SlideShare a Scribd company logo
1 of 16
Download to read offline
ለብሉስታር አባል ክሊኒኮች በነጻ የሚታደል-በየ3 ወሩ የሚዘጋጅ
Issue 2, OCTOBER- 2015
በየ3 ወሩ ተዘጋጅቶ ለብሉስታር አባል ክሊኒኮች በነጻ የሚታደል
Issue 3, November,2015
3. ኮከብ የብሉ ስታር እንግዳችን
1. የብሉ ስታር መልዕክት
2. ባለሙያው ምን ይላል?
የብሉ ስታር
መልዕክትውድ የተከበራችሁ የብሉ ስታር ጤና አውታር አባል አጋሮቻችን ከሁሉ
በፊት በማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ መላው ሠራተኞች ስም
የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁ፡፡
እንደሚታወቀው ድርጅታችን ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከግሉ
የጤና ዘርፍ ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚፈልገው እና እየሰራ ያለው
የግሉ ጤና ዘርፍ ካለው እምቅ አቅም አኳያ የእናቶቻችን ጤና
ለማሻሻል እና አማራጭ የስነ ተዋልዶ ጤና ለማህበረሰቡ ለማድረስ
እየተደረገ ባለው አገራዊ ጥረት ውስጥ ሊጫወቱ የሚችሉት ሚና
እጅግ በጣም የገዘፈ እንደሆነ ስለምናምን ነው፡፡ ከዚህ አንፃር
ድርጅታችን ከእናንተ ስልታዊ አጋሮቻችን /Strategic Part-
ners/ ጋር በመስራታችን አማራጭ የስነ ተዋልዶ ጤና እና
የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ለተጠቃሚዎች በማድረስ በኩል እያሳየን
ያለው ዉጤት እጅግ በጣም የሚያበረታታ ነው፡፡ ለአብነት ያህል
በ2007 ዓ.ም ብቻ ድርጅታችን ከብሉ ስታር የጤና ማዕከላት ጋር
በመስራት ቁጥራቸው ከ524,201 ለሚልቁ ዜጎች የተለያዩ የስነ
ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን ለመስጠት ተችሏል፡፡
በዚህ በያዝነው ዓመት (2015 እ.ኤ.አ) ድርጅታችን በዓለም አቀፍ
ደረጃ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት እ.ኤ.አ 1976 ጀምሮ 100
ሚሊዮን ተገልጋዮችን /100 Million Clients/ የአገልግሎት
ተደራሽ ያደረገበት አመት በመሆኑ ድርጅታችን በሚሰራባቸው አገሮች
ቡፖ|1
ዉስጥ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ ይህ እለትም በማሪስቶፕስ
ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በኩልም በድምቀት ተከብሮ አልፏል፡፡ በዚህ
የስኬት ሃዲድ ዉስጥ አብረውን የሚሰሩ የግል ክሊኒኮች አስተዋፅኦ
ከፍተኛ እንደሆነም የሚታወቅ ነው፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ዉስጥ አገልግሎት
መስጠት ከጀመረ እነሆ 25 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህንንም የ 25
አመታት ጉዞአችንን በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ እንገኛለን።
በዚህ በ25 ዓመታት ጉዞአችን ዉስጥ በድርጅታችን በኩል እየተሰጡ
በሚገኙ ዘርፈ ብዙ የጤና አገልግሎቶች ምክንያት አያሌ ዜጎች
ተጠቃሚ ከመሆናቸውም ባሻገር በስነተዋልዶ ጤና መረጃ እና
አገልግሎት ተደራሽነት ውስንነት ምክንያት በሴቶች ወገኖቻችን ላይ
ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና መታወኮችን ከመከላከል አኳያም ጉልህ ሚና
መጫወት እንደቻልን እናምናለን፡፡ ከዚህ ጉልህ ሚና እና ከተገኙ
ውጤቶች በስተጀርባ በመንግስት በኩል እየተደረገልን ባለው እገዛ
ከእናንተ ከብሉስታር አባል ክሊኒኮች ጋር በቅርብ መስራታችን እና
ከሁሉም በላይ ደግሞ በምንሰጠው የስነ ተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ
እቅድ አገልግሎት እንዲሁም የእናቶች እና ህጻናት ጤና አገልግሎት
ዙሪያ ዘወትር አስተያየት በመስጠት የተሻለ እና ጥራቱን የጠበቀ
አገልግሎት እንድንሰጥ የሚያተጉን የተገልጋዮች /Client/ ሚና
ታላቅ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ለዚህም ከፍተኛ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡
በቀጣዩ ዓመት 2016 (እ.ኤ.አ) ድርጅታችን ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል
ኢትዮጵያ በመንግስት በኩል የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት፣ የእናቶች እና
ህጻናት ጤና አገልግሎትን ለማዳረስ በዘረጋው እቅድ መሰረት ከብሉ
ስታር ክሊኒኮች ጋር በመተባበር በቀጣይነትም ገንቢ ሚና ለመጫወት
በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡
በመጨረሻም አጋር የብሉ ሰታር ክሊኒኮች ጥራቱን የጠበቀ እና
ተገልጋዮችን ሊያረካ የሚችል የስነተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ
እቅድ አገልግሎት በመስጠት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ በቀጣይነትም
እንድታበረክቱ እየጠየቅኩኝ በአገልግሎት አሰጣጣችሁ ዙሪያ እየታዩባችሁ
ያሉትን ድክመቶች ለማሻሻል እና እያሳያችሁት ያለውን ጠንካራ ጎን
ለማጎልበትም በምታደርጉት ጥረት ዉስጥ ድርጅታችን በቀጣይነትም
ከጎናችሁ በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እና እገዛ የሚያደርግ መሆኑንም
በመጠቆም ነው፡፡
ሰላም ቆዩ!
አበበ ሽብሩ
ምክትል ካንትሪ ዳይሬክተር እና
የስትራቴጂ እና ዴቨሎፕመንት ዳይሬክተር
ቅምጥሏ
ቅምጥል አፍቅሬ፣
ለሷ ተቸግሬ፣
ኩሽና እንዳትገባ ካልጋ እንዳትነሳ፣
ምግብ አብሳይ ቀጠርኩ ባስብላት ለሷ፡፡
የእንጀራ ጫፍ ጣቷን እንዳይቆርጣት ብዬ፣
አጉራሽም ቀጠርኩኝ አሳቢ መስዬ፡፡
ቅምጥሏን ፍቅሬን ድንገት ቢያስነጥሳት፣
ይማርሽ የምትል ሌላም ቀጠርኩላት፡፡
የሞልቃቃ ነገር፣
መጨረሻው አያምር፣
ቅጥ ያጣውን ፍቅሬን ውስጤን ስላየችው፣
ባል ቀጥረህ አምጣልኝ ብላኝ አረፈችው፡፡
		 በሰለሞን ወልዴ
ቡፖ|2
ዶ/ር ነጋ ተስፋው በማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የጥራትና
የክሊኒካል አገልግሎቶች ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ዛሬ ከእርሳቸው ጋር
በሚኖረን ቆይታ በሚከተሉት ሀሳቦች ዙሪያ ተወያየን፤ እናንተ
ደግሞ አንብባችሁ ጠቃሚ መረጃዎችን ታገኙ ዘንድ እንደሚከተለው
አቅርበነዋል፡፡
ብሉስታር ፦ የብሉ ስታር ክሊኒክ (የጤና እንክብካቤ ተቋማት)
ጥራት ወይም (Health- Care Quality) ስንል ምን ማለታችን
ነው?
ዶ/ር ነጋ ፦ የብሉ ስታር የጤና እንክብካቤ ተቋማት ጥራት ስንል
የተቋሙን ደንበኞች ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ፤ በአግባቡና ጥንቃቄ
በተሞላበት ሁኔታ ዘመናዊ ግኝቶችን በመጠቀም የሚሰጥ የጤና
አገልግሎት ማለታችን ነው፡፡ ይህ አይነቱ የጤና አገልግሎት አነስተኛ
ጥራትን፣ ደግሞ መስራትንና ብክነትን የሚቀንስ ሲሆን ጥራት አለው
እንላለን፡፡
ብሉስታር ፦ የጤና እንክብካቤ ተቋማት ጥራት መሟላት
የሚያስገኛቸው ጥቅሞች ምን ምን ናቸው?
ዶ/ር ነጋ ፦ የጤና እንክብካቤ ተቋማት ጥራት ከሚያስገኛቸው
ጥቅሞች መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ውጤታማ፣ በደንበኞች ፍላጎት
ላይ የተመሰረተ፣ ጊዜውን የጠበቀ፣ ሁለገብ፣ በቀላሉ የሚገኝ
በእኩልነት ላይ የተመሰረተ እና እሴቶችን የመጨመር አቅም ያለው
የጤና አገልግሎት ይገኝበታል፡፡
ብሉስታር ፦ የብሉ ስታር የጤና እንክብካቤ ተቋማት አገልግሎት
አሰጣጥ በማንኛውም ጊዜ ሊተገበሩ የሚገቡ ነገሮች ምንድን ናቸው
ይላሉ?
ዶ/ር ነጋ ፦ የብሉ ስታር ተቋማት ጥራትን ለማሟላት የደንበኞችን
መብት ሊያከብሩ ይገባቸዋል፡፡ የደንበኞች መብት ስንል ደንበኛው/ዋ
ሰብአዊ መብቱ/ትዋን በጠበቀ መልኩ መረጃን የማግኘት መብት፣
የአገልግሎቶች ተጠቃሚነት መብት፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ
የአገልግሎት ምርጫ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት፣ ምስጢሩ
የተጠበቀ የደንበኛ አገልግሎት፣ ምቾቱ የተጠበቀና ቀጣይነት ያለው
አገልግሎት ማለታችን ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በማንኛውም ጊዜ
ለድንገተኛ ህክምናዎች ዝግጁ መሆን እና ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር
ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን መተግበር ተገቢ መሆኑን ሊገነዘቡ
ይገባል፡፡
ባለሙያው
ምን ይላል?
ቡፖ|3
ኢንፌክሽንን እንዴት መከላከል
እንችላለን?
•	እጅን በመታጠብ
•	ጓንቶችን፣ ገዋኖችንና
	 መነጽሮችን በመጠቀም
•	ባክቴሪያ የሚገድሉ አንቲሴፕቲኮችን
	 በመጠቀም
•	በቀዶ ህክምና ወቅት ተገቢ
	 ጥንቃቄዎችን በመውሰድ
•	የህክምና መሳርያዎችን በንጽህናና
በጥንቃቄ በመጠቀም
•	ቆሻሻን በአግባበቡ በማስወገድ
ብሉስታር፦ በብሉ ስታር ክሊኒኮች ውስጥ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች
ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚኖራቸው ድርሻ ምን
ያህል ነው ይላሉ?
ዶ/ር ነጋ፦ የዚህ የብሉስታር መጽሄት ተደራሽ አካላት በብሉ ስታር
ክሊኒኮች ውስጥ የሚገኙ የጤና ሰራተኞችና የህክምና ባለሙያዎች
ናቸው፡፡ እናም ሁሉም የጤናው ተቋማት ባለሙያዎች ደረጃውን
የጠበቀ የህክምና እርዳታን የመስጠት ብቃት ማሟላት፣ የተቋሙን
አስተዳደራዊ አደረጃጀት ምቹ ማድረግ፣ በየጊዜው ተገቢውን
ስልጠና መውሰድ እንዲሁም ለባለሙያው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች
መሟላታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል
ኢትዮጵያ በይበልጥ ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ ነገሮች መካከል
በደንበኞች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት አሰጣጥና የተሟላ
የምክክር አገልግሎት ተደራሽነት ይገኙበታል፡፡ ይህንንም ተግባራዊ
ማድረግ የጤና ባለሙያዎቹ ድርሻ ነው ማለት ነው።
ብሉስታር፦ የብሉ ስታር ክሊኒኮች ከማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል
ኢትዮጵያ የሚያገኙት ድጋፍ ምን ይመስላል?
ዶ/ር ነጋ፦ ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ለብሉ ስታር
ክሊኒኮች የሚሰጠው ድጋፍ የምስረታ አባልነት ድጋፍ አንስቶ፦
የመሳሪያዎች ስልጠና እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ክትትል፣ የጥራት
ቴክኒክ እገዛና ቁጥጥር ድጋፍ ናቸው፡፡ ይህም የሚደረገው ጥራትን
በዘላቂነት ጠብቆ መጓዝና በየጊዜው አገልግሎቶች ላይ መሻሻል
ማድረግ የብሉ ስታር ክሊኒኮች ልዩ መለያ በመሆኑ ነው፡፡
ቡፖ|4
የሰራተኝነት ብቃትዎን ይፈትሹ
ከዚህ በታች የሚገኙት ጥያቄዎች ምን አይነት ሰራተኛ ነዎት የሚለውን
ይፈትሻሉ፡፡ እስቲ ጊዜ ወስደው ጥያቄዎቹን ለራስዎ በታማኝነት
ይመልሱ፡፡ ዉጤቱን በገጽ 12 ይመልከቱ::
1. ስራ ላይ በስራ ሰዓትዎ ይገኛሉ?
o	 አዎ እገኛለሁ
o	 አልገኝም
2. በስራ ላይ ከተመደበልዎት ስራ ውጪ ተጨማሪ ነገሮችን ይሰራሉ?
o	 አዎ እሰራለሁ
o	 አልሰራም
3. ከስራ ባልደረቦችዎ ጋር ሌሎች ሰራተኞችን ወይም ደንበኞችን 	
የማማት ልማድ አልዎት?
o	 አዎ አለኝ
o	 የለኝም
4. በስራዎ ሁልጊዜ ደስተኛ ነዎት?
o	 አዎ ነኝ
o	 አይደለሁም
5. የስራ ባልደረቦችዎንና ደንበኞችን በተለያዩ ነገሮች ለመርዳት 	
ምንጊዜም ዝግጁ ነዎት?
o	 አዎ ዝግጁ ነኝ
o	 ዝግጁ አይደለሁም
6. በስራ ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን የመፍታት አቅም አለኝ ብለው 	
ያምናሉ?
o	 አዎ አለኝ
o	 የለኝም
7. የተሰጥዎትን ስራ ምንጊዜም በተመደበልዎ ጊዜ ያጠናቅቃሉ?
o	 አዎ አጠናቅቃለሁ
o	 አላጠናቅቅም
8. የስራ ተነሳሽነት አልዎት?
o	 አዎ አለኝ
o	 የለኝም
ቡፖ|5
9. በቡድን የመስራት ልምድና ፍላጎት አለዎት?
o	 አዎ አለኝ
o	 የለኝም
10. ጊዜ ወስደው ከስራ ባልደረቦችዎ ጋር ለመተዋወቅና ለመግባባት 	
ይሞክራሉ?
o	 አዎ እሞክራለሁ
o	 አልሞክርም
11. በስራ ቦታ አለባበስዎ ለስኬት የሚያዘጋጅና ደንብን የተከተለ 	
ነው?
o	 አዎ ነው
o	 አይደለም
12. በስራ ላይ ከሚጠበቅብዎ በላይ እጅግ በላቀ መልኩ ተሽለው 	
ለመገኘት ጥረት ያደርጋሉ?
o	 አዎ እጥራለሁ
o	 አልጥርም
አገባሽ ነበረ
የቁመቴን ማጠር የመልኬን ማስከፋት፣
ከጉዳይ ባትቆጥሪው የገፄን ደም ግባት፣
ኮልታፋ አንደበቴን ሸካራውን ድምጼን፣
ሰምተሸ ባትንቂያቸው ለዛ አልባ ቃላቴን፣
ፍፁም ድህነቴን አምነሽ ብትቀበይ፣
ፍቅርን ብታስበልጭ ከዚች ምድር ሲሳይ፣
አገባሽ ነበረ እሽ ብትይ አንቺ፣
በተለይ በተለይ ባልሽን ብትፈቺ፡፡
		
		 ዘላለም ምህረቱ
	
ቡፖ|6
አቶ አበራ አያና ይባላሉ፡፡ በበቆጂ ከተማ የብሉ ስታር አባል የሆነው
የአበራ መለስተኛ ክሊኒክ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ፤
በዚህ ዓመት በማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የብሉ ስታር
የክሊኒካል አገልግሎቶች ምዘና 98% በማስመዝገብ የከፍተኛ
ውጤት ባለቤት ለመሆን በቅተዋል፡፡ አቶ አበራ ከዚህ በተጨማሪ
የ3 ዋንጫዎችና የተለያዩ ሰርተፊኬቶች ተሸላሚ ሲሆኑ በበቆጂ
ከተማ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ደንበኞችን
በማስተናገድ ድንቅ ውጤትን እያስመዘገቡ የሚገኙ የጤና ባለሙያ
ናቸው፡፡ የአበራ መለስተኛ ክሊኒክ ለዛሬ በአርአያነት ያቀረብነው የብሉ
ስታር ክሊኒክ ነው፡፡ ከአቶ አበራ ጋር ያደረግነውን ቃለምልልስ እነሆ።
ብሉስታር፦ በቅድሚያ የዚህ አስደሳች ውጤት ባለቤት በመሆንዎ
እንኳን ደስ አልዎት፡፡ የብሉ ስታር አባል የሆኑት መቼ ነበር?
የአባልነት ጊዜዎንስ እንዴት ይገልጹታል?
አቶ አበራ፦ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ አበራ ክሊኒክ በብሉ ስታር አባልነት
የተመዘገበ ክሊኒክ ነው፡፡ በኔትዎርኩ የአባልነት ጉዞዬ እጅግ በጣም
አስደሳች ነው፡፡ ክሊኒኩ ጥሩ ስም የነበረው ሲሆን አባል ከሆንን
ጀምሮ በይበልጥ በራሴ እንዲሁም በአካባቢው ዘንድ ከፍተኛ የሚባሉ
ለውጦችን በቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ዙሪያ ለመፍጠር በመቻሌ
በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡
ብሉስታር፦ የብሉ ስታር ኔትወርክን ከተቀላቀሉ ጀምሮ እስካሁን በዚህ
ዙሪያ በበቆጂ ምን ምን ለውጦች ተስተውለዋል?
አቶ አበራ፦ ብሉ ስታርን ከተቀላቀልን ጀምሮ በበቆጂ ብዙ ለውጦች
ታይተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል በዛ ያሉ ክሊኒኮች በኔትወርኩ
መታቀፋቸው፣ ልዩ ልዩ ስልጠናዎች መሰጠታቸው፣ ማሪ ስቶፕስ
በዞናዊ አስተዳደር ከተዋቀረ በኋላ ደግሞ ከሃላፊዎች ጋር በቀላሉ
ለመገናኘት መቻላችንና የረጅም እርቀት አድካሚ ጉዞና ድካምን
ማስቀረቱ፣ የአገልግሎቱ ተደራሽነትና የአገልግሎት ዓይነቶች መጨመርና
በአካባቢው ዘንድ በቤተሰብ እቅድ ላይ ያለው ግንዛቤ መቀየርና
የመሳሰሉት የታዩ ድንቅ ለውጦች ናቸው፡፡
ኮከብ
የብሉ
ስታር
እንግዳችን
ቡፖ|7
ብሉስታር፦ እንደ ጤና ባለሙያ በበቆጂ ከተማ በቤተሰብ እቅድ ላይ
ያለው የአስተሳሰብ ለውጥ ምን ይመስላል? መጀመሪያ የብሉ ስታር
ጽንሰ ሃሳብ ሲተገበርና አሁን ያለውስ ለውጥ ምን ያህል ነው?
አቶ አበራ፦ ለውጡ ከፍተኛ ነው፡፡ በፊት ሴቶች የቤተሰብ እቅድ
አገልግሎት ለማግኘት ወደተቋማችን የሚመጡት ተደብቀው ነበር አሁን
ግን በተደረጉ ቅስቀሳዎችና ግንዛቤ መፍጠሪያ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች
በነጻነትና በግልጽነት እንዲሁም ከባለቤቶቻቸውና ከቤተሰብ አባሎች
ጋር አብረው በመምጣት የሚገለገሉበት ሁኔታ እየተስተዋለ ነው፡፡
በዚህም የተነሳ የሚፈጠሩ አደጋዎች እየቀነሱና ክሊኒኩ በቀን ውስጥ
የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ቁጥርና የአገልግሎት
አይነቶች ከበፊቱ በእጅጉ ከፍ እንዲሉ ለማድረግ ተችሏል፡፡
ብሉስታር፦ አበራ ክሊኒክን ለዚህ ከፍተኛ ውጤት ያበቁት ነገሮች
ምንድን ናቸው ብለው ያስባሉ?
አቶ አበራ፦ ለዚህ ከፍተኛ ውጤት መገኘት ዋነኛ ምክንያት ብዬ
የማስቀምጣቸው ነገሮች የተለያዩ ስልጠናዎችን መውሰዴና መተግበሬ፣
በክሊኒኩ ከሚገኙት የጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበርና በመተጋገዝ
መስራቴ፣ ለአካባቢው ህብረተሰብ ጥሩ ውጤት ያስመዘገበና ጥራቱን
የጠበቀ አገልግሎት በመስጠታችን፣ ልዩ ልዩ የምክክርና የደንበኛ
ክትትል ስራን በመስራት ከደንበኞቻችን ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር
መቻላችን ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ቡፖ|8
ብሉስታር፦ የክሊኒካል ጥራት (clinical quality and
infection prevention) ለእርስዎ ምን ማለት ነው?
በክሊኒክዎ ውስጥስ ምን ዓይነት ድርሻ አለው?
አቶ አበራ፦ የመጀመሪያው የህክምና ህግ ንጽህና ነው፡፡ ንጽህና
ከተጠበቀ የሚደርሱ ጉዳቶች እጅጉን ይቀንሳሉ፡፡ በክሊኒኩ ውስጥ
ማንኛውንም የምንጠቀምበት እቃ ንጽህናው የተጠበቀ መሆኑን
በሚገባ እናረጋግጣለን፤ ባለሙያውም እጁን በሚገባ መታጠቡንና
ጓንቶች መጠቀሙን እናረጋግጣለን፡፡ ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድ፣
ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር ጥንቃቄ መውሰድና ቁስልን በሚገባ ማጠብ
ስቴሪያላይዘር፣ አልኮል፣ አዮዲን፣ ሀይድሮጅን ፐር ኦክሳይድና
የመሳሰሉትን መጠቀም ለክሊኒካል ጥራት ወሳኝነት አላቸው፡፡
ብሉስታር፦ የብሉ ስታር ኔትወርክ አሰራር ላይ ቢደረጉ የሚሉት
ማሻሻያዎች ወይም የበለጠ ለስራችን ጠቃሚ ይሆናሉ የሚልዋቸው
ጥቆማዎች ካሉ?
አቶ አበራ፦ እስካሁን እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ በጣም ጥሩ
ነው፤ ሆኖም በቆጂ ከተማ ውስጥ የቤት ለቤት ቅስቀሳ አናሳ ነው።
ህብረተሰቡ በቤተሰብ እቅድ ዙሪያ ግንዛቤን የሚፈጥሩ ዝግጅቶችን
እንዲታደም ማድረጉ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ የጤና በጎ ፈቃደኛ
ሰራተኞች ሰዎችን የማሳመንና የቤተሰብ እቅድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ
የማስተማር እንቅስቃሴዎችን ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ይህ ደግሞ ህብረተሰቡ
እንዲለወጥና በራሱ ተነሳሽነት ወደ ክሊኒኮቹ እንዲመጣ ያደርጋል፡፡
ብሉስታር፦ አቶ አበራ በድጋሚ እንኳን ደስ አልዎት! ለመጪው የስራ
ዘመን ደግሞ መልካሙን ሁሉ እንመኝልዎታለን፡፡ ስለነበረን አስደሳች
ቆይታ እጅግ በጣም እናመሰግናለን፡፡
አቶ አበራ፦ እኔም እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡
ቡፖ|9
ቡፖ|10
እስቲ ይሞክሩት
(የጠቅላላ እውቀትና የማስተዋል ጥያቄዎች)
1.ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የብሉ ስታር ሶሻል 	 	
ፍራንቻይዚንግ ፕሮግራሙን መቼ የጀመረ ይመስልዎታል?
2.በመላው አለም የብሉ ስታር አጋር የጤና አውታሮች በስንት 	
ሃገሮች ላይ ያሉ ይመስሎታል?
3.በኢትዮጵያ እንዲሁም በዓለም ላይ ስንት የብሉስታር አባል 	 	
ክሊኒኮች ያሉ ይመስልዎታል?
4.ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል አገልግሎት መስጠት የጀመረው መቼ 	
ይመስልዎታል?
5.ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ከብሉስታር አባል ክሊኒኮች ጋር በመሆን 	
እስካሁን ለምን ያህል አገልግሎት ፈላጊዎች አገልግሎት የሰጠ 	
ይመስልዎታል?
6.ከዚህ በታች የምታዩት ምስል ውስጥ ሻማ፣ በክብሪት ሳጥን 	
ውስጥ ያሉ ክብሪቶችና ስፒሎች በጠረጴዛው ላይ ተቀምጠው 	 	
ይታያሉ፡፡ ጥያቄው የበራውን ሻማ በሚታዩት ቁሳቁሶች ተጠቅመው 	
ከግድግዳው ላይ ማጣበቅ ሲሆን ሻማው ግን በፍጹም 	
ቀልጦ ጠረጴዛው ላይ እንዳይንጠባጠብ ማድረግ መቻል 	 	
ነው፡፡ እስቲ ይሞክሩት፡፡
7. ሁለት እናቶች አና ሁለት ሴቶች ልጆቻቸው አሳ በማጥመድ ላይ 	
ናቸው፡፡ እናም አንድ ትልቅ፣ አንድ ትንሽ፣ እና አንድ ወፍራም 	
አሳ አጠመዱ፡፡ የተጠመዱት አሳዎች ሶስት ቢሆኑም ሁሉም 	
ሴቶች አንድ አንድ አሳ ይዘዋል፡፡ እንዴት ሊሆን ቻለ?
8. የሚመለከቱትን ምስል ወደ አራት ተመሳሳይ ምስልና ቅርጽ 	
ወዳላቸው ምስሎች ይከፋፍሉ፡፡
ቡፖ|11
በብሉ ስታር አውታር ክሊኒኮች ውስጥ አባል በሆኑ 622 ክሊኒኮች ላይ ላለፉት 10
ወራቶች (ማለትም እ.ኤ.አ ከታህሳስ 01 እስከ ጥቅምት 31, 2015) ከተከናወኑ
አበይት አገልግሎቶች ውስጥ በከፊል፡-
➢	አጠቃላይ የቤተሰብ እቅድና ስነተዋልዶ ጤና እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ አገልግሎቶችን
የተጠቀሙ ተገልጋዮች ብዛት 537,108 ነው።
➢	ከላይ ከተጠቀሰው ቁጥር ውስጥ፡-
•	የአዩሲዲ (IUCD) ተጠቃሚዎች ብዛት 18,297 ነው።
•	የተለያዩ አይነት ኢምፕላንቶች (Implants) ተጠቃሚዎች ብዛት 46,972 ነው።
•	ፖስት አቦርሽን የቤተሰብ እቅድ (Post Abortion Family Planning)
አገልግሎት ተጠቃሚዎች ብዛት 49,974 ነው።
ምርጥ 20 የብሉ ስታር
ክሊኒኮች
አይ.ዩ.ሲዲ ኢንሰርሽን ኢምፕላንት
እ.ኤ.አ ከታህሳስ 1 እስከ ጥቅምት 31 ቀን 2015 ድረስ በረጅም ጊዜ የቤተሰብ
እቅድ አገልግሎቶች የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የብሉ ስታር አጋር ክሊኒኮች፡፡
1359
1040
718637590578
481435403345328279270168
129123
431
12081
24
669
533
173
8914294
110258
115
368459
273303
395436356
64
335367536
0
500
1000
1500
2000
2500
ImplantIUCDIns
የማስተዋል
ጥያቄዎች ምላሾች
1. እ.ኤ.አ በ2008
2. በ18 አገሮች ላይ
3. በኢትዮጵያ ከ620 ክሊኒኮች በላይ ሲሆን በዓለም ላይ 	 	
ደግሞ ከ3,600 በላይ ናቸው።
4. እ.ኤ.አ ጥር 1976 በዶክተር ቲም ብላክ
5. ከ100 ሚሊዮን በላይ
6. በክብሪት ሳጥኑ ውስጥ የሚገኙትን ክብሪቶች በሙሉ ካወጡ 	
በኋላ የክብሪት ሳጥኑን በስፒሎቹ ግድግዳው ላይ ያጣብቁት፤ 	
ሻማውን ይለኩሱና እንዳይወድቅ በቅላጩ የክብሪት ሳጥኑ ላይ 	
ይለጥፉታል፡፡ ጠረጴዛው ላይ ሻማው እንዳይንጠባጠብ የክብሪት 	
ሳጥኑ ይከላከላል፡፡
7. ሶስት ሴቶች ብቻ ናቸው አሳ ያጠመዱት፡፡ አንደኛዋ እናትም 	
የእናትዋ ሴት ልጅም ናት፡፡
8.
የሰራተኛነት ብቃት
መፈተሻ ምላሽ
ለጥያቄዎቹ ከሰጡት ምላሾች ውስጥ ከ10-12 የሚሆኑትን ’አዎ’
በማለት ከመለሱ እንኳን ደስ አልዎት፤ ከፍተኛ ብቃት ያልዎት
ሰራተኛ ነዎትና፡፡ ከምላሾችዎ ውስጥ ከ7-9 የሚሆኑት ’አዎ’ ከሆኑ
መካከለኛ የስራ ብቃት ያለዎት ሲሆን ’አዎ’ የሚለው ምላሽዎ 6
እና ከዛም በታች ከሆነ በሰራተኝነት ብቃትዎ ላይ መስራትና ለመሻሻል
ጥረት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
ቡፖ|12
Children by choice not chance
አስተያየት፣ ጥያቄ ወይም ይዘን እንድንቀርብላችሁ የምትፈልጉት እንግዳ ካለ
በነፃ የስልክ መስመር፦ 8044
ኢሜል፦ bluestar@mariestopes.org.et
ፖ.ሳ.ቁ 5775 ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

More Related Content

Featured

2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by HubspotMarius Sescu
 
Everything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTEverything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTExpeed Software
 
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsProduct Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsPixeldarts
 
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthThinkNow
 
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfAI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfmarketingartwork
 
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024Neil Kimberley
 
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)contently
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024Albert Qian
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsKurio // The Social Media Age(ncy)
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Search Engine Journal
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summarySpeakerHub
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Tessa Mero
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentLily Ray
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best PracticesVit Horky
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementMindGenius
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...RachelPearson36
 

Featured (20)

2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot2024 State of Marketing Report – by Hubspot
2024 State of Marketing Report – by Hubspot
 
Everything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPTEverything You Need To Know About ChatGPT
Everything You Need To Know About ChatGPT
 
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage EngineeringsProduct Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
Product Design Trends in 2024 | Teenage Engineerings
 
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental HealthHow Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
How Race, Age and Gender Shape Attitudes Towards Mental Health
 
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdfAI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
AI Trends in Creative Operations 2024 by Artwork Flow.pdf
 
Skeleton Culture Code
Skeleton Culture CodeSkeleton Culture Code
Skeleton Culture Code
 
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
PEPSICO Presentation to CAGNY Conference Feb 2024
 
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
Content Methodology: A Best Practices Report (Webinar)
 
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
How to Prepare For a Successful Job Search for 2024
 
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie InsightsSocial Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
Social Media Marketing Trends 2024 // The Global Indie Insights
 
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
Trends In Paid Search: Navigating The Digital Landscape In 2024
 
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
5 Public speaking tips from TED - Visualized summary
 
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
ChatGPT and the Future of Work - Clark Boyd
 
Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next Getting into the tech field. what next
Getting into the tech field. what next
 
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search IntentGoogle's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
Google's Just Not That Into You: Understanding Core Updates & Search Intent
 
How to have difficult conversations
How to have difficult conversations How to have difficult conversations
How to have difficult conversations
 
Introduction to Data Science
Introduction to Data ScienceIntroduction to Data Science
Introduction to Data Science
 
Time Management & Productivity - Best Practices
Time Management & Productivity -  Best PracticesTime Management & Productivity -  Best Practices
Time Management & Productivity - Best Practices
 
The six step guide to practical project management
The six step guide to practical project managementThe six step guide to practical project management
The six step guide to practical project management
 
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
Beginners Guide to TikTok for Search - Rachel Pearson - We are Tilt __ Bright...
 

MSIE Newsletter Dec 21_2

  • 1. ለብሉስታር አባል ክሊኒኮች በነጻ የሚታደል-በየ3 ወሩ የሚዘጋጅ Issue 2, OCTOBER- 2015 በየ3 ወሩ ተዘጋጅቶ ለብሉስታር አባል ክሊኒኮች በነጻ የሚታደል Issue 3, November,2015 3. ኮከብ የብሉ ስታር እንግዳችን 1. የብሉ ስታር መልዕክት 2. ባለሙያው ምን ይላል?
  • 2.
  • 3. የብሉ ስታር መልዕክትውድ የተከበራችሁ የብሉ ስታር ጤና አውታር አባል አጋሮቻችን ከሁሉ በፊት በማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ መላው ሠራተኞች ስም የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁ፡፡ እንደሚታወቀው ድርጅታችን ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከግሉ የጤና ዘርፍ ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚፈልገው እና እየሰራ ያለው የግሉ ጤና ዘርፍ ካለው እምቅ አቅም አኳያ የእናቶቻችን ጤና ለማሻሻል እና አማራጭ የስነ ተዋልዶ ጤና ለማህበረሰቡ ለማድረስ እየተደረገ ባለው አገራዊ ጥረት ውስጥ ሊጫወቱ የሚችሉት ሚና እጅግ በጣም የገዘፈ እንደሆነ ስለምናምን ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ድርጅታችን ከእናንተ ስልታዊ አጋሮቻችን /Strategic Part- ners/ ጋር በመስራታችን አማራጭ የስነ ተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ለተጠቃሚዎች በማድረስ በኩል እያሳየን ያለው ዉጤት እጅግ በጣም የሚያበረታታ ነው፡፡ ለአብነት ያህል በ2007 ዓ.ም ብቻ ድርጅታችን ከብሉ ስታር የጤና ማዕከላት ጋር በመስራት ቁጥራቸው ከ524,201 ለሚልቁ ዜጎች የተለያዩ የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን ለመስጠት ተችሏል፡፡ በዚህ በያዝነው ዓመት (2015 እ.ኤ.አ) ድርጅታችን በዓለም አቀፍ ደረጃ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት እ.ኤ.አ 1976 ጀምሮ 100 ሚሊዮን ተገልጋዮችን /100 Million Clients/ የአገልግሎት ተደራሽ ያደረገበት አመት በመሆኑ ድርጅታችን በሚሰራባቸው አገሮች ቡፖ|1
  • 4. ዉስጥ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ ይህ እለትም በማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በኩልም በድምቀት ተከብሮ አልፏል፡፡ በዚህ የስኬት ሃዲድ ዉስጥ አብረውን የሚሰሩ የግል ክሊኒኮች አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነም የሚታወቅ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ዉስጥ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ እነሆ 25 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህንንም የ 25 አመታት ጉዞአችንን በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ እንገኛለን። በዚህ በ25 ዓመታት ጉዞአችን ዉስጥ በድርጅታችን በኩል እየተሰጡ በሚገኙ ዘርፈ ብዙ የጤና አገልግሎቶች ምክንያት አያሌ ዜጎች ተጠቃሚ ከመሆናቸውም ባሻገር በስነተዋልዶ ጤና መረጃ እና አገልግሎት ተደራሽነት ውስንነት ምክንያት በሴቶች ወገኖቻችን ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና መታወኮችን ከመከላከል አኳያም ጉልህ ሚና መጫወት እንደቻልን እናምናለን፡፡ ከዚህ ጉልህ ሚና እና ከተገኙ ውጤቶች በስተጀርባ በመንግስት በኩል እየተደረገልን ባለው እገዛ ከእናንተ ከብሉስታር አባል ክሊኒኮች ጋር በቅርብ መስራታችን እና ከሁሉም በላይ ደግሞ በምንሰጠው የስነ ተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት እንዲሁም የእናቶች እና ህጻናት ጤና አገልግሎት ዙሪያ ዘወትር አስተያየት በመስጠት የተሻለ እና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እንድንሰጥ የሚያተጉን የተገልጋዮች /Client/ ሚና ታላቅ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ለዚህም ከፍተኛ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ በቀጣዩ ዓመት 2016 (እ.ኤ.አ) ድርጅታችን ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በመንግስት በኩል የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት፣ የእናቶች እና ህጻናት ጤና አገልግሎትን ለማዳረስ በዘረጋው እቅድ መሰረት ከብሉ ስታር ክሊኒኮች ጋር በመተባበር በቀጣይነትም ገንቢ ሚና ለመጫወት በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ በመጨረሻም አጋር የብሉ ሰታር ክሊኒኮች ጥራቱን የጠበቀ እና ተገልጋዮችን ሊያረካ የሚችል የስነተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት በመስጠት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ በቀጣይነትም እንድታበረክቱ እየጠየቅኩኝ በአገልግሎት አሰጣጣችሁ ዙሪያ እየታዩባችሁ ያሉትን ድክመቶች ለማሻሻል እና እያሳያችሁት ያለውን ጠንካራ ጎን ለማጎልበትም በምታደርጉት ጥረት ዉስጥ ድርጅታችን በቀጣይነትም ከጎናችሁ በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እና እገዛ የሚያደርግ መሆኑንም በመጠቆም ነው፡፡ ሰላም ቆዩ! አበበ ሽብሩ ምክትል ካንትሪ ዳይሬክተር እና የስትራቴጂ እና ዴቨሎፕመንት ዳይሬክተር ቅምጥሏ ቅምጥል አፍቅሬ፣ ለሷ ተቸግሬ፣ ኩሽና እንዳትገባ ካልጋ እንዳትነሳ፣ ምግብ አብሳይ ቀጠርኩ ባስብላት ለሷ፡፡ የእንጀራ ጫፍ ጣቷን እንዳይቆርጣት ብዬ፣ አጉራሽም ቀጠርኩኝ አሳቢ መስዬ፡፡ ቅምጥሏን ፍቅሬን ድንገት ቢያስነጥሳት፣ ይማርሽ የምትል ሌላም ቀጠርኩላት፡፡ የሞልቃቃ ነገር፣ መጨረሻው አያምር፣ ቅጥ ያጣውን ፍቅሬን ውስጤን ስላየችው፣ ባል ቀጥረህ አምጣልኝ ብላኝ አረፈችው፡፡ በሰለሞን ወልዴ ቡፖ|2
  • 5. ዶ/ር ነጋ ተስፋው በማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የጥራትና የክሊኒካል አገልግሎቶች ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ዛሬ ከእርሳቸው ጋር በሚኖረን ቆይታ በሚከተሉት ሀሳቦች ዙሪያ ተወያየን፤ እናንተ ደግሞ አንብባችሁ ጠቃሚ መረጃዎችን ታገኙ ዘንድ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ ብሉስታር ፦ የብሉ ስታር ክሊኒክ (የጤና እንክብካቤ ተቋማት) ጥራት ወይም (Health- Care Quality) ስንል ምን ማለታችን ነው? ዶ/ር ነጋ ፦ የብሉ ስታር የጤና እንክብካቤ ተቋማት ጥራት ስንል የተቋሙን ደንበኞች ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ፤ በአግባቡና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ዘመናዊ ግኝቶችን በመጠቀም የሚሰጥ የጤና አገልግሎት ማለታችን ነው፡፡ ይህ አይነቱ የጤና አገልግሎት አነስተኛ ጥራትን፣ ደግሞ መስራትንና ብክነትን የሚቀንስ ሲሆን ጥራት አለው እንላለን፡፡ ብሉስታር ፦ የጤና እንክብካቤ ተቋማት ጥራት መሟላት የሚያስገኛቸው ጥቅሞች ምን ምን ናቸው? ዶ/ር ነጋ ፦ የጤና እንክብካቤ ተቋማት ጥራት ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ውጤታማ፣ በደንበኞች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ፣ ጊዜውን የጠበቀ፣ ሁለገብ፣ በቀላሉ የሚገኝ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ እና እሴቶችን የመጨመር አቅም ያለው የጤና አገልግሎት ይገኝበታል፡፡ ብሉስታር ፦ የብሉ ስታር የጤና እንክብካቤ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ በማንኛውም ጊዜ ሊተገበሩ የሚገቡ ነገሮች ምንድን ናቸው ይላሉ? ዶ/ር ነጋ ፦ የብሉ ስታር ተቋማት ጥራትን ለማሟላት የደንበኞችን መብት ሊያከብሩ ይገባቸዋል፡፡ የደንበኞች መብት ስንል ደንበኛው/ዋ ሰብአዊ መብቱ/ትዋን በጠበቀ መልኩ መረጃን የማግኘት መብት፣ የአገልግሎቶች ተጠቃሚነት መብት፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የአገልግሎት ምርጫ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት፣ ምስጢሩ የተጠበቀ የደንበኛ አገልግሎት፣ ምቾቱ የተጠበቀና ቀጣይነት ያለው አገልግሎት ማለታችን ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በማንኛውም ጊዜ ለድንገተኛ ህክምናዎች ዝግጁ መሆን እና ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን መተግበር ተገቢ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ባለሙያው ምን ይላል? ቡፖ|3
  • 6. ኢንፌክሽንን እንዴት መከላከል እንችላለን? • እጅን በመታጠብ • ጓንቶችን፣ ገዋኖችንና መነጽሮችን በመጠቀም • ባክቴሪያ የሚገድሉ አንቲሴፕቲኮችን በመጠቀም • በቀዶ ህክምና ወቅት ተገቢ ጥንቃቄዎችን በመውሰድ • የህክምና መሳርያዎችን በንጽህናና በጥንቃቄ በመጠቀም • ቆሻሻን በአግባበቡ በማስወገድ ብሉስታር፦ በብሉ ስታር ክሊኒኮች ውስጥ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚኖራቸው ድርሻ ምን ያህል ነው ይላሉ? ዶ/ር ነጋ፦ የዚህ የብሉስታር መጽሄት ተደራሽ አካላት በብሉ ስታር ክሊኒኮች ውስጥ የሚገኙ የጤና ሰራተኞችና የህክምና ባለሙያዎች ናቸው፡፡ እናም ሁሉም የጤናው ተቋማት ባለሙያዎች ደረጃውን የጠበቀ የህክምና እርዳታን የመስጠት ብቃት ማሟላት፣ የተቋሙን አስተዳደራዊ አደረጃጀት ምቹ ማድረግ፣ በየጊዜው ተገቢውን ስልጠና መውሰድ እንዲሁም ለባለሙያው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች መሟላታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በይበልጥ ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ ነገሮች መካከል በደንበኞች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት አሰጣጥና የተሟላ የምክክር አገልግሎት ተደራሽነት ይገኙበታል፡፡ ይህንንም ተግባራዊ ማድረግ የጤና ባለሙያዎቹ ድርሻ ነው ማለት ነው። ብሉስታር፦ የብሉ ስታር ክሊኒኮች ከማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የሚያገኙት ድጋፍ ምን ይመስላል? ዶ/ር ነጋ፦ ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ለብሉ ስታር ክሊኒኮች የሚሰጠው ድጋፍ የምስረታ አባልነት ድጋፍ አንስቶ፦ የመሳሪያዎች ስልጠና እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ክትትል፣ የጥራት ቴክኒክ እገዛና ቁጥጥር ድጋፍ ናቸው፡፡ ይህም የሚደረገው ጥራትን በዘላቂነት ጠብቆ መጓዝና በየጊዜው አገልግሎቶች ላይ መሻሻል ማድረግ የብሉ ስታር ክሊኒኮች ልዩ መለያ በመሆኑ ነው፡፡ ቡፖ|4
  • 7. የሰራተኝነት ብቃትዎን ይፈትሹ ከዚህ በታች የሚገኙት ጥያቄዎች ምን አይነት ሰራተኛ ነዎት የሚለውን ይፈትሻሉ፡፡ እስቲ ጊዜ ወስደው ጥያቄዎቹን ለራስዎ በታማኝነት ይመልሱ፡፡ ዉጤቱን በገጽ 12 ይመልከቱ:: 1. ስራ ላይ በስራ ሰዓትዎ ይገኛሉ? o አዎ እገኛለሁ o አልገኝም 2. በስራ ላይ ከተመደበልዎት ስራ ውጪ ተጨማሪ ነገሮችን ይሰራሉ? o አዎ እሰራለሁ o አልሰራም 3. ከስራ ባልደረቦችዎ ጋር ሌሎች ሰራተኞችን ወይም ደንበኞችን የማማት ልማድ አልዎት? o አዎ አለኝ o የለኝም 4. በስራዎ ሁልጊዜ ደስተኛ ነዎት? o አዎ ነኝ o አይደለሁም 5. የስራ ባልደረቦችዎንና ደንበኞችን በተለያዩ ነገሮች ለመርዳት ምንጊዜም ዝግጁ ነዎት? o አዎ ዝግጁ ነኝ o ዝግጁ አይደለሁም 6. በስራ ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን የመፍታት አቅም አለኝ ብለው ያምናሉ? o አዎ አለኝ o የለኝም 7. የተሰጥዎትን ስራ ምንጊዜም በተመደበልዎ ጊዜ ያጠናቅቃሉ? o አዎ አጠናቅቃለሁ o አላጠናቅቅም 8. የስራ ተነሳሽነት አልዎት? o አዎ አለኝ o የለኝም ቡፖ|5
  • 8. 9. በቡድን የመስራት ልምድና ፍላጎት አለዎት? o አዎ አለኝ o የለኝም 10. ጊዜ ወስደው ከስራ ባልደረቦችዎ ጋር ለመተዋወቅና ለመግባባት ይሞክራሉ? o አዎ እሞክራለሁ o አልሞክርም 11. በስራ ቦታ አለባበስዎ ለስኬት የሚያዘጋጅና ደንብን የተከተለ ነው? o አዎ ነው o አይደለም 12. በስራ ላይ ከሚጠበቅብዎ በላይ እጅግ በላቀ መልኩ ተሽለው ለመገኘት ጥረት ያደርጋሉ? o አዎ እጥራለሁ o አልጥርም አገባሽ ነበረ የቁመቴን ማጠር የመልኬን ማስከፋት፣ ከጉዳይ ባትቆጥሪው የገፄን ደም ግባት፣ ኮልታፋ አንደበቴን ሸካራውን ድምጼን፣ ሰምተሸ ባትንቂያቸው ለዛ አልባ ቃላቴን፣ ፍፁም ድህነቴን አምነሽ ብትቀበይ፣ ፍቅርን ብታስበልጭ ከዚች ምድር ሲሳይ፣ አገባሽ ነበረ እሽ ብትይ አንቺ፣ በተለይ በተለይ ባልሽን ብትፈቺ፡፡ ዘላለም ምህረቱ ቡፖ|6
  • 9. አቶ አበራ አያና ይባላሉ፡፡ በበቆጂ ከተማ የብሉ ስታር አባል የሆነው የአበራ መለስተኛ ክሊኒክ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ፤ በዚህ ዓመት በማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የብሉ ስታር የክሊኒካል አገልግሎቶች ምዘና 98% በማስመዝገብ የከፍተኛ ውጤት ባለቤት ለመሆን በቅተዋል፡፡ አቶ አበራ ከዚህ በተጨማሪ የ3 ዋንጫዎችና የተለያዩ ሰርተፊኬቶች ተሸላሚ ሲሆኑ በበቆጂ ከተማ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ደንበኞችን በማስተናገድ ድንቅ ውጤትን እያስመዘገቡ የሚገኙ የጤና ባለሙያ ናቸው፡፡ የአበራ መለስተኛ ክሊኒክ ለዛሬ በአርአያነት ያቀረብነው የብሉ ስታር ክሊኒክ ነው፡፡ ከአቶ አበራ ጋር ያደረግነውን ቃለምልልስ እነሆ። ብሉስታር፦ በቅድሚያ የዚህ አስደሳች ውጤት ባለቤት በመሆንዎ እንኳን ደስ አልዎት፡፡ የብሉ ስታር አባል የሆኑት መቼ ነበር? የአባልነት ጊዜዎንስ እንዴት ይገልጹታል? አቶ አበራ፦ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ አበራ ክሊኒክ በብሉ ስታር አባልነት የተመዘገበ ክሊኒክ ነው፡፡ በኔትዎርኩ የአባልነት ጉዞዬ እጅግ በጣም አስደሳች ነው፡፡ ክሊኒኩ ጥሩ ስም የነበረው ሲሆን አባል ከሆንን ጀምሮ በይበልጥ በራሴ እንዲሁም በአካባቢው ዘንድ ከፍተኛ የሚባሉ ለውጦችን በቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ዙሪያ ለመፍጠር በመቻሌ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ብሉስታር፦ የብሉ ስታር ኔትወርክን ከተቀላቀሉ ጀምሮ እስካሁን በዚህ ዙሪያ በበቆጂ ምን ምን ለውጦች ተስተውለዋል? አቶ አበራ፦ ብሉ ስታርን ከተቀላቀልን ጀምሮ በበቆጂ ብዙ ለውጦች ታይተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል በዛ ያሉ ክሊኒኮች በኔትወርኩ መታቀፋቸው፣ ልዩ ልዩ ስልጠናዎች መሰጠታቸው፣ ማሪ ስቶፕስ በዞናዊ አስተዳደር ከተዋቀረ በኋላ ደግሞ ከሃላፊዎች ጋር በቀላሉ ለመገናኘት መቻላችንና የረጅም እርቀት አድካሚ ጉዞና ድካምን ማስቀረቱ፣ የአገልግሎቱ ተደራሽነትና የአገልግሎት ዓይነቶች መጨመርና በአካባቢው ዘንድ በቤተሰብ እቅድ ላይ ያለው ግንዛቤ መቀየርና የመሳሰሉት የታዩ ድንቅ ለውጦች ናቸው፡፡ ኮከብ የብሉ ስታር እንግዳችን ቡፖ|7
  • 10. ብሉስታር፦ እንደ ጤና ባለሙያ በበቆጂ ከተማ በቤተሰብ እቅድ ላይ ያለው የአስተሳሰብ ለውጥ ምን ይመስላል? መጀመሪያ የብሉ ስታር ጽንሰ ሃሳብ ሲተገበርና አሁን ያለውስ ለውጥ ምን ያህል ነው? አቶ አበራ፦ ለውጡ ከፍተኛ ነው፡፡ በፊት ሴቶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ለማግኘት ወደተቋማችን የሚመጡት ተደብቀው ነበር አሁን ግን በተደረጉ ቅስቀሳዎችና ግንዛቤ መፍጠሪያ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች በነጻነትና በግልጽነት እንዲሁም ከባለቤቶቻቸውና ከቤተሰብ አባሎች ጋር አብረው በመምጣት የሚገለገሉበት ሁኔታ እየተስተዋለ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የሚፈጠሩ አደጋዎች እየቀነሱና ክሊኒኩ በቀን ውስጥ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ቁጥርና የአገልግሎት አይነቶች ከበፊቱ በእጅጉ ከፍ እንዲሉ ለማድረግ ተችሏል፡፡ ብሉስታር፦ አበራ ክሊኒክን ለዚህ ከፍተኛ ውጤት ያበቁት ነገሮች ምንድን ናቸው ብለው ያስባሉ? አቶ አበራ፦ ለዚህ ከፍተኛ ውጤት መገኘት ዋነኛ ምክንያት ብዬ የማስቀምጣቸው ነገሮች የተለያዩ ስልጠናዎችን መውሰዴና መተግበሬ፣ በክሊኒኩ ከሚገኙት የጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበርና በመተጋገዝ መስራቴ፣ ለአካባቢው ህብረተሰብ ጥሩ ውጤት ያስመዘገበና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠታችን፣ ልዩ ልዩ የምክክርና የደንበኛ ክትትል ስራን በመስራት ከደንበኞቻችን ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር መቻላችን ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ቡፖ|8
  • 11. ብሉስታር፦ የክሊኒካል ጥራት (clinical quality and infection prevention) ለእርስዎ ምን ማለት ነው? በክሊኒክዎ ውስጥስ ምን ዓይነት ድርሻ አለው? አቶ አበራ፦ የመጀመሪያው የህክምና ህግ ንጽህና ነው፡፡ ንጽህና ከተጠበቀ የሚደርሱ ጉዳቶች እጅጉን ይቀንሳሉ፡፡ በክሊኒኩ ውስጥ ማንኛውንም የምንጠቀምበት እቃ ንጽህናው የተጠበቀ መሆኑን በሚገባ እናረጋግጣለን፤ ባለሙያውም እጁን በሚገባ መታጠቡንና ጓንቶች መጠቀሙን እናረጋግጣለን፡፡ ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድ፣ ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር ጥንቃቄ መውሰድና ቁስልን በሚገባ ማጠብ ስቴሪያላይዘር፣ አልኮል፣ አዮዲን፣ ሀይድሮጅን ፐር ኦክሳይድና የመሳሰሉትን መጠቀም ለክሊኒካል ጥራት ወሳኝነት አላቸው፡፡ ብሉስታር፦ የብሉ ስታር ኔትወርክ አሰራር ላይ ቢደረጉ የሚሉት ማሻሻያዎች ወይም የበለጠ ለስራችን ጠቃሚ ይሆናሉ የሚልዋቸው ጥቆማዎች ካሉ? አቶ አበራ፦ እስካሁን እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ በጣም ጥሩ ነው፤ ሆኖም በቆጂ ከተማ ውስጥ የቤት ለቤት ቅስቀሳ አናሳ ነው። ህብረተሰቡ በቤተሰብ እቅድ ዙሪያ ግንዛቤን የሚፈጥሩ ዝግጅቶችን እንዲታደም ማድረጉ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ የጤና በጎ ፈቃደኛ ሰራተኞች ሰዎችን የማሳመንና የቤተሰብ እቅድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማስተማር እንቅስቃሴዎችን ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ይህ ደግሞ ህብረተሰቡ እንዲለወጥና በራሱ ተነሳሽነት ወደ ክሊኒኮቹ እንዲመጣ ያደርጋል፡፡ ብሉስታር፦ አቶ አበራ በድጋሚ እንኳን ደስ አልዎት! ለመጪው የስራ ዘመን ደግሞ መልካሙን ሁሉ እንመኝልዎታለን፡፡ ስለነበረን አስደሳች ቆይታ እጅግ በጣም እናመሰግናለን፡፡ አቶ አበራ፦ እኔም እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ቡፖ|9
  • 12. ቡፖ|10 እስቲ ይሞክሩት (የጠቅላላ እውቀትና የማስተዋል ጥያቄዎች) 1.ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የብሉ ስታር ሶሻል ፍራንቻይዚንግ ፕሮግራሙን መቼ የጀመረ ይመስልዎታል? 2.በመላው አለም የብሉ ስታር አጋር የጤና አውታሮች በስንት ሃገሮች ላይ ያሉ ይመስሎታል? 3.በኢትዮጵያ እንዲሁም በዓለም ላይ ስንት የብሉስታር አባል ክሊኒኮች ያሉ ይመስልዎታል? 4.ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል አገልግሎት መስጠት የጀመረው መቼ ይመስልዎታል? 5.ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ከብሉስታር አባል ክሊኒኮች ጋር በመሆን እስካሁን ለምን ያህል አገልግሎት ፈላጊዎች አገልግሎት የሰጠ ይመስልዎታል? 6.ከዚህ በታች የምታዩት ምስል ውስጥ ሻማ፣ በክብሪት ሳጥን ውስጥ ያሉ ክብሪቶችና ስፒሎች በጠረጴዛው ላይ ተቀምጠው ይታያሉ፡፡ ጥያቄው የበራውን ሻማ በሚታዩት ቁሳቁሶች ተጠቅመው ከግድግዳው ላይ ማጣበቅ ሲሆን ሻማው ግን በፍጹም ቀልጦ ጠረጴዛው ላይ እንዳይንጠባጠብ ማድረግ መቻል ነው፡፡ እስቲ ይሞክሩት፡፡ 7. ሁለት እናቶች አና ሁለት ሴቶች ልጆቻቸው አሳ በማጥመድ ላይ ናቸው፡፡ እናም አንድ ትልቅ፣ አንድ ትንሽ፣ እና አንድ ወፍራም አሳ አጠመዱ፡፡ የተጠመዱት አሳዎች ሶስት ቢሆኑም ሁሉም ሴቶች አንድ አንድ አሳ ይዘዋል፡፡ እንዴት ሊሆን ቻለ? 8. የሚመለከቱትን ምስል ወደ አራት ተመሳሳይ ምስልና ቅርጽ ወዳላቸው ምስሎች ይከፋፍሉ፡፡
  • 13. ቡፖ|11 በብሉ ስታር አውታር ክሊኒኮች ውስጥ አባል በሆኑ 622 ክሊኒኮች ላይ ላለፉት 10 ወራቶች (ማለትም እ.ኤ.አ ከታህሳስ 01 እስከ ጥቅምት 31, 2015) ከተከናወኑ አበይት አገልግሎቶች ውስጥ በከፊል፡- ➢ አጠቃላይ የቤተሰብ እቅድና ስነተዋልዶ ጤና እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ አገልግሎቶችን የተጠቀሙ ተገልጋዮች ብዛት 537,108 ነው። ➢ ከላይ ከተጠቀሰው ቁጥር ውስጥ፡- • የአዩሲዲ (IUCD) ተጠቃሚዎች ብዛት 18,297 ነው። • የተለያዩ አይነት ኢምፕላንቶች (Implants) ተጠቃሚዎች ብዛት 46,972 ነው። • ፖስት አቦርሽን የቤተሰብ እቅድ (Post Abortion Family Planning) አገልግሎት ተጠቃሚዎች ብዛት 49,974 ነው። ምርጥ 20 የብሉ ስታር ክሊኒኮች አይ.ዩ.ሲዲ ኢንሰርሽን ኢምፕላንት እ.ኤ.አ ከታህሳስ 1 እስከ ጥቅምት 31 ቀን 2015 ድረስ በረጅም ጊዜ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቶች የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የብሉ ስታር አጋር ክሊኒኮች፡፡ 1359 1040 718637590578 481435403345328279270168 129123 431 12081 24 669 533 173 8914294 110258 115 368459 273303 395436356 64 335367536 0 500 1000 1500 2000 2500 ImplantIUCDIns
  • 14. የማስተዋል ጥያቄዎች ምላሾች 1. እ.ኤ.አ በ2008 2. በ18 አገሮች ላይ 3. በኢትዮጵያ ከ620 ክሊኒኮች በላይ ሲሆን በዓለም ላይ ደግሞ ከ3,600 በላይ ናቸው። 4. እ.ኤ.አ ጥር 1976 በዶክተር ቲም ብላክ 5. ከ100 ሚሊዮን በላይ 6. በክብሪት ሳጥኑ ውስጥ የሚገኙትን ክብሪቶች በሙሉ ካወጡ በኋላ የክብሪት ሳጥኑን በስፒሎቹ ግድግዳው ላይ ያጣብቁት፤ ሻማውን ይለኩሱና እንዳይወድቅ በቅላጩ የክብሪት ሳጥኑ ላይ ይለጥፉታል፡፡ ጠረጴዛው ላይ ሻማው እንዳይንጠባጠብ የክብሪት ሳጥኑ ይከላከላል፡፡ 7. ሶስት ሴቶች ብቻ ናቸው አሳ ያጠመዱት፡፡ አንደኛዋ እናትም የእናትዋ ሴት ልጅም ናት፡፡ 8. የሰራተኛነት ብቃት መፈተሻ ምላሽ ለጥያቄዎቹ ከሰጡት ምላሾች ውስጥ ከ10-12 የሚሆኑትን ’አዎ’ በማለት ከመለሱ እንኳን ደስ አልዎት፤ ከፍተኛ ብቃት ያልዎት ሰራተኛ ነዎትና፡፡ ከምላሾችዎ ውስጥ ከ7-9 የሚሆኑት ’አዎ’ ከሆኑ መካከለኛ የስራ ብቃት ያለዎት ሲሆን ’አዎ’ የሚለው ምላሽዎ 6 እና ከዛም በታች ከሆነ በሰራተኝነት ብቃትዎ ላይ መስራትና ለመሻሻል ጥረት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ቡፖ|12
  • 15. Children by choice not chance
  • 16. አስተያየት፣ ጥያቄ ወይም ይዘን እንድንቀርብላችሁ የምትፈልጉት እንግዳ ካለ በነፃ የስልክ መስመር፦ 8044 ኢሜል፦ bluestar@mariestopes.org.et ፖ.ሳ.ቁ 5775 ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ አዲስ አበባ