SlideShare a Scribd company logo
1 of 36
Download to read offline
1ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 www.temsalet.com
ትምህርት
በጥርስ
መካከል
ምክንያትና
ውጤቱ
ማህበራዊ
ድረ ገጾችና
ትምህርታዊ
ፋይዳ
የሥነ ምግባር
ጉዳይ
2 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
አገሬ
አገሬ ውበት ነው
ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት
ጸሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ።
አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ
አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ።
ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም
ክረምቱም አይበርድም፣
አይበርድም፣ አይበርድም።
አገሬ ጫካ ነው
እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነጻነት።
በሃገር መመካት፣
በተወላጅነት፣
በባለቤትነት.....
(ሰዓሊ እና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ)
ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
ክብርት ዶክተር
ስንዱ ገብሩ
10ጥያቄዎች
ለትምህርት ቢሮ
10ጥያቄዎች
ለግል ት/ቤቶች 	
	 ማሕበር
የነገ
ዛሬዎች
የሃይገር
ወጎች
ትምህርት
በጥርስ
መካከል
ምክንያትና
ውጤቱ
የሰው ልጅ አንጎል
ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ
የከፍተኛ ትምህርት
ዘይቤ
በእጓለ ገብረዮሃንስ
ማህበራዊ
ድረ ገጾችና
ትምህርታዊ
ፋይዳ
ከአዕምሮ ውስጥ
የሚሸት ጣፋጭ
የዩኒቨርሲቲ ትዝታ
የሥነ ምግባር
ጉዳይ …
1
3
25
14
16
19
23 28
9
10
11
በዚህ
ዕትም
www.temsalet.com
ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
በአገራችን ትምህርትን አስመልክቶ የሚነሳ አባባል አለ
ለወራት ችግር ጎመን፣ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ጤፍ ዝራ፤ ለአመታት
ችግርህ ማንጎ፣ ቡና ዝራ፤ ለመቶ አመታት ችግርህ ዛፍ ዝራ፤
ለዕድሜ ልክ ችግርህ ትምህርት ዝራ፤ ይባላል፡፡ እነዚህ
አባባሎች ከአባባል ባሻገር የሚሰጠው መልዕክት ትልቅ ነው።
ለዕድሜ ልክ ችግርህ መፍቻ የተጠቀሰው ትምህርት ምን
ያህል ትኩረት ተሰጥቶታል ብለን ያልን እንድሆን እንብዛም
ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ መንግስት ለትምህርት ቤቶች መስፋፋት
እያደረገ ያለው ጥረት እጅግ የሚበረታታ እና የሚደገፍ
ሆኖ ሳለ ዛሬም ለትምህርት ጥራት እንዲሁም ለትምህርት
ቤቶች የሚደረገው ድጋፍ የሚያበረታታ አይደለም፡፡
Africa.comBlog ኢትዮጵያ በአምስት የተመረጡ ዘርፎች
በኢንቨስትመንት ዓለምን የምትስብ ሀገር ናት ሲል ይገልፃል
፡፡ ከነዚህ ሳቢ ኢንቨስትመንቶች አንዱ ትምህርት ነው ፡፡
መንግስት ለማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ፣
ለእርሻ ኢንዱስትሪ፣ ለኢንዱስትሪ ማስፋፋያ እና ለአይ
ሲቲ ዘርፎች የሚደረግ የኢንቨስትመንት ልማት ቅድሚያ
የሚሰጥ ሲሆን እንደ ሆቴል እና አበባ ልማት የሚከናወኑ
ኢንቨስትመንቶች ላይ ከታክስ እና ግብር ቅናሳ ጀምሮ
ያለቀረጥ የሚገቡ መገልገያዎችን በነፃ እንዲገቡፈቅዷል ፡
፡ ለትምህርት አገልግሎት ሲሆን እነዚህ ማበረታቻዎች ለምን
ዝግ እና ቅድሚያ የሚሰጠው እንዳልሆነ ግልፅ አይደለም ፤
በተለይም ትምህርት በኢንቨስትመንት ሊታቀፍ የሚገባው
ዋና የኢንቨስትመንት መስክ ነውና፡፡ የሆነው ሆኖ ለሁሉም
ነገር መሰረት የሆነው ትምህርት ጠንካራ ድጋፍ ሊደረግለት
ይገባል፡፡
የተምሳሌት
አቋም
የተምሳሌት
አቋም
በትምህርት እና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር በየወሩ
የሚታተም መጽሔት ነው ፡፡ ተምሳሌት መጽሔት በኢትዮጽያ
ብሮድካስት ባለሥልጣን ምዝገባ ቁጥር 279/2006 እና በንግድ
ምዝገባ ቁጥር kik/AA/2/0003278/2007 ሐምሌ 15 ቀን
2006 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡
ዋና አዘጋጅ
ንጉስ ይልማ
አድራሻ: ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 09
የቤት ቁጥር 1711
negus@akbdmedia.com
ማኔጂንግ ዳይሬክተር
ከድር አህመድ
kedir@akbdmedia.com
ኤዲቶሪያል ቡድን
ደሳለኝ መኩሪያ desalegn@akbdmedia.com
አዲስ ፀጋዬ addis@akbdmedia.com
በለጠ ጌታቸው belete@akbdmedia.com
ዓለማየሁ ስሜነህ alemayehu@yahoo.com
አምደኞች
ወንድሙ ነጋሽ (ከሎንዶን)
ጽጌሬዳ ጎንፋ
መላኩ አላምረው (የእናት ልጅ)
ክቡር መተኪያ
ሄኖክ ሰይድ
አየለ ተሰፋዬ
ዲዛይን
በፀጋ ግርማ
ካርቱኒስት
ገነነው ውብሸት
የኮምፒዩተር ጽሁፍ
አዜብ ዓለማየሁ azeb@akbdmedia.com
ገበያ ስርጭት እና ክትትል
ዮርዳኖስ በቀለ
የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ
ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 3277 ዘርሽታ
ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 212
ስልክ ቁጥር 251 911225298 ፖ.ሳ.ቁ 54154
ኢ-ሜይል info@temsalet.com
www.temsalet.com
አሳታሚ
ኤኬቢዲ የፕሬስ የማስታወቂያና የማማከርአገልግሎት
www.akbdmedia.com
1ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
ክ
ብርት ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ከ1948 ዓ.ም. እስከ 1952 ዓ.ም.
ድረስ የመጀመሪያዋ የሴት የፓርላማ የሕግ መምሪያ ምክር
ቤት አባልና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ም/ሊቀመንበር ሆነው
በማገልገላቸው ታሪክ “የመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ አባል”
ብሎ መዝግቧቸዋል።
ትዉልድ እና እድገት
ከአጼ ቴዎድሮስ ጀምሮ እስከ አጼ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ድረስ
በከፍተኛ ሃላፊነት ያገለገሉት እና በወቅቱ ተራማጅ አስተሳሰብ ከነበራቸው
ቀደምት ኢትዮጵያዊ ምሁራን መካከል የሚመደቡት እና የጎንደር ከተማ
ከንቲባ የነበሩት ገብሩ ደስታ ወይም በብዙዎች ዘንድ በሚታወቁበት
ስማቸው ጆቤው እና ወይዘሮ ካሳዬ ይሌምቱ ከወለዷቸው በርካታና ዝነኛ
ልጆች መካከል ስንዱ ገብሩ የላቀ እዉቅናን የተጎናጸፉ ሴት ናቸው::እኚሁ
ሰው በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሃገር በመናገሻ አዉራጃ በአዲስ አለም ከተማ
በወረሃ ጥር በስድስተኛዉ ቀን በ1908 ዓ.ም ተወለዱ::የታላቅ ባላባት
ልጅ እንደመሆናቸው መጠን በመኖሪያ ቤታቸው መምህር ተቀጥሮላቸው
ሲማሩ ቆይተዋል:: ይህንን በወቅቱ እንደ ታላቅ ትምህርት ይቆጠር
የነበረዉን የአብነት ትምህርት እና ዳዊት መቁጠር ከተማሩ በኋላ በወቅቱ
በአቅራቢያቸው ይገኝ ከነበረው የስዊድን ወንጌላዊት ሚሲዮን ትምህርት
ቤት በመግባት የአንደኛ ደረጃ ትምህርትን በሚገባ አጠናቀቁ::
ከተቀዳሚዎቹ የዉጪ ተማሪዎች አንዷ
ከንቲባ ገብሩ ደስታ ዉጪ ሃገር ሄደው ከተማሩ ቀደምት እና ጥቂት
ኢትዮጵያዊያን ምሁራኖች መካከል የሚመደቡ ከመሆናቸው የተነሳ
እንዲሁም እንደ እነ ስንዱ ገብሩ ያሉ ህጻናቶች ስለ አባታቸው የዉጭ ሃገር
ቆይታ ብሎም የትምህርት አይነት አጥብቀው ይጠይቁ ስለነበር በወቅቱ
እንደ ብርቅ ይታይ የነበረዉን የዉጭ ሃገር ከፍተኛ ትምህርት ለመቅሰም
ስንዱ ገብሩከታናሽ እህታቸው ከየዉብዳር ገብሩ ጋር በአንድነት በመሆን
በአባታቸው በከንቲባ ገብሩ ደስታ አጃቢነት ወደ ስዊዘርላንድ ሃገር አመሩ::
ከንቲባ ገብሩ ደስታ(ጆቤው) ከአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ጋር ከፍተኛ
ቅርርብ ስለነበራቸው የልጆቻቸው የዉጭ ሃገር ትምህርት በቀላሉ እንዲሳካ
ረድቷቸዋል፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ነው የጆቤው ልጆች ወደ ዉጭ
ሃገር ሄደው እንዲማሩ የተወሰነው፤ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ከታናሽ እህታቸው
የዉብዳር ገብሩ ለትምህርት ወደ አውሮፓ ተጉዘዋል፡፡
ወደ ስዊዘርላንድ ሃገር ለከፍተኛ ትምህርት በሄዱበት ወቅት የመነጋገሪያው
ቋንቋ በርካታ ቢሆንም ስንዱ እና እህታቸው ባረፉበት ግዛት ይነገርበት
የነበረው ቋንቋ ጀርመንኛ ስለነበረ እና ቋንቋዉን ለመረዳት ከባድ
ስለሆነባቸው ለስድስት ወር የነበራቸውን የስዊዘርላንድ ቆይታ በመተው
ወደ ፈረንሳይ ሃገር አመሩ:: በጊዜው የገቡበት “ሞሚራይ” የተሰኘው
ትምህርት ቤት እድሜያቸው ከአስራ አምስት አመት በላይ የሆናቸውን
ልጃገረዶች ብቻ የሚቀበል የነበረ ተቋም ቢሆንም ከእሩቅ ሃገር
ትምህርትን ብለው ለመጡት ለእነዚህ ህጻናቶች ሲባል ብቻ መምህር በግል
ተመድቦላቸው ታላቅ እና ታናሽ እህትማማቾቹ ስንዱ እና የዉብ ዳር ገብሩ
የቀለም ትምህርትን እንዲማሩ እና ጥሩ እዉቀትን እንዲያገኙ ተደረገ::
(የዉብዳር ገብሩ በኋልኛው ዘመን በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የረቂቅ
ሙዚቃ ተጫዋች በመሆን በርካታ የሙዚቃ አልበምን ያሳተሙ ከጊዜያት
በኋላ ደግሞ እድሜያቸውን በምንኩስና ህይወት ለመምራት የመረጡ
የዉብዳር የተሰኘ የአለም ስማቸውን ትተው እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ
በሚል ስማቸው የሚታወቁ ሌላ ስመጥር ኢትዮጵያዊ ናቸው)::በወቅቱም
የቤት አስተዳደር የምግብ አዘገጃጀት የፒያኖ አጨዋወት የስፌት መኪና
ትምህርት የአመት በጀት አያያዝን ጨምሮ በወቅቱ ለሃገራችን ብርቅ የሆኑ
ትምህርቶችንበፈረንሳይ ሃገር ተምረውበዲፕሎማ ማዕረግትምህርታቸውን
በማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ::
በበርካቶች ዘንድ የወይዘሮ ስንዱ ቀዳሚነት እሚጠቀስላቸው የመጀመሪያዋ
የሴት ፓርላማ አባል የመሆናቸው ጉዳይ ቢሆንም በኢትዮጵያ እምብዛም
ያልተለመደውን የሴት መምህርነት እና የሴት ርዕሰ መምህርነት፣የሴት ጸሃፊ
ተዉኔትነት፣የሴት ደራሲነት፣የሴት ገጣሚነት ወዘተ በመስራት ለብዙ ሰዎች
አርአያ ለመሆን በቅተዋል::
ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ተቀጥረው ፈረንሳይኛ
አማርኛ ጽሁፍ እና ስለ ጤና አጠባበቅ ለማስተማር ችለዋል::በዚህ ሁኔታ
ለአንድ አመት ከቆዩ በኋላ ከአምባሳደር ብላታ ዶክተር ሎሬንዞ መብርሃቱ
ጋር ጋብቻ ፈጸሙ፡፡ ወይዘሮ ስንዱ ባለቤታቸው ብላታ ሎሬንዞ በቀድሞ
መጠሪያው የሃረርጌ ጠቅላይ ግዛት በአስተዳዳሪነት በመሾማቸው ከአዲስ
አበባ ወደ ሃረርጌ አቀኑ::ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ ደግሞ ባለቤታቸዉ
ሎሬንዞ የፍርድ ቤት ሹምና የዜና ስርጭት ኃላፊ ሆነው በመሾማቸው
ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ቻሉ::
የሴት አርበኝነት
በአድዋ ድል በቀመሰው የሽንፈት ቂም ይዞ ለአርባ አመታት ገደማ ሲያደባ
እና ጦር ሲያደራጅ የከረመው የፋሽት ኢጣልያ ወራሪ ጦር የአዉራዉን
የሞሶሎኒ የሮም አደባባይ ድንፋታ ተከትሎ እና የመረብ ወንዝን ተሻግሮ
የኢትዮጵያን ዋና ዋና ከተማዎች በተቆጣጠረበት ጊዜ ንጉሰ ነገስቱ አጼ
ክብርት ዶክተር
ስንዱ ገብሩበ ክቡር መተኪያ
2 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
ሃይለስላሴ በስደት ወደ እንግሊዝ ሃገር ሲጓዙ
አብረዋቸው እንዲጓዙ ከመረጧቸው የቅርብ
ዘመዶች ልጆች እና ታላላቅ ሹማምንቶች
መካከል ብላቴን ጌታ ሎሬንዞ ሲገኙበት ቆራጧ
አርበኛ ስንዱ ገብሩ ግን እምቢኝ ላገሬ ብለው
ሆለታ ከሚገኘው የአርበኛ ጦር እና ጎሬ ላይ
ከተቋቋመው ጊዜያዊ የኢትዮጵያ መንግስት
ባላደራ አርበኞቹ ከእነ ራስ እምሩ ጦር ጋር
ተቀላቀሉና ሃገራቸውን ከወራሪ ጦር የማስጣል
ስራ ጀመሩ::በዚህ ጊዜም ለአርበኝነት ይረዳቸው
ዘንድ ከወሰዱት ስልጠና ሁሉ የመትረየስ
አተኳኮስ ስልጠናው ቀዳሚ እና ተጠቃሽ ነው::
ወይዘሮ ስንዱ ተኩሰው ጠላትን ለመጣል
የሚንተገተግ ወኔ የነበራቸው እና ለነብሳቸው
ቅንጣት ታክል የማይሳሱ ጀግና አርበኛ የነበሩ
ቢሆንም ቀደም ብለው በፈረንሳይ ሃገር
በቀሰሙት እዉቀት ምክንያትነት እንዲሁም
በጊዜው የመጀመሪያ እርዳታ የሚሰጥ ሰው
ከአርበኞቹ መካከል እንደልብ ማግኘት ከባድ
ስለነበር በወቅቱ የአርበኞቹን መሪ ልዑል
ራስ እምሩ ሃይለስላሴን አማክረው አምስት
መቶ የኢትዮጵያ ብር በመቀበል የኢትዮጵያ
ቀይ መስቀል የህክምና እርዳታ መስጫ
ጣቢያ አቋቋሙ:: ከዛም በጦር ሜዳ ጉዳት
የደረሰባቸውን ሰዎች በማከም ለአርበኞች ደጀን
የመሆን ስራን ቀጥለው በርካታ የጦር ሜዳ
ጉዳት የደረሰባቸውን ተዋጊዎች ቁስል በመጥረግ
እና በመስፋት ወትሮ ሊያዩት የማይፈቅዱትን
የሰው ልጅ ስቃይ ለሃገራቸው ብለው ጨክነው
በማከም በዚህም አርበኛዉን ከሞት እና ከስቃይ
በማትረፍ ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በጀግኖች
አርበኞች መካከል በተሰገሰጉት ባንዳዎች
ጠቋሚነት ከበርካታ የጥቁር አንበሳ ፋኖ ሰራዊት
ጋር የወራሪዉ የጣልያን ጦር ምርኮ
ለመሆን ተገደዉ በግዞት ወደ አዲስ
አበባ መጡ::
ቀድሞ ገነተ ልኡል ቤተ መንግስት
ይባል የነበረው እና የኋላ ኋላ
የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ስድስት
ኪሎ ግቢ ፤የኢትዮጵያ አስተዳዳሪ
ፊልድ ማርሻል ግራዚያኒ ላይ
አብረሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም
የተባሉ ወጣቶች የግድያ ሙከራ
ማድረጋቸውን ተከትሎ የስንዱ ገብሩ
ወንድም መሸሻ ገብሩ ከሴራዉ ጋር
ተነካክቷል በሚል ምክንያት ከተማዉ
ዉስጥ በወራሪዉ ጦር በጥብቅ
ሲፈለጉ ከነበሩ ሰዎች መካከል ስለነበር
በግዞት ወደ አዲስ አበባ መጥተው
የነበሩት ስንዱ ገብሩ ወንድማቸውን
ለማዳን ሲያደርጉ የነበረዉን ጥረት
እግር በእግር ሲከታተል ከነበረው
የጣልያን ጦር እጅ ላይ በድጋሚ
ወደቁ እና በቅድሚያ በገነተ ልኡል
ቤተ መንግስት ከዛም አስመራ
ከዛም ምጽዋ ተወስደው ታሰሩ::
አስከትለዉም ከሶስት መቶ ወንዶች
መካከል ስምንት መቶ ሴቶች አብረው
በመሆን ወደ ጣልያን ሃገር “አዚናራ”
ወደተባለማጎሪያእስርቤትተወስደው
ለዘጠኝ ወር ከቆዩ በኋላ በከፍተኛ
ማስጠንቀቂያ ወደ ሃገራቸው
ተመልሰው ዳግመኛ በዚህ አይነት
የአርበኛነት ተግባር ላይ እንዳይገኙ
ማስፈራሪያ ቢደርሳቸውም እርሳቸው
ግን አርበኞችን በግጥም፣በወኔ ቀስቃሽ
ጽሁፍ፣በመረጃ ማቀበልና በመሳሪያ
ማመላለስ ፍጹም ድፍረት የተመላ
ስራን ለእናት ሃገራቸው ሲያከናዉኑ
ቆይተው የጓጉለት ነጻነት በ1933 ዓ.ም
እዉን ሊሆን ቻለ፡፡
3ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
10			
		
				
	 ጥያቄዎች
ለትምህርት ቢሮ
አ
ቶ ማስረሻ ዘሪሁን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ
ትምህርት ኢንስፔክሽን ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ሲሆኑ
ከተምሳሌት መጽሔት ጋር ከግል የትምህርት ተቋም አሰራር
እና የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ የሚነሱትን ጥያቄዎች
አስመልክተው የሰጡትን ቃለ መጠይቅ ይዘን ቀርበናል ፡፡
በመንግስት እና በግል ትምህርት ተቋማት መካከል አለ የሚባል መሰረታዊ
ልዩነት አለ?
አቶ ማስረሻ ፡- የአዲስ አበባ ት/ቢሮ በዋናነት ከሚሰራቸው አገልግሎት
አንዱ ትምህርትን ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ ማድረግ ነው ፡፡ ከዚህ አንጻር
መሰረታዊ መርህ (motto) የሆነው በተስማሚ ፕሮግራሞች ትምህርትን
ለዜጎች ማዳረስ የሚል ነው ፡፡ በመሆኑም ቢሮው በት/ት ተቋማት መስራት
የሚገባውን ሁሉ በመስራት ላይ መሆኑን ማረጋገጥ እንጂ በስያሜ በግልና
በመንግስት ላይ መሰረት ያደረገ ልዩነት የለም፡፡ነገር ግን የግል ተቋማት
አንዱ ያደረጃጀት እና የራሳቸው አወቃቀር ይለያቸዋል ፡፡ የመንግስት
ት/ቤቶች በመንግስት በጀት የሚተዳደሩ ሲሆኑ የግል ት/ቤቶች ደግሞ
ሃብታቸውን በትምህርት ላይ ኢንቨስት አድርገው በሚሰሩ ልማታዊ
ባለሃብቶች የተቋቋመ ት/ቤት መሆኑ ነው ፡፡
ለመንግስት ት/ቤቶች የሚበጀተው በጀት ምንን መሰረት ያደረገ ነው ?
ለሁሉም ተመሳሳይ ነው ወይስ ይለያያል ?
አቶ ማስረሻ ፡- የመንግስት ት/ቤቶች በጀት የሚወሰነው በዋናነት
ከተማሪዎች ቁጥር አንጻር ነው ፡፡ ስለሆነም እንደ ት/ቤቶች ተማሪዎች
የመቀበል አቅም አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሚይዘው እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የተለያዩ በመሆናቸው መጠነኛ ልዩነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ከአፀደ ህጻናት
እስከ ስምንተኛ፣ ከዘጠነኛ እስከ መሰናዶ ት/ቤት ተብሎ የተከፈለ የበጀት
አጠቃቀም ነው ያለው ፡፡ ምናልባት በቁጥር ደረጃ ለእያንዳንዱ ተማሪ (per
head) በዓመት 1700-2700 እንደ ትምህርት ደረጃው ሊመደብ ይችላል ፡፡
ይህ የራሱ ስሌት ስላለው በዚህ አግባብ ይሰተናገዳል ፡፡
ለግል ት/ቤቶች የሚደረጉ የማበረታቻ ድጋፎች አሉ ? በመንግስት የሚደረግ
ድጋፍ ከሚገለጥባቸው መንገዶች አንዱ የማስተማሪያ ቦታ በሊዝ ኪራይ
ማግኘትን፣ መጽሐፍቶችን ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ መፍቀድን፣ የቀረጥ
ቅነሳ ማድረግን የመሳሰሉትን መንግስት ለግል ትምህርት ተቋማት የሰጠበት
ሁኔታ አለ ?
አቶ ማስረሻ ፡- መንግስት ለት/ቤቶች በርካታ ድጋፎች ይደረጋል፡፡ በዋናነት
ስርዓተ ትምህርቱን የተከተለ መጽሐፍ ለሁሉም የግል ት/ቤቶች ተደራሽ
ማድረግ በጣም ትልቅ እና ስኬታማ የሆነ የት/ቢሮ ስራ ነው ብሎ መውሰድ
ይቻላል፡፡ ከዚህ በፊት በነበሩት ዓመታት ተሞክሮ የትኛውም የግል
ተቋም ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ መሰናዶ ያለውን መጽሐፍ ከመንግስት
አግኝቶ አያውቅም ፡፡ ከገበያው ላይ ወላጆች የሚገዙት በውድ ዋጋ
በመሆኑ ለብዝበዛ ዳርጓቸው ቆይቷል ከዚህ አንጻር የከተማ አስተዳደሩ
ለት/ቢሮ በሰጠው ከፍተኛ ድጋፍ የግል ት/ቤቶች መጽሐፍ ማግኘት
የሚችሉበትን ስርዓት እገዛ በማድረግ በቅርብ አመታት ውስጥ እየሰራ
ያለው ስራ አበረታች ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል ፡፡ ነገር ግን ይህንን
እገዛ ሁሉም ት/ቤቶች በአግባቡ እየተጠቀሙበት ነወይ ስንል አንዳንድ
የግል ት/ቤቶች እየሰጡ ያሉትን ስርዓተ ትምህርት ተከትሎ የማስተማሪያ
መጽሐፍ ወስደው ለተማሪዎቻቸው በማዳረስ ትክክለኛ ትምህርት ተደራሽ
ከማድረግ አንጻር ውስንነት ይታይባቸዋል ፡፡ መጽሐፍቶችን በተማሪዎች
ልክ አለመግዛት ከገዙም በኋላ ለተማሪዎች ከመስጠት ይልቅ ት/ቢሮው
በማያውቀው መልኩ ራሳቸው የሚዘጋጁትን “አጋዥ መጽሐፍት” በሚል
ለወላጆች ከፍተኛ ገንዘብ እየጠየቁ የሚሸጡ ት/ቤቶች ቁጥራቸው ትንሽ
ቢሆንም አሰራሩ ግን ትክክል አይደለም ብሎ ቢሮው ያምናል ፡፡ ይህም
እንዲስተካከል የተለያዩ የክክትትልና ድጋፍ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን፡፡
ሌሎች የድጋፍ ጥያቄዎችን በተመለከተ የግል ት/ቤቶች ህብረት በነዚህ
በተነሱት ጥያቄዎች ላይ በራሱ ተነሳስቶ ተወያይቷል ወይ የሚለው ጥያቄ
ሊታይ ይገባል፡፡ ጥያቄውን ያቀረቡት አካላት በእኔ በኩል ጉድለት አለ ወይ
ብሎ ማየቱ መልካም ነው ፡፡ አንድ ግለሰብ ቦታ ሊጠይቅ ይችላል ህብረቱ
ግን እንደ ህብረት በማስፋፊያ ቦታዎች ላይ የማስፋፊያ ጥያቄ በያቀርብ
የተሻለ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህንን ጥያቄ ሊያስተናግድ የሚችል
አግባብ ያለው አካል አለ፡፡ በዚህ መልኩ ቀርቦ ከሆነ እኔ ጥርጣሬ አለኝ፡
፡ ህብረቱ እንደገና ራሱን ቢፈትሽ ጥሩ ነው ፡፡ ከ1500 ባላይ የሚደርሱ
ት/ቤቶች ህብረት ሆነው ጠንክረው እየሰሩ ነወይ ? አንድነት ኃይል ነው
በሚል መሪ ቃል ስር ሆኖ ጥያቄያቸውን ማቅረብ የሚችሉበት አቅም
ላይ ናቸው ወይ ? እነዚህ ነገሮች አብረው ጎን ለጎን መታየት አለባቸው፡፡
በተረፈ ችግሮች የሉም ማለት አይደለም ፡፡ ችግሮቹን ለመፍታት መንግስት
እምነቱም ቁርጠኝነቱም ስላለው በሂደት የሚሰሩ ስራዎች ማሳያ ናቸው
ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ጥያቄው ለትምህርት ቢሮ ሊቀርብ
የሚገባው አይደለም፡፡ማሕበሩ ቢያንስ እየተጠናከረ የሚሄድበትን አግባብ
በማሳየት ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን ፣ እየሰሩ ያሉትን ልማታዊ ስራ
በማረጋገጥ ሪኮመንዴሽን ከመስጠት አንጻር የምንሰራቸው ስራዎች አሉ፡፡
ለአብነት ብንጠቅስ ግንቦት ወር ላይ ደንብና ህግን ተከትለው ህብረተሰቡን
የማገልገል ዓላማ ይዘው የተነሱ 60 የግል ት/ቤቶች ተቋሞቹ ክ/ከተማና
ወረዳ ተመርጠው በመምጣታቸው ት/ቢሮው እውቅና ሰጥቷቸዋል ፡፡ ይሄ
ቀላል ነገር አይደለም ፡፡ እንደነዚህ አይነት ተቋማትን ለማበራከት የት/ቢሮ
እምነትም ፍላጎትም ነው ፡፡ ተቋማቱ በተበራከቱ መጠን የህብረተሰቡን
ፍላጎት ማርካት ይቻላል ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ት/ቢሮው የግልንም
ሆነ የመንግስት ተቋም ያለ ምንም ልዩነት ጥራት ባለው መልኩ ትምህርትን
ተደራሽ በማድረግ ነገ አገር ተረካቢ ዜጎችን መፍጠር ነው ፡፡
4 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
የግል ት/ቤቶች መተዳደሪያ ደንብ ከወጣ
ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ 20 ዓመት ሆኖታል ፡፡
በደንቡ አንቀጽ 12(ለ) እንዲሁም አንቀጽ 23
ላይ ተደንግጓል ፡፡ መመሪያ አለው ? መመሪያ
ከሌለው መመሪያው ሊሸፍናቸው የሚገቡ
አሰራሮች በምን አግባብ ይሸፈናሉ ?
አቶ ማስረሻ ፡- የግል ት/ቤቶች መተዳደሪያ ደንብ
ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመመሪያ ቢታገዙ ጥሩ ነው
ብለን ባሰብናቸው ነጥቦች ላይ ት/ቢሮ፣ የንግድ
ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን እንዲሁም ከተማ
አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ ባለሙያዎች የተሳተፉበት
አንድ ረቂቅ ተዘጋጅቷል ፡፡ ይህ ረቂቅ በግል ት/
ቤቶች የአገልግሎት ክፍያ አፈጻጸም ስርዓት
መመሪያ በሚል የወጣ ነው ፡፡ ምናልባትም
ከአሰራር አንጻር፣ ከሂደት አንጻር የሚታዩ
ችግሮችን ሊቀርፍ ይችላል የሚል እምነት አለን
፡፡ ት/ቤቶች ዋጋ ለመተመን የሄድንበት ርቀት
አካሄዱ ፍትሃዊ ነው አይደለም ፤ አግባብነት
አለው ወይስ የለውም በሚሉ ጥያቄዎች ላይ
እገዛ የሚያደርግ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡
፡ የመመሪያ ረቂቅ በመጀመሪያ ዙር ረቂቁን
በባለሙያዎች እና በራሱ በግል ባለሃብቶች
እንዲተቹ የማድረግ ስራ ተሰርቷል ፡፡ ረቂቁ
ከዜሮ ጅምር ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች
ተወስደው የሁለተኛ ክለሳ ስራዎች በመሰራት
ላይ ነው ፡፡ ይህ ስራ እንዳበቃ የሚመለከተው
አመራር አካል አጽድቆ መመሪያ መሆን ይችላል
የሚል ሃሳብ ካሰፈረ ወደ ተግባር የሚኬድበት
አሰራር ይኖራል ፡፡
በግል ትምህርት ቤቶች ማቋቋሚያ ደንብ
አንቀጽ 17 የግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሪ
ለማድረግ ሲያስቡ ከ3 ወር በፊት ለወላጅ
ማሳወቅ አለባቸው ላል ፡፡ ነገር ግን በተግባር
እንደሚታየው የወላጆች ማወቅ ብቻ ሳይሆን
መስማማትም ይጠበቃል ፡፡ ይህ ከነጻ የገበያ
መርህ አንጻር እንዴት ይታያል?
አቶ ማስረሻ ፡- በግል ት/ቤቶች ማቋቋሚያ
ደንብ ቁጥር 206/87 እንደተደነገገው ት/
ቤቱ የአገልግሎት ክፍያ የመጨመር መብት
አለው የምትለዋን ዓ/ነገር ብቻ በማጉላት
እየተጠቀሙበት ነው ፡፡ የግል ትምህርት ተቋም
ክፍያመጨመርመብትአለው፤ሆኖምግንይህንን
ጭማሪውን ት/ቤቱ ከመከፈቱ ከ3ወር አስቀድሞ
ማሳወቅ እንደሚገባው ተጠቅሷል፡፡ እዚህ ላይ
ለማለት የተፈለገው መጨመር ለተፈለገው
ጉዳይ ምክያታዊ (የኢኮኖሚ ምክንያት)
ተብሎ የሚጠቀሱ ነገሮች አሉት ፡፡ ህብረተሰቡ
በዚህ አግባብ ተረድቶ የመክፈል አቅሙን
አገናዝቦ እንዲከፍል ነው ፡፡ ሌላ አማራጭ
ያለው አማራጩን እንዲፈልግ ወላጆች ት/ቤት
ከማጣት እንዳይሰተጓጎሉ ለማድረግ ነው ፡፡
በሌላ በኩል ታሳቢ የሚደረገው የዋጋ መጨመር
ጉዳይ የባለ ሃብቱ ቢሆንም ምክንያታዊነታቸው
በገሃድ የወጡና ህብረተሰቡ የሚያውቃቸው
ናቸው ወይ ብሎ ማየቱ ተገቢነት አለው ፡፡ ከዚህ
አንጻር ተዛማጅነት የሌላቸው ከነጻ ገበያ መርህ
ጋር የማይዛመዱ አንድ የሆነ አካል በፈለገ ጊዜ
ብቻ ብር እየጨመረ ብትፈልግ ክፈል ከሚል
ስሜት ሳይሆን ምንድነው የኢኮኖሚዟል፡፡
የውድድሩን ስርዓት ጤናማ ያደርገዋል ወይ፤
ራሱን የቻለ ስርዓት የለውም ወይ ነጻ ገበያ ስንል
፤ብሎ መፈተሸ አለበት ፡፡ ይህ አካሔድ ተገቢነት
አለው ብለን እናምናለን ፡፡ በዚህም ት/ቢሮ
በናሙና የተመረጡ ት/ቤቶችን የዳሰሳ ጥናት
ለማድረግ ሞክሯል ፡፡ በዚህም ህበረተሰቡ
እያቀረበ ያለው ቅሬታ መነሻ ምንድነው የሚለው
ተለይቷል ፡፡ በተደረገው ጥናት የግል ት/ቤቶች
ባለሃብቶችም፣ የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ፣
የአስተዳደሩ ንግድ ቢሮ የተሳተፉበት ስራዎች
ተሰርቷል ፡፡ የግል ት/ቤቶቹ የአከፋፈል ሁኔታ
በአግባቡ ያልተኬደበት ሁኔታ አለ ፡፡ ወጥ የሆነ
የክፍያ ስርዓት የለም ፡፡ በብሮሹር ይሄ ክፍያ
ተወስኖብሃል፤ በሚቀጥለው ዓመት ልጅህን
የምታስተምር ከሆነ ይህንን እንድትከፍል ወይም
በስልክ በቴክስት መልዕክት በመላክ ወይም
የትምህርት ማጠናቀቂያ ጊዜ ላይ በምትደረግ
ትንሽ ውይይት ላይ ያገኙትን ውጤት በመናገር
፣ የተሰሩትን ስራዎች በማስተዋወቅ ይህንን ት/
ቤት የምትፈልጉ ከሆነ ይህንን ያህል ገንዘብ
ያስጨምሯችኋል እንድታውቁት የሚል ነገር
ነው ያለው ፡፡ነገር ግን ከሚልኩት ማስታወሻ
ጋር ፈቃደኝነታቸውና ስምምነታቸው
የሚረጋገጥበት የሁለትዮሽ ውይይት የለም ፡፡
ቢሮው ይህ አሰራር መስተካከል አለበት ብሎ
ያምናል ፡፡ አጽንኦት ሰጥቶ የማስተካከያ እርምጃ
እየወሰደ ይገኛል ፡፡
ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሚሆን አማራጭ ት/
ቤት ችግር ከሌለ፣ በመንግስትና በግል ት/ቤቶች
መካከል ተመሳሳይ የማስተማሪያ ካሪኩለም
እና መመዘኛ ካለ ይህንኑ ሁሉም ት/ቤቶች
በተመሳሳይ ሁኔታ ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ
ከግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ
የሚነሳው አለመግባባት ለምን ይከሰታል ?
አቶ ማስረሻ ፡- በት/ቤቶች መካከል ሊኖር
የሚገባው ልዩነት ብዙ እና ትንሽ በማስከፈል
ሳይሆን ተማሪዎች በእውቀት ፣ በክህሎት
በአመለካከት ተለውጠዋል ወይ የሚለውን
5ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
ማሳየት ነው ፡፡ የትምህርት የመጨረሻው ግብ
የባህሪይ ለውጥ ማምጣት ነው ስንል ደግሞ
ምናልባትም እንደ ውጤት ሊሆን የሚችለው
በስራ ዓለም ውስጥ ውጤታማ የሆነ ሰው
መፍጠር መቻላችን ነው ፡፡ በት/ቤት ቆይታ
ውስጥ በስነ- ምግባር እየተሸሻለ በአእምሮ
የዳበረ፣ በዕውቀት ጎለበተ ልጅ መቅረጽ ማለት
ነው ፡፡ ኃላፊነት የሚሰማው በምክንያት
የሚያምን ሁለንተናዊ ስብዕና ያለው የተሟላ
ዜጋ ለመፍጠር የሚያስችል ማለት ነው ፡፡
ይህ በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ጥቂት ት/ቤቶች
የውጪ ሃገር ዜጎችን የት/ቤት መግቢያ በር
ላይ በማቆም የወላጆችን አስተሳሰብ በመቀየር
ገንዘብ የመሰብሰቢያ አማራጭ የማድረግ ሁኔታ
ይታያል ፡፡ እውነታው ግን ይሄ አይደለም ፡
፡ የተሸለ ስራ እየሰሩ ያሉት ውጤታማ የሆኑ
በሃገራችን የተለያዩ ሚዲያዎች የፕሮግራም
ሽፋን የተሰጣቸው በገጠር ተወልደው
እዚያው ተምረው የመጡ ዩኒቨርሲቲ በጥሩ
ውጤት ያለፉ ራዕይ ያላቸው ተማሪዎች
ማፍራታችን ልብ ሊባል ይገባል ፡፡ እንደዚህ
ያሉ ነገሮች ከህብረተሰቡ ጋር ጤናማ የንግድ
ውድድር ይኖራቸዋል የሚል ስሜት የለኝም ፡
፡ የሚመለከተው አካል በእርግጥ የንግዱን
ስርዓት ይከታተላል ፡፡ ነገር ግን ስርዓቱ ጤናማ
እንዲሆን ከተፈለገ እውነታውን በማሳየት ወላጅ
በአገልግሎቱ ረክቶ ከሆነ ቀድሞውንም ቅሬታ
ያቀርባል የሚል እምነት የለኝም ፡፡ የትምህርት
አገልግሎቱ እና እየከፈልኩት ያለው የትምህርት
ክፍያ ተገቢ ነወይ በሚል ሁሉንም ሊያግባባ
የሚችል በአገልግሎት ፈላጊና በአገልግሎት ሰጪ
የጋራ ውይይት መደረግ አለበት ፡፡ ግልጽነት
ሊኖር ይገባል፡፡
በቅርቡ የተለያዩ ሚዲያዎች እንደተገለጸውም
የፌዴራል ንግድ ውድድር እና ሸማቾች
ባለስልጣን ጤናማ የሆነ ውድድር በማይፈጥሩ
እና ህብረተሰቡን ባልተገባ መንገድ ክፍያ
ያስከፍላሉ ብሎ የያዛቸው ቀላል የማይባሉ ወደ
190 አካባቢ የሚደርሱ ት/ቤቶች መረጃዎችን
እስከ 3 ወር ከፈተሸ በኋላ ከት/ቢሮ ጋር በጋራ
ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል ፡፡ ይህን ማስጠንቀቂያ
የሰጠው ዋጋው ስለጨመረ ብቻ የተከሰሰ ት/ቤት
አይደለም ፡፡ አማራጩን ህበረተሰቡ በአግባቡ
እንዲጠቀም ያላደረጉበት ሂደት ነው የተከሰተው
፡፡ ቆም ብለው እንዲያስቡ ከማለት አንጻር ነው ፡
፡ ይሄ ከተስተካከለ አሁን በህብረተሰቡ እየተሰማ
ያለው ቅሬታ በሂደት ሊከስም ይችላል ፡፡
የግል ት/ቤቶች በትምህርት ይዘታቸው ደረጃ
እንደሚወጣላቸው ይነገራል እውነት ነው?
ይህ ከሆነ ደረጃው ምን መሰረት አድረጎ ነው
የሚሰጠው? ደረጃው በት/ቤቶች መካከል
አላስፈላጊ ውድድር አያመጣም?
አቶ ማስረሻ፡- ደረጃ የሚሰጣቸው ት/ቤቶች
በይዘታቸው አይደለም የትምህርት ቤቶቹን
ሰርተፊኬሽን ደረጃ ፍረጃ ወደ ተግባር የተገባው
በ2005 ዓ.ም በኋላ ነው ከጥራት አንፃር
የሚቀሩ ስራዎች ሲነሱ ይህንን የጥራት ችግር
ለመቅረፍ ከሚያግዙ ስራዎች አንዱ ነው ተብሎ
ታምኖበታል ፡፡ ውጤታማ እየሆነ ነውያለው
ህብረተሰባችን የተሻለ ነገር የመጠየቅና የማወቅ
ፍላጎት ስላለው የጥራት ጥያቄ ሁል ጊዜ ይነሳል፡
፡ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንደ አገር አጠቃላይ
የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ በ1999
ተቀርጾ 6 መርሃ ግብሮችን ይዞ ተግባራዊ
እየተደረገ ነው ያለው፡፡ የኢኒስፔክሽን ስራ
የሚያሳየው እነዚህ መርሃ ግብሮች መሬት ላይ
ወርደው በምን አግባብ እየሄደ ነው፡፡ ት/ቤቶችስ
ራሳቸውን እንዴት እያዩ ነው የሚሉትን ስራዎች
በ26 ስታንዳርድ የመፈተሽ ስራ እየተሰራ ነው፡
፡ ስለዚህ 26ቱ ስታንዳርድ ከግባዓት ከሂደት እና
ከውጤት አንፃር ሲፈተሹ ደረጃ አንድ ላይና
ደረጃ ሁለት ላይ የወደቁ ት/ቤቶች ተማሪዎቹን
ት/ቤት በማቆየት ብቻ እንጂ ትምህርት
እየሰጠ አይደለም ወደሚል ድምዳሜ ላይ
ነው የሚያደርሰው፡፡ ተወዳዳሪ ዜጋ መፍጠር
ያልቻለ ት/ቤት ብዙ ችግር አለበት መስተካከል
አለበት ፡፡ ደረጃ3 እና ደረጃ4 ደግሞ ሞዴል
መሆን የሚችሉ ት/ቤቶች ናቸው፡፡ ት/ቤቶቹ
ከቲዩሪ ወይም ከንድፈ ሃሳብ በዘለለ የተግባር
ትምህርት እየሰሩ መሆኑን ማወቅ የሚችሉበት
መንገድ ያመቻችላቸዋል፡፡ ደረጃ ማለት ጉድለት
እና ስኬት የሚያሳይ ማለት ነው፡፡ ደረጃ 1 እና
2 የሚገኙ ት/ቤቶች ያላሟሉት ነገር አላቸው
ስለዚህ ማስጠንቀቂያ ነው የማንቂያ ደወል ነው፡
፡ ደረጃ 3 ወደ ደረጃ 4 ለመሸጋገር የሚጎድልህ
ነገር አለ የሚል ማንቂያ አለው፡፡ ደረጃ 4
ማለት ለሌሎች ሞዴል ተቋም ነው፡፡ ውድድር
አይቆምም ሁል ጊዜ የተሻለ ስራ ውስጥ መግባት
መቻል አለበት ከሚል እሳቤ ተነስቶ የተሰራ ስራ
ነው፡፡ በተለይ አሁን የግል ት/ቤቶች በጭፍን
ከመወዳደር ይልቅ ሳይንሳዊ በሆነ ፍተሻ
እያለፉወይም ጤናማ እንዲያደርጉት አግዟቸዋል
ብለን እናምናለን፡፡ ወላጆች ብዙ ብር በከፈሉ
ቁጥር ጥራት ያለው ትምህርት ለልጆቻቸው
እየተሰጠ ነው ብሎ መደምደም የለባቸውም፡፡
ደረጃና የዋጋ ተመን የሚያገናኛቸው ነገር የለም፡
፡ ት/ቢሮ በዋጋ ተመን ስራ ላይ አይሰራም፡፡
በትምህርት ቤቶች ውስጥ ት/ቤት ከተዘጋ
በኋላ የማሻሻያ ክረምት ትምህርት መሰጠት
በት/ቢሮ አሰራር ይፈቀዳል? አጋዥ (ሪፈረንስ
መጽሐፍቶች) በግል ት/ቤቶች ቢዘጋጅ ት/
ቢሮው ይከለክላል ?
አቶ ማስረሻ፡-የማጠናከሪያ ትምህርት በጥሬ
ቃሉ የወሰድነው እንደሆነ ተማሪዎች በሁሉም
ትምህርት እኩል የሆነ የመረዳት ግንዛቤ
ላይኖራቸው ይችላል፡፡ አንዳንዱ ተማሪ
በሳይንስ ትምህርት ጥሩ ውጤት ሲያስመዘግብ
ሌላውያልቻለውን ጥሩ አረዳድ እንዲኖረው
ለማድረግ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት
ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ሁሉንም የትምህርት
አይነቶች በመደዳው በመስጠት መሆን
የለበትም ፡፡ ይህ ችግር በክረምት ብቻ ሳይሆን
በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ላይም ይታያል፡
፡ ወላጆችም ልጄ አልባሌ ቦታ ከሚውል ት/
ቤት ቢውል እመርጣለሁ የሚሉት አግባብነት
ይኖረዋል፡፡ ይህንን ስል በቀናነት ከት/ቤቶች
ጋር ተግባብቶ የሚሰሩ ስራዎች የወላጆችን
ቅሬታ አያመጣም ፡፡በግል ት/ቤቶች አልፎ
አልፎ የሚታዩ ችግሮች የክረምት የማጠናከሪያ
ትምህርት በሚል የመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም
እያስተማሩ ይገኛሉ፡፡ ይህ ስህተት ነው ት/
ቤቶቹ የሚያደርጉት አንድ እና ሁለት ምዕራፍ
በክረምት አስተምረው መስከረም ትምህርት
መጀመሪያ ላይ ከምዕራፍ ሦስት የሚጀምሩ አሉ፡
፡ ይሄ የተሳሳተ አሰራር ነው በት/ሚር የወረደው
የትምህርት አካዳሚ የትምህርት ጊዜ ከመስከረም
እስከ ሰኔ ያለው 10 ወራት ነውሁለቱ ወራቶች
የእረፍት ጊዜያቶች ናቸው፡፡ ተማሪዎች፣
መምህራን ራሳቸውን በማሳረፍ ለቀጣይ
ትምህርት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የሚደረግበት
ጊዜ ነው፡፡ ሌላው ችግር ት/ቤቶቹ በክረምት
አስተምረው ያልተማረውን ተማሪ በበጋው
መማር አትችልም በማለት የመማር መብቱን
የሚከለክሉበት አሰራር ነው፡፡ ይህ ስህተት
ነው፡፡ አሁን ምናወጣው መመሪያ ይህንን ሁሉ
የሚያስተካክል ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡
ለመማር ማስተማር የሚጠቅሙ መጻሕፍት እና
ማጣቀሻ ሪፈረንሶችን በጭራሽ አትስሩ ያልንበት
ሁኔታ የለም ፡፡ ነገር ግን እንደ ት/ቢሮ እምነት
ከትምህርት ጋር ያለ ህብረተሰብ ሁሌ ከማንበብ
ጋር የተዛመደ እውቀትን በመፈለግ ላይ ያለ
ነው ፡፡ ስለዚህ ጥሩ ነገሮች እንደሚፈጠሩ
እናምናለን ፡፡ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ
ስራዎች አድናቆትን ያተረፉ ስራዎች ከግል ት/
ቤቶች ተቋማት እያገኘን ነው ፡፡ እነዚህ ማጣቀሻ
6 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
ተ
ምሳሌት መፅሔት ከግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ
ለሚነሱ ጥያቄዎች የግል ት/ቤቶች ማህበር ዋና ጸሐፊ
ከሆኑት አቶ ሰለሞን ገሰሰ ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ
ይዘን ቀርበናል፡፡
የግል ት/ቤቶች ማህበር ሁሉንም ት/ቤቶች ተደራሽ ያደርጋል?
አቶ ሰለሞን ገሰሰ ፡- ከማንኛዉም የማህበሩ እንቅስቃሴና ዉጤት፤ ሁሉም
የግል ትምህርት ሊባል በሚችል ተጠቃሚ ነው፡፡ነገር ግን ሁሉም የግል
ት/ቤት የማህበሩ አባል አይደለም፡፡ ወደፊት በሂደት ሁሉም የግል ት/ቤት
የማህበሩ አባል የማይሆንበት ምክንያት አይታየኝም ፡፡ የግድ መተባበር
አለባቸዉ፡፡
የግል ት/ቤቶች ለአገሪቱ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ምንድን ነው ?
አቶ ሰለሞን፡- ትምህርት የሁሉም ነገር መሰረት ነው ፡፡ ትምህርት ላይ
በሃላፊነት ስሜት መስራት ሲቻል በየትኛውም መንገድ ለዉ ጥ ማምጣት
ይቻላል፡፡ የግል ት/ቤቶች ደግሞ ጥራት ላይ አድምተው የሚሰሩ ተቋማት
ናቸው ፡፡ ከዚህ አንፃር ለሃገሪቱ ባለውለታዎች ናቸው ፡፡ ብዙ አስቸጋሪና
ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቀቁመዉ ተማሪዎቻቸዉን በጥሩ ሁኔታ እያነጹ
ይገኛሉ ፡፡ ለምሳሌ በአገርአቀፍ ብሄራዊ ፈተናዎች ተማሪዎቻቸዉን ሙሉ
በሙሉ ሊባል በሚችል በማሳለፍ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ ፡
፡ ተማሪዎችን ከቀለም ትምህርት ባሻገር በስነ ምግባር በስራና በዘመናዊ
ስተሳሰብ ኮትኩቶ በማሳደግ ነገ ኃላፊነትን ለመሸከም የሚችሉ ተማሪዎችን
በማፍራት ረገድም የግል ት/ቤቶች ትልቅ አስተዋፅዎ አበርክተዋል ፡፡
ወደፊትም የተሻለ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በመንግስትና በግል ት/ቤቶች መካከል መሰረታዊ የሚባል ልዩነት አለ?
አቶ ሰለሞን፡- አኔ አለ ብዬ ነው የማምነው ፡፡ ከአንድነታቸው ብጀምር አንድ
አይነት ስርዓተ ትምህርት ይተገብራሉ ፣ በአንድ ወጥ ፖሊሲም ይመራሉ፤
ነገር ግን በጥራት ላይ ስንመጣ የግል ት/ቤቶች የተሻለ የጥራት ደረጃ
አላቸው ብዬ አምናለሁ ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ብዙ አመልካች መገለጫዎች
አሉት :: የግልት /ቤቶች በአስተዳደር ረገድ ጊዜያቸውንና የሰው ኃይላቸውን
በአግባቡ ይጠቀማሉ፡፡ ያ ደግሞ በብዙ ችግሮች ውስጥ ሆነዉም የተሻለ
ውጤት እንዲያስመዘግቡ ረድቷቸዋል ፡፡ ሃብትን በአግባቡ በመጠቀም
ስራን እግር በእግር ተከታትሎ በመስራት ረገድ የግልት /ቤቶች የተለየ
መገለጫቸው ነው ማለት ይቻላል ፡፡ ሌላው የግል ት/ቤቶች ከወላጆች
ጋር በቅርበት ይሰራሉ ፡፡ ተማሪዎቻቸዉንም አግር በአግር ይከታተላሉ፡
፡ትምህርት ቤቶችና ወላጆች አለት አለት ከመገናኘት ባሻገር በመደበኛ
ፕሮግራም ቢያንስ በዓመት ለአራት ጊዜ ተገናኝተዉ በተሻለ የትምህርት
አሰጣጥ ዙሪያ የሚመክሩበት በደካማም ሆነ ጠንካራ ጎናቸዉ የሚወያዩበት
10		
	 	
	 ጥያቄዎች
ለግል ት/ቤቶች 	
	 ማሕበር
መፅሐፎች በት/ቢሮ ሥ/ት/ዝ ባለሙያዎች ከስርዓተ ትምህርቱ ጋር
ተዛማጅነት ስለመኖሩ ማረጋገጥ የግድ ነው፡፡
የግል ት/ቤቶች ያለ አንዳች የኢኮኖሚ መሰረት የዋጋ ጭማሪ አናደርግም
የሚል አስተያየት አላቸው ት/ቢሮ የት/ቤቶቹን የዋጋ ጭማሪ ያለ አግባብ
ነው ብሎ ያምናል? በሌሎች ዘርፎችስ ከሚደረገው እርዳታ አንፃር ት/ቤቶቹ
እርዳታ አግኝተዋል?
አቶ ማስረሻ፡-ቀደም ብሎ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በተደረገው የዳሰሳ
ጥናት የግል ት/ቤቶች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ነበሩ እነዚህ ጥያቄዎች
የት/ቤት ኪራይ አገልግሎት በየጊዜው መናር ሁለተኛ መምህራንን
በክፍያ ለማቆየት የሚደረግ ነው ፡፡ሌሎች ተዛማጅነት ያላቸው የስቴሽነሪ
መገልገያዎች የመጨመር ሁኔታ አለ የሚሉ ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡ በእርግጥ
አንዳድ አሰራሮች በሂደት ሊስተካከሉ የሚችሉ ይመስለኛል በግሌ ሳየው
በተለይም ከአከራይ ተከራይ ውል ጋር የሚጨመርበት አግባብ ሊፈተሽ
የሚገባው ይመስለኛል፡፡ ሌላው የተቃረነ ነገር የምናየው ለመምህራን
ስራቸውን እንዳይለቁ ማቆያ የሚከፈለውን ክፍያ በተመለከተ አንዳንድ
መምህራኖች ት/ቢሮ ድረስ እየመጡ ሐምሌና ነሐሴን አናውቃቸውም ዞር
በሉ እንባላለን በእኛ ስም ጭማሪ ተጨምሮ ነገር ግን ለእኛ የሚደርሰን
አናገኝም የሚሉ ብሶቶች ይሰማሉ፡፡እንግዲህ ሚዛናዊነቱ የቱ ላይ ነው
ብሎ ማየቱ ጥሩ ነው፡፡በእርግጥ ይህ ሚዛን የደፋ ክስ አቤቱታ ነው ብሎ
ለማስቀመጥ ሳይሆን ችግሩን ያመለክታል ስለዚህ ከህብረተሰቡ ጋር በጉዳዩ
ዙሪያ መወያየቱ ተገቢነት ያለው ነው፡፡
እንደ ዜጋ ሁሉም በፈለገው ቦታና ት/ቤት ልጁን ማስተማር ይችላል፡፡ ነገር
ግን በመንግስ ኃላፊነት ላይ ያሉ ባለስልጣኖች በአብዛኛው ማለት ይቻላል
መንግስት ት/ቤት ልጁን ሲያስተምር አይታይም ለምን ይመስሎታል?
እርሶዎ ልጅ ካልዎት ልጅዎ የት ይማራል?
አቶ ማስረሻ፡-ዜጎች በተለያዩ ቦታዎች ያስተምራሉ ነገር ግን በዚህ ላይ በቂ
መረጃ የለኝም እንግዲህ የግል አስተያየት ይመስለኛል እኛ የምናምነው
ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ትምህርት በፍታሃዊነት፣ በእኩልነት፣ ያለ
አንዳች ልዩነት ማድረስ ነው፡፡ ከአቅርቦት አንፃር ሁሉንም ዜጎች ተደራሽ
ማድረግ ነው የሚል ነው ፡፡ት/ቢሮ አሰራሩም ይሁንንመርህ የተከተለ
ነው፡፡ ከዚህ ውጪየእገሌ ልጅ እዚህ ይማራል የእገሌ ልጅ እዛ የሚሉትን
አስተያየቶች እኔ የግለሰቦች አስተያየት ነው ብዬ ነው የምወስደው፡፡
እናመሰግናለን ፡፡
7ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
የግንኙነት መድረክ አላቸው ፡፡ በእነዚህ ቀናት
ወላጅና ፣ መምህሩ ከተማሪዉ ጋር በመሆን
ተማሪዉ በነበረዉ የትምህርት ትጋት አንዲሁም
ስነምግባር ዙሪያ በግልጽ ይመክራሉ ፡፡
ለልጆቹም መለወጥ የተናጠል ሃላፊነታቸዉን
ይወስዳሉ፡፡የግል ት/ቤቶች በያንዳንዱ ተማሪ
መሻሻልና ለዉጥ ላይ ክትትል ያደርጋሉ፡፡
የግል ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በየቀኑ
የሚገናኙበት የግንኙነት መስመር አላቸዉ፡
፡ communication book የሚባል እለታዊ
የመረጃ መለዋወጫ መፅሐፍ አላቸዉ ፡፡ ይህ
በብዙ የግል ት/ቤቶች የተለመደ አሰራር ነው ፡
፡ ሌላዉ የግል ት/ቤቶች ምናልባትም ከመንግስት
ት/ቤቶች በተሻለ ስርዓተ-ትምህርቱን በየጊዜው
ለማበልጸግ ቅርብ ናቸዉ፡፡ በክበባትና በቤተ
ሙከራ እንቅስቃሴዎችም የግል ተቋማት የተሻለ
የሚንቀሳቀሱ ይመስለኛል።
መንግስት ለግል ት/ቤቶች የሚያደርገው የተለየ
ድጋፍ አለ ?
አቶ ሰለሞን ፡- ቴክኒካላዊ የሆኑ እገዛዎች አሉ ፡፡
መንግስትያስቀመጠውንስታንዳርድለሟሟላትና
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የግል ት/
ቤቶችን የሚያግዙ ፤ መንግስት ያሰማራቸው
ሱፐርቫይዘሮች አሉ፡፡ እነዚህ ሱፐርቫይዘሮች
ዋና ስራቸው ትምህርት ቤቶችን ማገዝና መርዳት
ነው ፡፡ ሱፐርቫይዘሮች ተመድበው ት/ቤቶች
ጥራትና ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ አግባብና
ስርአት ባለው መልኩ ሲከናወን ጥሩ ነው ብዬ
አስባለሁ ፡፡
ነገርግንከመሬትአቅርቦት፣ከፋይናንስአቅርቦትና
ከቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚነት አንጻር ይህ ነው
የሚባል ተጨባጭ ድጋፍ በአሁን ሰአት የለም ፡፡
አቅም ያደረጁ የግል ት/ቤቶች ቁጥራቸው ትንሽ
ነው፡፡ አብዛኛዎቹ የግል ት/ቤቶች አቅማቸው
ውስን ነው ፡፡ይሁንና በብዙ ችግሮች ውስጥ
እያለፉም ባላቸው ውስን አቅም ድንቅ ስራ እየሰሩ
ይገኛሉ፡፡ መንግስት ተጨማሪ ድጋፍ እንደ
ሌሎች ሴክተሮች ለግል ት/ቤቶች ቢያደርግላቸው
ምን ሊሰሩ እንደሚችሉ መገመት አያቅትም፡
፡ በአጠቃላይ መንግስት ፊቱን ወደ ግል ት/
ቤቶች በማዞር ከመሬት አቅርቦት፡ ከፋይናንስ
አቅርቦት፡ ከቀረጥ ነጻ መብት መፍቀድና ሌሎች
መሰረታዊ እገዛዎችን ሊያደርግላቸው ይገባል፡፡
ይህም የዋጋና የጥራት ተፎካካሪነትን ይጋብዛል፡
፡ በዋና ከተሞች የተወሰነውም የግል ት/ቤቶች
ስርጭት በክልሎች እንዲስፋፋ ትልቅና ታሪካዊ
አስተዋጽዎ ያበረክታል፡፡
ከዚህ በፊት ለግል ትምህርት ተቋማት ያልተሰጡ
እንደ መጽሐፍ ማሳተም የመሳሰሉ ስራዎች
በት/ቢሮ ድጋፍ እየተደረገላችሁ እንደሆነ ነው
የሚገለጸው ፡፡ ማህበራችሁም ጠንካራ እንዳልሆነ
ይገለፃል ፡፡ የተለያዩ ጥያቄዎችን ከማቅረብ አንፃር
ማህበሩ ክፍተት ይታይበታል የሚል አስተያየት
አለ፡፡ እርስዎ ይህንን እንዴት ያዩታል ?
አቶሰለሞን ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ስርዓተ
ትምህርትን ስታስተገብር መጽሐፍ አሳትሞ
ለመንግስትም ሆነ ለግል የትምህርት ተቋማት
ማዳረስ የመንግስት ሃላፊነት ነው፡፡ በእኛ ሃገር
ስርአተ ትምህርትን የግል ተቋማት እንዲያወጡም
ሆነ እንዲያሻሻሽሉ አይፈቀድም፡፡ ስርዓተ
ትምህርት ይተግበር ብለህ ደግሞ መሳሪያው/
የመማሪያ መጽሀፍ የለም ካልክ ሁለቱ አንድ ላይ
አይሄዱም ፡፡ ያም ሆኖ ማህበራችን ትምህርት
ቤቶችን አስቸግሮ የመማሪያ መፃሕፍትን
ያሳተመበት ወቅትም ነበር፡፡ ከፍተኛ እጥረት
በነበረበት በተለይም አንድ መፅሐፍ በ150 እና
በ200 ብር በነጋዴ በሚሸጥበት ወቅት ገበያውን
ሰብሮ ገብቶ መጽሃፍ በማሳተምና ለግል ት/ቤቶች
በዋጋው በማሰራጨት ማህበሩ ዋጋን የማረጋጋት
ስራ የሰራበት ጊዜም ነበር፡፡ ከዚህ ውጪ ማህበሩ
መጠናከር አለበት ፤ አዎ መጠናከር አለበት፡
፡ ተጠናክሮ የተለያዩ ጥያቄዎችን ለመንግስት
ማቅረብ አለበት ፡፡
ማህበሩ ከሰራቸው በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ
ችግሮችን/ቀውሶችን ስርዓት ለማስያዝ ብዙ
ጊዜ አጥፍቷል ፡፡ ይህም ሆኖ ደረጃ ማህበሩ
ተጠናክሮና ከመንግስት ጋር ተቀራርቦ ሊሰራ
ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ የግል ት/ቤቶች በተሻለ
ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እንዲሁም ሃገርንና
ህብረተሰብን ለመጥቀም ሁሉም የማህበሩ አባልና
በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ተሳታፊ ሊሆን ይገባል፡፡
መንግስትም ማህበሩ እንዲጠናከር ማገዝ ያለበት
ይመስለኛል፡፡
በቅርቡ ወደ ተከሰተው ጉዳይ ልምጣና የግል
ትቤቶች በተጠቃሚው ላይ በተደጋጋሚ የክፍያ
ዋጋ እየጨመሩ ነው በሚል የአ/አ ት/ቢሮ እና
የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን
በጋራ አጥንተናል የሚሉት አንድ ጥናት ነበር ፡
፡ የግል ት/ቤቶች ማህበሩም እንደተሳተፍበትም
ይናገራሉ በዚህም መሰረት ከ194 በላይ ለሆኑ ት/
ቤቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል ይህንን ምን ያህል
ታውቃላችሁ? አብራችሁ ሰርታችኋል ?
አቶ ሰለሞን፡- እንግዲህ አይነት ማስጠንቀቂያ
ላይ እኛ የለንበትም:: በዚህ ረገድ የግል ት/ቤቶችን
ማስጠንቀቂያ የሚያሰጣቸው ምንም አይነት
ጥፋትም ሆነ ወንጀል ፈጽመዋል ብዬ ለመቀበል
ይከብደኛል ፡፡ ነገር ግን ከወላጆች በኩል አንዳንድ
ጥያቄዎች አሉ ከተባለ መምከሩ ተገቢ ነው ፡፡
ከዚህ አንፃር በዳሰሳ ጥናቱ ጅማሬ ላይ ተሳትፈን
፡፡ ነገር ግን ጥናቱ ብዙ ግድፈቶች ነበሩበት፡
፡ አቀራረቡም ተገቢ አልነበረም፡፡ ሲጀመር
ከ1500 በላይ የግል ትምህርት ቤቶች ባሉበት
ከተማ ውስጥ 16 ት/ቤቶችን ብቻ በናሙናነት
መውሰድ ትክክለኛውን ምስል ለማየት ይገድባል፡
፡ ይሔ በፐርሰንት ብታወጣው ምንያህል ነው?
ሁለተኛ እነዚህ ት/ቤቶች ደግሞ የተሻለ ገቢ
8 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
ያለውን የህብረተሰብ ክፍል የሚያስተናግዱ ናቸው፡፡ ይህ ምን ያህል ገላጭ
ነው ፡፡ ያም ሆኖ በአማካኝ የመጣው ከ70-150 ብር ወርሃዊ ጭማሪ ነው
የተደረገው ፡፡ ለእኔ ግን መሰረታዊው ነገር በሃገራችን የትምህርት ክፍያ
ጭማሬን የሚከለክል ወይም የሚገድብ ህግ አለ ወይ እስከማውቀው ድረስ
የለም፡፡ It’s just a free market.
የግል ት/ቤቶች የቤት ኪራይ አለባቸው ፣ በየዓመቱ የደሞዝ ጭማሪ
ለመምህራንና ሰራተኞች ያደርጋሉ፡፡ሲልም ሰራተኛ በሚለቅበት ሰአት
በአመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ጭማሬ ለማድረግ ይገደዳሉ፡፡ አስር ወር
አስተምረውና ገንዘብ ሰብስበው አስራ ሁለት ወር ደሞዝ፤የቤት ኪራይና
ሌሎች በርካታ ወጪዎችን መሸፈን ግዴታቸው ነው፡፡ መሰረታዊ የሆነው
ነገር ት/ቤቶች አድመው ጭማሪ አድርገዋል ወይ የሚል ነው ፡፡ በዚህ
ሁኔታ በአድማና በመመካከር በመወሰን፤ በማሴር ዋጋ የጨመሩ ሁለት
ት/ቤቶች እንኳን ፈፅሞ ማግኘት አይቻልም፡፡ አንዱ ከአንዱ በማንኛውም
ሁኔታ ተወዳዳሪና ተፎካካሪ ነው፡፡
በየዓመቱ ትምህርት ቤቶችኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖራቸውይጨምራሉ
፡፡ ይሄ መቼ ይቆማል ሲሉም የሚጠይቁ አሉ በዚህ ጉዳይ ላይ እርስዎ ምን
ይላሉ ?
አቶ ሰለሞን ፡- ይህ ጥያቄ ለእኔ መሰረታዊ አይመስለኝም:: ምክንያቱም
መንግስት ለህብረተሰቡ ትምህርትን በነፃ አቅርቧል፡፡ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ
ምክንያት የለም ቢባል እንኳን ማንኛውም ት/ቤት የራሱና በራሱ ልክ
የተሰፋ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ምክኒያቶች አሉት፡፡ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ
ምክንያቶች የሉም ብሎ በዚህ ሰአት መናገርም የሚከብድ ይመስለኛል፡፡
ወላጅ ይህ አማራጭ በግልፅ ተቀምጦለታል ፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ የግል
ት/ቤቶችን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይደለም ፡፡ የዋጋ ግሽበትን ጨምሮ
በርካታ የኢኮኖሚ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል ፡፡ የኢኮኖሚ ምክንያት
እኮ ባለሙያ ባልሆንም የተለያየ ነው፡፡ ለአንዱ የኢኮኖሚ ምክንያት
የሆነው ለሌላው ላይሆን ይችላል ፡፡ ት/ቤቶቹ በራሳቸው የውስጥ
አሰራር የኢኮኖሚ ምክንያት ይኖራቸዋል፡፡ አንድ ት/ቤት የዋጋ ጭማሪ
በማያደርግበት አጋጣሚ እንኳን ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ሆኖለት ነው
ማለት አይደለም ፡፡ የሚገጥሙትን ችግሮች ተቋቁሞ ነው፡፡ እንደነዚህ
አይነት ትምህርት ቤቶችን የበለጠ ማበረታታት ያስፈልጋል ፡፡ በየዓመቱ
የሚታየው ዋጋ ንረት ግልፅ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ባሉበት የግል ት/ቤቶች
ላይ ጣትን መቀሰር ተገቢ አይደለም፡፡ ያም ሆኖ የግል ት/ቤቶች የዋጋ
ጭማሬ ሲያደርጉ ከሞራል አኳያ የሚያስተምሩትን የህብረተሰብ ክፍል
አቅም ከግንዛቤ ቢያስገቡ ከሃገራዊ ሃላፊነቶቻቸው አንዱን የመወጣት ያህል
ይሰማኛል፡፡ ለዚህም ሞራላዊ ቅስቀሳና አስተምህሮ እንጂ ቁጣና ሃይለ ቃል
ሊሆን በፍጹም አይገባም፡፡ ት/ቤቶች ተስፋ እንዲቆርጡ ሳይሆን የበለጠ
ለሃገራቸውና ለህዝባቸው ጠንክረው እንዲሰሩ ማበረታታት ያስፈልጋል፡፡
ለግል ት/ቤቶች ደረጃ የማውጣት አሰራር አለ የትምህርት ቤቶቹ ደረጃ
በማህበረሰቡ መካከል የደረጃ ፍረጃ ልዩነት እንዲፈጠር ተፅዕኖ አያደርግም
?ከዚህ አንፃር ማህበሩ ያለው አቋም ምንድን ነው?
አቶ ሰለሞን፡- ደረጃ ማውጣቱ ችግር ያለው አይመስለኝም፡፡ችግር ሊሆን
የሚችለው ደረጃውን ተከትሎ አንድ ት/ቤት ይህንን ያህል ክፍያ ማስከፈል
አለበት የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡የደረጃ ማውጣት ግቡ፤ ለህብረተሰቡ
መረጃ ከማቅረብ የዘለለ መሆን የለበትም፡፡ ውሳኔ ሁልጊዜም ለወላጅ
ሊተው ይገባል፡፡ነገር ግን በማህበር ደረጃ ተመክሮበት የተሰራ ስራ የለም
፡፡ ስታንዳርድ መውጣት አለበት በሚል የሄድንበት ነገር የለም ፡፡ የደረጃ
ማውጣት ጉዳይ የወላጅ ቢሆን የተሻለ ነው የሚል እምነት አለኝ ፡፡ ወላጅ
ከፋሲሊቲ፤ ከሂደትና ከውጤት አንጻር የት/ቤቱ ታሪክና ወቅታዊ ሁኔታ
ፈቲሾና የራሱን ደረጃ አውጥቶ ነው ወደ ት/ቤቶች ልጆቹን የሚልከው፡
፡ ይበለጥ ግን መንግስት ቀደም ሲል ሲያደርግ እንደነበረው ት/ቤቶችን
በሱፐርቪዥን ፕሮግራሙ በማገዝ ት/ቤቶችን የማብቃት ስራ ተጠናክሮ
ሊቀጥል ይገባል፡፡
ሌላው በአለም አቀፍ ተቋማት አማካኝነት ለመንግስት ት/ቤቶች የሚደረጉ
የመጽሃፍት፤ የኮምፒውተሮችና ሌሎች የቁሳቁስ ድጋፎች የግል ት/ቤቶችን
በተወሰነ ደረጃ ቢያካትት ጥቅሙ ከግለሰብ ይልቅ ለሃገር ነው፡፡ የግልም ሆነ
የመንግስት ት/ቤቶች የሚቀርጹትና የሚያወጡት አንድ አይነት ዜጋ ነው፡፡
ከክረምት ትምህርት ጋር የሚነሳ ጥያቄ አለ የግል ትምህርት ተቋሞች
የመደበኛውን ትምህርት በክረምት ያስተምራሉ እንደውም አንድ እና ሁለት
ቻፕተር ድረስ ያስተምራሉ፣ ክረምት ያልተማረ ተማሪ በበጋ አይማርም፣
ጎበዝ ተማሪ በክረምት እንዲማር ይደረጋል፣ ገንዘብ ለመሰብሰቢያ
የሚጠቀሙበት ነው የሚሉ አስተያየቶች ይነሳሉ ይህንን እርስዎ እንዴት
ያዩታል?
አቶ ሰለሞን ፡- በክረምት ትምህርት ሲጀምር ጎበዝ ሰነፍ፣ አጭር ረጅም
ይማር ብሎ ማስቀመጥ ተገቢ አይደለም ፡፡ መሰረታዊ ሃሳቡ መማር የፈለገ
ይማር ነው ፡፡ በክረምት የሚማሩ ተማሪዎች በየትኛውም ቦታ የሚማሩት
እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ነው ፡፡ ተማሪዎች በዚህ ሰዓት እቤታቸው
ቢቀመጡ ምናልባትም በእንቅልፍ ነው የሚያሳልፉት ፡፡ ነገር ግን ንቁ
ሆነው በጠዋት ሄደው ት/ቤት ቆይተው ቢመለሱ ያቺን አጭር ሰአት
የተሻለ እውቀት ይገበያሉ ፡፡ በክረምት ፕሮግራም የሚሰጠው ትምህርት
ከማጠናከሪያነቱ ባሻገር የማዝናናት ተፈጥሮ ያለው ነው፡፡ የተለያዩ
የታቀዱ የሙዚቃ፤የስፖርት ውድድሮች፣ ጨዋታዎች ትምህርቱን ያጅባሉ፡
፡ ትምህርቱም ቢሆን ልጆቹ ለቀጣይ ዓመት ትምህርታቸው እንዲዘጋጁ
ያደርጋቸዋል ፡፡ ደከም ያሉበት ትምህርት ካለም እንዲያሻሽሉ እድሉን
ያገኛሉ፡፡ ጎበዝ ተማሪ ለምን በክረምት ይማራል የሚለው አስተሳሰብ
ግን አይገባኝም ፡፡ የክረምት ትምህርት ተማሪዎች የተለያዩ ክህሎቶችን
እንዲለማመዱ ይረዳል ፡፡ ጎበዝ ተማሪም ቢሆን እየተዝዝናና የተለያዩ
ክህሎቶችን እየቀሰመ ለሚቀጥለው የትምህርት ጊዜ ቢዘጋጅ ምንም
ችግር የለውም ፡፡ የክረምት ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎችን ያስገድዳሉ
የሚባለው አነጋገር ስህተት ይመስለኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ወላጆች ትምህርት
ቤት ከተዘጋ በኋላ ልጆቻቸውን ዘመድ ጋር ክ/ሀገርም ጭምር የሚልኩ አሉ
እንዴት ተደርጎ ነው ት/ቤቶቹ ክረምት ካልተማረ ብለው የሚያስገድዱት፡፡
ይህ ተደርጎም ከሆነ ትክክል አይደለም ፡፡እንደዚሁ የመደበኛውን ትምህርት
በክረምት ይጀምራሉ የሚባሉ ት/ቤቶች ካሉ ስህተት ሆኖ ይታየኛል ፡፡ ያም
ሆኖ ከግንዛቤ ችግር ካልሆነ በክፋት አልወስደውም፡፡
ት/ቤቶች እርስ በርሳቸው ወይም ከመንግስት አካላት ጋር በሚያደርጓቸው
ግንኙነቶች የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ማህበሩ ያለው ተሳትፎ
ምን ያህል ነው ?
አቶ ሰለሞን ፡- ከጥቂት ዓመታት በፊት በት/ቤቶች መካከልም ሆነ ከፍቃድ
ሰጪ መ/ቤቶች ጋር የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ከማህበሩ ኮሚቴ ተቋቁሞ
በወረዳና በክ/ከተማ ድረስ በመሄድ የማስማማትና የማግባባት ስራ ሲሰራ
ቆይቷል፡፡
9ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
ጂ
ቱ አለሙ ዲሪብሳ የቤተሰብ አካዳሚ ተማሪ ነች፡፡ ጂቱ
አንድ ብሎ ሁለት ያለውን የትምህርት ቤት ዳዴዋን
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በጥሩ ውጤት ወደ ዩኒቨርሲቲ
ለመግባት ተቃርባለች፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ደጃፍ
ላይ ቆማ ብዙ ታስባለች፤ አብዝታም ትጥራለች ይህ ጥረቷ ታዲያ በተለይ
በሳይንስ ትምህርቶች እጅጉን ውጤታማ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ ጂቱ
ትላለች “የሳይንስ ትምህርቶችን ከልቤ እወዳለሁ በዚህኛው ዘመናዊ ዓለም
ደግሞ ማንኛውም ነገር እውን የሚሆነው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ነው፡፡”
ይህ የሳይንስ ትምህርት ፍቅሯ ዛሬ ላገኘችው እድል በር ከፋች ሆኗል፡
፡ ሴቶችን በሳይንስ /Women in science/ ከመላው አፍሪካና አሜሪካ
ለተገኙ በሳይንስ የትምህርት ዓይነቶች ጥሩ ውጤት ላላቸው ሴት
ተማሪዎች በክረምት ወራት የሚሰጥ ስልጠና ነው ፡፡ የስልጠናው መጠሪያ
በአጭሩ ዊስ ካምፕ (Wisci Camp) ይባላል ፡፡ ይህ ስልጠና ሴቶች
በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ክህሎት እንዲያዳብሩ አቅማቸውን
የሚያሳድግ ስልጠና ነው፡፡
ስልጠናው ለ25 ቀናት በሩዋንዳ በሚገኘው በጋሻራ የልጃገረዶች አካዳሚ
ይሰጣል፡፡ ሴት ተማሪዎች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በአርት፣ በዲዛይን እና
በሒሳብ ዘርፎች ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ስልጠናው እድል ይሰጣል፡፡
ሴት ተማሪዎቹ አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አሸኛኘት
ሲደረግላቸው በስፍራው የተገኙት የአሜሪካ የዓለም አቀፍ አጋርነት
ምክትል ልዩ ተወካይ ቶማስ ዲባስ ይህ በተለያዩ አካላት ትብብር
የሚዘጋጀው ስልጠና ሴት ተማሪዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች
እውቀት እንዲጨብጡና ክህሎታቸውንም እንዲያሳድጉ እድል ይፈጥራል
፡፡ ከስልጠናው በኋላ ሴት ተማሪዎችም ለዓለም ኢኮኖሚ የሚያበረክቱት
አስተዋፅኦ ቀላል አይሆንም ብለዋል፡፡
የዊስ ካምፕ ስልጠና በአሜሪካ መንግስት፣ በማይክሮ ሶፍት፣ በኢንቴል
ኩባንያ፣ በአፍሪካ ሊደርሽፕ አካዳሚና ሌሎችም አካላት ትብብር
የሚዘጋጅ ነው፡፡ ለሦስት ሳምንታት በሚቆየው ስልጠና የኮምፒውተር
ሳይንስ፣ የሮቦት ቴክኖሎጂ፣ የዲዛይን፣ የአርት፣ የባህልና የፈጠራ ክህሎት
የሚሰጥ ሲሆን ተማሪዎቹ በቡድን በመሆን ትናንሽ ፕሮጀክቶችን ይሰራሉ፤
በአመራር፣ የገበያ ጥናትና በተለያዩ አነቃቂ ስልጠናዎችን ያገኛሉ ተብሏል፡
፡ ጂቱ ስልጠናውን ለመውሰድ ከአፍሪካ ሊደርሽፕ አካዳሚ ከኤስ ኦ ኤስና
ከልደታ ካቶሊክ ከተገኙ ሌሎች 12 ሴት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጋር
ወደ ሩዋንዳ ሄዳለች፡፡
በሩዋንዳው ጋሸራ የልጃገረዶች አካዳሚ ከጋና፣ ኬኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣
ታንዛንያ፣ ዩጋንዳና አሜሪካ ከተገኙ ሌሎች ሴቶች ጋር ቁጥራቸው 120
ይደርሳሉ፡፡ ህሊና ታመነ እና በአምላክ ታደሰም ከጂቱ ጋር ከሩዋንዳ
ስልጠና ሲመለሱ አገሪቱ በሳይንሱ ዘርፍ ለሰጠችው ትኩረት ትልቅ ሚና
እንደሚኖራቸው እርግጠኛ ሆነው ይናገራሉ፡፡
የነገ
ዛሬዎችፎቶአ.አአሜሪካኤምባሲ
10 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
ከ
ፒያሳ የተነሣው ‘ሃይገር ባስ’ መገናኛ ተሳፋሪ ሊያወርድ
ቁሟል። መገናኛ ላይ ለውዝ የሚያዞሩ ልጆች አሉ።
ባትፈቅድም አስገድደውና ይሉኝታ(“ሼም”) አስይዘው
ያስገዙኻል። ከአዟሪዎች አንዱ ወደ ተሳፈርንበት ‘ሃይገር’
ገብቶ ሦስትና አራት ፍሬ ለውዞች በየሰው እጅ እያስቀመጠ ሁሉንም
አዳረሰ። እጅህ የሆነ ነገር ይዞ ልትቀበለው ካልቻልክ ለውዙን የሸሚዝ
ኪስህ ውስጥ ጨምሮት ያልፋል። አጠገቤ የተቀመጠው ልጅ ለነገሩ እንግዳ
ስለሆነ ተደናግሯል። አንዴ ለውዝ ሻጩን፣ ከዛም እጁ ላይ ያለውን ለውዝ፣
መጨረሻ እኔን አፈራርቆ ተመለከተ። ሻጩ ኋላ ደርሶ ሲመለስ ለቅምሻ
እጃቸው ላይ ላስቀመጠላቸው ሁሉ በወረቀት የተጠቀለለ ለውዝ ጣል ጣል
አደረገላቸው።
“ምንድን ነው? ምን ላድርገው?” ከጎኔ የተቀመጠው ልጅ እንደተደናገረነው።
“የሃይገር ቁርስ ነው! እዚህ በቁርስ እየተንከባከቡ ነው የሚያደርሱህ”
አልኩት ሳቄ ከንፈሬ ላይ ተንጠልጥሎ።
“እንዴ!? እውነትክን ነው?” ልክ ቁርሱ መጥቶ ቡናው እንደዘገየበት
ሱሰኛ ፊትና ኋላ ተገላምጦ ረከቦት የተዘረጋበትን ቦታ ማፈላለግ ጀመረ።
ሳቅአፈነኝ። ሻጩ ‘ሃይገሯ’ን እንደታቦት ንግሥ ለሦስተኛ ጊዜ ዞራት። አሁን
ገንዘቡን እየለቀመነው። ወንበር የተጋራኝ ልጅ በእጁ ጭብጥብጥ አድረጎ
የያዛትን የመጓጓዣ ገንዘቡን ቆጠራት-አራት ብር።
“እህ!? ምን… ማለቴ…ምን ማለት ነው? እንዴት?” ሳልፈልግ… በሻጩ
መገደዱ አሞታል።
“አልበላኸውም አይደል? መመለስ ትችላለህ እኮ!”
“አስገደዱኝ አይደል እንዴ? አስገደዱኝ እኮ!”
“አልፈልግም አታስገድዱኝ! በል እያልኩህ ነው ሰውዬ”
“አታይም!? ሰው ሁሉ ከፈለኮ!”
“አንተ ግን ካልፈለከው አለመክፈል ትችላለህ”
“ሼም ይሆንብኛላ!!”
“እንግዲህ ወይ ሼምህን ወይ ብርህን አትርፍ” አበሳጨኝና መጽሐፌን
ገልጬ ለማንበብ ሞከርኩ።
“ይኼውልህ ወንድሜ… ቢኖረኝ እኮ…”
“ለምን ድምፅህን ለኔ ብቻ እንዲሰማ ትቀንሰዋለህ? ለቀቅ አድርገውና ሻጩ
ሰምቶ ይራራልህ ይሆናል።” ልጁን ማንቃት ከበደኝ፡፡ ልክ ማይምነትን
ለማስወገድ የዕድገት በሕብረት ዘመቻ የዘመትኩ ነው የመሰለኝ። ስንቱን
ፈርተን እንኖራለን? አንድ ወይም ሁለት ብር ከፍዬ ልላቀቀው ፈለኩግን
እንዲህ ዓይነቱ ሰው ነገም ‘ሼም’ን ፈርቶ ሌላውን ማስቸገሩ አይቀርም።
ኤጭ ምነው እቴ!?
“ለምን መብትህን ታስደፈጥጣለህ? አይሆንም አልከፍልም አትልም?
ምን ይመጣብኻል?” አንድ ወደ ጎልማሳነት በመገሥገሥ ላይ ያለ ወጣት
ንግግራችንን ሰምቶ ልጁን አደፋፈረው። ጎልማሳው በቲሸርት ላይሹራብ፣
በሹራብ ላይ ጠቆር ያለ ኮት ለብሷል። አውራ ጣቴን ቀስሬ ሐሳቡን “ላይክ”
ማድረጌን አሳየሁት።
“ይገርምሃል እኔ አልከፍልም አልኩ። አዳሜ ግን ‘ምናላት አንድ ብር…
ሁለት ብር ናት እኮ!’ ብለው::
አንድ ብር ለነሱ ቀላል ነገር መሆኗን ነገሩኝ። ሃቁ ግን ‘ሼም’ ይዟቸው ነው
እንጂ ሁለት ብር ለነሱም ቀላል አይደለም። እንደኔ ተጋፍቶና ቁሞ እየሔደ
አንድ ብር ምናላ ትይለኛል!” አጠገቡ ያሉትን ወረፋቸው። ሻጩ እንደ ጥሩ
አዛኝ እጃችንን ፈልቅቆ በጣቶቻችን ልክቆጥሮ ያዘጋጀውን የለውዝ ፍሬ
ያስጨብጠናል። ያልታሰበ ሲሳይ መጣልኝ ብሎ ወደ አፉ ከላከሰው ኪስ
ሁለት ብር ፈልቅቆ ይወስዳል።
“…እንዴት ለሁለት ብር ብለህ አትጨቃጨቅ ትሉኛላችሁ? ሁለት ብር
ቀላል ነገር ነው?...”
ሰውዬው በነካ አፌ ብሎ ነው መሰል ብሶቱን ቀጠለ።
“… አምና ከቤቴ ወጥቼ ከሻሼ ቁርስ ቤት አንድ ቆቆር(ፓስቲኒ) በሻይ
አወራርጄ ነበር ሥራ የምገባው። አሁን ግን አልሆነም። ሻሼ ራሷ በአርከበ
ሱቅ እየነገደች አንድ ፓስቲኒ ሦስት ብር ካልሆነ አልሸጥም አለች።
ስለዚህ እሷጋ ስደርስ ፊቴን አዙሬ ባላየ ‘ሙድ’ አለፍኳት። ታዲያ ለምን
ለምፈልገው ነገር ያላወጣሁትን እዚህ እንዳወጣ እገደዳለሁ?” ብሶቱን
ሲዘረግፈው የብሶታቸው ድምፅ ማጉያ የሆነላቸው ሁሉ ፊታቸውን
ኮስኩሰው(አጨፍግገው) ያዩታል። ሌሎች ደግሞ እነሱን የሚመለከት ጉዳይ
ያነሣ አላስመሰሉትም። እንዲያውም “ምን ለአንድ ብር ያጨቃጭቀዋል?…”
ይላሉ -በሹክሹክታ።
“…የኑሮ ውድነትና ገበያው በየምክንያቱ ደፍጥጠው ደፍጥጠው ረብየለሽ
ያደረጉትን ኑሮዬን እንደዚህ ዓይነት ጥቃቅን መንግሥታት ደግሞ ይኼው
በየምክንያቱ ይደፈጥጡታል። ባይሆን ትንንሽ መንግሥት የሆኑብንን
ተውን እንበላቸው እንጂ ጎበዝ!?
አሁን ብዙዎቹ በድንጋጤ አፍጥጠው እየተመለከቱት ነው።
“አህያውን ፈርቶ ዳውላውን!
ሆነ ነገር። አቦ ከፍ ብለህ ጩህ! ብትችል ቤተመንግሥት አካባቢ” ለውዝ
ሻጩ ብሩን ይዞ እየወረደ የተናገረው።
የሃይገር
ወጎች	 በ ወንድወሰን ውቤ
11ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
መግቢያ
‹‹ልጅያለውሰውሁሉልጁክፉንናበጎውንየሚለይበትን፣ንጉስናፈጣሪውን
የሚለይበትን እውቀትን ለማግኘት፤ የንባብንና የጽህፈትና ትምህርት
ያላስተማረ መቀጫውን 50 ብር እየከፈለ የመቀጫውን ገንዘብም ወደ ቤተ
እምነት እያገባ ለነዳያን ምግብና ልብስ ይሆናል ፡፡ የንስሀ አባትም የሆንክ
የንስሀ ልጆችህ ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ ምከር….ይህንን ሳትቀበል
ሳታስተምር የቀረህ እንደሆነ ግን በሹመትህ ትቀጣለህ፡፡››
ይህ አዋጅ የዘመናዊ ትምህርት ጅማሮን ያበሰረ፣ የትኛውም ወላጅ ልጁን
ወደ ትምህርት ቤት እንዲልክ የሚመክር፣የሚገስጽ ካልሆነም የሚቀጣ ህግ
የተቀመጠበት እ.አ.አ በ1921 ዓ.ም የወጣ አዋጅ ነበር ፡፡ አያሌው ሺበሺ /
ማኅተመሥላሴ ወልደ መስቀል ዝክረ ነገር/ ብለው በጻፉት መጽሀፍ ላይ
የተወሰደ ፡፡
ከሃይማኖት ንክኪ ነጻ የሆነና ዘመናዊውን ትምህርት በመላው ሀገሪቱ
እንዲሰጥ ንግሥት ዘውዲቱ የአጤ ሚኒሊክን ፈር በመከተል የወጡት
አዋጅም እንደሆነ ይነገራል፡፡ በ1908 እ.አ.አ አጤ ሚኒሊክ በስማቸው
የተሰየመውን የመጀመሪያውን ዘመናዊ ትምህርት ቤት ከፈረንሳይ መንግስት
ጋር በትብብር መክፈታቸውም ይታወሳል ፡፡
በመንግስት ትምህርት ቤት የተጀመረው የትምህርት ስርዓትና አካሄዳችን
በዘመናት ቆይታው የህዝብ ትምህርት ቤቶችን ከ1983 ወዲህ ደግሞ
በርካታ የግል ትምህርት ቤቶችንና ተቋምትን ማፍራት ችሏል፡፡አሁንም
በየአመቱ የትምህርት ቤቶቹ ቁጥር እያጨመረ መምጣቱን ማየት ይቻላል፡፡
ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ጎን ለጎን የግል ትምህርት ቤቶች እና
ተቋማት ለሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት የኩላቸውን ሚና እየተወጡ
ይገኛሉ፡፡ የተምሳሌት የዝግጅት ክፍልም ትምህርት ዘርፍ በአገልግሎቱ
መስክ ውስጥ ቢሆንም ከአንድ የአገልግሎት ዘርፍ ወይም ከሸቀጥ ሸመታ
በተለየ የሚታይበት መንገድ ባለመኖሩ የትምህርቱ ዘርፍ ተገቢው ድጋፍ
እየተደረገለት ነው ወይ ስትል ጥያቄ አንስታ ከሚመለከታቸው አካላት
ምላሽ አፈላልጋለች፡፡
ለትምህርቱ ዘርፍ የሚደረግ ድጋፍ
መንግስት በየዓመቱ የሚይዘውን የትምህርት በጀት ለመንግስት ትምህርት
ቤቶች እንደየደረጃቸውና እንደየተማሪዎቻቸው ብዛት የሚያከፋፈል
እንደሆነም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ይጠቁማል፡
፡ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 41/4 መንግስት የጤና የትምህርት እና
ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለህዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ
የሚሄድ ሃብት ይመድባል ይላል ፡፡ይሁን እንጂ በመንግስት ትምህርት
ቤቶች የሚታዩ የመጽሀፍት ፣ የቤተ ሙከራና የቁሳቁስ እጥረቶች
እንዲሁም የመምህራን በጊዜው ያለመመደብ ክፍተቶች አሳሳቢ ችግሮች
ሆነው ይታያሉ ፡፡ በተመሳሳይ ትምህርት ቢሮ ለግል ትምህርት ቤቶችም
መጽሀፍት አሳትሞ እንደሚያከፋፍል ይገልጻል ፡፡ ሆኖም የግል ትምህርት
ትምህርት
በጥርስ
መካከል	 በ አዲስ ፀጋዬ
12 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
ቤቶቹ መንግስት ከመጽሀፍ እደላው ባሻገር መንግስት መሰረታዊ የሚባሉ
እገዛዎችን እያደረገ አይደለም የሚል ስሜት አላቸው ፡፡ ለአብነት ያህል
የመሬት አቅርቦት ፡- መንግስት መሰረታዊውን የመሬት አቅርቦት ለግል
ትምህርት ቤቶቹ ለመስጠት ያሳየው ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ነገር የለም
ይላሉ፡፡
የፋይናንስ ድጋፍ፡- መንግስት ለትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረኩ
ነው ሲል ቢደመጥም በተለይ ለግል ትምህርት ቤቶች የፋይናንስ
ድጋፍ በመስጠት አቅማቸውን የሚያጎለብቱበትን መንገድ እንዲፈጥሩ
የሚያደርገው አስተዋጽኦ ዝቅተኛ ነው ሲል የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር
በበኩሉ ይጠቅሳል፡፡
የቀረጥ ነጻ መብት፡- በዚህ መብትም ተጠቃሚ ያለመሆናቸውን የግል
ት/ቤቶች ይገልጻሉ፡፡ እነዚህ መሰረታዊ ድጋፎች አለመኖራቸው ደግሞ
በትምህርት ዘርፉ ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል፡፡
ትምህርት ኢንቨስትመንት ወይስ ሸመታ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በተለይም ብዙ ካፒታል በሚጠይቁ
የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ትኩረት አድርጎ ይንቀሳቀሳል፡
፡ በማኑፋክቸሪንግ ፣በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ሰፋፊ እርሻዎችና ኢንዱስትሪ
ፓርክ አልሚዎች በሁለት መልኩ ማበረታቻ ይደረግላቸዋል ይላል ፡፡
የመጀመሪያው ማበረታቻ ከቀረጥ ነጻ ዕቃዎችን እንዲያስገቡ /duty free/
ማድረግ ሲሆን በዚህ እድል ማሽነሪዎችን እስከ 100% ነጻ እንዲሁም
የማሽኖቹን 15% የሚሆኑ መለዋወጫዎችን በነጻ ማስገባት ይችላሉ ፡
፡ ሌላው የገቢ ግብር እፎይታ ጊዜ /tax holiday/ መስጠት ሲሆን እንደ
ኢንቨስትመንቱ አይነትና እንደመገኛ ስፍራው ከሁለት እስከ አምስት አመት
ሊሰጥ ይችላል፡፡ ከነዚህ ዘርፎች በተጨማሪም መንግስት የአገልግሎት
ዘርፉ በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ይሸፈናል ብሎ ያምናል፡፡ በከፍተኛ
የትምህርት ተቋማት ላይ የሚሳተፉ የውጭ ባለሀብቶች ወደ ሀገር ሲገቡ
የራሳቸውን ህንጻ እንዲገነቡ ይገደዳሉ ፤ ይህም በቀላሉ ኢንቨስትመንቱን
ትተው እንዳይሄዱ የተወሰደ እርምጃ ነው ሲሉ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን
ይገልጻሉ ፡፡ እንደ ኮሚሽኑ ለትምህርት ቤቶች መገልገያ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን
በዝቅተኛ ቀረጥ በማስገባት መንግስት የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ
ይገልጻል ፡፡ ነገር ግን ለትምህርት ቤቶች በተለይም ለግል ትምህርት ቤቶች
ተብሎ የተዘጋጀ የኢንቨስትመንት መሬትና የገቢ ግብር እፎይታ ጊዜ
አለመኖሩን ያስቀምጣል፡፡
በኢንቨስትመንቱ ያን ያህልም ተጠቃሚ ያልሆነው የትምህርቱ ዘርፍ
ወላጆች አገልግሎትን በገንዘባቸው የሚገዙበት፤ ትምህርት ቤቶች ደግሞ
የሚያቀርቡ ሆነው በሸማችና በሸመታው ዘርፍ የሚዳኙበት አግባብ
እንዳለ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን ይጠቁማል፡፡ በዚህ ዘርፍ
ትምህርት ቤቶች የሚሰጡት የትምህርት ሁኔታ ወይም ትምህርቱ ጥራትን
ሳይሆን የክፍያ ዋጋ ላይ ብቻ ቁጥጥር ይደረጋል፡፡ በኢንቨስትመንት ዘርፉ
ብዙም ድጋፍ ያላገኘው የትምህርት ዘርፉ በአገልግሎት ሰጭና ተቀባይ
ወይም በሸመታው ዘርፍ የሚታይበትም አግባብ ተፈጥሯል ፡፡ ለዚህ
ደግሞ ሰሞነኛውን የግል ትምህርት ቤቶች ክፍያ ጭማሪና ይህንን ተከትሎ
የተነሳውን ውዝግብ ማንሳት ይቻላል፡፡
ነጻ ገበያና የክፍያ ተመን
በነፃገቢያየኢኮኖሚፅንሰሃሳብየግልየንግድተቋሙናሸማቹበሚስማሙት
መሰረት የሚከናወን የግብይት ስርዓት ነው፡፡ በዚህ ስርዓት መንግስት
በንግድ ውድድርና ሸማቾች አዋጅ እንደነገገው ለነጻ ገበያ አመቺነት ያለው
ስርዓት ከማስፈን እና የንግዱን ህብረተሰብ ከፀረ-ውድድርና ተገቢ ካልሆኑ
ተግባራት ከመከላከል በዘለለ በአቅርቦቱ እና በፍላጎቱ መካከል ጣልቃ
እንደማይገባ ተቀምጧል ፡፡ ነጻ ገበያ መሰረት የሚያደርገው ገበያውን ብቻ
ነው ፡፡ ይሁን እንጂ በአቅራቢዎቹም መካከል የግል ድርድር በማድረግ
ሸማቹ በሚገዛው ነገር ላይ ተመሳሳይ ዋጋ የማስተመን (Price setting)
ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ይህ ሆኖ ሳለ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ
ባለስልጣን የግል ት/ቤቶች በክፍያው ላይ በየዓመቱ ጭማሪ እያደረጉ ነው
ሲል ይከሳል ፡፡ የዋጋውን ተመን መሰረት በማድረግም ቅሬታ ያቀርባል ፡
፡ በሌላ በኩል ዋጋውን መሰረት ያደረገ የዋጋ ተመን በግል ት/ቤቶቹ ላይ
እንደማይጥል ያስታውቃል፡፡
የግል ት/ቤቶች ክፍያ
የአዲስ አበባ ት/ቢሮ በስሩ የሚገኙትን የግል እና የመንግስት ትምህርት
ቤቶች የትምህርት ስርዓት ይቆጣጠራል፡፡ ከዚህ ባሻገር የግል ት/ቤቶቹ
ክፍያ ላይ መንግስት እጁን ማስገባቱ ለምንድን ነው ሲሉ የሚጠይቁ አሉ ፡
፡ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የት/ቤቶቹ የክፍያ ጭማሪ
በየዓመቱ የሚደረግ እና የኢኮኖሚ ምክንያት የሌለው ነው ሲል 194
ለሚሆኑ የግል ት/ቤቶች ከት/ቢሮ ጋር በመሆን ማስጠንቀቂያ መስጠቱን
ለዝግጅት ክፍላችን ገልጧል ፡፡ ባለስልጣኑ የግል ት/ቤቶችን ጥራት ጉዳይ
የሚከታተለው የአዲስ አበባ ት/ቢሮ መሆኑንም አያይዞ አስቀምጧል ፡፡
ታዲያ ይህ ተግባር የአንድ ት/ቤትን አጠቃላይ የትምህርት አሰጣጥ ደረጃና
ብቃት ያገናዛባል ? በዋጋ ላይ ብቻ መሰረት ያደረገ ፍተሻ ማድረግስ ተገቢ
ነው ?
የኢኮኖሚ ምክንያት
የግል ት/ቤቶች ካለ በቂ ምክንያት በክፍያ ዋጋ ላይ ጭማሪ አድርገዋል
የሚሉ ሃሳቦች በተደጋጋሚ መነሳታቸውን እና ይህንንም አዲስ አበባ ት/
ቢሮም ሆነ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን በጥናት ማረጋገጣቸውን
ገልጸዋል፡፡ የኢኮኖሚ ምክንያት ምንድነው? ብለን ስንነሳ በዋናነት
የኢኮኖሚ ምክንያት በሀገሪቱ ካለው የእቃዎች ዋጋ መናርና ከዋጋ ግሽበት/
Inflation /ጋር ተያይዞ ሊነሳ የሚችል ነው፡፡
በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የትምህርት ተቋማት
ዓመት
2002
ዓ.ም
2003
ዓ.ም
2004
ዓ.ም
2005
ዓ.ም
2006
ዓ.ም
አማካይ
አመታዊ
እድገት
ትምህርት ቤቶች
/ተቋማት/
መዋዕለ
ህጻናት
3318 3418 3580 3688 4560 6.6
የመጀመሪያ
ደረጃ
20251 28349 29643 30495 32048 3.5
ሁለተኛ
ደረጃ
1335 1517 1710 1912 2333 11.8
የመምህራን
ትምህርት
29 32 32 34 34 3.2
ቴክኒክና
ሙያ
460 505 502 437 437 -1.0
ከፍተኛ
ተቋማት
70 74 91 99 124 12.1
ድምር 32163 33895 35561 36665 39536 4.2
የትምህርት ሚንስቴር አመታዊ የትምህርት ስታትስቲክስ 2006 ዓ.ም 2013/14
13ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008
ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ያናገርናቸው አንድ ምሁር እንደሚሉትም
“Inflationisdefinedasariseinthegeneralpricelevel.Inother
words, prices of many goods and services such as housing,
apparel, food, transportation, and fuel must be increasing
inorderforinflationtooccurintheoveralleconomy.Ifprices
of just a few types of goods or services are rising, there isn’t
necessarily inflation.”
ግሽበት የሚለካው በአጠቃላይ ዋጋ ጭማሪ መሰረት ነው ፡፡ በሌላ አነጋገር
ብዙ የአገልግሎት እና የሸቀጥ ዋጋዎች ጭማሪ ሲታይባቸው ነው ፡፡
እነዚህም ቤቶች ፣ አልባሳት፣ ምግብ፣ ትራንስፖርት፣ እና ነዳጅ ላይ የዋጋ
ጭማሪ የሚያደርግ ሲሆን ነው ፡፡ በጥቂት ግብይቶች ላይ የሚደረግ የዋጋ
ጭማሪ የዋጋ ግሽበትን አያስከትልም፡፡
በዚህ መረጃ ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ የዘንድሮ እና የዓምና ተመሳሳይ ወሮች
ኢንዴክስ የችርቻሮ ዋጋ 11.9 % ጭማሪ ማሳየቱን ለመረዳት ተችሏል ፡፡
በሌላ በኩል ትራንስፖርት 4.8 % መገናኛ 0.6 % ትምህርት 0.9 % ቅናሽ
አሳይቷል ፡፡ ተንከባላይ የዋጋ ግሽበት የሚባለው ረዘም ያለ ጊዜ ሲንከባለል
የመጣ የዋጋ ግሽበት ነው፡፡
ከዚህ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ሪፖርት መረዳት የሚቻለው ሁለት ነገር ነው
፡፡ የመጀመሪያው የት/ቤቶቹ የዋጋ ጭማሪ የኢኮኖሚ መሰረት የለውም
የሚለው ክስ በዚህ መረጃ መሰረት ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡
ሌላው በአገልግሎት ዘርፍ በተለይም በትራንስፖርት፣ በመገናኛና እንዲሁም
ከፍተኛ ጭማሪ እየታየበት ነው የሚባለው ትምህርት በአንጻራዊነት ቅናሽ
የሚያሳይ መሆኑን ለመረዳት ይቻላል ፡፡
የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን በግል ት/ቤቶች ውስጥ የተደረገው
ጭማሪ ለ3 ተከታታይ ዓመታት መሆኑንና 97% ያህል የሚሆኑ ት/ቤቶች
ጭማሪ ማድረጋቸውን ይህም በባለሥልጣኑ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች
መረጋገጡን ይገልጻል ፡፡እነዚህ የማዕከላዊ ስታስቲክስና የንግድ ውድድርና
ሸማቾች ባለስልጣን ሁለት መረጃዎች እርስ በእርሳቸው የተጣረሱና አንድ
አይነት መደምደሚያ ላይ ለመድረስም አሻሚ ሆነዋል፡፡
ወላጆች ምን ይላሉ?
ወላጅ 1
ወ/ሮ ስርጉት በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ መካከለኛ ገቢ ያላቸው
ሴት ናቸው፡፡ ሁለት ልጆቻቸውን በግል ት/ቤት ውስጥ የሚያስተምሩ
ሲሆን ወላጇ እንደሚሉት በየዓመቱ ለት/ቤት ከሚከፍሉት ዋጋ በተጨማሪ
ለተለያዩ መገልገያዎች የሚያወጡት ወጪ እንዳስመረራቸው እና መንግስት
ጣልቃ ገብቶ የዋጋ መረጋጋት ማድረግ እንዳለበት ይገልጻሉ፡፡
ወላጅ 2
ዶ/ር አብረሃም የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ናቸው ፡፡ ልጆቻቸውን
የሚያስተምሩት በግል ት/ቤት ነው ፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት ት/ቤቶቹ
በየዓመቱ ከሚጨምሩት ክፍያ ይልቅ ልጆቻቸው የተሻለ ትምህርት
አግኝተዋል ወይ ብለው ይጠይቃሉ ፡፡ መንግስት የዋጋ ተመን ውስጥ ገብቶ
ከሚሰራ ይልቅ በሀገሪቷ ላይ ያሉ ት/ቤቶች የግልም ሆነ የመንግስት ጥራት
ያለው ትምህርት ለዜጎች የሚሰጥበትን መንገድ ማመቻቸት አለበት ባይ
ናቸው፡፡ ዛሬ ልጄን በክፍያ መጨመር ምክንያት ወደ ት/ቤት ባልወስደው
ሌላ አማራጭ አለኝ ወይ ሲሉም ይጠይቃሉ ፡፡ ራሳቸው ሲመልሱም የለኝም
፡፡ በርካታ ጥራት ያላቸው ት/ቤቶች የሚፈጠሩ ከሆነ ወላጅ ብዙ አማራጭ
ይኖረዋል ፡፡ ይህ ሁኔታ ከተፈጠረም ወላጅ ዋጋ ብቻ ሳይሆን ጥራትንም
ማወዳደር ይጀምራል የሚል እምነት አላቸው፡፡
ማጠቃለያ
ለቀጣይ የኢትዮጵያ እድገት ወሳኙ የሰው ሀይል መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡
፡በተለይም የተማረ ራሱን ለእውቀት ያስገዛ ሀይል እጅጉን ትፈልጋለች፡
፡ እናም እነዚህ ሀይሎች የሚፈራባቸው ተቋማት ሳሙናና ብረት
ከምናገኝባቸው ፋብሪካዎች በተሻለ ወይም በበለጠ ድጋፍ ሊደርግላቸው
ይገባል፡፡ መንግስት በስሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን አቅም በማጎልበት
ተወዳዳሪነቱ ላይ በመስራት ለወላጆችና ለተማሪዎች አማራጭ መፍጠር
ይኖርበታል፡፡ ለግል ትምህርት ቤቶች የሚደረገው ድጋፍም ቸል ሊባል
አይገባም፡፡ የግል ትምህርት ተቋማቱም ከመንግስት የትምህርቱ አካላት
ጋር በአዎንታዊ አመለካከት ተቀራርበው መስራት ቢችሉ በየጊዜው
ለሚያነሷቸው የፋይናንስና የመሰረተ ልማት እጥረቶች መፍትሄ ሊያገኙ
ይችላሉ፡፡ በትምህርቱ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ አካላትም በትምህርት ተቋማቱ
ላይ እርምጃ ከመውሰዳቸው አስቀድመው ህገ መንግስቱን ጨምሮ
የሀገሪቱን ህጎች የሚጥስ ስላመሆኑ በእርምጃውም ወላጅና ማህበረሰቡ
ተጎጂ ስላለመሆናቸው ሊያረጋግጡ ይገባል፡፡ የሀገሪቱ ከኢንቨስትመንቱም
ከሸመታውም ዘርፍ ተጠቃሚ መሆን ያልቻለው የትምህርቱ ዘርፍ ብቁና
ተወዳዳሪ የሰው ሀይልን እንዲያፈራ በትንንሽ ምክንያቶች ጫና ከማብዛት
ይልቅ ቁጥጥሩንም ከድጋፉንም ማጠናከር ይገባል፡፡
የፌዴራል ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በሐምሌ ወር 2007 ዓ.ም ሪፖርቱም በሀገሪቱ
ባሉ አብዛኞቹ ምርቶች ላይ ጭማሪ ማሳየቱንይገልጻል ፡፡ ግሽበትም መኖሩን ያሳያል፡፡
ጥናት
የተደረገበት
ጊዜ
አገልግሎቶች ተንከባላይ
የዋጋ
ግሽበት
አጠቃላይ
ግሽበት
ምግብ ነክ
ምግብ ነክ
ያልሆኑ
2007
ዓ.ም
8.0% 8.0% 8.1 % 7.7 %
መረጃ ቁ. 29 2007 ዓ.ም
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages
Temsalet Magazine 2 Pages

More Related Content

Featured

2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by HubspotMarius Sescu
 
Everything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTEverything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTExpeed Software
 
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsProduct Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsPixeldarts
 
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthThinkNow
 
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfAI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfmarketingartwork
 
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024Neil Kimberley
 
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)contently
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024Albert Qian
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsKurio // The Social Media Age(ncy)
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Search Engine Journal
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summarySpeakerHub
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Tessa Mero
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentLily Ray
 
Introduction to Data Science
Introduction to Data ScienceIntroduction to Data Science
Introduction to Data ScienceChristy Abraham Joy
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best PracticesVit Horky
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementMindGenius
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...RachelPearson36
 

Featured (20)

2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot
 
Everything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTEverything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPT
 
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsProduct Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
 
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
 
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfAI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
 
Skeleton Culture Code
Skeleton Culture CodeSkeleton Culture Code
Skeleton Culture Code
 
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
 
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
 
How to have difficult conversations
How to have difficult conversations How to have difficult conversations
How to have difficult conversations
 
Introduction to Data Science
Introduction to Data ScienceIntroduction to Data Science
Introduction to Data Science
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best Practices
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project management
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
 

Temsalet Magazine 2 Pages

  • 1. 1ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 www.temsalet.com ትምህርት በጥርስ መካከል ምክንያትና ውጤቱ ማህበራዊ ድረ ገጾችና ትምህርታዊ ፋይዳ የሥነ ምግባር ጉዳይ
  • 2. 2 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 አገሬ አገሬ ውበት ነው ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት ጸሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት። አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ። አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ። ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም ክረምቱም አይበርድም፣ አይበርድም፣ አይበርድም። አገሬ ጫካ ነው እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት። እዚያ አለ ነጻነት። በሃገር መመካት፣ በተወላጅነት፣ በባለቤትነት..... (ሰዓሊ እና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ)
  • 3. ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 ክብርት ዶክተር ስንዱ ገብሩ 10ጥያቄዎች ለትምህርት ቢሮ 10ጥያቄዎች ለግል ት/ቤቶች ማሕበር የነገ ዛሬዎች የሃይገር ወጎች ትምህርት በጥርስ መካከል ምክንያትና ውጤቱ የሰው ልጅ አንጎል ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ በእጓለ ገብረዮሃንስ ማህበራዊ ድረ ገጾችና ትምህርታዊ ፋይዳ ከአዕምሮ ውስጥ የሚሸት ጣፋጭ የዩኒቨርሲቲ ትዝታ የሥነ ምግባር ጉዳይ … 1 3 25 14 16 19 23 28 9 10 11 በዚህ ዕትም www.temsalet.com
  • 4. ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 በአገራችን ትምህርትን አስመልክቶ የሚነሳ አባባል አለ ለወራት ችግር ጎመን፣ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ጤፍ ዝራ፤ ለአመታት ችግርህ ማንጎ፣ ቡና ዝራ፤ ለመቶ አመታት ችግርህ ዛፍ ዝራ፤ ለዕድሜ ልክ ችግርህ ትምህርት ዝራ፤ ይባላል፡፡ እነዚህ አባባሎች ከአባባል ባሻገር የሚሰጠው መልዕክት ትልቅ ነው። ለዕድሜ ልክ ችግርህ መፍቻ የተጠቀሰው ትምህርት ምን ያህል ትኩረት ተሰጥቶታል ብለን ያልን እንድሆን እንብዛም ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ መንግስት ለትምህርት ቤቶች መስፋፋት እያደረገ ያለው ጥረት እጅግ የሚበረታታ እና የሚደገፍ ሆኖ ሳለ ዛሬም ለትምህርት ጥራት እንዲሁም ለትምህርት ቤቶች የሚደረገው ድጋፍ የሚያበረታታ አይደለም፡፡ Africa.comBlog ኢትዮጵያ በአምስት የተመረጡ ዘርፎች በኢንቨስትመንት ዓለምን የምትስብ ሀገር ናት ሲል ይገልፃል ፡፡ ከነዚህ ሳቢ ኢንቨስትመንቶች አንዱ ትምህርት ነው ፡፡ መንግስት ለማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ለእርሻ ኢንዱስትሪ፣ ለኢንዱስትሪ ማስፋፋያ እና ለአይ ሲቲ ዘርፎች የሚደረግ የኢንቨስትመንት ልማት ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን እንደ ሆቴል እና አበባ ልማት የሚከናወኑ ኢንቨስትመንቶች ላይ ከታክስ እና ግብር ቅናሳ ጀምሮ ያለቀረጥ የሚገቡ መገልገያዎችን በነፃ እንዲገቡፈቅዷል ፡ ፡ ለትምህርት አገልግሎት ሲሆን እነዚህ ማበረታቻዎች ለምን ዝግ እና ቅድሚያ የሚሰጠው እንዳልሆነ ግልፅ አይደለም ፤ በተለይም ትምህርት በኢንቨስትመንት ሊታቀፍ የሚገባው ዋና የኢንቨስትመንት መስክ ነውና፡፡ የሆነው ሆኖ ለሁሉም ነገር መሰረት የሆነው ትምህርት ጠንካራ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል፡፡ የተምሳሌት አቋም የተምሳሌት አቋም በትምህርት እና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር በየወሩ የሚታተም መጽሔት ነው ፡፡ ተምሳሌት መጽሔት በኢትዮጽያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ምዝገባ ቁጥር 279/2006 እና በንግድ ምዝገባ ቁጥር kik/AA/2/0003278/2007 ሐምሌ 15 ቀን 2006 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡ ዋና አዘጋጅ ንጉስ ይልማ አድራሻ: ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 1711 negus@akbdmedia.com ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከድር አህመድ kedir@akbdmedia.com ኤዲቶሪያል ቡድን ደሳለኝ መኩሪያ desalegn@akbdmedia.com አዲስ ፀጋዬ addis@akbdmedia.com በለጠ ጌታቸው belete@akbdmedia.com ዓለማየሁ ስሜነህ alemayehu@yahoo.com አምደኞች ወንድሙ ነጋሽ (ከሎንዶን) ጽጌሬዳ ጎንፋ መላኩ አላምረው (የእናት ልጅ) ክቡር መተኪያ ሄኖክ ሰይድ አየለ ተሰፋዬ ዲዛይን በፀጋ ግርማ ካርቱኒስት ገነነው ውብሸት የኮምፒዩተር ጽሁፍ አዜብ ዓለማየሁ azeb@akbdmedia.com ገበያ ስርጭት እና ክትትል ዮርዳኖስ በቀለ የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 3277 ዘርሽታ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 212 ስልክ ቁጥር 251 911225298 ፖ.ሳ.ቁ 54154 ኢ-ሜይል info@temsalet.com www.temsalet.com አሳታሚ ኤኬቢዲ የፕሬስ የማስታወቂያና የማማከርአገልግሎት www.akbdmedia.com
  • 5. 1ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 ክ ብርት ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ከ1948 ዓ.ም. እስከ 1952 ዓ.ም. ድረስ የመጀመሪያዋ የሴት የፓርላማ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባልና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ም/ሊቀመንበር ሆነው በማገልገላቸው ታሪክ “የመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ አባል” ብሎ መዝግቧቸዋል። ትዉልድ እና እድገት ከአጼ ቴዎድሮስ ጀምሮ እስከ አጼ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ድረስ በከፍተኛ ሃላፊነት ያገለገሉት እና በወቅቱ ተራማጅ አስተሳሰብ ከነበራቸው ቀደምት ኢትዮጵያዊ ምሁራን መካከል የሚመደቡት እና የጎንደር ከተማ ከንቲባ የነበሩት ገብሩ ደስታ ወይም በብዙዎች ዘንድ በሚታወቁበት ስማቸው ጆቤው እና ወይዘሮ ካሳዬ ይሌምቱ ከወለዷቸው በርካታና ዝነኛ ልጆች መካከል ስንዱ ገብሩ የላቀ እዉቅናን የተጎናጸፉ ሴት ናቸው::እኚሁ ሰው በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሃገር በመናገሻ አዉራጃ በአዲስ አለም ከተማ በወረሃ ጥር በስድስተኛዉ ቀን በ1908 ዓ.ም ተወለዱ::የታላቅ ባላባት ልጅ እንደመሆናቸው መጠን በመኖሪያ ቤታቸው መምህር ተቀጥሮላቸው ሲማሩ ቆይተዋል:: ይህንን በወቅቱ እንደ ታላቅ ትምህርት ይቆጠር የነበረዉን የአብነት ትምህርት እና ዳዊት መቁጠር ከተማሩ በኋላ በወቅቱ በአቅራቢያቸው ይገኝ ከነበረው የስዊድን ወንጌላዊት ሚሲዮን ትምህርት ቤት በመግባት የአንደኛ ደረጃ ትምህርትን በሚገባ አጠናቀቁ:: ከተቀዳሚዎቹ የዉጪ ተማሪዎች አንዷ ከንቲባ ገብሩ ደስታ ዉጪ ሃገር ሄደው ከተማሩ ቀደምት እና ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ምሁራኖች መካከል የሚመደቡ ከመሆናቸው የተነሳ እንዲሁም እንደ እነ ስንዱ ገብሩ ያሉ ህጻናቶች ሾለ አባታቸው የዉጭ ሃገር ቆይታ ብሎም የትምህርት አይነት አጥብቀው ይጠይቁ ስለነበር በወቅቱ እንደ ብርቅ ይታይ የነበረዉን የዉጭ ሃገር ከፍተኛ ትምህርት ለመቅሰም ስንዱ ገብሩከታናሽ እህታቸው ከየዉብዳር ገብሩ ጋር በአንድነት በመሆን በአባታቸው በከንቲባ ገብሩ ደስታ አጃቢነት ወደ ስዊዘርላንድ ሃገር አመሩ:: ከንቲባ ገብሩ ደስታ(ጆቤው) ከአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ጋር ከፍተኛ ቅርርብ ስለነበራቸው የልጆቻቸው የዉጭ ሃገር ትምህርት በቀላሉ እንዲሳካ ረድቷቸዋል፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ነው የጆቤው ልጆች ወደ ዉጭ ሃገር ሄደው እንዲማሩ የተወሰነው፤ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ከታናሽ እህታቸው የዉብዳር ገብሩ ለትምህርት ወደ አውሮፓ ተጉዘዋል፡፡ ወደ ስዊዘርላንድ ሃገር ለከፍተኛ ትምህርት በሄዱበት ወቅት የመነጋገሪያው ቋንቋ በርካታ ቢሆንም ስንዱ እና እህታቸው ባረፉበት ግዛት ይነገርበት የነበረው ቋንቋ ጀርመንኛ ስለነበረ እና ቋንቋዉን ለመረዳት ከባድ ስለሆነባቸው ለስድስት ወር የነበራቸውን የስዊዘርላንድ ቆይታ በመተው ወደ ፈረንሳይ ሃገር አመሩ:: በጊዜው የገቡበት “ሞሚራይ” የተሰኘው ትምህርት ቤት እድሜያቸው ከአስራ አምስት አመት በላይ የሆናቸውን ልጃገረዶች ብቻ የሚቀበል የነበረ ተቋም ቢሆንም ከእሩቅ ሃገር ትምህርትን ብለው ለመጡት ለእነዚህ ህጻናቶች ሲባል ብቻ መምህር በግል ተመድቦላቸው ታላቅ እና ታናሽ እህትማማቾቹ ስንዱ እና የዉብ ዳር ገብሩ የቀለም ትምህርትን እንዲማሩ እና ጥሩ እዉቀትን እንዲያገኙ ተደረገ:: (የዉብዳር ገብሩ በኋልኛው ዘመን በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የረቂቅ ሙዚቃ ተጫዋች በመሆን በርካታ የሙዚቃ አልበምን ያሳተሙ ከጊዜያት በኋላ ደግሞ እድሜያቸውን በምንኩስና ህይወት ለመምራት የመረጡ የዉብዳር የተሰኘ የአለም ስማቸውን ትተው እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ በሚል ስማቸው የሚታወቁ ሌላ ስመጥር ኢትዮጵያዊ ናቸው)::በወቅቱም የቤት አስተዳደር የምግብ አዘገጃጀት የፒያኖ አጨዋወት የስፌት መኪና ትምህርት የአመት በጀት አያያዝን ጨምሮ በወቅቱ ለሃገራችን ብርቅ የሆኑ ትምህርቶችንበፈረንሳይ ሃገር ተምረውበዲፕሎማ ማዕረግትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ:: በበርካቶች ዘንድ የወይዘሮ ስንዱ ቀዳሚነት እሚጠቀስላቸው የመጀመሪያዋ የሴት ፓርላማ አባል የመሆናቸው ጉዳይ ቢሆንም በኢትዮጵያ እምብዛም ያልተለመደውን የሴት መምህርነት እና የሴት ርዕሰ መምህርነት፣የሴት ጸሃፊ ተዉኔትነት፣የሴት ደራሲነት፣የሴት ገጣሚነት ወዘተ በመስራት ለብዙ ሰዎች አርአያ ለመሆን በቅተዋል:: ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ተቀጥረው ፈረንሳይኛ አማርኛ ጽሁፍ እና ሾለ ጤና አጠባበቅ ለማስተማር ችለዋል::በዚህ ሁኔታ ለአንድ አመት ከቆዩ በኋላ ከአምባሳደር ብላታ ዶክተር ሎሬንዞ መብርሃቱ ጋር ጋብቻ ፈጸሙ፡፡ ወይዘሮ ስንዱ ባለቤታቸው ብላታ ሎሬንዞ በቀድሞ መጠሪያው የሃረርጌ ጠቅላይ ግዛት በአስተዳዳሪነት በመሾማቸው ከአዲስ አበባ ወደ ሃረርጌ አቀኑ::ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ ደግሞ ባለቤታቸዉ ሎሬንዞ የፍርድ ቤት ሹምና የዜና ስርጭት ኃላፊ ሆነው በመሾማቸው ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ቻሉ:: የሴት አርበኝነት በአድዋ ድል በቀመሰው የሽንፈት ቂም ይዞ ለአርባ አመታት ገደማ ሲያደባ እና ጦር ሲያደራጅ የከረመው የፋሽት ኢጣልያ ወራሪ ጦር የአዉራዉን የሞሶሎኒ የሮም አደባባይ ድንፋታ ተከትሎ እና የመረብ ወንዝን ተሻግሮ የኢትዮጵያን ዋና ዋና ከተማዎች በተቆጣጠረበት ጊዜ ንጉሰ ነገስቱ አጼ ክብርት ዶክተር ስንዱ ገብሩበ ክቡር መተኪያ
  • 6. 2 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 ሃይለስላሴ በስደት ወደ እንግሊዝ ሃገር ሲጓዙ አብረዋቸው እንዲጓዙ ከመረጧቸው የቅርብ ዘመዶች ልጆች እና ታላላቅ ሹማምንቶች መካከል ብላቴን ጌታ ሎሬንዞ ሲገኙበት ቆራጧ አርበኛ ስንዱ ገብሩ ግን እምቢኝ ላገሬ ብለው ሆለታ ከሚገኘው የአርበኛ ጦር እና ጎሬ ላይ ከተቋቋመው ጊዜያዊ የኢትዮጵያ መንግስት ባላደራ አርበኞቹ ከእነ ልሾ እምሩ ጦር ጋር ተቀላቀሉና ሃገራቸውን ከወራሪ ጦር የማስጣል ሾል ጀመሩ::በዚህ ጊዜም ለአርበኝነት ይረዳቸው ዘንድ ከወሰዱት ስልጠና ሁሉ የመትረየስ አተኳኮስ ስልጠናው ቀዳሚ እና ተጠቃሽ ነው:: ወይዘሮ ስንዱ ተኩሰው ጠላትን ለመጣል የሚንተገተግ ወኔ የነበራቸው እና ለነብሳቸው ቅንጣት ታክል የማይሳሱ ጀግና አርበኛ የነበሩ ቢሆንም ቀደም ብለው በፈረንሳይ ሃገር በቀሰሙት እዉቀት ምክንያትነት እንዲሁም በጊዜው የመጀመሪያ እርዳታ የሚሰጥ ሰው ከአርበኞቹ መካከል እንደልብ ማግኘት ከባድ ስለነበር በወቅቱ የአርበኞቹን መሪ ልዑል ልሾ እምሩ ሃይለስላሴን አማክረው አምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር በመቀበል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የህክምና እርዳታ መስጫ ጣቢያ አቋቋሙ:: ከዛም በጦር ሜዳ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በማከም ለአርበኞች ደጀን የመሆን ስራን ቀጥለው በርካታ የጦር ሜዳ ጉዳት የደረሰባቸውን ተዋጊዎች ቁስል በመጥረግ እና በመስፋት ወትሮ ሊያዩት የማይፈቅዱትን የሰው ልጅ ስቃይ ለሃገራቸው ብለው ጨክነው በማከም በዚህም አርበኛዉን ከሞት እና ከስቃይ በማትረፍ ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በጀግኖች አርበኞች መካከል በተሰገሰጉት ባንዳዎች ጠቋሚነት ከበርካታ የጥቁር አንበሳ ፋኖ ሰራዊት ጋር የወራሪዉ የጣልያን ጦር ምርኮ ለመሆን ተገደዉ በግዞት ወደ አዲስ አበባ መጡ:: ቀድሞ ገነተ ልኡል ቤተ መንግስት ይባል የነበረው እና የኋላ ኋላ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ግቢ ፤የኢትዮጵያ አስተዳዳሪ ፊልድ ማርሻል ግራዚያኒ ላይ አብረሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም የተባሉ ወጣቶች የግድያ ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ የስንዱ ገብሩ ወንድም መሸም ገብሩ ከሴራዉ ጋር ተነካክቷል በሚል ምክንያት ከተማዉ ዉስጥ በወራሪዉ ጦር በጥብቅ ሲፈለጉ ከነበሩ ሰዎች መካከል ስለነበር በግዞት ወደ አዲስ አበባ መጥተው የነበሩት ስንዱ ገብሩ ወንድማቸውን ለማዳን ሲያደርጉ የነበረዉን ጥረት እግር በእግር ሲከታተል ከነበረው የጣልያን ጦር እጅ ላይ በድጋሚ ወደቁ እና በቅድሚያ በገነተ ልኡል ቤተ መንግስት ከዛም አስመራ ከዛም ምጽዋ ተወስደው ታሰሩ:: አስከትለዉም ከሶስት መቶ ወንዶች መካከል ስምንት መቶ ሴቶች አብረው በመሆን ወደ ጣልያን ሃገር “አዚናራ” ወደተባለማጎሪያእስርቤትተወስደው ለዘጠኝ ወር ከቆዩ በኋላ በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ወደ ሃገራቸው ተመልሰው ዳግመኛ በዚህ አይነት የአርበኛነት ተግባር ላይ እንዳይገኙ ማስፈራሪያ ቢደርሳቸውም እርሳቸው ግን አርበኞችን በግጥም፣በወኔ ቀስቃሽ ጽሁፍ፣በመረጃ ማቀበልና በመሳሪያ ማመላለስ ፍጹም ድፍረት የተመላ ስራን ለእናት ሃገራቸው ሲያከናዉኑ ቆይተው የጓጉለት ነጻነት በ1933 ዓ.ም እዉን ሊሆን ቻለ፡፡
  • 7. 3ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 10 ጥያቄዎች ለትምህርት ቢሮ አ ቶ ማስረሻ ዘሪሁን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ሲሆኑ ከተምሳሌት መጽሔት ጋር ከግል የትምህርት ተቋም አሰራር እና የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ የሚነሱትን ጥያቄዎች አስመልክተው የሰጡትን ቃለ መጠይቅ ይዘን ቀርበናል ፡፡ በመንግስት እና በግል ትምህርት ተቋማት መካከል አለ የሚባል መሰረታዊ ልዩነት አለ? አቶ ማስረሻ ፡- የአዲስ አበባ ት/ቢሮ በዋናነት ከሚሰራቸው አገልግሎት አንዱ ትምህርትን ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ ማድረግ ነው ፡፡ ከዚህ አንጻር መሰረታዊ መርህ (motto) የሆነው በተስማሚ ፕሮግራሞች ትምህርትን ለዜጎች ማዳረስ የሚል ነው ፡፡ በመሆኑም ቢሮው በት/ት ተቋማት መስራት የሚገባውን ሁሉ በመስራት ላይ መሆኑን ማረጋገጥ እንጂ በስያሜ በግልና በመንግስት ላይ መሰረት ያደረገ ልዩነት የለም፡፡ነገር ግን የግል ተቋማት አንዱ ያደረጃጀት እና የራሳቸው አወቃቀር ይለያቸዋል ፡፡ የመንግስት ት/ቤቶች በመንግስት በጀት የሚተዳደሩ ሲሆኑ የግል ት/ቤቶች ደግሞ ሃብታቸውን በትምህርት ላይ ኢንቨስት አድርገው በሚሰሩ ልማታዊ ባለሃብቶች የተቋቋመ ት/ቤት መሆኑ ነው ፡፡ ለመንግስት ት/ቤቶች የሚበጀተው በጀት ምንን መሰረት ያደረገ ነው ? ለሁሉም ተመሳሳይ ነው ወይስ ይለያያል ? አቶ ማስረሻ ፡- የመንግስት ት/ቤቶች በጀት የሚወሰነው በዋናነት ከተማሪዎች ቁጥር አንጻር ነው ፡፡ ስለሆነም እንደ ት/ቤቶች ተማሪዎች የመቀበል አቅም አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሚይዘው እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ በመሆናቸው መጠነኛ ልዩነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ከአፀደ ህጻናት እስከ ስምንተኛ፣ ከዘጠነኛ እስከ መሰናዶ ት/ቤት ተብሎ የተከፈለ የበጀት አጠቃቀም ነው ያለው ፡፡ ምናልባት በቁጥር ደረጃ ለእያንዳንዱ ተማሪ (per head) በዓመት 1700-2700 እንደ ትምህርት ደረጃው ሊመደብ ይችላል ፡፡ ይህ የራሱ ስሌት ስላለው በዚህ አግባብ ይሰተናገዳል ፡፡ ለግል ት/ቤቶች የሚደረጉ የማበረታቻ ድጋፎች አሉ ? በመንግስት የሚደረግ ድጋፍ ከሚገለጥባቸው መንገዶች አንዱ የማስተማሪያ ቦታ በሊዝ ኪራይ ማግኘትን፣ መጽሐፍቶችን ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ መፍቀድን፣ የቀረጥ ቅነሳ ማድረግን የመሳሰሉትን መንግስት ለግል ትምህርት ተቋማት የሰጠበት ሁኔታ አለ ? አቶ ማስረሻ ፡- መንግስት ለት/ቤቶች በርካታ ድጋፎች ይደረጋል፡፡ በዋናነት ስርዓተ ትምህርቱን የተከተለ መጽሐፍ ለሁሉም የግል ት/ቤቶች ተደራሽ ማድረግ በጣም ትልቅ እና ስኬታማ የሆነ የት/ቢሮ ሾል ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ከዚህ በፊት በነበሩት ዓመታት ተሞክሮ የትኛውም የግል ተቋም ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ መሰናዶ ያለውን መጽሐፍ ከመንግስት አግኝቶ አያውቅም ፡፡ ከገበያው ላይ ወላጆች የሚገዙት በውድ ዋጋ በመሆኑ ለብዝበዛ ዳርጓቸው ቆይቷል ከዚህ አንጻር የከተማ አስተዳደሩ ለት/ቢሮ በሰጠው ከፍተኛ ድጋፍ የግል ት/ቤቶች መጽሐፍ ማግኘት የሚችሉበትን ስርዓት እገዛ በማድረግ በቅርብ አመታት ውስጥ እየሰራ ያለው ሾል አበረታች ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል ፡፡ ነገር ግን ይህንን እገዛ ሁሉም ት/ቤቶች በአግባቡ እየተጠቀሙበት ነወይ ስንል አንዳንድ የግል ት/ቤቶች እየሰጡ ያሉትን ስርዓተ ትምህርት ተከትሎ የማስተማሪያ መጽሐፍ ወስደው ለተማሪዎቻቸው በማዳረስ ትክክለኛ ትምህርት ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ውስንነት ይታይባቸዋል ፡፡ መጽሐፍቶችን በተማሪዎች ልክ አለመግዛት ከገዙም በኋላ ለተማሪዎች ከመስጠት ይልቅ ት/ቢሮው በማያውቀው መልኩ ራሳቸው የሚዘጋጁትን “አጋዥ መጽሐፍት” በሚል ለወላጆች ከፍተኛ ገንዘብ እየጠየቁ የሚሸጡ ት/ቤቶች ቁጥራቸው ትንሽ ቢሆንም አሰራሩ ግን ትክክል አይደለም ብሎ ቢሮው ያምናል ፡፡ ይህም እንዲስተካከል የተለያዩ የክክትትልና ድጋፍ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን፡፡ ሌሎች የድጋፍ ጥያቄዎችን በተመለከተ የግል ት/ቤቶች ህብረት በነዚህ በተነሱት ጥያቄዎች ላይ በራሱ ተነሳስቶ ተወያይቷል ወይ የሚለው ጥያቄ ሊታይ ይገባል፡፡ ጥያቄውን ያቀረቡት አካላት በእኔ በኩል ጉድለት አለ ወይ ብሎ ማየቱ መልካም ነው ፡፡ አንድ ግለሰብ ቦታ ሊጠይቅ ይችላል ህብረቱ ግን እንደ ህብረት በማስፋፊያ ቦታዎች ላይ የማስፋፊያ ጥያቄ በያቀርብ የተሻለ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህንን ጥያቄ ሊያስተናግድ የሚችል አግባብ ያለው አካል አለ፡፡ በዚህ መልኩ ቀርቦ ከሆነ እኔ ጥርጣሬ አለኝ፡ ፡ ህብረቱ እንደገና ራሱን ቢፈትሽ ጥሩ ነው ፡፡ ከ1500 ባላይ የሚደርሱ ት/ቤቶች ህብረት ሆነው ጠንክረው እየሰሩ ነወይ ? አንድነት ኃይል ነው በሚል መሪ ቃል ሾር ሆኖ ጥያቄያቸውን ማቅረብ የሚችሉበት አቅም ላይ ናቸው ወይ ? እነዚህ ነገሮች አብረው ጎን ለጎን መታየት አለባቸው፡፡ በተረፈ ችግሮች የሉም ማለት አይደለም ፡፡ ችግሮቹን ለመፍታት መንግስት እምነቱም ቁርጠኝነቱም ስላለው በሂደት የሚሰሩ ስራዎች ማሳያ ናቸው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ጥያቄው ለትምህርት ቢሮ ሊቀርብ የሚገባው አይደለም፡፡ማሕበሩ ቢያንስ እየተጠናከረ የሚሄድበትን አግባብ በማሳየት ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን ፣ እየሰሩ ያሉትን ልማታዊ ሾል በማረጋገጥ ሪኮመንዴሽን ከመስጠት አንጻር የምንሰራቸው ስራዎች አሉ፡፡ ለአብነት ብንጠቅስ ግንቦት ወር ላይ ደንብና ህግን ተከትለው ህብረተሰቡን የማገልገል ዓላማ ይዘው የተነሱ 60 የግል ት/ቤቶች ተቋሞቹ ክ/ከተማና ወረዳ ተመርጠው በመምጣታቸው ት/ቢሮው እውቅና ሰጥቷቸዋል ፡፡ ይሄ ቀላል ነገር አይደለም ፡፡ እንደነዚህ አይነት ተቋማትን ለማበራከት የት/ቢሮ እምነትም ፍላጎትም ነው ፡፡ ተቋማቱ በተበራከቱ መጠን የህብረተሰቡን ፍላጎት ማርካት ይቻላል ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ት/ቢሮው የግልንም ሆነ የመንግስት ተቋም ያለ ምንም ልዩነት ጥራት ባለው መልኩ ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ነገ አገር ተረካቢ ዜጎችን መፍጠር ነው ፡፡
  • 8. 4 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 የግል ት/ቤቶች መተዳደሪያ ደንብ ከወጣ ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ 20 ዓመት ሆኖታል ፡፡ በደንቡ አንቀጽ 12(ለ) እንዲሁም አንቀጽ 23 ላይ ተደንግጓል ፡፡ መመሪያ አለው ? መመሪያ ከሌለው መመሪያው ሊሸፍናቸው የሚገቡ አሰራሮች በምን አግባብ ይሸፈናሉ ? አቶ ማስረሻ ፡- የግል ት/ቤቶች መተዳደሪያ ደንብ ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመመሪያ ቢታገዙ ጥሩ ነው ብለን ባሰብናቸው ነጥቦች ላይ ት/ቢሮ፣ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን እንዲሁም ከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ ባለሙያዎች የተሳተፉበት አንድ ረቂቅ ተዘጋጅቷል ፡፡ ይህ ረቂቅ በግል ት/ ቤቶች የአገልግሎት ክፍያ አፈጻጸም ስርዓት መመሪያ በሚል የወጣ ነው ፡፡ ምናልባትም ከአሰራር አንጻር፣ ከሂደት አንጻር የሚታዩ ችግሮችን ሊቀርፍ ይችላል የሚል እምነት አለን ፡፡ ት/ቤቶች ዋጋ ለመተመን የሄድንበት ርቀት አካሄዱ ፍትሃዊ ነው አይደለም ፤ አግባብነት አለው ወይስ የለውም በሚሉ ጥያቄዎች ላይ እገዛ የሚያደርግ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡ ፡ የመመሪያ ረቂቅ በመጀመሪያ ዙር ረቂቁን በባለሙያዎች እና በራሱ በግል ባለሃብቶች እንዲተቹ የማድረግ ሾል ተሰርቷል ፡፡ ረቂቁ ከዜሮ ጅምር ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ተወስደው የሁለተኛ ክለሳ ስራዎች በመሰራት ላይ ነው ፡፡ ይህ ሾል እንዳበቃ የሚመለከተው አመራር አካል አጽድቆ መመሪያ መሆን ይችላል የሚል ሃሳብ ካሰፈረ ወደ ተግባር የሚኬድበት አሰራር ይኖራል ፡፡ በግል ትምህርት ቤቶች ማቋቋሚያ ደንብ አንቀጽ 17 የግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ ሲያስቡ ከ3 ወር በፊት ለወላጅ ማሳወቅ አለባቸው ላል ፡፡ ነገር ግን በተግባር እንደሚታየው የወላጆች ማወቅ ብቻ ሳይሆን መስማማትም ይጠበቃል ፡፡ ይህ ከነጻ የገበያ መርህ አንጻር እንዴት ይታያል? አቶ ማስረሻ ፡- በግል ት/ቤቶች ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 206/87 እንደተደነገገው ት/ ቤቱ የአገልግሎት ክፍያ የመጨመር መብት አለው የምትለዋን ዓ/ነገር ብቻ በማጉላት እየተጠቀሙበት ነው ፡፡ የግል ትምህርት ተቋም ክፍያመጨመርመብትአለው፤ሆኖምግንይህንን ጭማሪውን ት/ቤቱ ከመከፈቱ ከ3ወር አስቀድሞ ማሳወቅ እንደሚገባው ተጠቅሷል፡፡ እዚህ ላይ ለማለት የተፈለገው መጨመር ለተፈለገው ጉዳይ ምክያታዊ (የኢኮኖሚ ምክንያት) ተብሎ የሚጠቀሱ ነገሮች አሉት ፡፡ ህብረተሰቡ በዚህ አግባብ ተረድቶ የመክፈል አቅሙን አገናዝቦ እንዲከፍል ነው ፡፡ ሌላ አማራጭ ያለው አማራጩን እንዲፈልግ ወላጆች ት/ቤት ከማጣት እንዳይሰተጓጎሉ ለማድረግ ነው ፡፡ በሌላ በኩል ታሳቢ የሚደረገው የዋጋ መጨመር ጉዳይ የባለ ሃብቱ ቢሆንም ምክንያታዊነታቸው በገሃድ የወጡና ህብረተሰቡ የሚያውቃቸው ናቸው ወይ ብሎ ማየቱ ተገቢነት አለው ፡፡ ከዚህ አንጻር ተዛማጅነት የሌላቸው ከነጻ ገበያ መርህ ጋር የማይዛመዱ አንድ የሆነ አካል በፈለገ ጊዜ ብቻ ብር እየጨመረ ብትፈልግ ክፈል ከሚል ስሜት ሳይሆን ምንድነው የኢኮኖሚዟል፡፡ የውድድሩን ስርዓት ጤናማ ያደርገዋል ወይ፤ ራሱን የቻለ ስርዓት የለውም ወይ ነጻ ገበያ ስንል ፤ብሎ መፈተሸ አለበት ፡፡ ይህ አካሔድ ተገቢነት አለው ብለን እናምናለን ፡፡ በዚህም ት/ቢሮ በናሙና የተመረጡ ት/ቤቶችን የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ ሞክሯል ፡፡ በዚህም ህበረተሰቡ እያቀረበ ያለው ቅሬታ መነሻ ምንድነው የሚለው ተለይቷል ፡፡ በተደረገው ጥናት የግል ት/ቤቶች ባለሃብቶችም፣ የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ፣ የአስተዳደሩ ንግድ ቢሮ የተሳተፉበት ስራዎች ተሰርቷል ፡፡ የግል ት/ቤቶቹ የአከፋፈል ሁኔታ በአግባቡ ያልተኬደበት ሁኔታ አለ ፡፡ ወጥ የሆነ የክፍያ ስርዓት የለም ፡፡ በብሮሹር ይሄ ክፍያ ተወስኖብሃል፤ በሚቀጥለው ዓመት ልጅህን የምታስተምር ከሆነ ይህንን እንድትከፍል ወይም በስልክ በቴክስት መልዕክት በመላክ ወይም የትምህርት ማጠናቀቂያ ጊዜ ላይ በምትደረግ ትንሽ ውይይት ላይ ያገኙትን ውጤት በመናገር ፣ የተሰሩትን ስራዎች በማስተዋወቅ ይህንን ት/ ቤት የምትፈልጉ ከሆነ ይህንን ያህል ገንዘብ ያስጨምሯችኋል እንድታውቁት የሚል ነገር ነው ያለው ፡፡ነገር ግን ከሚልኩት ማስታወሻ ጋር ፈቃደኝነታቸውና ስምምነታቸው የሚረጋገጥበት የሁለትዮሽ ውይይት የለም ፡፡ ቢሮው ይህ አሰራር መስተካከል አለበት ብሎ ያምናል ፡፡ አጽንኦት ሰጥቶ የማስተካከያ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ፡፡ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሚሆን አማራጭ ት/ ቤት ችግር ከሌለ፣ በመንግስትና በግል ት/ቤቶች መካከል ተመሳሳይ የማስተማሪያ ካሪኩለም እና መመዘኛ ካለ ይህንኑ ሁሉም ት/ቤቶች በተመሳሳይ ሁኔታ ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ ከግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የሚነሳው አለመግባባት ለምን ይከሰታል ? አቶ ማስረሻ ፡- በት/ቤቶች መካከል ሊኖር የሚገባው ልዩነት ብዙ እና ትንሽ በማስከፈል ሳይሆን ተማሪዎች በእውቀት ፣ በክህሎት በአመለካከት ተለውጠዋል ወይ የሚለውን
  • 9. 5ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 ማሳየት ነው ፡፡ የትምህርት የመጨረሻው ግብ የባህሪይ ለውጥ ማምጣት ነው ስንል ደግሞ ምናልባትም እንደ ውጤት ሊሆን የሚችለው በስራ ዓለም ውስጥ ውጤታማ የሆነ ሰው መፍጠር መቻላችን ነው ፡፡ በት/ቤት ቆይታ ውስጥ በስነ- ምግባር እየተሸሻለ በአእምሮ የዳበረ፣ በዕውቀት ጎለበተ ልጅ መቅረጽ ማለት ነው ፡፡ ኃላፊነት የሚሰማው በምክንያት የሚያምን ሁለንተናዊ ስብዕና ያለው የተሟላ ዜጋ ለመፍጠር የሚያስችል ማለት ነው ፡፡ ይህ በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ጥቂት ት/ቤቶች የውጪ ሃገር ዜጎችን የት/ቤት መግቢያ በር ላይ በማቆም የወላጆችን አስተሳሰብ በመቀየር ገንዘብ የመሰብሰቢያ አማራጭ የማድረግ ሁኔታ ይታያል ፡፡ እውነታው ግን ይሄ አይደለም ፡ ፡ የተሸለ ሾል እየሰሩ ያሉት ውጤታማ የሆኑ በሃገራችን የተለያዩ ሚዲያዎች የፕሮግራም ሽፋን የተሰጣቸው በገጠር ተወልደው እዚያው ተምረው የመጡ ዩኒቨርሲቲ በጥሩ ውጤት ያለፉ ራዕይ ያላቸው ተማሪዎች ማፍራታችን ልብ ሊባል ይገባል ፡፡ እንደዚህ ያሉ ነገሮች ከህብረተሰቡ ጋር ጤናማ የንግድ ውድድር ይኖራቸዋል የሚል ስሜት የለኝም ፡ ፡ የሚመለከተው አካል በእርግጥ የንግዱን ስርዓት ይከታተላል ፡፡ ነገር ግን ስርዓቱ ጤናማ እንዲሆን ከተፈለገ እውነታውን በማሳየት ወላጅ በአገልግሎቱ ረክቶ ከሆነ ቀድሞውንም ቅሬታ ያቀርባል የሚል እምነት የለኝም ፡፡ የትምህርት አገልግሎቱ እና እየከፈልኩት ያለው የትምህርት ክፍያ ተገቢ ነወይ በሚል ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል በአገልግሎት ፈላጊና በአገልግሎት ሰጪ የጋራ ውይይት መደረግ አለበት ፡፡ ግልጽነት ሊኖር ይገባል፡፡ በቅርቡ የተለያዩ ሚዲያዎች እንደተገለጸውም የፌዴራል ንግድ ውድድር እና ሸማቾች ባለስልጣን ጤናማ የሆነ ውድድር በማይፈጥሩ እና ህብረተሰቡን ባልተገባ መንገድ ክፍያ ያስከፍላሉ ብሎ የያዛቸው ቀላል የማይባሉ ወደ 190 አካባቢ የሚደርሱ ት/ቤቶች መረጃዎችን እስከ 3 ወር ከፈተሸ በኋላ ከት/ቢሮ ጋር በጋራ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል ፡፡ ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠው ዋጋው ስለጨመረ ብቻ የተከሰሰ ት/ቤት አይደለም ፡፡ አማራጩን ህበረተሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀም ያላደረጉበት ሂደት ነው የተከሰተው ፡፡ ቆም ብለው እንዲያስቡ ከማለት አንጻር ነው ፡ ፡ ይሄ ከተስተካከለ አሁን በህብረተሰቡ እየተሰማ ያለው ቅሬታ በሂደት ሊከስም ይችላል ፡፡ የግል ት/ቤቶች በትምህርት ይዘታቸው ደረጃ እንደሚወጣላቸው ይነገራል እውነት ነው? ይህ ከሆነ ደረጃው ምን መሰረት አድረጎ ነው የሚሰጠው? ደረጃው በት/ቤቶች መካከል አላስፈላጊ ውድድር አያመጣም? አቶ ማስረሻ፡- ደረጃ የሚሰጣቸው ት/ቤቶች በይዘታቸው አይደለም የትምህርት ቤቶቹን ሰርተፊኬሽን ደረጃ ፍረጃ ወደ ተግባር የተገባው በ2005 ዓ.ም በኋላ ነው ከጥራት አንፃር የሚቀሩ ስራዎች ሲነሱ ይህንን የጥራት ችግር ለመቅረፍ ከሚያግዙ ስራዎች አንዱ ነው ተብሎ ታምኖበታል ፡፡ ውጤታማ እየሆነ ነውያለው ህብረተሰባችን የተሻለ ነገር የመጠየቅና የማወቅ ፍላጎት ስላለው የጥራት ጥያቄ ሁል ጊዜ ይነሳል፡ ፡ ይህንን ጥያቄ ለመመለሾ እንደ አገር አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ በ1999 ተቀርጾ 6 መርሃ ግብሮችን ይዞ ተግባራዊ እየተደረገ ነው ያለው፡፡ የኢኒስፔክሽን ሾል የሚያሳየው እነዚህ መርሃ ግብሮች መሬት ላይ ወርደው በምን አግባብ እየሄደ ነው፡፡ ት/ቤቶችስ ራሳቸውን እንዴት እያዩ ነው የሚሉትን ስራዎች በ26 ስታንዳርድ የመፈተሽ ሾል እየተሰራ ነው፡ ፡ ስለዚህ 26ቱ ስታንዳርድ ከግባዓት ከሂደት እና ከውጤት አንፃር ሲፈተሹ ደረጃ አንድ ላይና ደረጃ ሁለት ላይ የወደቁ ት/ቤቶች ተማሪዎቹን ት/ቤት በማቆየት ብቻ እንጂ ትምህርት እየሰጠ አይደለም ወደሚል ድምዳሜ ላይ ነው የሚያደርሰው፡፡ ተወዳዳሪ ዜጋ መፍጠር ያልቻለ ት/ቤት ብዙ ችግር አለበት መስተካከል አለበት ፡፡ ደረጃ3 እና ደረጃ4 ደግሞ ሞዴል መሆን የሚችሉ ት/ቤቶች ናቸው፡፡ ት/ቤቶቹ ከቲዩሪ ወይም ከንድፈ ሃሳብ በዘለለ የተግባር ትምህርት እየሰሩ መሆኑን ማወቅ የሚችሉበት መንገድ ያመቻችላቸዋል፡፡ ደረጃ ማለት ጉድለት እና ስኬት የሚያሳይ ማለት ነው፡፡ ደረጃ 1 እና 2 የሚገኙ ት/ቤቶች ያላሟሉት ነገር አላቸው ስለዚህ ማስጠንቀቂያ ነው የማንቂያ ደወል ነው፡ ፡ ደረጃ 3 ወደ ደረጃ 4 ለመሸጋገር የሚጎድልህ ነገር አለ የሚል ማንቂያ አለው፡፡ ደረጃ 4 ማለት ለሌሎች ሞዴል ተቋም ነው፡፡ ውድድር አይቆምም ሁል ጊዜ የተሻለ ሾል ውስጥ መግባት መቻል አለበት ከሚል እሳቤ ተነስቶ የተሰራ ሾል ነው፡፡ በተለይ አሁን የግል ት/ቤቶች በጭፍን ከመወዳደር ይልቅ ሳይንሳዊ በሆነ ፍተሻ እያለፉወይም ጤናማ እንዲያደርጉት አግዟቸዋል ብለን እናምናለን፡፡ ወላጆች ብዙ ብር በከፈሉ ቁጥር ጥራት ያለው ትምህርት ለልጆቻቸው እየተሰጠ ነው ብሎ መደምደም የለባቸውም፡፡ ደረጃና የዋጋ ተመን የሚያገናኛቸው ነገር የለም፡ ፡ ት/ቢሮ በዋጋ ተመን ሾል ላይ አይሰራም፡፡ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ት/ቤት ከተዘጋ በኋላ የማሻሻያ ክረምት ትምህርት መሰጠት በት/ቢሮ አሰራር ይፈቀዳል? አጋዥ (ሪፈረንስ መጽሐፍቶች) በግል ት/ቤቶች ቢዘጋጅ ት/ ቢሮው ይከለክላል ? አቶ ማስረሻ፡-የማጠናከሪያ ትምህርት በጥሬ ቃሉ የወሰድነው እንደሆነ ተማሪዎች በሁሉም ትምህርት እኩል የሆነ የመረዳት ግንዛቤ ላይኖራቸው ይችላል፡፡ አንዳንዱ ተማሪ በሳይንስ ትምህርት ጥሩ ውጤት ሲያስመዘግብ ሌላውያልቻለውን ጥሩ አረዳድ እንዲኖረው ለማድረግ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ሁሉንም የትምህርት አይነቶች በመደዳው በመስጠት መሆን የለበትም ፡፡ ይህ ችግር በክረምት ብቻ ሳይሆን በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ላይም ይታያል፡ ፡ ወላጆችም ልጄ አልባሌ ቦታ ከሚውል ት/ ቤት ቢውል እመርጣለሁ የሚሉት አግባብነት ይኖረዋል፡፡ ይህንን ስል በቀናነት ከት/ቤቶች ጋር ተግባብቶ የሚሰሩ ስራዎች የወላጆችን ቅሬታ አያመጣም ፡፡በግል ት/ቤቶች አልፎ አልፎ የሚታዩ ችግሮች የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት በሚል የመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም እያስተማሩ ይገኛሉ፡፡ ይህ ስህተት ነው ት/ ቤቶቹ የሚያደርጉት አንድ እና ሁለት ምዕራፍ በክረምት አስተምረው መስከረም ትምህርት መጀመሪያ ላይ ከምዕራፍ ሦስት የሚጀምሩ አሉ፡ ፡ ይሄ የተሳሳተ አሰራር ነው በት/ሚር የወረደው የትምህርት አካዳሚ የትምህርት ጊዜ ከመስከረም እስከ ሰኔ ያለው 10 ወራት ነውሁለቱ ወራቶች የእረፍት ጊዜያቶች ናቸው፡፡ ተማሪዎች፣ መምህራን ራሳቸውን በማሳረፍ ለቀጣይ ትምህርት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የሚደረግበት ጊዜ ነው፡፡ ሌላው ችግር ት/ቤቶቹ በክረምት አስተምረው ያልተማረውን ተማሪ በበጋው መማር አትችልም በማለት የመማር መብቱን የሚከለክሉበት አሰራር ነው፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡ አሁን ምናወጣው መመሪያ ይህንን ሁሉ የሚያስተካክል ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለመማር ማስተማር የሚጠቅሙ መጻሕፍት እና ማጣቀሻ ሪፈረንሶችን በጭራሽ አትስሩ ያልንበት ሁኔታ የለም ፡፡ ነገር ግን እንደ ት/ቢሮ እምነት ከትምህርት ጋር ያለ ህብረተሰብ ሁሌ ከማንበብ ጋር የተዛመደ እውቀትን በመፈለግ ላይ ያለ ነው ፡፡ ስለዚህ ጥሩ ነገሮች እንደሚፈጠሩ እናምናለን ፡፡ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች አድናቆትን ያተረፉ ስራዎች ከግል ት/ ቤቶች ተቋማት እያገኘን ነው ፡፡ እነዚህ ማጣቀሻ
  • 10. 6 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 ተ ምሳሌት መፅሔት ከግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጥያቄዎች የግል ት/ቤቶች ማህበር ዋና ጸሐፊ ከሆኑት አቶ ሰለሞን ገሰሰ ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ይዘን ቀርበናል፡፡ የግል ት/ቤቶች ማህበር ሁሉንም ት/ቤቶች ተደራሽ ያደርጋል? አቶ ሰለሞን ገሰሰ ፡- ከማንኛዉም የማህበሩ እንቅስቃሴና ዉጤት፤ ሁሉም የግል ትምህርት ሊባል በሚችል ተጠቃሚ ነው፡፡ነገር ግን ሁሉም የግል ት/ቤት የማህበሩ አባል አይደለም፡፡ ወደፊት በሂደት ሁሉም የግል ት/ቤት የማህበሩ አባል የማይሆንበት ምክንያት አይታየኝም ፡፡ የግድ መተባበር አለባቸዉ፡፡ የግል ት/ቤቶች ለአገሪቱ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ምንድን ነው ? አቶ ሰለሞን፡- ትምህርት የሁሉም ነገር መሰረት ነው ፡፡ ትምህርት ላይ በሃላፊነት ስሜት መስራት ሲቻል በየትኛውም መንገድ ለዉ ጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ የግል ት/ቤቶች ደግሞ ጥራት ላይ አድምተው የሚሰሩ ተቋማት ናቸው ፡፡ ከዚህ አንፃር ለሃገሪቱ ባለውለታዎች ናቸው ፡፡ ብዙ አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቀቁመዉ ተማሪዎቻቸዉን በጥሩ ሁኔታ እያነጹ ይገኛሉ ፡፡ ለምሳሌ በአገርአቀፍ ብሄራዊ ፈተናዎች ተማሪዎቻቸዉን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል በማሳለፍ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ ፡ ፡ ተማሪዎችን ከቀለም ትምህርት ባሻገር በስነ ምግባር በስራና በዘመናዊ ስተሳሰብ ኮትኩቶ በማሳደግ ነገ ኃላፊነትን ለመሸከም የሚችሉ ተማሪዎችን በማፍራት ረገድም የግል ት/ቤቶች ትልቅ አስተዋፅዎ አበርክተዋል ፡፡ ወደፊትም የተሻለ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በመንግስትና በግል ት/ቤቶች መካከል መሰረታዊ የሚባል ልዩነት አለ? አቶ ሰለሞን፡- አኔ አለ ብዬ ነው የማምነው ፡፡ ከአንድነታቸው ብጀምር አንድ አይነት ስርዓተ ትምህርት ይተገብራሉ ፣ በአንድ ወጥ ፖሊሲም ይመራሉ፤ ነገር ግን በጥራት ላይ ስንመጣ የግል ት/ቤቶች የተሻለ የጥራት ደረጃ አላቸው ብዬ አምናለሁ ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ብዙ አመልካች መገለጫዎች አሉት :: የግልት /ቤቶች በአስተዳደር ረገድ ጊዜያቸውንና የሰው ኃይላቸውን በአግባቡ ይጠቀማሉ፡፡ ያ ደግሞ በብዙ ችግሮች ውስጥ ሆነዉም የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ረድቷቸዋል ፡፡ ሃብትን በአግባቡ በመጠቀም ስራን እግር በእግር ተከታትሎ በመስራት ረገድ የግልት /ቤቶች የተለየ መገለጫቸው ነው ማለት ይቻላል ፡፡ ሌላው የግል ት/ቤቶች ከወላጆች ጋር በቅርበት ይሰራሉ ፡፡ ተማሪዎቻቸዉንም አግር በአግር ይከታተላሉ፡ ፡ትምህርት ቤቶችና ወላጆች አለት አለት ከመገናኘት ባሻገር በመደበኛ ፕሮግራም ቢያንስ በዓመት ለአራት ጊዜ ተገናኝተዉ በተሻለ የትምህርት አሰጣጥ ዙሪያ የሚመክሩበት በደካማም ሆነ ጠንካራ ጎናቸዉ የሚወያዩበት 10 ጥያቄዎች ለግል ት/ቤቶች ማሕበር መፅሐፎች በት/ቢሮ ሼ/ት/ዝ ባለሙያዎች ከስርዓተ ትምህርቱ ጋር ተዛማጅነት ስለመኖሩ ማረጋገጥ የግድ ነው፡፡ የግል ት/ቤቶች ያለ አንዳች የኢኮኖሚ መሰረት የዋጋ ጭማሪ አናደርግም የሚል አስተያየት አላቸው ት/ቢሮ የት/ቤቶቹን የዋጋ ጭማሪ ያለ አግባብ ነው ብሎ ያምናል? በሌሎች ዘርፎችስ ከሚደረገው እርዳታ አንፃር ት/ቤቶቹ እርዳታ አግኝተዋል? አቶ ማስረሻ፡-ቀደም ብሎ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በተደረገው የዳሰሳ ጥናት የግል ት/ቤቶች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ነበሩ እነዚህ ጥያቄዎች የት/ቤት ኪራይ አገልግሎት በየጊዜው መናር ሁለተኛ መምህራንን በክፍያ ለማቆየት የሚደረግ ነው ፡፡ሌሎች ተዛማጅነት ያላቸው የስቴሽነሪ መገልገያዎች የመጨመር ሁኔታ አለ የሚሉ ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡ በእርግጥ አንዳድ አሰራሮች በሂደት ሊስተካከሉ የሚችሉ ይመስለኛል በግሌ ሳየው በተለይም ከአከራይ ተከራይ ውል ጋር የሚጨመርበት አግባብ ሊፈተሽ የሚገባው ይመስለኛል፡፡ ሌላው የተቃረነ ነገር የምናየው ለመምህራን ስራቸውን እንዳይለቁ ማቆያ የሚከፈለውን ክፍያ በተመለከተ አንዳንድ መምህራኖች ት/ቢሮ ድረስ እየመጡ ሐምሌና ነሐሴን አናውቃቸውም ዞር በሉ እንባላለን በእኛ ስም ጭማሪ ተጨምሮ ነገር ግን ለእኛ የሚደርሰን አናገኝም የሚሉ ብሶቶች ይሰማሉ፡፡እንግዲህ ሚዛናዊነቱ የቱ ላይ ነው ብሎ ማየቱ ጥሩ ነው፡፡በእርግጥ ይህ ሚዛን የደፋ ክስ አቤቱታ ነው ብሎ ለማስቀመጥ ሳይሆን ችግሩን ያመለክታል ስለዚህ ከህብረተሰቡ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ መወያየቱ ተገቢነት ያለው ነው፡፡ እንደ ዜጋ ሁሉም በፈለገው ቦታና ት/ቤት ልጁን ማስተማር ይችላል፡፡ ነገር ግን በመንግስ ኃላፊነት ላይ ያሉ ባለስልጣኖች በአብዛኛው ማለት ይቻላል መንግስት ት/ቤት ልጁን ሲያስተምር አይታይም ለምን ይመስሎታል? እርሶዎ ልጅ ካልዎት ልጅዎ የት ይማራል? አቶ ማስረሻ፡-ዜጎች በተለያዩ ቦታዎች ያስተምራሉ ነገር ግን በዚህ ላይ በቂ መረጃ የለኝም እንግዲህ የግል አስተያየት ይመስለኛል እኛ የምናምነው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ትምህርት በፍታሃዊነት፣ በእኩልነት፣ ያለ አንዳች ልዩነት ማድረስ ነው፡፡ ከአቅርቦት አንፃር ሁሉንም ዜጎች ተደራሽ ማድረግ ነው የሚል ነው ፡፡ት/ቢሮ አሰራሩም ይሁንንመርህ የተከተለ ነው፡፡ ከዚህ ውጪየእገሌ ልጅ እዚህ ይማራል የእገሌ ልጅ እዛ የሚሉትን አስተያየቶች እኔ የግለሰቦች አስተያየት ነው ብዬ ነው የምወስደው፡፡ እናመሰግናለን ፡፡
  • 11. 7ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 የግንኙነት መድረክ አላቸው ፡፡ በእነዚህ ቀናት ወላጅና ፣ መምህሩ ከተማሪዉ ጋር በመሆን ተማሪዉ በነበረዉ የትምህርት ትጋት አንዲሁም ስነምግባር ዙሪያ በግልጽ ይመክራሉ ፡፡ ለልጆቹም መለወጥ የተናጠል ሃላፊነታቸዉን ይወስዳሉ፡፡የግል ት/ቤቶች በያንዳንዱ ተማሪ መሻሻልና ለዉጥ ላይ ክትትል ያደርጋሉ፡፡ የግል ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በየቀኑ የሚገናኙበት የግንኙነት መሾመር አላቸዉ፡ ፡ communication book የሚባል እለታዊ የመረጃ መለዋወጫ መፅሐፍ አላቸዉ ፡፡ ይህ በብዙ የግል ት/ቤቶች የተለመደ አሰራር ነው ፡ ፡ ሌላዉ የግል ት/ቤቶች ምናልባትም ከመንግስት ት/ቤቶች በተሻለ ስርዓተ-ትምህርቱን በየጊዜው ለማበልጸግ ቅርብ ናቸዉ፡፡ በክበባትና በቤተ ሙከራ እንቅስቃሴዎችም የግል ተቋማት የተሻለ የሚንቀሳቀሱ ይመስለኛል። መንግስት ለግል ት/ቤቶች የሚያደርገው የተለየ ድጋፍ አለ ? አቶ ሰለሞን ፡- ቴክኒካላዊ የሆኑ እገዛዎች አሉ ፡፡ መንግስትያስቀመጠውንስታንዳርድለሟሟላትና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የግል ት/ ቤቶችን የሚያግዙ ፤ መንግስት ያሰማራቸው ሱፐርቫይዘሮች አሉ፡፡ እነዚህ ሱፐርቫይዘሮች ዋና ስራቸው ትምህርት ቤቶችን ማገዝና መርዳት ነው ፡፡ ሱፐርቫይዘሮች ተመድበው ት/ቤቶች ጥራትና ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ አግባብና ስርአት ባለው መልኩ ሲከናወን ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ ፡፡ ነገርግንከመሬትአቅርቦት፣ከፋይናንስአቅርቦትና ከቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚነት አንጻር ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ድጋፍ በአሁን ሰአት የለም ፡፡ አቅም ያደረጁ የግል ት/ቤቶች ቁጥራቸው ትንሽ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ የግል ት/ቤቶች አቅማቸው ውስን ነው ፡፡ይሁንና በብዙ ችግሮች ውስጥ እያለፉም ባላቸው ውስን አቅም ድንቅ ሾል እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ መንግስት ተጨማሪ ድጋፍ እንደ ሌሎች ሴክተሮች ለግል ት/ቤቶች ቢያደርግላቸው ምን ሊሰሩ እንደሚችሉ መገመት አያቅትም፡ ፡ በአጠቃላይ መንግስት ፊቱን ወደ ግል ት/ ቤቶች በማዞር ከመሬት አቅርቦት፡ ከፋይናንስ አቅርቦት፡ ከቀረጥ ነጻ መብት መፍቀድና ሌሎች መሰረታዊ እገዛዎችን ሊያደርግላቸው ይገባል፡፡ ይህም የዋጋና የጥራት ተፎካካሪነትን ይጋብዛል፡ ፡ በዋና ከተሞች የተወሰነውም የግል ት/ቤቶች ስርጭት በክልሎች እንዲስፋፋ ትልቅና ታሪካዊ አስተዋጽዎ ያበረክታል፡፡ ከዚህ በፊት ለግል ትምህርት ተቋማት ያልተሰጡ እንደ መጽሐፍ ማሳተም የመሳሰሉ ስራዎች በት/ቢሮ ድጋፍ እየተደረገላችሁ እንደሆነ ነው የሚገለጸው ፡፡ ማህበራችሁም ጠንካራ እንዳልሆነ ይገለፃል ፡፡ የተለያዩ ጥያቄዎችን ከማቅረብ አንፃር ማህበሩ ክፍተት ይታይበታል የሚል አስተያየት አለ፡፡ እርስዎ ይህንን እንዴት ያዩታል ? አቶሰለሞን ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ስርዓተ ትምህርትን ስታስተገብር መጽሐፍ አሳትሞ ለመንግስትም ሆነ ለግል የትምህርት ተቋማት ማዳረስ የመንግስት ሃላፊነት ነው፡፡ በእኛ ሃገር ስርአተ ትምህርትን የግል ተቋማት እንዲያወጡም ሆነ እንዲያሻሻሽሉ አይፈቀድም፡፡ ስርዓተ ትምህርት ይተግበር ብለህ ደግሞ መሳሪያው/ የመማሪያ መጽሀፍ የለም ካልክ ሁለቱ አንድ ላይ አይሄዱም ፡፡ ያም ሆኖ ማህበራችን ትምህርት ቤቶችን አስቸግሮ የመማሪያ መፃሕፍትን ያሳተመበት ወቅትም ነበር፡፡ ከፍተኛ እጥረት በነበረበት በተለይም አንድ መፅሐፍ በ150 እና በ200 ብር በነጋዴ በሚሸጥበት ወቅት ገበያውን ሰብሮ ገብቶ መጽሃፍ በማሳተምና ለግል ት/ቤቶች በዋጋው በማሰራጨት ማህበሩ ዋጋን የማረጋጋት ሾል የሰራበት ጊዜም ነበር፡፡ ከዚህ ውጪ ማህበሩ መጠናከር አለበት ፤ አዎ መጠናከር አለበት፡ ፡ ተጠናክሮ የተለያዩ ጥያቄዎችን ለመንግስት ማቅረብ አለበት ፡፡ ማህበሩ ከሰራቸው በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ ችግሮችን/ቀውሶችን ስርዓት ለማስያዝ ብዙ ጊዜ አጥፍቷል ፡፡ ይህም ሆኖ ደረጃ ማህበሩ ተጠናክሮና ከመንግስት ጋር ተቀራርቦ ሊሰራ ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ የግል ት/ቤቶች በተሻለ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እንዲሁም ሃገርንና ህብረተሰብን ለመጥቀም ሁሉም የማህበሩ አባልና በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ተሳታፊ ሊሆን ይገባል፡፡ መንግስትም ማህበሩ እንዲጠናከር ማገዝ ያለበት ይመስለኛል፡፡ በቅርቡ ወደ ተከሰተው ጉዳይ ልምጣና የግል ትቤቶች በተጠቃሚው ላይ በተደጋጋሚ የክፍያ ዋጋ እየጨመሩ ነው በሚል የአ/አ ት/ቢሮ እና የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን በጋራ አጥንተናል የሚሉት አንድ ጥናት ነበር ፡ ፡ የግል ት/ቤቶች ማህበሩም እንደተሳተፍበትም ይናገራሉ በዚህም መሰረት ከ194 በላይ ለሆኑ ት/ ቤቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል ይህንን ምን ያህል ታውቃላችሁ? አብራችሁ ሰርታችኋል ? አቶ ሰለሞን፡- እንግዲህ አይነት ማስጠንቀቂያ ላይ እኛ የለንበትም:: በዚህ ረገድ የግል ት/ቤቶችን ማስጠንቀቂያ የሚያሰጣቸው ምንም አይነት ጥፋትም ሆነ ወንጀል ፈጽመዋል ብዬ ለመቀበል ይከብደኛል ፡፡ ነገር ግን ከወላጆች በኩል አንዳንድ ጥያቄዎች አሉ ከተባለ መምከሩ ተገቢ ነው ፡፡ ከዚህ አንፃር በዳሰሳ ጥናቱ ጅማሬ ላይ ተሳትፈን ፡፡ ነገር ግን ጥናቱ ብዙ ግድፈቶች ነበሩበት፡ ፡ አቀራረቡም ተገቢ አልነበረም፡፡ ሲጀመር ከ1500 በላይ የግል ትምህርት ቤቶች ባሉበት ከተማ ውስጥ 16 ት/ቤቶችን ብቻ በናሙናነት መውሰድ ትክክለኛውን ምስል ለማየት ይገድባል፡ ፡ ይሔ በፐርሰንት ብታወጣው ምንያህል ነው? ሁለተኛ እነዚህ ት/ቤቶች ደግሞ የተሻለ ገቢ
  • 12. 8 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 ያለውን የህብረተሰብ ክፍል የሚያስተናግዱ ናቸው፡፡ ይህ ምን ያህል ገላጭ ነው ፡፡ ያም ሆኖ በአማካኝ የመጣው ከ70-150 ብር ወርሃዊ ጭማሪ ነው የተደረገው ፡፡ ለእኔ ግን መሰረታዊው ነገር በሃገራችን የትምህርት ክፍያ ጭማሬን የሚከለክል ወይም የሚገድብ ህግ አለ ወይ እስከማውቀው ድረስ የለም፡፡ It’s just a free market. የግል ት/ቤቶች የቤት ኪራይ አለባቸው ፣ በየዓመቱ የደሞዝ ጭማሪ ለመምህራንና ሰራተኞች ያደርጋሉ፡፡ሲልም ሰራተኛ በሚለቅበት ሰአት በአመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ጭማሬ ለማድረግ ይገደዳሉ፡፡ አስር ወር አስተምረውና ገንዘብ ሰብስበው አስራ ሁለት ወር ደሞዝ፤የቤት ኪራይና ሌሎች በርካታ ወጪዎችን መሸፈን ግዴታቸው ነው፡፡ መሰረታዊ የሆነው ነገር ት/ቤቶች አድመው ጭማሪ አድርገዋል ወይ የሚል ነው ፡፡ በዚህ ሁኔታ በአድማና በመመካከር በመወሰን፤ በማሴር ዋጋ የጨመሩ ሁለት ት/ቤቶች እንኳን ፈፅሞ ማግኘት አይቻልም፡፡ አንዱ ከአንዱ በማንኛውም ሁኔታ ተወዳዳሪና ተፎካካሪ ነው፡፡ በየዓመቱ ትምህርት ቤቶችኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖራቸውይጨምራሉ ፡፡ ይሄ መቼ ይቆማል ሲሉም የሚጠይቁ አሉ በዚህ ጉዳይ ላይ እርስዎ ምን ይላሉ ? አቶ ሰለሞን ፡- ይህ ጥያቄ ለእኔ መሰረታዊ አይመስለኝም:: ምክንያቱም መንግስት ለህብረተሰቡ ትምህርትን በነፃ አቅርቧል፡፡ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የለም ቢባል እንኳን ማንኛውም ት/ቤት የራሱና በራሱ ልክ የተሰፋ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ምክኒያቶች አሉት፡፡ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች የሉም ብሎ በዚህ ሰአት መናገርም የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ ወላጅ ይህ አማራጭ በግልፅ ተቀምጦለታል ፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ የግል ት/ቤቶችን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይደለም ፡፡ የዋጋ ግሽበትን ጨምሮ በርካታ የኢኮኖሚ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል ፡፡ የኢኮኖሚ ምክንያት እኮ ባለሙያ ባልሆንም የተለያየ ነው፡፡ ለአንዱ የኢኮኖሚ ምክንያት የሆነው ለሌላው ላይሆን ይችላል ፡፡ ት/ቤቶቹ በራሳቸው የውስጥ አሰራር የኢኮኖሚ ምክንያት ይኖራቸዋል፡፡ አንድ ት/ቤት የዋጋ ጭማሪ በማያደርግበት አጋጣሚ እንኳን ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ሆኖለት ነው ማለት አይደለም ፡፡ የሚገጥሙትን ችግሮች ተቋቁሞ ነው፡፡ እንደነዚህ አይነት ትምህርት ቤቶችን የበለጠ ማበረታታት ያስፈልጋል ፡፡ በየዓመቱ የሚታየው ዋጋ ንረት ግልፅ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ባሉበት የግል ት/ቤቶች ላይ ጣትን መቀሰር ተገቢ አይደለም፡፡ ያም ሆኖ የግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሬ ሲያደርጉ ከሞራል አኳያ የሚያስተምሩትን የህብረተሰብ ክፍል አቅም ከግንዛቤ ቢያስገቡ ከሃገራዊ ሃላፊነቶቻቸው አንዱን የመወጣት ያህል ይሰማኛል፡፡ ለዚህም ሞራላዊ ቅስቀሳና አስተምህሮ እንጂ ቁጣና ሃይለ ቃል ሊሆን በፍጹም አይገባም፡፡ ት/ቤቶች ተስፋ እንዲቆርጡ ሳይሆን የበለጠ ለሃገራቸውና ለህዝባቸው ጠንክረው እንዲሰሩ ማበረታታት ያስፈልጋል፡፡ ለግል ት/ቤቶች ደረጃ የማውጣት አሰራር አለ የትምህርት ቤቶቹ ደረጃ በማህበረሰቡ መካከል የደረጃ ፍረጃ ልዩነት እንዲፈጠር ተፅዕኖ አያደርግም ?ከዚህ አንፃር ማህበሩ ያለው አቋም ምንድን ነው? አቶ ሰለሞን፡- ደረጃ ማውጣቱ ችግር ያለው አይመስለኝም፡፡ችግር ሊሆን የሚችለው ደረጃውን ተከትሎ አንድ ት/ቤት ይህንን ያህል ክፍያ ማስከፈል አለበት የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡የደረጃ ማውጣት ግቡ፤ ለህብረተሰቡ መረጃ ከማቅረብ የዘለለ መሆን የለበትም፡፡ ውሳኔ ሁልጊዜም ለወላጅ ሊተው ይገባል፡፡ነገር ግን በማህበር ደረጃ ተመክሮበት የተሰራ ሾል የለም ፡፡ ስታንዳርድ መውጣት አለበት በሚል የሄድንበት ነገር የለም ፡፡ የደረጃ ማውጣት ጉዳይ የወላጅ ቢሆን የተሻለ ነው የሚል እምነት አለኝ ፡፡ ወላጅ ከፋሲሊቲ፤ ከሂደትና ከውጤት አንጻር የት/ቤቱ ታሪክና ወቅታዊ ሁኔታ ፈቲሾና የራሱን ደረጃ አውጥቶ ነው ወደ ት/ቤቶች ልጆቹን የሚልከው፡ ፡ ይበለጥ ግን መንግስት ቀደም ሲል ሲያደርግ እንደነበረው ት/ቤቶችን በሱፐርቪዥን ፕሮግራሙ በማገዝ ት/ቤቶችን የማብቃት ሾል ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ሌላው በአለም አቀፍ ተቋማት አማካኝነት ለመንግስት ት/ቤቶች የሚደረጉ የመጽሃፍት፤ የኮምፒውተሮችና ሌሎች የቁሳቁስ ድጋፎች የግል ት/ቤቶችን በተወሰነ ደረጃ ቢያካትት ጥቅሙ ከግለሰብ ይልቅ ለሃገር ነው፡፡ የግልም ሆነ የመንግስት ት/ቤቶች የሚቀርጹትና የሚያወጡት አንድ አይነት ዜጋ ነው፡፡ ከክረምት ትምህርት ጋር የሚነሳ ጥያቄ አለ የግል ትምህርት ተቋሞች የመደበኛውን ትምህርት በክረምት ያስተምራሉ እንደውም አንድ እና ሁለት ቻፕተር ድረስ ያስተምራሉ፣ ክረምት ያልተማረ ተማሪ በበጋ አይማርም፣ ጎበዝ ተማሪ በክረምት እንዲማር ይደረጋል፣ ገንዘብ ለመሰብሰቢያ የሚጠቀሙበት ነው የሚሉ አስተያየቶች ይነሳሉ ይህንን እርስዎ እንዴት ያዩታል? አቶ ሰለሞን ፡- በክረምት ትምህርት ሲጀምር ጎበዝ ሰነፍ፣ አጭር ረጅም ይማር ብሎ ማስቀመጥ ተገቢ አይደለም ፡፡ መሰረታዊ ሃሳቡ መማር የፈለገ ይማር ነው ፡፡ በክረምት የሚማሩ ተማሪዎች በየትኛውም ቦታ የሚማሩት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ነው ፡፡ ተማሪዎች በዚህ ሰዓት እቤታቸው ቢቀመጡ ምናልባትም በእንቅልፍ ነው የሚያሳልፉት ፡፡ ነገር ግን ንቁ ሆነው በጠዋት ሄደው ት/ቤት ቆይተው ቢመለሱ ያቺን አጭር ሰአት የተሻለ እውቀት ይገበያሉ ፡፡ በክረምት ፕሮግራም የሚሰጠው ትምህርት ከማጠናከሪያነቱ ባሻገር የማዝናናት ተፈጥሮ ያለው ነው፡፡ የተለያዩ የታቀዱ የሙዚቃ፤የስፖርት ውድድሮች፣ ጨዋታዎች ትምህርቱን ያጅባሉ፡ ፡ ትምህርቱም ቢሆን ልጆቹ ለቀጣይ ዓመት ትምህርታቸው እንዲዘጋጁ ያደርጋቸዋል ፡፡ ደከም ያሉበት ትምህርት ካለም እንዲያሻሽሉ እድሉን ያገኛሉ፡፡ ጎበዝ ተማሪ ለምን በክረምት ይማራል የሚለው አስተሳሰብ ግን አይገባኝም ፡፡ የክረምት ትምህርት ተማሪዎች የተለያዩ ክህሎቶችን እንዲለማመዱ ይረዳል ፡፡ ጎበዝ ተማሪም ቢሆን እየተዝዝናና የተለያዩ ክህሎቶችን እየቀሰመ ለሚቀጥለው የትምህርት ጊዜ ቢዘጋጅ ምንም ችግር የለውም ፡፡ የክረምት ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎችን ያስገድዳሉ የሚባለው አነጋገር ስህተት ይመስለኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ወላጆች ትምህርት ቤት ከተዘጋ በኋላ ልጆቻቸውን ዘመድ ጋር ክ/ሀገርም ጭምር የሚልኩ አሉ እንዴት ተደርጎ ነው ት/ቤቶቹ ክረምት ካልተማረ ብለው የሚያስገድዱት፡፡ ይህ ተደርጎም ከሆነ ትክክል አይደለም ፡፡እንደዚሁ የመደበኛውን ትምህርት በክረምት ይጀምራሉ የሚባሉ ት/ቤቶች ካሉ ስህተት ሆኖ ይታየኛል ፡፡ ያም ሆኖ ከግንዛቤ ችግር ካልሆነ በክፋት አልወስደውም፡፡ ት/ቤቶች እርስ በርሳቸው ወይም ከመንግስት አካላት ጋር በሚያደርጓቸው ግንኙነቶች የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ማህበሩ ያለው ተሳትፎ ምን ያህል ነው ? አቶ ሰለሞን ፡- ከጥቂት ዓመታት በፊት በት/ቤቶች መካከልም ሆነ ከፍቃድ ሰጪ መ/ቤቶች ጋር የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ከማህበሩ ኮሚቴ ተቋቁሞ በወረዳና በክ/ከተማ ድረስ በመሄድ የማስማማትና የማግባባት ሾል ሲሰል ቆይቷል፡፡
  • 13. 9ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 ጂ ቱ አለሙ ዲሪብሳ የቤተሰብ አካዳሚ ተማሪ ነች፡፡ ጂቱ አንድ ብሎ ሁለት ያለውን የትምህርት ቤት ዳዴዋን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በጥሩ ውጤት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ተቃርባለች፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ደጃፍ ላይ ቆማ ብዙ ታስባለች፤ አብዝታም ትጥራለች ይህ ጥረቷ ታዲያ በተለይ በሳይንስ ትምህርቶች እጅጉን ውጤታማ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ ጂቱ ትላለች “የሳይንስ ትምህርቶችን ከልቤ እወዳለሁ በዚህኛው ዘመናዊ ዓለም ደግሞ ማንኛውም ነገር እውን የሚሆነው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ነው፡፡” ይህ የሳይንስ ትምህርት ፍቅሯ ዛሬ ላገኘችው እድል በር ከፋች ሆኗል፡ ፡ ሴቶችን በሳይንስ /Women in science/ ከመላው አፍሪካና አሜሪካ ለተገኙ በሳይንስ የትምህርት ዓይነቶች ጥሩ ውጤት ላላቸው ሴት ተማሪዎች በክረምት ወራት የሚሰጥ ስልጠና ነው ፡፡ የስልጠናው መጠሪያ በአጭሩ ዊስ ካምፕ (Wisci Camp) ይባላል ፡፡ ይህ ስልጠና ሴቶች በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ክህሎት እንዲያዳብሩ አቅማቸውን የሚያሳድግ ስልጠና ነው፡፡ ስልጠናው ለ25 ቀናት በሩዋንዳ በሚገኘው በጋሻራ የልጃገረዶች አካዳሚ ይሰጣል፡፡ ሴት ተማሪዎች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በአርት፣ በዲዛይን እና በሒሳብ ዘርፎች ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ስልጠናው እድል ይሰጣል፡፡ ሴት ተማሪዎቹ አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አሸኛኘት ሲደረግላቸው በስፍራው የተገኙት የአሜሪካ የዓለም አቀፍ አጋርነት ምክትል ልዩ ተወካይ ቶማስ ዲባስ ይህ በተለያዩ አካላት ትብብር የሚዘጋጀው ስልጠና ሴት ተማሪዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች እውቀት እንዲጨብጡና ክህሎታቸውንም እንዲያሳድጉ እድል ይፈጥራል ፡፡ ከስልጠናው በኋላ ሴት ተማሪዎችም ለዓለም ኢኮኖሚ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ቀላል አይሆንም ብለዋል፡፡ የዊስ ካምፕ ስልጠና በአሜሪካ መንግስት፣ በማይክሮ ሶፍት፣ በኢንቴል ኩባንያ፣ በአፍሪካ ሊደርሽፕ አካዳሚና ሌሎችም አካላት ትብብር የሚዘጋጅ ነው፡፡ ለሦስት ሳምንታት በሚቆየው ስልጠና የኮምፒውተር ሳይንስ፣ የሮቦት ቴክኖሎጂ፣ የዲዛይን፣ የአርት፣ የባህልና የፈጠራ ክህሎት የሚሰጥ ሲሆን ተማሪዎቹ በቡድን በመሆን ትናንሽ ፕሮጀክቶችን ይሰራሉ፤ በአመራር፣ የገበያ ጥናትና በተለያዩ አነቃቂ ስልጠናዎችን ያገኛሉ ተብሏል፡ ፡ ጂቱ ስልጠናውን ለመውሰድ ከአፍሪካ ሊደርሽፕ አካዳሚ ከኤስ ኦ ኤስና ከልደታ ካቶሊክ ከተገኙ ሌሎች 12 ሴት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጋር ወደ ሩዋንዳ ሄዳለች፡፡ በሩዋንዳው ጋሸራ የልጃገረዶች አካዳሚ ከጋና፣ ኬኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ዩጋንዳና አሜሪካ ከተገኙ ሌሎች ሴቶች ጋር ቁጥራቸው 120 ይደርሳሉ፡፡ ህሊና ታመነ እና በአምላክ ታደሰም ከጂቱ ጋር ከሩዋንዳ ስልጠና ሲመለሹ አገሪቱ በሳይንሱ ዘርፍ ለሰጠችው ትኩረት ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው እርግጠኛ ሆነው ይናገራሉ፡፡ የነገ ዛሬዎችፎቶአ.አአሜሪካኤምባሲ
  • 14. 10 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 ከ ፒያሳ የተነሣው ‘ሃይገር ባስ’ መገናኛ ተሳፋሪ ሊያወርድ ቁሟል። መገናኛ ላይ ለውዝ የሚያዞሩ ልጆች አሉ። ባትፈቅድም አስገድደውና ይሉኝታ(“ሼም”) አስይዘው ያስገዙኻል። ከአዟሪዎች አንዱ ወደ ተሳፈርንበት ‘ሃይገር’ ገብቶ ሦስትና አራት ፍሬ ለውዞች በየሰው እጅ እያስቀመጠ ሁሉንም አዳረሰ። እጅህ የሆነ ነገር ይዞ ልትቀበለው ካልቻልክ ለውዙን የሸሚዝ ኪስህ ውስጥ ጨምሮት ያልፋል። አጠገቤ የተቀመጠው ልጅ ለነገሩ እንግዳ ስለሆነ ተደናግሯል። አንዴ ለውዝ ሻጩን፣ ከዛም እጁ ላይ ያለውን ለውዝ፣ መጨረሻ እኔን አፈራርቆ ተመለከተ። ሻጩ ኋላ ደርሶ ሲመለሾ ለቅምሻ እጃቸው ላይ ላስቀመጠላቸው ሁሉ በወረቀት የተጠቀለለ ለውዝ ጣል ጣል አደረገላቸው። “ምንድን ነው? ምን ላድርገው?” ከጎኔ የተቀመጠው ልጅ እንደተደናገረነው። “የሃይገር ቁርስ ነው! እዚህ በቁርስ እየተንከባከቡ ነው የሚያደርሱህ” አልኩት ሳቄ ከንፈሬ ላይ ተንጠልጥሎ። “እንዴ!? እውነትክን ነው?” ልክ ቁርሱ መጥቶ ቡናው እንደዘገየበት ሱሰኛ ፊትና ኋላ ተገላምጦ ረከቦት የተዘረጋበትን ቦታ ማፈላለግ ጀመረ። ሳቅአፈነኝ። ሻጩ ‘ሃይገሯ’ን እንደታቦት ንግሥ ለሦስተኛ ጊዜ ዞራት። አሁን ገንዘቡን እየለቀመነው። ወንበር የተጋራኝ ልጅ በእጁ ጭብጥብጥ አድረጎ የያዛትን የመጓጓዣ ገንዘቡን ቆጠራት-አራት ብር። “እህ!? ምን… ማለቴ…ምን ማለት ነው? እንዴት?” ሳልፈልግ… በሻጩ መገደዱ አሞታል። “አልበላኸውም አይደል? መመለሾ ትችላለህ እኮ!” “አስገደዱኝ አይደል እንዴ? አስገደዱኝ እኮ!” “አልፈልግም አታስገድዱኝ! በል እያልኩህ ነው ሰውዬ” “አታይም!? ሰው ሁሉ ከፈለኮ!” “አንተ ግን ካልፈለከው አለመክፈል ትችላለህ” “ሼም ይሆንብኛላ!!” “እንግዲህ ወይ ሼምህን ወይ ብርህን አትርፍ” አበሳጨኝና መጽሐፌን ገልጬ ለማንበብ ሞከርኩ። “ይኼውልህ ወንድሜ… ቢኖረኝ እኮ…” “ለምን ድምፅህን ለኔ ብቻ እንዲሰማ ትቀንሰዋለህ? ለቀቅ አድርገውና ሻጩ ሰምቶ ይራራልህ ይሆናል።” ልጁን ማንቃት ከበደኝ፡፡ ልክ ማይምነትን ለማስወገድ የዕድገት በሕብረት ዘመቻ የዘመትኩ ነው የመሰለኝ። ስንቱን ፈርተን እንኖራለን? አንድ ወይም ሁለት ብር ከፍዬ ልላቀቀው ፈለኩግን እንዲህ ዓይነቱ ሰው ነገም ‘ሼም’ን ፈርቶ ሌላውን ማስቸገሩ አይቀርም። ኤጭ ምነው እቴ!? “ለምን መብትህን ታስደፈጥጣለህ? አይሆንም አልከፍልም አትልም? ምን ይመጣብኻል?” አንድ ወደ ጎልማሳነት በመገሥገሥ ላይ ያለ ወጣት ንግግራችንን ሰምቶ ልጁን አደፋፈረው። ጎልማሳው በቲሸርት ላይሹራብ፣ በሹራብ ላይ ጠቆር ያለ ኮት ለብሷል። አውራ ጣቴን ቀስሬ ሐሳቡን “ላይክ” ማድረጌን አሳየሁት። “ይገርምሃል እኔ አልከፍልም አልኩ። አዳሜ ግን ‘ምናላት አንድ ብር… ሁለት ብር ናት እኮ!’ ብለው:: አንድ ብር ለነሱ ቀላል ነገር መሆኗን ነገሩኝ። ሃቁ ግን ‘ሼም’ ይዟቸው ነው እንጂ ሁለት ብር ለነሱም ቀላል አይደለም። እንደኔ ተጋፍቶና ቁሞ እየሔደ አንድ ብር ምናላ ትይለኛል!” አጠገቡ ያሉትን ወረፋቸው። ሻጩ እንደ ጥሩ አዛኝ እጃችንን ፈልቅቆ በጣቶቻችን ልክቆጥሮ ያዘጋጀውን የለውዝ ፍሬ ያስጨብጠናል። ያልታሰበ ሲሳይ መጣልኝ ብሎ ወደ አፉ ከላከሰው ኪስ ሁለት ብር ፈልቅቆ ይወስዳል። “…እንዴት ለሁለት ብር ብለህ አትጨቃጨቅ ትሉኛላችሁ? ሁለት ብር ቀላል ነገር ነው?...” ሰውዬው በነካ አፌ ብሎ ነው መሰል ብሶቱን ቀጠለ። “… አምና ከቤቴ ወጥቼ ከሻሼ ቁርስ ቤት አንድ ቆቆር(ፓስቲኒ) በሻይ አወራርጄ ነበር ሼል የምገባው። አሁን ግን አልሆነም። ምሟ ልሡ በአርከበ ሱቅ እየነገደች አንድ ፓስቲኒ ሦስት ብር ካልሆነ አልሸጥም አለች። ስለዚህ እሷጋ ስደርስ ፊቴን አዙሬ ባላየ ‘ሙድ’ አለፍኳት። ታዲያ ለምን ለምፈልገው ነገር ያላወጣሁትን እዚህ እንዳወጣ እገደዳለሁ?” ብሶቱን ሲዘረግፈው የብሶታቸው ድምፅ ማጉያ የሆነላቸው ሁሉ ፊታቸውን ኮስኩሰው(አጨፍግገው) ያዩታል። ሌሎች ደግሞ እነሱን የሚመለከት ጉዳይ ያነሣ አላስመሰሉትም። እንዲያውም “ምን ለአንድ ብር ያጨቃጭቀዋል?…” ይላሉ -በሹክሹክታ። “…የኑሮ ውድነትና ገበያው በየምክንያቱ ደፍጥጠው ደፍጥጠው ረብየለሽ ያደረጉትን ኑሮዬን እንደዚህ ዓይነት ጥቃቅን መንግሥታት ደግሞ ይኼው በየምክንያቱ ይደፈጥጡታል። ባይሆን ትንንሽ መንግሥት የሆኑብንን ተውን እንበላቸው እንጂ ጎበዝ!? አሁን ብዙዎቹ በድንጋጤ አፍጥጠው እየተመለከቱት ነው። “አህያውን ፈርቶ ዳውላውን! ሆነ ነገር። አቦ ከፍ ብለህ ጩህ! ብትችል ቤተመንግሥት አካባቢ” ለውዝ ሻጩ ብሩን ይዞ እየወረደ የተናገረው። የሃይገር ወጎች በ ወንድወሰን ውቤ
  • 15. 11ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 መግቢያ ‹‹ልጅያለውሰውሁሉልጁክፉንናበጎውንየሚለይበትን፣ንጉስናፈጣሪውን የሚለይበትን እውቀትን ለማግኘት፤ የንባብንና የጽህፈትና ትምህርት ያላስተማረ መቀጫውን 50 ብር እየከፈለ የመቀጫውን ገንዘብም ወደ ቤተ እምነት እያገባ ለነዳያን ምግብና ልብስ ይሆናል ፡፡ የንስሀ አባትም የሆንክ የንስሀ ልጆችህ ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ ምከር….ይህንን ሳትቀበል ሳታስተምር የቀረህ እንደሆነ ግን በሹመትህ ትቀጣለህ፡፡›› ይህ አዋጅ የዘመናዊ ትምህርት ጅማሮን ያበሰረ፣ የትኛውም ወላጅ ልጁን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልክ የሚመክር፣የሚገስጽ ካልሆነም የሚቀጣ ህግ የተቀመጠበት እ.አ.አ በ1921 ዓ.ም የወጣ አዋጅ ነበር ፡፡ አያሌው ሺበሺ / ማኅተመሥላሴ ወልደ መስቀል ዝክረ ነገር/ ብለው በጻፉት መጽሀፍ ላይ የተወሰደ ፡፡ ከሃይማኖት ንክኪ ነጻ የሆነና ዘመናዊውን ትምህርት በመላው ሀገሪቱ እንዲሰጥ ንግሥት ዘውዲቱ የአጤ ሚኒሊክን ፈር በመከተል የወጡት አዋጅም እንደሆነ ይነገራል፡፡ በ1908 እ.አ.አ አጤ ሚኒሊክ በስማቸው የተሰየመውን የመጀመሪያውን ዘመናዊ ትምህርት ቤት ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በትብብር መክፈታቸውም ይታወሳል ፡፡ በመንግስት ትምህርት ቤት የተጀመረው የትምህርት ስርዓትና አካሄዳችን በዘመናት ቆይታው የህዝብ ትምህርት ቤቶችን ከ1983 ወዲህ ደግሞ በርካታ የግል ትምህርት ቤቶችንና ተቋምትን ማፍራት ችሏል፡፡አሁንም በየአመቱ የትምህርት ቤቶቹ ቁጥር እያጨመረ መምጣቱን ማየት ይቻላል፡፡ ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ጎን ለጎን የግል ትምህርት ቤቶች እና ተቋማት ለሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት የኩላቸውን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ፡፡ የተምሳሌት የዝግጅት ክፍልም ትምህርት ዘርፍ በአገልግሎቱ መስክ ውስጥ ቢሆንም ከአንድ የአገልግሎት ዘርፍ ወይም ከሸቀጥ ሸመታ በተለየ የሚታይበት መንገድ ባለመኖሩ የትምህርቱ ዘርፍ ተገቢው ድጋፍ እየተደረገለት ነው ወይ ስትል ጥያቄ አንስታ ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ አፈላልጋለች፡፡ ለትምህርቱ ዘርፍ የሚደረግ ድጋፍ መንግስት በየዓመቱ የሚይዘውን የትምህርት በጀት ለመንግስት ትምህርት ቤቶች እንደየደረጃቸውና እንደየተማሪዎቻቸው ብዛት የሚያከፋፈል እንደሆነም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ይጠቁማል፡ ፡ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 41/4 መንግስት የጤና የትምህርት እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለህዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ሃብት ይመድባል ይላል ፡፡ይሁን እንጂ በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚታዩ የመጽሀፍት ፣ የቤተ ሙከራና የቁሳቁስ እጥረቶች እንዲሁም የመምህራን በጊዜው ያለመመደብ ክፍተቶች አሳሳቢ ችግሮች ሆነው ይታያሉ ፡፡ በተመሳሳይ ትምህርት ቢሮ ለግል ትምህርት ቤቶችም መጽሀፍት አሳትሞ እንደሚያከፋፍል ይገልጻል ፡፡ ሆኖም የግል ትምህርት ትምህርት በጥርስ መካከል በ አዲስ ፀጋዬ
  • 16. 12 ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 ቤቶቹ መንግስት ከመጽሀፍ እደላው ባሻገር መንግስት መሰረታዊ የሚባሉ እገዛዎችን እያደረገ አይደለም የሚል ስሜት አላቸው ፡፡ ለአብነት ያህል የመሬት አቅርቦት ፡- መንግስት መሰረታዊውን የመሬት አቅርቦት ለግል ትምህርት ቤቶቹ ለመስጠት ያሳየው ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ነገር የለም ይላሉ፡፡ የፋይናንስ ድጋፍ፡- መንግስት ለትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረኩ ነው ሲል ቢደመጥም በተለይ ለግል ትምህርት ቤቶች የፋይናንስ ድጋፍ በመስጠት አቅማቸውን የሚያጎለብቱበትን መንገድ እንዲፈጥሩ የሚያደርገው አስተዋጽኦ ዝቅተኛ ነው ሲል የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር በበኩሉ ይጠቅሳል፡፡ የቀረጥ ነጻ መብት፡- በዚህ መብትም ተጠቃሚ ያለመሆናቸውን የግል ት/ቤቶች ይገልጻሉ፡፡ እነዚህ መሰረታዊ ድጋፎች አለመኖራቸው ደግሞ በትምህርት ዘርፉ ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል፡፡ ትምህርት ኢንቨስትመንት ወይስ ሸመታ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በተለይም ብዙ ካፒታል በሚጠይቁ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ትኩረት አድርጎ ይንቀሳቀሳል፡ ፡ በማኑፋክቸሪንግ ፣በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ሰፋፊ እርሻዎችና ኢንዱስትሪ ፓርክ አልሚዎች በሁለት መልኩ ማበረታቻ ይደረግላቸዋል ይላል ፡፡ የመጀመሪያው ማበረታቻ ከቀረጥ ነጻ ዕቃዎችን እንዲያስገቡ /duty free/ ማድረግ ሲሆን በዚህ እድል ማሽነሪዎችን እስከ 100% ነጻ እንዲሁም የማሽኖቹን 15% የሚሆኑ መለዋወጫዎችን በነጻ ማስገባት ይችላሉ ፡ ፡ ሌላው የገቢ ግብር እፎይታ ጊዜ /tax holiday/ መስጠት ሲሆን እንደ ኢንቨስትመንቱ አይነትና እንደመገኛ ስፍራው ከሁለት እስከ አምስት አመት ሊሰጥ ይችላል፡፡ ከነዚህ ዘርፎች በተጨማሪም መንግስት የአገልግሎት ዘርፉ በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ይሸፈናል ብሎ ያምናል፡፡ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚሳተፉ የውጭ ባለሀብቶች ወደ ሀገር ሲገቡ የራሳቸውን ህንጻ እንዲገነቡ ይገደዳሉ ፤ ይህም በቀላሉ ኢንቨስትመንቱን ትተው እንዳይሄዱ የተወሰደ እርምጃ ነው ሲሉ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ይገልጻሉ ፡፡ እንደ ኮሚሽኑ ለትምህርት ቤቶች መገልገያ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በዝቅተኛ ቀረጥ በማስገባት መንግስት የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ይገልጻል ፡፡ ነገር ግን ለትምህርት ቤቶች በተለይም ለግል ትምህርት ቤቶች ተብሎ የተዘጋጀ የኢንቨስትመንት መሬትና የገቢ ግብር እፎይታ ጊዜ አለመኖሩን ያስቀምጣል፡፡ በኢንቨስትመንቱ ያን ያህልም ተጠቃሚ ያልሆነው የትምህርቱ ዘርፍ ወላጆች አገልግሎትን በገንዘባቸው የሚገዙበት፤ ትምህርት ቤቶች ደግሞ የሚያቀርቡ ሆነው በሸማችና በሸመታው ዘርፍ የሚዳኙበት አግባብ እንዳለ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን ይጠቁማል፡፡ በዚህ ዘርፍ ትምህርት ቤቶች የሚሰጡት የትምህርት ሁኔታ ወይም ትምህርቱ ጥራትን ሳይሆን የክፍያ ዋጋ ላይ ብቻ ቁጥጥር ይደረጋል፡፡ በኢንቨስትመንት ዘርፉ ብዙም ድጋፍ ያላገኘው የትምህርት ዘርፉ በአገልግሎት ሰጭና ተቀባይ ወይም በሸመታው ዘርፍ የሚታይበትም አግባብ ተፈጥሯል ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሰሞነኛውን የግል ትምህርት ቤቶች ክፍያ ጭማሪና ይህንን ተከትሎ የተነሳውን ውዝግብ ማንሳት ይቻላል፡፡ ነጻ ገበያና የክፍያ ተመን በነፃገቢያየኢኮኖሚፅንሰሃሳብየግልየንግድተቋሙናሸማቹበሚስማሙት መሰረት የሚከናወን የግብይት ስርዓት ነው፡፡ በዚህ ስርዓት መንግስት በንግድ ውድድርና ሸማቾች አዋጅ እንደነገገው ለነጻ ገበያ አመቺነት ያለው ስርዓት ከማስፈን እና የንግዱን ህብረተሰብ ከፀረ-ውድድርና ተገቢ ካልሆኑ ተግባራት ከመከላከል በዘለለ በአቅርቦቱ እና በፍላጎቱ መካከል ጣልቃ እንደማይገባ ተቀምጧል ፡፡ ነጻ ገበያ መሰረት የሚያደርገው ገበያውን ብቻ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ በአቅራቢዎቹም መካከል የግል ድርድር በማድረግ ሸማቹ በሚገዛው ነገር ላይ ተመሳሳይ ዋጋ የማስተመን (Price setting) ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ይህ ሆኖ ሳለ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የግል ት/ቤቶች በክፍያው ላይ በየዓመቱ ጭማሪ እያደረጉ ነው ሲል ይከሳል ፡፡ የዋጋውን ተመን መሰረት በማድረግም ቅሬታ ያቀርባል ፡ ፡ በሌላ በኩል ዋጋውን መሰረት ያደረገ የዋጋ ተመን በግል ት/ቤቶቹ ላይ እንደማይጥል ያስታውቃል፡፡ የግል ት/ቤቶች ክፍያ የአዲስ አበባ ት/ቢሮ በስሩ የሚገኙትን የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች የትምህርት ስርዓት ይቆጣጠራል፡፡ ከዚህ ባሻገር የግል ት/ቤቶቹ ክፍያ ላይ መንግስት እጁን ማስገባቱ ለምንድን ነው ሲሉ የሚጠይቁ አሉ ፡ ፡ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የት/ቤቶቹ የክፍያ ጭማሪ በየዓመቱ የሚደረግ እና የኢኮኖሚ ምክንያት የሌለው ነው ሲል 194 ለሚሆኑ የግል ት/ቤቶች ከት/ቢሮ ጋር በመሆን ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጧል ፡፡ ባለስልጣኑ የግል ት/ቤቶችን ጥራት ጉዳይ የሚከታተለው የአዲስ አበባ ት/ቢሮ መሆኑንም አያይዞ አስቀምጧል ፡፡ ታዲያ ይህ ተግባር የአንድ ት/ቤትን አጠቃላይ የትምህርት አሰጣጥ ደረጃና ብቃት ያገናዛባል ? በዋጋ ላይ ብቻ መሰረት ያደረገ ፍተሻ ማድረግስ ተገቢ ነው ? የኢኮኖሚ ምክንያት የግል ት/ቤቶች ካለ በቂ ምክንያት በክፍያ ዋጋ ላይ ጭማሪ አድርገዋል የሚሉ ሃሳቦች በተደጋጋሚ መነሳታቸውን እና ይህንንም አዲስ አበባ ት/ ቢሮም ሆነ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን በጥናት ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢኮኖሚ ምክንያት ምንድነው? ብለን ስንነሳ በዋናነት የኢኮኖሚ ምክንያት በሀገሪቱ ካለው የእቃዎች ዋጋ መናርና ከዋጋ ግሽበት/ Inflation /ጋር ተያይዞ ሊነሳ የሚችል ነው፡፡ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የትምህርት ተቋማት ዓመት 2002 ዓ.ም 2003 ዓ.ም 2004 ዓ.ም 2005 ዓ.ም 2006 ዓ.ም አማካይ አመታዊ እድገት ትምህርት ቤቶች /ተቋማት/ መዋዕለ ህጻናት 3318 3418 3580 3688 4560 6.6 የመጀመሪያ ደረጃ 20251 28349 29643 30495 32048 3.5 ሁለተኛ ደረጃ 1335 1517 1710 1912 2333 11.8 የመምህራን ትምህርት 29 32 32 34 34 3.2 ቴክኒክና ሙያ 460 505 502 437 437 -1.0 ከፍተኛ ተቋማት 70 74 91 99 124 12.1 ድምር 32163 33895 35561 36665 39536 4.2 የትምህርት ሚንስቴር አመታዊ የትምህርት ስታትስቲክስ 2006 ዓ.ም 2013/14
  • 17. 13ቅፅ 1 ቁጥር 2 መስከረም2008 ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ያናገርናቸው አንድ ምሁር እንደሚሉትም “Inflationisdefinedasariseinthegeneralpricelevel.Inother words, prices of many goods and services such as housing, apparel, food, transportation, and fuel must be increasing inorderforinflationtooccurintheoveralleconomy.Ifprices of just a few types of goods or services are rising, there isn’t necessarily inflation.” ግሽበት የሚለካው በአጠቃላይ ዋጋ ጭማሪ መሰረት ነው ፡፡ በሌላ አነጋገር ብዙ የአገልግሎት እና የሸቀጥ ዋጋዎች ጭማሪ ሲታይባቸው ነው ፡፡ እነዚህም ቤቶች ፣ አልባሳት፣ ምግብ፣ ትራንስፖርት፣ እና ነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርግ ሲሆን ነው ፡፡ በጥቂት ግብይቶች ላይ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ የዋጋ ግሽበትን አያስከትልም፡፡ በዚህ መረጃ ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ የዘንድሮ እና የዓምና ተመሳሳይ ወሮች ኢንዴክስ የችርቻሮ ዋጋ 11.9 % ጭማሪ ማሳየቱን ለመረዳት ተችሏል ፡፡ በሌላ በኩል ትራንስፖርት 4.8 % መገናኛ 0.6 % ትምህርት 0.9 % ቅናሽ አሳይቷል ፡፡ ተንከባላይ የዋጋ ግሽበት የሚባለው ረዘም ያለ ጊዜ ሲንከባለል የመጣ የዋጋ ግሽበት ነው፡፡ ከዚህ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ሪፖርት መረዳት የሚቻለው ሁለት ነገር ነው ፡፡ የመጀመሪያው የት/ቤቶቹ የዋጋ ጭማሪ የኢኮኖሚ መሰረት የለውም የሚለው ክስ በዚህ መረጃ መሰረት ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡ ሌላው በአገልግሎት ዘርፍ በተለይም በትራንስፖርት፣ በመገናኛና እንዲሁም ከፍተኛ ጭማሪ እየታየበት ነው የሚባለው ትምህርት በአንጻራዊነት ቅናሽ የሚያሳይ መሆኑን ለመረዳት ይቻላል ፡፡ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን በግል ት/ቤቶች ውስጥ የተደረገው ጭማሪ ለ3 ተከታታይ ዓመታት መሆኑንና 97% ያህል የሚሆኑ ት/ቤቶች ጭማሪ ማድረጋቸውን ይህም በባለሥልጣኑ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች መረጋገጡን ይገልጻል ፡፡እነዚህ የማዕከላዊ ስታስቲክስና የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን ሁለት መረጃዎች እርስ በእርሳቸው የተጣረሱና አንድ አይነት መደምደሚያ ላይ ለመድረስም አሻሚ ሆነዋል፡፡ ወላጆች ምን ይላሉ? ወላጅ 1 ወ/ሎ ስርጉት በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሴት ናቸው፡፡ ሁለት ልጆቻቸውን በግል ት/ቤት ውስጥ የሚያስተምሩ ሲሆን ወላጇ እንደሚሉት በየዓመቱ ለት/ቤት ከሚከፍሉት ዋጋ በተጨማሪ ለተለያዩ መገልገያዎች የሚያወጡት ወጪ እንዳስመረራቸው እና መንግስት ጣልቃ ገብቶ የዋጋ መረጋጋት ማድረግ እንዳለበት ይገልጻሉ፡፡ ወላጅ 2 ዶ/ር አብረሃም የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ናቸው ፡፡ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት በግል ት/ቤት ነው ፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት ት/ቤቶቹ በየዓመቱ ከሚጨምሩት ክፍያ ይልቅ ልጆቻቸው የተሻለ ትምህርት አግኝተዋል ወይ ብለው ይጠይቃሉ ፡፡ መንግስት የዋጋ ተመን ውስጥ ገብቶ ከሚሰራ ይልቅ በሀገሪቷ ላይ ያሉ ት/ቤቶች የግልም ሆነ የመንግስት ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች የሚሰጥበትን መንገድ ማመቻቸት አለበት ባይ ናቸው፡፡ ዛሬ ልጄን በክፍያ መጨመር ምክንያት ወደ ት/ቤት ባልወስደው ሌላ አማራጭ አለኝ ወይ ሲሉም ይጠይቃሉ ፡፡ ራሳቸው ሲመልሱም የለኝም ፡፡ በርካታ ጥራት ያላቸው ት/ቤቶች የሚፈጠሩ ከሆነ ወላጅ ብዙ አማራጭ ይኖረዋል ፡፡ ይህ ሁኔታ ከተፈጠረም ወላጅ ዋጋ ብቻ ሳይሆን ጥራትንም ማወዳደር ይጀምራል የሚል እምነት አላቸው፡፡ ማጠቃለያ ለቀጣይ የኢትዮጵያ እድገት ወሳኙ የሰው ሀይል መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡ ፡በተለይም የተማረ ራሱን ለእውቀት ያስገዛ ሀይል እጅጉን ትፈልጋለች፡ ፡ እናም እነዚህ ሀይሎች የሚፈራባቸው ተቋማት ሳሙናና ብረት ከምናገኝባቸው ፋብሪካዎች በተሻለ ወይም በበለጠ ድጋፍ ሊደርግላቸው ይገባል፡፡ መንግስት በስሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን አቅም በማጎልበት ተወዳዳሪነቱ ላይ በመስራት ለወላጆችና ለተማሪዎች አማራጭ መፍጠር ይኖርበታል፡፡ ለግል ትምህርት ቤቶች የሚደረገው ድጋፍም ቸል ሊባል አይገባም፡፡ የግል ትምህርት ተቋማቱም ከመንግስት የትምህርቱ አካላት ጋር በአዎንታዊ አመለካከት ተቀራርበው መስራት ቢችሉ በየጊዜው ለሚያነሷቸው የፋይናንስና የመሰረተ ልማት እጥረቶች መፍትሄ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ በትምህርቱ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ አካላትም በትምህርት ተቋማቱ ላይ እርምጃ ከመውሰዳቸው አስቀድመው ህገ መንግስቱን ጨምሮ የሀገሪቱን ህጎች የሚጥስ ስላመሆኑ በእርምጃውም ወላጅና ማህበረሰቡ ተጎጂ ስላለመሆናቸው ሊያረጋግጡ ይገባል፡፡ የሀገሪቱ ከኢንቨስትመንቱም ከሸመታውም ዘርፍ ተጠቃሚ መሆን ያልቻለው የትምህርቱ ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሀይልን እንዲያፈራ በትንንሽ ምክንያቶች ጫና ከማብዛት ይልቅ ቁጥጥሩንም ከድጋፉንም ማጠናከር ይገባል፡፡ የፌዴራል ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በሐምሌ ወር 2007 ዓ.ም ሪፖርቱም በሀገሪቱ ባሉ አብዛኞቹ ምርቶች ላይ ጭማሪ ማሳየቱንይገልጻል ፡፡ ግሽበትም መኖሩን ያሳያል፡፡ ጥናት የተደረገበት ጊዜ አገልግሎቶች ተንከባላይ የዋጋ ግሽበት አጠቃላይ ግሽበት ምግብ ነክ ምግብ ነክ ያልሆኑ 2007 ዓ.ም 8.0% 8.0% 8.1 % 7.7 % መረጃ ቁ. 29 2007 ዓ.ም