Successfully reported this slideshow.
Your SlideShare is downloading. ×

Biotech quick facts

Ad
Ad
Ad
Ad
Ad
Ad
Ad
Ad
Ad
Ad
Ad

Check these out next

1 of 6 Ad

More Related Content

Advertisement

Biotech quick facts

  1. 1. በባዮቴክኖሎጂ ሰብሎች በዓለም ዙሪያ የተገኙ ጥቅሞች  በ2014 የተካሄደ አዲስና ግዙፍ ዓለም አቀፋዊ ጥናት ባለፉት 20 ዓመታት ከዘርፉ ፈርጀ ብዙ ጥቅሞች መገኘታቸውን አረጋግጧል። በ147 አገሮች በተካሄደው ጥናት ባለፉት 20 ዓመታት የልውጠ-ህያዋን ሰብሎችን የማላመድ ቴክኖሎጂ የፀረ-ተባይ ኬሚካል አጠቃምን በአማካይ በ37 በመቶ መቀነስ ማስቻሉን አረጋግጧል። በተጨማሪም የሰብል ምርታማነትን 22 በመቶ፤ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ደግሞ 68 በመቶ አሳድጓል።  በቅርቡ ይፋ የተደረጉ ጥናቶች ከ1996 እስከ 2013 ባሉት ጊዜያት የባዮቴክ ሰብሎች ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አሳይተዋል። ከዚህ ባለፈም የሰብል ምርታማነትን በማሳደግ 133 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ በማስገኘት፣ ከ1996 እስከ 2012 ባለው ጊዜ 500 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ፀረ-ተባይን በመቆጠብ የተሻለ አካባቢን በመፍጠር እንዲሁም በ2013 ብቻ 28 ቢሊዮን ኪሎ ግራም የካርበንዳይኦክሳይድ ልቀትን በመቀነስ ለዘላቂ ልማትና የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት አስተዋጽኦ አበርክቷል።
  2. 2. በዓለም ዙሪያ በባዮቴክኖሎጂ ሰብሎች የተገኙ ጥቅሞች  ከ1996 እስከ 2013 ባለው ጊዜ በ132 ሚሊዮን ሄክታር ላይ ብዝሃ ህይወትን በመጠበቅ ከ16 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚበልጡ አነስተኛ አርሶ አደሮችንና ከ65 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦቻቸውን ድህነት መቀነስ ችሏል።
  3. 3. የባዮቴክ ሰብል መጻኢ ዕድሎች  የባዮቴክ ሰብሎችን መፃኢ ዕድል አዎንታዊ ወይም ተስፋ ሰጪ ብሎ መግለጽ ይቻላል።  አሁን ባሉት ዋና የባዮቴክ ሰብሎች ከፍተኛ ማለትም ከ90 እስከ 100 እጅ በሆነው የመላመድ ፍጥነት የዳበረ ገበያ ባላቸው የታዳጊና በኢንዱስትሪ የበለጸጉ አገራት ጭምር ሰፊ የመስፋፋት ዕድል አለው።  ቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ሊቀርቡ በሚችሉ አዳዲስ የባዮቴክ የሰብል ምርቶች የተሞላ ነው። በአጭሩ ከ70 የሚልቁ ምርቶች በዝርዝር ተይዘዋል። ይህ ደግሞ በርካታ አዳዲስና የተለያዩ ባህሪያት ያላቸውን የሰብል ምርቶች ያካተተ ነው። እነዚህ ምርቶች የተለያዩ ተባዮች፣ በሽታና ፀረ-አረምን የመቋቋም አቅም ያላቸው ናቸው።
  4. 4. አምስቱ ከፍተኛ የባዮቴክ ሰብሎች አብቃይ አገራት 1. አሜሪካ 73 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ወይም ከዓለም 40 በመቶውን በመሸፈን ቀዳሚ አብቃይ አገር ናት። ከዚህ ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ ዋና ምርቷ የሆነውን በቆሎ ያላመደች ሲሆን 94 በመቶ አኩሪ አተርና 96 በመቶ ጥጥ ታበቅላለች። 2. ብራዚል ባለፉት አምስት ዓመታት በሄክታር ከዓመት ዓመት ዕድገት በማሳየት ቀዳሚ አገር ነበረች። እንደ እውሮፓውያን አቆጣጠር በ2014 አሜሪካ 3 ሚሊዮን ሄክታር በመሸፈን 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታር ከሸፈነችው ብራዚል ልቃ ቀዳሚ መሆን ችላለች። 3. አርጀንቲና እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2013 በዘር ከሸፈነችው 24 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር ወደ 24 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር ብትንሸራተትም የሦስተኛ ደረጃን ይዛ ቀጥላለች።
  5. 5. አምስቱ ከፍተኛ የባዮቴክ ሰብሎች አብቃይ አገራት 4. ሕንድ 11 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በቢቲ ጥጥ በመሸፈንና 95 በመቶውን በማላመድ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። 5. በአንፃሩ ካናዳ 11 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር ጎመን ዘር 95 በመቶ በማለማመድ አምስተኛዋ አገር ሆናለች። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2014 በአምስቱ ግዙፍ አብቃይ አገራት ከ10 ሚሊዮን ሄክታር በላይ የባዮቴክ ሰብል ማብቀል የተቻለ ሲሆን ለዘላቂ ዕድገት ሰፊና ጠንካራ መሰረት ተጥሏል።

×