SlideShare a Scribd company logo
1 of 2
Download to read offline
አምሳሉ ሁሉቃ (ኦፕሬሽን ማናጀር) 2007
ሆቴል እና የቤት አያያዝ ሰራተኞች ጉልህ ሚናዎች፤ አምሳሉ ሁሉቃ፡፡ ገፅ 1
ሆቴል እና የቤት አያያዝ ሰራተኞች ጉልህ ሚናዎች፡-
አምሳሉ ሁሉቃ፣ 2007 ዓ.ም
ኦፕሬሽን ማናጀር፣ (ፓራዳዝ ሎጅ አርባምንጭ)
መግቢያ
ብዙ ሰዎች የቤት አያያዝ ሰራተኞች የእንግዳ ክፍል እና ሌሎችን ስፍራዎች የሚያፀዱ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡
ይህ ማለት የቤት አያያዝ ሰራተኞች በእለት ስራ ላይ በሆኑበት ወቅት የክፍሉን ወይም የአከባቢውን ፅዳት
ብቻ የሚተገብሩ ቢሆን ኖሮ የሆቴሉ እና የእንግዶች ግንኙነት በሚቀርብላቸው የእንግዳ ክፍል ሁኔታ ላይ
በዘለቄታማነት በደስታ የታጀበ ላይሆን ይችላል ብለን ልንወስድ ይገባል፡፡
በአንድ እንግዳ ክፍል ውስጥ ከቤት አያያዝ ሰራተኛ የተሻለ ስለ ክፍሉ ይዘት እና አጠቃላይ ግናዛቤ ያለው
የሆቴል ሰራተኛ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይህም ሲባል አንድ የቤት አያያዝ ሰራተኛ የእንግዳ ክፍል
በጥልቀት እና በዝርዝር የመረዳት አቅም አላቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ የቤት አያያዝ ሰራተኞች አንድን የእንግዳ
ክፍል ለማፅዳት የሚጠቀሙበት የአሰራር ስርዓት የተበጀለት በመሆኑ እያንዳንዱን የክፍሉን ቁሳቁስ
የመንካት፣ የማየት፣ የመፈተሽ ተግባራትን በየእለቱ ስለሚከውኑ ነው፡፡ ይሀን አሰራር በበለጠ ሁኔታ
የዘመነ ለማድረግ ደግሞ የሆቴል አስተዳደሮች እና ባለቤቶች የስራ ክፍሉን በላቀ አደረጃጀት እና
በተፈላጊው መልኩ ማቀናጀት ይገባቸዋል፡፡
የቤት አያያዝ ሰራተኞች አያሌ የስራ ላይ ሚናዎች ቢኖራቸውም ከዚህ የሚከተሉት ግን ግንባር ቀደምት
ናቸው፡፡-
1. የውበት እና የፅዳት ሚና፡- በሆቴል ስራ አደረጃጀት ውስጥ የቤት አያያዝ ስራ ክፍል
የተመሰረተበት መሪ ዓለማ የውበት እና የፅዳት ሚና ነው፡፡ የቤት አያያዝ ሰራተኞች በሆቴሉ ቅጥር
ግቢ ውስጥ በተመደቡበት አከባቢ ሁሉ የውበት እና የፅዳት ሚና ይሰጣቸዋል፡፡ አከባቢውን
የመጥረግ፣ የመወልወል፣ የማጠብ፣ የመንከባከብ እና በአከባቢው ላይ እሴትን የመጨመር ትቅ
ሃላፊነት አላቸው፡፡ በአከባቢ ላይ እሴትን የመጨመር ሃላፊነት ሲባል ደግሞ በእንግዳ ክፍል፣
በምግብ አዳራሽ፣ በመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ በሰርግ እና በሌሎች ዝግጅቶች እናዲሁም በእብግዶች
መቀበያ ስፍራዎች ላይ የአበባ ስራዎችን በጥልቅ ጥበብ በመስራት እና ሌሎች ለዓይን ውበት
የሚሆኑ የጥበብ ስራዎችን በመስራት ነው፡፡ እንግዲህ እንግዶች ወደ ሆቴል የሚመላለሱበት
ሚስጠር ውበት እና ፅዳት ሚስጥር በቤት አያያዝ ስራ ክፍል ሰራተኖች ላይ የወደቀ አይነግቡ ሚና
ነው፡፡
2. የእንግዳ ክፍል ቁሳቁስ ቁጥጥር እና የንብረት ቆጠራ ሚና፡- በዘመናዊ የሆቴል አደረጃጀት ስሌት
መሰረት አንድ የእንግዳ ክፍል በጣም ውስብስብ የሆነ ስፍራ በመሆን ላይ ነው፡፡ እነዚህ
ለአንግዶች መገልገያነት ወደ ክፍል የሚገቡት በተለያየ ቅርፅ እና ይዘት ነው፡፡ ከፊሎቹ
ተንቀሳቃሽ፣ ከፊሎቹ አላቂዎች፣ ከፊሎቹ በተውሶ ለእንግዳው የሚቀርቡ፤ ከፊሎቹ
የማይንቀሳቀሱ፣ ከፊሎቹ በጣም ውድ ፤ ከፊሎቹ ተሰባሪ፣ ከፊሎቹ ባህላዊ እና ከፊሎቹ ደግሞ
የተለየ ጥንቃቄ የሚሹ እንዲያው ለአደጋ ቅርብ የሆኑ ቁሳቁስ ናቸው፡፡ በመሆኑም የእንግዳ ክፍል
ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ ሃላፊነት ያለባቸው የቤት አያያዝ ሰራተኞች እነዚህን ንብረት ከአደጋ
አምሳሉ ሁሉቃ (ኦፕሬሽን ማናጀር) 2007
ሆቴል እና የቤት አያያዝ ሰራተኞች ጉልህ ሚናዎች፤ አምሳሉ ሁሉቃ፡፡ ገፅ 2
ተጠብቀው እና ከቁጥር ሳይጎድሉ የማቆየት የቤት አያያዝ ሰራተኞች ተቀዳሚ የስራ ላይ ሚናቸው
ነው፡፡ ይህ ንብረትን የመጠበቅ እና የመቆጣጠር ሃላፊነት በተለይ በቤት አያያዝ የስራ ላይ
መሪዎች አስተባበሪነት እና የቅርብ ክትትል አቅም ላይ የሚወሰን ይሆናል፡፡ በእንግዳ ክፍሎች
ውስጥ ለአንግዶች መገልገያነት የሚቀርቡ ቁሳቁሶች በጣም የረቀቀ እና የተሳለጠ የቁጥጠር ስርዓት
ያልተበጀለት እንደሆነ ከእለታት እንድ ቀን “የማለዳ ጤዛ” የመሆን እድላቸው የሰፋ ነው፡፡ ይህም
የሆቴሉን አስተዳደር እና ባለቤቶች “ሳይቃጠል በቅጠል” ያስብላል፡፡
3. የደህንነት እና ፀጥታ ሚና፡- በምዕራቡ ዓለም ሆቴልን መሰረት አድርገው የሚሰሩ ወንጀል ነክ
ድራማዎች እና ፊልሞች በብዛት የቤት አያያዝ ስራ ክፍልን እና የሆቴሉን እንግዳ መቀበያ ስራ
ክፍል የሴራ መጠንሰሻ ያደርጉታል ወይም ለከረረው ወንጀል ሴራ ፍፃሜው በሆቴል ውስጥ
እንዲሆን ያደርጉታል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመረጃ እና የቴክኖሎጂ እድገት አለምን ሳትፈልገው በሚመሰል
መልኩ በመቆጣጠር እና አሰራሮችን ወደ ኮምፒውተር ተኮር አደረጋቸው እነጂ የሆቴል ደህንነት
በሰው ልጆች የማየት እና የመስማት አቅም ላይ ብቻ የተመሰረት ነበር፡፡ በሃገራችን አነጋገር “ቤት
ገመና ነው” ሲባል ሰዎች በዱር ውሎአቸው ከሌሎች ሸሽገውት የዋሉትን የግል ገመና ከቤት ሲገቡ
ለግላቸው እና ለቤተሰባቸው ግልጽ ያደርጉታል ማለት ይመስለኛል፡፡ የቤት አያያዝ ሰራተኞች
የአንግዶችን ገመና የመበርበር ፈቃድ እና ሞራል አላቸው ለማለት ባሆንም የእንግዶችን ባህሪ፣
የእንግዶችን እንቅስቃሴ፣ የእንግዶች የተለየ ሁኔታ፣ የእንግዶችን የተሸሸገ ጉዳይ፣ የእንግዶችን
አመለከከት እና ሌሎች ለሆቴሉ እና ለሃገር ጭምር ስጋት እና እድል ሊሆኑ የሚችሉ
አጋጣሚዎችን የመጠቆም እድል አላቸው፣ ከአደጋ በፊት የማስጠንቅ ደወል ማሰማት ይችላሉ
ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡
4. የንብረት ጥገና እና ማንበር ሚና፡-ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “ማንበር” የሚለውን ቃል
ከእንግሎዘኛው “ maintenance “ ጋር አቻ ትርጉም ሰጥቶት ጥሩ ምክር አስተላልፎበታል፡፡
በሃገራችን አገላለፅ ትገና ማለት አንድ ቁስ ከተሰበረ በኃላ ወይም አገልግሎት መስጠት ካቆመ በኃላ
የሚደረግ ማስተካከያ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ጥገና ማለት እንደ እንግሊዘኛው
የመከታተል፣ የማረም፣ የመጠበቅ፣ የመንከባከብ፣ እና አገልግሎት መስጠት ሲያቆም ወደ ቀድሞው
ተግበሩ መመለስ ነው፡፡ እንግዲህ በሆቴል ውስጥ የጥገና ተግባር በተለያዩ መልክ ሊሰጥ ችላል፡፡
ቅድመ መከላከል ጥገና፣ የዘወትር ጥገና፣ እና የማዳን ትገና ይከናወናል፡፡ የቤት አያያዝ ሰራተኛ
አንድን አልጋ በማንጠፍ ተግባር ላይ የአልጋው ማሰሪያዎች በምን ይዘት ላይ እንደሆኑ፣ የአልጋው
መቆሚያዎች በምን ሁኔታ ላይ እንደሆኑ፣ ፍራሹ በየትኛው ጫፍ ያለቀ መሆኑን፣ የአልጋው
ርብራት የረገበ እና ያልረገበ መሆንን እና ሌሎቹኑም የአልጋው ክፍላት የማየት የመዳበስ እና
መመረጃ የማስተላለፍ አሊያ የማስተካከል አጋጣሚዎች አላቸው፡፡ በዚሁ መልኩ ሌሎች
ቁሳቁሶችንም የማፅዳት ተግባር ሲፈፅሙ የማየት፣ የመዳበስ፣ በአገልግሎት ላይ ስለመሆናቸው
የመሞከር እና የማስታወቅ ተግባርን ይፈፅማሉ፡፡ ምሳሌ- ቲቪ፣ ስልክ፣ ሙቅ ውሃ፣ መብራት፣ እና
የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በሌላ አማርኛ ማፅዳት በራሱ የመጀመሪያ ደረጃ ጥገና መሆኑን
ልብ ልንል ይገባል፡፡
ይቀጥላል . . .

More Related Content

Featured

Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Kurio // The Social Media Age(ncy)
 

Featured (20)

AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfAI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
 
Skeleton Culture Code
Skeleton Culture CodeSkeleton Culture Code
Skeleton Culture Code
 
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
 
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
 
How to have difficult conversations
How to have difficult conversations How to have difficult conversations
How to have difficult conversations
 
Introduction to Data Science
Introduction to Data ScienceIntroduction to Data Science
Introduction to Data Science
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best Practices
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project management
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
 
Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...
Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...
Unlocking the Power of ChatGPT and AI in Testing - A Real-World Look, present...
 
12 Ways to Increase Your Influence at Work
12 Ways to Increase Your Influence at Work12 Ways to Increase Your Influence at Work
12 Ways to Increase Your Influence at Work
 
ChatGPT webinar slides
ChatGPT webinar slidesChatGPT webinar slides
ChatGPT webinar slides
 
More than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike Routes
More than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike RoutesMore than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike Routes
More than Just Lines on a Map: Best Practices for U.S Bike Routes
 

The role of room attendant (የቤት አያያዝ ሰራተኞች ሚና)

  • 1. አምሳሉ ሁሉቃ (ኦፕሬሽን ማናጀር) 2007 ሆቴል እና የቤት አያያዝ ሰራተኞች ጉልህ ሚናዎች፤ አምሳሉ ሁሉቃ፡፡ ገፅ 1 ሆቴል እና የቤት አያያዝ ሰራተኞች ጉልህ ሚናዎች፡- አምሳሉ ሁሉቃ፣ 2007 ዓ.ም ኦፕሬሽን ማናጀር፣ (ፓራዳዝ ሎጅ አርባምንጭ) መግቢያ ብዙ ሰዎች የቤት አያያዝ ሰራተኞች የእንግዳ ክፍል እና ሌሎችን ስፍራዎች የሚያፀዱ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ማለት የቤት አያያዝ ሰራተኞች በእለት ስራ ላይ በሆኑበት ወቅት የክፍሉን ወይም የአከባቢውን ፅዳት ብቻ የሚተገብሩ ቢሆን ኖሮ የሆቴሉ እና የእንግዶች ግንኙነት በሚቀርብላቸው የእንግዳ ክፍል ሁኔታ ላይ በዘለቄታማነት በደስታ የታጀበ ላይሆን ይችላል ብለን ልንወስድ ይገባል፡፡ በአንድ እንግዳ ክፍል ውስጥ ከቤት አያያዝ ሰራተኛ የተሻለ ስለ ክፍሉ ይዘት እና አጠቃላይ ግናዛቤ ያለው የሆቴል ሰራተኛ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይህም ሲባል አንድ የቤት አያያዝ ሰራተኛ የእንግዳ ክፍል በጥልቀት እና በዝርዝር የመረዳት አቅም አላቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ የቤት አያያዝ ሰራተኞች አንድን የእንግዳ ክፍል ለማፅዳት የሚጠቀሙበት የአሰራር ስርዓት የተበጀለት በመሆኑ እያንዳንዱን የክፍሉን ቁሳቁስ የመንካት፣ የማየት፣ የመፈተሽ ተግባራትን በየእለቱ ስለሚከውኑ ነው፡፡ ይሀን አሰራር በበለጠ ሁኔታ የዘመነ ለማድረግ ደግሞ የሆቴል አስተዳደሮች እና ባለቤቶች የስራ ክፍሉን በላቀ አደረጃጀት እና በተፈላጊው መልኩ ማቀናጀት ይገባቸዋል፡፡ የቤት አያያዝ ሰራተኞች አያሌ የስራ ላይ ሚናዎች ቢኖራቸውም ከዚህ የሚከተሉት ግን ግንባር ቀደምት ናቸው፡፡- 1. የውበት እና የፅዳት ሚና፡- በሆቴል ስራ አደረጃጀት ውስጥ የቤት አያያዝ ስራ ክፍል የተመሰረተበት መሪ ዓለማ የውበት እና የፅዳት ሚና ነው፡፡ የቤት አያያዝ ሰራተኞች በሆቴሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተመደቡበት አከባቢ ሁሉ የውበት እና የፅዳት ሚና ይሰጣቸዋል፡፡ አከባቢውን የመጥረግ፣ የመወልወል፣ የማጠብ፣ የመንከባከብ እና በአከባቢው ላይ እሴትን የመጨመር ትቅ ሃላፊነት አላቸው፡፡ በአከባቢ ላይ እሴትን የመጨመር ሃላፊነት ሲባል ደግሞ በእንግዳ ክፍል፣ በምግብ አዳራሽ፣ በመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ በሰርግ እና በሌሎች ዝግጅቶች እናዲሁም በእብግዶች መቀበያ ስፍራዎች ላይ የአበባ ስራዎችን በጥልቅ ጥበብ በመስራት እና ሌሎች ለዓይን ውበት የሚሆኑ የጥበብ ስራዎችን በመስራት ነው፡፡ እንግዲህ እንግዶች ወደ ሆቴል የሚመላለሱበት ሚስጠር ውበት እና ፅዳት ሚስጥር በቤት አያያዝ ስራ ክፍል ሰራተኖች ላይ የወደቀ አይነግቡ ሚና ነው፡፡ 2. የእንግዳ ክፍል ቁሳቁስ ቁጥጥር እና የንብረት ቆጠራ ሚና፡- በዘመናዊ የሆቴል አደረጃጀት ስሌት መሰረት አንድ የእንግዳ ክፍል በጣም ውስብስብ የሆነ ስፍራ በመሆን ላይ ነው፡፡ እነዚህ ለአንግዶች መገልገያነት ወደ ክፍል የሚገቡት በተለያየ ቅርፅ እና ይዘት ነው፡፡ ከፊሎቹ ተንቀሳቃሽ፣ ከፊሎቹ አላቂዎች፣ ከፊሎቹ በተውሶ ለእንግዳው የሚቀርቡ፤ ከፊሎቹ የማይንቀሳቀሱ፣ ከፊሎቹ በጣም ውድ ፤ ከፊሎቹ ተሰባሪ፣ ከፊሎቹ ባህላዊ እና ከፊሎቹ ደግሞ የተለየ ጥንቃቄ የሚሹ እንዲያው ለአደጋ ቅርብ የሆኑ ቁሳቁስ ናቸው፡፡ በመሆኑም የእንግዳ ክፍል ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ ሃላፊነት ያለባቸው የቤት አያያዝ ሰራተኞች እነዚህን ንብረት ከአደጋ
  • 2. አምሳሉ ሁሉቃ (ኦፕሬሽን ማናጀር) 2007 ሆቴል እና የቤት አያያዝ ሰራተኞች ጉልህ ሚናዎች፤ አምሳሉ ሁሉቃ፡፡ ገፅ 2 ተጠብቀው እና ከቁጥር ሳይጎድሉ የማቆየት የቤት አያያዝ ሰራተኞች ተቀዳሚ የስራ ላይ ሚናቸው ነው፡፡ ይህ ንብረትን የመጠበቅ እና የመቆጣጠር ሃላፊነት በተለይ በቤት አያያዝ የስራ ላይ መሪዎች አስተባበሪነት እና የቅርብ ክትትል አቅም ላይ የሚወሰን ይሆናል፡፡ በእንግዳ ክፍሎች ውስጥ ለአንግዶች መገልገያነት የሚቀርቡ ቁሳቁሶች በጣም የረቀቀ እና የተሳለጠ የቁጥጠር ስርዓት ያልተበጀለት እንደሆነ ከእለታት እንድ ቀን “የማለዳ ጤዛ” የመሆን እድላቸው የሰፋ ነው፡፡ ይህም የሆቴሉን አስተዳደር እና ባለቤቶች “ሳይቃጠል በቅጠል” ያስብላል፡፡ 3. የደህንነት እና ፀጥታ ሚና፡- በምዕራቡ ዓለም ሆቴልን መሰረት አድርገው የሚሰሩ ወንጀል ነክ ድራማዎች እና ፊልሞች በብዛት የቤት አያያዝ ስራ ክፍልን እና የሆቴሉን እንግዳ መቀበያ ስራ ክፍል የሴራ መጠንሰሻ ያደርጉታል ወይም ለከረረው ወንጀል ሴራ ፍፃሜው በሆቴል ውስጥ እንዲሆን ያደርጉታል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመረጃ እና የቴክኖሎጂ እድገት አለምን ሳትፈልገው በሚመሰል መልኩ በመቆጣጠር እና አሰራሮችን ወደ ኮምፒውተር ተኮር አደረጋቸው እነጂ የሆቴል ደህንነት በሰው ልጆች የማየት እና የመስማት አቅም ላይ ብቻ የተመሰረት ነበር፡፡ በሃገራችን አነጋገር “ቤት ገመና ነው” ሲባል ሰዎች በዱር ውሎአቸው ከሌሎች ሸሽገውት የዋሉትን የግል ገመና ከቤት ሲገቡ ለግላቸው እና ለቤተሰባቸው ግልጽ ያደርጉታል ማለት ይመስለኛል፡፡ የቤት አያያዝ ሰራተኞች የአንግዶችን ገመና የመበርበር ፈቃድ እና ሞራል አላቸው ለማለት ባሆንም የእንግዶችን ባህሪ፣ የእንግዶችን እንቅስቃሴ፣ የእንግዶች የተለየ ሁኔታ፣ የእንግዶችን የተሸሸገ ጉዳይ፣ የእንግዶችን አመለከከት እና ሌሎች ለሆቴሉ እና ለሃገር ጭምር ስጋት እና እድል ሊሆኑ የሚችሉ አጋጣሚዎችን የመጠቆም እድል አላቸው፣ ከአደጋ በፊት የማስጠንቅ ደወል ማሰማት ይችላሉ ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ 4. የንብረት ጥገና እና ማንበር ሚና፡-ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “ማንበር” የሚለውን ቃል ከእንግሎዘኛው “ maintenance “ ጋር አቻ ትርጉም ሰጥቶት ጥሩ ምክር አስተላልፎበታል፡፡ በሃገራችን አገላለፅ ትገና ማለት አንድ ቁስ ከተሰበረ በኃላ ወይም አገልግሎት መስጠት ካቆመ በኃላ የሚደረግ ማስተካከያ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ጥገና ማለት እንደ እንግሊዘኛው የመከታተል፣ የማረም፣ የመጠበቅ፣ የመንከባከብ፣ እና አገልግሎት መስጠት ሲያቆም ወደ ቀድሞው ተግበሩ መመለስ ነው፡፡ እንግዲህ በሆቴል ውስጥ የጥገና ተግባር በተለያዩ መልክ ሊሰጥ ችላል፡፡ ቅድመ መከላከል ጥገና፣ የዘወትር ጥገና፣ እና የማዳን ትገና ይከናወናል፡፡ የቤት አያያዝ ሰራተኛ አንድን አልጋ በማንጠፍ ተግባር ላይ የአልጋው ማሰሪያዎች በምን ይዘት ላይ እንደሆኑ፣ የአልጋው መቆሚያዎች በምን ሁኔታ ላይ እንደሆኑ፣ ፍራሹ በየትኛው ጫፍ ያለቀ መሆኑን፣ የአልጋው ርብራት የረገበ እና ያልረገበ መሆንን እና ሌሎቹኑም የአልጋው ክፍላት የማየት የመዳበስ እና መመረጃ የማስተላለፍ አሊያ የማስተካከል አጋጣሚዎች አላቸው፡፡ በዚሁ መልኩ ሌሎች ቁሳቁሶችንም የማፅዳት ተግባር ሲፈፅሙ የማየት፣ የመዳበስ፣ በአገልግሎት ላይ ስለመሆናቸው የመሞከር እና የማስታወቅ ተግባርን ይፈፅማሉ፡፡ ምሳሌ- ቲቪ፣ ስልክ፣ ሙቅ ውሃ፣ መብራት፣ እና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በሌላ አማርኛ ማፅዳት በራሱ የመጀመሪያ ደረጃ ጥገና መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡ ይቀጥላል . . .