Advertisement
Belayneh Rwanda Trip Memo
Belayneh Rwanda Trip Memo
Belayneh Rwanda Trip Memo
Belayneh Rwanda Trip Memo
Advertisement
Belayneh Rwanda Trip Memo
Upcoming SlideShare
April youth Peace Ambassador 1.pdfApril youth Peace Ambassador 1.pdf
Loading in ... 3
1 of 5
Advertisement

Belayneh Rwanda Trip Memo

  1. 1 የሩዋንዳ ቆይታይና የተማርኩት ሩዋንዳ ከምስራቅ አፍርካ ሀገራት ውስጥ አንዷ ናት፤ ልክ እንደ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ሀገር ስትሆን አብዛኛውን መልከዓ ምድሯ ተራራማ ቦታ ሲሆን “የሺህ ኮረብቶች ምድር” በመባል ትታወቃለች፡፡ ከአፍሪካ ታላላቅ ሀይቆች አንዱ በሆነው ከምድር ወገብ በስተደቡብ እና ከኪቩ ሀይቅ በስተምስራቅ የምትገኝ በመካከለኛው አፍሪካ ያለች ትንሽ ወደብ የለሽ፣ ኮረብታማ አገር ነች። እኔ ከተወለድኩበት ታላቁ የስምጥ ሸለቆ የምዕራብ ጫፍ ላይ የምትገኝ በሰሜን ከኡጋንዳ፣ በምስራቅ ከታንዛኒያ፣ በደቡብ ከብሩንዲ፣ በምዕራብ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (ኪንሻሳ) እና ከኪቩ ሀይቅ ትዋሰናለች። አገሪቷ 26,338 ኪሜ² ስፋት ያላት ሲሆን ከሌሎች ሀገሮች አንጻር ስትነጻጸር መቄዶንያ (ሪፐብሊክ) ታክላለች፣ ወይም ደግሞ ከአሜሪካ የሜሪላንድ ግዛት በመጠኑ አነስ ያለች ነች፡፡ እንደ እ.እ 2016 በተገኘ መረጃ መሠረት 11.5 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሲሆን (የሩዋንዳ የህዝብ ብዛት ከሰሃራ በስተደቡብ ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ትልቁ ነው፡፡) ዋና ከተማዋ እና ትልቁ ከተማ ኪጋሊ የምትባል ሲሆን ወደ አንድ ሚሊዩን የሚሆኑ ነዋሪዎች ይገኙበታል፡፡ አብዛኛውን ህዝብ ከሚናገረው ቋንቋዎች መካከል ኪንያርዋንዳ (የሩዋንዳ ኦፊሴላዊ ቋንቋ)፣ እንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ፣ ስዋሂሊ በብዛት ይነገርባታል፡፡ በ1890ዎቹ ጀርመን ሩዋንዳን በቅኝ ግዛት ስር አደረገቻት፡፡ እ.ኤ.አ. በ1916 ፣ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ፣ ጀርመን በእሷ ቀኝ ግዛት ስር የነበረችውን ሩዋንዳን ቤልጂየም በቅኝ እንድትገዛት ፈቀደችላት። በመቀጠልም ቤልጂየም ለአገዛዝ እንዲመቻት እያንዳንዱን ሰው ሁቱ(84%)፣ ቱትሲ(15%)፣ ትዋ(1%) በማለት በመከፋፈል ለሁሉም ዜጎች የብሔር መታወቂያ ካርዶችን አዘጋጅታ ለህዝቡ ሰጥታለች። በመቀጠልም ቤልጂየሞች ቱትሲዎችን ሁሉንም የመንግስት ቦታዎች እንዲይዙ እና በሁቱዎች ላይ የበላይ ሆነው እንዲገዙ ወሰኑ፤ ይህም በሁለቱ ቡድኖች(ብሔረሰቦች) መካከል ከፍተኛ ውጥረት ፈጠረ። ቱትሲዎች ከሁቱዎች ተለይተው የተመረጡበት ምክንያት ተብሎ የሚታሰበት ቤልጂይማውያኑ ቱትሲዎቹን በረዥሙ እና ከላቁ የሰውነት ቅርጻቸው የበለጠ “አውሮፓውያን” እንደሚመስሉ ያምኑ ስለነበረ ነው። ይህ ዘዴ በአውሮፓ ሀገራት በያዙት ሀገራት ላይ ልዩነት በመፍጠር ህዝቡን በመከፋፈል ለረዥም ጊዜ ለመግዛትና ሀገሪቱን በራሳቸው ሰው ከመምራት ይልቅ፣በእነዚህ ምስለኔ የሀገሪቱ ዜጎች ማስተዳደሩ መልካም መሆኑን ስለተረዱና አዋጭ መሆኑን ስለተገነዘቡ ነው፡፡በዚህም የቱትሲ ዘውዳዊ ስርዓተ መንግስት በማቋቋም በሁቱዎች ላይ የበላይ ሆነው እንዲያስተዳድሩ አድርገዋል፡፡ በበላይነህ ዘለለው
  2. 2 ከጊዜ በኋላ ግን ቱትሲዎች ከቤልጅይም ነጻ ለመውጣት እንቅስቃሴ በመጀመራቸው ቤልጅይሞች በዚህ በመናደድ ሁቱዎችን በቱትሲዎች ላይ እንዲነሱባቸው የጥላቻ ዘመቻ ጀምሩ፡፡ ቱትሲዎች እስከ ህዳር 1959 የሁቱ አመፅ እስከጀመረበት ጊዜ ድረስ መንግስትን መምራት ቀጠሉ። ሁቱዎች በፍጥነት ቱትሲዎችን እና የቤልጂየምን አገዛዝ በመገርሰስ በሺዎች የሚቆጠሩ ቱትሲዎችን ገድለው፤የቀሩትን ደግሞ ወደ ጎረቤት ሀገሮች እንዲሰደዱ አደረጎቸው። እ.ኤ.አ. ሐምሌ 1 ቀን 1962 ቤልጂየም ለሩዋንዳ በይፋ ነፃነቷን ሰጠች፤ ይህም አመፁ እንዲቆም አድርጓል። በዚያን ጊዜ ሁቱዎች የመንግስት ስልጣን ተቆጣጥረው ነበሩ፡፡እ.ኤ.አ. በ1959 ከነጻነት 3 ዓመታት በፊት ቀደም ብሎ ፣ አብላጫዉ ብሄረሰብ ሁቱስ ገዢውን የቱትሲ ንጉስ አስወገዱ። በሚቀጥሉት በርካታ ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ቱትሲዎች ተገድለዋል፣በነበረው የእርስ በእርስ ግጭት ከ150,000 ሺ እስከ 300,000 ሺ የሚጠጉ ቱትሲዎች ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል። እ.ኤ.አ. ጥቅምት 26 ቀን 1962 የሁቱ ተወላጅ ግሬጎየር ካይባንዳ የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ። ሁቱዎች በሩዋንዳ ላይ ስልጣን ከመያዛቸው ቱትሲዎችን ማፈናቀላቸውንና መበቀላቸውን ቀጠሉ። እንደ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በ1960ዎቹ አጋማሽ ከመጀመሪያዎቹ ቱትሲዎች ግማሹ ከሩዋንዳ ውጭ ይኖሩ እንደነበር ይገመታል። የእነዚህ ግዞተኞች ልጆች የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር (RPF) የተባለውን አማፂ ቡድን አቋቁመው በ1990 የእርስ በርስ ጦርነት ጀመሩ።ጦርነቱ ከበርካታ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውጣ ውረዶች ጋር፣ በኤፕሪል 1994 ወደ 800,000 የሚጠጉ ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ ሁቱዎችን የዘር ማጥፋት ሰለባ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን የአማፂው ቡድን መፈጠር የዘር ማጥፋቱን ዘመቻውን ያባባሰው። ከእነዚህ ሁሉ ታሪካ በፊት ግን በሩዋንዳ ሦስቱም ማህበረሰቦች በመጋባት፣በመዋላድና በጋራ በመኖር ባህላቸውን ጠብቀው ይኖሩ ነበር፡ ፡ልክ እንደ እኛው ሀገር ሁሉም ብሔረሰቦች አብረው በጋር ጠላቾቻቸው በጋራ በመመከትና በደህናው ጊዜ እርስ በእርስ በመጋባት፣ ግጭቶች ሲኖሩ በባህላዊ ግጭት አፈታት ችግራቸውን በመፍታት በትብብርና ተደጋግፈው ይኖሩ ነበር፡ ፡ይህ ሁኔታው ቢለያይም በሌሎች ሀገሮችም ያለ የሚኖር የማህበረሰብ አኗኗር ዘይቤ ነው፡፡ሰዎች በቡድን ሲኖሩ የተወሰኑት መሪዎች ሌሎቹ ደግሞ ተመሪዎች ይሆናሉ፡፡ነገር ግን ማህበረሰቡ እነዚህ መሪዎች ከየትኛውም የማህበረሰብ ክፍል ቢመጡ ማህበረሰቡ ዋና ሀሳቡ በአግባቡ እየመሩ ነው ወይ?የሚለው ጥያቄ እንጂ ሌላ ሀሳብ የላቸውም፡፡ከዚህ ውጭ ያለው ህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ በጣም ጠንካራ ሲሆን በተለይም በሁቱና ቱትሲዎች መካከል ያለው ግንኙነት በጣም ጠንካራ ነው፡፡አብሮ መጨፈር፣መብላትና መጠጣት፣የባህል ለባህል ልውውጥ ማድረግ ነበር፣ክፋትና መጥፎ አስተሳሰብ ሳይዘራ በፊት በፍቅርና በመተጋገዝ አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ ነገር ግን በሁለቱ ብሄረሰቦች መካከል በደንብ እንዲከፋፈሉ አንዱን ብሄረሰብ በመጥቀም ሌላውን በማግለል ቅራኔ እንዲሰፋ ያደርጋሉ፡፡ አንድን ብሄረሰብ አባላት ወደ ስልጣን በማምጣት ሌላው ብሄረሰብ የተገፋ እንዲመስለው በማድረግ
  3. 3 ጥላቻንና በቀለን እንዲቆጥሩ ጊዜና ሁኔታ ስኪፈጠር እንዲጠብቁ ያደርጋል፡፡ይህ ሁኔታ በሩዋንዳ የታየ ሲሆን በተለይም ቤልጅይሞች ቱትሲዎችን ወደ ስልጣኑና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ሁቱዎች የተገፋ እንዲመስላቸው አድርገዋል፡፡በተመሳሳይ እነዚህን አይነት ሁኔታዎች በኢትዬጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሲተገበር ቆይቷል፡፡በብሄር የተደራጁ ፖርቲዎች የራሳቸውን ብሄር ወደ ስልጣን እንዲመጣና በሰፈር፣ በጎጥ በማምጣት ሌላው ብሄረሰብ የተገፋ ያህል እንዲሰማው የማድረግ ስራ አውቀውትም ይሁን ሳያቁት ሲያደርጉት ነበር፤ እያደረጉት ይገኛል፡፡በዚህ ምክንያት ሁሉም ጊዜውንና ሁኔታዎችን እያየ ይገኛል፤ሁኔታዎች ሲመቻችላቸው ለበቀልና የእኛ ነው የሚሉትን በተመሳሳይ መንገድ ለማድግ ይዘጋጃሉ፡፡ በሩዋንዳ ባየሁት ሁኔታ በቱትሲዎችና ሁቱዎች መካከል ይህ ነው የሚባል ሰፋ ልዩነት ያላቸው ህዝቦች አይደሉም፡፡ለምሳሌ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው የሚጠቀሙት መግባቢያ ቋንቋ አንድ አይነት ነው፡፡እንግዲህ አስቡት እንደ ኢትዮጵያ ባለሀገር የተለያዩ ቋንቋዎችና ባህሎች ባለበት ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን እያየን የመጣነው ነገር ቢኖር እኛ የምንናገረውን ቋንቋ አትናገሩም፣ባህላችሁ ከእኛ ይለያል በማለት ውጥሉን ፤ከእናንተ ጋር ተመሳሳይ ቋንቋና ባህል ካለቸው ክልሎች ወይም ቦታ ሂዱ፣ውጥሉን የሚል ድምጾች እየበዛ ይገኛል፡ ፡በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ብሔረሰብን ማዕከል ያደረገ/ያነጣጠር ጥቃቶችና ግድያዎች በብዛት እያየን ይገኛል፡፡ለእነዚህ ጥቃቶችና ግድያዎች የሚሰጡት ምክንያቶች ልክ እንደ ሩዋንዳው ሁሉ ከዚህ ቀደም ስትበድሉንና ስትጮቅኑን ነበር፣ እኛ ዝቅ/አሳንሳችሁ አድርጋችሁ ነው የምታዩን፣የስልጣን ተቀናቃኝ የምትሆኑት እናንተ ናችሁ፣ስለዚህ ቀድመን እናጥፋችሁ የሚሉና ሌሎች ከሩዋንዳው ጋር ተመሳሳይ ምክንያቶች ይቀርባሉ፡፡ ከእነዚህ በየቦታው ከሚፈጸሙ ጥቃቶች ጀርባ የመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ አመራሮች ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡አብዛኛውን የጥላቻ ንግግሮች የሚመነጩት እና የሚሰራጩት ከመንግስት ሲሆን በየቦታው ያሉት የበታችኛው የአመራር እርከን ላይ ያሉ አመራሮች ደግሞ እነዚህ ጥላቻ ንግግሮች በማሰራጨትና ወጣቱ በጥላቻ ተሞልቶ ጠላቴ ባለው ማህበረሰብ ላይ ጥቃት እንዲፈጽ ይሆናል፡፡ በሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ጄቪናል ሀይኮሚን በ1973 በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ሲመጣ አዲስ አዋጅ አወጣ፤ ይህውም ሀገሪቱ ላይ ያለው የስልጣን ቦታዎች ሀገሪቶ ላይ ያለው የብሄር ስብጥር ሚዛን የጠበቀ መሆን እንዳለበትና ተማሪዎችም ወደ ዩቪርሲቲ ሲመደቡ ከፍተኛው ቦታ አብዛኛውን ቁጥር ላላቸው ሁቱዎች ሲሆን ቀሪው ትንሽ
  4. 4 ቁጥር ደግሞ ቱትሲዎችና ትዋ ብሄረሰቦች እንዲሆን አደረገ፡፡ለዚህ ምክንያቱ ሁቱዎች ብዙሃን ስለሆኑ ከፍተኛው የመንግስት ስልጣን ቦታዎችን መያዝ ያለባቸው እነሱ እንደሆኑ የሚደነግግ አዋጅ ነበር፡፡በተመሳሳይ አሁን ባለው የሀገራችን ፖለቲካ ልክ እንደሩዋንዳው ሁሉ የእኛ ብሄረሰብ አብዛኛውን ቁጥር ያለው ስለሆነ በልካችን የመንግስት ስልጣን እንይዛለን የሚል ሲሆን የዚህ ሀሳብ ዋና አራማጅ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር መሆኑ ደግሞ ሁኔታው በጣም አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡የዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ሊገፊት የፈለጉትን ብሄረሰብ በሀገሩ ላይ ሁለተኛ ዜጋ ማድረግ ነው፡፡እነዚህን የመሰሉ ጥላቻ ንግግሮች መንግስት በፕሮፖጋንዳ መሳሪያ ለህዝብ ያሰራጫል፡፡ባለስልጣናትም የመርዝ ንግግራቸውን በማድረግ አንድን ህዝብ በአንዱ ላይ በማነሳሳት የጥላቻ መርዛቸውን እየነዙ ይታያሉ፡፡ለዚህም ይሾማሉ፣ይሸለማሉ፡፡ በተመሳሳይ በሩዋንዳ እንደነበረው ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ቡድን በማቋቋም በቱትሲ ማህበረሰብ ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ አደራጅተዋቸው እና በመሳሪያ ድጋፍ አድርገው ለብዙሃን ዜጎች ሞት ምክንያት ዋና ተዋናይ ሆነዋል፡፡በተመሳሳይም በሀገራችን እንደምናየው አንድን ማህበረሰብ ለመግደልና ለማፈናቀል የተደራጀ ድርጅት ያለ ሲሆን ላለፊት ጥቂት አመታት በንጹሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡በሩዋንዳ እንደተካሄደው ጥቃት የሚፈጽሙባቸውን የቱትሲ ብሄረሰብ ተወላጆችን በስም ዝርዝር በመያዝ ግድያ እንደፈጸሙት ሁሉ በሀገራችን ውስጥም በተመሳሳይ ጥቃት የሚፈጸምባቸውን ማህበረሰቦችን በስም ዝርዝር በመያዝ ጥቃት ፈጽመዋል፤እየፈጸሙም ይገኛል፡፡ በሩዋንዳ በነበረኝ ቆይታ እያንዳንዱ ጥቃትና ግድያ በአንዴ የተከሰት ሳይሆን በተለያዩ ጊዜቶች የተጀመሩ መለስተኛ ጥቃቶች ናቸው በ1994 ለተከታታይ 100 ቀናቶች 800,000 ሺ በላይ ለሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው፡፡የዚህ አይነት ድርጊትም በሀገራችን እየታየ ይገኛል፡፡ዜጎች በጅምላ ይገደላሉ፤ ጠያቂም ተጠያቂም አካል የለም፤መንግስት ያስተባብላል፤ አንዳንዴም ግድያውን በተለያዩ ምክንያቶች በመስጠት ለማለፍ ይሞክራል፡ ፡ በሩዋንዳ እንደነበረው ሁኔታ አለም አቀፍ ማህበረሰቡም ለዚህ ጉዳይ ጆሮ ዳባ ወይም አይቶ እንዳለየ በዝምታ እያለፈ ሲሆን በሩዋንዳ የታየው እልቂት ሀገራችን ውስጥ ለመከሰት ደረጃው ጠብቆ እየሄደ ይመስላል፡፡ያው ህዝብ
  5. 5 ካለቀ በኋላ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ “Never Again” ወይም “በጭራሽ አይደገምም” የሚል የተለመደ መፈክራቸውን ማሰማቱን ይቀጥላሉ፡፡ ይህ ደግሞ የሚከሰተው መስተካከል በሚችልበት ደረጃ ልክ እንደ ሩዋንዳው እርምጃ ባለመውሰድ በመዘግየት ነው፡፡ ከሩዋንዳ ያገኘሁት ልምድ ቢኖር በተአምር ትኩረትን ከሚስቡ ነገሮች ሰዎች መታቀብ አለባቸው፡፡ለምሳሌ እኛ ሀገር “ጊዜው የእኛ ነው” የሚሉ አመለካከቶችና በተግባር መገለጻቸው የሚያመጡት ጣጣ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነና ሌላው ማህበረሰብ ቅናት እንዲፈጠርበት በማድግ ወደ ጥላቻ እንዲያድግ ምክንያት ይሆናል፡፡ በማንኛውም ምክንያት ሌላው ማህበረሰብ ዝቅ አድርገው/አሳንሰው ነው የሚያዩኝ የሚል አመለካከት እንዳይኖራቸው ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ተበደልኩ የሚለው ማህበረሰብ በቀጣይ ጊዜውን ጠብቆ በዳይ ሆኖ ይመጣል፤በደል በደልን ነው የሚወልደው፡፡ስለሆነም ህዝቦችን የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ በማድረግ፣ በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነታቸው የጠነከረ እንዲሆን ማድረጉ ትልቅ አስተዋጾ ያደርጋል፡፡ ዜጎች የመንግስት አካላትና ግብረ-ዓበሮቻቸው የሚነዙትን የጥላቻ መርዝ ንግግሮችን በጥንቃቄ ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የመንግስት አመራሮች ጊዜዊ ጥቅማቸውን ብቻ ሳይሆን ሀገር ከማስቀጠል አኳያ ነገሮችን ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡አሁን እየጠፋ ያለው የንጹሀን ዜጎች ሞት ነገ ተጠያቂ እንደሚያደርግና ብዙ እንደሚያስከፍል ተረድተው፤ከዚህ ባህሪያቸው መውጣት አለባቸው የሚል አስተያየት አለኝ፡፡ በሀገር ውስጥ ያለው ዜጋም ቢሆን እራሱን አደራጅቶ መብቱን ማስከበርና የሌላው ህዝብ ጉዳይ የእኛም ጉዳይ እንደሆነ በማሰብ በጋራ መቆም ይጠበቅበታል፡፡የሩዋንዳው አይነት ድርጊት ሟችን ብቻ ሳይሆን ገዳይንም የጎዳው ስለሆነ ከዚህ ትምህርት ወስደን በቂ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ አለም አቀፍ ማህበረሰቡም ዘርን ያነጣጠር ግድያዎችን ሲያይ ዝም ከማለት ብዙ አደጋ ሳይርስ አፋጣኝ እርምጃዎችንና ጫናዎችን በማድረግ፣ በተለያዩ ጊዜ እንደተፈጠሩት የዘር ፍጅቶች “Never Again” ወይም “በጭራሽ አይደገምም” እያለ ከአይሁዶች እስከ ሩዋንዳ ተመሳሳይ መፈክር ማሰማት ብቻ ሳይሆን በተግባር እንዳይፈጸም ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ለዚህም በአለም አቀፍ ያለው የዲፕሎማሲና የአለም አቀፍ ግንኙነት መሳሪያዎችና መርሆችን መዓከል ያደረጉ እርምጃዎችን በእደዚህ አይነት መንግስታት ላይ እርምጃ መወሰድ ይኖርበታ፤ነገሮች ከመዘግየታቸውና እልቂት ከመፈጠሩ በፊት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ እንደዚህ ያሉ እልቂቶችን እንዳይፈጸሙ ማድረግ አለበት፡፡ ሰላም ለሰው ዘር በሙሉ በላይነህ ዘለለው፣ሩዋንዳ፣ኪጋሊ ጳግሜ 04/2014 ዓ.ም
Advertisement