SlideShare a Scribd company logo
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቢ
ጉባኤ
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
ቸርነት እንግዳው(ገብረ ኪዳን)
11/13/2015
ጥበብና ምክር ፤ ሃይልም ከርሱ ነውና የእግዚአሔር ስም
ከዘላለም እስከ ዘላለም የተመሰገነ ይሁን (ዳን 2፡20)
በአክሱም ዩንቨርስቲ ግቢ ጉባኤ
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ማሳሰቢያ ፦ ኮፒ ማድረግ የተከለከለ ነው
እግዝትነ ማርያም
“የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ”
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
ተዋናይ
1. ሳምሶን
2. ሰናይት
3. ራሄል
4. እንደልቡ
5. ደባልቄ
6. ከበደ
7. ትግስት
8. ፖሊስ
9. ከበቡሽ
10. ዘበኛ
11. አረጋዊ ሽማግሌ
12. አረጋዊት ሴት
ትእይንት 1
ራሄል ፦ ሰናይት ዛሬስ ሳምሶን በጣም አረፈደ እንዳው ሙሁኖት ነው።ሁሌ ቶሎ ነበር
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
የሚመጣ።
ሰናይት፦ እማ ስራ አግኝቶ እየሰራ ይሆናል እንጅ ቶሎ ይመጣነበር።
ሳምሶን ፦ ምነው ዛሬስ ደግሞ እንዴት ያለ ቀን ነው ።ጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቁጭ ብየ ሁለት ብር ብቻ ነው
የሰራው ። አሁን ደግሞ እነማየ ብር ያመጣል እያሉ እየጠበቁኝ ይሆናል። በአንዲቱ ብር ዳቦ በለውባት ደግሞ አንዲት
ብር ብቻ ናት ያለችኝ ምነው ጌታ ዝናቡ ባጥለቀለቀውና ጭቃ በጭቃ ባደረገው ከዚያ ሁሉም ሊያስቀባ ይመጣ
ነበር።እያለ ይሄዳል እማ እንዴት ዋላቹ
ራሄል ፦ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ዋልክ ሳምሶንየ በጣም ዘገየህ።
ሳምሶን ፦ ደህና እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ናቹ ኧህ ብሎ ቁጭ ይላል።
ራሄል፦ ሰናይት እስኪ ትንሽ ብር ካለው ጠይቂው ና ጥሬ ጨው ገዝተሽ ነይ።
ሰናይት፦ ሳምሶን ካለህ ስጠኝ?
ሳምሶን ፦ አይ ሰናይት ዛሬ ይገርምሻል ምንም አልሰራሁ ግን የሰረዋት አለች እንች።
ተቀብላ ወደ ውጭ ትወጣለች
ራሄል፦ ሳምሶን ምሁነህ ነው ዛሬ ፊትህ ሁሉ ተከፍቷል
ሳምሶን ፦ እኔን ያልከፋ ማንን ይክፋው? የት/ቤት ጓደኞቼ ይሽሹኛል ። ሊስትሮ ተራ ከእኔ ዘንድ የሚያስቀባ
የለም ።ከዚህም በላይ በዚች ዶሳሳ ጎጆ እየኖርን ሲርበን ሳይ ለምን አልከፋም? መጨነቅ ይነሰኝ? እያለ ያለቅሳ
ራሄል፦ ተው ልጄ እንዲህ እየተጨነቅህ እኔንም እህትህንም አታስጨንቀን ።እኔ እንጀራ እየጋገርሁ አመጣለሁ
ለእለት ሆዳችን እንችላለን። ተው እግዚአብሔር ምግባችን ያዘጋጃል ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የሰማይ ወፎችን
ተመልከ,.....
ሰናይት ከውጭ ትመጣለች
ሰናይት፦ ይችን ትንሽ ትንሽ እያደረግን ለዚህ ሳምንት ትሆነናለች።
ሳምሶን፦ በይሰናይት ምሳ አቅርቢ እና እንብላ
ሰናይት፦ እሽ
ሲበ ሉ
ሳምሶን፦ እኔማ እማየ የሚገርመኝ ዓንድ ነገር አለ;ይችን ቁራሽ እንጀራ እንዲህ ሶስት ሆነን ስንበላ ሰላም እና ደስታ
ይሰማኛል ።የኛን ሰላም ሃብታሞች የሚያገኙት አይመስለኝም።
ራሄል፦ አይ ልጀ በዚም ትጠራጠራለህ? ሃብታም እንደሆነ ሁሌም ጭንቀታም ነው።አንድ ጊዜ እንኳን ሰላም
የለውም ።እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል መሰለህ ባለሃብት የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም
ባለሃብት የእግዚአብሔርን መንግስት ከሚወርሱ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብታልፍ በቀለለ። በዚህ አጋጣሚ ዱሮ
ከእናት እና ከአባቴ የወረስኳቸው እኒህ ሁለት ቀለበቶች አሉኝ ።ስለዚህ አሁን አስርላችኋለሁ ። ሳስርላቹ ዝም ብየ
አይደለም፤አደራ ልጆቼ በሀብትም ሆነ በብር እንዳያታልሏችሁ እምነታችሁን ጠብቁ ።የኔ የዕናታችሁ ፍቅር
እንዲያድርባችሁ አሰርኩላችሁ።
ሳምሶን፦ ሰንየ ት/ቤት እንሂድ
ሰናይት፦ እሺ ደህና ዋይ እማ!!!!
ትእይንት 2
ደባልቄ፦ ኧረ ከቤ ከበቡሽ አሰሚም እንዴ
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ከበቡሽ፦ አቤት!!!!ምሁነህ ነው ዝግ በል ልመጣ ነው!!!!!!!!
ደባልቄ፦ መጋዘኑን ዘግቸ ነው ቁጭ ያልኩት ምሳ አምጭ1!!!!!!!!!!!!!!!! ደግሞ ልትቆጣ
ከበቡሽ ምሳ ይዛ ትመጣለች
ደባልቄ፦ ኧረ ወዲያ አንሽልኝ፤ ትናትና ሽሮ ዛሬ ሽሮ ነገም ሽሮ ኧረ መቸ ነው ስጋ የምትሰሪ።
ነጋ ነጋ ሽሮ እየበለው እራሴም ፎረፎር ሆነ ሽሮው በአናቴ ወጣ!!!!!!!!!!!!!!
ከበቡሽ፦ ከተማውን በሞላ ዙሬዋለሁ ያላደረስኩት የለም አሁን እማ ስሰማ የኦርቶዶክስ
ጾም ነው አሉ ።
ደባልቄ፦ እነሱማ ወይ መጽሐፉን አያውቁ እረበሹን ። ታዲያ እንግዲህ የነሱ ጾም ባላለቀ
ግዜ እኛ በሽሮ አናልቅም ። በግ ቢሆን ገዝተን በብላት አለብን።
ከበቡሽ፦ እሱም አዎ ግን የሚገርመኝ ነገር አለ ። የኛን እንጀራ ጋጋሪ ታውቃት አይደል
ደባልቄ፦ ራሄል ናት
ከበቡሽ፦ አዎ አንድ ቀን ብላ ከኛ እንጀራ በልታ አታውቅም ።ብይ ብየ ስሰጣት እንኳ ስጋና
ቅቤ ያለበትን አትቀበልም ። ደረቁን እንጀራ ነው ይዛ የምትሄድ። በጣም ታሳዝነኛለች።
ደባልቄ፦ ግን ለልጆቹ ይዛላቸው ትሄዳለች ?
ከበቡሽ፦ እሱማ ትንሽ ትንሽ ይዛላቸው ትሄዳለች የልጆቿ ነገር ሞቷ ነው።
ደባልቄ፦ ታዲያ እንዲህ የምትወዳቸው ልጆች ሲራቡ ከምታይ ለምን ከኛ ገብተው
እንደልባቸው አይሆኑም ። ወንዱ ልጇ ጎበዝ ተማሪ ስለሆነ ልጆቻችን ያስረዳልናል ። ሴቲቱ
ደግሞ የቤቱን ስራ ትሰራለች ። ከዛ የኛ ልጆች ጎበዝ ይሆናሉ። በዛውም ጌታን ይቀበላሉ
ከበቡሽ፦ እሽ ብላ ትለቃቸው ብለህ ።የልጆቿ ነገር ሞቷ ነው።
ደባልቄ፦ የእኛ ልጆች በዳቦም በቸኮሌት በሌላ ነገርም አታለው ያመጧቸዋል
ከበቡሽ፦ እሱማ በቀር እነ ከቤ ለነዚህ ነው።
ደባልቄ፦ በይ እኔም መጋዘኑን ዘግቸ እስከ አሁን ደንበኞች እየመጡ ተመልሰው ይሆናል
በጣም ረፍዱአል ለልጆቹምሳ ስጫቸውና ይሂዱ።ደህና ዋሉ
ትእይንት 3
ሰናይት፦ እማየ የሰጠችን ቀለበት እንዴት ያምራል
ሳምሶን፦ አየሽ ላይ ከቀለበቱ የበለጠ የሚታየኝ የእማየ ፍቅር ነው።እማየየኛን ፍቅር
የምትገልጥበት ብታጣበዚህ ገለጠችልን። አይ እማ በጣምእኮነው የምትወደን።
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ሰናይት፦ አሁን እኔን ቢርበኝ ይህን ሽጨ ልብስ ጫማ ሌላም አደረገዋለው
ሳምሶን፦ ኧረ ዝም በይ” በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ” እንዴ ምን ነካሽ። ይህን ሸጥሽ ማለት
የናትሽን ፍቅር ሸጥሽማለት ነው። ደግመሽ ይህን ሐሳብ እንዳታነሽው
ከነ ከበደ ጋር ይገናኛል
ትግስት፦ ሳምሶን እንዴት ናቹ?
ሳምሶን፦ ደህናደና ናቹ? እያሉ ሰላምታ ይለዋወጣሉ
ትግስት፦ ግን እናንተ ሁሌ ተሎ የምትመጡ ምን ግዜ ቁርስ ትበላላቹ?
ሰናይት፦ እኛ እኮ ቁርስ ሁሌ አንበላም። አብዛኛው ቀን ጾምነው። ደግሞጾምባይሆን ማታ ከእራት
ከተረፈ ነው የምን በላ ።ለ ቁርስ ተብሎ በልተን አናውቅም።
ከበደ፦ አ!!!!!!! ትራፊ! የኛ ድመቶች ትራፊ ቀርቶ ዳቦ አይበሉም።ኽ!!!!!እኛ እኮኩርስ
የምንበላው በፕሮግራም ነው ። ሠኞ እሮብ እና አርብ እንቁላል ፍርፍር ሌላው ቀን ደግሞኬክነው
ትግስት፦ ደግሞ ምን እንደሆነ ታውቃላቹ የተረፈውን የሚበላው ስለሌለ ሽንት ቤት ይደፋል። ኧረ
ከቤ በ ኢየሱሴ የተሰጠነውን ዳቦ እንስጣቸው ። ይሰጡዋቸዋል
ኋላ የምናወራቹ ስላለ ጠብቁ
ሳምሶን፦ አንዲቱን በልተን አንዲቱንለእማ ይዘን እንሄ ዳለን።
ሰናይት፦ ኧረ ሁሉን ነው የምንበላ እቢ እኔ እርቦኛል።
ሳምሶን፦ ተይ እማንምእኮ ይርባታል ። እሷ እኳ ከእኛ ተለይታአትበላም
ሰናይት፦ እሺ
ሳምሶን፦ ቆይ እነሱ መናፍቅ ስለሆኑ ስጋቅቤ ጨምረውበት ይሆናል አንበላም። ደግሞዛሬ ጾም
ነው።
ሰናይት፦ ባክህ እርቦኛል እንብላ። አንተ ተወው እኔእበላለው።
ሳምሶን፦ ፍጽምአይሆን ም እንዳውም ቅዱስ ፓውሎስ መልክት እያነሳች ስለ ሃማኖታችን
ትነግረናለች።
ሳይበሉ ተነስተው ይሄዳሉ በመንገድ ላይ ይገናኛሉ
ትግስት፦ ሳምሶን ሳምሶን የምናወራቹ አለን ብለናቹ አይደል
ሳምሶን፦ አ ብላቹን ነበርለካ እረስተን እኮነው
ከበደ፦ እኛ እኮ የእናንተ ነገር በጣም ነው የሚያሳዝነን ፤ ስለዚህ ወደኛ ቤት እንሂድ እና እንደልባቹ
ትኖራላቹ ። ትምህርትህም ጎበዝትሆናለህ ።
ሳምሶን፦ ኧረ እናታችን ትተን አንሄድም
ትግስት፦ እናታችሁምከተስማማች ከእኛ ትሆናለች
ሳምሶን፦ እማየማ ትልቅ ነገር አላት ።እኛ ትተናት እንዳንሄድ፤ ሃይማኖታችን እንድንጠብቅ
በኦርቶዶክስ እንድንጸና ብላከእናት እናከአባቶቿ የወረሰያቸውን ሁለት ቀለበትለኛ ሰጠችን።ይህ ደግሞ
የናታችን ፍቅር በልባችን ሰርጿል። ምንምቢሆን አንሄድም።
ከበደ፦ በኦርቶዶክስ ተው እንጅ ያረጀ እምነት ይዘህ ስትጠራው አታፍርም ለማንኛውምአስቡበት
እንዲህ መከራህን አትይ ቻው
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ትእይንት 4
ከበደ፦ ደህናዋልሽ እማ
ከበቡሽ፦ ደህናደና መጣቹ ልጆቸ ። ዛሬስ ዘጋያቹ ምነው በሰላምነው
ከበደ፦ ትናንትናያወራቹን እያነጋገርናቸው ነበር።
ከበቡሽ፦ አይ የኔ ልጆ ጎበዝ እኮ ናቹ ። ታዲያ እንዴት አሏቹ
ትግስት፦ አይ እማ ቀላል መሰሉሽ። መጨረሻማ ምን አሉ መሰለሽ2
ከበቡሽ፦ ምን በጉጉት
ከበደ፦ ሁለት ድቃቃ ቀለበት አስረውይህ የእናታችን ትተን እንዳንሄድ ከአባቶቾቿ የወረሰቻቸው
ናቸው ብለው አሳዩን
ከበቡሽ፦ ይች ደሃ የትአባቷ አግኝታው ነው የኛን ሰርቃ ነው የሚሆን አፈርትብላባቷ ቆይ ይች ድሪቶ
ከከከከከ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ደባልቄ፦ ከውጭ ሃሎሃሎሃሎ መኪናው ደረሰ ቡና የያዘው መኪና አልደረሰም። ዛሬ በጣምነው
የተናደድኩት 10000ብር ብቻ ሰርቸ ልዋል ወይኔ ከሰርኩእዲያ ኢየሱሴ ጌታ ነው ሃሌ ሉያ ደና ዋላቹ
እንዴትዋላች ።ትምህርትስ እንዴት ነው ። የኔ ልጆች እኮጎበዝ ናቹ ዘንድሮተሸላሚ ናቹ።
ከበቡሽ፦ ባክህ አትነዝንዛቸው ምሳአልበሉምልስጣቸው።
ደባልቄ፦ ምን ነው እስከ አሁን ?
ከበቡሽ፦ ትናንት የነገርናቸውን እያወሩኝነበረ።ከቤ ሂዱ አመጣላችኋለው መኝታ ክፍል
ከበደ፦ እሺ እማዬ
ይወጣሉ
ከበደ፦ ስሚ ትግስት ኳስ ልጫወት ልሄድ ነው ኳስ ነው የሄደ ብትይ እየሱሴን አርድሻለው
ትግስት ፦ እኔም ከጓደኛቼ ጋር ልጫወት እሄዳለው
ደባልቄ፦ መቸም የኔ ልጆች ለነሱ ያመጧቸዋል ።
ከበቡሽ፦ ቀላል መሰሉህ እነዚያ ነቀዝ ናችው፤ ዓቤት ይገርማሉ ፤መጨረሻማ ምን አሏቸው መሰለህ ፤
ሁለት ቀለበት አስረው እናታችን ትተን ትተን እንዳንሄድ ከአባቶቾቿ የወረሰቻቸው ናቸው ብለውአሳዩን
አሉ
ደባልቄ ፦ ዝቦች ”ለአህያ ማር አጥማትም”አለ አባቴ። ይች ደሃ የኛን ሰርቃ ነው እንጅ እስከ ዝር ማንዝሯ
ደሃ አይደል ዘራቸው፤ ወይኔተጫወተችብኝ!!!!! ስለወርቁ ግን ችግር የለውም እኛ ብዙ ወርቅ ደማቅ
የሚያጭበረብር እንሰጣቸውና አታለውይዘዋቸው ይመጣሉ።
ከበቡሽ፦ አዎ የኛ ልጆች ባለፈው አመት ትዝአይልህምእነዚያን 5 ተዋህዶ ተከታዮች ሲያሳምኑ ትዝ
አይልህምእንዴ ?
ደባልቄ፦ አዎ እኛም እሷን እናሳድዳታለን፤ ክፉ አመል አለባት ሌባ ናት እያልኩ ከቦተዋ ሁሉ
አስለቅቃታለሁ። በይ አሁን መኪናው ስለ ሚገባ ልሂድ ። ሁሉንም ወርቅ አውጥተሽስጫቸውና ይሂዱ ።
ደና ዋሉ
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ትይንት 5
ሳምሶን ሊስትሮተራ ይታያል
ሳምሶን ፦ አባት ናጫማህን ላሳምርልህ አምጣው
እንደልብ፦ ዘወርበል የሌባ ልጅ እማጨስበትና እምቅምበት አጥቸ ጫማ ትለኛለህ ። አንገቱን ጨብጦ
ስማ ዳግምእንዲ ብትለኝእገልሃለህ እሽየገረድ ልጅ ሂድ
ሳምሶን ፦ እግዚአብሔር ተው እኔን ባሪያህን ስማኝ
ሰናይት ወደ ሳምሶን ትሄደለች
ከበደ፦ ዘራቸው ደካማ ድሃ ናቸው አሉ ።
ትግስት፦ አንዳንዱ ኦርቶዶክስነው እንጂደሃ እኮነው።
ከበደ ፦ ያ መጣች ሰኒ ሰናይት ቆይንማ እየጠራንሽአሰሚም።
ሰናይት፦ አልሰመዋቹምነበር።
ትግስት፦ ደህናነሽሰኒ ማር።
ሰናይት፦ እግዚአቤር ይመስገን ።
ከበደ ፦ ምን ነው የት እየሄድሽ ኑሮ ነው በጣምስንፈልግሽአገኘንሽ።
ሰናይት፦ ከሳምሶን ጋ ነበር የሚሄደው ምሳ ስላልበላና ልለው ። በሰላምነው የፈለጋቹኝ
ትግስት፦ የምትበሉት አጥታቹ ነው ወይኔሲያሳዝን ።
ሰናይት ፦ አይ አይደለምጥዋት ስለረፈደበትሳይበላሂዶ ነው
ትግስት ፦ ከኛ እኮ ብትሄዱ ይህን ወርቅናብር እንሰጣችኋለን
ከበደ ፦ እይ ተመልከች ብሩን ሁላ እይ
ሰናይት፦ ሲአምር
ከበደ፦ ደሞ ምን መሰለሽ ከኛ ከሆናቹ አንችምሳምሶንም በጣም ጎበዝ ትሆናላቹ ስራምእኮ የለባቹም
ትሄጃለሽአትሄጅም?
ሰናይት ፦ እናቴንናሳምሶንን ትቸ አልሄድም።
ሳምሶን ጋ ይደርሳሉ ሰላምታይለዋወጣሉ
ሳምሶን ፦ ዛሬስ በዚ መጣቹ በሰላምነው ከቤ ቲጅ
ትግስት፦ ሰኒን መንገድ ላይ አገኘናትና አንተን ሰላምእንበልህ ብለን መጣን።
ሳምሶን ፦ ነው ደናናቹ ።
ሰናይት ፦ የተገዛልንን ወርቅ ልናሳይህ ነው።
ከበደ ፦ ደግሞ ምን መሰለህ? እኛን እኮየናናንተ ነገር በጣም ነው የሚያስዝነን እዚ ፀሓይ ላይ ቁጭ ብለህ
ስትውል ታሳዝነናለህ ግን ወደኛ አትሄዱም
ትግስት ፦ አየህ የተገዛልን ወርቅ ተመልከት ከኛ ብትሄዱ ይህን እናሰጣችኋለን።
ሳምሶን፦ በጣምያምራን ግን የኛም እናታችን ቀለበት አለችን።
ከበደ ፦ አ!!!!!! ይህንና እሱን ቆሻሻ አንድ ታደርጋለህ ።
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ሳምሶን፦ አይ ከአሁኑ ከሚአጭበረብር ወርቅ የድሮው ደብዛዛው ይሻላል ይላሉ :: ደግሞቅዱስ ጳውሎስ
መመልክቱ እኛስ አገራችን በሰማይ ነው ብሏአል በሃብትና በንብረት ሃይማኖታችሁን አትለውጡ ሃብት
እረጋፊ ነው ነገር አላፊ ነው ይላል ። ምን አንሄድም ፍጹም
ከበደ ፦ አ!!!!!!!!!!!!!!! ቆሻሻ በዚህ አስተሳሰብህ እማ መቸምአትለወጥም ቅዱስ ጳውሎስ ምናምን
ትዘረዝራለህ እስከ ዘራቹ መጽሐፍ ቅዱሱን አውቃቹትነው ይልቅ አስብበትናወደኛ ብትመጣይሻልሃል
ቻውው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!1
ይለያያሉ
ሰናይት፦ ሳምሶን ወርቃቸው እንዴት ያምራል በማርያም አንዳንዴ እማ ሳትሰማ እየሄድን ከነሱ ጋ
አብረን እንዋል
ሳምሶን፦ ምን ተይ እማን ትተን የየትም ይሁን የትም አንሄድ !!!!!!!!!!!!!!!!!1 ደግመሽ እንዳታወሪኝ
!!!!!!!!
ሰናይት ፦ ከሁላቹም እኔ እኮነኝ በታም የተሰቃየሁ። አንተ በዛው ሰርተህ ትበላለህ እማየምእንጀራ
ከምትጋግርበት ትበላለች ። እኔግን ቤት ቁጭ ብየ እሰቃያለሁብላበንዴት ገፍታ ትጥለዋለች
ትእይንት 6 መዝ ኧረ አንች አለም
ከቤት ይደርሳሉ
ሰናይት፦ አሁን አልስማማምአልክአይደል
ሳምሶን፦ ተይኝ ተይኝ። እባክሽአትነዝንዥኝ !!!!!! ግን አታርፊም ሰይጣን እንዳያሳስትሽ ተጠንቀቂ
ልበ አምላክ ዳዊት እኔስ ከእግዚአብሔር ጋር መኖርን መረጥኩ ይላል ከዛ ሄድሽ ማለት እኮ
እግዚአብሔርን እረሳሽጸሎት አታደርጊ ደግሞብርሃነ አለምቅዱስ ጳውሎስ ምን ብሏል
ስለ፡ሥጋ፡ማሰብ፡ሞት፡ነውና፥ስለ፡መንፈስ፡ማሰብ፡ግን፡ሕይወትና፡ሰላም፡ነው።
፤ስለ፡ሥጋ፡ማሰብ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ጥል፡ነውና፤ለእግዚአብሔር፡ሕግ፡አይገዛምና፥መገዛትም፡
ተስኖታል፤፤በሥጋ፡ያሉትም፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡ሊያሠኙት፡አይችሉም ስለዚ ለስጋሽ ይመችሽ ይሆናል ለንፍስሽ
አይመችሽም
ዛሬ ወደ ንሰሐ አባታችን እንሄዳለን
ራሄል ከውጭ ትገባለች
ራሄል ፦ ምን ሆናቹ ነው የምትጮሁ ውጭ መንገድ ድረስ ይሰማል
ሳምሶን፦ ባክሽበማይሆን ነገር ነው የምትጨቀጭቀኝ።
ራሄል ፦ ምንድር ነው ሳምሶን ሰናይት
ሳምሶ፦ እነ ከበደ መጡ እና ከኛ ቤት እንሂድ አሉን ።
ራሄል፦ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱአምላክ አይ አምላኬየፈራሁትን ነገር አመጣህብኝ።
ኧረ ድንግል ማርያምእንደ ሃጢአቴ ሳይሆን እንደ ቸርነቱ እንዲሆንልኝ ለምኝልኝተይ ሰናይት በልተሽ
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ጠግበሽባታድሪ በእኔበናትሽፍቅር ጠግበሽታድሪያለሽ ይህን ሃሳብሽን አውጥተሽታይ፤ እኔስ ወንድምሽ
አናሳዝንሽም ። ተይ ኋላ ይቆረቁርሻል ። እያለች እያለቀሰች ትመክራታለች
ትእይንት 7
እንደልቡ፦ ዛሬስ ምን አይነት ቀን ነው ። ከኪሴ አንድምብር የለኝ ። በምን ቅሜ አጭሸ ነው የምውለው
ጌታ አንጠው እስከ ሻንጠው። ምን አማራጭ አለኝ። መስረቅ ግን በመነኻርያ አንድቱ ከአረብ ስትመለስ
ባገኛት ገልብጨነው የምጥላት ወይምሱቅ እዘርፋለው እያለ በድንገት ደባልቄንከሩቅ ያየዋል ያ ያው
መዝረፍ አለብኝ ። አውቀዋለሁእሱግን የሚያውቀኝአይመስለኝም
ይገናኛሉ
ደባልቄ፦ ሃይ እንደልቡ
እንደልቡ፦ ደናዋሉ አቶ ደባልቄ?
ደባልቄ፦ ስፈልግህ አገኘውህ ።
እንደልቡ፦በሰላም ነው?
ደባልቄ ፦ ሰላም ነው የኛን እንጀራ ጋጋሪ ታውቃታለህ።
እንደልቡ፦ የትኘዋን ብዙ ናቸው ሁለት ልጅ ያላት ራሄል ድሃዋ የምትባለው ናት ወይስ ሌላ ቀይረሃል
ደባልቄ ፦ አዎ ግን ልጆቿን ወደኔላመጣቸው ነበር ። እሷ ግን አልሰጠኝአለች ፤ ያላደረኩት የለምሌባ
ናት ብልምሲቸግራት ትለቃቸዋለችብል አለቀቀቻቸውም ። አሁን የቀረኝአንተን ብቻ ማናገር ነው ታዲያ
እንዴት ትላለህ ?
እንደልቡ፦ ሃሃሃሃሃሃሃ ታዲያ ለዚ ነው ግን ሃብታሞች ስትባሉ ትንሽቀርቀብ እ ትንሽጠቀም ያለች
ቻፓ ትጠይቃለች እንጅ እንኳን ይችን ዶሳሳቀርቶ ሌላምጉድ እሰራለሁ
ደባልቄ : ኸኸኸኸኸኸኸ ታዲአ ለብር ነው ወይኔደባልቄ ይህ መኪናና ፎቅ ምን ይሰራል ጌታ ይባረክና
መሰለህ ያዝ ዪሄው ከፊትህ ላይ ነው ዱቅ የማደርግልህ ግን አደራ
እንደልቡ፦ እሽ ችግር የለምደና ዋል።
ይለያያሉ
ሰናይት ወደነ ደበልቄ ስትሄድ ትታያለች (መዝሙር ዴማስ ሆይ ተመለስ)
እንደልቡ፦ እውር አሞራ ቀላቢው እግዚአብሔር እያንከለከለ አመጣው ስልክ አጥቶ
ይደውላል ሃሎ ዛሬ በታም እፈልግሃለሁ
ፖሊስ ፦ ሰርቀህ ተይዘህ ነው አንተ ሌባ ለማንኛውም መጣሁ ጠብቀኝ
እንደልቡ ፦ እሽ ቶሎ ና
ትእይንት 8
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ሳምሶን ፦ እማ ሰናይት ከሄደች ወዲ ሰላሜን አጣሁምንም እኳ በልተን ጠግበን ባናድር 3 ሁነን ቁጭ ስንል
ደስ ይለኝ ነበር ዛሬስ በጣምጨነቀኝየሰናይት ትታን መሄዷ ጉድ ሰራኝወይኔእህቴ የሚአልፍላት መስሏት
ተሰቃየች
ራሄል ፦ አይ ልጀ እሷማ ገንዘብ አታለላትና ትታን ሄደች በሆዴ ገብታ እረመረመችኝ እንዴትስ ልርሳት
ወይኔልጀ ለፍቸ አሳድጌትተሽኝሄድሽ ለማንኛውምድንግል ትከተልሽ።ልጀግን አታስብ እግዚአብሄር
ከፈቀደ አንድ ቀን ትመጣለች ። ሃዘን በተሞላ ድምጽ እያለቀሰች
ሳምሶን ፦ እማ ምግብ ከበላን ሶስት ቀናችን ነው ዛሬስ እራበኝችግሮች ሁላ ተደራረቡብን።ሊስትሮ ተራ
እየሰደቡኝ ነው የ ሄዱ አንዱስ ይባስ ብሎመታኝ ምን ባደርግ ይሻለኛል።ምን ስራ ልፈልግ ከሊስትሮውጭ
ሌላ አማራጭ የለኝም
ራሄል ፦ እንዴት ላርግ ልጀእንጀራ የምጋጋርላቸው እንኳ ምን እንዳደረግኋቸውሳላውቅ ኧባረሩኝምን
ላድርግ ጨነቀኝ ልጀእሱ ያመጠውን እሱ እስኪመልሰውዝምብሎ ማየት ነው
ሳምሶን ፦ እስከ መቸ ነው ጌታ እኛን የማያየን ብሎ ስቅ ስቅ ብሎያለቅሳል
ራሄል ፦ ተውልጀ ዝም በል እያለች እራሱን ትዳብሰዋለች
እንደልቡ ከፖሊስ ጋር ሁኖ ወደነሱ ይሄዳል
ፖሊስ ፦ ኧዚቤት ሰው የለም
ሳምሶን፦ አቤት ማን ነው ሲያያቸው ይደነግጣል
ፖሊስ ፦ እናትህ የለችምጥራትማ
ሳምሶን፦ እማየ ቦሊሱ ይጠራሻል
ራሄል ፦ ምን ሙሁኑአቸው ነው
ፖሊስ ፦ በዚ ሰፈር አንድ እቃ ጠፍቶ ሁሉን አይተን የናንተ ቤት ነው የቀረ አንዴ ወጣ በሉልን
ሳምሶን፦ ኧረምንምየለም ይችን ፌስታል ባለፈው በዝብርድ ስለሚገባብን ለመወተፊያ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ
አምጥቻለሁሌላ ምንም የለም
ፖሊስ ፦ ዝበል ሌባ ብሎ በጥፊ ይቃጠዋል
ራሄል ፦ ተው ልጀን እዳትመታብኝ ግቡናእዩ የደሃ ቤት ምንም የለው
ፖሊስ እናእንደልቡአዩን አላዩን ብለው የያዙትን ይደብቁና
ፖሊስ ፦ ወይዘሮራሄል ነይ አንተምና ይህ ማን ነው ያመጣው ተናገሪ!!!!!!!!!!!!1
ራሄል ፦ ኧረ እሱን አይቸው አላቅም ከኔ ቤትምአልነበረም
ፖሊስ፦ ኣ ምን አልነበረም እንግዲያ ማን አመጣው ይህ ሌባ ልጅሽነው ብለ
እያዳፉ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዘዋቸው ይሄዳሉ
በማረሚያ ቤት ውስጥ
ሳምሶን ፦ ብዙ ተኛው አይደል እማ ኧኧኽ ትናንት ብዙ በድለውሻል አይደል እኔእኮየመቱሽ
አልመሰለኝም
ራሄል ፦ ደናነኝ አንተን ነው የበደሉብኝ
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ትእይንት 9
ከበደ ፦ ሰናይት!!!!!!!!!!! አትመጭም እርቦኛል ምሳአምጭ ፈጠን አንች የገረድ ልጅ።
ሰናይት ፦ ከቤ ቤቱን እየወለወልኩ ምንምአላዝጋጀው ትንሽጠብቀኝ
ከበደ ፦ ኣኣ !!!!!!!!!!!!!1 ያነን ችጋርሽን በ ኔ ላይ ልትወጭ ነው አንች የሴት ልጅ ይልናበጥፊ ብሏት
ይሄዳል
ሰናይት፦ ወይኔያልፍልኛል ብየ እናቴንምወንድሜንምትቸ መጥቸ ልሰቃይ እማ ማሪኝመቸምእንግዲ
አላገኛቸውምበዚሁሌ ተደይኔመኖር ነው ሰቅሰቅ ብላታለቅሳለች
ትእይንት 10
ሳምሶን ፦ እማ መውጫችን እየደረሰ ነው
ራሄል ፦ አዎ አሁን እንወጣለን
ፖሊስ ፦ ወይዘሮራሄል የቅጣት ጊዜአቹን ጨርሳችኋል ደግማቹ ይህን ስራ እንዳትሰሩ አንተ ሌባ ዳግም
ይሂን ስራ እንዳትሰራ ። በሉ ጓዛችሁን ያዙናውጡ
ራሄል ፦ እሽ እግዚአብሔር ይስጥልኝደናሁኑ ጤና ችሁን ይስጣችሁ
በመንገድ
ሳምሶን ፦ እማ ተመልሰን ወደዚያ ወደ ቀድሞቤታችን ልንሄድ ነው ?
ራሄል ፦ አይ ልጀ በዚያ ተቀድሰን በነበርንበትእንዲ ሲያርክሱን ባልዋልንበት ነገር ሌላቦታነው
የምንሄድ አይዞህ በርታ እግዚአብሔር ባታ ያዘጋጅልናል
ሳምሶን ፦ እማ ቤተ ክርስቲያን እዚ አለ እንሳለም
ይጸልያሉ አቡነ ዘበሰማያት
ራሄል ፦ አቤቱ ልጆቸን ተብቅልኝ
ይቀመጣሉ
አንድ አረጋዊ ያገኛቸዋል
አረጋዊ ፦ አይ ጉልበት ደከመድሮእንዳሮጥኩበት ደህናዋላቹ ልጆቸ?
ራሄልና ሳምሶን ፦ እግዚአብሔር ይመስገን ደህናዋሉ አባታችን?
አረጋዊ ፦ እግዚኣብሔር ይመስገን ። ሳያችሁ ከሩቅ የመጣቹ ፤ የደከማቹ ትመስላላቹ፤ለቦታውም እንግዳ
ናቹ መሰለኝ።
ራሄል ፦ አዎ አባ ከሩቅ መንገድ ስለመጣን በጣም ነው የደከመን ።
አረጋዊ ፦ አፈር ልብላ ተነሱ የኔ ቤት እዚ ቅርብ ነው እንሂድ። ቤት የእግዚአብሔር ነው። ከወደየት
እየመጣቹ ነው ወዴትስ እየሄዳቹ ነው?
ራሄል ፦ ከቤት እንድረስ እናእናወረዋለን ። ብዙ ነው አባታችን
አረጋዊ ፦ አይዟቹ እየደረስን ነው ።
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
አረጋዊ፦ እንደልቤ ነይማ እንግዳ አምጣቻለው የሆነ ውሃም ምግብም ስጫቸው ከእሩቅ ነው
የመጡ
ይጋበዛሉ
ሽማግሌ ፦ ታዲያ እስኪ የት እንደመጣቹ ወዴትስ እየሄዳቹ ነው? ንገሩኝልጆቼ
ራሄል ፦ እኛማ ከሃዋሳከተማ አንዲት ትንሽሰፈር ነበር የምንኖር ፤ ምንም ሃብት አልነበረኝም ፤ሃብቴ
ድንግል ማርያምብቻ ነበረች ፤ የምንተዳደረው ልጀሊስትሮእየሰራ ፤ እኔ ደግሞበሰፈር እንጀራ እየጋገርኩ
ነበር የምን ኖር። አንዲት ሴት ልጅምነበረችኝ(በሃዘን)። እና ከሰፈራችን አንድ መናፍቅ ነበር :: እሱምበኔ
ላይ ከፍተኛ ጥላቻ አደረገብኝናሴቲቱን ልጀን ወሰደብኝ። እኔን እና ይህን ልጀን አሳደዱን ። አሁን ሌላ
የምንኖርበት ሃገር እየፈለግን ነው እንባ እያነባች
ሽማግሌ ፦ አይ ሁለት እግር ጤና የለው ሰይጣን በሰዎች ልቦናእያደረ ብዙ ነገር ይፈትነናል ግን ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድል እንዳደረገው እኛምማድማድረግ አለብን ።እኛ ግን ደካሞች ነን ።
እንደዚህ ያለ ነገር ሲመጣ በጸጋ መቀብል አለብን።የእመቤታች ድንግልማርያምስደት ማስታወስአለብሽ።
ስደትን እርሱ እግዚአብሔርወልድ ነው ተሰዶ ባርኮ የሰጠን ። ከዚ በኋላግን የትም አትሄዱምአዚ ከ እኔጋ
አብራቹ ትኖራላቹ ። ኧንተምትምህርትህን እየተማርክ በትርፍ ግዜህ እኔን በስራ እያገዝክ ትኖራለህ ።
አንችምእንዲሁከዚ ተቀመጭ ባለቤቴ ስለደከመች በስራ ታግዣታለሽ። ቤት የእግዚአብሔር ነው ።
ራሄል ፦ እሱማ ጥሩ ነው እሽ አባታችን እግዚአብሔር ይስጥልን።
ከትንሽቀን በኋላ
አረጋዊት ሴት ፦ ከወደ ውጭ ትገባና አንተ ምን እያደረክ ነው ?
ሳምሶን ፦ እማማ የቤት ስራ እየሰራሁነው።
አረጋዊት ሴት፦ የቤት ስራ ! እንጀራ እየጋገርክ ወይስ ወጥእየሰራህ ወረቀትህን ይዘህ አታውቅምብለህ ነው
ባይሆን ሌላባላውቅ የቤት ስራ ይጥፋኝ። ደግሞበኔ ልታሾፍ!!!! ወረቀቱን በልተህ ልታድር ነው ።የጣፉርዲ
ልጅ ደሞ ታሾፋለህ ። ደግሞየቤት ስራናትምህርት መለየት ያቅተኝ ።ተነስ ከቤት ውጣትፋኝ ድራሽህን
በዚ እንዳላይህ ብላበጥፊ ትመተዋለች።
ሳምሶን ፦ በጣም ያዝናል ። ከእናቱ ጋር ይገናኛል። እማ እንግዲህ ኧንችምእኔምበሰው ቤት ተቀምተን
ሰው ቅር ከምናስብል ። እኔ ወጣ ብየ ስራ ልፈልግ አንች ደግሞእኔእስክመጣ በዚህ ጠብቂኝ።
ራሄል ፦ አይ ልጀየዚያች ረመጫት ሆዴን እየበለኝደግሞ አንተ ትተኸኝልትሄድ አብረን ነው የምንሄድ
አንተን ከአይኔለደቂቃ እንኳ እንድትለየኝአልፈልግም ።
ሳምሶን ፦ እማ እኔብቻየን ነው መሄድ የምፈልገው ልቀቂኝብሎእየተላቀሱ ይጓተታሉ
ነጥቋት ይሮጣል ። ትንሽእንደሄደ
ሳምሶን ፦ አሁን የት ነው የምሄ ድ ኧረ ወይ ጨለማው ዋጠኝኧረ እማ ወዴት ልሂድ እማን አላገኛት እያለ
ያለቅሳል
ራሄል ፦ አቤቱ አምላኬ በሰላምልጆቸን በየአሉበት ጠብቅልኝ? አንተተከተለውእምቢብሎኝሄደ አይ
ሳምሶን እመቤቴ ትከተልህ ጥላከለላ ትሁን።
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ትእ ይንት 11
ከአም ስት አመት በኋላ
ሰበር ዜና አቶ ሳምሶን ዳኑኤል የሃገርቱ ንጉስ ሆነው ተመረጡ
ሰናይት ፦ አቤት እስመአልቦ ነገር ዘይስዓኖ ለእግዚአብሔር ። የኔወንድምሳምሶን ነው። ግን ለዚ እንዴት
ይበቃል ፎቶው ግን ትክክለኛ የሱነው ። አምላክ ተመስገን ፤ እኔ ግን በገንዘብ የእናቴንና የወንድሜን ፍቅር
ቀየርኩ ። ግን አሁንምይቅር ይለኝይሆናል ። ከአለበት እየጠየኩ እሄዳለሁ
ደባልቄ ፦ ጉድ ጉድ ዛሬ በጥዋቱ ምን አይነት ዜና አሰማኝ። ሳምሶን ዳኑኤል ንጉስ ወይ ጉዴ አይ ወይኔ
ከሰርኩጉድ ጉድ እያለ ቤቱ ገብቶ ቁጭ ይላል። ወይ ኢየሱሴ ምን አሰማኝ።
ሰናይት ፦ ጋሸ ምሁነህ ነው ዛሬ ?
ደባልቄ ፦ ውጭ ያንገሽግሽሽ። ይች ጥፍራም። ጓደኘው አደረገችኝ ። ምናባቷን !!!!
እንደልቡ፦ያ ቁርፋድ መናፍቅ አንዴ የልቡን ሰረውለት አሁን ጥፍት አለ ። ገልብጨነው የምጥለው ።
እንዳውምይህ ነው መሰል ቤቱ ቆይ እስቴ ልጠይቀው። ብሎያንኳኳል
ሰናይት ፦ አቤት ማን ነው ምን ሁነህ ነው ?
እንደልቡ፦አቶ ደባልቄ የሉም ?
ሰናይት ፦ አለ ግባ
እንደልቡ፦እንዴት ዋሉ አቶ ደባልቄ ።
ደባልቄ ፦ ደና ደና ዋልክ?
እንደልቡ፦ምሁነህ ነው የደነገጥክ ትመስላለህ መኪናዎች አደጋደረሰባቸው እንዴ ታዝናለህ ። ነው
ሳታተርፍ ቀረህ አይ ሃብታምሁሌ እኮ ጭንቀታምናቹ ።እኔ በምን
እንደምጨነቅ ታቃለህ ሲጋራና ጫት ሳጣ ነው አንዳንዴ ደ ሃ መሆኔን በጣም ደስ ይለኛል ነው ወረት
ከሰረብህ ? እኔእንኳ እማጨስባት ካገኘው አልጨነቅም። ወረቱ ከሰረ ብለህ ይሆናል ጭንቀታም
ደባልቄ ፦ ምን መኪና ምን እንዳልሆነ ነው። ወረቱስ። ገንዘብ ቢጠፋ ይተካል፤ ኧረ ያስጨነቀኝሌላነገር አለ
አንተንምይነካሃል ወይኔሳላስበው።
እንደልቡ፦ምንድር ነው ኧረ ንገረኝ? እኔን ሲጋራ ጠፋ ወይም ተከለከለ እንዳትለኝ እ
ደባልቄ ፦ ያኔ የዛሬ አምስት አመት ያሳደድነው ልጅ የሃገሪቱ መሪ ንጉስ ሆነ!!!!!!!!!!!!!
እንደልቡ፦ኦ!!! ምን አይነት ጉድ ነው!!እኔምአንተምተሎ ብለን ተሎከዚች ሃገር መውጣት አለብን ።
ደባልቄ ፦ ምን!!!!!!!!!!!!!!! ዛሬ ጥሩ ነገር አያሰማኝም እንዴ። መውጣት አንተ ከሆንክ ምንም የለህ ። እኔ
ይህን ፎቅ ስንቱን መኪናትቸ ነው የምሄደው ደግመህ እንዲ ያለ ወሬ እንዳታወራ
እንደልቡ፦እ ንጉስ አይከሰስም ሰማይ አይታረስም ሲባል ሰምተህአታቅም። እኔየራሴን ከዚ ወጥቸ
እሄዳለሁ።
ደባልቄ ፦ አይ ግን የዚያን ግዜ በኛ ምክንያት መሆኑን ያውቅ ብለህ ።
እንደልቡ፦ አይ አያውቀነምእኔምማንነቴን ቀይሬ ነው የገባው ። ባክህ አያውቀነም!!!!!1
ደባልቄ ፦ ግን ይች እህቱ ከነገረችው ሳያጠፋን አይመለስም። ልጅቱን አንድ ነገር ማድረግ አለብን ።
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
እንደልቡ ፦ እሷንማ ችግር የለውምእኔጥሩ ስልት አለኝ። በመርዝ እንግደላት?
ደባልቄ ፦ ኣ እውነትህን ነው ።ታዲያ መርዙን ማን ከየት የት ባመጣልን ። ደግሞስ እንዴት አድርገን ነው
የምናሰጣት ።
እንደልቡ ፦ መርዙ ከኔ አንድ ውሻ ከሰፈር ነበረ እሱን ለመግደል የገዘውት አለ ።ቆራርጦ ይጥላታል ።
ጥራትና ወደሱቅ ላካት ከዚያ መርዙን ከለስላሳ ጋር አደባልቀን እንሰጣታለን። እንዳትጠረጥር እየጠጣን
እንቆያታለን ።
ደባልቄ ፦ ሰናይት ነይ እማ ሳሙናከሱቅ ገዝተሽ ነይ አይጎበዝጀግና ጎበዝ እኮነሽ።
እንደልቡ፦ በፍጥነት መርዙን ይቀላቅለዋል። ግን ስትጠጠው እንዳናያትወጣብለን እንቆያለን።
ደባልቄ ፦ እሽ በቃ ። መጣሽ አይጎበዝበፍጥነት ነው የመጣሽ። ያሳድግሽ የጎበዝ ልጅ ።
እንደልቡ ፦ ምን በባዶው ትነዘንዛታለህ ። ምረቃ በኪስ አይከተትም። የልቅ ከዚ ከምንጠጣው ስጣት ።
ደባልቄ ፦ ደግሞ ለሰናይት ለለስላሳሌላምእሰጣት ነበር ።ያዥብሎመርዙ ያለበትን ይሰጣታል።
ተጠቃቅሰው ይወጣሉ።
ሰናይት ፦ ወንድሜ ንጉስ ሲሆን እንኳን ለስላሳቀርቶ ሌላእጠጣለሁ። ተመስገን አምላኬ።
ከበቡሽ ፦ በድንገት ከኩሽና ቤት ወጥታ አንች ደፋር እንዴ እኔ ኩሽና ቤት ቁጭ ብየ አንች ለስላሳ
ልትጠጭ ፤ ኣ !!!የገረድ ልጅ ገረድ በጥፊ ብላ ትቀማታለች ሂጅ እንጀራውን ጋገሪ። እኔሳልጠጣእሷ ደም
ያስጠጣት ይች የሌባ የሌባ ልጅ ።ወይጉድ ግን አንች ምን ታደርጊ ኧረ እሱ ነው ። ብላ ትጠጠዋለች በሃይል
ትወድቃለች። ትጮሃለችም
እንደልቡ፦ከውጭ ሁኖ ሰርቷል ሰርቷል አይ የኔጥበብ የታባቷ ጭጭ አደረጋት
ደባልቄ ፦ ሰርቷል ጨብጧል ያ ያ እየተሯሯጡ ይገባሉ
ከበቡሽ ወድቃ ትታያለች
እንደልቡ፦ወይኔ እጀን በጀ ቆረጥኩት ብሎእንቅ አድርጎ ይዞ ያለቅሳል።
መጋረጃ ይዘጋል
ትእይንት 12
ሰናይት ፦ ከውጭ ሁና አሁን እኔን አይደል ገደልሻት የሚሉኝተሎብየ መጥፋት አለብኝ። ብላትሄዳለች
።
ከቤት እያዘኑ ይቀመጣሉ
ከበደ ፦ ከቤት ውስጥቁጭ ብለው እናቴን የገደለ ሰው ማወቅ እፈልጋለሁ።ግን አንተ ነህ የገረድ ልጅ
አለቅህምወይ ገዳይዋን ትነግረኛለህ። አባቴነህ ብየእለቅህ ይመስልሃል አለቅህምስማ ትነግረኛልህ ።
የማነንምዱርየ እያመጣህ እናቴን ገደልካት እናቴ የምትሰጠኝን ፍቅር ካንተ ስለማላገኝ። ገዳይዋን ከተናገርክ
ጥሩ ካልተናገርክ አንተን እንደሷ ደምአስተፋሃለሁ። ንገረኝኝ!!!! ምን ታየኛለህ ንገረኝ !!!! ሽወጥ
አውጥቶ ይደግንባቸዋል። አንተ ዱርዬ አንተ ነህ !!!! የገደልካት
እንደልቡ፦ አ ኧኧኧኧረረ እኔ ብቻ አይደለም አብረን ነው።
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ከበደ፦ የኔ አባት ሚስተህን የልጆችህን እናት የእኛን እናት ገድለህ ምን ልትሆን አምሮህ ነው አንተ
ልትኖር ነው የማንንም ዱርዬ ገዝተህ አምጥተህ ያስገደልካት እሷን አጥቼ ብፍቅሯ ከምሰቃይ
አጥፍቸህ እጠፋለው ብሎ ሁለቱንም ይገልና እራሱም ይሞታል በራሱ ያጠፋል ፡
ትግስት ከውጬ የጥይቱን ድምጽ ሰምታ ትመጣለች
ትግስት፦ ውይኔ ዘመዶች ባንዴ ኧር ኡኡኡኡኡ ታለቅስና እናቴን አጣው ደግሞ ወንድሜንና አባቴን
ሳጣ ምን ኑሮ አለኝ እሷም እራሷን በራሷ ታጠፋለች
ትእይንት 13
ንጉስ ሳምሶን፦ አቤቱ አመሰግንሃለሁ። ለዚህ ማእረግ ስለ አበቃኸኝ። አሁን የምለምንህ አንድ ነገር አለኝ።
ያችን በድህነት ሁና ያሳደገችኝን እናቴን አገኛት ዘንድ ያንተ ቅዱስ ፈቃድህ ይሁንልኝ። እህቴንም አግኝቼ
በንስሐ ታጥባ የመግስትህ ወራሽ ትሆን ዘንድ። እኒዚያን ባለማወቅ ያሰደዱንን ሰዎችም አግኝቸ ይቅር
እላቸውና አመሰግናቸው ዘንድ ያንተ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልኝ። ወታደር ና ይህን ደብዳቤ ይዘህ በሙጃ
ሰፈር የኔ እናት ፈልገህ ታመጣለህ ። ስሟ ራሄል ሄኖክ ትባላለች እንዳገኘሃት ይህን ደብዳቤ አንብብላት እና
ትመጣልሃለች። ፈጠን ብለህ።
ወታደር ፦ አሁን የት ነው የማገኛት ካጠዋት ከፍ ብሎ አንገቴን ዝቅ ብሎባቴን ነው የሚቆርጠኝ ኧረ
አምላኬ እርዳኝ። ደህና ዋሉ እማማ አዚ ሰፈር ሰው ብጠይሽትነግሪኛለሽ ።
ራሄል ፦ ኧረ ወይድልኝፖሊስ አልወድም ። ልጆቸን ያሰደደብኝፖሊስ ነው።እኔአዚ መንገድ ላይ ነው
የምኖር
ወታደር ፦ አይ ችግር የለም እማማ ወ/ሮራሄል ሄኖክ የምትባል ሴት ታውቂአለሽ?
ራሄል ፦ ኧረ ደግሞ ምኑን አመጣህብኝ እኔ ልጀን ካጠው ወዲ ቤት የለኝም አይደል የምልህ ይህን ደግሞ
የሰፈሩ ሰው ያውቃል ጠይቅ ምን ልታደርገኝነው የመጣህ። ወይኔ ጉዴደግሞ በዚህምመከራ አለ። ምኑን
ልትለኝይሆን አምላኬ ከዚ ጉድ አውጣኝ
ወታደር ፦ አይ ችግር የለም ይህን ደብዳቤ አነብልሻለሁ
ደብዳቤው ይድረስ እንደጀራ ለምትርቢኝ፤ እንደ ውሃ ለምትጠሚኝለውዷ እናቴ ለወ/ሮራሄል እንዴት
አለሽልኝእማ እኔ ደህናነኝ መቸም ይህ ደበዳቤ ሲነበብልሽእውነትአይመስልሽምግን እውነት ነው እማ
እኔ ልጅሽሳምሶን ነኝ መቸም በህይወት የምኖር አይመስልሽም። እኔምአንች ያለሽአይመስለኝም ግን
አለሁእማ አሁን ግን ንጉስ ሁኘ አለሁ። እማ አታምኒምይገባኛል ።ግን እማ ምልክት እንዲሆንሽ
ያሰርሽልኝን ቀለበት እገልጽልሻለሁ።በይ እማ ይህን ደብዳቤ ያነበበልሽየኔወታደር ስለሆነ በሙሉ ልብሽ
አምነሽው ይዞሽይምጣ ። በሰላም እንገናኝ ውዷ እናቴ
ልጅሽሳምሶን ዳኑኤል
ራሄል ፦ እሽ እውነትህን አይሆንምእንጅ እሄዳለሁ። ሲሄዱይታያሉ
ወታደር ፦ ና በሩን ክፈተው ከንጉሱ ጋ ልንሄድ ነው ?
ዘበኛ ፦ ቆይቆይ ንጉሱ ሳይፈቅዱማ አይቻልም ከሱ ጠብቁኝ።
ንጉሱ ሽህ አመት ይንገሱ ። ወታደሩ ከአንዲት ሴት ጋር ሁነው ወእደ አንተ እንግባ ይላሉ
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
ንጉስ ፦ አዎ ፈጠን ብለህ አስገባቸው።
ዘበኛ ፦ ኑ ተፈቅዶላችኋል ግቡ
ራሄል ፦ አንተ የኔ ልጅ ሳምሶን ነህ በድንጋጤመንፈስ
ንጉስ ፦ አዎ እማ እኔ ሳምሶን ያንች ልጅ ነኝ ከዘመናት በፊት ያሰርሽልኝቀለበት ይሄው
ራሄል ፦ እኽኽኽ ልጀ ብላ እቅፍ አድርጋይዛ ታለቅሳለች ።
ንጉስ ፦ ወታደር ፈጠን ብለህ ወደ መጋረጃ ውሰዳትን ልብስ ቀይርላት። በዛውምትንሽትረፍ ምሳ በደንብ
ከኔ ከሚሰራው ስጥዋት
አቤቱ ስላደረክልኝሁሉ አመሰግንሃለሁ። አሁንምሁለት ነገር እለምንሃለሁ
አንድ ያችን ምስኪኗን እህቴን ታገናኘን ዘንድ
ሁለት እነዚያን ያሳደዱነን ሰውች አግኝቸ ይቅር እናአመሰግናቸው ዘንድ እለምንለሁ
ሰናይት በመንገድ እየሄደች ትታያለች አሁን ወንድሜ ይቅር አይለኝምግን እስቲ ልሂድ እማ ካለች እሷ
ታስታርቀኛለች
የኔ ወንድምየአዲሱ ንጉስ እህት ነኝእስቲ እባክህ አስገባኝ
ዘበኛ ፦ አ ዘወር በይ አንች ቆራጣ ነሽ የንጉስ እህት ። ከላ በይ ድሪቶ !!!!
ሰናይት ፦ ንገረውናሲያየኝ ስለሚያውቀኝ ይነግርሃል
ዘበኛ ፦ እንግዲያውስ አንድ ሰው ላምጣልሽናካወቅሽትገቢያለሽ። ወደዚያ ሸሻ ብለሽ ጠብቂኝ።
አንች ሸሻ በይ እመጣና ። የ ንጉሱ እናት የሰወ ልጅ ነኝ የምትል አንዲት ልጅ ውጭ
ስለምትፈልገወት ይምጡ ። ብሎይዟት ይሄዳል
ሰናይት ፦ ከሩቅ አይታ እየሮጠች ሂዳ ከጉልበቷ ትደፋልች ። እማ ይቅር በሉኝበድያችኋለሁ።
ራሄል ፦ ምን ይቅር አልልሽም። እንኳንስ እንዲህ ያለ ደስታወንድምሽንጉስ ሲሆን ፤ አንችንምሰይጣን
ነው ያሳሳተሽ ግን ይቅር እልሻለሁ። አሁን ከወንድምሽ ጋር አገናኝሻለሁ።
ሰናይት ፦ አይ እማ ወደሱ መሄድ የለብኝም በጣም ነው የበደልኩት ። ይቅርምአይለኝም። በድየዋለሁብላ
ታለቅሳለች።
ራሄል ፦ እኔ ያልኩትን ሁሉ ስለሚሰማ ችግር የለምይቅር ይልሻል ።ግድ የለሽምነንይሂጅ
ልጀ እባክህ ይችን እህትህን ይቅር በላት ። ሰይጣን አሳስቷት ነው
ንጉስ ፦ እሽ እማ አንች ካልሻት ችግር የለውምብቻ አንች ይቅር በያት። ብሎ እቅፍ አድርጎ ይዞ ይስማታል
ያለቅሳልም
እማ ግን እስከ ዛሬ እንዴት ብለሽኖርሽ በጣም ተንገላታሽ አይደል
ራሄል ፦ አይ እኔስ የናንተ ናፍቆት ነበር እንጅ የገደለኝጤነየን ደህና ነበርኩ። ያው አንተ ትትሄኝ ስትሄድ
የማወራውም የለኝ ነበር ዝም ብየ ቀርተት ባገኘውት እያደርኩ በየደብሩ እየዞርኩ የትሩፋት ስራዎችን
ለበረከት እየሰራሁ በዛው ትንሽ ምግብ እየሰጡኝ ከዛ ባላይ እናተን ሳስብ ልቤ ይሰበርና ለሞት
እዳረሳለው ትንፋሽ ያጥረኛል አይ ልጄ የዚች አለም ውጣ ውረድ ። ግን ሳምሶንዬ እንዴት ብለህ ለዚ
በቃህ።
ንጉስ ፦ አይ እማ የዚያን ግዜ ከአንች ጋራ ተለያይቸ የምገባበት ጠፍቶኝጨንቆኝሳለ ያጫካ ብሄደው
ብሄደው አላልቅልኝ ብሎ ውይ እማ ሲያስፈራ!!!!!!!! የአራዌቱ ድምጽ ታዴያ የእመቤታችን ስደት
እያስታወስኩ አለቅስም ደስ ይለኝም ነበር ። ከዜያ አንዲት ትንሽዬ ከተማ አገኘውና ሊስትሮ ስሰራ
የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ
አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ
አንድ የውጭ ሃገር ዜጋ ተገናኘውና ወስጀ ላስተምርህ አለች ። መቸም አንችን የማገኝሽ አልመሰለኝም
ይዞኝ ሄደ በዚያም ትምህርቴን ጨረስኩናለንግስናውድድር ቀረብኩ። ለድንግል ማርያም ነግሬያት
ወደ ውድድሩ ገባው እሷም እረዳችኝ አንደኛ ወጣው የአምላክን እናት አመሰግንኩት አምላኬንም
እንዲ አመሰገንኩት
የመጨረሻ መዝሙር 1 አልተወኝም ጌታ
2 እግዚአብሔር ይመስገን
3 ሁሉ ከንቱ
አነሳስቶ ላስጀመረን ለልኡል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

More Related Content

What's hot

Hist carnaval lenda do arlequim
Hist carnaval lenda do arlequimHist carnaval lenda do arlequim
Hist carnaval lenda do arlequimMaria Paula Pedro
 
A ovelha
A ovelhaA ovelha
A ovelha
Isabel Oliveira
 
A casa da mosca fosca
A casa da mosca foscaA casa da mosca fosca
A casa da mosca fosca
Jani Miranda
 
The Elephant with the Golden Tusks - A Jataka Tale (Eng & Malay).ppt
The Elephant with the Golden Tusks - A Jataka Tale (Eng & Malay).pptThe Elephant with the Golden Tusks - A Jataka Tale (Eng & Malay).ppt
The Elephant with the Golden Tusks - A Jataka Tale (Eng & Malay).ppt
OH TEIK BIN
 
Uma prenda de natal
Uma prenda de natalUma prenda de natal
Uma prenda de natalAcilu
 
Lua sorridente
Lua sorridenteLua sorridente
Lua sorridente
Maria Pereira
 
Lili st crow vol.3 gelozie
Lili st crow vol.3   gelozieLili st crow vol.3   gelozie
Lili st crow vol.3 gelozie
Alexandra Melania Vicol
 
Barbara mc cauley nopti de foc
Barbara mc cauley   nopti de focBarbara mc cauley   nopti de foc
Barbara mc cauley nopti de focRoxana Ion
 
2. cuentos para vivir emociones · versión 1
2. cuentos para vivir emociones · versión 12. cuentos para vivir emociones · versión 1
2. cuentos para vivir emociones · versión 1
sonia313795
 
Apresentação S. Martinho
Apresentação S. MartinhoApresentação S. Martinho
Apresentação S. MartinhoBibesEncantados
 
A menina que detestava livros texto integral
A menina que detestava livros   texto integralA menina que detestava livros   texto integral
A menina que detestava livros texto integralBrígida Ferreira
 
A história da bruxinha
A história da bruxinhaA história da bruxinha
A história da bruxinha
Katia Martinez
 
A velhinha-e-a-galinha-carijó
A velhinha-e-a-galinha-carijóA velhinha-e-a-galinha-carijó
A velhinha-e-a-galinha-carijóBela Catarina
 
Cerpen Pertama - Kasih yang Ku damba kan
Cerpen Pertama - Kasih yang Ku damba kan Cerpen Pertama - Kasih yang Ku damba kan
Cerpen Pertama - Kasih yang Ku damba kan Nazdiana Juma'ad
 
A Lenda Dos Ovos De Pascoa
A Lenda Dos Ovos De PascoaA Lenda Dos Ovos De Pascoa
A Lenda Dos Ovos De Pascoagabifrias
 
Iaci e a_boneca[2]
Iaci e a_boneca[2]Iaci e a_boneca[2]
Iaci e a_boneca[2]jifonteseca
 

What's hot (20)

Boneco de neve
Boneco de neveBoneco de neve
Boneco de neve
 
O inverno
O invernoO inverno
O inverno
 
Hist carnaval lenda do arlequim
Hist carnaval lenda do arlequimHist carnaval lenda do arlequim
Hist carnaval lenda do arlequim
 
A ovelha
A ovelhaA ovelha
A ovelha
 
A casa da mosca fosca
A casa da mosca foscaA casa da mosca fosca
A casa da mosca fosca
 
The Elephant with the Golden Tusks - A Jataka Tale (Eng & Malay).ppt
The Elephant with the Golden Tusks - A Jataka Tale (Eng & Malay).pptThe Elephant with the Golden Tusks - A Jataka Tale (Eng & Malay).ppt
The Elephant with the Golden Tusks - A Jataka Tale (Eng & Malay).ppt
 
Uma prenda de natal
Uma prenda de natalUma prenda de natal
Uma prenda de natal
 
Lua sorridente
Lua sorridenteLua sorridente
Lua sorridente
 
Lili st crow vol.3 gelozie
Lili st crow vol.3   gelozieLili st crow vol.3   gelozie
Lili st crow vol.3 gelozie
 
Barbara mc cauley nopti de foc
Barbara mc cauley   nopti de focBarbara mc cauley   nopti de foc
Barbara mc cauley nopti de foc
 
2. cuentos para vivir emociones · versión 1
2. cuentos para vivir emociones · versión 12. cuentos para vivir emociones · versión 1
2. cuentos para vivir emociones · versión 1
 
çocuk şarkıları
çocuk şarkılarıçocuk şarkıları
çocuk şarkıları
 
Apresentação S. Martinho
Apresentação S. MartinhoApresentação S. Martinho
Apresentação S. Martinho
 
Uma Prenda de Natal
Uma Prenda de NatalUma Prenda de Natal
Uma Prenda de Natal
 
A menina que detestava livros texto integral
A menina que detestava livros   texto integralA menina que detestava livros   texto integral
A menina que detestava livros texto integral
 
A história da bruxinha
A história da bruxinhaA história da bruxinha
A história da bruxinha
 
A velhinha-e-a-galinha-carijó
A velhinha-e-a-galinha-carijóA velhinha-e-a-galinha-carijó
A velhinha-e-a-galinha-carijó
 
Cerpen Pertama - Kasih yang Ku damba kan
Cerpen Pertama - Kasih yang Ku damba kan Cerpen Pertama - Kasih yang Ku damba kan
Cerpen Pertama - Kasih yang Ku damba kan
 
A Lenda Dos Ovos De Pascoa
A Lenda Dos Ovos De PascoaA Lenda Dos Ovos De Pascoa
A Lenda Dos Ovos De Pascoa
 
Iaci e a_boneca[2]
Iaci e a_boneca[2]Iaci e a_boneca[2]
Iaci e a_boneca[2]
 

Similar to የእናት ፍቅር

ቃል መስቀል ሓምሻይ ሕታም
ቃል መስቀል ሓምሻይ ሕታምቃል መስቀል ሓምሻይ ሕታም
ቃል መስቀል ሓምሻይ ሕታም
Robi Abraha
 
Tigrinya - Tobit.pdf
Tigrinya - Tobit.pdfTigrinya - Tobit.pdf
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም Gabani Computer Company
 
ጋዜጣ ቃል መስቀል ካልኣይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ካልኣይ ሕታምጋዜጣ ቃል መስቀል ካልኣይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ካልኣይ ሕታም
Gabani Computer Company
 
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታምጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታምGabani Computer Company
 

Similar to የእናት ፍቅር (6)

Orthodox christianfamilylesson11
Orthodox christianfamilylesson11Orthodox christianfamilylesson11
Orthodox christianfamilylesson11
 
ቃል መስቀል ሓምሻይ ሕታም
ቃል መስቀል ሓምሻይ ሕታምቃል መስቀል ሓምሻይ ሕታም
ቃል መስቀል ሓምሻይ ሕታም
 
Tigrinya - Tobit.pdf
Tigrinya - Tobit.pdfTigrinya - Tobit.pdf
Tigrinya - Tobit.pdf
 
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም
 
ጋዜጣ ቃል መስቀል ካልኣይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ካልኣይ ሕታምጋዜጣ ቃል መስቀል ካልኣይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ካልኣይ ሕታም
 
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታምጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታም
 

More from chernet engdaw

Wedasie mariam
Wedasie mariamWedasie mariam
Wedasie mariam
chernet engdaw
 
Seweruadega
SeweruadegaSeweruadega
Seweruadega
chernet engdaw
 
Melkamariam
MelkamariamMelkamariam
Melkamariam
chernet engdaw
 
36 the new innovative medical education system in ethiopia background and dev...
36 the new innovative medical education system in ethiopia background and dev...36 the new innovative medical education system in ethiopia background and dev...
36 the new innovative medical education system in ethiopia background and dev...
chernet engdaw
 
Fethanegest
FethanegestFethanegest
Fethanegest
chernet engdaw
 
Bahere hasab
Bahere hasabBahere hasab
Bahere hasab
chernet engdaw
 
15 hage
15 hage15 hage
12 yodit
12 yodit12 yodit
12 yodit
chernet engdaw
 
11 yonas
11 yonas11 yonas
11 yonas
chernet engdaw
 
10 eyob
10 eyob10 eyob
09 eyoel
09 eyoel09 eyoel
09 eyoel
chernet engdaw
 
01 genesis
01 genesis01 genesis
01 genesis
chernet engdaw
 

More from chernet engdaw (12)

Wedasie mariam
Wedasie mariamWedasie mariam
Wedasie mariam
 
Seweruadega
SeweruadegaSeweruadega
Seweruadega
 
Melkamariam
MelkamariamMelkamariam
Melkamariam
 
36 the new innovative medical education system in ethiopia background and dev...
36 the new innovative medical education system in ethiopia background and dev...36 the new innovative medical education system in ethiopia background and dev...
36 the new innovative medical education system in ethiopia background and dev...
 
Fethanegest
FethanegestFethanegest
Fethanegest
 
Bahere hasab
Bahere hasabBahere hasab
Bahere hasab
 
15 hage
15 hage15 hage
15 hage
 
12 yodit
12 yodit12 yodit
12 yodit
 
11 yonas
11 yonas11 yonas
11 yonas
 
10 eyob
10 eyob10 eyob
10 eyob
 
09 eyoel
09 eyoel09 eyoel
09 eyoel
 
01 genesis
01 genesis01 genesis
01 genesis
 

የእናት ፍቅር

  • 1. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቢ ጉባኤ የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ ቸርነት እንግዳው(ገብረ ኪዳን) 11/13/2015 ጥበብና ምክር ፤ ሃይልም ከርሱ ነውና የእግዚአሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም የተመሰገነ ይሁን (ዳን 2፡20) በአክሱም ዩንቨርስቲ ግቢ ጉባኤ
  • 2. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ማሳሰቢያ ፦ ኮፒ ማድረግ የተከለከለ ነው እግዝትነ ማርያም “የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ”
  • 3. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ ተዋናይ 1. ሳምሶን 2. ሰናይት 3. ራሄል 4. እንደልቡ 5. ደባልቄ 6. ከበደ 7. ትግስት 8. ፖሊስ 9. ከበቡሽ 10. ዘበኛ 11. አረጋዊ ሽማግሌ 12. አረጋዊት ሴት ትእይንት 1 ራሄል ፦ ሰናይት ዛሬስ ሳምሶን በጣም አረፈደ እንዳው ሙሁኖት ነው።ሁሌ ቶሎ ነበር
  • 4. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ የሚመጣ። ሰናይት፦ እማ ስራ አግኝቶ እየሰራ ይሆናል እንጅ ቶሎ ይመጣነበር። ሳምሶን ፦ ምነው ዛሬስ ደግሞ እንዴት ያለ ቀን ነው ።ጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቁጭ ብየ ሁለት ብር ብቻ ነው የሰራው ። አሁን ደግሞ እነማየ ብር ያመጣል እያሉ እየጠበቁኝ ይሆናል። በአንዲቱ ብር ዳቦ በለውባት ደግሞ አንዲት ብር ብቻ ናት ያለችኝ ምነው ጌታ ዝናቡ ባጥለቀለቀውና ጭቃ በጭቃ ባደረገው ከዚያ ሁሉም ሊያስቀባ ይመጣ ነበር።እያለ ይሄዳል እማ እንዴት ዋላቹ ራሄል ፦ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ዋልክ ሳምሶንየ በጣም ዘገየህ። ሳምሶን ፦ ደህና እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ናቹ ኧህ ብሎ ቁጭ ይላል። ራሄል፦ ሰናይት እስኪ ትንሽ ብር ካለው ጠይቂው ና ጥሬ ጨው ገዝተሽ ነይ። ሰናይት፦ ሳምሶን ካለህ ስጠኝ? ሳምሶን ፦ አይ ሰናይት ዛሬ ይገርምሻል ምንም አልሰራሁ ግን የሰረዋት አለች እንች። ተቀብላ ወደ ውጭ ትወጣለች ራሄል፦ ሳምሶን ምሁነህ ነው ዛሬ ፊትህ ሁሉ ተከፍቷል ሳምሶን ፦ እኔን ያልከፋ ማንን ይክፋው? የት/ቤት ጓደኞቼ ይሽሹኛል ። ሊስትሮ ተራ ከእኔ ዘንድ የሚያስቀባ የለም ።ከዚህም በላይ በዚች ዶሳሳ ጎጆ እየኖርን ሲርበን ሳይ ለምን አልከፋም? መጨነቅ ይነሰኝ? እያለ ያለቅሳ ራሄል፦ ተው ልጄ እንዲህ እየተጨነቅህ እኔንም እህትህንም አታስጨንቀን ።እኔ እንጀራ እየጋገርሁ አመጣለሁ ለእለት ሆዳችን እንችላለን። ተው እግዚአብሔር ምግባችን ያዘጋጃል ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የሰማይ ወፎችን ተመልከ,..... ሰናይት ከውጭ ትመጣለች ሰናይት፦ ይችን ትንሽ ትንሽ እያደረግን ለዚህ ሳምንት ትሆነናለች። ሳምሶን፦ በይሰናይት ምሳ አቅርቢ እና እንብላ ሰናይት፦ እሽ ሲበ ሉ ሳምሶን፦ እኔማ እማየ የሚገርመኝ ዓንድ ነገር አለ;ይችን ቁራሽ እንጀራ እንዲህ ሶስት ሆነን ስንበላ ሰላም እና ደስታ ይሰማኛል ።የኛን ሰላም ሃብታሞች የሚያገኙት አይመስለኝም። ራሄል፦ አይ ልጀ በዚም ትጠራጠራለህ? ሃብታም እንደሆነ ሁሌም ጭንቀታም ነው።አንድ ጊዜ እንኳን ሰላም የለውም ።እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል መሰለህ ባለሃብት የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም ባለሃብት የእግዚአብሔርን መንግስት ከሚወርሱ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብታልፍ በቀለለ። በዚህ አጋጣሚ ዱሮ ከእናት እና ከአባቴ የወረስኳቸው እኒህ ሁለት ቀለበቶች አሉኝ ።ስለዚህ አሁን አስርላችኋለሁ ። ሳስርላቹ ዝም ብየ አይደለም፤አደራ ልጆቼ በሀብትም ሆነ በብር እንዳያታልሏችሁ እምነታችሁን ጠብቁ ።የኔ የዕናታችሁ ፍቅር እንዲያድርባችሁ አሰርኩላችሁ። ሳምሶን፦ ሰንየ ት/ቤት እንሂድ ሰናይት፦ እሺ ደህና ዋይ እማ!!!! ትእይንት 2 ደባልቄ፦ ኧረ ከቤ ከበቡሽ አሰሚም እንዴ
  • 5. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ከበቡሽ፦ አቤት!!!!ምሁነህ ነው ዝግ በል ልመጣ ነው!!!!!!!! ደባልቄ፦ መጋዘኑን ዘግቸ ነው ቁጭ ያልኩት ምሳ አምጭ1!!!!!!!!!!!!!!!! ደግሞ ልትቆጣ ከበቡሽ ምሳ ይዛ ትመጣለች ደባልቄ፦ ኧረ ወዲያ አንሽልኝ፤ ትናትና ሽሮ ዛሬ ሽሮ ነገም ሽሮ ኧረ መቸ ነው ስጋ የምትሰሪ። ነጋ ነጋ ሽሮ እየበለው እራሴም ፎረፎር ሆነ ሽሮው በአናቴ ወጣ!!!!!!!!!!!!!! ከበቡሽ፦ ከተማውን በሞላ ዙሬዋለሁ ያላደረስኩት የለም አሁን እማ ስሰማ የኦርቶዶክስ ጾም ነው አሉ ። ደባልቄ፦ እነሱማ ወይ መጽሐፉን አያውቁ እረበሹን ። ታዲያ እንግዲህ የነሱ ጾም ባላለቀ ግዜ እኛ በሽሮ አናልቅም ። በግ ቢሆን ገዝተን በብላት አለብን። ከበቡሽ፦ እሱም አዎ ግን የሚገርመኝ ነገር አለ ። የኛን እንጀራ ጋጋሪ ታውቃት አይደል ደባልቄ፦ ራሄል ናት ከበቡሽ፦ አዎ አንድ ቀን ብላ ከኛ እንጀራ በልታ አታውቅም ።ብይ ብየ ስሰጣት እንኳ ስጋና ቅቤ ያለበትን አትቀበልም ። ደረቁን እንጀራ ነው ይዛ የምትሄድ። በጣም ታሳዝነኛለች። ደባልቄ፦ ግን ለልጆቹ ይዛላቸው ትሄዳለች ? ከበቡሽ፦ እሱማ ትንሽ ትንሽ ይዛላቸው ትሄዳለች የልጆቿ ነገር ሞቷ ነው። ደባልቄ፦ ታዲያ እንዲህ የምትወዳቸው ልጆች ሲራቡ ከምታይ ለምን ከኛ ገብተው እንደልባቸው አይሆኑም ። ወንዱ ልጇ ጎበዝ ተማሪ ስለሆነ ልጆቻችን ያስረዳልናል ። ሴቲቱ ደግሞ የቤቱን ስራ ትሰራለች ። ከዛ የኛ ልጆች ጎበዝ ይሆናሉ። በዛውም ጌታን ይቀበላሉ ከበቡሽ፦ እሽ ብላ ትለቃቸው ብለህ ።የልጆቿ ነገር ሞቷ ነው። ደባልቄ፦ የእኛ ልጆች በዳቦም በቸኮሌት በሌላ ነገርም አታለው ያመጧቸዋል ከበቡሽ፦ እሱማ በቀር እነ ከቤ ለነዚህ ነው። ደባልቄ፦ በይ እኔም መጋዘኑን ዘግቸ እስከ አሁን ደንበኞች እየመጡ ተመልሰው ይሆናል በጣም ረፍዱአል ለልጆቹምሳ ስጫቸውና ይሂዱ።ደህና ዋሉ ትእይንት 3 ሰናይት፦ እማየ የሰጠችን ቀለበት እንዴት ያምራል ሳምሶን፦ አየሽ ላይ ከቀለበቱ የበለጠ የሚታየኝ የእማየ ፍቅር ነው።እማየየኛን ፍቅር የምትገልጥበት ብታጣበዚህ ገለጠችልን። አይ እማ በጣምእኮነው የምትወደን።
  • 6. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ሰናይት፦ አሁን እኔን ቢርበኝ ይህን ሽጨ ልብስ ጫማ ሌላም አደረገዋለው ሳምሶን፦ ኧረ ዝም በይ” በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ” እንዴ ምን ነካሽ። ይህን ሸጥሽ ማለት የናትሽን ፍቅር ሸጥሽማለት ነው። ደግመሽ ይህን ሐሳብ እንዳታነሽው ከነ ከበደ ጋር ይገናኛል ትግስት፦ ሳምሶን እንዴት ናቹ? ሳምሶን፦ ደህናደና ናቹ? እያሉ ሰላምታ ይለዋወጣሉ ትግስት፦ ግን እናንተ ሁሌ ተሎ የምትመጡ ምን ግዜ ቁርስ ትበላላቹ? ሰናይት፦ እኛ እኮ ቁርስ ሁሌ አንበላም። አብዛኛው ቀን ጾምነው። ደግሞጾምባይሆን ማታ ከእራት ከተረፈ ነው የምን በላ ።ለ ቁርስ ተብሎ በልተን አናውቅም። ከበደ፦ አ!!!!!!! ትራፊ! የኛ ድመቶች ትራፊ ቀርቶ ዳቦ አይበሉም።ኽ!!!!!እኛ እኮኩርስ የምንበላው በፕሮግራም ነው ። ሠኞ እሮብ እና አርብ እንቁላል ፍርፍር ሌላው ቀን ደግሞኬክነው ትግስት፦ ደግሞ ምን እንደሆነ ታውቃላቹ የተረፈውን የሚበላው ስለሌለ ሽንት ቤት ይደፋል። ኧረ ከቤ በ ኢየሱሴ የተሰጠነውን ዳቦ እንስጣቸው ። ይሰጡዋቸዋል ኋላ የምናወራቹ ስላለ ጠብቁ ሳምሶን፦ አንዲቱን በልተን አንዲቱንለእማ ይዘን እንሄ ዳለን። ሰናይት፦ ኧረ ሁሉን ነው የምንበላ እቢ እኔ እርቦኛል። ሳምሶን፦ ተይ እማንምእኮ ይርባታል ። እሷ እኳ ከእኛ ተለይታአትበላም ሰናይት፦ እሺ ሳምሶን፦ ቆይ እነሱ መናፍቅ ስለሆኑ ስጋቅቤ ጨምረውበት ይሆናል አንበላም። ደግሞዛሬ ጾም ነው። ሰናይት፦ ባክህ እርቦኛል እንብላ። አንተ ተወው እኔእበላለው። ሳምሶን፦ ፍጽምአይሆን ም እንዳውም ቅዱስ ፓውሎስ መልክት እያነሳች ስለ ሃማኖታችን ትነግረናለች። ሳይበሉ ተነስተው ይሄዳሉ በመንገድ ላይ ይገናኛሉ ትግስት፦ ሳምሶን ሳምሶን የምናወራቹ አለን ብለናቹ አይደል ሳምሶን፦ አ ብላቹን ነበርለካ እረስተን እኮነው ከበደ፦ እኛ እኮ የእናንተ ነገር በጣም ነው የሚያሳዝነን ፤ ስለዚህ ወደኛ ቤት እንሂድ እና እንደልባቹ ትኖራላቹ ። ትምህርትህም ጎበዝትሆናለህ ። ሳምሶን፦ ኧረ እናታችን ትተን አንሄድም ትግስት፦ እናታችሁምከተስማማች ከእኛ ትሆናለች ሳምሶን፦ እማየማ ትልቅ ነገር አላት ።እኛ ትተናት እንዳንሄድ፤ ሃይማኖታችን እንድንጠብቅ በኦርቶዶክስ እንድንጸና ብላከእናት እናከአባቶቿ የወረሰያቸውን ሁለት ቀለበትለኛ ሰጠችን።ይህ ደግሞ የናታችን ፍቅር በልባችን ሰርጿል። ምንምቢሆን አንሄድም። ከበደ፦ በኦርቶዶክስ ተው እንጅ ያረጀ እምነት ይዘህ ስትጠራው አታፍርም ለማንኛውምአስቡበት እንዲህ መከራህን አትይ ቻው
  • 7. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ትእይንት 4 ከበደ፦ ደህናዋልሽ እማ ከበቡሽ፦ ደህናደና መጣቹ ልጆቸ ። ዛሬስ ዘጋያቹ ምነው በሰላምነው ከበደ፦ ትናንትናያወራቹን እያነጋገርናቸው ነበር። ከበቡሽ፦ አይ የኔ ልጆ ጎበዝ እኮ ናቹ ። ታዲያ እንዴት አሏቹ ትግስት፦ አይ እማ ቀላል መሰሉሽ። መጨረሻማ ምን አሉ መሰለሽ2 ከበቡሽ፦ ምን በጉጉት ከበደ፦ ሁለት ድቃቃ ቀለበት አስረውይህ የእናታችን ትተን እንዳንሄድ ከአባቶቾቿ የወረሰቻቸው ናቸው ብለው አሳዩን ከበቡሽ፦ ይች ደሃ የትአባቷ አግኝታው ነው የኛን ሰርቃ ነው የሚሆን አፈርትብላባቷ ቆይ ይች ድሪቶ ከከከከከ!!!!!!!!!!!!!!!!!!! ደባልቄ፦ ከውጭ ሃሎሃሎሃሎ መኪናው ደረሰ ቡና የያዘው መኪና አልደረሰም። ዛሬ በጣምነው የተናደድኩት 10000ብር ብቻ ሰርቸ ልዋል ወይኔ ከሰርኩእዲያ ኢየሱሴ ጌታ ነው ሃሌ ሉያ ደና ዋላቹ እንዴትዋላች ።ትምህርትስ እንዴት ነው ። የኔ ልጆች እኮጎበዝ ናቹ ዘንድሮተሸላሚ ናቹ። ከበቡሽ፦ ባክህ አትነዝንዛቸው ምሳአልበሉምልስጣቸው። ደባልቄ፦ ምን ነው እስከ አሁን ? ከበቡሽ፦ ትናንት የነገርናቸውን እያወሩኝነበረ።ከቤ ሂዱ አመጣላችኋለው መኝታ ክፍል ከበደ፦ እሺ እማዬ ይወጣሉ ከበደ፦ ስሚ ትግስት ኳስ ልጫወት ልሄድ ነው ኳስ ነው የሄደ ብትይ እየሱሴን አርድሻለው ትግስት ፦ እኔም ከጓደኛቼ ጋር ልጫወት እሄዳለው ደባልቄ፦ መቸም የኔ ልጆች ለነሱ ያመጧቸዋል ። ከበቡሽ፦ ቀላል መሰሉህ እነዚያ ነቀዝ ናችው፤ ዓቤት ይገርማሉ ፤መጨረሻማ ምን አሏቸው መሰለህ ፤ ሁለት ቀለበት አስረው እናታችን ትተን ትተን እንዳንሄድ ከአባቶቾቿ የወረሰቻቸው ናቸው ብለውአሳዩን አሉ ደባልቄ ፦ ዝቦች ”ለአህያ ማር አጥማትም”አለ አባቴ። ይች ደሃ የኛን ሰርቃ ነው እንጅ እስከ ዝር ማንዝሯ ደሃ አይደል ዘራቸው፤ ወይኔተጫወተችብኝ!!!!! ስለወርቁ ግን ችግር የለውም እኛ ብዙ ወርቅ ደማቅ የሚያጭበረብር እንሰጣቸውና አታለውይዘዋቸው ይመጣሉ። ከበቡሽ፦ አዎ የኛ ልጆች ባለፈው አመት ትዝአይልህምእነዚያን 5 ተዋህዶ ተከታዮች ሲያሳምኑ ትዝ አይልህምእንዴ ? ደባልቄ፦ አዎ እኛም እሷን እናሳድዳታለን፤ ክፉ አመል አለባት ሌባ ናት እያልኩ ከቦተዋ ሁሉ አስለቅቃታለሁ። በይ አሁን መኪናው ስለ ሚገባ ልሂድ ። ሁሉንም ወርቅ አውጥተሽስጫቸውና ይሂዱ ። ደና ዋሉ
  • 8. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ትይንት 5 ሳምሶን ሊስትሮተራ ይታያል ሳምሶን ፦ አባት ናጫማህን ላሳምርልህ አምጣው እንደልብ፦ ዘወርበል የሌባ ልጅ እማጨስበትና እምቅምበት አጥቸ ጫማ ትለኛለህ ። አንገቱን ጨብጦ ስማ ዳግምእንዲ ብትለኝእገልሃለህ እሽየገረድ ልጅ ሂድ ሳምሶን ፦ እግዚአብሔር ተው እኔን ባሪያህን ስማኝ ሰናይት ወደ ሳምሶን ትሄደለች ከበደ፦ ዘራቸው ደካማ ድሃ ናቸው አሉ ። ትግስት፦ አንዳንዱ ኦርቶዶክስነው እንጂደሃ እኮነው። ከበደ ፦ ያ መጣች ሰኒ ሰናይት ቆይንማ እየጠራንሽአሰሚም። ሰናይት፦ አልሰመዋቹምነበር። ትግስት፦ ደህናነሽሰኒ ማር። ሰናይት፦ እግዚአቤር ይመስገን ። ከበደ ፦ ምን ነው የት እየሄድሽ ኑሮ ነው በጣምስንፈልግሽአገኘንሽ። ሰናይት፦ ከሳምሶን ጋ ነበር የሚሄደው ምሳ ስላልበላና ልለው ። በሰላምነው የፈለጋቹኝ ትግስት፦ የምትበሉት አጥታቹ ነው ወይኔሲያሳዝን ። ሰናይት ፦ አይ አይደለምጥዋት ስለረፈደበትሳይበላሂዶ ነው ትግስት ፦ ከኛ እኮ ብትሄዱ ይህን ወርቅናብር እንሰጣችኋለን ከበደ ፦ እይ ተመልከች ብሩን ሁላ እይ ሰናይት፦ ሲአምር ከበደ፦ ደሞ ምን መሰለሽ ከኛ ከሆናቹ አንችምሳምሶንም በጣም ጎበዝ ትሆናላቹ ስራምእኮ የለባቹም ትሄጃለሽአትሄጅም? ሰናይት ፦ እናቴንናሳምሶንን ትቸ አልሄድም። ሳምሶን ጋ ይደርሳሉ ሰላምታይለዋወጣሉ ሳምሶን ፦ ዛሬስ በዚ መጣቹ በሰላምነው ከቤ ቲጅ ትግስት፦ ሰኒን መንገድ ላይ አገኘናትና አንተን ሰላምእንበልህ ብለን መጣን። ሳምሶን ፦ ነው ደናናቹ ። ሰናይት ፦ የተገዛልንን ወርቅ ልናሳይህ ነው። ከበደ ፦ ደግሞ ምን መሰለህ? እኛን እኮየናናንተ ነገር በጣም ነው የሚያስዝነን እዚ ፀሓይ ላይ ቁጭ ብለህ ስትውል ታሳዝነናለህ ግን ወደኛ አትሄዱም ትግስት ፦ አየህ የተገዛልን ወርቅ ተመልከት ከኛ ብትሄዱ ይህን እናሰጣችኋለን። ሳምሶን፦ በጣምያምራን ግን የኛም እናታችን ቀለበት አለችን። ከበደ ፦ አ!!!!!! ይህንና እሱን ቆሻሻ አንድ ታደርጋለህ ።
  • 9. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ሳምሶን፦ አይ ከአሁኑ ከሚአጭበረብር ወርቅ የድሮው ደብዛዛው ይሻላል ይላሉ :: ደግሞቅዱስ ጳውሎስ መመልክቱ እኛስ አገራችን በሰማይ ነው ብሏአል በሃብትና በንብረት ሃይማኖታችሁን አትለውጡ ሃብት እረጋፊ ነው ነገር አላፊ ነው ይላል ። ምን አንሄድም ፍጹም ከበደ ፦ አ!!!!!!!!!!!!!!! ቆሻሻ በዚህ አስተሳሰብህ እማ መቸምአትለወጥም ቅዱስ ጳውሎስ ምናምን ትዘረዝራለህ እስከ ዘራቹ መጽሐፍ ቅዱሱን አውቃቹትነው ይልቅ አስብበትናወደኛ ብትመጣይሻልሃል ቻውው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!1 ይለያያሉ ሰናይት፦ ሳምሶን ወርቃቸው እንዴት ያምራል በማርያም አንዳንዴ እማ ሳትሰማ እየሄድን ከነሱ ጋ አብረን እንዋል ሳምሶን፦ ምን ተይ እማን ትተን የየትም ይሁን የትም አንሄድ !!!!!!!!!!!!!!!!!1 ደግመሽ እንዳታወሪኝ !!!!!!!! ሰናይት ፦ ከሁላቹም እኔ እኮነኝ በታም የተሰቃየሁ። አንተ በዛው ሰርተህ ትበላለህ እማየምእንጀራ ከምትጋግርበት ትበላለች ። እኔግን ቤት ቁጭ ብየ እሰቃያለሁብላበንዴት ገፍታ ትጥለዋለች ትእይንት 6 መዝ ኧረ አንች አለም ከቤት ይደርሳሉ ሰናይት፦ አሁን አልስማማምአልክአይደል ሳምሶን፦ ተይኝ ተይኝ። እባክሽአትነዝንዥኝ !!!!!! ግን አታርፊም ሰይጣን እንዳያሳስትሽ ተጠንቀቂ ልበ አምላክ ዳዊት እኔስ ከእግዚአብሔር ጋር መኖርን መረጥኩ ይላል ከዛ ሄድሽ ማለት እኮ እግዚአብሔርን እረሳሽጸሎት አታደርጊ ደግሞብርሃነ አለምቅዱስ ጳውሎስ ምን ብሏል ስለ፡ሥጋ፡ማሰብ፡ሞት፡ነውና፥ስለ፡መንፈስ፡ማሰብ፡ግን፡ሕይወትና፡ሰላም፡ነው። ፤ስለ፡ሥጋ፡ማሰብ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ጥል፡ነውና፤ለእግዚአብሔር፡ሕግ፡አይገዛምና፥መገዛትም፡ ተስኖታል፤፤በሥጋ፡ያሉትም፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡ሊያሠኙት፡አይችሉም ስለዚ ለስጋሽ ይመችሽ ይሆናል ለንፍስሽ አይመችሽም ዛሬ ወደ ንሰሐ አባታችን እንሄዳለን ራሄል ከውጭ ትገባለች ራሄል ፦ ምን ሆናቹ ነው የምትጮሁ ውጭ መንገድ ድረስ ይሰማል ሳምሶን፦ ባክሽበማይሆን ነገር ነው የምትጨቀጭቀኝ። ራሄል ፦ ምንድር ነው ሳምሶን ሰናይት ሳምሶ፦ እነ ከበደ መጡ እና ከኛ ቤት እንሂድ አሉን ። ራሄል፦ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱአምላክ አይ አምላኬየፈራሁትን ነገር አመጣህብኝ። ኧረ ድንግል ማርያምእንደ ሃጢአቴ ሳይሆን እንደ ቸርነቱ እንዲሆንልኝ ለምኝልኝተይ ሰናይት በልተሽ
  • 10. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ጠግበሽባታድሪ በእኔበናትሽፍቅር ጠግበሽታድሪያለሽ ይህን ሃሳብሽን አውጥተሽታይ፤ እኔስ ወንድምሽ አናሳዝንሽም ። ተይ ኋላ ይቆረቁርሻል ። እያለች እያለቀሰች ትመክራታለች ትእይንት 7 እንደልቡ፦ ዛሬስ ምን አይነት ቀን ነው ። ከኪሴ አንድምብር የለኝ ። በምን ቅሜ አጭሸ ነው የምውለው ጌታ አንጠው እስከ ሻንጠው። ምን አማራጭ አለኝ። መስረቅ ግን በመነኻርያ አንድቱ ከአረብ ስትመለስ ባገኛት ገልብጨነው የምጥላት ወይምሱቅ እዘርፋለው እያለ በድንገት ደባልቄንከሩቅ ያየዋል ያ ያው መዝረፍ አለብኝ ። አውቀዋለሁእሱግን የሚያውቀኝአይመስለኝም ይገናኛሉ ደባልቄ፦ ሃይ እንደልቡ እንደልቡ፦ ደናዋሉ አቶ ደባልቄ? ደባልቄ፦ ስፈልግህ አገኘውህ ። እንደልቡ፦በሰላም ነው? ደባልቄ ፦ ሰላም ነው የኛን እንጀራ ጋጋሪ ታውቃታለህ። እንደልቡ፦ የትኘዋን ብዙ ናቸው ሁለት ልጅ ያላት ራሄል ድሃዋ የምትባለው ናት ወይስ ሌላ ቀይረሃል ደባልቄ ፦ አዎ ግን ልጆቿን ወደኔላመጣቸው ነበር ። እሷ ግን አልሰጠኝአለች ፤ ያላደረኩት የለምሌባ ናት ብልምሲቸግራት ትለቃቸዋለችብል አለቀቀቻቸውም ። አሁን የቀረኝአንተን ብቻ ማናገር ነው ታዲያ እንዴት ትላለህ ? እንደልቡ፦ ሃሃሃሃሃሃሃ ታዲያ ለዚ ነው ግን ሃብታሞች ስትባሉ ትንሽቀርቀብ እ ትንሽጠቀም ያለች ቻፓ ትጠይቃለች እንጅ እንኳን ይችን ዶሳሳቀርቶ ሌላምጉድ እሰራለሁ ደባልቄ : ኸኸኸኸኸኸኸ ታዲአ ለብር ነው ወይኔደባልቄ ይህ መኪናና ፎቅ ምን ይሰራል ጌታ ይባረክና መሰለህ ያዝ ዪሄው ከፊትህ ላይ ነው ዱቅ የማደርግልህ ግን አደራ እንደልቡ፦ እሽ ችግር የለምደና ዋል። ይለያያሉ ሰናይት ወደነ ደበልቄ ስትሄድ ትታያለች (መዝሙር ዴማስ ሆይ ተመለስ) እንደልቡ፦ እውር አሞራ ቀላቢው እግዚአብሔር እያንከለከለ አመጣው ስልክ አጥቶ ይደውላል ሃሎ ዛሬ በታም እፈልግሃለሁ ፖሊስ ፦ ሰርቀህ ተይዘህ ነው አንተ ሌባ ለማንኛውም መጣሁ ጠብቀኝ እንደልቡ ፦ እሽ ቶሎ ና ትእይንት 8
  • 11. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ሳምሶን ፦ እማ ሰናይት ከሄደች ወዲ ሰላሜን አጣሁምንም እኳ በልተን ጠግበን ባናድር 3 ሁነን ቁጭ ስንል ደስ ይለኝ ነበር ዛሬስ በጣምጨነቀኝየሰናይት ትታን መሄዷ ጉድ ሰራኝወይኔእህቴ የሚአልፍላት መስሏት ተሰቃየች ራሄል ፦ አይ ልጀ እሷማ ገንዘብ አታለላትና ትታን ሄደች በሆዴ ገብታ እረመረመችኝ እንዴትስ ልርሳት ወይኔልጀ ለፍቸ አሳድጌትተሽኝሄድሽ ለማንኛውምድንግል ትከተልሽ።ልጀግን አታስብ እግዚአብሄር ከፈቀደ አንድ ቀን ትመጣለች ። ሃዘን በተሞላ ድምጽ እያለቀሰች ሳምሶን ፦ እማ ምግብ ከበላን ሶስት ቀናችን ነው ዛሬስ እራበኝችግሮች ሁላ ተደራረቡብን።ሊስትሮ ተራ እየሰደቡኝ ነው የ ሄዱ አንዱስ ይባስ ብሎመታኝ ምን ባደርግ ይሻለኛል።ምን ስራ ልፈልግ ከሊስትሮውጭ ሌላ አማራጭ የለኝም ራሄል ፦ እንዴት ላርግ ልጀእንጀራ የምጋጋርላቸው እንኳ ምን እንዳደረግኋቸውሳላውቅ ኧባረሩኝምን ላድርግ ጨነቀኝ ልጀእሱ ያመጠውን እሱ እስኪመልሰውዝምብሎ ማየት ነው ሳምሶን ፦ እስከ መቸ ነው ጌታ እኛን የማያየን ብሎ ስቅ ስቅ ብሎያለቅሳል ራሄል ፦ ተውልጀ ዝም በል እያለች እራሱን ትዳብሰዋለች እንደልቡ ከፖሊስ ጋር ሁኖ ወደነሱ ይሄዳል ፖሊስ ፦ ኧዚቤት ሰው የለም ሳምሶን፦ አቤት ማን ነው ሲያያቸው ይደነግጣል ፖሊስ ፦ እናትህ የለችምጥራትማ ሳምሶን፦ እማየ ቦሊሱ ይጠራሻል ራሄል ፦ ምን ሙሁኑአቸው ነው ፖሊስ ፦ በዚ ሰፈር አንድ እቃ ጠፍቶ ሁሉን አይተን የናንተ ቤት ነው የቀረ አንዴ ወጣ በሉልን ሳምሶን፦ ኧረምንምየለም ይችን ፌስታል ባለፈው በዝብርድ ስለሚገባብን ለመወተፊያ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ አምጥቻለሁሌላ ምንም የለም ፖሊስ ፦ ዝበል ሌባ ብሎ በጥፊ ይቃጠዋል ራሄል ፦ ተው ልጀን እዳትመታብኝ ግቡናእዩ የደሃ ቤት ምንም የለው ፖሊስ እናእንደልቡአዩን አላዩን ብለው የያዙትን ይደብቁና ፖሊስ ፦ ወይዘሮራሄል ነይ አንተምና ይህ ማን ነው ያመጣው ተናገሪ!!!!!!!!!!!!1 ራሄል ፦ ኧረ እሱን አይቸው አላቅም ከኔ ቤትምአልነበረም ፖሊስ፦ ኣ ምን አልነበረም እንግዲያ ማን አመጣው ይህ ሌባ ልጅሽነው ብለ እያዳፉ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዘዋቸው ይሄዳሉ በማረሚያ ቤት ውስጥ ሳምሶን ፦ ብዙ ተኛው አይደል እማ ኧኧኽ ትናንት ብዙ በድለውሻል አይደል እኔእኮየመቱሽ አልመሰለኝም ራሄል ፦ ደናነኝ አንተን ነው የበደሉብኝ
  • 12. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ትእይንት 9 ከበደ ፦ ሰናይት!!!!!!!!!!! አትመጭም እርቦኛል ምሳአምጭ ፈጠን አንች የገረድ ልጅ። ሰናይት ፦ ከቤ ቤቱን እየወለወልኩ ምንምአላዝጋጀው ትንሽጠብቀኝ ከበደ ፦ ኣኣ !!!!!!!!!!!!!1 ያነን ችጋርሽን በ ኔ ላይ ልትወጭ ነው አንች የሴት ልጅ ይልናበጥፊ ብሏት ይሄዳል ሰናይት፦ ወይኔያልፍልኛል ብየ እናቴንምወንድሜንምትቸ መጥቸ ልሰቃይ እማ ማሪኝመቸምእንግዲ አላገኛቸውምበዚሁሌ ተደይኔመኖር ነው ሰቅሰቅ ብላታለቅሳለች ትእይንት 10 ሳምሶን ፦ እማ መውጫችን እየደረሰ ነው ራሄል ፦ አዎ አሁን እንወጣለን ፖሊስ ፦ ወይዘሮራሄል የቅጣት ጊዜአቹን ጨርሳችኋል ደግማቹ ይህን ስራ እንዳትሰሩ አንተ ሌባ ዳግም ይሂን ስራ እንዳትሰራ ። በሉ ጓዛችሁን ያዙናውጡ ራሄል ፦ እሽ እግዚአብሔር ይስጥልኝደናሁኑ ጤና ችሁን ይስጣችሁ በመንገድ ሳምሶን ፦ እማ ተመልሰን ወደዚያ ወደ ቀድሞቤታችን ልንሄድ ነው ? ራሄል ፦ አይ ልጀ በዚያ ተቀድሰን በነበርንበትእንዲ ሲያርክሱን ባልዋልንበት ነገር ሌላቦታነው የምንሄድ አይዞህ በርታ እግዚአብሔር ባታ ያዘጋጅልናል ሳምሶን ፦ እማ ቤተ ክርስቲያን እዚ አለ እንሳለም ይጸልያሉ አቡነ ዘበሰማያት ራሄል ፦ አቤቱ ልጆቸን ተብቅልኝ ይቀመጣሉ አንድ አረጋዊ ያገኛቸዋል አረጋዊ ፦ አይ ጉልበት ደከመድሮእንዳሮጥኩበት ደህናዋላቹ ልጆቸ? ራሄልና ሳምሶን ፦ እግዚአብሔር ይመስገን ደህናዋሉ አባታችን? አረጋዊ ፦ እግዚኣብሔር ይመስገን ። ሳያችሁ ከሩቅ የመጣቹ ፤ የደከማቹ ትመስላላቹ፤ለቦታውም እንግዳ ናቹ መሰለኝ። ራሄል ፦ አዎ አባ ከሩቅ መንገድ ስለመጣን በጣም ነው የደከመን ። አረጋዊ ፦ አፈር ልብላ ተነሱ የኔ ቤት እዚ ቅርብ ነው እንሂድ። ቤት የእግዚአብሔር ነው። ከወደየት እየመጣቹ ነው ወዴትስ እየሄዳቹ ነው? ራሄል ፦ ከቤት እንድረስ እናእናወረዋለን ። ብዙ ነው አባታችን አረጋዊ ፦ አይዟቹ እየደረስን ነው ።
  • 13. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ አረጋዊ፦ እንደልቤ ነይማ እንግዳ አምጣቻለው የሆነ ውሃም ምግብም ስጫቸው ከእሩቅ ነው የመጡ ይጋበዛሉ ሽማግሌ ፦ ታዲያ እስኪ የት እንደመጣቹ ወዴትስ እየሄዳቹ ነው? ንገሩኝልጆቼ ራሄል ፦ እኛማ ከሃዋሳከተማ አንዲት ትንሽሰፈር ነበር የምንኖር ፤ ምንም ሃብት አልነበረኝም ፤ሃብቴ ድንግል ማርያምብቻ ነበረች ፤ የምንተዳደረው ልጀሊስትሮእየሰራ ፤ እኔ ደግሞበሰፈር እንጀራ እየጋገርኩ ነበር የምን ኖር። አንዲት ሴት ልጅምነበረችኝ(በሃዘን)። እና ከሰፈራችን አንድ መናፍቅ ነበር :: እሱምበኔ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ አደረገብኝናሴቲቱን ልጀን ወሰደብኝ። እኔን እና ይህን ልጀን አሳደዱን ። አሁን ሌላ የምንኖርበት ሃገር እየፈለግን ነው እንባ እያነባች ሽማግሌ ፦ አይ ሁለት እግር ጤና የለው ሰይጣን በሰዎች ልቦናእያደረ ብዙ ነገር ይፈትነናል ግን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድል እንዳደረገው እኛምማድማድረግ አለብን ።እኛ ግን ደካሞች ነን ። እንደዚህ ያለ ነገር ሲመጣ በጸጋ መቀብል አለብን።የእመቤታች ድንግልማርያምስደት ማስታወስአለብሽ። ስደትን እርሱ እግዚአብሔርወልድ ነው ተሰዶ ባርኮ የሰጠን ። ከዚ በኋላግን የትም አትሄዱምአዚ ከ እኔጋ አብራቹ ትኖራላቹ ። ኧንተምትምህርትህን እየተማርክ በትርፍ ግዜህ እኔን በስራ እያገዝክ ትኖራለህ ። አንችምእንዲሁከዚ ተቀመጭ ባለቤቴ ስለደከመች በስራ ታግዣታለሽ። ቤት የእግዚአብሔር ነው ። ራሄል ፦ እሱማ ጥሩ ነው እሽ አባታችን እግዚአብሔር ይስጥልን። ከትንሽቀን በኋላ አረጋዊት ሴት ፦ ከወደ ውጭ ትገባና አንተ ምን እያደረክ ነው ? ሳምሶን ፦ እማማ የቤት ስራ እየሰራሁነው። አረጋዊት ሴት፦ የቤት ስራ ! እንጀራ እየጋገርክ ወይስ ወጥእየሰራህ ወረቀትህን ይዘህ አታውቅምብለህ ነው ባይሆን ሌላባላውቅ የቤት ስራ ይጥፋኝ። ደግሞበኔ ልታሾፍ!!!! ወረቀቱን በልተህ ልታድር ነው ።የጣፉርዲ ልጅ ደሞ ታሾፋለህ ። ደግሞየቤት ስራናትምህርት መለየት ያቅተኝ ።ተነስ ከቤት ውጣትፋኝ ድራሽህን በዚ እንዳላይህ ብላበጥፊ ትመተዋለች። ሳምሶን ፦ በጣም ያዝናል ። ከእናቱ ጋር ይገናኛል። እማ እንግዲህ ኧንችምእኔምበሰው ቤት ተቀምተን ሰው ቅር ከምናስብል ። እኔ ወጣ ብየ ስራ ልፈልግ አንች ደግሞእኔእስክመጣ በዚህ ጠብቂኝ። ራሄል ፦ አይ ልጀየዚያች ረመጫት ሆዴን እየበለኝደግሞ አንተ ትተኸኝልትሄድ አብረን ነው የምንሄድ አንተን ከአይኔለደቂቃ እንኳ እንድትለየኝአልፈልግም ። ሳምሶን ፦ እማ እኔብቻየን ነው መሄድ የምፈልገው ልቀቂኝብሎእየተላቀሱ ይጓተታሉ ነጥቋት ይሮጣል ። ትንሽእንደሄደ ሳምሶን ፦ አሁን የት ነው የምሄ ድ ኧረ ወይ ጨለማው ዋጠኝኧረ እማ ወዴት ልሂድ እማን አላገኛት እያለ ያለቅሳል ራሄል ፦ አቤቱ አምላኬ በሰላምልጆቸን በየአሉበት ጠብቅልኝ? አንተተከተለውእምቢብሎኝሄደ አይ ሳምሶን እመቤቴ ትከተልህ ጥላከለላ ትሁን።
  • 14. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ትእ ይንት 11 ከአም ስት አመት በኋላ ሰበር ዜና አቶ ሳምሶን ዳኑኤል የሃገርቱ ንጉስ ሆነው ተመረጡ ሰናይት ፦ አቤት እስመአልቦ ነገር ዘይስዓኖ ለእግዚአብሔር ። የኔወንድምሳምሶን ነው። ግን ለዚ እንዴት ይበቃል ፎቶው ግን ትክክለኛ የሱነው ። አምላክ ተመስገን ፤ እኔ ግን በገንዘብ የእናቴንና የወንድሜን ፍቅር ቀየርኩ ። ግን አሁንምይቅር ይለኝይሆናል ። ከአለበት እየጠየኩ እሄዳለሁ ደባልቄ ፦ ጉድ ጉድ ዛሬ በጥዋቱ ምን አይነት ዜና አሰማኝ። ሳምሶን ዳኑኤል ንጉስ ወይ ጉዴ አይ ወይኔ ከሰርኩጉድ ጉድ እያለ ቤቱ ገብቶ ቁጭ ይላል። ወይ ኢየሱሴ ምን አሰማኝ። ሰናይት ፦ ጋሸ ምሁነህ ነው ዛሬ ? ደባልቄ ፦ ውጭ ያንገሽግሽሽ። ይች ጥፍራም። ጓደኘው አደረገችኝ ። ምናባቷን !!!! እንደልቡ፦ያ ቁርፋድ መናፍቅ አንዴ የልቡን ሰረውለት አሁን ጥፍት አለ ። ገልብጨነው የምጥለው ። እንዳውምይህ ነው መሰል ቤቱ ቆይ እስቴ ልጠይቀው። ብሎያንኳኳል ሰናይት ፦ አቤት ማን ነው ምን ሁነህ ነው ? እንደልቡ፦አቶ ደባልቄ የሉም ? ሰናይት ፦ አለ ግባ እንደልቡ፦እንዴት ዋሉ አቶ ደባልቄ ። ደባልቄ ፦ ደና ደና ዋልክ? እንደልቡ፦ምሁነህ ነው የደነገጥክ ትመስላለህ መኪናዎች አደጋደረሰባቸው እንዴ ታዝናለህ ። ነው ሳታተርፍ ቀረህ አይ ሃብታምሁሌ እኮ ጭንቀታምናቹ ።እኔ በምን እንደምጨነቅ ታቃለህ ሲጋራና ጫት ሳጣ ነው አንዳንዴ ደ ሃ መሆኔን በጣም ደስ ይለኛል ነው ወረት ከሰረብህ ? እኔእንኳ እማጨስባት ካገኘው አልጨነቅም። ወረቱ ከሰረ ብለህ ይሆናል ጭንቀታም ደባልቄ ፦ ምን መኪና ምን እንዳልሆነ ነው። ወረቱስ። ገንዘብ ቢጠፋ ይተካል፤ ኧረ ያስጨነቀኝሌላነገር አለ አንተንምይነካሃል ወይኔሳላስበው። እንደልቡ፦ምንድር ነው ኧረ ንገረኝ? እኔን ሲጋራ ጠፋ ወይም ተከለከለ እንዳትለኝ እ ደባልቄ ፦ ያኔ የዛሬ አምስት አመት ያሳደድነው ልጅ የሃገሪቱ መሪ ንጉስ ሆነ!!!!!!!!!!!!! እንደልቡ፦ኦ!!! ምን አይነት ጉድ ነው!!እኔምአንተምተሎ ብለን ተሎከዚች ሃገር መውጣት አለብን ። ደባልቄ ፦ ምን!!!!!!!!!!!!!!! ዛሬ ጥሩ ነገር አያሰማኝም እንዴ። መውጣት አንተ ከሆንክ ምንም የለህ ። እኔ ይህን ፎቅ ስንቱን መኪናትቸ ነው የምሄደው ደግመህ እንዲ ያለ ወሬ እንዳታወራ እንደልቡ፦እ ንጉስ አይከሰስም ሰማይ አይታረስም ሲባል ሰምተህአታቅም። እኔየራሴን ከዚ ወጥቸ እሄዳለሁ። ደባልቄ ፦ አይ ግን የዚያን ግዜ በኛ ምክንያት መሆኑን ያውቅ ብለህ ። እንደልቡ፦ አይ አያውቀነምእኔምማንነቴን ቀይሬ ነው የገባው ። ባክህ አያውቀነም!!!!!1 ደባልቄ ፦ ግን ይች እህቱ ከነገረችው ሳያጠፋን አይመለስም። ልጅቱን አንድ ነገር ማድረግ አለብን ።
  • 15. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ እንደልቡ ፦ እሷንማ ችግር የለውምእኔጥሩ ስልት አለኝ። በመርዝ እንግደላት? ደባልቄ ፦ ኣ እውነትህን ነው ።ታዲያ መርዙን ማን ከየት የት ባመጣልን ። ደግሞስ እንዴት አድርገን ነው የምናሰጣት ። እንደልቡ ፦ መርዙ ከኔ አንድ ውሻ ከሰፈር ነበረ እሱን ለመግደል የገዘውት አለ ።ቆራርጦ ይጥላታል ። ጥራትና ወደሱቅ ላካት ከዚያ መርዙን ከለስላሳ ጋር አደባልቀን እንሰጣታለን። እንዳትጠረጥር እየጠጣን እንቆያታለን ። ደባልቄ ፦ ሰናይት ነይ እማ ሳሙናከሱቅ ገዝተሽ ነይ አይጎበዝጀግና ጎበዝ እኮነሽ። እንደልቡ፦ በፍጥነት መርዙን ይቀላቅለዋል። ግን ስትጠጠው እንዳናያትወጣብለን እንቆያለን። ደባልቄ ፦ እሽ በቃ ። መጣሽ አይጎበዝበፍጥነት ነው የመጣሽ። ያሳድግሽ የጎበዝ ልጅ ። እንደልቡ ፦ ምን በባዶው ትነዘንዛታለህ ። ምረቃ በኪስ አይከተትም። የልቅ ከዚ ከምንጠጣው ስጣት ። ደባልቄ ፦ ደግሞ ለሰናይት ለለስላሳሌላምእሰጣት ነበር ።ያዥብሎመርዙ ያለበትን ይሰጣታል። ተጠቃቅሰው ይወጣሉ። ሰናይት ፦ ወንድሜ ንጉስ ሲሆን እንኳን ለስላሳቀርቶ ሌላእጠጣለሁ። ተመስገን አምላኬ። ከበቡሽ ፦ በድንገት ከኩሽና ቤት ወጥታ አንች ደፋር እንዴ እኔ ኩሽና ቤት ቁጭ ብየ አንች ለስላሳ ልትጠጭ ፤ ኣ !!!የገረድ ልጅ ገረድ በጥፊ ብላ ትቀማታለች ሂጅ እንጀራውን ጋገሪ። እኔሳልጠጣእሷ ደም ያስጠጣት ይች የሌባ የሌባ ልጅ ።ወይጉድ ግን አንች ምን ታደርጊ ኧረ እሱ ነው ። ብላ ትጠጠዋለች በሃይል ትወድቃለች። ትጮሃለችም እንደልቡ፦ከውጭ ሁኖ ሰርቷል ሰርቷል አይ የኔጥበብ የታባቷ ጭጭ አደረጋት ደባልቄ ፦ ሰርቷል ጨብጧል ያ ያ እየተሯሯጡ ይገባሉ ከበቡሽ ወድቃ ትታያለች እንደልቡ፦ወይኔ እጀን በጀ ቆረጥኩት ብሎእንቅ አድርጎ ይዞ ያለቅሳል። መጋረጃ ይዘጋል ትእይንት 12 ሰናይት ፦ ከውጭ ሁና አሁን እኔን አይደል ገደልሻት የሚሉኝተሎብየ መጥፋት አለብኝ። ብላትሄዳለች ። ከቤት እያዘኑ ይቀመጣሉ ከበደ ፦ ከቤት ውስጥቁጭ ብለው እናቴን የገደለ ሰው ማወቅ እፈልጋለሁ።ግን አንተ ነህ የገረድ ልጅ አለቅህምወይ ገዳይዋን ትነግረኛለህ። አባቴነህ ብየእለቅህ ይመስልሃል አለቅህምስማ ትነግረኛልህ ። የማነንምዱርየ እያመጣህ እናቴን ገደልካት እናቴ የምትሰጠኝን ፍቅር ካንተ ስለማላገኝ። ገዳይዋን ከተናገርክ ጥሩ ካልተናገርክ አንተን እንደሷ ደምአስተፋሃለሁ። ንገረኝኝ!!!! ምን ታየኛለህ ንገረኝ !!!! ሽወጥ አውጥቶ ይደግንባቸዋል። አንተ ዱርዬ አንተ ነህ !!!! የገደልካት እንደልቡ፦ አ ኧኧኧኧረረ እኔ ብቻ አይደለም አብረን ነው።
  • 16. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ከበደ፦ የኔ አባት ሚስተህን የልጆችህን እናት የእኛን እናት ገድለህ ምን ልትሆን አምሮህ ነው አንተ ልትኖር ነው የማንንም ዱርዬ ገዝተህ አምጥተህ ያስገደልካት እሷን አጥቼ ብፍቅሯ ከምሰቃይ አጥፍቸህ እጠፋለው ብሎ ሁለቱንም ይገልና እራሱም ይሞታል በራሱ ያጠፋል ፡ ትግስት ከውጬ የጥይቱን ድምጽ ሰምታ ትመጣለች ትግስት፦ ውይኔ ዘመዶች ባንዴ ኧር ኡኡኡኡኡ ታለቅስና እናቴን አጣው ደግሞ ወንድሜንና አባቴን ሳጣ ምን ኑሮ አለኝ እሷም እራሷን በራሷ ታጠፋለች ትእይንት 13 ንጉስ ሳምሶን፦ አቤቱ አመሰግንሃለሁ። ለዚህ ማእረግ ስለ አበቃኸኝ። አሁን የምለምንህ አንድ ነገር አለኝ። ያችን በድህነት ሁና ያሳደገችኝን እናቴን አገኛት ዘንድ ያንተ ቅዱስ ፈቃድህ ይሁንልኝ። እህቴንም አግኝቼ በንስሐ ታጥባ የመግስትህ ወራሽ ትሆን ዘንድ። እኒዚያን ባለማወቅ ያሰደዱንን ሰዎችም አግኝቸ ይቅር እላቸውና አመሰግናቸው ዘንድ ያንተ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልኝ። ወታደር ና ይህን ደብዳቤ ይዘህ በሙጃ ሰፈር የኔ እናት ፈልገህ ታመጣለህ ። ስሟ ራሄል ሄኖክ ትባላለች እንዳገኘሃት ይህን ደብዳቤ አንብብላት እና ትመጣልሃለች። ፈጠን ብለህ። ወታደር ፦ አሁን የት ነው የማገኛት ካጠዋት ከፍ ብሎ አንገቴን ዝቅ ብሎባቴን ነው የሚቆርጠኝ ኧረ አምላኬ እርዳኝ። ደህና ዋሉ እማማ አዚ ሰፈር ሰው ብጠይሽትነግሪኛለሽ ። ራሄል ፦ ኧረ ወይድልኝፖሊስ አልወድም ። ልጆቸን ያሰደደብኝፖሊስ ነው።እኔአዚ መንገድ ላይ ነው የምኖር ወታደር ፦ አይ ችግር የለም እማማ ወ/ሮራሄል ሄኖክ የምትባል ሴት ታውቂአለሽ? ራሄል ፦ ኧረ ደግሞ ምኑን አመጣህብኝ እኔ ልጀን ካጠው ወዲ ቤት የለኝም አይደል የምልህ ይህን ደግሞ የሰፈሩ ሰው ያውቃል ጠይቅ ምን ልታደርገኝነው የመጣህ። ወይኔ ጉዴደግሞ በዚህምመከራ አለ። ምኑን ልትለኝይሆን አምላኬ ከዚ ጉድ አውጣኝ ወታደር ፦ አይ ችግር የለም ይህን ደብዳቤ አነብልሻለሁ ደብዳቤው ይድረስ እንደጀራ ለምትርቢኝ፤ እንደ ውሃ ለምትጠሚኝለውዷ እናቴ ለወ/ሮራሄል እንዴት አለሽልኝእማ እኔ ደህናነኝ መቸም ይህ ደበዳቤ ሲነበብልሽእውነትአይመስልሽምግን እውነት ነው እማ እኔ ልጅሽሳምሶን ነኝ መቸም በህይወት የምኖር አይመስልሽም። እኔምአንች ያለሽአይመስለኝም ግን አለሁእማ አሁን ግን ንጉስ ሁኘ አለሁ። እማ አታምኒምይገባኛል ።ግን እማ ምልክት እንዲሆንሽ ያሰርሽልኝን ቀለበት እገልጽልሻለሁ።በይ እማ ይህን ደብዳቤ ያነበበልሽየኔወታደር ስለሆነ በሙሉ ልብሽ አምነሽው ይዞሽይምጣ ። በሰላም እንገናኝ ውዷ እናቴ ልጅሽሳምሶን ዳኑኤል ራሄል ፦ እሽ እውነትህን አይሆንምእንጅ እሄዳለሁ። ሲሄዱይታያሉ ወታደር ፦ ና በሩን ክፈተው ከንጉሱ ጋ ልንሄድ ነው ? ዘበኛ ፦ ቆይቆይ ንጉሱ ሳይፈቅዱማ አይቻልም ከሱ ጠብቁኝ። ንጉሱ ሽህ አመት ይንገሱ ። ወታደሩ ከአንዲት ሴት ጋር ሁነው ወእደ አንተ እንግባ ይላሉ
  • 17. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ ንጉስ ፦ አዎ ፈጠን ብለህ አስገባቸው። ዘበኛ ፦ ኑ ተፈቅዶላችኋል ግቡ ራሄል ፦ አንተ የኔ ልጅ ሳምሶን ነህ በድንጋጤመንፈስ ንጉስ ፦ አዎ እማ እኔ ሳምሶን ያንች ልጅ ነኝ ከዘመናት በፊት ያሰርሽልኝቀለበት ይሄው ራሄል ፦ እኽኽኽ ልጀ ብላ እቅፍ አድርጋይዛ ታለቅሳለች ። ንጉስ ፦ ወታደር ፈጠን ብለህ ወደ መጋረጃ ውሰዳትን ልብስ ቀይርላት። በዛውምትንሽትረፍ ምሳ በደንብ ከኔ ከሚሰራው ስጥዋት አቤቱ ስላደረክልኝሁሉ አመሰግንሃለሁ። አሁንምሁለት ነገር እለምንሃለሁ አንድ ያችን ምስኪኗን እህቴን ታገናኘን ዘንድ ሁለት እነዚያን ያሳደዱነን ሰውች አግኝቸ ይቅር እናአመሰግናቸው ዘንድ እለምንለሁ ሰናይት በመንገድ እየሄደች ትታያለች አሁን ወንድሜ ይቅር አይለኝምግን እስቲ ልሂድ እማ ካለች እሷ ታስታርቀኛለች የኔ ወንድምየአዲሱ ንጉስ እህት ነኝእስቲ እባክህ አስገባኝ ዘበኛ ፦ አ ዘወር በይ አንች ቆራጣ ነሽ የንጉስ እህት ። ከላ በይ ድሪቶ !!!! ሰናይት ፦ ንገረውናሲያየኝ ስለሚያውቀኝ ይነግርሃል ዘበኛ ፦ እንግዲያውስ አንድ ሰው ላምጣልሽናካወቅሽትገቢያለሽ። ወደዚያ ሸሻ ብለሽ ጠብቂኝ። አንች ሸሻ በይ እመጣና ። የ ንጉሱ እናት የሰወ ልጅ ነኝ የምትል አንዲት ልጅ ውጭ ስለምትፈልገወት ይምጡ ። ብሎይዟት ይሄዳል ሰናይት ፦ ከሩቅ አይታ እየሮጠች ሂዳ ከጉልበቷ ትደፋልች ። እማ ይቅር በሉኝበድያችኋለሁ። ራሄል ፦ ምን ይቅር አልልሽም። እንኳንስ እንዲህ ያለ ደስታወንድምሽንጉስ ሲሆን ፤ አንችንምሰይጣን ነው ያሳሳተሽ ግን ይቅር እልሻለሁ። አሁን ከወንድምሽ ጋር አገናኝሻለሁ። ሰናይት ፦ አይ እማ ወደሱ መሄድ የለብኝም በጣም ነው የበደልኩት ። ይቅርምአይለኝም። በድየዋለሁብላ ታለቅሳለች። ራሄል ፦ እኔ ያልኩትን ሁሉ ስለሚሰማ ችግር የለምይቅር ይልሻል ።ግድ የለሽምነንይሂጅ ልጀ እባክህ ይችን እህትህን ይቅር በላት ። ሰይጣን አሳስቷት ነው ንጉስ ፦ እሽ እማ አንች ካልሻት ችግር የለውምብቻ አንች ይቅር በያት። ብሎ እቅፍ አድርጎ ይዞ ይስማታል ያለቅሳልም እማ ግን እስከ ዛሬ እንዴት ብለሽኖርሽ በጣም ተንገላታሽ አይደል ራሄል ፦ አይ እኔስ የናንተ ናፍቆት ነበር እንጅ የገደለኝጤነየን ደህና ነበርኩ። ያው አንተ ትትሄኝ ስትሄድ የማወራውም የለኝ ነበር ዝም ብየ ቀርተት ባገኘውት እያደርኩ በየደብሩ እየዞርኩ የትሩፋት ስራዎችን ለበረከት እየሰራሁ በዛው ትንሽ ምግብ እየሰጡኝ ከዛ ባላይ እናተን ሳስብ ልቤ ይሰበርና ለሞት እዳረሳለው ትንፋሽ ያጥረኛል አይ ልጄ የዚች አለም ውጣ ውረድ ። ግን ሳምሶንዬ እንዴት ብለህ ለዚ በቃህ። ንጉስ ፦ አይ እማ የዚያን ግዜ ከአንች ጋራ ተለያይቸ የምገባበት ጠፍቶኝጨንቆኝሳለ ያጫካ ብሄደው ብሄደው አላልቅልኝ ብሎ ውይ እማ ሲያስፈራ!!!!!!!! የአራዌቱ ድምጽ ታዴያ የእመቤታችን ስደት እያስታወስኩ አለቅስም ደስ ይለኝም ነበር ። ከዜያ አንዲት ትንሽዬ ከተማ አገኘውና ሊስትሮ ስሰራ
  • 18. የእናት ፍቅር መንፈሳዊ ድራማ አክሱም ዩንቨርስቲ ግቤ ጉባኤ አንድ የውጭ ሃገር ዜጋ ተገናኘውና ወስጀ ላስተምርህ አለች ። መቸም አንችን የማገኝሽ አልመሰለኝም ይዞኝ ሄደ በዚያም ትምህርቴን ጨረስኩናለንግስናውድድር ቀረብኩ። ለድንግል ማርያም ነግሬያት ወደ ውድድሩ ገባው እሷም እረዳችኝ አንደኛ ወጣው የአምላክን እናት አመሰግንኩት አምላኬንም እንዲ አመሰገንኩት የመጨረሻ መዝሙር 1 አልተወኝም ጌታ 2 እግዚአብሔር ይመስገን 3 ሁሉ ከንቱ አነሳስቶ ላስጀመረን ለልኡል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር