ጣፋጭ
	 የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከ7
ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ፣ ኮንትራትና
ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠሩን በስኳር ኮርፖሬሽን
የአገዳ ተክል ልማትና ፋብሪካ ግንባታ ዘርፍ ም/
ዋና ዳ...
2 ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት
	 የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት
በወልቃይትወረዳየቃሌማወንዝንበጊዚያዊነትገድቦ
እየሰራ መሆኑንና በመጪዎቹ የክረምት ወራትም በ3
ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ...
3ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት
አዲሱ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ...
በአርጆ ዴዴሳ ስኳር ልማት
ፕሮጀክት የዘር አገዳ ተከላ
እየተካሄደ ነው
	 በአርጆ ዴዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ2005 በጀት...
4 ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት
ቅፅ 1. ቁጥር 2 | ሰኔ 2005
የሚያደርግና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ
የሚያስችል መሆኑን አመለከቱ፡፡
	 ከቃሌማ ገበሬ ማኅበር በመምጣት ቆራሪ...
5ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት
* 31 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው የዋና ውሃ መውሰጃ ቦይ ግንባታም
ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል
	 በበለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመስመር መስኖ፣ በስፕሪንክለርና...
6 ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት
ቅፅ 1. ቁጥር 2 | ሰኔ 2005
በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በካይዘን የሙከራ
ትግበራ የላቀ አፈፃፀምና ውጤት ያስመዘገቡ የካይዘን
የልማት ቡድኖችና ሠራተኞች የማ...
7ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት
	 አሁን አሁን “በለስ” የሚለውን ቃል በመገናኛ ብዙሃንም ሆነ
በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ መስማት እየተዘወተረ መጥቷል፡፡ ስለ
ጣና በለስ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ...
8 ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት
ተመጣጣኝ የመኖሪያና የእርሻ ቦታ የማመቻቸት፣
መሰረተ ልማት የማሟላትና ካሳ የመክፈል ስራዎች
መከናወናቸውን አቶ መልኬ አስረድተዋል - እስካሁን
ለካሳ ክፍያ 53 ...
9ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት
ቆራሪት እንግዶቿን “ሁሉ
በደጄ” ብላ እየተቀበለች ነው
                                   
ከመስከረም ወር 2005 ዓ.ም. ወዲህ የተቆረቆረችው...
10 ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት
፤ በአካባቢው ቶሎ ወደ ህክምና ጣቢያ መድረስ
የማይቻል ስለነበር በሆዷ የያዘቸው ልጅ ቢተርፍም
እርሷ ግን እስከወዲያኛው አሸለበች፤ሶስት ልጆቻችን
እስካሁን ከሟቿ...
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
Upcoming SlideShare
Loading in …5
×

ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3

1,858 views

Published on

Ethiopian Sugar Corporation News letter - Sweet Volume 3 June 2013- ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3

 • Be the first to comment

 • Be the first to like this

ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3

 1. 1. ጣፋጭ የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከ7 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ፣ ኮንትራትና ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠሩን በስኳር ኮርፖሬሽን የአገዳ ተክል ልማትና ፋብሪካ ግንባታ ዘርፍ ም/ ዋና ዳይሬክተር ገለፁ፡፡ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አበበ ተስፋዬ እንደገለፁት በፕሮጀክቱ የእስካሁን ሂደት 6 ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች ጊዜያዊ እንዲሁም ለ1 ሺህ 111 ዜጎች ደግሞ ኮንትራትና ቋሚ የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ ከኮንትራትና ቋሚ ሠራተኞች ውስጥ 435ቱ በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠኑና እስከ “በልማቱ አስፈላጊነት ላይ አምነንበት ነው ወደ ቆራሪት የመጣነው ” ወ/ሮ ለታይ ግደይ “የማኅበራዊ አገልግሎቶችን በደጃችን ማግኘት ችለናል” በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴ አማካይነት ከቀያቸው ተነስተው ቆራሪት በተሰኘ ቦታ በፈቃደኝነት የሰፈሩ ነዋሪዎች በመንደር መሰባሰባቸው የማህበራዊ አገልግሎቶችን በደጃቸው እንዲያገኙ በማድረግ ቀደም ሲል ይገፉት የነበረውን ውጣ ውረድ የበዛበት ሕይወት የተሻለ እንዳደረገላቸው ገለጹ፡፡ በቆራሪት የተሰባሰቡ እነዚሁ ነዋሪዎች እንደገለጹት በመንደር በመሰባሰባቸው ደረጃውን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ፣ ልጆቻቸው ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ እንዳያቋርጡ የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከ7 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጠረ ከበለስ ጓሮ….. ›› ገጽ. 7 ቆራሪት እንግዶቿን “ሁሉ በደጄ” ብላ... ››ገጽ. 9 »» ገጽ.2 በስኳር ኮርፖሬሽን በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A Sugar_corp@ethionet.et www.etsugar.gov.et ራዕይ፡ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በአለም ተወዳዳሪ የሆነ የስኳር ኢንዱስትሪ መፍጠር »» ገጽ.4 ቅፅ 1. ቁጥር 3 ሰኔ 2005 ዓ.ም ዜና መፅሄትተወዳዳሪ የስኳር ኢንዱስትሪ መገንባት! Building Competitive sugar industry! በውስጥ ገፆች በደቡብ ኦሞ፣ ቤንች ማጂና ካፋ ዞኖች የሚካሄደውን የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በተመለከተ በኮማንድ ክልሉ ውስጥ ከሚገኙ የቤንች ማጂና ካፋ ዞኖች የአመራር አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ምሁራን ጋር ሰኔ 1 ቀን 2005 ዓ.ም በሚዛን አማን ከተማ ውይይት ተካሄደ፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ ላይ ልማቱ ለአካባቢው ህዝብና በሀገር ደረጃ ስለሚኖረው ጠቀሜታ ሰፊ ገለጻ የተደረገ ሲሆን፣ በቀጣይም ህብረተሰቡን በስፋት በማሳተፍ በልማቱ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ ከሁለቱም ዞኖች የተውጣጡ በጠቅላላው 162 የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም ታዋቂ የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ተወላጅ ምሁራን ተሳትፈዋል፡፡ በተጨማሪም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊና አራት ከአካባቢው ህዝብ የተወከሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በውይይቱ ላይ ተገኝተው ስለ ልማቱ ጠቀሜታ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከቤንች ማጂና ካፋ ዞኖች የአመራር አካላት፣ሀገር ሽማግሌዎችና ምሁራን ጋር በኩራዝ ስኳር ልማት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ የውይይቱ ተሳታፊዎች በከፊል አዲሱ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከ60 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር አመረተ አዲሱ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ግንባታን 98 በመቶ በማጠናቀቅ በሙከራ ምርት ከ60 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር በአንድ ወር ተኩል ጊዜ ውስጥ ማምረት መቻሉ ተገለጸ፡፡ አቶ አታክልቲ ተስፋዬ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ በፋብሪካው ተገኝቶ ለአነጋገራቸው የኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ እንደገለጹት አዲሱ ፋብሪካ በመጀመሪያ አቅሙ ብቻ ወደ ምርት ሲገባ የቀድሞዎቹ የወንጂ እና የሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች በአመት ያመርቱት የነበረውን ስኳር ከእጥፍ በላይ የማምረት አቅም ይኖረዋል፡፡ የፋብሪካውን ቀሪ የግንባታ ስራ በያዝነው የክረምት ወራት በማጠናቀቅ ከሙከራ ምርት ሂደቱ ጎን ለጎን የፍተሻ ስራ ይከናወናል ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ ፋብሪካው በ2006 ዓ.ም ጥቅምት ወር መጨረሻ አሊያም በኅዳር ወር መጀመሪያ ከ70 በመቶ በማያንስ የማምረት አቅሙ መደበኛ ስራውን እንዲጀምር አስፈላጊው ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ማንኛውም አዲስ የተገነባ ስኳር ፋብሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ምርት ሲገባ በሙሉ አቅም ማምረት እንደማይቻለው የጠቆሙት ዋና ስራ አስኪያጁ እስካሁን በተከናወነ የሙከራ ምርት እና የፍተሻ ስራ አዲሱ ፋብሪካ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ በሸንኮራ አገዳ ማስፋፊያ ስራ ረገድም ለፋብሪካው በቂ የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት እንዲኖር በዶዶታ በ3 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ አዲሱ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ»» ገጽ.3 በወልቃይት(ቆራሪት) በመንደር የተሰባሰቡ ነዋሪዎች * ወንጂ/ሸዋና መተሐራ በካይዘን ትግበራ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኑ
 2. 2. 2 ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በወልቃይትወረዳየቃሌማወንዝንበጊዚያዊነትገድቦ እየሰራ መሆኑንና በመጪዎቹ የክረምት ወራትም በ3 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ ለማልማት ዝግጅቱን እያፋጠነ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የተከዜ ወንዝን በፓምፕ አማካይነት ጥቅም ላይ በማዋልም በ2006 እና 2007 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 8 ሺህ ሄክታር ሸንኮራ አገዳ የሚያለማበት ዕቅድ ቀይሶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገለጸ፡፡ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪጅ አቶ አመናይ መስፍን በስፍራው ተገኝቶ ለአነጋገራቸው የስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ ግንኙነት ባልደረባ እንዳስታወቁት ለፕሮጀክቱ የሸንኮራ አገዳ ልማት የሚውለው የዛሬማ ሜይ-ደይ ግድብ ስራ እስኪጠናቀቅ ድረስ ጥቅም ላይ ከዋለው የቃሌማ ወንዝ በተጨማሪ የተከዜን ወንዝ ለመጠቀም ስትራተጂ ተነድፎ የዲዛይን እና ሰርቬይንግ ስራ መጠናቀቁን አመልከተው በወልቃይት ወረዳ በቃሌማ ገበሬ ማኅበር በሚገኝ የቃሌማ ወንዝ ላይ በሱር ኮንስትራክሽን ኃ/የተወሰነ የግል ማኅበር አማካይነት ባለፈው ዓመት ጊዚያዊና 3 ሺህ ሄክታር ሸንኮራ አገዳ ሊያለማ የሚችል ግድብ ተገንብቶ በ300 ሄክታር መሬት ላይ እንዲሁም በደቡብ ትግራይ ራያ ዞን በ 212 ሄክታር መሬት ላይ የዘር አገዳ መልማቱን አስረድተዋል፡፡ በአጠቃላይም የዛሬማ ሜይ-ደይ ግድብ ግንባታ አስኪጠናቀቅ ድረስ ከቃሌማ እና ከተከዜ ወንዞች ከ10 እስከ 11 ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ለመትከል መታቀዱንም አቶ አመናይ አክለው ገልጸዋል፡፡ የፋብሪካ ግንባታን በተመለከተ ኮንትራቱን የወሰደው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እንደ ኤክስካቬሽን ያሉ ስራዎችን በማጠናቀቅና አንዳንድ የሲቪል ስራዎች ግንባታን በማፋጠን ላይ እንደሚገኝ አቶ አመናይ አመልክተው የማሽነሪና የተለያዩ መሳሪያዎች(ኢኪዩፕመንት) የማጓጓዝ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡ ፡ የቤቶች ግንባታን በተመለከተም በሶስት ዙር የተከፋፈለ ግንባታ ለማከናወን ታቅዶ ከአምና ጀምሮ እየተከናወነ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስኪያጁ ጠቁመው የአቅም ችግር ፈታኝ ሆኖ እንደቆየና ቤቶቹ ከአግሮስቶን የሚሰሩ እንደመሆናቸውና ቴክኖሎጂው አዲስና ልምድ የሚጠይቅ ከመሆኑ አንፃር ምርቱ ከሌላ አካባቢ መጥቶ ቤቶቹ ሲሰሩ እንደቆዩና በአሁኑ ወቅት የአግሮስቶን ማምረቻ ፋብሪካው በፕሮጀክቱ ተገንብቶ ስራ እንደጀመረ ገልጸዋል፡፡ በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በተለያዩ የግንባታ ስራዎች ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ወደ አስራ ሦስት የሚሆኑ የፌዴራል፣የክልል እና የውጭ አገር ተቋማት መኖራቸውን ያመለከቱት አቶ አመናይ በእነዚህ ተቋማትና በፕሮጀክት ጽቤቱ አማካይነት እስካሁን ድረስ 10,217 በላይ የሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ገና ከጅምሩ እንኳ የተለያዩ የውጭና የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን መሳብ መጀመሩንና በዚህም በወረዳዋ የባለአራት ኮከብ ሆቴል ግንባታ ፣ የከብት ማድለቢያ ፣ የማደያ እና መሰል ግንባታዎች ጥያቄ ለወረዳ መስተዳድሩ እየቀረበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በያዝነው በጀት ዓመት የክረምት ወራት በሦስት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ ልማት ለማካሄድ የሚያስችለውን የመሬት ዝግጅት ስራ እያፋጠነ እንደሚገኝ እና ከዚህ ውስጥ በ800 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማው የዘር አገዳ መሆኑንና ቀሪው 2200 ሄክታር ደግሞ የኮሜርሻል አገዳ (ለፋብሪካ ግብዓት የሚውል አገዳ) እንደሆነ የሚገልጹት ኃላፊነት ደረጃ የደረሱ የአፋር ብሄረሰብ ተወላጆችና የአካባቢው ማህረሰብ መሆናቸውን ያመለከቱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ካሉት አጠቃላይ ሰራተኞችም 37 በመቶውን ድርሻ ይዘዋል ብለዋል፡፡ ወደ ፊት ፋብሪካው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር 50 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር እና በዚህ ጊዜም የአካባቢው ተወላጆች እና ነዋሪዎች ከአሁኑ በተሻለ ሰፊ የስራ ዕድል የሚያገኙበት ሁኔታ እንደሚኖር አክለው ተናግረዋል፡፡ ከአፋር ክልል ጋር በመተባበር በእርሻ ስራና በቴክኒክ ሙያዎች ላይ ስልጠናዎችን በማመቻቸት ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉትን ሄድ ማኖች፣ ፎርማኖች እንዲሁም የማሽን ኦፕሬተሮችና ሌሎች ስራዎችን የሚያከናውኑ ባለሙያዎች እየተቀጠሩ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ከስራ ዕድል ባሻገር ህዝቡን ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለማድረግ በመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ 12 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ በመስኖ የሚለማ የእርሻና የግጦሽ መሬት ለአካባቢው አርብቶ አደር አዘጋጅቶ ለማስረከብ እንደታቀደ አስታውቀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዱብቲ ጋብላይቱ፣ በአይሮላፍ፣ ጋሱሪና ኡንዳቡሪ መንደሮች እየተካሄዱ ካሉ የመስኖ መሬት ዝግጅት ስራዎች ውስጥ ለ2,167 አባወራ/እማወራ በማከፋፈል ማልማት ተጀምሯል፡፡ በተጨማሪም ት/ቤቶች፣ ጤና ተቋማት፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ መስጊድ፣ ወፍጮ ቤት እና ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ከመንደር ማሰባሰብ ስራ ጋር አብረው እየተካሄዱ መሆናቸውንና ከእነዚህ ውስጥም ግንባታቸው ተጠናቆ ርክክብ የተፈጸመባቸው ተቋማት እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ የአገዳ ተከላና የፋብሪካ ግንባታን በተመለከተ፣ በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ እየተገነባ የሚገኘው ፋብሪካ ከሚያስፈልገው 25 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ 10,500 ሄክታሩ በአገዳ መሸፈኑንና አጠቃላይ የፋብሪካው የግንባታ አፈጻጸምም ከ84 በመቶ በላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡ የሁለተኛውን ምዕራፍ ስራ አስመልክተው ሲናገሩም፣ በሳይት ላይ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀው፤ የመጀመሪያው ምዕራፍ አገልግሎት መስጠት በጀመረ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ሁለተኛው ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡ እንደ አቶ አበበ ገለፃ፣ ከተንዳሆ ግድብ ተነስቶ አገዳው በሙሉ እስከሚለማበት አሳኢታ ድረስ ካለው 67 ኪሎ ሜትር የዋና ውሃ መውሰጃ ቦይ (Main Canal) ውስጥ 42 ኪሎ ሜትሩ ተጠናቆ የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከ7 ሺህ በላይ ... የመስኖ ልማት ላይ ውሏል፡፡ በዚህም የዴት ባህሪና ዱብቲ አካባቢዎችን ይዞ 7 ሺህ ሄክታር መሬት የሚያለማበት ደረጃ ላይ መድረሱን ነው ኃላፊው አክለው የተናገሩት፡፡ በተመሳሳይ የሁለተኛውን ምዕራፍ 25 ሺህ ሄክታር መሬት ለመመገብ ጭምር የታቀደውና እስከ አሳኢታ ድረስ ያለው 30 ኪሎ ሜትር የሚሆን ካናልም እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ በአፋር ክልል 50 ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ማሳን የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ የሚገነባ ሲሆን፣ ግንባታው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 26 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፡፡ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን መጨረሻ የስኳር ምርት መጠኑ ደረጃ በደረጃ እያደገ 619 ሺህ ቶን ስኳር እና 63 ሺህ ሜትር ኪዩብ ኤታኖል እንደሚያመርት ይጠበቃል፡፡ ከራሱ ፍጆታ ውጭ ለናሽናል ግሪድ የሚያበረክተው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠንም ከ65 - 70 ሜጋ ዋት ይደርሳል ተብሎ ይገመታል፡፡ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በሦስት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ ለመትከል ዝግጅቱን እያፋጠነ ነው   እስከ 2007 በጀት ዓመት 8 ሺህ ሄክታር ሸንኮራአገዳ ለመትከልም አቅዷል                                    »» ገጽ.3 ቅፅ 1. ቁጥር 3 | ሰኔ 2005
 3. 3. 3ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት አዲሱ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ... በአርጆ ዴዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የዘር አገዳ ተከላ እየተካሄደ ነው በአርጆ ዴዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ2005 በጀት አመት 1,200 ሄክታር አገዳ ለመትከል በተያዘ ዕቅድ መሠረት የመሬት ዝግጅት፣ የመስኖ ዝርጋታና የዘር አገዳ ተከላ እየተካሄደ መሆኑን የፕሮጀክቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡ ከክፍሉ ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው የስኳር ፋብሪካው ግንባታ ከ90 በመቶ በላይ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በቀን 8 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም አለው፡፡ ከስኳር ምርት በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይልና ኢታኖል እንደሚያመርት የሚጠበቀው ይህ ፋብሪካ ወደፊት በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ መሆኑን መረጃው ይጠቁማል፡፡ ፋብሪካው በ2005ዓ.ም በሽያጭ ለኮርፖሬሽኑ ከመተላለፉ አስቀድሞ አል-ሀበሻ ስኳር ፋብሪካ በሚል መጠሪያ በአንድ የፓኪሰታን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ይተዳደር ነበር፡፡ የአርጆ ዴዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ ነቀምት - በደሌ በሚወስደው ዋና መንገድ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምስራቅ ወለጋ በኢሉ አባቦራና በጅማ ዞኖች የዴዴሳ ወንዝን ተከትሎ በዴዴሳ ሸለቆ ውስጥ ይገኛል፡፡ በኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለ 6 ሺህ 695 የአካባቢ ነዋሪዎች የስራ ዕድል ተፈጠረ በኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ 2005 በጀት ዓመት ለ 6 ሺህ 695 የአካባቢ ነዋሪዎች የስራ ዕድል መፈጠሩን የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ገለጹ፡፡ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ኑረዲን አሳሮ እንደገለጹት በ 2005 በጀት ዓመት 505 ቋሚ የስራ እድሎችን ጨምሮ በደቡብ ኦሞ ዞን ስምንቱም ወረዳዎች ለሚገኙ ለ 6 ሺህ 695 ሰዎች አዳዲስ የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ የፕሮጀክቱ የህዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት ዘርፍ በበኩሉ በፕሮጀክቱ አካባቢ ከሚገኙት 33 የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ውስጥ 17 ማህበራት ከ 30 ሺህ ብር በላይ መቆጠባቸውን አስታውቆ፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ተቋቁሞ የማህበራትን ጉዳይ በቅርበት መከታተል መጀመሩን አመልክቷል፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን በደቡብ ኦሞ ዞን ከሚገኙ ስምንት ወረዳዎችና ከጂንካ ከተማ በመጀመሪያ ዙር የተመለመሉ 202 አርብቶ እና አርሶ አደር ስራ ፈላጊ ወጣቶችን በግንባታ፣ በአናፂነት፣ በመሰረታዊ ብረት ብየዳ፣ በኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፣ በቀለም ቀቢነት እና በፕላስተሪንግ (ልስን) የሙያ መስኮች በማሰልጠን ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከኛንጋቶምና ሰላማጎ ወረዳዎች የተውጣጡ አስረኛ ክፍልን ያጠናቀቁ 30 የአርብቶ አደርና የአርሶ አደር ልጆች በትራክተር ኦፕሬተርነት የሶስት ወራት ስልጠና በጫንጮ የስልጠና ማዕከል አግኝተዋል፡፡ ደግሞ በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የእርሻ ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ሙሉ ናቸው፡፡ በያዝነው ክረምት ወራት በ3 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከሚለማው የሸንኮራ አገዳ መካከል በ800 ሄክታር ላይ የሚለማው የዘር ሸንኮራ አገዳ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አብርሃም ይህም ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በ2006 እና 2007 በጀት ዓመት ለሚያለማው 8000 ሄክታር የኮሜርሻል አገዳ የሚውል መሆኑን አመልክተዋል፡፡ አቶ ኃይሌ ገብረ መድኅን በፕሮጀክቱ የሕዝብ አደረጃጀት ምክትል ሥ/አስኪያጅ በበኩላቸው ከፕሮጀክት ልማቱ ጋር በተያያዘ ከቀያቸው ለሚነሱ የኅብረተሰብ አካላት በቆራሪት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ፣ የእርሻ መሬት እና የግጦሽ መሬት እንደተሰጣቸው አመልክተው በመንደር እንዲሰባሰቡ ሲደረግም በስኳር ኮርፖሬሽን በኩል የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫተቋማትደረጃቸውንበጠበቀመልኩ እንዲሟሉላቸው መደረጉን አመልክተዋል፡ ፡ አክለውም 12 የንጹህ መጠጥ ውኃ ጉድጓዶች፣ አንድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ሁለት መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ አንድ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል መማሪያ ት/ቤት ፣ አንድ ጤና ጣቢያ፣ የቀበሌ መስተዳድር ጽ/ቤትና አንድ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ጣቢያ በቆራሪት መገንባቱን አስታውቀዋል፡፡ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በሦስት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ... መልማቱንና እንዲሁም በወለንጪቲ ጎፋ ለመትከል ከታሰበው 6 ሺህ ሄክታር መካከል በ1 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአገዳ ልማት መከናወኑን ገልጸዋል፡፡ በወለንጪቲ ጎፋ ለሚለማው ቀሪ 5 ሺህ ሄክታር አገዳ ማሳ የዋና መስኖ ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የመለስተኛ መስኖ ስራም በአብዛኛው እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቶ ፈቀደ ስሜ በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የፋብሪካ አፕሬሽን ስራ አስኪያጅ በበኩላቸው በሙከራ ምርት የተገኘው ውጤት የሚያመላክተው ምርቱ አገር አቀፋዊና አለም አቀፋዊ መመዘኛዎችን የሚያሟላና የተከናወነው ግንባታም ከዲዛይን ጀምሮ ትክክለኛ ስራ መሆኑን ነው ብለዋል፡፡ ከቴክኖሎጂ አንፃር ሲታይ አዲሱ ፋብሪካ ብክነቶችን በመቀነስና አነስተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል በመጠቀም የተሻለ ምርት የሚያስገኝ፤ ከአካባቢ ብክለት የፀዳ፣ ፍሳሾች አካባቢ ላይ ጉዳት በማያስከትሉበት ደረጃ ተጣርተው የሚወገዱበት እንዲሁም የተለያዩ ባዕዳን ነገሮች ወደ ፋብሪካው ልዩ ልዩ ማሽኖች ገብተው ጉዳት እንዳያስከትሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ያካተተ እና የማሽነሪ ብልሽቶች ምርት እንዳያስተጓጉሉ መጠባበቂያ ማሽኖች የተገጠሙለት መሆኑንም አቶ ፈቀደ አብራርተዋል፡፡ አዲሱ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በመጀመሪያ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 6250 ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም የሚኖረው ሲሆን ደረጃ በደረጃ በማደግም በቀን ከ 10 እስከ 12 ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት ይችላል፡፡ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በካይዘን ትግበራ ያገኘው የዋንጫ ሽልማት በሌላ በኩል የካይዘን ኢንስቲትዩት ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. የካይዘን ፍልስፍና እና ስራ አመራር አተገባበርን አስመልክቶ በሸራተን ሆቴል ባከናወነው ሀገር አቀፍ ውድድር የወንጂ/ ሸዋ እና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ እንደቅደም ተከተላቸው አንደኛ እና ሁለተኛ ወጥተው የዋንጫና የምስክር ወረቀት ተሸለሙ፡፡ ኢንስቲትዩቱ ባካሄደው አገር አቀፍ ውድድር ቁጥራቸው ከመቶ በላይ የሚደርሱ የመንግሥት እና የግል ተቋማት መሳተፋቸው ታውቋል፡፡ የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ያነጋገራቸው አንዳንድ የማህበራቱ አባላት እንዳስታወቁት ፋብሪካው በሰጣቸው የመስሪያ ቦታ ከስራ አጥነት ተላቀው የራሳቸውን ገቢ መፍጠር ችለዋል፡፡ መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከተሰማራበት የስኳር ልማት ባሻገር መንግሥት የቀየሰውን የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማትን የማስፋፋትና ሥራ አጥነትን የማስወገድ ብሎም በኢንተርፕራይዞቹ አማካኝነት ለኢንዱስትሪ ልማት መሰረት የመጣል አቅጣጫን ለመተግበር ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የድርጅቱን ስቴት ሰርቪስ ጠቅሶ የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ዘግቧል፡፡ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት... ከገፅ 4 የዞረ በስኳር ኮርፖሬሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ
 4. 4. 4 ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት ቅፅ 1. ቁጥር 2 | ሰኔ 2005 የሚያደርግና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን አመለከቱ፡፡ ከቃሌማ ገበሬ ማኅበር በመምጣት ቆራሪት ላይ በተሰጣቸው ካሳ አማካይነት ቤት ሰርተው መኖር የጀመሩት ቄስ ገብረ ክርስቶስ ገብረ እግዚአብሔር ስኳር ልማቱ ከጅምሩ እንኳ ሕዝቡን የሕክምና ፣ የውኃ ፣ የትምህርት ቤት እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ተጠቃሚ ማድረግ መጀመሩን ይናገራሉ፡፡ “ ልጆቻችን ቃሌማ እያለን ከሁለት ሰዓት በላይ ተጉዘው ይማሩ ስለነበርና አካባቢው ፀሃያማ በመሆኑ ለብዙ ፈተና ይጋለጡ ነበር ፣በዚህ ላይ የነበረው ትምህርት ቤት እስከ 4ኛ ክፍል ድረስ ብቻ ነበር፣ እዚህ ቆራሪት ላይ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ሩቅ ሳይጓዙ የሚማሩበት ሁኔታ ተመቻችቷል፣ የሕክምና መስጫ ተቋም ፣ የውኃ ጉድጓድ በቅርባችን ማግኘት ምንችልበት ሁኔታ ተመቻችቷል ” ያሉት ቄስ ገብረ ክርስቶስ በመንደር የተሰባሰበው ሕዝብ በስኳር ልማቱ ትልቅ ተስፋ እንዳሳደረ ገልጸዋል፡፡ ከቃሌማ ገበሬ ማኅበር ወደ ቆራሪት መጥተውና በተሰጣቸው ካሳ ቤት ሰርተው መኖር “የማኅበራዊ አገልግሎቶችን ...” በበለስና በኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አካባቢዎች የሚኖሩ 60 ወጣቶች ለሶስት ወራት በጫንጮ የስልጠናማዕከልየተዘጋጀውንየትራክተር ኦፕሬተርነት ስልጠና አጠናቀው ግንቦት 17/2005ዓ.ም ተመረቁ፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመተባበር ከየካቲት 2005ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት በትራክተር ኦፕሬተርነት ያሰለጠናቸውን 60 የአርብቶ አደርና አርሶ አደር ወጣት ልጆች ባስመረቀበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ እንደገለጹት፣ሥልጠናው ለወጣቶቹ የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር በልማቱ ላይ የባለቤትነት ስሜት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ ወደፊትም በተለያዩ የሙያ መስኮች ቀጣይ ሥልጠናዎች እንደሚዘጋጁ አመልክተው የአሁኖቹ ተመራቂዎች ወደየአካባቢያቸው እንደተመለሱ ወደ ስራ የሚሰማሩበት ሁኔታ እንደሚመቻች ተናግረዋል፡፡ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች በባለፉት ዘመናት የትምህርት ዕድል ባለማግኘታቸው ሳቢያ የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዳልነበሩ የገለጹት አቶ ዳመነ፣ የአካባቢው ሕዝብ በፕሮጀክቶቹ በሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች እንዲሳተፍና እንዲጠቀም ለማስቻል ስኳር ኮርፖሬሽን ለአርብቶ አደርና አርሶ አደር ወጣቶችና ሴቶች የተለየ መለስተኛ የሙያ ክህሎት ስልጠና በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በማመቻቸትና በማህበር በማደራጀት ወደ ፕሮጀክቶቹ ተሰማርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ ለ ተ መ ራ ቂ ዎ ቹ ባስተላለፉት መልዕክትም ሠልጣኞቹ ወደየአካባቢያቸው ሲመለሱ የቀሰሙትን እውቀትና ያገኙትን ክህሎት ተግባራዊ በማድረግ ለፕሮጀክቶቹ መሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል፡፡ የሠልጣኞቹ ተወካዮች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን የሚለውጡበትን ሥልጠና በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸው፣ የተጣለባቸውን ከፍተኛ አደራ በመወጣት ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ የጀመሩት ወ/ሮ ለታይ ግደይ በበኩላቸው በመንደር በተሰባሰቡበት ቦታ የተለያዩ ማኅበራዊ ተቋማት አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ መመቻቸቱን ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ ለታይ አያይዘውም “ ወደ ቆራሪት ከመምጣታችን በፊት በተደጋጋሚ ከመንግስት ተወካዮች ጋር ተወያይተናል ፤ በልማቱ አስፈላጊነት ላይ አምነንበት ነው የመጣነው፤ የተሰጠን ካሳም በቂ ነው” በማለት ስኳር ኮርፖሬሽን ያስገነባቸው ትምህርት ቤቶች እና ጤና ጣቢያው ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ በሌላ በኩል በወልቃይት ወረዳ በልማቱ አማካይነት በመንደር በመሰባሰብ ላይ ከሚገኙ ሰባት ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት የተውጣጡ 204 ስራ የሌላቸውን ወጣቶች ስኳር ኮርፖሬሽን ከሁመራ ዞን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመጡ ባለሙያዎች ለሰላሣ ስምንት ቀናት በተለያዩ ሙያዎች በተግባር የተደገፈ ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ በሚያዚያ ወር 2005 ዓ.ም አጋማሽ ላይ አስመርቋል፡፡ ከሰልጠኞቹ መካከልም ሰላሳ ሁለቱ ሴቶች ናቸው፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ወቅትም ሰልጣኝ ተመራቂዎች በስልጠና ወቅት የገነቧቸው የማይጋባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ፣መታጠቢያና መጸዳጃ ቤት እንዲሁም የተለያዩ ስራዎች በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በአቶ አመናይ መስፍን እና በስኳር ኮርፖሬሽን የካሳ ክፍያና መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ደምስ ይግዛው አማካይነት በጋራ ተመርቆ ለጎብኝዎች ለዕይታ ቀርቧል፡፡ በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሕዝብ አደረጃጀት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይሌ ገብረ መድኅን በስፍራው ተገኝቶ ላነጋገራቸው የኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባልደረባ እንደገለጹት ከልማት ተነሽ ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት ተመልምለው በስምንት የሙያ መስኮች በተግባር በተደገፈ ሙያ ለ ሠላሳ ስምንት ቀናት ሰልጥነው የተመረቁ እነዚህን ስራ ያልነበራቸውን ወጣቶችን ለማሰልጠን ብር 940,514 በጀት ተመድቦ እንደተከናወነና ከዚህም ውስጥ ስኳር ኮርፖሬሽን ብር 865,514 እንደሸፈነ አመልክተዋል፡፡ ስልጠናውን ተከታትለው ለምረቃ የበቁት እነዚህ ወጣቶች ፕሮጀክቱን ጨምሮ በፕሮጀክቱ በተለያየ ስራ እየተሳተፉ በሚገኙ ተቋማት በኩል የስራ ዕድል እንደሚፈጠርላቸው ጠቁመዋል፡፡ ለጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት የመስሪያ ቦታ ድጋፍ ተደረገ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በጥቃቅንና አነስተኛ ሥራዎች ለተደራጁ 15 ማህበራት የመስሪያ ቦታ ድጋፍ አደረገ፡፡ ከፋብሪካው የህዝብ ግንኙነት ክፍል የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የፈንታሌ ወረዳ የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ሥራዎች ጽ/ቤት አደራጅቶ ህጋዊ ዕውቅና ለሰጣቸው 173 አባላትን ላቀፉ 15 ማህበራት ፋብሪካው ውስጥ ባሉ ስምንት የሰራተኞች መኖሪያ ካምፖች የመስሪያ ቦታ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ማህበራቱ በምግብና መጠጥ፣ በወተትና የወተት ተዋጽኦ፣ በሸቀጣ ሸቀጥና በአትክልትና ፍራፍሬ አቅርቦት፤ እንዲሁም በውበት ሳሎንና በወፍጮ ቤት አገልግሎት የተሰማሩ ናቸው፡፡ ከማህበራቱ አባላት መካከል ከዘጠና በመቶ በላይ ሴቶች ሲሆኑ፣ በማህበራቱ አማካኝነትም ከ18 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ ማህበራቱ ከተሰማሩባቸው የስራ መስኮች አንዱ “ እራሳችንንና ቤተሰቦቻችንን የምንለውጥበት ስልጠና አግኝተናል ” ሰልጣኞች »» ገጽ.3 የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ 60 ወጣቶች በትራክተር ኦፕሬተርነት ተመረቁ
 5. 5. 5ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት * 31 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው የዋና ውሃ መውሰጃ ቦይ ግንባታም ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል በበለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመስመር መስኖ፣ በስፕሪንክለርና በሬይን-ገን ዘመናዊ የውሃ ማጠጫ መሳሪያዎች በመታገዝ ከ1 ሺህ 500 ሄክታር መሬት በላይ በአገዳ ተሸፈነ፡፡ የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መልኬ ታደሰ እንደገለጹት በ7 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ተጨማሪ አገዳ ለመትከልም (6200 ሄ/ር የኮሜርሻል አገዳና 800ሄ/ር የዘር አገዳ) መሬት የማመቻቸት፣ የመሬት ስንጣቆ፣ የእርሻ፣ የክስከሳ እና መስመር የማውጣት ስራዎች በአጥጋቢ ሁኔታ ተከናውነዋል፡፡ የበለስ ወንዝ አቅጣጫን በማስቀየር ውሃው ወደ እርሻ ማሳዎች እንዲደርስ ለማድረግ 31 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው የዋና ውሃ መውሰጃ ቦይ (Main Canal) ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ዋና ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሶስት የስኳር ፋብሪካዎችን መገንባት ጀምሯል ያሉት ኃላፊው ከዚህ ግንባታ ጎን ለጎን የ10 ሺህ ሄ/ር መሬት የስፕሪንክለር ገጠማ ስራም በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ ለሶስቱ ፋብሪካዎች ከሚገነቡት 10 ሺህ መኖሪያና መኖሪያ ያልሆኑ ቤቶች ውስጥ ከ2004ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 2005ዓ.ም ድረስ በፕሮጀክቱ ከተሞችና የእርሻ መንደሮች ሰባት ቦታዎች ላይ 1 ሺህ 828 መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም 70 የጉልበት ሠራተኞች የሚኖሩባቸው እና 23 የአገልግሎት መስጫ ብሎኮች በአማራ ቤቶች ልማት ኤጀንሲ እየተገነቡ መሆኑን የጠቆሙት አቶ መልኬ ከእነዚህ ውስጥ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት የጀመሩና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ እንዳሉም ገልጸዋል፡፡ የሶስቱ ፋብሪካዎች ግንባታ ሲጠናቀቅ በ75 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማውን የሸንኮራ አገዳ ተጠቅመው እያንዳንዳቸው በቀን 12 ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት አጠቃላይ 726 ሺህ ቶን ስኳር እና 62 ሺህ 481 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል ያመርታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሀብትና ንብረት ግምት፣ የካሳ ክፍያ አፈፃፀም ሥርዓትና ተግዳሮቶችን በተመለከተ ስልጠና ተሰጠ ስኳር ኮርፖሬሽን የሀብትና ንብረት ግምት፣ የካሳ ክፍያ አፈፃፀም ሥርዓትና ተግዳሮቶችን በተመለከተ 82 ለሚሆኑ ከስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አካባቢ ለተውጣጡ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም ስራው ለሚመለከታቸው የፕሮጀክት ኃላፊዎች ስልጠና ሰጠ፡፡ ኮርፖሬሽኑ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ በመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም መጨረሻ ለሁለት ቀናት ባዘጋጀው በዚሁ ስልጠና፣ ለህዝብ ጥቅም ሲባል በሚለቀቅ መሬት ላይ ለሰፈረ ንብረት የሚከፈል ካሳን አስመልክቶ የወጡ አዋጆችና ደንቦች መሰረታዊ ይዘት፣ የሀብትና ንብረት ግምት፣ የካሳ አፈፃፀም ስርዓትና ተግዳሮቶች፣ የካሳ ክፍያ አፈፃፀም እና የፋይናንስ ፍሰት ተገቢው ግንዛቤ እንዲያዝ ማድረጉን የኮርፖሬሽኑ ህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በላከልን መግለጫ ገልጿል፡፡ በስልጠናው ላይ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና የምድር ባቡር የካሳ ክፍያ አፈፃፀም ልምዶች እንዲቀርቡ ተደርጎ ለቀጣይ ስራ የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር መቻሉ ታውቋል፡፡ በአፋር ብሔራዊ ክልል ዱብቲ ወረዳ በመንደር የተሰባሰቡ አርብቶአደሮች በመንደር የማሰባሰብ ፕሮግራሙ ቀደም ሲል ይገፉት የነበረውን ኋላቀር የአኗኗር ዘይቤ በማስቀረት የተለያዩ ማኅበራዊ ተቋማትንና መሰረተ ልማቶችን እንዲያገኙ ያስቻለ መሆኑን ገለጹ፡፡ በዱብቲ ወረዳ ቦይና በተሰኘ መንደር የተሰባሰቡት አርብቶአደሮች እንደገለጹት ስኳር ኮርፖሬሽን ከአፋር ክልል መስተዳድር ጋር በመሆን ትምህርት “በመንደር መሰባሰባችን ኋላቀር አኗኗራችንን አስወግዷል” በመንደር የተሰባሰቡ የአፋር ተወላጆች “በመንደር መሰባሰባችን ኑሯአችንን በእጅጉ የተሸለ አድርጎታል” ወጣት ሀቢብ አሊ ቤት፣የሰውና የእንስሳት ጤና ኬላዎች፣መስጂድ፣ወፍጮ ቤት፣ዳቦ ቤትና የህብረት ሱቅ እንዲሁም የአርብቶአደሮች ማሰልጠኛ ጣቢያ በመገንባታቸው የአኗኗር ዘይቤያቸው ተቀይሯል፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጋዜጠኞችና የኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባልደረባ በዱብቲ ወረዳ ቦይና መንደር ተገኝተው ያነጋገሩት አብዱ ዓሊ “ በመንደር ተሰባስበን መኖር ከመጀመራችን በፊት የነበረው አኗኗራችን ኋላ ቀር ነበር፤ ቀደም ሲል ምንም ዓይነት የማኅበራዊ እና የመሰረተ ልማት አገልግሎት የምናገኝበት ሁኔታ አልነበረም፤አኗኗራችን በተናጠል ከቦታ ቦታ ውኃ እና የግጦሽ መሬት ፍለጋ በመንከራተት ላይ ያተኮረ ስለነበር ችግር በገጠመን ጊዜ እንኳ አንዳችን ለአንዳችን የምንደርስበትና የምንተጋገዝበት ሁኔታ አልነበረም፤ አሁን ግን በመንደር በመሰባሰባችን እና ስኳር ኮርፖሬሽን እና የክልሉ መስተዳድር ማኅበራዊ አገልግሎቶችንና መሰረተ ልማቶችን በቅርባችን እንድናገኝ በማድረጋቸው እጅግ ኋላቀር የነበረው አኗኗራችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተወግዷል“ በማለት ገልጿል፡፡ ሌላው በቦይና መንደር ነዋሪ የሆነው ሀቢብ ዓሊ በመንደር ተሰባስቦ የመኖሩ ሁኔታ የፈጠረለትን ምቹ አጋጣሚ በበኩሉ ሲገልጽ “ ቀደም ሲል ለራሳችንም ሆነ ለከብቶቻችን ውኃ ፍለጋ ሩቅ ተጉዘን ዶቃ የተሰኘ ቦታ እንሄድ ነበር፤ አሁን በመንደር በመሰባሰባችን ማኅበራዊ አገልግሎቶችንና መሰረተ ልማቶችን በደጃችን እንድናገኝ አስችሎናል፤ በዚህ በቦይና መንደር በዘላቂነት መኖር በመጀመራችን ልጆቻችን ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ችለዋል፤እዚህ ቦይና ላይ አምስት መቶ የሚደርስ አባዎራ እና እማወራ ማኅበራዊ አገልግሎቶችና መሰረተ ልማቶች አጠገቡ ላይ እንዲያገኝ ተመቻችቶለት እየኖረ ይገኛል፤በአጠቃላይ እዚህ ኑሯችን በእጅጉ የተሻለ ነው “ በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ድጋፍ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጉርጃ በርሄ እንደገለጹት በዱብቲ ወረዳ ብቻ አስር መንደሮች ከተሟላ የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ጋር ይገነባሉ (ከእነዚህ መካከል ሦስቱ ተጠናቀው ርክክብ ተፈጽሟል) እንዲሁም በሚሌ ወረዳ ደግሞ አራት መንደሮች በተመሳሳይ ሁኔታ ይገነባሉ፡፡ ኮርፖሬሽኑ ከስኳር ልማት ስራው ጎን ለጎን በየፕሮጀክቶቹ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች በተለያየ ሁኔታ የመጀመሪያ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አቅጣጫ በመከተል በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ያሉት አቶ ጉርጃ እስካሁን ድረስ በአፋር ክልል ተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት አካባቢ ከተከፋፈለው በመስኖ የሚለማ መሬት መካከል የአካባቢውአርብቶአደሮችበ2,119ሄክታርመሬትላይበቆሎዘርተውምርትእንደሰበሰቡ አመልክተዋል፡፡ ለእያንዳንዱ አርብቶአደር አንድ ሄክታር በመስኖ የመለማ የእርሻ መሬት እንደተሰጠ የጠቆሙት ቡድን መሪው በሌላ በኩልም ከ 6,000 ሄክታር በላይ በሚበልጥ መሬት ላይ የመስኖና የመሬት ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እስከ ሰኔ 2005 ዓ.ም አጋማሽ ድረስም 1,500 የሚደርሱ አርብቶ አደሮች በመንደር መሰባሰባቸው ታውቋል፡፡ በበለስ ከ1ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የዘር አገዳ እየለማ ነው በስኳር ኮርፖሬሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ
 6. 6. 6 ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት ቅፅ 1. ቁጥር 2 | ሰኔ 2005 በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በካይዘን የሙከራ ትግበራ የላቀ አፈፃፀምና ውጤት ያስመዘገቡ የካይዘን የልማት ቡድኖችና ሠራተኞች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጣቸው፡፡ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ሚያዝያ 30/2005 ዓ.ም በተካሄደው የካይዘን የማበረታቻ ሽልማት ሥነ-ስርዓት ላይ የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ፀሐዬ ባደረጉት ንግግር የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አመራሮችና ሠራተኞች ካይዘንን ተግባራዊ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ላስመዘገቡት ከፍተኛ የወጪ ቅነሳ፣ የሥራ ተነሳሽነት እና አጥጋቢ የምርት ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ “ተጨማሪ በጀትና ማሽነሪ ሳትጠይቁ አዲስ አሰራርና ፈጠራ ተጠቅማችሁ በአገዳ ተከላ፣ እንክብካቤ፣ ቆረጣ እና ማጓጓዝ እንዲሁም የፋብሪካ ፍሳሽ በማስወገድ ሥራዎች እና በጋራዥ፣ መጋዘንና ወርክ ሾፕ ውስጥ በተጨባጭ የሚታዩ ለውጦች በማምጣታችሁ ኮርተንባችኋል፡፡” በማለትም ተናግረዋል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን የካይዘንና የአይ ቲ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ መንግስተአብ ገ/ኪዳን በበኩላቸው ሲናገሩ፣ በካይዘን የአመራር ፍልስፍና በ2005 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ በወንጂ፣ በፊንጫና በመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች በ10 ሚሊዮኖች ብር የሚገመት ወጪ ለማዳን መቻሉንና ከዚህ ውስጥ 71 በመቶው በወንጂ ስኳር ፋብሪካ መመዝገቡን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም በትግበራው ሂደት በአነስተኛ ወጪቀጣይነትያለውመሻሻልንማምጣትእንደሚቻል በሠራተኛውዘንድግንዛቤመዳበሩን፤ችግሮችንውጫዊ አድርጎ ከመመልከት ይልቅ ሠራተኞች ወደራሳቸው ማየት መጀመራቸውን፤ በቡድን የመስራትና ውሳኔ የመስጠት ሂደት እየዳበረ መምጣቱን፤ የአገልግሎት ሰጪና ተቀባይ ግንኙነት መሻሻሉን፤ የሥራ ቦታዎች ጽዱ፣ በአግባቡ የተደራጁና መስህብ ያላቸው እየሆኑ መምጣታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ለውጤቱ መገኘትም የኮርፖሬሽኑ እና የፋብሪካዎቹ አመራሮችና ሠራተኞች ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት ተጠቃሽ ነው ብለዋል፡፡ በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ውስጥ በሁሉም ዘርፎች 3,973 አባላት ያቀፉ 589 የልማት ቡድኖች ተቋቁመው ድርጅት አቀፍ የካይዘን ትግበራ በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ ያስታወቁት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አታክልቲ ተስፋዬ፣ በዚህ የተነሳ በሠራተኞች ዘንድ የተፈጠሩ የአመለካከት ለውጦች ከምንም በላይ ሚዛን የሚደፉ ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የካይዘን የስራ አመራር ፍልስፍና ከስራ አካባቢ ባሻገር የመኖሪያ አካባቢና የእያንዳንዱ ቤተሰብ አስተሳሰብ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች መከናወናቸውን አመልክተው፣ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ በመኖሪያ መንደሮች ተተግብሮ ጥሩ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም በህዝብ ተሳትፎ ወንጀልን ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችለው ማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ ሥርዓት /ኮሚኒቲ ፖሊሲንግ/ መተግበሩን አቶ አታክልቲ አክለው አስረድተዋል፡፡ በመጨረሻም የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ የካይዘን የልማት ቡድኖች፣ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የተዘጋጀላቸውን የማበረታቻ ሽልማት ከአቶ አባይ ፀሐዬ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር እና ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች እጅ ተቀብለዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የካይዘንን የአመራር ፍልስፍናን በስኳር ፋብሪካዎች፣ በፕሮጀክቶችና በዋናው መስሪያ ቤት በመተግበር የአመራሩንና የሠራተኛውን የአመለካከት ለውጥ በማምጣት ቀጣይነት ያለው የማምረቻና አስተዳደራዊ ወጪዎችን የሚቀንስ፣ የምርት ጥራትን የሚያሳድግ፣ የአቅም አጠቃቀምን የሚያሻሽል፣ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግ እንዲሁም ሁሉንም ሠራተኛ የሚያሳትፍ ሥርዓት በመዘርጋት ላይ ይገኛል፡፡ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የካይዘን የልማት ቡድኖችና ሠራተኞች ተሸለሙ   በካይዘን ትግበራ በሦስት ስኳር ፋብሪካዎች በ10 ሚሊዮኖች ብር የሚገመት ወጪ ለማዳን ተችሏል                                    ለሥልጠና ወደ ህንድ የተላኩ 57 ሠራተኞች ሥልጠናቸውን አጠናቀው ተመለሱ በህንድ ቫዛንዳዳ የስኳር ኢንስቲትዩት ከመጋቢት 2005ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት በአራት የስልጠና መስኮች የተሰጣቸውን ትምህርት ያጠናቀቁ ከስኳር ኮርፖሬሽን፣ ከስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የተውጣጡ 57 ሠራተኞች ወደ ስራ ቦታቸው ተመለሱ፡፡ ከኮርፖሬሽኑ የሰው ሃብት ልማትና አሠራር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው በሥልጠናው በSugar cane agronomy 16፣ በSugar technology 17፣ በSugar engineering 16 እና በElectrical engineering ስምንት ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡ በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለሠልጣኞቹ ሰኔ 10 ቀን 2005ዓ.ም የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል በተደረገበት ወቅት የሰው ሃብት ልማትና አመራር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አደባባይ አባይ ባደረጉት ንግግር ሠልጣኞቹ በህንድ ቆይታቸው ያገኟቸውን መልካም ተመክሮዎች ወደተግባር ለመለወጥከወዲሁበቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡ የሰው ሃብት ልማትና አሠራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ዳምጤ በበኩላቸው ሥልጠናውን አስመልክተው ባቀረቡት ሪፖርት ስልጠናው በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁንና ሠልጣኞቹም ተልዕኳቸውን በሚገባ መወጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ ሠልጣኞቹ በኢንስቲትዩቱ በነበራቸው ቆይታ መልካም ሥነ ምግባርን በተላበሰ መልኩ እውቀትን ለመቅሰም የተቻላቸውን ሁሉ ማድረጋቸውን በኢንስቲትዩቱ የበላይ ኃላፊዎች ሪፖርት መረጋገጡንም አስታውቀዋል፡፡ በቀጣይ ሠልጣኞቹ ያገኙትን እውቀት ለሌሎች ባልደረቦቻቸው የሚያስተላልፉበት ሁኔታ እንደሚመቻችም አክለው ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ በአራቱ የሥልጠና መስኮች የተገኙ ተመክሮዎችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች በቡድን ተወካዮች አማካኝነት በሪፖርት መልክ ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ በወቅቱ ከሠልጣኞቹ የሥራ ተነሳሽነትና የመለወጥ መንፈስን የሚያንጸባርቁ አስተያየቶች ተደምጠዋል፡፡ “…በተጨባጭ የሚታዩ ለውጦች በማምጣታችሁ ኮርተንባችኋል፡፡” የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አቶ አባይ ፀሐዬ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር
 7. 7. 7ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት አሁን አሁን “በለስ” የሚለውን ቃል በመገናኛ ብዙሃንም ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ መስማት እየተዘወተረ መጥቷል፡፡ ስለ ጣና በለስ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ፣ በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍል በስፋት ስለሚታወቀው እና በሌሎችም የአገሪቱ አካባቢዎች እየተለመደ ስለመጣው የበለስ ተክል ብዙ አድምጠናል፤ አይተናልም፡፡ ከቅርብ አመት ወዲህ ደግሞ በአገራችን ክረምት - ከበጋ ከሚፈሱ ወንዞች አንዱ ከሆነው በለስ ጋር ስለተዛመደው የበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ማድመጥ ጀምረናል፡፡ የዛሬው መጣጥፌም ትኩረት የሚያደርገው በዚሁ ፕሮጀክት ላይ ይሆናል፡፡ ወቅቱ የልማት እና የእድገት በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመንግሥት ጎን ተሰልፎ ድህነትን ታሪክ ለማድረግ በለውጥ ጎዳና መጓዝ ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል። በተለይም የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር በሕዝቡ በኩል ያለው ቁርጠኝነት አበረታች ነው። ይኸው አይነት የልማት እንቅስቃሴ ከሚደረግባቸው ዘርፎች ውስጥ ደግሞ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። በአምስቱ አመት የዕቅድ ዘመን ከሚገነቡት 10 የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ አንዱ የአማራና የቤኒሻንጉል ክልሎችን አማክሎና የበለስ ወንዝን መሰረት አድርጎ እየተካሄደ የሚገኘው የበለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ነው። የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የሸንኮራ አገዳ ማሳ 75 ሺህ ሄክታር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 50 ሺህ ሄክታር መሬት በአማራ ብሔራዊ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ፣ የተቀረው 25 ሺህ ሄክታሩ ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ዳንጉርና ፓዌ ወረዳዎች ይለማል፡፡ የዚህ ፕሮጀክት የልማት እንቅስቃሴ በሚዲያ ባለሙያዎች እንዲጎበኝ በማሰብ የስኳር ኮርፖሬሽን ከመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከመንግሥትና ከግል የመገናኛ ብዙሃን የተውጣጡ 31 የሚዲያ ባለሙያዎችን በመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ቦታው ድረስ በመውሰድ እየተካሄደ ያለውን ልማት አስቃኝቷል፡፡ ከአዲስ አበባ 650 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኘው ጃዊ ወረዳ መለስ ጠቅላይ ሠፈር የደረሰው የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን ለሁለት ቀናት ያህል የዋና እና መለስተኛ ካናል ግንባታ፣ የእርሻ ውስጥ የመስኖ መሰረተ ልማት እና የውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራዎች፣ የውሃ መቀልበሻ (ዊር) ስራ፣ የመስኖ የዘር አገዳ ልማት፣ የሸንኮራ አገዳ እርሻ መሬት ምንጣሮ እና ድልዳሎ ስራዎች፣ በስፕሪንክለር (በቅርብ ርቀት ውሃ የሚያጠጣ ዘመናዊ መሳሪያ) እና በሬይን-ገን (በአነስተኛ ትራክተር እየተጎተተ ከ40-70 ሜትር ያህል ውሃ የሚያጠጣ ዘመናዊ መሳሪያ) የመስኖ ዘዴ የሚለማ የዘር አገዳ ልማት ጣቢያ ፣ የፋብሪካ ግንባታ፣ የአግሮ ስቶን ፋብሪካ እና ሌሎችንም ተግባራት ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡ በ2003 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ በፕሮጀክቱ አማካኝነት ሁለት ፋብሪካዎችን ለማቋቋም ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ቢሆንም አካባቢው ለስኳር ምርት ካለው እምቅ አቅም፣ አመቺነት እና የመንግሥት የልማት ቁርጠኝነት አንፃር ወደ ሶስት ፋብሪካዎች ከፍ እንዲል ተወስኖ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህ መሰረት እያንዳንዳቸው 25 ሺህ ሄክታር የአገዳ ልማት ቦታን የሚጠቀሙ ሶስት ፋብሪካዎችን የመገንባት ስራ ተጀምሯል፡፡ ፋብሪካዎቹ ግንባታቸው ተጠናቆ በሙሉ አቅማቸው ማምረት ሲጀምሩ እያንዳንዳቸው በቀን 12 ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት አጠቃላይ 726 ሺህ ቶን ስኳር እና 62 ሺህ 481 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል ያመርታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለአገዳ ልማቱ ወሳኝ የሆነው የመስኖ ግንባታ ስራ ጉብኝታችንን አሀዱ ያልንበት አንዱ ክፍል ነበር፡፡ የመስኖ ውሃው የሸንኮራ አገዳውን ከማልማት ባሻገር ወደፊት ቆላማ የሆነውን አካባቢ ወደ አረንጓዴነትና ለምነት ለመለወጥ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ከወዲሁ ለመገመት አያዳግትም፡፡ በአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት እየተካሄዱ የሚገኙት የዋና ካናልና የእርሻ ውስጥ የመስኖ መሰረተ ልማት ግንባታዎች የጎብኝዎችን ቀልብ ከሳቡት ስራዎች ውስጥ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡ የበለስ ወንዝ አቅጣጫውን የሚቀይርበት ቦታ ላይ የተገነባው የውሃ መቀልበሻ (ዊር/አናት/) የልማቱ ዋነኛ ሞተር ብቻ ሳይሆን ለእይታም ማራኪ ነው፡፡ ስድስት በሮችን ያካተተው ይህ ዊር በሰከንድ 60 ሜትር ኪዩብ ውሃ የማሳለፍ አቅም አለው፡፡ የበለስ ወንዝን አቅጣጫ በማስቀየር ውሃው ወደ እርሻ ማሳዎች እንዲደርስ ለማድረግ 31 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው የዋና ውሃ መውሰጃ ቦይ (Main Canal) ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ ሌላው የጉብኝቱ ክፍል የአገዳ ልማት ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ከ 1,500 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ በመስመር መስኖ በስፕሪንክለርና በሬንገን የመስኖ ዘዴ አገዳ የተተከለ ሲሆን፣ በቲሹ ካልቸር የሚቀርቡ የሸንኮራ አገዳ ዘሮችን የማላመድ እና የተከላ ስራዎችም እየተከናወኑ መሆናቸውን በመስክ ላይ በባለሙያዎች ከተሰጠው ማብራሪያ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ለ7 ሺህ ሄክታር አገዳ ተከላ ስራ (6200 ሄ/ር የኮሜርሻል አገዳና 800ሄ/ር የዘር አገዳ) መሬት የማመቻቸት፣ የመሬት ስንጣቆ፣ የእርሻ፣ የክስከሳ እና መስመር የማውጣት ስራዎች በአጥጋቢ ሁኔታ መከናወናቸውን ከበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መልኬ ታደሰ ገለፃ ተረድተናል፡፡ የእርሻ ውስጥ እና የመጋቢ መንገዶች ግንባታዎችም በአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት እየተፋጠነ እንደሚገኝ ነው ባለሙያዎቹ የሚያብራሩት፡፡ አ ሁ ን ዋናው የፕሮጀክቱ አካል ወደሚገኝበት የፈንዲቃ ከተማ እያመራን ነው - ወደፊት ሸንኮራ አገዳውን ፈጭቶ ወደ ስኳር ከሚለውጠው ግዙፉ በለስ ቁጥር 1 ፋብሪካ፡፡ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሁለት አገር በቀል ኮንትራክተሮችን በማሳተፍ እየተከለ ባለው በዚህ ፋብሪካ መሰረት ከማውጣት ጀምሮ ያለው አጠቃላይ የሲቪል ስራው እየተካሄደ መሆኑን ተዘዋውረን ቃኝተናል፡፡ ለፕሮጀክቱ ስኬት መሟላት ከሚገባቸው ውስጥ መኖሪያና መኖሪያ ያልሆኑ ቤቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ለሶስቱ ፋብሪካዎች ከሚገነቡት 10 ሺህ መኖሪያና መኖሪያ ያልሆኑ ቤቶች ውስጥ ከ2004ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 2005 ዓ.ም ድረስ በፕሮጀክቱ ከተሞችና የእርሻ መንደሮች ሰባት ቦታዎች ላይ 1 ሺህ 828 መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም 70 የጉልበት ሰራተኞች የሚኖሩባቸውና 23 የአገልግሎት መስጫ ብሎኮች በአማራ ቤቶች ልማት ኤጀንሲ አማካኝነት እየተገነቡ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት የጀመሩና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ እንዳሉም ነው የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ያስታወቁት፡፡ ቤቶቹ በሚገነቡባቸው መንደሮች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እና የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራዎች እየተከናወኑ ከመሆናቸው ባሻገር በሶስት መንደሮች የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ በሌሎች መንደሮች ደግሞ አማራጭ ጀኔሬተሮችን በመትከል የመብራት አገልግሎት እየተሰጠ ነው፡፡ የልማት ቦታን ከማመቻቸት አኳያም በፕሮጀክቱ ምክንያት ከመኖሪያቸው ለተነሱ ነዋሪዎች የመንግሥት ሕግ በሚፈቅደው መሰረት የካሳ ክፍያ ተፈፅሟል፡፡ በዚህም ተግባር በአማራ ብሔራዊ ክልል በአዊ ዞን በጃዊ ወረዳ በአሊኩራንድና ኩምቡር ቀበሌዎች ቦታ ተመቻችቶ ከ1 ሺህ 900 በላይ የቤተሰብ ኃላፊዎችን በ2004ዓ.ም ለማስፈር ተችሏል፡፡ ለሰፋሪዎቹም ቆይታ በስኳር ኮርፖሬሽን በተገነባው የአሊኩራንድ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት የትምህርት እድል ያገኙ ታዳጊዎች »» ገጽ.8 በስኳር ኮርፖሬሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ከበለስ ጓሮ…
 8. 8. 8 ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት ተመጣጣኝ የመኖሪያና የእርሻ ቦታ የማመቻቸት፣ መሰረተ ልማት የማሟላትና ካሳ የመክፈል ስራዎች መከናወናቸውን አቶ መልኬ አስረድተዋል - እስካሁን ለካሳ ክፍያ 53 ሚሊዮን ብር፤ ለመሰረተ ልማት እና ለማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ደግሞ 59 ሚሊዮን ብር ስራ ላይ ውሏል በማለት ጭምር፡፡ በሁለቱ የሰፈራ ቦታዎች ከአካባቢው መስተዳድር እናከሕዝቡጋርበመተባበርከተከናወኑት ዋና ዋና ስራዎች ውስጥ ሁለት ት/ቤቶች፣ ሁለት ጤና ኬላዎች፣ 17 ኪ.ሜ ክረምት ከበጋ የሚያገለግል መንገድ እና 17 መለስተኛ የጥልቅ ጉድጓድ ውሃ ቁፋሮዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የፖሊስ ጣቢያዎች፣ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ እና የቀበሌ ማዕከላትም በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ እነዚህም የልማት ስራዎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን ከራሱ ከህብረተሰቡ ለመረዳት ችለናል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን ከተገነቡት ሁለት ት/ ቤቶች መካከል የአሊኩራንድ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤትን የመመልከት ዕድል ገጥሞናል፡፡ ከዚህ ቀደም 380 ተማሪዎች ብቻ ይማሩበት የነበረው የቀድሞው አሊኩራንድ ዛሬም ስያሜውን ሳይለቅ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ በአዲስ መልክ ተገንብቶ በአካባቢው ለሰፈሩ የአርሶ አደሩ ልጆች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ 16 የመማሪያና ሌሎች አራት የመገልገያ ክፍሎችን ባካተተው በዚህ ት/ቤት ከመስከረም 2005ዓ.ም ጀምሮ 1 ሺህ 285 ተማሪዎች የትምህርት አገልግሎት እያገኙ ናቸው፡፡ በጃዊ ወረዳ የአሊኩራንድ ቀበሌ ነዋሪ ቄስ ተሰራ ሙሉ ለልማቱ ቅድሚያ በመስጠት ከሚኖሩበት አካባቢ ከተነሱት ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ የበፊት ቀያቸው ለስኳር ልማት ፕሮጀክት ይውላል በመባሉ እሳቸውና ሌሎች አርሶ አደሮች አገር እንዲያድግ ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎትና ቁርጠኝነት በስምምነት ከመንደራቸው ተነስተው በተዘጋጀላቸው አካባቢ መስፈራቸውን ይናገራሉ - ለንብረታቸውም በቂ ካሳ ማግኘታቸውን በመግለፅ፡፡ በተጨማሪም “ልማቱ በአካባቢያችን መኖሩ የስራ ዕድል ከማግኘት ጀምሮ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንድንሆን አስችሎናል” ነው ያሉን፡፡ የስራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ አሁን ፕሮጀክቱ ባለበት ሁኔታ ከ12 ሺህ 600 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን አቶ መልኬ ነግረውናል - በሚሊዮን የሚቆጠሩ ብሮችን መቆጠባቸውንም አክለው፡፡ በእነዚሁ ዜጎች በሁሉም የፕሮጀክቱ የስራ መስኮች የሚደረገው ርብርብ የነገዋን የበለፀገች ኢትዮጵያ ለመገንባት ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ የፕሮጀክቱን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጨምሮ የአካባቢው ቆላማነት ሳይበግራቸው ቀንና ሌሊት ለልማት ዝግጁ የሆኑ በዘርፉ ከፍተኛ እውቀት ያካበቱ ባለሙያዎችን እና የቀን ሠራተኞችን የስራ ተነሳሽነት ማየት ደግሞ በእጅጉ ተስፋ ይሰጣል፤ ያበረታታልም፡፡ በተለይም በልማቱ ምክንያት ቀያቸውን የለቀቁ ከ300 በላይ የአርሶ አደር ልጆች በፕሮጀክቱ የጥበቃ ስራተኛነት ተቀጥረው እያገለገሉ ሲሆን፣ ህብረተሰቡ እራሱ የመለመላቸው ሌሎች በርካታ ወጣቶች ደግሞ በዶዘርና በግሬደር ኦፕሬተርነት በፕሮጀክቱ ቋሚ ሆነው ለመቀጠር የሚያስችላቸውን ስልጠና አግኝተዋል፡፡ በቀጣይም ተጨማሪ ወደ 50 የሚጠጉ ወጣቶች ተመሳሳይ ስልጠና ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የፋብሪካ ግንባታው በሚካሄድበት ሳይት ለስራ የተሰማራው የሰው ኃይል ተፍ ተፍ ማለት፤ የከባድ መኪናዎች፣ የዶዘር፣ የግሬደር እና የማሽኖች ድምፅ እንዲሁም ከመሰረታቸው ወጣ ወጣ ያሉ ግንባታዎች አካባቢውን የልማት ቀጠና አድርገውታል፡፡ በማየው ሁሉ እየተደመምኩ ነበር በስራ የተጠመደች አንዲት ወጣት የተመለከትኩት - አፀደ ቢተውልኝን፡፡ በዚህ አካባቢ ስራ አለ መባሉን ሰምታ ነው ከሰሜን ጎንደር የመጣችው፡፡ በአካባቢው እንደደረሰችም በቀን ሰራተኝነት ማገልገል ጀመረች፤ ይሁንና በዚህ ስራ ላይ ብዙም ሳትቆይ የ10+1 የትምህርት ማስረጃዋን ታያይዝና የሰዓት ተቆጣጣሪ ለመሆን በቃች፡፡ እዚህ በመምጣትሸ ምን ተጠቀምሽ? ለወጣቷ ያቀረብኩት ጥያቄ ነበር፡፡ “ይህንን ለመመለስ ቃላት ያጥረኛል፤ ምን ልበልህ በማገኘው ገቢ ኑሮዬን መምራት ጀምሬያለሁ፤ ወደፊትም እየሰራሁ እማራለሁ ብዬ አቅጃለሁ፡፡ በእውነት ይህ ፕሮጀክት ብዙ ስራ አጥ ነው ደግፎ ያለው፡፡ ይህ ዕድል ባይኖር እዚህ ያለው ሰራተኛ የት ይወድቅ ነበር?” አለችኝና ፊቷን ወደ ስራ መለሰች፡፡ በመለስ ጠቅላይ ሰፈር ሳለን አሁን አሁን በአገራችን እየተለመደ የመጣውን የስራ ፈጠራ ኢንፎርሜሽን አደመጥንና መቅረፀ ድምፅና ካሜራችንን ይዘን መረጃው ወደሚገኝበት ቦታ አመራን፡፡ ስራ የፈጠሩት ወጣቶች ስምንት ናቸው - አምስት ወንዶችና ሶስት ሴቶች፤ አምስቱ ወንዶች በተለያዩ ሙያዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን ሲሆኑ፣ ሶስቱ ሴቶች ዲፕሎማ አላቸው፡፡ እንደሰማነው ቀደም ሲል የበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተደራጁ ወጣቶች ካሉ እንዲያሳውቀው ለአዊ ዞን መስተዳድር ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ የዕድል ጉዳይ ሆነና እነዚህ ወጣቶች በማህበር የተደራጁ በመሆናቸው ሁኔታዎች ተመቻቸላቸውና ወደ ፕሮጀክቱ መጡ፡፡ የአብዛኛዎቹ ትውውቅ የሚጀምረው በአዊ ዞን ኮሶ በር የመለስተኛና ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ እንደነበር ያጫወተን ወጣትመኮንንአለሙይባላል፡፡ከባህርዳርዩኒቨርሲቲ በCultural study በ2004ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀው ይህ ወጣት ባቋቋሙት “ዘመኑ ጋሹና ጓደኞቹ የህብረት ሽርክና ማህበር” ውስጥ በገንዘብ ያዥነትና ሥራ አስኪያጁ በማይኖርበት ጊዜ ደግሞ ቦታውን ተክቶ በመስራት ያገለግላል፡፡ ወጣቶቹ በበለስ “አንድነት ካፌና ሬስቶራንት መዝናኛ ክበብ” ከፍተው እየሰሩ ሲሆን፣ የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ የመዝናኛ ክበብ አዳራሽ ከማመቻቸት ባለፈ 77 ሺህ ብር የሚያወጣ የሻይ ማሽን፣ በርካታ ወንበሮችና ጠረጴዛዎች፣ ውሃና መብራት፣ የጠረጴዛ ቴኒስ መጫወቻ፣ 18 ሺህ ብር የተገዛ የ11 ወራት የDSTV ካርድ እና ፍላት ስክሪን ቴሌቪዥን በነፃ በመስጠት እንደተባበራቸው መኮንን አውግቶናል፡ ፡ ስራ ከመጠበቅ ስራ ፈጥረው እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ለመለወጥ የተዘጋጁት እነዚህ መንፈሰ ብርቱ ወጣቶች ወደፊት ማህበራቸውን ትልቅ ደረጃ የማድረስ ዕቅድ እንዳላቸው ነው የተረዳነው፡፡ ሌላዋ በፕሮጀክቱ በተፈጠረው የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሆነችው አባይነሽ አቤ ከጃዊ ከተማ በስተሰሜን በኩል ከሚገኝ ወርቅ ሜዳ ከተባለ አካባቢ 20 ኪ.ሜ ያህል ተጉዛ ነው የመጣችው፡፡ እስከ 10ኛ ክፍል የተማረችው የ22 ዓመቷ አባይነሽ እንደሷ በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበር ከተደራጁ 28 ወጣቶች ጋር በመሆን “አገራችንን እናሳድግ” የሚል መጠሪያ ያለው ማህበር አቋቁመዋል፡፡ ከማህበሩ አባላት 20ዎቹ ሴቶች፣ ዘጠኙ ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን ገልፃ የአገዳ ተከላ ስራ መኖሩን ሰምተው ወደ ፕሮጀክቱ ከመጡ ሁለት ዓመት መቆጠሩን አውግታናለች፡፡ ወጣቷ የዘር አገዳ ችግኝ በማራባት ስራ /tissue cul- ture/ ተሰማርታ በምታገኘው ገንዘብ እራስዋን ከመቻል አልፋ ቤተሰብ እየረዳች መሆኑን ነው የነገረችን፡፡ ለወደፊትም ትምህርቷን በመቀጠል የተሻለ ደረጃ ላይ እንደምትደርስ ተስፋ ማድረጓን ከምላሿ ተረድተናል፡ ፡ በቆይታችን እድገትን አልሞና ለውጥን ሽቶ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ፕሮጀክቱ ለስራ የተመመው ኃይል የላቀ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለውንና የበርካታ ተረፈ ምርቶች ባለቤት የሆነውን የስኳር ኢንዱስትሪ እውን ለማድረግ በተባበረ ክንድ የተቀናጀ ልማት እያካሄደ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን እና የበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች የቅርብ ክትትል እንዲሁም የአካባቢው መስተዳድርና የሕብረተሰቡ ድጋፍ ያልተለየው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እና ኮንትራክተሮች ቆላማው ሜዳ ላይ ያውም ቀን ከሌሊት ሲከናወን ማየትና መስማት እርካታን ከመስጠት ባለፈ ያኮራል፤ የተነሳሽነት መንፈስንም ያጭራል፡፡ የሚዲያ ባለሙያዎችም በጉብኝታቸው ማጠቃለያ በተወካዮቻቸው አማካኝነት የገለፁት ይህንኑ ነበር፡፡ እኛ በተመለከትነው ሁሉ አድናቆትን ችረን እና ብሩህ ተስፋን ሰንቀን ወደ መዲናችን ተመለስን፤ ከበለስ ጓሮ ስኳር ለማፈስ በመለስ ጠቅላይ ሰፈር እና በሌሎች የፕሮጀክቱ መንደሮች እና ሳይቶች የተጀመረው የስኬት ሩጫ ግን ቀጥሏል! የዘር አገዳ ችግኝ ማራባት ስራ /tissue culture/ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል ከበለስ ጓሮ... ቅፅ 1. ቁጥር 3 | ሰኔ 2005
 9. 9. 9ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት ቆራሪት እንግዶቿን “ሁሉ በደጄ” ብላ እየተቀበለች ነው                                     ከመስከረም ወር 2005 ዓ.ም. ወዲህ የተቆረቆረችውና በትግራይክልል ሁመራ ዞን ወልቃይት ወረዳየምትገኘው ቆራሪት በአጭር ጊዜ ወደ ከተማነት እየተቀየረች መሆኑ ይነገራል፡፡ ታዲያ ቆራሪት የሚለው የትግርኛ ቃል ትርጉም ነፋሻማ እንደማለት ነው ፡፡ እውነትም አካባቢው ቆላማ መሆኑና ቆራሪት ደግሞ ቆላማ ግን ናፋሻማ መሆኗ ይህን ስሟን አሰጥቷታል፡፡ ከአንድ አሳዛኝ ታሪክ ካሰለፈ አባዎራ ቤተሰብ ውጭ ሰው ያልነበረባት ቆራሪት በአጭር ወራት ውስጥ ወደ ከተማነት የመቀየሯ ምስጢር ታዲያ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴ በአካባቢው መጀመር ነው፡ ፡ እናም ፕሮጀክቱ እንቅስቃሴ በጀመረባቸውና በልማቱ አማካይነት በአንደኛው ዙር ከቀያቸው የሚነሱ የቃሌማ እና የጸብሪ ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት የሚነሱ 2610 የሚሆኑ አባወራዎች ቆራሪት ላይ በተሰጣቸው ቦታ ቤታቸውን እየገነቡ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡ ቆራሪት ታዲያ እንግዶቿን ስትቀበል የነዋሪዎቿን የአኗኗር ዘይቤ የሚቀይርና ለእንግልትና ላልተመቻቸ ህይወት ይዳርጓቸው የነበሩትን የመሰረተ ልማትና የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ችግር ቀርፋና ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ አስገንብታ ነው፡፡ ቆራሪት እንግዶቿን የተቀበለችው አስራ ሁለት የውኃ ጉድጓዶች (6 ሃንድ ፓምፕ እና 6 ጥልቅ ጉድጓድ)፣ አንድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ አንድ ጤና ጣቢያ፣ሁለት መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ( ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል)፣አንድ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል መማሪያ ት/ቤት፣የቀበሌ መስተዳድር ጽ/ቤት እና አንድ የገበሬዎችማሰልጠኛጣቢያ ደረጃቸውንጠብቀው እንዲገነቡበማድረግሲሆንወጪውየተሸፈነውምበስኳር ኮርፖሬሽን ነው፡፡ ይህ የህዝብን ሁለንታዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ የስኳር ኮርፖሬሽን የአሰራር አቅጣጫ ደግሞ በደቡብ ኦሞ፣በጣና በለስ፣በከሰም-ተንዳሆ የኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶችም የተተገበረ የኮርፖሬሽኑንና የመንግስትን ሕዝባዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር ነው፡፡ እናም በቆራሪት እየሰፈሩ የሚገኙ እነዚህ የልማት ተነሺዎች ቀደም ሲል ይገፉት የነበረን እንግልትና ውጣ ውረድ የበዛበትን ሕይወት በነበር ሊያወሱት ሁሉ ነገር ተመቻችቷል፡፡ ቄስ ምሩጽ ገብረ ሚካኤል ከቆራሪት ሰፋሪዎች አንዱ ናቸው፡፡ ከቃሌማ ገበሬ ማኅበር እንደመጡና ሀብትና ንብረታቸው ተገምቶ በተሰጣቸው ካሳ ቆራሪት ላይ ቤት እንደሰሩ የገለጹት ቄስ ምሩጽ “ወደዚህ ከመምጣችን በፊት ከመንግስት ኃላፊዎች ጋር ብዙ ጊዜ ውይይት አድርገናል፤ የውኃ አቅርቦት፣የህክምና አገልግሎት፣የትምህርት ተቋማት፣ወዘተ እንደሚሟላልን ከጅምሩ ነግረውን ነበር ፣በተነገረን መሰረትም ሁሉም ነገር ተሟልቶ አግኝተነዋል “ ይላሉ፡፡ “ በነበርኩበት የቃሌማ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር የነበረው ትምህርት ቤት እስከ አራተኛ ክፍል ብቻ ስለነበር ልጆቼ ማይጋባ ከተማ ቤት ተከራይተው ይማሩ ነበር ፤ አሁን በቆራሪት ቤተሰባችን በአንድ ላይ ሆኖ ልጆቼም በቅርባቸው የሚማሩበት ሁኔታ በመመቻቸቱ እጅግ ተደስተናል “ ሲሉምቄስ ምሩጽ ቆራሪትለመላቤተሰባቸውሁሉ በደጄ ብላ እንደጠበቀቻቸው ይናገራሉ፡፡ ሌላው ከቃሌማ ገበሬ ማኅበር ወደ ቆራሪት መጥቶና ቤት ሰርቶ ኑሮውን በመግፋት ላይ የሚገኘው ወጣት ገብረ ሚካኤል ደጀን በነበረበት የቃሌማ ገበሬ ማኅበር መማር የቻለው እስከ አራተኛ ክፍል ብቻ እንደነበርና ትምህርቱን ለመቀጠል ማይጋባ መሄድ የግድ ይለው ስለነበርና ይህም የእርሻ ስራውን በጎን ለማካሄድ ስለማያስችለው ትምህርቱ በዚያው ተገትቶ እንደቆየ ይናገራል፡፡ ገብረ ሚካኤል አያይዞም “ ትምህርት ቤቱ ካለሁበት በጣም እሩቅ ስለነበር ከአራተኛ ክፍል አቋርጨ ነበር፤ አሁን ግን እዚህ ቆራሪት ሁሉ ነገር ስለተሟላ እስከመጨረሻ ለመማር አቅጃለሁ “ ይላል፡፡ ወደቆራሪት ስንመጣ ከመንግስት አካላት ጋር በተደጋጋሚ ተወያይተን፣ አምነንበትና ደስ ብሎን ነው የሚሉት ሌላዋ ሰፋሪ ወ/ሮ ለታይ ግደይ ናቸው፡፡ “ በቃሌማ ለነበረኝ ሀብትና ንብረት የተሰጠኝ የካሳ ክፍያ በቂ ነው፤ እዚህ ቆራሪት ቤት ሰርቻለሁ፤በእርግጥ ቤቴን በነበረኝ ገንዘብ ካሳ ሳይሰጠኝ ቀደም ብየ ነው የሰራሁት፤ሁሉም የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እዚህ ተሟልተዋል፤ የበፊት አኗኗራችን ውጣ ውረድ የበዛበት ነው ፤ ህክምና በበቂ ሁኔታና በቀላሉ አናገኝም ነበር፣ እዚህ ለእኛም ሆነ ለልጆቻችን ሁሉ ነገር በቅርብ ርቀት ይገኛል “ በማለትም ቆራሪት በአጭር ወራት ውስጥ ወደ ከተማነት እየተቀየረች መሆኗን ይናገራሉ፡፡ በቆራሪት ብቻውን አስራ ሁለት ዓመታት ለኖረ አንድ ገበሬ ታዲያ ማኅበራዊ ተቋማቱ እደጁ ድረስ መጥቷል፡ ፡ ይህ አባወራ ስሙ ፋንታሁን መኮንን ይባላል፡፡ ቀደም ሲል ህይወት በቆራሪት ምን ትመስል ነበር ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ “ በቆራሪት ለአስራ ሁለት ዓመት ኑሪያለሁ፤በእርሻ ነው የምተዳደረው፤ከብቶችና የንብ ቀፎም አለኝ “ ብሎ መናገር እንደጀመረ ፊቱን ቅጭም አድርጎ ከስድስት ዓመታት በፊት የገጠመውን አሳዛኝ ታሪክ እንዲህ አጫወተን፡፡ “ በ2000 ዓ.ም. ባለቤቴ ካላዛር በሚል ስያሜ በበረሃማ አካባቢዎች በሚታወቅ በሽታ እጅግ ታማብኝ ነበር፣ በዚህ ላይ ደግሞ ነብሰጡር ነበረች ፤ እናም አሁን እንደምታዩት ሳይሆን በቆራሪት እኔ ብቻ ከቤተሰቤ ጋር ነበር የምኖረው ፤ በዚህ የሚያልፍ ምንም መንገድም ሆነ የጤና፣የትምህርት ተቋም አልነበረም፤ ታዲያ የባለቤቴን ህይወት ለማዳን አስከ ዓዲ ረመጽ ድረስ በእግር የሰባት ሰዓት መንገድ በቃሬዛ ተሸክሜና ከዚያም ከዓዲ ረመጽ ወደ ሁመራ በመኪና ወስጄ ሀኪም ቤት ባደርሳትም ህይወቷን ማትረፍ አልቻልኩም፤ ቆይታ »» ገጽ.10 የቆራሪት መንደር በስኳር ኮርፖሬሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ
 10. 10. 10 ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት ፤ በአካባቢው ቶሎ ወደ ህክምና ጣቢያ መድረስ የማይቻል ስለነበር በሆዷ የያዘቸው ልጅ ቢተርፍም እርሷ ግን እስከወዲያኛው አሸለበች፤ሶስት ልጆቻችን እስካሁን ከሟቿ ባለቤቴ ወላጆች ጋር እየኖሩ ይገኛሉ፤ አሁን ታዲያ በስኳር ልማቱ አማካይነት ሚስቴን ያሳጣኝ የሕክምና አገልግሎት እጦት ተወግዶ ህክምናው እበሬ ድረስ መጥቷል፤ እኔና ልጆቼ ከእንግዲህ በህክምና ዕጦት ለሞት አንዳረግም ብዬ አምናለሁ “ ሲል ስኳር ልማቱ ያመጣለትን በረከት አቶ ፋንታሁን ፈጣሪውን እየጠራ ያመሰግናል፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን በወልቃይት ስኳር ልማት የስራ እንቅስቃሴ ሳቢያ ከቀያቸው ተነስተው በቆራሪት ከሚሰፍሩ ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት የተውጣጡ ስራ የሌለቸውን 204 ወጣቶችንም በተለያዩ ስምንት የሙያ ዘርፎች አሰልጥኖ በሚያዚያ ወር አጋማሽ ገደማ ማስመረቁና በማኅበራት ተደራጅተው በፕሮጀክቱ የስራ ዕድል የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸቱ ኮርፖሬሽኑ ከሚያከናውናቸው ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራቱ ሌላኛው ማሳያ ነው፡፡ከእነዚህ ሰልጣኞች መካከል ደግሞ 32 ሴቶች ናቸው፡፡ ወጣቶቹ በግንበኝነት፣በልስን፣ቀለም ቅብ፣በብረታ ብረት፣ ኤሌክትሪክ ኢንስታሌሽን፣በሳኒተሪ፣ ወዘተ ሙያዎች ከሁመራ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በመጡ መምህራን ተግባር ተኮር ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን በዚሁ በተግባር ላይ በተመሰረተ የስልጠና ወቅትም የማይጋባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ቢሮን፣ የቢሮውን መጸዳጃ እና መታጠቢያ ቤት ገንብተው በምረቃ በዓላቸው ወቅት ለጉብኝት እንዲበቃ አድርገዋል፡፡ አካል ጉዳተኝነቱ ሳይበግረው ስልጠናውን ተከታትሎ ያጠናቀቀው ወጣት አስበይ ግደይ የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን አጠናቆ ያለስራ በነበረበት ወቅት ይህ የስልጠና ዕድል ሲመጣ አካል ጉዳተኛነቱ ከመሳተፍ እንደማያግደው እርግጠኛ እንደነበርና ለስልጠናው ተመልምሎ በሳኒተሪ ሙያ እንደተመረቀ ይናገራል፡ ፡ “ ስልጠናውን አጠናቅቄ ስራ የማገኝበትን ዕድል ኮርፖሬሽኑ በማመቻቸቱና በስልጠና ወቅት የማረፊያ እና የኪስ ገንዘብ በመስጠቱ አጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ፤በተግባር የተደገፈ ስልጠና በማግኘቴ ወደፊት ስራየን ያለምንም ችግር ማከናወን የምችልበት አቅም ፈጥሬለሁ ፤ከስራ አጥነት በመገላገሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ “ በማለትም ስኳር ኮርፖሬሽን ስላደረገለት እገዛ ተናግሯል፡፡ አንድ ዓመት ያልሞላው ልጇን ይዛ በምረቃ በዓሉ ዕለት ያገኘናት ሌላዋ ሰልጣኝ ተመራቂ ማሾ ደሴ ትባላለች፡፡ ትዳር ከመሰረተች አንድ ዓመት እንደሆናት የምትገልጸውወ/ሮማሾበስልጠናውወቅትቤተሰቦቿም ሆኑ ባለቤቷ ልጇን በመንከባከብ ስልጠናውን እንድትከታተል እንዳገዟት ትናገራለች፡፡ “የሰለጠንኩት በቀለም ቅብ ሙያ ነው፤ስልጠናው ሙሉ አቅም ፈጥሮልኛል፤ከሰባተኛ ክፍል ያቋረጥኩትን ትምህርትም እየሰራሁ ለመቀጠል ዕቅድ አለኝ ፤በወልቃይት ቀደም ሲል ወላጆቻችን እንዲህ ዓይነት ዕድል አያገኙም ነበር፤ ሌሎች ሴት እሀቶቼም የእኔ ዓይነት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መልዕክቴን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ “ በማለት ወደ ስራ ዓለም የመትቀላቀልበት ወቅት ላይ በመድረሷ ደስተኛ መሆኗን ገልጻለች፡፡ በአንደኛ ዙር 204 ወጣቶችን በተለያየ ሙያ ለማሰልጠን ብር 940,514 ተመድቦ የተከናወነ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ስኳር ኮርፖሬሽን ብር 865,514 የወልቃይት ወረዳ መስተዳድር ጽ/ቤት ደግሞ ብር 75,000 መሸፈናቸውን የሚገልጹት ደግሞ አቶ ኃይሌ ገ/መድኅን በፕሮጀክቱ የሕዝብ አደረጃጀት ም/ስራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ በቀጣይም 130 የሚሆኑ ወጣቶችን ግብርና ተኮር በሆነ ሙያ ማለትም በመስኖ ልማት፣በከብት ዕርባታና ወተት ልማት፣ በዓሣ ልማት እና በምግብ ዝግጅት ሙያዎች ለማሰልጠን መታቀዱን አቶ ኃይሌ አብራርተዋል፡፡ በልማቱ ምክንያት ከቀያቸው ለሚነሱ አባወራና እማወራዎች በሚያዚያ ወር መጀመሪያ ገደማ የካሳ ክፍያ መከፈል መጀመሩን የጠቆሙት አቶ ኃይሌ በልማቱ ተነሺ የሆኑ የኅብረተሰቡ አካላት ከልማቱ የመጀመሪያ ተጠቃሚዎች እራሳቸው መሆናቸውንና የልማቱ ባለቤት እኛ ነን የሚል እምነት ስላላቸው በቆራሪት በተሰጣቸው ቦታ ላይ የካሳ ክፍያ መከፈል ከመጀመሩ በፊት በእራሳቸው ወጪ ቤታቸውን መገንባት መጀመራቸውን አውስተዋል፡፡ በቆራሪት ሰፈራ ጣቢያ እያንዳንዱ አባወራ ነባር ይዞታውን ባገናዘበ መልኩ ከ 0.75 አስከ 1.75 ሄክታር በመስኖ ሊለማ የሚችል የእርሻ መሬት ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቆ ወደ ተግባር መገባቱንና በአካባቢውም ሰፊ የግጦሽ መሬት እንዳለ አቶ ኃይሌ አያይዘው ገልጸዋል፡፡ በወልቃይትስኳርልማትፕሮጀክትናከፕሮጀክትልማቱ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የግንባታ ስራዎች እየተሳተፉ ባሉ አገር በቀልና የውጭ ተቋማት አማካይነት ከ 10,217 በላይ የሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው የሚገልጹት የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አመናይ መስፍን በበኩላቸው ወደፊት ፋብሪካው ተጠናቆ ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከ80 እስከ 100 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ይናገራሉ፡፡ በፕሮጀክቱ 18 ነባር እና 13 አዳዲስ ማኅበራት ተደራጅተው በፕሮጀክቱ በተለያየ ስራ ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ አቶ አመናይ በመግለጽ ፕሮጀክቱ ሌሎች የኢንቨስትመንት መስኮችን ገና ከአሁኑ መሳብ መጀመሩንና ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ፣ የከብት ማድለቢያ፣የነዳጅ ማደያ እና የመሳሰሉ ተቋማትን ለመገንባት የውጭና የአገር ውስጥ ባለሀብቶችመጠየቅእንደጀመሩያብራራሉ፡፡ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በግድብና መስኖ ግንባታ ፣ በቤቶች ልማት ፣ በፋብሪካ ግንባታ እና በዘር እና ኮሜርሻል አገዳ በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የያዛቸውን ተግባራት ለማሳካት የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሆነም አቶ አመናይ ገልጸዋል፡፡ በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የእርሻ ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪጅ አቶ አብርሃም ሙሉ ደግሞ በእርሻው ዘርፍ በሁለት ሳይቶች ማለትም በቃሌማና በራያ በ512 ሄክታር መሬት ላይ የዘር አገዳ ልማት እየተካሄደ እንደሆነ፣ በያዝነው ዓመት 3,000 ሄክታር የኮሜርሻል እና ዘር አገዳ ልማት ለማከናወን ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንና ከዚህም ውስጥ 800 ሄክታሩ የዘር አገዳ ልማት የሚከናወንበት እንደሆነ ያብራራሉ፡፡ ይህ በድምሩ በ1,312 ሄክታር ላይ የሚለማ የዘር አገዳ በ2006 እና በ2007 ዓ.ም. 8,000 ሄክታር ኮሜርሻል አገዳ ለማልማት እንደሚያስችል አቶ አብርሃም ያስረዳሉ፡፡ ታዲያ በቃሌማ በ300 ሄክታር መሬት ላይ ያለው የዘር አገዳ ልማት በኤሌክትሪክ ኃይል በፓምፕ አማካይነት የሚለማ በመሆኑና በኤሌክትሪክ መቆራረጥ ምክንያት በዘር አገዳ ልማቱ ላይ የውኃ ዕጥረት በማጋጠሙ ችግሩን ለመፍታት ከሽሬ ወደ ፕሮጀክቱ በእንጨት የኤሌክትሪክ ምሰሶ አማካይነት የሚተላለፈውን ኃይል በኮንክሪት ፖል የመተካት ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑንም አቶ አብርሃም ጠቁመዋል፡፡ ለወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሸንኮራ አገዳ ልማት የሚውለው ውኃ ዛሬማ ወንዝ ላይ የሚገነባውና 143 ሜትር ከፍታና 720 ሜትር ስፋት ያለው ግድብ ግንባታ እና 70 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚኖረው የዋና ካናል ግንባታ ወሳኝ ነው፡፡ ግንባታውን የሚያከናውነው አገር በቀል ተቋም የሆነው ሱር ኮንስትራክሽን ኃ.የተ. የግል ማኅበር ሲሆን የዚህ ተቋም የዛሬማ ሜይ-ደይ ግድብ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አርአያ ግርማይ በግድብ እና ዋና ካናል ግንባታው በኩል ተቋማቸው የደንበኛቸውን የስኳር ኮርፖሬሽንን እቅድ ግምት ውስጥ በማስገባት በ30 ወራት ውስጥ ግንባታውን ለማጠናቀቅ በተለይ በአሁኑ ወቅት 24 ሰዓት እየተሰራ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ የግድቡ ግንባታ እስካሳለፍነው ሚያዚያ ወር አጋማሽ ድረስ 10.5 % መሆኑን የጠቆሙት ኢንጂነር አርአያ እስከ መጪው መስከረም ወር አጋማሽ ድረስ ወንዙን ለመቀልበስ የሚያስችል የዳይቨርዥን ኮንዲዩት ስራ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑንና የዋና ካናል ግንባታ ስራውም ጎን ለጎን እየተካሄደ መሆኑን ያብራራሉ፡፡ እናም ስኳር ኮርፖሬሽን የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴን የአካባቢውን ሕዝብ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ ማከናወኑን ቀጥሏል፣ የወልቃይት አካባቢ ህዝብም ከልማቱ መጠቀም ጀምሯል፣ ከዚያም በላይ ደግሞ ትልቅ ተስፋ ሰንቋል፡፡ ወልቃይት ከመሰረተ ልማት አውታሮችና ከማኅበራዊ ተቋማት ጋር መተዋወቋ ብቻ ሳይሆን የባለሀብቶችን ዓይን የምትስብ የኢንዱስትሪ ዞን የመሆን ተስፋዋ ለምልሟልና፡፡ ታዲያ ቆራሪትም እንግዶቿን ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ ብላ መቀበሏን ቀጥላለች፤ ነገ እና ከነገ ወዲያ ቆራሪት ትልቅና ዘመናዊ ከተማ መሆኗ አይቀሬ ነው!! “ለሁሉም ጊዜውን ይጠብቅለታል” ተብሏልና! በቆራሪት መንደር የተገነባ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋም ቆራሪት እንግዶቿን... ቅፅ 1. ቁጥር 3 | ሰኔ 2005

×