SlideShare a Scribd company logo
 1. የፍርድ ቤት ሥልጣን
 2. የተከራካሪ ወገኖችና የክስ ምክንያቶች መጣመር
 3. ከክርክር በፊት ሊፈጸሙ ስለሚገባቸው የሥነ-ሥረዐት ደንቦች
 የአቤቱታ ምንነትና አቀራረብ
 አቤቱታን ስለማሻሻል
 4. የመጥሪያ አላላክ ሂደት
 5. ክስን ስለመስማት
 6. ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ፣ ብይን ወይም ትእዛዝ እንደገና
ስለሚከልስበት አግባብ
 7. እግድና ንብረት ማስከበርን በተመለከተ
 በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ 79(1) ላይ በግልጽ
እንደተደነገገው በፌድራልም ሆነ በክልል የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ
ቤቶች ነው፡፡
 ነገር ግን ፍ/ቤቶች የሚቀርቡላቸውን ሁሉንም ጉዳዮች በማየት
ውሳኔ ይሰጣሉ ማለት እንዳልሆነ ከዚሁ ህገመንግስት አንቀጽ 37
(1) ምንባብ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
 በዚሁ ድንጋጌ መሰረት ፍ/ቤት ለመዳኘት ሥልጣን የሚኖረው
ጉዳዩ በፍ/ቤት ሊወሰን የሚገባው ጉዳይ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
በመሆኑም ፍ/ቤቶች የሚቀርቡላቸውን ጉዳዮች ተመልክተው
ከመወሰናቸው በፊት በቅድሚያ ጉዳዩ በፍ/ቤት ታይቶ ውሳኔ
ለማግኘት የሚገባው ጉዳይ መሆን አለመሆኑን መለየት
ያስፈልጋቸዋል፡፡
 ለዳኝነት የቀረበው ጉዳይ በፍ/ቤት ሊወሰን የሚገባው ሆኖ ከተገኘ
ቀጣዩ ፍ/ቤቶች ሊያጤኑት የሚገባው ነገር ይህንኑ ጉዳይ ለመዳኘት
ስልጣን ያላቸው መሆን አለመሆኑን መመርመር ይኖርባቸዋል፡፡
 ማንኛውም ፍ/ቤት አንድን ጉዳይ ተመልክቶ ዳኝነት ለመስጠት
በህግ ስልጣን የተሰጠው ሊሆን ይገባል፡፡ የፍ/ቤት ስልጣን ማለት
አንድን ጉዳይ ሰምቶ ውሳኔ የመስጠት ችሎታ ማለት ነው፡፡
 የአንድ ፍ/ቤት ስልጣን በሶስት ክፍሎች የሚከፈል ሲሆን፣ እነዚህም፡
የብሄራዊ፣ የስረ ነገርና የአካባቢ (ግዛት ክልል) የስልጣን አይነቶች
ናቸው፡፡
 ብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን ማለት የአንድ ሀገር ፍርድ ቤት አንድን
ጉዳይ ሰምቶ ውሳኔ የመስጠት ችሎታ አለው? ወይስ የለውም?
የሚለውን የሚመልስ የስልጣን አይነት ነው፡፡
 የፍትሕብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን ይህንን አይነቱን የፍ/ቤት
የዳኝነት ሥልጣንን በተመለከተ የደነገገው ነገር የለም፡፡
 ፍ/ቤቶች በተለይም የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን የሚያስነሱ ጉዳዮች
ምን አይነት ሁኔታዎች ናቸው? ይህንን ሥልጣን መሰረት በማድረግ
በተከራካሪ ወገኖች መቃወሚያ መቼ ሊነሳ ይገባል? መቃወሚያ
ሳይቀርብ ውሳኔ ቢሰጥስ የውሳኔው እጣ ፋንታ ምን ይሆናል?
የሚሉትና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስ ችግር
ሲፈጥርባቸው ይስተዋላል፡፡
 አንድ ጉዳይ ለዳኝነት የቀረበለት የአንድ ሀገር ፍ/ቤት የብሄራዊ
የዳኝነት ስልጣን የሚኖረው ከተከሳሹ ወይም የክርክሩ ምክንያት
የሆነው ነገር ከተፈጸመበት ወይም የክርክሩ መነሻ የሆነው ንብረት
የሚገኝበት ሀገር ጋር በቂ ግንኙነት ያለው ሲሆን ወይም የተከራካሪ
ወገኖች በአንድ ሀገር ፍ/ቤት ለመዳኘት ስምምነት ያደረጉ እንደሆነ
ነው፡፡ እነዚህን አገናኝ ምክንያቶች መሰረት በማድረግ አንድ ሀገር
የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን ይኖረዋል ማለት ሌላ ሀገር በዚያው ጉዳይ
ይሄው የዳኝነት ስልጣን አይኖረውም ማለት አይደለም፡፡
 የብሔራዊ የዳኝነት ስልጣን ክርክር የሚነሳውም የብሄራዊ የዳኝነት
ስልጣን ላለው የአንድ ሀገር ፍ/ቤት የቀረበው ጉዳይ ጉዳዩ
ከቀረበለት ሀገር ፍ/ቤት በተጨማሪ የሌላ ሀገር/ሀገራት ፍ/ቤት
ለማየትና ውሳኔ ለመስጠት ስልጣን ሲኖረው ነው፡፡
 እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ብሄራዊ የዳኝነት
ስልጣን ባላቸው አንድ ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ ስልጣን ያለው የሌላ
ሐገር ፍ/ቤት ውሳኔ የሰጠበት ቢሆንና ይህንኑ ውሳኔ ወደ ጎን
በማለት ከተከራካሪዎቹ አንዱ እንደ አዲስ በኢትዮጵያ ፍ/ቤት ክስ
ቢያቀርብ፣ ሌላው ተከራካሪ ቀደም ሲል በሌላ ሀገር ፍ/ቤት
የተሰጠውን ውሳኔ በመጥቀስ መቃወሚያውን ቢያቀርብ
መቃወሚያ የቀረበለት ፍ/ቤት ምን ሊወስን ይችላል? የሚለው
ነው፡፡
 ከዚህ አንጻር በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 መሰረት በውሳኔዎቹ
የሚሰጠው የህግ ትርጉም የአስገዳጅነት ውጤት እንዲኖረው ስልጣን
የተሰጠው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዚህ ጉዳይ ላይ
በቅጽ 12 በሰ/መ/ቁ/ 54632 እና በሰ/መ/ቁ/ 59953 የሰጣቸውን
ተቀራራቢነት ያላቸውን ሁለት ውሳኔዎች መመልከት ይቻላል፡፡
 በነዚህ ውሳኔዎችም ላይ እንደተመለከተው አንድ በውጪ ሀገር ባለ
ፍ/ቤት የተሰጠን ውሳኔ በአንቀጽ 5 መሰረት በፍርድ ማለቅ መርህን
በመጥቀስ መቃወሚያ ሲቀርብ በፍትሐብሄር ስነ ስርዓት ህግ ከአንቀጽ
456 እስከ 461 የተደነገጉት ድንጋጌዎች በሚያሳዩት መልኩ በኢትዮጵያ
ፍርድ ቤቶች ተቀባይነትን ሊያገኝ የሚችልበትን ሁኔታ በግልፅ መሟላቱ
በመጀመሪያ መረጋገጥ ይኖርበታል በሚል ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ በዚህ
አይነት ጉዳዮች ላይ በዚሁ አግባብ መስራት የሚያስፈልግ ይሆናል፡፡
• አንድ ጉዳይ የቀረበለት ፍ/ቤት ጉዳዩን አይቶ ውሳኔ
ለመስጠት ምንም አይነት የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን
የሌለው መሆኑን የተረዳ እንደሆነ ፍ/ቤቱ
በፍታ/ሥ/ሥ/ህ ቁጥር 231 መሰረት መዝገቡን መዝጋት
ይኖርበታል፡፡
 ፍ/ቤቱ ስልጣን የሌለው መሆኑን ባለመረዳት ወይም በሌላ
በማንኛውም ምክንያት መዝገቡን ያልዘጋ እንደሆነ ተከሳሹ
በሚያቀርበው የጽሁፍ መልስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
በማቅረብ ፍ/ቤቱ መዝገቡን እንዲዘጋለት ለማድረግ ይችላል፡፡
 ነገር ግን ተከሳሹ ቀርቦ ምንም አይነት መቃወሚያ ያላቀረበ እንደሆነ
ጉዳዩ አንዲታይና ውሳኔ እንዲሰጥበት በተዘዋዋሪ የተስማማ
እንደሆነ በዝምታ ፈቃዱን እንደሰጠ ተቆጥሮ ፍ/ቤቱ የሚሰጠው
ውሳኔ በተከራካሪዎች ላይ አስገዳጅነት ይኖረዋል፡፡
 የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን የሌለው ፍ/ቤት የላከለትን መጥሪያ
ባለመቀበል ፍ/ቤት ያልቀረበ ተከሳሽ ላይ ፍ/ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ
አስገዳጅነት እንዴት ይታያል?
 የፍ/ቤት የግዛት ነገር ስልጣን በፍትሕብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን
ከአንቀጽ 19-30 ባሉት ድንጋጌዎች ተደንግጎ ይገኛል፡፡
 ይህ አይነቱ የፍ/ቤት የዳኝነት ሥልጣን አንድን ጉዳይ ተመልክቶ
ውሳኔ ለመስጠት የስረ-ነገር ሥልጣን ካላቸው ፍ/ቤቶች መካከል
በየትኛው ፍ/ቤት ሊታይ እንደሚገባ የሚወስን የዳኝነት ሥልጣን
አይነት ነው፡፡
 የዚህም የዳኝነት ሥልጣን አስፈላጊነት፣ ሌሎች ሁኔታዎች እንዳሉ
ሆኖ፣ በመርህ ደረጃ ለተከራካሪ ወገኖች በተለይም ለተከሳሹ
ማስረጃውን ለማቅረብና ክርክሩንም በተመቼ ሁኔታ ለማከናወን
እንዲያስችለው ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
 በመርህ ደረጃ የፍ/ቤቶች የግዛት ክልል ስልጣን በፍትሐ ብሄር ስነ-
ስርዓት ህጋችን አንቀጽ 19(1) እና (2) ላይ በግልጽ የተደነገገ ሲሆን
በዚህም መሰረት በህግ በሌላ መልኩ እስካልተደነገገ ድረስ
ማናቸውም ክስ መቅረብ የሚገባው ተከሳሹ ወይም ተከሳሾቹ
ከአንድ በላይ በሚሆኑ ጊዜ ከተከሳሾቹ አንዱ በሚኖርበት ወይም
ለግል ጥቅሙ በሚሰራበት ክፍል በሚያስችለው ባለስልጣን ፍ/ቤት
ነው፡፡
 ከዚህ ድንጋጌ አቀራረጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ሥነ-ሥርዓት
ህጋችን የግዛት ክልል ስልጣንን በመወሰን ረገድ ከላይ ለማመልከት
እንደተሞከረው በመርህ ደረጃ ተከሳሹን ማዕከል ያደረገ መሆኑን
ለመገንዘብ ይቻላል፡፡
 ይህም የሆነበት ምክንያት የተለያየ ቢሆንም በዋናነት ግን በአንድ
በኩል ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ ተገቢ የሚላቸውን የሰውና የሰነድ
ማስረጃ በማቅረብ በቀላሉ ለመከላከል እንዲችል ሲሆን ሌላውና
ዋናው ምክንያት ሊሆን የሚችለው ፍ/ቤቱ በቀረበው ክስ ላይ
በተከሳሹ ላይ ፍርድ ቢሰጥ ፍርዱን በቀላሉ ማስፈጸም እንዲቻል
ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል፡፡
 የመርሁ ልዩ ሁኔታዎች የክስ ምክንያትን መነሻ በማድረግ ሊታዩ
የሚገባቸው በየትኛው ፍ/ቤት መሆን እንዳለበት በፍትሕብሔር
ሥነ-ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 20 እና ተከታዮቹ ተመልክተዋል፡፡
 በልዩ ሁኔታ የተዘረዘሩትን ጉዳዮች ክሱን ለማየት በህጉ የግዛት ክልል
ሥልጣን ለተሰጠው ፍ/ቤት መቅረብ ያለበት መሆኑን እንዲሁም
ፍ/ቤቶች የቀረበላቸው በህጉ አግባብ መሆኑን የማረጋገጥ ሀላፊነት
ይኖርባቸዋል፡፡
 ይሁን እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 20 እና ተከታዩቹ ክሱ ተከሳሹ
ከሚኖርበት ወይም ለግል ጥቅሙ ከሚሰራበት ቦታ በተጨማሪ
በሌላ ቦታ ክስ ማቅረብ እንደሚቻል ተደንግጎ ከተገኘ (ቁጥር 24(1)
እና 27) ክሱ በከሳሹ ምርጫ ከሁለት በአንዱ ክስ የመመስረት
መብት ያለው መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
 ሌላው እዚህ ጋር ሊነሳ የሚገባው ነጥብ በህጉ አንቀጽ 29 ላይ
የተመለከተው የልዩ ሁኔታዎቹ ልዩ ሁኔታ ነው፡፡
 በዚሁ ድንጋጌ እንደተመለከተው ከአንድ የክስ ምክንያት በላይ የሆኑ ክሶች
ተጣምረው የሚቀርቡ እንደሆነና የክስ ምክንያቶቹ ከአንድ በላይ በሆኑ
የፍ/ቤት የግዛት ሥልጣን ስር የሚወድቁ ከሆነ የአንዱን የክስ ምክንያት
ለማየት በሚችለው ፍ/ቤት ቀርቦ ሊታይ የሚችል መሆኑን ነው፡፡
 ይህን በምሳሌ ለመግለጽ ያህል በተለያየ የፍ/ቤት የግዛት ሥልጣን ስር
የሚወድቁ የውልና ከውል ውጪ ሃላፊነት ክሶች ተጣምረው ቢቀርቡ
በህጉ አንቀጽ 24 ወይም 27 በተደነገገው በአንዱ የፍ/ቤት የግዛት
ሥልጣን መቅረብና መዳኘት የሚችሉበት አግባብ ነው፡፡
 የግዛት ክልል ሥልጣኑ ያልሆነ ክስ የቀረበለት ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ
10(1) አግባብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231(1) (ለ) መሠረት ሥልጣን
የሌለው መሆኑን በመግለፅ መዝገቡን መዝጋት ይኖርበታል፡፡
 ይሁንና በግዛት ክልል ሥልጣኑ የማይወድቅ ክስ የቀረበለት ፍ/ቤት
በቸልተኝነትም ሆነ በአተረጓጎም ችግር ከላይ በተጠቀሰው የሥነ-ሥርዓት
ህጉ አግባብ የክስ መዝገቡን ያልዘጋው እንደሆነ ተከሳሹ በሚያቀርበው
የመልስ ማመልከቻ ላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244(2)(ሀ) መሠረት
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 ይህ መቃወሚያ መቅረብ በሚገባው ጊዜ ካልቀረበ የግዛት ክልል ሥልጣን
አለመኖር ትክክለኛ ፍርድን ለመስጠት የሚያሰናክል ባለመሆኑ ተከሳሹ
እንደተወው ከሚቆጠሩት የመቃወሚያ ምክንያት አንዱ በመሆኑ ዘግይቶ
የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 መቅረብ በሚገባው ጊዜ መቃወሚያው ቀርቦ እንኳ ፍ/ቤቱ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 245 መሠረት ህጉን በተሳሳተ መንገድ ተርጉሞ
ሥልጣን አለኝ ብሎ ክርክሩን ቢቀጥል እና በመጨረሻም በዋናው
ነገር ላይ ውሳኔ ከሰጠ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 10 (2) መሰረት የግዛት
ክልል ሥልጣን በሌለው ፍ/ቤት በመታየቱ የተነሣ ፍትህ የተጓደለበት
መሆኑን ተከሳሹ ካላረጋገጠ በቀር የግዛት ክልል ሥልጣን በሌለው
ፍ/ቤት ታይቶ የተሰጠ ውሳኔ መሆኑን ብቻ መሠረት በማድረግ
ይግባኝ ሊቀርብበት አይችልም፡፡
 የፍ/ቤት የስረ-ነገር ስልጣን ማለት አንድን ጉዳይ በትክክል
ተመልክቶ አግባብነት ያለው፤ ፍትህን ያገናዘበ ፍርድ ለመስጠት
አቅም ያለው ፍ/ቤት የትኛው ነው የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ
የስልጣን አይነት ነው፡፡
 ይህ የስልጣን አይነት በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ ፍ/ቤቶች የዳኝነት
ሥራን የሚያከፋፍል ነው፡፡
 በዚህም ከፍ ያለው ጉዳይ በየደረጃው ከተቋቋሙት ፍ/ቤቶች
መካከል ከፍ ባለው እንዲሁም ቀለል ያሉ ጉዳዮች በዝቅተኛ እርከን
ላይ በሚገኙ ፍ/ቤቶች እንዲታዩ በማድረግ ፍትሃዊነት ያለው ፍርድ
መስጠትን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
 የፍ/ቤት የስረ ነገር ስልጣን በሁለት መልኩ ይወሰናል፡፡
 የመጀመሪያው በጉዳዩ አይነት ሲሆን ይህም ማለት የጉዳዮችን
ኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ ማህበራዊ ፋይዳ፣ ፖለቲካዊ አንድምታ
እንዲሁም ውስብስብነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ያላቸው
የገንዘብ መጠን ምንም ይሁን የሚዳኙበትን የፍርድ ቤት እርከን
በግልጽ ድንጋጌ የሚቀመጥበት አኳኋን ነው፡፡
 ሌላውና ሁለተኛው የፍ/ቤት የስረ-ነገር ስልጣን በክርክሩ ዳኝነት
የተጠየቀበትን የገንዘብ መጠን መሰረት በማድረግ ጉዳዩ በየትኛው
የፍ/ቤት እርከን እንደሚታይ የሚወሰንበት አግባብ ነው፡፡
 በክልላችን የሚገኝ አንድ ፍ/ቤት የቀረበለትን የፍትሃ ብሄር ጉዳይ
ከመመልከቱ በፊት የሥረ-ነገር ሥልጣን ያለው መሆኑን ሶስት ሁኔታዎችን
መሰረት በማድረግ መመርመር ይኖርበታል፡፡
 1ኛ. የቀረበለት ጉዳይ በመደበኛ ፍ/ቤት ሊታይ የሚቸል ነው ወይስ ሌላ
የዳኝነት አካል ይህንኑ ጉዳይ ለማየት በህግ ስልጣን ተሰጥቶታል
የሚለውን ነው፡፡
 በተለያዩ ህጎች የአስተዳደር ፍ/ቤት እንዲቋቋም በማድረግ የተለዩ
ጉዳዮችን እንዲመለከቱ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡
 ለምሳሌ ከግብር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን የሚመረምር የግብር
ይግባኝ ኮሚሽን፣ የመንግስት ሰራተኞችን ከስራቸው ጋር በተያያዘ
የሚነሱ ጥፋት ነክ ጉዳዮችን በመመርመር ውሳኔ ለመስጠት
የተቋቋመውን የሲቪል ሰርቪስ ፍ/ቤትን እንዲሁም በአሰሪና ሰራተኛ
አዋጅ ቁጥር 377/96 የሚተዳደሩ ሰራተኞችን በተመለከተ የሚነሳ የወል
የስራ ክርክርን የሚመለከተውን የስራ ክርክር ቦርዱን መጥቀስ ይቻላል፡፡
 2ኛ. ፍ/ቤቱ የቀረበለት ጉዳይ በፌደራል ወይም በክልሉ የዳኝነት
ሥልጣን ስር የሚወድቅ መሆኑን መለየት ይኖርበታል፡፡
 ይህም በተለይ በአሁኑ ጊዜ ከምንከተለው የፌደራል መንግስት
አወቃቀር አንጻር በኢፌደሪ ህገመንግስት አንቀጽ 50 መሰረት
የፌደራልና የክልል መንግስታት እንደሚኖሩና ሁለቱም መንግስታት
የራሳቸው ሶስት እርከን ያለው ፍ/ቤት እንደሚኖሯቸው ተደንግጓል፡፡
 ከዚህም በተጨማሪ በዚሁ ህገመንግስት አንቀጽ 80(1) እና (2) ላይ
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፌደራል ጉዳይ እንዲሁም የክልል
ጠቅላይ ፍ/ቤት በክልል ጉዳይ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጡ
ተደንግጓል፡፡
 ይህም የህገመንግስቱ አቀራረጽ በፌደራሉና በክልል መንግስታት
የሚቋቋሙ ፍ/ቤቶች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ሥልጣን
እንዳላቸው የሚገልጽ ነው፡፡ በመሆኑም በክልላችን የሚገኙ
ፍ/ቤቶች ለመዳኘት ሥልጣን የተሠጣቸውን ጉዳዮች ለይተው
ሊያውቁ ይገባል፡፡
 በፍሕብሔር ጉዳይ የሁለቱን መንግስታት በተለይም የፌደራል
መንግስቱንና የክልላችንን ፍ/ቤቶች የዳኝነት ሥልጣን ወሰንን
የፌደራል ፍ/ቤቶችን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 እንዲሁም
የአብክመ የፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 223/2007ን
በመመልከት በፌደራሉ ወይም በክልል የዳኝነት ሥልጣን ስር
የሚወድቁ ጉዳዮችን መለየት ይቻላል፡፡
 በዚህም መሰረት የአብክመ ፍ/ቤቶች የሚኖራቸውን የዳኝነት
ሥልጣንን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀጽ 13 (1)
ላይ በጥቅል እንደተመለከተው በግልጽ ተለይተው በፌደራሉ
መንግስት ፍ/ቤቶች ስልጣን ስር ከሚወድቁት ጉዳዮች በስተቀር
በሌሎች ጉዳዮች ላይ የመዳኘት ሥልጣን ይኖራቸዋል፡፡
 በዚህ የህጉ አቀራረብ መሰረት በክልላችን የሚገኙ ፍ/ቤቶች በምን
አይነት የፍትሃ ብሄር ጉዳዮች ላይ የመዳኘት ሥልጣን አላቸው
የሚለውን ለመረዳት የግድ ለፌደራል ፍ/ቤቶች ተለይተው
የተሰጡትን ጉዳዮች መገንዘብ የሚያስፈልጋቸው ይሆናል፡፡
 በዚህ ረገድ የፌደራል ፍ/ቤቶችን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር 25/88
በአንቀጽ 5 ላይ የፌደራል ፍ/ቤቶች የመዳኘት ሥልጣን ስር የሚወድቁ
የፍትሕብሔር ጉዳዮችን ዘርዝሮ ይደነግጋል፡፡
 እነዚህም፡- ከተከራካሪ ወገኖች ማንነት አንጻር፡ የፌደራል መንግስቱ አካል
ተከራካሪ በሆነበት ጉዳይ፣ መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልሎች ውስጥ
በሆኑ ሰዎች መካከል በሚነሱ ክርክሮች፣ የፌደራል መንግስቱ ባለስልጣኖችና
ሰራተኞች በስራቸው ወይም በሀላፊነታቸው ምክንያት ተጠያቂ
በሚሆኑባቸው ጉዳዮች፣ የውጭ ሀገር ዜጋ ተከራካሪ በሆነበት ጉዳይና
በፌደራል መንግስቱ አካላት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ የንግድ
ድርጅቶችና ማህበሮችን በሚመለከት በሚነሱ ክርክሮች፤ እንዲሁም
 ከአከራካሪው ጉዳይ አኳያ፡- በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች፣
በፈጠራ፣ በድርሰትና በስነ-ጥበብ ባለቤትነት መብቶች፣
በኢንሹራስ ውል ላይ በሚነሱ ክርክሮችና ተገዶ የመያዝ
ህጋዊነትን ለማጣራት በሚቀርብ አቤቱታ ላይ አከራክሮ ውሳኔ
ለመስጠት ብቸኛ ሥልጣን ያለው የፌደራል ፍ/ቤት እንደሆነ
ተደንግጓል፡፡
 ከላይ የተመለከቱትን ጉዳዮች የክልላችን ፍ/ቤቶች በኢፌዲሪ
ህገመንግስት አንቀጽ 80(2) እና(4) መሰረት በውክልና ለመዳኘት
ከሚችሉ በስተቀር በቀጥታ የመዳኘት ሥልጣን አይኖራቸውም፡፡
 አንድ ጉዳይ በክልሉ ፍ/ቤቶች ሊታይ የሚችል መሆኑ ከተረጋገጠ
በሶስተኛ ደረጃ ፍ/ቤቱ ሊያጤነው የሚገባው ነገር በየትኛው የክልሉ
ፍ/ቤት እርከን ጉዳዩ ታይቶ ውሳኔ ሊያገኝ ይገባል የሚለው ይሆናል፡፡
 ይህም በሁለት መልኩ የሚወሰን ሲሆን ይሄውም በጉዳዩ አይነት
ወይም የክስ አቤቱታው በያዘው የገንዘብ መጠን ነው፡፡ የአብክመ
የፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 223/2007 የፍ/ቤቶችን የሥረ-
ነገር ሥልጣንን በዋናነት የወሰነው የክርክሩ የገንዘብ መጠንን
መሰረት በማድረግ ነው፡፡
 በዚህም መሰረት የአዋጁ አንቀጽ 13 (2) እንደደነገገው
በሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ እስከ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ)
እንዲሁም በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ እስከ ብር 500,000
(አምስት መቶ ሺህ) እንዲሁም ከጉዳዮች አይነት አኳያ በዚሁ የአዋጁ
ድንጋጌ 13(3) መሰረት ወላጅነትን፣ አካልን ነጻ ማውጣትና ሌሎች
ዋጋቸው በገንዘብ በማይተመን የፍትሕብሔር ጉዳዮች ላይ የሚነሱ
ክርክሮችን አከራክሮ የመወሰን የሥረ-ነገር የዳኝነት ሥልጣኑ የወረዳ
ፍ/ቤቶች እንደሆነ ተደንግጓል፡፡
 የክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤቶች በውክልና የመዳኘት ሥልጣን ከተሰጣቸው
የፌደራል ጉዳዮች ውጪ በጠቅላላው በክልሉ ጉዳዮች የዳኝነት የስረ-
ነገር ሥልጣናቸው የተወሰነው በክርክሩ የገንዘብ መጠን ላይ ነው፡፡
 ከዚህ አንጻር ከላይ የተመለከተው አዋጅ አንቀጽ 15 ንዑስ ቁጥር (2)
እንደሚደነግገው የክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤቶች በሚንቀሳቀስ ንብረት
ላይ ከብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) እንዲሁም በማይንቀሳቀሱ
ንብረቶች ላይ ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ በሚነሱ
ክርክሮች ላይ የሥረ-ነገር የዳኝነት ሥልጣናቸው የተወሰነ ነው፡፡
 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 9(1) ላይ እንደተመለከተው የስረ-ነገር
የዳኝነት ስልጣን በሌለው ጉዳይ ላይ የክስ አቤቱታ የቀረበለት
ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231 በተነገረው ድንጋጌ መሰረት
ማመልከቻው ተቀባይነት የለውም በማለት መመለስ እንዳለበት
አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡
 በዚሁ ድንጋጌ መሰረትም የቀረበውን የገንዘብ ክስ ለመቀበል
የዳኝነት ስልጣን ያለው መሆኑን ፍ/ቤቱ የሚወስነው ከቁጥር 226-
228 የተመለከተውን ድንጋጌ በመከተልና በማመልከቻው ላይ
የተገለጸውን መሰረት በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 16(2) በግልጽ ይደነግጋል፡፡
 በመሆኑም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 16ም ሆነ ከ226-228
በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት የፍ/ቤቶች የሥረ-ነገር ሥልጣን
የሚወሰነው ከሳሹ በአቤቱታው ላይ በሚጠይቀው የገንዘብ መጠን
ላይ ነው፡፡
 ከዚህ በተለየ ከሳሽ በክሱ ላይ የጠቀሰውን የገንዘብ መጠን
ለመዳኘት የስረ-ነገር ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት አቤቱታውን ተቀብሎ
ተከሳሽን ከጠራ በኋላ ባለው የክርክሩ ሂደት የፍ/ቤቱ የስረ-ነገር
ሥልጣን ሊቀየር የሚችልባቸው ሶስት ሁኔታዎች በሥነ-ሥርዓት ህጉ
ላይ ይገኛሉ፡፡
 የመጀመሪያው ተከሳሹ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 250 መሰረት ከሳሽ
በአቤቱታው ላይ ያቀረበው የንብረት ግምት ላይ የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ ያቀረበ እንደሆነና ፍ/ቤቱም በመቃወሚያው መሰረት
የንብረቱን ትክክለኛ ዋጋ እንዲያጣራ በሚሾመው አካል ሲጣራ
የፍ/ቤቱን ሥረ-ነገር ሥልጣን የሚቀይር ከሆነ ነው፡፡
 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 250 ፍ/ቤቱ አከራካሪውን ንብረት ግምት ከተከሳሹ
መቃወሚያ ሲቀርብ በመቃወሚያው መሰረት ፍ/ቤቱ እንዲጣራ
ያደርጋል ከማለት ውጪ በተለይም በማጣራት ሂደት የአከራካሪው
ንብረት ግምት የፍ/ቤቱን ስልጣን የሚቀይር ቢሆን ምን አይነት ትእዛዝ
ሊሰጥ ይገባል በሚለው ላይ ምንም የሚለው ባይኖርም ሥልጣኑ
ያልሆነውን ነገር ሊመለከትና የጸና ፍርድ ሊሠጥ ስለማይችል መዝገቡን
ሥልጣን የሌለው መሆኑን ገልጾ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 245 መሰረት
መዝጋት ይኖርበታል፡፡
 ሌላውና ሁለተኛው ሁኔታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 16 (3) መሰረት ክሱ
ቀርቦ የማስረጃው መሰማት ከመጀመሩ በፊት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 242
እና 243 አግባብ አንደኛው ወገን የቀረበበትን ክስ በከፊል በማመኑ
ምክንያት በክሱ ላይ የተመለከተው የገንዘብ ልክ የተቀነሰ እንደሆነ ፍ/ቤቱ
ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው በተቀነሰው መጠን ስልጣን ላለው ፍ/ቤት
ያስተላልፈዋል ወይም ራሱ ማስረጃውን በመቀበል ውሳኔ ሊሰጥበት
የሚችልበት ሁኔታ ነው፡፡
 ሶስተኛው ሁኔታ አቤቱታ ማሻሻልን ተከትሎ የሚመጣ የፍ/ቤት
የስረ-ነገር ሥልጣን መቀየር ነው፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(5)
መሰረት በተለይም የአቤቱታ ማሻሻያው የፍ/ቤቱን የሥረ-ነገር
ሥልጣን ወደ ከፍያለው ፍ/ቤት የሚቀይር ከሆነ ክሱን የሚያየው
ፍ/ቤት ይህንኑ ክስ ለመመልከት ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ማስተላለፍ
እንደሚገባው ይደነግጋል፡፡
 የስረ-ነገር ሥልጣኑ ያልሆነ ክስ የቀረበለት ፍ/ቤት
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231(1)(ለ) መሰረት ሥልጣን የሌለው መሆኑን
ገልጾ መዝገቡን ያልዘጋና ተከሳሹ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት
ያላነሳው ቢሆንም እንኳ በየትኛውም የክርክሩ ደረጃ በተከሳሹ
ጠያቂነትም ሆነ በፍ/ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት መዝገቡን መዝጋት
ይኖርበታል፡፡
 ምክንያቱም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244(3) እንደተመለከተው አቅም
የሌለው ፍ/ቤት ፍትህን ያገናዘበ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ
ስለማይገመትና በዚህም የተነሣ የሥረ-ነገር ሥልጣን አለመኖር
ትክክለኛውን ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክል ሆኖ ስለሚገኝ
በመቃወሚያ ማቅረቢያ ጊዜ ባይቀርብም እንደተተወ
ከማይቆጠሩትና ከፍርድ በፊት በማናቸውም ጊዜ ሊቀርቡ
ከሚችሉት የመቃወሚያ ዓይነቶች አንዱ በመሆኑ ነው፡፡
 በዚህ አኳኋን ሳይታረም ሙሉ ክርክር ተደርጎ ማስረጃ ተሰምቶ
የተወሰነ መሆኑ፤ እንዲሁም የይግባኝ መብቱ እስከፈቀድ ድረስ
በየደረጃው ታይቶ ውሳኔ ያረፈበት መሆኑ ቢታወቅም፤ የሥረ-ነገር
ሥልጣን ጉዳይ ሊጣስ የማይገባው የመርህ ጥያቄ እንደመሆኑ
መጠን በየደረጃው በነበረው ክርክር የታየው ወጭ የባከነው ጊዜና
ድካም ግምት ውስጥ ሳይገባ በመጨረሻው በሰበር ደረጃም ቢሆን
ሊሻር የሚችል መሆኑ ሊተኮርበት የሚገባው ነጥብ ነው፡፡
 ነገር ግን አንድ ጉዳይ የስረ-ነገር ሥልጣኑ ያልሆነ ፍ/ቤት ተመልክቶ
ውሳኔ የሰጠ እንደሆነና ይሄው ውሳኔ በይግባኝ እስካልተሻረ ድረስ
ውሳኔው የሚጸና መሆኑ ነው፡፡
 በኢትዮጵያ የፍታብሔር የፍትህ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ በህግ
ፊት የማይጸና ወይም ፍርስ (null and void) የሚባል ውሳኔ
እንደሌለ በግልጽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 212 ላይ ተደንግጓል፡፡ በዚሁ
አግባብም የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 15
በሰበር መዝገብ ቁጥር 85718 ላይ በግልጽ ውሳኔ ሰጥቶ እናገኛለን፡፡
 ከስረ-ነገር ሥልጣን ጋር በተያያዘ በተግባር ከሚታዩ ችግሮች መካከል
አንዱ የክሱ ምክንያት የሆነው ነገር በገንዘብ ተገምቶ መቅረብ
እየቻለ አንዳንድ ክስ አቅራቢዎች በገንዘብ ሊገመት አይችልም
በማለት በፍትሕብሔር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 18 መሰረት ክስ
ሲያቀርቡና ፍ/ቤቶችም የክሱን አርዕስት ብቻ በመመልከት ክሱን
ተቀብለው አከራክረው ውሳኔ ሲሰጡ ይታያል፡፡
 እንዲህ አይነቱ የክስ አቀራረብ አንድም ባለማወቅ የሚቀርብ ሲሆን፣
አንዳንድ ከሳሾች ግን ሆነ ብለው የክሱ ምክንያት ተገምቶ ቢቀርብ
ጉዳዩ ከፍ ባለው ፍ/ቤት የሚታይ እንደሆነ በመረዳት ሥልጣን
በሌለው ፍ/ቤት ውሳኔ በማሰጠት የፍርድ ባለመብት ለመሆን
በማሰብ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ተገቢውን የፍ/ቤት የአገልግሎት
ክፋያ ላለመክፈል በሚል የሚያደርጉት የክስ አቀራረብ ነው፡፡
 በዚህ አግባብ ከሚቀርቡ ክሶች መካከል ከገጠር የመሬት ሁከት
ይወገድልኝ ክስ ጋር አብረው የሚያቀርቡት የአለባ ግምት ጥያቄ
ከመሬቱ ጋር በአንቀጽ 18 መሰረት የሚቀርብበት ሁኔታ፤ በገንዘብ
ተገምተው ሊቀርቡ የሚችሉ ንብረቶች ላይ ሁከት ተፈጽሞብኛል
በሚል የሚቀርቡ ክሶች፣ እንዲሁም ከውል ጋር በተያያዘ ውል
ይፍረስልኝ፣ ይፈጸምልኝና የመሳሰሉት በተደጋጋሚ በፍ/ቤቶች
ቀርበው ተገቢው የፍ/ቤት አገልግሎት ክፍያ ሳይፈጸምባቸው
አንዳንድ ጊዜም ሥልጣን በሌለው ፍ/ቤት ውሳኔ የሚያገኙ ጉዳዮች
ናቸው፡፡
 አንድ ክስ ለክርክር ችሎት ፊት ከመቅረቡ በፊት ሊከናወኑ
የሚገባቸው የተለያዩ የሥነ-ሥርዐት ደንቦችን አሟልቶ ማለፍ
ይኖርበታል፡፡
 እነዚህን የሥነ-ሥርዓት ደንቦች በዋናነት በሁለት ከፍሎ መመልከት
የሚቻል ሲሆን ይሄውም የአቤቱታ አቀራረብና የመጥሪያ አደራረስ
ደንቦች ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህም ሥነ-ሥርዐታዊ ደንቦች
በሚከተለው መልኩ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
 ማንኛውም የፍታብሄር ጉዳይ ወደ መደበኛ ክርክር የሚገባው ከሳሽ
ያቀረበውን የክስ አቤቱታ ፍ/ቤቱ ተቀብሎ ተከሳሹ በቀረበበት ክስ
ላይ ቀርቦ መልስ እንዲሰጥበት ሲያደርግ ነው፡፡
 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 80(1) ላይ እንደተመለከተው አቤቱታ ማለት
የክስ ማመልከቻ፣ የመልስ ማመልከቻ፣ የይግባኝ ማመልከቻ፣
ሌሎች ማመልከቻዎች፣ አቤቱታዎችና ሌላ ማንኛውም የክስ መነሻ
ሊሆን የሚችልና ለዚሁ ክስ መልስ የሚሆን ሰነድ ሁሉ አቤቱታ
ማለት እንደሆነ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡
የቀጠለ
 ከዚህ ትርጉም ለመረዳት እንደሚቻለው አንድ ለፍ/ቤት የሚቀርብ
ማመልከቻ ለክስ መነሻ ወይም ለቀረበ ክስ መልስ ያልሆነ
ማንኛውም ማመልከቻ አቤቱታ እንደማይባል ነው፡ በመሆኑም
እንደ በአደራ የተያዘ ገንዘብ እንዲለቀቅ እና የውሳኔ ግልባጭ
መጠየቂያ ማመልከቻዎች ወይም ሰነዶች በአቤቱታ ውስጥ
የማይጠቃለሉ እንደሆኑ ነው፡፡
 አንድ የክስ አቤቱታ ተሟልቶ መቅረቡ የተለያዩ ጥቅሞች ያሉት
ሲሆን በተለይም ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ በመረዳት መልሱን ከክሱ
አንጻር እንድያዘጋጅ ከመርዳቱም ባሻገር በፍ/ቤቱ የሚደረገውን
የክርክር አድማስ መወሰኑ በአንድ በኩል እንዲሁም የግራ ቀኙ
አቤቱታዎች በአግባቡ ተዘጋጅተው መቅረባቸው ፍ/ቤቱ በምርመራ
ጊዜ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርግና አግባብነት ያላቸውን
ጭብጦች እንዲይዝ በማድረግ የተፋጠነ ውሳኔ እንዲሰጥ ያስችላል፡፡
 ከላይ ከተጠቀሱት የአቤቱታ አይነቶች መካከል የክስ አቤቱታና
የመልስ አቤቱታ በፍ/ቤት ተቀባይነት እንዲኖራቸው ሊያሟሏቸው
የሚገቡ ነገሮች ምንድን ናቸው ሊሟሉ የሚገባቸው ነገሮች
ተሟልተው ያልተገኙ እንደሆነ የአቤቱታዎቹ እጣ ፋንታ ምን ሊሆን
ይችላል የሚሉትን ሁኔታዎች በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 213 መሰረት አንድ የክስ አቤቱታ በፍ/ቤቱ
ተቀባይነትየሚኖረው አቤቱታው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 80-93 እና
222-232 የተመለከቱትን ነገሮች አሟልቶ የቀረበ እንደሆነ ነው፡፡
 የክስ አቤቱታ ሲዘጋጅ ሊይዛቸው የሚገቡ ነገሮች ከላይ በተጠቀሱት
ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ የሚገኝ ሲሆን ስድስት ዋና ዋና ነገሮችን
የሚያካትት ነው፡፡
 የመጀመሪያው በክስ ላይ ሊካተት የሚገባው የክሱ መግቢያ
ማለትም ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ስምና አድራሻ፣ የከሳሽ-ተከሳሽ
ስምና አድራሻ፣ የክሱ አርእስት፣ ከሳሹ/እናተከሳሹ ክስ ለማቅረብ
ችሎታ የሌላቸው እንደሆነ ይህንኑ የሚገልጽ ነገር እንዲሁም ከሳሹ
በውክልና ክሱን ያቀረበ እንደሆነ ይህንኑ መግለጽ በመጀመሪያው
ክፍል የሚካተቱ ናቸው፡፡
 ከነዚህ ነገሮች መካከል አንዳንዶቹ የግድ በየትኛውም የክስ አቤቱታ
ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው ነገሮች ሲሆኑ ከፊሎቹ ደግሞ እንደ
አስፈላጊነቱ በክስ አቤቱታ ውስጥ ሊካተቱ የሚገቡ ነገሮች ናቸው፡፡
 እንደ አስፈላጊነቱ በክስ ውስጥ ሊጠቀሱ ከሚገባቸው ነገሮች
መካከል ለምሳሌ ብንመለከት የከሳሽ/ተከሳሽ ችሎታ አለመኖር
አንዱ ሲሆን እንዲህ አይነቱ ነገር ሊጠቀስ የግድ የሚለው
ከከሳሽ/ተከሳሹ አንዱ ወይም ሁለቱም ችሎታ የሌላቸው እንደሆነ
ነው፡፡
 ማንኛውም ሰው ችሎታ እንደሌለው እስካልተረጋገጠ ድረስ ችሎታ
እንዳለው የህግ ግምት እንደሚወሰድበት በፍትሃ ብሔር ህጋችን
አንቀጽ 196 ላይ በግልጽ ተመልክቷል፡፡
 በመሆኑም ከሳሹ በክስ አቤቱታው ላይ ችሎታን አስመልክቶ ምንም
ያላለ እንደሆነ ችሎታ ያለው መሆኑን ግምት መውሰድ ይኖርበታል፡፡
ይሁንና በሁሉም የክስ ማመልከቻዎች በሚባል ደረጃ “ችሎታ አለኝ”
በሚል ይገለጻል፡፡
 ከሳሽ ይህንን በክሱ አቤቱታ ላይ ያልገለጸ እንደሆነ እንኳ የፍ/ቤቱ
የመዝገብ ቤት ሹም ክሱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 222 መሰረት
ያልተሟላ መሆኑን በመግለጽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 229/ሀ/
መሰረት የክስ አቤቱታውን ብዙ ጊዜ አይቀበልም፡፡
 በመሆኑም የፍ/ቤት የመዝገብ ሹሞች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠቀሱ
የሚገባቸው ነገሮች በሁሉም የክስ አቤቱታዎች ካልተጠቀሱ
አቤቱታዎቹ ተቀባይነት የላቸውም በማለት ውድቅ የሚያደርጉበት
አሰራር ሊስተካከል ይገባል፡፡
 ሁለተኛው በክስ አቤቱታ ውስጥ ሊመለከት የሚገባው ነገር የክሱ
ምክንያት ነው፡፡ አንድ ክስ ተቀባይነት እንዲኖረው የክስ ምክንያት
ሊኖረው ይገባል፡፡ የክሱ ምክንያትም የሚገለጸው በክሱ ፍሬነገር ዝርዝር
ላይ ነው፡፡
 የአንድ ክስ አቤቱታ የክስ ምክንያት ያለው መሆኑን ለመወሰን ፍ/ቤቶች
የቀረበላቸው አቤቱታ የክስ ምክንያት አለው ወይም የለውም ብሎ
ለመወሰን በክስ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሽ የሆነው ወገን
የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ህግ ይፈቅድለታል ወይስ አይፈቅድለትም
የሚለውን ጥያቄ መመርመር ያለባቸው መሆኑን የፌደራሉ ጠቅላይ
ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 45247 የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡
 ይህንኑ መሰረት በማድረግ ፍ/ቤት የቀረበለትን የክስ አቤቱታ ሲመረምር
የክስ ምክንያት የሌለው ሆኖ ካገኘው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231(1-ሀ)
መሰረት አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
 አንድ የክስ አቤቱታ ሊይዘው የሚገባው ሶስተኛው ነገር ክሱ
የቀረበለት ፍ/ቤት ክሱን ለመመልከት ሥልጣን ያለው መሆኑን
ማሳየት ነው፡፡
 የፍ/ቤት ሥልጣን በክፍል አንድ ላይ ለመመልከት እንደሞከርነው
ሶስት አይነት የፍ/ቤት የሥልጣን አይነቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህ
መካከል አንዱ እንኳ የሌለው መሆኑን ፍ/ቤቱ ከተረዳ ክሱን
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231(1-ለ) መሰረት ውድቅ ማድረግ
ይኖርበታል፡፡
 የፍ/ቤትን ሥልጣን በተመለከተ ለፍ/ቤት በሚቀርቡ ክሶች/መልሶች
ላይ በተመሳሳይ “ፍ/ቤቱ ይህንን ጉዳይ ተመልክቶ ውሳኔ የመስጠት
ሥልጣን አለው” በሚል ይገለጻል፡፡ በዚህ መልኩ ሳይገለጽ የክስ
ማመልከቻው ለፍ/ቤቱ ቢቀርብ እንኳ የፍ/ቤቱ የመዝገብ ቤት ሹም
ክሱ ማሟላት የሚገባውን ነገር አላሟላም በሚል ክሱን
አይቀበለውም፡፡
 ነገር ግን በክስ ማመልከቻ ላይም ሆነ በመልስ ላይ በዚህ አግባቡ ፍ/ቤቱ
ሥልጣን አለው በሚል መገለጹ ፍ/ቤቱ በቀረበው ጉዳይ ላይ ሥልጣን
አይሰጠውም፡፡
 የፍ/ቤቱን ሥልጣን የሚወስነው ለምሳሌ የግዛት ክልል ሥልጣን አለው ወይንስ
የለውም የሚለውን እንደየክሱ ምክንያት አይነት የተከሳሹን አድራሻ፣ የክሱ
ምክንያት የተፈጸመበትን ቦታ፣ አከራካሪው ጉዳይ የሚገኝበትን ቦታ ወይም
የማስረጃ ዝርዝሩን በመመልከት ሊወሰን ከሚችል በቀር ፍ/ቤቱ ሥልጣን አለው
ስለተባለ ብቻ ፍ/ቤቱ ሥልጣን አይኖረውም፡፡
 በመሆኑም የፍ/ቤት የመዝገብ ቤት ሹሞች “ፍ/ቤቱ ሥልጣን አለው” በሚል
ያልተገለጸ እንደሆነ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በሚል ውድቅ
የሚያደርጉበት አሰራር ሊታረም ይገባል፡፡
 አንድ አቤቱታ ሊይዘው የሚገባው አራተኛ ነገር የሚጠይቀውን ዳኝነት ነው፡፡
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 224 መሰረት አቤቱታ አቅራቢው ቢወሰንለት ፍ/ቤቱ
እንዲሰጠው የሚፈልገውን ዳኝነት በዝርዝርና ግልጽ በሆነ ሁኔታ ማስቀመጥ
እንዳለበት ይደነግጋል፡፡
 ዳኝነቱንም ሲጠይቅ አቤቱታው የተለያዩ የክስ ምክንያቶችን መሰረት አድርጎ
የቀረበ እንደሆነ ለቀረቡት እያንዳንዱ የክስ ምክንያቶች የሚፈልገውን ዳኝነት
በግልጽ ማመልከት ይኖርበታል፡፡
 ከዚህ ውጪ በጥቅል የሚቀርብ ዳኝነት ለምሳሌ ከውል ውጪ በደረሰ
ጉዳት የቀረበ የክስ አቤቱታ የደረሰበትን ጉዳት ዘርዝሮ ዳኝነቱ ላይ ካሳ
ይከፈለኝ ብሎ ቢያቀርብ የዳኝነቱ አቀራረብ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 አምስተኛው ነጥብ አቤቱታው በእውነት የቀረበ መሆኑ መረጋገጥና ፊርማ
በአቤቱታው ውስጥ ሊካተት የሚገባው ነው፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 92
መሰረት በህግ በግልጽ በሌላ በኩል እስካልተደነገገ ድረስ ማንኛውም
አቤቱታ በእውነት የቀረበ መሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
 በተመሳሳይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 93 መሰረት ማንኛውም አቤቱታ
መፈረም ይኖርበታል፡፡ የአቤቱታው መረጋገጥ በዋናነት አስፈላጊ
የሚሆነው በሀሰት የቀረበ እንደሆነና ይህም ተጠያቂነት የሚያስከትል
ከሆነ በህግ አግባብ ሀላፊነት ያለበትን ሰው ተጠያቂ ለማድረግ ነው፡፡
በመሆኑም ማንኛውም ሰው አንድን ክስ በሀሰት እንዳያቀርብ የሚያደርግ
ይሆናል፡፡
 በአግባቡ ሳይረጋገጥ የቀረበን አቤቱታ የፍ/ቤቱ የመዝገብ ቤት ሹም
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 229/ሐ/ መሰረት ውድቅ የሚያደርገው ይሆናል፡፡
 የመጨረሻው በአንድ አቤቱታ ሊካተት የግድ የሚለው የማስረጃ
ዝርዝር ነው፡፡ ይህም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 (1) ሀ እና ለ ላይ
በግልጽ እንደተመለከተው ክርክሩ በሚሰማበት ጊዜ ምስክር
ይሆኑኛል የሚላቸውን ሰዎች የስም ዝርዝር ከነአድራሻቸው
የሚጠሩበትን ምክንያት እንዲሁም ማስረጃ ይሆኑኛል የሚላቸውን
ጽሁፎች፣ ጽሁፎቹን በእጁ የማይገኙ ሲሆን የሚገኙበትን ስፍራና
በማን እጅ እንደሚገኙ በመግለጽ እንዲሁም ለክሱ መነሻ ወይም
መሰረት የሆነውን ሰነድ ዋናውን ወይም ትክክለኛ ግልባጩን አያይዞ
ካቀረበው ዝርዝር በቀር ሌላ አስረጂ ወይም ማስረጃ የሌለው
መሆኑን አረጋግጦ በማሳወቅ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ምንም አይነት
የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ የሌለው እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ
223 (1-ሐ) አግባብ ይህንኑ የሚገልጽ መግለጫ ማያያዝ
ይኖርበታል፡፡ በዚህ አግባብ ያልቀረበ የክስ አቤቱታ በፍ/ቤቱ
መዝገብ ቤት ሹም ውድቅ የሚሆን ይሆናል፡፡
 አንድ ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 229 መሰረት በመዝገብ ቤት ሹሙ
ተቀባይነት ያላገኘ እንደሆነ የመዝገብ ቤት ሹሙ የክስ አቤቱታው
ለምን ተቀባይነት እንዳላገኘ በመግለጽ ክሱንና የክሱን አባሪ ለከሳሹ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 232 (1-ሀ) መሰረት ይመልስለታል፡፡
 ከሳሹ በመዝገብ ቤት ሹሙ ምክንያት ያልተስማማ እንደሆነ
አቤቱታውን ለፍ/ቤቱ ለማቅረብ የሚችል ይሆናል፡፡
 የክስ አቤቱታውን ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231 መሰረት
ያልተቀበለው እንደሆነ ከሳሹ ለፍ/ቤቱ የከፈለው የፍ/ቤት
አገልግሎት ክፍያ በደንቡ መሰረት ተቀናሽ ተደርጎና የክስ አቤቱታው
እንዲመለስለት በማድረግ ይሄው በፍታብሔር የክስ መዝገብ ውስጥ
እንዲመዘገብ ይደረጋል፡፡
 በፍ/ቤቱ የመዝገብ ሹምም ሆነ በፍ/ቤቱ የአንድ ክስ ተቀባይነት
አለማግኘት ከሳሹ በዚያው ጉዳይ ላይ በሌላ ጊዜ ክስ ከማቅረብ
የሚከለክለው አይሆንም፡፡
 የመከላከያ መልስ አቤቱታ የሚቀርበው በተከሳሹ ሲሆን መልሱም በፍታብሔር ሕጉ
የተመለከቱትን የመልስ አዘገጃጀትና ሊይዛቸው የሚገቡ ነገሮችን ከግምት ውስጥ
በማስገባት መቅረብ ይኖርበታል፡፡ አንድ የመከላከያ መልስ በዋናነት
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 መሰረት የሚቀርብ የማስረጃን ዝርዝር ጨምሮ ሶስት
ነገሮችን የሚያካትት ይሆናል፡፡
 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 234 (1-ሀ ና ለ) መሰረት በመከላከያ መልስ ውስጥ ሊካተት
የሚገባው የመጀመሪያው ነገር መግቢያ ሲሆን በዚህም የመከላከያ መልሱ የቀረበበት
ፍ/ቤት ስምና የሚገኝበት ቦታ፣ የከሳሽ-ተከሳሽ ስምና አድራሻ እንዲሁም የመዝገብ
ቁጥርን የሚመለከቱ መግለጫዎች የሚካተቱበት ነው፡፡
 አንዳንድ ጊዜ በመከላከያ መልስ ላይ በክሱ ማመልከቻ መግቢያ የሚጠቀሱ ነገሮች ሁሉ
በተመሳሳይ ሲጠቀሱ ይታያል፡፡ ነገር ግን ይህ አይነቱ አቀራረብ የመከላከያ መልሱን
ከማንዛዛት በስተቀር የቀረበውን ጉዳይ ለመወሰን መሰረታዊ የሆነ ጥቅም የለውም
ይሁንና በአንድ መከላከያ መልስ ላይ በክስ አቤቱታ መግቢያ ላይ ሊመለከቱ
የሚገባቸው ነገሮች ተካተው ቢገኙ የመከላከያ መልሱ በአግባቡ አልቀረበም በሚል
ውድቅ ሊሆን የሚችልበት ምክንያት አይኖርም፡፡
 እንዲሁም በተመሳሳይ አንድ የመከላከያ መልስ በክስ አቤቱታ መግቢያ ላይ ሊመለከቱ
የሚገባቸውን ነገሮች አካቶ ባይቀርብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 238(3) መሰረት ፍ/ቤቱ
ተቀባይነት የለውም በሚል ውድቅ ማድረግ አይኖርበትም፡፡
 በመከላከያ መልስ ውስጥ ሊካተት የሚገባው ሁለተኛው ነገር ተከሳሹ
ለቀረበበት ክስ የሚያቀርበው መልስ ነው፡፡ ተከሳሹ እንደቀረበበት ክስ
ምንነትና የከሳሹ ማንነት እንዲሁም ካለው መከራከሪያ አንጻር የተለያየ
ይዘት ያለው መልስ ሊያቀርብ የሚችል ሲሆን ከነዚህም መካከል
የሚከተሉት በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
 ሀ. የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ/መቃወሚያዎች፤ ተከሳሹ የቀረበበት
ክስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ/መቃወሚያዎች ፍ/ቤቱ ሊዘጋው
የሚችል ከሆነ ይህንኑ ጠቅሶ በመከላከያ መልሱ ላይ በግልጽ ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡
 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 234 (1-ሐ) ላይ እንደተመለከተው ከሳሽ ህጋዊ
ችሎታ የሌለው ሲሆን፣ ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ክርክሩን ለመስማት
ሥልጣን የሌለው ሲሆን ወይም የቀረበው ክስ በይርጋ ይታገዳል የሚባል
ሲሆን ይህ የተባለበትን ዝርዝር ምክንያት የሚገልጽ ጽሁፍ በመከላከያ
መልስ ውስጥ ሊካተት የሚገባው ነገር ነው፡፡
 እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ በዚህ ድንጋጌ የተመለከቱት የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያዎች ብቻ ናቸው በመከላከያ መልስ ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው
ወይንስ ሌሎችም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ካሉ መካተት የግድ
ይላቸዋል የሚለው ነው፡፡
 ማንኛውም ተከሳሽ የመከላከያ መልሱን ሲያቀርብ ሊከላከል የሚችልባቸውን
ነገሮች ሁሉ በመልሱ ላይ አጠቃሎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም
በመከላከያ መልሱ ያላቀረበውን አዲስ ነገር ለማቅረብ በክርክር ደረጃ ሥነ-
ሥርዐት ህጉ የሚፈቅድ ባለመሆኑ ነው፡፡
 ስለሆነም የሥነ-ሥርዐት ህጉ ድንጋጌ 234 (1-ሐ) በመጀመሪያ ደረጃ መቅረብ
የሚኖርባቸውን መቃወሚያዎች በምሳሌነት ከመጥቀስ ውጪ ሌሎች
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች በመከላከያ መልስ አቤቱታ ላይ ባይካተቱም
በክርክር ደረጃ ሊነሱ ይገባል የሚል አይደለም፡፡
 በመከላከያ መልስ አቤቱታ ያልተካተተ አዲስ ነገር በጉዳዩ የክርክር ደረጃ ሊነሳ
እንደማይችል ከፍታብሔር ሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር 82 እና 241 ምንባብ
እንዲሁም ቁጥር 234 (1-መ) “የመከላከያ መልስ በሚጻፍበት ጊዜ
በመከላከያው ያልተጠቀሰ አዲስ ነገር እንዳይፈጠር ወይም ከክሱ ማመልከቻ
ውጪ የሆኑ አዲስ ነገሮች እንዳይነሱ በማድረግ ተሟልቶ የተዘጋጀ መልስ” ሊሆን
ይገባል በሚል ከተመለከተው ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡
 ለ. ሌላው መልስ ሊይዘው የሚገባው ለቀረበው ክስ በፍሬ ነገር ረገድ
የሚሰጥ መልስ፤ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ኖረም አልኖረም ተከሳሹ
ለቀረበበት ክስ በፍሬ ነገር ረገድ መልሱን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 መልስ አጭርና ሁሉንም መከላከያ ይሆኑኛል የሚላቸውን መሰረታዊ ፍሬ
ነገሮች መሰረት በማድረግ እንደሆነ የሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር 80(2)፣ 82
እንዲሁም 234 (1-መ) በግልጽ ይደነግጋሉ፡፡
 ሐ. በመልስ ላይ በግልጽ መካድ አስፈላጊ መሆኑ፤ በፍታብሔር ክርክር
በክሱ ማመልከቻ ላይ ከተገለጹት ነገሮች ውሥጥ በግልጽ ያልተካዱት ሁሉ
እንደታመኑ የሚቆጠሩ እንደሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 83፣ 234(1-ሠ)
እንዲሁም 235(2) ላይ ተመልክቷል፡፡
 ተከሳሽ ወይም የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የቀረበበት ከሳሽ የተከሰሰበትን
ነገሮች ሁሉ በዝርዝርና በግልጽ በመካድ መቃወም ይኖርበታል፡፡ ከዚህ
ውጪ በክሱ ላይ የቀረበውን ነገር ሁሉ በዝርዝርና በግልጽ ያለመካድ
ወይም በመሸሽ ማስተባበል ነገሩን በከፊል ሆነ በሙሉ አምኖ
እንደመቀበል ያስቆጥራል፡፡
 በመሸሽ ማስተባበል ወይም በግልጽ አለመካድ ነገሩን እንደማመን
የማይቆጠርባቸው ሁለት ልዩ ሁኔታዎች በግልጽ ከላይ በተጠቀሱት
ድንጋጌዎች ላይ የተመለከቱ ሲሆን የመጀመሪያው ሁኔታ የካሳ ጥያቄ ላይ
የቀረበ የገንዘብ ልክን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ከሳሽ
ባቀረበው የካሳ መጠን ላይ ተከሳሹ በግልጽ ያልካደ ወይም ምንም ያላለ
እንደሆነ የካሳ መጠኑ ታምኗል ሊባል የሚችል አይሆንም፡፡ ምክንያቱም
በፍታብሔር ሕጉ ቁጥር 2141 መሰረት ጉዳት የደረሰበት ሰው የደረሰበትን
ጉዳት ልክና የአካባቢ ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ ተከሳሹን ካሳ
እንዲከፍለው ያለበትን ግዴታ የማስረዳት ሸክም እንዳለበት ስለሚደነግግ
ነው፡፡
 በዚሁ አግባብ የፌድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ. ቁ.
48632 ተከሳሹ የመከላከያ መልስ ባላቀረበበት ሁኔታና በካሳ መጠን
ጥያቄ ላይ በግልፅ ያልተካደ ፍሬ ነገር እንደታመነ ይቆጠራል የሚለው
የሥነ-ሥርዓት ህግ ተፈፃሚነት የሌለው እንደሆነ ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡
 ሌላው ልዩ ሁኔታ በሥነ-ሥርዐት ሕጉ ቁጥር 235(2) ላይ
እንደተመለከተው ችሎታ የሌላቸው ተከሳሾች ላይ ነው፡፡ ችሎታ የሌለው
ተከሳሽ ከሆነ ከፍ ብለን ለመመልከት እንደሞከርነው ከሳሽ ይህንኑ
የሚያውቅ ከሆነ በክስ ማመልከቻው ላይ መግለጽ ይኖርበታል፡፡
 ተከሳሹ ችሎታ ሳይኖረው ክስ ወይም ለቀረበበት ክስ የመከላከያ መልስ
ያቀረበ እንደሆነ ጉዳዩን የሚመለከተው ፍ/ቤት በሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር
34(2) መሰረት ክርክሩን አቋርጦ ተገቢው ህጋዊ ወኪል እንዲኖረው
በማድረግ በዚሁ ወኪሉ/ሞግዚቱ አማካኝነት ክርክሩን እንዲያከናውን
ማድረግ ይኖርበታል፡፡
 ሞግዚቱ ባቀረበው የጽሁፍ መከላከያ መልስ ላይ በመሸሽ ያስተባበለው
ወይም በግልጽ ያልካደው ነገር እንደታመነ ተደርጎ የሚወሰድ ከሆነ በህግ
ችሎታ የሌለውን ሰው ጥቅም ሊጎዳ ስለሚችል በህግ ችሎታ የሌለውን
ሰው ጥቅም ለመጠበቅ ሲባል የተደነገገ ልዩ ሁኔታ ነው፡፡
 መ. የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ካለ ይህንኑ አስተካክሎ በመልሱ ላይ
ማቅረብ አለበት፤ይህ አይነቱ ክስ የሚቀርበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ
215(2) መሰረት ተገቢው የፍ/ቤት አገልግሎት ክፍያ ተከፍሎ መሆን
ይኖርበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ፍ/ቤቱ
እንዲሰጠው የሚፈልገውን ዳኝነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 224 አግባብ
ለይቶ በአቤቱታው ላይ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
 ከተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በተመሳሳይ ተከሳሹ የመቻቻል ጥያቄ ካለው
ከመልሱ ጋር ሊያቀርብ ይገባል፡፡ እዚህ ላይ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስና
የመቻቻል ጥያቄን ያላቸውን መሰረታዊ ልዩነት ማየቱ ጠቃሚ
ይሆናል፡፡
 አንድ ተከሳሽ የመቻቻል ጥያቄ ለማቅረብ የሚፈልግ ከሆነ ይህንኑ
ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው እንደተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ሁሉ ለቀረበበት
ክስ መልስ በሚሰጥበት በመጀመሪያው ጊዜ ማቅረብ አለበት፡፡
 ነገር ግን የመቻቻል ጥያቄ ሊቀርብ የሚችለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ
236 (1) መሰረት የሚጠይቀው ገንዘብ ከፍርድ ቤቱ ሥልጣን ውጭ
ካልሆነ ብቻ ነው፡፡
 ይህ የመቻቻል ጥያቄ በማቅረብ ላይ የተጣለው የህግ ገደብ
ከተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አንጻር የሚታይ መሰረታዊ ልዩነት ነው፡፡
ሌላው ልዩነት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ማንኛውንም የክስ ምክንያት
መሰረት በማድረግ ሊቀርብ የሚችል ሲሆን የመቻቻል ጥያቄ
ሊቀርብ የሚችለው ግን ለገንዘብ ወይም ተመሳሳይ በሆኑትና
የመከፈያቸው ጊዜ በደረሰ እዳዎች መካከል ብቻ ላይ የተወሰነ
እንደሆነ የፍታብሄር ህጉ ቁጥር 1831 እና ተከታዮችን በመመልከት
ለመረዳት ይቻላል፡፡
 ከዚህም በተጨማሪ መቻቻል በመልስ ላይ ሊቀርብ የሚችለው
የሚጠይቀው ገንዘብ ተከሳሹንና ከሳሹን በግል መብታቸው ረገድ
የሚመለከታቸው ሲሆን ብቻ ነው፡፡
 በፍ/ብ/ህ/ቁ 1833 መሰረት መቻቻያ የማያስደርጉ
ሁኔታዎች
 የዕዳው አይነት ልዩ በመሆኑ ለባለገንዘቡ በእጁ
የሚከፈል ሲሆን ለምሳሌ ለቀለብ የሚከፈል ገንዘብ
ሲሆን
 ለመንግስትና ለመስሪያ ቤቶች የሚከፈል ገንዘብ ሲሆን
 ባለቤቱ በማይገባ የተወሰደበት እንዲመለስለት ሲጠይቅ
 በአደራ የሰጠውን ዕቃ እንዲመለስለት ሲጠይቅ
መቻቻያ ሊደረግ አይችልም፡፡
 የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ሲቀርብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 215(2)
መሰረት ተገቢው የፍ/ቤት አገልግሎት ክፍያ ተከፍሎ መሆን
እንዳለበት ተደንግጓል፡፡ የፍ/ቤት አገልግሎት ክፍያ በመቻቻል ጥያቄ
ላይስ ሊከፈል የሚገባ ነው ይላሉ ለምን?
 የመከላከያ መልሱ አቤቱታ በህጉ አግባብ ማካተት የሚገባውን ነገር
አካቶ የቀረበ መሆኑን የመመርመር ሥልጣን የተሰጠው ለፍ/ቤቱ
ነው (238(1)፡፡
 ይህንንም ሲያደርግ መከላከያው ከፍ ብለን የተመለከትናቸውን
መሟላት የሚገባቸውን ነገሮች አሟልቶ ያልቀረበ እንደሆነ ወይም
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 መሰረት ማስረጃ ያላያያዘ እንደሆነ
ወይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 92 መሰረት የመከላከያ አቤቱታው
ተረጋግጦ ያልቀረበ እንደሆነ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 229 ድንጋጌ
በተመሳሳይ ተፈጻሚ በማድረግ አቤቱታው ተሙዋልቶ እንዲቀርብ
ማድረግ ያለበት መሆኑን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 238 (1) ላይ
ተደንግጓል፡፡
 በዚህ አግባብ መከላከያው ተመርምሮ ተቀባይነትን ያገኘ እንደሆነና
አቤቱታው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስን ወይም የመቻቻል ጥያቄ ያካተተ
እንደሆነ ፍ/ቤቱ እንደ ተገቢነታቸው የቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስንና
የመቻቻል ጥያቄውን ፍ/ቤቱ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231 አንጻር
በመመርመር ተገቢውን ሊወስን ይገባል፡፡
 የተከሳሽ ከሳሽነቱ ክስ ወይም የመቻቻል ጥያቄው የክስ ምክንያት
የሌለው ከሆነ ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ወይም ከፍ/ቤቱ ሥልጣን
በላይ ከሆነ ከፍ/ቤቱ ሥልጣን በላይ የሆነው የመቻቻል ጥያቄው ከሆነ
የመቻቻል ጥያቄ ከፍ/ቤቱ ሥልጣን በላይ ሊቀርብ ስለማይችል
ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ፤ ከፍ/ቤቱ ሥልጣን በላይ የሆነው የተከሳሽ
ከሳሽነቱ ከሆነ የግራ ቀኙን ክርክር ለመዳኘት ሥልጣን የሚኖረው
ለዳኝነት ከቀረቡት የግራ ቀኙ ጥያቄዎች መካከል ከፍተኛውን ለመዳኘት
ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት በመሆኑ ከሳሽ የከፈለውን የዳኝነት ክፍያ
እንዲመለስለት በማድረግና የግራ ቀኙን መዝገብ በመዝጋት ጉዳዩን
ለመመልከት ሥልጣን ወዳለው ፍ/ቤት ማስተላለፍ ይኖርበታል፡፡
 የግራ ቀኙ አቤቱታ ማሟላት የሚገባቸውን ነገሮች አሟልተው
በመቅረባቸው በፍ/ቤቱ የመዝገብ ቤት ሹምና በፍ/ቤቱ ተቀባይነት
ካገኙም በኋላ ሥነ-ሥርዓት ህጉ በሚያስቀምጣቸው ምክንያቶች ሊሻሻሉ
ይችላሉ፡፡
 ሊሻሻሉ የሚችሉትም በተከራካሪ ወገኖች አመልካችነትና በፍ/ቤቱ
ፈቃጅነት ወይም በፍ/ቤቱ በራሱ አነሳሽነት በሚሰጥ ትእዛዝ ሊሆን
ይችላል፡፡
 ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 ለመረዳት እንደሚቻለው አንድ አቤቱታ በሶስት
ምክንያቶች ሊሻሻል የሚችል ሲሆን ይሄውም፡- (1) ለትክክለኛ
ፍትህ ሲባል፣
(2) የክስ ወይም የመከላከያ መልስ አቤቱታውን በተሻለ ለማብራራት ሲባል
ወይም
(3) አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮች ወይም የክርክሩን አመራር ሥርዓት
የሚያሰናክሉ ወይም ሁከትን የሚፈጥሩ ወይም ለትክክለኛው ፍትሕ
አሰጣጥ መሰናክል ሆነው የሚገመቱ ነገሮችን ለማስተካከል በሚል ሊሻሻል
የሚችል እንደሆነ ነው፡፡
 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(1) “ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በማናቸውም
ጊዜ ወይም ፍርድ ቤቱ ተገቢ ሆኖ ካገኘው ተከራካሪዎቹ ወገኖች
ክሳቸውን እንዲያሻሽሉና ክርክራቸውን እንዲለውጡ ሊፈቀድላቸው
ይችላል፡፡ ስለሆነም የዚህ ዓይነት መብት ለተከራካሪዎቹ ወገኖች
የሚሰጠው የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ነገሩን ይበልጥ
የሚያብራራ ወይም ትክክለኛ ፍትሕን ለመስጠት የሚረዳ ሆኖ
በተገመተ ጊዜ ብቻ ነው፡፡…” በሚል ይደነግጋል፡፡
 በዚህ ንዑስ ቁጥር ድንጋጌ የአማርኛ ቅጂ በተለይም “ፍርድ ቤቱ
ተገቢ ሆኖ ካገኘው ተከራካሪዎቹ ወገኖች ክሳቸውን እንዲያሻሽሉና
ክርክራቸውን እንዲለውጡ ሊፈቀድላቸው ይችላል” የሚለው
አገላለጽ ለትክክለኛ ፍትህ ሲባል ሊሻሻል የሚችለው የከሳሽ ክስ
ወይም ተከሳሽ የሚያቀርበው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስን ብቻ
የሚመለከት እንደሆነ ነው፡፡
 ይህም ተከሳሹ መከላከያውን ለትክክለኛ ፍትህ ሲባል ላሻሽል ቢል
የሚፈቅድ አይመስልም፡፡ ከዚህ አንጻር የዚሁኑ ንዑስ ቁጥር ድንጋጌ
የእንግሊዝኛ ቅጅ በምንመለከትበት ጊዜ ከአማርኛው ቅጅ በተለየ
መልኩ “…The court may at any time before judgment
allow either party to alter or amend his pleading…” በሚል
ይደነግጋል፡፡
 “pleading” የሚለው ቃል ሁለቱንም የክስና የመልስ አቤቱታን
የሚመለከት በመሆኑና የእንግሊዝኛው ቅጂ ግራ ቀኙን ተከራካሪ
ወገኖች በእኩልነት የሚያስተናግድ በመሆኑ ይሄው ቅጂ ከአማርኛው
ቅጂ ይልቅ ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚገባ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
 “ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራ ወይም ትክክለኛ ፍትሕን ለመስጠት”
የሚለው ምን ማለት ነው? አዲስ ነገርን በማሻሻያው ለማካተት
የሚፈቅድ ነውን? በአቤቱታ ማሻሻያ ውስጥ አዲስ ነገር መካተት
የለበትም በሚል በአንዳንድ የህግ ባለሙያዎች ክርክር ሲነሳ ይሰማል፡፡
 ይሁንና የሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር 90 እና 91 (1) ስንመለከት ለዚህ ጥያቄ
ግልጽ ምላሽ የሚሰጡን ድንጋጌዎች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡
 ከዚህ አንጻር የሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር 90 “አቤቱታን ለማሻሻል ካልሆነ
በቀር ተከራካሪዎቹ ወገኖች ቀድሞ ካቀረቡት ክርክር ወይም ጭብጥ
ውጭ የሆነና ከቀድሞው ክርክር ጋር ግንኙነት የሌለው አዲስ ነገር
ለማቅረብ አይቻልም፡፡” በሚል የሚደነግግ ሲሆን የዚህ ድንጋጌ ግልባጭ
ምንባብ በአቤቱታ ማሻሻያ ጊዜ ቀድሞ ከቀረበው ክርክር ወይም ጭብጥ
ውጭ የሆነና ከቀድሞው ክርክር ጋር ግንኙነት የሌለው አዲስ ነገር
ሊቀርብ የሚችል እንደሆነ ነው፡፡
 ከዚህም በተጨማሪ በቁጥር 91(1) “ተከራካሪዎቹ ወገኖች ክሳቸውን
እንዲያሻሽሉና ክርክራቸውን እንዲለውጡ ሊፈቀድላቸው ይችላል፡፡”
የሚለው በተለይም “ክርክራቸውን እንዲለውጡ” የሚለው የህጉ
አቀራረጽ አዲስ ነገር በአቤቱታ ማሻሻያ ውስጥ ሊኖር የሚችል እንደሆነ
ነው፡፡ በዚሁ አግባብም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በከሳሽ ቢኒያም ገረመውና በተከሳሽ የቻይና መንገድ ስራ ድርጅት
መካከል በነበረው የስራ ክርክር በሰ/መ/ቁ 20416 ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡
 በአቤቱታ ማሻሻያ አዲስ ነገር የሚካተት መሆኑ ግልጽ ከሆነ በቀጣይ
ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ በማሻሻያው ሊካተት የሚገባው አዲስ ነገር
አድማስ እስከምን ሊደርስ ይገባል የሚለው ነው፡፡ በዚህ ረገድ በሥነ-
ሥርዓት ህጉ በግልጽ የተመለከተ ነገር ባይኖርም “ለትክክለኛ ፍትህ
አሰጣጥ” ከሚለው ሀረግ በመነሳት የሚከተሉትን ሁኔታዎች ሊጨምር
እንደሚችል መረዳት ይቻላል፡፡
 የመጀመሪያው ሁኔታ ከቀረበው የክስ ምክንያት ጋር አብሮ ሊታይና
ውሳኔ ሊያገኝ የሚገባው ነገር ሲሆንና ከዚሁ የክስ ምክንያት ጋር
አብሮ ቀርቦ ካልታየ በአዲስ ክስ ከመታየት የሚታገድ ከሆነ ነው፡፡
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 216(4) ላይ
 እንደተመለከተው ከሣሽ ያቀረበው ክስ ባንድ ጉዳይ ላይ የተመሠረተ
ሆኖ የሚጠይቀው ዳኝነት ግን ከአንድ በላይ ሲሆን ፍርድ ቤቱ
ሳይፈቅድለት ሊጠይቅ ይገባው ከነበረው ዳኝነት ውስጥ በከፊል
ራሱ ቀንሶ ያስቀረውን መብት እንደገና ሊከስበት አይችልም፡፡
 ለምሳሌ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በህገወጥ መንገድ ከስራው
የተባረረ አንድ ሰራተኛ ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት የስራ ስንብት ክፍያ
እንዲከፈለው ብቻ ክስ በማቅረብ ሌሎች ሊጠይቃቸው የሚገቡ
የክፍያ ጥያቄዎች ሳያቀርብ ቀርቶ ከፍርድ በፊት የክስ አቤቱታውን
እነዚሁ የቀሩትን ጥቅማጥቅሞች በክሱ ለማካተት በሚል የማሻሻያ
አቤቱታ ቢያቀርብ ፍ/ቤቱ ይህንኑ ማመልከቻ ሊቀበለው ይገባል
ማለት ነው፡፡
 ምክንያቱም ክሱ ሳይሻሻል ቀርቶ ፍ/ቤቱ በስራ ስንብት ክፍያው ላይ
ብቻ ውሳኔ ቢሰጥ በሌሎቹ የክፍያ ጥያቄዎቹ በአዲስ ክስ ለማቅረብ
ከፍ ሲል የጠቀስነው የሥነ-ሥርዐት ህጉ ድንጋጌ ስለማይፈቅድለት
ነው፡፡ በዚሁ አግባብ ከፍ ብለን የጠቀስነው የፌደራሉ ጠቅላይ
ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሰጥቶበታል፡
 ሌላው አቤቱታን ለማሻሻል የሚያበቃ ሁኔታ የቁጥር ወይም ሌሎች
ስህተቶች ለማስተካከል በሚል የሚቀርብ ማመልከቻ ነው፡፡ ለምሳሌ
የአከራካሪውን የቤት ቁጥር ወይም የመኪና ታርጋ ቁጥር ለማሻሻል
ማመልከቻ ቢቀርብ እንዲህ አይነቱ መሻሻል አከራካሪውን ነገር
በበለጠ ግልጽ እንዲሆን ከማድረጉም ባለፈ ትክክለኛ ፍትህ
ለመስጠት የሚረዳ በመሆኑ ማመልከቻው ተቀባይነት ሊያገኝ
ይገባል፡፡
 ከዚህ በተለየ የክስ ምክንያቱን የሚቀይር ከሆነ ለምሳሌ
በመጀመሪያ የቀረበው የክስ ምክንያት ሁከት ይወገድልኝ ሆኖ
በማሻሻያው ውል ይፍረስልኝ በሚል የሚቀርብ ከሆነ ፍጹም የክስ
ምክንያቱን የቀየረና ሁለቱ ጉዳዮች የማይገናኙ በመሆናቸው
እንዲሁም በውል ማፍረስ በአዲስ መልክ ክስ በማቅረብ ውሳኔ
ለማግኘት የሚከለክል ነገር የሌለ በመሆኑ የሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር
91(1) እንዲህ አይነቱን የማሻሻል ጥያቄ የሚያስተናግድ
አይመስልም፡፡
 ከዚህ ባለፈ ተከራካሪ ወገኖች በመጀመሪያው የክርክሩ ደረጃ ሊያነሱ
የሚገባቸውን መከራከሪያዎች ለምሳሌ እንደመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ ያለ መከራከሪያ ሳያነሱ ቀርተው በአቤቱታ ማሻሻያ
ይህን አይነቱን መከራከሪያ እንዲያነሱ ሥነ-ሥርዐት ሕጉ የሚፈቅድ
አይደለም፡፡ በዚሁ አግባብ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት በሰ/መ/ቁ 55973 ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡
 ሌላው እዚህ ላይ ሊነሳ የሚገባው ነገር ማስረጃ ለማያያዝ በሚል
የአቤቱታ ማሻሻያ ጥያቄ አግባብነት እስከምን ድረስ ነው የሚለው
ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ተከራካሪ ወገኖች አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ
የረሷቸውን ማስረጃዎች ለማቅረብ በማሰብ የአቤቱታ ማሻሻያ
ማመልከቻ ለፍ/ቤት ሲያቀርቡ ይታያል፡፡
 ነገር ግን በመጀመሪያ ከክስ ወይም ከመልስ ጋር አብሮ ያልቀረበ ማስረጃ በጉዳዩ
የክርክር ደረጃ በምን አግባብ ሊቀርብ የሚችል እንደሆነ የሥነ-ሥርዐት ሕጉ
ራሱን የቻለ አግባብ ያስቀመጠ በመሆኑ ማስረጃን ለማያያዝ ሲባል ብቻ
የአቤቱታ ማሻሻያ ሊቀርብ አይገባም፤ ቢቀርብም ማሻሻያው ተቀባይነት ሊያገኝ
አይገባም፡፡
 ከዚህም በተጨማሪ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 የሚመለከተው አቤቱታን
ስለማሻሻል በመሆኑና አቤቱታ ወይም በእንግሊዝኛው “pleading” የሚለው
በዚህ ክፍል ስለአቤቱታ ምንነት ለመመልከት እንደሞከርነው የክስ መነሻ ሊሆን
የሚችል ነገር ወይም ለክስ የሚሰጥ መልስ እንደሆነ ነው፡፡
 የማስረጃ ዝርዝር ደግሞ ራሱን ችሎ የክስ መነሻ ወይም ለቀረበ ክስ መልስ
ሊሆን የሚችል አይደለም፡፡ ማስረጃ የክሱ ወይም የመልሱ አባሪ በመሆኑ
አቤቱታ የሚለውን የሚያሟላ አይደለም፡፡
 በመሆኑም ማስረጃ ለማያያዝ በሚል ብቻ አቤቱታ ሊሻሻል የሚፈቀድበት የህግ
መሰረት የለም፡፡ ይሁንና ይህ ማለት ግን በማሻሻያው አዲስ ነገር የቀረበ
እንደሆነና ይህንኑ አዲስ ነገር ለማስረዳት በሚል የሚያያዙ ማስረጃዎች
አግባብነት ያላቸው በመሆኑ ተቀባይነት ያላቸው እንደሆነ ግንዛቤ ሊወሰድበት
ይገባል፡፡
 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(2) በግልጽ እንደሚደነግገው በዚሁ ድንጋጌ
ንዑስ ቁጥር (1) መሰረት ክርክሩን እንዲያሻሽል ወይም ሙግቱን
እንዲቀይር በፍ/ቤቱ ፍቃድ ያገኘ ተከራካሪ ይህንኑ ፍ/ቤቱ በሰጠው
የጊዜ ገደብ ውስጥ ያላከናወነ እንደሆነና ፍ/ቤቱ የሰጠውን ጊዜ
ያላራዘመለት ከሆነ አቤቱታውን የማሻሻል መብቱን የሚያጣ
ይሆናል፡፡ በዚህ አግባብ መብቱን ያጣ ተከራካሪ በመጀመሪያ
ባቀረበው አቤቱታ መሰረት ክርክሩን የሚያደርግ ይሆናል ማለት
ነው፡፡
 ክስን በማሻሻል ሙግትን ለመቀየር በሚል ከሚደረግ የአቤቱታ ማሻሻያ
ባሻገር አቤቱታውን በተሻለ ለማብራራት በሚል በተከራካሪ ወገኖች
አመልካችነት ወይም በፍ/ቤቱ አነሳሽነት አቤቱታ እንዲሻሻል ሊደረግ
ይችላል፡፡
 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(3) ላይ እንደተመለከተው እንዲህ አይነቱ ማሻሻያ
የሚፈቀደው የክሱን ወይም የመከላከያውን ሁኔታ የሚያብራራ ወይም
የቀረበውን ክርክር በተሻሻለ ዓይነት ገልጾ የሚያስረዳ ወይም ሁኔታውን
በዝርዝር አገላለጽ የሚያመለክት ሆኖ መቅረቡ አስፈላጊ የሆነ እንደሆነ
ነው፡፡
 የዚህ አይነቱ የማሻሻያ ማመልከቻ አላማ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ
በሚል ከሚደረገው ማሻሻያ በመሰረታዊነት ያለው ልዩነት ሙግትን
በመቀየር አዲስ ነገር ለመጨመር በሚል የሚቀርብ ሳይሆን አቤቱታውን
የበለጠ ግልጽ ማድረግ ላይ ነው፡፡
 ፍ/ቤት ትክክለኛውን የችሎት አመራር የሚያሰናክሉ ወይም ሁከት
ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችንና የመሳሰሉትን ሁኔታዎች በችሎት
በንግግር ወይም በተግባር ሲፈጸሙ ብቻ ሳይሆን በጽሁፍ አቤቱታ
ላይ የተገለጹ ከሆነ እነዚህን ነገሮች እንዲስተካከሉ የማድረግ
ኃላፊነት አለበት፡፡
 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(4) በግልጽ እንደሚደነግገው እንዲህ አይነት
ነገሮች በአቤቱታ ማመልከቻ ላይ ተገልጸው ከሆነ ይሄው እንዲሻሻል
ወይም ከአቤቱታው ውስጥ ጨርሶ እንዲወጣ ማዘዝ ይኖርበታል፡፡
ይህ አይነቱ ማሻሻያ በተከራካሪዎቹ ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን
የግድ የሚፈጸም የማሻሻያ አይነት ነው፡፡
 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(5) ላይ እንደተመለከተው የክሱ መሻሻል
ነገሩን በመጀመሪያ ደረጃ ከቀረበለት ፍርድ ቤት ሥልጣን በላይ
ያደረገው እንደሆነ የመጀመሪያው ደረጃ ፍርድ ቤት ይህን ጉዳይ
ለመቀበል ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማስተላለፍ ይኖርበታል፡፡
 በድንጋጌው በግልጽ የተመለከተው “ክስ” በሚል ሲሆን ይህ ማለት
ግን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስንም የሚጨምር እንደሆነ መገንዘብ
ያስፈልጋል፡፡ በዚህ አግባብ መዝገቡ የተላለፈለት የበላይ ፍ/ቤት ነገሩ
እንዲሰማ ማድረግ እንዳለበት በዚሁ ድንጋጌ ላይ ተመልክቷል፡፡
 በአቤቱታ መሻሻል ምክንያት የስረ-ነገር ሥልጣኑ ከፍ ወዳለው
ፍ/ቤት የሚተላለፍ ከሆነ በአዲስ መልክ ለተጨመረው የዳኝነት
ጥያቄ የፍ/ቤት አገልግሎት ክፍያ የትኛው ፍ/ቤት ነው ሊያስከፍል
የሚገባው፡፡
 ፍ/ቤት ከተከራካሪ ወገኖች መቅረብ ጋር በተያያዘ የተለያዩ
ቀጠሮዎችን ይሰጣል፡፡ እንደቀጠሮዎቹ ምክንያት፣ አላማና
ያልቀረበው ተከራካሪ ማንነት አንጻር የተከራካሪ ወገኖች በተሰጠው
ቀነቀጠሮ ያልቀረቡ እንደሆነ ፍ/ቤቱ የተለያዩ ትእዛዛትን ይሰጣል፡፡
 ከነዚህም መካከል የጽሁፍ መልስና ማስረጃዎቹን የማቅረብ
መብትን ማለፍ “default proceeding”፣መዝገቡን የመዝጋት
“struck out of the suit”፣ ተከሳሹ በሌለበት ክርክሩ እንዲታይ
ትእዛዝ መስጠት “ex-parte”፣ ክሱን የመሰረዝ “dismissal of the
suit” በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እንደ ትእዛዙ አይነትም
ውጤታቸው የተለያየ ነው፡፡ በዚህ ክፍልም እነዚህን አራት
ሁኔታዎች ከሚያስከትሉት ውጤት ጋር በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
 ሀ. ተከሳሹ የፅሁፍ መልሱንና ማስረጃውን የማቅረብ መብቱን
የሚያጣበት ሁኔታ
 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 233 እንደሚደነግገው የከሳሽ የክስ አቤቱታ
በሥነ-ሥርዐት ሕጉ አግባብ ተቀባይነት ያገኘ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ
ለተከሳሹ ክሱንና ከክስ ማመልከቻው ጋር ተያይዞ የቀረበለት
ማናቸውም አስረጂና የጽሑፍ ግልባጭ ከመጥሪያው ጋር ለተከሣሹ
እንዲደርሰውና የመከላከያ መልሱን ጽፎ እንዲቀርብ ያዛል፡፡ ተከሣሹ
መከላከያውን ለፍርድ ቤቱ ሳያቀርብ የቀረ ወይም ራሱ መከላከያ
ሳይዝ የቀረበ እንደሆነ ክርክሩ በሌለበት የሚሰማ መሆኑ
በመጥሪያው ላይ ተገልጾ ይላክለታል፡፡
 “ተከሣሹ መከላከያውን ለፍርድ ቤቱ ሳያቀርብ የቀረ ወይም ራሱ
መከላከያ ሳይዝ የቀረበ እንደሆነ ክርክሩ በሌለበት የሚሰማ መሆኑ”
የሚለው በስነ-ሥርዐት ሕጉ ቁጥር 70(ሀ) ላይ ከተመለከተው ክሱ
ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ተከሳሹ ያልቀረበ እንደሆነ ክሱ በሌለበት
ይሰማል ከሚለው ጋር ተመሳሳይ በማድረግ ሲተረጎም ቆይቷል፡፡
 ይሁንና የፌድራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ተከሳሹ
መከላከያውን ለማቅረብ በተቀጠረበት ቀን ያልቀረበ ወይም ቀርቦ
መልሱን በጽሁፍ ይዞ ያልቀረበ እንደሆነ ሊሰጥ የሚገባው ትእዛዝ
በሌለበት የሚል ሳይሆን በጽሁፍ መከላከያውንና ማስረጃውን
የማቅረብ መብቱ ብቻ የሚታለፍበት “default proceeding”
እንደሆነ በሰ/መ/ቁ 15835 አስገዳጅ የሆነ ትርጉም ሰጥቷል፡፡
 ለዚህ ውሳኔውም መነሻ ያደረገው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 233
የእንግሊዝኛውን ቅጂ ሲሆን በተለይም “…. The court shall
cause… requiring him to appear with his statement of
defense to be fixed in the summons and informing
him that the case wile be proceeded
withnotwithstanding that he does not appear or that
he appears without his statement of defense.”የሚለውን
ነው፡፡
 ይህ አገላለጽ “default proceeding” ወይም መከላከያውን
የማቅረብ መብቱን ማጣት የሚለውን እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ
70(ሀ) ላይ የተመለከተውን “ex-parte” ወይም ክሱ በሌለበት
ይታያል የሚለውን እንዳልሆነ በዚሁ ውሳኔ ሀተታው ላይ
አስቀምጧል፡፡
 በመሆኑም ተከሳሹ የመከላከያ መልሱን ፍ/ቤቱ እንዲያቀርብ
በሰጠው ቀነ ቀጠሮ ያላቀረበ እንደሆነ ፍ/ቤቱ በሥነ-ሥርዐት ሕጉ
ቁጥር 199 መሰረት ተገቢ ነው ያለውን ትእዛዝ የሚሰጥ ሲሆን
በዚሁ ድንጋጌ (1) መሰረት መከላከያውን ያላቀረበው በተከሳሹ
በራሱ ችግር እንደሆነ የመከላከያ መልስ የማቅረብ መብቱን ማለፍ
ወይም ተከሳሹ መከለከያውን ማቅረብ ያልቻለው በእርሱ ችግር
ባልሆነ ምክንያት መሆኑን ማስረዳት የቻለና ይህንኑ ፍ/ቤቱ
የተቀበለው እንደሆነ በንዑስ ቁጥር (2) መሰረት ተለዋጭ ቀጠሮ
በመስጠት የመከለከያ መልሱን እንዲያቀርብ ለማዘዝ የሚችል
ይሆናል፡፡
 ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሳሽ ተከሳሹ የመከላከያ መልሱን ለማቅረብ
በተቀጠረበት ቀን ባይቀርብ በከሳሽ ላይ ፍ/ቤቱ ምን ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል
የሚለው ጥያቄ ነው፡፡
 በመርህ ደረጃ ከሳሽ በዚህ የቀጠሮ እለት የተከሳሽ የመከላከያ መልስ
ከመቀበል ባለፈ የሚያከናውነው ነገር የለም፡፡ የመከላከያ መልሱንም ቢሆን
በፍ/ቤቱ ሬጂስትራር በኩል ከቀጠሮው እለት በኋላም ቢሆን ለማግኘት
የሚችል በመሆኑ በዚህ ቀጠሮ መገኘቱ ያን ያህል አስፈላጊ አይሆንም፡፡
 ይሁንና በዚህ የፍ/ቤቱ የቀጠሮ እለት ፍ/ቤቱ በተለይ ተከሳሹ ያልቀረበ
እንደሆነ ተገቢውን ትእዛዝ ለመስጠት የከሳሽ መቅረብ ጠቃሚ እንደሚሆን
እርግጥ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ የፌደራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 14184
ከሳሽ ተከሳሽ መከላከያውን ለማቅረብ በተቀጠረበት ቀን ፍ/ቤት እንዲቀርብ
የግድ የሚለው ተግባር የሌለው በመሆኑ አለመቅረቡ መብቱን የሚነካ
ምንም አይነት ትእዛዝ አይኖርም በሚል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
ለ. መዝገቡን መዝጋት (struck out of the suit)
 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(1) ላይ እንደተመለከተው ተከራካሪ
ወገኖች ፍ/ቤቱ ነገሩን ለማየት በሰጠው ቀጠሮ ራሳቸው ወይም
ወኪሎቻቸው ተሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ፍ/ቤቱም
የግራ ቀኙ ወገኖች ተሟልተው መቅረባቸውን ካረጋገጠ በኋላ
ነገሩን መስማት ይጀምራል፡፡
 ነገር ግን ነገሩ ሊሰማ ፍ/ቤቱ በሰጠው የቀጠሮ እለት ተከራካሪ
ወገኖች ያልቀረቡ እንደሆነ ፍ/ቤት ሊሰጥ የሚችለው
የመጀመሪያው አይነት ትእዛዝ መዝገቡን መዝጋት ነው፡፡
 ይህም ትእዛዝ ሊሠጥ የሚችለው ነገሩ ሊሰማ በተቀጠረበት እለት ግራ ቀኙ
ያልቀረቡ እንደሆነ በሥነ-ሥርአት ህጉ ቁጥር 69(2) እንዲሁም በቁጥር
70(መ) አግባብ ከሳሽ በራሱ ቸልተኝነት ወይም ጉድለት መጥሪያውን
ለተከሳሽ ያላደረሰ እንደሆነ ነው፡፡
 የሥነ-ሥርዐት ሕጉ የአማርኛው ቅጂ በአዲስ ክስም ሆነ በይግባኝ ክርክር
መዝገቡ ይዘጋል በሚል በተመሳሳይ አገላለጽ ፍ/ቤቱ ትእዛዝ እንደሚሰጥ
ይገልጻል፡፡ የዚሁ ህግ የእግሊዝኛ ቅጂ ከዚህ በተለየ መልኩ ለአዲስ ክስ
“struck out of the suit” እንዲሁም በይግባኝ ደረጃ ላለ ክርክር
“dismissal of the suit” የሚል ትእዛዝ እንደሚሰጥ ይደነግጋሉ፡፡
 እነዚህ የትእዛዝ አይነቶች በውጤት ረገድ መሰረታዊ ልዩነት ያላቸው
ሲሆን ከሚያስከትሉት ውጤት አንጻር “struck out of the suit”
የሚለው መዝገብ መዝጋትን እንዲሁም “dismissal of the suit”
ደግሞ የክስ መዝጋትን (መሰረዝን) የሚያመለክት እንደሆነ
በተለይም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 245 (2)ን የአማርኛ ቅጂ
በመመልከት ለመረዳት ይቻላል፡፡
 በመሆኑም በነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት የመዝገብ መዝጋት ትእዛዝ
የሚሰጠው በአዲስ ክስ ሲሆን በይግባኝ ከሆነ ግን የክስ መሰረዝ
ትእዛዝ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70(መ) መሰረት ለተከሳሹ በከሳሹ ቸልተኝነት
ወይም ጉድለት መጥሪያ ያልደረሰው እንደሆነ ፍ/ቤቱ በአዲስ ክስ
ከሆነ መዝገቡን የመዝጋት ወይም በይግባኝ የቀረበ እንደሆነ ክሱን
የመዝጋት ወይም የመሰረዝ ትእዛዝ ለመስጠት እንደሚችል፤ ነገር
ግን ተገቢ መስሎ ከታየውም ክሱ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ
ሊለውጥ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ ለመሆኑ ፍ/ቤቱ በዚህ ሁኔታ ክሱ
የሚሰማበትን ቀጠሮ ለመቀየር የሚያስችሉ ተገቢ ናቸው የሚባሉ
ምን አይነት ነገሮችን የሚመለከት ነው::
ሐ. በሌለበት ወይም “ex-parte” በሚል የሚሰጥ ትእዛዝ
 ክርክሩ እንዲሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ከሳሽ ቀርቦ ተከሳሹ ያልቀረበ
እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70 መሰረት ፍ/ቤቱ እንደነገሩ ሁኔታ
የተለያዩ ትእዛዛትን የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 ከነዚህም ትእዛዛት መካከል ተከሳሹ ፍ/ቤቱ በሰጠው ቀነ ቀጠሮ ያልቀረበ
ቢሆንም መጥሪያው በትክክል የደረሰው መሆኑ ካልተረጋገጠ ፍርድ ቤቱ
በ70 ለ እንደተመለከተው ሁለተኛ መጥሪያ እንዲላክ ትእዛዝ የሚሰጥበት
አግባብ ነው፡፡
 እንዲሁም ተከሳሹ ያልቀረበው መጥሪያው በአግባቡ ደርሶት ነገር ግን
መጥሪያው ለተከሳሹ የደረሰበት ቀን ለክሱ መልስ ለመስጠት በቂ ጊዜ
አለመሆኑን ፍ/ቤቱ የተረዳው ከሆነ በ70 ሐ መሰረት የክርክሩን መሰማት
ለሌላ ቀነ ቀጠሮ የሚያስተላልፈው ይሆናል፡፡
 ሆኖም ተከሳሹ መጥሪያ በአግባቡ ደርሶት ፍ/ቤቱ ክርክሩን ለመስማት
በሰጠው ቀነ ቀጠሮ ያልቀረበ እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70 ሀ መሰረት
ክርክሩ ተከሳሹ በሌለበት ወይም “ex-parte” ጉዳዩ እንዲሰማ በሚል
ትእዛዝ ይሰጣል፡፡
 ተከሳሹ መከላከያ መልሱን አቅርቦ ክርክሩ ሊሳማ በተቀጠረበት ቀን
ባለመቅረቡ በሌለበት ክርክሩ እንዲታይ ትእዛዝ የተሰጠበት ቢሆንም
ተከሳሽ በክርክሩ ሂደት ተሳታፊ አይሁን እንጂ ፍ/ቤቱ ያቀረበውን
የጽሁፍ መልስ በአግባቡ ከግምት ውስጥ በማስገባት ክርክሩ
እንዲደ,ረግ በማድረግ ውሳኔ ላይ ሊደርስ ይገባል፡፡
መ. የክስ መዘጋት ወይም መሰረዝ “dismissal of the suit” በሚል
የሚሰጥ ትእዛዝ
 ከፍ ብለን እንደተመለከትነው በይግባኝ ጉዳይ ላይ ክርክሩ
ለመሰማት በተቀጠረበት እለት ግራ ቀኙ ያልቀረቡ እንደሆነ ወይም
ይግባኝ ባይ መጥሪያውን በራሱ ቸልተኝነት ወይም ጉድለት
ለይግባኝ መልስ ሰጪ ያላደረሰ እንደሆነ እንደቅደም ተከተላቸው
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(2) እና 70(መ) ላይ ተደንግጓል፡፡
 ከዚህም በተጨመሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት በአንድ ጉዳይ
ክስ ያቀረበ ሰው ክርክሩ እንዲሰማ በተቀጠረው ቀን ያልቀረበ
እንደሆነ እንደተከሳሹ መልስ ፍ/ቤቱ ክሱን የመዝጋት (የመሰረዝ)
ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡
 እንዲህ አይነት ትእዛዝ ሊሰጥ የሚችለው ተከሳሹ ቀርቦ ከሳሽ
ያቀረበበትን ክስ ሙሉ በሙሉ የካደ እንደሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ተከሳሹ
በሙሉ ወይም በከፊል ከሳሽ ያቀረበውን ክስ ያመነ እንደሆነ ከሳሹ
ባይቀርብም በተከሳሽ እምነት መሰረት ለከሳሽ ውሳኔ የሚሰጥ
ይሆናል፡፡
 የዚህ ድንጋጌ አገላለጽ የመጀመሪያ ደረጃ ክስን ብቻ ይመልከት
ወይም የይግባኝ መዝገብን ይጨምር ግልጽ አይደለም፡፡ ነገር ግን
የይግባኝ መዝገብን እንደሚመለከት የዚሁ ህግ ቁጥር 74(1) እና
32(2) በመመልከት ለመረዳት ይቻላል፡፡
 ተከሳሽ በአቀረበው መልስ ላይ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ቢያቀርብና
ክርክሩ ለመሰማት በተቀጠረው ቀን ያልቀረበ ቢሆን በተከሳሹ ላይ
ምን አይነት ትእዛዝ ሊሰጥ ይገባል? ማለትም ከሳሽ ባቀረበበት ክስ
ላይ በሌለበት እንዲሁም ራሱ ባቀረበው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላይ
ደግሞ ክሱን መሰረዝ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል?
 ተከራካሪ ወገኖች ባለመቅረባቸው ምክንያት ፍ/ቤቱ የሚሰጣቸው
የተለያዩ ትእዛዛት ግራ ቀኙ በክርክሩ ሂደት በሚኖራቸው ተሳትፎ
ወይም እንደነገሩ ሁኔታ በነገሩ የክስ ምክንያት ላይ የተለያየ ውጤትን
የሚያስከትሉ ይሆናል፡፡
 ሀ. የተከሳሹ የመከላከያ መልስ የማቅረብ መብት መታለፍ የሚኖረው
ውጤት
 ተከሳሹ መከላከያውን በሚያቀርብበት ቀን መልሱን ይዞ ያልቀረበ
ከሆነ ፍ/ቤቱ የመከላከያ መልሱን የማቅረብ መብቱን የሚያልፍበት
እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ ተከሳሹ የሚያጣው ዋናው መብት በጽሁፍ
መከላከያው ላይ የሚያቀርባቸውን መከራከሪያዎችናን ይህንኑ
መከራከሪያውን ለመደገፍ ሊያቀርብ የሚችላቸውን ማስረጃዎች
ለማቀረብ የማይችል መሆኑ ነው፡፡
 ሆኖም ይህ ትእዛዝ ተከሳሹ በክርክሩ ሂደት ከመሳተፍ የመከልከል
ውጤት አይኖረውም፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ
241 መሰረት ግራ ቀኙን በሚመረምርበት እለት ተከሳሹ በዚሁ
ሂደት ተሳታፊ እንደሚሆን እንዲሁም ከሳሽ የሚያቀርባቸውን
ምስክሮች መስቀለኛ ጥያቄ የመጠየቅና ሌሎች ከሳሽ
በሚያቀርባቸው አቤቱታዎች ላይ መቃወሚያ የማቅረብ መብቱ
የተጠበቀ ነው፡፡
 1 መልሱን የማቅረብ መብቱን ያጣ ተከሳሽ ከሳሽ በክርክሩ ሂደት
የክስ አቤቱታውን ለማሻሻል ጠይቆ ፍ/ቤቱ ይህንኑ የከሳሽ ጥያቄ
ተቀብሎ ክሱን እንዲያሻሽል ፍቃድ ቢሰጠውና አሻሽሎ ቢቀርብ
ተከሳሹ ከሳሽ ቀደም ብሎ ካቀረበው ክስ የተለየ ነገር ያቀረበ
በመሆኑ በማሻሻያው ላይ በጽሁፍ መልስ ልስጥበት በሚል ፍ/ቤቱን
ቢጠይቅ ፍ/ቤቱ የተከሳሽ አቤቱታ እንዴት ሊያስተናግደው ይገባል?
 2 የመከላከያ መልሱን የማቅረብ መብቱ የታለፈበት ተከሳሽ
በመጀመሪያው የክርክሩ መሰማት ቀን የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ ለማቅረብ ጥያቄ ለፍ/ቤቱ ቢያቀርብ ፍ/ቤቱ በዚህ
ጥያቄ ላይ ምን ሊወስን ይገባል ይላሉ?
 ለ. የመዝገብ መዘጋት የሚኖረው ውጤት
 ከፍ ብለን ለመመልከት እንደሞከርነው የመዝገብ መዘጋት የሚኖረው
በመጀመሪያ ደረጃ ክስ ላይ ብቻ ሲሆን ይሄውም በህጉ ቁጥር 69 (2)
መሰረት ክርክሩ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ግራ ቀኙ ያልቀረቡ እንደሆነና
በ70(መ) መሰረት ከሳሽ ለተከሳሽ በቸልተኝነት ወይም በራሱ ጉድለት
መጥሪያ ባግባቡ ያላደረሰ እንደሆነ ነው፡፡
 በዚህ አግባብ የሚዘጋ መዝገብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 71(1) መሰረት
የተዘጋውን መዝገብ ተገቢውን የዳኝነት ክፍያና የተወሰነበትን ኪሳራ
ከፍሎ ከማንቀሳቀስና እንደገና ነገሩ እንዲቀጥል ከማድረግ የሚከለክለው
ነገር የለም፡፡
 እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ፍ/ቤቱ ኪሳራ ሊወስን የሚችለው ለማን ነው
የሚለው ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የዚሁ ህግ ተመሳሳይ ድንጋጌ የእንግሊዝኛ
ቅጂ “…the plaintiff may bring a fresh suit on payment of full
court fees” በሚል የተደነገገ ሲሆን በዚህም ተከሳሹ ሙሉ የዳኝነት
ክፍያውን በመክፈል አዲስ ክስ ለማቅረብ ይችላል ከማለት ውጪ
ስለኪሳራ የሚለው ነገር የለም፡፡
 ልዩ ልዩ የሥነ-ሥርዐት ሕጉን ድንጋጌዎች ስንመለከት ኪሳራ የሚቆረጠው
አንደኛው ተከራካሪ ለክርክሩ መጓተት ምክንያት ሲሆን ለሌላኛው ተከራካሪ
የሚወሰንበት አግባብ ነው በዚህኛው ጉዳይ ግን ተከሳሹ ያልቀረበ መሆኑ
ኪሳራ ደርሶበታል ሊባል ስለማይችል ኪሳራ የሚቆረጥበት ምክንያት ግልጽ
አይደለም፡፡ በመሆኑም የአማርኛው ቅጂ በህጉን ኪሳራ ሊቆረጥ አስፈላጊ
የሚሆንበትን ምክንያት አላማ ያላገናዘበ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ
የእንግሊዝኛው ቅጂ ተፈጻሚነት ሊኖረው እንደሚገባ ለመረዳት ይቻላል፡፡
 ይሁን እንጂ በዚሁ ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር 71(2) መሰረት ከሳሽ የዳኝነት
ሳይከፍል የክስ መዝገቡን የሚያንቀሳቅስበት ልዩ ሁኔታ ተመልክቷል፡፡
ይሄውም ከሳሽ ያልቀረበው በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ያስረዳ እንደሆነና
ይህንንም ምክንያት ፍ/ቤቱ የተቀበለው እንደሆነ ነው፡፡ ይህ የሕጉ
አቀማመጥ ተፈጻሚነት የሚኖረው በተለይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(2)
መሰረት ክርክሩ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ላልቀረበ ከሳሽ ነው፡፡ ምክንያቱም
ስለከሳሽ አለመቅረብ የተመለከተው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70(መ) ሳይሆን
በ69 (2) ላይ በመሆኑ ነው፡፡
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx
የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx

More Related Content

Featured

Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
contently
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
Albert Qian
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Kurio // The Social Media Age(ncy)
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Search Engine Journal
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
SpeakerHub
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next
Tessa Mero
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Lily Ray
 
How to have difficult conversations
How to have difficult conversations How to have difficult conversations
How to have difficult conversations
Rajiv Jayarajah, MAppComm, ACC
 
Introduction to Data Science
Introduction to Data ScienceIntroduction to Data Science
Introduction to Data Science
Christy Abraham Joy
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best Practices
Vit Horky
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project management
MindGenius
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
RachelPearson36
 
Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...
Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...
Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...
Applitools
 
12 Ways to Increase Your Influence at Work
12 Ways to Increase Your Influence at Work12 Ways to Increase Your Influence at Work
12 Ways to Increase Your Influence at Work
GetSmarter
 
More than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike Routes
More than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike RoutesMore than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike Routes
More than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike Routes
Project for Public Spaces & National Center for Biking and Walking
 
Ride the Storm: Navigating Through Unstable Periods / Katerina Rudko (Belka G...
Ride the Storm: Navigating Through Unstable Periods / Katerina Rudko (Belka G...Ride the Storm: Navigating Through Unstable Periods / Katerina Rudko (Belka G...
Ride the Storm: Navigating Through Unstable Periods / Katerina Rudko (Belka G...
DevGAMM Conference
 
Barbie - Brand Strategy Presentation
Barbie - Brand Strategy PresentationBarbie - Brand Strategy Presentation
Barbie - Brand Strategy Presentation
Erica Santiago
 
Good Stuff Happens in 1:1 Meetings: Why you need them and how to do them well
Good Stuff Happens in 1:1 Meetings: Why you need them and how to do them wellGood Stuff Happens in 1:1 Meetings: Why you need them and how to do them well
Good Stuff Happens in 1:1 Meetings: Why you need them and how to do them well
Saba Software
 

Featured (20)

Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
 
How to have difficult conversations
How to have difficult conversations How to have difficult conversations
How to have difficult conversations
 
Introduction to Data Science
Introduction to Data ScienceIntroduction to Data Science
Introduction to Data Science
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best Practices
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project management
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
 
Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...
Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...
Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...
 
12 Ways to Increase Your Influence at Work
12 Ways to Increase Your Influence at Work12 Ways to Increase Your Influence at Work
12 Ways to Increase Your Influence at Work
 
ChatGPT webinar slides
ChatGPT webinar slidesChatGPT webinar slides
ChatGPT webinar slides
 
More than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike Routes
More than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike RoutesMore than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike Routes
More than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike Routes
 
Ride the Storm: Navigating Through Unstable Periods / Katerina Rudko (Belka G...
Ride the Storm: Navigating Through Unstable Periods / Katerina Rudko (Belka G...Ride the Storm: Navigating Through Unstable Periods / Katerina Rudko (Belka G...
Ride the Storm: Navigating Through Unstable Periods / Katerina Rudko (Belka G...
 
Barbie - Brand Strategy Presentation
Barbie - Brand Strategy PresentationBarbie - Brand Strategy Presentation
Barbie - Brand Strategy Presentation
 
Good Stuff Happens in 1:1 Meetings: Why you need them and how to do them well
Good Stuff Happens in 1:1 Meetings: Why you need them and how to do them wellGood Stuff Happens in 1:1 Meetings: Why you need them and how to do them well
Good Stuff Happens in 1:1 Meetings: Why you need them and how to do them well
 

የፍትሃ_ቤሔር_ሥነሥርዓት_ሕግ_ማሰልጠኛ_ማንዋል_2_Copy.pptx

  • 1.
  • 2.  1. የፍርድ ቤት ሥልጣን  2. የተከራካሪ ወገኖችና የክስ ምክንያቶች መጣመር  3. ከክርክር በፊት ሊፈጸሙ ስለሚገባቸው የሥነ-ሥረዐት ደንቦች  የአቤቱታ ምንነትና አቀራረብ  አቤቱታን ስለማሻሻል  4. የመጥሪያ አላላክ ሂደት  5. ክስን ስለመስማት  6. ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ፣ ብይን ወይም ትእዛዝ እንደገና ስለሚከልስበት አግባብ  7. እግድና ንብረት ማስከበርን በተመለከተ
  • 3.  በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ 79(1) ላይ በግልጽ እንደተደነገገው በፌድራልም ሆነ በክልል የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ነው፡፡  ነገር ግን ፍ/ቤቶች የሚቀርቡላቸውን ሁሉንም ጉዳዮች በማየት ውሳኔ ይሰጣሉ ማለት እንዳልሆነ ከዚሁ ህገመንግስት አንቀጽ 37 (1) ምንባብ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡  በዚሁ ድንጋጌ መሰረት ፍ/ቤት ለመዳኘት ሥልጣን የሚኖረው ጉዳዩ በፍ/ቤት ሊወሰን የሚገባው ጉዳይ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቶች የሚቀርቡላቸውን ጉዳዮች ተመልክተው ከመወሰናቸው በፊት በቅድሚያ ጉዳዩ በፍ/ቤት ታይቶ ውሳኔ ለማግኘት የሚገባው ጉዳይ መሆን አለመሆኑን መለየት ያስፈልጋቸዋል፡፡
  • 4.  ለዳኝነት የቀረበው ጉዳይ በፍ/ቤት ሊወሰን የሚገባው ሆኖ ከተገኘ ቀጣዩ ፍ/ቤቶች ሊያጤኑት የሚገባው ነገር ይህንኑ ጉዳይ ለመዳኘት ስልጣን ያላቸው መሆን አለመሆኑን መመርመር ይኖርባቸዋል፡፡  ማንኛውም ፍ/ቤት አንድን ጉዳይ ተመልክቶ ዳኝነት ለመስጠት በህግ ስልጣን የተሰጠው ሊሆን ይገባል፡፡ የፍ/ቤት ስልጣን ማለት አንድን ጉዳይ ሰምቶ ውሳኔ የመስጠት ችሎታ ማለት ነው፡፡  የአንድ ፍ/ቤት ስልጣን በሶስት ክፍሎች የሚከፈል ሲሆን፣ እነዚህም፡ የብሄራዊ፣ የስረ ነገርና የአካባቢ (ግዛት ክልል) የስልጣን አይነቶች ናቸው፡፡
  • 5.  ብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን ማለት የአንድ ሀገር ፍርድ ቤት አንድን ጉዳይ ሰምቶ ውሳኔ የመስጠት ችሎታ አለው? ወይስ የለውም? የሚለውን የሚመልስ የስልጣን አይነት ነው፡፡  የፍትሕብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን ይህንን አይነቱን የፍ/ቤት የዳኝነት ሥልጣንን በተመለከተ የደነገገው ነገር የለም፡፡  ፍ/ቤቶች በተለይም የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን የሚያስነሱ ጉዳዮች ምን አይነት ሁኔታዎች ናቸው? ይህንን ሥልጣን መሰረት በማድረግ በተከራካሪ ወገኖች መቃወሚያ መቼ ሊነሳ ይገባል? መቃወሚያ ሳይቀርብ ውሳኔ ቢሰጥስ የውሳኔው እጣ ፋንታ ምን ይሆናል? የሚሉትና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስ ችግር ሲፈጥርባቸው ይስተዋላል፡፡
  • 6.  አንድ ጉዳይ ለዳኝነት የቀረበለት የአንድ ሀገር ፍ/ቤት የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን የሚኖረው ከተከሳሹ ወይም የክርክሩ ምክንያት የሆነው ነገር ከተፈጸመበት ወይም የክርክሩ መነሻ የሆነው ንብረት የሚገኝበት ሀገር ጋር በቂ ግንኙነት ያለው ሲሆን ወይም የተከራካሪ ወገኖች በአንድ ሀገር ፍ/ቤት ለመዳኘት ስምምነት ያደረጉ እንደሆነ ነው፡፡ እነዚህን አገናኝ ምክንያቶች መሰረት በማድረግ አንድ ሀገር የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን ይኖረዋል ማለት ሌላ ሀገር በዚያው ጉዳይ ይሄው የዳኝነት ስልጣን አይኖረውም ማለት አይደለም፡፡
  • 7.  የብሔራዊ የዳኝነት ስልጣን ክርክር የሚነሳውም የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን ላለው የአንድ ሀገር ፍ/ቤት የቀረበው ጉዳይ ጉዳዩ ከቀረበለት ሀገር ፍ/ቤት በተጨማሪ የሌላ ሀገር/ሀገራት ፍ/ቤት ለማየትና ውሳኔ ለመስጠት ስልጣን ሲኖረው ነው፡፡  እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን ባላቸው አንድ ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ ስልጣን ያለው የሌላ ሐገር ፍ/ቤት ውሳኔ የሰጠበት ቢሆንና ይህንኑ ውሳኔ ወደ ጎን በማለት ከተከራካሪዎቹ አንዱ እንደ አዲስ በኢትዮጵያ ፍ/ቤት ክስ ቢያቀርብ፣ ሌላው ተከራካሪ ቀደም ሲል በሌላ ሀገር ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በመጥቀስ መቃወሚያውን ቢያቀርብ መቃወሚያ የቀረበለት ፍ/ቤት ምን ሊወስን ይችላል? የሚለው ነው፡፡
  • 8.  ከዚህ አንጻር በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 መሰረት በውሳኔዎቹ የሚሰጠው የህግ ትርጉም የአስገዳጅነት ውጤት እንዲኖረው ስልጣን የተሰጠው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዚህ ጉዳይ ላይ በቅጽ 12 በሰ/መ/ቁ/ 54632 እና በሰ/መ/ቁ/ 59953 የሰጣቸውን ተቀራራቢነት ያላቸውን ሁለት ውሳኔዎች መመልከት ይቻላል፡፡  በነዚህ ውሳኔዎችም ላይ እንደተመለከተው አንድ በውጪ ሀገር ባለ ፍ/ቤት የተሰጠን ውሳኔ በአንቀጽ 5 መሰረት በፍርድ ማለቅ መርህን በመጥቀስ መቃወሚያ ሲቀርብ በፍትሐብሄር ስነ ስርዓት ህግ ከአንቀጽ 456 እስከ 461 የተደነገጉት ድንጋጌዎች በሚያሳዩት መልኩ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነትን ሊያገኝ የሚችልበትን ሁኔታ በግልፅ መሟላቱ በመጀመሪያ መረጋገጥ ይኖርበታል በሚል ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ በዚህ አይነት ጉዳዮች ላይ በዚሁ አግባብ መስራት የሚያስፈልግ ይሆናል፡፡
  • 9. • አንድ ጉዳይ የቀረበለት ፍ/ቤት ጉዳዩን አይቶ ውሳኔ ለመስጠት ምንም አይነት የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን የሌለው መሆኑን የተረዳ እንደሆነ ፍ/ቤቱ በፍታ/ሥ/ሥ/ህ ቁጥር 231 መሰረት መዝገቡን መዝጋት ይኖርበታል፡፡
  • 10.  ፍ/ቤቱ ስልጣን የሌለው መሆኑን ባለመረዳት ወይም በሌላ በማንኛውም ምክንያት መዝገቡን ያልዘጋ እንደሆነ ተከሳሹ በሚያቀርበው የጽሁፍ መልስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማቅረብ ፍ/ቤቱ መዝገቡን እንዲዘጋለት ለማድረግ ይችላል፡፡  ነገር ግን ተከሳሹ ቀርቦ ምንም አይነት መቃወሚያ ያላቀረበ እንደሆነ ጉዳዩ አንዲታይና ውሳኔ እንዲሰጥበት በተዘዋዋሪ የተስማማ እንደሆነ በዝምታ ፈቃዱን እንደሰጠ ተቆጥሮ ፍ/ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ በተከራካሪዎች ላይ አስገዳጅነት ይኖረዋል፡፡
  • 11.  የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን የሌለው ፍ/ቤት የላከለትን መጥሪያ ባለመቀበል ፍ/ቤት ያልቀረበ ተከሳሽ ላይ ፍ/ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ አስገዳጅነት እንዴት ይታያል?
  • 12.  የፍ/ቤት የግዛት ነገር ስልጣን በፍትሕብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን ከአንቀጽ 19-30 ባሉት ድንጋጌዎች ተደንግጎ ይገኛል፡፡  ይህ አይነቱ የፍ/ቤት የዳኝነት ሥልጣን አንድን ጉዳይ ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት የስረ-ነገር ሥልጣን ካላቸው ፍ/ቤቶች መካከል በየትኛው ፍ/ቤት ሊታይ እንደሚገባ የሚወስን የዳኝነት ሥልጣን አይነት ነው፡፡  የዚህም የዳኝነት ሥልጣን አስፈላጊነት፣ ሌሎች ሁኔታዎች እንዳሉ ሆኖ፣ በመርህ ደረጃ ለተከራካሪ ወገኖች በተለይም ለተከሳሹ ማስረጃውን ለማቅረብና ክርክሩንም በተመቼ ሁኔታ ለማከናወን እንዲያስችለው ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
  • 13.  በመርህ ደረጃ የፍ/ቤቶች የግዛት ክልል ስልጣን በፍትሐ ብሄር ስነ- ስርዓት ህጋችን አንቀጽ 19(1) እና (2) ላይ በግልጽ የተደነገገ ሲሆን በዚህም መሰረት በህግ በሌላ መልኩ እስካልተደነገገ ድረስ ማናቸውም ክስ መቅረብ የሚገባው ተከሳሹ ወይም ተከሳሾቹ ከአንድ በላይ በሚሆኑ ጊዜ ከተከሳሾቹ አንዱ በሚኖርበት ወይም ለግል ጥቅሙ በሚሰራበት ክፍል በሚያስችለው ባለስልጣን ፍ/ቤት ነው፡፡  ከዚህ ድንጋጌ አቀራረጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ሥነ-ሥርዓት ህጋችን የግዛት ክልል ስልጣንን በመወሰን ረገድ ከላይ ለማመልከት እንደተሞከረው በመርህ ደረጃ ተከሳሹን ማዕከል ያደረገ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል፡፡
  • 14.  ይህም የሆነበት ምክንያት የተለያየ ቢሆንም በዋናነት ግን በአንድ በኩል ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ ተገቢ የሚላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማቅረብ በቀላሉ ለመከላከል እንዲችል ሲሆን ሌላውና ዋናው ምክንያት ሊሆን የሚችለው ፍ/ቤቱ በቀረበው ክስ ላይ በተከሳሹ ላይ ፍርድ ቢሰጥ ፍርዱን በቀላሉ ማስፈጸም እንዲቻል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል፡፡
  • 15.  የመርሁ ልዩ ሁኔታዎች የክስ ምክንያትን መነሻ በማድረግ ሊታዩ የሚገባቸው በየትኛው ፍ/ቤት መሆን እንዳለበት በፍትሕብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 20 እና ተከታዮቹ ተመልክተዋል፡፡  በልዩ ሁኔታ የተዘረዘሩትን ጉዳዮች ክሱን ለማየት በህጉ የግዛት ክልል ሥልጣን ለተሰጠው ፍ/ቤት መቅረብ ያለበት መሆኑን እንዲሁም ፍ/ቤቶች የቀረበላቸው በህጉ አግባብ መሆኑን የማረጋገጥ ሀላፊነት ይኖርባቸዋል፡፡  ይሁን እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 20 እና ተከታዩቹ ክሱ ተከሳሹ ከሚኖርበት ወይም ለግል ጥቅሙ ከሚሰራበት ቦታ በተጨማሪ በሌላ ቦታ ክስ ማቅረብ እንደሚቻል ተደንግጎ ከተገኘ (ቁጥር 24(1) እና 27) ክሱ በከሳሹ ምርጫ ከሁለት በአንዱ ክስ የመመስረት መብት ያለው መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
  • 16.  ሌላው እዚህ ጋር ሊነሳ የሚገባው ነጥብ በህጉ አንቀጽ 29 ላይ የተመለከተው የልዩ ሁኔታዎቹ ልዩ ሁኔታ ነው፡፡  በዚሁ ድንጋጌ እንደተመለከተው ከአንድ የክስ ምክንያት በላይ የሆኑ ክሶች ተጣምረው የሚቀርቡ እንደሆነና የክስ ምክንያቶቹ ከአንድ በላይ በሆኑ የፍ/ቤት የግዛት ሥልጣን ስር የሚወድቁ ከሆነ የአንዱን የክስ ምክንያት ለማየት በሚችለው ፍ/ቤት ቀርቦ ሊታይ የሚችል መሆኑን ነው፡፡  ይህን በምሳሌ ለመግለጽ ያህል በተለያየ የፍ/ቤት የግዛት ሥልጣን ስር የሚወድቁ የውልና ከውል ውጪ ሃላፊነት ክሶች ተጣምረው ቢቀርቡ በህጉ አንቀጽ 24 ወይም 27 በተደነገገው በአንዱ የፍ/ቤት የግዛት ሥልጣን መቅረብና መዳኘት የሚችሉበት አግባብ ነው፡፡
  • 17.  የግዛት ክልል ሥልጣኑ ያልሆነ ክስ የቀረበለት ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 10(1) አግባብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231(1) (ለ) መሠረት ሥልጣን የሌለው መሆኑን በመግለፅ መዝገቡን መዝጋት ይኖርበታል፡፡  ይሁንና በግዛት ክልል ሥልጣኑ የማይወድቅ ክስ የቀረበለት ፍ/ቤት በቸልተኝነትም ሆነ በአተረጓጎም ችግር ከላይ በተጠቀሰው የሥነ-ሥርዓት ህጉ አግባብ የክስ መዝገቡን ያልዘጋው እንደሆነ ተከሳሹ በሚያቀርበው የመልስ ማመልከቻ ላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244(2)(ሀ) መሠረት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡  ይህ መቃወሚያ መቅረብ በሚገባው ጊዜ ካልቀረበ የግዛት ክልል ሥልጣን አለመኖር ትክክለኛ ፍርድን ለመስጠት የሚያሰናክል ባለመሆኑ ተከሳሹ እንደተወው ከሚቆጠሩት የመቃወሚያ ምክንያት አንዱ በመሆኑ ዘግይቶ የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  • 18.  መቅረብ በሚገባው ጊዜ መቃወሚያው ቀርቦ እንኳ ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 245 መሠረት ህጉን በተሳሳተ መንገድ ተርጉሞ ሥልጣን አለኝ ብሎ ክርክሩን ቢቀጥል እና በመጨረሻም በዋናው ነገር ላይ ውሳኔ ከሰጠ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 10 (2) መሰረት የግዛት ክልል ሥልጣን በሌለው ፍ/ቤት በመታየቱ የተነሣ ፍትህ የተጓደለበት መሆኑን ተከሳሹ ካላረጋገጠ በቀር የግዛት ክልል ሥልጣን በሌለው ፍ/ቤት ታይቶ የተሰጠ ውሳኔ መሆኑን ብቻ መሠረት በማድረግ ይግባኝ ሊቀርብበት አይችልም፡፡
  • 19.  የፍ/ቤት የስረ-ነገር ስልጣን ማለት አንድን ጉዳይ በትክክል ተመልክቶ አግባብነት ያለው፤ ፍትህን ያገናዘበ ፍርድ ለመስጠት አቅም ያለው ፍ/ቤት የትኛው ነው የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ የስልጣን አይነት ነው፡፡  ይህ የስልጣን አይነት በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ ፍ/ቤቶች የዳኝነት ሥራን የሚያከፋፍል ነው፡፡  በዚህም ከፍ ያለው ጉዳይ በየደረጃው ከተቋቋሙት ፍ/ቤቶች መካከል ከፍ ባለው እንዲሁም ቀለል ያሉ ጉዳዮች በዝቅተኛ እርከን ላይ በሚገኙ ፍ/ቤቶች እንዲታዩ በማድረግ ፍትሃዊነት ያለው ፍርድ መስጠትን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
  • 20.  የፍ/ቤት የስረ ነገር ስልጣን በሁለት መልኩ ይወሰናል፡፡  የመጀመሪያው በጉዳዩ አይነት ሲሆን ይህም ማለት የጉዳዮችን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ ማህበራዊ ፋይዳ፣ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዲሁም ውስብስብነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ያላቸው የገንዘብ መጠን ምንም ይሁን የሚዳኙበትን የፍርድ ቤት እርከን በግልጽ ድንጋጌ የሚቀመጥበት አኳኋን ነው፡፡  ሌላውና ሁለተኛው የፍ/ቤት የስረ-ነገር ስልጣን በክርክሩ ዳኝነት የተጠየቀበትን የገንዘብ መጠን መሰረት በማድረግ ጉዳዩ በየትኛው የፍ/ቤት እርከን እንደሚታይ የሚወሰንበት አግባብ ነው፡፡
  • 21.  በክልላችን የሚገኝ አንድ ፍ/ቤት የቀረበለትን የፍትሃ ብሄር ጉዳይ ከመመልከቱ በፊት የሥረ-ነገር ሥልጣን ያለው መሆኑን ሶስት ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ መመርመር ይኖርበታል፡፡  1ኛ. የቀረበለት ጉዳይ በመደበኛ ፍ/ቤት ሊታይ የሚቸል ነው ወይስ ሌላ የዳኝነት አካል ይህንኑ ጉዳይ ለማየት በህግ ስልጣን ተሰጥቶታል የሚለውን ነው፡፡  በተለያዩ ህጎች የአስተዳደር ፍ/ቤት እንዲቋቋም በማድረግ የተለዩ ጉዳዮችን እንዲመለከቱ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡  ለምሳሌ ከግብር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን የሚመረምር የግብር ይግባኝ ኮሚሽን፣ የመንግስት ሰራተኞችን ከስራቸው ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥፋት ነክ ጉዳዮችን በመመርመር ውሳኔ ለመስጠት የተቋቋመውን የሲቪል ሰርቪስ ፍ/ቤትን እንዲሁም በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 የሚተዳደሩ ሰራተኞችን በተመለከተ የሚነሳ የወል የስራ ክርክርን የሚመለከተውን የስራ ክርክር ቦርዱን መጥቀስ ይቻላል፡፡
  • 22.  2ኛ. ፍ/ቤቱ የቀረበለት ጉዳይ በፌደራል ወይም በክልሉ የዳኝነት ሥልጣን ስር የሚወድቅ መሆኑን መለየት ይኖርበታል፡፡  ይህም በተለይ በአሁኑ ጊዜ ከምንከተለው የፌደራል መንግስት አወቃቀር አንጻር በኢፌደሪ ህገመንግስት አንቀጽ 50 መሰረት የፌደራልና የክልል መንግስታት እንደሚኖሩና ሁለቱም መንግስታት የራሳቸው ሶስት እርከን ያለው ፍ/ቤት እንደሚኖሯቸው ተደንግጓል፡፡  ከዚህም በተጨማሪ በዚሁ ህገመንግስት አንቀጽ 80(1) እና (2) ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፌደራል ጉዳይ እንዲሁም የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በክልል ጉዳይ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጡ ተደንግጓል፡፡
  • 23.  ይህም የህገመንግስቱ አቀራረጽ በፌደራሉና በክልል መንግስታት የሚቋቋሙ ፍ/ቤቶች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ሥልጣን እንዳላቸው የሚገልጽ ነው፡፡ በመሆኑም በክልላችን የሚገኙ ፍ/ቤቶች ለመዳኘት ሥልጣን የተሠጣቸውን ጉዳዮች ለይተው ሊያውቁ ይገባል፡፡  በፍሕብሔር ጉዳይ የሁለቱን መንግስታት በተለይም የፌደራል መንግስቱንና የክልላችንን ፍ/ቤቶች የዳኝነት ሥልጣን ወሰንን የፌደራል ፍ/ቤቶችን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 እንዲሁም የአብክመ የፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 223/2007ን በመመልከት በፌደራሉ ወይም በክልል የዳኝነት ሥልጣን ስር የሚወድቁ ጉዳዮችን መለየት ይቻላል፡፡
  • 24.  በዚህም መሰረት የአብክመ ፍ/ቤቶች የሚኖራቸውን የዳኝነት ሥልጣንን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀጽ 13 (1) ላይ በጥቅል እንደተመለከተው በግልጽ ተለይተው በፌደራሉ መንግስት ፍ/ቤቶች ስልጣን ስር ከሚወድቁት ጉዳዮች በስተቀር በሌሎች ጉዳዮች ላይ የመዳኘት ሥልጣን ይኖራቸዋል፡፡  በዚህ የህጉ አቀራረብ መሰረት በክልላችን የሚገኙ ፍ/ቤቶች በምን አይነት የፍትሃ ብሄር ጉዳዮች ላይ የመዳኘት ሥልጣን አላቸው የሚለውን ለመረዳት የግድ ለፌደራል ፍ/ቤቶች ተለይተው የተሰጡትን ጉዳዮች መገንዘብ የሚያስፈልጋቸው ይሆናል፡፡
  • 25.  በዚህ ረገድ የፌደራል ፍ/ቤቶችን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር 25/88 በአንቀጽ 5 ላይ የፌደራል ፍ/ቤቶች የመዳኘት ሥልጣን ስር የሚወድቁ የፍትሕብሔር ጉዳዮችን ዘርዝሮ ይደነግጋል፡፡  እነዚህም፡- ከተከራካሪ ወገኖች ማንነት አንጻር፡ የፌደራል መንግስቱ አካል ተከራካሪ በሆነበት ጉዳይ፣ መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልሎች ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል በሚነሱ ክርክሮች፣ የፌደራል መንግስቱ ባለስልጣኖችና ሰራተኞች በስራቸው ወይም በሀላፊነታቸው ምክንያት ተጠያቂ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች፣ የውጭ ሀገር ዜጋ ተከራካሪ በሆነበት ጉዳይና በፌደራል መንግስቱ አካላት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶችና ማህበሮችን በሚመለከት በሚነሱ ክርክሮች፤ እንዲሁም
  • 26.  ከአከራካሪው ጉዳይ አኳያ፡- በሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች፣ በፈጠራ፣ በድርሰትና በስነ-ጥበብ ባለቤትነት መብቶች፣ በኢንሹራስ ውል ላይ በሚነሱ ክርክሮችና ተገዶ የመያዝ ህጋዊነትን ለማጣራት በሚቀርብ አቤቱታ ላይ አከራክሮ ውሳኔ ለመስጠት ብቸኛ ሥልጣን ያለው የፌደራል ፍ/ቤት እንደሆነ ተደንግጓል፡፡  ከላይ የተመለከቱትን ጉዳዮች የክልላችን ፍ/ቤቶች በኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀጽ 80(2) እና(4) መሰረት በውክልና ለመዳኘት ከሚችሉ በስተቀር በቀጥታ የመዳኘት ሥልጣን አይኖራቸውም፡፡
  • 27.  አንድ ጉዳይ በክልሉ ፍ/ቤቶች ሊታይ የሚችል መሆኑ ከተረጋገጠ በሶስተኛ ደረጃ ፍ/ቤቱ ሊያጤነው የሚገባው ነገር በየትኛው የክልሉ ፍ/ቤት እርከን ጉዳዩ ታይቶ ውሳኔ ሊያገኝ ይገባል የሚለው ይሆናል፡፡  ይህም በሁለት መልኩ የሚወሰን ሲሆን ይሄውም በጉዳዩ አይነት ወይም የክስ አቤቱታው በያዘው የገንዘብ መጠን ነው፡፡ የአብክመ የፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 223/2007 የፍ/ቤቶችን የሥረ- ነገር ሥልጣንን በዋናነት የወሰነው የክርክሩ የገንዘብ መጠንን መሰረት በማድረግ ነው፡፡
  • 28.  በዚህም መሰረት የአዋጁ አንቀጽ 13 (2) እንደደነገገው በሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ እስከ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) እንዲሁም በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ እስከ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) እንዲሁም ከጉዳዮች አይነት አኳያ በዚሁ የአዋጁ ድንጋጌ 13(3) መሰረት ወላጅነትን፣ አካልን ነጻ ማውጣትና ሌሎች ዋጋቸው በገንዘብ በማይተመን የፍትሕብሔር ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ክርክሮችን አከራክሮ የመወሰን የሥረ-ነገር የዳኝነት ሥልጣኑ የወረዳ ፍ/ቤቶች እንደሆነ ተደንግጓል፡፡
  • 29.  የክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤቶች በውክልና የመዳኘት ሥልጣን ከተሰጣቸው የፌደራል ጉዳዮች ውጪ በጠቅላላው በክልሉ ጉዳዮች የዳኝነት የስረ- ነገር ሥልጣናቸው የተወሰነው በክርክሩ የገንዘብ መጠን ላይ ነው፡፡  ከዚህ አንጻር ከላይ የተመለከተው አዋጅ አንቀጽ 15 ንዑስ ቁጥር (2) እንደሚደነግገው የክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤቶች በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ከብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) እንዲሁም በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ በሚነሱ ክርክሮች ላይ የሥረ-ነገር የዳኝነት ሥልጣናቸው የተወሰነ ነው፡፡
  • 30.  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 9(1) ላይ እንደተመለከተው የስረ-ነገር የዳኝነት ስልጣን በሌለው ጉዳይ ላይ የክስ አቤቱታ የቀረበለት ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231 በተነገረው ድንጋጌ መሰረት ማመልከቻው ተቀባይነት የለውም በማለት መመለስ እንዳለበት አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡  በዚሁ ድንጋጌ መሰረትም የቀረበውን የገንዘብ ክስ ለመቀበል የዳኝነት ስልጣን ያለው መሆኑን ፍ/ቤቱ የሚወስነው ከቁጥር 226- 228 የተመለከተውን ድንጋጌ በመከተልና በማመልከቻው ላይ የተገለጸውን መሰረት በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 16(2) በግልጽ ይደነግጋል፡፡  በመሆኑም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 16ም ሆነ ከ226-228 በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት የፍ/ቤቶች የሥረ-ነገር ሥልጣን የሚወሰነው ከሳሹ በአቤቱታው ላይ በሚጠይቀው የገንዘብ መጠን ላይ ነው፡፡
  • 31.  ከዚህ በተለየ ከሳሽ በክሱ ላይ የጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ለመዳኘት የስረ-ነገር ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት አቤቱታውን ተቀብሎ ተከሳሽን ከጠራ በኋላ ባለው የክርክሩ ሂደት የፍ/ቤቱ የስረ-ነገር ሥልጣን ሊቀየር የሚችልባቸው ሶስት ሁኔታዎች በሥነ-ሥርዓት ህጉ ላይ ይገኛሉ፡፡  የመጀመሪያው ተከሳሹ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 250 መሰረት ከሳሽ በአቤቱታው ላይ ያቀረበው የንብረት ግምት ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ እንደሆነና ፍ/ቤቱም በመቃወሚያው መሰረት የንብረቱን ትክክለኛ ዋጋ እንዲያጣራ በሚሾመው አካል ሲጣራ የፍ/ቤቱን ሥረ-ነገር ሥልጣን የሚቀይር ከሆነ ነው፡፡
  • 32.  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 250 ፍ/ቤቱ አከራካሪውን ንብረት ግምት ከተከሳሹ መቃወሚያ ሲቀርብ በመቃወሚያው መሰረት ፍ/ቤቱ እንዲጣራ ያደርጋል ከማለት ውጪ በተለይም በማጣራት ሂደት የአከራካሪው ንብረት ግምት የፍ/ቤቱን ስልጣን የሚቀይር ቢሆን ምን አይነት ትእዛዝ ሊሰጥ ይገባል በሚለው ላይ ምንም የሚለው ባይኖርም ሥልጣኑ ያልሆነውን ነገር ሊመለከትና የጸና ፍርድ ሊሠጥ ስለማይችል መዝገቡን ሥልጣን የሌለው መሆኑን ገልጾ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 245 መሰረት መዝጋት ይኖርበታል፡፡  ሌላውና ሁለተኛው ሁኔታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 16 (3) መሰረት ክሱ ቀርቦ የማስረጃው መሰማት ከመጀመሩ በፊት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 242 እና 243 አግባብ አንደኛው ወገን የቀረበበትን ክስ በከፊል በማመኑ ምክንያት በክሱ ላይ የተመለከተው የገንዘብ ልክ የተቀነሰ እንደሆነ ፍ/ቤቱ ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው በተቀነሰው መጠን ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ያስተላልፈዋል ወይም ራሱ ማስረጃውን በመቀበል ውሳኔ ሊሰጥበት የሚችልበት ሁኔታ ነው፡፡
  • 33.  ሶስተኛው ሁኔታ አቤቱታ ማሻሻልን ተከትሎ የሚመጣ የፍ/ቤት የስረ-ነገር ሥልጣን መቀየር ነው፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(5) መሰረት በተለይም የአቤቱታ ማሻሻያው የፍ/ቤቱን የሥረ-ነገር ሥልጣን ወደ ከፍያለው ፍ/ቤት የሚቀይር ከሆነ ክሱን የሚያየው ፍ/ቤት ይህንኑ ክስ ለመመልከት ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ማስተላለፍ እንደሚገባው ይደነግጋል፡፡  የስረ-ነገር ሥልጣኑ ያልሆነ ክስ የቀረበለት ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231(1)(ለ) መሰረት ሥልጣን የሌለው መሆኑን ገልጾ መዝገቡን ያልዘጋና ተከሳሹ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያላነሳው ቢሆንም እንኳ በየትኛውም የክርክሩ ደረጃ በተከሳሹ ጠያቂነትም ሆነ በፍ/ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት መዝገቡን መዝጋት ይኖርበታል፡፡
  • 34.  ምክንያቱም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244(3) እንደተመለከተው አቅም የሌለው ፍ/ቤት ፍትህን ያገናዘበ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ስለማይገመትና በዚህም የተነሣ የሥረ-ነገር ሥልጣን አለመኖር ትክክለኛውን ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክል ሆኖ ስለሚገኝ በመቃወሚያ ማቅረቢያ ጊዜ ባይቀርብም እንደተተወ ከማይቆጠሩትና ከፍርድ በፊት በማናቸውም ጊዜ ሊቀርቡ ከሚችሉት የመቃወሚያ ዓይነቶች አንዱ በመሆኑ ነው፡፡  በዚህ አኳኋን ሳይታረም ሙሉ ክርክር ተደርጎ ማስረጃ ተሰምቶ የተወሰነ መሆኑ፤ እንዲሁም የይግባኝ መብቱ እስከፈቀድ ድረስ በየደረጃው ታይቶ ውሳኔ ያረፈበት መሆኑ ቢታወቅም፤ የሥረ-ነገር ሥልጣን ጉዳይ ሊጣስ የማይገባው የመርህ ጥያቄ እንደመሆኑ መጠን በየደረጃው በነበረው ክርክር የታየው ወጭ የባከነው ጊዜና ድካም ግምት ውስጥ ሳይገባ በመጨረሻው በሰበር ደረጃም ቢሆን ሊሻር የሚችል መሆኑ ሊተኮርበት የሚገባው ነጥብ ነው፡፡
  • 35.  ነገር ግን አንድ ጉዳይ የስረ-ነገር ሥልጣኑ ያልሆነ ፍ/ቤት ተመልክቶ ውሳኔ የሰጠ እንደሆነና ይሄው ውሳኔ በይግባኝ እስካልተሻረ ድረስ ውሳኔው የሚጸና መሆኑ ነው፡፡  በኢትዮጵያ የፍታብሔር የፍትህ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ በህግ ፊት የማይጸና ወይም ፍርስ (null and void) የሚባል ውሳኔ እንደሌለ በግልጽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 212 ላይ ተደንግጓል፡፡ በዚሁ አግባብም የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 15 በሰበር መዝገብ ቁጥር 85718 ላይ በግልጽ ውሳኔ ሰጥቶ እናገኛለን፡፡
  • 36.  ከስረ-ነገር ሥልጣን ጋር በተያያዘ በተግባር ከሚታዩ ችግሮች መካከል አንዱ የክሱ ምክንያት የሆነው ነገር በገንዘብ ተገምቶ መቅረብ እየቻለ አንዳንድ ክስ አቅራቢዎች በገንዘብ ሊገመት አይችልም በማለት በፍትሕብሔር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 18 መሰረት ክስ ሲያቀርቡና ፍ/ቤቶችም የክሱን አርዕስት ብቻ በመመልከት ክሱን ተቀብለው አከራክረው ውሳኔ ሲሰጡ ይታያል፡፡  እንዲህ አይነቱ የክስ አቀራረብ አንድም ባለማወቅ የሚቀርብ ሲሆን፣ አንዳንድ ከሳሾች ግን ሆነ ብለው የክሱ ምክንያት ተገምቶ ቢቀርብ ጉዳዩ ከፍ ባለው ፍ/ቤት የሚታይ እንደሆነ በመረዳት ሥልጣን በሌለው ፍ/ቤት ውሳኔ በማሰጠት የፍርድ ባለመብት ለመሆን በማሰብ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ተገቢውን የፍ/ቤት የአገልግሎት ክፋያ ላለመክፈል በሚል የሚያደርጉት የክስ አቀራረብ ነው፡፡
  • 37.  በዚህ አግባብ ከሚቀርቡ ክሶች መካከል ከገጠር የመሬት ሁከት ይወገድልኝ ክስ ጋር አብረው የሚያቀርቡት የአለባ ግምት ጥያቄ ከመሬቱ ጋር በአንቀጽ 18 መሰረት የሚቀርብበት ሁኔታ፤ በገንዘብ ተገምተው ሊቀርቡ የሚችሉ ንብረቶች ላይ ሁከት ተፈጽሞብኛል በሚል የሚቀርቡ ክሶች፣ እንዲሁም ከውል ጋር በተያያዘ ውል ይፍረስልኝ፣ ይፈጸምልኝና የመሳሰሉት በተደጋጋሚ በፍ/ቤቶች ቀርበው ተገቢው የፍ/ቤት አገልግሎት ክፍያ ሳይፈጸምባቸው አንዳንድ ጊዜም ሥልጣን በሌለው ፍ/ቤት ውሳኔ የሚያገኙ ጉዳዮች ናቸው፡፡
  • 38.  አንድ ክስ ለክርክር ችሎት ፊት ከመቅረቡ በፊት ሊከናወኑ የሚገባቸው የተለያዩ የሥነ-ሥርዐት ደንቦችን አሟልቶ ማለፍ ይኖርበታል፡፡  እነዚህን የሥነ-ሥርዓት ደንቦች በዋናነት በሁለት ከፍሎ መመልከት የሚቻል ሲሆን ይሄውም የአቤቱታ አቀራረብና የመጥሪያ አደራረስ ደንቦች ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህም ሥነ-ሥርዐታዊ ደንቦች በሚከተለው መልኩ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
  • 39.  ማንኛውም የፍታብሄር ጉዳይ ወደ መደበኛ ክርክር የሚገባው ከሳሽ ያቀረበውን የክስ አቤቱታ ፍ/ቤቱ ተቀብሎ ተከሳሹ በቀረበበት ክስ ላይ ቀርቦ መልስ እንዲሰጥበት ሲያደርግ ነው፡፡  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 80(1) ላይ እንደተመለከተው አቤቱታ ማለት የክስ ማመልከቻ፣ የመልስ ማመልከቻ፣ የይግባኝ ማመልከቻ፣ ሌሎች ማመልከቻዎች፣ አቤቱታዎችና ሌላ ማንኛውም የክስ መነሻ ሊሆን የሚችልና ለዚሁ ክስ መልስ የሚሆን ሰነድ ሁሉ አቤቱታ ማለት እንደሆነ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡
  • 40. የቀጠለ  ከዚህ ትርጉም ለመረዳት እንደሚቻለው አንድ ለፍ/ቤት የሚቀርብ ማመልከቻ ለክስ መነሻ ወይም ለቀረበ ክስ መልስ ያልሆነ ማንኛውም ማመልከቻ አቤቱታ እንደማይባል ነው፡ በመሆኑም እንደ በአደራ የተያዘ ገንዘብ እንዲለቀቅ እና የውሳኔ ግልባጭ መጠየቂያ ማመልከቻዎች ወይም ሰነዶች በአቤቱታ ውስጥ የማይጠቃለሉ እንደሆኑ ነው፡፡
  • 41.  አንድ የክስ አቤቱታ ተሟልቶ መቅረቡ የተለያዩ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን በተለይም ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ በመረዳት መልሱን ከክሱ አንጻር እንድያዘጋጅ ከመርዳቱም ባሻገር በፍ/ቤቱ የሚደረገውን የክርክር አድማስ መወሰኑ በአንድ በኩል እንዲሁም የግራ ቀኙ አቤቱታዎች በአግባቡ ተዘጋጅተው መቅረባቸው ፍ/ቤቱ በምርመራ ጊዜ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርግና አግባብነት ያላቸውን ጭብጦች እንዲይዝ በማድረግ የተፋጠነ ውሳኔ እንዲሰጥ ያስችላል፡፡  ከላይ ከተጠቀሱት የአቤቱታ አይነቶች መካከል የክስ አቤቱታና የመልስ አቤቱታ በፍ/ቤት ተቀባይነት እንዲኖራቸው ሊያሟሏቸው የሚገቡ ነገሮች ምንድን ናቸው ሊሟሉ የሚገባቸው ነገሮች ተሟልተው ያልተገኙ እንደሆነ የአቤቱታዎቹ እጣ ፋንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚሉትን ሁኔታዎች በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
  • 42.  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 213 መሰረት አንድ የክስ አቤቱታ በፍ/ቤቱ ተቀባይነትየሚኖረው አቤቱታው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 80-93 እና 222-232 የተመለከቱትን ነገሮች አሟልቶ የቀረበ እንደሆነ ነው፡፡  የክስ አቤቱታ ሲዘጋጅ ሊይዛቸው የሚገቡ ነገሮች ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ የሚገኝ ሲሆን ስድስት ዋና ዋና ነገሮችን የሚያካትት ነው፡፡  የመጀመሪያው በክስ ላይ ሊካተት የሚገባው የክሱ መግቢያ ማለትም ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ስምና አድራሻ፣ የከሳሽ-ተከሳሽ ስምና አድራሻ፣ የክሱ አርእስት፣ ከሳሹ/እናተከሳሹ ክስ ለማቅረብ ችሎታ የሌላቸው እንደሆነ ይህንኑ የሚገልጽ ነገር እንዲሁም ከሳሹ በውክልና ክሱን ያቀረበ እንደሆነ ይህንኑ መግለጽ በመጀመሪያው ክፍል የሚካተቱ ናቸው፡፡
  • 43.  ከነዚህ ነገሮች መካከል አንዳንዶቹ የግድ በየትኛውም የክስ አቤቱታ ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው ነገሮች ሲሆኑ ከፊሎቹ ደግሞ እንደ አስፈላጊነቱ በክስ አቤቱታ ውስጥ ሊካተቱ የሚገቡ ነገሮች ናቸው፡፡  እንደ አስፈላጊነቱ በክስ ውስጥ ሊጠቀሱ ከሚገባቸው ነገሮች መካከል ለምሳሌ ብንመለከት የከሳሽ/ተከሳሽ ችሎታ አለመኖር አንዱ ሲሆን እንዲህ አይነቱ ነገር ሊጠቀስ የግድ የሚለው ከከሳሽ/ተከሳሹ አንዱ ወይም ሁለቱም ችሎታ የሌላቸው እንደሆነ ነው፡፡  ማንኛውም ሰው ችሎታ እንደሌለው እስካልተረጋገጠ ድረስ ችሎታ እንዳለው የህግ ግምት እንደሚወሰድበት በፍትሃ ብሔር ህጋችን አንቀጽ 196 ላይ በግልጽ ተመልክቷል፡፡
  • 44.  በመሆኑም ከሳሹ በክስ አቤቱታው ላይ ችሎታን አስመልክቶ ምንም ያላለ እንደሆነ ችሎታ ያለው መሆኑን ግምት መውሰድ ይኖርበታል፡፡ ይሁንና በሁሉም የክስ ማመልከቻዎች በሚባል ደረጃ “ችሎታ አለኝ” በሚል ይገለጻል፡፡  ከሳሽ ይህንን በክሱ አቤቱታ ላይ ያልገለጸ እንደሆነ እንኳ የፍ/ቤቱ የመዝገብ ቤት ሹም ክሱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 222 መሰረት ያልተሟላ መሆኑን በመግለጽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 229/ሀ/ መሰረት የክስ አቤቱታውን ብዙ ጊዜ አይቀበልም፡፡  በመሆኑም የፍ/ቤት የመዝገብ ሹሞች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠቀሱ የሚገባቸው ነገሮች በሁሉም የክስ አቤቱታዎች ካልተጠቀሱ አቤቱታዎቹ ተቀባይነት የላቸውም በማለት ውድቅ የሚያደርጉበት አሰራር ሊስተካከል ይገባል፡፡
  • 45.  ሁለተኛው በክስ አቤቱታ ውስጥ ሊመለከት የሚገባው ነገር የክሱ ምክንያት ነው፡፡ አንድ ክስ ተቀባይነት እንዲኖረው የክስ ምክንያት ሊኖረው ይገባል፡፡ የክሱ ምክንያትም የሚገለጸው በክሱ ፍሬነገር ዝርዝር ላይ ነው፡፡  የአንድ ክስ አቤቱታ የክስ ምክንያት ያለው መሆኑን ለመወሰን ፍ/ቤቶች የቀረበላቸው አቤቱታ የክስ ምክንያት አለው ወይም የለውም ብሎ ለመወሰን በክስ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሽ የሆነው ወገን የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ህግ ይፈቅድለታል ወይስ አይፈቅድለትም የሚለውን ጥያቄ መመርመር ያለባቸው መሆኑን የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 45247 የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡  ይህንኑ መሰረት በማድረግ ፍ/ቤት የቀረበለትን የክስ አቤቱታ ሲመረምር የክስ ምክንያት የሌለው ሆኖ ካገኘው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231(1-ሀ) መሰረት አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  • 46.  አንድ የክስ አቤቱታ ሊይዘው የሚገባው ሶስተኛው ነገር ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ክሱን ለመመልከት ሥልጣን ያለው መሆኑን ማሳየት ነው፡፡  የፍ/ቤት ሥልጣን በክፍል አንድ ላይ ለመመልከት እንደሞከርነው ሶስት አይነት የፍ/ቤት የሥልጣን አይነቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህ መካከል አንዱ እንኳ የሌለው መሆኑን ፍ/ቤቱ ከተረዳ ክሱን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231(1-ለ) መሰረት ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡  የፍ/ቤትን ሥልጣን በተመለከተ ለፍ/ቤት በሚቀርቡ ክሶች/መልሶች ላይ በተመሳሳይ “ፍ/ቤቱ ይህንን ጉዳይ ተመልክቶ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን አለው” በሚል ይገለጻል፡፡ በዚህ መልኩ ሳይገለጽ የክስ ማመልከቻው ለፍ/ቤቱ ቢቀርብ እንኳ የፍ/ቤቱ የመዝገብ ቤት ሹም ክሱ ማሟላት የሚገባውን ነገር አላሟላም በሚል ክሱን አይቀበለውም፡፡
  • 47.  ነገር ግን በክስ ማመልከቻ ላይም ሆነ በመልስ ላይ በዚህ አግባቡ ፍ/ቤቱ ሥልጣን አለው በሚል መገለጹ ፍ/ቤቱ በቀረበው ጉዳይ ላይ ሥልጣን አይሰጠውም፡፡  የፍ/ቤቱን ሥልጣን የሚወስነው ለምሳሌ የግዛት ክልል ሥልጣን አለው ወይንስ የለውም የሚለውን እንደየክሱ ምክንያት አይነት የተከሳሹን አድራሻ፣ የክሱ ምክንያት የተፈጸመበትን ቦታ፣ አከራካሪው ጉዳይ የሚገኝበትን ቦታ ወይም የማስረጃ ዝርዝሩን በመመልከት ሊወሰን ከሚችል በቀር ፍ/ቤቱ ሥልጣን አለው ስለተባለ ብቻ ፍ/ቤቱ ሥልጣን አይኖረውም፡፡  በመሆኑም የፍ/ቤት የመዝገብ ቤት ሹሞች “ፍ/ቤቱ ሥልጣን አለው” በሚል ያልተገለጸ እንደሆነ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በሚል ውድቅ የሚያደርጉበት አሰራር ሊታረም ይገባል፡፡  አንድ አቤቱታ ሊይዘው የሚገባው አራተኛ ነገር የሚጠይቀውን ዳኝነት ነው፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 224 መሰረት አቤቱታ አቅራቢው ቢወሰንለት ፍ/ቤቱ እንዲሰጠው የሚፈልገውን ዳኝነት በዝርዝርና ግልጽ በሆነ ሁኔታ ማስቀመጥ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡  ዳኝነቱንም ሲጠይቅ አቤቱታው የተለያዩ የክስ ምክንያቶችን መሰረት አድርጎ የቀረበ እንደሆነ ለቀረቡት እያንዳንዱ የክስ ምክንያቶች የሚፈልገውን ዳኝነት በግልጽ ማመልከት ይኖርበታል፡፡
  • 48.  ከዚህ ውጪ በጥቅል የሚቀርብ ዳኝነት ለምሳሌ ከውል ውጪ በደረሰ ጉዳት የቀረበ የክስ አቤቱታ የደረሰበትን ጉዳት ዘርዝሮ ዳኝነቱ ላይ ካሳ ይከፈለኝ ብሎ ቢያቀርብ የዳኝነቱ አቀራረብ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡  አምስተኛው ነጥብ አቤቱታው በእውነት የቀረበ መሆኑ መረጋገጥና ፊርማ በአቤቱታው ውስጥ ሊካተት የሚገባው ነው፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 92 መሰረት በህግ በግልጽ በሌላ በኩል እስካልተደነገገ ድረስ ማንኛውም አቤቱታ በእውነት የቀረበ መሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡  በተመሳሳይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 93 መሰረት ማንኛውም አቤቱታ መፈረም ይኖርበታል፡፡ የአቤቱታው መረጋገጥ በዋናነት አስፈላጊ የሚሆነው በሀሰት የቀረበ እንደሆነና ይህም ተጠያቂነት የሚያስከትል ከሆነ በህግ አግባብ ሀላፊነት ያለበትን ሰው ተጠያቂ ለማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ሰው አንድን ክስ በሀሰት እንዳያቀርብ የሚያደርግ ይሆናል፡፡  በአግባቡ ሳይረጋገጥ የቀረበን አቤቱታ የፍ/ቤቱ የመዝገብ ቤት ሹም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 229/ሐ/ መሰረት ውድቅ የሚያደርገው ይሆናል፡፡
  • 49.  የመጨረሻው በአንድ አቤቱታ ሊካተት የግድ የሚለው የማስረጃ ዝርዝር ነው፡፡ ይህም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 (1) ሀ እና ለ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ክርክሩ በሚሰማበት ጊዜ ምስክር ይሆኑኛል የሚላቸውን ሰዎች የስም ዝርዝር ከነአድራሻቸው የሚጠሩበትን ምክንያት እንዲሁም ማስረጃ ይሆኑኛል የሚላቸውን ጽሁፎች፣ ጽሁፎቹን በእጁ የማይገኙ ሲሆን የሚገኙበትን ስፍራና በማን እጅ እንደሚገኙ በመግለጽ እንዲሁም ለክሱ መነሻ ወይም መሰረት የሆነውን ሰነድ ዋናውን ወይም ትክክለኛ ግልባጩን አያይዞ ካቀረበው ዝርዝር በቀር ሌላ አስረጂ ወይም ማስረጃ የሌለው መሆኑን አረጋግጦ በማሳወቅ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ምንም አይነት የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ የሌለው እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 (1-ሐ) አግባብ ይህንኑ የሚገልጽ መግለጫ ማያያዝ ይኖርበታል፡፡ በዚህ አግባብ ያልቀረበ የክስ አቤቱታ በፍ/ቤቱ መዝገብ ቤት ሹም ውድቅ የሚሆን ይሆናል፡፡
  • 50.  አንድ ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 229 መሰረት በመዝገብ ቤት ሹሙ ተቀባይነት ያላገኘ እንደሆነ የመዝገብ ቤት ሹሙ የክስ አቤቱታው ለምን ተቀባይነት እንዳላገኘ በመግለጽ ክሱንና የክሱን አባሪ ለከሳሹ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 232 (1-ሀ) መሰረት ይመልስለታል፡፡  ከሳሹ በመዝገብ ቤት ሹሙ ምክንያት ያልተስማማ እንደሆነ አቤቱታውን ለፍ/ቤቱ ለማቅረብ የሚችል ይሆናል፡፡  የክስ አቤቱታውን ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231 መሰረት ያልተቀበለው እንደሆነ ከሳሹ ለፍ/ቤቱ የከፈለው የፍ/ቤት አገልግሎት ክፍያ በደንቡ መሰረት ተቀናሽ ተደርጎና የክስ አቤቱታው እንዲመለስለት በማድረግ ይሄው በፍታብሔር የክስ መዝገብ ውስጥ እንዲመዘገብ ይደረጋል፡፡  በፍ/ቤቱ የመዝገብ ሹምም ሆነ በፍ/ቤቱ የአንድ ክስ ተቀባይነት አለማግኘት ከሳሹ በዚያው ጉዳይ ላይ በሌላ ጊዜ ክስ ከማቅረብ የሚከለክለው አይሆንም፡፡
  • 51.  የመከላከያ መልስ አቤቱታ የሚቀርበው በተከሳሹ ሲሆን መልሱም በፍታብሔር ሕጉ የተመለከቱትን የመልስ አዘገጃጀትና ሊይዛቸው የሚገቡ ነገሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት መቅረብ ይኖርበታል፡፡ አንድ የመከላከያ መልስ በዋናነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 መሰረት የሚቀርብ የማስረጃን ዝርዝር ጨምሮ ሶስት ነገሮችን የሚያካትት ይሆናል፡፡  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 234 (1-ሀ ና ለ) መሰረት በመከላከያ መልስ ውስጥ ሊካተት የሚገባው የመጀመሪያው ነገር መግቢያ ሲሆን በዚህም የመከላከያ መልሱ የቀረበበት ፍ/ቤት ስምና የሚገኝበት ቦታ፣ የከሳሽ-ተከሳሽ ስምና አድራሻ እንዲሁም የመዝገብ ቁጥርን የሚመለከቱ መግለጫዎች የሚካተቱበት ነው፡፡  አንዳንድ ጊዜ በመከላከያ መልስ ላይ በክሱ ማመልከቻ መግቢያ የሚጠቀሱ ነገሮች ሁሉ በተመሳሳይ ሲጠቀሱ ይታያል፡፡ ነገር ግን ይህ አይነቱ አቀራረብ የመከላከያ መልሱን ከማንዛዛት በስተቀር የቀረበውን ጉዳይ ለመወሰን መሰረታዊ የሆነ ጥቅም የለውም ይሁንና በአንድ መከላከያ መልስ ላይ በክስ አቤቱታ መግቢያ ላይ ሊመለከቱ የሚገባቸው ነገሮች ተካተው ቢገኙ የመከላከያ መልሱ በአግባቡ አልቀረበም በሚል ውድቅ ሊሆን የሚችልበት ምክንያት አይኖርም፡፡  እንዲሁም በተመሳሳይ አንድ የመከላከያ መልስ በክስ አቤቱታ መግቢያ ላይ ሊመለከቱ የሚገባቸውን ነገሮች አካቶ ባይቀርብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 238(3) መሰረት ፍ/ቤቱ ተቀባይነት የለውም በሚል ውድቅ ማድረግ አይኖርበትም፡፡
  • 52.  በመከላከያ መልስ ውስጥ ሊካተት የሚገባው ሁለተኛው ነገር ተከሳሹ ለቀረበበት ክስ የሚያቀርበው መልስ ነው፡፡ ተከሳሹ እንደቀረበበት ክስ ምንነትና የከሳሹ ማንነት እንዲሁም ካለው መከራከሪያ አንጻር የተለያየ ይዘት ያለው መልስ ሊያቀርብ የሚችል ሲሆን ከነዚህም መካከል የሚከተሉት በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡  ሀ. የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ/መቃወሚያዎች፤ ተከሳሹ የቀረበበት ክስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ/መቃወሚያዎች ፍ/ቤቱ ሊዘጋው የሚችል ከሆነ ይህንኑ ጠቅሶ በመከላከያ መልሱ ላይ በግልጽ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 234 (1-ሐ) ላይ እንደተመለከተው ከሳሽ ህጋዊ ችሎታ የሌለው ሲሆን፣ ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ክርክሩን ለመስማት ሥልጣን የሌለው ሲሆን ወይም የቀረበው ክስ በይርጋ ይታገዳል የሚባል ሲሆን ይህ የተባለበትን ዝርዝር ምክንያት የሚገልጽ ጽሁፍ በመከላከያ መልስ ውስጥ ሊካተት የሚገባው ነገር ነው፡፡
  • 53.  እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ በዚህ ድንጋጌ የተመለከቱት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ብቻ ናቸው በመከላከያ መልስ ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው ወይንስ ሌሎችም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ካሉ መካተት የግድ ይላቸዋል የሚለው ነው፡፡  ማንኛውም ተከሳሽ የመከላከያ መልሱን ሲያቀርብ ሊከላከል የሚችልባቸውን ነገሮች ሁሉ በመልሱ ላይ አጠቃሎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም በመከላከያ መልሱ ያላቀረበውን አዲስ ነገር ለማቅረብ በክርክር ደረጃ ሥነ- ሥርዐት ህጉ የሚፈቅድ ባለመሆኑ ነው፡፡  ስለሆነም የሥነ-ሥርዐት ህጉ ድንጋጌ 234 (1-ሐ) በመጀመሪያ ደረጃ መቅረብ የሚኖርባቸውን መቃወሚያዎች በምሳሌነት ከመጥቀስ ውጪ ሌሎች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች በመከላከያ መልስ አቤቱታ ላይ ባይካተቱም በክርክር ደረጃ ሊነሱ ይገባል የሚል አይደለም፡፡  በመከላከያ መልስ አቤቱታ ያልተካተተ አዲስ ነገር በጉዳዩ የክርክር ደረጃ ሊነሳ እንደማይችል ከፍታብሔር ሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር 82 እና 241 ምንባብ እንዲሁም ቁጥር 234 (1-መ) “የመከላከያ መልስ በሚጻፍበት ጊዜ በመከላከያው ያልተጠቀሰ አዲስ ነገር እንዳይፈጠር ወይም ከክሱ ማመልከቻ ውጪ የሆኑ አዲስ ነገሮች እንዳይነሱ በማድረግ ተሟልቶ የተዘጋጀ መልስ” ሊሆን ይገባል በሚል ከተመለከተው ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡
  • 54.  ለ. ሌላው መልስ ሊይዘው የሚገባው ለቀረበው ክስ በፍሬ ነገር ረገድ የሚሰጥ መልስ፤ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ኖረም አልኖረም ተከሳሹ ለቀረበበት ክስ በፍሬ ነገር ረገድ መልሱን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡  መልስ አጭርና ሁሉንም መከላከያ ይሆኑኛል የሚላቸውን መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች መሰረት በማድረግ እንደሆነ የሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር 80(2)፣ 82 እንዲሁም 234 (1-መ) በግልጽ ይደነግጋሉ፡፡  ሐ. በመልስ ላይ በግልጽ መካድ አስፈላጊ መሆኑ፤ በፍታብሔር ክርክር በክሱ ማመልከቻ ላይ ከተገለጹት ነገሮች ውሥጥ በግልጽ ያልተካዱት ሁሉ እንደታመኑ የሚቆጠሩ እንደሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 83፣ 234(1-ሠ) እንዲሁም 235(2) ላይ ተመልክቷል፡፡  ተከሳሽ ወይም የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የቀረበበት ከሳሽ የተከሰሰበትን ነገሮች ሁሉ በዝርዝርና በግልጽ በመካድ መቃወም ይኖርበታል፡፡ ከዚህ ውጪ በክሱ ላይ የቀረበውን ነገር ሁሉ በዝርዝርና በግልጽ ያለመካድ ወይም በመሸሽ ማስተባበል ነገሩን በከፊል ሆነ በሙሉ አምኖ እንደመቀበል ያስቆጥራል፡፡
  • 55.  በመሸሽ ማስተባበል ወይም በግልጽ አለመካድ ነገሩን እንደማመን የማይቆጠርባቸው ሁለት ልዩ ሁኔታዎች በግልጽ ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች ላይ የተመለከቱ ሲሆን የመጀመሪያው ሁኔታ የካሳ ጥያቄ ላይ የቀረበ የገንዘብ ልክን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ከሳሽ ባቀረበው የካሳ መጠን ላይ ተከሳሹ በግልጽ ያልካደ ወይም ምንም ያላለ እንደሆነ የካሳ መጠኑ ታምኗል ሊባል የሚችል አይሆንም፡፡ ምክንያቱም በፍታብሔር ሕጉ ቁጥር 2141 መሰረት ጉዳት የደረሰበት ሰው የደረሰበትን ጉዳት ልክና የአካባቢ ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ ተከሳሹን ካሳ እንዲከፍለው ያለበትን ግዴታ የማስረዳት ሸክም እንዳለበት ስለሚደነግግ ነው፡፡  በዚሁ አግባብ የፌድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ. ቁ. 48632 ተከሳሹ የመከላከያ መልስ ባላቀረበበት ሁኔታና በካሳ መጠን ጥያቄ ላይ በግልፅ ያልተካደ ፍሬ ነገር እንደታመነ ይቆጠራል የሚለው የሥነ-ሥርዓት ህግ ተፈፃሚነት የሌለው እንደሆነ ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡
  • 56.  ሌላው ልዩ ሁኔታ በሥነ-ሥርዐት ሕጉ ቁጥር 235(2) ላይ እንደተመለከተው ችሎታ የሌላቸው ተከሳሾች ላይ ነው፡፡ ችሎታ የሌለው ተከሳሽ ከሆነ ከፍ ብለን ለመመልከት እንደሞከርነው ከሳሽ ይህንኑ የሚያውቅ ከሆነ በክስ ማመልከቻው ላይ መግለጽ ይኖርበታል፡፡  ተከሳሹ ችሎታ ሳይኖረው ክስ ወይም ለቀረበበት ክስ የመከላከያ መልስ ያቀረበ እንደሆነ ጉዳዩን የሚመለከተው ፍ/ቤት በሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር 34(2) መሰረት ክርክሩን አቋርጦ ተገቢው ህጋዊ ወኪል እንዲኖረው በማድረግ በዚሁ ወኪሉ/ሞግዚቱ አማካኝነት ክርክሩን እንዲያከናውን ማድረግ ይኖርበታል፡፡  ሞግዚቱ ባቀረበው የጽሁፍ መከላከያ መልስ ላይ በመሸሽ ያስተባበለው ወይም በግልጽ ያልካደው ነገር እንደታመነ ተደርጎ የሚወሰድ ከሆነ በህግ ችሎታ የሌለውን ሰው ጥቅም ሊጎዳ ስለሚችል በህግ ችሎታ የሌለውን ሰው ጥቅም ለመጠበቅ ሲባል የተደነገገ ልዩ ሁኔታ ነው፡፡
  • 57.  መ. የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ካለ ይህንኑ አስተካክሎ በመልሱ ላይ ማቅረብ አለበት፤ይህ አይነቱ ክስ የሚቀርበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 215(2) መሰረት ተገቢው የፍ/ቤት አገልግሎት ክፍያ ተከፍሎ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ፍ/ቤቱ እንዲሰጠው የሚፈልገውን ዳኝነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 224 አግባብ ለይቶ በአቤቱታው ላይ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡  ከተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በተመሳሳይ ተከሳሹ የመቻቻል ጥያቄ ካለው ከመልሱ ጋር ሊያቀርብ ይገባል፡፡ እዚህ ላይ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስና የመቻቻል ጥያቄን ያላቸውን መሰረታዊ ልዩነት ማየቱ ጠቃሚ ይሆናል፡፡  አንድ ተከሳሽ የመቻቻል ጥያቄ ለማቅረብ የሚፈልግ ከሆነ ይህንኑ ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው እንደተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ሁሉ ለቀረበበት ክስ መልስ በሚሰጥበት በመጀመሪያው ጊዜ ማቅረብ አለበት፡፡
  • 58.  ነገር ግን የመቻቻል ጥያቄ ሊቀርብ የሚችለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 236 (1) መሰረት የሚጠይቀው ገንዘብ ከፍርድ ቤቱ ሥልጣን ውጭ ካልሆነ ብቻ ነው፡፡  ይህ የመቻቻል ጥያቄ በማቅረብ ላይ የተጣለው የህግ ገደብ ከተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አንጻር የሚታይ መሰረታዊ ልዩነት ነው፡፡ ሌላው ልዩነት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ማንኛውንም የክስ ምክንያት መሰረት በማድረግ ሊቀርብ የሚችል ሲሆን የመቻቻል ጥያቄ ሊቀርብ የሚችለው ግን ለገንዘብ ወይም ተመሳሳይ በሆኑትና የመከፈያቸው ጊዜ በደረሰ እዳዎች መካከል ብቻ ላይ የተወሰነ እንደሆነ የፍታብሄር ህጉ ቁጥር 1831 እና ተከታዮችን በመመልከት ለመረዳት ይቻላል፡፡  ከዚህም በተጨማሪ መቻቻል በመልስ ላይ ሊቀርብ የሚችለው የሚጠይቀው ገንዘብ ተከሳሹንና ከሳሹን በግል መብታቸው ረገድ የሚመለከታቸው ሲሆን ብቻ ነው፡፡
  • 59.  በፍ/ብ/ህ/ቁ 1833 መሰረት መቻቻያ የማያስደርጉ ሁኔታዎች  የዕዳው አይነት ልዩ በመሆኑ ለባለገንዘቡ በእጁ የሚከፈል ሲሆን ለምሳሌ ለቀለብ የሚከፈል ገንዘብ ሲሆን  ለመንግስትና ለመስሪያ ቤቶች የሚከፈል ገንዘብ ሲሆን  ባለቤቱ በማይገባ የተወሰደበት እንዲመለስለት ሲጠይቅ  በአደራ የሰጠውን ዕቃ እንዲመለስለት ሲጠይቅ መቻቻያ ሊደረግ አይችልም፡፡
  • 60.  የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ሲቀርብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 215(2) መሰረት ተገቢው የፍ/ቤት አገልግሎት ክፍያ ተከፍሎ መሆን እንዳለበት ተደንግጓል፡፡ የፍ/ቤት አገልግሎት ክፍያ በመቻቻል ጥያቄ ላይስ ሊከፈል የሚገባ ነው ይላሉ ለምን?
  • 61.  የመከላከያ መልሱ አቤቱታ በህጉ አግባብ ማካተት የሚገባውን ነገር አካቶ የቀረበ መሆኑን የመመርመር ሥልጣን የተሰጠው ለፍ/ቤቱ ነው (238(1)፡፡  ይህንንም ሲያደርግ መከላከያው ከፍ ብለን የተመለከትናቸውን መሟላት የሚገባቸውን ነገሮች አሟልቶ ያልቀረበ እንደሆነ ወይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 መሰረት ማስረጃ ያላያያዘ እንደሆነ ወይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 92 መሰረት የመከላከያ አቤቱታው ተረጋግጦ ያልቀረበ እንደሆነ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 229 ድንጋጌ በተመሳሳይ ተፈጻሚ በማድረግ አቤቱታው ተሙዋልቶ እንዲቀርብ ማድረግ ያለበት መሆኑን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 238 (1) ላይ ተደንግጓል፡፡
  • 62.  በዚህ አግባብ መከላከያው ተመርምሮ ተቀባይነትን ያገኘ እንደሆነና አቤቱታው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስን ወይም የመቻቻል ጥያቄ ያካተተ እንደሆነ ፍ/ቤቱ እንደ ተገቢነታቸው የቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስንና የመቻቻል ጥያቄውን ፍ/ቤቱ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 231 አንጻር በመመርመር ተገቢውን ሊወስን ይገባል፡፡  የተከሳሽ ከሳሽነቱ ክስ ወይም የመቻቻል ጥያቄው የክስ ምክንያት የሌለው ከሆነ ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ወይም ከፍ/ቤቱ ሥልጣን በላይ ከሆነ ከፍ/ቤቱ ሥልጣን በላይ የሆነው የመቻቻል ጥያቄው ከሆነ የመቻቻል ጥያቄ ከፍ/ቤቱ ሥልጣን በላይ ሊቀርብ ስለማይችል ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ፤ ከፍ/ቤቱ ሥልጣን በላይ የሆነው የተከሳሽ ከሳሽነቱ ከሆነ የግራ ቀኙን ክርክር ለመዳኘት ሥልጣን የሚኖረው ለዳኝነት ከቀረቡት የግራ ቀኙ ጥያቄዎች መካከል ከፍተኛውን ለመዳኘት ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት በመሆኑ ከሳሽ የከፈለውን የዳኝነት ክፍያ እንዲመለስለት በማድረግና የግራ ቀኙን መዝገብ በመዝጋት ጉዳዩን ለመመልከት ሥልጣን ወዳለው ፍ/ቤት ማስተላለፍ ይኖርበታል፡፡
  • 63.  የግራ ቀኙ አቤቱታ ማሟላት የሚገባቸውን ነገሮች አሟልተው በመቅረባቸው በፍ/ቤቱ የመዝገብ ቤት ሹምና በፍ/ቤቱ ተቀባይነት ካገኙም በኋላ ሥነ-ሥርዓት ህጉ በሚያስቀምጣቸው ምክንያቶች ሊሻሻሉ ይችላሉ፡፡  ሊሻሻሉ የሚችሉትም በተከራካሪ ወገኖች አመልካችነትና በፍ/ቤቱ ፈቃጅነት ወይም በፍ/ቤቱ በራሱ አነሳሽነት በሚሰጥ ትእዛዝ ሊሆን ይችላል፡፡  ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 ለመረዳት እንደሚቻለው አንድ አቤቱታ በሶስት ምክንያቶች ሊሻሻል የሚችል ሲሆን ይሄውም፡- (1) ለትክክለኛ ፍትህ ሲባል፣ (2) የክስ ወይም የመከላከያ መልስ አቤቱታውን በተሻለ ለማብራራት ሲባል ወይም (3) አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮች ወይም የክርክሩን አመራር ሥርዓት የሚያሰናክሉ ወይም ሁከትን የሚፈጥሩ ወይም ለትክክለኛው ፍትሕ አሰጣጥ መሰናክል ሆነው የሚገመቱ ነገሮችን ለማስተካከል በሚል ሊሻሻል የሚችል እንደሆነ ነው፡፡
  • 64.  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(1) “ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በማናቸውም ጊዜ ወይም ፍርድ ቤቱ ተገቢ ሆኖ ካገኘው ተከራካሪዎቹ ወገኖች ክሳቸውን እንዲያሻሽሉና ክርክራቸውን እንዲለውጡ ሊፈቀድላቸው ይችላል፡፡ ስለሆነም የዚህ ዓይነት መብት ለተከራካሪዎቹ ወገኖች የሚሰጠው የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራ ወይም ትክክለኛ ፍትሕን ለመስጠት የሚረዳ ሆኖ በተገመተ ጊዜ ብቻ ነው፡፡…” በሚል ይደነግጋል፡፡  በዚህ ንዑስ ቁጥር ድንጋጌ የአማርኛ ቅጂ በተለይም “ፍርድ ቤቱ ተገቢ ሆኖ ካገኘው ተከራካሪዎቹ ወገኖች ክሳቸውን እንዲያሻሽሉና ክርክራቸውን እንዲለውጡ ሊፈቀድላቸው ይችላል” የሚለው አገላለጽ ለትክክለኛ ፍትህ ሲባል ሊሻሻል የሚችለው የከሳሽ ክስ ወይም ተከሳሽ የሚያቀርበው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስን ብቻ የሚመለከት እንደሆነ ነው፡፡
  • 65.  ይህም ተከሳሹ መከላከያውን ለትክክለኛ ፍትህ ሲባል ላሻሽል ቢል የሚፈቅድ አይመስልም፡፡ ከዚህ አንጻር የዚሁኑ ንዑስ ቁጥር ድንጋጌ የእንግሊዝኛ ቅጅ በምንመለከትበት ጊዜ ከአማርኛው ቅጅ በተለየ መልኩ “…The court may at any time before judgment allow either party to alter or amend his pleading…” በሚል ይደነግጋል፡፡  “pleading” የሚለው ቃል ሁለቱንም የክስና የመልስ አቤቱታን የሚመለከት በመሆኑና የእንግሊዝኛው ቅጂ ግራ ቀኙን ተከራካሪ ወገኖች በእኩልነት የሚያስተናግድ በመሆኑ ይሄው ቅጂ ከአማርኛው ቅጂ ይልቅ ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚገባ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
  • 66.  “ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራ ወይም ትክክለኛ ፍትሕን ለመስጠት” የሚለው ምን ማለት ነው? አዲስ ነገርን በማሻሻያው ለማካተት የሚፈቅድ ነውን? በአቤቱታ ማሻሻያ ውስጥ አዲስ ነገር መካተት የለበትም በሚል በአንዳንድ የህግ ባለሙያዎች ክርክር ሲነሳ ይሰማል፡፡  ይሁንና የሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር 90 እና 91 (1) ስንመለከት ለዚህ ጥያቄ ግልጽ ምላሽ የሚሰጡን ድንጋጌዎች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡  ከዚህ አንጻር የሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር 90 “አቤቱታን ለማሻሻል ካልሆነ በቀር ተከራካሪዎቹ ወገኖች ቀድሞ ካቀረቡት ክርክር ወይም ጭብጥ ውጭ የሆነና ከቀድሞው ክርክር ጋር ግንኙነት የሌለው አዲስ ነገር ለማቅረብ አይቻልም፡፡” በሚል የሚደነግግ ሲሆን የዚህ ድንጋጌ ግልባጭ ምንባብ በአቤቱታ ማሻሻያ ጊዜ ቀድሞ ከቀረበው ክርክር ወይም ጭብጥ ውጭ የሆነና ከቀድሞው ክርክር ጋር ግንኙነት የሌለው አዲስ ነገር ሊቀርብ የሚችል እንደሆነ ነው፡፡
  • 67.  ከዚህም በተጨማሪ በቁጥር 91(1) “ተከራካሪዎቹ ወገኖች ክሳቸውን እንዲያሻሽሉና ክርክራቸውን እንዲለውጡ ሊፈቀድላቸው ይችላል፡፡” የሚለው በተለይም “ክርክራቸውን እንዲለውጡ” የሚለው የህጉ አቀራረጽ አዲስ ነገር በአቤቱታ ማሻሻያ ውስጥ ሊኖር የሚችል እንደሆነ ነው፡፡ በዚሁ አግባብም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በከሳሽ ቢኒያም ገረመውና በተከሳሽ የቻይና መንገድ ስራ ድርጅት መካከል በነበረው የስራ ክርክር በሰ/መ/ቁ 20416 ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡  በአቤቱታ ማሻሻያ አዲስ ነገር የሚካተት መሆኑ ግልጽ ከሆነ በቀጣይ ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ በማሻሻያው ሊካተት የሚገባው አዲስ ነገር አድማስ እስከምን ሊደርስ ይገባል የሚለው ነው፡፡ በዚህ ረገድ በሥነ- ሥርዓት ህጉ በግልጽ የተመለከተ ነገር ባይኖርም “ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ” ከሚለው ሀረግ በመነሳት የሚከተሉትን ሁኔታዎች ሊጨምር እንደሚችል መረዳት ይቻላል፡፡
  • 68.  የመጀመሪያው ሁኔታ ከቀረበው የክስ ምክንያት ጋር አብሮ ሊታይና ውሳኔ ሊያገኝ የሚገባው ነገር ሲሆንና ከዚሁ የክስ ምክንያት ጋር አብሮ ቀርቦ ካልታየ በአዲስ ክስ ከመታየት የሚታገድ ከሆነ ነው፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 216(4) ላይ  እንደተመለከተው ከሣሽ ያቀረበው ክስ ባንድ ጉዳይ ላይ የተመሠረተ ሆኖ የሚጠይቀው ዳኝነት ግን ከአንድ በላይ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ሳይፈቅድለት ሊጠይቅ ይገባው ከነበረው ዳኝነት ውስጥ በከፊል ራሱ ቀንሶ ያስቀረውን መብት እንደገና ሊከስበት አይችልም፡፡
  • 69.  ለምሳሌ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በህገወጥ መንገድ ከስራው የተባረረ አንድ ሰራተኛ ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት የስራ ስንብት ክፍያ እንዲከፈለው ብቻ ክስ በማቅረብ ሌሎች ሊጠይቃቸው የሚገቡ የክፍያ ጥያቄዎች ሳያቀርብ ቀርቶ ከፍርድ በፊት የክስ አቤቱታውን እነዚሁ የቀሩትን ጥቅማጥቅሞች በክሱ ለማካተት በሚል የማሻሻያ አቤቱታ ቢያቀርብ ፍ/ቤቱ ይህንኑ ማመልከቻ ሊቀበለው ይገባል ማለት ነው፡፡  ምክንያቱም ክሱ ሳይሻሻል ቀርቶ ፍ/ቤቱ በስራ ስንብት ክፍያው ላይ ብቻ ውሳኔ ቢሰጥ በሌሎቹ የክፍያ ጥያቄዎቹ በአዲስ ክስ ለማቅረብ ከፍ ሲል የጠቀስነው የሥነ-ሥርዐት ህጉ ድንጋጌ ስለማይፈቅድለት ነው፡፡ በዚሁ አግባብ ከፍ ብለን የጠቀስነው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሰጥቶበታል፡
  • 70.  ሌላው አቤቱታን ለማሻሻል የሚያበቃ ሁኔታ የቁጥር ወይም ሌሎች ስህተቶች ለማስተካከል በሚል የሚቀርብ ማመልከቻ ነው፡፡ ለምሳሌ የአከራካሪውን የቤት ቁጥር ወይም የመኪና ታርጋ ቁጥር ለማሻሻል ማመልከቻ ቢቀርብ እንዲህ አይነቱ መሻሻል አከራካሪውን ነገር በበለጠ ግልጽ እንዲሆን ከማድረጉም ባለፈ ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዳ በመሆኑ ማመልከቻው ተቀባይነት ሊያገኝ ይገባል፡፡  ከዚህ በተለየ የክስ ምክንያቱን የሚቀይር ከሆነ ለምሳሌ በመጀመሪያ የቀረበው የክስ ምክንያት ሁከት ይወገድልኝ ሆኖ በማሻሻያው ውል ይፍረስልኝ በሚል የሚቀርብ ከሆነ ፍጹም የክስ ምክንያቱን የቀየረና ሁለቱ ጉዳዮች የማይገናኙ በመሆናቸው እንዲሁም በውል ማፍረስ በአዲስ መልክ ክስ በማቅረብ ውሳኔ ለማግኘት የሚከለክል ነገር የሌለ በመሆኑ የሥነ-ሥርዐት ህጉ ቁጥር 91(1) እንዲህ አይነቱን የማሻሻል ጥያቄ የሚያስተናግድ አይመስልም፡፡
  • 71.  ከዚህ ባለፈ ተከራካሪ ወገኖች በመጀመሪያው የክርክሩ ደረጃ ሊያነሱ የሚገባቸውን መከራከሪያዎች ለምሳሌ እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያለ መከራከሪያ ሳያነሱ ቀርተው በአቤቱታ ማሻሻያ ይህን አይነቱን መከራከሪያ እንዲያነሱ ሥነ-ሥርዐት ሕጉ የሚፈቅድ አይደለም፡፡ በዚሁ አግባብ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 55973 ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡  ሌላው እዚህ ላይ ሊነሳ የሚገባው ነገር ማስረጃ ለማያያዝ በሚል የአቤቱታ ማሻሻያ ጥያቄ አግባብነት እስከምን ድረስ ነው የሚለው ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ተከራካሪ ወገኖች አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ የረሷቸውን ማስረጃዎች ለማቅረብ በማሰብ የአቤቱታ ማሻሻያ ማመልከቻ ለፍ/ቤት ሲያቀርቡ ይታያል፡፡
  • 72.  ነገር ግን በመጀመሪያ ከክስ ወይም ከመልስ ጋር አብሮ ያልቀረበ ማስረጃ በጉዳዩ የክርክር ደረጃ በምን አግባብ ሊቀርብ የሚችል እንደሆነ የሥነ-ሥርዐት ሕጉ ራሱን የቻለ አግባብ ያስቀመጠ በመሆኑ ማስረጃን ለማያያዝ ሲባል ብቻ የአቤቱታ ማሻሻያ ሊቀርብ አይገባም፤ ቢቀርብም ማሻሻያው ተቀባይነት ሊያገኝ አይገባም፡፡  ከዚህም በተጨማሪ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 የሚመለከተው አቤቱታን ስለማሻሻል በመሆኑና አቤቱታ ወይም በእንግሊዝኛው “pleading” የሚለው በዚህ ክፍል ስለአቤቱታ ምንነት ለመመልከት እንደሞከርነው የክስ መነሻ ሊሆን የሚችል ነገር ወይም ለክስ የሚሰጥ መልስ እንደሆነ ነው፡፡  የማስረጃ ዝርዝር ደግሞ ራሱን ችሎ የክስ መነሻ ወይም ለቀረበ ክስ መልስ ሊሆን የሚችል አይደለም፡፡ ማስረጃ የክሱ ወይም የመልሱ አባሪ በመሆኑ አቤቱታ የሚለውን የሚያሟላ አይደለም፡፡  በመሆኑም ማስረጃ ለማያያዝ በሚል ብቻ አቤቱታ ሊሻሻል የሚፈቀድበት የህግ መሰረት የለም፡፡ ይሁንና ይህ ማለት ግን በማሻሻያው አዲስ ነገር የቀረበ እንደሆነና ይህንኑ አዲስ ነገር ለማስረዳት በሚል የሚያያዙ ማስረጃዎች አግባብነት ያላቸው በመሆኑ ተቀባይነት ያላቸው እንደሆነ ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል፡፡
  • 73.  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(2) በግልጽ እንደሚደነግገው በዚሁ ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር (1) መሰረት ክርክሩን እንዲያሻሽል ወይም ሙግቱን እንዲቀይር በፍ/ቤቱ ፍቃድ ያገኘ ተከራካሪ ይህንኑ ፍ/ቤቱ በሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያላከናወነ እንደሆነና ፍ/ቤቱ የሰጠውን ጊዜ ያላራዘመለት ከሆነ አቤቱታውን የማሻሻል መብቱን የሚያጣ ይሆናል፡፡ በዚህ አግባብ መብቱን ያጣ ተከራካሪ በመጀመሪያ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት ክርክሩን የሚያደርግ ይሆናል ማለት ነው፡፡
  • 74.  ክስን በማሻሻል ሙግትን ለመቀየር በሚል ከሚደረግ የአቤቱታ ማሻሻያ ባሻገር አቤቱታውን በተሻለ ለማብራራት በሚል በተከራካሪ ወገኖች አመልካችነት ወይም በፍ/ቤቱ አነሳሽነት አቤቱታ እንዲሻሻል ሊደረግ ይችላል፡፡  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(3) ላይ እንደተመለከተው እንዲህ አይነቱ ማሻሻያ የሚፈቀደው የክሱን ወይም የመከላከያውን ሁኔታ የሚያብራራ ወይም የቀረበውን ክርክር በተሻሻለ ዓይነት ገልጾ የሚያስረዳ ወይም ሁኔታውን በዝርዝር አገላለጽ የሚያመለክት ሆኖ መቅረቡ አስፈላጊ የሆነ እንደሆነ ነው፡፡  የዚህ አይነቱ የማሻሻያ ማመልከቻ አላማ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ በሚል ከሚደረገው ማሻሻያ በመሰረታዊነት ያለው ልዩነት ሙግትን በመቀየር አዲስ ነገር ለመጨመር በሚል የሚቀርብ ሳይሆን አቤቱታውን የበለጠ ግልጽ ማድረግ ላይ ነው፡፡
  • 75.  ፍ/ቤት ትክክለኛውን የችሎት አመራር የሚያሰናክሉ ወይም ሁከት ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችንና የመሳሰሉትን ሁኔታዎች በችሎት በንግግር ወይም በተግባር ሲፈጸሙ ብቻ ሳይሆን በጽሁፍ አቤቱታ ላይ የተገለጹ ከሆነ እነዚህን ነገሮች እንዲስተካከሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(4) በግልጽ እንደሚደነግገው እንዲህ አይነት ነገሮች በአቤቱታ ማመልከቻ ላይ ተገልጸው ከሆነ ይሄው እንዲሻሻል ወይም ከአቤቱታው ውስጥ ጨርሶ እንዲወጣ ማዘዝ ይኖርበታል፡፡ ይህ አይነቱ ማሻሻያ በተከራካሪዎቹ ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የግድ የሚፈጸም የማሻሻያ አይነት ነው፡፡
  • 76.  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91(5) ላይ እንደተመለከተው የክሱ መሻሻል ነገሩን በመጀመሪያ ደረጃ ከቀረበለት ፍርድ ቤት ሥልጣን በላይ ያደረገው እንደሆነ የመጀመሪያው ደረጃ ፍርድ ቤት ይህን ጉዳይ ለመቀበል ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማስተላለፍ ይኖርበታል፡፡  በድንጋጌው በግልጽ የተመለከተው “ክስ” በሚል ሲሆን ይህ ማለት ግን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስንም የሚጨምር እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ አግባብ መዝገቡ የተላለፈለት የበላይ ፍ/ቤት ነገሩ እንዲሰማ ማድረግ እንዳለበት በዚሁ ድንጋጌ ላይ ተመልክቷል፡፡
  • 77.  በአቤቱታ መሻሻል ምክንያት የስረ-ነገር ሥልጣኑ ከፍ ወዳለው ፍ/ቤት የሚተላለፍ ከሆነ በአዲስ መልክ ለተጨመረው የዳኝነት ጥያቄ የፍ/ቤት አገልግሎት ክፍያ የትኛው ፍ/ቤት ነው ሊያስከፍል የሚገባው፡፡
  • 78.  ፍ/ቤት ከተከራካሪ ወገኖች መቅረብ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ቀጠሮዎችን ይሰጣል፡፡ እንደቀጠሮዎቹ ምክንያት፣ አላማና ያልቀረበው ተከራካሪ ማንነት አንጻር የተከራካሪ ወገኖች በተሰጠው ቀነቀጠሮ ያልቀረቡ እንደሆነ ፍ/ቤቱ የተለያዩ ትእዛዛትን ይሰጣል፡፡  ከነዚህም መካከል የጽሁፍ መልስና ማስረጃዎቹን የማቅረብ መብትን ማለፍ “default proceeding”፣መዝገቡን የመዝጋት “struck out of the suit”፣ ተከሳሹ በሌለበት ክርክሩ እንዲታይ ትእዛዝ መስጠት “ex-parte”፣ ክሱን የመሰረዝ “dismissal of the suit” በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እንደ ትእዛዙ አይነትም ውጤታቸው የተለያየ ነው፡፡ በዚህ ክፍልም እነዚህን አራት ሁኔታዎች ከሚያስከትሉት ውጤት ጋር በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
  • 79.  ሀ. ተከሳሹ የፅሁፍ መልሱንና ማስረጃውን የማቅረብ መብቱን የሚያጣበት ሁኔታ  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 233 እንደሚደነግገው የከሳሽ የክስ አቤቱታ በሥነ-ሥርዐት ሕጉ አግባብ ተቀባይነት ያገኘ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሹ ክሱንና ከክስ ማመልከቻው ጋር ተያይዞ የቀረበለት ማናቸውም አስረጂና የጽሑፍ ግልባጭ ከመጥሪያው ጋር ለተከሣሹ እንዲደርሰውና የመከላከያ መልሱን ጽፎ እንዲቀርብ ያዛል፡፡ ተከሣሹ መከላከያውን ለፍርድ ቤቱ ሳያቀርብ የቀረ ወይም ራሱ መከላከያ ሳይዝ የቀረበ እንደሆነ ክርክሩ በሌለበት የሚሰማ መሆኑ በመጥሪያው ላይ ተገልጾ ይላክለታል፡፡
  • 80.  “ተከሣሹ መከላከያውን ለፍርድ ቤቱ ሳያቀርብ የቀረ ወይም ራሱ መከላከያ ሳይዝ የቀረበ እንደሆነ ክርክሩ በሌለበት የሚሰማ መሆኑ” የሚለው በስነ-ሥርዐት ሕጉ ቁጥር 70(ሀ) ላይ ከተመለከተው ክሱ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ተከሳሹ ያልቀረበ እንደሆነ ክሱ በሌለበት ይሰማል ከሚለው ጋር ተመሳሳይ በማድረግ ሲተረጎም ቆይቷል፡፡  ይሁንና የፌድራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ተከሳሹ መከላከያውን ለማቅረብ በተቀጠረበት ቀን ያልቀረበ ወይም ቀርቦ መልሱን በጽሁፍ ይዞ ያልቀረበ እንደሆነ ሊሰጥ የሚገባው ትእዛዝ በሌለበት የሚል ሳይሆን በጽሁፍ መከላከያውንና ማስረጃውን የማቅረብ መብቱ ብቻ የሚታለፍበት “default proceeding” እንደሆነ በሰ/መ/ቁ 15835 አስገዳጅ የሆነ ትርጉም ሰጥቷል፡፡
  • 81.  ለዚህ ውሳኔውም መነሻ ያደረገው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 233 የእንግሊዝኛውን ቅጂ ሲሆን በተለይም “…. The court shall cause… requiring him to appear with his statement of defense to be fixed in the summons and informing him that the case wile be proceeded withnotwithstanding that he does not appear or that he appears without his statement of defense.”የሚለውን ነው፡፡  ይህ አገላለጽ “default proceeding” ወይም መከላከያውን የማቅረብ መብቱን ማጣት የሚለውን እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70(ሀ) ላይ የተመለከተውን “ex-parte” ወይም ክሱ በሌለበት ይታያል የሚለውን እንዳልሆነ በዚሁ ውሳኔ ሀተታው ላይ አስቀምጧል፡፡
  • 82.  በመሆኑም ተከሳሹ የመከላከያ መልሱን ፍ/ቤቱ እንዲያቀርብ በሰጠው ቀነ ቀጠሮ ያላቀረበ እንደሆነ ፍ/ቤቱ በሥነ-ሥርዐት ሕጉ ቁጥር 199 መሰረት ተገቢ ነው ያለውን ትእዛዝ የሚሰጥ ሲሆን በዚሁ ድንጋጌ (1) መሰረት መከላከያውን ያላቀረበው በተከሳሹ በራሱ ችግር እንደሆነ የመከላከያ መልስ የማቅረብ መብቱን ማለፍ ወይም ተከሳሹ መከለከያውን ማቅረብ ያልቻለው በእርሱ ችግር ባልሆነ ምክንያት መሆኑን ማስረዳት የቻለና ይህንኑ ፍ/ቤቱ የተቀበለው እንደሆነ በንዑስ ቁጥር (2) መሰረት ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት የመከለከያ መልሱን እንዲያቀርብ ለማዘዝ የሚችል ይሆናል፡፡
  • 83.  ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሳሽ ተከሳሹ የመከላከያ መልሱን ለማቅረብ በተቀጠረበት ቀን ባይቀርብ በከሳሽ ላይ ፍ/ቤቱ ምን ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል የሚለው ጥያቄ ነው፡፡  በመርህ ደረጃ ከሳሽ በዚህ የቀጠሮ እለት የተከሳሽ የመከላከያ መልስ ከመቀበል ባለፈ የሚያከናውነው ነገር የለም፡፡ የመከላከያ መልሱንም ቢሆን በፍ/ቤቱ ሬጂስትራር በኩል ከቀጠሮው እለት በኋላም ቢሆን ለማግኘት የሚችል በመሆኑ በዚህ ቀጠሮ መገኘቱ ያን ያህል አስፈላጊ አይሆንም፡፡  ይሁንና በዚህ የፍ/ቤቱ የቀጠሮ እለት ፍ/ቤቱ በተለይ ተከሳሹ ያልቀረበ እንደሆነ ተገቢውን ትእዛዝ ለመስጠት የከሳሽ መቅረብ ጠቃሚ እንደሚሆን እርግጥ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ የፌደራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 14184 ከሳሽ ተከሳሽ መከላከያውን ለማቅረብ በተቀጠረበት ቀን ፍ/ቤት እንዲቀርብ የግድ የሚለው ተግባር የሌለው በመሆኑ አለመቅረቡ መብቱን የሚነካ ምንም አይነት ትእዛዝ አይኖርም በሚል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
  • 84. ለ. መዝገቡን መዝጋት (struck out of the suit)  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(1) ላይ እንደተመለከተው ተከራካሪ ወገኖች ፍ/ቤቱ ነገሩን ለማየት በሰጠው ቀጠሮ ራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው ተሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙ ወገኖች ተሟልተው መቅረባቸውን ካረጋገጠ በኋላ ነገሩን መስማት ይጀምራል፡፡  ነገር ግን ነገሩ ሊሰማ ፍ/ቤቱ በሰጠው የቀጠሮ እለት ተከራካሪ ወገኖች ያልቀረቡ እንደሆነ ፍ/ቤት ሊሰጥ የሚችለው የመጀመሪያው አይነት ትእዛዝ መዝገቡን መዝጋት ነው፡፡
  • 85.  ይህም ትእዛዝ ሊሠጥ የሚችለው ነገሩ ሊሰማ በተቀጠረበት እለት ግራ ቀኙ ያልቀረቡ እንደሆነ በሥነ-ሥርአት ህጉ ቁጥር 69(2) እንዲሁም በቁጥር 70(መ) አግባብ ከሳሽ በራሱ ቸልተኝነት ወይም ጉድለት መጥሪያውን ለተከሳሽ ያላደረሰ እንደሆነ ነው፡፡  የሥነ-ሥርዐት ሕጉ የአማርኛው ቅጂ በአዲስ ክስም ሆነ በይግባኝ ክርክር መዝገቡ ይዘጋል በሚል በተመሳሳይ አገላለጽ ፍ/ቤቱ ትእዛዝ እንደሚሰጥ ይገልጻል፡፡ የዚሁ ህግ የእግሊዝኛ ቅጂ ከዚህ በተለየ መልኩ ለአዲስ ክስ “struck out of the suit” እንዲሁም በይግባኝ ደረጃ ላለ ክርክር “dismissal of the suit” የሚል ትእዛዝ እንደሚሰጥ ይደነግጋሉ፡፡
  • 86.  እነዚህ የትእዛዝ አይነቶች በውጤት ረገድ መሰረታዊ ልዩነት ያላቸው ሲሆን ከሚያስከትሉት ውጤት አንጻር “struck out of the suit” የሚለው መዝገብ መዝጋትን እንዲሁም “dismissal of the suit” ደግሞ የክስ መዝጋትን (መሰረዝን) የሚያመለክት እንደሆነ በተለይም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 245 (2)ን የአማርኛ ቅጂ በመመልከት ለመረዳት ይቻላል፡፡  በመሆኑም በነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት የመዝገብ መዝጋት ትእዛዝ የሚሰጠው በአዲስ ክስ ሲሆን በይግባኝ ከሆነ ግን የክስ መሰረዝ ትእዛዝ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
  • 87.  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70(መ) መሰረት ለተከሳሹ በከሳሹ ቸልተኝነት ወይም ጉድለት መጥሪያ ያልደረሰው እንደሆነ ፍ/ቤቱ በአዲስ ክስ ከሆነ መዝገቡን የመዝጋት ወይም በይግባኝ የቀረበ እንደሆነ ክሱን የመዝጋት ወይም የመሰረዝ ትእዛዝ ለመስጠት እንደሚችል፤ ነገር ግን ተገቢ መስሎ ከታየውም ክሱ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ሊለውጥ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ ለመሆኑ ፍ/ቤቱ በዚህ ሁኔታ ክሱ የሚሰማበትን ቀጠሮ ለመቀየር የሚያስችሉ ተገቢ ናቸው የሚባሉ ምን አይነት ነገሮችን የሚመለከት ነው::
  • 88. ሐ. በሌለበት ወይም “ex-parte” በሚል የሚሰጥ ትእዛዝ  ክርክሩ እንዲሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ከሳሽ ቀርቦ ተከሳሹ ያልቀረበ እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70 መሰረት ፍ/ቤቱ እንደነገሩ ሁኔታ የተለያዩ ትእዛዛትን የሚሰጥ ይሆናል፡፡  ከነዚህም ትእዛዛት መካከል ተከሳሹ ፍ/ቤቱ በሰጠው ቀነ ቀጠሮ ያልቀረበ ቢሆንም መጥሪያው በትክክል የደረሰው መሆኑ ካልተረጋገጠ ፍርድ ቤቱ በ70 ለ እንደተመለከተው ሁለተኛ መጥሪያ እንዲላክ ትእዛዝ የሚሰጥበት አግባብ ነው፡፡  እንዲሁም ተከሳሹ ያልቀረበው መጥሪያው በአግባቡ ደርሶት ነገር ግን መጥሪያው ለተከሳሹ የደረሰበት ቀን ለክሱ መልስ ለመስጠት በቂ ጊዜ አለመሆኑን ፍ/ቤቱ የተረዳው ከሆነ በ70 ሐ መሰረት የክርክሩን መሰማት ለሌላ ቀነ ቀጠሮ የሚያስተላልፈው ይሆናል፡፡  ሆኖም ተከሳሹ መጥሪያ በአግባቡ ደርሶት ፍ/ቤቱ ክርክሩን ለመስማት በሰጠው ቀነ ቀጠሮ ያልቀረበ እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70 ሀ መሰረት ክርክሩ ተከሳሹ በሌለበት ወይም “ex-parte” ጉዳዩ እንዲሰማ በሚል ትእዛዝ ይሰጣል፡፡
  • 89.  ተከሳሹ መከላከያ መልሱን አቅርቦ ክርክሩ ሊሳማ በተቀጠረበት ቀን ባለመቅረቡ በሌለበት ክርክሩ እንዲታይ ትእዛዝ የተሰጠበት ቢሆንም ተከሳሽ በክርክሩ ሂደት ተሳታፊ አይሁን እንጂ ፍ/ቤቱ ያቀረበውን የጽሁፍ መልስ በአግባቡ ከግምት ውስጥ በማስገባት ክርክሩ እንዲደ,ረግ በማድረግ ውሳኔ ላይ ሊደርስ ይገባል፡፡ መ. የክስ መዘጋት ወይም መሰረዝ “dismissal of the suit” በሚል የሚሰጥ ትእዛዝ  ከፍ ብለን እንደተመለከትነው በይግባኝ ጉዳይ ላይ ክርክሩ ለመሰማት በተቀጠረበት እለት ግራ ቀኙ ያልቀረቡ እንደሆነ ወይም ይግባኝ ባይ መጥሪያውን በራሱ ቸልተኝነት ወይም ጉድለት ለይግባኝ መልስ ሰጪ ያላደረሰ እንደሆነ እንደቅደም ተከተላቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(2) እና 70(መ) ላይ ተደንግጓል፡፡
  • 90.  ከዚህም በተጨመሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት በአንድ ጉዳይ ክስ ያቀረበ ሰው ክርክሩ እንዲሰማ በተቀጠረው ቀን ያልቀረበ እንደሆነ እንደተከሳሹ መልስ ፍ/ቤቱ ክሱን የመዝጋት (የመሰረዝ) ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡  እንዲህ አይነት ትእዛዝ ሊሰጥ የሚችለው ተከሳሹ ቀርቦ ከሳሽ ያቀረበበትን ክስ ሙሉ በሙሉ የካደ እንደሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ተከሳሹ በሙሉ ወይም በከፊል ከሳሽ ያቀረበውን ክስ ያመነ እንደሆነ ከሳሹ ባይቀርብም በተከሳሽ እምነት መሰረት ለከሳሽ ውሳኔ የሚሰጥ ይሆናል፡፡  የዚህ ድንጋጌ አገላለጽ የመጀመሪያ ደረጃ ክስን ብቻ ይመልከት ወይም የይግባኝ መዝገብን ይጨምር ግልጽ አይደለም፡፡ ነገር ግን የይግባኝ መዝገብን እንደሚመለከት የዚሁ ህግ ቁጥር 74(1) እና 32(2) በመመልከት ለመረዳት ይቻላል፡፡
  • 91.  ተከሳሽ በአቀረበው መልስ ላይ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ቢያቀርብና ክርክሩ ለመሰማት በተቀጠረው ቀን ያልቀረበ ቢሆን በተከሳሹ ላይ ምን አይነት ትእዛዝ ሊሰጥ ይገባል? ማለትም ከሳሽ ባቀረበበት ክስ ላይ በሌለበት እንዲሁም ራሱ ባቀረበው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላይ ደግሞ ክሱን መሰረዝ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል?
  • 92.  ተከራካሪ ወገኖች ባለመቅረባቸው ምክንያት ፍ/ቤቱ የሚሰጣቸው የተለያዩ ትእዛዛት ግራ ቀኙ በክርክሩ ሂደት በሚኖራቸው ተሳትፎ ወይም እንደነገሩ ሁኔታ በነገሩ የክስ ምክንያት ላይ የተለያየ ውጤትን የሚያስከትሉ ይሆናል፡፡  ሀ. የተከሳሹ የመከላከያ መልስ የማቅረብ መብት መታለፍ የሚኖረው ውጤት  ተከሳሹ መከላከያውን በሚያቀርብበት ቀን መልሱን ይዞ ያልቀረበ ከሆነ ፍ/ቤቱ የመከላከያ መልሱን የማቅረብ መብቱን የሚያልፍበት እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ ተከሳሹ የሚያጣው ዋናው መብት በጽሁፍ መከላከያው ላይ የሚያቀርባቸውን መከራከሪያዎችናን ይህንኑ መከራከሪያውን ለመደገፍ ሊያቀርብ የሚችላቸውን ማስረጃዎች ለማቀረብ የማይችል መሆኑ ነው፡፡
  • 93.  ሆኖም ይህ ትእዛዝ ተከሳሹ በክርክሩ ሂደት ከመሳተፍ የመከልከል ውጤት አይኖረውም፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 241 መሰረት ግራ ቀኙን በሚመረምርበት እለት ተከሳሹ በዚሁ ሂደት ተሳታፊ እንደሚሆን እንዲሁም ከሳሽ የሚያቀርባቸውን ምስክሮች መስቀለኛ ጥያቄ የመጠየቅና ሌሎች ከሳሽ በሚያቀርባቸው አቤቱታዎች ላይ መቃወሚያ የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • 94.  1 መልሱን የማቅረብ መብቱን ያጣ ተከሳሽ ከሳሽ በክርክሩ ሂደት የክስ አቤቱታውን ለማሻሻል ጠይቆ ፍ/ቤቱ ይህንኑ የከሳሽ ጥያቄ ተቀብሎ ክሱን እንዲያሻሽል ፍቃድ ቢሰጠውና አሻሽሎ ቢቀርብ ተከሳሹ ከሳሽ ቀደም ብሎ ካቀረበው ክስ የተለየ ነገር ያቀረበ በመሆኑ በማሻሻያው ላይ በጽሁፍ መልስ ልስጥበት በሚል ፍ/ቤቱን ቢጠይቅ ፍ/ቤቱ የተከሳሽ አቤቱታ እንዴት ሊያስተናግደው ይገባል?  2 የመከላከያ መልሱን የማቅረብ መብቱ የታለፈበት ተከሳሽ በመጀመሪያው የክርክሩ መሰማት ቀን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ለማቅረብ ጥያቄ ለፍ/ቤቱ ቢያቀርብ ፍ/ቤቱ በዚህ ጥያቄ ላይ ምን ሊወስን ይገባል ይላሉ?
  • 95.  ለ. የመዝገብ መዘጋት የሚኖረው ውጤት  ከፍ ብለን ለመመልከት እንደሞከርነው የመዝገብ መዘጋት የሚኖረው በመጀመሪያ ደረጃ ክስ ላይ ብቻ ሲሆን ይሄውም በህጉ ቁጥር 69 (2) መሰረት ክርክሩ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ግራ ቀኙ ያልቀረቡ እንደሆነና በ70(መ) መሰረት ከሳሽ ለተከሳሽ በቸልተኝነት ወይም በራሱ ጉድለት መጥሪያ ባግባቡ ያላደረሰ እንደሆነ ነው፡፡  በዚህ አግባብ የሚዘጋ መዝገብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 71(1) መሰረት የተዘጋውን መዝገብ ተገቢውን የዳኝነት ክፍያና የተወሰነበትን ኪሳራ ከፍሎ ከማንቀሳቀስና እንደገና ነገሩ እንዲቀጥል ከማድረግ የሚከለክለው ነገር የለም፡፡  እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ፍ/ቤቱ ኪሳራ ሊወስን የሚችለው ለማን ነው የሚለው ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የዚሁ ህግ ተመሳሳይ ድንጋጌ የእንግሊዝኛ ቅጂ “…the plaintiff may bring a fresh suit on payment of full court fees” በሚል የተደነገገ ሲሆን በዚህም ተከሳሹ ሙሉ የዳኝነት ክፍያውን በመክፈል አዲስ ክስ ለማቅረብ ይችላል ከማለት ውጪ ስለኪሳራ የሚለው ነገር የለም፡፡
  • 96.  ልዩ ልዩ የሥነ-ሥርዐት ሕጉን ድንጋጌዎች ስንመለከት ኪሳራ የሚቆረጠው አንደኛው ተከራካሪ ለክርክሩ መጓተት ምክንያት ሲሆን ለሌላኛው ተከራካሪ የሚወሰንበት አግባብ ነው በዚህኛው ጉዳይ ግን ተከሳሹ ያልቀረበ መሆኑ ኪሳራ ደርሶበታል ሊባል ስለማይችል ኪሳራ የሚቆረጥበት ምክንያት ግልጽ አይደለም፡፡ በመሆኑም የአማርኛው ቅጂ በህጉን ኪሳራ ሊቆረጥ አስፈላጊ የሚሆንበትን ምክንያት አላማ ያላገናዘበ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ የእንግሊዝኛው ቅጂ ተፈጻሚነት ሊኖረው እንደሚገባ ለመረዳት ይቻላል፡፡  ይሁን እንጂ በዚሁ ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር 71(2) መሰረት ከሳሽ የዳኝነት ሳይከፍል የክስ መዝገቡን የሚያንቀሳቅስበት ልዩ ሁኔታ ተመልክቷል፡፡ ይሄውም ከሳሽ ያልቀረበው በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ያስረዳ እንደሆነና ይህንንም ምክንያት ፍ/ቤቱ የተቀበለው እንደሆነ ነው፡፡ ይህ የሕጉ አቀማመጥ ተፈጻሚነት የሚኖረው በተለይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(2) መሰረት ክርክሩ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ላልቀረበ ከሳሽ ነው፡፡ ምክንያቱም ስለከሳሽ አለመቅረብ የተመለከተው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70(መ) ሳይሆን በ69 (2) ላይ በመሆኑ ነው፡፡