SlideShare a Scribd company logo
1 of 20
Download to read offline
ዜና መፅሔት
ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር
አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ!
ቅፅ 3 ቁጥር 3- መጋቢት 2007 ዓ.ም
www.etsugar.gov.et.com || facebook.com/etsugar
ጣፋጭ
በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት
:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ እና የወልቃይት ስኳር
ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ
በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራ
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ቡድን የተንዳሆ ስኳር
ፋብሪካ እና የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኘ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥር 17 ቀን 2007ዓ.ም የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን
ከጎበኙ እና በሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ስለፋብሪካው ገለጻ
ከተደረገላቸው በኋላ በሰጡት አስተያየት እንደተናገሩት ፋብሪካው
በ2007 ሁለተኛ ሩብ ዓመት ስራ መጀመር የነበረበት ቢሆንም፣
በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየት ታይቶበታል፡፡ ይሁንና በአሁኑ
ወቅት የነበሩ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየተቀረፉ በመምጣታቸው
ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት የሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል
ብለዋል፡፡ »» ወደ ገጽ 2 ዞሯል
የኮርፖሬሽኑ የውጤት ተኮር ሥርዓት ትግበራ
በይፋ ተጀመረ
“የተጀመሩ የለውጥ ትግበራዎችን ወደ ተሻለና የላቀ
ደረጃ ለማድረስ የውጤት ተኮር ሥርዓት ከፍተኛ
አስተዋጽኦ ይኖረዋል” አቶ ሽፈራው ጃርሶ
የስኳር ኮርፖሬሽን የውጤት ተኮር ሥርዓት ትግበራ የካቲት 30 ቀን
2007ዓ.ም በግዮን ሆቴል በተካሄደ ዝግጅት በይፋ ተጀመረ፡፡
በዝግጅቱላይተገኝተውየውጤትተኮርሥርዓትትግበራበይፋመጀመሩን
የተንዳሆና ከሰም ስኳር ፋብሪካዎች
አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው
»» ወደ ገጽ 2 ዞሯል
በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በፋብሪካ
ቁጥር 3 ዙሪያ የባለድርሻ አካላት እና የህዝብ
ውይይት ተካሄደ
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሙከራ ላይ የሚገኙት
የተንዳሆና የከሰም ስኳር ፋብሪካዎች የአካባቢያቸውን አርብቶ
አደሮች ተጠቃሚ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡
የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የባለድርሻ አካላት
ሰሞኑን በፋብሪካዎቹ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት እንደተገለጸው፣
ፋብሪካዎቹ በአካባቢያቸው ለሚገኙ አርብቶ አደሮች የስራ እድል
በመፍጠርና በማህበር ተደራጅተው ሸንኮራ አገዳ በማልማት
ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረጉ ነው፡፡
»» ወደ ገጽ 3 ዞሯል
በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካ ቁጥር 3 ግንባታና
የመሬት ዝግጅት እንዲሁም በቤንች ማጂና ካፋ ዞኖች አዋሳኝ ላይ ነዋሪ
የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያስችሉ የተለያዩ
»» ወደ ገጽ 4ዞሯል
በውስጥ ገጾች
ባለቤትነት እስከ ሕይወት
መስዋዕትነት ››ገጽ 14
የአብዲ ቦሩ የሸንኮራ አገዳ አብቃይና
አቅራቢ ማኀበር 64 አባላት በነፍስ
ወከፍ ከ50,000 እስከ 240,000 ብር
ተከፋፈሉ ››ገጽ 9
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወልቃይት ስኳር ልማት ፐሮጀክትን ሲጎበኙ
የቢኤስሲ ሰነድ ርክክብ
የባለድርሻዎችና የህዝብ ውይይቱ በተካሄደበት ወቅት
2 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት
የፋብሪካው መገንባት በዋነኛነት በአካባቢው የሚገኙ አርብቶ አደሮች
በመንደር ተሰባስበው የማህበራዊ ተቋማት አገልግሎት እንዲያገኙ እና
የሸንኮራ አገዳ እያለሙ ለፋብሪካው በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ያስችላቸዋል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ አክለውም ፋብሪካው
ለበርካታ ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል እየፈጠረ በመሆኑ አርብቶ አደሮች
በሥራ ከመሳተፋቸው በተጨማሪ ለሠራተኛው የሚያስፈልጉ ሸቀጣ
ሸቀጦችን በማቅረብ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያስፋፋበትን ሁኔታም
ያመቻቻል ብለዋል፡፡
ፋብሪካው ከስኳር ተረፈ ምርት ከሚያመነጨው 120 ሜጋ ዋት
የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ ለራሱ ፍጆታ ተጠቅሞ ቀሪውን ኃይል
በአካባቢው ለሚካሄዱ የልማት ሥራዎች ያውላል ያሉት አቶ
ኃይለማርያም፣ ከስኳር ተረፈ ምርት የእንስሳት መኖ በማቀነባበር
አርብቶ አደሮች በዘመናዊ የከብት ማድለብና ተዛማጅ ሥራዎች ላይ
ተሰማርተው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑንም
ገልጸዋል፡፡
ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን ጨምሮ በመጠናቀቅ ያሉ አዳዲስ ስኳር
ፋብሪካዎች ወደ ሥራ ሲገቡ ስኳር ኤክስፖርት በማድረግ አገሪቷ
ከዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችሏታልም ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራ
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ቡድን የካቲት 15 ቀን 2007ዓ.ም
የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎብኝቷል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት
ስለ ሜይ ዴይ ግድብ ግንባታ እና አጠቃላይ የፕሮጀክቱ የሥራ
እንቅስቃሴን በተመለከተ በስኳር ኮርፖሬሽን እና በሱር ኮንስትራክሽን
የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጓል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የውጤት ተኮር ሥርዓት ትግበራ...
ያበሰሩት በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ
ሽፈራው ጃርሶ በስኳር ልማት ዘርፍ የተጀመሩ የለውጥ ትግበራዎችን
ወደ ተሻለና የላቀ ደረጃ ለማድረስ የውጤት ተኮር ሥርዓት ከፍተኛ
አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
በኮርፖሬሽኑ ስር ከሚገኙ ዘርፎች፣ ስኳር ፋብሪካዎችና የስኳር ልማት
ፕሮጀክቶች የሥራ አመራሮች ጋር በውጤት ተኮር ሥርዓት ሰነድ ላይ
የተፈራረሙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣
ለውጡን በቁርጠኛነት በመተግበር ኮርፖሬሽኑ በ2016 ዓ.ም. በዓለም
ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ የመሰለፍ ራዕዩን
እንደሚያሳካ ገልጸዋል፡፡
የኮርፖሬት ካይዘን እና የለውጥ አመራር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር
አቶ መንግስተአብ ገ/ኪዳን በበኩላቸው ስትራቴጂያዊ አመለካከት
ያለው አመራርና ሠራተኛ በመፍጠር በካይዘን የተጀመረውን ውጤት
ለማስቀጠል ከ2007 አንደኛ ሩብ ዓመት ጀምሮ ላለፉት ሰባት ወራት
የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤትን ጨምሮ በሁሉም ስኳር ፋብሪካዎችና
ፕሮጀክቶች የሚገኙ ከ6892 በላይ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች
የውጤት ተኮር ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑን የውጤት ተኮር ሥርዓት በመገንባት ሂደት ወሳኝ የሆኑ
ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ ግቦችና ስትራቴጂያዊ እርምጃዎች መዘጋጀታቸውን
ጠቅሰው፣ ለፈፃሚ አካላት ግንዛቤ የመፍጠር፣ ዕቅድን የማውረድና
በየደረጃው ስኮር ካርድ የማዘጋጀት ስራዎችም በመጠናቀቃቸው የስራ
ክፍሎች በየደረጃው በተዘጋጁ ስኮር ካርዶች ላይ በመፈራረም ወደ
ስራ መግባታቸውን አስታውቀዋል፡፡
በዕለቱ የኮርፖሬሽኑ ባላንስድ ስኮር ካርድ የግንባታ ደረጃ ሂደት
በአቶ ታፈሰ አሰፋ የለውጥ አመራር ዳይሬክተር በፅሁፍ ቀርቧል፡፡
በመጨረሻም የኮርፖሬሽኑ የውጤት ተኮር ሥርዓት ዝግጅት ላይ የጎላ
አስተዋጽኦ ያበረከቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ከኮርፖሬሽኑ ዋና
ዳይሬክተር እጅ የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡
»» ከገጽ 1 የዞረ
»» ከገጽ 1 የዞረጠቅላይ ሚኒስትሩ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ እና ...
ጣፋጭ | 3
የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በሌሎች የስራ መስኮች ከተሰማሩት የአካባቢው አርብቶ አደር ልጆች በተጨማሪ 125 ወጣቶችን በማሽን እና በትራክተር
ኦፕሬተርነት መለስተኛ የሙያ ክህሎት ስልጠና ሰጥቶ ወደ ስራ ማሰማራቱ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በርካታ ወጣቶች በ20 ማህበራት ተደራጅተው በኮንስትራክሽንና በኢንዱስትሪ ዘርፎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸው ተጠቃሚ
ሆነዋል፡፡ በአጠቃላይ ፋብሪካው የአጭርና የረዥም ጊዜ ስልጠና በመስጠት ከ5ሺ ሰባት መቶ በላይ አርብቶ አደሮች በተለያዩ የስራ ዘርፎች
ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድል እንዲያገኙ አድርጓል፡፡
የአካባቢው አርብቶ አደሮች የሸንኮራ አገዳ አልምተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድም ከ1ሺ 147 እማ/አባ ወራ አርብቶ አደሮች በስድስት
ማህበራት ተደራጅተው 1ሺ 119 ሄክታር መሬት ሸንኮራ አገዳ በማልማት ላይ ይገኛሉ፡፡
በተመሳሳይ በከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ11 ማህበራት የተደራጁ 755 አርብቶ አደሮች የመስኖ መሰረተ ልማት የተሟላለት በነፍስ ወከፍ
አንድ ሄክታር መሬት ተሰጥቷቸው ሸንኮራ አገዳ ለማምረት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በተለያዩ የስራ መስኮች ለ220
የአካባቢው ተወላጅ ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፣ ሌሎች በርካታ የአካባቢው ወጣቶችም በ14 ማህበራት ተደራጅተው በተለያዩ የስራ
መስኮች ተሰማርተዋል፡፡
በቀጣይም ፋብሪካዎቹ የአካባቢያቸውን አርብቶ አደሮች የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ ገልጸዋል፡፡
»» ከገጽ 1 የዞረ
የተንዳሆና ከሰም ስኳር ፋብሪካዎች ...
ከሰም ስኳር ፋብሪካ
4 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት
በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ...
ተግባራት ላይ የባለድርሻ አካላት እና
የሕዝብ ውይይት ተካሄደ፡፡
በቤንች ማጂ ዞን ሚዛን አማን ከተማ
በተደረገው በዚህ ውይይት መድረክ ላይ
የተገኙት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ክልል የርዕሰ መስተዳድሩ
ተወካይና የክልሉ የአርብቶ አደር ጉዳዮች
ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳንሳ ፕሮጀክቱ
የፋብሪካ 1 ግንባታ ተግባራዊ ከመደረጉ
በፊት ከሚመለከታቸው የአርብቶ አደር
ተወካዮች እና በየደረጃው ከሚገኙ
የሚመለከታቸው አካላት ጋር ተደጋጋሚ
ውይይቶችን በማድረግ መግባባት ላይ
መድረሱን ተናግረዋል፡፡
በመቀጠልም በደቡብ ኦሞ ዞን በሳላማጎ
ወረዳ የቦዲ ማህበረሰብ በሚኖርበት
አካባቢ ለአርብቶ አደሩ አስፈላጊውን
ማህበራዊ ተቋማት በመገንባትና በመንደር
በማሰባሰብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን
ገልጸዋል፡፡
አርብቶ አደሩን በመንደር በማሰባሰቡ
ሂደት ጥርጣሬ የሚፈጥሩ የተለያዩ
አመለካከቶች በስፋት ይስተዋሉ እንደነበር
አቶ ንጋቱ አስታውሰው አርብቶ አደሮቹ
ፕሮጀክቱ ወዳዘጋጀላቸው ስፍራ በመግባት
ውጤታማ መሆን ሲጀምሩ ሌሎችም
የእነሱን ተሞክሮ በማየት በመንደር
በመሰባሰብ በስፋት ተጠቃሚ በመሆን ላይ
እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በሶስት መንደሮች የተሰባሰቡ
የቦዲ ማህበረሰብ አባላት በሸንኮራ
አብቃይ ህብረት ሥራ ማህበር በመደራጀት
ፕሮጀክቱ ያለማውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ
ተረክበው በመንከባከብ ላይ እንደሚገኙና
አገዳ ለሚያለሙበት መሬት የባለቤትነት
ማረጋገጫ ደብተር በመጠባበቅ ላይ
መሆናቸውን ኃላፊው አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም አርብቶ አደሮቹ ፕሮጀክቱ
ባዘጋጀላቸው በመስኖ የሚለማ መሬት ላይ
ለሦስት ተከታታይ ጊዜ በቆሎ አምርተው
ተጠቃሚ ከመሆናቸውም በላይ ለአራተኛ
ጊዜ ዘር በመዝራት ላይ እንደሚገኙ አቶ
ንጋቱ ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል፡፡
የስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ አደረጃጀትና
ተሳትፎ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር
አቶ ዳመነ ዳሮታ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ
በሸንኮራና ተጓዳኝ ምርቶች ዘርፍ ትኩረት
ሰጥቶ በመስራት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ
የራሱን አስተዋጽዖ ከማበርከት ባለፈ
ልማቱን በሚያከናውንባቸው አካባቢዎች
የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን
የመጀመሪያው ተጠቃሚ ማድረግ ተቀዳሚ
ተልዕኮው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት
ፋብሪካ 1 በመገንባት ላይ በሚገኝበት
አካባቢ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች
ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት በተመሳሳይ
መልኩ በቤንች ማጂና ካፋ ዞኖች
አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች
እንደሚከናወኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ
አብራርተዋል፡፡
በቤንች ማጂና ካፋ ዞኖች የሚገኙ የማጂ፣
የሱርማ፣ የሜኢንት ሻሻ እና ዴቻ ወረዳ
አርብቶ አደሮች በሰጡት አስተያየት
በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ የቦዲ
ማህበረሰብ አባላትን ተጠቃሚ ያደረጉ
ተግባራት በእነሱ አካባቢም ተከናውነው
የልማቱ ተጠቃሚ ለመሆን መጓጓታቸውን
ገልጸው መንግሥትም በፍጥነት ስራውን
እንዲጀምር ጠይቀዋል፡፡
የሁለቱ ዞኖች አስተዳዳሪዎችም ለልማቱ
ስኬት እና ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት
አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል
ገብተዋል፡፡
»» ከገጽ 1 የዞረ
የደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል የአርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
ጣፋጭ | 5
የፕሮጀክቱ የቤቶች ኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት ቡድን ከ9
ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አዳነ
በበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር
ዘርፍ የቤቶች ኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት ቡድን ከ9 ሚሊዮን
ብር በላይ ወጪ ማዳኑ ተገለጸ፡፡ ቡድኑ ወጪውን ያዳነው በራሱ
አቅም የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ መጋዘንና ድልድይ በመገንባት
መሆኑ ታውቋል፡፡
የፕሮጀክቱ የቤቶች ኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት ቡድን በዋናው
ግቢየሚገኘውንና 6.162ኪሎሜትርየሚረዝመውንየውስጥለውስጥ
መንገድ በራሱ አቅም ሠርቶ በ372,ዐ86 ብር ማጠናቀቅ መቻሉን
የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡
፡ መንገዱ በስራ ተቋራጮች ቢሰራ ከ6.4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ
ይወጣበት ነበር ብሏል ዘገባው፡፡
በተጨማሪ ፕሮጀክቱ የገጠመውን የመጋዘን /store/ እጥረት ለመቅረፍ
ቡድኑ 5ዐ2,739.15 ብር ወጪ ይጠይቅ የነበረ የአንድ መጋዘን ግንባታ
በ329,ዐ32 ብር በማከናወን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ማዳን
ችሏል፡፡
ከግልገል በለስ እስከ ጃዊ /ፈንድቃ/ ባለው መንገድ ላይ ቡድኑ ከፍተኛ
ክብደት መሸከም የሚችሉ ሁለት ድልድዮችንና የግማሽ ኪሎ ሜትር
መንገድ ስራ በአካባቢው የሚገኙ ግብአቶችን በመጠቀም መገንባቱንም
ነው ክፍሉ ያደረሰን ዘገባ ያመለከተው፡፡
ስራው በግል የስራ ተቋራጭ ቢሰራ 3,427,7ዐ3 ብር ወጪ ይጠይቅ
የነበረ ሲሆን ቡድኑ በ446,156 ብር ብቻ ገንብቶ አጠናቋል፡፡
የፕሮጀክቱ የቤቶች ኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት ቡድን በአጠቃላይ
በሶስቱም የግንባታ ስራዎች 9,177,168 ብር ማዳን ችሏል፡፡
ቁርጠኝነትና ቅንጅት የወለደው ውጤት
የተጣለበትን ሀገራዊ ተልዕኮ ለመወጣት በእንቅስቃሴ ላይ
የሚገኘው የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ በበጀት ዓመቱ በአገዳ የተሸፈነ
ማሳውን 21 ሺህ ሄክታር ለማድረስ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
እቅዱን ለማሳካትም የፋብሪካው የእርሻ ኦፕሬሽን ዘርፍ “ታላቁ
የአገዳ ተከላ ቀን” ሲል በሰየመው የካቲት 5 ቀን 2007 ዓ.ም
በዘመቻ መልክ 140 ሄክታር አገዳ ለመትከል አቅዶ 150.3 ሄክታር
በመትከል ከእቅዱ በላይ ማከናወን ችሏል፡፡
በተካሄደው ዘመቻ ከ2ሺ 800 በላይ የሆኑ የእርሻ ኦፕሬሽንና
የምርምር ዘርፍ ሠራተኞች፣ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የንግዱ
ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ የሥራ
ተቋራጭድርጅቶችሠራተኞችተሳታፊሆነዋል፡፡እነዚህምአካላት
ለአገዳ ተከላ ዘመቻው ስኬት የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋችውን
የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን ዘገባ ያመለክታል፡፡
ታላቁ የአገዳ ተከላ ዘመቻ ቀን የፈጠረውን መነቃቃት የበለጠ
በማጠናከር ለአጠቃላይ ድርጅታዊ ግብ ስኬት ሁሉም የሥራ
ዘርፎች መሰል ተግባራትን ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው
የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዱላ መኮንን በወቅቱ
አሳስበዋል፡፡
በፕሮጀክቶ የተሰራ መንገድ
6 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት
ኮርፖሬሽኑን ከአራት ስኳር ፋብሪካዎች ጋር
በኔትወርክ ለማስተሳሰር የሚከናወኑ ሥራዎች
በመጠናቀቅ ላይ ናቸው
የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤትን ከወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣
ፊንጫአ እና ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካዎች ጋር ለማስተሳሰር
በመከናወን ላይ የሚገኙ የኔትወርክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ
ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን የኮርፖሬት አይቲ
ዳይሬክቶሬት ገለጸ፡፡
ዳይሬክቶሬቱ እንዳስታወቀው ከአመት በፊት ጂሲኤስ ከተባለ
አገር በቀል ድርጅት ጋር ከ55 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ
ውል በመፈራረም ወንጂ የሚገኘውን የምርምርና ሥልጠና
ዘርፍን ጨምሮ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤትን፣ የአራት ስኳር
ፋብሪካዎች ዋና መ/ቤት እና አዲስ አበባ የሚገኙ የፋብሪካዎቹ
ላይዘን ቢሮዎችን እንዲሁም የበለስና ወልቃይት ስኳር ልማት
ፕሮጀክቶችን በመረጃ መረብ በማስተሳሰር ፈጣን አገልግሎት
ለመስጠት የሚያስችል የኔትወርክ ፕሮጀክት ቀርጾ እየሰራ
ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት የአራቱ ስኳር ፋብሪካዎች የኔትወርክ መሰረተ
ልማት ዝርጋታና ግንባታ ሥራዎች በመጨረሻ ምዕራፍ
ላይ እንደሚገኙ ያመለከተው ዳይሬክቶሬቱ፣ በቀጣይ
የመሰረተ ልማት ዝርጋታውን በሌሎች የስኳር ልማት
ፕሮጀክቶች ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች በመካሄድ
ላይ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
ከመሰረተ ልማት ዝርጋታ በኋላ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ
ፕላኒንግ (ERP) አፕሊኬሽን ሶፍትዌር ሥራ ላይ ለማዋል
የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን ዳይሬክቶሬቱ
ጠቁሞ፣ ትግበራውን በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ እና
በተሟላ ሁኔታ ለማስቀጠል ለፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች
አይቲ ባለሙያዎች የከፍተኛ ደረጃ /አድቫንስድ/ የአይቲ
ሥልጠናዎችን እያመቻቸ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ጣፋጭ | 7
ፕሮጀክቱ በጥጥ ምርት
የእቅዱን 85 በመቶ ገደማ
አከናወነ
ዛሬማ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ የሚገኘው የሜይ-ደይ
ግድብ ተጠናቆ ወደ ታቀደለት የሸንኮራ አገዳ ልማት
እስኪገባ ድረስ የጥጥ ተክል እያለማ የሚገኘው የወልቃይት
ስኳር ልማት ፕሮጀክት የዕቅዱን 84.8 በመቶ ማከናወን
ቻለ ፡፡
ፕሮጀክቱ በያዝነው በጀት ዓመት በ 2 ሺህ 545 .86
ሄክታር መሬት ላይ ጥጥ ለማልማት አቅዶ ተከላውን
በዕቅዱ መሰረት ሙሉ በሙሉ ያከናወነ ሲሆን፣ በበጀት
ዓመቱ 33 ሺህ ኩንታል የጥጥ ምርት ለመልቀም አቅዶ
እስከ መጋቢት ወር 2007 መጨረሻ ድረስ 28 ሺህ ኩንታል
ጥጥ ለቅሟል፡፡
አካባቢው ቀደም ሲል የጥጥ ምርት ይመረትበት ያልነበረ
በመሆኑ የጥጥ ምርቱ በአረም እንዳይጠቃ ከአካባቢው
ማኅበረሰብ ጀምሮ ከሰሜን ጎንደር፣ ከሁሉም የትግራይ
ወረዳዎችና ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ጭምር የሰው ኃይል
በማሰባሰብ አረም የመከላከል ከፍተኛ ርብርብ መደረጉ
ተመልክቷል፡፡
ከሰኔ ወር 2006 ዓ.ም. እስከ መስከረም 2007 ዓ.ም.
ድረስ በተከናወነ የአረም መከላከል ስራ እና ከጥቅምት
እስከ መጋቢት ወር 2007 ዓ.ም. ድረስ በተከናወነ የጥጥ
ምርት ለቀማ ስራ ለ18 ሺህ 869 ዜጎች ጊዚያዊ የስራ
እድል ተፈጥሯል፡፡ በጥጥ ለቀማ ስራው 243 የፕሮጀክቱ
ሠራተኞች በሁለት ዙር መሳተፋቸውንም የፕሮጀክቱ
የሕዝብ ግንኙነት በላከው ዘገባ አመልክቷል፡፡
የዛሬማ ሜይ-ዴይ ግድብ 840 ሜትር ስፋትና 135.5
ሜትር ቁመት የሚኖረው ሲሆን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ 3
ቢሊዮን 497 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም
ይኖረዋል፡፡
በአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት አዲስ ለተቀጠሩ 160 ሠራተኞች
የስራ ገለጻ ተደረገ ፡፡
ለሠራተኞቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እና ስለፕሮጀክቱ ገለጻ
ያደረጉት የፕሮጀክቱ የሰው ሃብት ስራ አመራር ቡድን መሪ አቶ ታከለ
አብዲሳ ሠራተኞቹ የፕሮጀክቱን ደንብ አክብረው በትጋት በመስራት
ለውጤት እንዲበቁ አሳስበዋል፡፡
በተፈጠረላቸው የሥራ እድል ራሳቸውን ከመጥቀም ባለፈ አገሪቱ
የጀመረችውን የዕድገት ጉዞ ከግብ ለማድረስም የድርሻቸውን እንዲወጡ
ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የፋብሪካው የቴክኒክ ቡድን መሪ አቶ ጌታቸው ሞገስ በበኩላቸው
ሠራተኞቹ ፋብሪካው የሚጠይቀውን ጥንቃቄ ማድረግ እና
ለፋብሪካው ውጤታማነት ሥነ-ምግባርን በተላበሰ መልኩ በቡድን
መስራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡ አንዴ ተቀጥሬያለሁ
ብለው ባለመዘናጋት ራሳቸውን ጊዜው ከሚፈልገው ቴክኖሎጂ ጋር
አብሮ ለማስኬድ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸውም አስታውቀዋል፡፡
በተመሳሳይ የፕሮጀክቱ ገጽታ ምን እንደሚመስል በህዝብ ግንኙነትና
ማህበራዊ ጉዳዮች ክፍል ለሠራተኞቹ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
ከገለጻው በኋላ ፋብሪካውን የጎበኙት ሠራተኞቹ ፕሮጀክቱን
አስመልክቶ በተደረገላቸው ገለፃ እና በጉብኝቱ መደሰታቸውን እና
ስራቸውንም የፕሮጀክቱን ደንብና መመሪያ ተከትለው በቁርጠኝነት
ለመስራት መነሳሳታቸውን ገልጸዋል፡፡
ፋብሪካው የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል፡፡
በአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት
ፕሮጀክት አዲስ ለተቀጠሩ
ሠራተኞች የሥራ ገለጻ ተደረገ
*ፋብሪካው የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል
አዲስ ለተቀጠሩ ሰራተኞች ገለጻ ሲደረግ
በፕሮጀክቱ የለማ ጥጥ
8 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት
በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል
ያስመዘገቡ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተሸለሙ
በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በተፈጠረላቸው የሥራ
እድል በማህበር ተደራጅተው በመስራት ላይ የሚገኙና ከ1
ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ የጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች ተሸለሙ፡፡
በፕሮጀክቱ 780 አባላት ያሏቸው 158 የጥቃቅንና አነስተኛ
ማህበራት ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች በመሳተፍ
ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ ለሌሎችም የስራ እድል በመፍጠር ላይ
ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል
ያስመዘገቡ ማህበራት ለሽልማት በቅተዋል፡፡
በሽልማት ሥነ ስርአቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የስኳር
ኮርፖሬሽን የህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ ዘርፍ ምክትል ዋና
ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ በስኳርና ተጓዳኝ ልማቶች ዜጎችን
ተጠቃሚ ማድረግ የመንግሥት ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በፕሮጀክቱ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው በመስራት
ውጤታማ የሆኑ ማህበራት የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ልዩ
ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ
አስታውቀዋል፡፡
በፕሮጀክቱ ለመስራት በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት
ተደራጅተው ለሚመጡ ወጣቶች ፕሮጀክቱ አስፈላጊውን
ድጋፍ እንደሚያደርግም የፕሮጀክቱ የህዝብ አደረጃጀት፣ ካሣና
መልሶ ማቋቋም ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስረስ አዳሮ
ተናግረዋል፡፡
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የስራ መሪዎችና ባለሙያዎች
የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን ጎበኙ
ከሁሉም የአገሪቷ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የስራ መሪዎችና
ባለሙያዎች በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በማህበር የተደራጁ ወጣቶችን
የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡
በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የኮንስትራክሽን ዘርፍን
ለማሳለጥ በሚረዱ ጉዳዮች ላይ በሰመራ ከተማ ውይይት ያደረጉት
የሥራመሪዎችናባለሙያዎቹየተንዳሆስኳርፋብሪካበኮንስትራክሽን
ዘርፍ በማህበር ለተደራጁ የአካባቢው ወጣቶች የፈጠረውን የስራ
ጣፋጭ | 9
እድል ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በተንዳሆ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ተጀምረው
ያልተጠናቀቁ እና ጥገና የሚያስፈልጋቸው የመኖሪያ
ቤቶች በኮንስትራክሽን ዘርፍ በጥቃቅንና አነስተኛ
በተደራጁ የአካባቢው ማህበረሰብ ወጣቶች
ግንባታቸው በመከናወን ላይ እንደሚገኝም በጉብኝቱ
ወቅት ተገልጿል፡፡
በውይይቱና በጉብኝቱ ወቅት የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ
በቋሚነት፣ በኮንትራትና በጊዜያዊነት ከ5 ሺህ ሰባት
መቶ ለሚበልጡ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት የስራ
እድል መፍጠሩ ተገልጿል፡፡
የአካባቢው አርብቶ አደር ማህበረሰብም በሸንኮራ
አገዳ አብቃይ ህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው
የሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በማቅረብ
ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን
ላይ እንደሚገኙ ለጎብኚዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በፋብሪካበስራላይየሚገኙትንማህበራትለማጠናከርና
አዳዲስ ማህበራትን አደራጅቶ ወደ ስራ ለማስገባት
እንዲሁም ከክልሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
ልማት ቢሮ ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ መስራት የሚያስችሉ
ጥናቶች መጠናቀቃቸውም ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም የፌዴራል የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት
ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው
አበበ በማህበር ለተደራጁ ዜጎች በስራ እድል ፈጠራ
ረገድ በሁሉም ዘርፎች ተመሳሳይነት እንዲኖራቸው
ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የአብዲ ቦሩ የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኀበር 64 አባላት
በነፍስ ወከፍ ከ50,000 እስከ 240,000 ብር ተከፋፈሉ
* አብዛኛዎቹ አርሶ አደሮችም ወደ ልማታዊ ባለሃብትነት እየተቀየሩ ነው
ሸንኮራ አገዳ አልምተው ለወንጂ ሸዋ ስኳር
ፋብሪካ በማቅረብ ሥራ ላይ ከተሰማሩ
ሸንኮራ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች ኀብረት
ሥራ ማኀበራት ዩኒየን መካከል አንዱ
የሆነው የአብዲ ቦሩ ማኀበር 64 አባላት
ካገኙት ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ
ውስጥ በነፍስ ወከፍ ከ50,000 እስከ
240,000 ብር ተከፋፈሉ፡፡
በምሥራቅ አርሲ ዞን በዶዶታ ወረዳ
ዴራ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ይህ
ማኅበር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ
የሚያስችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን
ተጠቅሞ አገዳ በማልማት ላይ ነው፡፡
በማኅበሩ የታቀፉ አርሶ አደሮች
እንደገለጹት መንግሥት አርሶ አደሮችን
ተጠቃሚ የሚያደርግ የልማት ስትራተጂ
ቀይሶ በመሥራቱ በልማቱ ተጠቃሚ
ሆነዋል፡፡ በተለይ በከፍተኛ ደረጃ የትርፍ
ክፍፍል ያደረጉት አርሶ አደሮች በርትተው
በመሥራታቸው ያስመዘገቡት ውጤት
እና ያገኙት ከፍተኛ ጥቅም ወደ ልማታዊ
ባለሃብትነት እንዲቀየሩ እንዳስቻላቸው
ተናግረዋል፡፡ መሰል ማኅበራትም የእነሱን
ፈለግ ተከትለው ከሰሩ ውጤታማ መሆን
እንደሚችሉ ነው መልዕክት ያስተላለፉት፡፡
በአሁኑ ወቅት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ
አካባቢ የሚገኙ 5ሺ 651 ወንዶችና
1ሺ 982 ሴቶች በጠቅላላው 7ሺ 633
አባላት ያሏቸው 34 ማኅበራት የሸንኮራ
አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በማቅረብ
በሚያገኙት ገንዘብ ተጠቃሚ በመሆን ላይ
ናቸው፡፡ ማኅበራቱ የሚያገኙትን ትርፍ
በአማካይ በየ18 ወራት ለአባላቶቻቸው
ያከፋፍላሉ፡፡
ፋብሪካው ለአርሶ አደሮቹ በመስኖ የለማ
መሬት በማዘጋጀት፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት
በማመቻቸት፣ ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍ
በመስጠት አርሶ አደሮቹ ሸንኮራ አገዳ
አልምተው ለፋብሪካው በመሸጥ ተጠቃሚ
እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል፡፡
ፋብሪካው በግብዓትነት ከሚጠቀመው
በ12ሺ 800 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ
የሸንኮራ አገዳ ውስጥ 7ሺ ሄክታሩ
በፋብሪካው አካባቢ በሚገኙ የሸንኮራ
አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኀበራት
የሚለማ ነው፡፡
10 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት
አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኮርፖሬሽኑ፣ በስኳር
ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ተከበረ
አለም አቀፍ የሴቶች ቀን “ሴቶችን ማብቃት
ህብረተሰቡን ማብቃት ነው” በሚል መሪ
ቃል በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት፣ በስኳር
ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በተለያዩ ዝግጅቶች
ተከበረ፡፡
በዋናው መ/ቤት መጋቢት 5 ቀን 2007 ዓ.ም.
ቀኑ ተከብሮ በዋለበት ወቅት ሴቶችን በማብቃት
ረገድ የተገኙ ስኬቶችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች፤
የኮርፖሬት ሥርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት ዓላማ፣
ተግባር እና ዐበይት ክንውኖች እንዲሁም የሴቶች
እኩልነትን ለማረጋገጥ የወጡ ህጎችና ያስገኙት
ለውጥ በሚሉ ርዕሶች ጹሑፎች ቀርበው ውይይት
ተካሂዷል፡፡
በተያያዘ ዜና መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ
አበባ ከተማ መነሻውንና መድረሻውን አትላስ ሆቴል አድርጎ በተካሄደ “ቅድሚያ ለሴቶች” የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ላይ 160 የሚሆኑ የዋና
መ/ቤት እንዲሁም የወንጂ ሸዋ፣ የመተሐራ፣ የፊንጫአ እና የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካዎች ላይዘን ኦፊስ ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአለም ለ104ኛ፣ በአገራችን ደግሞ ለ39ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡
አለም አቀፉ የሴቶች ቀን በዋና መስሪያ ቤት በተከበረበት ወቅት
ጣፋጭ | 11
በስኳር ኢንዱስትሪ የአትክልትና ፍራፍሬ
ልማትን የማስፋፋት ሥራዎች ተጀመሩ
በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት
ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ልማቱን ለማስፋፋትና ከዘርፉ
ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችሉ ሥራዎች ተጀመሩ፡፡ ለተግባራዊነቱም
ሥራውን የሚመራ የተጓዳኝ ምርቶችና አግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ ተቋቁሞ
በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
የዘርፉ ዋና ተግባር የእንስሳት፣ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት
ከስኳር ምርት በተጓዳኝነት ማልማት ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በመተሐራ
ስኳር ፋብሪካና በከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለሚገኘው 200
ሄክታር የፍራፍሬ እርሻ ሙያዊ እገዛ በማድረግ ላይ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በእያንዳንዱ ነባርና አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች
የፍራፍሬ ልማትን ከ200-300 ሄክታር መሬት ላይ በማልማት እና
የአካባቢውን ማህበረሰብ በአማከለ መልኩ በአዋጭነት ጥናት የተደገፈ
የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በማከናወን ምርቱን በፋብሪካ ማቀነባበር
የሚቻልበት ደረጃ ላይ ለማድረስ የተቋቋመ ዘርፍ ነው፡፡
በፍራፍሬ ልማት ከተካተቱት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ብርቱካንና ማንጎ
ሲሆኑ፣ ምርቶቹን በስኳር ፋብሪካዎች እና በፕሮጀክቶች አካባቢ
ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጠቀሜታ ከማዋል በተጨማሪ
ለአካባቢው ገበያ ለማቅረብ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ
ናቸው፡፡
በዚህ ዓመት በበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በአማራ ግብርና ቢሮ
በሚዘጋጅ የማንጎ ችግኝን በመጠቀም 50 ሄክታር ልማት ለማከናወን
የቦታ መረጣና የመስኖ ዲዛይን ሥራ በአማራ ውሃ ሥራዎች ዲዛይንና
ቁጥጥር እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በተመሳሳይበበጀትዓመቱበኩራዝስኳርልማትፕሮጀክትከአካባቢው
የችግኝ ማፍያ በማፈላለግ 35 ሄክታር የማንጎ ተከላ ሥራ ለማከናወን
በዕቅድ የተያዘ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱም ለተግባራዊነቱ እየተንቀሳቀሰ
ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ 25 ሄክታር ማንጎ
ለማልማት የሚያስችል ችግኝ የማልማት ስራ በፋብሪካው በኩል
ተጀምሯል፡፡
የብርቱካን ልማትን በተመለከተም በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በ0.5
ሄክታር ላይ በተቋቋመ ችግኝ ጣቢያ ከጥቅምት 2007 ዓ.ም ጀምሮ
45,000 የሚደርስ የብርቱካን መሠረተ ግንድ የሚሆን ኮምጣጤ
ተዘርቶ ከ16,000 በላይ በቅሏል፡፡
ዘርፉ በማልማት ላይ የሚገኘው የብርቱካን ችግኝ
12 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በዙሪያው ከሚገኙ 18 ገጠር
ቀበሌዎች ተወካዮችና ጐሣ መሪዎች ጋር ተወያየ
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በዙሪያው ከሚገኙ የ18
ገጠር ቀበሌ ተወካዮችና የጐሣ መሪዎች እንዲሁም
ከፈንታሌ ወረዳ መስተዳድር አካላት ጋር ውይይት
አካሄደ፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም፣ የፈንታሌ ወረዳ
አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ድሪርሣ፣ የስኳር ኮርፖሬሽን
የህዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት ዳይሬክተር አቶ ኤካል
ነትር እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በውይይቱ መግቢያ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ
አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም ለማህበረሰቡ ተወካዮችና
የሀገር ሽማግሌዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር
ካደረጉ በኋላ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት
ለፋብሪካው ስኬት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና
አቅርበዋል፡፡
በጋራ ውይይት መድረኩ ፋብሪካው ለማህበረሰቡ
ያከናወናቸው የመንገድ ሥራ፣ ለከብቶች መኖ
የሚውል የአገዳ ገለባ አቅርቦት፣ የመስኖ ውሃ
አቅርቦት፣ የኮምፖስት ማዳበሪያ አቅርቦት፣ የንፁህ
መጠጥ ውሃ ግንባታና ሌሎችም በምስል ተደግፈው
በስላይድ ቀርበዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የተገኙት ተወካዮችና የጐሣ
መሪዎች ከዚህ በፊት የፋብሪካውና የአካባቢው
ማህበረሰብ ግንኙነት ጥሩ እንዳልነበረ አስታውሰው
በዚህም የተነሳ የተወሰኑ ግለሰቦች ፋብሪካውን በጥላቻ
የሚመለከቱበት እና ለሀብትና ንብረቱ የማይጨነቁ
እንዲሁም አገዳው በከብቶች ጉዳት ሲደርስበት
በቸልታ ይመለከቱ እንደነበር አውስተዋል፡፡
ይሁንና ሁኔታው ከሁለት ዓመት ወዲህ በተደጋጋሚ
በተደረገ ውይይት መለወጡን ገልጸው ፋብሪካውና
የአካባቢው ማህበረሰብ ለጋራ ጥቅም በጋራ መቆም
መቻላቸው አስደሳች ነው ብለዋል፡፡
አያይዘውም ፋብሪካው ለአካባቢው ማህበረሰብ
ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ የሀገር ሀብት
መሆኑን በመረዳታቸው የባለቤትነት ስሜት
እንደፈጠረባቸውም አስረድተዋል፡፡
የፈንታሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ድሪርሣ
በበኩላቸው ፋብሪካው ከአካባቢው ማህበረሰብ
ጋር ያደረጋቸው ተከታታይ ውይይቶች ተጨባጭ
አዎንታዊ ለውጦች ማምጣታቸውን ገልጸውዋል፡፡
በስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት
ዳይሬክተር አቶ ኤካል ነትር በበኩላቸው የስኳር
ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ
ማህበረሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ የልማት
ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡
፡ በቀጣይ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ የሚገኙ
አርብቶ አደሮች የሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው
በማቅረብ የበለጠ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉበት
እድል እንዳለም ገልጸዋል፡፡
በየዓመቱ ይካሄድ የነበረው የፋብሪካውና የአካባቢው
ማህበረሰብ ውይይት በቀጣይ በየስድስት ወራት
እንደሚካሄድ መገለጹን የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን ዘገባ ያመለክታል፡፡
የስብሰባው ተካፋዮች በከፊል
ጣፋጭ | 13
ቆይታአካባቢያችን - ህልውናችን
ከተፈጥሮ ገፀ በረከቶች መካከል የሰው ልጅን
ሕይወት እንደወርቅ ፍልቃቂ የሚያንፀባርቁት
ዕፅዋት ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡
፡ ዕፅዋት ምትሃታዊ መስህብ ያላቸው እና
የተፈጥሮ መስተጋብርን የሚያወዙ ታላቅ
ፀጋዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ከሕይወታችን
ጋር እንደድርና ማግ የተሸመኑ የተፈጥሮ
ችሮታዎች በስራ አካባቢ መንከባከብ ብዙ
ተዓምራትን ይቸራሉ፡፡
አረንጓዴ ዕፅዋት የሕይወት ኢንጂነሮች
ናቸው፡፡ ጤናማ አስተሳሰብን የሚያዳብሩ
መንፈስን የሚያለመልሙና የሚያበረቱ
ምትሃቶች ናቸው፡፡ ድብርትን አራግፈው
መነቃቃትን በመፍጠር ዘና ፈታ ያደርጋሉ፡
፡ አዕምሮ አዎንታዊ ሃይልን እንዲያፈልቅ
በማድረግ አካላዊና አዕምሯዊ ብቃትን ከፍ
በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና እንዳላቸውም
በርካታ ምርምሮች ያስረዳሉ፡፡
ይህም ብቻ አይደለም በዕፅዋት የወዛ አካባቢ
ያማልላል፤ ሁሌም አትለዩኝ ያሰኛል፤
መልካም ግንኙነትን ይፈጥራል፤ ማህበራዊ
መስተጋብርንም ያጎለብታል፡፡
ዕፅዋትን የተላበሱ አካባቢዎች ከወርቅና
ከዕንቁ የላቁ ሃብቶች ናቸው፡፡ ዕፅዋት ቋንቋ
አላቸው፤ የሚያፅናና፣ የሚያረጋጋ እና ተስፋን
የሚፈነጥቅ፡፡ ለአካባቢ እንክብካቤ ስንተጋ
ይህ ሁሉ ችሮታ ከደጅ የሚታፈስ ነው ፡፡
እነዚህን ፀጋዎች ስናረክሳቸውና
ስናጎሳቁላቸው አፀፋው በራስ ላይ ጉስቁልናን
ማብቀል ይሆናል፡፡ ለዕፅዋት ዋጋና ክብር
የማይሰጥ አካባቢ ትልቅ ዋጋ ያስከፍለዋል፤
ያስገብረዋል፤ ውስብስብ ፈተናንም ይደቅናል፡
፡
በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የለውጥ ንቅናቄ
ውስጥ አካባቢን ለስራ ምቹና ፅዱ የማድረግ
ተግባር ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ነው፡፡
በዚህም የስራ አካባቢን በአረንጓዴ ዕፅዋት
የማስዋብ ስራዎች አበረታች ለውጥን
እያስመዘገቡ ነው፡፡ በፋብሪካ ዙሪያ፣
በቢሮዎችና በመኖሪያ መንደሮች አካባቢ
የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ላይ የሰራተኛውና
የቤተሰቡ ተሳትፎ ልምላሜን እየፈጠረ
ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት የስራና የመኖሪያ
አካባቢዎች ፅዱና ማራኪ፣ ለስራና ለኑሮ
ምቹና ተስማሚ እየሆኑ ነው፡፡
እንዲያም ሆኖ አካባቢን በዕፅዋት
የማሳመር ስራው ቀጣይ ሆኖ ሰፊ ጥረትን፣
ትጋትንና ቁርጠኝነትን ይጠይቃል፡፡ ስራው
ደግሞ ከአመለካከት ለውጥ ይጀምራል፡
፡ አካባቢያችን ጤናችን፣ ሰላማችንና
ውበታችን ነው፡፡ ኑሯችን፣ ፀጋችን እንዲሁም
ሕይወታችን ጭምርም ነው፡፡ ይህ እውን
የሚሆነው ግን ለአካባቢያችን አዎንታዊ
እንክብካቤ ስንሰጥ ብቻ ነው፡፡
እናም የስራንና የመኖሪያ አካባቢዎችን
በዕፅዋት የማሳመር ስራው ይበልጥ ሊጠናከር
ይገባዋል፡፡
በዚህ ረገድ ስንፍና፣ ቸልተኝነትና አያገባኝም
ባይነት የሕወት ኪሳራን እንጂ ትርፋማነትን
አይለግስም፡፡ ህይወት ልክ እንደዛፍ ናት፤
ስሩ ደግሞ ንቃተ ህሊና ነው፡፡ እናም ስሩ
ከተንሰራፋ ዛፉ ጤናማ ይሆናል፡፡ የእኛም
ጤናማ ሕይወት ለአረንጓዴ ልማት በሚኖረን
ንቃተ ህሊና እና ተሳትፎ ልክ የሚወሰን ነው፡፡
ስለሆነምአካባቢያችንሰርተንየምንከብርበት፣
ቀጣይና ጤናማ ትውልድን የምናፈራበት እና
በስኳር ልማት ረገድ ሀገራዊ ተልዕኳችንን
በብቃት የምንወጣበት እንዲሆን ዕፅዋትን
የማልማት ስራችን ተጠናክሮ መቀጠል
ይገባዋል፡፡ እስካሁንም አርዓያነት ያለው
ተግባራትን ያከናወኑ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡
፡ ያልጀመሩ ደግሞ ለራስ ህልውና ሲባል
እንዲያስቡበት ግድ ይላቸዋል፡፡
14 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት
ባለቤትነት እስከ ሕይወት
መስዋዕትነት
የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ለዘርፉ
ያላትን ምቹ የአየር ንብረት፣ በመስኖ መልማት
የሚችል ሰፊ መሬትና የውሃ ሀብት ጥቅም ላይ
ከማዋል ባሻገር በተቋቋሙባቸው አካባቢዎች
የሚገኙ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን
ተጠቃሚ ማድረግ ተቀዳሚ ዓላማቸው
ነው፡፡ ለአብነትም በአፋር ክልል ተግባራዊ
በመደረግ ላይ የሚገኙት የተንዳሆና የከሰም
እንዲሁም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ክልል የኦሞ ኩራዝ፣ በአማራ ክልል
የበለስ እና በትግራይ ክልል የወልቃይት ስኳር
ልማት ፕሮጀክቶች በአካባቢያቸው ለሚገኙ
አርብቶ አደሮች እና አርሶ አደሮች ሰፊ የስራ
ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የተለያዩ የመሠረተ
ልማትና የማህበራዊ ተቋማት ግንባታዎችን
በማከናወን የአካባቢዎቹን ማህበረሰብ
ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ፕሮጀክቶቹ በመሠረተ ልማትና
ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ
ብቻ ሳይወሰኑ አርብቶ አደሮቹ
ሸንኮራ አገዳ አልምተው
ለፋብሪካዎቹ በማቅረብና አገዳውን
በጉልበታቸው በመንከባከብ
በሚያገኙት ገቢ ተጠቃሚ
እንዲሆኑ እያደረጉ ይገኛሉ፡
፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ በመስኖ
የሚለማ መሬት አዘጋጅቶ ከማቅረብ ጀምሮ
አርብቶ አደሮቹ የሸንኮራ አገዳ እንዲያለሙ
የዘር አገዳ፣ ጸረ-አረም መድሀኒትና ሌሎች
ሙያዊ እገዛዎች እንዲያገኙ በማድረግ ላይ
ይገኛሉ፡፡
በተመሳሳይ ስኳር በማምረት ላይ የሚገኙት
ሦስቱ ነባር የስኳር ፋብሪካዎችም
በአካባቢያቸው ከሚገኙ የህብረተሰብ
ክፍሎች ጋር ያላቸው ቁርኝት እጅጉን የጠበቀ
ነው፡፡ በማሳያነትም በወንጂ ሸዋ ስኳር
ፋብሪካና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል
በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተውን
ዘለቄታዊ ትስስር መጥቀሱ በቂ ይሆናል፡
፡ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ለስኳር ምርቱ
በግብአትነት የሚጠቀምበትን የሸንኮራ
አገዳ ልማት ብንመለከት ፋብሪካው በራሱ
የሚያለማው የመሬት ስፋት 5 ሺህ 800
ሄክታር ሲሆን በአካባቢው አርሶ አደር
የሚለማው መሬት ፋብሪካው ከሚያለማው
ልቆ 7 ሺህ ሄክታር ደርሷል፡፡
ይህንን ያህል ስፋት ያለውን የሸንኮራ አገዳ
መሬት በማልማት ላይ የሚገኙት 7 ሺህ 633
አባ/እማ ወራዎች ናቸው፡፡ እነዚህ አርሶ
አደሮች የትዳር አጋርና በትንሹ አንድ አንድ
ልጅ ያላቸው ናቸው ተብሎ ቢታሰብ እንኳን
22 ሺህ 900 የሚሆኑ ሰዎች ኑሮ በቀጥታ
ከፋብሪካው ህልውና ጋር የተያያዘ ሆኖ
ይገኛል፡፡
በመሠረተ ልማት፣ በማህበራዊ ተቋማትና
በሥራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚ የሆኑና
በስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና ፋብሪካዎች
አካባቢ የሚገኙ ዜጎች ታዲያ ከዘርፉ ያገኙትን
ተጠቃሚነት የሚያደናቅፉ ሰው ሰራሽም
ሆነ የተፈጥሮ አደጋዎች ሲያጋጥሙም ሆነ
ያጋጥማሉተብሎሲታሰብተቆርቋሪነታቸውን
በተግባር ቀድመው በማረጋገጥ ተወዳዳሪ
አይገኝላቸውም፡፡ በቅርቡ በፊንጫአ ስኳር
ፋብሪካ የተስተዋለውም ይኸው ነው፡፡
እለተ ቅዳሜ መጋቢት 5/2007ዓ.ም
ለፊንጫአ ስኳር ፋብሪካና ለሠራተኞቹ
እንዲሁም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ
ኑሮአቸው ከፋብሪካው ጋር ለተያያዘው
የአካባቢው ህብረተሰብ እንደወትሮዋ ቅዳሜ
አልነበረችም፡፡ ከረፋዱ 5 ሰአት አካባቢ
ከሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ማቀጣጠያ ክፍል
ሳይታሰብ የተነሳው የእሳት አደጋ ያስከተለው
ጭስ ፋብሪካውን ሙሉ ለሙሉ ሸፍኖታል፡፡
ሠራተኛውና የአካባቢው ህብረተሰብ
እንዲሁምየኦሮሚያክልልየተለያዩተቋማትና
የፌደራል ፖሊስ የእሳት አደጋው
የፋብሪካው ልዩ ልዩ የማምረቻ
መሳሪያዎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ
ይከላከላል ባሉት ነገር ሁሉ እሳቱን
ለማጥፋት ከወዲህ ወዲያ ይላሉ፡
፡ የስኳር ፋብሪካው ከኤታኖል
ማምረቻ ፋብሪካው ብዙም ርቀት
የሌለው መሆኑ ደግሞ እሳቱን
በምንም አይነት መስዋእትነት
በፍጥነት የመጥፋቱን አስፈላጊነት የግድ
አድርጎታል፡፡
እሳቱ እንዳይዛመትና በስኳር ማምረቻ
“ፋብሪካው ከሚቃጠል እኔ
ተቃጥዬ ላድነው“
“
“
ጣፋጭ | 15
ፋብሪካው ላይ ከፍተኛ ጉዳት
እንዳያደርስ በተደረገው እልህ አስጨራሽ
ርብርብ ከፍተኛ መስዋትነት የከፈሉት
የፋብሪካው ሠራተኞች ነበሩ፡፡ ይህ
እልህ አስጨራሽ ርብርብ ደግሞ ውዱንና
መተኪያ የሌለውን የሰው ሕይወትና
የአካል መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ነበር፡፡
ፋብሪካው ለእርሱ እና ለቤተሰቡ
ዋልታ እንደሆነ የገባው ሠራተኛውና
የአካባቢው ህብረተሰብ መስዋዕትነት
ለመክፈል ሳያመነታ አስቸጋሪውን ፈተና
ተጋፍጦ እሳቱ ፋብሪካው ላይ የከፋ
ጉዳት ሳያደርስና እጅግ አውዳሚ ጥፋት
ሊያስከትል ወደሚችለው ወደ ኤታኖል
ፋብሪካውም ሳይዛመት በቁጥጥር ስር
አውሎታል፡፡
ይሁንና ይህ ፋብሪካውን ለማዳን
የተደረገው አስቸጋሪ ርብርብ
ፋብሪካውን ከውድመት ለመታደግ
ሲረባረቡ ከነበሩት ሠራተኞች መካከል
የሦስቱን ሕይወት ቀጥፏል፡፡ ሟቾቹ
ልጆቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን
የሚሰናበቱበት፣ ያሰቡትንና የልባቸውን
የሚተነፍሱበት፣ ያቀዱትን የሚያሳኩበት
ጊዜ ሳያገኙ ለአገራቸዉና ለሕዝባቸዉ
በድንገት መስዋእት ሆነዋል፡፡ በሌሎች
14 ሠራተኞች ላይም ከባድና ቀላል ጉዳት
ደርሶባቸዋል፡፡
የሕይወት መስዋዕትነት የጠየቀው ይህ
ፍጹም የባለቤትነት ስሜት ፋብሪካውን
ከውድመት ታድጎ በሦስት ቀናት ውስጥ
ወደ ሥራ እንዲገባ አስችሎታል፡፡
ጀግንነት በጦር ሜዳ ብቻ አይደለም
የሚገኘው፡፡ ማንኛውም ዜጋ
በተሰማራበት የሙያ መስክ ሁሉ
የተጣለበትን ኃላፊነት በትጋትና በቅንነት
ከተወጣ እርሱ ጀግና ነው፡፡ የአገርና
የሕዝብ ሀብት የሆነው ይህ ፋብሪካ
እንዳይጎዳ ቤቴን፣ ንብረቴን ሳይሉ
የሕይወት እና የአካል መስዋዕትነት
ካለማመንታት የከፈሉት እነዚህ
ወገኖችም ጀግኖቻችን ናቸውና ክብር
ይገባቸዋል፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽንና መላው ሠራተኛው
“ ፋብሪካው ከሚቃጠል እኔ ተቃጥዬ
ላድነው “ በማለት ክቡር የሕይወትና
የአካል መስዋዕትነት ለከፈሉ
ጀግኖች ቤተሰቦች አስፈላጊውን እገዛ
እንደሚያደርጉና በማንኛውም ጊዜ
ከጎናቸው እንደማይለዩ ያረጋግጣሉ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ በሆስፒታል ተገኝተው የተጎዱ ሰራተኞችን ሲጠይቁ
16 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት
ለአርብቶ አደሩ የልማት ጥያቄ ምላሽ እየሰጠ ያለው የኩራዝ
ስኳር ልማት ፕሮጀክት
ትናንት የከብቶቹን ጭራ ተከትሎ የግጦሽ መሬት እና ውኃ ፍለጋ ከቦታ
ቦታ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ በመጓዝ ኑሮውን ይገፋ የነበረው በደቡብ
ኦሞ የሰላማጎ ወረዳ አርብቶ አደር ከማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ
ተቋማትም ሆነ ከመሰረተ ልማት አገልግሎቶች ጋር ሳይተዋወቅ
ለዘመናት ኖሯል፡፡ ዛሬ ላይ ግን የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት
ይዞለት በመጣው በረከት የአርብቶ አደሩ የልማት ጥያቄ ምላሽ
ማግኘቱን ቀጥሏል፡፡
በኩራዝስኳርልማትፕሮጀክት
አማካኝነት በሰላማጎ ወረዳ
በምትገኝ አርብጆ በተሰኘች
ቦታ በሶስት መንደሮች
የተሰባሰቡ የአካባቢው
አርብቶ አደሮች በተገነባላቸው
የማኅበራዊ ተቋማት ተጠቃሚ
መሆን ሲጀምሩ ነበር በሌሎች
የወረዳዋ መንደሮችና አጎራባች
ዞኖች የሚኖሩ አርብቶ አደሮች
ለዘመናት ይገፉት የነበረውን
አስከፊ ኑሮ ፕሮጀክቱ
በምን ያህል ደረጃ ሊቀርፍ
እንደሚችል የተረዱት፡፡ እናም
የፕሮጀክቱ እንቅስቃሴ ተፋጥኖ እና ወደ እነርሱ አካባቢ ደርሶ እንደ
አርብጆ አካባቢ አርብቶ አደሮች የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ
ተቋማትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ቀን
መናፈቅና ጥያቄያቸውን ለመንግሥት ማቅረብ የጀመሩት ገና ከጅምሩ
ነበር፡፡
ፕሮጀክቱከፌዴራልናከክልሉመንግሥትጋርበመቀናጀትለአካባቢው
ተወላጅ አርብቶ አደሮች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠቱ ዛሬ ላይ አርብጆ
በተባለ ቦታ በሶስት መንደሮች ከተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች በተጨማሪ
ጉራ እና ማኪ በተሰኙ አካባቢዎች አርብቶ አደሮች በመንደር
ተሰባስበው የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና የመሰረተ
ልማት አውታሮች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡ በተጨማሪም የሙርሲ
ብሔረሰብ ተወላጆች በመንደር በተሰባሰቡበት ኃይሎዋ አንድ በተሰኘ
ቦታም የማኅበራዊ ተቋማት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣
ኃይሎዋ ሁለት በተባለ አካባቢም በመንደር ለሚሰባሰቡ አርብቶ
አደሮች የማኅበራዊ ተቋማት
ግንባታ ለማከናወን ግንባታውን
ከሚያከናውኑ ተቋማት ጋር ውል
እየተገባ ይገኛል፡፡
ራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት
በተጀመረባት የሰላማጎ ወረዳ
በፕሮጀክቱ ክልል አካባቢዎች
የሚኖሩ አርብቶ አደሮች ከእርሻ ስራ
ጋር የማይተዋወቁ ነበሩና ፕሮጀክቱ
ከሚመለከታቸው የመንግሥት
አካላት ጋር በመሆን ከከብት ማርባት ስራቸው በተጨማሪ የእርሻ
ስራ ማከናወን ይችሉ ዘንድ የእርሻ ስራን እንዲማሩ በመስኖ የሚለማ
የእርሻ መሬት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ይህ በመሆኑም መጀመሪያ
በመንደር የተሰባሰቡት የአርብጆ አካባቢ አርብቶ አደሮች በ2ሺህ
400 ሄክታር ላይ በሁለት ዙር በቆሎ አምርተው ተጠቅመዋል፡፡
ዛሬ ላይ ደግሞ በጉራ፣ማኪ እና
ኃይሎዋ አካባቢዎች በመንደር
የተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች በመስኖ
የሚለማ መሬት ተሰጥቷቸው
የመሬት ዝግጅት ስራው በፕሮጀክቱ
እየተከናወነላቸው ይገኛል፡፡
የአካባቢውን ተወላጅ አርብቶ አደር
ከፕሮጀክቱ የልማት እንቅስቃሴ
የመጀመሪያ ተጠቃሚ ለማድረግ
እየሰራ የሚገኘው የኩራዝ ስኳር
ልማት ፕሮጀክት ከፕሮጀክቱ ክልል
በርቀት የሚገኙ አርብቶ አደሮችም
የልማቱ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ
ላቀረቡት ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ
በመስጠት የተለያዩ ማኅበራዊ
ተቋማትና የመሰረተ ልማቶች እንዲሁም የመስኖ ውኃ ተጠቃሚ
እንዲሆኑ አስችሏል፡፡
የአካባቢው አርብቶ አደሮች ለስኳር ኮርፖሬሽን እና ለመንግሥት
ያቀረቡት የልማት ጥያቄ ምላሽ በማግኘቱ ዛሬ የአኗኗር ሁኔታቸው
በእጅጉ ከመለወጡ ባሻገር በፕሮጀክቱ በተለያዩ የስራ መደቦች
ተቀጥረው መስራት የቻሉበት ሁኔታም ተፈጥሯል፡፡
ኦሊሉ ቻርኔሌይ የሙርሲ ተወላጅ ነው፡፡ ጉራ በተባለው መንደር
እየተከናወነ በሚገኘው የፕሮጀክቱ የሸንኮራ አገዳ እርሻ ስራ የመሬት
ዝግጅት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ የአካባቢውን አርብቶ
አደር ልጆች አሰልጥኖ በፕሮጀክቱ ስራ ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ
ባደረገው እንቅስቃሴ በትራክተር ኦፕሬተርነት በ2005 ዓ.ም. በጫንጮ
ትራክተር ማሰልጠኛ ተቋም ሰልጥኖ በፕሮጀክቱ የአገዳ እርሻ ስራ
ላይ በሰለጠነበት ሙያ ተቀጥሮ እየሰራ ይገኛል፡፡ “አገሬ ሁልጊዜ
ጣፋጭ | 17
የምትታወቅበትን ድህነት ያስወግዳል ተብሎ ተስፋ በተጣለበት የስኳር
ልማት ዘርፍ እየተሳተፍኩ በመገኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ” የሚለው
ኦሊሉ ቻርኔሌይ ወደ ማሰልጠኛ ተቋሙ ገብቶ ከመሰልጠኑ በፊት
ምንም ዓይነት ልምድ ያልነበረውና ትራክተር ምን እንደሆነ ግንዛቤ
ያልነበረው እንደነበር ያወሳል፡፡
ሌላው በትራክተር ኦፕሬተርነት ሰልጥኖ እና በፕሮጀክቱ በቋሚነት
ተቀጥሮ የሚገኘው ካሳሁን ምታቸው ሲሆን የዲሜ ብሔረሰብ ተወላጅ
ነው፡፡ እንደ ኦሊሉ በፕሮጀክቱ በአገዳ ማሳ ዝግጅት ስራ በትራክተር
ኦፕሬተርነት እየሰራ የሚገኘው ካሳሁን ፕሮጀክቱ በአካባቢው
በመጀመሩ የልማቱ የመጀመሪያ ተጠቃሚ ሊሆን እንደቻለ በማውሳት
በፕሮጀክቱ እየተገነባ የሚገኘው ስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት ገብቶ ስኳር
ማምረት ሲጀምር ማየት ምኞቱ እንደሆነ ይናገራል፡፡
የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለአካባቢው አርብቶ አደሮች ልጆች
ጉራ በተባለ ቦታ ባስገነባው ጉራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት
በርዕሰ መምህርነት እያገለገለ የሚገኘው ምታቸው ደነቀ የዲሜ
ብሔረሰብ ተወላጅ ሲሆን የቦዲዎችን ቋንቋ አቀላጥፎ ይናገራል፡፡
በትምህርት ቤቱ 43 ተማሪዎች እየተማሩ እንደሚገኙና 18ቱ ህፃናት
ቀሪዎቹ 15ቱ ጎልማሳዎች ናቸው ይላል፡፡ ርዕሰ መምህር ምታቸውን
ታዲያ በእጅጉ የሚያስደንቀው በጎልማሳ አርብቶ አደር ተማሪዎቹ
ዘንድ የሚታየው የትምህርት ፍላጎት ነው፡፡ ትምህርት ቤቱ ደብተርና
እርሳስ ለተማሪዎቹ በማቅረብ ከማበረታት ባሻገር ለተማሪዎቹ ምሳ
እንዲሆን ገንፎ አዘጋጅቶ እንደሚያቀርብና በተለይ ሴት ተማሪዎችን
ለማበረታት አንድ ወር ሳታቋርጥ ትምህርቷን ለተከታተለች ተማሪ
ትምህርት ቤቱ አንድ ሊትር ዘይት እንደሚሰጥ ርዕሰ መምህሩ
አጫውተውናል፡፡ ጉራ በተባለው አካባቢ ቲካዎች የሚባለው መንደር
አርብቶ አደሮች የተሰባሰቡበት መንደር ሲሆን በዚህ ቦታ በተገነባ
የእህል ወፍጮ ስትገለገል ያገኘናት የቦዲ ብሔረሰብ ተወላጅ ጋታፓይ
ዞጊይ ትባላለች፡፡ ጋታፓይ በአካባቢው የትምህርት፣ የወፍጮ፣
የውኃ እንዲሁም ለከብቶቻቸው የህክምና አገልግሎቶች ማግኘት
እንደጀመሩ ገልፃ በአካባቢዋ በተገነባው ትምህርት ቤት ትምህርቷን
በሚገባ እየተከታተለች እንደምትገኝና በዚህም በትምህርት ቤቱ በኩል
የምግብ ዘይት እንደሚሰጣት ነው የምትናገረው፡፡
በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሕዝብ አደረጃጀት፣ካሳ ክፍያና
መልሶ ማቋቋም ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አስረስ
አዳሮ እንደሚገልጹት በመንደር ተሰባስበው በእርሻ ስራ በመሰልጠን
ማምረትና መጠቀም የጀመሩ አርብቶ አደሮች የወንጂ ሸዋ ስኳር
ፋብሪካን እና በአካባቢው የሚገኙ የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ
ማኅበራትን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ ለፕሮጀክቱ
በሸንኮራ አገዳ አብቃይነት ለመሳተፍ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
በዚህ መሰረት ፕሮጀክቱ ለ1ሺ 430 አርብቶ አደሮች 1ሺ 72 ሄክታር
መስኖ ገብ የእርሻ መሬት የዝግጅት ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
እያንዳንዱ አርብቶ አደር አንድ ሄክታር ማሳ እንዲኖረው በማድረግም
በ0.25 ሔክታር መሬቱ ላይ የተለያዩ ሰብሎችን እንዲያለማና በቀሪው
0.75 ሔክታር መሬት ላይ ደግሞ ሸንኮራ አገዳ አብቅሎ ለስኳር
ፋባሪካው የሚያቀርብበት ሁኔታ እንዲኖር ከወዲሁ ስራዎች በስፋት
እየተከናወኑ እንደሚገኙም ነው አቶ አስረስ የሚገልጹት፡፡
18 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት
የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ስራ ከጀመረ አንስቶ እስካሁን 36 ሺህ
ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል፤ 158 ማኅበራትም ተደራጅተው
ከተለያዩ ግንባታዎች ጀምሮ እስከ አገልግሎት መስጠት ስራዎች ድረስ
እየተሳተፉ እንደሚገኙም ነው የስራ ኃላፊው ያብራሩት፡፡ የአካባቢው
አርብቶአደሮችበፕሮጀክቱከጥበቃጀምሮእስከፋብሪካኦፕሬሽንስራ
ላይ በስፋት የሚሳተፉበት ስልትም በመንግሥት ተነድፎ እየተተገበረ
መሆኑንለመረዳትችለናል፡፡ለአብነትምፕሮጀክቱበቅርቡ30የሚሆኑ
ወጣቶችን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመስኖ ልማት አሰልጥኖ በአሁኑ
ወቅት በስራ ላይ እንደሚገኙ መጥቀስ ይቻላል፡፡
በአገራችን የስኳር ፋብሪካ የግንባታ ታሪክ አብዛኛው ግንባታው በአገር
በቀል ተቋማት የሚካሄድ እና ከፍተኛ የቴክኖሎጂ እና የዕውቀት
ሽግግር እየተከናወነበት የሚገኝ እንዲሁም ከተሞክሮ ትልቅ ስንቅ
የተሰነቀበትና ወደፊትም በአገራችን የሚገነቡ የስኳር ፋብሪካዎችን
ሙሉ በሙሉ ማከናወን የሚያስችል አቅም የተገነባበት የኦሞ ኩራዝ
ስኳር ልማት ፕሮጀክት የቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ነው
የሚሉት ደግሞ አቶ ካሳ ተስፋዬ የቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ
አስኪያጅ ናቸው፡፡
በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና የግንባታ ተቋራጭነት
ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር
ፋብሪካ ከጥቂት የቴክኖሎጂና የልምድ መካበትን ከሚጠይቁ ስራዎች
በስተቀር አብዛኛው የግንባታ ስራው በዋና ተቋራጩ፣ በበርካታ
አገር በቀል የግንባታ ተቋራጮችና አማካሪዎች እየተከናወነ የሚገኝ
መሆኑን አቶ ካሳ ጠቅሰዋል፡፡ በስራ ላይ በሚገኙ የአገሪቱ ነባር
ስኳር ፋብሪካዎች አገር በቀል ተቋራጮች ያልተሳተፉበት መሆኑን
ያስታወሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር
ፋብሪካ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ የተካበተበት ፕሮጀክት ነው በማለት
የአገራችንን ስኳር ፋብሪካዎች የግንባታ ታሪክ ያወሳሉ፡፡ በአሁኑ
ወቅት የፕሮጀክቱ የሸንኮራ አገዳ ማሳ ሽፋን ከ7ሺህ 300 ሄክታር
በላይ እንደደረሰና በ2007 በጀት ዓመት የታቀደውን 10ሺህ ሄክታር
መሬት በሸንኮራ አገዳ ለመሸፈን በሶስት ሽፍት የመሬት ዝግጅትና የዘር
አገዳ ተከላ ስራ በመከናወን ላይ እንደሆነ አቶ ካሳ ይናገራሉ፡፡
አቶ ዓለም ከበደ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብረካ ኦፕሬሽን
ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው በፕሮጀክቱ እየተከናወነ
ስለሚገኘው የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር የዋና ሥራ አስኪያጁን
ሀሳብ ሲያጠናክሩም የፕሮጀክቱ 60 የሚሆኑ የምህንድስና ባለሙያዎች
በሜካኒካል፣በኤሌክትሪካል እና በምርት ፕሮሰስ የፋብሪካው የግንባታ
ስራዎች ላይ መሳተፋቸውን ነው የጠቆሙት፡፡
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እና በእርሱ ስር የተለያዩ
ግንባታዎችን እያከናወኑ የሚገኙ አገር በቀል ተቋማት ባለሙያዎች
የግንባታ ሂደቱን እየገመገሙ የሚሰሩበት ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ
ተጠናክሮ እየተሰራበት የሚገኝ በመሆኑም የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ
ስኳር ፋብሪካ ግንባታ በአገራችን የስኳር ፋብሪካ ግንባታ ታሪክ ከፍተኛ
ተሞክሮ የተገኘበትና የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር የተከናወነበት
እንዲሁም የፕሮጀክቱ የምህንድስና ባለሙያዎች ወደፊት የኦፕሬሽን
ስራውን ሙሉ በሙሉ ተረክበው መስራት የሚችሉበትን መደላድል
የፈጠረ ነው ሲሉም ይገልፃሉ፡፡
አምስት ስኳር ፋብሪካዎች በሚገነቡበት በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት
ፕሮጀክት የቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካን የሚገነባው ኮምፕላንት
የተሰኘ የቻይና ኩባንያም የካምፕ ግንባታውን አጠናቆ ወደ ፋብሪካ
ግንባታ ስራው እየገባ ሲሆን፣ ሌላው የቻይና ኩባንያ የቁጥር ሶስት
ፋብሪካን ግንባታ ማከናወን ይችል ዘንድ የቅድመ ክፍያ ተፈጽሞለት
የሳይት ርክክብ መፈጸሙን የነገሩን ደግሞ የኩራዝ ቁጥር ሶስት ስኳር
ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አክሊሉ አዳኝ ናቸው፡፡ ከኦሞ ወንዝ
እስከ ቁጥር ሶስት ፋብሪካ የሚወስድ የ43 ኪሎ ሜትር የመንገድ ስራ
ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን፣ የዋና መስኖ ግንባታውን
ቁጥር ሶስት ስኳር ፋብሪካ እስከሚገነባበት ሻርማ እስከተባለ አካባቢ
ለማድረስበስኳርኮርፖሬሽንበኩልየሰርቬይንግእናዲዛይንእንዲሁም
በፕሮጀክቱ በኩል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ከአቶ
አክሊሉ ገለጻ ተረድተናል፡፡ ወደ ፋብሪካ ቁጥር 3 እና 4 የሚደርስ
የመንገድ ስራም በቻይና የመንገድ ስራ ተቋራጭ ኩባንያ ለመገንባት
የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመፋጠን ላይ ናቸው፡፡
እናም በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የቁጥር አንድ ስኳር
ፋብሪካ ግንባታ ስራ በአገራችን የስኳር ፋብሪካ የግንባታ ታሪክ ልዩ
ስፍራ ተሰጥቶት እንዲዘከር እየተከናወነበት ከሚገኘው የቴክኖሎጂና
የዕውቀት ሽግግር ባሻገር የአካባቢውን አርብቶ አደር ከዝቅተኛ የስራ
መደብ እስከ ፋብሪካ ማሽን ከፍተኛ ኦፕሬተርነት በማሳተፍም ነገ
የአካባቢው ተወላጅ አርብቶ አደሮች ልጆች በአመራር ደረጃ ሊሳተፉ
ጣፋጭ | 19
የወልቃይትስኳር ልማት
ፕሮጀክት
እናስተዋውቃችሁ
የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራባዊ
ዞን በወልቃይት ወረዳ ይገኛል፡፡ ይህ ከአዲስ አበባ በ1 ሺህ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ
የሚገኘው ፕሮጀክት በቀን 24 ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት ወይም 24 ሺህ ኩንታል ስኳር
ማምረት የሚችል ፋብሪካ የሚገነባበት ነው፡፡
የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በአመት 484 ሺህ ቶን
ስኳር እና 41ሺ 654 ሜትር ኩብ ኤታኖል እንደሚያመርት ይጠበቃል፡፡ ለዚህም በ50ሺህ
ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ በግብአትነት ይጠቀማል፡፡
ፋብሪካው ለሸንኮራ አገዳ ልማቱ የሚያስፈልገውን ውኃ የሚያገኘው በግንባታ ላይ ካለው
የዛሬማ ሜይ-ዴይ ግድብ ነው፡፡ የዛሬማ ሜይ-ዴይ ግድብ 840 ሜትር ስፋትና 135.5
ሜትር ቁመት የሚኖረው ሲሆን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ 3 ቢሊዮን 497 ሚሊዮን ሜትር
ኩብ ውኃ ይይዛል፡፡
በፕሮጀክቱ ለሚገነባው የስኳር ፋብሪካ የሚያስፈልገው ወጪ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ
የተገኘ በመሆኑ ግንባታው በቅርቡ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡
ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚያስፈልገውን ውኃ የሚይዘው የዛሬማ ሜይ-ዴይ ግድብ
እስኪጠናቀቅ ፕሮጀክቱ ከሌሎች ተያያዥ ስራዎች ጎን ለጎን ውኃ ገብ በሆኑ መሬቶች ላይ
ጥጥና ሰሊጥ በማልማት ላይ ይገኛል፡፡
:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A etsugar@hotmail.com
www.etsugar.gov.et || www.facebook.com/etsugar
የጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጉብኝት በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትና በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ

More Related Content

What's hot

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006Ethiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006 የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006 Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ምMeresa Feyera
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007Ethiopian Sugar Corporation
 

What's hot (13)

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
 
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006 የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
 
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
Ethiopian Sugar Corporation Research Division Booklet
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
 
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
 

More from Ethiopian Sugar Corporation

Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Ethiopian Sugar Corporation
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 

More from Ethiopian Sugar Corporation (17)

Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
 
Ethiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry ProfileEthiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry Profile
 
Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI] Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI]
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
 
Ethiopian sugar industry profile
Ethiopian sugar industry profileEthiopian sugar industry profile
Ethiopian sugar industry profile
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
 
Ethiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry ProfileEthiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry Profile
 
Comparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industryComparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industry
 
External vacancy
External vacancyExternal vacancy
External vacancy
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 3. ቁጥር 2 መጋቢት 2007

  • 1. ዜና መፅሔት ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ! ቅፅ 3 ቁጥር 3- መጋቢት 2007 ዓ.ም www.etsugar.gov.et.com || facebook.com/etsugar ጣፋጭ በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ እና የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ቡድን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ እና የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኘ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥር 17 ቀን 2007ዓ.ም የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን ከጎበኙ እና በሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ስለፋብሪካው ገለጻ ከተደረገላቸው በኋላ በሰጡት አስተያየት እንደተናገሩት ፋብሪካው በ2007 ሁለተኛ ሩብ ዓመት ስራ መጀመር የነበረበት ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየት ታይቶበታል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ወቅት የነበሩ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየተቀረፉ በመምጣታቸው ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት የሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡ »» ወደ ገጽ 2 ዞሯል የኮርፖሬሽኑ የውጤት ተኮር ሥርዓት ትግበራ በይፋ ተጀመረ “የተጀመሩ የለውጥ ትግበራዎችን ወደ ተሻለና የላቀ ደረጃ ለማድረስ የውጤት ተኮር ሥርዓት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል” አቶ ሽፈራው ጃርሶ የስኳር ኮርፖሬሽን የውጤት ተኮር ሥርዓት ትግበራ የካቲት 30 ቀን 2007ዓ.ም በግዮን ሆቴል በተካሄደ ዝግጅት በይፋ ተጀመረ፡፡ በዝግጅቱላይተገኝተውየውጤትተኮርሥርዓትትግበራበይፋመጀመሩን የተንዳሆና ከሰም ስኳር ፋብሪካዎች አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው »» ወደ ገጽ 2 ዞሯል በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በፋብሪካ ቁጥር 3 ዙሪያ የባለድርሻ አካላት እና የህዝብ ውይይት ተካሄደ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሙከራ ላይ የሚገኙት የተንዳሆና የከሰም ስኳር ፋብሪካዎች የአካባቢያቸውን አርብቶ አደሮች ተጠቃሚ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የባለድርሻ አካላት ሰሞኑን በፋብሪካዎቹ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት እንደተገለጸው፣ ፋብሪካዎቹ በአካባቢያቸው ለሚገኙ አርብቶ አደሮች የስራ እድል በመፍጠርና በማህበር ተደራጅተው ሸንኮራ አገዳ በማልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረጉ ነው፡፡ »» ወደ ገጽ 3 ዞሯል በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካ ቁጥር 3 ግንባታና የመሬት ዝግጅት እንዲሁም በቤንች ማጂና ካፋ ዞኖች አዋሳኝ ላይ ነዋሪ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያስችሉ የተለያዩ »» ወደ ገጽ 4ዞሯል በውስጥ ገጾች ባለቤትነት እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ››ገጽ 14 የአብዲ ቦሩ የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኀበር 64 አባላት በነፍስ ወከፍ ከ50,000 እስከ 240,000 ብር ተከፋፈሉ ››ገጽ 9 ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወልቃይት ስኳር ልማት ፐሮጀክትን ሲጎበኙ የቢኤስሲ ሰነድ ርክክብ የባለድርሻዎችና የህዝብ ውይይቱ በተካሄደበት ወቅት
  • 2. 2 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት የፋብሪካው መገንባት በዋነኛነት በአካባቢው የሚገኙ አርብቶ አደሮች በመንደር ተሰባስበው የማህበራዊ ተቋማት አገልግሎት እንዲያገኙ እና የሸንኮራ አገዳ እያለሙ ለፋብሪካው በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ አክለውም ፋብሪካው ለበርካታ ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል እየፈጠረ በመሆኑ አርብቶ አደሮች በሥራ ከመሳተፋቸው በተጨማሪ ለሠራተኛው የሚያስፈልጉ ሸቀጣ ሸቀጦችን በማቅረብ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያስፋፋበትን ሁኔታም ያመቻቻል ብለዋል፡፡ ፋብሪካው ከስኳር ተረፈ ምርት ከሚያመነጨው 120 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ ለራሱ ፍጆታ ተጠቅሞ ቀሪውን ኃይል በአካባቢው ለሚካሄዱ የልማት ሥራዎች ያውላል ያሉት አቶ ኃይለማርያም፣ ከስኳር ተረፈ ምርት የእንስሳት መኖ በማቀነባበር አርብቶ አደሮች በዘመናዊ የከብት ማድለብና ተዛማጅ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን ጨምሮ በመጠናቀቅ ያሉ አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች ወደ ሥራ ሲገቡ ስኳር ኤክስፖርት በማድረግ አገሪቷ ከዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችሏታልም ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ በጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ቡድን የካቲት 15 ቀን 2007ዓ.ም የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎብኝቷል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ስለ ሜይ ዴይ ግድብ ግንባታ እና አጠቃላይ የፕሮጀክቱ የሥራ እንቅስቃሴን በተመለከተ በስኳር ኮርፖሬሽን እና በሱር ኮንስትራክሽን የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጓል፡፡ የኮርፖሬሽኑ የውጤት ተኮር ሥርዓት ትግበራ... ያበሰሩት በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በስኳር ልማት ዘርፍ የተጀመሩ የለውጥ ትግበራዎችን ወደ ተሻለና የላቀ ደረጃ ለማድረስ የውጤት ተኮር ሥርዓት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ በኮርፖሬሽኑ ስር ከሚገኙ ዘርፎች፣ ስኳር ፋብሪካዎችና የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የሥራ አመራሮች ጋር በውጤት ተኮር ሥርዓት ሰነድ ላይ የተፈራረሙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ ለውጡን በቁርጠኛነት በመተግበር ኮርፖሬሽኑ በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ የመሰለፍ ራዕዩን እንደሚያሳካ ገልጸዋል፡፡ የኮርፖሬት ካይዘን እና የለውጥ አመራር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መንግስተአብ ገ/ኪዳን በበኩላቸው ስትራቴጂያዊ አመለካከት ያለው አመራርና ሠራተኛ በመፍጠር በካይዘን የተጀመረውን ውጤት ለማስቀጠል ከ2007 አንደኛ ሩብ ዓመት ጀምሮ ላለፉት ሰባት ወራት የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤትን ጨምሮ በሁሉም ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የሚገኙ ከ6892 በላይ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የውጤት ተኮር ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑን የውጤት ተኮር ሥርዓት በመገንባት ሂደት ወሳኝ የሆኑ ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ ግቦችና ስትራቴጂያዊ እርምጃዎች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው፣ ለፈፃሚ አካላት ግንዛቤ የመፍጠር፣ ዕቅድን የማውረድና በየደረጃው ስኮር ካርድ የማዘጋጀት ስራዎችም በመጠናቀቃቸው የስራ ክፍሎች በየደረጃው በተዘጋጁ ስኮር ካርዶች ላይ በመፈራረም ወደ ስራ መግባታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በዕለቱ የኮርፖሬሽኑ ባላንስድ ስኮር ካርድ የግንባታ ደረጃ ሂደት በአቶ ታፈሰ አሰፋ የለውጥ አመራር ዳይሬክተር በፅሁፍ ቀርቧል፡፡ በመጨረሻም የኮርፖሬሽኑ የውጤት ተኮር ሥርዓት ዝግጅት ላይ የጎላ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ከኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር እጅ የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡ »» ከገጽ 1 የዞረ »» ከገጽ 1 የዞረጠቅላይ ሚኒስትሩ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ እና ...
  • 3. ጣፋጭ | 3 የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በሌሎች የስራ መስኮች ከተሰማሩት የአካባቢው አርብቶ አደር ልጆች በተጨማሪ 125 ወጣቶችን በማሽን እና በትራክተር ኦፕሬተርነት መለስተኛ የሙያ ክህሎት ስልጠና ሰጥቶ ወደ ስራ ማሰማራቱ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም በርካታ ወጣቶች በ20 ማህበራት ተደራጅተው በኮንስትራክሽንና በኢንዱስትሪ ዘርፎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸው ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በአጠቃላይ ፋብሪካው የአጭርና የረዥም ጊዜ ስልጠና በመስጠት ከ5ሺ ሰባት መቶ በላይ አርብቶ አደሮች በተለያዩ የስራ ዘርፎች ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድል እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ የአካባቢው አርብቶ አደሮች የሸንኮራ አገዳ አልምተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድም ከ1ሺ 147 እማ/አባ ወራ አርብቶ አደሮች በስድስት ማህበራት ተደራጅተው 1ሺ 119 ሄክታር መሬት ሸንኮራ አገዳ በማልማት ላይ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይ በከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ11 ማህበራት የተደራጁ 755 አርብቶ አደሮች የመስኖ መሰረተ ልማት የተሟላለት በነፍስ ወከፍ አንድ ሄክታር መሬት ተሰጥቷቸው ሸንኮራ አገዳ ለማምረት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በተለያዩ የስራ መስኮች ለ220 የአካባቢው ተወላጅ ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፣ ሌሎች በርካታ የአካባቢው ወጣቶችም በ14 ማህበራት ተደራጅተው በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተዋል፡፡ በቀጣይም ፋብሪካዎቹ የአካባቢያቸውን አርብቶ አደሮች የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ ገልጸዋል፡፡ »» ከገጽ 1 የዞረ የተንዳሆና ከሰም ስኳር ፋብሪካዎች ... ከሰም ስኳር ፋብሪካ
  • 4. 4 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ... ተግባራት ላይ የባለድርሻ አካላት እና የሕዝብ ውይይት ተካሄደ፡፡ በቤንች ማጂ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በተደረገው በዚህ ውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የርዕሰ መስተዳድሩ ተወካይና የክልሉ የአርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳንሳ ፕሮጀክቱ የፋብሪካ 1 ግንባታ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከሚመለከታቸው የአርብቶ አደር ተወካዮች እና በየደረጃው ከሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግ መግባባት ላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ በመቀጠልም በደቡብ ኦሞ ዞን በሳላማጎ ወረዳ የቦዲ ማህበረሰብ በሚኖርበት አካባቢ ለአርብቶ አደሩ አስፈላጊውን ማህበራዊ ተቋማት በመገንባትና በመንደር በማሰባሰብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ አርብቶ አደሩን በመንደር በማሰባሰቡ ሂደት ጥርጣሬ የሚፈጥሩ የተለያዩ አመለካከቶች በስፋት ይስተዋሉ እንደነበር አቶ ንጋቱ አስታውሰው አርብቶ አደሮቹ ፕሮጀክቱ ወዳዘጋጀላቸው ስፍራ በመግባት ውጤታማ መሆን ሲጀምሩ ሌሎችም የእነሱን ተሞክሮ በማየት በመንደር በመሰባሰብ በስፋት ተጠቃሚ በመሆን ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሶስት መንደሮች የተሰባሰቡ የቦዲ ማህበረሰብ አባላት በሸንኮራ አብቃይ ህብረት ሥራ ማህበር በመደራጀት ፕሮጀክቱ ያለማውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ ተረክበው በመንከባከብ ላይ እንደሚገኙና አገዳ ለሚያለሙበት መሬት የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ኃላፊው አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም አርብቶ አደሮቹ ፕሮጀክቱ ባዘጋጀላቸው በመስኖ የሚለማ መሬት ላይ ለሦስት ተከታታይ ጊዜ በቆሎ አምርተው ተጠቃሚ ከመሆናቸውም በላይ ለአራተኛ ጊዜ ዘር በመዝራት ላይ እንደሚገኙ አቶ ንጋቱ ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በሸንኮራና ተጓዳኝ ምርቶች ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የራሱን አስተዋጽዖ ከማበርከት ባለፈ ልማቱን በሚያከናውንባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመጀመሪያው ተጠቃሚ ማድረግ ተቀዳሚ ተልዕኮው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ፋብሪካ 1 በመገንባት ላይ በሚገኝበት አካባቢ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት በተመሳሳይ መልኩ በቤንች ማጂና ካፋ ዞኖች አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚከናወኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡ በቤንች ማጂና ካፋ ዞኖች የሚገኙ የማጂ፣ የሱርማ፣ የሜኢንት ሻሻ እና ዴቻ ወረዳ አርብቶ አደሮች በሰጡት አስተያየት በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ የቦዲ ማህበረሰብ አባላትን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት በእነሱ አካባቢም ተከናውነው የልማቱ ተጠቃሚ ለመሆን መጓጓታቸውን ገልጸው መንግሥትም በፍጥነት ስራውን እንዲጀምር ጠይቀዋል፡፡ የሁለቱ ዞኖች አስተዳዳሪዎችም ለልማቱ ስኬት እና ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡ »» ከገጽ 1 የዞረ የደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል የአርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
  • 5. ጣፋጭ | 5 የፕሮጀክቱ የቤቶች ኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት ቡድን ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አዳነ በበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር ዘርፍ የቤቶች ኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት ቡድን ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳኑ ተገለጸ፡፡ ቡድኑ ወጪውን ያዳነው በራሱ አቅም የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ መጋዘንና ድልድይ በመገንባት መሆኑ ታውቋል፡፡ የፕሮጀክቱ የቤቶች ኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት ቡድን በዋናው ግቢየሚገኘውንና 6.162ኪሎሜትርየሚረዝመውንየውስጥለውስጥ መንገድ በራሱ አቅም ሠርቶ በ372,ዐ86 ብር ማጠናቀቅ መቻሉን የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡ ፡ መንገዱ በስራ ተቋራጮች ቢሰራ ከ6.4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ይወጣበት ነበር ብሏል ዘገባው፡፡ በተጨማሪ ፕሮጀክቱ የገጠመውን የመጋዘን /store/ እጥረት ለመቅረፍ ቡድኑ 5ዐ2,739.15 ብር ወጪ ይጠይቅ የነበረ የአንድ መጋዘን ግንባታ በ329,ዐ32 ብር በማከናወን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ማዳን ችሏል፡፡ ከግልገል በለስ እስከ ጃዊ /ፈንድቃ/ ባለው መንገድ ላይ ቡድኑ ከፍተኛ ክብደት መሸከም የሚችሉ ሁለት ድልድዮችንና የግማሽ ኪሎ ሜትር መንገድ ስራ በአካባቢው የሚገኙ ግብአቶችን በመጠቀም መገንባቱንም ነው ክፍሉ ያደረሰን ዘገባ ያመለከተው፡፡ ስራው በግል የስራ ተቋራጭ ቢሰራ 3,427,7ዐ3 ብር ወጪ ይጠይቅ የነበረ ሲሆን ቡድኑ በ446,156 ብር ብቻ ገንብቶ አጠናቋል፡፡ የፕሮጀክቱ የቤቶች ኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት ቡድን በአጠቃላይ በሶስቱም የግንባታ ስራዎች 9,177,168 ብር ማዳን ችሏል፡፡ ቁርጠኝነትና ቅንጅት የወለደው ውጤት የተጣለበትን ሀገራዊ ተልዕኮ ለመወጣት በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ በበጀት ዓመቱ በአገዳ የተሸፈነ ማሳውን 21 ሺህ ሄክታር ለማድረስ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ እቅዱን ለማሳካትም የፋብሪካው የእርሻ ኦፕሬሽን ዘርፍ “ታላቁ የአገዳ ተከላ ቀን” ሲል በሰየመው የካቲት 5 ቀን 2007 ዓ.ም በዘመቻ መልክ 140 ሄክታር አገዳ ለመትከል አቅዶ 150.3 ሄክታር በመትከል ከእቅዱ በላይ ማከናወን ችሏል፡፡ በተካሄደው ዘመቻ ከ2ሺ 800 በላይ የሆኑ የእርሻ ኦፕሬሽንና የምርምር ዘርፍ ሠራተኞች፣ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ የሥራ ተቋራጭድርጅቶችሠራተኞችተሳታፊሆነዋል፡፡እነዚህምአካላት ለአገዳ ተከላ ዘመቻው ስኬት የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋችውን የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን ዘገባ ያመለክታል፡፡ ታላቁ የአገዳ ተከላ ዘመቻ ቀን የፈጠረውን መነቃቃት የበለጠ በማጠናከር ለአጠቃላይ ድርጅታዊ ግብ ስኬት ሁሉም የሥራ ዘርፎች መሰል ተግባራትን ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዱላ መኮንን በወቅቱ አሳስበዋል፡፡ በፕሮጀክቶ የተሰራ መንገድ
  • 6. 6 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት ኮርፖሬሽኑን ከአራት ስኳር ፋብሪካዎች ጋር በኔትወርክ ለማስተሳሰር የሚከናወኑ ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤትን ከወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ እና ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካዎች ጋር ለማስተሳሰር በመከናወን ላይ የሚገኙ የኔትወርክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን የኮርፖሬት አይቲ ዳይሬክቶሬት ገለጸ፡፡ ዳይሬክቶሬቱ እንዳስታወቀው ከአመት በፊት ጂሲኤስ ከተባለ አገር በቀል ድርጅት ጋር ከ55 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ውል በመፈራረም ወንጂ የሚገኘውን የምርምርና ሥልጠና ዘርፍን ጨምሮ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤትን፣ የአራት ስኳር ፋብሪካዎች ዋና መ/ቤት እና አዲስ አበባ የሚገኙ የፋብሪካዎቹ ላይዘን ቢሮዎችን እንዲሁም የበለስና ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን በመረጃ መረብ በማስተሳሰር ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የኔትወርክ ፕሮጀክት ቀርጾ እየሰራ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአራቱ ስኳር ፋብሪካዎች የኔትወርክ መሰረተ ልማት ዝርጋታና ግንባታ ሥራዎች በመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ ያመለከተው ዳይሬክቶሬቱ፣ በቀጣይ የመሰረተ ልማት ዝርጋታውን በሌሎች የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ከመሰረተ ልማት ዝርጋታ በኋላ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ (ERP) አፕሊኬሽን ሶፍትዌር ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን ዳይሬክቶሬቱ ጠቁሞ፣ ትግበራውን በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ እና በተሟላ ሁኔታ ለማስቀጠል ለፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች አይቲ ባለሙያዎች የከፍተኛ ደረጃ /አድቫንስድ/ የአይቲ ሥልጠናዎችን እያመቻቸ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
  • 7. ጣፋጭ | 7 ፕሮጀክቱ በጥጥ ምርት የእቅዱን 85 በመቶ ገደማ አከናወነ ዛሬማ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ የሚገኘው የሜይ-ደይ ግድብ ተጠናቆ ወደ ታቀደለት የሸንኮራ አገዳ ልማት እስኪገባ ድረስ የጥጥ ተክል እያለማ የሚገኘው የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የዕቅዱን 84.8 በመቶ ማከናወን ቻለ ፡፡ ፕሮጀክቱ በያዝነው በጀት ዓመት በ 2 ሺህ 545 .86 ሄክታር መሬት ላይ ጥጥ ለማልማት አቅዶ ተከላውን በዕቅዱ መሰረት ሙሉ በሙሉ ያከናወነ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ 33 ሺህ ኩንታል የጥጥ ምርት ለመልቀም አቅዶ እስከ መጋቢት ወር 2007 መጨረሻ ድረስ 28 ሺህ ኩንታል ጥጥ ለቅሟል፡፡ አካባቢው ቀደም ሲል የጥጥ ምርት ይመረትበት ያልነበረ በመሆኑ የጥጥ ምርቱ በአረም እንዳይጠቃ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጀምሮ ከሰሜን ጎንደር፣ ከሁሉም የትግራይ ወረዳዎችና ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ጭምር የሰው ኃይል በማሰባሰብ አረም የመከላከል ከፍተኛ ርብርብ መደረጉ ተመልክቷል፡፡ ከሰኔ ወር 2006 ዓ.ም. እስከ መስከረም 2007 ዓ.ም. ድረስ በተከናወነ የአረም መከላከል ስራ እና ከጥቅምት እስከ መጋቢት ወር 2007 ዓ.ም. ድረስ በተከናወነ የጥጥ ምርት ለቀማ ስራ ለ18 ሺህ 869 ዜጎች ጊዚያዊ የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡ በጥጥ ለቀማ ስራው 243 የፕሮጀክቱ ሠራተኞች በሁለት ዙር መሳተፋቸውንም የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት በላከው ዘገባ አመልክቷል፡፡ የዛሬማ ሜይ-ዴይ ግድብ 840 ሜትር ስፋትና 135.5 ሜትር ቁመት የሚኖረው ሲሆን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ 3 ቢሊዮን 497 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም ይኖረዋል፡፡ በአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት አዲስ ለተቀጠሩ 160 ሠራተኞች የስራ ገለጻ ተደረገ ፡፡ ለሠራተኞቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እና ስለፕሮጀክቱ ገለጻ ያደረጉት የፕሮጀክቱ የሰው ሃብት ስራ አመራር ቡድን መሪ አቶ ታከለ አብዲሳ ሠራተኞቹ የፕሮጀክቱን ደንብ አክብረው በትጋት በመስራት ለውጤት እንዲበቁ አሳስበዋል፡፡ በተፈጠረላቸው የሥራ እድል ራሳቸውን ከመጥቀም ባለፈ አገሪቱ የጀመረችውን የዕድገት ጉዞ ከግብ ለማድረስም የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የፋብሪካው የቴክኒክ ቡድን መሪ አቶ ጌታቸው ሞገስ በበኩላቸው ሠራተኞቹ ፋብሪካው የሚጠይቀውን ጥንቃቄ ማድረግ እና ለፋብሪካው ውጤታማነት ሥነ-ምግባርን በተላበሰ መልኩ በቡድን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡ አንዴ ተቀጥሬያለሁ ብለው ባለመዘናጋት ራሳቸውን ጊዜው ከሚፈልገው ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ ለማስኬድ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸውም አስታውቀዋል፡፡ በተመሳሳይ የፕሮጀክቱ ገጽታ ምን እንደሚመስል በህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ጉዳዮች ክፍል ለሠራተኞቹ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ ከገለጻው በኋላ ፋብሪካውን የጎበኙት ሠራተኞቹ ፕሮጀክቱን አስመልክቶ በተደረገላቸው ገለፃ እና በጉብኝቱ መደሰታቸውን እና ስራቸውንም የፕሮጀክቱን ደንብና መመሪያ ተከትለው በቁርጠኝነት ለመስራት መነሳሳታቸውን ገልጸዋል፡፡ ፋብሪካው የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል፡፡ በአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት አዲስ ለተቀጠሩ ሠራተኞች የሥራ ገለጻ ተደረገ *ፋብሪካው የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል አዲስ ለተቀጠሩ ሰራተኞች ገለጻ ሲደረግ በፕሮጀክቱ የለማ ጥጥ
  • 8. 8 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተሸለሙ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በተፈጠረላቸው የሥራ እድል በማህበር ተደራጅተው በመስራት ላይ የሚገኙና ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተሸለሙ፡፡ በፕሮጀክቱ 780 አባላት ያሏቸው 158 የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች በመሳተፍ ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ ለሌሎችም የስራ እድል በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ማህበራት ለሽልማት በቅተዋል፡፡ በሽልማት ሥነ ስርአቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ በስኳርና ተጓዳኝ ልማቶች ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ የመንግሥት ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በፕሮጀክቱ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው በመስራት ውጤታማ የሆኑ ማህበራት የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡ በፕሮጀክቱ ለመስራት በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው ለሚመጡ ወጣቶች ፕሮጀክቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም የፕሮጀክቱ የህዝብ አደረጃጀት፣ ካሣና መልሶ ማቋቋም ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስረስ አዳሮ ተናግረዋል፡፡ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የስራ መሪዎችና ባለሙያዎች የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን ጎበኙ ከሁሉም የአገሪቷ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የስራ መሪዎችና ባለሙያዎች በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በማህበር የተደራጁ ወጣቶችን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የኮንስትራክሽን ዘርፍን ለማሳለጥ በሚረዱ ጉዳዮች ላይ በሰመራ ከተማ ውይይት ያደረጉት የሥራመሪዎችናባለሙያዎቹየተንዳሆስኳርፋብሪካበኮንስትራክሽን ዘርፍ በማህበር ለተደራጁ የአካባቢው ወጣቶች የፈጠረውን የስራ
  • 9. ጣፋጭ | 9 እድል ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ በተንዳሆ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ እና ጥገና የሚያስፈልጋቸው የመኖሪያ ቤቶች በኮንስትራክሽን ዘርፍ በጥቃቅንና አነስተኛ በተደራጁ የአካባቢው ማህበረሰብ ወጣቶች ግንባታቸው በመከናወን ላይ እንደሚገኝም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ በውይይቱና በጉብኝቱ ወቅት የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በቋሚነት፣ በኮንትራትና በጊዜያዊነት ከ5 ሺህ ሰባት መቶ ለሚበልጡ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት የስራ እድል መፍጠሩ ተገልጿል፡፡ የአካባቢው አርብቶ አደር ማህበረሰብም በሸንኮራ አገዳ አብቃይ ህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው የሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ለጎብኚዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በፋብሪካበስራላይየሚገኙትንማህበራትለማጠናከርና አዳዲስ ማህበራትን አደራጅቶ ወደ ስራ ለማስገባት እንዲሁም ከክልሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ መስራት የሚያስችሉ ጥናቶች መጠናቀቃቸውም ተገልጿል፡፡ በመጨረሻም የፌዴራል የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው አበበ በማህበር ለተደራጁ ዜጎች በስራ እድል ፈጠራ ረገድ በሁሉም ዘርፎች ተመሳሳይነት እንዲኖራቸው ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የአብዲ ቦሩ የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኀበር 64 አባላት በነፍስ ወከፍ ከ50,000 እስከ 240,000 ብር ተከፋፈሉ * አብዛኛዎቹ አርሶ አደሮችም ወደ ልማታዊ ባለሃብትነት እየተቀየሩ ነው ሸንኮራ አገዳ አልምተው ለወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በማቅረብ ሥራ ላይ ከተሰማሩ ሸንኮራ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች ኀብረት ሥራ ማኀበራት ዩኒየን መካከል አንዱ የሆነው የአብዲ ቦሩ ማኀበር 64 አባላት ካገኙት ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ውስጥ በነፍስ ወከፍ ከ50,000 እስከ 240,000 ብር ተከፋፈሉ፡፡ በምሥራቅ አርሲ ዞን በዶዶታ ወረዳ ዴራ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ይህ ማኅበር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ አገዳ በማልማት ላይ ነው፡፡ በማኅበሩ የታቀፉ አርሶ አደሮች እንደገለጹት መንግሥት አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የልማት ስትራተጂ ቀይሶ በመሥራቱ በልማቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በተለይ በከፍተኛ ደረጃ የትርፍ ክፍፍል ያደረጉት አርሶ አደሮች በርትተው በመሥራታቸው ያስመዘገቡት ውጤት እና ያገኙት ከፍተኛ ጥቅም ወደ ልማታዊ ባለሃብትነት እንዲቀየሩ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡ መሰል ማኅበራትም የእነሱን ፈለግ ተከትለው ከሰሩ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ነው መልዕክት ያስተላለፉት፡፡ በአሁኑ ወቅት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ የሚገኙ 5ሺ 651 ወንዶችና 1ሺ 982 ሴቶች በጠቅላላው 7ሺ 633 አባላት ያሏቸው 34 ማኅበራት የሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በማቅረብ በሚያገኙት ገንዘብ ተጠቃሚ በመሆን ላይ ናቸው፡፡ ማኅበራቱ የሚያገኙትን ትርፍ በአማካይ በየ18 ወራት ለአባላቶቻቸው ያከፋፍላሉ፡፡ ፋብሪካው ለአርሶ አደሮቹ በመስኖ የለማ መሬት በማዘጋጀት፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት በማመቻቸት፣ ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት አርሶ አደሮቹ ሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በመሸጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል፡፡ ፋብሪካው በግብዓትነት ከሚጠቀመው በ12ሺ 800 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ ውስጥ 7ሺ ሄክታሩ በፋብሪካው አካባቢ በሚገኙ የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኀበራት የሚለማ ነው፡፡
  • 10. 10 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኮርፖሬሽኑ፣ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ተከበረ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን “ሴቶችን ማብቃት ህብረተሰቡን ማብቃት ነው” በሚል መሪ ቃል በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት፣ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡ በዋናው መ/ቤት መጋቢት 5 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀኑ ተከብሮ በዋለበት ወቅት ሴቶችን በማብቃት ረገድ የተገኙ ስኬቶችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች፤ የኮርፖሬት ሥርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት ዓላማ፣ ተግባር እና ዐበይት ክንውኖች እንዲሁም የሴቶች እኩልነትን ለማረጋገጥ የወጡ ህጎችና ያስገኙት ለውጥ በሚሉ ርዕሶች ጹሑፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡ በተያያዘ ዜና መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ መነሻውንና መድረሻውን አትላስ ሆቴል አድርጎ በተካሄደ “ቅድሚያ ለሴቶች” የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ላይ 160 የሚሆኑ የዋና መ/ቤት እንዲሁም የወንጂ ሸዋ፣ የመተሐራ፣ የፊንጫአ እና የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካዎች ላይዘን ኦፊስ ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአለም ለ104ኛ፣ በአገራችን ደግሞ ለ39ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡ አለም አቀፉ የሴቶች ቀን በዋና መስሪያ ቤት በተከበረበት ወቅት
  • 11. ጣፋጭ | 11 በስኳር ኢንዱስትሪ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ሥራዎች ተጀመሩ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ልማቱን ለማስፋፋትና ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችሉ ሥራዎች ተጀመሩ፡፡ ለተግባራዊነቱም ሥራውን የሚመራ የተጓዳኝ ምርቶችና አግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ ተቋቁሞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የዘርፉ ዋና ተግባር የእንስሳት፣ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ከስኳር ምርት በተጓዳኝነት ማልማት ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካና በከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለሚገኘው 200 ሄክታር የፍራፍሬ እርሻ ሙያዊ እገዛ በማድረግ ላይ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በእያንዳንዱ ነባርና አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች የፍራፍሬ ልማትን ከ200-300 ሄክታር መሬት ላይ በማልማት እና የአካባቢውን ማህበረሰብ በአማከለ መልኩ በአዋጭነት ጥናት የተደገፈ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በማከናወን ምርቱን በፋብሪካ ማቀነባበር የሚቻልበት ደረጃ ላይ ለማድረስ የተቋቋመ ዘርፍ ነው፡፡ በፍራፍሬ ልማት ከተካተቱት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ብርቱካንና ማንጎ ሲሆኑ፣ ምርቶቹን በስኳር ፋብሪካዎች እና በፕሮጀክቶች አካባቢ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጠቀሜታ ከማዋል በተጨማሪ ለአካባቢው ገበያ ለማቅረብ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት በበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በአማራ ግብርና ቢሮ በሚዘጋጅ የማንጎ ችግኝን በመጠቀም 50 ሄክታር ልማት ለማከናወን የቦታ መረጣና የመስኖ ዲዛይን ሥራ በአማራ ውሃ ሥራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይበበጀትዓመቱበኩራዝስኳርልማትፕሮጀክትከአካባቢው የችግኝ ማፍያ በማፈላለግ 35 ሄክታር የማንጎ ተከላ ሥራ ለማከናወን በዕቅድ የተያዘ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱም ለተግባራዊነቱ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ 25 ሄክታር ማንጎ ለማልማት የሚያስችል ችግኝ የማልማት ስራ በፋብሪካው በኩል ተጀምሯል፡፡ የብርቱካን ልማትን በተመለከተም በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በ0.5 ሄክታር ላይ በተቋቋመ ችግኝ ጣቢያ ከጥቅምት 2007 ዓ.ም ጀምሮ 45,000 የሚደርስ የብርቱካን መሠረተ ግንድ የሚሆን ኮምጣጤ ተዘርቶ ከ16,000 በላይ በቅሏል፡፡ ዘርፉ በማልማት ላይ የሚገኘው የብርቱካን ችግኝ
  • 12. 12 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በዙሪያው ከሚገኙ 18 ገጠር ቀበሌዎች ተወካዮችና ጐሣ መሪዎች ጋር ተወያየ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በዙሪያው ከሚገኙ የ18 ገጠር ቀበሌ ተወካዮችና የጐሣ መሪዎች እንዲሁም ከፈንታሌ ወረዳ መስተዳድር አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም፣ የፈንታሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ድሪርሣ፣ የስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት ዳይሬክተር አቶ ኤካል ነትር እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በውይይቱ መግቢያ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም ለማህበረሰቡ ተወካዮችና የሀገር ሽማግሌዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ለፋብሪካው ስኬት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በጋራ ውይይት መድረኩ ፋብሪካው ለማህበረሰቡ ያከናወናቸው የመንገድ ሥራ፣ ለከብቶች መኖ የሚውል የአገዳ ገለባ አቅርቦት፣ የመስኖ ውሃ አቅርቦት፣ የኮምፖስት ማዳበሪያ አቅርቦት፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታና ሌሎችም በምስል ተደግፈው በስላይድ ቀርበዋል፡፡ በውይይት መድረኩ የተገኙት ተወካዮችና የጐሣ መሪዎች ከዚህ በፊት የፋብሪካውና የአካባቢው ማህበረሰብ ግንኙነት ጥሩ እንዳልነበረ አስታውሰው በዚህም የተነሳ የተወሰኑ ግለሰቦች ፋብሪካውን በጥላቻ የሚመለከቱበት እና ለሀብትና ንብረቱ የማይጨነቁ እንዲሁም አገዳው በከብቶች ጉዳት ሲደርስበት በቸልታ ይመለከቱ እንደነበር አውስተዋል፡፡ ይሁንና ሁኔታው ከሁለት ዓመት ወዲህ በተደጋጋሚ በተደረገ ውይይት መለወጡን ገልጸው ፋብሪካውና የአካባቢው ማህበረሰብ ለጋራ ጥቅም በጋራ መቆም መቻላቸው አስደሳች ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ፋብሪካው ለአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ የሀገር ሀብት መሆኑን በመረዳታቸው የባለቤትነት ስሜት እንደፈጠረባቸውም አስረድተዋል፡፡ የፈንታሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ድሪርሣ በበኩላቸው ፋብሪካው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያደረጋቸው ተከታታይ ውይይቶች ተጨባጭ አዎንታዊ ለውጦች ማምጣታቸውን ገልጸውዋል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት ዳይሬክተር አቶ ኤካል ነትር በበኩላቸው የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡ ፡ በቀጣይ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ የሚገኙ አርብቶ አደሮች የሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በማቅረብ የበለጠ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉበት እድል እንዳለም ገልጸዋል፡፡ በየዓመቱ ይካሄድ የነበረው የፋብሪካውና የአካባቢው ማህበረሰብ ውይይት በቀጣይ በየስድስት ወራት እንደሚካሄድ መገለጹን የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን ዘገባ ያመለክታል፡፡ የስብሰባው ተካፋዮች በከፊል
  • 13. ጣፋጭ | 13 ቆይታአካባቢያችን - ህልውናችን ከተፈጥሮ ገፀ በረከቶች መካከል የሰው ልጅን ሕይወት እንደወርቅ ፍልቃቂ የሚያንፀባርቁት ዕፅዋት ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡ ፡ ዕፅዋት ምትሃታዊ መስህብ ያላቸው እና የተፈጥሮ መስተጋብርን የሚያወዙ ታላቅ ፀጋዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ከሕይወታችን ጋር እንደድርና ማግ የተሸመኑ የተፈጥሮ ችሮታዎች በስራ አካባቢ መንከባከብ ብዙ ተዓምራትን ይቸራሉ፡፡ አረንጓዴ ዕፅዋት የሕይወት ኢንጂነሮች ናቸው፡፡ ጤናማ አስተሳሰብን የሚያዳብሩ መንፈስን የሚያለመልሙና የሚያበረቱ ምትሃቶች ናቸው፡፡ ድብርትን አራግፈው መነቃቃትን በመፍጠር ዘና ፈታ ያደርጋሉ፡ ፡ አዕምሮ አዎንታዊ ሃይልን እንዲያፈልቅ በማድረግ አካላዊና አዕምሯዊ ብቃትን ከፍ በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና እንዳላቸውም በርካታ ምርምሮች ያስረዳሉ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም በዕፅዋት የወዛ አካባቢ ያማልላል፤ ሁሌም አትለዩኝ ያሰኛል፤ መልካም ግንኙነትን ይፈጥራል፤ ማህበራዊ መስተጋብርንም ያጎለብታል፡፡ ዕፅዋትን የተላበሱ አካባቢዎች ከወርቅና ከዕንቁ የላቁ ሃብቶች ናቸው፡፡ ዕፅዋት ቋንቋ አላቸው፤ የሚያፅናና፣ የሚያረጋጋ እና ተስፋን የሚፈነጥቅ፡፡ ለአካባቢ እንክብካቤ ስንተጋ ይህ ሁሉ ችሮታ ከደጅ የሚታፈስ ነው ፡፡ እነዚህን ፀጋዎች ስናረክሳቸውና ስናጎሳቁላቸው አፀፋው በራስ ላይ ጉስቁልናን ማብቀል ይሆናል፡፡ ለዕፅዋት ዋጋና ክብር የማይሰጥ አካባቢ ትልቅ ዋጋ ያስከፍለዋል፤ ያስገብረዋል፤ ውስብስብ ፈተናንም ይደቅናል፡ ፡ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የለውጥ ንቅናቄ ውስጥ አካባቢን ለስራ ምቹና ፅዱ የማድረግ ተግባር ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ነው፡፡ በዚህም የስራ አካባቢን በአረንጓዴ ዕፅዋት የማስዋብ ስራዎች አበረታች ለውጥን እያስመዘገቡ ነው፡፡ በፋብሪካ ዙሪያ፣ በቢሮዎችና በመኖሪያ መንደሮች አካባቢ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ላይ የሰራተኛውና የቤተሰቡ ተሳትፎ ልምላሜን እየፈጠረ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት የስራና የመኖሪያ አካባቢዎች ፅዱና ማራኪ፣ ለስራና ለኑሮ ምቹና ተስማሚ እየሆኑ ነው፡፡ እንዲያም ሆኖ አካባቢን በዕፅዋት የማሳመር ስራው ቀጣይ ሆኖ ሰፊ ጥረትን፣ ትጋትንና ቁርጠኝነትን ይጠይቃል፡፡ ስራው ደግሞ ከአመለካከት ለውጥ ይጀምራል፡ ፡ አካባቢያችን ጤናችን፣ ሰላማችንና ውበታችን ነው፡፡ ኑሯችን፣ ፀጋችን እንዲሁም ሕይወታችን ጭምርም ነው፡፡ ይህ እውን የሚሆነው ግን ለአካባቢያችን አዎንታዊ እንክብካቤ ስንሰጥ ብቻ ነው፡፡ እናም የስራንና የመኖሪያ አካባቢዎችን በዕፅዋት የማሳመር ስራው ይበልጥ ሊጠናከር ይገባዋል፡፡ በዚህ ረገድ ስንፍና፣ ቸልተኝነትና አያገባኝም ባይነት የሕወት ኪሳራን እንጂ ትርፋማነትን አይለግስም፡፡ ህይወት ልክ እንደዛፍ ናት፤ ስሩ ደግሞ ንቃተ ህሊና ነው፡፡ እናም ስሩ ከተንሰራፋ ዛፉ ጤናማ ይሆናል፡፡ የእኛም ጤናማ ሕይወት ለአረንጓዴ ልማት በሚኖረን ንቃተ ህሊና እና ተሳትፎ ልክ የሚወሰን ነው፡፡ ስለሆነምአካባቢያችንሰርተንየምንከብርበት፣ ቀጣይና ጤናማ ትውልድን የምናፈራበት እና በስኳር ልማት ረገድ ሀገራዊ ተልዕኳችንን በብቃት የምንወጣበት እንዲሆን ዕፅዋትን የማልማት ስራችን ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል፡፡ እስካሁንም አርዓያነት ያለው ተግባራትን ያከናወኑ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡ ፡ ያልጀመሩ ደግሞ ለራስ ህልውና ሲባል እንዲያስቡበት ግድ ይላቸዋል፡፡
  • 14. 14 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት ባለቤትነት እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ለዘርፉ ያላትን ምቹ የአየር ንብረት፣ በመስኖ መልማት የሚችል ሰፊ መሬትና የውሃ ሀብት ጥቅም ላይ ከማዋል ባሻገር በተቋቋሙባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተቀዳሚ ዓላማቸው ነው፡፡ ለአብነትም በአፋር ክልል ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙት የተንዳሆና የከሰም እንዲሁም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የኦሞ ኩራዝ፣ በአማራ ክልል የበለስ እና በትግራይ ክልል የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በአካባቢያቸው ለሚገኙ አርብቶ አደሮች እና አርሶ አደሮች ሰፊ የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የተለያዩ የመሠረተ ልማትና የማህበራዊ ተቋማት ግንባታዎችን በማከናወን የአካባቢዎቹን ማህበረሰብ ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ፕሮጀክቶቹ በመሠረተ ልማትና ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ብቻ ሳይወሰኑ አርብቶ አደሮቹ ሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካዎቹ በማቅረብና አገዳውን በጉልበታቸው በመንከባከብ በሚያገኙት ገቢ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረጉ ይገኛሉ፡ ፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ በመስኖ የሚለማ መሬት አዘጋጅቶ ከማቅረብ ጀምሮ አርብቶ አደሮቹ የሸንኮራ አገዳ እንዲያለሙ የዘር አገዳ፣ ጸረ-አረም መድሀኒትና ሌሎች ሙያዊ እገዛዎች እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይ ስኳር በማምረት ላይ የሚገኙት ሦስቱ ነባር የስኳር ፋብሪካዎችም በአካባቢያቸው ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ያላቸው ቁርኝት እጅጉን የጠበቀ ነው፡፡ በማሳያነትም በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተውን ዘለቄታዊ ትስስር መጥቀሱ በቂ ይሆናል፡ ፡ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ለስኳር ምርቱ በግብአትነት የሚጠቀምበትን የሸንኮራ አገዳ ልማት ብንመለከት ፋብሪካው በራሱ የሚያለማው የመሬት ስፋት 5 ሺህ 800 ሄክታር ሲሆን በአካባቢው አርሶ አደር የሚለማው መሬት ፋብሪካው ከሚያለማው ልቆ 7 ሺህ ሄክታር ደርሷል፡፡ ይህንን ያህል ስፋት ያለውን የሸንኮራ አገዳ መሬት በማልማት ላይ የሚገኙት 7 ሺህ 633 አባ/እማ ወራዎች ናቸው፡፡ እነዚህ አርሶ አደሮች የትዳር አጋርና በትንሹ አንድ አንድ ልጅ ያላቸው ናቸው ተብሎ ቢታሰብ እንኳን 22 ሺህ 900 የሚሆኑ ሰዎች ኑሮ በቀጥታ ከፋብሪካው ህልውና ጋር የተያያዘ ሆኖ ይገኛል፡፡ በመሠረተ ልማት፣ በማህበራዊ ተቋማትና በሥራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚ የሆኑና በስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና ፋብሪካዎች አካባቢ የሚገኙ ዜጎች ታዲያ ከዘርፉ ያገኙትን ተጠቃሚነት የሚያደናቅፉ ሰው ሰራሽም ሆነ የተፈጥሮ አደጋዎች ሲያጋጥሙም ሆነ ያጋጥማሉተብሎሲታሰብተቆርቋሪነታቸውን በተግባር ቀድመው በማረጋገጥ ተወዳዳሪ አይገኝላቸውም፡፡ በቅርቡ በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ የተስተዋለውም ይኸው ነው፡፡ እለተ ቅዳሜ መጋቢት 5/2007ዓ.ም ለፊንጫአ ስኳር ፋብሪካና ለሠራተኞቹ እንዲሁም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ኑሮአቸው ከፋብሪካው ጋር ለተያያዘው የአካባቢው ህብረተሰብ እንደወትሮዋ ቅዳሜ አልነበረችም፡፡ ከረፋዱ 5 ሰአት አካባቢ ከሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ማቀጣጠያ ክፍል ሳይታሰብ የተነሳው የእሳት አደጋ ያስከተለው ጭስ ፋብሪካውን ሙሉ ለሙሉ ሸፍኖታል፡፡ ሠራተኛውና የአካባቢው ህብረተሰብ እንዲሁምየኦሮሚያክልልየተለያዩተቋማትና የፌደራል ፖሊስ የእሳት አደጋው የፋብሪካው ልዩ ልዩ የማምረቻ መሳሪያዎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ይከላከላል ባሉት ነገር ሁሉ እሳቱን ለማጥፋት ከወዲህ ወዲያ ይላሉ፡ ፡ የስኳር ፋብሪካው ከኤታኖል ማምረቻ ፋብሪካው ብዙም ርቀት የሌለው መሆኑ ደግሞ እሳቱን በምንም አይነት መስዋእትነት በፍጥነት የመጥፋቱን አስፈላጊነት የግድ አድርጎታል፡፡ እሳቱ እንዳይዛመትና በስኳር ማምረቻ “ፋብሪካው ከሚቃጠል እኔ ተቃጥዬ ላድነው“ “ “
  • 15. ጣፋጭ | 15 ፋብሪካው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርስ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ርብርብ ከፍተኛ መስዋትነት የከፈሉት የፋብሪካው ሠራተኞች ነበሩ፡፡ ይህ እልህ አስጨራሽ ርብርብ ደግሞ ውዱንና መተኪያ የሌለውን የሰው ሕይወትና የአካል መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ነበር፡፡ ፋብሪካው ለእርሱ እና ለቤተሰቡ ዋልታ እንደሆነ የገባው ሠራተኛውና የአካባቢው ህብረተሰብ መስዋዕትነት ለመክፈል ሳያመነታ አስቸጋሪውን ፈተና ተጋፍጦ እሳቱ ፋብሪካው ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስና እጅግ አውዳሚ ጥፋት ሊያስከትል ወደሚችለው ወደ ኤታኖል ፋብሪካውም ሳይዛመት በቁጥጥር ስር አውሎታል፡፡ ይሁንና ይህ ፋብሪካውን ለማዳን የተደረገው አስቸጋሪ ርብርብ ፋብሪካውን ከውድመት ለመታደግ ሲረባረቡ ከነበሩት ሠራተኞች መካከል የሦስቱን ሕይወት ቀጥፏል፡፡ ሟቾቹ ልጆቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚሰናበቱበት፣ ያሰቡትንና የልባቸውን የሚተነፍሱበት፣ ያቀዱትን የሚያሳኩበት ጊዜ ሳያገኙ ለአገራቸዉና ለሕዝባቸዉ በድንገት መስዋእት ሆነዋል፡፡ በሌሎች 14 ሠራተኞች ላይም ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ የሕይወት መስዋዕትነት የጠየቀው ይህ ፍጹም የባለቤትነት ስሜት ፋብሪካውን ከውድመት ታድጎ በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ እንዲገባ አስችሎታል፡፡ ጀግንነት በጦር ሜዳ ብቻ አይደለም የሚገኘው፡፡ ማንኛውም ዜጋ በተሰማራበት የሙያ መስክ ሁሉ የተጣለበትን ኃላፊነት በትጋትና በቅንነት ከተወጣ እርሱ ጀግና ነው፡፡ የአገርና የሕዝብ ሀብት የሆነው ይህ ፋብሪካ እንዳይጎዳ ቤቴን፣ ንብረቴን ሳይሉ የሕይወት እና የአካል መስዋዕትነት ካለማመንታት የከፈሉት እነዚህ ወገኖችም ጀግኖቻችን ናቸውና ክብር ይገባቸዋል፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽንና መላው ሠራተኛው “ ፋብሪካው ከሚቃጠል እኔ ተቃጥዬ ላድነው “ በማለት ክቡር የሕይወትና የአካል መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ቤተሰቦች አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉና በማንኛውም ጊዜ ከጎናቸው እንደማይለዩ ያረጋግጣሉ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በሆስፒታል ተገኝተው የተጎዱ ሰራተኞችን ሲጠይቁ
  • 16. 16 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት ለአርብቶ አደሩ የልማት ጥያቄ ምላሽ እየሰጠ ያለው የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ትናንት የከብቶቹን ጭራ ተከትሎ የግጦሽ መሬት እና ውኃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ በመጓዝ ኑሮውን ይገፋ የነበረው በደቡብ ኦሞ የሰላማጎ ወረዳ አርብቶ አደር ከማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም ሆነ ከመሰረተ ልማት አገልግሎቶች ጋር ሳይተዋወቅ ለዘመናት ኖሯል፡፡ ዛሬ ላይ ግን የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ይዞለት በመጣው በረከት የአርብቶ አደሩ የልማት ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን ቀጥሏል፡፡ በኩራዝስኳርልማትፕሮጀክት አማካኝነት በሰላማጎ ወረዳ በምትገኝ አርብጆ በተሰኘች ቦታ በሶስት መንደሮች የተሰባሰቡ የአካባቢው አርብቶ አደሮች በተገነባላቸው የማኅበራዊ ተቋማት ተጠቃሚ መሆን ሲጀምሩ ነበር በሌሎች የወረዳዋ መንደሮችና አጎራባች ዞኖች የሚኖሩ አርብቶ አደሮች ለዘመናት ይገፉት የነበረውን አስከፊ ኑሮ ፕሮጀክቱ በምን ያህል ደረጃ ሊቀርፍ እንደሚችል የተረዱት፡፡ እናም የፕሮጀክቱ እንቅስቃሴ ተፋጥኖ እና ወደ እነርሱ አካባቢ ደርሶ እንደ አርብጆ አካባቢ አርብቶ አደሮች የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ቀን መናፈቅና ጥያቄያቸውን ለመንግሥት ማቅረብ የጀመሩት ገና ከጅምሩ ነበር፡፡ ፕሮጀክቱከፌዴራልናከክልሉመንግሥትጋርበመቀናጀትለአካባቢው ተወላጅ አርብቶ አደሮች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠቱ ዛሬ ላይ አርብጆ በተባለ ቦታ በሶስት መንደሮች ከተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች በተጨማሪ ጉራ እና ማኪ በተሰኙ አካባቢዎች አርብቶ አደሮች በመንደር ተሰባስበው የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና የመሰረተ ልማት አውታሮች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡ በተጨማሪም የሙርሲ ብሔረሰብ ተወላጆች በመንደር በተሰባሰቡበት ኃይሎዋ አንድ በተሰኘ ቦታም የማኅበራዊ ተቋማት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ኃይሎዋ ሁለት በተባለ አካባቢም በመንደር ለሚሰባሰቡ አርብቶ አደሮች የማኅበራዊ ተቋማት ግንባታ ለማከናወን ግንባታውን ከሚያከናውኑ ተቋማት ጋር ውል እየተገባ ይገኛል፡፡ ራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በተጀመረባት የሰላማጎ ወረዳ በፕሮጀክቱ ክልል አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶ አደሮች ከእርሻ ስራ ጋር የማይተዋወቁ ነበሩና ፕሮጀክቱ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመሆን ከከብት ማርባት ስራቸው በተጨማሪ የእርሻ ስራ ማከናወን ይችሉ ዘንድ የእርሻ ስራን እንዲማሩ በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ይህ በመሆኑም መጀመሪያ በመንደር የተሰባሰቡት የአርብጆ አካባቢ አርብቶ አደሮች በ2ሺህ 400 ሄክታር ላይ በሁለት ዙር በቆሎ አምርተው ተጠቅመዋል፡፡ ዛሬ ላይ ደግሞ በጉራ፣ማኪ እና ኃይሎዋ አካባቢዎች በመንደር የተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች በመስኖ የሚለማ መሬት ተሰጥቷቸው የመሬት ዝግጅት ስራው በፕሮጀክቱ እየተከናወነላቸው ይገኛል፡፡ የአካባቢውን ተወላጅ አርብቶ አደር ከፕሮጀክቱ የልማት እንቅስቃሴ የመጀመሪያ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ የሚገኘው የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከፕሮጀክቱ ክልል በርቀት የሚገኙ አርብቶ አደሮችም የልማቱ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ላቀረቡት ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የተለያዩ ማኅበራዊ ተቋማትና የመሰረተ ልማቶች እንዲሁም የመስኖ ውኃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል፡፡ የአካባቢው አርብቶ አደሮች ለስኳር ኮርፖሬሽን እና ለመንግሥት ያቀረቡት የልማት ጥያቄ ምላሽ በማግኘቱ ዛሬ የአኗኗር ሁኔታቸው በእጅጉ ከመለወጡ ባሻገር በፕሮጀክቱ በተለያዩ የስራ መደቦች ተቀጥረው መስራት የቻሉበት ሁኔታም ተፈጥሯል፡፡ ኦሊሉ ቻርኔሌይ የሙርሲ ተወላጅ ነው፡፡ ጉራ በተባለው መንደር እየተከናወነ በሚገኘው የፕሮጀክቱ የሸንኮራ አገዳ እርሻ ስራ የመሬት ዝግጅት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ የአካባቢውን አርብቶ አደር ልጆች አሰልጥኖ በፕሮጀክቱ ስራ ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ ባደረገው እንቅስቃሴ በትራክተር ኦፕሬተርነት በ2005 ዓ.ም. በጫንጮ ትራክተር ማሰልጠኛ ተቋም ሰልጥኖ በፕሮጀክቱ የአገዳ እርሻ ስራ ላይ በሰለጠነበት ሙያ ተቀጥሮ እየሰራ ይገኛል፡፡ “አገሬ ሁልጊዜ
  • 17. ጣፋጭ | 17 የምትታወቅበትን ድህነት ያስወግዳል ተብሎ ተስፋ በተጣለበት የስኳር ልማት ዘርፍ እየተሳተፍኩ በመገኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ” የሚለው ኦሊሉ ቻርኔሌይ ወደ ማሰልጠኛ ተቋሙ ገብቶ ከመሰልጠኑ በፊት ምንም ዓይነት ልምድ ያልነበረውና ትራክተር ምን እንደሆነ ግንዛቤ ያልነበረው እንደነበር ያወሳል፡፡ ሌላው በትራክተር ኦፕሬተርነት ሰልጥኖ እና በፕሮጀክቱ በቋሚነት ተቀጥሮ የሚገኘው ካሳሁን ምታቸው ሲሆን የዲሜ ብሔረሰብ ተወላጅ ነው፡፡ እንደ ኦሊሉ በፕሮጀክቱ በአገዳ ማሳ ዝግጅት ስራ በትራክተር ኦፕሬተርነት እየሰራ የሚገኘው ካሳሁን ፕሮጀክቱ በአካባቢው በመጀመሩ የልማቱ የመጀመሪያ ተጠቃሚ ሊሆን እንደቻለ በማውሳት በፕሮጀክቱ እየተገነባ የሚገኘው ስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት ገብቶ ስኳር ማምረት ሲጀምር ማየት ምኞቱ እንደሆነ ይናገራል፡፡ የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለአካባቢው አርብቶ አደሮች ልጆች ጉራ በተባለ ቦታ ባስገነባው ጉራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በርዕሰ መምህርነት እያገለገለ የሚገኘው ምታቸው ደነቀ የዲሜ ብሔረሰብ ተወላጅ ሲሆን የቦዲዎችን ቋንቋ አቀላጥፎ ይናገራል፡፡ በትምህርት ቤቱ 43 ተማሪዎች እየተማሩ እንደሚገኙና 18ቱ ህፃናት ቀሪዎቹ 15ቱ ጎልማሳዎች ናቸው ይላል፡፡ ርዕሰ መምህር ምታቸውን ታዲያ በእጅጉ የሚያስደንቀው በጎልማሳ አርብቶ አደር ተማሪዎቹ ዘንድ የሚታየው የትምህርት ፍላጎት ነው፡፡ ትምህርት ቤቱ ደብተርና እርሳስ ለተማሪዎቹ በማቅረብ ከማበረታት ባሻገር ለተማሪዎቹ ምሳ እንዲሆን ገንፎ አዘጋጅቶ እንደሚያቀርብና በተለይ ሴት ተማሪዎችን ለማበረታት አንድ ወር ሳታቋርጥ ትምህርቷን ለተከታተለች ተማሪ ትምህርት ቤቱ አንድ ሊትር ዘይት እንደሚሰጥ ርዕሰ መምህሩ አጫውተውናል፡፡ ጉራ በተባለው አካባቢ ቲካዎች የሚባለው መንደር አርብቶ አደሮች የተሰባሰቡበት መንደር ሲሆን በዚህ ቦታ በተገነባ የእህል ወፍጮ ስትገለገል ያገኘናት የቦዲ ብሔረሰብ ተወላጅ ጋታፓይ ዞጊይ ትባላለች፡፡ ጋታፓይ በአካባቢው የትምህርት፣ የወፍጮ፣ የውኃ እንዲሁም ለከብቶቻቸው የህክምና አገልግሎቶች ማግኘት እንደጀመሩ ገልፃ በአካባቢዋ በተገነባው ትምህርት ቤት ትምህርቷን በሚገባ እየተከታተለች እንደምትገኝና በዚህም በትምህርት ቤቱ በኩል የምግብ ዘይት እንደሚሰጣት ነው የምትናገረው፡፡ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሕዝብ አደረጃጀት፣ካሳ ክፍያና መልሶ ማቋቋም ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አስረስ አዳሮ እንደሚገልጹት በመንደር ተሰባስበው በእርሻ ስራ በመሰልጠን ማምረትና መጠቀም የጀመሩ አርብቶ አደሮች የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን እና በአካባቢው የሚገኙ የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኅበራትን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ ለፕሮጀክቱ በሸንኮራ አገዳ አብቃይነት ለመሳተፍ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ በዚህ መሰረት ፕሮጀክቱ ለ1ሺ 430 አርብቶ አደሮች 1ሺ 72 ሄክታር መስኖ ገብ የእርሻ መሬት የዝግጅት ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ እያንዳንዱ አርብቶ አደር አንድ ሄክታር ማሳ እንዲኖረው በማድረግም በ0.25 ሔክታር መሬቱ ላይ የተለያዩ ሰብሎችን እንዲያለማና በቀሪው 0.75 ሔክታር መሬት ላይ ደግሞ ሸንኮራ አገዳ አብቅሎ ለስኳር ፋባሪካው የሚያቀርብበት ሁኔታ እንዲኖር ከወዲሁ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ነው አቶ አስረስ የሚገልጹት፡፡
  • 18. 18 | በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ስራ ከጀመረ አንስቶ እስካሁን 36 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል፤ 158 ማኅበራትም ተደራጅተው ከተለያዩ ግንባታዎች ጀምሮ እስከ አገልግሎት መስጠት ስራዎች ድረስ እየተሳተፉ እንደሚገኙም ነው የስራ ኃላፊው ያብራሩት፡፡ የአካባቢው አርብቶአደሮችበፕሮጀክቱከጥበቃጀምሮእስከፋብሪካኦፕሬሽንስራ ላይ በስፋት የሚሳተፉበት ስልትም በመንግሥት ተነድፎ እየተተገበረ መሆኑንለመረዳትችለናል፡፡ለአብነትምፕሮጀክቱበቅርቡ30የሚሆኑ ወጣቶችን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመስኖ ልማት አሰልጥኖ በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ እንደሚገኙ መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአገራችን የስኳር ፋብሪካ የግንባታ ታሪክ አብዛኛው ግንባታው በአገር በቀል ተቋማት የሚካሄድ እና ከፍተኛ የቴክኖሎጂ እና የዕውቀት ሽግግር እየተከናወነበት የሚገኝ እንዲሁም ከተሞክሮ ትልቅ ስንቅ የተሰነቀበትና ወደፊትም በአገራችን የሚገነቡ የስኳር ፋብሪካዎችን ሙሉ በሙሉ ማከናወን የሚያስችል አቅም የተገነባበት የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ነው የሚሉት ደግሞ አቶ ካሳ ተስፋዬ የቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና የግንባታ ተቋራጭነት ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ከጥቂት የቴክኖሎጂና የልምድ መካበትን ከሚጠይቁ ስራዎች በስተቀር አብዛኛው የግንባታ ስራው በዋና ተቋራጩ፣ በበርካታ አገር በቀል የግንባታ ተቋራጮችና አማካሪዎች እየተከናወነ የሚገኝ መሆኑን አቶ ካሳ ጠቅሰዋል፡፡ በስራ ላይ በሚገኙ የአገሪቱ ነባር ስኳር ፋብሪካዎች አገር በቀል ተቋራጮች ያልተሳተፉበት መሆኑን ያስታወሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ የተካበተበት ፕሮጀክት ነው በማለት የአገራችንን ስኳር ፋብሪካዎች የግንባታ ታሪክ ያወሳሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ የሸንኮራ አገዳ ማሳ ሽፋን ከ7ሺህ 300 ሄክታር በላይ እንደደረሰና በ2007 በጀት ዓመት የታቀደውን 10ሺህ ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ ለመሸፈን በሶስት ሽፍት የመሬት ዝግጅትና የዘር አገዳ ተከላ ስራ በመከናወን ላይ እንደሆነ አቶ ካሳ ይናገራሉ፡፡ አቶ ዓለም ከበደ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብረካ ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው በፕሮጀክቱ እየተከናወነ ስለሚገኘው የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር የዋና ሥራ አስኪያጁን ሀሳብ ሲያጠናክሩም የፕሮጀክቱ 60 የሚሆኑ የምህንድስና ባለሙያዎች በሜካኒካል፣በኤሌክትሪካል እና በምርት ፕሮሰስ የፋብሪካው የግንባታ ስራዎች ላይ መሳተፋቸውን ነው የጠቆሙት፡፡ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እና በእርሱ ስር የተለያዩ ግንባታዎችን እያከናወኑ የሚገኙ አገር በቀል ተቋማት ባለሙያዎች የግንባታ ሂደቱን እየገመገሙ የሚሰሩበት ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ እየተሰራበት የሚገኝ በመሆኑም የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ በአገራችን የስኳር ፋብሪካ ግንባታ ታሪክ ከፍተኛ ተሞክሮ የተገኘበትና የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር የተከናወነበት እንዲሁም የፕሮጀክቱ የምህንድስና ባለሙያዎች ወደፊት የኦፕሬሽን ስራውን ሙሉ በሙሉ ተረክበው መስራት የሚችሉበትን መደላድል የፈጠረ ነው ሲሉም ይገልፃሉ፡፡ አምስት ስኳር ፋብሪካዎች በሚገነቡበት በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካን የሚገነባው ኮምፕላንት የተሰኘ የቻይና ኩባንያም የካምፕ ግንባታውን አጠናቆ ወደ ፋብሪካ ግንባታ ስራው እየገባ ሲሆን፣ ሌላው የቻይና ኩባንያ የቁጥር ሶስት ፋብሪካን ግንባታ ማከናወን ይችል ዘንድ የቅድመ ክፍያ ተፈጽሞለት የሳይት ርክክብ መፈጸሙን የነገሩን ደግሞ የኩራዝ ቁጥር ሶስት ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አክሊሉ አዳኝ ናቸው፡፡ ከኦሞ ወንዝ እስከ ቁጥር ሶስት ፋብሪካ የሚወስድ የ43 ኪሎ ሜትር የመንገድ ስራ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን፣ የዋና መስኖ ግንባታውን ቁጥር ሶስት ስኳር ፋብሪካ እስከሚገነባበት ሻርማ እስከተባለ አካባቢ ለማድረስበስኳርኮርፖሬሽንበኩልየሰርቬይንግእናዲዛይንእንዲሁም በፕሮጀክቱ በኩል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ከአቶ አክሊሉ ገለጻ ተረድተናል፡፡ ወደ ፋብሪካ ቁጥር 3 እና 4 የሚደርስ የመንገድ ስራም በቻይና የመንገድ ስራ ተቋራጭ ኩባንያ ለመገንባት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመፋጠን ላይ ናቸው፡፡ እናም በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ስራ በአገራችን የስኳር ፋብሪካ የግንባታ ታሪክ ልዩ ስፍራ ተሰጥቶት እንዲዘከር እየተከናወነበት ከሚገኘው የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር ባሻገር የአካባቢውን አርብቶ አደር ከዝቅተኛ የስራ መደብ እስከ ፋብሪካ ማሽን ከፍተኛ ኦፕሬተርነት በማሳተፍም ነገ የአካባቢው ተወላጅ አርብቶ አደሮች ልጆች በአመራር ደረጃ ሊሳተፉ
  • 19. ጣፋጭ | 19 የወልቃይትስኳር ልማት ፕሮጀክት እናስተዋውቃችሁ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራባዊ ዞን በወልቃይት ወረዳ ይገኛል፡፡ ይህ ከአዲስ አበባ በ1 ሺህ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ፕሮጀክት በቀን 24 ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት ወይም 24 ሺህ ኩንታል ስኳር ማምረት የሚችል ፋብሪካ የሚገነባበት ነው፡፡ የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በአመት 484 ሺህ ቶን ስኳር እና 41ሺ 654 ሜትር ኩብ ኤታኖል እንደሚያመርት ይጠበቃል፡፡ ለዚህም በ50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ በግብአትነት ይጠቀማል፡፡ ፋብሪካው ለሸንኮራ አገዳ ልማቱ የሚያስፈልገውን ውኃ የሚያገኘው በግንባታ ላይ ካለው የዛሬማ ሜይ-ዴይ ግድብ ነው፡፡ የዛሬማ ሜይ-ዴይ ግድብ 840 ሜትር ስፋትና 135.5 ሜትር ቁመት የሚኖረው ሲሆን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ 3 ቢሊዮን 497 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ ይይዛል፡፡ በፕሮጀክቱ ለሚገነባው የስኳር ፋብሪካ የሚያስፈልገው ወጪ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ የተገኘ በመሆኑ ግንባታው በቅርቡ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚያስፈልገውን ውኃ የሚይዘው የዛሬማ ሜይ-ዴይ ግድብ እስኪጠናቀቅ ፕሮጀክቱ ከሌሎች ተያያዥ ስራዎች ጎን ለጎን ውኃ ገብ በሆኑ መሬቶች ላይ ጥጥና ሰሊጥ በማልማት ላይ ይገኛል፡፡
  • 20. :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A etsugar@hotmail.com www.etsugar.gov.et || www.facebook.com/etsugar የጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጉብኝት በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትና በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ