SlideShare a Scribd company logo
1 of 36
Download to read offline
|ገጽ 1| ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008
የረቡዕ እትም
ቅፅ 21 ቁጥር 1631 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ | ጳጉሜን 6 ቀን 1987 ተመሠረተ |ዋጋ ብር 7.00
ታህሳስ 6 ቀን 2008
FREE PRESS FREE SPEECH FREE SPRIT | ነፃ ፕሬስ ነፃ ሐሳብ ነፃ መንፈስ
በኦሮሚያ ግጭት ሕይወት እየጠፋና ንብረት እየወደመ ነው
በውድነህ ዘነበ
ኅዳር 10 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ
አበባና በኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ
የጋራ ማስተር ፕላን ምክንያት
የተነሳው ግጭት፣ ለሕይወትና ለንብረት
መጥፋት ምክንያት ሆኗል:: ግጭቱንና
አለመግባባቱን ለማብረድ የኦሮሚያ ክልል
ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሕዝቡን በማወያየት
ሥራ ቢጠመዱም፣ ግጭቱ ግን ተባብሶ
በመቀጠል ሕይወት እየቀጠፈ ነው::
በተለይ በምዕራብ ወለጋ፣ በደቡብ
ምዕራብ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ በሚገኙ
ከተሞች ለአብነትም ወሊሶ፣ ቶሌ፣
አመያ፣ ጨሊያ፣ ግንደ በረት፣ ጪቱ፣
ጉሊሶ፣ እናንጎና ጌዶ በተባሉ አካባቢዎች
በተፈጠረው ግጭት ሕይወት እየጠፋና
ንብረትም እየወደመ ይገኛል::
የኦሮሚያ ክልል ማረጋገጫ ባይሰጥም
እስካሁን ከ30 በላይ ሕይወት መጥፋቱና
ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ይነገራል::
መንግሥት ግን የተጠቀሰውን አኃዝ
አይቀበልም:: ይልቁንም በተቃውሞው
የተሳተፉ አምስት ሰዎች መሞታቸውን
ገልጾ፣ በየአካባቢው የሚገኙ የመንግሥት
ተሿሚዎችና የፀጥታ ኃይሎች
መገደላቸውን እየገለጸ ነው:: በንብረት በኩል
በተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ መንግሥታዊ
ተቋማት፣ የተሿሚዎች መኖርያ ቤቶች፣
የግል ኩባንያዎች ላይ ጉዳት ደርሷል::
ይህ ግጭት ተባብሶ የቀጠለው በማስተር
ፕላኑ መነሻ ይሁን እንጂ ሲንከባለል በቆየ
ብሶትና የመልካም አስተዳደር ዕጦት፣
ባለሥልጣናት በአደባባይ በሚሰጡት
ያልተገባ መግለጫ ሕዝብ በመበሳጨቱ
መሆኑን፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ
(ኦፌኮ) አመራር አባል አቶ በቀለ ገርባ
ለሪፖርተር ገልጸዋል::
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የኦሮሚያ
ክልል ምንጮች እንደሚሉት፣ ኅብረተሰቡ
ለጥቃቅን አገልግሎቶች የሚጠየቀው
ሕገወጥ ጉቦና በክልሉ የተንሰራፋው
አድሎአዊ አሠራር የክልሉን ሕዝብ
ሲያበሳጭ ቆይቷል::
በርካታ አመራሮችም በተለይ በልዩ
ዞኑ በሕገወጥ መንገድ ቦታ ይዘዋል
የሚለው ሌላው ጉዳይ ሲሆን፣ ማስተር
ፕላኑ በእርግጥ ተግባራዊ ከሆነ በሕገወጥ
ያፈሩትን ሀብት ማጣት፣ ከዚህም ከባሰ
መጋለጥ የሚያመጣባቸው በመሆኑ
ሕዝቡንም ውስጥ ለውስጥ ሲያነሳሱ
ቆይተዋል የሚል ሐሳብ እየተሰነዘረ
ይገኛል::
ክልሉን የሚመራው የኦሕዴድ
አባላት ለዚህ ችግር ተገቢውን ትኩረት
ካለመስጠታቸውም ባሻገር፣ ሕዝቡ
መድረክ የሟቾች ቁጥር ከ30 በላይ ነው አለ
በነአምን አሸናፊ
ለአዲስ አበባና ለኦሮሚያ ልዩ ዞን
የተዘጋጀውን የተቀናጀ የጋራ ማስተር
ፕላን በመቃወም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ
ከተሞች በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት
የሟቾች ቁጥር ከ30 በላይ መድረሱን፣
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ
አንድነት መድረክ (መድረክ) አስታወቀ::
የመድረክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር በየነ
ጴጥሮስ፣ ምክትል ፕሬዚዳንትና የውጭ
ግንኙነት ኃላፊው ዶ/ር መረራ ጉዲናና
የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጥላሁን
እንደሻው ይህን ያስታወቁት፣ ማክሰኞ
ታኅሳስ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. በፓርቲው
ጽሕፈት ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ
ነው::
‹‹ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአዲስ
አበባ ከተማን ከሕግ አግባብ ውጪ
ማስፋፋት ጋር በተያያዘ በሕዝቡ ዘንድ
ካደረው ሥጋት በመነሳት፣ የተቀሰቀሰውን
ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞን በኃይል
ለማስቆም የኢሕአዴግ መንግሥት
በወሰደው ዕርምጃ በርካታ ተማሪዎችና
ሌሎች ዜጎች መገደላቸውን መድረክ
በእጅጉ ይኮንነዋል፤›› በማለት መድረክ
በመግለጫው አስታውቋል::
ወደ ገጽ 8 ዞሯል ወደ ገጽ 8 ዞሯል
በጭልጋና በመተማ
ወረዳዎች የተነሳው
ግጭት ሞትን
ጨምሮ ከፍተኛ
ጉዳት አደረሰ
በሰለሞን ጐሹ
ከኅዳር 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ
በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙት በጭልጋና
በመተማ ወረዳዎች በተቀሰቀሰው ግጭት
የሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ በአካልና
በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የአማራ
ክልል ገለጸ:: ግጭቱ በፈጠረው ሥጋት
ዜጎች ከአካባቢያቸው እየተፈናቀሉ
እንደሆነ ምንጮች ለሪፖርተር የገለጹ
ቢሆንም፣ የክልሉ መንግሥት ለጉዳዩ
የተሰጠው መፍትሔ አንፃራዊ ሰላም
አምጥቷል ብሏል::
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ
ንጉሡ ጥላሁን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣
ድብቅ አጀንዳ ያላቸው አካላት በፈጠሩት
ብጥብጥ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት
የደረሰ ሲሆን፣ የክልሉ መንግሥት
ኃላፊዎች ከወረዳዎቹ አመራሮች፣
ከአገር ሽማግሌዎችና ከኅብረተሰቡ ጋር
በመመካከር በአንፃራዊነት ሰላም ለመመለስ
ተችሏል::
ታኅሳስ 5 ቀን 2008 ዓ.ም.
ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የክልሉ
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
በበኩላቸው፣ በወረዳዎቹ ተከስቶ የነበረው
አለመረጋጋት በቁጥጥር ሥር መዋሉን
ገልጸው፣ በሕዝቡ መካከል ያለውን ሰላምና
መረጋጋት በማናጋት ግጭቱ እንዲባባስ
በሚያደርጉ ‹‹ፀረ ሰላም›› ኃይሎች ላይ
ሰማያዊ ፓርቲና ኤፌኮ ለፖለቲካ ትግል የጋራ ግብረ ኃይል ሊያቋቁሙ ነው
የመድረክ ምክትል ፕሬዚዳንትና የውጭ ግንኙነት ኃላፊው ዶ/ር መረራ ጉዲናና ፕሬዚዳንቱ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ
ፎቶበሪፖርተር/መስፍንሰሎሞን
ፀረ ሽብር ግብረ ኃይል በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት ደርሷል አለ የክልሉ መንግሥት ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ
ወደ ገጽ 8 ዞሯል
የክልሉ መንግሥት መነሻው የ‹‹ፀረ-
ሰላም›› ኃይሎች ሴራ ነው ብሏል
ነዋሪዎች የአማራና የቅማንት
ማኅበረሰቦች ግጭት ነው ብለውታል
ገጽ 2|
www.ethiopianreporter.com
| ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008
ቅፅ 21 ቁጥር 1631
		
በጳጉሜን 6 1987 ተጀመረ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተም አድራሻ፡- ከቦሌ መድኃኒዓለም ወደ ብራስ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ከቦሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል አጠገብ 	
	 						 ስልክ 0910-885206/ 011-661 61 79/85/87		 ፋክስ: 011-661 61 89
አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 03 የቤት ቁጥር
2347 ፖስታ 7023 አ.አ ኢትዮጵያ
ማስታወቂያ ሽያጭና ስርጭት
0910 885206/ 011 6 61 61 79/ 85
mcc@ethionet.et
E-mail: mccreporter@yahoo.com
Website: www.ethiopianreporter.com
በሚዲያና ኮምዩኒኬሽንስ ሴንተር (ኤም.ሲ.ሲ)
ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ
ፋክስ: 011-661 61 89
ዋና ግራፊክ ዲዛይነር፡	 ይበቃል ጌታሁን
ከፍተኛ ግራፊክ ዲዛይነር 	 ቴዎድሮስ ክብካብ
ግራፊክ ዲዛይነሮች፡ 	 ፀሐይ ታደሰ
	 ፋሲካ ባልቻ
	 ስሜነህ ሲሳይ
		 	 ነፃነት ያዕቆብ
	 ቤዛዬ ቴዎድሮስ
			 ሳሙኤል ለገሰ
ዋና ፎቶግራፈር 		 ናሆም ተሰፋዬ
ፎቶግራፈሮች፡ 		 ታምራት ጌታቸው
		 መስፍን ሰሎሞን
ካርቱኒስት፡ 		 ኤልያስ አረዳ
ከፍተኛ ሪፖርተር፡ 	 ደረጀ ጠገናው
ሪፖርተሮች፡ 	 ምሕረተሥላሴ መኮንን
		 ሻሂዳ ሁሴን
ማርኬቲንግ ማናጀር፡ 	 እንዳልካቸው ይማም
ሴልስ፡ 		 Hና Ó`T'w¡ S<K<Ñ@'
		 ብሩክ ቸርነት፣ ራህዋ ገ/ኪዳን
ማስታወቂያ ፕሩፍሪደር፡ መሳይ ሰይፉ፤
ኤፍሬም ገ/መስቀል፣ መላኩ ገድፍ
ኮምፒውተር ጽሑፍ፡ 	 ብርቱካን አባተ፣ ሄለን ይታየው፣
		 ቤተልሔም ታደሰ፣ ቤዛዊት መኮንን፣
		 መስከረም ሽብሩ፣ ሰብለ ተፈራ
ማስታወቂያ ፅሁፍ: 	 እስከዳር ደጀኔ፣ መሠረት ወንድሙ፣ 		
	 	 ራሔል ሻወል፣ የሺሀረግ ሀይሉ
ሕትመት ክትትል፡ 	 ተስፋዬ መንገሻ፣
	 የየሱስወርቅ ማሞ፣ ገዛኸኝ ማንደፍሮ
ዌብ ሳይት፡ 		 ቤዛዊት ተስፋዬ፣ ቢኒያም ሐይሉ
ዋና ሥራ አስኪያጅ፡ 	 አማረ አረጋዊ
ማኔጂንግ ኤዲተር፡ 	 መላኩ ደምሴ
ዋና አዘጋጅ፡ 	 ዘካሪያስ ስንታየሁ
የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁ. 217
ከፍተኛ አዘጋጆች፡ 	 ዳዊት ታዬ
		 ሔኖክ ያሬድ
		 ሰለሞን ጎሹ
አዘጋጆች፡ 	 ምሕረት ሞገስ
ረዳት አዘጋጆች፡ 	 ታደሰ ገ/ማርያም
	 ምሕረት አስቻለው
	 ታምሩ ጽጌ
	 የማነ ናግሽ
ዮሐንስ አንበርብር
		 ብርሃኑ ፈቃደ
	 ውድነህ ዘነበ
ማስታወቂያ
ርእሰ አንቀጽርእሰ አንቀጽ
ረቡዕ ታህሳስ 6 ቀን 2008
መንግሥት ውስጡን ይፈትሽ!
ለአዲስ አበባና ለኦሮሚያ ልዩ ዞን በተዘጋጀው የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን ምክንያት በኦሮሚያ
ክልል የተለያዩ ሥፍራዎች የታዩት አመፆች፣ መንግሥት ውስጡን አብጠርጥሮ እንዲፈትሽ ያስገድዳሉ::
መንግሥት ውስጡን በሚገባ እንዲፈትሽ የሚገደደው በክልሉ ውስጥ በተከሰተው ሁከት ምክንያት
የሚሰሙት ቁጣዎች፣ በአብዛኛው በመንግሥት ሹማምንት ላይ ያነጣጠሩ በመሆናቸው ነው:: መንግሥት
በቃል አቀባዩ አማካይነት እንደገለጸው፣ ሁከት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች በየደረጃው ያሉ ሹማምንትና
የፀጥታ ሠራተኞች የጥቃት ዒላማ ሆነዋል:: በችግሩ ዙሪያ ከሚነገሩ ዋነኛ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል
የመልካም አስተዳደር ዕጦት፣ የፍትሕ መጓደልና ሙስና ዋነኞቹ ናቸው:: እነዚህ መንግሥት ውስጡን
እንዲፈትሽ ያስገድዳሉ::
በግንቦት 2007 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ከአጋሮቹ ጋር መቶ በመቶ
የፓርላማ መቀመጫዎችን በመቆጣጠር፣ በምርጫው በሕዝብ ድምፅ ይሁንታ ማግኘቱን አረጋግጧል::
በዚህም መሠረት ቀጣዮቹን አምስት ዓመታት የሚመራ መንግሥት መሥርቷል:: ይሁንና አፍታም
ሳይቆይ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የፍትሕ ዕጦትና ሙስና ጊዜ የማይሰጡ ፈተናዎች እንደሆኑበት
አስታውቋል:: ወዲያው ደግሞ ለዓመታት ያህል ተንጠልጥሎ የቆየውና የሰው ሕይወት ያለፈበት የማስተር
ፕላን ጉዳይ ሌላ አመፅ ቀስቅሶ፣ ሕይወት እያለፈና ንብረት እየወደመ ነው:: በዚህ ወሳኝ ጊዜ ላይ ሆኖ
ነው መንግሥት ራሱን መፈተሽ ያለበት:: ከሕግ የበላይነት፣ ከሰብዓዊ መብት አጠባበቅና ከዴሞክራሲ
ያፈነገጡ አሠራሮችን ያርም::
የመንግሥት አካላት የሆኑት ሕግ አውጪው፣ ሕግ ተርጓሚውና አስፈጻሚው እንዴት እየተናበቡ
ነው ሥራቸውን እየሠሩ ያሉት? የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓቱ ምን ይመስላል? አስፈጻሚው አካል
ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅሩ እንዴት እየሠራ ነው? ሕግ ተርጓሚው በትክክል ሥራውን እየሠራ
ነው ወይ? ሕግ አውጪው (ፓርላማው) ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ወይ? በሕዝብና በእነዚህ አካላት
መካከል ያለው ቅርርብ ምን ይመስላል? የሚሉትና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ይነሳሉ:: አስፈጻሚው አካል
በተደጋጋሚ እንዳመነው የመልካም አስተዳደር ዕጦት ሕዝብን እያስመረረ ነው:: በደላላ የሚመራው
ሙስና አገር እያጠፋ ነው:: የፍትሕ መስተጓጎል ሕዝቡን ደም እንባ እያስለቀሰ ነው:: የእነዚህ ሁሉ
ድምር ውጤት በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት አበላሽቶታል:: መቶ በመቶ የፓርላማ
መቀመጫ የያዘ መንግሥት አሁን ወሳኝ የሆነ ምዕራፍ ላይ በመድረሱ ራሱን ይፈትሽ:: ያለምንም
ርህራሔ ራሱን ይገምግም::
በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ሁከት የዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ነው:: የአካል ጉዳት እያደረሰ
ነው:: የንብረት ውድመትም እየታየበት ነው:: ይህ አመፅ በማስተር ፕላኑ ጉዳይ ላይ ተመሥርቶ
ቢቀሰቀስም፣ አሁን አቅጣጫውን ቀይሯል:: አመፁን የሚመራ የተደራጀ ኃይል ወይም ፓርቲ በግልጽ
አለመኖሩም ታይቷል:: ለዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች ውጤትም ይመስላል:: በዚህም ምክንያት
ጥያቄው የሕዝብ ነው ማለት ነው:: ምንም እንኳን ሌላ ዓላማ የሰነቁ ኃይሎች በማኅበራዊ ሚዲያ መሪ
ሆነው ለመታየት እየሞከሩ ቢሆንም፣ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር ያለበት ከሕዝብ ጋር
ብቻ ነው:: ሕዝቡን እንወክላለን ከሚሉ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ካሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ነው::
በመሆኑም ከፓርቲዎቹም ሆነ ከሕዝቡ ጋር ሲነጋገር ውስጡን ፈትሾ መሆን አለበት:: ጠንካራ ግምገማ
ማድረግ ይኖርበታል::
መንግሥት ከሕዝብ ጋር ሲነጋገር ራሱን ለትችትና ለወቀሳ ያዘጋጅ:: የነበሩትን ድክመቶች በትክክል
አምኖ ሕዝቡ በግልጽ ምን እንደሚፈልግ ይረዳ:: በሕዝብ ድምፅ ተመርጫለሁ ያለ መንግሥት ከምንም
ነገር በላይ ተጠሪነቱ ለሕዝብ ነው:: በመልካም አስተዳደር ዕጦት፣ በፍትሕ መጓደልና በሙስና የተመረረ
ሕዝብ ጥቅሜንና ፍላጎቴን ይፃረራል በሚል ጉዳይ ላይ ተቃውሞ ሲያቀርብ፣ በሚገባ አዳምጦ ለመፍትሔ
የሚረዳ አቋም ላይ መድረስ አለበት:: ሕዝብን ሲያስመርሩ የነበሩ ሹማምንት ራሳቸውን ከተጠያቂነት ነፃ
ለማውጣት በሚያደርጉት ጥረት፣ ሕዝብና መንግሥት የበለጠ እንዳይቃቃሩና አላስፈላጊ መስዕዋትነት
እንዳይከፈል ጥንቃቄ ይደረግ:: በመብት ጥያቄ ስም የኃይል ተግባር ውስጥ የገቡ ወገኖችንም ሕዝቡ
እንዲያስቆማቸው ማድረግ የሚቻለው፣ ሕዝብና መንግሥት ሲቀራረቡ ነው::
አሁን የመንግሥት ዋነኛው ተግባር መሆን ያለበት ራሱን ፈትሾ ችግሮቹን ማወቅ ነው:: ችግሮቹ
ደግሞ በተደጋጋሚ የሚገለጹት ሕዝብን የሚያማርሩ አጉል ተግባራት ናቸው:: በኦሮሚያ ክልል ውስጥ
ለተነሳው ሁከት መነሻው ማስተር ፕላኑ ቢሆንም፣ ሕዝቡ በየደረጃው ባሉ ሹማምንት የደረሱበት የመብት
ረገጣዎች የራሳቸው አሉታዊ ሚና አላቸው:: መንግሥት ይህንን የሹማምንት ጉዳይ ያለምንም ይሉኝታ
ይገምግም:: አጥፊዎችን ለፍትሕ ያቅርብ:: በምትካቸው ለሕዝብ አገልጋይ የሆኑትን ይመድብ:: አሁን
የቃላት ጋጋታ ሳይሆን የሚያስፈልገው ተግባራዊ ዕርምጃ ብቻ ነው:: በሕዝብ የሚቀልዱ ተገምግመው
ይወገዱ::
መንግሥት ሁከቱ ከተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች ጋር በሰላማዊ መንገድ በመምከር መረጋጋት
ይፍጠር:: ሕዝቡ ወደ እርሻው፣ ንግዱና ወደ መሳሰሉት ተግባሮቹ በፍጥነት ይመለስ:: ተማሪዎች ወደ
ትምህርት ገበታቸው ይመለሱ:: መደበኛው ሰላማዊ ሕይወት ይቀጥል:: በዚህ ሒደት ውስጥ የሕግ
የበላይነት ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ ይሰጠው:: ዜጎች ከሰላማዊ የመብት ጥያቄ ይልቅ ወደ አመፅና
ሁከት የሚያመሩት የሕግ የበላይነት ሳይከበር ሲቀር ነው:: በሙስና የሚከብሩ ሹማምንትና አጋፋሪዎቸው
ሕግ ሲጥሱ፣ ሌላው ዜጋም ያንኑ መንገድ ይከተላል:: በመሆኑም ዜጎች በሕግ የበላይነት ተማምነው
የመብቶቻቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጉ:: በዚህ ረገድም መንግሥት ራሱን ያለ ይሉኝታ ይፈትሽ::
ሕዝብ በማናቸውም ባልተመቹት ጉዳዮች ላይ የመብት ጥያቄ የማቅረብ ሕገ መንግሥታዊ መብት
አለው:: መንግሥትም ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለበት:: በመንግሥት ውስጥ ሌላ መንግሥት የመሠረቱ
የሚመስሉ ኃይሎች መንግሥትን ሕዝባዊነት ሲያሳጡ፣ ሕዝብ ከመንግሥት ጋር ይለያያል:: በዚህ
ቀዳዳም ሌላ ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች በመግባት አጋጣሚውን ለግጭት ይጠቀሙበታል:: በዚህም
ምክንያት ሰላማዊው ድባብ ወደ ብጥብጥ ይቀየራል:: ይህ ደግሞ ታይቷል:: በመሆኑም መንግሥት ራሱን
ለወቀሳ ያዘጋጅ:: የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የመገናኛ ብዙኃንን፣ የሕዝቡንና የሌሎችን ትችቶች ይቀበል::
ችግሮቹን ያርም:: በተፈጠረው ችግር ላይ ግልጽ መረጃ ይስጥ:: ችግሮችን ማድበስበስ ይቁም:: አመፁ
ተባብሶ ሰላምና መረጋጋትን እንዳያሳጣና ለሌሎች ጣልቃ ገብነት እንዳይገለጥ መንግሥት ከሕዝብ ጋር
ይሠለፍ:: ሕዝብን ያዳምጥ:: ከኃይል ዕርምጃ ይቆጠብ:: የሕዝብን የልብ ትርታ ይስማ:: ውስጣዊውን
ችግር ፀረ ሰላም ኃይሎች ያራግቡታል ቢባል እንኳ፣ መንግሥት በድፍረት ራሱን ፈትሾ ለመፍትሔ
ይትጋ:: ከሕዝብ የሚፈለግበትን ይወጣ:: ለዚህም ውስጡን ደጋግሞ ይፈትሽ!
|ገጽ 3
www.ethiopianreporter.com
| ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008
ቅፅ 21 ቁጥር 1631
ማስታወቂያ
የቤት ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ጆሽዋ ሁለገብ ኃላፈነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር
ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ ቤት በጨረታ መግዛት ይፈልጋል
1.	 የቤቱ አይነት፡ እስከ 7 ፎቅ ግንባታ የሚፈቀድለት፣
2.	 የቦታው ስፋት፡ ቦታው ከ 400 ካሬ ያላነሰ ፣
3.	 የቦታው ሁኔታ፡ ለቢሮ አገልግሎት ሕንፃ መገንባት በሚመች ሁኔታ የሚገኝ፣
4.	 ቦታው የሚገኝበት ልዩ ስፍራ፡ ካዛንቺስ፣ ባንቢስ፣ ኦሎምፒያ፣ ሰንጋተራ፣ ሜክሲኮ፣
ጎተራ፣ አራት ኪሎ፣መገናኛ፣ ቦሌ፣ መስቀል ፍላወር፣ አካባቢ ሆኖ በዋና መንገድ
ላይ የሚገኝ ወይም ለመሃል ከተማ ቅርብ የሆነ፣
5.	 የቦታው ህጋዊነት፡ የይዞታ ባለቤትነት ካርታ ያለው፣ ለቅይጥ አገልግሎት ግንባታ
ፕላን ስምምነት ያለው የወቅቱን የመሬት ግብር የከፈለ፣
6.	 ቤቱ በባንክ/ በአበዳሪ ድርጅቶች በብድር የተያዘ ከሆነ ዝርዝር የውል ሰነድ እና ቀሪ
ክፍያውን የሚገልፅ ህጋዊ ሰነድ ማቅረብ የሚችል፣
7.	 ቤቱ የሊዝ ክፍያ ካለበት የሊዝ ውልና ቀሪ ክፍያ ሰነድ ማቅረብ የሚችል፣
8.	 የሚፈለግበትን የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡ፣ የፍርድ ቤት
ጥያቄ ክርክር የሌለበት፣ቤቱን በባለሞያ ስትራክቸራል እንዲሁም ቴክኒካላዊ ይዘቱ
ለማስመርመር ፈቃደኛ የሆኑ፣
9.	 መጫረት የሚችሉት የቤቱ ባለቤቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ይሆናሉ፣
10.	ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ባንቢስ
አካባቢ ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ በመምጣት
መውሰድ ይችላሉ፣
11.	የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ብር ሰላሳ ሺ ብር ብቻ)::
12.	ተጫራቾች የሚሸጡትን ቤት አይነት እና ዋጋ በዝርዝር በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ
ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት
በመስሪያ ቤቱ ለዚህ በተዘጋጀ ቦታ ማስገባት አለባቸው፣
13.	ጨረታው ማክሰኞ ታህሳስ25/2008 ዓ.ምቀን በ6፡00 ተዘግቶ በዚያው እለት ከቀኑ
8፡00 ሰዓት ጨረታውን በገባበት ቦታ ይከፍታል:: በዚህ ወቅት ተጫራቾች ውይም
ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ መገኘት ይችላሉ፣
14.	ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 0565/66/67/71/72፣ ወይም ከአብዬት
አደባባይ ወደ ኡራኤል በሚወስደው መንገድ ኖክ ፊት ለፊ ትዝቋላ ኮምፕሌክስ ላይ 2ኛ
ፎቅ በድርጅቱ ቢሮ በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል::
በዮሐንስ አንበርብር
በግንባታ ላይ ከሚገኙት የኤሌክትሪክ
ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ውጪ፣
በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
ውስጥ ለተያዙ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ
ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የፋይናንስ አቅርቦት
ችግር ማጋጠሙን የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች
ለፓርላማው አሳወቁ::
የፓርላማው የአካባቢና የተፈጥሮ ሀብት
ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ
ሚኒስቴርና የተጠሪ መሥሪያ ቤቶችን የ2008
ዓ.ም. የሥራ ዕቅድና የመጀመርያው ሩብ ዓመት
የሥራ አፈጻጸምን ሰኞ ታኅሳስ 4 ቀን 2008
ዓ.ም. በገመገመበት ወቅት ነው ይህ የተገለጸው::
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በበጀት ዓመቱ
በዕቅድ የያዛቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ
ፕሮጀክቶች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና
ፕሮጀክቶቹ ሊገጥሟቸው ለሚችሉ ችግሮች
ወይም ሥጋቶች ምን ያህል ዝግጅት እንደተደረገ
ማብራሪያ የጠየቀው ቋሚ ኮሚቴው፣ በዕቅድ
የተያዙት ፕሮጀክቶች በፋይናንስ እጥረት
ምክንያት እስካሁን ወደ ተግባር አለመግባታቸው
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና በሚኒስቴሩ
የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጓል::
ለዚህ በጀት ዓመት ወደ ተግባር እንዲገቡ
በዕቅድ የተያዙት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች
ጨሞጋ ይዳ 278 ሜጋ ዋት፣ ገባ 214 ሜጋ ዋት፣
ሐለሌ ወራቤሳ 422 ሜጋ ዋት፣ አይሻ የንፋስ
ኃይል ማመንጫ 300 ሜጋ ዋት የማመንጨት
አቅም ያላቸው ፕሮጀክቶች ናቸው::
እነዚህ ፕሮጀክቶች እንዴት ወደ ትግበራ
ሊገቡ እንደሚችሉ ለቀረበው ጥያቄ የኢትዮጵያ
ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር
አዜብ አስናቀ በሰጡት ምላሽ ከላይ ለተገለጹት
ፕሮጀክቶች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ከውኃ፣
ከፀሐይ፣ ከጂኦተርማልና ከንፋስ መገኘት የሚችሉ
የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎችን ከነቦታቸው
መለየታቸውን ገልጸው፣ ‹‹እንዴት እንገነባቸዋለን
የሚለው ጥያቄ አለ:: ምክንያቱ ደግሞ የፋይናንስ
እጥረት ነው፤›› ብለዋል::
በዚህ የተነሳም በዚህ ዓመት ተግባራዊ
መደረግ የሚገባቸውን ፕሮጀክቶች በመለየት፣
አብዛኞቹ በውጭ ኢንቨስትመንት እንዲገነቡ
መወሰናቸውን ገልጸዋል::
‹‹ይኼም ማለት የውጭ አልሚዎች
በዕቅድ ለተያዙ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የፋይናንስ
አቅርቦት ችግር ማጋጠሙ ለፓርላማው ተገለጸ
የአገር ውስጥ ባንኮችና የውጭ ኢንቨስተሮች በአማራጭነት ታይተዋል
ኢንጂነር አዜብ አስናቀ
በዮሐንስ አንበርብር
የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውኃና
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ዓርብና
ቅዳሜ በሱዳን ባደረጉት ስብሰባ ኢትዮጵያ በግብፅ
ለተነሱ ሥጋቶች ከሁለት ሳምንት በኋላ ምላሽ
ይዛ ለመቅረብ ተስማማች::
ሦስቱ አገሮች ላለፉ ዘጠኝ ስብሰባዎች በጋራ
የቴክኒክ ኮሚቴዎቻቸው አማካይነት ሲወያዩ
የቆዩ ቢሆንም፣ የታላቁን የኢትዮጵያ የህዳሴ
ግድብ እንዲያጠኑ በተመረጡ ሁለት ኩባንያዎች
መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመቅረፍ
ጊዜ ፈጅቶባቸዋል::
ይህ አሳስቦኛል የምትለው ግብፅ ቀጣዩ ስብሰባ
ከሦስቱም አገሮች በሚወከሉ ሁለት ሁለት
ሚኒስትሮች አማካይነት ፖለቲካዊ ውይይት
እንዲካሄድ በጠየቀችው መሠረት ነው ውይይቱ
የተካሄደው::
በግብፅ በኩል በዋናነት ከተነሱት አጀንዳዎች
መካከል የህዳሴው ግድብ ግንባታ ከውይይቱ
ጋር ሲነፃፀር በፍጥነት እየተከናወነ በመሆኑ፣
ውይይቱ መስመር እስኪይዝ ድረስ ግንባታው
እንዲቆም ጥያቄ አቅርባለች::
ኢትዮጵያ በግብፅ ሥጋቶች ላይ ምላሽ
ይዛ ለመቅረብ ተስማማች
ወደ ገጽ 34 ዞሯል
በውድነህ ዘነበ
ከንግድ ይልቅ ወደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ
እንዲያዘነብሉ ግፊት ሲደረግባቸው የቆዩ ባለሀብቶች፣
በአሁኑ ወቅት እየተገነቡ ባሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች
ውስጥ ቦታ የሚያገኙበትን መንገድ የሚያመቻች
ኮሚቴ ተቋቋመ::
ኮሚቴው በኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ
አብተው የሚመራ ሲሆን፣ ንግድ ሚኒስቴር፣
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣
ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በአባልነት ተካተዋል::
ታኅሳስ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ከኤምኤች አማካሪ
ድርጅት ዶ/ር መሰለ ኃይሌ ጋር መግለጫ የሰጡት
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና
ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ገመቹ፣ ኮሚቴው የአገር ውስጥ
ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ዞኖች ውስጥ ቦታ እንዲያገኙ
ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ገልጸዋል::
‹‹የአገር ውስጥ ባለሀብቶች እንደፍላጎታቸው
የፋብሪካ ሕንፃዎችን ተከራይተው፣ በለማ መሬት ላይ
የራሳቸውን ግንባታ እንዲያከናውኑ ለማድረግ የፓርኮቹ
ዲዛይን ተዘጋጅቷል፤›› ብለዋል::
መንግሥት በሁለተኛው የዕድገትና
ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን አሥር ኢንዱስትሪ
ፓርኮች ለመገንባት አቅዷል:: ከሚገነቡት ኢንዱስትሪ
ፓርኮች ውስጥ በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ቁጥር ሁለት
186 ሄክታር፣ ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ 275 ሄክታር
ይለማል::
በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት
ላሳዩ ነጋዴዎች ቦታ የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቋመ
ወደ ገጽ 34 ዞሯል
ወደ ገጽ 33 ዞሯል
ገጽ 4|
www.ethiopianreporter.com
| ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008
ቅፅ 21 ቁጥር 1631
ማስታወቂያ
|ገጽ 5
www.ethiopianreporter.com
| ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008
ቅፅ 21 ቁጥር 1631
ማስታወቂያ
OFFRE D’EMPLOI : ASSISTANT(E) ADMINISTRATIF(VE)
L’Alliance éthio-française d’Addis-Abeba recrute un(e) assistant(e)
administratif(ve)
Poste Ă  pourvoir immĂŠdiatement
Missions principales auprès du Directeur et de l’Administrateur :
ADMINISTRATIF :
•	 Rédaction de documents de différents types (rapports, notes, formulaires,
tableau Excel, lettres, …)
•	 Secrétariat (prise de contact, organisation de réunion, accueil, traduction,
…)
COMPTABILITÉ :
•	 Préparer et vérifier différents documents comptables (salaires, rapports
financiers mensuels, . . .)
•	 Saisie comptable.
Cette liste n’est pas exhaustive, l’employé(e) sera appelé(e) à accomplir
d’autres taches en fonction des besoins de l’AEF.
Profil recherchĂŠ :
Bon niveau, oral et Êcrit, en français, anglais et amharique.
Parfaite maitrise de la suite Microsoft Office (Word, Excel, power point)
Notions en comptabilitĂŠ
Connaissance de l’application Quick Book Accounting
QualitÊs souhaitÊes :
Rigueur/sens de l’organisation, dynamisme, qualité relationnelle, flexibilité,
disponibilitĂŠ le soir, capacitĂŠ Ă  travailler en autonomie et en ĂŠquipe.
Salaire : nĂŠgotiable
Depot de candidature
Les candidatures doivent ĂŞtre dĂŠposĂŠes impĂŠrativement avant le 6 janvier
2016 soit par mail (comptabilite@allianceaddis.org) soit à l’Administrateur en
personne. Toute candidature devra comprendre un curriculum vitae complet
accompagné d’une lettre de motivation.
Invitation of Qualified Firms for Audit Work
The Population Council Inc. is an international NGO working in three main areas: HIV and
AIDS, reproductive health and poverty, gender and youth.
The Population Council would like to invite qualified and registered audit firms those are
recognized by the Charities and Societies Agency to submit their proposals to be appointed
as external auditor to undertake the audit of its accounts.
Eligibility criteria:
Any authorized audit firm who qualify to apply shall therefore fulfill the following minimum
criteria for eligibility
1.	 Relevant experience for at least 4 years in the INGO sector
2.	 Renewed trade license of the current year
3.	 Who meets the qualification criteria by Charities and Societies Agency and currently
in the list
4.	 VAT and Tin registration certificate
5.	 Chartered/Certified Accountant Certificate (Certificate of professional competence)
6.	 Who can commit contractual obligation for the next 3 (three) fiscal periods.
Procedures:
Qualified candidate audit firm can submit in the following procedures
1.	 Submit financial and technical proposals separately in a sealed envelope to Population
Council-Ethiopia Office within 10 working days starting from the next date of bid
announcement as appeared in the news paper
2.	 Selection will be only based on the above criteria and who should submit competitive
price with clear mode of payment. Any government tax should be included in the
proposal
3.	 Only shortlisted candidates will be contacted for further discussion and negotiation
All Proposals should be submitted to: The Population Council Inc. Ethiopia Office from
December 17 – December 30, 2015 between 8:00am – 5:00pm from the following address:
		
The Population Council Inc.
		 Heritage Plaza Building 4th
floor
		 Near Brass Hospital, opposite the Tanzania Embassy on the Bole
Medhanealem Road
		 P.O. Box 25562 Code1000
Tel 0116631712/14/16
		 Addis Ababa
በዮሐንስ አንበርብር
በኢትዮጵያና በቱርክ መንግሥታት መካከል
የተፈረመውን ለኤምባሲ፣ ለሚሲዮን መሪዎችና
ለዲፕሎማቶች መኖሪያ ግንባታ የመሬት
ልውውጥ ስምምነት ለማፅደቅ የቀረበው አዋጅ
ፓርላማውን አነጋገረ::
የስምምነቱ ማፅደቂያ ረቂቅ አዋጅ አባሪ
እንደሚገልጸው ስምምነቱ የተፈረመው እ.ኤ.አ.
በዲሴምበር 2010 ነው:: የስምምነቱ ዓላማም
በኢትዮጵያና በቱርክ መካከል እያደገ የመጣውን
የንግድ፣ የቱሪዝም፣ የኢንቨስትመንት፣
የቱሪዝምና የተለያዩ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ
ትብብሮች የበለጠ ለማጠናከር ነው::
የስምምነቱ መሠረት የቱርክ መንግሥት
3,000 ካሬ ሜትር ከክፍያ ነፃ የሆነ መሬት በቱርክ
አንካራ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ
ማኅበረሰብ የተከለለ ቦታና ለሚሲዮን፣
ለአምባሳደር መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል
መሬት የመስጠት ግዴታን ያስቀምጣል::
በአፀፋው ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት
7,192.8 ካሬ ሜትር በአዲስ አበባ የሚገኝ
ለሚሲዮን፣ አምባሳደርና ዲፕሎማቶች መኖሪያ
ግንባታ የሚውል መሬት ለመስጠት ግዴታ
መግባቱን በስምምነቱ ላይ ተጠቅሷል::
የኢትዮጵያ መንግሥት ከሚያቀርበው
7,192.8 ካሬ ሜትር ውስጥ፣ 4,192.8 ካሬ
ሜትር የሚሆነው መሬት 3,200,000 ዶላር ሊዝ
የሚከፈልበት መሆኑ ስምምነት ተደርጓል::
የግንባታ ቦታው የሚሰጠው በሰጥቶ
መቀበል መርህ ሆኖ፣ ሁለቱም ወገኖች መሬቱን
የሚጠቁሙበት የዲፕሎማቲክ ተልዕኳቸውን
ለማሳካት ብቻ መሆኑን ስምምነቱ ይገልጻል::
እያንዳንዱ ወገን ፕሮጀክቱንና ግንባታውን
መቼ እንደሚጀምር በግሉ መወሰን እንደሚችል
በስምምነቱ የተገለጸ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ተፈጻሚ
በሚሆንበት ወቅት እያንዳንዱ ወገን መሬቱን
የሰጠውን አገር ሕግ ደንብና ቴክኒካዊ መሥፈርቶች
በኢትዮጵያና በቱርክ መካከል የተደረሰው ለዲፕሎማቶች
መኖሪያ የመሬት ልውውጥ ስምምነት ፓርላማውን አነጋገረ
በዳዊት ታዬ
በኢትዮጵያ የመንገድ ግንባታ ታሪክ ውስጥ
የመጀመሪያ ነው የተባለው የዲዛይንና የጥገና
ሥራውን አጠቃልሎ ለአንድ ኮንትራክተር
የሚያሰጥ አዲስ የግንባታ አሠራር፣ 256 ኪሎ
ሜትር ርዝመት ባለው የነቀምት-ቡሬ መንገድ
ላይ ተግባራዊ ሊደረግ ነው::
ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው የዲዛይን፣
የግንባታና የጥገና ሥራን አጠቃልሎ ለአንድ
ኮንትራክተር ለመስጠት የሚያስችለው የነቀምት-
ቡሬ መንገድ ፕሮጀክት ዓለም አቀፍ ጨረታ
ሒደትም በመጠናቀቅ ላይ ነው:: የባለሥልጣኑ
የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ
ሳምሶን ወንድሙ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣
ለዚህ መንገድ ግንባታ ተወዳዳሪ ኮንትራክተሮች
ያቀረቡት ዋጋና ሌሎች መወዳደሪያ መሥፈርቶች
እየተገመገሙ ናቸው:: በቅርቡም ውጤቱ ይፋ
ሆኖ ጨረታውን ከሚያሸንፉ ኮንትራክተሮች ጋር
ስምምነት ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል::
በአዲሱ አሠራር የነቀምት-ቡሬ መንገድን
ለመገንባት በወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ
ከስምንት በላይ የሚሆኑ የቻይና፣ የህንድ፣
የቱርክና የስፔን ኮንትራክተሮች ተፎካካሪ ሆነው
ቀርበዋል::
256 ኪሎ ሜትሩ የመንገድ ፕሮጀክት
ለሦስት ተከፍሎ ለሦስት ኮንትራክተሮች የሚሰጥ
መሆኑንም፣ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
የተገኘው መረጃ ያስረዳል:: የነቀምት-ቡሬ መንገድ
ግንባታ በዚህ ዓመት ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቅ
መሆኑም ይኼው ከባለሥልጣኑ የተገኘው መረጃ
ያመለክታል::
በአገሪቱ የመንገድ ግንባታ ልምድ አንድ
ኮንትራክተር ግንባታውን ብቻ እንዲያከናውን፣
ዲዛይኑ ደግሞ በሌላ አማካሪ ድርጅት እንዲከናወን
ይደረግ የነበረው ኮንትራት ለረጅም ጊዜ ሲሠራበት
ቆይቷል:: ቆየት ብሎም በአንዳንድ ፕሮጀክቶች
ላይ ደግሞ ዲዛይንና ግንባታውን በማጣመር
እንዲሠራ እየተደረገ እንደነበርም ይታወሳል::
የዲዛይንና የጥገና ሥራን በአንድ ያጠቃለለ አዲስ የግንባታ
አሠራር ተግባራዊ ሊሆን ነው
አዲሱ አሠራር ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ በሚፈጀው የነቀምት-ቡሬ መንገድ ላይ ይጀመራል
በብርሃኑ ፈቃደ
ዓመታዊው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት
(ተመድ) የሰብዓዊ ልማት ሪፖርትን ለመላው
ዓለም ከኢትዮጵያ ይፋ ለማድረግ በአፍሪካ
ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ለጋዜጠኞች በሰጡት
መግለጫ፣ አገሮች ርካሽ ጉልበትን እንደ መልካም
የኢንቨስትመንት ዕድል ሲያስተዋውቁ የጉልበት
ብዝበዛ እንዳይፈጸም መጠንቀቅ እንዳለባቸው
የፕሮግራሙ ኃላፊ አሳሰቡ::
በተመድ የልማት ፕሮግራም አድሚንስትሬተር
ሔለን ክላርክ በአዲስ አበባ ተገኝተው ከጠቅላይ
ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር በመሆን፣
እ.ኤ.አ. የ2015 የሰብዓዊ ልማት ሪፖርትን ይፋ
አድርገዋል:: ሪፖርቱን በ25ኛ ዓመቱ መባቻ
ላይ ‹‹ሥራ›› ላይ ያተኮረው የተመድ ልማት
ፕሮግራም፣ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች
የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በማለት ርካሽ
ጉልበትን መስህብ ሲያደርጉት ይታያል ብሏል::
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ደግሞ በወር
ከሃምሳ ዶላር ያልበለጠ ደመወዝ እየተከፈላቸው
የሚሠሩ ሠራተኞች ያሉባት አገር በመሆኗ፣
ለኢንቨስትመንት ምቹ ከሚያደርጓት መካከል
አንዱ እንደሆነ ይገልጻል::
በአንፃሩ የተመድ የሰብዓዊ ልማት ‹‹ሥራ
ለሰብዓዊ ልማት›› በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው
የተመድ ልማት
ፕሮግራም ኃላፊ
‹‹ርካሽ ጉልበት››
ብዝበዛ ማለት
አይደለም ሲሉ
አሳሰቡ
ወደ ገጽ 8 ዞሯልወደ ገጽ 8 ዞሯል
ወደ ገጽ 8 ዞሯል
ገጽ 6|
www.ethiopianreporter.com
| ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008
ቅፅ 21 ቁጥር 1631
ማስታወቂያ
|ገጽ 7
www.ethiopianreporter.com
| ረቡዕ | ኅዳር 29 ቀን 2008
ቅፅ 21 ቁጥር 1629
ማስታወቂያ
መሬት በላይ ማልማት የሚችል መሆኑን የገለጹት
አቶ ያረጋል፣ እስከ 2007 በጀት ዓመት መጨረሻ
ድረስ በከርሰ ምድር ውኃ ተጠቅመው በመስኖ
ማልማት የተቻለው ግን 1,700 ሔክታር ብቻ
እንደሆነ ጠቁመዋል::
በሰሜን ወሎ ዞን በሦስቱ ወረዳዎች መቆፈር
ከነበረባቸው 450 ጉድጓዶች ውስጥ ግንባታቸው
የተጠናቀቀው 82 ብቻ ናቸው:: ከእነዚህ ጉድጓዶች
ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ወደ አርሶ አደሮቹ
ማሳ ውኃ ሳይለቁ ተዘግተው ተቀምጠዋል:: መቆፈር
የነበረባቸውን ያህል ጉድጓዶች ያለመቆፈራቸውም
ፕሮጀክቱ ተይዞለት በነበረው ዕቅድ መሠረት
ያልተከናወነ ስለመሆኑም ያመላክታል::
እንደ ቆቦው ሁሉ በደቡባዊ ትግራይ ዞን
በተመሳሳይ መንገድ እንዲገነቡ በዕቅድ ተይዘው የነበሩ
ጉድጓዶች ያለመቆፈራቸውን፣ ከተቆፈሩት ውስጥም
ወደ ሥራ የገቡት የተወሰኑ መሆናቸው በአካባቢ
ለታየው ድርቅ መባባስ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል::
በደቡባዊ ትግራይ ዞን ተስፋ ከተጣለባቸውና
ግንባታቸው ከተጠናቀቁ 125 ጉድጓዶች ውስጥ 36ቱ
ብቻ ሥራ ላይ መዋላቸውንም የወረዳው ኃላፊዎች
ይገልጻሉ:: የጉድጉዶቹ ወደ ሥራ አለመግባት ደግሞ
በድርቅ ወቅት በቀላሉ አምርተው ድርቁን መቋቋም
እንዳላስቻላቸው ይናገራሉ::
የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ አያሌው እያሱ፣
‹‹እነዚህ ጉድጓዶች ቢለቀቁ ኖሮ ዘንድሮ ለድርቅ
ባልተጋለጥን ነበር፤›› በማለት ከፍተኛ ወጪ
የወጣባቸው ጉድጓዶች ያለ ሥራ መቀመጣቸው
ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል::
የትግራይ ደቡባዊ ዞን የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ
ገብረ እግዚአብሔር አረጋዊ እንደገለጹት ከሆነ ደግሞ፣
በራያ አላማጣ ወረዳ ከተገነቡት 84 ጉድጓዶች ሥራ
ላይ የዋሉት 46 ናቸው:: ከእነዚህ ውስጥ ቀድሞ
በራያና አዘቦ ደግሞ ከተገነቡት 125 ጉድጓዶች
ውስጥ ሥራ የጀመሩት 35 ብቻ መሆናቸውንም
አስታውሰዋል:: 90 የሚሆኑ ጉድጓዶችም ከጥቅም
ውጪ ሆነዋል:: ጉድጓድ ተቀፍሮ ውኃው ወደ
ማሳቸው የገባላቸውና በመስኖ የሚጠቀሙ አርሶ
አደሮች ወቅታዊውን ድርቅ መቋቋም ሲችሉ፣
በቅርብ ርቀት የተቆፈሩት ጉድጓዶች ተዘግተው
የተቀመጡባቸው አርሶ አደሮች ደግሞ ማምረት
ባለመቻላቸው እጃቸውን ለዕርዳታ ዘርግተዋል::
እንደተዘነጋ የሚቆጠረው ይህ ፕሮጀክት በ2007
ዓ.ም. ከተከሰተው ድርቅ ጋር ተያይዞ ትኩረት
የተሰጠው ቢመስልም፣ አሁንም ጉድጓዶችን ከፍቶ
ወደ ማሳ ውኃ እንዲያሰራጩ የተደረጉት ጥቂቶች ብቻ
ናቸው::
ሙሉ ለሙሉ ግንባታቸው ባይጠናቀቅም በሰሜን
ወሎ ዞን አዲስ ቀኝ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ የጉድጓድ
ውኃን ወደ ማሳ በመልቀቅ ወደ 200 የሚጠጉ የአርሶ
አደሮች ማሳ ውስጥ እንዲገባ መደረግ ተጀምሯል::
እንዲህ ማድረግ ከተቻለ ሌሎቹንም ጉድጓዶች
ሥራ አስጀምሮ ድርቁን መከላከል ይቻል እንደነበር
የተመለከቱ አርሶ አደሮች በሁኔታው ማዘናቸውን
ገልጸዋል::
በአዲስ ቀኝ ቀበሌ የጉድጓድ ውኃው እንዲሳብ
የተደረገው ጄኔሬተር ተገጥሞ ሲሆን፣ ከዚህ ጉድጓድም
በሰከንድ 70 ሊትር ውኃ በማመንጨት ወደ ማሳዎቹ
ሲገባ በጉድጓዱ ዙሪያ ማሳ ያላቸው ገበሬዎችን ተስፋ
አለምልሟል::
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስቸኳይ
ውሳኔ ጄኔሬተር እንዲገባና አገልግሎት ሳይሰጥ
የቆየውን የጉድጓድ ውኃ ሥራ ለማስጀመር ቢቻልም፣
በአካባቢው ካለው ፍላጎት አንፃር ዕርምጃው እዚህ ግባ
የማይባል መሆኑን የሚናገሩ አሉ::
አቶ ያረጋል እንዳሉት ግን ተጨማሪ አራት
ጉድጓዶችን ሥራ ለማስጀመር የአራት ጄኔሬተሮች
ግዥ በመፈጸሙ በአካባቢው በድርቁ የተከሰተውን
ችግር እንዲህ ባለው የመስኖ ሥራ ለመታደግ ጥረት
እየተደረገ ነው:: ከእነዚህ ጉድጓዶችም በሁለትና በሦስት
ወራት ውስጥ እስከ 4,500 ሔክታር ለማልማት ዕቅድ
መያዙንም ገልጸዋል:: ይሁን እንጂ እስካሁን በጉድጓዶቹ
ውኃ ተጠቅመው እያለሙ ያሉ አርሶ አደሮች ከፍተኛ
ጠቀሜታ እያገኙ መሆኑን የተመለከቱ የአጎራባች ቀበሌ
አርሶ አደሮች፣ እነሱም ጉድጓዶቻቸው ተከፍተው እንደ
ጎረቤቶቻቸው ማልማት የሚሹ መሆኑን በመግለጽ
አቤቱታቸው ምላሽ እንዲያገኝ እየተማፀኑ ነው::
በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በጎረቤት ቀበሌ አምናና ዘንድሮ
የተከፈቱት ጉድጓዶች የሚለቁትን ውኃ በመጠቀም
በመስኖ ያለሙት አርሶ አደሮች፣ በዓመት ሦስት
ጊዜ እያመረቱ በመሆናቸው ይህ ዕድል ‹‹ለሁላችንም
መድረስ አለበት፤›› ይላሉ::
‹‹እኛ የዘራነው እህል ፍሬ አልባ ሲሆን፣ እነሱ
ድርቁ አልዳበሳቸውም:: ነገር ግን ከከርሰ ምድር ውኃ
በማውጣት ለመስኖ ሊውሉ ይችላሉ የተባሉ ጉድጓዶች
ተዘግተው እኛ የበይ ተመልካች ሆነናል፤›› በማለት
የጉድጓዶቹ አለመከፈት እንዳሳዘናቸው አንድ አርሶ አደር
ወደ ገጽ 22 ዞሯል
ሪፖርተር፡- የመረጃ ነፃነት ሕጉ ኅዳር 15 ቀን
2001 ዓ.ም. ከወጣ በኋላ ባሉት ዓመታት ምን ዓይነት
ለውጦች ታይተዋል?
ዶ/ር ደረጀ፡- ሕጉ በ2001 ዓ.ም. የወጣ ቢሆንም
የሕጉን አፈጻጸም የሚወስኑ ቅድመ ዝግጅቶች
መደረግ ነበረባቸው:: ሕጉ ራሱ እስከ ሦስት
ዓመት የሚደርስ የዝግጅት ጊዜን ይፈቅዳል::
ከሕጉ ጋር ተያይዘው የመጡ መርሆዎች በርካታ
ረጅም ዘመን የወሰዱ አሠራሮችንና አስተሳሰቦችን
መለወጥ ግድ የሚሉ ናቸው:: ስለዚህ ከ2004
ዓ.ም. በኋላ በነበሩት ጥቂት ዓመታት ይኼ ነው
የሚባል ትርጉም ያለው ለውጥ መጠበቅ ተገቢ
አይመስለኝም:: መጠነኛ የሆነ የለውጥ አዝማሚያ
አሳይቷል::
ሪፖርተር፡- ሥር የሰደደው የሕዝቡና የመንግሥት
አሠራር ባህል ሚስጥራዊነትን ያበረታታል:: ይህን
ለመቀየር ሕጉ ምን ሚና ይኖረዋል?
ዶ/ር ደረጀ፡- አዋጁ ከመውጣቱም በፊት
የመረጃ ነፃነት በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠ
መብት ነው:: ሕገ መንግሥቱ ተግባራዊ
በሆነባቸው ሃያ ዓመታት አንዳች ነገር መኖር
አለበት:: ከዜሮ የሚጀመር አይደለም:: ጥናቱ
የሚያሳየው ይህንን መሠረታዊ የሆነ የእሴት
ለውጥ የሚጠይቅ ሕግ ተፈጻሚ ለማድረግ እጅግ
በጣም ብዙ ርቀት እንደሚቀር ነው:: የመረጃን ዋጋ
ከመረዳት አንፃር ያለው ባህል ሕጉ ከሚያልመው
እውነታ በብዙ ርቀት የሚገኝ ነው:: የተለየ ንቃት
ያላቸው ጥቂት ተቋማት አሉ:: የሕጉ መሠረታዊ
መነሻ በመንግሥታዊ ተቋማት ይዞታ የሚገኝ
መረጃ የሕዝብ ነው፣ ተቋማቱ ባለአደራዎች
ናቸው የሚል ነው:: በተጨባጭ በተቋማቱና
ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው:: በቅርቡ በመረጃ ነፃነት ሕጉ አፈጻጸም ላይ በሒልተን ሆቴል የተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ዶ/ር
ደረጀ የመነሻ ጥናት አቅርበው ነበር:: በውይይቱ ላይ በቀረበው ጥናትና በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ሰለሞን ጎሹ አነጋግሯቸዋል::
‹‹የመንግሥት ሥልጣን ላይ ሕግን መሠረት ያደረገ ልጓም
የሚያደርጉ ተቋማት መፍጠር ለኢትዮጵያ አሁንም ፈተና ነው››
ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ተባባሪ ፕሮፌሰር
ጉዳዩ በሚመለከታቸው ኃላፊዎች ዘንድ ያለው
አመለካከት ግን የዚህ ቀጥተኛ ተቃራኒ ነው::
ሪፖርተር፡- በውይይቱ ተሳታፊዎች መንግሥት ሕጉ
እንዲወጣ ከማድረግ ባሻገር፣ ተፈጻሚነቱን የመከታተል
ቁርጠኝነት የለውም የሚል ወቀሳ ተሰንዝሯል:: ከሌሎች
አገሮች አንፃር ሕጉን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ
የወሰደው የዝግጅት ጊዜ በዝቷል ማለት ይቻላል?
ዶ/ር ደረጀ፡- የመረጃ ነፃነት ሕግን ነጥሎ
ማውጣት የቅርብ ጊዜ ጅምር ነው:: መሠረታዊው
ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ዳብሮ ሥር
የሰደደባቸው እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቶች
ውስጥ ለብዙ ዘመናት ይህንን ሕግ ማውጣት
አስፈላጊ አልነበረም:: ነገር ግን ሕጉ ባለመውጣቱ
መብቱ በመሠረታዊ ደረጃ የተገደበ አልነበረም::
በኢትዮጵያም ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትንና
ለዚህም አስፈላጊ የሆኑ ተዛማጅ መብቶችን እውን
ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ
ቢሆን ኖሮ፣ የዝግጅት ጊዜው ማጠርና መርዘም
አያከራክረንም ነበር:: ምናልባትም ሕጉ መውጣቱ
መንግሥታዊ ተቋማት የመረጃ አደረጃጀት
ሥርዓታቸውንና ግንዛቤያቸውን በመለወጥ ረገድ
አስገዳጅ ኃይል ያለው በመሆኑ ጥሩ ነው::
ሪፖርተር፡- ሕጉ በመንግሥት ወይም በገዥው ፓርቲ
ፍላጎት ሳይሆን ሻል ባሉ ጥቂት ተራማጅ ግለሰቦች
ግፊት ብቻ እንደወጣ አስተያየት ቀርቦ ነበር:: በዚህ
ይስማማሉ?
ዶ/ር ደረጀ፡- አስተያየቱ ወሳኝ የሆነ
የአገራችንን ማኅበረ ፖለቲካዊ ጉዳይ የሚያነሳ
ነው:: መርሁ በሕገ መንግሥቱ ያለ ነው::
ባለፉት 20 ዓመታት ይህ ተፈጻሚ ሳይሆን ለምን
እንደቀረ እንደ አንድ መላ ምት ሊወሰድ ይችላል::
|ገጽ 7
www.ethiopianreporter.com
| ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008
ቅፅ 21 ቁጥር 1631
ማስታወቂያ
ለትራንስፖርት አገልግሎት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ኢስት አፍሪካን ታይገር ብራንድስ ኃ/የተ/የግል ኩባንያ መነሻ አዲስ አበባ ከተለያዩ ቦታ ሆኖ
መድረሻ ቢሾፍቱ ከከተማዉ መግቢያ ኖክ ማደያ ሳይደርስ ወደ ቀኝ ታጥፎ 2.5 ኪ.ሜ በመግባት፤
መነሻዉ ከቢሾፍቱ እና ዱከም የተለያዩ ቦታዎች ሆኖ መድረሻዉ ኢ.አ.ታ.ብ.አ ከመንገድ 2.5
ኪ.ሜ ገባ ብሎ ሰራተኞችን ማስገባትና ማስወጣት የሚችሉ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች በጨረታ
አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::
በዚህም መሰረት
-- የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
-- ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
-- ለመኪናዎቻቸዉና ለተሳፋሪዎች የደህንነት ኢንሹራንስ የገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
-- በመስመር ላይ ያለ ተሽከርካሪ ቢበላሽ ወዲያዉኑ ሊተኩ የሚችሉ
-- ለሠራተኛዉ ምቹ የሆነ አቧራ የማያስገቡና በርና መስኮታቸዉ የሚዘጉና የሚከፈቱ ፅዳት
ያላቸዉ ተሽከርካሪዎችን ሊያቀርቡ የሚችሉ
-- ተጫራቾች ቢያንስ ሶስት የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ ባለንብረት ለመሆኑ የሚያረጋግጥ
ሊብሪ ሊያቀርብ የሚችል
-- ተጫራቾች ከ25 እስከ 63 ተሳፋሪዎች ሊይዙ የሚችሉ ተሽከርካሪዎችን ማቅረብ የሚችል
-- ካምፓኒዉ የሚያወጣዉን የጋራ መመሪያ እና ስርዓት ማክበር የሚችል
-- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10000 በ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል
-- የጨረታ ሰነዱ ከታህሳስ 7 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 11ቀን 2008 ዓ.ም በግንባር
በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መግዛት ይቻላል
-- የጨረታ ሰነዱ ታህሳስ 12ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ተወካዮች እና ባለንብረቶች
ባሉበት ይከፈታል
-- በጨረታዉ የተሸነፍ ወገኖች ያስያዙት CPO ሆነ ጥሬ ገንዘብ ወዲያዉኑ ተመላሽ
ይደረጋል
-- የጨረታ ሰነዱን በዋናዉ ቢሮ ቀርቦ መግዛት ይቻላል
-- ኩባንያዉ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
-- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-15-29-03 ወይም 09 11 60 82 30 ደዉለዉ
ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ
ኢስት አፍሪካን ታይገር ብራንድስ ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ
Invitation for Bid
Drilling of five (5) Water Wells
Bid reference No: GTLI/HQ/224/2015
1.	Global Team for Local Initiatives (GTLI), an international NGO working in South Omo
Zone, SNNPR, invites interested contractors to carry out the drilling and installation of
hand pumps of five (5) water wells in different kebeles of Dasenech Woredas of South
Omo Zone, SNNPRS.
The overall assignment will be drilling, installation of hand pumps, pump test, head
work and cattle trough constructions for five (5) water wells. The project sites are
located in five kebeles, which are all accessible, within a range of 13-48 kms from
Omorate town which is 840 km from Addis Ababa. The anticipated depths of the
boreholes range from 65 to 96m. Details are provided in the bid document.
2.	Eligible water well drilling and rehabilitation general contractors (GC) or WC of Grade
4 and above are invited to bid for the drilling & construction of boreholes for the project
sites indicated above. The contractor is expected to supply one drilling rig & related
machinery of the required specification for the work, deploy skilled & semi-skilled
labours, and accomplish the activities as per the design, drawings and specification
provided within Eight Weeks’ time, from the date of signing contract. Subcontracting
out the drilling works is strictly forbidden.
3.	Financing by: USAID
4.	Eligible bidders are invited to take part in the bid upon submission of copies of all
relevant renewed licenses, VAT & tax payer’s registration certificate.
5.	Bidding will be conducted through open local tender procedure.
6.	The bid document may be purchased from Global Team for Local Initiatives
(GTLI), Gollagul Building, Suite 1113, Addis Ababa, Ethiopia, 011.662.9937or Field
Coordination Office, Turmi, Hamar Woreda, Tell.046 899 0640, with payment of non-
refundable fee of Birr 100.00 during office hours.
7.	All bids must be accompanied by a bid bond amounting 1% of the total bid amount
including VAT, in the form of C.P.O. Bid bond in any other form shall not be acceptable.
8.	All bids must be submitted one original marked “original” and one copy signed in
the same way as the original and marked “copy” by stating the title, with wax-sealed
envelope at or before 5:00 P.M.(afternoon) on Tuesday, 22nd
December 2015.The
technical and financial offer must be placed together in a sealed envelope.
9.	 Bids will be opened in the presence of bidders and/or their official representatives
who wish to attend at Gollagul Building, Suite 1110, on Wednesday, 23rd
December
2015 at 11:00 AM (morning).
10.	 Failure to comply with any of the conditions indicated above will result in automatic
rejection.
11.	The Organization reserves the right to accept or reject any or all bids.
Global Team for Local Initiatives (GTLI)
ወደ ገጽ 34 ዞሯል
ሕጉ ተግባራዊ የማይሆነው በእምነት ወይም
በቁርጠኝነት እጦት ከሆነ በጣም አደገኛ ነው::
የማን እምነትና የማን መለኪያ የሚለውን ካነሳን
ችግር ነው:: ዝም ብሎ እመኑኝ እኔ ቁርጠኛ
ነኝ ማለት አይቻልም:: በሠለጠነ ሥርዓት ውስጥ
እመኑኝ ዋስትና ሊሆን አይችልም:: ሁሉም
ሊተማመኑበትና ሊገዙበት የሚችለው የሕግ
ቃል ኪዳን አለ:: ሕጉ ከየትም ቢቀዳ ተፈጻሚነቱ
ተግባራዊ የሚደረገው ሁሉም ላይ ነው:: ሕግ
ማውጣት በራሱ ተፈጻሚነቱን ግን አያረጋግጥም::
የሕጉ ተፈጻሚነት የሚወሰነው ሕጉ ሊተገበር
ባለበት ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መድረክ ላይ ባለው
ከባቢ ሁኔታ ነው:: በዚህ ሁኔታ ውስጥ የገዥው
ፓርቲ ልሂቃን ያላቸው እምነትና ፍልስፍና
ቁልፍ ነው:: በሕገ መንግሥቱ የሰፈረውም ሆነ
በመረጃ ነፃነት ሕጉ የተካተቱት መሠረታዊ
መርሆዎች ያለምንም ጥያቄ የሊበራል እሴቶች
ናቸው:: የኮሙዩኒስት እሴቶች አይደሉም፣
የአምባገነን እሴቶች አይደሉም:: ስለዚህ የገዥው
ፓርቲ ልሂቃን እነዚህን እሴቶች የማያምኑባቸው
ከሆነ በጣም አስቸጋሪ ነው:: ለአንድ ርዕዮተ
ዓለም ድጋፍ መስጠት ወይም ማጣጣል መብት
ነው:: ነገር ግን በአገሪቱ የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ
ከገባ ብትወድም ባትወድም ለዚያ መገዛት
አለብህ:: ባትገዛ ደግሞ ተጠያቂ የምትሆንበትን
ሥርዓት መዘርጋት ግድ ነው:: ይህ በሌለበት
ሁኔታ በሥልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ልባቸው
የማይወደው ሕግ ተፈጻሚ ይሆናል ብሎ ማሰብ
እጅግ የዋህነት ነው::
ሪፖርተር፡- ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 29(6) እና
(7) ላይ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ገደብ
የሚጣልበትን አካሄድ ደንግጓል:: በመረጃ ነፃነት ሕጉ
ላይ የተዘረዘሩት ገደቦች ብዛትና ገደቦቹን ለመግለጽ
የሚያሻሙና የሚያምታቱ፣ ግልጽነት የሚጎላቸው
ቋንቋዎችን መጠቀሙ ክፍተት መፍጠሩም ይነገራል::
በዚህ ግምገማ ይስማማሉ?
ዶ/ር ደረጀ፡- መረጃ የማግኘት መብት ገደብ
የማይጣልበት ፍፁም መብት አይደለም:: በሁሉም
አገሮች ተሞክሮ የሚንፀባረቅ ነው:: መረጃ
በሙሉ ለሕዝብ ተደራሽ መሆን አለበት የሚለው
ገዥ መርህ ነው:: ስለዚህ መረጃ መከልከል ልዩ
ሁኔታ ነው:: የክልከላ ምክንያቶቹን መሟላት
የማረጋገጥ ኃላፊነት የመንግሥት ተቋማት ነው::
በዚህ መሠረት የሚሰጡ የክልከላ ውሳኔዎች
አግባብነት የሚፈተሽበት የሕግ ማዕቀፍ መኖር
አለበት:: በኢትዮጵያ ሕግ የተቀመጡ እንደ የግል
ነፃነት ያለመደፈር መብት፣ የቢዝነስ ሚስጥሮች፣
ብሔራዊ ደኅንነት፣ የአገር መከላከያ፣ ዓለም
አቀፍ ግንኙነትና የመሳሰሉት የክልከላ ምክንያቶች
በሁሉም አገር ያሉ ናቸው:: ችግሩ ያለው እነዚህ
የክልከላ ምክንያቶች የሚተከሉበት ከባቢ ሁኔታ
ላይ ነው:: መብቱን በፍፁም የሚጠላ በሚስጥራዊ
አሠራር ውስጥ የኖረ ማኅበረሰብና ቢሮክራሲ
ውስጥ ስትወስደው የክልከላ ምክንያት የሚፈልጉ
ባለሥልጣናት ባሉበት ከባቢ ሁኔታ ካስገባኸው፣
የክልከላ ምክንያቷ አንዲትም ብትሆን ከመከልከል
አይመለስም:: መሠረታዊው ነገር የክልከላ
ምክንያቶቹ መብዛትና ማነስ አይደለም:: መለመን
መረጃ የማግኘት ወሳኝ የአሠራር መንገድ
በሆነበት ማኅበረሰብ ውስጥ፣ የክልከላ ምክንያቶች
ባይኖሩም እንኳን ተጠያቂነት በሌለበት ዓውድ
እንቢ መባሉ አይቀርም:: ለዚህ አንዱ ማሳያ
የሚሆነው ሕጉ የክልከላ ምክንያቶችን በጽሑፍ
መስጠት ቢያስገድድም በጥናቱ ከተሳተፉት ውስጥ
99 በመቶ የሚሆኑት በቃል ነው አይቻልም
የተባሉት:: ሳይብራሩ የተቀመጡ በጣም
ጥቅል የሆኑ የክልከላ ምክንያቶችን በሌሎች
ደንቦች፣ በአሠራር ማኑዋሎችና በመመርያዎች
ማፍታታትና መዘርዘር ያስፈልጋል::
ሪፖርተር፡- የመረጃ ነፃነት ሕጉ እንደ የሚስጥር
ሕግ፣ የመረጃ ምደባና ሚስጥራዊነት ማብቂያ ሕግ፣
የመረጃ ዋጋ ተመን ሕግ፣ የመረጃ አፈትላኪዎች ጥበቃ
ሕግ መውጣት ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንደሚያደርገው
ታሳቢ ተደርጎ የወጣ ነው:: የእነዚህ ሕግ አለመውጣት
በእናንተ ጥናትና በስብሰባው ተሳታፊዎች እንደ ተግዳሮት
ተጠቅሷል:: የፈጠረው ክፍተት ምን ይመስላል?
ዶ/ር ደረጀ፡- የእነዚህ ሕጎች አስፈላጊነት ላይ
ጥያቄ አይነሳም:: ነገር ግን በመብቱ አፈጻጸም ላይ
የሚኖራቸው ሚና ከፍና ዝቅ ሊል የሚችለው
በአጠቃላይ በአገር ውስጥ ባለው የሕግ የበላይነትና
የሰብዓዊ መብቶች አከባበር ደረጃ ነው:: እርግጥ
የሕጎቹ አለመውጣት ለመብቱ ተፈጻሚነት የራሱ
የሆነ አደናቃፊነት ሚና አለው:: ነገር ግን ይኼን
ጉዳይ የትኩረት አቅጣጫ ማድረግ ከእነዚህ ሕጎች
አለመውጣት ውጪ የመብቱ ጥበቃ ይዞታ ደህና
ነው የሚል የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ያደርሳል::
ሪፖርተር፡- የመረጃ ነፃነት ሕጉ ከመገናኛ ብዙኃን
ሕግ ጋር መቀላቀሉን እንደ ችግር ያዩት ተሳታፊዎች
ነበሩ:: የሚዲያ ተቋማትና ማንኛውም ግለሰብ መረጃ
የሚያገኙበት አሠራር ተመሳሳይ መሆኑ በሌሎች አገሮች
የተለመደ ነው?
ዶ/ር ደረጀ፡- ሕጉ ለሁሉም መረጃ ፈላጊዎች
ነው የሚለው:: ነገር ግን በመርህ ደረጃ መረጃ
ፈላጊዎችን ለሁለት ከፍለን ማየት አለብን:: በአንደ
በኩል ለዕለት ተዕለት ኑሮውና ለግል ሕይወቱ
እንደ ሜድካል ሪከርድ፣ የግብር መረጃ የሚፈልግ
አለ:: በሌላ በኩል ለአጠቃላይ ዴሞክራሲያዊ
ሥርዓት ግንባታ፣ ለተጠያቂነት፣ ለሰብዓዊ
መብት መከበርና ብልሹ አሠራሮችን ለመዋጋት
ቁልፍ የሆነ ሚና የሚጫወተው ሚዲያ አለ::
ሁለቱ መረጃ የሚፈልጉበት ምክንያት የተለያየ
ነው:: በግለሰብ በኩል መሻሻሎች አሉ:: ሚዲያውን
በተመለከተ ግን የምርመራ ሥራ የሚሠሩና
ተጠያቂነትንና የሕግ የበላይነትን የተመለከቱ
ጥያቄዎች ይዞ የሚሠራው ሚዲያ ያለበት ሁኔታ
እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው:: ይኼ ደግሞ በአጠቃላይ
እንደ ማኅበረሰብና አገር ከፍተኛ አደጋ ይደቅናል::
ነፃና ውጤታማ ሚዲያ በሌለበት ዴሞክራሲያዊ
ማኅበረሰብን መገንባት አይቻልም::
ሪፖርተር፡- አንዳንዶች እንዲያውም ሕጉ
ለጋዜጠኞች የዕለት ተዕለት ሥራ ተግባራዊ የሚሆን
አይደለም ብለው ተከራክረዋል::
ዶ/ር ደረጀ፡- የመረጃ ነፃነት ሕጉ ከመገናኛ
ብዙኃን ሕግ ጋር መቀላቀሉ አይደለም ይህን
ችግር ያመጣው:: አንድ ላይም ሆነ ተነጣጥለው
ቢወጡ ካልተፈጸመ ትርጉም የለውም:: መረጃ
የማግኘት መብት የሁሉም ዜጎች ነው:: እርግጥ
መረጃ የማግኘትን መብት ከሚዲያ አንፃር ብቻ
መመልከት የሕጉን አንድ ምዕላድ ገንጥሎ
እንደመጣል ነው:: ሆኖም ከግለሰብ ይልቅ ሚዲያ
መረጃ የታጠቀ ዜጋ ለመፍጠር ፍቱን ነው:: ይህ
ዓይነት ዜጋ ሕገ መንግሥታዊ መርሆዎችን
በማክበር ዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብን ለመፍጠር
ቁልፍ ሚና አለው:: ከዚህ አንፃር ከሚዲያ ይልቅ
በተናጠል ለግል ሕይወታቸው መረጃ እንዲያገኙ
ማድረግን መደፍጠጥ ይሻላል:: የአዋጁን ዋና
ዓላማ ካየን ሚዲያው ቅድሚያ የሚሰጠው ነው::
ሪፖርተር፡- የሕዝብ ግንኙነት ቢሮዎች በሕጉ
ሲቋቋሙ ዋናው ዓላማ የመረጃ ፍሰቱን ማሳለጥ
ቢሆንም፣ በተግባር መረጃ እንዳይሰጥ ዘብ እየቆመ
ነው የሚል ቅሬታ ቀርቧል:: የቢሮውን ሚናና የሕዝብ
ግንኙነት ኃላፊዎችን ሥራ እንዴት አዩት?
ዶ/ር ደረጀ፡- ይኼ ቅሬታ በአብዛኛው
የሚቀርበው በሚዲያ ባለሙያዎች ነው:: የዕለት
ተዕለት ሥራቸው ያገናኛቸዋል:: ነገር ግን በእኛ
ጥናት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ስለመረጃ
ነፃነት ሕጉ ያላቸው ግንዛቤ እጅግ ውስን መሆኑ
ተመልክቷል:: መረጃ ከመስጠታቸው በፊት
የኃላፊዎችን ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው
ያምናሉ:: መረጃ የመስጠትና ያለመስጠት
ውሳኔ በተግባር የሚሰጠው በሥራ ኃላፊዎች
እንጂ በሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች አይደለም::
ኃላፊዎቻቸው የማይደሰቱበትን ሥራ ቢሠሩ
የሥራ ዋስትና እንዳላቸው እርግጠኛ አይደሉም::
ስለዚህ ለችግሩ እነሱን ብቻ መውቀስ ተገቢ
አይመስለኝም:: የሥራ ኃላፊዎች እንደ ነገሥታት
ሁሉን አዛዥ በሆኑበት ሁኔታ በአንድ ጥግ
የተቀመጠ ምስኪን ሠራተኛ ሕጉ ላስቀመጠው
መርህ ተገዥ እንዲሆን መጠበቅ ተገቢ አይደለም::
ሪፖርተር፡- የመረጃ ነፃነት ሕጉን የማስፈጸም
ኃላፊነት የተሰጠው ለእንባ ጠባቂ ተቋም ነው:: ይህ
ውሳኔ ተቋሙ አስቀድሞ ከነበረው አቅምና ልምድ
አንፃር ቅሬታ ቀርቦበት ነበር:: ባለፉት ዓመታት ተቋሙ
የሄደበት አቅጣጫ ይህን ያፋለሰ ነው ይላሉ?
ዶ/ር ደረጀ፡- ጥያቄው በተወሰነ ደረጃ እኔ
ልመልሰው የምችል አይደለም:: የተወሰነ ሥራ
እንደሠራ አምናለሁ:: ለተቋሙ ኃላፊነቱን
የመስጠት ውሳኔው ፖለቲካው ውሳኔ እንደሆነ
ተገልጿል:: ጥቅምና ጉዳቱ ምናልባትም የወደፊት
የጥናት ነጥብ ሊሆን ይችላል:: በእኛ አገር
ተጨባጭ ሁኔታ ሌሎች እንደ ፍርድ ቤት ያሉ
አማራጭ ተቋማት ከእንባ ጠባቂ ተቋም የተሻሉ
የመረጃን ዋጋ ከመረዳት አንፃር
ያለው ባህል ሕጉ ከሚያልመው
እውነታ በብዙ ርቀት የሚገኝ ነው::
የተለየ ንቃት ያላቸው ጥቂት
ተቋማት አሉ:: የሕጉ መሠረታዊ
መነሻ በመንግሥታዊ ተቋማት
ይዞታ የሚገኝ መረጃ የሕዝብ ነው፣
ተቋማቱ ባለአደራዎች ናቸው የሚል
ነው:: በተጨባጭ በተቋማቱና ጉዳዩ
በሚመለከታቸው ኃላፊዎች ዘንድ
ያለው አመለካከት ግን የዚህ ቀጥተኛ
ተቃራኒ ነው::
ገጽ 8|
www.ethiopianreporter.com
| ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008
ቅፅ 21 ቁጥር 1631
ከገጽ 1 የዞረ
ከገጽ 1 የዞረ
ከገጽ 1 የዞረ በኦሮሚያ ግጭት...መድረክ የሟቾች...በጭልጋና በመተማ...
የሚያነሳቸውን ተገቢነት ያላቸው ጥያቄ ለመመለስ
ተነሳሽነትም እያሳዩ አይደሉም በማለት የሚወቅሱ
አሉ:: በእነዚህ ጉዳዮች የኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ሥራ
አስፈጻሚ አባልና የኦሕዴዱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
አቶ ዳባ ደበሌ በተደጋጋሚ አስተያየት እንዲሰጡ
ቢጠየቁም፣ እንደማይመቻቸው በመግለጽ አስተያየት
ሳይሰጡ ቀርተዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ
ሥጦታው ግን ማስተር ፕላኑ ለዚህ ግጭት ምክንያት
እንደማይሆን ለሪፖርተር ገልጸዋል:: አቶ አባተ
ግጭቱን ድብቅ ዓላማ ያላቸው አካላት በማስተር
ፕላኑ ስም ቀስቅሰውታል ብለው ያምናሉ::
ማክሰኞ ታኅሳስ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ምሽት የፀረ
ሽብር ግብረ ኃይል ባወጣው መግለጫ፣ ከፊት ለፊት
ማስተር ፕላኑን በመቃወም ከጀርባ ደግሞ ከሽብርተኛ
ኃይሎች ጋር በማበር የተሠለፉ መኖራቸውን ገልጿል::
ግብረ ኃይሉ እንዳለው፣ ውጭ ካለው የሽብር
ኃይል ጋር ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት
በመፍጠር የነውጡና የረብሻው አድማስ ወደ ከተሞችና
ወደተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት እንዲሰፋፋ
ተደርጓል:: በዚህም በርካታ የመንግሥት፣ የግል
ባለሀብቶችና የደሃ አርሶ አደሮች ንብረትና ሀብት
ወድሟል ያለው ግብረ ኃይሉ፣ የኅብረተሰቡን ሰላምና
ደኅንነት ለመጠበቅ በተሰማሩ የፌዴራልና የኦሮሚያ
ክልል ፖሊስ አባላት፣ እንዲሁም በመከላከያ ኃይል
አባላት ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል:: ሕገ
መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የሕዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ
በሽብርና በአመፅ ኃይሉ ላይ ሕጋዊና ተመጣጣኝ
ዕርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል::
በገጠርም ሆነ በከተማ የሚኖሩ አሁን ያለውን
ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት በትምህርት ተቋማትም ሆነ
ከትምህርት ተቋማት ውጪ የሚገኙ ልጆቻቸውንና
መላ ቤተሰባቸውን፣ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋና
ንብረት እንዳይወድም፣ ዘረፋ እንዳይስፋፋ፣ የሽብር
አመፅ አቀጣጣዮች ሰለባ እንዳይሆኑ የበኩላቸውን
ሚና እንዲወጡ አሳስቧል::
በተመሳሳይ የኦሮሚያ ክልል በወቅታዊ ጉዳዮች
ላይ ባወጣው የመንግሥት አቋም፣ በክልሉ የተለያዩ
ዞኖችና ወረዳዎች ማረሚያ ቤቶችን በመስበር፣ የሕግ
ታራሚዎችን በመልቀቅ፣ የፖሊስ ጽሕፈት ቤቶችን፣
የልማት ድርጅቶችን፣ የአርሶ አደር ምርቶችን፣
የግል መኖሪያ ቤቶችን በማቃጠልና በማውደም
በጦር መሣሪያ የታገዘ ጥፋት፣ የጥፋት ኃይሎች
ያላቸው ወገኖች በመፈጸም ላይ ናቸው ብሏል::
እነዚህ ኃይሎችም ከድርጊታቸው ይቆጠቡ በማለት
አስጠንቅቋል::
‹‹እነዚህ የጥፋት ኃይሎች አብሮ የመኖር፣
የመቻቻልና የዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ተምሳሌት
የሆነውን የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች
ወንድሞቹ ጋር የጎሪጥ እንዲተያይ፣ እንዲሁም
በእምነቶች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ
ከድርጊታቸው ጎን የቆመን ኃይሉ ሁሉ አሠልፈው
ወደ ሕገወጥ ተግባር ተሸጋግረዋል፤›› በማለት የክልሉ
መንግሥት ገልጿል::
በመሆኑም መንግሥት የእነዚህን የጥፋት ኃይሎች
ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን የመናድ ተግባር ለማስቆምና
የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ በሕገ መንግሥቱ
የተጣለበትን ግዴታ መሠረት በማድረግ በድርጊቱ
ዋና ዋና ተዋናዮች ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ
አስጠንቅቋል::
በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እየታየ ያለው
ሁከት ከማስተር ፕላን በዘለለ ሌላ አቅጣጫ እየያዘ
መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ:: ሀብቱ አድማሱን
ሊያሰፋ እንደሚችልም ሥጋታቸውን ይገልጻሉ::
‹‹መንግሥት መሠረታዊውን የጥናት ሐሳብ
ለሕዝቡ አቅርቦ የሕዝቡ ስሜት ምንድነው የሚለውን
ፈትሾ እንጂ ወደ ዝርዝር ጥናት የሚገባው፣ ዝም
ብሎ የጉልበተኛ ሥራ መሥራት ተገቢ አይደለም፤››
ሲሉ የመድረክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር በየነ ገልጸዋል::
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተለያዩ የኦሮሚያ
ከተሞች በተፈጠረው ረብሻ ሕይወታቸውን አጥተዋል
በማለት መድረክ በመግለጫው የዘረዘራቸው
30 ግለሰቦች ሲሆኑ፣ የሟቾችን ዝርዝር ስምና
የሞቱባቸውን ከተሞች አስታውቋል::
በዚህ መሠረት በምዕራብ ወለጋ ጉልሶ ወረዳ፣
በምዕራብ ሐረርጌ በደኖ ወረዳ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ
ቶሌ ወረዳ፣ አዳበርጋ ወረዳ ሙገር፣ ምዕራብ ሸዋ
ጨሊያ ወረዳ ባብቻ ከተማ፣ ምዕራብ ሸዋ ጨሊያ
ወረዳ ጌዶ ከተማ፣ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ፣
ሆሮ ጉድሮ ፊንጫ፣ ወሊሶ ከተማ፣ አመያ ከተማ፣
ወንጪ ከተማ፣ ግንደበረት ወረዳና ግንጪ ወረዳ
ግለሰቦች የሞቱባቸው ሥፍራዎች እንደሆኑ መድረክ
አስታውቋል::
የሚካሄዱት እንቅስቃሴዎች ሰላማዊ ከሆኑ ይህን
ያህል ሰዎች እንዴት ይሞታሉ? በአንዳንድ አካባቢዎች
ግጭቶች እየታዩና ከቁጥጥር ውጪ በመሆናቸው ይህ
ከምን የመነጨ ነው? ለሚሉ ጥያዎች፣ ‹‹ይህንን
ንብረት እናወድማለን ጥፋት እናደርሳለን ብሎ የተነሳ
እንቅስቃሴ አይደለም:: ሕገ መንግሥታዊ መብታችን
ተጣሰ በሚል መነሻ እንደሆነ ሊዘነጋ አይገባውም::
አንድ የተናደደ ወጣት ጠጠር ሊወረውር ይችላል:: ይህ
ተስፋ ከመቁረጥ የሚመነጭ ነው:: ሥርዓቱ ሕዝቡን
ወደ ተስፋ መቁረጥ እያሻገረው በመሆኑ የተከሰተ
ነው፤›› በማለት ፕሮፌስር በየነ ምላሽ ሰጥተዋል::
በቅርቡ የተከሰተውን ችግር ያፈነዳው የማስተር
ፕላኑ ጉዳይ ነው በማለት አስተያየት የሰጡት ዶ/ር
መረራ፣ ‹‹ነገር ግን በተጨማሪም ሕዝቡ በአመራሩ
የመሰልቸት፣ በተለይ የወጣቶች ተስፋ ማጣትና
የመሳሰሉት ነገሮች ናቸው ይህን የፈጠሩት፤›› በማለት
አክለው ገልጸዋል::
የችግሮቹን ሁኔታ አጥንቶ መፍትሔ ማዘጋጀት
አስቸኳይ ሥራ መሆን አለበት ያሉት ዶ/ር መረራ፣
ሁለት መፍትሔዎችን በአማራጭነት አቅርበዋል::
እነዚህም ጊዜያዊና ዘለቄታዊ የሚሉ ናቸው::
ጊዜያዊ መፍትሔው ‹‹ወጣ የተባለውን አዋጅ
መሻር ነው:: አዋጅ ደግሞ የሚሻረው በአዋጅ ነው፤››
በማለት በቅርቡ በጨፌ ኦሮሚያ የወጣውን የከተሞች
ማሻሻያ አዋጅ እንዲሻር የጠየቁ ሲሆን፣ ዘላቂ
መፍትሔው ብለው ያቀረቡት ደግሞ፣ ‹‹ኢሕአዴግ
በቃኝ የኢትዮጵያን ሕዝብ መምራት አልቻልኩም
ብሎ ከሥልጣን መውረድና ምርጫ ማካሄድ ነው::
ይህን ማድረግ አልፈልግም የሚል ከሆነ ደግሞ
ቢያንስ ጥምር መንግሥት አቋቁሞ ከዚያ በኋላ
ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ነው፤›› ሲሉ ዶ/ር መረራ
ተናግረዋል::
የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የመድረክ አባል
የሆነው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)
የተለያዩ መግለጫዎችን በማውጣት በጉዳዩ ላይ
ያላቸውን አቋም ሲገልጹ ከመቆየታቸው አንፃር፣
መድረክ መግለጫ ለማውጣት አልዘገየም ወይ ተብሎ
ከሪፖርተር ለቀረበ ጥያቄ፣ ‹‹መድረክ ዘገየ አልዘገየ
የሚለው ጉዳይ ይህን ያህል ብዙ ቦታ ልንሰጠው
የሚገባ አይመስለኝም:: ይህም ቢሆን ግን መድረክ
ምንም አላለም ማለት አይደለም:: በሕዝብ ግንኙነት
በኩል መረጃዎች ሲሰጥ ነበር፤›› በማለት ፕሮፌሰር
በየነ ምላሽ ሰጥተዋል::
ይህ በዚህ እንዳለ ሰማያዊ ፓርቲና ኤፌኮ በጋራ
ለመሥራት ስምምነት ላይ ደረሱ:: ሁለቱ ፓርቲዎች
ስምምነት ላይ የደረሱት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ
መግለጫ ለመስጠት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል::
የሁለቱ ፓርቲዎች አመራሮች ባደረጉት ስምምነት፣
በጋራ መግለጫ ከመስጠትም በላይ የጋራ ግብረ
ኃይል በማቋቋም የፖለቲካ ትግል እንደሚያደርጉ
አስታውቀዋል::
መንግሥት አስፈላጊውን ዕርምጃ ይወስዳል ብለዋል::
ነዋሪነታቸውን በጭልጋና በመተማ ያደረጉ
የሪፖርተር ምንጮች ግን በአካባቢው ውጥረቱ አሁንም
እንዳለ ገልጸው፣ የበርካታ ሰዎች ሕይወት እንደጠፋ፣
በአካልና በንብረት ላይም ጉዳት እየደረሰ እንደሆነ
አመልክተዋል:: በዚህም የተነሳ ሴቶችና ሕፃናትን
ወደ ሌሎች አካባቢዎች በተለይ ወደ ደምቢያ ወረዳ
እየሸሹ መሆኑንም ጠቁመዋል:: በአማራና በቅማንት
ሕዝቦች መካከል ያለው ግጭት እንደቀጠለ አክለዋል::
አቶ ንጉሡ በግጭቱ የሰው ሕይወት መጥፋቱን
የገለጹ ቢሆንም፣ ምን ያህል ሰው ሕይወቱን እንዳጣ
ግን መረጃ እንዳልደረሳቸው ገልጸዋል:: ይሁንና
ግጭቱ የሕዝብ ጥያቄ እንዳልሆነ ተከራክረዋል::
‹‹እንደሚወራው ማንነት ላይ በተሰጠው ምላሽ የተነሳ
ግጭት አይደለም:: የቅማንት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ
ሕገ መንግሥቱም ቢሆን የሚደግፈው በመሆኑ፣
ክልሉም አምኖበት ዕውቅና ሰጥቷል:: ራሱን በራሱ
እንዲያስተዳድርም ተወስኖ የአስተዳደር እርከን
ደረጃውን ለመወሰን ሥራዎች እየተሠሩ ነው:: ይህን
ሰበብ አድርገው ግጭት ያስነሱት ሌላ አጀንዳ ያላቸው
አካላት ናቸው፤›› ብለዋል::
የግጭቱ መነሻ የቅማንት ብሔረሰብ የማንነት
ጥያቄ እንደሆነ የሚገልጹ አካላት ደግሞ፣ ጉዳዩ
ሲንከባለል ለበርካታ ዓመታት መቆየቱን ያመለክታሉ::
አቶ ውብሸት ሙላት ‹‹አንቀጽ 39›› መጽሐፋቸው
ላይ ቅማንት የራሱ የሆነ የጋራ የትውልድ
አመጣጥ አፈ ታሪክ ያለው፣ እንደ አንዳንድ ሰዎች
ምስክርነት ከጭልጋ፣ ከላይ አርማጭሆና ከጎንደር
ከተማ ተያያዥነት ባለው አካባቢና በሌሎች የሰሜን
ጎንደር ወረዳዎች የሚኖር፣ የራሱ የሆነ ባህልና
ልማዳዊ ሥርዓቶችም ያለው ማኅበረሰብ እንደሆነ
ገልጸዋል:: አቶ ውብሸት በተጨማሪም በተራዘመው
የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታቸው እየከሰመና እየተዋጠ
ቢሄድም፣ የራሳቸው እምነትና ባህልም እንደነበራቸው
አመልክተዋል::
ቅማንት ጥያቄውን ለአማራ ክልል መጀመሪያ
ሲያቀርብ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 39(5)
ላይ የተቀመጠውን የተለየ ማንነት መሥፈርት
እንደማያሟላ ገልጾ ክልሉ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎት
ነበር:: የማኅበረሰቡ ተወካዮች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት
ይግባኝ አቅርበው፣ ምክር ቤቱም ባቋቋመው ኮሚቴ
አማካይነት ጥናት ለማድረግ የማኅበረሰቡ አባላት
በሚኖሩባቸው ቦታዎች በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የክልሉ
መንግሥት በራሱ ተነሳሽነት ችግሩን ለመፍታት
ኮሚቴ አቋቁሞ ኅብረተሰቡን በማነጋገር ለጉዳዩ
እልባት ለመስጠት ሥራ መጀመሩን በመግለጹ፣
ጥናቱ መቋረጡን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው
መረጃ ይጠቁማል::
ከዚህ በኋላ ክልሉ ጉዳዩን መርምሮ የክልሉ
ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባዔውን መጋቢት 3 ቀን
2007 ዓ.ም. ሲያከናውን፣ ማኅበረሰቡ ራሱን በራሱ
እንዲያስተዳድር ወስኗል:: ይሁንና የማኅበረሰቡ
አካላት ውሳኔው ከፊል መፍትሔ ነው ሲሉ ቅሬታ
አቅርበዋል:: ምክር ቤቱ የቅማንት ማኅበረሰብ ራሱን
ችሎ በሚኖርባቸው የጭልጋና የላይ አርማጭሆ
ወረዳዎች በሚገኙ 42 ቀበሌዎች ማዕከል አድርጎ
ራሱን በራሱ እንደሚያስተዳድር መወሰኑ ይታወሳል::
የቅማንት ማኅበረሰብ በአይከል፣ በመተማ፣ በቋራ፣
በወገራ፣ በደምቢያና በጐንደር ዙሪያ በተበታተነ
ሁኔታ ይገኛል የሚሉት የማኅበረሰቡ አባላት ግን፣
ውሳኔው የተሟላ አይደለም በማለት የቅማንት ሕዝብ
የሚገኝባቸውን ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ በቅማንት
አስተዳደር ሥር እንዲሆኑ ለማድረግ፣ የአስተዳደር
ደረጃውን በዞን ደረጃ ለማድረግ እንደሚታገሉ
መግለጻቸው ይታወሳል::
በዚሁ መሠረት ጉዳዩን በይግባኝ ለፌዴሬሽን
ምክር ቤት ያቀረቡ ሲሆን፣ ጉዳዩን የመረመረው ምክር
ቤትም ውሳኔውን ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ሰጥቷል::
ምክር ቤቱ የማኅበረሰቡ ተወካዮች የክልሉ መንግሥት
የሰጠው ውሳኔ ሁሉንም ቀበሌዎች ያላከተተና
የተሸራረፈ በመሆኑ ቅሬታ ማቅረባቸውን ያስታወሰው
ውሳኔ፣ ክልሉ ቅማንት ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር
የሰጠውን ውሳኔ እንዳፀደቀው ገልጿል:: ‹‹የክልሉ
መንግሥት በጀመረው አግባብ እንዲፈታ የሚል
መደምደሚያ ላይ ደርሷል፤›› ይላል::
እንደ ሪፖርተር ምንጮች ገለጻ፣ በጭልጋና
በመተማ የተነሳው ግጭት ቅማንቶች በውሳኔው ደስተኛ
ባለመሆናቸው፣ አማራዎች ደግሞ ቅማንቶች የተለየ
ማንነት አላቸው ብለው የሚያምኑ ባለመሆናቸው
ምክንያት ነው:: የክልሉ መንግሥት ግን እነዚህን
ጉዳዮች ሰበብ በማድረግ ግጭት እንዲፈጠር የፈለጉ
አካላት የፈጠሩት ችግር እንጂ፣ ሕዝቡ እንዲህ
ዓይነት አለመግባባት የለውም ሲል አስተባብሏል::
‹‹ፀረ ሰላም ኃይሎችም በአማራና በቅማንት ሕዝቦች
ዘንድ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ለዘመናት
በመፈቃቀርና በመረዳዳት ሲኖር የነበረውን ሕዝብ
ለማጋጨት የሚያደርጉትን ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ
ያቁሙ፤›› ሲሉ አቶ ገዱ አስጠንቅቀዋል::
አዲሱ አሠራር ግን ከዚህ በተለየ ዲዛይኑን፣
ግንባታውንና ከመንገዱ ግንባታ መጠናቀቅ በኋላም
የጥገና ሥራን የሚያካትት ነው:: ይህ አሠራር
ሦስቱንም ሥራዎች አጣምሮ ለመሥራት አሸናፊ
የሚሆነው ኮንትራክተር ኃላፊነት የሚወስድበት
ይሆናል:: የነቀምት-ቡሬ መንገድ ፕሮጀክት
አጠቃላይ ግንባታን ለማከናወን አሸናፊ የሚሆኑ
ኮንትራክተሮች፣ መንገዱን ካስረከቡ በኋላ
ለአምስት ዓመታት የጥገና ሥራ ያከናውናሉ::
ዲዛይን፣ ግንባታና የጥገና ሥራን አጣምሮ
ለአንድ ኮንትራክተር እንዲሰጥ የሚያስችለው
አሠራር ለአገሪቱ እንግዳ መሆኑን የጠቆሙት
አቶ ሳምሶን፣ ወደዚህ አሠራር መገባቱ የአገሪቱን
የመንገድ ግንባታ ክንውን ከፍ ወዳለ ምዕራፍ
መሸጋገሩን ያሳያል ብለዋል:: ቀልጣፋ አሠራርን
ይፈጥራል ሲሉም አክለዋል:: የነቀምት-ቡሬ
መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከተጀመረ በኋላም
ይህ አሠራር በሌሎች በተመረጡ የመንገድ
ፕሮጀክቶች ላይ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎም
ይጠበቃል::
የዲዛይንና የጥገና... ከገጽ 5 የዞረ
የማክበር ግዴታ እንዳለበት በስምምነቱ ሰፍሯል::
በሁለቱ ወገኖች መካከል አለመግባባት
ቢፈጠር በግልግል ዳኝነት የሚፈታ መሆኑን
ስምምነቱ ይገልጻል:: ስምምነት የገቡት አገሮች
ዋና መዲናቸውን ቢቀይሩ ስምምነት ለገባው አገር
ካሳና ምትክ ቦታ የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው
ያስረዳል::
ኢትዮጵያ በቱርክ የምትፈልገው ቦታ 3,000
ካሬ ሜትር ከሆነና መርሁም ሰጥቶ መቀበል
ከሆነ፣ ኢትዮጵያም መስጠት የሚገባት 3,000
ካሬ ሜትር ብቻ መሆን እንዳለበት፣ አለበለዚያ
እንደዚህ ዓይነት ስምምነት በኖረ ቁጥር ገንዘብ
ላለው መሬት ሲሸጥ ሊቀጥል ነው ወይ? በማለት
አንድ የምክር ቤቱ አባል ጥያቄያቸው በቋሚ
ኮሚቴ እንዲታይ ጠይቀዋል::
ሌሎች አባላት ደግሞ የሊዝ አዋጁ መሬት
በጨረታ በሊዝ እንደሚያዝ፣ እንዲሁም በምደባ
መንግሥት ሊዝ የሚከፈልበት መሬት ሊያቀርብ
እንደሚችል ደንግጐ ሳለ፣ ፓርላማው የሊዝ ዋጋ
ያለበትን ስምምነት ሊያፀድቅ እንደማይገባና ይህ
ምክር ቤት የሊዝ ዋጋ ሊወስን እንደማይችል
ገልጸዋል::
በመሆኑም የሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ
ጉዳዩን በዝርዝር እንዲመለከተው ጠይቀዋል::
የቀረበው የስምምነት ማፅደቂያ አዋጅም በአንድ
ድምፀ ተአቅቦ ለውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና
ለከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ
ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ ተመርቷል::
በኢትዮጵያና በቱርክ... ከገጽ 5 የዞረ
ሪፖርት ለሰው ልጅ ተስማሚ የኑሮ ከባቢ ሁኔታ
ለመፍጠር የሚያስችል ሥራ የደመወዝ ክፍያ
እንዲከፈል የሚያሳስበው የተመድ የልማት
ፕሮግራም፣ በቀን ከሁለት ዶላር በታች የሚያገኙ
ሰዎች ከ830 ሚሊዮን በላይ እንደሆኑ፣ 200
ሚሊዮን ሰዎች (74 ሚሊዮን ወጣቶችን ጨምሮ)
ሥራ አጥ እንደሆኑና 21 ሚሊዮን ሰዎች
በመላው ዓለም በግዳጅ ጉልበታቸው እየተበዘበዘ
እንደሚሠሩ በሪፖርቱ ጠቁሟል::
ሔለን ክላርክ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው
ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፣ እንደ ኢትዮጵያ
ያሉ አገሮች ለልማት ካላቸው ፍላጎትና ዓላማ
በመነሳት፣ ሀብታቸውን በመጠቀም ለማደግ
የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሰዎችን ጤና
የማያውክ የሥራ ዕድልና የመሥሪያ ቦታ
መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል::
‹‹ይህ ሲባል ግን ለሰዎች ሕይወት ሥጋት
በሚያሳድሩ የሥራ መስኮች ላይ እንዲሠሩ
የማያስገድዱ ዝቅተኛ ደረጃዎች መከበር
የለባቸውም ማለት አይደለም፤›› ያሉት ሔለን
ክላርክ፣ በዓለም ላይ እንደ ግንባታ ዘርፍ
ያሉ ለሰዎች ሕይወት መጥፋት አስተዋጽኦ
በሚያደርጉ ዘርፎችና በሌሎችም መስኮች
በምንም ዓይነት መጣስ የማገባቸው የደኅንነትና
የሥራ ላይ አደጋ መከላከያ ሥርዓቶች መተግበር
እንዳለባቸው አሳስበዋል::
በአንፃሩ በኢትዮጵያ በተከታታይ ጊዜያት
የሰብዓዊ ልማት የሚለኩባቸው እንደ የትምህርት
መስፋፋት፣ የእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ የዕድሜ
ጣሪያ፣ የንፁህ ውኃ አቅርቦት፣ የመሠረተ
ልማት መስፋፋቶች አገሪቱን ደረጃ እያሻሻሉ
መምጣታቸው ቢገለጽም፣ ከሌሎች ተመሳሳይ
ደረጃ ላይ ካሉ የአፍሪካ አገሮች አኳያ የኢትዮጵያ
ለውጥ ብዙ የሚቀረው ሆኗል::
ከሰሐራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ዘንድ
እ.ኤ.አ. ከ2000 ጀምሮ የታዩት ዕድገቶች ፈጣን
ሆነው ተመዝግበዋል:: ከሌሎች የዓለም ክፍሎች
ይልቅ ከሰሐራ በታች የአፍሪካ ዓመታዊ የሰብዓዊ
ልማት ዕድገት የ1.7 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ
ቀዳሚ ሆኗል:: ቦትስዋና፣ ኬፕቨርዴ፣ ኮንጎ፣
ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ጋቦን፣ ጋና፣ ሞሪሺየስ፣
ናሚቢያ፣ ሳኦ ቶሜ ኤንድ ፕሪንቺፒ እንዲሁም
የተመድ ልማት... ከገጽ 5 የዞረ
ዛምቢያ በአፍሪካ ከፍተኛ የሰብዓዊ ልማት ዕድገት
ያስመዘገቡ አገሮች ተብለዋል:: ኢትዮጵያ ከእዚህ
ዝርዝር ውስጥ የለችበትም:: ይህም ሆኖ በዓለም
ካሉ ሌሎች ቀጣናዎች ይልቅ ከሰሐራ በታች
የአፍሪካ አገሮች አሁንም ዝቅተኛውን የሰብዓዊ
ልማት መመዘኛ ያሟሉ ሆነዋል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ባደረጉት
ንግግር፣ ኢትዮጵያ በየዓመቱ በሰብዓዊ ልማት
መስክ የ3.3 በመቶ ዕድገት እያስመዘገበች
መምጣቷንና የሰዎች የዕድሜ ጣሪያም በአሁኑ
ወቅት 70 ዓመት መድረሱን፣ ድህነትም በግማሽ
መቀነስ መቻሉን ጠቅሰዋል:: ምንም እንኳ
የሥራ ዕድል ማግኘት ጠቃሚ ቢሆንም ዘላቂ
የሥራ ዕድሎችን በማግኘት ሰዎች ከራሳቸው
አልፈው ቤተሰቦቻቸውን የሚረዱበት ዕድል
መፈጠር እንሚያስፈልግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ
አስረድተዋል::
ባለፉት 25 ዓመታት በተመድ የልማት
ፕሮግራም አጥኚዎች እየተዘጋጀ ይፋ ሲደረግ
የቆየው ዓመታዊ የሰብዓዊ ልማት ሪፖርት፣
በሩብ ክፍለ ዘመኑ ሁለት ቢሊዮን ሰዎች
ከዝቅተኛ የሰብዓዊ ልማት ደረጃ መላቀቅ እንደቻሉ
አስፍሯል::
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631
Reporter issue-1631

More Related Content

Similar to Reporter issue-1631

Aeup pr2 082310_amharic
Aeup pr2 082310_amharicAeup pr2 082310_amharic
Aeup pr2 082310_amharictsehaydemeke
 
Haregot abreha defence minister -generals anti corruption day ppt
Haregot  abreha defence minister  -generals anti corruption day pptHaregot  abreha defence minister  -generals anti corruption day ppt
Haregot abreha defence minister -generals anti corruption day pptHeryBezabih
 
Zethiopia Newspaper Jan 2014
Zethiopia Newspaper Jan 2014Zethiopia Newspaper Jan 2014
Zethiopia Newspaper Jan 2014derejedesta
 
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.Ethio-Afric News en Views Media!!
 

Similar to Reporter issue-1631 (7)

Aeup pr2 082310_amharic
Aeup pr2 082310_amharicAeup pr2 082310_amharic
Aeup pr2 082310_amharic
 
Haregot abreha defence minister -generals anti corruption day ppt
Haregot  abreha defence minister  -generals anti corruption day pptHaregot  abreha defence minister  -generals anti corruption day ppt
Haregot abreha defence minister -generals anti corruption day ppt
 
Ethiopian hailoch ethio news
Ethiopian  hailoch ethio newsEthiopian  hailoch ethio news
Ethiopian hailoch ethio news
 
Zethiopia Newspaper Jan 2014
Zethiopia Newspaper Jan 2014Zethiopia Newspaper Jan 2014
Zethiopia Newspaper Jan 2014
 
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front EPRDF on The Run.
 
Ethiopia eritrea contradictions 2015
Ethiopia eritrea contradictions 2015Ethiopia eritrea contradictions 2015
Ethiopia eritrea contradictions 2015
 
Joint statement on_the_election
Joint statement on_the_electionJoint statement on_the_election
Joint statement on_the_election
 

Reporter issue-1631

  • 1. |ገጽ 1| ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008 የረቡዕ እትም ቅፅ 21 ቁጥር 1631 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ | ጳጉሜን 6 ቀን 1987 ተመሠረተ |ዋጋ ብር 7.00 ታህሳስ 6 ቀን 2008 FREE PRESS FREE SPEECH FREE SPRIT | ነፃ ፕሬስ ነፃ ሐሳብ ነፃ መንፈስ በኦሮሚያ ግጭት ሕይወት እየጠፋና ንብረት እየወደመ ነው በውድነህ ዘነበ ኅዳር 10 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን ምክንያት የተነሳው ግጭት፣ ለሕይወትና ለንብረት መጥፋት ምክንያት ሆኗል:: ግጭቱንና አለመግባባቱን ለማብረድ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሕዝቡን በማወያየት ሼል ቢጠመዱም፣ ግጭቱ ግን ተባብሶ በመቀጠል ሕይወት እየቀጠፈ ነው:: በተለይ በምዕራብ ወለጋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ በሚገኙ ከተሞች ለአብነትም ወሊሶ፣ ቶሌ፣ አመያ፣ ጨሊያ፣ ግንደ በረት፣ ጪቱ፣ ጉሊሶ፣ እናንጎና ጌዶ በተባሉ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ሕይወት እየጠፋና ንብረትም እየወደመ ይገኛል:: የኦሮሚያ ክልል ማረጋገጫ ባይሰጥም እስካሁን ከ30 በላይ ሕይወት መጥፋቱና ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ይነገራል:: መንግሥት ግን የተጠቀሰውን አኃዝ አይቀበልም:: ይልቁንም በተቃውሞው የተሳተፉ አምስት ሰዎች መሞታቸውን ገልጾ፣ በየአካባቢው የሚገኙ የመንግሥት ተሿሚዎችና የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን እየገለጸ ነው:: በንብረት በኩል በተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ መንግሥታዊ ተቋማት፣ የተሿሚዎች መኖርያ ቤቶች፣ የግል ኩባንያዎች ላይ ጉዳት ደርሷል:: ይህ ግጭት ተባብሶ የቀጠለው በማስተር ፕላኑ መነሻ ይሁን እንጂ ሲንከባለል በቆየ ብሶትና የመልካም አስተዳደር ዕጦት፣ ባለሥልጣናት በአደባባይ በሚሰጡት ያልተገባ መግለጫ ሕዝብ በመበሳጨቱ መሆኑን፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር አባል አቶ በቀለ ገርባ ለሪፖርተር ገልጸዋል:: ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የኦሮሚያ ክልል ምንጮች እንደሚሉት፣ ኅብረተሰቡ ለጥቃቅን አገልግሎቶች የሚጠየቀው ሕገወጥ ጉቦና በክልሉ የተንሰራፋው አድሎአዊ አሠራር የክልሉን ሕዝብ ሲያበሳጭ ቆይቷል:: በርካታ አመራሮችም በተለይ በልዩ ዞኑ በሕገወጥ መንገድ ቦታ ይዘዋል የሚለው ሌላው ጉዳይ ሲሆን፣ ማስተር ፕላኑ በእርግጥ ተግባራዊ ከሆነ በሕገወጥ ያፈሩትን ሀብት ማጣት፣ ከዚህም ከባሰ መጋለጥ የሚያመጣባቸው በመሆኑ ሕዝቡንም ውስጥ ለውስጥ ሲያነሳሱ ቆይተዋል የሚል ሐሳብ እየተሰነዘረ ይገኛል:: ክልሉን የሚመራው የኦሕዴድ አባላት ለዚህ ችግር ተገቢውን ትኩረት ካለመስጠታቸውም ባሻገር፣ ሕዝቡ መድረክ የሟቾች ቁጥር ከ30 በላይ ነው አለ በነአምን አሸናፊ ለአዲስ አበባና ለኦሮሚያ ልዩ ዞን የተዘጋጀውን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን በመቃወም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከ30 በላይ መድረሱን፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አስታወቀ:: የመድረክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ ምክትል ፕሬዚዳንትና የውጭ ግንኙነት ኃላፊው ዶ/ር መረል ጉዲናና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጥላሁን እንደሻው ይህን ያስታወቁት፣ ማክሰኞ ታኅሳስ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. በፓርቲው ጽሕፈት ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው:: ‹‹ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአዲስ አበባ ከተማን ከሕግ አግባብ ውጪ ማስፋፋት ጋር በተያያዘ በሕዝቡ ዘንድ ካደረው ሥጋት በመነሳት፣ የተቀሰቀሰውን ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞን በኃይል ለማስቆም የኢሕአዴግ መንግሥት በወሰደው ዕርምጃ በርካታ ተማሪዎችና ሌሎች ዜጎች መገደላቸውን መድረክ በእጅጉ ይኮንነዋል፤›› በማለት መድረክ በመግለጫው አስታውቋል:: ወደ ገጽ 8 ዞሯል ወደ ገጽ 8 ዞሯል በጭልጋና በመተማ ወረዳዎች የተነሳው ግጭት ሞትን ጨምሮ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ በሰለሞን ጐሹ ከኅዳር 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙት በጭልጋና በመተማ ወረዳዎች በተቀሰቀሰው ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የአማራ ክልል ገለጸ:: ግጭቱ በፈጠረው ሥጋት ዜጎች ከአካባቢያቸው እየተፈናቀሉ እንደሆነ ምንጮች ለሪፖርተር የገለጹ ቢሆንም፣ የክልሉ መንግሥት ለጉዳዩ የተሰጠው መፍትሔ አንፃራዊ ሰላም አምጥቷል ብሏል:: የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ድብቅ አጀንዳ ያላቸው አካላት በፈጠሩት ብጥብጥ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ የክልሉ መንግሥት ኃላፊዎች ከወረዳዎቹ አመራሮች፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ከኅብረተሰቡ ጋር በመመካከር በአንፃራዊነት ሰላም ለመመለሾ ተችሏል:: ታኅሳስ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው፣ በወረዳዎቹ ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት በቁጥጥር ሼር መዋሉን ገልጸው፣ በሕዝቡ መካከል ያለውን ሰላምና መረጋጋት በማናጋት ግጭቱ እንዲባባስ በሚያደርጉ ‹‹ፀረ ሰላም›› ኃይሎች ላይ ሰማያዊ ፓርቲና ኤፌኮ ለፖለቲካ ትግል የጋራ ግብረ ኃይል ሊያቋቁሙ ነው የመድረክ ምክትል ፕሬዚዳንትና የውጭ ግንኙነት ኃላፊው ዶ/ር መረል ጉዲናና ፕሬዚዳንቱ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ፎቶበሪፖርተር/መስፍንሰሎሞን ፀረ ሽብር ግብረ ኃይል በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት ደርሷል አለ የክልሉ መንግሥት ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ ወደ ገጽ 8 ዞሯል የክልሉ መንግሥት መነሻው የ‹‹ፀረ- ሰላም›› ኃይሎች ሴል ነው ብሏል ነዋሪዎች የአማራና የቅማንት ማኅበረሰቦች ግጭት ነው ብለውታል
  • 2. ገጽ 2| www.ethiopianreporter.com | ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008 ቅፅ 21 ቁጥር 1631 በጳጉሜን 6 1987 ተጀመረ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተም አድራሻ፡- ከቦሌ መድኃኒዓለም ወደ ብራስ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ከቦሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል አጠገብ ስልክ 0910-885206/ 011-661 61 79/85/87 ፋክስ: 011-661 61 89 አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 03 የቤት ቁጥር 2347 ፖስታ 7023 አ.አ ኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሽያጭና ስርጭት 0910 885206/ 011 6 61 61 79/ 85 mcc@ethionet.et E-mail: mccreporter@yahoo.com Website: www.ethiopianreporter.com በሚዲያና ኮምዩኒኬሽንስ ሴንተር (ኤም.ሲ.ሲ) ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ ፋክስ: 011-661 61 89 ዋና ግራፊክ ዲዛይነር፡ ይበቃል ጌታሁን ከፍተኛ ግራፊክ ዲዛይነር ቴዎድሮስ ክብካብ ግራፊክ ዲዛይነሮች፡ ፀሐይ ታደሰ ፋሲካ ባልቻ ስሜነህ ሲሳይ ነፃነት ያዕቆብ ቤዛዬ ቴዎድሮስ ሳሙኤል ለገሰ ዋና ፎቶግራፈር ናሆም ተሰፋዬ ፎቶግራፈሮች፡ ታምራት ጌታቸው መስፍን ሰሎሞን ካርቱኒስት፡ ኤልያስ አረዳ ከፍተኛ ሪፖርተር፡ ደረጀ ጠገናው ሪፖርተሮች፡ ምሕረተሥላሴ መኮንን ሻሂዳ ሁሴን ማርኬቲንግ ማናጀር፡ እንዳልካቸው ይማም ሴልስ፡ Hና Ó`T'wÂĄ S<K<Ñ@' ብሩክ ቸርነት፣ ራህዋ ገ/ኪዳን ማስታወቂያ ፕሩፍሪደር፡ መሳይ ሰይፉ፤ ኤፍሬም ገ/መስቀል፣ መላኩ ገድፍ ኮምፒውተር ጽሑፍ፡ ብርቱካን አባተ፣ ሄለን ይታየው፣ ቤተልሔም ታደሰ፣ ቤዛዊት መኮንን፣ መስከረም ሽብሩ፣ ሰብለ ተፈራ ማስታወቂያ ፅሁፍ: እስከዳር ደጀኔ፣ መሠረት ወንድሙ፣ ራሔል ሻወል፣ የሺሀረግ ሀይሉ ሕትመት ክትትል፡ ተስፋዬ መንገሻ፣ የየሱስወርቅ ማሞ፣ ገዛኸኝ ማንደፍሮ ዌብ ሳይት፡ ቤዛዊት ተስፋዬ፣ ቢኒያም ሐይሉ ዋና ሼል አስኪያጅ፡ አማረ አረጋዊ ማኔጂንግ ኤዲተር፡ መላኩ ደምሴ ዋና አዘጋጅ፡ ዘካሪያስ ስንታየሁ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁ. 217 ከፍተኛ አዘጋጆች፡ ዳዊት ታዬ ሔኖክ ያሬድ ሰለሞን ጎሹ አዘጋጆች፡ ምሕረት ሞገስ ረዳት አዘጋጆች፡ ታደሰ ገ/ማርያም ምሕረት አስቻለው ታምሩ ጽጌ የማነ ናግሽ ዮሐንስ አንበርብር ብርሃኑ ፈቃደ ውድነህ ዘነበ ማስታወቂያ ርእሰ አንቀጽርእሰ አንቀጽ ረቡዕ ታህሳስ 6 ቀን 2008 መንግሥት ውስጡን ይፈትሽ! ለአዲስ አበባና ለኦሮሚያ ልዩ ዞን በተዘጋጀው የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን ምክንያት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ሥፍራዎች የታዩት አመፆች፣ መንግሥት ውስጡን አብጠርጥሮ እንዲፈትሽ ያስገድዳሉ:: መንግሥት ውስጡን በሚገባ እንዲፈትሽ የሚገደደው በክልሉ ውስጥ በተከሰተው ሁከት ምክንያት የሚሰሙት ቁጣዎች፣ በአብዛኛው በመንግሥት ሹማምንት ላይ ያነጣጠሩ በመሆናቸው ነው:: መንግሥት በቃል አቀባዩ አማካይነት እንደገለጸው፣ ሁከት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች በየደረጃው ያሉ ሹማምንትና የፀጥታ ሠራተኞች የጥቃት ዒላማ ሆነዋል:: በችግሩ ዙሪያ ከሚነገሩ ዋነኛ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የመልካም አስተዳደር ዕጦት፣ የፍትሕ መጓደልና ሙስና ዋነኞቹ ናቸው:: እነዚህ መንግሥት ውስጡን እንዲፈትሽ ያስገድዳሉ:: በግንቦት 2007 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ከአጋሮቹ ጋር መቶ በመቶ የፓርላማ መቀመጫዎችን በመቆጣጠር፣ በምርጫው በሕዝብ ድምፅ ይሁንታ ማግኘቱን አረጋግጧል:: በዚህም መሠረት ቀጣዮቹን አምስት ዓመታት የሚመራ መንግሥት መሥርቷል:: ይሁንና አፍታም ሳይቆይ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የፍትሕ ዕጦትና ሙስና ጊዜ የማይሰጡ ፈተናዎች እንደሆኑበት አስታውቋል:: ወዲያው ደግሞ ለዓመታት ያህል ተንጠልጥሎ የቆየውና የሰው ሕይወት ያለፈበት የማስተር ፕላን ጉዳይ ሌላ አመፅ ቀስቅሶ፣ ሕይወት እያለፈና ንብረት እየወደመ ነው:: በዚህ ወሳኝ ጊዜ ላይ ሆኖ ነው መንግሥት ራሱን መፈተሽ ያለበት:: ከሕግ የበላይነት፣ ከሰብዓዊ መብት አጠባበቅና ከዴሞክራሲ ያፈነገጡ አሠራሮችን ያርም:: የመንግሥት አካላት የሆኑት ሕግ አውጪው፣ ሕግ ተርጓሚውና አስፈጻሚው እንዴት እየተናበቡ ነው ሥራቸውን እየሠሩ ያሉት? የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓቱ ምን ይመስላል? አስፈጻሚው አካል ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅሩ እንዴት እየሠራ ነው? ሕግ ተርጓሚው በትክክል ሥራውን እየሠራ ነው ወይ? ሕግ አውጪው (ፓርላማው) ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ወይ? በሕዝብና በእነዚህ አካላት መካከል ያለው ቅርርብ ምን ይመስላል? የሚሉትና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ይነሳሉ:: አስፈጻሚው አካል በተደጋጋሚ እንዳመነው የመልካም አስተዳደር ዕጦት ሕዝብን እያስመረረ ነው:: በደላላ የሚመራው ሙስና አገር እያጠፋ ነው:: የፍትሕ መስተጓጎል ሕዝቡን ደም እንባ እያስለቀሰ ነው:: የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት አበላሽቶታል:: መቶ በመቶ የፓርላማ መቀመጫ የያዘ መንግሥት አሁን ወሳኝ የሆነ ምዕራፍ ላይ በመድረሱ ራሱን ይፈትሽ:: ያለምንም ርህራሔ ራሱን ይገምግም:: በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ሁከት የዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ነው:: የአካል ጉዳት እያደረሰ ነው:: የንብረት ውድመትም እየታየበት ነው:: ይህ አመፅ በማስተር ፕላኑ ጉዳይ ላይ ተመሥርቶ ቢቀሰቀስም፣ አሁን አቅጣጫውን ቀይሯል:: አመፁን የሚመራ የተደራጀ ኃይል ወይም ፓርቲ በግልጽ አለመኖሩም ታይቷል:: ለዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች ውጤትም ይመስላል:: በዚህም ምክንያት ጥያቄው የሕዝብ ነው ማለት ነው:: ምንም እንኳን ሌላ ዓላማ የሰነቁ ኃይሎች በማኅበራዊ ሚዲያ መሪ ሆነው ለመታየት እየሞከሩ ቢሆንም፣ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር ያለበት ከሕዝብ ጋር ብቻ ነው:: ሕዝቡን እንወክላለን ከሚሉ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ካሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ነው:: በመሆኑም ከፓርቲዎቹም ሆነ ከሕዝቡ ጋር ሲነጋገር ውስጡን ፈትሾ መሆን አለበት:: ጠንካራ ግምገማ ማድረግ ይኖርበታል:: መንግሥት ከሕዝብ ጋር ሲነጋገር ራሱን ለትችትና ለወቀሳ ያዘጋጅ:: የነበሩትን ድክመቶች በትክክል አምኖ ሕዝቡ በግልጽ ምን እንደሚፈልግ ይረዳ:: በሕዝብ ድምፅ ተመርጫለሁ ያለ መንግሥት ከምንም ነገር በላይ ተጠሪነቱ ለሕዝብ ነው:: በመልካም አስተዳደር ዕጦት፣ በፍትሕ መጓደልና በሙስና የተመረረ ሕዝብ ጥቅሜንና ፍላጎቴን ይፃረራል በሚል ጉዳይ ላይ ተቃውሞ ሲያቀርብ፣ በሚገባ አዳምጦ ለመፍትሔ የሚረዳ አቋም ላይ መድረስ አለበት:: ሕዝብን ሲያስመርሩ የነበሩ ሹማምንት ራሳቸውን ከተጠያቂነት ነፃ ለማውጣት በሚያደርጉት ጥረት፣ ሕዝብና መንግሥት የበለጠ እንዳይቃቃሩና አላስፈላጊ መስዕዋትነት እንዳይከፈል ጥንቃቄ ይደረግ:: በመብት ጥያቄ ስም የኃይል ተግባር ውስጥ የገቡ ወገኖችንም ሕዝቡ እንዲያስቆማቸው ማድረግ የሚቻለው፣ ሕዝብና መንግሥት ሲቀራረቡ ነው:: አሁን የመንግሥት ዋነኛው ተግባር መሆን ያለበት ራሱን ፈትሾ ችግሮቹን ማወቅ ነው:: ችግሮቹ ደግሞ በተደጋጋሚ የሚገለጹት ሕዝብን የሚያማርሩ አጉል ተግባራት ናቸው:: በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለተነሳው ሁከት መነሻው ማስተር ፕላኑ ቢሆንም፣ ሕዝቡ በየደረጃው ባሉ ሹማምንት የደረሱበት የመብት ረገጣዎች የራሳቸው አሉታዊ ሚና አላቸው:: መንግሥት ይህንን የሹማምንት ጉዳይ ያለምንም ይሉኝታ ይገምግም:: አጥፊዎችን ለፍትሕ ያቅርብ:: በምትካቸው ለሕዝብ አገልጋይ የሆኑትን ይመድብ:: አሁን የቃላት ጋጋታ ሳይሆን የሚያስፈልገው ተግባራዊ ዕርምጃ ብቻ ነው:: በሕዝብ የሚቀልዱ ተገምግመው ይወገዱ:: መንግሥት ሁከቱ ከተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች ጋር በሰላማዊ መንገድ በመምከር መረጋጋት ይፍጠር:: ሕዝቡ ወደ እርሻው፣ ንግዱና ወደ መሳሰሉት ተግባሮቹ በፍጥነት ይመለስ:: ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሱ:: መደበኛው ሰላማዊ ሕይወት ይቀጥል:: በዚህ ሒደት ውስጥ የሕግ የበላይነት ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ ይሰጠው:: ዜጎች ከሰላማዊ የመብት ጥያቄ ይልቅ ወደ አመፅና ሁከት የሚያመሩት የሕግ የበላይነት ሳይከበር ሲቀር ነው:: በሙስና የሚከብሩ ሹማምንትና አጋፋሪዎቸው ሕግ ሲጥሱ፣ ሌላው ዜጋም ያንኑ መንገድ ይከተላል:: በመሆኑም ዜጎች በሕግ የበላይነት ተማምነው የመብቶቻቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጉ:: በዚህ ረገድም መንግሥት ራሱን ያለ ይሉኝታ ይፈትሽ:: ሕዝብ በማናቸውም ባልተመቹት ጉዳዮች ላይ የመብት ጥያቄ የማቅረብ ሕገ መንግሥታዊ መብት አለው:: መንግሥትም ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለበት:: በመንግሥት ውስጥ ሌላ መንግሥት የመሠረቱ የሚመስሉ ኃይሎች መንግሥትን ሕዝባዊነት ሲያሳጡ፣ ሕዝብ ከመንግሥት ጋር ይለያያል:: በዚህ ቀዳዳም ሌላ ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች በመግባት አጋጣሚውን ለግጭት ይጠቀሙበታል:: በዚህም ምክንያት ሰላማዊው ድባብ ወደ ብጥብጥ ይቀየራል:: ይህ ደግሞ ታይቷል:: በመሆኑም መንግሥት ራሱን ለወቀሳ ያዘጋጅ:: የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የመገናኛ ብዙኃንን፣ የሕዝቡንና የሌሎችን ትችቶች ይቀበል:: ችግሮቹን ያርም:: በተፈጠረው ችግር ላይ ግልጽ መረጃ ይስጥ:: ችግሮችን ማድበስበስ ይቁም:: አመፁ ተባብሶ ሰላምና መረጋጋትን እንዳያሳጣና ለሌሎች ጣልቃ ገብነት እንዳይገለጥ መንግሥት ከሕዝብ ጋር ይሠለፍ:: ሕዝብን ያዳምጥ:: ከኃይል ዕርምጃ ይቆጠብ:: የሕዝብን የልብ ትርታ ይስማ:: ውስጣዊውን ችግር ፀረ ሰላም ኃይሎች ያራግቡታል ቢባል እንኳ፣ መንግሥት በድፍረት ራሱን ፈትሾ ለመፍትሔ ይትጋ:: ከሕዝብ የሚፈለግበትን ይወጣ:: ለዚህም ውስጡን ደጋግሞ ይፈትሽ!
  • 3. |ገጽ 3 www.ethiopianreporter.com | ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008 ቅፅ 21 ቁጥር 1631 ማስታወቂያ የቤት ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ ጆሽዋ ሁለገብ ኃላፈነቱ የተወሰነ የህብረት ሾል ማህበር ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ ቤት በጨረታ መግዛት ይፈልጋል 1. የቤቱ አይነት፡ እስከ 7 ፎቅ ግንባታ የሚፈቀድለት፣ 2. የቦታው ስፋት፡ ቦታው ከ 400 ካሬ ያላነሰ ፣ 3. የቦታው ሁኔታ፡ ለቢሮ አገልግሎት ሕንፃ መገንባት በሚመች ሁኔታ የሚገኝ፣ 4. ቦታው የሚገኝበት ልዩ ስፍራ፡ ካዛንቺስ፣ ባንቢስ፣ ኦሎምፒያ፣ ሰንጋተራ፣ ሜክሲኮ፣ ጎተራ፣ አራት ኪሎ፣መገናኛ፣ ቦሌ፣ መስቀል ፍላወር፣ አካባቢ ሆኖ በዋና መንገድ ላይ የሚገኝ ወይም ለመሃል ከተማ ቅርብ የሆነ፣ 5. የቦታው ህጋዊነት፡ የይዞታ ባለቤትነት ካርታ ያለው፣ ለቅይጥ አገልግሎት ግንባታ ፕላን ስምምነት ያለው የወቅቱን የመሬት ግብር የከፈለ፣ 6. ቤቱ በባንክ/ በአበዳሪ ድርጅቶች በብድር የተያዘ ከሆነ ዝርዝር የውል ሰነድ እና ቀሪ ክፍያውን የሚገልፅ ህጋዊ ሰነድ ማቅረብ የሚችል፣ 7. ቤቱ የሊዝ ክፍያ ካለበት የሊዝ ውልና ቀሪ ክፍያ ሰነድ ማቅረብ የሚችል፣ 8. የሚፈለግበትን የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡ፣ የፍርድ ቤት ጥያቄ ክርክር የሌለበት፣ቤቱን በባለሞያ ስትራክቸራል እንዲሁም ቴክኒካላዊ ይዘቱ ለማስመርመር ፈቃደኛ የሆኑ፣ 9. መጫረት የሚችሉት የቤቱ ባለቤቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ይሆናሉ፣ 10. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ባንቢስ አካባቢ ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፣ 11. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ብር ሰላሳ ሺ ብር ብቻ):: 12. ተጫራቾች የሚሸጡትን ቤት አይነት እና ዋጋ በዝርዝር በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በመስሪያ ቤቱ ለዚህ በተዘጋጀ ቦታ ማስገባት አለባቸው፣ 13. ጨረታው ማክሰኞ ታህሳስ25/2008 ዓ.ምቀን በ6፡00 ተዘግቶ በዚያው እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታውን በገባበት ቦታ ይከፍታል:: በዚህ ወቅት ተጫራቾች ውይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ መገኘት ይችላሉ፣ 14. ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 0565/66/67/71/72፣ ወይም ከአብዬት አደባባይ ወደ ኡራኤል በሚወስደው መንገድ ኖክ ፊት ለፊ ትዝቋላ ኮምፕሌክስ ላይ 2ኛ ፎቅ በድርጅቱ ቢሮ በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል:: በዮሐንስ አንበርብር በግንባታ ላይ ከሚገኙት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ውጪ፣ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ለተያዙ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ማጋጠሙን የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች ለፓርላማው አሳወቁ:: የፓርላማው የአካባቢና የተፈጥሮ ሀብት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴርና የተጠሪ መሥሪያ ቤቶችን የ2008 ዓ.ም. የሥራ ዕቅድና የመጀመርያው ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን ሰኞ ታኅሳስ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በገመገመበት ወቅት ነው ይህ የተገለጸው:: የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የያዛቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና ፕሮጀክቶቹ ሊገጥሟቸው ለሚችሉ ችግሮች ወይም ሥጋቶች ምን ያህል ዝግጅት እንደተደረገ ማብራሪያ የጠየቀው ቋሚ ኮሚቴው፣ በዕቅድ የተያዙት ፕሮጀክቶች በፋይናንስ እጥረት ምክንያት እስካሁን ወደ ተግባር አለመግባታቸው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና በሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጓል:: ለዚህ በጀት ዓመት ወደ ተግባር እንዲገቡ በዕቅድ የተያዙት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ጨሞጋ ይዳ 278 ሜጋ ዋት፣ ገባ 214 ሜጋ ዋት፣ ሐለሌ ወራቤሳ 422 ሜጋ ዋት፣ አይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ 300 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው ፕሮጀክቶች ናቸው:: እነዚህ ፕሮጀክቶች እንዴት ወደ ትግበራ ሊገቡ እንደሚችሉ ለቀረበው ጥያቄ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሼል አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ በሰጡት ምላሽ ከላይ ለተገለጹት ፕሮጀክቶች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ከውኃ፣ ከፀሐይ፣ ከጂኦተርማልና ከንፋስ መገኘት የሚችሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎችን ከነቦታቸው መለየታቸውን ገልጸው፣ ‹‹እንዴት እንገነባቸዋለን የሚለው ጥያቄ አለ:: ምክንያቱ ደግሞ የፋይናንስ እጥረት ነው፤›› ብለዋል:: በዚህ የተነሳም በዚህ ዓመት ተግባራዊ መደረግ የሚገባቸውን ፕሮጀክቶች በመለየት፣ አብዛኞቹ በውጭ ኢንቨስትመንት እንዲገነቡ መወሰናቸውን ገልጸዋል:: ‹‹ይኼም ማለት የውጭ አልሚዎች በዕቅድ ለተያዙ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ማጋጠሙ ለፓርላማው ተገለጸ የአገር ውስጥ ባንኮችና የውጭ ኢንቨስተሮች በአማራጭነት ታይተዋል ኢንጂነር አዜብ አስናቀ በዮሐንስ አንበርብር የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውኃና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ዓርብና ቅዳሜ በሱዳን ባደረጉት ስብሰባ ኢትዮጵያ በግብፅ ለተነሱ ሥጋቶች ከሁለት ሳምንት በኋላ ምላሽ ይዛ ለመቅረብ ተስማማች:: ሦስቱ አገሮች ላለፉ ዘጠኝ ስብሰባዎች በጋራ የቴክኒክ ኮሚቴዎቻቸው አማካይነት ሲወያዩ የቆዩ ቢሆንም፣ የታላቁን የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ እንዲያጠኑ በተመረጡ ሁለት ኩባንያዎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመቅረፍ ጊዜ ፈጅቶባቸዋል:: ይህ አሳስቦኛል የምትለው ግብፅ ቀጣዩ ስብሰባ ከሦስቱም አገሮች በሚወከሉ ሁለት ሁለት ሚኒስትሮች አማካይነት ፖለቲካዊ ውይይት እንዲካሄድ በጠየቀችው መሠረት ነው ውይይቱ የተካሄደው:: በግብፅ በኩል በዋናነት ከተነሱት አጀንዳዎች መካከል የህዳሴው ግድብ ግንባታ ከውይይቱ ጋር ሲነፃፀር በፍጥነት እየተከናወነ በመሆኑ፣ ውይይቱ መሾመር እስኪይዝ ድረስ ግንባታው እንዲቆም ጥያቄ አቅርባለች:: ኢትዮጵያ በግብፅ ሥጋቶች ላይ ምላሽ ይዛ ለመቅረብ ተስማማች ወደ ገጽ 34 ዞሯል በውድነህ ዘነበ ከንግድ ይልቅ ወደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እንዲያዘነብሉ ግፊት ሲደረግባቸው የቆዩ ባለሀብቶች፣ በአሁኑ ወቅት እየተገነቡ ባሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ቦታ የሚያገኙበትን መንገድ የሚያመቻች ኮሚቴ ተቋቋመ:: ኮሚቴው በኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አብተው የሚመራ ሲሆን፣ ንግድ ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በአባልነት ተካተዋል:: ታኅሳስ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ከኤምኤች አማካሪ ድርጅት ዶ/ር መሰለ ኃይሌ ጋር መግለጫ የሰጡት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ገመቹ፣ ኮሚቴው የአገር ውስጥ ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ዞኖች ውስጥ ቦታ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ገልጸዋል:: ‹‹የአገር ውስጥ ባለሀብቶች እንደፍላጎታቸው የፋብሪካ ሕንፃዎችን ተከራይተው፣ በለማ መሬት ላይ የራሳቸውን ግንባታ እንዲያከናውኑ ለማድረግ የፓርኮቹ ዲዛይን ተዘጋጅቷል፤›› ብለዋል:: መንግሥት በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን አሥር ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት አቅዷል:: ከሚገነቡት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ቁጥር ሁለት 186 ሄክታር፣ ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ 275 ሄክታር ይለማል:: በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ላሳዩ ነጋዴዎች ቦታ የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቋመ ወደ ገጽ 34 ዞሯል ወደ ገጽ 33 ዞሯል
  • 4. ገጽ 4| www.ethiopianreporter.com | ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008 ቅፅ 21 ቁጥር 1631 ማስታወቂያ
  • 5. |ገጽ 5 www.ethiopianreporter.com | ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008 ቅፅ 21 ቁጥር 1631 ማስታወቂያ OFFRE D’EMPLOI : ASSISTANT(E) ADMINISTRATIF(VE) L’Alliance ĂŠthio-française d’Addis-Abeba recrute un(e) assistant(e) administratif(ve) Poste Ă  pourvoir immĂŠdiatement Missions principales auprès du Directeur et de l’Administrateur : ADMINISTRATIF : • RĂŠdaction de documents de diffĂŠrents types (rapports, notes, formulaires, tableau Excel, lettres, …) • SecrĂŠtariat (prise de contact, organisation de rĂŠunion, accueil, traduction, …) COMPTABILITÉ : • PrĂŠparer et vĂŠrifier diffĂŠrents documents comptables (salaires, rapports financiers mensuels, . . .) • Saisie comptable. Cette liste n’est pas exhaustive, l’employĂŠ(e) sera appelĂŠ(e) Ă  accomplir d’autres taches en fonction des besoins de l’AEF. Profil recherchĂŠ : Bon niveau, oral et ĂŠcrit, en français, anglais et amharique. Parfaite maitrise de la suite Microsoft Office (Word, Excel, power point) Notions en comptabilitĂŠ Connaissance de l’application Quick Book Accounting QualitĂŠs souhaitĂŠes : Rigueur/sens de l’organisation, dynamisme, qualitĂŠ relationnelle, flexibilitĂŠ, disponibilitĂŠ le soir, capacitĂŠ Ă  travailler en autonomie et en ĂŠquipe. Salaire : nĂŠgotiable Depot de candidature Les candidatures doivent ĂŞtre dĂŠposĂŠes impĂŠrativement avant le 6 janvier 2016 soit par mail (comptabilite@allianceaddis.org) soit Ă  l’Administrateur en personne. Toute candidature devra comprendre un curriculum vitae complet accompagnĂŠ d’une lettre de motivation. Invitation of Qualified Firms for Audit Work The Population Council Inc. is an international NGO working in three main areas: HIV and AIDS, reproductive health and poverty, gender and youth. The Population Council would like to invite qualified and registered audit firms those are recognized by the Charities and Societies Agency to submit their proposals to be appointed as external auditor to undertake the audit of its accounts. Eligibility criteria: Any authorized audit firm who qualify to apply shall therefore fulfill the following minimum criteria for eligibility 1. Relevant experience for at least 4 years in the INGO sector 2. Renewed trade license of the current year 3. Who meets the qualification criteria by Charities and Societies Agency and currently in the list 4. VAT and Tin registration certificate 5. Chartered/Certified Accountant Certificate (Certificate of professional competence) 6. Who can commit contractual obligation for the next 3 (three) fiscal periods. Procedures: Qualified candidate audit firm can submit in the following procedures 1. Submit financial and technical proposals separately in a sealed envelope to Population Council-Ethiopia Office within 10 working days starting from the next date of bid announcement as appeared in the news paper 2. Selection will be only based on the above criteria and who should submit competitive price with clear mode of payment. Any government tax should be included in the proposal 3. Only shortlisted candidates will be contacted for further discussion and negotiation All Proposals should be submitted to: The Population Council Inc. Ethiopia Office from December 17 – December 30, 2015 between 8:00am – 5:00pm from the following address: The Population Council Inc. Heritage Plaza Building 4th floor Near Brass Hospital, opposite the Tanzania Embassy on the Bole Medhanealem Road P.O. Box 25562 Code1000 Tel 0116631712/14/16 Addis Ababa በዮሐንስ አንበርብር በኢትዮጵያና በቱርክ መንግሥታት መካከል የተፈረመውን ለኤምባሲ፣ ለሚሲዮን መሪዎችና ለዲፕሎማቶች መኖሪያ ግንባታ የመሬት ልውውጥ ስምምነት ለማፅደቅ የቀረበው አዋጅ ፓርላማውን አነጋገረ:: የስምምነቱ ማፅደቂያ ረቂቅ አዋጅ አባሪ እንደሚገልጸው ስምምነቱ የተፈረመው እ.ኤ.አ. በዲሴምበር 2010 ነው:: የስምምነቱ ዓላማም በኢትዮጵያና በቱርክ መካከል እያደገ የመጣውን የንግድ፣ የቱሪዝም፣ የኢንቨስትመንት፣ የቱሪዝምና የተለያዩ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ትብብሮች የበለጠ ለማጠናከር ነው:: የስምምነቱ መሠረት የቱርክ መንግሥት 3,000 ካሬ ሜትር ከክፍያ ነፃ የሆነ መሬት በቱርክ አንካራ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ የተከለለ ቦታና ለሚሲዮን፣ ለአምባሳደር መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል መሬት የመስጠት ግዴታን ያስቀምጣል:: በአፀፋው ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት 7,192.8 ካሬ ሜትር በአዲስ አበባ የሚገኝ ለሚሲዮን፣ አምባሳደርና ዲፕሎማቶች መኖሪያ ግንባታ የሚውል መሬት ለመስጠት ግዴታ መግባቱን በስምምነቱ ላይ ተጠቅሷል:: የኢትዮጵያ መንግሥት ከሚያቀርበው 7,192.8 ካሬ ሜትር ውስጥ፣ 4,192.8 ካሬ ሜትር የሚሆነው መሬት 3,200,000 ዶላር ሊዝ የሚከፈልበት መሆኑ ስምምነት ተደርጓል:: የግንባታ ቦታው የሚሰጠው በሰጥቶ መቀበል መርህ ሆኖ፣ ሁለቱም ወገኖች መሬቱን የሚጠቁሙበት የዲፕሎማቲክ ተልዕኳቸውን ለማሳካት ብቻ መሆኑን ስምምነቱ ይገልጻል:: እያንዳንዱ ወገን ፕሮጀክቱንና ግንባታውን መቼ እንደሚጀምር በግሉ መወሰን እንደሚችል በስምምነቱ የተገለጸ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ተፈጻሚ በሚሆንበት ወቅት እያንዳንዱ ወገን መሬቱን የሰጠውን አገር ሕግ ደንብና ቴክኒካዊ መሥፈርቶች በኢትዮጵያና በቱርክ መካከል የተደረሰው ለዲፕሎማቶች መኖሪያ የመሬት ልውውጥ ስምምነት ፓርላማውን አነጋገረ በዳዊት ታዬ በኢትዮጵያ የመንገድ ግንባታ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ ነው የተባለው የዲዛይንና የጥገና ሥራውን አጠቃልሎ ለአንድ ኮንትራክተር የሚያሰጥ አዲስ የግንባታ አሠራር፣ 256 ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው የነቀምት-ቡሬ መንገድ ላይ ተግባራዊ ሊደረግ ነው:: ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው የዲዛይን፣ የግንባታና የጥገና ሥራን አጠቃልሎ ለአንድ ኮንትራክተር ለመስጠት የሚያስችለው የነቀምት- ቡሬ መንገድ ፕሮጀክት ዓለም አቀፍ ጨረታ ሒደትም በመጠናቀቅ ላይ ነው:: የባለሥልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ለዚህ መንገድ ግንባታ ተወዳዳሪ ኮንትራክተሮች ያቀረቡት ዋጋና ሌሎች መወዳደሪያ መሥፈርቶች እየተገመገሙ ናቸው:: በቅርቡም ውጤቱ ይፋ ሆኖ ጨረታውን ከሚያሸንፉ ኮንትራክተሮች ጋር ስምምነት ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል:: በአዲሱ አሠራር የነቀምት-ቡሬ መንገድን ለመገንባት በወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ከስምንት በላይ የሚሆኑ የቻይና፣ የህንድ፣ የቱርክና የስፔን ኮንትራክተሮች ተፎካካሪ ሆነው ቀርበዋል:: 256 ኪሎ ሜትሩ የመንገድ ፕሮጀክት ለሦስት ተከፍሎ ለሦስት ኮንትራክተሮች የሚሰጥ መሆኑንም፣ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ ያስረዳል:: የነቀምት-ቡሬ መንገድ ግንባታ በዚህ ዓመት ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑም ይኼው ከባለሥልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል:: በአገሪቱ የመንገድ ግንባታ ልምድ አንድ ኮንትራክተር ግንባታውን ብቻ እንዲያከናውን፣ ዲዛይኑ ደግሞ በሌላ አማካሪ ድርጅት እንዲከናወን ይደረግ የነበረው ኮንትራት ለረጅም ጊዜ ሲሠራበት ቆይቷል:: ቆየት ብሎም በአንዳንድ ፕሮጀክቶች ላይ ደግሞ ዲዛይንና ግንባታውን በማጣመር እንዲሠራ እየተደረገ እንደነበርም ይታወሳል:: የዲዛይንና የጥገና ሥራን በአንድ ያጠቃለለ አዲስ የግንባታ አሠራር ተግባራዊ ሊሆን ነው አዲሱ አሠራር ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ በሚፈጀው የነቀምት-ቡሬ መንገድ ላይ ይጀመራል በብርሃኑ ፈቃደ ዓመታዊው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ ልማት ሪፖርትን ለመላው ዓለም ከኢትዮጵያ ይፋ ለማድረግ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ አገሮች ርካሽ ጉልበትን እንደ መልካም የኢንቨስትመንት ዕድል ሲያስተዋውቁ የጉልበት ብዝበዛ እንዳይፈጸም መጠንቀቅ እንዳለባቸው የፕሮግራሙ ኃላፊ አሳሰቡ:: በተመድ የልማት ፕሮግራም አድሚንስትሬተር ሔለን ክላርክ በአዲስ አበባ ተገኝተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር በመሆን፣ እ.ኤ.አ. የ2015 የሰብዓዊ ልማት ሪፖርትን ይፋ አድርገዋል:: ሪፖርቱን በ25ኛ ዓመቱ መባቻ ላይ ‹‹ሥራ›› ላይ ያተኮረው የተመድ ልማት ፕሮግራም፣ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በማለት ርካሽ ጉልበትን መስህብ ሲያደርጉት ይታያል ብሏል:: የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ደግሞ በወር ከሃምሳ ዶላር ያልበለጠ ደመወዝ እየተከፈላቸው የሚሠሩ ሠራተኞች ያሉባት አገር በመሆኗ፣ ለኢንቨስትመንት ምቹ ከሚያደርጓት መካከል አንዱ እንደሆነ ይገልጻል:: በአንፃሩ የተመድ የሰብዓዊ ልማት ‹‹ሥራ ለሰብዓዊ ልማት›› በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው የተመድ ልማት ፕሮግራም ኃላፊ ‹‹ርካሽ ጉልበት›› ብዝበዛ ማለት አይደለም ሲሉ አሳሰቡ ወደ ገጽ 8 ዞሯልወደ ገጽ 8 ዞሯል ወደ ገጽ 8 ዞሯል
  • 6. ገጽ 6| www.ethiopianreporter.com | ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008 ቅፅ 21 ቁጥር 1631 ማስታወቂያ |ገጽ 7 www.ethiopianreporter.com | ረቡዕ | ኅዳር 29 ቀን 2008 ቅፅ 21 ቁጥር 1629 ማስታወቂያ መሬት በላይ ማልማት የሚችል መሆኑን የገለጹት አቶ ያረጋል፣ እስከ 2007 በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ በከርሰ ምድር ውኃ ተጠቅመው በመስኖ ማልማት የተቻለው ግን 1,700 ሔክታር ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል:: በሰሜን ወሎ ዞን በሦስቱ ወረዳዎች መቆፈር ከነበረባቸው 450 ጉድጓዶች ውስጥ ግንባታቸው የተጠናቀቀው 82 ብቻ ናቸው:: ከእነዚህ ጉድጓዶች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ወደ አርሶ አደሮቹ ማሳ ውኃ ሳይለቁ ተዘግተው ተቀምጠዋል:: መቆፈር የነበረባቸውን ያህል ጉድጓዶች ያለመቆፈራቸውም ፕሮጀክቱ ተይዞለት በነበረው ዕቅድ መሠረት ያልተከናወነ ስለመሆኑም ያመላክታል:: እንደ ቆቦው ሁሉ በደቡባዊ ትግራይ ዞን በተመሳሳይ መንገድ እንዲገነቡ በዕቅድ ተይዘው የነበሩ ጉድጓዶች ያለመቆፈራቸውን፣ ከተቆፈሩት ውስጥም ወደ ሼል የገቡት የተወሰኑ መሆናቸው በአካባቢ ለታየው ድርቅ መባባስ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል:: በደቡባዊ ትግራይ ዞን ተስፋ ከተጣለባቸውና ግንባታቸው ከተጠናቀቁ 125 ጉድጓዶች ውስጥ 36ቱ ብቻ ሼል ላይ መዋላቸውንም የወረዳው ኃላፊዎች ይገልጻሉ:: የጉድጉዶቹ ወደ ሼል አለመግባት ደግሞ በድርቅ ወቅት በቀላሉ አምርተው ድርቁን መቋቋም እንዳላስቻላቸው ይናገራሉ:: የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ አያሌው እያሱ፣ ‹‹እነዚህ ጉድጓዶች ቢለቀቁ ኖሮ ዘንድሮ ለድርቅ ባልተጋለጥን ነበር፤›› በማለት ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ጉድጓዶች ያለ ሼል መቀመጣቸው ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል:: የትግራይ ደቡባዊ ዞን የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረ እግዚአብሔር አረጋዊ እንደገለጹት ከሆነ ደግሞ፣ በራያ አላማጣ ወረዳ ከተገነቡት 84 ጉድጓዶች ሼል ላይ የዋሉት 46 ናቸው:: ከእነዚህ ውስጥ ቀድሞ በራያና አዘቦ ደግሞ ከተገነቡት 125 ጉድጓዶች ውስጥ ሼል የጀመሩት 35 ብቻ መሆናቸውንም አስታውሰዋል:: 90 የሚሆኑ ጉድጓዶችም ከጥቅም ውጪ ሆነዋል:: ጉድጓድ ተቀፍሮ ውኃው ወደ ማሳቸው የገባላቸውና በመስኖ የሚጠቀሙ አርሶ አደሮች ወቅታዊውን ድርቅ መቋቋም ሲችሉ፣ በቅርብ ርቀት የተቆፈሩት ጉድጓዶች ተዘግተው የተቀመጡባቸው አርሶ አደሮች ደግሞ ማምረት ባለመቻላቸው እጃቸውን ለዕርዳታ ዘርግተዋል:: እንደተዘነጋ የሚቆጠረው ይህ ፕሮጀክት በ2007 ዓ.ም. ከተከሰተው ድርቅ ጋር ተያይዞ ትኩረት የተሰጠው ቢመስልም፣ አሁንም ጉድጓዶችን ከፍቶ ወደ ማሳ ውኃ እንዲያሰራጩ የተደረጉት ጥቂቶች ብቻ ናቸው:: ሙሉ ለሙሉ ግንባታቸው ባይጠናቀቅም በሰሜን ወሎ ዞን አዲስ ቀኝ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ የጉድጓድ ውኃን ወደ ማሳ በመልቀቅ ወደ 200 የሚጠጉ የአርሶ አደሮች ማሳ ውስጥ እንዲገባ መደረግ ተጀምሯል:: እንዲህ ማድረግ ከተቻለ ሌሎቹንም ጉድጓዶች ሼል አስጀምሮ ድርቁን መከላከል ይቻል እንደነበር የተመለከቱ አርሶ አደሮች በሁኔታው ማዘናቸውን ገልጸዋል:: በአዲስ ቀኝ ቀበሌ የጉድጓድ ውኃው እንዲሳብ የተደረገው ጄኔሬተር ተገጥሞ ሲሆን፣ ከዚህ ጉድጓድም በሰከንድ 70 ሊትር ውኃ በማመንጨት ወደ ማሳዎቹ ሲገባ በጉድጓዱ ዙሪያ ማሳ ያላቸው ገበሬዎችን ተስፋ አለምልሟል:: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስቸኳይ ውሳኔ ጄኔሬተር እንዲገባና አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየውን የጉድጓድ ውኃ ሼል ለማስጀመር ቢቻልም፣ በአካባቢው ካለው ፍላጎት አንፃር ዕርምጃው እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን የሚናገሩ አሉ:: አቶ ያረጋል እንዳሉት ግን ተጨማሪ አራት ጉድጓዶችን ሼል ለማስጀመር የአራት ጄኔሬተሮች ግዥ በመፈጸሙ በአካባቢው በድርቁ የተከሰተውን ችግር እንዲህ ባለው የመስኖ ሼል ለመታደግ ጥረት እየተደረገ ነው:: ከእነዚህ ጉድጓዶችም በሁለትና በሦስት ወራት ውስጥ እስከ 4,500 ሔክታር ለማልማት ዕቅድ መያዙንም ገልጸዋል:: ይሁን እንጂ እስካሁን በጉድጓዶቹ ውኃ ተጠቅመው እያለሙ ያሉ አርሶ አደሮች ከፍተኛ ጠቀሜታ እያገኙ መሆኑን የተመለከቱ የአጎራባች ቀበሌ አርሶ አደሮች፣ እነሱም ጉድጓዶቻቸው ተከፍተው እንደ ጎረቤቶቻቸው ማልማት የሚሹ መሆኑን በመግለጽ አቤቱታቸው ምላሽ እንዲያገኝ እየተማፀኑ ነው:: በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በጎረቤት ቀበሌ አምናና ዘንድሮ የተከፈቱት ጉድጓዶች የሚለቁትን ውኃ በመጠቀም በመስኖ ያለሙት አርሶ አደሮች፣ በዓመት ሦስት ጊዜ እያመረቱ በመሆናቸው ይህ ዕድል ‹‹ለሁላችንም መድረስ አለበት፤›› ይላሉ:: ‹‹እኛ የዘራነው እህል ፍሬ አልባ ሲሆን፣ እነሱ ድርቁ አልዳበሳቸውም:: ነገር ግን ከከርሰ ምድር ውኃ በማውጣት ለመስኖ ሊውሉ ይችላሉ የተባሉ ጉድጓዶች ተዘግተው እኛ የበይ ተመልካች ሆነናል፤›› በማለት የጉድጓዶቹ አለመከፈት እንዳሳዘናቸው አንድ አርሶ አደር ወደ ገጽ 22 ዞሯል ሪፖርተር፡- የመረጃ ነፃነት ሕጉ ኅዳር 15 ቀን 2001 ዓ.ም. ከወጣ በኋላ ባሉት ዓመታት ምን ዓይነት ለውጦች ታይተዋል? ዶ/ር ደረጀ፡- ሕጉ በ2001 ዓ.ም. የወጣ ቢሆንም የሕጉን አፈጻጸም የሚወስኑ ቅድመ ዝግጅቶች መደረግ ነበረባቸው:: ሕጉ ልሹ እስከ ሦስት ዓመት የሚደርስ የዝግጅት ጊዜን ይፈቅዳል:: ከሕጉ ጋር ተያይዘው የመጡ መርሆዎች በርካታ ረጅም ዘመን የወሰዱ አሠራሮችንና አስተሳሰቦችን መለወጥ ግድ የሚሉ ናቸው:: ስለዚህ ከ2004 ዓ.ም. በኋላ በነበሩት ጥቂት ዓመታት ይኼ ነው የሚባል ትርጉም ያለው ለውጥ መጠበቅ ተገቢ አይመስለኝም:: መጠነኛ የሆነ የለውጥ አዝማሚያ አሳይቷል:: ሪፖርተር፡- ሼር የሰደደው የሕዝቡና የመንግሥት አሠራር ባህል ሚስጥራዊነትን ያበረታታል:: ይህን ለመቀየር ሕጉ ምን ሚና ይኖረዋል? ዶ/ር ደረጀ፡- አዋጁ ከመውጣቱም በፊት የመረጃ ነፃነት በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠ መብት ነው:: ሕገ መንግሥቱ ተግባራዊ በሆነባቸው ሃያ ዓመታት አንዳች ነገር መኖር አለበት:: ከዜሮ የሚጀመር አይደለም:: ጥናቱ የሚያሳየው ይህንን መሠረታዊ የሆነ የእሴት ለውጥ የሚጠይቅ ሕግ ተፈጻሚ ለማድረግ እጅግ በጣም ብዙ ርቀት እንደሚቀር ነው:: የመረጃን ዋጋ ከመረዳት አንፃር ያለው ባህል ሕጉ ከሚያልመው እውነታ በብዙ ርቀት የሚገኝ ነው:: የተለየ ንቃት ያላቸው ጥቂት ተቋማት አሉ:: የሕጉ መሠረታዊ መነሻ በመንግሥታዊ ተቋማት ይዞታ የሚገኝ መረጃ የሕዝብ ነው፣ ተቋማቱ ባለአደራዎች ናቸው የሚል ነው:: በተጨባጭ በተቋማቱና ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው:: በቅርቡ በመረጃ ነፃነት ሕጉ አፈጻጸም ላይ በሒልተን ሆቴል የተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ዶ/ር ደረጀ የመነሻ ጥናት አቅርበው ነበር:: በውይይቱ ላይ በቀረበው ጥናትና በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ሰለሞን ጎሹ አነጋግሯቸዋል:: ‹‹የመንግሥት ሥልጣን ላይ ሕግን መሠረት ያደረገ ልጓም የሚያደርጉ ተቋማት መፍጠር ለኢትዮጵያ አሁንም ፈተና ነው›› ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ተባባሪ ፕሮፌሰር ጉዳዩ በሚመለከታቸው ኃላፊዎች ዘንድ ያለው አመለካከት ግን የዚህ ቀጥተኛ ተቃራኒ ነው:: ሪፖርተር፡- በውይይቱ ተሳታፊዎች መንግሥት ሕጉ እንዲወጣ ከማድረግ ባሻገር፣ ተፈጻሚነቱን የመከታተል ቁርጠኝነት የለውም የሚል ወቀሳ ተሰንዝሯል:: ከሌሎች አገሮች አንፃር ሕጉን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ የወሰደው የዝግጅት ጊዜ በዝቷል ማለት ይቻላል? ዶ/ር ደረጀ፡- የመረጃ ነፃነት ሕግን ነጥሎ ማውጣት የቅርብ ጊዜ ጅምር ነው:: መሠረታዊው ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ዳብሮ ሼር የሰደደባቸው እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ውስጥ ለብዙ ዘመናት ይህንን ሕግ ማውጣት አስፈላጊ አልነበረም:: ነገር ግን ሕጉ ባለመውጣቱ መብቱ በመሠረታዊ ደረጃ የተገደበ አልነበረም:: በኢትዮጵያም ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትንና ለዚህም አስፈላጊ የሆኑ ተዛማጅ መብቶችን እውን ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ ቢሆን ኖሮ፣ የዝግጅት ጊዜው ማጠርና መርዘም አያከራክረንም ነበር:: ምናልባትም ሕጉ መውጣቱ መንግሥታዊ ተቋማት የመረጃ አደረጃጀት ሥርዓታቸውንና ግንዛቤያቸውን በመለወጥ ረገድ አስገዳጅ ኃይል ያለው በመሆኑ ጥሩ ነው:: ሪፖርተር፡- ሕጉ በመንግሥት ወይም በገዥው ፓርቲ ፍላጎት ሳይሆን ሻል ባሉ ጥቂት ተራማጅ ግለሰቦች ግፊት ብቻ እንደወጣ አስተያየት ቀርቦ ነበር:: በዚህ ይስማማሉ? ዶ/ር ደረጀ፡- አስተያየቱ ወሳኝ የሆነ የአገራችንን ማኅበረ ፖለቲካዊ ጉዳይ የሚያነሳ ነው:: መርሁ በሕገ መንግሥቱ ያለ ነው:: ባለፉት 20 ዓመታት ይህ ተፈጻሚ ሳይሆን ለምን እንደቀረ እንደ አንድ መላ ምት ሊወሰድ ይችላል::
  • 7. |ገጽ 7 www.ethiopianreporter.com | ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008 ቅፅ 21 ቁጥር 1631 ማስታወቂያ ለትራንስፖርት አገልግሎት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ኢስት አፍሪካን ታይገር ብራንድስ ኃ/የተ/የግል ኩባንያ መነሻ አዲስ አበባ ከተለያዩ ቦታ ሆኖ መድረሻ ቢሾፍቱ ከከተማዉ መግቢያ ኖክ ማደያ ሳይደርስ ወደ ቀኝ ታጥፎ 2.5 ኪ.ሜ በመግባት፤ መነሻዉ ከቢሾፍቱ እና ዱከም የተለያዩ ቦታዎች ሆኖ መድረሻዉ ኢ.አ.ታ.ብ.አ ከመንገድ 2.5 ኪ.ሜ ገባ ብሎ ሰራተኞችን ማስገባትና ማስወጣት የሚችሉ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: በዚህም መሰረት -- የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ -- ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ -- ለመኪናዎቻቸዉና ለተሳፋሪዎች የደህንነት ኢንሹራንስ የገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ -- በመስመር ላይ ያለ ተሽከርካሪ ቢበላሽ ወዲያዉኑ ሊተኩ የሚችሉ -- ለሠራተኛዉ ምቹ የሆነ አቧራ የማያስገቡና በርና መስኮታቸዉ የሚዘጉና የሚከፈቱ ፅዳት ያላቸዉ ተሽከርካሪዎችን ሊያቀርቡ የሚችሉ -- ተጫራቾች ቢያንስ ሶስት የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ ባለንብረት ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ሊብሪ ሊያቀርብ የሚችል -- ተጫራቾች ከ25 እስከ 63 ተሳፋሪዎች ሊይዙ የሚችሉ ተሽከርካሪዎችን ማቅረብ የሚችል -- ካምፓኒዉ የሚያወጣዉን የጋራ መመሪያ እና ስርዓት ማክበር የሚችል -- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10000 በ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል -- የጨረታ ሰነዱ ከታህሳስ 7 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 11ቀን 2008 ዓ.ም በግንባር በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መግዛት ይቻላል -- የጨረታ ሰነዱ ታህሳስ 12ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ተወካዮች እና ባለንብረቶች ባሉበት ይከፈታል -- በጨረታዉ የተሸነፍ ወገኖች ያስያዙት CPO ሆነ ጥሬ ገንዘብ ወዲያዉኑ ተመላሽ ይደረጋል -- የጨረታ ሰነዱን በዋናዉ ቢሮ ቀርቦ መግዛት ይቻላል -- ኩባንያዉ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ:: -- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-15-29-03 ወይም 09 11 60 82 30 ደዉለዉ ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ ኢስት አፍሪካን ታይገር ብራንድስ ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ Invitation for Bid Drilling of five (5) Water Wells Bid reference No: GTLI/HQ/224/2015 1. Global Team for Local Initiatives (GTLI), an international NGO working in South Omo Zone, SNNPR, invites interested contractors to carry out the drilling and installation of hand pumps of five (5) water wells in different kebeles of Dasenech Woredas of South Omo Zone, SNNPRS. The overall assignment will be drilling, installation of hand pumps, pump test, head work and cattle trough constructions for five (5) water wells. The project sites are located in five kebeles, which are all accessible, within a range of 13-48 kms from Omorate town which is 840 km from Addis Ababa. The anticipated depths of the boreholes range from 65 to 96m. Details are provided in the bid document. 2. Eligible water well drilling and rehabilitation general contractors (GC) or WC of Grade 4 and above are invited to bid for the drilling & construction of boreholes for the project sites indicated above. The contractor is expected to supply one drilling rig & related machinery of the required specification for the work, deploy skilled & semi-skilled labours, and accomplish the activities as per the design, drawings and specification provided within Eight Weeks’ time, from the date of signing contract. Subcontracting out the drilling works is strictly forbidden. 3. Financing by: USAID 4. Eligible bidders are invited to take part in the bid upon submission of copies of all relevant renewed licenses, VAT & tax payer’s registration certificate. 5. Bidding will be conducted through open local tender procedure. 6. The bid document may be purchased from Global Team for Local Initiatives (GTLI), Gollagul Building, Suite 1113, Addis Ababa, Ethiopia, 011.662.9937or Field Coordination Office, Turmi, Hamar Woreda, Tell.046 899 0640, with payment of non- refundable fee of Birr 100.00 during office hours. 7. All bids must be accompanied by a bid bond amounting 1% of the total bid amount including VAT, in the form of C.P.O. Bid bond in any other form shall not be acceptable. 8. All bids must be submitted one original marked “original” and one copy signed in the same way as the original and marked “copy” by stating the title, with wax-sealed envelope at or before 5:00 P.M.(afternoon) on Tuesday, 22nd December 2015.The technical and financial offer must be placed together in a sealed envelope. 9. Bids will be opened in the presence of bidders and/or their official representatives who wish to attend at Gollagul Building, Suite 1110, on Wednesday, 23rd December 2015 at 11:00 AM (morning). 10. Failure to comply with any of the conditions indicated above will result in automatic rejection. 11. The Organization reserves the right to accept or reject any or all bids. Global Team for Local Initiatives (GTLI) ወደ ገጽ 34 ዞሯል ሕጉ ተግባራዊ የማይሆነው በእምነት ወይም በቁርጠኝነት እጦት ከሆነ በጣም አደገኛ ነው:: የማን እምነትና የማን መለኪያ የሚለውን ካነሳን ችግር ነው:: ዝም ብሎ እመኑኝ እኔ ቁርጠኛ ነኝ ማለት አይቻልም:: በሠለጠነ ሥርዓት ውስጥ እመኑኝ ዋስትና ሊሆን አይችልም:: ሁሉም ሊተማመኑበትና ሊገዙበት የሚችለው የሕግ ቃል ኪዳን አለ:: ሕጉ ከየትም ቢቀዳ ተፈጻሚነቱ ተግባራዊ የሚደረገው ሁሉም ላይ ነው:: ሕግ ማውጣት በራሱ ተፈጻሚነቱን ግን አያረጋግጥም:: የሕጉ ተፈጻሚነት የሚወሰነው ሕጉ ሊተገበር ባለበት ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መድረክ ላይ ባለው ከባቢ ሁኔታ ነው:: በዚህ ሁኔታ ውስጥ የገዥው ፓርቲ ልሂቃን ያላቸው እምነትና ፍልስፍና ቁልፍ ነው:: በሕገ መንግሥቱ የሰፈረውም ሆነ በመረጃ ነፃነት ሕጉ የተካተቱት መሠረታዊ መርሆዎች ያለምንም ጥያቄ የሊበራል እሴቶች ናቸው:: የኮሙዩኒስት እሴቶች አይደሉም፣ የአምባገነን እሴቶች አይደሉም:: ስለዚህ የገዥው ፓርቲ ልሂቃን እነዚህን እሴቶች የማያምኑባቸው ከሆነ በጣም አስቸጋሪ ነው:: ለአንድ ርዕዮተ ዓለም ድጋፍ መስጠት ወይም ማጣጣል መብት ነው:: ነገር ግን በአገሪቱ የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ከገባ ብትወድም ባትወድም ለዚያ መገዛት አለብህ:: ባትገዛ ደግሞ ተጠያቂ የምትሆንበትን ሥርዓት መዘርጋት ግድ ነው:: ይህ በሌለበት ሁኔታ በሥልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ልባቸው የማይወደው ሕግ ተፈጻሚ ይሆናል ብሎ ማሰብ እጅግ የዋህነት ነው:: ሪፖርተር፡- ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 29(6) እና (7) ላይ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ገደብ የሚጣልበትን አካሄድ ደንግጓል:: በመረጃ ነፃነት ሕጉ ላይ የተዘረዘሩት ገደቦች ብዛትና ገደቦቹን ለመግለጽ የሚያሻሙና የሚያምታቱ፣ ግልጽነት የሚጎላቸው ቋንቋዎችን መጠቀሙ ክፍተት መፍጠሩም ይነገራል:: በዚህ ግምገማ ይስማማሉ? ዶ/ር ደረጀ፡- መረጃ የማግኘት መብት ገደብ የማይጣልበት ፍፁም መብት አይደለም:: በሁሉም አገሮች ተሞክሮ የሚንፀባረቅ ነው:: መረጃ በሙሉ ለሕዝብ ተደራሽ መሆን አለበት የሚለው ገዥ መርህ ነው:: ስለዚህ መረጃ መከልከል ልዩ ሁኔታ ነው:: የክልከላ ምክንያቶቹን መሟላት የማረጋገጥ ኃላፊነት የመንግሥት ተቋማት ነው:: በዚህ መሠረት የሚሰጡ የክልከላ ውሳኔዎች አግባብነት የሚፈተሽበት የሕግ ማዕቀፍ መኖር አለበት:: በኢትዮጵያ ሕግ የተቀመጡ እንደ የግል ነፃነት ያለመደፈር መብት፣ የቢዝነስ ሚስጥሮች፣ ብሔራዊ ደኅንነት፣ የአገር መከላከያ፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና የመሳሰሉት የክልከላ ምክንያቶች በሁሉም አገር ያሉ ናቸው:: ችግሩ ያለው እነዚህ የክልከላ ምክንያቶች የሚተከሉበት ከባቢ ሁኔታ ላይ ነው:: መብቱን በፍፁም የሚጠላ በሚስጥራዊ አሠራር ውስጥ የኖረ ማኅበረሰብና ቢሮክራሲ ውስጥ ስትወስደው የክልከላ ምክንያት የሚፈልጉ ባለሥልጣናት ባሉበት ከባቢ ሁኔታ ካስገባኸው፣ የክልከላ ምክንያቷ አንዲትም ብትሆን ከመከልከል አይመለስም:: መሠረታዊው ነገር የክልከላ ምክንያቶቹ መብዛትና ማነስ አይደለም:: መለመን መረጃ የማግኘት ወሳኝ የአሠራር መንገድ በሆነበት ማኅበረሰብ ውስጥ፣ የክልከላ ምክንያቶች ባይኖሩም እንኳን ተጠያቂነት በሌለበት ዓውድ እንቢ መባሉ አይቀርም:: ለዚህ አንዱ ማሳያ የሚሆነው ሕጉ የክልከላ ምክንያቶችን በጽሑፍ መስጠት ቢያስገድድም በጥናቱ ከተሳተፉት ውስጥ 99 በመቶ የሚሆኑት በቃል ነው አይቻልም የተባሉት:: ሳይብራሩ የተቀመጡ በጣም ጥቅል የሆኑ የክልከላ ምክንያቶችን በሌሎች ደንቦች፣ በአሠራር ማኑዋሎችና በመመርያዎች ማፍታታትና መዘርዘር ያስፈልጋል:: ሪፖርተር፡- የመረጃ ነፃነት ሕጉ እንደ የሚስጥር ሕግ፣ የመረጃ ምደባና ሚስጥራዊነት ማብቂያ ሕግ፣ የመረጃ ዋጋ ተመን ሕግ፣ የመረጃ አፈትላኪዎች ጥበቃ ሕግ መውጣት ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንደሚያደርገው ታሳቢ ተደርጎ የወጣ ነው:: የእነዚህ ሕግ አለመውጣት በእናንተ ጥናትና በስብሰባው ተሳታፊዎች እንደ ተግዳሮት ተጠቅሷል:: የፈጠረው ክፍተት ምን ይመስላል? ዶ/ር ደረጀ፡- የእነዚህ ሕጎች አስፈላጊነት ላይ ጥያቄ አይነሳም:: ነገር ግን በመብቱ አፈጻጸም ላይ የሚኖራቸው ሚና ከፍና ዝቅ ሊል የሚችለው በአጠቃላይ በአገር ውስጥ ባለው የሕግ የበላይነትና የሰብዓዊ መብቶች አከባበር ደረጃ ነው:: እርግጥ የሕጎቹ አለመውጣት ለመብቱ ተፈጻሚነት የራሱ የሆነ አደናቃፊነት ሚና አለው:: ነገር ግን ይኼን ጉዳይ የትኩረት አቅጣጫ ማድረግ ከእነዚህ ሕጎች አለመውጣት ውጪ የመብቱ ጥበቃ ይዞታ ደህና ነው የሚል የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ያደርሳል:: ሪፖርተር፡- የመረጃ ነፃነት ሕጉ ከመገናኛ ብዙኃን ሕግ ጋር መቀላቀሉን እንደ ችግር ያዩት ተሳታፊዎች ነበሩ:: የሚዲያ ተቋማትና ማንኛውም ግለሰብ መረጃ የሚያገኙበት አሠራር ተመሳሳይ መሆኑ በሌሎች አገሮች የተለመደ ነው? ዶ/ር ደረጀ፡- ሕጉ ለሁሉም መረጃ ፈላጊዎች ነው የሚለው:: ነገር ግን በመርህ ደረጃ መረጃ ፈላጊዎችን ለሁለት ከፍለን ማየት አለብን:: በአንደ በኩል ለዕለት ተዕለት ኑሮውና ለግል ሕይወቱ እንደ ሜድካል ሪከርድ፣ የግብር መረጃ የሚፈልግ አለ:: በሌላ በኩል ለአጠቃላይ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ፣ ለተጠያቂነት፣ ለሰብዓዊ መብት መከበርና ብልሹ አሠራሮችን ለመዋጋት ቁልፍ የሆነ ሚና የሚጫወተው ሚዲያ አለ:: ሁለቱ መረጃ የሚፈልጉበት ምክንያት የተለያየ ነው:: በግለሰብ በኩል መሻሻሎች አሉ:: ሚዲያውን በተመለከተ ግን የምርመራ ሼል የሚሠሩና ተጠያቂነትንና የሕግ የበላይነትን የተመለከቱ ጥያቄዎች ይዞ የሚሠራው ሚዲያ ያለበት ሁኔታ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው:: ይኼ ደግሞ በአጠቃላይ እንደ ማኅበረሰብና አገር ከፍተኛ አደጋ ይደቅናል:: ነፃና ውጤታማ ሚዲያ በሌለበት ዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብን መገንባት አይቻልም:: ሪፖርተር፡- አንዳንዶች እንዲያውም ሕጉ ለጋዜጠኞች የዕለት ተዕለት ሼል ተግባራዊ የሚሆን አይደለም ብለው ተከራክረዋል:: ዶ/ር ደረጀ፡- የመረጃ ነፃነት ሕጉ ከመገናኛ ብዙኃን ሕግ ጋር መቀላቀሉ አይደለም ይህን ችግር ያመጣው:: አንድ ላይም ሆነ ተነጣጥለው ቢወጡ ካልተፈጸመ ትርጉም የለውም:: መረጃ የማግኘት መብት የሁሉም ዜጎች ነው:: እርግጥ መረጃ የማግኘትን መብት ከሚዲያ አንፃር ብቻ መመልከት የሕጉን አንድ ምዕላድ ገንጥሎ እንደመጣል ነው:: ሆኖም ከግለሰብ ይልቅ ሚዲያ መረጃ የታጠቀ ዜጋ ለመፍጠር ፍቱን ነው:: ይህ ዓይነት ዜጋ ሕገ መንግሥታዊ መርሆዎችን በማክበር ዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ቁልፍ ሚና አለው:: ከዚህ አንፃር ከሚዲያ ይልቅ በተናጠል ለግል ሕይወታቸው መረጃ እንዲያገኙ ማድረግን መደፍጠጥ ይሻላል:: የአዋጁን ዋና ዓላማ ካየን ሚዲያው ቅድሚያ የሚሰጠው ነው:: ሪፖርተር፡- የሕዝብ ግንኙነት ቢሮዎች በሕጉ ሲቋቋሙ ዋናው ዓላማ የመረጃ ፍሰቱን ማሳለጥ ቢሆንም፣ በተግባር መረጃ እንዳይሰጥ ዘብ እየቆመ ነው የሚል ቅሬታ ቀርቧል:: የቢሮውን ሚናና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችን ሼል እንዴት አዩት? ዶ/ር ደረጀ፡- ይኼ ቅሬታ በአብዛኛው የሚቀርበው በሚዲያ ባለሙያዎች ነው:: የዕለት ተዕለት ሥራቸው ያገናኛቸዋል:: ነገር ግን በእኛ ጥናት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ስለመረጃ ነፃነት ሕጉ ያላቸው ግንዛቤ እጅግ ውስን መሆኑ ተመልክቷል:: መረጃ ከመስጠታቸው በፊት የኃላፊዎችን ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ያምናሉ:: መረጃ የመስጠትና ያለመስጠት ውሳኔ በተግባር የሚሰጠው በሥራ ኃላፊዎች እንጂ በሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች አይደለም:: ኃላፊዎቻቸው የማይደሰቱበትን ሼል ቢሠሩ የሥራ ዋስትና እንዳላቸው እርግጠኛ አይደሉም:: ስለዚህ ለችግሩ እነሱን ብቻ መውቀስ ተገቢ አይመስለኝም:: የሥራ ኃላፊዎች እንደ ነገሥታት ሁሉን አዛዥ በሆኑበት ሁኔታ በአንድ ጥግ የተቀመጠ ምስኪን ሠራተኛ ሕጉ ላስቀመጠው መርህ ተገዥ እንዲሆን መጠበቅ ተገቢ አይደለም:: ሪፖርተር፡- የመረጃ ነፃነት ሕጉን የማስፈጸም ኃላፊነት የተሰጠው ለእንባ ጠባቂ ተቋም ነው:: ይህ ውሳኔ ተቋሙ አስቀድሞ ከነበረው አቅምና ልምድ አንፃር ቅሬታ ቀርቦበት ነበር:: ባለፉት ዓመታት ተቋሙ የሄደበት አቅጣጫ ይህን ያፋለሰ ነው ይላሉ? ዶ/ር ደረጀ፡- ጥያቄው በተወሰነ ደረጃ እኔ ልመልሰው የምችል አይደለም:: የተወሰነ ሼል እንደሠራ አምናለሁ:: ለተቋሙ ኃላፊነቱን የመስጠት ውሳኔው ፖለቲካው ውሳኔ እንደሆነ ተገልጿል:: ጥቅምና ጉዳቱ ምናልባትም የወደፊት የጥናት ነጥብ ሊሆን ይችላል:: በእኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ሌሎች እንደ ፍርድ ቤት ያሉ አማራጭ ተቋማት ከእንባ ጠባቂ ተቋም የተሻሉ የመረጃን ዋጋ ከመረዳት አንፃር ያለው ባህል ሕጉ ከሚያልመው እውነታ በብዙ ርቀት የሚገኝ ነው:: የተለየ ንቃት ያላቸው ጥቂት ተቋማት አሉ:: የሕጉ መሠረታዊ መነሻ በመንግሥታዊ ተቋማት ይዞታ የሚገኝ መረጃ የሕዝብ ነው፣ ተቋማቱ ባለአደራዎች ናቸው የሚል ነው:: በተጨባጭ በተቋማቱና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ኃላፊዎች ዘንድ ያለው አመለካከት ግን የዚህ ቀጥተኛ ተቃራኒ ነው::
  • 8. ገጽ 8| www.ethiopianreporter.com | ረቡዕ | ታህሳስ 6 ቀን 2008 ቅፅ 21 ቁጥር 1631 ከገጽ 1 የዞረ ከገጽ 1 የዞረ ከገጽ 1 የዞረ በኦሮሚያ ግጭት...መድረክ የሟቾች...በጭልጋና በመተማ... የሚያነሳቸውን ተገቢነት ያላቸው ጥያቄ ለመመለሾ ተነሳሽነትም እያሳዩ አይደሉም በማለት የሚወቅሱ አሉ:: በእነዚህ ጉዳዮች የኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ሼል አስፈጻሚ አባልና የኦሕዴዱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ በተደጋጋሚ አስተያየት እንዲሰጡ ቢጠየቁም፣ እንደማይመቻቸው በመግለጽ አስተያየት ሳይሰጡ ቀርተዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ሥጦታው ግን ማስተር ፕላኑ ለዚህ ግጭት ምክንያት እንደማይሆን ለሪፖርተር ገልጸዋል:: አቶ አባተ ግጭቱን ድብቅ ዓላማ ያላቸው አካላት በማስተር ፕላኑ ስም ቀስቅሰውታል ብለው ያምናሉ:: ማክሰኞ ታኅሳስ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ምሽት የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ባወጣው መግለጫ፣ ከፊት ለፊት ማስተር ፕላኑን በመቃወም ከጀርባ ደግሞ ከሽብርተኛ ኃይሎች ጋር በማበር የተሠለፉ መኖራቸውን ገልጿል:: ግብረ ኃይሉ እንዳለው፣ ውጭ ካለው የሽብር ኃይል ጋር ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት በመፍጠር የነውጡና የረብሻው አድማስ ወደ ከተሞችና ወደተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት እንዲሰፋፋ ተደርጓል:: በዚህም በርካታ የመንግሥት፣ የግል ባለሀብቶችና የደሃ አርሶ አደሮች ንብረትና ሀብት ወድሟል ያለው ግብረ ኃይሉ፣ የኅብረተሰቡን ሰላምና ደኅንነት ለመጠበቅ በተሰማሩ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አባላት፣ እንዲሁም በመከላከያ ኃይል አባላት ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል:: ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የሕዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ በሽብርና በአመፅ ኃይሉ ላይ ሕጋዊና ተመጣጣኝ ዕርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል:: በገጠርም ሆነ በከተማ የሚኖሩ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት በትምህርት ተቋማትም ሆነ ከትምህርት ተቋማት ውጪ የሚገኙ ልጆቻቸውንና መላ ቤተሰባቸውን፣ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋና ንብረት እንዳይወድም፣ ዘረፋ እንዳይስፋፋ፣ የሽብር አመፅ አቀጣጣዮች ሰለባ እንዳይሆኑ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስቧል:: በተመሳሳይ የኦሮሚያ ክልል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው የመንግሥት አቋም፣ በክልሉ የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ማረሚያ ቤቶችን በመስበር፣ የሕግ ታራሚዎችን በመልቀቅ፣ የፖሊስ ጽሕፈት ቤቶችን፣ የልማት ድርጅቶችን፣ የአርሶ አደር ምርቶችን፣ የግል መኖሪያ ቤቶችን በማቃጠልና በማውደም በጦር መሣሪያ የታገዘ ጥፋት፣ የጥፋት ኃይሎች ያላቸው ወገኖች በመፈጸም ላይ ናቸው ብሏል:: እነዚህ ኃይሎችም ከድርጊታቸው ይቆጠቡ በማለት አስጠንቅቋል:: ‹‹እነዚህ የጥፋት ኃይሎች አብሮ የመኖር፣ የመቻቻልና የዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ተምሳሌት የሆነውን የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ወንድሞቹ ጋር የጎሪጥ እንዲተያይ፣ እንዲሁም በእምነቶች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ ከድርጊታቸው ጎን የቆመን ኃይሉ ሁሉ አሠልፈው ወደ ሕገወጥ ተግባር ተሸጋግረዋል፤›› በማለት የክልሉ መንግሥት ገልጿል:: በመሆኑም መንግሥት የእነዚህን የጥፋት ኃይሎች ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን የመናድ ተግባር ለማስቆምና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ በሕገ መንግሥቱ የተጣለበትን ግዴታ መሠረት በማድረግ በድርጊቱ ዋና ዋና ተዋናዮች ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል:: በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እየታየ ያለው ሁከት ከማስተር ፕላን በዘለለ ሌላ አቅጣጫ እየያዘ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ:: ሀብቱ አድማሱን ሊያሰፋ እንደሚችልም ሥጋታቸውን ይገልጻሉ:: ‹‹መንግሥት መሠረታዊውን የጥናት ሐሳብ ለሕዝቡ አቅርቦ የሕዝቡ ስሜት ምንድነው የሚለውን ፈትሾ እንጂ ወደ ዝርዝር ጥናት የሚገባው፣ ዝም ብሎ የጉልበተኛ ሼል መሥራት ተገቢ አይደለም፤›› ሲሉ የመድረክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር በየነ ገልጸዋል:: ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች በተፈጠረው ረብሻ ሕይወታቸውን አጥተዋል በማለት መድረክ በመግለጫው የዘረዘራቸው 30 ግለሰቦች ሲሆኑ፣ የሟቾችን ዝርዝር ስምና የሞቱባቸውን ከተሞች አስታውቋል:: በዚህ መሠረት በምዕራብ ወለጋ ጉልሶ ወረዳ፣ በምዕራብ ሐረርጌ በደኖ ወረዳ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ቶሌ ወረዳ፣ አዳበርጋ ወረዳ ሙገር፣ ምዕራብ ሸዋ ጨሊያ ወረዳ ባብቻ ከተማ፣ ምዕራብ ሸዋ ጨሊያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ፣ ሆሮ ጉድሮ ፊንጫ፣ ወሊሶ ከተማ፣ አመያ ከተማ፣ ወንጪ ከተማ፣ ግንደበረት ወረዳና ግንጪ ወረዳ ግለሰቦች የሞቱባቸው ሥፍራዎች እንደሆኑ መድረክ አስታውቋል:: የሚካሄዱት እንቅስቃሴዎች ሰላማዊ ከሆኑ ይህን ያህል ሰዎች እንዴት ይሞታሉ? በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች እየታዩና ከቁጥጥር ውጪ በመሆናቸው ይህ ከምን የመነጨ ነው? ለሚሉ ጥያዎች፣ ‹‹ይህንን ንብረት እናወድማለን ጥፋት እናደርሳለን ብሎ የተነሳ እንቅስቃሴ አይደለም:: ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ተጣሰ በሚል መነሻ እንደሆነ ሊዘነጋ አይገባውም:: አንድ የተናደደ ወጣት ጠጠር ሊወረውር ይችላል:: ይህ ተስፋ ከመቁረጥ የሚመነጭ ነው:: ሥርዓቱ ሕዝቡን ወደ ተስፋ መቁረጥ እያሻገረው በመሆኑ የተከሰተ ነው፤›› በማለት ፕሮፌስር በየነ ምላሽ ሰጥተዋል:: በቅርቡ የተከሰተውን ችግር ያፈነዳው የማስተር ፕላኑ ጉዳይ ነው በማለት አስተያየት የሰጡት ዶ/ር መረራ፣ ‹‹ነገር ግን በተጨማሪም ሕዝቡ በአመራሩ የመሰልቸት፣ በተለይ የወጣቶች ተስፋ ማጣትና የመሳሰሉት ነገሮች ናቸው ይህን የፈጠሩት፤›› በማለት አክለው ገልጸዋል:: የችግሮቹን ሁኔታ አጥንቶ መፍትሔ ማዘጋጀት አስቸኳይ ሼል መሆን አለበት ያሉት ዶ/ር መረራ፣ ሁለት መፍትሔዎችን በአማራጭነት አቅርበዋል:: እነዚህም ጊዜያዊና ዘለቄታዊ የሚሉ ናቸው:: ጊዜያዊ መፍትሔው ‹‹ወጣ የተባለውን አዋጅ መምር ነው:: አዋጅ ደግሞ የሚሻረው በአዋጅ ነው፤›› በማለት በቅርቡ በጨፌ ኦሮሚያ የወጣውን የከተሞች ማሻሻያ አዋጅ እንዲሻር የጠየቁ ሲሆን፣ ዘላቂ መፍትሔው ብለው ያቀረቡት ደግሞ፣ ‹‹ኢሕአዴግ በቃኝ የኢትዮጵያን ሕዝብ መምራት አልቻልኩም ብሎ ከሥልጣን መውረድና ምርጫ ማካሄድ ነው:: ይህን ማድረግ አልፈልግም የሚል ከሆነ ደግሞ ቢያንስ ጥምር መንግሥት አቋቁሞ ከዚያ በኋላ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ነው፤›› ሲሉ ዶ/ር መረል ተናግረዋል:: የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የመድረክ አባል የሆነው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የተለያዩ መግለጫዎችን በማውጣት በጉዳዩ ላይ ያላቸውን አቋም ሲገልጹ ከመቆየታቸው አንፃር፣ መድረክ መግለጫ ለማውጣት አልዘገየም ወይ ተብሎ ከሪፖርተር ለቀረበ ጥያቄ፣ ‹‹መድረክ ዘገየ አልዘገየ የሚለው ጉዳይ ይህን ያህል ብዙ ቦታ ልንሰጠው የሚገባ አይመስለኝም:: ይህም ቢሆን ግን መድረክ ምንም አላለም ማለት አይደለም:: በሕዝብ ግንኙነት በኩል መረጃዎች ሲሰጥ ነበር፤›› በማለት ፕሮፌሰር በየነ ምላሽ ሰጥተዋል:: ይህ በዚህ እንዳለ ሰማያዊ ፓርቲና ኤፌኮ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደረሱ:: ሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነት ላይ የደረሱት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ ለመስጠት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል:: የሁለቱ ፓርቲዎች አመራሮች ባደረጉት ስምምነት፣ በጋራ መግለጫ ከመስጠትም በላይ የጋራ ግብረ ኃይል በማቋቋም የፖለቲካ ትግል እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል:: መንግሥት አስፈላጊውን ዕርምጃ ይወስዳል ብለዋል:: ነዋሪነታቸውን በጭልጋና በመተማ ያደረጉ የሪፖርተር ምንጮች ግን በአካባቢው ውጥረቱ አሁንም እንዳለ ገልጸው፣ የበርካታ ሰዎች ሕይወት እንደጠፋ፣ በአካልና በንብረት ላይም ጉዳት እየደረሰ እንደሆነ አመልክተዋል:: በዚህም የተነሳ ሴቶችና ሕፃናትን ወደ ሌሎች አካባቢዎች በተለይ ወደ ደምቢያ ወረዳ እየሸሹ መሆኑንም ጠቁመዋል:: በአማራና በቅማንት ሕዝቦች መካከል ያለው ግጭት እንደቀጠለ አክለዋል:: አቶ ንጉሡ በግጭቱ የሰው ሕይወት መጥፋቱን የገለጹ ቢሆንም፣ ምን ያህል ሰው ሕይወቱን እንዳጣ ግን መረጃ እንዳልደረሳቸው ገልጸዋል:: ይሁንና ግጭቱ የሕዝብ ጥያቄ እንዳልሆነ ተከራክረዋል:: ‹‹እንደሚወራው ማንነት ላይ በተሰጠው ምላሽ የተነሳ ግጭት አይደለም:: የቅማንት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ሕገ መንግሥቱም ቢሆን የሚደግፈው በመሆኑ፣ ክልሉም አምኖበት ዕውቅና ሰጥቷል:: ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድርም ተወስኖ የአስተዳደር እርከን ደረጃውን ለመወሰን ሥራዎች እየተሠሩ ነው:: ይህን ሰበብ አድርገው ግጭት ያስነሱት ሌላ አጀንዳ ያላቸው አካላት ናቸው፤›› ብለዋል:: የግጭቱ መነሻ የቅማንት ብሔረሰብ የማንነት ጥያቄ እንደሆነ የሚገልጹ አካላት ደግሞ፣ ጉዳዩ ሲንከባለል ለበርካታ ዓመታት መቆየቱን ያመለክታሉ:: አቶ ውብሸት ሙላት ‹‹አንቀጽ 39›› መጽሐፋቸው ላይ ቅማንት የራሱ የሆነ የጋራ የትውልድ አመጣጥ አፈ ታሪክ ያለው፣ እንደ አንዳንድ ሰዎች ምስክርነት ከጭልጋ፣ ከላይ አርማጭሆና ከጎንደር ከተማ ተያያዥነት ባለው አካባቢና በሌሎች የሰሜን ጎንደር ወረዳዎች የሚኖር፣ የራሱ የሆነ ባህልና ልማዳዊ ሥርዓቶችም ያለው ማኅበረሰብ እንደሆነ ገልጸዋል:: አቶ ውብሸት በተጨማሪም በተራዘመው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታቸው እየከሰመና እየተዋጠ ቢሄድም፣ የራሳቸው እምነትና ባህልም እንደነበራቸው አመልክተዋል:: ቅማንት ጥያቄውን ለአማራ ክልል መጀመሪያ ሲያቀርብ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 39(5) ላይ የተቀመጠውን የተለየ ማንነት መሥፈርት እንደማያሟላ ገልጾ ክልሉ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎት ነበር:: የማኅበረሰቡ ተወካዮች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይግባኝ አቅርበው፣ ምክር ቤቱም ባቋቋመው ኮሚቴ አማካይነት ጥናት ለማድረግ የማኅበረሰቡ አባላት በሚኖሩባቸው ቦታዎች በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የክልሉ መንግሥት በራሱ ተነሳሽነት ችግሩን ለመፍታት ኮሚቴ አቋቁሞ ኅብረተሰቡን በማነጋገር ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት ሼል መጀመሩን በመግለጹ፣ ጥናቱ መቋረጡን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል:: ከዚህ በኋላ ክልሉ ጉዳዩን መርምሮ የክልሉ ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባዔውን መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ሲያከናውን፣ ማኅበረሰቡ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ወስኗል:: ይሁንና የማኅበረሰቡ አካላት ውሳኔው ከፊል መፍትሔ ነው ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል:: ምክር ቤቱ የቅማንት ማኅበረሰብ ራሱን ችሎ በሚኖርባቸው የጭልጋና የላይ አርማጭሆ ወረዳዎች በሚገኙ 42 ቀበሌዎች ማዕከል አድርጎ ራሱን በራሱ እንደሚያስተዳድር መወሰኑ ይታወሳል:: የቅማንት ማኅበረሰብ በአይከል፣ በመተማ፣ በቋራ፣ በወገራ፣ በደምቢያና በጐንደር ዙሪያ በተበታተነ ሁኔታ ይገኛል የሚሉት የማኅበረሰቡ አባላት ግን፣ ውሳኔው የተሟላ አይደለም በማለት የቅማንት ሕዝብ የሚገኝባቸውን ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ በቅማንት አስተዳደር ሼር እንዲሆኑ ለማድረግ፣ የአስተዳደር ደረጃውን በዞን ደረጃ ለማድረግ እንደሚታገሉ መግለጻቸው ይታወሳል:: በዚሁ መሠረት ጉዳዩን በይግባኝ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀረቡ ሲሆን፣ ጉዳዩን የመረመረው ምክር ቤትም ውሳኔውን ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ሰጥቷል:: ምክር ቤቱ የማኅበረሰቡ ተወካዮች የክልሉ መንግሥት የሰጠው ውሳኔ ሁሉንም ቀበሌዎች ያላከተተና የተሸራረፈ በመሆኑ ቅሬታ ማቅረባቸውን ያስታወሰው ውሳኔ፣ ክልሉ ቅማንት ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር የሰጠውን ውሳኔ እንዳፀደቀው ገልጿል:: ‹‹የክልሉ መንግሥት በጀመረው አግባብ እንዲፈታ የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል፤›› ይላል:: እንደ ሪፖርተር ምንጮች ገለጻ፣ በጭልጋና በመተማ የተነሳው ግጭት ቅማንቶች በውሳኔው ደስተኛ ባለመሆናቸው፣ አማራዎች ደግሞ ቅማንቶች የተለየ ማንነት አላቸው ብለው የሚያምኑ ባለመሆናቸው ምክንያት ነው:: የክልሉ መንግሥት ግን እነዚህን ጉዳዮች ሰበብ በማድረግ ግጭት እንዲፈጠር የፈለጉ አካላት የፈጠሩት ችግር እንጂ፣ ሕዝቡ እንዲህ ዓይነት አለመግባባት የለውም ሲል አስተባብሏል:: ‹‹ፀረ ሰላም ኃይሎችም በአማራና በቅማንት ሕዝቦች ዘንድ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ለዘመናት በመፈቃቀርና በመረዳዳት ሲኖር የነበረውን ሕዝብ ለማጋጨት የሚያደርጉትን ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ያቁሙ፤›› ሲሉ አቶ ገዱ አስጠንቅቀዋል:: አዲሱ አሠራር ግን ከዚህ በተለየ ዲዛይኑን፣ ግንባታውንና ከመንገዱ ግንባታ መጠናቀቅ በኋላም የጥገና ሥራን የሚያካትት ነው:: ይህ አሠራር ሦስቱንም ሥራዎች አጣምሮ ለመሥራት አሸናፊ የሚሆነው ኮንትራክተር ኃላፊነት የሚወስድበት ይሆናል:: የነቀምት-ቡሬ መንገድ ፕሮጀክት አጠቃላይ ግንባታን ለማከናወን አሸናፊ የሚሆኑ ኮንትራክተሮች፣ መንገዱን ካስረከቡ በኋላ ለአምስት ዓመታት የጥገና ሼል ያከናውናሉ:: ዲዛይን፣ ግንባታና የጥገና ሥራን አጣምሮ ለአንድ ኮንትራክተር እንዲሰጥ የሚያስችለው አሠራር ለአገሪቱ እንግዳ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሳምሶን፣ ወደዚህ አሠራር መገባቱ የአገሪቱን የመንገድ ግንባታ ክንውን ከፍ ወዳለ ምዕራፍ መሸጋገሩን ያሳያል ብለዋል:: ቀልጣፋ አሠራርን ይፈጥራል ሲሉም አክለዋል:: የነቀምት-ቡሬ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከተጀመረ በኋላም ይህ አሠራር በሌሎች በተመረጡ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎም ይጠበቃል:: የዲዛይንና የጥገና... ከገጽ 5 የዞረ የማክበር ግዴታ እንዳለበት በስምምነቱ ሰፍሯል:: በሁለቱ ወገኖች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር በግልግል ዳኝነት የሚፈታ መሆኑን ስምምነቱ ይገልጻል:: ስምምነት የገቡት አገሮች ዋና መዲናቸውን ቢቀይሩ ስምምነት ለገባው አገር ካሳና ምትክ ቦታ የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ያስረዳል:: ኢትዮጵያ በቱርክ የምትፈልገው ቦታ 3,000 ካሬ ሜትር ከሆነና መርሁም ሰጥቶ መቀበል ከሆነ፣ ኢትዮጵያም መስጠት የሚገባት 3,000 ካሬ ሜትር ብቻ መሆን እንዳለበት፣ አለበለዚያ እንደዚህ ዓይነት ስምምነት በኖረ ቁጥር ገንዘብ ላለው መሬት ሲሸጥ ሊቀጥል ነው ወይ? በማለት አንድ የምክር ቤቱ አባል ጥያቄያቸው በቋሚ ኮሚቴ እንዲታይ ጠይቀዋል:: ሌሎች አባላት ደግሞ የሊዝ አዋጁ መሬት በጨረታ በሊዝ እንደሚያዝ፣ እንዲሁም በምደባ መንግሥት ሊዝ የሚከፈልበት መሬት ሊያቀርብ እንደሚችል ደንግጐ ሳለ፣ ፓርላማው የሊዝ ዋጋ ያለበትን ስምምነት ሊያፀድቅ እንደማይገባና ይህ ምክር ቤት የሊዝ ዋጋ ሊወስን እንደማይችል ገልጸዋል:: በመሆኑም የሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን በዝርዝር እንዲመለከተው ጠይቀዋል:: የቀረበው የስምምነት ማፅደቂያ አዋጅም በአንድ ድምፀ ተአቅቦ ለውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና ለከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ ተመርቷል:: በኢትዮጵያና በቱርክ... ከገጽ 5 የዞረ ሪፖርት ለሰው ልጅ ተስማሚ የኑሮ ከባቢ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል ሼል የደመወዝ ክፍያ እንዲከፈል የሚያሳስበው የተመድ የልማት ፕሮግራም፣ በቀን ከሁለት ዶላር በታች የሚያገኙ ሰዎች ከ830 ሚሊዮን በላይ እንደሆኑ፣ 200 ሚሊዮን ሰዎች (74 ሚሊዮን ወጣቶችን ጨምሮ) ሼል አጥ እንደሆኑና 21 ሚሊዮን ሰዎች በመላው ዓለም በግዳጅ ጉልበታቸው እየተበዘበዘ እንደሚሠሩ በሪፖርቱ ጠቁሟል:: ሔለን ክላርክ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ለልማት ካላቸው ፍላጎትና ዓላማ በመነሳት፣ ሀብታቸውን በመጠቀም ለማደግ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሰዎችን ጤና የማያውክ የሥራ ዕድልና የመሥሪያ ቦታ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል:: ‹‹ይህ ሲባል ግን ለሰዎች ሕይወት ሥጋት በሚያሳድሩ የሥራ መስኮች ላይ እንዲሠሩ የማያስገድዱ ዝቅተኛ ደረጃዎች መከበር የለባቸውም ማለት አይደለም፤›› ያሉት ሔለን ክላርክ፣ በዓለም ላይ እንደ ግንባታ ዘርፍ ያሉ ለሰዎች ሕይወት መጥፋት አስተዋጽኦ በሚያደርጉ ዘርፎችና በሌሎችም መስኮች በምንም ዓይነት መጣስ የማገባቸው የደኅንነትና የሥራ ላይ አደጋ መከላከያ ሥርዓቶች መተግበር እንዳለባቸው አሳስበዋል:: በአንፃሩ በኢትዮጵያ በተከታታይ ጊዜያት የሰብዓዊ ልማት የሚለኩባቸው እንደ የትምህርት መስፋፋት፣ የእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ የዕድሜ ጣሪያ፣ የንፁህ ውኃ አቅርቦት፣ የመሠረተ ልማት መስፋፋቶች አገሪቱን ደረጃ እያሻሻሉ መምጣታቸው ቢገለጽም፣ ከሌሎች ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ካሉ የአፍሪካ አገሮች አኳያ የኢትዮጵያ ለውጥ ብዙ የሚቀረው ሆኗል:: ከሰሐራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ዘንድ እ.ኤ.አ. ከ2000 ጀምሮ የታዩት ዕድገቶች ፈጣን ሆነው ተመዝግበዋል:: ከሌሎች የዓለም ክፍሎች ይልቅ ከሰሐራ በታች የአፍሪካ ዓመታዊ የሰብዓዊ ልማት ዕድገት የ1.7 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ቀዳሚ ሆኗል:: ቦትስዋና፣ ኬፕቨርዴ፣ ኮንጎ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ጋቦን፣ ጋና፣ ሞሪሺየስ፣ ናሚቢያ፣ ሳኦ ቶሜ ኤንድ ፕሪንቺፒ እንዲሁም የተመድ ልማት... ከገጽ 5 የዞረ ዛምቢያ በአፍሪካ ከፍተኛ የሰብዓዊ ልማት ዕድገት ያስመዘገቡ አገሮች ተብለዋል:: ኢትዮጵያ ከእዚህ ዝርዝር ውስጥ የለችበትም:: ይህም ሆኖ በዓለም ካሉ ሌሎች ቀጣናዎች ይልቅ ከሰሐራ በታች የአፍሪካ አገሮች አሁንም ዝቅተኛውን የሰብዓዊ ልማት መመዘኛ ያሟሉ ሆነዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ በየዓመቱ በሰብዓዊ ልማት መስክ የ3.3 በመቶ ዕድገት እያስመዘገበች መምጣቷንና የሰዎች የዕድሜ ጣሪያም በአሁኑ ወቅት 70 ዓመት መድረሱን፣ ድህነትም በግማሽ መቀነስ መቻሉን ጠቅሰዋል:: ምንም እንኳ የሥራ ዕድል ማግኘት ጠቃሚ ቢሆንም ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን በማግኘት ሰዎች ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸውን የሚረዱበት ዕድል መፈጠር እንሚያስፈልግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል:: ባለፉት 25 ዓመታት በተመድ የልማት ፕሮግራም አጥኚዎች እየተዘጋጀ ይፋ ሲደረግ የቆየው ዓመታዊ የሰብዓዊ ልማት ሪፖርት፣ በሩብ ክፍለ ዘመኑ ሁለት ቢሊዮን ሰዎች ከዝቅተኛ የሰብዓዊ ልማት ደረጃ መላቀቅ እንደቻሉ አስፍሯል::