SlideShare a Scribd company logo
1 of 74
አዲሱ የአማራ ከልል የገጠር መሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ
በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሥር ለሚገኙ ለወረዳ እና ከፍተኛ
ፍ/ቤቶች ዳኞች የተዘጋጀ ስልጠና
በሪሁን አዱኛ ምሕረቱ
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
ታህሳስ 21 - 22/2010 ዓ/ም
ደሴ
ጥር 04 – 05/2010 ዓ/ም
እንጅባራ
1. መግቢያ
 መሬት በተፈጥሮ የተገኘ የማይንቀሳቀስ ንብረት
ከመሆኑም በላይ ሌሎች የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ
ንበረቶችን ለማፍራት አስፈላጊ የሆነ መተኪያ የሌለዉ
ሀብት ነው፡፡
 መሬት ከንብረት መብት አኳያ ለሀገራችን አርሶ አደር የኑሮ
ዋስትና ነው።
 ለኢንቨስትመንት እና በአጠቃላይ ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን በማረጋገጥ ረገድ ለመንግስት
ቁልፍ የፖለቲካል ኢኮኖሚው መገለጫ የሆነ ሀብት ነው።
 ይህን ትልቅ ዋጋ ያለው የሕዝብና የመንግስት ሀብት
በአግባቡ ለማስተዳደርና አጠቃቀሙን ለማሳለጥ
የሚያገለግሉ በፌደራል መንግስቱ እና በክልላችን የሕግ
ማዕቀፎች ወጥተው እየተሰራባቸው ይገኛል።
የቀጠለ
 ከግንቦት 21 ቀን 1998 ዓ/ም ጀምሮ በክልላችን
ውስጥ ሥራ ላይ የነበረው የገጠር መሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ አዋጅ ቁጥር
133/1998 እና ማስፈጸሚያ ደንቡ ቁጥር 51/1999
መሆኑ ይታወቃል፡፡
 ሆኖም እነዚህ ሕጎች ተግባራዊ ሲደረጉ በርካታ
ችግሮች በማጋጠማቸው ሕጎቹን ማሻሻል
በማስፈለጉ የተሻሻለው የአማራ ክልል የገጠር
መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር
252/2009 ታውጇል፡፡
 የዚህ አዋጅ ማስፈጸሚያ ረቂቅ ደንብም
የቀጠለ
 በመሰረቱ ፍትሕ ለማግኘት በሚደረግ ጥረት ውስጥ
በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ከሚቀርቡ ጉዳዮች ውስጥ
እጅግ የሚበዛው የመሬት ክርክር ነው፡፡
 ክርክሮቹ ከወረዳ ፍርድ ቤት ጀምሮ እስከ ክልሉ ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ የሚደርሱ እና በቅርቡ
ደግሞ እስከ ፌደሬሽን ም/ቤት የሚዘልቁና መቋጫ
የሌላቸው ሲሆኑ ይታያሉ።
 መቋጫ የለሽ ለሆነ የመሬት ክርክር ወይም የተዛባ ፍርድ
መንስኤዎች ምንድን ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ
በተግባር ከሚታዩ ችግሮች በመነሳት የተወሰኑ ምክንያቶች
ተለይተው ነበር።
 ከተለዩት ምክንያቶች አንደኛው በመሬት አስተዳደርና
የቀጠለ
 በሕጎቹ ላይ የሚታዩ ችግሮች ተብለው የተለዩት፡-
1. የክልሎች ሕግ የማውጣት ስልጣን በዜጎች ላይ ያመጣው
የመብት መለያየት ከውርስ መብት ጋር የተያያዘ ልዩነት፡-
በውርስ፣ በኪራይ፣ በስጦታ መብት እና ይዞታ መብት
የሚታጣባቸው ሁኔታዎች ላይ ከክልል ክልል ሰፊ ልዩነት
መኖሩ፤
2. የገጠር መሬት ውርስ ቅደም ተከተል ፍትሐዊ አለመሆኑ፤
3. የገጠር መሬት ክርክር በይርጋ የሚታገድ መሆን
አለመሆኑ በአግባቡ ሳይደነገግ መታለፉ፤
4. የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕጎች በየወቅቱ
ለባለይዞታዎች የተለያየ መብት በመስጠታቸው ቋሚና
የተረጋጋ መብት አለመኖሩ፤
5. ወጥ የሆነ የመሬት ግብይት ፎርማሊቲ አለመደንገጉ፤
6. የከራይ ዘመን መርዘም እና የኪራይ ተመን ገደብ
አለመኖር፤
የቀጠለ
 አዲሱ አዋጅ ከቀድሞው አዋጅ በእጥፍ ቁጥር ድንጋጌዎችን
የያዘ፣ በጣም ሰፊ መግቢያ እና በርካታ የትርጓሜ ንዑስ
አንቀጾችን ያካተተ እንዲሁም አዳዲስ ሀሳቦችን ያቀፈ ሆኖ
ታውጇል፡፡
 ለአዋጁ መሻሻል ምክንያት የሆኑ አስር መሰረታዊ
ነጥቦችም መግቢያው ላይ ተካተዋል፡፡ ይኸውም፡-
1. አርሶ አደሮችም ሆነ ከፊል አርብቶ አደሮች በያዙት
የገጠር መሬት ላይ ያላቸውን የተጠቃሚነት መብት
ይበልጥ ማስፋት ተገቢ ሆኖ በመገገቱ፤
2. በክልሉ ዉስጥ ተበታትኖ የሚኖረዉን አርሶ አደርና ከፊል
አርብቶ አደር ወደ ተወሰኑ ማዕከላት በማሰባሰብ
ሁለንተናዊ ለሆነ እድገት ተጠቃሚ የሚያደርጋቸዉን
ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
3. ሀገራችን የአርብቶ አደሮችን በመሬት የመጠቀም መብት
አስመልክቶ በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ ደረጃ
የቀጠለ
4. የግል ባለሀብቱ እና አግባብ ያላቸዉ ድርጅቶች
መሬትን በአግባቡ በማልማት፤ በመጠቀምና
በመጠበቅ ረገድ የሚኖራቸዉን ተሳትፎ ለማጠናከር
እና ጥረታቸዉ ከክልሉ መንግሥት የልማት
ዓላማዎች ጋር አንዲቀናጅ ለማድረግ በማስፈለጉ፤
5. በክልሉ ዉስጥ የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃን
በጥራት ለማደራጀትና ለባለይዞታዎች በአግባቡ
ለማሰራጨት የሚያስችል ምቹ እና ደረጃዉን የጠበቀ
የሕግ ማዕቀፍ በመፍጠር ሕጋዊ የመሬት
ባለይዞታዎች የይዞታ ዋስትናቸዉ ተጠናክሮ ማየት
በማስፈለጉ፤
6. ሕገ-ወጥ የወል መሬት ወረራን በመከላከልና በግልም
ሆነ በወል ይዞታቸዉ ላይም ቢሆን ያልተፈቀዱ
የቀጠለ
7. ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ግጭቶችን ለመቀነስ የክልሉ
መንግስት እና ባለይዞታዎች አስተማማኝ የመረጃ አገልግሎት
የሚያገኙበትን ዘመናዊ የመሬት መረጃ ስርዓት መዘርጋት እና
ገቢራዊ ማድረግ በማስፈለጉ፤
8. በተለያዩ የክልሉ የስነ ምህዳር ቀጠናዎች ላይ ተመስርቶ ፈርጀ-
ብዙ የገጠር መሬት አጠቃቀም እቅድ በማውጣትና
በመተግበር የተፈጥሮ ሀብታችን በዘላቂነት በመጠበቅ እና
በማልማት ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ አንዲቻል
አስተዳደሩንና አጠቃቀሙን በሕግ መደንገግ አስፈላጊ
በመሆኑ፤
9. ሴቶች፣ ሕጻናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካሞች እና
አረጋዊያን የገጠር መሬት ባለይዞታ የመሆን መብታቸው
እንዲጠናከር በዝርዝር መደንገግ በማስፈለጉ፤
10. በክልሉ ዉስጥ አንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች ወደ አቅራቢያዉ
የከተማ አስተዳደር ክልል በሚጠቃለሉበት ወይም የገጠር
መሬት ለሕዝብ አገልግሎት አንዲዉል በሚፈለግበት ጊዜ
የቀጠለ
 የዚህ አጭር ስልጠና አላማም የተሻሻለውን ገጠር መሬት
አስተዳዳርና አጠቃቀም አዋጅ ከረቂቁ ደንቡ ጋር
በማገናዘብ ለዳኞች በማሳወቅ ለቀጣይ ሥራቸው
እንዲጠቅማቸው ማድረግ ነው፡፡
 በመሆኑም በክልላችን ውስጥ የገጠር መሬትን
በማግኘት፣ በመጠቀም፣ በማስተላለፍ እና መብቱ ቀሪ
በሚሆንባው ሁኔታዎች ላይ ከቀድሞው ሕግ አንጻር
የተጨመሩ ወይም የተሻሻሉ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፡፡
 እንዲሁም አዋጁ ያካተታቸው ሌሎች መሰረታዊ ጉዳች
ይተነተናሉ፡፡
 የአዋጁ ማስፈፀሚያ ደንብ በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለ
በመሆኑ ከደንቡ ላይ የሚወሰዱ ሀሳቦች ያለቀላቸው
ስለማይሆኑ ዳኞች ይህን ግንዛቤ በመያዝ ወደፊት
2. የገጠር መሬት የማግኘት፣ የመጠቀም እና
የማስተላለፍ መብቶች
የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና ዘላኖች ለእረሻም ሆነ
ለግጦሽ የሚጠቀሙበት የገጠር መሬት በነጻ የማግኘት፣
የማጠቀም እና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት
ያላቸው መሆኑን የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ
40(4)(5) ይደነግጋል፡፡
በህገ መንግስቱ አንቀጽ 40(4) ላይ እንደተደነገገው
የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ሰው የሚከለከለው
መሬቱን መሸጥ እና በሌላ ንብረት መለወጥ ብቻ
እንደመሆኑ መጠን አርሶ አደሮችም ሆነ አርብቶ አደሮች
በነጻ ያገኙትን መሬት በተለያየ መልኩ የመጠቀም፣
በስጦታ ወይም በውርስ የማስተላለፍ፣ የማከራየት እና
ተያያዥ መብቶች ይኖራቸዋል፡፡
የእነዚህን ዝርዝር መብቶች አፈፃፀም በተመለከተ
በዝርዝር ሕጎች እንደሚወሰኑ ህገ መንግስቱ የሚደነግግ
2.1 የገጠር መሬት ባለይዞታ የመሆን መብት
አዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀጽ 2(4) “የይዞታ መብት ማለት
ማንኛውም አርሶ አደር፣ አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር
የገጠር መሬትን በግብርናና በተፈጥሮ ሀብት ልማት ተግባር
ላይ የማዋል፣ የማከራየት፣ ለቤተሰቡ አባልና ለሌሎች በሕግ
መብት ለተሰጣቸው ወራሾች ለማውረስ የሚኖረው መብት
ሲሆን በመሬቱ ላይ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ ንብረት
የማፍራትና ይህንንም በመሬቱ ላይ ያፈራውን ንብረት
የመሸጥ የመለወጥና የማውረስንም መብት ይጨምራል”
በማለት ደንግጓል፡፡
የክልላችን አዲሱ አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 2(24) የይዞታ
መብት ማለት ማንኛውም አርሶ-አደር፣ ከፊል አርብቶ-አደር
ወይም በሕጉ መብት የተሰጠው ማናቸውም ሌላ አካል በዚህ
አዋጅ መሰረት የተረጋገጡለትን የገጠር መሬት ባለይዞታ
የመሆን፣ በመሬቱ ላይ ንብረት የማፍራት፣ያፈራውን ንብረት
የማስተላለፍ፣ ከመሬቱ ያለመፈናቀል፣ መሬቱን ለግብርናና
ለተፈጥሮ ሃብት ልማትም ሆነ ለሌሎች ሕጋዊ ተግባራት
የቀጠለ
በአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 6 እንደተገለጸው የገጠር መሬት
ይዞታ በግል፣ በወል ወይም በመንግስት ሊያዝ የሚቸል
ቢሆንም ከህገ መንግስቱ ጀምሮ አዋጅ ቁጥር
456/1997ም ሆነ የክልላችን ገጠር መሬት ሕግ የገጠር
መሬት የማግኘት መብትን ቅድሚያ የሚሰጠው ለአርሶ
አደሩ ነው፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 7(1) እና 10(1) እንደተደነገገው የገጠር
መሬት ባለይዞታ ለመሆን ወይም መሬትን
ከሚያስተዳድረው አካል መሬትን በነጻ በድልድል
ለማገኘት ሶስት መሰረታዊ መስፈርቶች ያስፈልጋሉ፡፡
እነዚህም:-
1. የክልሉ ነዋሪ መሆን፤
2. በዋነኝነት በግብርና ሥራ መተዳደር ወይም በዚሁ
የቀጠለ
በዚህ አዋጅ የሁለተኛው መስፈርት መርህ ልዩ ሁኔታ ሆኖ
በአንቀጽ 7(2) ሥር የተደነገገው በምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ
በህዝብ ተወካዮችም ሆነ በክልል ምክር ቤት በቋሚነት
ያገለግሉ ዘንድ ለጊዜው አካባቢያቸውን የሚለቁ አርሶ አደሮች፣
አነስተኛ ወር ገቢ በሚያስገኝ እንደ ዘበኛነት፣ ፅዳት፣ ተላላኪና
ፖስተኛ አይነት ሥራ የተቀጠሩ ሠራተኞች እና በጡረታ
ሚተዳደሩ ሰዎች በቀጥታ በግብርና ሥራ እየተዳደሩ አይደለም
በሚል የገጠር መሬት ባለይዞታ ከመሆን የማይከለከሉ መሆኑ
ነው፡፡
 የሶስተኛው መስፈርት ልዩ ሁኔታም በአዋጁ አንቀጽ 10(2) ላይ
እንደተደነገገው 18 ዓመት ያልሞላቸው እና ወላጆቻቸውን
በሞት ያጡ ህጻናት በህጋዊ አሳዳጊዎቻቸው ወይም
ሞግዚቶቻቸው አማካይነት መሬት የማግኘት መብት አላቸው
የሚለው ነው፡፡
የቀጠለ
የገጠር መሬት ይዞታ የሚሰጥበት ስርዓት በተመለከተ
በክልሉ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም አርሶ አደር በጾታም
ሆነ በሌላ በማናቸውም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግት
መሬት በነጻ የማግኘት አኩል መብት ያለው መሆኑን
የአዋጁ አንቀጽ 5(2) ይደነግጋል፡፡
ሆኖም የዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 በገጠር መሬት
ድልድል ጊዜ ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት፣ ለአካል
ጉዳተኞች፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ለሴቶች እና ለአረጋውያን
ቅድሚያ እንዲሰጥ የሚያደርግ አሠራር ተቀርጾ በሥራ
ላይ እንደሚውል ይደነግጋል፡፡
የገጠር መሬት አሰጣጥ ሥርዓቱም በአዋጁ አንቀጽ 12
ላይ ተደንግጓል፡፡ ይኸውም፡-
የመሬት ጥያቄ የሚቀርብበትም ሆነ ምላሽ የሚሰጥበት
የቀጠለ
የመሬት አሰጣጥ ስርአቱ እንደጠያቂዎቹ የመሬት
ፍላጎት በህዝብ ተሳትፎ በሚወሰነው ቅደም ተከተል
መሰረት መሬት በይዞታ የማግኘት ላላቸው
አመልካቾች ሁሉ ያለአድልዎ እንዲተገበር ይደረጋል፡፡
ሊሰጥ የሚችለው የመሬት መጠን ችግሩ ላለባቸው
ጠያቂዎች ሁሉ እኩል ሊዳረስ የማይችል ሆኖ የተገኘ
እንደሆነ እንደ ቅደም ተከተላቸው ወላጆቻቸዉን
በሞት ላጡ ሕፃናት፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአቅመ
ደካሞች፣ ለሴቶች እና ለአረጋውያን እንደሚሰጥ
የገለጻል፡፡
የረቂቅ ደንቡ አንቀጽ 5(3) ደግሞ እነዚህ ቅድሚያ
ሊሰጣቸው የሚገቡ ሰዎች በሌሉበት ጊዜ ወይም
ቅድሚያ አግኝተዉ ትርፍ መሬት ካለ በህዝብ ተሳትፎ
የቀጠለ
ሀ. ጎጆ ለወጣ እና ልጅ ያለዉ፣
ለ ጎጆ የወጣ እና ልጅ ለሌለዉ፣
ሐ በትዳር ላይ ያለ ሰው የግል እና የጋራ ይዞታ ከሌለው
አንደኛዉ የትዳር አጋር የይዞታ መሬት የሌለዉ ተጋቢ
እና ጎጆ ላልወጡ ወጣቶች
መ. አነስተኛ የመሬት ይዞታ መጠን በታች መሬት
ያላቸዉ ባለይዞታዎች
ሠ. ከፍተኛ ይዞታ መጠን ጣራ ሳያልፍ ለሌሎች መሬት
ያላቸዉ እንደመሬት መጠናቸዉ እየታየ የይዞታ መሬት
እንደሚሰጣቸው ይደነግጋል፡፡
በመሰረቱ አርሶ አደሮች መሬትን ከሚያስተዳድረው
አካል በድልደል ከማግኘት ባሻገር የገጠር መሬትን
በውርስ ወይም በስጦታ የማግኘት መብትም አላቸው፡፡
የቀጠለ
ከአርሶ አደሮች በመቀጠል በክልሉ ውስጥ ሥራቸውን
የሚያካሂዱ ወይም ለማኅበረሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ
መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ
ድርጅቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት እና የብዙኃን ማኅበራት
ተግባራቸውን የሚያከናውኑት ለገንዘብ ትርፍ እስካልሆነ
ድረስ የአርሶ አደሮችን መሬት የማግኘት መብት
በማይፃረር ሁኔታ ለተልዕኳቸ መሳካት የሚጠቀሙበት
የገጠር መሬት ባለይዞታነት የማግኘት መብት ያላቸው
መሆኑን የአዋጁ አንቀጽ 10(6) ይደነግጋል፡፡
 እንዲሁም የግል ባለሀብቶች የሚጠቀሙበት መሬት
በሥራ ላይ ያለውን የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ በጠበቀ
ሁኔታ ከክልሉ ከመንግሥት በሊዝ ውል ወይም
ከማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ ጋር በሚደረግ
2.2 የገጠር መሬት ባለይዞታዎች መብቶች
የገጠር መሬትን በድልድል፣ በውርስም ሆነ በስጦታ
ያገኘ አርሶ አደር ከመሸጥና በሌላ ንብረት ከመለወጥ
ውጭ ለራሱ መጠቀም፣ በሌላ መሬት የመለወጥ፣
በህግ ለተሰቀደላቸው ሰዎች በውርስም ሆነ በስጦታ
የማስተላለፍ፣ የማከራየት እና በዋስትና አስይዞ
የመበደር መብት አለው፡፡ አዋጁ አንቀጽ 8(1)(2)
1. የመጠቀም መብት
የአዋጁ አንቀጽ 8(1) አርሶ አደሮች በዚህ አዋጅ መሠረት
በተሰጣቸው የገጠር መሬት ይዞታ ላይ ሙሉ
የባለይዞታነትና የመጠቀም መብት እንዳላቸው
ይደነግጋል፡፡
አርሶ አደሮች በይዞታቸው ሥር ያለውን መሬት መሬትን
የሚያስተዳድረው አካል በሚያዘጋጅላቸው ወቅታዊ
2. መሬትን በመሬት የመለዋወጥ መብት
ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ ማሳዉን በቀበሌዉ
ወይም በሌላ ቀበሌ ውስጥ ከሚገኝ ሌላ ባለይዞታ ጋር
መለዋወጥ እንደሚችል አንቀጽ 20(1) ይደነግጋል፡፡
 አነስተኛ ማሳዎች ለልማት አመቺ ይሆኑ ዘንድ የገጠር
መሬት ባለይዞታዎች በተናጠል ይዞታዎታቸውን
ኩታገጠም ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ሊያደርጉ
ይችላሉ፡፡ አንቀጽ 20(2)
 በባለይዞታዎች መካከል የሚደረግ ማናቸውም
የልውውጥ ወይም ኩታገጠም የማድረግ ውል በወረዳ
ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ
መመዝገብ አለበት፡፡ አንቀጽ 20(3)
የቀጠለ
መሬቱ የባልና ሚስት የጋራ ይዞታ ወይም ከአንድ በላይ
በሆኑ ባለይዞታዎች በጣምራ የተያዘ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ
ልውውጡ በሁሉም ባለዞታዎች ፈቃድ ላይ ተመስርቶ
መፈጸም ይኖርበታል፡፡ አንቀጽ 20(4)
የአዋጁ አንቀጽ 20(5) የተናጠል ይዞታዎቻቸውን ኩታ
ገጠም ለማድረግ አስበው የገጠር ልውውጥ ለሚያደርጉ
ባለይዞታዎች የሚሰጣቸው ማበረታቻ በደንብ
እንደሚወሰን ይናገራል፡፡
ረቂቅ ደንቡ አንቀጽ 13(3) ማበረታቻው የይዞታ
ማረጋገጫ ደብተር በነፃ ማደስ እና ከልኬታ ጋር የተያያዘ
አገልግሎት በነፃ ማግኘት መሆኑን ይደነግጋል፡፡
3. የይዞታ መሬትን በስጦታ የማስተላለፍ መብት
ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ የይዞታም ሆነ
የመጠቀም መብቱን በክልሉ ዉስጥ ለሚኖር እና
በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም በዚህ ሙያ
መተዳደር ለሚፈልግ ልጅ ወይም የልጅ ልጁ ወይም
ለማንኛውም ሌላ የቤተሰብ አባል ወይም በወቅቱ
እየጦረው ላለና አገልግሎኛል ወይም እያገለገለኝ ነው
ብሎ ላመነው ሰዉ በስጦታ ማስተላለፍ የሚችል
መሆኑን የአዋጁ አንቀጽ 16(1) ይደነግጋል፡፡
ሆኖም ላገለገለ ወይም እገለገለ ላለ ሰው የሚደረገው
ስጦታ ሊጸና የሚችለው ስጦታ ተቀባዩ ባለይዞታውን
በመጦር ላይ ያለ ወይም ሲንከባከብ የቆየ ስለመሆኑ
“ከቀበሌ ማኅበራዊ ፍ/ቤት” በጽሑፍ ማስረጃ አረጋግጦ
ሲቀርብ ብቻ ነው፡፡ አንቀጽ 16(2)
የቀጠለ
 ባለይዞታው ያደረገው ስጦታ አካለመጠን ያልደረሱ ልጆቹን
ወይም ሌሎች የቤተሰብ አባላትን መብት ሙሉ በሙሉ በሚጐዳ
ወይም ለነርሱ በቂ ድርሻ በማያስቀር ሁኔታ የተከናወነ ከሆነ በሕግ
ፊት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አንቀጽ 16(3)
 የስጦታ ውል ስምምነት በጽሑፍ ተደርጎ መሬቱ በሚገኝበት ወረዳ
ላለው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ
መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
 በቃል የተደረገ የስጦታ ዉል ስምምነት በሕግ ፊት ተቀባይነት
አይኖረውም፡፡
 ውሉም የጸና የሚሆነው ለወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ጽህፈት ቤት ቀርቦ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡
አንቀጽ 16(7-9)
 ባለይዞታውን ለመጦር መሬቱን በስጦታ የተቀበለ ማንኛውም
ሰው በገባው ውል መሰረት ሰጪውን አለመጦሩ የተረጋገጠ
እንደሆነ ሰጪዉ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በማቅረብ ውሉ
4. የይዞታ መብትን በውርስ የማስተላለፍ መብት
የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ማንኛውም ሰው
የይዞታም ሆነ የመጠቀም መብቶቹን በግብርና ሥራ
ለሚተዳደር ወይም በዚሁ ሙያ መተዳደር ለሚፈልግ
ማንኛውም ሌላ ሰው በኑዛዜ ሊያስተላለፍ እንደሚችል
አንቀጽ 17(1) ይደነግጋል፡፡
ሆኖም የባለይዞታው በኑዛዜ የማስተላለፉ ተግባር አካለ
መጠን ያላደረሰውን የተናዛዡን ልጅ ከህጋዊ ወራሽነት
መብቱ የሚነቅል ወይም የተናዣዡን የትዳር ጓደኛ ሕጋዊ
መብት የሚጎዳ ሆኖ የታየ እንደሆነ በሕግ ፊት የሚጸና
አይሆንም፡፡ አንቀጽ 17(3)
ስጦታ ላይ ለማን መሰጠት እናዳለበት ሕጉ በግልጽ
ሲደነግግ ኑዛዜ ላይ ግን በጣም ሰፊ በሆነ ሁኔታ
ለማንኛውም በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ሰው ሁሉ
የቀጠለ
በሌላ በኩል በስጦታ ጊዜ አካለመጠን ያልደረሱ ልጆቹን
ወይም ሌሎች የቤተሰብ አባላትን መብት ሙሉ በሙሉ
በሚጐዳ ከሆነ ተቀባይነት እንደማይኖረው ሲደነግግ
በኑዛዜ ጊዜ ግን ሕጉ ጥበቃ የሚያደርገው አካለመጠን
ላልደረሱ ልጆች ብቻ ነው፡፡
የኑዛዜው አደራረግ በፍ/ሕግ ውስጥ እንደተደነገገው
በግልጽ የሚካሄድ ኑዛዜ የሚሰጥባቸውን መስፈርቶች
ማሟላት እና በወረዳ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
ጽ/ቤት ቀርቦ መመዝገብ ያለበት መሆኑን አንቀጽ 17(4)
ይደነግጋል፡፡
በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ እየተናገረ ማንኛውም ሌላ
ሰው ወይም ተናዛዡ ራሱ የሚጽፈው ሲሆን ኑዛዜው
በተናዛዡና አራት ምስክሮች ፊት መነበብ፣ ቀን በግልጽ
የቀጠለ
 በእርግጥ በአንቀጽ 882 እንደተደነገገው ከምስክሮቹ
መካከል አንዱ ዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን
የተሰጠው አካል ሲሆንና ኑዛዜው የተደረገው ይህ ሰው
ሥራውን በሚያከናውንበት ቦታ ከሆነ የጸና ኑዛዜ
ለማድረግ ሁለት ምስክሮች ይበቃሉ።
ምስክሮቹም አካለመጠን የደረሱ፣ በፍርድ ወይም
በሕግ ያልተከለከሉ መሆን እና ኑዛዜው የተጻፈበትን
ቋንቋ የሚያውቁ እንዲሁም የተጻፈውን ለመስማት
ወይም ለማንበብ ራሳቸው ችሎታ ያላቸው መሆን
ይኖርባቸዋል። አንቀጽ 883
ባለይዞታው መሬቱን በኑዛዜ ሳያወርስ የሞተ ወይም
የሰጠው ኑዛዜ ፈራሽ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ መብቱ እንደ
ቅደም ተከታላቸው በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም
የቀጠለ
የሟች ልጆች/ከልጆቹ አንዱ ቀድመዉ ሞተዉ/ሞቶ
እንደሆነ እና ወደታች የሚቂጠሩ ተወላጆችን ትተዉ/ትቶ
እንደሆነ እነዚሁ ተወላጆቻቸዉ የሟቹ የቤተሰብ አባል
ሆነዉ ተገኝተዉ ካልወረሱ በስተቀር ቀድመዉ በሞቱት
ልጆች ምትክ ሆነዉ እንዲወርሱ ይደረጋል፡፡ አንቀጽ 17(6)
በመሰረቱ የውርስ ድንጋጌ አሁንም ያልተፈቱ ችግሮችን
ይዟል፡፡
ቅደም ተከተሉ ታስቦበት የተቀመጠ አይመስልም፡፡
የፍትሐዊነት ችግርንም የሚቀርፍ አይመስልም፡፡
ለደንቡም ስልጣን አይሰጥም፡፡
 ረቂቅ ደንቡ አንቀጽ 10 የይዞታ መሬቱን በኑዛዜ
ሳያወርስ የሞተ ሰዉ ወይም የተወዉ ኑዛዜ ፈራሽ ከሆነ
የይዞታ መብቱ በሚከተለዉ ቅደም ተከተል ለሟች
ወራሾች ይተላለፋል በማለት የሚከተለውን ይደነግጋል፡፡
የቀጠለ
ሀ. … ምንም አይነት ይዞታ መሬት የሌላቸዉ አካለ መጠን
ያልደረሱም ሆነ የደረሱ ልጆች፤
ለ. የራሳቸዉ የይዞታ መሬት ያላቸዉ አካለ መጠን ያልደረሱም ሆነ
የደረሱ ልጆች፤
ሐ. በፊደል ”ሀ” የተደነገገዉ ቢኖርም በ “ለ” ስር የተጠቀሱት ልጆች
አስቀድሞ ያላቸዉ መሬት አነስተኛ ሆኖ ሲገኝ በ “ሀ” ስር
የተጠቀሱት ወራሾች በ “ለ” ስር ያሉ ልጆች ያላቸዉን ዝቅተኛ
መሬት መጠን ያክል እንዲደርሳቸዉ ከተደረገ በኋላ ቀሪ የሟች
መሬት ካለ የመሬት መበጣጠስን እስካላስከተለ ድረስ “ሀ” እና “ለ”
መካከል እኩል ይከፋፈላሉ፡፡
መ. በፊደል ”ሐ” የተደነገገዉ ቢኖርም መሬት ባላቸዉ ልጆች
መካከል የመሬት መጠን መለያየት ካለ ከፍተኛ የመሬት መጠን
ያለዉን ልጅ መጠን ያክል እስከሚደርስ ድረስ የመሬት
መበጣጠስን በማያስከትል መልኩ እንዲመጣጠን ይደረጋል፡፡
ሠ. በፊደል ”ሀ” እና ”ለ” የተጠቀሱት ልጆች ከሌሉ አካለ መጠን
ያልደረሱም ሆነ የደረሱ የቤተሰብ አባላት በእኩል ደረጃ
ይወርሳሉ፤
ረ. በፊደል ”ሀ”፣ ”ለ” እና ”ሠ” የተጠቀሱት ወራሾች ከሌሉ የሟች
ወላጆች ይወርሳሉ፤
5. የይዞታ መሬትን የማከራየት መብት
ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ ራሱን ከይዞታው
እስከማፈናቀል በማያደርስ ሁኔታ በያዘው መሬት
የመጠቀም መብቱን ለሌላ ለማንኛውም ለግብርና
ሥራ ለሚያውል ሰው በኪራይ ውል ማስተላለፍ
እንደሚችል አንቀጽ 15(1)(2) ይደነግጋል፡፡
የገጠር መሬት ኪራይ ውል በጽሑፍ መሆን እና
የመሬቱን ስፋት፣ የኪራዩን ዘመን፣ የክፍያውን መጠን
እንዲሁም የአከፋፈሉን ሁኔታ በግልጽ የሚያሳይ
መሆን አለበት፡፡ አንቀጽ 15(3)(4)
የገጠር መሬት ኪራይ ውል ስምምነት እስከ ሁለት
ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ የተደረገ ከሆነ መሬቱ
ለሚገኝበት ቀበሌ አስተዳደር አጠቃቀም ጽ/ቤት እና
ከዚያ ለበለጠ ጊዜ የተደረገ ከሆነ ደግሞ ለወረዳ የገጠር
የቀጠለ
በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከፍተኛው የገጠር መሬት
ኪራይ ውል ዘመን ቋሚ የፍራፍሬ ተክሎችን ወይም
የተመረጡ የዛፍ ዝርያዎችን የተመለከተ እንደሆነ 30
ዓመት ሲሆን ዓመታዊ ሰብሎችን የተመለከተ ከሆነ
ደግሞ 10 ዓመት ይሆናል፡፡
ስለሆነም እንደተገቢነቱ ከ30 ዓመት እና ከ10 ዓመት
በላይ ለሆነ ጊዜ ተደርጎ የተገኘ የመሬት ኪራይ ውል
ስምምነት ቢኖር በዚህ አዋጅ መሰረት እንደቅደም
ተከተላቸዉ ለ30 ዓመት እና ለ10 ዓመት እንደተደረገ
ይቆጠራል፡፡ አንቀጽ 15(9)
የኪራይ ዉል ሕጋዊ የዉል ማቋቋሚያ ሁኔታዎችን
አሟልቶ ካልተገኘ ወይም ተከራዩ በተከራየዉ መሬት
ላይ ጉዳት ካደረሰ ወይም ከስምምነታቸው ዉጭ
የቀጠለ
የውል ማቋቋሚያ ሁኔታዎች ችሎታ፣ ጉድለት የሌለው
ፈቃድ፣ በቂ የሆነ እርግጠኛነት ያለው የሚቻልና ህጋዊ
የሆነ ጉዳይ እና የውል አጻጻፍ ፎርም ናቸው፡፡ የፍ/ሕ/ቁ
1678
በህጋዊ አሳዳሪ ወይም በሞግዚት ጥበቃ ስር
የሚተዳደሩ ሕፃናት፣ አረጋዊያን እና በፍርድ
የተከለከሉ ሰዎች ወይም የአእምሮ መታወክ ያለባቸው
ስለመሆኑ በፍርድ የተረጋገጠላቸው ባለይዞታዎች
የመሬት ይዞታቸውን ሲያከራዩ ውሉ የነርሱን ጥቅም
በማይጎዳ ሁኔታ ስለመደረጉ ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ
የቤተ ዘመድ ጉባኤ የመከረበትና ውል ለመዋዋል
ሥልጣን የተሰጠው አካል ያጸደቀው ሰነድ ከኪራይ
ውሉ ጋር ተያይዞ ለምዝገባ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
አንቀጽ 15(12)
6. መሬትን በዋስትና አስይዞ የመበደር መብት
ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ በዚህ አዋጅ
ከተፈቀደው ከ30 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ የመጠቀም
መብቱን በሀገሪቱ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ለተሰጠው
ሕጋዊ የገንዘብ ተቋም የብድር ዋስትና አድርጎ
ሊያስይዝ እንደሚችል አንቀጽ 19(1) ይደነግጋል፡፡
ተበዳሪው በብድር ውሉ ውስጥ በተጠቀሰው የጊዜ
ገደብ ዕዳውን ያልከፈለ እንደሆነ አበዳሪው በብድር
ውሉ ለተጠቀሰው ጊዜ በመሬቱ የመጠቀም መብት
የሚኖረው ሆኖ የተገኘ እንደሆነ የዚሁ መብቱ ወሰን
በመሬቱ ላይ ከተሰጠው የመጠቀም መብት ያለፈ
ሊሆን አይችልም፡፡ አንቀጽ 19(2)
አበዳሪው መሬቱን ራሱ የማያለማውና ከዚሁ የተነሳ
ለሶስተኛ ወገን በኪራይ የሚያስተላልፈው ከሆነ
መሬቱን ከአበዳሪው በውል ለመውሰድ እስከ ተስማማ
የቀጠለ
በገጠር መሬት የመጠቀም መብት መያዣ የተደረገበት
ማንኛውም ውል ባበዳሪዉ ተቋም መመዝገብ አለበት፣
ይኸው የተመዘገበው የኪራይ ውል አንድ ቅጅ መሬቱ
ለሚገኝበት ወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ ከባለይዞታው የግል ማህደር
ጋር መያያዝ ይኖርበታል፡፡ አንቀጽ 19(4)
አርሶ አደሮች መሬታቸውን በዋስትና አስይዘው
የመበደር መብት በአዲሱ አዋጅ የተካተተ አዲስ
መብት ነው፡፡
ይህ መብት በፌደራል የገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ አንቀጽ 16 ላይም የተደነገገ እና
ከ15 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ በዋስትና ማስያዝ
እንደሚቻል የተገለጠ ሲሆን ሀተታ ዘምክንቱ ላይ
የሰፈረው ሀሳብ የሚከተለውን ይመስላል፡፡
የቀጠለ
 አርሶ አደሮች በማስያዣ የሚሰጡት በመሬት የመጠቀም
መብታቸውን ነው፡፡ … ይህንን ማስያዣ ውል የሚገቡት ገንዘብ
ተበድረው በብድር ውሉ በመለከተው የጊዜ ገደብ መሰረት
መመለስ ባይችሉ ገንዘብ ጠያቂው የባለ ዕዳውን መሬት በውሉ
ለተመለከተው ጊዜ ብቻ በማረስ ወይም በማከራየት ተጠቅሞ
መሬቱን ለባለ ይዞታው ይመልሳል፡፡
 አበዳሪው መሬቱን ሊጠቀምበት የሚችለው ተበዳሪው በውሉ
መሰረት ገንዘቡን መመለስ ሳይችል ሲቀር ብቻ ነው፡፡
 ተበዳሪ በተጠቀሰዉ ጊዜ ብድሩን ያልከፈለ ከሆነ በዉሉ
ለተጠቀሰዉ ጊዜ ያህል ብቻ አበዳሪ በመሬቱ የመጠቀም መብት
ያለዉ ሲሆን የተበዳሪ ኃላፊነት በመሬቱ ላይ ከሰጠዉ
የመጠቀም መብት ያለፈ አይሆንም፡፡
 አበዳሪ መሬቱን በማልማት ያበደረዉን ያህል ገንዘብ በዉሉ
በተወሰነዉ ጊዜ ማግኘት ባይችል ሌላ የተበዳሪን ንብረት ወይም
ተጨማሪ ጊዜ በመሬቱ የመጠቀም መብት ለብደሩ ማስቻያ
ሊጠይቅ አይችልም፡፡
የቀጠለ
 በተመሳሳይ አበዳሪ መሬቱን በመጠቀም ከአበደረዉ ገንዘብ
የበለጠ ጥቅም ቢያገኝ ተበዳሪ ከዚህ የመጠየቅ መብት
የለዉም፡፡
 ይህ ድንጋጌ ከዚህ በፊት ከሚታወቀዉ የብድር ዋስትና የተለየ
ሲሆን ይህም የመሬትን ልዩ የንብረት ባህሪ ግምት ዉስጥ
በማስገባት አርሶ አደሮች እንዳይፈናቀሉና እንዳይጎዱ ለማድረግ
ታሳቢ ያደረገ ነዉ፡፡
 … ይህ አሰራር ገንዘብ የሌላቸው አርሶ አደሮች ለስራቸው
ግብዓት የሚሆን ገንዘብ በብድር መልክ እንዲያገኙ በማድረግ
የእርሻ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ስለሚረዳ ድሃ አርሶ አደሮች
በግብዓት እጥረት ምክንያት የእርሻ ስራቸውን ትተው
የሚያደርጉትን ፍልሰት ይቀንሳል፡፡
 አበዳሪዎችም ቢሆኑ የገንዘብ ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ ግለሰብ
አርሶ አደሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
 በመሆኑም አርሶ አደሮች ግብዓት ለመግዛት የገንዘብ እጥረት
በማጋጠሙ ምክንያት መሬታቸውን ያከራዩ የነበሩት ወይም
3. የገጠር መሬት ባለይዞታዎች ግዴታዎች እና
ግዴታዎችን አለመወጣት የሚያስከትለው ሀላፊነት
3.1 የገጠር መሬት ባለይዞታዎች
ግዴታዎች
በአዋጁ አንቀጽ 27 ሥር እንደተደነገገው ማንኛውም
የገጠር መሬት ባለይዞታ ወይም ተጠቃሚ የሚከተሉት
ግዴታዎች ይኖሩበታል፡፡
 በይዞታው ስር ያለውን መሬት የመንከባከብና
አካባቢውን የመጠበቅ፤
 በመሬቱ ዙሪያ አስቀድመው የበቀሉ ነባር እፅዋት
ቢኖሩ ዝርያቸው እንዳይጠፋ የመንከባከብ፤
 የአፈር ለምነትን የሚያሻሽሉና ለአካባቢ ደህንነት
ተስማሚ የሆኑ ዛፎችን የመትከልና ተንከባክቦ
የማሳደግ፤
የቀጠለ
 ተዳፋትነታቸው ከ60 በመቶ በላይ የሆኑ መሬቶችን
ከእርሻና ከልቅ ግጦሽ ይልቅ ለዛፍ፣ ለቋሚ ተክሎች እና
ለእንስሳት መኖ ልማት ብቻ የማዋል፤
 የዉሃ ምንጮች እንዳይደርቁ የጥንቃቄ እርምጃን
የመውሰድ፤
 የወል መሬት ይዞታዎችን ያለመዳፈር፣ በወሰን
የተከለሉ ሌሎች መሬቶችን ድንበር ያለመጋፋትና
የሕዝብ መንገዶችን ያለመዝጋት፤
 የሚመለከተው አካል የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ
አዘጋጅቶ ሲሰጠው በዕቅዱ መሰረት መጠቀም፤
 በመሬቱ አካባቢ የሚገኙ የዱር እንስሳትና አእዋፍ
እንዳይታወኩ ወይም እንዳይጎዱ ተገቢውን የጥንቃቄ
እርምጃ የመውሰድ፤
የቀጠለ
 የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በሚሰጥበት ጊዜ ተከታትሎ
የመውሰድ፣
 የይዞታ መብቱን በማናቸውም ምክንያት በሚያጣበት ጊዜ
የይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩን አግባብ ላለው አካል የመመለስ፤
 ክፉኛ የተጎዳ የገጠር መሬት ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ ነጻ
በማድረግ እንዲያገግም አድርጎ በወጣለት እቅድ መሰረት
የመጠቀም፤
 የመሬቱ ተጠቃሚ ባለሃብት ከሆነ ከዚህ በላይ ከሰፈሩት
ግዴታዎች በተጨማሪ ለተፈቀደለት ይዞታ ተገቢውን
የአጠቃቀም እቅድ በማዘጋጀት ለፈቀደለት የመሬት አስተዳደር
አካል አቅርቦ የማስጸደቅና በእቅዱ መሠረት መሬቱን ጥቅም
ላይ የማዋል፤ (በባለሀብቱ የሚያቀርበው የመሬት አጠቃቀም
ዕቅድ የኅብረተሰቡን ጤንነት፣ የአካባቢውን ደህንነትና የራሱን
የመሬቱን ለምነት አጠባበቅ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን
ይኖርበታል፡፡ )
3.2 ግዴታን አለመወጣት የሚያስከትለው
ኃላፊነት
 ከላይ የተዘረዘሩትን እና በሕግ የታወቁ ተመሳሳይ ግዴታዎችን
ያልተወጣ ባለይዞታ በቅድሚያ እንደ ሁኔታው የቃል ወይም
የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡ አንቀጽ 28(1)
 ባለይዞታው የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ተቀብሎ ስህተቱን
ሊያርም ያልቻለ ወይም ለማረም ፈቃደኛ ሆኖ ያልተገኘ
እንደሆነ በሚከተለው ቅደምተከተል አስተዳደራዊ እርምጃ
ሊወሰድበት ይችላል፡፡
 ሀ. የራሱ በሆነ ድክመት መሬቱን ካለመንከባከቡ የተነሳ
በመሬቱ ላይ ጉዳት ደርሶ ከተገኘ የመጠቀም መብቱን ለተወሰነ
ጊዜ መሬቱን የመንከባከብ ኃላፊነት ለሚወስድ ለሌላ ሰው
በኪራይ እንዲያስተላልፍ ሊወሰንበት ይችላል፡፡
 ለ. ከላይ የተመለከተው እርምጃ ተፈጻሚ ከሆነ በኋላ ጥፋቱን
በተመሳሳይ ሁኔታ የደገመ እንደሆነ በመሬቱ የመጠቀም
መብቱን ለተወሰነ ጊዜ ከማገድ ጀምሮ ላለማው ሀብት ብቻ ካሳ
ተከፍሎት መሬቱን ከናካቴው እንዲለቅ ሊወሰንበት ይችላል፡፡
የቀጠለ
በተመሳሳይ ሁኔታ የወል መሬት ተጠቃሚ የሆነ
ማንኛውም ሰው መሬቱን ለመንከባከብ ከሌሎች
ተጠቃሚዎች ጋር አልተባበርም ያለ እንደሆነ ሕግ
ባለማክበር ምክንያት እንደ ቅደም ተከተሉ የቃል
ወይም የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡
አንቀጽ 28(4)
ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው በኋላ ጥፋቱን በተመሳሳይ
ሁኔታ ከደገመ የወል መሬቱን ከናካቴው እንዳይጠቀም
ለተወሰነ ጊዜ ከማገድ ጀምሮ ለዘለቄታው እስከ
መከልከል የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወሰድበት
ይችላል፡፡ አንቀጽ 28(5)
በተጨማሪም ግዴታዎቹን ያላከበረ ማንኛውም
የገጠር መሬት ባለይዞታ ወይም ተጠቃሚ
እንደሁኔታው በወንጀል ሊጠየቅ ወይም ላደረሰው
4. የገጠር መሬት ይዞታ የሚታጣባቸው
ሁኔታዎች
በአዋጁ አንቀጽ 5(3) እንደተደነገገው በክልሉ ውስጥ
አርሶ አደሮች ያላቸው የገጠር መሬት ይዞታ መብት
የጊዜ ገደብ የለውም፡፡
ይህ ማለት ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ
መብቱ በዚህ ጊዜ ያበቃል ሳይባል በሕግ የተጠበቀ ነው
ማለት ነው፡፡
ሆኖም በልዩ ሁኔታ በሕግ በተደነገገ አግባብ
ባለይዞታው መሬቱን እንዲለቅ ሊደረግ ይችላል፡፡
የአዋጁ አንቀጽ 9፣ 21 እና 26
ስለሆነም የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ሰው
ይዞታውን በሚከተሉት ምክንያቶች እንዲያጣ ሊደረግ
ይችላል፡-
1. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 7 (2) ፊደል ተራ ቁጥር (ለ) ሥር
የቀጠለ
2. ይዞታውን ለሶስተኛ ወገን ማከራየቱን ወይም
የሚያስተዳድርለት ሰው መመደቡን ለወረዳ ገጠር
መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ሳያሳዉቅ
በተከታታይ ለ5 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ
ከመኖሪያ አካባቢው መጥፋት ወይም ወደ ውጪ
አገር ሂዶ መገኘት፤
3. ይዞታው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውል ሲወሰን፣
4. መሬቱን ያለበቂ ምክንያት እስከ 3 ዓመት ለዘለቀ ጊዜ
ጦም ማሳደር፤
5. ይዞታውን በተዘጋጀው የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ
መሠረት አለማልማት እና ይኸው ዕቅድ
ባልተዘጋጀላቸዉ አካባቢዎች ደግሞ መሬቱን
በእንክብካቤ ካለመያዙ የተነሳ ከባድ ጉዳት
የቀጠለ
የገጠር መሬት ይዞታውን በማናቸውም ምክንያት
እንዲያጣ የተደረገ ማንኛውም ሰው በመሬቱ ላይ
ላለማው ቋሚ ንብረት ተገቢውን ካሳ በቅድሚያ
የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ አንቀጽ 21(2)
አስቀድሞ የተሰማራበት ቋሚ መተዳደሪያ የግብርና
መስክ ሆኖ ሳለ በጥረቱ ተጨማሪ ሀብት መፍጠርና
ከዚሁ የተነሳም ወደ ኢንቨስትመንት ሥራ ለመሸጋገር
የበቃ ማንኛውም ታታሪ አርሶ አደር ለግብርና ሥራ
የተሰጠውን የገጠር መሬት ይዞታ በዚህ አዋጅ
መሠረት እንዲያጣ አይደረግም፡፡ አንቀጽ 22(3)
5. የገጠር መሬትን ስለመለካት፣ መረጃ አያያዝ
እና አጠቃቀሙን ስለመወሰን
5.1 የገጠር መሬትን መለካት እና መረጃ አያያዝ
በግል ይዞታነት፣ በወል ወይም በመንግስት የተያዘ፤
ለደን ልማት ወይም ለሌሎች መሰል ተግባራት
የተከለለ የትኛውም የገጠር መሬት በባህላዊ መንገድ
ወይም በዘመናዊ መሳሪያ ተለክቶ የባለይዞታዎችን
የይዞታ መጠንና አዋሳኝ ድንበሮች የሚያሳይ ካርታ
ተዘጋጅቶ ይህንኑ ከሚያረጋግጥ ደብተር ጋር
እንደሚሰጣቸው አዲሱ አዋጅ ይደነግጋል፡፡ አንቀጽ
33(1) - (3)
የትኛውም መሬት በሚለካበት ጊዜ በተቻለ መጠን
የመሬቱ አዋሳኝ ባለይዞታዎች ወይም ተወካዮቻቸው
በስፍራው ተገኝተው ድንበሮቻቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ
ይደረግላቸዋል፡፡ አንቀጽ 33(4)፤
የቀጠለ
በመሬቱ አለካክና በድንበሩ አከላለል ረገድ ቅሬታ
የተሰማው ማንኛውም ባለይዞታ ቅር የተሰኘበትን
ምክንያት በዝርዝር በመግለጽ ልኬታው በተጠናቀቀ
30 ቀናት ውስጥ ጉዳዩ እንደገና ይታይለት ዘንድ
በየደረጃው ለሚገኘው የገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም አካል የማቅረብ መብት አለው፡፡
በዚህ መልኩ አግባብ ባለው የገጠር መሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም አካል ኃላፊነት የተለካ
ማናቸውም የገጠር መሬት ይዞታ ለዚሁ ዓላማ
በተቋቋመው የመሬት መዝገብ ውስጥ ይመዘገባል፡፡
 ምዝገባውም የመሬቱን ባለይዞታ ሙሉ ስም፣
ይዞታው የተገኘበትን ሁኔታ፣ የመሬቱን አዋሳኞች፣
የለምነቱን ደረጃ፣ መሬቱ የሚውልበትን አገልግሎትና
የቀጠለ
የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃ ባሕረ-መዝገብ በሁለት
ቅጅ ተዘጋጅቶ አንደኛው ቅጂ በሚመለከተው ቀበሌ
ጽህፈት ቤትና ሁለተኛው ቅጅ ደግሞ ቀበሌው
በሚታቀፍበት ወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ጽ/ቤት ይቀመጣሉ፡፡ አንቀጽ 42(1)፤
በሁለቱ የባሕረ-መዝገብ ቅጂዎች መካከል ልዩነት
ተፈጥሮ የተገኘ እንደሆነ መረጃዉ እንደገና
እንዲጣራና እንዲስተካከል ይደረጋል፡፡
በሀሰተኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ የተካሄደ ማናቸውም
ምዝገባ ሕጋዊ ውጤት አይኖረውም፡፡
በመዝጋቢው ስህተት ምክንያት በማንኛውም ሰው
ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ ስህተቱን የፈጠረው
የመንግሥት አካል በፍትሐ ብሔር እና በወንጀል
የቀጠለ
በዚህ ሳቢያ ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግሥት አካል
በስህተቱ ለተጎዳው ወገን ካሳ እስከ መክፈል የደረሰ
እንደሆነ ይህንኑ እንዲመልስለት ስህተቱን
የፈጠረውንና ለባለዕዳነት የዳረገውን መዝጋቢ
ሠራተኛ በተራው የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡
ሆኖም መዝጋቢው ሠራተኛ በኃላፊነት የሚጠየቀው
ስህተቱን የሰራው ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት የሆነ
እንደሆነ ነው፡፡
አስመዝጋቢዉም ቢሆን በምዝገባዉ ለተፈጠረው
ስህተት የራሱ አስተዋፅኦ እንደነበረው የተረጋገጠ ከሆነ
በፍታብሔርና ተገቢ ሆኖ ሲገኝም በወንጀል ሕግጋት
ተጠያቂ ይሆናል፡፡
የገጠር መሬት ባለይዞታ ወይም የማሳ ወይም
የቀጠለ
የምዝገባ መረጃውን ወቅታዊ የማድረጉ ተግባር
በቀበሌ እና በወረዳ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
ኮሚቴዎች አማካኝነት ይከናወናል፡፡
ለሚመለከተው አካል በጊዜው ቀርቦ ወቅታዊ
ያልተደረገ ማናቸውም የገጠር መሬት የምዝገባ መረጃ
ለውጥ ወይም ማሻሻያ በሕግ ፊት ውጤት
አይኖረውም፡፡ አንቀጽ 43(1)፣(2) እና (6)
እንዲሁም ከመሬቱ ጋር ተያያዥነት ያለውን መብትና
ግዴታ የሚመለከት ማናቸውም ጉዳይ መሬቱ
በሚገኝበት ወረዳ ላለው የገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ ካልተመዘገበ በስተቀር
በሶስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብባቸው
አይችልም፡፡ አንቀጽ 34(3)
የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ማንኛውም ሰው
የቀጠለ
የወል መሬት ተጠቃሚዎች የሆኑ ባለይዞታዎች ይህንኑ
የሚያመለክት የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር
በስማቸው ተዘጋጅቶ ይሰጣቸዋል፡፡
የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆኑ ተቋማትም ይዞታ
ማረጋገጫ ደብተር በስማቸው ተዘጋጅቶ ይሰጣቸዋል፡፡
የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የባለይዞታው በሕግ
የተጠበቀ መብት ማስረጃ ነው፡፡
ይህንኑ የሚቃረን ጠንካራ የጽሑፍ ማስረጃ እና
ይበልጥ የሚያሳምን ምክንያት ካልቀረበ በስተቀር
የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በስሙ ተዘጋጅቶ
የተሰጠው ማንኛውም ሰው የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ
እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እያለ ዳኞች ሌሎችን
5.2 የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ስለማዘጋጀት
አዲሱ አዋጅ ያካተተው አንዱ አዲስ ነገር የመሬት
አጠቃቀም ዕቅድ እንዲዘጋጅ የሚያስገድድ
ድንጋጌዎችን መያዙ ነው፡፡ አንቀጽ 29(1-6)
ይኸውም የክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ቢሮ አገር አቀፉን የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ
መነሻ በማድረግ ወይም ከራሱ ነባራዊ ሁኔታዎች
በመነሳት በክልሉ ውስጥ የሚተገበር መሪ የመሬት
አጠቃቀም ዕቅድ ያዘጋጃል፡፡
የዞን ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
መምሪያዎች የክልሉን የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ
መሠረት በማድረግ በዞኑ ነባራዊ ሁኔታ የሚተገበር
የራሳቸውን መሪ የመሬት አጠቃቀም እቅድ ያዘጋጃሉ፡፡
የወረዳ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽህፈት
የቀጠለ
እንዲሁም አካባቢያዊ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ
ቀበሌን ወይም ተፋሰስን መሠረት ያደረገና ነዋሪውን
ሕብረተሰብ ያሳተፈ ሆኖ በወረዳ ገጠር መሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ጽህፈት ቤት የቴክኒክ ድጋፍ
ይዘጋጃል፡፡
የትኛውም የገጠር መሬት ለአንድ ለተወሰነ አገልግሎት
እንዲውል የመሬት አጠቃቀም እቅድ ሲዘጋጅ የተሻለ
የኢኮኖሚ ጠቀሜታ የሚሰጥ መሆኑ፣ በአካባቢ ላይ
የሚያስከትለው ተጽእኖ አለመኖሩ ወይም ተጽእኖው
አነስተኛ ሆኖ መገኘቱ እና አገልግሎቱ በተጠቃሚዎች
ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሆኑ እየተረጋገጠ መሆን
ይኖርበታል። አንቀጽ 29(7)
በጥናት ላይ ተመስርቶ ካልሆነ በስተቀር በማናቸውም
የቀጠለ
 በክልል፣ በዞንም ሆነ በወረዳ ደረጃ የሚዘጋጁ መሪ
የገጠር መሬት አጠቃቀም ዕቅዶች እንደተገቢነቱ አገር-
አቀፉን ዕቅድ ወይም የየአስተዳደር እርከኑን ዕቅዶች
ታሳቢ በማድረግ ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚሆን ጊዜ
ውስጥ ወቅታዊ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡ አንቀጽ30፤
 በአካባቢ ደረጃ የሚዘጋጅ አሳታፊ የገጠር መሬት
አጠቃቀም ዕቅድ እንደአስፈላጊነቱ የሚከለስበትና
ወቅታዊ የሚደረግበት ጊዜ ገደብ በደንብ ይወሰናል፡፡
አዋጁ የገጠር መሬት በዕቅድ እንዲመራ ለማድረግ
ትኩረት ከሰጠባቸው ሁኔታዎች አንዱ ለገጠር ቀበሌ
ማዕከላት መገንቢያ ቦታ አመራረጥ እና አሰጣጥ ጉዳይ
ነው፡፡
የቀጠለ
በገጠር ቀበሌ ማዕከላት ውስጥ የሚተገበረው
የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታ አሰጣጥ ስርዓትና
ግንባታው የሚያሟላቸው ስታንዳርዶች በደንብ
የሚወሰን ሆኖ ዕድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ
የሆነና በቀበሌው ውስጥ ቢያንስ ለተከታታይ ሁለት
ዓመት ነዋሪ ሆኖ በግብርና፣ በንግድ ወይም በሌሎች
በማናቸውም መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ
ድርጅቶች የሚሠራ ማንኛውም ሰው በገጠር ቀበሌ
ማዕከላት ውስጥ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ
ያገኛል፡፡ አንቀጽ 31(5)፤
ሆኖም ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሕፃናት፣ አካል
ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካሞች፣ ሴቶችና አረጋውያን እንደ
ቅደም ተከተላቸው በማዕከላቱ ውስጥ የመኖሪያ ቤት
የቀጠለ
በገጠር ቀበሌ ማዕከላት ውስጥ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች
ቢሮው ለገጠር ቤቶች አሠራር የሚያወጣውን የዲዛይንና
የግንባታ ጥራት መስፈርቶች አሟልተው ስለመገኘታቸው
በወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት
ካልተረጋገጠ በስተቀር ሊሸጡ፣ የዕዳ ዋስትና ሆነው
ሊያዙም ሆነ በማናቸውም መንገድ ለሶስተኛ ወገን
ሊተላለፉ አይችሉም፡፡ አንቀጽ 31(5)
የገጠር ቀበሌ ማዕከላት ተብለው ከተመረጡት ስፍራዎች
ውጭ በእርሻ፣ በግጦሽ፣ በወል እና በደን መሬቶች ላይ
ማናቸውንም አይነት አዲስ ግንባታ ማካሄድ የተከለከለ
ነው:: አንቀጽ 32(1)
ሆኖም የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ተዘጋጅቶ ባልተሰጠበት
አካባቢ አርሶ አደሩ በመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩ ላይ
ባስመዘገበው ይዞታ ውስጥ ለራሱና ለአካለ መጠን ለደረሱ
6. ከገጠር መሬት ጋር የተያያዙ አለመግባባቶች
የሚፈታባቸው መንገዶች
የገጠር መሬት ይዞታ መብት ዋስትናው የተረጋገጠ
ሊሆን የሚችልባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡
ከእነዚህም መካከል አንዱ አርሶ አደሮች ያላቸው
የመሬት ይዞታ መብት በጊዜ የተገደበ አለመሆኑን
በግልጽ በሕግ መደንገጉ ነው፡፡
ሁለተኛው ምክንያትም በየጊዜው የመሬት ሽግሽግ
እንዳይካሄድ በሕግ መከልከሉ ነው፡፡
ሶስተኛው ምክንያት ደግሞ የገጠር መሬት ባለይዞታ
መሆንን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ለባለይዞታው
መስጠት ነው፡፡
የገጠር መሬት ባለይዞታዎች መብት ጥበቃ በሕግ በበቂ
ሁኔታ መደንገጉ ብቻ በቂ አይደለም። ይልቁንስ
መብቶቹ በሚጣሱበት ጊዜ አጥፊዎችን ለማረምና
6.1 የአስተዳደራዊ ክንዋኔዎች አለመግባባት አፈታት
 በአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 33 - 43 ላይ የገጠር መሬትን
ከመለካት፣ ከመመዝገብ እና መረጃን ከመያዝ እና የይዞታ
ማረጋገጫ ደብተር ለባለይዞታዎች ከመስጠት ጋር የተያያዙ
የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አካላት ግዴታዎች እና
ሀላፊነቶች ተዘርዝረዋል፡፡
 የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አካላት እነዚህን
ሀላፊነቶች ለመወጣት በራሳቸው የሚሰጧቸው አስተዳደራዊ
ውሳኔዎች ይኖራሉ፡፡
 አስተዳደራዊ ዉሳኔ ማለት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ
ባለጉዳዮች፣ በይዞታ መብትና መጠቀም ጥያቄ ሲያቀርቡ
ወይም በተቃራኒው ግዴታወቻቸውን ሳይወጡ ሲቀሩ
አግባብነት ያላቸዉን የመረጃ ምንጮች በመጠቀምና አስፈላጊ
ሆኖ ሲገኝም በሕዝብ በማስተቸት ጉዳዩ በሚመለከተው
የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አካል ከተጣራ በኃላ በጽሁፍ
የሚሰጥ ማናቸውም ውሳኔ ሲሆን ከገጠር መሬት ልኬታ፣
ምዝገባ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አሰጣጥ፣ ከመሬት
የቀጠለ
አስተዳደራዊ ውሳኔዎች የሚሰጡት ብዙ ጊዜ የገጠር
መሬት ተጠቃሚዎች በሕግ የተጣለባቸውን ግዴታዎች
ሳይወጡ ሲቀሩ ነው፡፡ በአዋጅ ቁጥር 456/1997 አንቀጽ
10 እና 13 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ
27 ላይ የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ሰው ግዴታዎች
ተዘርዝረዋል፡፡
እነዚህም በይዞታም ሆነ በኪራይ የያዘውን መሬት
የመንከባከብ፣ ከመሬቱ አካባቢ ዛፍ መትከልና
ተንከባክቦ ማሳደግ፣ በአስተራረስ ወቅት ጥንቃቄ
ማድረግ፤ በመሬቱ አካባቢ የሚገኙ የዱር እንስሳትና
አዕዋፎች እንዳይጎዱ ተገቢውን ጥንቃቄ የማድረግ፤
ወሰናቸው የተከለለ መሬቶችን ድንበር ያለመጋፋትና
ተለይተው የሚታወቁ መንገዶችን ያለመዝጋት፤
ለመሬቱ በወጣለት የአጠቃቀም ዕቅድ መሰረት
የቀጠለ
እነዚህን ግዴታዎች ያልተወጣ ማንኛውም የገጠር
መሬት ባለይዞታ ወይም ተጠቃሚ የሆነ ሰው የፍትሐ
ብሔር እና የወንጀል ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ
አስተዳደራዊ እርምጃም ሊወሰድበት እንደሚችሉ
አዲሱ አዋጅ አንቀጽ 28 ይደነግጋል፡፡
ለመሆኑ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች የት ተጀምረው የት
ይጠናቀቃሉ? የሚለውን ቀጥለን እንመለከታለን፡፡
በመሬት አለካክና በድንበር አከላለል ረገድ ቅሬታ
የተሰማው ማንኛውም ባለይዞታ ቅር የተሰኘበትን
ምክንያት በዝርዝር በመግለጽ ልኬታው በተጠናቀቀ
30 ቀናት ውስጥ ጉዳዩ እንደገና ይታይለት ዘንድ
በየደረጃው ለሚገኘው የገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም አካል የማቅረብ መብት እንዳለው የአዋጁ
የቀጠለ
የገጠር መሬት ይዞታን በመመዝገብ እና በማረጋገጡ
ሂደት በባለይዞታዎች መካከል ክርክር የተነሳ እንደሆነ
ባለጉዳዮቹ አግባብ ባለው የመሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ኮሚቴ አቀራራቢነት እንዲስማሙ
ይደረጋል፡፡
በዚህ ያልተስማሙ እንደሆነ ኮሚቴው ከቀበሌው
የመሬት ዘርፍ ባለሙያ በሚገኘው መረጃና አስተያየት
ላይ ተንተርሶ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንደሚሰጥ አንቀጽ
38(1) ይደነግጋል፡፡
በዚህ የቀበሌው ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ወገን
አቤቱታውን በየደረጃው ለሚገኘው የገጠር መሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡
አንቀጽ 38(2)
የቀጠለ
የትኛውም የገጠር መሬት ይዞታ በምዝገባ ሂደት
ተረጋግጦ የተያዘ መረጃ የመጨረሻ ሆኖ ለዚሁ
በተቋቋመው መዝገብ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ቅሬታ
ያለው ወገን ቢኖር አቤቱታ የሚያቀርብበት ስነ ስርዓት
እና የጊዜ ገደብ በደንብ እንደሚወሰን የአዋጁ አንቀጽ
40(1) ይደነግጋል፡፡
ረቂቅ ደንቡ አንቀጽ 24 የገጠር መሬት በምዝገባ ሂደት
ተረጋግጦ የተያዘ መረጃ የመጨረሻ ሆኖ በገጠር መሬት
መዝገብ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ቅሬታ ያለዉ
ባለይዞታ በተመዘገበ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ
ቅሬታዉን መረጃዉን ለመዘገበዉ አካል በጽሁፍ
ማቅረብ ይችላል፡፡ ቅሬታ የቀረበለት አካል ቅሬታዉ
በቀረበ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ በጽሁፍ ምላሽ
የቀጠለ
ቅሬታ የቀረበለት አካል ምላሽ ካልሰጠዉ ወይም
የሰጠዉ ምላሽ ካላረካዉ ቅሬታ አቅራቢዉ ቀጥሎ
ላለዉ የተቋሙ እርከን በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ
ቅሬታዉን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላል፡፡ ቅሬታ
የቀረበለት የበላይ አካልም ቅሬታዉ በቀረበለት በሁለት
ወር ጊዜ ዉስጥ በጽሁፍ ምላሽ መስጠት አለበት፡፡ ይህ
አካል ምላሽ ካልሰጠዉ ወይም በሰጠዉ ምላሽ
ያልተስማማ ቅሬታ አቅራቢ ለመደበኛ ፍርድ ቤት
በሁለት ወር ጊዜ ዉስጥ አቤቱታዉን ማቅረብ ይችላል
በማለት ይደነግጋል፡፡
በሌላ በኩል የባለይዞታው ወይም የማሳ ወይም
የሁለቱም ለውጥ በሚያጋጥምበት ጊዜ የመሬት
ምዝገባ ሰነዱ በቀበሌ እና በወረዳ የመሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴዎች አማካኝነት
የቀጠለ
 ኮሚቴው በሰጠው አስተዳደራዊ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን
አቤቱታውን በጽሑፍ አዘጋጅቶ ለወረዳ ገጠር መሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 በጽ/ቤቱ ውሳኔ ያልተስማማ እንደሆነ ደግሞ ለዞኑ መሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም መምሪያ ወይም ለወረዳ ፍርድ ቤት
ማቅረብ ይችላል፡፡ አንቀጽ 43(3)
 በአጠቃላይ የአዋጁ አንቀጽ 52(6) እንደሚደነግገው የገጠር
መሬትን ከመለካት፣ ከማስተዳደርና ከሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች
ጋር በተየያዘ የወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
ጽ/ቤቶች በሚሰጡት አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ
ማንኛውም ወገን ይኸው በደረሰው በ30 ቀናት ውስጥ ክሱን
ለወረዳዉ ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 የወረዳዉ ፍ/ቤት የጽ/ቤቱን ውሳኔ ያጸናው እንደሆነ ይግባኙን
ለከፍተኛ ፍ/ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 ይግባኙ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤትም የሥር ፍ/ቤቱን ውሳኔ
ያጸናው እንደሆነ ውሳኔው የመጨረሻ ይሆናል፡፡
የቀጠለ
 ከዚህ መረዳት የሚቻለው አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ከቀበሌ
መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ጀመረው በይግባኝ
ለወረዳ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ከቀረቡ በኋላ
ቀጥሎ በቅሬታ አቅራቢው ምርጫ ለዞን መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም መምሪያ ይግባኝ ወይም ለወረዳ ፍ/ቤት ክስ
ሊቀርብ እንደሚችል ነው፡፡
 ይኸውም በየትኛውም ሁኔታ በየደረጃው ባሉት በመሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋማት አስተዳደራዊ ውሳኔ ያልረካ
ሰው ለወረዳ ፍ/ቤት ክስ ማቅረብ የሚቻል መሆኑን ያሳያል፡፡
 ይህም ከቀድሞው ሕግ በሁለት መልኩ የተለየ መሆኑን
እንገነዘባለን፡፡ የመጀመሪያው የቀድሞው ሕግ በወረዳ መሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት አስተዳደራዊ ውሳኔ
ያልተስማማ ሰው ለዞን መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
መምሪያ ይግባኝ የማቅረብ መብት አይሰጥም ነበር፡፡
 ሁለተኛው ልዩነት የቀድሞው ሕግ በወረዳ መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ጽ/ቤት አስተዳደራዊ ውሳኔ ያልተስማማ ሰው
የነበረው መብት ለወረዳ ፍ/ቤት ይግባኘ ማቅረብ ሲሆን
በአዲሱ ሕግ ግን አዲስ ክስ የማቅረብ መብት አለው፡፡
6.2 በመደበኛ ፍርድ ቤቶች የሚደረጉ ክርክሮች
 የገጠር መሬት ይዞታ ዋስትና ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች
አንዱ ፍትህ የማግኘት መብት ነው፡፡
 ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ
ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን
ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ የማግኘት መብት
ያለው መሆኑን የኢፌዲሪ ሕገ መንግስ አንቀጽ 37(1)
ይደነግጋል።
 በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 4 መሰረት በቀጥታ ወይም በግልጽ
ካልታገዱ ወይም ለሌላ አካል በሕግ ካልተሰጠ በቀር
በፍርድ ሊያልቁ የሚችሉ የፍትሐ ብሔር ክርክሮችን
አከራክሮ የመወሰን ስልጣን የመደበኛ ፍርድ ቤቶች ነው፡፡
 የገጠር መሬት ክርክር በፍርድ ሊያልቅ የሚችል
(Justiciable Matter) ስለሆነ በሕገ መንግስቱ
በተደነገገው አግባብ በመደበኛ ፍርድ ቤት ወይም በሕግ
የቀጠለ
በአለም ላይ በብዙ ሀገሮች ከመሬት ጋር የተያያዙ ክርክሮች
የሚፈቱት በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ቢሆንም አንዳንድ
ሀገሮች ልዩ የመሬት ክርክሮችን የሚያዩ ችሎቶች ወይም
ፍርድ ቤቶች (land courts) ያቋቁማሉ፡፡
 በሀገራችን በንጉሱ ዘመን አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴ
እንደተጠበቀ ሆኖ የመሬት ክርክር የሚታየው በመደበኛ
ፍርድ ቤቶች ነበር፡፡
አዋጅ ቁጥር 31/1967 ዓ/ም፣ አንቀጽ 28(1) ላይ አዋጁ
ከጸናበት ቀን ጀምሮ በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚገኙ የገጠር
መሬት ክርክሮች በሙሉ የተሰረዙ መሆኑን ስለሚደነግግ
ነው፡፡
በደርግ ዘመን የመሬት ክርክር በመደበኛ ፍርድ ቤት መሆኑ
ቀርቶ በገበሬዎች ማህበር ፍርድ ሸንጎ እንዲታይ ተደርጓል፡፡
አዋጅ ቁጥር 31/1967 ዓ/ም ፣ አንቀጽ 28 (2) (3) እና የገበሬ
ማህበራትን ለማጠናከር የወጣ አዋጅ ቁጥር 223/1974
የቀጠለ
 የገበሬ ማህበራትን ለማጠናከር በወጣው አዋጅ መሰረት የገጠር
መሬት ክርክር በቀበሌ፣ በወረዳና በአውራጃ ደረጃ በተቋቋሙ
ፍርድ ሸንጎዎች ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ይግባኝ የሚታይ
ነበር፡፡ አዋጅ ቁጥር 223/1974፣ አንቀጽ 36 - 40 እና ከአንቀጽ 53 -
60
 ስለሆነም በደርግ ዘመን በማንኛውም ሁኔታ የገጠር መሬት
ክርክር ለመደበኛ ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ ተደርጎ የነበረ
መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
 በአሁኑ ወቅት የገጠር መሬትን በተመለከተ ክርክር ሲነሳ
በቅድሚያ በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች እንዲፈታ
ጥረት ይደረጋል፡፡
 ይኸውም በቅድሚያ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ተከራካሪዎች
በውይይትና ስምምነት እንዲፈታ ጥረት ይደረጋል፡፡
 በስምምነት ሊፈታ ካልቻለ በተከራካሪ ወገኖች በተመረጡ
ሸማግሌዎች ወይም በክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና
የቀጠለ
የክልላችን አዲሱ አዋጅ አንቀጽ 52 የገጠር መሬት ይዞታና
የመጠቀም መብትን በሚመለከት የሚፈጠሩ
አለመግባባቶችና የሚነሱ ክርክሮች የሚፈቱበትን ስነ
ሥርዓት የደነግጋል፡፡
ይኸውም በመጀመሪያ ደረጃ በራሳቸው በባለጉዳዮቹ
መካከል በሚካሄድ ውይይት እና በሚደረግ ስምምነት
እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡
ተከራካሪ ወገኖች አለመግባባታቸውን በስምምነት ሊፈቱ
ካልቻሉ ራሳቸው በሚመርጧቸው ሽማግሌዎች
አስታራቂነት ጉዳያቸው እልባት እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
አለመግባባቱ በዕርቅ ያልተፈታ እንደሆነ ይኸው
ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ጉዳዩ
ለአቅራቢያው ወረዳ ፍ/ቤት ሊቀርብ ይችላል፡፡
የወረዳዉ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ተመልክቶ ውሳኔ
የሰጠበት ማናቸውም ጉዳይ በ30 ቀናት ውስጥ ለከፍተኛ
ፍርድ ቤት ይግባኝ ሊቀርብበት ይችላል፡፡
የቀጠለ
ይግባኝ የቀረበለት የከፍተኛ ፍ/ቤት የወረዳውን ፍ/ቤት
ውሳኔ ካጸናው ውሳኔው የመጨረሻ ይሆናል፡፡
ይግባኙ የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤቱን
ውሳኔ የሻረው ወይም ያሸሻለዉ እንደሆነ ግን ለክልሉ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ይግባኝ ሊቀርብበት
ይችላል፡፡
ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡
በመጨረሻ ደረጃ በተሰጡ የከፍተኛም ሆነ የጠቅላይ ፍርድ
ቤቶች ውሳኔዎች ላይ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት
የሚል ወገን አቤቱታዉን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 በገጠር መሬት ይዞታና የመጠቀም መብቶች ረገድ የሚነሱ
ክርክሮች ከመደበኛ ፍርድ ቤት እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች
ደግሞ አግባብ ካለቸው የገጠር መሬት አስተዳደርና
7. ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮች
7.1 የፍትሐ ብሔር ሕግ አግባብነት
የአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 54 በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15፣ 16 እና 17
ያልተሸፈኑ የገጠር መሬት ኪራይ፣ ስጦታ፣ ውርስና ሌሎች
ፍትሐ ብሔር ነክ ጉዳዮችን በተመለከተ እንደነገሩ ሁኔታ
አግባብነት ያላቸዉ 1952 ዓ.ም የፍትሐ ብሔር ሕግ
ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል በማለት ይደነግጋል፡፡
ይህ አገላለጽ ምን ማለት ነው? ለምሳሌ በመሬት አዋጁ
መሰረት ሊወርስ ወይም ስጦታ ሊቀበል የማይችል ሰው
የፍትሐ ብሔር ሕጉን መሰረት ተደረጎ ሊወርስ ወይም
ስጦታ ተቀባይ ሊሆን ይችላል ማለት ነው? አይደለም፡፡
 ይልቁንም የዚህ ድንጋጌ ይዘት በፍትሐ ብሔር ሕጉ
የሚታወቁ አንዳንድ ጽንሰ ሀሳቦች ለምሳሌ ከወራሽነት
መንቀል፣ ለውርስ ያልተገባ መሆን የሚሉና ተመሳሳይ
ሀሳቦች ቢያጋጥሙ በቀጥታ እነዚህን ሀሳቦች የሚመለከቱ
የቀጠለ
ይህን ሀሳብ የበለጠ ለማጉላት በፌደራል የገጠር
መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ
ላይ የተወሰደውን ሀሳብ ማየት ይጠቅማል፡፡
… በተጨማሪም ሌሎች በፍትሐ ብሔር ሕጉ
የተቀመጡ ጉዳዮችን እንደ አግባብነታቸው
ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡ ለምሳሌ መጥፋትን
ብንወስድ በፍትሐ ብሔር ሕጉ ተደንግጎ ያደረ ጉዳይ
ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው የመጥፋት ውሳኔ
ከተላለፈበት በፍትሐ ብሔር ሕጉ በሚያስቀምጠው
ገደብ መሰረት በጠፋው ሰው ይዞታ ስር የነበረውን
መሬት ወራሾች ጠይቀው ሊከፋፈሉት ይችላሉ፡፡
እነዚህን ዝርዝር ጉዳዮች በዚህ አዋጅ ከማየት ይልቅ
የፍትሐ ብሔር ሕጉድንጋጌዎች እንደ አግባብነታቸው
ተፈጻሚ እንደሚሆኑ አስቀምጦ ማለፉ የተሻለ ሆኖ
7.2 ስለ ይርጋ
የአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 55 የገጠር መሬትን በወረራ
ወይም በሌላ በማናቸውም ህገ ወጥ መንገድ ይዞ
በመገልገል ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው መሬቱን
እንዲለቅ በማንኛውም ሌላ ሰው ወይም ሥልጣን
ባለው የመንግሥት አስተዳደር አካል ሲጠየቅ ወይም
በመደበኛ ፍርድ ቤት ሲከሰስ የይርጋ ጊዜ ገደብን በሥነ
ስርዓት መቃወሚያነት ሊያነሳ አይችልም፡፡
ይህ አገላለጽ ሁሉንም አይነት የገጠር መሬት ክርክሮች
ይርጋ የላቸውም የሚያስብል ሆኖ መወሰድ
አይኖርበትም፡፡
ለምሳል ጉዳዩ የመሬት ውርስ ክርክር ቢሆን ይርጋ
የለውም ብሎ ለመተርጎም ይህ ድንጋጌ
አያካትተውም፡፡
የቀጠለ
 በፌደራል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ
አዋጅ ማብራሪያ ላይ የተወሰደ ሀሳብም ይህን ሀሳብ
ያጠናክራል፡፡
 የይርጋ ድንጋጌዎች ለምሳሌ ጉዳዩ ከውል ጋር የተያያዘ
ከሆነ የፍትሐ ብሔር ሕጉ አንቀጽ 1845 አግባብነት
ይኖረዋል፡፡ ሌሎች ከወል መሬት ወረራ ጋር የተያያዙ
ጉዳዮች ከመጀመሪያም ህገ ወጥ እና ወንጀል
በመሆናቸው መሬቱን ለማስመለስ የሚደረግ ክርክር
በይርጋ የሚታገድ አይሆንም፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ
እንደ ሁኔታው የፍትሐ ብሔር ሕጉ የይርጋ ድንጋጌ ሕጉ
ይቀበላቸዋል፡፡
7.3 የፍ/ቤት ውሳኔ በገጠር መሬት ይዞታ ላይ
ስለሚኖረው ውጤት
የአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 56 ማንኛውም የገጠር መሬት
ባለ ይዞታ የፍርድ ቤት ውሳኔን ለማስፈጸም በሚሰጥ
ትዕዛዝ ከይዞታው አይፈናቀልም ወይም ይዞታው ለዕዳ
መክፈያ በሚል ለሌላ አካል ሊተላለፍ አይችልም
በማለት ይደነግጋል፡፡
ይህ ድንጋጌ የገጠር መሬት አይሸጥም በሌላ ንብረት
አይለወጥም ከሚለው ህገ መንግስታዊ ክልከላ ጋር
ተያይዞ ነው መተርጎም ያለበት፡፡
 ይህ ማለት በፍትሐ ብሔር ለተፈጠረ ግንኙነት የገጠር
መሬት ለዕዳ መክፈያ ተብሎ አይያዝም ለማለት ነው፡፡
ይህ አተረጓጎምም ቢሆን በጠባቡ መታየት
ይኖርበታል፡፡
ለምሳሌ ከመሬቱ የሚገኘውን ምርት ወይም መሬቱን
7.4 የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች
የአዋጁ አንቀጽ 57 ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት ከገጠር
መሬት ይዞታና አጠቃቀም ጋር በተያያዙ በሌሎች ሕጐች
የተቋቋሙ መብቶችና ግዴታዎች ቀደም ሲል የነበሩ
ሕጐችን መሠረት አድርገው እስከተገኙና ይህንን አዋጅ
በግልጽ እስካልተቃረኑ ድረስ ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል፡፡
ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት ፍርድ ቤት ቀርበው
በመታየት ላይ ያሉ ማናቸውም መሬት-ነክ ጉዳዮች
በተጀመሩበት አግባብ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኙ
ይደረጋል፡፡
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ ይህንን አዋጅ በግልጽ
እስካልተቃረኑ ድረስ ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል የሚለው
አገላለጽ ምን ማለት ነው? ለምሳሌ በቀድሞው አዋጅ
መሰረት የቤተሰብ አባል በመሆን መሬት ካለው የሟች
ልጅ ቀድሞ የወረሰ ሰው ቢኖር አሁን ካለው አወራረስ
አመሰግናለሁ

More Related Content

More from getabelete

Conditions of Criminal Liability Lecture Note
Conditions of Criminal Liability Lecture NoteConditions of Criminal Liability Lecture Note
Conditions of Criminal Liability Lecture Notegetabelete
 
Business and Business Income Lecture Notes
Business and Business Income Lecture NotesBusiness and Business Income Lecture Notes
Business and Business Income Lecture Notesgetabelete
 
constitutional Law Lecture Notes in ppt:
constitutional Law Lecture Notes in ppt:constitutional Law Lecture Notes in ppt:
constitutional Law Lecture Notes in ppt:getabelete
 
Federalism and models of Intergovernmental relation
Federalism and models of Intergovernmental relationFederalism and models of Intergovernmental relation
Federalism and models of Intergovernmental relationgetabelete
 
Mining and Petroleum Tax Lecture Notes in ppt
Mining and Petroleum Tax Lecture Notes in pptMining and Petroleum Tax Lecture Notes in ppt
Mining and Petroleum Tax Lecture Notes in pptgetabelete
 
Ethiopian Tax Administration Lecture notes in ppt
Ethiopian Tax Administration Lecture notes in pptEthiopian Tax Administration Lecture notes in ppt
Ethiopian Tax Administration Lecture notes in pptgetabelete
 
Ethiopian Law of Evidence Lecture Notes ppt
Ethiopian Law of Evidence Lecture Notes pptEthiopian Law of Evidence Lecture Notes ppt
Ethiopian Law of Evidence Lecture Notes pptgetabelete
 
Law of criminal procedure Lecture Notes ppt
Law of criminal procedure Lecture Notes pptLaw of criminal procedure Lecture Notes ppt
Law of criminal procedure Lecture Notes pptgetabelete
 
The law Constitutional Law Lecture Notes
The law Constitutional Law Lecture NotesThe law Constitutional Law Lecture Notes
The law Constitutional Law Lecture Notesgetabelete
 
Employment income tax Lecture Notes: ppt
Employment income tax Lecture Notes: pptEmployment income tax Lecture Notes: ppt
Employment income tax Lecture Notes: pptgetabelete
 
Lecture Notes on Agricultural Taxes.pptx
Lecture Notes on Agricultural Taxes.pptxLecture Notes on Agricultural Taxes.pptx
Lecture Notes on Agricultural Taxes.pptxgetabelete
 
International Taxation Lecture Notes in ppt
International Taxation Lecture Notes in pptInternational Taxation Lecture Notes in ppt
International Taxation Lecture Notes in pptgetabelete
 
Law of property taxation lecture notes in ppt
Law of property taxation lecture notes in pptLaw of property taxation lecture notes in ppt
Law of property taxation lecture notes in pptgetabelete
 
Law of VAT and TOT Lecture Notes in ppts
Law of VAT and TOT Lecture Notes in pptsLaw of VAT and TOT Lecture Notes in ppts
Law of VAT and TOT Lecture Notes in pptsgetabelete
 
Income Tax Jurisdiction lecture notes ppt
Income Tax Jurisdiction lecture notes pptIncome Tax Jurisdiction lecture notes ppt
Income Tax Jurisdiction lecture notes pptgetabelete
 
Introduction to Public Finance and Taxation.pptx
Introduction to Public Finance  and Taxation.pptxIntroduction to Public Finance  and Taxation.pptx
Introduction to Public Finance and Taxation.pptxgetabelete
 
law of public enterprise lecture note- part one
law of public enterprise lecture note- part onelaw of public enterprise lecture note- part one
law of public enterprise lecture note- part onegetabelete
 
Law of public enterprise ( lecture two) ppt
Law of public enterprise ( lecture two) pptLaw of public enterprise ( lecture two) ppt
Law of public enterprise ( lecture two) pptgetabelete
 
International business transaction power point
International business transaction power pointInternational business transaction power point
International business transaction power pointgetabelete
 
DBE_Policy_Environment_&_Lease_Financing_May_2014_E_C_final.ppt
DBE_Policy_Environment_&_Lease_Financing_May_2014_E_C_final.pptDBE_Policy_Environment_&_Lease_Financing_May_2014_E_C_final.ppt
DBE_Policy_Environment_&_Lease_Financing_May_2014_E_C_final.pptgetabelete
 

More from getabelete (20)

Conditions of Criminal Liability Lecture Note
Conditions of Criminal Liability Lecture NoteConditions of Criminal Liability Lecture Note
Conditions of Criminal Liability Lecture Note
 
Business and Business Income Lecture Notes
Business and Business Income Lecture NotesBusiness and Business Income Lecture Notes
Business and Business Income Lecture Notes
 
constitutional Law Lecture Notes in ppt:
constitutional Law Lecture Notes in ppt:constitutional Law Lecture Notes in ppt:
constitutional Law Lecture Notes in ppt:
 
Federalism and models of Intergovernmental relation
Federalism and models of Intergovernmental relationFederalism and models of Intergovernmental relation
Federalism and models of Intergovernmental relation
 
Mining and Petroleum Tax Lecture Notes in ppt
Mining and Petroleum Tax Lecture Notes in pptMining and Petroleum Tax Lecture Notes in ppt
Mining and Petroleum Tax Lecture Notes in ppt
 
Ethiopian Tax Administration Lecture notes in ppt
Ethiopian Tax Administration Lecture notes in pptEthiopian Tax Administration Lecture notes in ppt
Ethiopian Tax Administration Lecture notes in ppt
 
Ethiopian Law of Evidence Lecture Notes ppt
Ethiopian Law of Evidence Lecture Notes pptEthiopian Law of Evidence Lecture Notes ppt
Ethiopian Law of Evidence Lecture Notes ppt
 
Law of criminal procedure Lecture Notes ppt
Law of criminal procedure Lecture Notes pptLaw of criminal procedure Lecture Notes ppt
Law of criminal procedure Lecture Notes ppt
 
The law Constitutional Law Lecture Notes
The law Constitutional Law Lecture NotesThe law Constitutional Law Lecture Notes
The law Constitutional Law Lecture Notes
 
Employment income tax Lecture Notes: ppt
Employment income tax Lecture Notes: pptEmployment income tax Lecture Notes: ppt
Employment income tax Lecture Notes: ppt
 
Lecture Notes on Agricultural Taxes.pptx
Lecture Notes on Agricultural Taxes.pptxLecture Notes on Agricultural Taxes.pptx
Lecture Notes on Agricultural Taxes.pptx
 
International Taxation Lecture Notes in ppt
International Taxation Lecture Notes in pptInternational Taxation Lecture Notes in ppt
International Taxation Lecture Notes in ppt
 
Law of property taxation lecture notes in ppt
Law of property taxation lecture notes in pptLaw of property taxation lecture notes in ppt
Law of property taxation lecture notes in ppt
 
Law of VAT and TOT Lecture Notes in ppts
Law of VAT and TOT Lecture Notes in pptsLaw of VAT and TOT Lecture Notes in ppts
Law of VAT and TOT Lecture Notes in ppts
 
Income Tax Jurisdiction lecture notes ppt
Income Tax Jurisdiction lecture notes pptIncome Tax Jurisdiction lecture notes ppt
Income Tax Jurisdiction lecture notes ppt
 
Introduction to Public Finance and Taxation.pptx
Introduction to Public Finance  and Taxation.pptxIntroduction to Public Finance  and Taxation.pptx
Introduction to Public Finance and Taxation.pptx
 
law of public enterprise lecture note- part one
law of public enterprise lecture note- part onelaw of public enterprise lecture note- part one
law of public enterprise lecture note- part one
 
Law of public enterprise ( lecture two) ppt
Law of public enterprise ( lecture two) pptLaw of public enterprise ( lecture two) ppt
Law of public enterprise ( lecture two) ppt
 
International business transaction power point
International business transaction power pointInternational business transaction power point
International business transaction power point
 
DBE_Policy_Environment_&_Lease_Financing_May_2014_E_C_final.ppt
DBE_Policy_Environment_&_Lease_Financing_May_2014_E_C_final.pptDBE_Policy_Environment_&_Lease_Financing_May_2014_E_C_final.ppt
DBE_Policy_Environment_&_Lease_Financing_May_2014_E_C_final.ppt
 

አዲሱ_የአማራ_ከልል_የገጠር_መሬት_ሕግ -አዲሱ_የአማራ_ከልል_የገጠር_መሬት_ሕግ -

  • 1. አዲሱ የአማራ ከልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሥር ለሚገኙ ለወረዳ እና ከፍተኛ ፍ/ቤቶች ዳኞች የተዘጋጀ ስልጠና በሪሁን አዱኛ ምሕረቱ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ታህሳስ 21 - 22/2010 ዓ/ም ደሴ ጥር 04 – 05/2010 ዓ/ም እንጅባራ
  • 2. 1. መግቢያ  መሬት በተፈጥሮ የተገኘ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከመሆኑም በላይ ሌሎች የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንበረቶችን ለማፍራት አስፈላጊ የሆነ መተኪያ የሌለዉ ሀብት ነው፡፡  መሬት ከንብረት መብት አኳያ ለሀገራችን አርሶ አደር የኑሮ ዋስትና ነው።  ለኢንቨስትመንት እና በአጠቃላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን በማረጋገጥ ረገድ ለመንግስት ቁልፍ የፖለቲካል ኢኮኖሚው መገለጫ የሆነ ሀብት ነው።  ይህን ትልቅ ዋጋ ያለው የሕዝብና የመንግስት ሀብት በአግባቡ ለማስተዳደርና አጠቃቀሙን ለማሳለጥ የሚያገለግሉ በፌደራል መንግስቱ እና በክልላችን የሕግ ማዕቀፎች ወጥተው እየተሰራባቸው ይገኛል።
  • 3. የቀጠለ  ከግንቦት 21 ቀን 1998 ዓ/ም ጀምሮ በክልላችን ውስጥ ሥራ ላይ የነበረው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ አዋጅ ቁጥር 133/1998 እና ማስፈጸሚያ ደንቡ ቁጥር 51/1999 መሆኑ ይታወቃል፡፡  ሆኖም እነዚህ ሕጎች ተግባራዊ ሲደረጉ በርካታ ችግሮች በማጋጠማቸው ሕጎቹን ማሻሻል በማስፈለጉ የተሻሻለው የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009 ታውጇል፡፡  የዚህ አዋጅ ማስፈጸሚያ ረቂቅ ደንብም
  • 4. የቀጠለ  በመሰረቱ ፍትሕ ለማግኘት በሚደረግ ጥረት ውስጥ በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ከሚቀርቡ ጉዳዮች ውስጥ እጅግ የሚበዛው የመሬት ክርክር ነው፡፡  ክርክሮቹ ከወረዳ ፍርድ ቤት ጀምሮ እስከ ክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ የሚደርሱ እና በቅርቡ ደግሞ እስከ ፌደሬሽን ም/ቤት የሚዘልቁና መቋጫ የሌላቸው ሲሆኑ ይታያሉ።  መቋጫ የለሽ ለሆነ የመሬት ክርክር ወይም የተዛባ ፍርድ መንስኤዎች ምንድን ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በተግባር ከሚታዩ ችግሮች በመነሳት የተወሰኑ ምክንያቶች ተለይተው ነበር።  ከተለዩት ምክንያቶች አንደኛው በመሬት አስተዳደርና
  • 5. የቀጠለ  በሕጎቹ ላይ የሚታዩ ችግሮች ተብለው የተለዩት፡- 1. የክልሎች ሕግ የማውጣት ስልጣን በዜጎች ላይ ያመጣው የመብት መለያየት ከውርስ መብት ጋር የተያያዘ ልዩነት፡- በውርስ፣ በኪራይ፣ በስጦታ መብት እና ይዞታ መብት የሚታጣባቸው ሁኔታዎች ላይ ከክልል ክልል ሰፊ ልዩነት መኖሩ፤ 2. የገጠር መሬት ውርስ ቅደም ተከተል ፍትሐዊ አለመሆኑ፤ 3. የገጠር መሬት ክርክር በይርጋ የሚታገድ መሆን አለመሆኑ በአግባቡ ሳይደነገግ መታለፉ፤ 4. የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕጎች በየወቅቱ ለባለይዞታዎች የተለያየ መብት በመስጠታቸው ቋሚና የተረጋጋ መብት አለመኖሩ፤ 5. ወጥ የሆነ የመሬት ግብይት ፎርማሊቲ አለመደንገጉ፤ 6. የከራይ ዘመን መርዘም እና የኪራይ ተመን ገደብ አለመኖር፤
  • 6. የቀጠለ  አዲሱ አዋጅ ከቀድሞው አዋጅ በእጥፍ ቁጥር ድንጋጌዎችን የያዘ፣ በጣም ሰፊ መግቢያ እና በርካታ የትርጓሜ ንዑስ አንቀጾችን ያካተተ እንዲሁም አዳዲስ ሀሳቦችን ያቀፈ ሆኖ ታውጇል፡፡  ለአዋጁ መሻሻል ምክንያት የሆኑ አስር መሰረታዊ ነጥቦችም መግቢያው ላይ ተካተዋል፡፡ ይኸውም፡- 1. አርሶ አደሮችም ሆነ ከፊል አርብቶ አደሮች በያዙት የገጠር መሬት ላይ ያላቸውን የተጠቃሚነት መብት ይበልጥ ማስፋት ተገቢ ሆኖ በመገገቱ፤ 2. በክልሉ ዉስጥ ተበታትኖ የሚኖረዉን አርሶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር ወደ ተወሰኑ ማዕከላት በማሰባሰብ ሁለንተናዊ ለሆነ እድገት ተጠቃሚ የሚያደርጋቸዉን ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤ 3. ሀገራችን የአርብቶ አደሮችን በመሬት የመጠቀም መብት አስመልክቶ በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ ደረጃ
  • 7. የቀጠለ 4. የግል ባለሀብቱ እና አግባብ ያላቸዉ ድርጅቶች መሬትን በአግባቡ በማልማት፤ በመጠቀምና በመጠበቅ ረገድ የሚኖራቸዉን ተሳትፎ ለማጠናከር እና ጥረታቸዉ ከክልሉ መንግሥት የልማት ዓላማዎች ጋር አንዲቀናጅ ለማድረግ በማስፈለጉ፤ 5. በክልሉ ዉስጥ የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃን በጥራት ለማደራጀትና ለባለይዞታዎች በአግባቡ ለማሰራጨት የሚያስችል ምቹ እና ደረጃዉን የጠበቀ የሕግ ማዕቀፍ በመፍጠር ሕጋዊ የመሬት ባለይዞታዎች የይዞታ ዋስትናቸዉ ተጠናክሮ ማየት በማስፈለጉ፤ 6. ሕገ-ወጥ የወል መሬት ወረራን በመከላከልና በግልም ሆነ በወል ይዞታቸዉ ላይም ቢሆን ያልተፈቀዱ
  • 8. የቀጠለ 7. ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ግጭቶችን ለመቀነስ የክልሉ መንግስት እና ባለይዞታዎች አስተማማኝ የመረጃ አገልግሎት የሚያገኙበትን ዘመናዊ የመሬት መረጃ ስርዓት መዘርጋት እና ገቢራዊ ማድረግ በማስፈለጉ፤ 8. በተለያዩ የክልሉ የስነ ምህዳር ቀጠናዎች ላይ ተመስርቶ ፈርጀ- ብዙ የገጠር መሬት አጠቃቀም እቅድ በማውጣትና በመተግበር የተፈጥሮ ሀብታችን በዘላቂነት በመጠበቅ እና በማልማት ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ አንዲቻል አስተዳደሩንና አጠቃቀሙን በሕግ መደንገግ አስፈላጊ በመሆኑ፤ 9. ሴቶች፣ ሕጻናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካሞች እና አረጋዊያን የገጠር መሬት ባለይዞታ የመሆን መብታቸው እንዲጠናከር በዝርዝር መደንገግ በማስፈለጉ፤ 10. በክልሉ ዉስጥ አንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች ወደ አቅራቢያዉ የከተማ አስተዳደር ክልል በሚጠቃለሉበት ወይም የገጠር መሬት ለሕዝብ አገልግሎት አንዲዉል በሚፈለግበት ጊዜ
  • 9. የቀጠለ  የዚህ አጭር ስልጠና አላማም የተሻሻለውን ገጠር መሬት አስተዳዳርና አጠቃቀም አዋጅ ከረቂቁ ደንቡ ጋር በማገናዘብ ለዳኞች በማሳወቅ ለቀጣይ ሥራቸው እንዲጠቅማቸው ማድረግ ነው፡፡  በመሆኑም በክልላችን ውስጥ የገጠር መሬትን በማግኘት፣ በመጠቀም፣ በማስተላለፍ እና መብቱ ቀሪ በሚሆንባው ሁኔታዎች ላይ ከቀድሞው ሕግ አንጻር የተጨመሩ ወይም የተሻሻሉ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፡፡  እንዲሁም አዋጁ ያካተታቸው ሌሎች መሰረታዊ ጉዳች ይተነተናሉ፡፡  የአዋጁ ማስፈፀሚያ ደንብ በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለ በመሆኑ ከደንቡ ላይ የሚወሰዱ ሀሳቦች ያለቀላቸው ስለማይሆኑ ዳኞች ይህን ግንዛቤ በመያዝ ወደፊት
  • 10. 2. የገጠር መሬት የማግኘት፣ የመጠቀም እና የማስተላለፍ መብቶች የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና ዘላኖች ለእረሻም ሆነ ለግጦሽ የሚጠቀሙበት የገጠር መሬት በነጻ የማግኘት፣ የማጠቀም እና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት ያላቸው መሆኑን የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 40(4)(5) ይደነግጋል፡፡ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 40(4) ላይ እንደተደነገገው የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ሰው የሚከለከለው መሬቱን መሸጥ እና በሌላ ንብረት መለወጥ ብቻ እንደመሆኑ መጠን አርሶ አደሮችም ሆነ አርብቶ አደሮች በነጻ ያገኙትን መሬት በተለያየ መልኩ የመጠቀም፣ በስጦታ ወይም በውርስ የማስተላለፍ፣ የማከራየት እና ተያያዥ መብቶች ይኖራቸዋል፡፡ የእነዚህን ዝርዝር መብቶች አፈፃፀም በተመለከተ በዝርዝር ሕጎች እንደሚወሰኑ ህገ መንግስቱ የሚደነግግ
  • 11. 2.1 የገጠር መሬት ባለይዞታ የመሆን መብት አዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀጽ 2(4) “የይዞታ መብት ማለት ማንኛውም አርሶ አደር፣ አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር የገጠር መሬትን በግብርናና በተፈጥሮ ሀብት ልማት ተግባር ላይ የማዋል፣ የማከራየት፣ ለቤተሰቡ አባልና ለሌሎች በሕግ መብት ለተሰጣቸው ወራሾች ለማውረስ የሚኖረው መብት ሲሆን በመሬቱ ላይ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ ንብረት የማፍራትና ይህንንም በመሬቱ ላይ ያፈራውን ንብረት የመሸጥ የመለወጥና የማውረስንም መብት ይጨምራል” በማለት ደንግጓል፡፡ የክልላችን አዲሱ አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 2(24) የይዞታ መብት ማለት ማንኛውም አርሶ-አደር፣ ከፊል አርብቶ-አደር ወይም በሕጉ መብት የተሰጠው ማናቸውም ሌላ አካል በዚህ አዋጅ መሰረት የተረጋገጡለትን የገጠር መሬት ባለይዞታ የመሆን፣ በመሬቱ ላይ ንብረት የማፍራት፣ያፈራውን ንብረት የማስተላለፍ፣ ከመሬቱ ያለመፈናቀል፣ መሬቱን ለግብርናና ለተፈጥሮ ሃብት ልማትም ሆነ ለሌሎች ሕጋዊ ተግባራት
  • 12. የቀጠለ በአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 6 እንደተገለጸው የገጠር መሬት ይዞታ በግል፣ በወል ወይም በመንግስት ሊያዝ የሚቸል ቢሆንም ከህገ መንግስቱ ጀምሮ አዋጅ ቁጥር 456/1997ም ሆነ የክልላችን ገጠር መሬት ሕግ የገጠር መሬት የማግኘት መብትን ቅድሚያ የሚሰጠው ለአርሶ አደሩ ነው፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 7(1) እና 10(1) እንደተደነገገው የገጠር መሬት ባለይዞታ ለመሆን ወይም መሬትን ከሚያስተዳድረው አካል መሬትን በነጻ በድልድል ለማገኘት ሶስት መሰረታዊ መስፈርቶች ያስፈልጋሉ፡፡ እነዚህም:- 1. የክልሉ ነዋሪ መሆን፤ 2. በዋነኝነት በግብርና ሥራ መተዳደር ወይም በዚሁ
  • 13. የቀጠለ በዚህ አዋጅ የሁለተኛው መስፈርት መርህ ልዩ ሁኔታ ሆኖ በአንቀጽ 7(2) ሥር የተደነገገው በምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ በህዝብ ተወካዮችም ሆነ በክልል ምክር ቤት በቋሚነት ያገለግሉ ዘንድ ለጊዜው አካባቢያቸውን የሚለቁ አርሶ አደሮች፣ አነስተኛ ወር ገቢ በሚያስገኝ እንደ ዘበኛነት፣ ፅዳት፣ ተላላኪና ፖስተኛ አይነት ሥራ የተቀጠሩ ሠራተኞች እና በጡረታ ሚተዳደሩ ሰዎች በቀጥታ በግብርና ሥራ እየተዳደሩ አይደለም በሚል የገጠር መሬት ባለይዞታ ከመሆን የማይከለከሉ መሆኑ ነው፡፡  የሶስተኛው መስፈርት ልዩ ሁኔታም በአዋጁ አንቀጽ 10(2) ላይ እንደተደነገገው 18 ዓመት ያልሞላቸው እና ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ህጻናት በህጋዊ አሳዳጊዎቻቸው ወይም ሞግዚቶቻቸው አማካይነት መሬት የማግኘት መብት አላቸው የሚለው ነው፡፡
  • 14. የቀጠለ የገጠር መሬት ይዞታ የሚሰጥበት ስርዓት በተመለከተ በክልሉ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም አርሶ አደር በጾታም ሆነ በሌላ በማናቸውም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግት መሬት በነጻ የማግኘት አኩል መብት ያለው መሆኑን የአዋጁ አንቀጽ 5(2) ይደነግጋል፡፡ ሆኖም የዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 በገጠር መሬት ድልድል ጊዜ ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ለሴቶች እና ለአረጋውያን ቅድሚያ እንዲሰጥ የሚያደርግ አሠራር ተቀርጾ በሥራ ላይ እንደሚውል ይደነግጋል፡፡ የገጠር መሬት አሰጣጥ ሥርዓቱም በአዋጁ አንቀጽ 12 ላይ ተደንግጓል፡፡ ይኸውም፡- የመሬት ጥያቄ የሚቀርብበትም ሆነ ምላሽ የሚሰጥበት
  • 15. የቀጠለ የመሬት አሰጣጥ ስርአቱ እንደጠያቂዎቹ የመሬት ፍላጎት በህዝብ ተሳትፎ በሚወሰነው ቅደም ተከተል መሰረት መሬት በይዞታ የማግኘት ላላቸው አመልካቾች ሁሉ ያለአድልዎ እንዲተገበር ይደረጋል፡፡ ሊሰጥ የሚችለው የመሬት መጠን ችግሩ ላለባቸው ጠያቂዎች ሁሉ እኩል ሊዳረስ የማይችል ሆኖ የተገኘ እንደሆነ እንደ ቅደም ተከተላቸው ወላጆቻቸዉን በሞት ላጡ ሕፃናት፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ለሴቶች እና ለአረጋውያን እንደሚሰጥ የገለጻል፡፡ የረቂቅ ደንቡ አንቀጽ 5(3) ደግሞ እነዚህ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ሰዎች በሌሉበት ጊዜ ወይም ቅድሚያ አግኝተዉ ትርፍ መሬት ካለ በህዝብ ተሳትፎ
  • 16. የቀጠለ ሀ. ጎጆ ለወጣ እና ልጅ ያለዉ፣ ለ ጎጆ የወጣ እና ልጅ ለሌለዉ፣ ሐ በትዳር ላይ ያለ ሰው የግል እና የጋራ ይዞታ ከሌለው አንደኛዉ የትዳር አጋር የይዞታ መሬት የሌለዉ ተጋቢ እና ጎጆ ላልወጡ ወጣቶች መ. አነስተኛ የመሬት ይዞታ መጠን በታች መሬት ያላቸዉ ባለይዞታዎች ሠ. ከፍተኛ ይዞታ መጠን ጣራ ሳያልፍ ለሌሎች መሬት ያላቸዉ እንደመሬት መጠናቸዉ እየታየ የይዞታ መሬት እንደሚሰጣቸው ይደነግጋል፡፡ በመሰረቱ አርሶ አደሮች መሬትን ከሚያስተዳድረው አካል በድልደል ከማግኘት ባሻገር የገጠር መሬትን በውርስ ወይም በስጦታ የማግኘት መብትም አላቸው፡፡
  • 17. የቀጠለ ከአርሶ አደሮች በመቀጠል በክልሉ ውስጥ ሥራቸውን የሚያካሂዱ ወይም ለማኅበረሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት እና የብዙኃን ማኅበራት ተግባራቸውን የሚያከናውኑት ለገንዘብ ትርፍ እስካልሆነ ድረስ የአርሶ አደሮችን መሬት የማግኘት መብት በማይፃረር ሁኔታ ለተልዕኳቸ መሳካት የሚጠቀሙበት የገጠር መሬት ባለይዞታነት የማግኘት መብት ያላቸው መሆኑን የአዋጁ አንቀጽ 10(6) ይደነግጋል፡፡  እንዲሁም የግል ባለሀብቶች የሚጠቀሙበት መሬት በሥራ ላይ ያለውን የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ በጠበቀ ሁኔታ ከክልሉ ከመንግሥት በሊዝ ውል ወይም ከማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ ጋር በሚደረግ
  • 18. 2.2 የገጠር መሬት ባለይዞታዎች መብቶች የገጠር መሬትን በድልድል፣ በውርስም ሆነ በስጦታ ያገኘ አርሶ አደር ከመሸጥና በሌላ ንብረት ከመለወጥ ውጭ ለራሱ መጠቀም፣ በሌላ መሬት የመለወጥ፣ በህግ ለተሰቀደላቸው ሰዎች በውርስም ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ፣ የማከራየት እና በዋስትና አስይዞ የመበደር መብት አለው፡፡ አዋጁ አንቀጽ 8(1)(2) 1. የመጠቀም መብት የአዋጁ አንቀጽ 8(1) አርሶ አደሮች በዚህ አዋጅ መሠረት በተሰጣቸው የገጠር መሬት ይዞታ ላይ ሙሉ የባለይዞታነትና የመጠቀም መብት እንዳላቸው ይደነግጋል፡፡ አርሶ አደሮች በይዞታቸው ሥር ያለውን መሬት መሬትን የሚያስተዳድረው አካል በሚያዘጋጅላቸው ወቅታዊ
  • 19. 2. መሬትን በመሬት የመለዋወጥ መብት ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ ማሳዉን በቀበሌዉ ወይም በሌላ ቀበሌ ውስጥ ከሚገኝ ሌላ ባለይዞታ ጋር መለዋወጥ እንደሚችል አንቀጽ 20(1) ይደነግጋል፡፡  አነስተኛ ማሳዎች ለልማት አመቺ ይሆኑ ዘንድ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች በተናጠል ይዞታዎታቸውን ኩታገጠም ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ አንቀጽ 20(2)  በባለይዞታዎች መካከል የሚደረግ ማናቸውም የልውውጥ ወይም ኩታገጠም የማድረግ ውል በወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ መመዝገብ አለበት፡፡ አንቀጽ 20(3)
  • 20. የቀጠለ መሬቱ የባልና ሚስት የጋራ ይዞታ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ባለይዞታዎች በጣምራ የተያዘ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ልውውጡ በሁሉም ባለዞታዎች ፈቃድ ላይ ተመስርቶ መፈጸም ይኖርበታል፡፡ አንቀጽ 20(4) የአዋጁ አንቀጽ 20(5) የተናጠል ይዞታዎቻቸውን ኩታ ገጠም ለማድረግ አስበው የገጠር ልውውጥ ለሚያደርጉ ባለይዞታዎች የሚሰጣቸው ማበረታቻ በደንብ እንደሚወሰን ይናገራል፡፡ ረቂቅ ደንቡ አንቀጽ 13(3) ማበረታቻው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በነፃ ማደስ እና ከልኬታ ጋር የተያያዘ አገልግሎት በነፃ ማግኘት መሆኑን ይደነግጋል፡፡
  • 21. 3. የይዞታ መሬትን በስጦታ የማስተላለፍ መብት ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ የይዞታም ሆነ የመጠቀም መብቱን በክልሉ ዉስጥ ለሚኖር እና በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም በዚህ ሙያ መተዳደር ለሚፈልግ ልጅ ወይም የልጅ ልጁ ወይም ለማንኛውም ሌላ የቤተሰብ አባል ወይም በወቅቱ እየጦረው ላለና አገልግሎኛል ወይም እያገለገለኝ ነው ብሎ ላመነው ሰዉ በስጦታ ማስተላለፍ የሚችል መሆኑን የአዋጁ አንቀጽ 16(1) ይደነግጋል፡፡ ሆኖም ላገለገለ ወይም እገለገለ ላለ ሰው የሚደረገው ስጦታ ሊጸና የሚችለው ስጦታ ተቀባዩ ባለይዞታውን በመጦር ላይ ያለ ወይም ሲንከባከብ የቆየ ስለመሆኑ “ከቀበሌ ማኅበራዊ ፍ/ቤት” በጽሑፍ ማስረጃ አረጋግጦ ሲቀርብ ብቻ ነው፡፡ አንቀጽ 16(2)
  • 22. የቀጠለ  ባለይዞታው ያደረገው ስጦታ አካለመጠን ያልደረሱ ልጆቹን ወይም ሌሎች የቤተሰብ አባላትን መብት ሙሉ በሙሉ በሚጐዳ ወይም ለነርሱ በቂ ድርሻ በማያስቀር ሁኔታ የተከናወነ ከሆነ በሕግ ፊት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አንቀጽ 16(3)  የስጦታ ውል ስምምነት በጽሑፍ ተደርጎ መሬቱ በሚገኝበት ወረዳ ላለው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡  በቃል የተደረገ የስጦታ ዉል ስምምነት በሕግ ፊት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡  ውሉም የጸና የሚሆነው ለወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽህፈት ቤት ቀርቦ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡ አንቀጽ 16(7-9)  ባለይዞታውን ለመጦር መሬቱን በስጦታ የተቀበለ ማንኛውም ሰው በገባው ውል መሰረት ሰጪውን አለመጦሩ የተረጋገጠ እንደሆነ ሰጪዉ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በማቅረብ ውሉ
  • 23. 4. የይዞታ መብትን በውርስ የማስተላለፍ መብት የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ማንኛውም ሰው የይዞታም ሆነ የመጠቀም መብቶቹን በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም በዚሁ ሙያ መተዳደር ለሚፈልግ ማንኛውም ሌላ ሰው በኑዛዜ ሊያስተላለፍ እንደሚችል አንቀጽ 17(1) ይደነግጋል፡፡ ሆኖም የባለይዞታው በኑዛዜ የማስተላለፉ ተግባር አካለ መጠን ያላደረሰውን የተናዛዡን ልጅ ከህጋዊ ወራሽነት መብቱ የሚነቅል ወይም የተናዣዡን የትዳር ጓደኛ ሕጋዊ መብት የሚጎዳ ሆኖ የታየ እንደሆነ በሕግ ፊት የሚጸና አይሆንም፡፡ አንቀጽ 17(3) ስጦታ ላይ ለማን መሰጠት እናዳለበት ሕጉ በግልጽ ሲደነግግ ኑዛዜ ላይ ግን በጣም ሰፊ በሆነ ሁኔታ ለማንኛውም በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ሰው ሁሉ
  • 24. የቀጠለ በሌላ በኩል በስጦታ ጊዜ አካለመጠን ያልደረሱ ልጆቹን ወይም ሌሎች የቤተሰብ አባላትን መብት ሙሉ በሙሉ በሚጐዳ ከሆነ ተቀባይነት እንደማይኖረው ሲደነግግ በኑዛዜ ጊዜ ግን ሕጉ ጥበቃ የሚያደርገው አካለመጠን ላልደረሱ ልጆች ብቻ ነው፡፡ የኑዛዜው አደራረግ በፍ/ሕግ ውስጥ እንደተደነገገው በግልጽ የሚካሄድ ኑዛዜ የሚሰጥባቸውን መስፈርቶች ማሟላት እና በወረዳ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ መመዝገብ ያለበት መሆኑን አንቀጽ 17(4) ይደነግጋል፡፡ በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ እየተናገረ ማንኛውም ሌላ ሰው ወይም ተናዛዡ ራሱ የሚጽፈው ሲሆን ኑዛዜው በተናዛዡና አራት ምስክሮች ፊት መነበብ፣ ቀን በግልጽ
  • 25. የቀጠለ  በእርግጥ በአንቀጽ 882 እንደተደነገገው ከምስክሮቹ መካከል አንዱ ዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው አካል ሲሆንና ኑዛዜው የተደረገው ይህ ሰው ሥራውን በሚያከናውንበት ቦታ ከሆነ የጸና ኑዛዜ ለማድረግ ሁለት ምስክሮች ይበቃሉ። ምስክሮቹም አካለመጠን የደረሱ፣ በፍርድ ወይም በሕግ ያልተከለከሉ መሆን እና ኑዛዜው የተጻፈበትን ቋንቋ የሚያውቁ እንዲሁም የተጻፈውን ለመስማት ወይም ለማንበብ ራሳቸው ችሎታ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል። አንቀጽ 883 ባለይዞታው መሬቱን በኑዛዜ ሳያወርስ የሞተ ወይም የሰጠው ኑዛዜ ፈራሽ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ መብቱ እንደ ቅደም ተከታላቸው በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም
  • 26. የቀጠለ የሟች ልጆች/ከልጆቹ አንዱ ቀድመዉ ሞተዉ/ሞቶ እንደሆነ እና ወደታች የሚቂጠሩ ተወላጆችን ትተዉ/ትቶ እንደሆነ እነዚሁ ተወላጆቻቸዉ የሟቹ የቤተሰብ አባል ሆነዉ ተገኝተዉ ካልወረሱ በስተቀር ቀድመዉ በሞቱት ልጆች ምትክ ሆነዉ እንዲወርሱ ይደረጋል፡፡ አንቀጽ 17(6) በመሰረቱ የውርስ ድንጋጌ አሁንም ያልተፈቱ ችግሮችን ይዟል፡፡ ቅደም ተከተሉ ታስቦበት የተቀመጠ አይመስልም፡፡ የፍትሐዊነት ችግርንም የሚቀርፍ አይመስልም፡፡ ለደንቡም ስልጣን አይሰጥም፡፡  ረቂቅ ደንቡ አንቀጽ 10 የይዞታ መሬቱን በኑዛዜ ሳያወርስ የሞተ ሰዉ ወይም የተወዉ ኑዛዜ ፈራሽ ከሆነ የይዞታ መብቱ በሚከተለዉ ቅደም ተከተል ለሟች ወራሾች ይተላለፋል በማለት የሚከተለውን ይደነግጋል፡፡
  • 27. የቀጠለ ሀ. … ምንም አይነት ይዞታ መሬት የሌላቸዉ አካለ መጠን ያልደረሱም ሆነ የደረሱ ልጆች፤ ለ. የራሳቸዉ የይዞታ መሬት ያላቸዉ አካለ መጠን ያልደረሱም ሆነ የደረሱ ልጆች፤ ሐ. በፊደል ”ሀ” የተደነገገዉ ቢኖርም በ “ለ” ስር የተጠቀሱት ልጆች አስቀድሞ ያላቸዉ መሬት አነስተኛ ሆኖ ሲገኝ በ “ሀ” ስር የተጠቀሱት ወራሾች በ “ለ” ስር ያሉ ልጆች ያላቸዉን ዝቅተኛ መሬት መጠን ያክል እንዲደርሳቸዉ ከተደረገ በኋላ ቀሪ የሟች መሬት ካለ የመሬት መበጣጠስን እስካላስከተለ ድረስ “ሀ” እና “ለ” መካከል እኩል ይከፋፈላሉ፡፡ መ. በፊደል ”ሐ” የተደነገገዉ ቢኖርም መሬት ባላቸዉ ልጆች መካከል የመሬት መጠን መለያየት ካለ ከፍተኛ የመሬት መጠን ያለዉን ልጅ መጠን ያክል እስከሚደርስ ድረስ የመሬት መበጣጠስን በማያስከትል መልኩ እንዲመጣጠን ይደረጋል፡፡ ሠ. በፊደል ”ሀ” እና ”ለ” የተጠቀሱት ልጆች ከሌሉ አካለ መጠን ያልደረሱም ሆነ የደረሱ የቤተሰብ አባላት በእኩል ደረጃ ይወርሳሉ፤ ረ. በፊደል ”ሀ”፣ ”ለ” እና ”ሠ” የተጠቀሱት ወራሾች ከሌሉ የሟች ወላጆች ይወርሳሉ፤
  • 28. 5. የይዞታ መሬትን የማከራየት መብት ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ ራሱን ከይዞታው እስከማፈናቀል በማያደርስ ሁኔታ በያዘው መሬት የመጠቀም መብቱን ለሌላ ለማንኛውም ለግብርና ሥራ ለሚያውል ሰው በኪራይ ውል ማስተላለፍ እንደሚችል አንቀጽ 15(1)(2) ይደነግጋል፡፡ የገጠር መሬት ኪራይ ውል በጽሑፍ መሆን እና የመሬቱን ስፋት፣ የኪራዩን ዘመን፣ የክፍያውን መጠን እንዲሁም የአከፋፈሉን ሁኔታ በግልጽ የሚያሳይ መሆን አለበት፡፡ አንቀጽ 15(3)(4) የገጠር መሬት ኪራይ ውል ስምምነት እስከ ሁለት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ የተደረገ ከሆነ መሬቱ ለሚገኝበት ቀበሌ አስተዳደር አጠቃቀም ጽ/ቤት እና ከዚያ ለበለጠ ጊዜ የተደረገ ከሆነ ደግሞ ለወረዳ የገጠር
  • 29. የቀጠለ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከፍተኛው የገጠር መሬት ኪራይ ውል ዘመን ቋሚ የፍራፍሬ ተክሎችን ወይም የተመረጡ የዛፍ ዝርያዎችን የተመለከተ እንደሆነ 30 ዓመት ሲሆን ዓመታዊ ሰብሎችን የተመለከተ ከሆነ ደግሞ 10 ዓመት ይሆናል፡፡ ስለሆነም እንደተገቢነቱ ከ30 ዓመት እና ከ10 ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ተደርጎ የተገኘ የመሬት ኪራይ ውል ስምምነት ቢኖር በዚህ አዋጅ መሰረት እንደቅደም ተከተላቸዉ ለ30 ዓመት እና ለ10 ዓመት እንደተደረገ ይቆጠራል፡፡ አንቀጽ 15(9) የኪራይ ዉል ሕጋዊ የዉል ማቋቋሚያ ሁኔታዎችን አሟልቶ ካልተገኘ ወይም ተከራዩ በተከራየዉ መሬት ላይ ጉዳት ካደረሰ ወይም ከስምምነታቸው ዉጭ
  • 30. የቀጠለ የውል ማቋቋሚያ ሁኔታዎች ችሎታ፣ ጉድለት የሌለው ፈቃድ፣ በቂ የሆነ እርግጠኛነት ያለው የሚቻልና ህጋዊ የሆነ ጉዳይ እና የውል አጻጻፍ ፎርም ናቸው፡፡ የፍ/ሕ/ቁ 1678 በህጋዊ አሳዳሪ ወይም በሞግዚት ጥበቃ ስር የሚተዳደሩ ሕፃናት፣ አረጋዊያን እና በፍርድ የተከለከሉ ሰዎች ወይም የአእምሮ መታወክ ያለባቸው ስለመሆኑ በፍርድ የተረጋገጠላቸው ባለይዞታዎች የመሬት ይዞታቸውን ሲያከራዩ ውሉ የነርሱን ጥቅም በማይጎዳ ሁኔታ ስለመደረጉ ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ የቤተ ዘመድ ጉባኤ የመከረበትና ውል ለመዋዋል ሥልጣን የተሰጠው አካል ያጸደቀው ሰነድ ከኪራይ ውሉ ጋር ተያይዞ ለምዝገባ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ አንቀጽ 15(12)
  • 31. 6. መሬትን በዋስትና አስይዞ የመበደር መብት ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ከ30 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ የመጠቀም መብቱን በሀገሪቱ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ለተሰጠው ሕጋዊ የገንዘብ ተቋም የብድር ዋስትና አድርጎ ሊያስይዝ እንደሚችል አንቀጽ 19(1) ይደነግጋል፡፡ ተበዳሪው በብድር ውሉ ውስጥ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ዕዳውን ያልከፈለ እንደሆነ አበዳሪው በብድር ውሉ ለተጠቀሰው ጊዜ በመሬቱ የመጠቀም መብት የሚኖረው ሆኖ የተገኘ እንደሆነ የዚሁ መብቱ ወሰን በመሬቱ ላይ ከተሰጠው የመጠቀም መብት ያለፈ ሊሆን አይችልም፡፡ አንቀጽ 19(2) አበዳሪው መሬቱን ራሱ የማያለማውና ከዚሁ የተነሳ ለሶስተኛ ወገን በኪራይ የሚያስተላልፈው ከሆነ መሬቱን ከአበዳሪው በውል ለመውሰድ እስከ ተስማማ
  • 32. የቀጠለ በገጠር መሬት የመጠቀም መብት መያዣ የተደረገበት ማንኛውም ውል ባበዳሪዉ ተቋም መመዝገብ አለበት፣ ይኸው የተመዘገበው የኪራይ ውል አንድ ቅጅ መሬቱ ለሚገኝበት ወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ ከባለይዞታው የግል ማህደር ጋር መያያዝ ይኖርበታል፡፡ አንቀጽ 19(4) አርሶ አደሮች መሬታቸውን በዋስትና አስይዘው የመበደር መብት በአዲሱ አዋጅ የተካተተ አዲስ መብት ነው፡፡ ይህ መብት በፌደራል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ አንቀጽ 16 ላይም የተደነገገ እና ከ15 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ በዋስትና ማስያዝ እንደሚቻል የተገለጠ ሲሆን ሀተታ ዘምክንቱ ላይ የሰፈረው ሀሳብ የሚከተለውን ይመስላል፡፡
  • 33. የቀጠለ  አርሶ አደሮች በማስያዣ የሚሰጡት በመሬት የመጠቀም መብታቸውን ነው፡፡ … ይህንን ማስያዣ ውል የሚገቡት ገንዘብ ተበድረው በብድር ውሉ በመለከተው የጊዜ ገደብ መሰረት መመለስ ባይችሉ ገንዘብ ጠያቂው የባለ ዕዳውን መሬት በውሉ ለተመለከተው ጊዜ ብቻ በማረስ ወይም በማከራየት ተጠቅሞ መሬቱን ለባለ ይዞታው ይመልሳል፡፡  አበዳሪው መሬቱን ሊጠቀምበት የሚችለው ተበዳሪው በውሉ መሰረት ገንዘቡን መመለስ ሳይችል ሲቀር ብቻ ነው፡፡  ተበዳሪ በተጠቀሰዉ ጊዜ ብድሩን ያልከፈለ ከሆነ በዉሉ ለተጠቀሰዉ ጊዜ ያህል ብቻ አበዳሪ በመሬቱ የመጠቀም መብት ያለዉ ሲሆን የተበዳሪ ኃላፊነት በመሬቱ ላይ ከሰጠዉ የመጠቀም መብት ያለፈ አይሆንም፡፡  አበዳሪ መሬቱን በማልማት ያበደረዉን ያህል ገንዘብ በዉሉ በተወሰነዉ ጊዜ ማግኘት ባይችል ሌላ የተበዳሪን ንብረት ወይም ተጨማሪ ጊዜ በመሬቱ የመጠቀም መብት ለብደሩ ማስቻያ ሊጠይቅ አይችልም፡፡
  • 34. የቀጠለ  በተመሳሳይ አበዳሪ መሬቱን በመጠቀም ከአበደረዉ ገንዘብ የበለጠ ጥቅም ቢያገኝ ተበዳሪ ከዚህ የመጠየቅ መብት የለዉም፡፡  ይህ ድንጋጌ ከዚህ በፊት ከሚታወቀዉ የብድር ዋስትና የተለየ ሲሆን ይህም የመሬትን ልዩ የንብረት ባህሪ ግምት ዉስጥ በማስገባት አርሶ አደሮች እንዳይፈናቀሉና እንዳይጎዱ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነዉ፡፡  … ይህ አሰራር ገንዘብ የሌላቸው አርሶ አደሮች ለስራቸው ግብዓት የሚሆን ገንዘብ በብድር መልክ እንዲያገኙ በማድረግ የእርሻ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ስለሚረዳ ድሃ አርሶ አደሮች በግብዓት እጥረት ምክንያት የእርሻ ስራቸውን ትተው የሚያደርጉትን ፍልሰት ይቀንሳል፡፡  አበዳሪዎችም ቢሆኑ የገንዘብ ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ ግለሰብ አርሶ አደሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡  በመሆኑም አርሶ አደሮች ግብዓት ለመግዛት የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት መሬታቸውን ያከራዩ የነበሩት ወይም
  • 35. 3. የገጠር መሬት ባለይዞታዎች ግዴታዎች እና ግዴታዎችን አለመወጣት የሚያስከትለው ሀላፊነት 3.1 የገጠር መሬት ባለይዞታዎች ግዴታዎች በአዋጁ አንቀጽ 27 ሥር እንደተደነገገው ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ ወይም ተጠቃሚ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል፡፡  በይዞታው ስር ያለውን መሬት የመንከባከብና አካባቢውን የመጠበቅ፤  በመሬቱ ዙሪያ አስቀድመው የበቀሉ ነባር እፅዋት ቢኖሩ ዝርያቸው እንዳይጠፋ የመንከባከብ፤  የአፈር ለምነትን የሚያሻሽሉና ለአካባቢ ደህንነት ተስማሚ የሆኑ ዛፎችን የመትከልና ተንከባክቦ የማሳደግ፤
  • 36. የቀጠለ  ተዳፋትነታቸው ከ60 በመቶ በላይ የሆኑ መሬቶችን ከእርሻና ከልቅ ግጦሽ ይልቅ ለዛፍ፣ ለቋሚ ተክሎች እና ለእንስሳት መኖ ልማት ብቻ የማዋል፤  የዉሃ ምንጮች እንዳይደርቁ የጥንቃቄ እርምጃን የመውሰድ፤  የወል መሬት ይዞታዎችን ያለመዳፈር፣ በወሰን የተከለሉ ሌሎች መሬቶችን ድንበር ያለመጋፋትና የሕዝብ መንገዶችን ያለመዝጋት፤  የሚመለከተው አካል የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ አዘጋጅቶ ሲሰጠው በዕቅዱ መሰረት መጠቀም፤  በመሬቱ አካባቢ የሚገኙ የዱር እንስሳትና አእዋፍ እንዳይታወኩ ወይም እንዳይጎዱ ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ የመውሰድ፤
  • 37. የቀጠለ  የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በሚሰጥበት ጊዜ ተከታትሎ የመውሰድ፣  የይዞታ መብቱን በማናቸውም ምክንያት በሚያጣበት ጊዜ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩን አግባብ ላለው አካል የመመለስ፤  ክፉኛ የተጎዳ የገጠር መሬት ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ ነጻ በማድረግ እንዲያገግም አድርጎ በወጣለት እቅድ መሰረት የመጠቀም፤  የመሬቱ ተጠቃሚ ባለሃብት ከሆነ ከዚህ በላይ ከሰፈሩት ግዴታዎች በተጨማሪ ለተፈቀደለት ይዞታ ተገቢውን የአጠቃቀም እቅድ በማዘጋጀት ለፈቀደለት የመሬት አስተዳደር አካል አቅርቦ የማስጸደቅና በእቅዱ መሠረት መሬቱን ጥቅም ላይ የማዋል፤ (በባለሀብቱ የሚያቀርበው የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ የኅብረተሰቡን ጤንነት፣ የአካባቢውን ደህንነትና የራሱን የመሬቱን ለምነት አጠባበቅ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡ )
  • 38. 3.2 ግዴታን አለመወጣት የሚያስከትለው ኃላፊነት  ከላይ የተዘረዘሩትን እና በሕግ የታወቁ ተመሳሳይ ግዴታዎችን ያልተወጣ ባለይዞታ በቅድሚያ እንደ ሁኔታው የቃል ወይም የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡ አንቀጽ 28(1)  ባለይዞታው የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ተቀብሎ ስህተቱን ሊያርም ያልቻለ ወይም ለማረም ፈቃደኛ ሆኖ ያልተገኘ እንደሆነ በሚከተለው ቅደምተከተል አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወሰድበት ይችላል፡፡  ሀ. የራሱ በሆነ ድክመት መሬቱን ካለመንከባከቡ የተነሳ በመሬቱ ላይ ጉዳት ደርሶ ከተገኘ የመጠቀም መብቱን ለተወሰነ ጊዜ መሬቱን የመንከባከብ ኃላፊነት ለሚወስድ ለሌላ ሰው በኪራይ እንዲያስተላልፍ ሊወሰንበት ይችላል፡፡  ለ. ከላይ የተመለከተው እርምጃ ተፈጻሚ ከሆነ በኋላ ጥፋቱን በተመሳሳይ ሁኔታ የደገመ እንደሆነ በመሬቱ የመጠቀም መብቱን ለተወሰነ ጊዜ ከማገድ ጀምሮ ላለማው ሀብት ብቻ ካሳ ተከፍሎት መሬቱን ከናካቴው እንዲለቅ ሊወሰንበት ይችላል፡፡
  • 39. የቀጠለ በተመሳሳይ ሁኔታ የወል መሬት ተጠቃሚ የሆነ ማንኛውም ሰው መሬቱን ለመንከባከብ ከሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር አልተባበርም ያለ እንደሆነ ሕግ ባለማክበር ምክንያት እንደ ቅደም ተከተሉ የቃል ወይም የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡ አንቀጽ 28(4) ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው በኋላ ጥፋቱን በተመሳሳይ ሁኔታ ከደገመ የወል መሬቱን ከናካቴው እንዳይጠቀም ለተወሰነ ጊዜ ከማገድ ጀምሮ ለዘለቄታው እስከ መከልከል የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወሰድበት ይችላል፡፡ አንቀጽ 28(5) በተጨማሪም ግዴታዎቹን ያላከበረ ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ ወይም ተጠቃሚ እንደሁኔታው በወንጀል ሊጠየቅ ወይም ላደረሰው
  • 40. 4. የገጠር መሬት ይዞታ የሚታጣባቸው ሁኔታዎች በአዋጁ አንቀጽ 5(3) እንደተደነገገው በክልሉ ውስጥ አርሶ አደሮች ያላቸው የገጠር መሬት ይዞታ መብት የጊዜ ገደብ የለውም፡፡ ይህ ማለት ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ መብቱ በዚህ ጊዜ ያበቃል ሳይባል በሕግ የተጠበቀ ነው ማለት ነው፡፡ ሆኖም በልዩ ሁኔታ በሕግ በተደነገገ አግባብ ባለይዞታው መሬቱን እንዲለቅ ሊደረግ ይችላል፡፡ የአዋጁ አንቀጽ 9፣ 21 እና 26 ስለሆነም የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ሰው ይዞታውን በሚከተሉት ምክንያቶች እንዲያጣ ሊደረግ ይችላል፡- 1. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 7 (2) ፊደል ተራ ቁጥር (ለ) ሥር
  • 41. የቀጠለ 2. ይዞታውን ለሶስተኛ ወገን ማከራየቱን ወይም የሚያስተዳድርለት ሰው መመደቡን ለወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ሳያሳዉቅ በተከታታይ ለ5 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከመኖሪያ አካባቢው መጥፋት ወይም ወደ ውጪ አገር ሂዶ መገኘት፤ 3. ይዞታው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውል ሲወሰን፣ 4. መሬቱን ያለበቂ ምክንያት እስከ 3 ዓመት ለዘለቀ ጊዜ ጦም ማሳደር፤ 5. ይዞታውን በተዘጋጀው የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ መሠረት አለማልማት እና ይኸው ዕቅድ ባልተዘጋጀላቸዉ አካባቢዎች ደግሞ መሬቱን በእንክብካቤ ካለመያዙ የተነሳ ከባድ ጉዳት
  • 42. የቀጠለ የገጠር መሬት ይዞታውን በማናቸውም ምክንያት እንዲያጣ የተደረገ ማንኛውም ሰው በመሬቱ ላይ ላለማው ቋሚ ንብረት ተገቢውን ካሳ በቅድሚያ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ አንቀጽ 21(2) አስቀድሞ የተሰማራበት ቋሚ መተዳደሪያ የግብርና መስክ ሆኖ ሳለ በጥረቱ ተጨማሪ ሀብት መፍጠርና ከዚሁ የተነሳም ወደ ኢንቨስትመንት ሥራ ለመሸጋገር የበቃ ማንኛውም ታታሪ አርሶ አደር ለግብርና ሥራ የተሰጠውን የገጠር መሬት ይዞታ በዚህ አዋጅ መሠረት እንዲያጣ አይደረግም፡፡ አንቀጽ 22(3)
  • 43. 5. የገጠር መሬትን ስለመለካት፣ መረጃ አያያዝ እና አጠቃቀሙን ስለመወሰን 5.1 የገጠር መሬትን መለካት እና መረጃ አያያዝ በግል ይዞታነት፣ በወል ወይም በመንግስት የተያዘ፤ ለደን ልማት ወይም ለሌሎች መሰል ተግባራት የተከለለ የትኛውም የገጠር መሬት በባህላዊ መንገድ ወይም በዘመናዊ መሳሪያ ተለክቶ የባለይዞታዎችን የይዞታ መጠንና አዋሳኝ ድንበሮች የሚያሳይ ካርታ ተዘጋጅቶ ይህንኑ ከሚያረጋግጥ ደብተር ጋር እንደሚሰጣቸው አዲሱ አዋጅ ይደነግጋል፡፡ አንቀጽ 33(1) - (3) የትኛውም መሬት በሚለካበት ጊዜ በተቻለ መጠን የመሬቱ አዋሳኝ ባለይዞታዎች ወይም ተወካዮቻቸው በስፍራው ተገኝተው ድንበሮቻቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ ይደረግላቸዋል፡፡ አንቀጽ 33(4)፤
  • 44. የቀጠለ በመሬቱ አለካክና በድንበሩ አከላለል ረገድ ቅሬታ የተሰማው ማንኛውም ባለይዞታ ቅር የተሰኘበትን ምክንያት በዝርዝር በመግለጽ ልኬታው በተጠናቀቀ 30 ቀናት ውስጥ ጉዳዩ እንደገና ይታይለት ዘንድ በየደረጃው ለሚገኘው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አካል የማቅረብ መብት አለው፡፡ በዚህ መልኩ አግባብ ባለው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አካል ኃላፊነት የተለካ ማናቸውም የገጠር መሬት ይዞታ ለዚሁ ዓላማ በተቋቋመው የመሬት መዝገብ ውስጥ ይመዘገባል፡፡  ምዝገባውም የመሬቱን ባለይዞታ ሙሉ ስም፣ ይዞታው የተገኘበትን ሁኔታ፣ የመሬቱን አዋሳኞች፣ የለምነቱን ደረጃ፣ መሬቱ የሚውልበትን አገልግሎትና
  • 45. የቀጠለ የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃ ባሕረ-መዝገብ በሁለት ቅጅ ተዘጋጅቶ አንደኛው ቅጂ በሚመለከተው ቀበሌ ጽህፈት ቤትና ሁለተኛው ቅጅ ደግሞ ቀበሌው በሚታቀፍበት ወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ይቀመጣሉ፡፡ አንቀጽ 42(1)፤ በሁለቱ የባሕረ-መዝገብ ቅጂዎች መካከል ልዩነት ተፈጥሮ የተገኘ እንደሆነ መረጃዉ እንደገና እንዲጣራና እንዲስተካከል ይደረጋል፡፡ በሀሰተኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ የተካሄደ ማናቸውም ምዝገባ ሕጋዊ ውጤት አይኖረውም፡፡ በመዝጋቢው ስህተት ምክንያት በማንኛውም ሰው ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ ስህተቱን የፈጠረው የመንግሥት አካል በፍትሐ ብሔር እና በወንጀል
  • 46. የቀጠለ በዚህ ሳቢያ ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግሥት አካል በስህተቱ ለተጎዳው ወገን ካሳ እስከ መክፈል የደረሰ እንደሆነ ይህንኑ እንዲመልስለት ስህተቱን የፈጠረውንና ለባለዕዳነት የዳረገውን መዝጋቢ ሠራተኛ በተራው የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡ ሆኖም መዝጋቢው ሠራተኛ በኃላፊነት የሚጠየቀው ስህተቱን የሰራው ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት የሆነ እንደሆነ ነው፡፡ አስመዝጋቢዉም ቢሆን በምዝገባዉ ለተፈጠረው ስህተት የራሱ አስተዋፅኦ እንደነበረው የተረጋገጠ ከሆነ በፍታብሔርና ተገቢ ሆኖ ሲገኝም በወንጀል ሕግጋት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ የገጠር መሬት ባለይዞታ ወይም የማሳ ወይም
  • 47. የቀጠለ የምዝገባ መረጃውን ወቅታዊ የማድረጉ ተግባር በቀበሌ እና በወረዳ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴዎች አማካኝነት ይከናወናል፡፡ ለሚመለከተው አካል በጊዜው ቀርቦ ወቅታዊ ያልተደረገ ማናቸውም የገጠር መሬት የምዝገባ መረጃ ለውጥ ወይም ማሻሻያ በሕግ ፊት ውጤት አይኖረውም፡፡ አንቀጽ 43(1)፣(2) እና (6) እንዲሁም ከመሬቱ ጋር ተያያዥነት ያለውን መብትና ግዴታ የሚመለከት ማናቸውም ጉዳይ መሬቱ በሚገኝበት ወረዳ ላለው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ ካልተመዘገበ በስተቀር በሶስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብባቸው አይችልም፡፡ አንቀጽ 34(3) የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ማንኛውም ሰው
  • 48. የቀጠለ የወል መሬት ተጠቃሚዎች የሆኑ ባለይዞታዎች ይህንኑ የሚያመለክት የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በስማቸው ተዘጋጅቶ ይሰጣቸዋል፡፡ የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆኑ ተቋማትም ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በስማቸው ተዘጋጅቶ ይሰጣቸዋል፡፡ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የባለይዞታው በሕግ የተጠበቀ መብት ማስረጃ ነው፡፡ ይህንኑ የሚቃረን ጠንካራ የጽሑፍ ማስረጃ እና ይበልጥ የሚያሳምን ምክንያት ካልቀረበ በስተቀር የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በስሙ ተዘጋጅቶ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እያለ ዳኞች ሌሎችን
  • 49. 5.2 የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ስለማዘጋጀት አዲሱ አዋጅ ያካተተው አንዱ አዲስ ነገር የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ እንዲዘጋጅ የሚያስገድድ ድንጋጌዎችን መያዙ ነው፡፡ አንቀጽ 29(1-6) ይኸውም የክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ አገር አቀፉን የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ መነሻ በማድረግ ወይም ከራሱ ነባራዊ ሁኔታዎች በመነሳት በክልሉ ውስጥ የሚተገበር መሪ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ያዘጋጃል፡፡ የዞን ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መምሪያዎች የክልሉን የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ መሠረት በማድረግ በዞኑ ነባራዊ ሁኔታ የሚተገበር የራሳቸውን መሪ የመሬት አጠቃቀም እቅድ ያዘጋጃሉ፡፡ የወረዳ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽህፈት
  • 50. የቀጠለ እንዲሁም አካባቢያዊ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ቀበሌን ወይም ተፋሰስን መሠረት ያደረገና ነዋሪውን ሕብረተሰብ ያሳተፈ ሆኖ በወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽህፈት ቤት የቴክኒክ ድጋፍ ይዘጋጃል፡፡ የትኛውም የገጠር መሬት ለአንድ ለተወሰነ አገልግሎት እንዲውል የመሬት አጠቃቀም እቅድ ሲዘጋጅ የተሻለ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ የሚሰጥ መሆኑ፣ በአካባቢ ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ አለመኖሩ ወይም ተጽእኖው አነስተኛ ሆኖ መገኘቱ እና አገልግሎቱ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሆኑ እየተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል። አንቀጽ 29(7) በጥናት ላይ ተመስርቶ ካልሆነ በስተቀር በማናቸውም
  • 51. የቀጠለ  በክልል፣ በዞንም ሆነ በወረዳ ደረጃ የሚዘጋጁ መሪ የገጠር መሬት አጠቃቀም ዕቅዶች እንደተገቢነቱ አገር- አቀፉን ዕቅድ ወይም የየአስተዳደር እርከኑን ዕቅዶች ታሳቢ በማድረግ ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚሆን ጊዜ ውስጥ ወቅታዊ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡ አንቀጽ30፤  በአካባቢ ደረጃ የሚዘጋጅ አሳታፊ የገጠር መሬት አጠቃቀም ዕቅድ እንደአስፈላጊነቱ የሚከለስበትና ወቅታዊ የሚደረግበት ጊዜ ገደብ በደንብ ይወሰናል፡፡ አዋጁ የገጠር መሬት በዕቅድ እንዲመራ ለማድረግ ትኩረት ከሰጠባቸው ሁኔታዎች አንዱ ለገጠር ቀበሌ ማዕከላት መገንቢያ ቦታ አመራረጥ እና አሰጣጥ ጉዳይ ነው፡፡
  • 52. የቀጠለ በገጠር ቀበሌ ማዕከላት ውስጥ የሚተገበረው የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታ አሰጣጥ ስርዓትና ግንባታው የሚያሟላቸው ስታንዳርዶች በደንብ የሚወሰን ሆኖ ዕድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነና በቀበሌው ውስጥ ቢያንስ ለተከታታይ ሁለት ዓመት ነዋሪ ሆኖ በግብርና፣ በንግድ ወይም በሌሎች በማናቸውም መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሠራ ማንኛውም ሰው በገጠር ቀበሌ ማዕከላት ውስጥ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ያገኛል፡፡ አንቀጽ 31(5)፤ ሆኖም ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካሞች፣ ሴቶችና አረጋውያን እንደ ቅደም ተከተላቸው በማዕከላቱ ውስጥ የመኖሪያ ቤት
  • 53. የቀጠለ በገጠር ቀበሌ ማዕከላት ውስጥ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ቢሮው ለገጠር ቤቶች አሠራር የሚያወጣውን የዲዛይንና የግንባታ ጥራት መስፈርቶች አሟልተው ስለመገኘታቸው በወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ካልተረጋገጠ በስተቀር ሊሸጡ፣ የዕዳ ዋስትና ሆነው ሊያዙም ሆነ በማናቸውም መንገድ ለሶስተኛ ወገን ሊተላለፉ አይችሉም፡፡ አንቀጽ 31(5) የገጠር ቀበሌ ማዕከላት ተብለው ከተመረጡት ስፍራዎች ውጭ በእርሻ፣ በግጦሽ፣ በወል እና በደን መሬቶች ላይ ማናቸውንም አይነት አዲስ ግንባታ ማካሄድ የተከለከለ ነው:: አንቀጽ 32(1) ሆኖም የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ተዘጋጅቶ ባልተሰጠበት አካባቢ አርሶ አደሩ በመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩ ላይ ባስመዘገበው ይዞታ ውስጥ ለራሱና ለአካለ መጠን ለደረሱ
  • 54. 6. ከገጠር መሬት ጋር የተያያዙ አለመግባባቶች የሚፈታባቸው መንገዶች የገጠር መሬት ይዞታ መብት ዋስትናው የተረጋገጠ ሊሆን የሚችልባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል አንዱ አርሶ አደሮች ያላቸው የመሬት ይዞታ መብት በጊዜ የተገደበ አለመሆኑን በግልጽ በሕግ መደንገጉ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያትም በየጊዜው የመሬት ሽግሽግ እንዳይካሄድ በሕግ መከልከሉ ነው፡፡ ሶስተኛው ምክንያት ደግሞ የገጠር መሬት ባለይዞታ መሆንን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ለባለይዞታው መስጠት ነው፡፡ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች መብት ጥበቃ በሕግ በበቂ ሁኔታ መደንገጉ ብቻ በቂ አይደለም። ይልቁንስ መብቶቹ በሚጣሱበት ጊዜ አጥፊዎችን ለማረምና
  • 55. 6.1 የአስተዳደራዊ ክንዋኔዎች አለመግባባት አፈታት  በአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 33 - 43 ላይ የገጠር መሬትን ከመለካት፣ ከመመዝገብ እና መረጃን ከመያዝ እና የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለባለይዞታዎች ከመስጠት ጋር የተያያዙ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አካላት ግዴታዎች እና ሀላፊነቶች ተዘርዝረዋል፡፡  የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አካላት እነዚህን ሀላፊነቶች ለመወጣት በራሳቸው የሚሰጧቸው አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ይኖራሉ፡፡  አስተዳደራዊ ዉሳኔ ማለት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ባለጉዳዮች፣ በይዞታ መብትና መጠቀም ጥያቄ ሲያቀርቡ ወይም በተቃራኒው ግዴታወቻቸውን ሳይወጡ ሲቀሩ አግባብነት ያላቸዉን የመረጃ ምንጮች በመጠቀምና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በሕዝብ በማስተቸት ጉዳዩ በሚመለከተው የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አካል ከተጣራ በኃላ በጽሁፍ የሚሰጥ ማናቸውም ውሳኔ ሲሆን ከገጠር መሬት ልኬታ፣ ምዝገባ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አሰጣጥ፣ ከመሬት
  • 56. የቀጠለ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች የሚሰጡት ብዙ ጊዜ የገጠር መሬት ተጠቃሚዎች በሕግ የተጣለባቸውን ግዴታዎች ሳይወጡ ሲቀሩ ነው፡፡ በአዋጅ ቁጥር 456/1997 አንቀጽ 10 እና 13 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 27 ላይ የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ሰው ግዴታዎች ተዘርዝረዋል፡፡ እነዚህም በይዞታም ሆነ በኪራይ የያዘውን መሬት የመንከባከብ፣ ከመሬቱ አካባቢ ዛፍ መትከልና ተንከባክቦ ማሳደግ፣ በአስተራረስ ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ፤ በመሬቱ አካባቢ የሚገኙ የዱር እንስሳትና አዕዋፎች እንዳይጎዱ ተገቢውን ጥንቃቄ የማድረግ፤ ወሰናቸው የተከለለ መሬቶችን ድንበር ያለመጋፋትና ተለይተው የሚታወቁ መንገዶችን ያለመዝጋት፤ ለመሬቱ በወጣለት የአጠቃቀም ዕቅድ መሰረት
  • 57. የቀጠለ እነዚህን ግዴታዎች ያልተወጣ ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ ወይም ተጠቃሚ የሆነ ሰው የፍትሐ ብሔር እና የወንጀል ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ አስተዳደራዊ እርምጃም ሊወሰድበት እንደሚችሉ አዲሱ አዋጅ አንቀጽ 28 ይደነግጋል፡፡ ለመሆኑ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች የት ተጀምረው የት ይጠናቀቃሉ? የሚለውን ቀጥለን እንመለከታለን፡፡ በመሬት አለካክና በድንበር አከላለል ረገድ ቅሬታ የተሰማው ማንኛውም ባለይዞታ ቅር የተሰኘበትን ምክንያት በዝርዝር በመግለጽ ልኬታው በተጠናቀቀ 30 ቀናት ውስጥ ጉዳዩ እንደገና ይታይለት ዘንድ በየደረጃው ለሚገኘው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አካል የማቅረብ መብት እንዳለው የአዋጁ
  • 58. የቀጠለ የገጠር መሬት ይዞታን በመመዝገብ እና በማረጋገጡ ሂደት በባለይዞታዎች መካከል ክርክር የተነሳ እንደሆነ ባለጉዳዮቹ አግባብ ባለው የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴ አቀራራቢነት እንዲስማሙ ይደረጋል፡፡ በዚህ ያልተስማሙ እንደሆነ ኮሚቴው ከቀበሌው የመሬት ዘርፍ ባለሙያ በሚገኘው መረጃና አስተያየት ላይ ተንተርሶ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንደሚሰጥ አንቀጽ 38(1) ይደነግጋል፡፡ በዚህ የቀበሌው ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ወገን አቤቱታውን በየደረጃው ለሚገኘው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ አንቀጽ 38(2)
  • 59. የቀጠለ የትኛውም የገጠር መሬት ይዞታ በምዝገባ ሂደት ተረጋግጦ የተያዘ መረጃ የመጨረሻ ሆኖ ለዚሁ በተቋቋመው መዝገብ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ቅሬታ ያለው ወገን ቢኖር አቤቱታ የሚያቀርብበት ስነ ስርዓት እና የጊዜ ገደብ በደንብ እንደሚወሰን የአዋጁ አንቀጽ 40(1) ይደነግጋል፡፡ ረቂቅ ደንቡ አንቀጽ 24 የገጠር መሬት በምዝገባ ሂደት ተረጋግጦ የተያዘ መረጃ የመጨረሻ ሆኖ በገጠር መሬት መዝገብ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ቅሬታ ያለዉ ባለይዞታ በተመዘገበ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ቅሬታዉን መረጃዉን ለመዘገበዉ አካል በጽሁፍ ማቅረብ ይችላል፡፡ ቅሬታ የቀረበለት አካል ቅሬታዉ በቀረበ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ በጽሁፍ ምላሽ
  • 60. የቀጠለ ቅሬታ የቀረበለት አካል ምላሽ ካልሰጠዉ ወይም የሰጠዉ ምላሽ ካላረካዉ ቅሬታ አቅራቢዉ ቀጥሎ ላለዉ የተቋሙ እርከን በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ቅሬታዉን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላል፡፡ ቅሬታ የቀረበለት የበላይ አካልም ቅሬታዉ በቀረበለት በሁለት ወር ጊዜ ዉስጥ በጽሁፍ ምላሽ መስጠት አለበት፡፡ ይህ አካል ምላሽ ካልሰጠዉ ወይም በሰጠዉ ምላሽ ያልተስማማ ቅሬታ አቅራቢ ለመደበኛ ፍርድ ቤት በሁለት ወር ጊዜ ዉስጥ አቤቱታዉን ማቅረብ ይችላል በማለት ይደነግጋል፡፡ በሌላ በኩል የባለይዞታው ወይም የማሳ ወይም የሁለቱም ለውጥ በሚያጋጥምበት ጊዜ የመሬት ምዝገባ ሰነዱ በቀበሌ እና በወረዳ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴዎች አማካኝነት
  • 61. የቀጠለ  ኮሚቴው በሰጠው አስተዳደራዊ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን አቤቱታውን በጽሑፍ አዘጋጅቶ ለወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡  በጽ/ቤቱ ውሳኔ ያልተስማማ እንደሆነ ደግሞ ለዞኑ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መምሪያ ወይም ለወረዳ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል፡፡ አንቀጽ 43(3)  በአጠቃላይ የአዋጁ አንቀጽ 52(6) እንደሚደነግገው የገጠር መሬትን ከመለካት፣ ከማስተዳደርና ከሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተየያዘ የወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤቶች በሚሰጡት አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ወገን ይኸው በደረሰው በ30 ቀናት ውስጥ ክሱን ለወረዳዉ ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡  የወረዳዉ ፍ/ቤት የጽ/ቤቱን ውሳኔ ያጸናው እንደሆነ ይግባኙን ለከፍተኛ ፍ/ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡  ይግባኙ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤትም የሥር ፍ/ቤቱን ውሳኔ ያጸናው እንደሆነ ውሳኔው የመጨረሻ ይሆናል፡፡
  • 62. የቀጠለ  ከዚህ መረዳት የሚቻለው አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ከቀበሌ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ጀመረው በይግባኝ ለወረዳ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ከቀረቡ በኋላ ቀጥሎ በቅሬታ አቅራቢው ምርጫ ለዞን መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መምሪያ ይግባኝ ወይም ለወረዳ ፍ/ቤት ክስ ሊቀርብ እንደሚችል ነው፡፡  ይኸውም በየትኛውም ሁኔታ በየደረጃው ባሉት በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋማት አስተዳደራዊ ውሳኔ ያልረካ ሰው ለወረዳ ፍ/ቤት ክስ ማቅረብ የሚቻል መሆኑን ያሳያል፡፡  ይህም ከቀድሞው ሕግ በሁለት መልኩ የተለየ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ የመጀመሪያው የቀድሞው ሕግ በወረዳ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት አስተዳደራዊ ውሳኔ ያልተስማማ ሰው ለዞን መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መምሪያ ይግባኝ የማቅረብ መብት አይሰጥም ነበር፡፡  ሁለተኛው ልዩነት የቀድሞው ሕግ በወረዳ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት አስተዳደራዊ ውሳኔ ያልተስማማ ሰው የነበረው መብት ለወረዳ ፍ/ቤት ይግባኘ ማቅረብ ሲሆን በአዲሱ ሕግ ግን አዲስ ክስ የማቅረብ መብት አለው፡፡
  • 63. 6.2 በመደበኛ ፍርድ ቤቶች የሚደረጉ ክርክሮች  የገጠር መሬት ይዞታ ዋስትና ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች አንዱ ፍትህ የማግኘት መብት ነው፡፡  ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ የማግኘት መብት ያለው መሆኑን የኢፌዲሪ ሕገ መንግስ አንቀጽ 37(1) ይደነግጋል።  በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 4 መሰረት በቀጥታ ወይም በግልጽ ካልታገዱ ወይም ለሌላ አካል በሕግ ካልተሰጠ በቀር በፍርድ ሊያልቁ የሚችሉ የፍትሐ ብሔር ክርክሮችን አከራክሮ የመወሰን ስልጣን የመደበኛ ፍርድ ቤቶች ነው፡፡  የገጠር መሬት ክርክር በፍርድ ሊያልቅ የሚችል (Justiciable Matter) ስለሆነ በሕገ መንግስቱ በተደነገገው አግባብ በመደበኛ ፍርድ ቤት ወይም በሕግ
  • 64. የቀጠለ በአለም ላይ በብዙ ሀገሮች ከመሬት ጋር የተያያዙ ክርክሮች የሚፈቱት በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ቢሆንም አንዳንድ ሀገሮች ልዩ የመሬት ክርክሮችን የሚያዩ ችሎቶች ወይም ፍርድ ቤቶች (land courts) ያቋቁማሉ፡፡  በሀገራችን በንጉሱ ዘመን አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴ እንደተጠበቀ ሆኖ የመሬት ክርክር የሚታየው በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ነበር፡፡ አዋጅ ቁጥር 31/1967 ዓ/ም፣ አንቀጽ 28(1) ላይ አዋጁ ከጸናበት ቀን ጀምሮ በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚገኙ የገጠር መሬት ክርክሮች በሙሉ የተሰረዙ መሆኑን ስለሚደነግግ ነው፡፡ በደርግ ዘመን የመሬት ክርክር በመደበኛ ፍርድ ቤት መሆኑ ቀርቶ በገበሬዎች ማህበር ፍርድ ሸንጎ እንዲታይ ተደርጓል፡፡ አዋጅ ቁጥር 31/1967 ዓ/ም ፣ አንቀጽ 28 (2) (3) እና የገበሬ ማህበራትን ለማጠናከር የወጣ አዋጅ ቁጥር 223/1974
  • 65. የቀጠለ  የገበሬ ማህበራትን ለማጠናከር በወጣው አዋጅ መሰረት የገጠር መሬት ክርክር በቀበሌ፣ በወረዳና በአውራጃ ደረጃ በተቋቋሙ ፍርድ ሸንጎዎች ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ይግባኝ የሚታይ ነበር፡፡ አዋጅ ቁጥር 223/1974፣ አንቀጽ 36 - 40 እና ከአንቀጽ 53 - 60  ስለሆነም በደርግ ዘመን በማንኛውም ሁኔታ የገጠር መሬት ክርክር ለመደበኛ ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ ተደርጎ የነበረ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡  በአሁኑ ወቅት የገጠር መሬትን በተመለከተ ክርክር ሲነሳ በቅድሚያ በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች እንዲፈታ ጥረት ይደረጋል፡፡  ይኸውም በቅድሚያ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ተከራካሪዎች በውይይትና ስምምነት እንዲፈታ ጥረት ይደረጋል፡፡  በስምምነት ሊፈታ ካልቻለ በተከራካሪ ወገኖች በተመረጡ ሸማግሌዎች ወይም በክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና
  • 66. የቀጠለ የክልላችን አዲሱ አዋጅ አንቀጽ 52 የገጠር መሬት ይዞታና የመጠቀም መብትን በሚመለከት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችና የሚነሱ ክርክሮች የሚፈቱበትን ስነ ሥርዓት የደነግጋል፡፡ ይኸውም በመጀመሪያ ደረጃ በራሳቸው በባለጉዳዮቹ መካከል በሚካሄድ ውይይት እና በሚደረግ ስምምነት እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡ ተከራካሪ ወገኖች አለመግባባታቸውን በስምምነት ሊፈቱ ካልቻሉ ራሳቸው በሚመርጧቸው ሽማግሌዎች አስታራቂነት ጉዳያቸው እልባት እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ አለመግባባቱ በዕርቅ ያልተፈታ እንደሆነ ይኸው ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ጉዳዩ ለአቅራቢያው ወረዳ ፍ/ቤት ሊቀርብ ይችላል፡፡ የወረዳዉ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ተመልክቶ ውሳኔ የሰጠበት ማናቸውም ጉዳይ በ30 ቀናት ውስጥ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሊቀርብበት ይችላል፡፡
  • 67. የቀጠለ ይግባኝ የቀረበለት የከፍተኛ ፍ/ቤት የወረዳውን ፍ/ቤት ውሳኔ ካጸናው ውሳኔው የመጨረሻ ይሆናል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ የሻረው ወይም ያሸሻለዉ እንደሆነ ግን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ይግባኝ ሊቀርብበት ይችላል፡፡ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡ በመጨረሻ ደረጃ በተሰጡ የከፍተኛም ሆነ የጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ውሳኔዎች ላይ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት የሚል ወገን አቤቱታዉን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሊያቀርብ ይችላል፡፡  በገጠር መሬት ይዞታና የመጠቀም መብቶች ረገድ የሚነሱ ክርክሮች ከመደበኛ ፍርድ ቤት እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ደግሞ አግባብ ካለቸው የገጠር መሬት አስተዳደርና
  • 68. 7. ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮች 7.1 የፍትሐ ብሔር ሕግ አግባብነት የአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 54 በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15፣ 16 እና 17 ያልተሸፈኑ የገጠር መሬት ኪራይ፣ ስጦታ፣ ውርስና ሌሎች ፍትሐ ብሔር ነክ ጉዳዮችን በተመለከተ እንደነገሩ ሁኔታ አግባብነት ያላቸዉ 1952 ዓ.ም የፍትሐ ብሔር ሕግ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል በማለት ይደነግጋል፡፡ ይህ አገላለጽ ምን ማለት ነው? ለምሳሌ በመሬት አዋጁ መሰረት ሊወርስ ወይም ስጦታ ሊቀበል የማይችል ሰው የፍትሐ ብሔር ሕጉን መሰረት ተደረጎ ሊወርስ ወይም ስጦታ ተቀባይ ሊሆን ይችላል ማለት ነው? አይደለም፡፡  ይልቁንም የዚህ ድንጋጌ ይዘት በፍትሐ ብሔር ሕጉ የሚታወቁ አንዳንድ ጽንሰ ሀሳቦች ለምሳሌ ከወራሽነት መንቀል፣ ለውርስ ያልተገባ መሆን የሚሉና ተመሳሳይ ሀሳቦች ቢያጋጥሙ በቀጥታ እነዚህን ሀሳቦች የሚመለከቱ
  • 69. የቀጠለ ይህን ሀሳብ የበለጠ ለማጉላት በፌደራል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ ላይ የተወሰደውን ሀሳብ ማየት ይጠቅማል፡፡ … በተጨማሪም ሌሎች በፍትሐ ብሔር ሕጉ የተቀመጡ ጉዳዮችን እንደ አግባብነታቸው ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡ ለምሳሌ መጥፋትን ብንወስድ በፍትሐ ብሔር ሕጉ ተደንግጎ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው የመጥፋት ውሳኔ ከተላለፈበት በፍትሐ ብሔር ሕጉ በሚያስቀምጠው ገደብ መሰረት በጠፋው ሰው ይዞታ ስር የነበረውን መሬት ወራሾች ጠይቀው ሊከፋፈሉት ይችላሉ፡፡ እነዚህን ዝርዝር ጉዳዮች በዚህ አዋጅ ከማየት ይልቅ የፍትሐ ብሔር ሕጉድንጋጌዎች እንደ አግባብነታቸው ተፈጻሚ እንደሚሆኑ አስቀምጦ ማለፉ የተሻለ ሆኖ
  • 70. 7.2 ስለ ይርጋ የአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 55 የገጠር መሬትን በወረራ ወይም በሌላ በማናቸውም ህገ ወጥ መንገድ ይዞ በመገልገል ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው መሬቱን እንዲለቅ በማንኛውም ሌላ ሰው ወይም ሥልጣን ባለው የመንግሥት አስተዳደር አካል ሲጠየቅ ወይም በመደበኛ ፍርድ ቤት ሲከሰስ የይርጋ ጊዜ ገደብን በሥነ ስርዓት መቃወሚያነት ሊያነሳ አይችልም፡፡ ይህ አገላለጽ ሁሉንም አይነት የገጠር መሬት ክርክሮች ይርጋ የላቸውም የሚያስብል ሆኖ መወሰድ አይኖርበትም፡፡ ለምሳል ጉዳዩ የመሬት ውርስ ክርክር ቢሆን ይርጋ የለውም ብሎ ለመተርጎም ይህ ድንጋጌ አያካትተውም፡፡
  • 71. የቀጠለ  በፌደራል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ ላይ የተወሰደ ሀሳብም ይህን ሀሳብ ያጠናክራል፡፡  የይርጋ ድንጋጌዎች ለምሳሌ ጉዳዩ ከውል ጋር የተያያዘ ከሆነ የፍትሐ ብሔር ሕጉ አንቀጽ 1845 አግባብነት ይኖረዋል፡፡ ሌሎች ከወል መሬት ወረራ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ከመጀመሪያም ህገ ወጥ እና ወንጀል በመሆናቸው መሬቱን ለማስመለስ የሚደረግ ክርክር በይርጋ የሚታገድ አይሆንም፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ እንደ ሁኔታው የፍትሐ ብሔር ሕጉ የይርጋ ድንጋጌ ሕጉ ይቀበላቸዋል፡፡
  • 72. 7.3 የፍ/ቤት ውሳኔ በገጠር መሬት ይዞታ ላይ ስለሚኖረው ውጤት የአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 56 ማንኛውም የገጠር መሬት ባለ ይዞታ የፍርድ ቤት ውሳኔን ለማስፈጸም በሚሰጥ ትዕዛዝ ከይዞታው አይፈናቀልም ወይም ይዞታው ለዕዳ መክፈያ በሚል ለሌላ አካል ሊተላለፍ አይችልም በማለት ይደነግጋል፡፡ ይህ ድንጋጌ የገጠር መሬት አይሸጥም በሌላ ንብረት አይለወጥም ከሚለው ህገ መንግስታዊ ክልከላ ጋር ተያይዞ ነው መተርጎም ያለበት፡፡  ይህ ማለት በፍትሐ ብሔር ለተፈጠረ ግንኙነት የገጠር መሬት ለዕዳ መክፈያ ተብሎ አይያዝም ለማለት ነው፡፡ ይህ አተረጓጎምም ቢሆን በጠባቡ መታየት ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ ከመሬቱ የሚገኘውን ምርት ወይም መሬቱን
  • 73. 7.4 የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች የአዋጁ አንቀጽ 57 ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት ከገጠር መሬት ይዞታና አጠቃቀም ጋር በተያያዙ በሌሎች ሕጐች የተቋቋሙ መብቶችና ግዴታዎች ቀደም ሲል የነበሩ ሕጐችን መሠረት አድርገው እስከተገኙና ይህንን አዋጅ በግልጽ እስካልተቃረኑ ድረስ ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል፡፡ ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት ፍርድ ቤት ቀርበው በመታየት ላይ ያሉ ማናቸውም መሬት-ነክ ጉዳዮች በተጀመሩበት አግባብ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ ይህንን አዋጅ በግልጽ እስካልተቃረኑ ድረስ ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል የሚለው አገላለጽ ምን ማለት ነው? ለምሳሌ በቀድሞው አዋጅ መሰረት የቤተሰብ አባል በመሆን መሬት ካለው የሟች ልጅ ቀድሞ የወረሰ ሰው ቢኖር አሁን ካለው አወራረስ