክር ማንኛውም አሽከርካሪ የትራፊክ ደሴት ቀኙን ወገን ብቻ
ተከትሎ መንዳት አለበት፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
6. አንድ መንገድ በሦስት ነጠላ መንገዶች ተከፋፍሎ ሲገኝ ማንኛውም አሽከርካሪ ሌላ ተሽከርካሪ
ለመቅደም ካልሆነ በስተቀር በመካከለኛው ነጠላ መንገድ ውስጥ እንዲነዳ አይፈቀድለትም፡፡
ሀ. እውነት ለ. ውሸት
7.በድፍን መስመር በተሠመረበት መንገድ ላይ ማንኛውም አሽከርካሪ ወደ ቀኝ መጠምዘዝ
አይፈቀድላቸውም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
8.ወደ ደሴቱ የተቃረበ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው፡፡
ሀ. ደሴቱን በመዞር ላይ ላሉ ለ. ወደ ደሴቱ ለተቃረቡ
ሐ. ደሴቱን ዞረው ለጨረሱ መ. በስተግራ አቅጣጫ ለሚዞሩ ተሽከርካሪዎች
9. በመንገድ አግድመት የሚሰመሩ መስመሮች የሚባሉት መንገድን በረድፍ የሚከፍሉ መስመሮች
ናቸው ሀ. እውነት ለ. ውሸት
10.በመንገድ አግድመት የሚሰመሩ መስመሮች ዞሮ ለመመለስ የምንጠቀምበትን ረድፍ ያመለክታሉ፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
11. ከሚከተሉት ውስጥ በመንገድ ላይ ከሚቀቡ ቅባች የማይመደበው የትኛው ነው?
ሀ. የመቆሚያ ሥፍራ ቅብ ለ. የማስተላለፊያ ምልክት ቅብ ሐ. ቅድሚያ ስጥ የሚል ምልክት ቅብ
መ. ዝቅተኛ የፍጥነት ወሰን
12. የእግረኛ መተላለፊያ መስመሮች ናቸው፡፡
ሀ. በመንገድ አግድመት የሚሰመሩ መስመሮች ለ. በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ መስመሮች
ሐ. በመንገድ ትይዩ የሚሰመሩ መስመሮች መ. ሁሉም መልስ ነው
13.የተቆራረጡ መስመሮች በድፍን መስመር ሲተኩ መንገዱ ግልጽ መሆኑን እየቀነሰ መምጣቱን
ይገልጻል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
14.አንድ አስፋልት ከመስመር በተሰራ ደሴት እኩል ለሁለት ሲከፈል በስተግራ በኩል መቅደም
የሚቻለው ደሴቱን ሳይረግጡ ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
15.ያልተቆራረጠ መስመር በተሰመረበት መስመር ላይ አሽከርካሪዎች እንደ መንገዱና እንደ ትራፊኩ
ሁኔታ ድፍኑን መስመር ሳይረግጡ መቅደም ይችላሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
16.በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ መስመሮች ውስጥ ጠመዝማዛ መንገድ ላይ የሚሰመረው …
መስመር ነው፡፡ ሀ. የተቆራረጠ ለ. ያልተቆራረጠ ሐ. ቀይ መስመር መ. ጥቁር መስመር
17.ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገዱ በተቆራረጠ ነጭ መስመር ለሁለት እኩል ሲከፈል መስመሩን አልፎ
መቅደም ይቻላል፡፡ : ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
18.የተቆራረጠ መስመር አንድ መንገድን ለሁለት እኩል ሲከፍል::
ሀ. መስመሩን አልፎ ወደ መጡበት ዞሮ መመለስ ይችላል ለ. መንገዱን ግልጽ አለመሆኑን ይጠቁማል
ሐ. መስመሩን አልፎ ታጥፎ መሄድ አይቻልም
መ. የትራፊክ መጨናነቅ መንገዱ ላይ እንዳለ ይጠቁመናል
20.መንገዱ ግልፅ መሆኑን የሚገልጽ የመንገድ መሃል መስመር ይባላል፡፡
ሀ. ድፍን መስመር ለ. የተቆራረጠ ሐ. ደሴት መ. ሁሉም
21.የመንገድ አካፋይ በድፋን መስመር የሚሰመረባቸው የትራፊክ መጨናነቁ አነስተኛ በሆኑ
መንገዶች ላይ ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
22. ድፍን መስመርን አቋርጦ ወደ ኋላ ዞሮ መመለስ ይቻላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
23. ዞሮ መመለስ መቅደምና መታጠፍን የሚከለክል የመንገድ ላይ መስመር ነው
ሀ. የተቆራረጠ የመንገድ ላይ መስመር
ለ. የመቆሚያ ሥፍራ ቅብ መስመር
ሐ. ያልተቆራረጠና የተቆራረጠ የመንገድ አካፋይ መስመር
መ. ድፋን የመንገድ ላይ መስመር
24.አሽከርካሪው አልፎ መመለስ፣ መቅደም እና ታጥፎ እንዳይሔድ የሚከለከለው የመንገድ ላይ ቅብ የቱ
ነው፡፡ሀ. ድፍን መሥመር ለ. የተቆራረጠ መሥመር ሐ. ድፍን እና የተቆራረጠ መሥመር መ. ሁሉም
25. አንድ መንገድ በተቆራረጠ እና ባልተቆራረጠ ሁለት መስመሮች ጎን ለጎን በተሠመሩ ጊዜ የሚቻለው
የትኛው ነው
ሀ. በተቆራረጠ መስመረ በኩል ያለው አሽከርካሪ ሁለቱንም መስመሮች አልፎ መቅደምና ታጥፎ መሔድ
ይቻላል
ለ. ባልተቆራረጠው መስመር በኩል ያለው አሽከርካሪ መስመሮችን አልፎ መቅደም ዞሮ መመለስና
መታጠፍ አይፈቀድለትም ሐ. ሀ እና ለ መልስ ናቸው መ. መልሱ የለም
26. ባለ አንድ አቅጣጫ መንገድ በተቆራረጠ ነጭ መስመር በረድፍ ሲከፋፈል ማድረግ የማንችለው
ከሚከተሉት ውስጥ የትኛው ነው?
ሀ. በራሰ እረድፍ ውስጥ በማሽከርከር ፍጥነት መጨመር ወይም መቀነስ
ለ. በራሰ እረድፍ ውስጥ ለመታጠፍ በሚፈልግበት ወቅት የተቆራሪጠውን መስመር አልፎ ማሽከርከር
ሐ. ዞሮ ወደ መጡበት መመለስ መ. ሁሉም መልስ ናቸው
27.በአጭር ርቀት ውስጥ እግረኞች መንገድ እንዲያቋርጡ የሚሰመር መስመር በመንገድ አግድመት
የሚሰመሩ መስመሮች ብለን እንጠራቸዋለን:: ሀ. እውነት ለ. ውሸት
3. የትራፊክ መብራት
ትራፊክ ማለት
 በማንኛውም መንገድ አንድ ወይም ብዙ ሆነው የሚተላለፉ እግረኞች ወይም
ሰው ተቀምጦባቸው ወይም እየተነዱ ወይም እየተጠበቁ የሚሄዱ እንስሶችና
ተሽከርካሪዎች ናቸው።
 በየብስ፣በባህርና በአየር የሚደረግ የእግረኞች፣የመርከቦችና የአውሮፕላኖች
መተላለፍ ማለት ነው።
የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራቶች
በሚሰጡት አገልግሎት በሁለት
ይከፈላሉ።እነርሱም
1.የእግረኞች ማስተላለፊያ መብራት
• ቀይ የእግረኛ ምስል፡- እግረኞች ያስቆማል
• አረንጓዴ የእግረኛ ምስል፡- እግረኞች ያስተላልፋል
2.የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት
1. ቀይ፡- መተላለፊያ መስመሩን ሳታልፍ ቁም
2.ቀይና ቢጫ፡- ለመሔድ ተዘጋጅ
3.አረንጓዴ፡- ወደ መረጥክበት አቅጣጫ እለፍ
4.ቢጫ፡-
፡- ወደ መገናኛ መንገድ በመምጣት ላየ ያሉ ለእግረኛ
የተሰመረውን ሳታልፉ ቁሙ
፡- መገናኛ መንገድ ቀድመው የገቡ አሽከርካሪዎች
በፍጥነት ለቃችሁ ውጡ የሚል መልእክት
ያስተላልፋል
ምንኛውም አሽከርካሪ መንገዱ ላይ አደገኛ ሁኔታ ሊኖር ስለሚችል
ፍጥነቱን በመቀነስ ለተላላፊዎች ቅድሚያ በመስጠት ተጠንቅቆ ማለፍ
ይችላል።
ብልጭ ድርግም የሚል ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ
ማንኛውም አሽከርካሪ መንገዱ ላይ አደገኛ ሁኔታ እንዳለ ተገንዝቦ ለእግረኛ
መተላለፊያ የተሰመረውን መስመር ሳያልፍ በመቆም አደጋ የማያስከትል
መሆኑን ሳያረጋግጥ እንዲያልፍ አይፈቀድለትም።
ብልጭ ድርግም የሚል ቀይ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ
1. ብልጭ ድርግም የሚል ቢጫ የተሽከርካሪዎች ማስተላለፊያ መብራት ለአብዛኛው የትራፊክ መጨናነቅ
በማይበዛበት ወቅት እንዳይቆሙና በጥንቃቄ መተላለፍ እንዲችሉ ያደርጋል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
2.ከአረንጓዴ የተሽከርካሪ ማሰተላለፊያ መብራት ቀጥሎ ቢጫ መብራት ብቻውን ሲበራ
የሚያስተላልፈው መልእክት ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ለመሄድ ይዘጋጃሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
3. የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራት ስንት ቀለሞች አሉት፡፡
ሀ. አንድ ለ. ሁለት ሐ. ሶስት መ. አራት
4.መብራት ባለበት መስቀለኛ መንገድ መሀከል ላይ ተሽከርካሪው እየተጓዘ እያለ ቢጫ የትራፊክ
መብራት ሲበራ ቆሞ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን ማሳለፍ አለበት፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
5.የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራት አቀማመጡ ከላይ ወደታች ምን ይመስላል?
ሀ. አረንጓዴ፣ ቢጫና፣ ቀይ ለ. ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ቀይ ሐ. ቀይ፣ ቢጫና፣ አረንጓዴ መ. ቀይና፣ አረንጓዴ
6. ተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ላይ የእግረኛ ምስል መቀመጥ አለበት ሀ. እውነት ለ.ሀሰት
7. ብልጭ ድርግም የሚል ቢጫ የተሽከርካሪ መስተላለፊያ መብራት ሲበራ አሽከርካሪው ተሽከርካሪውን
በማቆም ለተላላፊዎች ቅድሚያ በመስጠት በጥንቃቄ ማለፍ አለበት ሀ. እውነት ለ. ውሸት
8.ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ከአረንጓዴ መበራት ቀጥሎ ሲበራ የሚያስተላልፈው
መልዕክት ሀ. ቆመህ ከነበረ ለጉዞ ተዘጋጅ ለ. ቆመህ ከነበረ ጉዞ ጀምር
ሐ. መስቀለኛ መንገድ ውስጥ ከገባህ በፍጥነት ውጣ
መ. መስቀለኛ መንገድ ውስጥ ከገባህ ወደ ኋላ ተመለስ
9. -----------ማለት በየብስ፣ በባህር ወይም በአየር ላይ የሚደረግ የሰው፣ የመርከብ እና አውሮፕላን
እንቅስቃሴ ነው፡፡
ሀ. የመንገድ ትራንስፖርት ለ. ትራንስፖርት ሐ. ትራፊክ መ. መልስ የለም
10. -----መብራት ሲበራ ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች መሄድ ይችላሉ፡፡
ሀ. አረንጓዴ ለ. ቀይ ሐ. ቢጫ መ. ቀይና ቢጫ
11.ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ ወደ መገናኛው ሥፍራ የደረሰ አሽከርካሪ ማለፍ
ይችላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
12.ቢጫ የተሽከርካሪ መስተላለፊያ መብራት ሲበራ ወደ መገናኛው ስፍራ የደረሰ አሽከርካሪ ማለፍ
ይችላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
13.መብራት ሲበራ ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ለመሄድ ይዘጋጃሉ፡፡
ሀ. ቢጫ ለ. አረንጓዴ ሐ. ቀይ መ. ቀይና ቢጫ
14……..መብራት ብርት ጥፍት እያለ በተደጋጋሚ ሲበራ ፍጥነት በመቀነስ ግራና ቀኝ አይቶ
በጥንቃቄ ማለፍ ይቻላል፡፡ ሀ. አረንጓዴ ለ. ቀይ ሐ. ቢጫ መ. መልስ አልተሰጠም
15.ቀይና ቢጫ አንድ ላይ ሲበሩ ትርጉሙ የማቆሚያ መስመሩን ካለፍክ ፍጥነትህን ጨምረህ
መንገዱን አቋርጥ ማለት ነው፡፡ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
16.የሰው ምስል ያለበት ቀይ የተራፊክ ማስተላለፊያ መብራት ከበራ ለተሽከርካሪ ቁም ማለት ነው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
17.ቀይና ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት በአንድነት ሲበራ ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች
ጉዞ መቀጠል ይችላሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
18.መሰቀለኛ መንገድ ውስጥ ከገባህ በፍጥነት ውጣ የሚል የትራፊክ መብራት ነው፡፡
ሀ. ቀይ ለ. ቀይና ቢጫ ሐ. አረንጓዴ መ. ቢጫ
19.አለም አቀፍ የትራፊክ መብራቶች በአሰራር /በአበራር/ ቅደም ተከተላቸው፡፡
ሀ/ ቀይ፣አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ሐ/ አረንጓዴ፣ቀይናቢጫ፣ ቀይ፣ቢጫ
ለ/ ቀይ፣ቀይናቢጫ፣አረንጓዴ፣ቢጫ መ/ ቀይ፣ቢጫ፣አረንጓዴ፣ቀይ
20.አረንጓዴ የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራት በርቶ ከርቀት በማይታይበት ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት
እያሽከረከረ መገናኛ መንገዱን ማቋረጥ ይቻላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
21.ወደ መገናኛው መንገድ በመምጣት ላይ ያለ ተሸከርካሪዎች የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ሣያልፍ
እንዲቆሙ ወደ መገናኛው መንገድ ቀድመው የገቡ አሽከርካዎች በፍጥነት መንገድ ለቀው እንዲወጡ
የሚያዘው የአሸከርካሪ ማሰተላለፊያ መብራት የቱ ነው?
ሀ. ቢጫ ለ. ቀይ ሐ. አረንጓዴ መ ቀይ እና ቢጫ
22.ተሽከርካሪዎችን እንዲቆሙ የሚያዘው የተሽከርካሪ ትራፊክ ማስተላለፊያ መብራት ምን አይነት
ነው? ሀ. ቀይ ለ. ቢጫ ሐ. አረንጓዴ መ. ቀይና ቢጫ
23. ተሽከርካሪዎች ጉዞ ለመቀጠል እንዲዘጋጁ ነቅተው እንዲጠብቁ የሚያደርገው የተሽከርካሪ
ትራፊክ ማስተላለፊያ መብራት ምን አይነት ነው?
ሀ. ቀይ ለ. ቢጫ ሐ. አረንጓዴ መ. ቀይ እና ቢጫ አንድነት ሲበሩ
24. ተሽከርካሪዎች እንዲንቀሳቀሱ ወይም ጉዞአቸው እንዲቀጥሉ የሚፈቅደው ወይም የሚያዘው
የተሽከርካሪ ማሰተላለፊያ መብራት ቀለም ምን አይነት ነው?
ሀ. ቀይ ለ. ቢጫ ሐ. አረንጓዴ መ. ቀይ እና ቢጫ
4.የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክቶች
1 2 3
4 5 6 7
1 ከፊት ለፊት የሚመጡትን አሽከርካሪዎች እንዲቆሙ ያዛል
2 ከኃላ የሚመጡ ተሽከርካሪዎች እንዲቆሙ ያደርጋል
3 ከፊት ለፊትና ከኃላ ወደ መስቀለኛ መንገደ የሚመጡትን ተሽከርካሪዎች ያስቆማል
4 ከቀኝ ወደ ግራና ቀጥታ ታጥፈው ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ይፈቀዳል
5 ፊት ለፊት ቆመው ከነበሩ አሽከርካሪዎች ወደ ፊትና ወደ ቀኝ አንዲጓዙ ይፈቅዳል
6 ከኌላ ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ቀጥታ ወደ ፊትና ወደ ቀኝ ታጥፈው እንዲጓዙ
ይፈቀዳል
7 ከግራ ወደ ቀኝና ቀጥታ ታጥፈው ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ይፈቀዳል
5.የፍጥነት ወሰን ገደብ
የፍጥነት ወሰን ገደብ
የፍጥነት ወሰን ገደብ በሁለት ይከፈላል። እነርሱም
1.የከተማ ውስጥ
2.የከተማ ውጪ
ከከተማ ውጪ በሶስት መንገዶች ይገኛሉ። እነርሱም
ሀ.አንደኛ ደረጃ መንገድ፡- ሀገርን ከሀገር ያገናኛል።
ለ.ሁለተኛ ደረጃ መንገድ፡-ክልልን ከክልል ያገናኛል።
ሐ.ሶስተኛ ደረጃ መንገድ፡-ወረዳን ከወረዳ ያገናኛል።
የሀራችን የፍጥነት ወሰን ገደብ ሲደነገግ መነሻ የሚያደርገው ሁለት ነገሮችን ነው።
1.የተሽከርካሪ ክብደት/አይነት
2.የመንገድ ደረጃ
የተሽከርካሪ ክብደት/አይነት የከተማ ውስጥ የከተማ ውጪ
1ኛ 2ኛ 3ኛ
ከ3500 ኪ.ግ. በታች
አውቶሞቢል/አነስተኛ
ተሽከርካሪዎች
60 100 70 60
ከ3500 ኪ.ግ. -7500 ኪ.ግ.
የንግድ/መለስተኛ የህዝብና የደረቅ
ጭነት ተሽከርካሪዎች
40 80 60 50
ከ7500 ኪ.ግ. በላይ
ከፍተኛ የህዝብና የደረቅ ጭነት
ተሽከርካሪዎች
30 70 50 40
1.ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በታች ማሽከርከር ይቻላል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
2.አነስተኛ አውቶሞቢል ከከተማ ክልል ውጪ በዋና መንገድ በሰዓት ማሽከርከር የሚችለው የፍጥነት
ወሰን? ሀ. በ8ዐ ኪ.ሜትር ለ. በ7ዐ ኪ.ሜትር ሐ. በ1ዐዐ ኪ.ሜትር መ. በ6ዐ ኪ.ሜትር
3. አነስተኛ የጭነት ተሽከርካሪ ወይም አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ በአንደኛ ደረጃ መንገድ ላይ በሰዓት
የፍጥነት ወሰኑ ሀ. 8ዐ ኪ.ሜትር ለ. 75 ኪ.ሜትር ሐ. 6ዐ ኪ.ሜትር መ. 7ዐ ኪ.ሜትር
4. በከተማ ክልል ውስጥ ከ75ዐዐ ኪ.ግ በላይ ክብደት ያላቸው ተሽከርካሪዎች በከተማ መንገድ ላይ
በሰህት የፍጥነት ወሰኑ በኪ.ሜትር ነው፡፡
ሀ. 65 ኪ.ሜትር ለ. 8ዐ ኪ.ሜትር ሐ. 3ዐ ኪ.ሜትር መ. 6ዐ ኪ.ሜትር
5. በከተማ ክልል ውስጥ ከ35ዐዐ - 7ዐዐዐ ኪግ ክብደት ያላቸው ተሽከርካሪዎች በሰዓት የፍጥነት
ወሰኑ በኪ.ሜትር ሀ. 4ዐ ኪ.ሜትር ለ. 3ዐ ኪ.ሜትር ሐ. 6ዐ ኪ.ሜትር መ. 8ዐ ኪ.ሜትር
6.ማንኛውም አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን በፍጥነት ለማሽከርከር የማይፈቀድለት ምክንያት?
ሀ. የመንገዱ ሁኔታ ሐ. ተላላፊውን ለማየት በማይቻልበት የአየር ፀባይ
ለ. የትራፊኩ ብዛትና ሁኔታ መ. ሁሉመ ምልስ ነው
7.መሃከለኛ ክብደት ያላቸው ተሽከርካሪዎች በሁለተኛ ደረጃ አውራ ጐዳና ላይ የተፈቀደላቸው
የፍጥነት ወሰን በሰዓት ነው፡፡ ሀ. 8ዐ ለ. 6ዐ ሐ. 5ዐ መ. 4ዐ
8.ለከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢው በሁለተኛ ደረጃ አውራ ጐዳና ላይ የተፈቀደላቸው የፍጥነት
ወሰን በሰዓት ነው፡፡
ሀ. 1ዐዐ ኪ.ሜ ለ. 6ዐ ኪ.ሜ ሐ. 5ዐ ኪ.ሜ መ. 4ዐ ኪ.ሜ
9.ለአነስተኛ ተሽከርካሪ ከከተማ ክልል ውጭ በ3ኛ ደረጃ አውራጐዳና የተፈቀደለት የፍጥነት
ገደብ ኪ.ሜ በሰዓት ነው፡፡ ሀ. 6ዐ ለ. 5ዐ ሐ. 1ዐዐ መ. 7ዐ
10.ለከፍተኛ ተሽከርካሪ በአንደኛ ደረጃ አውራ ጐዳና ላይ የተፈቀደለት ከፍተኛ የፍጥነት ወሰን፡፡
ሀ. 3ዐ ኪ.ግ በሰዓት ለ. 8ዐ ኪ.ግ በሰዓት ሐ. 7ዐ ኪ.ግ በሰዓት መ. መልስ አልተሰጠም
11.ጠቅላላ ክብደታቸው ከ3,5ዐዐዐኪ.ግ በታች ለሆኑ ተሽከርካሪዎች በ2ኛ ደረጃ አውራጎዳና ላይ
የተፈቀደለት ከፍተኛ ፍጥነት ወሰን፡፡
ሀ. 7ዐ ኪ.ሜ በሰዓት ሐ. 4ዐ ኪ.ሜ በሰዓት
ለ. 6ዐ ኪ.ሜ በሰዓት መ. 5ዐ ኪ.ሜ በሰዓት
12.የአገራችን የፍጥነት ወሰን ገደብ ሲደነገግ መነሻ የሚያደረገው የቱን ነው
ሀ/ የመንገዱን ሁኔታ ሐ/ የተሸከርካሪውን የመቀመጫ ብዛት
ለ/ የተሸከርካሪውን ጠቅላላ ክብደት መ/ ሁሉም መልስ ነው
6.የመንገድ ስነ-ስርዓት
ተሽከርካሪ ለጊዜው ወይም ለረጅም ግዜ ማቆም የተከለከለባቸው
ስፍራዎች
• ከከተማ ክልል ውጪ በሆነ በማናቸውም መንገድ ላይ ተሽከርካሪ የሚያሽከርከር ማናቸውም
ሰው ከመንገዱ ላይ ለተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ ከሌለ በስተቀር ከመኪና ቢወርድም
ባይወርድም ትራፊክ በብዛት በሚተላለፍበት መንገድ ላይ ለጊዜው ወይም ለረጅም ግዜ
ተሽከርካሪ ማቆም የለበትም።
• ማንኛውም ሰው የመንገዱ ስፋት ከ12ሜትር በላይ ካልሆነ በቀር ተሽከርካሪውን ከሌላ
ተሽከርካሪ ተቃራኒ አንጻር ከመንገድ ላይ ለጊዜው ለረጅም ግዜ ማቆም የለበትም።
• ማንኛውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ በዚያው መንገድ የሚነዳ የሌላ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ
ከሁለቱም አቅጥጫ በ50ሜትር ርቀት ላይ ለማየት በማይችልበት ስፍራ ከመንገድ ላይ
ተሽከርካሪ ማቆም የለበትም።
• ከእሳት አደጋ ጣቢያ ወይም የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ከሚሰጥበት ጣቢያ ወይም ከሆስፒታል
መግቢያ በ12 ሜትር ውስጥ ወይም ከመግቢያው መካከል ጀምሮ ከመንገድ ግራና ቀኝ በ25ሜትር
ውስጥ መቆም ክልክል ነው
• ከአውቶቢስ ማቆሚያ በስተኃላ በስተፊት በ15ሜትር ውስጥ የመንገዱ ስፋት ከ12ሜትር በላይ ካልሆነ
በስተቀር በመንገዱ አንጻር ከአውቶቢስ ማቆሚያ በ30 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው።
• በመስቀለኛ መንገድ ውስጥ ወይም ከመስቀለኛ መንገድ በ12ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው።
• በሃዲድ መንገድ ማቋረጫ ከሚቀርበው ሀዲድ በ20 ሜትር ክልል ውስጥ መቆም ክልክል ነው
• ከባቡር ሀዲድ ማቋረጫ በ6ሜትር ክልል ውስጥ ማርሽ መለወጥ ክልክል ነው።
• ቁም የሚል ምልክት ወይም የመንገድ ምልክት ካለበት ስፍራ በ12 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው።
• በግል መንገድ ተሽከርካሪ በሚተላለፍበት የቤት መውጫ ወይም መግቢያ ወይም የመንገዱ ስፋት 12
ሜትር ያነሰ ሆኖ ሲገኝ መቆም ክልክል ነው።
• ከጎርፍ ማስተላለፊያ ፉካ ካለበት በ5 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው።
• በቤንዚን ማደያ አከባቢ ተሽከርካሪዎች ወደ ማደያ ገብተው ለመቅዳት በሚያዳግታቸው ሁኔታ
በ12 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው።
• በመገናኛ መንገድ አከባቢ አቅጣጫን ለመለየት የቀስት ምልክት በተቀባበት መስመር ላየ
በቅድሚያ መስመራቸውን ለይተው ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ያልተቆራረጠውን የመስመር ክልል
የግድ እነንዲያቀዋርጡ በሚያስገድዳቸው ርቀት ውስጥ አቅሞ መሔድ የተከለከለ ነው።
• ከአጥር ክልል ወይም ከግቢ ውስጥ ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንዲወጡበት በተሰራ መንገድ ላይ
መተላለፊያ ዘግቶ መቆም ክልክል ነው።
• ከመንገድ ጠርዝ ከ40 ሴ.ሜ. በላይ መቆም ክልክል ነው።
• በድልድይ ወይም በመለኪያ ላይ መቆም ክልክል ነው።
• በሶስተኝነት ተደርቦ መቅደም ክልክል ነው።
• በቀኝ በኩል መቅደም ክልክል ነው።
• በመንገዱ ቀኝ ዳርቻ መኪናን ለማቆሚያ አመቺ በሚሆን አይነት በመንገድ ባለስልጣን ለአንድ መኪና
ስፈቱም ቁመቱም ይበቃል ተብሎ በተቀባ ክልል ውስጥ አለአግባብ አቁሞ መሄድ ክልክል ነው።
• የመንገዱ ቀኝ ጠርዝ አስጠግትው በአግባቡ በቆሙ ተሽከርካሪዎች ጎን በተደራቢነት መቆም ክልክል
ነው።
• መንገዱ ባለ አንድ አቅጣጫ ካልሆነ በስተቀር በማናቸውም ጎዳና በስተግራ ወገን መቆም ክልክል ነው።
• በእያንዳንዱ አቅጣጫ ለትራፊክ አንድ ነጠላ መንገድ ብቻ ባለበትና መንገዱም በነጭ በተከፋፈለበት
ስፍራ መቆም ክልክል ነው።
አቅጣጫ ስለመለወጥ
ማናቸውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ
• አርቆ ወይም አሻግሮ ማየት ባልቻለ ጊዜ
• ከኮሮብታ ጫፍ፣ቁልቁለት፣ከድልድይ፣ተነድሎ ከተሰራ መሻለኪያ/ታነል/ ወይም ከጎባጣ
መንገድ ሲደርስ
• ከመስቀለኛ መንገድ ወይም ከሀዲድ መንገድ በ30 ሜትር ርቀት ውስጥ
• የማያቋርጥ የቀለም መስመር በተደረገበት መንገድ ለይ ወደ ግራ መጠምዘዝ
አይፈቀድለትም።
ስለአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች የተሰጠ ልዩ ደንብ
ማንኛውም የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ ተግባሩን በሚያከናውንበት ግዜ
• በዚህ ደንብ ወይም በሌላ ደንብ የተጻፈውን ግዴታ ሳይጠብቅ ተሽከርካሪን ለማቆም
• ቁም በሚል ምልክት ላይ ሳይቆሙ ለማለፍ
• ከተወሰነው ፍጥነት በላይ ለመንዳት እና
• ተግባሩን ለመፈጸም በሚያስፈልገው መጠን ስለትራፊክ የወጡ ደንቦችንና የመንገድ ምልክቶችን
ሳይመለከት በፈቀደው አቅጣጫ ለመጠምዘዝ ተፈቅዶለታል።
• ቀድሞ የሚሄድ የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ በሚፈጽመው ተግባር ተካፋይ የሆነ የሌላ የአደጋ
አገልግሎት ተሽከርካሪ ካልሆነ በስተቀር ማናቸው ሰው ከ100 ሜትር ባነሰ ርቀት ከአንድ
የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ ተጠግቶ መንዳትየለበትም።
የማስጠንቀቂያ ድምጽ ስለመጠቀም
• ማናቸውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ የሚገጥመውን አደጋ ለመከላከል ግድ አስፈላጊ
ካልሆነ፣አደጋውን የሚከላከልበት ሌላ መንገድ ከሌለውና የሚያሰማውም የማስጠንቀቂያ
ድምጽ በተቻለ መጠን አጭር ካልሆነ በስተቀር፣ በከተማ መንገድ ውስጥ የማስጠንቀቂያ ድምጽ
ማሰማት አይፈቀድለትም። ተሽከርካሪ በቆመበት ግዜ በማናቸውም አኳኃን የማስጠንቀቂያ
ድምጽ ማሰማት ክልክል ነው።
• ሆስፒታልና ትምህርት ቤት አከባቢ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ማሰማት ክልክል ነው።
ነዳጅ ስለመሙላት
• ማንኛውም ሰው የተሽከርካሪው ሞተር እየሰራ፣ ተሽከርካሪው የህዝብ ማመላለሻ ከሆነ
በተሽከርካሪ ውስጥ መንገዶች እያሉ ማናቸውም ነዳጅ መሙላት ወይም ማስሞላት
የለበትም።
• በተሽከርካሪው አጠገብ እሳት ወይም ሲጋራ የሚያጨስ ሰው ሲኖር በሞተር
ተሽከርካሪው ነዳጅ እንድሞላ ወይም የነዳጅ መክደኛ እንዲከፈት ወይም ሌላ ስው
ይህንን እንዲያደርግ መፍቀድ ክልክል ነው።
• ማናቸውም ሰው ተሽከርካሪውን ነዳጅ ሲሞላ በሞባይል ስልክ ማነጋገር ወይም ሌሎች
ኤሌክትሮኒክስ ነክ መሳሪያዎችን መጠቀም የለበትም።
የተበላሸ ተሽከርካሪ መንገድ ላይ ስለመጠገን
1.ማንኛውም ሰው በመንገድ ላይ ተሽከርካሪን ለመጠገን ወይም ለማደስ አይፈቀድለትም፣ከዚህም
ሌላ ተሽከርካሪው በማናቸውም አከኃን ያለ ማቀረጥ፣
• በከተማ ውስጥ ሲሆን ከ6 ሰአት በላይ
• ከከተማ ውጪ ሲሆን ከ48 ሰአት በላይ በአንድ ቦታላይ መቆቆት የለበት
2. ማንኛውም ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ቢበላሽ አሽከርካሪው ከተሽከርካሪው ፊትና ኃላ ባለው
መንገድ በ50 ሜትር ርቀት ላይ ለሌላ ትርፊክ በግልጽ በሚታይ መልኩ ባለ 3/ሶስት ማእዘን
አንጸባራቂ ሰሌዳ ማስቀመጥ አለበት
3. ማንኛውም ሰው የተጎዳ ወይም የተበላሸ ተሽከርካሪ መኪና ከመንገድ ላይበሚያነሳበት ግዜ
በመንገድ ላይ የወዳደቁን የመስታወትና ሌሎች ተላላፊ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ሁሉ
ከመንገድ ማስወገድ አለበት።
ረጅም የግንባር መብራት መጠቀም የሚከለከልባቸው ሁኔታዎች
• የመንገድ መብራት በቂ ካልሆነ በስተቀር በከተማ መንገድ ስታሽከረክር
• በተቃራኒ መንገድ የሚመጣ ተሽከርካሪ ሲቃረብና እስኪያልፍ ድረስ
• በ50 ሜትር ርቀት የምትከተለው ተሽከርካሪ ሲኖር
• ተሽከርካሪ በቆመበት ወቅት
• የማናቸውም ባለሞተር ተሽከርካሪ አሽከርካሪ በማብሪያ ግዜ ተሽከርካሪውን ሲያቆም
የማቆሚያ መብራት ማብራት አለበት።
የንግድ ሸቀጥ አጫጫን
• ጭነት ከተሽከርካሪው በስተፊት ባለው ጫፍ ከአንድ/1 ሜትር በስተኃላ ከተሽከርካሪው
ከሁለት/2 ሜትር በላይ ተርፎ መውጣት የለበትም።
• መብራት በሚበራበት ግዜ ከፊት ተርፎ በሚገኘው ጭነት ጫፍ ነጭ/ቢጫ ከኃላ ተርፎ
በሚገኘው ጭነት ላይ ቀይ መብራት መደረግ አለበት።
• መብራት በማያስፈልግበት ግዜ በተራፊው ጭነት ላይ በፊትና በኃላ ጫፍ 30 ሳ.ሜ. ካሬ
የሆነ ቀይ ጨርቅ ወይም ቀይ ቀለም የተቀባ ጠፍጣፋ ሰሌዳ መደረግ አለበት።
ተሽከርካሪ ስለመጎተት
• አንድ አሽከረካሪ በሌላ የሞተር ተሽከርካሪ በሚጎተትበት ጊዜ በመሀከላቸው
ያለው ርቀት ከ3 ሜትር የማይበልጠ ሆኖ ሁለቱ ተሽከርካሪዎች በሽቦ
ገመድ ወይም በጠንካራ የመሳቢያ የብረት ዘንግ በጥብቅ መያያዝ
አለባቸው።
• ማንኛውም የሞተር ተሽከርካሪ በአንድ ግዜ ከአንድ ተሽከርካሪ በላይ
እንዲጎትት አየፈቀድለትም።
1.በአገራችን የመንገድ ስነ-ስርዓት ህግ መሰረት ተሽከርካሪን መቅደም የሚቻለው በኩል ብቻ ነው፡፡
ሀ. በቀኝ ለ. በግራ ሐ. በመሀል መ. መልሱ አልተሰጠም
2.የተበላሸውን ተሽከርካሪ በከተማ ክልል ውስጥ እስከ ሶሰት ቀን ድረስ ማቆም ይፈቀዳል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
3.አንድ ተሽርካሪ ከመንገድ ጠርዝ በ ባልበለጠ ርቀት መቆም አለበት
ሀ. 30 ሳ.ሜ ለ. 40 ሳ.ሜ ሐ. 50 ሳ.ሜ መ. ሁሉም
4.ማንኛውም አሽከርካሪ ከመስቀለኛ ወይም ከሃዲድ መንገድ ማቁረጫ በ3ዐ ሜትር ርቀት ውስጥ ረድፍ
መቀየር አይቻልም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
5.አንድ የተበላሸ ተሽከርካሪ በሌላ ተሽከርካሪ በሚጐተትበት ጊዜ በመካከላቸው የለው ርቀት ከ
ሜትር በላይ መብለጥ የለበትም፡፡
ሀ. 3 ሜትር ለ. 5 ሜትር ሐ. 2 ሜትር መ. 4 ሜትር
6. ማንኛውም አሽከርካሪ አሻግሮ ወይም አርቆ ለማየት ካልቻለ ወደ ግራ መጠምዘዝ አይችልም፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
7.አንድ ተሽከርካሪ በከተማ ውስጥ ከ በላይ ሰዓት ተበላሽቶ መንገድ ላይ እንዲቆም አይፈቀድለትም፡፡
ሀ. ከ5 ሰዓት ለ. ከ6 ሰዓት ሐ. ከ1ዐ ሰዓት መ. ከ4 ሰዓት
8. ተሽከርካሪዎች የተጫነው ጭነት ከተሽከርካሪው አካል ተርፎ በወጣ ጭነት ላይ በጨለማ ሲጓዝ
ማድረግ ያለበት ምልክት?
ሀ. ከፊት ነጭ /ቢጫ/ ከኋላ ቀይ መብራት ሐ. ከፊት ቢጫ ከኋላ ሰማያዊ መብራት
ለ. ከፊት ቀይ ከኋላ ነጭ /ቢጫ/ መብራት መ. ከፊት ሰማያዊ ከኋላ ቢጫ መብራት
9.አንድን ተሽከርካሪ በዝግታ ለማሽከርክር ምክንያት ሊሆን የሚችለው፡፡
ሀ. በጠባብ ድልድይ ለ. በጠመዝማዛ መንገድ ሐ. የአሽከርካሪው የማየት ኋልይ በቀነሰበት ወቅት
መ. በመስቀለኛ መንገድና እግረኛ ማቋረጫ
10.ማንኛውም አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን በአጭር ወይም ለረዥም ጊዜ ለማቆም ከፈለገ በምን ያህል
ርቀት ከመንገድ ጠርዝ ትይዩ መሆን አለበት፡፡
ሀ. በ6ዐ ሜትር ርቀት ለ. በ4ዐ ሳ.ሜ ርቀት ሐ. በ3ዐ ሳ.ሜትር ርቀት መ. በ5ዐ ሳ.ሜትር ርቀት
11. ማንኛውም አሽከርካሪ ከባቡር ማቋረጫ ሲደርስ ግራና ቀኝ በመመልከት አደጋ የማያስከትል
መሆኑን ለማረጋገጥ በምን ያህል ርቀት ማርሽ መቀያየር የለበትም
ሀ. ከ1ዐ ሜትር በማያንስ ለ. ከ6 ሜትር በማያንስ ሐ. ከ2ዐ ሜትር በማያንስ መ. ከ15 ሜትር በማያንስ
12. ማንኛውም አሽከርካሪ ተሽከርካሪው መንገድ ላይ ቢበላሽ ባለሶስት ማዕዘን አንጸባራቂ
የማስጠንቀቂያ ምልክት ከፊትና ከኋላ ባለው መንገድ በምን ያህል ርቀት ማስቀመጥ አለበት?
ሀ. በ5ዐ ሜትር ለ. በ3ዐ ሜትር ሐ. በ6ዐ ሜትር መ. በ15 ሜትር
13.ከሁለት አቅጣጫ ለማየት በማይቻልበት ሥፍራ ተሽከርካሪን ማቆም የማይፈቀደው በ ሜትር
ርቀት ነው ሀ. በ4ዐ ሜትር ርቀት ለ. በ15 ሜትር ርቀት ሐ. በ5ዐ ሜትር ርቀት መ. በ6 ሜትር ርቀት
14.ማንኛውም አሽከርካሪ ለአጭር ወይም ለረዥም ጊዜ ተሽከርካሪን ከሌላ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አንፃር
ማቆም የሚከለከለው የመንገድ ስፋት ከስንት በታች መሆኑን አለበት
ሀ. ከ15 ሜትር ለ. ከ12 ሜትር ሐ. በ2ዐ ሜትር መ. ከ3ዐ ሜትር
15.ከሚከተሉት ውስጥ ወደ ግራ ኋላ ዞሮ መመለስ የማይፈቀደው ለየትኛው ምክንያት ነው
ሀ. አርቆ ወይም አሻግሮ ለማየት በማይችልበት ጊዜ ለ. ከድልድይና በማሿለኪያ ላይ
ሐ. በመስቀለኛ ወይም ሀዲድ መንገድ ማቋረጫ መ. ሁሉም መልስ ነው
16.በዳገት ወይም በቁልቁለት ላይ ተሽከርካሪዎች ሲገናኙ ቁልቁለት የሚወርደው ተሽከርካሪ
ሀ. ቅድሚያ ያገኛል ለ. ዳገት ለሚሄደው ቅድሚያ ይሰጣል
ሐ. ሀ እና ለ መልስ ነው መ. መልስ አልተሰጠም
17. ከተለያዩ አቅጣጫ ወደ መስቀለኛ መንገድ እኩል የደረሱ ተሽከርካሪዎች ቅድማያ መስጠት ያለበት
ሀ. በቀኝ በኩል ላሉ ተሽከርካሪዎች ለ. በግራ በኩል ላሉ ተሽከርካሪዎች
ሐ. ለመስቀለኛ መንገድ ቅርብ የሆኑ ተሽከርካሪዎች መ. በመሀል ላይ ላሉ ተሽከርካሪዎች
18. የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ተግባራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ
ሀ. ተሽከርካሪውን በተከለከለበት ቦታ ማቆም ይችላሉ ለ. በፈለጉት አቅጣጫ መጠምዘዝ ይችላሉ
ሐ. በተከለከለ አቅጣጫ መጓዝ ይችላሉ መ. ሁሉም መልስ ነው፡፡
19.ማንኛውም አሽከርካሪ ከባቡር ሀዲድ ማቋረጫ በ6 ሜትር ውስጥ የተሽከርካሪውን ማርሽ መለወጥ
የለበትም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
20.አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን በቁልቁለት መንገድ ላይ ባቆመ ጊዜ የተሽከርካሪውን የፊት እግሮች
ከመንገዱ በጣም ወደሚቀርበው ጠርዝ ማስጠጋት አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ውሸት
21. የተበላሸን ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ጥገና የሚያደርግ ሰው ተሽከርካሪው ባለበት ዙሪያ መስመር
ሰውነቱን ወደ መንገድ አውጥቶ መጠገን የለበትም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
22. ማንኛውም አሽከርካሪ በሃዲድ ማቋረጫ ሲደርስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለማቆም እንዲችል
ተሽከርካሪውን በዝግታ ለመንዳትና ለማቋረጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ይፈጽማል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ውሸት
23. አሽከርካሪዎች ከባቡር ሀዲድ ማቋረጫ አካባቢ ተሽከርካሪውን ከሀዲዱ በ2ዐሜትር ርቀት ማቆም
ይችላሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
24.ከከተማ ክልል ውጪ በማንኛውም መንገድ ላይ ተሽከርካሪን ለረጅም ጊዜ ማቆም ይቻላል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ውሸት
25. የመንገዱ ስፋት ከ12 ሜትር በላይ ካልሆነ በስተቀር ተሽከርካሪውን ከሌላ ተሽከርካሪ በተቃራኒ
ለጊዜው ማቆም አይቻልም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
26. በሁለት አቅጣጫ ከ5ዐ ሜትር ርቀት ላይ ለማየት በማይቻልበት ስፍራ ተሽከርካሪን ማቆም
የለበትም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
27.መስቀለኛ መንገድን አቋርጦ ወደ ግራ የሚታጠፍ አሽከርካሪ ከ15 ሜትር ርቀት በፊት ራሱን
ማዘጋጀት አለበት፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
28.ከአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ኋላ ማንኛውም ተሽከርካሪ ተጠግቶ መንዳት የማይፈቀድለት
ርቀት፡፡ሀ. በ5ዐ ሜትር ባነሰ ለ ለ4ዐ ሜትር ባነሰ ሐ. በ1ዐዐ ሜትር ባነሰ መ. በ8ዐ ሜትር ባነሰ
29. ማንኛውም አሽከርካሪ አሻግሮ ወይም በርቀት ማየት ካልቻለ ወደ ግራ መጠምዘዝ ይችላል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ውሸት
30. ማንኛውም አሽከርካሪ ከመስቀለኛ ወይም ከሃዲድ መንገድ ማቋረጫ በ3ዐ ሜትር ርቀት ውስጥ
ረድፍ መቀየር ይችላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
31.3ዐ ሜትር ርቀት ውስጥ አሽከርካሪዎች ወደ ግራ እንዳይጠመዘዙ የተከለከሉበት ሥፍራ
ሀ. በመስቀለኛ ወይም በሃዲድ መንገድ ማቋረጥ ለ. በኮረብታማ በመሿለኪያ ስፍራ
ሐ. በትምህርት ቤትና በሆስፒታል መ. በቤተክርስቲያንና በህጻናት መዋያ
32.ማንኛውም አሽከርካሪ ወደ ግራ ለመጠምዘዝ /ዞሮ ለመመለስ/ የማይፈቀድለት በየትኛው መንገድ
ላይ ነው፡፡
ሀ. በቁልቁለት ቦታ ለ. በድልድይ ላይ ሐ. በመሿለኪያ ቦታ መ. ሁሉም መልስ ነው
33.ማናቸውም አሽከርካሪ የመንገዱ ስፋት 12 ሜትር በላይ ካልሆነ በቀር ከአውቶቢስ መቆሚያ ትይዩ
ተሽከርካሪውን ለጊዜው ወይም ለረጅም ጊዜ ማቆም የለበትም ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
34.ማናቸውም አሽከርካሪ የመንገዱ ስፋት ከ22 ሜትር በላይ ካልሆነ በቀር ከአውቶቡስ መቆሚያ
ትይዩ ተሽከርካሪውን ለጊዜው ወይም ለረጅም ጊዜ ማቆም የለበትም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
35. ማናቸውም ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ቢበላሽ አሽከርካሪው ከተሽከርካሪው ፊትና ኋላ ባለው
መንገድ 3ዐ ሜትር ርቀት ላይ ለሌላ ትራፊክ በግልጽ በሚታይ መልኩ ቀይ ሠሌዳ ማስቀመጥ አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
36. የህዝብ ማመላለሻ የሆነ ተሽከርካሪ መንገደኞችን እንደጫነ ነዳጅ መሙላት ወይም ማስሞላት
ይችላል። ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
የጥፋት ዝርዝርና የገንዘብ ቅጣት
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf
የማሽከርከር ህግ.pdf

More Related Content

What's hot

【RUNMAX_3 Minutes To Know 『What's Defensive Driving』】
【RUNMAX_3 Minutes To Know 『What's Defensive Driving』】【RUNMAX_3 Minutes To Know 『What's Defensive Driving』】
【RUNMAX_3 Minutes To Know 『What's Defensive Driving』】RUNMAX
 
Aula direção defensiva
Aula  direção defensivaAula  direção defensiva
Aula direção defensivaJonatas Soares
 
How safe you are on road, by B C Das
How safe you are on road, by B C DasHow safe you are on road, by B C Das
How safe you are on road, by B C DasBimal Chandra Das
 
Educação no tânsito
Educação no tânsitoEducação no tânsito
Educação no tânsitoliline123
 
Inst. filipe direção defensiva
Inst. filipe direção defensivaInst. filipe direção defensiva
Inst. filipe direção defensivaFilipe Silva
 
Direção defensiva novo buzzero 2
Direção defensiva  novo buzzero  2Direção defensiva  novo buzzero  2
Direção defensiva novo buzzero 2Instrutor Portella
 
Direção Defensiva
Direção DefensivaDireção Defensiva
Direção DefensivaLM Frotas
 
Prevencao aos acidentes de transito
Prevencao aos acidentes de transitoPrevencao aos acidentes de transito
Prevencao aos acidentes de transitoRosimeire Cecato
 
Cuidados ao dirigir na chuva
Cuidados ao dirigir na chuvaCuidados ao dirigir na chuva
Cuidados ao dirigir na chuvaLM Frotas
 
Cartilha de Direção Defensiva - Instituto Nordeste Cidadania
Cartilha de Direção Defensiva - Instituto Nordeste CidadaniaCartilha de Direção Defensiva - Instituto Nordeste Cidadania
Cartilha de Direção Defensiva - Instituto Nordeste CidadaniaMarcus Vinicius Sampaio
 
Tips for Defensive Driving | Champion Truck Lines
Tips for Defensive Driving | Champion Truck LinesTips for Defensive Driving | Champion Truck Lines
Tips for Defensive Driving | Champion Truck LinesChampion Truck Lines
 
Direção Defensiva.pptx
Direção Defensiva.pptxDireção Defensiva.pptx
Direção Defensiva.pptxMarcela75599
 
APRESENTACAO%20DIRECAO%20DEFENSIVA[1].ppt
APRESENTACAO%20DIRECAO%20DEFENSIVA[1].pptAPRESENTACAO%20DIRECAO%20DEFENSIVA[1].ppt
APRESENTACAO%20DIRECAO%20DEFENSIVA[1].pptDamianemendes
 

What's hot (20)

Direção defensiva rosa
Direção defensiva rosaDireção defensiva rosa
Direção defensiva rosa
 
【RUNMAX_3 Minutes To Know 『What's Defensive Driving』】
【RUNMAX_3 Minutes To Know 『What's Defensive Driving』】【RUNMAX_3 Minutes To Know 『What's Defensive Driving』】
【RUNMAX_3 Minutes To Know 『What's Defensive Driving』】
 
Aula direção defensiva
Aula  direção defensivaAula  direção defensiva
Aula direção defensiva
 
How safe you are on road, by B C Das
How safe you are on road, by B C DasHow safe you are on road, by B C Das
How safe you are on road, by B C Das
 
Educação no tânsito
Educação no tânsitoEducação no tânsito
Educação no tânsito
 
Inst. filipe direção defensiva
Inst. filipe direção defensivaInst. filipe direção defensiva
Inst. filipe direção defensiva
 
Airport layout
Airport layoutAirport layout
Airport layout
 
Direção defensiva novo buzzero 2
Direção defensiva  novo buzzero  2Direção defensiva  novo buzzero  2
Direção defensiva novo buzzero 2
 
Direção Defensiva
Direção DefensivaDireção Defensiva
Direção Defensiva
 
Prevencao aos acidentes de transito
Prevencao aos acidentes de transitoPrevencao aos acidentes de transito
Prevencao aos acidentes de transito
 
Curso de Direção Defensiva - 2016
Curso de Direção Defensiva - 2016Curso de Direção Defensiva - 2016
Curso de Direção Defensiva - 2016
 
Direção defensiva
Direção defensivaDireção defensiva
Direção defensiva
 
Direção defensiva - Alessandro Leal
Direção defensiva - Alessandro LealDireção defensiva - Alessandro Leal
Direção defensiva - Alessandro Leal
 
Cuidados ao dirigir na chuva
Cuidados ao dirigir na chuvaCuidados ao dirigir na chuva
Cuidados ao dirigir na chuva
 
Defensive driving
Defensive drivingDefensive driving
Defensive driving
 
Apresentação transito
Apresentação transitoApresentação transito
Apresentação transito
 
Cartilha de Direção Defensiva - Instituto Nordeste Cidadania
Cartilha de Direção Defensiva - Instituto Nordeste CidadaniaCartilha de Direção Defensiva - Instituto Nordeste Cidadania
Cartilha de Direção Defensiva - Instituto Nordeste Cidadania
 
Tips for Defensive Driving | Champion Truck Lines
Tips for Defensive Driving | Champion Truck LinesTips for Defensive Driving | Champion Truck Lines
Tips for Defensive Driving | Champion Truck Lines
 
Direção Defensiva.pptx
Direção Defensiva.pptxDireção Defensiva.pptx
Direção Defensiva.pptx
 
APRESENTACAO%20DIRECAO%20DEFENSIVA[1].ppt
APRESENTACAO%20DIRECAO%20DEFENSIVA[1].pptAPRESENTACAO%20DIRECAO%20DEFENSIVA[1].ppt
APRESENTACAO%20DIRECAO%20DEFENSIVA[1].ppt
 

More from Abebaw31

Project management course for MSc STUDENTS CHAPTER 1
Project management course for MSc STUDENTS CHAPTER 1Project management course for MSc STUDENTS CHAPTER 1
Project management course for MSc STUDENTS CHAPTER 1Abebaw31
 
Project management course for MSC students Chapter 4 and 5
Project management course for MSC students Chapter 4 and 5Project management course for MSC students Chapter 4 and 5
Project management course for MSC students Chapter 4 and 5Abebaw31
 
Risk management Chapter 2 for project monument course for MSC students
Risk management Chapter 2 for project monument course for MSC studentsRisk management Chapter 2 for project monument course for MSC students
Risk management Chapter 2 for project monument course for MSC studentsAbebaw31
 
Yom Institute Presentations lecture notes of project management
Yom Institute Presentations lecture notes of project managementYom Institute Presentations lecture notes of project management
Yom Institute Presentations lecture notes of project managementAbebaw31
 
Yom Institute Presentation project management course
Yom Institute Presentation project management courseYom Institute Presentation project management course
Yom Institute Presentation project management courseAbebaw31
 
Project management course lecture Notes from Yom college
Project management course lecture Notes from Yom collegeProject management course lecture Notes from Yom college
Project management course lecture Notes from Yom collegeAbebaw31
 
Chapter-3.pdf
Chapter-3.pdfChapter-3.pdf
Chapter-3.pdfAbebaw31
 
Chapter-4.pdf
Chapter-4.pdfChapter-4.pdf
Chapter-4.pdfAbebaw31
 
Matching_Methods.ppt
Matching_Methods.pptMatching_Methods.ppt
Matching_Methods.pptAbebaw31
 
Essental of Project Management Lecture Slide.pdf
Essental of Project Management Lecture Slide.pdfEssental of Project Management Lecture Slide.pdf
Essental of Project Management Lecture Slide.pdfAbebaw31
 
2. PMBOK 5TH EDITION.pdf
2. PMBOK 5TH EDITION.pdf2. PMBOK 5TH EDITION.pdf
2. PMBOK 5TH EDITION.pdfAbebaw31
 

More from Abebaw31 (11)

Project management course for MSc STUDENTS CHAPTER 1
Project management course for MSc STUDENTS CHAPTER 1Project management course for MSc STUDENTS CHAPTER 1
Project management course for MSc STUDENTS CHAPTER 1
 
Project management course for MSC students Chapter 4 and 5
Project management course for MSC students Chapter 4 and 5Project management course for MSC students Chapter 4 and 5
Project management course for MSC students Chapter 4 and 5
 
Risk management Chapter 2 for project monument course for MSC students
Risk management Chapter 2 for project monument course for MSC studentsRisk management Chapter 2 for project monument course for MSC students
Risk management Chapter 2 for project monument course for MSC students
 
Yom Institute Presentations lecture notes of project management
Yom Institute Presentations lecture notes of project managementYom Institute Presentations lecture notes of project management
Yom Institute Presentations lecture notes of project management
 
Yom Institute Presentation project management course
Yom Institute Presentation project management courseYom Institute Presentation project management course
Yom Institute Presentation project management course
 
Project management course lecture Notes from Yom college
Project management course lecture Notes from Yom collegeProject management course lecture Notes from Yom college
Project management course lecture Notes from Yom college
 
Chapter-3.pdf
Chapter-3.pdfChapter-3.pdf
Chapter-3.pdf
 
Chapter-4.pdf
Chapter-4.pdfChapter-4.pdf
Chapter-4.pdf
 
Matching_Methods.ppt
Matching_Methods.pptMatching_Methods.ppt
Matching_Methods.ppt
 
Essental of Project Management Lecture Slide.pdf
Essental of Project Management Lecture Slide.pdfEssental of Project Management Lecture Slide.pdf
Essental of Project Management Lecture Slide.pdf
 
2. PMBOK 5TH EDITION.pdf
2. PMBOK 5TH EDITION.pdf2. PMBOK 5TH EDITION.pdf
2. PMBOK 5TH EDITION.pdf
 

የማሽከርከር ህግ.pdf

  • 2. 1.አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች በሚሰጡት ትርጉም ወይም በሚያስተላልፉት መልዕክት/ትዕዛዝ/ ልዩነት የተነሳ በሶስት ክፍሎች ይከፈላሉ። 1.የሚያስጠነቅቁ 2.የሚቆጣጠሩ 3.መረጃ የሚሰጡ
  • 3. 1.የሚያስጠነቅቁ • ቅርጻቸው - አብዛኞቹ ሶስት ማዕዘን ናቸው • መደባቸው - ነጭ • መልዕክቱ - በጥቁር ሆኖ በስዕል፣በምልክት፣በቁጥር...ይተላለፈል
  • 4. 1 በመንገዱ ላይ ጠባብ ድልድል ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ እለፍ:: 2 መንገዱን የሚጠግኑ ሠራተኞች ስላሉ ፍጥነትህን በመቀነስተጠንቅቀህ እለፍ:: 3 ባለ 4 አቅጣጫ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ቆመህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡ 4 ፊት ለፊት ወደ ግራ የሚያስኬድ መገናኛ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡ 5 ፊት ለፊትና ወደ ቀኝ የሚያስኬድ መገናመንገድ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡
  • 5. 6 መገናኛ መንገዱ ወደ ግራና ወደ ቀኝ የሚታጠፍ እንጂ ፊት ለፊት የማያስኬድ ስለሆነ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 7 የተበላሸ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡ 8 የምታሽከረክርበት መንገድ ወደ ግራ ስለሚታጠፍ የቀኝ ረድፍህን ይዘህ በጥንቃቄ እለፍ፡፡ 9 የምታሽከረክርበት መንገድ ወደቀኝ ስለሚታጠፍ የቀኝ ረድፍህን ጠብቀህ በጥንቃቄ እለፍ፡፡ 10 መጀመሪያ ወደ ግራ ቀጥሎ ወደ ቀኝ የሚታጠፍ ጠመዝማዛ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ እለፍ::
  • 6. 11 መጀመሪያ ወደ ቀኝ ቀጥሎ ወደ ግራ የሚታጠፍ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡ 12 ወደ ግራ እየጠበበ የሚሄድ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ እለፍ 13 ወደ ቀኝ እየጠበበ የሚሄድ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ እለፍ 14 መዝጊያ ያለው የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 15 መዝጊያ የሌለው የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለሚያጋጥምህ ቆመህ ባቡር አለመኖሩን አረጋግጠህ በጥንቃቄ እለፍ፡፡
  • 7. 16 አደገኛ ቁልቁለት ስለሚያጋጥምህ ከባድ ማርሽ በማስገባት ተጠንቅቀህ እለፍ:: 17 በአጭር እርቀት ውስጥ የተደጋገመ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ መኖሩን የሚያስጠነቅቅ ምልክት ነው፡፡ ሀ. ባለሦስት ሠረዙ በ25ዐ ሜትር ለ. ባለሁለት ሠረዙ 170 ሜትር ሐ. ባለአንድ ሠረዙ በ1ዐዐ ሜትር ርቀት ላይ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡ 18 በመንገድ ላይ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 19 የሁለት ባቡሮች ሐዲድ መንገዱን የሚያቋርጥ ስለሆነ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 20 በመንገድ ላይ ብዙ ሰዎች የሚተላለፉበት አካባቢ ስለሆነ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
  • 8. 21 ተማሪዎች የሚበዙበት አካባቢ ስለሆነ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 22 በአንድ አቅጣጫ ብቻ ለማሽከርከር በተፈቀደበት አካባቢ ላይ ለጊዜው በሁለቱም አቅጣጫ በኩል ተሽከርካሪዎች እንዲተላለፉበት ስለተፈቀደ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 23 በመንገዱ ላይ አስጊ ወይም አደገኛ ሁኔታ ስለአለ በጥንቃቄ አሽከርክር፡፡ 24 ወደ ፊት የትራፊክ መብራት አለ፡፡ 25 ወደ ግራ የሚታጠፍ አደገኛ ኩርባ /ምልክቱ ሲዞር ወደ ቀኝ የሚታጠፍ አደገኛ ኩርባ/፡፡
  • 9. 26 በመንገድ አግድም የሚነፍስ ሀይለኛ ንፋስ አለ፡፡ 27 ወደ ፊት ክብ አደባባይ አለ፡፡ 28 ሁለት ነጠላ መንገድ ወደ አንድ ነጠላ መንገድ ይለወጣል፡፡ 29 መንገዱ በስተቀኝና በግራበኩል ይጠባል። 30 በመንገድ ላይ የሚፈናጠር ድንጋይ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
  • 10. 31 ወደ ፊት የትራፊክ መጨናነቅ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 32 ወደ ፊት የቤት እንሰሳት ስለአሉ /መንገዱን ስለሚያቋርጡ/ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 33 የአካል ጉዳተኞች ስለአሉ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 34 ወደ ፊት የእርሻ መሣሪያዎች ስለአሉ/መንገዱን ስለሚያቋርጡ/ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 35 አደገኛ ጠመዝማዛ መንገድ ስለሚያጋጥም ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
  • 11. 36 ወደ ፊት የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ ስለአለ /የእሳት አደጋ መከላከያ ተሸከርካሪ ስለሚያቋርጥ/ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 37 ወደ ፊት የጭነት ተሸከርካሪዎች ስለአሉ/መንገዱን ስለሚያቋርጡ/ ፍጥነትህንበመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 38 ወደ ፊት የህጻናት መጫዎቻ ቦታ ስለአለ ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡ 39 መንገድ ለሁለት መከፈል የሚጀምርበት ስለሆነ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 40 ለሁለት ተከፍሎ የነበረው መንገድ ማብቂያ ስለሆነ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
  • 12. 41 ቁም የሚል ምልክት ወደ ፊት ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 42 ቅድሚያ ስጥ የሚል ምልክት ወደ ፊት ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 43 በጎን በኩል ማዕዘናዊ ቅርፅ ሰርቶ የሚገኝ መንገድ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 44 Y ቅርፅ ያለው መገናኛ መንገድ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 45 በባንዲራ ትራፊክን የሚያስተናግድ ሰው ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
  • 13. 46 መንገድ ቀያሽ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ፣ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 47 በቀኝ በኩል የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 48 በጎን በኩል ከተገናኘ መንገድ ትይዩ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 49 T ቅርፅ ካለው መንገድ ትይዩ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 50 የአስፋልት መንገድ መጨረሻ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
  • 14. 51 ናዳ ያለበት መንገድ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 52 ተ ተንቀሳቃሽ /ተነሺ/ ድልድይ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 53 ወደ ወንዝ ዳርቻ የሚወስድ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 54 የመንገዱ ዳር አደገኛ ስለሆነ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 55 ዝቅ ብለው የሚበሩ አውሮፕላኖች ስላሉ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
  • 15. 56 ከፊት ለፊት መሷለኪያ ስላለ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 57 ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 58 ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 59 ከፊት ለፊትህ የዱር አራዊት መንገዱን የሚያቋርጡ ስላሉ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡ 60 የሚያንሸራትት መንገድ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
  • 16. 2.የሚቆጣጠሩ የሚቆጣጠሩ አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች በሶስት ንዑሳን ክፍሎች ይከፈላል ሀ. የሚከለክሉ ለ. የሚያስገድዱ/ወሳኝ ሐ. ቅድሚያ የሚሰጡ
  • 17. ሀ. የሚከለክሉ • ቅርጻቸው - ክብ • መደባቸው - ነጭ • መልዕክቱ - በጥቁር ሆኖ በስእል፣በምልክት፣በቁጥር...ይተላለፈል
  • 18. 1 ማናቸውም ዓይነት ተሽከርካሪና በእጅ የሚገፉትም ጭምር እንዳያልፉበት የተዘጋ መንገድ፡፡ 2 ምልክቱ ባለበት አቅጣጫ እያሽከረከሩ ማለፍ ክልክል ነው፡፡ 3 ቀስቱ በሚያመለክተው አንጻር ወደ ቀኝ መታጠፍ የተከለከለ ነው፡፡ 4 ቀስቱ በሚያመለክተው አንጻር ወደግራ መታጠፍ የተከለከለ ነው፡፡ 5 ከሁለት እግር በላይ ያላቸውን አነስተኛ ተሽከርካሪዎች ምልክቱ ከተተከለበት ሥፍራ ጀምሮ «መጨረሻ» የሚል ሌላ ምልክት እስከሚታለፍበት ድረስ መቅደምየተከለከለ ነው፡፡
  • 19. 6 መቅደም ክልክል ነው የሚል ምልክት መጨረሻ፡፡ 7 ከሁለት እግር በላይ ያላቸው የሞተር ተሽከርካሪዎች በዚህ በኩል እንዳይሄዱ ተከልክለዋል፡፡ 8 ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር የተከለከለበት መንገድ፡፡ 9 በሞተር ኃይል የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ዓይነት ተሽከርካሪ እንዳያልፍ የተከለከለበት መንገድ፡፡ 10 ጠቅላላ ክብደቱ በኪሎ ግራም በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ማለፍ የተከለከለ፡፡
  • 20. 11 ጠቅላላ ክብደቱ በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ማንኛውም ዓይነት ተሽከርካሪ ማለፍ የተከለከለ፡፡ 12 ቀስቱ እንደሚያመለክተው በስተግራ ወደ ኋላ ዞሮ መመለስ ክልክል ነው፡፡ 13 ቀስቱ እንደሚያመለክተው በስተቀኝ ወደ ኋላ ዞሮ መመለስ ክልክል ነው፡፡ 14 ይህ ምልክት ባለበት መንገድ ብስክሌት እያሽከረከሩ ማለፍ ክልክል ነው፡፡ 15 ለማንኛውም እንሰሳና በእንሰሳት ለሚሳቡ ተሽከርካሪዎች ጭምር በዚህ በኩል ማለፍ የተከለከለ ነው 16 በሰው ኃይል የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን በዚህ በኩል ማሳለፍ ክልክል ነው፡፡
  • 21. 17 ይህ ምልክት በአለበት መንገድ ላይ እግረኞች እንዳይሄዱበት ይከለክላል፡፡ 18 የአክስሉ ጭነት በምልክቱ ላይ ከተመለከተው ኪሎ ግራም ክብደት በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ የተከለከለ፡፡ 19 ጠቅላላ ስፋቱ በሜትር በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ የተከለከለ፡፡ 20 ጠቅላላ ከፍታው በሜትር በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ የተከለከለ፡፡ 21 የከተማ ክልል ምልክት በከተማ ውስጥ ለማሽከርከር የተወሰኑትን ሕጎች አክብር፡፡
  • 22. 22 የከተማ ክልልና የፍጥነት ወሰን መጨረሻ፡፡ 23 ማንኛውንም ዓይነት የማስጠንቀቂያና የጡሩንባ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡ 24 ይህ ምልክት ከተተከለበት ስፍራ ጀምሮ፦ ሀ/ መገናኛ ወይም መስቀለኛ መንገድ እስክታልፍ ድረስ ወይም ለ/ በውስጡ «መጨረሻ» የሚል ጽሑፍ ያለበትን የዚህ ዓይነት ምልክት እስክታልፍ ድረስ ተሽከርካሪህን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡ 25 ይህ ምልክት ከተተከለበት ስፍራ ጀምሮ፦ ሀ/ የሚቀጥለውን መገናኛ ወይም መስቀለኛ መንገድ እስክታልፍ ድረስ ወይም ለ/ «መጨረሻ» የሚል ጽሑፍ የተፃፈበት የዚህ ዓይነት ሌላ ምልክት እስክታልፍ ድረስ ተሽከርካሪን በማዘግየት ማቆም የተከለከለ ነው፡፡ ነገር ግን አሽከርካሪው ከመኪናው ነሳይወጣ ሰዎችን ለማሳፈር ዕቃ ለመጫንና ለማውረድ ብቻ ለጥቂት ጊዜ ይቻላል፡፡ 26 ይህ ምልክት ባለበት መንገድ ላይ ከፊት ለፊት ለሚመጣ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ሳይሰጡ ማሽከርከር ክልክል ነው፡፡
  • 23. 27 ቁም! የጉምሩክ መ/ቤት /ፍተሻ ቦታ/ ነው፡፡ይህ ምልክት ባለበት ቦታ ሁሉ ማንኛውም አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን አቁሞ በጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች ሳያስፈትሽ እንዳያልፍ የሚከለክል ነው፡፡ 28 መኪና ለማቆም የሚከለክለው ምልክት ትዕዛዝ መጨረሻ መሆኑን የሚገልጽ ምልክት ነው፡፡ 29 ይህ ምልክት ካለበት ጀምሮ እስከሚቀጥለው መስቀለኛ መንገድ ወይም «መጨረሻ» ከሚል ቃል ጋር ቀጥሎ የሚገኝ የዚህ ዓይነት ምልክት እስከአለበት ድረስ ለአጭርም ሆነ ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ፡፡ 30 በምልክቱ ላይ ከሚታየው በአነሰተኘA ርቀት ተጠግቶ ማሽከርከር ክልክል ነው፡፡
  • 24. 31 አደገኛ ፍንዳታ የሚያስከትል ጭነት ለጫነ ተሸከርካሪ ማለፍ የተከለከለ ነው፡፡ 32 ለጭነት ተሸከርካሪ ማለፍ የተከለከለ፡፡ 33 የተበላሸ ተሸከርካሪ እየጎተቱ መጓዝ የተከለከለበት መንገድ፡፡ 34 ጠቅላላ ርዝመቱ በምልክቱ ላይ ከተጠቀሰው ሜትር በላይ ለሆኑ ተሸከርካሪዎች ማለፍ የተከለከለ፡፡ 35 ለጭነት ትከርካሪዎች ተሸከርካሪዎች ማለፍ የተከለከለ፡፡
  • 25. 36 ሞተር ሳይክ ለሚያሽከረክሩ ማለፍ የተከለከለ፡፡ 37 በሰዓት ከተሰጠው ፍጥነት በላይ ማሽከርከር ክልክል ነው 38 በሰዓት የተሰጠው ፍጥነት መጨረሻ 39 ሲጋራ ማጨስ ክልክል ነው፡፡ 40 በእንስሳ ለሚጎተቱ ተሸከርካሪዎች ማለፍ ክልክል ነው፡፡
  • 26. ለ. የሚያስገድዱ/ወሳኝ • ቅርጻቸው - ክብ • መደባቸው - ሰማያዊ • መልዕክቱ - በነጭ ሆኖ በስእል፣በምልክት፣በቁጥር፣በቀስት...ይተላለፈል
  • 27. 1 ብስክሌቶች ብቻ ለማሽከርከር የተፈቀደ መንገድ፡፡ 2 በመንገዱ ላይ የማሽከርከሪያ አነስተኛ ፍጥነት፡፡ 3 የአነስተኛ ፍጥነት መጨረሻ፡፡ 4 የጭነት ተሸከርካሪዎች እንዲተላለፉበት የተፈቀደ መንገድ፡፡ 5 አደገኛ ፍንዳታ የሚያስከትል ጭነትለጫነ ተሸከርካሪ የተፈቀደበትመንገድ፡፡
  • 28. 6 የደሴቱን ቀኝ በመያዝ አሽከርክር፡፡ 7 የደሴቱን ግራ በመያዝ አሽከርክር፡፡ 8 የቀስት ምልክቱ እንደሚያመለከተው በስተቀኝ በኩል ታጥፈህ ብቻ እለፍ፡፡ 9 የቀስት ምልክቱ እንደሚያመለከተው በስተቀኝ በኩል ብቻ እለፍ፡፡ 10 የቀስት ምልክቱ እንደሚያመለከተው በስተግራ በኩል ባለው መንገድ ላይ ብቻ እለፍ፡፡
  • 29. 11 ቀስቱ በሚያመለክተው አቅጣጫ በኩል ባለው ግራ መንገድ ላይ ብቻ አሽከርክር፡፡ 12 ቀስቱ በሚያመለክተው አቅጣጫ በኩል ባለው ቀኝ መንገድ ላይ ብቻ አሽከርክር፡፡ 13 ይህ ምልክት ባለበት ቦታ ላይ ወደ ትራፊኩ ክብ ወይም ደሴት አስቀድሞ ለገባ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ስጥ፡፡ 14 ምልክቱ በሚታይበት አቅጣጫ ቀስቱ እንደሚያመለክተው ከምልክቱ በስተግራና በስተቀኝ በኩል ብቻ እለፍ፡፡ 15 ይህ ምልክት ባለበት አካባቢ ለተሽከርካሪዎች ማቆሚያ የተዘጋጀ ወይም የተወሰነ ሥፍራ አለ፡፡ መኪናህን ቀስቱ ወደሚያመለክተው በኩል በሚገኘው የማቆሚያ ክልል ውስጥ ብቻ ማቆም ይኖርብሀል፡
  • 30. ሐ. ቅድሚያ የሚሰጡ • የተለያየ ቅርጽ አላቸው • አንድ አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ
  • 31. 1 ቁም! ይህ ምልክት ባለበት ማንኛውም የሚመጣ ተሸከርካሪ መስቀለኛ መንገድ ከመግባቱ በፊት መቆም አለበት፡፡ 2 ቅድሚያ ያለው መንገድ፡፡ 3 ቅድሚያ ያለው መንገድ የሚለው ምልክት ትዕዛዝ መጨረሻ፡፡ 4 ከወደፊት ለሚመጣ ተሸከራካሪ ቅድሚ ስጥ፡፡ 5 በመንገደኛ መንገድ ላይ ለተላላፊ ቅድሚያ በመስጠት ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
  • 32. 6 በተለያየ ረድፍ ውስጥ ተፈጻሚ እንዲሆን የተቀመጠ ከፍተኛ የፍጥነት ወሰን፡፡ 7 በተለያየ ረድፍ ውስጥ ተፈጻሚ እንዲሆን የተቀመጠ አነስተኛ የፍጥነት ወሰን፡፡ 8 ለአንድ ረድፍ ከተቀመጠው አነስተኛ ፍጥነት በላይ ማሽከርከር የሚያስገድድ፡፡
  • 33. 3.መረጃ ሰጪ መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች ቅርጻቸው አራት ማዕዘን ሆኖ በሁለት ይከፈላሉ። 1. መረጃ ሰጪ 2. አቅጣጫ አመልካች
  • 34. 1.መረጃ ሰጪ • አገልግሎት የምናገኝበትን ቦታ መረጃ ይሰጡናል
  • 35. 1 ለተበላሹ ተሽከርካሪዎች የጥገና አገልግሎት መስጫ 2 ቴሌፎን/ስልክ/ 3 የነዳጅ መቅጂያ/ማደያ/ 4 በእግር ጉዞ መጀመሪያ /ቦታ/ 5 ሆቴል ወይም ሞቴል
  • 36. 6 የጎብኝዎች ማረፊያ/መንደር/ 7 8 የወጣቶች መኖሪያ 9 የእግር ጉዞ አካባቢ /ክልል/የወጣቶች መኖሪያ 10 ሰረገላዎች/ ማረፊያ ድንኳኖች ያሉበት አካባቢ
  • 37. 11 መዝናኛ ወይም ቡና ቤት 12 ምግብ ቤት ያለበት አካባቢ 13 የማቆሚያ ቦታ 14 ድንገተኛ ህክምና መስጫ ቦታ
  • 38. 2.አቅጣጫ አመልካች • የመንገዶች ዘላቂ መሆንና አለመሆንን የሚገልጽ የመንገድ ዳር ምልክት ነው
  • 39. 1 ፊት ለፊት የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው 2 ወደ ቀኝ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው 3 ወደ ግራ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው 4 የመንገድ አቅጣጫ አመልካች 5 የመንገድ አቅጣጫ አመልካች
  • 40.
  • 41. 1.የመንገድ ዳር ምልክቶች በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 2. የሚያስጠነቅቁ የመንገድ ዳር ምልክቶች ቅርጻቸው ክብ እና ክፈፋቸው ቀይ ነው፡፡ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 3. አንድ አሽከርካሪ ዞሮ ለመመለስ ከመሞከሩ በፊት ዞሮ መመለስ ክልክል ነው የሚል ምልክት አለ መኖሩን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 4. የመንገድ ዳር ምልክቶች አገር አቀፍ እንጂ አለም አቀፍ አይደሉም ሀ. እውነት ለ. ውሸት 5.ቅርፃቸው 4 ማእዘን የሆነና የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን የሚያመለክቱ ምልክቶች ምን የመንገድ ዳር ምልክቶች ናቸው? ሀ. የሚከለክሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች ለ. ቅድሚያ የሚየሰጡ የመንገድ ዳር ምልክቶች ሐ. የሚያስገድዱ የመንገድ ዳር ምልክቶች መ. መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች 6.በአንድ አቅጣጫ ብቻ ለማሽከርከር ከተፈቀደበት መንገድ ላይ ለጊዜው በሁለቱም አቅጣጫ በኩል እንዲተላለፍ መፈቀዱን መልዕክት የሚያስተላልፍ፡፡ ሀ. የሚያስገድድ የመንገድ ዳር ምልክት ለ. ቅድሚያ ስጥ የሚል የመንገድ ዳር ምልክት ሐ. የሚያስጠነቅቅ የመንገድ ዳር ምልክት መ. መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክት
  • 42. 7.በአብዛኛው ቅርጻቸው ክብ፣ ዙሪያ ክባቸው ቀይና መደባቸው ነጭ የሆኑ የመንገድ ዳር ምልክቶች የሚያስጠነቅቁ ናቸው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 8.ከመንገድ ዳር ምልክቶች ውስጥ የሁለት ባቡሮች ሃዲድ መንገዱን እንደሚያቋርጥ መልዕክት የሚያስተላልፉ፡፡ ሀ. የሚያስገድድ ለ. አቅጣጫ አመልካች ሐ. የሚያስጠነቅቅ መ. ቅድሚያ ስጥ የሚል 9.የሚያስገድዱና የሚከለክሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች መደባቸው በአጠቃላይ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 10. መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች ወሳኝ ምልክቶች በመባል ይጠራሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 11. ከመንገድ ዳር ምልክቶች ውስጥ መጀመሪያ ወደ ቀኝ ቀጥሎ ወደ ግራ የሚታጠፍ ጠመዝማዛ መንገድ እንደሚያጋጥምህ መልዕክት የሚያስተላልፍ ሀ. መረጃ ሰጪ ለ. አቅጣጫ አመልካች ሐ. የሚያስጠነቅቅ መ. የሚከለክል 12.ቅድሚያ ስጥ የሚሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች፡፡ ሀ. በቅርጽ የተለያዩ ናቸው ለ. የሚቆጣጠሩ ምልክቶች ምድብ ይመደባሉ ሐ. ቅድሚያ ሰጥተን እንድናሽከረክር ያስገድዱናል መ. ሁሉም መልስ ናቸው
  • 43. 13.በከተማ ክልል ውስጥ ለፍጥነትና ሌሎች ህጐች ትዕዛዝ የሚያስተላልፈው የመንገድ ዳር ምልክት ከሚከለክሉት ውስጥ ይመደባል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 14.መንገዶችን ዘላቂ መሆንና አለመሆን የሚያስተላልፉ የመንገድ ዳር ምልክቶች …….ውስጥ ይመደባሉ፡፡ ሀ. የሚያስጠነቅቅ ለ. አቅጣጫ አመልካች ሐ. ቅድሚያ የሚያሰጡ መ. የሚቆጣጠሩ 15.መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች፡፡ ሀ. ወሳኝ መልክቶች ናቸው ለ. የሚከለክሉ ምልክቶች ናቸው ሐ. ቅድሚያ የሚሰጡ መልክቶች ናቸው መ. መልስ አልተሰጠም 16.የአገልግሎት ሰጪ ድርጅት ቦታንና አቅጣጫን ለማመልከት የምንጠቀምበት ምልክት…… ይመደባል፡፡ ሀ. የሚያስጠነቅቁ ምልክቶች ውስጥ ሐ. መረጃ ሰጪ ምልክቶች ውስጥ ለ. ቅድሚያ የሚሰጡ ውስጥ መ. የሚያስገድዱ ምልክቶች ውስጥ 17.በአውቶሞቢል ምደብ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማሽከርከር የሚቻለው ተሽከርካሪ የመጫን አቅሙ ነጂውን ጨምሮ ከ…. ሰው ያልበለጠ መሆን ካለበት ነው፡፡ ሀ. 12 ለ. 8 ሐ. 15 መ. 24
  • 44. 18.የመንገድ ዳር ምልክቶች በማንኛውም አካል ሊተከሉ ይችላሉ:: ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 19.መደባቸው ሰማያዊ የሚያስተላልፉት መልዕክት በነጭ ቀስት የተሠራ የመንገድ ዳር ምልክቶች፡፡ ሀ. አቅጣጫ አመልካች ለ. መረጃ ሰጪ ሐ. የሚያስገድድ መ. መልስ አልተሰጠም 20. መረጃ ሠጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች፡፡ ሀ. መንገዶች ወዴት እንደሚዘልቁ ይጠቁሙናል ለ.መቆምና መቅደም የተከለከለበትን ሥፍራ ይጠቁማል ሐ. የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ርቀት ይጠቁማል መ. “ሀ” እና “ሐ” መልስ ናቸው 21.አብዛኛውን ጊዜ በመገናኛ ደሴቶች ላይ አደገኛ የሆኑ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ምልክቶች ይባላሉ፡፡ ሀ. የሚያስገድዱ ለ. ወሳኝ ሐ. የሚከለክሉ መ. "ሀ" እና "ለ" መልስ ናቸው፡፡ 22.በቅርፅ የተለያዩና በመልዕክት ግን ተመሣሣይ የሆኑ መንገድ ዳር ምልክቶች ምን ይባላሉ፡፡ ሀ. የሚቆጣጠሩ ለ. የሚያስገድዱ ሐ. የሚከለክሉ መ. ቅድሚያ የሚሰጡ 23. መንገዶች ዘላቂ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን የሚገልፅ የመንገድ ዳር ምልክት ይባላል፡፡ ሀ. መረጃ ሰጪ ለ. የሚቆጣጠር ሐ. አገልግሎት አመላካች መ. መልሱ የለም 24. ከአለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች ውስጥ 3 ንዑስ ዘርፍ ያለው ይባላል፡፡ ሀ. የሚያስጠነቅቁ ለ. የሚቆጣጠሩ ሐ. መረጃ የሚሰጡ መ. መልሱ አልተሰጠም
  • 45. 25.ከፊት ለፊት ያለውን የመንገድ ሁኔታ አስቀድሞ የሚገልጽ የመንገድ ዳር ምልክት ይባላል፡፡ ሀ. መረጃ ሰጪ ለ. የሚያስጠነቀቅ ሐ. የማቆጣጠር መ. ሁሉም 26.በአሽከርካሪ የተፈጸመ ቀላል ጥፋት ለ1 አመት በሪከርድነት ይያዛል፡፡ ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት 27. በአሽከርካሪ የተፈጸመ ከባድ ጥፋት ለ 5 አመት በሪከርድነት ይያዛል፡፡ ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት 28.የሀገራችን አዲሱ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ በስንት ዋና ዋና ዓይነቶች ይመደባሉ፡፡ ሀ/ በ 5 ለ/ በ 6 ሐ/ በ 12 መ/ በ 7 29.አለም አቀፍ ይዘት የሌለው የትራንስፖርት ህግ የሆነዉ የቱ ነዉ ሀ/ የመንገድ ዳር ምልክቶች ሐ/ የፍጥነት ወሰን ገደብ ለ/ የመንገድ መሀል መስመሮች መ/ የትራፊክ መብራት 30. የሚቆጣጠሩ የመንገድ ዳር ምልክቶች ንዑስ ክፍል የሆነው የቱ ነዉ ሀ/ የሚያሰጠነቅቁ ለ/ የሚከለክሉ ሐ/ አቅጣጫ የሚጠቁሙ መ/ መረጃ ሰጪ
  • 46. 31.በመሰቀለኛና በመገናኛ ቦታዎች ላይ የምናገኛቸው መደባቸው ሰማያዊ የሆነ ምልክቶች የሚያሰተላልፋት መልዕክት በነጭ ቀለም በተሰራ ቀሰት ሰዕል ወይም ፀሑፍ የሆኑ የመንገድ ዳር ምልክቶች ምን ይባላሉ? ሀ. የሚከላከሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች ለ. ቅድሚያ የሚያሰጡ የመንገድ ዳር ምልክቶች ሐ. የሚያሰገድዱ የመንገድ ዳር ምልክቶች መ. መረጃ ሰጭ የመንገድ ዳር ምልክቶች 32. ቅርፃቸው ክብ የሆነ ዙሪያቸውን በቀይ ቀለም የተቀቡ ሆነው መድባቸው ነጭ የሚያሰተላልፉት መልዕክት ደግሞ በጥቁር ቀለም በተሰራ ሰዕል ወይም ቀሰት ወይም ፀሑፍ የሆነ የመንገድ ዳር ምልክቶች ምን ይባሉ? ሀ. የሚከላከሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች ለ. ቅድሚያ የሚሠጡ የመንገድ ዳር ምልክቶች ሐ. የሚያሰገድድ የመንገድ ዳር ምልክቶች መ. መረጃ ሰጭ የመንገድ ዳር ምልክቶች 33. ሰለሚያሰጠነቅቁ የመንገድ ዳር ምልክቶች ሰህተት የሆነው የቱ ነው? ሀ. ቅርፃቸው ሶሰት መአዘን ነው ለ. መደባቸው ነጭ ነው ሐ. የሚያሰተላልፉት መልዕክት በጥቁር ቀለም በምስል፣ በቀሰት፣ በቁጥር ወይም በምልክት በመቅረፅ ነው መ. አንዳንድ ጊዜ ቅርፃቸዋ ክብ እና አራት መአዘን ሆነው እናገኛቸዋለን
  • 47. 34.የአንድ የመንገድ ዳር ምልክት ወደ ጅማ የሚሄድ መሆኑን ካመለከተን ይህ የመንገድ ዳር ምልክት በየትኛው ምድብ ውስጥ ይመደባል ሀ/ ቅድሚያ በሚያሰጡ ለ/ በሚያስጠነቅቁ ሐ/ በመረጃ ሰጪ መ/ የሚያስገድዱ 35. ማናቸውም ዓይነት ተሽከርካሪና በእጅ የሚገፉትም ጭምር እንዳያልፉበት የተዘጋ መንገድ መኖሩን የሚያመለክት የመንገድ ዳር ምልክት የቱ ነዉ ሀ/ የሚያስገድድ ለ/ ቅድሚያ የሚያሰጥ ሐ/ የሚከላከል መ/ የሚያስጠነቅቅ
  • 48. 2.አለም አቀፍ የመንገድ ላይ መስመሮች
  • 49. መንገዶች ላይ የሚሰመሩ መስመሮች አገልግሎታቸው • የት ቦታ መቅደም እንደምንችል ይጠቁማሉ • መታጠፊያና ማዞሪያ ቦታ ይጠቁማል • የትራፊክ መብራት አከባቢ የምንቆምበትን ስፍራ ያመለክታል • የመንገድን መሀልና ጠርዝ ያመለክታል • የእግረኛና ማቋረጫን ያመለክታል • አንድን መንገድ ሁለት አቅጣጫ ይከፈላል • የመንገድ ዳር ምልክቶችን ተክተው ይሰራሉ
  • 50. አለም አቀፍ የመንገድ ላይ መስመሮች በሁለት ይከፈላሉ ሀ. በመንገድ አግድም የሚሰመሩ መስመሮች ለ. በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ መስመሮች
  • 51. ሀ. በመንገድ አግድም የሚሰመሩ መስመሮች • የእግረኛ ማስተላለፊያ መስመር ነው
  • 52. 2. በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ መስመሮች
  • 53. 1.የተቆራረጠ መስመር • የተቆራረጠ መስመር ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድን ሲከፍል • ግልጽና የትራፊክ መጨናነቅ የሌለበት ቦታ ይሰመራል • የተቆራረጠ መስመርን አቋርጦ መቅደም፣ወደ ግራ ዞሮ መመለስና ወደ ግራ መታጠፍ ይቻላል
  • 54. 2.ያልተቆራረጠ/ድፍን መስመር • ያልተቆራረጠ መስመር ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድን ሲከፍል • ግልጽ ያልሆነ ቦታናየትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ቦታ ይሰመራል • ድፍን መስመርን መስመርን አቋርጦ መቅደም፣ወደ ግራ ዞሮ መመለስና ወደ ግራ መታጠፍ አይቻልም
  • 55. 3.የተቆራረጠና ያልተቆራረጠ መስመር • በተቆራረጠ መስመር በኩል ያለው አሽከርካሪ ሁለቱን መስመሮች አልፎ መቅደም፣ወደ ግራ ዞሮ መመለስና ወደ ግራ መታጠፍ ይችላሉ። • ባልተቆራረጠው መስመር በኩል ያለው አሽከርካሪ መስመሮቹን አልፎ መቅደም፣ወደ ግራ ዞሮ መመለስና ወደ ግራ መታጠፍ አይቻልም። •
  • 56. ባለአንድ አቅጣጫ መንገድ በተቆራረጠ ነጭ መስመር በረድፍ ሲከፈል ማንኛውም አሽከርካሪ በራሱ ረድፍ ውስጥ በማሽከርከር ፍጥነት ለመጨመር፣ለመቀነስ ወይም ለመታጠፍ በሚፈልግበት ወቅት የተቆራረጠውን መስመር አልፎ ማሽከርከር ይችላል። መንገዱ ባለ አንድ አቅጣጫ በመሆኑ ዞሮ መመለስ ክልክል ነው።
  • 57. አንድ መንገድ ከመስመር በተሰራ የትራፊክ ደሴት ለሁለት ሲከፈል ማንኛውም አሽከርካሪ የትራፊክ ደሴትን ረግጦ መቅደም፣ወደ ግራ ዞሮ መመለስና ወደ ግራ መታጠፍ አይፈቀድለትም።ዞሮ መመለስና መታጠፍ የፈለገ አሽከርካሪ እንደ መንገዱና እንደ ትራፊኩ ሁኔታ በጥንቃቄ በደሴቱ ማረጫ ለመታጠፍና ለመዞር በተዘጋጀ ስፍራ ላይ ወደ ቀኝ አስፍቶ ዞሮ መመለስና መታጠፍ ይቻላል።በተጨማሪም ቀድሞ በተገለጸው ሁኔታ ደሴቱን ሳይረግጥ በራሱ ነጠላ መንገድ የግራ ረድፍን ይዞ መቅደም ይቻላል።
  • 58.
  • 59. በመንገድ ላይ የሚቀቡ ቅቦች በመንገድ ላይ የሚቀቡ ቅቦች በሶስት ይከፈላሉ።እነሱም፡- 1.የመቆሚያ ስፍራ ቅብ፡- አሽከርካሪዎች በምልክቱ ውስጥ ለማቆሚያ በተዘጋጀው ስፍራ ላይ ብቻ መቆም አለባቸው። 2.የማስተላለፊያ ምልክት ቅብ፡-የቀለም ነጠብጣብ ባላቸው ክልሎች ውስጥ ማሽከርከር ክልክል ነው 3.ቅድሚያ ስጥ የሚል ምልክት ቅብ፡- ምልክቱ/ቅቡ/ቅድሚያ ለተላላፊ በመስጠት በጥንቃቄ ማሽከርከር እንዳለብህ መልእክት ያስተላልፋል።
  • 60.
  • 61.
  • 62.
  • 63. 1. የመንገድ ላይ መስመሮች ጠቀሜታ የሆነው የቱ ነው? ሀ. አንድ አቅጣጫ መንገድን በረድፍ መከፈል ለ. አንድን መንገድ በሁለት ነጠላ መንገድ መክፈል ሐ. ለእግረኛ መተላለፊያ መንገድ ማመልከት መ. ሁሉም መልስ ነው 2. የመንገድ ላይ መሥመሮች ጠቀሜታ የሆነው የቱ ነው? ሀ. የት ቦታ ላይ አቅጣጫ ቀይረን ተሽከርካሪን መቅደም እንደምንችል ማመልከቱ ለ. መታጠፊያና ዞሮ መመለሻ መንገዶችን ማመላከት ሐ. የመንገድ መሀልና ጠርዝን ማመልከት መ. ሁሉም መልስ ነው 3. የተቆራረጠ የመንገድ መሀል መስመር በተሠመረበት መንገድ ላይ አሽከርካሪዎች መስመሩን አቋርጠው አቅጣጫ መቀየርም ሆነ ዞሮ መመለስ አይችሉም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 4.የማያቋርጥ የቀለም መሥመር በተሠመረበት መንገድ ላይ ማንኛውም አሽከርካሪ ወደ ቀኝ መጠምዘዝ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሃሰት 5. በትራፊክ ደሴት ዙሪያ የሚያሽከረክር ማንኛውም አሽከርካሪ የትራፊክ ደሴት ቀኙን ወገን ብቻ ተከትሎ መንዳት አለበት፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
  • 64. 6. አንድ መንገድ በሦስት ነጠላ መንገዶች ተከፋፍሎ ሲገኝ ማንኛውም አሽከርካሪ ሌላ ተሽከርካሪ ለመቅደም ካልሆነ በስተቀር በመካከለኛው ነጠላ መንገድ ውስጥ እንዲነዳ አይፈቀድለትም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት 7.በድፍን መስመር በተሠመረበት መንገድ ላይ ማንኛውም አሽከርካሪ ወደ ቀኝ መጠምዘዝ አይፈቀድላቸውም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት 8.ወደ ደሴቱ የተቃረበ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው፡፡ ሀ. ደሴቱን በመዞር ላይ ላሉ ለ. ወደ ደሴቱ ለተቃረቡ ሐ. ደሴቱን ዞረው ለጨረሱ መ. በስተግራ አቅጣጫ ለሚዞሩ ተሽከርካሪዎች 9. በመንገድ አግድመት የሚሰመሩ መስመሮች የሚባሉት መንገድን በረድፍ የሚከፍሉ መስመሮች ናቸው ሀ. እውነት ለ. ውሸት 10.በመንገድ አግድመት የሚሰመሩ መስመሮች ዞሮ ለመመለስ የምንጠቀምበትን ረድፍ ያመለክታሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 11. ከሚከተሉት ውስጥ በመንገድ ላይ ከሚቀቡ ቅባች የማይመደበው የትኛው ነው? ሀ. የመቆሚያ ሥፍራ ቅብ ለ. የማስተላለፊያ ምልክት ቅብ ሐ. ቅድሚያ ስጥ የሚል ምልክት ቅብ መ. ዝቅተኛ የፍጥነት ወሰን
  • 65. 12. የእግረኛ መተላለፊያ መስመሮች ናቸው፡፡ ሀ. በመንገድ አግድመት የሚሰመሩ መስመሮች ለ. በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ መስመሮች ሐ. በመንገድ ትይዩ የሚሰመሩ መስመሮች መ. ሁሉም መልስ ነው 13.የተቆራረጡ መስመሮች በድፍን መስመር ሲተኩ መንገዱ ግልጽ መሆኑን እየቀነሰ መምጣቱን ይገልጻል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 14.አንድ አስፋልት ከመስመር በተሰራ ደሴት እኩል ለሁለት ሲከፈል በስተግራ በኩል መቅደም የሚቻለው ደሴቱን ሳይረግጡ ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 15.ያልተቆራረጠ መስመር በተሰመረበት መስመር ላይ አሽከርካሪዎች እንደ መንገዱና እንደ ትራፊኩ ሁኔታ ድፍኑን መስመር ሳይረግጡ መቅደም ይችላሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 16.በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ መስመሮች ውስጥ ጠመዝማዛ መንገድ ላይ የሚሰመረው … መስመር ነው፡፡ ሀ. የተቆራረጠ ለ. ያልተቆራረጠ ሐ. ቀይ መስመር መ. ጥቁር መስመር 17.ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገዱ በተቆራረጠ ነጭ መስመር ለሁለት እኩል ሲከፈል መስመሩን አልፎ መቅደም ይቻላል፡፡ : ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
  • 66. 18.የተቆራረጠ መስመር አንድ መንገድን ለሁለት እኩል ሲከፍል:: ሀ. መስመሩን አልፎ ወደ መጡበት ዞሮ መመለስ ይችላል ለ. መንገዱን ግልጽ አለመሆኑን ይጠቁማል ሐ. መስመሩን አልፎ ታጥፎ መሄድ አይቻልም መ. የትራፊክ መጨናነቅ መንገዱ ላይ እንዳለ ይጠቁመናል 20.መንገዱ ግልፅ መሆኑን የሚገልጽ የመንገድ መሃል መስመር ይባላል፡፡ ሀ. ድፍን መስመር ለ. የተቆራረጠ ሐ. ደሴት መ. ሁሉም 21.የመንገድ አካፋይ በድፋን መስመር የሚሰመረባቸው የትራፊክ መጨናነቁ አነስተኛ በሆኑ መንገዶች ላይ ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 22. ድፍን መስመርን አቋርጦ ወደ ኋላ ዞሮ መመለስ ይቻላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 23. ዞሮ መመለስ መቅደምና መታጠፍን የሚከለክል የመንገድ ላይ መስመር ነው ሀ. የተቆራረጠ የመንገድ ላይ መስመር ለ. የመቆሚያ ሥፍራ ቅብ መስመር ሐ. ያልተቆራረጠና የተቆራረጠ የመንገድ አካፋይ መስመር መ. ድፋን የመንገድ ላይ መስመር
  • 67. 24.አሽከርካሪው አልፎ መመለስ፣ መቅደም እና ታጥፎ እንዳይሔድ የሚከለከለው የመንገድ ላይ ቅብ የቱ ነው፡፡ሀ. ድፍን መሥመር ለ. የተቆራረጠ መሥመር ሐ. ድፍን እና የተቆራረጠ መሥመር መ. ሁሉም 25. አንድ መንገድ በተቆራረጠ እና ባልተቆራረጠ ሁለት መስመሮች ጎን ለጎን በተሠመሩ ጊዜ የሚቻለው የትኛው ነው ሀ. በተቆራረጠ መስመረ በኩል ያለው አሽከርካሪ ሁለቱንም መስመሮች አልፎ መቅደምና ታጥፎ መሔድ ይቻላል ለ. ባልተቆራረጠው መስመር በኩል ያለው አሽከርካሪ መስመሮችን አልፎ መቅደም ዞሮ መመለስና መታጠፍ አይፈቀድለትም ሐ. ሀ እና ለ መልስ ናቸው መ. መልሱ የለም 26. ባለ አንድ አቅጣጫ መንገድ በተቆራረጠ ነጭ መስመር በረድፍ ሲከፋፈል ማድረግ የማንችለው ከሚከተሉት ውስጥ የትኛው ነው? ሀ. በራሰ እረድፍ ውስጥ በማሽከርከር ፍጥነት መጨመር ወይም መቀነስ ለ. በራሰ እረድፍ ውስጥ ለመታጠፍ በሚፈልግበት ወቅት የተቆራሪጠውን መስመር አልፎ ማሽከርከር ሐ. ዞሮ ወደ መጡበት መመለስ መ. ሁሉም መልስ ናቸው 27.በአጭር ርቀት ውስጥ እግረኞች መንገድ እንዲያቋርጡ የሚሰመር መስመር በመንገድ አግድመት የሚሰመሩ መስመሮች ብለን እንጠራቸዋለን:: ሀ. እውነት ለ. ውሸት
  • 69. ትራፊክ ማለት  በማንኛውም መንገድ አንድ ወይም ብዙ ሆነው የሚተላለፉ እግረኞች ወይም ሰው ተቀምጦባቸው ወይም እየተነዱ ወይም እየተጠበቁ የሚሄዱ እንስሶችና ተሽከርካሪዎች ናቸው።  በየብስ፣በባህርና በአየር የሚደረግ የእግረኞች፣የመርከቦችና የአውሮፕላኖች መተላለፍ ማለት ነው።
  • 70. የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራቶች በሚሰጡት አገልግሎት በሁለት ይከፈላሉ።እነርሱም 1.የእግረኞች ማስተላለፊያ መብራት • ቀይ የእግረኛ ምስል፡- እግረኞች ያስቆማል • አረንጓዴ የእግረኛ ምስል፡- እግረኞች ያስተላልፋል
  • 71. 2.የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት 1. ቀይ፡- መተላለፊያ መስመሩን ሳታልፍ ቁም 2.ቀይና ቢጫ፡- ለመሔድ ተዘጋጅ 3.አረንጓዴ፡- ወደ መረጥክበት አቅጣጫ እለፍ 4.ቢጫ፡- ፡- ወደ መገናኛ መንገድ በመምጣት ላየ ያሉ ለእግረኛ የተሰመረውን ሳታልፉ ቁሙ ፡- መገናኛ መንገድ ቀድመው የገቡ አሽከርካሪዎች በፍጥነት ለቃችሁ ውጡ የሚል መልእክት ያስተላልፋል
  • 72.
  • 73. ምንኛውም አሽከርካሪ መንገዱ ላይ አደገኛ ሁኔታ ሊኖር ስለሚችል ፍጥነቱን በመቀነስ ለተላላፊዎች ቅድሚያ በመስጠት ተጠንቅቆ ማለፍ ይችላል። ብልጭ ድርግም የሚል ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ ማንኛውም አሽከርካሪ መንገዱ ላይ አደገኛ ሁኔታ እንዳለ ተገንዝቦ ለእግረኛ መተላለፊያ የተሰመረውን መስመር ሳያልፍ በመቆም አደጋ የማያስከትል መሆኑን ሳያረጋግጥ እንዲያልፍ አይፈቀድለትም። ብልጭ ድርግም የሚል ቀይ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ
  • 74. 1. ብልጭ ድርግም የሚል ቢጫ የተሽከርካሪዎች ማስተላለፊያ መብራት ለአብዛኛው የትራፊክ መጨናነቅ በማይበዛበት ወቅት እንዳይቆሙና በጥንቃቄ መተላለፍ እንዲችሉ ያደርጋል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት 2.ከአረንጓዴ የተሽከርካሪ ማሰተላለፊያ መብራት ቀጥሎ ቢጫ መብራት ብቻውን ሲበራ የሚያስተላልፈው መልእክት ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ለመሄድ ይዘጋጃሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 3. የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራት ስንት ቀለሞች አሉት፡፡ ሀ. አንድ ለ. ሁለት ሐ. ሶስት መ. አራት 4.መብራት ባለበት መስቀለኛ መንገድ መሀከል ላይ ተሽከርካሪው እየተጓዘ እያለ ቢጫ የትራፊክ መብራት ሲበራ ቆሞ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን ማሳለፍ አለበት፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 5.የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራት አቀማመጡ ከላይ ወደታች ምን ይመስላል? ሀ. አረንጓዴ፣ ቢጫና፣ ቀይ ለ. ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ቀይ ሐ. ቀይ፣ ቢጫና፣ አረንጓዴ መ. ቀይና፣ አረንጓዴ 6. ተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ላይ የእግረኛ ምስል መቀመጥ አለበት ሀ. እውነት ለ.ሀሰት 7. ብልጭ ድርግም የሚል ቢጫ የተሽከርካሪ መስተላለፊያ መብራት ሲበራ አሽከርካሪው ተሽከርካሪውን በማቆም ለተላላፊዎች ቅድሚያ በመስጠት በጥንቃቄ ማለፍ አለበት ሀ. እውነት ለ. ውሸት
  • 75. 8.ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ከአረንጓዴ መበራት ቀጥሎ ሲበራ የሚያስተላልፈው መልዕክት ሀ. ቆመህ ከነበረ ለጉዞ ተዘጋጅ ለ. ቆመህ ከነበረ ጉዞ ጀምር ሐ. መስቀለኛ መንገድ ውስጥ ከገባህ በፍጥነት ውጣ መ. መስቀለኛ መንገድ ውስጥ ከገባህ ወደ ኋላ ተመለስ 9. -----------ማለት በየብስ፣ በባህር ወይም በአየር ላይ የሚደረግ የሰው፣ የመርከብ እና አውሮፕላን እንቅስቃሴ ነው፡፡ ሀ. የመንገድ ትራንስፖርት ለ. ትራንስፖርት ሐ. ትራፊክ መ. መልስ የለም 10. -----መብራት ሲበራ ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች መሄድ ይችላሉ፡፡ ሀ. አረንጓዴ ለ. ቀይ ሐ. ቢጫ መ. ቀይና ቢጫ 11.ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ ወደ መገናኛው ሥፍራ የደረሰ አሽከርካሪ ማለፍ ይችላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 12.ቢጫ የተሽከርካሪ መስተላለፊያ መብራት ሲበራ ወደ መገናኛው ስፍራ የደረሰ አሽከርካሪ ማለፍ ይችላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 13.መብራት ሲበራ ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ለመሄድ ይዘጋጃሉ፡፡ ሀ. ቢጫ ለ. አረንጓዴ ሐ. ቀይ መ. ቀይና ቢጫ
  • 76. 14……..መብራት ብርት ጥፍት እያለ በተደጋጋሚ ሲበራ ፍጥነት በመቀነስ ግራና ቀኝ አይቶ በጥንቃቄ ማለፍ ይቻላል፡፡ ሀ. አረንጓዴ ለ. ቀይ ሐ. ቢጫ መ. መልስ አልተሰጠም 15.ቀይና ቢጫ አንድ ላይ ሲበሩ ትርጉሙ የማቆሚያ መስመሩን ካለፍክ ፍጥነትህን ጨምረህ መንገዱን አቋርጥ ማለት ነው፡፡ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 16.የሰው ምስል ያለበት ቀይ የተራፊክ ማስተላለፊያ መብራት ከበራ ለተሽከርካሪ ቁም ማለት ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 17.ቀይና ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት በአንድነት ሲበራ ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ጉዞ መቀጠል ይችላሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 18.መሰቀለኛ መንገድ ውስጥ ከገባህ በፍጥነት ውጣ የሚል የትራፊክ መብራት ነው፡፡ ሀ. ቀይ ለ. ቀይና ቢጫ ሐ. አረንጓዴ መ. ቢጫ 19.አለም አቀፍ የትራፊክ መብራቶች በአሰራር /በአበራር/ ቅደም ተከተላቸው፡፡ ሀ/ ቀይ፣አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ሐ/ አረንጓዴ፣ቀይናቢጫ፣ ቀይ፣ቢጫ ለ/ ቀይ፣ቀይናቢጫ፣አረንጓዴ፣ቢጫ መ/ ቀይ፣ቢጫ፣አረንጓዴ፣ቀይ
  • 77. 20.አረንጓዴ የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራት በርቶ ከርቀት በማይታይበት ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት እያሽከረከረ መገናኛ መንገዱን ማቋረጥ ይቻላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 21.ወደ መገናኛው መንገድ በመምጣት ላይ ያለ ተሸከርካሪዎች የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ሣያልፍ እንዲቆሙ ወደ መገናኛው መንገድ ቀድመው የገቡ አሽከርካዎች በፍጥነት መንገድ ለቀው እንዲወጡ የሚያዘው የአሸከርካሪ ማሰተላለፊያ መብራት የቱ ነው? ሀ. ቢጫ ለ. ቀይ ሐ. አረንጓዴ መ ቀይ እና ቢጫ 22.ተሽከርካሪዎችን እንዲቆሙ የሚያዘው የተሽከርካሪ ትራፊክ ማስተላለፊያ መብራት ምን አይነት ነው? ሀ. ቀይ ለ. ቢጫ ሐ. አረንጓዴ መ. ቀይና ቢጫ 23. ተሽከርካሪዎች ጉዞ ለመቀጠል እንዲዘጋጁ ነቅተው እንዲጠብቁ የሚያደርገው የተሽከርካሪ ትራፊክ ማስተላለፊያ መብራት ምን አይነት ነው? ሀ. ቀይ ለ. ቢጫ ሐ. አረንጓዴ መ. ቀይ እና ቢጫ አንድነት ሲበሩ 24. ተሽከርካሪዎች እንዲንቀሳቀሱ ወይም ጉዞአቸው እንዲቀጥሉ የሚፈቅደው ወይም የሚያዘው የተሽከርካሪ ማሰተላለፊያ መብራት ቀለም ምን አይነት ነው? ሀ. ቀይ ለ. ቢጫ ሐ. አረንጓዴ መ. ቀይ እና ቢጫ
  • 79. 1 2 3 4 5 6 7
  • 80. 1 ከፊት ለፊት የሚመጡትን አሽከርካሪዎች እንዲቆሙ ያዛል 2 ከኃላ የሚመጡ ተሽከርካሪዎች እንዲቆሙ ያደርጋል 3 ከፊት ለፊትና ከኃላ ወደ መስቀለኛ መንገደ የሚመጡትን ተሽከርካሪዎች ያስቆማል 4 ከቀኝ ወደ ግራና ቀጥታ ታጥፈው ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ይፈቀዳል 5 ፊት ለፊት ቆመው ከነበሩ አሽከርካሪዎች ወደ ፊትና ወደ ቀኝ አንዲጓዙ ይፈቅዳል 6 ከኌላ ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ቀጥታ ወደ ፊትና ወደ ቀኝ ታጥፈው እንዲጓዙ ይፈቀዳል 7 ከግራ ወደ ቀኝና ቀጥታ ታጥፈው ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ይፈቀዳል
  • 82. የፍጥነት ወሰን ገደብ የፍጥነት ወሰን ገደብ በሁለት ይከፈላል። እነርሱም 1.የከተማ ውስጥ 2.የከተማ ውጪ ከከተማ ውጪ በሶስት መንገዶች ይገኛሉ። እነርሱም ሀ.አንደኛ ደረጃ መንገድ፡- ሀገርን ከሀገር ያገናኛል። ለ.ሁለተኛ ደረጃ መንገድ፡-ክልልን ከክልል ያገናኛል። ሐ.ሶስተኛ ደረጃ መንገድ፡-ወረዳን ከወረዳ ያገናኛል። የሀራችን የፍጥነት ወሰን ገደብ ሲደነገግ መነሻ የሚያደርገው ሁለት ነገሮችን ነው። 1.የተሽከርካሪ ክብደት/አይነት 2.የመንገድ ደረጃ
  • 83. የተሽከርካሪ ክብደት/አይነት የከተማ ውስጥ የከተማ ውጪ 1ኛ 2ኛ 3ኛ ከ3500 ኪ.ግ. በታች አውቶሞቢል/አነስተኛ ተሽከርካሪዎች 60 100 70 60 ከ3500 ኪ.ግ. -7500 ኪ.ግ. የንግድ/መለስተኛ የህዝብና የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች 40 80 60 50 ከ7500 ኪ.ግ. በላይ ከፍተኛ የህዝብና የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች 30 70 50 40
  • 84. 1.ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በታች ማሽከርከር ይቻላል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 2.አነስተኛ አውቶሞቢል ከከተማ ክልል ውጪ በዋና መንገድ በሰዓት ማሽከርከር የሚችለው የፍጥነት ወሰን? ሀ. በ8ዐ ኪ.ሜትር ለ. በ7ዐ ኪ.ሜትር ሐ. በ1ዐዐ ኪ.ሜትር መ. በ6ዐ ኪ.ሜትር 3. አነስተኛ የጭነት ተሽከርካሪ ወይም አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ በአንደኛ ደረጃ መንገድ ላይ በሰዓት የፍጥነት ወሰኑ ሀ. 8ዐ ኪ.ሜትር ለ. 75 ኪ.ሜትር ሐ. 6ዐ ኪ.ሜትር መ. 7ዐ ኪ.ሜትር 4. በከተማ ክልል ውስጥ ከ75ዐዐ ኪ.ግ በላይ ክብደት ያላቸው ተሽከርካሪዎች በከተማ መንገድ ላይ በሰህት የፍጥነት ወሰኑ በኪ.ሜትር ነው፡፡ ሀ. 65 ኪ.ሜትር ለ. 8ዐ ኪ.ሜትር ሐ. 3ዐ ኪ.ሜትር መ. 6ዐ ኪ.ሜትር 5. በከተማ ክልል ውስጥ ከ35ዐዐ - 7ዐዐዐ ኪግ ክብደት ያላቸው ተሽከርካሪዎች በሰዓት የፍጥነት ወሰኑ በኪ.ሜትር ሀ. 4ዐ ኪ.ሜትር ለ. 3ዐ ኪ.ሜትር ሐ. 6ዐ ኪ.ሜትር መ. 8ዐ ኪ.ሜትር 6.ማንኛውም አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን በፍጥነት ለማሽከርከር የማይፈቀድለት ምክንያት? ሀ. የመንገዱ ሁኔታ ሐ. ተላላፊውን ለማየት በማይቻልበት የአየር ፀባይ ለ. የትራፊኩ ብዛትና ሁኔታ መ. ሁሉመ ምልስ ነው
  • 85. 7.መሃከለኛ ክብደት ያላቸው ተሽከርካሪዎች በሁለተኛ ደረጃ አውራ ጐዳና ላይ የተፈቀደላቸው የፍጥነት ወሰን በሰዓት ነው፡፡ ሀ. 8ዐ ለ. 6ዐ ሐ. 5ዐ መ. 4ዐ 8.ለከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢው በሁለተኛ ደረጃ አውራ ጐዳና ላይ የተፈቀደላቸው የፍጥነት ወሰን በሰዓት ነው፡፡ ሀ. 1ዐዐ ኪ.ሜ ለ. 6ዐ ኪ.ሜ ሐ. 5ዐ ኪ.ሜ መ. 4ዐ ኪ.ሜ 9.ለአነስተኛ ተሽከርካሪ ከከተማ ክልል ውጭ በ3ኛ ደረጃ አውራጐዳና የተፈቀደለት የፍጥነት ገደብ ኪ.ሜ በሰዓት ነው፡፡ ሀ. 6ዐ ለ. 5ዐ ሐ. 1ዐዐ መ. 7ዐ 10.ለከፍተኛ ተሽከርካሪ በአንደኛ ደረጃ አውራ ጐዳና ላይ የተፈቀደለት ከፍተኛ የፍጥነት ወሰን፡፡ ሀ. 3ዐ ኪ.ግ በሰዓት ለ. 8ዐ ኪ.ግ በሰዓት ሐ. 7ዐ ኪ.ግ በሰዓት መ. መልስ አልተሰጠም 11.ጠቅላላ ክብደታቸው ከ3,5ዐዐዐኪ.ግ በታች ለሆኑ ተሽከርካሪዎች በ2ኛ ደረጃ አውራጎዳና ላይ የተፈቀደለት ከፍተኛ ፍጥነት ወሰን፡፡ ሀ. 7ዐ ኪ.ሜ በሰዓት ሐ. 4ዐ ኪ.ሜ በሰዓት ለ. 6ዐ ኪ.ሜ በሰዓት መ. 5ዐ ኪ.ሜ በሰዓት
  • 86. 12.የአገራችን የፍጥነት ወሰን ገደብ ሲደነገግ መነሻ የሚያደረገው የቱን ነው ሀ/ የመንገዱን ሁኔታ ሐ/ የተሸከርካሪውን የመቀመጫ ብዛት ለ/ የተሸከርካሪውን ጠቅላላ ክብደት መ/ ሁሉም መልስ ነው
  • 88. ተሽከርካሪ ለጊዜው ወይም ለረጅም ግዜ ማቆም የተከለከለባቸው ስፍራዎች • ከከተማ ክልል ውጪ በሆነ በማናቸውም መንገድ ላይ ተሽከርካሪ የሚያሽከርከር ማናቸውም ሰው ከመንገዱ ላይ ለተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ ከሌለ በስተቀር ከመኪና ቢወርድም ባይወርድም ትራፊክ በብዛት በሚተላለፍበት መንገድ ላይ ለጊዜው ወይም ለረጅም ግዜ ተሽከርካሪ ማቆም የለበትም። • ማንኛውም ሰው የመንገዱ ስፋት ከ12ሜትር በላይ ካልሆነ በቀር ተሽከርካሪውን ከሌላ ተሽከርካሪ ተቃራኒ አንጻር ከመንገድ ላይ ለጊዜው ለረጅም ግዜ ማቆም የለበትም። • ማንኛውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ በዚያው መንገድ የሚነዳ የሌላ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ከሁለቱም አቅጥጫ በ50ሜትር ርቀት ላይ ለማየት በማይችልበት ስፍራ ከመንገድ ላይ ተሽከርካሪ ማቆም የለበትም።
  • 89. • ከእሳት አደጋ ጣቢያ ወይም የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ከሚሰጥበት ጣቢያ ወይም ከሆስፒታል መግቢያ በ12 ሜትር ውስጥ ወይም ከመግቢያው መካከል ጀምሮ ከመንገድ ግራና ቀኝ በ25ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው • ከአውቶቢስ ማቆሚያ በስተኃላ በስተፊት በ15ሜትር ውስጥ የመንገዱ ስፋት ከ12ሜትር በላይ ካልሆነ በስተቀር በመንገዱ አንጻር ከአውቶቢስ ማቆሚያ በ30 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው። • በመስቀለኛ መንገድ ውስጥ ወይም ከመስቀለኛ መንገድ በ12ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው። • በሃዲድ መንገድ ማቋረጫ ከሚቀርበው ሀዲድ በ20 ሜትር ክልል ውስጥ መቆም ክልክል ነው • ከባቡር ሀዲድ ማቋረጫ በ6ሜትር ክልል ውስጥ ማርሽ መለወጥ ክልክል ነው። • ቁም የሚል ምልክት ወይም የመንገድ ምልክት ካለበት ስፍራ በ12 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው። • በግል መንገድ ተሽከርካሪ በሚተላለፍበት የቤት መውጫ ወይም መግቢያ ወይም የመንገዱ ስፋት 12 ሜትር ያነሰ ሆኖ ሲገኝ መቆም ክልክል ነው።
  • 90. • ከጎርፍ ማስተላለፊያ ፉካ ካለበት በ5 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው። • በቤንዚን ማደያ አከባቢ ተሽከርካሪዎች ወደ ማደያ ገብተው ለመቅዳት በሚያዳግታቸው ሁኔታ በ12 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው። • በመገናኛ መንገድ አከባቢ አቅጣጫን ለመለየት የቀስት ምልክት በተቀባበት መስመር ላየ በቅድሚያ መስመራቸውን ለይተው ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ያልተቆራረጠውን የመስመር ክልል የግድ እነንዲያቀዋርጡ በሚያስገድዳቸው ርቀት ውስጥ አቅሞ መሔድ የተከለከለ ነው። • ከአጥር ክልል ወይም ከግቢ ውስጥ ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንዲወጡበት በተሰራ መንገድ ላይ መተላለፊያ ዘግቶ መቆም ክልክል ነው። • ከመንገድ ጠርዝ ከ40 ሴ.ሜ. በላይ መቆም ክልክል ነው።
  • 91. • በድልድይ ወይም በመለኪያ ላይ መቆም ክልክል ነው። • በሶስተኝነት ተደርቦ መቅደም ክልክል ነው። • በቀኝ በኩል መቅደም ክልክል ነው። • በመንገዱ ቀኝ ዳርቻ መኪናን ለማቆሚያ አመቺ በሚሆን አይነት በመንገድ ባለስልጣን ለአንድ መኪና ስፈቱም ቁመቱም ይበቃል ተብሎ በተቀባ ክልል ውስጥ አለአግባብ አቁሞ መሄድ ክልክል ነው። • የመንገዱ ቀኝ ጠርዝ አስጠግትው በአግባቡ በቆሙ ተሽከርካሪዎች ጎን በተደራቢነት መቆም ክልክል ነው። • መንገዱ ባለ አንድ አቅጣጫ ካልሆነ በስተቀር በማናቸውም ጎዳና በስተግራ ወገን መቆም ክልክል ነው። • በእያንዳንዱ አቅጣጫ ለትራፊክ አንድ ነጠላ መንገድ ብቻ ባለበትና መንገዱም በነጭ በተከፋፈለበት ስፍራ መቆም ክልክል ነው።
  • 92. አቅጣጫ ስለመለወጥ ማናቸውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ • አርቆ ወይም አሻግሮ ማየት ባልቻለ ጊዜ • ከኮሮብታ ጫፍ፣ቁልቁለት፣ከድልድይ፣ተነድሎ ከተሰራ መሻለኪያ/ታነል/ ወይም ከጎባጣ መንገድ ሲደርስ • ከመስቀለኛ መንገድ ወይም ከሀዲድ መንገድ በ30 ሜትር ርቀት ውስጥ • የማያቋርጥ የቀለም መስመር በተደረገበት መንገድ ለይ ወደ ግራ መጠምዘዝ አይፈቀድለትም።
  • 93. ስለአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች የተሰጠ ልዩ ደንብ ማንኛውም የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ ተግባሩን በሚያከናውንበት ግዜ • በዚህ ደንብ ወይም በሌላ ደንብ የተጻፈውን ግዴታ ሳይጠብቅ ተሽከርካሪን ለማቆም • ቁም በሚል ምልክት ላይ ሳይቆሙ ለማለፍ • ከተወሰነው ፍጥነት በላይ ለመንዳት እና • ተግባሩን ለመፈጸም በሚያስፈልገው መጠን ስለትራፊክ የወጡ ደንቦችንና የመንገድ ምልክቶችን ሳይመለከት በፈቀደው አቅጣጫ ለመጠምዘዝ ተፈቅዶለታል። • ቀድሞ የሚሄድ የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ በሚፈጽመው ተግባር ተካፋይ የሆነ የሌላ የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ ካልሆነ በስተቀር ማናቸው ሰው ከ100 ሜትር ባነሰ ርቀት ከአንድ የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ ተጠግቶ መንዳትየለበትም።
  • 94. የማስጠንቀቂያ ድምጽ ስለመጠቀም • ማናቸውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ የሚገጥመውን አደጋ ለመከላከል ግድ አስፈላጊ ካልሆነ፣አደጋውን የሚከላከልበት ሌላ መንገድ ከሌለውና የሚያሰማውም የማስጠንቀቂያ ድምጽ በተቻለ መጠን አጭር ካልሆነ በስተቀር፣ በከተማ መንገድ ውስጥ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ማሰማት አይፈቀድለትም። ተሽከርካሪ በቆመበት ግዜ በማናቸውም አኳኃን የማስጠንቀቂያ ድምጽ ማሰማት ክልክል ነው። • ሆስፒታልና ትምህርት ቤት አከባቢ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ማሰማት ክልክል ነው።
  • 95. ነዳጅ ስለመሙላት • ማንኛውም ሰው የተሽከርካሪው ሞተር እየሰራ፣ ተሽከርካሪው የህዝብ ማመላለሻ ከሆነ በተሽከርካሪ ውስጥ መንገዶች እያሉ ማናቸውም ነዳጅ መሙላት ወይም ማስሞላት የለበትም። • በተሽከርካሪው አጠገብ እሳት ወይም ሲጋራ የሚያጨስ ሰው ሲኖር በሞተር ተሽከርካሪው ነዳጅ እንድሞላ ወይም የነዳጅ መክደኛ እንዲከፈት ወይም ሌላ ስው ይህንን እንዲያደርግ መፍቀድ ክልክል ነው። • ማናቸውም ሰው ተሽከርካሪውን ነዳጅ ሲሞላ በሞባይል ስልክ ማነጋገር ወይም ሌሎች ኤሌክትሮኒክስ ነክ መሳሪያዎችን መጠቀም የለበትም።
  • 96. የተበላሸ ተሽከርካሪ መንገድ ላይ ስለመጠገን 1.ማንኛውም ሰው በመንገድ ላይ ተሽከርካሪን ለመጠገን ወይም ለማደስ አይፈቀድለትም፣ከዚህም ሌላ ተሽከርካሪው በማናቸውም አከኃን ያለ ማቀረጥ፣ • በከተማ ውስጥ ሲሆን ከ6 ሰአት በላይ • ከከተማ ውጪ ሲሆን ከ48 ሰአት በላይ በአንድ ቦታላይ መቆቆት የለበት 2. ማንኛውም ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ቢበላሽ አሽከርካሪው ከተሽከርካሪው ፊትና ኃላ ባለው መንገድ በ50 ሜትር ርቀት ላይ ለሌላ ትርፊክ በግልጽ በሚታይ መልኩ ባለ 3/ሶስት ማእዘን አንጸባራቂ ሰሌዳ ማስቀመጥ አለበት 3. ማንኛውም ሰው የተጎዳ ወይም የተበላሸ ተሽከርካሪ መኪና ከመንገድ ላይበሚያነሳበት ግዜ በመንገድ ላይ የወዳደቁን የመስታወትና ሌሎች ተላላፊ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ሁሉ ከመንገድ ማስወገድ አለበት።
  • 97. ረጅም የግንባር መብራት መጠቀም የሚከለከልባቸው ሁኔታዎች • የመንገድ መብራት በቂ ካልሆነ በስተቀር በከተማ መንገድ ስታሽከረክር • በተቃራኒ መንገድ የሚመጣ ተሽከርካሪ ሲቃረብና እስኪያልፍ ድረስ • በ50 ሜትር ርቀት የምትከተለው ተሽከርካሪ ሲኖር • ተሽከርካሪ በቆመበት ወቅት • የማናቸውም ባለሞተር ተሽከርካሪ አሽከርካሪ በማብሪያ ግዜ ተሽከርካሪውን ሲያቆም የማቆሚያ መብራት ማብራት አለበት።
  • 98. የንግድ ሸቀጥ አጫጫን • ጭነት ከተሽከርካሪው በስተፊት ባለው ጫፍ ከአንድ/1 ሜትር በስተኃላ ከተሽከርካሪው ከሁለት/2 ሜትር በላይ ተርፎ መውጣት የለበትም። • መብራት በሚበራበት ግዜ ከፊት ተርፎ በሚገኘው ጭነት ጫፍ ነጭ/ቢጫ ከኃላ ተርፎ በሚገኘው ጭነት ላይ ቀይ መብራት መደረግ አለበት። • መብራት በማያስፈልግበት ግዜ በተራፊው ጭነት ላይ በፊትና በኃላ ጫፍ 30 ሳ.ሜ. ካሬ የሆነ ቀይ ጨርቅ ወይም ቀይ ቀለም የተቀባ ጠፍጣፋ ሰሌዳ መደረግ አለበት።
  • 99. ተሽከርካሪ ስለመጎተት • አንድ አሽከረካሪ በሌላ የሞተር ተሽከርካሪ በሚጎተትበት ጊዜ በመሀከላቸው ያለው ርቀት ከ3 ሜትር የማይበልጠ ሆኖ ሁለቱ ተሽከርካሪዎች በሽቦ ገመድ ወይም በጠንካራ የመሳቢያ የብረት ዘንግ በጥብቅ መያያዝ አለባቸው። • ማንኛውም የሞተር ተሽከርካሪ በአንድ ግዜ ከአንድ ተሽከርካሪ በላይ እንዲጎትት አየፈቀድለትም።
  • 100. 1.በአገራችን የመንገድ ስነ-ስርዓት ህግ መሰረት ተሽከርካሪን መቅደም የሚቻለው በኩል ብቻ ነው፡፡ ሀ. በቀኝ ለ. በግራ ሐ. በመሀል መ. መልሱ አልተሰጠም 2.የተበላሸውን ተሽከርካሪ በከተማ ክልል ውስጥ እስከ ሶሰት ቀን ድረስ ማቆም ይፈቀዳል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 3.አንድ ተሽርካሪ ከመንገድ ጠርዝ በ ባልበለጠ ርቀት መቆም አለበት ሀ. 30 ሳ.ሜ ለ. 40 ሳ.ሜ ሐ. 50 ሳ.ሜ መ. ሁሉም 4.ማንኛውም አሽከርካሪ ከመስቀለኛ ወይም ከሃዲድ መንገድ ማቁረጫ በ3ዐ ሜትር ርቀት ውስጥ ረድፍ መቀየር አይቻልም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት 5.አንድ የተበላሸ ተሽከርካሪ በሌላ ተሽከርካሪ በሚጐተትበት ጊዜ በመካከላቸው የለው ርቀት ከ ሜትር በላይ መብለጥ የለበትም፡፡ ሀ. 3 ሜትር ለ. 5 ሜትር ሐ. 2 ሜትር መ. 4 ሜትር 6. ማንኛውም አሽከርካሪ አሻግሮ ወይም አርቆ ለማየት ካልቻለ ወደ ግራ መጠምዘዝ አይችልም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
  • 101. 7.አንድ ተሽከርካሪ በከተማ ውስጥ ከ በላይ ሰዓት ተበላሽቶ መንገድ ላይ እንዲቆም አይፈቀድለትም፡፡ ሀ. ከ5 ሰዓት ለ. ከ6 ሰዓት ሐ. ከ1ዐ ሰዓት መ. ከ4 ሰዓት 8. ተሽከርካሪዎች የተጫነው ጭነት ከተሽከርካሪው አካል ተርፎ በወጣ ጭነት ላይ በጨለማ ሲጓዝ ማድረግ ያለበት ምልክት? ሀ. ከፊት ነጭ /ቢጫ/ ከኋላ ቀይ መብራት ሐ. ከፊት ቢጫ ከኋላ ሰማያዊ መብራት ለ. ከፊት ቀይ ከኋላ ነጭ /ቢጫ/ መብራት መ. ከፊት ሰማያዊ ከኋላ ቢጫ መብራት 9.አንድን ተሽከርካሪ በዝግታ ለማሽከርክር ምክንያት ሊሆን የሚችለው፡፡ ሀ. በጠባብ ድልድይ ለ. በጠመዝማዛ መንገድ ሐ. የአሽከርካሪው የማየት ኋልይ በቀነሰበት ወቅት መ. በመስቀለኛ መንገድና እግረኛ ማቋረጫ 10.ማንኛውም አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን በአጭር ወይም ለረዥም ጊዜ ለማቆም ከፈለገ በምን ያህል ርቀት ከመንገድ ጠርዝ ትይዩ መሆን አለበት፡፡ ሀ. በ6ዐ ሜትር ርቀት ለ. በ4ዐ ሳ.ሜ ርቀት ሐ. በ3ዐ ሳ.ሜትር ርቀት መ. በ5ዐ ሳ.ሜትር ርቀት
  • 102. 11. ማንኛውም አሽከርካሪ ከባቡር ማቋረጫ ሲደርስ ግራና ቀኝ በመመልከት አደጋ የማያስከትል መሆኑን ለማረጋገጥ በምን ያህል ርቀት ማርሽ መቀያየር የለበትም ሀ. ከ1ዐ ሜትር በማያንስ ለ. ከ6 ሜትር በማያንስ ሐ. ከ2ዐ ሜትር በማያንስ መ. ከ15 ሜትር በማያንስ 12. ማንኛውም አሽከርካሪ ተሽከርካሪው መንገድ ላይ ቢበላሽ ባለሶስት ማዕዘን አንጸባራቂ የማስጠንቀቂያ ምልክት ከፊትና ከኋላ ባለው መንገድ በምን ያህል ርቀት ማስቀመጥ አለበት? ሀ. በ5ዐ ሜትር ለ. በ3ዐ ሜትር ሐ. በ6ዐ ሜትር መ. በ15 ሜትር 13.ከሁለት አቅጣጫ ለማየት በማይቻልበት ሥፍራ ተሽከርካሪን ማቆም የማይፈቀደው በ ሜትር ርቀት ነው ሀ. በ4ዐ ሜትር ርቀት ለ. በ15 ሜትር ርቀት ሐ. በ5ዐ ሜትር ርቀት መ. በ6 ሜትር ርቀት 14.ማንኛውም አሽከርካሪ ለአጭር ወይም ለረዥም ጊዜ ተሽከርካሪን ከሌላ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አንፃር ማቆም የሚከለከለው የመንገድ ስፋት ከስንት በታች መሆኑን አለበት ሀ. ከ15 ሜትር ለ. ከ12 ሜትር ሐ. በ2ዐ ሜትር መ. ከ3ዐ ሜትር 15.ከሚከተሉት ውስጥ ወደ ግራ ኋላ ዞሮ መመለስ የማይፈቀደው ለየትኛው ምክንያት ነው ሀ. አርቆ ወይም አሻግሮ ለማየት በማይችልበት ጊዜ ለ. ከድልድይና በማሿለኪያ ላይ ሐ. በመስቀለኛ ወይም ሀዲድ መንገድ ማቋረጫ መ. ሁሉም መልስ ነው
  • 103. 16.በዳገት ወይም በቁልቁለት ላይ ተሽከርካሪዎች ሲገናኙ ቁልቁለት የሚወርደው ተሽከርካሪ ሀ. ቅድሚያ ያገኛል ለ. ዳገት ለሚሄደው ቅድሚያ ይሰጣል ሐ. ሀ እና ለ መልስ ነው መ. መልስ አልተሰጠም 17. ከተለያዩ አቅጣጫ ወደ መስቀለኛ መንገድ እኩል የደረሱ ተሽከርካሪዎች ቅድማያ መስጠት ያለበት ሀ. በቀኝ በኩል ላሉ ተሽከርካሪዎች ለ. በግራ በኩል ላሉ ተሽከርካሪዎች ሐ. ለመስቀለኛ መንገድ ቅርብ የሆኑ ተሽከርካሪዎች መ. በመሀል ላይ ላሉ ተሽከርካሪዎች 18. የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ተግባራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ሀ. ተሽከርካሪውን በተከለከለበት ቦታ ማቆም ይችላሉ ለ. በፈለጉት አቅጣጫ መጠምዘዝ ይችላሉ ሐ. በተከለከለ አቅጣጫ መጓዝ ይችላሉ መ. ሁሉም መልስ ነው፡፡ 19.ማንኛውም አሽከርካሪ ከባቡር ሀዲድ ማቋረጫ በ6 ሜትር ውስጥ የተሽከርካሪውን ማርሽ መለወጥ የለበትም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት 20.አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን በቁልቁለት መንገድ ላይ ባቆመ ጊዜ የተሽከርካሪውን የፊት እግሮች ከመንገዱ በጣም ወደሚቀርበው ጠርዝ ማስጠጋት አለበት፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
  • 104. 21. የተበላሸን ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ጥገና የሚያደርግ ሰው ተሽከርካሪው ባለበት ዙሪያ መስመር ሰውነቱን ወደ መንገድ አውጥቶ መጠገን የለበትም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት 22. ማንኛውም አሽከርካሪ በሃዲድ ማቋረጫ ሲደርስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለማቆም እንዲችል ተሽከርካሪውን በዝግታ ለመንዳትና ለማቋረጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ይፈጽማል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት 23. አሽከርካሪዎች ከባቡር ሀዲድ ማቋረጫ አካባቢ ተሽከርካሪውን ከሀዲዱ በ2ዐሜትር ርቀት ማቆም ይችላሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት 24.ከከተማ ክልል ውጪ በማንኛውም መንገድ ላይ ተሽከርካሪን ለረጅም ጊዜ ማቆም ይቻላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት 25. የመንገዱ ስፋት ከ12 ሜትር በላይ ካልሆነ በስተቀር ተሽከርካሪውን ከሌላ ተሽከርካሪ በተቃራኒ ለጊዜው ማቆም አይቻልም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት 26. በሁለት አቅጣጫ ከ5ዐ ሜትር ርቀት ላይ ለማየት በማይቻልበት ስፍራ ተሽከርካሪን ማቆም የለበትም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት
  • 105. 27.መስቀለኛ መንገድን አቋርጦ ወደ ግራ የሚታጠፍ አሽከርካሪ ከ15 ሜትር ርቀት በፊት ራሱን ማዘጋጀት አለበት፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት 28.ከአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ኋላ ማንኛውም ተሽከርካሪ ተጠግቶ መንዳት የማይፈቀድለት ርቀት፡፡ሀ. በ5ዐ ሜትር ባነሰ ለ ለ4ዐ ሜትር ባነሰ ሐ. በ1ዐዐ ሜትር ባነሰ መ. በ8ዐ ሜትር ባነሰ 29. ማንኛውም አሽከርካሪ አሻግሮ ወይም በርቀት ማየት ካልቻለ ወደ ግራ መጠምዘዝ ይችላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት 30. ማንኛውም አሽከርካሪ ከመስቀለኛ ወይም ከሃዲድ መንገድ ማቋረጫ በ3ዐ ሜትር ርቀት ውስጥ ረድፍ መቀየር ይችላል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ውሸት 31.3ዐ ሜትር ርቀት ውስጥ አሽከርካሪዎች ወደ ግራ እንዳይጠመዘዙ የተከለከሉበት ሥፍራ ሀ. በመስቀለኛ ወይም በሃዲድ መንገድ ማቋረጥ ለ. በኮረብታማ በመሿለኪያ ስፍራ ሐ. በትምህርት ቤትና በሆስፒታል መ. በቤተክርስቲያንና በህጻናት መዋያ 32.ማንኛውም አሽከርካሪ ወደ ግራ ለመጠምዘዝ /ዞሮ ለመመለስ/ የማይፈቀድለት በየትኛው መንገድ ላይ ነው፡፡ ሀ. በቁልቁለት ቦታ ለ. በድልድይ ላይ ሐ. በመሿለኪያ ቦታ መ. ሁሉም መልስ ነው
  • 106. 33.ማናቸውም አሽከርካሪ የመንገዱ ስፋት 12 ሜትር በላይ ካልሆነ በቀር ከአውቶቢስ መቆሚያ ትይዩ ተሽከርካሪውን ለጊዜው ወይም ለረጅም ጊዜ ማቆም የለበትም ሀ. እውነት ለ. ሐሰት 34.ማናቸውም አሽከርካሪ የመንገዱ ስፋት ከ22 ሜትር በላይ ካልሆነ በቀር ከአውቶቡስ መቆሚያ ትይዩ ተሽከርካሪውን ለጊዜው ወይም ለረጅም ጊዜ ማቆም የለበትም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት 35. ማናቸውም ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ቢበላሽ አሽከርካሪው ከተሽከርካሪው ፊትና ኋላ ባለው መንገድ 3ዐ ሜትር ርቀት ላይ ለሌላ ትራፊክ በግልጽ በሚታይ መልኩ ቀይ ሠሌዳ ማስቀመጥ አለበት፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት 36. የህዝብ ማመላለሻ የሆነ ተሽከርካሪ መንገደኞችን እንደጫነ ነዳጅ መሙላት ወይም ማስሞላት ይችላል። ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
  • 107.