SlideShare a Scribd company logo
1 of 130
1
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
የሥልጠናው ይዘት
ክፍል አንድ - ጠቅላላ መረጃ
ክፍል ሁለት - የአዋጁ ጠቅላላ ክፍል
ክፍል ሦስት - ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ “ሀ”)
ክፍል አራት - የቤት ኪራይ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ “ለ”)
ክፍል አምስት - ግብር የሚከፈልበት የንግድ ሥራ ገቢ፣ተቀናሽ የሚደረጉና የማይደረጉ ወጪዎች
ክፍል ስድስት - የማዕድንና የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር
ክፍል ሰባት - ዓለም አቀፍ ግብር
ክፍል ስምንት - የሰንጠረዥ “መ” ገቢ ግብር
ክፍል ዘጠኝ - የወል ድንጋጌዎች /በማንበብ የምታዳብሩት/
ክፍል አስር- ከግብር ለመሸሽ የሚደረገውን ጥረት ስለመከላከል
ክፍል አስራአንድ - አስተዳደራዊና የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች
ክፍል አስራሁለት - ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብርን ቀንሶ ስለማስቀረት
ክፍል አስራሦስት - የመመርመር ሥልጣን (Power of Investigation)
ክፍል አሥራ አራት - የግብር ከፋዮች ግዴታና ህጋዊ ውጤቱ /በማንበብ የምታዳብሩት/
2
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
ክፍል አንድ
አጠቃላይ መረጃ
ሀ/ መግቢያ
ሀ.1. የሥልጠናው ዓላማ
የሥልጠናው ዓላማዎች ጠቅለል ባለመልኩ ሲገለጽ የሚከተሉትን ዓላማዎች ለማሳካት ነው፡-
 በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ውስጥ የተጨመሩ ወይም የተካተቱ አዳዲስ ድንጋጌዎችን
እና ሐሳቦችን ግንዛቤ ለማስያዝ፤
 በአጠቃላይ በታክስ ህጉ ላይ ግንዛቤ እንዲፈጠር በማድረግ ህጉ የሚመለከታቸው ሁሉ
የሚጠበቅባቸውን ግዴታና ኃላፊነት ተረድተው ግዴታቸውንና ኃላፊነታቸውን በቀላሉ
እንዲወጡ ለማስቻልና በህግ ላይ የተመሰረተ ፍትሐዊ አገልግሎትና ምላሽ በመስጠት
የተሻለ የታክስ ህግ ተገዢነት እንዲመጣ ለማስቻል ነው፤
3
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
 የታክስ አዋጆች በየጊዜው ያለውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሁኔታ መሠረት በማድረግ የሚሻሻሉ ወይም አዳዲስ
የታክስ አይነቶች በህግ ተደንግግው የሚወጡ ሲሆን
 በፌደራል ገቢ ሰብሳቢ አካላት የሚጠቀምባቸዉ የግብርና ታክስ አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች አሉ ዋና
ዋናዎቹ፡- (464 ተለይተው በስራ ላይ ያሉት ወደ 242ቱ በ6የተለያየ ርእስ ባላቸው መጽሐፍቶች
ታትመዋል)
 የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994፣ ማሻሻያ 608/2001 እና 693/2003
 የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 78/1994 እና ማሻሻያ ቁጥር 164/2001
 የማዕድን ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 53/1985 እና ማሻሻያ 678/2002 እና 802/2005
 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 እና ደንብ ቁጥር 410/2009፣
 የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ 285/1994፣ ማሻሻያ 609/2001 እና 1157/2011
 የተጨማሪ እሴት ታክስ ደንብ 79/1995
 የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ 308/1995 እና ማሻሻያ 611/2001
 የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ 307/1995 ማሻሻያ 570/2000 610/2001፣ እና 1186/2012
 የቴምብር ቀረጥ አዋጅ 110/1990
 ለሁሉም የታክስ አይነቶች አስተዳደራዊ ጉዳዮች ተፈጻሚ የሚደረግ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር
983/2008 እና ደንብ ቁጥር 407/2009
 የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ደንብ ቁጥር 154/2000
 ከግብርና ቀረጥ አዋጆች ጋር የተያያዙ ሌሎች አዋጆች
 የኅብረት ሥራ ማኅበራት ማደራጃ አዋጅ
 የማእድን ስራ አዋጅ
 አነስተኛ የፋይናንስ ሥራ አዋጅ ቁጥር
 የውጪ ንግድ ቀረጥ ማበረታቻ አዋጁ ቁጥር
 የኢንቨስትመንት አዋጅ
 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ እና ሌሎች
4
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
23/02/2015 E.C
ለ/ አጠቃላይ ጽንሰ ሐሳቦች
1. የታክስ ሥርዓት ምንነት
2. የታክስ ሥርዓት ዓይነቶች
5
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
ለ.1- የታክስ ሥርዓት ምንነት
የታክስ ሥርዓት የምንለው በጠባቡ ሲታይ የታክስ አጣጣሉን፣ የታክስ ህጉን
አወቃቀርና ቅርጽ የሚገልጽ ሲሆን በሰፊው ሲታይ ግን የታክስ ህጉንና ይህን
የታክስ ህግ መሠረት በማድረግ በየደረጃው የሚወጡ መመሪያዎችና
የአሠራር ሥርዓቶች በታክስ ባለሥልጣኑ የሚዘረጉ የታክስ አወሳሰንና
አሰባሰብ፣ የኦዲት ሥርዓቱንና የመረጃ አስተዳደር ሥርዓቱን ጨምሮ
የአገልግሎት አሰጣጡንና የቅሬት አፈታት ሥርዓቱን በማጠቃለል “የታክስ
አስተዳደር ሥርዓት” ብለን የምንጠራውን አስተዳደራዊ ሥርዓት የሚወክል
መሠረታዊ ጽንሰ ሐሳብ ነው፡፡
6
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
ለ.2- የታክስ ሥርዓት ዓይነቶች/Types of Taxing System/
• በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት የታክስ ሥርዓቶች ያሉ ሲሆን እነዚህም፡-
 ግሎባል (aggregated) የታክስ ሥርዓት
 ስኬጁላር (disaggregated) የታክስ ሥርዓት ተብለው የሚታወቁ ናቸው፡፡
• ግሎባል የታክስ ሥርዓት ግብር ከፋዩ የሚያገኘውን ማንኛውንም ዓይነት ገቢ በአንድ ላይ
በመደመር በአንድ የግብር ማስከፈያ ምጣኔ ግብር እንዲከፍል የሚደረግበት ሥርዓት
ሲሆን በዚህ ሥርዓትም ውስጥ ቢሆን የስኬጁላር ታክስ ሥርዓት የሚመስሉ ሁኔታዎች
የሚታዩበት ሁኔታ ይኖራል፡፡
• ስኬጁላር የታክስ ሥርዓት የሚባለው አንድ ግብር ከፋይ የሚያገኛቸውን ገቢዎች
እንደየገቢው ዓይነት በመከፋፈል ወይም በመመደብ ለእያንዳንዱ የገቢ ዓይነት በስኬጁል
የተቀመጡ የግብር ማስከፈያ ምጣኔዎችን በመጠቀም የተለያየ ግብር በመወሰን የተለያዩ
የህግ መርሆዎችንና መሪ ድንጋጌዎች ተጠቅሞ ታክሱን የሚሰበስብበት ሥርዓት ነው፡፡
7
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
የታክስ ሥርዓት…
ሁለቱም የታክስ ሥርዓቶች የየራሳቸው የሆነ ደካማና ጠንካራ ጐን አሏቸው፡-
• ግሎባል የታክስ ሥርዓት የታክስ መሠረቱ እንዳይሸረሸር ወይም base erosion በማስወገድ
የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ የሚጠቅም መሆኑ ቢነገርለትም የታክስ አስተዳደሩን ስለሚያከብደውና
ስለሚያወሳስበው ብዙዎች አይመርጡትም፡፡
• የስኬጁላር ታክስ ሥርዓት የተለያየ ገቢ የሚያገኙ ግብር ከፋዮች በተለያየ ስኬጁል ሲስተናገዱ
ከግብር ነፃ በሆነው የገቢ መጠን (exempted threshold) እና በአነስተኛ የታክስ ብራኬት
ደጋግመው ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉበትን ዕድል ስለሚፈጥር ለኢፍትሃዊነትና ለገቢ መንጠባጠብ
ወይም ለታክስ መሠረት መሸርሸር የሚያጋልጥ ሲሆን የታክስ አስተዳደሩን ቀላልና ግልጽ
በማድረግና ግብር ከፋዩ ሣይሰማው ግብሩን እንዲከፍል እንዲሁም ወጪን በመቆጠብ ረገድ ግን
ተመራጭነት አለው፡፡
• የኢትዮጵያ የታክስ ሥርዓት ሁለተኛውን ዓይነት የታክስ ሥርዓት የሚከተል ነው፡፡
8
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
የታክስ ወሰን
• የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ለፌደራል መንግስት በህገ መንግስቱ በተሰጠው ታክስና ግብር
የመጣልና የማስከፈል ሥልጣን መሠረት በሁለት መሠረታዊ የታክስ አጣጣል ወሰኖች ላይ
ተመስርቶ የታክስ ህግ ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል፡፡
- ነዋሪነትን መሠረት በማድረግ፣
- የገቢ ምንጭን መሠረት በማድረግ፣
• እነዚህን ሁለት መሠረታዊ መመዘኛዎች መሠረት በማድረግ የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ፡-
- የኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች በዓለም ዙሪያ በሚያገኙት ገቢ ላይ
- የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች የኢትዮጵያ ከሆነ ምንጭ ባገኙት ገቢ ላይ
ግብር ይጥላል፣ አከፋፈሉን፣ አወሳሰኑንና አሰባሰቡን አስቀምጧል፡፡
9
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
ክፍል ሁለት - የአዋጁ ጠቅላላ ክፍል
መግቢያ ፡- የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 የነበሩ ክፍተቶች
የቀድሞው የገቢ ግብር አዋጅ የሚከተሉት ክፍተቶች ነበሩበት፡-
• የታክስ ሠንጠረዦቹ ለገቢ ከተሰጠው ትርጉም እና እኩል የገቢ ሽፋን (coextensive coverage of
income or source of income) ያልነበራቸው ስለሆነ በታክስ መረቡ ውስጥ ያልገቡ በርካታ የገቢ
ዓይነቶች ነበሩ፡፡ በህጉ ክፍተት ምክንያትም የማይሰበሰብ ገቢ ነበር፡
• በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያገኙት ገቢ ላይ ግብር መክፈል እንዳለባቸው
በቀድሞው አዋጅ አንቀጽ 3(2) የተመለከተ ቢሆንም አዋጁ በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች ኢትዮጵያ
ውስጥ በሚያገኙት ገቢ ላይ በምን ያህል ምጣኔ ግብር እንደሚከፍሉና እንዲሁም የገቢ ምንጮችንና
ዓይነቶችን ለይቶ የዊዝሆልዲንግ ክፍያ ሥርዓትንም ያላካተተ ስለነበረ በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች
ወይም ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያገኙት ገቢ ላይ ግብር እየከፈሉ አልነበረም፡
• የቀድሞው አዋጅ መሠረታዊ የታክስ ህጉንና የታክስ አስተዳደር ህጉን አቀላቅሎ የያዘ ስለነበረና በተለያዩ
የታክስ ህጐች ውስጥ ተመሣሣይ ድንጋጌዎች የተለያየ አገላለጽ እየተጠቀሙ ለአፈፃፀም አስቸጋሪ ሁኔታ
ይፈጥሩ ነበር፡
. በቀድሞው አዋጅ የተከራይ አከራዮች ወጪያቸው ተቀናሽ የሚደረግበት የህግ አግባብ አልነበረም፡፡ ህጉ
አከራዮችን ብቻ ታሳቢ ያደርግ ስለነበር፡
10
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
• በቀድሞው አዋጅ መሠረት የግብር ባለሥልጣኑ የአንድን ግብር ከፋይ ግብይት ውድቅ አድርጐ የዕቃ ዋጋ
በተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ የሚተምንበት ግልጽ ሥልጣን ስለማይሰጥ በተለይ ከንግድ ሥራ ሃብት (Asset)
ግብይት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ችግር ያጋጥም ነበር፡ (በታክስ አስተዳደር አዋጁ ውስጥ የተካተተ)፡
• የማዕድንና ፔትሮሊየም አዋጆች ከገቢ ግብር አዋጁ ተነጥለው በሌሎች አዋጆች የታወጁ ስለነበረ የታክስ
አዋጆቹና የገቢ ግብር አዋጁ ድንጋጌዎች ለማዕድንና ለፔትሮሊየም ገቢ ግብር አወሳሰንና አስተዳደር ተፈፃሚ
ለማድረግ አስቸጋሪ የሚሆንበት ሁኔታ ነበር፡፡
• የቀድሞው አዋጅ ኪሣራ ማሸጋገርን በሚመለከት ያስቀመጠው ድንጋጌ ግልጽነት የጐደለው ስለነበረ
በአፈፃፀም ሲያወዛግብ የነበረበት ሁኔታ ነበር ፡
• አዲስ ቤት (ህንፃ) የሚገነቡ ግብር ከፋዮች ያልተጠናቀቀ ህንፃ እያከራዩ የእርጅና ቅናሽ ጥያቄ የሚያቀርቡበትና
ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ድንጋጌ በቀድሞው አዋጅ አልተካተተም ነበር፡፡
• የቀድሞው አዋጅ በታክስ ሠንጠረዦቹ የማይሸፈኑ የገቢ ዓይነቶችን ወደ ታክስ መረቡ ለማስገባት የሚያስችል
“Residual tax rate” አያስቀምጥም ነበር፡
• የቀድሞው አዋጅ ሳይሻሻል ረዘም ላለ ጊዜ ስለቆየ የግብር ከፋይ ደረጃዎችን ለመለየት የተጠቀመባቸው
የገንዘብ መጠኖች (thresholds) ከገንዘብ የመግዛት አቅም ጋር ተገናዝበው ሳይሻሻሉ መቆየታቸው እንደ
ክፍተት ታይቷል፡፡
• እና ሌሎችም የመሣሰሉት
11
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
ክፍል ሁለት…
የአዋጁ ጠቅላላ ክፍል
2.1. የግብር ከፋይ ደረጃዎች
• ደረጃ “ሀ”
- ድርጅት (ጥቃቅን ኢንተርኘራይዞችን ይጨምራል;) እና
- ብር 1,ዐዐዐ,ዐዐዐ እና ከዚያ በላይ ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ያለው ግለሰብ ነጋዴ
• ደረጃ “ለ”
- ብር 5ዐዐ,ዐዐዐ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከብር 1,ዐዐዐ,ዐዐዐ የሚያንስ ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ
ያለው ግለሰብ ነጋዴ
• ደረጃ “ሐ”
- ከብር 5ዐዐ,ዐዐዐ ያነሰ ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ያለው ግለሰብ ነጋዴ
• ባለሥልጣኑ በየግብር ዓመቱ የግብር ከፋዩ ደረጃ የተለወጠ መሆን አለመሆኑን የሚከተሉትን
መረጃዎች መሠረት በማድረግ ይወስናል፡
- ግብር ከፋዩ የሚያሳውቀውን ግብር
- በማንኛውም መንገድ የሚያገኘውን ሌላ መረጃ፣
• የግብር ከፋይ ደረጃን ለመወሰን የሚያገለግለው ዓመታዊ ጠቅላላ የገቢ መጠን (threshold)
በሚኒስቴሩ በየአምስት ዓመቱ በጥናት እንደሚሻሻል ተደንግጓል፡፡
12
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
2.2. በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት
• በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት ነው የሚባለው ማንኛውም ሰው የንግድ ሥራውን በሙሉ ወይም
በከፊል የሚያከናውንበት የንግድ ሥራ ቦታ ነው፡፡
• ከላይ የተመለከተው ጠቅላላ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉት በቋሚነት የሚሠራ
ድርጅት እንዳለ ያስቆጥራሉ፡-
- የድርጅቱን አገናኝ ጽ/ቤት ሳይጨምር የአስተዳደር ሥራ የሚከናወንበት ቦታ፣ ቢሮ፣
ፋብሪካ፣መጋዘን ወይም ወርክሾኘ፣
- የማዕድን ማምረቻ ሥፍራ፣የነዳጅ ወይም የጋዝ ጉድጓድ፣የግንባታ ጠጠር ማምረቻ ወይም
ሌላ ማናቸውም የተፈጥሮ ሃብት ፍለጋ ወይም ማምረት ሥራ የሚከናወንበት ቦታ፣
• ለአንድ ወይም ለተያያዙ ኘሮጀክቶች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ183 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ
ተቀጣሪዎችን ወይም ሌሎች ሠራተኞችን በመመደብ (በመላክ) የምክር አገልግሎትን ጨምሮ
ሌሎች ማናቸውም አገልግሎቶች የሚሰጡበት ቦታ፣
13
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
• ከ183 ቀናት በላይ የሚቆይ የህንፃ ግንባት ሥራ የሚከናወንበት ሥፍራ፣ የግንባታ፣
የመገጣጠም ወይም የተከላ ኘሮጀክት ወይም ከእነዚህ ጋር የተገናኙ የቁጥጥር ሥራዎች
የሚሠሩበት ሥፍራ፣
• አንድ ሰው ወይም ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ የንግድ ወኪሉ አማካኝነት በስሙ
የውል ድርድር የሚደረግለትና ውል የሚገባለት ከሆነና የንግድ ዕቃዎችን በወኪሉ
አማካኝነት አከማችቶ የሚያቆይ ከሆነ ወኪሉ የወካዩ በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት ተደርጐ
ይቆጠራል፡
- ወኪሉ ደላላ፣የኮሚሽን ወኪል ወይም ሌላ ራሱን ችሎ የሚሠራ ወኪል
(independent) መሆን የለበትም፡
- ይህን ለመለየት የፋይናንስና የውል ግንኙነታቸውን ማየት ያስፈልጋል፡
- የተቀጽላ ድርጅቶች (subsidiaries) እና በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት ልዩነት ግልጽ መሆን
አለበት፡
 PE are not incorporated and independent
 Subsidiaries are incorporated and independent
14
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
2.3. ነዋሪነት
• የሚከተሉት የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ናቸው፡፡
- ነዋሪ የሆነ ግለሰብ
 ኢትዮጵያ ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ (domicile) ያለው፣
 በመንግስት ተመድቦ በውጭ አገር የሚሠራ ኢትዮጵያዊ ዜጋ፣
 በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ሳያቋርጥ ወይም በመመላለስ
ከ183 ቀናት በላይ የኖረ ግለሰብ፣
- ነዋሪ የሆነ ድርጅት
 ኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ /የተመሠረተ/፣
 ወሳኝ የሆነ የሥራ አመራር የሚሰጥበት ሥፍራ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው፣
የፌደራል መንግስት፣ የክልል መንግስታትና ከተማ አስተዳደሮች፣
• በ183 ቀናት ቆይታው ምክንያት ነዋሪ ነው የሚባል ግለሰብ ለግብር ዓመቱ እንደነዋሪ የሚቆጠረው
ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ከጀመረበት ቀን አንስቶ ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያ
ውስጥ ከኖረበት ቀን በፊት ላለው ጊዜ ነው፡፡
15
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
2.4. የገቢ ምንጭ
የሚከተሉት ገቢዎች ከኢትዮጵያ የመነጩ ናቸው፡
• በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚከናወን የቅጥር አገልግሎት የተገኘ ገቢ
- ክፍያው የሚፈፀምበት ሥፍራ የትም ቢሆን፣
- ውሉ የተፈረመው የትም ቢሆን፣
- የአሠሪው ነዋሪነት የትም ቢሆን፣
- ሠራተኛው የኢትዮጵያ ነዋሪ ቢሆንም ባይሆንም፣
• በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት፣በክልል መንግስታት ወይም በከተማ አስተዳደሮችና
በእነዚህ ስም ለቀጣሪው የተፈፀመ ክፍያ
- የቅጥር አገልግሎቱ የትም ቢከናወን፣
• በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያገኘው የግድ ሥራ ገቢ፣
(- በውጭ አገር ባለው በቋሚነት በሚሠራ ድርጅቱ አማካኝነት ከውጭ አገር የሚያገኘው
ገቢ ከውጭ ምንጭ የተገኘ ገቢ ነው፡፡)
16
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
• ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ ያልሆነ ሰው፣
- በቋሚነት በሚሠራ ድርጅት አማካኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚያካሂደው የንግድ ሥራ
የሚያገኘው ገቢ፣
- በቋሚነት የሚሠራው ድርጅት ከሚያስተላልፏቸው ዕቃዎች ወይም ሸቀጦች ጋር አንድ
ዓይነት ወይም ተመሣሣይ የሆኑ ዕቃዎችን ወይም ሸቀጦችን ኢትዮጵያ ውስጥ
በቀጥታ በማስተላለፍ የሚያገኘው ገቢ፣
- በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት ከሚያከናውናቸው ማናቸውም የንግድ ሥራዎች ጋር አንድ
ዓይነት ወይም ተመሣሣይ የሆኑ ሌሎች የንግድ ሥራ እንቅስቃሴዎችን ኢትዮጵያ
ውስጥ በቀጥታ በማከናወን የሚያገኘው ገቢ፣
17
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
ከላይ የተመለከቱት ቢኖሩም የሚከተሉት ገቢዎች ኢትዬጽያ ውስጥ የመነጩ ገቢዎች ይባላሉ/4/፡-
- በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ድርጅት የሚከፍለው የትርፍ ድርሻ፣
- የማይንቀሳቀስ ሃብትና በኢትዮጵያ የሚገኝን የሚንቀሳቀስ ሃብት በማከራየት የሚገኝ ገቢ፣
- በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝን የማይንቀሳቀስ ሃብት በማስተላለፍ ወይም ግንኙነት ባላቸው ሰዎች የተያዘንና
ከዋጋው 5ዐ% በላይ የሆነን የማይንቀሳቀስ ሃብት ጥቅም በማስተላለፍ የሚገኝ ገቢ፣
- በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ኩባንያ ያወጣው (የሚሸጠው) አክሲዮን ወይም ቦንድ፣
- በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኝ መድን ለተገባለት የአደጋ ሥጋት የሚከፈል የመድን አርቦን፣
- በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚከናወን የመዝናኛ ወይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚገኝ ገቢ፣
- በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄድን የዕድል ሙከራ በማሸነፍ የሚገኝ ገቢ፣
- የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው የኢትዮጵያ ነዋሪ ከሆነ ሰው የሚያገኘው የወለድ ገቢ፣
- የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው የኢትዮጵያ ነዋሪ ከሆነ ሰው የሚያገኘው የሮያልቲ ክፍያ ገቢ፣
- የኢትዮጵያ ነዋሪ ለሌላ የኢትዮጵያ ነዋሪ የሚከፍለው የወለድ እና የሮያልቲ ክፍያ ገቢ፣
- የኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት የኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆነ ሰው
የሚከፍሉት የሥራ አመራር ወይም የቴክኒክ አገልግሎት ክፍያ፣
 ከኢትዬጵያ ውስጥ ያልመነጨ ማንኛውም ገቢ የውጭ አገር ገቢ ነው የሚባለው/5/፡፡
18
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
2.5. የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ የህግ አንቀጽ የተደነገገው የኢትዮጵያ መንግስት ያለውንና ሊኖረው የሚገባውን የግብር
ሥልጣን (Tax jurisdiction) መሠረት በማድረግ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት አዋጁ
- የኢትዮጵያ ነዋሪ በሆኑ ሰዎች ላይ በዓለም ዙሪያ በሚያገኙት ገቢ ላይ ግብር እንዲከፍሉ፣
- የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑት ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ባገኙት ገቢ ላይ ወይም የኢትዮጵያ
ምንጭ በሆነ ገቢ ላይ ብቻ ግብር እንዲከፍሉ ደንግጓል፡፡
19
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
2.6. የገቢ ሠንጠረዦች
• በዚህ አዋጅ አምስት የግብር ሠንጠረዦች ይፋ ተደርገዋል፡-
- ሠንጠረዥ ሀ - ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ
- ሠንጠረዥ ለ - ከ(ቤት) ኪራይ የሚገኝ ገቢ
- ሠንጠዥ ሐ - ከንግድ ሥራ የሚገኝ ገቢ
- ሠንጠረዥ መ- ሌሎች ገቢዎች
- ሠንጠረዥ ሠ - ከግብር ነፃ የሆኑ ገቢዎች
• በአንድ ሠንጠረዥ ውስጥ የሚወድቁ የተለያዩ ገቢዎችን ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ያገኘ
ሰው ሁሉም ገቢዎች ተጣምረው በዚያው ሠንጠረዥ ሥር ግብር ይከፈልባቸዋል፡፡
20
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
2.7. የገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ
• ማንኛውም ገቢ የሚያገኝ ሰው በዚህ አዋጅና በታክስ አስተዳደር አዋጁ መሠረት ግብር
የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
• ይህ ድንጋጌ ገቢ ባገኘ ሰው ላይ ሁሉ አጠቃላይ ግብር የመክፈል ግዴታን የሚያቋቁም
ሲሆን በዚህ አዋጅና በታክስ አስተዳደር አዋጁ መሠረት ግብሩ መከፈል እንዳለበት
ስለሚደነግግ ከግብር ነፃ በሆኑ ገቢዎች ላይ ግብር የመክፈል ግዴታን አያስከትልም፡፡
• ግብር ከፋይ ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታ የተጣለበት ሰው ነው፡፡
• ግብር የመክፈል ግዴታ ያለበት ሰው ገቢ ያገኘ ሆኖ ከግብር ነጻ ያልተደረገ ሰው ነው፡፡
21
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
ክፍል ሦስት
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ “ሀ”)
• ከግብር ነፃ ከሆነው በስተቀር ቀጣሪው ለተቀጣሪው በሚከፍለው ማንኛውም የገንዘብ
መጠን ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ይከፈልበታል፡፡
• ቀጣሪ ማለት ተቀጣሪን የቀጠረ ወይም ለተቀጣሪው ደመወዝ የሚከፍል ሰው ነው፡፡
• ተቀጣሪ ማለት ደግሞ ራሱን ችሎ የሚሰራን የስራ ተቋራጭ ሳይጨምር በሌላ ሰው
/በቀጣሪው/ መሪነትና ቁጥጥር ስር ሆኖ አገልግሎት ለመስጠት በቋሚነት ወይም
በጊዜያዊነት የተቀጠረ ግለሰብ ሲሆን የድርጅት ዳይሬክተር፣ ወይም በድርጅቱ አመራር
ውስጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ሌላ ሰው እንዲሁም ተሿሚንና የህዝብ ተመራጭን ጨምሮ
የመንግስት ስራ ኃላፊን ያጠቃልላል፡፡
• ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 12 የተሰጠው ትርጉም ይኖረዋል፡፡
• በአዋጁ አንቀጽ 10 ላይ ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር የተጣለ ሲሆን የግብር
ማስከፈያ ምጣኔው በአንቀጽ 11 ተመልክቷል፡፡
22
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
• አንቀጽ 12 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ፡-
- ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
 ከሰራተኛው ቅጥር ጋር በተያያዘ ሰራተኛው የተቀበለው ደመወዝ /ምንዳ/፣ አበል፣ ጉርሻ፣
ኮሚሽን ፣ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማበረታቻ፣ ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ክፍያ፣
 ሰራተኛው ከቅጥር ውሉ ጋር በተያያዘ በዓይነት የሚቀበለው ማንኛውም ጥቅማጥቅም ዋጋ፣
 ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲለቅ ወይም ስራን እንዲለቅ ለማግባባት የሚከፈል
ገንዘብን ጨምሮ የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት ወይም በዳኝነት
ውሳኔ መሠረት የተቀበለ ማንኛውም የገንዘብ መጠን፣
• ቀጣሪው ለተቀጣሪው ከተከፈለው የገንዘብ መጠን ላይ ግብሩን ሳይቀንስ ከራሱ ግብሩን የከፈለ
እንደሆነ የተከፈለው ግብር በተቀጣሪው ደመወዝ ላይ ተደምሮ ግበሩ ይሰላል፡
• በዓይነት ለተቀጣሪው የሚሰጥ ጥቅማጥቅም ዋጋ የሚሰላበትና የሚወሰንበት ሁኔታ በደንብ
ይወሰናል፡፡ /የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር410/2009 ከአንቀጽ8-19/
23
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
ክፍል አራት
የቤት ኪራይ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ “ለ”)
• ከቤት ኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር የተጣለ መሆኑን አንቀጽ 13 የሚደነግግ ሲሆን የግብር
ማስከፈያ ምጣኔው በአንቀጽ 14 ስር ተመልክቷል፡፡
• ይህ ሠንጠረዥ አልፎ አልፎ ከሚከራዩ ንብረቶች በሚገኘው ገቢ ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን
የአዋጁ አንቀጽ 13(3) ደንግጓል፡፡
• ግብር የሚከፈልበት የኪራይ ገቢ የሚባለው፡-
- በግብር ዓመቱ ግብር ከፋዩ ቤት በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር
ከፋዩ የተፈቀደው ጠቅላላ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ የሚቀረው ገቢ ሲሆን የሚከተሉትን
ይጨምራል-፡
24
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
የቤት ኪራይ ገቢ ግብር…
 የኪራይ ዋጋ ጭማሪን ወይም ተመሳሳይ ክፍያዎችን ጨምሮ በኪራይ ወሉ መሠረት
ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የሚያገኘው ማናቸውም የገንዘብ መጠን፣
 በኪራይ ውሉ መሠረት ተከራይ አከራዩን በመወከል በግብር ዓመቱ ለሌሎች
የሚከፍላቸው ክፍያዎች፣
 ግብር ከፋዩ ጉዳቱን ለማስተካከል ያልተጠቀመበትና በቤቱ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት
ማስተካከያ ይሆን ዘንድ የያዘውና በግብር ዓመቱ ለግብር ከፋዩ ገቢ የተደረገው
ማናቸውም ቦንድ፣ዋስትና ወይም ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን፣
 ለግብር ከፋዩ ከሚከፈለው ኪራይ በተጨማሪ በኪራይ ውል መሠረት ተከራይ ራሱ
ለቤቱ እድሳት ወይም ማሻሻያ የሚያወጣው ገንዘብ፣
• ግብር ከፋዩ ቤቱን ያከራየው ከዕቃዎች ጋር በሚሆንበት ጊዜ ያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከዕቃዎቹ
የተገኘውን የኪራይ ገቢም ያጠቃልላል፡፡
25
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
የቤት ኪራይ ገቢ ግብር…
• በአንድ የግብር ዓመት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የሌለበት ግብር ከፋይ ግብር የሚከፈልበት ገቢ
በሚሰላበት ጊዜ የሚከተሉት ወጪዎች በተቀናሽ ይያዛሉ፡-
- ታክስን ሳይጨምር ለመሬቱ ወይም ከተከራየው ቤት ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩ ለመንግስት ወይም
ለከተማ አስተዳደር በግብር ዓመቱ ውስጥ የከፈላቸው ክፍያዎች፣
- ለቤቶች፣ለቤት ዕቃና መሳሪያ ማደሻ፣ መጠገኛና ለእርጅና መተኪያ የሚሆን ከቤት ዕቃና ከመሣሪያ ኪራይ
ከሚገኘው ጠቅላላ ገንዘብ ላይ 50% በመቶ፣
- ከላይ የተመለከተው አንቀጽ 15(5) በማናቸውም ሁኔታ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ላለባቸው ግብር
ከፋዮች ተፈፃሚ ሊሆን አይችልም፡
• የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ግብር ከፋይ በግብር ዓመቱ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚሰላበት ጊዜ ገቢውን
ለማግኘት የወጣና በግብር ከፋዩ የተከፈለ አስፈላጊ (necessary) የሆነ ወጪ ተቀናሽ የሚደረግ ሲሆን
ይህም ወጪ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-
- ቤቱ ያረፈበት የመሬት ኪራይ (lease)፣
- የጥገና ወጪ፣
- የቤቱ፣የቤት ዕቃዎችና የመሣሪያዎች የእርጅና ቅናሽ፣
- ወለድና የመድን አርቦን፣
- ታክስን ሳይጨምር ለመሬቱ ወይም ከተከራየው ቤት ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩ ለመንግስት ወይም
ለከተማ አስተዳደር የከፈላቸው ክፍያዎች፣
26
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
የቤት ኪራይ ገቢ ግብር …
• የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ያገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው የሚባለው የተከራይ
አከራይ በግብር ዓመቱ ከተቀበለው ጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ለዋናው አከራይ የሚከፍለው
ኪራይ እንዲሁም ገቢውን ለማግኘት ያወጣቸው ሌሎች ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚቀረው
ገንዘብ ነው፡፡
• ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ እንዲያከራይ የሚፈቅድ የቤት ባለቤት ተከራዩ ግብሩን
ሳይከፍል ቢቀር ስለእርሱ ሆኖ ግብሩን የመክፈል ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡
• ስራ ተቋራጭ እና የቤቱ ባለቤት ለኪራይ የሚሰራው ቤት እንደተጠናቀቀ ወይም ተከራይቶ
ከሆነ ከቤቱ ኪራይ በሚገኘው ገቢ ላይ ግብር መክፈል ያለበትን ሰው ስም፣አድራሻና የታክስ
ኪራይ መለያ ቁጥር ቤቱ ለሚገኝበት የቀበሌ አስተዳደር ወይም የአካባቢ አስተዳደር
ማስታወቅ አለባቸው፡፡
• የቀበሌ አስተዳደሩ ወይም የአካባቢ አስተዳደሩ ከስራ ተቋራጩና ከቤቱ ባለቤት ያገኙት መረጃ
ለግብር ባለሥልጣኑ መግለጽ አለባቸው፡፡
27
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
ክፍል አምስት
ግብር የሚከፈልበት የንግድ ስራ ገቢ፣ተቀናሽ የሚደረጉና የማይደረጉ
ወጪዎች
1. ግብር የሚከፈልበት የንግድ ስራ ገቢ /አ20/
- ግብር የሚከፈልበት የንግድ ስራ ገቢ የሚባለው በግብር ዓመቱ ውስጥ ከተገኘው ጠቅላላ
የንግድ ስራ ገቢ ላይ በህግ የተፈቀዱ ወጪዎች ተቀንሰው የሚገኘው የተጣራ የገቢ
መጠን ነው፡፡
- ግብር ከፋዩ የግብር ዓመቱን ግብር የሚከፍልበት የንግዱ ስራ ገቢ የሚወስነው
በፋይናንሻል ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች መሠረት በሚያዘጋጀው የትርፍና ኪሳራ ወይም
የገቢ መግለጫ ላይ በመመስረት ይሆናል፡፡
 የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች
 የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
 የሚኒስትሩ መመሪያ የተጠበቁ ናቸው፡፡
28
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
2. የንግድ ስራ ገቢ (21)
የንግድ ስራ ገቢ ነው የሚባለው የሚከተሉትን ይጨምራል፡፡
• ግብር ከፋዩ ዕቃዎችን በማስተላለፍ አገልግሎቶችን በመስጠት የሚያገኘውን የገንዘብ መጠን
ጨምሮ በግብር ዓመቱ ከንግድ ስራ ያገኘው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን፣
• የንግድ ስራ ሃብትን በማስተላለፍ የሚገኝ የገንዘብ መጠን (ከመዝገብ ዋጋ በላይ ያለው ዋጋ)፣
• በዚህ አዋጅ መሠረት የግብር ከፋዩ ገቢ ተደርገው የተወሰዱ ሌሎች ማናቸውም ገቢዎች፣
• የካፒታል ንብረት የሆነን የንግድ ስራ ሃብት በማስተላለፍ በሚገኘው ጥቅም ላይ ሁለት
ግብሮች ሊወሰኑ ይችላሉ፡-
- የንግድ ትርፍ ግብር
- የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር (59)
29
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
• ከንግድ ስራ ሃብቱ የመዝገብ ዋጋ በላይ የሆነው ትርፍ በንግድ ስራ ገቢ ውስጥ
የሚደመር ሲሆን ለንግድ ስራ ሃብት ከተደረገው ወጪ በላይ የሚገኘው ጥቅም
ደግሞ የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር ይከፈልበታል፡፡
• ለምሳሌ፡- Assume no inflation adjustment ለንግድ ቢሮ በብር 5,000,000
የተሰራ ህንጻ ከሁለት ዓመት በኋላ በብር 7,000,000 ቢሸጥ በብር 500,000 ላይ
የንግድ ትርፍ ግብር የሚከፈልበት ሲሆን በብር 2,000,000 ላይ ደግሞ የካፒታል
ዋጋ ዕድገት ግብር ይከፈልበታል፡፡ የእርጅና ቅናሹ ጠቅላላ ገቢ ላይ ይደመራል
ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በግብር ዓመቱ መጨረሻ ከዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ላይ
የህንጻው የእርጅና ቅናሽ እየተቀነሰ መጥቷል፡፡
• መመሪያ ቁጥር 8/2011 ተመልከቱ
30
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
3. ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎች (22)
የሚከተሉት ከጠቅላላ ገቢ ላይ ይቀነሳሉ፡፡
• በንግድ ስራ ገቢው ውስጥ የተካተቱትን ገቢዎች ለማግኘት፣ በንግዱ ስራ ዋስትና ለመስጠትና
የንግድ ስራውን ለማስቀጠል በግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የተደረጉ አስፈላጊ የሆኑ
ወጪዎች፣
• በግብር ዓመቱ ለተሸጠ የንግድ ዕቃ (trading stock) የወጣ ወጪ፣
• በንግድ ስራው ላይ ሲውሉ ዋጋቸው የሚቀንስ የንግድ ስራ ሃብቶችና ግዙፋዊ ህልወት
ለሌላቸው የንግድ ስራ ሃብቶች በግብር ዓመቱ የሚታሰበው ጠቅላላ የእርጅና ቅናሽ፣
• የንግድ ዕቃን ሳይጨምር ግብር ከፋዩ በዓመቱ ውስጥ የንግድ ስራ ሃብትን በማስተላለፍ
የገጠመው ኪሣራ፡፡
• በዚህ አዋጅ በተቀናሽነት የተፈቀዱ ሌሎች ወጪዎች፡፡
31
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
- የወለድ ወጪ፣
 ብድሩ ለንግድ ስራ ከዋለ፣
 ብድሩ ከባንክ ውጪ በሆነ አበዳሪ የተሰጠ ሆኖ በብሄራዊ ባንክና በንግድ ባንክ መካከል
በተደረገ የብድር ስምምነት ከሚታሰብ የወለድ ምጣኔ ከ2% በላይ የሚበልጥ ካልሆነ፣
 ከተፈቀደለት ባንክ ለተወሰደ ብድር የተከፈለ ወለድ ያለገደብ ይቀነሳል፡፡
 በሠንጠረዥ መ መሠረት ግብር የሚከፈልበት ካልሆነ በስተቀር ግብር ከፋዩ ግንኙነት ላለው
ነዋሪ የከፈለው ወለድ አይቀነስም፡፡
- ለበጎ አድራጎት ዓላማ የተደረገ ስጦታ፣
 የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ከሆነ፣
 በመንግስት በተደረገ ጥሪ መሰረት ለመንግስት የተደረገ ስጦታ ከሆነ፣
 ግብር ከሚከፈልበት ገቢ ከ10% ያልበለጠ ስጦታ ከሆነ፣
- የማይሰበሰብ ዕዳ
- የተፈቀደ ኪሳራ
- ከረጅም ጊዜ ውል ጋር በተያያዘ የግብር ዓመቱ የወጪ መቶኛ፡፡
32
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
4. የእርጅና ቅናሽ ስሌትና አሠራር (25)
• የእርጅና ቅናሽ ምጣኔና ዝርዝር አሠራር በደንብ የሚወሰን ይሆናል፡፡ /ደንብ ቁጥር 410/2009
አንቀጽ36-41/
• ዓመቱን ሙሉ አገልግሎት ያልሰጠ ወይም በከፊል ለንግዱ ስራ በከፊል ደግሞ ለሌላ ስራ የዋለ
የንግድ ስራ ሃብት ለንግድ ስራ በዋለበት መጠን ብቻ የእርጅና ቅናሽ እንደሚሰላ ተመልክቷል፡፡
• እርጅና መታሰብ የሚጀምረው የንግድ ስራ ሃብቱ ህንጻ ከሆነ የህንጻ ግንባታ መጠናቀቁን
የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከተሰጠበት ቀን በፊት ሊሆን አይችልም፡፡ ሌላ ንብረት ከሆነ
ለንግድ ስራ ዝግጁ ከሆነበትና አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ይሆናል፡፡
• የንግድ ስራ ሃብት የሚባለው ከአንድ ዓመት የሚበልጥ የአገልግሎት ዘመን ያለው ለንግድ ስራ
የዋለ ሀብት ወይም መብት ነው፡፡(25(7))፡፡
• የንግድ ስራ ሃብት ማለት የንግድ ስራ በማከናወን ሂደት በሙሉ ወይም በከፊል የንግድ ስራ ገቢ
ለማግኘት የተያዘ ወይም ጥቅም ላይ የዋለ ሃብት ነው(2(3))፡፡
33
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
5. ኪሳራን ስለማሸጋገር (26)
• የግብር ዓመቱ ወጪ ከግብር ዓመቱ ጠቅላላ ገቢ የበለጠ ከሆነ ከጠቅላላ ገቢው
በላይ ያለው ወጪ የግብር ከፋዩ ኪሳራ ነው፡፡
• ይህንን ኪሳራ ግብር ከፋዩ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት በማሸጋገር ማቀናነስ ይችላል፡፡
• ግብር ከፋዩ በአንድ የግብር ዘመን የደረሰበትን ኪሣራ ኪሣራው ከደረሰበት ዓመት
መጨረሻ ጀምሮ ከሚቆጠሩ ከአምስት ዓመታት በላይ ማሸጋገር አይችልም፡፡
• ከሁለት የግብር ዘመናት ኪሣራ በላይ ማሸጋገር አይፈቀድም፡፡
• ስለኪሳራ ማሸጋገር በደንቡ በዝርዝር ተገልጿል፡፡/410/2009 አንቀጽ42/
34
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
6. ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎችና ኪሣራዎች
የሚከተሉት ተቀናሽ አይደረጉም፡-
• የእርጅና ተቀናሽ የሚደረግባቸው የካፒታል ወጪዎች፣
• የኩባንያ አክሲዮን ወይም የሽርክና ማህበር መሠረት የሆነውን ካፒታል ለማሳደግ የሚወጣ ወጪ፣
• ከ15% በላይ የሆነ በቀጣሪው የሚከፈል የጡረታ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ መዋጮ፣
• የአክሲዮን ወይም የትርፍ ድርሻ፡
• በካሳ መልክ የተመለሰ ወይም ሊመለሰስ የሚችል ወጪ ወይም ኪሣራ፡
• ህግን ወይም የውል ግዴታን በመጣስ የሚጣል የገንዘብ ቅጣት ወይም የሚከፈል ኪሣራ፡
• ለወደፊት ወጪዎች ወይም ኪሣራዎች መጠባበቂያ የተያዙ ሂሳቦች፣
• የገቢ ግብር ወይም ተመላሽ የሚደረግ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣
• መስሪያ ቤቱን ለመወከል ለተቀጣሪ የሚከፈል ከመቀጠር ከሚያገኘው ገቢ ከ10% በላይ የሆነ
የኃላፊነት አበል፣
35
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
• ከሚከተሉት በስተቀር ለመዝናኛ የሚወጣ ወጪ፣
 የግብር ከፋዩ የንግድ ስራ የመዝናኛ አገልግሎት መስጠት ከሆነ ወይም
ለማኑፋክቸሪንግ፣ለማዕድንና ለግብርና ሰራተኞች መዝናኛ የተከፈለ ወጪ ይቀነሳል፡፡
ከ65(6) ጋር የሚታይ /ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርብ ከሆነ/ ፡፡
• በአንቀጽ 24 ከተመለከተው ውጪ የሚደረግ ስጦታ ወይም እርዳታ፣
• የግብር ከፋዩ የግል ወጪ፣
• የንግድ ስራ ሃብትን ግንኙነት ላለው ሰው በማስተላለፍ የሚያጋጥም ኪሣራ፡
• የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተቀናሽ አይደረጉም በማለት በደንብ የሚወስናቸው ወጪዎች፣
• መዝናኛ- ማለት ለማንኛውም ሰው የሚቀርብ ምግብ፣መጠጥ፣ትምባሆ፣
ማረፊያ፣ መደሰቻ ወይም ማናቸውም ዓይነት መስተንግዶ ነው፡
36
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
7. የታክስ ሂሳብ አያያዝ (28-33)
7.1. የሂሳብ ዓመት (28)
• ይህ አንቀጽ ተፈፃሚ የሚሆነው ከግብር ዓመቱ የተለየ የራሱ የሂሳብ ዓመት እንዲኖረው በተፈቀደለት
ግብር ከፋይና በድርጅቶች ላይ ነው፡፡
• የእነዚህ ግብር ከፋዮች የሂሳብ ዓመት ነው የሚባለው የግብር ከፋዩ ዓመታዊ የፋይናንስ ሂሳብ ሚዛን
በሚዘጋበት ጊዜ የሚጠናቀቀው የአስራሁለት ወራት ጊዜ ነው፡፡
• ማንኛውም ግብር ከፋይ ከባለሥልጣኑ የጽሁፍ ፈቃድ ሳያገኝና ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟላ የሂሳብ
ዓመቱን መቀየር አይችልም፡፡
• ግብር ከፋዩ ቅድመ ሁኔታዎቹን ያጓደለ እንደሆነ ባለሥልጣኑ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት
የሰጠውን ፈቃድ ሊሰርዘው ይችላል፡፡
• የግብር ከፋዩ የሂሳብ ዓመት ሲቀየር በነባሩ የሂሳብ ዓመት እና በአዲሱ የሂሳብ ዓመት መካከል ያለው ጊዜ
“የመሸጋገሪያ ዓመት” በመባል የሚታወቅ ሲሆን ይህ ጊዜ ራሱን እንደቻለ የሂሳብ ዓመት ይቆጠራል፡፡
• የግብር ከፋዩ የሂሳብ ዓመት ከበጀት ዓመቱ ጋር የማይገጥም በሚሆንበት ጊዜ ለሂሳብ ዓመቱ ተፈጻሚ
የሚሆነው ህግ በሂሳብ ዓመቱ ውስጥ በሚጠናቀቀው የበጀት ዓመት ተፈፃሚ የሚሆነው ህግ ነው፡፡
37
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
7.2. የሂሳብ አያያዝ ዘዴን ስለመለወጥ
• ግብር ከፋዩ የሂሳብ አያያዝ ዘዴውን ለመለወጥ ባለሥልጣኑን በጽሁፍ
ሊጠይቅ የሚችል ሲሆን ባለሥልጣኑም ለውጡ የግብር ከፋዩን ገቢ
በትክክል ለማስላት የሚያስፈልግ መሆኑን ሲያምንበት ግብር ከፋዩ የሂሳብ
አያያዝ ዘዴውን እንዲለውጥ በጽሁፍ ሊፈቅድለት ይችላል፡፡
• የግብር ከፋዩ የሂሳብ አያያዝ ዘዴ በሚለወጥበት የግብር ዓመት የግብር
ከፋዩ የግብር ከፋይ ደረጃም የሚለወጥ ከሆነ የግብር ከፋዩ ገቢ
ሳይመዘገብ እንዳይቀር ወይም በድጋሚ እንዳይመዘገብ ለማድረግ በገቢ
ርዕሶች፣በተቀናሽ ወጪዎች ወይም በታክስ ማካካሻ ሂሳቦች ላይ ከለውጡ
ጋር በተያያዘ ተገቢውን ማስተካከያ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
23/02/2015 E.C 38
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
7.3. የማይሰበሰቡ ዕዳዎች (30)
• የሚከተሉት ሲሟሉ ግብር ከፋዩ ሊሰበስበው ያልቻለ ዕዳ በተቀናሽነት ይያዝለታል፡፡
- ዕዳው ቀደም ሲል የንግድ ስራ ገቢ ሆኖ ተይዞ /ተመዝግቦ/ ከሆነ፣
- ዕዳው ከግብር ከፋዩ የሂሳብ መዝገብ የተሰረዘ እንደሆነ፣ እና
- ዕዳውን ለማስከፈል አስፈላጊ የህግ እርምጃ ተወስዶ ማስመለስ ያልተቻለ
እንደሆነ፣
• የሚቀነሰው የዕዳ መጠን ከግብር ከፋዩ የሂሳብ መዝገብ ከተሰረዘው የዕዳ መጠን
መብለጥ የለበትም፡፡
• ይህ አንቀጽ ለፋይናንስ ተቋማት ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
39
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
7.4. የፋይናንስ ተቋማትና የኢሹራንስ ኩባንያዎች (31)
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚከተሉትን በደንብ ይወስናል፡፡
• የፋይናንስ ተቋማት የሚይዙት የኪሳራ መጠባበቂያ ገንዘብ ተቀናሽ የሚደረግበት
ሁኔታ፣/410/2009(45)/
• የህይወት መድን ኢንሹራንስ ኩባንያዎችን ሳይጨምር የኢንሹራንስ ኩባንያዎች
ጊዜያቸው ካላለፈባቸው የኢንሹራንስ ዋስትናዎች ጋር በተያያዘ የሚይዙት
የመጠባበቂያ ሂሳብ ተቀናሽ ስለሚደረግበት ሁኔታ፣/410/2009(46)/
• የህይወት መድን ኩባንያዎች ግብር የሚከፍሉበት ገቢ ስለሚሰላበት
ሁኔታ፣/410/2009 (47)/
40
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
7.5. ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ውሎች (32)
• ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ውል ማለት በተጀመረበት የግብር ዓመት ውስጥ ያልተጠናቀቀ
የማምረት፣የመትከል ወይም የግንባታ ስራ እንዲሁም ከእነዚህ ጋር የተያያዘ አገልግሎት ነው፡፡
• የረጅም ጊዜ ውል ያለው ግብር ከፋይ የግብር ዓመቱ ወጪ ተቀናሽ የሚደረግበት ሁለት
ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው፡፡
- ሂሳቡን በተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳብ ዘዴ የሚይዝ ሲሆን፣
- በግብር ዓመቱ የተጠናቀቀውን ስራ መቶኛ መሠረት በማድረግ ገቢውን በንግድ ስራ
ገቢው ውስጥ መዝግቦ ያካተተ ሲሆን ነው፡፡
• ተቀናሽ የሚደረገው የግብር ከፋዩ ወጪ ግምት ጠቅላላ የውሉ ወጪ በተጠናቀቀው ስራ
መቶኛ ተባዝቶ የሚገኘው የግብር ዓመቱ ወጪ ነው፡፡
41
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
• ግብር ከፋዩ በአንቀጽ 26 መሠረት ኪሣራውን ወደፊት ማሸጋገር የሚፈቀድለት ቢሆንም
ይህን ማድረግ ያልቻለ እንደሆነ ወይም በውሉ ዘመን መጨረሻ በኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ
ስራ መስራት በማቆሙ ምክንያት ኪሣራውን ወደፊት ማሸጋገር ያልቻለ እንደሆነ
የደረሰበት ኪሣራ በቀደመው ዓመት ገቢ ላይ ይካካሳል (Loss carry backward).
• ግብር ከፋዩ ኪሣራውን በአምናው ገቢ ላይ ማካካስ ካልቻለ ያልተካካሰው ኪሳራ በካቻምና
ገቢ ላይ ይካካሳል፡፡
• ግብር ከፋዩ ኪሣራ ደርሶበታል የሚባለው የሚከተሉትን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች
በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ነው፡-
- በውሉ ይገኛል ተብሎ የተገመተው ግብር የሚከፈልበት ገቢ በእርግጠኛነት ከተገኘው
ግብር የሚከፈልበት ገቢ በልጦ ሲገኝና
- በብልጫ የታየው የውሉ ዓመታዊ ገቢ ወሉ በተጠናቀቀበት የግብር ዓመት ወጪና ገቢው
ተሰልቶ ከተገኘው የገቢ ልዩነት በልጦ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡
42
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
7.6. ለደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የተወሰነ ቀላል የታክስ ሥርዓት (33)
ከዚህ በታች የተመለከቱት እንደተጠበቁ ሆነው የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች ግብር የሚከፈልበት
ገቢ የሚሰላውና የሚወሰነው በገቢ ግብር አዋጁ መሠረት ይሆናል፡
- ግብር ከፋዩ የንግድ ስራ ገቢውንና ተቀናሽ ወጪውን የሚይዘው በጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ
ላይ በተመሠረተ የሂሳብ አያያዝ ዘዴ መሆን አለበት፡
- ለንግድ ስራ ሃብቶቹ የሚደረገው የእርጅና ቅናሽ 100% ይሆናል፡
- በግብር ዓመቱ ለንግድ ዕቃዎች የወጣ ወጪ በተቀናሽነት ይያዛል፡
- የሂሳብ መዛግብትን ይዞ ለመቆየት የሚገደድበት /የታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀጽ 17/2/ እና
የግብር ውሳኔን ለማሻሻል ለባለሥልጣኑ የተፈቀደው ጊዜ /የታክስ አስተዳደር አዋጅ
983/2008 አንቀጽ 28/2ለ/ ሦስት ዓመት ብቻ ነው፡
43
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
8. ድርጅቶች (34 እና 35)
8.1. አንድን ድርጅት በመቆጣጠር ረገድ የሚደረግ ለውጥ (34)
• አንድ ድርጅት የደረሰበትን ኪሣራ ወደ መሸጋገሪያ ዓመት ወይም ወደሚቀጥለው ዓመት
ማሸጋገር የሚችለው የኩባንያውን ከ50% በላይ የሆነውን የዋና ባለቤትነት ድርሻ የያዘው
ሰው ተመሳሳይ ሰው የሆነ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡/አ1/
• ነገር ግን /አ2/ ድርጅቱ በኪሣራው ዓመት፣በመሸጋገሪያው ዓመትና በሁሉም ጣልቃ ገብ
ዓመታት አንድ ዓይነት የንግድ ስራ እየሰራ ያለ ከሆነ፣ ወይም
• የዋና ባለቤትነት ለውጥ ከተደረገም በኋላ ድርጅቱ በሌላ የንግድ ስራ የተሰማራው
ኪሣራውን ከአዲሱ ስራ ገቢ ላይ ለማካካስና ገቢውን ለማሳነስ አለመሆኑ ከተረጋገጠ
ኪሣራውን እንዳያሸጋግር አይከለከልም፡፡
44
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
8.2. የኩባንያ እንደገና መደራጀት (35)
• አንድ ኩባንያ እንደገና ከመደራጀት ጋር ተያይዞ ለሌላ ኩባንያ የንግድ ስራ ሃብት
በሚያስተላልፍበት ጊዜ የንግድ ስራ ሃብቱ እንደተሸጠ፣ እንደተለወጠ ወይም እንደተሰጠ
(እንደተላለፈ) አይቆጠርም፡፡
• የንግድ ስራ ሃብቱን ያገኘው ድርጅት አስተላላፊው የንግድ ስራ ሃብቱን ለማግኘት
ከወጣው ወጪ ጋር እኩል የሆነ ወጪ በማውጣት እንዳገኘው ይቆጠራል (aquired at
Book value)፡፡
• የንግድ ስራ ሃብቱ የተላላፈለት ሰው በምትኩ አክሲዮን የሰጠ እንደሆነ ለአክሲዮኖቹ
የተደረገው ወጪ የተላለፈው ሃብት በተላለፈበት ጊዜ ከነበረው ዋጋ ጋር እኩል መሆን
ይኖርበታል፡፡
• ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም “ለንግድ ስራው ሃብት የተደረገው ወጪ” የሚለው የንግድ ስራ
ሃብቱ በተላለፈበት ጊዜ የነበረውን የተጣራ የመዝገብ ዋጋ የሚመለከት ነው፡፡
45
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
• “እንደገና መደራጀት (reorganization)”ማለት፡-
- ከሁለት በላይ የሆኑ ነዋሪ ኩባንያዎች መዋሃድ፡፡
- የአዲሱ ድርጅት አባል የሆነ አንድ ድርጅት የሌላውን ድርጅት 50% ልዩ የአክሲዮን ባለቤት
ድርሻ ከአዲሱ ድርጅት በሚገኘው የአክሲዮን ለውጥ ብቻ መያዝ፡፡
- እንደገና በሚደራጀው ድርጅት ውስጥ አባል የሆነ ድርጅት የሌላውን ከ50% በላይ የሆነ
የአክሲዮን ባለቤትነት ድርሻ ልዩ መብት በማያሰጥና የድምጽ ተሳትፎ ብቻ በሚያስገኝ
አኳኋን መጠቅለል፡፡
- የአንድ ድርጀት ወደ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ወደ ሆኑ ኩባንያዎች መከፋፈል፡፡
- የአንድ ድርጅት የተቀጽላዎችን ካፒታል የድርጅቱን ካፒታል ለያዘ ሌላ ድርጅት ማስተላፍ፡፡
• በእንደገና መደራጀት ሂደት የተላለፈ የንግድ ስራ ሃብት እንደተላለፈ አይቆጠርም የሚለው
የዚህ አንቀጽ ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነው የእንደገና መደራጀቱ ዓላማ ከታክስ ለመሸሽ
ያለመሆኑ በባለስልጣኑ ሲታመንበት ነው፡፡
46
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
ክፍል ስድስት
የማዕድንና የነዳጅ ስራዎች ገቢ ግብር/36-44/
ሀ/ የማዕድንና የነዳጅ ስራዎች ልዩ ባህሪ
• የማዕድንና የነዳጅ ስራ ከሌላው የንግድ ስራ ለየት የሚያደርገው፡-
- የገቢ ምንጩ ሊተካ የማይችል የመንግስት (የሃገር) የተፈጥሮ ሃብትን በመጠቀም የሚገኝ
በመሆኑ፡፡
- ስራው ከፍተኛ ስጋት (Risk) ያለበትና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፡፡
- የማዕድንና የነዳጅ ፈለጋ ስራ ረጅም ጊዜ የሚወስድና በስተመጨረሻም ውጤት እንደሚገኝ
አስቀድሞ እርግጠኛ መሆን የማይቻልበት ሁኔታ (uncertainity) ያለበት በመሆኑ፡፡
- ንግዱ የመንግስት ልዩ ፈቃድ የሚጠይቅና ልዩ ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግበት እንዲሁም
የመንግስት ድርሻ ያለበት በመሆኑ፡፡
- ንግዱ የመንግስትን ልዩ መብት (Royal interest of the state) የሚጋራና ከፍተኛ የመንግስት
ጥቅም ያለበት በመሆኑ ወዘተ ነው፡፡
47
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
ለ/ ፈቃድ በተሰጠው ሰውና በስራ ተቋራጭ ላይ ግብር ስለመጣል
• ማዕድን የማውጣት መብት በተሰጠው ባለፈቃድ (ፈቃድ የተሰጠው ሰው) እና ከመንግስት
ጋር የነዳጅ ስምምነት ባደረገው ስራ ተቋራጭ ላይ የተጣለው የንግድ ስራ ገቢ ግብር 25%
ነው፡፡
• ፈቃድ የተሰጠው ሰው በኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆነ ንዑስ ስራ ተቋራጭ ከሚፈጽመው
ማንኛውም ክፍያ ላይ የሞቢላይዜሽንና የዲሞቢላይዜሽን ወጪዎች ተቀንሰው በሚቀረው
መጠን ላይ 10% ግብር ቀንሶ ለባለስልጣኑ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የነዳጅ ንዑስ ስራ
ተቋራጭ ከዚህ ዓይነት ግብር ነጻ ተደርጓል፡፡
• ስለማዕድንና ነዳጅ ስራዎች ገቢ የሚደነግገው የአዋጁ ክፍል ከሌሎች የአዋጁ ድንጋጌዎች ጋር
ቢጋጭ ስለማዕድንና ስለነዳጅ ስራዎች የሚደነግጉት የአዋጁ ክፍሎች የበላይነት
እንደሚኖራቸው ተደንግጓል፡፡ ከዚህ ክፍል ጋር የማይቃረኑ ሌሎች የገቢ ግብር አዋጅ
ድንጋጌዎች ግን ከማዕድንና ነዳጅ ስራዎች በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡
48
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
ሐ/ በማዕድን ወይም በነዳጅ ስራዎች ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎችን ስለመገደብ
• ባለፈቃዱ ወይም ስራ ተቋራጩ ተቀናሽ የሚደረግላቸው ወጪ፣
- ባለፈቃዱና ስራ ተቋራጩ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ ፈቃድ በተሰጠበት አካባቢ ወይም የውል ክልል
ውስጥ በግብር ዓመቱ ካገኙት የንግድ ስራ ገቢ ላይ የዓመቱን ወጪ ተቀናሽ ማድረግ ይችላሉ፡፡
- የማዕድን ወይም የነዳጅ ስራን በሚሰሩበት ጊዜ ኪሳራ ያጋጠማቸው እንደሆነ ኪሳራው ወደሚቀጥለው
የግብር ዓመት ተሸጋግሮ ፈቃድ በተሰጠበት ክልል ወይም በውሉ ክልል የማዕድን ወይም የነዳጅ ስራ
በመስራት ከሚያገኙት የንግድ ስራ ገቢ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል፡፡
- የደረሰባቸው ኪሳራ ከቀጣዩ የግብር ዓመት በተገለጹት ክልሎች በተገኘው ገቢ የማይካካስ ከሆነ ኪሳራን
እስከሚቀጥሉት 10 የግብር ዓመታት ድረሰ ማሸጋገር ይችላሉ፡፡
- ባለፈቃዱና ስራ ተቋራጩ ኪሳራ ደረሰባቸው የሚባለው በግብር ዓመቱ ካገኙት ጠቅላላ የንግድ ስራ ገቢ
የግብር ዓመቱ ጠቅላላ ወጪ የበለጠ እንደሆነ ነው፡፡
- ከዚህ በላይ የተመለከቱት ገደቦች እንደተጠበቁ ሆነው ባለፈቃዱና ስራ ተቋራጩ የሚከተሉት ተቀናሾች
ይፈቀዱላቸዋል፡-
49
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
1/ የፍለጋ ወጪዎች
 የአገልግሎት ዘመናቸው አንድ ዓመት የሆኑ የፍለጋ ወጪዎች ግዙፋዊ ህልወት የሌላቸው የንግድ
ስራ ሃብቶች ተደርገው ይወሰዳሉ፡-
 ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍለጋ ስራ ጥቅም ላይ የዋለ የንግድ ስራ ሃብት የእርጅና ቀናሽ መጣኔው
100% ይሆናል፡፡
2/ የማልሚያ ወጪ፣
 የማልሚያ ወጪ ለአራት ዓመታት ያህል የሚያገለግል ግዙፋዊ ህልወት የሌለው የንግድ ስራ ሃብት
እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
 ምርት ማምረት ከመጀመሩ በፊት የወጣ የማልሚያ ወጪ ለንግድ የሚሆን ምርት ማምረት
በተጀመረበት ጊዜ እንዳወጣ ወጪ ተቆጥሮ የእርጅና ቅናሽ ይታሰብለታል (አ.25)፡፡
 ለንግድ የሚሆን ምርት ማምረት ከመጀመሩ በፊት ለማልሚያ ስራዎች አገልግሎት የሚውል
ዋጋው የሚቀንስ የንግድ ስራ ሃብት የተገዛ ወይም የተገነባ እንደሆነ ሃብቱ ለንግድ ስራ የሚሆን
ምርት በተጀመረበት ጊዜ እንደተገዛ ወይም እንደተገነባ ተቆጥሮ የእርጅና ቅናሽ
ይታሰብለታል (አ.25)፡፡
50
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
 ከላይ የተመለከቱት የእርጅና ቅናሽ ስሌቶች ቀመር በአዋጁ አንቀጽ 40(4) ላይ የተመለከተ
ሲሆን “ሀ*ለ/ሐ” ለንግድ ስራ ሃብቱ የተደረገው ወጪ ለንግድ ማምረት ከተጀመረበት ቀን
አንስቶ ለንግድ ማምረት በተጀመረበት የግብር ዓመት የመጨረሻ ቀን መካከል ባሉት ቀናት
ተባዝቶ ለንግድ የሚሆን ምርት ማምረት በተጀመረበት የግብር ዓመት ላሉት ቀናት ብዛት
ተካፍሎ የሚገኘው ስሌት የእርጅና ቅናሹ ይሆናል፡፡
 ከማዕድን ስራ መብት ወይም ከነዳጅ ስምምነት ከተገኘ መብት አንድ መብት የተላለፈ
እንደሆነ መብቱን በማስተላለፍ የተገኘው ጥቅም ተደርጎ የሚወሰደው ባለፈቃዱ ወይም
ስራ ተቋራጩ ተቀናሽ የተደረገላቸውንና ያልመለሱትን ሂሳብ ሳይጨምር የማስተላለፍ
ተግባር በተከናወነበት ጊዜ ያወጡት የማልሚያ ወጪ ከተቀነሰ በኋላ የሚገኘው ዋጋ ነው፡፡
51
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
3/ የመልሶ ማቋቋሚያ ወጪ/rehabilitation expenditure/፣
 በመልሶ ማቋቋሚያ ዕቅድ መሰረት ለመልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ የሚደረገው መዋጮ
መዋጮው በተደረገበት የግብር ዓመት በተቀናሽነት ይያዛል፡፡
 ከመልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ወጪ ተደርጎ ያልተተካ ለመልሶ ማቋቋሚያ የወጣ ወጪ ወጪው
በወጣበት የግብር ዓመት በተቀናሽነት ይያዛል፡፡
 በመልሶ ማቋቋም ስራ ከመልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ወጪ የሚደረግ የገንዘብ መጠን ከግብር
ነጻ ነው፡፡
 ከመልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ወጪ ተደርጎ ለባለፈቃዱ ወይም ለስራ ተቋራጩ ተመላሽ
የተደረገ የገንዘብ መጠን ገንዘቡ ተመላሽ በተደረገበት የግብር ዓመት እንደ ንግድ ስራ ገቢ
ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
 “መልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ” ማለት ፈቃድ የተሰጠበትን ክልል ወይም የውል ክልል መልሶ
ለማስተካከል የሚውል በነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር እና በባለፈቃዱ ወይም በስራ
ተቋራጩ በጋራ የሚተዳደር ገንዘብ ነው፡፡
52
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
4/ የኢንቨስትመንት ተቀናሽ /42/
 በፈቃድ ሰጪው ባለስልጣን በተፈቀዱ ሌሎች የልማት መስኮች ኢንቨስት ለሚደረግ የወጣ
የኢንቨስትመንት ወጪ ከእያንዳንዱ የግብር ዓመት ጠቅላላ ገቢ ላይ እስከ 5% ተቀናሽ
ይፈቀዳል፡፡
 ሆኖም ይህ የኢንቨስትመንት ገንዘብ ተቀናሽ ከተደረገበት የግብር ዓመት ቀጥሎ እስካለው
የግብር ዓመት መጨረሻ ድረስ ኢንቨስት ካልተደረገ በዚሁ የግብር ዓመት ጠቅላላ ገቢ ላይ
ይደመራል፡፡
53
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
መ/ የማዕድን ወይም የነዳጅ መብት ስለማስተላለፍ/43/
• የማዕድን ወይም የነዳጅ መብትን ማስተላፍ የሚቻል ቢሆንም መብቱ ሲተላለፍ
የሚከተሉት መሟላት አለባቸው፡
- ባለፈቃዱ ወይም ስራ ተቋራጩ መብቱ ከሚተላለፍለት ሰው ጋር “የማስተላለፍ ስምምነት”
ተብሎ የሚጠቀስ የጹሁፍ ስምምነት ማድረግ አለባቸው፡፡
- ለሚተላለፈው መብት የሚከፈለው ዋጋ፣
 መብት የተላለፈለት ሰው ሊከፍል የተስማማበትን ወጪ እና
 ባለፈቃዱ ወይም ስራ ተቋራጩ ካስቀረው የተወሰነ መብት የሚመነጩ ግዴታዎችን
መብቱ የተላፈለት ሰው መብት አስተላላፊውን ተክቶ ለመወጣት የሚገባውን ግዴታ
ለመፈጸም የሚያወጣውን ወጪ የሚጨምር መሆን አለበት፡፡
54
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
• የማዕድንና የነዳጅ መብትን ማስተላለፍ ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ፡-
- መብት አስተላላፊው ካስቀረው መብት ጋር በተያያዘ መብት የተላለፈለት ሰው
የሚያከናወነው ስራ ዋጋ መብት አስተላላፊው ለተላለፈው መበት በተቀበለው ዋጋ
ውስጥ ወይም በመብት አስተላላፊው የንግድ ስራ ገቢ ውስጥ አይካተቱም፡፡
- መብት አስተላላፊው ከተላለፈው መብት ጋር በተያያዘ ላወጣው ወጪ ያገኘው ተቀናሽ
ተመላሽ እንደተደረገ ወጪ ተቆጥሮ በአንቀጽ 73 /የተመለሰ ወጪ- የሚያካክስ የገንዘብ
መጠን የተቀበለ እንደሆነ/ መሰረት ገንዘቡን በተቀበለበት የግብር ዓመት እንደተገኘ ገቢ
ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- አንቀጽ 73 ተፈጻሚ የሚሆበት ተቀናሽ ወጪ መብት አስተላላፊው ከተቀበለው የገንዘብ
መጠን የበለጠ እንደሆነ በብልጫ የታየው ገንዘብ የተላለፈው መብት ዋጋ ተደርጎ
ይወሰዳል፡፡
55
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
ሠ/ የማዕድን ወይም የነዳጅ መብትን በተዘዋዋሪ መንገድ ስለማስተላለፍ /44/
• የባለፈቃዱ ወይም የስራ ተቋራጩ ድርጅት ዋና ባለቤትነት ከ10% በላይ ከተለወጠ ባለፈቃዱ
ወይም ስራ ተቋራጩ ለውጡን ለባለስልጣኑ ወዲያወኑ በጹሁፍ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
• ከላይ የተገለጸውን ማስታወቂያ የመስጠት ግዴታ ያለበት የመብት አስተላላፊ የኢትዮጵያ ነዋሪ
ያልሆነ እንደሆነ ባለፈቃዱ ወይም ስራ ተቋራጩ /ፈቃድ የተሰጠው ማለት ነው/ በኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆነው
የመብት አስተላላፊ ወኪል እንደሆነ ተቆጥሮ ከመብት ማስተላለፉ ጋር ተያይዞ በዚህ አዋጅ
መሰረት ሊከፈል የሚገባውን ግብር የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡
• ከላይ በተገለጸው ሁኔታ በባለፈቃዱ ወይም በስራ ተቋራጩ የኢትዮጰያ ነዋሪ ያልሆነውን የመብት
አስተላላፊ በመወከል የተከፈለ ማንኛውም ግብር ከመብት አስተላላፊው (ነዋሪ ካልሆነው ሰው)
ላይ ከሚፈለገው የታክስ ዕዳ ጋር ይካካሳል፡፡
• ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል በማዕድን ወይም በነዳጅ ስራ በተሰማራ አንድ ድርጅት ውስጥ ያለ
የአባልነት ጥቅም እንደ ንግድ ስራ ሃብት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
56
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
ክፍል ስምንት
ዓለም አቀፍ ግብር
1. በውጭ አገር የተከፈለን የንግድ ስራ ገቢ ስለማካካስ (45)
• ዓለም አቀፍ ግብር እንዲከፍሉ የሚወሰንባቸው የኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ከኢትዮጵያ ውጪ ከሆነ የገቢ
ምንጭ የንግድ ስራ ገቢ ያገኙ እንደሆነ ነው፡፡ ምክንያቱም ከኢትዮጰያ ውጪ በተገኘ ገቢ ላይ ግብር
የመክፈል ግዴታ በአዋጁ የተጣለው የኢትዮጵያ ነዋሪ በሆኑ ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡
• በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው በውጭ አገር ካገኘው የንግድ ስራ ገቢ ላይ የውጭ አገር ግብር የከፈለ እንደሆነ
በውጭ አገር የከፈለው የንግድ ስራ ገቢ ግብር የሚካካስለት ሲሆን የሚካካሰው ግብር ከሚከተሉት
ከአነስተኛው አይበልጥም፡-
- በውጭ አገር ከተከፈለው ገቢ ግብር
- በውጭ አገር በተገኘው ገቢ ላይ በዚህ አዋጅ መሰረት ሊከፈል ከሚገባው የንግድ ስራ ገቢ ግብር፡-
• ከውጭ አገር በተገኘው ገቢ ላይ በዚህ አዋጅ መሰረት ሊከፈል የሚገባው የንግድ ስራ ገቢ ግብር የሚሰላው
የውጭ አገር ገቢ በተገኘው ግብር ላይ ተፈጻሚ የሚሆነውን የንግድ ስራ ገቢ ግብር መጠኔ በመጠቀም ነው፡፡
57
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
• በዚህ አንቀጽ መሰረት በውጭ አገር የተከፈለ ግብር ሊካካስ የሚችለው፣
- ግብር ከፋዩ ሊከፈል የሚገባውን ግብር ገቢው ከተገኘበት የግብር ዓመት ቀጥሎ ባሉት
ሁለት የግብር ዓመታት ወይም ደግሞ ባለስልጣኑ በሚፈቅደው ተጨማሪ ጊዜ ውስጥ
የከፈለ እንደሆነና
- ግብር ከፋዩ በውጭ አገር ለከፈለው ግብር ከውጭ አገር የታክስ ባለስልጣን የተሰጠ ደረሰኝ
ያለው እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
• በውጭ አገር ለተከፈለ ግብር የተፈቀደ ማካካሻ ከሌሎች ማናቸውም የግብር ማካካሻዎች
አስቀድሞ ተግባራዊ መደረግ አለበት፡፡
• በአንድ የግብር ዓመት ተካክሶ ያላለቀ የውጭ አገር ግብር ወደ ሌሎች የግብር ዓመታት
አይሸጋገርም ፡፡(Loss Cary forward or Loss Cary back ward አይፈቀድም፡፡)
• የተጣራ የውጭ አገር ገቢ ነው የሚባለው፣
- በአንድ የግብር ዓመት ውስጥ ግብር ከፋዩ ካገኘው ጠቅላላ የውጭ አገር ገቢ ላይ
የሚከተሉት ተቀንሰው የሚገኘው ገቢ ነው፡፡
 የውጭ አገር ገቢውን ለማግኘት ሲባል ብቻ የተደረገ ወጪ፡
 የውጭ አገር ገቢ ራሱን የቻለ የገቢ ዓይነት ሆኖ የሚመደብ በመሆኑ የውጭ አገር
ገቢውን ለማግኘት በወጣው መጠን በዚህ አዋጅ አንቀጽ 76 መሰረት ተከፋፍሎ
የተመደበ ወጪ፡
58
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
2. የውጭ አገር የንግድ ስራ ኪሳራዎች
• ግብር ከፋዩ በውጭ አገር ያገኘውን ገቢ ለማግኘት ያወጣው ወጪ ተቀናሽ የሚደረገው በውጭ
አገር ካገኘው ገቢ ላይ ብቻ ነው፡፡
• በግብር ዓመቱ በውጭ አገር ያጋጠመውን ኪሳራ ግብር ከፋዩ ከሚቀጥለው የግብር ዓመት በተገኘ
ገቢ ላይ በማካካስ በሰንጠረዠ “ሐ” መሰረት ተቀናሽ ይደረግለታል፡፡
• በሚቀጥለው የግብር ዓመት ተቀናንሶ ያላለቀ ኪሳራ እስከሚቀጥሉት አምስት የግብር ዓመታት
ድረስ ሊሸጋገርና ሊቀናነሱ ይችላሉ፡፡ ከአምስት ዓመት በላይ የውጭ አገር ኪሳራን ማሸጋገርና
ማቀናነስ ወይም ማካካስ አይፈቀድም፡፡
• ወደሚቀጥሉት የግብር ዓመታት ማሸጋገር የሚቻለው የሁለት ግብር ዓመታት ኪሳራ ብቻ ነው፡፡
• የውጭ አገር ኪሳራ ስለሚሸጋገርበት ዝርዝር ሁኔታ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ያወጣል፡፡
/410/2009 አ.42/
• በውጭ አገር የደረሰ ኪሳራ የሚባለው በሰነጠረዥ “ሐ” መሰረት ግብር የሚከፈልበት የውጭ አገር
ገቢ ለማግኘት ግብር ከፋዩ ያወጣቸው ወጪዎች መጠን ከጠቅላላው የውጭ አገር ገቢ በልጦ
ሲገኝ ነው፡፡
59
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
3. ለኩባንያ ካፒታል የሚወሰድ ብድር (Thin capitalization) /47/
• በውጭ አገር ባለአክሲዮኖች ቁጥጥር ስር ያለና በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ኩባንያ የግብር ዓመቱ
አማካይ ዕዳ ከአማካይ የካፒታል መዋጮው ጋር ሲነጻጸር ከ2ለ1 ሬሽዮ የበለጠ እንደሆነ ኩባንያው
ከዚህ ሬሽዮ በላይ በሆነው ዕዳ የከፈለው የወለድ ክፍያ ወጪ አይቀነስለትም፡፡
• ሆኖም በውጭ ባለአክሲዮኖች ቁጥጥር ስር ያለው ኢትዮጵያዊ ኩባንያ አማካይ ዕዳ እና አማካይ
የካፒታል መዋጮ ከ2ለ1 ሬሽዮ ቢበልጥም የኩባንያው የግብር ዓመቱ አማካይ ዕዳ ግንኙነት
ከሌላቸው ሰዎች ከተወሰደው ዕዳ የማይበልጥ ከሆነ ከላይ የተመለከተው ገደብ ተፈጻሚ
አይሆንም፡፡
• ከላይ የተመለከቱት በኢትዮጵያ በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት ባለው የኢትዮጵያ ነዋሪ ባልሆነ ሰው
ላይም ተፈጻሚ የሚሆኑ ሲሆን በዚህ ጊዜ፡-
- ኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት በውጭ አገር ባለአክሲዮኖች ቁጥጥር ስር እንዳለ
ኩባንያ ሆኖ ይቆጠራል፡
- በቋሚነት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራው ድርጅት አማካይ ዕዳና አማካይ የካፒታል መዋጮ
የሚሰላው፡-
60
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
 በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ኩባንያ በቋሚነት ለሚሰራ ድርጅት ለማዋል የወሰደው ብድር፣ እና
 በኢትዮጰያ ነዋሪ ያልሆነው ኩባንያ በቋሚነት ለሚሰራው ድርጅት መንቀሳቀሻ የመደበው ወይም
ያዋለው የካፒታል መዋጮ ከግምት ውስጥ ገብቶ ነው፡፡
• “ግንኙነት ከሌላቸው ሰዎች የተወሰደ ዕዳ” ማለት በውጭ አገር ባለአክሲዮኖች ቁጥጥር ስር
የሚገኘውን ኢትዮጰያዊ ኩባንያ በሚመለከት አንድ የፋይናንሰ ተቋም ኩባንያው የሚገኝበትን
ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ግንኙነት በሌላቸው ሰዎች መካከል በሚደረግ ግብይት ዓይነት
ሊያበድረው የሚችል ገንዘብ ነው፡፡
• ለምሳሌ አንድ መቶ ሚሊዮን ካፒታል ያለውንና በኢትዮጵያ የሚገኘውን ኩባንያ 50% የአክሲዮን
ባለቤትነት የተቆጣጠረ የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ የውጭ ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ኩባንያ ሦስት
መቶ ሚሊዮን ዶላር በወለድ ቢያበድረው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ተበዳሪ ኩባንያ በብድር በተሰጠው
ሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር ላይ የከፈለውን ወለድ ተቀናሽ ማድረግ የሚችል ሲሆን በቀሪው አንድ መቶ
ሚሊዮን ዶላረ ላይ የከፈለው ወለድ ግን ተቀናሽ ሊደረግለት አይችልም፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው
ኩባንያ ይህን ብድር ግንኙነት ከሌለው የፋይናንሰ ተቋም መበደር የሚችል መሆኑን ማስረዳት ከቻለ
በብድሩ ላይ የከፈለው ወለድ በሙሉ ሊቀነስለት ይችላል፡፡
61
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
4. ግብርን በሚመለከት የሚደረጉ ስምምነቶች (tax treaties) /48/
• ግብርን የሚመለከቱ ስምምነቶች ከውጭ አገር መንግስት ወይም መንግስታት ጋር የሚደረጉት
በሚኒስቴሩ ነው፡፡
• የሚከተሉትን ሳይጨምር በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጻሚነት ባለው የግብር ስምምነት የውል
ቃላትና በዚህ አዋጅ መካከል አለመጣጣም የተፈጠረ እንደሆነ የስምምነቱ ድንጋጌ ተፈጻሚነት
ይኖረዋል፡፡
- በተዋዋይ አገር ነዋሪ ያልሆነ ሰው ከ50% በላይ ባለቤት የሆነበት ድርጅት የታክስ ነጻ መብትን
በሚያሰጥና የግብር ማስከፈያ መጣኔ ቅነሳን በሚያስከትል የግብር ስምምነት ተጠቃሚ
ሊሆን አይችልም የሚለውን ንዑስ አንቀጽ 3 ሳይጨምር፡፡
- ከግብር ለመሸሽ የሚደረግን ጥረት ስለመከላከል የሚደነግገውን ክፍል ስምንት ሳይጨምር፡፡
• በተዋዋይ አገር ነዋሪ ባልሆነና ከ50% በላይ የአክሲዮን ባለቤትነት ባለው ሰው ቁጥጥር ስር ያለ
ድርጀት ቢሆንም የሚከተሉት ሁኔታዎች ከተሟሉ በታክስ ስምምነቱ ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡-
62
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
- የተዋዋይ አገር ነዋሪ ባልሆነ ሰው ከ50% በላይ በባለቤትነት የተያዘው ድርጀት በተዋዋዩ
አገር የአክሲዮን ገበያ ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ኩባንያ ከሆነ ወይም፣
- በተዋዋዩ አገር በሚገባ የሚንቀሳቀስ የንግድ ስራ ላይ የተሰማራ እንደሆነና በኢትዮጵያ
ለተገኘው ገቢ ምንጭ የሆነው ይኽው የንግድ ስራ የሆነ እንደሆነ፡፡
• “በሚገባ የሚንቀሳቀስ የንግድ ስራ” የሚለው ቃል ኩባንያው የገንዘብ ተቋም ወይም
የኢንሹራንስ ኩባንያ ካልሆነ በስተቀር የአክሲዮን፣ የዋስትና ሰነዶች ወይም የሌሎች
ኢቨስትመንቶች ባለቤት መሆንን ወይም ማስተዳደርን አይጨምርም፡፡
• “የግብር ስምምነት” ማለት ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረትና ታክስ ላለመክፈል የሚደረግን
የግብር ስወራ (Tax Evasion) ለመከላከል የሚደረግ ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው፡፡
63
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
ክፍል ስምንት
የሰንጠረዥ “መ” ገቢ ግብር (ሌሎች ገቢዎች) /51-64/
1. በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች ገቢ
• በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያገኘው፡-
- የትርፍ ድርሻ ገቢ ላይ 10%
- የወለድ ገቢ ላይ 10%
- የሮያልቲ ገቢ ላይ 5%
- የስራ አመራር ክፍያ ላይ 15%
- የቴክኒክ አገልግሎት ክፍያ ላይ 15%
- የመድን አርቦን ላይ 5% ግብር ይከፍላል፡፡
• በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ከላይ የተገለጹትን ገቢዎች ያገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት የሚሰራ
ድርጀት ከሚያናውነው የንግድ ስራ የሆነ እንደሆነ ተፈጻሚ የሚሆነው በሰንጠረዥ “ሐ” የተመለከተው
የንግድ ትርፍ ግብር ወይም እንደሁኔታው በሰንጠረዥ ”መ” የተመለከቱት ሌሎች መጣኔዎች ናቸው፡፡
64
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
2. በሚተካ የቴክኒክ አገልግሎት ክፍያና ሮያልቲ ላይ ስለሚከፈል ግብር
• በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት ሳይሆን በራሱ የቴክኒክ
አገልግሎት ወይም የመሳሪያ ኪራይ (ሊዝ) አገልግሎት
- ከኢትዮጵያ ውጪ ያለውን በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት ሳይጨምር የኢትዮጰያ ነዋሪ ለሆነ ሰው
ወይም ኢትዮጰያ ውስጥ በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት የኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆነ ሰው
የሰጠ እንደሆነ እና
- የቴክኒክ አገልግሎቱ ወይም የሮያልቲ ክፍያ የተከፈለው ከአገልግሎት ተቀባዩ ጋር ግንኙነት ባለው
የኢትዮጵያ ነዋሪ ባልሆነ ሰው ከሆነ፣ እንዲሁም
- ክፍያውን የፈጸመው ከአገልግሎት ተቀባዩ ጋር ግንኙነት ያለው ሰው የቴክኒክ አገልግሎት ወይም
የሮያልቲ ክፍያውን ከአገልግሎት ተቀባዩ መልሶ የጠየቀ እንደሆነ፣
ግንኙነት ያለው ሰው ለአገልግሎት ተቀባዩ የቴክኒክ አገልግሎቱን ወይም የመሳሪያውን ሊዝ አገልገሎት
እንደሰጠና የተተካው ገንዘብ ለቴክኒክ አገልግሎቱ ወይም ለማሳሪያው ሊዝ የተከፈለ ክፍያ እንደሆነ
ተቆጥሮ የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
65
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
ለምሳሌ፡- የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ የእንግሊዝ ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ
ለሚኖር ኩባንያ የቴክኒክ አገልግሎት ቢሰጥና የአገልግሎት ዋጋውን
ጣሊያን አገር ከሚገኘውና በኢትዮትያ ኩባንያ ውስጥ 60% የአክሲዮን
ድርሻ ካለው ነዋሪ ያልሆነ ኩባንያ ቢቀበል የጣሊያኑ ኩባንያ የአገልግሎት
ዋጋውን የኢትዮጵያው ኩባንያ እንዲተካለት በሚጠይቅበት ጊዜ
የጣሊያኑ ኩባንያ ለኢትዮጰያ ኩባንያ አገልግሎቱን ራሱ እንደሰጠ
ተቆጥሮ ግብሩ ከክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረግበታል ማለት ነው፡፡
66
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
3. በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ የመዝናኛ አገልግሎት ሰጪዎች ግብር
• በኢትዮጵያ ውስጥ የመዝናኛ አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ወይም
ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ባገኘው ጠቅላላ ገቢው ላይ 10% ግብር ይከፍላል፡፡
• ከመዝናኛ አገልግሎቱ በሚገኘው ገቢ ተጠቃሚው አዝናኙ ሳይሆን ሌላ ሰው የሆነ እንደሆነ
ይህ ሰው በሚያገኘው ጠቅላላ ገቢ ላይ ከላይ የተጠቀሰውን ግብር ይከፍላል፡፡
4. ሮያልቲ
• በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው ሮያልቲ ያገኘ እንደሆነ በጠቅላላው የሮያልቲ ክፍያ ላይ 5%
ግብር ይከፍላል፡፡
• የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት
አማካኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ የሮያልቲ ገቢ ያገኘ እንደሆነ በጠቅላላ የሮያልቲ ክፍያው ላይ
ከላይ የተመለከተውን ግብር ይከፍላል፡፡
67
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
5. የትርፍ ድርሻ
• በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው የትርፍ ድርሻ ያገኘ እንደሆነ በጠቅላላው የትርፍ ድርሻ ገቢ ላይ
10% የገቢ ግብር ይከፍላል፡፡
• በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት
አማካኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ የትርፍ ድርሻ ገቢ ያገኘ እንደሆነ በጠቅላላ የትርፍ ድርሻው
ላይ 10% ገቢ ግብር ይከፍላል፡፡ /ሲልክ/
6. ወለድ
• በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው በገንዘብ ተቋማት ገንዘቡን በቁጠባ አስቀምጦ በሚያገኘው
ጠቅላላ ወለድ ላይ 5% ግብር ይከፍላል፡፡
• በሌላ በማናቸውም ሁኔታ በሚያገኘው ጠቅላላ ወለድ ላይ 10% ግብር ይከፍላል፡፡
• ከላይ የተመለከቱት የግብር መጣኔዎች በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ
በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት በሁለቱ ሁኔታዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ባገኘው ወለድ
ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
68
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
7. ከዕድል ሙከራ የሚገኝ ገቢ
• በኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረጉ የዕድል ሙከራዎች ተሳትፎ ገቢ ያገኘ ሰው ባሸነፈው
ጠቅላላ ገቢ ላይ 15% የገቢ ግብር ይከፍላል፡፡
• ግብር ከፋዩ የዕድል ሙከራውን ሲያደርግ የደረሰበት ኪሳራ ቢኖር ተቀናሽ
አይደረግም፡፡
• በዕድል ሙከራ የተገኘው ገንዘብ ከ1000 ብር በታች ከሆነ ግብር አይከፈልበትም፡፡
8. ሃብትን አልፎ አልፎ በማከራየት የሚገኝ ገቢ
• በኢትዮጵያ ውስጥ አልፎ አልፎ ሃብት (መሬት፣ቤት፣ የሚንቀሳቀስ ሃብት) በማከራየት
በሚገኝ ጠቅላላ ገቢ ላይ 15% ገቢ ግብር ይከፈላል፡፡
• የሮያልቲ ግብር በሚከፈልበት ሃብት ላይ ይህ ግብር ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
69
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
9. የካፒታል ሃብቶችን በማስተላፍ ከሚገኝ ጥቅም የሚከፈል ግብር
• የማይንቀሳቀስ የካፒታል ሃብት በማስተላለፍ በሚገኝ ጥቅም ላይ 15% የካፒታል ዋጋ
ዕድገት ግብር ይከፈላል፡፡
• አክሲዮን ወይም ቦንድ በማስተላለፍ በሚገኝ ጥቅም ላይ 30% የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር
ይከፈላል፡፡
• ግብር የሚከፈልበትን ሃብት በማስተላለፍ የሚገኘው ጥቅም ሃብቱን በማስተላለፍ
የተገኘው ዋጋ ሃብቱ በተላለፈበት ጊዜ ከነበረው ዋጋ በልጦ የተገኘው የገንዘብ መጠን ነው፡፡
• በግብር አመቱ ውስጥ ግብር የሚከፈልበትን ሃብት በማስተላለፍ የሚደርስ ኪሳራ በዚያው
የግብር ዓመት ተመሳሳይ ሃብት በማስተላለፍ ከተገኘው ገቢ ጋር ብቻ እንዲቻቻል
ይደረጋል፡፡ ኪሳራው ከሌላ ገቢ ጋር አይካካስም፡፡
• በዚህ ሁኔታ ያልተካካሰ ኪሳራ ላልተወሰነ ጊዜ ይሸጋገራል፡፡
70
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
• ግንኙነት ባላቸው ሰዎች መካከል በተደረገ የካፒታል ሃብት ማስተላለፍ የሚደርስ ኪሳራ
አይካካስም፡፡
• የካፒታል ሃብትን በማስተላለፍ የሚደርስ ኪሳራ ሊካካስ የሚችለው ግብር ከፋዩ የደረሰበትን
ኪሳራ ባለስልጣኑን በሚያሳምን መንገድ ማስረዳት የቻለ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
• ግብር የሚከፈልበትን የካፒታል ሃብት በማስተላለፍ ደረሰ የሚባለው ኪሳራ ሃብቱ
በተላለፈበት ጊዜ ለሃብቱ የወጣው ወጪ ሃብቱ ከተላለፈበት ዋጋ በልጦ የተገኘው ዋጋ ነው፡፡
• የተላለፈው ሃብት የንግድ ስራ ሃብት ሲሆን አንቀጽ 35 ተፈጻሚ ይሆናል (በተጣራ መዝገብ
ዋጋውና ለሃብቱ በወጣው ወጪ መካከል ያለው ልዩነት ወደ ንግድ ስራ ገቢ ተወስዶ
ይደመራል፡፡)
71
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
10. ንፋስ አመጣሽ ትርፍ
• ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ ከተመለከቱት የንግድ ስራዎች በሚገኝ ንፋስ አመጣሽ ትርፍ
ላይ በመመሪያው በተመለከተው የማስከፈያ መጣኔ (ልክ) ግብር ይከፈልበታል፡፡
• ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ፡-
- ነፋስ አመጣሽ ትርፍ ነው ሊባል የሚችለውን የገቢ መጠን፡፡
- ግብሩ የሚመለከታቸውን የንግድ ስራዎች አይነት፡፡
- ግብሩን ለማስከፈል የወጣው መመሪያ ስራ ላይ የሚውልበትን ቀን፡፡
- የግብር አወሳሰኑን ዘዴና ለግብሩ አወሳሰን መሰረት የሚሆኑ ታሳቢዎችን ይወሰናል (እንዲወስን
ስልጣን ተሰጥቶታል)፡፡
• ለተለያዩ የንግድ ስራዎች የሚወሰነው የነፋስ አመጣሽ ትርፍ መጠንና የግብር ማስከፈያ
መጣኔውም የተለያየ እንዲሆን ሚኒስትሩ ሊወሰን ይችላል፡፡
• “ንፋስ አመጣሽ ትርፍ” ያለልፋት (ያለጥረት፣ ያለተጨማሪ ወጪ ወዘተ) የሚገኝ ያልተጠበቀ
ወይም ሌላ ተደጋግሞ የማይገኝ ትርፍ ነው፡፡
72
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
11. ያልተከፋፈለ ትርፍ
• በአንድ የግብር ዓመት ግብር ከተከፈለ በኋላ ለአባላቱ ያልተከፈለ እና መልሶ ኢንቨስት
ያልተደረገ የተጣራ የድርጅት ትርፍ 10% ግብር ይከፈልበታል፡፡
12. በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት ወደ ውጭ የሚላክ ትርፍ
• በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት በሚሰራ ድርጀት አማካኝነት የንግድ ስራ የሚያከናውን
በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው በቋሚነት ከሚሰራ ድርጅት
በሚላክለት ትርፍ ላይ 10% ግብር ይከፈልበታል፡፡
• አፈጻሙ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ የሚወሰን ይሆናል፡፡
13. ሌሎች ገቢዎች
• በሰንጠረዥ “ሀ” ፣ “ለ”፣ “ሐ” እና በሰንጠረዠ “መ” ሌሎች ድንጋጌዎች የማይሸፈን ገቢ
ያገኘ ማንኛውም ሰው በጠቅላላ ገቢው ላይ 15% ግብር ይከፍላል፡፡
73
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
14. ለሰንጠረዥ “መ” የሚያገለግሉ የወል ድንጋጌዎች
• በሰንጠረዥ “መ” መሰረት የሚጣል ግብር በሌሎች ሰንጠረዦች ግብር በሚከፈልበት ገቢ
ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
• የሰንጠረዥ “መ” ግብር የመጨረሻ ግብር ነው፡፡
• አብዛኛው የሰንጠረዥ “መ” ግብር የሚወሰነው በጠቅላላ ገቢው ላይ ነው፡፡
• በሰንጠረዥ “መ” መሰረት ግብር የሚከፈልበት የውጭ አገር ገቢ ያገኘ ሰው በውጭ አገር
የከፈለውን ግብር እንዲያካክስ ይፈቀድለታል፡፡
• ሆኖም ተካክሶ ተቀናሽ ያልተደረገ በውጭ አገር የተከፈለ ግብር ወደኋላም ሆነ ወደፊትም
አይሸጋገርም፡፡
• ግብሩን ቀንሶ የመያዝ ኃላፊነት ያለበት ሰው ግብሩን ቀንሶ ያስቀረ እንደሆነ የሰንጠረዥ “መ”
ግብር ከፋይ ግብሩን እንደከፈለ ይቆጠራል፡፡
74
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
ክፍል ዘጠኝ /ይህን ክፍል በማንበብ አዳብሩ/
የወል ድንጋጌዎች /66-77/
ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት የወል (common) ድንጋጌዎች ለሁሉም የግብር ሰንጠረዦችና የግብር
ዓይነቶች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡
1. ሃብት ስለማግኘት (66)
• አንድ ሰው ሃብት አገኘ (የሃብት ባለቤት ሆነ) የሚባለው የሃብቱ ባለቤትነት(ownersip
tittle) በስሙ ከተላለፈበት ወይም በስሙ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡
• ሃብቱ መብት ወይም ምርጫ በሚሆንበት ጊዜ ሃብቱ ተላለፈ የሚባለው መብቱ ወይም
ምርጫው በተሰጠበት ቀን ነው፡፡
2. ሃብት ስለማስተላለፍ (67)
• አንድ ሰው ሃብቱን አስተላለፈ የሚባለው ሃብቱን ሲሸጥ ሲለውጥ ወይም በሌላ
ማናቸውም መንገድ በሃብቱ ላይ ያለውን የባለቤትነት መብት ሲያስተላልፍ ነው፡፡
• አንድ ሰው፡-
- በሃብቱ ላይ ያለው ባለቤትነት ከመዝገብ እንዲሰረዝ ካደረገ፣
- ሃብቱን ለቀድሞው ባለቤቱ እንዲመለስ ካደረገ፣
- ሃብቱ ከጠፋ ወይም ከወደመ፣
75
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
- የመብት መጠቀሚያ ጊዜው እንዲያልፍ ካደረገ፣
- ለሌላ ሰው ሃብቱን ከሰጠ ወይም እንዲሰጥ ካደረገ፣
- ሃብቱን አስተላለፈ ማለት ይሆናል፡፡
• አንድ ሰው ሌላን ሰው አስቀድሞ ያልነበረውን ሃብት እንዲኖረው ያደረገ እንደሆነ ይህን
ያደረገው ሰው ሃብቱ በተፈጠረበት ጊዜ በባለቤትነቱ ስም የነበረውን ሃብት ለሁለተኛው ሰው
እንዳስተላለፈ ይቆጠራል፡፡
• ሃብት በውርስ ወይም በኑዛዜ የተላለፈ እንደሆነ ሃብቱ በተላለፈበት ጊዜ ሟች ሃብቱን
እንዳስተላለፈ ይቆጠራል፡፡
• ሃብትን ማስተላለፍ የአንድን የንግድ ስራ ሃብት የተወሰነ ክፍል ማስተላለፍን ይጨምራል፡፡
• አንድን ሃብት ለንብረት አጣሪ፣ በኪሳራ ሂደት ለተሰየመ ባለአደራ ወይም ለተቀባይ (ለንብረት
አስተዳዳሪ) መስጠት ሃብቱን እንደተላለፈ አያስቆጥረውም ፡፡ ስለሆነም ከዚሁ ሃብት ጋር
በተያያዘ በአጣሪው፣ በባለአደራው ወይም በተቀባዩ የሚከናወኑ ተግባራት በሙሉ ባለቤቱ
እንዳከናወናቸው ይቆጠራሉ፡፡
76
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
3. ለሃብት የሚደረገ ወጪ (68)
• የአንድን ሃብት ወጪ ማወቅ የሚያስፈልገው ለእርጅና ቅናሽ መሰረት የሚሆነውን ወጪ
ለመወሰንና ሃብቱ ሲተላለፍ የሚገኘውን ጥቅም ወይም የኪሳራ መጠን ለመወሰን
እንዲቻል ነው፡፡
• የአንድ ዋጋው የሚቀንስ ሃብት (depreciable asset) ወጪ የሚከተሉት ድምር ይሆናል፡፡
- ሃብቱ በተገኘበት ጊዜ በዓይነት የተሰጠ ሃብት ትክክለኛ የገበያ ዋጋን ጨምሮ ባለሃብቱ
ለሃብቱ የከፈለው ጠቅላላ ዋጋ፣
- ሃብቱ የተገኘው በመገንባት፣ በማምረት ወይም በማልማት የሆነ እንደሆነ
ለግንባታ፣ ለማምረት ወይም ለማልማት የወጣው ወጪ፣
- ሃብቱን በማግኘት ወይም በማስተላለፍ ሂደት የወጣ ማንኛውም ወጪ፣
- ሃብቱን ለመትከል፣ ለመቀየር፣ ለማደስ፣ መልሶ ለመገንባት ወይም ለማሻሻል
ባለሃብቱ ያወጣው ማንኛውም ወጪ፡፡
77
23/02/2015 E.C
Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx
Training doc on income tax proc for Risk  employees.pptx

More Related Content

What's hot

BE Chapter 10 : Inflation And Unemployment
BE Chapter 10 : Inflation And UnemploymentBE Chapter 10 : Inflation And Unemployment
BE Chapter 10 : Inflation And UnemploymentPeleZain
 
Fiscal policy updated
Fiscal policy updatedFiscal policy updated
Fiscal policy updatedMj Payal
 
Understanding Goods and Services Tax (GST) India
Understanding Goods and Services Tax (GST) IndiaUnderstanding Goods and Services Tax (GST) India
Understanding Goods and Services Tax (GST) IndiaAcTouch Technologies
 
Overview of Model GST Law
Overview of Model GST LawOverview of Model GST Law
Overview of Model GST LawCA Mohit Singhal
 
Econ606 chapter 29 2020
Econ606 chapter 29 2020Econ606 chapter 29 2020
Econ606 chapter 29 2020sakanor
 
Scrutiny of returns in GST
Scrutiny of returns in GSTScrutiny of returns in GST
Scrutiny of returns in GSTCA PRADEEP GOYAL
 
Fiscal policy
Fiscal policyFiscal policy
Fiscal policyHassan Abdu
 
GST & its Rationale in India by Mohmed Amin Mir
GST   & its Rationale in India by Mohmed Amin MirGST   & its Rationale in India by Mohmed Amin Mir
GST & its Rationale in India by Mohmed Amin MirDr. Mohmed Amin Mir
 
GST TRAINING ON VARIOUS CONCEPTS OF GST
GST TRAINING ON VARIOUS CONCEPTS OF GSTGST TRAINING ON VARIOUS CONCEPTS OF GST
GST TRAINING ON VARIOUS CONCEPTS OF GSTGST Law India
 
Issues in indian economy
Issues in indian economyIssues in indian economy
Issues in indian economyPradeep Panda
 
CONFLICT OF SOURCE AND RESIDENCE PRINCIPLES OF TAXATION
CONFLICT OF SOURCE AND RESIDENCE PRINCIPLES OF TAXATIONCONFLICT OF SOURCE AND RESIDENCE PRINCIPLES OF TAXATION
CONFLICT OF SOURCE AND RESIDENCE PRINCIPLES OF TAXATIONksanu
 
The solow swan model
The solow swan modelThe solow swan model
The solow swan modelGurudayalkumar
 
Life cycle income hypothesis
Life cycle income hypothesisLife cycle income hypothesis
Life cycle income hypothesispunjab university
 
A Study of Short-run Consumption Function and its Modification with Some Spec...
A Study of Short-run Consumption Function and its Modification with Some Spec...A Study of Short-run Consumption Function and its Modification with Some Spec...
A Study of Short-run Consumption Function and its Modification with Some Spec...iosrjce
 
TAX AVOIDANCE AND TAX EVASION -DIFFERENCE AND EFFECT ON INDIAN ECONOMY
TAX AVOIDANCE AND TAX EVASION -DIFFERENCE AND EFFECT ON INDIAN ECONOMY TAX AVOIDANCE AND TAX EVASION -DIFFERENCE AND EFFECT ON INDIAN ECONOMY
TAX AVOIDANCE AND TAX EVASION -DIFFERENCE AND EFFECT ON INDIAN ECONOMY Sundar B N
 
Aula 3 macro- modelo clĂĄssico
Aula 3 macro- modelo clĂĄssicoAula 3 macro- modelo clĂĄssico
Aula 3 macro- modelo clĂĄssicoNeli Chastinet
 
Taxation in Pakistan Presentation-I.
Taxation in Pakistan Presentation-I.Taxation in Pakistan Presentation-I.
Taxation in Pakistan Presentation-I.Azfar Javed
 

What's hot (20)

Innovations in Tax Compliance
Innovations in Tax ComplianceInnovations in Tax Compliance
Innovations in Tax Compliance
 
BE Chapter 10 : Inflation And Unemployment
BE Chapter 10 : Inflation And UnemploymentBE Chapter 10 : Inflation And Unemployment
BE Chapter 10 : Inflation And Unemployment
 
Fiscal policy updated
Fiscal policy updatedFiscal policy updated
Fiscal policy updated
 
Understanding Goods and Services Tax (GST) India
Understanding Goods and Services Tax (GST) IndiaUnderstanding Goods and Services Tax (GST) India
Understanding Goods and Services Tax (GST) India
 
Contabilidade nacional
Contabilidade nacionalContabilidade nacional
Contabilidade nacional
 
Overview of Model GST Law
Overview of Model GST LawOverview of Model GST Law
Overview of Model GST Law
 
Econ606 chapter 29 2020
Econ606 chapter 29 2020Econ606 chapter 29 2020
Econ606 chapter 29 2020
 
Scrutiny of returns in GST
Scrutiny of returns in GSTScrutiny of returns in GST
Scrutiny of returns in GST
 
Fiscal policy
Fiscal policyFiscal policy
Fiscal policy
 
GST & its Rationale in India by Mohmed Amin Mir
GST   & its Rationale in India by Mohmed Amin MirGST   & its Rationale in India by Mohmed Amin Mir
GST & its Rationale in India by Mohmed Amin Mir
 
GST TRAINING ON VARIOUS CONCEPTS OF GST
GST TRAINING ON VARIOUS CONCEPTS OF GSTGST TRAINING ON VARIOUS CONCEPTS OF GST
GST TRAINING ON VARIOUS CONCEPTS OF GST
 
Issues in indian economy
Issues in indian economyIssues in indian economy
Issues in indian economy
 
CONFLICT OF SOURCE AND RESIDENCE PRINCIPLES OF TAXATION
CONFLICT OF SOURCE AND RESIDENCE PRINCIPLES OF TAXATIONCONFLICT OF SOURCE AND RESIDENCE PRINCIPLES OF TAXATION
CONFLICT OF SOURCE AND RESIDENCE PRINCIPLES OF TAXATION
 
The solow swan model
The solow swan modelThe solow swan model
The solow swan model
 
Life cycle income hypothesis
Life cycle income hypothesisLife cycle income hypothesis
Life cycle income hypothesis
 
A Study of Short-run Consumption Function and its Modification with Some Spec...
A Study of Short-run Consumption Function and its Modification with Some Spec...A Study of Short-run Consumption Function and its Modification with Some Spec...
A Study of Short-run Consumption Function and its Modification with Some Spec...
 
TAX AVOIDANCE AND TAX EVASION -DIFFERENCE AND EFFECT ON INDIAN ECONOMY
TAX AVOIDANCE AND TAX EVASION -DIFFERENCE AND EFFECT ON INDIAN ECONOMY TAX AVOIDANCE AND TAX EVASION -DIFFERENCE AND EFFECT ON INDIAN ECONOMY
TAX AVOIDANCE AND TAX EVASION -DIFFERENCE AND EFFECT ON INDIAN ECONOMY
 
Aula 3 macro- modelo clĂĄssico
Aula 3 macro- modelo clĂĄssicoAula 3 macro- modelo clĂĄssico
Aula 3 macro- modelo clĂĄssico
 
Taxation in Pakistan Presentation-I.
Taxation in Pakistan Presentation-I.Taxation in Pakistan Presentation-I.
Taxation in Pakistan Presentation-I.
 
Aula de introdução à economia
Aula de introdução à economiaAula de introdução à economia
Aula de introdução à economia
 

Training doc on income tax proc for Risk employees.pptx

  • 1. 1 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 2. የሥልጠናው ይዘት ክፍል አንድ - ጠቅላላ መረጃ ክፍል ሁለት - የአዋጁ ጠቅላላ ክፍል ክፍል ሦስት - ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ “ሀ”) ክፍል አራት - የቤት ኪራይ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ “ለ”) ክፍል አምስት - ግብር የሚከፈልበት የንግድ ሼል ገቢ፣ተቀናሽ የሚደረጉና የማይደረጉ ወጪዎች ክፍል ስድስት - የማዕድንና የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር ክፍል ሰባት - ዓለም አቀፍ ግብር ክፍል ስምንት - የሰንጠረዥ “መ” ገቢ ግብር ክፍል ዘጠኝ - የወል ድንጋጌዎች /በማንበብ የምታዳብሩት/ ክፍል አስር- ከግብር ለመሸሽ የሚደረገውን ጥረት ስለመከላከል ክፍል አስራአንድ - አስተዳደራዊና የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች ክፍል አስራሁለት - ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብርን ቀንሶ ስለማስቀረት ክፍል አስራሦስት - የመመርመር ሥልጣን (Power of Investigation) ክፍል አሥራ አራት - የግብር ከፋዮች ግዴታና ህጋዊ ውጤቱ /በማንበብ የምታዳብሩት/ 2 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 3. ክፍል አንድ አጠቃላይ መረጃ ሀ/ መግቢያ ሀ.1. የሥልጠናው ዓላማ የሥልጠናው ዓላማዎች ጠቅለል ባለመልኩ ሲገለጽ የሚከተሉትን ዓላማዎች ለማሳካት ነው፡-  በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ውስጥ የተጨመሩ ወይም የተካተቱ አዳዲስ ድንጋጌዎችን እና ሐሳቦችን ግንዛቤ ለማስያዝ፤  በአጠቃላይ በታክስ ህጉ ላይ ግንዛቤ እንዲፈጠር በማድረግ ህጉ የሚመለከታቸው ሁሉ የሚጠበቅባቸውን ግዴታና ኃላፊነት ተረድተው ግዴታቸውንና ኃላፊነታቸውን በቀላሉ እንዲወጡ ለማስቻልና በህግ ላይ የተመሰረተ ፍትሐዊ አገልግሎትና ምላሽ በመስጠት የተሻለ የታክስ ህግ ተገዢነት እንዲመጣ ለማስቻል ነው፤ 3 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 4.  የታክስ አዋጆች በየጊዜው ያለውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሁኔታ መሠረት በማድረግ የሚሻሻሉ ወይም አዳዲስ የታክስ አይነቶች በህግ ተደንግግው የሚወጡ ሲሆን  በፌደራል ገቢ ሰብሳቢ አካላት የሚጠቀምባቸዉ የግብርና ታክስ አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች አሉ ዋና ዋናዎቹ፡- (464 ተለይተው በስራ ላይ ያሉት ወደ 242ቱ በ6የተለያየ ርእስ ባላቸው መጽሐፍቶች ታትመዋል)  የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994፣ ማሻሻያ 608/2001 እና 693/2003  የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 78/1994 እና ማሻሻያ ቁጥር 164/2001  የማዕድን ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 53/1985 እና ማሻሻያ 678/2002 እና 802/2005  የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 እና ደንብ ቁጥር 410/2009፣  የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ 285/1994፣ ማሻሻያ 609/2001 እና 1157/2011  የተጨማሪ እሴት ታክስ ደንብ 79/1995  የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ 308/1995 እና ማሻሻያ 611/2001  የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ 307/1995 ማሻሻያ 570/2000 610/2001፣ እና 1186/2012  የቴምብር ቀረጥ አዋጅ 110/1990  ለሁሉም የታክስ አይነቶች አስተዳደራዊ ጉዳዮች ተፈጻሚ የሚደረግ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 እና ደንብ ቁጥር 407/2009  የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ደንብ ቁጥር 154/2000  ከግብርና ቀረጥ አዋጆች ጋር የተያያዙ ሌሎች አዋጆች  የኅብረት ሼል ማኅበራት ማደራጃ አዋጅ  የማእድን ሾል አዋጅ  አነስተኛ የፋይናንስ ሼል አዋጅ ቁጥር  የውጪ ንግድ ቀረጥ ማበረታቻ አዋጁ ቁጥር  የኢንቨስትመንት አዋጅ  የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ እና ሌሎች 4 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 5. ለ/ አጠቃላይ ጽንሰ ሐሳቦች 1. የታክስ ሥርዓት ምንነት 2. የታክስ ሥርዓት ዓይነቶች 5 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 6. ለ.1- የታክስ ሥርዓት ምንነት የታክስ ሥርዓት የምንለው በጠባቡ ሲታይ የታክስ አጣጣሉን፣ የታክስ ህጉን አወቃቀርና ቅርጽ የሚገልጽ ሲሆን በሰፊው ሲታይ ግን የታክስ ህጉንና ይህን የታክስ ህግ መሠረት በማድረግ በየደረጃው የሚወጡ መመሪያዎችና የአሠራር ሥርዓቶች በታክስ ባለሥልጣኑ የሚዘረጉ የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ፣ የኦዲት ሥርዓቱንና የመረጃ አስተዳደር ሥርዓቱን ጨምሮ የአገልግሎት አሰጣጡንና የቅሬት አፈታት ሥርዓቱን በማጠቃለል “የታክስ አስተዳደር ሥርዓት” ብለን የምንጠራውን አስተዳደራዊ ሥርዓት የሚወክል መሠረታዊ ጽንሰ ሐሳብ ነው፡፡ 6 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 7. ለ.2- የታክስ ሥርዓት ዓይነቶች/Types of Taxing System/ • በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት የታክስ ሥርዓቶች ያሉ ሲሆን እነዚህም፡-  ግሎባል (aggregated) የታክስ ሥርዓት  ስኬጁላር (disaggregated) የታክስ ሥርዓት ተብለው የሚታወቁ ናቸው፡፡ • ግሎባል የታክስ ሥርዓት ግብር ከፋዩ የሚያገኘውን ማንኛውንም ዓይነት ገቢ በአንድ ላይ በመደመር በአንድ የግብር ማስከፈያ ምጣኔ ግብር እንዲከፍል የሚደረግበት ሥርዓት ሲሆን በዚህ ሥርዓትም ውስጥ ቢሆን የስኬጁላር ታክስ ሥርዓት የሚመስሉ ሁኔታዎች የሚታዩበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ • ስኬጁላር የታክስ ሥርዓት የሚባለው አንድ ግብር ከፋይ የሚያገኛቸውን ገቢዎች እንደየገቢው ዓይነት በመከፋፈል ወይም በመመደብ ለእያንዳንዱ የገቢ ዓይነት በስኬጁል የተቀመጡ የግብር ማስከፈያ ምጣኔዎችን በመጠቀም የተለያየ ግብር በመወሰን የተለያዩ የህግ መርሆዎችንና መሪ ድንጋጌዎች ተጠቅሞ ታክሱን የሚሰበስብበት ሥርዓት ነው፡፡ 7 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 8. የታክስ ሥርዓት… ሁለቱም የታክስ ሥርዓቶች የየራሳቸው የሆነ ደካማና ጠንካራ ጐን አሏቸው፡- • ግሎባል የታክስ ሥርዓት የታክስ መሠረቱ እንዳይሸረሸር ወይም base erosion በማስወገድ የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ የሚጠቅም መሆኑ ቢነገርለትም የታክስ አስተዳደሩን ስለሚያከብደውና ስለሚያወሳስበው ብዙዎች አይመርጡትም፡፡ • የስኬጁላር ታክስ ሥርዓት የተለያየ ገቢ የሚያገኙ ግብር ከፋዮች በተለያየ ስኬጁል ሲስተናገዱ ከግብር ነፃ በሆነው የገቢ መጠን (exempted threshold) እና በአነስተኛ የታክስ ብራኬት ደጋግመው ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉበትን ዕድል ስለሚፈጥር ለኢፍትሃዊነትና ለገቢ መንጠባጠብ ወይም ለታክስ መሠረት መሸርሸር የሚያጋልጥ ሲሆን የታክስ አስተዳደሩን ቀላልና ግልጽ በማድረግና ግብር ከፋዩ ሣይሰማው ግብሩን እንዲከፍል እንዲሁም ወጪን በመቆጠብ ረገድ ግን ተመራጭነት አለው፡፡ • የኢትዮጵያ የታክስ ሥርዓት ሁለተኛውን ዓይነት የታክስ ሥርዓት የሚከተል ነው፡፡ 8 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 9. የታክስ ወሰን • የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ለፌደራል መንግስት በህገ መንግስቱ በተሰጠው ታክስና ግብር የመጣልና የማስከፈል ሥልጣን መሠረት በሁለት መሠረታዊ የታክስ አጣጣል ወሰኖች ላይ ተመስርቶ የታክስ ህግ ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል፡፡ - ነዋሪነትን መሠረት በማድረግ፣ - የገቢ ምንጭን መሠረት በማድረግ፣ • እነዚህን ሁለት መሠረታዊ መመዘኛዎች መሠረት በማድረግ የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ፡- - የኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች በዓለም ዙሪያ በሚያገኙት ገቢ ላይ - የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች የኢትዮጵያ ከሆነ ምንጭ ባገኙት ገቢ ላይ ግብር ይጥላል፣ አከፋፈሉን፣ አወሳሰኑንና አሰባሰቡን አስቀምጧል፡፡ 9 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 10. ክፍል ሁለት - የአዋጁ ጠቅላላ ክፍል መግቢያ ፡- የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 የነበሩ ክፍተቶች የቀድሞው የገቢ ግብር አዋጅ የሚከተሉት ክፍተቶች ነበሩበት፡- • የታክስ ሠንጠረዦቹ ለገቢ ከተሰጠው ትርጉም እና እኩል የገቢ ሽፋን (coextensive coverage of income or source of income) ያልነበራቸው ስለሆነ በታክስ መረቡ ውስጥ ያልገቡ በርካታ የገቢ ዓይነቶች ነበሩ፡፡ በህጉ ክፍተት ምክንያትም የማይሰበሰብ ገቢ ነበር፡ • በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያገኙት ገቢ ላይ ግብር መክፈል እንዳለባቸው በቀድሞው አዋጅ አንቀጽ 3(2) የተመለከተ ቢሆንም አዋጁ በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያገኙት ገቢ ላይ በምን ያህል ምጣኔ ግብር እንደሚከፍሉና እንዲሁም የገቢ ምንጮችንና ዓይነቶችን ለይቶ የዊዝሆልዲንግ ክፍያ ሥርዓትንም ያላካተተ ስለነበረ በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች ወይም ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያገኙት ገቢ ላይ ግብር እየከፈሉ አልነበረም፡ • የቀድሞው አዋጅ መሠረታዊ የታክስ ህጉንና የታክስ አስተዳደር ህጉን አቀላቅሎ የያዘ ስለነበረና በተለያዩ የታክስ ህጐች ውስጥ ተመሣሣይ ድንጋጌዎች የተለያየ አገላለጽ እየተጠቀሙ ለአፈፃፀም አስቸጋሪ ሁኔታ ይፈጥሩ ነበር፡ . በቀድሞው አዋጅ የተከራይ አከራዮች ወጪያቸው ተቀናሽ የሚደረግበት የህግ አግባብ አልነበረም፡፡ ህጉ አከራዮችን ብቻ ታሳቢ ያደርግ ስለነበር፡ 10 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 11. • በቀድሞው አዋጅ መሠረት የግብር ባለሥልጣኑ የአንድን ግብር ከፋይ ግብይት ውድቅ አድርጐ የዕቃ ዋጋ በተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ የሚተምንበት ግልጽ ሥልጣን ስለማይሰጥ በተለይ ከንግድ ሼል ሃብት (Asset) ግብይት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ችግር ያጋጥም ነበር፡ (በታክስ አስተዳደር አዋጁ ውስጥ የተካተተ)፡ • የማዕድንና ፔትሮሊየም አዋጆች ከገቢ ግብር አዋጁ ተነጥለው በሌሎች አዋጆች የታወጁ ስለነበረ የታክስ አዋጆቹና የገቢ ግብር አዋጁ ድንጋጌዎች ለማዕድንና ለፔትሮሊየም ገቢ ግብር አወሳሰንና አስተዳደር ተፈፃሚ ለማድረግ አስቸጋሪ የሚሆንበት ሁኔታ ነበር፡፡ • የቀድሞው አዋጅ ኪሣራ ማሸጋገርን በሚመለከት ያስቀመጠው ድንጋጌ ግልጽነት የጐደለው ስለነበረ በአፈፃፀም ሲያወዛግብ የነበረበት ሁኔታ ነበር ፡ • አዲስ ቤት (ህንፃ) የሚገነቡ ግብር ከፋዮች ያልተጠናቀቀ ህንፃ እያከራዩ የእርጅና ቅናሽ ጥያቄ የሚያቀርቡበትና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ድንጋጌ በቀድሞው አዋጅ አልተካተተም ነበር፡፡ • የቀድሞው አዋጅ በታክስ ሠንጠረዦቹ የማይሸፈኑ የገቢ ዓይነቶችን ወደ ታክስ መረቡ ለማስገባት የሚያስችል “Residual tax rate” አያስቀምጥም ነበር፡ • የቀድሞው አዋጅ ሳይሻሻል ረዘም ላለ ጊዜ ስለቆየ የግብር ከፋይ ደረጃዎችን ለመለየት የተጠቀመባቸው የገንዘብ መጠኖች (thresholds) ከገንዘብ የመግዛት አቅም ጋር ተገናዝበው ሳይሻሻሉ መቆየታቸው እንደ ክፍተት ታይቷል፡፡ • እና ሌሎችም የመሣሰሉት 11 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 12. ክፍል ሁለት… የአዋጁ ጠቅላላ ክፍል 2.1. የግብር ከፋይ ደረጃዎች • ደረጃ “ሀ” - ድርጅት (ጥቃቅን ኢንተርኘራይዞችን ይጨምራል;) እና - ብር 1,ዐዐዐ,ዐዐዐ እና ከዚያ በላይ ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ያለው ግለሰብ ነጋዴ • ደረጃ “ለ” - ብር 5ዐዐ,ዐዐዐ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከብር 1,ዐዐዐ,ዐዐዐ የሚያንስ ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ያለው ግለሰብ ነጋዴ • ደረጃ “ሐ” - ከብር 5ዐዐ,ዐዐዐ ያነሰ ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ያለው ግለሰብ ነጋዴ • ባለሥልጣኑ በየግብር ዓመቱ የግብር ከፋዩ ደረጃ የተለወጠ መሆን አለመሆኑን የሚከተሉትን መረጃዎች መሠረት በማድረግ ይወስናል፡ - ግብር ከፋዩ የሚያሳውቀውን ግብር - በማንኛውም መንገድ የሚያገኘውን ሌላ መረጃ፣ • የግብር ከፋይ ደረጃን ለመወሰን የሚያገለግለው ዓመታዊ ጠቅላላ የገቢ መጠን (threshold) በሚኒስቴሩ በየአምስት ዓመቱ በጥናት እንደሚሻሻል ተደንግጓል፡፡ 12 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 13. 2.2. በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት • በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት ነው የሚባለው ማንኛውም ሰው የንግድ ሥራውን በሙሉ ወይም በከፊል የሚያከናውንበት የንግድ ሼል ቦታ ነው፡፡ • ከላይ የተመለከተው ጠቅላላ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉት በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት እንዳለ ያስቆጥራሉ፡- - የድርጅቱን አገናኝ ጽ/ቤት ሳይጨምር የአስተዳደር ሼል የሚከናወንበት ቦታ፣ ቢሮ፣ ፋብሪካ፣መጋዘን ወይም ወርክሾኘ፣ - የማዕድን ማምረቻ ሥፍራ፣የነዳጅ ወይም የጋዝ ጉድጓድ፣የግንባታ ጠጠር ማምረቻ ወይም ሌላ ማናቸውም የተፈጥሮ ሃብት ፍለጋ ወይም ማምረት ሼል የሚከናወንበት ቦታ፣ • ለአንድ ወይም ለተያያዙ ኘሮጀክቶች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ183 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ተቀጣሪዎችን ወይም ሌሎች ሠራተኞችን በመመደብ (በመላክ) የምክር አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች ማናቸውም አገልግሎቶች የሚሰጡበት ቦታ፣ 13 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 14. • ከ183 ቀናት በላይ የሚቆይ የህንፃ ግንባት ሼል የሚከናወንበት ሥፍራ፣ የግንባታ፣ የመገጣጠም ወይም የተከላ ኘሮጀክት ወይም ከእነዚህ ጋር የተገናኙ የቁጥጥር ሥራዎች የሚሠሩበት ሥፍራ፣ • አንድ ሰው ወይም ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ የንግድ ወኪሉ አማካኝነት በስሙ የውል ድርድር የሚደረግለትና ውል የሚገባለት ከሆነና የንግድ ዕቃዎችን በወኪሉ አማካኝነት አከማችቶ የሚያቆይ ከሆነ ወኪሉ የወካዩ በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት ተደርጐ ይቆጠራል፡ - ወኪሉ ደላላ፣የኮሚሽን ወኪል ወይም ሌላ ራሱን ችሎ የሚሠራ ወኪል (independent) መሆን የለበትም፡ - ይህን ለመለየት የፋይናንስና የውል ግንኙነታቸውን ማየት ያስፈልጋል፡ - የተቀጽላ ድርጅቶች (subsidiaries) እና በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት ልዩነት ግልጽ መሆን አለበት፡  PE are not incorporated and independent  Subsidiaries are incorporated and independent 14 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 15. 2.3. ነዋሪነት • የሚከተሉት የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ናቸው፡፡ - ነዋሪ የሆነ ግለሰብ  ኢትዮጵያ ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ (domicile) ያለው፣  በመንግስት ተመድቦ በውጭ አገር የሚሠራ ኢትዮጵያዊ ዜጋ፣  በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ሳያቋርጥ ወይም በመመላለስ ከ183 ቀናት በላይ የኖረ ግለሰብ፣ - ነዋሪ የሆነ ድርጅት  ኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ /የተመሠረተ/፣  ወሳኝ የሆነ የሥራ አመራር የሚሰጥበት ሥፍራ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው፣ የፌደራል መንግስት፣ የክልል መንግስታትና ከተማ አስተዳደሮች፣ • በ183 ቀናት ቆይታው ምክንያት ነዋሪ ነው የሚባል ግለሰብ ለግብር ዓመቱ እንደነዋሪ የሚቆጠረው ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ከጀመረበት ቀን አንስቶ ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ከኖረበት ቀን በፊት ላለው ጊዜ ነው፡፡ 15 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 16. 2.4. የገቢ ምንጭ የሚከተሉት ገቢዎች ከኢትዮጵያ የመነጩ ናቸው፡ • በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚከናወን የቅጥር አገልግሎት የተገኘ ገቢ - ክፍያው የሚፈፀምበት ሥፍራ የትም ቢሆን፣ - ውሉ የተፈረመው የትም ቢሆን፣ - የአሠሪው ነዋሪነት የትም ቢሆን፣ - ሠራተኛው የኢትዮጵያ ነዋሪ ቢሆንም ባይሆንም፣ • በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት፣በክልል መንግስታት ወይም በከተማ አስተዳደሮችና በእነዚህ ስም ለቀጣሪው የተፈፀመ ክፍያ - የቅጥር አገልግሎቱ የትም ቢከናወን፣ • በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያገኘው የግድ ሼል ገቢ፣ (- በውጭ አገር ባለው በቋሚነት በሚሠራ ድርጅቱ አማካኝነት ከውጭ አገር የሚያገኘው ገቢ ከውጭ ምንጭ የተገኘ ገቢ ነው፡፡) 16 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 17. • ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ ያልሆነ ሰው፣ - በቋሚነት በሚሠራ ድርጅት አማካኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚያካሂደው የንግድ ሼል የሚያገኘው ገቢ፣ - በቋሚነት የሚሠራው ድርጅት ከሚያስተላልፏቸው ዕቃዎች ወይም ሸቀጦች ጋር አንድ ዓይነት ወይም ተመሣሣይ የሆኑ ዕቃዎችን ወይም ሸቀጦችን ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጥታ በማስተላለፍ የሚያገኘው ገቢ፣ - በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት ከሚያከናውናቸው ማናቸውም የንግድ ሥራዎች ጋር አንድ ዓይነት ወይም ተመሣሣይ የሆኑ ሌሎች የንግድ ሼል እንቅስቃሴዎችን ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጥታ በማከናወን የሚያገኘው ገቢ፣ 17 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 18. ከላይ የተመለከቱት ቢኖሩም የሚከተሉት ገቢዎች ኢትዬጽያ ውስጥ የመነጩ ገቢዎች ይባላሉ/4/፡- - በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ድርጅት የሚከፍለው የትርፍ ድርሻ፣ - የማይንቀሳቀስ ሃብትና በኢትዮጵያ የሚገኝን የሚንቀሳቀስ ሃብት በማከራየት የሚገኝ ገቢ፣ - በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝን የማይንቀሳቀስ ሃብት በማስተላለፍ ወይም ግንኙነት ባላቸው ሰዎች የተያዘንና ከዋጋው 5ዐ% በላይ የሆነን የማይንቀሳቀስ ሃብት ጥቅም በማስተላለፍ የሚገኝ ገቢ፣ - በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ኩባንያ ያወጣው (የሚሸጠው) አክሲዮን ወይም ቦንድ፣ - በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኝ መድን ለተገባለት የአደጋ ሥጋት የሚከፈል የመድን አርቦን፣ - በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚከናወን የመዝናኛ ወይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚገኝ ገቢ፣ - በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄድን የዕድል ሙከራ በማሸነፍ የሚገኝ ገቢ፣ - የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው የኢትዮጵያ ነዋሪ ከሆነ ሰው የሚያገኘው የወለድ ገቢ፣ - የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው የኢትዮጵያ ነዋሪ ከሆነ ሰው የሚያገኘው የሮያልቲ ክፍያ ገቢ፣ - የኢትዮጵያ ነዋሪ ለሌላ የኢትዮጵያ ነዋሪ የሚከፍለው የወለድ እና የሮያልቲ ክፍያ ገቢ፣ - የኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት የኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆነ ሰው የሚከፍሉት የሥራ አመራር ወይም የቴክኒክ አገልግሎት ክፍያ፣  ከኢትዬጵያ ውስጥ ያልመነጨ ማንኛውም ገቢ የውጭ አገር ገቢ ነው የሚባለው/5/፡፡ 18 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 19. 2.5. የተፈፃሚነት ወሰን ይህ የህግ አንቀጽ የተደነገገው የኢትዮጵያ መንግስት ያለውንና ሊኖረው የሚገባውን የግብር ሥልጣን (Tax jurisdiction) መሠረት በማድረግ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት አዋጁ - የኢትዮጵያ ነዋሪ በሆኑ ሰዎች ላይ በዓለም ዙሪያ በሚያገኙት ገቢ ላይ ግብር እንዲከፍሉ፣ - የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑት ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ባገኙት ገቢ ላይ ወይም የኢትዮጵያ ምንጭ በሆነ ገቢ ላይ ብቻ ግብር እንዲከፍሉ ደንግጓል፡፡ 19 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 20. 2.6. የገቢ ሠንጠረዦች • በዚህ አዋጅ አምስት የግብር ሠንጠረዦች ይፋ ተደርገዋል፡- - ሠንጠረዥ ሀ - ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ - ሠንጠረዥ ለ - ከ(ቤት) ኪራይ የሚገኝ ገቢ - ሠንጠዥ ሐ - ከንግድ ሼል የሚገኝ ገቢ - ሠንጠረዥ መ- ሌሎች ገቢዎች - ሠንጠረዥ ሠ - ከግብር ነፃ የሆኑ ገቢዎች • በአንድ ሠንጠረዥ ውስጥ የሚወድቁ የተለያዩ ገቢዎችን ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ያገኘ ሰው ሁሉም ገቢዎች ተጣምረው በዚያው ሠንጠረዥ ሼር ግብር ይከፈልባቸዋል፡፡ 20 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 21. 2.7. የገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ • ማንኛውም ገቢ የሚያገኝ ሰው በዚህ አዋጅና በታክስ አስተዳደር አዋጁ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ • ይህ ድንጋጌ ገቢ ባገኘ ሰው ላይ ሁሉ አጠቃላይ ግብር የመክፈል ግዴታን የሚያቋቁም ሲሆን በዚህ አዋጅና በታክስ አስተዳደር አዋጁ መሠረት ግብሩ መከፈል እንዳለበት ስለሚደነግግ ከግብር ነፃ በሆኑ ገቢዎች ላይ ግብር የመክፈል ግዴታን አያስከትልም፡፡ • ግብር ከፋይ ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታ የተጣለበት ሰው ነው፡፡ • ግብር የመክፈል ግዴታ ያለበት ሰው ገቢ ያገኘ ሆኖ ከግብር ነጻ ያልተደረገ ሰው ነው፡፡ 21 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 22. ክፍል ሦስት ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ “ሀ”) • ከግብር ነፃ ከሆነው በስተቀር ቀጣሪው ለተቀጣሪው በሚከፍለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ይከፈልበታል፡፡ • ቀጣሪ ማለት ተቀጣሪን የቀጠረ ወይም ለተቀጣሪው ደመወዝ የሚከፍል ሰው ነው፡፡ • ተቀጣሪ ማለት ደግሞ ራሱን ችሎ የሚሰራን የስራ ተቋራጭ ሳይጨምር በሌላ ሰው /በቀጣሪው/ መሪነትና ቁጥጥር ሾር ሆኖ አገልግሎት ለመስጠት በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት የተቀጠረ ግለሰብ ሲሆን የድርጅት ዳይሬክተር፣ ወይም በድርጅቱ አመራር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ሌላ ሰው እንዲሁም ተሿሚንና የህዝብ ተመራጭን ጨምሮ የመንግስት ሾል ኃላፊን ያጠቃልላል፡፡ • ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 12 የተሰጠው ትርጉም ይኖረዋል፡፡ • በአዋጁ አንቀጽ 10 ላይ ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር የተጣለ ሲሆን የግብር ማስከፈያ ምጣኔው በአንቀጽ 11 ተመልክቷል፡፡ 22 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 23. • አንቀጽ 12 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ፡- - ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡  ከሰራተኛው ቅጥር ጋር በተያያዘ ሰራተኛው የተቀበለው ደመወዝ /ምንዳ/፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን ፣ የመልካም ሾል አፈፃፀም ማበረታቻ፣ ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ክፍያ፣  ሰራተኛው ከቅጥር ውሉ ጋር በተያያዘ በዓይነት የሚቀበለው ማንኛውም ጥቅማጥቅም ዋጋ፣  ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲለቅ ወይም ስራን እንዲለቅ ለማግባባት የሚከፈል ገንዘብን ጨምሮ የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት ወይም በዳኝነት ውሳኔ መሠረት የተቀበለ ማንኛውም የገንዘብ መጠን፣ • ቀጣሪው ለተቀጣሪው ከተከፈለው የገንዘብ መጠን ላይ ግብሩን ሳይቀንስ ከራሱ ግብሩን የከፈለ እንደሆነ የተከፈለው ግብር በተቀጣሪው ደመወዝ ላይ ተደምሮ ግበሩ ይሰላል፡ • በዓይነት ለተቀጣሪው የሚሰጥ ጥቅማጥቅም ዋጋ የሚሰላበትና የሚወሰንበት ሁኔታ በደንብ ይወሰናል፡፡ /የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር410/2009 ከአንቀጽ8-19/ 23 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 24. ክፍል አራት የቤት ኪራይ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ “ለ”) • ከቤት ኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር የተጣለ መሆኑን አንቀጽ 13 የሚደነግግ ሲሆን የግብር ማስከፈያ ምጣኔው በአንቀጽ 14 ሾር ተመልክቷል፡፡ • ይህ ሠንጠረዥ አልፎ አልፎ ከሚከራዩ ንብረቶች በሚገኘው ገቢ ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን የአዋጁ አንቀጽ 13(3) ደንግጓል፡፡ • ግብር የሚከፈልበት የኪራይ ገቢ የሚባለው፡- - በግብር ዓመቱ ግብር ከፋዩ ቤት በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀደው ጠቅላላ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ የሚቀረው ገቢ ሲሆን የሚከተሉትን ይጨምራል-፡ 24 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 25. የቤት ኪራይ ገቢ ግብር…  የኪራይ ዋጋ ጭማሪን ወይም ተመሳሳይ ክፍያዎችን ጨምሮ በኪራይ ወሉ መሠረት ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የሚያገኘው ማናቸውም የገንዘብ መጠን፣  በኪራይ ውሉ መሠረት ተከራይ አከራዩን በመወከል በግብር ዓመቱ ለሌሎች የሚከፍላቸው ክፍያዎች፣  ግብር ከፋዩ ጉዳቱን ለማስተካከል ያልተጠቀመበትና በቤቱ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ማስተካከያ ይሆን ዘንድ የያዘውና በግብር ዓመቱ ለግብር ከፋዩ ገቢ የተደረገው ማናቸውም ቦንድ፣ዋስትና ወይም ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን፣  ለግብር ከፋዩ ከሚከፈለው ኪራይ በተጨማሪ በኪራይ ውል መሠረት ተከራይ ልሹ ለቤቱ እድሳት ወይም ማሻሻያ የሚያወጣው ገንዘብ፣ • ግብር ከፋዩ ቤቱን ያከራየው ከዕቃዎች ጋር በሚሆንበት ጊዜ ያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከዕቃዎቹ የተገኘውን የኪራይ ገቢም ያጠቃልላል፡፡ 25 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 26. የቤት ኪራይ ገቢ ግብር… • በአንድ የግብር ዓመት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የሌለበት ግብር ከፋይ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚሰላበት ጊዜ የሚከተሉት ወጪዎች በተቀናሽ ይያዛሉ፡- - ታክስን ሳይጨምር ለመሬቱ ወይም ከተከራየው ቤት ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩ ለመንግስት ወይም ለከተማ አስተዳደር በግብር ዓመቱ ውስጥ የከፈላቸው ክፍያዎች፣ - ለቤቶች፣ለቤት ዕቃና መሳሪያ ማደሻ፣ መጠገኛና ለእርጅና መተኪያ የሚሆን ከቤት ዕቃና ከመሣሪያ ኪራይ ከሚገኘው ጠቅላላ ገንዘብ ላይ 50% በመቶ፣ - ከላይ የተመለከተው አንቀጽ 15(5) በማናቸውም ሁኔታ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ተፈፃሚ ሊሆን አይችልም፡ • የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ግብር ከፋይ በግብር ዓመቱ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚሰላበት ጊዜ ገቢውን ለማግኘት የወጣና በግብር ከፋዩ የተከፈለ አስፈላጊ (necessary) የሆነ ወጪ ተቀናሽ የሚደረግ ሲሆን ይህም ወጪ የሚከተሉትን ይጨምራል፡- - ቤቱ ያረፈበት የመሬት ኪራይ (lease)፣ - የጥገና ወጪ፣ - የቤቱ፣የቤት ዕቃዎችና የመሣሪያዎች የእርጅና ቅናሽ፣ - ወለድና የመድን አርቦን፣ - ታክስን ሳይጨምር ለመሬቱ ወይም ከተከራየው ቤት ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩ ለመንግስት ወይም ለከተማ አስተዳደር የከፈላቸው ክፍያዎች፣ 26 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 27. የቤት ኪራይ ገቢ ግብር … • የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ያገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው የሚባለው የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ከተቀበለው ጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ለዋናው አከራይ የሚከፍለው ኪራይ እንዲሁም ገቢውን ለማግኘት ያወጣቸው ሌሎች ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚቀረው ገንዘብ ነው፡፡ • ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ እንዲያከራይ የሚፈቅድ የቤት ባለቤት ተከራዩ ግብሩን ሳይከፍል ቢቀር ስለእርሱ ሆኖ ግብሩን የመክፈል ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡ • ሾል ተቋራጭ እና የቤቱ ባለቤት ለኪራይ የሚሰራው ቤት እንደተጠናቀቀ ወይም ተከራይቶ ከሆነ ከቤቱ ኪራይ በሚገኘው ገቢ ላይ ግብር መክፈል ያለበትን ሰው ስም፣አድራሻና የታክስ ኪራይ መለያ ቁጥር ቤቱ ለሚገኝበት የቀበሌ አስተዳደር ወይም የአካባቢ አስተዳደር ማስታወቅ አለባቸው፡፡ • የቀበሌ አስተዳደሩ ወይም የአካባቢ አስተዳደሩ ከስራ ተቋራጩና ከቤቱ ባለቤት ያገኙት መረጃ ለግብር ባለሥልጣኑ መግለጽ አለባቸው፡፡ 27 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 28. ክፍል አምስት ግብር የሚከፈልበት የንግድ ሾል ገቢ፣ተቀናሽ የሚደረጉና የማይደረጉ ወጪዎች 1. ግብር የሚከፈልበት የንግድ ሾል ገቢ /አ20/ - ግብር የሚከፈልበት የንግድ ሾል ገቢ የሚባለው በግብር ዓመቱ ውስጥ ከተገኘው ጠቅላላ የንግድ ሾል ገቢ ላይ በህግ የተፈቀዱ ወጪዎች ተቀንሰው የሚገኘው የተጣራ የገቢ መጠን ነው፡፡ - ግብር ከፋዩ የግብር ዓመቱን ግብር የሚከፍልበት የንግዱ ሾል ገቢ የሚወስነው በፋይናንሻል ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች መሠረት በሚያዘጋጀው የትርፍና ኪሳራ ወይም የገቢ መግለጫ ላይ በመመስረት ይሆናል፡፡  የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች  የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ  የሚኒስትሩ መመሪያ የተጠበቁ ናቸው፡፡ 28 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 29. 2. የንግድ ሾል ገቢ (21) የንግድ ሾል ገቢ ነው የሚባለው የሚከተሉትን ይጨምራል፡፡ • ግብር ከፋዩ ዕቃዎችን በማስተላለፍ አገልግሎቶችን በመስጠት የሚያገኘውን የገንዘብ መጠን ጨምሮ በግብር ዓመቱ ከንግድ ሾል ያገኘው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን፣ • የንግድ ሾል ሃብትን በማስተላለፍ የሚገኝ የገንዘብ መጠን (ከመዝገብ ዋጋ በላይ ያለው ዋጋ)፣ • በዚህ አዋጅ መሠረት የግብር ከፋዩ ገቢ ተደርገው የተወሰዱ ሌሎች ማናቸውም ገቢዎች፣ • የካፒታል ንብረት የሆነን የንግድ ሾል ሃብት በማስተላለፍ በሚገኘው ጥቅም ላይ ሁለት ግብሮች ሊወሰኑ ይችላሉ፡- - የንግድ ትርፍ ግብር - የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር (59) 29 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 30. • ከንግድ ሾል ሃብቱ የመዝገብ ዋጋ በላይ የሆነው ትርፍ በንግድ ሾል ገቢ ውስጥ የሚደመር ሲሆን ለንግድ ሾል ሃብት ከተደረገው ወጪ በላይ የሚገኘው ጥቅም ደግሞ የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር ይከፈልበታል፡፡ • ለምሳሌ፡- Assume no inflation adjustment ለንግድ ቢሮ በብር 5,000,000 የተሰራ ህንጻ ከሁለት ዓመት በኋላ በብር 7,000,000 ቢሸጥ በብር 500,000 ላይ የንግድ ትርፍ ግብር የሚከፈልበት ሲሆን በብር 2,000,000 ላይ ደግሞ የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር ይከፈልበታል፡፡ የእርጅና ቅናሹ ጠቅላላ ገቢ ላይ ይደመራል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በግብር ዓመቱ መጨረሻ ከዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ላይ የህንጻው የእርጅና ቅናሽ እየተቀነሰ መጥቷል፡፡ • መመሪያ ቁጥር 8/2011 ተመልከቱ 30 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 31. 3. ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎች (22) የሚከተሉት ከጠቅላላ ገቢ ላይ ይቀነሳሉ፡፡ • በንግድ ሾል ገቢው ውስጥ የተካተቱትን ገቢዎች ለማግኘት፣ በንግዱ ሾል ዋስትና ለመስጠትና የንግድ ስራውን ለማስቀጠል በግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የተደረጉ አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎች፣ • በግብር ዓመቱ ለተሸጠ የንግድ ዕቃ (trading stock) የወጣ ወጪ፣ • በንግድ ስራው ላይ ሲውሉ ዋጋቸው የሚቀንስ የንግድ ሾል ሃብቶችና ግዙፋዊ ህልወት ለሌላቸው የንግድ ሾል ሃብቶች በግብር ዓመቱ የሚታሰበው ጠቅላላ የእርጅና ቅናሽ፣ • የንግድ ዕቃን ሳይጨምር ግብር ከፋዩ በዓመቱ ውስጥ የንግድ ሾል ሃብትን በማስተላለፍ የገጠመው ኪሣራ፡፡ • በዚህ አዋጅ በተቀናሽነት የተፈቀዱ ሌሎች ወጪዎች፡፡ 31 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 32. - የወለድ ወጪ፣  ብድሩ ለንግድ ሾል ከዋለ፣  ብድሩ ከባንክ ውጪ በሆነ አበዳሪ የተሰጠ ሆኖ በብሄራዊ ባንክና በንግድ ባንክ መካከል በተደረገ የብድር ስምምነት ከሚታሰብ የወለድ ምጣኔ ከ2% በላይ የሚበልጥ ካልሆነ፣  ከተፈቀደለት ባንክ ለተወሰደ ብድር የተከፈለ ወለድ ያለገደብ ይቀነሳል፡፡  በሠንጠረዥ መ መሠረት ግብር የሚከፈልበት ካልሆነ በስተቀር ግብር ከፋዩ ግንኙነት ላለው ነዋሪ የከፈለው ወለድ አይቀነስም፡፡ - ለበጎ አድራጎት ዓላማ የተደረገ ስጦታ፣  የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ከሆነ፣  በመንግስት በተደረገ ጥሪ መሰረት ለመንግስት የተደረገ ስጦታ ከሆነ፣  ግብር ከሚከፈልበት ገቢ ከ10% ያልበለጠ ስጦታ ከሆነ፣ - የማይሰበሰብ ዕዳ - የተፈቀደ ኪሳራ - ከረጅም ጊዜ ውል ጋር በተያያዘ የግብር ዓመቱ የወጪ መቶኛ፡፡ 32 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy 23/02/2015 E.C
  • 33. 4. የእርጅና ቅናሽ ስሌትና አሠራር (25) • የእርጅና ቅናሽ ምጣኔና ዝርዝር አሠራር በደንብ የሚወሰን ይሆናል፡፡ /ደንብ ቁጥር 410/2009 አንቀጽ36-41/ • ዓመቱን ሙሉ አገልግሎት ያልሰጠ ወይም በከፊል ለንግዱ ሾል በከፊል ደግሞ ለሌላ ሾል የዋለ የንግድ ሾል ሃብት ለንግድ ሾል በዋለበት መጠን ብቻ የእርጅና ቅናሽ እንደሚሰላ ተመልክቷል፡፡ • እርጅና መታሰብ የሚጀምረው የንግድ ሾል ሃብቱ ህንጻ ከሆነ የህንጻ ግንባታ መጠናቀቁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከተሰጠበት ቀን በፊት ሊሆን አይችልም፡፡ ሌላ ንብረት ከሆነ ለንግድ ሾል ዝግጁ ከሆነበትና አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ይሆናል፡፡ • የንግድ ሾል ሃብት የሚባለው ከአንድ ዓመት የሚበልጥ የአገልግሎት ዘመን ያለው ለንግድ ሾል የዋለ ሀብት ወይም መብት ነው፡፡(25(7))፡፡ • የንግድ ሾል ሃብት ማለት የንግድ ሾል በማከናወን ሂደት በሙሉ ወይም በከፊል የንግድ ሾል ገቢ ለማግኘት የተያዘ ወይም ጥቅም ላይ የዋለ ሃብት ነው(2(3))፡፡ 33 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 34. 5. ኪሳራን ስለማሸጋገር (26) • የግብር ዓመቱ ወጪ ከግብር ዓመቱ ጠቅላላ ገቢ የበለጠ ከሆነ ከጠቅላላ ገቢው በላይ ያለው ወጪ የግብር ከፋዩ ኪሳራ ነው፡፡ • ይህንን ኪሳራ ግብር ከፋዩ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት በማሸጋገር ማቀናነስ ይችላል፡፡ • ግብር ከፋዩ በአንድ የግብር ዘመን የደረሰበትን ኪሣራ ኪሣራው ከደረሰበት ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ከሚቆጠሩ ከአምስት ዓመታት በላይ ማሸጋገር አይችልም፡፡ • ከሁለት የግብር ዘመናት ኪሣራ በላይ ማሸጋገር አይፈቀድም፡፡ • ስለኪሳራ ማሸጋገር በደንቡ በዝርዝር ተገልጿል፡፡/410/2009 አንቀጽ42/ 34 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 35. 6. ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎችና ኪሣራዎች የሚከተሉት ተቀናሽ አይደረጉም፡- • የእርጅና ተቀናሽ የሚደረግባቸው የካፒታል ወጪዎች፣ • የኩባንያ አክሲዮን ወይም የሽርክና ማህበር መሠረት የሆነውን ካፒታል ለማሳደግ የሚወጣ ወጪ፣ • ከ15% በላይ የሆነ በቀጣሪው የሚከፈል የጡረታ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ መዋጮ፣ • የአክሲዮን ወይም የትርፍ ድርሻ፡ • በካሳ መልክ የተመለሰ ወይም ሊመለሰስ የሚችል ወጪ ወይም ኪሣራ፡ • ህግን ወይም የውል ግዴታን በመጣስ የሚጣል የገንዘብ ቅጣት ወይም የሚከፈል ኪሣራ፡ • ለወደፊት ወጪዎች ወይም ኪሣራዎች መጠባበቂያ የተያዙ ሂሳቦች፣ • የገቢ ግብር ወይም ተመላሽ የሚደረግ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ • መስሪያ ቤቱን ለመወከል ለተቀጣሪ የሚከፈል ከመቀጠር ከሚያገኘው ገቢ ከ10% በላይ የሆነ የኃላፊነት አበል፣ 35 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 36. • ከሚከተሉት በስተቀር ለመዝናኛ የሚወጣ ወጪ፣  የግብር ከፋዩ የንግድ ሾል የመዝናኛ አገልግሎት መስጠት ከሆነ ወይም ለማኑፋክቸሪንግ፣ለማዕድንና ለግብርና ሰራተኞች መዝናኛ የተከፈለ ወጪ ይቀነሳል፡፡ ከ65(6) ጋር የሚታይ /ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርብ ከሆነ/ ፡፡ • በአንቀጽ 24 ከተመለከተው ውጪ የሚደረግ ስጦታ ወይም እርዳታ፣ • የግብር ከፋዩ የግል ወጪ፣ • የንግድ ሾል ሃብትን ግንኙነት ላለው ሰው በማስተላለፍ የሚያጋጥም ኪሣራ፡ • የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተቀናሽ አይደረጉም በማለት በደንብ የሚወስናቸው ወጪዎች፣ • መዝናኛ- ማለት ለማንኛውም ሰው የሚቀርብ ምግብ፣መጠጥ፣ትምባሆ፣ ማረፊያ፣ መደሰቻ ወይም ማናቸውም ዓይነት መስተንግዶ ነው፡ 36 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 37. 7. የታክስ ሂሳብ አያያዝ (28-33) 7.1. የሂሳብ ዓመት (28) • ይህ አንቀጽ ተፈፃሚ የሚሆነው ከግብር ዓመቱ የተለየ የራሱ የሂሳብ ዓመት እንዲኖረው በተፈቀደለት ግብር ከፋይና በድርጅቶች ላይ ነው፡፡ • የእነዚህ ግብር ከፋዮች የሂሳብ ዓመት ነው የሚባለው የግብር ከፋዩ ዓመታዊ የፋይናንስ ሂሳብ ሚዛን በሚዘጋበት ጊዜ የሚጠናቀቀው የአስራሁለት ወራት ጊዜ ነው፡፡ • ማንኛውም ግብር ከፋይ ከባለሥልጣኑ የጽሁፍ ፈቃድ ሳያገኝና ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟላ የሂሳብ ዓመቱን መቀየር አይችልም፡፡ • ግብር ከፋዩ ቅድመ ሁኔታዎቹን ያጓደለ እንደሆነ ባለሥልጣኑ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሰጠውን ፈቃድ ሊሰርዘው ይችላል፡፡ • የግብር ከፋዩ የሂሳብ ዓመት ሲቀየር በነባሩ የሂሳብ ዓመት እና በአዲሱ የሂሳብ ዓመት መካከል ያለው ጊዜ “የመሸጋገሪያ ዓመት” በመባል የሚታወቅ ሲሆን ይህ ጊዜ ራሱን እንደቻለ የሂሳብ ዓመት ይቆጠራል፡፡ • የግብር ከፋዩ የሂሳብ ዓመት ከበጀት ዓመቱ ጋር የማይገጥም በሚሆንበት ጊዜ ለሂሳብ ዓመቱ ተፈጻሚ የሚሆነው ህግ በሂሳብ ዓመቱ ውስጥ በሚጠናቀቀው የበጀት ዓመት ተፈፃሚ የሚሆነው ህግ ነው፡፡ 37 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 38. 7.2. የሂሳብ አያያዝ ዘዴን ስለመለወጥ • ግብር ከፋዩ የሂሳብ አያያዝ ዘዴውን ለመለወጥ ባለሥልጣኑን በጽሁፍ ሊጠይቅ የሚችል ሲሆን ባለሥልጣኑም ለውጡ የግብር ከፋዩን ገቢ በትክክል ለማስላት የሚያስፈልግ መሆኑን ሲያምንበት ግብር ከፋዩ የሂሳብ አያያዝ ዘዴውን እንዲለውጥ በጽሁፍ ሊፈቅድለት ይችላል፡፡ • የግብር ከፋዩ የሂሳብ አያያዝ ዘዴ በሚለወጥበት የግብር ዓመት የግብር ከፋዩ የግብር ከፋይ ደረጃም የሚለወጥ ከሆነ የግብር ከፋዩ ገቢ ሳይመዘገብ እንዳይቀር ወይም በድጋሚ እንዳይመዘገብ ለማድረግ በገቢ ርዕሶች፣በተቀናሽ ወጪዎች ወይም በታክስ ማካካሻ ሂሳቦች ላይ ከለውጡ ጋር በተያያዘ ተገቢውን ማስተካከያ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ 23/02/2015 E.C 38 Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 39. 7.3. የማይሰበሰቡ ዕዳዎች (30) • የሚከተሉት ሲሟሉ ግብር ከፋዩ ሊሰበስበው ያልቻለ ዕዳ በተቀናሽነት ይያዝለታል፡፡ - ዕዳው ቀደም ሲል የንግድ ሾል ገቢ ሆኖ ተይዞ /ተመዝግቦ/ ከሆነ፣ - ዕዳው ከግብር ከፋዩ የሂሳብ መዝገብ የተሰረዘ እንደሆነ፣ እና - ዕዳውን ለማስከፈል አስፈላጊ የህግ እርምጃ ተወስዶ ማስመለስ ያልተቻለ እንደሆነ፣ • የሚቀነሰው የዕዳ መጠን ከግብር ከፋዩ የሂሳብ መዝገብ ከተሰረዘው የዕዳ መጠን መብለጥ የለበትም፡፡ • ይህ አንቀጽ ለፋይናንስ ተቋማት ተፈፃሚ አይሆንም፡፡ 39 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 40. 7.4. የፋይናንስ ተቋማትና የኢሹራንስ ኩባንያዎች (31) የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚከተሉትን በደንብ ይወስናል፡፡ • የፋይናንስ ተቋማት የሚይዙት የኪሳራ መጠባበቂያ ገንዘብ ተቀናሽ የሚደረግበት ሁኔታ፣/410/2009(45)/ • የህይወት መድን ኢንሹራንስ ኩባንያዎችን ሳይጨምር የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጊዜያቸው ካላለፈባቸው የኢንሹራንስ ዋስትናዎች ጋር በተያያዘ የሚይዙት የመጠባበቂያ ሂሳብ ተቀናሽ ስለሚደረግበት ሁኔታ፣/410/2009(46)/ • የህይወት መድን ኩባንያዎች ግብር የሚከፍሉበት ገቢ ስለሚሰላበት ሁኔታ፣/410/2009 (47)/ 40 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 41. 7.5. ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ውሎች (32) • ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ውል ማለት በተጀመረበት የግብር ዓመት ውስጥ ያልተጠናቀቀ የማምረት፣የመትከል ወይም የግንባታ ሾል እንዲሁም ከእነዚህ ጋር የተያያዘ አገልግሎት ነው፡፡ • የረጅም ጊዜ ውል ያለው ግብር ከፋይ የግብር ዓመቱ ወጪ ተቀናሽ የሚደረግበት ሁለት ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው፡፡ - ሂሳቡን በተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳብ ዘዴ የሚይዝ ሲሆን፣ - በግብር ዓመቱ የተጠናቀቀውን ሾል መቶኛ መሠረት በማድረግ ገቢውን በንግድ ሾል ገቢው ውስጥ መዝግቦ ያካተተ ሲሆን ነው፡፡ • ተቀናሽ የሚደረገው የግብር ከፋዩ ወጪ ግምት ጠቅላላ የውሉ ወጪ በተጠናቀቀው ሾል መቶኛ ተባዝቶ የሚገኘው የግብር ዓመቱ ወጪ ነው፡፡ 41 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 42. • ግብር ከፋዩ በአንቀጽ 26 መሠረት ኪሣራውን ወደፊት ማሸጋገር የሚፈቀድለት ቢሆንም ይህን ማድረግ ያልቻለ እንደሆነ ወይም በውሉ ዘመን መጨረሻ በኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ሾል መስራት በማቆሙ ምክንያት ኪሣራውን ወደፊት ማሸጋገር ያልቻለ እንደሆነ የደረሰበት ኪሣራ በቀደመው ዓመት ገቢ ላይ ይካካሳል (Loss carry backward). • ግብር ከፋዩ ኪሣራውን በአምናው ገቢ ላይ ማካካስ ካልቻለ ያልተካካሰው ኪሳራ በካቻምና ገቢ ላይ ይካካሳል፡፡ • ግብር ከፋዩ ኪሣራ ደርሶበታል የሚባለው የሚከተሉትን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ነው፡- - በውሉ ይገኛል ተብሎ የተገመተው ግብር የሚከፈልበት ገቢ በእርግጠኛነት ከተገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ በልጦ ሲገኝና - በብልጫ የታየው የውሉ ዓመታዊ ገቢ ወሉ በተጠናቀቀበት የግብር ዓመት ወጪና ገቢው ተሰልቶ ከተገኘው የገቢ ልዩነት በልጦ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡ 42 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 43. 7.6. ለደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የተወሰነ ቀላል የታክስ ሥርዓት (33) ከዚህ በታች የተመለከቱት እንደተጠበቁ ሆነው የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች ግብር የሚከፈልበት ገቢ የሚሰላውና የሚወሰነው በገቢ ግብር አዋጁ መሠረት ይሆናል፡ - ግብር ከፋዩ የንግድ ሾል ገቢውንና ተቀናሽ ወጪውን የሚይዘው በጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ላይ በተመሠረተ የሂሳብ አያያዝ ዘዴ መሆን አለበት፡ - ለንግድ ሾል ሃብቶቹ የሚደረገው የእርጅና ቅናሽ 100% ይሆናል፡ - በግብር ዓመቱ ለንግድ ዕቃዎች የወጣ ወጪ በተቀናሽነት ይያዛል፡ - የሂሳብ መዛግብትን ይዞ ለመቆየት የሚገደድበት /የታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀጽ 17/2/ እና የግብር ውሳኔን ለማሻሻል ለባለሥልጣኑ የተፈቀደው ጊዜ /የታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀጽ 28/2ለ/ ሦስት ዓመት ብቻ ነው፡ 43 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 44. 8. ድርጅቶች (34 እና 35) 8.1. አንድን ድርጅት በመቆጣጠር ረገድ የሚደረግ ለውጥ (34) • አንድ ድርጅት የደረሰበትን ኪሣራ ወደ መሸጋገሪያ ዓመት ወይም ወደሚቀጥለው ዓመት ማሸጋገር የሚችለው የኩባንያውን ከ50% በላይ የሆነውን የዋና ባለቤትነት ድርሻ የያዘው ሰው ተመሳሳይ ሰው የሆነ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡/አ1/ • ነገር ግን /አ2/ ድርጅቱ በኪሣራው ዓመት፣በመሸጋገሪያው ዓመትና በሁሉም ጣልቃ ገብ ዓመታት አንድ ዓይነት የንግድ ሾል እየሰራ ያለ ከሆነ፣ ወይም • የዋና ባለቤትነት ለውጥ ከተደረገም በኋላ ድርጅቱ በሌላ የንግድ ሾል የተሰማራው ኪሣራውን ከአዲሱ ሾል ገቢ ላይ ለማካካስና ገቢውን ለማሳነስ አለመሆኑ ከተረጋገጠ ኪሣራውን እንዳያሸጋግር አይከለከልም፡፡ 44 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 45. 8.2. የኩባንያ እንደገና መደራጀት (35) • አንድ ኩባንያ እንደገና ከመደራጀት ጋር ተያይዞ ለሌላ ኩባንያ የንግድ ሾል ሃብት በሚያስተላልፍበት ጊዜ የንግድ ሾል ሃብቱ እንደተሸጠ፣ እንደተለወጠ ወይም እንደተሰጠ (እንደተላለፈ) አይቆጠርም፡፡ • የንግድ ሾል ሃብቱን ያገኘው ድርጅት አስተላላፊው የንግድ ሾል ሃብቱን ለማግኘት ከወጣው ወጪ ጋር እኩል የሆነ ወጪ በማውጣት እንዳገኘው ይቆጠራል (aquired at Book value)፡፡ • የንግድ ሾል ሃብቱ የተላላፈለት ሰው በምትኩ አክሲዮን የሰጠ እንደሆነ ለአክሲዮኖቹ የተደረገው ወጪ የተላለፈው ሃብት በተላለፈበት ጊዜ ከነበረው ዋጋ ጋር እኩል መሆን ይኖርበታል፡፡ • ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም “ለንግድ ስራው ሃብት የተደረገው ወጪ” የሚለው የንግድ ሾል ሃብቱ በተላለፈበት ጊዜ የነበረውን የተጣራ የመዝገብ ዋጋ የሚመለከት ነው፡፡ 45 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 46. • “እንደገና መደራጀት (reorganization)”ማለት፡- - ከሁለት በላይ የሆኑ ነዋሪ ኩባንያዎች መዋሃድ፡፡ - የአዲሱ ድርጅት አባል የሆነ አንድ ድርጅት የሌላውን ድርጅት 50% ልዩ የአክሲዮን ባለቤት ድርሻ ከአዲሱ ድርጅት በሚገኘው የአክሲዮን ለውጥ ብቻ መያዝ፡፡ - እንደገና በሚደራጀው ድርጅት ውስጥ አባል የሆነ ድርጅት የሌላውን ከ50% በላይ የሆነ የአክሲዮን ባለቤትነት ድርሻ ልዩ መብት በማያሰጥና የድምጽ ተሳትፎ ብቻ በሚያስገኝ አኳኋን መጠቅለል፡፡ - የአንድ ድርጀት ወደ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ወደ ሆኑ ኩባንያዎች መከፋፈል፡፡ - የአንድ ድርጅት የተቀጽላዎችን ካፒታል የድርጅቱን ካፒታል ለያዘ ሌላ ድርጅት ማስተላፍ፡፡ • በእንደገና መደራጀት ሂደት የተላለፈ የንግድ ሾል ሃብት እንደተላለፈ አይቆጠርም የሚለው የዚህ አንቀጽ ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነው የእንደገና መደራጀቱ ዓላማ ከታክስ ለመሸሽ ያለመሆኑ በባለስልጣኑ ሲታመንበት ነው፡፡ 46 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 47. ክፍል ስድስት የማዕድንና የነዳጅ ስራዎች ገቢ ግብር/36-44/ ሀ/ የማዕድንና የነዳጅ ስራዎች ልዩ ባህሪ • የማዕድንና የነዳጅ ሾል ከሌላው የንግድ ሾል ለየት የሚያደርገው፡- - የገቢ ምንጩ ሊተካ የማይችል የመንግስት (የሃገር) የተፈጥሮ ሃብትን በመጠቀም የሚገኝ በመሆኑ፡፡ - ስራው ከፍተኛ ስጋት (Risk) ያለበትና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፡፡ - የማዕድንና የነዳጅ ፈለጋ ሾል ረጅም ጊዜ የሚወስድና በስተመጨረሻም ውጤት እንደሚገኝ አስቀድሞ እርግጠኛ መሆን የማይቻልበት ሁኔታ (uncertainity) ያለበት በመሆኑ፡፡ - ንግዱ የመንግስት ልዩ ፈቃድ የሚጠይቅና ልዩ ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግበት እንዲሁም የመንግስት ድርሻ ያለበት በመሆኑ፡፡ - ንግዱ የመንግስትን ልዩ መብት (Royal interest of the state) የሚጋራና ከፍተኛ የመንግስት ጥቅም ያለበት በመሆኑ ወዘተ ነው፡፡ 47 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 48. ለ/ ፈቃድ በተሰጠው ሰውና በስራ ተቋራጭ ላይ ግብር ስለመጣል • ማዕድን የማውጣት መብት በተሰጠው ባለፈቃድ (ፈቃድ የተሰጠው ሰው) እና ከመንግስት ጋር የነዳጅ ስምምነት ባደረገው ሾል ተቋራጭ ላይ የተጣለው የንግድ ሾል ገቢ ግብር 25% ነው፡፡ • ፈቃድ የተሰጠው ሰው በኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆነ ንዑስ ሾል ተቋራጭ ከሚፈጽመው ማንኛውም ክፍያ ላይ የሞቢላይዜሽንና የዲሞቢላይዜሽን ወጪዎች ተቀንሰው በሚቀረው መጠን ላይ 10% ግብር ቀንሶ ለባለስልጣኑ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የነዳጅ ንዑስ ሾል ተቋራጭ ከዚህ ዓይነት ግብር ነጻ ተደርጓል፡፡ • ስለማዕድንና ነዳጅ ስራዎች ገቢ የሚደነግገው የአዋጁ ክፍል ከሌሎች የአዋጁ ድንጋጌዎች ጋር ቢጋጭ ስለማዕድንና ስለነዳጅ ስራዎች የሚደነግጉት የአዋጁ ክፍሎች የበላይነት እንደሚኖራቸው ተደንግጓል፡፡ ከዚህ ክፍል ጋር የማይቃረኑ ሌሎች የገቢ ግብር አዋጅ ድንጋጌዎች ግን ከማዕድንና ነዳጅ ስራዎች በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡ 48 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 49. ሐ/ በማዕድን ወይም በነዳጅ ስራዎች ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎችን ስለመገደብ • ባለፈቃዱ ወይም ሾል ተቋራጩ ተቀናሽ የሚደረግላቸው ወጪ፣ - ባለፈቃዱና ሾል ተቋራጩ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ ፈቃድ በተሰጠበት አካባቢ ወይም የውል ክልል ውስጥ በግብር ዓመቱ ካገኙት የንግድ ሾል ገቢ ላይ የዓመቱን ወጪ ተቀናሽ ማድረግ ይችላሉ፡፡ - የማዕድን ወይም የነዳጅ ስራን በሚሰሩበት ጊዜ ኪሳራ ያጋጠማቸው እንደሆነ ኪሳራው ወደሚቀጥለው የግብር ዓመት ተሸጋግሮ ፈቃድ በተሰጠበት ክልል ወይም በውሉ ክልል የማዕድን ወይም የነዳጅ ሾል በመስራት ከሚያገኙት የንግድ ሾል ገቢ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል፡፡ - የደረሰባቸው ኪሳራ ከቀጣዩ የግብር ዓመት በተገለጹት ክልሎች በተገኘው ገቢ የማይካካስ ከሆነ ኪሳራን እስከሚቀጥሉት 10 የግብር ዓመታት ድረሰ ማሸጋገር ይችላሉ፡፡ - ባለፈቃዱና ሾል ተቋራጩ ኪሳራ ደረሰባቸው የሚባለው በግብር ዓመቱ ካገኙት ጠቅላላ የንግድ ሾል ገቢ የግብር ዓመቱ ጠቅላላ ወጪ የበለጠ እንደሆነ ነው፡፡ - ከዚህ በላይ የተመለከቱት ገደቦች እንደተጠበቁ ሆነው ባለፈቃዱና ሾል ተቋራጩ የሚከተሉት ተቀናሾች ይፈቀዱላቸዋል፡- 49 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 50. 1/ የፍለጋ ወጪዎች  የአገልግሎት ዘመናቸው አንድ ዓመት የሆኑ የፍለጋ ወጪዎች ግዙፋዊ ህልወት የሌላቸው የንግድ ሾል ሃብቶች ተደርገው ይወሰዳሉ፡-  ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍለጋ ሾል ጥቅም ላይ የዋለ የንግድ ሾል ሃብት የእርጅና ቀናሽ መጣኔው 100% ይሆናል፡፡ 2/ የማልሚያ ወጪ፣  የማልሚያ ወጪ ለአራት ዓመታት ያህል የሚያገለግል ግዙፋዊ ህልወት የሌለው የንግድ ሾል ሃብት እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡  ምርት ማምረት ከመጀመሩ በፊት የወጣ የማልሚያ ወጪ ለንግድ የሚሆን ምርት ማምረት በተጀመረበት ጊዜ እንዳወጣ ወጪ ተቆጥሮ የእርጅና ቅናሽ ይታሰብለታል (አ.25)፡፡  ለንግድ የሚሆን ምርት ማምረት ከመጀመሩ በፊት ለማልሚያ ስራዎች አገልግሎት የሚውል ዋጋው የሚቀንስ የንግድ ሾል ሃብት የተገዛ ወይም የተገነባ እንደሆነ ሃብቱ ለንግድ ሾል የሚሆን ምርት በተጀመረበት ጊዜ እንደተገዛ ወይም እንደተገነባ ተቆጥሮ የእርጅና ቅናሽ ይታሰብለታል (አ.25)፡፡ 50 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 51.  ከላይ የተመለከቱት የእርጅና ቅናሽ ስሌቶች ቀመር በአዋጁ አንቀጽ 40(4) ላይ የተመለከተ ሲሆን “ሀ*ለ/ሐ” ለንግድ ሾል ሃብቱ የተደረገው ወጪ ለንግድ ማምረት ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ለንግድ ማምረት በተጀመረበት የግብር ዓመት የመጨረሻ ቀን መካከል ባሉት ቀናት ተባዝቶ ለንግድ የሚሆን ምርት ማምረት በተጀመረበት የግብር ዓመት ላሉት ቀናት ብዛት ተካፍሎ የሚገኘው ስሌት የእርጅና ቅናሹ ይሆናል፡፡  ከማዕድን ሾል መብት ወይም ከነዳጅ ስምምነት ከተገኘ መብት አንድ መብት የተላለፈ እንደሆነ መብቱን በማስተላለፍ የተገኘው ጥቅም ተደርጎ የሚወሰደው ባለፈቃዱ ወይም ሾል ተቋራጩ ተቀናሽ የተደረገላቸውንና ያልመለሱትን ሂሳብ ሳይጨምር የማስተላለፍ ተግባር በተከናወነበት ጊዜ ያወጡት የማልሚያ ወጪ ከተቀነሰ በኋላ የሚገኘው ዋጋ ነው፡፡ 51 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 52. 3/ የመልሶ ማቋቋሚያ ወጪ/rehabilitation expenditure/፣  በመልሶ ማቋቋሚያ ዕቅድ መሰረት ለመልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ የሚደረገው መዋጮ መዋጮው በተደረገበት የግብር ዓመት በተቀናሽነት ይያዛል፡፡  ከመልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ወጪ ተደርጎ ያልተተካ ለመልሶ ማቋቋሚያ የወጣ ወጪ ወጪው በወጣበት የግብር ዓመት በተቀናሽነት ይያዛል፡፡  በመልሶ ማቋቋም ሾል ከመልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ወጪ የሚደረግ የገንዘብ መጠን ከግብር ነጻ ነው፡፡  ከመልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ወጪ ተደርጎ ለባለፈቃዱ ወይም ለሾል ተቋራጩ ተመላሽ የተደረገ የገንዘብ መጠን ገንዘቡ ተመላሽ በተደረገበት የግብር ዓመት እንደ ንግድ ሾል ገቢ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡  “መልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ” ማለት ፈቃድ የተሰጠበትን ክልል ወይም የውል ክልል መልሶ ለማስተካከል የሚውል በነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር እና በባለፈቃዱ ወይም በስራ ተቋራጩ በጋራ የሚተዳደር ገንዘብ ነው፡፡ 52 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 53. 4/ የኢንቨስትመንት ተቀናሽ /42/  በፈቃድ ሰጪው ባለስልጣን በተፈቀዱ ሌሎች የልማት መስኮች ኢንቨስት ለሚደረግ የወጣ የኢንቨስትመንት ወጪ ከእያንዳንዱ የግብር ዓመት ጠቅላላ ገቢ ላይ እስከ 5% ተቀናሽ ይፈቀዳል፡፡  ሆኖም ይህ የኢንቨስትመንት ገንዘብ ተቀናሽ ከተደረገበት የግብር ዓመት ቀጥሎ እስካለው የግብር ዓመት መጨረሻ ድረስ ኢንቨስት ካልተደረገ በዚሁ የግብር ዓመት ጠቅላላ ገቢ ላይ ይደመራል፡፡ 53 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 54. መ/ የማዕድን ወይም የነዳጅ መብት ስለማስተላለፍ/43/ • የማዕድን ወይም የነዳጅ መብትን ማስተላፍ የሚቻል ቢሆንም መብቱ ሲተላለፍ የሚከተሉት መሟላት አለባቸው፡ - ባለፈቃዱ ወይም ሾል ተቋራጩ መብቱ ከሚተላለፍለት ሰው ጋር “የማስተላለፍ ስምምነት” ተብሎ የሚጠቀስ የጹሁፍ ስምምነት ማድረግ አለባቸው፡፡ - ለሚተላለፈው መብት የሚከፈለው ዋጋ፣  መብት የተላለፈለት ሰው ሊከፍል የተስማማበትን ወጪ እና  ባለፈቃዱ ወይም ሾል ተቋራጩ ካስቀረው የተወሰነ መብት የሚመነጩ ግዴታዎችን መብቱ የተላፈለት ሰው መብት አስተላላፊውን ተክቶ ለመወጣት የሚገባውን ግዴታ ለመፈጸም የሚያወጣውን ወጪ የሚጨምር መሆን አለበት፡፡ 54 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 55. • የማዕድንና የነዳጅ መብትን ማስተላለፍ ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ፡- - መብት አስተላላፊው ካስቀረው መብት ጋር በተያያዘ መብት የተላለፈለት ሰው የሚያከናወነው ሾል ዋጋ መብት አስተላላፊው ለተላለፈው መበት በተቀበለው ዋጋ ውስጥ ወይም በመብት አስተላላፊው የንግድ ሾል ገቢ ውስጥ አይካተቱም፡፡ - መብት አስተላላፊው ከተላለፈው መብት ጋር በተያያዘ ላወጣው ወጪ ያገኘው ተቀናሽ ተመላሽ እንደተደረገ ወጪ ተቆጥሮ በአንቀጽ 73 /የተመለሰ ወጪ- የሚያካክስ የገንዘብ መጠን የተቀበለ እንደሆነ/ መሰረት ገንዘቡን በተቀበለበት የግብር ዓመት እንደተገኘ ገቢ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ - አንቀጽ 73 ተፈጻሚ የሚሆበት ተቀናሽ ወጪ መብት አስተላላፊው ከተቀበለው የገንዘብ መጠን የበለጠ እንደሆነ በብልጫ የታየው ገንዘብ የተላለፈው መብት ዋጋ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ 55 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 56. ሠ/ የማዕድን ወይም የነዳጅ መብትን በተዘዋዋሪ መንገድ ስለማስተላለፍ /44/ • የባለፈቃዱ ወይም የስራ ተቋራጩ ድርጅት ዋና ባለቤትነት ከ10% በላይ ከተለወጠ ባለፈቃዱ ወይም ሾል ተቋራጩ ለውጡን ለባለስልጣኑ ወዲያወኑ በጹሁፍ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ • ከላይ የተገለጸውን ማስታወቂያ የመስጠት ግዴታ ያለበት የመብት አስተላላፊ የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ እንደሆነ ባለፈቃዱ ወይም ሾል ተቋራጩ /ፈቃድ የተሰጠው ማለት ነው/ በኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆነው የመብት አስተላላፊ ወኪል እንደሆነ ተቆጥሮ ከመብት ማስተላለፉ ጋር ተያይዞ በዚህ አዋጅ መሰረት ሊከፈል የሚገባውን ግብር የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡ • ከላይ በተገለጸው ሁኔታ በባለፈቃዱ ወይም በስራ ተቋራጩ የኢትዮጰያ ነዋሪ ያልሆነውን የመብት አስተላላፊ በመወከል የተከፈለ ማንኛውም ግብር ከመብት አስተላላፊው (ነዋሪ ካልሆነው ሰው) ላይ ከሚፈለገው የታክስ ዕዳ ጋር ይካካሳል፡፡ • ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል በማዕድን ወይም በነዳጅ ሾል በተሰማራ አንድ ድርጅት ውስጥ ያለ የአባልነት ጥቅም እንደ ንግድ ሾል ሃብት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ 56 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 57. ክፍል ስምንት ዓለም አቀፍ ግብር 1. በውጭ አገር የተከፈለን የንግድ ሾል ገቢ ስለማካካስ (45) • ዓለም አቀፍ ግብር እንዲከፍሉ የሚወሰንባቸው የኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ከኢትዮጵያ ውጪ ከሆነ የገቢ ምንጭ የንግድ ሾል ገቢ ያገኙ እንደሆነ ነው፡፡ ምክንያቱም ከኢትዮጰያ ውጪ በተገኘ ገቢ ላይ ግብር የመክፈል ግዴታ በአዋጁ የተጣለው የኢትዮጵያ ነዋሪ በሆኑ ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡ • በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው በውጭ አገር ካገኘው የንግድ ሾል ገቢ ላይ የውጭ አገር ግብር የከፈለ እንደሆነ በውጭ አገር የከፈለው የንግድ ሾል ገቢ ግብር የሚካካስለት ሲሆን የሚካካሰው ግብር ከሚከተሉት ከአነስተኛው አይበልጥም፡- - በውጭ አገር ከተከፈለው ገቢ ግብር - በውጭ አገር በተገኘው ገቢ ላይ በዚህ አዋጅ መሰረት ሊከፈል ከሚገባው የንግድ ሾል ገቢ ግብር፡- • ከውጭ አገር በተገኘው ገቢ ላይ በዚህ አዋጅ መሰረት ሊከፈል የሚገባው የንግድ ሾል ገቢ ግብር የሚሰላው የውጭ አገር ገቢ በተገኘው ግብር ላይ ተፈጻሚ የሚሆነውን የንግድ ሾል ገቢ ግብር መጠኔ በመጠቀም ነው፡፡ 57 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 58. • በዚህ አንቀጽ መሰረት በውጭ አገር የተከፈለ ግብር ሊካካስ የሚችለው፣ - ግብር ከፋዩ ሊከፈል የሚገባውን ግብር ገቢው ከተገኘበት የግብር ዓመት ቀጥሎ ባሉት ሁለት የግብር ዓመታት ወይም ደግሞ ባለስልጣኑ በሚፈቅደው ተጨማሪ ጊዜ ውስጥ የከፈለ እንደሆነና - ግብር ከፋዩ በውጭ አገር ለከፈለው ግብር ከውጭ አገር የታክስ ባለስልጣን የተሰጠ ደረሰኝ ያለው እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ • በውጭ አገር ለተከፈለ ግብር የተፈቀደ ማካካሻ ከሌሎች ማናቸውም የግብር ማካካሻዎች አስቀድሞ ተግባራዊ መደረግ አለበት፡፡ • በአንድ የግብር ዓመት ተካክሶ ያላለቀ የውጭ አገር ግብር ወደ ሌሎች የግብር ዓመታት አይሸጋገርም ፡፡(Loss Cary forward or Loss Cary back ward አይፈቀድም፡፡) • የተጣራ የውጭ አገር ገቢ ነው የሚባለው፣ - በአንድ የግብር ዓመት ውስጥ ግብር ከፋዩ ካገኘው ጠቅላላ የውጭ አገር ገቢ ላይ የሚከተሉት ተቀንሰው የሚገኘው ገቢ ነው፡፡  የውጭ አገር ገቢውን ለማግኘት ሲባል ብቻ የተደረገ ወጪ፡  የውጭ አገር ገቢ ራሱን የቻለ የገቢ ዓይነት ሆኖ የሚመደብ በመሆኑ የውጭ አገር ገቢውን ለማግኘት በወጣው መጠን በዚህ አዋጅ አንቀጽ 76 መሰረት ተከፋፍሎ የተመደበ ወጪ፡ 58 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 59. 2. የውጭ አገር የንግድ ሾል ኪሳራዎች • ግብር ከፋዩ በውጭ አገር ያገኘውን ገቢ ለማግኘት ያወጣው ወጪ ተቀናሽ የሚደረገው በውጭ አገር ካገኘው ገቢ ላይ ብቻ ነው፡፡ • በግብር ዓመቱ በውጭ አገር ያጋጠመውን ኪሳራ ግብር ከፋዩ ከሚቀጥለው የግብር ዓመት በተገኘ ገቢ ላይ በማካካስ በሰንጠረዠ “ሐ” መሰረት ተቀናሽ ይደረግለታል፡፡ • በሚቀጥለው የግብር ዓመት ተቀናንሶ ያላለቀ ኪሳራ እስከሚቀጥሉት አምስት የግብር ዓመታት ድረስ ሊሸጋገርና ሊቀናነሱ ይችላሉ፡፡ ከአምስት ዓመት በላይ የውጭ አገር ኪሳራን ማሸጋገርና ማቀናነስ ወይም ማካካስ አይፈቀድም፡፡ • ወደሚቀጥሉት የግብር ዓመታት ማሸጋገር የሚቻለው የሁለት ግብር ዓመታት ኪሳራ ብቻ ነው፡፡ • የውጭ አገር ኪሳራ ስለሚሸጋገርበት ዝርዝር ሁኔታ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ያወጣል፡፡ /410/2009 አ.42/ • በውጭ አገር የደረሰ ኪሳራ የሚባለው በሰነጠረዥ “ሐ” መሰረት ግብር የሚከፈልበት የውጭ አገር ገቢ ለማግኘት ግብር ከፋዩ ያወጣቸው ወጪዎች መጠን ከጠቅላላው የውጭ አገር ገቢ በልጦ ሲገኝ ነው፡፡ 59 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 60. 3. ለኩባንያ ካፒታል የሚወሰድ ብድር (Thin capitalization) /47/ • በውጭ አገር ባለአክሲዮኖች ቁጥጥር ሾር ያለና በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ኩባንያ የግብር ዓመቱ አማካይ ዕዳ ከአማካይ የካፒታል መዋጮው ጋር ሲነጻጸር ከ2ለ1 ሬሽዮ የበለጠ እንደሆነ ኩባንያው ከዚህ ሬሽዮ በላይ በሆነው ዕዳ የከፈለው የወለድ ክፍያ ወጪ አይቀነስለትም፡፡ • ሆኖም በውጭ ባለአክሲዮኖች ቁጥጥር ሾር ያለው ኢትዮጵያዊ ኩባንያ አማካይ ዕዳ እና አማካይ የካፒታል መዋጮ ከ2ለ1 ሬሽዮ ቢበልጥም የኩባንያው የግብር ዓመቱ አማካይ ዕዳ ግንኙነት ከሌላቸው ሰዎች ከተወሰደው ዕዳ የማይበልጥ ከሆነ ከላይ የተመለከተው ገደብ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ • ከላይ የተመለከቱት በኢትዮጵያ በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት ባለው የኢትዮጵያ ነዋሪ ባልሆነ ሰው ላይም ተፈጻሚ የሚሆኑ ሲሆን በዚህ ጊዜ፡- - ኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት በውጭ አገር ባለአክሲዮኖች ቁጥጥር ሾር እንዳለ ኩባንያ ሆኖ ይቆጠራል፡ - በቋሚነት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራው ድርጅት አማካይ ዕዳና አማካይ የካፒታል መዋጮ የሚሰላው፡- 60 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 61.  በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ኩባንያ በቋሚነት ለሚሰራ ድርጅት ለማዋል የወሰደው ብድር፣ እና  በኢትዮጰያ ነዋሪ ያልሆነው ኩባንያ በቋሚነት ለሚሰራው ድርጅት መንቀሳቀሻ የመደበው ወይም ያዋለው የካፒታል መዋጮ ከግምት ውስጥ ገብቶ ነው፡፡ • “ግንኙነት ከሌላቸው ሰዎች የተወሰደ ዕዳ” ማለት በውጭ አገር ባለአክሲዮኖች ቁጥጥር ሾር የሚገኘውን ኢትዮጰያዊ ኩባንያ በሚመለከት አንድ የፋይናንሰ ተቋም ኩባንያው የሚገኝበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ግንኙነት በሌላቸው ሰዎች መካከል በሚደረግ ግብይት ዓይነት ሊያበድረው የሚችል ገንዘብ ነው፡፡ • ለምሳሌ አንድ መቶ ሚሊዮን ካፒታል ያለውንና በኢትዮጵያ የሚገኘውን ኩባንያ 50% የአክሲዮን ባለቤትነት የተቆጣጠረ የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ የውጭ ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ኩባንያ ሦስት መቶ ሚሊዮን ዶላር በወለድ ቢያበድረው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ተበዳሪ ኩባንያ በብድር በተሰጠው ሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር ላይ የከፈለውን ወለድ ተቀናሽ ማድረግ የሚችል ሲሆን በቀሪው አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላረ ላይ የከፈለው ወለድ ግን ተቀናሽ ሊደረግለት አይችልም፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ኩባንያ ይህን ብድር ግንኙነት ከሌለው የፋይናንሰ ተቋም መበደር የሚችል መሆኑን ማስረዳት ከቻለ በብድሩ ላይ የከፈለው ወለድ በሙሉ ሊቀነስለት ይችላል፡፡ 61 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 62. 4. ግብርን በሚመለከት የሚደረጉ ስምምነቶች (tax treaties) /48/ • ግብርን የሚመለከቱ ስምምነቶች ከውጭ አገር መንግስት ወይም መንግስታት ጋር የሚደረጉት በሚኒስቴሩ ነው፡፡ • የሚከተሉትን ሳይጨምር በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጻሚነት ባለው የግብር ስምምነት የውል ቃላትና በዚህ አዋጅ መካከል አለመጣጣም የተፈጠረ እንደሆነ የስምምነቱ ድንጋጌ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡ - በተዋዋይ አገር ነዋሪ ያልሆነ ሰው ከ50% በላይ ባለቤት የሆነበት ድርጅት የታክስ ነጻ መብትን በሚያሰጥና የግብር ማስከፈያ መጣኔ ቅነሳን በሚያስከትል የግብር ስምምነት ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም የሚለውን ንዑስ አንቀጽ 3 ሳይጨምር፡፡ - ከግብር ለመሸሽ የሚደረግን ጥረት ስለመከላከል የሚደነግገውን ክፍል ስምንት ሳይጨምር፡፡ • በተዋዋይ አገር ነዋሪ ባልሆነና ከ50% በላይ የአክሲዮን ባለቤትነት ባለው ሰው ቁጥጥር ሾር ያለ ድርጀት ቢሆንም የሚከተሉት ሁኔታዎች ከተሟሉ በታክስ ስምምነቱ ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡- 62 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 63. - የተዋዋይ አገር ነዋሪ ባልሆነ ሰው ከ50% በላይ በባለቤትነት የተያዘው ድርጀት በተዋዋዩ አገር የአክሲዮን ገበያ ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ኩባንያ ከሆነ ወይም፣ - በተዋዋዩ አገር በሚገባ የሚንቀሳቀስ የንግድ ሾል ላይ የተሰማራ እንደሆነና በኢትዮጵያ ለተገኘው ገቢ ምንጭ የሆነው ይኽው የንግድ ሾል የሆነ እንደሆነ፡፡ • “በሚገባ የሚንቀሳቀስ የንግድ ስራ” የሚለው ቃል ኩባንያው የገንዘብ ተቋም ወይም የኢንሹራንስ ኩባንያ ካልሆነ በስተቀር የአክሲዮን፣ የዋስትና ሰነዶች ወይም የሌሎች ኢቨስትመንቶች ባለቤት መሆንን ወይም ማስተዳደርን አይጨምርም፡፡ • “የግብር ስምምነት” ማለት ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረትና ታክስ ላለመክፈል የሚደረግን የግብር ስወራ (Tax Evasion) ለመከላከል የሚደረግ ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው፡፡ 63 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 64. ክፍል ስምንት የሰንጠረዥ “መ” ገቢ ግብር (ሌሎች ገቢዎች) /51-64/ 1. በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች ገቢ • በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያገኘው፡- - የትርፍ ድርሻ ገቢ ላይ 10% - የወለድ ገቢ ላይ 10% - የሮያልቲ ገቢ ላይ 5% - የስራ አመራር ክፍያ ላይ 15% - የቴክኒክ አገልግሎት ክፍያ ላይ 15% - የመድን አርቦን ላይ 5% ግብር ይከፍላል፡፡ • በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ከላይ የተገለጹትን ገቢዎች ያገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት የሚሰራ ድርጀት ከሚያናውነው የንግድ ሾል የሆነ እንደሆነ ተፈጻሚ የሚሆነው በሰንጠረዥ “ሐ” የተመለከተው የንግድ ትርፍ ግብር ወይም እንደሁኔታው በሰንጠረዥ ”መ” የተመለከቱት ሌሎች መጣኔዎች ናቸው፡፡ 64 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 65. 2. በሚተካ የቴክኒክ አገልግሎት ክፍያና ሮያልቲ ላይ ስለሚከፈል ግብር • በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት ሳይሆን በራሱ የቴክኒክ አገልግሎት ወይም የመሳሪያ ኪራይ (ሊዝ) አገልግሎት - ከኢትዮጵያ ውጪ ያለውን በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት ሳይጨምር የኢትዮጰያ ነዋሪ ለሆነ ሰው ወይም ኢትዮጰያ ውስጥ በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት የኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆነ ሰው የሰጠ እንደሆነ እና - የቴክኒክ አገልግሎቱ ወይም የሮያልቲ ክፍያ የተከፈለው ከአገልግሎት ተቀባዩ ጋር ግንኙነት ባለው የኢትዮጵያ ነዋሪ ባልሆነ ሰው ከሆነ፣ እንዲሁም - ክፍያውን የፈጸመው ከአገልግሎት ተቀባዩ ጋር ግንኙነት ያለው ሰው የቴክኒክ አገልግሎት ወይም የሮያልቲ ክፍያውን ከአገልግሎት ተቀባዩ መልሶ የጠየቀ እንደሆነ፣ ግንኙነት ያለው ሰው ለአገልግሎት ተቀባዩ የቴክኒክ አገልግሎቱን ወይም የመሳሪያውን ሊዝ አገልገሎት እንደሰጠና የተተካው ገንዘብ ለቴክኒክ አገልግሎቱ ወይም ለማሳሪያው ሊዝ የተከፈለ ክፍያ እንደሆነ ተቆጥሮ የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ 65 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 66. ለምሳሌ፡- የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ የእንግሊዝ ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖር ኩባንያ የቴክኒክ አገልግሎት ቢሰጥና የአገልግሎት ዋጋውን ጣሊያን አገር ከሚገኘውና በኢትዮትያ ኩባንያ ውስጥ 60% የአክሲዮን ድርሻ ካለው ነዋሪ ያልሆነ ኩባንያ ቢቀበል የጣሊያኑ ኩባንያ የአገልግሎት ዋጋውን የኢትዮጵያው ኩባንያ እንዲተካለት በሚጠይቅበት ጊዜ የጣሊያኑ ኩባንያ ለኢትዮጰያ ኩባንያ አገልግሎቱን ልሹ እንደሰጠ ተቆጥሮ ግብሩ ከክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረግበታል ማለት ነው፡፡ 66 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 67. 3. በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ የመዝናኛ አገልግሎት ሰጪዎች ግብር • በኢትዮጵያ ውስጥ የመዝናኛ አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ወይም ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ባገኘው ጠቅላላ ገቢው ላይ 10% ግብር ይከፍላል፡፡ • ከመዝናኛ አገልግሎቱ በሚገኘው ገቢ ተጠቃሚው አዝናኙ ሳይሆን ሌላ ሰው የሆነ እንደሆነ ይህ ሰው በሚያገኘው ጠቅላላ ገቢ ላይ ከላይ የተጠቀሰውን ግብር ይከፍላል፡፡ 4. ሮያልቲ • በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው ሮያልቲ ያገኘ እንደሆነ በጠቅላላው የሮያልቲ ክፍያ ላይ 5% ግብር ይከፍላል፡፡ • የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው በቋሚነት የሚሰራ ድርጅት አማካኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ የሮያልቲ ገቢ ያገኘ እንደሆነ በጠቅላላ የሮያልቲ ክፍያው ላይ ከላይ የተመለከተውን ግብር ይከፍላል፡፡ 67 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 68. 5. የትርፍ ድርሻ • በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው የትርፍ ድርሻ ያገኘ እንደሆነ በጠቅላላው የትርፍ ድርሻ ገቢ ላይ 10% የገቢ ግብር ይከፍላል፡፡ • በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ የትርፍ ድርሻ ገቢ ያገኘ እንደሆነ በጠቅላላ የትርፍ ድርሻው ላይ 10% ገቢ ግብር ይከፍላል፡፡ /ሲልክ/ 6. ወለድ • በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው በገንዘብ ተቋማት ገንዘቡን በቁጠባ አስቀምጦ በሚያገኘው ጠቅላላ ወለድ ላይ 5% ግብር ይከፍላል፡፡ • በሌላ በማናቸውም ሁኔታ በሚያገኘው ጠቅላላ ወለድ ላይ 10% ግብር ይከፍላል፡፡ • ከላይ የተመለከቱት የግብር መጣኔዎች በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት በሁለቱ ሁኔታዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ባገኘው ወለድ ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ 68 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 69. 7. ከዕድል ሙከራ የሚገኝ ገቢ • በኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረጉ የዕድል ሙከራዎች ተሳትፎ ገቢ ያገኘ ሰው ባሸነፈው ጠቅላላ ገቢ ላይ 15% የገቢ ግብር ይከፍላል፡፡ • ግብር ከፋዩ የዕድል ሙከራውን ሲያደርግ የደረሰበት ኪሳራ ቢኖር ተቀናሽ አይደረግም፡፡ • በዕድል ሙከራ የተገኘው ገንዘብ ከ1000 ብር በታች ከሆነ ግብር አይከፈልበትም፡፡ 8. ሃብትን አልፎ አልፎ በማከራየት የሚገኝ ገቢ • በኢትዮጵያ ውስጥ አልፎ አልፎ ሃብት (መሬት፣ቤት፣ የሚንቀሳቀስ ሃብት) በማከራየት በሚገኝ ጠቅላላ ገቢ ላይ 15% ገቢ ግብር ይከፈላል፡፡ • የሮያልቲ ግብር በሚከፈልበት ሃብት ላይ ይህ ግብር ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ 69 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 70. 9. የካፒታል ሃብቶችን በማስተላፍ ከሚገኝ ጥቅም የሚከፈል ግብር • የማይንቀሳቀስ የካፒታል ሃብት በማስተላለፍ በሚገኝ ጥቅም ላይ 15% የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር ይከፈላል፡፡ • አክሲዮን ወይም ቦንድ በማስተላለፍ በሚገኝ ጥቅም ላይ 30% የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር ይከፈላል፡፡ • ግብር የሚከፈልበትን ሃብት በማስተላለፍ የሚገኘው ጥቅም ሃብቱን በማስተላለፍ የተገኘው ዋጋ ሃብቱ በተላለፈበት ጊዜ ከነበረው ዋጋ በልጦ የተገኘው የገንዘብ መጠን ነው፡፡ • በግብር አመቱ ውስጥ ግብር የሚከፈልበትን ሃብት በማስተላለፍ የሚደርስ ኪሳራ በዚያው የግብር ዓመት ተመሳሳይ ሃብት በማስተላለፍ ከተገኘው ገቢ ጋር ብቻ እንዲቻቻል ይደረጋል፡፡ ኪሳራው ከሌላ ገቢ ጋር አይካካስም፡፡ • በዚህ ሁኔታ ያልተካካሰ ኪሳራ ላልተወሰነ ጊዜ ይሸጋገራል፡፡ 70 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 71. • ግንኙነት ባላቸው ሰዎች መካከል በተደረገ የካፒታል ሃብት ማስተላለፍ የሚደርስ ኪሳራ አይካካስም፡፡ • የካፒታል ሃብትን በማስተላለፍ የሚደርስ ኪሳራ ሊካካስ የሚችለው ግብር ከፋዩ የደረሰበትን ኪሳራ ባለስልጣኑን በሚያሳምን መንገድ ማስረዳት የቻለ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ • ግብር የሚከፈልበትን የካፒታል ሃብት በማስተላለፍ ደረሰ የሚባለው ኪሳራ ሃብቱ በተላለፈበት ጊዜ ለሃብቱ የወጣው ወጪ ሃብቱ ከተላለፈበት ዋጋ በልጦ የተገኘው ዋጋ ነው፡፡ • የተላለፈው ሃብት የንግድ ሾል ሃብት ሲሆን አንቀጽ 35 ተፈጻሚ ይሆናል (በተጣራ መዝገብ ዋጋውና ለሃብቱ በወጣው ወጪ መካከል ያለው ልዩነት ወደ ንግድ ሾል ገቢ ተወስዶ ይደመራል፡፡) 71 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 72. 10. ንፋስ አመጣሽ ትርፍ • ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ ከተመለከቱት የንግድ ስራዎች በሚገኝ ንፋስ አመጣሽ ትርፍ ላይ በመመሪያው በተመለከተው የማስከፈያ መጣኔ (ልክ) ግብር ይከፈልበታል፡፡ • ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ፡- - ነፋስ አመጣሽ ትርፍ ነው ሊባል የሚችለውን የገቢ መጠን፡፡ - ግብሩ የሚመለከታቸውን የንግድ ስራዎች አይነት፡፡ - ግብሩን ለማስከፈል የወጣው መመሪያ ሾል ላይ የሚውልበትን ቀን፡፡ - የግብር አወሳሰኑን ዘዴና ለግብሩ አወሳሰን መሰረት የሚሆኑ ታሳቢዎችን ይወሰናል (እንዲወስን ስልጣን ተሰጥቶታል)፡፡ • ለተለያዩ የንግድ ስራዎች የሚወሰነው የነፋስ አመጣሽ ትርፍ መጠንና የግብር ማስከፈያ መጣኔውም የተለያየ እንዲሆን ሚኒስትሩ ሊወሰን ይችላል፡፡ • “ንፋስ አመጣሽ ትርፍ” ያለልፋት (ያለጥረት፣ ያለተጨማሪ ወጪ ወዘተ) የሚገኝ ያልተጠበቀ ወይም ሌላ ተደጋግሞ የማይገኝ ትርፍ ነው፡፡ 72 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 73. 11. ያልተከፋፈለ ትርፍ • በአንድ የግብር ዓመት ግብር ከተከፈለ በኋላ ለአባላቱ ያልተከፈለ እና መልሶ ኢንቨስት ያልተደረገ የተጣራ የድርጅት ትርፍ 10% ግብር ይከፈልበታል፡፡ 12. በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት ወደ ውጭ የሚላክ ትርፍ • በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት በሚሰራ ድርጀት አማካኝነት የንግድ ሾል የሚያከናውን በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው በቋሚነት ከሚሰራ ድርጅት በሚላክለት ትርፍ ላይ 10% ግብር ይከፈልበታል፡፡ • አፈጻሙ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ የሚወሰን ይሆናል፡፡ 13. ሌሎች ገቢዎች • በሰንጠረዥ “ሀ” ፣ “ለ”፣ “ሐ” እና በሰንጠረዠ “መ” ሌሎች ድንጋጌዎች የማይሸፈን ገቢ ያገኘ ማንኛውም ሰው በጠቅላላ ገቢው ላይ 15% ግብር ይከፍላል፡፡ 73 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 74. 14. ለሰንጠረዥ “መ” የሚያገለግሉ የወል ድንጋጌዎች • በሰንጠረዥ “መ” መሰረት የሚጣል ግብር በሌሎች ሰንጠረዦች ግብር በሚከፈልበት ገቢ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ • የሰንጠረዥ “መ” ግብር የመጨረሻ ግብር ነው፡፡ • አብዛኛው የሰንጠረዥ “መ” ግብር የሚወሰነው በጠቅላላ ገቢው ላይ ነው፡፡ • በሰንጠረዥ “መ” መሰረት ግብር የሚከፈልበት የውጭ አገር ገቢ ያገኘ ሰው በውጭ አገር የከፈለውን ግብር እንዲያካክስ ይፈቀድለታል፡፡ • ሆኖም ተካክሶ ተቀናሽ ያልተደረገ በውጭ አገር የተከፈለ ግብር ወደኋላም ሆነ ወደፊትም አይሸጋገርም፡፡ • ግብሩን ቀንሶ የመያዝ ኃላፊነት ያለበት ሰው ግብሩን ቀንሶ ያስቀረ እንደሆነ የሰንጠረዥ “መ” ግብር ከፋይ ግብሩን እንደከፈለ ይቆጠራል፡፡ 74 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 75. ክፍል ዘጠኝ /ይህን ክፍል በማንበብ አዳብሩ/ የወል ድንጋጌዎች /66-77/ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት የወል (common) ድንጋጌዎች ለሁሉም የግብር ሰንጠረዦችና የግብር ዓይነቶች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡ 1. ሃብት ስለማግኘት (66) • አንድ ሰው ሃብት አገኘ (የሃብት ባለቤት ሆነ) የሚባለው የሃብቱ ባለቤትነት(ownersip tittle) በስሙ ከተላለፈበት ወይም በስሙ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ • ሃብቱ መብት ወይም ምርጫ በሚሆንበት ጊዜ ሃብቱ ተላለፈ የሚባለው መብቱ ወይም ምርጫው በተሰጠበት ቀን ነው፡፡ 2. ሃብት ስለማስተላለፍ (67) • አንድ ሰው ሃብቱን አስተላለፈ የሚባለው ሃብቱን ሲሸጥ ሲለውጥ ወይም በሌላ ማናቸውም መንገድ በሃብቱ ላይ ያለውን የባለቤትነት መብት ሲያስተላልፍ ነው፡፡ • አንድ ሰው፡- - በሃብቱ ላይ ያለው ባለቤትነት ከመዝገብ እንዲሰረዝ ካደረገ፣ - ሃብቱን ለቀድሞው ባለቤቱ እንዲመለስ ካደረገ፣ - ሃብቱ ከጠፋ ወይም ከወደመ፣ 75 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 76. - የመብት መጠቀሚያ ጊዜው እንዲያልፍ ካደረገ፣ - ለሌላ ሰው ሃብቱን ከሰጠ ወይም እንዲሰጥ ካደረገ፣ - ሃብቱን አስተላለፈ ማለት ይሆናል፡፡ • አንድ ሰው ሌላን ሰው አስቀድሞ ያልነበረውን ሃብት እንዲኖረው ያደረገ እንደሆነ ይህን ያደረገው ሰው ሃብቱ በተፈጠረበት ጊዜ በባለቤትነቱ ስም የነበረውን ሃብት ለሁለተኛው ሰው እንዳስተላለፈ ይቆጠራል፡፡ • ሃብት በውርስ ወይም በኑዛዜ የተላለፈ እንደሆነ ሃብቱ በተላለፈበት ጊዜ ሟች ሃብቱን እንዳስተላለፈ ይቆጠራል፡፡ • ሃብትን ማስተላለፍ የአንድን የንግድ ሾል ሃብት የተወሰነ ክፍል ማስተላለፍን ይጨምራል፡፡ • አንድን ሃብት ለንብረት አጣሪ፣ በኪሳራ ሂደት ለተሰየመ ባለአደራ ወይም ለተቀባይ (ለንብረት አስተዳዳሪ) መስጠት ሃብቱን እንደተላለፈ አያስቆጥረውም ፡፡ ስለሆነም ከዚሁ ሃብት ጋር በተያያዘ በአጣሪው፣ በባለአደራው ወይም በተቀባዩ የሚከናወኑ ተግባራት በሙሉ ባለቤቱ እንዳከናወናቸው ይቆጠራሉ፡፡ 76 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy
  • 77. 3. ለሃብት የሚደረገ ወጪ (68) • የአንድን ሃብት ወጪ ማወቅ የሚያስፈልገው ለእርጅና ቅናሽ መሰረት የሚሆነውን ወጪ ለመወሰንና ሃብቱ ሲተላለፍ የሚገኘውን ጥቅም ወይም የኪሳራ መጠን ለመወሰን እንዲቻል ነው፡፡ • የአንድ ዋጋው የሚቀንስ ሃብት (depreciable asset) ወጪ የሚከተሉት ድምር ይሆናል፡፡ - ሃብቱ በተገኘበት ጊዜ በዓይነት የተሰጠ ሃብት ትክክለኛ የገበያ ዋጋን ጨምሮ ባለሃብቱ ለሃብቱ የከፈለው ጠቅላላ ዋጋ፣ - ሃብቱ የተገኘው በመገንባት፣ በማምረት ወይም በማልማት የሆነ እንደሆነ ለግንባታ፣ ለማምረት ወይም ለማልማት የወጣው ወጪ፣ - ሃብቱን በማግኘት ወይም በማስተላለፍ ሂደት የወጣ ማንኛውም ወጪ፣ - ሃብቱን ለመትከል፣ ለመቀየር፣ ለማደስ፣ መልሶ ለመገንባት ወይም ለማሻሻል ባለሃብቱ ያወጣው ማንኛውም ወጪ፡፡ 77 23/02/2015 E.C Mahlet Amde, Director , Risk and compliance strategy