SlideShare a Scribd company logo
1 of 9
Download to read offline
ጣፋጭ 
ዜና መፅሔት 
ራዕይ፡ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በአለም ተወዳዳሪ የሆነ የስኳር ኢንዱስትሪ መፍጠር 
ቅፅ 3. ቁጥር 1- መስከረም 2007 ዓ.ም 
www.etsugar.gov.et.com || www.facebook.com/etsugar 
ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የበጀት አመት 
መሻሻል የታየበት አፈጻጸም አስመዘገበ 
ስኳር ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው የበጀት አመት በዋናው መሥሪያ 
ቤት፣ በስኳር ፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች መሻሻል የታየበት አፈጻጸም 
አስመዘገበ፡፡ 
የ2006 በጀት ዓመት እቅድንና ፍኖተ-ካርታውን መሰረት አድርገው 
የተሰሩ ሥራዎችና የተመዘገቡ ውጤቶች ኮርፖሬሽኑን በ2005 ዓ.ም 
መጨረሻ ከነበረበት ወደፊት ያራመዱና ለቀጣይ የዘርፉ የልማት ስራዎች 
መሠረት የጣሉ መሆናቸውን አመታዊ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት 
አመልክቷል ፡፡ 
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተዘጋጀው የፍኖተ-ካርታ እቅድ መሰረት 
ተንዳሆን ጨ ምሮ በ አራት ስ ኳር ፋ ብሪካዎች 4 93,321 ቶ ን ስ ኳር 
የውጤት ተኮር ሥርዓት ሥልጠና ተሰጠ 
ስትራቴጂያዊ የአመራር ሥርዓትን በመተግበር የስኳር ኮርፖሬሽንን 
ራዕይና ተልዕኮ እውን ለማድረግ የሚረዳ አቅም ለመፍጠር 
የሚያስችል የውጤት ተኮር (ቢኤስሲ) ሥርዓት ስልጠና ለኮርፖሬሽኑ 
405 ከፍተኛና መካከለኛ የስራ መሪዎች ተሰጠ፡፡ 
ስልጠናው ለስራ መሪዎቹ የውጤት ተኮር ሥርዓትን በተመለከተ 
በቂ ግንዛቤ፣ ዕውቀትና ክህሎት ያስጨበጠ መሆኑንና 
ለትግበራውም የስትራቴጂ አመራር ቡድን፣ የስትራቴጂ ቀረጻ ቡድን፣ 
የኮሚዩኒኬሽንና የለውጥ አስተግባሪ ቡድን መቋቋሙን የኮርፖሬሽኑ 
የለውጥ ትግበራ ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡ 
»» ወደ ገጽ 4 ዞሯል 
የኦሞ-ኩራዝ ስኳር ልማትፕሮጀክት 
አካባቢ ነዋሪዎች 
ልማቱ እንዲፋጠን ጠየቁ 
የኦሞ-ኩራዝ ስኳር ልማት እየተካሄደ በሚገኝበት አካበቢ ነዋሪ የሆኑ 
የአካባቢው ተወላጆች የስኳር ልማቱ ተፋጥኖ ወደሚኖሩበት አካባቢ 
እንዲደርስና በፕሮጀክቱ የስራ እንቅስቃሴ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆን 
እንዲችሉ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ 
»» ወደ ገጽ 4 ዞሯል 
»» ወደ ገጽ5 ዞሯል 
የስልጠናው ተሳታፊዎች 
በፕሮጀክቱ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች የልማቱ 
ተጠቃሚ መሆናቸውን ተረድተዋል 
መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልዎ! 
በውስጥ ገፆች 
መተሐራ ስኳር ፋብሪካ የካይዘን አንደኛ ደረጃ 
ትግበራ አገር አቀፍ ውድድር አሸናፊ ሆነ ››ገጽ 6 
ተጓዳኝ ምርቶችና አግሮ ፕሮሰሲንግ የስኳር 
ኢንዱስትሪው ተጨማሪ አቅም ››ገጽ 12 
“…ለእኔና ለወገኖቼ በፈነጠቀው ብርሃን ስደሰት 
እነዚያ ጓደኞቼ ይህንን ሳያዩ በማለፋቸው ክፉኛ 
አዝናለሁ፡፡” ››ገጽ 13 
በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት 
:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A
የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት 
በአሁኑ ወቅት በአገራችን የስኳር ፍላጎት የደረሰበት ደረጃ ሲታይ የዛሬ 60 ዓመት 
በላንድሮቨር መኪና በየገበያው በመዘዋወር ስኳርን ከሕዝባችን ጋር ለማስተዋወቅ ብርቱ 
ጥረት ተደርጎ እንደነበር ማመን ይከብዳል፡፡ በወቅቱ ሻይ በ”ቅመሱልኝ” በነጻ በመጋበዝ 
ሕዝቡን ከምርቱ ጋር ለማላመድ የተደረገው እንቅስቃሴ ከብዙ ጥረት በኋላ ውጤት 
ማስገኘት ችሏል፡፡ በዚህ ሁኔታ የተጀመረው የስኳር ትውውቅ ዛሬ ላይ ታሪኩን ለውጦ 
ከሕዝባችን የኑሮ መሻሻል እና ስኳርን በግብዓትነት ከሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት 
ጋር በተያያዘ በጣም ተፈላጊ ምርት እየሆነ መጥቷል፡፡ 
ይህም በማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የነባር ስኳር ፋብሪካዎችን በማዘመን የማምረት 
አቅማቸውን ለማሳደግ ዋንኛው ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህን ተከትሎም ግዙፉ የተንዳሆ ስኳር 
ፋብሪካን ከመገንባት አንስቶ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን “የስኳር አብዮት” 
በሚያስብል ሁኔታ በዘርፉ መጠነ ሰፊ የስኳር ልማት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ 
አኳያ በተለያዩ የአገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች 10 አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት 
የሚያስችሉ የመስኖ፣ የአገዳ ተከላ፣ የፋብሪካ እና የቤቶች ግንባታ መጠነ ሰፊ ሥራዎች 
ከተጀመሩ አራት አመታት ተቆጥረዋል፡፡ 
በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ የመጣውን የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎት ለማሟላት እና 
ምርቱን ኤክስፖርት በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 
ክቡር አቶ ሽፈራው ጃርሶ 
በሚኒስትር ማዕረግ 
የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር 
ባደረግነው ርብርብ ያቀድናቸውን ግቦች ሙሉ 
በሙሉ ባናሳካም እንኳ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል 
የታየበት አፈጻጸም ማስመዝገብ ችለናል፡፡ 
ከዚህ አንጻር የተከናወኑት ሥራዎች በ2005 
ዓ.ም መጨረሻ ከነበርንበት ወደፊት ያራመዱንና 
ለቀጣዩ ልማት ትልቅ መሠረት የጣሉ ናቸው ብሎ 
መውሰድ ይቻላል፡፡ 
ባሳለፍነው የዕቅድ ዘመን ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን 
ጨምሮ 493ሺህ 231 ቶን ስኳር ለማምረት የታቀደ 
ቢሆንም ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በተያዘለት ጊዜ 
ውስጥ ወደ ምርት ባለመግባቱ፣ የፊንጫአ ስኳር 
ፋብሪካም በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ 
በዘነበው ከባድ ዝናብ እና ከሌሎች የፋብሪካ 
የቴክኒክ ሥራዎች ጋር በተያያዙ ውስጣዊ 
ችግሮች ምክንያት ከእቅድ በታች 325ሺህ 
25ቶን ስኳር ተመርቷል፡፡ ይሁንና ይህ የስኳር 
መጠን ከ2005 በጀት ዓመት ምርት ጋር ሲነጻጸር 
የ1ሚሊዮን ኩንታል ያህል ብልጫ አሳይቷል፡፡ 
የአገዳ ልማትን በተመለከተም በነባርና አዳዲስ 
ፕሮጀክቶች በ2007 ወደ ምርት የሚገቡ ፋብሪካዎችን የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት 
አስተማማኝ ለማድረግ 30,733 ሄክታር መሬት በአገዳ መሸፈን ተችሏል፡፡ ይህ 
አፈጻጸም በ2005 በጀት ዓመት መጀመሪያ ላይ ከደረስንበት 8ሺህ ሄክታር ጋር 
ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ 129ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች 
ተጨማሪ የስራ እድል መፍጠር የቻልንባቸው በርካታ ውጤታማ ሥራዎች ለቀጣይ 
ግቦቻችን ስኬት አስተማማኝ መደላድል ናቸው ብለን እናምናለን፡፡ 
በያዝነው ዓመት ተንዳሆ 1 እና 2፣ ከሰም፣ አርጆ ዲዴሳ፣ ጣና በለስ 1 እና 2 እንዲሁም 
የኩራዝ 1 ስኳር ፋብሪካዎች ወደ ምርት እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡ ከፋብሪካ ግንባታ 
ጎን ለጎንም በስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ተጨማሪ 33,574 ሄክታር መሬት የአገዳ 
ልማት በማካሄድ የፕሮጀክቶችን አጠቃላይ የአገዳ ልማት 82ሺህ ሄክታር ያህል 
ለማድረስ ታቅዷል፡፡ በነባር ስኳር ፋብሪካዎችም 5,009 ሄ/ር መሬት ያህል የሸንኮራ 
አገዳ ለመትከል የሚያስችሉ ሥራዎችን ለማከናወን ውጥን ተይዟል፡፡ 
የስኳር ምርትን በተመለከተም በ2007 በጀት ዓመት መጨረሻ ከ1.2 ሚሊዮን ቶን 
በላይ ስኳር ለማምረት የታቀደ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 665 ሺህ 438 ቶን ወደ ውጭ 
በመላክ 311 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል፡፡ አመታዊ የኤታኖል ምርትን 
አሁን በመተሃራ እና ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች አማካኝነት ከደረስንበት 19 
ሚሊዮን 745 ሺህ ሊትር ወደ 30 ሚሊዮን 278 ሺህ ሊትር የማሳደግ ግብም 
ተጥሏል፡፡ 189 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል በማምረት 46 ሜጋ ዋቱን ለአገሪቱ 
ማዕከላዊ የኃይል ቋት የማቅረብ ሥራዎችም የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ ግቦቻችን 
ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ 
ሌላው የዕቅዳችን አካል የሆነው ሞላሰስና ባጋስ በመባል የሚታወቁትን የስኳር ተረፈ 
ምርቶች ከሌሎች ተጨማሪ ውህዶች ጋር በማደባለቅ የእንስሳት መኖ የማቀነባበሪያ 
ፋብሪካ ለማቋቋም የጀመርነው እንቅስቃሴ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የስኳር ተረፈ 
ምርቶችን በግብአትነት ተጠቅሞ የእንስሳት መኖ በማቀነባበር ጥሩ ተሞክሮ ካለው 
የሱዳኑ ኬናና ስኳር ኩባንያ ልምድ ተወስዷል፡፡ ከመኖ ማዘጋጀቱ ሥራ በተጎዳኝም 
የእንስሳት ማድለብያ ጣቢያ ለማቋቋም የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች በመከናወን 
ላይ ሲሆኑ፣ እነዚህ ሥራዎች በብዙ መልኩ ለአገሪቱ የጎላ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ 
አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለስኳር ኢንደስትሪው 
ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥሩ ይታመናል፡፡ 
ኮርፖሬሽኑ በተያዘው በጀት ዓመት በዘርፉ ከ100ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች 
ተጨማሪ የሥራ እድል ለመፍጠር ከሚያመቻቸው መደላድል በተጨማሪ የስኳር 
ልማት በሚካሄድባቸው የቆላማ አካባቢዎች ለረጅም ዘመን የልማት ተጠቃሚ 
ሳይሆኑ ለቆዩ ሕዝቦች በመስኖ ሊለማ የሚችል መሬት ከማመቻቸት ጀምሮ 
የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመሰረተ ልማት አውታሮችን የመገንባት 
ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ 
በአጠቃላይ ለዕቅድ ዓመቱ ግቦቻችን ስኬት በቅርቡ ተግባራዊ የምናደርገውን 
ስትራቴጂያው የውጤት ተኮር ሥርዓት ሥራ ላይ ለማዋልና አሁን ውጤት 
እያመጣንበት ያለውን የካይዘን የአመራር ፍልስፍና ይበልጥ አጠናክረን ለመቀጠል 
የሚያስችለንን የለውጥ ሥርዓት እየተከተልን እንገኛለን፡፡ 
ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት በአገራችን በ”ቅመሱልኝ” ተዋውቆ ዛሬ ላይ ተፈላጊነቱ 
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ስኳር ለአገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ 
የሚያስገኝበት ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡ በዚህ ረገድ በአዲሱ አመት አዲስ ብስራት 
ለማሰማት ተስፋ መሰነቃችንን ስገልጽ መላው ኢትዮጵያውያን በተሰማሩባቸው 
የሥራ መስኮች ሁሉ የአገራችንን ህዳሴ እውን ለማድረግ የጀመሩት ጥረት የተሳካ 
እንዲሆን በመመኘት ነው፡፡ 
መልካም ዘመን!
ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r 
በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት 
ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የበጀት... የውጤት ተኮር ሥርዓት ሥልጠና... »» ከገጽ 1 የዞረ »» ከገጽ 1 የዞረ 
በዋና መስሪያ ቤት፣ በፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች ለሚገኙ 
ሠራተኞች ተመሳሳይ ሥልጠና መስጠትና የኮርፖሬሽኑን 
ውጤት ተኮር ሥርዓት ስትራቴጂያዊ ሰነድ ማዘጋጀት ቀጣይ 
ስራዎች እንደሚሆኑም ዳይሬክቶሬቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡ 
የውጤት ተኮር ሥርዓቱ ከኮርፖሬሽኑ ራዕይና ተልዕኮ 
የመነጨ ስትራቴጂያዊ እቅድ በማዘጋጀት ሀብት በአግባቡ 
ተጠቅሞ ለውጤት የማብቃት፤ የቡድንና የግለሰብ 
ተግባራትና አፈፃፀም ከተቋሙ ስትራቴጂያዊ እቅድ ጋር 
አስተሳስሮ ለመፈጸም፤ የተቋም፣ የቡድንና የግለሰብ አፈፃፀም 
ውጤትን ለመመዘንና ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲሻሻል 
ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ዳይሬክቶሬቱ 
አስረድቷል፡፡ እንዲሁም የተቋሙን ስትራቴጂያዊ እቅድ 
አፈፃፀም ውጤትን ከማትጊያ ሥርዓት ጋር በማስተሳሰር 
የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ ይረዳል ብሏል፡፡ 
ስትራቴጂያው የውጤት ተኮር ሥርዓትና የካይዘን የአመራር 
ፍልስፍና አንዱ የአንዱን ክፍተት በመሙላት እርስ በርስ 
ተሳስረውና ተመጋግበው የኮርፖሬሽኑን ራዕይና ተልዕኮ 
ለማሳካት የሚረዱ የለውጥ መሳሪያዎች መሆናቸውም 
ተገልጿል፡፡ 
የውጤት ተኮር ሥርዓት በካይዘንና በሌሎች የለውጥ 
መሳሪያዎች የተገኘውን ውጤት ለመመዘን የሚያስችል 
የለውጥ መሳሪያ ከመሆኑም በላይ ስትራቴጂያዊ የውጤት 
ተኮር ሥርዓትና ካይዘን ፈፃሚዎች የጋራ ግብ ይዘው የቡድን 
ስሜትን በመፍጠር የጋራና የቡድን ውጤት ለማምጣት 
እንዲሰሩም ይረዳል ተብሏል፡፡ 
ስትራቴጂያዊ የውጤት ተኮር ሥርዓትና ካይዘን አመለካከትን 
በመቀየር ቀጣይነት ያለው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ 
የሚያስችሉ የለውጥ መሳሪያዎች በመሆናቸው ኮርፖሬሽኑን 
ውጤታማ ለማድረግ ሁለቱንም በቅንጅት ስራ ላይ ማዋሉ 
ተገቢ እንደሆነም ነው ዳይሬክቶሬቱ ያመለከተው፡፡ 
የውጤት ተኮር ሥርዓት አንድ ተቋም ከተሰጠው ራዕይና 
ተልዕኮ አንፃር ሀብቱን ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድ 
በመምራት ለውጤት የሚያበቃበት፣ ያስመዘገበውን ውጤት 
የሚለካበትና የተግባቦት (ኮሚዩኒኬሽን) ስራ የሚሰራበት 
የለውጥ መሳሪያ ነው፡፡ 
የኦሞ-ኩራዝ ስኳር ልማትፕሮጀክት አካባቢ ነዋሪዎች ልማቱ እንዲፋጠን ጠየቁ 
የኦሞ-ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት 
እየተካሄደ በሚገኝበት አካባቢ ነዋሪ የሆኑ 
የቦዲ፣ የሙርሲና የሜኢኒት ብሔረሰቦች 
የጎሳ መሪዎች፣የአገር ሽማግሌዎች፣ሴቶችና 
ወጣቶች ከስኳር ኮርፖሬሽንና ከደቡብ 
ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ 
መስተዳድር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር 
በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ባደረጉት 
ውይይት የስኳር ልማቱ ሥራ የደረሰበት 
አካባቢ ሕብረተሰቡ በከፍተኛ ደረጃ 
ተጠቃሚ እንደሆነ ማየታቸውን በመጥቀስ 
መንግሥት ልማቱን አንዲያሳልጥና 
ወደሚኖሩበት አካባቢ እንዲያደርስና 
እነሱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡ 
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን ሄደው 
መጎብኘት እንደቻሉና በዚህም 
በአካባቢያቸው እየተገነባ ያለው ስኳር 
ፋብሪካ ስኳር ማምረት የሚጀምርበትን ጊዜ 
በጉጉት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ እነዚሁ 
ከደቡብ ኦሞ፣ከከፋ እና ከቤንቺ ማጂ ዞኖች 
የተውጣጡና የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑ 
የቦዲ፣የሙርሲና የሜኢኒት ብሔረሰቦች 
ተወላጆች አመልክተዋል፡፡ 
የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ በአካባቢያቸው 
በመጀመሩ ከእርሻ ስራ ጋር በመተዋወቅ 
አምርተው መጠቀም ከመቻላቸው ባሻገር 
የተለያዩ መሰረተ ልማት አውታሮችና 
የማኅበራዊ ተቋማት አገልግሎት 
ተጠቃሚዎች መሆን እንደቻሉ የውይይቱ 
ተሣታፊዎች የገለጹ ሲሆን በአካባቢያቸው 
እየተገነቡ የሚገኙት ስኳር ፋብሪካዎች 
ስኳር ማምረት ሲጀምሩ ለማየት እጅግ 
መጓጓታቸውን ገልጸዋል፡፡ 
ፕሮጀክቱ ወደፊት በሚደርስባቸው 
አካባቢዎች ማለትም በደቡብ ኦሞ ዞን 
የሙርሲ፣ በከፋ ዞን ዴቻ ወረዳና በቤንች 
ማጂ ዞን የሜኢኒት ብሔረሰቦች ተወላጆች 
የሆኑ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው 
መንግስት የስኳር ልማት ስራውን አፋጥኖ 
እንደሌሎቹ ሁሉ እነርሱም የተለያዩ መሰረተ 
ልማት አውታሮችና ማህበራዊ አገልግሎቶች 
ተጠቃሚ እንዲሆኑ መንግስት ልማቱን 
ያፋጥን ዘንድ አሳስበዋል፡፡ 
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ 
መለስ ዜናዊ እዚህ ተገኝተው ስለስኳር 
ልማቱ የገቡልን ቃል ወደ ተግባር ተለውጦ 
ማየታችን ምንም ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታ 
ቢገጠመን እንኳን በጽናት እንድንወጣው 
የሚያደርግ ነው ያሉት የውይይቱ 
ተሳታፊዎች በልማቱ ሳቢያ ቀድሞ እንደ 
ጠላት እንተያይ የነበርን የአካባቢው 
ተወላጆች ለልማቱ መፋጠን በጋራ 
መቆም ችለናል ሲሉ ልማቱ ያስገኘላቸውን 
ማኅበራዊ ትስስር ገልጸዋል፡፡ 
በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና 
ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በበኩላቸው 
በውይይቱ የተነሱት ሀሳቦች የስኳር ልማት 
ስራው ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለ የሚያመላክት 
መሆኑን ጠቅሰው ከመስኖ አውታር 
ጀምሮ የመሰረተ ልማት አውታሮችም ሆኑ 
የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት 
የስኳር ልማቱ በሚደርስባቸውም ሆነ 
በማይደርስባቸው አካባቢዎች እንዲገነቡ 
መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እያከናወነ 
እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም 
ሕብረተሰቡ በጠየቀው መሰረት የልማት 
ስራው በተገቢው ደረጃና ፍጥነት 
እንዲከናወን የአካባቢው ተወላጆች 
የድርሻቸውን እንዲወጡ አሣስበዋል፡፡ 
አቶ ታገሰ ጫፎ የደ/ብ/ብ/ሕ ክልል ምክትል 
ርዕሰ መስተዳድር በበኩላቸው የክልሉም 
ሆነ የፌደራሉ መንግስት የልማት ስራዎችን 
በአካባቢው የሚያከናውኑት የአካባቢውን 
ተወላጆች ተጠቃሚነት ባረጋገጠ ሁኔታ 
መሆኑን አመልክተው የኦሞ ወንዝን 
መንግስት እንዲጠለፍ ሲያደርግ መጀመሪያ 
ላይ ተጠቃሚ የደረገው የአካባቢውን 
ነዋሪዎችን መሆኑን አውስተዋል፡፡ 
አቶ ሞሎካ ውብነህ የደቡብ ኦሞ ዞን 
ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸው እንደገለጹት 
የተካሄደው ውይይት ከዚህ በፊት 
ይንጸባረቁ የነበሩ ጥርጣሬዎችና ችግሮች 
መወገዳቸውን ያመላከተ ነው፡፡ እየተካሄደ 
የሚገኘው በመንደር የማሰባሰብ ስራ 
የአካባቢዎቹ ተወላጆች የመሰረተ ልማት 
አውታሮችና ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ 
ተቋማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል 
ብለዋል፡፡ 
የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ175 
ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ 
አገዳ መሬት የሚኖረውና በአጠቃለይ 
አምስት ስኳርፋብሪካዎች የሚገነቡበት 
በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል በደቡብ ኦሞ፣በከፋ እና 
ቤንች ማጂ ዞን የሚገኝ ግዙፍ ፕሮጀክት 
ነው፡፡ 
»» ከገጽ 1 የዞረ 
ለማምረት ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ 
በቅርቡ ማምረት እንደሚጀምር 
የሚጠበቀው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ 
በተለያዩ ምክንያቶች በተያዘለት ጊዜ 
ማምረት ባለመጀመሩ በሦስቱ ነባር 
ፋብሪካዎች ብቻ 325 ሺህ 25 ቶን 
ስኳር ለማምረት ተችሏል፡፡ 
በበጀት አመቱ ፋብሪካዎቹ ያመረቱት 
የስኳር ምርት በ2005 የበጀት 
አመት ካመረቱት የምርት መጠን ጋር 
ሲነጻጸር አንድ መቶ ሺህ ቶን የሚጠጋ 
ብልጫ አሳይቷል፡፡ 
ብቸኞቹ የኤታኖል አምራች የሆኑት 
የመተሐራና የፊንጫአ ስኳር 
ፋብሪካዎች በበጀት አመቱ 19 
ሚሊዮን 745 ሺህ ሊትር ኤታኖል 
ያመረቱ ሲሆን፣ ምርቱ ከአምናው 
ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ5 
ሚሊዮን 61 ሺህ ሊትር ብልጫ 
አሳይቷል፡፡ 
በፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች 
የካይዘን አሠራር ፍልስፍና ተግባራዊ 
በመደረጉ በሠራተኞች ዘንድ 
መነቃቃት እንዲፈጠርና በባለቤትነት 
መንፈስ እንዲንቀሳቀሱ በማስቻሉ 
በበጀት አመቱ በመቶ ሚሊዮኖች 
የሚቆጠር ገንዘብ ማዳን መቻሉንም 
አመታዊው የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት 
ያመለክታል፡፡ 
በካይዘንና የለውጥ አመራር ዘርፍ 
በኩል በበጀት አመቱ ለ18 ሺህ 289 
የፋብሪካ እና የፕሮጀክት ሠራተኞች 
በመሠረታዊ የካይዘን ፍልስፍና እና 
አድቫንስድ ካይዘን ኮርሶች ስልጠና 
ተሰጥቷል፡፡ 
በአገዳ ተከላ፣ በቤቶችና መስኖ 
ግንባታ፣ በፋብሪካ ተከላ ረገድም 
ኮርፖሬሽኑ ከ2005 ዓ.ም የበጀት 
አመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የተሻሉ 
ውጤቶችን ማስመዝገቡን ሪፖርቱ 
ጠቁሟል፡፡ 
የፕሮጀክት መዘግየት፣ በፊንጫአ 
ስኳር ፋብሪካ ዝናብ በከፍተኛ 
መጠንና ለተራዘመ ጊዜ በመዝነቡ 
ምክንያት አገዳ ለፋብሪካ ለማቅረብ 
አለመቻሉ፣ እንዲሁም የአቅም 
ውስንነቶችና የአቅርቦት መጓተት 
በበጀት አመቱ የተስተዋሉ ዋና ዋና 
ተግዳሮቶች እንደነበሩ ነው ሪፖርቱ 
ያመለከተው፡፡ 
ኮርፖሬሽኑ በተያዘው የ2007 የበጀት 
አመት 1 ሚሊዮን 217 ሺህ 438 ቶን 
ስኳርና 30 ሚሊዮን 278 ሺህ ሊትር 
ኤታኖል ለማምረት አቅዷል፡፡ ከስኳር 
የምርት መጠን ውስጥም 665 ሺህ 
438 ቶን ለውጭ ገበያ በማቅረብ 
311 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ 
ለማግኘት መታቀዱ ተገልጿል፡፡ 
በበጀት አመቱ 189 ሜጋ ዋት 
የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 
ከፋብሪካዎች ፍጆታ የሚቀረውን 46 
ሜጋ ዋት ኃይል ወደ ብሔራዊ ቋት 
ለማስገባትም ኮርፖሬሽኑ አቅዷል፡፡ 
የአገዳ ልማትን በተመለከተም 
በነባር ፋብሪካዎች 5 ሺህ ዘጠኝ 
ሄክታር ለመትከል የታቀደ ሲሆን፣ 
በፕሮጀክቶች ደግሞ ተጨማሪ 33 
ሺህ 574 ሄክታር አገዳ በመትከል 
የፕሮጀክቶችን የአገዳ ልማት 81 
ሺህ 914 ሄክታር ለማድረስ በበጀት 
አመቱ እንደሚሰራ የኮርፖሬሽኑ 
እቅድ ያመለክታል፡፡ 
በአንድ መቶ ሄክታር ላይ የእንስሳት 
መኖ ማዘጋጀትና አንድ የእንስሳት 
ማድለቢያ ጣቢያ አቋቁሞ ወደስራ 
መግባት በተጓዳኝ ምርቶችና አግሮ 
ፕሮሰሲንግ ዘርፍ በበጀት አመቱ 
ለማከናወን ከታቀዱት መካከል 
ተጠቃሾች ናቸው፡፡ 
በ2007 የበጀት አመት በስኳር 
ኢንደስትሪው ከ100 ሺህ በላይ 
ለሆኑ ዜጎች ተጨማሪ የስራ እድል 
ለመፍጠር ኮርፖሬሽኑ እንደሚሰራ 
እቅዱ ያመለክታል፡፡ 
አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶቹ 
እየተካሄዱ የሚገኙባቸው አካባቢዎች 
የመሰረተ ልማት አውታሮች 
ያልነበሩባቸው በመሆናቸው 
ኮርፖሬሽኑ ከስኳር ልማት ስራው 
ባሻገር እ ነዚህን በ ማሟላት ስ ራ 
እንዲጠመድ ያደረጉ መሆናቸው 
ይታወሳል፡፡ 
4 
5
ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r 
በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት 
የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ስራ ለስኳር ልማት ትልቅ ፋይዳ አለው 
የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ስራ ውሃን 
በሰፊው ለሚጠቀመው የስኳር ልማት 
ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው በሚኒስትር 
ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር 
አቶ ሽፈራው ጃርሶ ገለጹ፡፡ 
የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች 
በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ 
ጉራራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ 
ችግኝ ተክለዋል፡፡ 
አቶ ሽፈራው በዚሁ ወቅት 
እንደተናገሩት የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ 
ስራ ለስኳር ልማት ጥቅም ላይ የሚውለውን 
የመስኖ ውሃ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማግኘት 
ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡ 
ለዚህም ሲባል በስኳር ፕሮጀክቶች 
አካባቢም ኮርፖሬሽኑ ሰፊ የአካባቢ ጥበቃ 
ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ አቶ ሽፈራው 
ተናግረዋል፡፡ 
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች 
መተሐራ ስኳር ፋብሪካ የካይዘን አንደኛ ደረጃ ትግበራ አገር 
አቀፍ ውድድር አሸናፊ ሆነ 
መተሐራ ስኳር ፋብሪካ የኢትዮጵያ ካይዘን መትከላቸው ይታወሳል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ችግኝ ሲተክሉ 
ኢንስቲትዩት በአገር አቀፍ ደረጃ ባዘጋጀው 
የካይዘን የመጀመሪያ ደረጃ ትግበራ ውድድር 
አሸናፊ ሆነ፡፡ 
የወንጂ ሸዋና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች የአገዳ ቆረጣና የዘር አገዳ 
ዝግጅት ሠራተኞች አሸኛኘት ተደረገላቸው 
የወንጂ ሸዋና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች 
በ2ዐዐ6 ዓ.ም የምርት ዘመን በጊዜያዊነት 
በአገዳ ቆረጣና በዘር አገዳ ዝግጅት ስራ 
ተሰማርተው ለነበሩ ከ2 ሺህ 800 በላይ 
ሠራተኞች ለእረፍት ወደ ትውልድ ቀዬአቸው 
ሲሄዱ የክብር አሸኛኘት አደረጉላቸው፡፡ 
ሐምሌ 8 እና 14 ቀን 2006 ዓ.ም ሽኝት 
ከተደረገላቸው ሠራተኞች መካከል 1224 
የሚሆኑት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ፣ 
16ዐዐቱ ደግሞ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ 
በአገዳ ቆረጣና በዘር አገዳ ዝግጅት ሲሰሩ 
የነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡ 
በበጀት ዓመቱ በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ 
በአገዳ ቆረጣ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩት 
ሰራተኞች ከ6.8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ 
ሸንኮራ አገዳ የመቁረጥ ስራ አከናውነዋል ፡፡ 
በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ይሰሩ የነበሩት 
ደግሞ ከ6866.3 ሄክታር ማሳ ላይ 11. 5 
ሚሊዮን ኩንታል የሸንኮራ አገዳ የቆረጡ 
ሲሆን፣ የዘር ዝግጅት ሰራተኞቹ በበኩላቸው 
ከ300.4 ሄክታር ማሳ ላይ ከግማሽ ሚሊዮን 
ኩንታል በላይ የዘር አገዳ የመቁረጥ ስራ 
አከናውነዋል፡፡ 
በሁለቱም ፋብሪካዎች ሲሰሩ ለቆዩ 
እየተከናወነ በሚገኘው የአካባቢ ጥበቃና 
እንክብካቤ ስራ የደረቁ ወንዞች ቀደም ሲል 
ወደነበሩበት ሁኔታ መመለስ መጀመራቸው 
የስራውን ውጤታማነት እንደሚያሳይ ዋና 
ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ 
የአካባቢን የደን ሽፋን በማሳደግ 
አገሪቱ ከካርቦን ንግድ የምታገኘውን ገቢ 
ማሳደግ ይቻላል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ 
በየጊዜው የሚተከሉ ችግኞችን መንከባከብ 
እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ 
በተከላው ላይ የተሳተፉ 
የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞችም አረንጓዴ 
ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ 
ውስጥ በመሳተፋቸው የተሰማቸውን ደስታ 
ገልጸዋል፡፡ 
የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች 
አምናም ለታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ 
መታሰቢያ በተዘጋጀ ፓርክ ውስጥ ችግኞችን 
ሰራተኞች የፋብሪካዎቹ 
የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት 
የክብር መሸኛ መርሐ ግብሩ 
መከናወኑን ከፋብሪካዎቹ 
የሕዝብ ግንኙነት ክፍሎች 
የደረሱን ዘገባዎች 
አመልክተዋል፡፡ 
በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ 
በተከናወነው የሽኝት መርሐ 
ግብር የፋብሪካው ዋና ስራ 
አስኪያጅ አቶ ፉሮ በቀታ 
ባሰሙት ንግግር ሠራተኞቹ 
በበጀት አመቱ ፋብሪካው 
ላስመዘገበው ስኬት ላበረከቱት ከፍተኛ 
አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ 
በተመሳሳይ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ዋና 
ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም በወቅቱ 
በተወካያቸው አማካኝነት ባስተላለፉት 
መልዕክት ሠራተኞቹ ዕድሜያቸው ያለፈ፣ 
ደረቅና ለመቁረጥ አስቸጋሪ የሆኑ አገዳዎችን 
ጭምር በመቁረጥ ላሣዩት ጥንካሬ 
አመስግነዋል፡፡ 
በተጨማሪም የዘር አገዳ ዝግጅት ሠራተኞቹ 
እጅግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፋብሪካው እርሻ 
ሰራተኞቹ በሽኝት መርሃ ግብሩ ደስተኛ ነበሩ 
የዘር አገዳ ፍላጐት ባሻገር ለከሰም ስኳር 
ፋብሪካ ግብዓት እንዲውል ታስቦ በአሚባራ 
እርሻ ልማት በ6ሺህ ሔክታር መሬት 
ላይ ለተተከለው ሸንኮራ አገዳ የዘር አገዳ 
በማቅረብ ረገድ ለተጫወቱት ከፍተኛ ሚና 
ኩራት እንደተሰማቸው አክለው ገልጸዋል፡፡ 
በአሸኛኘቱ መርሐ ግብር ላይ በምርት 
ዘመኑ በሥራ አፈፃፀማቸው ግንባር ቀደም 
ለሆኑና ከየምድባቸው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ 
ዘጠኝ ምስጉን ሠራተኞች የገንዘብ ሽልማት 
ተሰጥቷል፡፡ 
የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እጅ የዋንጫ ሽልማት ሲቀበሉ 
ኢንስቲትዩቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ 
ጊዜ ሰኔ 21 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም አዲስ አበባ 
በሚገኘው በካፒታል ሆቴል ያዘጋጀው 
የመጀመሪያ ደረጃ የካይዘን ትግበራ 
ውድድር የተካሄደው በሰው ሀብት ልማት፣ 
በኤክስፖርት ምርቶች ኢንዱስትሪ እና በገቢ 
ምርቶች ኢንዱስትሪ ነው፡፡ 
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በእነዚህ ዘርፎች 
በተካሄደ አጠቃላይ ውድድር በግል፣ በልማት 
ቡድንና በተቋም ደረጃ አንደኛ በመውጣት 
የወርቅና የዋንጫ ሽልማት ከእለቱ የክብር 
እንግዳ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር 
አቶ ደመቀ መኮንን እጅ ተቀብሏል፡፡ 
ፋብሪካው ከዚህ በኋላ በየአመቱ በሚካሄዱ 
የመጀመሪያ ደረጃ የካይዘን ትግበራ 
የሽልማት ሥነ-ስርዓቶች ላይ የክብር ወንበር 
እንደሚይዝም በዕለቱ ተበስሯል፡፡ 
በሌላ በኩል የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የኪነ- 
ጥበብ ማዕከል በሽልማት ሥነ-ስርዓቱ ላይ 
ተጋባዥ በመሆን ያቀረበው ትወና ከፍተኛ 
አድናቆት ተችሮታል፡፡ ማዕከሉ ባሳየው 
ብቃትም በማንኛውም ሀገራዊ የካይዘን 
ንቅናቄ መድረኮች ላይ አስተማሪ ሆኖ እንዲገኝ 
ዕድሉ ተሰጥቶታል፡፡ 
በተያያዘ ዜና ፋብሪካው አሸናፊ በሆነበት 
ሥነስርዓት ላይ ተሳታፊ ለነበረው የልዑካን 
ቡድን አባላት የፈንታሌ ወረዳ እና 
የመተሐራ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል 
አድርገውለታል፡፡ በወቅቱም የፈንታሌ 
ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ድሪርሳ እና 
የመተሐራ ከተማ ከንቲባ አቶ መሐመድ ከማል 
ውጤቱ የወረዳውና የህብረተሰቡ የጋራ ድል 
ጭምር መሆኑን በአቀባበል ሥነ ስርዓቱ ላይ 
ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ የመተሐራ ስኳር 
ፋብሪካ ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው መተሐራ 
ስኳር ፋብሪካ በሚገኘው ስታዲየም በመገኘት 
ድሉን በጋራ አክብረዋል፡፡ 
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ 
አቶ ዘነበ ይማም በአቀባበል ሥነ-ስርዓቱ ላይ 
ባስተላለፉት መልዕክት የተገኘው ወርቃማ 
ድል የመላው አመራር፣ የሠራተኛውና 
የቤተሰቡ እንዲሁም በፋብሪካው ዙሪያ 
የሚገኘው ማህበረሰብ ጭምር የትጋትና 
የጥረት ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ 
ብለዋል፡፡ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካትም 
የሁሉም ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል 
እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የግልና የልማት 
ቡድን ተሸላሚዎች በበኩላቸው በየተራ 
ባሰሙት ንግግር የተገኘውን ድል በቀጣይም 
አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማስታወቃቸውን 
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ህዝብ ግንኙነት 
ክፍል ዘግቧል፡፡ 
በተያያዘም የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በካይዘን 
ፍልስፍና ያካበተውን ልምድ ለኦሞ ኩራዝ 
ስካር ልማት ፕሮጀክት ማካፈሉ ታውቋል፡፡ 
የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለጣፋጭ 
ዜና መጽሔት ዝግጅት ክፍል ያደረሰው ዘገባ 
እንዳመለከተው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ 
በካይዘን ለረጅም አመታት ያካበተውን ልምድ 
ለሌሎች ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች 
በማስተላለፍ የክህሎትና የዕውቀት ሽግግር 
የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በመወጣት ላይ 
ይገኛል፡፡ 
የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ስራ 
አስኪያጅ አቶ ካሳ ተስፋዬ ፕሮጀክታቸው 
መተሐራን ከመሳሰሉ እህት ስኳር ፋብሪካዎች 
ልምድ በመቅሰምና ባለሙያዎችን 
በማስመጣት ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር ጥረት 
በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ 
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለፕሮጀክቱ 
በተለያዩ ዘርፎች እያደረገ ከሚገኘው ድጋፍ 
ጎን ለጎን ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር በመቀናጀት 
በፕሮጀክቱ በመገኘት ለሠራተኛው ልምዱን 
በማካፈሉ አመስግነው በካይዘን ትግበራ 
በ2007 በጀት አመት ፕሮጀክቱን ተሸላሚ 
ለማድረግ ከመላው ሠራተኛና አመራር ጋር 
በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡ 
ለአራት ቀናት በዘለቀው የልምድ ልውውጥ 
ከ1 ሺህ 250 በላይ የሆኑ የፕሮጀክቱ ቋሚ፣ 
ጊዜያዊና በማህበር ተደራጅተው በመስራት 
ላይ የሚገኙ ሰዎች ተሳታፊ መሆናቸው 
ታውቋል፡፡ 
6 7
ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r 
በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት 
የፕሮጀክቱ የአገዳ ተከላ እቅድ አፈፃፀም ስኬታማ መሆኑ ተገለፀ 
አቶ አስራቴ አለኸኝ የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ 
የፈንድቃ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች የፕሮጀክቱ ደጋፊ መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠዋል 
የጣና በለስ ስኳር ልማት 
ፕሮጀክት የ2006 የበጀት አመት 
የአገዳ ተከላ እቅድ አፈጻጸም 
ስኬታማ መሆኑን ዋና ሥራ 
አስኪያጁ ገለጹ፡፡ 
የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ 
አቶ አስራቴ አለኽኝ በዘር 
አገዳ ቆረጣና ተከላ፣ ስራዎችን 
ቆጥሮ በመስጠትና በመቀበል፣ 
እንዲሁም በየዕለቱ ግምገማ 
በማድረግ ውጤታማነትን 
ለማሳደግ ጥረት በመደረጉ 
በበጀት አመቱ 8 ሺህ ሄክታር 
መሬት በአገዳ ለመሸፈን ታቅዶ 
ከዕቅድ በላይ መከናወኑን 
አስታውቀዋል፡፡ 
በበጀት ዓመቱ በ8 ሺህ 31 
ሄክታር መሬት ላይ የተከናወነው 
የአገዳ ተከላ በአጠቃላይ 
በፕሮጀክቱ በአገዳ የተሸፈነ 
መሬት ወደ 10 ሺህ ዘጠኝ 
ሄክታር ከፍ እንዲል አስችሏል፡፡ 
በበጀት አመቱ ፕሮጀክቱ በቀን 
ከ120 እስከ 130 ሄክታር አገዳ 
የመትክል አቅም ላይ መድረሱን 
ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸው፣ 
ይህም ለቀጣይ ስራዎች 
ከፍተኛ ተሞክሮ የተገኘበት 
ነው ብለዋል፡፡ የአገዳ ተከላው 
ለአካባቢው ማህበረሰብ በርካታ 
የስራ እድል መፍጠሩንም ነው 
ዋና ስራ አስኪያጁ የተናገሩት፡፡ 
በፕሮጀክቱ አካባቢ የሚገኙ 
ነዋሪዎች የልማት ባለቤትነት 
ስሜት የበለጠ እየዳበረ 
መምጣቱን አቶ አስራቴ 
ጠቁመው፣ በማሳያነትም የጃዊ 
ወረዳ ፈንድቃ ከተማ እና 
አካባቢዋ የንግዱ ማህበረሰብ፣ 
አርሶ አደሮችና የመንግሥት 
ሠራተኞች በበጀት አመቱ 
5 ሄክታር መሬት በዘመቻ 
መትከላቸውን ጠቅሰዋል፡፡ 
በተመሳሳይ የፕሮጀክቱ ድጋፍ 
ሰጭ ሠራተኞችም 3 ነጥብ 5 
ሄክታር መሬት ላይ በዘመቻ አገዳ 
በመትከል ያሳዩት አጋርነት 
አበረታችና የፕሮጀክቱን 
አጠቃላይ ንእቅስቃሴ 
እያገዘ የመጣ በመሆኑ 
ድጋፋቸውን አጠናክረው 
እንዲቀጥሉ ዋና ሥራ አስኪያጁ 
ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 
ከጣና በለስ ስኳር ልማት 
ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ 
በአጠቃላይ 17 ሺህ 190 ዜጎች 
በተለያዩ የሙያ መስኮች የስራ 
እድል ተፈጥሮላቸው በመስራት 
ላይ እንደሚገኙ ከፕሮጀክቱ 
የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ዘገባ 
ለማወቅ ተችሏል፡፡ 
የስራ እድሉ የተፈጠረላቸው 
ዜጎች ከ10 ነጥብ 54 
ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ 
የገንዘብ ተቋማት በመቆጠብ 
ለለውጥ ራሳቸውን እያዘጋጁ 
መሆናቸውም ታውቋል፡፡ 
የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ 
የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት 
ቤት ከሰኔ 9 እስከ 30 ቀን 2006 ዓ.ም 
በመንግስት ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና 
ፕሮግራሞች እንዲሁም በሕዝብ ግንኙነትና 
ልማታዊ ሚዲያ የሠጠውን ስልጠና 
የተከታተሉ የፌዴራል መንግስት መስሪያ 
ቤቶች የኮሚዩኒኬሽን የስራ ኃላፊዎችና 
ባለሙያዎች ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም 
በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የስራ ጉብኝት 
አድርገዋል፡፡ 
130 የሚሆኑት እነዚህ ጎብኝዎቹ 
በፋብሪካው የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና 
ትግበራ ውጤቶችን ፣ በባለሙያዎች የተሰሩ 
የፈጠራ ውጤቶችን፣ የአዲሱ ፋብሪካ የምርት 
ሂደት፣ የመስኖ መሠረተ ልማት ዝርጋታ 
እና በአካባቢው አርሶ አደር በመልማት ላይ 
የሚገኘውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ ተዘዋውረው 
የጎበኙ ሲሆን፣ የፋብሪካው አመሰራረትና 
አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ በፎቶግራፍ 
ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ 
የስራ ኃላፊዎቹና ባለሙያዎቹ በጉብኝታቸው 
ወቅት እንደገለጹት የስኳር አመራረት ሂደት 
ውስብስብና ከባድ መሆኑን መረዳታቸውን 
ተናግረዋል፡፡ 
የስኳር ኢንዱስትሪ ሰፊ የሰው ኃይል 
በማሳተፍና ተጠቃሚ በማድረግ ላይ 
እንደሚገኝም በተግባር መመልከታቸውን 
ገልፀው፣ የተጀመሩት የስኳር ልማት 
ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ለበርካታ 
ኢትዮጵያውያን የስራ እድል እንደሚያስገኙ 
ተስፋ አድርገዋል፡፡ 
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ካይዘንን በመተግበሩ 
ባመጣው ለውጥና ባስመዘገባቸው ስኬቶች 
መደነቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ 
የአካባቢው አርሶ አደሮች ሸንኮራ አገዳ 
እያለሙ ለፋብሪካው በመሸጥ ተጠቃሚ 
የሆኑበት አሰራር የስኳር ልማቱ በተለያዩ 
መልኮች ልማቱ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች 
ነዋሪዎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን 
የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ 
ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከስኳር ተረፈ 
ምርቶች የኤሌክትሪክ ኃይል አመንጭቶ 
የራሱን ፍላጎት አሟልቶ ቀሪውን ለብሔራዊ 
የኃይል ቋት ማስገባቱ ልማቱ ዘርፈ ብዙ 
ጠቀሜታ ያለው መሆኑን አመላካች ነውም 
ብለዋል ጎብኝዎቹ፡፡ 
በጉብኝቱ ተሳታፊ የነበሩት የመንግስት 
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር 
ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ከጉብኝቱ በኋላ 
በሰጡት አስተያየት ፋብሪካው በማድረግ 
ላይ የሚገኘው እንቅስቃሴ በዘርፉ ስኬት 
ማስመዝገብ እንደሚቻል አመላካች ነው 
ብለዋል፡፡ በቀጣይም የፋብሪካው የስራ 
ኃላፊዎችና ሠራተኞች አሁን በማድረግ 
ላይ የሚገኙትን እንቅስቃሴ አጠናክረው 
እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡ 
የሥራ ጉብኝት አደረጉ 
ከአርጆ ዲዴሳ እና ከሰም ስኳር ልማት 
ፕሮጀክቶች አካባቢዎች የተውጣጡ 19 
ወጣቶች በትራክተር ኦፕሬተርነት ተመረቁ 
8 
9 
የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎቹና ባለሙያዎቹ ፋብሪካውን በጎበኙበት ወቅት 
ስኳር ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመተባበር 
ከአርጆ ዲዴሳ እና ከከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አካባቢዎች 
የተውጣጡ 19 አርብቶ አደርና አርሶ አደር ወጣቶችን በትራክተር 
ኦፕሬተርነት አሠልጥኖ ለሁለተኛ ጊዜ ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም 
አስመረቀ፡፡ ኮርፖሬሽኑ እስካሁን በትራክተር ኦፕሬተርነት ያሰለጠናቸው 
ወጣቶች ቁጥር 79 ደርሷል፡፡ 
ሠልጣኞቹ በጊንጪና ጫንጮ ትራክተር ኦፕሬተር ማሠልጠኛ ተቋም 
ለሁለት ወራት የሠለጠኑ ሲሆን፣ ወደመጡበት አካባቢዎች እንደተመለሱ 
በፕሮጀክቶቹ ተቀጥረው የሚሰሩበት ሁኔታ እንደሚመቻች በምረቃው 
ወቅት ተገልጿል፡፡ 
ሥልጠናው ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር በየአካባቢዎቹ ህዝብ 
ዘንድ የባለቤትነት ስሜት እንዲፈጠር እና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ 
በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በምረቃው ሥነ ስርዓት ላይ 
ስኳር ኮርፖሬሽንን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ ኤካል ነትር የህዝብ 
አደረጃጀትና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡ 
ወደፊትም በልማቱ ዙሪያ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ 
ሥልጠናዎችን የመስጠቱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለሠልጣኞችም 
በየፕሮጀክቶቹ የሥራ ዕድል እንደሚመቻች አክለው አስታውቀዋል፡፡ 
ኮርፖሬሽኑ ከስኳር ልማት አካባቢዎች የተውጣጡ አርብቶ አደርና 
አርሶ አደር ወጣቶችንና ሴቶችን በቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት 
የመለስተኛ ሙያ ክህሎት ሥልጠና በመስጠት፣ በማደራጀትና ወደ ሥራ 
በማስገባት ተጠቃሚ ማድረግ ከጀመረ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ በትራክተር 
ኦፕሬተርነት 79 እንዲሁም በኮንስትራክሽን፣ በማኒፋክቸሪንግ፣ በግብርና 
እና በመሳሰሉት የሙያ መስኮች 1 ሺህ 237 ዜጎች ሥልጠና ወስደው 
በስኳር ልማት ሥራዎች ላይ ተሰማርተዋል፡፡ 
በአርጆ ዲዴሳና ከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ለሰልጣኞቹ የስራ ዕድል ተመቻችቷል
ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r 
በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት 
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የ2006 በጀት ዓመት አፈጻጸም 
ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ 
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በ2ዐዐ6 በጀት 
ዓመት 1 ሚሊዮን 149 ሺህ ኩንታል ስኳር 
በማምረት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ 
ተገለጸ፡፡ ውጤቱ ከ2ዐዐ5 በጀት ዓመት 
ጋር ሲነፃፀር በ35ዐ ሺህ ኩንታል ብልጫ 
አሳይቷል፡፡ 
ፋብሪካው ባለፈው የምርት ዘመን 11 
ሚሊዮን 555 ሺህ 499 ኩንታል ሸንኮራ 
አገዳ የፈጨ ሲሆን፣ ይህም አሀዝ በ2005 
በጀት ዓመት ከፈጨው ጋር ሲነፃፀር በ2 
ሚሊዮን 536 ሺህ 186 ኩንታል ሸንኮራ 
አገዳ ብልጫ አሳይቷል፡፡ 
የፋብሪካ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ 
አቶ ላይንአዲስ በቀለ፣ የምርት ክፍል 
ቡድን መሪ አቶ ካሣሁን ምርከና እንዲሁም 
የቴክኒክ ቡድን መሪ አቶ ፋሚ ዳውድን 
ጠቅሶ የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነት 
ክፍል እንደዘገበው ለበጀት አመቱ የምርት 
መጠን ማደግ በአዎንታዊ አመለካከት 
ግንባታ ላይ የተሠሩ ሥራዎች ቁልፍ ሚና 
ተጫውተዋል፡፡ 
በካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍና 
አማካኝነት በልማት ቡድን ተደራጅቶ 
ችግሮችን በመፍታትና የፈጠራ ስራዎችን 
በማከናወን፤ በሠራተኛው ዘንድ 
የተፈጠረው የባለቤትነት ስሜትና ከፍተኛ 
ተነሣሽነት፣ እንዲሁም የታየው ከፍተኛ 
ዝግጁነትና ተግባራዊ ርብርብ ለምርቱ 
ማደግ ጉልህ ድርሻ እንደነበራቸው የሥራ 
ኃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡ 
ፋብሪካው ቀድሞ ከነበረበት ውጤታማ 
ያልሆነ አሰራር ተላቆ በአንድ አመት ዕድገት 
እንዲያስመዘግብ ከረዱት መሠረታዊ 
ጉዳዮች መካከል አንዱ ከጥገና ወራት 
ጀምሮ እስከ 2006 ምርት ዘመን መገባደጃ 
ድረስ ተጠያቂነት የሰፈነበት ጠንካራ 
አሠራር በመፈጠሩ መሆኑንም ዘገባው 
አመልክቷል፡፡ 
ከዚህ በተጨማሪ የክህሎትና የአመለካከት 
ክፍተቶችን ለማስተካከልና ሠራተኛውን 
ለማብቃት እንዲቻል በየደረጃው 
የተሠጡት ስልጠናዎችም ለምርታማነቱ 
ጉልህ ድርሻ እንደነበራቸው ተመልክቷል፡፡ 
የፋብሪካው አገዳ የመፍጨት አቅም 
ማደግና በፋብሪካው ምርታማነት ላይ 
ቀደም ባሉት አመታት እንቅፋት ከነበሩት 
ችግሮች መካከል አንዱ በሆነው ዕድሜ 
ጠገብ የሸንኮራ አገዳ ላይ የተወሰደው 
የመፍትሄ እርምጃ ፋብሪካው ውጤታማ 
እንዲሆን እንዳስቻሉት ተመልክቷል፡፡ 
በስኳር ኮርፖሬሽን በኩል የተሰጡ 
ተከታታይ ድጋፎችም ለምርታማነቱ ከፍ 
ማለት ቁልፍ ሚና እንደተጫወቱ ነው 
የሥራ ኃላፊዎቹ የገለፁት፡፡ 
በሥራ ኃላፊዎቹ መግለጫ በምርት 
ዘመኑ ፋብሪካውን ካጋጠሙት የቴክኒክ 
ተግዳሮቶች መካከል በዋናነት የተለያዩ 
ማሽኖች ተደጋጋሚ የቴክኒክ ብልሽቶች 
ተጠቃሽ ናቸው፡፡ 
እነዚህ የቴክኒክ ብልሽቶች በፋብሪካው 
የካይዘን የልማት ቡድን የይቻላል 
አስተሳሰብ እና የጊዜ መስዋዕትነት 
እንደተጠገኑ ነው ኃላፊዎቹ የገለጹት፡፡ 
የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የአካባቢውን ሕብረተሰብ ተጠቃሚነት 
ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው 
የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት 
በአካባቢው የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን 
ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራት 
በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡ 
የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን 
ዘገባ እንደሚያመለክተው በደቡብ ኦሞ ዞን 
ሳላማጎ ወረዳ ማኪና ጉራ በተሰኙ ቀበሌዎች 
በመንደር ለተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች የተገነቡ 
የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት 
በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ 
ብሏል፡፡ 
ፕሮጀክቱ በመስኖ የሚለማ ከ1 ሺህ 600 
ሄክታር በላይ መሬት 
አዘጋጅቶ በወረዳዎቹ 
በመንደር የተሰባሰቡ 
አርብቶ አደሮች ሸንኮራ 
አገዳ አልምተው 
ለፋብሪካው በመሸጥ 
ተጠቃሚ እንዲሆኑ 
በመስራት ላይ መሆኑን 
የፕሮጀክቱ የሕዝብ 
ግንኙነትና የማሕበራዊ 
ጉዳዮች ቡድን መሪ አቶ 
ብርሃኑ አረጋን ጠቅሶ 
የሕዝብ ግንኙነት 
ክፍሉ ዘግቧል፡፡ 
ኦሞ ኩራዝ ስካር ልማት ፕሮጀክት በካፋ 
ዞን የፕሮጀክቱ አዋሳኝ የሆኑ ቀበሌዎችን 
ከወረዳ ማዕከል ጋር የሚያገናኝ 54 ኪሎ 
ሜትር መንገድ በራሱ ማሽኖች በመስራት 
ላይ እንደሚገኝና ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ1 
ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ቡድን 
መሪው መግለጻቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡ 
በመገንባት ላይ የሚገኘው ይህ መንገድ ቀድሞ 
ምንም ዓይነት መሠረተ ልማት ያልነበራቸውን 
ቀበሌዎች ከወረዳ ማዕከል ጋር ከማገናኘት 
ባለፈ በርካታ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ 
ጠቀሜታ እንደሚያስገኝላቸው አቶ ብርሃኑ 
ተናግረዋል፡፡ 
በዞኑ ዴቻ ወረዳ የነዳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት 
አርብቶ አደር ወርማይ ወርካግዶን የመንገዱ 
መገንባት ምርቶቻቸውን ያለችግር ወደ 
ገበያ ለመውሰድና የህክምና እርዳታ በቀላሉ 
ለማግኘት እንደሚረዳቸው መናገራቸው 
ተገልጿል፡፡ 
በአሚባራ እርሻ ልማት የሸንኮራ 
አገዳ ተከላ ተጠናቀቀ 
በ2007ዓ.ም ሥራ ለሚጀምረው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ዋነኛ 
የሸንኮራ አገዳ አቅራቢ እንደሚሆን በሚጠበቀው በአሚባራ 
እርሻ ልማት በመካሄድ ላይ የነበረው የሸንኮራ አገዳ ተከላ ሙሉ 
በሙሉ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ 
በእርሻ ልማቱ በስድስት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ለተከናወነው 
የሸንኮራ አገዳ ልማት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ጥራቱን የጠበቀ 
የዘር አገዳ ማቅረቡ ታውቋል፡፡ 
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ አመራር ቡድን እና የመተሐራ እርሻ 
ምርምር ጣቢያ ባለሙዎች በእርሻ ልማቱ በመገኘት የሸንኮራ 
አገዳ ተከላና እንክብካቤ ሥራዎችን ተዘዋውረው ጐብኝተዋል፡፡ 
በዚሁ ወቅት የእርሻ ልማቱ የእስካሁን አፈፃፀም አበረታች መሆኑ 
ተገልጿል፡፡ 
በጉብኝቱ ወቅት በሥራው ላይ በተስተዋሉ ክፍተቶች ላይ 
ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት ኦፕሬሽናል 
ስታንዳርድን አስጠብቆ መሥራት እና በታዩ የአሠራር ክፍተቶች 
ላይ የማስተካከያ ዕቅዶችን በመንደፍ አፋጣኝ ርብርብ ማድረግ 
እንደሚገባ ስምምነት ተደርሶባቸዋል፡፡ 
በተለይም የአሚባራ እርሻ ልማት የካይዘን ሥራ አመራር 
ፍልስፍናን መተግበር ላይ ማተኮር እንዳለበት እና ለዚህም 
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ 
መሆኑ በውይይቱ ላይ ተመልክቷል በማለት የዘገበው የመተሐራ 
ስኳር ፋብሪካ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው፡፡ 
የአሚባራ እርሻ ልማት ኃ/የተ/የግል ማህበር በሸንኮራ አገዳ 
አብቃይነትና አቅራቢነት ከከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት ጋር 
ለመስራት ስምምነት የተፈራረመው መጋቢት 8 ቀን 2006 ዓ.ም 
ነው፡፡ 
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከ 8 ነጥብ 6 
ሚሊዮን ሊትር በላይ ኤታኖል አመረተ 
* ምርቱ በፋብሪካው ታሪክ ከፍተኛው ነው 
የመተሐራ ኤታኖል ፋብሪካ 
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በ2ዐዐ6 
በጀት ዓመት ከ8.6 ሚሊዮን 
ሊትር በላይ ኢታኖል በማምረት 
የእቅዱን 85 በመቶ ማሳካቱ 
ተገለጸ፡፡ ምርቱ የኤታኖል 
ፋብሪካው ከተቋቋመ ከ2002 
ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛው መሆኑም 
ታውቋል፡፡ 
በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ 
የኤታኖል ምርት ክፍል ቡድን መሪ 
አቶ በቀለ ምርከና ሰሞኑን በሰጡት 
መግለጫ በ2006 በጀት አመት 
የተመረተው የኤታኖል ምርት 
መጠን ፋብሪካው ከተቋቋመበት 
ከ2ዐዐ2ዓ.ም አንስቶ ካመረተው 
ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ 
አሳይቷል፡፡ 
የ2006 ምርት ካለፉት አመታት 
ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ 
ሊያሳይ የቻለው በመተሐራ 
ስኳር ፋብሪካ የተተገበረው 
የካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍና 
በመላው ሠራተኛ ዘንድ ከፍተኛ 
ተነሳሽነት በመፍጠሩ መሆኑን 
የቡድን መሪው አቶ በቀለ ምርከና 
ገልጸዋል፡፡ 
የመተሐራ ኤታኖል ፋብሪካ ምርት 
ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን 
ድረስ 10 ሚሊዮን 621 ሺህ 
112 ሊትር ሬክቲፋይድ ስፒሪት 
እንዲሁም 17 ሚሊዮን 756 ሺህ 
865 ሊትር ኢታኖል በማምረት 
ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረቡንም 
አቶ በቀለ አስታውቀዋል ፡፡ 
የኤታኖል ፋብሪካው በ2007 
በጀት አመት 12 ሚሊዮን ሊትር 
ኤታኖል ለማምረት ያቀደ ሲሆን፣ 
ዕቅዱን ለማሳካትም አመራሩና 
ሰራተኛው ከወዲሁ በቁርጠኝነት 
እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ 
ለማወቅ ተችሏል፡፡ 
ኤታኖል ከነዳጅ ጋር ተደባልቆ 
ለተሽከርካሪዎች የሀይል ፍጆታ 
በመዋል የውጭ ምንዛሪ ከማዳን 
ባለፈ አካባቢን ከብክለት 
በመከላከል ይታወቃል፡፡ 
ኢታኖል የሚመረተው በስኳር 
ምርት ሂደት ከሚገኙት ተረፈ 
ምርቶች መካከል አንዱ በሆነው 
ሞላሰስ ሲሆን፣ ከኢታኖል 
የሚገኘው ቪናስ የተባለው 
ተረፈ ምርት ደግሞ ከፊልተር 
ኬክ ጋር ተደባልቆ ለሸንኮራ 
አገዳ ማዳበሪያነት እንደሚውል 
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ህዝብ 
ግንኙነት ክፍል ያደረሰን ዘገባ 
ያመለክታል፡፡ 
በፕሮጀክቱ ለአካባቢው ህብረተሰብ ከገነባቸው የማሕበራዊ ተቋማት መካከል የንጹህ 
10 11 
መጠጥ ውሃ ይገኝበታል
ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r 
በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት 
ቆይታ 
“…ለእኔና ለወገኖቼ በፈነጠቀው ብርሃን ስደሰት እነዚያ ጓደኞቼ ይህንን ሳያዩ 
በማለፋቸው ክፉኛ አዝናለሁ፡፡” 
ተይዤ እሞታለሁ እያልኩ በስጋት ላይ ሳለሁ 
በአካባቢው ላይ የስኳር ልማት ተጀመረ፡፡ 
አሁን የስኳር ልማቱን ተከትሎ የህክምና 
እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች 
በመመቻቸታቸው ወባና መሰል በሽታዎች 
ስጋት የመሆናቸው ሁኔታ አብቅቶ በማየቴ 
የተለየ የደስታ ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡ 
የእነዚያ የጓደኞቼ ሞት ግን ልቤን ሰብሮ ነው 
ያለፈው፡፡ እግዚአብሔር ዕድሜ ሰጥቶኝ 
በዚህ ቦታ ላይ ለእኔና ለወገኖቼ በፈነጠቀው 
ብርሃን ስደሰት እነዚያ ጓደኞቼ ይህንን ሳያዩ 
በማለፋቸው ክፉኛ አዝናለሁ፡፡ 
ይህ ብቻ አይደለም ልማቱ በተለየዩ ክልሎች 
ለሚገኙ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠሩ የስኳር 
ልማቱ የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ 
ከማድረግ ባለፈ ብሔር ብሔረሰቦችንም 
አሰባስቧል፡፡ 
የህክምና አገልግሎት፣ ውሃ፣ መንገድ፣ 
መብራትና ሌሎች መሰረተ ልማቶችም 
በፕሮጀክቱ አማካይነት በመመቻቸት 
ላይ ይገኛሉ፡፡ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጅ፣ 
ሆስፒታልና መሰል አገልግሎቶች እሩቅ 
በማይባል ጊዜ ውስጥ እንደሚመቻቹ ተስፋ 
አደርጋለሁ፡፡ እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን 
የሚያስደስት ነገር አለ ? ለእኔ በዚህ አካባቢ 
እንዲህ ዓይነት ልማት ሲካሄድ ከማየት በላይ 
የሚያስደስተኝ ነገር የለም፡፡ 
አቶ አቡአለም ቡታ 
ተጓዳኝ ምርቶችና አግሮ ፕሮሰሲንግ የስኳር ኢንዱስትሪው ተጨማሪ አቅም 
በስኳር ምርት ሂደት የሚገኙትን ተረፈ ምርቶች 
በግብአትነት በመጠቀም ከሚመረቱት ተጓዳኝ 
ምርቶች መካከል በአብዛኛው ህብረተሰብ ዘንድ 
የሚታወቁት ኤታኖልና የኤሌክትሪክ ኃይል 
ናቸው፡፡ 
ኤታኖል ለተሽከርካሪ ከሚውለው ነዳጅ 
ጋር በተወሰነ መጠን በመደባለቅ አገልግሎት 
ላይ ውሎ ከፍተኛ ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታ 
ከማስገኘቱም በተጨማሪ ለአልኮል፣ለቀለም 
እና መድኃኒት ፋብሪካዎችና ለመሳሰሉት 
ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት በመዋል የውጭ 
ምንዛሪ ያድናል፡፡ 
የስኳር ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም የሚመረተው 
የኤሌክትሪክ ኃይልም አምራች ፋብሪካዎቹ 
የራሳቸውን የኃይል ፍላጎት ተጠቅመው ቀሪውን 
ኃይል ለብሔራዊ ቋት በማስረከብ በገቢ 
ተጠቃሚ ከመሆናቸውም ባሻገር የአገሪቱን 
የኃይል ፍላጎት ለማሟላት የሚደረገውን ጥረት 
ያግዛሉ፡፡ 
ፋብሪካዎቹ ከላይ ከተጠቀሱት ተጓዳኝ 
ምርቶች በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ ምጣኔ 
ሀብታዊ ጠቀሜታ የሚያስገኙ ተጓዳኝና 
ተያያዥ ምርቶችን በማምረት የአገሪቱ የምጣኔ 
ሀብት መስኮችን መደገፍ የሚያስችል ስራ 
መስራት እንደሚችሉ የበርካታ አገሮች ልምድና 
ተሞክሮዎች ያመለክታሉ፡፡ የየአገራቱ ልምድና 
ተሞክሮዎች ብቻም ሳይሆኑ በዘርፉ የተደረጉ 
ጥናቶችም ይህንን አረጋግጠዋል፡፡ 
ስኳር ኮርፖሬሽንም እነዚህን እውነታዎች 
መሠረት በማድረግ የተጓዳኝ ምርቶችንና ሌሎች 
ተያያዥ ስራዎችን በበላይነት የሚመራ “የተጓዳኝ 
ምርቶችና አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ” አቋቁሞ 
ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ 
ይገኛል፡፡ የዘርፉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ 
አታክልቲ ተስፋይ ዘርፉ የተቋቋመበትን ዓላማ 
ሲገልፁ የስኳር ፋብሪካዎች ስኳር ማምረት 
የመጨረሻ ግባቸው ቢሆንም ብዙ ሊሰሯቸው 
የሚችሉትና የሚገቡ ተጓዳኝ ስራዎች አሉ 
ይላሉ፡፡ 
ከነዚህ ስራዎች መካከል ኢትዮጵያ ካላት 
የእንስሳት ሀብት ተገቢውን ጥቅም እንዳታገኝ 
ማነቆ ሆኖ የቆየውን የእንስሳት መኖ በሚፈለገው 
መጠንና ጥራት ለማምረት ሞላሰስና ባጋስ 
በመባል የሚታወቁትን የስኳር ተረፈ ምርቶች 
ከሌሎች ተጨማሪ ውህዶች ጋር በማደባለቅ 
የሚዘጋጀው የእንስሳት መኖ የማቀነባበር ሥራ 
በዋነኛነት ይጠቀሳል፡፡ 
በዚህ መነሻነት ኮርፖሬሽኑ ከስኳር ተረፈ ምርት 
በፋብሪካ ተቀነባብሮ የሚዘጋጀውን የእንስሳት 
መኖ በመጠቀም በራሱ ቦታ የእንስሳት እርባታ 
ማካሄድ፣ ከብት ማድለብ፣ የወተት ላሞችን 
ማርባትና የወተት ተዋጽዖዎችን ማቀነባበሪያ 
ፋብሪካ ማቋቋም የመሳሰሉ ስራዎችን መስራት 
ይችላል፡፡ 
በሌላ በኩል በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለረጅም 
ጊዜ ሲሰራበት የቆየውን የፍራፍሬ ማልማት 
ተሞክሮ ወደ ሌሎች ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች 
በማስፋፋት በስፋት ፍራፍሬ ማልማትና 
በፋብሪካ ማቀነባበር የሚቻልበት ሰፊ እድልም 
መኖሩን ነው ዳይሬክተሩ የሚያብራሩት፡፡ 
እነዚህን ስራዎች ለመፈጸምም የዘርፉን የሰው 
ኃይል ከማሟላት ባለፈ የተለያዩ ተግባራት 
በመከናወን ላይ ናቸው፡፡ 
“ስራው በሃሳብ ደረጃ ሲታሰብ ከእኛ 
አስቀድመው ስራውን የጀመሩ የሌሎች አገሮችን 
ተሞክሮ መቅሰም የግድ ነበር፡፡ ለዚህም ሲባል 
ከኮርፖሬሽናችን ጋር ለመስራት የመግባቢያ 
ሰነድ የተፈራረመውን የሱዳኑን ኬናና ስኳር 
ኩባንያ ጎብኝተናል፡፡ ኩባንያው የስኳር ተረፈ 
ምርቶችን በግብአትነት ተጠቅሞ የእንስሳት 
መኖ በማቀነባበር ረገድ ጥሩ ተሞክሮ አለው፡፡ 
ይህም በ2007 የበጀት አመት ልናከናውናቸው 
ለምናስባቸው ተግባራት እንደመነሻ ሆኖልናል” 
በማለት ይገልጻሉ፡፡ 
በዚህ ረገድ መንግስት ቴክኖሎጂውና 
ፋይናንሱ ካላቸው አገሮች ወይም 
ድርጅቶች ጋ ር በ ጋራ መ ስራት አ ስፈላጊ 
መሆኑን ያምናል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በዘርፉ ያለውን 
እምቅ አቅምና በተለይም በቴክኖሎጂና በገበያ 
ትስስር ረገድ አብሮ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት 
የሚገልጽ የፍላጎት መግለጫ በስኳር ልማቱ 
ከኮርፖሬሽኑ ጋር በመስራት ላይ ለሚገኙት 
ኮምፕላንትና ካሚስ ለሚባሉ ሁለት የቻይና 
ኩባንያዎች ልኳል፡፡ 
ከሁለቱ ኩባንያዎች መካከል የወልቃይት 
ስኳር ፋብሪካን ለመገንባት ወደ ስራ 
በመግባት ላይ የሚገኘው ካሚስ ዘርፉ ቀድሞ 
ብዙ እንዲያስብና እንዲሰራ የሚያደርጉ 
ምክረ ሐሳቦችን (ፕሮፖዛል) በአጭር ጊዜ 
ማቅረቡን አቶ አታክልቲ ይናገራሉ፡፡ ምክረ 
ሐሳቦቹ ከስኳር ተረፈ ምርቶች የእንስሳት 
መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እንዴት መገንባት 
እንደሚቻል፣ የወተት ላሞች እርባታ ጣቢያ 
ማቋቋም የሚያስችል ዲዛይን፣ የሸንኮራ አገዳ 
ገለባ ወይም ባጋስ በቀላሉ ለእንስሳት ምግብነት 
እንዲውል ወይም (ሃይድሮላይዝ) የሚያደርግ 
ቴክኖሎጂ እና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ወይም 
(ኦርጋኒክ ፈርትላይዘር) ማምረት የሚያስችል 
ቴክኖሎጂዎችን ያካተቱ ናቸው፡፡ 
ዘርፉ አገሪቱ ከእንስሳት ሃብት ተጠቃሚ መሆን የሚያስችላትን 
ተግባራት እንደሚያከናውን ይጠበቃል 
“ቀጣይ የዘርፉ ስራ የሚሆነው የትኛውን ስራ 
የት እንስራ የሚሉትን ጥያቄዎች የኮርፖሬሽኑ 
ማኔጅመንት ከወሰነ በኋላ ብዙ ቴክኖሎጂ 
የማይጠይቀውን የከብቶች ማድለብንና የሰብልና 
የፍራፍሬ ልማቱን በሁሉም ፋብሪካዎችና 
ፕሮጀክቶች ማስፋፋት ነው፡፡ ይህ ደግሞ 
የተያዘው በጀት አመት ዓቢይ ተግባር ይሆናል” 
በማለት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የበጀት 
አመቱን የዘርፉን እቅድ ያብራራሉ፡፡ 
ከዚህ ቀደም በተለምዶ ከሸንኮራ አገዳ ልማት 
ጋር በስብጥር የሚዘሩት የቦሎቄ፣ የአኩሪ አተርና 
የጥጥ ምርቶች በስብጥርና ጦም በሚያድሩ 
መሬቶች ላይ የማስፋፋት ስራዎችም በበጀት 
አመቱ ከሚከናወኑ የዘርፉ ተግባራት መካከል 
ይገኛሉ፡፡ 
ስኳር ኮርፖሬሽን እነዚህን ተጓዳኝ ምርቶች 
በማምረት ተጠቃሚ ከመሆን ባሻገር የአገሪቱን 
የእንስሳት ሃብት በመደገፍ ዘርፉን ወደላቀ ደረጃ 
እንዲደርስ ማድረግ ዋና ዓላማው ነው ይላሉ 
አቶ አታክልቲ፡፡ መንግስት ለዚህ ስራ ትኩረት 
የሰጠው ከዚህ እውነታ በመነሳት እንደሆነ 
በማከል፡፡ 
“አገሪቱ ካላት እምቅ የእንስሳት ሃብት አኳያ 
ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም 
አላገኘችም፡፡ ዘርፉም ማደግ በሚገባው ደረጃ 
አላደገም፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት የእንስሳት 
መኖ በብዛትና በጥራት አለመገኘት ነው፡፡ 
ኮርፖሬሽኑ ደግሞ ይህንን ክፍተት የመሙላት 
አቅም አለው፡፡ ይህንንም ታላቅ አገራዊ ተልዕኮ 
እናሳካለን” ይላሉ፡፡ 
በመጨረሻም ስራው ካለው ስፋት አንጻር 
ኮርፖሬሽኑ ብቻውን የሚያከናውነው ባለመሆኑ 
በዘርፉ መሠማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች 
እድሉ ክፍት መሆኑን አቶ አታክልቲ ይናገራሉ፡፡ 
«ይህንን አካባቢ በቅርበት ስለማውቀው 
ለልማት ውሎ ሳይ ይገርመኛል፡፡ የአል- 
ሀበሻ ኃላፊነቱ የተወሰነ የስኳር ፋብሪካ 
በዚህ አካባቢ የስኳር ልማት ከመጀመሩ 
በፊት አካባቢው በረዣዥም ሳርና 
እጽዕዋት የተሸፈነ በመሆኑ የአንበሳ፣ 
ጎሽ፣ አ ጋዘን፣ ጉ ማሬ፣ ዝ ንጀሮና ሌ ሎች 
የዱር አራዊት መናኸሪያ ነበር፡፡ በዚህ 
ቦታ ላ ይ የ ስኳር ልማት ይ ካሄዳል ብ ዬ 
አስቤ አላውቅም ፡፡ መንግስት በዚህ ቦታ 
ልማት እንዲካሄድ አድርጎ እኔንና ቤተሰቦቼን 
እንዲሁም ሌሎች ወገኖቼን የልማቱ 
ተጠቃሚ በማድረጉ አመሰግናለሁ» በማለት 
የሚናገሩት የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት 
ፕሮጀክት ሰራተኛ ናቸው፡፡ 
ፕሮጀክቱ በተቋቋመበት አካባቢ ተወልደው 
ያደጉ በመሆናቸው አካባቢውን ጠንቅቀው 
ያውቁታል፡፡ በአካባቢው ልማት ሲካሄድ 
ከማየት በላይ የሚያስደስታቸው ነገር 
እንደሌለም ነው የሚናገሩት፡፡ የፕሮጀክቱ 
የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ከእንግዳው 
ጋር ያደረገውን ቆይታ እንደሚከተለው 
አቅርበነዋል፡፡ 
ጥያቄ፡ ስምዎትን የቤተሰብዎን ሁኔታ 
በአጭሩ ቢነግሩን ? 
ስሜ አቡዓለም ቡታ ሁሉቃ ይባላል፡፡ የስራ 
ድርሻዬ በፋይናንስ፣ አቅርቦትና ፋሲሊቲ 
ማኔጅመንት ዘርፍ የጠቅላላ መጋዘን ኃላፊ 
ነኝ፡፡ ባለትዳርና የስድስት ልጆች አባት ነኝ፡፡ 
ጥያቄ፡ የዲዴሳ ሸለቆ የስኳር ልማቱ 
በአካባቢው ከመጀመሩ በፊት ምን ይመስል 
ነበር? 
የስኳር ል ማት ፕ ሮጀክቱ 
በተቋቋመበት የዲዴሳ ሸለቆ ተወልጄ 
ያደግሁበት አካባቢ በመሆኑ ጠንቅቄ 
አውቀዋለሁ፡፡ ምቹ እንዲሆን ተደርጎ ለልማት 
መዋሉ ይገርመኛል፡፡ የአል-ሃበሻ ኃላፊነቱ 
የተወሰነ የስኳር ፋብሪካ ከመቋቋሙ በፊት 
አካባቢው በረዣዥም ሳርና እፅዋት የተሸፈነ 
ስለነበር የአንበሳ፣ የጎሽ፣ የአጋዘን፣ የጉማሬ፣ 
የዝንጀሮና የሌሎች የዱር አራዊት መናኸሪያ 
ነበር፡፡ 
በዚህ ቦታ ላይ የስኳር ልማት ይካሄዳል ብዬ 
አስቤ አላውቅም፡፡ ዛሬ ይህ ቦታ በተለምዶ 
“ነጩ ወርቅ” ተብሎ የሚጠራው ስኳር 
የሚመረትበት ቦታ ለማድረግ የተሰሩት 
ስራዎች በጣም አስደሳች ናቸው፡፡ መንግስት 
በዚህ ቦታ ላይ ልማት እንዲካሄድ አድርጎ 
እኔንና ቤተሰቦቼን እንዲሁም ሌሎች 
ወገኖቼን የልማቱ ተጠቃሚ በማድረጉ 
ሳላመሰግነው አላልፍም፡፡ 
ጥያቄ፡ የስኳር ልማቱ ለእርስዎና ለአካባቢው 
ሕብረተሰብ ምን ጥቅም አስገኘ? 
ፕሮጀክቱ ለእኔና ለአካባቢው ማሕበረሰብ 
ያስገኘውን ጠቀሜታ ከራሴ ገጠመኝ 
ተነስቼ ልንገርህ፡፡ በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ 
አሁን ኮማንድ - ሁለት ተብሎ በሚጠራው 
የሸንኮራ አገዳ ማሳ አካባቢ የእርሻ መሬት 
ነበረኝ፡፡ ሌሎች ሁለት ጓደኞቼም በዚሁ 
አካባቢ የእርሻ መሬት ስለነበራቸው የእርሻ 
ስራውን በጋራ ነበር የምንሰራው፡፡ 
አካባቢው ቆላማና ኃይለኛ የወባ ወረርሽኝ 
የነበረበት ከመሆኑም በላይ እንዳሁኑ 
የሕክምና እና የሌሎች መሰረተ-ልማት 
ተቋማት አልነበሩም፡፡ 
እነዚያ ሁለት ጓደኞቼ በወባ በሽታ ታመው 
በህክምና ዕጦት በሞት ተለዩኝ፡፡ የእኔም 
ዕጣ ፈንታ በወባ በሽታ ተይዞ መሞት 
እንደሆነ ነበር የማስበው፡፡ ከዛሬ ነገ በወባ 
12 13
ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r 
14 በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት 
15 
አርጆ ዲዴሳ ስኳር 
ስኳር ልማት ፕሮጀክት 
የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት 
በምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ብሔራዊ 
ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ወለጋና 
በኢሉአባቦራ ዞኖች በዲዴሳ ሸለቆ 
ውስጥ ከአዲስ አበባ ጅማ-በደሌ-ነቀምቴ 
በሚወስደው መንገድ 540 ኪሎ ሜትር 
ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ 
ፕሮጀክቱ በኢሉአባቦራ፣ በምስራቅ 
ወለጋና በጅማ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ 49 
ቀበሌዎችን የሚያካትት ሲሆን በ50 ሺህ 
ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ 
አገዳ መሬት ባለቤት ነው፡፡ የአካባቢው 
ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ በአማካይ 1350 
ሜትር ሲሆን፣ የአየር ሁኔታው ሞቃታማ 
ነው፡፡ አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኑ 
ደግሞ 1400 ሚሊ ሊትር ይደርሳል፡፡ 
የዝናብ ስርጭቱም ከግንቦት እስከ ጥቅምት 
ይዘልቃል፡፡ በአብዛኛው ጥቁርና አልፎ 
አልፎ ቀይ ቡናማ አፈር የሚገኝበት ይህ 
አካባቢ ከአየር ንብረቱ ጋር ተዳምሮ 
ለሸንኮራ አገዳ ልማት ምቹና ተስማሚ 
እንዲሆን አስችሎታል፡፡ 
የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት አል 
ሐበሻ ስኳር ፋብሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ 
የግል ኩባንያ በሚል መጠሪያ የፓኪስታን 
ዜግነት ባለው ባለሃብት እ.ኤ.አ አቆጣጠር 
በ2009 ተቋቁሞ የነበረ ሲሆን፣ ኩባንያው 
ፕሮጀክቱን ማስቀጠል ባለመቻሉ ከስኳር 
ኮርፖሬሽን ጋር የሽያጭ ውል በመፈጸም 
እ.ኤ.አ ከነሐሴ 2012 ጀምሮ ወደ ስኳር 
ኮርፖሬሽን ንብረትነት ተዘዋውሯል፡፡ 
ፕሮጀክቱ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን 
በተዘዋወረበት ወቅት የፋብሪካው የግንባታ 
ስራ ከዘጠና በመቶ በላይ የተጠናቀቀ 
ሲሆን፣ ከ2005 በጀት ዓመት ጀምሮ የስራ 
አመራር አባላት ተመድቦለትና በየደረጃው 
የሰው ኃይል ተሟልቶለት ተልዕኮውን 
ለማሳካት እየሰራ ይገኛል፡፡ በፕሮጀክቱ 
የተገነባው ፋብሪካ በመጀመሪያ ምዕራፍ 
በቀን 8 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም 
ይኖረዋል፡፡ አጠቃላይ ዲዛይኑ ግን ወደፊት 
12 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም 
እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ 
ፋብሪካው በግብአትነት የሚጠቀምበትን 
ሸንኮራ አገዳ ለማልማት የሚውለው ውሃ 
ከዲዴሳ ወንዝ የሚያገኝ ሲሆን፣ በወንዙ 
ላይ የሚገነባውን ግድብ የኦሮሚያ ውሃ 
ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት በማከናወን 
ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በቀጥታ 
ከወንዙ ውሃ በፓምፕ በመሳብ 1 ሺህ 665 
እናስተዋውቃችሁ 
ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ መሸፈን 
ተችሏል፡፡ ፋብሪካው ከስኳር ምርቱ 
በተጨማሪ ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም 
የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ራሱን 
ከመቻል አልፎ ቀሪውን ለብሔራዊ ቋት 
እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡ ከፍተኛ 
የኤታኖል ምርት የማምረት አቅምም 
ይኖረዋል፡፡ 
በ2007 የበጀት አመት ምርት እንደሚጀምር 
የሚጠበቀው የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ 
በአሁኑ ጊዜ የፋብሪካውን ቀሪ የግንባታ 
ስራ ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ አስፈላጊ 
ቅድመ ዝግጅቶች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡ 
ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ስራ 
በሚጀምርበት ወቅት በራሱ ይዞታ 
ከሚያለማው የሸንኮራ አገዳ በተጨማሪ 
የአካባቢውን አርሶ አደሮች በአውትግሮወር 
ልማት በማደራጀት የሸንኮራ አገዳ 
አልምተው ለፋብሪካው በማቅረብ 
ኑሮአቸውን እንዲያሻሽሉ እንቅስቃሴዎች 
በመደረግ ላይ ናቸው፡፡ ለዚህም እንዲረዳ 
ከዞን፣ ከወረዳና ከቀበሌ አመራር አካላት 
ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች 
ተደርገዋል፡፡ 
የሥራ ድርሻ ያልገደበው 
የምርታማነት ርብርብ በፊንጫአና 
ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች 
(የክረምቱን ወራት ለመሻማት 
የፋብሪካዎቹ አመራሮችና የቢሮ 
ሰራተኞች በእርሻ ማሳ)
መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልዎ!

More Related Content

What's hot

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ምየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006Ethiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርEthiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006 የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006 Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ምMeresa Feyera
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007Ethiopian Sugar Corporation
 

What's hot (12)

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ምየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006ጣፋጭ ዜና መጽሄት  ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 2. ቁጥር 3 መጋቢት 2006
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
 
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006 የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
 

More from Ethiopian Sugar Corporation

Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Ethiopian Sugar Corporation
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 

More from Ethiopian Sugar Corporation (17)

Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
 
Ethiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry ProfileEthiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry Profile
 
Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI] Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI]
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
 
Ethiopian sugar industry profile
Ethiopian sugar industry profileEthiopian sugar industry profile
Ethiopian sugar industry profile
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
 
Ethiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry ProfileEthiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry Profile
 
Comparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industryComparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industry
 
External vacancy
External vacancyExternal vacancy
External vacancy
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 3. ቁጥር 2 መስከረም 2007

  • 1. ጣፋጭ ዜና መፅሔት ራዕይ፡ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በአለም ተወዳዳሪ የሆነ የስኳር ኢንዱስትሪ መፍጠር ቅፅ 3. ቁጥር 1- መስከረም 2007 ዓ.ም www.etsugar.gov.et.com || www.facebook.com/etsugar ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የበጀት አመት መሻሻል የታየበት አፈጻጸም አስመዘገበ ስኳር ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው የበጀት አመት በዋናው መሥሪያ ቤት፣ በስኳር ፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች መሻሻል የታየበት አፈጻጸም አስመዘገበ፡፡ የ2006 በጀት ዓመት እቅድንና ፍኖተ-ካርታውን መሰረት አድርገው የተሰሩ ሥራዎችና የተመዘገቡ ውጤቶች ኮርፖሬሽኑን በ2005 ዓ.ም መጨረሻ ከነበረበት ወደፊት ያራመዱና ለቀጣይ የዘርፉ የልማት ስራዎች መሠረት የጣሉ መሆናቸውን አመታዊ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አመልክቷል ፡፡ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተዘጋጀው የፍኖተ-ካርታ እቅድ መሰረት ተንዳሆን ጨ ምሮ በ አራት ስ ኳር ፋ ብሪካዎች 4 93,321 ቶ ን ስ ኳር የውጤት ተኮር ሥርዓት ሥልጠና ተሰጠ ስትራቴጂያዊ የአመራር ሥርዓትን በመተግበር የስኳር ኮርፖሬሽንን ራዕይና ተልዕኮ እውን ለማድረግ የሚረዳ አቅም ለመፍጠር የሚያስችል የውጤት ተኮር (ቢኤስሲ) ሥርዓት ስልጠና ለኮርፖሬሽኑ 405 ከፍተኛና መካከለኛ የስራ መሪዎች ተሰጠ፡፡ ስልጠናው ለስራ መሪዎቹ የውጤት ተኮር ሥርዓትን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ፣ ዕውቀትና ክህሎት ያስጨበጠ መሆኑንና ለትግበራውም የስትራቴጂ አመራር ቡድን፣ የስትራቴጂ ቀረጻ ቡድን፣ የኮሚዩኒኬሽንና የለውጥ አስተግባሪ ቡድን መቋቋሙን የኮርፖሬሽኑ የለውጥ ትግበራ ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡ »» ወደ ገጽ 4 ዞሯል የኦሞ-ኩራዝ ስኳር ልማትፕሮጀክት አካባቢ ነዋሪዎች ልማቱ እንዲፋጠን ጠየቁ የኦሞ-ኩራዝ ስኳር ልማት እየተካሄደ በሚገኝበት አካበቢ ነዋሪ የሆኑ የአካባቢው ተወላጆች የስኳር ልማቱ ተፋጥኖ ወደሚኖሩበት አካባቢ እንዲደርስና በፕሮጀክቱ የስራ እንቅስቃሴ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ »» ወደ ገጽ 4 ዞሯል »» ወደ ገጽ5 ዞሯል የስልጠናው ተሳታፊዎች በፕሮጀክቱ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች የልማቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተረድተዋል መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልዎ! በውስጥ ገፆች መተሐራ ስኳር ፋብሪካ የካይዘን አንደኛ ደረጃ ትግበራ አገር አቀፍ ውድድር አሸናፊ ሆነ ››ገጽ 6 ተጓዳኝ ምርቶችና አግሮ ፕሮሰሲንግ የስኳር ኢንዱስትሪው ተጨማሪ አቅም ››ገጽ 12 “…ለእኔና ለወገኖቼ በፈነጠቀው ብርሃን ስደሰት እነዚያ ጓደኞቼ ይህንን ሳያዩ በማለፋቸው ክፉኛ አዝናለሁ፡፡” ››ገጽ 13 በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A
  • 2. የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት በአሁኑ ወቅት በአገራችን የስኳር ፍላጎት የደረሰበት ደረጃ ሲታይ የዛሬ 60 ዓመት በላንድሮቨር መኪና በየገበያው በመዘዋወር ስኳርን ከሕዝባችን ጋር ለማስተዋወቅ ብርቱ ጥረት ተደርጎ እንደነበር ማመን ይከብዳል፡፡ በወቅቱ ሻይ በ”ቅመሱልኝ” በነጻ በመጋበዝ ሕዝቡን ከምርቱ ጋር ለማላመድ የተደረገው እንቅስቃሴ ከብዙ ጥረት በኋላ ውጤት ማስገኘት ችሏል፡፡ በዚህ ሁኔታ የተጀመረው የስኳር ትውውቅ ዛሬ ላይ ታሪኩን ለውጦ ከሕዝባችን የኑሮ መሻሻል እና ስኳርን በግብዓትነት ከሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ጋር በተያያዘ በጣም ተፈላጊ ምርት እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህም በማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የነባር ስኳር ፋብሪካዎችን በማዘመን የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ ዋንኛው ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህን ተከትሎም ግዙፉ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን ከመገንባት አንስቶ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን “የስኳር አብዮት” በሚያስብል ሁኔታ በዘርፉ መጠነ ሰፊ የስኳር ልማት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ አኳያ በተለያዩ የአገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች 10 አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት የሚያስችሉ የመስኖ፣ የአገዳ ተከላ፣ የፋብሪካ እና የቤቶች ግንባታ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ከተጀመሩ አራት አመታት ተቆጥረዋል፡፡ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ የመጣውን የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎት ለማሟላት እና ምርቱን ኤክስፖርት በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ክቡር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ባደረግነው ርብርብ ያቀድናቸውን ግቦች ሙሉ በሙሉ ባናሳካም እንኳ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል የታየበት አፈጻጸም ማስመዝገብ ችለናል፡፡ ከዚህ አንጻር የተከናወኑት ሥራዎች በ2005 ዓ.ም መጨረሻ ከነበርንበት ወደፊት ያራመዱንና ለቀጣዩ ልማት ትልቅ መሠረት የጣሉ ናቸው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ባሳለፍነው የዕቅድ ዘመን ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን ጨምሮ 493ሺህ 231 ቶን ስኳር ለማምረት የታቀደ ቢሆንም ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ወደ ምርት ባለመግባቱ፣ የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካም በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ በዘነበው ከባድ ዝናብ እና ከሌሎች የፋብሪካ የቴክኒክ ሥራዎች ጋር በተያያዙ ውስጣዊ ችግሮች ምክንያት ከእቅድ በታች 325ሺህ 25ቶን ስኳር ተመርቷል፡፡ ይሁንና ይህ የስኳር መጠን ከ2005 በጀት ዓመት ምርት ጋር ሲነጻጸር የ1ሚሊዮን ኩንታል ያህል ብልጫ አሳይቷል፡፡ የአገዳ ልማትን በተመለከተም በነባርና አዳዲስ ፕሮጀክቶች በ2007 ወደ ምርት የሚገቡ ፋብሪካዎችን የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት አስተማማኝ ለማድረግ 30,733 ሄክታር መሬት በአገዳ መሸፈን ተችሏል፡፡ ይህ አፈጻጸም በ2005 በጀት ዓመት መጀመሪያ ላይ ከደረስንበት 8ሺህ ሄክታር ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ 129ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች ተጨማሪ የስራ እድል መፍጠር የቻልንባቸው በርካታ ውጤታማ ሥራዎች ለቀጣይ ግቦቻችን ስኬት አስተማማኝ መደላድል ናቸው ብለን እናምናለን፡፡ በያዝነው ዓመት ተንዳሆ 1 እና 2፣ ከሰም፣ አርጆ ዲዴሳ፣ ጣና በለስ 1 እና 2 እንዲሁም የኩራዝ 1 ስኳር ፋብሪካዎች ወደ ምርት እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡ ከፋብሪካ ግንባታ ጎን ለጎንም በስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ተጨማሪ 33,574 ሄክታር መሬት የአገዳ ልማት በማካሄድ የፕሮጀክቶችን አጠቃላይ የአገዳ ልማት 82ሺህ ሄክታር ያህል ለማድረስ ታቅዷል፡፡ በነባር ስኳር ፋብሪካዎችም 5,009 ሄ/ር መሬት ያህል የሸንኮራ አገዳ ለመትከል የሚያስችሉ ሥራዎችን ለማከናወን ውጥን ተይዟል፡፡ የስኳር ምርትን በተመለከተም በ2007 በጀት ዓመት መጨረሻ ከ1.2 ሚሊዮን ቶን በላይ ስኳር ለማምረት የታቀደ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 665 ሺህ 438 ቶን ወደ ውጭ በመላክ 311 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል፡፡ አመታዊ የኤታኖል ምርትን አሁን በመተሃራ እና ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች አማካኝነት ከደረስንበት 19 ሚሊዮን 745 ሺህ ሊትር ወደ 30 ሚሊዮን 278 ሺህ ሊትር የማሳደግ ግብም ተጥሏል፡፡ 189 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል በማምረት 46 ሜጋ ዋቱን ለአገሪቱ ማዕከላዊ የኃይል ቋት የማቅረብ ሥራዎችም የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድ ግቦቻችን ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ሌላው የዕቅዳችን አካል የሆነው ሞላሰስና ባጋስ በመባል የሚታወቁትን የስኳር ተረፈ ምርቶች ከሌሎች ተጨማሪ ውህዶች ጋር በማደባለቅ የእንስሳት መኖ የማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለማቋቋም የጀመርነው እንቅስቃሴ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የስኳር ተረፈ ምርቶችን በግብአትነት ተጠቅሞ የእንስሳት መኖ በማቀነባበር ጥሩ ተሞክሮ ካለው የሱዳኑ ኬናና ስኳር ኩባንያ ልምድ ተወስዷል፡፡ ከመኖ ማዘጋጀቱ ሥራ በተጎዳኝም የእንስሳት ማድለብያ ጣቢያ ለማቋቋም የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች በመከናወን ላይ ሲሆኑ፣ እነዚህ ሥራዎች በብዙ መልኩ ለአገሪቱ የጎላ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለስኳር ኢንደስትሪው ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥሩ ይታመናል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በተያዘው በጀት ዓመት በዘርፉ ከ100ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ተጨማሪ የሥራ እድል ለመፍጠር ከሚያመቻቸው መደላድል በተጨማሪ የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው የቆላማ አካባቢዎች ለረጅም ዘመን የልማት ተጠቃሚ ሳይሆኑ ለቆዩ ሕዝቦች በመስኖ ሊለማ የሚችል መሬት ከማመቻቸት ጀምሮ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመሰረተ ልማት አውታሮችን የመገንባት ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ በአጠቃላይ ለዕቅድ ዓመቱ ግቦቻችን ስኬት በቅርቡ ተግባራዊ የምናደርገውን ስትራቴጂያው የውጤት ተኮር ሥርዓት ሥራ ላይ ለማዋልና አሁን ውጤት እያመጣንበት ያለውን የካይዘን የአመራር ፍልስፍና ይበልጥ አጠናክረን ለመቀጠል የሚያስችለንን የለውጥ ሥርዓት እየተከተልን እንገኛለን፡፡ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት በአገራችን በ”ቅመሱልኝ” ተዋውቆ ዛሬ ላይ ተፈላጊነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ስኳር ለአገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝበት ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡ በዚህ ረገድ በአዲሱ አመት አዲስ ብስራት ለማሰማት ተስፋ መሰነቃችንን ስገልጽ መላው ኢትዮጵያውያን በተሰማሩባቸው የሥራ መስኮች ሁሉ የአገራችንን ህዳሴ እውን ለማድረግ የጀመሩት ጥረት የተሳካ እንዲሆን በመመኘት ነው፡፡ መልካም ዘመን!
  • 3. ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የበጀት... የውጤት ተኮር ሥርዓት ሥልጠና... »» ከገጽ 1 የዞረ »» ከገጽ 1 የዞረ በዋና መስሪያ ቤት፣ በፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች ለሚገኙ ሠራተኞች ተመሳሳይ ሥልጠና መስጠትና የኮርፖሬሽኑን ውጤት ተኮር ሥርዓት ስትራቴጂያዊ ሰነድ ማዘጋጀት ቀጣይ ስራዎች እንደሚሆኑም ዳይሬክቶሬቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡ የውጤት ተኮር ሥርዓቱ ከኮርፖሬሽኑ ራዕይና ተልዕኮ የመነጨ ስትራቴጂያዊ እቅድ በማዘጋጀት ሀብት በአግባቡ ተጠቅሞ ለውጤት የማብቃት፤ የቡድንና የግለሰብ ተግባራትና አፈፃፀም ከተቋሙ ስትራቴጂያዊ እቅድ ጋር አስተሳስሮ ለመፈጸም፤ የተቋም፣ የቡድንና የግለሰብ አፈፃፀም ውጤትን ለመመዘንና ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲሻሻል ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ዳይሬክቶሬቱ አስረድቷል፡፡ እንዲሁም የተቋሙን ስትራቴጂያዊ እቅድ አፈፃፀም ውጤትን ከማትጊያ ሥርዓት ጋር በማስተሳሰር የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ ይረዳል ብሏል፡፡ ስትራቴጂያው የውጤት ተኮር ሥርዓትና የካይዘን የአመራር ፍልስፍና አንዱ የአንዱን ክፍተት በመሙላት እርስ በርስ ተሳስረውና ተመጋግበው የኮርፖሬሽኑን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት የሚረዱ የለውጥ መሳሪያዎች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡ የውጤት ተኮር ሥርዓት በካይዘንና በሌሎች የለውጥ መሳሪያዎች የተገኘውን ውጤት ለመመዘን የሚያስችል የለውጥ መሳሪያ ከመሆኑም በላይ ስትራቴጂያዊ የውጤት ተኮር ሥርዓትና ካይዘን ፈፃሚዎች የጋራ ግብ ይዘው የቡድን ስሜትን በመፍጠር የጋራና የቡድን ውጤት ለማምጣት እንዲሰሩም ይረዳል ተብሏል፡፡ ስትራቴጂያዊ የውጤት ተኮር ሥርዓትና ካይዘን አመለካከትን በመቀየር ቀጣይነት ያለው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ የለውጥ መሳሪያዎች በመሆናቸው ኮርፖሬሽኑን ውጤታማ ለማድረግ ሁለቱንም በቅንጅት ስራ ላይ ማዋሉ ተገቢ እንደሆነም ነው ዳይሬክቶሬቱ ያመለከተው፡፡ የውጤት ተኮር ሥርዓት አንድ ተቋም ከተሰጠው ራዕይና ተልዕኮ አንፃር ሀብቱን ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድ በመምራት ለውጤት የሚያበቃበት፣ ያስመዘገበውን ውጤት የሚለካበትና የተግባቦት (ኮሚዩኒኬሽን) ስራ የሚሰራበት የለውጥ መሳሪያ ነው፡፡ የኦሞ-ኩራዝ ስኳር ልማትፕሮጀክት አካባቢ ነዋሪዎች ልማቱ እንዲፋጠን ጠየቁ የኦሞ-ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት እየተካሄደ በሚገኝበት አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የቦዲ፣ የሙርሲና የሜኢኒት ብሔረሰቦች የጎሳ መሪዎች፣የአገር ሽማግሌዎች፣ሴቶችና ወጣቶች ከስኳር ኮርፖሬሽንና ከደቡብ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መስተዳድር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ባደረጉት ውይይት የስኳር ልማቱ ሥራ የደረሰበት አካባቢ ሕብረተሰቡ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ እንደሆነ ማየታቸውን በመጥቀስ መንግሥት ልማቱን አንዲያሳልጥና ወደሚኖሩበት አካባቢ እንዲያደርስና እነሱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን ሄደው መጎብኘት እንደቻሉና በዚህም በአካባቢያቸው እየተገነባ ያለው ስኳር ፋብሪካ ስኳር ማምረት የሚጀምርበትን ጊዜ በጉጉት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ እነዚሁ ከደቡብ ኦሞ፣ከከፋ እና ከቤንቺ ማጂ ዞኖች የተውጣጡና የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑ የቦዲ፣የሙርሲና የሜኢኒት ብሔረሰቦች ተወላጆች አመልክተዋል፡፡ የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ በአካባቢያቸው በመጀመሩ ከእርሻ ስራ ጋር በመተዋወቅ አምርተው መጠቀም ከመቻላቸው ባሻገር የተለያዩ መሰረተ ልማት አውታሮችና የማኅበራዊ ተቋማት አገልግሎት ተጠቃሚዎች መሆን እንደቻሉ የውይይቱ ተሣታፊዎች የገለጹ ሲሆን በአካባቢያቸው እየተገነቡ የሚገኙት ስኳር ፋብሪካዎች ስኳር ማምረት ሲጀምሩ ለማየት እጅግ መጓጓታቸውን ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ወደፊት በሚደርስባቸው አካባቢዎች ማለትም በደቡብ ኦሞ ዞን የሙርሲ፣ በከፋ ዞን ዴቻ ወረዳና በቤንች ማጂ ዞን የሜኢኒት ብሔረሰቦች ተወላጆች የሆኑ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መንግስት የስኳር ልማት ስራውን አፋጥኖ እንደሌሎቹ ሁሉ እነርሱም የተለያዩ መሰረተ ልማት አውታሮችና ማህበራዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ መንግስት ልማቱን ያፋጥን ዘንድ አሳስበዋል፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ እዚህ ተገኝተው ስለስኳር ልማቱ የገቡልን ቃል ወደ ተግባር ተለውጦ ማየታችን ምንም ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ቢገጠመን እንኳን በጽናት እንድንወጣው የሚያደርግ ነው ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች በልማቱ ሳቢያ ቀድሞ እንደ ጠላት እንተያይ የነበርን የአካባቢው ተወላጆች ለልማቱ መፋጠን በጋራ መቆም ችለናል ሲሉ ልማቱ ያስገኘላቸውን ማኅበራዊ ትስስር ገልጸዋል፡፡ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በበኩላቸው በውይይቱ የተነሱት ሀሳቦች የስኳር ልማት ስራው ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለ የሚያመላክት መሆኑን ጠቅሰው ከመስኖ አውታር ጀምሮ የመሰረተ ልማት አውታሮችም ሆኑ የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የስኳር ልማቱ በሚደርስባቸውም ሆነ በማይደርስባቸው አካባቢዎች እንዲገነቡ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ሕብረተሰቡ በጠየቀው መሰረት የልማት ስራው በተገቢው ደረጃና ፍጥነት እንዲከናወን የአካባቢው ተወላጆች የድርሻቸውን እንዲወጡ አሣስበዋል፡፡ አቶ ታገሰ ጫፎ የደ/ብ/ብ/ሕ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በበኩላቸው የክልሉም ሆነ የፌደራሉ መንግስት የልማት ስራዎችን በአካባቢው የሚያከናውኑት የአካባቢውን ተወላጆች ተጠቃሚነት ባረጋገጠ ሁኔታ መሆኑን አመልክተው የኦሞ ወንዝን መንግስት እንዲጠለፍ ሲያደርግ መጀመሪያ ላይ ተጠቃሚ የደረገው የአካባቢውን ነዋሪዎችን መሆኑን አውስተዋል፡፡ አቶ ሞሎካ ውብነህ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸው እንደገለጹት የተካሄደው ውይይት ከዚህ በፊት ይንጸባረቁ የነበሩ ጥርጣሬዎችና ችግሮች መወገዳቸውን ያመላከተ ነው፡፡ እየተካሄደ የሚገኘው በመንደር የማሰባሰብ ስራ የአካባቢዎቹ ተወላጆች የመሰረተ ልማት አውታሮችና ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል፡፡ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ175 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ መሬት የሚኖረውና በአጠቃለይ አምስት ስኳርፋብሪካዎች የሚገነቡበት በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል በደቡብ ኦሞ፣በከፋ እና ቤንች ማጂ ዞን የሚገኝ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ »» ከገጽ 1 የዞረ ለማምረት ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ በቅርቡ ማምረት እንደሚጀምር የሚጠበቀው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በተለያዩ ምክንያቶች በተያዘለት ጊዜ ማምረት ባለመጀመሩ በሦስቱ ነባር ፋብሪካዎች ብቻ 325 ሺህ 25 ቶን ስኳር ለማምረት ተችሏል፡፡ በበጀት አመቱ ፋብሪካዎቹ ያመረቱት የስኳር ምርት በ2005 የበጀት አመት ካመረቱት የምርት መጠን ጋር ሲነጻጸር አንድ መቶ ሺህ ቶን የሚጠጋ ብልጫ አሳይቷል፡፡ ብቸኞቹ የኤታኖል አምራች የሆኑት የመተሐራና የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች በበጀት አመቱ 19 ሚሊዮን 745 ሺህ ሊትር ኤታኖል ያመረቱ ሲሆን፣ ምርቱ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ5 ሚሊዮን 61 ሺህ ሊትር ብልጫ አሳይቷል፡፡ በፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች የካይዘን አሠራር ፍልስፍና ተግባራዊ በመደረጉ በሠራተኞች ዘንድ መነቃቃት እንዲፈጠርና በባለቤትነት መንፈስ እንዲንቀሳቀሱ በማስቻሉ በበጀት አመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ማዳን መቻሉንም አመታዊው የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያመለክታል፡፡ በካይዘንና የለውጥ አመራር ዘርፍ በኩል በበጀት አመቱ ለ18 ሺህ 289 የፋብሪካ እና የፕሮጀክት ሠራተኞች በመሠረታዊ የካይዘን ፍልስፍና እና አድቫንስድ ካይዘን ኮርሶች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በአገዳ ተከላ፣ በቤቶችና መስኖ ግንባታ፣ በፋብሪካ ተከላ ረገድም ኮርፖሬሽኑ ከ2005 ዓ.ም የበጀት አመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የተሻሉ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ የፕሮጀክት መዘግየት፣ በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ዝናብ በከፍተኛ መጠንና ለተራዘመ ጊዜ በመዝነቡ ምክንያት አገዳ ለፋብሪካ ለማቅረብ አለመቻሉ፣ እንዲሁም የአቅም ውስንነቶችና የአቅርቦት መጓተት በበጀት አመቱ የተስተዋሉ ዋና ዋና ተግዳሮቶች እንደነበሩ ነው ሪፖርቱ ያመለከተው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በተያዘው የ2007 የበጀት አመት 1 ሚሊዮን 217 ሺህ 438 ቶን ስኳርና 30 ሚሊዮን 278 ሺህ ሊትር ኤታኖል ለማምረት አቅዷል፡፡ ከስኳር የምርት መጠን ውስጥም 665 ሺህ 438 ቶን ለውጭ ገበያ በማቅረብ 311 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መታቀዱ ተገልጿል፡፡ በበጀት አመቱ 189 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ከፋብሪካዎች ፍጆታ የሚቀረውን 46 ሜጋ ዋት ኃይል ወደ ብሔራዊ ቋት ለማስገባትም ኮርፖሬሽኑ አቅዷል፡፡ የአገዳ ልማትን በተመለከተም በነባር ፋብሪካዎች 5 ሺህ ዘጠኝ ሄክታር ለመትከል የታቀደ ሲሆን፣ በፕሮጀክቶች ደግሞ ተጨማሪ 33 ሺህ 574 ሄክታር አገዳ በመትከል የፕሮጀክቶችን የአገዳ ልማት 81 ሺህ 914 ሄክታር ለማድረስ በበጀት አመቱ እንደሚሰራ የኮርፖሬሽኑ እቅድ ያመለክታል፡፡ በአንድ መቶ ሄክታር ላይ የእንስሳት መኖ ማዘጋጀትና አንድ የእንስሳት ማድለቢያ ጣቢያ አቋቁሞ ወደስራ መግባት በተጓዳኝ ምርቶችና አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ በበጀት አመቱ ለማከናወን ከታቀዱት መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በ2007 የበጀት አመት በስኳር ኢንደስትሪው ከ100 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች ተጨማሪ የስራ እድል ለመፍጠር ኮርፖሬሽኑ እንደሚሰራ እቅዱ ያመለክታል፡፡ አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶቹ እየተካሄዱ የሚገኙባቸው አካባቢዎች የመሰረተ ልማት አውታሮች ያልነበሩባቸው በመሆናቸው ኮርፖሬሽኑ ከስኳር ልማት ስራው ባሻገር እ ነዚህን በ ማሟላት ስ ራ እንዲጠመድ ያደረጉ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ 4 5
  • 4. ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ስራ ለስኳር ልማት ትልቅ ፋይዳ አለው የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ስራ ውሃን በሰፊው ለሚጠቀመው የስኳር ልማት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ ገለጹ፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጉራራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ችግኝ ተክለዋል፡፡ አቶ ሽፈራው በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ስራ ለስኳር ልማት ጥቅም ላይ የሚውለውን የመስኖ ውሃ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማግኘት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ለዚህም ሲባል በስኳር ፕሮጀክቶች አካባቢም ኮርፖሬሽኑ ሰፊ የአካባቢ ጥበቃ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ አቶ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች መተሐራ ስኳር ፋብሪካ የካይዘን አንደኛ ደረጃ ትግበራ አገር አቀፍ ውድድር አሸናፊ ሆነ መተሐራ ስኳር ፋብሪካ የኢትዮጵያ ካይዘን መትከላቸው ይታወሳል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ችግኝ ሲተክሉ ኢንስቲትዩት በአገር አቀፍ ደረጃ ባዘጋጀው የካይዘን የመጀመሪያ ደረጃ ትግበራ ውድድር አሸናፊ ሆነ፡፡ የወንጂ ሸዋና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች የአገዳ ቆረጣና የዘር አገዳ ዝግጅት ሠራተኞች አሸኛኘት ተደረገላቸው የወንጂ ሸዋና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች በ2ዐዐ6 ዓ.ም የምርት ዘመን በጊዜያዊነት በአገዳ ቆረጣና በዘር አገዳ ዝግጅት ስራ ተሰማርተው ለነበሩ ከ2 ሺህ 800 በላይ ሠራተኞች ለእረፍት ወደ ትውልድ ቀዬአቸው ሲሄዱ የክብር አሸኛኘት አደረጉላቸው፡፡ ሐምሌ 8 እና 14 ቀን 2006 ዓ.ም ሽኝት ከተደረገላቸው ሠራተኞች መካከል 1224 የሚሆኑት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ፣ 16ዐዐቱ ደግሞ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በአገዳ ቆረጣና በዘር አገዳ ዝግጅት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በበጀት ዓመቱ በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በአገዳ ቆረጣ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩት ሰራተኞች ከ6.8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሸንኮራ አገዳ የመቁረጥ ስራ አከናውነዋል ፡፡ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ይሰሩ የነበሩት ደግሞ ከ6866.3 ሄክታር ማሳ ላይ 11. 5 ሚሊዮን ኩንታል የሸንኮራ አገዳ የቆረጡ ሲሆን፣ የዘር ዝግጅት ሰራተኞቹ በበኩላቸው ከ300.4 ሄክታር ማሳ ላይ ከግማሽ ሚሊዮን ኩንታል በላይ የዘር አገዳ የመቁረጥ ስራ አከናውነዋል፡፡ በሁለቱም ፋብሪካዎች ሲሰሩ ለቆዩ እየተከናወነ በሚገኘው የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ስራ የደረቁ ወንዞች ቀደም ሲል ወደነበሩበት ሁኔታ መመለስ መጀመራቸው የስራውን ውጤታማነት እንደሚያሳይ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ የአካባቢን የደን ሽፋን በማሳደግ አገሪቱ ከካርቦን ንግድ የምታገኘውን ገቢ ማሳደግ ይቻላል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በየጊዜው የሚተከሉ ችግኞችን መንከባከብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ በተከላው ላይ የተሳተፉ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞችም አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች አምናም ለታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ በተዘጋጀ ፓርክ ውስጥ ችግኞችን ሰራተኞች የፋብሪካዎቹ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የክብር መሸኛ መርሐ ግብሩ መከናወኑን ከፋብሪካዎቹ የሕዝብ ግንኙነት ክፍሎች የደረሱን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በተከናወነው የሽኝት መርሐ ግብር የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፉሮ በቀታ ባሰሙት ንግግር ሠራተኞቹ በበጀት አመቱ ፋብሪካው ላስመዘገበው ስኬት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በተመሳሳይ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም በወቅቱ በተወካያቸው አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት ሠራተኞቹ ዕድሜያቸው ያለፈ፣ ደረቅና ለመቁረጥ አስቸጋሪ የሆኑ አገዳዎችን ጭምር በመቁረጥ ላሣዩት ጥንካሬ አመስግነዋል፡፡ በተጨማሪም የዘር አገዳ ዝግጅት ሠራተኞቹ እጅግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፋብሪካው እርሻ ሰራተኞቹ በሽኝት መርሃ ግብሩ ደስተኛ ነበሩ የዘር አገዳ ፍላጐት ባሻገር ለከሰም ስኳር ፋብሪካ ግብዓት እንዲውል ታስቦ በአሚባራ እርሻ ልማት በ6ሺህ ሔክታር መሬት ላይ ለተተከለው ሸንኮራ አገዳ የዘር አገዳ በማቅረብ ረገድ ለተጫወቱት ከፍተኛ ሚና ኩራት እንደተሰማቸው አክለው ገልጸዋል፡፡ በአሸኛኘቱ መርሐ ግብር ላይ በምርት ዘመኑ በሥራ አፈፃፀማቸው ግንባር ቀደም ለሆኑና ከየምድባቸው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ዘጠኝ ምስጉን ሠራተኞች የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡ የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እጅ የዋንጫ ሽልማት ሲቀበሉ ኢንስቲትዩቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኔ 21 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በካፒታል ሆቴል ያዘጋጀው የመጀመሪያ ደረጃ የካይዘን ትግበራ ውድድር የተካሄደው በሰው ሀብት ልማት፣ በኤክስፖርት ምርቶች ኢንዱስትሪ እና በገቢ ምርቶች ኢንዱስትሪ ነው፡፡ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በእነዚህ ዘርፎች በተካሄደ አጠቃላይ ውድድር በግል፣ በልማት ቡድንና በተቋም ደረጃ አንደኛ በመውጣት የወርቅና የዋንጫ ሽልማት ከእለቱ የክብር እንግዳ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እጅ ተቀብሏል፡፡ ፋብሪካው ከዚህ በኋላ በየአመቱ በሚካሄዱ የመጀመሪያ ደረጃ የካይዘን ትግበራ የሽልማት ሥነ-ስርዓቶች ላይ የክብር ወንበር እንደሚይዝም በዕለቱ ተበስሯል፡፡ በሌላ በኩል የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የኪነ- ጥበብ ማዕከል በሽልማት ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተጋባዥ በመሆን ያቀረበው ትወና ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል፡፡ ማዕከሉ ባሳየው ብቃትም በማንኛውም ሀገራዊ የካይዘን ንቅናቄ መድረኮች ላይ አስተማሪ ሆኖ እንዲገኝ ዕድሉ ተሰጥቶታል፡፡ በተያያዘ ዜና ፋብሪካው አሸናፊ በሆነበት ሥነስርዓት ላይ ተሳታፊ ለነበረው የልዑካን ቡድን አባላት የፈንታሌ ወረዳ እና የመተሐራ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል፡፡ በወቅቱም የፈንታሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ድሪርሳ እና የመተሐራ ከተማ ከንቲባ አቶ መሐመድ ከማል ውጤቱ የወረዳውና የህብረተሰቡ የጋራ ድል ጭምር መሆኑን በአቀባበል ሥነ ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው መተሐራ ስኳር ፋብሪካ በሚገኘው ስታዲየም በመገኘት ድሉን በጋራ አክብረዋል፡፡ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም በአቀባበል ሥነ-ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የተገኘው ወርቃማ ድል የመላው አመራር፣ የሠራተኛውና የቤተሰቡ እንዲሁም በፋብሪካው ዙሪያ የሚገኘው ማህበረሰብ ጭምር የትጋትና የጥረት ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካትም የሁሉም ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የግልና የልማት ቡድን ተሸላሚዎች በበኩላቸው በየተራ ባሰሙት ንግግር የተገኘውን ድል በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማስታወቃቸውን የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ዘግቧል፡፡ በተያያዘም የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በካይዘን ፍልስፍና ያካበተውን ልምድ ለኦሞ ኩራዝ ስካር ልማት ፕሮጀክት ማካፈሉ ታውቋል፡፡ የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለጣፋጭ ዜና መጽሔት ዝግጅት ክፍል ያደረሰው ዘገባ እንዳመለከተው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በካይዘን ለረጅም አመታት ያካበተውን ልምድ ለሌሎች ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በማስተላለፍ የክህሎትና የዕውቀት ሽግግር የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ካሳ ተስፋዬ ፕሮጀክታቸው መተሐራን ከመሳሰሉ እህት ስኳር ፋብሪካዎች ልምድ በመቅሰምና ባለሙያዎችን በማስመጣት ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለፕሮጀክቱ በተለያዩ ዘርፎች እያደረገ ከሚገኘው ድጋፍ ጎን ለጎን ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር በመቀናጀት በፕሮጀክቱ በመገኘት ለሠራተኛው ልምዱን በማካፈሉ አመስግነው በካይዘን ትግበራ በ2007 በጀት አመት ፕሮጀክቱን ተሸላሚ ለማድረግ ከመላው ሠራተኛና አመራር ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡ ለአራት ቀናት በዘለቀው የልምድ ልውውጥ ከ1 ሺህ 250 በላይ የሆኑ የፕሮጀክቱ ቋሚ፣ ጊዜያዊና በማህበር ተደራጅተው በመስራት ላይ የሚገኙ ሰዎች ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡ 6 7
  • 5. ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት የፕሮጀክቱ የአገዳ ተከላ እቅድ አፈፃፀም ስኬታማ መሆኑ ተገለፀ አቶ አስራቴ አለኸኝ የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ የፈንድቃ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች የፕሮጀክቱ ደጋፊ መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠዋል የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የ2006 የበጀት አመት የአገዳ ተከላ እቅድ አፈጻጸም ስኬታማ መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ገለጹ፡፡ የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አስራቴ አለኽኝ በዘር አገዳ ቆረጣና ተከላ፣ ስራዎችን ቆጥሮ በመስጠትና በመቀበል፣ እንዲሁም በየዕለቱ ግምገማ በማድረግ ውጤታማነትን ለማሳደግ ጥረት በመደረጉ በበጀት አመቱ 8 ሺህ ሄክታር መሬት በአገዳ ለመሸፈን ታቅዶ ከዕቅድ በላይ መከናወኑን አስታውቀዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ በ8 ሺህ 31 ሄክታር መሬት ላይ የተከናወነው የአገዳ ተከላ በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ በአገዳ የተሸፈነ መሬት ወደ 10 ሺህ ዘጠኝ ሄክታር ከፍ እንዲል አስችሏል፡፡ በበጀት አመቱ ፕሮጀክቱ በቀን ከ120 እስከ 130 ሄክታር አገዳ የመትክል አቅም ላይ መድረሱን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸው፣ ይህም ለቀጣይ ስራዎች ከፍተኛ ተሞክሮ የተገኘበት ነው ብለዋል፡፡ የአገዳ ተከላው ለአካባቢው ማህበረሰብ በርካታ የስራ እድል መፍጠሩንም ነው ዋና ስራ አስኪያጁ የተናገሩት፡፡ በፕሮጀክቱ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች የልማት ባለቤትነት ስሜት የበለጠ እየዳበረ መምጣቱን አቶ አስራቴ ጠቁመው፣ በማሳያነትም የጃዊ ወረዳ ፈንድቃ ከተማ እና አካባቢዋ የንግዱ ማህበረሰብ፣ አርሶ አደሮችና የመንግሥት ሠራተኞች በበጀት አመቱ 5 ሄክታር መሬት በዘመቻ መትከላቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በተመሳሳይ የፕሮጀክቱ ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞችም 3 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ በዘመቻ አገዳ በመትከል ያሳዩት አጋርነት አበረታችና የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ንእቅስቃሴ እያገዘ የመጣ በመሆኑ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ በአጠቃላይ 17 ሺህ 190 ዜጎች በተለያዩ የሙያ መስኮች የስራ እድል ተፈጥሮላቸው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ከፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ዘገባ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የስራ እድሉ የተፈጠረላቸው ዜጎች ከ10 ነጥብ 54 ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ የገንዘብ ተቋማት በመቆጠብ ለለውጥ ራሳቸውን እያዘጋጁ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ከሰኔ 9 እስከ 30 ቀን 2006 ዓ.ም በመንግስት ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ፕሮግራሞች እንዲሁም በሕዝብ ግንኙነትና ልማታዊ ሚዲያ የሠጠውን ስልጠና የተከታተሉ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የኮሚዩኒኬሽን የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ 130 የሚሆኑት እነዚህ ጎብኝዎቹ በፋብሪካው የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና ትግበራ ውጤቶችን ፣ በባለሙያዎች የተሰሩ የፈጠራ ውጤቶችን፣ የአዲሱ ፋብሪካ የምርት ሂደት፣ የመስኖ መሠረተ ልማት ዝርጋታ እና በአካባቢው አርሶ አደር በመልማት ላይ የሚገኘውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን፣ የፋብሪካው አመሰራረትና አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ በፎቶግራፍ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ የስራ ኃላፊዎቹና ባለሙያዎቹ በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት የስኳር አመራረት ሂደት ውስብስብና ከባድ መሆኑን መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡ የስኳር ኢንዱስትሪ ሰፊ የሰው ኃይል በማሳተፍና ተጠቃሚ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም በተግባር መመልከታቸውን ገልፀው፣ የተጀመሩት የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል እንደሚያስገኙ ተስፋ አድርገዋል፡፡ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ካይዘንን በመተግበሩ ባመጣው ለውጥና ባስመዘገባቸው ስኬቶች መደነቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ የአካባቢው አርሶ አደሮች ሸንኮራ አገዳ እያለሙ ለፋብሪካው በመሸጥ ተጠቃሚ የሆኑበት አሰራር የስኳር ልማቱ በተለያዩ መልኮች ልማቱ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች ነዋሪዎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከስኳር ተረፈ ምርቶች የኤሌክትሪክ ኃይል አመንጭቶ የራሱን ፍላጎት አሟልቶ ቀሪውን ለብሔራዊ የኃይል ቋት ማስገባቱ ልማቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን አመላካች ነውም ብለዋል ጎብኝዎቹ፡፡ በጉብኝቱ ተሳታፊ የነበሩት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ፋብሪካው በማድረግ ላይ የሚገኘው እንቅስቃሴ በዘርፉ ስኬት ማስመዝገብ እንደሚቻል አመላካች ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም የፋብሪካው የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች አሁን በማድረግ ላይ የሚገኙትን እንቅስቃሴ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡ የሥራ ጉብኝት አደረጉ ከአርጆ ዲዴሳ እና ከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አካባቢዎች የተውጣጡ 19 ወጣቶች በትራክተር ኦፕሬተርነት ተመረቁ 8 9 የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎቹና ባለሙያዎቹ ፋብሪካውን በጎበኙበት ወቅት ስኳር ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመተባበር ከአርጆ ዲዴሳ እና ከከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አካባቢዎች የተውጣጡ 19 አርብቶ አደርና አርሶ አደር ወጣቶችን በትራክተር ኦፕሬተርነት አሠልጥኖ ለሁለተኛ ጊዜ ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም አስመረቀ፡፡ ኮርፖሬሽኑ እስካሁን በትራክተር ኦፕሬተርነት ያሰለጠናቸው ወጣቶች ቁጥር 79 ደርሷል፡፡ ሠልጣኞቹ በጊንጪና ጫንጮ ትራክተር ኦፕሬተር ማሠልጠኛ ተቋም ለሁለት ወራት የሠለጠኑ ሲሆን፣ ወደመጡበት አካባቢዎች እንደተመለሱ በፕሮጀክቶቹ ተቀጥረው የሚሰሩበት ሁኔታ እንደሚመቻች በምረቃው ወቅት ተገልጿል፡፡ ሥልጠናው ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር በየአካባቢዎቹ ህዝብ ዘንድ የባለቤትነት ስሜት እንዲፈጠር እና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በምረቃው ሥነ ስርዓት ላይ ስኳር ኮርፖሬሽንን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ ኤካል ነትር የህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡ ወደፊትም በልማቱ ዙሪያ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ ሥልጠናዎችን የመስጠቱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለሠልጣኞችም በየፕሮጀክቶቹ የሥራ ዕድል እንደሚመቻች አክለው አስታውቀዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ከስኳር ልማት አካባቢዎች የተውጣጡ አርብቶ አደርና አርሶ አደር ወጣቶችንና ሴቶችን በቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት የመለስተኛ ሙያ ክህሎት ሥልጠና በመስጠት፣ በማደራጀትና ወደ ሥራ በማስገባት ተጠቃሚ ማድረግ ከጀመረ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ በትራክተር ኦፕሬተርነት 79 እንዲሁም በኮንስትራክሽን፣ በማኒፋክቸሪንግ፣ በግብርና እና በመሳሰሉት የሙያ መስኮች 1 ሺህ 237 ዜጎች ሥልጠና ወስደው በስኳር ልማት ሥራዎች ላይ ተሰማርተዋል፡፡ በአርጆ ዲዴሳና ከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ለሰልጣኞቹ የስራ ዕድል ተመቻችቷል
  • 6. ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የ2006 በጀት ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በ2ዐዐ6 በጀት ዓመት 1 ሚሊዮን 149 ሺህ ኩንታል ስኳር በማምረት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ፡፡ ውጤቱ ከ2ዐዐ5 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ35ዐ ሺህ ኩንታል ብልጫ አሳይቷል፡፡ ፋብሪካው ባለፈው የምርት ዘመን 11 ሚሊዮን 555 ሺህ 499 ኩንታል ሸንኮራ አገዳ የፈጨ ሲሆን፣ ይህም አሀዝ በ2005 በጀት ዓመት ከፈጨው ጋር ሲነፃፀር በ2 ሚሊዮን 536 ሺህ 186 ኩንታል ሸንኮራ አገዳ ብልጫ አሳይቷል፡፡ የፋብሪካ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላይንአዲስ በቀለ፣ የምርት ክፍል ቡድን መሪ አቶ ካሣሁን ምርከና እንዲሁም የቴክኒክ ቡድን መሪ አቶ ፋሚ ዳውድን ጠቅሶ የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል እንደዘገበው ለበጀት አመቱ የምርት መጠን ማደግ በአዎንታዊ አመለካከት ግንባታ ላይ የተሠሩ ሥራዎች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍና አማካኝነት በልማት ቡድን ተደራጅቶ ችግሮችን በመፍታትና የፈጠራ ስራዎችን በማከናወን፤ በሠራተኛው ዘንድ የተፈጠረው የባለቤትነት ስሜትና ከፍተኛ ተነሣሽነት፣ እንዲሁም የታየው ከፍተኛ ዝግጁነትና ተግባራዊ ርብርብ ለምርቱ ማደግ ጉልህ ድርሻ እንደነበራቸው የሥራ ኃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡ ፋብሪካው ቀድሞ ከነበረበት ውጤታማ ያልሆነ አሰራር ተላቆ በአንድ አመት ዕድገት እንዲያስመዘግብ ከረዱት መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ ከጥገና ወራት ጀምሮ እስከ 2006 ምርት ዘመን መገባደጃ ድረስ ተጠያቂነት የሰፈነበት ጠንካራ አሠራር በመፈጠሩ መሆኑንም ዘገባው አመልክቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የክህሎትና የአመለካከት ክፍተቶችን ለማስተካከልና ሠራተኛውን ለማብቃት እንዲቻል በየደረጃው የተሠጡት ስልጠናዎችም ለምርታማነቱ ጉልህ ድርሻ እንደነበራቸው ተመልክቷል፡፡ የፋብሪካው አገዳ የመፍጨት አቅም ማደግና በፋብሪካው ምርታማነት ላይ ቀደም ባሉት አመታት እንቅፋት ከነበሩት ችግሮች መካከል አንዱ በሆነው ዕድሜ ጠገብ የሸንኮራ አገዳ ላይ የተወሰደው የመፍትሄ እርምጃ ፋብሪካው ውጤታማ እንዲሆን እንዳስቻሉት ተመልክቷል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን በኩል የተሰጡ ተከታታይ ድጋፎችም ለምርታማነቱ ከፍ ማለት ቁልፍ ሚና እንደተጫወቱ ነው የሥራ ኃላፊዎቹ የገለፁት፡፡ በሥራ ኃላፊዎቹ መግለጫ በምርት ዘመኑ ፋብሪካውን ካጋጠሙት የቴክኒክ ተግዳሮቶች መካከል በዋናነት የተለያዩ ማሽኖች ተደጋጋሚ የቴክኒክ ብልሽቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ የቴክኒክ ብልሽቶች በፋብሪካው የካይዘን የልማት ቡድን የይቻላል አስተሳሰብ እና የጊዜ መስዋዕትነት እንደተጠገኑ ነው ኃላፊዎቹ የገለጹት፡፡ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የአካባቢውን ሕብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በአካባቢው የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡ የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተው በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ ማኪና ጉራ በተሰኙ ቀበሌዎች በመንደር ለተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች የተገነቡ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ብሏል፡፡ ፕሮጀክቱ በመስኖ የሚለማ ከ1 ሺህ 600 ሄክታር በላይ መሬት አዘጋጅቶ በወረዳዎቹ በመንደር የተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች ሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በመሸጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመስራት ላይ መሆኑን የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነትና የማሕበራዊ ጉዳዮች ቡድን መሪ አቶ ብርሃኑ አረጋን ጠቅሶ የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ ዘግቧል፡፡ ኦሞ ኩራዝ ስካር ልማት ፕሮጀክት በካፋ ዞን የፕሮጀክቱ አዋሳኝ የሆኑ ቀበሌዎችን ከወረዳ ማዕከል ጋር የሚያገናኝ 54 ኪሎ ሜትር መንገድ በራሱ ማሽኖች በመስራት ላይ እንደሚገኝና ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ቡድን መሪው መግለጻቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡ በመገንባት ላይ የሚገኘው ይህ መንገድ ቀድሞ ምንም ዓይነት መሠረተ ልማት ያልነበራቸውን ቀበሌዎች ከወረዳ ማዕከል ጋር ከማገናኘት ባለፈ በርካታ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታ እንደሚያስገኝላቸው አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡ በዞኑ ዴቻ ወረዳ የነዳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርብቶ አደር ወርማይ ወርካግዶን የመንገዱ መገንባት ምርቶቻቸውን ያለችግር ወደ ገበያ ለመውሰድና የህክምና እርዳታ በቀላሉ ለማግኘት እንደሚረዳቸው መናገራቸው ተገልጿል፡፡ በአሚባራ እርሻ ልማት የሸንኮራ አገዳ ተከላ ተጠናቀቀ በ2007ዓ.ም ሥራ ለሚጀምረው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ዋነኛ የሸንኮራ አገዳ አቅራቢ እንደሚሆን በሚጠበቀው በአሚባራ እርሻ ልማት በመካሄድ ላይ የነበረው የሸንኮራ አገዳ ተከላ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ በእርሻ ልማቱ በስድስት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ለተከናወነው የሸንኮራ አገዳ ልማት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ጥራቱን የጠበቀ የዘር አገዳ ማቅረቡ ታውቋል፡፡ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ አመራር ቡድን እና የመተሐራ እርሻ ምርምር ጣቢያ ባለሙዎች በእርሻ ልማቱ በመገኘት የሸንኮራ አገዳ ተከላና እንክብካቤ ሥራዎችን ተዘዋውረው ጐብኝተዋል፡፡ በዚሁ ወቅት የእርሻ ልማቱ የእስካሁን አፈፃፀም አበረታች መሆኑ ተገልጿል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት በሥራው ላይ በተስተዋሉ ክፍተቶች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት ኦፕሬሽናል ስታንዳርድን አስጠብቆ መሥራት እና በታዩ የአሠራር ክፍተቶች ላይ የማስተካከያ ዕቅዶችን በመንደፍ አፋጣኝ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ስምምነት ተደርሶባቸዋል፡፡ በተለይም የአሚባራ እርሻ ልማት የካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍናን መተግበር ላይ ማተኮር እንዳለበት እና ለዚህም የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተመልክቷል በማለት የዘገበው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው፡፡ የአሚባራ እርሻ ልማት ኃ/የተ/የግል ማህበር በሸንኮራ አገዳ አብቃይነትና አቅራቢነት ከከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት ጋር ለመስራት ስምምነት የተፈራረመው መጋቢት 8 ቀን 2006 ዓ.ም ነው፡፡ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከ 8 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሊትር በላይ ኤታኖል አመረተ * ምርቱ በፋብሪካው ታሪክ ከፍተኛው ነው የመተሐራ ኤታኖል ፋብሪካ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በ2ዐዐ6 በጀት ዓመት ከ8.6 ሚሊዮን ሊትር በላይ ኢታኖል በማምረት የእቅዱን 85 በመቶ ማሳካቱ ተገለጸ፡፡ ምርቱ የኤታኖል ፋብሪካው ከተቋቋመ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛው መሆኑም ታውቋል፡፡ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የኤታኖል ምርት ክፍል ቡድን መሪ አቶ በቀለ ምርከና ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ በ2006 በጀት አመት የተመረተው የኤታኖል ምርት መጠን ፋብሪካው ከተቋቋመበት ከ2ዐዐ2ዓ.ም አንስቶ ካመረተው ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ አሳይቷል፡፡ የ2006 ምርት ካለፉት አመታት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ ሊያሳይ የቻለው በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የተተገበረው የካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍና በመላው ሠራተኛ ዘንድ ከፍተኛ ተነሳሽነት በመፍጠሩ መሆኑን የቡድን መሪው አቶ በቀለ ምርከና ገልጸዋል፡፡ የመተሐራ ኤታኖል ፋብሪካ ምርት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ 10 ሚሊዮን 621 ሺህ 112 ሊትር ሬክቲፋይድ ስፒሪት እንዲሁም 17 ሚሊዮን 756 ሺህ 865 ሊትር ኢታኖል በማምረት ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረቡንም አቶ በቀለ አስታውቀዋል ፡፡ የኤታኖል ፋብሪካው በ2007 በጀት አመት 12 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል ለማምረት ያቀደ ሲሆን፣ ዕቅዱን ለማሳካትም አመራሩና ሰራተኛው ከወዲሁ በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኤታኖል ከነዳጅ ጋር ተደባልቆ ለተሽከርካሪዎች የሀይል ፍጆታ በመዋል የውጭ ምንዛሪ ከማዳን ባለፈ አካባቢን ከብክለት በመከላከል ይታወቃል፡፡ ኢታኖል የሚመረተው በስኳር ምርት ሂደት ከሚገኙት ተረፈ ምርቶች መካከል አንዱ በሆነው ሞላሰስ ሲሆን፣ ከኢታኖል የሚገኘው ቪናስ የተባለው ተረፈ ምርት ደግሞ ከፊልተር ኬክ ጋር ተደባልቆ ለሸንኮራ አገዳ ማዳበሪያነት እንደሚውል የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡ በፕሮጀክቱ ለአካባቢው ህብረተሰብ ከገነባቸው የማሕበራዊ ተቋማት መካከል የንጹህ 10 11 መጠጥ ውሃ ይገኝበታል
  • 7. ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት ቆይታ “…ለእኔና ለወገኖቼ በፈነጠቀው ብርሃን ስደሰት እነዚያ ጓደኞቼ ይህንን ሳያዩ በማለፋቸው ክፉኛ አዝናለሁ፡፡” ተይዤ እሞታለሁ እያልኩ በስጋት ላይ ሳለሁ በአካባቢው ላይ የስኳር ልማት ተጀመረ፡፡ አሁን የስኳር ልማቱን ተከትሎ የህክምና እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች በመመቻቸታቸው ወባና መሰል በሽታዎች ስጋት የመሆናቸው ሁኔታ አብቅቶ በማየቴ የተለየ የደስታ ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡ የእነዚያ የጓደኞቼ ሞት ግን ልቤን ሰብሮ ነው ያለፈው፡፡ እግዚአብሔር ዕድሜ ሰጥቶኝ በዚህ ቦታ ላይ ለእኔና ለወገኖቼ በፈነጠቀው ብርሃን ስደሰት እነዚያ ጓደኞቼ ይህንን ሳያዩ በማለፋቸው ክፉኛ አዝናለሁ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ልማቱ በተለየዩ ክልሎች ለሚገኙ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠሩ የስኳር ልማቱ የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ብሔር ብሔረሰቦችንም አሰባስቧል፡፡ የህክምና አገልግሎት፣ ውሃ፣ መንገድ፣ መብራትና ሌሎች መሰረተ ልማቶችም በፕሮጀክቱ አማካይነት በመመቻቸት ላይ ይገኛሉ፡፡ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጅ፣ ሆስፒታልና መሰል አገልግሎቶች እሩቅ በማይባል ጊዜ ውስጥ እንደሚመቻቹ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን የሚያስደስት ነገር አለ ? ለእኔ በዚህ አካባቢ እንዲህ ዓይነት ልማት ሲካሄድ ከማየት በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም፡፡ አቶ አቡአለም ቡታ ተጓዳኝ ምርቶችና አግሮ ፕሮሰሲንግ የስኳር ኢንዱስትሪው ተጨማሪ አቅም በስኳር ምርት ሂደት የሚገኙትን ተረፈ ምርቶች በግብአትነት በመጠቀም ከሚመረቱት ተጓዳኝ ምርቶች መካከል በአብዛኛው ህብረተሰብ ዘንድ የሚታወቁት ኤታኖልና የኤሌክትሪክ ኃይል ናቸው፡፡ ኤታኖል ለተሽከርካሪ ከሚውለው ነዳጅ ጋር በተወሰነ መጠን በመደባለቅ አገልግሎት ላይ ውሎ ከፍተኛ ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታ ከማስገኘቱም በተጨማሪ ለአልኮል፣ለቀለም እና መድኃኒት ፋብሪካዎችና ለመሳሰሉት ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት በመዋል የውጭ ምንዛሪ ያድናል፡፡ የስኳር ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም የሚመረተው የኤሌክትሪክ ኃይልም አምራች ፋብሪካዎቹ የራሳቸውን የኃይል ፍላጎት ተጠቅመው ቀሪውን ኃይል ለብሔራዊ ቋት በማስረከብ በገቢ ተጠቃሚ ከመሆናቸውም ባሻገር የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት የሚደረገውን ጥረት ያግዛሉ፡፡ ፋብሪካዎቹ ከላይ ከተጠቀሱት ተጓዳኝ ምርቶች በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታ የሚያስገኙ ተጓዳኝና ተያያዥ ምርቶችን በማምረት የአገሪቱ የምጣኔ ሀብት መስኮችን መደገፍ የሚያስችል ስራ መስራት እንደሚችሉ የበርካታ አገሮች ልምድና ተሞክሮዎች ያመለክታሉ፡፡ የየአገራቱ ልምድና ተሞክሮዎች ብቻም ሳይሆኑ በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶችም ይህንን አረጋግጠዋል፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽንም እነዚህን እውነታዎች መሠረት በማድረግ የተጓዳኝ ምርቶችንና ሌሎች ተያያዥ ስራዎችን በበላይነት የሚመራ “የተጓዳኝ ምርቶችና አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ” አቋቁሞ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የዘርፉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ ተስፋይ ዘርፉ የተቋቋመበትን ዓላማ ሲገልፁ የስኳር ፋብሪካዎች ስኳር ማምረት የመጨረሻ ግባቸው ቢሆንም ብዙ ሊሰሯቸው የሚችሉትና የሚገቡ ተጓዳኝ ስራዎች አሉ ይላሉ፡፡ ከነዚህ ስራዎች መካከል ኢትዮጵያ ካላት የእንስሳት ሀብት ተገቢውን ጥቅም እንዳታገኝ ማነቆ ሆኖ የቆየውን የእንስሳት መኖ በሚፈለገው መጠንና ጥራት ለማምረት ሞላሰስና ባጋስ በመባል የሚታወቁትን የስኳር ተረፈ ምርቶች ከሌሎች ተጨማሪ ውህዶች ጋር በማደባለቅ የሚዘጋጀው የእንስሳት መኖ የማቀነባበር ሥራ በዋነኛነት ይጠቀሳል፡፡ በዚህ መነሻነት ኮርፖሬሽኑ ከስኳር ተረፈ ምርት በፋብሪካ ተቀነባብሮ የሚዘጋጀውን የእንስሳት መኖ በመጠቀም በራሱ ቦታ የእንስሳት እርባታ ማካሄድ፣ ከብት ማድለብ፣ የወተት ላሞችን ማርባትና የወተት ተዋጽዖዎችን ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ማቋቋም የመሳሰሉ ስራዎችን መስራት ይችላል፡፡ በሌላ በኩል በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለረጅም ጊዜ ሲሰራበት የቆየውን የፍራፍሬ ማልማት ተሞክሮ ወደ ሌሎች ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በማስፋፋት በስፋት ፍራፍሬ ማልማትና በፋብሪካ ማቀነባበር የሚቻልበት ሰፊ እድልም መኖሩን ነው ዳይሬክተሩ የሚያብራሩት፡፡ እነዚህን ስራዎች ለመፈጸምም የዘርፉን የሰው ኃይል ከማሟላት ባለፈ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው፡፡ “ስራው በሃሳብ ደረጃ ሲታሰብ ከእኛ አስቀድመው ስራውን የጀመሩ የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ መቅሰም የግድ ነበር፡፡ ለዚህም ሲባል ከኮርፖሬሽናችን ጋር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረመውን የሱዳኑን ኬናና ስኳር ኩባንያ ጎብኝተናል፡፡ ኩባንያው የስኳር ተረፈ ምርቶችን በግብአትነት ተጠቅሞ የእንስሳት መኖ በማቀነባበር ረገድ ጥሩ ተሞክሮ አለው፡፡ ይህም በ2007 የበጀት አመት ልናከናውናቸው ለምናስባቸው ተግባራት እንደመነሻ ሆኖልናል” በማለት ይገልጻሉ፡፡ በዚህ ረገድ መንግስት ቴክኖሎጂውና ፋይናንሱ ካላቸው አገሮች ወይም ድርጅቶች ጋ ር በ ጋራ መ ስራት አ ስፈላጊ መሆኑን ያምናል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በዘርፉ ያለውን እምቅ አቅምና በተለይም በቴክኖሎጂና በገበያ ትስስር ረገድ አብሮ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት የሚገልጽ የፍላጎት መግለጫ በስኳር ልማቱ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በመስራት ላይ ለሚገኙት ኮምፕላንትና ካሚስ ለሚባሉ ሁለት የቻይና ኩባንያዎች ልኳል፡፡ ከሁለቱ ኩባንያዎች መካከል የወልቃይት ስኳር ፋብሪካን ለመገንባት ወደ ስራ በመግባት ላይ የሚገኘው ካሚስ ዘርፉ ቀድሞ ብዙ እንዲያስብና እንዲሰራ የሚያደርጉ ምክረ ሐሳቦችን (ፕሮፖዛል) በአጭር ጊዜ ማቅረቡን አቶ አታክልቲ ይናገራሉ፡፡ ምክረ ሐሳቦቹ ከስኳር ተረፈ ምርቶች የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እንዴት መገንባት እንደሚቻል፣ የወተት ላሞች እርባታ ጣቢያ ማቋቋም የሚያስችል ዲዛይን፣ የሸንኮራ አገዳ ገለባ ወይም ባጋስ በቀላሉ ለእንስሳት ምግብነት እንዲውል ወይም (ሃይድሮላይዝ) የሚያደርግ ቴክኖሎጂ እና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ወይም (ኦርጋኒክ ፈርትላይዘር) ማምረት የሚያስችል ቴክኖሎጂዎችን ያካተቱ ናቸው፡፡ ዘርፉ አገሪቱ ከእንስሳት ሃብት ተጠቃሚ መሆን የሚያስችላትን ተግባራት እንደሚያከናውን ይጠበቃል “ቀጣይ የዘርፉ ስራ የሚሆነው የትኛውን ስራ የት እንስራ የሚሉትን ጥያቄዎች የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት ከወሰነ በኋላ ብዙ ቴክኖሎጂ የማይጠይቀውን የከብቶች ማድለብንና የሰብልና የፍራፍሬ ልማቱን በሁሉም ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ማስፋፋት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የተያዘው በጀት አመት ዓቢይ ተግባር ይሆናል” በማለት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የበጀት አመቱን የዘርፉን እቅድ ያብራራሉ፡፡ ከዚህ ቀደም በተለምዶ ከሸንኮራ አገዳ ልማት ጋር በስብጥር የሚዘሩት የቦሎቄ፣ የአኩሪ አተርና የጥጥ ምርቶች በስብጥርና ጦም በሚያድሩ መሬቶች ላይ የማስፋፋት ስራዎችም በበጀት አመቱ ከሚከናወኑ የዘርፉ ተግባራት መካከል ይገኛሉ፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን እነዚህን ተጓዳኝ ምርቶች በማምረት ተጠቃሚ ከመሆን ባሻገር የአገሪቱን የእንስሳት ሃብት በመደገፍ ዘርፉን ወደላቀ ደረጃ እንዲደርስ ማድረግ ዋና ዓላማው ነው ይላሉ አቶ አታክልቲ፡፡ መንግስት ለዚህ ስራ ትኩረት የሰጠው ከዚህ እውነታ በመነሳት እንደሆነ በማከል፡፡ “አገሪቱ ካላት እምቅ የእንስሳት ሃብት አኳያ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም አላገኘችም፡፡ ዘርፉም ማደግ በሚገባው ደረጃ አላደገም፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት የእንስሳት መኖ በብዛትና በጥራት አለመገኘት ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ ደግሞ ይህንን ክፍተት የመሙላት አቅም አለው፡፡ ይህንንም ታላቅ አገራዊ ተልዕኮ እናሳካለን” ይላሉ፡፡ በመጨረሻም ስራው ካለው ስፋት አንጻር ኮርፖሬሽኑ ብቻውን የሚያከናውነው ባለመሆኑ በዘርፉ መሠማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች እድሉ ክፍት መሆኑን አቶ አታክልቲ ይናገራሉ፡፡ «ይህንን አካባቢ በቅርበት ስለማውቀው ለልማት ውሎ ሳይ ይገርመኛል፡፡ የአል- ሀበሻ ኃላፊነቱ የተወሰነ የስኳር ፋብሪካ በዚህ አካባቢ የስኳር ልማት ከመጀመሩ በፊት አካባቢው በረዣዥም ሳርና እጽዕዋት የተሸፈነ በመሆኑ የአንበሳ፣ ጎሽ፣ አ ጋዘን፣ ጉ ማሬ፣ ዝ ንጀሮና ሌ ሎች የዱር አራዊት መናኸሪያ ነበር፡፡ በዚህ ቦታ ላ ይ የ ስኳር ልማት ይ ካሄዳል ብ ዬ አስቤ አላውቅም ፡፡ መንግስት በዚህ ቦታ ልማት እንዲካሄድ አድርጎ እኔንና ቤተሰቦቼን እንዲሁም ሌሎች ወገኖቼን የልማቱ ተጠቃሚ በማድረጉ አመሰግናለሁ» በማለት የሚናገሩት የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሰራተኛ ናቸው፡፡ ፕሮጀክቱ በተቋቋመበት አካባቢ ተወልደው ያደጉ በመሆናቸው አካባቢውን ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ በአካባቢው ልማት ሲካሄድ ከማየት በላይ የሚያስደስታቸው ነገር እንደሌለም ነው የሚናገሩት፡፡ የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ከእንግዳው ጋር ያደረገውን ቆይታ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ ጥያቄ፡ ስምዎትን የቤተሰብዎን ሁኔታ በአጭሩ ቢነግሩን ? ስሜ አቡዓለም ቡታ ሁሉቃ ይባላል፡፡ የስራ ድርሻዬ በፋይናንስ፣ አቅርቦትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዘርፍ የጠቅላላ መጋዘን ኃላፊ ነኝ፡፡ ባለትዳርና የስድስት ልጆች አባት ነኝ፡፡ ጥያቄ፡ የዲዴሳ ሸለቆ የስኳር ልማቱ በአካባቢው ከመጀመሩ በፊት ምን ይመስል ነበር? የስኳር ል ማት ፕ ሮጀክቱ በተቋቋመበት የዲዴሳ ሸለቆ ተወልጄ ያደግሁበት አካባቢ በመሆኑ ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፡፡ ምቹ እንዲሆን ተደርጎ ለልማት መዋሉ ይገርመኛል፡፡ የአል-ሃበሻ ኃላፊነቱ የተወሰነ የስኳር ፋብሪካ ከመቋቋሙ በፊት አካባቢው በረዣዥም ሳርና እፅዋት የተሸፈነ ስለነበር የአንበሳ፣ የጎሽ፣ የአጋዘን፣ የጉማሬ፣ የዝንጀሮና የሌሎች የዱር አራዊት መናኸሪያ ነበር፡፡ በዚህ ቦታ ላይ የስኳር ልማት ይካሄዳል ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡ ዛሬ ይህ ቦታ በተለምዶ “ነጩ ወርቅ” ተብሎ የሚጠራው ስኳር የሚመረትበት ቦታ ለማድረግ የተሰሩት ስራዎች በጣም አስደሳች ናቸው፡፡ መንግስት በዚህ ቦታ ላይ ልማት እንዲካሄድ አድርጎ እኔንና ቤተሰቦቼን እንዲሁም ሌሎች ወገኖቼን የልማቱ ተጠቃሚ በማድረጉ ሳላመሰግነው አላልፍም፡፡ ጥያቄ፡ የስኳር ልማቱ ለእርስዎና ለአካባቢው ሕብረተሰብ ምን ጥቅም አስገኘ? ፕሮጀክቱ ለእኔና ለአካባቢው ማሕበረሰብ ያስገኘውን ጠቀሜታ ከራሴ ገጠመኝ ተነስቼ ልንገርህ፡፡ በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ አሁን ኮማንድ - ሁለት ተብሎ በሚጠራው የሸንኮራ አገዳ ማሳ አካባቢ የእርሻ መሬት ነበረኝ፡፡ ሌሎች ሁለት ጓደኞቼም በዚሁ አካባቢ የእርሻ መሬት ስለነበራቸው የእርሻ ስራውን በጋራ ነበር የምንሰራው፡፡ አካባቢው ቆላማና ኃይለኛ የወባ ወረርሽኝ የነበረበት ከመሆኑም በላይ እንዳሁኑ የሕክምና እና የሌሎች መሰረተ-ልማት ተቋማት አልነበሩም፡፡ እነዚያ ሁለት ጓደኞቼ በወባ በሽታ ታመው በህክምና ዕጦት በሞት ተለዩኝ፡፡ የእኔም ዕጣ ፈንታ በወባ በሽታ ተይዞ መሞት እንደሆነ ነበር የማስበው፡፡ ከዛሬ ነገ በወባ 12 13
  • 8. ለ በ ለ ጠ መ ረ ጃ የ ኮ ር ፖ ሬ ሽ ኑ ን ድ ረ ገ ጽ ይ ጎ ብ ኙ W W W . e t s u g a r . g o v . e t | | f a c e b o o k . c o m / e t s u g a r 14 በ ስ ኳ ር ኮ ር ፖ ሬ ሽ ን የ ኮ ሚ ዩ ኒ ኬ ሽ ን ዳ ይ ሬ ክ ቶ ሬ ት በ የ 3 ወ ሩ የ ሚ ዘ ጋ ጅ ዜ ና መ ጽ ሔ ት 15 አርጆ ዲዴሳ ስኳር ስኳር ልማት ፕሮጀክት የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ወለጋና በኢሉአባቦራ ዞኖች በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ ከአዲስ አበባ ጅማ-በደሌ-ነቀምቴ በሚወስደው መንገድ 540 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ በኢሉአባቦራ፣ በምስራቅ ወለጋና በጅማ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ 49 ቀበሌዎችን የሚያካትት ሲሆን በ50 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ መሬት ባለቤት ነው፡፡ የአካባቢው ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ በአማካይ 1350 ሜትር ሲሆን፣ የአየር ሁኔታው ሞቃታማ ነው፡፡ አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኑ ደግሞ 1400 ሚሊ ሊትር ይደርሳል፡፡ የዝናብ ስርጭቱም ከግንቦት እስከ ጥቅምት ይዘልቃል፡፡ በአብዛኛው ጥቁርና አልፎ አልፎ ቀይ ቡናማ አፈር የሚገኝበት ይህ አካባቢ ከአየር ንብረቱ ጋር ተዳምሮ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ምቹና ተስማሚ እንዲሆን አስችሎታል፡፡ የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት አል ሐበሻ ስኳር ፋብሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በሚል መጠሪያ የፓኪስታን ዜግነት ባለው ባለሃብት እ.ኤ.አ አቆጣጠር በ2009 ተቋቁሞ የነበረ ሲሆን፣ ኩባንያው ፕሮጀክቱን ማስቀጠል ባለመቻሉ ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር የሽያጭ ውል በመፈጸም እ.ኤ.አ ከነሐሴ 2012 ጀምሮ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን ንብረትነት ተዘዋውሯል፡፡ ፕሮጀክቱ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን በተዘዋወረበት ወቅት የፋብሪካው የግንባታ ስራ ከዘጠና በመቶ በላይ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ከ2005 በጀት ዓመት ጀምሮ የስራ አመራር አባላት ተመድቦለትና በየደረጃው የሰው ኃይል ተሟልቶለት ተልዕኮውን ለማሳካት እየሰራ ይገኛል፡፡ በፕሮጀክቱ የተገነባው ፋብሪካ በመጀመሪያ ምዕራፍ በቀን 8 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፡፡ አጠቃላይ ዲዛይኑ ግን ወደፊት 12 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ ፋብሪካው በግብአትነት የሚጠቀምበትን ሸንኮራ አገዳ ለማልማት የሚውለው ውሃ ከዲዴሳ ወንዝ የሚያገኝ ሲሆን፣ በወንዙ ላይ የሚገነባውን ግድብ የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በቀጥታ ከወንዙ ውሃ በፓምፕ በመሳብ 1 ሺህ 665 እናስተዋውቃችሁ ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ መሸፈን ተችሏል፡፡ ፋብሪካው ከስኳር ምርቱ በተጨማሪ ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ራሱን ከመቻል አልፎ ቀሪውን ለብሔራዊ ቋት እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡ ከፍተኛ የኤታኖል ምርት የማምረት አቅምም ይኖረዋል፡፡ በ2007 የበጀት አመት ምርት እንደሚጀምር የሚጠበቀው የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በአሁኑ ጊዜ የፋብሪካውን ቀሪ የግንባታ ስራ ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ስራ በሚጀምርበት ወቅት በራሱ ይዞታ ከሚያለማው የሸንኮራ አገዳ በተጨማሪ የአካባቢውን አርሶ አደሮች በአውትግሮወር ልማት በማደራጀት የሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በማቅረብ ኑሮአቸውን እንዲያሻሽሉ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡ ለዚህም እንዲረዳ ከዞን፣ ከወረዳና ከቀበሌ አመራር አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች ተደርገዋል፡፡ የሥራ ድርሻ ያልገደበው የምርታማነት ርብርብ በፊንጫአና ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች (የክረምቱን ወራት ለመሻማት የፋብሪካዎቹ አመራሮችና የቢሮ ሰራተኞች በእርሻ ማሳ)