1
ወጣቶች በሀገር እና በሀገረ-መንግስት ግንባታ
ዉስጥ ያላቸዉ ሚና
መሪ ቃል
"ሀገሬን እገነባለሁ ሀላፊነቴንም እወጣለሁ"
ሚያዚያ/2017 ዓ/ም
አዲስአበባ
2
ይዘት
መግቢያ.............................................................................................................................................................4
ዓላማ................................................................................................................................................................5
የሚጠበቁ ውጤቶች............................................................................................................................................5
የወጣቶች ታሪካዊ ዳራ በኢትዮጵያ.........................................................................................................................6
ክፍል አንድ፡ ሀገር እና ሀገረ- መንግስት ግንባታ..........................................................................................................8
1.1. የሀገር (Nation) ፅንሰ-ሀሳብ...................................................................................................................8
1.2. የሀገረ-መንግስት (State) ፅንሰ-ሀሳብ........................................................................................................8
1.3. ሀገረ-መንግስት ግንባታ............................................................................................................................9
1.4. ሀገር-ግንባታ...........................................................................................................................................9
1.4.1. ዜግንነትና የመልካም ወጣት ዜጋ መገለጫዎች..................................................................................10
1.4.2 ብሄራዊ ትርክት ግንባታ...................................................................................................................12
1.4.3 ብሔራዊ መግባባት........................................................................................................................13
1.4.4 ብሄራዊነት ና አርበኝነት...................................................................................................................15
 ብሄራዊነት........................................................................................................................................15
 አርበኝነት..........................................................................................................................................15
ክፍል ሁለት..................................................................................................................................................16
2. የሰላም እሴት ግንባታ.................................................................................................................................16
2.1. የሰላም ፅንሰ- ሀሳብ...........................................................................................................................16
2.2. የሰላም ግንባታ..................................................................................................................................16
2.3. የሰላም ባህል........................................................................................................................................17
2.4. የሰላም ግንባታ ስራዎች..........................................................................................................................18
2.5. የወጣቶች የሚዲያ አጠቃቀም ለሰላም ግንባታ......................................................................................19
3
2.5.1. ሚዲያ ለሰላም ግንባታ...............................................................................................................19
2.5.2. የወጣቶች የሚዲያ አጠቃቀም.....................................................................................................21
ክፍል ሦስት.....................................................................................................................................................22
3. የወጣቶች ሚና..........................................................................................................................................22
3.1. በሀገረና ሀገረ-መንግስት ግንባታ ወጣቶች ያላቸው ሚና..........................................................................22
3.2. በሰላም እሴት ግንባታ ወጣቶች ያላቸው ሚና.........................................................................................23
ማጠቃለያ........................................................................................................................................................24
4
መግቢያ
የአንድን ሀገር ዘላቂ ሰላም እና እድገት ለማረጋገጥ የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት መሰረታዊ ነው፡፡
በኢትዮጵያ 70% ያህሉ ወጣቶች በመሆናቸው በሀገር እና ሀገረ-መንግስት ግንባታ እንዲሁም በሠላም እሴት ግንባታ ላይ
ባላቸው ሚና በማህበረሰቡ ውስጥ ልዩ ስፍራ ይሰጣቸዋል፡፡ ወጣቶች የሚጠበቅባቸውን ሚና በአግባቡ ተረድተው ታሪካዊና
የዜግነት ሃላፊነትን መወጣት እንዲችሉ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ሁኔታዎች ላይ ግልፅ ግንዛቤ ኖሯቸው እና
የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ማድረግ ይጠበቃል፡፡
ሰነዱ ከሀገራችንን ወጣቶች ታሪካዊና አሁናዊ ሁኔታዎች በመነሳት ከወጣቱ የሚጠበቁ ሀገራዊ ሀላፊነቶችን በዝርዝር
ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ አንፃር ወጣቶች በሀገር ግንባታ፣ በሰላም ግንባታ፣ በብሄራዊነት ገዢ ትርክት ግንባታ እና በሚዲያ
አጠቃቀም ላይ ስለሚኖራቸው ሚና በሰነዱ ውስጥ ተካቷል፡፡
በመሆኑም በሁሉም የወጣት አደረጃጀቶች ያሉ ወጣቶች በሰነዱ ላይ በጥልቀት እንዲወያዩና ተቀራራቢ የሆነ ግንዛቤና
አመለካከት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ እንዲሁም ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ይህ የውይይት መነሻ ሰነድ ተዘጋጅቷል።
5
ዓላማ
የዚህ ሰነድ ዓላማ ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩ መነሻ ሀሳቦችን በመስጠት ያላቸውን ግንዛቤ፣
ልምድና እውቀት በእርስ በርስ ውይይት በማዳበር ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የተቀራረበ አረዳድ ኖሯቸው የጋራ
መግባባት ላይ በመድረስ እና ፅኑ አቋም በመያዝ ከግል እስከ ሀገር ያለባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ማስቻል፤
የሚጠበቁ ውጤቶች
በዚህ ሰነድ መነሻነት ከሚደረጉ ውይይቶች በኋላ የሚከተሉት ውጤቶች ይጠበቃሉ፡፡
I. በሀገርና ሀገረ- መንግስት እንዲሁም በሰላም እሴት ፅንሰ ሀሳቦች ላይ በቂ ግንዛቤ ያላቸው ወጣቶችን
መፍጠር፤
II. ለሀገርና ሀገረ- መንግስት ግንባታ እንዲሁም ለሰላም እሴት ግንባታ ያላቸውን ሚና በመለየት ድርሻቸውን
የሚወጡ ወጣቶችን መገንባት፤
III. ምክንያታዊ የሆነ የሚዲያ አጠቃቀም ስልትን በመከተል ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን የሚወጡ ወጣቶችን
ማፍራትና ማብዛት፤
IV. የወጣቶች ተሳትፎን በማሳደግና መስተጋብር በመፍጠር ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር፤
V. ያደገ የወጣቶች ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ አበርክቶ እንዲሁም ሁለንተናዊ ተሳትፎና
ተጠቃሚነትን ማሳደግ፤
6
የወጣቶች ታሪካዊ ዳራ በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ እንደ አንድ የአለም አካል በርካታ ከአለም ህዝቦች ጋር የሚያስማማት እና የሚያመሳስላት የአኗኗር
ዘይቤ፣ የግንኙነት መሰረታውያን እና ባህሎች አሏት፡፡ ሆኖም ከሌሎች የአለም ክፍሎች ለየት ባለ መልኩ እኛ
ኢትዮጵያውያን ብዝኃ -ባህል ፣ ቋንቋ፣ እምነትና ማንነት ያለን፤ ብዝኃ- መልክ፣ የኑሮ ዘይቤና አካባቢ ያለን፤ ብዝኃ -
መሰረት፣ ስልጣኔ፣ ቅርስና ታሪክ ያለን፤ ሉዓላዊነታችንን ሳናስደፍር የኖርን፤ ለአፍሪካ ነፃነት ተምሳሌት የሆንን፤
ከባድ ፈተናዎችን በአሸናፊነት የተሻገርን፤ የሰው ዘር መገኛ ምድር፤ የዴሞክራሲ ስርዓት የጀመርን፤ አህጉራዊና
አለምአቀፍ ተቋማትን የፈጠርን ፤ ልዩ ስነ-ህንፃ ያስተዋወቅን፤ ስነ-ጽሁፍ የፈጠርን፤ የአለም ረጅም ወንዝ መነሻና
የአፍሪካ የውሀ ማማ የሆንን ፤ ልዩ የአዕዋፍና ብርቅዬ አራዊት ዝርያ መገኛ የሆንን፤ የእፅዋት እና የቡና መገኛ
ባለቤት የሆንን፤ የተለየ መልከዓ-ምድርና የተስተካከለ አየር ንብረት የታደልን፤ ብዙ አይነት ማዕድናት ያለን፤ ሰፊና
ለም መሬት ባለቤት የሆንን፤ ብዙ ቅርሶችና ፓርኮች ያሉን፤ እንግዳ ተቀባይና አክባሪ የሆንን፤ በችግር ጊዜ
የምንተባበር፤ ግብረገብነት መገለጫችን የሆነ ህዝቦች ነን፡፡ በኢትዮጵያ በየዘመናቱ የነበሩ ወጣቶች ታሪክ
በመስራትና የሀገራችንን አኩሪ ታሪክ በመጠበቅ እንዲሁም በማስቀጠል ሚናቸውን ሲወጡ ቆይተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ ወጣቶች በሰላም እና ሀገረመንግስት ግንባታ ላይ የበኩላቸውን ሚናሲያበረክቱ
ቆይተዋል፡፡በ 1960 ዎቹ የነበረው "መሬት ለአራሹ!"/land for the tailer በሚል ትግል ውስጥ የወጣቶች ሚና
ከፈተኛ ነበር፡፡ ይሄውም ሂደት ለንጉሳዊ ስርዓት ዉድቀት አነዱ ምክንያት ሆኗል፡፡
በደርግ መንግስት ስርዓት (1974-1991) የሶሻሊዝም ርዕዮት አለምን በገጠሩ ማህበረሰብ ዉስጥ ለማስረፅ
ወጣቶች "እድገት በህብረት" በሚል ዘመቻ የልማት ሥራዎች ላይ በግንባር ቀደምትነት ሲሳተፉ ነበር፡፡ ይሁን
እንጂ ስርዓቱ ለወጣቱ ትውልድ ምቹ ባለመሆኑ ምክንያት የወጣቱ ያላሰለሰ ትግል ለስርዓቱ ውድቀት ተጠቃሽ
ምክያት ሆኗል፡፡
የመጀመሪያዉ የብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ በ 1994 ዓ.ም በወጣቶች፤ስፖርትና ባህል ሚኒስቴር ወጥቷል፡፡
ሚኒስቴሩ በፌዴራል ደረጃ የወጣቶች ጉዳዮችን የመከታተል፣ የመምራትና የማስተባበር ኃላፊነት አለዉ። በአገራዊ
የወጣቶች ፖሊሲ መሰረትም ክልሎች ወጣቶችን በተመለከተ የመንግስትን አቅጣጫ ለማስፈፀምና ለማስተባበር
የወጣቶች ቢሮዎችን አቋቁመዉ ወደ ስራ ገብተዉ ነበረ።
7
ወጣቱ በዴሞክራሲያዊ አመለካከት፣ ሙያዊ ብቃት፣ ክህሎትና ስነ-ምግባር የታነጸ ብቁ ዜጋ ሆኖ በዴሞክራሲያዊ
ሥርዓት ግንባታው ውስጥ በብቃት እንዲሳተፍና ወጣቶች በሀገሪቱ እየተመዘገበ ካለው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
ዕድገት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ወሳኝ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚያስፈልግ የወጣቶች ፖሊሲው
ያመለክታል። እንዲሁም ፖሊሲው ወጣት ኢትዮጵያውያን ጨቋኝ መንግስታት ለመጣል በተደረገዉ ትግል ውስጥ
ያላቸውን ንቁ ሚና እውቅና ይሠጣል። በተለይም በ 1960 ዎቹ ወጣት ተማሪዎች ማህበረሰባቸውን በማስተባበር
በሀገሪቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦችን ለማምጣት ያደረጉትን ሚና እውቅና በመስጠት
የወጣቶች ሚና የጎላ መሆኑን ያስቀምጣል።
በኢህአዴግ ስርዓት ውስጥም ፀረ ዴሞክራሲያዊነት እየገነገነ በመምጣቱ ስርዓቱ በሰላማዊና ህገ መንግስታዊ መንገዶች
ሊለወጥ እንደማይችል ዜጎች ጠንካራ እምነት እንዲይዙ አድርጓቸዋል። በዚህ ሁኔታ የሀገራችንን ወጣቶች በየቦታው
ለምሬትና ለአመጽ ዳርጓቸው የሀገራችንን ሰላምና ደኅንነት አደጋ ውስጥ በመውደቁ በመላ ሀገሪቱ እምቢተኝነት ተቀጣጥሎ
በትግል ሂደቱም ወጣቶች ግንባር ቀደም ሆነው ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን በመወጣት ሀገራዊ ለውጡ እውን እንዲሆን
አድርገዋል፡፡
የለዉጡ መንግስትም ባለፉት ስድስት አመታት የተለያዩ ፈተናዎችን በመቋቋም ሀገር ወደ ፊት የሚያስቀጥሉና ትዉልድን
የሚገነቡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ተግባራትን ሲፈፅም ቆይቷል፤ እየፈፀመም ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የዘመናት ታሪክ ውስጥ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ከመሆኑም ባሻገር ሀገራችን ኢትዮጵያ በየወቅቱ
የተጋረጠባትን ፈተና በድል እንዲትወጣ ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከትና ሀገር እንድትቀጥል በማስቻል ታሪካዊ ባለውለታዎች
ሆነዋል፡፡
8
ክፍል አንድ፡ ሀገር እና ሀገረ- መንግስት ግንባታ
1.1. የሀገር (Nation) ፅንሰ-ሀሳብ
ሀገር የተለያዩ ብዛሃ-ማንነቶች በስነ ሕዝብ አወቃቀር እና በባህል የተሳሰሩ፣ ተቀራራቢ ማህበረሰባዊ ስሜት
ያላቸው እና በፖለቲካዊ መንገድ እራሳቸውን በአንድ ስርዓተ-መንግስት የሚመሩ ቋሚ ህዝቦች የሚገኙበት፣
አለም አቀፍ እውቅና ያለው ድንበር እና ግዛት ያለው፣ የሚያስተዳደር መንግስት ያለው፣ ሉአላዊነቱ የተከበረ እና
እውቅና ያለው መልካምድራዊ ወሰን ነው። ሀገር ማለት እንደ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ዘር፣ ባህል፣ ግዛት ካሉ የጋራ
ባህሪያት ጥምር በጋራ ማንነት እና ዓላማዊ ትሥሥር ያላቸው ማህበረሰቦች የተገነባ ትልቅ የማህበራዊ ድርጅት
አይነት ነው።
1.2. የሀገረ-መንግስት (State) ፅንሰ-ሀሳብ
የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ሀገረ-መንግስትን በተለያዩ መንገዶች ይተረጉሙታል። በጥቅሉ አረዳድ ሲታይ የአንድ
ህዝብ ፖለቲካዊ አደረጃጀት ወይም በአንድ ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ የመንግስት ተቋማት ስብስብ ሀገረ-መንግስት
ይባላል። በጥቅሉ “ሀገረ-መንግስት ማለት በመንግስት የሚመራ ቋሚ ህዝብ የሚኖርበት ድንበርና ዓለም አቀፍ
እውቅና ያለዉ ግዛት” መሆኑን ሁሉም የዘርፉ ምሁራን ይስማሙበታል።
ግዛት፡- በአንድ ሀገረ-መንግስት ቁጥጥር ስር ወይም በሀገረ-መንግስቱ ሉዓላዊ የስልጣን ክልል
ውስጥ የሚገኝ ጅኦግራፊያዊ ወሰን ማለት ነዉ። ሀገረ-መንግስት በበላይነት የሚቆጣጠረዉ ግልፅ
ዓለም አቀፋዊ ወሰን ያለዉ ነው፡፡
ህዝብ፡- ሀገረ-መንግስቱ በሚቆጣጠረዉ ግዛት ውስጥ በሀገረ-መንገስቱ ሉዓላዊ ህግና ስርዓት
የሚኖር ማህበረሰብ ማለት ነዉ። ህዝብ የሌለበት ግዛት ሀገረ-መንግስት ሊባል አይችልም።
መንግስት፡- ሀገረ-መንግስቱን ወይም በሀገረ-መንግስቱ የግዛት ወስን ውስጥ የሚኖረዉን ህዝብ
የሚመራ ስርዓት ወይም አካል ማለት ነዉ። በሌላ አባባል መንግስት በተወሰነ ግዛት ውስጥ
የቁጥጥር ስርዓት ለማበጀት ህግን የማዉጣትና የመተግበር ሉዓላዊ ስልጣን ያለዉ አካል ወይም
ቡድን ነዉ። ተቆጣጣሪ መንግስት የሌለዉ ግዛት ቋሚ ህዝብ ቢኖረዉም ሀገረ-መንግስት ሊባል
አይችልም።
ዓለም አቀፍ እዉቅና፡- አስቀድሞ እውቅና ያላቸው ሀገረ-መንግስታት አዲስ የተፈጠረዉ ሀገረ-
መንግስት ሉዓላዊ መሆኑን በግልፅ መቀበል ማለት ነዉ። እዉቅና ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ ዓለም አቀፍ
9
ህጎችን የማክበር፤ ግዴታዎችን የመፈፀምና በሉዓላዊነቱ ከሌሎች ሀገረ-መንግስታት እኩል በዓለም
አቀፍ ጉዳዮች የመሳተፍ መብት ይኖረዋል።
1.3. ሀገረ-መንግስት ግንባታ
መንግስት የተደራጀ ማህበረሰብን የሚያስተዳድር ስርዓት ወይም የሰዎች ስብስብ ነው። ሰፋ ባለ የአሶሲዬቲቭ
ትርጉሙ፣ መንግስት በመደበኛነት ህግ አውጪ፣ አስፈፃሚ እና ተርጓሚን ያካትታል። መንግሥት ፖሊሲዎች
የሚተገበሩበት ተቋም ፣ እንዲሁም ፖሊሲን የሚወስኑበት ዘዴ ነው። የሀገር መንግስት ግንባታ የረጅም ጊዜ
ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ልማትን ለመደገፍ አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን የመፍጠር እና የማጠናከር
ሂደት ነው፡፡ ይህም የመንግስትን አገልግሎት የመስጠት፣ ህግ የማስከበር፣ ደህንነትን የማስጠበቅ እና
ኢኮኖሚን የመምራት አቅም ማዳበርን ያካትታል።
የሀገረ-መንግስት ግንባታ ማለት በሀገራዊ ወሰን ውስጥ የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል ህዝባዊ
መዋቅር መመስረት፣ መልሶ ማቋቋም እና ማጠናከር ማለት ነው።
1.4. ሀገር-ግንባታ
ሀገር-ግንባታ ማለት የተለያየ መነሻ፣ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት ያላቸው ህዝቦች በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ወሰን
ውስጥ ተቀራራቢ መንፈስ፣ አንድነት፣ ትብብር እና የጋራ ራዕይ እና ማንነት እንዲኖራቸው የሚሰራ የረጅም ጊዜ
ስራ ነው፡፡ ይህንንም እውን ለማድረግ በህዝቦች መካከል መቀራረብን፣ መተማመንን፣ የጋራ እሴቶችን፣ የጋራ
ታሪክ፣ በመንፈስም በተግባርም የሚጋሯቸው የጋራ ህልሞችና ጥቅሞች እንዲኖሯቸው የማድረግና እና
በህዝቦች መካከል ብሔራዊ መግባባትን የማዳበር ሂደት ነው፡፡
ሀገር ግንባታ የህዝቦች ጠንካራ ማህበራዊ ግንኙነቶች፣ በሀገራዊ ቅኝት የተቃኘ የትምህርት ስርዓት፣ ጠንካራ
ተቋማት፣ ብዝሃነትን በሚያንፀባርቁ ሀገራዊ ፖሊሲዎች ውስጥ የሚሰራ የረጅም ጊዜ ፕሮጀክት ነው፡፡
ከዚህ አንፃር ሀገራችን ኢትዮጵያ ለረዥም ዘመናት መንግስት መስርታና ነጻነቷን ጠብቃ የኖረች ሀገር ስትሆን
ባሳለፈችው ረዥም የታሪክ ወቅትም ህዝቦቿ የተለያዩ የውስጥ ችግሮቻቸውንና የውጭ ወራሪዎችን አብረው
ተጋፍጠዋል፡፡ በዘመኗ ሁሉ የተለያዩ ባህል፣ ቋንቋና የኑሮ ዘይቤ ያላቸው ህዝቦች በጋብቻ፣ በንግድ፣ በእምነትና
በተለያዩ ማኀበራዊ እሴቶች ውህደትና መስተጋብር ተሳስረው የሚኖሩባት ሀገር ናት፡፡
ይሁን እንጂ ይህ ለዘመናት የተሳሰረውን አብሮነትና አኩሪ ታሪክ ወደተሳካ የሀገረ ግንባታ አልተሸጋገረም፡፡
ለዚህም አንዱ ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት ሀገሪቷን ያስተዳደሯት መሪዎች ሀገሪቷን ለመቅረጽ የሄዱበት መንገድ
የሀገረ ግንባታ ጉዞ ከሀገረ መንግስቱ ግንባታ ጉዞ አንፃር ወደ ኋላ እንዲቀር አድርጐታል፡፡ ስለሆነም ተገቢ
10
ለውጦችና ማሻሻያዎች ተደርገው በመንግስትና በህዝብ እንዲሁም በህዝቦች መካከል ትስስርና መተማመን
ተፈጥሮ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ የጋራ ራዕይና ሀገራዊ አንድነት ሊኖር ይገባል፡፡
1.4.1. ዜግነትና የመልካም ወጣት ዜጋ መገለጫዎች
 ዜግነት
ዜግነት ማለት የአንድ ማህበረሰብ አባልነት ስሜት እና ከእሱ ጋር የሚመጡ መብቶች እና ግዴታዎች መኖር
ነው፡፡ አንድ ወጣት ዜጋ ሙሉ እና ህጋዊ የግዛት አባል ሲሆን መብቶቹን የሚቀበል እና የአባልነት ግዴታዎችን
የሚወጣ ነው። ከዚህ አንፃር ዜግነት በዜጎች እና በመንግስት መካከል የመብትና ግዴታ ግንኙነት ነው። የዜጎች
መብቶች የመንግስት ተግባራት እና የዜጎች ግዴታዎች የመንግስት መብቶች ናቸው፡፡
 የዜጎች መብቶች
የአንድ ዜጋ መብቶች በመንግስት እውቅና የተሰጣቸውን እና የሚተገበሩትን የይገባኛል ጥያቄዎች እና ልዩ
መብቶችን ያመለክታሉ። ዜጎቹ በህብረተሰቡ ውስጥ ጠቃሚ፣ ንቁ እና ሚዛናዊ ህይወትን ለመኖር እነዚህን
መብቶች መጠቀም ይኖርባቸዋል። እነዚህ መብቶች ዜጎች መልካም፣ ኃላፊነት የሚሰማቸው እና ውጤታማ
የህብረተሰብ አባላት እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። በብዙ አገሮች ከተለመዱት የዜጎች መብቶች መካከል በሕይወት
የመኖር፣ የንብረት ባለቤትነት መብት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት፣ ሐሳብ የመያዝ መብት፣ የመሰብሰብ
ነፃነት፣ የመማር መብት፣ በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት፣ የመልማት መብት፣ ንፁህና ጤናማ አካባቢ
…
የማግኘት መብት፣ ወዘተ ይገኙበታል፤ ስለሆነም ወጣቶች መብታቸውን አውቀው መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡
 የዜጎች ግዴታዎች
አንድ ዜጋ እንደ አንድ ሀገር አባልነቱ ለሁሉም የሚጠቅም እና የህብረተሰቡን ደህንነት የሚያግዝ ባህሪ ማሳየት
አለበት። መብትና ግዴታ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። በብዙ ሀገራት ከተለመዱት የዜጎች ተግባራት
መካከል የሀገርን ሉዓላዊነትና ብሄራዊ ጥቅም ማስጠበቅ፣ ለሀገር ታማኝ መሆን፣ ለሀገር ህገ መንግስት ተገዢ
መሆን፣ ሌሎች ህጎችን ማክበር፣ ብሄራዊ በጎ ፍቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት ላይ መሳተፍ፤
ለአዎንታዊ ሰላም አበርክቶ ማድረግ፤ ሚዛናዊ የሚዲያ አጠቃቀም ስርዓት መከተል እና የመሳሰሉ ይገኙበታል፡፡
ስለሆነም ወጣቶች መብቶቻቸውን በአግባቡ በመጠቀም እና ግዴታቸውን በመወጣት የበኩላቸውን ድርሻ
ማበርከት አለባቸው፡፡
 የመልካም ዜጎች(ወጣቶች) መገለጫዎች
መልካም ዜጎች(ወጣቶች) የሚከተሉትን መገለጫዎችን ያንፀባርቃሉ፡፡
11
 ታማኝነት እና እውነተኝነት፡- እምነት የሚጣልባቸው እና እውነትን የሚይዙ፤
 ተጠያቂ፡- ለድርጊታቸው እና ለውሳኔዎቻቸው ሀላፊነት የሚወስዱ፡፡
 የሀገር ፍቅር፡- ለአገር ጥቅም ተግባራዊ መስዋዕትነትን ማንፀባረቅ፤
 ህግጋትን ማክበር እና ተገዢ መሆን፡ ለህግ የበላይነት መቆም፤
 በበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት ውስጥ መሳተፍ፤
 ምክንያታዊነት፤
 ብዝሃነትን ማክበር፤
 ለአገር ሉዓላዊነትና ብሄራዊ ጥቅም መቆም፤
 ዓለም አቀፍ ዜግነትና እሴቶች
የዓለማቀፋዊ ዜግነት ጽንሰ-ሐሳብ የሚመነጨው ሁሉም የሰው ልጆች የጋራ ምክንያቶች፣ ሁለንተናዊ ተፈጥሮ
እና ተመሳሳይ ፍላጎቶች እንዳላቸው ከማመን ነው፡፡ ዓለም አቀፋዊ ዜግነት ሁላችንም የአንድ ዓለም ዜጎች
መሆናችንን ማወቅ እና ለዓለማችን እና በዛ ላይ ላሉት ሰዎች ያለንን አክብሮት በሚያሳይ መንገድ መግለፅን
ይጨምራል።
አለም አቀፋዊ ዜጋ የሚከተሉትን እሴቶች እና አመለካከቶች የሚያሳይ ነው፡-
 ርህራሄ፡- የሌሎችን ህዝቦች ስሜት መረዳት እና እራስን በሌሎች ህዝቦች ጫማ ውስጥ ማስገባት፤
 ለማህበራዊ ፍትህ እና ፍትሃዊነት ቁርጠኝነት፡- የህዝቦች የኋላ ታሪክ ልዩነት ምንም ይሁን ምን ለፍትህ
እና ለፍትሃዊነት መቆም፤
 ልዩነትን ማክበር፡- ልዩነቶችን መቀበል እና የሌሎችን ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ሀይማኖቶች፣ እሴቶች፣
አስተያየቶች እና የመሳሰሉትን ማክበር፤
 ለአካባቢ ጥበቃ እና ለዘላቂ ልማት ቁርጠኝነት፡- አካባቢን መጠበቅ እና የወደፊት ትውልዶችን እና
የወደፊት ሁኔታዎችን ያገናዘበ ልማት ማረጋገጥ፤
 ሰዎች ለውጥ ሊያመጡ እንደሚችሉ ማመን፡- በሰዎች ዋጋ እና ለማህበረሰቡ በሚያበረክቱት
አስተዋፅዖ ማመንን ያካትታል፡፡
12
1.4.2 ብሄራዊ ትርክት ግንባታ
ትርክት አንድ ማህብረሰብ ከራሱ ባህል፣ ወግ፣ ማንነት፣ የአኗኗር መስተጋብር ጋር ተያይዞ ከትውልድ
ወደ ትውልድ የሚሸጋገርለት እና ከሌላው ማህበረሰብ ጋር ለዘመናት በአብሮነት በጋራ የሚያኖረው ልዩ
መለያው እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚሄድ አስተሳሳብ ነው፡፡
ነገር ግን ይኸው የአንድ ማህበረሰብ መለያ እና በሌላው አካል በበጎ ጎኑ የሚታወቀው ትርክቱ በተሳሳተ
ምልከታ እና ፍረጃ ሲሸረሸር በሌላው ዘንድ በወንድማማችነት እና እህትማማችነት ሲታይ የነበረው
ማንነቱ በሌሎች ዘንድ ለአሉታዊ አስተሳሰብ እና ምልከታ ሊዳረግ ይችላል፡፡ በዚሁ መሠረት ስለትርክት
አስተሳሰብ የምንረዳው ጉዳይ ትርክት የአንድ ማህበረሰብ መገለጫ ከመሆኑም ባለፈ ከሌሎች
በአካባቢ አብረው ከሚኖሩ የማህበረሰብ ወግ ወይም አኗኗር ዘይቤ ጋር የማይጣረስ፣ ይልቁንም
በአብሮነት የሚያኖረው ሲሆን ከሌላው ማህበረሰብ ጋር እንደ ድርና ማግ የተጋመደ ነው፡፡ ይህም
የአንዱ ማህበሰረሰብ የዕምነት አስተምሮ ሌላውን በማይጋፋ እና በሚያከብር ሁኔታ ከመካሄዱም ባለፈ
የሌላውን አብሮት የሚኖረው ወይም የጎረቤቱ ሀዘንና ደስታን እንደራሱ አድርጎ በመውሰድ የመልካም
እና የክፉ ጊዜ ደራሽ በሚያደርገው መስተጋብር እንዳይለያይ ተደርጎ የተጣመረ ነው፡፡
ገዥ ትርክታችን የሆነው ብሔራዊነት፣ አስተሣሣሪ ትናንቶች እና አስተሣሣሪ ነገዎቻችን የሚጸኑበት ትርክት ነው፡፡
ሕዝባችን ብዙ አስተሣሣሪ ትናንቶች አሉት፡፡ ዘመናት መጥተው ዘመናት ቢሄዱ የማይናወጠው ለሉዓላዊነት እና
ለሀገራዊ ነጻነታችን ትልቅ ዋጋ የምንሰጥ ሕዝቦች ነን፣ ምንም እንኳን በየወቅቱ በውስጣዊ አንድነት ብንፈተንም
ሀገራዊ ህልውናችንን ሊፈታትን የሚመጣን ጠላት አሳፍሮ የመመለስ አኩሪ ታሪክ አለን፡፡
በመሆኑም ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ በመንቀሳቀስ
የነገይቱን የለማች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን በመገንባት ቀጣዩ ትውልድ በኩራት የሚኖርባት ታላቅ እና ገናና
ሀገር እንድትኖረን ለማድረግ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአንድነት በትብብርና በጋራ የአመለካካትና የተግባር አንድነትን
በማላቅ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ሁሉ ውጤታማ ሥራ በመስራት እና የላቀ ዉጤት በማስመዝገብ
ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል፡፡
1.4.3 ብሔራዊ መግባባት
ብሔራዊ መግባባት ማለት ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የዴሞክራሲ መርህን መሰረት በማድረግ ምልዓተ ሕዝቡ
በምክክርና በውይይት ምክንያታዊ የሆነ የጋራ መግባባትና መተማመን ላይ መድረስ ሲሆን ለተግባራዊነቱ የተሟላ
የአስተሳሰብ ዝግጁነትን የሚያረጋግጥ የመግባባት ደረጃ ነው፡፡ በሃገር ግንባታ ሂደት ውስጥ መግባባት ከሚፈልጉ
መሰረታዊ ጉዳዮች ውስጥ ሀገራዊ ማንነት፣ ሀገራዊ ጥቅም እና ሀገራዊ እሴቶች ዋነኞቹ ናቸው፡፡
 ሀገራዊ ማንነት
13
የአንድን ሀገር ህዝቦች ስብስብ የሚያስተሳስር እና የዜጎችን የአንድ ሀገር እና ማህበረሰብ አካል እና አባል
የመሆኑ መገለጫ የሚያጎለብት የጋራ ባህል፣ ታሪክ እና ህልም መፍጠር የሚችል ብሔራዊ ማንነት ያስፈልጋል።
ኢትዮጵያ የበርካታ ብዛሃ ማንነቶች ባለቤት ፣ በጋራ ለረጅም ዘመናት የተጋሩ፣ አብሮ የመኖር እና ዘርፈ ብዙ
ትስስር ፈጥረው እንዲኖሩ መሰረት የሆኗት የጋራ ማንነቶች አሏት፡፡ ሆኖም እነዚህ ማንነቶች በግልፅ ተለይተው
የጋራ መግባባት አልተፈጠረባቸውም፡፡ ይልቁንም ልዩነታችን ላይ ያተኮሩ ትርክቶች እና አካሄዶች ጠንካራ
ብሔራዊ አንድነት እንዳንገነባ ማነቆ ከመሆኑ በላይ ለሃገራዊ እድገታችንን ፈተና ሆኗል፡፡ በመሆኑም ብሔራዊ
ማንነቶቻችን በአግባቡ መለየት እና ከሌሎች ማንነቶቻችን ጋር በማጣጣም ብሔራዊ መግባባት ማስፈን
ያስፈልገናል፡፡
 ሀገራዊ ጥቅም
ብሄራዊ ጥቅም አንድ ሀገር ወደፊት ሊያራምደው እና ሊጠብቀው የሚፈልጋቸው፣ በውስጣዊ ኩነቶችም ይሁን
በዓለም ዓቀፍ ግንኙነቶች ልታሳካ የምትፈልጋቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የጋራ ግቦች፣ እሴቶች፣
ሀብቶች እና ዓላማዎችን መሰረት ያደረገ ምክንያታዊ የሆነ እሳቤ ነው፡፡
ብሔራዊ ጥቅማችን መጠበቅ እና መከበር የምናረጋግጠው መደበኛ በሆነው የውጭ ግንኙነት ሂደታችን ብቻ
ሳይሆን በሁሉም ዜጋ የሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ውጭ በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች እና ድርጊቶች
ሊያከብርና ሊያስከብራቸው ሲችል ነው፡፡ ተቋማዊ እና ግለሰባዊ ስራዎቻችን ከሀገራችን ጥቅም ጋር
የሚኖራቸውን ተዛማጅነት እና ልዩነት በአግባቡ መረዳት እና መጠበቃቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ እንደ ዜጋ
የምንሰማራባቸው የስራ መስኮች እና የምናደርጋቸው ግንኙነቶች ከሀገራችን ጥቅም አንፃር መቃኘት እና
በአካልም በሀሳብም የገዘፈች ሀገር የመገንባት ሂደት ውስጥ ሚናችንን የመወጣት ሃላፊነት አለብን፡፡
አስተሳሰባችን እና ቁሳዊ ፍላጎታችን ከሃገራዊ ጥቅማችን ጋር የማይጋጭ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡
በታሪካችን ሀገራዊ ጥቅሞች ትኩረት ካደረጉባቸው ጉዳዮች መካከል፡- የሀገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ፣
ሀገራዊና ቀጠናዊ ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ፣ የሀገሪቱን የግዛት አንድነት ማስጠበቅ ፣ ሀገራዊ ቅርሶችንና
እሴቶች መጠበቅ እና የአፍሪካ ነፃነትና ፓን-አፍሪካዊነት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡
 ሀገራዊ እሴቶች
ብሔራዊ እሴቶች ሥነምግባራዊ/ሞራላዊ፣ ባህላዊ እና ማኅበራዊ ደንቦችን እንዲሁም የሀገሪቷን ብሔራዊ
መለያ/መገለጫ ይመለከታል፡፡ የሃገራዊ እሴቶች ዋና ሚና ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ መረጋጋትን
14
ማሳደግ፣ ተቋማዊ ውጤታማነትን ማሻሻል፣ የዴሞክራሲ ሂደቶችን ማጠናከር እና ጠንካራ ብሄራዊ ማንነትን
ማጎልበት ነው።
ዜጎች የሚጋሯቸው፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስሩ፣ የጋራ ምናባዊ እንደሁም ተጨባጭ አንድነትን
መፍጠር የሚችሉ የሀገር መገለጫ የሆኑ ብሔራዊ እሴቶች ሊኖሩ ይገባል፡፡ በትውልድ ቅብብሎሽ ዘመናትን
የሚሻገሩ፣ የባህላችን፣ የባህሪያችን፣ የስነምግባራችን እና የግንኙነት መርሃችን ሊሆኑ የሚገቡ ሃገራዊ
እሴቶችን መለየትና ማስጠበቅ ይጠበቅብናል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ እሴቶች ከሀገሪቱ ህገመንግስት እና ከማኅበረ-ባህላዊ ተቋማት የሚመነጩ ሲሆን እንደ
ሰላማዊነት፣ ፍትሃዊነት፣ ሰብዓዊነት፣ አርበኝነት፣ መረዳዳት፣ ወ.ዘ.ተ ያሉትን በመለየት እና የጋራ መግባበት
ላይ በመድረስ ሁሉም የሃገራችን ዜጎች እንዲጋሯቸው እና እንዲላበሷቸው መስራት ይኖርብናል፡፡
1.4.4 ብሄራዊነት ና አርበኝነት
ብሄራዊነት
'ብሔራዊነት' ማለት 'ሕገ-መንግስታዊነትን መሠረት ያደረገ ኀብረ-ብሔራዊ አንድነት' ማለት ነው፡፡ ብሄራዊነት
አካታች ነው፤ በተናጠልና በወል ማንነቶችና መብቶች መካከል ያለውን ሚዛን በመጠበቅ በትብብር ላይ
የተመሰረተ ጠንካራ አንድነት መገንባት ነው፡፡ ብሔራዊነት በአንድነት የሚጸና ብዝኃነት ነው፣ በብዝኃነት የሚዋብ
አንድነት ነው፡፡ ብሔራዊነት ኢትዮጵያ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላብ እና ደም ድምር ጥረት የተገነባች፣ በድምር
ጥረቶቻቸው የምትበለጽግ ሀገር ናት ብሎ ማሰብ ነው፡፡
አርበኝነት
ሁሉም የአለም ሀገራት ህዝቦችን እና አገራቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ የማሸጋገር አላማን በማሳካት ከሚያደንቋቸው
ታላላቅ እሴቶች አንዱ አርበኝነት ስሜት ነው። አርበኝነት ኩራት፣ ታማኝነት እና የሀገር ፍቅር ስሜት እንዲሁም
ከሌሎች ሀገር ወዳድ ዜጎች ጋር የመተሳሰብ ስሜት ነው። አርበኝነት ከሀገር ፍቅር ስሜት የሚነሳ ለሀገር
ሉዓላዊነት ታማኝ መሆን እና የቡድን ታማኝነት ለአባሎቻቸው እና ለሚኖሩበት ምድር ባለው ታማኝነት ይገለጻል።
15
ክፍል ሁለት
2. የሰላም እሴት ግንባታ
2.1. የሰላም ፅንሰ- ሀሳብ
ሰላም የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ በተለያዩ አውዶች የሚታይ የተለያየ ትርጉም ያለው ነው። መሰረታዊ ትርጉሙ ሰላም
ማለት መረጋጋት፤ ጦርነት አለመኖር ፤ኃይል አለመጠቀም ወይም ግጭት አለመኖር ነው። ሆኖም ይህ ጽንሰ-
ሐሳብ ከጦርነት ወይም ከአካላዊ ግጭት አለመኖር በላይ የሚሄድ ነው።የሰላም ጽንሰ-ሐሳብ በሚከተሉት
መንገዶች ሊገለጽ ይችላል።
አሉታዊ ሰላም (Negative peace):-ይህ ቀጥተኛ ግጭት፣ጦርነት ወይም አካላዊ ግጭት አለመኖርን
ያመለክታል። ይህ በጣም ቀላል የሆነ የሰላም መልክ ነው፣ በዚህ ሁኔታ ውስጥ አንድም የኃይል ግጭት ወይም
ጦርነት አይኖርም፡፡ አሉታዊ ሰላም ሲኖር ሁሉ አማን የሆነ ሊመስል ይችላል ሆኖም ሁከቱን እንጅ የሁከቱን ስረ-
ምክንያት ስለማያስቀረው ወደ ፊት ሁከት የመነሳት እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
አዎንታዊ ሰላም (Positive peace): ይህ ከግጭት አለመኖር በላይ የሚሄድ ሲሆን ፍትህ፣ እኩልነት እና
ደህንነትን ያካትታል። አዎንታዊ ሰላም ማለት ሰዎች የሚያድጉበትንና የሚበለጽጉበትን ማህበረሰብ መፍጠር
ነው፡፡
2.2. የሰላም ግንባታ
የሰላም ግንባታ ጽንሰ-ሃሳብ በቀድሞው የተ.መ.ድ ዋና ጸሃፊ Boutros Boutros Ghali የተዋወቀ ሲሆን
ይህም የሰላም አጀንዳ (Agenda for Peace 1995) በሚለው ሪፖርት ላይ ተብራርቷል፡፡ ይህ ሪፖርት
የሰላም ግንባታ በርካታ ተግባራትን የሚያጠቃልል ሲሆን ትኩረቱም ሰላምን የሚያጠናክሩና አንድ ማህበረሰብ
መልሶ ወደ ግጭት እንዳይገባ የሚያደርጉ መዋቅሮችን መለየትና መደገፍን ይመለከታል፡፡
የሰላም ግንባታ በፖለቲካና ኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ የሚደረጉ ትግበራዎችን ከማሳለጥ በዘለለ የግጭት
መሰረታዊ መነሻዎችንና ሁኔታዎችን መፍታት ማስቻል ይኖርበታል፡፡ ይህም ቀጣይነት ያለውን ፕሮግራም
በመቅረጽ የአንድን ሃገር የፖለቲካና የደህንነት ሁኔታዎችን ሊያሸጋግሩ የሚችሉ ግለሰባዊ፣ ቤተሰባዊ፣
ማህበረሰባዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ባህላዊ ትስስሮችን የሚያሳድጉ እርምጃዎችን መውሰድ ያካትታል፡፡ ከዚህ
16
አንጻር የሰላም ግንባታ ዋነኛ ግብ ተብሎ የሚወሰደው ትስስሮችን መልሶ መገንባትና የጋራ ሃላፊነትንና ትብብርን
ማሳደግ ላይ ነው፡፡
በአጠቃላይ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ግብ አንድ ማህበረሰብ የግጭት መሰረታዊ መነሻዎችን ለመፍታት
ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ባለፈ በተቃራኒ ወገኖች መካከል የሚፈጠረውን ተለዋዋጭ የአመለካከት ኡደቶችንና
ትስስሮችን የሚቃኝበት አካሄድ ነው፡፡ የሰላም ግንባታ አብይ ስራ አዎንታዊ ሰላምን መፍጠር ሲሆን ይህም
የተረጋጋ ማህበራዊ አማካይ ላይ በመድረስ የሚፈጠሩ አዳዲስ ግጭቶች ወደ ሁከትና ጦርነት ደረጃ
የማያድጉበትን ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡
2.3. የሰላም ባህል
የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በሰላም ባህል ድንጋጌው መግቢያ ላይ
ጦርነት የሚጸነሰው በሰው ልጆች አዕምሮ ውስጥ እንደመሆኑ የመከላከል ስራ መሰራት ያለበትም የሰዎችን
ልጆች አዕምሮ በመለወጥ መሆን እንዳለበት አትቷል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድንጋጌ «የሰላም ባህል ቀጥሎ
የተዘረዘሩትን የሚያንጸባርቅና የሚያነሳሳ የእሴቶች፣ የአመለካከቶች፣ የባሕሪ ስልቶችና የሕይወት ዘይቤዎች
ስብስብ» መሆኑን ይገልጻል፡-
 ለሕይወትና ለሁሉም ሰብአዊ መብቶች አክብሮት መስጠት፤
 ሁከትን በሁሉም መንገድ መቃወም እንዲሁም ሁከትን በድርድርና በጥልቅ ውይይት ከስር መሰረቱ
የመፍታት ቁርጠኝነት መኖር ፤
 የአሁኑንና የወደፊቱን ትውልድ ፍላጎቶች በእኩል ለማሟላት በሚደረገው ሂደት ሙሉ ተሳትፎ የማድረግ
መስዋዕትነት፤
 የእኩል ተጠቃሚነት መብቶች እንዲኖር ማስቻል፤
 የሰዎችን ሀሳብ በነጻነት የመግለጽ፣ የማሰብና የመረጃ ነጻነት መብት እውቅና መስጠት
 ለነፃነት፣ ለፍትሕ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለመቻቻል፣ ለኅብረት፣ ለትብብር፣ ለብዙሃንና የባህል-ብዝሃነት፣
በአገራት፣ በብሔረሰቦች፣ በሃይማኖቶች፣ በባሕሎችና በሌሎች ቡድኖች እንዲሁም ግለሰቦች መካከል
ለሚደረግ የንግግርና የመረዳት መርሆዎች ቁርጠኛ መሆንን ያካትታል፡፡
2.4. የሰላም ግንባታ ስራዎች
 ግጭትን መከላከል፡- የግጭት መንስኤዎችን ወደ ሁከት ከማምራታቸው በፊት መለየትና መፍትሄ
መስጠትን ይጨምራል። አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የቅድመ ማስጠንቀቂያ
ሥርዓቶችን፣ ውይይት እና ሽምግልናን ያካትታል።
17
 ማስታረቅ፡- እርቅ ግጭት ዉስጥ የገቡ ግለሰቦች እና ቡድኖች በማስታረቅ ግንኙነቶችን የማደስ ሂደት ነው።
ብዙውን ጊዜ እውነት መናገርን ፣ይቅርታን እና መተማመንን እንደገና የመገንባት ጥረቶችን ያካትታል።
 ተቋማትን ማጠናከር፡- የሰላም ግንባታ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መቆጣጠር የሚችሉ፣ ፍትሃዊነትንና
ጸጥታን የሚያረጋግጡ ተቋማትን ማቋቋምና ማጠናከር ይጠይቃል። ይህም የሕግ መህቀፎችን ማሻሻል፣
አስተዳደርን ማሻሻል እና ውጤታማ የሕግ አስከባሪ ኤጀንሲዎችን መገንባትን ይጨምራል።
 የኢኮኖሚ ልማት፡- የኢኮኖሚ አለመረጋጋት እና ድህነት አብዛኛውን ጊዜ የግጭት መንስኤዎች ናቸው።
የሰላም ግንባታ ጥረቶች የኢኮኖሚ ልማትን ማጎልበት፣ የስራ እድል መፍጠር እና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን
ማረጋገጥ የገቢ ልዩነቶችን መቀነስ ይገኙበታል።
 ማህበራዊ ትስስር፡- ማህበራዊ ትስስርን መገንባት በማህበረሰቡ ውስጥ በተለያዩ ቡድኖች መካከል
የመተሳሰብ እና የመከባበር ስሜት መፍጠርን ያካትታል። ይህ ሁሉን አቀፍ ፖሊሲዎች፣ ባህላዊ ግንዛቤን
በማሳደግ እና የማህበረሰብ ውይይትን በማበረታታት ሊገኝ ይችላል።
 የማህበረሰብ ተሳትፎ፡- የሰላም ግንባታ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች በሰላም ሂደት ውስጥ ማሳተፍ
አስፈላጊ መሆኑን ያጎላል። ግለሰቦች እና ማህበረሰቦች በውሳኔ አሰጣጥ ላይ እንዲሳተፉ ማብቃት የሰላም
ግንባታ ጥረቶች ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይረዳል።
 ትምህርት እና ግንዛቤ፡- ትምህርት መቻቻልና ልዩነትን በማክበር እሴቶችን በማሳደግ በሰላም ግንባታ
ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ለግጭት አስተዋፅዖ የሚያደርጉ
አመለካከቶችንና ባህሪያትን ለመለወጥ ይረዳል።
 የሰብአዊ መብት ጥበቃ፡- የሰብአዊ መብቶች ጥበቃን ማረጋገጥ ለሰላም ግንባታ መሰረታዊ ነው። ይህም
የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፍታት፣ ፍትህን ማስፈን እና ሁሉም ግለሰቦች መብቶቻቸው እንዲከበርላቸዉ
ማድረግን ይጨምራል።
 የአካባቢ ጥበቃ፡- የአካባቢ መራቆት እና የሀብት እጥረት ወደ ግጭት ያመራል። የሰላም ግንባታ ጥረቶች
ብዙውን ጊዜ ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ልምዶችን ማሳደግ እና የተፈጥሮ ሀብትን ፍትሃዊ ተደራሽነት
ማረጋገጥን ያካትታሉ።
2.5. የወጣቶች የሚዲያ አጠቃቀም ለሰላም ግንባታ
2.5.1. ሚዲያ ለሰላም ግንባታ
ሚዲያ ሀገራዊ አንድነትን በማጎልበት ለአገር ግንባታ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በመንግሥትና በሕዝብ መካከል
እንደ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ነው። ሚዲያ በዜና ዘገባ፣ በምርመራ
18
ጋዜጠኝነት እና በህዝባዊ ክርክሮች ዜጎች ስለሀገራዊ ፖሊሲዎች፣ አስተዳደር ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ
ጉዳዮች መረጃ እንዲኖራቸው ይረዳል። ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ሰዎች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ
እንዲወስኑ እና በአገር ግንባታ ሂደቶች ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ ስለሚያስችል አስፈላጊነቱ የጎላ ነው።
በተጨማሪም ሚዲያ ህብረተሰቡን ስለመብቱና ግዴታው በማስተማር የዜጎችን ተሳትፎ በማሳደግ በአገር
ልማት፣ በማህበራዊ ፍትህ እና በመልካም አስተዳደር ላይ ገንቢ ውይይቶችን ያበረታታል። የተሳሳቱ መረጃዎችን
እና ፕሮፓጋንዳዎችን በመከላከል ኃላፊነት የሚሰማው ሚዲያ በማህበረሰቡ ውስጥ መከፋፈልን እና ግጭቶችን
ለመከላከል ይረዳል።
በኢትዮጵያ ያሉ ሚዲያዎች ለሀገር ግንባታ አወንታዊ አስተዋፅዖ ለማድረግ የሚያስችል አቅም ቢኖራቸውም
በርካታ ተግዳሮቶች ሚናቸዉን በአግባቡ እንዳይወጡ ያደርጋቸዋል፡፡አንዱና ትልቁ ፈተና ደካማ የመገናኛ ብዙሃን
የህግ ማህቀፍ እና ወጥነት የሌላቸው አፈፃፀሞችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግሮችን እና
የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመግታት ህጎች ቢኖሯትም የክትትል እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚሰሩ ስራዎች ግን
በቂ አይደሉም፡፡ሌላዉ ተግዳሮት በቂ የሆነ የሚዲያ አጠቃቀም እውቀት በማህበረሱቡ ዝንድ አለመኖሩ ነዉ፡፡
በዚህ ምክንያት ብዙ ዜጎች ለተሳሳተ መረጃ እና አሉታዊ ለሆኑ መረጃዎች ሲጋለጡ ይሥተዋላሉ፡፡
በኢትዮጵያ አንዳንድ ሚዲያዎች የፖለቲካ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦችን በማስፋፋት፤ የህብረተሰብ ክፍፍልን እና
የጎሳ ግጭቶችን በማባባስ የመለያየትና የግጭት መንስኤ ሆነዉ ቆይተዋል። በመገናኛ ብዙኃን የሚሰነዘሩ
የጥላቻ ንግግሮች እና ቅስቀሳዎች ሁከትና ብጥብጥ እንዲባባስ ሚና ተጫውተዋል፤ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው
ግለሰቦች እና አክቲቪስቶች በሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ቀስቃሽ ንግግሮችን ፤የተሳሳቱ
መረጃዎችን እና የውሸት ዜናዎችን በማሰራጨት አለመግባባቶች እና ግጭቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነዋል፡፡
ማሕበራዊ ሚዲያ ብዙ ጊዜ ተቃውሞዎችን፤አድማዎችን ለማደራጀት እና አንዳንዴም የአመጽ ድርጊቶችን
ለመቀስቀስ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል። እንደ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም እና ቲክ ቶክ ያሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች
የአመፅ ጥሪዎችን ለማሰራጨት በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ይህም አሉታዊ ትርክቶችን እና ጎጂ የሆኑ
መልዕክቶችን ስርጭት ለመከላከል አስቸጋሪ ያደርገዋል። እንዲሁም አንዳንድ ሚዲያዎች ታሪካዊ ቅሬታዎችን
በማባባስ፤ የከፋፋይ ትርክቶችን በማሰራጨት ግጭቶችን ይቀሰቅሳሉ፡፡ ከዚህም በላይ ስሜት ቀስቃሽ
ዘገባዎችን በማቅረብ እና ስዕላዊ ይዘትን በመጠቀም ሁከትን በማወደስ በህብረተሰቡ ላይ አሉታዊ የሆነ የስነ
ልቦና ተፅእኖ ያሳድራሉ፡፡
ሚዲያ በአገር ግንባታ ላይ ውጤታማ እንዲሆን በታማኝነት፣ በሙያዊ ብቃት እና በገለልተኝነት መንቀሳቀስ
ይኖርበታል። መገናኛ ብዙሀን በኃላፊነት ስሜት በመጠቀም ሰላምን፣ ልማትን እና የጋራ ሀገራዊ ራዕይን
ለማስፈን ጠንካራ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል።
19
2.5.2. የወጣቶች የሚዲያ አጠቃቀም
ወጣቶች በኢትዮጵያ ትልቁ የማህበረሰብ ክፍል እንደመሆናቸዉ መጠን ሚዲያን በሀላፊነት መጠቀም
አለባቸው። በዲጂታል ዘመን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ መስተጋብር መድረኮች ላይ በመሳተፍ
ንቁ ከሆኑ ተጠቃሚዎች መካከል አንዱ ናቸው።እንደ Facebook፣TikTok፣Instagram እና X (የቀድሞው
ትዊተር) ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ወጣቶች ሀሳባቸውን እንዲገልጹ፣አለምአቀፍ እና አካባቢያዊ
ክስተቶችን እንዲያውቁ እድል ይሰጣቸዋል፡፡
ወጣቶች በሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ ግድፈቶች ይስተዋላሉ፡፡ ስለሆነም ወጣቶች የሚዲያ አጠቃቀም
እዉቀታቸውን በማሳደግ ሚዲያን በጥበብ፤ በምክንያታዊነት በሚዛናዊነት እንዲሁም ለፈጠራ ስራዎች
መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡ በሚዲያ የሚሰራጩትን ዘገባዎች በጥንቃቄና በሀላፊነት ስሜት እንዲሁም
በሚዛናዊነትና በምክንያታዊነት መረጃዎችን በመለየት፣በመተንተን፣ በመጠቀምና በማሰራጨት ለሀገር ጥቅም
እንዲያውሉ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ መረጃ ከማጋራታቸው በፊት የመረጃ ምንጮችን በማጣራት የተሳሳቱ
መረጃዎችን መከላከል ይገባቸዋል፡፡ የሚዲያ ይዘትን በጥልቀት በመተንተን ትክክለኛ መረጃን ከፕሮፓጋንዳ
በመለየት ሁከትን የሚቀሰቅሱ የውሸት ትርክቶችን መከላከል ያስፈልጋል፡፡ወጣቶች የሚዲያ አጠቃቀምን
ግንዛቤ በማሳደግ በማህበረሰባቸው ውስጥ የተሳሳቱ መረጃዎች ስርጭትን መከላከል አለባቸዉ፡፡ወጣቶች
ሚዲያን ለአዎንታዊ እንቅስቃሴ፤ለሰላም፤ለልማት እና ለማህበራዊ ትስስር መሳሪያ አድርገው መጠቀም
አለባቸዉ፡፡ አንድነትን፤መቻቻልን እና ገንቢ ውይይትን የሚያበረታታ ይዘትን በመፍጠር እና በማሰራጨት የጥላቻ
ንግግር እና ከፋፋይ ትርክቶችን መከላከል ይኖርባቸዋል፡፡የወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ስነምግባርን
የተላበሰ መሆን አለበት፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ጎጂ ይዘቶችን ሪፖርት ማድረግ እና በጥላቻ
ንግግሮች ላይ ተሳትፎ ማድረግ የለባቸዉም፡፡
20
ክፍል ሦስት
3. የወጣቶች ሚና
3.1. በሀገረና ሀገረ-መንግስት ግንባታ ወጣቶች ያላቸው ሚና
ወጣቶች የእድገት፣ የፈጠራ እና የማህበራዊ ለውጥ አንቀሳቃሾች በመሆናቸው ለሀገርና ለሀገረ- መንግስት
ግንባታ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። አቅማቸው እና የፈጠራ ችሎታቸው ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለፖለቲካዊ መረጋጋት
እና ለማህበራዊ ትስስር አስተዋፅኦ ትልቅ ሚና አለው፡፡
ወጣቶች በየደረጃው ባለው የአስተዳደር እርከን በሚያደርጉት ተሳትፎ በዴሞክራሲ ግንባታ፣ በአመራር ልማት
፣ ተቋማትን በማጠናከር እና ተጠያቂነትን በማስፈን ለሀገርና ሀገረ-መንግስት ግንባታ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ
፡፡
21
ወጣቶች በኢኮኖሚ፣ በስራ ፈጠራ፣ በሰው ሃይል ምርታማነት እና በቴክኖሎጂ እድገት ላይ ያላቸው ተሳትፎ
ለሀገር ግንባታ መሰረት ይጥላል። ወጣቶች በማህበራዊ ልማት ፤ በሰላም ግንባታ፣ በበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ
አገልግሎት ፕሮግራም እና በባህል ጥበቃ እንዲሁም አገራዊ አንድነት እንዲፀና የሚያደርጉት አስተዋፅኦ
ትልቅ ነው
3.2. በሰላም እሴት ግንባታ ወጣቶች ያላቸው ሚና
የኢትዮጵያን ሁለንተናዊና ዘላቂ ሰላምና የሰላም ግንባታ ሥራ በአንድ አካል ወይም ተቋም ብቻ የሚሠራ ሳይሆን
ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍልና የሀገሪቱን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ባቀፈ መልኩ የሚከናወን
ነው። እንደዚሁም ዘላቂ ሰላምን የማረጋገጥ ሂደት በሁሉም መልኩ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ጠንካራ
ቁርኝትና ትስስር ያገናዘበና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። ሁለንተናዊና ዘላቂ ሠላምን የማስፈን ስራ እጅግ ከባድና
ጊዜና ትዕግስት የሚጠይቅ ሂደት ስለሆነ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት መወጣት
ይገባቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ወጣቶች ሠላምን ለመትከል/ለማስረጽ በትኩረት መስራትና ሚናቸውን መወጣት
ይጠበቅባቸዋል፡፡
 ወጣቶች በማህበረሰባቸው ዉስጥ በውይይት፣ ተግባቦት በመፍጠር እና በግጭት አፈታት አጋዥ ሆኖ
በማገልገል ለሰላም ግንባታ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
 በግጭት በተጎዱ ማህበረሰቦች ውስጥ ወጣቶች እንደ ድልድይ ሆነው የተለያዩ ቡድኖችን በግልፅ
ማወያየት፣ በሰላማዊ ንግግሮች ውስጥ በንቃት መሳተፍ፤ የተዛባ አመለካከቶችን ማረም ፣ መከፋፈልን
የሚያበረታቱ ትርክቶችን መቃወም ፣ መግባባትን እና እርቅን ማሳደግ ፣ በሰላም አብሮ የመኖር እና ተባብሮ
የማደግ ሁኔታዎች መፍጠር የወጣቶች ሚና ሊሆን ይገባል፡፡
 ወጣቶች ካላቸው ትልቅ ጥንካሬዎች ውስጥ ጉልበታቸው እና የፈጠራ አስተሳሰባቸው ለዘላቂ ሰላም
ግንባታ ወሳኝ ሚና አለው፡፡
 ወጣቶች ብዙውን ጊዜ ግጭቶችን በአዲስ የመፍትሄ ሀሳቦች ለመፍታት ዝግጁ ይሆናሉ፤ ወጣቶች
በማይበገር ጉልበታቸው ማህበረሰቡን ለሰላም ግንባታ ስራዎች በማነሳሳት፣ በዘመቻ ወይም በትምህርታዊ
ፕሮግራሞች፣ የአንድነት እና የትብብር መልእክቶች በማሰራጨት የበኩላቸውን ሚና ይወጣሉ፡፡
22
 ወጣቶች ዛሬ በፍጥነት እየተለዋወጠ ባለው ዓለም ማህበራዊ ትስስርን ለማጎልበት ዲጂታል ሚዲያን
በመጠቀም በማህበራዊ ሚዲያ የተሳሳቱ መረጃዎችን መቃወም፣ የሰላም መልዕክቶችን ማሰራጨት እና
ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ አይተኬ ሚና መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡
 ወጣቶች በአከባቢው ማህበረሰቦች ውስጥ በሰላም ግንባታ ፕሮግራሞች፤ በበጎ ፈቃደኝነት፣ የአንድነት
መልክቶችን የሚያጎለብቱ ጥበብን፣ ሙዚቃን፣ ቲያትርንና ተረትን በመጠቀም ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡
 ወጣቶች በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች እና በሰላም ግንባታ መርሃ ግብሮች ላይ በመሳተፍ የዘላቂ ሰላም ዋና
መሃንዲሶች መሆን ይገባቸዋል፡፡
ማጠቃለያ
ወጣቶች አንድ ሀገር ሊኖረው ከሚችለው ታላቅ ገፀ በረከቶች ውስጥ አንዱ ናቸዉ።ዛሬ ላይ ሆነው፤ ነገ የሚመሯትን
ሀገር በራሳቸው እጅ መገንባት የሚችሉ በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ልዩ ስፍራ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍል
ናቸው።ለሀገር ግንባታና ሰላም መስፈን የሚመነዘር ብርቱ ጉልበት ያላቸው፤ የእምቅ ሃይል ባለቤት በመሆናቸው አንዲት
ሀገር በምን ያህል ደረጃ ራሷን መተካትና ማስቀጠል ስለመቻሏ ጥሩ ማሳያ ናቸው፡፡
አገራችን ያስመዘገበቻቸው ለውጦች በዋነኛነት በወጣቶች ተሳትፎና መስዋዕትነት የመጡ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር
የለውም። በታሪክ ውስጥ ወጣቶች ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲ እና ለሀገራዊ እድገት በሚደረገው ትግል ግንባር ቀደም ሆነው
በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ውስጥ የጎላ ሚና ተጫውተዋል።
ሀገራዊ ለውጡ እንደሁሉም የሀገራችን የህብረተሰብ ክፍሎች ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደረጉ ትሩፋቶችን ያስገኘ ሲሆን
በተለየ መልኩም የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉና በትውልድ ውስጥ ያላቸውን ሚና በብቃት ለመወጣት
የሚችሉባቸውን እድሎች ይዞ መጥቷል።
ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በቂና የተቀራረበ አረዳድ በመያዝ እና በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮችና አጀንዳዎች ላይ
በስፋትና በሀላፊነት ስሜት በመሳተፍ ለተግባራዊነቱ ድርሻቸዉን በመወጣት ለሀገረ መንግስት እና ለሰላም ግንባታ ሂደት
አይተኬ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ የዚህ ዘመን ወጣቶች የሀገርና የሕዝብ ፍቅርን በመላበስ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን
ወደ እድል በመቀየር የበለፀገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ ይጠበቅበታል።
ወጣቶች ጉልበታቸውን እና የፈጠራ አስተሳሰባቸውን ለሀገር ልማት፣ለሰላም ግንባታ እና ለማህበራዊ እድገት ሊጠቀሙ
ይገባል፡፡ ከለውጥ ጋር መራመድ እና አዲስ የብልጽግና እድሎችን መፍጠርም ይኖርባቸዋል፡፡
ወጣቶች በአስተዳደርና ሰላም ግንባታ ውስጥ ከሚጫወቱት ሚና በተጨማሪ በስራ ፈጠራ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ
ማምጣት ይችላሉ። ወጣቶች ክህሎታቸውን በማዳበር በአምራችነት በተሰማሩ እንደ ግብርና፣ቴክኖሎጂ እና
ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በመሰማራት ለስራ እድል ፈጠራ እና ለሀገራዊ እራስን መቻል አስተዋፅኦ ማድረግ አለባቸዉ፡፡
23
በተጨማሪም የወጣቶች ሚና በማህበራዊ ትስስር እና ሀገራዊ አንድነት ላይ የሚጫወተው ሚና በቀላሉ የሚታለፍ
አይደለም። ወጣቶች የህብረተሰቡ የጀርባ አጥንት እንደመሆናቸው መጠን በተለያዩ ጎሳ፣ ሀይማኖታዊ እና ማህበራዊ
ቡድኖች መካከል ያለውን ልዩነት የማገናኘት ሃይል አላቸው። በተለያዩ ማህበረሰቦች መካከል ውይይት፣ መቻቻል እና
ሰላማዊ አብሮ መኖርን በማጎልበት ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡በጎ ፈቃደኝነት እና ማህበረሰብ ልማት ላይ በመሳተፍ
ወጣቶች ሀገራዊ መተባበርን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
የሀገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ በወጣቶቹ እጅ ላይ የወደቀ በመሆኑ ከሚመለከተዉ አካል ጋር በትኩረት በመስራት እና
እድል በመፍጠር የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በሀገርና ሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ የወጣቶች ሚና " አድስ አበበ

  • 1.
    1 ወጣቶች በሀገር እናበሀገረ-መንግስት ግንባታ ዉስጥ ያላቸዉ ሚና መሪ ቃል "ሀገሬን እገነባለሁ ሀላፊነቴንም እወጣለሁ" ሚያዚያ/2017 ዓ/ም አዲስአበባ
  • 2.
    2 ይዘት መግቢያ.............................................................................................................................................................4 ዓላማ................................................................................................................................................................5 የሚጠበቁ ውጤቶች............................................................................................................................................5 የወጣቶች ታሪካዊዳራ በኢትዮጵያ.........................................................................................................................6 ክፍል አንድ፡ ሀገር እና ሀገረ- መንግስት ግንባታ..........................................................................................................8 1.1. የሀገር (Nation) ፅንሰ-ሀሳብ...................................................................................................................8 1.2. የሀገረ-መንግስት (State) ፅንሰ-ሀሳብ........................................................................................................8 1.3. ሀገረ-መንግስት ግንባታ............................................................................................................................9 1.4. ሀገር-ግንባታ...........................................................................................................................................9 1.4.1. ዜግንነትና የመልካም ወጣት ዜጋ መገለጫዎች..................................................................................10 1.4.2 ብሄራዊ ትርክት ግንባታ...................................................................................................................12 1.4.3 ብሔራዊ መግባባት........................................................................................................................13 1.4.4 ብሄራዊነት ና አርበኝነት...................................................................................................................15  ብሄራዊነት........................................................................................................................................15  አርበኝነት..........................................................................................................................................15 ክፍል ሁለት..................................................................................................................................................16 2. የሰላም እሴት ግንባታ.................................................................................................................................16 2.1. የሰላም ፅንሰ- ሀሳብ...........................................................................................................................16 2.2. የሰላም ግንባታ..................................................................................................................................16 2.3. የሰላም ባህል........................................................................................................................................17 2.4. የሰላም ግንባታ ስራዎች..........................................................................................................................18 2.5. የወጣቶች የሚዲያ አጠቃቀም ለሰላም ግንባታ......................................................................................19
  • 3.
    3 2.5.1. ሚዲያ ለሰላምግንባታ...............................................................................................................19 2.5.2. የወጣቶች የሚዲያ አጠቃቀም.....................................................................................................21 ክፍል ሦስት.....................................................................................................................................................22 3. የወጣቶች ሚና..........................................................................................................................................22 3.1. በሀገረና ሀገረ-መንግስት ግንባታ ወጣቶች ያላቸው ሚና..........................................................................22 3.2. በሰላም እሴት ግንባታ ወጣቶች ያላቸው ሚና.........................................................................................23 ማጠቃለያ........................................................................................................................................................24
  • 4.
    4 መግቢያ የአንድን ሀገር ዘላቂሰላም እና እድገት ለማረጋገጥ የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት መሰረታዊ ነው፡፡ በኢትዮጵያ 70% ያህሉ ወጣቶች በመሆናቸው በሀገር እና ሀገረ-መንግስት ግንባታ እንዲሁም በሠላም እሴት ግንባታ ላይ ባላቸው ሚና በማህበረሰቡ ውስጥ ልዩ ስፍራ ይሰጣቸዋል፡፡ ወጣቶች የሚጠበቅባቸውን ሚና በአግባቡ ተረድተው ታሪካዊና የዜግነት ሃላፊነትን መወጣት እንዲችሉ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ሁኔታዎች ላይ ግልፅ ግንዛቤ ኖሯቸው እና የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ማድረግ ይጠበቃል፡፡ ሰነዱ ከሀገራችንን ወጣቶች ታሪካዊና አሁናዊ ሁኔታዎች በመነሳት ከወጣቱ የሚጠበቁ ሀገራዊ ሀላፊነቶችን በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ አንፃር ወጣቶች በሀገር ግንባታ፣ በሰላም ግንባታ፣ በብሄራዊነት ገዢ ትርክት ግንባታ እና በሚዲያ አጠቃቀም ላይ ስለሚኖራቸው ሚና በሰነዱ ውስጥ ተካቷል፡፡ በመሆኑም በሁሉም የወጣት አደረጃጀቶች ያሉ ወጣቶች በሰነዱ ላይ በጥልቀት እንዲወያዩና ተቀራራቢ የሆነ ግንዛቤና አመለካከት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ እንዲሁም ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ይህ የውይይት መነሻ ሰነድ ተዘጋጅቷል።
  • 5.
    5 ዓላማ የዚህ ሰነድ ዓላማወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩ መነሻ ሀሳቦችን በመስጠት ያላቸውን ግንዛቤ፣ ልምድና እውቀት በእርስ በርስ ውይይት በማዳበር ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የተቀራረበ አረዳድ ኖሯቸው የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ እና ፅኑ አቋም በመያዝ ከግል እስከ ሀገር ያለባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ማስቻል፤ የሚጠበቁ ውጤቶች በዚህ ሰነድ መነሻነት ከሚደረጉ ውይይቶች በኋላ የሚከተሉት ውጤቶች ይጠበቃሉ፡፡ I. በሀገርና ሀገረ- መንግስት እንዲሁም በሰላም እሴት ፅንሰ ሀሳቦች ላይ በቂ ግንዛቤ ያላቸው ወጣቶችን መፍጠር፤ II. ለሀገርና ሀገረ- መንግስት ግንባታ እንዲሁም ለሰላም እሴት ግንባታ ያላቸውን ሚና በመለየት ድርሻቸውን የሚወጡ ወጣቶችን መገንባት፤ III. ምክንያታዊ የሆነ የሚዲያ አጠቃቀም ስልትን በመከተል ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን የሚወጡ ወጣቶችን ማፍራትና ማብዛት፤ IV. የወጣቶች ተሳትፎን በማሳደግና መስተጋብር በመፍጠር ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር፤ V. ያደገ የወጣቶች ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ አበርክቶ እንዲሁም ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማሳደግ፤
  • 6.
    6 የወጣቶች ታሪካዊ ዳራበኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እንደ አንድ የአለም አካል በርካታ ከአለም ህዝቦች ጋር የሚያስማማት እና የሚያመሳስላት የአኗኗር ዘይቤ፣ የግንኙነት መሰረታውያን እና ባህሎች አሏት፡፡ ሆኖም ከሌሎች የአለም ክፍሎች ለየት ባለ መልኩ እኛ ኢትዮጵያውያን ብዝኃ -ባህል ፣ ቋንቋ፣ እምነትና ማንነት ያለን፤ ብዝኃ- መልክ፣ የኑሮ ዘይቤና አካባቢ ያለን፤ ብዝኃ - መሰረት፣ ስልጣኔ፣ ቅርስና ታሪክ ያለን፤ ሉዓላዊነታችንን ሳናስደፍር የኖርን፤ ለአፍሪካ ነፃነት ተምሳሌት የሆንን፤ ከባድ ፈተናዎችን በአሸናፊነት የተሻገርን፤ የሰው ዘር መገኛ ምድር፤ የዴሞክራሲ ስርዓት የጀመርን፤ አህጉራዊና አለምአቀፍ ተቋማትን የፈጠርን ፤ ልዩ ስነ-ህንፃ ያስተዋወቅን፤ ስነ-ጽሁፍ የፈጠርን፤ የአለም ረጅም ወንዝ መነሻና የአፍሪካ የውሀ ማማ የሆንን ፤ ልዩ የአዕዋፍና ብርቅዬ አራዊት ዝርያ መገኛ የሆንን፤ የእፅዋት እና የቡና መገኛ ባለቤት የሆንን፤ የተለየ መልከዓ-ምድርና የተስተካከለ አየር ንብረት የታደልን፤ ብዙ አይነት ማዕድናት ያለን፤ ሰፊና ለም መሬት ባለቤት የሆንን፤ ብዙ ቅርሶችና ፓርኮች ያሉን፤ እንግዳ ተቀባይና አክባሪ የሆንን፤ በችግር ጊዜ የምንተባበር፤ ግብረገብነት መገለጫችን የሆነ ህዝቦች ነን፡፡ በኢትዮጵያ በየዘመናቱ የነበሩ ወጣቶች ታሪክ በመስራትና የሀገራችንን አኩሪ ታሪክ በመጠበቅ እንዲሁም በማስቀጠል ሚናቸውን ሲወጡ ቆይተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ ወጣቶች በሰላም እና ሀገረመንግስት ግንባታ ላይ የበኩላቸውን ሚናሲያበረክቱ ቆይተዋል፡፡በ 1960 ዎቹ የነበረው "መሬት ለአራሹ!"/land for the tailer በሚል ትግል ውስጥ የወጣቶች ሚና ከፈተኛ ነበር፡፡ ይሄውም ሂደት ለንጉሳዊ ስርዓት ዉድቀት አነዱ ምክንያት ሆኗል፡፡ በደርግ መንግስት ስርዓት (1974-1991) የሶሻሊዝም ርዕዮት አለምን በገጠሩ ማህበረሰብ ዉስጥ ለማስረፅ ወጣቶች "እድገት በህብረት" በሚል ዘመቻ የልማት ሥራዎች ላይ በግንባር ቀደምትነት ሲሳተፉ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ስርዓቱ ለወጣቱ ትውልድ ምቹ ባለመሆኑ ምክንያት የወጣቱ ያላሰለሰ ትግል ለስርዓቱ ውድቀት ተጠቃሽ ምክያት ሆኗል፡፡ የመጀመሪያዉ የብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ በ 1994 ዓ.ም በወጣቶች፤ስፖርትና ባህል ሚኒስቴር ወጥቷል፡፡ ሚኒስቴሩ በፌዴራል ደረጃ የወጣቶች ጉዳዮችን የመከታተል፣ የመምራትና የማስተባበር ኃላፊነት አለዉ። በአገራዊ የወጣቶች ፖሊሲ መሰረትም ክልሎች ወጣቶችን በተመለከተ የመንግስትን አቅጣጫ ለማስፈፀምና ለማስተባበር የወጣቶች ቢሮዎችን አቋቁመዉ ወደ ስራ ገብተዉ ነበረ።
  • 7.
    7 ወጣቱ በዴሞክራሲያዊ አመለካከት፣ሙያዊ ብቃት፣ ክህሎትና ስነ-ምግባር የታነጸ ብቁ ዜጋ ሆኖ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው ውስጥ በብቃት እንዲሳተፍና ወጣቶች በሀገሪቱ እየተመዘገበ ካለው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ወሳኝ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚያስፈልግ የወጣቶች ፖሊሲው ያመለክታል። እንዲሁም ፖሊሲው ወጣት ኢትዮጵያውያን ጨቋኝ መንግስታት ለመጣል በተደረገዉ ትግል ውስጥ ያላቸውን ንቁ ሚና እውቅና ይሠጣል። በተለይም በ 1960 ዎቹ ወጣት ተማሪዎች ማህበረሰባቸውን በማስተባበር በሀገሪቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦችን ለማምጣት ያደረጉትን ሚና እውቅና በመስጠት የወጣቶች ሚና የጎላ መሆኑን ያስቀምጣል። በኢህአዴግ ስርዓት ውስጥም ፀረ ዴሞክራሲያዊነት እየገነገነ በመምጣቱ ስርዓቱ በሰላማዊና ህገ መንግስታዊ መንገዶች ሊለወጥ እንደማይችል ዜጎች ጠንካራ እምነት እንዲይዙ አድርጓቸዋል። በዚህ ሁኔታ የሀገራችንን ወጣቶች በየቦታው ለምሬትና ለአመጽ ዳርጓቸው የሀገራችንን ሰላምና ደኅንነት አደጋ ውስጥ በመውደቁ በመላ ሀገሪቱ እምቢተኝነት ተቀጣጥሎ በትግል ሂደቱም ወጣቶች ግንባር ቀደም ሆነው ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን በመወጣት ሀገራዊ ለውጡ እውን እንዲሆን አድርገዋል፡፡ የለዉጡ መንግስትም ባለፉት ስድስት አመታት የተለያዩ ፈተናዎችን በመቋቋም ሀገር ወደ ፊት የሚያስቀጥሉና ትዉልድን የሚገነቡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ተግባራትን ሲፈፅም ቆይቷል፤ እየፈፀመም ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የዘመናት ታሪክ ውስጥ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ከመሆኑም ባሻገር ሀገራችን ኢትዮጵያ በየወቅቱ የተጋረጠባትን ፈተና በድል እንዲትወጣ ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከትና ሀገር እንድትቀጥል በማስቻል ታሪካዊ ባለውለታዎች ሆነዋል፡፡
  • 8.
    8 ክፍል አንድ፡ ሀገርእና ሀገረ- መንግስት ግንባታ 1.1. የሀገር (Nation) ፅንሰ-ሀሳብ ሀገር የተለያዩ ብዛሃ-ማንነቶች በስነ ሕዝብ አወቃቀር እና በባህል የተሳሰሩ፣ ተቀራራቢ ማህበረሰባዊ ስሜት ያላቸው እና በፖለቲካዊ መንገድ እራሳቸውን በአንድ ስርዓተ-መንግስት የሚመሩ ቋሚ ህዝቦች የሚገኙበት፣ አለም አቀፍ እውቅና ያለው ድንበር እና ግዛት ያለው፣ የሚያስተዳደር መንግስት ያለው፣ ሉአላዊነቱ የተከበረ እና እውቅና ያለው መልካምድራዊ ወሰን ነው። ሀገር ማለት እንደ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ዘር፣ ባህል፣ ግዛት ካሉ የጋራ ባህሪያት ጥምር በጋራ ማንነት እና ዓላማዊ ትሥሥር ያላቸው ማህበረሰቦች የተገነባ ትልቅ የማህበራዊ ድርጅት አይነት ነው። 1.2. የሀገረ-መንግስት (State) ፅንሰ-ሀሳብ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ሀገረ-መንግስትን በተለያዩ መንገዶች ይተረጉሙታል። በጥቅሉ አረዳድ ሲታይ የአንድ ህዝብ ፖለቲካዊ አደረጃጀት ወይም በአንድ ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ የመንግስት ተቋማት ስብስብ ሀገረ-መንግስት ይባላል። በጥቅሉ “ሀገረ-መንግስት ማለት በመንግስት የሚመራ ቋሚ ህዝብ የሚኖርበት ድንበርና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለዉ ግዛት” መሆኑን ሁሉም የዘርፉ ምሁራን ይስማሙበታል። ግዛት፡- በአንድ ሀገረ-መንግስት ቁጥጥር ስር ወይም በሀገረ-መንግስቱ ሉዓላዊ የስልጣን ክልል ውስጥ የሚገኝ ጅኦግራፊያዊ ወሰን ማለት ነዉ። ሀገረ-መንግስት በበላይነት የሚቆጣጠረዉ ግልፅ ዓለም አቀፋዊ ወሰን ያለዉ ነው፡፡ ህዝብ፡- ሀገረ-መንግስቱ በሚቆጣጠረዉ ግዛት ውስጥ በሀገረ-መንገስቱ ሉዓላዊ ህግና ስርዓት የሚኖር ማህበረሰብ ማለት ነዉ። ህዝብ የሌለበት ግዛት ሀገረ-መንግስት ሊባል አይችልም። መንግስት፡- ሀገረ-መንግስቱን ወይም በሀገረ-መንግስቱ የግዛት ወስን ውስጥ የሚኖረዉን ህዝብ የሚመራ ስርዓት ወይም አካል ማለት ነዉ። በሌላ አባባል መንግስት በተወሰነ ግዛት ውስጥ የቁጥጥር ስርዓት ለማበጀት ህግን የማዉጣትና የመተግበር ሉዓላዊ ስልጣን ያለዉ አካል ወይም ቡድን ነዉ። ተቆጣጣሪ መንግስት የሌለዉ ግዛት ቋሚ ህዝብ ቢኖረዉም ሀገረ-መንግስት ሊባል አይችልም። ዓለም አቀፍ እዉቅና፡- አስቀድሞ እውቅና ያላቸው ሀገረ-መንግስታት አዲስ የተፈጠረዉ ሀገረ- መንግስት ሉዓላዊ መሆኑን በግልፅ መቀበል ማለት ነዉ። እዉቅና ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ ዓለም አቀፍ
  • 9.
    9 ህጎችን የማክበር፤ ግዴታዎችንየመፈፀምና በሉዓላዊነቱ ከሌሎች ሀገረ-መንግስታት እኩል በዓለም አቀፍ ጉዳዮች የመሳተፍ መብት ይኖረዋል። 1.3. ሀገረ-መንግስት ግንባታ መንግስት የተደራጀ ማህበረሰብን የሚያስተዳድር ስርዓት ወይም የሰዎች ስብስብ ነው። ሰፋ ባለ የአሶሲዬቲቭ ትርጉሙ፣ መንግስት በመደበኛነት ህግ አውጪ፣ አስፈፃሚ እና ተርጓሚን ያካትታል። መንግሥት ፖሊሲዎች የሚተገበሩበት ተቋም ፣ እንዲሁም ፖሊሲን የሚወስኑበት ዘዴ ነው። የሀገር መንግስት ግንባታ የረጅም ጊዜ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ልማትን ለመደገፍ አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን የመፍጠር እና የማጠናከር ሂደት ነው፡፡ ይህም የመንግስትን አገልግሎት የመስጠት፣ ህግ የማስከበር፣ ደህንነትን የማስጠበቅ እና ኢኮኖሚን የመምራት አቅም ማዳበርን ያካትታል። የሀገረ-መንግስት ግንባታ ማለት በሀገራዊ ወሰን ውስጥ የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል ህዝባዊ መዋቅር መመስረት፣ መልሶ ማቋቋም እና ማጠናከር ማለት ነው። 1.4. ሀገር-ግንባታ ሀገር-ግንባታ ማለት የተለያየ መነሻ፣ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት ያላቸው ህዝቦች በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ወሰን ውስጥ ተቀራራቢ መንፈስ፣ አንድነት፣ ትብብር እና የጋራ ራዕይ እና ማንነት እንዲኖራቸው የሚሰራ የረጅም ጊዜ ስራ ነው፡፡ ይህንንም እውን ለማድረግ በህዝቦች መካከል መቀራረብን፣ መተማመንን፣ የጋራ እሴቶችን፣ የጋራ ታሪክ፣ በመንፈስም በተግባርም የሚጋሯቸው የጋራ ህልሞችና ጥቅሞች እንዲኖሯቸው የማድረግና እና በህዝቦች መካከል ብሔራዊ መግባባትን የማዳበር ሂደት ነው፡፡ ሀገር ግንባታ የህዝቦች ጠንካራ ማህበራዊ ግንኙነቶች፣ በሀገራዊ ቅኝት የተቃኘ የትምህርት ስርዓት፣ ጠንካራ ተቋማት፣ ብዝሃነትን በሚያንፀባርቁ ሀገራዊ ፖሊሲዎች ውስጥ የሚሰራ የረጅም ጊዜ ፕሮጀክት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ሀገራችን ኢትዮጵያ ለረዥም ዘመናት መንግስት መስርታና ነጻነቷን ጠብቃ የኖረች ሀገር ስትሆን ባሳለፈችው ረዥም የታሪክ ወቅትም ህዝቦቿ የተለያዩ የውስጥ ችግሮቻቸውንና የውጭ ወራሪዎችን አብረው ተጋፍጠዋል፡፡ በዘመኗ ሁሉ የተለያዩ ባህል፣ ቋንቋና የኑሮ ዘይቤ ያላቸው ህዝቦች በጋብቻ፣ በንግድ፣ በእምነትና በተለያዩ ማኀበራዊ እሴቶች ውህደትና መስተጋብር ተሳስረው የሚኖሩባት ሀገር ናት፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ለዘመናት የተሳሰረውን አብሮነትና አኩሪ ታሪክ ወደተሳካ የሀገረ ግንባታ አልተሸጋገረም፡፡ ለዚህም አንዱ ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት ሀገሪቷን ያስተዳደሯት መሪዎች ሀገሪቷን ለመቅረጽ የሄዱበት መንገድ የሀገረ ግንባታ ጉዞ ከሀገረ መንግስቱ ግንባታ ጉዞ አንፃር ወደ ኋላ እንዲቀር አድርጐታል፡፡ ስለሆነም ተገቢ
  • 10.
    10 ለውጦችና ማሻሻያዎች ተደርገውበመንግስትና በህዝብ እንዲሁም በህዝቦች መካከል ትስስርና መተማመን ተፈጥሮ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ የጋራ ራዕይና ሀገራዊ አንድነት ሊኖር ይገባል፡፡ 1.4.1. ዜግነትና የመልካም ወጣት ዜጋ መገለጫዎች  ዜግነት ዜግነት ማለት የአንድ ማህበረሰብ አባልነት ስሜት እና ከእሱ ጋር የሚመጡ መብቶች እና ግዴታዎች መኖር ነው፡፡ አንድ ወጣት ዜጋ ሙሉ እና ህጋዊ የግዛት አባል ሲሆን መብቶቹን የሚቀበል እና የአባልነት ግዴታዎችን የሚወጣ ነው። ከዚህ አንፃር ዜግነት በዜጎች እና በመንግስት መካከል የመብትና ግዴታ ግንኙነት ነው። የዜጎች መብቶች የመንግስት ተግባራት እና የዜጎች ግዴታዎች የመንግስት መብቶች ናቸው፡፡  የዜጎች መብቶች የአንድ ዜጋ መብቶች በመንግስት እውቅና የተሰጣቸውን እና የሚተገበሩትን የይገባኛል ጥያቄዎች እና ልዩ መብቶችን ያመለክታሉ። ዜጎቹ በህብረተሰቡ ውስጥ ጠቃሚ፣ ንቁ እና ሚዛናዊ ህይወትን ለመኖር እነዚህን መብቶች መጠቀም ይኖርባቸዋል። እነዚህ መብቶች ዜጎች መልካም፣ ኃላፊነት የሚሰማቸው እና ውጤታማ የህብረተሰብ አባላት እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። በብዙ አገሮች ከተለመዱት የዜጎች መብቶች መካከል በሕይወት የመኖር፣ የንብረት ባለቤትነት መብት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት፣ ሐሳብ የመያዝ መብት፣ የመሰብሰብ ነፃነት፣ የመማር መብት፣ በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት፣ የመልማት መብት፣ ንፁህና ጤናማ አካባቢ … የማግኘት መብት፣ ወዘተ ይገኙበታል፤ ስለሆነም ወጣቶች መብታቸውን አውቀው መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡  የዜጎች ግዴታዎች አንድ ዜጋ እንደ አንድ ሀገር አባልነቱ ለሁሉም የሚጠቅም እና የህብረተሰቡን ደህንነት የሚያግዝ ባህሪ ማሳየት አለበት። መብትና ግዴታ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። በብዙ ሀገራት ከተለመዱት የዜጎች ተግባራት መካከል የሀገርን ሉዓላዊነትና ብሄራዊ ጥቅም ማስጠበቅ፣ ለሀገር ታማኝ መሆን፣ ለሀገር ህገ መንግስት ተገዢ መሆን፣ ሌሎች ህጎችን ማክበር፣ ብሄራዊ በጎ ፍቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት ላይ መሳተፍ፤ ለአዎንታዊ ሰላም አበርክቶ ማድረግ፤ ሚዛናዊ የሚዲያ አጠቃቀም ስርዓት መከተል እና የመሳሰሉ ይገኙበታል፡፡ ስለሆነም ወጣቶች መብቶቻቸውን በአግባቡ በመጠቀም እና ግዴታቸውን በመወጣት የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከት አለባቸው፡፡  የመልካም ዜጎች(ወጣቶች) መገለጫዎች መልካም ዜጎች(ወጣቶች) የሚከተሉትን መገለጫዎችን ያንፀባርቃሉ፡፡
  • 11.
    11  ታማኝነት እናእውነተኝነት፡- እምነት የሚጣልባቸው እና እውነትን የሚይዙ፤  ተጠያቂ፡- ለድርጊታቸው እና ለውሳኔዎቻቸው ሀላፊነት የሚወስዱ፡፡  የሀገር ፍቅር፡- ለአገር ጥቅም ተግባራዊ መስዋዕትነትን ማንፀባረቅ፤  ህግጋትን ማክበር እና ተገዢ መሆን፡ ለህግ የበላይነት መቆም፤  በበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት ውስጥ መሳተፍ፤  ምክንያታዊነት፤  ብዝሃነትን ማክበር፤  ለአገር ሉዓላዊነትና ብሄራዊ ጥቅም መቆም፤  ዓለም አቀፍ ዜግነትና እሴቶች የዓለማቀፋዊ ዜግነት ጽንሰ-ሐሳብ የሚመነጨው ሁሉም የሰው ልጆች የጋራ ምክንያቶች፣ ሁለንተናዊ ተፈጥሮ እና ተመሳሳይ ፍላጎቶች እንዳላቸው ከማመን ነው፡፡ ዓለም አቀፋዊ ዜግነት ሁላችንም የአንድ ዓለም ዜጎች መሆናችንን ማወቅ እና ለዓለማችን እና በዛ ላይ ላሉት ሰዎች ያለንን አክብሮት በሚያሳይ መንገድ መግለፅን ይጨምራል። አለም አቀፋዊ ዜጋ የሚከተሉትን እሴቶች እና አመለካከቶች የሚያሳይ ነው፡-  ርህራሄ፡- የሌሎችን ህዝቦች ስሜት መረዳት እና እራስን በሌሎች ህዝቦች ጫማ ውስጥ ማስገባት፤  ለማህበራዊ ፍትህ እና ፍትሃዊነት ቁርጠኝነት፡- የህዝቦች የኋላ ታሪክ ልዩነት ምንም ይሁን ምን ለፍትህ እና ለፍትሃዊነት መቆም፤  ልዩነትን ማክበር፡- ልዩነቶችን መቀበል እና የሌሎችን ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ሀይማኖቶች፣ እሴቶች፣ አስተያየቶች እና የመሳሰሉትን ማክበር፤  ለአካባቢ ጥበቃ እና ለዘላቂ ልማት ቁርጠኝነት፡- አካባቢን መጠበቅ እና የወደፊት ትውልዶችን እና የወደፊት ሁኔታዎችን ያገናዘበ ልማት ማረጋገጥ፤  ሰዎች ለውጥ ሊያመጡ እንደሚችሉ ማመን፡- በሰዎች ዋጋ እና ለማህበረሰቡ በሚያበረክቱት አስተዋፅዖ ማመንን ያካትታል፡፡
  • 12.
    12 1.4.2 ብሄራዊ ትርክትግንባታ ትርክት አንድ ማህብረሰብ ከራሱ ባህል፣ ወግ፣ ማንነት፣ የአኗኗር መስተጋብር ጋር ተያይዞ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገርለት እና ከሌላው ማህበረሰብ ጋር ለዘመናት በአብሮነት በጋራ የሚያኖረው ልዩ መለያው እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚሄድ አስተሳሳብ ነው፡፡ ነገር ግን ይኸው የአንድ ማህበረሰብ መለያ እና በሌላው አካል በበጎ ጎኑ የሚታወቀው ትርክቱ በተሳሳተ ምልከታ እና ፍረጃ ሲሸረሸር በሌላው ዘንድ በወንድማማችነት እና እህትማማችነት ሲታይ የነበረው ማንነቱ በሌሎች ዘንድ ለአሉታዊ አስተሳሰብ እና ምልከታ ሊዳረግ ይችላል፡፡ በዚሁ መሠረት ስለትርክት አስተሳሰብ የምንረዳው ጉዳይ ትርክት የአንድ ማህበረሰብ መገለጫ ከመሆኑም ባለፈ ከሌሎች በአካባቢ አብረው ከሚኖሩ የማህበረሰብ ወግ ወይም አኗኗር ዘይቤ ጋር የማይጣረስ፣ ይልቁንም በአብሮነት የሚያኖረው ሲሆን ከሌላው ማህበረሰብ ጋር እንደ ድርና ማግ የተጋመደ ነው፡፡ ይህም የአንዱ ማህበሰረሰብ የዕምነት አስተምሮ ሌላውን በማይጋፋ እና በሚያከብር ሁኔታ ከመካሄዱም ባለፈ የሌላውን አብሮት የሚኖረው ወይም የጎረቤቱ ሀዘንና ደስታን እንደራሱ አድርጎ በመውሰድ የመልካም እና የክፉ ጊዜ ደራሽ በሚያደርገው መስተጋብር እንዳይለያይ ተደርጎ የተጣመረ ነው፡፡ ገዥ ትርክታችን የሆነው ብሔራዊነት፣ አስተሣሣሪ ትናንቶች እና አስተሣሣሪ ነገዎቻችን የሚጸኑበት ትርክት ነው፡፡ ሕዝባችን ብዙ አስተሣሣሪ ትናንቶች አሉት፡፡ ዘመናት መጥተው ዘመናት ቢሄዱ የማይናወጠው ለሉዓላዊነት እና ለሀገራዊ ነጻነታችን ትልቅ ዋጋ የምንሰጥ ሕዝቦች ነን፣ ምንም እንኳን በየወቅቱ በውስጣዊ አንድነት ብንፈተንም ሀገራዊ ህልውናችንን ሊፈታትን የሚመጣን ጠላት አሳፍሮ የመመለስ አኩሪ ታሪክ አለን፡፡ በመሆኑም ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ በመንቀሳቀስ የነገይቱን የለማች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን በመገንባት ቀጣዩ ትውልድ በኩራት የሚኖርባት ታላቅ እና ገናና ሀገር እንድትኖረን ለማድረግ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአንድነት በትብብርና በጋራ የአመለካካትና የተግባር አንድነትን በማላቅ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ሁሉ ውጤታማ ሥራ በመስራት እና የላቀ ዉጤት በማስመዝገብ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ 1.4.3 ብሔራዊ መግባባት ብሔራዊ መግባባት ማለት ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የዴሞክራሲ መርህን መሰረት በማድረግ ምልዓተ ሕዝቡ በምክክርና በውይይት ምክንያታዊ የሆነ የጋራ መግባባትና መተማመን ላይ መድረስ ሲሆን ለተግባራዊነቱ የተሟላ የአስተሳሰብ ዝግጁነትን የሚያረጋግጥ የመግባባት ደረጃ ነው፡፡ በሃገር ግንባታ ሂደት ውስጥ መግባባት ከሚፈልጉ መሰረታዊ ጉዳዮች ውስጥ ሀገራዊ ማንነት፣ ሀገራዊ ጥቅም እና ሀገራዊ እሴቶች ዋነኞቹ ናቸው፡፡  ሀገራዊ ማንነት
  • 13.
    13 የአንድን ሀገር ህዝቦችስብስብ የሚያስተሳስር እና የዜጎችን የአንድ ሀገር እና ማህበረሰብ አካል እና አባል የመሆኑ መገለጫ የሚያጎለብት የጋራ ባህል፣ ታሪክ እና ህልም መፍጠር የሚችል ብሔራዊ ማንነት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ የበርካታ ብዛሃ ማንነቶች ባለቤት ፣ በጋራ ለረጅም ዘመናት የተጋሩ፣ አብሮ የመኖር እና ዘርፈ ብዙ ትስስር ፈጥረው እንዲኖሩ መሰረት የሆኗት የጋራ ማንነቶች አሏት፡፡ ሆኖም እነዚህ ማንነቶች በግልፅ ተለይተው የጋራ መግባባት አልተፈጠረባቸውም፡፡ ይልቁንም ልዩነታችን ላይ ያተኮሩ ትርክቶች እና አካሄዶች ጠንካራ ብሔራዊ አንድነት እንዳንገነባ ማነቆ ከመሆኑ በላይ ለሃገራዊ እድገታችንን ፈተና ሆኗል፡፡ በመሆኑም ብሔራዊ ማንነቶቻችን በአግባቡ መለየት እና ከሌሎች ማንነቶቻችን ጋር በማጣጣም ብሔራዊ መግባባት ማስፈን ያስፈልገናል፡፡  ሀገራዊ ጥቅም ብሄራዊ ጥቅም አንድ ሀገር ወደፊት ሊያራምደው እና ሊጠብቀው የሚፈልጋቸው፣ በውስጣዊ ኩነቶችም ይሁን በዓለም ዓቀፍ ግንኙነቶች ልታሳካ የምትፈልጋቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የጋራ ግቦች፣ እሴቶች፣ ሀብቶች እና ዓላማዎችን መሰረት ያደረገ ምክንያታዊ የሆነ እሳቤ ነው፡፡ ብሔራዊ ጥቅማችን መጠበቅ እና መከበር የምናረጋግጠው መደበኛ በሆነው የውጭ ግንኙነት ሂደታችን ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዜጋ የሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ውጭ በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች እና ድርጊቶች ሊያከብርና ሊያስከብራቸው ሲችል ነው፡፡ ተቋማዊ እና ግለሰባዊ ስራዎቻችን ከሀገራችን ጥቅም ጋር የሚኖራቸውን ተዛማጅነት እና ልዩነት በአግባቡ መረዳት እና መጠበቃቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ እንደ ዜጋ የምንሰማራባቸው የስራ መስኮች እና የምናደርጋቸው ግንኙነቶች ከሀገራችን ጥቅም አንፃር መቃኘት እና በአካልም በሀሳብም የገዘፈች ሀገር የመገንባት ሂደት ውስጥ ሚናችንን የመወጣት ሃላፊነት አለብን፡፡ አስተሳሰባችን እና ቁሳዊ ፍላጎታችን ከሃገራዊ ጥቅማችን ጋር የማይጋጭ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ በታሪካችን ሀገራዊ ጥቅሞች ትኩረት ካደረጉባቸው ጉዳዮች መካከል፡- የሀገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ፣ ሀገራዊና ቀጠናዊ ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ፣ የሀገሪቱን የግዛት አንድነት ማስጠበቅ ፣ ሀገራዊ ቅርሶችንና እሴቶች መጠበቅ እና የአፍሪካ ነፃነትና ፓን-አፍሪካዊነት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡  ሀገራዊ እሴቶች ብሔራዊ እሴቶች ሥነምግባራዊ/ሞራላዊ፣ ባህላዊ እና ማኅበራዊ ደንቦችን እንዲሁም የሀገሪቷን ብሔራዊ መለያ/መገለጫ ይመለከታል፡፡ የሃገራዊ እሴቶች ዋና ሚና ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ መረጋጋትን
  • 14.
    14 ማሳደግ፣ ተቋማዊ ውጤታማነትንማሻሻል፣ የዴሞክራሲ ሂደቶችን ማጠናከር እና ጠንካራ ብሄራዊ ማንነትን ማጎልበት ነው። ዜጎች የሚጋሯቸው፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስሩ፣ የጋራ ምናባዊ እንደሁም ተጨባጭ አንድነትን መፍጠር የሚችሉ የሀገር መገለጫ የሆኑ ብሔራዊ እሴቶች ሊኖሩ ይገባል፡፡ በትውልድ ቅብብሎሽ ዘመናትን የሚሻገሩ፣ የባህላችን፣ የባህሪያችን፣ የስነምግባራችን እና የግንኙነት መርሃችን ሊሆኑ የሚገቡ ሃገራዊ እሴቶችን መለየትና ማስጠበቅ ይጠበቅብናል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ እሴቶች ከሀገሪቱ ህገመንግስት እና ከማኅበረ-ባህላዊ ተቋማት የሚመነጩ ሲሆን እንደ ሰላማዊነት፣ ፍትሃዊነት፣ ሰብዓዊነት፣ አርበኝነት፣ መረዳዳት፣ ወ.ዘ.ተ ያሉትን በመለየት እና የጋራ መግባበት ላይ በመድረስ ሁሉም የሃገራችን ዜጎች እንዲጋሯቸው እና እንዲላበሷቸው መስራት ይኖርብናል፡፡ 1.4.4 ብሄራዊነት ና አርበኝነት ብሄራዊነት 'ብሔራዊነት' ማለት 'ሕገ-መንግስታዊነትን መሠረት ያደረገ ኀብረ-ብሔራዊ አንድነት' ማለት ነው፡፡ ብሄራዊነት አካታች ነው፤ በተናጠልና በወል ማንነቶችና መብቶች መካከል ያለውን ሚዛን በመጠበቅ በትብብር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ አንድነት መገንባት ነው፡፡ ብሔራዊነት በአንድነት የሚጸና ብዝኃነት ነው፣ በብዝኃነት የሚዋብ አንድነት ነው፡፡ ብሔራዊነት ኢትዮጵያ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላብ እና ደም ድምር ጥረት የተገነባች፣ በድምር ጥረቶቻቸው የምትበለጽግ ሀገር ናት ብሎ ማሰብ ነው፡፡ አርበኝነት ሁሉም የአለም ሀገራት ህዝቦችን እና አገራቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ የማሸጋገር አላማን በማሳካት ከሚያደንቋቸው ታላላቅ እሴቶች አንዱ አርበኝነት ስሜት ነው። አርበኝነት ኩራት፣ ታማኝነት እና የሀገር ፍቅር ስሜት እንዲሁም ከሌሎች ሀገር ወዳድ ዜጎች ጋር የመተሳሰብ ስሜት ነው። አርበኝነት ከሀገር ፍቅር ስሜት የሚነሳ ለሀገር ሉዓላዊነት ታማኝ መሆን እና የቡድን ታማኝነት ለአባሎቻቸው እና ለሚኖሩበት ምድር ባለው ታማኝነት ይገለጻል።
  • 15.
    15 ክፍል ሁለት 2. የሰላምእሴት ግንባታ 2.1. የሰላም ፅንሰ- ሀሳብ ሰላም የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ በተለያዩ አውዶች የሚታይ የተለያየ ትርጉም ያለው ነው። መሰረታዊ ትርጉሙ ሰላም ማለት መረጋጋት፤ ጦርነት አለመኖር ፤ኃይል አለመጠቀም ወይም ግጭት አለመኖር ነው። ሆኖም ይህ ጽንሰ- ሐሳብ ከጦርነት ወይም ከአካላዊ ግጭት አለመኖር በላይ የሚሄድ ነው።የሰላም ጽንሰ-ሐሳብ በሚከተሉት መንገዶች ሊገለጽ ይችላል። አሉታዊ ሰላም (Negative peace):-ይህ ቀጥተኛ ግጭት፣ጦርነት ወይም አካላዊ ግጭት አለመኖርን ያመለክታል። ይህ በጣም ቀላል የሆነ የሰላም መልክ ነው፣ በዚህ ሁኔታ ውስጥ አንድም የኃይል ግጭት ወይም ጦርነት አይኖርም፡፡ አሉታዊ ሰላም ሲኖር ሁሉ አማን የሆነ ሊመስል ይችላል ሆኖም ሁከቱን እንጅ የሁከቱን ስረ- ምክንያት ስለማያስቀረው ወደ ፊት ሁከት የመነሳት እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ አዎንታዊ ሰላም (Positive peace): ይህ ከግጭት አለመኖር በላይ የሚሄድ ሲሆን ፍትህ፣ እኩልነት እና ደህንነትን ያካትታል። አዎንታዊ ሰላም ማለት ሰዎች የሚያድጉበትንና የሚበለጽጉበትን ማህበረሰብ መፍጠር ነው፡፡ 2.2. የሰላም ግንባታ የሰላም ግንባታ ጽንሰ-ሃሳብ በቀድሞው የተ.መ.ድ ዋና ጸሃፊ Boutros Boutros Ghali የተዋወቀ ሲሆን ይህም የሰላም አጀንዳ (Agenda for Peace 1995) በሚለው ሪፖርት ላይ ተብራርቷል፡፡ ይህ ሪፖርት የሰላም ግንባታ በርካታ ተግባራትን የሚያጠቃልል ሲሆን ትኩረቱም ሰላምን የሚያጠናክሩና አንድ ማህበረሰብ መልሶ ወደ ግጭት እንዳይገባ የሚያደርጉ መዋቅሮችን መለየትና መደገፍን ይመለከታል፡፡ የሰላም ግንባታ በፖለቲካና ኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ የሚደረጉ ትግበራዎችን ከማሳለጥ በዘለለ የግጭት መሰረታዊ መነሻዎችንና ሁኔታዎችን መፍታት ማስቻል ይኖርበታል፡፡ ይህም ቀጣይነት ያለውን ፕሮግራም በመቅረጽ የአንድን ሃገር የፖለቲካና የደህንነት ሁኔታዎችን ሊያሸጋግሩ የሚችሉ ግለሰባዊ፣ ቤተሰባዊ፣ ማህበረሰባዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ባህላዊ ትስስሮችን የሚያሳድጉ እርምጃዎችን መውሰድ ያካትታል፡፡ ከዚህ
  • 16.
    16 አንጻር የሰላም ግንባታዋነኛ ግብ ተብሎ የሚወሰደው ትስስሮችን መልሶ መገንባትና የጋራ ሃላፊነትንና ትብብርን ማሳደግ ላይ ነው፡፡ በአጠቃላይ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ግብ አንድ ማህበረሰብ የግጭት መሰረታዊ መነሻዎችን ለመፍታት ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ባለፈ በተቃራኒ ወገኖች መካከል የሚፈጠረውን ተለዋዋጭ የአመለካከት ኡደቶችንና ትስስሮችን የሚቃኝበት አካሄድ ነው፡፡ የሰላም ግንባታ አብይ ስራ አዎንታዊ ሰላምን መፍጠር ሲሆን ይህም የተረጋጋ ማህበራዊ አማካይ ላይ በመድረስ የሚፈጠሩ አዳዲስ ግጭቶች ወደ ሁከትና ጦርነት ደረጃ የማያድጉበትን ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡ 2.3. የሰላም ባህል የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በሰላም ባህል ድንጋጌው መግቢያ ላይ ጦርነት የሚጸነሰው በሰው ልጆች አዕምሮ ውስጥ እንደመሆኑ የመከላከል ስራ መሰራት ያለበትም የሰዎችን ልጆች አዕምሮ በመለወጥ መሆን እንዳለበት አትቷል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድንጋጌ «የሰላም ባህል ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የሚያንጸባርቅና የሚያነሳሳ የእሴቶች፣ የአመለካከቶች፣ የባሕሪ ስልቶችና የሕይወት ዘይቤዎች ስብስብ» መሆኑን ይገልጻል፡-  ለሕይወትና ለሁሉም ሰብአዊ መብቶች አክብሮት መስጠት፤  ሁከትን በሁሉም መንገድ መቃወም እንዲሁም ሁከትን በድርድርና በጥልቅ ውይይት ከስር መሰረቱ የመፍታት ቁርጠኝነት መኖር ፤  የአሁኑንና የወደፊቱን ትውልድ ፍላጎቶች በእኩል ለማሟላት በሚደረገው ሂደት ሙሉ ተሳትፎ የማድረግ መስዋዕትነት፤  የእኩል ተጠቃሚነት መብቶች እንዲኖር ማስቻል፤  የሰዎችን ሀሳብ በነጻነት የመግለጽ፣ የማሰብና የመረጃ ነጻነት መብት እውቅና መስጠት  ለነፃነት፣ ለፍትሕ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለመቻቻል፣ ለኅብረት፣ ለትብብር፣ ለብዙሃንና የባህል-ብዝሃነት፣ በአገራት፣ በብሔረሰቦች፣ በሃይማኖቶች፣ በባሕሎችና በሌሎች ቡድኖች እንዲሁም ግለሰቦች መካከል ለሚደረግ የንግግርና የመረዳት መርሆዎች ቁርጠኛ መሆንን ያካትታል፡፡ 2.4. የሰላም ግንባታ ስራዎች  ግጭትን መከላከል፡- የግጭት መንስኤዎችን ወደ ሁከት ከማምራታቸው በፊት መለየትና መፍትሄ መስጠትን ይጨምራል። አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን፣ ውይይት እና ሽምግልናን ያካትታል።
  • 17.
    17  ማስታረቅ፡- እርቅግጭት ዉስጥ የገቡ ግለሰቦች እና ቡድኖች በማስታረቅ ግንኙነቶችን የማደስ ሂደት ነው። ብዙውን ጊዜ እውነት መናገርን ፣ይቅርታን እና መተማመንን እንደገና የመገንባት ጥረቶችን ያካትታል።  ተቋማትን ማጠናከር፡- የሰላም ግንባታ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መቆጣጠር የሚችሉ፣ ፍትሃዊነትንና ጸጥታን የሚያረጋግጡ ተቋማትን ማቋቋምና ማጠናከር ይጠይቃል። ይህም የሕግ መህቀፎችን ማሻሻል፣ አስተዳደርን ማሻሻል እና ውጤታማ የሕግ አስከባሪ ኤጀንሲዎችን መገንባትን ይጨምራል።  የኢኮኖሚ ልማት፡- የኢኮኖሚ አለመረጋጋት እና ድህነት አብዛኛውን ጊዜ የግጭት መንስኤዎች ናቸው። የሰላም ግንባታ ጥረቶች የኢኮኖሚ ልማትን ማጎልበት፣ የስራ እድል መፍጠር እና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን ማረጋገጥ የገቢ ልዩነቶችን መቀነስ ይገኙበታል።  ማህበራዊ ትስስር፡- ማህበራዊ ትስስርን መገንባት በማህበረሰቡ ውስጥ በተለያዩ ቡድኖች መካከል የመተሳሰብ እና የመከባበር ስሜት መፍጠርን ያካትታል። ይህ ሁሉን አቀፍ ፖሊሲዎች፣ ባህላዊ ግንዛቤን በማሳደግ እና የማህበረሰብ ውይይትን በማበረታታት ሊገኝ ይችላል።  የማህበረሰብ ተሳትፎ፡- የሰላም ግንባታ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች በሰላም ሂደት ውስጥ ማሳተፍ አስፈላጊ መሆኑን ያጎላል። ግለሰቦች እና ማህበረሰቦች በውሳኔ አሰጣጥ ላይ እንዲሳተፉ ማብቃት የሰላም ግንባታ ጥረቶች ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይረዳል።  ትምህርት እና ግንዛቤ፡- ትምህርት መቻቻልና ልዩነትን በማክበር እሴቶችን በማሳደግ በሰላም ግንባታ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ለግጭት አስተዋፅዖ የሚያደርጉ አመለካከቶችንና ባህሪያትን ለመለወጥ ይረዳል።  የሰብአዊ መብት ጥበቃ፡- የሰብአዊ መብቶች ጥበቃን ማረጋገጥ ለሰላም ግንባታ መሰረታዊ ነው። ይህም የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፍታት፣ ፍትህን ማስፈን እና ሁሉም ግለሰቦች መብቶቻቸው እንዲከበርላቸዉ ማድረግን ይጨምራል።  የአካባቢ ጥበቃ፡- የአካባቢ መራቆት እና የሀብት እጥረት ወደ ግጭት ያመራል። የሰላም ግንባታ ጥረቶች ብዙውን ጊዜ ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ልምዶችን ማሳደግ እና የተፈጥሮ ሀብትን ፍትሃዊ ተደራሽነት ማረጋገጥን ያካትታሉ። 2.5. የወጣቶች የሚዲያ አጠቃቀም ለሰላም ግንባታ 2.5.1. ሚዲያ ለሰላም ግንባታ ሚዲያ ሀገራዊ አንድነትን በማጎልበት ለአገር ግንባታ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በመንግሥትና በሕዝብ መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ነው። ሚዲያ በዜና ዘገባ፣ በምርመራ
  • 18.
    18 ጋዜጠኝነት እና በህዝባዊክርክሮች ዜጎች ስለሀገራዊ ፖሊሲዎች፣ አስተዳደር ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መረጃ እንዲኖራቸው ይረዳል። ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ሰዎች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲወስኑ እና በአገር ግንባታ ሂደቶች ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ ስለሚያስችል አስፈላጊነቱ የጎላ ነው። በተጨማሪም ሚዲያ ህብረተሰቡን ስለመብቱና ግዴታው በማስተማር የዜጎችን ተሳትፎ በማሳደግ በአገር ልማት፣ በማህበራዊ ፍትህ እና በመልካም አስተዳደር ላይ ገንቢ ውይይቶችን ያበረታታል። የተሳሳቱ መረጃዎችን እና ፕሮፓጋንዳዎችን በመከላከል ኃላፊነት የሚሰማው ሚዲያ በማህበረሰቡ ውስጥ መከፋፈልን እና ግጭቶችን ለመከላከል ይረዳል። በኢትዮጵያ ያሉ ሚዲያዎች ለሀገር ግንባታ አወንታዊ አስተዋፅዖ ለማድረግ የሚያስችል አቅም ቢኖራቸውም በርካታ ተግዳሮቶች ሚናቸዉን በአግባቡ እንዳይወጡ ያደርጋቸዋል፡፡አንዱና ትልቁ ፈተና ደካማ የመገናኛ ብዙሃን የህግ ማህቀፍ እና ወጥነት የሌላቸው አፈፃፀሞችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግሮችን እና የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመግታት ህጎች ቢኖሯትም የክትትል እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚሰሩ ስራዎች ግን በቂ አይደሉም፡፡ሌላዉ ተግዳሮት በቂ የሆነ የሚዲያ አጠቃቀም እውቀት በማህበረሱቡ ዝንድ አለመኖሩ ነዉ፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ዜጎች ለተሳሳተ መረጃ እና አሉታዊ ለሆኑ መረጃዎች ሲጋለጡ ይሥተዋላሉ፡፡ በኢትዮጵያ አንዳንድ ሚዲያዎች የፖለቲካ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦችን በማስፋፋት፤ የህብረተሰብ ክፍፍልን እና የጎሳ ግጭቶችን በማባባስ የመለያየትና የግጭት መንስኤ ሆነዉ ቆይተዋል። በመገናኛ ብዙኃን የሚሰነዘሩ የጥላቻ ንግግሮች እና ቅስቀሳዎች ሁከትና ብጥብጥ እንዲባባስ ሚና ተጫውተዋል፤ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች እና አክቲቪስቶች በሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ቀስቃሽ ንግግሮችን ፤የተሳሳቱ መረጃዎችን እና የውሸት ዜናዎችን በማሰራጨት አለመግባባቶች እና ግጭቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ማሕበራዊ ሚዲያ ብዙ ጊዜ ተቃውሞዎችን፤አድማዎችን ለማደራጀት እና አንዳንዴም የአመጽ ድርጊቶችን ለመቀስቀስ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል። እንደ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም እና ቲክ ቶክ ያሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች የአመፅ ጥሪዎችን ለማሰራጨት በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ይህም አሉታዊ ትርክቶችን እና ጎጂ የሆኑ መልዕክቶችን ስርጭት ለመከላከል አስቸጋሪ ያደርገዋል። እንዲሁም አንዳንድ ሚዲያዎች ታሪካዊ ቅሬታዎችን በማባባስ፤ የከፋፋይ ትርክቶችን በማሰራጨት ግጭቶችን ይቀሰቅሳሉ፡፡ ከዚህም በላይ ስሜት ቀስቃሽ ዘገባዎችን በማቅረብ እና ስዕላዊ ይዘትን በመጠቀም ሁከትን በማወደስ በህብረተሰቡ ላይ አሉታዊ የሆነ የስነ ልቦና ተፅእኖ ያሳድራሉ፡፡ ሚዲያ በአገር ግንባታ ላይ ውጤታማ እንዲሆን በታማኝነት፣ በሙያዊ ብቃት እና በገለልተኝነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል። መገናኛ ብዙሀን በኃላፊነት ስሜት በመጠቀም ሰላምን፣ ልማትን እና የጋራ ሀገራዊ ራዕይን ለማስፈን ጠንካራ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል።
  • 19.
    19 2.5.2. የወጣቶች የሚዲያአጠቃቀም ወጣቶች በኢትዮጵያ ትልቁ የማህበረሰብ ክፍል እንደመሆናቸዉ መጠን ሚዲያን በሀላፊነት መጠቀም አለባቸው። በዲጂታል ዘመን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ መስተጋብር መድረኮች ላይ በመሳተፍ ንቁ ከሆኑ ተጠቃሚዎች መካከል አንዱ ናቸው።እንደ Facebook፣TikTok፣Instagram እና X (የቀድሞው ትዊተር) ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ወጣቶች ሀሳባቸውን እንዲገልጹ፣አለምአቀፍ እና አካባቢያዊ ክስተቶችን እንዲያውቁ እድል ይሰጣቸዋል፡፡ ወጣቶች በሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ ግድፈቶች ይስተዋላሉ፡፡ ስለሆነም ወጣቶች የሚዲያ አጠቃቀም እዉቀታቸውን በማሳደግ ሚዲያን በጥበብ፤ በምክንያታዊነት በሚዛናዊነት እንዲሁም ለፈጠራ ስራዎች መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡ በሚዲያ የሚሰራጩትን ዘገባዎች በጥንቃቄና በሀላፊነት ስሜት እንዲሁም በሚዛናዊነትና በምክንያታዊነት መረጃዎችን በመለየት፣በመተንተን፣ በመጠቀምና በማሰራጨት ለሀገር ጥቅም እንዲያውሉ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ መረጃ ከማጋራታቸው በፊት የመረጃ ምንጮችን በማጣራት የተሳሳቱ መረጃዎችን መከላከል ይገባቸዋል፡፡ የሚዲያ ይዘትን በጥልቀት በመተንተን ትክክለኛ መረጃን ከፕሮፓጋንዳ በመለየት ሁከትን የሚቀሰቅሱ የውሸት ትርክቶችን መከላከል ያስፈልጋል፡፡ወጣቶች የሚዲያ አጠቃቀምን ግንዛቤ በማሳደግ በማህበረሰባቸው ውስጥ የተሳሳቱ መረጃዎች ስርጭትን መከላከል አለባቸዉ፡፡ወጣቶች ሚዲያን ለአዎንታዊ እንቅስቃሴ፤ለሰላም፤ለልማት እና ለማህበራዊ ትስስር መሳሪያ አድርገው መጠቀም አለባቸዉ፡፡ አንድነትን፤መቻቻልን እና ገንቢ ውይይትን የሚያበረታታ ይዘትን በመፍጠር እና በማሰራጨት የጥላቻ ንግግር እና ከፋፋይ ትርክቶችን መከላከል ይኖርባቸዋል፡፡የወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ስነምግባርን የተላበሰ መሆን አለበት፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ጎጂ ይዘቶችን ሪፖርት ማድረግ እና በጥላቻ ንግግሮች ላይ ተሳትፎ ማድረግ የለባቸዉም፡፡
  • 20.
    20 ክፍል ሦስት 3. የወጣቶችሚና 3.1. በሀገረና ሀገረ-መንግስት ግንባታ ወጣቶች ያላቸው ሚና ወጣቶች የእድገት፣ የፈጠራ እና የማህበራዊ ለውጥ አንቀሳቃሾች በመሆናቸው ለሀገርና ለሀገረ- መንግስት ግንባታ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። አቅማቸው እና የፈጠራ ችሎታቸው ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለፖለቲካዊ መረጋጋት እና ለማህበራዊ ትስስር አስተዋፅኦ ትልቅ ሚና አለው፡፡ ወጣቶች በየደረጃው ባለው የአስተዳደር እርከን በሚያደርጉት ተሳትፎ በዴሞክራሲ ግንባታ፣ በአመራር ልማት ፣ ተቋማትን በማጠናከር እና ተጠያቂነትን በማስፈን ለሀገርና ሀገረ-መንግስት ግንባታ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ ፡፡
  • 21.
    21 ወጣቶች በኢኮኖሚ፣ በስራፈጠራ፣ በሰው ሃይል ምርታማነት እና በቴክኖሎጂ እድገት ላይ ያላቸው ተሳትፎ ለሀገር ግንባታ መሰረት ይጥላል። ወጣቶች በማህበራዊ ልማት ፤ በሰላም ግንባታ፣ በበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም እና በባህል ጥበቃ እንዲሁም አገራዊ አንድነት እንዲፀና የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ትልቅ ነው 3.2. በሰላም እሴት ግንባታ ወጣቶች ያላቸው ሚና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊና ዘላቂ ሰላምና የሰላም ግንባታ ሥራ በአንድ አካል ወይም ተቋም ብቻ የሚሠራ ሳይሆን ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍልና የሀገሪቱን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ባቀፈ መልኩ የሚከናወን ነው። እንደዚሁም ዘላቂ ሰላምን የማረጋገጥ ሂደት በሁሉም መልኩ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ጠንካራ ቁርኝትና ትስስር ያገናዘበና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። ሁለንተናዊና ዘላቂ ሠላምን የማስፈን ስራ እጅግ ከባድና ጊዜና ትዕግስት የሚጠይቅ ሂደት ስለሆነ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት መወጣት ይገባቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ወጣቶች ሠላምን ለመትከል/ለማስረጽ በትኩረት መስራትና ሚናቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡  ወጣቶች በማህበረሰባቸው ዉስጥ በውይይት፣ ተግባቦት በመፍጠር እና በግጭት አፈታት አጋዥ ሆኖ በማገልገል ለሰላም ግንባታ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።  በግጭት በተጎዱ ማህበረሰቦች ውስጥ ወጣቶች እንደ ድልድይ ሆነው የተለያዩ ቡድኖችን በግልፅ ማወያየት፣ በሰላማዊ ንግግሮች ውስጥ በንቃት መሳተፍ፤ የተዛባ አመለካከቶችን ማረም ፣ መከፋፈልን የሚያበረታቱ ትርክቶችን መቃወም ፣ መግባባትን እና እርቅን ማሳደግ ፣ በሰላም አብሮ የመኖር እና ተባብሮ የማደግ ሁኔታዎች መፍጠር የወጣቶች ሚና ሊሆን ይገባል፡፡  ወጣቶች ካላቸው ትልቅ ጥንካሬዎች ውስጥ ጉልበታቸው እና የፈጠራ አስተሳሰባቸው ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ወሳኝ ሚና አለው፡፡  ወጣቶች ብዙውን ጊዜ ግጭቶችን በአዲስ የመፍትሄ ሀሳቦች ለመፍታት ዝግጁ ይሆናሉ፤ ወጣቶች በማይበገር ጉልበታቸው ማህበረሰቡን ለሰላም ግንባታ ስራዎች በማነሳሳት፣ በዘመቻ ወይም በትምህርታዊ ፕሮግራሞች፣ የአንድነት እና የትብብር መልእክቶች በማሰራጨት የበኩላቸውን ሚና ይወጣሉ፡፡
  • 22.
    22  ወጣቶች ዛሬበፍጥነት እየተለዋወጠ ባለው ዓለም ማህበራዊ ትስስርን ለማጎልበት ዲጂታል ሚዲያን በመጠቀም በማህበራዊ ሚዲያ የተሳሳቱ መረጃዎችን መቃወም፣ የሰላም መልዕክቶችን ማሰራጨት እና ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ አይተኬ ሚና መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡  ወጣቶች በአከባቢው ማህበረሰቦች ውስጥ በሰላም ግንባታ ፕሮግራሞች፤ በበጎ ፈቃደኝነት፣ የአንድነት መልክቶችን የሚያጎለብቱ ጥበብን፣ ሙዚቃን፣ ቲያትርንና ተረትን በመጠቀም ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡  ወጣቶች በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች እና በሰላም ግንባታ መርሃ ግብሮች ላይ በመሳተፍ የዘላቂ ሰላም ዋና መሃንዲሶች መሆን ይገባቸዋል፡፡ ማጠቃለያ ወጣቶች አንድ ሀገር ሊኖረው ከሚችለው ታላቅ ገፀ በረከቶች ውስጥ አንዱ ናቸዉ።ዛሬ ላይ ሆነው፤ ነገ የሚመሯትን ሀገር በራሳቸው እጅ መገንባት የሚችሉ በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ልዩ ስፍራ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍል ናቸው።ለሀገር ግንባታና ሰላም መስፈን የሚመነዘር ብርቱ ጉልበት ያላቸው፤ የእምቅ ሃይል ባለቤት በመሆናቸው አንዲት ሀገር በምን ያህል ደረጃ ራሷን መተካትና ማስቀጠል ስለመቻሏ ጥሩ ማሳያ ናቸው፡፡ አገራችን ያስመዘገበቻቸው ለውጦች በዋነኛነት በወጣቶች ተሳትፎና መስዋዕትነት የመጡ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። በታሪክ ውስጥ ወጣቶች ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲ እና ለሀገራዊ እድገት በሚደረገው ትግል ግንባር ቀደም ሆነው በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ውስጥ የጎላ ሚና ተጫውተዋል። ሀገራዊ ለውጡ እንደሁሉም የሀገራችን የህብረተሰብ ክፍሎች ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደረጉ ትሩፋቶችን ያስገኘ ሲሆን በተለየ መልኩም የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉና በትውልድ ውስጥ ያላቸውን ሚና በብቃት ለመወጣት የሚችሉባቸውን እድሎች ይዞ መጥቷል። ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በቂና የተቀራረበ አረዳድ በመያዝ እና በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮችና አጀንዳዎች ላይ በስፋትና በሀላፊነት ስሜት በመሳተፍ ለተግባራዊነቱ ድርሻቸዉን በመወጣት ለሀገረ መንግስት እና ለሰላም ግንባታ ሂደት አይተኬ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ የዚህ ዘመን ወጣቶች የሀገርና የሕዝብ ፍቅርን በመላበስ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር የበለፀገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ ይጠበቅበታል። ወጣቶች ጉልበታቸውን እና የፈጠራ አስተሳሰባቸውን ለሀገር ልማት፣ለሰላም ግንባታ እና ለማህበራዊ እድገት ሊጠቀሙ ይገባል፡፡ ከለውጥ ጋር መራመድ እና አዲስ የብልጽግና እድሎችን መፍጠርም ይኖርባቸዋል፡፡ ወጣቶች በአስተዳደርና ሰላም ግንባታ ውስጥ ከሚጫወቱት ሚና በተጨማሪ በስራ ፈጠራ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ። ወጣቶች ክህሎታቸውን በማዳበር በአምራችነት በተሰማሩ እንደ ግብርና፣ቴክኖሎጂ እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በመሰማራት ለስራ እድል ፈጠራ እና ለሀገራዊ እራስን መቻል አስተዋፅኦ ማድረግ አለባቸዉ፡፡
  • 23.
    23 በተጨማሪም የወጣቶች ሚናበማህበራዊ ትስስር እና ሀገራዊ አንድነት ላይ የሚጫወተው ሚና በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም። ወጣቶች የህብረተሰቡ የጀርባ አጥንት እንደመሆናቸው መጠን በተለያዩ ጎሳ፣ ሀይማኖታዊ እና ማህበራዊ ቡድኖች መካከል ያለውን ልዩነት የማገናኘት ሃይል አላቸው። በተለያዩ ማህበረሰቦች መካከል ውይይት፣ መቻቻል እና ሰላማዊ አብሮ መኖርን በማጎልበት ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡በጎ ፈቃደኝነት እና ማህበረሰብ ልማት ላይ በመሳተፍ ወጣቶች ሀገራዊ መተባበርን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ የሀገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ በወጣቶቹ እጅ ላይ የወደቀ በመሆኑ ከሚመለከተዉ አካል ጋር በትኩረት በመስራት እና እድል በመፍጠር የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡