SlideShare a Scribd company logo
1 of 2
-ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዴት እናንብባቸው?
1. ተራ ጠብቆ ማንበብ
ቅዱሳት መጻሕፍት ስመ ሥላሴን ጠርተው ከሚጀምሩበት የመጀመሪያ ምዕራፍ አንሥቶ እስከ ፍጻሜያቸው የሐሳብ የታሪክ ቅደም
ተከተል አላቸው፡፡የሚያነባቸው ሰው ሊረዳቸው የሚችለው ይህንን ቅደም ተከተል ጠብቆ ሲጓዝ ነው፡፡አንዳንድ ጊዜ በመካከል ለየት ያሉ ታሪኮች
ሲገጥሙን እንኳን ለጊዜው ተያያዥነታቸውን ባንረዳውም የኋላ ኋላ ግን እየተረዳነው እንሔዳለን፡፡የተጻፈበት ዓላማ ግልጽ እየሆነልን የሚመጣበት
ጊዜ አለ፡፡ከዚህ አንጻር ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ የሚጀምረው ሰው በዘፈቀደ በተገኘው ሥፍራ ገልጦ ከማንበብ ይልቅ መስመሩን ጠብቆ
የማንበብ ልማድ ሊኖረው ይገባል፡፡
የቅዱሳን መላእክትን ተአምራት የሚናገሩ ድርሳናትን ስናነብ ከመጀመሪያው አንሥቶ እያንዳንዱ ምዕራፍ የሚያስተላልፈው መልእክት
አለ፡፡የመልአኩን የስም ትርጉም፣ነገዱን፣የተሰጠውን የአገልግሎት ጸጋ፣ከብሉያት በሐዲሳት የሠራውን ተአምራት በየተራ እየነገረን ይሔድና ከዚያ
በኋላ ከሐዋርያት ዘመን በኋላ እስካለንበት ዘመን ድረስ የተደረጉትን ተአምራት በየተራ ይዘረዝርልናል፡፡ ለቅዱሳን መላእክት የተሰጠን ጸጋ
እግዚአብሔር ተረድተን በአማላጅነታቸው ለእኛም ተአምራት እንዲደረግልን እምነታችንን ያጎለምስልናል፡፡
የቅዱሳን አባቶችን ገድል ስናነብ ደግሞ ከቅዱሱ አባት የዘር ሐረግ ጀምሮ ከዚያ የእናትና አባታቸውን የተቀደሰ አኗኗር፣ ቅዱሳት
ከመወለዳቸው በፊት የተነገሩ ትንቢታትን እየዘረዘረ ይተርክልናል፡፡ከዚያም ቅዱሳን ሲወለዱ የነበረውን ሁኔታ አስተዳደጋቸውን ካደጉ በኋላ
በተጋድሎ መጽናታቸውን በጥሩ ሁኔታ ይተርክልናል፡፡በመጨረሻም ስለተጋድሎአቸው በዘመናቸው ፍጻሜ ጌታችንን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ተገልጦ ቃል ኪዳን ሲሰጣቸው ያስነብበናል፡፡ገድላቱን ስናነባቸው የቅዱሳንን የተጋድሎ ሕይወት አስነብበው እኛም ፍኖታቸውን እንድንከተል
መንፈሳዊ ቅናት እንዲያድርብን ሲያደርጉ በተጨማሪም የቅዱሳንን ቃል ኪዳን አንብበን ተጠቃሚ ለመሆን ራሳችንን እንድናዘጋጅ ያነሣሡናል፡፡
አንድ ሰው ድርሳናትን ወይም ገድላትን ሲያነብ ከመካከል ከጀመረ ወይም ፍጻሜያቸው ላይ ከተነሣ የቅዱሳት መጻሕፍቱን ሐሳብ
ለመረዳት፣ታሪካቸውም ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ ለማወቅ ይከብደዋል፡፡ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍትም ሲነበቡ እንዲሁ ተራቸውን ጠብቆ ቢነበቡ
መልካም ነው፡፡አንዳንድ ወጣቶች ብዙ መጻሕፍትን እንዳነበቡ እየነገሯችሁ ነገር ግን ያነበቡትን መጽሐፍ ታሪክ ስትጠይቋቸው ሲጀመር አልያ
ሲፈጸም ያለውን ብቻ ያስትውሳሉ፡፡ይህ አሟልቶ ባለማንበብ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡ሌሎችም ከአራትና አምስት ምዕራፍ በላይ ሳያነቡ ይህን
መጽሐፍ አንብቤዋለሁ ሲሉ የሚሰሙበት ጊዜ አለ፡፡ይህ አንባቢ ለመባል ያህል እንጂ መጻሕፍቱን ለማወቅና ለመረዳት አይመስልም፡፡
2. ማስታወሻ መያዝ
ቅዱሳት መጻሕፍት በውስጣቸው የያዙት ምስጢር ተዝቆ የማያልቅ ነው፡፡በእያንዳንዱ መጽሐፍ ውስጥ የምናገኘው ምስጢር ሁልጊዜም
አዲስ ነው፡፡ ስናነባቸው ባጠገባችን ማስታወሻ ይዘን ከሆነ የምናገኘውን ምስጢር እየመዘገብን ለማኖር ይረዳናል፡ ታሪክ ሲሆን የተረዳነውን በአጭሩ
ጽፈን ብናኖር፣ምስጢር ሲሆን ደግሞ እንዲገባን አድርገን ማስታወሻ ብንይዝ፣አንብበን ከፈጸምን በኋላ ስለዚያ መጽሐፍ ተመልሰን ለመከለስ
ይረዳናል፡፡አንዳንድ ሰው ብዙ መጻሕፍትን እንዳነበበ እየተናገረ ምን እንዳነበበ ግን በፍጹም የማያስታውስ አለ፡፡ይህ የሚሆነው ማስታወሻ
ካለመያዝ ነው፡፡ለጊዜው ደስ ደስ እያለን አንብበን ማስታወሻ ካልያዝን ወዲያውኑ እንዘነገዋለን፡፡ይልቁንም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
እንዳስተማረን አዕዋፍ የተባሉ አጋንንት ከልቦናችን እርሻ ላይ ስለሚለቅሙት ፈጥነን ልንዘነጋው እንችላለን /ማቴ፲፫-፭/፡፡
ማስታወሻ እየያዝን ስናነብ መጻሕፍቱ የሚሉትን ብቻ ለመጻፍ መሞከር አለብን፡፡አሳጥረን የምንጽፈው ታሪክ ሲኖረንም ሐሳቡን
እንዳይለቅ መጠንቀቅ አለብን፡፡የራሳችንን ሐሳብ ቀላቅለን ደባልቀን ከጻፍን ያንን እያነበብን ለስሕተት እንዳረጋለን፡፡ስለዚህ እንዳናሳስት ሁልጊዜም
ቅዱሳት መጻሕፍት የሚሉትን እርሱን ብቻ ሳንቀንስ ሳንጨምር ለማስፈር መሞከር አለብን፡፡የአበው የአነጋገር ዘይቤ በራሱ የመጻሕፍት ውበት
ነው፡፡ይህንን በራሳችን አባባል እንተካው ብለን ለዛውን ምስጢሩን እንዳናጠፋው መጠንቀቀ አለብን፡፡
ወጣቱ ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር ያለውን ግንኙነት በማጥበቅ እያንዳንዱን ቁም ነገር በማስታወሻ በመከተብ ቢጓዝ መንፈሳዊ ዕውቀቱን
ያበለጽጋል፡፡መሠረታዊ የሆነ መንፈሳዊ ዕውቀት እንዲኖረው የማንበብ ብቻ ሳይሆን በጥሩ መልኩ ማስታወሻ የመያዝና ከመምህራን እየጠየቀ
ትርጉሙን የመረዳት ልማድ ሊኖረው ይገባል፡፡የቀደሙ አበው በጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሆነው ያዩትን የሰሙትን ባይጽፉልን ኖሮ ቅዱሳት መጻሕፍትን
ለማንበብ እድል አይኖረንም ነበር፡፡እነርሱ ጽፈው በማስቀመጣቸው ግን ከብዙ ሺህ ዓመታት በኋላ አብረናቸው ያለን ያህል እያንዳንዱን ታሪክ
በንባብ እንከታተላለን፡ እንደዚሁ ለትውልድ ባይተርፍ እንኳን ለራሱና እንዲሁም ለቤተሰቡ ለጓደኞቹ እንዲሆን ወጣቱ ማስታወሻ እየያዘ ማንበብ
አለበት፡፡ያነበባቸውን ምክሮች፣ትምህርታዊ ጽሑፎች፣ታሪኮች በማስታወሻ መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
3. ያልተረዱትን መጠየቅ
የንግሥት የህንደኬ ባለሟል /የቃቤት በጅሮወንዷ/ የሚሆን ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ከኢየሩሳሌም እጅ ነስቶ ሲመለስ ትንቢተ ኢሳይያስን
ያነብ ነበር፡፡መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያው ፊሊጶስን ይኽን ባለ ሠረገላ ተከተለው አለው፡፡ፊሊጶስም ተከተለው፡፡በአጠገቡ በደረሰ ጊዜ ትንቢተ
ኢሳይያስን ሲያነብ አገኘው፡፡ሐዋርያው የምታነበውን ታስተዉለዋለህን? ብሎ ጠየቀው፡፡ጃንደረባውም መለሰለት የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት
ይቻለኛል»አለው/ሐዋ ፰-፴/ ፡፡በቅዱሳት መጻሕፍት ያለን መንፈሳዊ ምስጢር ማንም እንደገዛ ፈቃዱ እንዲተረጉም አልተፈቀደልም
ተርጓሚ/ምስጢሩን አብራርቶ የሚያስረዳ መምህር/ከሌለ መረዳት ማወቅ አይቻልም፡፡አበው በጸጋ መንፈስ ቅዱስ ተመርተው የጻፉት በመሆኑ
ተርጓሚ ያስፈልገዋል፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ ስለዚህ ነገር ሲጽፍ ‹‹ይህን በመጀመሪያ ዕወቁ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም
አልተፈቀደለትም ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ ››፪ጴጥ
፩-፳/ብሏል፡፡ሐዋርያው እንዳለው በመንፈሳዊ ቅኔ የተሞሉ፡፡አላፊያትን መፂያትን በአንድነት የያዙ የፈጣሬን የዘመናት ድንቅ ሥራ የሚተርኩ ቅድሳት
መጻሕፍትን ለመረዳት በመጻሕፍት እውቀት የበሰለ መምህር ተርጓሚ አመስጣሪ ያስፈልጋል፡፡
ማርቲን ሉተር ባመጣው ፍልስፍና የተወሰዱ መናፍቃን ሁሉ አንደፈቀደው አንዲያነብ እንዳሰበው እንደተረጉም ያስተምራሉ፡፡ይህ
አካሔድ ከጌታችን ከሐዋርያት አስተምህሮ የተለየ ነው፡፡እነርሱ ሁሉን እንዳሻህ ተርጉም የሚሉት በየትኛውም መንገድ ተጉዞ ቢሳሳት ከመንገዱ
ቢወጣ ስለማያሳስባቸው ግድ ስለማይላቸው ነው፡፡ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ግን የቀደመው የአበው ትምህርት ሳይበረዝ ሳይከለስ ለትውልድ
እንዲተላለፍ ትሻለች።ልጆቿ መስመሩን ጠብቀው በሃይማኖት ጸንተው እንዲኖሩ ትሻለች፡፡ስለዚህ ሁልጊዜም በራስ ፈቃድ ከማንበብና ከመተርጎም
ይልቅ ከአበው ከመምህራን እንድንጠይቅ ትመክረናለች፡፡
ወጣቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን የማንበብ ልምዱን እያዳበረ ከዚህ ጋር ወደ መምህራን ቀርቦ ያልተረዳውን መጠየቅንም ተግባሩ ማድረግ
አለበት፡፡ቅዱስ ጳውሎስ‹‹በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ አደንቃለሁ፡፡እርሱ
ግን ሌላ ወንጌል አይደለም የሚያናውጣችሁ የክርስቶስን ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ››/ገላ ፩-፮/ይለናል፡፡ሐዋርያዉ እንዳለው
መጻሕፍትን አጣመው የሚተረጉሙ መናፍቃን ሊገጥሙት ስለሚችሉ ትክክለኛውን ትርጉም መረዳት ወጣቱን ከጥፋት ይጠብቀዋል፡፡ሰለዚህም
ከጥሩ ምንጭ እየተቀዳ የሚቀርበውን የአባቶች ትምህርት ለማግኘት መምህራንን መፈለግ ተገቢ ነዉ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Email ThisBlogThis!Share to TwitterShare to FacebookShare to Pinterest

More Related Content

Featured

How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
ThinkNow
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Kurio // The Social Media Age(ncy)
 

Featured (20)

2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot
 
Everything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTEverything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPT
 
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsProduct Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
 
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
 
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfAI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
 
Skeleton Culture Code
Skeleton Culture CodeSkeleton Culture Code
Skeleton Culture Code
 
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
 
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
 
How to have difficult conversations
How to have difficult conversations How to have difficult conversations
How to have difficult conversations
 
Introduction to Data Science
Introduction to Data ScienceIntroduction to Data Science
Introduction to Data Science
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best Practices
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project management
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
 

Danial

  • 1. -ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዴት እናንብባቸው? 1. ተራ ጠብቆ ማንበብ ቅዱሳት መጻሕፍት ስመ ሥላሴን ጠርተው ከሚጀምሩበት የመጀመሪያ ምዕራፍ አንሥቶ እስከ ፍጻሜያቸው የሐሳብ የታሪክ ቅደም ተከተል አላቸው፡፡የሚያነባቸው ሰው ሊረዳቸው የሚችለው ይህንን ቅደም ተከተል ጠብቆ ሲጓዝ ነው፡፡አንዳንድ ጊዜ በመካከል ለየት ያሉ ታሪኮች ሲገጥሙን እንኳን ለጊዜው ተያያዥነታቸውን ባንረዳውም የኋላ ኋላ ግን እየተረዳነው እንሔዳለን፡፡የተጻፈበት ዓላማ ግልጽ እየሆነልን የሚመጣበት ጊዜ አለ፡፡ከዚህ አንጻር ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ የሚጀምረው ሰው በዘፈቀደ በተገኘው ሥፍራ ገልጦ ከማንበብ ይልቅ መስመሩን ጠብቆ የማንበብ ልማድ ሊኖረው ይገባል፡፡ የቅዱሳን መላእክትን ተአምራት የሚናገሩ ድርሳናትን ስናነብ ከመጀመሪያው አንሥቶ እያንዳንዱ ምዕራፍ የሚያስተላልፈው መልእክት አለ፡፡የመልአኩን የስም ትርጉም፣ነገዱን፣የተሰጠውን የአገልግሎት ጸጋ፣ከብሉያት በሐዲሳት የሠራውን ተአምራት በየተራ እየነገረን ይሔድና ከዚያ በኋላ ከሐዋርያት ዘመን በኋላ እስካለንበት ዘመን ድረስ የተደረጉትን ተአምራት በየተራ ይዘረዝርልናል፡፡ ለቅዱሳን መላእክት የተሰጠን ጸጋ እግዚአብሔር ተረድተን በአማላጅነታቸው ለእኛም ተአምራት እንዲደረግልን እምነታችንን ያጎለምስልናል፡፡ የቅዱሳን አባቶችን ገድል ስናነብ ደግሞ ከቅዱሱ አባት የዘር ሐረግ ጀምሮ ከዚያ የእናትና አባታቸውን የተቀደሰ አኗኗር፣ ቅዱሳት ከመወለዳቸው በፊት የተነገሩ ትንቢታትን እየዘረዘረ ይተርክልናል፡፡ከዚያም ቅዱሳን ሲወለዱ የነበረውን ሁኔታ አስተዳደጋቸውን ካደጉ በኋላ በተጋድሎ መጽናታቸውን በጥሩ ሁኔታ ይተርክልናል፡፡በመጨረሻም ስለተጋድሎአቸው በዘመናቸው ፍጻሜ ጌታችንን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ቃል ኪዳን ሲሰጣቸው ያስነብበናል፡፡ገድላቱን ስናነባቸው የቅዱሳንን የተጋድሎ ሕይወት አስነብበው እኛም ፍኖታቸውን እንድንከተል መንፈሳዊ ቅናት እንዲያድርብን ሲያደርጉ በተጨማሪም የቅዱሳንን ቃል ኪዳን አንብበን ተጠቃሚ ለመሆን ራሳችንን እንድናዘጋጅ ያነሣሡናል፡፡ አንድ ሰው ድርሳናትን ወይም ገድላትን ሲያነብ ከመካከል ከጀመረ ወይም ፍጻሜያቸው ላይ ከተነሣ የቅዱሳት መጻሕፍቱን ሐሳብ ለመረዳት፣ታሪካቸውም ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ ለማወቅ ይከብደዋል፡፡ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍትም ሲነበቡ እንዲሁ ተራቸውን ጠብቆ ቢነበቡ መልካም ነው፡፡አንዳንድ ወጣቶች ብዙ መጻሕፍትን እንዳነበቡ እየነገሯችሁ ነገር ግን ያነበቡትን መጽሐፍ ታሪክ ስትጠይቋቸው ሲጀመር አልያ ሲፈጸም ያለውን ብቻ ያስትውሳሉ፡፡ይህ አሟልቶ ባለማንበብ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡ሌሎችም ከአራትና አምስት ምዕራፍ በላይ ሳያነቡ ይህን መጽሐፍ አንብቤዋለሁ ሲሉ የሚሰሙበት ጊዜ አለ፡፡ይህ አንባቢ ለመባል ያህል እንጂ መጻሕፍቱን ለማወቅና ለመረዳት አይመስልም፡፡ 2. ማስታወሻ መያዝ ቅዱሳት መጻሕፍት በውስጣቸው የያዙት ምስጢር ተዝቆ የማያልቅ ነው፡፡በእያንዳንዱ መጽሐፍ ውስጥ የምናገኘው ምስጢር ሁልጊዜም አዲስ ነው፡፡ ስናነባቸው ባጠገባችን ማስታወሻ ይዘን ከሆነ የምናገኘውን ምስጢር እየመዘገብን ለማኖር ይረዳናል፡ ታሪክ ሲሆን የተረዳነውን በአጭሩ ጽፈን ብናኖር፣ምስጢር ሲሆን ደግሞ እንዲገባን አድርገን ማስታወሻ ብንይዝ፣አንብበን ከፈጸምን በኋላ ስለዚያ መጽሐፍ ተመልሰን ለመከለስ ይረዳናል፡፡አንዳንድ ሰው ብዙ መጻሕፍትን እንዳነበበ እየተናገረ ምን እንዳነበበ ግን በፍጹም የማያስታውስ አለ፡፡ይህ የሚሆነው ማስታወሻ ካለመያዝ ነው፡፡ለጊዜው ደስ ደስ እያለን አንብበን ማስታወሻ ካልያዝን ወዲያውኑ እንዘነገዋለን፡፡ይልቁንም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን አዕዋፍ የተባሉ አጋንንት ከልቦናችን እርሻ ላይ ስለሚለቅሙት ፈጥነን ልንዘነጋው እንችላለን /ማቴ፲፫-፭/፡፡ ማስታወሻ እየያዝን ስናነብ መጻሕፍቱ የሚሉትን ብቻ ለመጻፍ መሞከር አለብን፡፡አሳጥረን የምንጽፈው ታሪክ ሲኖረንም ሐሳቡን እንዳይለቅ መጠንቀቅ አለብን፡፡የራሳችንን ሐሳብ ቀላቅለን ደባልቀን ከጻፍን ያንን እያነበብን ለስሕተት እንዳረጋለን፡፡ስለዚህ እንዳናሳስት ሁልጊዜም ቅዱሳት መጻሕፍት የሚሉትን እርሱን ብቻ ሳንቀንስ ሳንጨምር ለማስፈር መሞከር አለብን፡፡የአበው የአነጋገር ዘይቤ በራሱ የመጻሕፍት ውበት ነው፡፡ይህንን በራሳችን አባባል እንተካው ብለን ለዛውን ምስጢሩን እንዳናጠፋው መጠንቀቀ አለብን፡፡ ወጣቱ ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር ያለውን ግንኙነት በማጥበቅ እያንዳንዱን ቁም ነገር በማስታወሻ በመከተብ ቢጓዝ መንፈሳዊ ዕውቀቱን ያበለጽጋል፡፡መሠረታዊ የሆነ መንፈሳዊ ዕውቀት እንዲኖረው የማንበብ ብቻ ሳይሆን በጥሩ መልኩ ማስታወሻ የመያዝና ከመምህራን እየጠየቀ ትርጉሙን የመረዳት ልማድ ሊኖረው ይገባል፡፡የቀደሙ አበው በጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሆነው ያዩትን የሰሙትን ባይጽፉልን ኖሮ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ እድል አይኖረንም ነበር፡፡እነርሱ ጽፈው በማስቀመጣቸው ግን ከብዙ ሺህ ዓመታት በኋላ አብረናቸው ያለን ያህል እያንዳንዱን ታሪክ በንባብ እንከታተላለን፡ እንደዚሁ ለትውልድ ባይተርፍ እንኳን ለራሱና እንዲሁም ለቤተሰቡ ለጓደኞቹ እንዲሆን ወጣቱ ማስታወሻ እየያዘ ማንበብ አለበት፡፡ያነበባቸውን ምክሮች፣ትምህርታዊ ጽሑፎች፣ታሪኮች በማስታወሻ መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  • 2. 3. ያልተረዱትን መጠየቅ የንግሥት የህንደኬ ባለሟል /የቃቤት በጅሮወንዷ/ የሚሆን ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ከኢየሩሳሌም እጅ ነስቶ ሲመለስ ትንቢተ ኢሳይያስን ያነብ ነበር፡፡መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያው ፊሊጶስን ይኽን ባለ ሠረገላ ተከተለው አለው፡፡ፊሊጶስም ተከተለው፡፡በአጠገቡ በደረሰ ጊዜ ትንቢተ ኢሳይያስን ሲያነብ አገኘው፡፡ሐዋርያው የምታነበውን ታስተዉለዋለህን? ብሎ ጠየቀው፡፡ጃንደረባውም መለሰለት የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል»አለው/ሐዋ ፰-፴/ ፡፡በቅዱሳት መጻሕፍት ያለን መንፈሳዊ ምስጢር ማንም እንደገዛ ፈቃዱ እንዲተረጉም አልተፈቀደልም ተርጓሚ/ምስጢሩን አብራርቶ የሚያስረዳ መምህር/ከሌለ መረዳት ማወቅ አይቻልም፡፡አበው በጸጋ መንፈስ ቅዱስ ተመርተው የጻፉት በመሆኑ ተርጓሚ ያስፈልገዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ስለዚህ ነገር ሲጽፍ ‹‹ይህን በመጀመሪያ ዕወቁ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደለትም ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ ››፪ጴጥ ፩-፳/ብሏል፡፡ሐዋርያው እንዳለው በመንፈሳዊ ቅኔ የተሞሉ፡፡አላፊያትን መፂያትን በአንድነት የያዙ የፈጣሬን የዘመናት ድንቅ ሥራ የሚተርኩ ቅድሳት መጻሕፍትን ለመረዳት በመጻሕፍት እውቀት የበሰለ መምህር ተርጓሚ አመስጣሪ ያስፈልጋል፡፡ ማርቲን ሉተር ባመጣው ፍልስፍና የተወሰዱ መናፍቃን ሁሉ አንደፈቀደው አንዲያነብ እንዳሰበው እንደተረጉም ያስተምራሉ፡፡ይህ አካሔድ ከጌታችን ከሐዋርያት አስተምህሮ የተለየ ነው፡፡እነርሱ ሁሉን እንዳሻህ ተርጉም የሚሉት በየትኛውም መንገድ ተጉዞ ቢሳሳት ከመንገዱ ቢወጣ ስለማያሳስባቸው ግድ ስለማይላቸው ነው፡፡ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ግን የቀደመው የአበው ትምህርት ሳይበረዝ ሳይከለስ ለትውልድ እንዲተላለፍ ትሻለች።ልጆቿ መስመሩን ጠብቀው በሃይማኖት ጸንተው እንዲኖሩ ትሻለች፡፡ስለዚህ ሁልጊዜም በራስ ፈቃድ ከማንበብና ከመተርጎም ይልቅ ከአበው ከመምህራን እንድንጠይቅ ትመክረናለች፡፡ ወጣቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን የማንበብ ልምዱን እያዳበረ ከዚህ ጋር ወደ መምህራን ቀርቦ ያልተረዳውን መጠየቅንም ተግባሩ ማድረግ አለበት፡፡ቅዱስ ጳውሎስ‹‹በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ አደንቃለሁ፡፡እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም የሚያናውጣችሁ የክርስቶስን ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ››/ገላ ፩-፮/ይለናል፡፡ሐዋርያዉ እንዳለው መጻሕፍትን አጣመው የሚተረጉሙ መናፍቃን ሊገጥሙት ስለሚችሉ ትክክለኛውን ትርጉም መረዳት ወጣቱን ከጥፋት ይጠብቀዋል፡፡ሰለዚህም ከጥሩ ምንጭ እየተቀዳ የሚቀርበውን የአባቶች ትምህርት ለማግኘት መምህራንን መፈለግ ተገቢ ነዉ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር Email ThisBlogThis!Share to TwitterShare to FacebookShare to Pinterest